ሀ ለ ሐ መ ሠ ረ ሰ ሸ ቀ በ ተ ቸ ኀ ነ ኘ አ ከ ኸ ወ ዐ ዘ ዠ የ ደ ጀ ገ ጠ ጨ ጰ ጸ ፀ ፈ ፐ
በ [1]፡-ኹለተኛ ፊደል፤ በግእዝ አልፍ ቤት በአበገደ። ስሙ ቤት፤ ቍጥሩ ኹለት፤ አኃዝ ሲኾን በ ክልኤት ቱ ይባላል። ዕብራውያን ግን፤ ኹለትን መደብ አድርገው ከራሱ ላይ ነቍጣ እየጨመሩ ኹለት እልፍ ይሉታል። ኹለተኛ ማለት፤ ምስጢሩ ሰኞንና የሰኞን ፍጥረት መደብ አድርጎ ኹለተኛውን አካል ወልድን ያሳያል ፡-(ዘፍ፩ ፡-፮–፰)።
[2]፡-(ደቂቅ አገባብ) በቁም ቀሪ ፥ ማድረጊያ ን ፥ ጋራ ፥ ቸልታ ፥ ጊዜ ፥ ለ ፥ ወደ ፥ እንደ ፥ ስለ ይኾናል። ማድረጊያ ሲኾን በኹሉ ይገባል፤ የቀረውን ባገባብ ተመልከት ፡-(ዕር፳፩። ቍ–፻፱)።
በሓ ባሕ ፡-(ዐረ በኅ አይዞኽ) የሰላምታ የቡራኬ ቃል፤ ፍሥሓ ፥ ሰላም። እንዴት ዋልኽ እንዴት አደርኽ፤ ጤና ይስጥኽ፤ ደስታ ሰላም። ላንተ ይኹን፤ ጠላትኽን ያውድቅ ቢሰኛኽን ያርቅ ማለት ነው፤ በሓከ ኪ፤ በሓክሙ ክን እያለ በቅርብ በቅርቦች ይዘረዝራል። ኢትበሎ በሓ ወአመ ይቤለከ በሓ። በሓ በልዋ ተሳለምዋ። ወበሓሂ ኢትበልዎ። ባሕ ሄርማ። ኢትበልዎሙ ባሕ ፡-(፬ነገ ፡-፬ ፡-፳፱። ድጓ። ፪ዮሐ ፡-፲። ሄርማ፩ ፡-፪። ቀሌ)። በሓከ ባሮክ። ባሕከ ሄርማ። በሓኪ ማርያም። በሓክሙ አበው ቅዱሳን። ባሕክን አው በሓክን ፡-(ራእ ፡-ባሮ። ሄርማ ፡-ገ፳፩። ደራሲ። ማቴ፳፰ ፡-፱)።
በሃሊ ፡-(ሊት ልያን ያት፤ በሀልት) ያለ የሚል የሚናገር፤ ባይ ተናጋሪ፤ አልኹ ባይ እንዲሉ። ከመ ኢይኩን በሃሌ አነ አብዐልኩ አብራምሀ። ኦሆ በሃሊ። ወእመሰ ይቤ በሃሊ። በሀልተ ጽድቅ ፡-(ኩፋ ፡-፲፫። ያዕ፫ ፡-፲፯። አፈ ፡-ተ፳፮። አዋል)።
በሃም ፡-(ምት ማን ማት) ድዳ፤ መናገር የማይችል፤ ከድምጥ በቀር ፍሬ ቃል የማይሰጥ። ኮነ ጽሙመ ወበሃመ እምአውሥኦትክሙ። ኢትከውን እንከ በሃመ። ወከመ በሃም ዘኢይከሥት አፉሁ። ለበሃማን ኮኖሙ ቃለ ፡-(ግንዘ። ሕዝ፳፬ ፡-፳፯። መዝ ፡-፴፯። ኪዳ)።
በሐተ ፡-(ዋሐደ። ዐረ በሑተ፤ ጥሩ ኾነ) ባተ ገባ ተሾመ፤ ተዠመረ ተቈጠረ፤ የወር ያመት። ብቸኛ ኾነ፤ ከሰው ተለየ ተነጠለ፤ እንደ መባቻ ቀን አንድ ተባለ። መጽሐፍ ግን በበሐተ ፈንታ ባሕተወ ይላል።
በሀነ ፡-(ይብህን ይብሀን ብሂን። ዕብ ባሐን፤ ፈተነ) በነነ ቡን አለ፤ የዶቄት ያመድ የትቢያ
በሐኵ ፡-በሐዂ፤ ፡-(ብ አባሐዂ፤ አብሓዂ) የበግ የፍየል ተባት፤ አውራ፤ ኰርማ የሚታዘል የሚንጠለጠል። በሐዂ እንዘ ይሜብል ላዕለ መርዔት። በሐኵ ወዳቤላ። ዳቤላት ወአባሕኵ። አባሕኩ አባግዕ። አባሕኵ ዘአባግዕ ወዘአጣሊ ፡-(ምላ፳፬ ፡-፷፮። ሕዝ፴፬ ፡-፲፯። ፴፱ ፡-፲፰። መዝ ፡-፷፬። ዘፀ፴፩ ፡-፲ ፡-፲፪። ፴ ፡-፴፭)።
በሕቁ [1]፡-በጅጉ፤ በጥቂቱ፤–ሐቂቅ ሐቀ፤ ሐቀቀ፤ ሕቅ።
[2]፡-በጥቂቱ፤ በጅጉ ባያሌው።
በኍበኈ ፡-(ብሕአ) ቦኽቦኸ፤ ቦነቸ ል በሰበሰ፤ ተበላሸ፤ ነቀዘ ጠነጠነ፤ ተላ፤ ገማ ከረፋ በሸቀጠ፤ የንጨት የግንድ ፥ የገላ የቍስል። በኍበኈ ሥጋየ በዕፄያት። በቍስለ ኀጢአት ሥጋየ በኍበኈ ወጼአ ፡-(ኢዮ፯ ፡-፭። ስንክ ፡-ነሐ፳፩)። ይበልዕ ፥ ይትከዐው በማለት ፈንታ ይበኈብኍ ይላል ስሕተት ነው ፡-(ኢዮ፲፰ ፡-፲፫። ሕዝ፯ ፡-፲፯። ፳፩ ፡-፯)።
በሕብሐ ፡-በሕብሐ፤ ፡-(ዕብ ቃራጽ፤ ቀረጸ) ሣለ መሰለ፤ ዐነጠ ቀረጠ፤ ሠራ ፈጠረ፤ የቡሖ የጭቃ፤ የዳቦ የብስኵት፤ የሠምዕ የልሕኵት።
በለሳን ፡-(ዐረ በልሳን። ዕብ ባሳም። ጽር ሚራ። ሮማይ ባልሳኑም) ሽቱ፤ የሽቱ ዕንጨት ስም፤ በይሁዳና በገሊላ ይልቁንም በኢያሪሖ የሚበቅል፤ ከዕፀወ ዕጣን አንዱ መዠመሪያው ፥ ሽታው ከሽቱ ዕንጨት ኹሉ የሚበልጥ፤ ጳጳሳት ቅብዐ ቅዱስ ሜሮን የሚያደርጉት። ዝንቱ በለሳን ዘተከልናሁ ይነብር ዝየ እስከ ለዓለም። ቅብዐ በለሳን። በእንተ በለሳን ወዕጣን። ተኀትመ ገጾ በቅብዐ በለሳን። በለሳነ ኮነ ሀፈ ሥጋሁ በቍሎ ፡-(ስንክ ፡-ግን፳፬። ዲድ ፡-፲፯። ቅዳ። ግንዘ። ሕዝ፳፯ ፡-፲፯። ደራሲ)።
በለስ ፡-(ብ በለሳት፤ አብላስ። ዐረ በለስ። ዕብ ባላስ) በቁሙ፤ የተክል ዕንጨት ስም፤ ከወይን ጋራ የሚተከል፤ የሾላ ወገን ወተታም። ዕንጨቱም ፍሬውም በለስ ይባላል። ዘተከለ በለሰ ይበልዕ ፍሬሃ። እምበለስ አእምሩ አምሳሊሁ። ቦ በለስ እምርት ውስተ ዐጸደ ወይን። አውያን ወአብላስ፤ ዛፍ ፡-(ምሳ፳፯ ፡-፲፰። ማቴ፳፬ ፡-፴፪። ሉቃ፲፫ ፡-፮። መጽ ፡-ምስ)። ረከቡ በምሥያጥ በለሰ ሐዲሰ ወተሣየጡ እምኔሁ። ረከበ እልኩ በለሳተ ሐዲሳነ። ወመልአት ጽፍነታ ጥሕነ ወበለሰ፤ ፍሬ ፡-(ስንክ ፡-ሐም፳፬። ራእ ፡-ባሮ። ዮዲ፲ ፡-፭)። በለስ፤ ፍሬ በለስ፤ በኵረ በለስ በማለት ፈንታ፤ ዐጽቀ በለስ፤ በለሰ ማእረር ይላል፤ ስሕተት ነው ፡-(ኤር፳፬ ፡-፪)። ዳግመኛም በስግላ ፈንቃ በለስ ይላል፤ ሰግላን ተመልከት። ዕፀ በለስ። ተቃራሜ በለስ ሾላ ፡-(፪ዜና ፡-፱ ፡-፳፯። ዓሞ፯ ፡-፲፬)።
በለሶን ፡-ዕፀ አእምሮ፤ የገነት በለስ፤ አዳምና ሔዋን ፍሬውም በልተው ቅጠሉን የለበሱት፤ ኋላም የልደት ለት በታምራት መልአክ አምጥቶላት፤ ዳግሚት ሔዋን ለልጇ ለዳግማይ አዳም ያለበለችው። ክደነቶ እሙ ቈጽለ በለሶን ፡-(ድጓ። ኩፋ ፡-፫። ዘፍ፫ ፡-፯)። ፡-(ሥላሴ ቅኔ) በለሰ ገነት ለአዳም ወሔዋን መቲሮተቶሙ መንክረ ልደት አምላከ መንገሌሆሙ ሰሐበ፤ ወገብርኤልሀ ዜናዌ ቀጸበ። እንተ ከመ ዝሰ ግብር እምከመ ለአዳም ተውህበ ፥ ወረከበት ሔዋን ዘኢተረክበ ፥ ካዕበ ይስሐብ ኀቤሆሙ አበ ፥ ለበለስ ይምትርዎ ካዕበ።
በለዝ ፡-(ጽር ቦሎዝ። ዕብ ቦዐዝ) የዐምድ ስም፤ ሰሎሞን በመቅደሱ ደጅ አፍ በበረንዳው በደጀ ሰላሙ ካቆማቸው ከኹለቱ አዕማድ አንዱ በስተስሜን ያለው የግራው ዐምድ። ቦ ዕዘዝ ፥ ሎ ዕዘዝ ፥ ኀይሉ ወጽንዑ ዕዘዙ ለመቅደስ ማለት ነው፤ ባለብሉዮች ግን ርትዕ ይሉታል ፡-(፫ነገ ፡-፯ ፳፩)። .
በለድ ፡-(ትግሬ ወዐረ) የተወለዱበት አገር።
(ጥ) በሊኅ ፡-(ኃን ኃት ላኅ) የበላ የሰላ የሾለ፤ ስል ሹል፤ ትብ፤ ደፋር ጨካኝ፤ ፈጣን ብልኀተኛ፤ ጽሩይ ረቂቅ። መላጺ በሊኅ። ሰይፍ በሊኅ። ቀኖት በሊኅ። ኵያንው በሊኃን። ስባራተ ማህውበሊኃት። በበሊኅ ልሳን። ብእሲ በሊኅ በምግባሩ። በሊኅ እገሪሆሙ ለክዒወ ደም። በበሊኅ ዐይነ ልብክን ትነጽራ ፡-(መዝ ፡-፶፩። ራእ፩ ፡-፲፮። ግብ፱ ፡-፭። አርጋ። ሢራ፵፫ ፡-፱። ስንክ ፡-መጋ፬። ምሳ፳፪ ፡-፳፱። መዝ ፡-፭። ቄር)። በበላኅ ፈንታ ብልኅት ይላል፤ አያሰኝም። ዘሩን መስሎ የሚገኝ ቅጽል ፥ ኀጺር ነዊኅ፤ ገዚፍ ጸሊም፤ ጠቢብ ሐኪም፤ ጸቢብ ርሒብ፤ ረቂቅ ቀጢን፤ ይህን የመሰለ ኹሉ መንገዱ አንድ ነው፤ ከብዙዎች በቀር ላንዲቱ ሴት ምእላድ የላትም። ቅጽልነቱም ሣልስና ሳድስ ያለበት ቱሲሕ ውስጠ ዘ ስለ ኾነ፤ ኀጻሪ ነዋኂ ገዛፊ ጸላሚ ጠባቢ ረቃቂ፤ ወይም ንዉኅ ጥቡብ ርቁቅ ቅጡን አያሰኝም። አንዳንድ ጊዜ ግን ሣልስ ትቶ በሳድስ ብቻ፤ ኅጹር ግዙፍ ጽሉም እያለ ይገኛል።
(ላ) በሊኅ ኆት ፡-(በልኀ ይበልኅ ይብላኅ) መብላት፤ መስላት፤ መሾል፤ መፍጠን፤ ስል ሹል ፈጣን መኾን። ይበልኅ እምሰይፍ። ሚ ይበልኅ እምሠርት። በልኀት ኵናት ፡-(ዕብ፬ ፡-፲፪። ፈላስ። ሕዝጃ፳፩ ፡-፲፩)። ይበዝኅ ይጸንዕ በማለት ፈንታ ይበልኅ ይላል ፡-(ዘፀ፲፱ ፡-፲፱)።
፡-መበለኅ፤ ብልኅ ዐዋቂ መኾን፤ መባል እገሌ ምላጭ ነው እንዲሉ ፡-(ዐማርኛ)።
በሊል ሎት ፡-(በለ ይበልል ይብልል፤ ትግ በለለ። ዕብ ባላል) መብለል፤ ማብለል፤ ማጥፋት፤ ማበላሸት፤ መደባለቅ፤ መዘባረቅ፤ መቀላቀል፤ ማመሳቀል፤ መንከር ማራስ ማርጠብ ማበስበስ፤ ማማሰል፤ መለወስ። በልየና በልበለ የዚህ ዐጽቆች ናቸው።
በሊቅ ቆት ፡-(በለቀ ይበልቅ ይብልቅ፤ ትግ በልቀ። ዕብ ባላቅ፤ ለየ ከፈለ) መባለቅ፤ ለዘር መብቃት፤ ማደግ መጐልመስ፤ በሕልም ወይም በውን ዘር ማፍሰስ ሴት መዳሰስ።
በሊን በሊኖ ፡-(ዕብ ባልናር) ልብሰ ቤተ ምኅፃብ፤ ጠጕራም ፎጣ፤ ታላቅ መንዲል፤ መክፌ፤ ሠርመዲ። በሊን ዘፀምር። በሊኖ ፡-(አቡሻ ፡-፶። ሲኖዶ)።
በሊዕ ዖት ፡-(በልዐ ይበልዕ ይብላዕ። ዕብ ባላዕ። ሱር ብላዕ። ዐረ በሊዐ፤ ዋጠ) መብላት፤ መጕረሥ፤ መንከስ፤ መጋጥ መግመጥ፤ ማላመጥ መዋጥ፤ መሰልቀጥ፤ ምግብን በገዛ እጅ ሰጪና ተቀባይ መኾን፤ መዝገብ መሰብሰብ፤ መቀበል መክተት፤ የሕያው ፍጥረት፤ አከለን እይ። በሊዕ ወሰትይ። ያደዊ ብዝኀ በሊዕ። ብላዕ በዐቅም ፡-(መክ፭ ፡-፲፯። ሢራ፴፯ ፡-፴። ምሳ፳፭ ፡-፲፮)።
፡-ማቃጠል ማንደድ፤ መፍጀት ማረድ፤ ማጥፋት መጕዳት። በልዐቶሙ እሳት። በልዐቶሙ መጥባሕት።ፈኖከ መዐትከ ወበልዖሙ ከመ ብርዕ። ቅናአተ ቤትከ በልዐኒ ፡-(ሆሴ፯ ፡-፯። ኤር፪ ፡-፴። ዘፀ፲፭ ፡-፯። መዝ ፡-፷፰)።
፡-ማማት መንቀፍ፤ መቀማት መዝረፍ። በሊዐ ሥጋ ቢጽ በሐሜት። በልዕዎ ለእስራኤል። ይበልዑ ስጋሆሙ ለሕዝብየ ፡-(ቀሌ። ኤር፲ ፡-፳፭። ሚክ፫ ፡-፫)።
በላቲ ፡-(ቲት ትያን ያት) የሚበልት በላች፤ በጋማች፤ ሥጋ ቤት፤ ዐራጅ ባለወግ።
በላዒ ፡-(ዒት ዕያን ያት ላዕት) የሚበላ የሚያቃጥል፤ በላተኛ ሆዳም፤ አጥፊ ዘራፊ። ይወድቁ ውስተ አፈ በላዒ። በላዒተ ሰብእ አንቲ። ነበልባለ እሳት በላዒ። ሥሡዓን በላያን። በላዕተ ሰብእ ፡-(ናሆ፫ ፡-፲፪። ሕዝ፴፮ ፡-፲፫። ኢሳ፳፬ ፡-፮። መቃ ፡-ገ፱። መጽ ፡-ምስ)።
በላዪ ፡-(ዪት ይያን ያት) የሚያረጅ፤ የሚያልፍ የሚጠፋ። እስመ ውእቱ ግብር በላዪ ወዘይማስን። ዓለም በላዪ ፡-(ጥበ፲፬ ፡-፰። ስንክ ፡-ጥቅ፳። ኅዳ፲፰)።
በል ፡-ትእዛዝ፤–ብህለ፤ ቤለ ይቤ። ቤልከ ትቤ ትበል በል።
በልሐ ፡-ተሳለ፤–በልኀ።
በልቀም ፡-(ዐረ በልዐም) መሬታዊ ባሕርይ፤ የሚዝል የሚደክም፤ የሚተኛ የሚጋደም። ላሕስሐን ተመልከት ፡-(ፈላስ ፡-ገ፲፮)።
በልበለ [1]፡-አረጀ፤–በሊል በለ። በልየ።
[2]፡-(የበልየና የበለ ዲቃላ። ዕብ ባልቤል) አረጀ አፈጀ፤ ዐለቀ ተበጣጠሰ፤ የልብስ የምንጣፍ የመሣሪያ። በልይንና በሊልን ተመልከት።
(ጥ) በልቶ ቶት ፡-(በለተ ይቤልት ይበልት። ዐረ በለተ፤ ቈረጠ። ዕብ ቢልቲ፤ ብቻ ያለ) መበለት፤ መለየት መነጠል፤ ሥጋን በየብልቱ ማውጣት። ማደኽየት፤ ድኻ ብቸኛ ማድረግ፤ ብቻ ማስቀረት።
በልይ ዮት ፡-(በልየ ይበሊ ይብለይ። ዕብ ባላህ። ሱር ብሊይ። ዐረ በሊየ) ማርጀት ማፍጀት፤ መለወጥ መበላሸት፤ መበስበስ መበጣጠስ፤ ማለፍ መቅረት፤ ማለቅ መጨረስ፤ መጥፋት መታጣት፤ ዘንዱ ይበለይ ነው፤ በለየ ካላለ ይብሊ አያሰኝም፤ ኀረየንና ፈረየን ጸገየን ተመልከት። ኵሉ ዘነፍስ ይበሊ ከመ ልብስ። ኵሉ ግብር ይበሊ ወየኀልቅ። በልየ ሥጋየ ወማእስየ። ክብርየ ተወለጠ ወበልየ። ወበልየ ነገር እምኔሆሙ ፡-(ሢራ፲፬ ፡-፲፯ ፡-፲፱። ሰቈ፫ ፡-፬። ዳን፲ ፡-፰። ኢዮ፴፪ ፡-፲፭)።
በልግ ፡-(ዐማርኛ) የበጋ ዝናም፤ ጸደይ።
በሰከ ፡-(ዐማርኛ) በቲክ በተከ፤ በጠሰ። ሰና ተ ይዋረሳሉ፤ ይልቁንም በዐረብ በሱርስት፤ ሶር ቶር።
በሲል ሎት ፡-(በሰለ፤ ይበስል ይብስል። ዕብ ባሻል። ሱር ብሼል) መብሰል፤ መሟከክ መንደርከክ፤ በእሳት በፀሓይ መለስለስ፤ ተጋግሮ ተነፍሮ ታምሶ ተጠብሶ ለመበላት መድረስ፤ ለጥርስ መግራት፤ መሸት መጐምራት። ኢበልዐት ምንተኒ በእሳት ዘበሰለ። ሠዊት ዘበሰለ። ዘእንበለ ደብስል ፡-(ስንክ ፡-ጥቅ፩። ኢሳ፲፯ ፡-፭። ኤር፴፩ ፡-፴፪)
በሲስ ሶት ፡-(በሰ ይበስስ ይብስስ) መበሰስ ማደን፤ በሳስ መኾን፤ የወሬ ያውሬ። በስበሰን እይ፤ የዚህ ዲቃላ ነው። ማለዘብ ማለስለስ፤ የነገር የልብስ።
በሣሪ መበሥር ፡-የሚያበሥር አብሣሪ፤ ወሬ ነጋሪ፤የምሥራች ባይ። ገብርኤል መበሥር ፡-(ሰንክ ፡-ታኅ፳፪)።
በሥሮ ፡-(ጥ) ፡-(በሠረ ይቤሥር፤ ይበሥር) አው በሢር፤ ሮት፤ ፡-(በሠረ ይበሥር ይብሥር። ዐረ በሺረ። ዕብ ባሤር) ማብሠር፤ የምሥራች ማለት፤ ሐዲስ የደስታ ወሬ ማውራት መንገር፤ መልካም ትንቢት መናገር። ሥጋ ማልበስ፤ ሥግው ማድረግ፤ ምስጢረ ሥጋዌን መስበክ ማስተማር፤ በወሬ በትንቢት ማስፈሣት፤ ደስ ማሰኘት። መጻሕፍት ግን በበሠረ ፈንታ አብሰረ ይላሉ ባስደራጊና በሳቱ ሰ ያማርኛ ነው፤ ሆከን አወከ እንደ ማለት። ገብርኤል አብሣሬ ትስብእትከ። አብሠራ ለማርያም። አብሠሮ ለዘካርያስ በእንተ ልደቱ ለዮሐንስ። ወንጌለ መንግሥት ያበሥር ፡-(ቄድር። መዋሥ። ስንክ ፡-ታኅ፳፪። ፈላስ)። ብርስንና ምስር የሚጣፍ። በሳት ሰ ነውና ሠዉም በዚህ ምክንያት ተሳስቷል።
በስብሶ ሶት ፡-(በስበሰ ይበሰብስ ይበስብስ። ዐረ በጸ፤ በጽበጸ። ዕብ ባጻጽ ባጽቤጽ፤ ፈለቀ መነጨ) መክፈት መግለጥ ማቍለጭለጭ፤ የዐይን። መነስነስ መቍላት ማወዛወዝ፤ የዥራት። በቁሙ መበስበስ፤ መራስ ፣መርጠብ፤ መበላሸት ፡-(ዐማርኛ)። በኍበኈን እይ። ዘሩ በሲስ በሰ፤ በሰሰ ነው።
በሶንስ በሸንስ ብሸንሶ ፡-(ቅብጥ ፓሾንስ) የግብጦች ወር ግንቦት። ብሸንሶ ይሰመይ በሰንጹስ፤ ወካዕበ ይሰመይ ማኹን ፡-(አቡሻ ፡-፰)።
በረሓ ፡-በቁሙ፤ ምድረ በዳ ፡-(ዐማርኛ)።
በረምሃት ፡-(ቅብጥ) ዝኒ ከማሁ፤ ስመ ወርኅ መጋቢት። በጽርእ ፋሚኑት ይባላል። በረምሃት ይሰመይ ፋሚኑት ፡-(አቡሻ ፡-፰። ተረ ፡-ቄር፳፭)።
በረረ ፡-(ሰረረ) በቁሙ፤ ሮጠ ከነፈ ተጣደፈ። ዐለፈ ዘለቀ፤ በሳ ነደለ። ወፅአ ኀጺኑ በሪሮ። ረገዞ ለአሐዱ ውስተ ሰንበዑ ወወፅአት ኵናት በሪራ እንተ ዘባኑ ወወግአቶ ለካልኡ። በረረ ቅትራት ውስተ እገሪሁ። በረሮ እስከ ዘባኑ። ኢይበርሮ ቀስተ ብርት ፡-(፪ነገ ፡-፪ ፡-፳፪። ገድ ፡-ተክ። ስንክ ፡-ነሐ፲፬። መሳ፫ ፡-፳፪። ኢዮ፳ ፡-፳፬)።
በረቅ ፡-በቁሙ፤ ነጭ ዐፈር ደንጊያ፤ ብሕካ ጠመኔ የኖራ ዐይነት።
በረከት ፡-(ታት) በቁሙ፤ ማበርከት፤ መበርከት፤ አበረካከት፤ ብርከታ ብዛት። ምስጋና ምርቃት፤ ቡሩክ መባል ጸጋ፤ ጸጋ ፥ ሀብት ፥ ድልብ ዐላባ፤ መልካም ነገር ኹሉ። በረከተ ኅብስት። በረከተ አሮን ፈኑ ላዕለ ሕዝብከ። ክብር ወስብሐት ወበረከት። ኵሉ በረከት እለ ባረከኒ እግዚ። በረከተ ግብጽ። ትበልዑ ቤረከተ ፡-(ትር ፡-ወን። ሢራ፴፮ ፡-፳፪። ራእ፭ ፡-፲፪ ፡-፲፫። ኩፋ ፡-፲፱። ዘፍ፵፭ ፡-፲፰። ኢሳ፶፭ ፡-፪)።
በረየ ፡-በቁሙ፤ ፡-(ጥየ) በረየ፤ በረገገ በሬኛ ወገሸ ደነበረ፤ ፈራ ደነገጠ። ፡-(ተረት) እባብ ያየ ልጥ ቢያይ በረየ። አበራየ አረባየ፤ አኼደ አስኬደ አስረገጠ አስጠቀጠቀ። ማበራየት ያውድማ፤ ማረባየት የጤፍ ዕርሻ ነው፤ መሬቱ እንዲጠብቅ ከብት ይነዱበታል። በሬ በረት ባሪያ ባሬታ ማለት ዐማርኛው ከዚህ ወጥቷል፤ በዐረን እይ። የወዲያኛው ትግሬ ሐባብም ክሕደ ሲል በረየ ይላል፤ ምስጢሩ ፈራ ደነገጠ ካለው ይገባል።
በረድ [1]፡-(ብ አብራድ። ዕብ ባራድ። ሱር ባርዳ። ዐረ በረድ) በቁሙ በረዶ የዝናም ደንጊያ የውሃ ጠጠር፤ በነፋስና በደመና ወንጭፍ ከላይ ከሰማይ የሚወርድ የሚወረወር ዝናመ መዐት፤ መጠኑ የበጠጥ ከዚያም የሚበልጥ፤ የሚዛን ዐዋቂ የሚያካክል ፡-(ዘፀ፱ ፡-፲፰። ኢሳ፴ ፡-፴። ሕዝ፴፰ ፡-፳፪። ራእ፲፮ ፡-፳፩)። ወገሮሙ እግዚ እምሰማይ በእብነ በረድ። ሞፀፈ መዐቱ ያወርድ አብራደ ፡-(ኢያ፲ ፡-፲፩። ጥበ፭ ፡-፳፫)።
፡-ሰው ሠራሽ ምድራዊ በረዶ፤ በመኪና ከውሃ ለይተው የሚያወጡት ግንድ ግርንቡድ የሳንቃ ስባሪ የሚያካክል።
[2]፡-በረድ፤ ፡-(ዕብ ሼሌግ ቄራሕ) ብትን በረዶ፤ ውርጭ ዐመዳይ ተበትኖ ወርዶ የሚረጋና የሚጋገር፤ ባዘቶ ንድፍ የሚመስል ፡-(መዝ ፡-፻፵፯ ፡-ኢዮ፮ ፡-፲፮)። በረድ ወአስሐትያ። ቈረ ከመ በረድ። ኣጻዐድዎ ከመ በረድ። በረድ ይዘንም ላዕለ ሰልሞን ፡-(ጥበ፲፮ ፡-፳፪። ኩፋ ፡-፳፫። ኢሳ፩ ፡-፲፰። መዝ ፡-፰)።
[3]፡-በረድ፤ ነጭ የብርሌ የብርጭቆ ዐይነት፤ ንጣቱ የረጋና የተጋገረ ውርጭ የሚመስል። አርኣያ ዘሕብረ በረድ። ባሕር ከመ እንተ በረድ ፡-(ሕዝ፩ ፡-፳፪። ራእ፬ ፡-፮)። የእብንን አፈታት ተመልከት።
በረጽ ፡-(ዐረብ) ለምጽ፤ ነጭ የሚብለጨለጭ።
በሪህ ሆት ፡-(በርሀ ይበርህ ይብራህ። ዐረ በሪሀ፤ በሀረ። ዕብ ባሀር) መብራት፤ መበራት፤ መታየት መገለጥ፤ ብርሃን መኾን ደስ ማሰኘት። ምንት ይበርህ እምነ ፀሓይ። ኢይበርሁ ከዋክብተ ሰማይ። ይበርሁ ከመ ብርሃነ ሰማይ። ወይበርህ ሎሙ ብርሃነ አምላክ። ወምድር በርሀት እምስብሐቲሁ። ዘይገብር ምጽዋተ እንዘ ይበርህ ገጹ። በርሀ ልቦሙ ወኅሊናሆሙ ፡-(ሢራ፲፯ ፡-፴፩። ኢሳ፲፫ ፡-፲። ዳን፲፪ ፡-፫። ሔኖ፩ ፡-፰። ሕዝ፵፫ ፡-፪። ቀሌ)።
በሪር ሮት ፡-(በረ ይበርር ይብርር። ዕብ ባራር። ሱር ባር። ዐረ በረ፤ በሪረ) መምረጥ መለየት፤ መልቀም ማጥራት፤ ጽሩይ ጸዐዳ ማድረግ፤ የማዕደናት። በርበረን እይ።
በሪቅ ቆት ፡-(በረቀ ይበርቅ ይብርቅ። ዕብ ባራቅ። ሱር ብራቅ። ዐረ በረቀ) መብረቅ ብልጭ ማለት፤ መፍለቅ ማንጸብረቅ፤ መወርወር መመዘዝ፤ የመብረቅ የሰይፍ። ብርቅ ድንቅ ታይቶ የማያውቅ መኾን፤ መታየት መገለጥ። በሪጽና በሪቅ አንድ ዘር ናቸው፤ በሪጽ ከበሪቅ ወጥቷል። በዕጠሱ ይበርቅ ብርሃን። ወላትው ይበርቅ። በረቀ ሥጋሆሙ። ግብተ በረቀ መብረቅ ዲቤሁ እምሰማይ ፡-(ኢዮ፵፪ ፡-፱። ናሖ፫ ፡-፫። መቃ ፡-ገ፪። ድጓ። ግብ፬ ፡-፫)። መበርቋት መገርጣት፤ ያዝመራ።
በሪዕ ዖት ፡-(በርዐ ይበርዕ ይብራዕ። ዐረ የሪዐ። ዕብ ያራዕ) መራድ መንቀጥቀጥ፤ መታወክ መናወጥ፤ መገፋት መናጥ፤ መወዛወዝ፤ ከፍርሃት ከንፋስ የተንሣ ፡-(ማቴ፲፩ ፡-፯)።
በሪክ ኮት ፡-(በረከ ይበርክ ይብርክ። ዕብ ባራኽ። ሱር ብሬኽ። ዐረ በረከ) መብረክ፤ መብረክረክ፤ መንበርከክ፤ ጕልበትን ማጠፍ በጕልበት መቆም፤ መስገድ፤ ተንበርክኮ መኼድ፤ ተጣጥፎ መተኛት ፡-(ጥኰ) መኰድኰድ ፡-(ዘኍ፳፪ ፡-፳፯)። ሶበ በጽሐ ገመል ኀበ ውእቱ መካን በረከ በብረኪሁ ወኢተንሥአ ፡-(ስንክ ፡-ነሐ፲፱)።
በሪዝ ዞት ፡-(በረዘ ይበርዝ ይብርዝ። ዐረ። ዕብ ባራዝ) ማግለል መለየት ዕዳሪ መውጣት ለመናጻት። መበረዝ መበጥበጥ ጠጅ መጣል፤ ጠላ መዘለል፤ ፈሳሽን ከፈሳሽ መቀላቀል።
በሪድ ዶት ፡-(በረደ ይበርድ ይብርድ። ዕብ ባራድ። ዐረ በሩደ) መብረድ መቀዝቀዝ፤ በረዶ መኾን መውረድ መርጋት፤ የዝናም የውሃ። በረዶ መምሰል፤ በረዶ መልበስ በውርጭ በበረድ መሸፈን መታፈን፤ የደጋ የተራራ እንደ የወልና እንደ ቧሒት።
በሪጽ ጾት ፡-(በረጸ ይበርጽ ይብርጽ። ዕብ ባራጽ፤ ዐለፈ ተረፈ፤ ፈልቶ ገንፍሎ) ማንጸብረቅ ማሸብረቅ፤ ማወልወል ማጽደልደል፤ የመልክ የፊት።
በራ ፡-ስመ ኪሩብ ገጸ ሰብእ፤ ወልዳዊ ወልደ ሰብኣዊ ማለት ነው። ፪ኛም ፥ ባር ብሎ ጐሽ የበረሓ እንስሳ ይላልና፤ ገጸ ላሕምንም ያሳያል። ፫ኛም ፥ ባርቡር ብሎ ዐንገተ ረዥም ወፍ ዋነተኛ የባሕር አሞራ ይላልና፤ ገጸ ንስርንም ያሳያል። ፬ኛም ፥ በርና ዕጓል አንድ ናቸውና፤ ዕጓላዊ ዕጓለ አንበሳዊ አሰኝቶ ገጸ አንበሳን ያሳያል። በራ መራ መሊጦን ሱርትዮን ፡-(መዋሥ)።
(ጥ) በራህ ፡-በራ መላጣ፤–በርሐ።
በራሕ ፡-(ሓን ሓት) በራ መላጣ፤ ራሰ ገላጣ፤ ጠጕሩ የሸሸ ከቦታው የታጣ፤ የራሱ ቈርበት መሳልና ነት ሳንባና ጕበት የሚመስል ፡-(ዘሌ፲፫ ፡-፵። ፬ነገ ፡-፪ ፡-፳፫)። ለኤልሳዕ ነዊኅ ቆሙ ወበራሕ ርእሱ ፡-(ስንክ ፡-ሠኔ፪)። በረኸኛ የበረሓ ሰው፤ ዐዳኝ መነኵሴ።
በራሪ ፡-(ሪት ርያን ያት) በቁሙ፤ የሚያልፍ የሚዘልቅ።
በራቂኒም ፡-(ዕብ ባርቃኒም) ነጫጭ እሾኾች ኰሸሽሎች፤ ወይም ግራሮች የግራር ዐይነቶች፤ አንዱን ባርቃን ይላል። አርቆሚንን እይ፤ ከዚህ ጋራ አንድ ነው ፡-(መሳ፰ ፡-፲፮)።
በራዲ ብሩድ ፡-የበረደ በራድ፤ ብርዳም በረዷም፤ በሪድ ቀዝቃዛ።
በር [1]፡-በቁሙ፤ ደጅ አፍ መውጫ መግቢያ መዝለቂያ ማለፊያ ፡-(ዐማርኛ)። ነቅጸን ተመልከት።
[2]፡-(ሱር ወዕብ ባር) ወንድ ልጅ፤ ተማሪ ደቀ መዝሙር። በር ጤሜዎስ። በር ባን ፡-(ማር፲ ፡-፵፮። ማቴ፳፯ ፡-፲፮)።
በርህ ፡-(ሃት) ብርሃን ጸዳል ውጋጋን። እሳት ፍሕም ነበልባል። በርህ ሠረቀ ለጻድቃን። በርህ ወጽልመት ፡-(መዝ ፡-፺፮። ዳን፯ ፡-፵፯። ድጓ)። ይስኅን መንገለ በርህ ፡-(ማር፲፬ ፡-፶፬። ሉቃ፳፪ ፡-፶፮)። በርህ እሳት መባሉ መላሾች በእሳት ቦታ ስለ ጣፉት እንጂ ፍችው ኹኖ አይዶለም።
በርሖ ሖት ፡-(በርሐ ይቤርሕ ይበርሕ፤ ዐረ በሪሐ። ዕብ ባራሕ፤ ሸሸ) መብራት መገለጥ፤ መቦሕየት፤ በራ መኾን መመለጥ፤ መሸሽ ማምለጥ፤ መሮጥ መፈርጠጥ፤ ከዱር ከበረሓ መግባት። ስንሐንና ቀርሐን ተመልከት፤ የዚህ ጎሮች ናቸው።
በርሙዳ ፡-(ቅብጥ) የወር ስም ሚያዝያ፤ በጽርእ ፊርሙ(ቲ) ኒ ይባላል ፡-(ገድ ፡-አዳ። አርጋ ፡-፪ ፡-፮)። በርሙዳ ይሰመይ ፈርሙኒ ፡-(አቡሻ ፡-፰። ተረ ፡-ቄር)።
በርሞስ ፡-አስቄጥስ የነመክሲሞስ የናርሳንዮስ ገዳም፤ ደብረ ሮም ገዳመ ሮም ማለት ነው ፡-(ስንክ ፡-መጋ፳፭)።
በርበሪ ፡-በርበራዊ የበርበር ሰው።
በርበሬ [1]፡-(ዐረ ፊልፊል ባባሪ) ቍንዶ፤ ቍንደዶ ጠጕር ያረረ የተኰማተረ። ቍንዶ በርበሬ፤ መልኩ የበርበርን ጠጕር የሚመስል። ቍንዶ መባልን ከሻንቅላ ጠጕር ወስዶታል፤ መመሳሰል የጋራ ነውና። ገብር ጸሊም ይቤ አርኣያየ ጸሊም ወጸጕረ ርእስየ በርበሬ ፡-(ፈላስ፤ ገ ፡-፰)።
[2]፡-(ጽር ፕፕሬ) በቁሙ፤ ቀዮ በርበሪ በርበራዊ ከበርበር የመጣ የበርበር አታክልት። ስሙ ፍልፍል ሲኾን ከበርበር አገር ስለ መጣ በርበሪ ሬ ይባላል፤ ይኸውም ጐንደሬ፤ በጌምድሬ እንደ ማለት ነው፤ ዐደስ ከምስር አገር ስለ መጣ፤ ምስር ፥ ግብጥ ምስር እንዲባል ፡-(መጽ ፡-ፈው)። በፕፕሬ አንጻር ሲፈቱት ግን ቀይሕ እሳታዊ ነበልባላዊ ማለት ነው፤ በርበራዊነቱ ሳይቀር መልኩንም ግብሩንም ያሳያል፤ ፐፒራን ተመልከት። ፡-(ሙሾ በቴዎ ጊዜ) በሺዋ። በትግሬ በወሎ በላስታ በጐዣም ያላችኹ ፥ አንድ እግር በርበሬ መንቀል ተስኗችኹ ፥ ተኵሶ ለብልቦ አቃጥሎ ይፍጃችኹ። ቍንዶውም ቢኾን እንደ ቍራ ኋላ ይጥቈር እንጂ ጥንቱን ሲያፈራ ቀይ ነው ይባላል።
በርበር [1]፡-ዘረፋ ምርኮ፤ የብርበራ የዘረፋ ገንዘብ። እሬስየኪ በርበረ ለአሕዛብ። እለ ይትካፈሉ በርበረ ፡-(ሕዝ፳፭ ፡-፯። ኢሳ፱ ፡-፫። ምሳ፩ ፡-፲፫)።
[2]፡-ያልተማረ ያልሠለጠነ ሕዝብ፤ ፊደልና ጽሕፈት ሕግና ሥርዐት የሌለው በቅሚያ የሚኖር ጭንጩ አረመኔ፤ ሽፍታ ወያኔ። ስመ ነገድ ስመ ሀገር፤ ከግብጽ ቀጥሎ የሚገኝ የአፍሪቃ ክፍል። የሱማሌም አገር በርበራ አቅኝውና ዘሩ የበርበር ቍራጭ ነው ይባላል፤ በርበርነቱንም ግብሩ ይመሰክራል። ወመጽኡ በርበር አረማውያን ከመ ያመዝብሩ አብያተ መነኮሳት። በመጥባሕተ በርበር ተቀትሉ። አዘዞ እግዚእነ ከመ ይሑር ሀገረ በርበር ፡-(ስንክ ፡-ጥቅ፳። ጥር፳፮። ሠኔ፳፮። መስ ፡-፩)።
በርቢር ፡-(ዕብ ቦር፤ ብኤር) ዐዘቅት፤ የውሃ ወይም የእኽል ጕድጓድ፤ ዋሻ ጐሬ መቃብር፤ ውስጡ የተቦረቦረ ፡-(ሕዝ፴፪ ፡-፲፰። ፴፬ ፡-፲፪ ፡-፲፭)።
በርባሪ ፡-በርበራዊ የበርበር ሰው።
በርባር ፡-የዛፍ ስም፤ ብርብራ ቅጠሉና ፍሬው ዓሣ የሚያሰክር ባሕር የሚያሸብር።
በርባሮስ ፡-(ጽር ቦርቦሮስ) ዝኒ ከማሁ፤ ታላቅ ሰፊ ጕድጓድ፤ ዕመቀ ምድር መሠረተ ምድር፤ የጥልቅ ጥልቅ መጨረሻ ዕመቅ ፡-(አዋል)።
በርብሮ ሮት ፡-(በርበረ ይበረብር ይበርብር። በሪር በረ በረረ) መበርበር መዝረፍ፤ መበዝበዝ፤ የቤትን ድልብ በቤት ያለን ገንዘብ ጐርጕሮ መውስድ፤ ባዶ ማስቀረት። ጕድጓድ ቈፋሪ ዐፈሩን አውጥቶ ውስጡን ባዶ እንዲያደርግ እንደዚያ ማለት ነው። አልቦ ዘይክል በዊአ ቤተ ኀያል ወበርብሮ ንዋዩ እመ ኢቀደመ አሲሮቶ ለኀያል፤ ወእምዝ ይበረብር ቤቶ። እበረብሮሙ ኀይሎሙ። በርብሩኒ ኵሎ ንዋይየ ፡-(ማር፫ ፡-፳፯። ኢሳ፲ ፡-፲፫። ጦቢ፩ ፡-፳። መዝ ፡-፻፰)።
በርዮድስ ፡-(ጽር ፔሪዎዶስ) ቀመር፤ የቀመር ስም፤ የጨረቃ ቢኾን ፲፱፤ የፀሓይ ቢኾን ፳፰ ዓመት። ሲያበዛ በርዮድሳት ይላል ፡-(አቡሻ ፡-፳፭)።
በርደደ ፡-በረደደ፤ ረጋ ጸና፤ ደነገየ፤ በርዳዳ ኾነ። መታ ቀጠቀጠ፤ ሞረደ። ወበአእባን ሥጋሁ በርደዱ ፡-(ስንክ ፡-ግን፰)።
በቀለ ፡-(ዐቢይ አገባብ) ስለ፤ ፈንታ። ብፁዕ ዘይትቤቀለኪ በቀለ ተበቀልክነ ፡-(መዝ ፡-፻፴፮። ዕር፲፱ ፡-ቍ፷፱)።
በቀል ፡-(ላት) በቁሙ፤ ቅጣት የክፉ ብድራት፤ ዕዳ ፍዳ፤ ቂም ደም። እትቤቀሎሙ አርባዕተ በቀለ። እትቤቀል በቀለ ህየንተ አዕይንትየ። ከመ ያግብኡ በቀል እምኀበ እግዚ ለምድያም። በቀለ እኁሁ ፡-(ኤር፲፭ ፡-፫። መሳ፲፮ ፡-፳፰። ዘኁ፴፩ ፡-፫። ፪ነገ ፡-፫ ፡-፳፯)።
በቀልት ፡-(ታት) ሰሌን ዘንባባ፤ ፍሬው ተዘርቶ የሚበቅል፤ ቁመታም። ዘቆምኪ ይመስል በቀልተ። ወፈረየት ይእቲ በቀልት ዐሠርተ ወክልኤተ አስካለ ሶቤሃ። በቀልተ ተመርት። በቀልታት ወተምራት። በቀልታተ ወፀበራተ አሥዐለ ፡-(ማሕ፯ ፡-፯ ፡-፰። ስንክ ፡-ሚያ፳። ኢዮ፳፱ ፡-፲፰። ስንክ ፡-ጥር፳፪። አርጋ ፡-፬)። በቀልት ግንዱ፤ ፀመርት ቅጠሉ ፥ ተምር ፍሬው። ፀምርንና ተምርን ተመልከት።
በቍላ ባቌላ ባቄላ ፡-(ዐረ ባቂለን፤ ባቂላእ) በቁሙ፤ ባቄላ ፉል፤ ያበባ እኸል፤ በቈልት የሚኾን። ፡-(የውርድ ነዥ ስድብና ምላሽ) ከሰው ክፉ ዲቃላ፤ ከእኸል ክፉ ባቄላ፤ ከልብስ ክፉ ነጠላ። ጠላት ይገፋል ዲቃላ፤ ወራት ይገፋል ባቄላ ያግደረድራል ነጠላ።
በቍላዊ ፡-የቡቃያ የተክል፤ ተክላም ባለተክል። ኀይል በቍላዊ ወእንስሳዊ ፡-(አዋል)።
በቍል ሎት [1]፡-(በቈለ ይበቍል ይብቍል። ዐረ በቀለ) መብቀል ማጐንቈል፤ ካፈር ከመሬት መዛመድ መዋሐድ፤ መጽደቅ ሥርን ወደ ታች ቅጠልን ወደ ላይ መስደድ፤ መፀነስ መቋጠር መወለድ መፈጠር፤ መሥረጽ መውጣት። ይበቍል ውስቴቱ ሣዕር ወሦክ። ኢበቈለ ሥርዎሙ። ይበቍል ክነፊሆሙ። ይበቍሉ ከመ ሣዕር። ሦክ ወአሜከላ ይብቍልከ ፡-(ኢሳ፭ ፡-፮። ፵ ፡-፳፬ ፡-፴፩። ፵፬ ፡-፬። ኩፋ ፡-፫። ዘፍ፫ ፡-፲፰)።
[2]፡-በቍል፤ ፡-(ላት፤ አብቋል) ቡቃያ፤ በቈልት ብቅል፤ያታክልት ፍል ችግኝ ግልግል፤ እኽል ተክል ሣር ቅጠል፤ ሳይዘሩት የሚበቅል ማናቸውም ኹሉ። ይሴሰይ በቍላተ ምድር። አሕማላተ በቍላት። በቍላት ቀታልያን። ሥዕርተ ርእስከ ዘስሙር አብቋሉ ፡-(ስንክ ፡-ጥር፳፰። ግን፲። ፍ ፡-ነ ፳፫። ደራሲ)።
በቂቅ ቆት ፡-(በቀ ይበቅቅ ይብቅቅ) መሠንጠቅ፤ መተርተር፤ ዕዳሪ ማውጣት የርሻ።
በቍዔት ፡-ልመና ምልጃ ጸሎት፤ በጸሎትና በልመና የሚገኝ ጥቅም። አንተ ተወከፍ ዘኵልነ ሰክዮተ ወበቍዔተ ፡-(ሊጦን)።
በቍዕ ዖት ፡-(በቍዐ ይበቍዕ ይብቋዕ። በቀወ) መብቃት፤ መኾን መገባት፤ መርባት መጥቀም ግዳጅ መፈጸም፤ መርዳት አይዞኽ ማለት፤ ልመናን ምልጃን መስማት መቀበል፤ ዕሺ በጎ ማለት። ምስክሩን በተራው ተመልከት። ይሥሐቅ ይበቍዕ ለዛቲ ሢመት። ዘይበቍዕ ለምግበ ንዋዩ። ምንት ይበቍዕ ሠዊዕ ለአማልክት። ዐርክ ወማኅፈር ይበቍዕ በመዋዕሊሆሙ። እግዚ በቍዐነ በኵሉ። እስእለክሙ ብቍዐኒ። ብቍዐኒ ከመ ትገብር ፡-(ስንክ ፡-ኅዳ፱። ፍ ፡-ነ ፡-፴፪። ሢራ፴ ፡-፲፱። ፵ ፡-፳፫። ዮሴፍ። ፩ጴጥ ፡-፪ ፡-፲፩። ፩ዕዝ ፡-፬ ፡-፵፮)። አንዳንድ መጽሐፍ በተበቍዐ ፈንታ በቍዐ ይላል፤ አያሰኝም። ትሬእዩ ከመ አልቦ ዘትበቍዑ። አልቦ ዘበቋዕኩ። አልቦ ዘይበቍዕ ዘይረቂ። ፈቀደ ይትባረክ ይብቋዕ እምኔከ ፡-(ስንክ ፡-መጋ፳፪። ፩ቆሮ ፡-፲፫ ፡-፫። መክ፲ ፡-፲፩። ፊልክ ፡-፶፮)።
በቂው ዎት ፡-(በቀወ ይበቁ ይብቁ። ዐረ በቀ። ዕብ ባቃዕ፤ ከፈተ) መክፈት፤ መለቀቅ፤ ክፍት መኾን ዋሻ መምሰል፤ ለመጕረሥ ለመከተት፤ የአፍ የጕድጓድ። በቀወት ምድር ወውኅጠቶ ለዳታን። መጽሐፍ ግን አብቀወት ይላል፤ አያሰኝም ፡-(መዝ ፡-፻፭)። ለቀወን እይ።
በቍጽ ጾት ፡-(በቈጸ ይበቍጽ ይብቍጽ) ማንደድ ማቃጠል፤ ማያያዝ ማጋም፤ ማፋም ማምረት ማብሰል ማንደርከክ፤ መጫር መተርከስ፤ መዝገን ማፈሥ፤ የከሰል የፍም። ነሃቢ ዘይበቍጽ አፍሓመ። ወይበቍጹ አፍሓመ ፡-(ኢሳ፶፬ ፡-፲፮። ዮሐ፲፰ ፡-፲፰)።
በቃሊ ፡-(ሊት ልያን ያት) የሚበቀል ተበቃይ፤ ቂመኛ ደም መላሽ ብድር ከፋይ። መጽሐፍ ግን እንዳማርኛው ተበቃሊ ይላል። እግዚ ተበቃሊ ለእለ ይትገፍዑ እምእደ ገፋዕያኒሆሙ። ይገፍዖ እግዚ ለገፋዒ ወይትቤቀሎ ለተበቃሊ ፡-(መቃ ፡-ገ፮። ቀሌ)።
በቅል ልት ፡-(ዐረ በቅል። ዕብ ፌሬድ) በቅሎ፤ አጋሰስ፤ ካህያ ከፈረስ የሚዴቀል አባቱ አህያ እናቱ ፈረስ። ተባቱና እንስቱ ዘር ለመስጠትና ለመቀበል ርስ በርሳቸው የማይገጥሙ የማይሰማሙ እጅግ ቅብጥብጦች ስለ ኾኑ መውለድና መርባት የላቸውም፤ ሲገናኙ ግን ይወልዳሉ፤ አንድ የሰላሌ ሰው በቅሎው ወልዳ ላፄ ምኒልክ ከነግልገሏ አምጥቶ እንዳሳየ። ፍችው መስተበቅል፤ አንዳንድ መምህራን ግን ሐዲስ ቡቃያ ይሉታል፤ ከጥንት ያልነበረ ማለት ነው። ፡-(ተረትና ቅኔ) በቅሎ ቢወልዷት እንጂ አትወልድ። እኔም እንዳላማ ልቁም ዐዋጅ ሲነገር፤ ምንይልኽ ሰብአ ሺዋ ቅኔ ተዘርቶ በቅሎ ቢቀር። ኢትኩኑ ከመ ፈረስ ወበቅል ፡-(መዝ ፡-፴፩)።
በቅል ፤ (ሱማሌ ሐረር ጕራጌ) ፤ የቍጥር ስም ፤ መቶ። ሸማኖችና ዝሓ አዝጊዎች ወይም ድር አድሪዎች መቶውን ጥንድ አንድ በቅል እንዲሉት።
(ጥ) በቅሎ ሎት ፡-(በቀለ ይቤቅል ይበቅል። ዐረ በቀረ። ዕብ ባቄር) መመርመር መጠየቅ፤ ግፍን በደልን መርምሮ ማወቅ፤ ማሰብ መቍጠር፤ ከዚህ የተነሣ መበቀል መቀየም፤ መቅጣት፤ ፍዳውን መስጠት ማስበበት። በለበቅ በጨንገር መግረፍ፤ ማስለፍለፍ፤ የሕፃንና የቤተ ሰብ ቅጣት። መጽሐፍ ግን በበቀለ ፈንታ አብቀለ ተበቀለ ይላል ባስደራጊና በተደራጊ አንቀጽ፤ ኹሉም ስሕተት ነው ፥ አያሰኝም፤ ተ ያማርኛ ነው። ሳብዕተ በቀለ ያበቅል። ዮጊ ኢትክል ተበቅሎቶ ለዘአበሰ። ዘይትቤቀሎሙ ለጸላእቱ ፡-(ዘፍ፬ ፡-፲፭። ሢራ፯ ፡-፮። ፴ ፡-፮)።
በቅበቀ ፡-በቀበቀ፤ ኰተኰተ፤ የማሽላ።
በቋሊ ፡-(ሊት ልያን ያት፤ ቈልት) የሚበቅል የሚሠርጽ፤ በቃይ፤ ዘር ቅንጣት።
በቋዒ ፡-(ዒት ዕያን ያት) የሚበቃ የሚጠቅም ጠቃሚ፤ ግዳጅ ፈጻሚ። ኮነ በቋዒ ለኵሉ። በቋዔ ተድላ። አኀው በምንዳቤ በቋዕያነ ይከውኑ። ኮኑ በቋዕያነ ከመ ይሥርዑ ንዋዮሙ ፡-(አርጋ ፡-፩። ኪዳ። ምሳ፲፯ ፡-፲፯። ፍ ፡-ነ ፡-፳፬ ፡-፫)። በበቋዒ ፈንታ ባቍዕ ፡-(ዕት ዓን ዓት) ይላል፤ ፍችው አንድ ነው። ባቍዕት። ባቍዓኒሃ። ባቍዓን ፡-(አርጋ ፡-፩። ዘካ፮ ፡-፲። ሄርማ)።
(ጥ) በበ ፡-(ደቂቅ አገባብ) በየ እየ፤ ደጊመ ቃል። ከተጸውዖ ስም በቀር በብትን ኹሉ እየገባ ይዘረዝራል፤ ሲዘረዝር እንዳለ በቁሙ ይፈታል፤ ባይዘረዝርም ተዘርዝሮ ወይም በደጊመ ቃል ይፈታል። በበ ነገዱ ወበበ ዘመዱ፤በበ አሐዱ፤ በየ እየ። በበ ነግህ በበ ሠርክ ጧት ጧት ፥ ማታ ማታ። በበ ዕለት፤ በየለቱ ፥ ዕለት ዕለት፤ ዘወትር።በበ ወርኅ በበ ዓመት፤ በበ በዓል፤ በበ ሕቅ በበ ንስቲት እያለ እንደዚህ ይፈታል። ነሥኡ በበ ዲናር፤ ድሪም ድሪም፤ አንዳንድ ድሪም። ፈነዎሙ በበ ክልኤቱ፤ ኹለት ኹለቱን ወይም ኹለት ኹለቅ አርጎ። ወረፈቁ በበ ምእት ወበበ ኀምሳ፤ ፻፻ው፤ ፶፶ው፤ ወይም ፻፻ና ፶፶ እየኾኑ ያሰኛል። ለለንና ዘዘን ተመልከት፤ የዚህ ጎር ናቸው።
በበ ሕቅ ፡-ጥቂት ጥቂት፤ በየጥቂቱ። በበ ሕቅ ልህቀ ፡-(ቅዳ ፡-ድጓ)።
በበ አሐዱ በበ አሐዱ አሐዱ ፡-በያንዳንዱ፤ በየብቻው፤ በየራሱ፤ በየራስ በየራሱ ፡-(ሱቱ ፡-ዕዝ፲፩ ፡-፳)።
በበበይኑ ፡-በበበይኑ፤ ፡-(በበ በይኑ) በየራሱ በየብቻው፤ ራስ ራሱ፤ ብቻ ብቻው። በበን ተመልከት። አናብስት መሠጥ ወመንኰራኵራት ዘበበ በይኑ ፡-(ስንክ ፡-መጋ፪)።
በበይነ ፡-(በ በይን) ዝኒ ዓዲ ከማሁ፤ ስለ። በ እንደ እን አዳማቂ ነው፤ ሥራ የለውም። በበይነ ነፍሱ ለዝንቱ ብእሲ። በበይነ ዚኣክሙ። አኮ በበይነ ወርቅ። በበይነ እግዚ። በበይነ መኑ። በበይነ ምንት ፡-(ዮና፩ ፡-፲፬። ሚክ፫ ፡-፲፪። ኢሳ፵፰ ፡-፲። ፳፱ ፡-፲፭። ፩ነገ ፡-፲፬ ፡-፴፰። ሚል፩ ፡-፪)።
በበይኑ ፡-በብቻው፤ በራሱ ወይም ለብቻው፤ ብቻውን።ጻማዊ ወፈጻሜ መልእክት ዘበበይኑ ፡-(ስንክ ፡-ኅዳ፬)።
በበይናቲሁ ፡-ርስ በርሱ፤ አንዱ ካንዱ ጋራ። በበይናቲሃ ከ ቲነ እያለ ይዘረዝራል። ተባሀሉ በበይናቲሆሙ። ተኣምኑ በበይናቲክሙ ፡-(ዘፍ፵፪ ፡-፳፩። ቅዳ)።
በበይናት ፡-በኹለት ወገን፤ በኹለት ክፍል፤ ኹለት ወገን ኹኖ።
በቢክ ፡-ፍሬ ዕፀ ገነት፤ አዳም ይበላው የነበረ ወይም እንዳይበላው በትእዛዝ እሾክ የታጠረ፤ ቢበሉት ቢያክ ቢያክ የሚያሰኝ ፡-(ገድ ፡-አዳ)።
በተነ ፡-(ይበትን፤ ዐማርኛ) በቁሙ በተነ በታተነ፤ ዘረወ ዘርዐ።
በቲር ሮት ፡-(በተረ ይበትር ይብትር። ትግ በትረ። ዕብ ባታር) መቍረጥ መከርከም፤ ማረቅ ማቅናት፤ ቀጥ ለጥ ማድረግ፤ የንጨት። መምታት መውቃት፤ መነረት። መተረን ተመልከት፤ የዚህ መንቲያ ነው።
በቲት ቶት ፡-(በተ ይበትት ይብትት። በልየ) መበተት፤ ብትቱ መኾን ማለቅ ማርጀት፤ የልብስ። በልበለን ተመልከት።
በቲክ ኮት ፡-(በተከ ይበትክ ይብትክ። ዐረ በተከ። ዕብ ባቴቅ፤ ናታቅ) መበተክ፤ መበሰክ፤ መቍረጥ መበጠስ፤ አባላ መምታት፤ መንቀል መፈንቀል፤ መናድ ማፍረስ፤ መስበር መሠንጠር። እበትክ ማኅሜከ። በተከ ማእሰረ ፡-(ነሐ፩ ፡-፲፫። ኤር፭ ፡-፭)። በበተከ ፈንታ አብተከ ይላል፤ አያሰኝም። ታበትክ ቃሎሙ በኀበ እግዚ ፡-(ዘፀ፲፰ ፡-፲፱)። ዕብራይስጡ ግን ውሄቤእታ ይላል፤ ታበውእ ታበጽሕ ታቀርብ ማለት ነው። መብተክ መብተክተክ፤ መብሰክሰክ፤ መበላሸት ከንቱ መኾን፤ የግብር የነገር ፡-(ዐማርኛ)።
በታሮን ፡-(ጽር ፓቴሮን) አበው፤ ከአዳም እስከ ኖኅ ያሉ ዐሥሩ አባቶች፤ ወይም ሌሎች። ደብረ በታሮን፤ ዘውእቱ ብሂል ደብረ አበው ፡-(ስንክ፤ ሠ፲፰)።
በትረ ብርዕ ፡-የሸንበቆ ምርኵዝ፤ ኅለት ውስጠ ክፍት ፡-(ሕዝ፳፱ ፡-፮። ኢሳ፴፮ ፡-፮)
በትረ ወርቅ ፡-ከወርቅ የተሠራ በወርቅ የተጌጠ የጳጳስና የንጉሥ በትር ፡-(አስቴ፭ ፡-፪። ፰ ፡-፬)።
በትረ ኅጺን ፡-የብረት ዘንግ፤ ባለብረት ጅንፎ፤ ጅንፏም በትር ፡-(መዝ ፡-፪። ራእ፪ ፡-፳፯)።
በትረ መሃፒል ፡-ዐጭር ወፍራም መንዶ፤ እንደ ጩንቻ እንደ መሮ መምቻ ያለ፤ ዐጣቢ ቀለም አግቢ ልብስ የሚመታበት ፡-(ስንክ ፡-ጥቅ፳፯)።
በትረ መዐት ፡-መቅጫ፤ ለበቅ ጨንገር፤ ረኃብ ጦር፤ ዐባር ቸነፈር ፡-(ኢሳ፲ ፡-፭)።
በትረ ነገድ ፡-የነገድ አለቃ በኵር ሹም፤ ግንባር ቀደም ፡-(፩ነገ ፡-፱ ፡-፳። ስንክ ፡-ግን፲)
በትረ ያርክ ፡-(ጽር ፓትሪአርኻ) ሊቀ ጳጳስ፤ አብ ቀዳማዊ፤ ወይም መዠመሪያ ታላቅ ደገኛ አባት ማለት ነው ፡-(ስንክ ፡-መጋ፲፫። ታኅ፩)።
በትር [1]፡-(ብ አብትር) በቁሙ፤ ዘንግ ሽመል፤ ምርኵዝ ዱላ ጐመድ ከንተሮ መንደርቶ ለበቅ ጨንገር። ትወፅእ በትር እምሥርወ እሴይ። አብትረ ልብኔ። ቍስለ አብትር። በትርከ ወቀስታምከ። ዘይምህክ በትሮ ፡-(ኢሳ፲፩ ፡-፩። ኢዮ፵ ፡-፲፯። ሢራ፳፰ ፡-፲፯። መዝ ፡-፳፪። ምሳ፲፫ ፡-፳፬)።
፡-ሥልጣን አገዛዝ ቀንበር። በትር እንተ ዲበ ክሣዱ። በትረ መንግሥትከ ፡-(ኢሳ፱ ፡-፬። አስቴ፬ ፡-፲፩። መዝ ፡-፵፬)።
[2]፡-በትር፤ ወገን ነገድ፤ ዘር ትውልድ። በበ በትርክሙ ወበበ ሕዝብክሙ። በትረ ይሁዳ ወብንያም ፡-(፩ነገ ፡-፲ ፡-፲፱። ፫ነገ ፡-፲፪ ፡-፳)።
በትበተ ፡-(ይበተብት) በቁሙ፤ በተበተ፤ ቦጠቦጠ ፈለፈለ፤ ውስጥ ውስጡን በላ አቃጠለ፤ የውሻና የዥብ የእሳት አበላል። መቦጥቦጥና መፈልፈል የእሸትና የዳቦ በሊታ። ፡-(ተረት) በገዛ ዳቦዬ ልብ ልቡን ዐጣኹት። ኹሉም ዐማርኛ ነው፤ ያማርኛ ቃል፤ ከግእዝ ሲዴቀል ተቀጥላም ኹኖ ሲነገር፤ አበቃቀሉና አወጣጡ እንዲህ እንደ ኾነ አስተውል። ሥረ ነገሩ ከሦስት ቅንጣት ፊደል አይበልጥም ፥ አያንስም፤ ቋንቋነቱ ሴማዊ ነውና፤ ፩ኛ ዕር ፮ቍ ተመልከት።
(ጥ) በንቶ ፡-(በነተ ይቤንት ይበንት) አው በኒት፤ ቶት፤ ፡-(በነተ ይበንት ይብንት። ዕብ ማናህ) መስጠት ማደል መገበር፤ በፍቅርና በክብር በፈቃድ። ዐሥራት ማውጣት። ሴት ልጅ መውለድ፤ በሴት መበከር። ወለዘሂ ጸባሕተ ጸብሑ ወለዘሂ ብነተ በንቱ፤ ዐሥራት ፥ ዐሹራ ፡-(ሮሜ፲፫ ፡-፯)።
በአት [1]:-መግባት፤–በዊእ ቦአ።
[2]፡-(ጥ) በአት፤–ዋሻ፤ በዊእ ቦአ፤ በኣት።
[3]፡-በአት፤ ዐቢይና ንኡስ ደቂቅ አገባብ ፥ የብትን ሰዋስው መግለጫ እኹል ገብ ቃልና ፊደል።
በኡናህ ባውኒ ፡-(ቅብጥ ፓዎኒ) የግብጦች ፲ኛ ወር ሠኔ ፡-(አቡሻ ፡-፰)።
በዓለ መንበር ፡-ባለወንበር፤ መምህር ጳጳስ ፥ ኤጲስቆጾስ ፡-(ፍ ፡-ነ ፡-፬)።
በዓለ ሰይፍ ፡-ዐራጅ፤ ፈላጭ ቈራጭ ባለወግ፤ ዳንዴ ወንበዴ ፡-(ስንክ ፡-የካ፮። ፊልክ)።
በዓለ እድ ፡-እጃም፤ እጀኛ፤ ባለእጅ፤ እጀታ ያለው ዕቃ መሣሪያ፤ ሠራተኛ ቀጥቃጭ፤ ሌባ።
በዓለ ኪን ፡-ተንኰለኛ፤ ብልኀተኛ፤ ተግባረ እድ ያለው።
በዓለ ሐመር ፡-መርከበኛ ባለመርከብ፤ የመርከብ አለቃ፤ መሪ ቀዛፊ ፡-(ዮሴፍ)።
በዓለ ኅምሳ ፡-ጰራቅሊጦስ፤ የትንሣኤ ፶ኛ ፡-(ድጓ)።
በዓለ ሕብር ፡-ባለቀለም፤ ልብስ አቅላሚ፤ ቀለም አግቢ፤ ወይም ሸያጭ ቀማሚ ፡-(ፍ ፡-ነ ፡-፳፫)።
በዓለ መርዓ ፡-ሰርግ፤ የሙሽሮች በዓል ፡-(ራእ፲፱ ፡-፱)።
በዓለ መዛግብት ፡-የገንዘብ ሹም፤ ዕቃ ቤት ጠባቂ ፡-(ዮሴፍ)።
በዓለ መጽሐፍ ፡-ባለመጣፍ፤ ጸሓፊ ዐታሚ፤ ሸያጭ፤ ተርጓሚ የመጣፍ መምር ፡-(ዮሴፍ)።
በዓለ ምሳሌ ፡-ባለተረት፤ ምሳሌ ዐዋቂ፤ ኹሉን በምሳሌ የሚናገር ፡-(ማቴ፲፫ ፡-፴፬)።
በዓለ ምድር ፡-ባለርስት፤ ዐራሽ ቈፋሪ፤ ጃን ገበር ፡-(ኢዮ፴፩ ፡-፴፬)።
በዓለ ርዴ ፡-ባላራጣ፤ ገንዘቡን በወለድ የሚያበድር ፡-(ቄድር)።
በዓለ ቤት ፡-ባለቤት፤ የቤት ጌታ፤ ሠራዒ መጋቢ፤ አሳዳሪ ፡-(ሉቃ፲፫ ፡-፳፭)።
በዓለ አርብዓ ፡-ዕርገት፤ የትንሣኤ ፵ኛ ፡-(ሲኖዶ)።
በዓለ እቶን ፡-ጋጋሪ፤ የሀገር ዐበዛ፤ ባለወግ፤ ጋግሮ የሚሼጥ ወይም የሚጋግር ብቻ ፡-(ፍ ፡-ነ ፡-፳፫)።
በዓለ ዕዳ ፡-አበዳሪ፤ ወይም ተበዳሪ፤ ዕዳ ከፋይ ፡-(ኢሳ፳፬ ፡-፪)።
በዓለ ውዴት ፡-ነገረ ሠሪ፤ ከሳሽ ባለጋራ ፡-(ፍ ፡-ነ ፡-፭)።
በዓለ ጊዜ ፡-ዘመናይ፤ ሹም ባለጠጋ ንጉሥ፤ እንደ ወደደ የሚያደርግ። ፡-(ተረትና ግጥም ስላጤ ቴ) ዘመናይ ቅል ደንጊያ ይሰብራል። ያን የጐሹን ገዳይ አበጀኹ ቢላችኹ፤ ይህን ባለጊዜ ምን ትሉታላችኹ።
በዓለ ጸብኅ ፡-ወጥ ቤት፤ ወጥ ዐዋቂ ቀቃይ አብሳይ ፡-(ስንክ ፡-የካ፲፪)።
በዓላት ዐዋድያት ፡-የሚዞሩ፤ የሚወጡና የሚወርዱ ወደ ላይ ወደ ታች የሚሉ፤ ከነነዌ እስከ ምሕላ ድኅነት ያሉ። መዞር ግን እንደ መሐረም ነው ፡-(አዋል)።
በዓል [1]፡-(ላት) በቁሙ፤ የደስታ የዕረፍት ቀን፤ ባመት በወር በሳምንት የሚከበር፤ ያለፈ ነገር የሚታሰብበት ተዝካር፤ ሕዝብ የበዓሉን ምስጢር እያሰበ ደስ ብሎትና ለብሶ አጊጦ የሚዘፍንበት የሚዘምርበት እልል የሚልበት፤ ሽብሸባ ጭብጨባ ቀኒጽ ነፈርዓጽ የሚያደርግበት፤ ሲያረግድ እስክታ ሲወርድ ባንገቱ የሚቀጭበት፤ እንደ ጥጃ የሚፈጭበት። ደምፁ እለ ይገብሩ በዓለ። ግበሩ በዓለ በትፍሥሕት። በዓሎሙ ለአእዱገ ገዳም። በዓላት እሙራት። በዓለ ልደት ወበዓለ ጥምቀት። በዓላት ዘርሑቅ እምጽድቅ ፡-(መዝ ፡-፵፩። ፻፲፯። ኢሳ፴፪ ፡-፲፬። ፈ ፡-መ ፡-፲፫። ፍ ፡-ነ ፡-፲፬። ጥበ፲፪)።
[2]፡-(ብ በዓሊም፤ ጽርእ ወዕብራ) ስመ ጣዖት ከነዓናውያን የሚያመልኩት፤ ጌታ ማለት ነው። ተቀንየ ለበዓል ወሰገደ ሎቱ። ወገብረ ምሥዋዐ ለበዓል። ተቀንየ ለበዓሊም ወሰገደ ሎሙ። ወአምለኩ በዓሊመ ፡-(፫ነገ ፡-፲፮ ፡-፴፩ ፡-፴፪። ፳፪ ፡-፶፬። መሳ፪ ፡-፲፩)።
[3]፤ (ብ አብዕልት። ሴ በዓልት ታት) ፤
ምት ባል
፤ ሚስት ያለው ወንድ ፤ የሴት ገዥ አዛዥ ጌታ ባለቤት (ዘፍ፫ ፡ ፲፮። ፩ቆሮ ፡ ፲፩ ፡ ፫)። (ግጥም ፤ መጥፎ ሚስት) ያውና እዚያ ማዶ በግ ይነዳል ሰው ፤ ታላየ ታልሰማ ባላህያ ነው። ብእሲት በዓልተ ቤት። ንኡሳት ያውስባ ወይትዋለዳ ወይኩና በዓልታተ ቤት (፫ነገ ፡ ፲፯ ፡ ፲፯። ፩ጢሞ ፡ ፭
፡ ፲፬)።
በዓልተ ክልኤ ጸራይቅ [1]፡-ባለኹለት ጸሪቅ፤ የጸናጽል ቫኵራ የሚመስል ፪ የናስ ቅጠል ያላት ከዚያ በቀር ሌላ ትርፍ ገንዘብ የሌላት፤ ይህን ብሰጥ ምን እውጥ ሳትል ያንኑ ጨርሳ ከሙዳየ ምጽዋት ያገባች፤ የድኻ ለጋስ ጨካኝ ቈራጥ ባልቴት ፡-(ፊልክ ፡-፶፬። ሉቃ፳፩ ፡-፪)።
[2] ፡-በዓልተ የውሀት ወሰላም ፤ ገር ፍቅረኛ ፤ ቂም በቀል የሌላት (ፊልክ
፡ ፻፭)።
በኣሲ ፡-(ሲት ስያን ያት) የሚብስ፤ የሚከፋ፤ ጐጂ አስቀያሚ።
በዓታዊ ፡-ባታም ባተ መልካም፤ ወይም እግረ ደንዳና፤ ደንብ እግር።
(ጥት) በኣት ፡-(ታት) የመነኵሴ ቤት፤ ጐሬ ዋሻ ፍርኵታ፤ ውስጥ ያለው ቦታ፤ ጋጥ በረት። በደብረ መቃርዮስ ኀበ ተሐንጸ በኣት። ንበር በበአትከ። ወኮነ ይትፋለስ እምበኣት ውስተ በኣት፤ ቤት ፡-(ስንክ ፡-የካ፭። ፊልክ ፡-፳፬። ፶፮)። በኣተ ፈያት። በኣተ መዛግብት፤ በኣታተ ኰኵሕ። በኣታት ለመራዕይሁ፤ ዋሻ ፡-(ኤር፮ ፡-፲፩። ቀሌ። ኢዮ፴፱ ፡-፳፫። ፪ዜና ፡-፴፪ ፡-፳፰)። ቦታ ማለት ከዚህ ወጥቷል። ፈረንሳዊ ቧት የሚለውም ከዚህ ይሰማማል፤ ዱብልንና ሴክልን ተመልከት።
(ጥ) በዓት [1]፡-ዋሻ ፍርኵታ፤–በዊእ ቦአ፤ በኣት።
[2]፡-(ላ) በዓት፤ ባት፤ ከቋንጃ እስከ ተረከዝ።
በዓዲ ፡-(ዲት ድያን ያት) የሚለይ የሚያርቅ፤ ባዕድ የሚያደርግ።
በእንተ [1]፡-ዐቢይና ደቂቅ አገባብ። ስለ ፥ በ ፥ ነገር ፥ ምክንያት ፥ ቃለ ስኢል፤ ደስ አይበለው ብሎ፤ ደስ አይበለው ሲል ይኾናል። በኀላፊና በአርእስት በስም በግብር በቦታ ይገባል፤ በኀላፊ አንቀጽ ሲገባ ዘን በር ከፋች ያደርጋል። በእንተ ዘተወልደ እምኔሃ፤ የመሰለው ኹሉ፤ በእንቲኣየ ከ ኪ ሁ ሃ ነ እያለ ይዘረዝራል። አገባብነቱ ለክፉም ለበጎም ይኾናል፤ ለክፉ ሲኾን በ ላይ፤ ለበጎ ሲኾን ስለ፤ ይኸውም ፥ ራእይ ዘርእየ በእንተ ይሁዳ ወበእንተ ኢየሩሳሌም ባለው ያታወቃል ፡-(ኢሳ፩ ፡-፩)። በእንተ ውእቱ ሕፃን። ወበእንተሰ ይእቲ ዕለት፤ ነገር ፡-(ማቴ፪ ፡-፰። ፳፬ ፡-፴፮)። ይፀርፉ በእንቲኣክሙ። ይቀትሉክሙ በእንቲኣየ፤ ምክንያት። በእንተ ማርያም ወላዲትከ ልመና፤ መሐላና ምጥንታ ሲኾን ግን በ ይኾናል። በእንተ ጸላኢ፤ ደስ አይበለው ብሎ፤ ሲል። አርእስት ሲኾን ፥ በረዥም ባጭርም ቃል፤ በምዕራፍ በክፍል፤ በተለየ አንቀጽ፤ በድርሳን በተግሣጽ ይገባል። በእንተ ሰብአ ሰገል። በእንተ እለ ተቀትሉ ሕፃናት። በእንተ ትምህርተ ኅቡኣት። አንቀጽ ቀዳማዊ በእንተ ቤተ ክር። ድርሳን በእንተ መልከ ጼዴቅ። ተግሣጽ በእንተ ከመ ኢመፍትው ይቅበጹ ተስፋ ፡-(ማቴ። ኪዳ። ፍ ፡-ነ። ቄር። አፈ ፡-ተ ፡-፱)። በድርድር ሲገባ፤ በእንተ ኀጢአት፤ ወበእንተ ጽድቅ፤ ወበእንተ ኵነኔ ይላል ፡-(ዮሐ፲፮ ፡-፰–፲፩)። ሲዘረዘር ደግሞ በበቂነት በቅጽልነት ይፈታል፤ ዘበእንቲኣሁ ቀብዐኒ፤ በርሱ ቅብነት። ዘበእንቲኣሁ ተመራሕነ፤ በርሱ መሪነት መምርነት እያሰኘ ሌላውን ኹሉ ያሳያል። የቀረ ቢኖር አገባብ ተመልከት።
[2]፡-–ስለ፤–እንተ ፡-በ። አገባብ፤ እይ ፡-(ዕር፲፱ ፡-ቍ፷፰)።
በኵር ፡-(ራት፤ አብኳር። ዕብ ብኮር። ሱር ቡክራ። ዐረ ቢክር) በቁሙ፤ መዠመሪያ ልጅ፤ ፍሬ፤ ቀዳማዊ፤ ታላቅ አለቃ ፥ ሹም፤ አንጋፋ ግንባር ቀደም፤ ፊት የተወለደ የበሰለ፤ መብሰል የፍሬ ነው። ጭፍራ የሌለው አለቃ እንዳይባል፤ ታናሽ ተከታይ የሌለውም ዋሕድ እንጂ በኵር አይባልም። እፎ አሐደ ወሊዳ ውእቱ ይቤ ዘበኵራ፤አላ እስመ ኢወለደት እምድኅሬሁ ፡-(ቄር)። ኵሉ በኵር። በኵረ ወልድከ። በኵሩ ለላሕም፤ በኵሩ ለበገግዕ ወለአድግ። ደቀቀ ዳዊት አብኳር ቀደምት። አብኳረ እስራኤል። በኵረ በለስ። በኵራት ይሰዐሩ። ዓሥራት መበኵራት ፡-(ዘፀ፲፩ ፡-፭። ፳፪ ፡-፳፰። ፴፬ ፡-፲፱ ፡-፳። ፩ዜና ፡-፲፰ ፡-፲፯። ክብ ፡-ነገ። ሆሴ፱ ፡-፲። ስንክ ፡-ታኅ፳፰። ፍ ፡-ነ ፡-፲፰)።
በኵርና ብኵርና ፡-(ናት) በኵርነት፤ በኵር መኾን፤ በፊት መወለድ፤ ልቅና ቅድምና። ተሣየጠ እምኔሁ ብኵርናሁ። ብፅዕናት ወብኵርናት ፡-(ስንክ ፡-ነሐ፳፰። ቀሌ። ዕብ፲፪ ፡-፲፮። አፈ ፡-ድ፴፩)። በብኵርና ፈንታ ያንዱን በብዙ፤ ብኵርናት ይላል፤ አያሰኝም። አውፅኦ ለሮቤል እምኍልቈ አኀዊሁ ወጸገዎ ብኵርናቶ ለዮሴፍ ፡-(ግንዘ)።
በኵሕ ሖት ፡-(በኵሐ ይበኵሕ ይብኳሕ። ዕብ ፉዋሕ፤ ያፋሕ፤ ናፋሕ፤ ነፍኀ) መንፋት፤ እፍ ማለት፤ እሳትን በአፍ ወይም በወናፍ። ከአፍ እሳት ማውጣት፤ ነበልባል መትፋት፤ በምትሀት። መጽሐፍ ግን በበኵሐ ፈንታ አብኵሐ ይላል፤ አያሰኝም፤ አ ያማርኛ ነው። ፡-(ሕዝ፳፪ ፡-፳ ፡-፳፩)። ኵሎሙ ያበኵሑ እሳተ እምአፉሆሙ ፡-(ገድ ፡-ተክ)። መለምለም መርጠብ፤ ከነፋስ ከውሃ ጠል መንሣት።
በኵር ሮት ፡-(በኰረ ይበኵር ይብኵር። ዕብ ባኬር) በብኰር መበኰር፤ መዠመሪያ መውለድ ማፍራት፤ መውለድንና ማፍራትንመዠመር፤ በካር መኾን። መጽሐፍ ግን በበኰረ ፈንቃ ተበኵረ ይላል፤ አያሰኝም። ዕጐላት እለ በኵራ። አባግዕ እለ ተበኵራ። መካን ተበኵረት ዮሐንስሀ ፡-(፩ነገ ፡-፮ ፡-፯። ክብ ፡-ነገ፸፫። መዋሥ)።
፡-በኵር ማድረግ፤ ማላቅ ማብለጥ፤ የብኵርና ክብር መስጠት፤ ወልድየ ዘበኵርየ ማለት ፡-(ዘፍ፳፯ ፡-፳፬። ፵፱ ፡-፰። ዘፀ፬ ፡-፳፪። ዕብ፩ ፡-፭ ፡-፮። መዝ፹፰ ፡-፳፯ ፡-፳፰)።
፡-ማብከር፤ ማስታጐል፤ ማቆም ማቋረጥ መተው። መጽሐፍ ግን በበኰረ ፈንታ አብኰረ ይላል፤ አ ያማርኛ ነው። ሰማይኒ ለእመ አብኰረት ዝናመ ፡-(፪ዜና ፡-፮ ፡-፳፮)።
በኪክ ኮት ፡-(በከ ይበክክ ይብክክ። ዕብ ባቃቅ። ዐረ በቀ፤ በካእ) ማብከክ፤ ማብከት፤ ባዶ ጠፍ ብላሽ ከንቱ ማድረግ፤ ወይም መኾን። እባክክ ማለት ከዚህ የወጣ ነው። መጽሐፍ ግን በበከከ ፈንታ በከየ ይላል፤ የተሳሳተ ነው። ኢይሬኢኑ ፀሓየ ዘያበርህ ወይጠፍእ፤ ወወርኅኒ ትበኪ ፡-(ኢዮ፴፩ ፡-፳፮)።
በካዪ ፡-(ዪት ይያን ያት፤ በከይት) የሚያለቅስ አልቃሽ፤ እንብ አፍላሽ፤ ልቅሶኛ። ብፅዓን እንተ ተብህለት ለሕዙናን ወለበካይያን ፡-(ፊልክ ፡-፸፬። ገድ ፡-አዳ)።
በኬሴል ፡-(ዕብ ባሴቤል) ባ በ፤ ሴቤል ሸክም፤ በሸክም ፥ በመሸከም ወይም ተሸክመው ፡-(ነሐ፬ ፡-፲፯)።
በክ ፡-በክት፤ ሙቶ ያደረ። ባዶ ጠፍ ብቻ፤ ከንቱ ብላሽ፤ዋዛ ፈዛዛ፤ እንዲያው፤ የዝም ብሎ። ኵሉ ክበቡ በክ። ትንበር በከ። ነበሩ እስራኤል በበክ። አብድ ያፈደፍድ ነቢበ በክ። አኮ በክ በከመ ትሬእይዎ ለዝንቱ ኅብስት ፡-(ሔኖ፸፫ ፡-፭። ፩ቆሮ ፡-፯ ፡-፲፩። ስንክ ፡-የካ፳፮። ሆሴ፫ ፡-፬። መክ፪ ፡-፲፭። ቅዳ ፡-ሕር)።
በክይ ዮት ፡-(በከየ ይበኪ ይብኪ። ዕብ ባካ። ሱር ብካ። ዐረ በከ) ማልቀስ፤ እንብ ማፍሰስ፤ ዋይ ማለት መጮኽ፤ መንሰቅሰቅ። ኀደገት በክየ። ብክዮ ለዘሞተ። ኢይበክይዎሙ። በእንተ ኵሉ ምንዱብ እበኪ ፡-(ጦቢ፮ ፡-፩። ሢራ፳፪ ፡-፲፩። ኤር፰ ፡-፪። ኢዮ፴ ፡-፳፭)።
በኳሪ ፡-(ሪት ርያን ያት) በካር ዠማሪ፤ በኵር አድራጊ፤ አስታጓይ።
በዊሕ ሖት ፡-(ቦሐ ይበውሕ ይባሕ። ዐረ ባሐ) መታየት መገለጥ፤ መጕላት ብሩህ ጽዱል ጸዐዳ መኾን፤ ኖራ በረቅ ብሕካ መምሰል። ቡሔ ቡሓ ብሓ ማለት ከዚህ የወጣ ነው። መሠልጠን፤ ሹመት መብት ማግኘት፤ ፈቃድ ሥልጣን መቀበል፤ ከበላዩ። ብሕተን ተመልከት፤ የዚህ መንቲያ ነው።
በዊእ ኦት ፡-(ቦአ ይበውእ ይባእ። ዕብ ቦእ። ዐረ ባእ) መግባት፤ መከተት፤ ጥልቅ ስምጥ ማለት፤ ማደር፤ ወደ ውስጥ ማለፍ መኼድ፤ ውሳጣዊ ማእከላዊ መኾን። ቦአ ቤቶ። ባኡ ሀገረ። ባእ ውስተ ታቦት። ኢትባኢ ውስተ ገራህተ ባዕድ ፡-(ዳን፪ ፡-፲፯። ኤር፬ ፡-፭። ዘፍ፯ ፡-፩። ሩት፪ ፡-፰)። በቦአ ፈንታ ተባውአ ይላል፤ ስሕተት ነው። ፡-(ሮሜ፭ ፡-፳። ገላ፪ ፡-፬። ፪ጢሞ ፡-፫ ፡-፮)። በዊእና በዪት አንድ ሥር ናቸው።
በዊዝ ፤ ዞት ፤ (ቦዘ ይበውዝ ይቡዝ) ፤ መቦዝ ፤ መፍዘዝ ፤ መቦዘን ፥ መስነፍ።
በዋኢ ፡-(ኢት እያን ያት) የሚገባ ገቢ፤ መጪ። ጽፉቅ በዋኤ ቤታ። ኀበ ብዙኅ በዋኢቱ። በእንተ ብዝኀ በዋእያን ወወፃእያን ፡-(ምሳ፳፱ ፡-፴፭። ሢራ፵፪ ፡-፮። ፊልክ ፡-፻ ፡-፳፪)።
በዘ [1]፡-(ዐቢይ አገባብ) ፍችው ገንዘብ፤ ምስጢሩ እንደ ፥ ስለ ፥ ዘንድ። በኀላፊና በትንቢት ይገባል፤ በዘወድአ ሞት ኵሎ። በዘቀነዮሙ ሞት፤ ሞት ኹሉን በጨረሰ ገንዘብ፤ በገዛቸው ገንዘብ። ወትሜህር በዘታስሕቶሙ፤ በምታስታቸው ገንዘብ። ገብሩ በዘያምዕዑኒ በሚያሳዝኑኝ ገንዝብ። በምስጢር እንጂ በንባብ እንደና ስለ ሲኾን ምስክር የለውም። በርሥኣኑ፤ እንዘ አልቦ በማለት ፈንታ በዘረሥአ በዘአልቦ እያለ ይገኛል፤ የመላሽ ስሕተት ነው ፡-(ዘፍ፳፬ ፡-፴፮። ፵ ፡-፲፭)።
[2]፡-(በ ዘ) በ በቁም ቀሪ፤ ዘ ቅጽልና በቂ፤ ወይም የዘርፍ ደፊ ይኾናል። ለምንት ትትናገር በዘይሰምዑ ሕዝብ፤ በሚሰሙት ቋንቋ። በዘርእየ ወበዘሰምዐ ሰማዕተ ይከውን። ባየው በሰማው ነገር፤ እንደ ፊተኛውም ባየ በሰማ ገንዘብ ያሰኛል፤ ምስጢሩ እንዳየ እንደ ሰማ መጠን፤ ስላየ ስለ ሰማ፤ ያየውን የሰማውን፤ አይቶ ሰምቶ ማለት ነው፤ ይህ ኹሉ የበን አፈታት ያሳያል። በዘአዶኒራም ዕፅ ወበዘአቤሴሎም እብን፤ ባዶኒራም ዕንጨት ባቤሴሎም ደንጊያ፤ በቁም ቀሪና ደፊ። አንዳንድ ጊዜም ዘ ቅጽል ሲኾን ፥ በ አዳማቂ ኹኖ ይቀራል። ነሥአ ሰይፈ በዘይቀትል። ልብስ በዘያስተባሪ፤ ምክንያት በዘያስተዋርድ። በንና ዘን ተመልከት ፡-(ዕር፲፱ ፡-ቍ፸፬)።
በዚኅ ኆት ፡-(በዝኀ ይበዝኅ ይብዛኅ) መብዛት፤ መርባት መበርከት፤ መውለድ መክበድ መፈድፈድ፤ ማየል መበርታት ፡-(ዘፍ፯ ፡-፳፪ ፡-፳፰። ፰ ፡-፲፯። ዘፀ፩ ፡-፯)። ደንዐ ማይ ወበዝኀ። በዝኀ ድምፀ ሁከት ፡-(ዘፍ፯ ፡-፲፰ ፡-፲፱። ፩ነገ ፡-፲፬ ፡-፲፱)።
በዚዝ ዞት ፡-(በዘ ይበዝዝ ይብዝዝ። ዐረ ዕብ ባዛዝ) መዛት፤ ጕራ መንዛት።
በዛቲ ፡-(ቲት ትያን ያት) የሚያባዝት አባዛች፤ እጀ ሥራ አግቢ።
በዝበዘ ፡-(ዕብ ባዝቤዝ) በቁሙ፤ በዘበዘ ዘረፈ ቀማ በረበረ። ዘራ በተነ፤ መነዘረ አባከነ በከንቱ። ዐማ ነቀፈ፤ ሰደበ አዋረደ፤ ናቀ አቃለለ።
በዝቶ ቶት ፡-(በዘተ ይቤዝት ይበዝት) ማባዘት፤ መፈልቀቅ ማፍታታት፤ መንቀስ እጀ ሥራ ማግባት፤ ለመፍተል። እንዘ ትቤዝት ፀምረ ፡-(ምሳ፳፱ ፡-፴፩)።
በዪል ሎት ፡-(ቤለ ይበይል ይቢል፤ ወይም ቤለ ይቤ ይበል። ዐረ ቃል። ዕብ ንኡም፤ አማር) ማለት፤ መንገር መናገር፤ ፍሬ ቃል መስጠት ማስማት፤ በአፍ በመጽሐፍ መንበብ፤ ማንበብ። ብሂል ፪ ነገር ይኾናል፤ አንቀጽና አገባብ። በአንቀጽንቱ ኣንቀጽ ይስባል፤ ስም ይተረጕማል። ባገባብነቱ ማሰሪያ ያስቀራል፤ አገባቡን ባገባብ ተመልከት። ብሂለ ይብሉ። እስመ ጼዴቅ ብሂል ጽድቅ ብሂል። ብህለ ካልአ፤ በከመ ብህልከ። ዘብህልዎ አበዊነ። ከዊነ ውላጤ ዘብህሎ ቅዱስ አባ ወግሪስ። እሳት እንተ ብህላ እግዚእነ ፡-(ኤር፴፰ ፡-፳፪። አፈ ፡-ድ፲፪። አዋል። አረጋ) መሐለነ እይ የዚህ መንቲያ ነው። የብህለና የክህለ አካኼድ አንድ ስለ ኾነ ፥ ሀ በካልኣያቸው እየታጣ በሣልሳያቸው ይገኛል፤ ባላገባቦች ግን ብህለን ከክህለ ለይተው ይብህል ይሉታል፤ አያሰኝም። ፪ኛም በበዪል አካኼድ እንደ ሐባብና እንዳሮጌው ግእዝ፤ ቤለ ይበይል ይቢል፤ ወይም ቤለ ይቤ ይበል በማለት ፈንታ ብህለንና ቤለን አዛንቀው፤ ቤለን አውጥተው በርሱ ፈንታ ይቤን አግብተው፤ የብህለን ካልኣይ ይብልን ለይቤ ሰጥተው፤ ይቤ ይብል ይበል እያሉ አለመንገዱ ያረቡታል።መጻሕፍትም ከዚህ የተነሣ በቤለ ፈንታ ይቤ ይብል ይበል ሲሉ እንጂ፤ በብሂል አካኼድ ብህለ ብለው፤ ይብህል ሲሉ አይገኙም። ሀሎ የሀለወ ክፋይ መንቲያው ወንድሙ እንደ ኾነ፤ ይቤም ከበዪል የወጣ፤ የቤለ ካልኣይ የይበይል ድርብ ወይም መንቲያ ትንቢት አንቀጽ ሲኾን፤ መምህራን አርእስትና ዘር ቦዝና ቅጽል የለውም ነባር አንቀጽ ነው ብለው ፥ እኩሌቶቹም የብህለ ድርብ ነው ብለው ቀዳማይ አንቀጽ ማድረጋቸው፤ ትንቢትነቱ ስላልታወቀ ነው። በኃምስ መጕረዱም በመካከሉ የ ስላለበት ነው። ፪ኛም ለን የ የሚሉ ሰዎች የለ ጸያፎች፤ ብህለን ሲያረቡ ብህየ ይብይ ይበይ ይላሉና፤ በጸያፍ አንደበት የገባ ነው ልንል እንችላለን። ይብልን ይብይ እንደሚሉት፤ ይብይን ደግሞ ይቤ ብለውት ይኾናል፤ አልዚያስ በኃምስ ሲጐርድ ባልተገኘም። በጸያፍ አንደበት መለወጥም የግስ ልማድ ነው፤ ረን ለ የሚሉ ሰዎች የረ ጸያፎች ፥ በሐረረ ፈንታ ሐለለ ብለው ኹለተኛ አንቀጽ እንዳወጡ። ባማርኛም ለን የ ይወርሰዋል፤ ይልቁንም በሣልስ ቅጽል። ቀታሊ ከሃሊ ሐባሊ ጠንቋሊ ገዳይ ቻይ ዐባይ ጠንቋይ፤ የመሰለው ኹሉ። ጐራጅነቱም ለሩቅ ወንድና ሴት ለቅርድቡ ወንድና ለአነ ለንሕነ ለነዚህ ላምስቱ ብቻ ነው። ይህም ቤለ ይቤ ይበል። ቤለት ትቤ ትበል። ቤልከ ትቤ በል። ቤልኩ እቤ እበል። ቤልነ ንቤ ንበል እያለ መኼዱን ያሳያል። በቀሩት ግን ባምስቱ ሰራዊት፤ ቤሉ ይቤሉ ይበሉ። ቤላ ይቤላ ይበላ። ቤልኪ ትቤሊ በሊ። ቤልክሙ ትቤሉ በሉ። ቤልክን ትቤላ በላ እያለ ዘሩን በዪልን መስሎ ተካክሎ ይኼዳል። የበዪል ዘርና የቤለ ካልኣይ የይበይል ወንድም ፍጹም ትንቢት አንቀጽ መኾኑ፤ ነባር ቀዳማይ አለመኾኑ በ፫ ምስክር ይረዳል። መዠመሪያ፤ በሣልሳዩና ባምስቱ ሰራዊት ለን እየጨመረ በመኼዱ፤ ፈጽሞ ባለመጕረዱ። ኹለተኛ፤ የትንቢት አሥራው መነሾቹ ፬ ፊደሎች የተአነ ብቻ ናቸውና፤ ይቤ ትቤ እቤ ንቤ እያለ በነዚህ ባራቱ በመኼዱ። ሦስተኛ፤ ለነባር አንቀጽ ካልኣይ ሣልሳይ የለውምና፤ በዘንዱና በትእዛዙ ይታወቃል። አስተውል፤ ነባር ቀዳማይ ፥ ወይም ትእዛዝ አንቀጽ ኹኖ ቢኾን መንገዱ እንደ ሀብና እንደ ነዐ ነበር፤ ሀብና ነዐ ሥርወ ቀለሙን ሳይለውጥ በጫፉ ሌላ ባዕድ ፊደል ሳይጨምር፤ ሀብ ቡ ቢ ባ፤ ነዐ ንዑ ንዒ ንዓ ተብሎ ባራት ቅርቦች ብቻ እንዲረባ፤ ይቤም ሥርወ ቀለሙን ሳይለውጥ፤ ለን ከቤለ ከብህለ ሳይቀላውጥ፤ ባራት ሰራዊት በሩቆች ብቻ ይቤ ይቡ ይቢ ይባ ተብሎ በተረባ ነበር። የብሂል አፈታት ጓዙ ብዙ ነውና የቀረውን በርባ ቅምርና ባገባብ በሠምና ወርቅ ተመልከት ፡-(፪ኛና ፡-፲፱ኛ ፡-፳፪ኛ ፡-ዕር። ፳፬ ፡-፹፫ ፡-፻፳፭ቍ)።
በዪት ቶት ፡-(ቤተ ይበይት ይቢት። ሱር ቡት፤ ባት። ዐረ ባተ) ማደር፤ ባሉበት ቦታ ከሠርክ እስከ ነግህ መቈየት፤ የትም ውሎ ወደ ቤት መመለስ፤ መግባት መክተት፤ ከሰው መጠጋት። መኖር፤ ባንድ አገር መወሰን፤ ቦታ መያዝ ቤት መሥራት፤ አጽንዖ በኣት። ቤትኩ ወወዐልኩ እንዘ እጸብት። ቤቱ ክልኤሆሙ በይእቲ ሌሊት። ትበይት ሌሊተ ውስተ ዖም። አልቦ ንብረት ዘኀበ መስዮ ይበይት። ኀቤየ ትበይት ዮም፤ ዐደረ ገባ ተኛ ፡-(፪ቆሮ ፡-፲፩ ፡-፳፭። ጦቢ፰ ፡-፱። ኢሳ፳፩ ፡-፲፫። ሢራ፴፮ ፡-፴፩። ዘፍ፴ ፡-፲፮)። ይበይት ውስተ በኣታተ ኰኵሕ። በጸጋሁ ተፈጥረ ኵሉ ወበኂሩቱ ይበይት፤ ኖረ ፡-(ኢዮ፴፬ ፡-፳፯ ፡-፳፰። ቅዳ ፡-ግሩ)።
በዪጽ ጾት ፡-(ቤጸ ይበይጽ ይቢጽ። ዕብ ባጻዕ። ዐረ በፀዐ) መለየት መምረጥ፤ አስተካክሎ መቍረጥ። ወቤጸ ያዕቆብ አባግዒሁ። እበይጽ እምውስቴትክሙ ኃጥኣነ። ዘይበይጽ በከናፍሪሁ ኵሎ እኩየ፤ ለየ ፡-(ዘፍ፵ ፡-፵። ሕዝ፳ ፡-፴፰። ምሳ፲፮ ፡-፴)።
፡-መንጣት መገርጣት፤ ብጭጭ ማለት፤ ዕንቍላል ወይም የበሰለ ቅጠል መምሰል።
በያቲ ፡-(ቲት ትያን ያት) የሚያድር ዐዳሪ፤ ነዋሪ ቤት ሠሪ።
በያኒ ፡-(ኒት ንያን ያት) የሚበይን በያኝ፤ ዐዋቂ ፈራጅ፤ አስተዋይ፤ ዳኛ መምር።
በያጺ ፡-(ጺት ጽያን ያት) የሚለይ፤ መራጭ፤ ቈራጭ።
በይረሙን ፡-(፤ ፡-(ዐረ በይራም) ቅድሳት፤ ዕለተ ቅድሳት፤ አስተርእዮ ጥምቀት ፡-(ስንክ ፡-ጥቅ፲)።
በይነ ፡-(በይን። ዕብ ቤን። ሱር ባይናይ። ዐረ በይነ፤ ማእከል) ዐቢይና ደቂቅ አገባብ። ስለ፤ ምክንያት። ዐቢይ ሲኾን ዘን በር ከፋች አድርጎ፤ ተሰብአ በይነ ዘአፍቀረ ሰበአ፤ ተቀብዐ በይነ ዘተሰብአ፤ ተሰምየ መሲሐ በይነ ዘተቀብዐ እያለ ይገባል። ፡-(ዕር፲፱ ፡-ቍ፷፰)። ደቂቅ ሲኾን እንደ ቤዛ በብትን ይገባል፤ በይነ ምንት፤ ስለ ምን በምን ምክንያት። በይኑ በይና በይንከ ኪ ክሙ ክን እያለ ይዘረዝራል።
በይኑ ፡-ለሊሁ፤ ብቻው፤ ርሱ፤ ራሱ ባለቤቱ።
በይናት ፡-ኹለት ወገን፤ ኹለት ክፍል፤ ጥንድ፤ ዘውግ መንታ፤ እንደ እጅና እግር ያሉ፤ ተባባሮች ተነጻጻሮች፤ ተመሳሳዮች።
በይን ፡-ብቻ፤ ርስ ራስ፤ ባለቤት፤ እኔ የሚል የተለየ አካል። ፩ ፡-ወገን፤ ፩ ፡-ክፍል፤ ፩ ፈርጅ፤ ነጠላ ቀንጃ።
(ጥ) በይኖ ኖት ፡-(በየነ ይቤይን ይበይን። ዐረ ባነ። ዕብ ባን) መበየን፤ መለየት መምረጥ፤ ማስተዋል መመልከት፤ ለይቶ ማወቅ መረዳት፤ አስተውሎ መፍረድ። ይቤይንዎሙ ወያነጽሕዎሙ። ለምንት ኢትቤይን እምውስቴቶን እለ የዐብያሆን። ወሠርዌ ዘውስተ ዐይንከ ኢትቤይን። ይቤይኖ ለኃጥእ እንበለ ይግበር ኀጢአተ ፡-(ዳን፲፪ ፡-፲። ሄርማ። ማቴ፯ ፡-፫። ቅዳ ፡-ኤጲ)። በበይኖ ፈንታ አበይኖ ይላል፤ አያሰኝም። ሕቱ በአበይኖ ፡-(ቅዳ ፡-እት። ፩ቆሮ ፡-፲፬ ፡-፲፮)።
በደለ ፡-(ትግሬ ወዐረ) ለወጠ፤ ቀየረ። ፡-(ዐማርኛ) በቁሙ፤ በደለኛ ኾነ፤ በመልካም ፈንታ ክፉ ሠራ። ምስጢሩ ከዚያው ይገባል።
በደዶ ፡-ፈንጣጣ፤ ኩፍኝ፤ ልዩ ብቸኛ በሽታ፤ የሚገድል የሚያቈስል፤ ፊት የሚነቍር ዐይን የሚያሳውር የዕከክ ዐይነት። ሕማመ በደዶ ፡-(አዋል)።
በዲር ሮት ፡-(በደረ ይበድር ይብድር። ዐረ በደረ፤ ቈረጠ። ዕብ ባዴር፤ በተነ) መሮጥ፤ መፍጠን፤ መንገድን በሩጫ መቍረጥ። ከዚህ የተነሣ መቅደም፤ ዐልፎ መኼድ፤ ፊተኛ መኾን። ይበድሩ እምተኵላተ ዐረብ። ይበድሩ እምአንስርት አፍራሲሆሙ። ከመ ይብድር እምረዋጺ፤ ሮጠ ፈጠነ ፡-(ዕንባ፩ ፡-፰። ኤር፬ ፡-፲፫። ቅዳ ፡-ዮሐ)። ሕቀ በደሩክሙ። ትበድር ይእቲ ወትመውእ ለከ ጸላኢከ። ብድሮሙ ተንሥእ። ይበድረኒ ኀበ ገነት። በደሮ ለጴጥሮስ በጺሐ ኀበ መቃብር፤ ቀደመ ፡-(፪ነገ ፡-፲፯ ፡-፳። ሢራ፳፱ ፡-፲፫። ፴፬ ፡-፳፩። ፊልክ ፡-፫። ዮሐ፳ ፡-፬)።
፡-ማበደር ማለቃት፤ አስቀድሞ መስጠት ኋላ ለመቀበል ፡-(ዐማርኛ)።
፡-መውደድ፤ መምረጥ፤ ማክበር ማብለጥ። ኢኮነ ለዘበደረ ወለዘሮጸ ፡-(ሮሜ፱ ፡-፲፮)። መጽሐፍ ግን በበደረ ፈንታ አብደረ ይላል፤ አያሰኝም። እመ አብደሩ ዘአነ እፈቅድ። ምጽዋተ ኣበድር እመሥዋዕት። አብደሩ ሞተ እምሕይወት። አብደረ ይሕምም ምስለ ሕዝቡ። ዘያበድር ርእሶ እምነ እግዚኡ። እስመ ኀረያ እግዚ ወአብደራ ፡-(ኢሳ፶፭ ፡-፬። ሆሴ፮ ፡-፮። ኤር ፡-፰ ፡-፫። ዕብ፲፩ ፡-፳፭። ዲድ ፡-፳፭። መዝ ፡-፻፴፩)።
በዲቅ ፡-(በደቀ። ዕብ ባዳቅ) ማደስ መጠገን። እስከ ማእዜኑ ኢትቤድቁ ቤቶ ለእግዚ ፡-(ጊ ፡-ወ ፡-ሐ ፡-ገ፺)።
በዲን ኖት ፡-(በድነ፤ በደነ ይበድን ይብድን) መብደን መፍዘዝ፤ መሞት መገነዝ፤ ሬሳ መኾን፤ መግማት መበስበስ፤ መፍረስ። ሥጋ ትበድን በንዋም ከመ ዘምዉት። ነፍስት አመ ፀአተ ነፍስ ይበድን ፡-(መጽ ፡-ምስ)።
በዲው ዎት ፡-(በድወ ይበዱ ይብዱ። ትግ በድዐ፤ በዳ)። መውደም፤ መጥፋት መፈታት፤ መፍረስ መደምሰስ፤ ውድማ በረሓ ባዶ ባድማ ምድረ ባዳ መኾን፤ ያገር የመዲና የድንግል ና። ምድርክሙኒ በደወ። በድወት ኢየሩሳሌም። ንኅለት ወበድወት። አብያቲሆሙ በድዋ ወተመዝበራ ፡-(ኢሳ፩ ፡-፯። ስንክ ፡-የካ፩። አቡሻ ፡-፶)።
በዲድ ዶት ፡-(በደ፤ በደደ ይበድድ ይብድድ። ዕብ ባዳድ) ለየ ነጠለ፤ ብቻ አስቀረ፤ ብቸኛ አደረገ። በድበደ በዲድ በደ ካለው የወጣ ነው። ፡-(ዲቃላ ፡-ግስ)።
በዳ ፡-ዝኒ ከማሁ። ኢትሑር ፍኖተ በዳ። ትከውን ምድረ ግብጽ በዳ ወበድወ ፡-(ሢራ፴ ፡-፳። ሕዝ፳፱ ፡-፱)።
በዳሪ ፡-(ሪት፤ ርያን ያት፤ በደርት) የሚሮጥ፤ የሚቀድም፤ ሯጭ፤ መንገድ ቈራጭ።
በድራ ፡-(ዐረ በድረት) ሚዛን፤ የሚዛን ስም። ቍጥሩና ልኩ በየሀገሩ ይለያያል፤ እልፍ ድሪም፤ ቪሕ ድሪም፤ ፯ ቪሕ ይሉታል፤ ርግጡ ኣልተገኘም። ፯ ሺሕ ማለት ይለያል እንጂ ሺሕ ማለትና እልፍ ማለት ሊታረቅ ይችላል፤ እልፍን ተመልከት። ኹለተኛም፤ በድራ ማለት፤ ብድር ከማለት ይሰማማል። ወወሀቦሙ ሠለስተ ምእተ በድራ ወርቅ ፡-(ዮሴፍ)።
በድር ፡-ቅድድም፤ ፍክክር፤ ሩጫ ፍጥነት፤ መልካም ሥራ፤ ገድል ትሩፋት። በድርየኒ ፈጸምኩ። ፈጸመ በድሮ ሠናየ። ፡-(፪ጢሞ ፡-፬ ፡-፯። ስንክ ፡-ታኅ፲፬። ጥር፲፬ ፡-፳። የካ፱። ግን፱)።
፡-የጾመ አይሁድ ድሮ ቅበላ፤ ጹመው ከሚውሉበት ከጾማቸው ቀን የሚቀድም፤ ዋዜማ ድራር ማታ የሚዠመር። ይኸውም የጥቅምት ጨረቃ በበቀለች በ፱ ቀን ነው ፡-(ዘሌ፳፫ ፡-፳፯–፴፪)። ወጾመ ቢድሮሙ በእንተ ላሐ ያዕቆብ ፡-(መጽ ፡-ምስ)።
በድበደ ፡-(በድወ። ዐረ ባደ) ታመመ፤ ሞተ፤ ጠፋ ተበላሸ፤ ዛገ መረተ። ወርቆሙኒ በድበደ ፡-(ሆሴ፱ ፡-፮) አብደን ተመልከት፤ የዚህ ጎር ነው። ትግሬ ግን በድበደ ብሎ ሰደበ አዋረደ ይላል።
በድን ፡-(ብ አብድንት) በቁሙ፤ ሙት ሬሳ፤ ነፍስ የተለየችው የማይላወስ የማይንቀሳቀስ፤ የፈዘዘ የተገነዘ ባዶ ሥጋ፤ አስክሬን። ዘአንሥአ በድነ እምነ ሙታን። መዊቶሂ ተነበየ በድኑ። አልቦ ቤት ዘአልቦ በድን ውስቴታ። በዝኃ አብድንቲሆሙ። ወተንሥኡ ብዙኃን አብድንቲሆሙ ለጻድቃን ፡-(ሢራ፵፰ ፡-፭ ፡-፲፫። ኩፋ ፡-፵፱። ኢሳ፭ ፡-፲፫። ማቴ፳፯ ፡-፶፪)።
በድው ፡-ምድረ በዳ፤ ውድማ ባድማ፤ ደረቅ በረሓ፤ ባዶ። በድወ ፋራን። በምድረ በድው ኀበ አልቦ ዕፀ ወማይ። ባሕር በድወ ይመስሎ። በድወ ትከውን ኵላ ምድር። በድው ውእቱ እምሰብእ ወእንስሳ ፡-(ኩፋ ፡-፲፯። መዝ ፡-፷፪። ኢዮ፵፩ ፡-፳፪። ኤር፬ ፡-፳፯። ፵ ፡-፲)።
በገነ ፡-(ዕብ ናጌን) ቃኘ ነዘረ፤ መታ ደረደረ፤ የንዋየ ማሕሌት። ሲጠብቅ ግን ነደደ ተቈጣ ያሰኛል።
በገና ፡-በቁሙ፤ መዝሙር ፡-(ዐማርኛ)።
በገን ፡-(ትግሬ) ጨብጥ፤ የሽንት ምጥ። ፀበጠን ተመልከት።
በጊር ሮት ፡-(በገረ ይበግር ይብግር። ዕብ ባጋር) ማደግ መጐልመስ፤ ከልጅነት ወዳዋቂነቅ መውጣት፤ ከታላላቆች መጨመር፤ ዐብሮ መቈጠር፤ አቶ እገሌ መባል። በቁሙ መበገር፤ መሞከር፤ መንደፍ፤ የሥዕል። ብግር ማውጣት፤ ብግራም መኾን። ብግር ፪ ወገን ነው፤ የውርዛዌና የደዌ።
በግዕ ፡-(ዕት። ዕብ ባግ) የምግብ ክፍል፤ ዕድል ፈንታ ድርሻ መቍነን ድርጎ። በቁሙ ተባት በግ፤ የክርስቶስና የውነተኛ ክርስቲያን ምላሌ፤ በጎ ማለት ከዚህ ወጥቷል። በግዕ ዘተኀጥአ። ወመጽአ ይጠባሕ ከመ በግዕ። አሐቲ በግዕት ፡-(ኢሳ፲፫ ፡-፲፬። ፶፫፤ ፯። ሕዝ፵ ፡-፲፭። ፍ ፡-ነ ፡-፴)።
በግዖ ዖት ፡-(በግዐ ይቤግዕ ይበግዕ) በጋ ፥ መንጋ መኾን መንጋጋት ወደ ወሰዱት መኼድ መነዳት። በጋ የጊዜ የወራት፤ መንጋ የሰው የከብት። ምስጢሩ ግን በጎነትና ቅንነት መሥዋዕትነት፤ እንደ ይሥሐቅ እንደ ዮፍታሔ ልጅ።
(ጥ) በጢሕ ፡-(ሓት። ዐረ በጢኅ) በቁሙ፤ የዱባ ዐይነት ተክል፤ ውስጠ ቀይ ክብ እንክብል፤ ማር ማር የሚል፤ በጥተው አይተው የሚገዙት። በምጥዋ ብርጭቅ ይባላል።
በጢሕ ሖት ፡-(በጥሐ ይበጥሕ ይብጣሕ። ዕብ ባጻዕ። ሱር ብዛዕ። ዐረ እበፀዐ) መብጣት፤ መፍታት፤ መተፍተፍ፤ መሠንበጥ፤ ለፈውስ ወይም ለጌጥ። ፡-(ተረት) ሲያጌጡ ይመላለጡ። ጠቢባን ሶበ ይበጥሑ በጽኑዕ እስከ ይረክብዎ ለሕማም ይጠበቡ ሶቤሃ በዘያዐርፍዎ ለሕሙም እምተሀውኮ ወእምድንጋፄ ነፍስ፤ ወኢይበጥሑ ዳግመ፤ አላ ይወድዩ ፈውሰ። ሚ መጠነ ይጼዐሉ እለ ይበጥሑ እምእለ ይበጥሕዎሙ። ኢትብጥሑ ሥጋክሙ ፡-(አፈ ፡-ተ፴። ዘሌ፳፩ ፡-፭)።
በጢል ሎት ፡-(በጠለ ይበጥል ይብጥል። ዕብ ባጣል። ሱር ቤጤል። ዐረ በጠለ) መቦዘን፤ ማረፍ፤ መስነፍ፤ ሥራ መፍታት። መጥፋት መፍረስ፤ መሻር መቅረት፤ ከንቱ ብላሽ መኾን። ኢበጠለ ጸልዕ አላ ጸናዐ። በጠለት ትንቢት በስብከተ ሐዋርያት። ትበጥል እንተ መከርኩ። በጠለ ዐቂበ ትአዛዝ እምኔየ። በጠለ ተአምኖቱ ቦቱ። ዘስሕተታት በጠላ በትእዛዝከ ፡-(መጽ ፡-ምስ። ክብ ፡-ነገ።አርጋ ፡-፭። ፍ ፡-ነ ፡-፵፱ ፡-፫። ኪዳ)። በበጠለ ፈንታ ተበጥለ ይላል፤ አያሰኝም። እመ ትትቤጠል ኦሪት በሃይማኖት ፡-(ቄር። ገድ ፡-አዳ)።
በጢስ ሶት ፡-(በጠሰ ይበጥስ ይብጥስ) መበጠስ መበጣጠስ፤ መቍረጥ መቈጥቈጥ፤ የቅጠል የዐጽቅ።
በጢር ሮ ት ፡-(በጠረ ይበጥር ይብጥር) መበጠር ማበጠር፤ ማንጠርጠር፤ ማንፈስ መንቀስ የእኽል የጠጕር የነገር። ከግእዝ ወዳማርኛ ስለ ኼደ ባለቅኔዎች አይገሱትም።
በጢጥ ጦት ፡-(በጠ ይበጥጥ ይብጥጥ) መበጠጥ፤ በጠጥ ፋንድያ መጣል፤ ባጥ እንጣጥ ማለት ለመራገጥ የእንስሳ። መዝለል ጮቤ መምታት መራገጥ የጐበዛዝት። በጥ ለጥ ሰጥ ብሎ በልብ መተኛት ዠርባን ለገራፊና ለረጋጭ አስመችቶ መስጠት። ትግሬ በጥ በል ፥ ዐማራ ውደቅ ወይም ጣለው እንዲል።
በጣሒ ፤ (ሒት ሕያን ያት) ፤
የሚበጣ ፤ በጭ ፤ በጪ። በጣሕያን (አፈ ፡ ተ፴)።
በጣሊ ፡-(ሊት ልያን ያት ል በጠልት) የሚጠፋ ጠፊ፤ ፈራሽ ቀሪ ኀላፊ። መንግሥተ ምድር በጣሊ። መርዓ በጣሊ ፡-(ስንክ ፡-ሐም፰። መስ፳፯)።
በጣጣ በጣጥስ ፡-(ዐረብ) ድንች፤ የድንች ወገን።
በጥሐ ፡-(ዕብ ባጣሕ) እመነ፤ ተወከለ፤ ተስፋ አደረገ፤ ዐረፈ ተዘለለ፤ ገላውን ሰደደ፤ ምን አለብኝ አለ፤ የድውይ የባለጤና።
በጥሪቃ ፡-(ሮማ ፓትሪሺያ። ዐረ በጥሪቀት) ታላቅ ወይዘሮ ባላባት፤ የነገሥታት ወገን፤ ልዕልት፤ እግዝእት። ዛቲ ይእቲ ቀዳሚት በጥሪቃ ዘሀገረ ቍስጥንጥንያ ፡-(አዋል። ገድ ፡-ዳን)።
በጥበጠ ፡-በቁሙ፤ በጠበጠ፤ ጣለ፤ የኮሶ የድፍድፍ የጠጅ። ጥሕለን ተመልከት። ለቤተ ክሲያንም ይኾናል። ደብረ በጥብጥ እንዲሉ።
በጸል ፡-(ዐረ በጸል። ዕብ ባጻል። ሱር ቤጽላ) ቀይ ሽንኵርት፤ የቀይ ሽንኵርት ዐይነት የሚላጥ የሚመለጥ፤ ኹለንተናው ተልጦ የሚያልቅ የሚሸለቀቅ። ኢይባርኩ ላዕለ በጸል ፡-(ፍ ፡-ነ ፡-፲፯)።
በጸወ ፡-አንቀላፋ፤–በፀወ።
በጺሕ ሖት ፡-(በጽሐ ይበጽሕ ይብጻሕ። መጽአ፤ ለጸቀ) መድረስ፤ መምጣት መቅረብ መለጠቅ መንካት፤ ማግኘት፤ የእጅና የእግር የራስ የመሌሊት። ኑኁ በጽሐ ሰማየ። ዘእንበለ ይብጽሑ ምድረ ግብ። በጽሐ ብርሃንኪ። ዘበጽሐ እምኤዶም። በጽሐ ማኅፈርነ። ይበጽሕ ደመናተ ርእሱ። በጽሐቶሙ አምሳል ዘመሰሉ። ዘበጽሐ እምትድምርት ፡-(ዳን፬ ፡-፲፯። ፮ ፡-፳፬። ኢሳ፷ ፡-፩። ፷፫ ፡-፩። ሢራ፳፱ ፡-፳፯። ሕዝ፴፩ ፡-፫። ፪ጴጥ ፡-፪ ፡-፳፪። አቡሻ ፡-፴)።
፡-ማደግ መጐልመስ፤ አካለ መጠን ማድረስ። መኾን መደረግ፤ መምላት መፈጸም መጨረስ፤ የትንቢት የዘመን። መርታት፤ ድል መንሣት፤ የውጊያ የሙግት። እምከመ ኢበጽሐ ቃሉ ወኢኮነ በከመ ይቤ። በጽሐ በከመ ነገረ። ከመ ይብጻሕ ቃለ ነቢያት። ዳዊትሰ ልህቀ ወበጽሐ መዋዕሊሁ፤ መላ ተፈጸመ ፡-(ዘዳ፲፰ ፡-፳፪። ኩፋ ፡-፵። ማቴ፳፮ ፡-፶፮። ፳፯። ፩ዜና ፡-፳፫ ፡-፩)። ጌጋይ በዘኢይክሉ በጺሖቶ። አልቦ እኩይ ዘበጽሑ ሎቱ። ረታ ፡-(ግብ፳፭ ፡-፯ ፡-፲፰)።
፡-መውጣት፤ ተለይቶ መያዝ ሰጠት፤ የዕፃ የሹመት የርስት የቦታ፤ የመሰለው ኹሉ። ወበጽሐ ዕፃ ላዕለ በትረ ብንያም ፡-(፩ነገ ፡-፲ ፡-፳ ፡-፳፩። ፲፬ ፡-፵፩። ኢያ፲፰ ፡-፲፩። ፲፬ ፡-፩)። ለከ ይበጽሐከ ርስታ፤ መክፈልት ቡርክት በጽሐት ለሴም ፡-(ጦቢ፯ ፡-፲፪። ኩፋ ፡-፰)።
በጺል ሎት ፡-(በጸለ ይቤጽል ይብጽል። ዐረ በጸለ። ዕብ ፋጼል) መላጥ መምለጥ መቅረፍ፤ መሸልቀቅ መግፈፍ መገሽለጥ፤ መበጨቅ መጋጥ መንጨት፤ መሳብ መጐተት። ከለባት ይቤጽልዎሙ ፡-(ኤር፲፭ ፡-፫)።
በፂዕ ዖት ፡-(በፅዐ ይበፅዕ ይብፃዕ። ዕብ ባፃዕ። ዐረ ፡-በፀዐ፤ ቤጸ) መቍረጥ መወሰን፤ መገምገም፤ መገመት ይህን ያኽል ማለት፤ የዋጋ የስለት። በቁሙ መብፃት ብፃዐት መግባት፤ በገንዘብ በመሷዕት ወይም በራስ በሰውነት መሳል፤ ይህን እሰጣለኹ እንዲህ አደርጋለኹ ማለት፤ ከዚያ በኋላ እንደ ውሉ ራስን ገንዘብን መቀደስ መለየት፤ ለባለቤቱ ማቅረብ መስጠት፤ የተናገሩትን መፈጸም። ይበፅዕ ሤጦ ካህን ወበከመ በፅዖ ከማሁ ይከውን። ወእመ በፅዐ ብእሲ ቤቶ ለእግዚ ወቀደሳ። ዘበፅዐ ብፅዐተ። በፃዕከ ሊተ ብፅዐተ። እንበል ትብፃዕ አስተዳሉ ብፅዐቲከ። እመ ኢበፃዕኩ ለኢየሩሳሌም። በፃዕነ ንጹም። በፃዕከ ትሕንጽ። ብእሲት ዘበፅዐት ከመ ኢትትወሰብ። ዘበፅዐት ርእሳ ለእግዚአብሔር ፡-(ዘሌ፳፯ ፡-፲፪ ፡-፲፬። ዘፀ፴፭ ፡-፳፬። ዘፍ፴፩ ፡-፲፫። ሢራ፲፰ ፡-፳፫። መዝ ፡-፻፴፮። ፩ዕዝ ፡-፰ ፡-፵፱። ፬ ፡-፵፭። ፈ ፡-መ ፡-፭ ፡-፲፮። ፮ ፡-፲፪)።
በፂው ዎት ፡-(በፀወ ይበፁ ይብፁ። ዕብ ባጤእ፤ ነበበ። ዐረ በጡአ፤ ኖመ) ማሸለብ ማንቀላፋት፤ መተኛት መጋደም ጧ ብሎ መዘርጋት። መቃዠት መቀባጠር፤ መጫዎት ማቧለት ያልኾነ ነገር መናገር። ብላዕ ሣዕረ ወልበስ ሣዕረ ወብፁ ዲበ ሣዕር ፡-(ፊልክ ፡-፸፮)። ነፀወን እይ የዚህ መንቲያ ነው።
በጻሒ ፡-(ሒት ሕያን ያት) የሚደርስ ደራሽ፤ መጪ።በጻሕያን ኀበ ብጽሐቶሙ ፡-(ግንዘ)።
በጼቃ ፡-(ዐረ ቡጻቅ። ዕብ ባጼቅ፤ ሊጥ ቡሖ) ነጭ ደንጊያ በረቅ፤ ብሓ ብሕካ፤ ጠመኔ፤ ኖራ የሚመስል። ከመ ርእየተእ በጼቃ ፡-(አዋል)። ባዜቃን ተመልከት፤ የዚህ ሞክሼ ነው።
በጽሒ ፡-(ትግሬ) ዝኒ ከማሁ፤ ውርዝው፤ ወሬዛ ሕፃን፤ ብጹሐ አምጣን።
በጽዐ ፡-ብጽዐት ገባ፤–በፂዕ በፅዐ።
ቡሩክ ፡-(ካን ካት ርክት) በቁሙ፤ የተባረከ የተመስገነ፤ ክቡር ምስጉን ምሩቅ። ሙሴ ዘቡሩክ ዝክሩ። ቡሩክ አንተ አምላክነ። ቡርክት አንቲ እምአንስት ወቡሩክ ፍሬ ከርሥኪ። ቅብዕ ቡሩክ፤ ቅዱስ ፡-(ሢራ፵፭ ፡-፩። ዮዲ፲፫ ፡-፲፯። ሉቃ፩ ፡-፵፪። ዘፀ፳፱ ፡-፳፩)።
ቡራት ቡራቴ ፡-(ጽር ብራቲ። ዕብ ብሮት) ስመ ዕፅ፤ ብርቱ ጠንካራ ዕንጨት የጥድ የዶቅማ ዐይነት እንዳዝጋሮ ያለ ምዑዝ ዐዚዝ። ወይም ርሲው ራሱ ጥዱ ዶቅማው፤ ቤሩሽን እይ ዕብራይስጡ ብሮሽን ሲያበዛ ብሮት ይላልና ፥ ቡራቴ ውስጠ ብዙ ነው፤ ምስጢሩም ከብሩርና ከብርት ይሰማማል።
ቡራኬ ፡-(ክያት) ሳቢና ጥሬ ዘር። መባረክ፤ ፡-(ጥባ) መባረክ፤ አበራረክ፤ በቁሙ ቡራኬ፤ ምስጋና ምርቃት። ባርከኒ አባ ለወልድከ ዝኬ፤ እስመ ልማዱ፤ ለመምህር ቡራኬ። ጸሎተ ቡራኬ። ቡራኬሁ ለሴም። ቡራኬ ወመርገም። ተጽናስ ኮነ መርገመ ወብዕልሰ ኮነ ቡራኬ ፡-(ደራሲ። ቅዳ። ያዕ፫ ፡-፲። አፈ ፡-ተ፲፰)።
፡-የመክፈልት ወግ፤ ታላቅ ዕድል ለባለወጎች የሚሰጥ። እሊሁም መሪጌታና ቄስ ዐቃቢ ናቸው።
ቡቅ ፡-(ብ አብዋቅ) ቀንዳ መለከት፤ ሥሥ ውስጠ ክፍት። ወይትነፋኅ ቀርን ወብዕዛት ወአብዋቅ ፡-(ሥር ፡-አኵ)። አንቦቀቦቀ ተንቦቀቦቀ ቦቅቧቃ ማለት ከዚህ ወጥቷል።
(ጥ) ቡባ ፡-አሻነጕሊት በወንድ ወይም በሴት ልጅ አምሳል የሚሠራ፤ የልጅ የሕፃን መጫዎቻ። ልጅን ና ልዘልኽ ሲሉ እንቡ እንቡቡ ማለት ከዚህ የወጣ ነው።
ቡአት በአት ፡-መግባት፤ አገባብ፤ መባት፤ አባባት። በበአትከ ወበፀአትከ። በአተነ ወፀአተነ በሰላም ዕቀብ። ጥንት ወበአት ውስተ ትሥጉት። በዛቲ ዕለት ኮነ በአቱ ውስተ ቤተ መቅደስ። በአተ ክረምት። በአተ ሰንበት። በለተ ሌሊት። በአተ ጾም ፡-(ዘዳ፳፰ ፡-፮። ግንዘ። ቄር ፡-ጰላ። ስንክ ፡-የካ፰። ሠኔ፳፭። ማር፲፭ ፡-፵፪። አቡሻ ፡-፲፪። መር ፡-ዕዉ)።
ቡዓዴ ፡-መለየት፤ አለያየት፤ ልዩነት ርሕቀት። ሥላሴ ድሙር በአቡዓዴ ወኢቱሳሔ። አልቦ አመክንዮ ወኢቡዓዴ ለኀበ ዚኣሁ ህላዌ። ኅቡራን በኢቡዓዴ ወፅሙራን በኢቱሳሔ። ኢውላጤ ዘእንበለ ቱስሕት ወኢቡዓዴ ፡-(ሃይ ፡-አበ። ቅዳ ፡-ግሩ፤ ቄር። ሳታት)።
ቡዲር ፡-(ትግሬ) ዱሮ ቀድሞ፤ ጥንት፤ ከኹሉ በፊት።
ቢሓት ብሔያት ፡-ጕማሮች፤ ጕማሬዎች። አክይስት ወዐናብርት ወሐርገፃት ወዐናጉግ ወቢሓት ወቈርነናዓት ፡-(መቃ ፡-ገ፲፪)።
ቢሕ ብሔ ፡-(ዕብ ብሄሞት) ጕማሬ፤ የወንዝ የባሕር አውሬ። ብህመን እይ። ተጠምቀ በማይ ዕራቁ ከመ ቈርነናዓት ወዐንጐጕ ወብሔ ፡-(መጽ ፡-ምስ)።
ቢስ [1]፡-(ዐማርኛ። ሱር ቢሳእ) በቁሙ፤ ክፉ፤ ንፉግ ጩቅ፤ ቡዳ ባላይነ ወርቅ። ቢስ አይይኽ፤ ቢሰኛኽን ያርቅ፤ ልበ ቢስ ቀልበ ቢስ እንዲሉ።
[2]፡-በቁሙ፤ ንፉግ፤ ጨባጭ፤–ብእሰ ብኢስ።
ቢሶም ፡-(ዕብ ቦሼም፤ ባሳም) የሽቱ ዕንጨት ዛፍ፤ መልካም ሽታ ያለው ማናቸውም ኹሉ፤ በየስሙና በያይነቱ። ባለብሉዮች ግን ለይተው ሾላ ብሳና ይሉታል ፡-(ኩፋ ፡-፳፩)።
ቢሶስ ቢሶን ፡-(ጽር ቢሱስ። ዕብ ቡጽ። ሱር ቡጻ። ዐረ በዝ) ክታን ልብሰ ክታን ልዝብ ለስላሳ፤ ወይም ነዶው ፈትሉ። ቢሶስ ክዑብ ፡-(ዘፀ፳፭ ፡-፬። ፳፮ ፡-፩ ፡-፴፩ ፡-፴፮። ሉቃ፲፮ ፡-፲፱)። ሲያበዛ ቢሶሳት ይላል። አልባሰ ቀጠንት ወቢሶሳት ወሢራያት ፡-(መቃ ፡-ገ፳፪)።
ቢረሌ ፡-(ልያት። ጽር ቢሪሊዎን) ዕነቍ ፈርጥ፤ የብርሌ የብርጭቆ ደንጊያ ፡-(ዘፀ፳፰ ፡-፳። ጦቢ፲፫ ፡-፲፯)። ሳምን በቢረሌ ወታስዕ በወራውሬ። አናቅጽኪ ዘቢረሌ ፡-(ራእ፳፩ ፡-፳። ኢሳ፶፬ ፡-፲፪)። በቁሙ፤ ብርሌ ብርጭቆ ነጭ ጥሩ። ይሰትዩ ወይነ በማህው ወቢረሌ። ምስክ ዘውስተ ቢረሌ። ቢረልያት ብዙኃት ፡-(ዓሞ፮ ፡-፮። ፍ ፡-ነ ፡-፴፫ ፡-፬። ፊልክ ፡-፻፴፮)።
ቢራ ባሪ ፡-(ዕብ ቢራህ። ጽር ባሪ) ስመ ሀገር፤ መዲና፤ የንጉሥ ከተማ፤ ታላቅ ሕንጻ፤ ጽኑ አንባ፤ ዕርድ ምሽግ ፡-(ዳን፰ ፡-፪። ፩ዕዝ ፡-፮ ፡-፪)።
ቢዖላ ፡-(ዕብ ብዑላ) ባል ያላት ሴት፤ ባለባል፤ ክብርት ብዕልት። ምድርክሙኒ ቢዖላ ፡-(ኢሳ፷፪ ፡-፬)።
ቢዝው ፡-(ዋን ዋት ዙት) የዳነ፤ የተዋጀ ውጁ፤ ቤዛ ያገኘ።
ቢዶን ፡-(ዕብ ኪዶን። ጽር ጋይሶ) ጦር ዘገር፤ ረምሕ፤ የሚወረወር ዐጭር መጠነኛ። ባለብሉዮች ግን ፬ ገጽ ያለው የብረት በሎታ፤ መድፍ ነፍጥ በድል ነጐድ ይሉታል ፡-(ኤር፶ ፡-፵፪)። በዕብራይስጥ ቤትና ካፍ ተመሳሳዮች ስለ ኾኑ በኪ ፈንታ ቢ ተጽፏል።
ቢጽ ፡-(ዐረ ጻሕብ፤ ቀሪብ ል ሺሪክ። ዕብ ሐቤር ል ሬዕ) ባልንጀራ፤ እኩያ አምሳያ፤ ወንድም መንቲያ፤ ወዳጅ ዘመድ፤ ወገን ጎረ ቤት፤ ጓደኛ ባልደረባ አቻ ሚስት፤ ዘማች ወታደር ሰራዊት፤ ኅብረት አንድነት ትክክልነት ያለው ማናቸውም ኹሉ። ባለመጣፎች መጣፋቸውን ተከትለው፤ ቢጽ እንደ ሰብእ ውስጠ ብዙና አስተጋባኢ ነው፤ ላንድም ለብዙም ለወንድም ለሴትም ይነገር ይላሉ፤ ባለቅኔዎች ግን ቢጽና ፀር ላንድ ብቻ እንጂ ለብዙ አይኾንም ይላሉና ፥ ፀርን ተመልከት። አፍቅር ቢጸከ ከመ ነፍስከ። ኢኮንኩ አነ እግዚእከ አላ ቢጽከ። ዘያፈቅር ቢጾ ውስተ ብርሃን ይነብር፤ ወዘሰ ይጸልእ ቢጾ። ብእሲ እምቢጹ። ንግበር ሎቱ ቢጸ። ቢጸ እስራኤል ወቢጸ ይሁዳ ፡-(ዘሌ፲፱ ፡-፲፰። ዕር ኢሳ፰ ፡-፭። ፩ዮሐ ፡-፪ ፡-፲ ፡-፲፩። መክ፬ ፡-፬። ዘፍ፪ ፡-፲፰። ፩ነገ ፡-፲፭ ፡-፬)።
ባህል ፡-(ላት) በቁሙ፤ ነገር ክርክር፤ አባባል፤ አነጋገር፤ የነገር ስልት፤ ትርጓሜ ምስጢር፤ ድርሳን፤ ልማድ ሕግ ሥርዐት፤ የሃይማኖት ትምርት፤ ቃል ድምፅ። ባህለ ልሳን። ከሠትከ ባህለ መጻሕፍት ክዱነ። ወካዕበ ይቤ አባ ቄርሎስ በውስተ አሐዱ እምባህላት። ይቤ በእንተ ትርጓሜ ባህላት። ያስተናክሩ ሥነ ባህሎሙ። ባህለ ብካይ ሰሚዖ ፡-(መዝ ፡-፴። ስንክ ፡-ጥር፱። ፈ ፡-መ ፳፪ ፡-፬። ማር ፡-ይሥ፩። ቄር ፡-ጰላ። ስንክ ፡-ጥቅ፩)።
ባሕረ ሐሳብ ፡-ቍጥር ያለው ዘመን፤ ዓመተ ዓለም። ሐሳበ ባሕር፤ የዘመን ቍጥር። ወበመስፈርት ሰፈሮ ለባሕር ፡-(ሱቱ ፡-ዕዝ፪ ፡-፵፮)።
ባሕረ ብርት ፡-የብርት ውሃ፤ በብርት ምዕቃል የተመላ መታጠቢያ ኩሬ ሰሎሞን እንደ ባሕር አስፍቶ የሠራው ፡-(ኤር፶፪ ፡-፲፯። ፬ነገ ፡-፲፮ ፡-፲፯)።
ባሕረ እሳት ፡-በቁሙ፤ ረቂቅ ሰማያዊ እሳት፤ ወይም ፍል ውሃ ፡-(መቃ ፡-ገ፱)።
ባሕረ ጥበባት ፡-ስመ ስርጋዌ፤ ዮሐንስ ወንጌላዊ ፡-(ድጓ)።
ባሕረረ ፡-(ዐረ በሒረ) ተቀጥላ ግስ፤ ባነነ በረገገ፤ ደነገጠ ደነበረ ፥ ከባሕር ልግባ አለ።
ባሕሩስ ፡-ቀለም፤ የጐሽ መቃ፤ የሸንበቆ የሰንበሌጥ ዐይነት፤ ቀጫጭን ውስጠ ክፍት ዐረቦች ብርዕ አድርገው የሚጥፉባት፤ በወንዝ ዳር በባሕር ጠረፍ የሚበቅል። ቅልጥሙ ቀጥ ያለ የተካከለ ስለ ኾነ ላንገትና ለጣት ምሳሌ ኹኖ ይነገራል፤ ጣተ መቃ ዐንገተ መቃ እንዲሉ። ፡-(ሙሾ፤ ጣተ መልካም እቱ ስለ ሞተች ወንድሟ) ትመታኝን ብዬ ሴቲቱ ወንዱን፤ በመቃጣቷ ነው እኔስ የማዝን። ብርዐ ባሕሩስ። በትረ ባሕሩስ ፡-(ኢሳ፩ ፡-፴፩። ፬ነገ ፡-፲፰ ፡-፳፩)። ጽሕድ በማለት ፈንታ ብሮሽ እንደማለት ባሕሩስ ይላል፤ የተሳሳተ ነው። ለየዐይ ባሕሩስ። ኀጺን ኮነ ብዙኀ ከመ ዕፀ ባሕሩስ ወከመ ብርዐ ገዳም ፡-(ዘካ፲፩ ፡-፪። ክብ ፡-ነገ)።
ባሕራዊ ፡-የባሕር፤ የምዕራብ፤ ምዕራባዊ።
ባሕር [1]፡-(ብ አብሕርት። ዐረ በሕር። ሱር ባሕራ) በቁሙ፤ መካነ ማይ፤ ምቋመ ማይ፤ ዓለመ ማይ፤ ምእላደ ማይ፤ ሰፊ ጥልቅ ዕሙቅ፤ ውሃው የማያልቅ የማይደርቅ፤ ስፋቱ ከየብስ የሚበልጥ ፫ እጅ የሚልቅ ፡-(ዘፍ፩ ፡-፱ ፡-፲)። ባሕር ዐቢይ። ባሕረ ኤርትራ። አብሕርት ወቀላያት ፡-(ዳን ፡-፯ ፡-፪። ዘፀ፲ ፡-፲፱። ኩፋ ፡-፪)። ስፋት ለሌለውም ለታናናሹ ሐይቅ፤ ለኩሬ ሳይቀር ለወንዝ ለፈሳሽ ይነገራል። ባሕረ ጼው፤ ባሕረ ገሊላ፤ ባሕረ ዟይ፤ ባሕረ ጣና እንዲሉ። ባሕረ ኒል። ተከዜ ዮርዳኖስ ባሕር ፡-(አቡሻ ፡-፰። ስንክ ፡-ሠኔ፬። መስ፪)።
[2]፡-ምዕራብ፤ ግራ ፡-(ዘፍ፲፪ ፡-፰። ፲፫ ፡-፲፬። ፳፰ ፡-፲፬። ዳን፰ ፡-፬)። እመንገለ ባሕር ባሕረ፤ ወአመንገለ ጽባሕ ጽባሐ ፡-(ሕዝ፵፭ ፡-፯)።
፡-ንኡስ ማእዝን በሰሜንና በምዕራብ ማኽል ያለ፤ የሰሜን ምዕራብ፤ የሊባ አፋዛዥ ትይዩና አንጻር። ባሕረ ወሊባ ፡-(ቅዳ)።
ባሕርያዊ ፡-የባሕርይ። ስምን ግብርን፤ አካልን ያሳያል።
ባሕርይ [1]፡-(ያት። ዐረ በሕሪይ) ባሕራይ ባሕራዊ፤ የባሕር ዕንቍ፤ ሉል ከሰደፍ የሚገኝ፤ ደረቅ ከራራ ጠንካራ እብናዊ፤ የወፍ ዕንቍላል የሚመስል፤ ታናሽ ክብ እንክብል ድብልብል፤ የሚበርቅ የሚያንጸበርቅ። ዕንቍላል ቅሉ ዕንቈ ሉል ማለት ነው፤ ስሙን ከሉል ወስዷል፤ መመሳሰል የጋራ ነውና ፡-(ማቴ፯ ፡-፮። ፲፫ ፡-፵፭ ፡-፵፮። ራእ፳፩ ፡-፳፩)። እስመ ሰደፍ ይወልዶ ለዕንቍ። ተናገር ዕንቈ ባሕርይ ወክሥት እፎ ህላዌከ። ባሕርይ ዘያንጸበርቅ። እማንቱ ዕንቈ ባሕርያት ክቡራት። መጽሐፈ ባሕርይ ፡-(ማር ፡-ይሥ፳፰። ሃይ ፡-አበ ፡-ኤፍ። አርጋ ፡-፪። ስንክ ፡-ሚያ፰። ቄድር)።
፡-ክቡር ደንጊያ፤ የየብስ ዕንቍ፤ ሉል የሚመስል፤ ባሕርያዊ። እብነ ባሕርይ ፡-(ሔኖ፲፰ ፡-፯። ጥበ፯ ፡-፱። ፲፰ ፡-፳፬። ዮሴፍ)።
[2] ፡-(ዐረ ጀውሀር። ዕብ ዔጼም) በቁሙ፤ የነገር ኹሉ ሥር መሠረት ምንጭ፤ መውጫ መፍለቂያ መገኛ፤ ጠባይዕ ህላዌ ክዋኔ። ጀውሀር በዐረብ ፥ ዔጼም በዕብራይስጥ፤ ባሕርይም አካልም ይኾናል፤ እንደ ህላዌና እንደ ጠባይዕ ነው፤ ባሕርይ ግን በግእዝ ቋንቋ አካላዊ ፍጹመ አካል ቢባል እንጂ ፥ አካል አይባልም፤ አካልም ባሕርያዊ ሕያወ ባሕርይ ቢባል እንጂ ፥ ባሕርይ አይባልም። በምድር ያለ የፍጥረት ኹሉ ሥር ማይ መሬት ነፋስ እሳት ናቸው፤ እሊህ አራቱ፤ ባሕርያትም ጠባይዓትም ይባላሉ፤ ባሕርይ ከብሕረ እንደ ወጣ ፥ ጠባይዕም ከጠብዐ ይወጣል። ባሕር ለታውፅእ ተብላ ብዙ ሥነ ፍጥረት እንዳስገኘች፤ ባሕርይም መገኛ ማስገኛ ስለ ኾነ፤ የአካል የስም የህላዌ ጥንት ፥ የሥራ ምንጭ የግብር መሠረት ይባላል፤ ይኸውም አንቀጽና ቅጽል ብትን ጥሬ ኹሉ ከዘር እንዲገኝ እንደዚያ ማለት ነው። ከባሕርይ ለሚገኝ ባሕርያዊ ሥራ ሠሪው አካል መሣሪያው ባሕርይ ነው፤ አካል ሠሪ እንዲባል ባሕርይ ደግሞ ሠሪ አይባልም፤ ማጭድ ማጨጃ እንጂ ዐጫጅ እንዳይባል፤ አሠሪም ቢሉት ምስጢሩ ከዚያው ከመሣሪያነት ይገባል፤ የሥራ ባለቤት ወትሮ አካል ነው። ወአካላኒ ፡-(ሠሪዋ ፈጻሚዋ) እግዚአብሔር ውእቱ ፡-(አረጋ ፡-ድ፲፰)። አካልን ከባሕርይ ገባሪን ከግብር በየስሙና በየስልቱ ለይቶ የማያውቅ መምህር ግን፤ አካል ሲሉት ባሕርይ ፥ ባሕርይ ሲሉት አካል እያለ፤ የግእዝን ቋንቋ የመጻሕፍትን ቃል የሊቃውንትን ባህል ፥ ትርጓሜና ምስጢር ያበላሻል። እስመ ብሂሎቱ ኀየሰ እመላእክት አኮ ዘይኤምር ኀበ ባሕርዪሁ ዘእምአብ፤ እስመ ባሕርየ መለኮቱ አኮ ዘኮነ ሥጋ አላ ተወልደ፤ ወባሕቱ ይኤምር ኀበ ባሕርየ ሥጋዌሁ ፡-(አፈ ፡-ድ፩። ዕብ ፡-፩ ፡-፬)። የፈጣሪ ባሕርይ እንደ ፍጡር ባሕርይ ካባት ወደ ልጅ የማይወርድ ሊቀዳ ሊከፈል ወይም ሊበረዝ የማይቻል አንድ ሥር አንድ ነቅ ስለ ኾነ፤ ወልድ በተለየ አካሉ የኛን ባሕርይ ነሥቶ ፍጹም ሰው በኾነ ጊዜ፤ ሰው የኾነው አካሉ ነው እንጂ ባሕርዩ ሰው አልኾነምና፤ አኮ ዘኮነ ሥጋ አለው። በተዋሕዶ ወልድ ዋሕድ አንድ አካል አንድ ልጅ ብሎ በተዐቅቦ ኹለት ባሕርይ ማለት ስለዚህ ነው። ፫ መለኮት የሚሉ ግን፤ ጥንቱን ከተዋሕዶ በፊት ወይም ተለውጦ ሰው የኾነ አይዶለም ብለው እንደ ባህላቸው ይፈቱታል፤ ባህላቸውም ባሕርዩ ሰው ኹኖ አንድ ባሕርይ ኹኗል ማለት ነው። ቅዱሳት መጻሕፍት ሊቃውንት አሐዱ ያሉትን የሥላሴን ባሕርይ ከፋፍሎ ሠለስቱ ማለት፤ በተዐቅቦ ክልኤቱ ያሉትን የወልድን ባሕርያት ቀላቅሎ አሐዱ ማለት ፥ ያሉታና የሸፍጥ የምፀት ቃል ነው፤ እውነተኛ ትርጓሜና አፈታት አይዶለም፤ ምንም ለተርጓሚው ቀኝ ቢኾን ለሰሚው ግራ ነው። ይወልደዋል ብሎ አይቀድመውም አይበልጠውም ማለት ባሕርይ ባይከፈል ነውና፤ ባሕርዩ ሰው ቢኾን አባቱ መንፈሱ ሳይቀሩ በግድ ሥላሴ ሰው ኾኑ ያሰኛል፤ እንደ አካላትም ሠለስቱ ቢሉት በግድ ሦስት አማልክት ያሰኛል፤ ኹሉም የተነቀፈና የተወገዘ ነው። ሰው ነው መኾንና ሥጋ መልበስ አካቶ ፈጽሞ ለአካል ብቻ እንጂ ለባሕርይ ሊነገር አይቻልም። ናወግዝ እለ ይብሉ አው ይኄልዩ ከመ ሥሉስ ቅዱስ ዘውእቶሙ ሠለስቱ አካላት ተሠገዉ፤ በብሂሎትሙ ከመ መለኮት ኵለንታሁ ዘንሬኢ ከመ ውእቱ በአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ተሠገወ። ወናወግዝ ዓዲ እለ ይብሉ ሠለሰተ መለኮተ እንተ ዘአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ። ወለእመ ትቤ መለኮት ሞተ አንተ ትከውን ቀታሊሆሙ ለሥሉስ ቅዱስ፤ እስመ ባሕርየ ሥላሴ አሐዱ ውእቱ፤ ዘውእቱ መለኮት ፡-(ሃይ ፡-አ ፡-ዮሐ ፡-ዘእስ ፡-ወዘአን። አግና)። ከዚህ የቀረውን የባሕርይን ምስጢርና አፈታት በህላዌና በጠባይዕ በመለኮት ተራ ተመልከት።
ባሕቀቀ ተባሕቀቀ ፡-አወከ ታወከ፤–ሐብቀቀ።
ባሕቀወ ፡-አንባሕቀወ፤–አፋሸገ፤–በቀወ።
ባሕተወ ፡-(በሐተ) ብቸኛ ኾነ፤ ተለየ፤ ተነጠለ። ኢባሕተወ መለኮቱ እምትስብእቱ ወኢትስብእቱ እመለኮቱ ፡-(መጽ ፣ መስ)። ዐዘነ አለቀሰ፤ ፈራ ተጨነቀ፤ ብቻ ከመኾን የተነሣ። ምናሴ ኀሠሠ ገጸ አግዚአብሔር ወባሕተወ በሕቁ እምቅድመ ገጹ ለአምላከ አበዊሁ ወጸለየ ፡-(ዲድ ፡-፯። ፪ዜና ፡-፴፫ ፡-፲፪)። በባሕተወ ፈንታ ተባሕተወ ይላል፤ በዐገለ ፈንታ ተዐገለ እንዲል። ፍችው አንድ ነው፤ አይለወጥም። ወአመ ወለዶ ኢተባሕተወ አቡሁ ሎቱ። አመ ይትባሐቶ ወይትባአስ ምስለ ጎልያድ። እለ ይትባሐተዉ ውስተ አድባር ወየዐይሉ ውስተ ገዳማት ፡-(ቅዳ ፡-ግሩ። መዝ ፡-፻፶፩። አፈ ፡-ተ ፡-፲)።
ባሕቱ ፡-(ባሕት) ብቻ፤ እንጂ፤ ግን ግና ነገር ግን። እንጂ ሲኾን ዐቢይ አገባብ ነው፤ እንደ አኮኑና እንደ ዳእሙ በፊትም በኋላም ይገባል። በዝንቱ ባሕቱ፤ ብቻ። ባሕቱ ዘንተ ረከብኩ። መበለተ ባሕቱ ኢታውስብ፤ ግን ፡-(ዘፍ፴፬ ፡-፲፭። መክ፯ ፡-፴። ዘሌ፳፩ ፡-፲፬)። ብቻ የሚኾን አገባብ ባሕቱ ብቻ ነበረ፤ በመጽሐፍ ግን ዳእሙ አብቶት እጅግ አይገኝም። ያባተበትም ምክንያት መላሽና ጣፊ በባሕቱ ስፍራ፤ ኢትፍራህ ተአመን ዳእሙ። ወለዘሂ ቈላፍ በአሚን ዳእሙ ያጸድቆ። እሉኑ ዳእሙ ደቂቅከ እያሉ ስላገቡት ነው። የዳእሙን ፍች ተመልከት ፡-(ዕር፲፱ ፡-ቍ፹፩)።
ባሕቲት ፡-(ዕብ ልባድ) ብቻ፤ ብቸታ፤ ብቻነት፤ ጥራት፤ ጥሩነት። ቅጽልና ዐጸፋ ይኾናል፤ ባሕቲቱ ታ ቶሙ ቶን፤ ባሕቲትየ እያለ እስካሥር ይረባል፤ ሳይዘረዘር ግን በሳድስነት አይገኝም፤ እንደ ለልና እንደ ባሕቱ ነው። ኖኅ ባሕቲቱ። ኀጢአት ባሕቲታ። ለከ ለባሕቲትከ። እሉ ባሕቲቶሙ። አነ ባሕቲትየ። ኪያሁ ባሕቲቶ። ባሕቲቶ ዘበልዐ እስመ ይመውት ባሕቲቶ። ፡-(ኩፋ ፡-፭። ውዳ ፡-፮። መዝ ፡-፶። ዮሐ፲፯ ፡-፳። ኢዮ፩ ፡-፲፭። ማቴ፬ ፡-፲። ቅኔ)። በፈቃደ ባሕቲቱ፤ በራሱ በብቻው ፈቃድ። በባሕቲቶሙ ተስእልዎ፤ ብቻቸውን በኾኑ ጊዜ፤ ኹነው። ሠሐቀት በባሕቲታ፤ በራሷ፤ በሰውነቷ። ዕብራይስጡ ግን ብቂርባ ይላል። በሆዷ በልቧ በሐሳቧ ብቻ፤ ጥርስ ሳይገጥ ከንፈር ሳይገለጥ ማለት ነው። አቀሞን እንተ ባሕቲቶን፤ ለብቻቸው፤ እየብቻቸው፤ ብቻቸውን፤ ለ እየ ን የእንተ ፍች ነው ፡-(ፍ ፡-ነ ፡-፮። ማር፬ ፡-፲። ዘፍ፲፰ ፡-፲፪። ፳፩ ፡-፳፰)።
ባሕታዊ ፡-(ዊት ውያን ያት) ብቻውን የሚኖር፤ ባታይ ባተሌ፤ ብቸኛ ስደተኛ፤ የዘመድ ድኻ። እስመ ባሕታዊ ወነዳይ አነ። ከመ ዖፍ ባሕታዊ። ርድአኒ ለተ ለባሕታዊት። ተሣሀልኮሙ ለክልኤ ባሕታውያን ፡-(መዝ ፡-፳፬። ፻፩። አስቴ፬ ፡-፲፯። ጦቢ፰ ፡-፲፯። መዝ ፡-፷፮)።
፡-በቁሙ፤ መናኝ መነኵሴ፤ ዝጉሕ፤ ከዓለም ከሰው። ተለይቶ ከአራዊት ጋራ በዱር በጣሻ በገደል በዋሻ የሚኖር፤ ከቀድሞ ሰዎች እንደ ኤልያስ እንደ ዮሐንስ፤ ከኋላ ሰዎች እንደ ጳውሊና እንደ እንጦንስ ያለ። ጳውሊ ፹ ዘመን ሰው ሳያይ በበረሓ ኑሯል፤ ስለዚህ ሊቀ ባሕታውያን ይባላል ፡-(ስንክ ፡-የካ፪)። ባሕታዊ ዘሞቅሐ ርእሶ በጾማዕቱ። መነኮስ ባሕታዊ። ወነበረ ሐቅለ ምስለ አራዊት ፡-(ፈ ፡-መ ፡-፫ ፡-፯። ስንክ ፡-ታኅ፳፫። ማር፩ ፡-፲፫)።
ባሕትዎ ተባሕትዎ ፡-ብቻ ብቸኛ መኾን፤ ብቸኝነት። ወፂእ እማኅበር ወተባሕትዎ ውስተ በኣት ፡-(ፊልክ ፡-፵፬)።
ባህን ባህናን ፡-ብናኝ፤ ትቢያ፤ ጕድፍ።
ባህንኖ ኖት ፡-(ባህነነ ይባሀንን ይባህንን) መብነን መባከን፤ ብን ብን፤ ብንን ብንን ማለት፤ ማነስ፤ መጕደል፤ መጥፋት መበላሸት፤ ከንቱ መኾን። መጽሐፍ ግን በባህነነ ፈንታ ተባህነነ ይላል፤ አያሰኝም። ይኄይሰኒ መዊት እምይትባሀነነኒ ምዝጋናየ ፡-(፩ቆሮ ፡-፱ ፡-፲፭። ስንክ ፡-መስ፭)።
፡-በቁሙ፤ መባነን፤ መበርገግ፤ ደንግጦ ከንቅልፍ መነሣት ፡-(ዐማርኛ)።
ባሉጥ ፡-(ዐረ በሉጥ። ሱር ባሉጣ) የዛፍ ስም፤ ጥኑ ጠንካራ ዕድሜያም ዛፍ፤ ብዙ ቪሕ ዓመት የሚኖር፤ ጥንካሬው ከዕፀዋት ኹሉ የሚበልጥ፤ ዕንጨቱም ከሰሉም በውድ የሚሼጥ። ዐብየ ብሎ በለጠ ማለት ዐማርኛው ከዚህ የወጣ ነው፤ ድርስንና ባላንን ተመልከት። ዕድሜያምነቱም ሊታወቅ በአብርሃም ዘመን የነበረው ሳይደርቅና ሳይፈልስ ሳይገረሰስ እስከ ዛሬ አለ። ዛሬም ርሱ ስላረጀ ከዚያው ከሥሩ በርሱው አምሳል ፫ ዐጽቅ ያለው ጕንድ ወጥቶ ሰው ኹሉ እየኼደ ያየዋል። ዮሴፍም በታሪክ ፥ ከጥንት ከፍጥረት የነበረ ቀዳማዊ ነው ይላል። ዐሠርቱ ወክልኤቱ ዕፀወ ባሉጥ ፡-(ስንክ ፡-ጥቅ፳። ሆሴ ፡-፲፫)። ዕብራይስጥ ግን ዛፉን አሎን ብሎ ፍሬውን ብቻ ባሉጥ ይላል።
ባላሒ መባልሒ ፡-የሚያድን፤ አዳኝ ታዳጊ። ባላሔ ኵልነ። ባላሒ ለዕጓለ ማውታ። መባልሒት ፡-(ቅዳ። ኪዳ። አርጋ)።
ባላቅ [1]፡-(ትግሬ) ብዙ ደንጊያ፤ ጕር፤ የደንጊያ ክምር፤ ገዎቻ ቋጥኝ፤ ኰኵሕ፤ አለት። የሰው ስም ሲኾን ግን፤ እንደ ዕብራይስጡ ከፋሊ ነሣቲ ማለት ነው ፡-(ዘኍ፳፫ ፡-፩)።
[2]፡-(ብ አብላቅ። ጽር ፕላኬስ) የደንጊያ ሉሕ፤ ሰሌዳ ገበታ ጽሌ። ወአልቦ ዘሀሎ ውስተ ይእቲ ታቦት ዘእንበለ ክልኤቱ አብላቅ ዘአንበረ ሙሴ በደብረ ኰሬብ ፡-(፪፳ዜና ፡-፭ ፡-፩)።
[3]፡-(ዐረ፤ ሩኃም። ዕብ ሻይሽ። ጽር ማርማሩ) ነጭ ደንጊያ፤ እብነ በረድ። አዕማደ ባላቅ። ኀጺነ ወባላቀ ፡-(ማሕ፭ ፡-፲፭። ራእ፲፰ ፡-፲፪)።
[4]፡-(ዕብ ሾሀም። ጽር ኦኒኪ) ክቡር ደንጊያ፤ ዕንቍ። አንክዮንንና ሶምን ሰርድዮንን እይ፤ ከዚህ ጋራ አንድ ነው። ኢበባላቅ ቅድው ወኢበሰንፔር። እምኀበ አብላቅኑ አው እምኀበ አእባን ፡-(ኢዮ፳፰ ፡-፲፮። አፈ ፡-ድ፩)።
ባላን ፡-(ጽር ባላኖስ። ዕብ አሎን። ዐረ በሉጥ) የዛፍ ስም። ድርስንና ባሉጥን ተመልከት፤ ከዚህ ጋራ ፩ ነው፤ ባለብሉዮች ግን ግራር ይሉታል። ታሕተ ዕፀ ባላን ፡-(ዘፍ፴፭ ፡-፰። መሳ፱ ፡-፮። ኩፋ ፡-፲፫)።
ባልሖ ሖት ፡-(ባልሐ ይባልሕ ይባልሕ። ዕብ ባሎሕ፤ መዝለል፤ መንጐራደድ) ማዳን ማውጣት፤ መታደግ መቤዠት፤ ከተያዙ ከገቡ በኋላ። ይባልሖ ለንጹሕ። ኢይክልኑ ባልሖ። አልቦ ዘያድኅን ወዘይባልሕ። ለባልሖትየ ፡-(ኢዮ፳፪ ፡-፴። ኢሳ፶ ፡-፪። መዝ ፡-፯። ስንክ ፡-ጥቅ፳፬)።
ባማ ፡-(275) ፡-(ዕብራ) የቦታ ስም፤ ልዑል፤ አዳጋ ቍሊልታ፤ ተራራ ኰረብ፤ በተራራ ላይ የተሠራ ቤተ ጣዖት፤ ምሧዐ ጣዖት፤ የመቃብር ቤት። ባማ ለርኩስ እንጂ ለቅዱስ አይነገርም፤ ሲያበዛ ባሞት ይላል። ምንት ውእቱ ባማ ዘተሐውሩ አንትሙ ህየ፤ ወተሰምየ ስሙ ባማ ፡-(ሕዝ፳ ፡-፴፱)።
ባሲላዊ ፡-(ጽር ባሲሌፍስ) ንጉሣዊ፤ የንጉሥ ወገን። ባሲላውያን ፡-(ቀሌ)።
ባሲልያ ፡-መንግሥት፤ ጌትነት ንጉሥነት። መጽሐፍ ግን ባሲልያሱ በማለት ፈንታ ፋሲልያሱ ይላል፤ ሱ ዝርዝር ነው ከ። አምንስቲቲን እይ።
ባስልዮስ ፡-የሰው ስም፤ ንጉሥ ንጉሣዊ ማለት ነው።
ባሦር ፡-(ዕብ ባሣር። ሱር ቤስራ) ሥጋ፤ የሥጋ ክፍል። ወገብረ ለርእሱ ባሦረ ግሩመ ወለብሰ እምኔሃ ለድንግል ፡-(ቀሌ)። ዐረቡ ግን በሸር እብን እልበሸር ብሎ ሰብእ ወልደ ሰብእ ይላል።
ባረከ ፡-በቁሙ፤ አማተበ፤ ጸሎተ ቡራኬ ደገመ። አአኰተ ፡-(አኰተ) ባረከ ወፈተተ። ኅቡረ ይባርኩ ማእደ በውስተ ጸሎት። ኢይባርኩ ላዕለ በጸል ፡-(ቅዳ። ግብ፪ ፡-፵፪። ፍ ፡-ነ ፡-፲፯)።
፡-መረቀ፤ መልካም ስጦታን ስለ ሰው ተመኘ ተናገረ፤ አዘዘ ሰጠ። አከበረ ሾመ፤ አበዛ አበረከተ ፡-(ዘፀ፩ ፡-፳፪ ፡-፳፰። ፲፪ ፡-፪ ፡-፫። ፲፯ ፡-፲፮)። ወዘእንበለ ካሕድ ዘየዐቢ ይባርኮ ለዘይንእስ። ብሔር ኀበ በልዑ ኅብስተ ዘባረከ እግዚእነ ፡-(ዕብ፯ ፡-፯። ዮሐ፮ ፡-፳፫)።
፡-ሰደበ አዋረደ፤ ዐማ ነቀፈ፤ ረገመ ካደ። ውስተ ገጽከ ይባርከከ። ባርኮ ለእግዚ ወሙት። ባረካሁ ለእግዚ ወለንጉሥኒ ፡-(ኢዮ፩ ፡-፲፪። ፪ ፡-፭ ፡-፱። ፫ነገ ፡-፳፩ ፡-፲ ፡-፲፫። ስንክ ፡-ታኅ፩)።
ባሪ ፡-(ጽርእ) መዲና፤ ግንብ አዳራሽ። ቢራን ተመልከት፤ ከዚህ ጋራ ፩ ነው። ሱሳ ዘባሪ ፡-(ዳን፰ ፡-፪)።
ባርኮ ኮት ፡-(ባረከ ይባርክ ይባርክ) ማመስገን፤ ከመንበርከክ ጋራ ወይም ተንበርክኮ ምስጋና ማቅረብ። ባርኮና በሪክ በሴም ቋንቋ ኹሉ አንድ ዘር ነው፤ የዱሮ ሰዎች አበው ቀደምት ነቢያት ካህናት የፈጣሪን ስም ሲጠሩ ሲጸልዩ ሲያመሰግኑ ሰግደው ተንበርከው ነበረና፤ ባረከ ማለት የኹሉንም ስልት ያሳያል። ይባርክዎ ኵሉ ግብረ እግዚ ለእግዚ። ወባረኩ ዘ ቡራኬ። ባርኩ ለስሙ በኵሉ ጊዜ ፡-(ዳን፫ ፡-፶፯ – ፹፰። ዘፀ፲፭ ፡-፩። ሢራ፴፱ ፡-፴፭)።
ባርዮ ዮት ፡-(ባረየ ይባሪ ይባሪ። ዐረ በረይ) መለወጥ መተካት፤ ማፈራረቅ ማስተጋገዝ ማስተራረፍ። መግዛት ባሪያ ማድረግ። መጻሕፍት ግን በባረየ ፈንታ አስተባረየ ይላሉ። ያስተባሪ ክረምተ በሐጋይ ወመፀወ በጸደይ። ኀምስተ ዐራዘ በዘያስተባሪ። ያስተባሪ ወርኅ ምልአተ ወሕጸተ ዐውደ ብርሃኑ። ይዕጥኑ በአስተባርዮ እደው። ከመ ዘያስተባሪ የማኖ ልዑል ፡-(መጽ ፡-ምስ። ዘፍ፵፭ ፡-፳፪። አርጋ ፡-፩። ግንዘ። መዝ ፡-፸፮)። አባረየ አስተባረየ ቢል አድራጊ ኹኖ ከባረየ ቢደረብ እንጂ ለብቻው አስደራጊ አይኾንም።
ባቍዕ ፡-(ዓት) በቍዔት፤ ጥቅም ትርፍ፤ የሚበቃ ዋጋ። ጻማሆሙ ዘእንበለ ባቍዕ። አልባቲ ባቍዕ። ይሁብ አብድ ዘአልቦ ባቍዕ። ለዘአልቦ ባቍዕ ወሀብኩ ኀይልየ ፡-(ጥበ፫ ፡-፲፩። ዕብ፯ ፡-፲፰። ሢራ፳ ፡-፲፬። ኢሳ፵፱ ፡-፬)።
ባቅቡቅ ፡-(ዕብ) ታናሽ የውሃ ዕቃ፤ ቅል መንቀል ጠርሙዝ፤ አፈ ጠባብ ዐንገተ ረዥም። ጋላም ቅሉን ቡቄ ይለዋል።
ባበለ ፡-ተቀላቀለ፤ ተዘባረቀ። ተዘራ ተበተነ። በባበለም ፈንታ በልበለ ይላል፤ ፍችው ፩ ነው። ወተሰምየ ውእቱ መካን ባቢሎን እስመ ባቲ ተበልበሉ ልሳናት ፡-(ጊ ፡-ወ ፡-ሐ ፡-ገ፲፫)።
ባበየ ቤበየ ፡-(ይቤቢ) ሠየ፤ ጐመዠ፤ ሮጠ ናወዘ፤ ተቅበዘበዘ፤ የዝሙት። በበ ሠርክ ትቤቢ በውስተ ፍናዊሃ ፡-(ኤር፪ ፡-፳፫)። ዕብራይስጡ ግን ፈጣን ቀላል፤ መንገዷ ቶታን የሚመስል ይላል።
ባቡቴ ፡-ክብ እንክብል ኅብስት ሴቶች በዔሊ አምሳል የሚጋግሩት፤ ይልቁንም የቡልጋ ሰዎች ለሙታን መክፈልት የሚያደርጉት። ዳቦ ድፎ ነብሩቴ፤ ፵ ባቡቴ እንዲሉ።
ባቡት ፡-ዔሊ ደንጊያ ልብሱ፤ ሽልምልም።
ባቢል ፡-(ዐረ አባቢል) ስመ ዖፍ፤ የተረት ወፍ እንደ ፊንክስ ያለ፤ በፍጥረታት ውስጥ የሌለ፤ ያልነበረ ያልተፈጠረ፤ ሙሐመዳውያን ሱር በሚባለው መጣፋቸው የሚያወሩት የሚናገሩት፤ ወይም ባቢሎን ታመልከው የነበር። አዕዋፈ ባቢል ዘውእቱ አጎርጋናት ሠለስቱ ምእት ፡-(አዋል)።
ባቢሎሳን ፡-ቱሱሓን፤ ኅዉሣን ዝርዋን። አባቢሎሳን ፡-(ዲድ)።
(ላ) ባባ ፡-አያት፤ ቅድም አያት፤ አበ አበው፤ የሮም ጳጳስ ፓፓ ፡-(ሐረርና ዐረብ)። እንዳማርኛ ግን ጠብቆ ሲነገር፤ አንቀጽ ኹኖ ባባ አባባ እያሰኘ ፈሪነትንና ብቡነትን ያሳያል።
ባባህ ፡-(ዐረ። ቅብጥ ፓዎፒ፤ ፖፔ፤ ፋዎፊ) ስመ ወርኅ፤ የግብጦች ኹለተኛ ወር ጥቅምት። ቃሉ የቅብጥ ፊደሉ የዐረብ ስለ ኾነ ፐ ለበ ተለውጧል። ግበሩ በዓለ በመንፈቀ ባባህ ፡-(አቡሻ ፡-፰)። በዕብራይስጥ ግን ብንተ ዐይን ያይን ሚሚቶ ብሌን ማለት ነው።
ባቤል ፡-(ዐረ አባቢል) ስመ ዖፍ፤ የተረት ወፍ እንደ ፊንክስ ያለ፤ በፍጥረታት ውስጥ የሌለ፤ ያልነበረ ያልተፈጠረ፤ ሙሐመዳውያን ሱር በሚባለው መጣፋቸው የሚያወሩት የሚናገሩት፤ ወይም ባቢሎን ታመልከው የነበር። አዕዋፈ ባቢል ዘውእቱ አጎርጋናት ሠለስቱ ምእት ፡-(አዋል)።
ባብ ፡-(ዐረብ) በር፤ ደጅ አፍ፤ መዝጊያ። ነደበን እይ።
ባተለ ፡-(ዐማርኛ) በቁሙ፤ ባተሌ ኾነ፤ ደነገለ።
ባቱል ፡-(ዕብ ብቱላ) ድንግል፤ ወንድ ያላወቃት ሴት ልጅ ልጃገረድ ፡-(አዋል)።
(ጥ) ባት ፡-(ዕብራ) የርጥብ መስፈሪያ፤ የዘይት ገንቦ ማድጋ። መስፈርተ ባት። ባተ ጽድቅ ፡-(፫ነገ ፡-፲፭ ፡-፲፩። ሕዝ፵፭ ፡-፲ ፡-፲፩)።
ባእ ፡-ስንዝር፤–ባዕ።
ባዕ ፡-ስንዝር፤–በዊዕ ቦዐ።
፡-ስንዝር፤ ውስጥ እጅ። ባለብሉዮች ግን ክንድ ይሉታል ፡-(ዘፀ፳፴፮ ፡-፲፮)።
ባዕላይ ፡-ባለብዙ ንዋይ፤ ባለጠጋ፤ ወይም ባለጠጎች። ላንድም ለብዙም ይነገራል፤ ማእከላዊ ነው። ኮንከ ከመ ነዳይ ሊባኖስ ክቡር ወልደ ባዕላይ። ኢይምሕሮ ለነዳይ ወኢየኀፍሮ ለባዕላይ። ባዕላይከኒ ኢአምኑ ወነዳያኒከኒ ኢሰምዑ ፡-(መዋሥ። ድጓ)።
ባዕል ፡-(ልት፤ ብ አብዕልት) ቅጽልና ጥሬ። ባለጠጋ ሀብታም፤ ከበርቴ፤ ጌታ። ባዕል ደንጻዊ። ብእሲት ክብርት ወባዕልት። አብዕልትኒ ወነዳይኒ። አግብኦ ለአብዕልቲሃ ፡-(ሢራ፳፭ ፡-፪። ስንክ ፡-ሐም፲፭። መዝ ፡-፵፰። ጦቢ፫ ፡-፲፫)። ባዕል ቅጽልና ጥሬ ስለ ኾነ በጥሬነቱ በዓልን ይመስላልና ፥ በበዓል ፈንታ ባዕል ይላል፤ ፍችው ጌታ ባለቤት፤ ባል ማለት ነው። ባዕለ ንዋይ። ባዕለ ላሕም። ባዕለ ቤት። ባዕለ ብሔር። ባዕለ ዕዳ። ባዕለ ጸጋ ፡-(ዘሌ፭ ፡-፳፬። ዘፀ፳፩ ፡-፳፰። ፳፪ ፡-፯። ዘፍ፵፪ ፡-፴፫። ኢሳ፳፬ ፡-፪። ስንክ ፡-መስ፳፰)።
(ሳት) ባእስ ፡-ብርቱ ጥል፤ ጠብ፤ ሙግት፤ ክርክር፤ ስድብ። ቦኑ ባእሰ ተባአሰ ምስለ እስራኤል። በባእስ ወበዝጓጔ ይፌንዎሙ። ጋእዝ ወባእስ ፡-(መሳ፲፩ ፡-፳፭። ኢሳ፳፯ ፡-፰። ምሳ፲፯ ፡-፲፬)።
ባዕድ [1]፡-(ድት ዳን ዳት) ዝኒ ከማሁ ቅጽልና ጥሬ። በቁሙ፤ ልዩ ሌላ፤ ነኪር። ባዕድ ሰብእ። አልቦ ባዕድ ዘእንበሌሁ። ይዘግብ ለባዕድ። በብሔረ ባዕድ። ወቦ ባዕዳንሂ። ወባዕዳትሂ ብዙኃት ፡-(ዘፀ፴ ፡-፴፪። ዘዳ፬ ፡-፴፭። ሢራ፲፬ ፡-፬። ኤር፭ ፡-፲፱። ግብ፲፯ ፡-፴፪። ማር፲፭ ፡-፵፩)።
[2]፡-(ጥሬ ዘር) የፊደል ስም አገልጋይ ፊደል፤ የጥሬ ዘር ተውሳክ፤ ከቅጽል ከጥሬ እየተጨመረ መነሻ ኹኖ የሚነገር። ባዕድ የሚኾኑ ፊደላት ዋነኞቹ ደ–፬ ናቸው፤ አመተነ፤ ግእዛቸው ብቻ ስለ ተነገረ ከነ በቀር ካዕባቸው ራብዓቸው ሳድሳቸውና ሳብዓቸው ተለይቶ አይቀርም። አ የማድረግና የማስደረግ ልማድ እየኾነ በቀዳማይ አንቀጽ ይገባና ወዲያው ለጥሬው ባዕድ ይኾናል። ፡-(ማስረጃ) ርእየ አርአየ፤ አርኣያ። ከለለ አከለለ፤ አክሊል። መሰለ አምሰለ፤ አምሳል። ሰትዐ አስትዐ፤ አስትዓ። ገዝአ አግዝአ፤ እግዚእ። ለትሐ አልትሐ፤ እልታሕ። ነገደ አንገደ፤ እንግዳ፤ የመሰለው ኹሉ።መ ባዕድ ሲኾን፤ ቀደሰ መቅደስ፤ ነበረ መንበር፤ ደበለ መድበል። ሙ፤ ውሕዘ ሙሓዝ፤ ወፅአ ሙፃእ፤ ወረደ ሙራድ። ማ፤ አመረ ማእምር፤ ሒበ ማሕየብ፤ ሐረጸ ማሕረጽ። ም፤ ገብረ ምግባር፤ ሖረ ምሕዋር፤ ቆመ ምቅዋም :: ሞ፤ ወሠረ ሞሠርት፤ ወፈጠ ሞፈጥ፤ ወፀፈ ሞፀፍ ይላል። ሙና ሞ ካዕብና ሳብዕ መኾናቸው ወን ስለ ጐረዱ ነውና ፥ በወ ከሚንሣ ከወ ግስ በቀር በሌላ አይገኙም። ተ ደግሞ የመደረግና የመደራረግ ልማድ እየኾነ በቀዳማይ አንቀጽ ይገባና እንደ አ ወዲያው ለጥሬው ባዕድ ይኾናል፤ ይኸውም ጥሬ ዘር ኹሉ ከሚመስለው እንጂ ከማይመስለው አንቀጽ እንዳይወጣ በግልጥ ያስረዳል። ፡-(ማስረጃ) ገሠጸ ተገሠጸ፤ ተግሣጽ። ወለጠ ተወለጠ፤ ተውላጥ። ሜጠ ተመይጠ፤ ተምያጥ። ፈጸመ ተፈጸመ፤ ተፍጻም። ቀረመ ቀሠመ ተቀርመ ተቀሥመ፤ ተቅራም ተቅሣም፤ የመሰለው ኹሉ። ታ፤ ሐጸ ተሓጸ፤ ታሕጻጽ። ኀሠ ተኀሠ፤ ታኅሣሥ። ኀመሰ ተኀመሰ፤ ታኅማስ። ት፤ መክሐ ተመክሐ፤ ትምክሕት። ሠለሰ ተሠለሰ፤ ትሥልስት። ሠገወ ተሠገወ፤ ትሥጉት። ደመረ ተደመረ፤ ትድምርት። ወፈየ ተወፈየ፤ ትውፊት፤ የመሰለው ኹሉ። ነ፤ ባዕድ ሲኾን፤ በነ ከሚነሣ ከነ ግስ በቀር በደጊመ ቃል ግስ እየገባ ከአ ተለይቶ ይቀርና የጥሬ መነሻ ይሆናል። ፡-(ማስረጃ) በልበለ አንበልበለ፤ ነበልባል። በስበሰ አንበስበሰ፤ ነበስባስ። ጐድጐደ አንጐድጐደ፤ ነጐድጓድ። ገርገረ ጐርጐረ፤አንገርገረ አንጐርጐረ፤ ነገርጋር ነጐርጓር። ቀጥቀጠ ቀልቀለ፤ አንቀጥቀጠ አንቀልቀለ፤ ነቀጥቃጥ ነቀልቃል፤ የመሰለው ኹሉ። አንና አስተም በአ ምክንያት ልማድ እየኾኑ ይገቡና ለጥሬ ለቅጽል ባዕድ ይኾናሉ፤ አን፤ እንዳለና እን እየኾነ በደጊመ ቃል ግስ ሲገባ፤ በስበሰ አንበስበሰ፤ አንበሳ። ገለገ አንገለገ፤ እንግልጋ። ሶሰወ አንሶሰወ፤ እንስሳ። ጎገወ አንጎገወ፤ እንጉግው። ጌገየ አንጌገየ፤ እንጌግይ፤ የመሰለው ኹሉ። የቀረውን በአንና በእን ተመልከት፤ ከዚያ ተነግሯል። አስተ እስት እየኾነ ሲገባ፤ ነፍሰ አንፈሰ አስተንፈሰ፤ እስትንፋሰ። ገብአ አግብአ አስተጋብአ፤ እስትጉቡእ። ረከበ አርከበ አስተርከበ፤ እስትርኩብ፤ የመሰለው ኹሉ። መ ደግሞ አን እየጐረደ አስተ በገባበት ይገባል፤ ይህም አስተፍሥሐ መስተፍሥሕ፤ አስተመክሐ መስተመክሕ፤ አስተስረየ መስተስርይ ምስትስራይ እያለ ሌላውን ኹሉ ያሳያል።
ባውኒ ፡-የወር ስም፤–በኡናህ።
ባውላ ፡-ስመ ጭፍራ፤ ከቡልዮስ ቄሳር የወጣ ፡-(ዮሴፍ)።
ባዚቃ ፡-(ዕብ ባዛቅ) መብረቅ፤ ነጸብራቅ ፡-(ሕዝ፩ ፡-፲፬)።
ባዜቃ ፡-(ዐረ ዘይበቅ) በቁሙ፤ ፈሳሽ የማዕደን ዐይነት የሚዝቦቀቦቅ። ጥሩ ብር ቅልቅል የሌለው። እንዘ ትሰወጢ ከመ ባዜቃ ፡-(ደራሲ)።
ባዝራ ፡-(ዐማርኛ) በቁሙ፤ እንስት ፈረስ፤ ፍሬያማ ፍሬያም፤ መፍርዪት።
ባዝግና ፡-–ዝርግፍ፤–ዘጊን ዘገነ።
ባዶስ ፡-(ጽር ባቶስ። ዕብ ባት) የልክ የመስፈሪያ ስም፤ የርጥብ መስፈሪያ፤ የዘይት ገንቦ። ምእተ በመስፈርተ ባዶስ ቅብዐ ፡-(ሉቃ፲፮ ፡-፮)። መስፈሪያነቱም የሖሜርን ፲ኛ ክፍል ያነሣል፤ የባትና የኢፍ ልካቸው አንድ ነውና ፥ ኢፍን ተመልከት ፡-(ሕዝ፵፭ ፡-፲፩)። ከዚህ የተነሣ ባዶስን ፥ ቤዶ ፥ላዳን ፥ የቤት ቍና ይሉታል፤ ቤዶ የወሎ የተንታ የደላንታ ነው። ወአሐቲ አስፈሬዳ ታገምር አርባዕተ ባዶሰ ፡-(ገድ ፡-ተክ)።
ባጎር ፡-ጐበዝ ጕልማሳ፤ ብግራም፤ ሕፃንነቱን የጨረሰ አካለ መጠን ያደረሰ፤ ባለአእምሮ፤ የካያ፤ ዓመት ልጅ ወይም የሚበልጥ። ጥበበ ባጎር ወልደ ብዙ ፡-(ጥበ ፡-፩)። ባጎር ሰሎሞን፤ ብኵ ዳዊት።
ባጦስ [1]፡-እምባ(ቧ) ጮ የሚቈረጥ የሚቈጠቈጥ፤ ለጋውን ልጆች እየላጡ የሚበሉት። ፡-(ዘፈን) ስለሚያለቅስ ልጅ፤ እናትኽ ውሃ ወርዳለች፤ እምባጮውን ታመጣልኻለች።
[2]፡-(ጽር ባቶስ። ዕብ ስኔ) ጳጦስ፤ ሳቤቅ፤ የሾኽ ቍጥቋጦ፤ እሾኻም ዛፍ፤ ፍሬው ቀይ፤ መዐዛው ሠናይ። ዕፀ ባጦስ ፡-(ዘዳ፴፫ ፡-፲፮። ሉቃ፳ ፡-፴፯)። ሳቤቅንና ጳጦስን እይ።
ቤለ ይቤ ይበል ፡-አለ፤–ብህለ ይብል ይብሀል።
ቤል ፡-(ዕብ)
የባቢሎን ከፊል፤ ስመ ጣዖት ባቢሎናዊ፤ ናቡከደነጾር ያቆመው ምስል። ባለብሉዮች ግን የፈረስ ምስል ይሉታል ፡-(ኢሳ፷፮ ፡-፩። ዳን፫ ፡-፩)።
፡-ቤል፤–የባቢሎን ከፊል፤–በዪል።
ቤልሖር ፡-(ጽር ቤሊአር። ዕብ ብሊያዐል) ሰይጣን፤ የሰይጣን ስም፤ ለሰውም ይኾናል። ክፉ ጥፉ፤ ልክስክስ ምናምንቴ፤ ሕገ ወጥ ቀንበር ሰበር፤ ዳንዴ ፥ ወንበዴ ፥ ቀማኛ ሽፍታ ማለት ነው። መኑ ዘያኀብሮ ለክርስቶስ ምስለ ቤልሖር። ወኢይኰንኖሙ መንፈሰ ቤልሖር ፡-(፪ቆሮ ፡-፮ ፡-፲፭። ኩፋ ፡-፩)።
ቤሩሲም በርሲም ፡-(ዕብ ብሮሽም) ዝኒ ከማሁ፤ ጥዶች። ዕፀወ በርሲም ፡-(፫ነገ ፡-፭ ፡-፩)።
ቤሩሽ ፡-(ዕብ ብሮሽ። ጽር ኪፓሪሶስ) ጥድ፤ የጥድ ዐይነት ዛፍ ወፍራም ረዥም መለሎ። ለየዐውዩ ቤሩሽ እስመ ወድቀ ዘግባ ፡-(ዘካ፲፩ ፡-፪)።
ቤርሳቤሕ ፡-(ዕብ ብኤር ሻባዕ) ዐዘቅተ መሐላ፤ የመሐላ ጕድጓድ ፡-(ዘፍ፳፩ ፡-፴፩)።
ቤርሴክታን ፡-(ጽርእ) ሣጥን፤ ታቦት፤ የገንዘብ የሬሳ። ኤርጋብን እይ ፡-(፩ነገ ፡-፮ ፡-፰)።
ቤቃ ፡-ስመ አምላክ፤ እንደ ኣካዕ ያለ። ቤ ኹለተኛ አካል፤ ቃ ቃል ቀዳማዊ፤ በሌላው አንቀጽ መቅድመ ቃል ብሎ ይፈታዋል ፡-(ሔኖ)።
ቤበየ ፡-ሠየ ጐመዠ፤–ባበየ።
ቤተ መዋጽሕት ፡-ማፈኛ፤ መክደኛ ጐባባ ፡-(ዘፀ፳፭ ፡-፳፱)።
ቤተ እግር ፡-መጫሚያ፤ ሹራብ፤ ሱሪ ገንባሌ፤ ድርማንቅ ቦለሌ።
ቤተ ክርስቲያን ፡-(ብ አብያተ ክርስቲያናት) በቁሙ ፥ ቤተ ክሲያን፤ የምእመናን መሰብሰቢያ። ቤተ ክርስቲያንሰ ቤተ ጸሎት ይእቲ ፡-(ፍ ፡-ነ ፡-፩)።
፡-የክርስቶስ መንጋ ጉባኤ ማኅበር፤ ሕዝበ ክርስቲያን። ከኒሳን እይ፤ ከዚህ ጋራ ፩ ነው። ንግራ ለቤተ ክርስቲያን። ሰብዑ አብያተ ክርስቲያናት ፡-(ፍ ፡-ነ ፡-፩። ማቴ፲፰ ፡-፲፯። ራእ፩ ፡-፬)።
ቤተ ወይን ፡-የጠጅ ቤት፤ የወይን ጠጅ በበርሚል በጋን የሚሾምበት ፡-(ማሕ፪ ፡-፬)።
ቤተ ድዉያን ፡-በሽተኞች እስኪድኑ የሚተኙበት፤ ሐኪምና ፈውስ ያለበት ንጹሕ ቦታ ፡-(ቀኖ ፡-ኒቅ)።
ቤተ ግዝእ ፡-የድግስ የመሸታ ቤት፤ ሣቅ ጨዎት ስካርና ዝሙት ያለበት ፡-(መክ፯ ፡-፪)።
ቤተ ሐኖት ፡-ቤተ ዝሙት፤ የገበያ ቤት መብል መጠጥ የሚሸጥበት ፡-(ስንክ ፡-ግን፲፪)።
ቤተ ላሕ ፡-የሐዘን ቤት፤ ማልቀሻ እንብ ማፍሰሻ ፡-(መክ፯ ፡-፪)።
ቤተ ልሔም ፡-ስመ ሀገር ቤተ፤ ኅብስት ፡-(ዘፍ፴፭፤ ፲፱)።
ቤተ ልብስ ፡-ጋን ሣጥን፤ ዕቃ ቤት የቤተ ክሲያን ልብስ የሚከተትበት ፡-(ትእ ፡-ጴጥ)።
ቤተ መምህራን ፡-ታላቅ የተማሪ ቤት የፈላስፎች ትምርት ያለበት ፡-(ስንክ ፡-ግን፲፪)።
ቤተ መቅደስ ፡-በቁሙ፤ ቤተ እግዚ፤ መቅደሰ ኦሪት፤ መቅደሰ ወንጌል፤ ቤተ ክሲያን።
ቤተ መበስላን ፡-የወጥ የንፍሮ ቤት፤ ማብሰያ መቀቀያ።
ቤተ መዛግብት ፡-ዕቃ ቤት ግምጃ ቤት ዕቃና ልብስ በሣጥን መልቶ የሚቀመጥበት ፡-(ዳን፩ ፡-፪)።
ቤተ መያሲ ፡-የመሸታ ቤት፤ ከዚያው እየጠጡ የሚሰክሩበት ፡-(ኢሳ፭ ፡-፲፩)።
ቤተ መጻሕፍት ፡-የመጣፍ ቤት መጣፍ ኹሉ በያይነቱ የሚገኝበት፤ ፡-(ቢብሊዮቴክ) ትርጓሜ የሚነገርበት፤ የመጣፍ መክተቻ ሣጥን ማኅደር፤ ዕቃ ቤት ዋሻ ፡-(ገድ ፡-አዳ)።
ቤተ ሙታን ፡-መቃበር፤ የመቃበር ቤት፤ ሲኦል ፡-(ስንክ ፡-የኳ፰)።
ቤተ ማይ ፡-ሠገራ፤ ዐዘቅተ ኵስሕ ፡-(ስንክ ፡-የካ፳፩)።
ቤተ ምሳሕ ፡-አዳራሽ፤ ግብር ማግቢያ፤ ምሳ ማቅረቢያ ፡-(ዳን፭ ፡-፲)።
ቤተ ምሥያጥ ፡-ሱቅ መደብር፤ የንግድ ቤት ፡-(ዮሐ፪ ፡-፲፮)።
ቤተ ምርፋቅ ፡-የምግብ ቤት፤ ዳስ ደጀ ስላም፤ ቤተ ልሔም።
ቤተ ሞቅሕ ፡-የግዞት ቤት፤ ወንጀለኞች የሚታሰሩበት ፡-(መክ፬ ፡-፲፬)።
ቤተ ስምዕ ፡-ደብተራ ስምዕ፤ የሙሴ ድንኳን፤ ፡-(፩ዜና ፡-፮ ፡-፴፪። ፪ዜና ፡-፩ ፡-፫)።
ቤተ ስታይ ፡-የድግስ የመሸታ ቤት፤ ያረቄ መደብር መጠጥ ኹሉ በያይነቱ የሚገኝበት ፡-(ሢራ፴፭ ፡-፮)። ቤት በነገር ኹሉ እየተናበበ በዚህ አምሳል እንደ ዘርፉ ስልት ደፈታል፤ ዘርፍና ቅጽል ባለቤትን ወይም ስምና ግብርን እንዲገልጥ አስተውል።
ቤተ ርእስ ፡-ቆብ ባርኔጣ፤ የካባ የበርኖስ ቍንጮ።
ቤተ ብለኔ ፡-የውሽባ ቤት፤ መታጠቢያ፤ ሽቱ መዝገቢያ ፡-(ቀሌ)።
ቤተ ነግድ ፡-እንግዳ የሚያርፍበት፤ ሰተት ብሎ የሚገባበት ልኳንዳ፤ ሆቴል ፡-(ስንክ ፡-ነሐ፲፭)።
ቤተ አማልክት ፡-የጣዖታት ቤት፤ ብዙ ዐይነት ጣዖት ያለበት መስጊድ።
ቤተ አፈው ፡-የሽቱ መደብ የበቀለበት የተተከለበት ፡-(ማሕ፮ ፡-፪)።
ቤተ እድ ፡-እጅጌ እጀ ጠባብ፤ የእጅ ቤዛ፤ ሹራብ። የዕቃ ዦሮ) ቀለበት ፡-(ዘፀ፳ ፡-፳፭)።
ቤተ እግዚ ፡-የሙሴ ድንኳን፤ መቅደሰ ሰሎሞን፤ ቤተ ክሲያን፤ ጉባኤ ምእመናን ፡-(ቀሌ)።
ቤተ ክሣድ ፡-ዐንገትጌ የቀሚስ አፍ፤ ራስ ማግቢያ።
ቤተ ዝሙት ፡-የዝሙት መደብር፤ ያመንዝሮች ቤት ከኀፍረት በቀር ሌላ ነገር የማይሸጥበት ፡-(ሕዝ፲፮ ፡-፴፱)።
ቤተ ጣዖት ፡-የሰይጣን ቤት፤ ሰይጣን በጣዖቱ ዐድሮ የሚመለክበት ፡-(ኩፋ ፡-፲፪)።
ቤተ ጸሎት ፡-ታናሽ ምኵራብ፤ የሥዕል ቤት፤ ከጸሎት በቀር መሧዕት የማይቀርብበት፤ ወይም ታላቅ መቅደስ፤ ቤተ ክሲያን ፡-(ኢሳ፶፮ ፡-፯)።
ቤተ ፍሥሓ ፡-የሰርግ የመሸታ ቤት ፡-(መክ፯ ፡-፭)።
ቤተ ፍንዱቅ ፡-ዝኒ ከማሁ፤ ቤተ ነግድ ፡-(ትእ ፡-ጴጥ)።
ቤታዊ አብያታዊ ፡-የቤት፤ ቤታም ባለቤት፤ ቤት አባት፤ አዛዥ መጋቢ፤ ቤተ ሰብ ዘመድ፤ የቤት ውልድ። ገብረ ንጉሥ ሰበእ አብያታዊ ፡-(ዮሐ፬ ፡-፵፮ ፡-፵፱)።
ቤጤልዋ ፡-ስመ ሀገር ፡-(ዮዲ፬ ፡-፮)።
ቤት [1]፡-(ብ አብያት። ዕብ ባይት። ሱር ቤታ። ዐረ በይት) በቁሙ ማደሪያ መኖሪያ፤ ሥራ መሥሪያ፤ በደንጊያ በብረት፤ በጡብና በንጨት፤ በኖራ በጭቃ በሣር በጨፈቃ የሚሠራ። ውስጠ ክፍትነት ያለው ዕቃ ቦታ፤ ዋሻ ፍርኵታ፤ ጐሬ ጕጓድ፤ ታላቁም ታናሹም ማናቸውም ኹሉ። እቀትሎ ለቤተ ምክራም ወለቤተ ሐጋይ፤ ይትሀጐሉ አብያት ዘቀርነ ነጌ ወይተከሉ አብያት ካልኣን። ይቀሥፎ ለዐቢይ ቤት በድቀት ወለንኡስ ቤት በንፅኀት። ባእ ቤተከ። ቤት ምሩግ ፡-(ዓሞ፫ ፡-፲፭። ፮ ፡-፲፩። ኢሳ፳፮ ፡-፳። ምሳ፳፩ ፡-፱)።
፡-ወገን ነገድ፤ ዘር ትውልድ፤ ጉባኤ ማኅበር፤ ጭፍራ ወታደር በያለቃው። ርስዒ ሕዝበኪ ወቤተ አቡኪ። ቤተ ያዕቀብ፤ ቤተ ዳዊት፤ ቤተ እስራኤል፤ ቤተ ክርስቲያን፤ ቤተ ከህነት፤ ቤተ መንግሥት።
[2]፡-ገንዘብ፤ ዘመድ፤ ቤተ ሰብ ፡-(ማቴ፳፫ ፡-፲፬። ዘፀ፩ ፡-፳፩)።
፡-ስመ ፊደል ካልእ፤ በ ቅርጹ ቤትና ደጅ አፍ የሚመስል ፡-(መዝ ፡-፻፲፰ ፡-፱–፲፮። ሰቈ፩ ፡-፪። ፪ ፡-፪። ፫ ፡-፭። ፬ ፡-፪)። ስሙንና መልኩን ከቤት ወስዷል።
[3]፡-–በቁሙ፤ ስመ ፊደል፤–በዪት ቤተ፤ በ።
ቤዘ ፡-–ተቤዠ፤–በዪዝ ቤዘ።
ቤዘወ ፡-–ተቤዠ፤–በዪዝ ቤዘ።
ቤዛ (ዛት)
[1]፡-በቁሙ፤ ዋጋ፤ ካሳ፤ ለውጥ፤ ምትክ፤ ዐላፊ፤ ዋቢ፤ ዋስ፤ መድን፤ ተያዥ፤ ጫማ ጥላ ጋሻ የመሰለው ኹሉ። ቤዛ ነፍሱ ለብእሲ ጥሪተ ብዕሉ። አኮ በቤዛ። ቤዛ ኵሉ ኀጢአትከ። ማእስ ቤዛ ማእስ ፡-(ምሳ፲፫ ፡-፰። ኢሳ፵፭ ፡-፲፫። ኤር፲፭ ፡-፲፫። ኢዮ፪ ፡-፬)።
[2]፡-(ደቂቅ አገባብ) ስለ፤ ፈንታ፤ ምክንያት። እሜጡ ነፍስየ ቤዛ አባግዕየ፤ ስለ በጎቼ። ዐይን ቤዛ ዐይን፤ ወስን ቤዛ ስን፤ በዐይን ፈንታ፤ በጥርስ ፈንታ። ተሰቀለ ቤዛነ፤ ስለኛ በኛ ምክንያት፤ ወይም ቤዛችን ተብሎ በቂ ይኾናል። ቤዛሁ ሃ እያለ ይዘረዝራል፤ በብትን እንጂ በአንቀጽ አይገባም።
ቤዛዊ ፡-(ዊት ውያን ያት፤ ዘውት) የሚቤዥ፤ የሚታደግ፤ ታዳጊ። ማርያም ቤዛዊተ ዓለም። እስመ ቤዛዊሃ ለነፍስየ አንተ ፡-(ደራሲ)።
ቤዝ ፡-(ብ ቤዛት፤ አብያዝ) ጕልሕ ኮከብ፤ ኮከበ ጽባሕ ብርሃኑ የሚቦዝ የሚበዘብዝ። አንተ ቤዝ ኮከበ ጽባሕ። አዕይንቲሃ ይመስል ሥርቀተ ቤዝ። በሰዓተ ሞታ ደመነ ቤዝ። በከመ ኮከበ ጽባሕ። ይፈደፍድ ብርሃነ እምዘተርፉ ቤዛት። ሰላም ለአዕይንትኪ ዘተመሰላ አብያዘ ፡-(ቄድር። ገድ ፡-ተክ። ስንክ ፡-መስ፲፩። ፊልክ ፡-፪፻፸። ደራሲ። አርጋ ፡-፮። ኢዮ፮ ፡-፱)።
ቤዝዎ ዎት ፡-(ቤዘወ ይቤዙ ይቤዙ። ዐረ ፡-ባዘ፤ ሸሸ። ዕብ ፋዳ) መቤዠት ማዳን፤ መታደግ፤ ማስጣል፤ ከጭንቅ ከባርነት ማውጣት፤ ከባለዳ እጅ መግዛት፤ መዋጀት፤ ለውጥ መስጠት፤ ገንዘብን ወይም ራስን፤ እንደ ክርስቶስ። አኮ በወርቅ ዘእቤዝወክሙ። በነፍስክሙኑ ትቤ ዝውዋ ለነፍስየ። መጽአ ይቤዝወነ እምኵሉ አበሳነ ፡-(ኢሳ፶፪ ፡-፫። ኢዮ፲፮ ፡-፬። መዋሥ። ዘፀ፲፫ ፡-፲፫። ፴፬ ፡-፳)። በቤዘወ ፈንታ ተቤዘወ ይላል፤ አያሰኝም፤ ተ ያማርኛ ነው። ተቤዘውዎሙ ለፂዉዋን። አልቦ ዘይክል ተቤዝዎትየ። ኢያድኅን ወርቅ ወኢይትቤዘው ብሩር ፡-(ዲድ ፡-፳፩። አርጋ። ስንክ ፡-ሐም፬። ዘሌ፳፭ ፡-፴፩ ፡-፴፫። ፩ጴጥ ፡-፩ ፡-፲፰)። ቤዘወ የቤዘ ቅጥይ እንደ ኾነ አስተውል።
ቤዴቅ ፡-(ዕብራ) የግንብ ንቃቃት፤ ነቁ ሥንጥቁ፤ ወይም ሊናድ የቀረበ፤ ያረገዘ ያዘበዘበ የቤት ግንብ። ያጥር የቅጥር ካብ። ማናቸውም የሚታደስና የሚጠገን ኹሉ። ወያጸንዑ ቤዴቀኪ ፡-(ሕዝ፳፯ ፡-፱። ፬ነገ ፡-፲፪ ፡-፭)።
ቤጣ [1]፡-ስመ ፊደል፤–በየጣ።
[2]፤ (ጽር ቤታ) ፤ ፪ኛ ፊደል በ ቤት በጽርእና በቅብጥ። አልፋ ወቤጣ። ምንት ውእቱ ቤጣ (ሥር ፡ ጳኵ። ኪዳ)።
ቤጻ ብጻ ፡-ብጫ፤ ብጫቴ፤ ዐይነቱ የንቍላል አስኳል ፥ ዐደይ የሚመስል፤ አስፈርን እይ።
ብሁል ፡-(ላን ላት ብህልት) የተባለ፤ የተነገረ፤ ንግር። አላ ብሁል ሊተ ፡-(አፈ ፡-ድ፲)።
ብሁም ፡-(ህምት) ድዳ የኾነ፤ አፍ እያለው የማይናገር። ብእሲት ብህምት ፡-(ስንክ ፡-ሐም፰)።
ብሑት [1] ፡-(ታን ታት ሕት) ብዉሕ፤ የሠለጠነ የተሾመ፤ መብት ያለው። ወደቂቀ አሮንሰ ብሑታን በበ እብሬቶሙ። ሳቁኤል ብሑት ዲበ መናፍስት። ኦ ዛቲ ዕለት ብሕት ከመ አብ፤ ህሉት ከመ ወልድ፤ ስፍንት ከመ መንፈስ ቅዱስ ፡-(፩ዜና ፡-፳፬ ፡-፩። ስንክ ፡-ሐም፭። ቅዳ ፡-አት)።
[2] ፡-የባተ ፤
ብቸኛ የኾነ ፤ ብቸኛ። ብሑተ ልደት። ብሑት ዘእንበለ አዝማድ። መነኮስ ብሑት። ገዳማዊ ብሑት (ኪዳ።
ቅዳ ፡ ኤጲ። ፊልክ ፫። ስንክ ፡ የካ፯)።
ብሑእ ፡-(ኣን ኣት ሕእት) የቦካ፤ የበሰለ፤ የሖመጠጠ። ምስለ ኅብስት ዘብሑእ። ኢትግበርዎ ብሑአ። ኢትዝባሕ በብሑእ ደም፤ ያደረ ፡-(ዘሌ፯ ፡-፲፫። ፪ ፡-፲፩። ዘፀ፳፫ ፡-፲፰)። በብሑእ ፈንታ ብሒእ ይላል ል አያሰኝም። ብሒእ ወይን። ብሒእ ሜስ። ሐምለ ብሒእ ፡-(ዘኍ፮ ፡-፫። ፱ ፡-፲፩። ዘፀ፲፪ ፡-፰)።
ብሂል ሎት ፡-(ብህለ ይብል ይብሀል። ዐረ በሀለ፤ ተረገመ። ዕብ ባሄል፤ ደነገጠ) አው
፡-ብሂል፤ በዪል፤ መምታት፤ በበትር ማለት መደብደብ፤ ወይም አስቀድሞ መስደብ፤ በነገር መቀንደብ ፥ ጽዕለትን ተመልከት። ብሂላና ብላዕ፤ ባማርኛ ይተባበራሉ፤ ብላ ብላ።
ብሂም ሞት ፡-(ብህመ ይብህም ይብሀም) ድዳ መኾን፤ አለመናገር፤ ልናገርም ቢሉ አለመቻል፤ እንደ ከብት መኾን። ይኄይስ ብሂም እምነቢብ በሐሰት። ይብህም ልሳን። ብህመ ልሳኑ። ሜጥኩ ገጽየ ወብህምኩ ፡-(ፈላስ። ግንዘ። ስንክ የካ፯። ዳን፲ ፡-፲፭)።
ብሒር ሮት ፡-(ብሕረ ይብሕር ይብሐር። ዐረ በሐረ። ዕብ ባሐር፤ መረጠ) መስፋት መንጣለል፤ መዘርጋት፤ ሰፊ ዝርግ ወርዳም ረዥም መኾን፤ የቦታ የመሬት የርስት የግዛት።
ብኊባኌ ፡-ብኅባኄ፤ ግማት ክርፋት፤ ሽታው የሚያሰቅቅ የሚጐፈንን። እሬኢ ንስኀተ ሥጋየ ከመ ብኅባኄ አንበሳ ፡-(ኢዮ፮ ፡-፯)። ባለብሉዮች ግን ኀይል ብርታት ይሉታል።
ብኊብኊ ፡-ብሕቡኅ፤ የኖኸቦኸ፤ የቦነቸ። ከመ ዕፅ ብኅቡኅ ፡-(ኢዮ፳፬ ፡-፳። ፵፩ ፡-፲፰)።
ብሒት ቶት ፡-(ብሕተ ይብሕት ይብሐት፤ ቦሐ) መሠልጠን፤ መሾም፤ መብት ችሎት ምቾት ማግኘት። እንዘ ትብሕት አንተ በኵለሄ። ወሶበ ብሕትኩ አልእክ ዘይጼውዐከ ፡-(አርጋ ፡-፪። ግብ፳፬ ፡-፳፭)።.
ብሒእ ፡-ርሾ፤ ሎሰን እይ። መጣጣ ዐይብ፤ ዐዞ ከል፤ የተበላሸ ጠጅ፤ ሖምጣጤ። ትጸብኂ ኅብስተኪ በብሒእ። ወአስተዩኒ ብሒአ ለጽምእየ። ከመ ብሒእ ኢይደልዎ ለቍስል። ወቦ ህየ ፃምዔ ብሒእ ዘምሉእ፤ ወመልኡ ሰፍነገ እምብሒእ ፡-(ሩት፪ ፡-፲፬። መዝ ፡-፷፰። ምሳ፳፭ ፡-፲። ዮሐ፲፬ ፡-፳፱)።
ብሒእ ኦት ፡-(ብሕአ ይብሕእ ይብሐእ። ዕብ፤ ቦሄእ፤ እጅግ፤ ፈራ፤ ተደነቀ) መቡካት፤ መሖምጠጥ፤ መብሰል። ሐሊብ ዘኢብሕአ። ይፈርሆሙ ኢይብሐኡ፤ እስመ ጻሕብ ዘቅቡል ፍጡነ ይብሕእ ፡-(ግንዘ። ሄርማ ፡-ገ፵፰)። በብሕአ ፈንታ ተብሕአ ይላል፤ አያሰኝም። እስከ ይትበሐእ ፡-(ሆሴ፯ ፡-፬። ዘፀ፲፪ ፡-፴፬)። በኍበኈን ተመልክት፤ የዚህ መንቲያ ነው።
ብሄማ ፡-(ዕብራ። ዐረ በሀኢም) ከብት እንስሳ፤ ኢነባቢ።
ብሄሞት [1]፡-(ዕብራ) ጕማሬ የወንዝ አውሬ፤ የባሕር ፈረስ፤ በአፍሪቃ ወንዞች በየሐይቆቿ የሚገኝ፤ ከውሃ እየወጣ ሣርና ቅጠል የሚበላ፤ ታላቅ ገናና፤ ቈርበተ ወፍራም ዐንገተ ደንዳና፤ ቈርበቱ ኰርባጅ ዐለንጋ የሚኾን፤ መልኩ ያንድስ ፥ ድምጡ የፈረስ፤ ሲያሽካካ ፈረስ የሚመስል። ዲኖ ጅን የባሕር የበረሓ ጐሽ፤ ጠባዩ ያውሬ፤ መልኩ የበሬ። ናሁኬ ብሄሞት ዘገበርክዎ ምስሴከ ይበልዕ ሣዕረ ከመ ላሕም ፡-(ኢዮ፵ ፡-፲፭)።
[2]፡-በቁሙ፤ የየብስ ዐንበሪ ከባሕር ተፈጥሮ በየብስ የሚኖር፤ ግሩማን አራዊት የሚፈሩትና የሚገዙት ከአራዊት ኹሉ የሚበልጥ መጨረሻ ግዙፍ ፥ የእንስሳት ራስ የአራዊት ንጉሥ፤ በኵራቸው ቀዳማያቸው፤ በተፈጥሮ የሌዋታን ወንድም ባሏ መስሏ። የሌዋታንን ፍች ተመልከት፤ ባለብሉዮች ግን ዝኆን ይሉታል። ወይትከፈሉ በይእቲ ዕለት ክልኤቱ ዐናብርት፤ ዐንበሪ አንስቲያዊት ዘስማ ሌዋታን ከመ ትኅድር በልጐተ ባሕር፤ ወለተባዕታይ ስሙ ብሄሞት ዘይእኅዝ በእንግድዓሁ በድወ ዘኢያስተርኢ፤ ወስሙ ዴንዳ በምሥራቀ ገነት ፡-(ሔኖ፷ ፡-፰)።
ብሔሞት ፡-በቁሙ፤–ብሂም ብህመ።
ብሔር ፡-(ራት፤ በሓይርት፤ በሓውርት። ዐረ ቢሓር፤ ብ በሕረት) ቦታ ሰፈር፤ ስፍራ፤ በሀገር ውስጥ ያለ ታናናሽ ክፍል። ይጸብበነ ብሔር፤ ግበሪ ለነ ብሔረ ኀበ ንነብር። ቦ ብሔር እምኀበ ይወፅእ ብሩር። አይቴ ብሔራ ለጥበብ። ገዳም ውአቱ ብሔር። ወበጺሖሙ ብሔረ ዘስሙ ጎልጎታ። ወወፅአ ስሙዓቱ በኵሉ በሓውርተ አድያም ፡-(ኢሳ፵፱ ፡-፳። ኢዮ፳፰ ፡-፩ ፡-፲፪። ማቴ፲፬ ፡-፲፭። ፳፯ ፡-፴፫። ሉቃ፬ ፡-፴፯)። ብሔር ጥሉል፤ ወፍራም ሥብ ውሃማ መሬት ለተክል የተመቸ። ብሔር ሥዑር፤ ሣራም፤ የሣር ቦታ መስክ ጨፌ ከልከል ፡-(ኢሳ፭ ፡-፩። መዝ ፡-፳፪)።
፡-ምድር፤ ሀገር፤ ከተማ፤ ገጠር፤ አውራጃ ግዛት፤ ታላላቅ ክፍል በስምና በሹም በወሰን በደንበር የተለየ። መላይቱ ምድር፤ የብስ ዓለመ ሰብእ። አይቴ ብሔርከ። ብሔረ ሕያዋን፤ ብሔረ ብንያም። ኢመሀኮሙ ለበሓውርት ኀበ ነበረ ሎጥ። በሓውርተ አሕዛብ። ውእቱ ተርፈ ለብሔር። ነሥእዎ እምነ ብሔር ፡-(ዮና፩ ፡-፰። መዝ ፡-፶፭። ኤር፩ ፡-፩። ሢራ፲፮ ፡-፰። ኢሳ፲ ፡-፲፫። ሢራ፵፬ ፡-፲፯። ፵፬ ፡-፲፬)።
፡-ሰው፤ ወገን ነገድ፤ ሕዝብ አሕዛብ በቋንቋ በመንግሥት በሕግ በሥርዐት የተለየ። ኵሉ ብሔር ኢመስሐ። መፍቅደ ብሔር። አንከሩከ በሓውርት። መጽኡ ኵሉ በሓውርት ውስተ ግብጽ። ኵሉ በሓውርት ዘቤተ እስራኤል። በበ በሓውርቲክሙ ደቂቀ ዕጓለ ፡-(፩ነገ ፡-፲፬ ፡-፳፬። ሢራ፴፰ ፡-፴፬። ፵፯ ፡-፲፯። ዘፍ፵፩ ፡-፶፯። ኤር፪ ፡-፬። መዝ ፡-፵፰)።
፡-ሰማይና ምድር፤ ሰማይ ከነግሉ ምድር ከነልብሱ፤ መላው ዓለም። ላዩም ታቹም ያንድ አምላክ ግዛት ስለ ኾነ፤ በምሳሌ ብሔር ተብሏል። ከመ ዝ ይቤ እግዚአ ብሔር ፡-(እግዚአብሔር) ሰማይኒ መንበርየ ወምድርኒ መከየደ እገርየ። እስመ ዚኣየ ውእቱ ኵሉ ዓለም በምልኡ ፡-(ኢሳ፷፮ ፡-፩ ፡-፪። መዝ ፡-፵፱)።
፡-ጊዜ፤ ሰዓት፤ ወራት ባመትና በወር በዕለት ያለ ክፍል። ክረምት ብሔር። እስመ ነግህ ብሔሩ። ወጸቢሖ 'ብሔር። እስከ ጸብሐ ብሔር። ጽልመት ብሔር። መስየ ብሔር ፡-(፩ዕዝ ፡-፲ ፡-፲፫። ግብ፪ ፡-፲፭። ፳፯ ፡-፴፫። ፩ነገ ፡-፳፭ ፡-፴፮። ሢራ፳፫ ፡-፲፰። ገድ ፡-ተክ)።
፡-የመጽሐፍ ክፍል፤ ታላቅ ዐቢይ አንቀጽ፤ አንድ ክፍል መጽሐፍ፤ ለብቻው አንድ ተብሎ የሚቈጠር፤ በውስጡ ብዙ ምዕራፍ ያለበት፤ እንደ ኦሪትና እንደ ነገሥት፤ እንደ ወንጌል እንደ ሐዲሳት ያለ። ይቤ በኦሪት ውስተ ሣልስ ብሔር ዘሌዋውያን። በውስተ ዳግም ብሔረ ኦሪት። ለኦሪት ባቲ ኀምስቱ ብሔር። አርባዕቱ ብሔረ ነገሥት። ክፍል ኃምስ እምዳግም ብሔር ዘመጽሐፈ ነገሥት ፡-(ፈ ፡-መ ፡-፪ ፡-፮ ፡-፬ ፡-፩። አብጥ ፡-፹፩። አቡሻ ፡-፲፱)።
ብህመት ፡-ድዳ መኾን፤ ድዳነት። ብህመተ ልሳን። ተፈትሐ ልሳኑ እምብህመት ፡-(መጽ ፡-ምስ። ስንክ ፡-ሠኔ)።
ብሕባሔ ፡-መፍጠር፤ መፈጠር፤ አፈጣጠር ፈጠራ፤ ተፈጥሮ። ዕብራይስጡ ሜሖሜር ቆራጽቲ ያለውን፤ ግእዙ ተቀረጽኩ ተገለፍኩ በማለት ፈንታ፤ እምጽቡር ብሕባሔከ ወእምኔሁ ቅሳሜነ ይላል፤ ፡-(ኢዮ፴፫ ፡-፮)። ከዚህ በቀር በሕብሐ ብሎ ፈጠረ የሚል አይገኝም።
ብኅባኄ ፡-–መፈጠር፤–በሕብሐ።
ብኍባኌ ብኅባኄ ፡-ግማት ክርፋት፤ ሽታው የሚያሰቅቅ የሚጐፈንን። እሬኢ ንስኀተ ሥጋየ ከመ ብኅባኄ አንበሳ ፡-(ኢዮ፮ ፡-፯)። ባለብሉዮች ግን ኀይል ብርታት ይሉታል።
ብሕታዌ ፡-ብቻ መኾን፤ ብቻ ብቸታ፤ ብቻነት። ትምህርት መዜንው በውስተ ሐዊር ወበብሕታዌ። ሰላም ለብሕታዌሁ። ብሕታዌ ንብረት ፡-(ፈላስ። ስንክ ፡-ጥር፳፪። ግን፲፭)።
ብሕትው ፡-(ዋን ዋት ቱት) ብቻውን የኾነ፤ ብቻውን የሚኖር፤ ብቸኛ ለብቻው የቆመ የተለየ፤ ገላ አካል ሰውነት። ትኩን ብሕቱተ በእንተ ጸሎት። ብሕቱትየ ፡-(ኪዳ።መዝ ፡-፳፩። ፴፬)።
ብሕትውና ፡-ባሕታዊነት፤ ብቸኝነት፤ ፍጹም ምናኔ። በእንተ ዘከመ ይኄይስ ሥርዐተ ብሕትውና እምሥርዐተ ማኅበር። ለመደ ብሕትውና በኣተ ብሕትውና ፡-(ፊልክ ፡-፩። ስንክ ፡-ሐም፲። ፈ ፡-መ ፡-፫ ፡-፯)።
ብሕትውናዊ ፡-የብሕትውና፤ የባሕታዊነት፤ ግብር አናዎር ሕግ ሥርዐት። ምንኵስና ብሕትውናዊት ፡-(ገድ ፡-ተክ)።
ብህኑን ፡-(ናን ናት ንንት) የባነነ፤ የበነነ የባከነ፤ ብኑን ከንቱ፤ በናና በካና፤ ፍሉጥ ብዑድ። ቃላተ ሕስወ ወብህኑነ ታርኢ። ይሜህሩ ብህኑነ ሥጋዌ ዘእንበለ ፅምረተ መለኮት፤ ኢብህኑን ትስብእቱ አምድማሬ መለኮቱ፤ ወኢብሕትው መለኮቱ እምትስብአቱ ፡-(ቄር ፡-ጰላ። መጽ ፡-ምስ)።
ብሕአት ፡-መቡካት፤ አቦካክ፤ ቡሖነት፤ ርሾ ፡-(ማቴ፲፮ ፡-፲፩ ፡-፲፪)።
ብሕእ ፡-(ኣት) ቡሖ፤ ርሾ ፡-(ሉቃ፲፪ ፡-፩)። በብሑእ ፈንታ ብሒእ እንደሚል፤ በብሕእ ፈንታ ብሑእ ይላል፤ ጥሬን በቅጽል ቅጽልን በጥሬ መለዋወጥ የጣፊና የመላሽ ስሕተት ነው። ወለእመ ኮነት ቀዳሚሃ ቅድስተ ወብሑእኒ ቅዱስ ከማሁ፤ ቡሖ ሊጥ። ኅዳጥ ብሑእ ብዙኀ ሐሪጸ ያብሐእ። አንጽሑ እንከ ብሑአ ብሉየ እምኔክሙ። ብሑአ ዘነሥአት ብእሲት ወኀብአቶ ውስተ ሐሪጽ፤ ርሾ ፡-(ሮሜ፲፩ ፡-፲፯። ፩ቆሮ ፡-፭ ፡-፮ ፡-፯። ማቴ፲፫ ፡-፴፫)።
ብሕውስ ፡-(ዕብ ባእሻህ) አብሾ አስተናግር፤ የዶሮ ኵስ፤ ግማታም ቅጠል፤ በባድማና በድብድባ የሚበቅል ቋያ፤ መጥፎ ቡቃያ። ወኮነት ሀገር በድወ፤ ወበቈለ ላዕሌሃ ሦክ ወአሜከላ፤ ወኮነት ብሕውሰ ወምጕሕያ ፡-(መቃ ፡-ገ፲፫)።
ብለኔ ፡-(ጽር ባላኔዎን። ዐረ ሐማም) መታጠቢያ፤ መነከሪያ፤ የውሽባ ቤት፤ ፍል ውሃ፤ ወይም ዐጣቢው ባለቤቱ። ኢይባእ ቤተ ብለኔ። ይበውእ ቤተ ብለኔ። ዘይትኀፀብ ምስለ አንስት በቤተ ብለኔ ፡-(ፈ ፡-መ ፡-፳፮ ፡-፭። ቀሌ። ቀኖ ፡-ሎዶ ፡-፳፱)።
ብሉሕ ፡-(ሓን ሓት ልሕት) የዳነ የወጣ ያመለጠ። ብሉሕ እመቅሠፍት ፡-(አዋል)።
ብሉል ፡-(ዕብ ባሉል) ቅይጥ፤ ውጥንቅጥ፤ ነከርት፤ የራሰ የለዘዘ፤ ርጥብ።
ብሉር ፡-(ዐረ በሉር። ሱር ቤሉራ። ጽር ቢሪሊዎን) ብርሌ ብርጭቆ። ዕንቍ። ፈርጥ፤ የብርሌ ዐይነት ፡-(ክብ ፡-ነገ ፡-፲፯)። ቢረሌን ተመልከት፤ ከዚህ ጋራ አንድ ነው።
ብሉቅ ፡-(ቃን ቃት ልቅት) የባለቀ፤ ያደገ የላቀ፤ ለዘር የበቃ። ፡-(ተረት) ያታወበ እጅ ያልባለቀ ልጅ።
ብሉት ፡-(ታን ታት ልት) የተበለተ፤ የተለየ ልዩ፤ ብቸኛ።
ብሉዕ ፡-(ዓን ዓት ልዕት) የበላ፤ የጠገበ። የተበላ፤ የተቃጠለ ፡-(ሄርማ ፡-ገ፷፯–፷፱)።
ብሉየ መዋዕል ፡-ዘመኑ ያረጀ፤ ዘመን ያስረጀው፤ የዘመን አሮጌ ሽበታም ፡-(ዳን፯ ፡-፱)።
ብሉየ መዋዕልና ፡-ቀዳማዊነት፤ ቅድምና፤ ዓለም ሳይፈጠር ዘመን ሳይቈጠር ቅድመ ዓለም መኖር። ዕሩያን በመለኮት ወበህላዌ ወበብሉየ መዋዕልና፤ በባሕርይ በአካል በቅድምና ፡-(ሃይ ፡-አበ)።
ብሉይ ፡-(ያን ያት ሊት) በቁሙ ያረጀ ያፈጀ፤ አሮጌ አንቲካ፤ ጥንታዊ ቀዳማዊ፤ የዱሮ የቀድሞ የፊት፤ ሕግ ኪዳን፤ መዋዕል ዘመን፤ መሣሪያ ልብስ መጽሐፍ፤ የመሰለው ኹሉ። ብሉይ መጽሐፍ። ብሉይ ብእሲ። ሕግ ብሊት። መጻሕፍተ ብሊት። ጻድቃነ ብሊት። ብሉያተ ረሰይኮን ለመዋዕልየ ፡-(ሮሜ፯ ፡-፮። ኤፌ፬ ፡-፳፪። ፈ ፡-መ ፡-፬ ፡-፩። ስንክ ፡-ሐም፲፩። ነሐ፰። መዝ ፡-፴፳)።
ብላተንዓሻ ፡-(ዐረ በናት ነዕሺን) ብላተ በናት፤ አዋልድ ታናናሽ ከዋክብት፤ ንዓሻ ነዕቪን፤ ታላቅ አባት ኮከብ፤ ወቦ የሚባል ባለብዙ ጭፍራ። ባለብሉዮች ጨረቃ ይሉታል። ተአምርኑ ጊዜሃ ለብላተንዓሻ ፡-(ኢዮ፴፰ ፡-፴፪)። ዕብራይስጡ ግን ታወፅእኑ ማዛሮተ በጊዜሁ ወትመርሖኑ ለዐይሽ ምስለ አዋልዲሁ ይላል፤ ማዛሮት መገብተ አውራኅ ናቸው።
ብላታ ብላቴና ን ፡-(ዐማርኛ) ሥልጡን ስብቅል አሽከር። ብሳቴን ጌታ፤ እግዚእ ሥሉጥ፤ መልአከ ምክር፤ መጋቢ።
(ጥ) ብላዕ ፡-(ዓት) ብላቶ፤ ትራፊ። ብላዐ አርዌ።ብላዐ ቍንቍኔ። ብላዐ ፃፄ ፡-(ዘሌ፭ ፡-፪። ፯ ፡-፳፬። ኢዮ፳፯ ፡-፲፰። ናሆ፩ ፡-፲)። በብላዕ ፈንታ ብልዕ ይላል፤ አያሰኝም።
ብሌን ፡-(ዐረ ሚል። ጽር ሚሊ) የኵል መኳያ ሣር፤ ወይም ሌላ ነገር ለዚሁ ብቻ የተሠራ። ያይንን ማሚቶ ብረቲቱን ብሌን ማለት ከዚህ የወጣ ነው። እንዳይን ብሌን ይጠብቅኽ እንዲሉ። አድባራተ ኵልሕ የኀልቁ በብሌን፤ ወከማሁ ዕድሜሁ ለብእሲ በዕለታት ፡-(ትእ ፡-ጴጥ)።
፡-ስመ ነገድ፤ ቋንቋ በሐማሴን ክፍል ውስጥ ያለ።
ብልኅ ፡-(ኃት) [1]፡- ስለት ሹለት፤ የሰይፍና የጦር አፍ አንደበት። ብልኀ ሰይፍ ትነድድ። ቅትሎሙ በብልኀ ሰይፍ። በብልኀ ሰይፍ እሙንቱ ረከቡ አክሊለ። ብልኀ ኵናት ዘተረግዘ ቦቱ እግዚእነ። በብልኀ ኵናት ገቦሁ ደጐጸ። ፡-(ፍ ፡-ነ ፡-፵፮። አፈ ፡-ተ፲፩። ስንክ ፡-ኅዳ፭። ግን፳፭)።
[2]፡-ብልኅ፤ ፡-(ዐማርኛ) በቁሙ፤ አስተዋይ ዐዋቂ።
ብልኀት ፡-በቁሙ፤ መስላት፤ መሾል፤ መፍጠን አሰላል፤ አሿሿል አፈጣጠን፤ ስለት ሹለት ፍጥነት፤ ብልኅነት ፈጣንነት። ወእምቅድመ ያስተርኢ ብልኀተ መብረቅ፤ ስለቱ ፍጥነቱ ብልጭታው ፡-(ቅዳ ፡-ግሩ)።
ብልባሌ ፡-ማርጀት ማለቅ፤ እርጅና፤ አሮጌነት። ጨርቅ፤ አሮጌ ማቅ፤ ዕላቂ ውዳቂ፤ ቍረንጮ ቅርንጥስ፤ የሐዘን የድኽነት ልብስ። ወኣቀንተክሙ ብልባሌ ውስተ ሐቌክሙ ፡-(ዓሞ፰ ፡-፲። ኢሳ፳፪ ፡-፲፪። ጥበ ፡-ጦቢ። አርጋ ፡-፯)።
ብልቲት ፡-ብልጩት፤ እዝኅ፤ ሥጋ የሚቈርጥ የሚበልት ስለታም ደንጊያ፤ እዝኅን እይ።
ብልዐት ፡-መብላት፤ መበላት፤ አበላል። ብልዐተ እክል። ለብልዐት። ብልዐተ ዕፄ ረከቦሙ ፡-(መዝ ፡-፶፪። ኩፋ ፡-፳፫። ኢዮ፬ ፡-፲፬)።
ብልየት ፡-ማርጀት፤ እርጅና፤ አሮጌነት። ሐደሶ ለቤት እምብልየቱ። ተሐደሳ እምብልየት አብያተ ክርስቲያናት።ርቱዕ ናሰስል እምላዕሌን ዘንተ ብልየተ ፡-(ፍ ፡-ነ ፡-፴፫ ፡-፬።ስንክ ፡-ግን፩። አፈ ፡-ተ፲፬)።
ብሉት ፡-(ታን ታት ልት) የተበለተ፤ የተለየ ልዩ፤ ብቸኛ።
ብሱል ፡-(ላን ላት ስልት) የበሰለ የተቀቀለ፤ ቅቅል። ረከቦ ለውእቱ ጸብኅ ፍሉሐ ወብሱለ ፡-(ስንክ ፡-ታኅ፲፩)። ኢብሱል በማለት ፈንታ ብሱል ይላል ፡-(ዘፀ፱ ፡-፴፪)።
ብስሎ ፡-ብስል ቅቅል አንፊላ። ብስሉን ቅቅሉን። ጥራዮ ወኢብስሎ በማይ ፡-(ዘፀ፱ ፡-፴፪)።
ብሥራታዊ ፡-ባለምሥራች፤ ወንጌላዊ፤ ሠናየ ዜና። ሰላም ለከ ገብርኤል ብሥራታዊ። አባ ብሥራታዊ ማርቆስ ፡-(ደራሲ። አቡሻ ፡-፶)።
ብሥራት ፡-(ታት) በቁሙ፤ የምሥራች ሐዲስ ነገር፤ ደስ የሚያሰኝ ወሬ፤ ስብከት ትንቢት፤ ወንጌል ትሥጉተ ቃል። ብሥራተ እግዚ በልሳነ ገብርኤል ዘአብሠራ ለቅድስት ድንግል። ብሥራተ ማቴዎስ ፡-(አቡሻ ፡-፴፰። ማቴ ፡-፩)። ብሥራትከ ኪ እያለ ይዘረዝራል፤ የምሥራች ደስ ይበልኽ ማለት ነው። ብሥራትከ ኦ ንጉሥ ፡-(ገድ ፡-ተክ)። ንኡስ አገባብ ፡-(ዕር፲፫ ፡-ቍ፻፲፩)።
ብስራት ፡-ባሶር፤–በሢር በሠረ፤ ብሥራት፤ ባሦር።
ብረት ፡-(ዐማርኛ) በቁሙ፤ ኀጺንን ተመልከት። ብርቱ ማለት ከዚህ ወጥቷል።
ብሩህ ፡-(ሃን ሃት ርህት) የበራ የጠራ ነጭ፤ የታየ ግልጥ። ደመና ብሩህ። ካህናት ብሩሃን ከመ ፀሓይ። ከመ ይኩና አዕይንቲከ ብሩሃተ ላዕለ ዝንቱ ቤት። ጽዕዱት ወብርህት ፡-(ማቴ፲፯ ፡-፭። መዋሥ። ፪ዜና ፡-፮ ፡-፳። ማሕ፰ ፡-፭)።
ብሩር [1]፡-(ራን ራት ርርት) የተመረጠ የተለየ፤ ልቅም ጥሩ ነጭ ማዕደን።
[2]፡-(ብ በራውር፤ ብሩራት) ብር፤ ክቡር ገንዘብ የወርቅ ምክትል። ብሩር ጽሩይ። ብሩር ኅሩይ። ሠላሳ ብሩር። ህየንተ ወርቅ ወብሩር ጸዐዳ ፡-(መዝ ፡-፲፩። ምሳ፰ ፡-፲፱። ማቴ፳፮ ፡-፲፭። ደራሲ)።
ብሩክ ፡-(ካን ካት ርክት) የበረከ የተንበረከከ እንብርክ።
ብሩዝ ፡-(ዛን ዛት ርዝት) የተበረዘ የተቀላቀለ፤ ቅልቅል፤ ቱሱሕ።
ብራና ፡-(ዐማርኛ። ጽር ሜምብራና) በቁሙ፤ ብርሃና፤ በርሀን ተመልከት። ኅልፍ አሐደ ብራና ወእምዝ ኀሊፈከ ሰመንተ አዕማደ ወዐሠርተ ወሠለስተ መሥመራተ ትረክብ መትልወ ዝንቱ ቃል ፡-(አዋል)።
ብሬት እብሬ ት ፡-ፈረቃ ፈንታ፤ ተራ ሰሞን፤ የጊዜ ክፍል። አመ በጽሐ ዕለተ እብሬታ ለአስቴር ከመ ትባእ ኀበ ንጉሥ። ወፈጺሞ መዋዕለ እብሬቱ አተወ ቤቶ። ሊቀ ካህናት ዘእብሬቱ ይእቲ ዓመት። መዋዕለ እብሬትከ እብሬተ ርትዕ ወሣህል። እብሬተ ሰዐታት ፡-(አስቴ፪ ፡-፲፭። ሉቃ፩ ፡-፳፫። ዮሐ፲፩ ፡-፵፱። ስንክ ፡-ጥር፯። ፩ዜና ፡-፳፫ ፡-፴፪)። አንዳንድ ጊዜም በበእንተ ፈንታ እየገባ፤ ስለና ምክንያት ይኾናል። ከመ ትሕየው ነፍስየ በእብሬትኪ። ይትቀነይ ሎቱ በእብሬትከ ፡-(ዘፍ፲፪ ፡-፲፫። ዮዲ፲፩ ፡-፯)።
ብርሐት ፡-በራ ቡሓ መኾን ቡሕነት፤ በራነት መላጥነት። ሽሽት በረሓ መግባት ፡-(ዘሌ፲፫ ፡-፵፪ ፡-፵፫)። ብርሐት ትፃእኪ። ውስተ ኵሉ ርእስ ብርሐት። ጴጥሮስ ቦቱ ብርሐት ፡-(ኢሳ ፡-፳፬። ፲፭ ፡-፪። ቀሌ)።
ብርሃነ ልብ ፡-ጥሩ ዕውቀት፤ ጥበብ ትምርት፤ መንፈሳዊ ሀብት ፡-(ፊልክ)።
ብርሃነ መብረቅ ፡-ነጸብራቅ ብልጭታ፤ ብልጭልጭታ ፡-(ዕን ፡-፲፩)።
ብርሃነ ስብሐት ፡-የክብር ብርሃን፤ ጮራ ምዕዛር ፡-(ዕብ፩ ፡-፫)።
ብርሃነ ዐይን ፡-ማሚቶ ብሌን፤ ጥራት ጥሩነት ፡-(መዝ ፡-፴፯)።
ብርሃነ ገጽ ፡-ይቅርታ ቸርነት፤ ባለሟልነት፤ የደስታና የፍቅር ምልክት ፡-(መዝ ፡-፬)።
ብርሃና ፡-ብራና የተፋቀ የተራመመ ነጭ ሰሌዳ ማእስ ወይም ወረቀት ክርታስ። ብርኒንና ብራናን ተመልከት፤ የዚህ ዘሮች ናቸው።
ብርሃናዊ ፡-ብርሃናም ተፈጥሮው ከብርሃን የኾነ፤ ንጹሕ ብሩህ ጽሩይ ጸዐዳ። መልአክ ብርሃናዊ። ብርሃናውያን። ብርሃናዊት ፡-(ቅዳ ፡-ሕር። ክብ ፡-ነገ። ገድ ፡-አዳ)።
ብርሃን ፡-(ናት) ዝኒ ከማሁ፤ በቁሙ፤ መዓልት፤ መብራት፤ ፀሓይ ጨረቃ ኮከብ፤ የእሑድና የረቡዕ ፍጥረት ፡-(ዘፍ ፡-፩ ፡-፫ ፡-፬ ፡-፲፬–፲፰)። ወይከውን ብርሃነ ወርኅ ከመ ብርሃነ ፀሓይ። ብርሃነ ማኅቶት። ወበእደዊሆሙ ይጸውሩ ብርሃናተ እሳት ፡-(ኢሳ፴ ፡-፳፮። ሉቃ፰ ፡-፲፮። ተረ ፡-ኤር)።
[1]፡-ዐይን፤ ማየት። ጸጎከ ለዕዉር ብርሃነ ፡-(ስንክ ፡-ነሐ፲፭)።
[2]፡-ብርሃን፤ ፡-(ዐረ ቡርሃን) መምህር አብነት፤ መፈክር መተርጕም ገልጦ የሚያስረዳ ፡-(ማቴ፭ ፡-፲፬። አቡሻ ፡-፶፫)።
ብርህርህት ፡-ብርህርህት፤ የለምጽ ቡቃያ፤ ነጫጭ ነቍጣ ነጠብጣብ ፡-(ዘሌ፲፫ ፡-፴፰)።
ብርስኔ ፡-ብርስኔ፤–ባርሰነት፤–ምርስኔ።
ብርስን ፡-ብርስን፤ ፡-(ዐረ ቡልስን፤ ዐደስ። ዕብ ዐዳሻ) ምስር፤ ጥሩ ያበባ እኸል ወጥ የሚኾን፤ ቅንጣቱ ታናናሽ ክኩ ቀይ። ምስራዊ ዘእምስር ማልት ነው፤ የግብጥ ብርስን ካገር ኹሉ ብርስን የሚያምር የሚበልጥ በውድ የሚሼጥ ስለ ኾነ የሻም ዐረብ ዐደስ መስሪ እንዲል ምስራዊ ሲል፤ ተርሙስ ግብጦ እንዲባል ብርስንም ምስር ይባላል፤ ጥንተ ስሙ ዐደስ በምርስኔና በብርስኔ ሞክሼ ወደ ባርሰነት ኺዷል። ፪ኛም ስለ ቅላቱ ግብጥ ይባላል፤ ግብጥ ምስር እንዲሉ። ልባም ሴት በጥሩ ዐዋዜ ሠርታ ስታቀርበው በቅላት ላይ ቅላት ተጨምሮለት መልኩ ጁሕ ጃዊ እንድኪ ፍሕሶ፤ ዐረብ አንቀልባ የሲፍ አበባ ይመስላልና፤ የምሥራች ለሚል ምስር ብላ ማለት ስለዚህ ነው፤ የምሥራች ቅሉ ከምስር ወጥ መጥቷል። ሽማግሎችም የምስር ወጥ ብኵርና የሚያሼጥ ይሉታል ፡-(ዘፍ፳፭ ፡-፴፬። ኩፋ ፡-፳፪)።
ዐተረ ወብርስነ። ገራህት ዘምሉእ ብርስነ ፡-(፪ነገ ፡-፲፯ ፡-፳፰። ፳፫ ፡-፲፩። ሕዝ፬ ፡-፱)። የምስር ዐይነት ፫ ነው፤ ከዚህ ሌላ ያይጥ ምስር የገመል ምስር የሚባል አለ። ይበልዑ ሠለስተ ብርስነ ፡-(ስንክ ፡-ኅዳ፲፫)።
ብርቅ ፡-በቁሙ፤ ወትሮ የማይታይ በኹሉ የማይገኝ ድንቅ ሥራ ፥ ጕድ ታምራት ፥ መንከራት።
ብርቡር ፡-(ራን ራት ብርት) የተበረበረ የተዘረፈ፤ ውስጠ ክፍት ባዶ።
ብርባሬ ፡-(ሳቢና ጥሬ ዘር) መበርበር ፡-(ጥበ) መበርበር፤ አበራበር፤ ብርበራ፤ ብዝበዛ ዘረፋ ወረራ ፡-(አዋል)።
ብርት ፡-(ታት። በሪር በረ፤ ብሩር) በቁሙ፤ የብረት ወገን የብር ምክትል፤ ብርቱ ማዕደን፤ መዳብ ፥ ንሓስ፤ መዳብ ቀዩ፤ ንሓስ ብጫው። ግብረ ብርት ወኀጺም። ብርት ርሱን። ብርተ ሊባኖስ። ፍጽምከ ዘብረት ፡-(ዘፍ፬ ፡-፳፪። ሕዝ፵ ፡-፫። ራእ፩ ፡-፲፭። ኢሳ፵፰ ፡-፬)።
ብርትኳን ፡-(ዐረብ) በቁሙ፤ በኵረ ሎሚ፤ ጥሩ ጥፍጥ ተክል።
ብርኒ ፡-ድመት የጽርኒ ዐይነት። ዐይነ ብር ዐይናማ ማለት ነው፤ ለድመት አያበሩላት እንዲሉ።
ብርእ ፡-–መቃ ሸንበቆ፤–በሪዕ በርዐ፤ ብርዕ።
ብርዕ ፡-(ብ አብራዕ) ሸንበቆ፤ የጐሽ መቃ፤ የሸንበቆ ዐይነት ውስጠ ክፍት፤ አገዳ ቅልጥም። በቁሙ የጸሓፊ ብር፤ የገብስ የስንዴ ብር፤ ገለባ ሣር ቈሻሻ። በትረ ብርዕ። ብርዐ ባሕሩስ። አብትር ፅቡሳን ወአብራፅ ቅጥቁጣን።
ዐምዳ ወአብራዒሃ ፡-(ኢሳ፴፮ ፡-፮። ፩ ፡-፴፩። መጽ ፡-ምስ። ዘፀ፳፭ ፡-፴፩–፴፮)። ሰብዐቱ ሰብል ዘሠዊት ዘሠረጹ እምአሐዱ ብርዕ። ብርዐ ይመስሎ መፍጽሕ። ሣዕር ወብርዕ ዘይየብስ። እሳት እንተ ትበልዕ ብርዐ ፡-(ዮሴፍ። ኢዮ፵፩ ፡-፳። ፲፫ ፡-፳፭። ዮኤ፪ ፡-፭። ዓብድ ፡-፲፰። ዘፀ፭ ፡-፲፪። ፲፭ ፡-፯)። ብርእ ተብሎ እንደ ዕብራይስጡ በአልፍ ሲጣፍ ግን፤ የማግስኞ ፍጥረት ያሰኛል ፡-(ዘፍ፩ ፡-፲፩ ፡-፲፪)።
ብርኵታ ፡-(ዐማርኛ) በቁሙ፤ በፍም የሚበስል ርሚጦ ቂጣ፤ ሲበሉት የሚያጠግብ የሚመክት የሚበረክት፤ የጭብጦ ዐይነት። ከመ በላዕሌሁ ያስተርኢ ግብረ በሊታ፤ ዘዕውሩ ተወልደ ብርኵታ ፡-(ቅኔ)።
ብርኵት ፡-የደንጊያ ግርንቡድ፤ ወይም የብረት ዙሓ ከባድ። ወቦኡ ክልኤቱ እምአግብርቲሁ በሌሊት ወአንበሩ ዲበ ገጹ ለበምከር ንጉሠ ፋርስ ብርኵተ፤ ወነበረ አሐዱ እምኔሆሙ ዲበ ርእሱ ወካልኡ ዲበ እገሪሁ እስመ ውእቱ አረጋዊ ዐቢይ ወሞተ ሶቤሃ ፡-(ጊ ፡-ወ ፡-ሐ ፡-ገ፵፰)።
ብርክ ፡-(ብ ብረክ፤ አብራክ) ጕልበት ጭን፤ ማቀፊያ፤ መታጠፊያ መንበርከኪያ። አዕደወኒ እስከ ብርክ። ወደክመኒ ብረክየ በጾም። አብራኪከ እለ አውተራ ስግደተ። ሐቂፍ በአብራክ። በእንተ አብራኪሃ እለ ሐቀፋከ ፡-(ሕዝ፵፯ ፡-፬። መዝ ፡-፻፰። ደራሲ። አርጋ ፩። ሳታት)። ብራኳ ብርኵማ ማለት ከዚህ የወጣ ነው።
ብርዝ ፡-(ትግ በቲሐ) በቁሙ፤ በተሓ ለጋ ጠጅ ጌሾ ያልበዛው ያልበሰለ።
ብርያል ፡-(ጽር ቤሪያል) የሰይጣን ስም፤ ቤልሖርእን እይ፤ ከዚህ ጋራ አንድ ነው ፡-(ዕር ፡-ኢሳ፩ ፡-፰። ፪ ፡-፬። ፫ ፡-፲፩ ፡-፲፫። ፬ ፡-፪ ፡-፲፮ ፡-፲፰። ፭ ፡-፩ ፡-፲፭ )።
ብርያሚን ፡-–ሕጹጻን፤–ድርያሚን።
ብርፎሪኮን ፡-(ጽር ፕሮፎሪኮስ) የትቢትና የስብከት የተግሣጽ ቃል ጩኾ ገንትቶ አሰምቶ የሚናገሩት። ወብርፎሪኮንኒ ውእቱ ቃል ዘሰምዕዎ ነቢያት እምእግዚ ወውእቱ ቃለ ትንቢት ፡-(ሃይ ፡-አበ ፡-ጎር)።
ብቁዕ ፡-(ዓን ዓት ቍዕት) የበቃ፤ የተጠቀመ ባለጥቅም ፡-(ሄርማ)። ዳግመኛም በብቁዕ ፈንታ ባቍዕ ይላል፤ አያሰኝም። ባቍዐ ረስየኒ። ባቍዐ ሎቱ ጸግዎ ፡-(ሄርማ። መስተ)።
ብቁጽ ፡-(ጻን ጻት ቍጽት) የተጫረ፤ የመረተ፤ የበሰለ፤ የሟከከ፤ የተንደረከከ። ረከቡ ፍሕመ ብቁጸ። አንጻሕኮ ለኢሳይያስ በፍሕመ አሳት ብቁጽ ፡-(ዮሐ፳፩ ፡-፱። ጥበ ፡-ጠቢ። ስንክ ፡-ታኅ፳፯። ሠኔ፲፬። መጽ ፡-ምስ)።
ብቍዐት በቍዔት ፡-(ታት) መብቃት፤ ብቃት። መጥቀም፤ መጠቀም፤ አጠቃቀም፤ ጥቅም ትርፍ፤ ረብ ርባታ ጠቀሜታ። ኢይክል በቍዔታ ለነፍሱ። ኢይከውነከ ለበቍዔትከ። እመ ኢተፈጸመ ነሢአ በቍዔት ባቲ። ምስለ በቍዔታት። እስመ ጾም በቍዔት ባቲ። ከመ ያርዒ ዕበየ በቍዔታ ለሕማማት ፡-(ሢራ፴፯ ፡-፲፬። ፪ነገ ፡-፲፰ ፡-፳፪። ፍ ፡-ነ ፡-፳፰። ድጓ። አፈ ፡-ድ፰)።
ብቃው ፡-አፍ፤ ክፍቱ ዋሻው የሚጮኸው የሚናገረው።
ብቅወት ፡-መከፈት፤ አከፋፈት፤ ክፍትነት።
ብቅው ፡-(ዋን ዋት ቁት) የተከፈተ የተለቀቀ፤ ክፍት ልቅ፤ ለቃቃ፤ አፈ ሰፊ። ብቅው ለውኂጥ። ብቅወ ጕርዔ ወአፍ ፡-(አርጋ ፡-፩። ደራሲ)።
ብቱል ፡-(ላን ላት። ዐረብ) ድንግል፤ ሴት ያላወቀ ወንድ። ባተሌ፤ ፈት መዐስብ፤ ሚስቱ ሙታ ወይም በነውር ተፈታ ብቻውን የሚኖር፤ ድንግላይ ማለት ነው።
ብቱክ ፡-(ካን ካት ትክት) የበተከ፤ የተበተከ የተቈረጠ የተበጣጠሰ፤ ብጥስጥስ። መሥገርት ብቱክ። አሣእን ብቱክ ፡-(ኢሳ ፡-፲፱ ፡-፬። ኢያ፱ ፡-፫)።
ብትከት ፡-መቍረጥ፤ መቈረጥ መበጠስ፤ አበጣጠስ ብጠሳ፤ ብጥስነት። በይብሰት ፈንታ ብትከት ይላል፤ ስሕተት ነው። እለ አልቦሙ ብትከት ፡-(መሳ፲፮ ፡-፯ ፡-፰)።
ብትክ ፡-አባላ የተመታ፤ ጥንብ ውዳቂ፤ ታርዶ የሰነበተ ፡-(ዘሌ፲፬ ፡-፯። ግብ፳፩ ፡-፳፭)።
ብነት ፡-(ዕብ ምናት። ሱር ምናታ፤ ክፍል ዕድል) ዐሥራት፤ እጅ መንሻ፤ በረከት፤ በፈቃድ የሚሰጥ ስጦታ፤ እንቍጣጣሽ ገብረ ሰላም ያክፋይ የጦም ቈሎ የባል ዶሮ፤ የሸማኔ የቀጥቃጭ የመጣፍ ገላጭ ይህን የመሰለ ኹሉ ፡-(ግብ፲፱ ፡-፲፮ ፡-፲፱)።
ብናሴ ፡-ጨረቃ ፣ የጨረቃ ስም። እብላንና ኤራስን ተመልከት።
ብንት [1]፡-(ዕብ ባት። ዐረ ቢንት። ሱር ባዲታ) ሴት ልጅ፤ ወለት፤ እንስት፤ ቄብ ልጃገረድ።
[2]፡-(ዕብ ኢሾን) ያይን ማሚቶ ጥቍሩ ብረቱ ብሌኑ፤ እንደ መስታዮት የሰው መልክ የሚታይበት፤ ብርሃን የሚሣልበት። ዕቀበኒ ከመ ብንተ ዐይን። ብንተ አዕይንቲሁ ይሬኢ ጽልመተ። ብንተ አዕይንቲሁ ከመ ኵሕል። ኢታረምም ብንተ ዐይንኪ ፡-(መዝ፲፮ ፡-፱። ምሳ፳ ፡-፳። ስንክ ፡-ታኅ፲፩። ስቈ፪ ፡-፲፰)።
ብዑል ፡-(ላን ላት ዕልት) የከበረ፤ የበለጠገ፤ የዘመነ የጌተየ፤ ብዙ ገንዘብ ያለው። ዕደው ብዑላን። አንስት ብዑላት። ሀገር ብዕልት። አልቦ ብዕል ዘይፈደፍድ እምነፍስ ብዕልት ፡-(ሢራ፵፬ ፡-፮። ኢሳ፵፪ ፡-፬። ፴፫ ፡-፳። ፈላስ)። በብዖል ፈንታ ባዕል፤ በባዕል ፈንታ ብዑል ይላል፤ ፍችው አንድ ነው ፡-(ራእ፪ ፡-፬። ፫ ፡-፲፯)።
ብኡስ ፡-(ሳን ሳት እስት) የባሰ የከፋ፤ የተጠላ፤ ክፉ መጥፎ። ብዑድ ርሑቅ ግዱፍ በማለት ፈንታ ብኡስ ይላል አያሰኝም ፡-(፪ነገ ፡-፲፬ ፡-፲፱)።
ብዑድ ፡-(ዳን ዳት ዕድ) የተለየ ልዩ፤ ሌላ ዐይነት፤ ሩቅ ጥልቅ፤ ረቂቅ። ዘከመ ተፈልጦ ማእከለ አሮን ወማእከለ ክርስቶስ ብዑድ ፈድፋደ ከማሁ። ብዑዳን ብዙኃን። ብዑድ ሥነ ላሕይ። ብዑድ እምኅሊና ፡-(አፈ ፡-ተ፲፩። ቄር ፡-እስት። ቅዳ ፡-ግሩ)።
ብዒል ሎት ፡-(ብዕለ ይብዕል፤ አው በዐለ፤ ይቤዕል ይብዐል። ዕብ ባዐል። ዐረ በዐለ። ሱር ብዓል) መክበር መበልጠግ መጌትየት፤ ብዙ ገንዘብ ማግኘት፤ መላቅ መብበለጥ፤ በሀብት ማደግ። ሚስት ማግባት፤ ባል መኾን። ነድይኒ ወብዒልኒ እምኀበ እግዚ። ሠያጢ ወሰካሪ ኢይብዕል። ዘይብዕለከ። ምንት ይብዕላ ለጥበብ። በከመ ይብዕል ወሬዛ ድንግለ ፡-(ሢራ፲፩ ፡-፲፬። ፲፱ ፡-፩። ፰ ፡-፪። ጥበ፰ ፡-፭። ኢሳ፷፪ ፡-፭)። አካኼዱ በጥሕረና በጸዐለ መንገድ ስለ ኾነ፤ በዐለ ይቤዕል፤ በከመ ይቤዕል ሲል ይገኛል። ኹለተኛም ፥ በብዕለ ፈንታ ተብዕለ ይላል፤ አያሰኝም። እለ ይትበዐላ ደርገ ፡-(ስንክ ፡-ሐም፳፯)።
ብኢስ ሶት ፡-(ብእሰ ይብእስ ይብአስ። ዕብ ባአሽ፤ ገማ። ዐረ በኢሰ) መባስ መጽናት፤ መክፋት፤ ማገርሸት፤ መቈጣት፤ እየባሰ መኼድ፤ መጕዳት። መጠላት ማስጠየፍ፤ ማስቀየም፤ የደዌ የቍስል የጠባይ የግብር የክፉ ነገር። በሽታ ቢስ ማለት ከዚህ የወጣ ነው። ወእመሂ አርመምኩ ይብእሰኒ ሕማምየ። ዘላዕለ ኃጥኣን ይብእስ ምስብዒተ ዝንቱ ኵሉ። ይብእሰከ ረጊፅ ውስተ ቀኖት በሊኅ። ብእሶ ለንጉሠ ፋርስ። እበድ ዘይብእሶሙ ፡-(ኢዮ፲፮ ፡-፮። ሢራ፵ ፡-፰። ግብ፱ ፡-፭። ፬ነገ ፡-፲፯ ፡-፬። ፩ጢሞ ፡-፮ ፡-፱)።
፡-ማደግ፤ መጐልመስ፤ አካለ መጠን ማድረስ፤ መግነን፤ ፍጹም ጐበዝ መኾን። መድፈር መጨከን፤ መቀልጠፍ መፍጠን፤ ያርበኛ። ተብዐን እይ፤ የዚህ ጎር ነው።
ብዒር ሮት ፡-(በዐረ ይብዕር ይብዐር። ዕብ ባዐር) ጨርሶ መብላት፤ ማብላት ማቃጠል፤ ከብትን እሳትን ወደ ሣርና ወደ ቋያ መስደድ መልቀቅ። ሞኝ አላዋቂ መኾን፤ ከዚህ የተነሣ ከብት እንስሳ መባል። ማረስ መቁፈር፤ መማስ መመንቀር፤ መደደቅ መደንጐር፤ ገብር ገበሬ መኾን።
ብዒድ ዶት ፡-(በዐደ ይብዕድ ይብዐድ። ዐረ በዒደ ራቀ) ማባድ፤ ባዕድ፤ ማድረግ፤ መለየት መነጠል፤ ማራቅ ማስገለል፤ መለወጥ መቀየር፤ ሌላውን በሌላ ወይም ያነኑ አንዱን፤ እንደ በትረ ሙሴ። ዘአመ በዐደ ገጾ እምቅድሜሁ ለአቤሜሌክ። አኮ መዪጥ ርእሶ ውበዒድ እምፍጥረቱ ፡-(አርእስተ ፡-መዝ ፡-፴፫። መጽ ፡-ምስ)። አንዳንድ መጽሐፍ በበዐደ ፈንታ አብዐደ ይላል፤ አያሰኝም። ሰብአ ከማነ ይሬስይዎ ወያብዕድዎ እምወልድ ፡-(ቄር ፡-ጰላ)።
ብዔል ፡-(ጽር ቤኤል። ዕብ ባዓል) ዝኒ ከማሁ፤ ስመ ጣዖት፤ ሞአባውያን የሚያመልኩት። ብዔል ፌጎር፤ ብዔል ጣዖቱ፤ ፌጎር ሥርዐቱ። ፌጎርን ተመልከት ፡-(ዘኍ፳፭ ፡-፫። ዘዳ፬ ፡-፫። መዝ ፡-፻፭)።
ብዔል ዜቡል ፡-(ጽርእ። ዕብ ወዐረ ባዓል ዝቡል) የሰይጣን ስም፤ ያጋንንት አለቃ፤ ብዔል በዓል፤ ዜቡል መንገድ ቤት፤ በተገናኝ መሪ አሳዳሪ ባለቤት ማለት ነው ፡-(ማቴ፲፪ ፡-፳፬ ፡-፳፯)። በዝብል ዘይቤ ሲፈቱት ግን፤ የጕድፍ ጋኔን ልክስክስ፤ ጕድፍ ሰራዊቱ ከሰማይ ተጠርጎ የወደቀ፤ ጕድፋም ጨምላቃ የጕድፎች አለቃ ያሰኛል። ምስጢሩ ከሐራውያ ይሰማማል፤ ዘበለንና ዜቡልን ተመልከት።
ብዕል ፡-(ላት) በቁሙ፤ ብልጥግና ባለጠግነት፤ ክብር ድልብ ብዙ ገንዘብ። ብኩኅ ብዕልየ። ብዕል ዓለማዊት። ብዕል ዘይትዐቀብ በኀበ ዘአጥረየ ፡-(ኢዮ፴፩ ፡-፳፭። ፈ ፡-መ ፡-፲፰ ፡-፩። መክ፭ ፡-፲፪)።
፡-ምላት ስፋት፤ ብዛት ብዙነት። ብዕለ ስብሐቲሁ። ብዕለ ጥበቢሁ ፡-(ሮሜ፱ ፡-፳፫። ፲፩ ፡-፴፫)።
ብእሰት ፡-መባስ ፣ መክፋት፤ አባባስ አከፋፍ፤ ብሶት ችግር።
ብእሲ ፡-(ዕብ ኢሽ) ጕልማሳ፤ ኀይለኛ ወጣት፤ የ፳ የ፴ ዓመት ጐበዝ፤ ምሉ ሰው፤ ባል፤ ተባት ወንድ፤ ሰውነት። ተፈሣሕ ኦ ብእሲ በውርዙትከ። ወአመ ኮንኩ ብእሴ ነሣእኩ ብእሲተ። ኮነ ብእሴ ወተስቅለ። ብእሲ ምስለ ብእሲቱ። ትወልድ ወልደ ብእሴ። አስመ ወለደት ብእሴ። እብል በእንተ ብሉይ ብእሲ ፡-(መክ፲፩ ፡-፱። ጦቢ፩ ፡-፱።ጸሎ ፡-ሃይ። ኤር፮ ፡-፲፩። ፍ ፡-ነ ፳፬ ፡-፮። ዮሐ፲፮ ፡-፳፩። ኤፌ፬ ፡-፳፬)።
ብእሲ ብእሲ ፡-ሰው ኹሉ፤ አንዱም አንዱም፤ በየራሱ ፡-(ዘፀ፲፮ ፡-፳፱። ሕዝ፲፬ ፣ ፬። ዘሌ፲፭ ፡-፪)።
ብእሲሁ ፡-ሰው ኹሉ፤ አንዱም አንዱም፤ በየራሱ ፡-(ዘፀ፲፮ ፡-፳፱። ሕዝ፲፬ ፣ ፬። ዘሌ፲፭ ፡-፪)።
ብእሲታ ፡-ይች ሴት፤ ያች ሴት፤ ሴቲቱ፤ ሴትዮይቱ፤ ሴቷ ሴትነት። ምንት ብእሲታ ፡-(ሉቃ፯ ፡-፴፱)።
ብእሲት ፡-(ዕብ ኢሻ፤ ኢሽት) ቈንዦ፤ ምሉ ሴት፤ ሚስት። ብእሲት ድንግል። ብእሲ ወብእሲት። ብእሲተ ብእሲ ፡-(ዘሌ፳፩ ፡-፲፫። ዘፀ፳፩ ፡-፳፰። ዘዳ፭ ፡-፲፯)።
ብእሲቶ ፡-የቅርብ ሰሚ ተጠሪ፤ አንች ሴት፤ ሴቶ፤ እሜቶ፤ ወይዘሮ ፡-(ዮሐ፪ ፡-፬። ፬ ፡-፳፩። ፳ ፡-፲፫ ፡-፲፭)። ብእሲና ብእሲት እንደ ወርቅና እንደ ሐራ ውስጠ ብዙዎች ስለ ኾኑ፤ ግልጠ ብዙነት የላቸውም፤ ብእሲ ከዕደው፤ ብእሲት ከአእንስት ይገባሉ።
ብእሴ ሐቅል ፡-በረኸኛ፤ ዐዳኝ፤ ወንበዴ፤ ሽፍታ ወያኔ ፡-(ዘፍ፳፭ ፡-፳፯)።
ብእሴ ኅይል ፡-ኀይለኛ ጕልበታም ባለአእምሮ ፡-(፩ነገ ፡-፩ ፡-፵፪)።
ብእሴ ምድር ፡-ዐራሽ ገበሬ፤ ጃን ገበር፤ የርሻ ባለቤት ፡-(ዘፍ፵፱ ፡-፲፭)።
ብእሴ ሰላም ፡-ፍቅረኛ፤ ፍቅር ወዳድ፤ አስታራቂ ፡-(መዝ ፡-፴፮)። ብእሲ፤ በስም በግብር በዘር በነባር እየተናበበ በዚህ አምሳል እንደ ስልቱ እንዳመጣው ይፈታል።
ብእሴ ዐመፃ ፡-ዐመጠኛ፤ ዋሾ፤ ግፈኛ፤ ሐሳዊ መሲሕ ፡-(፪ተሰ ፡-፪ ፡-፫)።
ብእሴ እግዚ ፡-ነቢይ፤ ሐዋርያ፤ ጻድቅ፤ ሰማዕት፤ ቅዱስ ፡-(፩ነገ ፡-፱ ፡-፮ ፡-፲። ፩ጢሞ ፡-፮ ፡-፲፩)።
ብእሴ ደም ፡-ደም አፍሳሽ፤ ነፍስ ገዳይ፤ ዐርበኛ የጦር ሰው ፡-(መዝ ፡-፭)።
ብእሴ ፍትወት ፡-መውደድ መወደድ ያለው፤ ሥልጡን ስብቅል ፡-(ዳን፲ ፡-፲፩)።
ብዕራዊ ፡-የበሬ፤ በሬማ፤ በሬያም ባለበሬ፤ ዐራሽ ገበሬ፤ ባሪያ ሎሌ ቅን አሽከር፤ ተገዥ አገልጋይ። ብእሲት ብዕራዊት ታስተፌሥሖ ለምታ ፡-(ሢራ፳፮ ፡-፪)።
ብዕር ብዕራ ብዕራይ ፡-(ዕብ፤ ብዒር፤ ከብት። ሱር ብዒራ። ዐረ በዒር፤ ገመል አጋሰስ) በሬ፤ የቀንድ ከብት፤ ተጠምዶ የሚያርስ የሚያሳርስ። ሞኝ አላዋቂ፤ እገሌ በሬ ነው እንዲሉ። ብዕር ላንድ ብቻ፤ ብዕራ ብዕራይ ላንድም ለብዙም ይኾናል፤ እንደ ሐራና እንደ ባዕላይ ነው። አድግ ወእመሂ ብዕራ። ፅምደ ብዕራ። አርዑተ ብዕራ። ተያፍም ወብዕራ። መጺኦ ዐቢይ ብዕራይ በልዖሙ። ብዕራይ ዘብርት። ዘይቀሥፍ ብዕራዪሁ ፡-(ዘፀ፳፪ ፡-፲። ኢሳ፭ ፡-፲ ፡-፲፰። ስንክ ፡-ሠኔ፲፩። ዮሴፍ። ስንክ ፡-መስ፳፯። ሢራ፴፰ ፡-፳፭)።
ብዕዛ ፡-(ዛት። ትግሬ በዕዛ) ሳላ የፍየል ዐይነት፤ የዱር የበረሓ እንስሳ እንደ ቦኸር እንዳጋዘን ያለ ቀንዳም፤ ቀንዱ ቀጫጭን ረዥም ቀጥ ያለ የተካከለ፤ በትር የሚመስል። ቱልቱላ የሳላ ቀንድ፤ እንደ እንቢልታ እንደ መለከት በአፍ የሚነፋ፤ ወይም በሳላ ቀንድ አምሳል የተሠራ መለከት ንዋየ ማሕሌት፤ የሚነፋ ኹሉ። ባሉብሉዮች ግን ቃጭል ጸናጽል ነጋሪት ይሉታል። ቀርንና ብዕዛ በመጻሕፍት እንደሚገባቸው አልተፈቱም፤ መላሾች ቀርንን ከበሮ ነጋሪት፤ ብዕዛን እንቢልታ መለከት ብለውታል፤ በበገናና በመስንቆ በሌላውም ፈንታ ብዕዛ ተጥፎ ይገኛል። በአቅርንት ወበብዕዛ። አርጋኖን ወብዕዛ። ቃለ ቃርን ወእንዚራ ወመሰንቆ ወብዕዛ ወማሕሌት። ወምስሴሁ መዘምራን እለኒ በጸናጽል ወእለኒ በከበሮ ወእለኒ በብዕዛ ወበአቅርንት ፡-(፪ዜና ፡-፲፭ ፡-፲፬። ስንክ ፡-መስ፲፰። ዳን፫ ፡-፭። ፪ዜና ፡-፲፫ ፡-፰)።
ብዕድና ፡-ባዕድነት፤ ልዩነት፤ ውላጤ። ዘእንበለ ኑፋቄ ወብዕድና ፡-(ቄር ፡-እስት)።
ብኵ ፡-ብኩይ፤–በከየ።
ብኩር ፡-(ራን ራት ኵርት) የተበኰረ፤ በኵር የኾነ የተባለ፤ የቀረ የታጐለ።
ብኩይ ፡-(ያን ያት ኪት) ያለቀሰ አልቃሽ፤ ሐዘንተኛ።
ብካይ ፡-(ያት) ልቅሶ፤ ዋይታ ፍጅጅት፤ መራራ ጩኸት ከእንብ ጋራ። በከየ ብካየ ዐቢየ። ብካየ ኢያዜር። ብካይ ወላሕ። ቃለ ብካይ ወቃለ ዐውያት ፡-(ኤር፴፰ ፡-፫። ኢሳ፲፮ ፡-፱። ፳፪ ፡-፲፪። ፷፭ ፡-፲፱)።
(ጥ) ብክ ብኵ ፡-(ዕብ ቦኬ) ስመ ሰብእ፤ ዳዊት፤ በካዪ ፥ ብኩይ ፥ አልቃሽ እንባማ ማለት ነው። ባጎር ወልደ ብኵ ፡-(ጥበ፩። መዝ፮ ፡-፮–፰)። የባጎርን ፍች ተመልከት።
ብውሕና ፡-ጌትነት፤ ሥሉጥነት። ኀልዮተ ብውሕናሁ ፡-(ማር ፡-ይሥ፪ ፡-፱)።
ብዉሕ [1]፡-(ሓን ሓት ውሕት) የሠለጠነ፤ ሥሉጥ፤ የተገባ። ብእሲት ኢኮነት ብውሕተ ላዕለ ርእሳ፤ ወከማሁ ብእሲኒ ኢኮነ ብዉሐ። ወአኮሰ ዘኢኮነ ብዉሓነ። ኢኮነኑ ብዉሐ ለብሓዊ ይግበር ፡-(፩ቆሮ ፡-፯ ፡-፬። ፪ተስ ፡-፫ ፡-፱። ሮሜ፱ ፡-፳፩)።
[2]፡-(ይደሉ፤ መፍትው፤ርቱዕ) ይገባል፤ የተገባ፤ የሚገባ፤ ግቡ፤ አገባብ። ይደሉ ሲኾን በቁሙ፤ ውስጠ ዘ ሲኾን ውእቱ አለበት። ኢብዉሕ ይባእ ውስተ ቤተ መቅደስ ዘእንበለ ካህን። ብዉሕ ለኤጲስቆጶስ ከመ ይፍታሕ። ብዉሕ ለከ ትንብብ ወትግበር ዘፈቀድከ። ኢኮነሁ ብዉሐ ለልዑል ይግበር ዘፈቀደ ፡-(ዮሴፍ። ፈ ፡-መ ፡-፮ ፡-፪። ቀሌ። ኢዮ፳፪ ፡-፲፪)።
ብዙኅ ፡-(ኃን ኃት ዝኅት) የበዛ፤ ብዙ እጅግ፤ ዐያሌ። ዕንቍ ዘብዙኅ ሤጡ። ብዙኃን እምውሉደ ግብጽ። ብዙኃት አዋልድ። ሀገር ብዝኅተ ሰብእ ፡-(ዮዲ፲ ፡-፳፩። ኩፋ ፡-፵፪። አስቴ፪ ፡-፰። ሕዝ፴፬ ፡-፲፮)።
ብዙኀት ፡-በዝቶ፤ ብዙ ኹኖ፤ ብዙ ጊዜ፤ በብዙ። መጽአ ብዙኀ ወተመይጠ ኅዳጠ። ኢትትአመኖ ብዙኀ። ዘብዘኀ ተመንደበ ብዙኀ ይትሜየን ፡-(ዘረፋ። ሢራ፮ ፡-፯። ፴፩ ፡-፲፩)።
ብዙት ፡-የተባዘተ፤ ብዝት፤ ባዘቶ፤ ፍልቅቅ። ፀምር ብዙት ፡-(መሳ፮ ፡-፲፯። ስንክ ፡-ታኅ፲፮)።
ብዝኀት ፡-መብዛት፤ አበዛዝ፤ ብዛት፤ ብዙነት። ብዝኀተ ሰብአ ፡-(ዮሴፍ)።
ብዝኅ ፡-(ኃት) ብዛት፤ ብዙነት፤ ብዥ። ብዝኀ መዋዕል። ብዝኀ ዓሣት። በብዝኀ ዓመታት ወበብዝኀ ንብረት ፡-(ዘካ፰ ፡-፲። ዮሐ፳፩ ፡-፮። ኢዮ፲፪ ፡-፲፪)።
ብዝር ክታን ፡-ብዝር ክታን፤ የተልባ ፍሬ፤ እንቡጡ ቅንጣቱ።
ብዩን ፡-(ናን ናት ይንት) የተለየ፤ የታወቀ፤ የተረዳ፤ግልጥ ጕልሕ። ዝንቱ ብዩን ፡-(ዮሴፍ)።
ብዩጽ ፡-(ጻን ጻት ይጽት) የተለየ፤ ልዩ ምርጥ።
ብያኔ ፡-(ያት) መለዮ፤ ልዩነት፤ በቁሙ፤ ብይን ፍርድ፤ አፈራረድ፤ ፈሊጥ ዕውቀት፤ ሥርዐት። ማእምረ ብያኔ። ብያኔ ልባዊ። ብያኔ ሮማዊ ፡-(ታሪ ፡-ነገ። ፍ ፡-ነ ፡-፱)።
ብዱር ፡-(ራን ራት ድርት) የተበደረ፤ የተቀደመ፤ የተወደደ፤ ምርጥ።
ብዱት ፡-የተፈታች ባዶ፤–በድወ።
ብዳ ፡-(ዐረ ቤዳ) ነጭ፤ ንጣቱ ዕንቍላል ዐመድ ወይም ያህያ ሆድ የሚመስል። ሕብረ ከብድ ባለው ብዳ ይላል። ባለብሉዮች ግን ብጫ ይሉታል ፡-(ዘፀ፴፮ ፡-፱)።
ብድብድ ፡-ዛሕል ዝገት። ሞተ ግብት፤ ቸነፈር፤ መቅሠፍት፤ ሰውነትን ቶሎ የሚያዝግ የሚያጠወልግ፤ ፈጥኖ የሚገድል፤ እንደ ነፍጥ ያለ በሽታ። ባለወግ መልአክ ለመዐት ለመቅሠፍት የሚላክ፤ አጥፊ ቀሣፊ። ክፉ ጨካኝ ንጉሥ፤ እንደ ሄሮድስ እንደ ቴዎድሮስ ያለ ፡-(ዘኍ፲፯ ፡-፲፪–፬። ፪ነገ ፡-፳፬ ፡-፲፭–፲፯። ዕብ፲፩ ፡-፳፰)። ወአውሥእዎ ለውእቱ ብድብድ ንጉሥ። ጕጉእ ወመግእዝ ወነባቢ ብድብድ ስሙ ፡-(መቃ ፡-ገ፩። ምሳ፳፩ ፡-፳፬)።
ብድወት ፡-መጥፋት መፈታት፤ ውድማነት ባዶነት። ኢይርአይ ብድወታ ለኢየሩሳሌም ፡-(ስንክ ፡-ሚያ፫)።
ብድው ፡-(ዋን ዋት ዱት) የጠፋ የወደመ፤ ባዶ ባድማ የኾነ፤ የተፈታ። ምድር ብዱት። ገዳም ብዱት ፡-(ዮሴፍ። ስንክ ፡-መስ፫)።
ብጡሕ ፡-(ሓን ሓት ጥሕት) የተበጣ፤ ብጥ ሥንብጥ፤ ትፍትፍ።
ብጡል ፡-(ላን ላት ጥልት) የበጠለ፤ የጠፋ ጥፉ፤ መጥፎ፤ ብልሹ ከንቱ። ስብሐት ብጡል። ዝንቱ ብጡል። ኦሪተ አይሁድ ብጡል። ዛቲ ተደምሮ ብጥልት እምሕገ ሰብሳብ ወእሰምያ ኀጢአተ ፡-(ፊልክ ፡-፳፱። ገድ ፡-ተክ። ፍ ፡-ነ ፡-፵፪ ፡-፩። አቡሻ። ፈ ፡-መ ፡-፲ ፡-፫)። ድልድል ቅምጥል፤ ሥራ ፈት አውታታ፤ ወይም ዘመናይ ጌታ። ብጡል፤ ወሌ ብጡል እንዲል ፡-(የጁዬ)።
ብጥሐት ፡-ሙብጣት፤ መበጣት፤ አበጣጥ፤ ብጥነት፤ ብጥታት። ብጥሐተ ገጽ ፡-(መ ፡-ፈ –፲)።
ብጥለት ፡-መጥፋት፤ አጠፋፍ፤ ጥፋት፤ ከንቱነት። እስመ አበው ዘዝንቱ ዘመን ረሰይዎ ብጥለተ ፡-(ፈ ፡-መ ፡-፲፫)።
ብጥም ቡጥም ፡-(ዐረ ቡጥም። ሱር ቤጥማ) በቁሙ፤ የዛፍ ስም፤ ወርቤንቶስን እይ፤ ከዚህ ጋራ አንድ ነው። ይዘብሑ ታሕተ ባሉጥ ወቡጥም ወገውዝ ወለውዝ ፡-(ሆሴ፬ ፡-፲፫። አቡሻ ፡-፵፯)።
ብጹሐ መዋዕል ፡-ቀኑ የደረሰ፤ ዕድሜ የጠገበ፤ ዕለተ ሞቴ የቀረበ፤ አሮጌ ፡-(፩ዜና ፡-፳፱ ፡-፳፰)።
ብጹሕ ፡-(ሓን ሓት ጽሕት) የደረሰ፤ ያደገ የጐለመሰ፤ የመላ የተፈጸመ ፍጹም። ብጹሐ አምጣን። ብጽሕተ አምጣን። ብጹሓነ አምጣን እምዕሥራ ዓመት ወከሃ። ብጹሓነ ሠላሳ ዓመት ፡-(ኤፌ፬ ፡-፲፫። ሲኖዶ። ፩ዜና ፡-፳፫ ፡-፫ ፡-፳፬)።
ብጹሕ ውስተ ትሩፍ ፡-ብጹሕ ውስተ ትሩፍ፤ ከፍጹምነት የደረሰ፤ በትሩፋት የተፈጸመ፤ ባሕታዊ።
ብፁዓዊ ፡-የብፁዕ ወገነ ንጹሕ፤ ወጣኒ መንፈሳዊ፤ ወይም ብፁዕ የተባለ ብፁዕነት ያለው ማእከላዊ፤ ፍጹም ቅዱስ። ብፁዓዊ ተክለ ሃይማኖት። አሐዱ እምብፁዓውያን ፡-(ገድ ፡-ተክ። ፊልክ ፡-፰)።
ብፁዕ ፡-(ዓን ዓት ፅዕት) ብፅዐት የገባ ባለብፅዐት፤ የብፅዐት ልጅ የብፅዐት ገንዝብ። ኵሉ ዘብፁዕ ዘበፅዑ መሀይምናን ፡-(ሃይ ፡-አበ፫)። በቁሙ የታመነ የተመሰገነ፤ሥራውና ልቡ የቀና፤ የተከናወነ፤ ክቡር ምስጉን ምሩቅ፤ ቡሩክ ቅዱስ፤ ጻድቅ ቸር፤ ብእሴ እግዚአብሔር፤ እንደ ኢዮብና እንደ አብርሃም እንደ ዳዊት ያለ። ብፁዕ ብእሲ ዘኢሖረ በምክረ ረሲዓን። ብፁዐ ረሰይከኒ። ኢትበሉ ብፁዐ ዘእንበለ ትርአይ ደኃሪቶ። ብፅዕት ነፍስ እንተ ትፈርሆ ለእግዚ። ብፁዓም ነዳያን በመንፈስ ፡-(መዝ ፡-፩። ሱቱ ፡-ዕዝ፲፪ ፡-፲፬። ሢራ፲፩ ፡-፳፰። ፴፩ ፡-፲፯። ማቴ፭ ፡-፫–፲፩)። ስምነቱ ማእከላዊ ነው፤ ከንጹሕ በላይ ከቅዱስ በታች፤ ስለዚህ ለፈጣሪ ሳይቀር ለወጣኒና ለፍጹም ለኹሉ ይኾናል። ለብፁዕ እግዚአብሔር ፡-(፩ጢሞ ፡-፩ ፡-፲፩)።
(ጥ) ብጻል ፡-ልጥ ቅርፍት፤ ቅራፊ ብጫቂ ብጭቅጫቂ፤ ዕላቂ ብጣሽ ቍራጭ። ረከብኩ ብጻላቲሃ ወአጽርቅቲሃ ፡-(ኤር ፡-፲፫ ፡-፯)።
ብፃው ፡- (ዋት)
፤ እንቅልፍ
እንጕልቻ ፤ ቅዠት ፤ ጨዎታ ቧልት አለውቀት። ከደኖን ለቀራንብቲከ በብፃወ ኀጣውእ። ወእመኒ መጽአኒኢ ብፃው ለአፅርዖ ጸሎት እንቅልፍ (መጽ ፡ ምስ። አርጋ ፡ ፪)። ወለእመኒ አእመርዎሙ እከዮሙ ይብሉ በበፃው ገበርነ ፤ ጨዎታ (ምሳ፳፱ ፡ ፲፱)።
ብጽሐት ፡-(ታት) መድረስ፤ መምጣት አደራረስ። ብጽሐትከ ኀቤየ። ሶበ አእመረ ብጽሐቶሙ እምቤተ መቅደስ። ጊዜ ብጽሐተ ሐጋይ። መጽሐፍ በጽሐት ወአስተፍሥሐኒ በብጽሐታ ፡-(ገድ ፡-ተክ። ዮሴፍ። ፍ ፡-ነ ፡-፲ ፡-፮። ዮሴፍ)።
፡-ምርመራ ፍተሻ፤ የተጣፈን ቍጥር ቀመርን ጉበቶ ማየት ድርሱን ማግኘት፤ ማወቅ መረዳት ፡-(አቡሻ ፡-፱)።
ብጽሕ ፡-(ሓት) ድርሻ ፈንታ፤ ክፍል ዕድል።
ብፅዐት ፡-(ታት) መሳል፤ ብፁዕ መባል። ስለት የስለት ገንዝብ፤ የብፅዐት ሥራ። ኢታጐንዲ ውሂበ ብፅዐትከ። ፍዲ ብፅዐተ–። ብፅዐተ ሕይወትየ። መሥዋዕት ዘዘልፍ ወዘብፅዐት። ብፅዐት ቦሙ። በእንተ ብፅዐታት። አንተ ውእቱ ዘትትዌከፍ ብፅዐታተ ወዓሥራተ ፡-(ሢራ፲፰ ፡-፳፪።ናሖ፪ ፡-፩። መዝ ፡-፵፩። ዮዲ፬ ፡-፲፬። ግብ፲፰ ፡-፲፰። ፍ ፡-ነ ፡-፲፰። ማር ፡-ይሥ)። ብፅዐትና ብልኅ ባማርኛ ይተባበራሉ፤ ስለት በመባል። ፡-(ሙሾ፤ ልጆቿ በሰይፍ ያለቁባት) የቤተ ክሲያን ገንዘብ አትንኩ ስላችኹ ፥ ምነዋ ልጆቼ ስለት የበላችኹ።
ብፅዓን ፡-(ናት) ዝኒ ከማሁ፤ ክብር ምስጋና። ብፅዓን ወፍሥሓ ለክሙ። ቃላተ ብፅዓን። ብፅዓን ይደልዎ ለገብር ምእመን። የኀጥእ ብፅዓነ እንተ ተብህለት ለሕዙናን። ታወሥኦሙ ለኅሩያን በቃለ ብፅዓን ፡-(ዮሴፍ። አፈ ፡-ተ፯።ፈ ፡-መ ፡-፪ ፡-፲፩። ፊልክ ፡-፸፱። ቅዳ ፡-ያዕ)።
ብፅዕ ፡-(ዓት) ክብር ምስጋና፤ ብፁዕ ማለት፤ መባል፤ የቡራኬ ቃል። ጴጥሮስ ረከበ ብፀዐ እምኀበ መድኅን፤ ወይቤሎ ብፁዕ አንተ። ወሀበ እግዚ ለእሉኒ ብፅዐ፤ በብሂሎቱ ብፁዓን መሓርያን ፡-(ቀሌ። ፊልክ ፡-፶፩)።
ብፅዕና ፡-ብፁዕነት፤ ክብር ምስጋና ቅድስና። ብፁዓን እሙንቱ ወዓዲ ለነሂ ብፅዕና ፡-(ገድ ፡-ኪሮ)። በብፅዐት ፈንታ ብፅዕና ብፅዕናት ይላል፤ ስሕተት ነው። ብፅዕናት ወብኵርናት ፡-(ቀሌ)።
ቦ ፡-ነባር አንቀጽ። አለ፤ ኖረ፤ ነበረ፤ ኾነ። ላንድም ለብዙም ለወንድም ለሴትም ይከታል። ቦ ዐርክ ኀላፊ። ቦ ጻድቃን ውሉደ ቤትከ። ቦ ብእሲት እንተ ትሤኒ እምብእሲት። ወቦ አንስትኒ እለ ጌሣ ኀበ መቃብር። ቦ ቦቱ ባለው በዝርዝርነት ሲፈታ ግን ላንድ ብቻ እንጂ ለብዙ አይኾንም። ይህም ፥ አለው አለለት አለበት እያለ መኼዱን ያሳያል። ቦቱ ከቦ ተለይቶ በርሱ በት ይኾናል። ዘቦቱ ኵሉ ኮነ፤ ኹሉ በርሱ የተፈጠረ፤ ወይም የተፈጠረበት። ኵሉ ዘየአምን ቦቱ፤ የሚያምንበት ኹሉ። በርሱ ቢል ፥ በት ቢል ስልቱ አንድ ነው። ለክፉም ለበጎም ይኾናል።
ቦሁ ቦኑ ፡-(ቦ ሁ፤ ቦ ኑ) ቦ ነባር አንቀጽ፤ ሁ ኑ የጥያቄ ቃል፤ በተገናኝ አለን፤ አለ ይኾን ያሰኛል። ቦሁ ኀበ ይሴወሩ እምኔየ። ቦሁ ዘተርፈ ኀቤከ። ቦኑ ረኣይ ዝየ፤ እወ ቦ ፡-(ኤር፳፫ ፡-፳፬። ዓሞ፮ ፡-፲። ፩ነገ ፡-፱ ፡-፲፩)። ኹለተኛም በትርፍ ዐማርኛ በውኑ፤ እውን እያሰኘ ጥያቄን መደብ አድርጎ ምርመራን ወቀሣን ተግሣጽን ያሳያል። ትርፍ ዐማርኛ ማለት፤ ቦ አንቀጽነቱን ሳይለቅ፤ ቦሁ ዘሰአልኩክሙ፤ ቦኑ ዘዐመፅኩክሙ እያለ ይህን በመሰለ ሲገባ፤ በውኑ የለመንኋችኹ የበደልኋችኹ አለን ያሰኛል ፥ ስለዚህ ነው። አንቀጹ ሌላ ሲኾን ግን ፍችው በውኑ ብቻ ነው፤ ስለዚህ በጥያቄ ኹሉ ይገባል፤ በውኑ ማለት ርሱው ራሱ ጥያቄ ነውና። ቦኑ በኣተ ፈያት ውእቱ ቤትየ። ቦኑ፤ለባሕቲቶሙ ለአይሁድ እግዚ። ቦኑ አባእክሙ ሊተ መሥዋዕተ ወቍርባነ። ዘአባእክሙ ቢል ግን አለን ያሰኛል፤ በውኑ ሲጨመር ያምርለታል ፡-(ኤር፯ ፡-፲፩። ሮሜ፫ ፡-፳፱። ግብ፯ ፡-፵፪)።
ቦቀ ፡-(ይበውቅ ይቡቅ፤ በዊቅ። ዐረብ በወቀ) ነፋ መታ አስጮኸ፤ ባፍ በትንፋሽ።
ቦኑ ፡-(ቦ ኑ) በውኑ፤ አለን። ቦሁን ተመልከት፤ ፍችው ከዚያ አለልኽ።
ቦአ ፡-ገባ፤–በዊእ ቦአ።
ቦዐ ፡-(ዐረ ባዐ) ዘረጋ፤ ጋተ፤ ሰነዘረ።
ቦአኔርጌስ ፡-(ጽርእ። ዕብ ብኔይ ፡-ርጎሽ) ደቂቀ ነጐድጓድ ፡-(ማር፫ ፡-፲፯)። |
ቦክ [1]፡-(ዕብ ቡኽ) በዊከ፤ መባከን መቅበዝበዝ፤ እንቡዝ መኾን፤ ተለል ተለል ማለት፤ የመንገደኛ የድውይ። ባለብሉዮች ግን ቍስለ ሥጋ ይሉታል። መጽአከ ሕማም ወገሰሰከ ቦክ ፡-(ኢዮ፬ ፡-፭)። ክዳም ገዚፍ በማለት ፈንታ ክዳነ ቦክ ይላል፤ የተሳሳተ ነው። ዕብራይስጡ ግን ማክቤር ይላል፤ ልብድ ለሐፍ የሌት ልብስ እንደ ቡልኮ ያለ ማለት ነው ፡-(፬ነገ ፡-፰ ፡-፲፭)።
[2] ፡-ቦክ፤–መባከን፤–በዊክ።
No comments:
Post a Comment