~ዐ~

                                 

-ዐሥራ ስድስተኛ ፊደል በግእዝ አልፍ ቤት በአበገደ፤ ስሙ ዐይን፤ ቍጥሩ ሰባ፤ አኃዝ ሲኾን ሰብዓ ይባላል።

ዐህ -አዬአህ።

ዐለስ -(ዐረብ) ዐጃ የስንዴ ዐይነት፤ ፍሬው ቀጫጭን፤ ቅንጣቱ ቀጠጦ እንደሚባል ማሽላ በያንዳንዱ ቂንድ መንታነት ያለው ጣዕሙና መልኩ የስንዴ ወገን ስለ ኾነ፤ መጽሐፍ በሥርናይ ፈንታ ዐለስ ይላል፤ የመላሽ ስሕተት ነው -(ሉቃ፳፪ -፴፩። ዲድ -፴፩) ሐንፈጸን ተመልከት።

ዐለቅት -(ዕብ ዐሉቃህ። ሱር ዓላቅታእ። ዐረ ዐለቀት) ዐልቅት፤ የትል ዐይነት፤ ከውሃ ከረግረግ የሚገኝ፤ የሚነክስ የሚጣበቅ ያዘ የማይለቅ፤ ደም የሚመጥ የሚመጠምጥ ውጋት፤ ቍርጥማት ያለበት ሰው እንዳጋሚና እንደ ዋጋምት የሚሻው የሚያስፈልገው ለዐለቅት ባቲ ሠላስ አዋልድ -(ምሳ፴ -፲፭)

ዐለየ -(ዐለወ) ወነጀለ፤ ሸፈተ፤ ዐሌ አለ እንቢ አለ ጠመመ፤ ለገመ። ወና ተወራራሾች ስለ ኾኑ በዐለወ ፈንታ ዐለየ ይላል ዐለዩ ወሜጡ ልቦሙ -(ግብ፯ -፴፱)

ዐለደ -አከማቸአልዶ አለደ

ዐሊው -ዐሊው፤ መፈጸም መምላት፤ መተው የሥራ የሹመት። መቅዳት መገልበጥ፤ መተርጐም መመለስ፤ ከመጽሐፍ ወደ መጽሐፍ ቋንቋ ወደ ቋንቋ። መጽሐፍ ግን በዐለወ ፈንታ ኹሉንም አዕለወ ይላል፤ አድራጊውን ባስደራጊ አንቀጽ እለ ዕለዉ ምግቦሙ በንጽሕ። አዕሉ ንከሰ ወንትሓሰብ ምግበከ -(ቅዳ -ዮሐ። ሉቃ፲፮ -) አንበበ ዘውስቴታ ወአዕለዋ ፈነውነ ለከ ዕሊወነ ብኒ መጽሐፈ ከመ ዕልዎ፤ ቀዳ። አስተሐመመ አዕልወቶ አዕለዋ ምልሳነ ጽርእ ኀበ ልሳነ ዐረቢ ወዘአዕለዋ ሕጹጽ ወኃጥእ -(ኩፋ -፰። ተረ - ሄርማ። ፊልክ አፈ -ወር -)

ዐሊው ዎት -ዐሊው፤ ዎት -(ዐለወ የዐሉ ይዕሉ ዐለየ ዕብ ዐዌል ሱር ዑል ዐረ ዓል) መቀበል፤ ማስተጋባት፤ የሰሙትን ዜማ መልሶ መጮኽ፤ መናገር የገደል የተራራ፤ የተመሪ የደብተራ ድምፀ ቃል ዘአድባር መፍርሃን እለ ያወሥኡ ወየዐልዉ ድምፀ በበይናቲሆሙ። ወአኮ ይባቤ አድባር -(ጥበ፲፯ -፲፰ ሕዝ፯ -)

 -መወንጀል መበደል፤ ልብን ሐሳብን ወደ ክፉ መመለስ፤ ውልን መሐላን ቃል ኪዳንን ማፍረስ፤ መሸፈት መሸፈጥ መክዳት መካድ ዐሎ ማለት ይህ ኹሉ የወንጀል ስልት ነው ዘዐለወ በወግዝ ዐለዉ ልቦሙ ከመ የኀልዩ ዐለዉ ሕገከ ዐለዉ ኪዳንየ። ዐለወ ሕዝበ እስራኤል እምቤተ ዳዊት ዐለወቶ ለምታ ዐለዎ ሴዴቅያስ ለንጉሠ ባቢሎን ልክሙ ተዐልዉኒ -(፩ዜና - -፯። ኢሳ፶፱ -፲፭። ዳን፯ -፲፩ ሆሴ፰ - ፪ዜና - -፲፱። ሢራ፳፫ -፳፫ ኤር፶፪ -፫። ማቴ፳፮ -፴፩)

 -ምክርን ትምርትን፤ መልክን ባይን መለወጥ፤ መገልበጥ። ዕልዋ እግዚኦ ለምክሩ። ይፈቅዱ ይዕልዉ ትምህርቶ እከዪሃ የዐልዎ ራእያ -(፪ነገ -፲፭ -፴፩። ገላ፩ -፯። ሢራ፳፭ -፲፯)

ዐላማ -(ትግሬ ዐለመት) በቁሙ፤ ምልክት፤ ባንዴራ። ንደቅን ተመልከት -(ዐማርኛ)

ዐላሞት -(ዕብራ) ንዋየ ማሕሌት፤ የበገና ስም አንድ ዐይነት በገና ባለስድስት አውታር ላዕለ ዐላሞት -(፩ዜና -፲፭ -)

ዐላዊ -(ዊት ውያን ያት) (ዊት ውያን ያት) ወንጀለኛ፤ እንቢተኛ፤ ሽፍታ፤ ለዋጭ፤ ገልባጭ፤ መላሽ። ዐላዌ ነጋሢ ወአዕመሮ ዐላዊ ዐላውያነ ጽድቅ -(ዮሐ፲፱ - ቲቶ፫ -፲፩ ሮሜ፪ -) በዐላዊ ፈንታ አዕላዊ ይላል፤ የተሳሳተ ነው። ወአዕላዊሁኒ -)

ዐልሎ ሎት -(ዐለለ ይዔልል የዐልል። ዕብ ዐላል ጽኑ ሥራ ሠራ) ማለል፤ ዐለላ ቀለም ማግባት መንከር ዘዘ ይልበሱ ክርስቲያን ወአይሁዳውያን ልብሰ ጸዐዳ ግሙራ፤ አላ የዐልሉ ብሶሙ በኒል -(ስንክ -ኅዳ፳፩)

 -መውገዝ፤ መለየት፤ ሕርም ማለት፤ ለገዳም ለቤተ ክሲያን ልት መጐለት። እምዘዐለልዎ። አዐልሎ ሎቱ ወለአህጉሪሁ -(ዘሌ፲፬ -፵፮። ዘኍ፳፩ -)

ዐልሞ ሞት -(ዐለመ ይዔልም የዐልም ዐረብ) ማለም ማመልከት ስምን መጣፍ ማተም፤ መፈረም። በቅድመ እለ ቆሙ ወዐሰሙ ውስተ ይእቲ መጽሐፍ -(ኤር፴፱ -፲፪)

 -ማስተማር፤ መስበክ፤ መንገር። አበው ናሁ ዐለሙ፤ ወሰመዩ ትሕትና በአስማት ሠናያት ወትእምርት ትርፍት -(ፊልክ -፻፶፪)

ዐልው ዓልዋ -(ጽር፤ አልዎይ። ዐልዋይ ዕብ ኣሃል። ዐረ ዑድ) ሽቱ፤ የሽቱ ስም፤ ዋግራ፤ ሬት። ከርቤ ወዐልው ዕፀው ዘዓልዋ -(ማሕ፬ -፲፬ ሔኖ፴፩ -፪። ዮሐ፲፱ -፴፱)

ዐልጋ -በቁሙ መተኛ፤ ትእምርተ ክብር

ዐልጌን -ተራዳ ረዥም ዕንጨት፤ የሰው መስቀያ። አዘዘ ርያኖስ ከመ ይስቅልዎ በዐልጌን ወይንድፍዎ በአሕጻ ወአልቦ ዘለከፎ -(ስንክ -የካ፳)

ዐልጎ ጎት -(ዐለገ ይዔልግ የዐልግ ዐረ ዐለጀ) ማሸነፍ መጣል ድል መንሣት፤ በላይ መኾን፤ የትግል የውጊያ። መሟጠጥ መጋጠጥ፤ ከሥሩ መቍረጥ፤ የኀፍረት። ትግሬ ግን ዐለገ ብሎ ሰወረ ደበቀ ይላል ምስጢሩ ኀፍረት ነው።

ዐመ ዐመመ -(ዐረ ዓመ ዕብ ዐሜም) ጠቈረ ጨለመ፤ አደፈ ጐደፈ፤ ደፈረሰ በዛ ጸና በረታ ጌመን እይ

ዐመፃ -ዐመጥ በደል፤ ግፍኀጢአት ክፋት ውሸት። ዐመፃ ወፅአት እመዛግብቲሃ ልህቀት ዐመፃ ዲበ ምድር በርተ ዐመፃ -(ሔኖ ኩፋ መዝ፲፫ -)

ዐሚቅ ቆት -(ዐመቀ የዐምቅ ይዕምቅ። ዕብ ዐማቅ። ዐረ ዐሙቀ) መታመቅ፤ ዕሙቅ መኾን፤ መጐድጐድ፤ መጥለቅ፤ መሰወር መራቅ፤ ከመታየትና ከመታወቅ። እስከ የዐምቅ ምድሩ የዐምቅ ምነ ቀላይ ምክራ እምቅድመ ይዕምቁ ቀላያት ምቅድመ ይዕምቅ ባሕር -(ገድ -ተክ። ራ፳፬ -፳፱ ቅዳ -አፈ መጽ -ምስ)

ዐማኑኤል -(ጽር ሄማኑኢል ዕብ ዒማኑኤል) የሥግው ቃል በኩነት በተዋሕዶ የተሰጠው ዒማኑ ምስሌነ ኤል አምላክ በተገናኝ አምላክ ምስሌነ፤ ወይም ምስሌነ አምላክ። አምላክ ጋራ -(ማቴ፩ -፳፫ ኢሳ፯ -፲፬) ሊቃውንት ግን አምላክ ወሰብእ ብለው የምስጢር አፈታት ይፈቱታል። ዐማኑኤል ዘበትርጓሜሁ አምላክ ወሰብእ ስመ ውእቱ ምላክ በመለኮቱ ወሰብእ በትስብእቱ ዘነሥኦ ወዝ ስም ውእቱ ዐማኑኤል ዐቢይ ጥቀ ወኢይደሉ ፈሊጦቱ ወውእቱ ዘበአማን ምስጢር ለጽንቦዐ ሃይማኖት -(ሃይ -አበ -ቴዎዶ ዘው ሳዊ -ዘአን) ኢየሱስን ተመልከት።

ዐማዲ -የሚደግፍ፤ ደጋፊ፤ የሚያቆም የሚያጸና። ዐማዴ ሰማይ ወምድር -(ሊጦን)

ዐማፂ -(ፂት ፅያን ያት) ዐመጠኛ፤ በደለኛ ክፉ ዋሾ። ዐማፂ ወጽልሕው። ዐማፅያነ ጸላእኩ -(መዝ -፻፲፫ ፻፲፰)

ዐም -(ዕብ) ሕዝብ ነገድ፤ ብዙ ሰው ቋንቋውና ሕጉ ግዛቱ መንግሥቱ አንድ የኾነ ጉባኤ ሰብእ ማኅበረ ሰብእ።

ዐምሐራ [1]:-ዐማራዐመመ።

[2]-(ዐም ሐራ) ዐማራ ሕዝብ፤ ነጻነት ያለው ባለነጻ፤ ግዑዝ አግዓዚ ሐረረን ተመልከት ወኮነ በምድረ ዐምሐራ -(ገድ -ተክ)

ዐምሐራይ -ያማራ ወገን፤ ልሳን ቋንቋ፤ ዐማርኛ፤ ከዐረብና ከዕብራይስጥ ግእዝ ከአራም የወጣ።

ዐምበር -ሽቱዐንበር።

ዐምዓም [1]-(ዐረ ዐም፤ ጅም ቀምቃም፤ ድፍርስ ግም እድፍ ውሃ) ውሃማ ቦታ፤ ማጥ ረግረግ፤ ጭቃው የሚውጥ የሚያሰምጥ። ጽቡረ ዐምዓም። ውፅአኒ ምውስተ ዘቅተ ዐምዓም። ዐምዓሙሰ ወዐዘቅቱ ዐምዓመ ኀጢአት -(ኢሳ፲፬ -፳፫ መዝ -፴፱። ሮክ። ሕዝ፵፯ -፲፩ ግንዘ)

[2]:-ረግረግ፤ዐመመ።

ዐምዳዊ ዘዐምድ -የዐምድ እንደ ዐምድ ቁሞ፤ በዐምድ ራስ ላይ ማማ ሠርቶ ወይም ካምዱ ጋር ታስሮ ተቈራኝቶ የሚኖር ስምዖን ዐምዳዊ። ጋቶን ዘዐምድ -(ፊልክ -፵፮ ስንክ -መስ፲፬)

ዐምድ -(ዕብ ዐሙድ ሱር ዓሙዳእ ዐረ ዐሙድ ዒማድ) በቁሙ፤ ዋና፤ ቀዋሚ፤ ተሸካሚ፤ ድጋፍ፤ ባላ፤ ምሰሶ ወጋግራ ተራዳ፤ ቅልጥም አገዳ፤ ጣዖት፤ ሐውልት፤ የመጽሐፍ ገጽ። ዐምደ ኀጺን። ዐምደ ሰኖባር። ዐምደ መር ዐምደ ጾም፤ ዘውእቱ ርብዓ ዕለት ዐምዳ ወአብራዒሃ ዐምደ ሀገረ ፀሓይ -(ኤር፩ -፲፰ ስንክ -ሐም - -፳፬። አቡሻ -፳፯ ዘፀ፳፭ -፴፩። ኤር፶ -፲፫) ሉሕ ጠርብ ሳንቃ ሰሌዳ በማለት ፈንታ ዐምድ ይላል ቀዋሚነቱን ሲያይ -(ዘፀ፳፯ -፳፫፳፬)

()          ዐምዶ ዶት -(ዐመደ ይዔምድ የዐምድ ዕብ ዐማድ፤ ቆመ ቀጥ አለ) መደገፍ፤ ማስደገፍ፤ ማቆም ማጽናት፤ ማሸራሸት፤ እንዳይወድቅ እንዳይነቃነቅ ማድረግ ረበቦ ከመ ሠቅ ወበነፋስ ዐመዶ በኪኑ ዐመዶ ሰማይ በነፋስ። ይዌስን በኆጻ ወይዔምድ በነፋስ። ዘዐመድካ ለምድር በሥላሴከ -(መቃ ቅዳ ግሩ ድጓ) ባለቅኔዎች ግን ፈጠረ ብለው ይጨምሩበታል።

ዐምፆ ዖት -(ዐመፀ ይዔምፅ የዐምፅ ዕብ ሐማስ ሐሜጽ) ማመጥ፤ መሸፈት፤ መበደል፤ ክፉ መኾን፤ ግፍ መሥራት፤ መስረቅ መቀማት። ኢዐመፅነ ኪዳነከ ይዔምፅኑ እግዚ ወዐመፅክሙ ዐስቦሙ -(መዝ -፵፫። ሮሜ፫ -፭። ያዕ፭ -)

ዐሰረ [1]:-በቁሙአሲር አሰረ።

[2]:-ቀጠረ፤ዐሥሮ ዐሠረ

ዐሠር -ፍለጋአሠረ።

ዐሠርቱ -(የወንድ) ዝኒ ከማሁ፤ ዐሥር፤ ዐሥሩ፤ ዐሥረኛው፤ አርቲክል ነው። ርፉ ዐሠርቱ ዐሠርቱ ወአሐዱ። ዐሠርቱ ምእት ዐሠርቲሆሙ -(ዓሞ፮ -፱። ዘካ፩ -፯። መዝ -፻፬ ሱቱ -ዕዝ፫)

ዐሠቀ -ሠራ፤ዐስቆ ዐሰቀ።

()           ዐሰበ -(ዕብ ዐዛብ) ተወ ለቀቀ ጣለ የያዘውን የተከራየውን፤ ሚስት ገረድ።

ዐሠየ -ዋጋ ሰጠ፤ዐስይ ዐሰየ

ዐሡር [1]-ቀጠሮ የቀጠሮ ቀን ጊዜ ሰዓት ሶበ በጽሐ ዐሡር -(ሉቃ፲፬ -፲፯)

 [2]-ዐሥር ዐሥረኛ፤ የዕለት ቅጽል ምድኅረ ዐሡር ዕለት። በዐሡር ሠርቅ። ዐሡረ ወረቡዐ መዋዕለ ዐሡረ ት። ጾመ ዐሡር -(ኤር፵፱ -፯። ፶፪ -፬። ጦቢ፰ -፲፱ ዳን፩ - ዘካ፰ -፲፰)

ዐሳቂ መዐስቅ -ልብስ የሚሠራ ጥበብ ድርብ ሠሪ፤ ሸማኔ ጠላፊ ሠርዌ ዐጥፍ ዘመዐስቃን -(፪ነገ -፳፩ -፲፱ ስንክ -ታኅ፳፫)

ዐሳብ ዕሱብ ምንደኛ ሙያተኛ ደሞዘኛ ቶፋ። ዐሳብ ዘለለ ዕለት። ወዐሳብሰ ይጐይይ ስመ ዐሳበ ውእቱ። ተዐሳቢ ወዐሳብ (ኢዮ፯ ፩። ዮሐ፲ ፲፫ ፴፮)

ዐሳቢ -የሚከራይ፤ ደመ ወዝ ሰጪ በዐሳቢ ፈንታ ተዐሳቢ ይላል -( - -፴፮)

ዐሳባዊ -የክራይ፤ የሙያ፤ ሙያተኛ፤ ባለደመ ወዝ ተክለ ሃይማኖት ሐዱ ምዐሳባውን ዘሠርክ -(ደራሲ። ገድ -ኪሮ። አፈ -ተ፲፪)

ዐሳዪ -የሚሰጥ ሰጪ፤ ቸር ለጋስ፤ እጀ ፊ፤ ዐዳይ አሳላፊ። ወፈጺሞ ውእቱ ኮነ ዐሳዬ ሕይወት ለኵሎሙ እለ ይትኤዘዙ ሎቱ -(ዕብ፭ -)

ዐሥሩ -(የሴት) ዐሥር -( ) የቍጥር ስም፤ መዠመሪያ ቀመር ያንድ ቤት ፍጻሜ፤ የዘጠኝ ተከታይ፤ በዘጠኝና በካያ መካከል ያለ ቍጥር፤ ካንድ እስከ ዘጠኝ ያሉትን አኃዞች በመጫፈርና በመናበብ እስከ ኻያ  ድረስ የሚዘምት አርቲክል ኹኖ በቁሙ ይፈታል። ያበስላ ዐሥሩ ንስት ኅብስትክሙ በአሐዱ እቶን። ዐሥሩ መካልየ ብሩር ዐሥሮን ቃላት ዐሥሮን ደናግል ዐሥሩ ወአሐቲ -(ዘሌ፳፮ -፳፮ ጦቢ፬ - መጽ -ምስ። ማቴ፳፭ -፩። ራእ፳፩ -)

ዐሥሮ ሮት -(ዐሠረ ይዔሥር የዐሥር ዕብ ወሱር ዐሣር ዐረ ዐሸረ) ዐሥር ማድረግ፤ ዐሥራት ማውጣት፤ ካሥር አንድ መስጠት ወይም መቀበል፤ መውሰድ ዐሠረ ምኵሉ ከመ የዐሥር ዐሥሮ። ፈጸምከ ዐሥሮተ ኵሉ ዐሥራት። ዐሥራተ ይዔሥር -(ኩፋ -፴፫። ዘዳ፳፮ -፲፪ መቃ)

 -መጥራት ኑልኝ ማለት ማደም፤ መቅጠር ዐዋጅ መንገር ሕዝብን ሰራዊትን መሰብሰብ፤ ማከብ በልዎሙ ለእለ ዐሠርናሆሙ። ገብረ ምሳሐ ዐቢየ ወዐሠሮሙ ብዙኃን። ዐሥሩ ጸብአ -(ማቴ፳፪ - -፰። ሉቃ፲፬ -፲፮፲፯ ዮኤ፫ -)

ዐስቅ -ጥሩ ግምጃ፤ ክቡር ልብስ፤ ዝንጕርጕር፤ ባላራት ሕብር ወርቀ ዘቦ፤ የተጌጠ የተሸለመ። ክዳን ዘሕብረ ዐስቅ። አልባስ ዘተገብረ በዐስቀ ሜላት አልባሰ ወርቅ ወአልባሰ ዐስቅ -(ዘፍ፴፯ -፫። ሢራ -፲። ኢሳ፫ -፳፫)

ዐስቆ ቆት -(ዐሰቀ ይዔስቅ የዐስቅ ዕብ ዐሻቅ ነፈገ ጨበጠ በውድ ሼጠ) መሥራት፤ መታታት፤ መጥለፍ ማቈላለፍ፤ ልብስን በብዙ ዐይነት ፈትል በወርቀ ዘቦ ማስጌጥ፤ ማንቈጥቈጥ እንዲያምር እንዲከብር በውድ እንዲሼጥ ማድረግ፤ የሰፊ የሸማኔ

ዐስብ -በቁሙ የጕልበት ዋጋ ደመ ወዝ ምንዳ ክራይ፤ ወይም ክርካር። ምንት ውእቱ ዐስብከ ሀቦሙ ዐስቦሙ ዐስበ ሐመር -(ዘፍ፳፱ -፲፭ ማቴ፳ -፰። ስንክ -ነሐ፴)

ዐስቦ ቦት -(ዐሰበ ይዔስብ የዐስብ ዐረ ዐሰፈ) ዐስብ ክራይ መስጠት፤ የጕልበት ዋጋ መክፈል መከራየት መዋዋል፤ መሰማማት በቍርጥ መግዛት። ዐሰበኒ ወኮንክዎ ካህነ። ወዐሰብዎ ለሶርያ። ዐሰቡ ሰብአ ዕሌየ። ተዐስብዎ ለነሃቢ -(መሳ፲፰ -፬። ፪ነገ - -፮። ፪ዕዝ - -፲፪። ኢሳ፵፮ -) በዐሰበ ፈንታ ተዐሰበ ይላል፤ የተሳሳተ ነው ዐሰብኩ በዐሠርቱ ወኀምስቱ ጠፋልሐ ብሩር። ዘተዐሰበ ዐጸደ ለለ ኵሉ ውራኅ በዲናር ወኢያእመረ ኍልቈ ሎን ውራኅ ይከውኖ ተዐሳቢ እምድኅረ አሐዱ ወርኅ ከመ ያብጥል ሥርዐተ ተዐስቦ ረከበ ሐመረ ወተዐሰበ -(ሆሴ፫ - - -፴፮። ዮና፩ -)

()          ዐስይ ዮት -(ዐሰየ የዐሲ ይዕሲ። ዕብ ዐሳህ ገብረ) ዋጋ መስጠት ማደል መክፈል፤ ብድር መመለስ፤ አብዝቶ አትርፎ ልክ አሳልፎ እሺ ማለት ንዘ ተዐሲ ዕሴተ ሠናየ ምንተኑ ዐስዮ ለእግዚ በእንተ ኵሉ ዘገብረ ሊተ ዕስዮ ገብርከ ዘየዐሲ እኩየ ህየንተ ሠናይ የዐስየከ ቅሥተ ወተስናነ በንዋይከ -(ቅዳ። መዝ -፻፲፭ና -፲፰ ምሳ፲፯ -፲፫ ሢራ፳፱ -)

ዐረር -(ሐረር፤ ሐረረ። ዕብ ዖፌሬት ሱር አባራ ዐረ ረጻጽ) በቁሙ ርሳስ፤ የማዕደናት ወገን፤ ጥቍር ከባድ፤ ልሕሉሕነት ያለው፤ ከቀለሕ ጋራ የሚጠየት ዘሩ ሐሪር ነው ለዐ ተለውጧል ናእከን ተመልከት ተሰጥሙ ከመ ዐረር ውስተ ማይ መክሊተ ዐረር ምንት ይከብድ እምነ ዐረር -(ዘፀ፲፭ -፲። ዘካ፭ -፯። ሢራ፳፪ -፲፬)

ዐረቀ -(ዕብ ዐራቅ) በቁሙ፤ -(ጥረ) ዐረቀ አጐበጠ አጠመመ፤ ቀለሰ አስጐነበሰ ቀናውን የሙጭ የደጋን የከዘራ የመሰለው ኹሉ። አቀና፤ አረታ፤ ቀጥ ለጥ አደረገ፤ አስተካከለ ጐባጣውን ሰፈረ መጠነ በማለት ፈንታ ዐረቀ ይላል፤ የመላሽ ስሕተት ነው -(ሕዝ፵ -)

 -አስታረቀ፤ አሰማማ፤ ዑቁ ፍጡነ ዕርቅዎሙ ወግበሩ ሰላመ ማእከሎሙ ወዐረቀ ትዝምደ ሰብእ ምስለ እግ ካህናቲሁ ለአብ ፍቅረ ለነ ቡከ ገበርከ ወዐረቀ ማእከሌነ ዕርቅ ወአርትዕ ጠዋየ -(ዲድ -፲ና -፴፫። ኪዳ። ኢሳ፶፰ -)

ዐረቅ -(ዐረብ) ወዝ ላበት የደም ዐረቂ የሚያሰክር መጠጥ ከበለስ ወይን ሌላም ትክልት የሚወጣ ወዳጁን ገዳይ ጠላቱን ፈሪ ያጩን አክባሪ።

ዐረቢ -ዐረብኛ፤ የዐረብ ቋንቋ፤ የግእዝና የዕብራይስጥ የሱርስት ወንድም። ወእምዐረቢ ለግእዝ ልሳነ ቅብጢ ወዐረቢ -(ሃይ -አበ። ስንክ -መስ፬ ታኅ፳፱)

ዐረባዊ -የዐረብ ወገን መጽኡ ዐረባውያን -(ስንክ -ሚያ፱)

 -ምዕራባዊ፤ ዘምዕራብ። ነፋስ ዐረባዊ -(ሢራ፵፫ -፲፯ ራእ፳፩ -፲፫)

ዐረብ [1]-(ዕብ ዐራባ) ሜዳ፤ ምድረ በዳ ሣር ዕንጨት የሌለው፤ የዮርዳኖስ ማዶ ወረዳ፤ ከጥብርያዶስ እስከ ባሕረ ያለ በረሓ መንገለ ዐረባ ሞአብ -(ዘኍ፳፪ -፩። ዘዳ፩ -፩። ኢያ፭ - ዮዲ፩ -)

[2]-(ዕብ ዔሬብ) ሠርክ፤ ምሴት፤ ማታ፤ ድግዝታ፤ ጭልምልምታ፤ የመዓልት ጫፍ የሌሊት ሥር መዠመሪያ፤ ሰው እስኪከተት ዥብ እስኪያኰተኵት ያለው ጊዜ ተኵላተ ዐረብ እለ ያበይቱ ለነግ -(ሶፎ፫ -፫። ዕን፩ -፰። ስንክ -ታኅ፳፱) ብራይስጡ ግን፤ ዝኤቤይ ዔሬብ ይላል የማታ ዥቦች ማለት ነው

 [3]-(ዕብ ዐሮቤት ሱር ዐሩብታ) ስመ ዕለት፤ ስድስተኛ ቀን፤ በኀሙስና በቀዳም መካከል ያለ የፍጥረት የሥራ የመና ፍጻሜ፤ መካተቾ፤ ድራረ ሰንበት፤ ዋዜማ ቅበላ ማለት ነው ወኮነ ሳድስተ ዕለተ እመ ዕለ ዐርብ። ወበሳኒታ እንተ ይእቲ ምድኅረ ርብ። ዕለተ ዐርብሰ ወሰንበት -(ዘፍ፩ -፴፩። ዘፀ፲፮ - ፳፪ ማቴ፳፯ - - -፲፭)

[4]-ስመ ነገድ የነገድና የቋንቋ ስም ብሔረ ዐረብ ተተርጐመ እምልሳነ ቅብጢ ዐረብ -(ገላ፬ -፳፭ ሃይ -አበ፩)

ዐረቦን -(ዕብ ዔራቦን) በቁሙ መያዣ፤ ፈለማ፤ መዠመሪያ፤ የስጦታ ድራር የጸጋ ዋዜማ፤ ከብዙውና ከፍጹሙ ታላቁ ዋጋ በፊት የሚሰጡት፤ የሚቀበሉት ወሀበነ ዐረቦነ መንፈስ። ዘውእቱ ዐረቦነ ርስትነ ዐረቦን ዘፍኅረት -(፪ቆሮ -፳፪ -፭። ኤፌ፲ -፲፬ - -፳፬ -፫። ፴፫)

ዐረዘ -(ዕብ ሄራዜ) በቁሙ፤ ከሳ ቀጠነ መነመነ ለሰለ አነሰ ኰሰሰ፤ ሣሣ እንጀራ ዐርዟል፤ ወጥ ዐርዟል፤ ጭ፣ጨምሩ እንዲሉ። ግስነቱ ያማርኛ እንጂ፤ የግእዝ አይዶለም።

ዐረየ -ለቀመ፤አርይ አረየ

ዐረፈ -(ዐረብ ዕብ ዐራፍ ፈሰሰ ወረደ ነጠበ መልቶ) ቀዳ፤ ጨለፈ ጠለቀ።

ዐረፍት -ግድግዳ፤አረፈ አረፍት

ዐሪሥ -(ዐረ ዐሪሽ ዐሪሥ) የወይን ዳስ የዳስ ዐይነት ድንኳን። ወገብረ ዐሪሠ ውስተ ናሕሰ ቤት -(ዮዲ፰ -) ባለብሉዮች ግን ጐዦ ምግላል ቦታ፤ የጾም በኣት ይሉታል።

ዐሪስ -ዳሰ ወይንዐሪሥ

ዐሪቅ ቆት -(ዐርቀ የዐርቅ ይዕርቅ ዕብ ዐራህ ዐረ ዐሪየ) መራቈት፤ መገፈፍ መገለጥ፤ ባዶ መኾን፤ ብቻ መቅረት። ዐረቁ ወአልበስክሙኒ ዝቃተ ወይንነ ዐርቀ ወበልየ ዐርቀ ኵሉ ህጉር። ዐርቀት ንተ ሰብዐተ ወለደት -(ማቴ፳፭ -፴፮። ኢያ፱ -፲፩ ኤር፬ -፳፱ ፲፭ -) በዐርቀ ፈንታ ተዐርቀ ይላል፤ አያሰኝም። ትሰክሪ ወትትዐረቂ ቀሲስ ለእመ ሰክረ ወተዐርቀ ባሉ በቅድመ ሰብእ ተዐርቁ ምሠናያት ዘተውህቦሙ ተዐርቀት ሀገር ምነ ዕደው ከዋክብት ምዕበየ ብርሃኖሙ ዐርቁ -(ሰቈ፬ -፳፩ - - -፭። አፈ -ድ፳፪ ዮሴፍ። ቅዳ -ጎር) መላብ መውዛት ዐረቂ ማውጣት።

ዐሪብ ቦት -(ዐርበ የዐርብ ይዕርብ ዕብ ወሱር ዐራብ ዐረ ዐረበ) መምሸት፤ ሠርክ መኾን፤ መውረድ መዘቅዘቅ፤ መግባት መጥለቅ፤ የፀሓይ። እስከ የዐርብ ፀሓይ ወሶበ ዐርበ ፀሓይ። ዘእንበለ ይዕርብ ፀሓይ -(ጦቢ፪ - -፯። ኤፌ፬ -፳፮)

 -መነገድ፤ መሼጥ መለወጥ፤ መተካት፤ ሸቀጥን ካገር ወዳገር ማውጣት ማግባት መውሰድ ማምጣት

ዐሪክ ኮት -(ዐረከ የዐርክ ይዕርክ። ዕብ ዐራኽ) መሰደር፤ መደርደር፤ ማነጣጠር በያምሳያውና በያኳያው ማኖር ፊት ለፊት ጐን ለጐን ወይም ላይና ታች

ዐሪዝ ዞት -(ዐረዘ የዐርዝ ይዕርዝ። አው፤ ዐርዞ ይዔርዝ) ማልበስ፤ ልብስ መስጠት። ይሴስያ ወይዔርዛ። ይዔርዙኒ ልባስየ ወመዋጥሕየ። ውፅአ ሎሙ ዘይዔርዞሙ። አልባስ ወክዳናት ዘዐረዘቶን ዶርቃስ -(ቀሌ። ሆሴ፪ -፯። ፬ነገ - -፳፪ ግብ፱ -፴፱)

ዐሪግ ጎት -(ዐርገ የዐርግ ይዕርግ ዐራግ ፈተወ) ማረግ፤ ከፍ ማለት ከታች ወደ ላይ ወደ ሰማይ መውጣት ለዐለን ተመልከት፤ የዚህ ጎረ ቤት ነው። ርቱዐ የዐርግ ምነ ምድር ዐርገ ናሕሰ ዐርገ ደብረ ዐርገ ሰማየ -(፩ነገ -፳፰ -፲፬ ግብ፲ -፱። ሉቃ፱ -፳፰ ፳፬ -፶፩)

 -መንቃት፤ መነሣት፤ መታሰብ፤ መውጣት መውረድ መብቀል፤ የኅሊና የዐጽቅ። ውስተ ብእ ዘኢተኀለየ ወኢዐርገ ዐርገ ዲበ ኅሊናሁ ይግበር ለምንት ዘከመ ኅሊና የዐርግ ውስተ ልብክሙ። ትወፅእ በትር ምሥርወ እሴይ ወየዐርግ ዐጽቅ ምጕንዱ -(መስተ። ፪ዜና -፳፬ -፬። ሉቃ፳፬ -፴፰። ኢሳ፲፩ -)

 -በመጽሐፍ በልብ መጣፍ፤ መቈጠር፤ ከቍጥር መግባት የክፋ የበጎ። ኢየዐርግ ውስተ መጽሐፈ ሕይወት። ወኀጢአት ተዐርግ በእንቲኣሁ ውስተ መጻሕፍት -(ኩፋ -፴፮ -፴፱)

ዐሪፍ ፎት -(ዐረፈ የዐርፍ ይዕርፍ። ዕብ ራፋህ፤ ደከመ ዛለ ዐረፈ ዐረ ረፋ፤ አሳረፈ) ማረፍ፤ መተንፈስ፤ ጸጥ ማለት፤ አለመታወክ ቦታ ይዞ መቆም መቀመጥ መደገፍ መተኛት፤ መሞት ማንቀላፋት፤ ሀድአንና ንህየን ተመልከት። መጽሐፍ ግን በዐረፈ ፈንታ አዕረፈ ይላል አያሰኝም። ዕረፈ እምኵሉ ብሩ ያዕርፉ ምጻማሆው። እነብብ ከመ ኣዕርፍ። አዕረፈት ድር እምነ ቀትል። አዕረፈት ታቦት ዲበ ርእሰ ባር ወአዕርፉ ወአዕረፈ ምስለ በዊሁ አኀዊክሙ እለ ዕረፉ በሃይማኖተ ርስቶስ -(ዘፍ፪ -፪። ራእ፲፬ -፲፫። ኢዮ፴፪ -፳። ኢያ፲፩ -፳፫ ኩፋ - ማቴ፳፮ -፴፭። ሢራ፵፯ -፳፫ ዲድ -፴፬)

ዐራቂ -የሚያርቅ የሚያስታርቅ፤ አስታራቂ ዐራቂ ዘይፈቅድ ይዕርቅ ዐራቄ ኪዳን ሐዲስ ከዊነ ዐራቂ -(አፈ -ድ፴፫ - -፳፬ -)

ዐራቅይና -ዐራቂነት፤ አስታራቂነት በዐራቅይናሁ ለሊቀ ካህናት በእደዊሆሙ ወበዐራቅይናሆሙ -(አፈ -ድ፴፫ ማር -ይሥ፩ -)

ዐራቦት -(ጽርእ ዕብ ዐራባ) ረሓ ዐረብን ተመልከት ዚህ ጋራ አንድ ነው ወፅ ንተ ዐራቦት -(፬ነገ -፬ና -)

ዐራት ታት -(ዕብ ሚጣ ዔሬሥ ሱር ዓርሣ) ዐልጋ፤ መተኛ፤ መጋደሚያ፤ ቈጥ፤ የሬሳ ማንሻ፤ አራት እግር ያለው። አርባዕቱን አራት ማለት ዐማርኛው ከዚህ የወጣ ነው ዐራት ዘወርቅ ስርግው በባሕርይ። ዐራተ ጺን ዐራተ ሕማም ዐራታት -(ዮሴፍ። ስንክ -ግን፲፱ መዝ -፵። ፪ነገ -፲፯ -፳፰ ማር፮ -፶፭)

()           ዐራዝ -(ዛት) ልብስ፤ የውስጥ ቀሚስ፤ ገላ ነክ። ሲሳየነ ወዐራዘነ ተካፈሉ ልባስየ ወተዓፀዉ ዲበ ዐራዝየ ሙሴ ረሰየ ጽለ ሆሳዕና ዐራዞ አልባስ ወዐራዛት -(፩ጢሞ - -፰። መዝ -፳፩ ስንክ -መስ፫ - - -)

ዐራጊ -የሚያርግ፤ የሚወጣ። ኤልያስ ዐራጌ ሰማያት -(ስንክ -ታኅ፩)

ዐርሞን -የተክል ዕንጨት ስም ኤላጤን እይ፤ ከዚህ ጋራ ነው። አክዋል ዘዐርሞን -(መቃ -ገ፫ ድጓ።

ዐርብ -(ዕብ ዐሮቤት ሱር ዐሩብታ) ስመ ዕለት፤ ስድስተኛ ቀን፤ በኀሙስና በቀዳም መካከል ያለ የፍጥረት የሥራ የመና ፍጻሜ፤ መካተቾ፤ ድራረ ሰንበት፤ ዋዜማ ቅበላ ማለት ነው ወኮነ ሳድስተ ዕለተ እመ ዕለ ዐርብ። ወበሳኒታ እንተ ይእቲ ምድኅረ ርብ። ዕለተ ዐርብሰ ወሰንበት -(ዘፍ፩ -፴፩። ዘፀ፲፮ - ፳፪ ማቴ፳፯ - - -፲፭)

ዐርቦት -(ዕብራ) ኵሓ ችባሓ ወንዝ ድምቅ፤ የመሰለው ኹሉ ቄዳር ዘስሙ ዐርቦት -(ኩፋ -፳፩)

ዐርኬ -የስንክሳር መርገፍ ምስጢሩ ያነኑ እናቱን የሚመስል።

ዐርክ ዓርክ -(ክት ካን ካት) ወዳጅ፤ ባለሟል፤ ባልንጀራ፤ ዐብሮ አደግ፤ እኩያ አምሳያ፤ ጓደኛ ቤተ ሰብ፤ ሎሌ ገረድ፤ መንፈሳዊ ዘመድ፤ የጡት ያደራ የክርስትና ልጅ አበ ልጅ ብርሃም ዐርከ እግ ዐርክ ምእመን ዘወድቀ ዐርክ ምስለ ዐርክቱ። ዐርካነ እግዚእ ዐርካት ዘጥምቀተ ከርስትና -(ኩፋ -፲፱ ራ፮ -፬። ቄድር ቅዳ -ግሩ - -፵፰)

ዐርዝ -ዛፍ፤አርዝ።

ዐርይ -(ዐረየ ይዔሪ ይዕሪ) ገቢርና ዐጕል። መደልደል፤ ማስተካከል፤ ቀጥ ለጥ ማድረግ ጺሑ ፍኖቶ ወዐርዩ መጽያሕቶ ከመ ተዐርዩ በ። ዐርዮ ግዕዝ። እስመ ኮነ ዐርዮ በማእከሎሙ -(ኢሳ፵ -፫። ፩ጴጥ - -፰። ሄርማ ኩፋ -፴፮)

 -መምሰል፤ መተካከል፤ ትክክል መኾን እስመ መልክእ ይዔሪ ለመልክኡ፤ ወአርኣያ ለአርኣያሁ ይምላእ ኵሉ ማዕምቅ ወይዕሪ ምድር ወይዕሪ ፍኖት መብእስ። እስከ ይልህቅ ወይዔሪ ጽሕምክሙ ይዔሪ መዓልት ወሌሊት ዕሥራ ወኀሙሱ ለመጋቢት ኵሉ ዐረየ ወኅቡረ ዐለወ -(ባሮ፭ -፯። ሉቃ፫ -፭። ፩ዜና -፲፱ -፭። ዲድ -፴። መዝ -፲፫)

 -ማበር፤ መተባበር፤ መሰማማት፤ አንድ መኾን። ማከሩ ኅቡረ ወዐረዩ ኢይዔርዩ ምክር ሠናይ ወምስለ ብሉይ የዐሪ -(መዝ - ኪዳ ሉቃ፭ -፴፮)

ዐቀባት -እሾኾች። እከይድ ሥጋክሙ ምስለ ዐቀባት -(መሳ፰ -፯ና -፲፮)

ዐቀብ -(ዕብ ዐቆብ ዐረ ዐቀበት) በቁሙ፤ ዳገት፤ ዐቀበት ቍልቍለት፤ የተራራ መንገድ ጠማማ ስያፍ ቀጥታ የሌለው፤ ግድምና ሽቅብ የሚወስድ መውጫ መውረጃ በውስተ ዐቀባ ለሉዊት አህጉር እለ ውስተ ዐቀብ። ወዐርጋ ዐቀበ ቤጤሌዋ። ዐቀበ ሙራደ ዐቀብ -(ኢሳ፲፭ -፭። ዮዲ፮ -፯። ፲፫ - ሢራ፳፭ - ሉቃ፲፱ -፴፯)

ዐቍር ሮት -(ዐቈረ የዐቍር ይዕቍር ዕብ ዐቃር ነቀለ) ማቈር፤ መቋጠር፤ ማኖር መክተት፤ መሸጐጥ፤ መታቀፍ የዐቍሮ ማይ በደመናሁ። ወአሰርዎ ዐቍሮሙ ኵሎ ወርቀ። መኑ የዐቍር እሳተ ውስተ ሕፅኑ -(ኢዮ፳፮ -፰። ፬ነገ -፲፪ - ምሳ፮ -፳፮)

ዐቍን ኖት -(ዐቈነ የዐቍን ይዕቍን። ዐረ ሐቀነ፤ ዐጀነ) ማርጋት፤ መግፋት መናጥ፤ ቅቤ ማውጣት፤ ማቡካት ማምጠጥ፤ የወተት ያይብ።

ዐቂል ሎት -(ዐቀለ የዐቅል ይዕቅል ዕብ ዐቄል ካበ ከበበ) ማጐድጐድ ማጥለቅ፤ ዙሪያውን መዝጋት፤ መገንባት። በውስጡ ውሃን መሰብሰብ፤ ማከማቸት፤ማጠራቀም መምላት። ዐቀለ ብሂል ደነገገ -(ጥሬ -)

ዐቂብ ቦት -(ዐቀበ የዐቅብ ይዕቀብ። ዕብ ዐቃብ አደባ) መጠበቅ፤ መከልከል ጠንቅቆ ማየት መመልከት መጐብኘት ማቈየት ማዘግየት። ለወለትከ አጽንዕ ዐቂቦታ። የዐቅብ ገነተ ምአዕዋፍ። ከመ ትዕቀቡ ዕጓለ ማውታ። ብድ ይክል ዐቂበ ነገ ዘሰምዐ -(ሢራ፳፮ -፲። ኩፋ -፫። ያዕ፩ -፳፯ ራ፰ -፲፯)

ዐቂድ ዶት -(ዐቀደ የዐቅድ ይዕቅድ ዕብ ዐቃድ) መቀየድ መኰድኰድ እግር ተወርች ማሰር መቀፍደድ የፍሪዳ በቁሙ ማቀድ፤ ማስጐብደድ፤ መቀሰት፤ እንደ ደጋን ማጕበጥ የሕንጻ የግንብ። ማዋቀር መማገር፤ መሠመር የጣራ የባጥ

ዐቂጽ ጾት -(ዐቀጸ የዐቅጽ ይዕቅጽ ዐቀደ፤ ዐቀፈ) መሰንከል፤ መሸንከፍ እግርን መያዝ፤ ማሰር መጥለፍ፤ መዘርጠጥ፤ ማንቀፍ ዐቂጸ ዐቀጽክኒ ወለትየ ሰይጣን ይዔቅጽ በስዉር -(መሳ፲፩ -፴፭። ፊልክ -) በዐቀጸ ፈንታ አዕቀጸ ይላል፤ ስሕተት ነው አዕቀጾ ለይሥሐቅ ኵሉ እኍ አዕቀ ያዐቅጽ። ዕቅጾቶሙ እምፍኖተ ጽድቅ በውስተ ርሥ ዕቀጾ ለእኍሁ -(ዘፍ፳፪ -፱። ኤር፱ -፬። ኩፋ -፩። ሆሴ፲፪ -)

ዐቂፍ ፎት -(ዐቀፈ የዐቅፍ ይዕቅፍ ዐረ ዐቀፈ አጐበጠ) ማንቀፍ ዕንቅፋት መኾን፤ ማሰናክል። መጽሐፍ ግን በዐቀፈ ፈንታ አዕቀፈ ተዓቀፈ ይላል፤ አያሰኝም። ኢያዐቅፈከ ብነ ዕቅፍት። አዕቀፈኒ ሰይጣን ከመ ኢያዕቅፍ ትምህርቶ ክርስቶስ። ዝኑ ያዐቅፈክሙ ተንሥአ መልአክ ይትዓቀፎ፤ ወፃእኩ እትዓቀፍከ -(ኢሳ፰ -፲፬ ፩ተሰ - -፲፰ ገላ፭ -፯። ዮሐ፮ -፷፩። ዘኍ፳፪ -፳፪ና -)

ዐቃሚ -የሚወስን ወሳኝ፤ ቈራጭ -( - -፲፰)

ዐቃር -(ሱር ዐቃራ ዐረ ዐቃር) ቅመም፤ ጥርቅም፤ የሽቱ፤ የመድኀኒት፤ የሌላውም ሉ።

ዐቃርብት -ጊንጦች፤ እሾኾች። ወሀብከነ ሥልጣነ ከመ ንኪድ ከይሴ ወዐቃርብተ ማእከለ ዐቃርብት ትነብር። እቀሥፈክሙ በዐቃርብት -(ቅዳ። ሕዝ፪ -፮። ፫ነገ -፲፪ -፲፬)

ዐቃቂር [1]:-ቅመሞችዐቃር

[2]-በቁሙ፤ ቅመሞች፤ ጥርቅሞች ባንድነት የሚጣፈጡ። ዐቃቂረ ፈውስ በከመ ይትረከብ በውስተ ፈውስ ብዙኅ ዐቃቂር ሠናያት ወአሐዱ እምኔሆሙ ይኄይል በገቢረ ፈውስ -( - - -፬። አፈ -ተ፱) ወመጽኡ ገባርያነ ዐቂቃር ወአምጽኡ መክሊተ ዐረር ወገንዐ ዐቢየ ዘብርት ወሰብዐተ ልጥረ ቅብዕ ዘሰሊጥ፤ ወደመሩ ውስቴቱ ሥብሐ ወመዓረ ግራ ወቅብዐ ላሕም ወዐቃቂረ ብዙኀ ዘያነድዶ ለላህበ ሳት ዘምስለ ቃር ወፒሳ ወተይ ወቅጥራን ወሰብዐተ ልጥረ ምነ ልፎንያ ወልካ ወቀለምጤዳ ወሰጣጵዮን ወዕፀወ ብዙኀ ወአምጽኡ ዐቃቂረ ዘአብሰልዎ ወአምሀውዎ ውስተ ገንዕ -(ስንክ -ሐም፭ -፲፭)

ዐቃቢ -(ቢት ብያን ያት ቀብት) የሚጠብቅ፤ ጠባቂ፤ ተመልካች፤ ከልካይ። ቦኑ ዐቃቢሁ አነ ለእኍ ብእሲት ርማሚት ወዐቃቢተ ልሳን። ካህናት ዐቃብያነ ሕጉ እግዚ ዐቀበተ ቤተ ሞቅሕ -(ዘፍ፬ -፱። ፈላስ ቀሌ። ኩፋ -፴፱) በዐቃቢ ፈንታ ዑቃቤ፤ ተዐቃቢ ይላል፤ ስሕተት ነው ዘዝከ ዑቃቤ ላዕሌየ ኮነ ተዐቃቤ ለሕገ እግዚ -(ኢዮ፯ -፲፪ ስንክ -መጋ፲፱)

ዐቃቤ ሥራይ -ሐኪም፤ ባለመድኀኒት መድኀኒቱን ጠብቆ ጠንቅቆ፤ አጣፍጦ ቀምሞ ሐኪም የሚሼጥ። ሕሙማን ይፈቅድዎ ዐቃቤ ሥራይ -(ማቴ፭ -፴፩)

ዐቃብ -(ዕብ ዐቅባ፤ ሽንገላ ክሕደት ጠማምነት) እሾኽ፤ አሜከላ ሸሽላ ታናሽ ዐረም፤ ዐቃቅማ ኵርንችት፤ እሾኻም ዐቃብ ምልኅት ማሁ ኵሎሙ -(፪ነገ -፳፫ -)

ዐቃፊ -(ፊት ፍያን ያት) የሚያነቅፍ ዐንቃፊ አሰናካይ

ዐቅል -(ዐረብ) ጥልቅ ጠባይዓዊ ዕውቀት፤ ጥበብ፤ ብልኀት አንደፊር አበ ሂሮድስ ውስቴቱ ምክር ወዐቅል -(ዮሴፍ)

ዐቅም -ወሰን ደንበር፤ ልክ መጠን ፍጻሜ አልቦ ዐቅም ስፍሐ መንግሥቱ። ሰትየ ወይን ዘእንበለ ዐቅም። ሕግ ዐቅመ መዋዕል ልቦ ዐቅም ለመለኮትከ -(ቅዳ -ኤጲ ቀሌ። ኩፋ -፮። አርጋ -)

()          ዐቅሞ ሞት -() -(ዐቀመ፤ ይዔቅም የዐቅም። ዐረ ዐቀመ፤ አመከነ። ዕብ ዐቄም፤ አጣመመ) መያዝ ማሰር ማቈየት ማስቀረት ወዐቀመ ስምዖንሀ ባሕቲቶ -(ኩፋ -፵፪)

 -መቍረጥ፤ መፈጸም፤ መጨረስ ይዔቅም ቃሎ -(መዝ -፻፲፩)

 -መለካት፤ መመጠን፤ መደንገግ፤ መወሰን። ጥዑይ ንዋሙ ዘይዔቅማ ለከርሡ በመስፈርት ዘዐቀመ ለነ እግዚ። ባሕረ ዐቀመ ከመ ትትዐደው እምዐቅማ -(ሢራ፴፬ -፳። ፪ቆሮ - -፲፫ ኪዳ)

ዐቅረብ -(ዐረ እልዐቅረብ) ኮከብ የኮከብ ስም፤ መልኩ ጊንጥ የሚመስል። ኮከብነቱም የጥቅምት ነው፤ ከፀሓይ ጋራ ፳፱ ዕለት ኬክሮስ ይመግባል -(አቡሻ)

ዐቅራብ [1]:-እንቧዮች፤ቀረብ፤ አቅራብ

[2]-(ዕብ ዐቅራብ ሱር ዓቅርባ ዐረ ዐቅረብ) ጊንጥ መርዛም፤ ዥራታም፤ ክፉ በዥራቱ ጫፍ የሚነድፍ፤ መርዙ የሚሣቅይ። ዘይፀብጥ ዐቅራበ። ዐቅራብ ሶበ ይነድፍ ሰብአ ዘነበ ዐቅራብ ዐቅራበኑ ይሁቦ -(ሢራ፳፮ -፯። ራእ፱ - -፲። ሉቃ፲፩ -፲፪)

 -እሾኻም ዕንጨት እንዳጣጥ እንደ ዝንኪላ ያለ በወጋ ጊዜ እንደ ጊንጥ መርዝ የሚያሳምም

ዐቅድ -የሥራ መልክ፤ አሠራር ውቅር ዐቅዶን -(ገድ -ላሊ)

()           ዐበለ -(ዕብ ያባል) ፈሰሰ ወረደ ጋለበ ደ፤ ታወከ ተናጠ፤ ተደረጠ የጐርፍ የባሕር። ጐርፉ ይናብላል ውሃው ሣር ይበላል እንዲሉ

ዐበቅ -ዕከክ፤አበቅ።

ዐበየ -ንቢ አለአብይ አበየ

ዐበይት -ታላቆች ታላላቆች፤ አለቆች፤ ሽማግሎች። ብርሃናት ዐበይት። ዐበይት መዋቅሕት ዐበይት ሰብእ። ዐበይተ ነገድክሙ -(ዘፍ፩ -፲፮። ራእ፳ -፩። ሢራ፰ -፩። ዘዳ፳፱ -)

ዐቢር ሮት -(ዐብረ የዐብር ይዕበር ዕብ ዐባር) ማለፍ መኼድ መሻገር የቦታ የዘመን። ማርጀት መድረቅ፤ መምከን ርጥበት ልምላሜ ማጣት፤ ድርቅ በጋ ቦና መኾን። ዐብረ ኵሉ ወፍር ዘውስተ ገዳም። ኵሉ ይየብስ ወየዐብር የዐበር ወይንክሙ ዓመታት ኀዙ ይዕብሩ -(ኤር፳፫ - ኢሳ፲፱ -፯። ሚል፫ -፲፩። ኩፋ -፲፩)

ዐቢይ -(ያን ያት ባይ) ታላቅ ገናና ብርቱ፤ ብዙ፤ ፍጹም ዐቢይ እግዚአብሔር ወዐቢይ ኀይሉ ተኣምራት ዐቢያን ወስቡሓን ፉሁ ይነብብ ዐቢያተ። ሀገር ዐባይ። ዐቢይ ክርስቲያን -(መዝ -፻፵፮ ሔኖ፴፮ -፬። ዳን፯ -፰። ዮና፩ - ግብ፳፮ -፳፰)

ዐቢጥ ጦት -(ዐበጠ የዐብጥ ይዕብጥ። ዕብ ዐቤጥ) ማሰናክል፤ ማስተጓጐል፤ መንገድ ማውጣት፤ በግድ መያዝ፤ መሳብ መጐተት፤ መግፋት ማዳፋት። ወለዘሂ ዐበጠከ ሐደ ምዕራፈ ሑር ምስሌሁ ክልኤተ። ዐበጥዎ ለስምዖን ከመ ይጹር መስቀሎ -(ማቴ፭ -፵፩። ፳፯ -፴፪። ማር፲፭ -፳፩ ዲድ -፴፭። ድጓ)

ዐባር -ድርቀት ድርቅ በጋ ቦና፤ ችጋር፤ ቀጠና፤ ከዝናም ዕጦት የተነሣ ዐቧር ዐቧራ ማለት ዚህ ወጥቷል። ዐባረ ዝናም። በዓመተ ዐባር ቀሠፍኩክሙ በዐባር -(ኤር፲፬ -፩። ፲፯ -፰። ጌ፪ -፲፯)

()          ዐብሎ ሎት -(ዐበለ ይዔብል የዐብል) መሥራት፤ መሣሪያ ማውጣት፤ ፊት ጕጠቱን መዶሻውን፤ ቀጥሎ ሌላውን የብረት። የተሠራውን ማደስ ማሾል፤ መወልወል መሰንገል። መበለን እይ የዚህ መንቲያ ነው

ዐብይ ዮት -(ዐብየ የዐቢ ይዕበይ ዕብ ዐባህ ሱር ዐብያእ) መወፈር፤ መግዘፍ፤ መደንደን። ማደግ መብለጥ፤ ታላቅ መኾን መክበር መግነን፤ ከፍ ከፍ ማለት፤ ማየል መጽናት መበርታት መብዛት መፈድፈድ፤ መመንዘል መክበድ ዐብየ በጥበብ ወበጸጋ። እስመ አብ የዐብየኒ ዐብየ መርዶኬዎስ። ዐብየ ወተለዐለ ከመ አርዝ። ዐብየ ማዕበለ ባሕር ወዐብየ ረኀብ ጥቀ። ዐብየ ገዓሮሙ፤ ዐብየት ኀጢአቶሙ -(ሉቃ፪ -፪። ዮሐ፲፬ -፳፰ አስቴ፪ -፳፩ መዝ -፴፮። ዮና፩ -፬። ዘፍ፵፯ -፲፫ ፲፱ -፲፫ ፲፰ -)

ዐብደ -ሰነፈ፤አቢድ አብደ።

ዐብድ -(ዐረ። ዕብ ዔቤድ) አገልጋይ ሎሌ ባሪያ የተገዛ የተማረከ ዐበድ ልመሲሕ ዐበድ ናገ -(ዳን፩ -)

ዐተር -በቁሙ ያበባ እኽል ፍሬው ክብ፤ እንክብል ድብልብል ዐተረ ወስጕርንደ ብርስነ ወዐተረ። ዐተር ይቡስ -(ገድ -ተክ። ሕዝ፬ -፱። ስንክ -ጥቅ፴) ባማርኛ ዐተረ፤ ዕትራት ማለት ከዚህ የወጣ ነው። 

ዐቲብ ቦት -(ዐተበ የዐትብ ይዕትብ፤ ኀተመ) ማተብ፤ መቍረጥ፤ መፈጸም መጨረስ ማተም፤ ማስመሰል ዐተቦ እግዚ ዘቦቱ ቀብዐነ ወዐተበነ ወዐተቡክሙ -(ዮሐ፫ -፴፫። ፪ቆሮ - -፳፪ ኤፌ፩ -፲፫ -)

 -መባረክ፤ ማማተብ፤ በጣት በመስቀል፤ ፊትን ወይም ሌላውን። ዐተበኒ  በትእምርተ መስቀል ወአርስዓ ዐቲበ ገጻ። ይዕትብ ባሎሙ። ወይዕትቦሙ ሥልሰ -(ቀሌ - -፫። ቅዳ)

()          ዐትሞ ሞት -(ዐተመ ይዔትም፤ የዐትም ዐረ ዐተበ ዕብ ዐቶብ በጢስ መታፈን መጨለም) መቈጣት መናደድ እንደሚጤስ እሳት ቱግ ማለት።

ዐኒቅ ቆት -(ዐነቀ የዐንቅ ይዕንቅ ዕብ ዐናቅ ዐረ ዐነቀ) መክበብ፤ ማጠር ዐንገትን በጌጥ፤ ማሰር ማንገት፤ ባንገት መሸከም ማንጠልጠል። መርዘም፤ መብለጥ ዕንቆ ውስተ ክሣድከ ብፁዕ ዘጾሮ ወዘዐነቆ በክሣዱ ዝንቱ ጸሎት ሰላም ክሣድኪ ቃማ ንጽሕ ዘዐነቀ -(ምሳ፫ -፫። ግንዝ። ደራሲ) በዐነቀ ፈንታ ተዐነቀ ይላል፤ ስሕተት ነው። ወይትዐነቅ ቀጸላ ወርቅ -(አዋል)

ዐኒን -(ዐረብ) አባለ ዘርዕ ደካማ ሳሳ የታሸ የተኰላሸ ፍሬው የወጣ፤ ወይም ያበጠ የተነፋ፤ ደዌ ያደረበት ዘይትበሀል ልዐኒን ውእቱ ፍረተ ሥጋ ንኡስ -( - -፲፪ -)

ዐኒግ ጎት -(ዐነገ የዐንግ ይዕንግ ዐረ ሐነጀ) መሥራት፤ መጠምዘዝ፤ ማጕበጥ የቀለበት። ማንገት፤ ማሰር ማንጠልጠል፤ የጌጥ የክታብ።

ዐናስር -(ዐረ ዐናጺሩ) ህላውያት፤ አሥራወ ፍጥረት፤ አራቱ ባሕርያት። ደንገፁ ኵሉ ዐናስረ ፍጥረት፤ ወአንክሩ ሎሙ ፍጡራን -(ሃይ -አበ ገድ -አዳ) መተርጕማን ግን አለቆች ይሉታል

ዐናብርት -ዐንበሪዎች፤ ታላላቅ ዓሦች፤ ብሄሞትና ሌዋታን -(ዘፍ፩ -፳፩ ኩፋ -፪። ኢዮ፱ -፲፫) ብሄሞትን ተመልከት

ዐናት -(ትግ ወዐም) በቁሙ ማኽል ራስ የናላ ርግብግቢት።

ዐናቶት -(ዕብራ) ስመ ሀገር፤ ስጣዌ -(ኤር፩ -)

ዐናጉግ -የባሕር አራዊት አርጃኖች -(መቃ -ገ፲፪)

ዐንሰር -(ዐረ ዑንጹር) የፍጥረት ጠባ ባሕርይ።

ዐንሰበ -(ዐሰበ፤ ሐሰበ) ነሲብ ጣለ፤ ገመተ፤ አሟረተ። ስሯጽ ግስ ነው፤ ዐሰበን ተመልከት

ዐንበሳ -በቁሙ፤አንበሳ በስበሰ።

ዐንበሪ -(ዕብ ዳግ ታኒን ሊውያታን) ታላቅ ዓሣ እንደ ዘንዶ ያለ ዐንበሪ ዐቢይ። ዐንበሬ ባሕር። ዐንበሪ አንስቲያዊት ዘስማ ሌዋታን ይባርክዎ ዐንበር ወኵሉ ዘይትሐወስ ውስተ ማይ -(ዮና፪ -፩። መዝ -፷፬። ሔኖ፰ -፯። ጸሎ - -ደቂ) ስምነቱ ከዐበረና ከነበረ ኹለቱ የተዴቀለ ነው፤ ምስጢሩም ታላቅነትና ነባርነት ነው፤ አንባ እንደ ማለት

 

 

ዐንበር -(ዐረ ዕብ ዐንባር) የሽቱ ጭቃ ሲፈጭ ሲደቈስ ወይም በእሳት ሲጤስ ሽታው የሚገን የሚጣፍጥ። በዐንበር ፈንታ ዐምበር ይላል፤ የተሳሳተ -(ዮሴፍ)

ዐንበዘ -ተነበዘ፤ነበዘ፤ አንበዘ

ዐንዘረ -አስጮኸ ዘረ አንዘረ

ዐንገት -(ዐረ ዑንጉግ) በቁሙ ክሣድ ማንገቻ የጌጥ የሽልማት ማሰሪያ

ዐንጉግ -ዐንገታም ዐንገተ ወፍራም። የባሕር አውሬ፤ አርጃኖ -(ዘሌ፲፩ -)

ዐንግ -(ዕብ ኔዜም። ጽር ሄኖቲያ) ትቻ፤ ቀለበት፤ ንፎ መንደልት ያፍንጫ ወይም የዦሮ ጌጥ ንፎ ያፍንጫ መንደልት የዦሮ።

ዐንጐ -(ጓት ዝኒ ማሁ ዐንጐጓት ወብሔ -(መጽ -ምስ)

 

ዐንፀወ -ደረቀነፀወ አንፀወ

ዐንፄዋ -ዐይጥነጽይ ነጸየ፤ አንጼዋ

ዐከለ -በላ በቃአኪል አከለ

ዐከየ -ከፋ፤አክይ አከየ

ዐኪክ ኮት -(ዐከከ የዐክክ ይዕክክ) መጥገብ፤ መጠገብ፤ መሰልቸት ዕክክ ማለት። ብዙ ውሃ መያዝ፤ እስካፍ እስከ ንፈር መንተርፈፍ መምላት፤ የጋን የማድጋ -(ዮሐ፫ -)

ዐኪው ዎት -(ዐከወ የዐኩ ይዕኩ) መከልክል፤ ማስቀረት፤ እንዳይገባ ማድረግ።

ዐኮ -አይዶለምአኪው አከወ አኮ

ዐኮት -(ዕብ ዐሮብ) ከልካይ አጋፋሪ የበር መቅሠፍት ተባይ፤ ተናካሽ ፍጥረት፤ በየስሙና በየመልኩ፤ የሚነድፍ የሚቈነጥጥ፤ የሚያቈስል የሚያሳብጥ፤ የሚያሳክክ የሚያንገበግብ፤ ተርብ የውሻ ንብ፤ የበሬ የበረሓ ዝንብ፤ ትንኝ ቅማል፤ ቍንጫ ትዃን፤ ዘመሚት ጕንዳን፤ የመሰለው ኹሉ ፈነወ ዐኮተ ወበልዖሙ -(መዝ -፸፯ -፻፬ ጥበ፲፱ -)

ዐዊም ሞት -(ዖመ የዐውም ይዑም። ዐረ ዐመ፤ ቀመ። ዕብ ዑብ) መሸፈን፤ ማልበስ ማጨለም፤ የዛፍ የቅጠል፤ የጉም ጥሬው በቀር አንቀጹ አይገኝም።

ዐዊር ሮት -(ዖረ የዐውር ይዑር ዕብ ዐዌር ሱር ዓዋር።። ዐረ ዐዊረ ዐወረ ነቈረ) መታወር፤ ዕውር መኾን፤ ማየት መከልከል፤ መደናበር ዐይን ፈርጦ ገበጣ መስሎ ተደፍኖ ተጨፍኖ፤ ወይም ፈጦ ጐርጦ፤ ፈዞ በልዞ እቀሥፍ ፍራሰ ሕዛብ በዐዊር ዖሩ አግብርት እግዚ ዖራኒ አዕይንትየ እምአንብዕ ተዐውር ወኢትሬኢ ፀሓየ። አዕይንት ጻርያት የዐውራ -(ዘካ፲፪ - ኢሳ፵፪ -፲፱። ኢዮ፲፯ -፯። ግብ፲፫ - ፲፩ ግንዘ)

ዐዊቅ ቆት -(ዖቀ የዐውቅ ይዑቅ ዕብ ዑቅ ሣቀየ አሳመመ) ማወቅ ማስተዋል፤ ምስጢሩ ጥበቃ ጥንቀቃ ነው ዑቅ ትእዛዘ ወግበር ዑቅዎሙ ለከለባት። ዑቅ ዘንተ ከመ ታግብኦ ወልድየ። ዑቁኬ ኢያስሕቱክሙ። ዑቁ ርእሰክሙ -(ኩፋ -፳፩ ፊልጵ፫ - ማቴ፳፬ -፬። ማር፲፫ -)

ዐዊት -ስመ ሀገርዊት

ዐዊድ ዶት -(ዖደ የዐውድ ይዑድ ዕብ ዒዌድ ዐረ ዓደ) መዞር መሽከርከር መገላበጥ ለራሱ ማወድ በዙሪያ መኼድ መመላለስ፤ ማጠር መክበብ፤ ዙሮ መግጠም አገር ላገር መንደር ለመንደር መዞር፤ ለማየት፤ ለመስማት፤ የሹትን ለማግኘት። ማወጅ፤ እየዞሩ መልፈፍ ዐዋጅ መንገር፤ ስማ ስማ ማለት። ባዩት በሰሙት ምስክር መኾን፤ ተጠርቶ መመስከር ወይም ታሪክ ጥፎ ማኖር ከመ መንኮክት እንተ ዐውድ ወለለ ዖድዎ ለውእቱ መንበር ከመ ቀስተ ደመና የዐውዶ ራኄ ድኩ እንዘ አኀሥሣ ዖደ ዐዋዲ የዐውድ ይንግር ለከ ዘወሀበከ -(ሢራ፳፮ -፭። መክ፳፮ -፲፬ ቅዳ። ሳታ። ጥበ፰ -፲፰። መክ፯ -፳፭ ዘፍ፵፩ -፵፫። ሢራ፳ -፲፭)

ዐዊግ ጎት -(ዖገ የዐውግ ይዑግ ዐረ ዐዊገ) መጥመም፤ መጕበጥ፤ መወላገድ፤ ጠማማ ቈልማማ፤ ዐንካሳ ወንካራ፤ ጠንባሳ ሸውራራ መኾን አለመተካከል፤ የሕዋስ

ዐዊፍ ፎት -(ዖፈ የዐውፍ ይዑፍ። ዕብ ዐፍ ያዑፍ) አፈፍ ወፈፍ በርደግ ማለት፤ ክንፍን መዘርጋት፤ ብር ቱር ማለት መብረር መስረር፤ እንደ ደመና በአየር መኼድ መክነፍ። ወፈፍተኛ ማለት ከዚህ የወጣ ነው።

ዐዋር -(ዐረብ) ውር ንባሳ ዐይኑ የጠፋ የፈሰሰ የዐዊር ምስጢር ከብርሃኑ ይልቅ ዐይኑ ብሌኑ ወጣ በኋላ ባዶውን ያለ ድጓድና ቈርበት ያሳያል።

ዐዋውርት -ዕውሮች ዕውራኖች መርሐ ዐዋውርት -(ገድ -ዘሚ)

ዐዋዲ -(ዲት ድያን ያት) የሚዞር ዘዋሪ ለፋፊ ዐዋጅ ነጋሪ። ብእሲት ዐዋዲት ዘኢትከድን ፍረታ ቃለ ዐዋዲ ሐዋርያ ወዐዋዲ -(ፈላስ። ዮሐ፩ -፳፫ ፩ጢሞ - -)

ዐዋድ -ዐዋጅ፤ ለሕዝብ የሚነገር የንጉሥ ሕግና ደንብ ውሳኔ። መጽሐፍ ግን በዐዋድ ፈንታ ዐዋጅ ይላል። ወአንገረ ዐዋጀ -(ታሪ -)

ዐዌት -(ትግሬ) ድል፤ አሸናፊነት፤ አስጯኺነት።

ዐውሎ -(ታት ሱር ዑላታእ፤ ዐላታእ። ዕብ ዐልዖል) በቁሙ፤ ጥቅል ነፋስ፤ ሮ፤ ኵርፊት የትቢያ ማዕበል የሚያስነሣ፤ ቤት የሚያናውጥ የሚገለብጥ፤ ተግብ ከዝናብ በፊት የሚነፍስ። ነፋስ የሚያስነሣው ማዕበል ሞገድ የባሕር ሁከት። ከመ ጸበል ዘይነሥኦ ዐውሎ። ዐውሎ ያል ያነቅዓ ዐውሎ ማይ። ተንሥኡ ዕሌየ ዐውሎታት ወመዋግድ ተለዐሉ ዕሌየ -(ኢዮ፳፩ -፲፰ ሕዝ፲፫ -፲፩ መዝ -፷፰። ፊልክ -፳፰)

ዐውስት -አሞራ፤ውስት።

ዐውቅ -(ቃን) ዐውቂያ የሚያውቁት፤ ምስጢር የሚነግሩት፤ ወዳጅ፤ ባልንጀራ። ዐውቅየ ወከመ ዐውቃንየ ኮንኩ በማእከሎሙ -(መዝ -፶፬። አረጋ -ድ፳፩)

ዐውየወ -(ዐረ ዐወይ ሱር ዐዋእ) ጮኸ ቡታ ሰደደ፤ ዋይ ዋይ አለ። ዐውየወ በሕቁ የዐወይዉ እምብዝኀ መስተዐግላን ወዐውየወት በሕማማ። አኀዝኩ እብኪ ወአዐውዩ -(ዮዲ፲፬ -፲፮ ኢዮ፴፭ -፱። ኢሳ፳፮ -፲፯ ሔኖ፹፱ -፷፱)

ዐውያ -(ያት) ጩኸ ቡታ እሪታ ልቅሶ ዋይታ ጊዜ ዐውያከ ዐውያተ ነዳያን ዐውየወት ዐውያተ ዐበይተ -(ኢሳ፶፰ -፱። ኢዮ፴፬ -፳፰ ሔኖ፹፭ -)

ዐውደ ማኅተም -፸፮ ዓመት። ማኅተምን ተመልከት

ዐውደ ቀመር -፻፴፪ ዓመት፤ በዚህ ዕለት ወንጌላዊ አበቅቴ ይገናኙበታል፤ ዕለቱ ሠሉስ ወንጌላዊው ማቴዎስ፤ አበቅቴው አልቦ ነው። ይህ ኹሉ ቃል የመርሐ ዕዉር ነው

ዐውደ ነገሥት -የጥንቈላ መጽሐፍ፤ ፲፮ ክብ ንጠረዥ ያለው ያቡሻህርና የመርሐ ዕዉር ወደረኛ። በየሰንጠረዡ ፲፮ ነገር አለበት፤ ትምርቱን ግን ከጥቂት ሰዎች በቀር ኹሉ ያውቀውም መጣፉም በጠንቋይ ኹሉ ዘንድ አይገኝም።

ዐውደ አበቅቴ -፲፱ ዓመት፤ በዚህ ረቃና ፀሓይ መንገዳቸውን እየፈጸሙ ተራክቦ ያደርጉበታል።

ዐውደ ዓመት -የፀሓይ ዐውዳመት፤ ፫፻፷፭ ለት፤ ሩብ።

ዐውደ ዕለት -ባት ቀን፤ ከእሑድ እስከ ቀዳም።

ዐውደ ወርኅ [1]-ሠላሳ ቀን፤ (ልደታ) መባቻ እስከ መባቻ።

[2]-የጨረቃ ዐውዳመት ፫፻፶፬ ቀን

ዐውደ ፀሓይ -፳፰ ዓመት በዚህ ዕለ ወንጌላዊ ይገናኙበታል ዕለቱ ረቡዕ፤ ወንጌላዊው ማቴዎስ

ዐውድ [1]-ዐውድማ ሸንጎ ጉባኤ፤ አደባባይ ዐውደ እክል። ዐውደ ማእረር። አምጽእዎ ኀበ ዐውድ። ንንሥት ዐውደ -(ሩት፫ -፪። ዳን፪ -፴፭። ግብ፲፰ -፲፪። ፲፱ -፴፱)

[2]-ዐውድ፤ ዙሪያ ክበብ በር እስከ በር ካመት እስካመት ያለ ለታጠረ ለተወስነ ክበብ ላለው ኹሉ ይነገራል። ወበዐውዱ ለውእቱ መንበር ይቀውሙ ዐውዶ ዐውደ ፀሓይ ዐውደ ወርኅ። ዐውደ ዓመት -(ራእ፬ -፬። ኢሳ፮ - አቡሻ -፳፫። ድጓ)

ዐዘቃት -ዐዘቅቶች፤ ድጓደች ኵሉ ዐዘቃት ዘከረዩ ደቀ ብርሃም -(ዘፍ፳፮ -፲፭)

ዐዘቅት -(ታት) በቁሙ፤ ጕድጓድ ኵሬ ዐዘቅት ዘኢይነፅፍ ማዩ። ዐዘቅት ንፅፍት። ወውስተ ዐዘቅታት -(ኢሳ፶፰ -፲፩ ፪ጴጥ - -፲፯ ፩ነገ -፲፫ -)

ዐዘበ [1]:-ፈሰሰዐዚብ ዐዘበ

[2]-(ዕብ ዐዛብ) አዳነ ዐገዘ ረዳ፤ ናሣ፤ የሸክም። ጸርኩ እመ ዘይዔዝበኒ ሰብእ ወአልቦ -(ሢራ፶፩ -፯። ዘፀ፳፫ -)

 -ተወ ጣለ ወረወረ። ሰበቀን ተመልከት፤ ከዚህ ጋራ አንድ ነው

ዐዘዘ -ቁሙአዝዞ አዘዘ

ዐዚር ሮት -(ዐዘረ የዐዝር ይዕዝር ዕብ ዐዛር ረዳ ዐገዘ) መበተን፤ መዘርዘር መርጨት፤ መፈንጠቅ።

ዐዚቅ ቆት -(ዐዘቀ የዐዝቅ ይዕዝቅ ዐረ ዐዘቀ። ዕብ ዓዜቅ) መፋር መቈፈር፤ መብሳት መሰርሰር፤ ማጐድጐድ ማጥለቅ፤ ማዘቅ፤ ዝቅ ማድረግ፤ የኵሬ የጕድጓድ።

ዐዚዝ -(ዛን ዛት ዛዝ) ጥኑ ብርቱ ንካራ ልባም መንፈስ ዐዚዝ ገሥት ዐዚዛን ብእሲት ዐዛዝ -(መዝ -፶። ሔኖ፴፰ -፭። ምሳ፲፪ -) ዐዞ ዐዛውንት ማለት ከዚህ ወጥቷል።

ዐዛል -ብርቱአዛል 

ዐዛባ -በቁሙ የቦካ እበት ፍግ ፋንድያ ወደርሻ የሚጣል

ዐዜራህ -(ዕብ፤ ዐዛራህ) የምሥዋዕ ዕርከን፤ የሕንጻው ዝናር ዙሪያውን የሚከብ መደብ -(ሕዝ፵፫ -፲፬)

ዐዝዞ ዞት -(ዐዘዘ ይዔዝዝ የዐዝዝ ዐረ ዐዘ። ዕብ ዐዛዝ) መጽናት፤ መበርታት መጠንከር፤ መሠልጠን። ማጽናት፤ ማበርታት ልብን ሰውነትን። ከመ የዐዝዝ ወየኀይል ዲበ ምድር ወዐዘዘ ዕለ ትዕይንተ ግብ ዐዝዝ ዘይዔዝዝ ትፍሥሕት -(ሔኖ፶፪ - ዘፀ፲፬ -፳፬ ቅዳ መዝ -፵፯) አዘዘን ተመልከት።

ዐዠም -(ዐረ ዐጀም) ስመ ነገድ ርስ፤ የፋርስ ሕዝብ -(አቡሻ) ሀገሪትን ተመልከት።

ዐየነ [1]-ተከባከበአይኖ አየነ

[2]-() ዐየነ፤ -(ዕብ ዐዬን) ዐይናማ ኾነ ዐይን አወጣ ምንጭ ፈለገ፤ ቦታ ሰለለ፤ ጐበኘ ለሰፈር። ዐይኑን ጣለ ትክ ብሎ አየ አስተዋለ አጥልቆ ዐሰበ፤ መረመረ፤ ፈተሸ፤ ቀመለ፤ የነገር ገመተ፤ ገመገመ፤ ይህን ያኽል አለ፤ የዋጋ የካሳ። በዕጹብ እመ ዐየነ ንረክብ ምግባረ ዘውስተ ምድር። የዐይኑ ሎሙ ዘይሁብዎሙ -(ጥበ፱ -፲፱ ዘሌ፲፱ -፳። ዘፀ፳፩ -፴፩። ፪ቆሮ - -፲፪) በዐየነ ፈንታ ተዐየነ ይላል፤ አያሰኝም። እንዘ ይትዔየኖ ዘልፈ እመ ይፈርህ ወይጸንዕ፤ በጽኑዕ ይትዔየነኒ -(ገድ -ኪሮ) ርእየን ተመልከት።

[3]-(ትግሬ) አበደ እብድ ኾነ ልቡ

ዐየየ -መሰለ፤አይይ አየየ።

ዐዪል ሎት -(ዔለ የዐይል ይዒል ዐላህ) ላይ ላዩን መዞር፤ መባከን መብረር፤ ማውተት መንከርተት፤ ያሞራ የወፍ ርቆ መኼድ ጋራ ዙሮ ወንዝ ተሻግሮ መሸሽ መሰደድ። ወደ ዱር ወደ በረሓ ወደ ጋራ ወደ ራራ መውጣት መሰምረት፤ መናወዝ መቃበዝ ባውን ተሬውን ዋሻውን ጐሬውን መሰለል መጐብኘት፤ የዐዳኝ የመናኝ። አዐይል ውስተ ድባር ከመ ዖፍ ንዘ የዐይል አድባረ ወአውግረ። በውስተ ድው ኀበ ዔልክሙ በበ መራዕይክሙ ንዒል ውስተ ድባር ወበኣታት ወግበበ ምድር -(መዝ -፲። ስንክ -ታኅ፲ ሆሴ፲፫ -፮። ድጓ) በዔለ ፈንታ ተዐየለ ይላል፤ አያሰኝም። አሐተ ዕለተ እንዘ ይትዐየል ውስተ በድው -(ስንክ -ጥር፳፱)

ዐያል -( ሊት) የሚዞር፤ ዘዋሪ ቅብዝብዝ። እንዘ ዐያለ የሐውሩ ንህብ ዐያሊት ከማሁ ዮሐኒ ዘዔለ -(ሄርማ። ገድ -አዳ። ድጓ)

ዐያም -(ዕብራ) ብርቱ ንካራ ዐያሌ ብዙ፤ የሕዝብ የመንጋ።

ዐይ -ምንአይ

()          ዐይሮ ሮት -(ዐየረ ይዔይር የዐይር ዐረ ዐየረ። ዕብ ሔሬፍ) ማየር መቀላቀል፤ የማዕደናት። መስደብ ማዋረድ፤ መገደር መላገድ፤ መናቅ ማቅለል፤ አሳልፎ መስጠት፤ ራስን ወይም ሌላውን። ሕዝብ ዘዐየረ ነፍሶ ሞት -(መሳ፭ -፲፰) መጽሐፍ ግን በዐየረ ፈንታ ተዐየረ ይላል፤ አድራጊውን በተደራጊ የተሳሳተ ነው። ይትዐየር ንዘ ይብል ዕዉር ጽሙም ሕጹጽ ብር ፀጋማዊ ሀካይ፤ ወዘተርፉ ትዕይርታተ ጸሐፈ እንዘ ይትዔየሮ ለእግዚ ወእመሰ ዘተዐየሩክሙ በእንተ ስሙ ዘይትዔየር በክብረ ርእሱ -( - -፱። ፪ዜና -፴፪ -፲፯ ፩ጴጥ - -፲፬ አርጋ -)

ዐይነ -ወርቅ፤ የወፍ በሽታ ዐይንን ጥፍርን ሽንትን ሰውነትን ብጫ የሚያደርግ፤ ወርቅ የሚያስመስል። የክፋ ዐይን ደዌ፤ አስተያየቱ እንደ ጦር ኹኖ የሚወጋ። ተዘከር ከመ እኩይ ዐይነ ሰብእ። ነጸራ በመዐት ወመጽለወት -(ሢራ፴፬ -፲፫ አስቴ፭ -)

ዐይነ ማኅተም -የማኅተም ዐይነት፤ በማኅተም ላይ የተሣለ፤ የተቀረጸ መልክ፤ ወይም የታተመ የማኅተም ቅድ -(ዘፀ፳፰ -፲፩ -፳፩)

ዐይነ ምድር -ጕድጓድ ዐዘቅተ ኵስሕ የጕድጓድ ምንጭ፤ ውሃው ከውስጥ ከመሬት የሚፈልቅ፤ እንዳዲስ አበባ ያለ

ዐይነ ወርቅ -የወፍ በሽታ ዐይንን ጥፍርን ሽንትን ሰውነትን ብጫ የሚያደርግ፤ ወርቅ የሚያስመስል። የክፋ ዐይን ደዌ፤ አስተያየቱ እንደ ጦር ኹኖ የሚወጋ። ተዘከር ከመ እኩይ ዐይነ ሰብእ። ነጸራ በመዐት ወመጽለወት -(ሢራ፴፬ -፲፫ አስቴ፭ -)

ዐይን [1] -(ዕብ ዐዪን። ዐረ ዐይን ሱር ዐይና) በቁሙ፤ የማየት ሕዋስ፤ ማያ መመልከቻ ማኅቶቱ ሥጋ፤ ውእቱ ዐይንከ ይትራአዩ ዐይነ በዐይን -(ማቴ፮ -፳፪። ኤር፴፱ -)

[2] ሰብአ ዐይን ላይ፤ በኛ መልክተኛ። ወፈነወ ዳዊት አዕይንተ። አኮኑ አዕይንት እሙንቱ ፈኑ ደወ ሰብአ ዐይን -(፩ነገ -፳፮ -፬። ፪ነገ - -፫። - -)

[3]-ዐይነት መልክ ሕብር ፊት ለፊት ያለ ትይዩ አንጻር ዐይን የሚያየው የሚያርፍበት

[4]-ዐይነታ ዋና ጭገሬታ እመ ኢተረክበ ዐይኑ ያገብእ ምሳሊሁ -( - -፴፭)

 -የሚዛን ምላስ፤ ውልብልቢት፤ ላንሴታ እንተ ታገብእ ዐይነ መዳልው -(ኢሳ፵ -፲፭)

 -ብስ፤ ነዳላ፤ ሽንር፤ ፍልፍል፤ የገበጣ የሰፈፍ ዐይነት፤ ሸካራ፤ ጠቃጠቆ። የመርፌ ዐይን፤ ገበጣ ዐይን፤ ዐይናማ ደንጊያ እንዲሉ።

ዐይይ ዮት -(ዐየየ የዐይይ ይዕየይ ይዕይይ። ዐረ ዐዪየ) መሳት መሳሳት፤ መንገድ መውጣት፤ መዞር መባከን፤ ፈልጎ ማጣት። ወየዐይይ እንተ በኵለሄ በአይ ፍና ስመ ዐየይኩ -(ቅዳ -ሕር ቄር -)

ዐይን ምንጭ ውሃው እንደ እንብ ኹኖ ሲወጣ ሲፈልቅ የሚታይበት። ይትከሀልኑ ይፃእ እምአሐዱ ዐይን ማይ መሪር ማይ ጥዑም ወሀለዉ ህየ ዐሠርቱ ወክልቱ ዐይን። አቀመ ዕይንቲሁ ለተከዚ (ያዕ፫ ፲፩። ዘፀ፲፭ ፳፯ ሱቱ ዕዝ፲፫ ፵፬። ድጓ)

ዐይገን -(ዕብ አጋን ሱር አጋና ዐረ ኢጋነት) ጣሳ ፍንጃል፤ ኵባያ፤ ዳካ ለገን። ቄጆ ማለቢያ፤ የስፌት ዕቃ ደም ተቀብቶ እንደ ሸክላና እንደ ንጃል ያለ፤ ውሃ የሚይዝ የሚቋጥር ዐይገን ቢይ። ወመልአ ዐይገነ -(መሳ፭ -፳፭ -፴፰)

ዐይጋን -ባዮች፤ ፍንጃሎች፤ የሸክላ ጥዎች፤ እጀታ ዦሮ ያላቸው። አርባዕቱ ምእት ዐይጋነ ወይን -(ገድ -) ጋን ማለት ከዚህ ይሰማማል፤ ገንዕን ተመልከት።

ዐይግ -(ጋት) ኵሬ፤ የውሃ መቋሚያ፤ መጠራቀሚያ፤ ጐድጓዳ ቦታ፤ ዐውደ ማይ፤ ጉባኤ ማይ፤ ታናሽ ባሕር። በአሐቲ ዐይገ ማይ ወውእቱ ዐይገ ማይ ሠጠ -(ሔኖ፹፱ -፳፫ -፳፬፳፮)

ዐይጥ -(ዕብራ ዐይጥማ አሞራ) በቁሙ፤ የሌት ወፍ፤ ነገደ አንጼዋ።

ዐደለ -በቁሙ፤ ሰጠ አሳለፈ -(ዐማርኛ) ከፈለን ተመልከት

ዐደመ -ቀላ አማረ፤አዲም አደመ 

ዐደነ -በቁሙ፤ ፈለገ -(ዐማርኛ)

ዐደይ -(ትግ -ሐባ) ሹጥ የሆድ ትል ኮሶ የሚባል። በቁሙ ብጫቴ አበባ። -(ግጥም) ዐደይ ዐደይ የመስከረም፤ ሱስንዮስ ንጉሠ ሮም።

ዐዲው ዎት -(ዐደወ የዐዱ ይዕዱ ዕብ ዐዳህ ሱር ዐዳእ ዐረ ዐደእ) መሻገር ማለፍ፤ መዝለል መራመድ ዐልፎ ዘሎ ተራምዶ መኼድ መብዛት መትረፍ ልክ ማለፍ፤ መተላለፍ እመኒ ዐዶከ ማየ። ድዊ ፈለገ ዐደወ እሞት ውስተ ሕይወት። ወዐዲዎን ምተዓይን። እስከ ዐደዉ ምደማስቆ። ዘብዙኀ መስፈርት የዐዱ -(ኢሳ፵፫ -፪። ፵፯ - ዮሐ፭ -፳፬ ዮዲ፲፫ - ፲፭ -፭። ስንክ -መስ፳፰) በዐደወ ፈንታ ተዐደወ ይላል፤ አድራጊውን በተደራጊ፤ የስሕተት መንገድ ነው፤ አያሰኝም። እትዐደዋ አረፍት። ዘይትዐዶ ወሰነ ድንኒ ወንትዐዶኪ። ጸሎተ ዳይ ትትዐዶ ምደመና ትዐደዊ እምወሰንኪ -(መዝ -፲፯ ሆሴ፭ - ኢሳ፶፩ -፳፫ ሢራ፴፫ -፳፩ ቅዳ) ቃዕደወንና አንቃዕደወን እይ፤ የዚህ ዘር ነው፤ ሰንቀወ የነቀወ ዘር እንደኾነ

ዐዲድ -(ዐደ፤ ዐደደ የዐድድ ይዕድድ ዐረ ዐደ ጠረ) ማራቅ ማሶገድ ማዋረድ በፊትና በቀኝ የነበረውን ወደ ጐን ወደ ኋላ ወደ ግራ ማድረግ። ብርሃን ዘዐ() ደዶ ጽልመት -(ቅዳ -ዮሐ) የዐደደ ፍች ስለ ታጣ ዐደደ ወደ ሰደደ ተለውጧል ይህን የመሰለ ብዙ አለ

ዐዳዊ -(ዊት ውያን ያት) የሚሻገር፤ ተሻጋሪ፤ ዐላፊ ተላላፊ። በዐዳዊ ፈንታ ተዐዳዊ ይላል፤ ያማርኛ ነው፤ የግእዝ አይዶለም ተዐዳዌ ትእዛዝ። ተዐዳዌ ሕግ ተዐዳዊተ ሕግ -(መቃ። ጥበ፫ -፲፮ - -፳፬ -)

ዐዳዪ -(ዪት ይያን ያት) የሚከፍል ፋይ።

ዐድ -(ዕብራ) ዘልፈ፤ ለዓለም፤ ፍጻሜ የሌለው ጊዜ ዘመን። ይነግሥ እግዚ ለዓለመ ዓለም ወዐድ። አንዳንድ መጽሐፍ ግን ወዓዲ ይላል ስሕተት ነው -(ዘፀ፲፭ -፲፰)

ዐድል -(ዐረ ፍርድ ዕብ ቶኔት) ኪታ፤ ጥብቆ፤ ለስላሳ የውስጥ ልብስ፤ ዐጭር የገላ ቀሚስ፤ መጐናጠፊያ ልግም በገላ የክት ሸማ ኮት ጀባ ካባ የሚደረብ።

()          ዐድሞ ሞት -(ዐደመ ይዔድም የዐድም ዐረ ዐደ። ያዓድ) ማደም፤ መቅጠር ጊዜ መወሰን ቀኝ መስጠት ለሰርግ ለጉባኤ፤ ለኹሉ ሰብዓ ሰንበታተ ዐድሞሙ ለሕዝብከ ኮኑ ዐደምከ ዕድሜ። ወአስተብቍዖ ከመ የዐድሞ ስከ ሠሉስ ዕለት እዔድመክሙ ኅዳጠ መዋዕለ -(ዳን፱ -፳፬ -፲፪ -፲፮ ታሪ)

ዐድይ ዮት -(ዐደየ የዐዲ ይዕዲ ዐረ ዐደይ) መክፈል፤ ብድርን መመለስ የክፉ የበጎ።

ዐጉል -(ዕብ ዓጎል) በቁሙ፤ ዐጓጕል ክብ፤ እንክብል፤ ድንብልብል፤ ቅርጽ ገጽ ማእዝን የሌለው፤ የኩብ የኳስ ዐይነት ከካብ አይገባ እንዲሉ እብን ዘመነንዋ ደቅት -(መዝ -፻፲፮)

ዐጊል ሎት -(ዐገለ የዐግል ይዕግል) ማደስ፤ መሥራት፤ መሰደር መደርደር፤ መቈለል መከመር የደንጊያ የንጨት ዘዘ ቂሮስ በእንተ ቤተ መቅደስ ከመ ይትሐነጽ ወይዕግልዎ እንተ ሠለስቱ ዐግለ ብን፤ ወእንተ ሐቲ ዐግለ ዕፅ -(፩ዕዝ - - -)

 -መውለድ መፈልፈል የልጅ የንቍላል ማገል፤ መንቀል መትከል፤ መቍረጥ መቈጥቈጥ፤ መክተብ ማራከብ፤ ማረም መኰትኰት ዐፈር ማስታቀፍ ያታክልት። ተክል ዐጋይ እንዲሉ

ዐጊት ቶት -(ዐገተ የዐግት ይዕግት) ማገት፤ ዋስን መያዝ፤ ማሰር። መክበብ ማጠር፤ መወሰን፤ ዙሪያውን መዝጋት፤ መግጠም የክፉ የበጎ። ዐገቱኒ ከመ ንህብ መዓረ። ናሁ ማይ ዐገተኪ። ዕግትዎ ንጉሥ -(መዝ -፻፲፯ ናሖ፫ -፲፬ ፬ነገ -፲፩ -)

ዐጋሊ -(ተዐጋሊ) የሚቀማ ቀሚ ቀማኛ በደለኛ። ንጉሥ ዳየ አእምሮ ጸባሕተ ቢየ ተዐጋሌ ይከውን -(ምሳ፳፰ -፲፮ - -፴፭)

ዐጋሢ -(መዐግሥ፤ መስተዐግሥ) የሚያስታግሥ፤ አስታጋሽ አስቻይ።

ዐጌ -(ግያት) ተልባ የተልባ እግር ሐብለ ዐጌ። ልብሰ ዐጌ ልብስ ዘተአንመ በፀምር ወበዐጌ ወለብሰት አልባሰ ዐግያት -(ሕዝ፵ -፫። ዘሌ፮ -፫። ዳ፳፪ -፲፩ ዮዲ፲፮ -)

ዐግል -(ዕብ ጊል ጋል) የደንጊያ ክምር ልል ስድር ድርድር ያታክልት ረድፍ የዛፉ ተራ ቃዳው ተለላው መደቡ። ጓል ሊት መኰላ የረጋ መሬት ፍንቅሉ

ዐግሎ ሎት -(ዐገለ ይዔግል የዐግል። ዐረ ዐጊለ) መፍጠን መቀልጠፍ፤ መቀማት መመንተፍ፤ መበደል መግፋት መታገል ማጥቃት መጽሐፍ ግን በዐገለ ፈንታ ተዐገለ ይላል ገበረ ፈንታ ተገበረ እንዲል ኹሉም ስሕተት ነው ለእ ተዐገለ ልብሰ ዘይትዔገል ነዳየ ይትዔገሎ ባዕል ለነዳይ። ተዐገለ ነሢአ መንግሥት ምእኁሁ -( - -፴፭። ምሳ፲፬ -፴፩። ሢራ፲፫ -፲፬ ዮሴፍ)

()          ዐግሦ ሦት -(ዐገሠ ይዔግሥ የዐግሥ። ዐረ ዐጀሰ) ማስታገሥ፤ ማቆም መግታት፤ ማቈየት ማሰንበት፤ ማስቀረት። መጽሐፍ ግን በዐገሠ ፈንታ አስተዐገሠ ይላል፤ አያሰኝም፤ ፈሥሐን እይ እሞን ታስተዔግሦን ወትብሎን ጽንዓ ቡሃ ኮነ ያስተዔግሣ። ተስፋ ያጸንዕ ወያስተዔግሥ -(ስንክ -መስ - -፲፫። አፈ -ድ፲)

ዐግዋል -(ላት) አስካል፤ ዘለላ ሕንባቡ ፍሬው ክብ እንክብል የኾነ። ይሁብዎ ፍሬሁ በበ ጊዜሁ ባለው፤ በበ ዐግዋሊሁ ይላል -(ማቴ፳፩ -፴፩)

ዐጠንት -ዐጣኞች ካህናተ ሰማይ ቅዉማን በዕበይ ዐጠንተ መንበሩ ለአዶናይ -(ሳታ)

ዐጢስ ሶት -(ዐጠሰ የዐጥስ ይዕጥስ ዐረብ ዕብ ዐጣሽ) ማንጠስ፤ ድንገት ባፍና ባፍንጫ መጮኽ፤ መተንፈስ፤ ከጕንፋን ወይም ክፉ ሽታ የተነሣ። ማፋሸግ ማላቀቅ ማዛጋት፤ አፍን መክፈት፤ ዋሻ ማስመሰል።

ዐጢቅ ቆት -(ዐጠቀ የዐጥቅ ይዕጥቅ) መታጠቅ መቀነት፤ ወገብን ማሰር ማጥበቅ ማሸረጥ ማሸንፈጥ፤ ማገልደም። ዕጥቆ ውስተ ሐቌከ እለ የዐጥቁ ቅናተ መንግሥት። ገብሩ ሎሙ ሞራአ ዘየዐጥቁ -(ኤር፲፫ -፪። አፈ -ተ፳ ቀሌ)

ዐጢን ኖት -(ዐጠነ የዐጥን ይዕጥን ዕብ ቃጣር ቀተረ) ማጠን ማጤስ ማብነን፤ በጢስ ማፈን፤ መሥዋዕት መሠዋት፤ ማንደድ ማቃጠል። ዐጢነ ዕጣን። ከመ ይዕጥን ዕጣነ ሦዑ ወዐጠኑ ለአጋንንት። ሶበ ኀደግነ ዐጢነ ንግሥተ ሰማይ -(ኩፋ -፶። ፪ዜና - -፬። ኢሳ፷፭ -፫። ኤር፶፩ -፲፰)

ዐጢፍ ፎት -(ዐጠፈ የዐጥፍ ይዕጥፍ። ዐረ ዐጠፈ ዕብ ወሱር ዐጣፍ) መሥራት፤ ማጠፍ፤ መጠቅለል፤ ማልበስ መሸፈን ማጐናጠፍ፤ መጠቅለያውን፤ የሸማኔ። ዐጸፈን ተመልከት፤ የዚህ ጎረ ቤት ነው

ዐጣርድ -(ዐረ ዐጣሪድ) ኮከብ፤ የኮከብ ስም ወይም ሥዕሉ ምስሉ ብአ ልስጥራን የሚያመልኩት። ሄርሜንን ተመልከት ከዚህ ጋራ አንድ ነው ወሰመይዎ ለአሐዱ ምኔሆሙ መሽተሪ ወለካልኡ ዐጣርድ -(አፈ -ተ፳፮ ግብ፲፬ -)

ዐጣቂ -(ቂት ቅያን ያት) የታጠቀ የሚታጠቅ፤ ታጣቂ። ሐቌከ ሰላም ቅናተ ልቡና ዐጣቂ -(ደራሲ)

ዐጣኒ -(ኒት ንያን ያት) የሚያጥን፤ የሚያጤስ ዐጣኝ

ዐጥቅ -በቁሙ፤ ያገዳና የቅልጥም ወሰን መገናኛው፤ እንደ ትጥቅ ያለው። ዐጥቅ የለሽ እንዲሉ ወሰን የለሽ ሲሉ

ዐጥፍ -በቁሙ፤ የተሠራ ልብስ። ሠርዌ ዐጥፍ ዘመዐስቃን -(፪ነገ -፳፩ -፲፱)

ዐጸባ -(ባት) ጭንቅ፤ መከራ፤ ችጋር፤ ቀጠና ዕጦት ድኽነት ፍቁር አማናዊ ይትአመር በጊዜ ዐጸባ። ሶበ ረከቦሙ ዐጸባ። ንግደት ርሕቅት እንተ ኮነት በእንተ ዐጸባ -(ትእ -ጥ። ጥበ፲፮ -፫። - -፳፬ -) በዐጸባ ፈንታ ጽብና ይላል የጣፊ ስሕተት ነው። ዕጽብና ዐቢይ ውስተ ዛቲ ገዳም ዕጽብናተ ገዳም -(ስንክ -ጥቅ፳። ጥር -፲፯)

ዐጸብጺብ -የጭንቅ ጭንቅ ጥፍ ድርብ ጭንቅ፤ ቍርጥ ነገር ትእዛዝ፤ በኹለት ወገን የሚያስጨንቅ፤ ቢያደርጉትም ባያደርጉትም ጕዳት ያለበት ተናገረ ምስሌሆሙ ዐጸብጺበ -(ኩፋ -፵፪)

ዐፀወ -(ዐጸወ) በረታ ጠጠረ ጠነከረ ጣለ አወጣ ዐፀፀን ተመልከት፤ የዚህ ዲቃላ ነው

ዐጸውት -ዘጎች፤ ዘጊዎች፤ በረኞች። ዐጸውተ ሲኦል -(ኢዮ፳፰ -፲፯)

ዐፀደ -ዐጨደዐጺድ ዐጸደ

(ጥጸ )        ዐጸድ [1]-የሚያጭዱ፤ ዐጣጫጆች። ወበጊዜ ማእረር ብሎሙ ለዐጸድ፤ ወዐጸድኒ መላእክት ሙንቱ -(ማቴ፲፫ - -፴፱። ያዕ፭ -)

[2]-ቦታ ወልወል ደጅ ምድምድ ርስት፤ ወዠድ፤ የምድር ክፍል፤ ያንዳንድ ሰው ድል፤ ፈንታው ድርሻው፤ በዙሪያው ዐጥር ቅጥር ወሰን ደንበር ያለው፤ የዝሪት ያታክልት ስፍራ የሰው የእንስሳት ሰፈር፤ ቤት በረት ያለበት ገጠር መንደር ቦቱ ዐዘቅት ውስተ ዐጸድ ወሤጡ ዐጸዶሙ ዐጸደ ወይን ዐጸደ ሐምል። ዐጸደ ይት። ዓለም ውእቱ ዐጸደ ገቢር ወዘይመጽእሰ ዐጸደ ዕሴት፤ ዓለምኒ ዐጸደ ጻማ ወድካም፤ ወዘይመጽእኒ ዐጸደ ፍግዓ ወዕረፍት -(፪ነገ -፲፯ -፲፰ ግብ፭ -፩። መክ፪ -፭። ዘዳ፮ -፲፩ ዮሴፍ) በቦታው ላይ የሚበቅለውም ዛፍ ዐጸድ ይባላል። ዐጸደ ቤተ ክሲያን፤ ዐጸዳም እንዲሉ። -(ተረት) ዐጸድ የሌለው ደብር፤ ጽሕም የሌለው መምር።

ዐፂም ሞት -(ዐፀመ የዐፅም ይዕፅም። ዕብ ዐጻም) መጥናት መበርታት፤ ዐጥንት መኾን።

ዐጺር -የተጠመቀ ጥማቂ ውጤት። ኢይሰቲ ንከ ምዝንቱ ዐጺረ ፍሬ ወይን፤ እስከ ሰትዮ ሐዲሰ -(ማቴ፳፮ -፳፱)

ዐጺቅ ቆት -(ዐጸቀ የዐጽቅ ይዕጽቅ ዕብ ያጻቅ መረ አፈሰሰ የውሃ) ማጐምጐም፤ ማፈጥፈጥ፤ መብቀል፤ መክበብ፤ ዙሪያውን፤ መውጣት ማደግ መርዘም፤ ቁመት መጨመር የቅጠል የዛፍ መጽሐፍ ግን በዐጸቀ ፈንታ አዕጸቀ ይላል፤ ስሕተት ነው -(ሄርማ -ገ፶)

ዐጺብ ቦት -(ዐጸበ የዐጽብ ይዕጽብ። ዕብ ዐጻብ) ዐጸባ መኾን፤ መጭነቅ፤ መክበድ፤ መባስ፤ መክፋት፤ የጊዜ የሥራ የመከራ ምንት ትኄልዩ ዘየዐጽብ። ይዕጽብከ ዝንቱ ነገር ወዐጸቦ ለሐማን ዝንቱ ኵሉ -(ሉቃ፲፪ -፳፮ ፪ነገ -፲፩ -፳፭። ዮሴፍ)

ዐጺው ዎት -(ዐጸወ የዐጹ ይዕጹ ዕብ ዐጻህ) መዝጋት፤ መግጠም፤ መቈለፍ ማተም፤ ማገድ መከልከል፤ እንዳይወጣ እንዳይገባ ማድረግ፤ ማጠር መቅጠር፤ ማሰር ማጋዝ መድፈን መምረግ መደበቅ ማሥረግ ዕጹ ኆኅትከ አልቦ ዘይክል ዐጺዎታ። ዐጸወ ዕሌሁ። እመ ዐጸወ ዕለ ሰብእ መኑ ያርኁ  የዐጹ ምሕረቶ ምኔሁ ዕጽዎ ነገር ወኅትም መጽሐፎ -(ኢሳ፳፮ -፳። ራእ፫ -፰። -፫። ኢዮ፲፪ -፲፬ ዮሐ፫ -፲፯ ዳን፲፪ -)

ዐጺድ ዶት -(ዐጸደ የዐጽድ ይዕጽድ። ዕብ ዐጻድ፤ ገዘመ። ሱር ዐረ ሐጻድ) ማጨድ መቍረጥ፤ መቈጥቈጥ፤ ያዝመራ የሣር የቅጠል መክፈል፤ መወሰን፤ የቦታ የርስት፤ የዘመን። ማእረር በጽሐ ለዐጺድ። ዘየዐጽድኒ ይነሥእ ዐስቦ። ዕጽድ ሣዕረ -(፩ነገ -፲፫ -፳፩ ዮሐ፬ -፴፮። ምሳ፳፯ -፳፬) ጸደየን ተመልከት የዚህ ዘር

ዐፂፅ ዖት -(ዐፀ ዐፀፀ የዐፅፅ ይዕፅፅ። ዐፀወ) መፈታት ዱር ደን ዕንጨታም መኾን ያገር የመንደር

ዐጺፍ ፎት -(ዐጸፈ የዐጽፍ ይዕጽፍ። ዐጠፈ) ማጠፍ መደረብ፤ ዕጥፍ ድርብ ማድረግ። መልበስ መጐናጠፍ። ብፀዕት ነፍስ ንተ ምቅድመ ትዕጽፍ አብራኪሃ በውስተ ጸሎት ይሠርቅ ዕሌሃ ጸዳል። ወዕጽፍ ሳድስተ ሠቀ -(አረጋ -ድ፴፪። ዘፀ፳፮ -)

ዐጻሪ -የሚጠምቅ ማቂ ንጉሥ ሓዲ ዐጻሬ ሰማዕታት በምክያድ -(ስንክ -መስ፲፰)

ዐጻዊ -(ዊት ውያን ያት) የሚዘጋ ዘጊ፤ በረኛ። ዐጻዊኒ ያርኅዎ። መት ዐጻዊት። ጻውያነ ዋኅው -(ዮሐ፲ -፫። ፲፰ -፲፯)

ዐጻዲ -(ዲት ድያን ያት) የሚያጭድ ዐጫጅ፤ ቈራጭ ፋይ ወሳኝ

ዐጻፊ -(ፊት ፍያን ያት ጸፍት) የሚያጥፍ ዐጣፊ፤ ተጐናጣፊ። ዐጸፍተ ብርሃናት -(ኪዳ)

ዐፅ -ምድረ በዳ፤ዐፂፅ ዐፀፀ

 -() ዐፅ -(ዓፅ) ዱር በረሓ፤ ባዶ ባድማ ወማ የአራዊት ስፍራ ከመ ኢትኩን ምድር ዐፀ። ኮነት በድወ ወዐፀ በብሔረ ዐፅ። ዐፅ ይእቲ ምሰብእ ወእምአንስሳ -(ዘፀ፳፫ -፳፱ መቃ -፲፫ ኤር፪ -፮። ፴፱ -፵፫)

ዐጽም -በቁሙ፤ዐፅም 

ዐፅም -(ዕብ ዔጼም ዐረ ዐጥም) በቁሙ፤ ዐጥንት፤ የሕዋሳት ክፍል በሰው በእንስሳ ገላ የሚገኝ፤ የሥጋና የደም መሠረት፤ ደረቅ ጠንካራ፤ የተላጠ ንጨት የሚመስል ዕንጨትማ በየክፍሉ ብዙ ስም ያለው። ዛቲ ዐፅም ምዐፅምየ ኢትስብሩ ዐፅሞ -(ዘፍ፪ -፳፫ ዘፀ፲፪ -፵፮)

ዐጽሮ ሮት -(ዐጸረ ይዔጽር የዐጽር። ዐረ ዐጸረ ሱር ዐጻር) መጥመቅ መጭመቅ፤ ማሸት መርገጥ፤ ማፍተልተል ማፍረጥረጥ፤ መዘለል፤ የወይን የዘይት የድፍድፍ፤ የልብስ ለሰውም ይኾናል። ሶበ የዐጽርዋ ትገብር ደመ ስካል። ስተርከቡ ወዐጸሩ ውስተ ፉሁ። ለእ ዐጸርከ አንፈከ ይወፅእ ደም። ዐጸሮ ውእቱ ፀምር። አብእዎ ውስተ ምስካበ ኀጺን ወዐጸርዎ -(መቃ -ገ፳። ዮሐ፲፱ -፳፱ ምሳ፳፬ -፷፰። መሳ፮ -፴፰። ስንክ -ግን፲፱)

ዐጽቅ -በቁሙ ቅጥይ ክንፍ ቅርንጫፍ ውልብልቢት ለኵሉ ዐጽቅ ዘኢይፈሪ ሥርዎሙ ወኢዐጽቆሙ -(ዮሐ፲፭ - ሚል፫ -፲፱)

ዐፅይ ዮት -(ዐፀየ የዐፂ ይዕፂ ዕብ ቱሎፅ) መትላት፤ ትል ማውጣት። ዐፀየ ወጼአ። ይጸይኡ ወየዐፅዩ ዘበጦ መልአከ እግዚ ለአግሪጳስ ወዐፀየ ወሞተ(ዘፀ፲፮ -፳። ኤር፲፭ - ዮሴፍ። ግብ፲፪ -፳፫)

ዐጽፍ -(ፋት) በቁሙ መጐናጠፊያ መደረቢያ የላይ ልብስ ካባ በርኖስ ጋቢ ጃኖ ድርብ፤ ቋሬ፤ ልግም በገላ፤ የሌት ልብስ የመሰለው ኹሉ። ልብስየ ወዐጽፍየ ወዳዊትኒ ቅኑት በዐጽፍ ዘዕጹብ ሤጡ። ዘዐጽፈ ትጉሃን ዐጽፉ ሰላም ለበርሶማ ትርሲተ ዓለም ዘገደፈ፤ ስከ ኢያጥረየ ዐጽፈ -(ዕዝ፱ -፫። ፩ዜና -፲፭ -፳፯ ስንክ -ጥር፲፯ ጳጕ፭)

ዐፈር -(ዕብ ዐፋር። ሱር ዐፍራ) በቁሙ፤ መሬት ትቢያ ዐቧራ -( -) የመሬትን ፍች እይ። -(ግጥም) ከቤተ ክሲያን ጓሮ ጥቂት ጥጥ ቢኖረኝ፤ ለልብስኽ አታስብ ዐፈራለኹ አለኝ።

ዐፈየ -(ትግ ዐረ) ዳነ ተፈወሰ ጤና አገኘ፤ ባለጤና ኾነ

ዐፊር ሮት -(ዐፈረ የዐፍር ይዕፍር። ዕብ ካፋር። ሱር ዐፋር) መሸፈን ማልበስ፤ መቅባት መለቅለቅ። ከፈረን ተመልከት።

ዑረት -ዝኒ ከማሁ፤ ዕውርነት። በእኪት ዑረት ልቡ ዑረተ የአኪ ምዑረተ ዐይን -(ዲድ - ሲኖዶ ማር፫ -፭። ሮሜ -፲፩ -፳፭)

ዑቀት -ማወቅ፤ መታወቅ፤ አስተዋወቅ፤ ዕውቅነት፤ ዕውቀት ዕውቂያ -( - -፴፫)

ዑቃቤ -ዝኒ ከማሁ፤ መጠበቅ፤ ጥበቃ፤ ጥንቃቄ። ዑቃቤ ሕግ ቃቤ ሰንበት። ዑቃቤ ጥንቁቅ፤ ሰብአ ዑቃቤ። በዐቢይ ዑቃቤ -(አርጋ። መጽ -ምስ አቡሻ -፫። ቀሌ)

 -ውቃቢ፤ መንፈስ፤ መልአክ፤ ቆሌ፤ በሰው ያደረ ሀብት፤ ግርማ፤ ሞገስ፤ ቀልብ፤ ለዛ፤ ጣዕም፤ ውበት ደም ግባት። ባማርኛ ለክፉም ለበጎም ይነገራል፤ ቆሌ በጭራሽ የክፉ ነው ውቃቤ ቢስ ቆሊያም ቆሌ ቢስ፤ ቀልበ ቢስ፤ ክፉ ውቃቢያም፤ ቀልባም በርስዎ ውቃቢ፤ በጎ። -(ተረት) ሐሰት ቢናገሩ ውቃቢ ይርቃል

ዑታቤ -ዝኒ ከማሁ፤ ቡራኬ አበራረክ። በስመ ዚኣሁ ደሉ ኵሉ ዑታ -(መጽ -ምስ)

ዑደት -(ታት) በቁሙ፤ መዞር፤ አዟዟር ዙረት ዑደተ ሆሳዕና። ዑደተ ፀሓይ ዘእንበለ ይግበር ዑደታተ ከዋክብት ለአዝማን -(ቅዳ። አቡሻ -፴፯ መቃ) በዑደት ፈንታ ዕዋዴ ይላል አንድ ነው ሶበ ፈጸመ ዕዋዴሁ -(አቡሻ -፲፫)

ዑድ -(ዐረብ) የሬት ዕንጨት፤ ሽታው የሚያውድ ከሩቅ የሚሸት ቀናንሞስ ወሰሊኆት ወዑድ -(ዲድ -፳፭ መጽ -አዳር - -) ዐልውን ተመልከት

ዑድር -(ዐረብ) ምክንያት፤ ሰበብ፤ ሳብ፤ የነገር ማፍረሻ፤ ራስን በደል ለማንጻት። ነገሮ ዑድሮ ወተወክፎ ፍምፍምዮስ። ልብክሙ ዑድር። ኢሊተ ድር ሕይወትክሙ -(ዮሴፍ)

ዑጋት -ዕንጐቻ ሥሥ ክብ፤ የጣቢታ ዐይነት ዑጋተ ገም -(ሕዝ፬ -፲፪)

ዑፃዌ -ዕፃ መጣጣል ዕፃ። መጽሐፈ ዑፃዌ በጽሖ በዑፃዌ አንበሩ ዑፃዌ -(ኩፋ -፱። መጽ -ምስ ስንክ -ሚያ፫ አርጋ -)

ዑጻፌ -ማጠፍ፤ መታጠፍ፤ አስተጣጠፍ፤ ጥፈት፤ ዐጠፋ። መልበስ፤ መደረብ። ዐጽፍ፤ መደረቢያ -(ስንክ -ሐም፳፩)

ዒለት -መዞር፤ ዙረት አዟዟር።

()ሥራት -በቁሙ፤ ዐሥረኛ፤ እጅ፤ ክፍል ካሥር አንድ፤ ቀረጥ፤ ግብር ወሀቦ ዓሥራተ ድ። ዓሥራታ ለኢ ዓሥራቱ ዓሥራት። ዓሥራቲቲሁ ለባት -(ዘፍ፲፬ -፳። ዘፀ፳፱ -፵። ዘኍ፲፰ -፳፮ ሕዝ፵፭ -፲፬)

ዓለማዊ -የዓለም፤ ዓለመኛ፤ ዘመናይ፤ ሥጋዊ፤ ሕዝባዊ ካህን መነኵሴ ያይዶለ ብዕል ዓለማዊ ደብተራ ዓለማዊ። ግብራትን ዓለማውያት እመሂ ካህን ወእመሂ ዓለማዊ - -፲፰ -፩። አፈ -ድ፲፭ ፊልክ -፫። ቀሌ)

ዓለም [1]-(ዕብ ቴቤል። ዐረ መስኩነት) በቁሙ፤ ዓለመ ሰብእ፤ ሰው የሚኖርበት ምድር፤ መሬት፤ የአዳም ክፍል፤ የልጆቹ ቦታ ለእግ ምድር በምልኣ ዓለምኒ ወኵሎሙ እለ ይነብሩ ውስቴታ -(መዝ -፳፫ ኢሳ፲፬ -፲፯ ፴፬ -፩። ኩፋ -)

[2]-ዓለም፤ -(ማት) ዐረብ ላም ሱር ዓላም) ጊዜ፤ ዘመን፤ ትውልድ፤ ያለፈ ቅድም፤ ጥንት፤ ትካት፤ ወይም ወደ ፊት የሚመጣ ወራት ወትር፤ ዘልፍ ድንት መቼም መች የሰው ድሜ መዋዕለ ሕይወት በከመ መዋዕለ ዓለም ወለዓለምኒ ደምት ኮነ ርኣያ ለዓለም ይነስሑ ቢያት እለ እምዓለም -(ሚክ፯ -፲፬። ፪ጴጥ - -፭። ሢራ፵፬ -፲፮ ግብ፫ -፳፩)

 -ፍጥረት፤ ዘመደ ፍጥረት፤ እግዜር ከእሑድ እስከ ዐርብ የፈጠረው፤ ሰማይ ከነዜጋው፤ ምድር ከነመንጋው። ወይም ሰማይ ከነግሱ ከነደመናው ምድር ነልብሱ ነጕተናው። እምፍጥረተ ዓለም እምቅድመ ዓለም ሰማያት ወምድር ምስለ ኵሉ ዓለሞሙ -(ኢዮ፫ -፲፰ ቅዳ -ዲዮ ግሩ)

 -ው፤ የሰው ነገድ፤ ነፍስ ያለችው ሥጋ ወፅአ ትእዛዝ ይጸሐፍ ኵሉ ዓለም። ዓለምኒ ቦቱ ኮነ ወዓለምሰ ኢያአመሮ ዝንቱ ዓለም -(ሉቃ፪ -፩። ዮሐ፩ - ሮሜ፰ -)

 -ከተማ መዲና፤ ሹመት ብዕል፤ ሥጋዊ አናዎር ነበረ ውስተ ዓለም ምቅድመ ይመንኵስ ዕሥራ ዓመተ። ፈለሱ ገዳመ ወመነኑ ዓለመ -(ስንክ -ሐም፰። ቀሌ)

ዓለም ዘይመጽእ -ዓለመ ነፍስ፤ ሞትና ኅልፈት በኋላ የሚመጣው በዝ ዓለም፤ ወኢበዘይመጽእ -(ማቴ፲፪ -፳፪)

ዓመተ ምሕረት -ዝኒ ማሁ የይቅርታ ዘመን፤ ዘመነ ሥጋዌ

ዓመተ ሥጋዌ -ቃል ሥጋ ኹኖ ከተወለደበት፤ ዓለም በሐዲስ ተፈጥሮ ከተፈጠረበት፤ ዳግማይ አዳም ከክርስቶስ ወዲህ ያለው ዘመን

ዓመተ ዓለም -ከጥንት ፍጥረት ከአዳም ምሮ ያለው ዘመን

ዓመት -(ታት) በቁሙ፤ ዝኒ ከማሁ። በቀዳሚ ዓመተ መንግሥቱ ትመውት በዝንቱ ዓመት ምእት ወኀምሳ ዓመት ሎቱ ዓመታተ ብዙኀ ሐይወ። ኍልቈ ዓመታቲከ -(ዳን፯ -፩። ኤር፴፭ -፲፮ ጦቢ፲፬ -፲፩ ኢዮ፴፰ -፳፩)ዓመትበቁሙ፤ዓም

-በቁሙ፤ዓም

ዓም -(ዐረብ) ዓመት ዘመን ብዙ ቀን የዕለታት ድምር፤ ዐውዳቸውና ቀመራቸው፤ ፻፷፭ ለት ከዕለት ርቦ በውስጡ አራት ክፍሎች፤ ዐሥራ ኹለት ወሮች ያሉት። ሥሩና ምንጩ ዐመመ ነው በአልፍ ሲጣፍ ግን እመምና ገዝም ያሳያል በውእቱ ሳብዕ ዓም። በሣልስ ዓም እምዘነግሠ በኵሱ ዓም ወዓመት ዓም ምዓም ዓመ ከመ ዮም እመ ትፈሪ ለዓሙ -(ዘሌ፳፭ - አስቴ፩ -፫። ኩፋ - -፪። ዘፍ፲፰ -፲። ሉቃ፲፫ -)

ዓሣ -(ዕብ ዓሽ ዐረ ዑሸት ዕፄ) በቁሙ፤ የባሕር እንስሳ መልኵና ነገዱ የተለየ የስሙ ምስጢር እንደ ትልና እንደ ይሲ አለእግር መኼድ በልብ መሳብ ነው፤ ዋነተኛነትም አለበት እገሌ ዓሣ ነው እንዲሉ በከመ ዓሣ ሶበ ወፅአ ማይ ይመውት ፍጡነ ዓሣተ ባሕር ወአዕዋፈ ሰማይ -(ፊልክ -፷፩። ዘፍ፩ -፳፮)

ዓሥራይ -( ሪት) ዝኒ ማሁ ዐሥረኛ። በዓሥራይ ወርኅ -(ሕዝ፴፫ -፳፩)

ዓሥር -ዐሥረኛ። በዓሥር ዓመት መንግሥቱ በዓሥር ወኃምስ ዓመት። ወዓሥሮሙ ነግር -(ኤር፴፱ - ፪ዜና -፲፭ -፲። ራ፳፭ -)

ዓናቅ ዔናቅ -ረዐይታዊ ያል ርበኛ እጅግ ብርቱ፤ መለሎ ረዥም ወርዳም ቁመታም መጠኑ ከሰው ልክ ያለፈ። ርኢነ ትውልዶ ለዔናቅ። ወኮነ ቅድሜሆሙ ከመ አናብጥ -(ዘኍ፲፫ -፳፰ -፴፫) ናፌልን እይ ከዚህ ጋራ ነው

ዓው -ጭን፤ የጭን ራስ፤ መብቀያው፤ ሆድ ጋራ የተያያዘው ማጠፊያው ማውዱ ሥርው ዘሀሎ ውስተ ዓወ እግሩ -(ዘፍ፴፪ -)

ዓዲ [1]-ዳግመኛ፤ዐድይ ዐደየ።

 [2]-(ዕብ ) ንኡስ አገባብ፤ ገና፤ ደግሞ፤ ዳግመኛ፤ አኹን፤ እንጂ ዋዌ ይኾናል እንጂ ሲኾን ዐቢይ አገባብ ነው፤ ዳግመኛነቱን ግን አይለቅም። ዓዲ ኢበጽሐ ጊዜሁ ተዐገሡ ዓዲ ሙሰ መዋዕለ እስከ ዓዲሁ ዓዲ ሊተኒ -(ዮሐ፯ -፰። ዮዲ፰ -፴። አፈ -ድ፬ ፊልጵ፪ -፳፯) ዓዲየ ዓዲነ እያለ እስካሥር ይዘረዝራል። ዋዌ ሲኾን፤ ሄሮድስ ወጲላጦስ ተንሥኡ ቅድመ ንበለ ፍትሕ ላዕለ ቡሁ ቀባዒ ወላዕለ ወልዱ ቅቡዕ ማሆሙ ተንሥኡ በግፍዕ ታንክርዋ ለዘትመጽእ ኀቤነ መከራ ዘሃይማኖት ስመ ፍዳ ዕሴት ኀዊነ -(ቅኔ) -(ዕር፲፱ -ቍ፹)

ዓዶት -(ትግ ሐባ ዳት) ሕግ ሥርዐት፤ የአበው ትውፊት፤ ልማደ ሀገር -(ማር፯ -) ሐማሴኖች እናቴ ሲሉ ዓደይ፤ ጋሎችም ዓደቶ የሚሉት ከዚህ ይሰማማል።

-(አራም) ስመ ፊደል፤ ዐይን በዐረብ በግእዝ በዕብራይስጥ ዐይን የሚባለው፤ በአራም ቋንቋ ይባላል ገበርከ ፍትሐ ወጽድቀ -(መዝ፻፲፰ -፻፳፩ ሰቈ፩ -፲፮ -፲፮ -፵፬። -፲፮)

ዔላ -(ላት) ዐዘቅተ ማይ፤ የውሃ ድጓድ፤ መከማቻ መጠራቀሚያ። ዔላ ዘውእቱ ምእላደ ማይ . . . . . ያመጽኡ ሎሙ ማየ ወይመልእዎ በዔላት -(ታምረ -ማር)

ዔመ -አፈገ፤ መሰገ አገባ፤ አጐረ።

ዔረግ [1]-(ዕብ ሄሬግ የሰይፍ ሞት ዐረ ሒርግ) ወጥመድ፤ አሽክላ፤ ያውሬ መያዣ እስመ ፍቅረ ወይን ብህለ ሰይጣን ዔረጉ -(ደራሲ)

[2]-(ዕብ ክሉብ) ቀፎ፤ ቅርጫት የአዕዋፍ ቤት፤ ቀማጭን ሐረግ ወይም ሽቦ የተሠራ፤ ሐረገን ተመልከት። ዔረግ ዘምሉእ ዕዋፈ -(ኤር፭ -፳፯) በፍሬ ፈንታ ዔረግ በዔረግ ፈንታ ሙዳይ ይላል፤ የተሳሳተ ነው ሙዳየ ረግ -(ዓሞ፰ -) ዕብራይስጡ ግን ሉብ ቃይጽ ይላል፤ የበጋ ቅርጫት ማለት ነው፤ ፍሬ የተመላ ማለትን ያሳያል። ባለብሉዮች ግን በለው ይፍ፤ ጻብታ ፃግታ ይሉታል፤ የበዳ ጸብት ንዋየ ቅል ማለት ነው። ዳግመኛም ሙዳየ ዔረግ በማለት ፈንታ ቄረጽ፤ ይቄርጽ ይላል፤ ይህን ደግሞ፤ መቀስ ይሉታል፤ ንባቡም፤ ፍችውም አልተሳካም።

 [3]-ወጥመድ፤ዐየረ

ዔር [1]-(ዕብ ዒር) ጠባቂ መልአክ። ምስጢሩ ግን ነሣቲ ደያኒ ማለት ነው። ወናሁ ዔር ቅዱስ -(ዳን፬ -)

 [2]-ዔርጠባቂ መልአክ፤ዐየረ

ዔቦር -(682) -(ዕብ ዔቤር) የሰው ም፤ የሴም ፭ኛ ትውልድ -(ዘፍ፲፩ -፲፬ ሉቃ፫ -፴፭)

ዔዴን -(ዕብራ) ምቹ ቦታ፤ ወፍራም ሥብ መሬት፤ አሻል ፋልማ። ከቦታው የሚገኝ ፍጹም ተድላ ጣዕም ሥን መዐዛ፤ ጽል ልምላሜ ተከለ እግ ምላክ ገነተ በዔዴን ምቅድም፤ ወሤሞ ህየ ለአዳም ዘለሐኮ -(ዘፍ፪ -) አንዳንድ መጽሐፍ ኤድም ኤይም ይላል፤ የተሳሳተ ነው። ኤዶምን ተመልከት ባለብሉዮች ግን ምሥራቅ ይሉታል ምሥራቅ የሚባል ቅድም ነው እንጂ ዔዴን አይዶለም።

»ዕለት -(ታት) መዋል አዋዋል፤ ውሎ ውለታ። ቀን ጊዜ በዕለተ ምንዳቤ በዕለት ሪት ኅጹር ዕለትየ ዕለተ ነግ ወሠርክ -(ሢሪ፪ -፲፩ ኢሳ፵፱ -፰። ዕብ፲፩ -፴፪ ኩፋ -)

 -መዓልት ከነግህ እስከ ርክ ሣልስተ እዴሆሙ ለዕለት ወለሌሊት በእፎ ዕለት እምዕለት ትነውኅ ዕለታት ወለያልይ -(ራእ፰ - ሢራ፴፮ -፯። ቅዳ)

 -በቁሙ፤ የጊዜ ክፍል ከ፯ አንድ፤ መዓልትና ሌሊት ፳፬ ዓት ዕለት ብሂል ዘያስተዛውጎሙ ለሌሊ ወለመዓልት ወኮነ ምሴተ፤ ወኮነ ጽባሐ፤ አሐደ ዕለ ሰቡዐ ዕለታተ በዕለት ሳምንት -(አዋል። ዘፍ፩ -፭። ፩ነገ -፲፩ -፫። ኩፋ -፲፭)

 -ቢይና ደቂቅ አገባብ ሲኾን፤ ሰዓ ሰዓተ እንደሚገቡ ባል ዕለ ተወልደ በዕ ሰቅለ፤ ምዕ ትበልዑ ምዕ ፍረቶ። ዕጼውዐ እያለ ካገባብ ጋራ በኀላፊና ንቢት ይገባል ደቂቅ ሲኾን በዕ ቀትል እያለ በጥ ይገባል ፍችው ቀንና ጊዜን ይለቅም። ዘወትር ኹል ለት ለት ለቱ ለቱን በዚያው ቀን በዚያው ጊዜ ወዲያው ሳይመሽ፤ ወይም ይነጋ ኛል በግዜር ዘንድ ግን ለት የሚባለው ሺሑ ዓመት ነውና -(መዝ -፹፱። ጴጥ - -) ፭፻ው ዓመ እኩል ቀን ይባ «ይቤሎ ፈሰ እግብሔር ዘውእቱ ቃል ስተር ምሳ መልአክ» ለእክንድር፤ እመ በጽሐ ዘመኑ ትየ ሙስ ወበመፈቀ ብስ ሥጋሁ ዳም አቡከ እን ልወቱ -( -እስ -ክ፮)

ዕሉል -(ላን ላት ልልት) የተለየ ልዩ ውጉዝ፤ ብቸኛ። ይኩን ዕሉለ ይሰመዩ ፈሪሳውያን ወትርጓሜሁ ስም ዕሉላን -(ዮሴፍ)

 -የታለለ፤ ቀለም የገባ። አልባሰ ምሥዋዕ ይኩኑ ጽዕድዋነ ወአኮ ዕሉላነ በዘዘ ዚኣሁ ሕብራት -( - -፴፩ -)

ዕሉም -ዕልም ያለ ኅቡእ ረቂቅ ስዉር ድብቅ። መጽሐፍ ግን በዕሉም ፈንታ ዓለም ይላል ወዓለምነሂ ውስተ ብርሃነ ጽከ -(መዝ -፹፱)

ዕሉይ -ወንጀለኛ፤ ክፉ ወስላታ ብድ ወዕሉየ ኅሊና -(መቃ)

ዕልወት -(ታት) መወንጀል፤ መለወጥ፤ ወንጀል፤ ዐመፅ፤ ክዳት፤ እንቢታ፤ አደጋ ጥፋት እስመ ልወተ ሕግ ውእቱ ብር አዝማነ ዕልወታት ንትሉ በዕልወትነ ትበጽሖሙ ዕልወቶሙ ምኀበ እግዚ ኮነት ዕልወተ ካዝያስ -(ዲድ -፲፭ ስንክ -ነሐ፳። ኤር፲፰ -፲፪። ኢዮ፳፩ -፲፯ ፪ዜና -፳፪ -)

 -መቅጃ፤ መዝገብ፤ ረቂቅ፤ መዠመሪያ የወጣ መጽሐፍ። ወይም ቅጅ፤ ግልባጭ፤ ከዚያው ከምንጩ የተቀዳ፤ የቅጅ ቅጅ ያይዶለ። ሀሎ ኀቤነ ዕልወቱ ውእቱ መጽሐፍ -(ተረ -ቄር፲፭)

ዕልው -(ዋን ዋት ሉት) የወንጀለ፤ ዐመፀኛ፤ ክፉ፤ ጠማማ ልውጥ፤ ከሓዲ። ንጉሥ ልው ትውልድ ዕሉ ለዕልዋን ልወ ፍኖተ ይፌኑ ሎሙ። ዕልዋነ ሃይማኖት። ዕልዋን ወመናፍቃን -(ስንክ -መጋ፰ መዝ -፸፯። ምሳ፳፩ -፰። ዲድ -፴፫። ቀሌ)

ዕልገት -ማሸነፍ፤ መጣል፤ መግደል፤ መስለብ መግፈፍ የድል ምልክት ምርኮ ሰለ የደም ሸማ፤ ትምክሕት፤ ድንፋታ፤ ልዕልና ከፍታ፤ ቅርርት ፍከራ፤ የዠግንነት ሥራ። ዕልገተ ቈላፋን። ዘብዙኅ ዕልገቱ። ወሎቱሰ አግብኡ ሎቱ ዕልገቶ በእልፍ። በመጥባሕትከ ዕልገትከ ያነብሮሙ በዕልገቶሙ መልዕልተ -(፩ነገ -፲፰ -፳፭ ፪ነገ -፳፫ ሢራ፵፯ -፮። ዘዳ፴፫ -፳፱ ኢዮ፴፮ -)

ዕመቅ -(ቃት) ጥልቀት፤ ጥልቅነት፤ አጠለቅ ጥልቅ ዕመቀ ቀላይ። ዕመቃቲሆሙ ለአብሕርት። ዕመቀ ምስጢር። ዕመቂሁ ለብዕለ ጥበቢሁ -(ኢዮ፲፩ -፰። ቅዳ -ሕር ቄር። ሮሜ፲፩ -፴፫)

ዕሙቅ -(ቃን ቃት ምቅት) በቁሙ የጠለቀ ጥልቅ ወደ ቻች የራቀ ሩቅ ኅቡእ ረቂቅ የማይታይ የማይታወቅ፤ጨለማ ውድቅት። ሰማይ ልዑል ወምድር ዕሙቅ ቈላ ዕሙቅ ሙቅ። ቀላ ዕሙቅ። ይከሥት ዕሙቃተ ምጽልመት። ይመክሩ ዕሙቀ ምክረ ዕሙቅ ከናፍሪሁ። ሊተ ዕሙቀ -(ምሳ፳፭ -፫። ሔኖ፳፮ -፫። መዝ -፷፰። ኢዮ፲፪ -፳፪። ኢሳ፳፱ -፲፭ ሕዝ፫ -፭። ኪዳ)

ዕሙፅ -(ፃን ፃት ምፅት) የተገፋ የተበደለ ዘከዐወ ደመ ዐማፂ ዕለ ደመ ዕሙፅ ዕሙፃን -(ዮሴፍ። ፊልክ -)

ዕሡር -የተጠራ፤ ዕድመኛ -(ስንክ -የካ፳)

ዕሱቅ -የታ የተለሰቀ፤ ክታን ከሐር ጥፍ ድርብ ኹኖ የተሠራ። ግብረ ማእነም ዕሱቅ። ወክዳኑ ለአንቀጸ ዐጸድ ዕሱቅ በደርከኖ ልብሰ። ሜላት ዘወርቅ ወመረግድ ወዕንቍ ዘብዙኅ ዕሱቅ ውስቴቱ -(ዘፀ፴፮ -፲፭ ፴፯ -፲፮ ዮዲ፲ -፳፩)

ዕሱይ -የተቀበለ፤ ዋጋውን ያገኘ።

ዕሴት -( ዕስያት) ዋጋ ደመወዝ ስጦታ መባእ ምጽዋት -(እሺታ) ሀጕሉ ዕሴቶሙ ውእቱኬ ዘይነሥእ ሴቶ ወዕሴትየኒ ምስሌየ ውእቱ ፍድዮ ለኵሉ ለለ ሐዱ -(ማቴ፮ - ፩ቆሮ - -፲፬። ራእ፳፪ -፲፪)

ዕሥራ -ካያ ኻያ -( ) ኹለት ጊዜ ዐሥር፤ ወይም ዐሥር ጊዜ ኹለት ካዕበተ ዮድ ምክዕቢተ የውጣ። ዕሥራ በእመት ዕሥራ ሰቅል ምእት ወዕሥራ -(ዘካ፭ - ሕዝ፬ -፲። ግብ፩ -፲፭ ራእ፬ -)

ዕሥር -ዐሥር የጊዜ ቅጽል። ዕሥር ወኅምስ በእመት -(ዘፀ፳፯ -፲፬)

ዕስቁፍ -ኤጲስቆጶስ፤እስቁፍ

ዕረፍት -(ታት) በቁሙ፤ ማረፍ፤ ዕርፊት፤ ሞት። መካነ ዕረፍት። ባእ ውስተ ዕረፍቱ ሠለስቱ ዕረፍታት። ሶበ በጽሐ በጊ ዕረፍቱ ለአዳም -(ሱቱ -ዕዝ፮ -፩። ዕብ፬ - -፫። አፈ -ድ፮)

ዕሩቅ -(ቃን ቃት ርቅት) የተራቈተ፤ የተገለጠ፤ የታረዘ የተገፈፈ፤ ግንዱን መለመላውን የኾነ ዕሩቅ ወዕዉር። ይኩን ዕሩቀ ባል ቅድመ መኑሂ። ወልብስየኒ ለዕሩቃን። ኮኑ ዕሩቃነ ምጸጋ ዘላዕሌሆሙ -(ራእ፫ -፲፯ - - -፫። ጦቢ፩ -፲፯ ቀሌ)

 -ባዶ ወና ብላሽ፤ ከንቱ። መሳብክት ዕሩቃት ከርሥ ዕርቅት ትወልድ ፍትወተ በእንተ ስብሐት ዕሩቅ -(መሳ፯ -፲፮ አፈ -ተ፳፱ ፊልክ -)

()          ዕሩዝ -(ዛን ዛት ርዝት) የለበሰ፤ ልቡስ። ኵሎሙ እሊኣ ዕሩዛን እሙንቱ -(ምሳ፳፱ -፴፱። ዲድ -)

ዕሩይ -(ያን ያት ሪት) የተካከለ የተመሳሰለ ትክክል፤ አንድ ዐይነት። አእመረ ከመ ውእቱ ዕሩይ ምስለ ሎሙ ርድእት። ዘዕሩይ ምስለ በመለኮቱ። መፍትው ለነ ንመጽውት ላዕለ ኵሉ በዕሩይ ንዘ እንሌሊ ጽኑሳነ ሩየ ጸልኡ በኀበ እግዚ ረሲዕኒ ወርስዓኑ -( - - -፮። ቅዳ አፈ -ተ፲ ጥበ፲፬ -)

ዕሩግ -ያረገ፤ ልዑል፤ ሥሙር፤ ውኩፍ። ወይኩን ለኵልነ ሩገ ወፈውሰ -(ሥር ቅዳ)

ዕሩፍ -(ፋን ፋት ርፍት) ያረፈ ጸጥ ያለ፤ የረጋ። ዕሩፈ ይነበር። ከመ ይኩን ልብየ ዕሩፈ በላዕሌክሙ -(ኢሳ፴ -፱። ዜና -፲፪ -፲፯ መዝ -፺፩)

ዕሪና -መተካከል፤ አንድነት፤ ትክክልነት፤ አለመበላለጥ ዘኢየአምን በአካላተ ሥሉስ፤ ዘኢየአምን ሪናሁሙ በባሕርይ ወበአምላክና ዘዘ ክብሮቶሙ በዕሪና እፎ ትከውን ክብር በዕሪና። ለይረሱ በዕሪና -( - -፳፯ -፯። ዮሴፍ አፈ -ድ፴፫ - -፵፪ -)

ዕራቅ -(ዕብ ሪቅ) ዝኒ ማሁ ዕራቍት ግንድ መለመላ ባዶ ብቻ፤ ልብስ ጭማሪ አልባ ዕራቅየ ወፃእኩ ምከርሠ ምየ ወዕራቅየ ገብእ ህየ ሑር ዕራቀከ ዘእንበለ አሣእን ወአሦጡ ቀሣውቲሆው ዕራቆ። ዘዕራቁ ለእለ ዕራቆሙ ትስተይ ማየ ራቆ ተጠምቀ በማይ ዕራቁ ጳውሎስ ሳሚሳጤ ይቤ እስመ ክርስቶትስ ሰብእ ዕራቁ፤ ብቻ -(ኢዮ፩ -፳፩ ኢሳ፳ - ኤር፲፬ -፫። ሱቱ -ዕዝ፭ -፳፭ ጢሞ - -፳፫ መጽ -ምስ - -መቅ) ኢምንት በማለት ፈንታ ራቅ ይላል ምስጢሩ አንድ ነው ሰቀላ ምድር ዲበ ራቃ -(ኢዮ፳፮ -)

ዕራይ -እኩያ፤ መሰል፤ አምሳያ ወከመ ዕራይሁ ቀዳማይ ነገር ንሌብዎ ለዝንቱኒ -(ቄር)

ዕርቃና -ዕርቅነት፤ ስምምነት። ሰላም ወዕርቃና ወተሰናእዎ -(ቀኖ -ስርድ፲፬)

ዕርቃን በቁሙ ራቍት ዕራቍትነት ባዶነት ንጽሕና (ግጥም) እኔ ድኻ መስሎኝ ዕርቃኑን ባየው ርሱስ ጌታ ኑሯል የተሰቀለው። ሀበኒ እክድን ዕርቃኖ በልብስ ዘከደነ ዕርቃንየ በዮርዳኖስ (ድጓ) ከመ ይኵን ሎቱ ዕርቃን ለገቢረ ኵሉ ትእዛዛት። ዕርቃኖሙ ሕፃናት እምኅሊናት ሕሥምት (ፊልክ ፵፬ ፪፻፴፭)

o ብልት የወንድ የሴት ኀፍረት አባለ ዘርዕ አፈ ማሕፀን ወኢርእዩ ዕርቃነ ቡሆሙ። ከመ ትክድን ዕርቃነከ ይደሉ ይነጽር ብእሲ ዕርቃነ ብእሲት (ዘፍ፱ ፳፫ ራእ፫ ፲፰ )

ዕርቅ -በቁሙ ሰላም መታረቅ፤ መስማማት ስምምነት። ስከ ይገብሩ ዕርቀ በበይናቲሆሙ ገብረ ዕርቀ ነሣኤ ዋሕስ ምስለ በዓለ ዕዳ -( - -፳፩ -፬። - -፳፯)

ዕርቅና -ዕራቍትነት፤ ዕርዝታ። በረኀብ ወጽምእ ወበዕርቅና -(ዘዳ፳፰ -፴፰)

ዕርበት -ምሸት፤ የፀሓይ ግባት። እስከ ዕርበተ ፀሓይ -(ዘፀ፲፯ -፲፪)

ዕርዝና -(ዕብ ራዞን) ክሳት፤ ቅጥነት ቀጠና፤ ዕርዝታ ችጋር ዕጦት፤ ድኽነት -(ተረት) በርግዝና ላይ ዕርዝና

ዕርየት -መተካክል እኩያ አምሳያ መኾን ይከውን ድልወ ዕርየት ምስለ ባሕታውያን -(ፊልክ -)

ዕርገተ ቍርባን -ቍርባንን ተቀብሎ መስጠት፤ ማቀበል። ወኢይፃእ አሐዱሂ እምቤተ ዘእንባለ በግብር ጹብ፤ እምድኅረ ተነበ ወንጌል ቅዱስ ዘእንበለ ይትፈጸም ዕርገተ ርባን ወበረከተ ካህን -( - -፲፪) ይህም ርገት ተቀባዮቹን ሰማያት ያሰኛል፤ ምስጢሩ ያው ነው

ዕርገተ ዕጣን -ማዕጠንትን በመሥዋዕቱ ላይ ሦስት ጊዜ ማዞር ኹለተኛም ጢሱን ታፍኖ መሥዋዕቱን በእጅ ማጠን። ይንሣእ ህን ማዕጠንተ ወያዑድ ዲበ ርእሰ ምሥዋዕ በዝየ ዕርገተ ዕጣነ ወይዕጥን በእዴሁ -(ቅዳ)

ዕርገት -ማረግ መውጣት፤ አወጣጥ ወተፈጺሞ መዋዕለ ዕርገቱ። ርገቱ ለኢየሱስ ውስተ ሰማይ ዐርገ ያለቡ ዕርገተ ጻድቃን -(ሉቃ፱ -፶፩ ቀሌ። መቅ -ወን)

-በቁሙ ዐቢይ በዓል የትንሣኤ አርባ ኀሙስ ቀን የሚውል ዐቃቦች የሚዘክሩት (ተረት) ባመት እንደርገት ዋዜማ ዘዕርገት። ወዕርገቱ ዮም ሰማያተ (ድጓ)

-መጽሐፍ የመጽሐፍ ስም ፤ የብሉይ አዋልድ ኢሳይያስ ስለ ሥግው ቃል እንደ ሔኖክ በተመሥጦ ያየው ጕልሕ ራእይ ደረቅ ትንቢት ዕርገተ ሳይያስ ነቢይ (ገጽ )

ዕርፍ [1]-መቅጃ፤ መጨለፊያ፤ ማንካ፤ ጭልፋ የዕጣን የቍርባን መሣሪያ፤ ጌታ የተወጋበት የጦር ምሳሌ፤ ትእምርተ መስቀል ያለበት። ግበር እዴከ ዕለ ዛቲ ዕርፈ መስቀል ሠሪዐ ሥጋሁ ወደሙ። ዲያቆን ኢሕጥምቅ ወኢያቅርብ በእዴሁ ዘእንበለ ምጽዋዕ በዕርፈ መስቀል። ዕርፍ ማንካው፤ መስቀል መያዣው -(ሥር -ቅዳ - -፴፩ -)

[2]-በቁሙ፤ የማረሻ እጀታ፤ ዐራሽ የሚይዘው ድጕርን ተመልከት። ዘያጸንዕ ዕርፎ ልቦ ዘይእኅዝ ዕርፈ ወየሐርስ ድኅሪት። ውሂበ ዕርፍ ለጕሕላዊ። እለ ሐረስዋ ምድር በዕርፈ መስቀልከ -(ሢራ፴፰ -፳፭ ሉቃ፱ - ቅዳ -ዮሐ ኩፋ -፲፩)

ዕቀድ -እስራት፤ ማገር። መታሰር መቀየድ

ዕቁም -(ማን ማት ቅምት) የተወሰነ ተቈረጠ የተለየ የተመረጠ፤ የተመደበ፤ የተዘጋጀ። ሥሩዐ ወዕቁመ ወውሱነ በሩ። በሥምረት ዕቁም ሕዝብ ዘዕቁም እምኵሎሙ ዲበ ምድር። ሀሎ ዕረፍት ኀበ ይበውኡ ሕዝበ እግዚአብሔር ሥሩዕ ወዕቁም። ዕቁም በኵሉ ምግባር ከመ የኀሊ -(፩ቆሮ -፲፬ -፵። ኪዳ። -፲፱ አፈ -ድ፮ ዘፀ፴፩ -)

ዕቁር -(ራን ራት ርት) የታቈረ፤ የተቋጠረ ጥር። ዕቁር በአልባሲሆሙ -(ዘፀ፲፪ -፴፬)

ዕቍር -( ዕቈር) ቋጠሮ፤ ጥራት፤ የዐጽቅ ያበባ ችቦ ማቈሪያ መቋጠሪያ፤ ጨርቅ ከረጢት ማድጋ። ዕቍረ ማየ ልብን። ዕቍረ ወርቅ ዕቍረ ስቁር ወርቆሙ በዕቈሪሆሙ -(ማሕ፩ -፲፫ ድጓ። ምሳ፯ -፳። ዘፍ፵፪ -፳፯ና -፴፭። ሐጌ፩ -፮። ኩፋ -፵፪)

ዕቁብ -(ባን ባት ቅብት) የተጠበቀ የተጠነቀቀ፤ ጥብቅ፤ ጥንቁቅ፤ ንቡር፤ ድልው መዝገብ ዕቁብ ውሉዳ ዕቁበ ይትናገር ዘዕቁብ በቃሉ ዕቁብ ለነ ወለክሙ ብእሲት ዕቅብት ብርሲ -( - - - ምሳ፳፩ -፳፰ ቀሌ ጴጥ - - ዘሌ፲፱ -)

ዕቁድ -የታቀደ፤ የተቀየደ ቅይድ ዕቁደ እግር -(ስንክ -ሚያ፲፯)

ዕቁፍ -(ፋን ፋት ቅፍት) የተነቀፈ የተሰናከለ፤ ንቅፋት ያገኘው ወራዳ። ንከውን ዕቁፋነ ወዕዩራነ በቅድመ እለ ያጠረዩነ -(ዮዲ፰ -፳፪)

ዕቃሜ -ውሳኔ፤ ሥርዐት፤ ጠፍታ ክትነት። ሥርዐተ አኀ ወዕቃሜ። ዕቃሜ እለ ይትለአክዎ -(ሥር -ጳኵ። ፫ነገ - -) ዕብራይስጡ ግን መዓማድ ይላል፤ ምቅዋም ቁመት ማለት ነው። በዕቃሜ ፈንታ ዕቅመት ይላል፤ አያሰኝም -(ገድ -)

ዕቅበት -(ላጥ) መጠበቅ፤ አጠባበቅ፤ ጥበቃ። እን የዐቅቡ ዕቅበተ ማኅደር። መሀረክሙ ትእዛዛቲሁ ወዕቅበተ ሃይማኖቱ ጸልዩ በእንተ ማኅበርነ ወዕቅበተ ለኵልነ -(፩ዜና - -፲፱ ዮሴፍ። ሥር -ቅዳ)

ዕቅብት -(ታት። ዕቁባት) ቁባት፤ ምልምል፤ ሥራ ቤት፤ ገረድ፤ ሚስትነት የሌላት። ብእሲት ዕቅብት። ዕቅብታት። አንስት ዕቁባት -(መሳ፲፱ -፩። ዮሴፍ ፪ነገ - -፲፫)

ዕቅጸት -መሰንከል፤ መሰናከ ል፤ ስንከላ ዕቅጸቶሙ ለረሲዓን -(ምሳ፲፩ -)

ዕቅፍት -(ታት) ንቅፋት፤ መሰናክል፤ ወጥመድ እክል ትደይ ዕቅፍተ ቅድመ ዕዉር። የዐቅበከ ምዕቅፍት ብነ ዕቅፍት ትከውኖ ዕቅፍተ -(ዘሌ፲፱ -፲፱ ሢራ፴፩ -፲፱ ኢሳ፰ -፲፬ ነገ -፲፰ -፳፩)

ዕቋን -ለጋ ቅቤ፤ አንቋሊት፤ ርጎ -(ዘፍ፲፰ -፰። ምሳ፭ -፳፭) አዘዘ ከመ ያስትዮሙ ሐሊበ ወመዓረ ወዕቋነ እስከ ምለመ ርዔሆሙ ወአማዑቶሙ -(ዮሴፍ)

ዕበይ -(ያት) ልዕልና ከፍታ፤ ብልጫ ክብር፤ ታላቅነት፤ ገናንነት፤ ብዛት፤ ጽናት። ለዕበይ ወለክብር ንቲ ውእቱ ዕበዮሙ ለእስራኤል በከመ ዕበዪሁ ከማሁ ዕበየ ምሕረቱ። ዕበየ ኀይሉ -(ኩፋ - ዮዲ፲፭ -፱። ሢራ፪ -፲፰ ኤፌ፩ -፲፬)

ዕቡር -(ራን ራት ብርት) የደረቀ፤ ደረቅ። ሐምለ ቅብዕ ዕቡር። ቀጢናን ወዕቡራን -(ኢሳ፶፩ - ዘፍ፵፩ - - -፳፯)

ዕቡይ -(ያን ያት ቢት) በቁሙ፤ ትቢተኛ ልቡ ያበጠ የተነፋ ዕቡየ ልብ ዕቡየ መንፈስ ዕቡየ ዐይን -(ምሳ፲፬ -፲፬ መክ፯ -፰። -)

ዕቤራዊ -(ራይ) ሽማግሌ የባልቴት ባል፤ ሚስቱ እኩያው የኾነች፤ ወይም የምትበልጠው።

ዕቤራዊት -(ይት) አሮጊት፤ ባልቴት እምከ ዕቤራዊት። መአንዝርት ዕቤራይት -(ሔኖ፴፪ -፮። ስንክ -መስ፲፰)

ዕቤር -(ራት) ባልቴት ዕድሜዋ ካምሳ ዓመት ያለፈ፤ ፈጽማ ያረጠች፤ የመውለድ ተስፋ የቈረጠች፤ ሙቀት ልምላሜ የተለያት። ደራቁቻ ባልቴት እንዲሉ ወለእመ ኀረይከ ቤረ፤ ኅረይ ንተ ስሳ ክረምታ መሐደምተ ዕቤራት። ወመኰንኖን ዕቤራት -(፩ጢሞ - -፱። - ፯። መዝ -፷፯)

ዕብራዊ -(ዊት ውያን ያት) የዔቦር ወገን ልጅ ልጆቹ አንዱ። ዕብራዊ ዘእምዕብራውያን አኮ ከመ አንስተ ብጽ፤ ዕብራውያት -(ፊልጵ፫ -፭። ዘፀ፩ -፲፱)

ዕብራዊት -(ጽር አንድሪያ) ወንዲላ ደረቅ ብርቱ፤ ልባም፤ ወንዲት ዐጅሪት የምትባል፤ -(ሢራ፳፮ -) ግእዝ ግን በዕብራዊት ፈንታ ብዕራዊት ይላል፤ ብዕረን ተመልከት።

ዕብራይስጥ -(ጽር ሄብራዬስቲ) የዔቦር ቋንቋ፤ እስራኤል የሚናገሩበት፤ ኦሪት ነቢያት መዠመሪያ የተጣፉበት፤ የብሉይ ኪዳን ምንጭ የሱርስት የዐረብ የግእዝ ወንድም። ኢትንግረነ ዕብራይስጠ። ጽሑፋት በዕብራይስጥ። ወጸርሐ በነገረ ዕብራይስጢ -(ኢሳ፴፮ -፲፩ ኩፋ -፲፪። ፪ዜና - -፲፰)

ዕብሬት -ፈረቃ ተራ፤ባርዮ ባረየ፤ እብሬት

ዕቱብ -(ኅቱም) የታተበ፤ የተቈረጠ፤ ርጥ። እስመ ዕቱብ ገር -(ጥበ፪ -)

 -የተባረከ የታተመ ዕቱባን ንትሙ በቅድስት ጥምቀት ምሕላነ ረሲ ዕቱበ -(ቀሌ። ደራሲ)

ዕትበት -ማተብ መታተብ፤ ማማተብ፤ በአንብሮተ እድ መባረክ መሾም፤ ወይም ቡራኬን ሹመትን መቀበል። እስመ ዕትበትሰ ይከውን ውስተ ሥዩም በእንተ መልእክት -( - -)

ዕትብት -በቁሙ፤ የታተበች፤ የተቈረጠች።

ዕንሰራ (ዕብ ዐጻራ) የሕዝብ ስብሰባ ጉባኤ ዐቢይ በዓል በዓለ መዊት በዓለ ኀምሳ ጰራቅሊጦስ። በዓለ ዕንሰራ (ዮሴፍ) ሥሩና ምንጩ ዐጸረ ነው ከነስረም ጋራ ይሰማማል

ዕንቍ -ክቡር ደንጊያ፤ ብዙ ዐይነት ያለው፤ ያንገት ጌጥ ሽልማት፤ ተሰክቶ ባንገት የሚታሰር፤ የሚሰደር የሚደረደር። ህየ ሀሎ ዕንቍ ዘየኀቱ ወዕንቍ ሐመልሚል። እማንቱ ዕንቈ ባሕርያት ክቡራት። ዕንቍ ዘተሰክዐ በፈትለ ሜላት። ዕንቈ ያሰጲድ -(ዘፍ፪ - ስንክ -ሚያ፰ አርጋ ራእ፬ -)

ዕንቈራ -የማር ሰፈፍ፤ነቍር ነቈረ፤ እንቈራ።

ዕንዚራ -የዘፈን ነዘረ እንዚራ።

ዕንጐት -(ታት። ዱዳኢም። ዐረ ሉፋሕ ጽር ማንድራጐሬ) ዕንጐችት የሽቱ ቅጠል ሽቱነት ያለው። ዕንጐችት ዐይነት ነው፤ ታላቅና ታናሽ። ኮልን ተመልከት ዚህ ጋራ አንድ ነው፤ ባለብሉዮች ግን ትርንጎ ይሉታል በገነቶሙ ዕንጐታት ተረክቡ -(ስንክ -ጥቅ፳፰ ማሕ፯ -፲፬ ዘፍ፴ -፲፬)

ዕንፎራ -(ጽር አናፎራ) አኰቴት ኅብስተ መሥዋዕት። ጸሎተ ዕንፎራ -(ቅዳ)

()           ዕወር -መታወር ዕውርነት ይቀሥፈከ በድቀት ወበዕወር -(ዘዳ፳፰ -፳፰)

ዕዋል -(ላት። ዕብ ዑል፤ ዐይር) ዕጓል፤ ታናሽ ልጅ ሕፃን ግልገል፤ ውርንጫ ዕዋል ዕጓለ ድግት ትረክቡ ድግተ ወዕዋለ -(ዘካ፱ -፱። ማቴ፳፩ -)

ዕዉር -(ራን ራት ውርት) ቁሙ የታወረ፤ ዝኒ ማሁ ለዐዋር ቀትል በመጥባሕት ተሰምየ ሞተ ዉር። ዕዉራን ይሬእዩ ብእሲ ዘዕውርት አሐቲ ዐይኑ -(ዮሴፍ። ማቴ፲፩ -፭። ስንክ -ሐም፲፩)

ዕዉቅ -(ቃን ቃት ውቅት) የታወቀ የተረዳ ዕውቅ፤ ግልጥ። አኮ ዲበ መታት ዕዉቃት -(ስንክ -መጋ፲፬)

ዕዉድ ዕውድ -የታወደ፤ የተከበበ፤ ክብ የታሰረ የተጠመጠመ፤ ጥምጥም። ጽጌ ደንጐላ ዘዕዉድ በአሥዋክ ይኩን ቀሚስ ስፉየ ወዕዉደ መዛርዐ ሚስ ይኩኑ ዕውዳነ ፈቃድ ዕውድ በምግባር ዕውድ በሜላት ውስተ ሕባለ ቢሶስ -(አዋል - -፴፩ -፭። አፈ -ተ፲፮ ስቴ፩ -)

ዕዘዝ -ጥናት፤ ብርታት ጥንካሬ ኀይል፤ ሥልጣን ክብር ልዕልና ዕዘዘ መዝራዕትከ ማስ ዘአርአየ ዕዘዞ ሞት በዕዘዝ ይኄይስ እምሐዪው በኀሳር። ዕዘዝክሙ ወሰርጐ ክብርክሙ ኀስሩ ምድኅረ ዕዘዝ። እመ አውዐይኮ ለመቅደስ ይትአተት ዕዘዞሙ -(ጥበ፲፩ -፳፪ ስንክ -የካ፪። ዮሴፍ)

ዕዙዝ -(ዝዝት) የጠና የበረታ፤ ብርቱ ጠንካራ፤ የማይፈርስ ዕዙዘ መንግሥት። ጐዩ ውስተ ዕዙዝ ደብር ወበረድሰ ብዙኅ ጥቀ ወዕዙዝ -(ቅዳ። መቃ። ዘፀ፱ -፳፬)

ዕዝል [1]-(ሕዝል ሐዘለ) የዜማ ስም፤ ፪ኛ ዜማ። ሠለስቱ ዜማ፤ ዘውእቱ ግእዝ ወዕዝል ወአራራይ -(ስንክ -ግን፲፩)

[2]-ዕዝል፤ -(ላት) መዝሙር የመዝሙር ስም ዜማው ዕዝል የኾነ፤ በዕዝል ዜማ የሚያዜሙት ዕዝል ዘነግህ ዕዝል ዘማርያም ህየንተ ዕዝል ዘነግህ ግእዝ። ዕዝል ዘሙታን -(ድጓ። ግንዘ)

ዕዝን -አዚን አዘነ።

»ዕየት -ተኵስ ትኵሳት፤ እሳት የፈጀው ገላ ስሉ ዕትራቱ። ዕየት ህየንተ ዕየት -(ዘፀ፳፩ -፳፭ ዘሌ፲፫ -፳፰)

ዕዩር -(ራን ራት ይርት) የተሰደበ ስዱብ፤ ወራዳ ጥቁ ንከውን ዕዩራነ -(ዮዲ፰ -፳፪)

ዕዩን -(ናን ናት ይንት) የተጐበኘ፤ የተመረመረ፤ የተገመገመ የተመረጠ የተለቀመ፤ ምርጥ ዕጣን ዕዩን ዘድቁቅ -(ዘሌ፲፮ -፲፪)

ዕዩይ -(ያን ያት ይይት) ራሱ የዞረ እንቡዝ ባካና ዘእንበለ ልብ ዕዩይ ኢለቦከ ምስጢረ ዘእምባሕር ወእሞት ዕዩይ። ዕዩያነ ኅሊና -(ተረ -ቄር። አፈ -ተ፫)

ዕይር -በቁሙ ቅልቅል ድብልቅ የታየረ

ዕደድ -ኀላር ውርደት ጕስቍልና ንዴት። ውእቱ ብእሲ እን አፍቀረ ዕደደ እምኀየሶ ሶበ ኢተወልደ፤ ያግብእከ ፈቀደ -(ደራሲ) ብዙው መጣፍ ግን በዕደድ ፈንታ እበድ ይላል የተሳሳተ ነው። ዐደዳ ዲደን ማለት ዚህ ወጥቷል፤ ዐደዳ ንዝንዝ ውዝግብ ጭቅጭቅ ዲደን ኀይለኛ ነፋስ ነው።

ዕዱም -(ማን ማት ድምት) የታደመ የተቀጠረ፤ ዕድመኛ።

ዕዳ [1]-በቁሙ፤ዐድይ ዐደየ።

 [2]-በቁሙ ብድር፤ ልቆ የብድር ገንዘብ። ደገ ሎቱ ዳሁ። ለመኑ እፈዲ ዕዳ። አግብአ አኅዘ ዕዳሁ ንቅንዮ ለነዳይ በዕዳነ -(ማቴ፲፰ -፳፯ ኢሳ፶ -፩። ሕዝ፲፰ - ዓሞ፰ -)

[3]-በደል ጢአት ክፋት መቀጮ ቅጣት ልቦ ላዕሌሁ ዕዳ። ዳእሙ ይጸንዕ ዕዳሃ ለዛቲ ጢአት። ሶበ ሰተይክሙ ዝናመ ትምህርት ምኢኮነክሙ ዕዳ -( - -፳፪ - -፲፫ -ድ፲)

ዕዳዊ -ባለዳ፤ አበዳሪ፤ ወይም ተበዳሪ ገረ ዳውያን -( - -፳፯)

ዕዳው [1]-(ዋት) መንታ መንገድ ምስቅል መንገድ።  ኀበ ዕዳዋት -(ማር፲፩ -)

 [2]-ድፍአዲው አደወ

ዕድ [1]:-እጅአዲው አደወ።

[2]:-ወንድዐዲው ዐደወ 

[3]-( ዕደው) ወንድ ተባት ብእሲ ዕድ ወአንስት ደው ጠቢባን። ዕደወ ስም -(ቅዳ። ሢራ፳፮ -፳፰። ዘፍ፮ -)

ዕድሜ -(ያት) በቁሙ፤ ቀጠሮ የተወሰነ ጊዜ ዘመን ወራት የሳምንት የወር ያመት በዓል ሄሮድያኖስ የአምር ዕድሜሁ። ኢኀልቀ ዕድሜሁ ራእይ ዕድሜ ሐዘን በበዓላት ወበዕድሜያት -(ኤር፰ -፯። ዳን፰ -፲፱ - -፳፬ - ሕዝ፵፮ -፲፩)

ዕድወት -መሻገር፤ ማለፍ፤ መታለፍ፤ መተላለፍ ልፊት ዐለፌታ እልፍ ትርፍ። ዕድወተ ቀዳማይ ብእሲ፤ ዕድወቱ ለአዳም -(ቄር -)

ዕድው [1]-(ዋን ዋት ዱት) የታለፈ የተዘለለ ሌሎች ያለፉት፤ የተሻገሩት።

[2]-ያለፈ፤ የተሻገረ፤ ወንዝን ሕግን ዐልፎ ተሻግሮ የኼደ

[3]-(ጥሬ ዐረ ዐዱው) ወደረኛ ባለጋራ ደመኛ ጠላት። ይከውነከ ዕድወ ዘኢኮነ ምስሌየ ዕድውየ ውእቱ ለእመ ረከብኩ ዕድዋኒሃ ለሃይማኖት። ዕድዋኒነ -(ሢራ፮ -፲፪ ማቴ፲፪ -፴። ተረ -ኤር ቄር)

ዕገሌ -እከሌእገሌ

ዕጕል -(ዕብ ዔጌል። ሱር ዔግላእ። ዐረ ዒጊል) ልጅ፤ ጥጃ እንቦሳ ግልገል ጫጩት፤ ቡችላ፤ ውርንጭላ፤ ያትክልት ፍል፤ ግልግል ችግኝ። ምስጢሩ ለጋ ወጣት፤ ርጥብ ቅላ ቡቃያ ማለቅ ነው ላላደገ ኹሉ ይነገራል። ዕጕለ ልሕምት ዕጕለ መራዕይ ዕጕለ ዕዋፍ ዕጕለ ናብስት -(ዘዳ፴፪ -፲፬። ፳፰ -፶፩። ኢዮ፭ -፯። መዝ -፻፫)

ዕጉል -(ላን ላት ግልት) የተቀማ የተነጠቀ፤ የጠፋ፤ የተሰረቀ። ያግብኡ ንዋየ ዕጉል ምተዐጋሊ ኵለንታሁ ለእ ወለጠ ዐይነ ዕጉል -( - -፴፭)

ዕጉሥ -(ሣን ሣት ግሥት) በቁሙ የታገሠ ቻይ፤ ትዕግሥተኛ። ዕጉሥ ዘእንበለ መዐት መምህር የዋህ ወዕጉሥ ንደዩ ዕጉሣኒሆሙ -(ቅዳ -ኤጲ ዲድ -፮። ስንክ -መጋ፲፫)

ዕጕሥታር -ሬት፤ጉትሣር ዐገተ

ዕጉት -(ታን ታት ግት) የታገተ የታሰረ የተከበበ። እስመ አነ ዕጉት በዝንቱ ሞቅሕ ዕጉት ውስተ አረፋቲሃ -(ግብ፳፰ -፳። መዝ -፶፭)

ዕጉትሣር -(ዕጉት ሣዕር፤ ሥዕረ) ቃጫ ሬት የሬት ወገን፤ መራራ ክፉ ቅጠል ሽቱና መድኀኒት የሚኾን። ዕዉደ ዐጽቅ ክቡበ ጽል ማለት ነው በተረትም አቀማመጡ ሰውና ጥርሱ ማጭድኛ ይባላል። መጽሐፍ ግን በቀሐመ ፈንታ ቀምሐ እንዲል በዕጉትም ፈንታ ዕጉሥት ይላል። በከመ ያማስኖ ዕጕሥታር ጣዕመ መዓር፤ ማሁ ያማስኖ ግዕዝ እኩይ ምግባረ ሠናይ። ደመ ዕጕሥታር ማየ ዕጕሥታር -(ፈላስ። መጽ -ምስ። ኤር፳፫ -፲፭ ራእ፰ -፲፩)

ዕግተት -መክበብ፤ መከበብ፤ አከባበብ፤ ከበባ ወሶበ ጸንዐ ዕሌሆሙ ዕግተት ወፅኡ በሌሊት ለእመ እእመረ ገብር ዕግተተ በእንተ ሀዪዶተ እግዝእቱ ወኢረድኣ ያውዕይዎ -(ዮሴፍ - -፵፰)

ዕጐል -ልጆች እንቦሶች፤ ግልገሎች፤ ጫጩቶች ቡችሎች ወኀደገ ዕጐሊሁ ውሉደ ሳነ ይትሐፀኑ ዕጐሊሆሙ። ርግብ ምስለ ዕጐሊሃ -(መቃ ኢሳ፲፩ -፯። -)

ዕጐልት -(ላት) ጊደር፤ ያደገች፤ የተጠቃች በካር ካዕቤ ዕጐልት። ቅብዐ ዕጐልት ዕጐልተ ባሳን ዕጐላት ምዕጐሎን -(ዕብ - -፲፫ ዘዳ፴፪ -፲፬ ዓሞ፬ -፩። ፩ነገ - -፯። ደራሲ)

ዕጓለ መሕያዊ -ሰብኣዊ፤ አዳማዊ፤ ምድራዊ መሬታዊ ፍጥረት ዕጓለ መሕያዊ በከመ ምግባረ መላእክት መንፈሳውያን ይትሌዐል ምግባረ ዕጓለ መሕያውያን -(ፊልክ - -)

ዕጓለ መሕያው -(ምሕያው) ዳም የአዳም ልጅ ሰው መሕያውን እይ ዕጓል ልጅ መሬት ሕያው ፈጣሪ ሕያው ከመሬት ያስገኘው ከምድር የወለደው የምድር ልጅ ምድር እናቱ ሕያው አባቱ ዳም ወልደ እግዚአብሔር -(ሉቃ፫ -፴፰) የአዳምን ፍች ተመልከት፤ ዚህ ጋራ ንድ ነው ዳግመኛም መሕያው በማለት ፈንታ እመ ሕያው ይላል፤ እም ሔዋን፤ ዕጓልና ሕያው አንድ ወገን ው፤ የሔዋን ልጅ ማለት ነው እስመ ይእቲ እመ ኵሉ ሕያው -(ዘፍ፫ -) እመን ለአዳም፤ ሕያውን ሔዋን ሰጥቶ ቢፈቱት ግን አዳምን የሔዋን መገኛ፤ እናቷ ወላጃ ያሰኛል ዕጓለ እመ ሕያው የአዳም ልጅ ሰው ይህ ኹሉ መላሾች ያበጁት የቀጣጠሉት ነው፤ ጽርኡ አንስሮፖስ ይላል፤ ማለት ነው ዕብራይስጡም አዳም ይላል፤ እንጂ ዕጓል አይልም፤ ስንኳን የዘርፍ ዘርፍ አንድ ዘርፍ የለውም ሦስተኛ ደግሞ ጐርዶ አሳጥሮ እምሔው ይላል ዕጓለ ምሔው፤ ያያት የሚታ ልጅ አባቱና አያቱ አንድ የኾነ፤ እናቱም ታላቅ እኅቱ የኾነች ያሰኛል ያያት የሚታ ልጅ የሚባል እንደ ሞአብ እንደ ዓሞን ያለ እናቱ ካባቷ ወልዳ ልጅ ወንድሜ ብላ የምትጠራው የልጅ ወንድም ነው -(ዘፍ፲፱ -፴፮፴፰) ሎጥ ከሴቶች ልጆቹ ኹለቱም ኹለት ወንዶች ወልዶ ለልጅ ልጆቹ ባትና አያት እንደ ኾነ፤ ጌታም እንደ ኹለት ሴቶች መዠመሪያ ሰማይና ምድርን ኹለቱን ፈጥሮ፤ ዚያ በኋላ ከሰማይ ሰማያውያንን፤ ምድር መሬታውያንን ስላስገኘ፤ ለፍጥረቱ እንዳባት እንዳያት ነውና፤ እምሔው ማለት ይህነን ያሳያል። በምሳሌም ዶሮ ለልጆቿ አያት ነች ይባላል፤ ርሱም ራሱ ባለቤቱ ባባትነቱ ላይ አያትነቱን ለማስታወቅ፤ ልዑል ራሱን በንስር በዶርሆ መስሎታል -(ዘዳ፴፪ -፲፩ ማቴ፳፫ -፴፯)

ዕጓለ ማውታ -የሙት ልጅ ለወንድም ሴትም ይከታል። ጓለይ እንዲል ትግሬ ኢየኀድገክሙ ትኩኑ ዕጓለ ማውቷ -(ዮሐ፲፬ -፲፰)

ዕጓል -ልጅ ወይፈን፤ ደቦል ጠቦት ጡት የተወ ያደገ ራሱን የቻለ። ጎቶልያ ርእየት ሞተ ዕጓለ። ዕጓለ ሕም ሥቡሕ። ይሁዳ ዕጓለ ንበሳ ዕጓለ ራዊተ ምድር -(፪ዜና -፳፰ -፲። ፩ነገ -፳፰ -፳፬ ዘፍ፵፱ -፱። ኢሳ፴ -)

ዕጠስ -ዕንጥስታ፤ ንጥሻ፤ ፍሽጊያ፤ ክፍት አፍንት። ባለብሉዮች ግን ቅንድብ ይሉታል። በዕጠሱ ይበርቅ ብርሃን ዕጠስ ወሀኬት -(ኢዮ፵፩ -፱። አፈ -ተ፳፯)

ዕጠቅ -መታጠቅ፤ አስተጣጠቅ፤ ትጥቅ፤ ማጠቆ ወዕጠቆሙ ይፈትሑ ሐራ -(ደራሲ)

ዕጡፍ -የተሠራ፤ የታጠፈ፤ የተጠቀለለ መዘራዝር፤ የገባ ዕጡፈ ፀምር ዘአልጸቀ ይግምድዎ -(ኢሳ፴፰ -፲፪)

ዕጣነ ሞገር -ቅኔ የቅኔ ስም ዕጣንና ከቍርባን በኋላ የሚቀኙት -(መጽ -ቅኔ)

ዕጣን -(ናት) በቁሙ፤ ሽቱ፤ የሽቱ ቅመም፤ ለቤተ መቅደስ የተበጀ የተዘጋጀ፤ መሥዋዕት ርባን የሚኾን የሚጤስ የሚታጠን ገበርተ ዕጣን ወአፈው ጸሎተ ዕጣን ሰዓተ ዕጣን ምሥዋዕ ዘዕጣን። ዕጣን ቅድው -(፩ዜና - -፴። ቅዳ ሉቃ፩ - ዘሌ፴ -፩። ፴፭፴፯)

ዕጥነት [1]-ማጠን፤ መታጠን፤ አስተጣጠን። ይዕጥን ውስቴቱ ዕጥነተ ዘዘልፍ -(ዘፀ፴ -)

[2]-ዕጥነት፤ ሽታ መዐዛ ዕጥነታ ርቤ ወስኂን ምኵሉ ጸበለ ፈው -(ማሕ፫ -)

ዕፀ ፋርስ -ፋርሳዊ ቅጠል፤ ከፋርስ የመጣ፤ ነገረን ተመልከት።

ዕጸብ -(ባት) ጭንቀት፤ ጭንቅ፤ ጽናት፤ መከራ፤ ወጥመድ እመ ዘክሕደ በእንተ ንዴት ወዕጸብ። ዕጸበ ግብሮሙ። ረስዮ ለዕጸብየ ቀሊለ ዕጸቢሁ ሞት -( - -፲፮ -፫። ፀ፮ -፱። ጥበ - ፪ነገ -፳፪ -)

ዕፀታት -(ዕፃት) ዛፎች፤ ዕንጨቶች፤ ዕጣዎች። ውስተ ዕፀታት። ዕፃት -(ራእ፯ - -፫። ሄርማ -ገ፶)

ዕፀት -ዕንጨትነት፤ ዕንጨት፤ የንጨት ወገን ጥቋጦ፤ ጭራሮ፤ ጭፍጫፊ ዝንጣፊ፤ እሾኻም፤ ቅጠላም፤ ታናናሽ ቀጫጭን፤ በጣም የማያድግ፤ ዛፍ የማይኾን፤ እንደ እንቧጮ ያለ። እምዕፀት ይነድድ እሳት፤ ወዕፀታ ኢትውዒ። ዕፀት ምልምት -(ዘፀ፫ -፬። ስንክ -ታኅ፳፱)

 -ፍ፤ የዛፍ ወገን ኹሉ፤ ታላላቅ ወፍራም፤ ረዣዥም። ቅሩብ ዕፀት ነዋኅ -(ዘዳ፲፩ -) ዕብራይስጡ ግን -(ዔሎኔይ ሞሬ) ዕፀወ ሞሬ ይላል -(ዘፍ፲፪ -)

ዕፀው -(ዋት) ንጨቶች ዛፎች ዕፀው ዘይፈርዩ ዕፀወ ም። ዕፀወ ገዳም። ወጣሕከ ዕፀወ ዲበ እሳት -(መክ፪ -፭። ኤር፫ -፮። ኩፋ -፲፫። ሢራ፰ -)

ዕጹብ -(ባን ባት ጽብት) የጨነቀ ጭንቅ አስቸጋሪ ጽኑ ክቡድ ቃለ ንክሮ ድንቅ። እፎ ዕጹብ። ዕጽብት ገቢር ትእዛዝ ዕጹብ ብር ዕጹብ። ዕጹብ ቀሊል ለከ ዕጹብ ይመስሎ ዝንቱ ወልድ ለጦቢት። ዕጹብ ለዐይን ሥነ ጽዕዱቱ -(ማር፲ -፲፬። ፊልክ -፫። ዳን፪ -፲፭። ፀ፩ -፲፬ ድጓ ጦቢ፯ - ሢራ፵፫ -፲፰)

ዕጹድ -የታጨደ፤ ዕጭድ ነዶ ቃርሚያ ምድሩንም እኽሉንም ያሳያል።

ዕጹፍ ዑጹፍ -የታጠፈ፤ ዕጥፍ፤ ድርብ፤ ዱብል። ቢሶስ ዕጹፍ ወነት ዕጹፍ። እስመ ዕጹፍ ውእቱ -(ዘፀ፳፮ -፩። ኢዮ፲፩)

 -የለበሰ ያጣፋ፤ የደረበ፤ ያጌጠ፤ የተጐናጠፈ። ዑጹፍ ወስርግው። ዑጽፍት ወሑብርት -(አፈ -ተ፴፪። መዝ -፵፬)

ዕጻ -ጣ፤ዐፀወ፤ ዕፃ

ዕፃ -በቁሙ፤ ዝኒ ማሁ መክፈልት ዘኢወፅአ በዕፃሁ። ወረደ ዕፃ ዕለ ዮናስ። ወበጽሐ ዕፃ ዲበ ማትያስ -(ኩፋ -፱። ዮና፩ -፯። ግብ፩ -፳፮)

ዕፄ ያት -(ዕብ ቶላዕ) ትል፤ ብል ነቀዝ፤ ተምች፤ ፌንጣ፤ ችግኝ ግንደ ርቍር፤ የመሰለው ኹሉ። ይፌኑ እሳተ ወዕፄ ውስተ ሥጋሆሙ። ብልዐተ ዕፄ። ከመ ዕፄ ለዕፀ። በልዑ ኅጠ ወዕፄ ዘሀሎ ውስተ ኵስሐ አፍራስ። ዘአትረፈ ዕፄ በልዐ ንበጣ

ዕፄ ሶበ ይበውእ በእዝን -(ዮዲ፲፮ -፲፯ ኢዮ፬ -፲፱ ምሳ፲፪ -፬። ዮሴፍ ዮኤ፩ -፬። -)

ዕፅ [1]-(ዕብ ዔፅ) ጥኑ፤ ጠንካራ ዕንጨት ዛፍ ባለብዙ ክንፍ፤ ዐይነቱና ስሙ ሽታውና ጣዕሙ ልዩ ልዩነት ያለው ሥራና ለመሣሪያ ኹሉ የሚፈለግ፤ ፍሬው የሚበላ፤ የማይበላ ለታብቍል ምድር ሐመልማለ ዕር ዘይዘራዕ ዘርዑ ወዕፀ መፍርየ ዘይገብር ፍሬ በበ ዘመዱ ዕፀ ሕይወት። ታሕተ ዕፅ ኀበ ልቦ ዕፅ እስመ እምፍሬሁ ይትዐወቅ ዕፅ ዕፀ ወይን ዕፀ ዘይት -(ዘፍ፩ -፲፩ -፱። ፲፰ -፬። መዝ -፪። ማቴ፲፪ -፴፫። ሕዝ፲፭ -፪። ሢራ፳፬ -፲፬)

[2]-ዕፃ፤ ዕጣ፤ የንጨት የወረቀት፤ የጠጠር ምልክት ያለው ስም የተጣፈበት። ዕጣው የወደቀበት ክፍል፤ ድርሻ፤ ዕድል ፈንታ ዛቲ መክፈልት ወፅአት በዕፁ ለሴም። ወወረደ ዕፁ ዕለ ዐሡሩ ወረቡዑ ሠርቀ አዳር። እስመ ሎሙ ረከቦሙ ዕፅ -(ኩፋ -፰። አስቴ፫ -፯። ፩ዜና - -፶፬። ዘሌ፲፮ -)

ዕጽበት -(ታት) መጨነቅ፤ ጭንቀት፤ ጭንቅነት፤ ጭንቅ በእንተ ዕጽበተ ህድአት። ዕጽበተ ተቃትሎ -(ፊልክ - -፻፮)

ዕጽወት -መዝጋት፤ መዘጋት፤ አዘጋግ፤ ዝግነት መዋዕለ ዕጽወትከ -(ሕዝ፬ -)

ዕጽው ዕጽው -(ዋን ዋት ጹት) የተዘጋ ዝግ፤ ኅቡእ። ናሁ ዕጽው ኅተ ገነት። መስቴማ እሱር ወዕጽው ዕጽው ወኅቱም ገሩ -(ዳን፩ -፳። ኩፋ -፵፰። ዳን፲፪ -)

ዕፍረት -(ታት) ሽቱ፤ የሽቱ መረቅ፤ ቅባት፤ የነጠረ፤ የተጣፈጠ። ዕፍረት ምዑዝ። ዕፍረት ቅድው። ቅብዐ ዕፍረት። መቅድመ ዕፍረታት -(ጥበ፪ - ዓሞ፮ -፮። አስቴ፪ -፲፪። ማሕ፬ -፲፬)

-(ጽር ዖሜጋ) ስመ ፊደል ደኃራዊ፤ ታላቅ የሚባል እንደ ታው ያለ የፊደላተ ጽርእ መጨረሻና መደምደሚያ፤ የአልፋ ትይዩና አንጻር የደኃራዊነት አምሳል -(ራእ፩ -፰። ፳፩ -፮። ፳፪ -፲፫) ባለቅኔዎች ግን ስመ አምላክ ይሉታል።

ዖማት -ለምለሞች ዱሮች ዛፎች ዕፀው እለ ይፈርዩ ወዖማት -(ኩፋ -)

ዖም -ለምለም፤ ሣር ቅጠል ግጫ ሸንበቆ፤ የመሰለው ኹሉ፤ ምድር የሚያለብስ የሚሸፍን ጽፍቅ ዱር ደን ወማ ጫካ፤ ታላላቅ ዛፍ ክንፋም ቅጠላም። ኵሉ ብርዕ ወኅለት ይበቍል ውስተ በድው -(ኢሳ፲፱ -፮። ፴፭ -) ኵሉ ጽፉቅ ታሕተ ኵሉ ዘቦ ጽላሎት። ዖመ ባሳን -(፬ነገ -፲፮ - ኤር፪ - ዘካ፲፩ -)

ዖርያ -ሠናይት፤አርያ።

ዖገ -(ዕብ ዓግ ያዑግ) ጋገረ ዐነጐተ ክብ አደረገ የሊጡን ቅርጥ

ዖፍ [1]-(ዕብ ዖፍ። ሱር ዓውፋ) በቁሙ፤ ወፍ ባለክንፍ፤ የሚበር የሚሰር፤ ታናሹም ላቁም ያንድነት ስም ነው። ዖፍ ዘይሰርር። ከመ ዖፍ ፍርኅቲሃ ዘትሴውር በክንፉ -(ኢሳ፴፩ -፭። ደራሲ)

[2]-(ትግሬ) አንበሳ፤ ዕጓለ አንበሳ።



 

No comments:

Post a Comment

ማውጫ

ሀ   ለ   ሐ   መ   ሠ   ረ   ሰ   ሸ   ቀ   በ   ተ   ቸ   ኀ   ነ   ኘ   አ   ከ   ኸ   ወ   ዐ   ዘ   ዠ   የ   ደ   ጀ   ገ   ጠ   ጨ   ጰ   ጸ   ፀ   ፈ   ፐ