ሀ ለ ሐ መ ሠ ረ ሰ ሸ ቀ በ ተ ቸ ኀ ነ ኘ አ ከ ኸ ወ ዐ ዘ ዠ የ ደ ጀ ገ ጠ ጨ ጰ ጸ ፀ ፈ ፐ
ነ [1] ፡ ፲፬ኛ ፊደል በግእዝ
አልፍ ቤት
በአበገደ፤ ስሙ ነሐስ ፥ ቍጥሩ ዐምሳ፤
አኃዝ ሲኾን ፡ (ነ–፶) ኀምሳ ይባላል።
[2] ፡ ነባር አንቀጽ፤ የ ፡ (ሀ ወ) መሪና በር ከፋች እየኾነው እንደ በና እንደ ለ ባሥር መደብ ይዘረዘራል። ነየ፤ ፡ (ነየከ ነየኪ ነያ ነዮ፤ ናሁ ነው ነዋ) ነኝ ፥ እንሆኝ፤ ከዚህ አለኹ። ነ መኖርንና መኾንን፤ የ ቦታንና የተጠሪን አካል ያሳያል፤ የጥሪ ተስጦ ሲኾን ግን ፥ ወይ አቤት እሜት ማለት ነው፤ ኦሆ እንደ ማለት ዘፍ፳፪ ፡ ፩። ኢሳ፶፰ ፡ ፱። ግብ፱ ፡ ፲)። ነዮና ናሁ ነው ነዋ ፩ ወገን ናቸው፤ ነው ላማርኛ ብቻ ተሰጥቷል፤ ፍቻቸውን በየቦታቸው እይ። ነየ አነ ወደቂቅ። ነያ ብእሲትከ። ነያ እምከ። ነዮ ፡ (ኢሳ፰ ፡ ፲፯። ዘፍ፲፪ ፡ ፲፱። ዮሐ፲፱ ፡ ፲፯። ስንክ ፡ ሠኔ፪)። ነየነ፤ ፡ (ክሙ ክን ፥ ዮሙ ዮን) ነን ነነ፤ እንሆነ ከዚህ አለነ። ነየነ ንሕነ አግብርቲከ። ነዮሙ እምከ ወአኀዊከ። ነዮን ጽሑፋት ፡ (ኩፋ ፡ ፵፫። ማር፫ ፡ ፴፪። ፪ዜና ፡ ፱ ፡ ፳፱)።
[3] ፡ የእስከና የእም በር ከፋች ፥ ወይም መሪ። እምሥራቀ ፀሓይ እስከነ ዐረብ። እምነ መኑ ፀነስኪ ፡ (መዝ ፡ ፻፲፪። ነገረ ፡ ማር)። ሲዘረዝር ግን ፥ እስከኔሁ፤ እምኔሁ እያለ ግእዝነቱን እንደ ኀበና እንደ ምስለ ወደ ኃምስነት ይለውጣል።
[4] ፡ የንሕነ ዝርዝር፤ አቅራቢና ጠቃሽ። ለሊነ፤ ኀቤነ፤ ምስሌነ፤ ከማነ። ሥርወ ትንቢት ፥ ለንሕነ ብቻ፤ ሳድሱም ን ሳይቀር። ሐዮነ ነሐዩ፤ ሞትነ ንመውት።
ነሐሰ ፡ (ይንሕስ ይንሐስ) ናሰ መደበ፤ ንሓስን መዳብን፤ ወይም ናስን ግንብን መደብን ሠራ ገነባ። ፡ (ሙሾ ጐዣሚት፤ ባሏ ውሽማዋን ገድሎ መደቡን አፍርሶ ቈፍሮና ቀብሮ በላዩ ሐዲስ መደብ ስለ ሠራበት) ሞጣ ቀራንዮ ጽላሎና ጐንጅ፤ ረ ሰውናሰው ሰውናስው እንጅ። ፡ (የባልዮው መልስ) ጭቃውም አይቡካ እንደ ፈረሰው፤ ናሰው ብለሽ ላኪ እንድጨርሰው ፡ (ሌላውን ደግሞ)። ኀፈደንና ነደቀን ፥ ጠቀመን እይ።
ነሐሴ ፡ በቁሙ፤ ናሴ፤ መጨረሻ ወር የመስከረም ፲፪ኛ። ውእቱ ጾም፤ ወጥንቱ ቀዳሜ ነሐሴ ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፲፭)።
ነሐስ ፡ (ዕብ ናሓሽ፤ እባብ) ስመ ፊደል ነ ፥ የአልፍ ፲፬ኛ በግእዝ አልፍ ቤት በአበገደ። ዘይቤው እባብ፤ ሽቦ ማለትንም ያሳያል፤ ከይሲንና ኖንን ተመልከት፤ ከዚህ ጋራ ፩ ነው። እባብ ያሰኘውም መልኩና ቅርጡ ነው፤ በጽርእና በላቲን ሳይቀር በፊደላት ኹሉ እባብ ይመስላል።
ነሀረ ፡ ንህረ፤ ፡ (ዕብ ናሀር) ፈሰሰ ወረደ፤ ናረ ዘለለ ፥ ጮኸ።
ነሃር ፡ ፈሳሽ ወንዝ ዥረት ፥ ፈለግ ባለብዙ ውሃ። ሲያበዛ ንሃሪም ፥ ንሃሮት ይላል። ግእዙ ውስተ አፍላገ ባቢሎን ባለው፤ ዕብራይስጡ ፥ ዐል ንሃሮት ባቤል እንዲል ፡ (መዝ ፡ ፻፴፮)።
ነኃር ምንኃር ፡ ወንዝ መስኖ፤–ነሀረ።
ነሃቢ ፡ (ቢት ብያን ያት፤ ሀብት) ባለጅ፤ ብረት ሠሪ ፥ ቀጥቃጭ ብር አፍሳሽ ፥ አንጥረኛ ጃን ሸላሚ ፡ (አናቢ፤ ቀሣሚ)። ነሃቤ ኀጺን። ነሀብት ብሩር ወወርቅ። ነሃቤ ምስል ፡ (፩ነገ ፡ ፲፫ ፡ ፲፱። ጥበ፲፭ ፡ ፱። ፍ ፡ ነ ፡ ፳፫)።
ነሃዪ ፡ (ዪት ይያን ያት) ያረፈ፤ የሚያርፍ ዐራፊ፤ እፎይ ባይ።
ነሀገ ፡ (ዕብ ናሀግ። ዐረ ነሀጀ ገ) ነዳ ፥ አሰማራ፤ ወሰደ መራ። መጽሐፍ ግን በነሀገ ፈንታ አንሀገ ይላል፤ ስሕተት ነው ፡ (ሄርማ ፡ ገ፶፫)። ንህከና መሀከ የዚህ ጎሮች ናቸው።
ነመረ ፡ (ይኔምር ይነምር። ዕብ ናሜር) በቁሙ፤ አዝጐረጐረ፤ ተዝጐረጐረ ዝንጕርጕር ኾነ ፥ ዐይነቱ መልኩ፤ ሓበረን እይ። ጣፈ ቈጠረ አመለከተ፤ በፊደል በአኃዝ በነቍጣ፤ ምስጢሩ ያው ማዝጐርጐር ነው።
ነምራዊ ፡ ነብርማ ፥ የነብር ዐይነት ወገን፤ ቀጭኔ። ነብራም ባለነብር፤ የነብር ቦታ ፥ ወይም ጌታ። ስሳ አናብስት ግሩማን ወስሳ አናምርት ለለ ሠርቅ ይትለአኩከ ዘልፈ በብዙኅ ጻሕቅ ፡ (ደራሲ)።
ነምር ፡ (ብ አንማር፤ አናምርት። ዕብ ናሜር። ዐረ ነሚር። ሱር ኒምራ) በቁሙ፤ ነብር ፥ ሕንብርቡር ፥ ዝንጕርጕር፤ ነጣቂ አውሬ የፍየል ጠላት። ይዌልጥኑ ኢትዮጵያዊ ማእሶ ወነምር ሕንብርብሬሁ። የዐርፍ ነምር ምስለ ጠሊ። አድባረ አናምርት ፡ (ኤር፲፫ ፡ ፳፫። ኢሳ፲፩ ፡ ፪። ማሕ፬ ፡ ፰)።
ነሰሕሳሕ ፡ (ሓት) መነሣሣት፤ መንቀሳቀስ፤ አነሣሥ፤ ተነሣሽነት። ውዝወዛ ንቅነቃ ቅስቀሳ። ከመ ንዉም ዘእንበለ ድምፅ ወኢነሰሕሳሕ። አእምሮ ወሰሚዕ ወርእይ ወኀሊና ወነሰሕሳሕ
፡ (ፊልክ ፡ ፺፰። ቀሌ)።
ነሠወ ፡ ፈተነ፤–ነሲው ነሰወ።
ነሰየ ፡ (ዐረ ነሲየ) ረሳ ዘነጋ፤ ከልቡ ኣጠፋ። ናሕሰየ ከነሐሰና ከነሰየ ከኹለቱ ሥር የወጣ ነው፤ ንሒስን እይ።
ነሠገ ፡ (ነሢግ። ዕብ ናሣግ፤ ተመለሰ) ሰነገ፤ ቈለፈ ፥ ወረወረ፤ የመዝጊያ። የሐውር በዓለ ቤት ነሢጎ ወቀቲሮ። አንቀጸ ዝናም ኤልያስ ነሠገ ፡ (ፈ ፡ መ ፡ ፲፯ ፡ ፯። ድጓ)። ነትገን እይ፤ የዚህ መንቲያ ነው።
ነሲኅ ኆት ፡ (ነስኀ ይነስኅ ይንሳኅ) መከርፋት፤ መቀርናት ፥ መግማት መበሽቀጥ፤ ከደዌ ከርስሐት የተነሣ። ነጽሐን እይ፤ የዚህ አፍራሽ ነው።
ነሲስ ሶት ፡ (ነሰ፤ ነሰሰ ይነስስ ይንስስ። ዕብ ኖሴስ፤ ሂትኖሴስ) ማጌጥ ፥ መጌጥ፤ መኵነስነስ፤ ነስ ነስ ማለት፤ መወዛወዝ መንቀሳቀስ። ሶሰወንና አንሶሰወን እይ፤ የዚህ ጎር ነው። ማመልከት፤ ታምራት ምልክት ማድረግ። ኔሳንን እይ፤ የዚህ ዘር ነው።
ነሲቅ ቆት ፡ (ነሰቀ ይነስቅ ይንስቅ። ዐረ ነሰቀ። ዕብ ናሻቅ፤ሳመ) መሰደር መደርደር፤ ማስተላለፍ መግጠም ማሳሳም፤ መጥረብ መውቀር ፥ ማነጥ መቅረጥ የደንጊያ የንጨት። ነሰከንና ወሰቀን እይ፤ የዚህ ጎር ናቸው።
ነሢት ቶት ፡ (ነሠተ ይነሥት ይንሥት። ዕብ ናታሽ፤ ናታጽ ፥ ነቀለ አፈረሰ። ናሻት፤ ደረቀ ፥ ፈረሰ ተናደ) ማፍረስ ፥ መስበር፤ መናድ መቈፈር፤ መንቀል መፈንቀል፤ መገልበጥ ገፍቶ መጣል። ጊዜ ለነሢት። እመ ነሠተ መኑ የሐንጽ። ነሠቱ በኀጺን አቅርንተ ምሥዋዒከ። እነሥት ጸቈና። ነሠተ አህጉረ። ነሠተ መናብርቲሆሙ ለመላእክት ፡ (መክ፫ ፡ ፫። ኢዮ፲፪ ፡ ፲፬። ዮዲ፱ ፡ ፰። ኢሳ፭ ፡ ፭። ፲፬ ፡ ፲፯። ሢራ፲ ፡ ፲፬)። ፈትሐ ሰዐረ በማለት ፈንታ ነሠተ ይላል ፡ (ግብ፲፬ ፡ ፴፬ ፡ ፵)።
ነሢእ ኦት ፡ (፤ ፡ (ነሥአ ይነሥእ ይንሣእ። ዕብ ናሣእ) መንሣት ፥ መቀበል፤ ገንዘብ ማድረግ። ንሥኢ መንፈሰ ቅዱሰ። ብፁዕ ዘይሁብ እምዘይነሥእ። ነሢእሰ ይትበሀል በእንተ ዐቅመ ትስብእቱ ፡ (ዮሐ፳ ፡ ፳፪። ግብ ፡ ፳ ፡ ፴፭። ሃይ ፡ አበ)። የመንሣት ምስጢር ፪ ነው፤ ከሰጭው እጅ በክፍል መቀበልና ከተቀባዩ እጅ መልሶ መውሰድ፤ ወይም ሰጠኹ ካሉ በኋላ መክዳት። ፡ (ተረት) የሰጠ ቢነሣ የለበት ወቀሣ። መከልከልና እንቢታም፤ ነሢእ ይባላል። ፡ (ግጥም ፥ ስለ አይሁድ) እኒህ ሥሡ ረ እኒህ ሥሡ፤ ለዝናብ ጌታ ውሃ ነሡ።
ነሲክ ኮት ፡ (ነሰከ ይነስክ ይንስክ። ዕብ ናሻኽ። ሱር ንካስ) መንኮስ፤ በጥርስ መያዝ መውጋት ማሳመም፤ መንጨት መበጨቅ መዘብተር፤ መጋጥ መግመጥ ማልገጥገጥ። አሐቲ አርዌ ምድር ነሰከታ ውስተ ልባ ወአሐቲ ውስተ ገቦሃ። ከመ ኢይንስክ ሰኰና እገርየ። ይንስክዎ ፡ (ስንክ ፡ ነሐ፲፭። ኅዳ፳። ዮሴፍ)።
ነሲው ዎት ፡ (ነሰወ ይነሱ ይንሱ። ዕብ ኒሳህ። ሱር ናሴይ) መፈተን፤ መመርመር መሞከር፤ ጠባዩን ትምርቱን ዕውቀቱን እምነቱን ዐቅሙን ለማወቅ።
ነሳሒ ፡ (ሒት ሕያን ያት) በቁሙ፤ ንስሓ ገቢ፤ ተጸጻች ተመላሽ ፥ ራሱን በራሱ ወይም በቄስ የሚወቅሥ የሚከስ ፥ በደሉን የሚያፈስ። ይቁም ምስለ ነሳሕያን ፡ (ፈ ፡ መ ፡ ፬ ፡ ፪። ዲድ። አፈ ፡ ተ፴፩)።
ነሣቲ ፡ (ቲት ትያን ያት) የሚያፈርስ አፍራሽ፤ ነቃይ ፈንቃይ፤ አጥፊ ገዳይ። ነሣቲሃ ለሕግ። ሳዊሮስ ዕልዋነ በሰይፈ ሃይማኖት ነሣቲ ፡ (መጽ ፡ ምስ። ስንክ ፡ ታኅ፲)።
ነሣኢ ፡ (ኢት እያን ያት) የሚነሣ ፥ የሚያነሣ፤ ነሺ አንሺ፤ ተቀባይ ያዥ ተሸካሚ ወሳጅ። ነሣኤ ዋሕስ። ነሣኤ አክሊል። ነሣኤ ኵሉ። ትኩነኒ እምየ መቃብርየ ወማሕፀና ነሣኢትየ። ነሣኢ ዘኢያገብእ ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፳፯። ስንክ ፡ የካ፳፭። ታኅ፲፰። ኤር፳ ፡ ፲፰። ግንዘ)። ነሢአ ገጽ ፥ ነሣኤ ገጽ ቢል ፡ (ዲድ ፡ ፬። ቅዳ) ዘይቤው መንሣት መቀበል፤ ምስጢሩ አድላዊነትና ግብዝነት ነው ፡ (፩ነገ ፡ ፲፮ ፡ ፯)።
ነሳኪ መንስክ ፡ የሚነክስ ነካሽ።
ነሳዊ መንስው ፡ የሚፈትን ፈታኝ፤ መርማሪ ሞካሪ።
ነስሐ ፡ (ይኔስሕ ይነስሕ፤ ነስሖ። ዕብ ናሳሕ፤ ነቀለ) ንስሓ ገባ፤ ዐዘነ፤ ተጠጠተ ፥ ተመለሰ፤ ክፉ ዐመሉን ተወ ፥ ጠባዩን ለወጠ። እስከ ይኔስሕ ንስሓ ፍጽምተ። ነስሑ እምፍኖቶሙ አኩይ፤ ወእግዚአብሔርኒ ነስሐ እምዘነበበ። ነስሕ አበሳከ ፡ (ፊ ፡ መ ፡ ፮ ፡ ፪። ዮና፫ ፡ ፲። ሢራ፲፯ ፡ ፳፭)። በነስሐ ፈንታ ተነስሐ ተናስሐ ይላል፤ የጣፊ ስሕተት ነው። ተነሳሕያን። ገብኡ ውስተ ዓለም ወአውሰቡ፤ ወእምድኅረ ውእቱ ተናስሑ ወነስሑ ፡ (ፊልክ)። ተነስሑ እስመ ቀርበት። ተነሲሖ ፡ (ማቴ፬ ፡ ፲፯። ኪዳ)።
ነስረ ፡ (ዕብ ናሻር) ነሰረ፤ ወረደ ፥ ወደቀ ተወረወረ፤ በፈቃዱ።
ነስር ፡ በቁሙ፤ ነዝር ያፍንጫ ደም፤ ነዝረን እይ። የበሰለ ፍሬና ቅጠል፤ ሳይነኩት የሚወርድ የሚወድቅ።
ነሥነሠ ፡ ነሰነሰ፤–ነሲስ ነሰ፤ ነስ ነሰ።
ነስነሰ ፡ (ተቀ ግ። ነሲስ ነሰ) ነሰነሰ፤ ረጨ በተነ ፈነጠቀ፤ አዘነመ አረበረበ፤ አጠጣ አረካ። ሥሩና ምንጩ ነሲስ ነው፤ ለዥራትና ለጭራም ይኾናል። ነስነስኩ ምስካብየ መጽርየ። ይነሰንሱ ጽድቀ ደመናት። ነስነሱ ላዕሌሁ ብዙኃተ ዕፍረታተ። ነስነሳ ማየ። በእንተ ማያተ አፍላግ ከመ ያዕርግ ማያተ ወይነስንሰነ ውስተ ኵሉ ገጸ ምድር ለጽሙኣን። ዘነስነስከ ምሕረተከ በመዋዕለ ሙሴ ከማሁ ነስንስ ምሕረትከ ላዕሌነ ፡ (ምሳ፯ ፡ ፲፯። ኢሳ፵፭ ፡ ፪። ስንክ ፡ ነሐ፳፬። ሄርማ። ቄድር)። ሮሐን እይ፤ የዚህ ጎር ነው።
ነስናሲ መነስንስ ፡ የሚነሰንስ ነስናሽ፤ ጭራ ያዥ ባለጭራ።
ነሥአ [1] ፡ ያዘ አነሣ ፥ ተሸከመ፤ ወሰደ ፥ ይዞ ኼደ። ነሥአ በእደዊሁ እሳተ ወመጥባሕተ። ይነሥኦሙ ፍርሀት ወረዓድ። ንሥኡ ትእምርተ ለአሕዛብ። ንሥኡ አርዑትየ ላዕሌክሙ። ነሥኦ ዲያብሎስ ውስተ ሀገር። ነሥኦሙ ኢየሱስ ፡ (ኩፋ ፡ ፷ ሔኖ፩ ፡ ፭። ኢሳ፷፪ ፡ ፲። ማቴ፲፩ ፡ ፳፱። ፬ ፡ ፭። ፲፯ ፡ ፩)።
[2] ፡ አወሣ፤ አሞሸ ቈዘመ፤ ገሣ ቃሉን አነሣ። ጐሥዐን እይ፤ የዚህ ጎር ነው። ትነሥእ በአፉከ ሥርዐትየ። ንሥኢ ሰቈቃወ በከናፍርኪ። ንሣእ ሰቈቃወ ላዕለ ፡ (መዝ ፡ ፵፱። ኤር ፡ ፯ ፡ ፳፱። ሕዝ፲፱ ፡ ፩)።
፡ መረጠ፤ መርጦ ወሰደ ፥ አቀረበ፤ ለሹመት ለባለሟልነት። ፡ (ይቤ ንስጥሮስ) ኢኮነ ሥጋ ዘእግዚአብሔር ቃል፤ አላ ነሥአ ሰብአ ፡ (ቄር ፡ እስት)። በነሥአ ፈንታ አንሥአ ይላል፤ አያሰኝም። እብነ መከራ ሶበ ያንሥእዎ። ኢታንሥእ ክቡደ። አንሥአኒ መንፈስ ማእከለ ፡ (ሢራ፮ ፡ ፳፩። ፲፫ ፡ ፪። ሕዝ፰ ፡ ፫)።
ነስአ ፡ ወሰደ ተቀበለ፤–ነሢእ ነሥአ።
ነሶሳው [1] ፡ ምልልስ፤–ሶሰወ።
[2] ፡ ነሶሳው ፣ ፡ (ዋት) መመላለስ፤ ምልልስ፤ ርቆ መኼድ፤ መንቀሳቀስ። ውስተ አየራት ነሶሳዉ። ዘፍጡን ነሶሳዉ። ኢተክህሎ ለህርቃኖስ ነሳሶው በእንተ ሰንበት። ዘእንበለ ነፍስ ወኢነሶሳው ፡ (ቅዳ ፡ ኤጲ። ጥበ፯ ፡ ፳፪። ዮሴፍ። ጥበ፲፭ ፡ ፭)።
ነሦጣጥ ፡ መደንገጥ ፥ መሰቅጠጥ፤ ስቅጠጣ ፥ ስቅጥጥታ፤ ኀፍረት ፍርሀት። ድንጋፄ ወነሦጣጥ ፡ (ኤር፭ ፡ ፴)።
ነቀለ ፡ (ነቂል። ዐረ ነቀለ፤ ፈለሰ) በቁሙ፤ መዘዘ አወጣ ፥ መነገለ አፈለሰ፤ ከበቀለበት ከተተክከበት ካለበት ቦታ ከሥሩ። ፈንቀለን እይ፤ የዚህ ዲቃላ ነው። ትሥሩ ወትንቅል፤ ትንሥት ወትሕንጽ። ነቀለ እምዐመ ገቦሁ አሐደ። አውድዎ እመስቀል ነቂሎሙ ቅንዋተ። ንቅል ሊተ ሦክ ኀጢአት። ነቀለ ደብረ ወተከለ ደብረ ፡ (ተረ ፡ ቄር ፡ ፩። ኤር፩ ፡ ፲። ሲኖዶ። ስንክ ፡ ነሐ፩። ኅዳ፲። ታኅ፮)።
ነቀልቃል [1] ፡ ንውጽውጽታ፤–ቀልቀለ፤ አን።
[2] ፡ ነቀልቃል፤ ፡ (ላት) ድብልቅልቅ፤ ሽብር፤ ንውጽውጽታ፤ ነውጥ፤ የባሕርይ ጦር። ኀይለ መንፈስ ቅዱስ እምድኅረ ተዐቅቦ ብዝኅት ለሕዋሳት ወለነቀልቃላት፤ ትትወሀብ ለድልዋን ላቲ ፡ (ፊልክ ፡ ፲፰)።
ነቀሰ ፡ (ዐረ ነጂሰ) አደፈ፤ ረከሰ፤ እድፋም ጕድፋም ንቃሻም ኾነ። ነቃቀሰ፤ ንቃሽ አወጣ። አጠቈረ ፥ በሾኽ በቀለም። ኀተመን እይ፤ ንቅሳት እንዲሉ፤ ጥቍራት ሲሉ። በቁሙ፤ ቀነሰ አሳነሰ፤ የዋጋ፤ ነቅጸን እይ።
ነቀተ ፡ (ነቂት) በቁሙ፤ ነከተ ደቀቀ እንቀት ኾነ።
ነቀዝ ፡ (ዛት፤ አንቃዝ) በቁሙ፤ ታናሽ ፃፄ ዕንጨትን እኽልን ድልብን የሚያበላሽ፤ የሚበሳሳ የሚበላ ፥ ከዚያው ከውስጡ የሚፈላ፤ ይልቁንም ከስንዴ ከገብስ ከማሽላ። ከመ ቍንቍኑ ለልብስ ወነቀዝ ለዕፀ። ኀበ ኢይከርዮ ሰራቂ ወኢያማስኖ ነቀዝ። ብእሲት ወውሉድ ነቀዙ ለንዋይ ፡ (ምሳ፳፭ ፡ ፲፱። ፊልክ። ፈላስ)።
ነቀጥቃጥ [1] ፡ በሽታ፤–ቀጥቀጠ፤ አን።
[2] ፡ በሽታ፤ እንቅጥቅጥ፤ መንዘፍዘፍ መንቀጥቀጥ፤ መንጠርጠር። አዝልፎ ስካር ያመጽእ ነቀጥቃጠ ወጥፍአተ ልብ ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፶። ገድ ፡ አዳ)።
ነቀፈ ፡ (ነቂፍ፤ ነጊፍ ነገፈ። ዕብ ናቃፍ፤ ናጋፍ። ዐረ ነቀፈ) በቁሙ፤ አጸየፈ ፥ ዐነቀፈ ፥ ዕንቅፋት ኾነ፤ መታ አረገፈ፤ ላጠ ቀረፈ። ኢትንቅፉ ግድፈቶ። ወነቀፈ ቅርፍተ ዕፅ ወወገረ ህየ ፡ (አዋል። ፬ነገ ፡ ፮ ፡ ፮)። ቀረፈንና ዐቀፈን ነገፈን እይ፤ ሥሩና ምንጩ ነጊፍ ሲኾን ቀና ገ ተወራርሰዋል።
ነቍር ፡ (ነቈረ ይነቍር ይንቍር። ዕብ ናቃር። ሱር ንቃር። ዐረ ነቀረ) መነቈር፤ መጠቅጠቅ፤ መጫር መቈፈር። ሰቈረንና ወቀረን ዐቈረን እይ፤ የዚህ ጎሮች ናቸው፤ ጥንቁርም የነቈረ ዘር ነው።
ነቍጥ ፡ (ጣት። ዐረ ኑቅጠት። ዕብ ንቁዳ። ሱር ኑቅዛ) በቁሙ ፥ ነቍጣ አንዲት ወይም ኹለት ጠብታ ፡ ( ፡ ) የነጥብ እኩሌታ፤ ታናሽ ምልክት የቃል መለያ፤ ጌጥነትና ወሰንነት ያለው በያንዳንዱ ኅርመት በየስኩ በየሣጥኑ የሚገባ። ጥንታዊው ያሮጌው ግእዝ ነቍጥ እንደ የውጣ ዘንግ ፡ (፤) ወይም እንደ ዜማ ይዘት አንድ ቅንጣት ብቻ ፡ (.) ነበረ፤ ዘንጉና አንዱ ቀርቶ ኹለት የኾነ በኋላ ዘመን ነው። ቃልከ ነቍጥ እንዘ ክልኤቲ ልሳንከ አሐቲ ይእቲ ፡ (ቅኔ)።
ነቂህ ሆት ፡ (ነቅሀ ይነቅሀ ይንቃህ። ዐረ ነቂሀ። ዕብ ያቃጽ) መንቃት ብንን ማለት፤ ከእንቅልፍና ከሞት መመለስ፤ ዐይንን መክፈት፤ መነሣት መትጋት መቀቀር፤ ለማየት ለመስማት። ኖመ ባዕል ወአልቦ ነቂህ። ነቅሀ እምንዋሙ። ወአንተሰ ንቃህ ወጥብብ በኵሉ። ሶበ ሰምዐት ቃሎ ነቅሀት በልባ። ለእመ ነበርከ ምስለ ማእምራን ትጋህኬ ወንቃህ ከመ ትስማዕ ቃሎሙ ፡ (ኢዮ፳፯ ፡ ፲፱። ዘፍ፳፰ ፡ ፲፮። ፪ጢሞ ፡ ፬ ፡ ፭። ስንክ ፡ ሐም፭። ፈላስ)።
፡ መዳን መፈወስ፤ ማምለጥ መውጣት። አመ ነቅሀ እምደዌሁ ዘቀብጸ እምኔሃ ተስፍ ፈውስ። ይንቅሁ እመሥገርተ ሰይጣን፤ እስመ ወድአ አሥገሮሙ ፡ (ፈላስ ፡ ገ፳። ፪ጢሞ ፡ ፪ ፡ ፳፮)።
ነቂብ ቦት ፡ (ነቀበ ይነቅብ ይንቅብ፤ ነቈረ። ዕብ ናቃብ፤ ናቃር) መውጋት መብሳት ፥ መንደል መፈልፈል መሰርሰር። መለየት ማራቅ፤ ማውጣት ማስለቀቅ፤ ፍልፋዩን ከውስጥ ከቦታው። ማስፋት ማስፋፋት፤ ሰፊ ማድረግ፤ መንቀብ እንቅብ መስፋት።
ነቂዕ ዖት ፡ (ነቅዐ ይነቅዕ ይንቃዕ። ዐረ ነቀዐ። ዕብ ናቃዕ፤ ተለየ ራቀ። ናቃቅ) መንቃት መሠንጠቅ፤ መፈንዳት ጧ ማለት፤ መተርተር፤ መለየት መክፈል። ይነቅዕ ደብረ ዘይት። ትነቅዕ ኰኵሕ። ለይንቃዕ ምሥዋዕ። ኅብስት ዘተርፈ እምትማልም አው ዘነቅዐ። አጽደፍዎሙ እምርእሰ ቀልቀል ወኵሎሙ ነቅዑ ፡ (ዘካ፻፬ ፡ ፬። ኢሳ፵፰ ፡ ፳፩። ፫ነገ ፡ ፲፫ ፡ ፫። ፈ ፡ መ ፡ ፳፮። ፪ዜና ፡ ፳፭ ፡ ፲፪)።
፡ መውጣት መፍለቅ፤ መመንጨት መፍሰስ። ከዚያው ከነቁ ከሥንጥቁ። ነቅዐ ማይ በውስተ በድው። ወነ6ቅዐ ሎሙ ፈለግ እምእብን። ምክሩ ይነቅዕ ከመ ማየ ሕይወት ፡ (ኢሳ፴፭ ፡ ፮። ዮሴፍ። ሢራ፳፩ ፡ ፲፫)። በሐብጠ ፈንታ ነቅዐ ይላል፤ የመላሽ ስሕተት ነው። እገሪሆሙ ኢነቅዓ ፡ (ነሐ፱ ፡ ፳፩)።
ነቂው ዎት ፡ (ነቀወ ይነቁ ይንቁ። ዐረ ፡ ነቀ፤ ነሀቀ። ዕብ ናሀቅ) አፍን ከፍቶ መጮኽ መጓጐር፤ ማግሣት ማናፋት፤ መትመም መክለል፤ በታላቅ ቃል መጥራት ፥ ታላቅ ድምጥ መስጠት። በቀወን እይ፤ የዚህ መንቲያ ነው፤ ሰንቀወም የአንቀወ ድርብ ይባላል። ነቀወ ከመ ሐራውያ ገዳም በመዐት። ይነቅዉ አራዊተ ገዳም። ዘእንበለ ይንቁ ዶርሆ። ይነቁ ተኵላ ወይጼውዕ አብያጺሁ ለቀቲለ እንስሳ። እብንኒ ትነቁ። ብርት ዘይነቁ። ግብር ዘአልቦ ነፍስ ይነቁ ፡ (መቃ ፡ ገ፪። ሶፎ፪ ፡ ፲፬። ማቴ፳፮ ፡ ፴፬። ሥር ፡ ጳኵ። ሱቱ ፡ ዕዝ፫ ፡ ፰። ፩ቆሮ ፡ ፲፫ ፡ ፩። ፲፬ ፡ ፯)።
ነቂዝ ዞት ፡ (ነቅዘ፤ ነቀዘ ይነቅዝ ይንቅዝ። ዕብ ናቆዝ፤ ሀቄዝ፤ በጣ ዐገመ) መንቀዝ፤ መጠንጠን ማርጀት፤ መሻገት መበላሸት። ዕፀ ዘኢይኔቅዝ ብልከሙኒ ነቅዘ ፡ (ኢሳ፵ ፡ ፳። ያዕ፭ ፡ ፪)። ጸንጸነንና ቈንቈነን እይ።
ነቃሂ ፡ (ሂት ህያን ያት) የነቃ የሚነቃ ንቅ። ከመ ይኩኑ ለባውያነ ወነቃህያነ ፡ (ዮሴፍ)። በነቃሂ ፈንታ ንቁሃዊ ይላል ፡ (ፊልክ)።
ነቃዊ ፡ (ዊት ውያን ያት፤ ቀውት) የሚጮኽ ጯኺ፤ ድምጣም። ሰላም ለከ ነቃዌ መጽሐፍ ማዕነቅ ፊቅጦር። ዶርሆ ነቃዊ ፡ (ስንክ ፡ ኅዳ ፡ ፲፭ና ፳፯)።
ነቄጥሩ ፡ (ሮማይ ኔክታር። ዕብ ቅጦሬት፤ ዕጣን) ጥሩ ጥፍጥ፤ የተነጠረ ሽቱ መጠጥ፤ ንቦች የሚቀሥሙት ያበባ ውሃ። የሽቱ ዕንጨት የዕጣን ዛፍ ፥ ደምና ሙጫ ወለላ ያለው። ወይወፅእ ማይ እምኔሁ ከመ ነቄጥሩ ዘስሙ ሳሪራ ወከልበኔ ፡ (ሔኖ፴፩ ፡ ፩)።
ነቈረ ፡ ወጣ ጠፋ፤ ፈረጠ ፥ ፈሰሰ፤ ጐደጐደ፤ ገበጣ መሰለ። ዐይኑ ዘየማን ነቍረ ይነቍር። ዐይንከ እንተ ነቈረት ፡ (ዘካ፲፩ ፡ ፲፯። አዋል)።
ነቈጠ አው ነቍጠ ፡ (ዐረ ነቀጠ። ዕብ ናቃድ) ነጠበ፤ ጠብ አለ። ነጥበን እይ፤ ከዚህ ጋራ አንድ ነው።
ነቅሪስ ፡ ነቀርሳ ምሽሮ፤ ፈንጣጣ ቂጥኝ።
ነቅዕ ፡ (ብ አንቅዕት ታት) በቁሙ ነቅ ፥ ሥንጥቅ። ምንጭ ፥ ዐይነ ማይ፤ ታናናሽ ወንዝ። ነቅዐ ማየ ሕይወት። ንስቲት ነቅዐ ማይ እንተ ኮነት ፈለገ። ዘይፌኑ አንቅዕተ ውስተ ቈላት። ወተዐጽዉ አንቅዕተ ቀላይ። ወነዋ አንቅዕታት ተርኅዉ ዲበ ምድር ፡ (ኤር፪ ፡ ፲፫። አስቴ ፡ ፩። መዝ ፡ ፻፫። ዘፍ፰ ፡ ፪። ሔኖ፹፬ ፡ ፫)። በምዕቃል ፈንታ ነቅዕ ይላል፤ አያሰኝም። ሐነጸ አንቅዕተ ማያት ፡ (ሢራ፶ ፡ ፫)።
ነቅጸ ፡ (ነቂጽ። ዐረ ነቀጸ፤ ነቀሰ ፥ አጐደለ) ደረቀ ከረረ፤ ነቃ ተሠነጠቀ ፥ ክፍት ኾነ፤ ከዚህ የተነሣ አነሰ ፥ ቀለለ ጐደለ፤ ዋጋው ሚዛኑ። ነቅጻ ከመ ሣዕር አዕፅምትየ። ነቅጸ አቡነ በሐዘን ለመዊት ፡ (መዝ ፡ ፻፩። ኩፋ ፡ ፵፫)። ነፀወንና የብሰን እይ፤ የዚህ ጎሮች ናቸው።
ነቅጽ ፡ ድርቅ፤ ነቅ ሥንጥቅ፤ ክፍት ባዶ።
ነቋር ፡ በቁሙ፤ አንድ ዐይና፤ ዐይኑ የወጣ ገበጣ ዐይን። ታመጽኡ ነቋረ ለመሥዋዕትየ ፡ (ሚል፩ ፡ ፰። ማቴ፲፰ ፡ ፬። ማር፱ ፡ ፵፯)።
ነበሕቃው ፡ ፍሽጊያ፤ የአፍ አከፋፈት፤ ከፈታ ክፍቻ ለቀቃ።
ነበሕባሕ ፡ የውሃ ጩኸት ፥ ድምጡ ተመማው።
ነበልባላዊ ፡ እሳታዊ፤ የእሳት፤ እሳታም፤ እሳትማ። ነበልባላዊት ጽዮን እመ ገሠጸቶ ፥ ተዋረደ ወኀደገ ቤቶ ፡ (ቅኔ)።
ነበልባል ፡ (ላት) በቁሙ፤ የእሳት ላንቃ፤ ነዲዱ ብርሃኑ ወላፈኑ። ነበልባል ዘአንደድክሙ። ነበልባለ እሳት ክርስቶስ ዘተባየጽከ ጳጦሰ ፡ (ኢሳ፶ ፡ ፲፩። ዮኤ፩ ፡ ፲፱። ደራሲ)።
ነበስባስ [1] ፡ የዐይን የሸፋሽፍት አገላለጥ፤ አስተያየት ጥቅሻ። ዐይንን ማፍጠጥ ማጕረጥ መበልጠጥ፤ ከፍ ዝቅ ቈለል ቈለል ከብለል ከብለል ማድረግ፤ በዐይን ዐለንጋ መግረፍ መሸንቈጥ መገርመም መግጠጥ መገላመጥ። አልቦ ቀዲመ ህላዌ ለአብ እምወልድ ኢመጠነ ቅጽበተ ዐይን ወኢመጠነ ነበስባሰ ቀራንብት። ሰላም ለቀራንብቲከ ዘነበስባሶን ይዋሄ ፡ (መጽ ፡ ምስ። ደራሲ)።
፡ ነፋስ እስትንፋስ፤ ሽው ሽው፤ እፍ እፍ ማለት፤ ሽውታ እፍታ። አንብቦ መጻሕፍት ከመ ነበስባሰ ነፋሳት ውስተ አፉሁ ለአብድ፤ ይትሜካሕ በአንብቦታ ወኢየአምር ዘውሳጢታ ፡ (መጽ ፡ ምስ)።
[2] ፡ ነበስባስ፤–ያይን አገላለጥ፤–በስበሰ።
ነበርፃው ፡ የቅምጥ እንቅልፍ እንጕልቻ። ፃው የብፃው ክፋይ ነው፤ በፀወን እይ። በነበርፃው ፈንታ ነበጽራይው ይላል፤ ፍችውን በቦታው ተመልከት። ነበርጻው ተብሎ በጸደይ ሲጣፍ ግን የበረጸ ዘር ነውና ለምጥን መደብ አድርጎ ቡሕነትንና ቋቍሻን ያሳያል ፡ (ኩፋ ፡ ፳፫)።
ነበዘ ፡ (ይነብዝ፤ ይንብዝ፤ ነቢዝ) በቁሙ፤ ሰረቀ ወሰደ፤ አጠፋ አበላሽ፤ የሌባ የደዌ ፡ (ዐማርኛ)።
ነበየ ፡ (ይኔቢ ይነቢ፤ ነብዮ። ነቢብ ነበ ነበበ) ነባ ተነባ ፥ ነቢይ ኾነ፤ ትንቢት ተናገረ። መጽሐፍ ግን በነበየ ፈንታ ተነበየ ይላል፤ ስሕተት ነው። ወፈጺሞ ተነብዮ። በከመ ተነበየ ሔኖክ። ተነበይ ለነ። ተነበየ በትንቢት መለኮታዊት። ብእሲ ተነባዪ ፡ (፩ነገ ፡ ፲ ፡ ፲፫። ይሁ ፡ ፲፬። ሉቃ፳፪ ፡ ፷፬። ስንክ ፡ የካ፲፭። ዮሴፍ)።
ነበጠ ፡ (ዐረ። ዕብ ናባጥ) ፈላ ገነፈለ፤ በዝቶ ወጣ በቀለ፤ ያንበጣ ያሸን የጕንዳን የቡቃያ፤ የመሰለው ኹሉ።
ነበጽራው ፡ (ዕብ ባጾሬት፤ ባጸር ፥ ከበበ አስጨነቀ ውሃ ነሣ) ውኅደተ ዝናም ፥ ሕጸጸ ማይ ፥ ሕጸጸ ሲሳይ፤ ጭንቅ ጥብ ዐጸባ፤ ንዳድ ትኵሳት ወባ። በነበጽራው ፈንታ ነበርፃው ይላል፤ የቅምጥ እንቅልፍ ማለት ነው ፡ (ኩፋ ፡ ፳፫)።
ነቢሕ ሖት ፡ (ነብሐ ይነብሕ ይንባሕ። ዕብ ናባሕ። ሱር ንባሕ። ዐረ ነበሐ) መጮኽ፤ ቡሕ ቡሕ ማለት፤ የውሻ የጕንፋናም። ይነብሕ ከመ ከልብ ፡ (ገድ ፡ ተክ)።
ነቢር ሮት ፡ (ነበረ፤ አው ነብረ ይነብር ይን(ብ) በር) ሀልዎ፤ መኖር መቈየት ፥ መዘግየት። ኢይትበደር ብዕል እምነቢረ ጥዑይ። ነበረ ህየ አሐደ ወርኀ። እስመ መጠነ ዝ መዋዕል ይነብራ እንዘ ይትኄረሳ ፡ (ሢራ፴፭ ፡ ፱። ዮዲ፫ ፡ ፲። እስቴ፪ ፡ ፲፪)።
፡ መቀመጥ፤ ጕብ ጕች ቍጭ ዘርፈጥ ማለት፤ በምድር ላይና በወንበር ላይ ማረፍ መተጣጠፍ። ንበሪ ውስተ ምድር። ነበረ ዲበ መንበር። ነቢረ ፍጽም በውስተ አዕዋዳት። ነበሩ ዐውደ ለኩንኖቱ ፡ (ኢሳ፵፯ ፡ ፩። ፩ነገ ፡ ፳፰ ፡ ፳፫። ማቴ፳፫ ፡ ፮። ቅዳ ፡ ግሩ)። ተጽሕፈ ተነግረ ተብህለ በማለት ፈንታ ነበረ ይላል። ነበረ ውስተ ቀኖና ዘነገሥት ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፴፪)።
ነቢብ ፡ (ጥሬ ዘር) ንባብ ፥ ሙኸት ነገር፤ ለፈፋ ልፍለፋ ድጋም። ዕለት ለዕለት ትጐሥዕ ነቢበ። ከመ ትጽደቅ በነቢብከ። ዐቃቤ ነቢብ። ለዘያበዝኅ ነቢበ ይትቌጥዕዎ ፡ (መዝ ፡ ፲፰ና ፡ ፶። ግብ፳፬ ፡ ፩። ሢራ፳ ፡ ፰)።
ነቢብ ቦት ፡ (ነበ፤ ነበበ ይነብብ ይንብብ። ዐረ ነበ፤ ነብነበ) መንበብ፤ መጮኽ። ከበሮው ይነባል እንዲሉ። ከመ ርግብ እነበብ። ኢነቀዉ ወኢነበቡ ፡ (ኢሳ፴፰ ፡ ፲፬። ፩ቆሮ ፡ ፲፬ ፡ ፯)።
፡ መናገር ፥ መቀባጠር፤ መድገም ፥ ማነብነብ። መቀባጠርና ማነብነብ የክፉ ናቸው፤ ነበየን እይ፤ የዚህ መንቲያ ነው። ነቢበ ብዙኅ ነገር። ሶበ አኅለቁ ነቢበ ዘንተ ነገረ። ንብብ ለእመ አብሑከ። አፉሁ ለእግዚ ነበበ ከመ ዝ ፡ (ኢዮ፴፬ ፡ ፴፯። ሱቱ ፡ ዕዝ፭ ፡ ፩። ሢራ፴፭ ፡ ፯። ኢሳ፳፬ ፡ ፫)። በነበበና በሰብሐ ፈንታ አንበበ ተናበበ ይላል፤ ስሕተት ነው። ወአንበበት ዮዲት በዛቲ ስብሐት። ኣነብብ ለስምከ። መንፈሰ እግዚ ይትናበብ በላዕሌከ። ወይትናበብ በእሳት። ኢይደሉ ለባሕታዊ ተናብቦ ቃል ስርግው ፡ (ዮዲ፲፮ ፡ ፩። ኢሳ፳፭ ፡ ፩። መቃ ፡ ገ፳፭። ሳታት ፡ ፊልክ)።
ነቢዕ ዖት ፡ (ነብዐ ይነብዕ ይንባዕ። ዕብ ናባዕ። ሱር ንባዕ። ዐረ ነበዐ) መንባት ፥ መመንጨት፤ መፍለቅ መፈልፈል፤ መፍሰስ መገንፈል፤ የውሃ የእንብ።
ነቢያን ፡ (ያት። ዕብ ንቢኢም) በቁሙ፤ ነቢያቶች። ያን የወንዶች ፥ ያት የሴቶች ነው፤ ያ በጣም ይጠብቃል፤ ይኸውም ዐቢይ ያን ያት እንደ ማለት ነው። መጽሐፍ ግን ወንድና ሴት ሳይለይ የሴቶቹን ለወንዶች ሰጥቶ ያነኑም አላልቶ በነቢያን ፈንታ ነቢያት ይላል፤ የመላሽ ስሕተት ነው። ኵሎሙ ነቢያት እለ እምአመ ሳሙኤል። ወቦቱ ሐሳውያነ ነቢያት። እስመ መንፈሰ ነቢያት ይትኤዘዝ ለነቢያት። ዐሠርቱ ወክልኤቱ ነቢያት ፡ (ግብ፫ ፡ ፳፬። ፪ጴጥ ፡ ፪ ፡ ፩። ፩ቆሮ ፡ ፲፬ ፡ ፴፪። ሢራ፵፱ ፡ ፲)። ዳግመኛም፤ ዜና መዋዕል በማለት ፈንታ ነቢያት ኖብያት ይላል፤ የተሳሳተ ነው። ውስተ መጽፈ ፡ (ነቢ) ኖብያቲሆሙ ለነገሥተ ይሁዳ። መጽሐፈ ፡ (ኖብ) ነቢያት መዋዕሊሆሙ ለነገሥተ ይሁዳ ፡ (፫ነገ ፡ ፲፬ ፡ ፳፱። ፲፭ ፡ ፯)።
ነቢያዊ ፡ (ዊት ውያን ያት) የነቢይ ወገን ነቢይ፤ ረድ ደቀ መዝሙር፤ ሀብተ ነቢይ የተሰጠው ፥ እንደ ኢያሱና እንደ ኤልሳዕ ያለ። ማርያም ነቢያዊት። ሴቴነዋ ነቢያዊት ፡ (ዘፀ፲፭ ፡ ፳። ስንክ ፡ ኅዳ፪)።
ነባሪ ፡ (ሪት ርያን ያት፤ በርት) በቁሙ ፥ የሚኖር ኗሪ ነዋሪ ነባር ተቀማጭ። ማኅደር ነባሪ። ነበርተ ዐውድ ፡ (ግንዘ አዋል)።
፡ ቤተ ሰብ ፥ ባሪያ የቤት ውልድ፤ አሽከር ወታደር ሎሌ። ነባሪከ ዘይትቀነይ ለከ። ወሤመ ዳቂት ነባሬ ውስተ ሶርያ። ነባሪ ወአግዓዚ ፡ (ሢራ፬ ፡ ፬። ፪ነገ ፡ ፰ ፡ ፮። ገላ፫ ፡ ፳፰)።
ነባር ፡ (ራት) በቁሙ፤ ብቸኛ ቃል ፥ የግስ ፪ኛ ክፍል፤ አንቀጽና ስም አገባብ።
ነባቢ ፡ (ቢት ብያን ያት) በቁሙ፤ የሚነብ የሚጮኽ፤ ተናጋሪ ቀባጣሪ፤ አፈኛ ምላሰኛ፤ ለፋፊ ለፍላፊ። ብእሲ ነባቢ። ነፍስ ነባቢት። ልሳን ነባቢት ዘታወፅእ ቃለ። ነባብያነ ሐሰት ፡ (መዝ ፡ ፻፴፱። ቅዳ። ፈላስ። ፩ጢሞ ፡ ፬ ፡ ፪)።
ነባዪ ፡ (ዪት ይያን ያት። አው ነቢይ ይት ያን ያት። ዕብ ናቤእ። ሱር ንቢያ። ዐረ ነቢይ) በቁሙ፤ የሚተነባ ተንቢ ነባቢ፤ መንፈሰ ትንቢት ያደረበት ፥ ራእይ የሚያይ ፥ ትንቢት የሚናገር፤ ሰባኪ መምህር። ነቢየ ያነሥእ ለክሙ እምአኀዊክሙ። ኢኮንኩ ነቢየ ወኢወልደ ነቢይ። ሶበሁ ነቢይ ውእቱ እምኢያእመረኑ ምንት ብእሲታ ፡ (ዘዳ፲፰ ፡ ፲፭። ዓሞ፯ ፡ ፲፬። ሉቃ፯ ፡ ፴፱)። ብእሲት ነቢይት። ሕልዳና ነቢይት። ሐና ነቢይት። ዜብላ ነቢይተ ዚኣሆሙ ለዕልዋን ፡ (ኢሳ፰ ፡ ፫። ፬ነገ ፡ ፳፪ ፡ ፲፬። ሉቃ፪ ፡ ፴፮። ዲድ ፡ ፳፭)።
ነብሕ አው ንባሕ ፡ የውሻ ጩኸት፤ አጪጯኽ።
ነተፈ ፡ ነተፈ፤ ፡ (ነቲፍ። ነቀፈ፤ ነጸየ፤ በጸለ) አነተበ፤ ነጨ በጨቀ፤ ቈረጠ በጠሰ፤ ቀማ መነተፈ። እለ ይነትፉ በመጭባሕተ ልሳኖሙ ሥጋ ቢጾሙ። ዘማእሰረ ኀጢአት ይነትፍ ተአስረ በአጽርቅት። ወለአዕዋፍሰ ኢነተፎን ፡ (ሥር ፡ ጳኵ። መጽ ፡ ምስ። ኩፋ ፡ ፲፬)።
ነቲን ፡ (ነተነ ይነትን ይንትን። ዕብ ናታን) መስጠት ማበርከት፤ ማሲያዝ ማስጨበጥ ፥ ማስረከብ፤ ዋጋን ዕዳን ጨርሶ መክፈል። መተነን እይ።
ነቲዕ ዖት ፡ (ነትዐ ይነትዕ ይንታዕ። ዕብ ናቶዕ ሂናቴዕ፤ ከሥሩ ፈለሰ ተነቀለ) መሸሽ መሮጥ ፥ መኰብለል፤ ለማምለጥ። ከመ ዘይነትዕ በውስተ ቀትል። ነትዑ እምቅድመ ገጽነ። ወይነትዕ ሰብእ። ይእቱ ብሔሮ (ሢራ፵ ፡ ፮። ኢያ፮ ፡ ፲፭። ኢሳ፲፫ ፡ ፲፬)። መተከል ፥ መዘርጋት ፤ የድንኳን የጥላ። መቅላት ነት መኾን ፥ ቀይ ቀለም መግባት ፤ የቈርበት።
ነቲግ ጎት ፡ (ነትገ ይነትግ ይንትግ። ወተገ፤ ነሠገ) መንተግ፤ ተግ ማለት መቆም መገታት፤ መቈረጥ መቅረት፤ ማነስ መጕደል መቅለል፤ ጥቂት መኾን። ወተገንና ነሠገን እይ፤ የዚህ ጎሮች ናቸው። ርቱዕ ይንትጉ እለ የሀውኩክሙ። ነትገ ማይ። ኢነትገ አንብዕየ። ለዘነትገ ትክቶሃ። መዋዕል አኀዙ ይንትጉ እምዐሠርቱ ወተስዐቱ ኢዮቤልዮ። እምውስቴቶሙ ኢይትከሀል ነቲግ ፡ (ገላ፭ ፡ ፲፪። ዘፍ፰ ፡ ፰። ግብ፳ ፡ ፴፩። መ ፡ ፈ። ኩፋ ፡ ፳፫። መክ፫ ፡ ፲፬)። በነትገ ፈንታ ተነትገ ይላል፤ የጣፊ ስሕተት ነው፤ ፡ (ዘፍ፰ ፡ ፩ ፡ ፭ ፡ ፯ ፡ ፲፩)።
(ጥት) ነት ፡ (ቅብጥ ናት) ቀይ ቀለም፤ የቀይ ቀለም ዛፍ፤ ፍሬው ቅጠሉ ቀይ ቀለም የሚኾን። በቁሙ ፥ ነትዕ ቀይ ቈርበት ዐረብ አንቀልባ፤ በነት ቀለም የተነከረ ፥ ቀይ ቀለም የገባ፤ ልብስ ፈትል። ኳኳን እይ፤ ከዚህ ጋራ አንድ ነው ፡ (ዘፀ፳፭ ፡ ፬። ፳፮ ፡ ፩። ፳፰ ፡ ፭ ፡ ፰ ፡ ፲፭)።
ነትረ ፡ (ነቲር። ዕብ ናታር፤ ዘለለ ታወከ) ነተረ፤ ኈረጠ በሰለ፤ የጠላ የወጥ። ነጥረን እይ፤ የዚህ ጎር ነው።
ነትዕ ፡ (ብ አንትዕት) ሽሽት፤ ሩጫ ፥ ኵብለላ። በቁሙ ፥ ነት ቀይ ቈርበት፤ የድንኳን ልብስ። አንትዕት ዘማእሰ በግዕ ፡ (ዘፀ፴፱ ፡ ፲፰)።
ነነዌ ፡ (ዕብ ኒንዌ) ስመ ሀገር፤ የአሶር መዲና። ውቢቱ ውቢት ፥ ዐባይ ልዕልት ቀዳሚት ማለት ነው ፡ (ዘፍ፲ ፡ ፲፩። ዮና፫ ፡ ፫)።
ነዐ [1] ፡ ና ምጣ፤–ነዐወ።
[2] ፡ (ንዑ ንዒንዓ) ትእዛዝ አንቀጽ፤ ላራቱ ሰራዊት ለቅርቦች ብቻ። ና ፥ ምጣ፤ ቅረብ። ነዐ ኀቤየ። ንዑ ትልዉኒ። ንዒ ዝየ ወብልዒ። ንዓ ትርአያ መካኖ ፡ (፩ነገ ፡ ፲፯ ፡ ፵፬። ማቴ፬ ፡ ፲፱። ሩት፪ ፡ ፲፬። ማቴ፳፰ ፡ ፮)። የወሀበን ትእዛዝ ሀብ ፡ (ቡ ቢ ባ) ን እይ፤ ይኸም እንደዚያ ነው። ኀላፊውና ትንቢቱ ዘንዱ፤ ተነዐውከ ፡ (ክሙ ኪ ክን) ትትነዐው ፡ (ዉ ዊ ዋ) ሲኾን፤ ትእዛዙን ተነዐው በማለት ፈንታ ተንና ወን ጐርዶ ነዐ ፡ (ንዑ ዒ ዓ) ይላል። ዐመሎች ፡ (አዐ ሀሐኀ ወየ) ያሉት ግስ መጕረድና መዋጥ ፥ መንገድ መለወጥ ሕጉ ነው።
ነዐለ ፡ (ይንዕል ይንዐል፤ ንዒል። ዐረ ወዕብ) ተጫማ፤ ጫማ ለበሰ ቈለፈ ዘጋ።
ነአከ ፡ ዐየረ ከለሰ ቀላቀለ፤ ማዕደንን ከማዕደን።
ነዐወ ፡ (ንዒው። ዕብ ናዕ፤ ናወዘ ተቅበዘበዘ) ዐደነ ፥ ከደን ገባ፤ ሻ ፈለገ፤ አደባ ሸመቀ፤ ወጥመድ አኖረ፤ ለመያዝ ለመግደል። ጠራ ፥ ና ወዴህ አለ፤ ሳበ አቀረበ፤ በቃል በፉጨት። ፃእ ሐቅለ ወነዐው ሊተ። ንዒወ ነዐዉኒ ፀርየ ከመ ዖፍ። ዘይንዑ ክብረ እምኀበ ሰብእ። ይጸንሕ ወይንዑ። ከመ ይንዐወነ መንገሌሁ ፡ (ዘፍ፳፯ ፡ ፫። ሰቈ፫ ፡ ፶፩። ማር ፡ ይሥ፩ ፡ ፬። መዝ ፡ ፱። አፈ ፡ ድ፭)።
ነዓል አው ናዕል ፡ ጫማ ፥ መጫሚያ፤ የግር ልብስ የሚወልቅ።
ነኣስ ፡ ያነሰች ትንሽ፤ አነስተኛ። ነኣስ መርዔት። ንህብ እንዘ በአካል ነኣስ። ወለት ነኣስ። ፡ (ሉቃ፲፪ ፡ ፴፪። ድጓ። ፬ነገ ፡ ፭ ፡ ፪)።
ነዓዊ ፡ (ዊት ውያን ያት፤ ዐውት) የሚያድን፤ ዐዳኝ ፈላጊ። ለምንት ኮንከ ነዓዊ አራዊት። መሥገርት ነዓዊት። እለ ይንዕዉ ነዐውት ፡ (ገድ ፡ ተክ። መዝ ፡ ፺። ሆሴ፭ ፡ ፪)።
ነኣዲ መንእድ ፡ የሚያከብር፤ አመስጋኝ።
ነከሕካሕ ፡ ነከሕካሕ፤ አው ሰከሕካሕ፤ ፍትፍት። እከሽ ካካ፤ ሐሠር ዐይነ ምድር፤ ተቅማጥ ሻታ እሕታ የሆድ በሽታ፤ ከብርድ የተነሣ ፡ (ኩፋ ፡ ፳፫)።
ነከሰ ፡ (ዐማርኛ። ሱር ንካስ) በቁሙ፤ ነከሰ ፥ ነካከሰ፤ ንክስ አደረገ ፥ በጥርሱ ያዘ፤ ጋጠ ገመጠ። ዕብራይስጡ ግን ናካሽ ብሎ ዐረመ ነቀለ ይላል፤ ጣትን እንጂ ጥርስን አያሳይም።
ነከራ ፡ ድንቅ ፥ ታምር፤ ድንቅነት ልዩነት፤ ድንቂያ ላቂያ ብልጫ። ቅቡዕ በቅብዐተ ነከራ። በነከራ ተወልደ ፡ (ቄር ፡ ጰላ)። ሚጠተ ብርሃናት ነከራ። በቃለ ማሕሌት ዘነከራ ፡ (ስንክ ፡ ሐም፳፩። ጥር፲፬)።
ነከበ ፡ (ነኪብ። ዐረ ነከበ) አስጐነበሰ፤ ዐጠፈ ሳበ ፥ ሰበሰበ፤ የዐጽቅና የክንፍ የእጅና የእግር የኵንቢ፤ ለኅሊናም ይኾናል።
ነኪራዊ ፡ (641) እብድ፤ ባዕድ ፥ አፍኣዊ ፡ (ዕር ኢሳ፲፩ ፡ ፲፱)። ብእሲት ነኪራዊት ፡ (ቀኖ ፡ ኒቅ)።
ነኪር ፡ (ራን ራት ርት ካር) ልዩ ፥ ሌላ፤ ባዕድ። ብእሲ ነኪር። ሕዝብ ነኪራን። አንስት ነኪራት። ብእሲት ነኪርት ፡ (ዘዳ፲፯ ፡ ፲፭። ኢሳ፲፰ ፡ ፪። ነሐ፲ ፡ ፲። ምሳ፯ ፡ ፭)።
፡ ግሩም ፥ ድንቅ፤ ጉድ ብርቅ ፥ ልውጥ። በሕይወቱ ገብረ ነኪረ። ነኪር ነገሩ በእንቲኣኪ። ወነካር ይእቲ ለአዕይንቲነ ፡ (ሢራ፵፰ ፡ ፲፭። መዝ ፡ ፹፮። ፻፲፯)።
ነኪር ሮት ፡ (ነከረ ይነክር ይንክር። ዐረ ወሱር። ዕብ ናኬር፤ ካደ ከዳ) መንከር መዝፈቅ ከውሃ ማግባት ፡ (ዐማርኛ)። መለየት ፥ ባዕድ ማድረግ፤ እንደ ሥጋና እንደ ቈርበት። መግረም ፥ መድነቅ፤ ዕጹብ ድንቅ መኾን፤ የክፉ የበጎ።
ነካዪ ፡ (ዪት ይያን ያት) የሚነካ፤ የሚጐዳ። ደዌ ሥጋ ፍጥረታዊት ነካዪት። ረኀብ ወጽምእ ነካይያን ፡ (ገድ ፡ ኪሮ። ፍ ፡ ነ ፡ ፵፫ ፡ ፬)።
ነክነከ ፡ (ተቀ ግ፤ ነከየ) ነከነከ፤ ነቀነቀ ፥ ወዘወዘ፤ ለመንቀል ለመፈንቀል። ነሠቱ አናቅጺሃ ወነክነኩ አዕማዲሃ። ረከቡ ርእሰ ምዉት ወነክነኮ አባ ሲኖዳ በበትሩ እንዘ ይብል ተንሥእ ኦ ምዉት። አጋገንት እኩያን እለ ይሰርሩ በነፋሳት ወይነከንኩ ነፍሳተ አምሥጋ ግብተ። ይነክንኮ ለጽዋዕ በትእምርተ መስቀል ፡ (መጽ ፡ ምስ። ስንክ ፡ ታኅ፲፩። ግንዘ። ቅዳ)።
ነክናኪ ፡ የሚነቀንቅ፤ ወዝዋዥ ነቅናቂ። ከና ቀ ይዋረሳሉ።
ነክዐ ፡ (ዐረ ነከዐ) ነከየ፤ ነካ ጐዳ ፥ ጐነጠ። ዘሩ ነክይ ነው፤ የ በዐ ተለውጧል።
ነክይ ዮት ፡ (ነከየ ይነኪ ይንኪ። ዐረ ነከዐ፤ ነከይ። ዕብ ናካህ። ሱር ንካእ) መንካት መጕዳት፤ መስበር ማጕደል። ነከዐን እይ፤ የዚህ ዘር ነው ፡ (ኢሳ፲፩ ፡ ፱። ፷፭ ፡ ፳፭። ማር፲፮ ፡ ፲፰። ሉቃ፬ ፡ ፴፭። ፲ ፡ ፲፱)። አናብስት ኢነከይዎሙ። አልቦ ዘይነክየኒ ለእመ ወሀብክዎ መንፈቀ ፡ (አቡሻ ፡ ፶። ጦቢ፲፪ ፡ ፪)።
ነኮላል [1] ፡ የራስ በሽታ፤ አዞሪቴ፤ ስካር። አኀዘኒ ነኮላል ወአሐምም። እምትንታኔ ዘነኮላለ ጌጋይ፤ እስመ በነኮላለ ጌጋይ ልብየ አንበዘ ከመ ዘሰትየ ወይነ መስዖዝዘ ፡ (ኤር፰ ፡ ፳፩። አርጋ ፡ ፬)።
፡ የራስ ጠጕር ሥራ፤ ዙሪያ ክብ ጥምጥም ሥር። ኢታንኅ ሥዕርተ ርእስከ ወኢትሕፅኖ ወኢትቅብዖ ዕፍረተ፤ ወኢትኅድጎ ስፉሐ ወኢፍቱለ ወኢፅፉረ፤ ወኢትረሲ ለከ ድንጉዛተ ወነኮላለ ፥ አላ ላጽዮ ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፶፩)።
[2] ፡ አዞሪቴ፤–ኮለለ አን።
ነኰርኳር [1] ፡ መገለባበጥ፤ ግልብጥብጦሽ። ዘአዕረጎ ለሔኖክ በነኰርኳረ ነፋሳት። እፎኬ አርመሙ ነኰርኳረ መባርቅት ወኢያውዐዩከ ፡ (ደራሲ። ሔና፶፪ ፡ ፩። መጽ ፡ ምስ)።
[2] ፡ ነኰርኳር፤–ግልብጥብጦሽ፤–ኰርኰረ።
ነወየ ፡ (ነውይ ነዋ) ገነዘበ፤ ገንዘብ አገኘ ፥ ገንዘብ አደረገ፤ ወይም ተገነዘበ ፥ ገንዘብ ኾነ ፥ ተሰጠ ታደለ ፥ ነዋ ተባለ። ተሸለመ፤ አጌጠ ተጌጠ።
(ጥ ዊ) ነዊኅ ፤ (ኃን ፤ ነዋኅ ኃት) ፤ ረዥም ፥ ታላቅ ምጡቅ ፤ ሰፊ ፥ ብዙ እጅግ ፥ ሩቅ። ነዊኅ የወንድ ፥ ነዋኅ የሴት ነው ፤ ጠቢብ ጠባብ ፥ ዐቢይ ዐባይ እንደ ማለት። ወኮነ ነዊኀ በቆሙ። አሕባል ነዊኃን። ነዊኀ መንፈስ። አድባር ነዋኃት። ለነዋኅ መዋዕል። እስከ ነዋኅ ብሔር። እስመ ነዋኅ ኀበ አምሠጥከ (ስንክ ፡ ግን፲፫። ሔኖ፷፩ ፡ ፩። አፈ ፡ ተ፴፪። መዝ ፡ ፺፬። ፳። ሚክ፬ ፡ ፫። ሢራ፳፯ ፡ ፳)።
ነዊኅ ኆት ፡ (ኖኀ ይነውኅ ይናኅ፤ አው ይንዋኅ፤ ይኗኅ፤ ይኑኅ። ዕብ ኑዋሕ። ዐረ ነሓ። ሱር ናሕ፤ ንህየ) ማረፍ ፥ መትረፍ መቅረት ፥ ቦታ መያዝ፤ መስፋት መንሰራፋት ፥ ጧ ዟ ብሎ መዘርጋት። ይምጻእ መንፈስከ ሕያው ወቅዱስ፤ ይረድ ወይንበር ይኅድር ወይኑኅ። ኢያረምም ወኢይነውኅ ፡ (ቅዳ ፡ ዮሐ። ሱቱ ፡ ዕዝ፪ ፡ ፵፮። መጽ ፡ ምስ)።
መርዘም ፤
መብዛት መፈድፈድ
፤ የቁመት
የቍጥር። ኖኅኵ ከመ በቀልት። ኖኃ አዕጹቅየ። ከመ ይኑኅ መዋዕሊክሙ። እመኒ ኖኀ መንበርቶሙ ውስተ ምድር። ኖኀ እምሥዕርተ ርእስየ ጌጋይየ። ወይነውኅ እምአርዝ
ፍሬሁ (ሢራ፳፬ ፡ ፲፬ ፡ ፲፮። ዘዳ፬ ፡ ፵። ጥበ፫ ፡ ፲፯። መዝ ፡ ፴፯። ፸፩)። በኖኀ ፈንታ ተነውኀ ይላል ፤ ስሕተት
ነው። ከመ ፍጹመ ይኵን ኅሊናሁ እንዘ ለኵሉ ሰብእ ይትኔዋኅ (ኪዳ)።
ነዊም ሞት ፡ (ኖመ ይነውም ይኑም። ዕብ ኑም። ሱር ናም። ዐረ ናመ) መተኛት ፥ ማንቀላፋት፤ መጋደም ማረፍ መሞት። ኢንኑም አላ ንንቃህ። ያፈቅሩ ነዊመ። ከመ ይኑሙ ንዋመ ዘለዓለም። በእንተ እለ ኖሙ ፡ (፩ተሰ ፡ ፭ ፡ ፮። ኢሳ፶፮ ፡ ፲። ኤር፳፰ ፡ ፴፱። ቅዳ)። በኖመ ፈንታ ነወመ ተነወመ ይላል፤ ስሕተት ነው ፡ (ኤር፳፫ ፡ ፴፩)።
ነዊር ሮት ፡ (ኖረ፤ ነወረ ይነውር ይኑር) መኖር ፥ መቀመጥ፤ ወይም ነወር ማለት ፥ መናር ከቅምጥ መነሣት ፡ (ዐማርኛ)። መብራት መቃጠል፤ ወይም ማብራት ፥ መለኰስ ማቃጠል፤ ኖራ ማውጣት ፡ (ዐረብ)። መነወር ፥ ነውር ጸያፍ መኾን፤ ወይም መባል፤ የግብር የነገር።
ነዋ ፡ (ነ ነዮ ናሁ፤ ነው) እንሆ፤ ይኸው ፥ ይኸውና። ናሁን እይ፤ ከዚህ ጋራ አንድ ነው። ነዋ ንጉሥኪ። ነዋ በግዑ። ነዋ ወልድኪ። ነዋ ወንጌለ መንግሥት። ነዋ ዝየ፤ ወነዋ ከሃ። ነወየና ንዋይ ከዚህ ወጥቷል።
ነዋሚ ፡ (ሚት ምያን ያት) የተኛ ፥ የሚተኛ ፥ እንቅልፋም፤ ሟች። ኵሉ ነዋሚ። ሰመዮሙ ለምዉታን ነዋምያነ፤ እስመ ይትነሥኡ ፡ (ምሳ፳፫ ፡ ፳፩። ግንዘ)።
ነዌ ፡ ንዋያም ፥ ገንዘባም ፥ ባለብዙ ገንዘብ፤ ዘወትር የሚያጌጥ የሚሸለም። ወይም በጭራሽ ኖኅ ማለት ነው፤ ይኸውም ሊታወቅ ጽርእና ላቲን ኖኅ ሲሉ ፥ ኖኄ እንደ ማለት ኖዬ ይላሉ፤ ኖኅን እይ። ወሀሎ አሐዱ ባዕል ዘስሙ ነዌ ፡ (ግንዘ። ሉቃ፲፮ ፡ ፲፱)። የግእዝ ወንጌል ዘስሙ ነዌ የሚለው ግን መተርጕማን ከግንዘት ወስደው ያገቡት ነው እንጂ የጽርእ አብነት አይዶለም።
ነውር ፡ (ራት) በቁሙ፤ ሕጸጽ ገመና፤ ነውረኛነት፤ የመልክ የሕዋስ የግብር። ምማቴን እይ፤ ከዚህ ጋራ ፩ ነው። አልብኪ ነውር ወኢምንትኒ ላዕሌኪ። ወራዙት እለ አልቦሙ ነውር። ይገብር ለክ ነውረ በዘአልብከ። ነውር ውእቱ ዘከመ ሰራቂ ወጐያዪ ወዘይሠይን ላዕለ መንጸፉ። አብዕልተ ነውራት። ርሕቀ እምኵሉ ነውራት ፡ (ማሕ፬ ፡ ፯። ዳን፩ ፡ ፬። ሢራ፲፩ ፡ ፴፩። ፍ ፡ ነ ፡ ፴፫ ፡ ፫። ፈ ፡ መ ፡ ፮ ፡ ፫። ፳ ፡ ፭)።
ነዘህሊል ፡ ንዝህላል፤–ዛህለለ።
ነዘለ ፡ (ነዚል። ዐረ ናዚለ። ዕብ ናዛል) ፈሰሰ ወረደ፤ ወደ ታች ኼደ ፥ ተቈለቈለ። እንዝል እንዲል፤ ውረድ ሲል ፡ (ዐረብ)።
ነዘረ ፡ (ሱር ንዛር፤ ደወለ መታ፤ አቃጠለ) ጮኸ ከለለ፤ ናረ ተመመ። መጽሐፍ ግን በነዘረ ፈንታ አንዘረ ይላል፤ ስሕተት ነው። ሶበ አንዘረት፤ ወታነዝር እግዝእቶን ለአንህብት። ከመ ቃለ አርጋኖን አንዛሪ ፡ (አዋል። ግንዘ)።
ነዘፈ ፡ (ነዚፍ። ዐረ ነዘፈ፤ ዘለለ ፈነጨ) ወነዘፈ ፥ አወነዘፈ፤ ለበሰ አጣፋ፤ ቀኝ ክንዱን አወጣ፤ የስላሞችና የገረዶች የደንገጥሮች አለባበስ።
ነዚህ ሆት ፡ (ነዝሀ ይነዝህ ይንዛብ። ዕብ ናዛህ፤ ተረጨ) መንዛት፤ መርጨት ማፍሰስ፤ መበተን መፈንጠቅ፤ መረብረብ መነስነስ። ትነዝሀኒ በአዛብ ወእነጽሕ። እነዝሀክሙ በማይ ንጹሕ። ነዝሀ ደመ ወወይነ። ይነሥእ ደመ ላሕም ወጠሊ ምስለ ማይ ወይነዝህ ፡ (መዝ ፡ ፶። ሕዝ፴፮ ፡ ፳፭። ኩፋ ፡ ፮። ዕብ፱ ፡ ፲፱ ፡ ፳፩)።
ነዚር ሮት ፡ (ነዘረ ይኔዝር ይንዝር) መንዘር፤ መንከስ መተርጨጭ፤ መዘብተር መበታተን፤ በጥርስ መቃወም መንደፍ፤ መውጋት ጠቅ ማድረግ፤ በመርዝ መጤቅ፤ ለሽመልና ለዱላም ይኾናል። ሰነነንና ነሰከን እይ። እንዘ ይኔዝሩ በስነኒሆሙ። እለ ይኔዝርዎሙ ፡ (ሔኖ፹፮ ፡ ፭። ሚክ፫ ፡ ፭)። መናዘር ፥ መዛዘን፤ ማመንዘር መቀንዘር። ድመቱ ናዘረ እንዲሉ።
ነዚዝ ፡ (ነዘ፤ ነዘዘ ይነዝዝ ይንዝዝ። ሐዘዘ) ማንዘዝ፤ ትን ማለት ፥ ባፍንጫ መውጣት።
ነዚፋ ፡ ኵታ፤ ነጠላ የኵታ እኩሌታ ፥ የሚጣፋ የሚወነዘፍ።
ነዛሂ ፡ (ሂት ህያን ያት) የሚነዛ ፥ የሚረጭ፤ ነዢ ረጪ። ጭብጥ ያዥ ውርድ ነዥ እንዲሉ።
ነዝሐ ፡ ነዛ ረጨ፤–ነዚህ ነዝሀ።
ነዝኀ አንዝኀ ፡ (ዝኅነ ፥ አዝኀነ፤ ዝኂን) በአዝኀነ ፈንታ አንዝኀ ይላልና፤ ዝኅነን ተመልከት። ጸጋ እንተ ታነዝኅ። ከመ ያንዝኅ አኃተ።
ነዝር ንዝሮ ፡ ንዝሪያ ፥ አነዛዘር፤ የደምና የዘር የመግል ቃንዛ፤ አውጡኝ አውጡኝ አፍርጡኝ የሚል። ነስር ፥ አነሳሰር፤ የነስርና የፍቅታት ደም፤ በሥንጥር ጓጕጠው ነድፈውና ጋርጠው ፥ በምላጭ ፈቅተው ወይም ቈርተው ካፍንጫ ከግንባር የሚያፈሱት። ነሰረን እይ፤ ዘና ሰ ይዋረሳሉ።
ነዝነዘ [1] ፡ (ተቀ ግ) ነዘነዘ፤ ወዘወዘ ፥ ሣቀየ ነዘረ፤ የቍስል የነገር።
[2]:-በቁሙ፤–ነዚዝ ነዘ።
ነዝዐ ፡ (ነዚዕ። ዐረ ነዘዐ። ዕብ ናሣዕ፤ ናዛሕ) ነቀለ፤ መዘዘ አፈለሰ፤ ከበቀለበት ከተተከለበት አነሣ ወሰደ። ቀማ ነጠቀ ፡ (ትግ ፡ ሐባ)። ወነዝዐ መትከለ እምነ አረፍት ፡ (መሳ፲፮ ፡ ፲፬)። በነዝዐ ፈንታ ነጥዐ አንጥዐ ይላል ፥ የተሳሳተ ነው፤ ነጥዐ የዕብራይስጥ እንጂ የግእዝ አይዶለም፤ ፍችውም ተከለ ዘራ ማለት ነው። እስመ ያነጥዖ ለልብስ ፡ (ማቴ፱ ፡ ፲፮)።
ነየ ፡ የነ ዝርዝር፤ እንሆኝ። ነ እንደ በና እንደ ለ ነባር አንቀጽ ሲኾን የሀወን በር ከፋች አድርጎ እንዴት እንዲረባ በመዠመሪያው ነ ተመልከት፤ ከዚያ ተጥፏል።
ነየድ ፤ በቁሙ ፥
ነዲድ ነበልባል
ላንቃ ፤
የእሳት ልሳን ወላፈን። በአምጣነ ዕፁ ለእሳት የዐቢ ነዱ።ቃሉ ከመ ነድ ያውዒ። አዕይንቲሁ ከመ ነደ እሳት (ሢራ፳፰ ፡ ፲። ፵፰ ፡ ፩። ራእ፩ ፡ ፲፬)።
ነዪእ ፡ (ኔአ ይነይእ ይኒእ) መቅረብ ፥ መዘጋጀት፤ ለመብሰል
ነይሩዝ ፡ (ዐረ ኒሩዝ፤ ኑሩዝ) የፋርስ ዐውደ ዓመት፤ የመስከረም መባቻ። ወረሰዩ ነይሩዞሙ ዘውእቱ ቀዳሜ ዓመቶሙ በሠርቀ ተውት ፡ (አቡሻ ፡ ፰)።
ነደበ ፡ (ነዲብ። ዕብ ናዳብ፤ ዐሰበ ቈረጠ፤ ለማድረግ) ጨነቀ ጠበበ፤ ጭንቅ ጥብ ኾነ፤ የቦታ የመንገድ ፥ የሕማም የግዞት ፥ የጊዜ የወራት።
ነዲል ሎት ፡ (ነደለ ይነድል ይንድል) መንደል፤ መብሳት ፥ መሸንቈር።
ነዲቅ ቆት ፡ ነዲቅ፤ ቆት፤ ፡ (ነደቀ ይነድቅ ይንድቅ። ሐነጸ፤ ጠቀመ፤ ኀፈደ) መንደቅ ፥ መሥራት፤ መመሥረት ፥ በመሠረት ላይ መናስ መጥቀም ፥ መገንባት ማጋጠም፤ ደንጎቹነ በኖራ በጭቃ ማዛመድ ማዋሐድ። ነደቃ ለይእቲ ዐፅም ወረሰያ ብእሲተ። ነደቃ ለነነዌ። ንንድቅ ሀገረ ወማኅፈደ። ኀደጉ ነዲቆታ ለሀገር ፡ (ዘፍ፪ ፡ ፳፪። ፲ ፡ ፲፩። ፲፩ ፡ ፬ ፡ ፰)። መብሳት፤ መንደል።
ነዲእ ኦት ፡ (ነድአ ይነድእ ይንዳእ። ዕብ ናዴህ፤ አራቀ አሶገደ ወገዘ) መንዳት፤ መውሰድ መሸኘት ማጀብ መከተል ማድረስ። ይንድኡ እንስሳሆሙ እለ ይነድኡ መርዔተ ዘኢኮነ ሎሙ። ወነድእዋ ምስለ ወለታ። ይነድእ ቃለ ኀበ ሥርዉ። ለኵሉ ዕለቱ ይነድኦ ፡ (ዘፀ፲፬ ፡ ፲፭። ፍ ፡ ነ ፡ ፵፱። ዮዲ፲ ፡ ፲፯። አፈ ፡ ድ፴፫። ሢራ፴፱ ፡ ፴፬)። ከዚህ ወደዚያ መናድ መፈንቀል ማንከባለል፤ ወይም ከዚያ ወደዚህ እየገፉና እየነዱ ማምጣት ማቅረብ። ከመ ይንዳእ ኀበ ነፍስ ፡ (ማር ፡ ይሥ፲፭)።
ነዲድ ዶት ፡ (ነደ፤ ነደደ ይነድድ ይንድድ። ዕብ ናዳድ፤ ተናደ ሸሸ ዘለለ ወዲያ ወዲህ አለ ታወከ፤ የፍርሀት የቍጣ) መንደድ ፥ መናደድ መቃጠል ፥ ቦግ ቱግ ቧ ማለት፤ የእሳት የመዐት የፍቅር። እመ ነፋኅካሃ ለፍሕም ትነድድ። ይነድድ መዐቱ። ይነድድ ፍቅራ ከመ እሳት። ነዱ በፍትወቶሙ ፡ (ሢራ፳፰ ፡ ፲፪። ኢሳ፴ ፡ ፳፯። ሢራ፱ ፡ ፰። ሮሜ፩ ፡ ፳፯)።
ነዲፍ ፎት ፡ (ነደፈ ይነድፍ ይንድፍ። ዐረ ነደፈ አጠራ፤ ነዲፍ ጥሩ። ዕብ ናዳፍ፤ አዘራ አነፈሰ) መንደፍ፤ መጠዝጠዝ፤ የደጋን የጥጥ ፥ የንብና የተርብ የባብና የጊንጥ። ነደፉክሙ ከመ ንህብ። ነደፉ አፍራሰ። ብእሲት ትትሜሰል በዐቅራብ ዘይነድፍ ሰብአ ፡ (ዘዳ፩ ፡ ፵፬። ስንክ ፡ ጥር፲፰። ፈላስ ፡ ገ፲፯። ራእ፱ ፡ ፭)።
፡ መወርወር፤ መውጋት፤ የቀስት የፍላጻ። ኢይነድፍ ውስቴታ ሐጸ። ነዲፍ በይምን ወበፅግም። ነደፈ ቀስት፤ ውርወራ ፡ (ኢሳ፴፯ ፡ ፴፫። ፩ዜና ፡ ፴፪ ፡ ፪። ስንክ ፡ ሠኔ፳፱)። ንድፍ ጸላኤ። ኢትትሀከዩ ነዲፎታ። ነደፈኒ ኵልያትየ በአሕጻሁ ፡ (ኩፋ ፡ ፴፰። ኤር፳፯ ፡ ፳፱። ሰቈ፫ ፡ ፲፫)።
፡ መበገር ፥ ማመልከት ፥ መሣል ፥ ሐረግ መጣል ፤ ያናጢ የገንቢ የጣፊ
ያንጥረኛ።
ነዳቂ ፡ (ቂት ቅያን ያት፤ ደቅት) በቁሙ ፥ የሚነድቅ የሚንስ ገንቢ፤ የመሐንድዝ በታች። እንተ አንተ ለሊከ ኬንያሃ ወነዳቂሃ። እብን ዘመነንዋ ነደቅት። ነደቅተ አረፍት ፡ (ቅዳ ፡ ዮሐ። መዝ ፡ ፻፲፯። ፩ዜና ፡ ፲፬ ፡ ፩)።
ነዳኢ ፡ (ኢት እያን ያት እት። ዕብ ኖጌሽ፤ ኖግሽም) የሚነዳ ነጂ፤ አስቸኳይ የሚያሮጥ የሚያጣድፍ ፡ (እረኛ ሹም ሌባ ዘራፊ)። ነዳእተ ገባር። ነዳእቶሙ ያጔጕዕዎሙ ፡ (ዘፀ፫ ፡ ፯። ፭ ፡ ፲፫)።
ነዳይ ፡ (ይት ያን ያት) በቁሙ ፥ ድኻ ችጋረኛ ፥ አይቶ ዐጣ ፥ ዘዋሪ ቀላዋጭ። ብፁዕ ዘይሌቡ ላዕለ ነዳይ። ብእሲት ነዳይት። ነዳያን በመንፈስ ፡ (መዝ ፡ ፵። ማር፲፪ ፡ ፵፫። ማቴ፭ ፡ ፫)።
ነዳዲ ፡ (ዲት ድያን ያት) ነዳድ የሚነድ የሚቃጠል፤ ነዳጅ ተቃጣይ። አፍሓመ እሳት ነዳዲ። ንባበ ግዘት ሰሚዖ እምልሳንከ ነዳዲ። ማኅቶት ነዳዲ ፍትወት ነዳዲት ፡ (ስንክ ፡ መስ፮። ታኅ፮ ፡ ፳፰። ፍ ፡ ነ ፡ ፳፬ ፡ ፭)።
ነዳፊ ፡ (ፊት ፍያን ያት፤ ደፍት) በቁሙ ፥ የሚነድፍ ወርዋሪ ወጊ ባለቀስት። ሐጸ መስተቃትል ነዳፊ። ረከብዎ ነዳፍያን በነዲፍ። ወፃፍያን ወነደፍተ ሐጽ ፡ (ኤር፳፯ ፡ ፱። ፩ዜና ፡ ፲ ፡ ፫። ፪ዜና ፡ ፲፬ ፡ ፰)።
ነድ ፡ በቁሙ፤–ነዲድ ነደ።
ነድሐ ፡ (ዕብ ናዳሕ) በኀይል ገፋ፤ ገፈተረ። ወጋ ደደቀ አናፈረ፤ አነሣ አጓነ፤ የበሬ የጐሽ። ወነድሖ ላሕም ፡ (፪ነገ ፡ ፮ ፡ ፮) ነፅኀን እይ፤ የዚህ መንቲያ ነው።
ነድዐ ፡ ነዳ ወሰደ፤–ነዲእ ነድአ።
ነድይ ዮት ፡ (ነድየ፤ አው ነደየ ይነዲ ይንደይ ዲ) መንደይ ፥ መደኽየት፤ ነዳይ ድኻ መኾን። ነድይኒ ወብዒልኒ። ከመ ነዲይየ ኢይስርቅ። ቦኑ ኵሎሙ ይነድዩ በሀኬቶሙ። ዘነድየ በጊዜሁ ይብዕል፤ ወዘብዕለ በጊዜሁ ይነዲ ፡ (ሢራ፲፩ ፡ ፲፬። ምሳ፳፬ ፡ ፴፪። አፈ ፡ ተ፲፩። ድጓ)።
ነገስት ፡ ንጉሦች፤–ነጊሥ ነግሠ ነጋሢ።
ነገሥጋሥ ፡ ሁከት ሽብር ድብልቅልቅ ንውጽውጽታ፤ የባሕርይ ጦር። ኦ አርጌንስ ሀዋኪ እፎ ታፈቅር ነገሥጋሠ ከመ ትግበር ነቀልቃለ ለቤተ ክርስቲያን። በነገሥጋሠ ነፍስት መዋቲት ዘይእቲ ደዌ ነፍስት ኢመዋቲት ፡ (መጽ ፡ ምስ። ገድ ፡ ኪሮ)።
ነገር ፡ (ራት፤ አንጋር) በቁሙ፤ ቃል ንባብ ፥ ወሬ የቃል ፍሬ ከድምፅ ጋራ የሚሰማ ፥ በጥፈት ባንደበት የሚገለጥ ፥ ከልብና ከአፍ የሚወጣ ክፉውም በጎውም ማናቸውም ኹሉ። በብዙኅ ነገር። ጸሐፍ ኵሎ ነገረ ፍጥረት። ካህናት ይዕቀቡ ነገራተ እግዚ ፡ (ዕብ፩ ፡ ፩። ኩፋ ፡ ፪። ቀሌ። አፈ ፡ ድ፲)።
፡ ቋንቋ፤ ልሳን። እመኒ አእመርኩ ነገረ ሰብእ ወመላእክት። ይነብባ በነገረ ከነዓን። ዘይሜህሮ ለዖፍ ነገረ ሰብእ ፡ (፩ቆሮ ፡ ፲፫ ፡ ፩። ኢሳ፲፱ ፡ ፲፰። ቀሌ)።
ነገርጋር [1] ፡ መውደቅ መንከባለል፤ መንፈራፈር፤ የጋኔን ትግያ ትግል፤ በየወሩ ጨረቃ ስትበቅል የሚኾን። ዘአኀዞ ጋኔን ወነገርጋር። እለ ቦሙ ነውር ዘነገርጋር ወዘጋኔን ኢይሠየሙ ውስተ ቤተ ክርስቲያን። እለ ነገርጋር። በእንተ ዘነገርጋር ፡ (ቀሌ። ማቴ፬። ፳፬። ፲፯ ፡ ፲፬። ሉቃ፱ ፡ ፴፰)።
[2] ፡ የጋኔን ጥሎሽ፤–ገሪር ገረ።
ነገበ ፡ (ዕብ ናጋብ) ደረቀ ፥ ፈረሰ ተፈታ፤ የቦታ።
ነገድ ፡ (ብ አንጋድ። ዕብ ኔኬድ። ዐረ ነጅል) በቁሙ፤ ወገን ያንድ አባት ዘር፤ ልጅ የልጅ ልጅ ፥ ዘመድ ተወላጅ፤ እንደ ንህብና እንደ ንግድ ገንዘብ እየበዛ እየተራባ አውራ እያበጀ የሚኼድ። ቤትንና በትርን እይ፤ ከዚህ ጋራ አንድ ነው። ወተፈልጡ በበ ነገዶሙ። አንጋደ እስራኤል ፡ (ኢያ፯ ፡ ፲፯። ሕዝ፵፯ ፡ ፳፩)። ሰራዊተትና ቤተ ሰብም ላለቃውና ለጌታው እንደ ልጅ ነውና፤ ነገድ ይባላል፤ አለቆችም ላለቆቻቸው ነገድ ይባላሉ፤ ወገን አለቃ ማለት ነው። ኀዲጎ ተስዓ ወተስዐተ ነገደ። ሰራዊተ ሚካኤል በበ ነገዶሙ ፡ (ድጓ። ቅዳ ፡ ያዕ)። በአንጋድ ፈንታ አናግድ ይላል፤ የጣፊ ስሕተት ነው። ሕጹጻነ አናግድ። አናግደ ሲሞን መሠርይ፤ አናግደ መቅዶንዮስ ፡ (ገድ ፡ አዳ። ፈ ፡ መ ፡ ፳፯ ፡ ፯)።
ነጐአ ፡ መታ ገጨ፤–ነጐዐ።
ነጕዐ ፡ (ይነጕዕ ይንጓዕ፤ ነጕዕ። ዕብ ናጋዕ፤ ነካ ገጨ) ነጓ ጮኸ ፥ ዷ ጓ ኳ አለ፤ ሲማታና ሲጋጭ። ወለቀ ተናጋ ፥ ተሰበረ ተቀለጠመ፤ ያገዳ ያጥንት።
ነጊህ ሆት ፡ (ነግሀ ይነግህ ይንጋህ። ዕብ ናጋህ። ሱር ንጋህ። አው ነግይ ነገየ። ነጊው ነገወ) መንጋት፤ መብራት ጧት መኾን። ማእዜ ይነግህ ፡ (ምሳ፳፫ ፡ ፴፭)።
ነጊል ሎት ፡ (ነገለ ይነግል ይንግል) መንገል፤ መፍለስ መነቀል። መገለጥ መታየት፤ ማጌጥ መሸለም፤ ለመታየት። ገለየን እይ፤ የዚህ መንቲያ ነው።
ነጊሥ ሦት ፡ (ነግሠ፤ አው ነገሠ ይነግሥ ይንግሥ። ዕብ ናጋሽ፤ ገፋ አዳፋ። ዐረ ነጀ(ገ) ሸ፤ ነዳ አባረረ) መንገሥ ፥ መምለክ፤ በመንበረ መንግሥት መቀመጥ፤ መሠልጠን ጌታ መኾን። መለከን እይ፤ ከዚህ ጋራ አንድ ነው። እምቅድመ ይንግሡ ተንባላት በግብጽ። እግዚ ነግሠ። አመ ነግሠ በሱሳ። እመ ገብር ነግሠ ፡ (ስንክ ፡ ጥር፰። መዝ ፡ ፺፪። አስቴ፩ ፡ ፪። መክ፬ ፡ ፲፬)።
ነጊር ሮት ፡ (ነገረ፤ ይነግር ይንግር። ዕብ ናጎር፤ ሂናጌር ፥ ፈሰሰ ወረደ። ናጌር፤ ጠረበ ላገ) መንገር፤ መስበክ ማስተማር ፥ ማውራት ማብሠር፤ ነገርን ሳያቋርጡ እንደ ውሃና እንደ ዝናም ማፍሰስ ማውረድ ማንጐድጐድ፤ ሐሳብን ምስጢርን በቃል መግለጥ ፥ በንባብ ማስጌጥ፤ መልክ እያወጡ ምሳሌ እየሰጡ ማነጥና መቅረጥ፤ እንደ ቅኔ። ኢትኅፈር ነጊረ ጌጋይከ። መኑ ይክል ነጊረ ምሕረቱ ጥንቁቀ። ዘአቅደመ ነጊረ በአፈ ነቢያት። ለምንት ትነግር ሕግየ። ፈሪህየ ከመ እንግርክሙ ዘእኄሊ ፡ (ሢራ፬ ፡ ፳፯። ፲፭ ፡ ፭። ሮሜ፩ ፡ ፪። መዝ ፡ ፵፱። ኢዮ፴፪ ፡ ፮)። በነገረ ፈንታ ተናገረ ይላል፤ ስሕተት ነው። ጎርጎርዮስ ተናጋሬ መለኮት። ነፍስ ተናጋሪት። ኵሉ ክርስቲያናዊ ነባቢ ወተናጋሪ። ተናጋርያን ፅሩዐ ፡ (ስንክ ፡ ጥር፴። ቄር። ቄድር። ኪዳ)።
ነጊድ ፡ (ነገደ ይነግድ ይንግድ። ሱር ናጋድ፤ ይንጎድ፤ መራ ወሰደ፤ ፈሰሰ ወረደ) ርቆ መኼድ ፥ መንጐድ፤ መነገድ ፥ የብሱን ዙሮ ባሕሩን ተሻግሮ መሼጥ መለወጥ ማትረፍ። ኢይክል ነጊደ። እለ ይነግዱ በባሕር ወበየብስ። ወዐርገ ውስተ ሐመር ይንግድ ምስሌሆሙ። ጸባሕት እምኀበ እለ ይነግዱ። ነገደ በመክሊት ፡ (ኩፋ ፡ ፴፩። ኪዳ። ዮና፩ ፡ ፫። ፫ነገ ፡ ፲። ፲፭። ስንክ ፡ ጥቅ፳፯)።
ነጊፍ ፎት ፡ (ነገፈ ይነግፍ ይንግፍ። ዕብ ናጋፍ) መንገፍ ፥ ማንገፍገፍ፤ መምታት ማርገፍ ማራገፍ፤ ርግፍ አርጎ መተው፤ መጣል ፥ ማሽቀንጠር። ንግፉ ጸበለ እገሪክሙ። ነገፍኩ ጽንፈ ልብስየ ወእቤ ከመ ዝ ለይንግፎ። ዕፀ ጠርቤንቶስ ዘነገፈት ቈጽላ። ንግፍ ላሐከ። ነገፎሙ ለግብጽ ማእከለ ባሕር ፡ (ማቴ፲ ፡ ፲፬። ነሐ፭ ፡ ፲፫። ኢሳ፩ ፡ ፴። ሢራ፴፰ ፡ ፲፯። ዘፀ፲፬ ፡ ፳፯)። በነገፈ ፈንታ ተናገፈ ይላል፤ ስሕተት ነው። ተናገፊ ጸበለኪ ፡ (ኢሳ፶፪ ፡ ፪)።
ነጋሢ ፡ (ሢት ሥያን ያት፤ ገሥት ፥ ታት። ዐረ እነጃሺ። ዕብ ኖጌሽ፤ ግፈኛ) በቁሙ፤ የነገሠ ንጉሥ ነጋሽ። ጌታ አለቃ አውራ፤ የሕዝብ ቀንድ። አበ ነጋሢ። ወልደ ነጋሢ። ነገሥት አበውኪ ፥ ወነጋሥያት ሐፃንያትኪ። ነገሥታተ አኵስም ፡ (፩ነገ ፡ ፲ ፡ ፳፬። ፪ነገ ፡ ፲፮ ፡ ፲፮። ድጓ። ታሪ ፡ ነገ)። ኢይትዐበይ ረድእ ላዕለ መምህሩ ወኢወዓሊ ላዕለ ነጋሢ። ነገሥተ ሰራዊት። ነገሥተ አሕማር፤ ጌታ አለቃ ፡ (ዲድ ፡ ፭። ዘኍ፴፩ ፡ ፵፰። ሔኖ ፡ ፸፱)።
ነጋሪ ፡ (ሪት ርያን ያት) በቁሙ፤ የሚነግር የሚያወራ ፥ የሚጮኽ የሚተም የሚነብ ነባቢ። ወሬ ነጋሪ፤ ዐዋጅ ነጋሪ፤ ባለነጋሪት እንዲሉ። ዜነወንና ነበበን እይ።
ነጋዲ ፡ (ዲት ድያን ያት) የሚኼድ ኸያጅ፤ የሚነግድ ነጋጅ፤ ነጋዴ መንገደኛ። ውሉደ ብእሲ ነጋዲ። ርእዮ ለዝክቱ ብእሲ ነጋዲ። ወናሁ ነጋድያን ፡ (ፊልክ ፡ ፩። መሳ፲፱ ፡ ፲፯። ዘፍ፴፯ ፡ ፳፯)።
ነጌ ፡ ዝኆን፤–ነግሀ ነገየ።
፡ (ብ ነግያት፤ ነግይ ነገየ) ዝኆን፤ በእስያና በአፍሪቃ ቈላ በዝቶ የሚገኝ ታላቅ አውሬ ከአራዊት ኹሉ የሚበልጥ፤ ጤናማ ዕድሚያም ፥ እንደ ርኩምና እንደ ቍራ እስከ ፻፶ ዓመት ከዚያም የሚበልጥ የሚኖር ባላራት እግር ፥ ባለረዥም ኵንቢ ፥ ቈርበተ ወፍራም ጥርሰ ረዥም፤ ብዙ ጕልበት ዕውቀትና ብልኅት ማስተዋል ያለው፤ ሣርና ቅጠል ዕንጨት የሚበላ፤ ኹለት ጥርሶቹ ቀንድ የሚመስሉና ቀንድ የሚባሉ ወፍራሞች ረዣዥሞች፤ በብዙ ዋጋ የሚሼጡ ፥ እንደ ቀንድ የሚነጠጡ ፥ ቤትን ንዋያትን የሚያስጌጡ። ፍችው ፥ ነግሃዊ፤ ሰላማዊ። ነግሃዊ፤ እንዳራዊት ሌት አለመውጣቱን ፥ እንደ ሰው ከሠርክ እስከ ነግህ መከተቱን ፥ በነግህ መውጣቱን ያሳያል። ሰላማዊ፤ ከሰው ከእንስሳ አለመጣላቱን ፥ ካልነኩት አለመንካቱን ፥ ሰው መውደዱን ቶሎ መልመዱን፤ ከለመደም ወዲያ እንደ ቤት እንስሳ ታዛዥና ተገዥ ኣገልጋይ መኾኑን ያሳያል።
ይኸውም ሊታወቅ ህንዳውያን እንዳህያና እንደ ገመል እንደ ፈረስ በቅሎ ይጭኑታል። ሌላም ብዙ ሥራ ያሠሩታል፤ ይልቁንም በጦርነት ጊዜ። ዝኆን ማለት ደግሞ ዝኁን ማለት ነው፤ ህድአቱን ህዱእነቱን እንዳባት በሬ መኾኑን ያሳያል፤ ዝኅነን እይ። ጋሎች ሰላምታ ሲሰጡ ፥ ነጌ ነጋያ፤ ስም ሲያወጡ ፥ ነገዎ የሚሉት፤ ዐማሮችም ንጋቱ ንጋቷ የሚሉት ከዚህ ይሰማማል። ቀርነ ነጌ። ማኅፈድ ዘቀርነ ነጌ። አብያት ዘቀርነ ነጌ። ወወፅአ ኀቤሁ ንጉሠ ህንድ ምስለ ብዙኃን ነጌያት። ወገብረ ነጌያተ ብርት፤ ወተቃተሉ ነጌያት ምስለ ነጌያት ፡ (ማሕ፳፭ ፡ ፲፬። ፯ ፡ ፬። ዓሞ፫ ፡ ፲፭። ዮሴፍ። ዜና ፡ እስክ)።
ነግህ ፡ በቁሙ፤ ንጋት የጧት ብርሃን፤ ጧት ማለዳ፤ ፀሓይ ሲወጣ ከጎሕና ከጽባሕ በኋላ ከሠለስት በፊት ያለ ጊዜ፤ ቀዳማይ ሰዓተ መዓልት። በበ ነግህ። እምነግህ እስከ ሠርክ። ነግሀ በጽባሕ ፡ (ዘፀ፲፮ ፡ ፳፩። ፲፰ ፡ ፲፫። ኩፋ ፡ ፵፪)። ጌሠምን ነገ ማለት ዐማርኛው ከዚህ ወጥቷል።
ነግሥ ፡ በቁሙ፤ የድርሰት መጽሐፍ እግዜር ነግሥ ፥ እንደ ስንክሳር ካመት እስካመት የተሠራ ፥ በማሕሌት ጊዜ የሚባል።
ነግድ ፡ (ዳን) እንግዳ ፥ መንገደኛ ፥ ዐድሮ ኸያጅ። አፍቅሮ ነግድ። ተቀብሎ ነግድ። ወነግዳን አንትሙ እምሥርዐተ ተስፋ። ፍቅረ ነግዳን ፡ (ሮሜ፲፪ ፡ ፲፫። ዕብ፲፫ ፡ ፪። ኤፌ፪ ፡ ፲፪። ስንክ ፡ ጥቅ፳፩)።
ነጐርጓር [1] ፡ (ራት) በቁሙ፤ ማጕረምረም መድረምረም፤ ማንጐራጐር፤ እንጕርጕሮ፤ የቍጣ የንቢታ የሐሜት የስድብ የነቀፌታ ቃል፤ ክፉ ነገር። ጓሮ አንባ ጓሮ ማለት ከዚህ ወጥቷል ፡ (ዘፀ፲፮ ፡ ፯ ፡ ፰። ዘኍ፲፬ ፡ ፳፯። ኢሳ፶፰ ፡ ፱)። አኅደግዎሙ እኩየ ነጐርጓረ። ተዐቀቡኬ እምነጐርጓር። ዘእንበለ ነጐርጓር ወኑፋቄ ፡ (ሢራ፵፮ ፡ ፯። ጥበ፩ ፡ ፲፩። ፊልጵ፪ ፡ ፲፬)።
[2] ፡ ነጐርጓር፤–ጕርምርምታ፤–ጐርጐረ።
ነጎት [1] ፡ (ነጊው ነገወ። ትግ ሐባ ኑጎት) የዝኆን ኵንቢ መሣሪያው ፥ እንደ ዘንዶ የሚስብ የሚጠልፍ ፥ ኹሉን ወዳፋ እየሳበ የሚያቀርብበት። ሲበዛ ነጎታት ፥ ወይም ነገዋት ያሰኛል።
[2] ፡ ኵንቢ፤–ነግሀ ነገወ የ።
ነጐድጓድ [1] ፡ በቁሙ፤–ጐድጐደ አን።
[2] ፡ (ዳት) በቁሙ፤ የመብረቅ ጓታ ነጐዳ፤ ታላቅ ግሩም ድምጥ፤ የሚያስፈራ የሚያስደነግጥ፤ የሚያርድ የሚያንቀጠቅጥ ፡ (መዝ ፡ ፸፮። ፻፫። ኢዮ፵ ፡ ፬። ማር፫ ፡ ፲፯)። መብረቅ ወፀፃዕ ወነጐድጓድ። ወሰማዕኩ ቃሎ ከመ ነጐድጓድ። ነጐድጓዳት ወመባርቅት ፡ (ራእ፬ ፡ ፭። ፮ ፡ ፩።ኩፋ ፡ ፪)።
ነጎጋው [1] ፡ ዝኒ ከማሁ፤ ብክነት ሁከት ቅብዝብዝታ፤ ቍጣ ብስጭት የቅለት ሥራ። መፍትው ለነ ንሑር በህድአት ሰሲለነ እምነጎጋው ከመ ኢንደቅ። ዘእንበለ ፍርሀት ወነጎጋው ፡ (አፈ ፡ ተ፴፬)። እበድ ውእቱ ነጎጋው አመ መዐት፤ ወተቀይሞ እምድኅረ ዕርቅ። ኂሩቱ ለልቡና ትዕግሥት ወሕሠሙሂ ነጎጋው ወጕጕኣ ፡ (ፈላስ)።
[2] ፡ ነጎጋው፤–መባከን፤–ጎግዎ ጎገወ።
ነጠ ፡ (ይነጥጥ ይንጥጥ፤ ነጢጥ። ዐረ ነጠ) ዘለለ ፥ ፈነጨ፤ ባጥ እንጣጥ ፊናጥ አለ። አነጠነጠ ፥ ተቍነጠነጠ፤ ርግብኛ ጮኽ፤ የሕፃን የጨቅላ። ዐነጠ፤ አነጠጠ ፥ አንጣጭ ኾነ።
ነጠቀ ፡ ነጠቀ፤ ፡ (ዕብ ናታቅ፤ ነቀለ) በቁሙ፤ ቀማ በኀይል ወሰደ ፡ (ዐማርኛ)። መጠቀን እይ፤ የዚህ መንቲያ ነው።
ነጠብጣብ ፡ ጠብቶች ፥ ጠብታዎች፤ ነጥቦች ፥ ነጠብጣቦች፤ ጠፈጠፎች። ነጠብጣበ ዝናም። ሕንባባተ ነጠብጣብ። ከመ ነጠብጣበ ማሕየብ ፡ (ኢዮ፴፮ ፡ ፳፯። ፴፰ ፡ ፳፰። ኢሳ፵ ፡ ፲፭)። ዳግመኛም በነጥብ ፈንታ ነጠብጣብ እያለ ያንዱን በብዙ ይጥፋል፤ ስሕተት ነው። ከመ አሐቲ ነጠብጣበ ማይ ውስተ ኵሉ ማየ ባሕር። አሐቲ ነጠብጣበ አንብዕ። ዘንተ ፈጠርከ በንስቲት ነጥብጣብ ዘይትዐቈር ውስተ ማሕፀን። ነጠብጣብ ልምልምት
፡ (ሢራ፲፰ ፡ ፲። ቀሌ። ዲድ ፡ ፴፰። ማር ፡ ይሥ፳፰)።
፡ ዕይር ፥ ቅልቅል ዐይነት፤ ኰሰኰስ ዝንጕርጕር፤ ቱሱሐ ሕብር፤ የማዕደን የደንጊያ የጠጕር። ደብረ ወርቅ ወደብረ ነጠብጣብ ፡ (ሔኖ፶፪ ፡ ፪)።
ነጠየ ፡ (ይነጢ ይንጢ) ናጠ ፥ ገፋ፤ ወዘወዘ፤ የወተት የጥና። ዐጣ ነጣ፤ መናጢ ኾነ።
ነጢር ሮት ፡ (ነጥረ፤ ነጠረ ይነጥር ይንጥር። ዐረ ወዕብ ናጣር፤ ጠበቀ) መንጠር ፥ መነጠር፤ መቅለጥ መፍሰስ፤ የቅቤ የማዕደን ፥ ለነገርና ለኳስም ይኾናል። መበለጭ ፥ ብልጭ ማለት፤ መፈንዳት። ነጥረ እሳተ ነፍጥ እምነጌያተ ብርት። መብረቅ ዘይነጥር ፡ (ዮሴፍ። ጥበ ፡ ጠቢ። አርጋ ፡ ፩)።
ነጢብ ቦት ፡ (ነጥበ፤ ነጠበ ይነጥብ ይንጥብ። ዕብ ናጣፍ። ሱር ንጣፍ) መንጠብ፤ ጠብ ኮለል፤ ማለት ተጠቅልሎ ሕንባብ መስሎ ሞውረድ፤ የውፃ የዝናም የላበት የደም። ማየ መቍረርሂ ኢይንጥብ እምአፍ። ተክዕወ ወነበ ደሙ። መጽለወ ሥጋሁ ወኮነ ከመ ምድር ይቡስ፤ ወአሐተ ዕለተ ከዐዉ ላዕሌሁ ምልአ ኮራ ማየ፤ ወኢነጥበ ዘእንበለ ንስቲት እምብዝኀ ይብሰተ ሥጋሁ ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፲፫። ስንክ ፡ ጥቅ፲፱። መስ፳፯)።
ነጢፍ ፎት ፡ (ነጠፈ ይነጥፍ ይንጥፍ። ዕብ ናጣፍ፤ ዛቃቅ) ማጥራት፤ ማፍሰስ መከለስ፤ ማንጠር ማቅለጥ፤ ለማጥራት። እለ ጻጹት ትነጥፉ። ወይነጥፎሙ ለደቂቀ ሌዊ። ይነጥፍዎ ለወርቅ ውስተ እሳት ፡ (ማቴ፳፫ ፡ ፳፬። ሚል፫ ፡ ፫። ስንክ ፡ ግን፪)። መከረንና ፈተነን እይ።
ነጥበ ፡ ነጠበ ፥ ሰደበ ነቀፈ፤ ተቈጣ ዘለፈ ፡ (ዐማርኛ)። መጐጸን እይ።
ነጥብ ፡ ጠብታ፤ የፈሳሽ ቅንጣት ፥ ከብላላ ጠቅላላ። ነጥበ ማይ። ነጥበ ጠል ፡ (ፈ ፡ መ ፡ ፲፬ ፡ ፲። ጥበ፲፩ ፡ ፳፫)።
፡ በቁሙ፤ የንባብ ወሰን ፥ የቃል መለያ ፥ ታላቅ ምልክት፤ ንኡስ ምዕራፍ ባለ፱ ነቍጣ ፥ ፬ቱ ጥቍር ፭ቱ ቀይ። ፍቅደ ነጥብ በዓላተ ወልድ ቅዱሳን ተስዐቱ ፡ (ቅኔ)። ቀዩም ቢቀር መደበኛው ጥቍሩ ነውና፤ አራቱ ብቻ ነጥብ ይባላል። ነጥብ ጽኑዕ ዘኢይትፋለስ። ወይእቲ ነጥብ ነጥበ ዕሪና ፡ (አቡሻ ፡ ፴፯)። በነጥብ ፈንታ ንጥበት ይላል። ኢይትዔረይ ንጥበተ ተድላሃ አሐቲ ከመ ተድላ ዓለም በምልኣ። ንጥበተ ደሙ ፡ (አፈ ፡ ተ፳፰። መጽ ፡ ምስ)።
ነጸለ ፡ (ነጺል። ዕብ ናጻል። ዐረ ፡ ነጸለ) ነጠለ ለየ፤ መነጠለ፤ አዳነ አወጣ አስጣለ፤ አወለቀ አስለቀቀ፤ ከመከራ ከፍንጅ ከጠላት እጅ። ጸንጸለን እይ ፥ የዚህ ዲቃላ ነው፤ ነቀወ ብሎ ሰንቀወ እንደ ማለት።
ነጸረ ፡ ለየ ነጠለ፤–ነፂር ነፀረ።
ነፀረ ፡ አየ አስተዋለ፤–ነጽሮ ነጸረ።
ነጸብራቅ [1] ፡ ነጸብራቅ፤–ብልጭታ፤–በረቀ ጸብረቀ።
[2] ፡ (ቃት) ብልጭታ፤ ብርሃን፤ ጸዳል፤ ጽርየት። ያስተርኢ ብርሃኑ ወነጸብራቁ ወጸዳሉ። ኢርኢኩ ነጸብራቀ ሐሤት ውስተ ገጽከ ፡ (አፈ ፡ ፴፫። ፈላስ)።
ነፀወ ፡ (ነፂው። በፀወ፤ ነቅጸ) ደረቀ ከረረ፤ ኳ ክው ክሽልል አለ። መጽሐፍ ግን በነፀወ ፈንታ አንፀወ ይላል፤ አያሰኝም። በጽባሕ ይሠርጽ፤ ወሠርክሰ ይወድቅ የቢሶ ወአንፂዎ ፡ (መዝ ፡ ፹፱)።
ነፀፈ ፡ ዘረጋ አነጠፈ፤–ነጺፍ፤–ነጸፈ።
ነፀፍፃፍ ፡ ጠፈጠፍ፤–ጸፈ ጸፍጸፈ።
ነጸፍጻፍ ፡ (ፋት) ጠፈጠፍ፤ ፍሳሽ፤ ፈሳሽ፤ ጠብታ፤ እንጥብጣቢ። ወኮነ ሀፉ ከመ ነጸፍጻፈ ደም ዘይወርድ ውስተ ምድር። ጻዕደወት ምድር እምነጸፍጻፈ ሐሊበ አጥባተ እሞሙ። አምሕለኪ ማርያም በነጸፍጻፈ ደም ዘጎልጎታ ፡ (ሉቃ፳፪ ፡ ፵፬። መጽ ፡ ምስ። አርጋ ፡ ፩። ደራሲ)።
ነፂር ሮት ፡ (ነፀረ ይኔፅር ይንፅር። ሠጸረ) መለየት፤ መክፈል መሠንጠቅ። ነፅር። ነፂረ እኔፅራ ለመንግሥትከ እምነ እዴከ። ለፅኑሳት ነፀሮን ፡ (ቅዳ። ፫ነገ ፡ ፲፩ ፡ ፲፩ ፡ ፴፩። ፬ነገ ፡ ፲፭ ፡ ፲፮)። በነፅኀ ፈንታ ነፀረ ይላል፤ የተሳሳተ ነው። ትኔፅር ሕፃናቲሆሙ ፡ (፬ነገ ፡ ፰ ፡ ፲፪)።
ነጺፍ ፎት ፡ (ነጸፈ ይነጽፍ ይንጽፍ። ዕብ ያጻዕ) ማንጠፍ ፥ መዘርጋት ፥ መጐዝጐዝ መነስነስ ማመቻቸት። ጸፍጸፈን እይ፤ የዚህ ዲቃላ ነው። ነጸፉ አልባሲሆሙ። ዘርቤታተ ነጸፍኩ። ህየ ነጸፍኪ ምስካበኪ። ንነጽፍ ሎቱ ዐራተ። ሠቀ ወሐመደ ነጸፉ ሎሙ ፡ (ማቴ፳፩ ፡ ፰። ምሳ፯ ፡ ፲፮። ኢሳ፶፯ ፡ ፯። ፬ነገ ፡ ፬ ፡ ፲። አስቴ፬ ፡ ፫)። በነጸፈ ፈንታ አንጸፈ ይላል፤ ስሕተት ነው። አንጽፎ ሐመድ ወፍሬ ዕፀው ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፵፮)።
ነፂፍ ፎት ፡ (ነፅፈ ይነፅፍ ይንፅፍ። ዐረ ነሸፈ፤ ነፀበ) መንጠፍ መድረቅ፤ ማለቅ መሥረግ፤ ምጥጥ ማለት፤ የፈሳሽ። ፈልፈል ዘኢይነፅፍ። ፈለግ ይነፅፍ ወይየብስ። ይነፅፍ ማየ ዮርዳኖስ። ከመ ኢይነፅፋ ዐዘቃቲከ ፡ (አርጋ ፡ ፩። ኢዮ፲፬ ፡ ፲፩። ኢያ፫ ፡ ፲፫። ምሳ፬ ፡ ፳፩)።
ነጻሒ ንጹሕ ፡ (ሓን ሓት ጽሕት) የነጻ የጠራ፤ በቁሙ ጥሩ ነጭ ብሩህ። ዘንጹሕ ልቡ ወንጹሕ እደዊሁ። ብፁዓን ንጹሓነ ልብ። ወይለብሱ ንጹሐ። ሕያዋት ወንጹሓት። ንጽሕት ወብርህት ፡ (መዝ ፡ ፳፫። ማቴ፭ ፡ ፰። ራእ፲፭ ፡ ፮። ዘሌ፲፬ ፡ ፬። ውዳ ፡ ማር)።
ነጻሪ ፡ (ሪት ርያን ያት) የሚያይ የሚመለከት አስተዋይ፤ ጠባቂ ተመልካች፤ ተኳር ዐይናማ ልባም። ረኣዬ ኅቡኣት ወነጻሬ ነገር። ዐይን ነጻሪት ተዐውር። ይገብር ብዙኀ ግብረ በዘይት ፌሥሑ ነጻርያን ፡ (ቅዳ ፡ ጎር። ግንዘ። አፈ ፡ ተ፲፮)።
ነጻፊ መንጸፊ ፡ መንጸፊ፤ ፡ (ፊት ፍያን ያት) የሚያነጥፍ ፥ አንጣፊ፤ ጐዝጓዥ።
ነጽሐ [1] ፡ (ነጺሕ። ጥሂር ጠሀረ) ነጻ ነይ ነጣ ፥ ነጭ ኾነ። ታጠበ ጠራ፤ ታደሰ ከርስሐት ተለየ። ጠሀረን እይ፤ ከዚህ ጋራ አንድ ነው። መኑ ይነጽሕ እምርስሐት። ኢትክል ምድር ነጺሐ እምደም። ንጽሑ ወወልጡ አልባሲክሙ ፡ (ኢዮ፲፬ ፡ ፬። ኩፋ ፡ ፳፩። ፴፩)።
[2]:-ጣለ አንከባለለ፤–ነፅኀ።
ነፅሐ ፡ ነፅሐ፤–ነጣ ነጻ፤–ነጽሐ።
ነፅኀ [1] ፡ (ዕብ ናጣሽ) ጣለ አንከባለለ ፥ ከምድር ፈጨ አንቈጨቈጨ፤ አፈረጠ ፈጠፈጠ፤ ሰበረ። ዕጐልት ሶበ ነፅኅዋ ለጦቢሕ ወለደት በግዕ። ወይነፅኁኪ ውስተ ምድር። ይነፅኁ ውሉዶሙ በቅድሜሆሙ። ይነፅኁ አንቆቅሖሆሙ። ይነፅኆሙ ውስተ ኰኵሕ። ወነፀኁ ዝክተ መሳብክተ ፡ (ዮሴፍ። ኢሳ፫ ፡ ፳፮። ፲፫ ፡ ፲፮። ፳፰ ፡ ፮። መዝ ፡ ፻፴፮። መሳ፯ ፡ ፲፱ ፡ ፳)።
[2] ፡ (ዕብ ናጻሕ) ድል ነሣ፤ አሸነፈ አዋረደ፤ አጠቃ ገዛ ረገጠ ፥ ምድር አስጋጠ። ምስጢሩ ከዚያው ይገባል። እነፅኆሙ በኵናት። ትነፅኆሙ ለአህጉር ጽኑዓት። ከመ ኢይንፀኅዎሙ አሕዛብ። ነፅኃ እግዚ ለወለት ድንግል ፡ (ኤር፲፱ ፡ ፯። ኢሳ፳፮ ፡ ፭። ዮኤ፪ ፡ ፲፯። ሰቈ፩ ፡ ፲፭)።
ነጽሮ ሮት ፡ (ነጸረ ይኔጽር ይነጽር። ዕብ ናጻር። ሱር ንጣር። ዐረ ነዘረ) ተኵሮ ማየት ፥ ማስተዋል ፥ መመርመር፤ መጠበቅ ፥ መመልከት፤ የዐይን የልብ። ስእንኩ ነጽሮ ኀበ እግዚ ሰማየ። ንባበ ዚኣየ ነጽር። ነጽሩ ነፍሰክሙ። ሰአልዎ ያስትጋብእ ማኅበረ ከመ ይነጽሩ በእንተ ክሕደቶሙ ለእሉ ሠለስቱ ከሓድያን ፡ (ኢሳ፴፰ ፡ ፲፬። ምሳ፬ ፡ ፳። ኪዳ። ስንክ ፡ የካ፩)።
ነጽይ ዮት ፡ (ነጸየ ይነጺ ይንጺ። ዕብ ናጻህ። ሱር ንጻእ። ዐረ ነጻእ) መንጨት፤ መንቀል መምለጥ፤ መጋጥ መግመጥ።ነጸይኩ ሥዕርተ ርእስየ ወጽሕምየ። ለምንት ይነጽዩ ሥዕርተ ርእሶሙ። ኢይንጺ ሥዕርተ ርእሱ ፡ (ዕዝ፬ ፡ ፫። አፈ ፡ ተ፬። ፍ ፡ ነ ፡ ፳፪። ፵፭)።
ነጽፈ ፡ ነጠፈ ደረቀ፤–ነፂፍ ነፅፈ።
ነጽፍ ፡ (ፋት፤ አንጽፍት፤ ገበር ገላ ነክ፤ ውሳጣዊ ልብስ ከግምጃ ጋራ የሚሰፋ። ወደዩ ሎቱ ነጽፈ ዘደርከኖ ፡ (ዘፀ፴፮ ፡ ፵)።
ነጾራር ፡ አዞሪቴ፤–ፆረረ።
ነፆራር ፡ (ዕብ ጺር) ሸውራርነት። ጣር ጋር ሥቃይ ሐዘን፤ ምጥ፤ የጭንቅ ጨኸት። ይዋሕየኒ ነፆራር። አኀዞሙ ፍርሀት ወረዓድ ወድንጋፄ ወነፆራር። አኀዞ ነፆራረ ሐዘን ወኢክህለ ያርምም ወከልሐ ፡ (ኢዮ፴ ፡ ፲፭። ግንዘ። ዮሴፍ)።
ነፈረ ፡ (ነፊር። ሱር ንፋር። ዐረ ፋረ) በቁሙ፤ እጅግ ሞቀ ፥ ፈላ ገነፈለ፤ የውሃ። ኣነብራ ዲበ አፍሓም እስከ ይነፍር ፡ (ሕዝ፳፬ ፡ ፲፩)። ተቈጣ ጠብ ፈለገ፤ አገሣ ወገሸ አገረገረ፤ የበሬ።
ነፈርዓጽ [1] ፡ ዝላይ መርታ፤–ፈርዐጸ።
[2] ፡ ዝላይ፤ መርታ፤ ተድላ፤ ደስታ፤ ሴስን ቅንዝር። ፍሥሓ ወሐሤት ወነፈርዓጽ። እምኀይለ ነፈርዓጻ ፡ (አፈ ፡ ተ፴፪። ራእ፲፰ ፡ ፫)።
ነፈየ ፡ (ነፍይ። ዕብ ናፋሀ) ነፋ ፥ አንዘረዘረ፤ ነቀነቀ አዞረ ወዘወዘ። ዘርዘረን እይ ፡ (መ ፡ ፈ)። ነፈየና ነፍኀ ባማርኛ ይተባበራሉ። ፡ (ግጥም ፥ ደብተራ ሚስቱ ተቈጥታ ስላኰረፈች) እንደ ሰው ገርድፋ መች ትተወዋለች፤ ተነፋች ደስታ ትሠልቀዋለች።
ነፈጠ ፡ ጋዝ አወጣ፤ ተኰሰ አቃጠለ፤ እንፍ አለ ፥ ተናፈጠ።
ነፊቅ ፡ (ነፈቀ ይነፍቅ ይንፍቅ። ዐረ ነፊቀ። ሱር ንፋቅ፤ ወጣ ተለየ ከቍጥር ካንድነት) መንፈቅ ፥ መሠንጠቅ፤ አስተካክሎ መክፈል መለየት። ሠጠቀንና ፈረቀን እይ፤ የዚህ ጎሮች ናቸው። ወነፈቆ ለሕዝብ ዘምስሌሁ። ዘነፈቃ ለባሕረ ኤርትራ ወከፈላ። ተዋሕዶ አምላክ ወሰበእ ለክልኤ ነፈቀ። ወነፈቆን እማእከል ፡ (ዘፀ፴፪ ፡ ፰። መዝ ፡ ፻፴፫። ስንክ ፡ መስ፯። ኩፋ ፡ ፲፬)። በነፈቀ ፈንታ ናፈቀ ይላል፤ ስሕተት ነው። ናፋቄ መንግሥት፤ ዘይናፍቅ መንግሥተ እምደቂቀ ሴም። ዕድወ ደም ኢይናፍቁ መዋዕሊሆሙ ፡ (ክብ ፡ ነገ ፡ ፯ና ፡ ፱። መዝ ፡ ፶፬)።
ነፊፍ ፡ (ነፈ፤ ነፈፈ ይነፍፍ ይንፍፍ። ዕብ ናፌፍ) ማረም፤ መኰትኰት። ነፋፋ መኾን፤ ሞኝነት ነፋፍነት። ለፈፈን እይ፤ የዚህ መንቲያ ነው።
ነፋኂ ፡ (ኂት ኅያን ያት፤ ኅት) የሚነፋ ነፊ፤ መች አጋፋች። ነፋኄ ቀርን። ነፋኄ እንዚራ ወተውኔት ፡ (ነሐ፬ ፡ ፲፰። ፈ ፡ መ ፡ ፴፬ ፡ ፩)።
ነፋስ ፡ (ሳት) በቁሙ ፥ አየር፤ ረቂቅ ርጉዕ ህዉክ፤ ከሰማይ በታች በኅዋ በምድር ባራቱ ማእዝን በኹሉ የመላ፤ በገዛ ኀይሉ የሚታወክና የሚናወጥ ሌላውንም ኹሉ የሚያናውጥ፤ የሚያገዝፍ የሚያረዝም የሚያሳድግ፤ ሕይወትና ጤና የሚሰጥ ካራቱ ባሕርያት አንዱ፤ ጽልመትና ይብሰት ቍረት ያለው፤ በጽልመቱ ከመሬት ፥ በይብሰቱ ከእሳት ፥ በቍረቱ ከውሃ የሚሰማማ። ረበቦ ለሰማይ ከመ ሠቅ፤ ወበነፋስ ፀመዶ። ይዌስን በኆጻ ወይዔምድ በነፍስ። ጠባይዕ ነፋሳዊ። መሬት ቱሱሕ በእሳት ወነፋስ ወማይ ፡ (መቃ ፡ ገላ፲። ቅዳ ፡ ግሩ። ፈላስ። ቀሌ)። ወርኢኩ አርባዕተ ነፋሳተ እለ ይጸውርዋ ለምድር ወለጽንዐ ሰማይ፤ ወርኢኩ ከመ ነፋሳት ይረብብዋ ለልዕልና ሰማይ፤ ወእሙንቱ ይቀውሙ ማእከለ ሰማይ ወምድር። ወበአጽናፈ ምድር ርኢኩ ዐሠርተ ወክልኤተ ኅዋኅወ ርኅዋተ እለ እምኔሆሙ ይወፅኡ ነፍሳት ወይነፍኁ፤ ወበአርባዕቱ እምኔሆሙ ይወፅኡ ነፍሳተ በረከት ወሰላም፤ ወእምእልኩ ሰመንቱ ይወፅኡ ነፋሳተ መቅሠፍት ፡ (ሔኖ ፡ ፲፰ና ፡ ፶፮ ፡ ክፍል)።
፡ ማእዝን፤ የማእዝን ቦታ። ያስተጋብእዎሙ ለኅሩያኒሁ እምአርባዕቱ ነፋሳት ፡ (ማር፲፫ ፡ ፳፯)። ትንፋሽ ፥ ላበት እንፏለት ወሬ፤ ከአፍ ከገላ የሚወጣ።
ነፋቂ ፡ (ቂት ቅያን ያት) የሚነፍቅ ፥ የሚከፍል፤ ክፋይ ሠንጣቂ።
ነፋዪ ፡ (ዪት ይያን ያት) የሚነፋ ነፊ፤ አጥሪ አንዘርዛሪ።
ነፋጺ ፡ (ጺት ጽያን ያት) የሚሸሽ ሸሺታ፤ ኰብላይ ፥ ፈርጣጭ። ገብአ እምኀበ ኮነ ነፋጼ። ኢያትረፈ ነፋጼ ለዝክር ፡ (ስንክ ፡ ግን፲፩። ሚያ፲። ዘዳ፫ ፡ ፮)።
ነፍኀ ፡ (ዐረ ነፈኀ። ዕብ ናፋሕ። ሱር ንፋሕ) ነፋ፤ ቀበጠጠ ፥ አሳበጠ፤ የደዌ የትንፋሽ። ዝንቱ ማይ ይነፍኅ ኵሎ ሥጋሃ ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፳፬ ፡ ፮። ዘኍ፭ ፡ ፳፯)።
፡ አነፋ ፥ አናፋ ጮኸ ፥ አስጮኸ በትንፋሽ ፤
የመለከት ፥ አነፈን እይ ፤ የዚህ ጎር ነው። ንፍኁ ቀርነ። ይነፍኅ በቀርን ዐቢይ (ሆሴ፭ ፡ ፰። ኢሳ፳፯ ፡ ፲፫)።
፡ እፍ አስ ፥ ተነፈሰ ፤ ትንፋሽ አወጣ ፤ ለመምላትና ለማሳደር ለመንፋት ለማንደድ ፥ ወይም ለማራቅ ለማሶገድ ፤ የአፍ የወናፍ። እመ ነፋኅካሃ ለፍሕም ትነድድ። ነፍኀ ላዕሌሆሙ። እመ ኢረከቡ ማየ ይንፍኁ እደዊሆሙ። አባእክሙ ቤተ ወነፋኅክዎ (ሢራ፳፰ ፡ ፲፪። ዮሐ፳ ፡ ፳፪። ፍ ፡ ነ ፡ ፲፬። ሐጌ፩ ፡ ፱)።
፡ ነፈሰ ነፋፈስ ፥ ሽው ሽው አለ ፤ የአየር የነፋስ ፤ ነፍሰን እይ ፤ ከዚህ ጋራ አንድ ነው። ይነፍኅ ነፋስ ጽባሓዊ። ነፍኁ ነፋሳት። ተንሥእ ሰሜን ወነዐ ደቡብ ወንፍኅ ገነትየ (ሢራ፵፫ ፡ ፲፮። ማቴ፮ ፡ ፳፯። ማሕ፬ ፡ ፲፮)።
ነፍሰ አው ነፈሰ ፡ (ይነፍስ ይንፈስ፤ ይንፍስ። ዕብ ናፎሽ) ነፈሰ፤ ሽው ሽው አለ። ነፍኀን እይ፤ የዚህ መንቲያ ነው። አርባዕቱ ነፋሳት ነፍሱ። ነፋሳት ይነፍሱ ዲበ ምድር። ነፍኁ ይነፍኁ የሚልም ይገኛል ፡ (ዳን፯ ፡ ፪። ሔኖ፸፮ ፡ ፩)።
፡ ዐረፈ ፥ ተነፈሰ፤ እፍ እህ እፎይ አለ። መጽሐፍ ግን በነፍሰ ፈንታ አንፈሰ፤ አስተንፈሰ ይላል፤ አያሰኝም። አራዊት ዘያነፍሱ እሳተ ዘይነፍኅ ወይልህብ። ዐቢየ ግብረ ፈጸምከ ወአንፈስከ። በእብሬትኪ አንፈሱ ሕዝበ ኢትዮጵያ። ፈጸመ ስምዖ ወተከለለ፤ ወአንፈሰ እምዝ ዓለም ፡ (ጥበ፲፩ ፡ ፲፬። ሢራ፯ ፡ ፳፭። ስንክ ፡ ኅዳ፲፪። መጽ ፡ ምስ)። እስከ ሶበ ያስተነፍስ ዕለት። ከመ ያስተንፍስ ወልደ አመትከ ፡ (ማሕ፪ ፡ ፲፯። ፬ ፡ ፮። ዘፀ፳፫ ፡ ፲፪)።
ነፍሳዊ ፡ (ዊት ውያን ያት) በቁሙ ፥ የነፍስ የልብ፤ መንፈሳዊ። ሕማም ነፍሳዊት። ይደልዎ ኵነኔ ነፍሳዊ ወሥጋዊ። ተደምሮ ዘመድ ይትከፈል ኀበ ክልኤ ክፍል ነፍሳዊ ወሥጋዊ ፡ (ፊልክ ፡ ፻፺፪። ፈ ፡ መ ፡ ፬ ፡ ፩። ፭ ፡ ፪)።
ነፍስ ፡ (ሳት) በቁሙ፤ ረቂቅ አካል የሥጋ ሕይወት ፥ የሥጋ ባለቤት፤ ነባቢት ለባዊት። ሀለወት ነፍሱ በላዕሌሁ። አልጸቀት ትባእ ነፍሳ። ትግባእ ነፍሱ ላዕሌሁ። ነፍስ ነባቢት። ትረክቡ ክፍለ ምስለ ነፍሳተ ጻድቃን። እስመ ክልኤቲ ነፍሳት ሀለዋ ኀበ ሰብእ፤ አሐቲ መንፈሰ ሕይወት ዘወፅኦት እምአፉሁ ለእግዚ ወኢትትኄለቍ ምስለ ጠባይዕ ወኢትመውትሂ፤ ወአሐቲመ ደመ ነፍስት ይእቲ እምጠባይዕ፤ ወይእቲሰ መዋቲት ፡ (ግብ፳ ፡ ፲። ዘፍ፴፭ ፡ ፲፰። ፫ነገ ፡ ፲፯ ፡ ፳፩። ቅዳ ፡ አፈ። ዲድ ፡ ፴፬። አርጋ)።
፡ ትንፋሽ ፥ እስትንፋስ፤ ሕቅታ። አምጣነ ሕያው አንተ ወሀለወት ነፍስከ። ነፍሱሂ ፍሕም ይእቲ። እስከ ነፍስ ደኃሪት ፡ (ሢራ፴ ፡ ፳፬። ኢዮ፵፩ ፡ ፲፫። ቅዳ)።
፡ ልብ፤ ልቡና። ኵሉ ነፍስ ይደነግፅ። በኵሉ ነፍስከ አክብሮ ለአቡከ። ወአቅም ምክረ ነፍስከ ፡ (ኢሳ፲፫ ፡ ፯። ሢራ፮ ፡ ፳፮። ፴፯ ፡ ፲፫)።
–ሰው፤ ሰውነት። ወተወስኩ ሠላሳ ምእት ነፍስ። ዕቀቡ ነፍሰክሙ። የኀሥሥዋ ለነፍሰ ዝ ሕፃን ፡ (ግብ፪ ፡ ፵፩። ዘዳ፬ ፡ ፲፭። ማቴ፪ ፡ ፳)።
፡ ሕያው ፍጥረት ትንፋሽና ደመ ነፍስ ያለው ፥ የሚላወስ ተንቀሳቃሽ። ኵሉ ነፍስ ይሴብሖ ለእግዚ ፡ (መዝ ፡ ፻፶)።
ነፍስት ፡ (ታት) ሰውነት፤ ሥጋ ገላ ሕዋስ፤ አካል ብልት ፥ መልክ ፊት፤ ሆድ አባለ ዘርዕ። እንዘ ከመ በድን ነፍስቶሙ። እመኒ ትቤ እግር ኢኮንኩ እምውስተ ነፍስት። ርኢ ነፍስተነ ወነፍስቶሙ ለደቅ እለ ይሴሰዩ እማእደ ንጉሥ። ኢይክበድከ ነፍስትከ። ትገዝሩ ከተማ ነፍስትክሙ ፡ (ዕብ፲፩ ፡ ፲፪። ፩ቆሮ ፡ ፲፪ ፡ ፲፭። ዳን፩ ፡ ፲፫ ፡ ፲፭። ሢራ፴፬ ፡ ፲፱። ዘፍ፲፯ ፡ ፲፩)።
ነፍር ፡ ንፍሮ፤ እንግርግብ ፥ አንፊላ።
ነፍቅ ፡ (ቃት) [1] ፡ ቃሬዛ ፥ የሬሳ ዐልጋ፤ ሣጥን ታንኳ መርከብ ፥ ሞላላ ውስጠ ክፍት። ቀርበ ወአኀዘ ነፍቆ። ሞተ ዮሴፍ ወሤምዎ በነፍቅ። ነሥአት እሙ ንፍቀ፤ ወሶበ ርእየታ ለይእቲ ነፍቅ። ቦአ ውስተ ነፍቀ ታቦት ፡ (ሉቃ፯ ፡ ፲፬። ዘፍ፶ ፡ ፳፮። ዘፀ፪ ፡ ፫ ፡ ፭። ማቴ፳፬ ፡ ፴፰)። ነፍቅና ታቦት ኹለቱ አንድ ሲኾን እንደ መክፌ ለንጽ ተደርቧል።
[2] ፡ (ዕብ ጋዲሽ) መቃብር፤ የመቃብር ዐፈር ፥ የደንጊያ ክምር፤ ጕባ አጐበር ጣራ ፥ በመቃብር ላይ የሚሠራ። ውእቱ ይተግህ ውስተ ነፍቁ። ወገብሩ ሎቱ ነፍቀ ፡ (ኢዮ፳፩ ፡ ፴፪። ኢያ፰ ፡ ፳፱)።
ነፍነፈ ፡ (ዲቃ ግ። ነፊፍ ነፈ ነፈፈ) ነፈነፈ፤ አብዝቶ በላ፤ ነጨ ጋጠ፤ የንስላና ያውሬ የሆዳም ፡ (ዐማርኛ)። አካፋ ፥ ወረደ ፥ ተረጨ በነነ፤ የውሃ፤ ከዝናም በኋላ ወይም በጉም ጊዜ። ወዝናምሂ ኢነፍነፈ እንከ ዲበ ምድር። ኢለከፎ ዝናም ዘነፍነፈ ፡ (ዘፀ፱ ፡ ፴፫። ስንክ ፡ ኅዳ፳፱)። አነፈን እይ፤ የዚህ ጎር ነው።
ነፍኒፍ ፡ ካፊያ የጉም ሽንት፤ የዝናም ተረፍ ፥ ቅሬታው ጭላጩ፤ ልዝብ ዝናም። ያርሕሶሙ ነፍኒፍ ወጠለ ገዳም። ነፍኒፈ ሌሊት። ወረደ ጠል ከመ ነፍኒፈ ዝናም። ኀሊፎ ዝናም ተርፈ ነፍኒፍ። ወይከውን በነፍኒፎሙ ለዝንቱ ሕዝብ ፡ (ኢዮ፳፬ ፡ ፰። ማሕ፭ ፡ ፪። ገድ ፡ ተክ። ሱቱ ፡ ዕዝ ፡ ፪። ሚክ፪ ፡ ፲፩)።
ነፍገ አው ነፈገ ፡ በቁሙ፤ ሣሣ ሠሠተ ቤሰ፤ ንፉግ ኾነ።
ነፍጥ ፡ (ዕብ ኔፍጥ) ጋዝ፤ የጋዝ ዐይነት፤ ከምድር የሚወጣ የምድር ቅባት ፥ የሚቃጠልና የሚበራ ፈሳሽ። ዐይን ዘታነቅዕ ነፍጠ፤ ወነፍጥኒ ይወፅእ ላዕለ ገጸ ማይ ፡ (ዮሴፍ)።
፡ በቁሙ ፥ ጠመንዣ የጦር መሣሪያ ፥ በቀስትና በፍላጻ ፈንታ የገባ ፥ ብዙ ስምና ዐይነት ያለው ፥ ጯኺ ፈጣን እሳታም። ወነደፍዎ ለግራኝ በነፍጥ ፡ (ታሪ ፡ ነገ)። ያፍንጫ ዛሕል፤ ንፍጥ፤ ምስጢሩ ፈሳሽነት ነው። ፡ (ስድብና ተረት) ንፍጣም፤ የንፍጥ ዋንጫ። አላዋቂ ሳሚ ንፍጥ ይለቀልቃል።
ነፍጸ አው ነፈጸ ፡ (ነፊጽ። ዕብ ናፋጽ) ሸሸ ራቀ፤ ኰበለለ ፥ ጠፋ ታጣ፤ በነነ ተዘራ ፥ ተበተነ። ነፍጸ ንዋም እምአዕይንትየ። ነፍጸ ሕዝብ። አይቴ ትነፍጹ። ነፍጸ እምገጸ ሰብእ ፡ (ዘፍ፴፩ ፡ ፵። ዘፀ፲፬ ፡ ። ሔኖ። ስንክ ፡ ሚያ፲)።
ኑ ፡ (ሁ) ጥያቄና አንክሮ ፥ የሁ መንቲያ፤ ፍችው ን። ዘንተኑ ገበርኪ። ዳኅንኑ አቡክሙ፤ እወ ዳኅን። አንተኑ ዘይመጽእ። ዘወድቀ ኢይትንሣእኑ። ዘኖመሰ ኢይነቅህኑ ፡ (ዘፍ፫ ፡ ፲፫። ፵፫ ፡ ፳፯። ማቴ፲፩ ፡ ፫። ኤር፰ ፡ ፬። መዝ ፡ ፵)። መ ሲጨመርበት በጥያቄነት ላይ ነው ይኾናል፤ መኑን ተመልከት።
ኑኀት ፡ ኑኀት፤ መርዘም፤ አረዛዘም፤ ርዝመት፤ ረዥምነት። ይትዓረይ ቦቱ ሌሊት ምስለ መዓልት በኑኀት ወበኅጽረት ፡ (አቡሻ ፡ ፲፬)።
ኑኅ ፡ (ኑኃት፤ አንዋኅ) ርዝማን ርዝመት ፥ ሞላልነት ፥ ምጥቀት ርሕቀት፤ ብዛት ስፋት። ኢይትዐወቅ ኑኃ ወግድማ ወኢቆማ። ወይከውን ኑኃ ለይእቲ ዕለት ከመ ሰብዐቱ ዓመት። እርአይ ኑኆ ለሰማይ። ስማዕ ጸሎቶሙ ውስተ ኑኀ ሰማይ። ሚ መጠን ኑኀ ትዕግሥቱ ለእግዚ ፡ (ቀሌ። ሱቱ ፡ ዕዝ፮ ፡ ፲፮)። ጸሎ ምና። ግንዘ። መጽ ፡ ምስ)። አንዳንድ ጊዜም በ ሲወድቅበት ፥ ሳይወድቅበትም ኵሉ ይኾናል። አንሰ እቤ በኑኀ መዋዕልየ። በኑኀ ዕለት። በኑኀ ሌሊት። ኑኀ ሠለስቱ ዕለት።
ኑልው ፡ (ዋን ዋት ሉት) የተጠበቀ ፥ ጥብቅ፤ ባለረኛ።
ኑር ፡ (ዐረ ወሱር። ዕብ ኔር) ብርሃን ጸዳል፤ እሳት ፋና። ብርሃን ዘእምብርሃን ባለው ፥ ዐረቡ ኑር ምኑር እንዲል ፡ (ጸሎ ፡ ሃይ)።
ኑባሬ ፡ (ርያት) ዝኒ ከማሁ፤ አናዎር ኑሮ፤ አቀማመጥ። ተዘምዶ ዘኑባሬ። ሥነ ሥርዐቶሙ ወኑባሬሆሙ። ማእከለ እንስሳ ኑባሬ ፡ (ፍ ፡ ነ ፶፪ ፡ ፫። ድጓ። ስንክ ፡ ኅዳ፫)።
ኑታጌ ፡ ዝኒ ከማሁ። ኢይትሌዐሉ በፍድፋዴ ወኢየሐጽጹ በኑታጌ። ኢሀሎ ኑታጌ ስብሐት ላዕለ መንፈስ ቅዱስ። ይሜህር ኑታጌ እምጠባይዕ ፡ (መጽ ፡ ምስ። ያዕ ፡ ዘእል)።
፡ መቅረት፤ መታጐል። ሰላም ለቁመቱ ዘአልቦ ኑታጌ እስከ ተመሰለ እግሩ ከመ እግረ ነጌ ፡ (ስንክ ፡ የካ፳፭)።
ኑዛዜ ፡ (ያት) በቁሙ፤ ፡ (ላ ጥ ና) መናዘዝ ፥ ማ(መ) ረጋጋት ርጋታ፤ የልቡና ዕረፍት። መጽሐፈ ኑዛዜ። ናዘዝኮ ኑዛዜ መንፈሳዊተ። ሠናየ ኑዛዜ ትናዝዘኒ ፡ (አዋል። ግንዘ። ኩፋ ፡ ፴፯)።
ኑፉቅ ፡ (ቃን ቃት ፍቅት) የተናፈቀ፤ ተናፋቂ። የተጠረጠረ፤ ተጠርጣሪ። መናፍቅ ተጠራጣሪ ፥ ልቡ ሐሳቡ ኹለት የኾነ። ልብ እኩይ ወኑፉቅ። ኑፉቀ ሃይማኖት። ኢትኩኑ ኑፉቃነ ፡ (ዕብ፫ ፡ ፲፪። መጽ ፡ ምስ። ፪ቆሮ ፡ ፮ ፡ ፲፬)። ናፈቀ የነፈቀ። ዘር ስለ ኾነ በኑፉቅ ፈንታ ንፉቅ ይላል፤ የባረከ ቤት ነውና ፥ አያሰኝም። ውሂበከ ኢትናፍቅ፤ እስመ ንፉቅ እምእግዚ ይርሕቅ። ንፉቃነ ሃይማኖት ፡ (ገድ ፡ ተክ። ፪ጢሞ ፡ ፫ ፡ ፰)።
ኑፋቄ ፡ (ያት) በቁሙ፤ መክፈል ፥ መከፈል፤ ክፍያ አከፋፈል። ጥርጥር ፥ ጥርጠራ፤ ምንታዌ። ዘእንበለ ኑፋቄ ወብዕድና። እለ እንበለ ኑፋቄ። ዘእንበለ ኑፋቄ ልብ አመንክሙ ብየ ፡ (ቄር። ኪዳ)።
ኒ [1] ፡ (ወ ሂ) ዋዌ፤ ም ፥ ደግሞ ኹኖ፤ ስንኳ ፥ ግን። ዘበሰማይኒ ወዘበምድርኒ። እመ ኀደግሙ ለሰብእ አበሳሆሙ ለክሙኒ የኀድግ አቡክሙ። በቃልከኒ ወበምግባርከኒ አክብሮ ለአቡከ። ወሚካኤልኒ ሊቀ ፡ (ጸሎ ፡ ሃይ። ማቴ፮ ፡ ፲፬። ሢራ፫ ፡ ፰። ይሁ ፡ ፱)። የወንና የሂን አፈታት እይ።
[2] ፡ የአነ ዝርዝር ፥ ወይም ጠቃሽ፤ ፍችው ኝ። ኅፀበኒ ወአንጽሐኒ። ቀተለኒ፤ ገደለኝ፤ ገደለልኝ ፥ ገደለብኝ ፡ (ልኝ የበጎ፤ ብኝ የክፋ)።
ኒሉስ ፡ (ዕብራ) ፈለገ ኒል፤ ግዮን ኤፌሶን ነጭ አባይና ጥቍር አባይ፤ ውሃቸው ነጭ ኒል ፥ ጥቍር ኒል ፥ የሚመስል።
ኒል ፡ (ዐረ) በቁሙ፤ ህንዳዊ ቀለም ፥ ልብሰ ማርያም፤ ካንድ ዐይነት ዕንጨት የሚወጣ ፥ ሕብሩ ሰማያዊ፤ ዘረቀንና አዝረቅን ዐለለን እይ። ፡ (ስንክ ፡ ሐም፰። ኅዳ፳፩)።
ኒእ አው ንያእ ፡ (ዐረ ወዕብ ናእ) ያልበሰለ ርጥብ፤ ሥጋ ሽክላ ሊጥ።
ኒካዑ ፡ (ጽር ኔካዖ። ዕብ ንኮ) ንኩይ ንኩዕ ፥ ንካ ስባራ ዐንካሳ። ፈርዖን ኒካዑ ፡ (፬ነገ ፡ ፳፫ ፡ ፳፱)።
ና ፡ የጥሬና የስም ምእላድ፤ ፍችው እነትና መኾን፤ ምስጢሩ ባሕርይ፤ ወይም የባሕርይ ኹነታ ፥ አኳኾን። ቅድም ፥ ቅድምና፤ ሰብእ ፥ ሰብእና። ወልድ ፥ ወልድና፤ ልጅነት ፥ ልጅ መኾን ያሰኛል።
ናሁ ፡ (ነ ነዮ ነዋ። ዕብ ሄን፤ ሂኔህ። ዐረ ኢነ) ንኡስ አገባብ፤ የቅርብ ያጠገብ ፥ ያጸፋ የጨበጣ ቃል፤ አኹን ቶሎ እንሆ ይኸው ፥ ይኸውና። የነን አፈታት እይ፤ ሥሩና ምንጩ ርሱ ነው። ናሁ ነዐርግ ኢየሩሳሌም። ወናሁ ሳድስ ዝንቱ ወርኅ። ናሁ ይመጽእ በደመና ሰማይ ፡ (ማር፲ ፡ ፴፫። ሉቃ፩ ፡ ፴፮። ራእ፩ ፡ ፯)። አንዳንድ ጊዜም በሊቃውንት ውስጥ ፍችው እንደ እስመ ና ይኾናል። ወሥጋሂ እምድኅረ ትንሣኤሁ ኮነ ዘኢይማስን ወዘኢይመውት፤ ናሁ ኮነ አሐደ ምስለ እግዚአብሔር ቃል ፡ (ሃይ ፡ አበ ፡ አትና)። ዳግመኛም ፥ ሚ ምንት በማለት ፈንታ ናሁ ይላል፤ የመላሽ ስሕተት ነው። ናሁ ሠናይ ወናሁ አዳም ፡ (መዝ ፡ ፻፴፪)። ፫ኛም ፥ ነያ በማለት ፈንታ ናሁ አመትከ። ናሁ ድንግል። ወናሁ ኤልሳቤጥኒ ይላል፤ አያሰኝም። ርኢ ጽዮንሃ ባለውም ናሁ ጽዮን ይላል ፡ (ኢሳ፴፫ ፡ ፳)።
ናሕሰየ ፡ (ተቀ ግ። ዐረ ነሲየ። ሱር ንሻእ። ዕብ ናሳህ) ረሳ ዘነጋ፤ ቸል አለ። ረስዐንና ዘንግዐን እይ፤ ከዚህ ጋራ አንድ ነው።
ናሕስ ፡ (ብ አንሕስት) ናስ ግንብ፤ መደብ። ይዴቅስ እንዘ ቅዉም ውእቱ ፥ ወታሕተ እዴሁ ናሕስ ዘያሰምክ ቦቱ ፡ (ስንክ ፡ የካ፱)።
፡ ደርብ ሰገነት፤ ተሥላስ መረባ፤ ፪ኛና ፫ኛ ፬ኛ ቤት ፥ ወደ ላይ። የግንብ ጣራ ባጥ ፥ ጠፈር መዋቅር ፥ ቅስት ዕቅድ በስተላይ ያለው፤ ዐፈር መሬት ኖራ ሽሚንት ፥ ወይም ሣርና ገል ቈርቈሮና ርሳስ የሚከድኑት እስከ ቍንጮው እስከ ጕልላቱ ፡ (ግብ፲ ፡ ፱። ማቴ፳፬ ፡ ፲፯ ፡ ፴፩። ሉቃ፲፯ ፡ ፴፩)። ዐርጉ ውስተ ናሕሰ ማኅፈድ። ናሕስ ንሡት። ሣዕረ አንሕስት። እለ ይሰግዱ በአንሕስት ፡ (መሳ፱ ፡ ፶፩። ምሳ፳፭ ፡ ፳፬። መዝ ፡ ፻፳፰ ፡ ፴። ሶፎ፩ ፡ ፭)። የልብስ ዘርፍ፤ ጫፍ ክፈፍ ፡ (ዘፀ፳፰ ፡ ፴)። ጸናጽላተ ወርቅ የዐውዶ ለናሕሰ መልበስት ፡ (አርጋ ፡ ፬)።
ናኅር ፡ ኵርፊያ፤ እንኵርፊያ፤ ጩኸት ያለው ትንፋሽ ፥ ያፍንጫና የጕረሮ ድምጥ። መናኂር እንዲል ፥ አፍንጫ ሲል ፡ (ዐረብ)።
ናህብ ፡ (ባት) ድንጋግ፤ ወደብ ገደብ፤ ውሃ ያረደው የጐደበው ፥ በውስጡ ጣዝማና ማጓ የሚገኝበት። የወንዝ ዳር ሰብል ንቦች የሚቀሥሙት፤ ወይም የውሃው ጐርፍ ፥ ማዕበል ሞገድ ጠራርጎ የሚወስድ። እምናህበ ፈለግ ፡ (ኢሳ፳፯ ፡ ፲፪)።
ናሕብ ፡ ድንጋግ፤–ንሂብ ነሀበ ናህብ።
ናሕንሐ ፡ (ዲቃ ግ) ናና በዛ ፥ ከልክ ዐለፈ ተረፈ ፥ ትርፍርፍ አለ፤ ታወከ ፈላ ገነፈለ፤ የባሕር የፈሳሽ ነገር። ዛሕዝሐንና ነክነከን እይ፤ የዚህ ጎሮች ናቸው። መጽሐፍ ግን በናሕንሐ ፈንታ ተናሕንሐ ይላል፤ ስሕተት ነው። ይትናሐናሕ ወኢይክል ፡ (ኤር፭ ፡ ፳፪)።
ናህከ ፡ ሐዘን ልቅሶ፤ ሐሳብ እህህታ። እስመ ብዙኅ ናህክየ። ኀልቀ እንከ ሕማም ወትካዝ ወናህክ ፡ (ሰቈ፩ ፡ ፳፪። ኢሳ፶፩ ፡ ፲፩)። ሀና አ ተወራራሾች ስለ ኾኑ በናህክ ፈንታ ናእክ ይላል፤ ፍችው ፩ ነው፤ ንእከን እይ።
ናሕክ ፡ ሐዘን ልቅሶ፤–ንህከ።
ናህይ ፡ ፍጹም ዕረፍት ፥ እፎይታ፤ ከህድአት በቀር ሁከት የሌለበት። ሀባ ናህየ ወዕረፍት ለዛቲ ነፍስ። አልብየ ናህይ። ወለእለሂ ይላሕዉ ናህየ ወዕረፍተ ጸጉ ፡ (ግንዘ። ቀሌ። ቅዳ ፡ መስተ)።
ናሖም ፡ (ዕብ ናሑም) የሰው ስም ፥ ነቢይ ካ፲፪ቱ ደቂቀ ነቢያት አንዱ፤ ናዛዚ መናዝዝ ፥ ወይም ኑዛዜ ዕረፍት ህድአት። ነሐምያም ማለት ዘሩና ፍችው ከዚህ ጋራ አንድ ነው። ዕፀ ሕይወት ፈዋሲተ ቍስሉ ለናሖም ፡ (ቅዳ ፡ ሕር። ናሖ፫ ፡ ፲፱)። ቅፍርናሖም፤ ፡ (ዕብ ክፋር ናሑም) ሀገረ ኑዛዜ ወዕረፍት፤ ከፈረን እይ ፡ (ማቴ፬ ፡ ፲፫)።
ናላ [1] ፡ ኑልው፤ በቁሙ ፥ አንጎል የራስ ቅል ፍሬ፤ ፈላስፎች ነቅዐ ዘርዕ መካነ አእምሮ የሚሉት። ሄጶ ውስተ ፍጽሙ ወረከቦ ናላሁ። እስከ ይውሕዝ ናላሁ እምአንፉ። ናላ ልምሉም ውእቱ በግዕዘ ጠባይዕ፤ በእንተ ዝ ሐነጸ ፈጣሪሁ ክበበ ዐፅም ከመ እንተ እብን በዲበ ናላ ዘይከውን ጸወነ ወምጽላለ ወአስተጻንዖ ከመ ኢይሰቈር። ይቤልዎ ለሰሎሞን አይቴ መካነ ልቡና፤ ይቤ በናላ። ዝንጉዕ በአማስኖ ናላሁ ፡ (ሢራ፵፯ ፡ ፬። ስንክ ፡ ግን፲፱። አፈ ፡ ተ፭። ፈላስ። ፍ ፡ ነ ፡ ፵፪)። ድማኅ ርእስ በማለት ፈንታ ናላ ይላል፤ የመላሽ ስሕተት ነው። ሖሩ ይቅብርዋ ወኢረከቡ ዘእንበለ ናላሃ ፡ (፬ነገ ፡ ፱ ፡ ፴፭)።
[2] ፡ በቁሙ አንጎል፤–ኖለወ።
ናሴብ [1] ፡ ዘበኛ፤–ናስየብ።
[2] ፡ ናሴብ፤ ፡ (ዕብ ንጺብ) ወታደር ጭፍራ ዘበኛ፤ ከተማ ጠባቂ ፥ ሹም። ምስጢሩ መቆም ነው፤ ዐምድና ሐውልትም ያሳያል። ህየ ሀሎ ናሴብ ኢሎፍላዊ ፡ (፩ነገ ፡ ፲ ፡ ፭)።
ናሥታ ፡ መጋቢያ፤ የፍርድ ቃል ፥ በይግባኝ የሚፈርስ የሚገሰስ። አስትዓ፤ እጅ መንሻ ግብር፤ ወይም ስፍር ቍጥር፤ ሰትዐን እይ። ወሤመ ውስተ መንግሥቱ ምእተ ወዕሥራ መሳፍንተ፤ ወሠለስቱ ይትሌዐሉ እምኔሆሙ ከመ ኀቤሆሙ ያግብኡ ናሥታ ፡ (ዳን፮ ፡ ፩ ፡ ፪)።
ናስታ ፡ መጋቢያ፤–ነሠተ ናሥታ።
ናርኤል ፡ ስመ ኮከብ ዐቢይ፤ መጋቤ ክረምት። ናር ፥ እሳት ብርሃን፤ ኤል ፥ አምላክ፤ በተገናኝ ብርሃነ አምላክ ፡ (ሔኖክ)።
ናርዱ ናርድ ፡ (ዕብ ኔርድ) የሽቱ ስም፤ አንድ ዐይነት ሽቱ ቅጠሉ ቡቃያው ታናናሽ ፡ (ማር ፡ ፲፬ ፡ ፫። ዮሐ፲፪ ፡ ፫)። ናርጅ ፥ የንጨት ሙዳይ፤ የታነጠ የተነጠጠ ፥ የተሸለመ የተጌጠ ወሎዬ ሥራ ፥ የሽቱና የቅቤ ማኖሪያ። ስሙን ከሽቱው ወስዷል።
ናርዶስ ፡ (ጽር። ዐረ ናርዲኒ። ዕብ ናርዲኖን) ናርዳዊ ዘናርዱ፤ የናርዱ ሽቱ መረቁ ቅባቱ የነጠረው የተጣፈጠው። ከመ ናርዶስ ዘጸገየ በጸዐድዒድ ፡ (አርጋ ፡ ፪። ማሕ፩ ፡ ፲፪። ፬ ፡ ፲፫። ኩፋ ፡ ፲፮)። ስማራግዶስ በማለት ፈንታ ናርዶስ ይላል፤ የተሳሳተ ነው፤ መረግድን እይ። ዘግቡር በናርዶስ ፡ (ድጓ)።
ናቀት ፡ (ዐረ። ዕብ ሜኒቆት) የግመል ጥገቶች እመጫቶች፤ የሚያጠቡ የሚታለቡ። አንዲቱን ናቅ ኑቅ ይላል ፡ (ዘፍ፴፪ ፡ ፲፭)። ባለብሉዮች ግን የግመል ጊደር ይሉታል።
ናበለ ፡ (ዕብ ናባል፤ አረጀ ደረቀ ተለየ ተነጠለ) በቁሙ፤ ጮኸ ተመመ፤ የጐርፍ የማዕበል።
ናብል ናብሊስ ፡ (ሳት። ዕብ ኔቤል። ጽር ናብሌስ) ንዋየ ማሕሌት፤ ውስጠ ክፍት በቈዳ የተጠፈረ የክራርና የበገና የነጋሪት ዐይነት። ስሙ አንድ ሲኾን ዐይነቱ ብዙ ነው፤ ፭ና ፡ ፮ ይኾናል። ሰላም ለቃልኪ እምድምፀ ናብሊስ አዳም ፡ (ደራሲ። ፪ነገ ፡ ፮ ፡ ፭። ፩ዜና ፡ ፲፭ ፡ ፳፯። ፪ዜና ፡ ፱ ፡ ፲፩)።
ናቱሪም ፡ (ዕብ ታኑረም) እቶኖች፤ ቤተ ልሔሞች ፥ የማድ ቤቶች። ባለብሉዮች ግን አንባሻ ይሉታል። ማኅፈደ ናቱሪም ፡ (ነሐ፫ ፡ ፲፩)።
ናታኒም ፡ (ጽር ናቲንም። ዕብ ንቲኒም) ንቱናን፤ ውሁባን ፥ ለቤተ መቅደስ የተሰጡ የግዜር አገልጋዮች፤ እስራኤል ያይደሉ አሕዛብ የገባዖን ሰዎች ፡ (ኢያ፱ ፡ ፳፪ ፡ ፳፫ ፡ ፳፯)። በናታኒም ፈንታ ንቱናን እንደ ማለት ኹሉ ፥ ናቴኒም ናታናውያን ናቲናውያን ናትናውያን ይላል፤ ኹሉም የጣፊ ስሕተት ነው ፡ (ዕዝ፪ ፡ ፸። ፯ ፡ ፯። ፰ ፡ ፲፯ ፡ ፳)። ናታናውያን ማለት ግን የናታን ወገኖች ያሰኛል ፡ (፪ነገ ፡ ፯ ፡ ፪)።
ናለወ ፡ ጠበቀ፤–ነውለወ።
ናእስ ፡ ዝኒ ከማሁ፤ ታ፤ናሽነት እንሻ፤ ሕጸጽ ቅለት። በእንተ ራሕበ ብሔር ወናእሰ ዚኣሃ። አው በናእሰ ልብ ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፭። ቅዳ)።
ናእት [1] ፡ ቂጣ፤–ነዪእ ኔአ።
[2] ፡ በቁሙ ፥ ቂጣ፤ ብርኵታ ርሚጦ ጥረሾ፤ ሊጡ ሳይቦካና ርሾ ሳይገባበት ወዲያው ተለውሶ የሚጋገር። ናእትው ትበልዑ። ኅብስተ ናእት። በዓለ ናእት። ናእት አንትሙ ፡ (ዘፀ፲፪ ፡ ፰። ፳፱ ፡ ፪። ዘሌ፳፫ ፡ ፮። ፩ቆሮ ፡ ፭ ፡ ፯)።
ናዕት ፡ ቂጣ፤–ነዪእ ኔአ ናእት።
ናእክ [1] ፡ ናኽ ቃታ፤ ክቡድ ሐዘን፤ መራራ ጩኸት። ኀደገኒ ውስተ ናእክ። ሕማመ ልብ ወገዐር ወናእክ። እምብዙኅ ናእክ ፡ (ኢዮ፴ ፡ ፳፪። መስተ። ደራሲ)።
[2] ፡ (ዕብ አናኽ። ሱር አንካ። ዐረ አኑክ) ዐረር ጥቍር ርሳስ ፥ የርሳስ ደንጊያ ከባድ፤ ዕይር ቅልቅል። እብነ ናእክ ውስተ እዴሁ። ብርት ወናእክ። ዐረር ወናእክ ወኣሴስል ኵሎ ናእከኪ ፡ (ዘካ፬ ፡ ፩። ሕዝ፳፪ ፡ ፲፰። ዘኍ፴፩ ፡ ፳፪። ኢሳ፩ ፡ ፳፭)።
-፤ ዛሕል ዝገት ፥ እድፍ። ንጽሕ ዘእንበለ ናእክ ወደነስ ፡ (ደራሲ)።
[3] ፡ (ዕብ ብዲል) ነጭ ርሳስ ቀላል ፥ ለማዕደናት ኹሉ መጣብቅ የሚኾን የሚያነጣና የሚያጠራ ብር የሚያስመስል። የርሳስ ዐይነት፤ ታኒካ ቈርቈሮ፤ የመሰለው ኹሉ። ዘገብካሁ ለወርቅ ከመ ዐረር፤ ወከመ ናእክ መላእካሁ ለብሩር ፡ (ሢራ ፡ ፵፯ ፡ ፲፰)።
ናዕዌ ንዓዌ ፡ ንዓዌ፤ ዝኒ ከማሁ፤ ዐደን። ወመጽአ ዔሳው እምንዓዌሁ። ንሣእ ንዋየ ናዕዌከ። ዘነዐወ ናዕዌ ወቀተለ አርዌ ፡ (ዘፍ፳፯ ፡ ፴። ኩፋ ፡ ፳፮። ዘሌ፲፯ ፡ ፲፫)።
ናዘረ ፡ (ናዝሮ። ዕብ ናዛር) ተሳለ ፥ ብፅዐት ገባ፤ የብፅዐት ልጅ ኾነ፤ ከሕዝብ ተለየ በፈቃዱ፤ ወይም ካባት ከናቱ ለግዜር ተሰጠ፤ በንጽሕና በቅድስና በትሕርምት በተባሕትዎ ለመኖር፤ እንደ የፍታሔ ልጅ ፡ (መሳ፲፩ ፡ ፴ ፡ ፴፩ ፡ ፴፬–፵)። በፅዐን እይ።
ናዘዘ ፡ (ይናዝዝ፤ ናዝዞ) በቁሙ፤ አጸናና አረጋጋ፤ አይዞኽ አለ ተስፋ ሰጠ፤ በምክር በነገር ደስ አሰኘ። ኀጣእኩ ዘይናዝዘኒ። ኢይናዝዝዎሙ በእንተ ዘሞተ። ናዘዝካሁ ለልበ አመትከ። ወአልቦ ዘይናዝዞሙ ፡ (መዝ ፡ ፷፰። ኤር፲፮ ፡ ፯። ሩት፪ ፡ ፲፫። መክ፬ ፡ ፩)።
ናዛሪ [1] ፡ (ሪት ርያን ያት) የሚነዝር ፥ የማናዝር፤ ነዘር ናዜራ ፥ ዳሞትራ ጊንጥ፤ ተናካሽ ነዳፊ፤ መርዛም ጥርሳም። ነዘር እባብ እንዲሉ ፡ (ዘኍ፳፩ ፡ ፮)።
[2] ፡ ንዙር፤ ፡ (ዕብ ናዚር። ሱር ንዚራ። ዐረ ነዚር። ጽር አጊዎስ) የተሳለ፤ ብፅዐት የገባ፤ የብፅዐት ልጅ፤ ብፁዕ ቅዱስ፤ ጠጕሩን ምላጭና መቀስ የማይነካው። መጽሐፍ ግን ናዛሪ ንዙር በማለት ፈንታ ናዝራዊ ይላል፤ የመላሽና የጣፊ ስሕተት ነው ፡ (መሳ፲፫ ፡ ፭ ፡ ፯። ፲፮ ፡ ፲፯። ስንክ ፡ መጋ፴)። የብፅዐትም ሥራ ፪ ወገን ነው፤ ፩ኛው ፍጻሜና ከፊል የሌለው፤ ፪ኛው ፍጻሜ ያለው ነው ፡ (፩ነገ ፡ ፩ ፡ ፲፩። ዘኍ፮ ፡ ፪–፭ ፡ ፲፰)። ናዚር ማለት ደግሞ በዕብራይስጡ ከብፅዐት ልጅ ሌላ ፪ ልዩ ነገር ያሳያል፤ ፩ኛው የሕዝብ አለቃ ንጉሥ ባለዘውድ፤ ፪ኛው ዐጽቁ በመቀስ ያልተቈረጠ ያልተቈጠቈጠ ቅጠላም ሐረግ የወይን ጕንድ።
ናዛዚ ፡ (ዚት ዝያን ያት) የሚናዝዝ፤ ናዛዥ አረጋጊ ጸጥ አድራጊ። ናዛዚ ወመናህይ። ናዛዜ ሕዙናን። ናዛዚትየ እምሐዘን ፡ (ግንዘ። ድጓ። ደራሲ)።
ናዝራዊ ፡ (ዊት ውያን ያት። ጽር ናዞሬዎስ። ዕብ ናጽሪ) ናዝሬታዊ የናዝሬት፤ በናዝሬት የሚኖር ፥ ከናዝሬት የወጣ፤ ምኑን ኅሱር ፥ ወልደ ናዝሬት ብእሴ ናዝሬት። ከመ ናዝራዊ ይሰመይ ወልድየ። ኢየሱስ ናዝራዊ። ምኑን በኀበ ሰብእ ፥ ወትሑት በውስተሕዝብ ፡ (ማቴ፪ ፡ ፳፫። ማር፲ ፡ ፵፯። መዝ ፡ ፳፩። ኢሳ፶፫ ፡ ፫)። በዕብራይስጥ ግን ንጻሬት የነጸረ ዘር ነው፤ ናጻር ብሎ ጠበቀ ሰወረ ይልና ኔጼር ንጻሬት ፥ ተክል ሐመልማል ዐጽቅ ልምሉም ይላል። ናዝራዊን ደግሞ በዚህ አወራረድ ሲፈቱት ቸር እረኛ ያዳም ፪ኛ እንደ መኾኑ ፥ ጥበቃውን መደብ አድርጎ ይህን ቃል ያሳያል ፡ (ዘፀ፫ ፡ ፪። ኢሳ፲፩ ፡ ፩። ኤር፳፫ ፡ ፭። ፴፫ ፡ ፲፭። ዘካ፫ ፡ ፰። ፮ ፡ ፲፪)። ናዝሬትንም የተክል ቦታ ገነት ያሰኛል። እንደ ፊተኛውም በንዙርና በናዚር ዘይቤ ቢፈቱት የብፅዐቱ ሥራ ንጽሕናውና ቅድስናው ብሕትውናው ሳይቀር እግዜር እንደ መልከ ጼዴቅ በመንፈሱ ቀብቶ የሾመውና የተከለው ንጉሥ ካህን ጕንደ ወይን መኾኑን ያሳያል ፡ (ግብ፲ ፡ ፴፰። መዝ ፡ ፪ ፡ ፮። ፻፱ ፡ ፬። ዮሐ፲፭ ፡ ፩)። ምእመናንም ከዐጽቆቹ ከሐዋርያት ዠምሮ በናዝራዊው መሲሕ ስላመኑ በአይሁድ ቋንቋ በዕብራይስጥ ኖጽሪም ይባላሉ፤ ናዝራውያን ናዝሬታውያን ማለት ነው። ሕዝበ ናዝራውያን። ኢየሱስ ናዝራዊ አምላኮሙ ለናዝራውያን ፡ (ግብ፳፬ ፡ ፭። መጽ ፡ ምስ)።
ናዝሬት ፡ (ጽር ናዛሬት። ዕብ ንጻሬት። ዐረ ናጺረት) በቁሙ ፥ ስመ ሀገር ታናሽ ከተማ ፥ ከገሊላ አውራጃ በዛብሎን ክፍል ካንዲት ተራራ ላይ የተሠራች ፥ ደብረ ታቦርና ቅፍርናሖም የሚያማክሏት፤ የቀድሞ ሰዎቿ እጅግ የተናቁ የተዋረዱ፤ ኋላም ጌታችን የሱስ የተፀነሰባት ያደገባትና የኖረባት። ዘይቤው ምንንት ኅስርት ማለት ነው፤ ስሟን እንደ ብፅዐት ልጆች በኅሱርነት ከሚኖሩ ከሕዝቧ ወርሳለች። ውእተ አሚረ ይሰምይዋ ለናዝሬት በስመ ኀሳር። ይትከሀልኑ ይፃእ ኄር እምናዝሬት። ኅሥሥ ከመ እምገሊላ ኢይትነሣእ ነቢይ ፡ (ትር ፡ ወን። ዮሐ፩ ፡ ፵፮ ፡ ፵፯። ፶፪)።
ናዪን ፡ (ጽር። ዕብ ናዒም) ስመ ሀገር፤ የደብረ ታቦር ቅርብ አጠገብ። ሠናይት መስተፍሥሒት ማለት ነው ፡ (ሉቃ፯ ፡ ፲፪)።
ናይናን ፡ (ቅብጥ ናይ ናን) መሐር ኪያነ፤ መሐረነ ፡ (ግብ ፡ ሕማ)።
ናዳ ናደት ፡ (ዐማርኛ) በቁሙ፤ መርግ። ረግሐን እይ።
ናዳብ ዐሚናዳብ ፡ (ዕብ) የሰው ስም፤ ዐሚ ፥ ሕዝቤ ወገኔ። ናዳብ ፥ ፈቃደኛ ቅን ቸር፤ በፈቃዱ ለግዜር አምኃና መሧዕት የሚሰጥ፤ ካሥር አንድ አውጥቶ ደግሞ ከዘጠኙ የሚያወጣ ፡ (፩ዜና ፡ ፮ ፡ ፫ ፡ ፳፪)።
ናጌብ ፡ (ጽር። ዕብ ኔጌብ) ደቡብ፤ ደቡባዊ ቦታ የብስ ሜዳ ቈላ በረሓ ምድረ በዳ፤ የምድረ እስራኤል ዳርቻ የብንያምና የይሁዳ ክፍል ከቃዴስ በርኔ የሚዋሰን፤ ቃዴስ በርኔም ሳይቀር። አዜብን እይ ፡ (ኢያ፲፪ ፡ ፰። ሕዝ፳ ፡ ፵፮ ፡ ፵፯። ፳፩ ፡ ፬። ኤር፲፫ ፡ ፲፱)። ውቅያኖስ፤ ግበ ማይ ምግባአ ማይ ፥ ውሆችን ኹሉወደ ርሱ የሚስብ የሚሰበስብ ፥ የሚሸከምና የሚያነግብ ማለት ነው። ንባቡም ምስጢሩም ለይትጋባእ ማይ ካለው ይሰማማል፤ ገብአና ጋብአን ገበበን እይ፤ ምስጢሩም ጕድጓድነትና ቈላነት ነው። ወአመ ኀሙስ ትቤሎ ለዝኩ ማየ ናጌብ ከመ ያውፀአ አዕዋፈ ወዓሣተ። እምቅድመ ይዕምቅ ማየ ናጌብ። አውፅኦሙ ለዘመደ አዕዋፍ እማየ ናጌብ ፡ (ሱቱ ፡ ዕዝ፬ ፡ ፶፬ ፡ ፶፰። መጽ ፡ ምስ ፡ ገ፳፯። ፷፯)።
ናግራን ፡ ስመ ሀገር፤ ብሔረ ዐረብ ፥ በየመን ውስጥ ያለች መዲና ፥ ዛሬ ስንዓ የሚሏት፤ ቅዱስ ጳውሎስ በጥንተ ስብከቱ ገብቶ ያስተማራት ፡ (ገላ፩ ፡ ፲፭–፲፰)። ኋላም ባምስተኛው ፡ (ሴክል) መቶ ፊንሐስ አይሁዳዊ ተነሥቶ ፥ ብዙ እልፍ ሕዝቧን ሰማዕታቷንና ሊቃውንቷን ፈጅቶ ቢያጠፋትና ቢያቃጥላት ፥ ሐፄ ካሌብ ከዚህ ተሻግረው ርሱን ድል ነሥተው አባረው እንደ ገና መልሰው ዐድሰው ሠርተዋታል ፡ (ድጓ። ስንክ ፡ ኅዳ፳፮። ገድ ፡ ናግ። ታሪ ፡ ነገ)።
ናጥራን ናጥሮን ፡ (ዐረ ነጥሩን። ዕብ ኔቴር) የደንጊያ ስም፤ ከጨው መካክል የሚገኝ ሸካራና ዐይናማ፤ በውሃ የሚቀልጥ የሚሟሟ፤ እንደ ሳሙና ልብስ የሚያሳጥብ እደፍ የሚያጠራ፤ ለጋዝ መብራትና ለኢሊትሪክ ፥ ብርሌ ብርጭቆ የሚኾን። ዐዘቅተ ናጥራን። ቀሲሰ ዘደብረ ናጥሮን ፡ (ስንክ ፡ ጥቅ፲፫። ፊልክ ፡ ፲፰)። ይኸውም ዐዘቅት አስቄጥስ አጠገብ ይገኛል።
ናፈለ ፡ (ናፍሎ። ዕብ ናፋል) ወደቀ ፥ ተወረወረ፤ ወረደ ተጣለ ፥ ተምዘገዘገ፤ በፈቃዱ ፥ የትቢትና የጥጋብ እንደ ዲያብሎስ።
ናፈቀ ፡ (ይናፍቅ፤ ናፍቆ) በቁሙ፤ ወደደ ተመኘ፤ ሻ ፈለገ፤ ተጠማ። ጠረጠረ፤ ተጠራጠረ አመነታ ፥ ኹለት ልብ ኾነ፤ ተገበዘ። እንዘ ንናፍቅ እመ ውእቱሂ። ተአመነ ወኢናፈቀ። ልብ ዘይናፍቅ። ናፍቆ ወተሓምዮ። ናፍቆት ፡ (ኪዳ። ሮሜ፬ ፡ ፲፱። ሢራ፪ ፡ ፲፪። ፩ጴጥ ፡ ፪ ፡ ፩። ሄርማ ፡ ገ፲፯)።
ናፋቂ ፡ በቁሙ፤ ፡ (ዐማርኛ)። ጠርጣሪ፤ ተጠራጣሪ፤ የሚጠራጠር። ኢትኩን ናፋቄ አላ እመን ፡ (ዮሐ፳ ፡ ፳፯)። ምስጢሩ የነፈቀ ነው፤ ፈጽሞ አለማመንና ጨርሶ አለመካድ።
ናፌል ፡ (ጽር ናፊሊም። ዕብ ናፊል፤ ንፊሊም) ናፋሊ ንፉል፤ የወደቀ ውዱቅ፤ ዔናቃዊ ረዐይታዊ ፥ ጋኔን። ም አብዢ ነው ፥ ውዱቃን ያሰኛል፤ በናፊልም ፈንታ ናፌዲ(ድ) ም ይላል፤ የተሳሳተ ነው። ባለብሉዮች ግን ፪ ቃል መስሏቸው ናፌድምን ኀያላን፤ ናፊልን ድኩም ይሉታል፤ ዔናቅን እይ ፡ (ራእ፲፪ ፡ ፱)። ወወለዱ ውሉደ ናፌድመ፤ ወኵሎሙ ኢይትማሰሉ፤ ወይበልዕ አሐዱ አሐዱ ካልኦ፤ ያርብሕ በልዖ ለናፊል ወናፊል ለኤልዩ ፡ (ኩፋ ፡ ፯)።
ናፌድም ፡ ውዱቃን፤–ናፌሊም ናፈለ።
ኔ ፡ ዝኒ ከማሁ፤ እነት። አሐተኔ፤ አንድነት። አሐቲን እይ፤ ከአሐቲ በቀር በሌላ አይገኝም።
ኔሎቄ ፡ መሎኬ። የተሳሳተ ነው፤ መለከን እይ። ዕፀ ሐዲስ ኔሎቄ ፡ (ስንክ ፡ ኅዳ፳፱)።
ኔሳን [1] ፡ (ሱር ወዕብ ኒሳን። ጽር ኔዎን) ስመ ወርኅ፤ ሚያዝያ። ቀድሞ በዕብራይስጥ አቢብ የሚባለው ከባቢሎን ምርኮ በኋላ ኔሳን ተብሏል፤ ምልክታም ባለምልክት ፥ ባለታምራት ማለት ነው፤ ፪ኛም ፀአትንና ሽሽትን ፈተናን ያሳያል። ንሻን ማለት ደግሞ ከኔሳን ጋራ ይሰማማል፤ ሥሩና ምንጩ ነሰሰና ነሰወ ናቸው። ኔሳን፤ ዘውእቱ ሚያዝያ። ዕቀብ ወርኀ ኔሳን፤ እስመ በወርኀ ኔሳን ወፃእከ እምድረ ግብጽ ፡ (ተረ ፡ ባሮ። ዘዳ፲፮ ፡ ፩)።
[2] ፡ ኔሳን፤–የወር ስም ሚያዝያ፤–ነየሰ።
ኔሣን ፡ የወር ስም፤–ኔስ ኔሳን።
ኔስ ፡ (ዕብ) ተራዳ፤ ረዥም ምጡቅ ያላማ ሰንደቅ ፥ የባንዴራ ዕንጨት፤ የመርከብ ምሰሶ።
ኔስራ ፡ (ጽር ኔሳራን። ዕብ ኔዕጻር። ዐረ መሕጹረን) ደጀ ጠኒ፤ ከሰው ተለይቶ ብቻውን፤ የቀረ፤ ለጸሎት ለመሧዕት። ወሀሎ ህየ ኔስራ ቅድመ እግዚ። ሕጹረ ዕጉተ ክሉእ ጽኑሐ ማለት ነው ፡ (፩ነገ ፡ ፳፩ ፡ ፯)። ባለብሉዮች ግን ቦታ ሰጐን ይሉታል።
ኔስታሊ [1] ፡ (ጽር ኔስታን። ዕብ ንሑሽታን) የንሓስ እባብ፤ ሙሴ በአርዌ ምድር አምሳል የሠራው። ነሐሰን እይ ፡ (፬ነገ ፡ ፲፰ ፡ ፬)። በኔስ ዘይቤ ሲፈቱት ግን ኔስታሊን ታሌ ኔስ፤ በዕብራይስጥም ታሉይ ዐል ሀኔስ ያሰኛል። ታሊ ታሉይ ስቁል፤ ኔስ ተራዳ፤ በተገናኝ ስቁለ ኔስ ፥ ዘስቁል ዲበ ኔስ ማለት ነው፤ ተለወን ከነቍራኛው እይ ፡ (ዘኍ፳፩ ፡ ፰ ፡ ፱። ዮሐ፫ ፡ ፲፬)።
[2] ፡ የንሓስ እባብ፤–ኔስ ነየሰ።
ኔሥታሊ ፡ የባብ ምስል፤–ኔስ ኔሳን።
ኔባል ፡ (ዕብ ኔቤል) የማስ ፊቀን፤ ቀርበታ ፥ ርኰት ራዎት። ዝቅን እይ፤ ከዚህ ጋራ አንድ ነው፤ ባለቅኔዎች ግን ገንቦ በፍሻት ይሉታል። በመስፈርተ ኔባል ወይነ ፡ (፩ነገ ፡ ፩ ፡ ፳፬። ፪ነገ ፡ ፲፮ ፡ ፩። ሆሴ፫ ፡ ፪። ገድ ፡ ተክ)።
ኔአ ፡ ቀረበ ተዘጋጀ፤–ነየአ።
ኔኪፉር ፡ (ከፈረ) የሰው ስም፤ ይቅር ባይ ፥ ኀዳጌ በቀል ፡ (ማር ፡ ይሥ ፡ መቅ)። ከፈረን እይ፤ በነ ምክንያት ወደዚህ መጥቷል።
ኔዎን ፡ (ጽር ኔዖን) መፀው፤ የጽጌ የፍሬ የልምላሜ ወራት፤ በእስያና በኤውሮፓ። ይኸውም ሚያዝያና ግንቦት ነው፤ አቢብንና መፀውን እይ። ከመ ጽጌ ረዳ በወርኀ ኔዎን ፡ (ሢራ፶ ፡ ፰። ፳፬ ፡ ፳፭)።
ኔጌር ኔጎር ፡ (ጽር ኒጌር) የሰስው ስም፤ ጥቍር ጠቋራ፤ ወይም ነ(ጋ) ጃር ፥ ዐናጢ ጠራቢ። ስምዖን ዘተሰምየ ኔጎር ፡ (ግብ፲፫ ፡ ፩)።
ን ፡ አብዢ ምእላድ፤ ፍችው ዎች። ኪሩብ ፥ ኪሩቤን፤ ሱራፊ ፥ ሱራፌን፤ ኪሩቦች ሱራፎች። ጻድቅ ቃን፤ ኃጥእ ኣን። ንጹሕ ሓን፤ ቅዱስ ሳን እያለ በወንድ አንቀጽ ኹሉ ይገባል፤ የአንና የያን የትን አፈታት እይ። የጥሬ ምእላድ ሲኾን ግን ጌጥነት እንጂ አብዢነት የለውም። በርሀ ብርሃን፤ በፅዐ ብፅዓን ፤ ግዕዘ ግዕዛን፤ ፈረቀ ፍርቃን፤ ቀረበ ቍርባን የመሰለው ኹሉ።
ንሓስ ፡ (ዕብ ንሖሼት። ሱር ንሓሻ። ዐረ ኑሓስ) በቁሙ፤ መዳብ ብርት ዐይነቱ ቀይ ወይም ብጫ የብር ምክትል ፥ ዕቃ መሣሪያ ገንዘብ የሚኾን ፥ እንደ ወርቅ እንደ ብር የሚያትሙት። መጣፍ ግን በንሓስ ፈንታ ናሕስ ይላል፤ የጣፊ ስሕተት ነው። መወልጣን እለ ይቶስሑ ላዕለ ወርቅ ብሩረ፤ አው ናሕሰ ፡ (ፈ ፡ መ ፡ ፲፱ ፡ ፪)።
ንኁል ፡ (ላን ላት ኅልት) የፈረሰ ፥ የተናደ፤ ባዶ ባድማ፤ ወይም ሊፈርስና ሊናድ የቀረበ ፥ ያረገዘ ያዘበዘበ። ከመ ጥቅም ዘባቤል ረስዩ ንኁለ። አረፋት ንኁላት ከመ አረፍት ጽንንት ወከመ ጥቅም ንኁል ፡ (ደራሲ። ፪ዜና ፡ ፴፪ ፡ ፭። መዝ ፡ ፷፩)።
ንሁብ ፡ (ባን ባት ህብት) የተናበ የተሠራ፤ ፍስ ቅጥቅጥ።
ንሁይ ፡ (ያን ያት ሂት) ያረፈ የረጋ፤ እህ እፎይ ያለ። ከመ ያዕርፍ ነፍሶሙ ንሁየ ፡ (ቅዳ ፡ ሕር)።
ንኂል ሎት ፡ (ንኅለ፤ አው ነኀለ ይንኅል ይንኀል። ዕብ ናሐል፤ ወረሰ ያዘ) መፍረስ ፥ መናድ፤ መርከስ ፥ መዋረድ፤ ባዶ ባድማ መኾን። ከመ ሀገር ዘንኀለ ጥቅማ። እምቅድመ ይንኀል ዝ ቅጽር ሣልሳይ። ንኅለ ጠፈር ላዕሌሁ። እስመ ንኅለ ሀገረ መቅደስከ ፡ (ምሳ፳፭ ፡ ፳፰። ዮሴፍ። ፊልክ ፡ ፹፩። ኢሳ፰፬ ፡ ፲)። በንኅለ ፈንታ ወድቀ እንደ ማለት ተንኀለ ይላል፤ ስሕተት ነው። ተንኅለ ምታር ዐቢይ። ቅጽር ዘተንኅለ ፡ (ዮሴፍ)። ወእምዝ ተንኅለት በድወት ፡ (ስንክ ፡ የካ፩)።
ንሒሳ ንሒስ ፡ ሟርት ጥንቈላ። ስመ ሀገር፤ ኒቅያ ወይም ሌላ። ኮከበ ንሒሳ ፡ (ደራሲ። ያቦ ፡ ገድል)።
ንሒስ ሶት ፡ (ነሐሰ ይንሕስ ይንሐስ። ዕብ ናሔሽ) እባብ መኾን ፥ ከይሲ መባል፤ በስምና በግብር ፥ ወይም በባሕርይ፤ እንደ በትረ ሙሴ ተለውጦ። መጠንቈል ማሟረት፤ በድምፀ ብርት በድምፀ አራዊት ፥ ወይም ባሾክሿኪ።
ንኂር ሮት ፡ (ንኅረ ይንኅር ይንኀር። ዐረ ነኀረ። ዕብ ናሐር። ሱር ፡ ንሓር) ማኵረፍ፤ መቈጣት አፍንጫን መንፋት፤ ማንኰራፋት፤ የጠብ። ማንኳረፍ ፥ ማላዘን፤ እንደ ታረደ ከብት መኾን፤ የንቅልፋም የፍሪዳ። ኖመ ወንኅረ ፡ (ዮና፩ ፡ ፭)። አነፈን እይ።
ንሂብ ቦት ፡ (ነሀበ ይንሀብ ይንሀብ። ወሀበ። ዐነገ) መናብ፤ መሥራት መቀጥቀጥ ፥ ማፍሰስ ማቅለጥ፤ የወርቅ የብር የማዕደናት ኹሉ። ይንሀቡ ሎሙ ንዋየ ሐቅል። ሰአለቶ ከመ ይንሀብ ላቲ አዕኑገ ለአእዛኒሃ ፡ (፩ነገ ፡ ፲፫ ፡ ፳። ስንክ ፡ ሐም፲)።
፡ ማነብ፤ ንቦች ማርባት ፥ የንብ ጠባይ ማወቅ፤ ያናቢ። መቅሠም መምጠጥ፤ ማጣም ማጣፈጥ፤ የንሀብ። የሥራውን ስልት መለየት ነው እንጂ ምስጢሩ ከመሥራት አይወጣም።
ንሕለ ፡ ፈረሰ ተናደ፤–ንኂል ንኅለ።
ንኅለት ፡ መፍረስ፤ አፈራረስ ፥ ፍርሻ ፥ ፍራሽ፤ ነዳላ ብስ። ንኅለተ ቅጽር። ከመ ያርሕቡ ውእተ ንኅለተ ፡ (ዮሴፍ)።
ንህረ ፡ አንኳረፈ፤–ንኂር ንኅረ።
ንህበት ፡ መሥራት ፥ መሠራት ፥ አሠራር፤ ሥራ ቅጥቀጣ። ንዋየ ንህበት አው ልብስ ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፵)።
ንህብ ፡ (ብ አንሃብ፤ አንህብት። ዐረ ኑብ፤ ነሕል። ዕብ ድቦራህ) በቁሙ ፥ ንብ ያበባ ዝንብ ፥ ጽጌያትን ኹሉ የምትቀሥም የማር የሰፈፍ ዐበዛ ፥ ወይም አንጥረኛ። ሑር ኀበ ንህብ ወአእምር ከመ መስተገብርት ይአቲ። እምኵሉ አዕዋፍ ትንእስ ንህብ። ፅንስ እንበለ ሩካቤ ከመ ንህብ ዘእምቃለ ንባብ። አንሃብሰ ይፀንሳ በምዕር ሶበ አንዘረት ንግሥቶን፤ ወታነዝር እግዝእቶን ለአንህብት ፡ (ምሳ፮ ፡ ፰። ሢራ፲፩ ፡ ፫። ቅዳ ፡ ሕር። አዋል)።
ንሕነ ፡ (ዕብ ናሕኑ፤ አኑ፤ አናሕኑ። ሱር አናሕና። ዐረ ነሕኑ) ውስጠ ብዙ ቃል፤ የአነ ብዢ ፥ ወንድና ሴት የሚያስተባብር፤ የአንትሙና የአንትን አንጻር ፥ ከብዙዎች አንዱ ስለ ራሱና ስለ ሕዝቡ የሚናገረው። ፍችው ፥ እኛ ራሳችን ቅላችን ባለቤታችን፤ ነን ነነ፤ አለን ነበርን። አነንና ነን ውእቱን ተመልከት። ንሕነሰ ንሰብክ ክርስቶስሀ። ንሕነ ጠፈር ወንሕነ መሠረት ፡ (፩ቆሮ ፡ ፪ ፡ ፳፫። ቅዳ ፡ ግሩ)።
ንሕኑሕ ፡ (ሓን ሓት ንሕት) የናና የበዛ ፥ ከልክ ያለፈ የተረፈ፤ እልፍ ትርፍ ጭማሪ ያለው። መስፈርት ንሕኑሕ ፡ (ሉቃ፮ ፡ ፴፰)።
ንሕናሔ ፡ መብዛት ፥ መትረፍረፍ ከልክ ማለፍ፤ ብዛት ብዙነት።
ንህከ ፡ (ንሂክ። ንእከ) ዐዘነ ተከዘ ፥ ዐሰበ ተወዘወዘ ፥ እህህ አለ። አልብክሙ ንሂክ እምኔነ፤ አላ ንህክሙ በልብክሙ። ከመ በፍሥሓ ይግበርዎ ለዝንቱ ወኢይንሀኩ። ከርሥየ ንህከት ለትካዘ ዝ ዓለም ፡ (፪ቆሮ ፡ ፮ ፡ ፲፪። ዕብ፲፫ ፡ ፲፯። መጽ ፡ ምስ)።
ንህይ ዮት ፡ (ንህየ፤ አው ነሀየ ይንሂ ይንሀይ። ዕብ ወሱር ናሕ) ማረፍ መርጋት ፥ መጸናናት፤ እፎይ ማለት፤ ከሐዘን ከሁከት ከመክራ ፥ ወይም ከሥራ። ይንሀዩ ትኩዛን። ወትንሀይ ነፍስ እምአበሳሃ ፡ (ቅዳ ፡ ዮሐ። ግሩ)።
ንምራ አው ንምሮ ፡ (ላቲን ኑሜሩስ፤ ኑሜሮ) ቍጥር፤ የቍጥር ምልክት፤ አኃዝ ፊደል ነቍጣ ነጥብ ነጠብጣብ . . .።
ንሱሕ ፡ (ሓን ሓት ስሕት) ንስሓ የገባ፤ ያዘነ የተጠጠተ፤ ከክፋቱ የተመለሰ። ውእቱ ንሱሕ በእንተ ኀጣይኢሁ። መብልዑ ለንሱሕ አልቦ ዘእንበለ ኅብስት ወጼው ፡ (ፊልክ ፡ ፻፸፩። ቀሌ)። ቍጡ ብስጩ፤ የጠላውን ሥራ መልሶ የሚወድ ፡ (፪ጴጥ ፡ ፪ ፡ ፳፩ ፡ ፳፪)። ወይም ተስፋ ቈርጦ ራሱን የሚገድል የሚጐዳ፤ እንደ ይሁዳ። ኢትኩን ንሱሐ ላዕለ ዘኀለፈ ግብር ፡ (ቀሌ)።
ንሱቅ ፡ (ቃን ቃት ስቅት) የተጠረበ የተወቀረ፤ የታነጠ የተቀረጠ፤ ስድር ድርድር። ዘቆሙ ስሳ በእመት ወንድቁ በእብን ንሱቅ ፡ (ዕዝ፮ ፡ ፳፬)። በንሱቅ ፈንታ ምሱቅ ውሱቅ ይላል፤ ስሕተት ነው።
ንሡት ፡ (ታን ታት ሥት) የፈረስ ፥ የተፈታ፤ ፍራሽ ጠፍ ባድማ። ናሕስ ንሡት። ወረከብዎ ንሡተ ለምሥዋዕ። ተሐንጸት አረፍታ ወኢተርፈ ንሡት ላዕሌሃ ፡ (ምሳ፳፭ ፡ ፳፬። መሳ፮ ፡ ፳፰። ነሐ፮ ፡ ፩)። ግሑሥ ርሑቅ በማለት ፈንታ ንሡት ኵነኔከ ይላል።
ንሡእ ፡ (ኣን ኣት ሥእት) የተነሣ ፥ የተወሰደ፤ ምርጥ ምልምል።
ንሱክ ፡ (ካን ካት ስክት) የተነከሰ፤ በጥርስ የተወጋ የቈስለ።
ንሡግ ፡ (ጋን ጋት ሥግት) የተሰነገ ስንግ፤ የተቈለፈ ዝግ። ረከብነ ቤተ ሞቅሕ ንሡገ ወቅቱረ ፡ (ግብ፭ ፡ ፳፫)።
ንሳሔ ፡ (ሕያት) መነስሕ ፥ ንስሓ መግባት፤ ጥጠታ ምለሳ፤ ንስሓ አገባብ አመላለስ፤ ንሱሕነት ፡ (መጽ ፡ ምስ)።
ንስሓ ፡ (ሓት) በቁሙ ፥ ሐዘን ጸጸት ቍጭት ምላሽ፤ መቀጮ ቅጣት ፥ ቀኖና የኀጢአት ካሳ። እምድኅረ ሞት አልቦ ንስሓ። መፍትው ይትወከፉ ንስሓሆሙ ለእለ ተመይጡ። ንስሓ ፍጽምት። ሀብዎ ንስሓ ተስዐተ ሱባዔ በኅብስት ወማይ እስከ ተስዐቱ ሰዓት ፡ (ዲድ ፡ ፬ና ፡ ፮። ፈ ፡ መ ፡ ፮ ፡ ፲፫። ቀሌ)። በመሥገርት ፈንታ ንስሓ ይላል ፡ (ምሳ፳ ፡ ፳፭)።
ንስኀት ፡ ክርፋት ፥ ቅርናት፤ ግማት ክፉ ሽታ የሚጐፈንን የሚያሰቅቅ። እሬኢ ንስኀተ ሥጋየ ከመ ብኅባኄ አንበሳ። ወየዐርግ ንስኀቱ ፡ (ኢዮ፮ ፡ ፯። ዮኤ፪ ፡ ፳)።
ንስራኒ ፡ (ዐረ ንጽራኒ። ዕብ ኖጽሪ) ክርስቲያናዊ በናዝ(ጽ) ራዊው መሲሕ በየሱስ ያመነ፤ ናዝሬትን እይ። ንስራኒ ኮነ ስምዐ ፡ (አዋል)። በንስር ዘይቤ ሲፈቱት ግን ንስራዊ ዘንስር ያሰኛል።
ንስር ፡ (ብ አንስርት። ዕብ ኔሼር። ሱር ኒሽራ። ዐረ ኒስር) በቁሙ፤ ታላቅ ነጣቂ አሞራ ርቆ መጥቆ የሚኼድ፤ ዐይነ ጥሩ። ዮሐንስ በራሪ ንጉሠ አዕዋፍ ንስር። ኦ ንስር ዘእሙር በብርሃነ አዕይንቲከ ፣ ዝኩአ ንስር ዐቢይ። ንስር ኔኪፉር ፡ (ስንክ ፡ የካ፴። ተረ ፡ ባሮ። ሕዝ፲፯ ፡ ፫። ማር ፡ ይሥ። ማቴ፳፬ ፡ ፳፰)።
ንስቀት ፡ መግጠም ማጋጠም፤ የከንፈር የጠርዝ።
ንሥተት ፡ መፍረስ፤ ማፍረስ ፥ አፈራረስ፤ ፍርሻ ፥ ፍራሽ። እስከ ንሥተተ መቅደስ ዳግም። ንሥተተ ሥርዐተ ሰብሳብ። ንሥተተ ዚኣሁ ፡ (ዮሴፍ። ጥበ፲፬ ፡ ፳፮። ማር ፡ ይሥ፲፪ ፡ ፪)።
ንስቲት ፡ መፍረስ፤ ማፍረስ ፥ አፈራረስ፤ ፍርሻ ፥ ፍራሽ። እስከ ንሥተተ መቅደስ ዳግም። ንሥተተ ሥርዐተ ሰብሳብ። ንሥተተ ዚኣሁ ፡ (ዮሴፍ። ጥበ፲፬ ፡ ፳፮። ማር ፡ ይሥ፲፪ ፡ ፪)።
ንስኑስ ፡ የተነሰነሰ፤ የተረጨ በት። መዐዛ ጽጌ ውስቴታ ንስኑስ ፡ (ድጓ)።
ንሥአት ፡ መንሣት ፥ መነሣት፤ አነሣሥ አቀባበል ቅበላ። ቦ እለ ይብሉ ከመ ይከውን ንሥአተ መንፈሰ ሕይወት ውስተ ሥጋሆሙ ለሕፃት እምንፍኀት መንፈሱ ለእግዚ። ንሥአተ ቅዱስ ምስጢር ፡ (መጽ ፡ ምስ። ቅዳ ፡ ሐዋ። ዮሐ)።
ንስከት ፡ መንከስ፤ መነከስ አነካከስ ፥ ንክሻ። ኀልቁ በንስከተ አራዊት ምድር። ንስከተ አንበጣ ወጽንጽንያ። መካነ ንስከት ፡ (ጥበ፲፮ ፡ ፭ ፡ ፱። መ ፡ ፈ)።
ንቁህ ፡ (ሃን ሃት ቅህት) የነቃ ንቁ፤ ትጉህ ልባም አስተዋይ። ውእቱ እንዘ ንቁህ። አነ ንዉም ወልብየ ንቅህት። ይኩና አዕይንቲከ ንቁሃተ። ልቡ ንቁህ ለርእየ ኀጣይእ። ንቁሃነ ኩኑ ወኢትትሀከዩ ለንስሓ ፡ (ቄድሮ። ማሕ፭ ፡ ፪። ፪ዜና ፡ ፮። ፊልክ ፡ ፻፴፭። ቀሌ)።
ንቁር ፡ (ራን ራት ቍርት) የወጣ የጠፋ ፥ የፈረጠ የፈሰሰ። ዘንቁር ዐይኑ። ንቁረ ዐይን ወምቱረ እዝን ፡ (ቀኖና። አዋል)።
ንቁብ ፡ (ባን ባት ቅብት) የተበሳ የተነደለ፤ ብስ ነዳላ ፥ ፍልፍል ሽንቍር። የተሰፋ ስፍ፤ ሰፊ እንቅብ አፍ።
ንቁዕ ፡ (ዓን ዓት ቅዕት) የነቃ ንቅ ሥንጥቅ፤ ምንጫም ውሃማ። ጸድፍ ብሔሩ ወንቁዕ ምድሩ እምነ ማያት ፡ (ሄርማ)። በንቁዝ ፈንታ ንቁዕ ይላል፤ የጣፊ ስሕተት ነው። ዕፅ ንቁዕ ወጽንጹን ፡ (ኩፋ ፡ ፳፩)።
ንቁዝ ፡ (ዛን ዛት ቅዝት) የነቀዘ የጠነጠነ የሻገተ ሻጋታ። ዘይዘርዕ። ሥርናየ ንቁዘ። ወኅብስት ሥንቆሙኒ ይቡስ ወንቁዝ ፡ (አረጋ። ኢያ፱ ፡ ፭)።
ንቁጽ ፡ (ጻን ጻት ቅጽት) በቁሙ፤ የደረቀ ደረቅ፤ ሕጹጽ። ንቁጸ ወሕሩጸ ይለውሱ በመዓር። ዘይምህክ አውሥኦ ቃል ንቁጽ ማእምር ፡ (መ ፡ ፈ። ምሳ፲፯ ፡ ፳፯)።
ንቁፍ ፡ (ፋን ፋት ቅፍት) በቁሙ ፥ የተነቀፈ ነውረኛ ስዱብ፤ የተላጠ የተመለጠ። ወትሬስዮሙ ንቁፋነ ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፵፫ ፡ ፲፫)።
ንቃህ ፡ ዝኒ ከማሁ። ከመ ዘንቃህ እምንዋም ፡ (መዝ ፡ ፸፪ና ፡ ፸፯)።
ንቃው ፡ ጩኸት ጥሪ፤ ታላቅ ድምጥ። ንቃወ አዕዋፍ ወአራዊት። ንቃወ አፍራስ። ንቃወ ዜማ ንህብ ፡ (መቃ ፡ ገ፳፪። ቀሌ። ስንክ ፡ ሚያ፻፲፯)።
ንቄባ ፡ (ዕብራ) ንቅብት፤ ሴት እንስት፤ ቄብ። ነቃቢት ፥ የምትሰፋ የምትታታ።
ንቅሀት ፡ መንቃት አነቃቅ፤ ንቃት ትጋት፤ ንቅነት። ኑኀ ንቅሀትከ ወኢሰኪቦትከ። እምድኅረ ንቅሀተ ሌሊት። ሀሉ ወትረ በንቅሀት ወተዐቅቦ እንዘ ትጸንሕ ምጽአተ ቀትል። ይቁሙ ውስተ ቤተ ክርስቲያን በህድአት ወበንጽሕ ወበንቅሀት ዐቢይ ለሰሚዐ ነገረ እግዚ ፡ (ፈላስ። ዮዲ ፡ ፲፪ ፡ ፭። አፈ ፡ ተ፭። ፍ ፡ ነ ፡ ፲፪)።
ንቅበት ፡ (ታት። ዐረ ኑቅበት) የሥራ ልብስ፤ ዐጭር ቀሚስ ጌጥነት ያለው። ድግ መቀነት ዝናር የሴቶች ሥራ፤ እንደ ወንፊት የተበሳሳ ትት ዘርፋም። ባለብሉዮች ግን ጁኅ ጀባ ይሉታል። ሰንዱናተ ገብረት ወጸገወቶ ለምታ ወንቅበታተ ለከነናውያን ፡ (ምሳ፳፱ ፡ ፵፪። ዲድ ፡ ፫)። ዕብራይስጡ ግን ስንዱነ ትገብር ወትሠይጥ ፥ ወመቅነተ ትሁብ ለከነዓናዊ ይላል፤ ለነጋዴ ማለት ነው ፡ (ምሳ፴፩ ፡ ፳፬)።
ንቅዐት ፡ (ታት። ዕብ ንቂቅ) መንቃት መሠንጠቅ ፥ አነቃቅ፤ ንቃቃት ነቅ ፥ ሠንጣቃ ሥንጥቅ። ንቅዐተ ምድር ዕሙቅ። ንቅዐታተ ኰኵሕ። ለእመ ቦ ንቅዐት ውስተ ኅብስት። ዝንቱ ንቅዐት ፡ (ሔኖ፲፰ ፡ ፲፩። ኢሳ፪ ፡ ፲፱። ቄድር። ስንክ ፡ ግን፳፰)። ነቅዐና ንቅዐት ከነቅሀና ከንቅሀት ጋራ ባማርኛ እንዲተባበሩ በምስጢርም ይጎራበታሉ።
ንቅወት ፡ መጮኽ ፥ አጯጯኽ ጩኸት። ጊዜ ንቅወት ዶርሆ ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፫)።
ንቅው ፡ (ዋን ዋት ቁት፤ ቅውት) የጮኸ ጯኺ፤ የተጮኸ፤ የተጮኸበት።
ንቅጥቁጥ ፡ የሚንቀጠቀጥ፤ ተንቀጥቃጭ፤ ቀጥቃጣ፤ እንቅጥቅጣም ፡ (ገድ ፡ አዳ)።
ንቅጸት ፡ መድረቅ፤ ድርቅና ፥ ሕጸጽ።
ንቅፈት ፡ መንቀፍ፤ መነቀፍ፤ አነቃቀፍ፤ ነቀፋ ነቀፌታ። ሰቈራር ወንቅፈት ወግማኔ። ምእመን ወጠቢብ ዘርሑቅ እምንቅፈት ወድኁን እምነውር ፡ (ኩፋ ፡ ፴፫። ፍ ፡ ነ ፡ ፵፫ ፡ ፩)።
ንቆት ታ ኒቆታ ፡ (ጽር ኔኾታ። ዕብ ንኮት) ጥሩ ሽቱ የነጠረ የተጣፈጠ፤ ከቅባታም ዕንጨት የሚወጣ፤ ወይም የሽቱ ቅመም የጢስ ዕንጨት የነከተ ነካታ ደቃቅ፤ ንቁት የነቀተ። የሐኪም መድኀኒት፤ እንደ ሽቱ የተቀመመ ፥ የተበጀ የተዘጋጀ፤ የኖረ ድልብ ፥ የቈየ የዘገየ መዝገብ። ባለብሉዮች ግን የቃ ቤት የሥዕል ቤት ይሉታል። ወአርአዮሙ ቤተ ኒቆታሁ ፡ (፬ነገ ፡ ፳ ፡ ፲፫። ኢሳ፴፱ ፡ ፪)።
ንበት ፡ መንበብ፤ መነበብ፤ አነባበብ፤ ንባብ። ጽንዐ ንበቱ፤ ተሊወ ንበቱ። በመትልወ ንበቱ ፡ (መቅ ፡ ወን። ሄርማ)።
ንቡረ እድ ፡ እጁን የጫነ ያኖረ፤ ወይም እጅ የተጫነበት ፥ በሹመትና በቡራኬ ጊዜ። ያኵስምን አለቃ ነብሪድ ማለት ከዚህ ወጥቷል፤ በአንብሮተ እድ የተሾመና የሚሾም ጳጳስ ሊቀ ጳጳስ ማለት ነው። ኦ አበዊነ ንቡራነ እድ ሥዩማን እለ መትልዋነ ሐዋርያት ፡ (ቅዳ ፡ ሕር)።
ንቡር ፡ (ራን ራት ብርት) ያለ የኖረ የነበረ፤ የተቀመጠ ቅምጥ፤ ጽሑፍ። ትዜኀር ንቡረከ ውስተ ቤትከ። ልማድ ንብርት። ዘንቡር ውስተ ዝንቱ አንቀጽ ፡ (፬ነገ ፡ ፲፬ ፡ ፲። መቅ ፡ ወን። ፍ ፡ ነ ፡ ፴፯)።
ንቡብ [1] ፡ (ባን ባት ብብት) የነበበ ፥ የተነበበ የተነገረ።
[2] ፡ (ዕብ ናቡብ) ውስጠ ክፍት፤ ባዶ ፍልፍል፤ የሚነፋና የሚመታ ንዋየ ማሕሌት፤ እንቢልታ ዋሽንት ፥ ቱልቱላ ቀንደ መለከት፤ ከበሮ ነጋሪት።
ንቡይ ፡ (ያን ያት ቢት) የተተነባ፤ የተነገረ ንግር።
ንባብ ፡ በቁሙ፤ ነገር ቃል፤ ጩኸት። ንባብኪ አዳም። ንባበ እግዚ። ተወከፍ ንባበ ዚኣየ በአብዝኆ ንባቦሙ ፡ (ማሕ፬ ፡ ፫። ኩፋ ፡ ፰። ምሳ፬ ፡ ፲፫። ማቴ፮ ፡ ፯)። በፍጻሜ ፈንታ ንባብ ይላል ፡ (መክ፲፪ ፡ ፲፫)።
ንቤ ፡ እንላለን፤–ቤልነ ብህልነ።
ንብረት ፡ በቁሙ፤ መኖር መቀመጥ አቀማመጥ፤ ኗሪነት አናዎር ፥ ኑሮ። ኀላፊ ውእቱ ንብረተ ዝ ዓለም። ንብረተ ከዋክብት። ንብረተ ነፍስየ ወሥጋየ በእዴሁ እኁዝ። እምንብረቱ ላዕለ መንበር። ንብረት መናቅዕትኪ። ናሁ ንብረታ ለዛቲ ሀገር ሠናይት ፡ (፩ቆሮ ፡ ፯ ፡ ፳፱። ጥበ፯ ፡ ፲፱። ስንክ ፡ ኅዳ፮። ፊልክ ፡ ፲፭። ማሕ፯ ፡ ፪። ፬ነገ ፡ ፪ ፡ ፲፱)።
ንብቲራ ፡ (ጽር ኒፒቲር) የማጠቢያና የመታጠቢያ ዕቃ፤ ለገን ዋዲያት ኵስኵስት፤ ሰንና ብርት። ንብቲራ ዘውስቴታ ማይ ፡ (ዮሐ፲፫ ፡ ፭። ፊልክ ፡ ፻፳፱። ፍ ፡ ነ ፡ ፲፬። ስንክ ፡ ሐም፰)።
ንቱር [ [ ፡ (ላቲን ናቱር ራ፤ ባሕርይ ጠባይ ፥ ፍጥረት) የነተረ የኈረጠ፤ ጥሩ ብርቱ።
ንቱግ ፡ (ጋን ጋት ትግት) ያነሰ የጐደለ፤ ጐደሎ ሕጹጽ። ኢንቱግ ወኢብዑድ እምህላዌሁ። ደለወከ እግዚ ወረከበከ ሕጹጸ ወንቱገ። ኩኑ ምሉኣነ ወአኮ ንቱጋነ ፡ (መጽ ፡ ምስ። ዮሴፍ። ግንዘ)።
ንቱፍ ፡ (ፋን ፋት ትፍት) የነተበ ንትብ፤ የተነጨ የተበጨቀ፤ ቍርጥርጥ ብጥስጥስ።
ንታፌ ፡ ዝኒ ከማሁ። ወንታፌ ሎቱ። ብዕል ይትሀጐል በንታፌ እኩይ ፡ (መክ፪ ፡ ፳፫። ፭ ፡ ፲፫)።
ንትገት ፡ ማነስ መጕደል፤ አጐዳደል ጕድለት ጐደሎነት፤ ሕጸጽ ጕዳይ ፡ (ሲኖዶ)።
ንትግ ንትጋ ፡ (ብ ንትጋት) ሕጸጽ ጕዳይ ፥ ቅሬታ። ከመ ይምላእ ስብሐቲሁ ውስተ ንትገ ዚኣከ። ወልድ መላኤ ንትጋ። አፍቅርኒ እንበለ ንትጋ። ንትጋት ፡ (መቃ ፡ ገ፳፫። ጥበ ፡ ጠቢ። ደራሲ። ፊልክ። ፪ቆሮ ፡ ፰ ፡ ፲፬)።
ንትፈት ፡ መንጨት፤ መነጨት፤ አነጫጭ አቈራረጥ፤ ቈረጣ ብጠሳ፤ ንጥቂያ ቅሚያ፤ ንጭታት። ንትፈተ ሥጋሁ በኀጺን ፡ (ስንክ ፡ መጋ፮)።
ንዑልት ፡ (ትግ ሐባ ነዕልት። ዕብ ይባማ፤ ይቤሜት፤ ምራት) የተጫማች ባለጫማ፤ ጫማ የምትፈታ የምታወልቅ፤ አይት፤ የወንድም ሚስት ዋርሳ፤ ባሏ ሳይወልድላት ቢሞት ወንድሙ የቅርብ ዘመዱ የሚወርሳት። አልወርስም ቢላት ግን በኦሪቱ ሥርዐት ጫማውን ከግሩ ታወልቅበታለች ፥ በፊቱም ትተፋበታለች፤ ንዑልት ያሰኛት ይህ ጫማ ማውለቅ ነው። ይቤሎ ይሁዳ ለአውናን ወልዱ፤ ባእ ኀበ ብእሲተ እኁከ ወረስያ ንዑልተከ ወአንሥእ ዘርዐ ለእኁከ ፡ (ኩፋ ፡ ፵፩። ዘዳ፳፭ ፡ ፭–፲። ሩት፬ ፡ ፯ ፡ ፰)።
ንኡስ ፡ (ሳን ሳት እስት) ያነሰ፤ ታናሽ ትንሽ። ሕፃን ንኡስ። ቈናጽል ንኡሳን። ንኡሳት መበለታት። ነያ ድንግል ንእስት በአካል ፡ (ኢሳ፲፩ ፡ ፰። ማሕ፪ ፡ ፲፭። ዲድ ፡ ፲፬። ድጓ)። በዐረብ ግን እኩሌታ መንፈቅ ማለት ነው።
ንኡድ ፡ (ዳን ዳት፤ እድ ድት) የከበረ ምስጉን፤ ድንቅ።
ንኢስ ሶት ፡ (ንእሰ ይንእስ ይንአስ። አኒስ አነሰ) ማነስ መጕደል ፥ ትንሽ መኾን። ዘይንእስ ብርሃን። ዘይንእሶ የዐብዮ። ንእሰት መንፈስነ። ኵላ እኪት ትንእስ እምእኪት ብእሲት ፡ (ዘፍ፩ ፡ ፲፮። ማቴ፲፩ ፡ ፲፩። ሔኖ። ሢራ፳፭ ፡ ፳፮)። በንእሰ ፈንታ ተንእሰ ይላል፤ ስሕተት ነው። እለ ይትነአሱ ፡ (፬ነገ ፡ ፲፰ ፡ ፳፬)። አሂስን እይ፤ የዚህ ጎር ነው።
ንኢድ ዶት ፡ (ንእደ ይንእድ ይንአድ። ዐረ፤ ነሀደ) ማክበር ማመስገን፤ ማላቅ ማድነቅ፤ ከፍ ከፍ ማድረግ። ለሊከ ትንእድ ርእሰከ። ይንእዱ ርእሶሙ ከመ ጠቢባን እሙንቱ። ርቱዕሰ ንንአዶሙ ለእልክቱ። ለነዳይ ይንእድዎ በጥበቢሁ ፡ (ዮሐ፰ ፡ ፲፫። ሄርማ ፡ ገ፺፱። አፈ ፡ ተ፪። ሢራ፲ ፡ ፴)። በንእደ ፈንታ አንአደ ይላል፤ ስሕተት ነው። አኮ በአንአዶ አቡከ ፡ (፩ዜና ፡ ፲፱ ፡ ፫)።
ንኤጼል ፡ (ዕብ ኔእጻል) ተለየ፤ ልዩ ኾነ፤ በሥራ በልክ ፡ (ሕዝ፵፪ ፡ ፮)።
ንዕሰ ፡ አነሰ፤–ንኢስ ንእሰ።
ንእስ ንእስና ፡ ማነስ፤ ታናሽነት ሕፃንነት ጕልማስነት። እምንእስየ እስከ ይእዜ። ኀጢአተ ንእስየ። ብእሲተ ንእስከ ፡ (መዝ ፡ ፸። ኢዮ፲፫ ፡ ፳፯። ምሳ፭ ፡ ፲፰። ስንክ ፡ ጥር፲፭)።
ንእከ ፡ (ዕብ አናሕ፤ ናአቅ) አናኽ አቃሰተ፤ ጮኸ ተንሰቀሰቀ፤ ከሩጫ ከሸክም ከደዌ ከሥቃይ ከሐዘን ከብካይ የተነሣ። ንህከን እይ፤ የዚህ መንቲያ ነው። ይንእኩ ዲቤክሙ ፡ (ሔኖ፺፮ ፡ ፪)።
ንዕወት ፡ ማደን፤ መታደን፤ አስተዳደን ፥ ዕደና ፥ ዐደን። አራዊት መሣጥያን እለ ኢይሤንዩ ለንዕወት። መካነ ንዕወት። ዘይሜህር ንዕወተ፤ አው ቀትለ ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፴፫ ፡ ፬። ፵፯። ቈስጠ)።
ንዕው ፡ (ዋን ዋት ዑት፤ ዕውት) የታደነ ፥ የተያዘ፤ ዕድን።
ንዕደ ፡ አከበረ፤–ንኢድ ንእደ።
ንእደት ፡ መክበር ፥ ማክበር ማመስገን፤ ክብር ምስጋና። ኀሢሦ ክብረ ወንእደተ በእንተ ንጽሑ ፡ (ቀኖ ፡ ስርድ ፡ ፲፩)።
ንኩር ፡ (ራን ራት ክርት) የተነከረ፤ ልዩ ድንቅ ፥ ውብ ምስጉን። ወንኩር ሥነ ላሕያ፤ ብርሃን ንኩር። ንክርት ክብር ፡ (ዮሴፍ። ቄር ጰላ)።
ንኩይ ፡ የተነካ ንክ፤ ስባራ ዐንካሳ ጐደሎ ፡ (ፊልክ)።
ንካይ ፡ ንኪት ፥ ጕዳት፤ ስብራት። እምንካይ ወእምበቍዔት ፡ (ፊልክ ፡ ፻፸፪)።
ንክኑክ ፡ የተናጋ፤ የተነቃነቀ።
ንክናኬ ፡ (ላ ጥ ነ) መነቅነቅ፤ አነቃነቅ ፥ ንቅነቃ፤ ውዝወዛ። አዕማድ እለ ኢይጸንኑ በንክናኬ ፡ (መጽ ፡ ምስ)።
ንክየት ፡ መንካት ፥ መነካት፤ አነካክ፤ ንኪት ጕዳት ጥፋት። ዘእንበለ ንክየት እመንገሌሁ። ዘያመጽእ ንክየተ ካልኡ። ዘወደየ እሳተ ውስተ ሀገር አው በሐቅል እንዘ የኀሥሥ ንክየተ ሰብአ ዚኣሃ ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፴፭። ፴፯። ፶ ፡ ፮)።
ንክፈት ፡ ነቀፋ ፥ ንቅፈት ፡ ነቀፈ።
ንዋም ፡ እንቅልፍ ፥ ሽልብታ ፥ መኝታ፤ ሞት ፥ ፍጹም ዕረፍት። አንቅሆ ፥ እምዐቢይ ንዋም ለዘይነውም። ንዋመ ሞት። ይቤ ጠቢብ ሞት ንዋም ነዊኅ፤ ወንዋምሰ ሞት ኅዳጥ ፡ (ሢራ፳፪ ፡ ፯። ዮሐ፲፩ ፡ ፫። ግንዘ)።
ንዋየ ለብሓ ፡ ሸክላ ፥ የሸክላ ዐይነት ዕቃ የሚሰበር። ንዋየ ማእስ ፥ ንዋየ ዕፅ ቢል፤ ከቈርበት ከንጨት የተሠራ ማለት ነው። ንዋየ ተውኔት ፥ ንዋየ ማሕሌት ቢል ግን፤ የዘፈን ዕቃ ፥ ለዘፈን ተብሎ የተሠራ እያሰኘ ባለቤትነትን ያሳያል።
ንዋየ ወርቅ ፡ የወርቅ ገንዘብ ፥ ወይም መሣሪያ።
ንዋየ ውስጥ ፡ የሆድ ዕቃ፤ አንዠት ጕበት ጨጓራ ፥ ሌላውም ኹሉ።
ንዋየ ሐቅል ፡ የበዳ ጸብት ፥ የሰልፍ ዕቃ መሣሪያ።
ንዋየ ጐሜእ ፡ የሸንበቆ ታንኳ ፥ ፍልኳ ፡ (ኢሳ፲፰ ፡ ፪)።
ንዋይ ፡ (ብ ንዋያት። ዕብ ኖይ፤ ርሱይ ስርግው) በቁሙ ፥ ገንዘብ ጥሪት ቅርስ ፥ ወርቅ ብር ከብት። ንዋየ ዝ ዓለም። ንዋየ ልቃሕ። ንዋየ ማሕፀንት ፡ (ማቴ፮ ፡ ፳፬። ሢራ፳፩ ፡ ፰። ፵፩ ፡ ፲፱)።
፡ የቤት ዕቃ ፥ መሣሪያ ከሣር ከንጨት ከማዕደን ከብረት ከጭቃ ከቈርበት ከሌላውም ኹሉ የማሠራ፤ በየስሙና በያይነቱ መልክ ጌጥ ያለው። ንዋይ ኅሩይ። ንዋየ ቤተ እግዚ። ንዋየ ማእድ ፡ (ግብ፱ ፡ ፲፭። ዳን፩ ፡ ፪። ስንክ ፡ ግን፲፯)።
ንዉር ፡ (ራን ራት ውርት) የተነወረ ፥ የተነቀፈ፤ ነውረኛ ፥ ነውራም። ማእደ እግዚ ንዉር ውእቱ ፡ (ሚል፩ ፡ ፯ ፡ ፲፪)።
ንዉም ፡ (ማን ማት ውምት) የተኛ ፥ እንቅልፍ የወሰደው፤ ያረፈ የሞተ ምዉት ፡ (ማሕ፭ ፡ ፪። ፩ተሰ ፡ ፭ ፡ ፲። ፊልክ ፡ ፺፰)። እስመ ሰብአ አይሁድ ኮኑ ንዉማነ በእንተ ድካሞሙ ወረኃቦሙ ፡ (ዮሴፍ)።
ንዙህ ፡ (ሃን ሃት ዝህት) የተነዛ የተረጨ፤ የተረጨበት። ልብስ ዘንዙህ በደም ፡ (ራእ፲፱ ፡ ፲፫። አፈ ፡ ድ፲፮። ቅዳ ፡ ግሩ)።
ንዝሀት ፡ መርጨት፤ መረጨት ፥ አረማጭ። ንዝሀተ ደም ፡ (ዕብ፲፪ ፡ ፳፬። ፩ጴጥ ፡ ፩ ፡ ፪። ዲድ ፡ ፩)። በቁሙ ፥ ንዛት ፩ ጊዜ የሚረጭ የሚበተን።
ንዝህላል ፡ ዞላነት፤ ንዝህላልነት፤ አለል ዘለልታ፤ ዝሙት፤ ትዕቢት ክፋት። ሀኬት ወንዝህላል። ንዝህላል ወትዝኅርት። ኢይሑራ ውስተ ሐውዘ መባልዕት ወንዝህላል። እለ ወድቁ ውስተ ንዝህላል። ናሁ ተበየነ ንዝህላልከ ፡ (አፈ ፡ ድ፴፪። ፊልክ ፡ ፭። ዲድ ፡ ፲፬። ቄር ፡ ጰላ። ዮሴፍ)። በንዝህላል ፈንታ ነዘህላል ይላል፤ ፍችው አንድ ነው። ነዘህላለ ፍትወት ያፈልስ ልበ የዋሃን ፡ (ጥበ፬ ፡ ፲፪)።
ንደት ፡ መንደድ ፥ መናደድ ፥ መቃጠል፤ መቈጣት፤ ቍጣ ብስጭት። ከመ ንደተ እሳት። ይቈርር ዘውስተ ልቡ ንደት ፡ (ዘፀ፳፬ ፡ ፲፯። ዮሴፍ)።
ንዱል ፡ (ላን ላት ድልት) የተነደለ፤ ብስ ነዳላ ሽንቍር።
ንዱቅ ፡ (ቃን ቃት ድቅት) የተነደቀ ፥ የተገነባ ግንብ። እንበለ ንዱቅ ቤት ወእንበለ ሕኑጽ ማኅደር ፡ (ስንክ ፡ የካ፳፰። ዘኍ፳፩ ፡ ፳)።
ንዱእ ፡ (ኣን ኣት ድእት) የተነዳ ንድ፤ ተነጅ ፥ ተነድቶ ኸያጅ።
ንዱይ ፡ (ዲት ድይት) የደኸየ ፥ የተቸገረ ችጉር ወራዳ። ኮነ ንዱየ በእገንተ ዝ ብዕልነ። ንዱይ ወድኩም ሥርዐት ፡ (ቄር)።
ንዱድ ፡ (ዳን ዲት ድድት) የነደደ የተቃጠለ፤ ሙቅ ትኩስ፤ ቍጡ ተናዳጅ። ኩን ንዱደ በእሳተ መንፈስ ከመ ታውዕያ ለፍትወት እኪት። ንዱዳነ ልብ ፡ (አፈ ፡ ተ፲፩። ፩ጢሞ ፡ ፬ ፡ ፪)።
ንዱፍ ፡ (ፋን ፋት ድፍት) የተነደፈ ንድፍ፤ የተወጋ ውግ። ንዱፍ በሐጽ። ንድፍት አነ በፍቅሩ ፡ (ስንክ ፡ ጥር፳፭። ማሕ፭ ፡ ፰)።
ንዳድ ፡ በቁሙ፤ ወባ አሶ የቈላ በሽታ የሚያሞቅ የሚያተኵስ፤ አሰወን እይ። ሕማመ ንዳድ ፡ (መ ፡ ፈ)።
ንድለት ፡ (ታት) መንደል ፥ መነደል ፥ አነዳደል ንድሎሽ። ዋሻ ፍርኵታ፤ ሠንጣቃ ብስ ነዳላ ፪ ደጃፍ ያለው ፥ እንደ ዋልድባው ደብር እንደ ሰቋር ያለ። ንድለታተ ምድር ወንቅዐታተ ኰኵሕ ፡ (ሔኖ፺፮ ፡ ፪)።
ንድቀት ፡ መን(ነ) ደቅ፤ አሠራር አነዳደቅ ንድቂያ። ንድቀት ወመጋብርት ለማኅደር ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፳፰)።
ንድቅ ፡ (ቃት) በቁሙ፤ በመሠረት ላይ የሚሠራ ሥራ ግንብ ናስ፤ የቤት የቅጥር። አሚንሰ መሠረት ይእቲ ወካልኣኒሃ ሕንጻ ወንድቅ። ይትሐነጽ ቤተ እግዚ በንድቅ ክቡር። ንድቁ ወእበኒሁ። ከመ ንድቀ ክረምት። ንድቅ ጽኑዕ ዘቦቱ ቅጽር። ንድቀ ማኅፈድ ፡ (አፈ ፡ ወር። ጦቢ፲፬ ፡ ፭። ማር፲፫ ፡ ፩። ሢራ፳፩ ፡ ፰። መቃ ፡ ገ፳፬። ዮሴፍ)።
ንድአት ፡ መንዳት ፥ መነዳት ፥ አነዳድ፤ ነድቶ መውሰድ ተነድቶ መኼድ።
ንድየት ንዴት ፡ መደኽየት፤ ድኽነት ችጋር ዕጦት፤ ኀሳር ውርደት። ኢተሀበኒ ብዕለ ወንዴተ። ምንት ውእቱ ንዴት ዘእንበለ ከዊነ ሰብእ። ንዴተሰ ወትሕትና አንቲኣሁ ንብል በተሰምዮ ሐዋርያ ወሊቀ ካህናት።
ንድፈት ፡ መንደፍ ፥ መነደፍ ፥ አነዳደፍ አወጋግ፤ ነደፋ ውጊያ። ውግታት፤ ቍስል። ሐመ ፈድፋደ እምንድፈት። ሀለወ ይትፌወስ ንድፈቶ ኀበ ነደፍዎ ሶርያ ፡ (፩ነገ ፡ ፴፩ ፡ ፫። ፬ነገ ፡ ፱ ፡ ፲፮)።
ንድፍት ፡ የበቅሎ በሽታ ፥ ቶሎ የሚገድል።
ንጉሣዊ ፡ (ዊት ውያን ያት) መለካዊ፤ የንጉሥ። ግብር ንጉሣዊ። አርኣያ ንጉሣዊ። ንጉሣውያን ፡ (አፈ ፡ ድ፳፮። ፍ ፡ ነ ፡ ፱። መጽ ፡ ምስ)።
ንጉሥ ፡ (ሣን ሣት ግሥት፤ ታት) ዝኒ ከማሁ፤ በቁሙ ሐፄ ባለዘውድ። ሹም ፥ አለቃ። ንጉሥ ዐቢይ። ንጉሠ ነገሥት ፡ (ኢሳ፴፮ ፡ ፲፫። ዳን፪ ፡ ፵፯)። እስመ ዘሤሞ ንጉሥ ንጉሥ ውእቱ። ሄሮድስ ንጉሠ ገሊላ።
ንጉር ፡ (ራን ራት ግርት) የተነገረ ፥ የተወራ የተባለ ንግር። ማርያም ንግርት በነቢያት ፡ (መቅ ፡ ታም)።
ንጉፍ ፡ (ፋን ፋት ግፍት) የተነገፈ ፥ የረገፈ፤ የወደቀ። ንጉፈ ለይኩን። ከመ ጽጌ ንጉፍ ፡ (ነሐ፭ ፡ ፲፫። ስንክ ፡ ጥቅ፲፪)። ንእስ ውርዙት በማለት ፈንታ ንጉፋን ይላል ፡ (መዝ ፡ ፻፳፮)።
ንጋፍ ፡ (ፋት) ርጋፊ፤ ትቢያ ብናኝ ጕድፍ። ንጋፍ ዘያመጽኦ ነፋስ ፡ (ኢሳ፳፱ ፡ ፭)።
ንግማጢስጤ ፡ (ጽር ኤኒግማቲስቴ። ዕብ ሞሽሊም) መሐደምት፤ ተራቾች ተረተኞች ባለምሳሌዎች ፡ (ዘኍ፳፩ ፡ ፳፯)። ባለብሉይና ባለቅኔ ወግ ታሪክ ይሉታል።
ንግሥ ፡ መንገሥ ፥ አነጋገሥ፤ ንጉሥነት ፥ መንግሥት። ዜና ንግሡ ላዕለ ዮናናውያን። ወኮነ ንግሡ ለኢዮሳፍጥ በሰላም። መኑ የአምር በዝንቱ መዋዕል ንግሠኪ። በእንተ ኵሉ ንግሡ ለዳዊት። ሶበ ጸንዐ ንግሡ ፡ (ዮሴፍ። ፪ዜና ፡ ፳ ፡ ፴። አስቴ፬ ፡ ፲፬። ፩ዜና ፡ ፳፱ ፡ ፴። ዮሴፍ)።
ንግሥት ፡ በቁሙ፤ ባባቷ ፈንታ የነገሠች፤ እንደ ማክዳና እንደ ህንደኬ እንደ፤ ዘውዲቱና እንደ ቢክቶርያ ያለች ባለሙሉ ሥልጣን። ንግሥተ ሣባእ። ንግሥተ ኢትዮጵያ። ንግሥታተ ፋርስ ፡ (፫ነገ ፡ ፲ ፡ ፩። ግብ፰ ፡ ፳፯። መቃ ፡ ገ፲፩)።
፡ የንጉሥ ሚስት እተጌ ፥ ባሏ ከርሱ ጋራ ያነገሣት። እሌኒ ንግሥት። አስጢን ንግሥት። ንግሥታት ወዕቁባት። ወትቀውም ንግሥት በየማንከ ፡ (ድጓ። አስቴ፩ ፡ ፱። ማሕ፮ ፡ ፰። መዝ ፡ ፵፬)።
ንግደት ፡ መኼድ፤ መነገድ፤ እንግድነት። ንግደትከ ወእትወትከ። ንግደተ ኢየሩሳሌም። ወይኩን ንግደቱ ኀቤከ ዘእንበለ ፍርሀት ፡ (መዝ ፡ ፻፳። ገድ ፡ ተክ። ግንዘ)።
ንግድ ፡ በቁሙ፤ የገበያ ሥራ ፥ ገበያ። ለእመ ሖረ ውስተ ንግድ፤ አው ውስተ ብሔር ርሑቅ ፡ (ፈ ፡ መ ፡ ፲፫። ስንክ። የካ፯)።
ንግድና ፡ ንግድ፤ ነጋዴነት፤ እንግድነት ፡ (ፊልክ ፡ ፻፶፱)።
ንጡፍ ፡ (ፋን ፋት ጥፍት) ምኩር ፍቱን፤ የጠራ ጥሩ፤ ጠፍ ያለ። ወርቅ ንጡፍ። ጽሩይ ወንጡፍ እምወርቅ። ወይን ንጡፍ ፡ (ዕዝ፪ ፡ ፷፱። ድጓ። አብጥ ፡ ፪)።
ንጥር ፡ (ራት፤ አንጥር) በቁሙ፤ ንጡር ፥ የነጠረ የተነጠረ፤ የጠራ የበራ የተጠበቀ፤ ወርቅ ብር። ንጥር ቅቤ እንዲሉ። ነሥአ ዲናረ ወርቅ እምንጥረ አበዊሁ ፡ (ስንክ ፡ ታኅ፲)።
፡ ብልጭታ ፥ ብራቅ ነጸብራቅ ፥ ጓታ ፍንዳታ። ንጥር ዘእመብረቀ ስብሐት አይኅአ። ንጥረ እሳት። አንጥረ መባርቅት። ሞቱ በንጥረ መሬት ወሐመድ ፡ (አርጋ። ዮሴፍ። ጦማር። አዋል)። ልጥርን ነጥር ማለት ከዚህ የወጣ ነው።
ንጥበት ፡ መንጠብ፤ ማንጠብ ፥ አነጣጠብ ነጠባ ፥ ንጥቢያ፤ ጠብታ።
ንፁኅ ፡ (ኃን ኃት ፅኅት) የተጣለ፤ ውዱቅ።
ንጹል ፡ (ላን ላት ጽልት) የተነጠለ፤ ልዩ ውልቅ ንቁል።
ንጹር ፡ (ራን ራት ጽርት) የታየ የጐላ ግልጥ።
ንጹይ ፡ (ያን ያት ጺት) የተነጨ የተነጫጨ። ንጹይ ጽሕሙ።
ንጹፍ ፡ (ፋን ፋት ጽፍት) የተነጠፈ የተጐዘጐዘ፤ የተጸፈጸፈ። ቦታውንና ምንጣፋን ኹለቱንም ባንድነት ያሳያል። ፍኖተ ሀካያን ንጹፍ በአሥዋክ። ጽርሕ ንጹፍ ወርሱይ። ምስካብ ንጹፍ። ወንጹፍ ጸፍጸፉ በሕብረ ወርቅ ወብሩር። ውስጡ ንጹፍ በእብነ ሰንፔር ፡ (ምሳ፲፭ ፡ ፲፱። ማር፲፬ ፡ ፲፭። ስንክ ፡ መጋ፰። መቃ ፡ ገ። ማሕ፫ ፡ ፲)።
ንፁፍ ፡ (ፋን ፋት ፅፍት) የነጠፈ የደረቀ፤ ምጥጥ ያለ፤ ደረቅ። ከረዩ ሎሙ ዐዘቅተ ንፁፈ። ዐዘቅት ንፅፍት ፡ (ኤር፪ ፡ ፲፫። ፪ጴጥ ፡ ፪ ፡ ፲፯)።
ንጻል ፡ (ላት) ንጣይ ነጠላ፤ የጸናጽል ሻኵራ አንዳንዲቱ ቅጠል።
ንጻሬ ፡ (ርያት) ማየት ፥ መታየት፤ አስተያየት፤ ንጸራ የዐይን ሥራ። ዘእንበለ ፈቲው በንጻሬ። ሠናየ ንጻሬ። ልደተ ንጻሬ እምዐይን። ንጻሬ አዕይንት ፡ (ፈ ፡ መ ፡ ፲፬ ፡ ፰። አዋል። ያዕ ፡ ዘእል። ደራሲ)።
፡ ዐይን ብሌን፤ የሚያይ ነጻሪ። ንጻሬ ዘይሬኢ እምርሑቅ ተኀትመ። ከሠተ ንጻሬየ። ፈታሒ ይኩን ድኁነ ምስማዕ ወንጻሬ። አልዕል ንጻሬከ ወልበከ ኀበ ሰማይ ፡ (ግንዘ። አፈ ፡ ድ፪። ፍ ፡ ነ ፡ ፵፫ ፡ ፩። ፊልክ ፡ ፻፲)።
ንጻይ ንጼ አው ኖጻ ፡ (ዕብ ኖጻህ) ላባ ጭገር፤ የዶሮ የአዕዋፍ ጠጕር፤ የሚነጭ የሚነቀል። ምሉአ ኖጻ ዘሎቱ ኰሳኵስ። ዘዐቢይ ክነፊሁ ወምሉእ ኖጻቲሁ ፡ (ሕዝ፲፯ ፡ ፫ ፡ ፯)። ኖጻቲሁ ባለው ጽፈሪሁ ይላል፤ የመላሽና የጣፊ ስሕተት ነው።
ንጽሐት ፡ መንጻት ፥ አነጻጽ፤ ንጹሕነት ፥ ንጣት ጥራት። አልቦ ክቡር በኀበ እግዚ ከመ ንጽሐተ ልብ ፡ (ፊልክ ፡ ፲፭)።
ንፅኀት ፡ ተጥሎ መውደቅ፤ መንቃት መሠንጠቅ፤ ወይም ጥሎ መስበር ማድቀቅ፤ ጥሎሽ አጣጣል ፥ ስብራት። ይቀሥፎ ለዐቢይ ቤት በድቀት ወለንኡስ ቤት በንፅኀት ፡ (ዓሞ፮ ፡ ፲፩)።
ንጽሕ ፡ ንጽሕና ፥ ጥራት ጥሩነት፤ ከዝሙት ከርስሐት መራቅ መጠበቅ። ንጽሐ ነፍስ ወአኮ ንጽሐ ሥጋ። ያገብእ ለከ ንጽሐከ። በሃይማኖት ወበንጽሕ ፡ (ቅዳ ፡ ሕር። ኢዮ፳፪ ፡ ፳፭። ፩ጢሞ ፡ ፬ ፡ ፲፪)።
ንጽሕና ፡ በቁሙ፤ ንጹሕነት ንጹሕ መኾን። ይኄይስ ንጽሕና ምስለ ንዴት እምብዕል ምስለ ዝሙት። ናጥሪ እንከ ትሕትና ምስለ ንጽሕና ፡ (ፈላስ። ቅዳ)።
ንጽብሩቅ ፡ (እን) የጠራ፤ የበራ፤ ጽሩይ። ንጽብሩቀ ሥን ፡ (አዋል)።
ንጽየት ፡ መንጨት፤ መነጨት አነጫጭ ፥ ንጭታት።
ንፉኅ ፡ (ኃን ኃት ፍኅት) የተነፋ ያበጠ፤ ዕቡይ ኵሩ። ሥዕለ ነጌያት ዘብርት ንፉኅ። ዕቡየ ዐይን ወንፉኀ ልብ ፡ (ዮሴፍ። መጽ ፡ ምስ)።
ንፉር ፡ (ራን ራት ፍርት) የነፈረ ንፍር፤ ሙቅ ፍል፤ ማየ አይኅ። የተነፈረ ፥ የተቀቀለ ቅቅል፤ ከንፍር ውሃ የገባ።
ንፉቅ ፡ (ቃን ቃት ፍቅት) የተከፈለ ፥ ክፉል፤ ፍሩቅ ሥጡቅ። መንግሥቱ ንፉቅ። እንስሳ ዘንፉቅ ሰኰናሁ ፡ (ዳን፪ ፡ ፵፩። ዘሌ፲፩ ፡ ፫–፯)።
ንፍኀት ፡ መንፋት ፥ መነፋት፤ አነፋፍ ንፋት፤ ንፍፊት ዕብጠት። መንፈስ መተንፈስ፤ እፍ ማለት ፥ እፍታ ትንፋሽ፤ ጸጋ ሀብት። በደኃሪ ንፍኀተ ቀርን። ፈትለ ሣሬት ኢይክል ተዐግሦ ንፍኀተ ነፋስ። ወዓዲ አክበሮ በንፍኀቱ። ተውህቦ ንፍኀተ መንፈስ ቅዱስ። ንፍኀተ እስትንፍሰ አፉሁ። ወነሥአ እመንፈስ ቅዱስ ንፍኀተ ፡ (፩ቆሮ ፡ ፲፭ ፡ ፶፪። አፈ ፡ ተ፴፬ ፡ መቅ ፡ ወን። ቀሌ። አርጋ ፡ ፪። ስንክ ፡ ሐም፯)።
ንፍቀት ፡ መክፈል ፥ መከፈል፤ አከፋፈል ፥ ከፈላ ክፍያ፤ ክፉልነት።
ንፍቃ አው ንፍቅ ፡ ግማሽ አላድ፤ ንኡስ ክፍል መንፈቅ። እመት ወንፍቃ። እምንፍቃሃ ለዲድርክም። እስከ ንፍቀ ሌሊት ፡ (ዘፀ፳፭ ፡ ፲፯። ፴ ፡ ፲፭። ግብ፳ ፡ ፯)። ተወራጅ፤ ምክትል። ንፍቀ(ቅ) ዲያቆን። ንፍቀ(ቅ) ካህን። ንፍቅ ቀሲስ ፡ (ቅዳ)።
ንፍገት ፡ ፤ በቁሙ ሥሥት ቢስነት። ንፍገት ለነዳይ ወውሂብ ለባዕል ፡ (መጽ ፡ ኑዛ)። ደንጸወንና ቄቀየን መትሀን እይ።
ኖኀ ፡ ረዘመ በዛ፤–ነዊኅ ኆት።
ኖኅ ፡ (ዘፍ፭ ፡ ፳፱) የሰው ስም ፥ ወልደ ላሜኽ፤ ዕረፍት ፥ ተረፍ። ርሱ ከነልጆቹ ከሰብአ ትካት መከራና ጥፋት የሚያርፍ የሚተርፍ ስለ ኾነ ፥ ቅድማያቱ ሔኖክ ገና ሲወለድ አስቀድሞ በትንቢት መጽሐፉ ሰይሞታል። እምድኅረ መዋዕል ነሥአ ወልድየ ማቱሳላ ለወልዱ ላሜኽ ብእሲ ወፀነሰት እምኔሁ ወወለደት ወልደ። . . . ወሶበ ተንሥአ እምእዴሃ ለመወልዲት ከሠተ አፉሁ ወተናገረ ለእግዚአ ጽድቅ። ወፈርሀ ላሜኽ አቡሁ እምኔሁ፤ ወጐየ ወመጽአ ኀበ አቡሁ ማቱሳላ ወይቤሎ ፥ አነ ወለድኩ ወልደ ውሉጠ። ኢኮነ ከመ ሰብእ አላ ይመስል ደቂቀ መላእክተ ሰማይ ፥ ወፍጥረቱ ካልእት ወኢኮነ ከማነ ፥ ወአዕይንቲሁ ከመ እግረ ፀሓይ ወገጹ ስቡሕ። ወይመስለኒ ከመ ኢኮነ እምኔየ አላ እመላእክት ውእቱ፤ ወእፈርህ ከመ ኢይትገበር መንክር በመዋዕሊሁ ዲበ ምድር። ወይእዜኒ እስእል እምኀቤከ ከመ ትሑር ኀበ ሔኖክ አቡነ ወትስማዕ እምኀቤሁ አማነ እስመ ውእቱ ምስለ መላእክት ንብረቱ። ወሶበ ሰምዐ ማቱሳላ ነገረ ወልዱ መጽአ ኀቤየ . . . ወይቤለኒ በእንተ ጻሕቅ ዐቢይ መጻእኩ ኀቤከ ወበእንተ ራእይ ዕጹብ . . .። ወአውሣእኩ አነ ሔኖክ ወእቤሎ ይሔድስ እግዚ ሐዲሳተ ዲበ ምድር፤ ወዘንተ ወጻእኩ ወርኢኩ በራእይ ወአይዳዕኩ፤ . . .። ወዝ ወልድ ዘተወልደ ለክሙ ውእቱ ይተርፍ ዲበ ምድር፤ ወሠለስቱ ደቂቁ ይድኅኑ ምስሌሁ ሶበ ይመውቱ ኵሉ ሰብእ በዲበ ምድር . . .። ወይእዜኒ አይድዕ ለወልድከ ላሜኽ እስመ ዘተወልደ ወልዱ ውእቱ በጽድቅ፤ ወጸውዕ ስሞ ኖኅ እስመ ውእቱ ይከውን ለክሙ ተረፈ ፡ (ሔኖ ፡ ፺)። ፪ኛም፤ በተረፍነት ላይ ፥ ነዊኀ ዕድሜ ፥ ዘርዕ ዘነዋኀ የሐዩ ማለትን ያሳያል። ወሐይወ ኖኅ እምድኅረ ማየ አይኅ ሠለስተ ምእተ ወኀምሳ ዓመተ፤ ወኮነ ኵሉ መዋዕለሁ ለኖኅ ተስዐቱ ምእት ወኀምሳ ዓመት ወሞተ ፡ (ዘፍ፱ ፡ ፳፰ ፡ ፳፱)። ታላቅ ዝናም ደግሞ ኖኅ ይባላል ፡ (ዐማርኛ)።
ኖላዊ ፡ (ዊት ውያን ያት፤ ሎት፤ ነዋልው) የሚጠብቅ ጠባቂ፤ መሪ ነጂ እረኛ፤ ንጉሥ ጳጳስ። ኖላዌ አባግዕ። ወጸውዐ ሰብዓ ኖላውያነ። ኖሎተ እንስሳ። ወወፅኡ ዐሠርቱ ወክልኤቱ ነዋልው ፡ (ዘፍ፬ ፡ ፪። ሔኖ ፡ ፹፱። ዘኍ፴፪ ፡ ፬። ገድ ፡ ተክ)። በኖለወና በኖላዊ ፈንታ ተኖለወ ተኖላዊ ይላል፤ ስሕተት ነው። ሌሊተ ተኖልዎሙ። ምሕረትከ ይትኖልወኒ። በተኖልዎ ወአስተሐምሞ። አንሰ ኮንኩ አዐቅበከ ወእትኖልወከ እምዘየኀሥሥ ሥራዌከ። ተኖላዊሆሙ ለጸላእተ ክርስቶስ። ምጽዋት ተኖላዊት ይእቲ ለገባሪሃ ፡ (ቅዳ ፡ ያዕ። ቄድር። አፈ ፡ ተ፴፯። ዮሴፍ። አብጥ ፡ ፵፱። አፈ ፡ ተ፴፪)።
ኖል ፡ (ዐረ) ዐስበ ኖላዊ፤ የባቡር ክራይ ፥ ሰውን ከነጓዙ ሰብስቦ ጠብቆ ተሸክሞ የመውሰዱና የመንዳቱ ዋጋ።
ኖልዎ ዎት ፡ (ኖለወ ይኖሉ። ዕብ ናሄል) ማረን ፥ እረኛ መኾን፤ መጠበቅ ፥ መንዳት ማስምረት ማስቸኰል ማጣደፍ፤ ማሮጥ ማስሮጥ ፥ ቶሎ ቶሎ ማስኬድ፤ የከብት የባቡር የሠረገላ። ረዐየን እይ።
ኖመ ፡ ተኛ፤–ነዊም ኖመ።
ኖራ ፡ በቁሙ፤ ነጭ ብሩህ ጽሑድ ፥ የደንጊያ ዐመድ።
ኖብያት ፡ ዜና መዋዕል፤–ነበየ።
ኖት አው ኖታ ፡ (ላቲን) በቁሙ ፥ የበንክ ወረቀት፤ ህየንተ ብሩር ወወርቅ። ፍችው ማሰቢያ ማስታወሻ ፥ ምልክት፤ ዘሩ ነዊጥ ኖጠ ነው ፥ ጠና ተ ተወራርሰዋል፤ ኖጠን እይ። ምስጢሩም ካንዱ ወዳንዱ ማለፍ ነው። በንክ ደግሞ በጀርመን ቋንቋ የሰራፎች ፡ (መንዛሮች) ማእድ ፥ የገንዘብ ሰደቃ ይባላል ፡ (ማቴ፳፩ ፡ ፲፪። ዮሐ፪ ፡ ፲፭)።
ኖትያ ኖትያዊ ፡ (ብ ነዋትያን፤ አው ኖትያት። ጽር ናውቲስ። ዐረ ኑቲይ) መርከበኛ ፥ ባለመርከብ፤ የመርከብ አገልጋይ ፥ መሪ ቀዛፊ፤ ቋትለኛ። ተመትሮ ማዕበለ ደም እንተ ኢፈርሀ ልብከ ገብረ መርዓዊ ኖትያ። ኖትያዊ ይኔጽር ኀበ ከዋክብት። ፈነወ ኪራም በሐመር ዕደወ ኖትያተ እለ የአምሩ ባሕረ። ወፈርሁ ኖትያት ፡ (ቅኔ። ማር ፡ ይሥ። ፫ነገ ፡ ፱ ፡ ፳፯። ዮና፩ ፡ ፭)። ባለቅኔዎች ግን ኖተወ ዋኘ ይሉና ፥ ኖትያን ከዚህ ያወጣሉ፤ ፍችውንም ዋነተኛ ብለው ይተዉታል።
ኖትያ ፡ መርከበኛ፤–ነወተ።
ኖን [1] ፡ (ዕብ ኑን) ስመ ፊደል ነ፤ የአሌፍ ፲፬ኛ። ፍችው በሱርስት ረዥም ዓሣ ፥ እባብ የሚመስል ፥ የባብ ዐይነት። ነሐስን እይ፤ ከዚህ ጋራ ፩ ነው። ኖን ፡ (ኔር) ማኅቶት ለእግርየ ፡ (መዝ ፡ ፻፲፰ ፡ ፻፭–፻፲፪። ሰቈ፩ ፡ ፲፬። ፪ ፡ ፲፬። ፫ ፡ ፴፱። ፬ ፡ ፲፬)። ባለዳዊቶች ግን ስመ አምላክ ብለው ፍችውን ንጉሥ ይሉታል።
[2] ፡ ኖን፤–ስመ ፊደል ነ፤–ነወነ።
ኖጠ ፡ (ዕብ ናጥ) ናጠ አናወጠ፤ ወይም ተናጠ ተናወጠ፤ ዞረ ባከነ ፥ ወዲያ ወዲህ አለ። ኖትንና ኖትያን እይ።
ኖጻ ፡ ላባ፤–ነጽይ ነጸየ።

No comments:
Post a Comment