ሀ ለ ሐ መ ሠ ረ ሰ ሸ ቀ በ ተ ቸ ኀ ነ ኘ አ ከ ኸ ወ ዐ ዘ ዠ የ ደ ጀ ገ ጠ ጨ ጰ ጸ ፀ ፈ ፐ
ገ ፡-ሦስተኛ ፊደል፤ በግእዝ አልፍ ቤት በአበገደ፤ ስሙ ገምል ቍጥሩ ፫፤ አኃዝ ሲኾን ገ ሠለስት ቱ ይባላል። ዕብራውያን ግን ሦስትን መደብ አድርገው በራሱ ላይ ነቍጣ እየጨመሩ ሦስት እልፍ ይሉታል። ምስጢሩ ሠሉስንና የሠሉስን ፍጥረት መደብ አድርጎ ፫ኛውን አካል መንፈስ ቅዱስን ፥ የመንፈስ ቅዱስን ሀብትነት ፍሬ ጸጋውን ያሳያል፤ ገመልን እይ ፡-(ዘፍ፩ ፡-፲፩ ፲፪)።
ገሃህ ገሀህ ፡-የጨረቃ ምላት ብርሃኗ፤ በተወለደች ወይም በበቀለች ባ፲፭ኛ ቀን መልቶ ተካክሎ ዐውድማ መስሎ የሚታየው። ከመ ወርኅ ምልእት በዕለተ ገሃህ። ወርኅ ተፈጥረ ምሉአ ብርሃን ከመ ዕለተ ገሃሁ። ሥኑ ለወርኅ ገሀህ። በቀዳሚ ወርኅ አመ ገሃሁ። ወርኅ ዘአሜ ገሀህ ፡-(ሢራ፶ ፡-፮። አቡሻ ፡-፲፫። አርጋ ፡-፮። ሕዝ፴፪ ፡-፲፯። ደራሲ)።
ገሓሢ ፡-(ሢት ሥያን ያት፤ ሐሥት) የሚገባ ገቢ መጪ፤የሚርቅ የሚያገል፤ አግላይ ፈቅቅ ባይ፤ መናኒ።
ገሃነማዊ ፡-የገሃነም፤ ሥቃይ እሳት ጭፍራ ሰራዊት። ላህብ ገሃነማዊ ፡-(ጥበ ፡-ጠቢ)።
ገሀነም ገሃነም ፡-(ጽር ጌሄና። ዕብ ጌይሂኖም። ዐረ ጀሀነም) የቦታ ስም፤ ከደብረ ጽዮን የተያያዘ፤ የተራራው እግር፤ የቄድሮንና የግዮን ወንዝ ማየ ሰሊሖም የሚወርድበት፤ የኢየሩሳሌም ቅርብ አጠገብ በስተደቡብ ያለው ጐድጓዳ ቈላ ሸለቆ ወንዛወንዝ መቀራቅርት፤ እስራኤል ልጆቻቸውን ለሞሎኽ ይሠዉበትና ይጦብሱበት ያቃጥሉበት የነበረ፤ የከተማው ኵስ ውስጥ ለውስጥ ወደ ርሱ የሚጐርፍበት የጥንብና የጕድፍ መጣያ ርኩስ ቦታ፤ የውነተኛው ገሃነም ምሳሌ። ሄኖም የሚባል ሰው ያቀናው የወረሰው የሄኖም ወንዝ፤ ወይም ከሄኖም ልጆች ላንዱ የደረሰ ያንደኛው ልጁ ክፍል ማለት ነው። ጣፌጥን እይ፤ ከዚህ ጋራ አንድ ነው ፡-(ኢያ፲፭ ፡-፰። ኤር፯ ፡-፴፩ ፡-፴፪። ፬ነገ ፡-፲፮ ፡-፫። ፳፫ ፡-፲)። በቁሙ ሲኦል መቃብር፤ የእሳት ጕድጓድ ዐዘቅት፤ መካነ ኃጥኣን ከሞቱ በኋላ የሚኖሩበት የሥቃይ ቦታ፤ እሳቱና ትሉ የማይጠፋ የማያንቀላፋ ፡-(ምሳ፩ ፡-፲፪። ፲፭ ፡-፲፩። መክ፱ ፡-፲)። እቶነ ገሃነም። እሳተ ገሃነም። ሥቃያት ዘገሃነም። ወሞትሰ ዳግም ገሃነም ዘእሳት ፡-(ሱቱ ፡-ዕዝ፮ ፡-፩። ማቴ፭ ፡-፳፪። ዕር ፡-ኢሳ፩ ፡-፫። ራእ፳ ፡-፲፬። ማር፱ ፡-፵፫። ኢሳ፷፮ ፡-፳፬)።
ገሓይ ግሔ ፡-(ሕያት። ዕብ ሻፋን። ዐረ ወብር። ጽር ኪሮግሊዩ) ሽኮኮ አሽኮኮ እንደ ጥንቸል ያለ ሣር ቅጠል ቡቃያ የሚበላ፤ ማለዳ ጎሕ ሲቀድ የሚጮኽ የሚያሽካካ። ፈሪ ድኩም ጎሓዊ ማለት ነው። ከርሥከሂ ጾላዕት ምጕያየ ግሔ ረኃብ። ወግሕያት ሕዝብ ዘኢኮኑ ጽኑዓነ ቈናጽል ወግሕያት ፡-(ቅኔ። መዝ ፡-፻፫። ምሳ፴ ፡-፴፮። ሔኖ፺፮ ፡-፪)።
ገሃደ ፡-ገልጦ ተገልጦ፤ ግልጥ ኹኖ፤ በግልጥ በገሃድ። ዘገሃደ ተነበይኩ። ገሃደ ይመጽእ። ዐርገ ጽሚተ ወአኮ ገሃደ ፡-(ዕር ፡-ኢሳ፬ ፡-፳። መዝ ፡-፵፱። ዮሐ፯ ፡-፲)።
ገሀድ ገሃድ ፡-በቁሙ፤ የልደት የጥምቀት ዋዜማ፤ እንዳርብና ረቡ የሚጦም። ሰላም እብል ለጾመ ዕለት ዋሕድ፤ ዘስሙ ገሀድ ፡-(ስንክ ፡-ጥር፲)።
ገሃድ ገሃዲ ፡-(ዲት ድያን ያት) በቁሙ፤ የሚጋድ የሚገለጥ፤ ተገላች ተገላላጭ ግልጥ። ኵሉ ዘገሃድ ብርሃን ውእቱ። ኢኮነኑ ገሃደ ይእዜ ከመ ኮነ አማነ። ወብዙኀ ይጌሥጾሙ ከመ ገሃደ ኢይረስይዎ ፡-(ኤፌ፭ ፡-፲፫። ቄር። ማር፫ ፡-፲፪)።
ገሓፊ ፡-(ፊት ፍያን ያት፤ ሐፍት) የሚግፍ የሚጠርግ፤ ጋፊ ጋፋፊ ጠራጊ፤ ሆዳም።
ገሓፍት ፡-(ዐረ ቁፈት። ዕብ ሳል) ቅርጫት መሶብ እንቅብ፤ አገልግል ቅንብቻ፤ ኰፈዳ ግትቻ። ወታነብሮ ገሓፍት ፡-(ዘፍ ፡-፳፱ ፡-፫። ፳፫ ፡-፴፪)።
ገህግሀ ፡-(ዕብ ጋሃህ። ሱር ግሃእ። ዐረ ጀህጅሀ) አራቀ አስገለለ፤ ለየ ከላ ከለከለ። ኀጢአት እንተ አልባቲ ዘይገሀግሃ ፡-(፪ጴጥ ፡-፪ ፡-፲፬)። ዘሩ ግሂህ ነው፤ ገህሀን እይ።
ገለሠ ፡-ተቀመጠ፤ ሸነጓ፤–ገሊስ ገለሰ።
ገለባት ፡-ዠማ ነጋዴ ቅፍለት፤ ማኅበር ኹኖ አጋሰሱን ጭኖ እንደ ጐርፍ የሚኼድ የሚያረብድ።
ገለብ [1]፡-መግለብ ት፤ መቃጥን መንጠቆ፤ መግለቦ ዘረ መትር ያሣ ወጥመድ መያዣ መጋፈፊያ። ከመ በመግለብት ወበመዋቅሕተ ኀጺን ተሐውር ፡-(ዕር ኢሳ፫ ፡-፮)። ጀልባ ታንኳ ፍልኳ ዓሣ ወጋሮች የሚቀመጡበት። አንዳንድ መጽሐፍ በገለብ ፈንታ ጌልያ ብሎ መርከብ ይላል። ገለባ ንፋሽ እንጕላይ ፡-(ዐማርኛ)።
[2]፡-(ትግሬ) ፤ ጋዛ ፀጋም፤ በግራ የሚያዝ የሚነገብ አላባሽ አግሬ።
ገለዓድ ፡-(ዕብ ጊልዓድ) ስመ ሀገር፤ ተራራ፤ ከዮርዳኖስ ማዶ ያለ ፡-(ዘኍ፴፪ ፡-፩)።
ገለድ ፡-(ትግሬ) ኪዳን፤ ሰላም፤ ዕርቅ ፍቅር ስምምነት፤ ቅርበት ልጽቀት።
ገለዶ ፡-(ዐማርኛ) ታላቅ ቢላዎ ካራ፤ የበጎች ጠጕር መሸለቻ፤ ቈርበት የሚቀፍ ቈዳ የሚቀድ፤ የሰፎችና የፋቆች መሣሪያ።
ገሊላ ፡-(ዕብ ግሊላ፤ ጋሊል) ስመ ሀገር፤ የምድረ እስራኤል ሰሜን፤ በዮርዳኖስና በጥብርያዶስ በዐቢይ ባሕር መካከል ያለ፤ የይሳኮርና የዛብሎን ክፍል፤ ታችኛው፤ ላይኛውም የአሕዛብ ክፍል ሳይቀር። ገለልተኛ ገጠር ዐልፎ ዐልፎ ሀገርና መንደር ያለበት፤ ዐውድ ዘውር ማለት ነው ፡-(ኢያ፳ ፡-፯። ፫ነገ ፡-፱ ፡-፲፩)። ናዝሬት ዘገሊላ። ቃና ዘገሊላ። ወገሊላ ዘአሕዛብ ፡-(ሉቃ፩ ፡-፳፮። ዮሐ፪ ፡-፩። ማቴ፬ ፡-፲፭)።
ገሊል ሎት ፡-(ገለ አው ገለለ ይገልል ይግልል። ዕብ ጋላል) መምረጥ ማንጓለል፤ መለየት ማስገለል። ማንጋለል በዥርባ ማስተኛት። ገልገለ የዚህ ዲቃላ ነው።
ገሊስ ሶት ፡-(ገለሰ ይገልስ ይግልስ። ትግ ገልሰ። ዕብ ጋላስ። ዐረ ጀለሰ፤ ተቀመጠ) መለበድ ልብድ መስፋት፤ ቈርበት ማልበስ መደጐስ፤ መደልደል ማመቻቸት፤ መሸብለል መጠቅለል፤ የኮርቻና የጭነት።
ገሊብ ቦት ፡-(ገለበ ይገልብ ይግልብ። ዐረ ጀለበ፤ ሳበ) ማጥመድ፤ መቃጥን መስደድ መረብ መንዛት፤ መሳብ መጐተት፤ መግለቦ መሥራት፤ ያሣ ወጋሪ። እንዘ ንገልብ ፡-(ኪዳ)። መግለብ መግለጥ፤ የኀፍረት የቂጥ። መሸሽ መሮጥ፤ መጋለብ ማምለጥ፤ መዘራት መበተን መቅለል መንጓለል ፍሬ ቢስ መኾን፤ የገለባ።
ገሊዕ ዖት ፡-(ገልዐ ይገልዕ ይግላዕ። ዕብ ጋሎዕ) መንቃት መሠንጠቅ፤ መስበር መድቀቅ፤ መንከት መነካት፤ መጐዳት፤ የሸክላ ያጥነት።
ገሊው ዎት ፡-(ገለወ ይገሉ ይግሉ። ገለበ፤ ገለደ) መጐለብ መለጐም፤ መሸፈን መጋረድ ማልበስ መለበጥ፤ መጐለብ የስፌት፤ መለጐም የባላፍ ያታሞ የከበሮ፤ መሸፈን ማልበስ ለኹሉ፤ መለበጥ ከንጨት ከደንጊያ ለተሠራ ለቤት ለሣጥን። ይገልዎሙ ልቦሙ። ከመ ከበሮ ዘገለውዎ። ጎሞር ዘገለውዎ በቈጽለ ወርቅ ፡-(፪ቆሮ ፡-፫ ፡-፲፭። ድጓ። መጽ ፡-ምስ። ዘፀ፲፮ ፡-፴፫። ፫ነገ ፡-፮ ፡-፲፭)።
ገሊጽ ጾት ፡-(ገለጸ ይገልጽ ይግልጽ) መግለጥ መግፈፍ ማሳየት፤ መንገር መተርጐም ማስረዳት።
ገሊፍ ፎት ፡-(ገለፈ ይገልፍ ይግልፍ። ሱር ግላፍ። ዕብ ጋላፍ) መቅረጥ ማነጥ ማንጠጥ፤ ጣዖት መሥራት፤ በንጨት በደንጊያ፤ በልብስ ላይ መሣል መመሰል መፈደል መጠረዝ መጥለፍ። እለ ይገልፍዎ ለዕፅ። ይክል ገሊፈ አምሳል። ገለፈ ላዕሌሁ በቀልተ ወአክሊላተ። ይግልፍዎ ውስተ ኰኵሕ። እለ ይገልፉ ወየኀርዉ ዐይነ ማኅተም። ግልፍ ላዕሌሆሙ አስማተ። ቀጠንት ዘያሰረግውዎሙ በሕብራት ዘገለፉ ቦሙ ፡-(ኢሳ፵፭ ፡-፳። ፪ዜና ፡-፪ ፡-፲፬። ፫ ፡-፭ ፡-፯። ኢዮ፲፱ ፡-፳፬። ሢራ፴፰ ፡-፳፯። ዘፀ፳፰ ፡-፱። ፍ ፡-ነ ፡-፳፫)።
ገላሜዎስ ፡-ኅሥሥት፤–ከሜሌዎን።
ገላዊ መግልው ፡-የሚጐልብ የሚሸፍን፤ ጋራጅ ለባጭ።
ገላዲ መገልድ ፡-(ዲት ዳን ዳት) የሚደጕስ ደጓሽ፤ ቈርበት አልባሽ፤ አንጣፊ።
ገላፊ ፡-(ፊት ፍያን ያት፤ ለፍት) የሚቀርጽ አንጣጭ ምስል አፍሳሽ።
ገልበበ ፡-(ተቀ ግ። ዐረ ጀልበበ፤ ገለወ) ሸፈነ ከደን፤ አለበሰ አከናነበ፤ ጋረደ፤ ለበጠ መረገ፤ ለሰነ ቀባ። ገልበቡ ርእሶሙ። ይገልብብ አፉሁ። ይገለብብዎ ገጾ። ሥብሕ ዘይገለብብ ከርሦ። ዘይገለብቦ ለሰማይ በደመና። ወገልበቡ ኵሎ ዘውስቴቱ እምዕፅ በነፍጥ ብዙኅ። ገልበበታ ለንፍቅ ፒሳ ፡-(ኤር፲፬ ፡-፬። ዘሌ፲፫ ፡-፵፭። ሉቃ፳፪ ፡-፷፬። ዘፀ፳፱ ፡-፳፪። መዝ ፡-፻፵፮። ዮሴፍ። ኩፋ ፡-፵፯)።
ገልባቢ መገልብብ ፡-የሚሸፍን፤ ከዳኝ አልባሽ፤ ጋራጅ አከናናቢ።
ገልዓት አግልዕት ፡-ገሎች፤ ገላልት። አሰሩ ውስተ ከሣዱ ሐብለ ወዲቤሁ ሰቀሉ ገልዓተ ዘአጽለምዎሙ በፍሕም። ከመ ዘያስተጣግዕ አግልዕተ ፡-(ስንክ ፡-መጋ፳፯። ሢራ፳፪ ፡-፯)።
ገልእ ፡-የሸክላ ስባሪ፤–ገሊዕ ገልዐ።
ገልዕ ፡-(ዕብ ሔሬሽ) ገል፤ የሸክላ ስባሪ እንክትካች የሳት መጫሪያ። እሳት በገል ውሃ በቅል እንዲሉ። ብሩር ዘይትወሀብ ምስለ ሕብል ከመ ገልዕ ውእቱ። የብሰ ሥጋሁ ከመ ገልዕ። ትጽሐፍ ኅሊናሃ ውስተ ገልዕ ፡-(ምሳ፳፯ ፡-፳፫። ገድ ፡-ተክ። ስንክ ፡-ጥር፳፮። ኢዮ፪ ፡-፰። መዝ፳፩ ፡-፲፮)።
ገልይ ዮት ፡-(ገለየ አው ገልየ ይገሊ ይግለይ። ዕብ ጋላህ፤ ገለጠ) መቍረጥ መቈጥቈጥ መለየት፤ መግለጥ መግፈፍ ማሳየት፤ ራቍቱን ግንዱን መለመላውን መተው፤ የዛፍ የሰው። ይገልይዎ ፡-(ዮሐ፲፭ ፡-፮)።
ገልድ ፡-(ዕብ ጌሌድ። ዐረ ጊልድ። ሱር ጌልዳ) ቈዳ ቈርበት፤ ዠንዲ ነት፤ ዐጥፍ ዳባ፤ ሌጦ አንቀልባ፤ የባሕር ዐረብ፤ ብራና ቅርፍተ ዕፅ።
(ጥግ) ገልዶ ዶት ፡-(ገለደ ይጌልድ ይገልድ። ዕብ ጋላድ፤ ገልድ ለበሰ) መደጕስ፤ ቈርበት ማልበስ። ማንጠፍ፤ መክፈፍ፤ ዐልጋን መኝታን በዠንዲ በነት ወይም በሰርፍ በለሐፍ መሸፈን ማስጌጥ። በቀጠንት ገለድኩ ምስካብየ ወዘርቤታተ ነጸፍኩ ፡-(ምሳ፯ ፡-፲፮። ዲድ ፡-፪)።
ገልገለ ፡-(ገሊል ገለ) ገለገለ ገላገለ፤ ለየ ነጠለ አላቀቀ፤ የሰው። ዘረገፈ ቀዳ ገለበጠ፤ አጋባ ባዶ አደረገ፤ የዕቃ። ወገልገልዋ ለሙዳየ ምጽዋት ፡-(፪ዜና ፡-፳፬ ፡-፲፩)።
ገልገላ ዕብ ፡-(ጊልጋል) ስመ ሀገር፤ መንኰራኵራት ማለት ነው። እሊሁም በይሁዳ ክፍል ያሉ ፪ አህጉር ናቸው፤ አንዲቱ የኢያሪሖ ቅርብ አጠገብ ፡-(ኢያ፭ ፡-፬። ፩ነገ ፡-፯ ፡-፲፮)። ፪ኛዪቱ በኬብሮን። ያለች ፡-(ዘዳ፲፩ ፡-፴። ኢያ፲፪ ፡-፳፫)።
ገልጋሊ ፡-ገልጋይ ገላጋይ፤ ዘርጋፊ ዘራፊ፤ ወራሪ በርባሪ።
(ጥ) ገልጎ ጎት ፡-(ገለገ ይጌልግ ይገልግ። ዕብ ጋላግ) ማጌጥ መሸለም፤ መልበስ መፀረር፤ መከናወን መበጃጀትና መዘጋጀት፤ ወደ ሸንጎ ወደ ገበያ ወደ ሰርግ ወደ ቤተ ክሲያን ለመኼድ።
ገልፈፈ ፡-(ተቀ ግ) ገፈፈ ገለፈፈ፤ የቈርበት የከንፈር።(ዐማርኛ)።
ገመላት አግማል ፡-(ላት) ገመሎች፤ ግመሎች፤ ቀጭኔዎች። ጸጕረ ገመል። ነሥአ ዐሠርተ አግማለ እምአግማለ እግዚኡ። አግማላቲሆሙ ፡-(ማቴ፫ ፡-፬። ዘፍ፳፬ ፡-፲። መሳ፮ ፡-፭)።
ገመላዊ ፡-ግመልማ፤ የግመል ዐይነት፤ የግመል ሳቢ ጠባቂ፤ የግመል እረኛ ባለግመል። ቈሪል ገመላዊ ፡-(ስንክ ፡-ታኅ፳፱)።
ገመል ፡-ገምል፤ ፡-(ዕብ ጋማል። ሱር ጋምላ። ዐረ ጀመል) በቁሙ፤ ግመል የቤት እንስሳ የጭነት የኮርቻ ከብት፤ በረሓ ቈላ የሚደፍር ውሃ ጥም የሚችል ዐንገተ ረዥም ነዊኀ ቅልጥም፤ ካህያ ካጋሰስ አብልጦ የሚይዝ የሚሸከም። ቀጭኔ የበዳ ግመል፤ ነብርማ ዝንጕርጕር የበዳ አህያ የሚመስል፤ ዐዳኞች እንዳውሬ የሚገድሉት።
ገመመ ፡-(ይጌምም ይገምም፤ ገምሞ) ያዘ ጨበጠ፤ ላጨ ቈረጠ፤ ከረከመ፤ የለጓሚና የላጭታ። ጋማ ጋሜ ማለት ከዚህ ወጥቷል። ኹለተኛም ገሚም ገመ ይገምም ይግምም ብሎ ዲቃላውን ገምገመ ሲሉት ገመገም ከዚህ ይወጣል። ጌመንና ጉማን ተመልከት፤ ፍችው ከዚህ ጋራ አንድ ነው።
ገመስ ፡-(ብ አግሙስ) ምንዛሪ ታናናሽ ገንዘብ የተሸረፈ የተመነዘረ፤ ከአላድ እስከ ሶልድ እስከ ቤሳና እስከ ድዋኔ ያለ። ባለሐዲሶች ግን ሰንኬቶ ቀለበት ይሉታል። ደኃሪተ ገመስ ፡-(ሉቃ፲፪ ፡-፶፱)። ዳግመኛም ድርህማት ዲናራት በማለት ፈንታ አግሙስ። ይላል። ዐሥሩ አግሙስ ፡-(ሉቃ፲፭ ፡-፰)።
ገመር ፡-(ብ ገመራት አግማር) በቁሙ፤ ታላቅ ዝንጀሮ ባለብዙ ጅር፤ ጐምቱ ሽማግሌ ያገር ቀንድ፤ መምህር አበ ማኅበር። ፡-(ተረት) መምሩ ገመሩ። ምስጢሩ ታላቅነት ነው።
ገመታ ፡-ግምጋማሚ፤ ግምት፤ የጭገሬታ ለውጥ። በእንተ ተዓስቦ ቤት ወውሂበ ንዋይ ለምድር ዘከመ ገመታ ፡-(ፍ ፡-ነ ፡-መቅ)።
ገማኒ ፡-(ኒት ንያን ያት) የሚያገምን፤ የሚያሳድፍ የሚያረክስ።
ገመድ ፡-በቁሙ፤ ሐብል። ሐቢልን ተመልከት።
ገመገም ፡-ገመገም፤ በቁሙ፤ ፡-(ዐማርኛ)።
ገሙስ ጋሙስ ፡-(ሱር ጋሙሻ) ጐሽ ቀንደ ሹል የበረሓ እንስሳ፤ መልኩ የላም የበሬ ፥ ጠባዩ ያውሬ፤ እንዳንበሳና እንደ ነብር ዐዳኙን የሚሻ የሚከተል በቀንዱና በግሩ የሚበቀል። ወይሴሰይ እምሐሊበ ገሙስ እሉ እሙንቱ አልሕምት ጸሊማን ዘገዳም ፡-(ስንክ ፡-መስ፭)። ዘገዳም ማለቱ ግብጦችና ህንዶች የሚያልቡትና የሚጠምዱት ጠጕረ ሥሥ ፥ ቀንደ ገላላ ፥ ሻኛ የሌለው ገራም ጭምት የቤት ጐሽ አለና ፥ ከዚያ ሲለይ ነው።
ገሚስ ሶት [1]፡-(ገመሰ ይገምስ ይግምስ። ፈተተ) መግመስ መገማመስ፤ መቍረስ መቈራረስ፤ መሽረፍ መሸራረፍ። መመንዘር፤ አንድ የነበረውን ብዙ ማድረግ ለብዙ መለወጥ። መግመስ መቍረስ የንጀራ፤ መሽረፍ የገነንዘብ፤ ለንጀራም ይኾናል፤ መመነዘር ግን ለገንዘብ ብቻ ነው።
[2]፡-ገሚስ፤ ዝኒ ከማሁ፤ ግማሽ። ጼው መጠነ ገሚስ ፡-(መ ፡-ፈ)።
ገሚር ሮት ፡-(ገመረ ይገምር ይግምር። ሱር ግማር። ዕብ ጋማር) ማግመር፤ መጨረስ መፈጸም፤ መቻል መያዝ መወሰን፤ መድፈር ጨርሶ መናገር። ፡-(መጐምራት። መጐመር፤ ማደግ። መጋመር፤ መዳበር፤ የሴት)። መጽሐፍ ግን በገመረ ፈንታ አግመረ ይላል አድራጊውን ባስደራጊ። ለእመ አግመረ ገራህተ እንዘ ይበልዕ። ብሑእ ዘአግመሮ ለሐሪጽ። እለ ይፈቅዱ ያግምርዋ ለምድር ባሕቲቶሙ። እግዚ ዘያገምር ኵሎ ወኢያገምሮ መካን። ኢታገምር ፍኖታ ዘእንበለ አሐቲ ኪደተ እግረ ብእሲ። በከመ አግመረ አፈ ኢሳይያስ ወይቤ ፡-(ዘፀ፳፪ ፡-፬። ቅዳ ፡-ዮሐ። ኢሳ፭ ፡-፰። ግንዘ። ሱቱ ፡-ዕዝ፭ ፡-፯። ተረ ፡-ቄር፲፮)።
ገሚት ቶት ፡-(ገመተ ይገምት ይግምት) መገመት መገምገም፤ ይህን ያኽል ማለት።
ገሚእ ኦት ፡-(ገምአ ይገምእ ይግማእ። ዕብ ጋሜእ ማገ፤ ጠጣ፤ አሸተተ) መግማት መበሽቀጥ፤ ጽዩእ መኾን።
ገሚድ ዶት ፡-(ገመደ ይገምድ ይግምድ፤ አው ገምዶ ዶት፤ ገመደ ይጌምድ ይገምድ። ዕብ ጋማድ ዐረ ጀመደ) መጕመድ መጐማመድ፤ መቍረጥ ማጨድ መጨርገድ፤ መገዝገዝ ማረድ። መቍረስ መገምደል። መግመድ መፍተል፤ ማክረር። ጊዜ ገሚድ በጽሐ። ዘእንበለ ይግምድዎ። ይገምዱ አስካለ። እስከ ማእዜኑ ትገምዲ መጥባሕት። ገመዱ መሌሊቶሙ ከመ ሥጋ ውስተ ጽህርት። ይጌምድ ሥጋሁ በእብን ፡-(ማሕ፪ ፡-፲፪። ኢዮ፰ ፡-፲፪። ኢሳ፲፰ ፡-፭። ኤር፳፱ ፡-፮። ማር፭ ፡-፭)። መላላቱና መጥበቁ ቱሱሕ ስለ ኾነ ነው፤ የቱሱሕን ፍች ተመልክት።
ገሚጽ ጾት ፡-(ገመጸ ይገምጽ ይግምጽ፤ አው ገምጾ ጾት፤ ገመጸ ይጌምጽ ይገምጽ) መግመጥ መጋጥ፤ መዘንተር መዘብተር፤ ማማት መንቀፍ። ሰላም ለስምዖን እንተ ለሐቌሁ አጽንዖ በሐብለ በቀልት ይቡስ እንተ ይጌምጾ ወይበልዖ። ወገሚጽኒ እምዕጸበ አስተሐቅሮ ፡-(ስንክ ፡-ነሐ፫። ማር ፡-ይሥ፳፪ ፡-፩)።
፡-ማጕበጥ፤ ማስጐንበስ፤ ማጥመም መቈልመም መቀለስ፤ ማጽንን ማዘንበል፤ ወዳንድ ወገን ማድላት መድፋት፤ ራስን ወይም ሌላውን። ዘይጌምጽ ክሣዶ። እምንእሶሙ ግምጽ ክሣዶሙ። ወርቅ ገመጾሙ ልቦሙ ለነገሥት። ለገሚጸ ፍትሕ። ኢትግምጽ ፍትሐ ነዳይ ፡-(መጽ ፡-ምስ። ሢራ፯ ፡-፳፫። ፰ ፡-፪። ዘፀ ፳፫ ፡-፪። ዲድ ፡-፱)። ትግሬ ግን ገመጸ ብሎ ደኸየ ድኻ ኾነ ይላል።
ገማሲ ፡-(ሲት ስያን ያት፤ መስት) የሚገምስ ገማሽ ቈራሽ፤ ሰራፍ ሸራፊ መንዛሪ ዐራሽ።
ገማዒ መገምዕ ፡-(ዕት ዓን ዓት) የሚቈርጥ፤ ሸላች ላጭታ፤ ገያሪ ሸክላ ሠሪ።
ገማዲ ፡-(ዲት ድያን ያት) የሚጐምድ፤ ቍራጭ ዐጫጅ፤ ገማጅ።
ገማዲም ፡-ስመ ነገድ፤ ስመ ትውልድ ያፌታውያን፤ የጎሜር ቍራጮች ፡-(ሕዝ፳፯ ፡-፲፩)።
ገምል ፡-ስመ ፊደል ሣልስ ገ፤ በአበገደ። ዐረቦች ጂም ፥ ጀ ይሉታል።
ገምኖ ኖት ፡-(ገመነ ይጌምን ይገምን) ማግመን ማሳረር፤ መጥበስ። ማሳደፍ ማኵለፍለፍ፤ ማርከስ ማስነወር፤ መለወጥ መቀየር፤ የቃል የነገር። ኀፀብኩ እገርየ እፎኑ እጌምኖን። እለ ኢገመኑ አልባሲሆሙ። ገመነ ይሁዳ መቅደስየ። እለ ይጌምኑ ስመ ቅዱሰ፤ እስመ ገመንዋ ለዲና እኅቶሙ። ኢይገምን ቃሎ ፡-(ማሕ፭ ፡-፫። ራእ፫ ፡-፬። ሚል፪ ፡-፲፩። ኩፋ ፡-፴። ዘኍ፴ ፡-፫)። አንዳንድ መጣፍ በገመነ ፈንታ አግመነ አገመነ ይላል፤ አያሰኝም። አገመኑ መሥዋዕተ። ያጌምንዎ ለሥጋሆሙ ፡-(አዋል። ፪ጴጥ ፡-፪ ፡-፲። ይሁ ፡-፰። ራእ፳፩ ፡-፰። ኩፋ ፡-፪። ዘኍ፭ ፡-፲፱ ፡-፳። አመረን አእመረ እንደሚል፤ ይህም እንደዚያ ነው።
ገምዖ ዖት ፡-(ገምዐ ይጌምዕ ይገምዕ) መቍረጥ መሸለት፤ መላጨት፤ የጠጕር። ገምዒ ርእሰኪ። ወይገምዖ ጽሕሞሂ ፡-(ሚክ፩ ፡-፲፮። ኢሳ፯ ፡-፳)። ማለዘብ መፋቅ መላግ ማስተካከል፤ ልጩ ራስ ማስመሰል፤ የርጥብ ሸክላ የምርግ የልስን። ትግሬ ግን ገምዐ ብሎ መከረ ይላል፤ ምስጢሩ ከዚያው ከማለዘብ ይገባል።
ገሞራ ፡-(ጽር ጎሞራ። ዕብ ዐሞራ) ስመ ሀገር፤ አካቶ ፈጽሞ እሳተ መዐት ከዘነመባቸው ካምስቱ አህጉረ ሰዶም ኣንዲቱቴ ፡-(ዘፍ፲፫ ፡-፲)። ዘይገብሩ ግብረ ገሞራ ፡-(ፍ ፡-ነ ፡-፵፰)።
ገሞራዊ ፡-የገሞራን ሥራ የሚሠራ፤ ወንድ ኹኖ ወደ ወንድ የሚኼድ፤ በሴት ፈንታ ወንድ የሚፈልግ ከወንድ የሚዛወግ አድራጊ ወንድ፤ ወይም ተደራጊ ወንዳገረድ፤ ወንድነቱን ክዶ በማይገባ ለወንዶች እንደ ሴት የሚኾን መቀመጫውን የሚደቅን። ገሞራውያን ፡-(ፍ ፡-ነ ፡-፵፰)።
ገሠሠ ፡-፣-ዳሰሰ፣-ገሲስ ገሰ ገሰሰ።
ገሲስ ሶት ፡-(ገሰ፤ ገሰሰ ይገስስ ይግስስ። ዕብ ጋሻሽ። ሱር ጋሽ፤ ግሻ። ዐረ ጀሰ) መግሰስ፤ መዳሰስ መዳበስ በእጅ መንካት ማባበስ፤ መያዝ መጨበጥ። ወዘገሰሳሁ እደዊነ። ዘኢይከውኖሙ ለገሲስ በአደዊሆሙ። ኢትግስሱ መሲሓንየ። ኢትግስስ ወኢትልክፍ ፡-(ዮሐ፩ ፡-፩። ዮዲ፲፩ ፡-፲፫። መዝ ፡-፻፲፫። ቆላ፪ ፡-፳፩)።
ገሳሲ ፡-(ሲት ስያን ያት) ፡-(334) የገሰሰ፤ የሚገስ ገሳሽ፤ ዳሳሽ። ማቴዎስ ገሳሴ ቍስልከ። ገሳሲት ፡-(አዋል። አርጋ ፡-፩)።
ገሣጺ ፡-(ጺት ጽያን ያት) በቁሙ፤ የሚገሥጽ፤ ቀጭ ተቈጭ፤ መካር መምር። ገሣጼ ሕዝብ አብዳን ፡-(ስንክ ፡-ኅዳ፲፫)።
ገሥገሠ ፡-(ጌሠ) በቁሙ፤ ቸኰለ አረበደ ፈጠነ።
ገሥጾ ጾት ፡-(ገሠጸ ይጌሥጽ ይገሥጽ። ዕብ ያሳር) መገሠጽ፤ መቅጣት መቈጣት፤ አጥብቆ መላልሶ መምከር ማስተማር፤ እንደ ደንጊያ መውቀር፤ በነገር ባለንጋ መግረፍ ማሰንበር፤ ያባት የመምር የወዳጅ። ገሥጾሰ ገሠጸኒ እግዚ ወለሞትሰ ኢመጠወኒ። እመ ብከ ውሉድ ገሥጾሙ ወመሀሮሙ። ንጉሥ ጠቢብ ይጌሥጽ አሕዛቢሁ። ገሥጾ ለዐርክከ። በእንተ ገሥጾቱ ለአብድ። ገሠጽኮ ለዮናስ በቀስታመ ባሕር ፡-(መዝ ፡-፻፲፯። ሢራ ፡-፳፫። ፲፰ ፡-፲፫። ፲፱ ፡-፲፫። ፵፪ ፡-፰። ቅኔ)።
ገረማ ፡-በቁሙ፤ ሲናር ጌንጭ፤ የገብስ ዐረም ፡-(ዐማርኛ)።
ገረሠ ፡-(ዐረ ጀረሰ፤ ከካ። ዕብ ጋራስ፤ ተክካ) ጐረሠ ቃመ፤ አላመጠ ቈረጠመ፤ ሰለቀ አላመ፤ አለዘበ። ገረሸ ፡-አገረሸ፤ የደዌ። ባለቅኔዎች ግን ሠራ ይሉታል። ገረሠሠ ተገረሠሠ ማለት ከዚህ ወጥቷል።
ገረዘ ፡-(ዕብ ጋራዝ) በቁሙ፤ ቈረጠ ገረዘዘ። ገዘረን እይ፤ ከዚህ ጋራ ፩ ነው፤ ነከሰ ፥ ነሰከ፤ ቀሐመና ቀምሐ ፩ እንደ ኾኑ፤ እነዚህም እንደነዚያ ናቸው።
ገረፋ ጐረፋ ፡-የፍርድ ቅጣት፤ ግርፋት እስራት። ፍዳ መርገም፤ ፍትወት፤ የአዳም ኀጢአት እንደ ጐርፍ ከላይ ወደ ታች ካባት ወደ ልጅ የሚወርድ። ባልሐነ እምጐረፋነ ወእምቀዳሚት አበሳነ ፡-(ቄር)።
ገሪህ ሆት ፡-(ገርሀ ይገርህ ይግራህ። ገበረ፤ ረየፀ። ዕብ ጋሬህ፤ አፍርሀ አርዐደ) ማረስ፤ መነገድ፤ ማግራት መገራት፤ ገር ማድረግ፤ ማለስለስ ማለዘብ፤ የመሬት የከብት።
ገሪማ ፡-የሰው ስም፤ ገባሬ ተኣምር ግሩም፤ ከተስዐቱ ቅዱሳን አንዱ ይሥሐቅ። ገሪማ የግብር ስም ነው። ገሪማ ገረምከኒ ፡-(ድጓ)።
ገሪም ሞት ፡-(ገረመ ይጌርም ይግርም። ዕብ ጋራም፤ ሰበረ ጐረመመ) መግረም መድነቅ፤ መፈራት፤ ግሩም መኾን፤ ማስገረም ማስደነቅ ማስፈረት፤ ሌላውን፤ የመልክና የክብር የታላቅነት፤ ወይም የክፋት። ገረሞሙ ዘኢኮነ ግሩመ። ወይጌርም እምነገሥት ምድር። ትጌርሞ ወታደነግፆ። ለፈሄ እግዚአብሔር አልቦ ዘይጌርም። መንግሥት እንተ ትጌርም እምኵሉ መንግሥት ፡-(መዝ ፡-፲፫። ፸፭። ሢራ፬ ፡-፲፯። ፴፩ ፡-፲፰። ሱቱ ፡-ዕዝ፲፪ ፡-፲፯)።
ገሪር ሮት ፡-(ገረ፤ ገረረ ይግርር ይግርር። ገነየ) መገዛት፤ መታዘዝ፤ ዜጋ ገባር መኾን። ለሊሆሙ ገረሩ። ፈቀዱ ይግርሩ ሎቱ። ኢይግርር ኤጲስቆጶስ ዘኢየሩሳሌም ለካልኡ እምኤጲስቆጶሳት። ኢይገርር ለሕገ እግዚ ፡-(ኢያ፲ ፡-፩። ዮሴፍ። ፍ ፡-ነ ፡-፬። ሮሜ፰ ፡-፯)። ገርገረን እይ፤ የዚህ ዲቃላ ነው።
ገሪዛን ፡-(ጽር ጋሪዚን። ዕብ ግሪዚም) የተራራ ስም፤ ቍርጥ የኾኑ የቡራኬ ቃሎች የሚነገሩበት ተራራ። ጌባልን እይ፤ የዚህ ወንድም ነው ፡-(ዘዳ፳፯ ፡-፲፪)።
ገሪድ ዶ ት ፡-(ገረደ ይገርድ ይግርድ። ዕብ ጋራድ) ማግረድ፤ ማምረት፤ ግርድ ቂንድ ማውጣት፤ ፍሬን ከገለባ መለየት፤ መፈልፈል ማሸት። መጋረድ መሸፈን። ገረድ ግሪዶ መኾን። ከርደደን እይ፤ የዚህ ዲቃላ ነው። ጋሬዳ ማለት ከዚህ ወጥቷል።
ገሪፍ ፡-ወጥመድ፤ ዘረ መትር፤ መረብ መግለቦ፤ ያሣ መያዣ፤ መጋፈፊያ ፡-(ማቴ፲፫ ፡-፵፯)። ኀሠሡ ከመ ይግበር ሎሙ ገሪፈ። መሥገርተ ገሪፍ እንተ ታስተጋብእ ዘመደ ኵሎን ዓሣት ፡-(ፊልክ ፡-፻፳፭። አርጋ ፡-፫)። ዓምና ያለፈው ዓመት።
ገሪፍ ፎት ፡-(ገረፈ ይገርፍ ይግርፍ። ዕብ፤ ጋራፍ፤ ሳበ) መግረፍ፤ መሸንቈጥ፤ በጅራፍ ባለንጋ መቅጣት። መግለቦ መሥራት፤ የተሠራውን መውገር መጣል ከባሕር ማግባት፤ ዓሣው ሲመላ መሳብ መጐተት ወደ የብስ ማውጣት።
ገራሂ ፡-(ሂት ህያን ያት፤ ህት) ዐራሽ ቈፋሪ፤ ነጋዴ ዐጣሪ፤ ፈረስ በቅሎ ገሪ።
ገራህታት ገራውህ ፡-ዕርሾች፤ ቅብቅቦች። አጥረየ አባግዐ ወአልሕምተ ወገራውሀ ብዙኀ። ውስተ ኵሉ ገራውህ ኀበ ሀሎ አብራም። መንገለ ገራውህ። እመ ቦ ውስተ ካልእ ብሔር ገራውህ ፡-(ዘፍ፳፮ ፡-፲፬። ኩፋ ፡-፲፩። ማቴ፲፪ ፡-፩። ሲኖዶ)።
ገራህት ገርዋህ ፡-(ዐረ ቀራሕ ቂርዋሕ) ዕርሻ ቅብቅብ፤ የለዘበ የለሰለሰ፤ ዘር ለመቀበል የደረሰ። ዕርሻ የሚመስል የበረሓ መሬት፤ ሣርና ቅጠል ዛፍ። የሌለበት አሸዋ ድቡሽት። ሠናየ ዘርዐ ዘራዕከ ውስተ ገራህትከ ፡-(ማቴ፲፫ ፡-፳፯)።
ገራሪ ፡-(ሪት ርያን ያት) የሚገዛ ተገዥ፤ ታዛዥ። አማንያን ለቃለ እግዚ ወገራርያን ለነገረ አኀው ፡-(ገድ ፡-ኪሮ)።
ገርሃት ገራህው ፡-ጣቆች የንግድ ዕቆች፤ ሸቀጦች። መጽሐፍ ግን ገራህው በማለት ፈንታ ገራውህ ይላል፤ ባለሐዲሶችም ፍችውን ዕርሻ ይሉታል፤ ንባቡም ፍችውም ተሳስቷል። ዘይሣየጥ ሎሙ ገራውሂሆሙ ፡-(ራእ፲፰ ፡-፲፩)። ገራውህ ያለውን ከዚያው ባ፲፪ና ባ፲፫ ቍ ዘርዝሮ ተርትሮ የንግድ ዕቃነቱን ይናገራል።
ገርህ ፡-ገር የዋህ ገራም ጭምት፤ ልሙጽ ልዝብ ለስላሳ፤ ጕጣምና ሸካራ ያይዶለ የመሳል ዐይነት። ካህን ዘያዐርግ ቍርባነ ኢይግበሮ ገርሀ፤ አላ ይኩን ኵለንታሁ ምስቁለ በማኅተም ፡-(ፈ ፡-መ)። መዳ ጣቃ የንግድ ዕቃ፤ ሸቀጥ የሚሼጥና የሚለወጥ፤ አስረው አክተው በሣጥን መልተው ካገር ወዳገር የሚወስዱት። ገርህ ማለት ሥራው ያለቀለት ዝግጁ መኾኑን ያሳያል ፡-(ሕዝ፳፯ ፡-፳፬)።
ገርሣ ፡-ልዝብ ለስላሳ ሣር፤ ልሻ የጠጕር ዐይነት፤ እንደ ጭድ እንደ ገለባ ከጭቃ የሚስማማ፤ ጕርሻ ጕርሦ፤ ግርሻ ፡-(ዐማርኛ)።
ገርሣኒ ፡-ያርብሓዊ ረዐይታዊ፤ ኀይለኛ ጣሽ ጠምላሽ። ኀጺናዊ ማሕረጻዊ ማለት ነው፤ ጐራሽነትንም ያሳያል ፡-(ገድ ፡-አዳ)። ለሽጕጥና ለነፍጥም ይሰማማል፤ ፮ ጐራሽ ፥ ፱ ጐራሽ እንዲሉ።
ገርሥ ፡-(ሣት) የመዝጊያ ብረት ሳንቃውን ከመቃን የሚያዛውግ፤ የሚያቈራኝና አንድ የሚያደርግ፤ ወንዴና ሴቴ ብረት፤ ወንዴው በመቃን ላይ ሴቴው በመዝጊያ ላይ ተቸንክሮ ርስ በርሱ የሚሳካና የሚጓረሥ፤ ወይም በሳንቃው ላይ እንደ ሳንቃ ኹኖ የሚለበጥና የሚጠረቅ። ወካዕበ አስተዳለወ ብርተ ብዙኀ ዘአልቦ መድሎት ለገርሣተ ኀዋኅው፤ ወለባዕድኒ ግብር ፡-(፩ዜ ፡-፳፪ ፡-፫)። ባለብሉዮች ግን ሰንሰለት ይሉታል።
ገርዋህ ፡-(ትግሬ) አጋዘን፤ ቡኸር። ገራገር ማለት ነው።
ገርዜን ፡-(ገንዜን፤ ገኒዝ ገነዘ) ቀጭን ሸማ፤ ጥሩ በፍታ ሻሽ፤ ሐዲስ ልብሰ ክታን። አምጽኡ ልብሰ ገርዜን ለግንዘተ ሥጋሁ። በሰንዱነ ገርዜን ተገንዘ ወተቀብረ። ዘተጠብለለ በልብሰ ገርዜን። ለምሥዋዕ ይኩን መንጦላዕት ዘገርዜን ንጹሕ ዘአልቦ ነውር። ክድንኒ ገርዜነ ጸጋ ዘኢአነምዎ ጠቢባን በኪን ፡-(ቅዳ አፈ። ተረ ፡-ቄር፲፮። አርጋ። ኪዳ። ደራሲ)።
ገርገረ ፡-(ገሪር ገረ ገረረ። ዕብ ጋራር) ሳበ ጐተተ፤ ተሳበ ተጐተተ፤ የጋሪ። በቁሙ ገረገረ አቆመ፤ የይሎ የንጨት። ወገሸ አገረገረ፤ ግር ግር አለ፤ የከብት። ግርግር ፍግርግር ወጋግራ ግርግራ ገረገራ ማለት ከዚህ ወጥቷል።
ገበለ ፡-(ዕብ ጋቤል) ለወሰ አቦካ አላቈጠ፤ የዶቄት የጭቃ።
ገበታ [1]፡-(ብ ገባትው) በቁሙ፤ የንጨት ለገን ወጭት፤ ማቡኪያ ማሻ መለወሻ ቆሬ፤ ወይም ማሣሻ ዝርግ ጠፍጣፋ፤ ሉሕ፤ ሰደቃ። ዋልታም ይኾናል። ወዲበ ገባትው በዘይገብሩ ናእተ ፡-(፩ዜና ፡-፳፫ ፡-፳፱)።
[2]፡-ገበታ፤ ፡-(ዕብ ጋብታ። ጽር ጋባታ) የቦታ ስም፤ ከፍታና ሜዳነት ያለው ፡-(ዮሐ፲፱ ፡-፲፫)።
ገበታ ሐዋርያ ፡-(ዐማርኛ) የመጽሐፍ ስም፤ ገበታዋሪያ ት ሰባቱ የሐዋርያት መልእክታ ከያዕቆብ እስከ ይሁዳ ያሉት። መጽሐፋን ገበታ ያሰኘው ዕንጨቱ ነው፤ ፍችውም ማእድ ፥ ማእደ ትምህርት ዘሠርዕዎ ሐዋርያት እንደ ማለት ነው።
ገበነ ፡-(ዕብ ጋቤን) አረጋ ዐየበ፤ ዐይብ አደረገ፤ ወተቱን።
ገበዝ ፡-ዳር ዳርቻ፤ ጠረፍ። ተቀበሎ ዲበ ገበዘ ተከዚ ፡-(ዘፀ፯ ፲፭)።
፡-ብርቱ ጠባቂ ዘበኛ፤ በረኛ። እምነ ጽዮን ገበዘ አኵስም። ሰዴድዎ እምሀገር እለ ገበዘ አኵስም፤ ዕጣና ለገበዝ። ቦአ ውስተ ቤተ ክርስቲያን ዘገበዘ አኵስም። ገበዝ የጽዮን ቅጥል ነው ፡-(ሥር ፡-አኵ ፡-ገ፹፱። መዋሥ። ስንክ ፡-ግን፲፩)።
፡-የሹመት ስም፤ የቤተ ክሲያን ሹም አስተንታኝ፤ የሰሞነኞች አለቃ። ምስጢሩ ያው ጠባቂነት ነው። ቀይሰ ገበዝ። ኢይትለአክ ከመ ካህናት ወኢይኩን ሊቀ ካህናት ወኢይቀድስ ከመ ገበዝ ፡-(ሥር ፡-አኵ። ቄድር ፡-ገ፹፰)። ,
፡-መሐንድዝ፤ ሊቀ ነደቅት። ገበዝ አንባ እንዲሉ።
ገበያዊ ፡-መንገደኛ፤ ነጋዴ ገበያተኛ።
ገበይ ፡-(ትግሬ) መንገድ ጐዳና፤ ገበያ። ዘሩና ሥሩ ጉባኤ ነው።
ገበጣ ፡-በቁሙ፤ የጠጠር ጨዎታ፤ ልቅሞሽ ቅልሞሽ፤ ግብጦች ወይም ጠጠር ጣዮች ያወጡት። ፡-(ተረት) ገበጣ ላዋቂ ወሬ ለጠያቂ። ኢይትላሀዩ ግብረ ሰንጠረዥ ወገበጣ ፡-(ፈ ፡-መ ፡-፴፪ ፡-፯)።
ገበጥባጥ ፡-የሆድ ትል፤ ወስፋት ሹጥ፤ ሥራይ። ዘከመ ዝንቱ ደዌ ወገበጥባጥ ፡-(ኩፋ ፡-፳፫)።
ገቢስ ሶት ፡-(ገበሰ ይገብስ ይግብስ። ዕብ ጋባሽ፤ መላ። አው ገብስሶ፤ ሶት፤ ገብሰሰ ይገበስስ ይገብስስ) ማጋበስ መሰብሰብ፤ የሣር የንጨት የኵረት፤ መምላት ማስተካከክል፤ መምረግ መለሰን መቅባት መለቅለቅ፤ የግድግዳ የግንብ። መምላት ፥ ውስጡን በኵረት፤ መለሰን አፍኣውን በጭቃ፤ መለቅለቅ፤ በኖራ በበረቅ። ገየረን እይ።
ገቢር ሮት ፡-(ገብረ ይገብር ይግበር። ዕብ ጋባር፤ ኀየለ ጸንዐ) መሥራት ማድረግ መፍጠር፤ ያልነበረ ነገር ማስገኘት፤ የነበረውን ማዘጋጀት፤ ፍጥረትን ከፍጥረት ጨምሮ ሌላ ህላዌ ማቆም፤ እንደ ሥጋና እንደ ሸክላ እንደ ቤት እንደ ምንጣፍ። በሚሠሩት ሥራ ማየል መበርታት መሠልጠን፤ ከሃሊ መኾን። ስዱሰ ዕለተ ትገብር ግብረ። ገቤረ ግበር በከመ አዘዝኩ። ዘገብረ ሰማየ ወምድረ። ወገብሮ እግዚ ለሰብእ መሬተ እምድር። ገብረ ወይነ እምፍሬ ፡-(ዘሌ፳፫ ፡-፫። ዮዲ፪ ፡-፲፫። መዝ ፡-፻፳፫። ዘፍ፪ ፡-፯። ኩፋ ፡-፯)። ገብረ በሥራ ኹሉ እየገባ እንደ ሥራው ስልት ይፈታል። ይግበሩ ውስተ ማሕቶት ቅብዐ፤ ይደዩ። ግበር እዴከ ዲበ ዛቲ ጻሕል፤ ሢም አንብር ያሰኛል ፡-(ስንክ ፡-ጥቅ፳። ቅዳ)።
ገቢእ ኦት ፡-(ገብአ ይገብእ ይግባእ። ቦአ መጽአ። ገብአ ትግ ኮነ ይከውን) መግባት መጥለቅ መዝለቅ፤ ወደ ውስጥ። መመለስ ወደ ኋላ መዞር መታጠፍ ተመልሶ መምጣት። ገቢኦትከ ውስተ ሥጋ። ይትመየጥ ለገቢእ። ገብአ ቤቶ እገብእ ውስተ ምድር። ገብኡ እምፍኖት እኩይ ፡-(ዕር ፡-ኢሳ፰ ፡-፳፯። መክ፭ ፡-፲፬። ጦቢ፰ ፡-፲፩። ኢዮ፩ ፡-፳፩። ኤር፵፪ ፡-፲፭)።
፡-መኾን፤ መያዝ መስጠት። ገብኡ ታሐተ እደ ትሑት። ገብኡ ከመ ዘኢተወልዱ። ደኃርት ይገብኡ ቅድመ፤ ኮኑ ይከውኑ። ገባእነ ውስተ እደ ጸላእትነ። ይግባእ ውስተ እደ ሰብእ ፡-(ሢራ፲፩ ፡-፵፬ ፡-፱። ማር፲ ፡-፴፩። ሱቱ ዕዝ፲ ፡-፴፮። ሉቃ፳፬ ፡-፯)።
ገቢዝ ዞት ፡-(ገበዘ ይገብዝ ይግብዝ) መለካት መወሰን፤ ዙሪያውን መቍረጥ መከለል፤ የመሬት የሕንጻ። መጐበዝ፤ መገበዝ፤ ጐበዝ ግብዝ መኾን። መጋበዝ ፡-(ዐማርኛ)።
ገባሪ ፡-(ሪት ርያን ያት፤ በርት) የሚሠራ ሠሪ፤ አድራጊ ፈጣሪ ፈጻሚ። አሐዱ ገባሪ በማለት ፈንታ አሐዱ ግብር ይላል የጣፊ ስሕተት ነው ፡-(ሃይ ፡-አበ ፡-ጎር። ብን)። ግብር ምስለ ገባሪሁ። ጥበብ ገባሪተ ኵሉ። ገባርያነ ብርት። ገበርተ ዐመፃ ፡-(ጥበ፲፬ ፡-፲። ፰ ፡-፭። ፲፭ ፡-፱። መዝ ፡-፭)። ገብረ በመላላቱ የቀተለ ሰርዌ ሺኾን በመጥበቁ ቀደሰን ይመስላል፤ መምሰሉም ይህ ነው።
ገባራዊ ፡-ዝኒ ከማሁ፤ ገበሬ፤ የነገር የሥራ ፡-(፪ጢሞ ፡-፪ ፡-፲፭። ክብ ፡-ነገ። ስንክ ፡-ኅዳ፲)።
ገባር ፡-(ራት። ዕብ ጊቦር፤ ብርቱ) በቁሙ፤ ገበሬ ሠራተኛ፤ በግድ የሚሠራ፤ ጕልበቱን ገንዘቡን ለሹም የሚያፈስ ሹማምት እንደ ወደዱ የሚያደርጉት ባለርስት ባሪያ። ፡-(ግጥም፤ ቡልጌ ያበቡት ባለጌ ጤፍ ሲወቃ) የየጀርሳ ዝኆን የከረመ እንደኾን ፥ ስንኳን ገባር ጢሰኛም ሰው አይኾን። መጽሐፍ ግን በገባራት ፈንታ ገባር ይላል፤ አያሰኝም። ወገባሩ ኅዳጥ፤ ከመ ይወስክ ገባረ። ናሁ ዐስቦሙ ለገባር። ወሢመ ዲቤሆሙ ሊቃነ ገባር ከመ ይሣቅይዎሙ በግብር። ነዳእተ ገባር ፡-(ማቴ፱ ፡-፴፯። ያዕ፭ ፡-፬። ዘፀ፩ ፡-፲፩። ፫ ፡-፯)። ገባረ ሪፍ። ገባራት። አምጽአ ገባራተ ከመ ያንኅሉ አረፍተ ቤት ፡-(ታም ፡-ማር። ስንክ ፡-ነሐ፩። አዋል)።
ገባኢ ፡-(ኢት እያን ያት፤ እት) ቅጽልና ጥሬ፤ የሚገባ ገቢ፤ ተመላሽ፤ ተመላላሽ። ገበሬ ዐራሽ፤ የለት ምንደኛ ሙያተኛ፤ ዐራሚ ቈፋሪ፤ አሽከር ወታደር አገልጋይ ሎሌ። ገባኢ ዘይጻሙ በተገብሮታ ለምድር። ገባኢ ዘይሌፎ ዐስቦ። ይትዓሰብ ገባእተ። ገባኢሁ ለኤፍሬም ፡-(ጥበ፲፯ ፡-፲፮። ኢዮ፯ ፡-፪። ማቴ፳ ፡-፩። ዮዲ፮ ፡-፪)።
ገብላ ፡-(ላት) ገንዳ፤ ከግንድ ከደንጊያ የሚሠራ ማቡኪያ ማላቈጫ፤ የከብቶች ውሃ ማጠጫ፤ እንደ ገበታ የተጠረበ የተፈለፈለ። ዘየአምር ወኢይገብር ይመስል ገብላ ዘምሉእ ማየ ዘእምኔሁ ይሰትዩ ብዙኃን ወያነጽሕ ብዙኃነ እምርስሐቲሆሙ። ገብላተ እብን ዘያሰትዩ ባቲ አፍራሰ ፡-(ፊልክ ፡-፻፱። ስንክ ፡-መስ፩። ዘፍ፴ ፡-፴፰ ፡-፵፩። ዘፀ፪ ፡-፲፮)።
ገብሳሲ ፡-(ሲት ስያን ያት፤ ሰስት) የሚለስን ለሳኝ፤ ቀቢ ለቅላቂ።
ገብስ ፡-በቁሙ፤ ሰገም የብር እኽል፤ ነጭ ነጫነጭ ማለት ነው። ገብስማ ዶሮ እንዲሉ።
ገብር ፡-(ብ አግብርት) ባሪያ ተገዥ፤ አገልጋይ ሰው፤ የተማረከ ወይም የተገዛ ግዝ፤ ውላጅ። ገብር ከመ እግዚኡ። ቦኑ ውእቱ ገብር ያዕቆብ አው ልደ ቤት። ነሥአ አርኣያ ገብር። ከመ ኪያነ ይቤዙ እግዚእ ኮነ ገብረ። አግብርትየ ወአእማትየ። አግብርተ ኀጢአት ፡-(ኢሳ፳፬ ፡-፪። ኤር፪ ፡-፲፬። ፊልጵ፪ ፡-፯። ድጓ። ግብ፪ ፡-፲፰። ሮሜ፮ ፡-፲፯)።
(ጥ) ገብሮ ሮት ፡-(ገበረ ይጌብር ይገብር) (ገበረ ይጌብር ይገብር) ፡-(ጥገ) መገበር ማረስ መቈፈር፤ ገበሬ መኾን፤ መነገድ ንግድ ማድረግ። ፡-(ጥበ) መገበር፤ ግብር መስጠት፤ በግድ መሥራት፤ ባሪያ ገባር ዜጋ መኾን። መጽሐፍ ግን በገብረና በገበረ ፈንታ ተገበረ ይላል፤ አያሰኝም። ተገበሩ ጽድቀ።አለ ይትጌበሩ ሜላተ። ዘይትጌበራ ለምድር። ዘይትጌበር ገራህቶ። ሐመር እንተ ትትጌበር እምርሑቅ። ተገበሩ እንከ እስከ አአቱ። ንትጌበር ወንረብሕ ፡-(ዕብ፲፩ ፡-፴፫። ኢሳ፲፱ ፡-፱። ምሳ፲፪ ፡-፲፩። ፳፰ ፡-፲፱። ፳፱ ፡-፴፪። ሉቃ፲፱ ፡-፲፫ ፡-፲፭። ያዕ፬ ፡-፲፫)።
ገብቦ ቦት ፡-(ገበበ ይጌብብ ይገብብ። ዕብ ጋባብ) መሰብሰ፤ ማግባት መክተት። መቈፈር፤ መቅበር። ማጓበብ መንጓበብ፤ ጕባ ጐባባ መኾን፤ እንደ ቀስት። ጕቦ መስጠት መቀበል።
ገብገብ ገብገቦ ፡-አዳራሽ ሰቀላ በረንዳ። ሸንጎ አደባባይ፤ ዐውደ ምቅታል። ወወፅአ ውስተ ገብገብ። አዘዘ ይሰድዋ ኀበ ገብገቦ ወይምትርዋ ክሣዳ ፡-(ዮዲ፲ ፡-፳፪። ስንክ ፡-ታኅ፮)።
ገብጥ ፡-የሆድ በሽታ፤ ብስና ጓታ እህታ፤ የሚቈርጥ የሚጐራብጥ የሚያስቀምጥ። ቅንጣዌ ወገብጥ። ያበዝኆ ለገብጥ ሥሥዕት ፡-(ሢራ፴፬ ፡-፳። ፴፯ ፡-፴)።
ገቦ [1]፡-ጐን፤–ገቢእ ገብአ።
[2]፡-ገቦ፤ ፡-(ብ ገበዋት። ሱር ጋባእ። ዐረ ጀንብ፤ ጃኒብ) ጐን ጐድን ወገብ፤ ወገን ማእዝን፤ ቅርብ አጠገብ። ግንቦት ማለት ከዚህ ወጥቷል፤ ገቦ ክረምት ማለት ነው፤ ከጻዴ ጋራ ይሰማማል። ትሰክብ በገቦከ ዘፀጋም። ለገብር እኩይ ሥትሮ ገበዋቲሁ። ይትዐጸፍ ርትዐ ውስተ ገቦሁ። ወልድከ ዘወፅአ እምገበዋቲከ። በገቦ መስዕ። ወእምገበዋቲሁ ለውእቱ መንበር። አዝማድ እለ ገበዋት። ገዳም ዘገቦ ይታይም። ኖመት በገቦሁ ፡-(ሕዝ፬ ፡-፬። ሢራ፵፪ ፡-፭። ኢሳ፲፩ ፡-፭። ፫ነገ ፡-፰ ፡-፲፮። መዝ ፡-፵፯። ራእ፬ ፡-፮።ፍ ፡-ነ ፡-፳፬ ፡-፪። ዮዲ፬ ፡-፮። ስንክ ፡-ሠኔ፴)።
ገቦታ ፡-የሰው ስም። ምስለ ገቦታ ወታራ ፡-(አስቴ፩ ፡-፲፪)።
ገቲት ቶት ፡-(ገተ፤ ገተተ ይገትት ይግትት) መጐተት ማንገላታት፤ እንዳለወገን ማድረግ። ገትገተ ብሎ ፥ ገተገተ ገትጋታ ማለት ዐማርኛው ከዚህ ወጥቷል።
(ጥ) ገት [1]፡-(ትግሬ) ብዕል ሀብት፤ ጌትነት።
[2]፡-(ጥ) ገት –ብዕል ሀብት፤–ገዪት ጌተ።
ገነ ፡-(ይገንን ይግንን፤ ገኒን። ዕብ ጋናን) ገነነ፤ ገናና ኾነ፤ ታበየ ኰራ ተንጠራራ። ተከለ ጋረደ መከተ፤ ዐጠረ ቀጠረ። መገን ከዚህ ወጥቷል፤ ጋሻ ማለት ነው፤ ገነገነና ጐነጐነም የዚህ ዘር ናቸው፤ ግስነቱ ሐውልትና ገቢር እንደ ኾነ አስተውል።
ገነበ ፡-(ዕብ ጋናብ፤ ሰረቀ) ገነባ ግንብ ሠራ፤ ወይም አፈረሰ፤ ቈፈረ ሰረሰረ፤ ለመስረቅ። መገንባት የሸክላንና የጡብንም ሥራ ያሳያል። ገንቦ ገንቦኛ እንዲሉ።
ገነት ፡-(ታት። ዕብ ጋን። ሱር ጋንታ። ዐረ ጀነት) የተክል ቦታ ብዙ ዛፍና ዕንጨት ሽቱ ቅመም የሚበቅልበት፤ ምንጭ ያለው ውሃ የሚገባው፤ የታጠረ የተቀጠረ። ገነት ዕጹት። ገነተ አቅማሕ። ወቦ ህየ ገነት ዐጸደ ሐምል። ወውስተ ውአቱ ገነት። ዐቃቤ ገነት። ገበርኩ ሊተ አዕጻደ ሐምል ወገነታተ ወተከልኩ ውስቴቶሙ ዕፀወ ዘይፈርዩ ፡-(ማሕ፬ ፡-፲፪። ዳን ፯። ዮሐ፲፰ ፡-፩። ፲፱ ፡-፵፩። ፳ ፡-፲፭። መክ፪ ፡-፭ ፡-፮)።
፡-ዓለመ ጻድቃን፤ አዳምና ሔዋን የነበሩበት፤ እግዜር ያበጀው ያዘጋጀው፤ የዕረፍትና የሕይወት የተድላ የደስታ ቦታ፤ ስለ ልዕልናው ሰማይ የሚባል ልዑል ሀገር ልዑል ማኅደር ፡-(ዘፍ፪ ፡-፰ ፡-፱። ፫ ፡-፳፫ ፡-፳፬። ፲፫ ፡-፲። ፪ቆሮ ፡-፲፪ ፡-፪ ፡-፬)። ገነትሰ በእንተ ልዕልናሁ እምድር ይሰመይ ሰማየ፤ ወሐዋርያኒ ነዋ ሰመያ ለገነት ሰማየ ሣልሲተ። ቀዳሚታሰ ይእቲ ምጽናዓት እንተ ይቤ በእንቲኣሃ እግዚ በውስተ ኦሪት በልሳነ ሙሴ ነቢይ፤ በቀዳሚ ገብረ እግዚ ሰማየ ወምድረ። ወካልእታኒ ይእቲ ጠፈር ዘፈለጣ እግዚአብሔር ማእከለ ማያት። ወሣልሲት ይእቲ ገነት በከመ ሰመያ ጳውሎስ ሐዋርያ፤ ወነፍሳቲሆሙ ለጻድቃን ይከውና ውስተ ገነት እስከ አመ ይመጽእ እግዚእ ለፍዳ፤ ወአሜሃ ይከውን ሎሙ ተሳትፎ ምስለ ክርስቶስ። ወያጌጹ በእንተ ውእቱ ቃለእግዚእነ ለፈያታዊ ዘየማን ዮም ትሄሉ ምስሌየ ውስተ ገነት ፡-(ፊልክ ፡-፰። ሉቃ፳፫ ፡-፵፫)።
፡-መጽሐፍ የመጽሐፍ ስም፤ ዜና አበው ገድለ መነኮሳት። እስመ ጸሓፌ ገነት ይቤ። መጽሐፈ ገነት ዘጸሐፎ ጰላድዮስ ፡-(ፊልክ ፡-፲፮ና ፡-፴፱)። በገነት መልካምና ክፉ የሚያሳውቅ ዕፀ አእምሮ እንዳለበት፤ በዚህም ጽድቅን ከኀጢአት ከሐሰትና ከምትሀት የሚያስለይ፤ ያምላክንና የመልአክን መንገድ ከሰይጣናት መንገድ ለይቶ የሚያሳይ የሚያስረዳ፤ የገነትን ተድላ የሚያወራ እንደ ማየ ሕይወት የጠራ ዕውቀትና ትምርት ስላለበት፤ በምሳሌ ገነት ብለውታል፤ ብርሃን ማለት ነው። አበዊነ ይሰምይዎ ለብርሃነ አእምሮ እግዚአብሔር ገነተ። ልቡ ለባሕታዊ ገነተ ተድላ ውእቱ ፡-(አረጋ ፡-ድ፲፮። ፵፮)።
ገነጰ ፡-(ዐረ ከነበ) ሰበሰበ አከበ፤ አከተ ከተተ።
ገነፈ ፡-(ይገንፍ ይግንፍ። ገለፈ) ጐነፈ፤ ሣለ መሰለ፤ ቀረጸ። ዐጠበ አጠራ፤ ወይም ለማጥጠብ ፥ ባመድ በረመጥ ጐነፈ ቀቀለ፤ የልብስ የሸክላ። ገነፋ አገነፋ አማሰለ። ዝሓን በሙቅ ውሃ ዘፈቀ ነከረ።
ገኒሕ ሖት ፡-(ገንሐ ይገንሕ ይግናሕ። ዕብ ጋናሕ) መገንታት መጮኽ መቈጣት፤ ድምፅን ማግነን ቃልን ማበርታት፤ መታበይ መኵራት፤ ኀይለ ቃል ማውጣት። ገሠጾ እግዚ ለዳዊት በቃለ ነቢይ እንዘ ይገንሕ። ወትገንሖሙ ለኃጥኣን በቃለ ስክየት ፡-(መጽ ፡-ምስ። ቅዳ ፡-ያዕ)። ጐሀነን ተመልከት፤ የዚህ መንቲያ ነው።
ገኒን ፡-(ዐረ ጀኒን) ሽል ጭንጋፍ፤ የተናቀ፤ ወራዳ ታናሽ ርካሽ። ኢትሢጣ በሤጠ ገኒን ፡-(ፈ ፡-መ ፡-፲፰)።
ገኒዝ ዞት ፡-(ገነዘ ይገንዝ ይግንዝ። ዕብ ጋናዝ፤ ቀበረ ሰወረ) መገነዝ መከፈን፤ መጠቅለል መለፈፍ፤ ማልበስ ማጐናጠፍ፤ ማሰር መቋጠር መክተት የሬሳ የገንዘብ ፡-(ማቴ፳፯ ፡-፶፱። ዮሐ፲፱ ፡-፵)። ገነዞ ሴት ወአንበሮ ውስተ ታቦት። ምስለ አፈዋት ገነዘ ወቀበረ በድኖ። ኢትግንዝዎ እስመ ሕያው ውእቱ። ሶበ ሞተት ብእሲት በወሊድ ይኅፅብዋ ወይግንዝዋ በካልእ ልብስ። ፡-(ግጥም) አጥበው ገንዘው ሲሰጡት፤ ምን ይብላ መሬት ፡-(ቀሌ። ስንክ ፡-ነሐ፩። ባሮክ። ፍ ፡-ነ ፡-፳፪)።
ገናሒ ግኑሕ ፡-የሚቈጣ ቍጡ፤ ጯኺ ተሳዳቢ።
ገናዊ ፡-(ዊት ውያን ያት፤ ነውት) የተጀነነ የሚጀነና፤ ጋኔን ሳቢ፤ ዛራም ጋኔናም ካህነ ጣዖት ነቢየ ሐሰት። ገናዌ አማልክት። ገነውቱ ለቤል። ገነውቱ ለዳጎን። ወገብረ ገነውተ አማልክት ፡-(ቈስጠ ፡-፳፯። ዳን፲፫ ፡-፰። ፩ነገ ፡-፭ ፡-፭። ፫ነገ ፡-፲፪ ፡-፴)።
ገናዚ ፡-(ዚት ዝያን ያት) የሚገንዝ ገናዥ፤ አማዋች ቀባሪ ከታች።
ገናዪ ፡-(ዪት ይያን ያት፤ ነይት) የሚገዛ ተገዥ፤ ሰጋጅ አመስጋኝ።
(ጥ) ገናፍ ገናፊ ፡-(ጽር ግናፊስ። ዕብ ኮቤስ) ልብስ ዐጣቢ። ዐጺደ ገናፊ ፡-(፬ነገ ፡-፲፰፤ ፲፯)።
ገንሕ አው ገንዕ ፡-(ዓት፤ አግንዕት) ጋን፤ ገናና ታላቅ የሸክላ ዕቃ፤ የጠላ የጠጅ መጥመቂያ፤ የልብስ ማጨቂያ። የጋን ሸማ እንዲሉ። ገንዐ ወልጕነ ፡-(ገድ ፡-ተክ)።
ገንበረ ፡-ገነበረ ፥ አገነበረ፤ ባዕድ ኾነ።
ገንታ ፡-ቀንዳ መለከት፤ ቱልቱላ፤ ገንትቶ የሚጮኽ። ዐዊዶሙ ምስለ ገንታ ወግርጣጥ በከበሮ ወጸናጽል ፡-(ታሪ ፡-አኵ)።
ገንዕ ፡-ጋን፤–ገኒሕ ገንሐ ገንሕ፤ ዕ። ዐና ሐኀ እንዲወራረሱ አስተውል።
ገንዎ ዎት ፡-(ገነወ ይጌኑ ይገኑ። ዐረ ጀነ) መጀነን፤ ጋኔን መሳብ፤ ለጋኔን ለጣዖት መገዛት ማገልገል፤ ካህነ ጣዖት መኾን መባል። ገነየንና ገኒንን እይ፤ የዚህ ጎር ናቸው።
ገንዘብ ፡-(ሱር ግኑዝባ) በቁሙ፤ መድፍን የተቀበረ ወርቅ፤ ወይም በሣጥን የሚደበቅ ፡-(ዲድ ፡-፮)። ብ ከዘገበ መጥቶ በገንዘ ላይ ተደርቧል።
ገንዜ ፡-ዝኒ ከማሁ፤ ልብሰ መግነዝ። ገርዜንን እይ፤ ንና ር ስለ ተዋረሱ ገረዘ ወስዶታል።
ገንዜን ፡-ዝኒ ከማሁ፤ ልብሰ መግነዝ። ገርዜንን እይ፤ ንና ር ስለ ተዋረሱ ገረዘ ወስዶታል።
ገንይ ዮት ፡-(ገነየ ይገኒ ይግኒ፤ አው ገንየ ይገኒ ይግነይ። ዐረ ጀነአ። ሱር ግናእ። ዕብ ካናዕ) መገዛት ማጐንበስ መስገድ፤ መዋረድ፤ መታዘዝ ማገልገል፤ መጸለይ ማመስገን፤ መየበብ ምስጋና ማቅረብ፤ መለማመጥ ማቈላመጥ። ምስጢሩ ፪ ነው፤ መገዛትና የመገዛት ሥራ። ወለጽድቀ እግዚአብሔርሰ ስእኑ ገንየ። ግነዮ ወስገዱ። አፎ ሠመርክሙ ከመ ትግነዩ ለአቢባል። ኵሉ ልሳን ይገኒ ለእግዚ። እገኒ ለከ እግዚኦ በኵሉ ልብየ። ወነዳይሰ ለሊሁ ይትገፋዕ ወለሉሁ ይገኒ ፡-(ሮሜ፲ ፡-፫። ዳን፫ ፡-፭። ዮሴፍ። ኢሳ፵፭ ፡-፳፫። መዝ ፡-፱። ሢራ፲፫ ፡-፫)። በገነየ ፈንታ ተጋነየ ይላል፤ በጐንደየ ፈንታ ተጐናደየ እንዲል። እትጋነያ ለብእሲትየ። እንዘ ይትጋነይ ላቲ። ተጋነይ ሶበ ትኤብስ። ተጋነየ ለገጸ እግዚ። ተጋነዩ ወሰገዱ ቅድሜሆሙ። ስኢል ወተጋንዮ ፡-(ኢዮ፲፱ ፡-፲፯። አስቴ፯ ፡-፰። ሢራ፲፰ ፡-፳፩። ፬ነገ ፡-፲፫ ፡-፬። ቀሌ። ፩ጢሞ ፡-፪ ፡-፩)።
፡-መገኘት፤ መምጣት መፈጠር መወለድ ፡-(ዐማርኛ)።
ገንደበ ፡-(ትግሬ) አረጀ ገነጀበ፤ ገንጀባ ኾነ።
ገንዶር [1]፡-ጕንደ እግር፤ ማእሰረ እግር፤ የግር ግንድ የንጨት ዛንጅር። ወስከምት የቀንበር ዐይነት፤ መንቈር ባላ እንዛዝላ የወይፈን መቅጫ። አዘዘ ይደዩ ውስተ ክሣዶሙ ጋጋተ ወገንዶራተ ውስተ እገሪሆሙ ወይሰድዎሙ ውስተ ቤተ ሞቅሕ። አክብድ ገንዶራቲሁ ፡-(ስንክ ፡-ታኅ፲፪። ሢራ፴ ፡-፴፰)።
[2]፡-ግንደ ቈርቍር ጢንዝዛ፤ በዚያው በግንዱ ውስጥ ማር የሚሠራ፤ ወይም የጢንዝዛ ወገን ሌላ ጥቍር ደረቅ ራሳም ሸካራ።
ገንጰለ ፡-(ተቀ ግ) ለወጠ ገለበጠ፤ ገለባበጠ ፡-(ገነበለ፤ አገነበለ፤ ገንባሌ ለበሰ)። እንዘ ይገነጵሉ ጽድቀ ውስተ ዘኢመፍትው። ፈድፋደ ይዔምፁ በዝንቱ ገንጲሎሙ ጽድቀ በሐሰቶሙ። ወገንጰለ መናብርቲሆሙ ፡-(ቄር ፡-ጳላ። ገድ ፡-ተክ)።
ገንጳሊ መገንጵል ፡-የሚለውጥ የሚገለብጥ፤ ለዋጭ ገልባጭ።
ገንፈለ ፡-(ገለፈ) አቦካ ለወሰ፤ ጡብ ሠራ ተኰሰ። ወይገነፍሉ ፡-(ታሪ ፡-አኵ)። በቁሙ፤ ገነፈለ ወደ ላይ አለ ፈላ ፈሰሰ፤ የወጥ የመጠጥ ፡-(ዐማርኛ)።
ገንፎ ፡-(ዐማርኛ) በቁሙ፤ ገዐት በውሃ የበሰለ ዱቄት፤ የጕንፋን መድኀኒት። ፡-(ተረት) ለጕንፋን ምሱ ገንፎ በትኩሱ።
ገአረ ፡-ጋረ ጣረ ጮኸ፤–ግዒር ገዐረ።
ገዐር ገዓር ፡-ገዓር፤ ጩኸት ጭንቅ፤ ጣር ጋር፤ መራራ ቃል፤ የሐዘን የደዌ የመከራ ስሜት። ገዓረ ምስኪናን። ብካየ ገዓሮሙ። ገዓሮሙ ለሙቁሓን፤ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዐርየ ፡-(ኢዮ፴፬ ፡-፳፰። ኤር፫ ፡-፳፩። መዝ ፡-፸፰ ፡-፻፩)።
ገአት ፡-ገንፎ፤–ግዒት ገዐተ።
ገዐት ፡-ገንፎ መንካኮ፤ አጥሚት እንቀት፤ ያራስ የሕፃን ያሮጌ የበሽተኛ ምግብ። ፡-(ተረት) ብኖር ዓመት ብበላ ገዐት። አስተዳሉ ሎሙ ኅዳጠ ገዐተ እስመ ድዉያን እሙንቱ ፡-(ፊልክ ፡-፸፱)።
ገዐዘ ግዕዘ ፡-ነቀፈ፤ ቈጠረ አጋዘ፤–ግኢዝ ገአዘ፤ ግእዘ ግእዝ።
ገዓሪ ግዑር ፡-(ራን ራት ዕርት) የጋረ የጣረ፤ ጋረኛ ጣረኛ። ግዑራን ፡-(ቄር ፡-ጰላ)።
ገኣዚ ፡-(ዚት ዝያን ያት፤ አዝት) የሚነቅፍ ነቃፊ፤ ወቃሽ ከሳሽ፤ ፈራጅ ፡-(ያዕ፬ ፡-፲፩)።
ገዓዝ ጋዕዝ ፡-ጓዝ፤ መንገደኛ፤ ቤተ ሰብ። ተቃወመከ በፍኖት ወአምተረከ ጋዕዘከ እለ ጻመዉ በድኅሬከ። ተንሥኡ ምስለ ገዓዞሙ ፡-(ዘዳ፳፭ ፡-፲፰። ዘኍ፲ ፡-፲፪።)
ገዊሕ ሖት ፡-(ጎሐ ይገውሕ ይጉሕ። ዕብ ጊያሕ)። መጎሕ፤ ሙውገግ መፍገግ፤ ወገግ ፈገግ ማለት፤ የንጋት ምልክት ማሳየት፤ ሐመድ ያህያ ሆድ መምሰል፤ የሰማይ። ሶበ ይገውሕ። እንዘ ይገውሕ ጽባሕ። ኮከበ ጽባሕ ዘይሠርቅ ሶበ ይገውሕ። ወይገውሕ ሶቤሃ ብርሃንከ ፡-(ኢያ፮ ፡-፲፭።፪ነገ ፡-፲፯ ፡-፳፪። ኢሳ፲፬ ፡-፲፪። ፶፰ ፡-፷)።
ገዊል ሎት ፡-(ገወለ ይገውል ይጉል። ዐረ ጃል ጋል)። ማጠር መቅጠር ዘለሳ መጣል፤ መካብ መክበብ ዙሪያውን መዝጋት፤ የበረት ያታክልት፤ ገዘዘንና ጸቈነን ተመልከት።
ገዊር ሮት ፡-(ጎረ ይገውር ይጉር። ዕብ ጋር) መቅረብ መጠጋት፤ ቅርብ አጠገብ ጥገኛ መኾን፤ በቤት በቦታ። ጕር ጐሬ ማለት ከዚህ ወጥቷል።
ገውሣን ፡-(ዐረ ገውሻን) የሰልፍ ልብስ ጌጥ ሽልማት፤ ድርዕ ጥሩር፤ የመሰለው ኹሉ። ወኮነ ላዕሌሁ ገውሣን ዘወርቅ ዘንኩር ግበሪሁ ፡-(ዮሴፍ)።
ገውዛ ፡-(ዐረ እልጀውዛ) ኮከብ፤ ስመ ኮከብ ካ፲፪ መናዝል አንዱ። ዕጥፍ ጥንድ መንታ ኹለት ማለት ነው፤ መልኩ በሥዕል ሲያዩት ባልና ሚስት ፥ ወንድና ሴት ይመስሳል። ኮከብነቱም የግንቦት ነው፤ ከፀሓይ ጋራ ፴፩ ዕለት ፴ ኬክሮስ ይመግባል ፡-(አቡሻ ፡-፬)።
ገውዝ ፡-(ዕብ ኤጎዝ። ሱር ጋውዛ። ዐረ ጀውዝ) በቁሙ፤ የታወቀ የተክል ዛፍ ስም፤ የፍሬው ዐጥንት ደረቅ ጠንካራ፤ ውስጡ የሚበላ መንታነት ያለው ዘይት የሚኾን፤ ሌላውም የገውዝ ዐይነት ኹሉ። ገውዝ ወለውዝ። እመ ተከልከ ገውዘ ይበቍልኑ ወይን ፡-(ሆሴ፬ ፡-፲፫። መቃ ፡-ገ፭)።
ገዚም ሞት ፡-(ገዘመ ይገዝም ይግዝም። ዕብ ጋዛም። ሱር ግዛም። ዐረ ጀዘመ) መግዘም መቍረጥ፤ መጐንደብ መመንደብ፤ መመልመል መጨፍጨፍ፤ ድል መንሣት ማሸነፍ። ጐደበን እይ የዚህ ጎር ነው። ግዝሙ ዕፀዊሃ። ይገዝም በጕድብ ኵሎ መሠንየ አርዝከ። ገዘማ ከመ ዕፀ ለሕይወትየ ፡-(ኤር፮ ፡-፮። ፳፪ ፡-፯። ኢዮ፲፱ ፡-፲)።
ገዚረት ፡-(ዐረ ጀዚረት) ደሴት የየብስ ቍራጭ፤ ባሕር ያጠረው የከበበው መሬት አገር። አፈ ወርቅ ዘሞተ በስደት በውስተ ገዚረት ፡-(መጽ ፡-ምስ)።
ገዚር ሮት ፡-(ገዘረ ይገዝር ይግዝር። ሱር ግዛር። ዕብ ጋዛር፤ ናማል። ዐረ ጀዘረ፤ ኀተነ) መግዘር መግረዝ፤ የብልትን ሸንኰፍ ቈርጦ፤ መጣል፤ ወይም በጭራሽ መስለብ ፡-(ዘፍ፲፯ ፡-፲ ፡-፲፩ ፡-፳፫። ሉቃ፩ ፡-፶፱። ፪ ፡-፳፩)። ዘገዘረ ወልዶ በእንተ ደዌ። ግዝሩ እከየ ልብክሙ ፡-(ፈ ፡-መ ፡-፴፫ ፡-፭። ኤር፬ ፡-፬። ዘዳ፲ ፡-፲፮)።
ገዚእ ኦት ፡-(ገዝአ ይገዝእ ይግዛእ። ዐረ ጀዘአ፤ ሰጠ ዐደለ) መግዛት መዋጀት፤ መጌትየት፤ ጌታ መኾን፤ በገንዘብ በዜጋ መሠልጠን። መቍረስ መክፈል፤ መስጠት ማደል፤ ማሳለፍ ማገልገል፤ በጌትነት ወይም ባሽከርነት። ማብላት መቀለብ መከባከብ ለማሳደግና ለማሥባት፤ የሕፃን የከብት። መጽሐፍ ግን በገዝአ ፈንታ አመግዝአ ይላል። ይእተ አሚረ ያመገዝእ ሰብእ ዕጐልተ ወክልኤተ አባግዐ ፡-(ኢሳ፯ ፡-፳፩)። ግዕዘን እይ፤ የዚህ ጎር ነው።
ገዚዝ ዞት ፡-(ገዘ፤ ገዘዘ ይገዝዝ ይግዝዝ። ዕብ ጋዛዝ፤ ጊዛህ) መግዝዝ፤ መሸለት መቍረጥ መቈጥቈጥ፤ ማጨድ መጨርገድ የጠጕር የፀምር የሣር የቅጠል። የተቈረጠውን መጀጐል፤ ማጠር መቅጠር መጋረድ መከለል የቡቃያ የተክል፤ ገድገደን ተመልከት። መጽሐፍ ግን በገዘዘ ፈንታ አግዘዘ ይላል፤ አያሰኝም። አግዘዝኩ ሎቱ። በክንፍክሙ ዐውድየ አግዝዙ ፡-(ኢሳ፭ ፡-፪። ስንክ ፡-ኅዳ፳፬)።
(ጥ) ገዚፍ ፡-(ፋን ፋት ዛፍ) የገዘፈ ወፍራም ደጓሳ ደንዳና፤ ጕልሕ ሥጋዊ። ገዚፈ አባል። ለምንት አውሰብከ ብእሲተ ንእስተ ወአንተኒ ብእሲ ገዚፍ ወዐቢይ። ገዚፍ ዐምድ። ልብስ ገዚፍ። አምእስት ገዚፋን። አብትር ዘኀጺን ገዚፋት። ምክር ገዚፍ ፡-(ፈላስ ፡-ገ፶፫። ፹፩። ስንክ ፡-ጳግ፩። ፍ ፡-ነ ፡-፳፫። ፲ ፡-፮። ገድ ፡-ተክ። ማር ፡-ይሥ፳፪ ፡-፩)።
ገዚፍ ፎት ፡-(ገዝፈ ይገዝፍ ይግዘፍ) መግዘፍ መወፈር መደንደን፤ መዳጐስ መሥባት፤ ወፍራም ደንደሳም መኾን። አጽባዕትየ ይገዝፍ ይጸንዕ እምሐቌ አቡየ። ናሁ ገዝፋ አልባቢክሙ ወኮና ከመ አእባን። ከመ ኢይግዝፍ ልቡ ወኢይጽልም አእምሮቱ ፡-(፪ዜና ፡-፲ ፡-፲። ዮሴፍ። ፍ ፡-ነ ፡-፭)።
ገዛሚ ፡-(ሚት ምያን ያት፤ ዘምት) የሚገዝም የሚቈርጥ ቈራጭ።
ገዛሪ ፡-(ሪት ርያን ያት፤ ዘርት) በቁሙ፤ የሚገዝር፤ ገራዥ ባለወግ። ትቤሎ ማርያም ለዮሴፍ አምጽእ ሊተ ገዛሬ ጠቢበ ፡-(ስንክ ፡-ጥር፮)።
ገዛእ ገዛኢ ፡-ገዛእ፤ ገዛኢ፤ ፡-(ኢት እያን ያት፤ እት) የሚገዛ፤ ገዥ ጌታ፤ ሹም ባለቤት። የሚሰጥ የሚናኝ፤ ቀጅ አሳላፊ ዐዳይ፤ የድግስ አገልጋይ። ደቀቀ ገዛእየ። በወይነ ማሕሌት እንተ ይቀድሕ ገዛኢ። ደቀ ጽርሕ ወገዛእት። ቦአት ይእቲ ወክልኤ ገዛእቲሃ። ወገዛእትሰ እለ ቀድሕዎ ፡-(ኢዮ፲፱ ፡-፲፯። ስንክ ፡-ታኅ፳፱። ኢሳ፴፱ ፡-፯። ዳን፩ ፡-፵፮። ዮሐ፪ ፡-፱)።
ገዛዚ መግዝዝ ፡-የሚቈርጥ፤ የሚጀጕል፤ ጀጐል ሠሪ።
ገዝም ፡-(ማት) በቁሙ፤ ቃዳ ተለላ፤ ፈፋ እመም መዛሪያ ትልም፤ በዘርና ባረም ባጨዳ ጊዜ ሠራተኞች ከዳር እስከ ዳር የሚያወጡት ክፍል።
ገዝአ ፡-ገዘገዘ፤–ገዝዐ።
ገዝዐ ፡-(ዕብ ጋዛዕ። ዐረ ጀዘዐ) ከረከረ ገዘገዘ፤ ቈረጠ ገረዘዘ፤ የመጋዝ። አዘዘ መኰንን ይቀንውዎ ወይሥትሩ ሥጋሁ ወይዝሐቁ አምእስቲሁ ወይግዝዕዎ በመጋዝዕ እደዊሁ ወእገሪሁ ፡-(ስንክ ፡-ጥቅ፳፭)።
ገዪም ፤ ሞት ፤ (ጌመ ይገይም ይጊም። ዐረ ዓመ) ፤ መጎም መዳመን ፤ ደመና መልበስ በጉም መታፈን መሸፈን ፤ መጮኽ ማስገምገም ፤ ማስተጋባት ፤ የሰማይና የተራራ። ገመገም ማለት የዚህ ዘር ነው ፤ ጐሀነን እይ።
ገዪሥ ሦት ፡-(ጌሠ ይገይሥ ይጊሥ። ዕብ ጋየስ፤ ሰበሰበ)። ፡-(ጥሰ) መሰብሰብ መከተት፤ መሰለፍ ለጦር ለመንገድ መዘጋጀት፤ ከዚህ በኋላ መዝመት መገሥገሥ፤ ማልዶ መኼድ ከነግህ አስቀድሞ ጎሕ ሲቀድ ወይም ዶሮ ሲጮኽ መነሣት። ገዩሠክሙ በጽባሕ። አሌለያ ገዪሠ። በሌሊት ትገይሥ መንፈስየ ኀቤከ። ነቂሀነ እምንዋም ንጊሣ ለቤተ ክርስቲያን ፡-(ዘፀ፲፱ ፡-፲፮። ሉቃ፳፬ ፡-፩። ኢሳ፳፮ ፡-፱። ድጓ)። ገሥገሠን እይ፤ የዚህ ድርብ ነው።
ገዪድ ዶት ፡-(ጌደ ይገይድ ይጊድ። ዐረ ጀይድ፤ ጃደ፤ በረታ) መፍጠን መሮጥ መፈርጠጥ መበርታት።
ገያሢ ፡-ገያሢ ፡-(ሢት ሥያን ያት) የሚገሠግሥ ገሥጋሽ፤ ማላጅ ማለዳ ኻያጅ። ፡-(ተረት) ገበያ ላርፋጅ፤ ቤተ ክሲያን ለማልጅ።
ገያሪ መገየር ፡-(ርት ራን ራት) አቅራቢ አስጠጊ፤ ይሁዲ አድራጊ። ኖራ አውጭ ሸያጭ፤ ለሳኝ ቀቢ ለቅላቂ። ለመገይራን ወለወቀርት እብን ፡-(፬ነገ ፡-፲፪ ፡-፲፪)።
ገይሮ ሮት ፡-(ገየረ ይጌይር ይገይር። ዕብ ጋየር) በፍቅር በትምርት መሳብ ማቅረብ ማስጠጋት፤ አሕዛብን ከጣዖት ማፍለስ በኦሪት ማሳመን፤ መግዘር ይሁዲ ማድረግ
፡-ኖራ ማውጣት፤ በኖራ ጭቃ መምረግ መለሰን መቅባት መለቅለቅ። ገበሰሰን እይ። እለ ገየርዋ ለአረፍት። ከመ አረፍት እንተ ገየሩ ፡-(ሕዝ፲፫ ፡-፲፭። ኢሳ፲፮ ፡-፲፩)።
ገይብ [1]፡-(ዐረ ጀይብ) ጀብ ኪስ፤ የጀይብን ፍች ተመልከት።
[2]፡-(ዕብ ጋቢያዕ። ዐረ ጣስ) ኮራ ታላቅ ጽዋ ረዥም እግራም፤ እንደ ጐሽ ዋንጫ በስተላይ ሰፊ ለቃቃ፤ በስተታች ጠባብ ሸልቋቋ፤ ውሃ አንጥፈው ያበባ ችቦ የሚያኖሩበት፤ ወይን ቀድተው የሚጠጡበት። ገይበ ብሩር ዘቦቱ ይሰቲ እግዚእየ። ኦ ገይበ ወርቅ ምቅዳሐ ስብሐት ፡-(ዘፍ፵፬ ፡-፭ ፡-፮። አርጋ)። ባለብሉዮች ግን አንኮላ ሽክና ዐቦሬ ሽልም ኵባያ ካቦ ይሉታል።
(ጥይ) ገይድ ፡-(ዳን) ቅጽል። ብርቱ ጮሌ ፈጣን ሯጭ ፈርጣጭ። ፈረስ ገይድ ከመ ዐርክ ኄር። ወገይዳን ከመ እንተ ወይጠል ፡-(ሢራ፴፮ ፡-፮። ፩ዜና ፡-፲፪ ፡-፰)።
ገደላ ፡-(ላት) ውዳቂ ሬሳ ጥንብ፤ ገደል ገብ ፡-(ዘፀ፳፩ ፡-፴፬–፴፮)። ኀበ ሀሎ ገደላ ህየ ይትጋብኡ አንስርት ፡-(ማቴ፳፬ ፡-፳፰። ሉቃ፲፯ ፡-፴፯)።
ገደል ፡-(ዕብ ጋዶል፤ ዐቢይ) በቁሙ፤ ጸድፍ። ፡-(ተረት) ዛፍና ወፍ፤ ገደልና አፋፍ። በሬ ሆይ በሬ ሆይ ፥ ሣሩን አየኽና ገደሉን ሳታይ።
ገዲል ሎት ፡-(ገደለ ይገድል ይግድል፤ ቀተለ። ዕብ ጋዳል፤ ዐብየ) መግደል ማቍሰል፤ ማረድ መቅተል፤ ማነቅ ገደል መጣል። ፈነወ ሐጾ ወነደፎ ለዔሳው እኍሁ ወገደሎ። ወገደሎ ዳቤላ ጠሊ ፡-(ኩፉ ፡-፴፰። ዳን፰ ፡-፯)። በጠብሐ ፈንታ ገደለ ይላል። ወገደለ ንጉሥ እምጥሪተ ዚኣሁ፤ ወመላእክትኒ ገደሉ ለሕዝብ። እገድላ ለዛቲ ዶርሆ ለተዝካረ አቡየ ፡-(፪ዜና ፡-፴፭ ፡-፯። ገድ ፡-ተክ ፡-ታም)።
ገዲም ሞት ፡-(ገደመ ይገድም ይግድም። ዕብ ጋዳም፤ ገዘመ) መጋደም፤ መተኛት። ፡-(ጥደ) መገደም መደበር መከለል፤ ዳሩ እሳት ማኽሉ ገነት ይኹን ማለት። መነየነ ተመልከት፤ የዚህ ጎር ነው።
ገዲው ዎት ፡-(ገደወ ይገዱ ይግዱ) መስጦት ማቅረብ ማስረከብ። መጋዳት መከልከል።
ገዲድ ዶት ፡-(ገደ፤ ገደደ ይገድድ ይግድድ። ዕብ ጋዳድ። ዐረ ጀደ) ፡-(ጥገ) መገደድ በግድ መያዝ፤ ማስገደድ ግድ ማለት፤ የዳኛ የባለዳ። መወንበድ መሸፈት መጨከን፤ የሰራዊት። መባስ መታደስ፤ ማገርሸት፤ የደዌ የክፋት። መግደድ ማግደድ፤ መወላገድ፤ መጥመም መጣመም፤ የመልክ የጠባይ፤ ኹሉም የክፉ ነው።
ገዲፍ ፎት ፡-(ገደፈ ይገድፍ ይግድፍ። ዐረ ጀደፈ። ዕብ ጋዴፍ፤ ሰደበ አረከሰ) መግደፍ፤ መጣል መተው፤ መርሳት፤ ማጥፋት፤ የጣፊ የተማሪ ለጧሚም ይኾናል፤ ገዳፍ ዘኢያገድፍ እንዲሉ። መወርወር ማሽቀንጠር፤ ጥሎ መኼድ፤ የጕድፍ የሸክም፤ የመሰለው ኹሉ። ገደፈቶ ለሕፃን ታሕተ ዕፅ። ንግድፎ ውስተ ግብ። ይግድፉ ውሉዶሙ ውስተ ፈለግ። ግድፋ ውስተ ምድር። አስተዋፅጽኡ ወገደፉ ውስተ ባሕር ንዋዮሙ ፡-(ዘፍ፳፩ ፡-፲፭። ፴፯ ፡-፳። ኩፋ ፡-፵፯። ዘፀ፬ ፡-፫። ዮና፩ ፡-፭)።
ገዳሊ ፡-(ሊት ልያን ያት) የሚገድል ገዳይ ዐራጅ፤ ገደል ስዳጅ።
ገዳሚ ፡-(ሚት ምያን ያት) የሚጋደም ተጋዳሚ፤ ጋድም። ገዳሚ ደባሪ፤ ገዳም ሠሪ።
ገዳማዊ ፡-የገዳም ሰው በረኸኛ፤ ዐዳኝ መነኵሴ ባሕታዊ።
ገዳም ፡-(ማት። ዕብ ሚቅላጥ) በቁሙ፤ ምኔት ደብር የመነኮሳት ሰፈር፤ ታላቅ ቤተ ክሲያን፤ በደለኛ ሸሽቶ የሚጠጋበት ደውሎ የሚማጠንበት ደብረ ምስካይ ፡-(ኢያ፳ ፡-፩ – ፱)። ዱር ጫካ ወማ በረሓ ምድረ በዳ፤ ከሀገር ከመንደር የራቀ የአራዊት ክፍል። ውስተ ገዳም ዐቢይ።አራዊተ ገዳም። ገዳም ውእቱ ብሔር። ገዳማት ወአድባራት። ቦአ ውስተ ውሳጤ ገዳማተ በድው ፡-(ዮዲ፩ ፡-፭። ዘፍ፪ ፡-፳። ማቴ፲፬ ፡-፲፭። ስንክ ፡-ጥር፳፪። የካ፲፭)።
ገዳፊ ፡-(ፊት ፍያን ያት) በቁሙ፤ የሚገድፍ የሚጥል፤መናኒ። ገዳፍያነ ዓለም ፡-(ፊልክ ፡-፫)።
(ላት) ገድል ፡-በቁሙ፤ ትግል ፈተና፤ ውጊያ ሰልፍ፤ ድልና አክሊል እስኪገኝ ድረስ የሚደክሙት ድካም፤ የሚሠመሩት ሥራ፤ የሚቀበሉት መከራ። ገድለ መዊእ። ገድል ጽኑዕ። ነበረ በዝንቱ ገድል ሠለስተ ዓመተ። እለ ተጋደሉ ሠናየ ገድለ ወሞቱ በእንተ ክርስቶስ። ዕሴተ ገድላቲሆሙ ወድካማቲሆሙ። ለሰማዕታት ገድላቲሆሙ ተጽሕፈ ለነ ንትመሀር ሃይማኖቶሙ። ገድላቲሆሙ ለቅዱሳን ፡-(ጥበ፬ ፡-፪። ፲ ፡-፲፪። ገድ ፡-ተክ። ዲድ ፡-፳፭። ፈ ፡-መ ፡-፩ ፡-፪። መዋሥ። አፈ ፡-ድ፳፰)።
፡-መንፈሳዊ ዜና፤ ወግ ታሪክ፤ የቅዱሳንን መከራና ጸጋ ተጋድሏቸውን የሚናገር መጽሐፍ። ገድለ አዳም ፥ ገድለ አብርሃም ፥ ገድለ ሐዋርያት፤ የመሰለው ኹሉ።
ገድገደ ፡-(ገዲድ ገደ። ገዘ) በቁሙ፤ ገደገደ አቆመ አጸና ተከለ፤ የይሎ የድንኳን።
ገድገድ ፡-ግድግዳ፤ ካብ ቅጥር የድንኳን ካስማ አውታር፤ የሸማ ዐጥር። በዐውደ ገድገደ ቤቱ። በዐጸደ ገድገዱኒ ለደብተራ ፡-(መቃ ፡-ገ፩። ፲፰)። አንገደገደ ተንገደገደ፤ ገድጋዳ ማለት ከዚህ ወጥቷል።
ገግጾ ጾት ፡-(ገገጸ ይጌግጽ ይገግጽ) መገገጽ ተግ ማለት መቆም መገታት፤ ማፈግፈግ ማሸግሸግ ወደ ኋላ ማለት፤ ዐፍሮ ፈርቶ ደንግጦ። ኢይጌግጽ እመዋቲ። ኢይጌግጽ እምገጾሙ። ኢይጌግጽ እምጸብእ ወቀትል። ገገጹ እምንጻሬ ምት። እንዘ ይጌግጹ። ሰላም ለአዕይንቲከ እለ ኢገገጻ እምርእይ ፡-(ኢዮ፴፪ ፡-፴፩። ፴፬ ፡-፲፱። ዮሴፍ። አፈ
፡-ድ፬። ሄርማ። ደራሲ)።
ገጽን ተመልከት የዚህ ዘር ነው።
ገጸወ ፡-(ይጌጹ ይገጹ። ተቀ ግ) ታየ ተገለጠ፤ ጐላ ተረዳ፤ ፊት ለፊት ኾነ ተነጻጸረ። መጽሐፍ ግን በገጸወ ፈንታ ተገጸወ ይላል፤ አያሰኝም። ዛቲ ኀጢአት ትትጌጾ ኀበ ብዙኅ ጾታ ገጻት። እንዘ ይትጌጾ በትእምርተ መስቀል ፡-(ፈ ፡-መ ፡-፭ ፡-፩። መጽ ፡-ምስ)።
ገጽ ፡-(ጻት፤ ገገጸ። ሱር ሐዛእ። ዕብ ሓዛህ፤ ሙል) በቁሙ፤ ፊት ግንባር፤ ዐይንና አፍንጫ አፍ ያሉበት፤ ካንገት በላይ እስከ ራስ ጠጕር ወደ ታችም እስከግር ጥፍር በስተፊት ያለው ክፍል። ፊት ለፊት የሚታይ፤ በፊት አንጻር ያለ ዐይን የሚያርፍበት ሰማዩም ምድሩም ማናቸውም ኹሉ። ይከድኑ ገጾሙ። ሰዐረ ኵሎ አንብዐ እምኵሉ ገጽ። ከደነኒ ኀፍረት ገጽየ። ከመ ኣስሕቶ በገጽየ። ገጸ ሰማያት ተአምሩ። አስተፍሥሕ ገጻ ለምድር ፡-(ኢሳ፮ ፡-፪። ፳፭ ፡-፰። መዝ ፡-፵፫። ዮዲ፲፫ ፡-፲፮። ማቴ፲፮ ፡-፫። ቅዳ)።
፡-ድፍረት፤ ቀረቤታ ሟልነት፤ ግልጥ ገሃድ። ገጽ ብነ ኀበ እግዚ። ከመ ንርክብ ገጸ። ወሀበኒ እግዚ ገጸ ወሞገሰ።ዘእንበል ኀፍረት ትቤሎ በገጽ ፡-(፩ዮሐ ፡-፫ ፡-፳፩። ፪ ፡-፳፰። ጦቢ፩ ፡-፲፫። ምሳ፯ ፡-፲፯)።
፡-አካል ቁመና ቁመት። መድኀኔ ገጽየ። አሐደ ገጸ ነአምኖ ለእግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ። ክልኤቱ ገጻት በበ አካሎሙ ፡-(መዝ ፡-፵፩። ቄር ፡-ጰላ። አፈ ፡-ድ፫)።
፡-ወገን ማእዝን፤ መንገድ፤ ስልት ተራ፤ ምክንያት፤ የመጽሐፍ አንቀጽ ክፍል ምዕራፍ። እምአርባዕቱ ገጹ።አርባዕቱ ገጸ ምድር። ዐርገ እንተ ካልእ ገጽ። ወሖረ እንተ ካልእ ገጽ። ከመ ንንግር በበ ገጹ። በምንትኒ ገጽ ዘኮነ። በብዙኅ ገጸ መካን። ፡-(ሕዝ ፵ ፡-፵፯። አዋል። ዮሐ፲ ፡-፩። ገድ ፡-ተክ። ዕብ፱ ፡-፭። ፈ ፡-መ ፡-፲ ፡-፭። አፈ ፡-ድ፲)። ገጽ በነገር ኹሉ እየተናበበ ሳይናበብም ወድቆ በሚስማማው ይፈታል፤ ደቂቅ አገባብ ነው፤ ገገጸን ተመልከት።
ገፊር ሮት ፡-(ገፈረ ይገፍር ይግፍር) መገፈር መቸፈር፤ ማጋፈር ማጐፈር፤ ገፈራ አጋፋሪ ጐፈሬ ማለት ከዚህ ወጥቷል።
ገፊት ቶት ፡-(ገፈተ ይገፍት ይግፍት) መገፈት፤ ማጋፈት፤ ገፋች አጋፋች ገፈታም መኾን።
ገፊዕ ዖት ፡-(ገፍዐ ይገፍዕ ይግፋዕ። ዐረ ጀፋ፤ ተቈጣ ሰደበ) መግፋት መገፍተር፤ ለመጣል ለማራቅ። ግፍ መሥራት መጭቈን ማጣበቅ ማስጠበብ ማስጨነቅ መበደል መቀማት መንጠቅ መመንጠቅ፤ በኀይል መውሰድ። ገፍዕዎ ለውእቱ ቤት ወኢወድቀ። ለሊሁ ይገፍዕ ወለሊሁ ይትመዐዕ። ግፍዕ ዘገፋዕክሙ። ወእመሂ ቦ ዘገፋዕክዎ እፈድዮ ትርብዕተ። አባ ሙሴ ጸሊም ገፍዓ ለመንግሥት ሰማያት ፡-(ማቴ፯ ፡-፳፭። ሢራ፲፫ ፡-፫። ሔኖ፺፰ ፡-፰። ሉቃ፲፱ ፡-፰። ስንክ ፡-ሠኔ፳፬)። ገፍትዐን ተመልከት ፥ የዚህ ስሯጽ ነው፤ ስሯጹም ት ነው።
ገፊፍ ፎት ፡-(ገፈ ይገፍፍ ይግፍፍ) መግፈፍ መገልፈፍ፤ መጋፈፍ ፡-(ዐማርኛ)። ኹለተኛም ገፍገፈ አንገፍገፈ ብሎ፤ ገፈገፈ አንገፈገፈ ተንገፈገፈ ማለት፤ ከዚህ የወጣ ነው።
ገፋዒ ፡-(ዒት ዕያን ያት፤ ዕት) የሚገፋ፤ ግፍ የሚሠራ፤ ገፊ ግፈኛ፤ በዳይ ቀማኛ። ብእሲ ገፋዒ። አነ ውእቱ ገፋዒ። መኳንንት ገፋዕያን። ኖሎት ገፋዕያነ መርዔቶሙ። ኖሎት ገፋዕተ አባግዖሙ ፡-(ምሳ፳፱ ፡-፳፯። ፩ዜና ፡-፳፩ ፡-፲፯። ጥበ፮ ፡-፲። ቀሌ። ዕር ፡-ኢሳ፫ ፡-፳፬)።
ገፍታዒ ፡-(ዒት ዕያን ያት) የሚጥል የሚገለብጥ ገልባጭ ገላባጭ ገለባባጭ። ገፍታዔ መናብርተ ኀያላን ፡-(መቃ ፡-ገ፲፯)።
ገፍትዐ ፡-ገፈተረ፤ ጣለ አራቀ፤ ገለበጠ፤ ደፋ፤ የውስጡን በላይ የላዩን በታች አደረገ አፈረሰ። ለወጠ ቀየረ፤ ሌላ አደረገ፤ አጠመመ ቈለመመ። ትገፈትዕዎ ለሕዝብ እምግብሩ ፡-(አራቀ)። እገፈትዕ መናብርተ ነገሥት ወእገፈትዕ ሠረገላተ ወመስተጽዕናነ። ገፍትዖሙ ለአድባር እመሠረቶሙ። ገፍታዕኩ ኵሎ ንዋዮ አፍኣ፤ ጣለ ፡-(ሐጌ፪ ፡-፳፪። ኢዮ፳፰ ፡-፱። ነሐ፲፫ ፡-፰)። አንተኑ ዘትገፈትዖሙ ለእስራኤል። ፍትወት ገፍትዐ ልበከ። እለ ትገፈትዕዋ ለርትዕ። ከመ ይገፍትዕ ፍትሐ ምስኪን፤ ለወጠ ፡-(፫ነገ ፡-፲፰ ፡-፲፯። ዳን፩ ፡-፶፮። ሚክ፫ ፡-፱። ኢሳ፴፪ ፡-፯)።
ጉማ [1]፡-ታላቅ ጩኸት፤ ጕህና ተመማ፤ የብዙ ሰው ዜማ። ገብርኤል ዘራማ አዕራጌ ስብሐት በጉማ። ጉማ ቃሎሙ ሐዋዝ ወጥዑም። ይመልእ ኵሎ ቤተ ዕበየ ጉማ ቃሎሙ ፡-(ደራሲ። ሢራ፵፯ ፡-፱። ፶ ፡-፲፰)። በቁሙ፤ የነፍስ ዋጋ፤ ያውም የቀንድ ከብት የገዳይ ወገን ቀንበር ተሸክሞ እግዚኦ እያለ ለሟች ወገን የሚሰጠው ካሳ። ገመገመ ግምጋሚ ማለት ከጉማ የወጣ ቃል ነው፤ ርኅራኄና ለውጥ ያሳያል።
[2]፡-ድምፅ ዜማ፤–የነፍስ ዋጋ፤–ገዪም ጌመ።
ጉማዕ ፡-(ዓት) በቁሙ፤ ጉማ ሙዳ፤ የሥጋ ቍራጭ ታናሽ ክፍል፤ ለብቻው ጉም ያለ።
ጉምጉማ ፡-(ትግ ሐባ) ርኩም፤ አፈ ረዥም ክንፈ ውዥምዥም ድምጡ እንደ ከበሮ የሚተም፤ እንደ ነጋሪት የሚጐሰም፤ እንደ ሰማይ የሚያስገመገም።
ጉር ጎር ፡-(ዕብራ) ያንበሳ ግልገል፤ የዥብ የተኵላ የውሻ ቡችላ የናቱን ጡት አጥብቆ የሚመጥ የሚመጠምጥ።
ጉቡእ እስትጉቡአ ፡-(ኣን ኣት ብእት) የተያዘ የተሰበሰበ፤ ስብስብ ክምቹ። ቅምም ጥርቅም። ጉቡእ በእድ። ኵሉ እስራኤል ምስሌሁ ጉቡኣን። እለ ጉቡኣን ውስተ ኢየሩሳሴም ፡-(ምሳ፲፩ ፡-፬። ፩ዜና ፡-፯ ፡-፰። ፲፪ ፡-፭)። እስትጉቡእ ዝንቱ መጽሐፍ እመጻሕፍት አምላካውያት ወቀኖናት። ወእምዝ አትለወ በዝንቱ ከመ ተግሣጽ እስትጉቡእ። ወዝንቱ ውእቱ ዘእስትጉቡእ። ለኵሉ ፡-(ፍ ፡-ነ ፡-መቅ። አፈ ፡-ድ፴፫። ተ፴፬)። በእስትጉቡእ ፈንታ ምስትጉቡእ ይላል፤ ስሕተት ነው። ምስትጉቡኣት አእላፍ እምነ መላእክት ፡-(አፈ ፡-ድ፴፪)።
ጉባኤ ፡-(እያት) መሰብስብ፤ ፡-(ጥሰ) መሰብሰብ፤ አሰባሰብ፤ ስብሰባ እከባ አንድነት። መስብሰቢያ፤ ፡-(ጥሰ) መሰብስቢያ፤ መሰባሰቢያ መገናኛ ጊዜ ቦታ፤ ገበያ ሸንጎ አደባባይ ገዳም ቤተ ክሲያን የትምርትና የሰርግ የልቅሶ ቤት፤ የመሰለው ኹሉ። ወይም በቁሙ፤ የተሰበሰበው ማኅበር እንግልጋ፤ ገበያተኛ የሰው መንጋ። በጉባኤከ። ጉባኤ ቀኖናት። በመካነ ጉባእያት ዘከመ መራሕበት ወምሥያጣት፤ ቦታ ፡-(ዘፀ፳፫ ፲፮። ፈ ፡-መ ፡-፩ ፡-፪። ፍ ፡-ነ ፡-፵)። ተጋበኡ ላዕሌሆሙ እምሮም ጉባኤ ብዙኅ። ጉባኤ ፀርየ ዝሩ። ጉባኤ ሐራ። ጉባኤ ኤጲስዎጶሳት። ጸሐፈ መጽሐፈ ጉባኤ። ቤተ ክርስቲያን እንተ ላዕለ ኵሉ ጉባኤ ዘሐዋርያት፤ ብዙ ሰው ፡-(ዮሴፍ። ስንነክ ፡-ነሐ፲፪። አርጋ። ቀኖ ፡-ኒቅ። ቅዳ)።
ጉባኤ ቃና ፡-የቅኔ ስም፤ መዠመሪያ ቅኔ ባለ፪ ቤት። የስሙ ንባብና ምስጢር ከወንጌል መጥቷል ፡-(ዮሐ፪ ፡-፲፩)።
ጉንባሕ ፡-(ዐረ ጁንቡሕ፤ ወፍራም ረዥም) ጉ ንባሕ፤ ጉ ጉ እያለ የሚመጮኽ ታላቅ አሞራ፤ ርኩም፤ ወይም የርኩም ዐይነት ሌላ። ዖፈ ጉንባሕ። አበ ጉንባሕ፤ አባ ጉንባሕ፤ የጩኸት ባለቤት ፡-(ፈላስ ፡-ገ፲፯። ዘዳ፲፬ ፡-፲፰)።ትግሮች ግን አባ ጉንባሕ ማለት ጐንባሳ ማለት ነው ይላሉ። አብ አባ ካልተጨመረ ጉንባሕ ብቻ ርኩምነቱን አያሳይም፤ ማእከላይ ስም ነው። ስምነቱም ከገነበና ከነብሐ ከኹለቱ ሥር የወጣ ነው፤ ነብሐን እይ።
ጉጋ ጕጋ ፡-ጕጕት፤ የጕጕት ዐይነት አሞራ። ባለብሉዮች ቍንጫ ይሉታል ፡-(መዝ ፡-፻፩። ዘሌ፲፩ ፡-፲፯። ዘዳ፲፬ ፡-፲፯)። ቆቃሕ በማለት ፈንታ ጉጋ ይላል፤ ስሕተት ነው ፡-(፩ነገ ፡-፳፮ ፡-፳)።
ጕሀን
ጉሃን ፡-ስዋሬ፤ ስውር ድብቅ፤ ስወራ ድበቃ፤ ስርቆሽ። ወሀብዎ በዓላተ በጕሃን ወመሥዋዕተ በምስጢር ፡-(ጥበ፲፬ ፡-፲፭)።
ጕሑቍ ፡-(ቋን ቋት ሕቍት) የጐበጠ ጐባጣ፤ ቀላሳ ተርካሳ።
ጕሒል ሎት ፡-(ጕሕለ አው ጐሐለ ይጕሕል ይጕሐል።ዐረ ጀሐለ። ዕብ ጋሓል፤ ጋለ ጋመ) ማፍረስ መጣስ፤ ማቃጠል መተኰስ፤ የሕግ የቅጥር የቤት። መስረቅ መቀማት፤ መውረር መዝረፍ።
ጕሒቍ ቆት ፡-(ጕሕቈ ይጕሕቍ ይጕሐቍ። ዐረ ጀኃ) መጕበጥ፤ መጐንበስ መጽነን፤ እንደ ደጋን መኾን፤ በደዌ በርግና ፡-(ሉቃ፲፫ ፡-፲፩)። መካን ዘጕሕቈ ወምተ ማሕፀና። ዕቤራይት ዘጕሕቈት እምአብዙኆ ውሉድ ፡-(አፈ ፡-ድ፳፭። መጽ ፡-ምስ)።
ጕሂን ኖት ፡-(ጕህነ አው ጐሀነ ይጕህን ይጕሀን) መሰወር መደበቅ። መጮኽ ማዜም ማጕረምረም። ገንሐንና ገነየን ተመልከት፤ የዚህ ጎር ናቸው። መጓን፤ ማጓን ወደ ላይ ፡-(ዐማርኛ)።
ጕሕላዌ
፡-ጕሕሉት፤ መታለል ማታለል አታላይነት። ሽንገላ ልብለባ፤ ክዳት ተንኰል፤ ሰይጣናዊ ባህል። ልማደ አራዊት ጕሕላዌ። ወገብረ ኢዮአብ ዘንተ ጕሕሉተ።ክዒወ ደመ ሰብእ በጕሕሉት። ወጕሕሉት ቃለ አፉሆሙ። ጕሕሉት ወጽልሑት ፡-(ቅኔ። ፪ነገ ፡-፲፬ ፡-፳። ቀሌ። ኤር፱ ፡-፰። ማር፯ ፡-፳፪)።
ጕሕልው ፡-(ዋን ዋት ሉት) የተታለለ የተሸነገለ፤ ሽንግል ድልል፤ ሌሎች ያታለሉት የሸነገሉት።
ጕሕቈት ፤ መጕበጥ ፤ አጐባበጥ ፤ ጐባጥነት ፤ ጕብጠት።
ጕህና ፡-ጕህና፤ በቁሙ፤ ዐቢይ ዜማ፤ ስልት ያለው ጩኸት ጉማ ተመማ፤ ወፍራም ድምጥ። ዝማሬ ዘበልሳን ወጣዕመ ቃል ዘበጕህና። ወሕንጸቱሂ ይእቲ ዘታቀርበነ ኀበ እግዚ በአእኵቶ ማሕሌቱ ውስቴታ በዘይደምፅ ጕህና ኀቤነ ፡-(አረጋ ፡-ድ፯። ዮሴፍ)።
ጕህን ፡-(ናት) ኅቡእ ነገር፤ ረቂቅ ምስጢር፤ በትምርትና በብቃት የሚገኝ። ጳውሎስ ዘበኵሉ ጠቢብ መጋቤ ጕህናቱ ለክርስቶስ ፡-(ቄር ፡-ጰላ)። ኅቡኣቲሁ ምስጢራቲሁ ማለት ነው፤ አንዳንድ መጽሐፍ ጕህነት ይላል፤ አያሰኝም።
ጕሉሕ ጕልሕ ፡-በቁሙ፤ የጐላ፤ የተገለጠ ግልጥ፤ ፈጽሞ የሚታይ የሚሰማ።
ጕላ አው
ጕሌ ፡-(ብ ጐላል። ዐረ ወዕብ ጉሎት። ጽር ጉላት) አፍላል፤ መንቀል፤ የሸክላ ቅል፤ ጕልላት የመንቀል ዐይነት። ወገብረ ክልኤተ አዕማደ ወመልዕልቴሆሙ ጕላተ ፡-(፪ዜና ፡-፬ ፡-፲፪)። አንዳንድ መጣፍ ጎላት ብሎ በሳብዕ ይጥፋል።
ጕልሓዊ ፡-(ትግ ጕልሓይ። ዕብ ጋሉሕ) ልጩ፤ ንጩ፤ራሱን ጽሕሙን ኀፍረቱን የላጨ የነጨ መላጣ ቡሓ፤ ጐዳ፤ ራሰ በዳ። ፡-(ተረት) የሴት ላጪ፤ የወንድ ነጪ።
ጕልማ
፡-(ዐማርኛ) በቁሙ፤ አባት ለልጁ ፥ ጌታ ላሽከሩ የሚሰጠው መሬት ግዛት። ፡-(ግጥም፤ ተጠማኝ። ወይም ተጋዥ) አይኾንም እንጂ ከኾነማ፤ ከመጋዞ ይሻላል ጕልማ።
ጕልበት ፡-በቁሙ፤ ብርክ ኀይል ብርታት ጥንካሬ። ፡-(ግጥም፤ ፪ ደጃዝማቾች ሲዋጉ ትቢተኛው ድል ስለ ኾነ) አላዋቂ ሰፊ ሱሪ አሳጥሮበት፤ የደጃች እገሌ ጕልበቱ ታየበት።
ጕልት ፡-(ታት) ጕልቻ። በቁሙ ዐዲስ ርስት፤ ሰው በፈቃዱ ለዘመድ ለባዕድ ወይም ለገዳም የሚያወርሰው፤ ገንዘብ ጥሪት፤ ቦታ መሬት። ንሕነ ጐለትነ ጕልተ ለገበዘ አኵስም። ብፅዓታት ወጕልታት ፡-(ክብ ፡-ነገ። ፍ ፡-ነ ፡-፲፰)።
፡-የማይፈልስ ቀለም ገቢር ተገብሮ የሚከት የማይለወጥ። ስሱ ስብዑ፤ ዮም ትማልም አፉሁ እዴሁ፤ የመሰለው ኹሉ።
ጕሎ ፡-ስመ፤ ዕፅ፤ ፍሬው ዘይት የሚኾን ቅባታም፤ ሐኪሞች ለሆድ መፈወሻ ፥ ዐበዞች ለምጣድ ማሠሻ ፋቆች ለቈርበት ማራሻ ለማለስለሻ የሚሹት፤ ዕንጨቱ ግብዝ ውስጠ ክፍት። ፡-(ተረት) የጕሎ ዘንግ፤ የባሪያ ደግ።
ጕመሮ ገመሮ ፡-የቈላ ዕንጨት ፥ ዐረጋም እሾኻም የቀንጠፋ ወንድም፤ ወንዴና ሴቴ ያለው።
ጕማሪ ጐማሪ ፡-በቁሙ፤ የባሕር አውሬ፤ ጕምር ተጐማሪ ፡-(መ ፡-ፈ)።
ጕሥዐት ፡-ማግሣት፤ መናገር፤ አገሣሥ አነጋገር፤ ግሣት ትፋት ቅርሻት፤ ልብ ወለድ ፈጠራ ነገር። ከመ ጕሥዐተ ልቦሙ ይትናገሩ። ጕሥዐተ ኅሊና ሰይጣናዊ። ለፈላስፋ ኢተቶስሐ ልቦሙ በሃይማኖት ወኢበርሁ በብርሃነ ዚኣሃ፤ አላ ይትአመኑ በጕሥዐተ ልቦሙ። ይሜህሩ ፈጠራ ዘእምጕሥዐተ ልቦሙ ፡-(ዕር ፡-ኢሳ፫ ፡-፳፩። ቄር ፡-ገ፫። አፈ ፡-ድ፳፪። መጽ ፡-ምስ)።
ጕርን ፡-(ዕብ ጎሬን። ዐረ ጁርን) ምክያድ፤ ዐውድማ፤ የበሬ የገበሬ ሸንጎ፤ አዝመራ መከር ታጭዶ ተሰብስቦ የሚወቃበት የሚበራይበት፤ ተመሽኖ ፡-(ንሽቶ) የሚመረትበት። ጕርነ ኦርና። ኦርና የሰው ስም ፡-(፩ዜና ፡-፳፩ ፡-፲፭ ፡-፲፰ ፡-፳፩። ፪ዜና ፡-፫ ፡-፩)።
ጕርዑይ ፡-(ያን ያት ዒት) የታነቀ፤ የተሰረነቀ፤ ታንቆ የሞተ።
ጕርዒት ፡-ዕንቂት ዕንቂያ፤ ጕረሮ አያያዝ አስተናንቅ፤ የማነቅና የመቃነቅ ሥራ።
ጕርዔ ፡-(ብ ጐራዒት። ዕብ ጋሮን) ዐንገት ማንቍርት፤ ጕረሮ የሆድ ደጃፍ፤ ውስጠ ክፍት፤ መዋጫ መሰልቀጫ፤ ማግቢያ ማውጫ፤ መጮኺያ፤ የዜማ የንባብ የምግብ ጣዕም የሚታወቅበት። መተረ ጕርዔ። ጥዑም ለጕርዔየ።ጕርዔ ይፈልጦ ለኵሉ ጣዕመ እክል። ጕርዔየ ይነብብ። ኢትክሉ ነቢበ በጕርዔክሙ። ከመ መቃብር ክሡት ጐራዒቶሙ ፡-(ስንክ ፡-ጥቅ፮። መዝ ፡-፻፲፰። ሢራ ፡-፳፮ ፡-፳፬። ኢዮ፮ ፡-፴። ቀሌ። ሮሜ፫ ፡-፲፫)።
ጕርዔያዊ ፡-ጯኺ ቀባጣሪ፤ ሆዳም ኹሉን ውጨው የሚል።
(ጥ) ጊኑይ ፡-ገናዊ፤ ጋኔናም፤ ጋኔን ያደረበት እብድ ፡-(፩ነገ ፡-፳፩ ፡-፲፬)። ገነወን እይ።
ጕኑድ ፡-(ዳን ዳት ንድ) የጐነደ፤ ጕንድ የኾነ የደነደነ። ኦ አብዳን ወጕኑዳነ ልብ ፡-(መጽ ፡-ምስ)።
ጕንደ ማኅፈድ ፡-የግንብ ዐምድ ዐልፎ ዐልፎ የቆመ፤ ወይም ወገቡ መካከሉ ፡-(ሄርማ)።
ጕንደ ማእሰር ፡-እግር ግንድ ፡-(ግብ፲፮ ፡-፳፬)።
ጕንደ ዳዊት ፡-ወገን ዘር የትውልድ ሥር ፡-(አርጋ ፡-፩)።
ጕንዱየ ፡-ቈይቶ ሰንብቶ፤ አዝግሞ ዝግ ብሎ። መጽአ ጕንዱየ፤ ሖረ ጕንዱየ።
ጕንዱይ ፡-(ያን ያት ዲት) የቈየ የዘገየ፤ የሰነበተ የኖረ፤ ዳ ያለ ዳተኛ፤ ዝግተኛ። ጕንዱይ ለነቢብ፤ ጕንዱይ ለመዐት። ጕንዱየ መዐት። ጕንዱያነ ልብ ፡-(ያዕ፩ ፡-፲፱። ነሐ፱ ፡-፲፯። ሉቃ፳፬ ፡-፳፭)። ብዙ እጅግ ዐያሌ። እሕየው ጕንዱየ ዓመተ። እምጕንዱይ ዕለት። በጕንዱይ መዋዕል። እምድኅረ ጕንዱይ መዋዕል ፡-(ኢዮ፳፱ ፡-፲፰። ሮሜ፲፭ ፡-፳፫። ኢሳ፴ ፡-፳፯። ኤር፲፫ ፡-፮)።
ጕንዳን ፡-በቁሙ፤ ዝግተኛ፤ ታናሽ ጥቍር፤ ትንኳሽ ተናካሽ ተቈናጣጭ።
ጕንድ ፡-(ዳት አጕናድ) በቁሙ ግንድ በሥርውና በዐጽቅ መካከል ያለ፤ ሥሩም ሳይቀር፤ ወፍራም ደንዳና፤ የኖረ የቈየ፤ የዘገየ ዕንጨት። ሥርዎ ወጕንዶ። ጕንደ ወይን። ጕንደ ዕፀው። ወለለ አሐቲ ጕንድ በበ ሠላሳ ወአሐዱ እልፍ አዕጹቂሃ። ጕንዳት። አጕናደ በቀልት ፡-(ዮሐ፲፭ ፡-፬። ማቴ፫ ፡-፲። ቀሌ። ሔኖ፹፫ ፡-፬። ስንክ ፡-ሚያ፳፫)።
፡-ሥር መብቀበያ፤ ወገብ አጠገብ፤ ወይና ደጋ። አዘዘ ያውቅዩ ልሳና አምጕንዱ። እምጕንደ ደብር። አሰርዎ ጕንደ ደብር ፡-(ስንክ ፡-መስ፭። ጥቅ፲፰። ዮዲ፯ ፡-፲፪። ፮ ፡-፲፫)።
ጕንዶ ፡-(ዐማርኛ) ታላቅ የማር መስፈሪያ ፲፮ ነጥር የሚይዝ። ጕንዶ ማር እሰጥ እንዲሉ።
ጕንፋ ፡-(ትግሬ) በቁሙ፤ ጕንፋን ገር በሽታ፤ ከክርፋትና ከትንፋገን ከክፋ ሽታ የሚመጣ።
ጕዕ ፡-(ብ ጕዓት ቆዕ) ጓሚያ፤ ቃሪያ እንጭጭ ያልበሰለ። ጓ ድብድብ፤ የጥጥ ያበባ እንቡጥ።
ጕዕቱይ ፡-(ያን ያት ቲት) የተሞኘ የተታለለ፤ ፍጻሜው ከንቱ የኾነ። ኦ ጕዕቱይ ተወለድከ ዕራቀከ ወትቀውም በከሃ ዕራቀከ ፡-(ግንዘ)።
ጕዕትያ ፡-(ጽር ጎዒቲያ) ሟርት ጥንቈላ፤ የጥንቈላ ሥራ፤ ጋኔን መጥራት ምትሀት ማሳየት፤ ማታለል መሸንገል ማሞኘት፤ ከንቱ ነገር። ትግል ትግያ ትንንቅ፤ ጣር ድካም ልፋት፤ የጕልበት ሥራ። በከመ ሰርሐ በሥራያቲሁ ወበብዝኀ ጕዕትያሁ። ስብሐቶሙ ኢኮነ ከመ ስብሐተ ዝንቱ ዓለም በጕዕትያ እለ ይገብሩ ፡-(ቀሌ)። ወእምድኅረ ብዙኅ ጕዕትያ። በሀፍ በጕዕትያ ወጻማ። በፈቃደ እግዚ ተውህበ ኵሉ መንግሥተ ዓለም ለዘርዐ ሴም፤ ወግብርናት ለዘርዐ ካም፤ ወጕዕትያ ለዘርዐ ያፌት ፡-(ፊልክ ፡-፲፬። መቃ ፡-ገ፲፩። ክብ ፡-ነገ፸፫)።
ጕዛ ፡-(ዕብ ጋዝ፤ ጋስ) ነጣቂ ወፍ አሞራ፤ ጭላት የጭላት ዐይነት ፡-(ዘሌ፲፭ ፡-፲፮። ዘዳ፲፬ ፡-፲፯)። በንስር ፈንታ ጕዛ ይላል፤ ስሕተት ነው። ከመ ክንፈ ጕዛ ፡-(ዘፀ፲፱ ፡-፬)።
ጕየት ፡-መሸሽ መኰብለል፤ ሽሽት ኵብለላ ስደት፤ ሩጫ ፍርጠጣ። ይጼዕሉ ጕየቶ እል ኢየአምሩ ትስብእቶ። ነጽር ከመ ጕየተ ሕፃን አጕየዮ ለዲያብሎስ ፡-(ተረ ፡-ቄር፲)።
ጕዩይ ፡-(ያን ያት ይይት) የሸሸ የራቀ፤ የኰበለለ። ተረክቡ ጕዩያነ እምሥርዐተ መላእክት ፡-(አዋል)።
ጕያ [1]፡- ዝኒ ከማሁ፤ ሽሽት ስደት ኵብለላ ፡-(ማቴ፳፬ ፡-፳። ኢሳ፶፪ ፡-፲፪)። ይከውን ዐቢይ ምንዳቤ ወጕያ ወክዕወተ ደም። ዑቁ በሰንበት ኢይኩን ጕያክሙ። ጕያከ እምቤት ልሔም ደብረ ቍስቋም ፡-(ኪዳ። ድጓ። አዋል)።
[2]፡-ጕያ፤ በቁሙ፤ የጭንና የጭን መካከል፤ የሕፃን መሸሻ መደበቂያ። የናት ጕያ እንዲሉ።
ጕዱዕ ፡-(ዓን ዓት ድዕት) የተጐዳ የተነካ ንክ፤ ስባራ ከሻዋ ኰሳሳ።
ጕድለት ፡-በቁሙ፤ መጕደል አጐዳደል፤ ጐደሎነት። በጕድለት ፈንታ ጐደሎ ይላል፤ አያሰኝም። አቡነ ምሉእ ዘአልቦ ጐደሎ ፡-(ገድ ኪሮ)።
ጕድባ ፡-በቁሙ፤ የታረደ የተቈረጠ፤ ዕርድ ምሽግ። ማንኵት ፈፋ፤ ውሃ የበላው መሬት።
ጕድብ ፡-(ባት። ዕብ ጋርዜን፤ ቃርዱም። ዐረ ፋስ) ምግዛም፤ ገዠሞ፤ የብረት መሣሪያ፤ መጥረቢያ ምሣር። ኹለት አፍ ብረት ምሣርና ዶማ፤ የሚቈርጥና የሚቈፍር፤ እጀታው አንድ ምላሱ ጥንድ በኹለት ወገን የሚሠራ ፡-(ዘዳ፲፱ ፡-፭። መሳ፱ ፡-፲፰። ፩ነገ ፡-፲፫ ፡-፳። ኢሳ፲ ፡-፲፭። መዝ ፸፫። ሉቃ፫ ፡-፱። ሕዝ፱ ፡-፪)። ከመ ምሣር ዘይሤጽር ወከመ ጕድብ ዘይሰብር ፡-(ዲድ ፡-፲። አዋል)።
ጕድዐት ፡-መጕዳት መጐዳት አጐዳድ አነካክ፤ ጕዳት ንኪት ስብራት።
ጕድፍ ፡-(ፋት) በቁሙ፤ ጥራጊ ውዳቂ ዝብል ተጠርጎ የሚጣል። ከመ ኵሉ ይኩስትር ቤቶ አው መሬተ አው ጕድፈ ይገር ውስተ መቃብሪሁ። ወኮነ ወግረ ዐቢየ ውእቱ ጕድፍ ፡-(ስንክ ፡-መስ፲፯። መጋ፲)።
ጕጉእ ፡-(ኣን ኣት ጕእት) የጓጓ ጕጉ፤ የቸኰለ ችኵል፤ፈጣን ቀልጣፋ ትጉ። አፍ ጕጉእ። ሰማዕት ጕጉእ። ጕጉእ በከናፍሪሁ። እመ ርኢከ ብእሴ ጕጉአ በቃል ፡-(ምሳ፲ ፡-፲፬። ፲፪ ፡-፲፱። ፲፫ ፡-፫። ፳፱ ፡-፳)።
ጕጕኣ ፡-ችኰላ፤ ጥድፊያ ቅልጠፋ፤ ትጋት ጥረት፤ ድንጋፄ። ፈነዎሙ በብዙኅ ጕጕኣ። ኀለፈ በጕጕኣ። ጕጕኣ ገቢረክሙ። ቃል ወሁከት ወነጐድጓድ ወድልቅልቅ ወጕጕኣ ላዕለ ምድር ፡-(ጥበ፲፱ ፡-፪። መዝ ፡-፸፯። ፪ጴጥ ፡-፩ ፡-፭። አስቴ፩ ፡-፲፪። ሔኖ፴፱ ፡-፪)።
ጕጓኤ ፡-መጓጓት፤ ጕጕት። መቸኰል አቸኳኰል፤ ችኰላ ችኵልነት ፡-(ዮሴፍ)። በጕጓኤ ፈንታ ጕጕአት ይላል፤ አያሰኝም። አምብዝኀ ጕጕአት ፡-(ስንክ ፡-ጥር፲፮)።
ጕጠት ፡-(ታት) (ታት) በቁሙ፤ መቈንጠጫ፤ አጥብቆ አጣብቆ መያዣ፤ እንደ መቀስ ፪ ጣት ያለው። ፍሕም ዘነሥአ በጕጠት። መጠዋ በጕጠተ እሳት እምሥጋሁ ወደሙ ለክርስቶስ። ወደዩ አፍሓመ አሳት ዲበ እደዊሁ ወአኀዝዎ በጕጠት ብዙኀ ጊዜ። ወጕጠታቲሃ ፡-(ኢሳ፮ ፡-፮። ስንክ ፡-ነሐ፲፭። ታኅ፳፬። ዘኍ፬ ፡-፱)።
፡-ሹካ ሜንጦ መኈሥሥ፤ የሥጋ ማውጫ የወጣውን እየወጉ ማንሻ፤ እንደ መንሽ ፫ ፡-፬ ፡-ጣት ያለው። ጕጠት ዘሠላስ ከተማት። ጕጠታተ ሥጋ ፡-(ፊልክ ፡-፭። ፩ዜና ፡-፳፰ ፡-፲፯። ፪ዜና ፡-፬ ፡-፲፩)።
ጕጽፋር ፡-(ራት) ዕከክ ፎከት፤ ደረመን ፈረሳቤት፤ የጥፍር ንኪት።
ጊሜ [1]፡-(ዐረ ዐይም። ሱር፤ ዓይማ) ጉም ብዙ ደመና፤ ከምድር ወርዶ ተራራ ኰረብታ የሚሸፍን፤ ወዠድ ለወዠድ የሚጐተት የቀን ጨለማ። ከመ ጊሜ ከደንክዋ ለምድር። ወረሰየ ላቲ ደመና ልብሳ ወበጊሜ ጠብለላ። ወከደነ ርእሰ ደብር በጊሜ ጠብለላ። ፡-(ሢራ፵፬ ፡-፫። ኢዮ፴፰ ፡-፱። ውዳ ፡-ማር፫)።
፡-ብትነ በረዶ፤ ውርጭ፤ ጠል ካፊያ። በረድ ወጊሜ። ይዘርዎ ለጊሜ ከመ ሐመድ። ከመ ጊሜ ውስተ ፀምር።ወፈውሰ ኵሉ ፍጡነ ጊሜ ፡-(ዳን ፡-፵፱። መዝ ፡-፻፵፯። ዘዳ፴፪ ፡-፪። ሢራ፵፫ ፡-፳፪)።
[2]፡-ጉም፤–ገዪም ጌመ።
ጊሠት ፡-መገሥገሥ፤ አገሣገሥ ገሥጋሽነት ግሥገሣ ማለዳ።
ጊር ፡-(ዕብራ። ዐረ ጀይር) ዐዲስ ትኩስ ኖራ ውሃ ያልነካው እሳቱ ያልጠፋ ያልበረደ።
ጊዛን ፡-የዕቃ ቤት፤–ጋዛ።
ጊዜ [1]፡-(ብ ጊዝያት) በቁሙ፤ የተለየ የተወሰነ ሰዓት ዕለት ወርኅ ዓመት ዘመን ዕድሜ፤ ሰው እስኪሞት እስኪሻር የሚኖርበት፤ የሚያርፍበት የሚሠራበት ሌትና መዓልት፤ ፳፬ ፡-ሰዓት። ፡-(ሙሾ ያጤ ቴ ዘመን ስለ በዛ) እስኪ ቀደም ብለኽ ጥቂት እኽል ቅመስ፤ ሰዉ ያልቅ የለሞይ ያንተ ጊዜ እስኪደርስ። ቦ ጊዜ ለኵሉ። በጊዜ እምጊዝያት። ጊዝያቲሆሙ ለአውራኅ፤ በኵሉ ጊዜ ፡-(መክ፫ ፡-፩–፱። ዮሴፍ። ኩፋ ፡-፳፱)።
[2]፡-ዐቢይና ደቂቅ አገባብ ቅጽል ይኾናል፤ አመና ሶበ ሰዓትና ዕለት በሚገቡበት እየገባ ጊዜነቱን ሳይለቅ ይፈታል። ዐቢይ ሲኾን በኀላፊ፤ ጊዜ ሖረ። ቅጽል ሲኾን በትንቢት፤ ጊዜ ይመጽእ። ደቂቅ ሲኾን በጥሬ፤ ጊዜ ቀትል ጊዜ ሞት እያለ ይገባል፤ አመንና ሶበን ተመልከት።
ጊደር ፡-(ዐማርኛ) በቁሙ ያልሸረፈችና ያልተጠቃች ዕጐልት።
ጊጉይ ፡-(ያን ያት ጊት) የሳተ ስሑት፤ አላዋቂ፤ በደለኛ ኃጥእ። ብእሲ አብድ ወጊጉይ። ጊጉይ ውእቱ። ምስለ ጊጉያን ተኈለቈ ፡-(ሢራ ፲፮ ፡-፳፫። ፲፱ ፡-፪። ቅዳ ፡-ዮሐ)።
ጊጳ ፡-(ጽር ጊፓ። ትግ ጋብ) የጥንብ አሞራ ፡-(ዘሌ፲፩ ፡-፲፬። ዘዳ፲፬። ፲፪)።
ጋ ፡-እን ፡-ሲጨመርበት ፡-(እንጋ ፡-እንጃ) ደቂቅ አገባብ ይኾናል።
ጋህረተ ፡-ተጋ፤–ሀጊር ሀገረ፤ ሀግረተ።
ጋሕር ፡-(ትግ ገሕር። ዕብ ጊሖር፤ ፍጹም ቀይ) ፍሕም ፍም፤ የእሳት ምርት፤ የበሰለ ዕንጨት፤ ብስል በርበሬ የሚመስል።
ጋሕፍ ፡-(ትግ ጋሕፎ) የባሕር ዔሊ፤ ደንጊያ ልብሱ።
ጋሌ ፡-(ጽር ጋሊ። ዕብ ሔሌድ) ፋሮ ፋደት፤ መጠማጥ የዱር ድመት፤ ሸላ ሙጭሙጭላ፤ ዶሮ የሚያድን የሚበላ፤ መሬት የሚፍር የሚቈፍር፤ ታናሽ ክፉ አውሬ። ዐይነቱና ስሙ ብዙ ነው፤ ባለብሉዮች ግን ፪ አፍ ያለው እባብ ይሉታል ፡-(ዘሌ፲፩ ፡-፴)።
ጋልሙት ፡-(ዕብ ጋልሙድ) ዛዛኝ ሴሰኛ አውሬ፤ የድመት የሙጭሙጭላ ዐይነት። በቁሙ፤ ጋለሞታ ባለመሸታ።
(ጥ) ጋማ [1]፡-(ጽርእ ወቅብጥ) ስመ ፊደል ሣልስ ገ። አልፋ ወቤጣ ወጋማ ፡-(ሥር ጳኵ)።
[2]፡-(ዐማርኛ) በቁሙ፤ የፈረስ የበቅሎ ያህያ ጠጕር፤ ያንገት የማዥራት ጭራ። የጋማ ከብት እንዲሉ። ያንበሳ ጐፈር አንፋሮ በራስ የሚታሰር። ጋሜ የሰው ራስ ወጕር፤ ማኽሉ ተላጭቶ በዙሪያው የሚቀር፤ ዐብሮ በቀል ጐፈር።
ጋሜ ፡-የደጋን ዕንጨት ቀጥታ ዘለግታ ያለው ለብለቦ ሲያርቁት እንደ ቅን አሽክር የሚታዘዝ ፡-(ግጥም፤ ሽበታም ወይዘሮ የ፰ ዓመት ልጅ) ራሴ ጥጥ ኹኖ ፈታይ ስለምን ፥ ልቤ ተነደፈ በጋሜ ደጋን።
ጋሜል ፡-(ዕብ ጊሜል) ዝኒ ከማሁ፤ ስመ ፊደል ገ። ፍችው ፍጹም ዐሰብ ዕሴት ፍዳ። ጋሜል ዕስዮ ለገብርከ ፡-(መዝ ፡-፻፲፰ ፡-፲፯)።
ጋስ አው ጋሶ ፡-ዝንጕርጕር፤ ነጭና ጥቍር ጕሬዝማ፤ የበዳ አህያ ዐይነት ሽልምልም፤ ወይም ቧሔ ቡሕማ። ጋስ ወጸዐዳ፤ ወይወልዳ ኵሎን አባግዕ ጋሶ ወኵሎ ዘቦ ትእምርት ወኰስኵስ ፡-(ኩፋ ፡-፳፰)።
ጋርሣ ፡-(ገዐት፤ ገርህ) የላመ የጣመ ምግብ፤ ገንፎ መንካኮ፤ ወይም ወፍራም ትኩስ ለስላሳ ዳቦ። ባለመጣፎች ግን አንባዘ ዓሣ ይሉታል። ውስተ መካነ አኀው ድዉያን አልቦ ዘይበልዕ ጋርሣ ወኢዘይሰቲ ወይነ ዘእንበለ ዘይደዊ። አው ጸብኀ አው ጋርሣ ፡-(ሥር ፡-ጳኵ። ሃይ ፡-አበ)።
ጋርዜን ፡-(ዕብ) መግረዣ መቍረጫ የብረት መሣሪያ፤ ምላጭ፤ መጥረቢያ ማጤ፤ ምሣር።
(ጥ) ጋብ ፡-(ዕብራ) ረዥም ቤት፤ ሰገነት የደርብ ደርብ፤ ዕንቍላል ግንብ። ወያንኅሉ ጋቤኪ ፡-(ሕዝ፲፮ ፡-፴፱)።
ጋብኦ ኦት ፡-(ጋብአ ይጋብእ ይጋብእ። ዐረ ጀባእ፤ ተቀበለ። ሱር ግባእ) መሰብሰብ ማከብ፤ ማጋበስ ማግበስበስ ማከማቸት፤ መልቀም ማጠራቀም መክተት። ማጠፍ መኰርተም፤ የሕዋስ። መጽሐፍ ግን በጋብአ ፈንታ አስተጋብአ ይላል፤ በሳተፈና በባረየ ፈንታ አስተሳተፈ አስተባረየ እንዲል። መራዕየከ አስተጋብአ። አስተጋብአ ንዋየ ብዙኀ። ያስተጋበእ ሥርናዮ ውስተ መዝገቡ። ያስተጋብኡ ክነፊሆሙ። ታስተጋብእ እዴከ ፡-(ኩፋ ፡-፴፭።ስንክ ፡-ሠኔ፲፫። ማቴ፫ ፡-፲፪። ሕዝ፩ ፡-፳፬። ምሳ፮ ፡-፲)።
ጋኔናይ ዊ ፡-ዝኒ ከማሁ፤ ዘጋኔን። እንስሳ ጋኔናዊ፤ አው አብድ። የሚወገሽ ተዋጊ ደንባሪ ጋግርታም፤ ወይም አበያ ደደብ ፡-(ፍ ፡-ነ ፡-፴፫ ፡-፫)።
ጋኔን ፡-(ብ አጋንንት። ዐረ ጂን፤ ጃን። ዕብ ሼድ) በቁሙ፤ መንፈስ ርኩስ፤ ዲያብሎስ፤ የዲያብሎስ ጭፍራ፤ ክፉ ጨካኝ ዕቡይ፤ የሚያሳብድ፤ ከባሕር ከገደል የሚሰድ፤ ከምድር የሚፈጭ የሚያንቈጨቍጭ፤ ከእሳት የሚጥል የሚያንከባልል፤ የሚያስፈጥጥና የሚያስገጥጥ፤ የሚያንቅ የሚያስጨንቅ፤ እንደንጨት የሚያደርቅ። ምስጢሩ ትቢትና ጨካኝነት ነው፤ ባለመጣፎች ግን ሩቅ ውዱቅ ጥንብ ሻጋታ ይሉታል ፡-(ማር፱ ፡-፲፯ ፡-፲፰ ፡-፳፪። ፭ ፡-፲፫)። ጋኔን እኩይ። ጋኔነ ቀትር። ጋኔን ርኩስ። በመልአኮሙ ለአጋንንት ያወፅኦሙ ለአጋንንት ፡-(ጦቢ፫ ፡-፰። መዝ ፡-፺። ራእ፲፰ ፡-፪። ማቴ፱ ፡-፴፬)።
ጋን ፡-(ትግሬ) ታላቅ አሞራ ጋን የሚያኽል ጯኺ ልዑለ ቃል ፡-(ራእ፮ ፡-፮። ፰ ፡-፲፫)።
ጋዕት ፡-ጋት ጥርኝ፤ መጋቻ መለኪያ። ፮ቱ ጋት ፩ ክንድ ይኾናል።
ጋእዝ ፡-(ዛት) ጠብ ክርክር ሙግት፤ ንዝንዝ ስድብ ውዝግብ ጭቅጭቅ። ለደም ይቀድሞ ላኳ ወጋእዝ።ጋእዞሙ ስራሕ ለዘይሰምዖ። ነገረ ጋእዝ። ሰይጣን አብአ ፍልጠተ ወጋእዘ ውስተ ቤተ ክርስቲያን። መቲረ ጋእዛት ፡-(ሢራ ፡-፳፪ ፡-፳፬። ፳፯ ፲፭። ፩ጢሞ ፡-፮ ፡-፬። ዲድ ፡-፴፪። ፍ ፡-ነ ፡-፬)። በቁሙ ጋዝ ላንባ ሽታውና ጢሱ እንደ ክፉ ነገር የሚያስቀይም፤ ነፍጥን እይ።
ጋዛ [1]፡-ጊዛን፤ ፡-(ጽር ጋዛ ጋዚስ። ዕብ ኦጻር። ዐረ ኀዛኢን) የቃ ቤት ግምጃ ቤት ጐተራ የብዕል የገንዝብ መክተቻ ማድለቢያ መሰብሰቢያ፤ ቤተ መዛግብት። ቤት ዘጋዛ። እምቤተ መንግሥትየ ዘጋዛ። ለኵሉ ጋዛ። ንዋየ ቤተ ጊዛን ፡-(ዕዝ፭ ፡-፲፯። ፯ ፡-፳ ፡-፳፩። ኢሳ፴፱ ፡-፪)።
[2]፡-ጋዛ፤ ፡-(ጽር ጋዛ። ዕብ ዐዛ) ስመ ሀገር የይሁዳ ክፍል፤ ካምስቱ አህጉረ ኢሎፍሊ አንዲቱ የፍልስጥዔም ደቡብ፤ እንደ ዘጌ እንደ ቈራጣ በባሕር ጠረፍ ያለች ፡-(ኢያ፲፭ ፡-፵፯። ግብ፰ ፡-፳፮)።
ጋይሥ ፡-(ብ አጋይሥ) ዝኒ ከማሁ፤ እንግዳ መንገደኛ፤ ዐድሮ ኻያጅ ገሥጋሽ ፡-(ትግሬ)።
ጋይሶ ፡-(ጽርእ። ዕብ ኪዶን) ጦር ዘገር የሚወረወር፤ ዐጭር መጠነኛ። ባለብሉዮች ግን ላማርኛ ስለ ቀረበ ጋሻ ይሉታል። አልዕል እዴከ በጋይሶ ፡-(ኢያ፰ ፡-፲፰)። ቢዶንን እይ።
ጋይጽ ጌጽ ፡-ጌጥ ሽልማት፤ ልብስ መሣሪያ።
ጋይጾ ጾት ፡-(ጋየጸ ይጋይጽ። ግእዘ) መንቀፍ መስደብ መገደር፤ መናቅ ማጥቃት፤ ማስጨንቅ ማስቸገር። ማጌጥ መጌጥ፤ መልበስ መሸለም፤ መፀረር ማማር፤ ከዚህ የተነሣ መኵራት መታበይ። መጽሐፍ ግን በጋየጸ ፈንታ ተጋየጸ ይላል፤ አያሰኝም። እጸልእ ጸላኢከ ወእትጋየጽ ዘይትጋየጸከ። ይትጋየጾ ጎረ ቤቱ ፡-(ዘፀ፳፫ ፡-፳፪። ኢዮ፳ ፡-፳፮)። አይቴ ሀለዉ እለ ይትጋየጹ በሥን ወበላሕይ። ኢርቱዕ ንትዐበይ ወንትጋየጽ በምንትኒ እምግብር ፡-(ግንዘ። አፈ ፡-ተ፪)።
ጋዳ [1]፡-ጋድ፤–በቁሙ፤–ገዲው ገደወ።
[2]፡-ጋዳ፤ ፡-(ዳት) እጅ መንሻ በረከት መተያያ በፈቃድ የሚሰጥ። ነገሥተ ሳባ ወዐረብ ጋዳ ያመጽኡ። ጸባሕት ወጋዳ። አስትዓ ወጋዳ። የሀበነ ሰላመ ጋዳ ፡-(መዝ ፡-፸፩። ማቴ፲፯ ፡-፳፭። ሔኖ፶፫ ፡-፩። ድጓ)።
ጋድ ፡-ጋድ፤ የሰው ስም፤ ገድ ብዕል በረከት ማለት ነው ፡-(ዘፍ፴ ፡-፲፩)።
ጋግ ጋጋ ፡-(ብ፤ ጋጋት። ዕብ ጋግ፤ ጠፈር መዋቅር ባጥ) መንቈር ቀንበር ዛንጅር፤ የቅጣትና ያገዛዝ መሣሪያ ፡-(ዘዳ፳፰ ፡-፵፰። ፫ነገ ፡-፲፪ ፡-፬ ፡-፱ ፡-፲። ሢራ፮ ፡-፳፬ ፳፱። ዕን፪ ፡-፮)። ግድፊ ጋጋ እምክሣድኪ። አንትሙ እሱራን በሰናስል ወበጋጋ ወበመዋቅሕት። ያከብዱ ለነ ጋጋተ ውስተ ክሣውዲነ ዘኢንክል ጸዊሮቶ። ወደዩ አርባዕተ ጋጋተ አሐደ ውስተ ክሣዱ ወአሐደ ውስተ ገቦሁ ወአሐደ ውስተ ሐቌሁ ወአሐደ ውስተ አብራኪሁ(ኢሳ፶፪ ፣ ፪። ዮሴፍ። ቀሌ። ስንክ ፡-የካ፲፫)።
፡-ያንገት ጌጥ ሽልማት፤ ልሻን ማርዳ ድሪ። ጋጋ ዘወርቅ ፡-(ስንክ ፡-ጥር፲፮)።
ጌ ፡-(ጽር ጊ) ምድር ሀገር፤ ርስት። ባለጌ ሐፄጌ እተጌ እንዲሉ። ሐፀየን እይ።
ጌልጌል ጌልጌላ ፡-(ዕብ ጋልጌል ጋልጋል) ዝኒ ከማሁ፤ መንኰራኵሮች የሠረገላ እግሮች ተሽከርካሮች ተንከባላዮች ፡-(ሕዝ፲ ፡-፪ ፡-፲፫)። ባለቅኔዎች ግን ሰማይ ይሉታል። ደመና ሰማይ ብርህት እንተ ይብልዋ ጌልጌላ ፡-(ደራሲ)።
ጌሰ ፡-ገሠገሠ፤–ገዪሥ ጌሠ።
ጌሠም ፡-(ዕብ ጌሸም፤ ብርቱ ዝናም) ነገ፤ ጧት ማለዳ፤ ከርሞ ላመት። እስከ ጌሠም። ጌሠመ ዘ ጊዜ። ጌሠመ ንመውት። አነ ዮም ወአንት ጌሠም። ኢትተክዙ ለጌሠም እስመ ጌሠምሰ ትኄሊ ለርእሳ ፡-(፩ነገ ፡-፳ ፡-፲፩። ዘፀ፱ ፡-፲፰። ሢራ፲ ፡-፲። ፴፰ ፡-፳፪። ማቴ፮ ፡-፴፬)። ጌሠም እንደ ዮምና እንደ ትማልም ጕልት ነው ፥ አይፈልስም፤ መጽሐፍ ግን ጌሠመ ይላል ፥ አያሰኝም።
ጌሰም ፡-ነገ ነገታ፤–ገይሥ ጌሠ፤ ጌሠም።
ጌሴራሴም ፡-(ዕብ ጌእ ሐራሽም) ያናጦችና የጠራቦች የጠቢቦች ቦታ፤ በተራሮች ማኽል ያለ ቈላ፤ ሸለቆ ወንዛወንዝ ፡-(፩ዜና ፡-፬ ፡-፲፬)።
ጌራ [1]፡-(ብ ጌራት) ቍርዕ ቍር፤ ቦርቦርቲ የራስ ጋሻ ከወፍራም ቈርበት የሚሠራ ላዩ ብረት ውስጡ ቈርበት በጦርነት ጊዜ የሚለበስ ፡-(፩ተስ ፡-፭ ፡-፰። ኤፌ፮ ፡-፲፯።ራእ፱ ፡-፱ ፡-፲፯)። ጌራ መድኀኒት። ጌራተ ኀጺን ፡-(ኢሳ፶፱ ፡-፲፯። ስንክ ፡-ሐም፲፭)። የራስ ጌጥ ሽልማት ራስ ወርቅ፤ ሜትራ ዘውድ አክሊል ኵፌት ቆብ ባርኔጣ፤ የመሰለው ኹሉ። ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ። ተቀጸለ ጌራ ዐቢየ ዲበ ርእሱ አሕጺጾ ጌራ ክህነት ቅዱስ። ወገብሩ ዲበ ርእሱ ጌራ ንጉሥ ወውስተ እዴሁ በትረ ወርቅ። ወያአትቱ ጌራቲሆሙ እምርእሶሙ ፡-(ደራሲ። ዮሴፍ። ሕዝ፳፮ ፡-፲፮)።
[2]፡-(ዕብ ጌራህ) የገንዘብ ስም፤ ታናሽ ግርሽ የሰቅል ኻያኛ፤ የአቦሊ እኩያ። ወሰቅል ዕሥራ ጌራ ፡-(ሕዝ፵፭ ፡-፲፪)።
[3]፡-ራስ ቍር፤–ገየረ።
ጌርዮስ ፡-(ጽር ኪርዮስ) እግዚእ፤ እግዚአብሔር ፡-(ቅዳ)።
ጌርጌል ፡-መንኰራኵር፤–ጌልጌል።
ጌባል ፡-(ጽርእ። ዕብ ዔባል) የተራራ ስም፤ የገሪዛን ወንድም ቅርብ አጠገብ፤ የርግማን ቃሎች የሚነገሩበት ከገሪዛን በስተሰሜን ያለ ፀጋማይ ተራራ። ኹለቱም በኤፍሬም ዕፃ ውስጥ ናቸው ፡-(ዘዳ፲፩ ፡-፳፱። ፳፯ ፡-፲፫)።
ጌተ ፡-(ይገይት ይጊት፤ ገዪት። ገዝአ)። ጌተየ፤ ጌታ ኾነ ተባለ።
ጌቴሴማን ፡-(334) ፡-(ጽር፤ ጌትሲማኒ። ዕብ ጋት ሽማኔይ) የቦታ ስም፤ የደብረ ዘይት እግር፤ የዐጸደ ሐምል ቅርብ አጠገብ። ግበ ዘይት፤ ምክያደ ዘይት ማለት ነው ፡-(ማቴ፳፮ ፡-፴፮)።
ጌት ፡-ስመ ሀገር፤ የኢሎፍሊ ክፍል። ፈለሰት ታቦተ አግዚአብሔር ውስተ ጌት ፡-(፩ነገ ፡-፭ ፡-፰)። ሴት ጌትያዊ ፡-(፪ነገ ፲፰ ፡-፪)።
ጌና [1]፡-ገና ልደት፤–ገኒን ገነ።
[2]፡-(ጽር) ገና የልደት ዋዜማ፤ ድራር። ገሃድ ወይም ልደት፤ በዓለ ልደት። የሴቶች ገና፤ የወንዶች ገና እንዲሉ። እንተ በኵሉ ክብርት ጌና ዘይእቲ ልደቱ በሥጋ ፡-(ተረ ፡-ቄር፳፭። ስንክ ፡-ታኅ፳፰ ፡-፳፱)። ጌነሆይ ማለት ከዚህ ወጥቷል፤ ይኸውም ሊታወቅ ጽርኡ ብእሲቶ ሲል ጊኒ፤ ከፋም እመ ቤቴ ሲል ጌኒ ይላል።
ጌዴር ፡-(ዕብ ጋዴር) ዐጥር ቅጥር ካብ ግንብ መካበቢያ ፡-(ሕዝ፵፪ ፡-፯)።
ጌዶር ፡-(ጽር ጌዱር። ዕብ ግዱድ) ወራሪ ዘራፊ ፋኖ ወያኔ፤ የሽፍታ ሰራዊት የወንበዴ ጭፍራ። ገዲድን እይ።እዴግኖሙኑ ለእሉ ጌዶር ፡-(፩ነገ ፡-፴ ፡-፰)።
ጌጋዪ ፡-(ዪት ይያን ያት) የሚስት የሚሳሳት ተሳሳች፤ አጥፊ በዳይ።
(ያት) ጌጋይ ፡-ስሕተት፤ በደል ወንጀል፤ ኀጢአት ክፋት። ዐስበ ጌጋይ። ምንት ጌጋይነ። ኢይመውቱ አበው በጌጋየ ውሉዶሙ። መጽሐፈ ጌጋዩ። በጌጋየ ልቦሙ ፡-(ይሁ ፡-፲፩። ኤር ፡-፲፮። ፬ነገ ፡-፲፬ ፡-፮። ማር ፲፭ ፡-፳፮። ኤር፳፫ ፡-፲፯)።
ጌግዮ ዮት ፡-(ጌገየ ይጌጊ። ጎገወ) መሳት መሳሳት፤ ከመንገድ መውጣት፤ በስሕተት መበደል፤ ኀጢአት መሥራት። የጊ እጌጊ እስመ እንተ ፍኖተ ደብር መጻእኩ። ይጌግዩ ኵሎ ሥርዐተ ዘዓመታት። ጌገዩ በስካር። አበሱ ወጌገዩ ፡-(ራእ ፡-ባሮ። ኩፋ ፡-፮። ሢራ፵፰ ፡-፮)።
ግሑሥ ፡-(ሣን ሣት ሕሥት) የገባ የመጣ። የራቀ ያገለለ፤ የተለየ ልዩ፤ ፍጹም ባሕታዊ ከረኸኛ። ትንሣኤ ዘግሑሥ እምሐሰት። ልደት ቀዳማዊ ዘግሑሥ እምአዝማን። ዐላውያን እለ ርሑቃን ወግሑሣን እምኔከ። ይኩን ግሑሠ እምቤተ ክርስቲያን። ነበረ ግሑሠ በውላጤ ገዳም ፡-(ፍ ፡-ነ ፡-፳፪። ማር ፡-ይሥ፲፫። ዳን፫ ፡-፰። ቀሌ። ስንክ ፡-ሠኔ፳፬)።
ግሁድ ፡-(ዳን ዳት ህድ) የተጋደ፤ የተገለጠ ግልጥ የታየ የጐላ የተረዳ ጕልሕ። ኵሉ ክሡት ቅድሜከ ወግሁድ። ምግባርየ ዘዐመፃ ግሁድ ቅድሜየ። ለኵሉ። ዕዉቅ ወግሁድ ከመ . . .) ወበእንተ ዝ ግህደ ኮነት ከመ ወላዲተ አምላክ ይእቲ ፡-(ሔኖ፱ ፡-፭። ግንዘ። ቄር። ውዳ ፡-ማር፭)።
ግሑፍ ፡-(ፋን ፋት ሕፍት) የተጋፈ የተጠረገ የታፈሠ።
ግሂህ ሆት ፡-(ገህሀ ይግህህ ይግሀህ) መብራት ማብራት መጽደል፤ መምላት መተካከል፤ ምሉእ ፍጹም መሆን፤ መድመቅ፤ ገሃ ብሕካ በረቅ መምሰል፤ የወርኅ።
ግሒሥ ሦት ፡-(ግሕሠ፤ ገሐሠ ይግሕሥ ይግሐሥ። የጌሠ ጎር) መግባት ማረፍ ማደር መጠጋት፤ መምጣት መቅረብ ፡-(ዘፍ፲፰ ፡-፭። ፲፱ ፡-፪ ፡-፫። መሳ፬ ፡-፲፰)። ወይቤሎ ገሐሥ ወንበር ዝየ ንትናገር፤ ወግሕሠ ወነበረ ፡-(ሩት፬ ፡-፩)።
፡-ከቦታ ወደ ቦታ መፍለስ፤ ከመንገድ መውጣት መጐዳኘት፤ ማግለል መራቅ፤ ገለል ፈቀቅ ማለት፤ ለማደር ለመስፈር የመንገደኛ ፡-(መሳ፲፰ ፡-፲፭። ፲፱ ፡-፲፭)። እስመ ጐንደየ ግሒሠ ህየ፤ ወግሕሠ ህየ ይብላዕ እከለ ፡-(፬ነገ ፡-፬ ፡-፰)። ዳግመኛም በግሕሠ ፈንታ ተግሕሠ ይላል፤ አያሰኝም ፡-(ሚል፪ ፡-፰። ዘፍ፴፰ ፡-፲፪። ዘኍ፲፪ ፡-፲፭)። ተገሐሥ እምነ ዐመፃ ወትትገሐሥ እምኔከ ለሊሃ። ተግሕሡ ማያት እምዲበ ገጻ ለምድር ውስተ አሐዱ መካን። ይትገሐሥ መንፈስ ቅዱስ እምብዙኃን ፡-(ሢራ፯ ፡-፪። ኩፋ ፡-፪። ዕር ኢሳ፫ ፡-፳፮)። አንቀጹን ተግሕሠ ካለ ዘንድ ጥሬውን ደግሞ ትግሕሥት ይላል። ትሜንን ትግሕሥቶሙ እምፍኖት ርቱዕ ፡-(አፈ ድ፪ና ፡-፱)። አንዳንድ መጽሐፍ ግን ተግሕሦቶሙ ይላል።
ግሂድ ዶት ፡-(ግህደ አው ገሀደ ይግህድ ይግሀድ። ዐረ፤ ጀሀደ፤ ጀሀረ) ፡-(ጥጋ) መጋድ መገለጥ መታየት፤ ግልጥ ገሃድ መኾን፤ መታወቅ መረዳት። መጽሐፍ ግን በገሀደ ፈንታ ተግህደ ይላል፤ አያሰኝም። ተግህደ ሃይማኖተ ክርስቶስ። ደትገሀድ ተኣምሪከ አሜሃ። ለእመ ጸንዐት ዛቲ ወተግህደት። ዘተግህዱ በወፂእ እምትእዛዛት ፡-(መጽ ፡-ምስ። ስንክ ፡-ሐም፴። ፈ ፡-መ ፡-፪ ፡-፲፩። ፍ ፡-ነ ፡-፲፰)።
ግሒፍ ፎት ፡-(ገሐፈ ይግሕፍ ይግሐፍ። ዐረ ጀሐፈ) መጋፍ መጥረግ፤ ማፈሥ መውስድ፤ ማንሣት ማስገለል። መጋፈፍ ማጋፈፍ፤ አብዝቶ መብላት መጠጣት አለማትረፍ፤ ቢተርፍም በልብስ መታቀፍ፤ በኰፋዳ መክተት መወተፍ። ከመ ጸበል ዘይግሕፎ ነፋስ ፡-(ጥበ፭ ፡-፲፭። መዝ ፡-፩)።
ግሕሠት ፡-መግባት፤ መራቅ አራራቅ ርቀት ሽሽት ስደት። ምማቴ ወግሕሠት ፡-(ምሳ፳ ፡-፴)።
ግሕይ ዮት ፡-(ገሐየ ይግሒ ይግሐይ። ትግ ገሔ) መፍራት መጨነቅ። መማለድ፤ ማለዳ መነሣት። ጎሐን እይ የዚህ ጎር ነው።
ግህደት ፡-መገለጥ አገላለጥ፤ ግልጥነት ገሃድነት። አብኦ በግህደት ውስተ መንግሥተ ሰማያት። አሜሃ ይቀውም ጻድቅ በብዙኅ ግህደት ፡-(ግንዘ። ጥበ፭ ፡-፩)።
ግህድና ፡-ዝኒ ከማሁ፤ ገሃድነት፤ መገለጥ። ረከብነ ንሕነሂ ቦቱ ግህድና ፍኖት ኀበ እግዚ። ብነ ግህድና ውስተ በዊአ ቅዱሳን ፡-(ቄር ፡-ጰላ)።
ግሕፈት ፡-መጥረግ መጠረግ አጠራረግ፤ ጠረጋ።
ግሉል ፡-(ላን ላት ልልት) የተለየ የተገለለ፤ የተንጓለለ የተንጋለለ።
ግሉይ ፡-(ያን ያት ሊት። ዕብ ጋሉይ) የተገለጠ ግልጥ፤ ቍርጥ።
ግሉድ ፡-(ዳን ዳት ልድ) የተገለደ፤ የለበሰ የተደጐሰ። የተነጠፈ የተጌጠ፤ ደጓሳ ወፍራም።
ግሉጽ ፡-(ጻን ጻት ልጽት) የተገለጠ ግልጥ።
ግሉፍ ፡-(ፋን ፋት ልፍት) የተቀረጸ፤ የተጣፈ የተሣለ። ፡-(ግልፍተኛ ቍጡ)። እብነ ባሕርይ ግሉፍ። ግሉፍ ውስተ ጽሌ ልቦሙ። ጽላት ጽሑፍ ወግሉፍ። ወግሉፋን ኪሩቤል ወፀበራት ፡-(ጥበ፲፰ ፡-፳፬። ኤር፲፯ ፡-፩። ስንክ ፡-ነሐ፳። ሕዝ፵፩ ፡-፲፰)።
ግላ [1]፡-ጨለማ፤–ገሊው ገለወ።
[2]፡-መሸፈኛ፤ ጥቍር መጋረጃ፤ ጨለማ። ቀላዔ ግላ። አምሳለ ግላ። ጽልመተ ግላ። እስመ ውእቱ ግላ ነበረ ውስተ ሕግ ብሉይ ፡-(ጥበ ፡-ጠቢ። ስንክ ፡-ሐም፭። አርጋ ፡-፪። ፪ቆሮ ፡-፫ ፡-፲፭ ፡-፲፮)።
ግላል ፡-እንጕላይ ንፋሽ፤ ሐሠር ምራጭ፤ እንግሊላ የኋሊት።
ግላስ ፡-በቁሙ፤ የኮርቻ ልብስ፤ ምንጣፉ ምቹው መቀመጫው ፡-(ዐማርኛ)።
ግላውቃ ፡-ግላውቃ፤ ፡-(ጽር ግላፍካ) ያሞራ ስም፤ ጕጕት፤ የቀን ዕውር የሌት ዐይነ ብር። ባለብሉዮች ግን ጫት አሞራ ይሉታል ፡-(ዘሌ፲፩ ፡-፲፬። ዘዳ፲፬ ፡-፲፭)።
ግልቡብ ፡-ግልቡብ፤ ፡-(ባን ባት ብብት) የተሸፈነ፤ የተከናነበ፤ ሽፍን ሽፍንፍን። ግልቡብ ርእሱ። እንዘ ግልቡባን ገጾሙ። ብእሲ ዘግልቡብ ርእሱ። ንግልቡባት ፡-(፪ነገ ፡-፲፭ ፡-፴። ሔኖ፲፫ ፡-፱። ቆሮ ፡-፲፩ ፡-፬። ዲድ ፡-፫)።
ግልባብ ቤ ፡-ግልባብ፤ ቤ፤ ፡-(ባባት ብያት) መሸፈኛ መጋረጃ፤ ልብስ ክዳን፤ ክንብንብ ሠርመዲ ሻል፤ የሐር የሻሽ መንዲል፤ ጥላ ቀጸላ። ክሥቲ ግልባበኪ። ነሥኡ ግልባብየ። ከሠተ ግልባበ ገጹ። ለብሰት ግልባቤ። ቀራንብት ሥዩማት እማንቱ ህየንተ ምስዋር ወግልባቤ። እምሐሩረ መርቄ ወእምቍረ ኵሉ ምንዳቤ አክናፊክሙ ይኩናነ ግልባቤ። ግልባቡ ፡-(ኢሳ፵፯ ፡-፪። ማሕ፭ ፡-፯። ስንክ ፡-ሠኔ፩። ኩፈ ፡-፵፩። ደራሲ። ስንክ ፡-ኅዳ፲፫። መስ፳፩)።
ግልወት ፡-መሸፈን፤ ፡-(ጥሸ) መሸፈን አሸፈፈን፤ ሽፈና ልበጣ። መሸፈኛ ሽፋን፤ መጋረጃ፤ ልባጥ ሰሌዳ። ግልወታ በወርቅ። አመ ፂዋዌ አወፈየ ኤርምያስ ኵሎ ንዋየ ግበሪሃ ለደብተራ ለሥጠተ ኩኵሕ፤ወተመጢዋ ኮነቶ ከመ ግልወተ ኀጺን ፡-(አዋል። መጽ ፡-ምስ)።
ግልው ፡-(ዋን ዋት ሉት) የተሸፈነ ሽፍን፤ ጕልብ ልጕም ልብጥ።
ግልየት ፡-መግለጥ፤ መገለጥ፤ አገላለጥ ገለጣ ቈረጣ። የመጽሐፍ ገጽ፤ ሉሕ ፊት ለፊት ተገልጦ የሚታየው የሚነበበው። በተለየ ግን ግልየት የሚባል፤ ወንዙን ጥራዙን ማጠፊያውን ወሰን አድርጎ በጥፈትና በዕጥፋት ማኽል ወዲያ ማዶና ወዲህ ማዶ ያለው ባዶ ስፍራ ነው።
ግልያ ፡-ዝኒ ከማሁ ገጽ፤ ግልየት፤ ሢራክ ሰንጠረዥ። ሐሳበ እግርሰ ነዋ ውስተ ግልያሁ፤ ስፍረ ሰዓት ፡-(አዋል)።
ግልፈት ፡-መቅረጽ፤ መቀረጽ አቀራረጽ። ቅርጽ ንጥ ፍልፍል፤ ያበጠ የሰመጠ። ግልፈተ ዐይነ ማኅተም። ወግልፈት ላዕሌሃ። አልባስ እለ አልቦሙ ግልፈት ፡-(ዘፀ፳፰ ፡-፳፩። ፪ዜና ፡-፬ ፡-፭። አፈ ፡-ተ፳፰)።
ግልፎ ፡-(ብ ግልፍ(ፈ) ዋት) ቅርጽ ንጥ፤ የተቀረጸ ጣዖት፤ የሰው ምስል። አርእስተ አዕማድ ዘግልፎ። ኵሉ ግልፎሃ። ወአቅንእዎ በግልፎሆሙ። ግልፍዋተ ኢትግበሩ። ግልፍዋትተ ጣዖት ፡-(፫ነገ ፡-፯ ፡-፳፯። ሚክ፩ ፡-፯። መዝ ፡-፸፯። ኩፋ ፡-። አርጋ ፡-፬)። ግንፋልን እይ።
ግሙስ ፡-(ሳን ሳት ምስት) የተገመሰ የተቈረሰ፤ ግምስ ቍርስ።
ግሙራ ፡-(ደቂቅ አገባብ) ፣ ጭራሽ፤ አካቶ ፈጽሞ፤ ካንዱ ዘንዱ፤ መቼም መች። ለእግዚአብሔርሰ አልቦ ዘርእዮ ግሙራ። ግሙራ ኢያስተርአየ ዘከመ ዝ። ኢትምሐሉ ግሙራ ፡-(ዮሐ፩ ፡-፲፰። ማቴ፱ ፡-፴፫። ፭ ፡-፴፬)። ለ ሲወድቅበት ለዘወትር ለዘላለም ያሰኛል፤ ምስጢሩ ከዚያው ይገባል። ቦኑ ለግሙራ አረምም እንከ። አሐተ መሥዋዕተ ገብረ እንተ ለግሙራ። ከመ ኢይርአይ ለግሙራ። ትረስዐኒ ለግሙራ ፡-(ኢሳ፵፪ ፡-፲፬። ዕብ፲ ፡-፲፬። መዝ ፡-፱። ፲፪)።
ግሙር ፡-(ራን ራት ምርት) የተጨረሰ የተካተተ፤ የተቻለ የተወስነ ውሱን። የጐመራ ጐምር፤ የተጐመረ ጕምር፤ የጋመረ የዳበረ።
ግሙን ፡-(ናን ናት ምንት) የገመነ፤ ያደፈ የረከሰ፤ ርኩስ። ግሙን ቍርባኖሙ ለኃጥኣን። ልሳን ግሙን። ግሙናነ መንፈስ። ኵሉ ፍናዊሆሙ ግሙናን። ምድር ግምንት ፡-(ሢራ፴፩ ፡-፳፪። ፶፩ ፡-፭። ዲድ ፡-፳፩። ቅዳ ፡-ሕር። ኩፋ ፡-፳፪። ፩ዕዝ ፡-፰ ፡-፹)። ሐረርም ዘማይንቱ ግምንት ሲል ግሙና ይላል።
ግሙእ ፡-(ኣን ኣት ምእት) የገማ ግም በሽቃጣ። ፡-(ተረት) ግም ለግም ቢተቃቀፍ አይነቃቀፍ።
ግሙዕ ፡-የተላጨ ልጩ ሽልት፤ ልዝብ ፍሑቅ።
ግሙድ ፡-(ዳን ዳት ምድ) የተቈረጠ ቍርጥ፤ ጕምድ ጐማዳ። ቶማስ ዘአባላቲሁ ግሙድ። ያዕቆብ ግሙድ ፡-(ስንክ ፡-ነሐ፳፬። ኅዳ፳፯)።
ግማስ ፡-(ሳት) ግማሽ እኩሌታ፤ መንፈቅ። ፡-(ተረት) ግማሹን ፣ ተላጭታ ፣ ግማሹን ፡-ተቀብታ። አሐደ ኅብስተ አው ግማሰ ኅብስት ፡-(አዋል)።
ግማኔ ግምነት ፡-ዝኒ ከማሁ። እምኵሉ ግማኔ ኀጢአት። ግማኔ ነፍስ ፡-(ኩፋ ፡-፳። ጥበ፲፬ ፡-፳፮)። ማረር መግመን፤ ማሳረር ማግመን፤ አገማመን፤ ገመና ዐራራነት ጥቍረት፤ ነውረ ኅብስት። ለእመ ቦ ንቅዐት ውስተ ኅብስት አው ግምነት ኢታዕርግዎ ፡-(ቄድር ፡-ገ፹፱)።
ግማን ፡-(ናት) እድፍ ርስሐት፤ ትክቶ፤ ዝሙት ኀጢአት፤ ገመና ነውር የሚያሳፍር። ምድር ርኵስት ይእቲ በግማኖሙ ለአሕዛበ ምድር ፡-(ዕዝ፱ ፡-፲፩)።
ግማዔ ፡-መላጨት ፡-(ጥላ) መላጨት አለጫጭ፤ ቈረጣ ሽለታ።
ግምአት ፡-መግማት፤ አገማም ግማት ክፉ ሽታ።
ግምኤ ፡-ማሰሮ፤–ገምዖ ገምዐ፤ ግምዔ።
ግምዔ ፤ (ዕያት ፤ ገማዕይ ው) ፤
ምንቸት ማሰሮ ዐይነት ጭንቍላ ፤ ታናሽ ሸክላ ፤ ልጩ ራስ ጭንቅላት የምትመስል ፤ የዘይት ዕቃ። (ተረት) ፤ ጋኖች ዐለቁና ምንቸቶች ጋን ኾኑ። ግምዔ ልሕኵት። ግምዔ ቅብዕ። ኵሉ ግምዕያቲሃ ዘቅብዕ። ነሥኣ ቅብዐ በገማዕይሆን (ዘኍ፭ ፡ ፲፯። ዮዲ ፡ ፭። ዘኍ፬ ፡ ፱። ማቴ፳፭ ፡፬)።
ግምደት ግማዴ ፡-መቍረጥ መቈረጥ፤ አቈራረጥ ቈረጣ ዐጨዳ፤ ጐማድነት።
ግምድ ግማድ ፡-(ዳት) ቍራጭ፤ ጐመድ ጕማጅ፤ ጕራጅ ዕራፊ፤ ቅናሽ ሙዳ ጉማ። ፡-(ግጥም) ኢየሩሳሌምን ይመኛል ሰው ኹሉ፤ ግሸን አይዶለም ወይ ግማደ መስቀሉ። ግማድ ዘተርፈ እምዕፅ። ግምደ ደርግሐ ልብስ። በግማደ ልብሱ። ግማደ ሥጋ። ግማዳት ዘኵሉ አባል። ግማዳተ አብድ ፡-(ጥበ፲፫ ፡-፲፫። ማር፪ ፡-፳፩። ፊልክ ፡-፲። ፪፻፵፫። ሕዝ፳፬ ፡-፬። ኢዮ፲፮ ፡-፮። ቅኔ)።
ግሰት ፡-(ጥዳ) መዳሰስ አደሳሰስ፤ ዳሰሳ ዳበሳ።ኢልኩፋን በግሰተ አጻብዕ። በግሰተ ከናፍሪሁ ለዳንኤል ፡-(መጽ ፡-ምስ)።
ግሱስ ፡-(ሳን ሳት ስስት) የተያዘ የተዳሰሰ፤ የተደመሰሰ።
ግሡጽ ፡-(ጻን ጻት ሥጽት) የተገሠጸ፤ የተማረ የተመከረ፤ ምሁር ምኩር፤ የተሠራ የተቀጣ፤ የተገራ ሥሉጥ፤ ሽቍጥቍጥ። ወልድ ግሡጽ ያስተፌሥሕ አበዊሁ፤ ሰብእ ግሡጻን። ግሡጽ በትምህርተ መንፈስ ዐቢይ ወአኮ ሕጹጽ ፡-(ፈላስ። ስንክ ፡-ጥር፰)።
ግሣጼ ፡-መገሠጽ፤ ፡-(ጥገ) መገሠጽ፤ አገሣሠጽ፤ ግሠጻ፤ ተግሣጽ ቍጣ። ነቢየ ምህሮ ወግሣጼ ፡-(ስንክ ፡-ጥቅ፳፩)።
ግስ ፡-ጓዝ እክት፤ ግስንግስ ዕቃ ግሴት፤ የሚያዝና የሚዳሰስ ኹሉ። ሰማይ ከነግሱ ምድር ከነልብሱ እንዲሉ፤ ከነጓዙ ሲሉ። ጋሰሰ አጋስስ ማለት ከዚህ ወጥቷል።
፡-በቁሙ፤ የቋንቋ መጣፍ የዘርና የነባር መድበል፤ መዝገበ ቃል፤ ንባቡ በፊደል ተራ የታከተ የተከተተ። ምስጢሩ ግን ተወራራሽ ቃል ማለት ነው፤ አንዱ አንቀጽ እስከ ሰማንያ፤ ነባሩና ጥሬው እስካሥር መርባቱ በመወራረስ ነውና።
ግስላ ፡-(ዐማርኛ) ያውሪ ስም፤ ቍጡ ብስጩ ግልፍተኛ። ተገሰለብኝ ይገስላል እንዲሉ፤ ተቈጣ ሲሉ።
ግረት [1]፡-መገዛት፤ አገዛዝ፤ ሥጋዊ ሥራ። እስመ ግረትሰ በሥጋ ለኅዳጥ ዘመን ትበቍዕ ፡-(፩ጢሞ ፡-፬ ፡-፰። ገድ ፡-ኪሮ)።
[2]፡-ስመ ዕፅ፤ ግራር የግራር ዐይነት ዛፍ፤ ቀንበር። ዕፀ ፡-7ረት ፡-(ስንክ ፡-ሠኔ፲፯። መጽ ፡-ምስ)።
ግሩም ፡-(ማን ማት ርምት) በቁሙ፤ የተፈራ የሚያስፈራ፤ አስፈሪ፤ ገናና ታላቅ፤ ውብ ድንቅ። እስመ ልዑል ወግሩም እግዚ። ግሩመ ገጽ። ኢኮኑ ግሩማነ ለዘይገብር ሠናየ። ሚ መጠን ግርምት። ወለብሰት አልባሰ ክብራ ወኮነት ግርምተ ፡-(መዝ ፵፮። ዘዳ፳፰ ፡-፶። ሮሜ፲፫ ፡-፫።ቅዳ። አስቴ ፡-፭)።
ግሩር ፡-(ራን ራት ርርት) ዝኒ ከማሁ፤ የተገዛ ተገዥ። ግሩር ታሕተ መከየድ ፡-(አርጋ ፡-፩። ግብ፳፮ ፡-፮)።
ግሪጳ ፡-(ጽር ፡-ግሪፕስ። ዕብ ፔሬስ) ታላቅ አሞራ ግድንግዲ፤ ንጣቂ ግልገል አንሣ፤ ቅልጥም ሰባሪ፤ የሎስ ጐሤ ጆፌ። ጐሤ። ያንሣኽ እንዲሉ። ባለብሉዮች ግን ዘማች አሞራ ይሉታል ፡-(ዘሌ፲፩ ፡-፲፫። ዘዳ፲፬ ፡-፲፫)።
ግራ [1]፡-የንብ እንጀራ ዕጩ ጐመጩ ሰፈፉ ሳይቀር ከነማሩ ከነወለላው። የማር ሰፈፍ የተነጠረ ሠም ልጥልጡ ግግሩ ነጋሪቱ። ነገረን እይ፤ ዘሩና ምንጩ ርሱ ነው። መጽሐፍ ግን ግራ መዓር በማለት ፈንታ መዓረ ግራ ይላል፤ መዓርን እይ ፡-(ኢሳ፷፬ ፡-፪። ዮዲ፲፮ ፡-፲፭። ሱቱ ፡-ዕዝ፲፫ ፡-፭)። እንገር እንጀራ ሙጌራ ማለት ከዚህ የወጣ ነው።
[2]፡-ግራ፤ ፡-(ዕብ ጋሩዕ፤ ሕጽጹ) በቁሙ፤ ፀጋም፤ ሀካይ ድኩም ፡-(ዐማርኛ)።
ግራም ፡-የሚዛን ስም፤ እጅግ ታናሽ ክፍል የኪሎ ሺሕኛ።
ግራብ ፡-(ባት። ዐረ ጅራብ። ትግ ፡-ገራቢት) ቀርብ ቀርበታ፤ ርኮት ራዎት፤ ቈርባብቻ፤ የማር የቅቤ የዘይት ስልቻ፤ ማሰሮ ገንቦ። ለእመ ኀሠሥከ ቅብዐ ዘይት ትረክብ ኀበ ግራባቲሃ ፡-(መጽ ፡-ምስ)።
ግርማ ፡-በቁሙ፤ ማስፈረት አስፈሪነት፤ የመፈረት የመወደድ ሀብት፤ ክብር ባለሟልነት፤ የመልክ ውበት ደም ግባት፤ ደመ ግቡነት። ዘበዝኀ ሠሐቁ የሐጽጽ ግርማሁ። አንበረ ግርማሁ ዲበ ኵሉ አሕዛብ። ብኪ ግርማ ራእይ ዘየዐቢ እምግርማ ሱራፊል። ኢትርአይ ግርማ ርእየቱ ለኤልያብ ፡-(ፈላስ ፡-ገ፳፩። ፩ዜና ፡-፲፬ ፡-፲፯። ውዳ ፡-፩። ፩ነገ ፡-፲፮ ፡-፲፯)።
ግርጣጥ ፡-ታናሽ ሙዚቃ፤ የዘፈን ዕቃ፤ የሙዚቃ ዐይነት። ገንታ ወግርጣጥ ፡-(ሥር ፡-አኵ)።
ግበ ዐይን ፡-ያይን ጕድጓድ ዋሻው ሠርጓዳው ምዕቃሉ፤ ብርንዶው እንደ ፈርጥ የተሰካበት፤ ወይም እንደ ውሃ የመላበት ፡-(ምሳ፳፬ ፡-፶፪። ፶፪። ዘካ፲፬ ፡-፲፪)።
ግቡር ፡-(ራን ራት ብርት) የተሠራ የተደረገ፤ ፍጡር። ግቡር በጽድቅ ወበርትዕ። ኀጺን ግቡር። ማእሰ በግዕ ግቡረ መሓን። ለግቡራንሂ ይቤልዎሙ ኢኮኑ ግቡራነ ወኢተፈጥሩሂ፤ አላ ሀለዉ ዘእንበለ ጥንት ፡-(መዝ ፡-፻፲። ሕዝ፳፯ ፡-፲፱። ዘፀ፴፭ ፡-፯። አፈ ፡-ድ፳፪)።
ግቡእ ፡-(ኣን ኣት ብእት) የገባ፤ የተመለሰ፤ ምልስ ቅልስ።
ግብ ፡-ጕድጓድ ጐሬ፤–ገብቦ ገበበ።
፡-(ብ ግበብ፤ ባት፤ አግባብ። ዕብ ጎብ። ሱር ጉባ።ዐረ ጉብ) መክተቻ መከተቻ፤ ጕድጓድ ዐዘቅት፤ ዋሻ ጐሬ መቃብር የምድር ቤት፤ የመሰለው ኹሉ። ዘከረየ ግበ ለቢጹ ይወድቅ ውስቴቱ። ግበበ ምድር። ይድፍኑ ግበባተ። እለ አብያቲሆሙ ውስተ ግበበ ኰኵሕ። ግበበ አራዊት። እለ ይወርዱ ውስተ ግብ ፡-(ሢራ፳፯ ፡-፳፮። ዕብ፲፩ ፡-፴፰። ዮሴፍ። ኢዮ፴ ፡-፮። ኤር፱ ፡-፲፩። ሕዝ፴፪ ፡-፲፰)። ጕብ፤ ጕቦ ማለት ዐማርኛው ከዚህ ወጥቷል።
ግብሱስ ፡-(ሳን ሳት ስስት) የተመረገ የተለሰነ፤ ምርግ ልስን ቅብ ልቅልቅ። አረፍት ግብስስት። መቃብር ግብሱሳን ፡-(ግብ፳፫ ፡-፫። ማቴ፳፫ ፡-፳፯)።
ግብስስ ፡-(ጽር ጊብሶስ። ዕብ ሲድ) ኖራ በረቅ፤ የደንጊያ ዐመድ ነጭ ደቃቅ። አውዐዩ አዕፅምቲሁ ለንጉሥ ለግብስስ። ዐጥንቱ ዐመድ እስኪኾን ኖራ እስኪመስል ማለት ነው፤ ባለብሉዮች ግን ግብስስ ለሚባል ጣዖት ይሉታል ፡-(ዓሞ፪ ፡-፩)። አምጽኡ ግብስሰ። ከመ ግብስስ ድቁቅ ፡-(ሄርማ ፡-ገ፹፭። ኢሳ፳፯ ፡-፱)
፡-ልስናት ልቅልቃት። የተላጠ የተቀረፈ ምርጊት፤ የፈረሰ የተናደ ቤት።
ግብረት ፡-ማድረግ፤ መደረግ መሠራት መፈጠር፤ አሠራር አደራረግ፤ ሥራ። ከመ ግብረተ ግንፋል። ግብረተ ዕጣን። ግብረተ ፍትሎ። ለኵሉ ግብረቱ ለደብተራ። እምቅድመ ግብረተ ሰማያት። ወሠናይ ግብረቱ። ወግብረቶንሂ ግብረተ እግዚእ ፡-(ዘፀ፳፬ ፡-፲። ፴ ፡-፴፭። ፴፮ ፡-፳፪። ፴፭ ፡-፳፩። ቅዳ ፡-ግሩ። ዮሴፍ። አርጋ ፡-፫)።
ግብር [1]፡-ኵርህ፤ ግድ ግዴታ። በግብር ዘእንበለ ፈቃዱ። በግብር ይከውን ዘነበበ ዮናስ። ግብረ ይመጽእ መንሱት ፡-(ፈ ፡-መ ፡-፭ ፡-፲፪። ጦቢ ፡-፲፱ ፡-፰። ሉቃ፲፯ ፡-፩። ዕብ፱ ፡-፲፮)። እወ አማን በማለት ፈንታ ግብር ይላል፤ አያሰኝም ፡-(ሉቃ፬ ፡-፳፫)።
[2]፡-በቁሙ፤ ጸባሕት አምኃ ድኻ ለመንግሥት የሚሰጠው። ከመ የሀቡ ግብረ። እለ ይቀውሙ ላዕለ ግብር። ርኡሰ ግብር። ይሁብዎ ግብረ በበ ዓመት ፡-(፪ዜና ፡-፰ ፡-፰ ፡-፲። ፲፰። ፳፯ ፡-፭)።
[3]፡-በቁሙ፤ ጸባሕት አምኃ ድኻ ለመንግሥት የሚሰጠው። ከመ የሀቡ ግብረ። እለ ይቀውሙ ላዕለ ግብር። ርኡሰ ግብር። ይሁብዎ ግብረ በበ ዓመት ፡-(፪ዜና ፡-፰ ፡-፰ ፡-፲። ፲፰። ፳፯ ፡-፭)።
ግብርናት ፡-ባርነት ገባርነት፤ ተገዥነት። ግዕዝክሙ እምግብርናእት። ገብር ለእመ ግዕዘ እምግብርናቲሁ። ፄወዎሙ ወወሀቦሙ ለግብርናት ፡-(ዲድ ፡-፴፫። ዮሴፍ።ስንክ ፡-ኅዳ፳፮)።
»ግብተ ፡-ድንገት በድንገት፤ ወዲያው ቶሎ በቅርብ፤ ሳይቈይ ሳይዘገይ። ግብተ መጽኡ። ግብተ በረቀ። ግብተ ሀለዉ። ሐደሰ ግብተ ፡-(ሉቃ፪ ፡-፲፫። ግብ፬ ፡-፫። ዮዲ፬ ፡-፫። ዕብ፲ ፡-፳)።
»ግብታዊ ፡-ድንገተኛ፤ የድንገት በድንገት የኾነ ያልታሰበ። ሞተት በሞት ግብታዊ ፡-(አዋል)።
ግብት ፡-ድንገት፤– ወጊብ ወገበ።
፡-»ግብት፤ ድንገት፤ ግጭት፤ አደጋ፤ አስቀድሞ ሳይታሰብና ሳይታወቅ እንዲያው ደርሶ የሚኾን ነገር፤ እጅግ ታናሽ ጊዜ እንደ ደቂቃና እንደ ሴኮንድ እንደ ቅጽበት ያለ። እመሰ ግብት ት ውእቱ። ኀጢአት ዘግብት ፡-(ዘኍ፴፭ ፡-፳፪። ፈ ፡-መ ፡-፪ ፡-፲፩)። ባዕድ ነግድ በማለት ፈንታ ዐርከ ግብት አምላከ ግብት ይላል፤ ድንገት የተገኘ ማለት ነው፤ ፡-(ሢራ፱ ፡-፲። መዝ ፡-፹)።
ግብን ግብነት ፡-(ዕብ ግቢና። ሱር ግቤንታ። ዐረ ጁብን) ጅብና፤ ርጎ ዐይብ፤ ያይብ ልጥልጥ፤ በሚዛን የሚሼጥ። ከመ ሐሊብ ሐለብከኒ ወአርጋዕከኒ ከመ ግብነት። የሐልቦሙ ለእንስሳ ወይገብር ግብነተ። ግብነት ዘላሕም ፡-(ኢዮ፲ ፡-፲። ስንክ መስ፲፰። ሥር ፡-ጳኵ)።
ግብአት ፡-መግባት መመለስ፤ አገባብ አመላለስ፤ ግቢ ምለሳ፤ መያዝ መስጦት። ግብአተ መንጦላላዕት። ሑረት ወግብአት። ግብአትከ ውስተ ርስትከ። ዜና ግብአቱ ለአግሪጳስ ኀበ ሮሜ። እፈድየከ በግብአትየ። በእንተ ግብአቱ ለክርስቶስ ፡-(ቅዳ። ዘካ፯ ፡-፲፬። ቀሌ። ዮሴፍ። ሉቃ ፲ ፡-፴፭። ማቴ፳፮ ፡-፵፯)።
ግብጦ ፡-ያበባ እኽል መኬ የሚመስል ተርሙስ፤ ግብጣዊ ማለት ነው።
ግብጽ ፡-(ጽር ኤጊብት። ዕብ ሚጽራይም። ዐረ ሚጽር) ግብጥ፤ ስመ ነገድ ስመ ሀገር የካም ዕፃ። መካነ ጻዕር ልሳነ ባሕር፤ የእስያና ያፍሪቃ ወሰን ደንበር ማለት ነው። በግብጽ ፈንታ ቅብጥ ይላል ፍችው አንድ ነው። ብሔረ ግብጽ። ልሳነ ቅብጥ ፡-(መዝ ፡-፻፬። ሃይ ፡-አበ)።
ግተት ፡-ግትቻ ሰባራ፤ የማይረባ፤ ሥራ የማይዝ፤ ዕላቂ ውዳቂ፤ ውራጅ አሮጌ ዕቃ። ወኮነ ከመ ግተት በውስተ አሕዛብ፤ ግተት ዘለምንትሂ ኢይበቍዕ ፡-(ሆሴ፰ ፡-፰። ኤር፳፪ ፡-፳፰)።
ግቱት ፡-ያረጀ ያለቀ፤ የተጠገነ የተናቀ ፡-(ኢያ፱ ፡-፭)።
ግኑዝ ፡-(ዛን ዛት ንዝት) የተገነዘ ግንዝ፤ ስውር ድብቅ ሽፍን። ሶበ ታወፅኦ ለግኑዝ። ከሣቴ ትምህርት ግኑዝ ፡-(ግንዘ። ስንክ ፡-ታኅ፲፰)።
ግኑይ ፡-(ያን ያት ኒት) የተገዛ ትሑት አገልጋይ ፡-(አርጋ)። ,
ግናሓት አግናሕ ፡-ጩኸቶች፤ ቍጣዎች፤ ተግሣጾች ኀይለ ቃሎች። ወይእዜኒ ኀቤከ ነገርየ ዘልዑለ ታሌዕል አግናሒነ ላዕለ ኵሉ ፡-(ተረ ፡-ቄር፰)። መተርጕማን ግን አግናሒ ብለው ጥሬውን በቅጽልነት ይፈቱታል።
ግናሕ ፡-(ዕብ ግኒሓ) ጩኸት ቡታ እሪታ፤ ታላቅ ድምፅ፤ ቍጣ ተግሣጽ፤ ኀይለ ቃል ስድብ፤ ብርቱ ትእዛዝ የኵራትና የቅቢት ቃል፤ የሚገባ የማይገባ። እስመ ውእቱ አኮ ዘይትናገረክሙ በቃለ ግናሕ ከመ መኰንን ወከመ ሊቅ ዐቢይ። ኮኑ ድንዚዛነ እንዘ ይትሜክሑ ወደለዎ ከመ ይትናገሮሙ በቃለ ግናሕ ዘያሐምም። በትዕቢተ ፀር በበግናሕ ፡-(አፈ ፡-ተ፬። ድር፳፩። ቄር ፡-ገ፯)።
ግናይ ፡-(ያት)
[1]፡-አገልግሎት፤ አገዛዝ ምስጋና፤ ቍልምጫ ልመና፤ የመዝሙር ስም ግነዩ ግነዩ የሚል። አይኑ ግናይ ወአይኑ አኰቴት። ግናይ ለክሙ ሥሉስ ቅዱስ። ዘለከ ስብሐት፤ ሰጊድ ወግናይ። ያቅርብ ለእግዚ መሥዋተ ስብሐት ወግናየ ጸሎታት። እምድኅረ አንበቡ ወዘመሩ ግናየ ስብሐት ፡-(ቅዳ ፡-ዮሐ። ደራሲ። ቄድር። ኪዳ። ፪ዜና ፡-፳ ፡-፳፪)።
፡-ረድፍ ተራ፤ የመዘምራን ክፍል ስድሩ ድርድሩ፤ ግራና ቀኝ ኹኖ ግናያትን እየደገመና እያዜመ እያስተዛዘለ የሚኼድ የሚያውድ። ወአቀምኩ ክልኤተ ግናያት ዐበይት እለ የሐውሩ ይምነ፤ ወካልእ ግናያት እለ የሐውሩ ፅግመ፤ ወአነ ድኅሬሆሙ ፡-(ነሐ፲፪ ፡-፴፩ ፡-፴፯)። መዘምራኑን ግናያት ያሰኘ የመዝሙሩ ስም ነው።
[2]፡-(ዕብራ ወትግሬ) ጕድ ድንቅ፤ ጐባጣ ተርካሳ፤ ዐጭር ግጭር ድንክ ኰሳሳ፤ ልምሾ ዐንካሳ፤ ዕውር ጠንባሳ፤ ምኑን ኅሱር ሕሡም ጥፉ፤ መልከ ክፋ። ፡-(ግጥም ትግሪኛ) ሰበይቲ እንግዳ ግናይ ወሊዳ። ጕድ ለክፉም ለበጎም ለብርቅና ለድንቅ ይነገራል፤ እንደ ታምራት ነው። ፡-(ግጥም) የሚጣቅ ዐማኔል ያንተ ጕድ አያልቅም ፥ የፈረስ ገላ እንደ ጨርቅ ስትጠቅም።
ግንባር ፡-በቁሙ፤ ፍጽምን እይ። ገ ከገጽ የመጣ ነው።
ግንባት ፡-(ታት) ገንቦ ዳብሬ ዶጮ ርኮት ራዎት፤ ታናሽ ቀርበታ። ወወሀበታ ለወለታ ትጹር ግንባተ ወይን ፡-(ዮዲ፲ ፡-፭)።
ግንቦት ፡-ስመ ወርኅ፤ ታስዕ እመስከረም፤ ገቦ ክረምት ጎረ ክረምት፤ ገቦንና ጻዴን እይ። በግንብ ዘይቤ ሲፈቱት ግን ወርኀ ሡራሬ ያሰኛል፤ የባቢሎን ግንብ ሳይቀር ፪ቱ መቅደሶች በግንቦት ተመሥርተዋል ፡-(፫ነገ ፡-፮ ፡-፩። ዕዝር፫ ፡-፰–፲፫)። ያገዳን እኽል ገነበበ ማለት ዐማርኛው ከገነበ ሥር የወጣ ነው።
ግንዘት ፡-(ዐረ ጅናዝ፤ ፍታት) መገነዝ ፡-(ጥገ) መገነዝ አገናነዝ ግነዛ፤ ግንዛት። ግንዘት ሥጋኪ በመዋጥሐ ክታን። ገነዞ ለጴጥሮስ ግንዘተ ሠናየ። ያሤኒ ግንዘተ ደናግል ፡-(ደራሲ። ስንክ ፡-ሐም፮ ፡-መስ፲፱)።
፡-የመቃበር ሸማ ክፈን፤ ሣጥን ሰሌን። ሬሳ፤ የሬሳ ምስል አጐበር ዐልጋ። የፍታት መጽሐፍ። ያቅድም ሤጠ ግንዘቱ። ይሑር ቅድመ ዐራተ ግንዘቱ። ነሥአት ግንዘተ ወገነዘት። አሠረ ግንዘቱ ተኀድገ። ግንዘት ዘይትነበብ ላዕለ ሙታን ፡-(ፍ ፡-ነ ፡-፵፪ ፡-፩። ፳፪። ፩ነገ ፡-፲፱ ፡-፲፫። ስንክ ፡-ጥቅ፳፰። ግንዘ ፡-ገ፩)።
ግንጱል ፡-(ላን ላት ጵልት) የተለወጠ፤ ልውጥ ግልብጥ።
ግንጵሊት ፡-ግልብጮ የኋሊት የግርንግሪት። እመ ይረስዎ ግንጵሊተ ይከፍእ ጸጋሁ ለምስጢር፤ መልኩ ፡-(ተረ ፡-ቄር)።
ግንፋል ፡-(ላት) የጡብ ጭቃ የተቦካ የተገነፋ። ጡብ የሸክላ ዐይነት ደንጊያ፤ ከጭቃ ተሠርቶ በፀሓይ ደርቆ በእሳት የሚበስል የሚፈተን፤ ለሕንጻ የሚኾን። ንጥፋሕ ግንፋለ ወናብስሎ በእሳት። በጽቡር ወበግንፋል። ወድቀ ግንፋል። ንሣእ ግንፋለ ወሠዐል ላዕሌሃ ሀገረ ፡-(ዘፍ፲፱ ፡-፫። ዘፀ፩ ፡-፲፬። ኢሳ፱ ፡-፲። ሕዝ፬ ፡-፩)። የጡብ ዱቄት የደቀቀው የተሰለቀው። በቍስሉ ወደዩ ግንፋለ። ደመረ ጼወ ምስለ ግንፋል። ከመ ይቅብዕዎ በጼው ወብሒእ ወግንፋል። ፡-(ስንክ ፡-ግን፮ ፡-፳፮። ሐም፰)።
ግኡዝ ፡-(ዛን ፡-ዛት፤ እዝት) የተጋዘ የጠላ፤ የተነቀፈ ንቁፍ።
ግዑዝ ፡-(ዛን ዛት ዕዝት) የተጓዘ፤ ነጻ የወጣ። ግዑዝ ውስተ ምዉታን። እመኒ ግዕዝት ደብተራ። ይሬስዮሙ ግዑዛነ ፡-(መዝ ፡-፹፯። ዘኍ፩ ፡-፶፩። ፩ነገ ፡-፲፯ ፡-፳፭። ፍ ፡-ነ ፡-፴፩)።
ግዒር ሮት ፡-(ግዕረ፤ ገዐረ ይግዕር ይግዐር። ዐረ ጀዐረ። ዕብ ጋዓር። ሱር ግዓር) መጋር መጮኽ፤ መጨነቅ፤ ማጣር። ገዐርኩ ኀቤከ። ይግዕሩ እመዝራዕት ብዙኃን። የዐወይዉ ወይግዕሩ። ገዐሩ እምግብሮሙ። ገዐረ በዐቢይ ቃል። ግዒሮ ሞተ ፡-(ኢዮ፴ ፡-፲፱። ፴፭ ፡-፱። ኤር፳፱ ፡-፪። ዘፀ፪ ፡-፳፫። ማር፲፭ ፡-፴፬ ፡-፴፯ ፡-፴፱)።
ግዒት ቶት ፡-(ገዐተ ይግዕት ይግዐት። ወግዐ። ጠፍሐ) ማገንፋት፤ መጋት ማጠጣት ማስጐንጨት፤ በጋት በጥርኝ መስፈር መለካት። ኢይግዕቱ ሎሙ ወኢይፌትቱ ሎሙ ኅብስተ። ኢያስትይዎሙ ማለት ነው። ፡-(ኤር፲፮ ፡-፯)።
ግኢዝ ዞት ፡-(ግእዘ፤ አው ገአዘ ይግእዝ ይግአዝ። ሱር ግዓጽ፤ ጋየጸ) ማዘን መቈጣት፤ መበሳጨት። መንቀፍ መጥላት መጣላት፤ መውቀሥ መክሰስ። ገአዝኩ ሕይወትየ። ለምንት እንከ ትግእዝ ፈቃደ እግዚ። ወዳእነ ግእዝናሆሙ። ወግእዘ ጽንዐ ልቦሙ። ምንተ ረከቡ በላዕሌየ በዘይግእዙኒ፤ ሶበ ይግእዘከ ዐርክከ። ግእዞ ሕዝብ ለሙሴ ፡-(ኩፋ ፡-፳፯። ሢራ፵፩ ፡-፬። ሮሜ፫ ፡-፬። ማር፲፮ ፡-፲፬። ኤር፪ ፡-፭። ምሳ፳፭ ፡-፰። ዘፀ፲፯ ፡-፬ ፡-፯)
፡-ማጋዝ ከግዞት ቤት ማግባት፤ ግእዝ መማር እየቈጠሩ ማንበብ።
ግዒዝ ዞት ፡-(ግዕዘ ይግዕዝ ይግዐዝ) መጓዝ፤ ካሉበት መነሣት እግርን መንቀል ጕዞ መዠመር፤ ማዝገም ቀስ እያሉ መኼድ መዝመት። ወግዕፅዙ ደቂቀ እስራኤል እምራምሴ ውስተ ሱኮት። ወይግዕዙ ግብጽ ድኅሬዎሙ። ወግዕዝክሙ ውስተ ገዳም ፡-(ዘፀ፲፪ ፡-፴፯። ፲፬ ፡-፲። ዘዳ፩ ፡-፵)።
፡-መበተን መበታተን፤ መዘራት መሠራጨት። ግዕዙ አሕዛብኪ ውስተ አድባር ወአልቦ ዘያስተጋብእ ፡-(ናሖ፫ ፡-፲፰)።
፡-ሐራ መውጣት፤ መፈታት መለቀቅ፤ ነጻ መኾን። ግዕዝክሙ እምግብርናት። ገብር ለእመ ግዕዘ እምግብርናቲኩ። ይግዐዝ ገብር እምአግዚኡ ፡-(ዲድ ፡-፴፫። ዮሴፍ። ፍ ፡-ነ ፡-፴)። በግዕዘ ፈንታ ተግዕዘ ይላል፤ ስሕተት ነው። ይትገዐዙ ወይፈቅዱ ይፃኡ እምኔከ። ተግዕዝክሙ እምኀጢአት። ግዕዛነ ኢተግዕዘት ፡-(ሢራ፴ ፡-፴፬። ሮሜ፮ ፡-፲፰። ዘሌ፲፱ ፡-፳)።
ግዕት ፡-ግት፤ ወሽ ጡት፤ የእንስሳት።
ግእዘ ፡-ተጓዘ፤ ነጻ ወጣ፤–ግዒዝ ግዕዘ።
ግእዘት ፡-ማጋዝ መጋዝ። መንቀፍ መነቀፍ፤ አነቃቀፍ፤ ነቀፋ ነቀፌታ፤ ወቀሣ፤ ከሰሳ። በእንተ ግእዘት ዘግእዝዎ። እንበለ ተካሕዶ ወግእዘት ፡-(ዘፀ፲፯ ፡-፯። ደራሲ)።
ግዕዘት ፡-መጓዝ አጓጓዝ፤ ጕዞ። ነጻ መውጣት፤ ነጻነት ሐርነት። ግዕዘት እምትፅርርት ኀበ ሰላም ፡-(ፊልክ ፡-፻፭)።
ግዕዛን ፡-ነጻ፤ ነጻነት። እስብክ ግዕዛነ ለፂዉዋን። ወጸጎከነ እምግብርናት ግዕዛነ። በእንተ ግእዛን ወግብርናት። ወኢይዔምፅ ግዕዛኖሙ ፡-(ሉቃ፬ ፡-፲፱። ኪዳ። ፍ ፡-ነ ፡-፴፩። ፊልክ ፡-፻፹፩)።
ግእዝ [1]፡-የቋንቋ ስም፤ ሴማዊ አዳማዊ ቋንቋ የዕብራይስጥ ወንድም፤ ከዐረብ ከሱርስት የሚገጥም። ዘይቤው አልፍ እንደ ማለት አንድ መዠመሪያ፤ ምስጢሩ ጥንታዊ አዳማዊ ልሳን ማለት ነው ፡-(ዘፍ፲፩ ፡-፩)። ፪ኛም እንደ ሌላው ቋንቋ ብዙ ድካም ስለሌለበት ቅን ገር ብለው ይፈቱታል። ተተርጐመ እምልሳነ ቅብጢ ለዐረብ ወ እምዐረቢ ለግእዝ ፡-(ሃይ ፡-አበ ፡-፩)።
[2]፡-የፊደል ስም፤ አንድ ወጣት አንድ ቅንጣት አንድ በቀል፤ ዕዝል ቅጥል ነቍጣ ምክትል፤ ዋየል አጣማጅ ኹለተኛ ፈርጅ የሌለው ቀንጃ ነጠላ ፊደል ፡-(ኮንሶን) ከአ እስከ ፐ ያለ፤ አ በ ገ ደ ሀ ወ ዘ። ከሰላማ በፊት ከካዕብ እስከ ሳብዕ ድረስ ሳይኖረው ርሱው ራሱ ግእዙ ብቻ ነበረና፤ ቋንቋውን ግእዝ ያሰኘው ይህ ነው ይባላል። ከዚያ ወዲህ ግን ከካዕብ እስከ ሳብዕ ላሉት በኵር ግንባር ቀደም ባለ፮ ወንድም ስለ ኾነ አንደኛ ወይም መዠመሪያ ይባላል። አ ግእዝ፤ ቡ ካዕብ፤ ጊ ሣልስ፤ ዳ ራብዕ፤ ሄ ኃምስ፤ ው ሳድስ፤ ዞ ሳብዕ እንዲሉ። ግእዝ አንድ አንደኛ መባሉ በአ ምክንያት ነው።
[3]፡-የንባብ ስም፤ መዠመሪያ ንባብ፤ ሕፃናት የፊደልን ቍጥር እጅ እግሩን ከለዩ በኋላ ከነቍጥ እስከ ነቍጥ እየጐተቱ የሚያግዙት ማጋዝ። ለንባብ ትምርት በየስልቱ ፬ ስም አለው፤ ግእዝ ፥ ወርድ ፥ ዐቢይ ፥ ድጋም።
[4] ፡-የዜማ ስም፤ አንደኛ ስልት መዠመሪያ ዜማ፤ ፪ኛው ዕዝል ፥ ፫ኛው አራራይ ይባላል። ሠለስቱ ዜማ ዘውእቱ ግእዝ ወዕዝል ወአራራይ። ወእምዝ ትብል ጸሎተ ዘእምዳዊት በዜማ ግእዝ። ህየንተ ዕዝል ዘነግህ ግእዝ ፡-(ስንክ ፡-ግን፲፩። ግንዘ። ድጓ)።
ግዕዝ ፡-(ዛት) ኹነታ አኳኻን ጽንዕ ልማድ፤ ሐሳብ ኅሊና ፈቃድ፤ ባሕርይ ጠባይ፤ የባሕርይ ሥራ ዐመል፤ መንገድ ጕዞ አካኼድ አረማመድ የክፉ የበጎ። ሰብአ ዐይን አንትሙ ወመጻእክሙ ትርአዩ ግዕዘ ብሔር። ሰብእ ሠናያነ ግዕዝ። ስምዐ ግዕዝነ። ወልድከ ዘኢየሐውር በገዕዝከ። እምከመ ዐረዩ ግዕዛቲሆሙ። ሰማይ ጥቀ ሠናይት ወብርህት ፈድፋደ በግዕዛ። በግዕዘ ጠባይዕ ወበባሕርይ። ወነያ ይእቲ በዓልተ ጥዒና ሐዳስ፤ ምስለ አራዊት ዘተኀድር ነፍስ፤ እንዘ እምነ ሰብእ ትትገሐሥ፤ እስመ ግዕዘ አርዌ ዐቢይ፤ ወግዕዘ ሰብእ ንኡስ። ዝንቱ ውአቱ ግዕዝኪ እምንእስኪ ፡-(ዘፍ፵፪ ፡-፱።ዮሴፍ። ሢራ፴፭ ፡-፳፪። ፊልክ ፡-፬። አፈ ፡-ተ፲፮። ድር፪። ቅኔ። ኤር፳፪ ፡-፳፩)።
ግዕዝና [1]፡-ዝኒ ከማሁ፤ ነጻነት ፡-(ሄርማ ፡-ገ፶፬)።
ግዘት ፡-በቁሙ ውግዘት፤–ወጊዝ ወገዘ።
[2]፡-»ግዘት፤ ፡-(ታት) ዝኒ ከማሁ፤ መገዘት ፡-(ጥገ) መገዘት አገዛዘት፤ በቁሙ ግዝት ርግማን። ግዘት ዘነበበ ባቲ ዮሐንስ ዘቡርልስ። አንቀጸ ግዘት። ንባበ ግዘት ፡-(ሃይ ፡-አበ። ስንክ ፡-ታኅ፮)።
ግዙም ፡-(ማን ማት ዝምት) የተቈረጠ የተጨፈጨፈ፤ ቍርጥ ምልምል። ዕፀው ግዙማን ፡-(መጽ ፡-ምስ)።
ግዙር ፡-(ራን ራት ዝርት) በቁሙ የተገዘረ ግርዝ፤ ብልተ ጥሩ፤ ይሁዲ ፈላሻ እስላም፤ ቢጽ ሐሳዊ ወንጌል እንበለ ኦሪት ጥምቀት እንበለ ግዝረት፤ አትረባም አትጠቅምም አታጸድቅም የሚል። ግዙር ወቈላፍ። በእንተ ኅጽዋን ወግዙራን ፡-(ሮሜ ፡-፴። ፈ ፡-መ ፡-፴፫። ግብ፲፭ ፡-፩ ፡-፭ ፳፬)።
ግዙእ ፡-(ኣን ኣት ዝእት) ግዙ ግዝ፤ የተገዛ ተገዥ ዜጋ፤ ገብር ገባር።
ግዙፍ ፡-(ፋን ፋት ዝፍት) በቁሙ፤ ዝኒ ከማሁ። ይኩን ልብሶሙ እምፀምር ግዙፍ። ግዙፈ ክሣድ። ግዙፋነ ልብ ፡-(ፍ ፡-ነ ፡-፲ ፡-፮። ዘዳ፱ ፡-፲፫። አርጋ ፡-፯)።
(ጥ) ግዛም ፡-(ማት) ጕማጅ፤ ቍራጭ ጭፍጫፊ፤ ዝንጣፊ።
(ጥ) ግዛዕ ፡-(ዓት። ዕብ ጌዛዕ። ዐረ ጂዝዕ) ጕንደ ዕፅ፤ ከሥር በላይና ከዐጽቅ በታች በመካከል ያለው፤ አዕጹቅን እንደ ዐምድ ኹኖ የሚሸከም። በትግርኛ ግን አንዳች ማለት ነው።
ግዝመት ፡-መግዘም መገዘም አገዛዘም፤ አቈራረጥ፤ ቈረጣ ምልመላ ጭፍጨፋ።
ግዝረት ፡-በቁሙ መግዘር መገዘር፤ አገዛዘር ገዘራ፤ ግዙርነት፤ ግዝራት። ወሀበክሙ ሙሴ ግዝረተ። ወግዝረትሰ ግዝረተ ጽላሌ ልብ በመንፈስ። ወምንትኑ ስላጤሃ ለግዝረት። በእንተ ግዝረት ፡-(ዮሐ፯ ፡-፳፪። ሮሜ፪ ፡-፳፱። ፫ ፡-፩። ፍ ፡-ነ ፡-፶፩)።
ግዝሮ ፡-ግዝረት፤ ግዝራት። ዝ ደመ ግዝሮሁ ለወልድየ። ኢየሐጽጽ ሕማመ ግዝሮሁ ለአረጋይ እምሕማመ ሕርደቶሙ ለንኡሳን ፡-(ዘፀ፬ ፡-፳፭። መጽ ፡-ምስ)። ግዝረት የሚገባ ለወንድም ለሴትም ሲኾን፤ በወንድ ላይ ብቻ ይነገራል። ሴት ልጅ ካልተገዘረች ጡቷ አይገንም ፥ አይፋፋም፤ ታላላቅ አይኾንም። የፈላስፎች መጽሐፍ፤ ጡት የሚገዝፍበት የሚያብጥበት የሚነፋበት ምክንያቱ ግዝረት ነው ይላል። አነ ቅጽር ወአጥባትየ ከመ ማኅፈድ ያለውም ይህንን ያስረዳል ፡-(ማሕ፰ ፡-፩)።
ግዝአት ፡-መግዛት መገዛት፤ አገዛዝ ግዙነት፤ ግዛት ይዘታ ርስት ጕልት። እስመ እሙንቱ ቅኑያቱ ወምልክናሁ ወግዝአት ሎቱ። አሐዱ ግዝአት ፡-(ቅዳ ፡-ሕር። አዋል)።
(ኣት) ግዝእ ፡-ጋሬዳ ድግስ መሰናዶ፤ ፍሪዳ ያለበት የመብል የመጠጥ የምሳ በዓል። ወገብረ ግዝአ ዐቢየ። ቤተ ግዝእ። መዋዕለ ግዝእ ፡-(ኩፋ ፡-፲፯። መክ፯ ፡-፪። ኢዮ፩ ፡-፭)።
ግዝፈት ፡-መግዘፍ መወፈር አወፋፈር፤ ወፍራምነት፤ ውፈራ ወፍር፤ ውፋሬ ድንዳኔ። በግዝፈተ ልብከ፤ በግዝፈተ ክሣድከ ፡-(መቃ ፡-ገ፮። ፲፬። ስንክ ፡-ታኅ፮)። .
ግዝፍ ግዘፍ ፡-በቁሙ፤ ወፍር ድንዳኔ። ግዝፈ ምድር። ግዝፈ ልብ። ግዘፈ ደመናት። ግዘፈ ዕፅ። ግዘፊሆን ለአልባቢከ ፡-(መዝ፤ ፻፵። አርጋ ፡-፯ ፡-፩። ሕዝ፵፩ ፡-፳፭። ዮሴፍ)።
ግዩር ፡-ግዩር፤ ፡-(ዕብ ጌር። ሱር ጊዮራ) መጤ መጣተኛ ስደተኛ፤ ካገሩ ከሕጉ የፈለሰ ፈላሻ የአይሁድ ጥገኛ፤ በኦሪት ያመነ ግዙር። አሐዱ ሕግ ይኩን ለክሙ ወለግዩር ዘማእከሌክሙ። ግዩራን ወፈላስያን ፡-(ዘፀ፲፪ ፡-፵፱። ዘሌ፳፭ ፡-፳፫)።
፡-የተለሰነ ልስን፤ ቅብ ልቅልቅ።
ግያሬ ፡-ኖራ አወጣጥ አለላለን፤ ልሰና ልቅለቃ።
ግይርና ፡-ስደት ፣ ስደተኛነት ፈላሽነት ፡-(አርጋ)።
ግዮን [1]፡-(ጽር ጌዖን። ዕብ ጊሖን) ስመ ፈለግ፤ ካራቱ በበይት አፍላጋት ኹለተኛው ወንዝ ነጭ አባይ፤ ከአፍሪቃ ደቡብ ተነሥቶ ወደ ሰሜን ወደ ሱዳን አገር የሚፈስ ፡-(ዘፍ፪ ፡-፲፫)። ነቁን ባለጊዎግራፎች ፮ ያኽል ነው ይሉታል፤ ውሃው ነጭ ኒል ስለ መሰለ ነጭ አባይ ይባላል፤ የአባይን ፍች ተመልከት። ጊሖን ማለት ግን፤ ዘየሐውር በኀይል ወይርዕም ወድምፀ ማዩ ዐቢይም ወግሩም ማለት ነው፤ የውሃውን ብዛት የመልካውን ስፋት፤ ያካኼዱን ኀይል የጩኸቱን ግርማ ፏፏቴውንና ተመማውን ድምጡ እንደ ነጐድጓድ መኾኑን ያሳያል። ከአፍሪቃ ወንዞች ተለይተው ነጭ ኒል ጥቍር ኒል የሚመስሉ በኦሪትም ግዮን ኤፌሶን የሚባሉ ነጭ አባይና ጥቍር አባይ ናቸው ይባላል። እሊህም ኹለቱ ወንድማማች ወንዞች፤ ከየምንጮቻቸው በኀይል ተነሥተው ግርማቸውን ለብሰው ፥ ተሰልፈው ፥ በየፊታቸው ያለውን ሐይቅ እንደ መርከብ ሠንጥቀው ዐልፈው ሰራዊታቸውን ከግራና ከቀኝ አስከትለው ፥ እንደ ኹለት ንጉሥ ከርቱም ሲገናኙ ኹለትነታቸው ይቀርና አንድ ወንዝ ብቻ ይኾናሉ፤ ከክርቱም ደግሞ እስካትበራ ወርደው ከተከዚ ጋራ ይገጥማሉ። ከዚያ በኋላ ግን የሌላ ወንዝ ውሃ ሳይጨምሩ ባንድነት መላ ምድረ ግብጽን ከላይ እስከ ታች አጠጥተው አጥግበው አርክተው ፥ ዐልፈው ተርፈው ወደ ስሜን ጐርፈው ሜዲተራኒ ከሚባለው ከታላቁ ባሕር ይገባሉ።
[2]፡-የየሩሳሌም ወንዝ ሰሊሖም ሰሎሞን የነገሠበት፤ ከከተማዪቱ በስተደቡብ ያለ ፡-(፫ነገ ፡-፩ ፡-፴፫። ኢሳ፰ ፡-፮)።
ግደት ፡-መገደድ፤ ማስገደድ፤ ግዴታ ግድ ግዳጅ፤ ጥናት ብርታት። እመ ወድቀ ብሑት ውስተ እከይ እመ አኮ በእንተ ድካመ ሥጋ አው በእንተ ግደተ ገድል ፡-(ፊልክ ፡-፬)።
ግዱል ፡-(ላን ላት ድልት) የተገደለ የተጣለ፤ ገደል የገባ።
(ጥ) ግዱድ ፡-(ዕብ ግዱድ፤ ወራሪ ዘራፊ) በግድ የተያዘ፤ ወይም የሚይዝ የሚያስገድድ ጨካኝ ወንበዴ ሽፍታ። ወኀይላኒ ከመ ብእሲ ግዱድ ፡-(ሆሴ፮ ፡-፱)
፡-የባሰ የጸና፤ የበረታ ብርቱ። እስመ ኀጢአቶሙ ዐቢይ ወግዱድ በኀበ እግዚ ፡-(ቄድር)።
ግዱፍ ፡-(ፋን ፋት ድፍት) የተገደፈ፤ የተጣለ የወደቀ የተኛ የተጋደመ፤ የጠፋ የታጣ፤ የረከሰ የተናቀ። ከመ ፀፍዕ ግዱፍ ከማሁ ሀካይ በኀበ ሰከበ። ረከበ ቢድኖ ግዱፈ ውስተ ምድር። ግዱፍ ውስተ ዴዴሁ። ግዱፋነ ይርከብ። ኵሉ ተግባረ እግዚ ሠናይ ወአልቦ ግዱፍ ወኢምንትኒ ፡-(ሢራ፳፪ ፡-፪። ዮዲ፲፬ ፡-፲፭። ሉቃ፲፮ ፡-፳። ኪዳ። ፩ጢሞ ፡-፬ ፡-፬)።
ግዳሜ ፡-ጋድም፤ የመስቀል ክንፍ። በትረ ከርካዕ ውእቱ ዕፀ መስቀል ወበትረ ለውዝ ይትሜሰል በግዳሜሁ ፡-(መጽ ፡-ምስ። ኤር፩ ፡-፲፩)።
ግድ ፡-በቁሙ፤ ውድና ፈቃድ የሌለበት መጽሐፍ ግን በግድ ፈንታ ግዱድ ይላል፤ አያሰኝም። አዘዘ ይጥዐምዎ በግዱድ ፡-(ግንዘ)።
ግድም ፡-(ብ ግደም፤ ግድማት) በቁሙ፤ አግድሞ፤ ወርድ ስፋት። ወእመኒ ሖርክሙ ግድመ አነኒ አሐውር ግድመ ምስሌክሙ። ወግድሙ ስድስቱ በእመት። አልብነ ኑኅ ወግድም። ኢይትአመር ኑኃ ወግድማ ወኢቆማ። እምግደሚሁ ለደብተራ ፡-(ዘሌ፳፮ ፡-፳፩–፳፬። ዳን፫ ፡-፩። ቀሌ። ዘፀ፳፮ ፡-፲፫)።
ግድዓ እንግድዓ ፡-(ዓት) ደረት እንቢያ፤ ፍርእንቢያ።እን ምልአተ ንባብ ነው፤ ከአንጐድጐደ መጥቷል። ግድዓ፤ ደረት በሐዘን ጊዜ የሚመታ የሚደሰቅ። ድጕዓን እይ። እንግድዓሁ ዘብሩር። ልብሰ እንግድዓ። በጐዲዐ እንግድዓ ንጕዳዕ እንግድዓቲነ። ኦ እምኔከ ሞት እስመ ኬድከ በሰኩናከ እንግድዓቲሆሙ ለካህናት ፡-(ዳን፪ ፡-፴፪። ዘፀ፳፰ ፡-፬። አፈ ፡-ተ፳፯። ፊልክ ፡-፻፲። ግንዘ)። ልብ ሆድ ትዕግሥት አእምሮ። ሑሪ በእንግድዓኪ። ለብእሲ ጸቢበ እንግድዓ በግዕዙ ይጸልእዎ ሰብእ። አጥሪ ትዕግሥተ ወርሕበተ እንግድዓ። ብእሲ ድኩመ ኅሊና ወጸቢበ እንግድዓ አብድ ውእቱ ፡-(ዘፍ፫ ፡-፲፬። ፈላስ ፡-ገ፶፮። ፶፯። አፈ ፡-ተ፲፱)።
ግድፈት ፡-በቁሙ፤ መግደፍ መጣል፤ መገደፍ አገዳደፍ ገደፋ ርሳታ ዝንጋታ፤ ገዳፍነት። ግድፈተ ቃል ፡-(ፍ ፡-ነ ፡-መጨረሻው)።
ግጋጼ ፡-ማፈግፈግ፤ ኀፍረት ፍርሀት፤ ድንጋጤ ሽሽት። ቀርበት ለመዊት እንበለ ግጋጼ። ሰማዕታተ ክርስቶስ እንበለ ግጋጼ ፡-(ዮሴፍ። ስንክ ፡-ነሐ፲)።
ግግጽና ፡-ዝኒ ከማሁ፤ አፈግፋጊነት። ሖረ ምስሌሆሙ እንበለ ግግጽና ፡-(ስንክ ፡-ሚያ፪)።
ግጻዌ [1]፡-መታየት መገለጥ፤ መታወቅ መረዳት፤ ባለሟልነት፤ ትርጓሜ አፈታት። በከመ ደለዎ ግጻዌ ለዮሐንስ።አእምሮትከ ዘመልዕልተ ኵሉ ግጻዌ። ግጻዌ ትምህርተ ሕግ ወሥርዐት ወተግሣጽ። ግጻዌ ድርሳን ዘቅዱስ ቄርሎስ ከመ አሐዱ ክርስቶስ ፡-(ፊልክ። ጥበ ፡-ጠቢ። ሲኖዶ። ቄር ፡-ጰላ)። ባለመጣፎች ግን ግጽው ብለው በቅጽል አፈታት ይፈቱታል።
[2]፡-ግጽው የንባብ መጣፍ እንደ ድጓ ካመት እስካመት የተሠራ፤ በጸሎት በቅዳሴ ጊዜ የሚነበብ፤ ቃሉ ለዘመን ለበዓል የሚስማማ፤ ከብሉይ ከሐዲስ የወጣ። መጽሐፈ ግፃዌ ዘአባ መቃርስ። መጻሕፍተ ግጻዌ። በውስተ ግጻዌ ፡-(ስንክ ፡-መስ፲። ኅዳ፲፯። ግን፲፪)።
[3]፡-ግጻዌ፤ ገጽ ያለው አካል፤ ህላዌ። ነአምን አበ በአካሉ ወበግጻዌሁ ዘኢይትፈለጥ እምከዊነ አብ ኀበ ከዊነ ወልድ።አቀመ ግጻዌ ባሕቲቶ በአብ። እመን በሥላሴ ወተጋነይ በግጻዌ መለኮት። በስመ ግጻዌ ሠላስ ዕሩያነ ክብር ወንግሥ። አሐዱ ውእቱ ዘበሠለስቱ ግጻዌ ፡-(አትና። መጽ ፡-ምስ። አዋል። ቅዳ ፡-ሕር)።
ግጽው ፡-(ዋን ዋት ጹት) የታየ የተገለጠ፤ ግልጥ ጕልሕ፤ ፊት ለፊት ያለ፤ ሥዕል ምስል፤ ባለሟል። ግጽው መንገለ ሰሜን። ሊተ ግጽው ቅድመ አዕይንትየ ኢየሱስ ፡-(መጽ ፡-ምስ)።
፡-የመጽሐፍ ስም ከሐዋርያት ሲኖዶስ አንዱ ክፍል። ፍትሐ ነገሥት ረስጠብ ይለዋል፤ ሐዋርያት ለቀሌምንጦስ የሰጡት ኹለተኛ መጽሐፍ ማለት ነው። ግጽው ወሥርዐት ወአብጥሊስ ፡-(ሲኖዶ)።
ግፉዕ ፡-(ዓን ዓት ፍዕት) በቁሙ፤ የተገፋ የተበደለ፤ የተጠቃ። ዐውያተ ግፉዕ። አድኅኑ ግፉዐ። ሰብእ ግፉዓን ፡-(ሢራ፴፪ ፡-፲፮። ኢሳ፩ ፡-፲፯። ፳፭ ፡-፫)።
ግፍቱዕ ፡-(ዓን ዓት ትዕት) የተለወጠ የተገለበጠ፤ ልውጥ ግልብጥ፤ ጠማማ ቈልማማ። ይወፅእ ሕግ ግፍቱዐ። ትውልድ ዕሉት ወግፍትዕት። ግፍቱዓነ ልብ። ዐላውያን ወግፍቱዓን ፡-(ዕን፩ ፡-፬። ዘዳ፴፪ ፡-፭። ሔኖ፻ ፡-፰። ፊልጵ፪ ፡-፲፭)።
ግፍታዔ ፡-መገልበጥ፤ መደፋት መፍረስ፤ ሥራዌ ጥፋት። ወአውፅኦ እማእከለ ግፍታዔ። ግፍታዔ ሰዶም ፡-(ኩፋ ፡-፲፮። መጽ ፡-ምስ)።
ግፍዐት ፡-መግፋት መገፋት፤ አገፋፍ።
ግፍዕ ፡-(ዓት) በቁሙ፤ ግፍ በደል፤ ቅሚያ፤ ሕገ ወጥ ሥራ፤ ስድብ መከራ። ዐመፃ ወግፍዕ። ከመ ትግበሩ ላዕሌነ ዐቢየ ግፍዐ። ወባሕቱ እነግረከ ግፍዐከ። እመ ተዐገሥክሙ ግፍዐክሙ ፡-(ኩፋ ፡-፴፭። ዮዲ፯ ፡-፳፬። ኢዮ፴፫ ፡-፰። ፩ጴጥ ፡-፳)።
ጎሀ ፡-ነጋ በራ፤– ገዊሕ ጎሐ።
ጐሓሊ ፡-(ሊት ልያን ያት፤ ሐልት) ጕሕልያ፤ ፡-(ያት) ክፉ አድራጊ፤ ሌባ ቀጣፊ፤ ዳንዴ ወንበዴ ቀማኛ፤ የቀን ወራሪ የሌት ሰባሪ፤ ቤት አቃጣይ ነፍሰ ገዳይ። ጕሒላ እንዲል ፡-(ትግሬ)። መጽሐፍ ግን፤ ሰራቂ ፡-ወጕሕልያ፤ ሰረቅት ወጕሕልያ እያለ እንደ ፀር እንደ ቢጽ ላንድም ለብዙም ያደርገዋል፤ የጣፊ ስሕተት ነው ፡-(፪ጢሞ ፡-፪ ፡-፱። ዮሐ፲ ፡-፩ ፡-፰። ዐብድ ፡-፭። ስንክ ፡-ኅዳ፲፪)።
ጐሃኒ ፡-(ኒት ንያን ያት፤ ሀንት) የሚሰውር ደባቂ፤ ጯኺ። የሚጕን፤ የሚያጕን።
ጐሐየ ፡-(ዐረ ፡-ጀሓ) ዐረመ፤ ነቀለ መነገለ አፈለሰ።
ጎህ ፡-ወገግታ፤–ገዊሕ ጎሐ፤ ጎሕ።
ጎሕ
፡-ወገግታ፤ ውጋጋን ፈገገን፤ የንጋት ብርሃን፤ ከጽባሕ በፊት የሚታይ ያጥቢያ ኮከብ ዘመን። ከነግህ ጽባሕ እንዲቀድም ከጽባሕ ደግሞ ጎሕ ይቀድማል፤ ጨርሶ እስኪታይ ጎሕ ይባላል፤ ከታየ በኋላ ፀሓይ እስክቶጣ ጽባሕ ይባላል፤ ነግህ ከዚያ በኋላ ነው። የሦስቱ ኹሉ ዘራቸውና አንቀጻቸው የተለየ ነው። ሶበ ዐርገ ጎሕ። እምጊዜ የዐርግ ጎሕ። ከመ ጎሕ ድልው ለወሊደ ፀሓይ። ርእየ ጎሕ ወኢርእየ ጽባሐ ፡-(መሳ፲፱ ፡-፳፭። ነሐ፬ ፡-፳፩። አርጋ ፡-፪። ፬)።
ጐሊሕ ሖት ፡-(ጐልሐ ይጐልሕ ይጕላሕ። ዕብ ጋሌሕ። ትግ ገልሔ ላጨ) መጕላት መግዘፍ፤ መታየት መገለጥ፤ እንደ ልጩ ራስ መኾን። የጥፈት የሥዕል የመልክአ ፊደል፤ የነገር የምስጢር የድምፅ የቃል።
ጐሊም ሞት ፡-(ጐለመ ይጐልም ይጕልም። ዕብ ጎሌም) መጐለም፤ ጕልማ መስጠት። መጐልመስ ማደግ፤ መጐላመም ጐልማማ ባለጕልማ መኾን። ጐለም እንዲሉ ጐልማሜ ሲሉ።
ጐላቲ ፡-(ቲት ትያን ያት) የሚጐልት ጐላች፤ ሰጭ አውራሽ። ወለእመ ፈቀደ ጐላቲ ከመ ይሠየም ዲበ ዘጐለተ ፡-(ፍ ፡-ነ ፡-፲፰)።
ጎላት ፡-መንቀሎች፤–ጐልሎ ጐለለ።
ጎል [1]፡-(ብ አግዋል ላት) በረት የከብቶች ማደሪያ መታጐሪያ። ወአልሕምትኒ ኢይትረከቡ በውስተ ጎል። አግዋላት ለእንስሳሁ ፡-(ዕን፫ ፡-፲፯። ፪ዜና ፡-፴፪ ፡-፳፰)።
[2]፡-(ዐረ ማዝወድ። ዕብ ኤቡስ) ግርግም፤ በዚያው በበረቱ ውስጥ ዙሪያውን ወይም ባንድ ወገን እንደ ገንዳ ኹኖ የሚሠራ የእንስሳት ማእድ ገለባ ደፈጫ የሚቅሙበት። አስከበቶ እሙ ውስተ ጎለ እብን። በጎለ እንስሳ ተወድየ ፡-(ድጓ። ቅዳ ፡-ዲዮ)። በግርግም ውስጥ ማለት ነው።
[3]፡-(ዐረ ማዝወድ። ዕብ ኤቡስ) ግርግም፤ በዚያው በበረቱ ውስጥ ዙሪያውን ወይም ባንድ ወገን እንደ ገንዳ ኹኖ የሚሠራ የእንስሳት ማእድ ገለባ ደፈጫ የሚቅሙበት። አስከበቶ እሙ ውስተ ጎለ እብን። በጎለ እንስሳ ተወድየ ፡-(ድጓ። ቅዳ ፡-ዲዮ)። በግርግም ውስጥ ማለት ነው።
ጐልሎ ሎት ፡-(ጐለለ ይጔልል ይጐልል) መጐለል፤ በቤት ራስና በጕልቻ ላይ ማስቀመጥ ማኖር፤ መጣድ ማስረር።
ጐልበተ ፡-(ትግ ገልበተ፤ ገለበጠ) በቁሙ፤ ጐለበተ ጕልበታም ኾነ፤ ዐየለ በረታ ፡-(ዐማርኛ)።
ጐልቶ ቶት ፡-(ጐለተ ይጔልት ይጐልት) መጐለት መትከል፤ የጕልቻ። ማውረስ መስጠት፤ የገንዘብ የርስት። ይጐልቶሙ ለአብያተ ክርስቲያናት። በጊዜ ጐልቶቱ። ወለእመ ጐለተ ላቲ ኢትሰድ ፡-(ስንክ ፡-ጥር፳፫። ፍ ፡-ነ ፡-፲፰። ፳፬ ፡-፭)።
ጎልጎል [1]፡-(ዕብ ጊልጋል) ስመ ሀገር፤ ፡-(ዘዳ፲፩ ፡-፴)።
[2]፡-(ዕብ ጉልጎሌት) የራስ ቅል፤ የራስ ዐጥንት፤ መላው ካንገት በላይ ያለው። ናላን አንጎል ማለት ከዚህ የወጣ ነው።
ጎልጎታ ፡-(ዕብ ጎልጎልታ) መካነ ርእስ መካነ ድማኅ። ይችውም የአዳም ራስ ቅል የተቀበረባት፤ ዳግማይ አዳም የተሰቀለባት ቀራንዮ ናት ፡-(ዮሐ፲፱ ፡-፲፯)።
ጐልጐታ ፡-ጎልጎታ፤–ገዊል ጎለ፤ ጎል።
ጐሚት ፡-ታላቅ ጐምቱ እባብ ዐይጥ የሚውጥ የሚሰለቅጥ፤ ባላገሮች ጐሚት ገና የሚሉት።
ጐሜእ ፡-(ዕብራ) ስመ ዕፅ በግብጽ ወንዝ ዳር የሚበቅል፤ ውስጠ ክፍት የሸንበቆ የቀርክሓ ዐይነት ታንኳ ፍልኳ የሚኾን። ንዋየ ጐሜእ ፡-(ኢሳ፲፰ ፡-፪)።
ጐምር ፡-በቁሙ፤ የበሰለ የደረሰ፤ እሸትነቱን የጨረሰ ፡-(ዐማርኛ)።
ጐሞር ጎሞር ፡-(ጽርእ። ዕብ ዖሜር) ታናሽ ልክ፤ የኽል መስፈሪያ እንደ ድርጎና እንደ ቍልቢጥ እንደ ቈለምሸሽ ያለች፤ የኢፍን ካሥር አንድ የምቲዝ ፡-(ዘፀ፲፮ ፡-፲፰)። ኢፍን እይ።
ጐሢዕ ዖት ፡-(ጐሥዐ ይጐሥዕ ይጕሣዕ። ዐረ ጀሸአ፤ ጀሸዐ። ሱር ግሣእ። ዕብ ጋሣህ፤ ጋዓህ) መግሣት ማግሣት መጮኽ፤ አፍን መክፈት፤ መትፋት መቀርሸት ቋቅ ማለት፤ የጠብ የጥጋብ። ፡-(ግጥም) ሚጣቅ እሾላው ሥር ዐማኔል ቢያገሣ ፥ በሽታዬ ኹሉ እክቱን አነሣ። ኀበ ነቀወ፤ ዶርሆከ ወጐሥዐ ሶረ ብዕራይከ ህየ ንበር። ወእጐሥዕ እምሐዘነ ልብየ። ኵሉ ዘይጐሥዕ ማይ ፡-(ታሪ ፡-ነገ። መዝ ፡-፴፯። ዘሌ፲፩ ፡-፲)።
፡-መናገር፤ ኀይለ ቃል ማውጣት፤ ደፍሮ ተራቆ፤ የክፉ የበጎ የድርስት የትንቢት። ቦ እለ ይጐሥዑ በእንቲኣየ ቃላተ ዐመፃ። ዕለት ለዕለት ትጐሥዕ ነቢበ። ጐሥዐ ልብየ ቃለ ሠናየ። ወጐሥዐ ልብየ ጥቀ ጥበበ። ዘጐሥዐ መጻሕፍተ ጥበብ ኵሎ ፡-(ተረ ፡-ቄር፲፭። መዝ ፡-፲፰። ፵፬። ሱቱ ፡-ዕዝ፲፬ ፡-፵፪። ስንክ ፡-የካ፲)።
፡-መፍላት፤ መገንፈል፤ መልቶ ተርፎ መፍሰስ። መንፈስ ቅዱስ ይጐሥዕ ውስተ ልቡ በከመ ይጐሥዑ አፍላጋት ወይውሕዙ። እምነ ሐዋርያት ጐሥዐ መንፈስ ቅዱስ ላዕለ ኵሎሙ ቅዱሳን መሀይምናን ፡-(ስንክ ፡-የካ፲። ጥቅ፳፩)።
ጐሪጽ ጾት ፡-(ጐረጸ ይጐርጽ ይጕርጽ) መብጣት መፍቃት፤ መቍረጥ መሠንበጥ፤ መውጋት መጋረጥ፤ መሰርሰር መንደፍ፤ ደም ለማውጣት፤ የግንባር ያፍንጫ። ማጕረጥ ማፍጠጥ፤ ያይን። ጕርጥ ጐረጥ ማለት ከዚህ ወጥቷል።
ጐሪፍ ፎት ፡-(ጐረፈ ይጐርፍ ይጕርፍ) በቁሙ፤ መጕረፍ መፍሰስ።
ጎሬም ፡-(ብ ጎራይም) ዐጋሚ ሐኪም፤ ባለዋገምት። ማገሚያ ዋገምት፤ የቀንድ የብርጭቆ።
ጎር ፡-(ዐረ ጃር። ዕብ ሽኼን) ጓሮ የቤት ኋላ። በቁሙ ጎረ ቤት፤ ቤቱ የቤት ቅርብ ጐን ሕፅን አጠገብ የኾነ፤ የርስት የመሬት የቦታ አዋሳኝ ደንበረተኛ፤ በዙሪያ ላለ ለቅርብ ኹሉ ይነገራል። ካልእ ዘጎሩ። ወቤቱ ጎረ ምኵራብ። በኀበ ጎርየ። ጎር እኩይ እለ ይገስሱ ርስትየ። ወቦ ዐጸደ ሐምል ጎረ ቤቱ ፡-(ዘፀ፲፪ ፡-፬። ግብ፲፰ ፡-፯። መዝ ፡-፴። ኤር፲፪ ፡-፲፬። ዳን፩ ፡-፬)።
፡-ጎረ ቤት፤–ገወረ።
ጐርዐየ ፡-(ተቀ ግ) ዐነቀ ፈጠረቀ፤ ጕረሮ ያዘ። ጐርጐረን እይ።
ጎርየመ [1]፡-(ይጎረይም ይጎሪም) ዐገመ ዐከመ፤ ጠባ ሳበ መጠመጠ፤ ደምን እንደ ወተት ለማውጣት። ሐገመን እይ።
[2]፡-ዐገመ፤–ጉር ገወረ።
ጐርጐረ ፡-(ዕብ፤ ጋርጌር) በቁሙ፤ ጐረጐረ፤ ጓጐጠ ነካ፤ ቋቅ አለ ለማስመለስ፤ የጕረሮ። ጕረሮ ቅሉ ከዚህ ወጥቷል የዚህ ዘር ነው። ሻ በረበረ፤ አጥብቆ ፈለገ፤ ለማግኘት። ፡-(ተረት) ዓሣ ጐርጓሪ ዘንዶ ያወጣል፤ የሰው ፈላጊ የራሱን ያጣል። ጐርጐረ ካማርኛ በቀር በግእዝ ቃላት ውስጥ አለልማድ አይነገርም።
ጐኒድ ዶት ፡-(ጐነደ ይጐንድ ይጕንድ) መጐነድ፤ ጕንድ ጐናዴ መኾን፤ ጐዦ መውጣት፤ ለብቻ መቆም መተክል፤ ራስን መቻል፤ መወፈር መደንይን፤ የዛፍ የሰው።
ጐናኵ ፡-(ኵት ኵያን ያት) ሰብሳቢ ሰንዳቂ፤ ከማሪ ቈላይ ተሸካሚ።
ጎን [1]፡-(ዕብራ) መልክ ሕብር ዐይነት፤ አንጻር አርኣያ አምሳል። በቁሙ ጐን፤ ገቦ ፡-(ዐማርኛ)።
[2]፡-መልክ፤–ገወን።
ጐንኮ ኮት ፡-(ጐነኰ ይጔንኵ ይጐንኵ) መሰብሰብ፤ መጐቸት መሰንደቅ፤ መከመር መቈለል ቤት ማስመሰል፤ ወይም እያሰሩ መሸከም መደብለል፤ የነዶ የሣር። ያክይዱ ወይነ ወይጔንኩ ከላስስተ በዕለተ ሰንበት ፡-(ነሐ፲፫ ፡-፲፭)።
ጐንደር ፡-ጕንደ ሀገር፤ የፋሲል ከተማ ከግራኝ በኋላ የቀናች ባላ፵፬ ደብር፤ ዳግም ግራኝና ሣልስ ግራኝ ፡-(ቴዎ ፡-ደር) ተከታትለው እስኪያጠፏት ድረስ መናገሻ ታላቅ መዲና የነበረች።
ጐንደየ ፡-(ተቀ ግ) ቈየ ዘገየ፤ ሰነበተ፤ ሥር ያዘ፤ ቀረ ወደ ኋላ አለ፤ ኖረ ተቀመጠ። ጐንደየ እንዘ ይጐደጕድ። ኢይጐነዲ ንዋዩ። ወልድየሰ ሞተ ወበእንተ ዝ ጐንደየ።ኢትጐንዲ ውስተ መካና። ጐንደዩ አንጾኪያ። ከመ ኢይጐንዲ ውስተ እስያ ፡-(ግብ፲፪ ፡-፲፮። ኢዮ፲፭ ፡-፳፱። ጦቢ፲ ፡-፩። ምሳ፱ ፡-፲፰። ግብ፲፭ ፡-፴፭። ፳፤ ፲፮)። በጐንደየ ፈንታ ተጐናደየ ይላል። ኢትትጐናደይ ላዕለ ገቢረ ሠናይ። ኢመፍትው ንትጐናደይ ተጠምቆ። ሶበ ተጐናደየ ሞተ አበሁ ፈቀደ ይቅትሎ ፡-(ፈላስ። አፈ ፡-ተ፲፫። ዮሴፍ)።
ጐዕተየ ፡-አሞኘ አታለለ፤ ተሞኘ ተታለለ።
ጐዝጐዘ ፡-(ዐማርኛ። ገለደ ነጸፈ) በቁሙ፤ ጐዘጐዘ አነጠፈ፤ አመቻቸ።
ጐዝጐዝ ፡-(ብ ጐዛጕዝ፤ ዛት) ዐልጋ፤ በቁሙ ጕዝጓዝ ሰርፍ፤ ስጋጃ ምንጣፍ፤ የሌት ልብስ ለሐፍ። አምጽኡ ዐሠርተ ዐራታተ ወጐዛጕዛተ ፡-(፪ነገ ፡-፲፯ ፡-፳፪)።
ጐየጸ ፡-(የጌገየና የጐየ ጎር) ሳተ ለቀቀ፤ የሕፃን የድውይ። ሸሸ አመለጠ ፥ ያይነ ምድር የፈስ፤ ሬሳ ሽሽ እንዲሉ። ፈሰወን ተመልክት።
ጐያዪ ፡-(ዪት ይያን ያት፤ የይት) የሚሸሽ ሸሽታ፤ ኰብላይ፤ ፈሪ ደንባሪ፤ ሯጭ ፈርጣጭ፤ ዐመለኛ። ጐያዬ ከዊኖ። ብእሲ ጐያዪ። እንስሳ ጐያዪ ፡-(ቄር። ፈ ፡-መ ፡-፳፫ ፡-፬። ፍ ፡-ነ ፡-፴፫ ፡-፫። ፵)።
ጐይ ዕብ ጎይ ፡-ሕዝብ፤ ያንድ አገርና ያንድ መንግሥት ሰው ቋንቋውና ሕጉ አንድ የኾነ። ሲያበዛ ጎይም ይላል ፥ አሕዛብ ማለት ነው፤ ጐይይ ጐየ ማለት ከዚህ ሥር ወጥቷል።
ጐይይ ዮት ፡-(ጐየ፤ ጐየየ ይጐይይ ይጕየይ። ዕብ ጎይ፤ ሕዝብ) መሸሽ መኰብለል። መራቅ መሰደድ፤ ካሉበት ከነበሩበት መጥፋት መታጣት፤ ወደ ሌላ ሕዝብ መኬድ መጠጋት፤ ሕግን ባንዲራን መለወጥ፤ ሌላ ሕዝብ መኾን መባል። ፈለሰን እይ፤ የዚህ ጎር ነው። ጐየ እምገጸ ዔላው። ከመ ዘይጐይይ እምአርዌ እኩይ ከማሁ ጕየይ እምኀጢአት። ጕዩ እማእከለ ባቢሎን። ወአይቴ እጐይይ እምቅድመ ገጽከ። ጕየይ ብሔረ ግብጽ ፡-(ኩፋ ፡-፴፩። ሢራ፳፩ ፡-፪። ኤር፳፰ ፡-፮። መዝ ፻፴፰። ማቴ፪ ፡-፲፫። ፲ ፡-፳፫)።
ጐደላዊ ፡-(ዊት ውያን ያት) ዝኒ ከማሁ፤ ያነሰው የጐደለው። ጐደላውያን እምውስተ ትምህርት ዘበእንተ አእምሮ ወጽንዕ ወሙቀተ ፍቅር። ጐደላውያን ንሕነ እምአበው ፡-(ፊልክ ፡-፵፭። ፪፻፲፯)።
ጐደሎ ፡-በቁሙ፤ ጕዱል ያነሰ የጐደለ፤ ሕጹጽ። ዘርቱዐ ግዕዝ ወሥርዐቱ ጐደሎ በእንተ ልኅላኄ ኅሊናሁ ፡-(ፊልክ ፡-፪)።
ጐደዳ ፡-(ዐማርኛ) ያዛባ ጡብ ል የኵበት ጠገራ ከባድ ጥፍጥፍ፤ ሲማገድ ከእሳት ሲዋሐ የሚጓደድ ብርቱ ጠንካራ። ፡-(ተረት) ሆድ ዕዳ ፥ ያስበላል ጐደዳ።
ጐደፈ ፡-በቁሙ፤ አደፈ ተኵለፈለፈ። እድፋም ጕድፋም ኾነ ፡-(ዐማርኛ)።
ጐዲል ሎት ፡-(ጐደለ ይጐድል ይጕድል፤ ዐማርኛ) ሐጺጽ ነቲግ ንኢስ፤ መጕደል ማነስ፤ ሕጹጽ መኾን። ለእመ ኮነት ምግባራቲከ ሕጽጽተ እምጸብአ ሰይጣናት አላ ኅሊናከሰ ርትዕት ወኢጐደለት ፡-(ፊልክ ፡-፵፯። ፶፬)።
ጐዲብ ቦት ፡-(ጐደበ ይጐድብ ይጕድብ) መጐደብ ማረድ፤ መቈፈር ማጐድጐድ፤ መቍረጥ፤ የመሬት። መመንደብ መጕረድ መጕመድ፤ መጨፍጨፍ መመንጠር መለበድ፤ ካንቻ መምታት፤ የንጨት። መገደብ መወደብ፤ መክተር ማገድ የውሃ። የሦስቱ ኹሉ ስልት አንድ ነው፤ ምስጢሩ ከመቍረጥ አይወጣም፤ ገዘመንና ገመድን ይመስላል፤ አንቀጹ ካማርኛ በቀር በግእዝ ቃላት አይገኝም።
ጐዲዕ ዖት ፡-(ጐድዐ ይጐድዕ ይጕዳዕ። ዕብ ጋዳዕ) መጕዳት መንካት መጐነጥ፤ መምታት መደሰቅ፤ መሰባበር ማድቀቅ። መውጋት፤ መውገጥ መለጥልጥ። ጐድዖ ገቦሁ። ጐዳዐ እንግድዓሁ። ጐድዖ ነፋስ ለቤት። ለሊሃ ትጐድዕ ወለሊሃ ትኬልሕ። አኀዘ ይጕድዖሙ ለእልኩ አባግዕ።ኢይጐድዖ ዐይነ እኩይ። ቅበዐ ንሒጕ ንጕዳዕ፤ ወጐድዑ በተባርዮ ፡-(ግብ፲፪ ፡-፯። ሉቃ፲፰ ፡-፲፫። ፳፫ ፡-፵፰። ኢዮ፩ ፡-፲፱። ሢራ፲፫ ፡-፪። ሔኖ፹፭ ፡-፬። ደራሲ። ድር ፡-መድ)።
ጐዲድ ዶት ፡-(ጐደ፤ ጐደደ ይጐድድ ይጕድድ) መጓደድ መቈነን፤ ያካኼድ ያረማመድ፤ የታቦት የዑደት።
ጐዳና ጐድን ፡-(ዐማርኛ) በቁሙ፤ አውራ መንገድ፤ ገቦ ዐፅመ ገቦ።
ጐዳዒ ፡-(ዒት ዕያን ያት) የሚጐዳ የሚነካ፤ ጕዳት የሚያመጣ።
ጎድ [1]፡-ኀይል፤–ገወድ።
[2]፡-(የግዱድ ከፊል) ኀይል ሰራዊት። ይመጽእ በጎድ ፡-(መቃ) በንግሊዝ ቋንቋ ግን አምላክ ማለት ነው።
ጐድአ ፡-መታ ደሰቀ፤–ጐዲዕ ጐድዐ።
ጐድጐደ [1]፡-(ጐዲዕ ጐድዐ) ደጅ መታ ቀበቀበ፤ እጅ ጸፋ አጨበጨበ፤ ለማስከፈት። ግስነቱ ከጐዲዕና ከገዲድ ከኹለቱ የተዴቀለ ነው። ሶበ ጐድጐደ ኆኅተ። ነሥአ እብነ ወጐድጐደ ቦቱ አንቀጸ። ቦአ ወጐድጐደ በኀበ ዐጸድ ዘቅድመ ደብተራ። ወለዘኒ ጐድጐደ ይትረኀዎ ፡-(ፊልክ ፡-፶፭። ስንክ የካ፪። ዮዲ፲፬ ፡-፲፬። ማቴ፯ ፡-፰)።
[2]፡-ከተተ፤ ከቤት ከጓዳ ከጕድጓድ አገባ። ጐደጐደ ጕድጓድ ኾነ ፡-(ዐማርኛ)።
ጐጕኦ ኦት ፡-(ጐጕአ ይጔጕእ ይጐጕእ፤ መጓጓት መመኘት፤ ተስፋ ማድረግ፤ መሠየት መጐምዠት፤ ከዚህ የተነሣ መቸኰል መጣደፍ፤ መፍጠን መቀልጠፍ መጣር መፍጨርጨር፤ መትጋት። ጉጕአ ከመ ይፃእ እምህየ። ጐጕአ ከመ ይዕርግ። ይጔጕእ ዘተነድፈ ይምላኅ ሐጸ። እስመ ቦ ዘይጔጕእ ወይሰርሕ። ይጔጕእ ይብዐል ፡-(፪ዜና ፡-፳፮ ፡-፳። ፲ ፡-፲፰። ሢራ፲፱ ፡-፲፪። ፲፩ ፡-፲፩። ምሳ፳፰ ፡-፳፪። ፪ጴጥ ፡-፲ ፡-፲፭። ፫ ፡-፲፬)።
ጎግ ፡-ጎግ፤ ሰራዊት መንጋ በዝቶ የሚኼድ የሚንጋጋ።
ጎግ ማጎግ ፡-ጎግ ስመ ሀገር፤ ማጎጋውያን የወረሱት ፡-(ቃውቃዝ)። ማጎግ ስመ ነገድ የያፌት ልጅ፤ የመስኮቦች አባት ፡-(ሕዝ፵፰ ፡-፪። ራእ፳ ፡-፰። ዘፍ፲ ፡-፪)። ኹለተኛም ጎግ ብዙ፤ ማጎግ የብዙ ብዙ፤ ወይም ጎግ ጀርመን፤ ማጎግ መስኮብ ይባላል፤ ምስጢሩ ብዛት ነው። አይሁድ ግን ከኦሪት ዘዳግም ፡-(፴፪ ፡-፰ ፡-፱) አያይዘው ፸ ቋንቋ ፸ ነገድ ብለው በፊደል ቍጥር ይፈቱታል፤ አፈታታቸውም እንዲህ ነው። ገ ሳብዕ መኾኑ ወን ጐርዶ ነውና ሲጥፉ ገወግ ማገወግ፤ ሲያነቡ ግን እንደኛ ጎግ ማጎግ ይሉታል። ገወግ ፲፪፤ ማገወግ ፶፪ ፡-፷፬። በዚህ ላይ ደግሞ ገወግ ማገወግ ፯ ብለው ነጠላ ቍጥር ይቈጥሩና ከ፷፬ ጋራ ሲገጥሙት ፸፩ ይኾናል። ፸ው ወይም ፸፩ዱ አሕዛብ፤ ፸፪ኛው እስራኤል ይላሉ፤ ይህ ደግሞ ፡-(ዘፍ፩ ፡-፳፰)። ብዝኁ ወተባዝኁ ወምልእዋ ለምድር ያለውን ያዳምን ዘር ኹሉ ያሳያል።
ጎግዎ ዎት ፡-(ጎገወ ይጎጉ ይጎጉ፤ ገዊግ) መሳት መሳሳት፤ ከሕግ ከሥርዐት ከመንገድ መውጣት፤ ከጽድቅ መራቅ። ጌገየንና ሳኰየን ጠዐወን እይ፤ የዚህ ጎሮች ናቸው።
፡-መንጋጋት መርባት መብዛት፤ መንጋ መኾን፤ የሰው የከብት። መንጋ ማለት ቅሉ ከዚህ ወጥቷል።
ጐጓኢ ፡-(ኢት እያን ያት) የሚቸኵል ቸኳይ። አንተ ብእሲ ጐጓኢ ፡-(ሄርማ)።
ጐጣዪ ፡-(ዪት ይያን ያት) የሚወጋ የሚጓጕጥ፤ የሚያጣብቅ የሚቈነጥጥ።
ጐጥ ጕጥ ፡-በቁሙ፤ ዐባጣ ሸካራ፤ የምድር የመሬት፤ የበትር የንጨት፤ ለእጅም ይኾናል። እጄ ጕጥ አወጣ እንዲሉ።
ጐጥይ ዮት ፡-(ጐጠየ ይጐጢ ይጕጢ) መጓጐጥ መጐጥጐጥ፤ መሠቅሠቅ፤ መቈፈር መሰርሰር መውጋት መትከል። ማጣበቅ መቈንጠር፤ አጣብቆ መያዝ።
ጐጻጕጽ ፡-(ጻት) ጐጣጕጥ፤ ሥርጥ ዐባጣ ጐባጣ ስንከልካላ። ፍኖት እንተ አልባቲ ማዕቅፍ ወአሥዋክ ወጐጻጕጽ ወአጽዳፍ። አኮ ብነ ዝየ ሀገር አጽዳፍ ወጐጻጕጽ ፡-(ሲኖዶ። ቅዳ ፡-አትና)። ,
ጐጽፈረ ፡-(ዲቃ ግ፤ ደጐጸ፤ ጸፈረ) ጐደፈረ፤ ማሰ ቈፈረ፤ ጫረ ሟጨረ ጐፈጨረ፤ ያውሬ፤ ዐከከ ፎከተ፤ የሰው። የደጐጸና የጸፈረ ዘር ነው።
ጎፍ [1]፡-(ትግ። ዕብ ጉፍ) ህላዌ ጠባይዕ፤ ገላ ግዘፍ፤ ሥጋ ሬሳ፤ የሚታይና የሚዳሰስ ማናቸውም ግዙፍ ነገር ኹሉ። ገፋፋ ጐፋፋ ጕፋያ ማለት ከዚህ ወጥቷል።
[2]፡-ሀላዌ፤–ገወፍ።
ጓ ፡-(ንኡስ አገባብ) እኮን ቢያ፤ ማ እንኳ ስንኳ። አንተሂጓ ተሠገርከ ከማነ። አንተስጓ ሀሎከ ምስሌየ። ከለባትኒጓ ፡-(ኢሳ፲፬ ፡-፲። ሉቃ፲፭ ፡-፴፩። ፊልክ ፡-፫። ማቴ፲፭ ፳፯)።
ጓሕለወ ፡-(ይጓሐሉ ይጓሕሉ) ሸነገለ አታለለ፤ ዋሸ ዐበለ፤ ከዳ ተተነኰለ። ወዘኢጓሕለወ በልሳኑ። ወጓሕለዉ በልሳናቲሆሙ ፡-(መዝ፲፬ ፡-፫። ሮሜ፫ ፡-፲፫)። ብዙ መጽሐፍ ግን በጓሕለወ ፈንታ ተጓሕለወ ይላል ፡-(ዘኍ፳፭ ፡-፲፰። ፍ ፡-ነ ፡-፳፱ ፡-፴፮)። አሐውርኑ በተጓሕልዎ ወበተጠብቦ ፡-(ዮሴፍ)።
ጓሕላዊ ፡-(ዊት ውያን ያት) የሚሸነግል የሚያታልል፤ ሸንጋይ አታላይ፤ ዋሾ ዐባይ፤ ዐላዊ ከዳተኛ ተንኰለኛ ፡-(አፈ ፡-ተ፳፫)። መጽሐፍ ግን በጓሕላዊ ፈንታ ጕሕልያ እንደ ማለት ጕሕላዊ ይላል፤ አያሰኝም። ብእሴ ደም ወጕሕላዊ። እስመ ውእቱ ብእሲ ጕሕላዊ። ሰይጣን ሐሳዊ ወጕሕላዊ ውእቱ። እኩያን ወጕሕላውያን ኖሎት ፡-(መዝ ፡-፭። ዮሴፍ። ፈ ፡-መ ፡-፳፫ ፡-፩። ዲድ ፡-፮። ሮሜ፩ ፡-፳፱)። ፪ኛም በጓሕላዊ ፈንታ ጕሕልው ይላል፤ ስሕተት ነው። መስተመይናን ወጕሕልዋን ፡-(አፈ ፡-ድ፴፫)።
ጓልሕ ፡-ድሪ፤ ቅንጥ፤ የአፍኣ። ወይም የውስጥ መገላለጥ።
ጓያ ፡-በቁሙ፤ የታወቀ ያበባ እኽል፤ እግርን ከጕልበት በታች የሚሰብር የሚያወጫምድ፤ የሚያስነክስ የሚያሽመደምድ። ፡-(ተረት) አህያና ጓያ ባምሳያ።
ጓጓ ፡-ጋጋኖ፤ እኅወ ቀቀኖ። የጥንብ አሞራ፤ እንደ ጋጋኖ በዝቶ ተንጋግቶ የሚኼድ።
No comments:
Post a Comment