~ጸ~

                                 

ዐሥራ ስምንተኛ ፊደል በጥንታዊው ተራ፤ በግእዝ አልፍ ቤት በአበገደ ስሙ ጸደይ ጥሩ ዘጠና አኃዝ ሲኾን ይባላል
ጸሐለ (ጸሊሕ ጸልሐ፤ ጸልሐወ) ጣፈ፤ ቀረጸ፤ በደንጊያ ይ፤ እንዳሠርቱ ቃላት።
ጸሓም (ማን ጸሐምት) ጢማም ሪዛም፤ ባለጢም፤ ጢመ ረዥም ጸሓም ወጸጓር (ገድ ፡ ፊቅ)
ጸሓቂ (ቂት ቅያን ያት) የሚወድ የሚተጋ ዐሳ ጸሓቂ በመንፈሱ ወጻማዊ በገድሉ ለባዊ ወጸሓቂ ፊልጶስ ጸሓቂ ውስተ ትምህርት ጸሓቅያን ለሠናይ ፡ (ገድ ፡ ተክ። ኪዳ። ቄር )
ጸሐየ (ዕብ ጻሐሕ) ጸሐወ፤ በራ ጠራ፤ ጽሩይ ኾነ ጽርየቱ መልክ የሚያሳይ እስኪኾን ድረስ የውሃ የሸክላ የማዕደን ጽሕወና ጸሐየ አንድ ዘር ናቸው
ጸሓይ በቁሙ ፀሓይ ኹለተኛውን ተመልከት፤ ሊጣፍ የሚገባው በዚህ ነበረ፤ ስለ ልማድ ወደ ፀጳ ኺደል
ጸሓፊ (ፊት ፍያን ያት ሐፍት) የሚጥፍ ጣፊ ጣሪ ሹም ዐዋቂ ብልኅ ጠቢብ ቀለመ ጸሓፊ ጸሓፌ ሰራዊት ጸሐፍተ መባእ ዕዝራ ጸሓፌ ሕጉ እግዚ ጸሓፌ ሀገር ሐፍተ ሀገር ፡ (መዝ ፡ ፵፬። ኢሳ፴፮ ፳፪። ዘዳ፲፮ ፲፰ ዝ፯ ፲፩። ማቴ፳፪ ፡ ፴፭። ሉቃ፲፩ ፵፭)
ጸለሎ ጥላት፤ የጥቀርሻ ዐይነት። ከመ ጸለሎ መቅፁት ያዴምኖ ገጽ ፡ (አርጋ ፡ ፪። ዮኤ፪ ፮። ናሖ፪ )
ጸለተ [1] (ዲቃ ) ጋገረ ጠፈጠፈ በት ስመሰለ አሣሣ ለመ ጠቀጠቀ፤ የቂጣ የመጠቃ የጥረሾ። ሐማሴኖች ጎጎ ይሉታል።
 [2]ጸለተጋገረ፤ጸለየ ጽላት።
ጸለወ (ዐረ ጸላ ዕብ ጻላህ) ጠበሰ አበሰለ፤ በፍም በነዲድ። አዘዘ ይጽልውዎ ገጾ ውስተ እቶነ ብለኔ ፡ (ስንክ ፡ ሠኔ፲፱)
()            ጸለጠ (ዐረ ጸለተ) ጨለጠ መጠጠ ባዶ አደረገ ወይጸልጥ ፡ (አዋል)
()            ጸሊል ሎት (ጸለለ ይጸልል ይጽልል። ዕብ ጻላል። ዐረ ጸለ ሱር ጻሊል) መጥለል፤ መጥራት፤ ጥሩ መኾን፤ መፍሰስ መቅለጥ፤ መንጠር፤ ለመጥራት። አድራጊም ይኾናል
  መስፈፍ፤ መንካፈፍ፤ መንጓለል፤ መዋኘት። ጸለለ ዝክቱ ጺን ጸለለት ታቦት ላዕለ ማይ። ተሠርሙ ውስተ ባሕር አላ ጸለሉ መልዕልተ ማይ (፬ነገ ፮ ፡ ፮። ዘፍ፯ ፲፰ መቃ ፡ ገ፪) ፋኤል መልአከ ራማ ባሕረ ሥጋዌ ጸበተ ንዘ ምነ ጽል ይነሥእ ርኣያ ወእምነ ሐመር ምሳለ ባሕረ ሥጋዌ ዕሌሁ ጸለለ። ዕመቀ ባሕርዩሰ ይርአይ ፈጣሪ በእንቲኣነ ህለ ወረደ ታሕተ ወተቈልቈለ መሰ እማእከል ኢተርፈ ወኢተለዐለ አርአየነ ጻሁ መስቀለ (ሥላሴ ፡ ቅኔ)
  በአየር በኅዋ መርበብ፤ መሰቀል፤ ረቦ ተዘርግቶ መኼድ፤ ያሞራ የደመና የመሰለው ኹሉ ጸለለ መንፈስ ቅዱስ ዕለ ማያት ወመንፈሰ እግዚ ይጸልል መልዕልተ ማይ (ቀሌ ዘፍ፩ )
  (ጥጠ) መጠለል፤ ጥላ መያዝ፤ ከጥላ ማረፍ መጠጋት። መጽሐፍ ግን በጸለለ ፈንታ አጽለለ ይላል ስሕተት ነው ያጸልል ታሕተ ኵሉ ዕፀው። ረከበ ዕፀ ጽፍቅተ ወአጽለለ ያጸልሉ ታሕቴሁ ራዊተ ገዳም (ሢራ፳፮ ፲፪ ተረ ባሮ ዳን፬ )
()            ጸሊም (ማን ማት ላም ለምት) ጥቍር፤ ጠቋራ፤ ከሰልማ፤ ቅጽልና በቂ ይኾናል ጽሑፍ በጸሊም አባ ሙሴ ጸሊም። ፍራስ ጸሊማን። ጸላም አነ። ይመጽእ ለቢሶ ጸሊመ ለምንትኑ በስከ ጸሊማተ ፡ (አቡሻ ፴፫። ስንክ ፡ ኔ፳፬ ዘካ፩ ፰። ማሕ፩ ፭። ዮሴፍ። ፈላስ)
ጸሊም ሞት (ጸልመ ይጸልም ይጽልም ዕብ ጼሌም። ሱር ጸልማ ለማ፤ ሥዕል፤ ምስል) መጨለም፤ መምሸት፤ ውድቅት ጨለ መኾን፤ ጨለማ መልበስ መጥቈር፤ ጥላት መምሰል፤ መፍዘዝ፤ ከማየት መከልከል ወድአ ጸልመ እስመ ጽልመትኒ ኢይጸልም በኀቤከ ጸልመ ኵሉ ዓለም። ጸልመ ፀሓይ። ጸልመ ገጹ። ጸል ዐይንነ ተጸለለ ወጸልመ (ዮሐ፮ ፲፯ መዝ ፻፴፰ ማቴ፳፯ ፵፭። ራእ፮ ፲፪። አስቴ፯ ሰቈ፭ ፲፯ ግብ፲፫ ፲፩)
 ፡ መክዳት መካድ ከዳተኛ መኾን። ጠለመን እይ የዚህ ጎር ነው።
ጸሊብ ቦት (ጸለበ ይጸልብ ይጽልብ፤ ዐረብ ሱር ጻላብ ዕብ ታላህ) መስቀል፤ ማንጠልጠል፤ በችንካር በሐብል የፈያት የንዋያት። ኔስታሊንና ሰቀለን ተመልከት።
ጸሊእ ኦት (ጸልአ ይጸልእ ይጽላእ ሳኔእ ሱር ስናእ ዐረ ሸነአ) መጥላት፤ መጠየፍ፤ መቈጣት መንቀፍ፤ መቀየም፤ መናቅ ልብን ማራቅ ጊዜ ጸሊእ። ፈድፈዱ ጸሊኦቶ ዘትጸልእ ለርእስከ ትግበር ዲበ ቢጽከ አፍቀሩ ዘጸላእኩ አነ ጣዖተ ጸልአት ፍስየ (መክ፫ ፰። ዘፍ፴፯ ፰። ዲድ ፩። ኢሳ፷፮ ፬። ኩፋ ፡ ፳፩) ምዝርና ጸልአ ባማርኛ ይተባበራሉ። ፡ (ግጥም) ጮማውና ጠጁ መልቶ በቤታቸው እግዚያሔር ጠላና እንጀራ ነሣቸው
ጸሊዕ ዖት ፡ (ጸልዐ ይጸልዕ ይጽላዕ ጸልአ) ማቄም መለገም ማድፈን፤ ማቅበር ማበጥ መቍሰል፤ መፍረጥ መምገል ጸምአና ጸምዐ አንድ እንደ ኾኑ፤ ጸልአና ጸልዐም አንድ ዘር ናቸው በአ መለወጡ የቍስሉን ዐይን አፉንና ፍንጩን ያሳያል
ጸሊው ዎት (ጸለወ ይጸሉ ይጽሉ ጸለየ) መቀቀር፤ ማቀርቀር፤ ማዘንበል፤ የዦሮ መስማት ማድመጥ፤ መታዘዝ ወጽልዉ ዝነክሙ ኀበ ቃለ ፉየ ጸመመት እዝን እምጸሊዎቱ ሶበ ጸለወ ትእዛዘ ንጉሥ ፡ (መዝ ፸፯። አዋል ስንክ ፡ ሠኔ፳፩)
ጸላሊ (ሊት ልያን ያት) የሚጠል፤ የሚሰፍ፤ የሚረብ የሚከንፍ፤ የሚጠለል፤ ከጥላ የሚያርፍ
ጸላኢ (ኢት እያን ያት) የሚጠላ ጠላት፤ ምቀኛ፤ ባለጋራ፤ ደመኛ። በእንተ ጸላኢ ከመ ትንሥቶ ጸላኢ ጸላእያንየ ወቀናእያንየ ጸላእያነ እግዚ አፍቅሩ ጸላእተክሙ ፡ (መዝ ፰። ዮሴፍ ሮሜ፩ ፴። ማቴ፭ ፵፬)
ጸላዊ መጽልው (754) የሚጠብስ፤ ጠባሽ፤ ብሳይ።
ጸላዪ (ዪት ይያን ያት) የሚጸልይ ጸላይ ጸሎተኛ። ፈሪሳዊ ጸላዪ ወመጸብሓዊ ጸላዪ (ፊልክ ፡ ፴፭)
ጸልሐ (ዕብ ጻላሕ) ጣስ ሠንጥቆ ዐለፈ አማረ ተዋበ፤ ተከናወነ፤ በመልክ በግብር ባነጋገር።
ጸልሀወ ጸልሀወ፤ሸነገለጸልሐ።
ጸልሐወ (ተቀ ) ሸነገለ፤ አሞኘ ታለለ ጸልሐዉ በልሳኖሙ ፡ (መዝ ፡ ፭። ቄር)
ጸልሓዊ (ዊት ውያን ያት) የሚሸነግል፤ ሸንጋይ፤ አታላይ፤ ዳተኛ። መጽሐፍ ግን በጸልሓዊ ፈንታ ጽልሕው ይላል የጣፊና የመላሽ ስሕተት ነው ብእሲ ዐማፂ ወጽልሕው ኃጥኣን ወጽልሕዋን ፡ (ዮሴፍ። ቀሌ)
()            ጸልሎ ሎት (ጸለለ ይጼልል ይጸልል) መጸለል፤ በላይ ኹኖ ማጥላት፤ ጥላ መኾን፤ ማልበስ መክደን፤ መሸፈን መክለል መጋረድ፤ ማጨለም። ይጼልላ ደመና ለደብተራ። ወአዘዘ እግዚ ሐምሐመ ወበቈለ ወጸለሎ መልዕልተ ርእሱ ዮናስ። ጸለለ ከመ ወይን ማኅደሮ አልከወኒ ወጸለለኒ ዕይንትየ። ይጼልሉ ወይቀትሉ (ዘኍ፱ ፲፰ ዮና፬ ፮። ሰቈ፪ ፮። ኢዮ፲፮ ኩፋ ፡ )
  እጅን ክንፍን ወደ ላይ በስተላይ መዘርጋት፤ በውስጥ ማደር መምላት ንሰፍሕ ለከ አዳወ መዝራዕት ወንጼልል ዲበ ዝንቱ መሥዋዕት ስመ ኪሩብ ጸለሉ ክነፊሆሙ መልዕልተ መካና ወጸለልዋ ለታቦት ወስእነ ሙሴ በዊአ ውስተ ደብተራ፤ እስመ ጸለለ ደመና። ኀይለ ልዑል ይጼልለኪ። ወይጼልል ዲቤሆሙ ፡ (ቅዳ ጎር ነገ ፰ ፡ ፯። ዘፀ፵ ፳፱ ሉቃ፩ ፴፭። ራእ፯ ፲፭)
ጸልመተ (ጽልመት፤ ጸልመ) ጨለመ፤ ጠቈረ፤ ደነቈረ። በጸልመ ፈንታ ጸልመተ እያለ ይገኛል ይጸለምቱ በእንተ መንሱት። ትጸለምት ነፍሳቲሆሙ። ይጸለምት ልቡ ወይረስዖ እግዚ ፡ (ፊልክ ፡ ፲፬ ፴፩ ፻፶፮)
ጸልቦ (ዐረ ጸሊብ) መስቀል፤ መስቀያ፤ መሰቀያ። ሰላም ስቅለትከ መልዕልተ ቅዱስ ጸልቦ ሶበ ተረክበ ጸልቦሁ ለወልድ ሥሉጠ ልደት ክርስቶ ወመሥዋዕተ ዘዲበ ጸልቦ (ስንክ ፡ ኅዳ፰ መጋ፳፯ ድጓ። ቅኔ)
ጸልእ ስልጸሊዕ ጸልዐ።
ጸልዕ (ዐረ ሰልዐት) ቍስል ዕባጭ የበትር የደዌ የመቅሠፍት ችፌ ጭንቍር፤ ዋጣ ጥኝ ኰብሽ፤ ነቀርሳ፤ የመሰለው ኹሉ። ጸልዕ ዘይመግል። ወሰኩኒ ዲበ ጸልዕየ ቍስለ ወመጽአ ዕሌሆሙ ጸልዕ እኩይ ፡ (ኢሳ፩ ፮። መዝ ፡ ፷፰። ራእ፲፮ ) ምስጢሩ ጽልእን አይለቅም፤ የሚጠላና የሚያስጠላ የሚያስቀይም፤ የሚያስጠይፍ ማለት ነው
()            ጸልዮ ዮት (ጸለየ ይዴሊ ይጸሊ ጸለወ) መጸለይ፤ መለመን፤ መሳል፤ ማመስገን፤ ከአምላክ ጋራ መነጋገር ውተረ ጸልዮ። ንትሙሰ ሶበ ትጼልዩ ከመ በሉ ጸሎተ ጸለየ እግዚ እንዘ ይብል ፡ (ሉቃ፳፪ ፡ ፵፬። ማቴ፮ ፰። ኩፋ ፳፯)
ጸሎት [1] በቁሙ፤ ጸለየ ጸልዮና ጸሊው አንድ ዘር ናቸው ወና ተወራራሾች ስለ ኾኑ በጸሌት ፈንታ ጸሎት ይላል፤ ጸለየን ተመልከት።
 [2](ታት። ሱር ጽሎታ። ዐረ ጸላዋት) በቁሙ፤ ልመና፤ ምስጋና። ጸሎትሰ ተናግሮተ ሰብእ እግ ልዑል እንዘ የአኵቶ ወይሴብሖ ወይትአመን በእግዚእናሁ፤ ወበተአምኖ በአበሳሁ ወኀሢሥ ምኔሁ በዘያሠምሮ ቦቱ ወጸሎትሰ ዘተአዘዘ ላዕለ ኵሎሙ ምእመናን በኵሉ ዕለት ሰብዐቱ ጊዜያት ቤትየሰ ቤተ ጸሎት። ሠናይ ውእቱ ጸሎት ፡ ( ፲፬ ኢሳ፶፮ ፯። ጦቢ፲፪ ፡ )
[3](ዕብ ኔዴር) ስለት፤ ብፅዐት በፅዐን ተመልከት ጸለይኩ ጸሎተ ጐየይኩ ምገጸ ዔሳው እኁየ ጸሎታ ዘከመ ነበበት በከናፍሪሃ። ወሀቦ ልዑል ጸሎተከ (ኩፋ ፡ ፴፩። ዘኍ፴ ፯። መዝ ፡ ፵፱)
 [4]በቁሙ፤ጸለወ፤ ጸለየ
ጸመመ አሰረ ጠቀለለ ፈወሰ፤ፀመመ።
ጸመተ [1]ጨመተ ዝም አለ ረጋ ጭምት ኾነ
[2]:-መተ፤ጸሚም።
ጸመደ ጠመደፀሚድ ፀመደ
ጸሚሕ ሖት (ጸምሐ ይጸምሕ ይጽማሕ። ዕብ ጻማሕ) መብቀል፤ መውጣት ማደግ፤ የቡቃያ
ጸሚም ሞት (ጸመ ይጸምም ይጽምም ዐረ ጸሚመ) መዘጋት፤ መደፈን፤ መደንቈር የዦሮ የአፍ ጸሙ ዘኒሆሙ ከመ ይስምዑ ይትመሰው አባሉ ወይጸምም እዝኑ (መቃ ገ፭ ግንዘ)
  መጥመም፤ መለገም፤ ዝም ቸል ችላ ማለት እያዩ እየሰሙ እንዳላየና እንዳልሰማ መኾን። መጽሐፍ ግን ጸመ ጸመመ በማለት ፈንታ ተጽመመ ተጸመመ ይላል፤ አያሰኝም። መኑ ጸውዖ ወተጸመሞ ፍረት ተጸምሞቱ ዘይጼውዐከ እግዚኦ ኢትጸመመኒ ስእለትየ ይጸመም ከመ ዘኢይሰምዕ። እመ ጸመምኪ ዮም ፡ (ሢራ፪ ፵፩ ፡ ፳። መዝ ፡ ፻፰ ቅዳ ግሩ። አስቴ፬ ፲፬)
ጸሚቅ ቆት (ጸመቀ ይጸምቅ ይጽምቅ ዕብ ጸማቅ ደረቀ) መጭመቅ መጥመቅ ውሃውን ለማውጣት ለማድረቅ ጠመቀን እይ፤ የዚህ መንቲያ ነው
ጸሚእ  ኦት (ጸምአ ይጸምእ ይጽማእ። ዕብ ጻሜእ) መጥማት፤ መጠማት፤ ውሃ መጠጥ መፈለግ፤ መናፈቅ። ጸምዐን ተመልከት የዚህ መንቲያ ነው እለ ጸምኡ ይሑሩ ማይ። ዘጸምአ ይምጻእ ቤየ ወይስተይ ጸምአት ፍስየ ምላኪየ ሕያው ነፍስየኒ ከመ ምድረ በድው ጸምአተከ (ኢሳ፶፭ ፩። ዮሐ፯ ፴፯። መዝ ፡ ፵፩ ፡ ፻፵፪)
ጸማም (ምት ማን ማት) ማማ ልግመኛ፤ ቸልተኛ፤ ደንቈሮ ፡ (ትግሬ)
ጸምሀየ ጠወለገ፤ጸምሐ
ጸምሐየ (ተቀ ) መጽለወ፤ ጠወለገ ፈራ ዛለ ተሽመለመለ፤ ተለወጠ፤ መድረቅ ዠመረ ጸሐየ ለው የመጣ ነው ጸምሐየ ከመ ሐምለ መሎኬ በውስተ ሐሩር ርኢ ከመ ጸምሐየ በለስ ደቂቅኪ እለ ጸምሐዩ። ወዘኢጸመሒ ዘእንበለ ይጸምሒ ፡ (ኢዮ፳፬ ፳፬ ተረ ባሮ ኢሳ፶፩ ፩ጴጥ ፩ ፡ ጥበ፪ ፡ ) በጸምሐየ ፈንታ ተጸምሐየ ይላል፤ ስሕተት ነው በእንተ ትሕርምቶሙ ወድካሞሙ ደግደገ ሥጋሆሙ ወተጸምሐየ ተጸምሐያ በረኃብ ንስት ወሶበሂ ትጸውሙ ትጸምሕዩ (ፊልክ ፲፮ ሰቈ፭ ፡ ማቴ፮ ፲፮) ኹለተኛም ጸምሐየየ ተጸምሐየየ እያለ ኹለተኛ ይጨምራል፤ የጣፊ ስሕተት ነው ፡ (ማር ፡ ይሥ፲፫ )
ጸምላጥ [1] ፡ ጨምጫማ በልጣጣ፤ ማዝ የያዘው ዐይን ቅንድቡ የተመለጠ የተገለበጠ ውስጡ የጐሽ ጠጕ የሚወጣበት። ከነጸየና ለሐጸ መጥቶ ተደርቧል ዘጸምላጥ አዕይንቲሁ ጸምላጠ ዐይን (ዘሌ፳፩ ፳። ቀሌ)
 [2] ምጫማመለጠ።
()            ጸምዎ (ጸመወ ዐረ ጸመተ) መጨመት ዝም ዕክም ጸጥ ማለት፤ ሕዋሳተ አፍኣን መጠበቅ፤ አለመታወክ፤ ዳተኛ ዝምተኛ መኾን ከማስተዋል ጋራ የመነኵሴ። ሀድአን ተመልከት፤ የዚህ ተማ ነው
ጸምር የበግ የፍየል ጠጕርፀምር
ምቶ ቶት (ጻመተ ይጻምት። ዕብ ጻማት አጠፋ) ማለቅ መጣመት ተጨርሶ መጥፋት።
ጸምዐ (ጸሚእ፤ ሰሚዕ) መስማት ፈለገ ለሰሚዕ ቸኰለ ልስማ ልስማ አለ። ዘሩ ጸሚእ ነው ከሰሚዕ መጥቶ በአ ፈንታ ገብቷል፤ ምስጢሩ ጽምእን አይለቅም ፡ (ዓሞ፰ ፲፩)
ጸምአ ቀረበ አደመጠ ጸምዐ
ጸሪሕ ሖት (ጸርሐ ይጸርሕ ይጽራሕ ዕብ ጻራሕ ዐረ ጸረኀ) መጮኽ መጥራት፤ ማልቀስ፤ ቡታ መስደድ መጸለይ፤ አቤት ቤት ማለት ርሐት በዐቢይ ቃል። እጸርሕ ኪያከ ጸራሕኩ ጽራሐ መሪረ። ጸርሕ ወአዐወዩ። ሶበ አኅለቀት ጸሪሐ እግዚ ፡ (ሱቱ ዕዝ፲ ፡ ፴፱። ስንክ ፡ ነሐ፲፫ ሔኖ፷፭ ፭። ሰቈ፫ ፰። ዮዲ፲ )
ጸሪቅ [1](ቃት፤ ጸራይቅ) የንሓስ ገንዘብ፤ ሥሥ፤ ታናሽ፤ መጨረሻ፤ ወራዳ፤ የተናቀ፤ ስምና መልክ ያልታተመበት፤ የአሶርዮን ሩብ። አንዱ ጸሪቅ ሳንቲምና የሳንቲም ሩብ ይኾናል፤ ሳንቲም መቶኛ ወይም የመቶ አንደኛ ነው እንተ ረሰይከ እግዚኦ ጸሪቀ መበለት ውኩፈ እምእለ ብኡ ብዑላን ዘተርፈ (ደራሲ) ክልኤ ጸራይቅ በክልኤቲ ጸሪቀ አሶርዮን ፡ (ማር፲፪ ፪። ሉቃ፲፪ ) ባለሐዲሶች ግን ሻሜ መሐልቅ፤ ኃምስ ደዋኔ፤ ግርሽ፤ የሙርኝ እንጀራ ይሉታል። ሙርኝ የጤፍ ዐይነት ሣር ነው፤ ዳልጋውና ፍሬው ጥቍር ጤፍ ይመስላል።
[2](ዕብ ራቂቅ) ሥሥ ረቂቅ ዕንጐቻ። ለግንን ተመልከት። ጸራይቀ ናእት። ጸራይቀ ኅብዝት። በበ ጸሪቃት ኅብዝተ ጤጉን (ዘፀ፳፱ ፩ዜና ፲፮ ፫። ፪ነገ ፮ ፡ ፲፱)
ጸሪቅ ቆት (ጸረቀ ይጸርቅ ይጽርቅ ዐረ ጸረቅ) ማሣሣት፤ ማርቀቅ፤ መዘርጋት ሥሥ ዝርግ ማድረግ፤ የቂጣ የንሓስ። መጨረቅ ማለቅ ውሃ መምሰል መበጨቅ መበጫጨቅ፤ ጨርቅ ውራጅ መኾን፤ የልብስ። ከጥሬው በቀር አንቀጹ አይገኝም። ጨረቃ ማለት ከዚህ ወጥቷል
ጸሪብ ቦት (ጸረበ ይጸርብ ይጽርብ ዐረ ፀረበ መታ ዕብ ራብ ነደ ውዕየ) መጥረብ፤ መሸለት፤ መላግ፤ ንጨትን ማነጥ መቅረጥ፤ ማስጌጥ፤ አሳምሮ መሥራት ዘይጸርብ ምውስተ ዕፅ ጸረቦሙ በምሣራተ ጺን። ጸረበ ሎቱ መስቀረ ፡ (ዘፀ፴፩ ፭። ፩ዜና ፡ ፫። ሔኖ፳፱ )
ጸራቢ (ቢት ብያን ያት ረብት) የሚጠርብ፤ ጠራቢ፤ ዐናጢ። ዘገብሮ ጸራቢ። ጸረብተ ዕፀው። ሊቀ ጸረብት ፡ (ኢሳ፵ ፲፱ና ፡ ዜና፲፬ ፩። ፩ቆሮ ፡ ፫ ፡ )
(ጥራ)          ጸራብ ዝኒ ከማሁ። ብእሲ ጸራብ ፡ (አዋል)
ጸራዒት (ዕብ ክሳሊም ጽር ሚሪዎን) ብሽሽት ጭቅና፤ የኵላሊት ቦታ፤ ዙሪያው አጠገቡ። ሥብሕ ዘውስተ ጸራዒት (ዘሌ፫ ፬ ፡ ፲። ፲፭ ፬ ፡ ፱ ፡ ፯ ፡ ) ጸራዒት ዘውግ ነው የግራና የቀኝ ላንድ ሲኾን ግን ጽርዔ ያሰኛል።
ጸርሰ ጠረሰፀሪስ ፀርሰ።
ጸርቅ ( አጽርቅት) ጨርቅ የልብስ ላቂ ውራጅ ጐራጅ ቍሩጭ ዕራፊ። ዘጸርቅ። ጸርቀ ትክቶ ይከድን ሥጋሁ በጸርቅ ብሉይ ፈሐቁ ቍስሎ በአጽርቅተ ጸጕር ጠብለልዎ በአጽርቅት፤ ጕራጅ ፡ (ማቴ፭ ፳፪። ኢሳ፷፬ ፮። ስንክ ፡ ጥቅ፴ ፲፬ ሐም፲ ቅዳ ዮሐ)
ጸርብ ( አጽራብ) ጠርብ፤ ፍልጥ የቤት ዕንጨት።
ጸርአ ቦዘነፀርዐ።
ጸርእ (ትግ ጸር ዕብ ጺርዓ ንህብ) ማኅበረ ሕዝብ፤ ጉባኤ ሕዝብ፤ እንደ ንህብ አውራውን የሚከብ፤ ሰልፍ ዐጀብ።
ጸርይ ዮት (ጸርየ ይጸሪ ይጽረይ አው ጸረየ ይጸሪ ይጽሪ) መጥራት፤ መንጣት፤ ጥሩ መኾን፤ ከርስሐት መለየት ወለል ኮለል ማለት ከመ ወርቅ ዘይጸሪ እምጺአቱ ይጸርዩ ቦቱ እምከመ  ጸርየት ኅሊና ፡ (ሄርማ። ፈላስ)
ጸቍን ዝኒ ከማሁ፤ የካብ ደንጊያ፤ ጥሬ ካብ፤ ዐፈር ቃም፤ ርስ በርሱ የተጨቋቈነ።
ጸቍን ኖት ዝኒ ከማሁ፤ የካብ ደንጊያ፤ ጥሬ ካብ፤ ዐፈር ቃም፤ ርስ በርሱ የተጨቋቈነ።
ጸቂው ዎት (ጸቀወ ይጸቁ ይጽቁ ዐረ ጸቀበ) መምታት፤ መትከል፤ መቸከል መቀብቀብ ምድር ማጣበቅ የካስማ የችካል ወጸቀወቶ ፡ (መሳ፬ ፳፩) ጺቅ ጢቅ ማለት፤ መትፋት የንህብ፤ ጸየቀን ተመልከት
ጸቃውዕ ዓት (ቀውዕ ቅያእ) ወለላ ማር፤ የማር ወለላ፤ የንቦች ትፋት ከጽጌያትና ከአዕጹቅ እየቀሠሙ በሰፈፋ ዐይን በየጕድጓዱ የሚተፉትና የሚመሉት፤ ፈሳሽ ከቆዕ መጥቷል ስለዚህ ንባቡ ቀውፅን ምስጢሩ ቅያእን ይመስላል። ጸቃውዕ የብዙ ነው ያንድ ሲኾን ጸቆዕ ጸቁዕ ወይም ጸቂዐት ያሰኛል ጸቃውዓት ግን የብዙ ብዙ ነው ጸቃውዐ መዓር። እግዚ ገብረ ጸቃውዐ ምቈጽል ወጽጌያት ጥዑማን ጸቃውዕ ዘእምነ እንቈ ትትቀዳሕ። ኢያማዕርር ርዔየ ጸቃውዐ ዘማ ኅስርት (ምሳ፲፮ ፳፬ ቀሌ። አርጋ ፡ ፭። ስንክ ፡ ጥቅ፳፱)
ጸቈን (ናት አጽቋን) ካብ ዐጥር ቅጥር ጀጐል፤ገረገራ ለፌ ጸቈን ወለፌ ጸቈን ዘይነሥት ጸቈነ ይነስኮ ርዌ ምድር ወገብረ ሎቱ ጸቈነ (ዘኍ፳፪ ፡ ፳፬ መክ፲ ፡ ማቴ፳፩ ፴፫)
ጸበል (ላት) ብናኝ ትቢያ ዐቧራ ደቃቅ ዐፈር ንግፉ ጸበለ ገሪክሙ ይደፍነኪ ጸበል እምብዝኀ ፍራሲሁተናገፊ ጸበለኪ (ማቴ፲ ፲፬ ሕዝ፳፮ ፲። ኢሳ፶፪ ) በጸበለ ፈንታ ጸብለየ ተጸብለየ ይላል፤ ስሕተት ሰላም ብል ኅሊናከ ጽሩየ ዘኢረስሐ ምንተ ወኢጸብለየ ፡ (ስንክ ፡ መጋ፮)
ጸበርት ዐጽቃም ቅጠላም ዛፍ ዝንጣፊ፤ፀበርት።
ጸበጠ በጠ፤ፀቢጥ ፀበጠ
ጸቢሕ ሖት (ጸብሐ ይጸብሕ ይጽባሕ ዐረ ጸባሕ፤ ጧት) መጥባት፤ መንጋት ወገግ ማለት ጧት መኾን ሶበ ጸብሐ ስከ ጸብሐ። እምከመ ጸብሐ ፡ (ሩት፫ ፲፫ ፩ነገ ፫ ፡ ፲፭ ኢዮ፳፬ ፲፯) ለጸቢሐ ርብ ላርብ አጥቢያ ሙስ ማታ (ቅዳ ኤጲ) ለጸቢሐ ሑድ በጽባሐ እሑድ እሑድ ጧት፤ ማለዳ ፡ (ማቴ፳፰ ) ወጸቢሖ፤ እንተ ጸቢሖ በነጋ ጊዜ፤ ሲነጋ ሲጠባ ጧት ማለዳ፤ ፡ (ግብ፲፪ ፮። ፳፯ ፴፫)
ጸቢኅ ኆት (ጸብኀ ይጸብኅ ይጽባኅ ዐረ ጠበኀ) ማወጥ፤ ማጣፈጥ ወጥ መሥራት፤ መቀቀል። መጥቀስ፤ መጥለቅ፤ መንከር መዝፈቅ እንጀራን በወጥ በመረቅ ወኮነ ይትጌበር ኵሎ ግብረ ቤት እስከ ቀዲሐ ማይ ወኰስትሮ ኵስሕ ወአንድዶ እሳት፤ ወጸቢኀ ጸብኅ ወኀቢዘ ኀብዝ(ስት) ዘይጸብኅ ምስሌየ ጸብኀ ኅብስት ወመጠዎ ፡ (ስንክ ፡ ጥቅ፱ ማቴ፳፮ ፳፫ ማር፲፬ ዮሐ፲፫ ፳፮ ሩት፪ ፲፮)
ጸቢል ሎት (ጸበለ ይጸብል ይጽብል። ዘበለ) መብነን፤ ሐመድ ትቢያ መኾን። ማደፍ መጕደፍ ዐቧራ መልበስ።
ጸቢር ሮት (ጸበረ ይጸብር ይጽብር። ዕብ ጻባር) መርገጥ፤ ማላቈጥ፤ መሰብሰብ መቈለል፤ አርባጫ ይሳ ማስመስል፤ የጭቃ። በጸበረ ፈንታ አጽበረ ይላል፤ ስሕተት ነው ርጊ ውስተ ጽቡር ወአጽብሪ በሐሠር ፡ (ናሆ፫ ፲፬)
  በግድ ማሠራት፤ ረግጦ መግዛት አልቦ ዘይጸብር ጽቡረ ዘእንበለ ያእምር አባስ ፡ (ሥር ጳኵ)
ጸቢብ (ባን ባት) የጠበበ ጠባብ። መካን ጸቢብ ማዕምቅ ጸቢብ። ጸቢበ እንግድዓ (ዘኍ፳፪ ፡ ፳፮ ሔኖ። መጽ ፡ ምስ)
ጸቢብ ቦት (ጸበ ጸበበ ይጸብብ ይጽብብ ዐረ ፀበ፤ ጠበቀ) መጥበብ ማነስ ታናሽ ጠባብ መኾን የቦታ ይጸብበነ ብሔር ወትጸብቢዮሙ እለ ይነብሩ ውስቴትኪ። ዘሰማይ ኢያገምሮ፤ ኢጸበቦ ማሕፀነ ድንግል። ወቦ ቅንዋት አርድእት እለ ተመይጡ እምእሉ ካልከ ማኅደር ጸበበነ እንዘ ይብሉ (ኢሳ፵፱ ፲፱ና ፡ ተረ ፡ ር፲፰ ቅኔ። ፬ነገ ፮ ፡ )
  መጭነቅ መቸገር፤ ጭንቅ መኾን። ሶበ ጸበበቶ ብር ፡ (ስንክ መስ፫)
ጸቢት ቶት (ጸበተ ይጸብት ይጽብት። ዕብ ጻባት፤ ጠግዐ ብረ) መዋኘት፤ በባሕር ላይ መስፈፍ መንካፈፍ፤ መሳብ መጐተት፤ ጸበየን ተመልከት። እለ የአምሩ ጸቢተ ወኮነ ጽኑዐ በተጽዕኖ ፍራስ ወጸቢተ ማይ ይፈቅድ ኅሊናየ ይጽብት ዕመቀ ብሕርቲሁ ቀላይ ውእቱ ዘኢይጸብትዎ ዓሣት። ወዐልኩ እንዘ ጸብት ውስተ ዕመቀ ባሕር። ባሕረ መጻሕፍት ጸበተ ሳኑ ቃውሞቶ መዋግድ ስእኑ ፡ (ግብ፳፯ ፵፫። ስንክ ፡ ሐም፲፭ ቅዳ ሕር፤ ኤጲ ፪ቆሮ ፡ ፲፩ ፳፭ ስንክ ፡ ጥቅ፲፯)
ጸቢእ ኦት (ጸብአ ይጸብእ ይጽባእ። ጻባእ) አሽከር ወታደር መኾን፤ መፋነን፤ በፈቃድ ወይም በግድ መዝመት፤ ተሰብስቦ ወደ ጦርነት መኼድ፤ ጠብ ማንሣት ማጫር ፊት ለፊት መግጠም፤ መውጋት፤ መዋጋት፤ ማሸነፍ፤ ማጥፋት፤ መግደል መሰየፍ፤ መስለብ መግፈፍ መማረክ መዝረፍ። ሰበከ ሳኦል ለኵሉ ሕዝብ ከመ ይጽብኡ ወይረዱ ውስተ ቄዐላ ወፅኡ ሕዝብከ ጸቢአ ዓይነ ፀሮሙ። ይሑር ይጽብኦ ካልእ ንጉሥ (፩ነገ ፳፫ ፰። ፪ዜና ፮ ፡ ፴፬። ሉቃ፲፬ ፴፩)
መስፈር መከተም ሰፈር ተማ ማድረግ ሀገር እንተ ጸብኣ ዳዊት (ኢሳ፳፱  )
ጸቢዕ ዖት (ጸብዐ ይጸብዕ ይጽባዕ ዕብ ብዕ፤ ጠምዐ) መጣት ጣትን ማንሣት፤ መቀሰር፤ ቅትርት ማስመሰል፤ በጣት መያዝ መንካት፤ ማመልከት መጠንቈል፤ መሻኰት። ፈሰሰን ተመልከት።
ጸባኂ (ኂት ኅያን ያት) ወጥ ሠሪ ወጥ ቤት፤ ወጥ አውጭ አሳላፊ፤ ጠቃሽ፤ ጠላቂ
ጸባሒ መጸብሒ የሚገብር፤ ገባሪ ግብር ሰጭ አቅራጭ ኮንዎሙ መጸብሔ። ወረሰዮሙ መጸብሔ (ኢያ፲፬ ፵፰። ነገ ፲ ፡ ፳፪። መሳ፩ ፳፰)
ጸባሕት (ሓት) ግብር ቀረጥ ለመንግሥት የሚገባ ገንዘብ፤ ስጦታ። ወሠርዐ ጸባሕተ ዕሴሆሙ። የሀቡ ጸባሕተ ፈርዖን እለ ጸባሕተ ይነሥኡ እስመ ጾም ጸባሕተ ሥጋ ውእቱ ወጸሎትኒ ጸባሕተ ነፍስ በከመ ምጽዋት ጸባሕተ ንዋይ ፡ (ኩፋ ፡ ፴፬። ፬ነገ ፳፫ ፴፬። ማቴ፲፯ ፳፬ አቡሻ ፴፰። ፲፭)
ጸባብ (ባት) ዝኒ ከማሁ፤ የጠበበች፤ ጠባባ ታናሽ ስመ ጸባብ ፍናዊሁ። ዐዘቅት ጸባብ። ባሕር ጸባብ። ባኡ እን ጸባብ አንቀጽ ፡ (ዮዲ፬ ፯። ምሳ፳፫ ፯። ዘካ፲ ፡ ፲፩ ማቴ፯ ፲፫)
ጸባቲ የሚዋኝ ዋነተኛ። የዕጨጌ ሹም ምስለኔው፤ እንደ ራሴው
ጸባኢ (ኢት እያን ያት) የሚዘምት፤ የሚዋጋ፤ ዘማች፤ ጠበኛ፤ ሐርበኛ። ቃልከ መዋኢ ወጸባኢ ሰብእ ጸባእያን (ጥበ፲፰ ፲፭ ኤር፵፭ )
ጸባኢት (ኢት እያን ያት) የሚዘምት፤ የሚዋጋ፤ ዘማች፤ ጠበኛ፤ ሐርበኛ። ቃልከ መዋኢ ወጸባኢ ሰብእ ጸባእያን (ጥበ፲፰ ፲፭ ኤር፵፭ )
ጸባኦት (ዕብ ጽባኦት፤ ጺብአት። ጽር ሣባዖት) ዝኒ ከማሁ፤ ሰራዊት። እግዚአብሔር ጸባኦት ፡ (ኢሳ፩ ፳፬ ፲፩ ፭ ፡ ፱። ፮ ፡ ) ባለብሉዮች ግን እግዚአ ጸባኦት ስላላለ ለእግዚ ስምና ቅጽል አድርገው አሸናፊ ብለው ይፈቱታል፤ የተሳሳተ ነው፤ ገዝአን ተመልከት በሥጋዌሁ ለጸባኦት ፡ (አርጋ )
ጸብሀ ጠለቀጸቢኅ ጸብኀ
ጸብኅ (ኃት) ወጥ፤ የተቀቀለ የበሰለ ጸብኀ ብርስን ተብሲለ ወጸብኀ ኢይብላዕ ጸብኀ ኅብስተ ይቡሰ ወጼወ በልዐት ምንተኒ ጸብኀ ዘአብሰልዎ በእሳት ፡ (ኩፋ ፡ ፴፯። ገድ ተክ ቄድር ስንክ ፡ ጥቅ፩)
(ጥብ)         ጸብሖ ሖት (ጸብሐ ይጼብሕ ይጸብሕ) መገበር ማቅረጥ ግብር ቀረጥ መስጠት ኰነኑ ቄሌ ዘሶርያ ወጸብሑ ሎሙ። ዘሂ ጸባሕተ ጸብሑ ከመ  ይጸብሑ ያዕቆብ ፡ (፩ዕዝ ፳፯ ሮሜ፲፫ ፯። ኩፋ ፡ ፴፰) በጸብሐ ፈንታ አጽብሐ ይላል፤ የተሳሳተ ነው። ለእመ አጽባሕክሙ ጸባሕተ ፡ (መቃ ገ፯)
ጸብሰ ደከመ ላላፀቢስ ፀብሰ
ጸብረቀ (በረጸ፤ በረቀ) ከበረጸ ወጥቶ በበረቀ ላይ ተደርቧል፤ ዘሩ በሪቅ ነው የበሪጽንና የበሪቅን ፍች ተመልከት
ጸብር [1]ጭቃ፤ ዐዛባ። ጸብረ ግንፋል። ተኀፂባ ገብአት ዲበ ጸብር ፡ (አዋል። ፪ጴጥ ፡ ፳፪) ጸብር ባለው ጺላ ጺላሃ ይላል፤ የጣፊ ስሕተት ነው
[2](ትግሬ ወዐረብ) ፌት፤ ትዕግሥት።
ጸብት ዋና፤ ውስወሳ፤ የውሃ ላይ መንገድ አካኼድ ንዋየ ሐቅል።
ጸብኣት (አጽባእ እት ኣት) ጠቦች ሰልፎች፤ ጦርነቶች ብዙኀ ደመ ከዐውከ ወዐበይተ ጸብኣተ ገብርከ በእንተ ጽባእ ዘዐውዱ። የኀድጉ አጽባኢሆሙ። አጽባእት ወድምፀ ጸባኢት ጽባእት ብዙኅ ፡ (፩ዜና ፡ ፳፪ ፡ ፰። ነገ ፭ ፡ ሱቱ ዕዝ፲፫ ፴፰። ማር፲፫ ፯። አፈ ተ፳፯)
ጸብእ ጠብ፤ ጥል፤ ሰልፍ፤ ዘመቻ፤ ውጊት ጦርነት፤ አንባ ጓሮ፤ ክርክር፤ ሙግት። ዘይገብር ጸብአ በዕለተ ሰንበት። በእንተ ዛቲ ጸብእ። ወታቀንተኒ ኀይለ በጸብእ። መድምም አንተ በኵሉ ጸብእከ። ክብረ ሆሳዕና ገር ለእ ተወጥነ ንሥአት ጸብአ ምስለ ሰሎሜ ድግት እንዘ ትብል ኢይኅድር ውስተ ልብኪ ትምክሕት ምጣነ ውእቱ ሀብትኪ ስደት፤ ወእመ ተሐዝሊ ሆሳዕና አዕቀጹኪ አእባን ወዐገቱኪ ፈያት ሊተሰ እመ ሐዘልኩ ሆሳዕና ኵሉ ፍጥረት በስብሐት ተቀበሉኒ አእሩግ ወሕፃናት፤ ወተንሥኡ ሊተ አእባነ ርሑቅ ፍኖት፤ እንዘ ይብሉ ሆሳዕና መጽአ በስብሐት ፡ (ኩፋ ፡ ፶። ኢሳ፳፯ ፬። መዝ ፡ ፲፯ ዮዲ፲፩ ፰። ቅኔ)
ጸብይ ዮት (ጸበየ ይጸቢ ይጽቢ ጾበ ጸወበ ተጸውበ) መፍሰስ፤ መውረድ መንዣረር፤ የወተት የቅባት። እስከ ተበጽለ ሥጋሁ መለያልዪሁ ወአንጕዑ ይጸቢ እምአዕፅምቲሁ ፡ (ስንክ ፡ መጋ ፡ ፲፯) ጸወበንና ጸበተን ተመልከት የዚህ መንቲያ ነው።
  መዋኘት፤ መስፈፍ፤ በባሕር ላይ፤ መኼ፤ እየተሳቡ እየወሰወሱ ላይ ላዩን ማለፍ፤ መንካፈፍ። ውእቱ መስቀር ይጸቢ ዲበ ማይ (ሔኖ፹፱ )
ጸቲም ሞት (ጸተመ ይጸትም ይጽትም። ጻመተ ) መግጨት፤ ማጋጨት፤ መስበር ማድቀቅ፤ መቀጥቀጥ መሰንጋት ማሸት፤ ማኰላሸት። ጸተሞ ያዕቆብ ለጣዖተ ራሔል ፡ (መጽ ምስ ኩፋ ፡ ፴፩)
  ማጥመም፤ ማግደድ፤ ገዳዳ ወልጋዳ መኾን ማድረግ፤ የጠባይ የመልክ።
ጸታም ጥመት፤ ጠማምነት፤ ውልግድግድነት። የኀድግኑ ዘይት ጸታሞ ፡ (ኤር፲፫ ፳፫) ዕብራይስጥና ጽርእ ዐረብ ሳይቀር፤ ይዌልጥኑ ፡ (ኢትዮጵያዊ) ኵሻዊ ማእሶ ያሉትን፤ የግእዝ መላሽ ዘይት፤ ጸታም ብሎ አለስሙ አለዘይቤው ተርጕሞታል።
ጸኒሕ ሖት (ጸንሐ ይጸንሕ ይጽናሕ። ዕብ ጻናሕ፤ ጸነ ወድቀ ቃዌህ ) ደጅ መጥናት፤ መቈየት መጠበቅ መታገሥ ተስፋ ማድረግ፤ ማድባት ማሸመቅ፤ ማድፈጥ፤ መዘጋጀት፤ የክፉ ጸኒሐ ጸናሕክዎ ለእግዚ መንግሥትከ ይጸንሐከ ዐይነ ዘማዊ ይጸንሕ ጽልመተ አስከ እትመየጥ መንገሌከ ጽንሐኒ ጸኒሐ፤ ስመ ድኅረ ሞቱ ሰብእ አልቦቱ ስሓ። ጽንሕዋ ምሕረቱ። ጽናሕ ፍሬሃ ቡሩከ ይጸንሕ ወይትኀባእ ከመ አንበሳ። ይጸንሕ መሠፍት ለእኩያን ፡ (መዝ ፡ ፴፱። ዳን፬ ፳፫ ኢዮ፳፬ ፲፭ ደራሲ ሢራ፪ ፯። ፮ ፡ ፲፱ መዝ ፡ )
ጸኒን ኖት (ጸነ ይጸንን ይጽንን ደነነ ዕብ ጻናን ቈረ) መጽነን፤ መጐንበስ መዘንበል፤ ማድላት ማጋደል፤ ማርገዝ ማዘብዘብ፤ የካብ የግንብ። ኀይለ ሃይማኖት ዘኢይጸንን። ወኅሊና ንጹሐ ዘኢይጸንን ጸግወነ ሶበ ርእየ ከመ ጸነ ትጽንኑ መንገለ ፍኖተ ሕገጋት ፍኣዊት። ለእመ ጸነ ረፍት መንገለ ፍኖት ፡ (ኪዳ ስንክ መስ፫ መ ፡ ፲፰ ፩። ፴፯) ጸንጸነን ተመልከት፤ የዚህ ዲቃላ ነው በጸነ ፈንታ አጽነነ ይላል፤ ስሕተት ነው። አጽነነት ታቦት። ታጸንን ምድር ፡ (፩ዜና ፡ ፲፫ ፱። ኢሳ፳፬ )
ጸኒዕ ዖት (ጸንዐ ይጸንዕ ይጽናዕ ዕብ ጻናዕ ታገሠ) መጥናት፤ መጠንክር፤ መበርታት ማየል መድረቅ መክረር፤ ጸንቶ መኖር ቀዋሚ መኾን ጸንዐ ልቡ ወጸንዓ እገሪሁ ወሐቌሁ ጸንዐ ዕሌሆሙ ቀትል። ትጸንዕ ምኰኵሕ ሀገር ትጸንዕ በጥበቢሆሙ ለሊቃውንት ይጸንዕ ቃሉ (ዘፀ፯ ፲፫ ግብ፫ ፯። ኢሳ፵፪ ፳፭ ሕዝ፫ ፱። ፵፩ ፡ )
ጸኒፍ ፎት (ጸንፈ ይጸንፍ ይጽነፍ። ዕብ ጻናፍ) ማልበስ ማጐናጠፍ፤ ማጠፍ፤ ጫፍና ጫፉ መግጠም፤ ወይም መጠምጠም፤ መጠቅለል፤ የልብስ የፈትል። ዳርቻ መኾን፤ ወደ ዳር መውጣት፤ ዳር ዳር ማለት
ጸናሒ (ሒት ሕያን ያት) ደጀ ጠባቂ ሸማቂ። ጸናሒ ወመስተዐግሥ። ጸናሕያነ ተስፋ ክቡር። ጸናሕያነ ፍኖት ፡ (ጥበ ፡ ስንክ ፡ የካ፳፰ ዮሴፍ። ምሳ፲፱ ፳፱)
ጸናኒ (ኒት ንያን ያት) የሚጸን የሚጠም፤ ጠማማ አድላዊ።
ጸናዒ (ዒት ዕያን ያት፤ ዕት) ጽናዒ፤ የሚያጠና፤ የሚያበረታ፤ አይዞኽ ባይ፤ ኀያል ርበኛ፤ የጦር አለቃ ምስለ ሠለስቱ ጸናዕት ዕደው ጸናዕት ፡ (፩ዜና ፲፩ ፲፪ ፳፩ ) ጽኑዓን ኀያላን በማለት ፈንታ ጸናዕት ይላል፤ አያሰኝም ህጉር ጸናዕት። ኵሎ ሰራዊተ ጸናዕተ ፡ (፪ዜና ፰ ፡ ፬። ዜና ፲፱ )
ጸናጺት ዝኒ ከማሁ፤ ዝንብ፤ የዝንብ ገን፤ ትንኝ ዐኮት፤ ተቈናጣጭ ፍጥረት። ጻጹትንና ኮትን ተመልከት ይስሕቦ እግ ጸናጺት ወለንህብኒ (ኢሳ፯ ፲፰። ዘፀ፰ ፲፯፳፯) በጸናጺት ፈንታ ጻጹት ይላል፤ ፍችው ነው ብቻ ታናሽነትን ያሳያል
ጸናፊ (ፊት ፍያን ያት) የሚጸንፍ ዳርቻ የሚኾን፤ ጽንፋይ አፍኣዊ፤ ዘአፍኣ። ዐጸድ ጸናፊ። ጸናፌ ጽልመት። ጸናፊት ደብተራ ፡ (ራእ፲፩ ማቴ፰ ፲፪ ዕብ፱ )
ጸንሕሐ (ተቀ ) ጤሰ ነደደ ተቃጠለ ሸተተ፤ መሥዋዕት ኾነ። በጸንሕሐ ፈንታ ተጸንሕሐ ይላል አያሰኝም፤ የጸንሐ ቅጥይ ነው (አርጋ)
ጸንሰ ፀነሰ አረገዘፀኒስ ፀንሰ
(ጥን)          ጸንሶ ሶት (ጸነሰ ይጼንስ ይጸንስ) መቸገር ማጣት መደኽየት፤ አይቶ ዐጣ ችጋረኛ መኾን መዋረድ መመስከን። ዘሩና ምስጢሩ የፀንሰ ነው ፅንስ እያደገና እየጠና እንዲኼድ የችግሩን ጽናት ያሳያል። መጽሐፍ ግን በጸነሰ ፈንታ ተጸነሰ ይላል ያማርኛ ነው የጸነሰ ፍች ተቸገረ ማለት ስለ ኾነ  ጸሓፊና መላሽ አላገባቡ ጥፈውታል። እምከመ ተጸነሰ ልእከ ይጼነሱ ክለ ወማየ። እምይእዜሰ ኢይጼነስ ንከ (ዘሌ፳፭ ፴፱። ሕዝ፬ ፲፯ ሢራ፲፩ ፳፬)
ጸንቀቀ (ጠንቀቀ) ነከረ፤ ዘፈቀ፤ አጨቀየ አጨማለቀ፤ ለወሰ በከለ ፈጽሞ አሳደፈ፤ አኵለፈለፈ። ዘብሑ ዳቤላ ጠሊ ወጸንቀቁ ልብሶ ዮሴፍ በደም ፡ (ኩፋ ፴፬። ዘፍ፴፯ ፴፩) ዘሩ ጠንቀቀ ነው ለጸ ተለውጧል፤ ምስጢሩም ፈጽሞ ጠንቅቆ ያሰኛል። ጽንጕን ማለት ከዚህ ወጥቷል ቀና በብዙ ቦታ ይወራረሳሉ ጸና እንዲወራረሱ።
ጸንአ ጠና በረታጸኒዕ ጸንዐ
() ጸንዖ ዖት (ጸንዐ ይጼንዕ ይጸንዕ) አጽንዖ ማጥናት ማበርታት ማጠንከር ማደስ መጠገን። ጸንዖሙ ለአኀዊከ ወአስተርአዮ መልአከ ዘይጼንዖ። ዘይጼንዑ መፍቅደ ብሔር በዘይጼንዑ ቤደቀ (ሉቃ፳፪ ፡  ፴፪ና ፡  ፵፫። ራ፴፰  ፴፬። ነገ  ፪ ፡  )
ጸንገፈ ጨነገፈ ጣለ አሶረደ።
ጸንጰወ (ጸነፈ፤ ጸንፈወ) ጨቈነ ደፈጠጠ፤ መታ ቀጠቀጠ፤ አጦዘ ጠመዘዘ ከልብስ ዕጥበትና ዘፈረ ልብስን ከማክረር ከመፍተል ከመቋጨት የመጣ ቃል ነው፤ ጸነፈን ተመልከት። ምንእሱ አጸንጵዎ አዕፅምተ ገበዋቲሁ። ወያጸንጵዉኒ አዕፅምትየ (ሢራ፴ ፲፪ መዝ ፡ ፵፩)
ጸንጶላዕት የእሳት እራት። ወከመ ጸንጶላዕት ትወድቁ ማእከለ እሳት ፡ (ድር ሰን)
ጸንጸነ (ጸኒን ጸነ) ጠነጠነ ነቀዘ፤ አረጀ ተበላሸ፤ ከንቱ ኾነ
ጸንጸል ( ጸናጽል ላት) ሻኵራ ቃጭል፤ በቁሙ ጸናጽል ወገብሩ ጸናጽለ ዘወርቅ ርባዕተ ምእተ ጸናጽለ ጸናጽላተ ብሩር። እለኒ በጸናጽል ወእለኒ በከበሮ ጸናጽል ዘሠናይ ቃሉ (ዘፀ፴፮ ፴፩። ፪ዜና ፡ ፬ ፡ ፲፫ መጽ ፡ ምስ ዜና ፲፫ መዝ ፡ ፻፶)
ጸንጻሊ የሚያቃጭል የሚያንሿሿ ደዋይ አቃጫይ ፡ (አርጋ )
ጸንጽሎ ሎት (ጸንጸለ ይጸነጽል ይጸንጽል። ዕብ ጻልጼል) መጸንጸል መምታት ማንሿሿት መደወል ማቃጨል ማቅጨልጨል የማዕደን ዘሩ ነጸለ ነው
ጸንፈርት ወፈንጠርፀንፈርት
ጸአለ ሰደበ፤ጽዒል ጸዐለ።
ጸዐመ ጮኸ፤ጽኢም ጸአመ
ጸአነ ጽዒን ጸዐነ።
ጸዐዳ (ዓድው) ነጭ፤ ጥሩ። እኁየሰ ጸዐዳ ወቀይሕ። ልብሱ ጸዐዳ ከመ በረድ። ዘጸዐዳ ጸጕሩ ፍራስ ጸዓድው ልባስ ጸዓድው ክሊላት ጸዓድው ፡ (ማሕ፭ ፲። ዳን፯ ፱። ዘፍ፴ ዘካ፩ ፰። ራእ፬ ፬። አርጋ)
ጸዐድዒድ (ድት ዳን ዳት) ፍጹም ነጭ፤ ነጫነጭ፤ ጸዐዳዊ ወደ ነጭነት የሚያደላ ናርዶስ ዘጸገየ በጸዐድዒድ ጽጌያት ሥነክሙ ጸዐድዒደ እግዚ ይርአይ እምሰማይ ወረደ። ሕብራት ጸዐድዒዳን ፡ (አርጋ ፡ ስንክ ፡ መስ፳፰። ፈላስ)
ጸአጠ ቀመመ አጣፈጠ፤ጽዒጥ ጸዐጠ።
ጸዓሊ (ሊት ልያን ያት) የሚጥል ጣይ፤ የሚሰድብ፤ ሰዳቢ ተሳዳቢ፤ ስድብ ዐዋቂ ቡይ ወጸዓሊ ብእሲት ጸዓሊት። ብያተ ጸዓልያን ያንኅል እግዚ ፡ (ሢራ፳፫ ምሳ፲፭ ፳፭ ፳፭ ፳፬) ጸዓሊና ፀሓይ ባማርኛ ይተባበራሉ። ፡ (ግጥም) መሸ መሰለኝ ሊጨልም፤ እንደ ቀን ጣይ የለም።
ጸዓኒ (ኒት ንያን ያት፤ ዐንት) የሚጭን፤ የሚያሸክም፤ ጫኝ አሸካሚ።
ጸዓዕ ብልጭታ፤ፀዓዕ
ጸዓዲ (ዲት ድያን ያት) የሚኼድ የሚጥድ ጣጅ። (ተረት) የቤት ጣጅ የዱር ጠማጅ
ጸዓጢ የሚቀምም፤ የሚያጣፍጥ አጣፋጭ ሽቱ ሸያጭ
ጸክ ጸኵ ጸኵ፤ ( ጸኳት) ጭን ሹልዳ፤ ታፋ ነደፍዎ በሐጽ ጸኮ። እግዚአብሔር ተጋደሎ ወአስዖዘዘ ጸኮ ወሰመዮ እስራኤል ወበ እን ኢይበልዑ አይሁድ ሥርዋተ ጸኵ (፩ነገ ፴፩ ፡ ፫። ዮሴፍ። ስንክ ፡ ነሐ፳፰) ባለብሉዮች ግን ትከሻ ይሉታል ጋላም ነቡኤ ይላል ትከሻ ወረደኝ ሲል፤ ጨኩና ጫንቃ ይመሳሰላሉ አንድ ወገን ናቸው ቍጽን ተመልከት።
ጸወሰ ለመሸ፤ፆሰ ፀወሰ
ጸወን (ናት) ጥግ፤ መጠጊያ፤ አንባ ዕርድ ምሽግ፤ ገዳም አልቦ ጸወን ትጸወን ፍሬም። ተሰብረ ጸወንክሙ። አረፍተ ጸወንከ ሀገረ ጸወናት ፡ (ኢሳ፲፯ ፫። ፳፫ ፲፭ ፳፭ ፲፪። ፪ዜና ፡ ) ጽዮንን ተመልከት፤ ከዚህ ጋራ አንድ ነው
ጸዊም ሞት (ጾመ ይጸውም ይጹም ዕብ ጻም ሱር ጻም ዐረ ጻመ) መጾም፤ ጥሉላትን ፈጽሞ መተው፤ ሰውነትን ከመብል ከመጠጥ ሌላውም ኹሉ ከክፉ ነገር መከልከል መጠበቅ ቦኑ ጾመ ዘጾምክሙ ሊተ ጾምሰ ጸዊም ምኅብስት ወማይ ባሕቲቱ ይጹም ልሳንክሙ እምነገረ ውዴት። ለእመ ኮንከ ዘኢትክል ትጹም መባልዕት ጹም እንከ ምኅሊናት እኪት ፡ (ዘካ፯ ፭። ፫። ስንክ ታኅ፲፫ ፊልክ ፡ ፪፻፵)
ጸዊር ሮት (ጾረ ይጸውር ይጹር ዕብ ጻዬር ሳበጐተተ) መሸከም አንሥቶ መያዝ፤ መውሰድ ማንገት፤ ማንጠልጠል፤ ማቀፍ፤ ማዘል፤ መፅነስ ማርገዝ በሆድ መቋጠር፤ ማገዝ መርዳት መደገፍ መጦር፤ መታገሥ መቻል፤ መወሰን ማግመር ይኄይስ ትጹር ኆጻ ወጼ ሥአ ደዌነ ወጾረ ሕማመነ እስእለከ ከመ ትጹረነ ዘጾሮ ወዘዐነቆ በክሣዱ ጾሮ በሥዕርተ ርእሱ ወአብጽሖ። ጾሮሙ በእንግድዓሁ። ጾርኪዮ በከርሥኪ። ጹር ርሥኣኒሁ ለአቡከ ትክል ጸዊሮቶሙ ለእኩያን። ኢትክሉ ጸዊሮቶ ይእዜ (ሢራ፳፪ ፡ ፲፭ ኢሳ፶፫ ፬። ስንክ ፡ ነሐ፴ ልፋ ፡ ጽድ ዳን፲፫ ፴፭። ዘዳ፴፪ ፲፩ ኤፍ ፡ ፮። ራ፫ ፲፪። ራእ፪ ፡ ፪። ዮሐ፲፮ ፲፪)
ጸዊብ ቦት (ጾበ ጸወበ ይጸውብ ይጹብ ጸበየ አጽበየ) ማፍሰስ መገልበጥ፤ ማንቀር መጨለጥ ባዶ ደረቅ ማድረግ። ትሰትዪዮ ወትጸውቢዮ ፡ (ሕዝ፳፫ ፴፬)
ጸዊት ቶት (ጾተ ጸወተ ይጸውት ይጹት። ዕብ ጾቴት) መጮኽ መልፈፍ መንገር ማስታወቅ፤ ያዋጅ የትእዛዝ። መማለድ አቤት አቤት ማለት፤ የልመና። መሣቅ መጫወት፤ መንጫጫት፤ የብዙ ሰው መሰደር፤ መደርደር በተራ ማኖር መናገር። ፡ (ተረት) ነገር በተርታ፤ ሥጋ በገበታ
ጸዋሚ (ሚት ምያን ያት) የሚጦም ጧሚ፤ ጠመኛ ፡ ( ነ ፡ ፲፭ አቡሻ ፡ ፴፰)
ጸዋሪ (ሪት ርያን ያት፤ ወርት) የሚጦር ጧሪ ዋሪ የሚሸከም፤ ተሸካሚ፤ ያዥ ወሳጅ፤ አምጭ ታጋሽ። ጸወርተ ወላትው ጸዋሬ ንዋየ ሐቅሉ ለኢዮአብ። ጸዋሬ ክታብ። ጸዋሬ ዜና። ለውንትዮስ ጸዋሬ መቅሠፍት ፡ (አርጋ ፫። ዜና ፲፱ ፡ ፴፱። አዋል ደራሲ። ስንክ ፡ ኔ፩)
()            ጸዋር ዝኒ ከማሁ፤ ገባር፤ ተገዥ፤ ዜጋ ኮነት ጸዋረ (ሰቈ፩ )
ጸዋዒ የሚጠራ ጠሪ ለፋፊ ዐዋጅ ነጋሪ ጳውሎስ ጸዋዒ። እኩን ጸዋዔ ሰብእ ውስተ ምልኮትከ ፡ (ቅዳ። ዮሴፍ)
ጸውብ (ባት) እድፍ፤ እንቃሪ፤ እዝኅ፤ መግል ወትሰቀይ ምድር እምነ ጸውብከ (ሕዝ፴፫ ፮። ኢዮ፯ )
ጸውት ( ጸዋት፤ አጽዋት) ጩኸት፤ ልመና፤ ምልጃ፤ጸሎት፤ መስተብቍዕ ወትብል ጸዋተ ሠለስቱ ጸዋት በእንተ እለ ይነግዱ በእንተ እለ ኖሙ በእንተ ሰላም ወጸሎተ ሃይማኖት ፡ (ግንዘ)
  ዎት፤ ጨዎታ፤ ጫጫታ፤ የብዙ ሰው ድምፅ (ዐማርኛ)
ጸውኖ ኖት (ጸወነ ይጼውን ይጸውን። ዐረ ጻን። ዕብ ጺና፤ ጋሻ) መጠበቅ ማዳን፤ መጋረድ መተገን፤ ማስጠጋት ጥግ ጋሻ መከታ መኾን። ዘበመንፈስ ለአዳም ጸወኖ ወአሕየዎ ፡ (ኪዳ አርጋ ፡ )
ጸውአ ጠራ፤ጸውዖ ጸውዐ።
ጸውዖ ዖት (ጸውዐ ይጼውዕ ይጸውዕ ዕብ ጻዋሕ ሾዋዕ፤ ጮኸ) መጥራት ናልኝ ማለት፤ ስምን ማውጣት እገሌ ብሎ ሐዲስ ስም መስጠት፤ ማውጣት መስየም። ጸውዕዎ ይርድአነ ጸውዖ ኪያሁኒ ውስተ በዓል። ወኵሉ ዘጸውዐ ስመ እግ ይድኅን ወበከመ ጸውዖሙ ከማሁ ኮነ ስሞሙ። ወጸውዐ ስሞ ሮቤል ፡ (ዮዲ፷ ፲፯ ጦቢ፱ ፪። ግብ፪ ፡ ፳፩ ኩፋ ና ፡ ፳፰)
ጸዪሕ ሖት (ጼሐ ይጸይሕ ይጺሕ። ዕብ ጻሕ ጠራ፤ በራ ነጣ) መጥረግ ማስወገድ፤ መደልደል፤ ማስተካከል፤ ማበጀት ማዘጋጀት፤ የመንገድ ጺሑ ፍኖተ ቅድመ ገጹ ጺሑ ፍኖተ ሕዝብ። ኢጼሐ መንገደ ዘይጸይሕ ፍኖተከ (ኢሳ፶፯ ፲፬ ፷፮ ፲። ኤር፲ ፳፫ ማር፩ )
ጸዪእ ኦት (ጼአ ይጸይእ ይጺእ ኣህ ኵስ) መግማት፤ መሽተት መቈነስ መበስበስ፤ እስኪተላ ድረስ። ወፅአን ተመልከት የዚህ መንቲያ ነው። ይጸይእ ተከዚ ጼአ ምድር ወድአ ጼአ ይጸይእ አፉሁ። ጼአ ቍስሊሁ ብእ እምከመ ሞተ ይጸይእ እንዘ ሕያው ትጸይእ ነፍስቱ ፡ (ዘፀ፯ ፲፰ ዮሐ፲፩ ፴፰። ዮሴፍ ኢዮ፲፬ ሢራ፲ ፡ )
ጸያሒ (ሒት ሕያን ያት) የሚጠርግ፤ ጠራጊ። ዮሐንስ ያሔ መብእስ ፡ (ድጓ)
ጸያቂ የሚጤቅ፤ ጤቀኛ መርዘኛ፤ መስተዋድይ፤ ሰብቀኛ፤ አጥፊ፤ ቀጣፊ፤ ተንኰለኛ። እስመ ጸያቂ ውእቱ ከመ አቡሁ ዲያብሉስ ፡ (መቃ ፡ ገ፲፮ ሲኖዶ ዮሐ፰ ፵፬። ዘፍ፫ ፩። ነገ ፳፪ ፲፬፳፪)
ጸያፍ (ፍት ፋን ፋት) በቁሙ፤ አለስልቱ አላገባቡ የተጣፈ የተነገረ ቃል፤ ልታፋ ሲሉት የሚል። ጸያፍ ወላዕላዐ ልሳን አነ። ልሳን ጸያፍ ወአፉየ ሙሴ ለእመ ኮነ ጸያፈ ራቅሊጦስ አሮን ይኩነኒ በሃማን ወጸያፋን (ዘፀ፬ ፮ ፡ ፴። ኢሳ፳፱ ፳፬ ፴፪ ፬። ደራሲ ቀሌ)
ጸይቆ ቆት (ጸየቀ ይጼይቅ ይጸይቅ ዕብ ጻቅ ያጻቅ ወደየ ከዐወ) መጤቅ መበከል፤ ጢቅ ማለት፤ የመርዝ የምራቅ፤ የስድብ የሰብቅ፤ ከባብ ከሰይጣን ከክፉ ሰው አፍ የሚወጣ ፡ (ራእ፲፪ ፡ ፲፭ ኢዮ፩ ፲፩ ፭። መዝ ፵፫ ፡ ፲፮)
ጸይፎ  ፎት (ጸየፈ ይጼይፍ ይጸይፍ) (ጥየ) መጸየፍ፤ ጸያፍ መኾን፤ መባል፤ መነቀፍ፤ መኰላተፍ። የቅኔ የነገር፤ የጥፈት፤ ያንደበት። ማጸየፍ፤ መንቀፍ፤ ጸያፍ መያዝ። ፡ (ጥጸ) መጸየፍ፤ መጥላት።
ጸደና (ናት) ጋዣ፤ ማራም ሣር የበረሓ ንብ፤ ገራም ጭምት የማይናደፍ ማሩና ቤቱ ምድር ውስጥ የሚገኝ ጸጅ ማለት ከዚህ ወጥቷል አንበጣ ወመዓረ ጸደና ተሰሴይከ መዓረ ጸደና ፡ (ድጓ። ማር፩ )
ጸደያዊ ወርኀ ጸደይ፤ መጋቢት በጥንተ ሐመል ዘውእቱ ሪና ጸደያዊ ዘይከውን በዘመነ ተዐርዮ ጸደያዊ ፡ (አቡሻ ፡ ፴፰ና ፶፫)
ጸደይ [1](ዐጸደ) ዐጨዳ ያጨዳ ወራት ዘመነ በልግ፤ በወዲያ መከር በወዲህ በልግ የሚደርስበት፤ የሚታጨድበት፤ ወዲያውም የሚዘራበት ወርኀ ዘርዕ ክፍለ ዓመት፤ ያመት ርቦ ፺፩ ቀን ወይም ወር በሐጋይና በክረምት መካከል ያለ ክፍል ያዘንም ክሙ ጸደየ ወመፀወ። ዝናመ ደይ ወመፀው እግዚ ሠርዐ ደየ ወመፀወ ማእከለ ጸደይ ወዝናም (ዮኤ፪ ፳፫ ዘካ፲ ፲፩ ቀሌ ኩፋ ፡ ፳፱)
[2](ዐረ ጻድ) ስመ ፊደል ዐሥር ወታስዕ መዠመሪያውን ተመልከት
ጸዲል ሎት (ጸደለ ይጸድል ይጽድል። ዕብ ጻሀል) መጽደል መብራት ብርሃን መኾን አስተርአየ ኮከብ ዐቢይ ዘጸዳሉ ብሩህ ጥቀ ወቍድስኒ ይጸድል በውእቱ ኮከብ ከመ ጸዳለ መዓልት በእንተ ምንትኑ ይጸድል ገጽክሙ። ትጸድል ምሥነ ርዮብ ፡ (ዮሴፍ። ርጋ )
ጸዲቅ ቆት (ጸድቀ ይጸድቅ ይጽደቅ። ዕብ ጸዳቅ። ሱር ዳቅ። ዐረ ጸደቀ) መጽደቅ፤ እውነተኛ መኾን፤ መርታት፤ በፍርድ ከሐሰት ከበደል መንጻት መጥራት፤ መብለጥ መሻል ምስለ ጻድቅ ትጸድቅ ከመ  ትጽደቅ በነቢብከ ለእመ ይጸድቅ ጳውሎስ እን ይነግር ይክል መዐትም ወዐማፂ ጸዲቀ ኢይጸድቅ መያሲ እምዐምፆት ጸድቀት ትእማር እምኔየ ፡ (መዝ ፡ ፲፯ና ፡ ፶። ቄር ላ። ሢራ፩ ፳፪ ፳፮ ፳፱ ዘፍ፴ ፳፮)
ጸዲፍ ፎት (ጸድፈ ይጸድፍ ይጽደፍ። ዐረ ጸደፈ፤ ከመንገድ ወጣ) መጽደፍ መውደቅ ገደል መግባት፤ ከባሕር መጥለቅ ከላይ ወደ ታች ተወርውሮ መውረድ መንከባለል። ጸድፈ እምተሥላስ፤ ጸድፉ ውስተ ባሕር። ትጸድፍ ውስተ ሲኦል (ግብ፳ ፬። ማር፭ ፲፫። ኢሳ፲፬ ፲፭)
  መጣደፍ፤ መቀልጠፍ፤ መችኰል ማረበድ የሥራ የመንገድ ፡ (ዐማርኛ)
ጸዳል (ላት) በቁሙ፤ ብርሃን ውጋጋን ብልጭታ ጮራ ረር ምዕዛር፤ የብርሃን ቀርን ዐይን የዐይን ብሌን። ቈባር ይእቲ ወአልባቲ ጸዳል። ወጸዳሉቲ ከመ ብርሃን። ጸዳለ ብረቅ። ጸዳለ ብርሃን። ጸዳለ ስብሐቲሁ። ወይጸልማ እለ ይሬእያ በጸዳል ፡ (ዓሞ፭ ፳። ዕን፫ ፲፩ ጥበ፯ ብ፩ ፫። አፈ ድ፩ መክ፲፪ ) ደመና፤ ቀላይ፤ ሌላውም መልካም የኾነ ጥሩ ነገር ኹሉ ጸዳልና ብርሃን ይባላል መኑ ፈጠሮሙ ለፀሓይ ወለወርኅ ወለከዋክብት ወለጸዳላት ወለብርሃናት ፡ (ሲኖዶ)
ጸድፍ ( አጽዳፍ) ገደል ተራራ የተራራ ዙሪያ። ጕድጓድ ዐዘቅት፤ ዕርድ ምሽግ ራንጕር፤ ወጥ ገብ፤ ጐጣጕጥ፤ ሥርጥ መንገድ ወይከውን ዐቢየ ጸድፈ። ጸድፍ ቢይ ይከልአነ እግዚ ውደቆ ለሰይጣን ውስተ ጸድፈ ገሃነም። እስመ ጸድፍ ብሔሩ ወንቁዕ ምድሩ። ጸድፍ ሞፃእታ። ጽዳፍ ወጐጻጕጽ (ዘካ፲፬ ፬።  ሉቃ፲፮ ፳፮። ፫ ፡ ፩።  ሄርማ ራ ፡ ፳፩ ፴፩። ቅዳ ፡ አት)
ጸጕር (ዐረ ሸጀር ዛፍ) ጠጕ ጭገር፤ ጭራ፤ ጋማ፤ ባ። የገላ የሥጋ ቡቃያ ማለት ነው፤ ሥጋ ላለው ኹሉ ይነገራል፤ ሥዕርትን ተመልከት ጸጕረ ርእስ። ጸጕረ ጽሕምከ ጸጕረ ቀራንብቲሁ ኵሎ በግ ዘጸዐዳ ጸጕሩ ጸጕረ ገመል ጸጕረ ጣዎስ ፡ (ሔኖ ፲፩። ስንክ ፡ ግን፲፫ ዘፍ፴ ፪። ማቴ፫ ፬። መጽ ፡ )
 ፡ ጭረት የዕፀዋት ጭገር ቃጫ ናጫ ዶቢ የመሰለው ኹሉ አባ ጳውሊ ኮነ ይለብስ ልብሰ ዘጸጕረ በቀልት። በዊነ ይለብሱ አልባሰ ጸጕር ዘበቀልት (ስንክ ፡  የካ፪ ግን፲፱)
ጸጐሮ ሮት (ጸጐረ ይጼጕር ይጸጕር) መጠ() ጐር፤ ጠጕ ማውጣት፤ ጠጕራም ጭገራም መኾን።
ጸጊብ  ቦት (ጸግበ ገበ ይጸግብ ይጽገብ። ዘገበ) መጥገብ፤ አብዝቶ መብላት፤ መክተት፤ መባልዕትን እንደ ጥን ኹኖ መዝገብ መሰብሰብ። ዘገበን ተመልከት የዚህ ወንድም ነው ገበ የገንዘብ፤ ጸግበ የምግብ። ትበልዑ ወትጸግቡ ኢትኩን ከመ  ዘኢይጸግብ። ወጸጊቦሙ። ዘካርያስ ጸግበ ስከ ክሣዱ፤ ወአትረፈ ለዮሐንስ ወልዱ ፡ (ዘሌ፳፭ ፲፱ ሢራ፴፬ ፲፯ ዮሐ፮ ፲፪ ቅኔ)
  መሰልቸት፤ መጥላት መሰቀቅ ብላዕ በዐቅም ከመ ትጽገብ ወኢትቂእ አንብብ እንዘ  ኢትጸግብ ከመ ይጽገብከ ወኢይጽላእከ እንተ ጸገበቶ ለምታ (ምሳ፳፭ ፲፮ ማር ይሥ፩ ፱። ራ፳፭ ፲፯። ሕዝ፲፮ ፵፭)
ጸጕጕ ጎት (ጸጐጐ ይጸጕጕ ይጽጕጕ ዕብ ያጻእ) ነጻ መውጣት ወይም ለልጅ መሰጠት፤ ልጅን ተከትሎ መኼድ የባሪያ የሎሌ። ትጸጐጕ በከመ ይጸጐጓ እማት ፡ (ዘፀ፳፩ )
  ቤት ወደ ደጅ፤ ወደ ጕዳይ ወዳደባባይ መውጣት፤ የበሽተኛ የመልክተኛ። መጨገግ፤ ጭጋግ መኾን ጢስ መምሰል
ጸጋ (ጋት) በቁሙ፤ ሀብት፤ መልካም ስጦታ ዕድል ፈንታ ትምርት፤ ስርየት ይቅርታ ብዕል ክብር ሕዋስ ሞገስ የቸርነት ሥራ አለዋጋ የሚሰጥና የሚደረግ ምሉአ ጸጋ ወጽድቅ ወእምተረፈ ዚኣሁ ነሣእነ ኵልነ ጸጋ በዲበ ጸጋ ሰብአ ጸጋ። ኢትንሥአኒ ጸጋየ ዘእንበለ ሙት ረከብኪ ጸጋ ጸጋ ዘነሣእክሙ በጸጋ ሀቡ ወእመ አኮሰ ጸጋ ኢይከውን ጸጋ (ዮሐ፩ ፲፬ና ፡ ፲፮ ዮሴፍ። ኤፍ ፡ ፬። ማቴ፲ ፡ ፰። ሮሜ፲፩ )
  የሃይማኖት ስም፤ ቅባቶች ለተዋሕዶ ባህል ያወጡት የደብረ ሊባኖስ ሊቃውንት፤ በተዋሕዶ ወልድ ዋሕድ የሱስ ዐማኑኤል ፍጹም አምላክና ፍጹም ሰብእ። በቅባት መሲሕ ክርስቶስ ካህንና ንጉሥ፤ ነቢይ ሐዋርያ ዳግማይ አዳም፤ ቀዳሜ ጸጋ በኵረ ልደት ለኵሉ ፍጥረት ብለው በፋሲልና በዮሐንስ ዘመን ኹለት ጊዜ ስለ ረቷቸው ጠላት ይቀባል ጥላት እንደሚሉት የንስጥሮስን በጸጋ ሞክሼ  ለመቅባት ተዋሕዶቹን ጸጎች የጸጋ ልጆች ይሏቸዋል።
ጸጋም ግራ፤ፀጋም፤ ፀጊም ፀገመ
ጸጋዊ (ዊት ውያን ያት) የሚሰጥ ለጋስ ቸር ብእሲ ጸጋዊ ወመሓሪ ጸጋዊ ይድኅርዎ በሥነ ምግባሩ። ይኩኑ ጸጋውያነ። እዴሁ ጸጋዊተ ምጽዋት ፡ (ኩፋ ፡ ፴፯። ራ፴፬ ፳፫ ፩ጢሞ ፡ ፮ ፡ ፲፰ ስንክ ፡ ግን፰)
ጸጋዪ (ዪት ይያን ያት) የሚያብብ ባቢ፤ አበባ የሚሰጥ
ጸግዐ ተጠጋፀጊዕ ግዐ
ጸግዎ ዎት (ጸገወ ይጼጉ ይጸጉ ዕብ ዛካህ ነጽሐ ጸርየ ጸድቀ) መስጠት፤ መለገስ መመጽወት፤ መቸር ማስተማር፤ ይቅር ማለት ስርየት መስጠት፤ የሚበቃ ዋጋ ካሳ ሳይፈልጉ ለዘሞተ ኢትኅድግ ጸግዎ ዘለነፍሱ ይጠውዕ መኑ ሀለዎ ይጸጉ እስመ ሠናየ ጸጋ እጼግወክሙ። ጸግዉኒያ ዛቲ አበሳየ ፡ (ሢራ፯ ፡ ፴፫። ፲፬ ፭። ምሳ፬ ፪ቆሮ ፲፪ ፲፫)
ጸግይ ዮት ፡ (ጸግየ ይጸጊ ይጽገይ አው ጸገየ ይጸጊ ይጽጊ) ማበብ፤ አበባ ማውጣት፤ ማፍራት። ፈረየን ተመልከት፤ የዚህ ዘውግ ነው። የጸገየና የጸገወ ዘራቸው አንድ ነው በወና በየ  ተለያይቷል። ይጸጊ ርካዕ አውያን ጸገዩ መስቀል ጸገየ ጽገዩ ገዳም ወከመ ይጸጊ ጽጌ በውስተ ጠለ ገዳም ጽገዩ (መክ፲፪ ፭። ማሕ፪ ፲፫ ድጓ ሢራ፴፬ ፲፫)
ጸጓር (ራን ራት) ጠጕራም፤ ጭገራም ባለብዙ ጠጕር ገላው ንደንስሳ ጠጕ የመላበት ወኮነ ርኣያሁ ዮሐንስ መጥምቅ ጸጓረ ኵለንታሁ ፡ (ስንክ ፡ ኔ፪። ዘፍ፳፭ ፳፭ ፳፯ ፲፩ ኩፋ ፲፱ ነገ ፩ ፡ ) ጨጓራ አባ ጨጓሬ ማለት ከዚህ የወጣ ነው
ጸጥ (ዐረ ጸህ። ዕብ ሀስ) በቁሙ፤ ዝም ዕክም ማለት፤ ጸጥታ ዝምታ፤ ርጋታ፤ አለድምፅና፤ አለሁከት መኾን። ወጸጥ ይብል እስመ አልቦ ድምፅ ወቃል ፡ (ሱቱ ፡ ዕዝ፮ ፴፱)
  ትእዛዝ አንቀጽ፤ ዝም በል፤ ዕሽ ዕሻ፤ አርምም ተፈፀም፤ ወህዳእ ብሂል
ጸጰ ስመ ፊደል፤ፀጰ
ጸፈረ ታታ፤ጐነጐነ፤ፀፊር ፀፈረ።
ጸፈን ጽፍን (ዐረ ጹፍን) የውሃ ዕቃ የሸክላ የቈርበት፤ ማድጋ ፊቀን፤ ገንቦ መንቀል ርኰት ራዎት፤ ቀርበታ፤ የመሰለው ኹሉ፤ ጻሕብን ተመልከት ጸፈነ ማይ ፡ (፩ነገ ፳፮ ፲፩ ፡ ፲፪)
()            ጸፊሕ (ፋሕት) ካቤላ፤ ገልባጣ፤ ለማጣ ደረታም ዘሩ ጠፊሕ ነው ጠን ስለ ወረሰው ወደዚህ መጥቷል። ዘጸፋሕት እገሪሁ ፡ (ኪዳ)
ጸፊር ሮት (ጸፈረ ይጸፍር ይጽፍር) ማጣፈር እንስሳ ሲወለድ ጥፍሩን በጥፍር መቍረጥ መከርከም፤ ለሰውም ይኾናል። ትላጽያ ርእሳ ወትጸፍራ ፡ (ዘዳ፳፩ ፲፪)
  ጥፍራም መኾን፤ በጥፍር መቧጠጥ፤ መጐፍጨር በቃሪያ ጥፊ መምታት። ምስጢሩ ጥፍሮችን ይሻል፤ አጣፍረው እንዲሉ ጥፊው ብስል ሲኾን ግን የጣቶችን እንደ ጠፍር መኾን ለንጋነትን ያሳያል።
ጸፊቅ ቆት (ጸፈቀ ይጸፍቅ ይጽፍቅ። ዐረ ጸፊቀ ዕብ ሳፋቅ ጠፍሐ) መጽፈቅ፤ ጽፍቅ ማድረግ፤ ማብዛት፤ ማፈግ መቸፈግ። የዘር የተክል የምሕን የዐርብ፤ የመሰለው ኹሉ መጨፈቅ፤ መጀጐል፤ መዝጋት መድፈን፤ መወተፍ መጠቅጠቅ የይሎ የሽምጥ። በጸፈቀ ፈንታ አጽፈቀ ይላል፤ ጸፈቀን ሐውልት አድርጎ። እለ ያጸፍቁ ንስሓ ፡ (ሄርማ)
ጸፊን ኖት (ጸፈነ ይጸፍን ይጽፍን ዐረ ጸፈን ዕብ ጻፋን) ማፈን መጨፈን፤ መዝጋት መድፈን፤ ድዳ ደንቈሮ ዕውር ማድረግ፤ የጋኔን። መሰወር መደበቅ፤ መክተት ማኖር ለመጠበቅ። መጽሐፍ ግን በጸፈነ ፈንታ አጽፈነ ይላል፤ ባስደራጊ። ወቦ ዘአጽፈኑ ወቦ ለዘወርኃዌ ረሰይዎ ፡ (መጽ ምስ)
ጸፊዕ ዖት ፡ (ጸፍዐ ይጸፍዕ ይጽፋዕ ጠፍሐ) መጽፋት፤ በጥፊ መምታት፤ መጠፍጠፍ፤ ማጮል የከበሮ የፊት ያዛባ የበት፤ ፀፍዕን እይ፤ ከዚህ የወጣ ነው ይመይጥ መልታሕቶ ለዘጸፍዖ። ከመ ዘይጸፍዕዎ ለብእሲ መልታሕቶ። ወይጸፍዕዎ ገጾ። ዘጸፍዐ ገጾ ዲበ ምዉት እስከ የሐብጥ ሥጋሁ ወይቈስል አዘዘ ይጽፍዕዖዎ አፉሁ (ሰቈ፫ ፳፱ ሆሴ፲፩ ፬። ማር፲፬  ፷፭። ቄድር። ግብ፳፫ ) በጸፍዐ ፈንታ አጽፍዐ ይላል፤ የጣፊ ስሕተት ነው ናጸፍዖ (ስንክ ፡ መስ፲፰)
ጸፍዕ እበት በትፀፍዕ። ሊጣፍ የሚገባው በዚህ ነበረ ስለ ልማዱ ወደ ፀጳ ኺዷል
ጸፍጸፈ (ዕብ ጹፍ ጻፍ ጻፍጼፍ) አፏጨ ወፍኛ ጮኸ፤ ጺፍ ጺፍ ጭው ጭው አለ ፈሰሰ ወረደ፤ ተንጠፈጠፈ።
ጸፍጸፍ በቁሙ፤ ጥፍጣፍ፤ የደንጊያ ንጣፍ ልባጥ፤ ነጣፋ ፍጣፋ ጡብ ደንጊያ ሊቶስጥሮስ ዘውእቱ ጸፍጸፍ። አዘዘ ይኅፀቡ ጸፍጸፎ በማይ። ወጥቀ ሠናይ ጸፍጸፉ። ሰሌዳ በረድ ፍጸፈ ዐውዱ ፡ (፪ዜና ፡ ፯ ፡ ፫። ዮሴፍ አስቴ፩ ፮። ቅዳ ኤጲ)
ጸፍጽፎ  ፎት (ጸፍጸፈ ይጸፈጽፍ ይጸፍጽፍ። ነጺፍ ነጸፈ) መጸፍጸፍ፤ ደንጊያን ወይም ሌላውን ምድር ላይ ማንጠፍ መለጠፍ ምድርን በጠፍጣፋ ድንጋይ መምረግ መለበጥ፤ መሸፈን ማስጌጥ፤ በዝናብ ጊዜ ጭቃ እንዳይኾን፤ ዐፈሩን ጐርፍ እንዳይወስደው፤ ውሃው ወደ ዐዘቅት እንዲገባ ወጸፍጸፉ ኵሎ ምድረ ፈለግ በብርት ፡ (ዮሴፍ ሥር ፡ አኵ)
  መጠፍጠፍ፤ ማጠፍጠፍ፤ ጠፍጣፋ ዝርግ መኾን ማድረግ። መጨፍጨፍ።
ጹረት መሸከም፤ ማሸከም፤ አሸካከም፤ ሸከማ መጦር ጧጧር፤ ጡረታ።
ጺም (ዕብ ጺይይ ይም) የዱር የበረሓ አራዊት፤ በምድረ በዳ የሚኖሩ ጺም ምስለ ም ፡ (ኤር፶ ፴፱) ጺያ ጭው ያለ በረሓ፤ ጺይም በረኸኞች የኢምን ፍች በቦታው ተመልከት። ባለብሉዮች ግን ኢምን ቀኝ ጺምን ግራ የብስ ይሉታል
ጺንው (ዋን ዋት ኑት፤ ንውት) የሸተተ፤ ሽታው የተለወጠ የገማ የበሸቀጠ።
ጺአት መግማት አገማም ግምነት ግማት ዐይነ ምድር እድፍ ርስሐት ዝገት የዐርግ ጺአቱ ይጼኑ ጺአቶሙ መሬት ወሐመድ ወዕፄ ወጺአት። ጺአቱ ወርቅ ይጸሪ ምጺአቱ ፡ (ዮኤ፪ ፡ ፳። ኢሳ፴፬ ፫። መቃ። መዋሥ። ገድ አዳ። ሄርማ)
ጺእ ግማት፤ ክፉ ሽታ። ምሉኣነ ጺእ ወርኵስ ወትዕግልት (መቃ)
ጺኦት መስክ፤ ጨፌዖት።
ጺጽ ( ጻይጽ ዕብራ) አበባ ድብድብ በጣም ያልፈካ ያልፈነዳ፤ ወይም የእሸት ወለባ ገለባ ጥርጣሪ አፒልያኖስ ወሀቦ ውስተ ዴሁ ጺጸ ወይቤሎ ገር ውስተ ገጹ ዝንቱ ነዳይ ፡ (ስንክ ሐም፰)
ጻሕላት (አጽሓል፤ አጽሕል ልት) ሕሎች ጻሕላት ዘብሩር። አጽሕለ ወመዳምሐ። ወአጽሕልት ዕሥራ ወተስዐቱ (ስንክ ሠኔ፲፫ ፀ፴፰ ፲፪። ዕዝ፩ )
ጻሕል (ዕብ ጻላሐት ሱር ጽሊሓ) በቁሙ፤ ወጭት፤ ሳሕን፤ ዝርግ፤ ጠፍጣፋ፤ ክብ ወይም ሞላላ። ለጐድጓዳውም ይነገራል። ሀበኒ በጻሕል ርእሶ ለዮሐንስ እለ ተኀፅቡ ጽዋዐ ወጻሕለ ጻሕለ ዐቢየ ዘወርቅ ንጡፍ (ማቴ፲፬ ፰። ፳፫ ፳፭ና ፡ ፮። ዮሴፍ)
ጻሕስ ሽብሸባ፤ፅሒስ ፀሐሰ።
ጻሕቅ (ቃት) ፈቃድ፤ ሐሳብ፤ ትጋት ጻሕቅክሙ ላዕለ ሰሚዕ ኢይትሀከይ ጻሕቆሙ እለ የኀሥሡ ንስሓ ይሚጥ ጻሕቃተ በአስተዳልዎ ዘይትፈቀድ ጻሕቀ ጽድቅ ፡ (አፈ ድ፬ ዲድ ፮። ፳፬ ፡ ቄር )
ጻሕብ [1]ዝብዘባ፤ ንዝንዝ፤ ጭቅጭቅ፤ ሙግት፤ ድካም፤ መከራ። ተዐቀብ ከመ ኢያብእከ ውስተ ጻሕብ። በኢፈቂደ ጻሕብ ቀብ ኵለነ ዘእንበለ ጻሕብ። አዕረፈ ዮም እምጻሕቡ (ሢራ፳፪ ፲፫ ፳፱ ፯። ቅዳ። ስንክ ፡ ታኅ፱)
[2](ባት፤ አጽሕብት) ሸክላ የሸክላ ቃ፤ ከጣባ እስከ ዋዲያት ከጋን እስከ ምንቸት፤ ከጕልላት እስከ መግላሊት፤ በየስሙና በያይነቱ። ፍችው ደካማ፤ ድኩም ማለት ነው የማስ ፊቀን፤ ርኩት፤ ራዎት፤ የመሰለው ኹሉ። ዝቅንና ኔባልን ተመልከት ጻሕብ ስቁር። ጻሕበ ማይ ወድቀ ጻሕብ። ጻሕብ ዘልሕኵት። ሥአት ክልኤተ አጽሕብተ ወይን ፡ (ሢራ፳፩ ፲፬ ማር፲፬ ፲፫ ኢሳ፴ ፲፬ ሕዝ፬ ፱። ፩ነገ ፳፭ ፲፰)
ጻሕው ትእዛዝ፤ጻው።
ጻሕየየ (ተቀ ) አየ ተመለከተ፤ በመስታዮት፤ በመነጽር ወንሕነሰ ክሡት ገጸ ንጻሐይይ ፡ (ድጓ) በጻሕየየ ፈንታ ተጻሕየየ ይላል፤ ስሕተት ነው ዘኢተጻሕየይከ በመጽሔተ ለኢየሱስ ፡ (መጽ ፡ ምስ)
  ዐረመ፤ አጠራ፤ የፊቱን ጕድፍ የጥርሱን እድፍ የመጽሐፍን ጸያፍ። ነቀለ ቈረጠ፤ ጠቈጠ። ጻሕይይ ክርዳደ። ወንጻሕይይ እምኔሃ አሥዋከ ረሲዓን። እንዘ ትጻሐይዩ እምኔሆሙ ኵሎ ምግባራተ እኩይ ፡ (ኪዳ። ቀሌ)
»ጻሕጻሕ [1] ፡ የቤት ውስጥ ፍሳሽ፤ የጣራ ብጣብ ፍ። ጻሕጻሕ ያወፅ ምቤቱ በመዋዕለ ክረምት ፡ (፳፯ ፲፭) በዚያው በቤቱ ውስጥ ካንዱ ወዳንዱ ማለት፤ መንራጠጥ ስፍራ መለወጥ ነው እንጂ ቤት መውጣት የለም ባለብዮች ግን ጐርፍ ተቅማጥ ሉታል። ፡ (ተረት) እግዜር ሲቈ በዝናም ጊዜ ዐር ያመ
 [2] ፍሳሽ፤ ጠፈጠፍ፤ወጺሕ ወጽሐ
ጻሕፍ (ፋት) ጥፈት ጥር ወዝንቱ ጻሕፍ ቀዳሚ (ሉቃ፪ )
ጻማ (ማት) ጣመን፤ ድካም ሥራ ሥቃይ፤ መከራ ጻማሆሙ ዘእንበለ ባቍዕ ይሴሰዩ ምጻማ እደዊሆሙ የዐርፉ ጻድቃን እምጻማ ኃጥኣን ምግባራቲሁ ወጻማቲሁ ፡ (ጥበ፫ ፡ ፲፩ ስንክ ፡ ጥር፲፯ ሔኖ፶፯ ፫። ፊልክ ፡ )
ጻማዊ [1](ዊት ውያን ያት) የሚደክም፤ ተግቶ የሚጥር የሚሠራ ጻማዊ በገድሉ (ገድ ፡ ክ። ስንክ ፡ ኅዳ፬ መጋ፲፯)
[2](ጻማ ) የድካም፤ ባለድካም ደካማ።
ጻምቶ ቶት (ጻመተ ይጻምት። ዕብ ጻማት፤ አጠፋ) ማለቅ መጣመት፤ ተጨርሶ መጥፋት።
ጻምዎ ዎት (ጸመወ ይጻሙ። ጾመ) መጣመን፤ መድከም፤ መሥራት፤ መጣር መትጋት ለሥራ። ጾመንና ደክመን ተመልከት በከ ጻመውኩ። ባሕቲትየ ዘጻመውኩ ሐምሐም ዘኢጻመውከ ጻሙ ምህሮ ፡ (ኢሳ፵፱ ፬። ራ፳፬ ፴፬። ዮና፬ ፪ጢሞ ፩ ፡ )
ጻባ (ትግሬ) ወተት፤ ርጎ የላም ልጅ (፩ጴጥ )
ጻዕር (ራት) ጣር፤ ጭነቅ፤ ሥቃይ መከራ ደዌ ሕማም፤ የሕማም ስሜት የሞት ዋዜማ ጻዕረ ሞት ጻዕረ ሕማም ጻዕረ ደይን ዛቲ ባይ ጻዕር ወርእያ ፍሬም ለደዌሁ ወለጻዕሩ ፡ (መዝ ፡ ፲፯ ዮሴፍ ፪ጴጥ ፪ ፡ ፬። ሔኖ፳፪ ፲፩ ሆሴ፭ ፲፫)
ጻዕቅ (ቃት) ጭንቅ ጥብ፤ ግፊ፤ ሥቃይ መከራ ብዙኅ ሰብእ ውስተ ሀገር ወኢመካን ዕሩቅ ዘእንበለ ጻዕቀ ሰብእ ጽፉቅ በዕለተ ጻዕቆሙ ወጻሕቦሙ ምንዳቤ ወጻዕቅ። ሐዘናተ ወጻዕቃተ ፡ (ዮሴፍ። ሔኖ፵፰ ፰። ስንክ ፡ ጥቅ፲፪ ማር ይሥ፲፫)
ጻዕደወ (ትግ ጸዕደ) ነጣ ነጭ ኾነ ጠራ በራ ንጣቱ ጥራቱ ልክ ዐለፈ። ወአልባሲሁኒ በረቁ ወጻዕደዉ ጥቀ ከመ በረድ ዘኢይክል መሀፒል አጻዕድዎ ከማሁ። ጻዕደዉ ምበረድ ተኀፅበኒ ወእጻዐዱ እምበረድ። ይጻዐዱ አርእስተ ደቂቅ በሢበት ወለእመ ጻዕደወ ቋዕ ከመ ራዛ ፡ (ማር፱ ፫። ሰቈ፬ ፯። መዝ ፶። ኩፋ ፳፫ና ፡ ፴፯)
ጻዕዳዊ (ዊት ውያን ያት) የሚነጣ የሚጠራ፤ ንጣት ጥራት የሚሰማማው። ቢያጥቡ አይጠራ እንዲሉ።
ጻእጻእ ጭንጋፍፃእፃእ ወፅአ
ጻዕፍ (ዐረ ጸዕፍ) ጕሽ እንቡሽቡሽ ድፍርስ ብጥብጥ፤ ገና ያልፈላ ያልበሰለ መጠጥ ዐዲስ የማር የወይን ጻዕፈ ጸግቡ ወሰክሩ ልቦ ዘይሰቲ ራሜ ወይፈቅድ ጻዕፈ። ወይሰትዩ ደሞሙ ከመ ጻዕፍ ፡ (ግብ፪ ፡ ፲፫ ሉቃ፭ ፴፱። ኢሳ፵፱ ፳፮)
ጻው (ዕብራ) ክፉ ልማድ ትእዛዝ የኢዮርብዓም ሕግ። መጽሐፍ ግን በጻው ፈንታ ጻሕው ይላል፤ የተሳሳተ ነው ባለብሉዮችም የዓሣ ዐጥንት ምስል ጥርኝ ይሉታል አኀዙ ይትልዉ ጻሕወ ፡ (ሆሴ፭ ፲፩)
ጻውር (ዕብ ጻዋር) ንገት ማንገቻ መሸከሚያ ክሣድን ተመልከት።
ጻውዕ (ዓት) (ዓት) አስማት የጥንቈላ ብረት ርተኞች የሚደግሙትና የሚመቱት ሙታንን ሰይጣንን የሚጠሩበት፤ አስጠንቋዮችም የሚያምኑበትና የሚያመልኩት፤ የሚማማሉበት እንደ ሺዋ ጋላ ዘይገብር ስብዐ ወመቅሰመ በጻውዕ እለ ያነቅሁ በጻውዕ እለ በጻውዕ ዘበጻውዕ (ቀሌ ኢሳ፵፬ ፳፭ ፰ ፡ ፲፱ ፲፱ ፡ ፫። ፷፭ ፡ ፲፩ ዘዳ፲፰ ፡ ፲፩)
ጻዴ (ዕብራ) ዝኒ ከማሁ፤ ከመ  ፊደል ጸ። ገቦ፤ ሕፅን፤ ወይም ጻድቅ ማለት ነው ፡ (መዝ ፡ ፻፲፰)
ጻድቅ (ቅት ቃን ቃት) በቁሙ እውንተኛ፤ ቅን፤ መልካም ደግ በጎ ንጹሕ፤ ጥሩ ወዮሴፍሰ ፈኃሪሃ እስመ ጻድቅ ውእቱ ፡ (ማቴ፩ ፲፱)
ጻጹት ታናሽ ዝንብ፤ ትንኝ፤ የዝንብ የትንኝ ጫጩት፤ ዘመሚት ቍጫጭ የዶሮ የወፍ ገላግልት ምስጢሩ ታናሽነት ነው፤ መንጫጫትንም ያሳያል። አሐቲ ጻጹት ነሰከቶ እለ ጻጹተ ትነጥፉ ወእለ ገመለ ትውኅጡ ፡ (ስንክ ፡ ግን፮። ማቴ፳፫ ፳፬) ጸናጺትን ተመልከት።
ጻጼ ብል ትል፤ፃፄ
ጻፍናት [1](ዕብራ) ኅቡኣት፤ ዕሙቃት ረቂቃት ምስጢራተ ራእይ ወሕልም
[2]ፋዕኔሕ ፋዕኔሐ ጻፍናት ከሣቴ ኅቡኣት ብሂል። እስፍንቶፎኔሕን ተመልከት ዚህ ጋራ አንድ ነው
ጻፍጻፋ ጻፍጻፋ፤ የዛፍ ስም፤ እንደ ዘግባና እንደ በቀልት ምጥቀት ርዝመት ቀጥታ ያለው በውሃማ መሬት የሚበቅል። ርጥብ፤ ረግረግ፤ ጐርፋም ጠፈጠፋም ቦታ ፡ (ሕዝ፲፯ )
ጼተሎ (ዕብ ጺታ፤ ጺቲት፤ ዲን ክብሪት) የሚያሰክር መጠጥ፤ ሰውነትን የሚያነድና የሚያቃጥል፤ ርሱም ራሱ የሚቃጠል። ዲናዊ ክብሪታዊ፤ ወይም ዲኖ ክብሪቶ ማለት ነው ባለብሉዮች ግን ጕሽ ጅ፤ የማር ይሉታል ውጻሕከ ሎቱ ወይነ ወጼተሎ ፡ (ሚክ፪ ፲፩ ሆሴ፰ )
ጼና (ናት) ሽታ፤ መዐዛ ረን ጼና ሕሡም ወጽዩእ ወፍጉግ ጥቀ ንኩን ንጹሓነ እምኵሉ ጼና ኀጢአት። ወአልቦ ዕሌሆሙ ዘእሳት። ጼና ተይ ዕፍረት ጥዑም መዐዛሁ (ግንዘ። ቅዳ። ዳን፯ ፳፯ ሔኖ ስንክ የካ፭ መዋሥ)
ጼናታም ጤናዳም፤ የሚሸት፤ ሽታማ፤ ባለሽታ አዛብ ወጼናታም ፡ (ሉቃ፲፩ ፡ )
  ጤናዳምነወ።
ጼናዊ (ዊት ውያን ያት ነውት) የሚሸት፤ የሚገማ፤ ግም ግማታም፤ በሽቃጣ። ጨናዊ እንዲል ፡ (ትግሬ)
ጼንዎ ዎት (ጼነወ ይጼኑ ምዕዘ) መሽተት፤ ሽታ መዐዛ መስጠት የክፉ የበጎ ጺአ ለክፉ ብቻ ጼነወ ለኹሉ ይኾናል። ይጼኑ ጺአቶሙ። ሶበ ጼነ ይጐይይ ወሶበ ጼነዎ ናሁ ለዝክቱ ጋኔን ጐየ፤ የክፉ (ጦቢ፮ ፲፰ ) ዘሠናየ ይጼኑ። ዘትጼኑ ቆፀ ወጼነወ ጼና ምዑዝ ፈድፋደ ጼነዎ ጼና ዕፍረት ፡ (አርጋ ፩። ስንክ ፡ ጥቅ፯ና የካ፭)
ጼአ ገማ ሸተተጸዪእ ጼአ
ጼዋት ጽያው አጽያው ጨዎች ዐሸቦዎች፤ አሞሌዎች። ዐሸቦ አንኳሩ ብትኑ፤ አሞሌ ጥርቡ ምእዙኑ። ፡ (ተረት) ምላጭ ዐበጠ በምን ይበጡ ጨው ዐለጠ በምን ያጣፍጡ። የመነኵሴ ሎሌ፤ የክረምት አሞሌ። ሐራ ብሎ ጨዋ ማለት ዐማርኛው ዚህ ወጥቷል ምስጢሩም የጨው ነው
ጼው [1] ው፤ጸየው።
 [2](ዐረ ጸዋ ዕብ ጺያ ደረቅ በረሓ ምድረ በዳ) ው፤ ዐሸቦ አሞሌ፤ በቈላ በረሓ ከውህማ መሬት የሚገኝ፤ በውሃ የሚቀልጥ የሚሟሟ መጣጣ ሖምጣጣ፤ መባልዕትን ኹሉ የሚያጣፍጥ፤ ከኹል ገብ፤ በብዙ ወገን የሚፈለግ ንትሙ ምድር ወእመሰ ስሐ በምንት እንከ ይቄስምዎ። ወዘርዐ ውስቴታ ጼወ። ሐውልተ ወረሰያ ምድር ባሕረ ጼው ገዳመ ጼው ፡ (ማቴ፭ ፲፫ ማር፱ ፶። መሳ፱ ፵፭። ዘፍ፲፱ ፳፮ መዝ ፻፮ ኩፋ ፲፫ ስንክ ፡ ግን፳፰)
ጼደነት [1] ፡ ዛር ጋኔን፤ጸየደነት።
[2](ታት። ዕብ ጼዳኒ ተንኰለኛ፤ አጥማጅ ዐዳኝ) የዱር የበረሓ ዛር ጋኔን ይትራከቡ ህየ ጋንንት ወጼደነታት ወይጸርሑ ኵሎሙ ፡ (ኢሳ፴፬ ፲፩ ፡ ፲፬) ሰገኖ በማለት ፈንታ ጼደነት ይላል፤ የተሳሳተ ነው፤ ባለብሎዮች ግን ኹሉንም ሔለይ ወይም ዔሊ ደንጊያ ልብሱ ይሉታል። አዋልደ ጼደነታት። ይበክዩ ከመ ጼደነታት ፡ (ኤር፳፯ ፴፱። ሔኖ፺፮ ) መጽአሞንና ጽግነትን ተመልከት።
ጼዴን ጼዴንያ ጣዝማ፤ የጣዝማ ማር። ጼዴን ንህቡ፤ ዴንያ ማሩ
ጼዴንያ ስመ ሀገር ፡ (መቅ ታም)
ጽሑቅ (ቃን ቃት ሕቅት) የተጋ፤ ትጉህ፤ ንቁህ። ጽሑቅ ለፍቅር። ጽሕቅተ ኩኒ ውሂበ መፍቅድየ ጽሕቅት ለተሣህሎ (አርጋ ደራሲ)
ጽሑድ (ዳን ዳት ሕድ) የጠዳ ጥዱ፤ ልዝብ ልሙጽ ስላሳ ልም፤ ንጹሕ እስመ ጽሑድ ክርስቶስ፤ ወመንክር ጽሕደተ ሥጋሁ (መጽ ምስ)
ጽሑፍ ፡ (ፋን ፋት ሕፍት) የተጣፈ፤ የተቈጠረ ኵሎ ዘጽሑፍ ውስተ ዝንቱ መጽሐፍ ጽሑፋን በበ ስማቲሆሙ ጽሑፋት በዕብራይስጥ። መጽሐፍ ጽሕፍት (ኤር፳፭ ፲፫ ፩ዜና ፡ ፬ ፡ ፵፩። ኩፋ ፲፪። ራእ፭ ) አገባብ ሲወድቅበት፤ ባይወድቅበትም፤ ቀዳማይ ቦዝ አንቀጽ ይኾናል። እስመ ጽሑፍ፤ በከመ ጽሑፍ ቢል፤ እንደ ተጣፈ፤ ተጥፎ፤ እንዳለ። ጽሑፍ ለእግዚ ትስግድ፤ ተጥፏል ያሰኛል።
ጽሒም ሞት (ጸሐመ ይጽሕም ይጽሐም። ዕብ ጻማሕ) መብቀል፤ መውጣት፤ ማደግ መርዘም የሣር የጠጕር የጥርስ የቀንድ የመሰለው ኹሉ ጸምሐን ተመልከት የዚህ መንቲያ ነው ምስጢራቸው ወገን ሲኾን ንባባቸው በፊደል መዛወር ተለያይቷል መዛወሩም ቀሐመን ቀምሐ ብለው እንደሚገሱት ነው።
ጽሒቅ ቆት (ጽሕቀ ይጽሕቅ ይጽሐቅ። ዕብ ጻሔቅ፤ ሣቀ። ሹቅ ፈተወ) መውደድ፤ መመኘት፤ መፈለግ መሻት ማሰብ መትጋት ፈተወን ተመልከት፤ የዚህ ከተማ ነው ኅሊናሁ ይጽሕቅ ምንኵስና። የኀሥሡ ወይጽሕቁ ገጾ ለሰሎሞን። እጽሕቅ ክሙ ዘልፈ ኢንጽሐቅ ለግብረ ዓለም ፡ (ስንክ መስ፲፬ ፪ዜና ፡ ፱ ፡ ፳፫ ጴጥ ፩ ፡ ፲፪ አፈ ተ፳፯)
ጽሒብ ቦት (ጸሐበ ይጽሕብ ይጽሐብ ዐረ ጸዐበ ዐጸበ) መድከም መታከት መሰልቸት፤ መሰቀቅ፤ መቸገር መጨነቅ ከዝብዘባ ብዛት የተነሣ፤ ነጠየን ተመልከት
ጽሒው ዎት (ጽሕወ ጸሐወ ይጽሑ ይጽሐው። ሱር ጻሕዋ። ዐረ ጸሒየ፤ ጸሓ) መብራት መጥራት፤ ብራ መኾን የሰማይ የዝናም። አኀዘ ያንጠብጥብ ዝናም ወእምዝ ጽሕወ (ስንክ ፡ ሚያ፳፬)
  መንቃት፤ መመለስ፤ መትጋት ከንቅልፍ ከስካር ከሀኬት ሶበ ጽሑ ምንዋምየ ሶበ ጽሕወ ምወይኑ። ንጽሐው ምንዋመ ስካር። ጸሐዉ እምስካረ ወይን ወጸሐዉ ለጸሎት (አርጋ ፡ ፬። ዘፍ፱ ፳፬ መጽ ፡ ምስ። ቄር ጰላ ጴጥ ፬ ፡ )
ጽሒድ ዶት (ጽሕደ ይጽሕድ ይጽሐድ) መጥዳት መለዘብ፤ መለስለስ፤ ልሙጽ መኾን ወጽሕደ እምቅብዕ ገሩ (መዝ ፡ ፶፬)
ጽሒፍ ፎት (ጸሐፈ ይጽሕፍ ይጽሐፍ። ዐረ ጸሐፈ) መጣፍ፤ ፊደልን ብራና ከወረቀት ላይ በቀለም መሣል መንደፍ ሰሌዳው የዕፅፅ የእብን የማዕደን ቢኾን፤ ቀለም የወደቀበትን መቈፈር መፈልፈል ለማስመጥ ወይም ዙሪያውን መንቀስ መቅረጥ ለማሳበጥ እንደ ማኅተም። ማሰብ መቍጠር በፊደል በአኃዝ። የተጣፈውን የተቈጠረውን ጠንቅቆ ማወቅ በልቡና ማኖር ጠቢባን ሙንቱ ውስተ ጽሒፍ። ጸሐፍኩ በእዴየ ሐፎ በጽሌ ብከ ወይጽሕፎሙ ሕፃን። ጸሐፊዮ ብእሲ ከመ ዘምተ ፡ (ሱቱ ፡ ዝ፲፬ ፳፯ ፊልሞ ፡ ፲፱ ምሳ፫ ፫። ኢሳ፲ ፡ ፲፱) ከተበን ተመልከት።
ጽሕም (ማት አጽሓም) በቁሙ ም፤ ሪዝ፤ ሸንጐበት ሸፋሽፍት፤ ባገጭ፤ በጕንጭና በጕንጭ፤ በከናፍር ላይ የሚበቅል ጠጕር። ሥዕርተ ጽሕምየ። ወኮነ ጽሕሙ ነዊኀ ወይበጽሕ አስከ ኅባኔሁ። ልጺያን አጽሓሚሆሙ (ዕዝ፬ ፫። ንክ ፡ ግን፲፫ ኤር፵፰ ) ምስጢሩ ካደጉ በኋላ የሚሠርጽ የኋላ ቡቃያ ማለት ነው።
ጽሕርት ድስት ጽህርት።
ጽህርታት ጻህራት ድክቶች፤ ምንቸቶች። ጽህርታት ወኰከማት። ሳኵሳት ወጽህርታት። ወይከውና ጻህራት ከመ ኮራት ፡ (ኤር፶፪ ፲፰ ማር፯ ፰። ዘካ፲፬ )
ጽህርት ድስት፤ ምንቸት፤ አፍላል አፈ ክብ፤ ማብሰያ፤ መቀቀያ ይእቲ ጽህርት ወንሕነ ሥጋ። ሰክትት ጽህርተ። ታሕተ ጽህርት ፡ (ሕዝ፲፩ ፫። ፳፬ ፫። መክ፯ )
ጽህቀ ወደደጽሒቅ ጽሕቀ
ጽሕው (ዋን ዋት ሑት) የጠራ የበራ፤ ቍልጭ ያለ። ጽሕው ብሔር። አየ ጽሕወ ኮነ (ማቴ፲፮ ፪። አፈ ፡ ድ፳፪)
ጽሕዩይ (ያን ያት ይይት) የታረመ ረም እድፍ ድፍ ጸያፍ የሌለበት።
ጽሕያይ ዐረም ረምቻ እድፍ ድፍ
ጽሕደት መለዘብ፤ አለዛዘብ፤ ልዝብነት፤ ልስላሴ፤ ጥዳት፤ ንጽሕና። ከመ ሜላት ንጹሕ ጽሕደተ ሥጋሃ ማርያም፤ እስመ በቁለ ውስቴታ ኀጣውእ። ጽሕደተ ሜላት ፡ (መጽ ምስ አርጋ )
(ጥድ)         ጽሕድ [1]በርሚል፤ የንጨት ጋን፤ ከለሀበ ጠርብ የሚሠራ የሸክላ ጋን ማድጋ ፊቀን። ዕብራይስጡ ግን ጥልቅ ልሙጽ ጕድጓድ ይላል። ጽሕድ ስቍርት ዘማዊት በጽሕድ ፈንጽ ዕድ ይላል፤ የጣፊ ስሕተት ነው ፡ (ምሳ፳፫ ፳፯)
[2](ዳት አጽሓድ) አርዝ፤ ጥድ ዘግባ፤ የጥድ የዘግባ ዐይነት፤ የሊባኖስ ዛፍ፤ መዐዛው የጠዳ፤ ሲጠርቡትና ሲያለዝቡት ስለት የሚቀበል፤ ጽሕደት የሚሰማማው፤ የማይፍረከረክ። አርዝን ተመልከት፤ ከዚህ ጋራ ነው። ንግዝም ግላ ወጽሕደ። ዕፀ ጽሕድ። ፍሬ ጽሕድ (ኢሳ፱ ፲። ዘሌ፲፬ ፡ ፬ና ፡ ፮። መ ፡ )
ጽኅድ ጥድ ዛፍ፤ጽሒድ ጽሕደ።
ጽሕፈት (ታት) መጣፍ፤ ፡ (ጥጣ) መጣፍ አጣጣፍ፤ ጥፈት ቍጥር ጽሕፈተ ሠናየ የአምር መሃሬ ጽሕፈት ጽሕፈታተ ደዊሆሙ ፡ (ስንክ ኅዳ፱ ፲፩ ያዕ ዘእል)
ጽሉል (ላን ላት ልልት) የተጋረደ የተሸፈነ፤ ሽፍን፤ ድፍን ጽሉል ዕይንቲሆሙ ናሁ ጽሉል ቦሙ ወእዘኒሆሙ ብዳን ወጽሉላነ ልብ (ሔኖ ፡ ፹፱። ፴፫። ኤር፮ ፲። ዲድ )
ጽሉም የጨለመ፤ የጠቈረ ጭልም ያለ የጨለማ ቦታ። ጽሉም ኅሊናሆሙ። ጽሉመ ልብስ። ጽሉማነ ምድር ፡ (ኤፌ፬ ፲፰ ቀሌ መዝ ፡ ፸፫)
ጽሉብ (ባን ባት ልብት) የተሰቀለ ስቁል፤ ቅንው ቅቱል
ጽሉእ (ኣን ኣት ልእት) የተጠላ የተነቀፈ ንቁፍ። ለእመ ኮነ ውእቱ ግብር ጽሉ ምኢገብርዎ። ጽሉእ በኀበ እግዚ ትዕቢት ትከውኑ ጽሉኣነ በእንተ ስምየ (ዮሴፍ። ራ፲ ፯። ማቴ፲ ፳፪)
ጽሉይ የተጸለየበት፤ ጸሎት የደረሰበት። ዘይት ጽሉይ ማየ ምንዛህ ጽሉይ (መጽ ምስ)
ጽላሌ መጋረድ፤ ፡ (ጥጋ) መጋረድ፤ ገራረድ ግርዶሽ፤ ለማ፤ ዕውርነት። ጽላሌ ይል ዘመንፈስ ቅዱስ። ወጽላሌ ኀለ እምአዕይንተ ይሥሐቅ ወርእየ ዝረትሰ ጽላሌ በመንፈስ። በእበ ወበጽላሌ ልቦሙ። ጽላሌ ዐይን (ቅዳ ሕር ኩፋ ፡ ፴፩። ሮሜ፪ ፡ ፳፱ ኤፌ፬ ፲፰ አርጋ ፡ )
ጽላል (ላት) ጥላ ድባብ አጐበር የሚወጠር የሚገተር ፀሓይ የሚከለክል።
ጽላሎተ  ሞት (ዕብ ጻልማዌት) የሞት ጥላ፤ ውድቅት ጽፉቅ ድቅድቅ ለማ ሃነም ፡ (ኢዮ፫ ፭። መዝ ፡ ፹፯። ማቴ፬ ፲፮)
ጽላሎት (ታት ዕብ ) በቁሙ፤ ጥላ ታች ከፊፍ ለማ፤ አርኣያ አምሳል፤ የዛፍ የገደል የሌላውም ኹሉ፤ በፀሓይ ጊዜ የሚታይ የሚለይ፤ ብርሃነ ፀሓይ የሌለበት። ጽላሎተ ዕፅ። ጽላሎተ ድባር። ጽላሎቱ ለአምላክ ሰማይ። ስመ ጽላሎታ ይእቲ ሪት ለእን ትመጽእ ሠናይት (ሕዝ፮ ፲፫ መሳ፱ ፴፮። መዝ ፺። ዕብ፲ ፡ )
  ቤት፤ ድንኳን፤ ማረፊያ ማደሪያ። አብእ ነዳየ ወአኅድሮ ውስተ ጽላሎትከ ጽላሎተ ቤትየ (ኢሳ፶፰ ፯። መዝ ፡ ፲፬ና ፻፴፩)
ጽሌ የመጣፍ ገበታ፤ጸልዮ ጸለየ
[1] ጽሌ፤ (ላት) የጸሎት መጣፍ፤ እንደ ሳታትና እንደ ዳዊት፤ እንደ ቅዳሴ ያለ
[2]ጽሌ፤ (ለውሕ ሰሌዳ) የመጣፍ ገበታ ከመጣፉ ጋራ በቶታን በጥራዝ በድጕስ ርበት የሚያያዝ ከቈርበቱ ላይ ብዙ ዐይነት ሐረግ ሥዕል መስቀል የሚሣልበት የሚታተምበት፤ ጌጣም ሽልምልም
  ታቦት፤ የመጽሐፍ ዐይነት፤ ሐረጉና ጌጡ በመጽሐፍ ድጕስ አምሳል የሚሠራ፤ በላዩ ስመ አምላክና ዐሠርቱ ቃላት ባጭር ቃል የሚጣፉበት መሥዋዕት የሚሠዋበት፤ ከዕፅ ከእብነ በረድ የሚቀረጽ ታቦትን ተመልከት ወአኮ በጽሌ ዘእብን ዘእንበለ ጽሌ ልብ ዘሥጋ ወወሀቦ ሙሴ በደብረ ክልኤ ጽላተ ሕግ ጽላተ ዘእብን (፪ቆሮ ፡ ፫ ፡ ፫። ዘፀ፴፩ ፲፰) ጽሌ ጽላት ለዕፅና እብን ለማዕደን ብቻ እንጂ ለክርታስና ለብራና አይኾንም። ጽላተ ሰማይ። ጽላተ ብርት፤ ጽላተ ብሩር ጽላተ ሐመር ፡ (ኩፋ ፡ ፫። ዮሴፍ። ስንክ ግን፳፩) ጽሌ ላንድ፤ ጽላት ለኹለት፤ ለብዙም ይኾናል። ባማርኛ ግን አንዱ ብቻ ጽላት ይባላል ይኸውም ሥራው በመጽሐፍ አምሳል መኾኑን ያሳያል፤ አንድ ቅጠል ክርታስ ወይም ብራና በኹለት ወገን ስለ ተጣፈበት ኹለት ገጽ እንዲባል፤ ጽላት ማለትም እንደዚህ ነው
ጽልሑት ንገላ፤ ክዳት፤ ተንኰል፤ የፑሊቲክ ቃል ዐመፃ ወጽልሑት። ይገብሩ ዕሌሁ ጽልሑተ። ዘእንበለ ጽልሑት ወኢሀኬት ፡ (ዘካ፩ ፱። ዳን፲፩ ፳፫ ነ ፡ )
ጽልሕው (ዋን ዋት ሑት) የተሸነገለ ሽንግል፤ ሞኝ፤ ተላላ ዘላላ
ጽልመት (ዐረ ዙልመት። ዕብ ሖሼኽ) መጨለም፤ መጥቈር አጨላለም። ጨለማ፤ ሌሊት፤ የጨረቃ ጠፍ፤ ወይም ሠርቅ ጥቍረት ጥቍርነት። በምስጢር፤ ኀጢአት ክሕደት፤ ድንቍርና፤ ሐዘን መከራ ይኾናል። ጸልመት ፀሓይ ሶበ ርእየት ፈጣሪሃ ስቁለ ወኮነ መጠነ ጽልመታ ምጊዜ ስድስቱ ሰዓ እስከ ጊዜ ተስዐቱ ሰዓት ወጽልመት መልዕልአተ ቀላይ፤ ወፈለጠ እግ ማእከለ ብርሃን ወጽልመት፤ ወሰመዮ ለብርሃን መዓልተ ወለጽልመት ሌሊተ በካልእ ወርኅ ዐሡሩ ወሰኑዩ ጽልመት ስል ይእቲ ልብ ወጽልመት ለገጽ ወሐዘን ነፍስ ብእሲት እኪት። ወገጹ ዘፍፁም በጽልመት (ስንክ ፡ መጋ፳፯ ዘፍ፩ ፪ና ፬ ፡ ፭። ፯ ፡ ፲፩ ፬። ራ፳፭ ፳፫ ኪዳ)
ጽልሙት (ጽሉም) የጨለመ፤ የጠቈረ ጥቍር፤ ጨለማ ጥቍረት የጸናበት። እንዘ ብሩሃን ንሕነ ዘኢጽልሙታን። ዋክብት ጽልሙታን ጽልሙታነ ራእ ሕዝብ አባ ሙሴ ጽልሙት ፡ (አፈ ድ፩ ይሁ ፡ ፲፫ ራደሲ ፊልክ ፡ ፴፮)
ጽልአት መጥላት፤ መጠላት አጠላል ላትነት።
ጽልእ (ኣት) ጥል ጠብ፤ ቂም ፍጺመ ጽልአ ጸላእክዎሙ በልቦሙ ይሠይሙ ጽልአ ኅድጋ ለጽልእ ፡ (መዝ ፡ ፻፴፰ ኤር፱ ፡ ፰። ራ፳ ፭። ፴፬ ፡ ፲፮)
ጽልው (ዋን ዋት ሉት) የቀቀረ፤ ያዘነበለ የነቃ የተጋ ሰላም ለአእዛኒከ ጽልዋተ እለ ኮና ምኃ ነገር ያብኣ መኰን ውስጥ ኅሊና። ኢትኩን ሣኤ ገጽ ወኢጽልወ ልብ አኀ መስተጋድላን ጽልዋን ጸሎት ዘወትር (ደራሲ። ዲድ ፡ ፴፭። ቄድር)
ጽመ [1] ፡ ዝም ብሎ፤ጸመመ።
 [2]ዝም ብሎ፤ በዝምታ፤ በጸጥታ። ባሕቲቱ ይነብር ጽመ ውስተ ምግሓሠ ጽርሑ ወጽመ ይትገደፍ ፡ (መሳ፫ ፳፬ ማቴ፲፭ ፲፯። ማር፯ ፲፱)
ጽሙም (ማን ማት ምምት) ደንቈሮ ዦሮው የተዘጋ የተደፈነ፤ ዝም ቸል ያለ ትንብብ ሕሡመ ላዕለ ጽሙም ሃም ወጽሙም ከመ ጽሙም ዘኢይሰምዕ። ለጽሙማን መፈወስ ፡ (ዘሌ፲፱ ፲፬ ሉቃ፲፩ ፲፬ መዝ ፴፯ና ፡ ፶፯። ኪዳ)
  ደረቅ ጥብቅ። ኰኵሕ ጽሙም (ማር ይሥ፳፰ )
ጽሙቂም (ዕብራ) ዘቢብ ደረቅ የወይን ዘለላ፤ የበለስ ቋንጣ ፡ (፩ነገ ፳፭ ፲፰) ሙዳየ ዘቢብ ባለው ጽሙቂም እያለ ይገኛል፤ ጼሜቅ አንድ ጽሙቂም ብዙ
ጽሙና ጭምትነት ድካም ጸጥታ የገዳም ሥርዐት፤ ጾም ትሕርምት ምናኔ፤ ብችነት። ትሜህረነ ጽሙና ወትዕግሥተ ወጸሎተ መፍቀሬ ጽሙና ወጸሎት ኅሩያን መነኮሳት ዘንብረቶሙ ጽሙና ፈለሰ ገዳመ ውስተ ጽሙና ፡ (ዲድ ፡ ፳፱ ስንክ ሚያ፲ ሐም፳፩ ፊልክ ፡ ) ጾመ ጻመወ፤ ጸመወ እሊህ ዘር ናቸው
ጽሙእ (ኣን ኣት ምእት) የተጠማ የናፈቀ ወበከመ ጽሙእ ዘየሐልም እንዘ ይሰቲ ማየ ወነቂሆ ዓዲሃ ጽምእት ነፍሱ ዘእሙንቱ ጽሙኣን እምቃለ እግዚ ከመ ይትመርሑ በቃላቲከ እለ ጽሙኣን ነጽሮትከ (ኢሳ፳፱ ፰። መጽ ምስ አረጋ ድ፪)
ጽሚተ ጽምሚተ ዝም ብሎ፤ ቀስ መሰስ ብሎ፤ በቀስታ ውሮ፤ ተሰውሮ፤ በስውር በምስጢር በስርቆሽ በድብቅ በሹልክታ በሹክሹክታ ማይ ዘየሐውር ጽምሚተ መከረ  ሚተ ይኅድጋ። ዐርገ ጽሚተ ወአኮ ገሃደ። አልቦ ዘተናገርኩ ጽምሚተ ወኢምንተኒ ፡ (ኢሳ፰ ፮። ማቴ፩ ፲፱ ዮሐ፯ ፲፰ )
ጽሚት ጽምሚት ጥመት፤ ጠማምነት፤ ልግም፤ ቸልታ ዝምታ፤ ቀስታ፤ ድበቃ ስወራ ምስጢራዊ ሥራ። ከመ ቅትሎ ለንጹሕ በጽሚት። ሀብት ዘበጽሚት። ዘአስሐቶ ልብየ በጽምሚት ፡ (መዝ ፡ ፱። ምሳ፳፩ ፲፬ ኢዮ፴፩ ፳፯)
ጽማዌ መጨመት፤ ጭምትነት፤ ዝምታ፤ ጫታ ርጋታ ጸጥታ ሶበ ይከውን ጽማዌ ብእሲ ጠቢብ ያመጽእ ጽማዌ። ሰላም ወጽማዌ። ጽማዌ ፍስ። ወሰደደቶ ውስተ መካነ ጽማዌ ፡ (ምሳ፯ ፱። ፲፩ ፲፪ ፩ዜና ፬ ፡ ፵። ስንክ ታኅ፭ አፈ ፡ ተ፲፬)
()            ጽም ድንቍርና፤ ዝምታ፤ ጸጥታ፤ ከንቱ ብላሽ፤ ስሕ፤ ዐዘቅተ ስሕ
ጽምሑይ (ያን ያት ሒት) ምጽልው የጠወለገ ሣዕር ጽምሑይ። ኮነ ገጹ ድሙነ ወሕብሩ ጽምሑየ (ሄርማ። ፊልክ ፻፷፬)
ጽምእ (ኣት) ጥም ጥማት፤ የውሃ ዕጦት፤ የመጠጥ ችጋር ጽምአ ማይ። ብሔረ ጽምእ እመውት በጽምእ (ዓሞ፰ ፲፩ ዘዳ፴፪ ፲። መሳ፲፭ ፲፰)
ጽምው (ውት ዋን ዋት) የረጋ የጨመተ፤ ጭምት፤ ዝም ዕክም ጸጥ ያለ ዝምተኛ፤ ህዱእ ጽምው በቃሉ ወራትዕ በልሳኑ። የዋህ ወጽምው። ውስተ መካን ግሑሥ ወጽምው፤ ጭር ያለ (ሲኖዶ። ሄርማ። ግንዘ)
ጽሩብ (ባን ባት ርብት) የተጠረበ፤ ጥርብ፤ ልዝብ ወረከብናሁ በትር ዘይጌሥጻ ሮሜ፤ ጽሩብ በንባብ ወቅሩጸ በትርጓሜ ፡ (ቅኔ። ሃይ ላዊ ፫ነገ ፲ ፡ ፲፩ ፬ነገ ፲፪ ፡ ፲፪)
ጽሩይ (ያን ያት ሪት) የጠራ፤ የበራ፤ ንጹሕ፤ ጥሩ ፍትኖ ጽሩይ ውእቱ። ብሩር ጽሩይ ወርቅ ጽሩይ ወይን ጽሩይ ማየ ትምህርት ጽሩይ። ልብ ጽሩይ። ኅሊና ጽሪት። ጽሩይ እምነውር ፡ (ዘካ፲፩ ፲፫ መዝ ፲፩ ቀሌ ስንክ ሠኔ፳፭ )
ጽሩፊም (ዕብ ጾርፊም) ብር አፍሳሾች፤ አንጥረኞች፤ ቀጥቃጮች ፡ (ነሐ፫ )
ጽራሕ (ሓት) ኸት ጥሪ ልቅሶ ጽራሕ ወብካይ። ወለቡ ጽራሕየ ጽራሓት ፡ (አስቴ፬ ፫። መዝ ፭። ሔኖ፱ )
()            ጽራብ (ባት) ጥራቢ የንጨት ገለባ እብቅ ወድቀ ቅድሜሁ ከመ ጽራባተ ዕፅ ፡ (ስንክ ፡ ጥር፭)
ጽራእ (ዐረ ኀሩብ ሱር ወዕብ ሐሩብ) የዛፍ ም፤ እንቡጣም፤ እንቡጠ ወፍራም ሖሞርን ተመልከት ፡ (ሉቃ፲፭ ፡ ፲፮)
ጽራግ (ትግሬ) ዐንገትጌ ያንገት ጌጥ ሽልማት፤ ለራስም ይኾናል።
ጽራግ ማሰሬ የንጉሥ አልባሽ መዘይነ ንጉሥ፤ ያሽከሮች አለቃ ጃን ሸላሚ ዘየነን ተመልከት
ጽርሕ (ዐረ ጸርሕ። ዕብ ጽሪሕ) አዳራሽ፤ ታላቅ ቤት፤ ግንብ፤ ምኵራብ ቤተ ጉሥ ቤተ መቅደስ፤ ጥሩ ረዥም፤ ደርብ፤ ተሥላስ ገነት ዕልፍኝ፤ ዋሻ በኣት ምስጢሩ ጥራትና ምጥቀት ታላቅነት፤ ጩኸትና ማስተጋባት ነው ጽርሐ መንግሥት ጽርሐ መቅደስ። ጽርሐ አርያም። ደቀ ጽርሕ። ዐርጉ ጽርሐ ወውእቱ ያርእየክሙ ጽርሐ ዐቢየ ወንጹፈ ወርሱየ (ኢሳ፴፱ ፯። ግብ፩ ፲፫ ማር ፲፬ ፲፭)
ጽርበት መጥረብ፤ መጠረብ፤ አጠራረብ ረባ ልጎሽ፤ በቁሙ ጥርበት፤ ጥርብነት። መሀርዎ ግብረ ጽርበት ወተምህረ ገብረ ጽርበት ዘምክያደ አእባን ወምሕዋራተ ማይ (ስንክ ፡ ኅዳ፳፩ ግን፲)
ጽርኒ ጥርኝ የዝባድ አውሬ ድመት የምታኽል፤ ድመት የምትመስል ጠረናም ጠረነ ልካም ዝባድን እይ።
ጽርንዕት (ዕብ ጻራዓት፤ ለምጽ) ቋቍሻ ቡሓ፤ ቈረቈር፤ ዕከክ፤ ብግር። ዘቦ ጽርንዕት ላዕሌሁ ፡ (ዘሌ፳፩ ፳። ፳፪ ፳፪)
ጽርእ ያገር የቋንቋ ስም፤ ግሬክ፤ ዮናን። ፍችው ኅቡር እስትጉቡእ ማለት ነው ኩባኒያ ኮምፓኝ እንደ ማለት። አንዳንድ ኤውሮፖች ግን በጥንታዊው ግእዝ በሕምያር ቋንቋ ምዕራብ ምዕራባዊ ማለት ነው ይላሉ ወቦ እምሰብአ ጽርእ ወጽሑፍ በጽርእ ተአምርኑ ጽርአ (ዮሐ፲፪ ፡ ፲፱ ግብ፳፩ ፴፰) ጽርዕ ተብሎ በዐይን ቢጣፍ ግን ነጭ ማለት ነው፤ ዕብራይስጥ ጻራዕ ብሎ ነጣ ይላልና
ጽርየት መጥራት አጠራር ጥራት ጥሩነት ወአልቦ ተሐምጎ ውስተ ጽርየታ። በእንተ ጽርየተ ንጽሕ ከመ ይኩን ምልኮቶሙ በንጽሕ ወበጽርየት ተግሒሦሙ እምአምልኮ ባዕድ። ፡ (አፈ ፡ ተ፳፫ ጥበ፯ ፳፬። ዮሴፍ)
ጽቍንቍን በካብ በጕር የሚኖር ገበሎ በና፤ እንቃቅላ፤ የእንሽላሊት ዐይነት። ባለብሉዮች ግን ፍልፈል ይሉታል። ንጼዋ ወጽቍንቍን ፡ (ዘሌ፲፩ ፳፱)
ጽበት መጥበብ መጭነቅ፤ መጠበብ መጨነቅ፤ ጥበት ጭንቀት፤ ጠባብነት ጽበተ ብሔር ጽበተ ርሥ ጐየ ሞን እምጽበተ ነፍሱ (ገድ ኪሮ ቅዳ ሕር ፊልክ ፻፬)
ጽቡል (ላን ላት ብልት) ትቢያ የኾነ፤ ትቢያ የመላበት የበነነበት። ትሬእየነ ጽቡላነ ምቀትል ፡ (ተረ ፡ ቄር፰)
ጽቡር የጨቀየ የላቈጠ የተቦካ የተረገጠ፤ ልል ጽቡረ ዐምዓም ከመ  ጽቡረ ለብሓዊ ዘይከይድ ጽቡሮ። ዝንቱሰ ውስጡ ጽቡር ንዋየ ጽቡር ፡ (መዝ ፡ ፵፬። ኤር፵፩ ፳፭። ዳን፲፫ ፡ ፯። ንክ የካ፴) በጸብር ፈንታ ጽቡር ጽቡራዊ ይላል ስሕተት ነው ይህ የጠቀስነው ኹሉ ጸብር እንጂ ጽቡር አያሰኝም ሥጋ ጽቡራዊት (ማር ይሥ፪ )
ጽቡብ (ባን ባት ብብት) ዝኒ ዓዲ ማሁ፤ የጠበበ፤ የጨነቀ የጠበበው የጨነቀው፤ የተጠበበ የተጨነቀ፤ እስራት የጠበቀበት፤ ደዌ መከራ የወደቀበት። ተዘከር እግዚኦ ጥዉቃነ ወጽቡባነ (ግንዘ)
ጽቡእ (ኣን ኣት ብእት) የተወጋ፤ ውግ የተዘመተበት ጽቡእ ብሔሩ ፡ (ሄርማ)
ጽባሓዊ (ሓይ) የጧት የማለዳ፤ ምሥራቃዊ የምሥራቅ። ኮከበ ብርሃን ጽባሓዊ። አንቀጸ ቤት ጽባሓዊ ነፋ ጽባሓይ (ራእ፳፪ ፡ ፲፮። ሕዝ፵፩ ፩። ሔኖ፸፮ )
ጽባሕ (ሓት) ጥባት ንጋት ወገግታ፤ ጧት፤ ማለዳ ወፍ ሲጮኽ በጊዜ ጽባሕ። ሶበ ጎሐ ጽባሕ። ኮከበ ጽባሕ። በጽባሕ እቀውም ቅድሜከ (፩ነገ ፲፩ ፲፩ ዘፍ፵፬ ኢዮ፴፰ ፲፪። መዝ )
  ለት፤ መዓልት፤ ቀን። ፈጸሙ ሎቱ ርብዓ ጽባሐ ወገብኡ በአርብዓ ጽባሕ ፡ (ዘፍ፶ ፫። ዘኍ፲፫ ፳፭)
  ነገታ፤ ሳኒታ፤ ማግስት። ዘትወልድ ጽባሕ። ጾመ ልደት ወተፍጻሜተ ዘጽባሒሁ ዕለተ በዓለ ልደት ፡ (ምሳ፳፯ አቡሻ ፴፰)
   ምሥራቅ፤ የንጋት የወገግታ ቦታ የፀሓይ መውጫ መገለጫ ዐቢይ ማእዝን፤ የምዕራብ ትይዩና አንጻር ብሔረ ጽባሕ። ነፋሰ ጽባሕ። መንገለ ጽባሕ። እስመ ኢእምጽባሕ ወኢእምዐረብ። ጽባሓቲሁ(ኢዮ፩ ፫። ሔኖ፳፯ ፳፮። ሕዝ፲፩ ፩። መዝ ፸፬። ኩፋ )
ጽብሐት መጥባት፤ መንጋት ወገግ ፈገግ ማለት። በጽብሐት ፈንታ ጸብሐት ይላል የጣፊ ስሕተት ነው።
ጽብአት (740) መውጋት መወጋት አወጋግ፤ ውግታት። ዝክርኪ ኅሊናኪ በማለት ፈንታ ጽብአትኪ ይላል፤ የተሳሳተ ነው ፡ (ኢሳ፶፯ )
ጽቱም (ማን) (ማን) የተሰበረ፤ ቅጥቅጥ፤ ሰንጋ፤ ሙክት ዘጽቱም ወዘምቱር ፡ (ዘሌ፳፪ ፡ ፳፬)
ጽነት መጽነን መዘንበል፤ መጥመም፤ መጣመም ጠማምነት እመ ኮነ ጽነቱ መንገለ ሐጹር። ንዕቀብ ሃይማኖተ ርትዕተ ዘእንበለ ጽነት ( ነ ፡ ፴፯። ሃይ አበ)
ጽነፍ አጽናፍ፤ ጫፎች። ጽነፊሁ ለልብስ። ጽነፈ ልባስ። አጽናፈ ዓለም፤ ጽናፈ ሰማይ። ጽናፈ ምድር። ውስተ ኵሉ ጽናፍ መላኬ ኵሉ አጽናፍ ፡ (ዘፀ፴፮ ፳፬ ዘኍ፲፭ ፴፰። መዝ፲፰ና ፡ ቅዳ። ስንክ ፡ መስ፪)
ጽኑሕ (ሓን ሓት ንሕት) ያደባ የሸመቀ፤ የተዘጋጀ፤ ዝግጁ አንበሳ ዘጽኑሕ ለመሢጥ ጽኑሕ መልአከ እግዚ በሰይፍ ይሥጽርከ ጽኑሕ ሎቱ ሳር ዕጹብ። ወበከመ ጽኑሕ ለሰብእ ምዕረ መዊት (መዝ ፡ ፲፮ ዳን፩ ፶፱። ኢዮ፲፰ ፲፪። ዕብ፱ ፳፯)
ጽኑስ (ሳን ሳት ንስት) የተቸገረ፤ ችጉር፤ አይቶ ዐጣ፤ ችጋረኛ፤ ድኻ ወራዳ፤ ለማኝ ጋች ጦም ዐዳሪ ምስኪን ወኢትትሀከይ ቢረ ሠናይ ለጽኑስ ጽኑሳን ምኵሉ ሠናያት አል ምውስቴቶሙ ጽኑስ ፡ (ምሳ፫ ፳፯ ኢዮ፴ ፬። ግብ፬ ፴፬) ዘታጼንስ ዘታስተጼንስ በማለት ፈንታ ዘጽንስት ይላል፤ አያሰኝም። ዘጽንስት ጥቀ አውፅኦታ ፡ (ፊልክ መጨ)
ጽኑን (ናን ናት ንንት) የጸነነ የዘነበለ፤ ያረገዘ ያዘበዘበ፤ ወድቅ፤ ሊናድ የቀረበ። ከመ ረፍት ጽንንት ፡ (መዝ ፡ ፷፩)
ጽኑዕ [1] (ዓን ዓት ንዕት) የጠና ጥኑ ብርቱ፤ ጠንካራ፤ ጥብቅ፤ ደረቅ ከራራ። እብን ጽኑዕ ኰኵሕ ጽንዕት አመ ጽኑዐ ይገብር መሠረታተ ምድር። አጽዋናት ጽኑዓን። ህጉር ጽኑዓት ፡ (ጥበ፲፩ ፬። ኢሳ፶፩ ፩። ምሳ፰ ፳፱ ፪ቆሮ ፬። ኩፋ ፡ ፲፩)
 ካኝ ዐርበኛ ታላቅ ብዙ ጽኑዐ ጽኑዕ በውስተ ቀትል ሕዝብ ጽኑዕ (ምሳ፲፯   ራ፵፮  ፩። ኢሳ ፰ ፡  ፳፪)
 [2]የተጠና፤ የተለመደ፤ በቃል የተያዘ።
ጽናሴ መቸገር ማጣት፤ ችግር ዕጦት፤ ድኽነት ፡ (ፊልክ)
ጽናኔ ዝኒ ከማሁ በርትዕ ዘእንበለ ጽናኔ (አፈ ፡ ተ፴፬ ፵፩ ፡ )
ጽናዔ ማጥናት፤ መጠናት አጠናን ጥናት ጥኑነት ከመ  ያስተርኢ ጽናዔሃ ወአፍቅሮታ (ፊልክ ፡ ፻፵)
ጽናፌ ዝኒ ከማሁ። ውስተ ብካይ ወሐቅየ ስነን ወጽናፌ ጽልመት ፡ (ቀሌ)
ጽንሓሕ (ሓሓት) የሚቃጠል መሥዋዕት፤ ቍርባን፤ ሥበሕ ዕጣን፤ ጢሱ መዐዛው ምሥዋዑ ጥናው አዕረገ ጽንሓሐ ዲበ ምሥዋዕ ወጽንሓሐኒ ትሠምር። ጽንሓሐ መሥዋዕት ተዐጥን ጽንሓሐ ወተዐውድ ወትጸርሕ። አዐርግ ጽንሓሐ ለእግዚ ፡ (ኩፋ ፮። መዝ ፶። መዋሥ ግንዘ። መጽ ፡ ምስ) በጽንሓሕ ፈንታ ጽንሓሔ ይላል የተሳሳተ ነው ፡ (፪ዜና ፯ ፡ ፲፪ ፲፫ ፲፩)
ጽንሐት መቈየት፤ መታገሥ፤ አቈያየት። ቁይታ፤ ደጅ ጥናት ሽመቃ
ጽንሕ ዝኒ ከማሁ ቈይታ፤ ሽመቃ
ጽንቁቅ (ቃን ቃት ቅቅት) የተነከረ በርስሐት በደም የተበከለ እድፋም ጨምላቃ ልፍልፍ አመ ኮንኪ ራቀኪ ወሀሎኪ ጽንቅቅተ በደምኪ ፡ (ሕዝ፲፮ ፳፪)
ጽንቃቄ መነከር መዘፈቅ፤ መጨማለቅ። እድፍ ርስሐት፤ ጭቅቅት።
ጽንዐት (ታት) መጥናት፤ መጠንከር፤ ጥናት፤ ጥንካሬ፤ ጭካኔ፤ ብዛት፤ ብርታት፤ ብርቱነት። ጽንዐተ ልብ። ትክለተ ወጽንዐተ። ሶበ ርእየ ጽንዐቶሙ። ጽገዐተ ዝኩ ሥቃይ። ንዐተ (አፈ ፡ ድ፮ ቅዳ ስንክ ኅዳ፳፮ አፈ ፡ ድ፯ ግብ፳፰ )
ጽንዕ (ዓት) ጥናት ብርታት ኅይል፤ ጥንካሬ፤ ጠፈር ጽንዐ ልብ። በብዝኀ ጽንዑ ጽንዐ ሰማይ ፡ (ማር፲፮ ፲፬ መዝ ፡ ዘፀ፳፬ )
ጽንጉፍ (ነገፈ) ጥኑ፤ ከባድ፤ ጣሉኝ ጣለኝ የሚል፤ ጥንብ ዐይነ ምድር፤ ሬሳ፤ ጭንጋፍ ሙቶ የሚወርድ የሚወለድ። ነገፈን ተመልከት፤ አባቱ ርሱ ነው ክቡድ ብን ወጽንጉፍ ጾረ ኆጻ ፡ (ምሳ፳፯ )
ጽንጕን (ጸንቀቀ) ጭቃ። ከመ ጽንጕን ዘይከይዱ። ጽንጕነ  ፍኖት። ጽንጕነ መርሕብ ፡ (ሚክ፯ ፲። ዘካ፱ ፫። ፭።  መዝ ፡ ፲፯)
ጽንጵው (ዋን ዋት ጱት) የተጨቈነ፤ የተቀጠቀጠ፤ ቅጥቅጥ ጠማማ ቈልማማ። ዘጽንጵው ወዘጽቱም። መንኮብያቲሁ ጽንጵዋት (ዘሌ፳፪ ፡ ፳፬ ኪዳ)
ጽንጹል የተመታ የተቃጨለ ቅጭል ቅጭል የሚል
ጽንጹን (ናን ናት ጽንት) የጠነጠነ፤ የነቀዘ ያረጀ ያፈጀ፤ የዣዠ ዥዡ የተበላሸ ብልሹ ጥንጣናም ነቀዛም ከንቱ። ብሂልሰ ሀሎ ቃለ ግዚ ሕስው ወዘጽንጹን ኅሊና ገር ውእቱ። ያርኢ ጳውሎስ በኵሉ ከመ ክህነት ዘኦሪት እንተ በደም ወጢስ ከመ  ጽንጽንት ይእቲ ወኢትበቍዕ ወአልባቲ ኀይል ሙራ (ቄር ፡ እስት። ተረ) ሐሳብ በእንተ ጽንዕት ወጽንጽንት ፈቃ ዕንጨት የሚቈረጥበት ወራት በመስከረም ስከ ዐሠርቱ ወኀምስቱ ጽንዕት ወእምዝ ጽንጽት በጥቅምት እስከ ዕሥራ ወሠለስቱ ጽንዕት ወእምዝ ጽንጽንት ( ) ኅዳር እስከ ነሐሴ ላሉትም ወሮች እንደዚሁ ጽንዕትና ጽንጽንት አላቸው።
ጽንጻሌ መቅጨልጨል፤ መንሿሿት፤ ጸናጽል አያያዝ፤ አመታት።
ጽንጽንያ (ያት) ጥንጣን፤ ነቀዝ ዝንብ ትንኝ። ጽንጽንያ ምዉት። በዓለ ጽንጽንያ። ጽንጽንያት ንኡሳን ፡ (መክ፲ ፲፩። ነገ ፩ ፡ ፲፪)
ጽንፈት ዳርቻ መኾን፤ ዳርቻነት። አፍኣ ዳሪ፤ ከውስጥ ቤት ከቅጥር ውጭ ዘዘ ያውፅእዎ ኀበ ጽንፈተ ጽልመት (ቀኖ ፡ ኒቅ ፡ ፷፬)
ጽንፍ (ዐረ ጺንፍ) ዘርፍ፤ ዳርቻ ጠረፍ፤ ወደብ ገደብ፤ ወሰን ደንበር። ጽንፈ ልብስ ጽንፈ ውሒዝ። ጽንፈ ባሕር። ጽንፈ ምድር ፡ (ሩት፫ ፬። ሢራ፵ ፲፮ ፪ዜና ፡ ፰ ፡ ፲፯ ሔኖ፲፰ )
ጽዑር (ራን ራት ርት) የተጨነቀ የተሣቀየ፤ የሚያጥር፤ የሚጣጣር፤ ጣር የያዘው ለሞት የቀረበ ያዘነ የተከዘ ጥቀ ጽዑር ሕሙም ወጽዑር ፊልጶስ ጽዑረ ሥጋ በመቅሠፍት። ጽዑራነ ፍስ ይከውኑ ጽዑራነ ዛዜ ወትፍሥሕት ጽዑራን ፡ (ማቴ፰ ፮። አፈ ተ፬ ስንክ ኅዳ፲፰ ኢዮ፫ ፳። ጥበ፬ ፲፱ ማር ፡ ይስ፲፫)
ጽዑል (ላን ላት ዕልት) የተጣለ የተሰደበ ዱብ፤ ነውረኛ ንቁፍ ዘማ ወጽዕልተ ኢያውስ (ዘሌ፳፩ ፯ና ፡ ፲፬ ኢሳ፰ ፲፭ ምሳ፳፬ ፶፰)
ጽዑቅ የጠበበ፤ ባብ፤ ጭንቅ። ጽዕቅት ፍኖት ፡ (ማቴ፯ ፲፬ አፈ ፡ ተ፳፱)
  የተጨነቀ፤ የተጠበበ፤ መከረኛ።
ጽዑን (ናን ናት ዕንት) የተጫነ፤ የተጫነበት ሸክም፤ ተሸካሚ ዘጽዑን ዲበ ድግ እንዘ ጽዑን ምስሌሁ ዲበ ፈረስ ገመል ጽዑን ጽዑናን አግማሊሆሙ ፈዋተ (ስንክ የካ፲፩ ኅዳ፳፭ ሐም፳፭ ዘፍ፴፯ ፳፭)
ጽዑድ (ዳን ዳት ዕድ) የተጣደ ጥዶ ያለ፤ የተደላደለ።
ጽዑጥ (ጣን ጣት ) የተጣፈጠ የተነጠረ፤ ጥሩ ዝግጁ የተቀባ ቅቡዕ። ዕፍረተ መዐዛ ጽዑጥ። ፈዋተ ርሔ ጽዑጣን ዘይትዐቀብ በቀርነ ቅብዕ ዘጽዮን ፡ (ስንክ ፡ የካ፲ መጽ ምስ)
ጽዒል ሎት (ጸዐለ ይጼዕል ይጽዐል። ዕብ ጼኤል፤ እሾኻም የሽቱ ዕንጨት) መጣል ማጣጣል፤ መስደብ ማርከስ፤ ማዋደድ ማሳነስ፤ ማቃለል ማኰሰስ፤ መንቀፍ፤ ማጸየፍ ሹል አፍ እሾኽ አፍ መኾን፤ መባል። በእንተ ፀሪፍ ወጽዒል። ለእመ ዕበይለ ፉከ ወጸዐልካሁ እንዘ ይጼዕልዎ ኢጸዐለ ወይጼዕሉኒ ኵሎሙ ጸላእትየ ( ሢራ፳፪ ፡ ፳፪። ጴጥ ፡ ፪ ፡ ፳፫ መዝ ፡ ፵፩) ጸልአን ተመልከት፤ የዚህ መንቲያ ነው
ጽኢም ሞት (ጸአመ ይጽእም ይጽአም ዜመ ይዘይም) መጮኽ፤ ማስተጋባት ዜመን ተመልክት
ጽዒር ሮት (ጽዕረ ጸዐረ ይጽዕር ይጽዐር ሱር ጻዐር ያጻር) መጣር መጋር መፍገርገር መፍጨርጨር፤ በፍጹም ኀይል በፍጹም ትጋት መሥራት፤ መድከም መቃተት መቃሰት
  ማዘን መተከዝ፤ በጻዕር መያዝ መጨነቅ መዋለል፤ ሥቃይ መቀበል እስመ ጽዕረ ፈድፋደ ወትጼዕረኒ ልብየ (ስንክ ሐም፰ መዝ ፲፪) በጽዕረ ፈንታ ተጽዕረ ይላል፤ አያሰኝም ያማርኛ ነው። የጽዕረና የጸዐረ ፍች ተሣቀየ ተጨነቀ ማለት ስለ ኾነ ግእዙን እንዳማርኛው አስኪዶታል፤ ጭፍራነቱ የጥሕረና የጸዐለ ነው መኑ ውእቱ ዘተጽዕረ ከማየ። ተጽዕረ በምንዳቤ። እስመ ይጼዐር ወይላሑ እለ ይጼዐሩ በህየ (ኢዮ፲፫ ፲፱ ስንክ ፡ ጥር፲፭ ጥበ፲፬ ፲፭ ተ፩)
ጽዒቅ ቆት (ጸዐቀ ይጽዕቅ ይጽዐቅ ዕብ ጻዐቅ ጮኸ ከጭንቅ የተነሣ) መጭነቅ መጥበብ፤ ጭንቅ ጥብ መኾን የቦታ የጊዜ፤ ጸበበንና ዐጸበን ተመልከት። ለትጽዐቆ ምድር (አርጋ )
ጽዒን ኖት (ጸዐነ ይጽዕን ይጽዐን ዕብ ጻዐን ተጽዕነ) መጫን ማሸከም ማሳዛል፤ መጥመድ ማስነገት ሸክምን በተሸካሚ ላይ ማስቀመጥ ማኖር ወይም ርሱ ጋራ ማቈራኘት ማሰር ዘዞሙ ይሣየጡ በውእቱ ዋይ ክለ ወይጽዐንዎ በሐመር። ለአድግሰ ጸዐኖ። ጸዐነ ንስቲያሁ። ጸዐና ለእምከ ጸዐኑ አእዱጊሆሙ ጸዐነት አብቅሊሃ ወእጼዕን ሠረገላ ዲበ መሠንየ ክሣዱ ፡ (ዮሴፍ። ሢራ፴ ፴፫። ኩፋ ፡ ፳፱ ፴፩ ፡ ፵፫። ሆሴ፲ ፲፩) በጸዐነ ፈንታ አጽዐነ ይላል፤ ስሕተት ነው። አጽዐኖ ዲበ ፈረስ። ወአጽዐንከ ሰብአ ዲበ አርእስቲነ ወዲበ ልዑላት ያጼዕነኒ ፡ (አስቴ፮ ፲፩ መዝ ፡ ፷፭። ዕን፫ ፡ ፲፱)
ጽዒድ ዶት (ጸዐደ ይጽዕድ ይጽዐድ። ዕብ ጻዐድ) አጥብቆ መኼድ መራመድ፤ በኀይል መርገጥ እግርን ማንሣት፤ መር መር አፈፍ አፈፍ ማለት የጐበዝና የወታደር የሰልፈኛ አካኼድ አረጋገጥ። ርምጃ ርግጫ እንዲል (ሰልፍ አስተማሪ)
  መጣድ ማስረር በሦስት ልቻ ላይ ማኖር በውስጡ ያካኼድ ምስጢር አለበት፤ ከጕልቻ እስከ ልቻ ያለው መጠነ ምሥጋርን፤ ቢያንስም መጠነ ሰኰናን የድስቱና የምጣዱ ምጥቀት በእግር አነሣሥ ልክ መኾኑን ከዚያ አለመብለጡን ያሳያል ቢበልጥም በመዝለልና በመፈንጨት ጮቤ በመምታት ይመስላል።
ጽዒጥ ጦት (ጽዕጠ ጸዐጠ ይጽዕጥ ይጽዐጥ ዐረ ጸዐጠ) መቀመም ማጣፈጥ፤ ማንጠር ማቅለጥ፤ መቅባት መርጨት መረብረብ፤ የሽቱ የመድኀኒት። ዐቀብተ ሥራይ ይጽዕጡ ፈውሰ ለቍሱላን በዘይተ ሃይማኖት። ዕፍረት ዘእደ ዮሴፍ ዐጠ። አእዳወ ፍቅርኪ በላዕሌየ ይጽዐጣ ዕፍረተ መዐዛ ወቅብዕ ዘብዙኅ ጸዐጡ ሥጋየ በከርቤ ወበሰሊክ (መጽ ምስ ስንክ መጋ፳፯ ነሐ፲፮ አቡሻ ፡ ፵፯)
ጽዕለት (ታት) መስደብ፤ መሰደብ፤ አሰዳደብ። ስድብ፤ የቃል በትር ቍስሉ የማይሽር። ፡ (ተረት) የባለጌ ኀይለ ቃል፤ እንደ ሽመል ይወቃል እምአፈ አብዳን ትወፅእ በትረ ጽዕለት ጽዕለተ ብዑላን። ከመ ይደቅ ውስተ ጽዕለት። ክብሩ ብእሲ ተከልኦ ምጽዕለት (ሢራ። መዝ ፻፳፪ ፩ጢሞ ፫ ፡ ፯። ምሳ፳ ) ጥለት ማለት ከዚህ የወጣ ነው
ጽዕብ ብት (ዕብ ጻቡዕ። ዐረ ፀቡፅ) ነጣቂ አውሬ፤ የዥብ የውሻ ወገን፤ ማሽ ፋሪ መቃብር ቈፋሪ ሬሳ እያወጣ የሚበላ ባለብሉዮች ግን ተቈናጣጭ ዝንብ ይሉታል።
ጽዕደት ጽዕደት፤ መጣድ፤ ፡ (ጥጣ) መጣድ፤ አጣጣድ ጥዶሽ፤ በቁሙ ጥደት፤ ምጣድ፤ ዝርግ ክብ የሸክላ የብረት። ዲያቆናት ግን በጽዕደት ፈንታ ጽዕዱት ይሉታል፤ ስሕተት ነው
ጽዕዳዌ (ውያት) መንጣት፤ መጥራት፤ ንጣት ጥራት፤ አነጣጥ፤ ነጭነት። እግዚአብሔር አክበረከ በጽዕዳዌ ጸጕር ጽዕዳዌ ፀምር። ጽዕዳዌ ወልታ ፡ (አፈ ፡ ተ፯ና ፡ ፲፪። ስንክ ፡ መስ፳፱) በጽዕዳዌ ፈንታ ጻዕዳ ጽዕዱት ይላል፤ ስሕተት ነው ስተርአየ ጻዕዳሆን ለእማንቱ ብትር ዕጹብ ዐይን ሥነ ጽዕዱቱ ፡ (ዘፍ፴ ፴፯። ሢራ፵፫ ፲፰)
ጽዕድው (ዋን ዋት ዱት) የነጣ የጠራ ኖራ የመሰለ ጽዕድዋን ርጋብ አእዱግ ጽዕድዋን። ጽዕዱት ወብርህት። ወጽዕዱት ይእቲ ከመ ባሕርይ ፡ (ስንክ ፡ ጥር፲፩። መሳ፭ ፲። ማሕ፰ ፭። ራእ፳፩ ፲፩)
()            ጽዕጥ ጽዒጥ ጥሩ ሽቱ። ጽዒጥ ዘጸዓጢ ጽዒጥ ወዕጣን ፡ (ዘፀ፴ ፳፭ና ፡ መቃ)
ጽዋዔ መጥራት፤ መጠራት፤ አጠራር ጥሪ ጩኸ ስም ዘጽሑፍ በእንተ ጽዋዔ ሕዛብ ደጉ ጽዋዔሆሙ። በካዕብ ጽዋዔ። በጽዋዔሁ ቅዱስ። ሠለስቱ ጽዋዔ ክርስቲያን መሲሓውያን ናዝራውያን ፡ (ዲድ ፡ ፴፫። ፊልክ ፡ ፭። ግንዘ ጢሞ ፩ ፡ ፱። መጽ ምስ)  
ጽዋዕ (ዓት) በቁሙ፤ ጥዋ ኵባያ ዋንጫ የመጠጥ መሣሪያ፤ ከሸክላ ንጨት ቀርን ማዕደን የሚሠራ የተጠሩ ዎች የሚጠጡበት ጽዋዐ ወይን ጽዋዐ ማይ ሪር ጽዋዕ ዘቍርባን ወኢይላእ ጽዋዐ እስከ ንፈራ። ጽዋዕ ዘብሩር። ጽዋዓተ ወርቅ (ኪዳ። ቀሌ ስንክ ጥር፳፩ ነ ፡ ፲፫። ኩፋ ፡ ፵፫። አስቴ፩ )
  መጠጥ፤ በጽዋ ተቀድቶ የሚሰጥ ያሰትይዎሙ ጽዋዐ ወሰተይኩ ጽዋዐ ይኅልፍ እምኔየ ዝንቱ ጽዋዕ ጽዋዐ ዘወሀበኒ ቡየ የኀድግ ዘእንበለ ስተይ (ኤር፲፮ ፯። ሱቱ ዕዝ፲፬ ማቴ፳፮ ፴፱። ዮሐ፲፰ ፲፪) ኮሰን ተመልከት
  ፍያል ምንዛህ፤ ጽንሓሕ። የፍያልን ፍች ተመልከት ጠታተ ሥጋ ወጽዋዓተ ወርቅ። ወገብረ ካዕበ ጽዋዓተ ወርቅ ምእተ ወያጸንዑ ኵሎሙ ጽዋዓተ ዘምሉእ ዕጣነ (፩ዜና ፡ ፳፰ ፲፯ ፪ዜና ፬ ፡ ፷። ራእ፭ ፰። ፲፭ ፯። ፲፮ )
ጽዉን (ናን ናት ውንት) የተጠበቀ፤ የተጠጋ፤ የተከበበ። ጽዉን አነ በጸሎትኪ (አርጋ ፡ )
ጽውዓ ጥሪ፤ አጠራር። ለጽውዓ እግዚአብሔር ፡ (ፊልጵ፫ ፲፬)
ጽዉም (ማን ማት ውምት) የጦመ ጦመኛ፤ ጦሙን የዋለ። ተንሣእኩ ጽዉምየ ይእቱ ጽዉሞ ወኢይብላዕ ፈንዎሙ ጽዉማነ (፩ዕዝ ፡ ፰ ፡ ፸። ሥር ፡ ጳኵ። ማቴ፲፭ ፴፪)
ጽዉር (ራን ራት ውርት) የተጫነ የተሸከመ። ጽዉራኒሆሙ ይረውጹ ፡ (ዮኤ፪ )
 ፡ የተያዘ ሸክም የኾነ ተርእየ ጽዉረ ለተወድዮ ውስተ መቃብር እግዚእነ ክርስቶትስ ጽዉር ውስተ ደዊሁ(ሃይ ፡  በ። አቡሻ ፡  ፵፯)
 ፡ ጡረተኛ አሮጌ ሽማግሌ ድውይ በሽተኛ ራሱን የጣለ
ጽዉዕ (ዓን ዓት ውዕት) የተጠራ የተሰየመ የታደመ (ሮሜ፩ ፮። ይሁ ፩። ማቴ፳ ፲፮)
ጽዩሕ (ሓን ሓት ይሕት) የተጠረገ፤ የተደለደለ፤ የቀና ቅን ትክክል ፍኖት ጽዩሕ ወርሒብ ኵሉ ብር ይከውን ጽዩሐ በኀቤነ ስመ ትሩፎሙ ጽይሕት ግብር ፡ (አፈ ፡ ተ፲፱ና ፳፮ ፊልክ )
ጽዩእ (ኣን ኣት ይእት) የገማ ግም ግማታም፤ የቈነሰ፤ የበሰበሰ። ጼና ጽዩእ ደመና ጽዩእ ወጸሊም በረድ ይሁዳዊ ዕልው ወጽልሕው ወጽዩአ ወርኩሰ ናፍር ልቃ መዋዕልየ እንዘ ጽዩኣት። ኵሉ ሰብእ ያንሶስዉ ዕለ ብድንት ወላዕለ ጽዩእ ስከ በልዑ ጽዩአ (ግንዘ። ስንክ መስ፲፰ ሲኖዶ ኢዮ፲፯ ፲፩። ዮሴፍ)
ጽያሕ (ሓት) ጥርጊያ፤ አውራ መንገድ ታላቅ ጐዳና፤ እሾኽ ዕንቅፋት የሌለበት። ጽያሐ ንጉሥ (ቄር ፡ )
ጽያቄ መጤቅ፤ ጢቅታ፤ ምራቅ፤ መርዝ ሰብቅ ተንኰል
ጽዮን (ዕብ ጺዮን) ስመ ሀገር፤ የኢያውሴዎን አንባ፤ ዳዊት የያዛት፤ ሀገረ ዳዊት። ፍችው ጸወን፤ ምልክት ማለት ነው (መዝ )
ጽዱል (ላን ላት ድልት) የጸደለ፤ የበራ ብሩህ ንጹሕ ጽሩይ። ይበርህ በበርሃን ጽዱል። ማኅቶት ጽዱል። ዋክብት ብሩሃን ወጽዱላን። ጽዱላት ከመ ዛቲ ሜላት ጽድልተ ሥን ፡ (ጥበ፲፯ ፲፱ ስንክ ጥር፲፰ ድጓ አርጋ አፈ ተ፲፬)
ጽዱቃዊ እውነተኛ፤ ርግጠኛ፤ የበቃ፤ እሙን ይደልወነ ንእመን ዘይትበሀል በእንተ ቅዱሳን ምዜናውያን ወጽዱቃውያን (ፊልክ ፡ ፲፮)
ጽዱቅ (ቃን ቃት ድቅት) የጸደቀ የታመነ የተረዳ፤ የቀና የተካከለ። ቃል ጽዱቅ ዘኢኮነ ጽዱቀ። ሃይማኖቱሰ ትርፍት ወጽድቅት። ወመዳልዊከኒ ርቱዐ ወጽዱቀ ይኩን ፡ (ዘፀ፳፫ ፰። ቄር ፫ ፡ ፮። ዘዳ፳፭ ፲፭)
ጽዱፍ (745) (ፋን ፋት ድፍት) የወደቀ ገደል የገባ። የቸኰለ፤ የተጣደፈ፤ ችኵል።
ጽድቅ (ቃት) በቁሙ እውነትኛ ርግጥ ቅንነት፤ የሚገባ ነገር፤ ሕግ ትእዛዝ፤ ባሕርያዊ መጽሐፋዊ ሥራ ዘየሐውር በንጹሕ ወይገብር ጽድቀ። የዐስየኒ እግዚ በከመ ጽድቅየ ኢኮነ ጽድቀ በሊዕ ዘስርቅ ወኢያማሰነ ምንተኒ ምአምሳለ ጽድቅ። ኢዐቀብክሙ ኵሎ ጽድቃቲሁ አላ አግዘፍክሙ ክሣደክሙ። ሀበኒ ዘአልብየ እምጽድቃቲከ ሐደ በከመ ወሀብከ መካን ወልደ (መዝ ፡ ፲፬ና ፲፯ ጦቢ፪ ፡ ፲፫። ሃይ አበ ኤጲ ባሮክ። ስንክ ፡ ሚያ፲፯)
ጽድፈት መውደቅ፤ አወዳደቅ። ጥድፊያ ቅልጠፋ ችኰላ
ጽጕ [1]( ጽጐጕ፤ ጓት) አፍኣ ደጅ ሸንጎ አደባባይ፤ መተላለፊያ። ያንሶሱ ጽጐ ዖዱ ጽጐ ወጽጐ ሀገራ። ዱፍ ውስተ ጽጐ ሀገር ውስተ ጽጐጕ ወምሥያጣት እንዘ የኀልፍ ጽጐጐ ረከበ ብእሴ ቅቱለ ወኢያስሕትከ ጽጐጕሃ በእንተ ፍናዋት ወጽጐጓት ወመራሕብት (ዘፀ፳፩ ፲፱ መክ፲፪ ፡ ፭። ራእ፳፩ ፳፩ ስንክ ጥቅ፱ አፈ ፡ ተ፳፰ ስንክ ፡ መስ፲፰ ሢራ፱ ፯። ፴፯)
[2]ሽጕ ሽግ ችቦ ዳቦት፤ የጭራሮ የቅጥቅጥ፤ ፋኖስ፤ እውጭ ሲወጡ የሚያበሩት። አዘዘ ያውዕይዎሙ በመኃትወ ጽጕ ወይሕርር ሥጋሆሙ ወሖሩ ህየ በመኃትወ ጽጕ (መቃ ገ፪ ዮሐ፲፰ )
ጽጉብ (ባን ባት ግብት) የጠገበ ጥጉብ፤ ሆዱ የመላ፤ የረካ ጽገብ አነ መሥዋዕተ ሐራጊት ጽጉባነ ሐሊብ። ጽጉባነ ኵሉ ዐመፃ ጽግብት ፍስ ጸቃውዐ መዓር ትሜንን (ኢሳ፩ ፲፩። ሔኖ፶፩ ፬። ሮሜ፩ ፳፱ ምሳ፳፯ )
  የተጠገበ፤ የተሰለቸ፤ የተጠላ።
ጽጉይ (ያን ያት ጊት) ያበበ አበባ የያዘ የተሸከመ፤ አበባማ ባላበባ ክሊል ጽጉይ ጽጉያነ ምዑዝ ረዳ ጽጉያነ በረከት። ክዳን ጽጉይ ትርሲተ ሰማይ ጽጊት ፡ (አርጋ ፬። ስንክ መስ፴ ድጓ። ፪ነገ ፲፫ ፲፰ ስንክ ፡ ታኅ፯)
ጽጋብ (ባት) በቁሙ፤ ጥጋብ፤ ምልአተ ርሥ ጽጋብ ይምጽአኒ መዋዕለ ጽጋብ። እለ የአምሩ ጽጋበ ፡ (ሢራ፳፫ ፮። ዘፍ፵፩ ፳፬ ኢሳ፶፮ ፲፩)
ጽጋዌ መስጠት፤ መሰጠት፤ አሰጣጥ፤ ስጦታ ልገሳ፤ ሰጭነት፤ ለጋስነት። ኢአመዝገነ ጽጋዌነ ዕሌሁ ንመውአከ በአሠንዮትነ ወንጼግወከ ጽጋዌ። አኮ በህላዌ አላ በጽጋዌ ፡ (ዮሴፍ መጽ ፡ ምስ)
ጽጌ (ጌያት ገያት) አበባ፤ የፍሬ ምልክት፤ ውበት ደም ግባት ያለው። ጽጌየኒ ፍሬ ክብር ወስብሐት። ጽጌ ንጐላት። ርእዩ ጽጌያተ ገዳም ሰርጎካ ለምድር በሥነ ጽገያት (ሢራ፳፬ ፲፯ ማሕ፪ ማቴ፮ ፳፰። ድጓ) በጽጌ ፈንታ ጽጋይ ጽጋያት ይላል የቀድሞ ልማድ ነው ድሙረ ጽጋይ ፡ (ዘፀ፳፰ ፲፬) ርእስ ወይም ጽሩይ በማለት ፈንታ ጽጌ ይላል፤ ስሕተት ነው ጽጌ ርቤ ፡ (ዘፀ፴ ፳፫)
  ያበባ ምሳሌ፤ መልክ ጌጥ፤ በሸክላ በንጨት በደንጊያ በብረት የሚቀረጥና የሚነጠጥ በጥፈት በስፌት፤ በቀለም በግብረ ምእናም የሚሠራ ወጽጌያቲሃ እምውስቴታ ይትገበር (ዘፀ፳፭ ፴፩)
  መፀው፤ ወርኀ ጽጌ ዘመነ ጽጌ ቀን መስከረም ፳፮ እስከ ኅዳር ፮። ማሕሌተ ጽጌ ዋዜማ ዘጽጌ። ሰንበት ዘጽጌያት ፡ (አዋል)
ጽግነት (ታት) የሌት ወፍ የሌት አውሬ ሌሊት የሚያይ የሚወጣ ፡ (ዘሌ፲፩ ፲፱ ዳ፲፬ ፲፰) አክይስት ማለት  ፈንታ ጽግነት ይላል፤ የተሳሳተ ነው ኮንኩ እኍሆን ለጽግነት ወቢጾን ለአዕዋፍ ፡ (ኢዮ፴ ፳፱) ዕብራይስጡ ግን ኮንኩ እኅወ ለአክይስት ወቢጸ ለአዋልደ ሰገኖ ይላል።
ጽግን (ዐረ ድጅን ድጅም) ጭጋግ ጭጋጋም፤ ጉማም፤ የቀን ለማ ያለበት።
ጽግው (ዋን ዋት ጉት) የተሰጠ የተሰጠው ሀብታም፤ ድላም።
ጽጓጕ ጽጋግ በቁሙ፤ ጭጋግ ጭጐጐት
ጽፈር ጽፍራት፤ ጥፍሮች፤ ሰኰኖች ሰኰናዎች ጽፈሪሁ ከመ ንስር ጽፋረ አዴከ ዘሕበሪሆን ጸዐዳ ጽፍራተ ደዊሆሙ ወእገሪሆሙ ፡ (ዳን ፡ ፬ ፡ ፴። ደራሲ። ስንክ ሐም፰ና ፳፭) ሌላውም በጥፍር አምሳል የተሠራ ኹሉ ጥፍር ይባላል። አዘዘ ይሥትርዎሙ በአጽፋረ ጺን ከመ ይዘርዘር ሥጋሆሙ ፡ (ስንክ ፡ ታኅ፲፪)
ጽፈን አጽፋን የውሃ ዕቆች።
ጽፉር (ራን ራት ፍርት) የተጣፈረ ጥፍሩን የቈረጠ፤ የተቈረጠ።
ጽፉቀ በዝቶ ጽፍቅ ኹኖ ተጻፍቆ ተጫንቆ።
ጽፉቅ (ቃን ቃት ፍቅት) የተጨፈቀ፤ ጽፍቅ የኾነ፤ ብዙ፤ ጭፍቅ፤ ጥቅጥቅ ያለ የተወሳሰበ። ታሕተ ኵሉ ጽፉቅ ዘቦ ጽላሎት። ዕፅ ዘጽፉቅ ቈጽሉ አዕዋም ጽፉቃት እለ ያጸልሉ ወረከበ ዕፀ ጽፍቅተ ፡ (፫ነገ ፡ ፲፬ ፳፫ ሢራ፲፬ ፲፰ ጥበ፲፯ ፲፯ ተረ ባሮ)
ጽፉን የተጨፈነ ጭፍን፤ ጨፋና ዕውር
ጽፉዕ (ዓን ዓት ፍዕት) የተጸፋ የተጠፈጠፈ ፊቱ በጥፊ የተመታ
ጽፍሕ ስፋት ወርድ፤ስፍሕ ሰፍሐ። ፡ (ዘፀ፳፭ ፲፯ ፡ ፳፫ ፳፮ ፰ ፡ ፲፮። ፳፯ ፩ ፡ ፲፪ )
ጽፍር (ዕብ ጺፎሬን ሱር ጥፋር ጢፍራ ዐረ ጡፍር) ጥፍር፤ አፍኣዊ ዐጥንት፤ የጣቶች ቀንድ ነጭ ስለታም። ይምትር ጽፍሮ ጽፍረ ደዊከ ወእገሪከ (ቀሌ። መቃ)
  ሰኰና፤ ሸኾና፤ ጥቍር፤ ክብ ንፍቅ፤ ጽፍቅ፤ የእንስሳት ያብቈለ ቀርነ ወጽፍረ ጽፍረ ሕም ዘሥጡቅ ጽፍሩ (መዝ ፡ ፷፰። ኢሳ፲፫ ፳፪ ዘሌ፲፩ )
ጽፍቀት መጨፈቅ፤ ፡ (ጥጨ) መጨፈቅ፤ አጨፋፈቅ፤ ጭፈቃ ጨፈቃነት፤ ብዛት፤ ጽፍቅነት።
ጽፍነት (ታት ዐረ ጸፍነት) የሥንቅ አቅማዳ፤ ቍናማት ፋዳ፤ ረጆ ፊኛ ማፉዳ የገንዘብ መያዣ፤ ኹለንተናው ርበት የኾነ መልአት ጽፍነታ ጥሕነ ወወደየቶ ውስተ ጽፍነታ ዘእክል። ወኢጽፍነተ (ዮዲ፲ ፭። ፲፫ ፲ ፡ ፲፭ ማቴ፲ ፲። ማር፮ ፰። ሉቃ፱ )
ጽፍዐት (ታት) መጽፋት፤ መጸፋት፤ አጸፋፍ፤ ጽፋት፤ የመዝሙር አባባል። በጥሬ መምታት መመታት፤ አመታት፤ ምት፤ ጥፊ፤ የጥፊ በትር መዘምር መድኀኔ ዓለም ተምህረ ጽፍዐተ እንዘ በእዴሁ ይእኅዝ ጸናጽለ ጺን ቀኖተ። ንዑ ትርአዩ ጽፍዐተ መላትሕ ምገብር ጽፍዐተ ወልድኪ (ቅኔ። ቅዳ ፡ ኢሳ፶ ፮። አርጋ )
ጽፍጹጥፍ የተነጠፈ የተጸፈጸፈ ልቡጥ። ወጽፍጹፍ በእብን ዘሕብረ መረግድ። መካን ጽፍጹፍ በርኳም (አስቴ፩  ፮። ዮሴፍ)
ጾሀር (ዕብራ) ፉካ፤ ላዕላይ መስኮት፤ አፈ ፡ ድስት የኾነ፤ ጮራ ጨረር፤ ጸዳል ምዕዛር የፀሓይ እግር የሚገባበት።
ጾላዕ (ዐረ ጹላዕ። ዕብ ሴላዕ) ቋጥኝ ገዎቻ፤ ታላቅ ደንጊያ መርግ ርድ ገደል ዋሻ ኰኵሕን ተመልከት። ከመ ብነ ጾላዕ ጾላዕኒ ሐሠረ ይመስሎ ፡ (ኢዮ፵፩ ፲፭ ሢራ፳፪ ፩። ድጓ)
ጾላእ ቋጥኝ፤ጸውልዐ፤ ላዕ
ጾላዕት ጸዋልዕት ዋሾች፤ ዋሻዎች ቋጥኞች መርጎች ገደሎች ወጾላዕት ምጕያዮን ለግሔ። ጾላዕት ተሠጥቁ። ዐርጉ ውስተ ጸዋልዕት። ድምፀ ጸዋልዕት እለ ያንኰረኵሩ በግርማ ፡ (መዝ ፡ ፻፫ ቀሌ። ኤር፬ ፳፱ ጥበ፲፯ ፲፰)
ጾመ ጦመ፤ጸዊም ጾመ።
ጾማዕት [1](ታት ዐረ ጸውመዐት) ዋሻ፤ በኣት፤ የመነኵሴ ቤት፤ የባሕታዊ ቦታ እለ ውስተ ጾማዕት ቦኡ ኀበ መነኮስ እን ሀሎ በጾማዕቱ ጾማዕተ ባሕታዊ ወየኀሥሡ ተዘግሖ ውስተ ጾማዕታት፤ እንዘ አልቦ ውስቴታ ረባሕ ፡ (አርጋ ፡ ፯። ፈላስ። ስንክ ፡ ሚያ፳ ፊልክ ፪፻፵፩)
 [2] ዋሻ በኣት፤ጸወማዕት
ጾም በቁሙ፤ ጦም፤ ምግብ መተው ጾምሰ ተከልኦተ ብእሲ መብልዕ በጊዜ ዕዉቅ ጾመ ረቡዕ ወጾመ ሙስ ፡ ( ነ ፡ ፲፭ ዘካ፰ ፲፱ መዝ ፡ ፴፬)
ጾር [1]( አጽዋር) ሸክም፤ ጭነት፤ ቀንበር ዕዳ ግብር ግፍ ጡር ተይዞ የሚኼድ የሚወሰድ ነገር። ጾር ክቡድ። ጾረ ክልኤቱ አብቅል ትገድፍ ጾሮ ምላዕለ ክሣድከ አዶኒራም ዕለ ጾር ኢታንሥኡ ምንተኒ ጾረ ፡ (ሢራ፳፩ ፲፮ ፬ነገ ፭ ፡ ፲፯። ዘፍ፳፯ ፵። ፪ነገ ፳፬ ኤር፲፯ )
[2]ጮራ፤ መረር፤ የፀሓይ እግር ቀርኑ ምዕዛሩ
[3]በቁሙ፤ ጦር፤ ዘገር፤ ሐርበኞች የሚሸከሙት። ኵናትን ተመልከት
[4] የሰሌን ሙሽራ፤ ጦር የሚመስል። በቀልት ወጾር ፡ (ስንክ መጋ፪)
ጾታ [1](ታት፤ ጸዋትው ሱር ጺውታ፤ ጻውታ፤ ኅብረት አንድነት ጉባኤ) ተራ ረድፍ ክፍል ማዕርግ ዐይነት ስልት ወገን ነገድ፤ የቅዳሴ ጸሎት፤ ጓዝ፤ ከሚ መጠን እስከ አኰቴተ ርባን ያለው። አርባዕቱ ጾታሁ ጾታ ዘእብን ወጾታ ላእካኒሁ። ጸዋትወ መሪር ወጣዕም ፈቱ ስማዕ ዐሠርተ አውታረ ዜማሆሙ ወጾታሆሙ በበ ጾታት ፍሉጣት። ጸዋትዊሆሙ፤ መላእክት። ጸዋትወ ቅዳሴ ፡ (ዘፀ፳፰ ፲፯፳። ዜና ፱ ፡ ፬። ደራሲ ስንክ ሐም፰ ፍ ፡ መቅ አርጋ ፬። አዋል)
 [2] ተራ ረድፍ፤ጸዊት ጸወተ
ጾጥ (ዕብ ጢጥ ዐረ ፀዊጠት) ጭቃ ዐዛባ አንቃህከ በድነ ራውያ ምጾጥ (ስንክ ፡ ሠኔ፲፭)

No comments:

Post a Comment

ማውጫ

ሀ   ለ   ሐ   መ   ሠ   ረ   ሰ   ሸ   ቀ   በ   ተ   ቸ   ኀ   ነ   ኘ   አ   ከ   ኸ   ወ   ዐ   ዘ   ዠ   የ   ደ   ጀ   ገ   ጠ   ጨ   ጰ   ጸ   ፀ   ፈ   ፐ