ሀ ለ ሐ መ ሠ ረ ሰ ሸ ቀ በ ተ ቸ ኀ ነ ኘ አ ከ ኸ ወ ዐ ዘ ዠ የ ደ ጀ ገ ጠ ጨ ጰ ጸ ፀ ፈ ፐ
አ [1] ፡ (ፊደልና አኃዝ) አንደኛ መዠመሪያ ፊደል፤ የፊደል ኹሉ ራስ፤ በኵር ቀዳማይ ባለም ቋንቋ ኹሉ፤ ይልቁንም በጥንታዊው ተራ በግእዝ አልፍ ቤት በአበገደ። ስሙ አልፍ ፥ ቍጥሩ አንድ፤ አኃዝ ሲኾን አ አሐድ ፥ አሐዱ ይባላል። ምስጢሩ እሑድንና የእሑድን ፍጥረት መድብ አድርጎ ፈጣሪን ያሳያል። ፡ (ዘፍ፩ ፡ ፩–፭። ራእ፩ ፡ ፰ ፡ ፲)። ዳግመኛም በዕብራይስጥ ዐዋጅ አለነቍጣ አሐዱ ይባል የነበረው ያው አንዱ አሌፍ አ በራሱ ላይ ነቍጣ ሲኾንበት በነቍጣው ምክንያት እልፍ እንዲባል ፥ በግእዝም ሥርዐት እ እልፍ ይባላል፤ እልፍ ያሰኘውም ያሰኘውም የራሱ ነቍጣ ነው፤ አለፈን ተመልከት።
[2] ፡ የማብዛት ልማድ ፥ አብዢ፤ ፍችው ዎች። ደብር አድባር ፥ ወግር አውግር ፥ ፈለግ አፍላግ፤ ተራሮች ኰረብቶች ወንዞች። አንዳንድ ጊዜም ት ምእላድ እየኾነለት ከት ጋራ ያበዛል፤ ጥብ አጥባት ፥ ነቅዕ አንቅዕት ፥ ባሕር አብሕርት። ዳግመኛም በአ ብቻ የሚበዛ ቃል ት ሲጨመርበት የብዙ ብዙ ይኾናል፤ አድባር ራት ፥ አውግር ራት ፥ አፍላግ ጋት። በአና በት የሚበዛም የብዙ ብዙ ለመኾን ኹለተኛ ት ይፈልጋል፤ ነቅዕ ባሕር ርእስ ብሎ አንቅዕት አንቅዕታት፤ አብሕርት አብሕርታት፤ አርእስት እርእስታት። የተን አፈታት እይ።
[3] ፡ የማስደረግ ልማድ፤ አስደራጊ፤ ፍችው አስ። ቀተለ አቅተለ፤ ክህለ አክሀለ፤ ገብረ አግበረ። ዳግመኛም ቆመ ቦአ ወፅአ መጽአ ይህን በመሰለ በሐውልትና ባጓጕል ግስ ላይ ሲጨመር የማድረግና የማስደረግ ልማድ እየኾነ አንዱን አንቀጽ በ፪ ጾታ ያስፈታል። አቀመ፤ አቆመ አስቆመ። አብአ፤ አገባ አስገባ። አውፅአ፤ አወጣ አሶጣ። አምጽአ፤ አመጣ አስመጣ። ባለቅኔዎች ግን አ ከወደቀበት ማናቸውም ግስ በ፪ ጾታ ይፈታል ብለው ያውጁና አእመረን ዐወቀ አሳወቀ ብለው ይፈታሉ ፥ የተሳሳተ ነው፤ አሳወቀ እንጂ ዐወቀ አያሰኝም፤ አመረን ተመልከት። ሦስተኛም በካልኣይና በሣልሳይ ራሱን እየጐረደ የትንቢት መነሾች አሥራውን ኹሉ ራብዕ ያደርጋል። አቅተለ ያቀትል ያቅትል። አግበረ ያገብር ያግብር። አእመረ ያአምር ያእምር። ቀዳማዩን አመረ አኰተ ዐረፈ በማለት ፈንታ አእመረ አእኰተ አዕረፈ ብሎ ፥ ካልኣዩን ደግሞ የአምር የአኵት የዐርፍ ማለት ዕጥፍ ድርብ ስሕተት ይባላል፤ በነዚህ በሦስቱ ሌላውን ኹሉ ማየት ነው።
[4] የትንቢት መነሻ፤ የካልኣይ ሥር፤ አነ ለሚል ብቻ ላንድ አካል። ግእዙ ብቻ ስለ ተነገረ ሳድሱ አይቀርም። ሖርኩ አሐውር ፥ ዐረጉ አዐርግ ፥ ወረድኩ እወርድ። በማስደረግ ጊዜ ፪ኛ አ ስላለበት ራብዕ ይኾናል። አሖርኩ ኣሐውር፤ አዕረጉ ኣዐርግ፤ አውረድኩ ኣውርድ። አእመርኩ ኣአምር።
[5] የግስ ልማድ፤ ጠባይና አካኼድ የሚለውጥ። በ፫ ፊደል ግስ ፥ ከዚያውም በቀተለ ቤት፤ መነሻ መድረሻ ማእከል ሲኾን ፥ ሳድስ ይኾን የነበረውን ግእዝና ራብዕ፤ ግእዝ ይኾን የነበረውን ሳድስ ያደርጋልና፤ አደራረጉና አገባቡ እንዴት እንደ ኾነ በርባ ቅምር ክፍል ተመልከት
፡ (ዕር፪ ፡ ቍ፲፭)።
[6] አ፤
፡ (ንኡስ አገባብ) እንደ ሶና እንደ ኬ እንደ መ ትራስ ኹኖ በመጨረሻ ቃል እየገባ ቃለ መልእክት ፥ አጋኖ ፥ አስተብቍዖ ፥ ተጋንዮ ይኾናል፤ ምስጢሩም ቍልምጫና ከበሬታ ነው። አፈታቱንና ምስክሩን በንኡስ አገባብ ተመልከት
፡ (ዕር፳ ፡ ቍ፺፱)።
አሓ ፡ ላም በሬ፤–አኀወ አኃ።
አኃ ፡ (ሐባብ። ቅብጥ ኤሔ) ላም በሬ፤ የቀንድ ከብት፤ ባንድ በረት የተወለደ የላም መንጋ። ፅምደ አልሕምት ባለው ፅምደ አኃ እንዲል
፡ (ሉቃ፲፬ ፡ ፲፱)።
አህ ፡ (ዕብ አሀህ) ንኡስ አገባብ። የሐዘን የጭንቅ ያሉታ የነቀፌታ ቃል፤ መታመም መጐሰም። አይ አዬ፤ ዋይ ወዮ፤ ወዲያልኝ ወዲያ፤ እህ እህህ፤ ሐሰ ኅድግ፤ ይኾናል። ፡ (ግጥም) ሰው ኹሉ ገብቶ አገሩን፤ እህናኔ
፡ (እኔ) ቀረን። አህ አህ እምዛቲ ኀፍረት። አህ እምዛቲ ሕሠም
፡ (አፈ ፡ ተ፲፩። ፲፭። ሕዝ፬ ፡ ፲፬)። ኹለተኛም አንክሮና ብፅዓን የደስታ ቃል ይኾናል፤ ሐሰ ኅድግ ከማለት በቀር ዐማርኛው አይለወጥም። አህ አህ ለድምፀ ቅኔሆሙ። አህ አህ ሚ መንክር ወመድምም። አህ አህ አንደደኒ ፍቅርከ
፡ (ግንዘ። አረጋ)።
አኈለቈ ፡ አስቈጠረ አሳሰበ፤ ቍጥር አስተማረ።
አሀለወ ፡ አኖረ፤ አስኖረ፤ አስቀመጠ፤ ነዋሪ አደረገ፤ አስደረገ። ወምስለ ብዙኅ ምሕረት ታሄልወነ ፡ (ጥበ፲፪ ፡ ፲፰)።
አኀለየ ፡ አሳሰበ፤ አስመለከተ፤ አሳተ አነሣሣ። ይኄልዮ ዘኅቡእ ያእምር። ተፋቅሮ ኢያኄሊ እኩየ። ነገሩ ኵሎሙ በከመ አኀለዮሙ ልቦሙ። ሰይጣን አኀለዮ ለዳዊት ከመ ይኈልቍ እስራኤልሀ ፡ (ሢራ፴፱ ፡ ፯። ፩ቆሮ
፡ ፲፫ ፡ ፭። ገድ ፡ ላሊ። ፩ዜና ፡ ፳፩ ፡ ፩)።
አኀመየ ፡ (ያኄሚ ያኀሚ) አሳሰረ፤ ላሳሪ ሰጠ።
አኃሪ ፡ ደኃሪ፤ ኋለኛ፤ የኋላ፤ የዠርባ። ለአኃሪ ዐምድ
፡ (ዘፀ፳፮ ፡ ፳፯)።
አሐርተመ ፡ አዋረደ አጐሰቈለ፤ አከፋ አጠፋ ጐዳ። ሕርቱም ዘአሐርተምዎ ዳኅፃቲሁ ፡ (ግንዘ)።
አኀበለ አስተኀበለ ፡ አስደፈረ አስጨከነ፤ በሉ በሉ አለ።
አሓበረ አስተሓበረ ፡ አስቀለመ አስነከረ፤ ቀለም አስገባ አስቀባ፤ አስጌጠ።
(ጥት) አሐተ [1] ፡ አንዲት አንድያ መዠመሪያ።
[2] ፡ (አሐተዩ) አንዲቱን አንደኛይቱን፤ አንዷን አንደኛዋን። መነሻው አ ግእዝ ሲኾን ፥ የጅምላ፤ ኣ ራብዕ ሲኾን ፥ የተራ ቍጥር እንደ ኾነ አስተውል።
አሐተኔ ፡ አንድነት፤ ባንድነት፤ አንድ ላይ፤ አንድጋ። ነበርነ አሐተኔ። ተጋቢአነ አሐተኔ። ያስተጋብኦሙ አሐተኔ። እንዘ ሀለዉ አሐተኔ
፡ (ቀሌ። ዲድ ፡ ፩። ዮሐ፲፩ ፡ ፶፪። ግብ፪ ፡ ፩)።
አሐቲ ፡ (አሐትዩ) አንዲቱ፤ አንደኛይቱ፤ መዠመሪያይቱ፤ ወይም አንዷ አንደኛዋ መዠመሪያዋ።
(ጥት) አሐት ፡ አንዲት አንድያ መዠመሪያ።
(ጥ) ፤–አንዲት፤–አሐድ፤ እሒድ አሐደ
አኃት እኅታት ፡ እኅታት፤ እቶች፤ እኅቶች፤ እትማማቾች። መነኮሳይያት። እኅተ አኃትኪ። ወለንኡሳት ከመ ዘለአኃቲከ። አኀዊነ ወአኃቲነ። አኃት ክቡራት። ይሑር ኀበ ምኔት ወይሥርዖን ለእኅታት
፡ (ሕዝ፲፮ ፡ ፵፭። ፩ጢሞ ፡ ፭
፡ ፪። ቅዳ። ቄር። ፊልክ ፡ ፲፮)።
አሀከየ ፡ አሀከየ፤ አሰነፈ አታከተ፤ አሰለቸ። እስመ በአኅጽሮ ይኄይስ ድርሳን፤ ከመ እምብዝኁ ኢያህኪክሙ
፡ (ተረ ፡ ቄር፳፩)። በአህክየ ፈንታ አስተህከየ፤ አስተሀከየ ይላል፤ ፍችው አንድ ነው። ዛቲ መጽሐፍ መዜንው ሠናይ፤ ኢያዐቅፋ ትጋሀ ሌሊት ወኢያደክማ ወኢያስተሀክያ ብዝኀ ነጽሮ ፡ (ፈላስ)።
አሐዘበ አስተሐዘበ ፡ አሳሰሰበ፤ አስጠረጠረ። አኀዘ አንደፊር ይድግም ዘንተ ነገረ ኀበ ህርቃኖስ ወያሐዝቦ ለእኁሁ። ተዘከር ከመ ኢይጐነዲ ሞት ወኢታስተሐዝብከ ዕለተ ሞት
፡ (ዮሴፍ። ሢራ፲፬ ፡ ፲፪)።
አኃዚ ፡ (ዚት ዝያት ያት፤ አኀዝት) የሚይዝ ያዥ፤ ዐጋች፤ ጨባጭ ቈጣቢ ንፉግ፤ የሚገዛ ገዥ፤ አዛዥ፤ ጌታ ጠባቂ። እደ ሞት አኃዚ። አኃዜ አኅዝ። ነጋሢ አኃዚ። እንዘ ነገሥታት ወመኳንንት ወእንዘ አኃዝያን እሙንቱ በዲበ ምድር። አኃዜ ኵሉ እግዚአብሔር አምላክነ። አኃዜ ነፍሱ እምነ ፍትወታት
፡ (ስንክ ፡ መጋ፲፪። ፍ ፡ ነ ፡ ፳፯። ጥበ፲፬ ፡ ፲፱። መቃ ፡ ገ፬። ቅዳ። ፍ ፡ ነ ፡ ፮)።
(ጥት) አሐዱ [1] ፡ (አሐ(ድ) ት) አንድ ብቻ፤ አንዳች። አሐድነ በየማንከ ወአሐድነ በፀጋምከ ፡ (ማር፲ ፡ ፴፯)።
[2] ፡ (አሐቲ)። ዕብ ኤሐድ። ሱር ሐድ። ዐረ አሐደ) የቍጥር ስም፤ መዠመሪያ ቍጥር፤ ከኹለት እስከ ምእልፊት ላለ ቍጥር ኹሉ ጥንትና መሠረት መነሻ። አንድ አንዱ።
አኀዝ ፤
ትእዛዝ አንቀጽ
፤ ያዝ
ጨብጥ ፤
አትልቀቅ።
አኃዝ ፡ (ዛት) መዠመሪያ፤ ዥምር ውጥን፤ አንድ እንደ ማለት። በቁሙ፤ ቍጥር ሒሳብ፤ የቍጥር ፊደል ወይም ምልክት፤ ከአ እስከ እ ያለ፤ ይኸውም እም(፩) አሐድ እስከ
፡ (፻፻) እልፍ ማለት ነው። የሕዝብ የገንዘብ የስፍር የሚዛን፤ የሰዓት የዕለት የወርኅ የዓመት የሥራ ኹሉ ልክ፤ ማነስ መብዛቱ ክፍሉና ዐይነቱ በየስሙ በየነገዱ ተዘርዝሮና ተደምሮ ተለይቶ የሚታወቅበት። አኃዘ ቢስ፤ አኃዝ የሌለው ነገር እንዲሉ። ወለለ ኍልቈ አኃዙ ቦቱ አኃዝ ዘበሢራኩ። አእሚረከ አኃዘ ኍልቍ። ዮድ ዘይቤ የውጣ ፥ ዝ ውእቱ አምሳለ ዐሠርቱ ፡ (፲) አኃዝ፤ ርቱዕ ውእቱ እንበለ ጸኒን
፡ (መቅ ፡ ወን። ጥሬ ፡ ሰዋ)።
አሓዝ ቁጥር ፡ ቍጥር፤–እኂዝ አኀዘ።
አኀየለ አስተኀየለ ፡ አጠና አበረታ አጠነከረ፤ ኀይለኛ አደረገ፤ አበዛ። ናዘዘቶ ወአኀየለቶ በውስተ መከራሁ። ያኄይለከ እግዚ ያኀይልከ ለገቢረ ጽድቅ ፡ (ፊልክ ፡ ፶፰። ዘፀ፲፰ ፡ ፳፫። ኩፋ ፡ ፳፪)።
አሐደሰ አስተሐደሰ ፡ አሳደሰ አስጠገነ፤ ሐዲስ አስደረገ። ወአስተሐደሰ ቤተ ምሥዋዕ ፡ (፪ዜና ፡ ፲፭ ፡ ፰)።
አሐዱ
አሐዱ ፡ አንዱም
አንዱም ፤
ራስ
ራሱ ፤
አንዳንዱ ሰው
(ዘፍ፵ ፡ ፭።
ዘፀ፴፪ ፡ ፳፯።
፴፭ ፡ ፳፩)።
አሓዲ መእሕድ ፡ አንድ የሚያደርግ፤ የሚያዋሕድ፤ አዋሓጅ።
አሐድ (ዳት)
[1] ፡ ኅብረት፤ አንድነት። የተዋሐደ ኅቡር፤ አንድነቱ በራስ ቅሉ ብቻ ያይዶለ፤ ብዙነት ያለው አንድ፤ እንደ ሰው ባሕርይ የተቀመመ የተጠራቀመ። ያንድ ቤት ቍጥር፤ ካንድ እስከ ዘጠኝ ያለ። አሐዳት
፡ (አቡሻ ፡ ፲፩)።
[2] ፡ (ጥት) አሐድ፤ ፡ (አሐ(ድ) ት) አንድ ብቻ፤ አንዳች። አሐድነ በየማንከ ወአሐድነ በፀጋምከ
፡ (ማር፲ ፡ ፴፯)።
አሐድ አሐዱ ፡ (አሐ(ድ) ት
፡ አሐቲ) አንደኛው፤ መዠመሪያው ፥ መነሻው። ዝርዝሩ በቁም ቀሪ ኹኖ ያነኑ ባለቤቱን እንጂ ፥ ሌላ አካል አያይም፤ ብእሲሁ ብእሲታ እንደ ማለት ነው፤ ስሙም ዐጸፋ ይባላል፤ ዐጸፋም ቀድሞ ለታወቀ ለተነገረ ነው። በሌሎች ቋንቋ ግን አርቲክል ይባላል፤ የስም አገባብ ወይም ተውሳከ ስም ማለት ነው፤ የሚገባም በመነሻ እንጂ በመድረሻ አይዶለም፤ እልን ተመልከት። የግእዝ አርቲክል ዝርዝር ብቻ ስለ ኾነ ካንዳንድ ጊዜ በቀር በስም ኹሉ አይገባም፤ ባፈታት ግን ሰብአ ወእንስሳ ታድኅን፤ ሰዉን እንስሳዉን። ዘገበርከ ሰማየ ወምድረ፤ ሰማዩን ምድሩን ያሰኛል። አሐዱ እግዚአብሔር፤ ወአሐዱ ሃይማኖት፤ ወአሐቲ ጥምቀት። አዳም ኮነ ከመ አሐዱ እምኔነ። ኩን ከመ አሐዱ እምኔሆሙ። አሐቲ አነ ለአቡየ። አሐቲ እምአሐቲ። እሠይም ሎሙ አሐደ ኖላዌ። ዘአሐተ ብእሲተ አውሰበ
፡ (ኤፌ፬ ፡ ፭። ዘፍ፫ ፡ ፳፪። ሢራ፴፫ ፡ ፩። ጦቢ፫ ፡ ፲። መክ፯ ፡ ፳፯። ሕዝ፴፬ ፡ ፳፫። ፩ጢሞ ፡ ፫ ፡ ፪)። በተገብሮ አሐዱ አሐቲ ያለውን በገቢር ጊዜ አሐደ አሐተ ማለቱ ፥ አርቲክል ስለ ኾነ ነው፤ አርቲክል ባይኾን ግን የካዕብ ወራሽ ሳብዕ የሣልስ ወራሽ ኃምስ ነውና ፥ አሐዶ አሐቴ ባለ ነበር። ሌላው ኹሉ ያንድ ቤት አኃዝ እንዲህ እንደ ኾነ አስተውል። ከዚህ የቀረውን በርባ ቅምርና በአኃዝ ቅጽል ተራ እይ ፡ ( ዕር፩ ፡ ቍ፲፫። ዕር፲፭ ፡ ቍ፻፳፭)።
አኀው ፡ ወንድሞች፤ ወንድማማቾች፤ ዘመዶች ዘመዳሞች፤ ሰዎች ያዳምና የሔዋን ልጆች፤ መነኮሳት ማኅበር ኹነው በየገዳሙ የሚኖሩ። ይሁዳ ወአኀዊሁ። ወረከበ ክልኤተ አኀወ። አንትሙሰ አኀው አንትሙ። እነግሮሙ ስመከ ለአኀውየ። ይቤሉ አኀው፤ ማኅበረ አኀው
፡ (ማቴ፩ ፡ ፪። ፬ ፡ ፲፰ ፡ ፳፩። ግብ፯ ፡ ፳፮። መዝ ፡ ፳፩። ፊልክ)።
አኀውና ፡ ወንድሞችነት፤ ከዊነ አኀው። መዓርገ አኀውና
፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፲ ፡ ፮)።
አሑር [1] ፡ አውራ፤–ሐዊር ሖረ፤ አሖረ።
[2] ፡ አውራ፤ ኰርማ፤ አለሌ። ሐርጌ አሕሩግ በማለት ፈንታ አሑር አሑረ በግዕ ይላል፤ የተሳሳተ ነው ፡ (ዕዝ፲ ፡ ፲፱)።
አሔሰ አሕየሰ ፡ አስነቀፈ፤ አስነወረ። ኢታሒስ ርእሰከ። ያሐይስ ርእሶ ፡ (ሢራ፴ ፡ ፴፩። ምሳ፱ ፡ ፯)።
አኄሰ አኅየሰ ፡ አሻለ አበለጠ፤ አሳመረ አስጌጠ። አኅየስኩከ ወገበርኩከ ከመ ጽቡረ ለብሓዊ። ወኮኑ መንፈቀ ሰብእ ያኄይሱ ግብረ አሐዱ፤ ወመንፈቆሙ ያኄይሱ ግብረ ካልኡ። ሰይጣን ይኄይስ መልእክተ ኀቤሆሙ። ወእምአኄስኩ ዘእነብብ
፡ (ኢሳ፵፭ ፡ ፱። ፊልክ ፡ ፩። ፶። ኢዮ፲፮
፡ ፭)።
፡ አዳነ ተቤዠ። ከመ ይኂስ ኅላዌነ እሞት ወእሙስና
፡ (ቄር ፡ ጰላ)። በአኅየሰ ፈንታ አስተኀየሰ ይላል፤ ፍችው አንድ ነው። አስተኀየስክዎሙ ለእለ ሞቱ ኅቡረ እምሕያዋን
፡ (መክ ፡ ፪)።
አኄረወ ፡ አቸረ፤ አስቸረ፤ ቸር ገር አደረገ፤ አለዘበ። ያኄርዉ ኅሊናሁ ፡ (አረጋ ፡ ድ፲)።
አሕ ፡ አዬ ወዲያ፤–አህ።
አሕለለ ፡ (አሕረረ) አሳረረ፤ አቃጠለ። ፈነወ እሳት ወአሕሰሎን ለአዕፅምትየ። ሶበ ለልብየ እሳተ ሐዘን አሕለሎ።እቶነ እሳት ኢያሕለላ ፡ (ሰቈ፩ ፡ ፲፫። ደራሲ። ስንክ ፡ ሐም፳፭)።
አሕለመ ፡ አሳለመ፤ ሕልም አሳየ።
አኅለቀ ፡
ፈጀ ጨረሰ ፈጸመ፤ አጠፋ። ወኢያኅለቀ ብዙኀ ብርተ። እሳት አኅለቀ ሥነ ገዳም። አኅለቆሙ በነደ እሳት። አኅለቁ ኵሎ በሓውርተ አሞን ፡ (፪ዜና ፡ ፬ ፡ ፲፰። ዮኤ፩ ፡ ፲፬። ሢራ፵፭
፡ ፲፱። ፩ዜና ፡ ፳ ፡ ፩)።
፡ አሳለቀ አስፈጀ አስጨረሰ፤ አስደራጊ። አኅለ ዐጸደ ወይንየ በአባግዒሁ
፡ (ክብ ፡ ነገ ፡ ፸፪)። በአኅለቀ ፈንታ አስተኀ(ኅ) ለቀ ይላል፤ ፍችው አንድ ነው ፡ (ሉቃ፳፪ ፡ ፮)።
አኅለፈ ፡ አሳለፈ፤ ኦሻገረ። አኅለፍከነ ማእከለ እሳት ወማይ ፡ (መዝ ፡ ፷፭)። በአኅለፈ ፈንታ። አስተኀለፈ ይላል፤ ፍችው አንድ ነው። ያተክት ወያስተኀልፍ ዕድሜሁ። ኢታስተኀልፍ ዕለተ እምዕለት። ከመ ያስምዑ ወያስተኀልፉ ነገረ በኵሉ በሓውርት ፡ (ሢራ፳፱ ፡ ፭። ኩፋ
፡ ፵፬። ነሐ፰ ፡ ፲፭)።
አሕመለ ፡ አስረገዘ፤ ጫነ አሸከመ፤ አስለቀመ።
አሕመልመለ ፡ (ተቀ ግ) ለመለመ ረጠበ፤ ወጣ በቀለ፤ ተገኘ ተፈጠረ፤ ቅጠል መሰለ። ያሕመለምል አውግር። ወእምአሐቲ መዝገብ ዝእምእስትንፋሰ አፉሁ ይሠርጻ ወያሕመለምላ ነፍሳት። ሕብር እንተ ታሕመለምል። ወርቀ ዐረብ ዘያሕመለምል ፡ (ዓሞ፱ ፡ ፲፫። ቅዳ ፡ ግሩ። ዘሌ፲፫ ፡ ፵፱። አርጋ)።
፡ አለመለመ፤ አረጠበ፤ አበቀለ አስገኘ። አሕመልምል ሊተ ሣዕረ ዘየብሰ። አሕመልምል ሊተ ጎፍስየ። ያሕመለምል ሣዕረ ለእንስሳ ፡ (ሱቱ ፡ ዕዝ፫ ፡ ፵፰። ፊልክ። ቅዳ ፡ ኤጲ)። አመለመለ፤ ጠቀለለ፤ የጥጥ የፀምር ለመፍተል።
አሕመመ ፡ ዐመመ፤ አሳመመ፤ አሞቀ አተኰሰ፤ አሳዘነ አስጨነቀ። አሕመሞ ፀሓይ ርእሶ። ኢያሕመሞሙ ላህበ ፀሓይ። ሀሎ ዘያሐምም ወያስተፌሥሕ። ኢያሕመሞ ይሁዳ ለኤፍሬም ፡ (ዮና፬ ፡ ፰። ኢሳ፵፱ ፡ ፲። ሢራ፯ ፡ ፲፩። ኢሳ፲፩ ፡ ፲፫)።
አሕመቀ አስተ(ሕ) ሐመቀ ፡ አሳበደ፤ እብድ አደረገ፤ አስመሰለ። ናቀ ነቀፈ፤ አቃለለ። ፍኖተ እንተ ትደሉ ለትስብእት ኢያስተሐሚቆ ልደተ ተወልደ ፡ (ቄር ጰላ)።
አሕመየ ፡ አሳማ አስነቀፈ፤ አሰደበ።
አሕመደ ፡ አሳመደ፤ አስበላ አስጠፋ።
አሕመገ ፡ አሳመገ፤ አስደፈረስ አስፈዘዘ።
አሕማሚ ፡ መሕምም፤ የሚያሳምም፤ አሳዛኝ አስጨናቂ። ደዌ ወሕማሕም አማምያን ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፵፫ ፡ ፬)።
አሕሰለ ፡ አስለበበ፤ አሰበሰበ አስከተተ አስጫነ።
አሕሠመ ፡ አከፋ፤ አስከፋ፤ ክፉ አደረገ፤ አስደረገ። አሠንዩ ወአሕሥሙ። ኢትቅናእ ከመ ታሕሥም። ለምንት አሕሠምከ በዝ ሕዝብ። ኢታሕሥም ዲበ ነባሪከ። ኢታሕሥሙ ላዕለ እሉ። ሀኬት ወድካም አሕሣምያን
፡ (ኢሳ፵፩ ፡ ፳፫። መዝ
፡ ፴፮። ዘፀ፭ ፡ ፳፪ ፡ ፳፫። ሢራ፯ ፡ ፳። ዘፍ፲፱ ፡ ፯። ፍ ፡ ነ ፡ ፵፫ ፡ ፬)።
አኅሰረ ፡ (አከሰረ፤ ክሳራ አመጣ) አዋረደ አጐሰቈለ፤ ሰደበ ነቀፈ። ያኀስሮሙ ለዕቡያን። ከመ ያኅስሩ ነፍስቶሙ። አኀዝዎ ሐራ ለዝንቱ አብ ወአኅሰርዎ። እኅስሮቱ ለብእሲ ጻድቅ አኮ ሠናይ
፡ (፩ጴጥ ፡ ፭ ፡ ፭። ሮሜ፩ ፡ ፳፬። ስንክ ፡ መጋ፲፫። ምሳ፲፯ ፡ ፳፮)።
አኅሰርሰረ ፡ የውርደት ስም ቀባ ቀባባ፤ አነካካ፤ አብዝቶ መላልሶ አካቶ ፈጽሞ፤ ጥቂት ሳይተው። ኵሎ ያኅሰረስር ፡ (ምሳ፳፪ ፡ ፲)።
አሕሰወ አሐሰወ ፡ አሷሸ፤ አሳበለ ዐሎ አሰኘ፤ ውሸት አስተማረ። አሕሰወ ስምዐ ፡ (ኦርጋ ፡ ፪)።
፡ አስተባበለ፤ ዋሾ አደረገ፤ እውነቱን ውሸት፤ እውነተኛውን ሐሰተኛ አለ። አርመሙ ወኢአሐሰውዎ፤ እስመ እሙነ ኮነ ነገሩ። መነ እምእሉ ታጸድቅ ወመነ ታሔሱ። ኢታሐስውዎ ለነገረ ቅዱስ
፡ (ዮሴፍ። ሱቱ ፡ ዕዝ፪
፡ ፳፯። ሔኖ፻፬ ፡ ፱)።
አሕሰየ ፡ (ያሐሲ ያሕሲ) አሳሸ አስለፋ፤ አስረገጠ አስበራየ።
አኅሥዐ ፡ አሳረፈ ዝም አሰኘ፤ አበረደ አስታገሠ። ሞገደ ባሕር አኅሥዐ ክርስቶስ። መዐተ ብእሲ ያኀሥዕ ገብር ጠቢብ። አኅሥዐ መቅሠፍተ። ኢይክሉ ያኅሥዑ አጽባአ ዕጹባተ ፡ (ኪዳ። ምሳ፲፰ ፡ ፲፬። ጥበ፲፰ ፡ ፳፩። ፊልክ ፡ ፻፵፯)።
አሕረመ ፡ አሳረመ፤ ሕርም አሰኘ አስተወ፤ ከለከለ፤ አስከለከለ። እምስቴ ማይ አሕረምከ ጕርዔከ። አሕረመ ሕይወቶ እምነጽሮ አንስት። ኀጢአት ዘአሕረመ እግዚ። ከማሁ ለዕደውኒ አሕረሞሙ እግዚ ቀሪበ አንስቲያሆሙ በመዋዕለ ትክቶሆን
፡ (ስንክ ፡ ነሐ፳፬። ፈ ፡ መ ፡ ፪ ፡ ፮። ፲ ፡ ፩)። በሐረመ ፈንታ አሕረመ ይላል፤ ስሕተት ነው። ገብሩ ሎሙ ምስለ ወአሕረሙ ዖመ ውስተ ኵሉ አድባር። አሕረምዎን ለርእሶሙ ፡ (፬ነገ ፡ ፲፯ ፡ ፲። አስቴ፱ ፡ ፴)።
አሕረሰ ፡ አሠራ፤ አሳረሰ። ያሐርሶሙ ገራህቶ ፡ (፩ነገ ፡ ፰ ፡ ፲፪)።
አኅረሰ ፡ አሶለደ፤ አዋለደ። እንተ ታኀርስ ፡ (ዘፍ፴፭ ፡ ፲፯)።
አሕረረ ፡ አሳረረ፤ አቃጠለ። ያሐርሮ ለሣዕር ከመ እሳት ፡ (ሢራ፵፫ ፡ ፳፩)።
አኅረየ ፡ አስመረጠ፤ ምረጥ አለ።
አሕረደ ፡ አሳረደ፤ መሥዋዕት አሠዋ።
አሕረጸ ፡ አስፈጨ፤ አስላመ አስደቈሰ። አሕረጽዎ ለሶምሶን እክለ ከመ አመት
፡ (ዮሴፍ)።
አሕቀረ ፡ (አስተሐ(ሕ) ቀረ) አስቈፈረ አስመረመረ፤ አስናቀ።
አሕቀየ ፡ አስፋጨ፤ አስገጠጠ፤ እንዲያፋጭ እንዲያጋጭ አደረገ፤ የጋኔን የደዌ። ያሐቅዮ ስነኒሁ። ሕማመ አዕይንት ወርእስ ዘይቀጠቅጥ አዕፅምተ ወይቀጸቅጽ ርእሰ ወያሐቂ ስነነ ፡ (ማር፬ ፡ ፲፰። መ ፡ ፈ)።
አሕቀፈ ፡ አሳቀፈ፤ አስታቀፈ፤ አሲያዘ አስቀበለ፤ አስከበበ። ወአሕቀፎ በዐጽፉ ፡ (ገድ ፡ ዮሐኒ)።
አሕበለ ፡ አሳበለ፤ አስገመደ፤ ቀላድ አስጣለ፤ አሳሰረ።
አኅበረ ፡ አሳበረ፤ አስተባበረ፤ አጋጠመ አንድ አደረገ፤ አሰማማ። ኵሎ አኀዊሆሙ አኅበሩ ምስሌሆሙ። ዘአኅበረ ምስሌሆሙ ሐዊረ። አኅብር ሠቃተ። መኑ ዘያኀብሮ ለክርስቶስ ምስለ ቤልሖር ፡ (ዕዝ፭ ፡ ፫። ዘኍ፩ ፡ ፶፩። ዘፀ፳፮ ፡ ፲፩። ፪ቆሮ ፡ ፮ ፡ ፲፭)።
፡ አማሰለ፤ አዋሐደ። አኅብሪዮ እንዲል
፡ (ትግሬ)።
አኅበዘ ፡ አሳበዘ፤ አስጋገረ ዐበዛ አደረገ።
አሕበየ ፡ አስጠበቀ፤ አሾመ አስዋሰ፤ አሰጠ አስገበረ።
አሕበጠ ፡ (ዕብ ሐባጥ፤ ወቃ አረገፈ፤ የፍሬ) አሳበጠ ነፋ፤ አቈሰለ፤ በበትር።
አኅብአ ፡ አሳባ አስደበቀ፤ አሰወረ።
አኅተመ ፡ አሳተመ አስመሰከረ፤ ማኅተም ምልክት አስደረገ።
አሕተተ ፡ አስመረመረ፤ አስጠየቀ።
አኅተወ ፡ አቃጠለ ለኰሰ፤ አያያዘ አበራ አስበራ
፡ (መሳ፲፭ ፡ ፬)። አነ ኣኀቱ ማኅቶተ ጥበብ ውስተ ልብከ። መናረት እንተ ታኀቱ ፡ (ሱቱ ፡ ዕዝ፲፬ ፡ ፳፰)።
አኅነቀ ፡ አሳነቀ፤ አስገደለ።
አሕነጸ ፡ አሳነጠ አሠራ። ምኵራበ ጣዖት ዘአሕመጸ አንጥያኮስ ፡ (ዮሴፍ)።
አህካዪ መሀክይ ፡ የሚያሰንፍ አስናፊ። ጽሒፍ ሊተሰ ኢመሀክይ ወሰክሙሰ ጽኑዕ ፡ (መጽ ፡ ምስ)።
አሕዘለ ፡ አሳዘለ አሸከመ፤ ጫነ አስደበለለ።
አሕዘነ ፡ አሳዘነ አስቈረቈረ፤ አስቀየመ አስከፋ፤ አስቈጣ። ኢታሕዝኖ ለአቡከ በሕይወቱ። ከመ ኢያሕዝንከ። ኢያሐዝኖ በእንተ አባግዕ። ወአሕዘኖ ለቃየን ጥቀ ፡ (ሢራ፫ ፡ ፲፪። ፫ ፡ ፲። ዮሐ፲ ፡ ፲፫። ዘፍ፬ ፡ ፭)።
አሕዘዘ ፡ አስጐነጨ፤ አስጐረጐጨ። ነሥኦ ሰፍነገ መመልኦ ብሒኦ ወአሰረ በኅለት ወአሕዘዞ ፡ (ማቴ፳፯ ፡ ፵፰)።
አኅዝ ፡ (ዛን ዛት) መያዣ ዕግት ቃቢ። ተያዥ ዋስ መድን፤ ተጠሪ ቶፋ። ሀበኒ አኅዘ፤ መያዣ
፡ (ዘፍ፴፰ ፡ ፲፯ ፡ ፲፰። ዘዳ፳፬ ፡ ፲–፲፫። ሕዝ፲፰ ፡ ፯)። አልብየ አኅዝ፤ ዋስ ፡ (ኢዮ፴፬ ፡ ፴፩። አፈ ፡ ድ፳፮። ፍ ፡ ነ ፡ ፳፯)።
አሕየወ ፡ አዳነ ፈወሰ፤ ዐደሰ ሕያው አደረገ፤ አስደረገ። ጥበብ ታሐይዎ ለዘአጥረያ ረሶሙ ሕገ ዘያሐይዎሙ። ወገሰሶ እዝኖ ወአሕየዎ። ያሕይዉ አረፍተ ወመቅደሰ። አሕየወ ምሥዋዐ ዘመዝበረ ፡ (መክ፯ ፡ ፲፪። ሢራ፲፯ ፡ ፲፩። ሉቃ፳፪ ፡ ፶፩። ዕዝ፪ ፡ ፲፯። ፫ነገ ፡ ፲፰ ፡ ፴፪)።
አህየየ ፡ ቸል አሰኘ፤ አሰነፈ አስተወ፤ አስጣለ። ኢፈቀደ አምላክ ያርኢከ ሙስናሃ ለሀገር ወአምጽአ ኑዛዜ ላዕሌከ ወአህየየከ ፡ (ራእ ፡ ባሮ)።
(ጥያ) አህያ ፤ (ቅብጥ ሄያ ፤ ሄሄያ) ፤ በቁሙ ፤
አድግ ፤
ሲጮኽ ሀሀሀ
የሚል። (ተረት) ፤
ዳኛ ቢያጋድል
በዳኛ ፤ አህያ
ቢያጋድል በመጫኛ።
አህያ ሠባ ፤
ካልተበላ ምን
ረባ።
(ላ) አህያ ሸራህያ ፡ (ዕብ ኤህዬ አሼር ኤህዬ) ስመ አምላክ፤ እሄሉ ዘእሄሉ ወይም እከውን ዘእከውን
፡ (ዘፀ፫ ፡ ፲፬)። ሦስተኛም በዚሁ ቍጥር ከዚሁ አያይዞ ኤህዬ ሽላሐኒ ይላል፤ እሄሉ ፈነወኒ ማለት ነው፤ አንቀጹን ስም አድርጎታል። ዘይቤው ላባቶቻችኹ ለሦስቱ ኹሉ በጭንቀታቸው ጊዜ እሄሉ ምስሌከ ያላቸው አምላክ ያሰኛል፤ ምስጢሩ ግን እንደ አዶናይ ምስጢረ ሥላሴ አለበት፤ ባ፲፬ ቍጥር ያነበበውን ከዚያው ባ፲፭ኛው ተርጕሞታል፤ ባለብሉዮች ግን ዘይቤውን ሳይሹ ዘሀሎ ወይሄሉ ብለው የምስጢር አፈታት ይፈቱታል። ያህና ይሆዋን ተመልከት፤ ከዚህ ጋራ አንድ ነው።
አኅደረ ፡ አሳደረ አስገባ፤ አኖረ አስጠጋ፤ አስቀመጠ። አብእ ነዳየ ወአኅድሮ ውስተ ጽላሎትከ። ሎጥ አኅዳሬ እንግዳ። ለእመ አኅደርከ ነኪረ ምስሌከ። ያኀስረከ ዘአኅደርከ። ወአኅደሮሙ ህየ ለደቂቀ እስራኤል ፡ (ኢሳ፶፰ ፡ ፯። ፍ ፡ ነ ፡ ፲፩። ሢራ፲፩ ፡ ፴፬። ፳፱ ፡ ፳፰። ፪ዜና ፡ ፰ ፡ ፪)።
አኅደገ ፡ አስተወ አስጣለ፤ ታደገ አዳነ፤ አፋታ። አኅደጉነ ዘነተ አሠረ። መኑ ያኅድገነ ፍቅሮ ለክርስቶስ። ከመ ታኅድጎ ለምታ እምእደ ዘባጢ። ሰአለቶ ለእኁሃ ከመ ያኅድጋ እምታ ወአኅደጋ ፡ (ኢሳ፴ ፡ ፲፩። ሮሜ፰ ፡ ፴፭ ፡ ፴፰። ዘዳ፳፭ ፡ ፲፩። ዮሴፍ)።
አህዳኢ መህድኢ እ ፡ ጸጥ የሚያደርግ፤ የሚያስታግሥ፤ አእኵቶ መህድኤ ንዴት ውእቱ ፡ (ፈላስ)።
አህድአ ፡ ጸጥ አደረገ ዝም አሰኘ፤ አስታገሠ አረጋጋ። በኀይሉ አህድኣ ለባሕር። ያሀድእ ሀውከ ሞገድ። አህድአ ህርቃኖስ ኵሎ አሕዛበ እለ ይጸብኡ ምድረ ይሁዳ ወሞኦሙ። አኀዙ አግብርቲሁ ይናዝዝዎ ወያህድእዎ። ወአህድኦሙ መልአከ ሰላም በቃሉ ፡ (ኢዮ፳፮ ፡ ፲፪። ተረ ፡ ቄር። ዮሴፍ። አክሲ)።
አህጐለ ፡ አጐለ፤ አስታጐለ አስቀረ። አጠፋ፤ አስጠፋ። ንጉሥ አብድ ያህጕል ሕዘቢሁ። ያሀጕሎሙ ለረሲዓን። ከመ አህጕሎሙ እምገጸ ምድር። ኀጢአት ነፍሶሙ ታሀጕል ፡ (ሢራ፲ ፡ ፫። ሔኖ፩ ፡ ፱። ፵፭ ፡ ፮። ምሳ፩ ፡ ፲፬)።
አህጓሊ ማህጐሊ ፡ (ሊት ልያን ያት) የሚያጕል አጓይ፤ አስታጓይ፤ አስተጓጓይ። አጥፊ አስጠፊ፤ ጐጂ ገዳይ አስገዳይ። ዝንቱ ደዌ ማህጐሊ። ዛቲ ኀጢአት ማህጐሊት። ፍትወት እኩይ፤ ማህጐሌ ነፍሳት። እመ መስሕት ወማህጐሊ አንተ ፡ (ፈ ፡ መ ፡ ፫ ፡ ፯። ፭ ፡ ፩። ዲድ፲፬ ፡ ፴፪)። ሞት ገሃነም በማለት ፈንታ ማህጐሊ ይላል። ሲኦል ወማህጐሊ ኢይጸግቡ ፡ (ምሳ፳፯–፳)።
አኅጥአ ፡ ኅጢአት አሠራ፤ አሳተ። አሳጣ አደኸየ፤ ባዶ አስቀረ። ከመ ያኅጥኦሙ ረባሐ። ምንተ አኅጣእኩከ። ወኢያኅጥኦሙ እምዘፈቀዱ ፡ (ፊልክ ፡ ፶። ፫ነገ ፡ ፲፩ ፡ ፳፪። መዝ
፡ ፸፯)።
አሕጸረ ፡ አሳጠረ አስቀጠረ፤ ዐጥር ቅጥር አሠራ፤ አስከበበ።
አኅጸረ ፡ አሳጠረ አሳነሰ። አነ ዘኣኀጽሮ ለዕፅ ነዋኅ። ወሶበ አኮ ዘአኅጸሮን ለእማንቱ መዋዕል። በአኅጽሮ ይኄይሱ ድርሳናት ፡ (ሕዝ፲፯ ፡ ፳፬። ማር፲፫ ፡ ፳። ተረ ፡ ቄር፳፩)።
አኅፀበ ፡ አሳጠበ አስቃጠበ፤ ውሃ ጨመረ ፡ (፬ነገ ፡ ፫ ፡ ፲፩)።
አኅጸወ ፡ አስጐመደ፤ አሰለበ አሰነጋ።
አሕፀየ ፡ አሳጨ፤ ማጫ አሰጠ።
አሕጸጸ ፡ ኦጐደለ፤ አስጐደለ፤ አሳነሰ፤ ከፈለ፤ ቀነሰ፤ ናቀ አቃለለ። ወይቤ አሐዱ እምጸሐፍተ ሐሳብ ዘሀሎ እምኍልቆሙ ለአይሁድ እለ አምኑ ወተጠምቁ ብእሲ ማእምረ ኦሪት ወመጻሕፍተ ነቢያት። ወውእቱ ቦአ ኀበ ቈስጠንጢኖስ ንጉሥ ወአይድዖ ከመ ካህናት አይሁድ አሕጸጹ እምዓመታተ ልደቶሙ ለአበው ቀደምት ዘይትዌሰክ ዐሠርተ ወኀምስተ ምእተ ፡ (ሺሕ ካ፭፻) ዓመተ ወፈቀዱ በዝብቱ ያብጥሉ ምጽአቶ ለክርስቶስ። ሰብዓ ዓመተ አሕጸጸ እምዐሠርቱ ምእት ዓመት። ሕቀ አሕጸጽኮ እመላእክቲከ። ግፍዕ ያሐጽጽ መዋዕለ። ተቀጸለ ጌራ ዐቢየ አሕጺጾ ጌራ ክህነት ቅዱስ ፡ (ጊ ፡ ሐ ፡ ገ፻፸፩። ኩፋ ፡ ፬። መዝ ፡ ፰። ፈላስ ፡ ገ፴፱። ዮሴፍ)።
አኅፈረ ፡ አሳፈረ፤ አሳዘነ። መጽሐፍ ግን በአኅፈረ ፈንታ አስተኀፈረ ይላል፤ ፍችው ፩ ነው፤ ካስደራጊነት አይወጣም። ኢታስተኀፍረኒ እምተስፋየ። ታስተኀፍር አባሃ። ግብር ዘያስተኀፍር። ገሥጽዎሙ ወአስተኀፍርዎሙ
፡ (መዝ ፡ ፻፲፰። ሢራ፳፪ ፡ ፭። ፍ ፡ ነ ፡ ፵፪። ቀሌ)።
አኅፋሪ ማኅፈሪ ፡ የሚያሳፍረ አሳፋሪ ፡ (ግንዘ)።
አሖሰ ፡ (ያሐውስ፤ ያሑስ) አስቸኰለ፤ አሳዘነ፤ አድራጊ። አስነቀነቀ፤ አስደራጊ።
አሖረ አስተ ፡ (ሕ) ሐወረ ፡ አስተ(ሕ) ሐወረ፤ አኼደ አስኼደ፤ ነዳ ወሰደ። ወአሖሩ ሠረገላቲሆሙ። አነ ኣንጐግዋ ወኣሐውራ በድወ። ያረተዕ መዝራዕተ እድ ይቡስ ወያሐውር እግረ ሐንካስ
፡ (፬ነገ ፡ ፱ ፡ ፳፩። ሆሴ፪ ፡ ፲፮። ቅዳ ፡ ዮሐ)። አሠራ አስደረገ።
አሖዘ አስተሐ(ሕ) ወዘ ፡ አጣመ አጣፈጠ፤ አሳመረ አሰማማ።
አለለ ፡ ቀለም አገባ፤–ዐልሎ ዐለለ።
አለም ፡ አለመለመ አረጠበ፤ አለሰለሰ አለዘበ። ያለመልሞ ለሥጋሁ ከመ ዘሕፃን። ወአለምለመት ነገራ
፡ (ኢዮ፴፭ ፡ ፳፭። ስንክ ፡ ሠኔ፴)።
አለምለመ ፡ አለመለመ አረጠበ፤ አለሰለሰ አለዘበ። ያለመልሞ ለሥጋሁ ከመ ዘሕፃን። ወአለምለመት ነገራ
፡ (ኢዮ፴፭ ፡ ፳፭። ስንክ ፡ ሠኔ፴)።
አለቅሐ ፡ አስለቃ አስበደረ፤ ከልቆ ከብድር አገባ።
አለቅት ፡ በቁሙ፤–ዐለቅት።
አለበወ ፡ አለበመ፤ ልብ አስደረገ፤ አሳሰበ አስታወቀ፤ አስተማረ። ፍኖተ ጽድቅከ አለብወኒ። ዕፅ እንተ ታሌቡ ሠናየ ወእኩየ። ኣሴብወእ ዘሀለወከ ትንብብ። ከመ ያለብዎሙ ለእስራኤል
፡ (መዝ ፡ ፻፲፰። ዘፍ፪ ፡ ፱። ዘፀ፬ ፡ ፲፪። ሢራ፵፭ ፡ ፲፯)።
አለበየ ፡ (ያሌቢ ያለቢ) አሳሳተ ፥ አጠፋ አበላሸ፤ ከንቱ አደረገ። እመኒ ይትቈጥዑ ዕልዋን እለ ያሌብይዋ ለሃይማኖት ፡ (ቄር ጰላ)። አለበየ በማለት ፈንታ አስተላበየ ይላል፤ ስሕተት ነው። ወዝሰ ዘይብሉ ደዌ አይሁድ ወአረሚ ዘያስተላብዩ ፍኖተ መስቀል ፡ (ቄር ፡ ጰላ)።
(ጥ) አለገ ፡ ድል ነሣ፤ ሰለበ፤–ዐልጎ ዐለገ፤ ዕልገት።
አሊቄ ፡ (ጽር አሊኪ) ጨው፤ ጨዋም፤ ባሕረ ጼው። ወኮነ ደወሎሙ እምነ ሊባ እስከ አሐዱ ኅብር ዘባሕረ አሊቄ
፡ (ኢያ፲፭ ፡ ፪)። አሎንን ተመልከት፤ አሊቄና አሎን አንድ ስም ነው ፡ (ዘፍ፲፬ ፡ ፫)።
አሊፍ ፎት ፡ ( አለፈ የአልፍ ይእልፍ። ዕብ አላፍ) መማር፤ ፊደል መቍጠር፤ አ አሌፍ ማለት። ማብዛት ማርባት፤ እልፍ ማድረግ፤ አ አንድ፤ እ እልፍ ማለት፤ የቍጥር።
አሊፍሎሳውያን ፡ (ጽርእ) ዐጸውተ አናቅጽ፤ የቤተ ክሲያን በረኞች።
(ጥላ) አላ ፡ (ዐረ ኢላ። ዕብ ኤላ) ዐቢይና ንኡስ አገባብ፤ ሥሩና ምንጩ አለለ ነው። እንጂ፤ ግን፤ ዋዌ፤ ዳግመኛ፤ ስ፤ ይኾናል፤ እንጂና ግን መደበኞች፤ የቀሩት ትርፎች ናቸው። ባለመጽሐፎች እንዳወራረዱ ሲፈቱ አላን ይለዋውጡታል፤ አላ ብርሃነ ሀበነ ሲል ፡ (ኪዳ) ዋዌ ዓዲ። አላ ብሁል ሊተ ሲል ፡ (አፈ ፡ ወ) ነገርስ። አላ አትሒቶ ርእሶ ነሥአ አርኣያ ገብር ሲል ፡ (ቆላ) የሌለውንስ ብለው ይፈቱታል። አኮ አንትሙ ዘኀረይክሙኒ አላ አነ ኀረይኩክሙ፤ እንጂ። ዝኒ ይከውን ሕዝበ ዐቢየ አላ እኁሁ ዘይንእስ የዐብዮ፤ ግን
፡ (ዮሐ፲፭ ፡ ፲፮። ዘፍ፵፰ ፡ ፲፱)። ፡ (ዕር፲፱ ፡ ቍ፹፩)።
አላኅልኀ ፡ አላላ ፥ ኦረገበ፤ አሰነፈ። ያላኀልኆ ለፈቃድ ወለኅሊና ፡ (ማር
፡ ይሥ፫ ፡ ፲፬)።
አላቲኖን ፡ (ጽር አላቲኖስ) አማን በአማን፤ እውነት በውነት
፡ (ቅዳ)።
አላዲ ፡ (ዲት ድያን ያት) የሚለቅም የሚሰበስብ ለቃሚ ሰብሳቢ። አላዲሁ ለዝንቱ መጽሐፍ
፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፲፭)።
አላዳስ ኤላድ ፡ (ጽር ሄላዶስ፤ ሄላዳ። ዕብ ያዋን) የግሬክ አገር ስም መላው። አንድ ታላቅ ደሴት፤ በግሬክ አገር ውስጥ ያለ
፡ (ኢሳ፷፮ ፡ ፲፱። ግብ፳ ፡ ፪። ስንክ ፡ ግን፱)። ከዚህ የተነሣ የግእዝ መጻሕፍት ደሴት ሲሉ አላዳስ ይላሉ፤ ስሕተት ነው። ለአላዳስ ወለአህጉር። ለባሕር ወለአላዳስ። በባሕር ወበየብስ በአሕቁል ወበአላዳስ
፡ (ክብ ፡ ነገ። መጽ ፡ ምስ) ዳግመኛም ዝብል ፀፍዕ ድኩዕ በማለት ፈንታ አላዳስ ይላል ፡ (ሉቃ፲፬ ፡ ፴፭)።
አላድ ፡ (ዐማርኛ) በቁሙ፤ የገንዘብ ስም፤ ወርቅ ብር ስመ ንጉሥ መልክአ ንጉሥ ያለበት፤ ግማሽ እኩሌታ ገንዘብ፤ ምሉ ያይዶለ። አርእዩኒ አላደ ዲናር
፡ (ማቴ፳፪ ፡ ፲፱)። የጽርኡ አብነት ግን፤ ወርቀ ጸባሕት ፥ ንዋየ ጸባሕት ይላል። ባለሐዲሶችም አላድን መልክእ ይሉታል።
አላዶር ፡ የቀኖት ስም፤ ኹለተኛ ቀኖት የቀኝ እጅ። አዴራን ተመልከት።
አላጸየ አስተላጸየ ፡ አስተላጸየ፤ አስላጨ።
አላፊ ፡ (ፊት ፍያን፤ ያት፤ አለፍት) አሌፍ የሚል ተማሪ፤ ፊደል ቈጣሪ።
አሌ ፡ (ዕብ አልላይ፤ ኦይ) ቃለ ብካይ ወዐውያት፤ ቃለ ተግሣጽ ወመዐት፤ ወዮ፤ ዋይታ፤ ወዮታ። አሌ ሊተ፤ አሌ ለከ፤ አሌ ሎቱ እያለ እንደ ወይ በለ ይዘምታል፤ ወዮልኝ ወዮልኽ ወዮለት ማለት ነው፤ ገና ወደ ፊት የሚመጣን መከራና ሐዘን ያሳያል። ወይን ተመልከት፤ የዚህ ጎር ነው፤ አሌ የግእዝ ፥ ወይ የዐረብና ያማርኛ። አሌ ለኪ ሀገር እንተ ንጉሥኪ ወሬዛ። አሌ ላ ለሰይፍ ኢየሩሳሌም በላዕሌሃ እስመ ውሕዘ ደም። አሌ ለክሙ ጸሐፍት ወፈሪሳውያን ፡ (መክ፲ ፡ ፲፮። ቅኔ። ማቴ፳፫ ፡ ፲፫)።
አሌለየ ፡ (አስለየ አስነጠለ፤ አለያየ)። ሌሊት አስነሣ፤ አነቃ አተጋ፤ አማለደ፤ ራሱን ወይም ሌላውን። ያሌሊ በጸሎት። አሌለየ ገዪሠ። አሌልዮ ጸሎት። አሌለየ እምህየ በነግህ ወአጽዐነ አድጎ። በጽባሕ ተንሥአ ወአሌለየ ጥቀ
፡ (ሉቃ፮ ፡ ፲፪። ፳፬ ፡ ፩። አፈ ፡ ተ፲፬። ኩፋ ፡ ፲፰። ማር፩ ፡ ፴፭)።
አሌፋት ፡ ፊደላት ከአሌፍ እስከ ታው ያሉ። መክብባቸው አሌፍ ስለ ኾነ በርሱ ስም አሌፋት ተብለው ይጠራሉ፤ በሆይ ሆህያት ተብለው እንዲጠሩ። አሌፋት ወግናያት
፡ (አዋል)። እሊህም ፳፪ቱ አሌፋት እግዜርንና አዳምን መደብ አድርገው ከሰማይ እስከ አዳም ያሉ ፳፪ቱን ሥነ ፍጥረትና ከሴት እስከ ያዕቆብ ያሉ ፳፪ቱን አርእስተ አበው የሚያሳስቡ ስለ ኾኑ፤ ኤርምያስና ዳዊት ፬ ፡ ፬ ጊዜ መላልሰው በመሥመር በመሥመር እያገቡ የቃል መነሻ አድርገዋቸዋል ፡ (ሰቈ፩
፡ ፩–፳፪። ፪ ፡ ፩–፳፪። ፫ ፡ ፩–፷፮። ፬ ፡ ፩–፳፪)። ፡ (መዝ፳፬ ፡ ፩–፳፪። ፴፫ ፡ ፩–፳፪። ፻፩ ፡ ፩–፲። ፻፲፩ ፡ ፩–፲)። በ፻፲፰ኛው መዝሙር ግን ለየብቻቸው አንዳንድ መዝሙር እየኾኑ በሰፋፊና በረዣዥም ቃሎች ስለ ገቡ ፥ ለያንዳንዱ ፰ ፰ ቍጥር አላቸው፤ የመላው ፻፸፮ ይኾናል።
አሌፍ አልፍ አልፋ ፡ ፊደል፤ ስመ ፊደል አ። አሌፍ፤ የዕብራይስጥ፤ አልፍ የግእዝና የዐረብ፤ አልፋ የጽርእ አጠራር ነው። አሌፍ ላም በሬ የቀንድ ከብት። አልፍ ፋ፤ ቀንድ የበሬ ራስ። ምስጢሩ ፥ ቀዳማይ ርእስ በኵር ጥንት። አባግዐኒ ወአልሕምተ ባለው ዕብራይስጡ ጾኒ ወአላፊም እንዲል አልሕምተ ሲል ፡ (መዝ፰ ፡ ፯)። ቀዳማዊነቱም፤ በተፈጥሮ ከሰው እንስሳ፤ ከፍጥረት ፈጣሪ እንዲቀድም እንደዚያ ማለት ነው
፡ (መዝ፻፲፰ ፡ ፩)። ወእምዝ ትብል አሌፍ እስከ ላሜድ። እምአሌፍ እስከ ታው። ሆህያተ አልፋ። ሆህያተ ጽርእ እምአልፋ ወቤጣ ወጋማ ፡ (ግንዘ። ቄድር ፡ አፈ ፡ ድ፱። ሥር ፡ ጳኵ)።
አል ፡ (ዕብ አል) አሉታ፤ በቁሙ አል። ባማርኛ፤ አልበላም አልጠጣም፤ አልገባም አልወጣም፤ አልኼደም አልመጣም እያለ በኹሉ ይገባል፤ በረ ግስ ላይ ሲገባ ለና ረ ተወራራሾች ስለ ኾኑ፤ ረ ልን እየዋጠ ይጠብቃል። ረባ ረጋ ረሳ፤ አረባም አረጋም አረሳም። በጥፈትም ባነጋገርም አልረሳም አያሰኝም፤ አለዚያ ጥፈትና ቋንቋ ይበላሻል። በግእዝ ግን ከበ በቀር በሌላ ፊደል አይገባም፤ ይህም ቦ ቦቱ፤ አልቦ አልቦቱ፤ አልባ አልባቲ፤ አልብከ ኪ፤ አልብየ ነ። አልቦሙ ቦን፤ አልብክሙ ክን ማለቱን ያሳያል። ባለቅኔዎች ግን ያውም ሊቃውንቱ ብሉይ ተሐዲስ የሚያስማሙቱ፤ ቦና አልቦ ቀተለ ኢቀተለ እንደ ማለት ያለ ሲኾን፤ ጽድቅና አሉታ በመኾኑ ኹለት ልዩ አንቀጽ መስሏቸው ኹለቱንም ባንድ ቅኔ ውስጥ ያገቡታል። ፡ (መወድስ ዘድንቆ ማርቆስ)። ለዘጐየ ሰብእ እምገጸ አንበሳ ኮኖ ዕጹበ ሶበ ተኵላ ገዳም ረከቦ፤ ወአመ ውስተ ቤት ቦአ ተረክቦተ አርዌ ዐጸቦ። ንብረተ ዝንቱሰ ይመስል ንብረተ አዳም በሲኦል እንዘ ቦ፤ እስከ መንገሌከ ትቀጽቦ፤ ሥሉጠ ልደት ክርስቶስ ወመሥዋዕተ አብ ዘዲበ ጸልቦ። እምዝኒ እሰምየከ ምክንያተ ኵሉ የብቦ፤ ዘመድ ጽሩየ ፍቅር እንበሌከ እስመ አልቦ፤ እመኒ ትሁቦ ዕረፍተ ወሀብተ መከራ ትሁቦ፤ እምርእስየ ለርእስየ አንተ ትቀርቦ።
አልሐመ ፡ አላመ፤ አስላመ፤ ሰለመንና አስለመን እይ
፡ አጸና አባሰ። አልሐሙ በእንተ ተጻብኦቱ ክቡተ ወገሃደ። በእንተ ዝኬ ያልሕሙ ሰይጣናት ተጻብኦቶሙ። አልቦ ዘበቍዓ ዘእንበለ ዘአልሐማ ፡ (ፊልክ ፡ ፳። ፸። ማር፭ ፡ ፳፮)።
አልኈሰ አልኈሰሰ ፡ ሹክ ሹክ አለ፤ መላልሶ አብዝቶ። አብሠራ ገብርኤል ለማርያም አልኈሲሶ በእዝና ወይቤላ፤ ትወልዲ ወልደ። ሙባኡ ለቃል እዝና ርኅው፤ ወሙፃኡ ማሕፀና ዕጽው ፡ (መዋሥ። ቅኔ)
፡ ደገመ ደጋገመ፤ አልከሰከሰ አውተፈተፈ፤ ቃሉን ሳያሰማ ምላሱን ከንፈሩን በማንቀሳቀስ፤ የጸሎት የአስማት።
፡ (ተረት) ዳዊት በሹክሹክታ፤ ሳታት በጋጋታ።
አልሀቀ ፡ አላቀ አሳደገ፤ ታላቅ አደረገ። ውሉደ ወለድኩ ወአልሀቁ። ቀላይ አልሀቆ። እስመ ኪያከ አልሀቀ እግዚ ፡ (ኢሳ፩ ፡ ፪። ሕዝ፴፩ ፡ ፬። ዳን፩ ፡ ፶)
፡ አስረጀ አሸመገለ፤ ዕድሜ ሰጠ። ወይእዜኒ አልሀቀኒ እግዚእ በከመ ይቤ ፡ (ኢያ፲፬ ፡ ፲)።
አልሃቂ ፡ መልሀቂ፤ መልህቅ) የሚያልቅ፤ አሳዳጊ።
አልሀበ ፡ አነደደ ፥ አቃጠለ፤ አሞቀ አተኰሰ፤ አላበ አወዛ። ለተጋብኦ ብዙኅ በቍዔት፤ ወውእቱ ዘያልህቦ ለእሳተ ፍቅር። አልሀበ እቶነ። አልሀበቶ ፀሓይ ርእሶ ለዮናስ ፡ (አፈ ፡ ተ፲፱። አዋል። ስንክ ፡ መስ፳፭)።
አልሐኰ ፡ አሠራ፤ አስፈጠረ።
አልሐወ አላሐወ ፡ አሳዘነ፤ አስለቀሰ። ሣቀይዋ ወአልሐውዋ ፡ (ራእ፲፰ ፡ ፯)።
አልሐፈ አስተልሐፈ ፡ አሳዘነ፤ አስጨነቀ። ዘኅቡእሰ ኢያስተልሕክፍከ ፡ (ሢራ፫ ፡ ፳፪)።
አልሕሐ ፡ አልሕሐ፤ ፡ (ሱር ላሕሌሕ) አራሰ አረጠበ፤ አለዘበ። እፍ እፍ ፥ እንትፍ እንትፍ፤ ወይም እፍፍ ፥ እንትፍትፍ አለ፤ ለማብረድ ለማንደድ። ዘያልሕሓ ለትዝኅርቱ ያነድዳ ለእሳት
፡ (ሢራ፳፰ ፡ ፲፩)።
አልሖሰሰ ፡ ሹክ አለ፤–ለኊስ ለኈሰ አልኈሰሰ።
(ጥ) አልሎ ሎት ፡ (አለለ ይኤልል የአልል። ዕብ አሌል) መሻት መፈለግ፤ አይቴ ቤተ ዘማ ማለት፤ ማመንዘር መቀንዘር፤ መዝለል መከመር፤ የተባት። እልል ማለት እንቍራሪትኛ መጮኽ የእንስት።
አልመደ ፡ አለመደ፤ አስለመደ፤ አስተማረ አሳወቀ። ኢታልምዶ መሐላ ለአፉከ። አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ያለምዱ። አልምዳ ለነፍስከ ትዕግሥተ ላዕለ ኵሉ መከራት ፡ (ሢራ፳፫ ፡ ፱። ቅዳ ፡ ሕር። ፈላስ ፡ ፳፯)። በለመደና በልማድ ፈንታ አልመደ ይላል፤ አያሰኝም። ዘከመ ያለምድ ፡ (ዘኍ፳፬ ፡ ፩። ማር፲ ፡ ፩። ኪዳ)። በአልመደም ፈንታ ለመደ ይላል፤ ስሕተት ነው። ንሕነሰ ኦንለምድ ወኢቤተ ክርስቲያኑ ፡ (፩ቆሮ ፡ ፲፩ ፡ ፲፮)።
አልመጸ ፡ አለመጠ፤ አላመጠ። ለምጣም አደረገ፤ አለዘበ አለሰለሰ። መደመደ ፥ ደለደለ፤ አስተካከለ። ከመ ያልምጹ ጐጻጕጸ ፡ (ዮሴፍ)።
አልስሐ ፡ አላሸ ፥ ዐልጫ አደረገ፤ አደከመ አሰነፈ፤ አስናቀ አስነቀፈ። አልስሕ ሕምዘ ዘከዐወ ቀታሊ። በሃይማኖተ ዚኣሁ አልስሐ ኵሎ መዋቅሕቲሁ። ወዘሰ ይነብብ በከመ ረከበ ያለስሕ ርእሶ፤ ወአልቦ ሞገስ ለቃሉ። ያለስሓ ለምክሮሙ
፡ (ግንዘ። ድጓ። ሢራ፳ ፡ ፳፱። ኢሳ፵፬ ፡ ፳፭)።
አልሻዳይ ፡ ስመ አምላክ፤–ሰደየ።
አልቀሰ ፡ አስለቀሰ፤ አሳዘነ። ባማርኛ ግን አድራጊ ነው።
አልበሰ ፡ አለበሰ፤ ከደነ ፥ ሸፈነ። ኣለብሶ አልባሲከ። አልበስከኒ ማእሰ። አልበሱ ምሥዋዐ ሠቀ ፡ (ኢላ፳፪ ፡ ፳፩። ኢዮ፲ ፡ ፲፩። ዮዲ፬ ፡ ፲፩)። አስለበሰ፤ አስከደነ። አስደራጊ።
አልበጠ ፡ አስለበጠ፤ አሸፈነ። ወአልበጦ ለውእቱ ቤት በወርቅ ጽሩይ ፡ (፪ዜና ፡ ፫ ፡ ፯–፲። ፱ ፡ ፲፯)። አጽንዐ ጸወናቲሁ በማለት ፈንታ ፥ አልበጠ መዛግብቲሁ ይላል፤ የመላሽ ስሕተት ነው ፡ (፪ዜና ፡ ፲፩ ፡ ፲፩)።
አልባስጥሮስ ፡ (ጽር አላባስትሮስ) የሽቱ ቢልቃጥ፤ የብርሌ የብርጭቆ ዐይነት፤ ጥሩ ሽቱ ያለበትና የመላበት፤ እንዳይተነፍስ ታትሞ ተገጥሞ የሚኖር ፡ (ማር፲፬ ፡ ፫። ሉቃ፯ ፡ ፴፯)።
አልቦ [1] ፡ (አል ቦ) የቦ አሉታ፤ የለም አልኖረም፤ አልነበረም፤ የቦን አፈታት ተመልከት። አልቦ ነገር ወአልቦ ነቢብ
፡ (መዝ ፡ ፲፰)።
[2] ፡ (ዐማርኛ) በቁሙ፤ የእግር ጌጥ ሽልማት፤ ግርጃ ድኰት፤ ጥምዝ፤ የብር ዶቃ፤ ከወይዛዝር በቀር በማንም ሴት እግር የማይገኝ፤ ሴቶች ኹሉ የማያደርጉት። ፡ (ግጥም) አንጥረኛው ብዙ በቴዎድሮስ ቤት፤ ባላልቦ አደረጉት ይኸን ሁሉ ሴት
፡ (ባል አልቦ፤ አለባል)።
አልቦቱ ፡ (አል ቦቱ) የለውም፤ የለበትም፤ አልኖረውም፤ አልነበረውም፤ አልነበረ(ለ) በትም። አልቦቱ ጥንት ወኢተፍጻሜት
፡ (ቅዳ)።
አልትሐ ፡ አጐረሠ፤ አስጐረሠ ፥ አስጐነጨ፤ አስከተተ ፥ አስገባ።
አልዐለ ፡ አነሣ፤ አስነሣ፤ ከፍ ከፍ አደረገ፤ ወደ ላይ አወጣ አሳረገ፤ አላቀ አበለጠ፤ አከበረ አገነነ፤ አመሰገነ። ኣሌዕል እደውየ ኀበ እግዚ ልዑል። ዘያሌዕለኒ እምአናቅጸ ሞት። ኣሌዕለከ ንጉሥየ ወአምላኪየ
፡ (ዘፍ፲፬ ፡ ፳፪። መዝ ፡ ፱። ፻፵፬)። ፈነወ ሰፍሐ በማለት ፈንታ አልዐለ ይላል፤ ስሕተት ነው። ዮጊ ያሌዕል እዴሁ ወይነሥእ። አልዐለ እዴሁ ወነሥአ መጥባሕተ ፡ (ዘፍ፫ ፡ ፳፪። ፳፪ ፡ ፲። ፩ነገ
፡ ፲፬ ፡ ፳፮። ፳፪ ፡ ፲፯)። ዳግመኛም በአልዐለ ፈንታ አስተል(ለ) ዐለ ይላል፤ ፍችው አንድ ነው ፥ ከዚያው ካድራጊነት አይወጣም። ናስተልዕል ዕበዮ ወንነግር ግብሮ ፡ (አፈ ፡ ተ፳፰)።
አልዓሊ መልዐሊ መልዕል ፡ (ልት ላን ላት) የሚያነሣ፤ ከፍ ከፍ የሚያደርግ፤ የሚያሳድግ፤ አሳራጊ። እግዚአብሔር መልዐሌ ትሑታን። ክብርየ ወመልዕለ ርእስየ
፡ (መቃ ፡ ገ፲፯። መዝ ፡ ፫)። በመልዕል ፈንታ ምልዓል ይላል፤ አያሰኝም
፡ (አርጋ)።
አልክአ ፡ አስለካ፤ አስጣፈ አሳተመ። እመ ነታዕክሙ አልካእክሙ ለክሙ ዝንጓጔ ህልወ ፡ (ዮሴፍ)።
አልከወ ፡ አፈዘዘ። አልከወኒ ወጸለለኒ አዕይንትየ ፡ (ኢዮ፲፮ ፡ ፲)። ዕብራይስጡ ግን ያበልኅ ብየ አዕይንቲሁ ይላል፤ ማፍጠጥና ማጕረጥ ያሳያል።
አልከፈ ፡ አለከፈ፤ አቀመስ። አስለከፈ አስነካ። አልከፈኒ ውስተ አፉየ ወይቤለኒ፤ ናሁ ለከፈከ ዝንቱ ከናፍሪከ ፡ (ኢሳ፮ ፡ ፯)።
አልያጦን ፡ (ጽር አሊዬቶስ) የባሕር አሞራ ዓሣ የሚያድን የሚለቅም። ባለብሉዮች እባብ ዋጭ ይሉታል። በአሶር ቋንቋ ኑን የሚባል የባብ ዐይነት ዓሣ አለና፤ ምስጢሩ ከዚያው ይገባል፤ የኖንን አፈታት ተመልከት
፡ (ዘሌ፲፩ ፡ ፲፫። ዘዳ፲፬ ፡ ፲፪)።
(ጥ) አልዶ ዶት ፡ (አለደ ይኤልድ የአልድ) መልቀም መሰብሰብ መከመር፤ መካብ መደርደር፤ በላይ በላዩ መጨመር ካንድ ላይ መቈለል፤ መጐቸት ማከማቸት
፡ (ዘኍ፲፩ ፡ ፰። ዘፀ፭ ፡ ፲፪። ዘፍ፴፩ ፡ ፵፩)። ላዕለ እስጢፋኖስ አይሁድ አለዱ እብነ፤ ወውእቱ ወግረ ስምዕ ኮነ። አለደቶን ውስተ ፍኖት ለብዙኃት አንስት ከመ ይጽዐላሃ ለማርያም
፡ (ቅኔ። ዮሴፍ)።
አልጐመ ፡ አስለጐመ ፥ አስጐረሠ፤ ዝም አሰኘ አፍ አሲያዘ። ባማርኛ ግን ዐጕል አንቀጽ ነው፤ ዝም አለ ያሰኛል። አልጕም፤ ክፋ ዝምተኛ።
አልጸቀ ፡ አለጠቀ፤ አስለጠቀ። አስጠጋ፤ አቀረበ። ታለጽቆሙ ለርሑቃን
፡ (ቅዳ ፡ ዮሐ)። ዳግመኛም አብጽሐ አቅረበ በማለት ፈንታ ፥ አልጸቀ አስተልጸቀ እንደ ማለት ኹሉ ፥ ባደራራጊ አስተላጸቀ ይላል፤ ስሕተት ነው። በተቃርቦ አስተላጸቀ ለርእሱ ካልአ ብእሴ። ተዓርኮ ከመ ዝ ውእቱ፤ ዘየአምኖ ለፍቁሩ ወያስተላጽቆ በፍሥሓ ወኢይትዔበይ ላዕሌሁ። እለ ያስተላጽቁ ሰንበታተ ሐሰት። እመ አስተላጸቅሙ ወአዝለፍክሙ ኀልዮ ፡ (ቄር ፡ ጰላ። ፈላስ ፡ ገ፲፭። ዓሞ፮ ፡ ፫። አፈ ፡ ድ፴፫)።
አልፋ [1] ፡ ስመ አምላክ፤ ቀዳማዊ
፡ (ራእ፩ ፡ ፰። ፳፩ ፡ ፮። ፳፪ ፡ ፲፫)። ክርስቶስ አልፋ። በሥምረተ አልፋ። ሰላም ለርደትከ ጰራቅሊጦስ አልፋ ፡ (ስንክ ፡ ጥር፳፬። መጋ፲፪። ግን፲፰)።
[2] ፡ ቅድስት ሥላሴ፤ አ አብ፤ ል ወልድ፤ ፋ መንፈስ ቅዱስ። ምስጢሩ ግን ያው ቅድምና ነው፤ አይለወጥም። ኢይቀድም አሐዱ እምካልኡ ወካልኡ እምሣልሱ። አሐቲ ቅድምናሆሙ ለሥላሴ
፡ (ሃይ ፡ አበ)።
አሎን [1] ፡ (ጽር አሎስ) ጨው። ባሕረ አሎን፤ ባሕረ ጼው
፡ (ኢያ፫ ፡ ፲፮። ፲፪ ፡ ፫)።
[2] ፡ አሎን፤
፡ (ዕብራ፤ ብ አሎኒም) የዛፍ ስም፤ እንደ ባንባ እንደ ዋርካ ያለ ታላቅ፤ የወፍራም ቀሊል፤ መቅዘፊያ የሚኾን የባሳን ዛፍ ፡ (ሕዝ፳፯ ፡ ፮)።
አመ ፡ ፥ ፡ (ዐቢይ አገባብ) በ ጊዜ፤ የ። በና ጊዜ አንድ ወገን ናቸው፤ የ ሲኾን ደግሞ ጊዜነቱ አይቀርም፤ እንደ ዘ ይዘረዝራል። አመ አሚሩ፤ አመ ዕለተ ደይን። አመ ሞትኩ ቅብረኒ። ይበጽሕ መዋዕል አመ ይብሉ ብፁዓት መካናት እለ ኢወለዳ። አልቦ አመ ኢሀሎ ወአልቦ አመ ተኀጥአ ፡ (ማቴ፲፩ ፡ ፳፪። ጦቢ፬ ፡ ፫። ቅዳ ፡ ግሩ)። አንዳንድ ሰዎች እንዘ ይኾናል ይላሉ፤ ምስክራቸው አያጠግብም። ፲፱ኛ ዕርከን ፸፯ ቍጥር ተመልከት።
አመልትሐ ፡ ፊት አስመለሰ፤ አሳፈረ፤ ወይም በጥፊ አስመታ።
አመልዐ ፡ አስኬደ፤ አስቸኰለ ፥ አነሣሣ።
አመልአከ ፡ አለቃ ሾመ፤ አለቃ አደረገ፤ መልአክ አሰኘ። መልአከ ፀሓይ ፥ መልአክ ብርሃን ፥ መልአከ ገነት እንዲሉ።
አመምዐ ፡ አሸበረ፤ አስጨነቀ። እፎ ተስዕረ ዘያሜምዕ ፡ (ኢሳ፲፬ ፡ ፬)።
አመሥረተ ፡ አስመሠረተ፤ መሠረት አስጣለ።
አመስቀለ ፡ አመሳቀለ፤ መስቀል አደረገ።
አመስጠረ ፡ (ሰጠረ) ምስጢር አደረገ፤ ሰወረ ደበቀ፤ አረቀቀ። ነጽርኬ ዘከመ አመስጠረ እሎንተ በአሐቲ ቃል። አመስጠረ ፍካሬሁ። በአመስጥሮ ፡ (አፈ ፡ ድ፫ና ፡ ፰። መጽ ፡ ምስ)።
አመራሮ ፡ መራራ የደጋ ዕንጨት፤ ወይም ቀላዎ ውስጠ ክፍት።
አመርዐወ ፡ አወየዘረ፤ አስወየዘረ፤ ወይዘሮ አደረገ፤ አስደረገ፤ ሸለመ አስጌጠ አንቈጠቈጠ። አመርዓዌ አረፍት
፡ (ፊልክ ፡ ፻፳፮)።
አመርግሐ ፡ ናደ ፈነቀለ፤ አንከባለለ፤ ገፋ መርግ ሰደደ። አመርግሑ እብነ ላዕሌሆሙ
፡ (ዮዲ፮ ፡ ፲፪)።
አመበለ ፡ አሠለጠነ፤ ሾመ ወከለ። ወአመበሎ ዲበ ኵሉ ቤቱ ፡ (ኩፋ ፡ ፵)።
አመት [1] ፡ (ብ አእማት። ዕብ አማህ። ሱር አምታ። ዐረ አመት) ሴት ባሪያ፤ ገረድ፤ ደንገጥር። አመት እንተ ትነብር ዲበ ማሕረጽ። ለሠዪጠ ገብር ወአመት። አግብርት ወአእማት
፡ (ዘፀ፲፩ ፡ ፭። ኩፋ ፡ ፲፩። ዘፍ፴፪
፡ ፮)።
[2] ፡ አመት፤–በቁሙ፤–ዓመት።
አመነነ ፡ አስመነነ ፣ አስናቀ። ዘያሜንን ወይነ ፡ (ስንክ ፡ ጥር፲፩)።
አመነየ ፡ አስመኘ አስጐመዠ። ኪያሁ አመነየት መአነበየት። ዘያሜኒ ኵሎ ወያስተሴፉ ፡ (ቅዳ ፡ አት። ደራሲ)።
አመንሰወ ፡ (አንሰወ) አስፈተነ፤ አስሞከረ፤ አስጠፋ።
አመንተወ ፡ አመነታ፤ አስመነታ ፥ መንታ አሶለደ።
አመንክዮስ ፡ የመናፍቅ ስም፤ ማኒ መነናዊ፤ ምትሀት ጽላሎት የሚል። እስመ ሥጋ ፀረ አመንክዮስ
፡ (ቄር)።
አመንኰሰ ፡ አመነኰሰ፤ አስኬማ አለበሰ። ሰአለቶ ከመ ያመንኵሳ ፡ (ስንክ ፡ ታኀ፲። ሚያ፲፩)።
አመንዘዘ ፡ አመነቸከ፤ አጥብቆ ያዘ ፥ አስጨነቀ አስቸገረ፤ በነገር። ያቴክዝዎ ወያመነዝዝዎ። ወበከንቱ አመንዘዝዋ ለነፍስየ። አኀዙ ያመንዝዝዎ ወይትቀየምዎ ፡ (ሢራ፳፭ ፡ ፲፰። መዝ ፡ ፴፬። ሉቃ፲፩ ፡ ፶፫)።
አመንደበ ፡ አስመነደበ አስቈረጠ፤ አስመታ አስደበደበ።
አመከረ ፡ አስሞከ፤ አስፈተነ።
አመኵሰየ ፡ (ያመኰሲ ያመኵሲ) አሞካሸ፤ ሞክሼ አደረገ።
አመክሐ አስተመክሐ ፡ አስመካ፤ አስከበረ፤ አኰራ አስታበየ። አልበሶ ወአስተመክሖ በኵሉ። አንስት ኢይልበሳ ወርቀ ዘተገብረ በልብስ ዘያስተሜክሕ ፡ (ሢራ፵፭ ፡ ፰። ፍ ፡ ነ ፡ ፳፫)።
አመክነየ ፡ አመካኘ፤ ምክንያት ሰጠ፤ ዋሸ። ለእመ ቦ ዘተርፈ ቦቱ ምክንያት ዘያመከኒ በእንተ ርእሱ። ምንተ ታመከንዩ ወታወሥእዎ ለእግዚ። እስመ አልቦ ውስተ ህላዌሁ አመክንዮ ፡ (ዮሴፍ። ዲድ ፡ ፲፪። ፪)። አንዳንድ መጽሐፍ በአመክነየ ፈንታተመክነየ ተመካነየ ይላል፤ ስሕተት ነው። እስመ ዕልዋን ይትመከነዩ በዝንቱ ስም ፡ (ዘውእቱ ክርስቶስ) ከመ ይኂጥዎሙ ለየዋሃን። አየ ምክንያተ ንትመከነይ፤ እስመ አልብነ ፍርሀት። እመ ቦ ዘተጸውዐ ኀበ ጉባኤ ኢያስተቃልል ለበጺሕ ዘእንበለ ለእመ ተዳደቆ ተመክንዮት ዕዉቅ፤ ወይጽሐፍ መልእክተ እንዘ ይነግር ተመክንዮቶ። ተመካነየ ላዕሌሁ ሰይጣን ፡ (አፈ ፡ ተ፰። ድ፲። ፍ ፡ ነ ፡ ፭። ስንክ
፡ የካ፫)።
አመክዐበ ፡ (ከዐበ፤ ከዓቢ መክዕብ) ዐጠፈ ደረበ፤ ዕጥፍ አደረገ። አኀዙ ያመክዕቡ ላዕሌሁ ጾመ ወጸሎተ። ወአመክዐብኪ ፍናወኪ
፡ (ፈ ፡ መ ፡ ፫ ፡ ፯። ኤር፪ ፡ ፴፮)።
አመዝበረ ፡ አፈረሰ፤ አስፈረሰ፤ አስጠፋ። አህጉረ ጽኑዓተ አመዝበረት። ያማስኖ ወያመዘብሮ ነኪር። ግፈዕ ያመዘብር አብያተ ወያሐጽጽ መዋዕለ ፡ (ሢራ፳፰ ፡ ፲፱። ኢሳ፩
፡ ፯ ፈላስ
፡ ገ፴፱)።
አመዝገነ ፡ (አስደራጊ) አስመሰገነ፤ ምስጉን አሰኘ።
አመዝጋኒ ፡ የሚያስመሰግን፤ አስመስጋኝ። ልማዱ ግን አድራጊነት ነው። ሰብእ አመዝጋንያን ፡ (ፈላስ ፡ ገ፳፬)።
አመየነ አስተመየነ ፡ አስተነኰለ፤ ተንኰል አስተማረ።
አመድረወ ፡ ከምድር አስገባ፤ አስከተተ።
አመገበ ፡ አስመገበ፤ አስጠበቀ ዐደራ ሰጠ፤ ሾመ አሠለጠነ፤ መጋቢ አደረገ። መጋቢ ዘአመገብዎ። እግዚ አመገበከ ትቅትል ወታሕዮ። ኣሜግቦ ምግበከ። ኢታመግብ ነኪረ ላዕለ ቤትከ ፡ (ፈ ፡ መ ፡ ፭ ፡ ፲፬። መቃ ፡ ገ፫። ኢሳ፳፪ ፡ ፳፩። ሢራ፳ ፡ ፳)።
አመግደመ ፡ አግድሞ አየ፤ የተንኰል የክፋት የንቀት የስርቆት አተያይ።
አመጐጸ ፡ (ያሜጕጽ ያመጕጽ) አስቈጣ፤ አስነቀፈ። አስደራጊ ነው፤ ፫ኛ አካል ያሳያል።
አመጽለወ ፡ አጠወለገ፤ አሳፈረ፤ አነወረ፤ ነቀፈ፤ አጸየፈ፤ ሰደበ። አመጽሉ ገጾ ለነሣኤ ገጽ ፡ (አፈ ፡ ተ፭)። ይኸውም ስለ ሃይማኖት ነው፤ ስለ ሌላ አይዶለም
፡ (ሉቃ፳፬ ፡ ፳፭። ግብ፯ ፡ ፶፩–፶፬። ፳፫ ፡ ፫)።
አሚር አሜር ፡ (ጽር ኢሜራ። ቅብጥ አሜሪ) መዓልት፤ ፀሓይ መጋቤ መዓልት፤ ዕለት ጊዜ ወራት፤ አንድ። ኵሎ አሚረ፤ ኹል ቀን፤ ኹል ጊዜ፤ ዘወትር ፀሓይ በሠረቀ ቍጥር። ውእተ አሚረ፤ ያን ቀን፤ ያን ዕለት፤ ያን ጊዜ፤ ወይም በዚያ ቀን በዚያ ወራት። አመ አሚሩ ለመስከረም፤ በመስከረም ባንድ ቀን፤ የመባቻ ለት። ሰላም ለመልክእኪ ዘተሰርገወ አሚረ ዘያበርህ ወትረ። እንተ ተሰደ በእግረ አሚር
፡ (ደራሲ። ራእ፲፪ ፡ ፩። ጥበ፪ ፡ ፬)። ባላገባቦች አሜር አስፌር ?ምና ይኾናል ይላሉ፤ ምስክር የለውም።
(ላ) አሚር ፤ ሮት
፤ (አመረ
የአምር ይእ)
ማወቅ ፤
መረዳት ፤
ድርሱን ርግጡን
ማግኘት። መውደድ
፤ ወደ
ሴት መግባት።
ሠነየ ቀደወ
ብሎ አማረ
ማለት ዐማርኛው
ከዚህ የወጣ
ነውና ፤
አሚር ማማር
ይኾናል። መጽሐፍ
ግን በአመረ
ፈንታ አእመረ
ይላል ፥
አያሰኝም ፤
አድራጊውን ባስደራጊ
አንቀጽ ማርባት
ፍጹም ስሕተት
ነው። የወዲያኛው
ትግሬ ሐባብ
እንኳ ዐወቀ
ሲል አመረ
እንጂ አእመረ
አይልም ፤
ይህን የመሰለ
አእኰተ አዕረፈ
ሌላም ብዙ
ስሕተት አለ።
የፊደልን ተራ
ያፋለሱና ያቃወሱ
ሰዎች ፤
አባቶቻችንም ሳይቀሩ
ግሱን እንደ
ቅኔ ስላስኬዱት
፤ የቋንቋውን
ሥር መብቀያውንና
መነሻውን መንገዱንና
አካኼዱን ፈጽመው
አላገኙትም ፤
ብህለንና ይቤን
ተመልከት። ‹‹የሴም
ቋንቋ ግስ
እንደ አዳም
አርኣያ ሥላሴ
ነውና ፥
ዘሩ ሥረ
ነገሩ ከሦስት
ቅንጣት ፊደል
አይወጣም›› ፤
አእመረ ግን
ለግእዝ ቋንቋ
የርባ መዠመሪያ
መኾኑ ስሕተቱና ስሕተትነቱ ስላልታወቀ ነው።
አሚን ፤ (ዐረ
አሚኑ) ፤
ስም ፤ እሙን
ማለት ነው
(ራእ፫ ፡ ፲፬)።
አሚን ኖት
፡ (አምነ የአምን ይእመን ይእ። ዕብ አማን። ዐረ አሚነ። ሱር ሃይሜን) ማመን መቀበል፤ ተስፋ ማድረግ፤ አለመጠራጠር፤ መናዘዝ እውነት መናገር መመስከር፤ እወ አማን ማለት። ጻድቅአ በአሚን የሐዩ። የዋህ የአምን ኵሎ ነገረ። ኢትእመንዎሙ ለአኀዊክሙ። አምነ ወኢክሕደ። አምኑ ወተኰነኑ። ዘአምነኒ በገጸ ሰብእ አአምኖ አነኒ በገጸ አቡየ ፡ (ሮሜ፩ ፡ ፲፯። ምሳ፲፬ ፡ ፲፭። ኤር፱ ፡ ፬። ዮሐ፩ ፡ ፳። አስቴ ፡ ፩። ዲድ ፡ ፳፭)። አምኖ ማመስገን፤ መውደድ መፍቀድ። መኑ የአምነከ። ዘበአሚንክሙ ፡ (መዝ፮ ፡ ፭። ፳፱ ፡ ፲፪። ዘዳ፲፪ ፡ ፮ ፡ ፲፯)። በአምነ ፈንታ ተአመነ ይላል፤ ስሕተት ነው፤ ተ ያማርኛ እንጂ የግእዝ አይዶለም። መኑ ተአመነ በእግዚ ወተኀፍረ። ኢትትአመኖ ብዙኀ። ኢትትአመን ኵሎ ቃለ ዘነገሩከ። ቴዎዶስዮስ ተአማኒ በጽድቅ። እትአመነክሙ ከመ ትፈጽሙ። ነአምን ወንትአመን። እንዘ ይትአመኑ ኀጣውኢሆሙ ፡ (ሢራ፪ ፡ ፲። ፮ ፡ ፯። ፲፱ ፡ ፲፭። ሃይ ፡ አበ። ሮሜ፲፭ ፡ ፲፬። ቅዳ። ማቴ፫ ፡ ፮)።
አማኂ ፡ (ኂት ኅያን ያት) እጅ የሚነሣ፤ የሚሳለም፤ እጅ መንሻ ሰላምታ ሰጭ አቅራቢ።
አማህረከ ፡ (ያማሀርክ) አስማረከ፤ አዘረፈ።
አማኅበረ ፡ (ዲቃ ግ) ሰበሰበ፤ ማኅበር ሠራ፤ ጉባኤ አደረገ፤ ሸነጓ። ዘአፍጠንክሙ ለተጋብኦ ወለአማኅብሮ። ኢያማኅበረታ፤ አላ ረሰየታ ለባሕቲታ ፡ (ስንክ ፡ ኅዳ፲። አዋል)።
አማሕፀነ ፡ (ዲቃ ግ) አማጠነ አረዳ፤ ከለከለ። ዐደራ አለ፤ ዐደራ ሰጠ አስጠበቀ። ብሩር ዘአማሕፀነ ኀበ ራጉኤል። አማሕፀንኩክሙ ፌቤንሃ እኅተነ። አባ ውስተ እዴከ እማሐፅን ነፍስየ
፡ (ጦቢ፬ ፡ ፩። ሮሜ፲፮ ፡ ፩። ሉቃ፳፫ ፡ ፵፮)።
አማሰነ ፡ በቁሙ፤ አጠፋ ፥ አስጠፋ አበላሸ። ሞት ዘኵሎ ያማስን። በአማስኖ ናላሁ። እንስሳት አማሳንያን። አማሳኒሃ ለነፍስ ፡ (ሔኖ፷፱ ፡ ፲፩። ፍ ፡ ነ ፡ ፴፪። ፵፯። ቅዳ
፡ ያዕ)።
አማሲኒት ፡ (ጽር አማሴኒት። ዕብ ሀሽማኒት) ንዋየ ማሕሌት፤ በገና ክራር ባለ፰ አውታር
፡ (፩ዜና ፡ ፲፭ ፡ ፳፩)።
አማረየ ፡ አስተማረየ፤ አስጠነቈለ፤ አስሟረተ ማርተኛ ጠየቀ። አናገረ አስለፈለፈ፤ ሟርተኛ አደረገ። ሰይጣን ይጼዐን በሰብእ ለአስተማርዮ ፡ (መጽ ፡ ምስ)። ማረየ የባረከ ቤት ስለ ኾነ ፥ አስተማረየ ከአማረየ ተለይቶ ባደራራጊነት ሲፈታ፤ አጠናቈለ አጠነቋቈለ ፥ አሞራረተ ያሰኛል።
አማሪ [1] ፡ (ሪት ርያን ያት) የሚያመለክት፤ አመልካች፤ ጠቋሚ፤ ጠንቋይ፤ መካር።
[2] ፡ አማሪ፤
፡ (ሪት ርያን ያት) የሚያውቅ ዐዋቂ የሚወድ ወዳጅ።
አማሪት ፡ (ዐማርኛ) በቁሙ ሴት ዘፋኝ ቀንቃኝ አርኾ ባለረዥም ድምጥ። የከበሮ ቂጥ፤ አታሞይቱ። የበገና አውታር ኹለቱ።
አማኑኤል ፡ ስመ ሥጋዌ፤–ዐማኑኤል።
አማኒ ፡ (ኒት ንያን ያት) የሚያምን አማኝ፤ እውነተኛ፤ ክርስቲያን። ብእሲ አማኒ ዘዘመወ በብእሲት ኢአማኒት። ትውልድ ኢአማኒት
፡ (ፈ ፡ መ፮ ፡ ፲፭። ማቴ፲፯ ፡ ፲፯)።
አማናዊ ፡ ባሕርያዊ፤ እውነተኛ፤ ዋነኛ፤ መደበኛ፤ አምሳል መርገፍ ያይዶለ። አምላክ አማናዊ። ድንግልና አማናዊ ድንጋሌ ነፍስ ይእቲ
፡ (ፈ ፡ መ ፡ ፮ ፡ ፩። አፈ ፡ ተ፳፰)።
አማን ፡ የታመነ፤ እውነት ፥ በውነት። እመ አማንኑ ውእቱ ለሐዊር ምስሌከ። እመ አማነ ኮነ ወጥዩቀ ነገሩ። አማንክሙኑ ኢታመልኩ። አማነ ትቤ። እስመ አማን ከማሁ ውእቱ
፡ (ጦቢ፭ ፡ ፱። ዘዳ፲፫ ፡ ፲፭። ዳን፫ ፡ ፲፬። ቄር ፡ ጰላ። ዮዲ፲፩ ፡ ፲)።
አማንየ ፡ ቃለ መሐላ፤ እውነቴ። አማንየ እብለከ
፡ (ስንክ ፡ ሐም፰)።
አማዕረየ ፡ (አዕረየ) አስተካከለ፤ አበጃጀ፤ አዘጋጀ። እወ እግዚኦ ፍታሕ ወአግዕዝ፤ ቀድስ ወአምዕዝ፤ አንጽሕ ወአጽሪ፤ አሠኒ ወአማዕሪ፤ እሎንተ አግብርቲከ ወአእማቲከ
፡ (ግንዘ)።
አማዕቀበ ፡ (አዕቀበ) አስጠበቀ፤ ዐደራ አለ፤ አማጠነ። ብእሲት ዘአማዕቀብዎ። ብእሲ ዘአማዕቀቡ ኪያሁ። አማዕቀቦሙ በክርስቶስ ፡ (ፈ ፡ መ ፡ ፭ ፡ ፲፬። ፲፪
፡ ፭። ስንክ ፡ መስ፱)።
አማዕበለ ፡ ማዕበል አስነሣ፤ አወከ ደረጠ፤ አናወጠ፤ አጐረፈ፤ የነፋስ
፡ መላ፤ ተማላ፤ ወሰደ፤ ይዞ ኼደ። ገፋ አዳፋ፤ ለጋ አማታ፤ አንገላታ፤ የማዕበል። ይፈቅድ ኅሊናየ ይጽብት ዕመቀ አብሕርት፤ ወያማዐብሎ መዋግድ
፡ (ቅዳ ፡ ሕር)።
አማዕተበ ፡ (ዐተበ) አማተበ፤ አመሳቀለ፤ ጣቱን እጁን። አማዕቲቦ በትእምርተ መስቀል። በሂዜ ቅዳሴ ሶበ ያማዐትብ እደ። አቅረበ ሎቱ ዮሴፍ ክእኤተ ደቂቆ ከመ ይባርኮሙ፤ ወአማዕተበ እዴሁ ዲበ አርእስቲሆሙ
፡ (ገድ ፡ ተክ። ስንክ ፡ ታኅ፲፱። ነሐ፳፰)።
አማእከለ ፡ (ዲቃላ ግስ) አማከለ፤ ከበበ፤ ከማኽል አገባ።
አማዳሮት ፡ (ዕብ ደሀሮት) ሩጫ ግልቢያ፤ የፈረስ
፡ (መሳ፭ ፡ ፳፪)።
አሜ ፡ ጊዜ፤ ሰዓት፤ ወራት። ፀሓይ ዘአሜ ክረምት። ወርኅ ዘአሜ ገሀህ። ይትፌሥሑ አሜ ሞቶሙ። እስከ አሜ ሞቱ ለሄሮድስ
፡ (ገድ ፡ ተክ። ደራሲ። ድጓ። ማቴ፪ ፡ ፲፭)። አሜሁ ሃ አሜከ ኪ እያለ ይዘረዝራል።
አሜሃ ፡ ጊዜዋ፤ በጊዜዋ፤ ያን ጊዜ፤ በዚያች ጊዜ፤ ወዲያው፤ ፈጥኖ ቶሎ። እምአሜሃ። እስከ አሜሃ። ኦ ዘአሜሃ ትውልድ
፡ (ማቴ፬ ፡ ፲፯። ኩፋ ፡ ፴፫
፡ ቅዳ ፡ ግሩ)። አመና እመ እም፤ እኒህ ፫ቱ አገባቦች የአመመ ዘሮች ናቸው እንጂ፤ ነባሮች አይዶሉም።
አሜሰ ፡ (ያመይስ ያሚስ) አስመሸተ አስጠጀ፤ አስመለሰ።
አሜቴስጢኖስ ፡ (ጽር አሜቲስቶስ) ዕንቍ፤ የዕንቍ ስም
፡ (ራእ፳፩ ፡ ፳። ዘፀ፳፰ ፡ ፲፱)።
አሜን ፡ (ዕብራ) የንባብና የዜማ ፍጻሜ፤ መጨረሻ ቃል፤ የጸሎትና የበረከት የርግማን ተሰጦ። እውነት፤ በውነት፤ ይኹን ይደረግ። ዘሎቱ ስብሐት ለዓለመ ዓለም ፥ አሜን። ወትብል ይእቲ ብእሲት አሜን ወአሜን
፡ (ገላ፩ ፡ ፭። ዘኍ፭ ፡ ፳፪)።
አሜከላ ፡ (ዕብ ዳርዳር) በቁሙ፤ ኰሸሽላ፤ የኰሸሽላ ዐይነት፤ ኹለንተናው እሾኽ የተመላ፤ እሾኻም ራሳም። ሦክ ወአሜከላ
፡ (ዘፍ፫ ፡ ፲፰። ኩፋ ፡ ፫። ዕብ፮ ፡ ፰)።
አሜጠ ፡ (ያመይጥ ያሚጥ) አስመለሰ፤ አስለወጠ።
አሜፌቅ ፡ (ጽር አማፌት። ዕብ ሚፍታን) መድረክ፤
፡ (፩ነገ ፡ ፭ ፡ ፬)።
አምኃ (ኃት) [1] ፡ ሰላምታ፤ ስዕመት፤ የቃል የእጅ ያንገት። እፎኑ ዘከመ ዝ አምኃ። አምኃ ዘአምኀ ባቲ አብ ለወልድ። ጸሎተ አምኃ
፡ (ሉቃ፩ ፡ ፳፱። ቄድር። ቅዳ)።
[2] ፡ አምኃ፤ በቁሙ፤ እጅ መንሻ፤ በረከት መተያያ፤ እጅ ነሥቶ ወዲያው የሚሰጡት ስጦታ ገንዘብ፤ ማማለጃ ጕቦ። ያመጽኡ አምኃ ለንጉሠ ሰማይ። ወአብኡ ሎቱ አምኃ። ኢትንሣእ ሕልያነ ወአምኃ ፡ (ጦቢ፲፫ ፡ ፲፩። ማቴ፪ ፡ ፲፩። ኩፋ፳፩)።
አምሐለ ፡ አማለ፤ አስማለ፤ አማጠነ። አምሐሎ በደመ አቤል ከመ። አምሐሎሙ በእንተ አዕፅምቲሁ። ኣምሕለከ በእግዚ ከመ ኢትሣቅየኒ። ይከውን ጌጋዩ ላዕለ ዘአምሐሎ
፡ (ቀሌ። ኩፋ ፡ ፵፮። ማር፭ ፡ ፯። ፍ ፡ ነ ፡ ፵፫)።
አምሀረ ፡ አስማረ ፥ አስተማረ፤ ለመምህር ሰጠ ፥ ከተማሪ ቤት አገባ።
አምሐረ ፡ አስማረ፤ ይቅር አሰኘ። አራራ፤ አሳዘነ። ያምሕሩቲኒ እሉ አሕዛብ። ወአምሐርዎ ለኢየሱስ ፡ (ማቴ፲፭ ፡ ፴፪። ፳ ፡ ፴፬። ማር፰ ፡ ፪)።
አምሀወ ፡ አሟሟ፤ አቀለጠ፤ ውሃ አደረገ ፡ (ስንክ ፡ ሐም፭)።
አምኀፀ ፡ አስማጠ አስጨነቀ ፥ እሕ አሰኘ።
እምሔው አማሑት [1] ፡ አያት፤–ሐዪው ሐይወ።
[2] ፡ (ውት ዋን ዋት ፤ አማሑት) ፤ ዝኒ ከማሁ ፤ አዳም። እንደ አዳም ያለ ወንድ አያት እሚታ ፤ ያባት የናት ወላጅ ጕንድ ሥርው መዠመሪያ አባት ፫ኛውን ትውልድ የልጅ ልጅ ያየ። እም አገባብ
ኹኖ መነሻነትን ተከፋይነትን
ያሳያል። እግዚ ይቤሎሙ ለእምሔው ወለእምሔውት
ቀዳማውያን ፤ ብዝኁ ወተባዝኁ ፤ ወላድያን ወእምሔዋን። አሮን እምሔወ ቀደምቶሙ። በቤተ መላልኤል
እምሔውየ። ሐና እምሔውተ አምላክ በሥጋ። አበዊከ ወአማሑቶሙ (ፍ ፡ ነ ፡ ፳፬። ዕዝ፯ ፡ ፭። ሔኖ፷ ፡ ፰። ስንክ ፡ ኅዳ፲፩። ዘፀ፲ ፡ ፮)። አማሑት ወንድና ሴት ያስተባብራል። አበ እምሔው
፤ ያያት አባት ቅድም አያት። እምሔወ እምሔው ፤ ያያት አያት ምዝላት። እግዜርም ለአዳም እምሔው
ይባላል ፤
ዕጓልን እይ። ሐፃኒ አበ ማሕፀንት በማለት ፈንታ እምሔው
አማሑት ይላል ፤
አያሰኝም። ላዕለ እምሔው ወመገብት። ነገሥት አማሑትኪ (ገላ፬ ፡ ፪። ኢሳ፵፱ ፡ ፳፫)።
አምኆ ኆት ፡ (አምኀ ይኤምኅ፤ የአ) እጅ መንሣት፤ ባንገት በወገብ በጕልበት መስገድ፤ ጫማ ጕልበት እጅ መሳም መሳለም፤ ሰላምታ እጅ መንሻ መስጠት ማቅረብ፤ በቃል በእጅ። ሰገድከ ሊተ ወአማኅከኒ። እኤምኅ አእጋሪከ። አምኁ ኵሎ ቅዱሳነ፤ አምኁክሙ አኀዊነ። አዘዞሙ ለኵሎሙ ዐበይቱ ከመ የአምኅዎ ንዋየ በከመ ክሂሎቶሙ። እለ ይኤምኁከ ወርቀ
፡ (ማቴ፬ ፡ ፱። ደራሲ። ፊልጵ፬ ፡ ፳፩። ዮሴፍ። ስንክ ፡ መጋ፳፱። ሚያ፮)።
አምለሰ ፡ አስመለሰ፤ ቋቅ አሰኘ አስተፋ አስቀረሸ።
አምለከ ፡ አስመልከ፤ አስገዛ፤ አስደራጊ። አነገሠ አጌተየ አሠለጠነ፤ ሌላውን በሌላ ወይም በራሱ፤ አድራጊ። ኢያኴንንዎሙ ወኢያመልክዎሙ
፡ (ሢራ፴፰ ፡ ፴፫)።
፡ አመለከ፤ አምላክ አደረገ ፥ አምላኬ አምላኬ አለ፤ ፈጣሪውን ወይም ሌላውን። እስመ ጽሑፍ ለእግዚ አምላክከ ትስግድ ወኪያሁ ባሕቲቶ ታምልክ። ከመ ታምልኩ ዕፀ ወእብነ። እለ ያመልኩ ጣዖተ ፡ (ማቴ፬ ፡ ፲። ሕዝ፳ ፡ ፴፪። ራእ፳፪ ፡ ፲፭)።
፡ አከበረ አመሰገነ፤ የአምላክ ወገን አደረገ። ሀለዉ እለ ይቤሉ፤ ለዕፅኑ ታመልኩ ወለዕፅኑ በዓለ ትገብሩ ኢቀደሶኑ ደሙ ክቡር ለዕፀ መስቀል ወበእንተ ዝ ንሕነ ናመልኮ፤ ናከብሮ ማለት ነው ፡ (ድጓ)።
አምለጠ ፡ (ዕብ ሂማሌጥ) አስመለጠ፤ አመለጠ፤ አዳነ አወጣ፤ ራሱን ወይም ሌላውን፤ ሙልጭልጭ ከማለት የተነሣ። መሠጠን እይ።
አምላካዊ ፡ (ዊት ውያን ያት) ያምላክ፤ ወገን ገንዘብ፤ አምላክማ፤ አምላካም ባላምላክ። ፈቃድ አምላካዊ። ጳውሎስ አምላካዊ። ኀደጉ ጽዋዔሆሙ አምላካዊተ። መጻሕፍት አምላካውያት ፡ (ፈ ፡ መ ፡ ፪ ፡ ፩። ፲ ፡ ፬። ፊልክ ፡ ፭። ፍ ፡ ነ ፡ ፪)።
አምላክ [1] ፡ በቁሙ፤–መሊክ መለከ፤ መለክ።
[2] ፡ አምላክ፤
፡ (ብ አማልክት) በቁሙ፤ ፈጣሪ ገዥ ፈራጅ፤ ዳኛ ሠሪ ቀጭ ፥ ፈላጭ ቈራጭ፤ መልእክ፤ ጣዖት። አምላክ የመለክ ብዢ ሲኾን ላንድ አካል ብቻ መነገሩ በልማድ አፈታት ነው እንጂ ፥ በሰዋስው ሕግ አይዶለም፤ አማልክትም የብዙ ብዙ ነው፤ ኤሎሄን እይ። እወ እግዚኦ አምላክ ኵሉ። ወአምላክ ዓለም። አምላኪየ ወአምላክክሙ። ረሰይኩከ አምላኮ ለፈርዖን። ክሞስ አምላክለ ፡ (ቅዳ ፡ ኤጲ። ሔኖ፩ ፡ ፫። ዮሐ፳ ፡ ፲፯። ዘፀ፯ ፡ ፩። መሳ፲፩ ፡ ፳፬)። አምላከ አማልክት። ማኅበረ አማልክት፤ አንሰ እቤ አማልክት አንትሙ። ይሰድዎ ኀበ አማልክት። ኢትትልዉ አማልክተ ፡ (መዝ ፡ ፵፱ ፡ ፹፩። ዘፀ፳፩ ፡ ፮። ዘሌ፲፱ ፡ ፬)።
አምላክና ፡ አምላክነት፤ አምላክ መኾን። አኀልዮ ለአዳም አምላክና። ንብሎ ሰብአ በሰብእናሁ ወአምላክ በአምላክናሁ ፡ (ፈ ፡ መ ፡ ፫። ሃይ
፡ አበ)።
አምልኀ ፡ አስነቀለ፤ አስመዘዘ።
አምልኮ ፡ በቁሙ፤ ሃይማኖት፤ ማምለክ ማስመለክ፤ አምላክ ማድረግ። አትናቴዎስ ስሙይ በሥነ አምልኮ
፡ (ቄር ፡ እስት)።
(ጥ) አምሞ ሞት ፡ (አመመ ይኤምም የአ። ዕብ ሀማም) ማመም፤ መጮኽ መትመም። አማሚ መኾን፤ ያረም ያጨደ የቍፋሮ። ማነት፤ እናት ማድረግ፤ እማማ ማለት።
አምሰለ ፡ አመሰለ፤ አስመሰለ። ብዕልክሙ ያመስለክሙ ጻድቃነ። ከመ ዘእምካልእ ሕዝብ ያመስሉኒ። ዐርከ አምሰልዎ። እንዘ ታመስሉኒ ኤርምያስሀ
፡ (ሔኖ፺፮ ፡ ፬። ኢዮ፲፬ ፡ ፲፭። ጥበ፩ ፡ ፲፮። ተረ ፡ ባሮ)። ፪ኛም በመሰለና በሐሰበ ፈንታ አምሰለ ይላል፤ ስሕተት ነው። ያመስል ለሰብእ ከመ ውእቱ ያፈቅረኒ። ወአምሰላ ዔሊ ከመ ስክርት
፡ (ዮሴፍ። ፩ነገ ፡ ፩ ፡ ፲፫)።
አምሰየ ፡ አመሸ፤ አስመሸ ፥ እስከ ማታ ቈየ አስቈየ። ተጊሀ ወአምስዮ ፡ (ማቴ፳፭ ፡ ፲፪)።
አምሠጠ ፡ አስነጠቀ፤ አስቀማ አሶሰደ፤ የያዘውን ፥ ወይም ራሱን።
አምሳል ፡ መልኮች ፥ ዐይነቶች ፥ ባንድ አካልና ባንድ ገላ ያሉ የብዙ ሕዋሳት አርኣያዎች። በአምሳለ ዚኣሁ ገብሮሙ። ተመሰለ በአምሳለ ንስር። በበ ዘመዶሙ ወበበ አምሳሎሙ። አነ ሰይጣን እትሜሰል በኵሉ አምሳል ፡ (ሢራ፲፯ ፡ ፫። ተረ
፡ ባሮ። ኩፋ ፡ ፫። ቀሌ)። ባለቅኔዎች ግን ሊካድ የማይቻል ብዙነቱን ክደው ዐቢይና ንኡስ አገባብ እያሉ በከመ ዘይቤ ይፈቱታል፤ እውነተኛ የመጽሐፍ ምስክር የለውም።
አምሴር አምሺር ፡ (ቅብጥ ሜኺር፤ ማሺር) የግብጦች ፮ኛ ወር የካቲት
፡ (አቡሻ ፡ ፰)።
አምስሐ ፡ አመሳ፤ ምሳ አበላ። አእምር ኵሎ ዘአምስሐከ ቢጸከ። ወአምስሐ መኳንንቲሁ
፡ (ሢራ፴፬ ፡ ፲፭። ማር፮ ፡ ፳፩)።
አምረረ ፡ አመረረ፤ አስመረረ አሳዘነ ፥ አስቈጣ። ወበሕምዘ መቅሠፍት ጳስኮራዊ አምረሩ መዓረ ዘባኑ ለኤርምያስ ንህብ። አምረራ ለነፍስየ። እስመ አምረሩከ እግዚኦ። ወእለ መኑ እሙንቱ እለ ሰምዑ ወአምረርዎ ፡ (ቅኔ። ኢዮ፳፯ ፡ ፪። መዝ ፡ ፭። ዕብ፫ ፡ ፲፮)።
አምረተ ፡ አመረተ፤ አስመረተ አዛገ።
አምረገ ፡ አስመረገ፤ አስለሰነ አስቀባ አስለቀለቀ።
አምርሐ ፡ አመራ ፥ አስመራ፤ መሪ ሰጠ ለተመሪ።
(ጥ) አምሮ ሮት ፡ (አመረ ይኤምር የአምር የአ። ዕብ አማር፤ ብህለ ነበበ። ዐረ አመረ፤ አዘዘ) ማመልከት፤ ማሳየት፤ መጠቈም መጠንቈል፤ መንገር ማስተማር፤ በእጅ በቃል። ታምራት ማድረግ። ወአመሮ በእዴሁ ከመ ይነጽር ድኅሬሁ። አመረኒ በክልኤቱ ትእምርት። አመረ ባሕረ ለኀበ ሥርዐተ ብሕትውና፤ ወዐውሎታተ ለኀበ መከራት
፡ (ዮሴፍ። ዲድ ፳፱። ፊል ፳፰)። በአመረ ፈንታ አአመረ ይላል፤ አያሰኝም። ወናኤምር ከመ እስትጉቡእ። ያኤምር፤ በዝንቱ ፡ (ፍ ፡ ነ። አፈ ፡ ተ፲፱)።
አምተረ ፡ አስመተረ፤ አስቈረጠ። አስቀረ፤ አስታጐለ፤ አቋረጠ። ሄሮድስ ለዮሐንስ ርእሶ አምተረ። ታመትርኑ ዕጣና ለገበዝ
፡ (መዋሥ)።
አምትሀ ፡ አስመታ፤ ምትሀት አስደረገ።
(ጥ) አምቶ ቶት ፡ (አመተ ይኤምት የአምት። ዕብ አሜት) ማመት መገመት፤ ማሰብ መገምገም፤ የዋጋ የነገር። መከንዳት፤ በእጅ መስፈር መለካት፤ በጣት ማሳየት ማመልከት። መግዛት፤ መቅጠር፤ አገልጋይ ማድረግ፤ የሴት ልጅ።
አምንስቲቲ ሙኪርያ ፡ (ጽር ምንስቲቲሙ ኪሪዬ) ተዘከረኒ እግዚኦ። አንቲ ፋሲልያሱ
፡ (ጽር ኤንቲ ፡ (በ) ባሲሊያሱ) በመንግሥትከ ፡ (ግብ ፡ ሕማ። ሉቃ፳፫ ፡ ፵፪)።
አምዐለ ፡ ኦሶነጀለ፤ አስካደ አስከዳ።
አምዐረ ፡ አምዐርዐረ፤ አጣፈጠ ፥ አጠፋፈጠ፤ ማር አደረገ ፥ ማር አላሰ ፥ በማር ለወሰ። እንተ ለጊዜሃ ታመዐርዕሮ ከመ ኢያምዐርዕር ጕርዔከ ፡ (ምሳ፭ ፡ ፫። ፳፬ ፡ ፲፫)። አንዳንድ መጣፍ አመርዐረ ብሎ ምርዕርና ይላል፤ ስሕተት ነው።
አምአተ ፡ አበዛ፤ ዐሥሩን መቶ፤ ወይም መቶውን ሺሕ አደረገ። አምስተ ወአመክዐበ ፡ (ድጓ። ሉቃ፰ ፡ ፰)።
አምዐወ ፡ አረጠበ አራሰ፤ አለሰለሰ። አገባ ከተተ፤ ስፍራ አሲያዘ።
አምዐዘ ፡ አማዛ ፥ አሸተተ፤ ሽቱ ቀባ፤ ረጨ ረበረበ፤ ቀመመ አጣፈጠ። ብእሲት እንተ ትሰድድ ፃፄ ከመ ኢያማስኑ አልባሲሃ ወታምዕዞሙ በአፈዋት። አምዐዝዎ ለኖኅ ወቀበርዎ። ሐዋርያት አምዐዙ ኵሎ ዓለመ። አምዕዘነ ፡ (አፈ ፡ ተ፳። አቡሻ ፡ ፵፯። ቀሌ። ቅዳ)።
አምኣታት
፤ መቶ
ጊዜ መቶ ፤ ዐሥር ቪሕ ፥ ወይም አንድ እልፍ።
አምኣት ፡ (ታት) መቶዎች፤ ዐሥር መቶ ፥ ወይም መቶ ጊዜ ዐሥር፤ አንድ ሺሕ። ይገብር ሣህለ ለአምኣት ወለአእላፍ። መላእክተ አምኣት
፡ (ኩፋ ፡ ፳፫። ፩ዜና ፡ ፳፰ ፡ ፲)።
አምዕዐ ፡ አስቈጣ አበሳጨ፤ አሳዘነ አናደደ፤ አስጮኸ አስወገሸ። ኵሉ ዘያምዕዕ እኋሁ በከንቱ። ኣቀንኦሙ ወኣምዕዖሙ። እንተ አምዕዑቶሙ ለነገሥት ፡ (ማቴ፭ ፡ ፳፪። ሮሜ፲ ፡ ፲፱። ኢሳ፳፫ ፡ ፲፩)። በአድክመ ፈንታ አምዕዐ ይላል ፡ (ሚል፪ ፡ ፲፯)።
አምከረ ፡ አስመከረ፤ ምከሩ አለ ፥ ስሞታ ነገረ። መምከሪና መምከር ከዚህም ይወጣሉና፤ እንደዚህ ደግሞ ባስደራጊነት ይፈታሉ።
አምከነ ፡ አምከነ፤ አመከነ፤ መካን አደረገ፤ መውለድ ከለከለ፤ ወይም ልጅ አሳጣ ፥ ሾተላይ ኾነ። አምከነተኪ መጥባሕት። በከመ አምከነቶን ኵናትከ ለአንስት ከማሁ ትምክን እምከ። ወኢትደግም እንከ አምክኖቶሙ ፡ (ሰቈ፩ ፡ ፳። ፩ነገ ፡ ፲፭ ፡ ፴፫። ሕዝ፴፮ ፡ ፲፪)።
አምዳሮት አምዳር ፡ ምድሮች፤–መዲር መደረ፤ ምድር።
አምድ ፡ በቁሙ፤–ዐምዶ ዐመደ፤ ዐምድ።
አምገለ ፡ አምገለ፤ አመገለ አፈረጠ። ያመግል ፡ (መ ፡ ፈ)።
አምጠቀ ፡ አመጠቀ አረዘመ፤ አስመጠቀ አስረዘመ፤ ምጡቅ ረዥም አደረገ፤ ወይም አስደረገ። አብድ ሶበ የሐንጽ ቤቶ ያመጥቅ ሕንጻሁ እምአግዋሪሁ ከመ ይትመካሕ ላዕሌሆሙ ፡ (ፈላስ ፡ ገ፵፬)።
አምጻኢ መምጽኢ ፡ እ፤ የሚያመጣ አምጭ፤ አስመጭ፤ አስገኝ። አምጻኤ ኵሉ ዓለም። መምጽ(ኤ) አ ምስጢር ፡ (ፈላስ። ቄር)።
አምጽአ ፡ አመጣ፤ አስመጣ፤ አስገኘ። ኣመጽእ እኪተ እምደቡብ። በእንተ ዘፈጠረነ ወአምጽአነ ፡ (ኤር፬ ፡ ፮። አፈ ፡ ድ፬)። በአምጽአ ፈንታ አስተማጽአ ይላል፤ ስሕተት ነው። እመጻሕፍቶሙ ዘይበቍዕ ውስተ ዝንቱ አስተማጺእየ ምዝማረ ፡ (ቄር እስት)። ዳግመኛም አንሥአ ፥ ፈነወ ፥ ረሰየ በማለት ፈንታ አምጽአ ይላል፤ ምስክሩን በተራው እይ። ኣመጽእ ላዕሌከ እኪተ እምነ ቤትከ። አምጽአ ነፋሰ። ታመጽእ ጽልመተ ፡ (፪ነገ ፡ ፲፪ ፡ ፲፩። ዮና፩ ፡ ፬። መዝ ፡ ፻፫)።
አሞቀ ፡ በቁሙ፤ አተኰሰ። ፡ (አስሞቀ አስተኰሰ)። እሳት ያመውቆ ለኀጺን። አሐቲ ኆኅት ታመውቅ ሞቀ። ያመውቆ ፀሓይ ለውእቱ ዕፄ ወይከውን ዖፈ። አሙቅ ላሕዎቶ ፡ (ቄር ፡ ጰላ። ሔኖ፸፭ ፡ ፯። ዲድ ፡ ፳፭። ሢራ፴፰ ፡ ፲፯)። በአሞቀ ፈንታ አስተማወቀ ይላል፤ አድራጊነት ካደራራጊነት ያሳያል። ተሐቅፎ ወታስተማውቆ። አስተማወቅዎ እስትንፋሰ አድግ ወላሕም ፡ (፫ነገ ፡ ፩ ፡ ፪። ቅዳ ፡ ሕር)።
አሞቅሐ ፡ አሳሰረ አስጋዘ፤ ያዙት እሰሩት አለ። ወአሞቅሖ እስከ አመ ይፈድዮ ፡ (ማቴ፲፰ ፡ ፴)።
አሞተ ፡ ገደለ፤ አጠፈ፤ ለየ። አሙተኒ ወኢታሙቶ። ለአሙቶቱ ወለቀቲሎቱ። አሙትዋ ለነፍስክሙ እምኵሉ ምግባረ እኩይ ፡ (ዮሴፍ። ኩፋ
፡ ፴፫። ቀሌ)።
አሞአ ፡ ድል አስነሣ፤ አጸና አበረታ፤ አሠለጠነ። ኢያመውኦ ሶበ ይትዋቀሥ ፡ (አርጋ ፡ ፩)። ዘአሞኦ እግዚ ላዕለ ካልኡ። ከመ ታሙኦ ለዘፈቀድከ። ውእቱ ያመውአከ በዳራ ወበመንግሥቱ ፡ (ዮሴፍ)።
አሞገሰ ፡ ወደደ አከበረ፤ ባለሟል አደረገ፤ አወደሰ አመሰገነ፤ በቅኔ በግጥም። ኣሤንያ ወኣሞግሳ ፡ (ዘካ፬ ፡ ፯)።
አሞገደ ፡ አስሞገደ፤ ማዕበል ሞገድ አስነሣ። እለ ያሞግዱ ወየሀውኩ
፡ (አፈ ፡ ተ፴፬)።
አሞጥሐ ፡ አስለበሰ፤ አስጌጠ።
አሞጸ ፡ አስካሰ፤ ካሳ አሰጠ።
አሠለሰ ፡ በቁሙ፤ አሠገረ፤ ሦስት አስደረገ፤ ሦስት አሰኘ።
አሰለጠ ፡ አስፈጸመ፤ አስጨረሰ። መጽሐፍ ግን በሰለጠ ፈንታ አስለጠ አሰለጠ ይላል፤ ያድራጊውን ባስደራጊ። መብልዕ ኢያሰልጠነ። ወኢያስለጠት ምንተኒ ኦሪት። እስመ ጸሎተ ጻድቅ ትክል ወታሰልጥ። መሀሮ ለወልድከ ወያሰልጠከ። ምንት ያሰልጥ ደምየ ፡ (፩ቆሮ ፡ ፰ ፡ ፰። ዕብ፯ ፡ ፲፱። ያዕ፭ ፡ ፲፮። ሢራ፴ ፡ ፲፫። መዝ
፡ ፳፱)።
አሠለጥ ፡ (ዐማርኛ) የቤት ውልድ፤ ቤት አባት አሠልጣኝ።
አሠልጠነ ፡ ዝኒ ከማሁ፤ የአሥለጠ ድርብ። ዲበ ዝ ኵሉ አሠልጠኖ። እግዚ አሠልጠኖሙ ለሮም በዝ አዝማን ፡ (ኩፉ ፡ ፪። ዮሴፍ። አርጋ ፡ ፩። ቅዳ)።
አሰሰለ ፡ አራቀ፤ አስራቀ አስወገደ፤ አጠፋ አስጠፋ። አሰሰለት ሠቀ። ይቤ ያሰስሉ ኵሎ ሰብአ እምቅድሜሁ። አሰስል ፍትወተ እምኔየ። ኣሴስሎሙ እማእከለ ምድር። ለአሰስሎ
፡ (ዮዲ፲ ፡ ፫። ዘፍ፵፭ ፡ ፩። ሢራ፳፫ ፡ ፭። ኩፋ ፡ ፩። ሔኖ ፡ ፩)።
አሰሳሊ መሰስል ፡ (ልት ላን ላት) የሚያርቅ፤ የሚያስርቅ፤ አራቂ አስራቂ፤ አስወጋጅ። አሰሳሌ እከያት። ጸሎት መድኀኒት ውእቱ ወአሰሳሌ ኵሉ ኀጣውእ ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ መቅ። አፈ ፡ ተ፳፯)።
አሠሥዐ ፡ አሣሣ፤ አሠሠተ፤ ሆዳም ሥሥታም አደረገ ፡ (ገድ ፡ አዳ)።
(ጥ) አሰረ ፡ ቀጠረ፤ ዐሥር አደረገ፤–ዐሥሮ፤ ዐሠረ።
አሠረ [1] ፡ (ትግሬ) ተከተለ፤ ተከትሎ ኼደ፤ ሻ ፈለገ።
[2] ፡ (ጥ) አሠረ፤–ቀጠረ፤ ካሥር አንድ አወጣ፤–ዐሥሮ ዐሠረ።
[3] ፡ (ላ) አሠረ፤–በቁሙ፤–አሲር አሰረ።
አሠረ ንጉሥ ፡ የቅኔ ስም፤ ለንጉሥ የሚሰጥ የዕጣነ ሞገር ተቀጥላ።
አሠር ራት ፡ (ዐረብ ኢሽር፤ አሰር። ሱር አትራ። ዕብ አሹር) ፍለጋ፤ ዱካ፤ ርጋጭ፤ መከየድ፤ መንገድ ጥርጊያ ጐዳና፤ ርምጃ አካኼድ፤ አብነት። ደምሰሰ አሠርየ። አሠረ ምንት ዝንቱ። እሬኢ አሠረ ዕደው ወአንስት። እደ ኬደ አሠረ ውሉደ ሰብእ። ንሑር በአሠሩ። አሠር ንጹሕ ዘአልቦ አሥዋክ። ወየኀድግ ውስተ ፍኖት አሠሮ
፡ (ኢዮ፴ ፡ ፲፫። ዳን፲፫ ፡ ፲፱ ፡ ፳። ኩፋ ፡ ፴፪። ሚክ፬
፡ ፪። ቅዳ ፡ ኤጲ። መዝ ፡ ፹፬)።
፡ ምልክት፤ ጠንክ፤ ዕትራት፤ ጠባሳ ጐዳኒሳ፤ ቦታ
፡ ስፍራ። አሠሩ ለልብ ፍሡሕ ፥ ገጽ ብሩህ። አሠረ ደም። አሠረ ደዌ። አሠረ ቅንዋት ወአሠረ ርግዘት። አሠራት አምላካውያት፤ መካናት
፡ (ሢራ፲፫ ፡ ፳፮። ስንክ ፡ መስ፫።ሐም፳፬። ፍ
፡ ነ ፡ ፲፱)።
አሰር ፡ ፍለጋ፤–አሢር አሠረ።
አሰርገወ [1] ፡ (አድራጊ) ሰረገ፤ ሰርገወ፤ የሰረገን ፍች ተመልከት።
[2] ፡ (አስደራጊ) አስጌጠ አሸለመ፤ ሽልማት አሰጠ።
አሰብሰበ ፡ አሰበሰበ፤ ስብስቦ አሰረ፤ ማገረ፤ የሣርና የንጨት። ሠብሠበንና ሰበበን እይ።
አሠነየ ፡ አሳመረ፤ አሰማመረ አስጌጠ፤ አበጀ፤ አዘጋጀ፤ መልካም አደረገ። ኢያሠነይኩ ጽሒፈ። አሠነየ ሥዕርተ ርእሱ ወጽሕሞ። ከመ ያሠኒ ሎቱ አሣእኒሁ። ያሤንዩ መሥዋዕቶ ለልዑል። ለንኡስኒ ወለዐቢይኒ አሠኒ ግዕዘከ ወቃለከ ፡ (ዕር ፡ ኢሳ። ዮሴፍ። አቡሻ ፡ ፶። ሢራ፶ ፡ ፲፬። ፳፱ ፡ ፳፫)። በአሠነየ ፈንታ አስተ(ሠ) ሣነየ ይላል፤ አያሰኝም። ከመ ያስተሣኒ ምብዓሎ። ወታስተሣንዩ ዝኅሮሙ ለጻድቃን። መስተሠንይ ፡ (ሢራ፴፰ ፡ ፳፰። ማቴ፳፫ ፡ ፳፱። ማር፩ ፡ ፲፱። ፍ ፡ ነ ፡ ፳፫)።
አሰንበተ ፡ አከበረ፤ አስከበረ፤ ዐረፈ አሳረፈ፤ ቦዘነ፤ ሥራ ተወ ፈታ፤ ስለ በዓል። አሰንበተ በዕለተ ሰንበት። አሰንብቱ ሰንበታቲክሙ
፡ (ዘፀ፲፮ ፡ ፴። ዘሌ፴፫ ፡ ፴፪። አፈ
፡ ድ፰)።
አሰከ ፡ (የአስክ ይእስክ፤ አሲክ ኮት) ዐሸ አኰላሸ፤ ሰነጋ፤ ቀጠቀጠ፤ ሰለበ ቈረጠ። ደረሰ ነካ፤ አዋደደ ሰካ፤ የተባት ያለሌ ፥ ያውራ።
አሰክት ፡ ጭጕኝ የጕያ ጠጕር ሸከራ ቍርንድድ። አሽክት ወይም አሸክት የገብስና የባቄላ ዐረም ሸካራ ቅጠል በወይና ደጋ የሚበቅል።
፡ (ተረት) ያይጥ ዱለት ማሰሪያው አሽክት።
አሰየ ፡ ሰጠ፤–ዐስይ
፡ ዐሰየ።
አሰድ ፡ (ዐረ እልአሰድ) አንበሳ። ኮከብ፤ የኮከብ ስም፤ አንበሳዊ አንበስ አንበሶ ማለት ነው። ኮከብነቱም የሐምሌ ነው። ከፀሓይ ጋራ ፴፩ ዕለት ፲ ኬክሮስ ይመግባል
፡ (አቡሻ ፡ ፫)።
አሰፈወ አስተሰፈወ ፡ (ሰፈወ) አስታመነ። ንባቡ አስደራጊ፤ ፍችው አድራጊ። አና አስተ አለቦታቸው ገብተዋል።
አሲር ሮት ፡ (አሰረ የአስር ይእስር ይእ። ዕብ አሳር። ሱር ኤሳር። ዐረ አሰረ) ማሰር፤ ማቈራኘት፤ ማጣመር ማዛወግ፤ ኹለቱን ሦስቱን ፥ ወይም ብዙውን አንድ ማድረግ፤ ማከት መተብተብ፤ ማጋዝ ማውገዝ፤ መገዘት መለየት። እስሮ በእዴሁ ወእገሪሁ። ወአሰረ ኅሊናሁ ምስለ እግዚ። የአስር በአሥራው። እስርዎሙ ከላስስተ። የአስሩ ጾረ ዐቢየ። አሰሮ ለሰይጣን። አውገዝነ ወአሰርነ ፡ (ሔኖ፲ ፡ ፬። ፊልክ ፡ ፳፬። ቅዳ ፡ ግሩ። ማቴ፲፫ ፡ ፴። ፳፫ ፡ ፬። ድጓ። መቅ ፡ ታም)።
አሲው ዎት ፡ (አሰወ የአሱ ይእሱ። ዕብ ሱር ዐረ አሳ) መፈወስ ማዳን፤ መሾም ማሠልጠን።
፡ (ጥፈ) መፈወስ መዳን፤ ጤና ማግኘት ባለጤና መኾን በመዳኒት ወይም በታምራት።
፡ አስት ማውጣት፤ ቡላድ መምታት፤ ማንደድ ማቃጠል፤ ማሞቅ ማተኰስ፤ ማጋል ማጋም እሳት ማድረግ።
አሣሀለ አስተሳሀለ ፡ (ሣሀለ) ዝኒ ከማሁ፤ ወዓዲ። ይቅር አባባለ፤ አስተራረቀ አሰማማ ፡ (አደራራጊ)።
አሳሪ ፡ (ሪት ርያን ያት፤ አሰርት) በቁሙ፤ የሚያስር አንድ የሚያደርግ። አግዕዘነ ለኵልነ እማእሰረ ኀጢአት ዘአሰረነ አሳሪ። ወአሳሪሁ
፡ (ግንዘ። መቅ ፡ ወን)።
አሳዊ ፡ (ዊት ውያን ያት) የሚፈውስ፤ የሚፈወስ፤ ፈዋሽ ተፈዋሽ።
አሤበ አው አሥየበ ፡ አሸበተ፤ አስረጀ። አሻገተ፤ አስደራጊም ይኾናል።
አሤጠ አው አሥየጠ ፡ አሼጠ፤ አገበረ አስገደደ፤ ለመሼጥ። ተአመነ ከመ መንፈስ ቅዱስ አሥየጠ በሤጥ ፡ (ፈ ፡ መ
፡ ፳፭ ፡ ፩)።
አስ ፡ (ዐማርኛ) የማስደረግ ልማድ፤ አቅተለ፤ አስገደለ። ተ ሲጨመርበት አስተ እየኾነ ወደ ማደራረግ ይለወጣል፤ አስተቃተለ አጋደለ፤ አገዳደለ። በሰ ግስ ላይ ሲነገር ሰን እየዋጠ ይጠብቃል። አስበረ አስተሳበረ፤ አሰበረ አሳበረ አሰባበረ። አስገደ አሥገረ፤ አስገደ አሠገረ። የአንና የአስተን አፈታት ተመልከት። ፪ኛም ሰ በሌለበት ግስ እየገባ ከአ ተለይቶ የጥሬ መነሻ ይኾናል። ዐዘዘ አስዐዘዘ አስዖዘዘ ሰዖዛዝ።
አስሐለ ፡ አሳለ፤ አስሞረደ፤ ስል ሹል አስደረገ።
አሥሀለ አስተሥሀለ ፡ (ሠሀለ) ይቅር አሰኘ፤ አስማረ።
አሥሐቀ ፡ አሣቀ፤ ደስ አሰኘ። ምንት አሥሕቃ ለሳራ ፡ (ዘፍ፲፰ ፡ ፲፫)።
አስሐበ ፡ አሳበ፤ አስጐተተ፤ ሳቡ ጐትቱ አለ።
አሥኀተ ፡ (ያሤኅት) አሳረፈ፤ ዕረፍት ሰጠ ፥ መከራ አቀለለ፤ ተወ ይቅር አለ። ኑዛዜ ነገርክሙ ኢያሤኅተኒ። እስከ ማእዜኑ ኢታሤኅተኒ። ወአንተኒ ዮም ኅድግ ወአሥኅት እምክበደ ቅኔ አቡከ ፡ (ኢዮ፮ ፡ ፳፮። ፯ ፡ ፲፱። ፪ዜና
፡ ፲ ፡ ፬)። በአሥኀተ ፈንታ ሥኅተ ሠኀተ ይላል፤ አያሰኝም። ሥኅተኒ ከመ አዕርፍ። ኢይሥኅቶሙ። ጾረት ክቡደ ወኢሠኀትዋ። ሠኀተነ እምቅኔነ። አንተ አምላክነ ሠኀትከነ እምኀጢአትነ ፡ (መዝ
፡ ፴፰። ኢሳ፪ ፡ ፱። ሰቈ፩ ፡ ፱። ዕዝ፬ ፡ ፰ ፡ ፲፫)።
አስሐተ [1] ፡ አሳተ፤ አሳሳተ፤ ከመንገድ አወጣ፤ አታለለ፤ አስካደ ኀጢአት አሠራ። ወአስሐቶሙ ውስተ በድው ዘኢኮነ ፍኖተ። ዘያስሕቶ ፍኖተ ለዕዉር። ወለብዙኃን አስሐቶሙ ትዝኅርቶሙ። ተሠነየት ጥቀ እስከ ታስሕት ዐይኖሙ ለዕደው። ዑቁ አልቦ ዘያስሕተክሙ፤ እስመ ብዙኃን ይመጽኡ በስምየ ወብዙኃነ ያስሕቱ። ለሔዋን እንተ አስሐታ ከይሲ ፡ (መዝ ፡ ፻፮። ዘዳ፳፯ ፡ ፲፰። ሢራ፫ ፡ ፳፬። ዮዲ፲ ፡ ፬። ማቴ፳፬ ፡ ፬ ፡ ፭። ኤፍ ፡ ፪)።
[2] ፡ (ዕብ ሂሽሒት) አጠፋ፤ አስጠፋ፤ ጐዳ፤ አጥፊ ኾነ፤ አበላሸ።
አስሓቲ መስሐቲ አስሓቲ
፡ መስሐቲ፤ ክስቶ የሚያስት፤ አሳች፤ አሳሳች፤ አጥፊ፤ አስጠፊ። ሰይጣን አስሓቲ። እንበለ ያስሕቶ መስሐቲ ፡ (ቄድር። ፈ ፡ መ ፡ ፫ ፡ ፩። አፈ ፡ ድ፳፰)።
አሥኃቲ መሥኀቲ ኅት ፡ የሚያሳርፍ አሳራፊ፤ ዕረፍት ሰጪ።
አስሐትያ [1] ፡ ውርጭ፤–ስሒት ስሕተ፤ አስሐተ።
[2] ፡ (ዕብ ቂጦር፤ ጢስ) ውርጭ፤ ዐመዳይ፤ አጥፊ፤ ቡቃያ የሚያደርቅ የሚያሳርር፤ ዋግ የሚኾን፤ ከውሃ ላይ ሲያርፍ የሚረጋ። ከመ ዝቅ ውስተ አስሐትያ። እሳት ወበረድ ወአስሐትያ። ከመ አስሐትያ ቀጢን። አስሐትያ ይረግዕ ዲበ ማይ። ቀተለ ወይኖሙ በበረድ ወበለሶሙኒ በአስሐትያ ፡ (መዝ ፡ ፻፲፰። ፻፵፰። ጥበ፭ ፡ ፲፭። ሢራ፵፫ ፡ ፳። መዝ
፡ ፸፯)።
[3] ፡ (ዕብ ሼሌግ፤ ባራድ) ብትን በረዶ የውርጭ ዐይነት፤ ጠጠር በረዶ የደንጊያ ዐይነት፤ የውሃ በረዶ እብነ በረድ፤ የረጋ ውሃ ሉሕ ጡብ የሚያካክል፤ የስኳር ዐይነት፤ ከመጠጥ ገብቶ የሚያረካ የሚያቀዘቅዝ፤ በሚዛን የሚሼጥ።ከመ ፀአተ አስሐትያ በጊዜ ማእረር። ወእምከመ ረግዐ አስሐትያ ይትፈለጽ ከመ ስባራተ ማህው በሊኃት። እብነ አስሐትያ። ዝናም ወአስሐትያ አጥፍኡ እሳተ
፡ (ምሳ፳፭ ፡ ፲፫። ሢራ ፡ ፵፫ ፡ ፲፱። ሔኖ፸፩ ፡ ፭። ስንክ ፡ ሚያ፴)።
አስኀነ ፡ አሞቀ አተኰሰ፤ አበሰለ፤ አነደደ አጤሰ፤ ለማብሰል።
አስሐከ ፡ እሻከረ፤ አደረቀ፤ ሸካራ ደረቅ አደረገ፤ አስደረገ። ጢስ ምንሃብ ያስሕክ ሥጋሁ። አባላቲሁ አስሐከ በጾም ፡ (ሢራ፴፰ ፡ ፳፰። ስንክ ፡ ጥቅ፲፫)።
አስሓኪ መስሕክ ፡ የሚያሻክር፤ አሻካሪ፤ ሸካራ አድራጊ፤ አስደራጊ።
አስሐወ [1] ፡ አወለቀ፤–ስሒው ስሐወ።
[2] ፡ ሳበ ጐተተ፤ አሳበ አስዋኘ። አወለቀ፤ አስወለቀ፤ አስገፈፈ፤ የልብስ። ኢጸንሐ ለአስሕዎ ሐመር አላ ቀነጸ እምዲበ ሐመር ወተወርወ ውስተ ባሕር። አስሐወ ሎሙ ፊቃሮ ቅድስተ ወመጠዎሙ ክሣዶ ለጋላት ፡ (መጽ ፡ ምስ። ድጓ)።
አስህርት ፡ ሠርቀ ወርኆች፤–ሣህር።
አስለመ ፡ (ጥ ሰለ) አሰለመ፤ እስላም አደረገ፤ ራሱን ወይም ሌላውን። ፡ (ግጥም በራስ ዐሊ ጊዜ) የበጌምድር ዶቄት ክፉ ነው ቢያ ሽርንክት፤ እኛስ አስልመን በላነው ይብላኝ ለቀረ ሰው።
አሥለቀ ፡ አሠለቀ፤ አዘበተ፤ አስላጠ አስመለጠ።
አሥለጠ አው አሠለጠ ፡ አሠለጠነ፤ ሾመ አነገሠ፤ ሥልጣን ሰጠ። አሥለጦ ከመ ይብላዕ። ወኢያሥለጦ። ርድአኒ ለወጢኖቱ ወአሠልጠኒ ካዕበ ለፈጽምቱ
፡ (ማር ፡ ይሥ፳፪ ፡ ፩። መክ፮ ፡ ፪። አርጋ)።
አስል ፡ (ትግሬ፤ ዐረ) ዘር፤ ሥር፤ ጕንድ የትውልድ ምንጭ።
አሥልስት ፡ ሥልሶች፤ ሦስት እጆች፤ ክፍሎች ጊዜዎች። ሠለስተ አሥልስተ ዲናር
፡ (ስንክ ፡ ኅዳ፲፪)።
አሥመረ ፡ ሠመርኩ አሰኘ አሶደደ፤ አስፈቀደ። አገለገለ፤ ደስ አሰኘ። አሥመሮ ሔኖክ ለእግዚ። ኦ ንጉሥ ያሥምርከ ምክርየ። ኢያሠምሮ ለጻድቅ እኩይ ምንት
፡ (ዘፍ፭ ፡ ፳፬። ዳን፬ ፡ ፳፬። ምሳ፲፪ ፡ ፳፩)። አሠመረ አሰነበረ፤ ሠራ ቀጻ፤ የብራና የድጕስ የኅብስተ መሧዕት።
አስመረ ፡ አበጀ አሳመረ፤ አበቀለ አሳደገ፤ ፍሬያም አደረገ። እስከ ሶበ ያረውያ ለምድር ወያበቍቶ ወያሰምር። አስምሮ አዝርዕት። ወአስምሮ ለማእረራ። ያሰምር ማእረረ ጽድቅክሙ ፡ (ኢሳ፶፭ ፡ ፲። አርጋ ፡ ፩። መዝ ፡ ፷፬። ፪ቆሮ ፡ ፱ ፡ ፲)።
አስመከ ፡ አስጠጋ፤ አስደገፈ፤ አንተራሰ። አስምከኒ ላዕሌሆን። አስመከ ርእሶ ውስተ ሙዳየ በለስ። ያሰምክ መዝራዕቶ ቦቱ። ለወልደ ዕጓለ መሕያውሰ አልቦ ኀበ ያሰምክ ርእሶ ፡ (መሳ፲፮ ፡ ፳፮። ራእ ፡ ባሮ። ኤር፲፯ ፡ ፭። ሉቃ፱ ፡ ፶፰)።
አስመየ ፡ አሰየመ፤ ስም አስጠራ፤ እገሌ አሰኘ፤ የክፉ የበጎ። ዕደው እለ አስመዩ በኀይሎሙ ፡ (ሢራ፴፱ ፡ ፪። ፵፬ ፡ ፫። ሕዝ፳፫ ፡ ፳፫)።
አስማድዮስ ፡ (ጽር አስሞዴዎስ) የጋኔን ሰም፤ ሾተላይ ጋኔን፤ በሴት ዐድሮ ወንዶች በወንዶች ዐድሮ ሴቶች የሚፈጅ
፡ (ጦቢ፫ ፡ ፰ ፡ ፲፯። ዮሐ፬ ፡ ፲፰። ማቴ፳፪ ፡ ፳፭–፳፯)።
አስምዐ ፡ አሰማ፤ አስደመጠ፤ አረዳ አስረዳ አስታወቀ፤ አስጠነቀቀ፤ ስሞታ ነገረ፤ አስመስከረ። ለጽሙማን ያሰምዖሙ። አስምዐኒ ቃለከ። በሰማዕት አስምዐ ለነ። አስምዕ ላዕሌሆሙ ከመ ኢየሀቡ። አስምዕ ሰበአ ምእመናነ። ናሰምዕ ለክሙ ሰማየ ወምድረ
፡ (ማር፯ ፡ ፴፯። ማሕ፪ ፡ ፲፪። ዘፍ፵፫ ፡ ፫። ኩፋ ፡ ፴። ኢሳ፰ ፡ ፪። ዮዲ፯ ፡ ፳፰)። ዳግመኛም በሰምዐ ፈንታ አስምዐ ይላል፤ ስሕተት ነው። እስመ እግዚ አስምዐ ማእከሌከ ወማእከለ ብእሲትከ ፡ (ሚል፪ ፡ ፲፬)።
አስረረ ፡ በቁሙ፤ በላይ፤ አደረገ፤ ጣደ። ፡ (ተረት) ከበሮውን አስረሽ ምችው። አጠፋ አራቀ አበረረ። ኀልዮ ንዋይ ያሰርር ንዋመ። ያሰርር ውስተ አርያም ዕጐሊሁ ፡ (ሢራ፴፬ ፡ ፩። ዕን፪ ፡ ፱)።
አሥረቀ [1] ፡ አወጣ፤ አበቀለ፤ አበራ፤ ገለጠ፤ ብልጭ አደረገ። እስመ ውእቱ ያሠርቅ ፀሓየ። ያሠርቅ እግዚ ጽድቀ ወሐሤተ። አሥረቀ ንስቲተ መለኮቶ ፡ (ማቴ፭ ፡ ፵፭። ኢሳ፷፩ ፡ ፲፩። ቅዳ)። አሠረቀ አባተ።
[2] ፡ ማለደ ፥ አማለደ፤ አዘወተረ፤ የጧት መዝሙር ስብሐተ ነግህ ማቅረብ። በአጽዋም ለእመ ሀሎ አሥርቆት። አርያም ዘአሥርቶት ፡ (ሥር ፡ ድጓ)።
አስረቀ ፡ አሰረቀ፤ ስረቁ አለ፤ ስርቆት አስተማረ።
አሥረከ ፡ ወዘመ፤ ዋዜማ ቆመ፤ የሠርክ ጸሎት አቀረበ። ያሠርክ በጸሎት ፡ (ቄድር)።
አስረየ አስተረየ ፡ አስተሰረየ፤ ይቅር አሰኘ፤ ይቅርታ ለመነ፤ አማለደ፤ በካሳ በጸሎት በመሥዋዕት። ያስተስሪ ሎሙ ካህን። ካህን ዘያስተሰሪ ኀጣውአ ሕዝብ ፡ (ዘሌ፬ ፡ ፳። ፱ ፡ ፯። ፲፪ ፡ ፯ ፡ ፰። ፲፬ ፡ ፲፱። መጽ ፡ ምስ)።
አሥረጸ ፡ አበቀለ፤ አስበቀለ፤ አወጣ፤ አስገኘ። ያሠርጽ ሣዕረ ለእንስሳ። ኣሠርጽ ለዳዊት ሠርጸ ጽድቅ። ዘአሥረጸ ልብ ኪያሆን ፡ (መቃ። ኤር፵ ፡ ፲፭። ፍ ፡ ነ ፡ መቅ)።
አሥራም ፡ ረግረጎች፤ ጥልቆች። እሞገደ አሥራም
፡ (አርጋ። ቄር)።
አስራብ ፡ ፈሳሾች፤–ሰሪብ ሰረበ፤ ሰርብ።
አሥራው ፡ ዝኒ ከማሁ። አዕፅምት ወአሥራው። ደዌ አደግደገ ሥጋሁ፤ ወተዐውቀ አሥራወ እንግድዓሁ ፡ (ተረ ፡ ቄር። ዮሴፍ)።
አሥራግ [1] ፡ መስኖች፤–ሠርግ ሠረገ።
[2] ፡ መስኖዎች። ዲበ አሥራጊሆሙ ፡ (ዘፀ፯ ፡ ፲፱። ፷ ፡ ፭)።
አስርሐ ፡ አሰራ፤ አደከመ፤ አሸከመ፤ አሰለቸ። ብእሲ ኃጥእ ያሰርሖ ለቢጹ። አስርሕዎሙ ለእለ ለቅሕዎሙ። አስራሕክሙ ብዙኃነ በሕግ። ለምንት ታሰርሑኒ ፡ (ሢራ፳፰ ፡ ፬። ፳፱ ፡ ፪። ሚል፪ ፡ ፰። ኢዮ፲፬ ፡ ፳፪)።
አስቀለ ፡ አሰቀለ፤ አስመዘነ።
አስቀሎባ ፡ አስቀሎባ፤ አርስጣላብ፤ የፍልስፍና ክታብ፤ መጽሐፈ ኮከብ። አስቀሎባና አርስጣላብ አንድ ስም ናቸው። ወገብረ በጥበብ መጽሐፈ አስቀሎባ ወራእየ ከዋክብት ወመዳልወ ፀሓይ
፡ (ክብ ፡ ነገ)።
አስቀጢን ፡ ፣ ፡ (ጽር ስታክት) ጥሩ ሽቱ፤ ከዕጣን ከከርቤ የሚወጣ፤ ለትኵሳት ሬሳ የሚቀባ፤ ሬሳን እንዳይገማና እንዳይፈርስ እንዳይበሰብስ የሚያደርግ። ሐነጠንና ሰጡቃጤን እይ፤ ከዚህ ጋራ አንድ ነው ፡ (አቡሻ ፡ ፵፰)።
አስቄጥስ ፡ (ሮማይ አስኬታ) በረሓ፤ የበረሓ ስም በምድረ ግብጽ ውስጥ ያለ፤ የመቃርዮስ ክፍል ገዳመ ሲሃት። አ አልቦ፤ ስኬታ ጽላሎት፤ በተገናኝ አልቦ ጽላሎት ማለት ነው። ቀድሞ ብዙ ገዳማት ነበሩበት፤ ዛሬ ያሉት ግን ፬ ብቻ ናቸው፤ የታላቁ መቃርዮስና የመክሲሞስ የዱማቴዎስ ያባ ብሶይና የዮሐንስ ከማ
፡ (ስንክ ፡ መጋ፳፯ ፡ ፊልክ)። በቅብጥ ቋንቋ ግን ሚዛን፤ የሚዛን ሳሕን ማለት ነው ይላሉ። ገዳመ አስቄጥስ ዘበትርጓሜሁ መዳልወ አልባብ ፡ (ስንክ ፡ ጥቅ፳)።
አስቈረ ፡ አሸነቈረ፤ አስበሳ አስነደለ።
አስቈረረ ፡ (ተቀ ግ) አስጠየፈ፤ አሽቈረረ፤ አስጠያፊ ኾነ፤ ለሌላው። ተጠየፈ፤ ተሸቈረረ፤ ተጠያፊ ኾነ፤ ጦላ ተሰቀቀ፤ እንደ ርኵስ አየ፤ ሌላውን። ብእሴ ደም ወጕሕላዌ ያስቈርር እግዚ። ታስቈርር ጣዖተ። ጸሊኦቶ ወአስቈርሮቶ ፡ (መዝ
፡ ፭። ሮሜ፪ ፡ ፳፪። ዮሴፍ)።
አስቈቀወ ፡ (ተቀ ግ) ጮኸ ዋይ አለ፤ የወደደውን ስላጣ፤ እንደ ሕፃን ተንሰቀሰቀ፤ አልቅሶ አስለቀሰ፤ አሞሸ ቈዘመ፤ ሙሾ አወጣ፤ ተቀኘ ገጠመ። ቀነየንና ነቀወን ሰንቀወን ተመልከት፤ የዚህ ጎር ናቸው። አስቈቅዉ ሰቈቃወ። አስቈቀውነ ለክሙ ወኢበከይክሙ። አንስት ይበክያሁ ወያስቈቅዋሁ ለተሙዝ። እለ ይበክዩ ወያስቈቅዉ ፡ (ሚክ፪ ፡ ፬። ማቴ፲፩ ፡ ፲፯። ሕዝ፰ ፡ ፲፬። ቀሌ)።
አስቈቈ አስተስቈቈ ፡ አሻ አስፈለገ፤ አስመኘ አስጐመዠ ፡ (ገድ ፡ ኪሮ)።
አስበረ ፡ አሰበረ፤ ስበሩ አለ፤ ድል አስደረገ። አሸበረ ማለት የዚህ ዘር ነው።
አሥበጠ ፡ (ትግ ሐባ የብጠ፤ ቀለተ) ኣቀረበ ፥ አስታረበ፤ ጋበዘ አጐረሠ፤ አሲያዘ አስበበተ፤ ሥንቅ ሰጠ፤ አስቋጠረ። አልብየ ዘኣሠብጦ። ወያሠብጦሙ ለዕሙፃን ፡ (ሉቃ፲፩ ፡ ፮። ፊልክ
፡ ፫)።
አሥባሒ ፡ መሥብሒ ሕ፤ የሚያሠባ፤ አሥቢ ቀላቢ።
አስባብ [1] ፡ ዘበኞች፤–ሰቢብ ሰበ፤ ሰበበ።
[2] ፡ ሰበቦች፤ በሰበብ ባስባብ እንዲሉ። ከባቦች፤ ዘበኞች፤ በዙሪያ ያሉ፤ ኀያላን ያርብሓን። ወዕደውሰ እለ አስባብ ኵሎሙ በቅድመ አብያቲሆሙ ይቢቱ ወያጽንዑ ዐቂበ። አንቅህዎሙ ለአስባቢሃ ፡ (ነሐ፯ ፡ ፫። ኤር፳፰ ፡ ፲፪)።
አሥብሐ ፡ አሠባ፤ አወፈረ አገዘፈ። አሥብሕ መሥዋዕተከ። ቦሙ አሥብሐ መክፈልቶ። ወአሥብሐ ኪያሃ። አሠንዮ ሥጋ ወአሥብሖቶ ፡ (ሢራ፴፰ ፡ ፲፩። ዕን፩ ፡ ፲፮። ፍ ፡ ነ ፡ ፴፭። አፈ ፡ ተ፲፰)።
አስብአ ፡ አጠገበ፤ አስረገዘ።
አስተ ፡ (አስ
፡ ተ) አስ የማስደረግ ተ የመደረግና የመደራረግ ልማድ። በተገናኝ ኹለቱ አንድ ሲኾን፤ አስተ የማድረግና የማስደረግ የማደራረግ ይኾናል፤ መደቡ ግን የማደራረግ ነው። የማድረግና የማስደረግ ሲኾን ሥርወ ቀለሙን ግእዝና ሳድስ ያደርጋል፤ ይኸውም በአ ፈንታ ስለ ገባ ነው። ግእዝ ሲያደርግ፤ ገበረ አስተገበረ፤ ሐመመ አስተሐመመ፤ ሐመቀ አስተሐመቀ፤ ሐቀረ አስተሐቀረ፤ ዐጸበ አስተዐጸበ፤ ቀጸለ አስተቀጸለ፤ ረሰየ አስተረሰየ ይላል። ሳድስ ሲያደርግ፤ በፅዐ አስተብፅዐ፤ በቍዐ አስተብቍዐ፤ ነፍሰ አስተንፈሰ፤ ነተነ አስተንተነ፤ ፈሥሐ አስተፍሥሐ፤ ርእየ አስተርአየ፤ ሰረየ አስተስረየ ይላል። የማደራረግ ሲኾን ግን ሥርወ ቀለሙን ራብዕ ያደርጋል፤ መለዮው ይህ ነው። ይህም በደረ አስተባደረ፤ ወደየ አስተዋደየ፤ ነበረ አስተናበረ፤ ሠነየ አስተሣነየ፤ ቀተለ አስተቃተለ እያለ መኼዱን ያሳያል። ልማድን ተመልከት።
አስተኃለቀ ፡ አስተላለቀ፤ አጫረሰ፤ አለያየ አፈራቀቀ።
አስተኃለፈ ፡ አስተላለፈ፤ አመሳቀለ። አስተኃለፈ እዴሁ ፡ (ዘፍ፵፰ ፡ ፲፰)።
አስተሐመመ ፡ (አስተሕመመ) የሐመመና የአሕመመ ድርብ፤ ገቢርና ዐጕል። አሳመመ፤ ለሕማም እጠ። እግዚ ፊተወ ያስተሐምሞ
፡ (ተረ ፡ ቄር፩)።
፡ አስታመመ ረዳ፤ ጠበቀ፤ ሰበሰበ። እለ አስተሐመምዎ ለአትናቴዎስ። ዘኢክህለ ሠሪዐ ቤቱ እፎ ያስተሐምም ቤተ እግዚ። አስተሐምም ዘውስተ ገዳም ሐመልማለ ፡ (አዋል።፩ጢሞ ፡ ፫ ፡ ፭። ምሳ፳፯ ፡ ፳፬)።
፡ ዐሰበ አስተነተነ፤ ተጋ እንቅልፍ ዐጣ። ምስጢሩ ከዚያው ከማስታመም ይገባል። ያስትሐምሙ ኀበ ዘይትሌዐል። ሙት እምፍትወታቲሁ ለዝ ዓለም ወአስተሐምሞቱ። ተኀሥሥ አስተሐሚማ እስከ ትረክብ ፡ (አፈ ፡ ድ፳፯። ፊልክ ፡ ፫። ሉቃ፲፭ ፡ ፰)።
አስተሓመመ ፡ አስተማመመ፤ አመቀኛኘ። ነገር ሠርቶ፤ መድኀኒት ሰጥቶ።
አስተሓመወ ፡ አስተማመቸ፤ አስተጫጨ፤ አዛመደ።
አስተኃሠሠ ፡ አፈላለገ አመራመረ።
አስተሓረደ ፡ አስተራረደ፤ አጋደለ አቈራረጠ።
አስተሓቀፈ ፡ አስተቃቀፈ፤ አያያዘ አጣመረ፤ አቀባበለ።
አስተኃበለ ፡ አዳፈረ አደፋፈረ፤ አጨካከነ።
አስተሃከየ ፡ አሳነፈ፤ አሰናነፈ፤ አደራራጊ።
አስተሓወረ ፡ አካኼደ ፥ አዋሰደ አናዳ፤ የእግር የነገር። ያስተሓውሩ ነቢበ። ኢያስተሓውራ ነገረ ፡ (ነሐ፮ ፡ ፲፱። ቲቶ፪ ፡ ፫)።
አስተሓወዘ ፡ አጣጣመ አጠፋፈጠ፤ አሰማመረ። አስተሓዊዘከ ግስስ። ያስተሓውዝ ሎሙ ጽሙና። ያስተሓውዝ ፍትወተ ውስተ ልብ
፡ (ምሳ፱ ፡ ፲፯። ፊልክ
፡ ፺። አርጋ ፡ ፪)።
አስተሓዘለ ፡ አስተዛዘለ፤ የዜማ የድጋም። ይበል በአስተሓዝሎ ፡ (ድጓ)።
አስተሓዘበ ፡ አስተዛዘበ፤ አጠራጠረ፤ አስተማማማ።
አስተኃየለ ፡ አበራታ አበረታታ፤ አጠነካከረ።
አስተኃየሰ ፡ አሻሻለ፤ አበላለጠ። ንዑ ናስተኃይስ ነገረ። ተቃንኦ በእንተ አስተኃይሶ ወበእንተ ክብር
፡ (ዕዝ፫ ፡ ፭። ሄርማ ፡ ገ፸)።
አስተኃደረ ፡ አስተዳደረ። አስማማ፤ አስተካከለ፤ የሕንፃ። መኑ አስተኃደረ ማእዘኒሃ ፡ (ኢዮ፴፰ ፡ ፮)።
አስተኃደገ ፡ አፋታ አላቀቀ፤ አለያየ ገላገለ። ተባአሱ ከልኤሆሙ ወአልቦ ዘያስተኃድጎሙ በማእከሎሙ ፡ (፩ነገ ፡ ፲፬ ፡ ፮)።
አስተላሀቀ ፡ አላላቀ፤ አበላለጠ።
አስተላሀየ ፡ (አስደራጊና አደራራጊ) አስጫወተ፤ አጨዋወተ። እልኩ መጽኣ ኀቤየ ወያስተላህያኒ ፡ (ሄርማ ፡ ገ፹፭)።
አስተላቀሰ ፡ አላቀሰ፤ አለቃቀሰ አስተዛዘነ። ስሕልት ሰይፍከ ብእሲ ልዑል፤ ፡ (የተሳለች ሰይፍኽ ታላቅሰው) ለሰብአ ሞረት ወመርሐ ቤቴ አምኃ ኢየሱስ መስተጋድል ፡ (ቀጠፋ ቅኔ)። መጽሐፍ ግን በናዘዘ ፈንታ አስተላቀሰ እንደ ማለት አላቀሰ ይላል፤ ስሕተት ነው። ወብዙኃን እምነ አይሁድ እለ ሖሩ ኀበ ማርያ ወማርታ ከመ ያላቅስዎን በእንተ እኍሆን
፡ (ዮሐ፲፩ ፡ ፲፱)።
አስተላዐለ ፡ አናሣ አጫጫነ፤ ከፍ ከፍ አዳረገ። አስተላዕል ምስሌሁ ፡ (ዘዳ፳፪ ፡ ፬)።
አስተላክአ ፡ አላካ ፥ አለካካ፤ እገጣጠመ።
አስተላጸቀ ፡ አላጠቀ፤ አጣጋ አቃረበ። ዛቲ መጽሐፍ አስተላጻቂተ ርሑቃን። በአስተላጽቆ ፡ (ፈላስ። ስንክ ፡ ሠኔ፲፪)።
አስተማሐረ ፡ አማማረ አላመነ፤ አመላለደ አስተዛዘነ። ተፋቅሮ ያስተማሕር
፡ (፩ቆሮ ፡ ፲፫ ፡ ፬)።
አስተማህረከ ፡ አማረከ፤ አመራረከ። እንደ አማህረከም ባስደራጊነት ይፈታል።
አስተማለሰ ፡ አማለሰ፤ አመላለሰ ፡ (አደራራጊ)።
አስተማልኀ ፡ አማዘዘ፤ አናቀለ። ወይን ያስተማልኆሙ መጣብሒሆሙ
፡ (ዕዝ፫ ፡ ፳፩)።
አስተማልዐ ፡ አዋሰደ ፥ አወሳሰደ፤ አናዳ አካኼደ። ማእዜ ይሠርቅ ወርኅ ንምላዕ ወናስተማልዕ(ዓሞ፰ ፡ ፭)።
አስተማሰለ ፡ አማሰለ፤ አመሳሰለ ፥ አነጻጸረ። ምስጢሩ ማድረግና ማደራረግ ነው፤ ባድራጊነቱ ከመዠመሪያው ዐምድ ይደረባል። ረድኡ ለሊቀ ምኔት ይኩን አስተማሳሌ ግብረ ኤልሳዕ ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፲)።
አስተማዕዐ ፡ አጣላ አጋጨ፤ አቋጣ አበሰጫጨ። ኢያስተማዕዕ ፡ (፩ቆሮ ፡ ፲፫ ፡ ፭)።
አስተማከረ ፡ አማከረ፤ አመካከረ፤ ተማከሩ አለ፤ ምክር አካፈለ።
አስተማወቀ ፡ አሞቀ፤ አሟሟቀ። በዝየ ያስተማውቅ እዴሁ ካህን ላዕለ ማዕጠንት። አንዘ ያስተማውቆሙ በኵሉ ምዕዳን ፡ (ቅዳ። ገድ
፡ ኪሮ)።
አስተማወጸ ፡ አካካሰ፤ አስተራረቀ። ለዘተጻዐለ ያስተማውጽዎ ፡ (ሢራ፳፯ ፡ ፳፩)።
አስተማጽአ ፡ አማጣ አመጣጣ፤ አናዳ አማጭ ኾነ፤ በእግር በነገር። ወልድየ ኢትደመር ለአስተማጽኦ ብእሲት ፡ (ፈላስ)።
አስተምሐረ ፡ ለመነ ማለደ፤ አማለደ አስማረ፤ ማረኝ ማርልኝ አለ። አስተምሕር ለነ ሚካኤል። ሰአሉ ለነ አስተምሕሩ ለነ ፡ (መሥዋ። ድጓ)።
አስተሟቅሐ ፡ (ያስተሟቅሕ፤ አው አስተም(መ) ዋቅሐ ያስተመዋቅሕ) አስተሳሰረ።
አስተሰናአወ ፡ አጋጠመ፤ አገጣጠመ፤ አሰማማ፤ አስታረቀ፤ አንድ አደረገ። እለ ያስተሰናእዉ ለግብረ ዝሙት። አስተሰናአዎሙ በበይናቲሆሙ። ይእቲ እንተ ታስተሰናኡ። መኑ ያስተሰናእዎሙ ለአክልብት ምስለ አዝእብት። ወልደ እግዚ አስተሰናአወ አናብስተ ምስለ ዳንኤል ፡ (ፈ ፡ መ ፡ ፮ ፡ ፲፫። አፈ
፡ ድ፪። ያዕ፫ ፡ ፲፯። ሢራ፲፫ ፡ ፲፰። ሲኖዶ)።
አስተሰናኣዊ ፡ የሚያሰማማ የሚያጋጥም፤ አንድ የሚያደርግ፤ አስታራቂ። ልሳን አስተሰናኣዊት ይእቲ ማእከለ ዘተዘርወ
፡ (ፈላስ)።
አስተሳለመ ፡ አስታረቀ፤ አሰማማ፤ አፋቀረ፤ አንድ አደረገ፤ አሳለመ፤ አገናኘ። ለመስተፃርራን አስተሳልምዎሙ። አስተሳለመ በመስቀሉ ዘበሰማይ ወዘበምድር። ፈቀደ እስክንድር ያስተሳልሞሙ። ታስተሳልሞ ለበድን ኀበ ታቦት ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፵፫ ፡ ፰። ቄር። ዮሴፍ። ግንዘ)።
አስተሣለቀ ፡ አሣለቀ፤ አዘባበተ አጨዋወተ።
አስተሳመከ ፡ አዋደደ፤ አጋጠመ፤ አሰማማ። አናበበ፤ አዛረፈ።
አስተሳምዐ ፡ አሰማማ አደማመጠ፤ እንዲሳሙ እንዲዳመጡ አደረገ፤ የስልክና ያምጃር።
አስተሳረቀ ፡ አሳረቀ፤ አሰራረቀ፤ አቀላቀለ፤ አደባለቀ። እመስኬ አሐተ ህላዌ ዘወልድ ንነግር ዘተሰገወ ግብረ ነአምን ቱስሕተ ወኁሠተ ወናስተሳርቅ ህላዌ ትስብእት እንተ በላዕሌሁ ፡ (ቄር ፡ ጰላ)።
አስተሳረየ ፡ አካካሰ፤ አስተራረቀ፤ ይቅር አባባለ፤ ፡ (አርጋ)።
አስተሳተፈ ፤
(ሳተፈ) ፤
አሳተፈ ፤
አስተባበረ። ሳተፈን ተመልከት ፤ የባረከ ቤት ተደራጊው ከተደራራጊው እንዲደረብ አደራራጊውም ካድራጊው አንቀጽ ይደረባል።
ናፈቀንና ሣሀለን ሣረረን ተመልከት።
አስተሳነነ ፡ አጣላ፤ አሟገተ አከራከረ፤ አፋረደ። እስከ ታስተሳንኑ። አስተሳንኖት
፡ (፩ቆሮ ፡ ፮ ፡ ፮። ፈ ፡ መ ፡ ፳፫ ፡ ፯)።
አስተሳአለ ፡ አላመነ፤ አለማመነ፤ አጠያየቀ፤ አሟገተ አከራከረ፤ ተጠየቅ አስኘ።
አስተሣየመ ፡ አሿሿመ፤ አቀማመጠ።
አስተሣየጠ ፡ አሻሻጠ አሻጠረ፤ አገበያየ አዋጀ አወጃጀ።
አስተሳጠወ ፡ አጠያየቀ፤ አባባለ፤ አከራከረ፤ እንደ ቈስጠንጢኖስ።
አስተራሐቀ ፡ አራራቀ፤ አለያየ፤ ገላገለ፤ ከፋፈለ። ቆመ ማእከሎሙ ወአስትራሐቆሙ። አስተራሕቅዎሙ ዘዘ ዚኣሆሙ ፡ (፬ነገ
፡ ፪ ፡ ፲፩። ዳን፩ ፡ ፶፩። ዘፍ፴፪ ፡ ፲፮)።
አስተራመመ ፡ (አደራራጊ) ዝም አስኛኘ፤ ገላገለ፤ እንዳይባባል አደረገ።
አስተራብሐ ፡ አራባ፤ አባዛ፤ አጠቃቀመ። አስተራብሖ ንዋይ ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፴፬)።
አስተራትዐ ፡ አረታታ። አቃና፤ አቀናና፤ አዘገጃጀ። ታስተራትዕ ኵሎ ነፍሰ። ታስተራትዕ ምድረ
፡ (ዮዲ፲፩ ፡ ፯። ኢሳ፵፱ ፡ ፰)።
አስተራአየ ፡ አስተያየ፤ አነጻጸረ ፊት ለፊት፤ ዐይን ለዐይን።
አስተራከበ ፡ አራከበ፤ አጋባ፤ የተክል። አገናኘ አጋጠመ፤ ሰበሰበ። ወአስተራከቦ ምስለ ውሉዱ ኀበ ያስተራክቡ ክነፊሆሙ። ወአስትራክብ ኵሎ ተዓይነ ፡ (ስንክ ፡ መጋ፲፱። ፫ነገ ፡ ፮ ፡ ፳፪። ዘሌ፰ ፡ ፫)።
አስተራኰሰ ፡ አራከሰ፤ አረካከሰ፤ አስተዳደፈ። ዐማርኛው አድራጊ ይመስላል።
አስተራድኦ ፡ አራዳ አረዳዳ፤ አስተጋገዘ።
አስተራገፀ ፡ አራገጠ፤ አፈራገጠ፤ የጋኔን። ይነፅኆ ወያስተራግፆ
፡ (ማር፩ ፡ ፳፮። ፱ ፡ ፲፰ ፡ ፳)።
አስተርአየ ፡ (አርአየ) አሳየ፤ ገለጠ። ባለቅኔዎች ግን ታየ አሳየ ብለው በኹለት ጾታ ይፈቱታል፤ ታየ ማለት ስሕትት፤ አሳየ ማለት፤ እውነት። ወዘንተሰ አማነ ትቤሊ ፡ (ዮሐ፬ ፡ ፲፰)።
አስተርከበ ፡ (የአርከበ ድርብ) አቀረበ፤ አስነካ። ወአስተርከቡ ወዐጸሩ ውስተ አፉሁ ፡ (ዮሐ፲፱ ፡ ፳፱)።
አስተቀየመ ፡ አስቀየመ፤ አሳዘነ፤ ክፉ አሳሰበ።
አስተቍጥዐ ፡ አስቈጣ፤ አሳዘነ፤ አበሳጨ፤ አስወገሸ። ፈድፋደ አስተቍጥዐኒ ሕይወቶሙ። ነገሮሙ ለአብዳን ያስተቈጥዕ ፡ (ሢራ፳፭ ፡ ፪። ፳፯ ፡ ፲፫)። ኹለተኛም፤ አቈጥዐ ያቌጥዕ፤ አስተቈጥዐ ያስተቌጥዕ ያሰኛል።
አስተቃለሰ ፡ አስታገለ፤ አዋጋ፤ አመላለሰ። ዲበ አርእስተ አድባር ለተነ ጊሜ ዘያጠይሶ፤ እንበለ ረዓም ዘያገሕሦ፤ ውስተ አየራት ዘያስተቃልሶ
፡ (መጽ ፡ ምስ)።
አስተቃሠመ ፡ አሟረተ፤–ቀሰመ።
አስተቃሰመ ፡ (አደራራጊ) አጠናቈለ፤ አጠነቋቈለ፤ መላ አማታ።
አስተቃረበ ፡ አቃረበ፤ አቀራረበ። አሌ ሎሙ ለእለ ያስተቃርቡ ገራህተ ምስለ ገራህት
፡ (ኢሳ፭ ፡ ፰። ዲድ ፡ ፩)። አቅረበ አስተቅረበ በማለት ፈንታ አስተቃረበ ይላል፤ ስሕተት ነው። ነሥአ ብእሴ ወኪያሁ አስተቃረቦ ለርእሱ
፡ (ቄር ፡ ጰላ)።
አስተቃረነ ፡ አዋጋ፤ አጣላ፤ አከራከረ፤ አወዳደረ።
አስተቃተለ ፡ አጋደለ፤ አገዳደለ፤ አዋጋ አጣላ፤ አፋጀ አጫረሰ፤ አስተላለቀ። ብዙኃነ አዕርክተ አስተቃተለ። ከመ ያስተቃትሎሙ በኀጺን ወበረኀብ ፡ (ሢራ፳፰ ፡ ፲፫። ራእ፮ ፡ ፰)።
አስተቃነጸ ፡ አዛለለ አፈናጨ። ፈረስከ ዘትጼዐኖ እንዘ ያስተቃንጽ እግሮ
፡ (ደራሲ)።
አስተቃንአ ፡ አቃና፤ አቀናና፤ ብእሲት እንተ ታስተቃንእ ፡ (ሢራ፳፮ ፡ ፮)።
አስተቃወመ ፡ አቋቋመ፤ አሟገተ፤ አከራከረ፤ አወዳደረ፤ አፈካከረ።
አስተቈናደየ ፡ አዛለለ፤ አቃበጠ፤ አስታበየ አጓደደ።
አስተቋጸረ ፡ አቋጠረ፤ አቈጣጠረ፤ አስተሳሰረ።
አስተበውሐ ፡ አስፈቀደ፤ ዕሺ አሰኘ፤ አስጨከነ አስደፈረ። አስተበዊሖ በኀበ ሊቀ ካህናት መጽአ ከመ ይሞቅሕ ኵሎ። እስተበውሓ ለበሊዐ ዕፀ ዕልወት። አስተበውሖቶሙ ለበሊዐ ንዋየ ውስጥ ፡ (ግብ፱ ፡ ፲፬። መጽ ፡ ምስ። ጥበ፲፪ ፡ ፭)።
አስተባሀለ ፡ አባባለ፤ አሟገተ አከራከረ።
አስተባልሐ ፡ (አስደራጊና አደራ ራጊ) አስዳነ አስቤዠ፤ አስወጣ። አዳዳነ አዋጣ፤ ዐገዘ ረዳ፤ ለማዳን ለማውጣት። እስመ ኢያስተባልሐከ እግዚ
፡ (መቃ ፡ ገ፳፩)።
አስተባልዐ ፡ አባላ፤ አናከሰ፤ አፋጀ፤ አስተላለቀ።
አስተባረከ ፡ አበራረከ አመራረቀ፤ አመሰጋገነ። ዳግመኛም አባረከ በማለት ፈንታ አስተባረከ ይላል፤ ምክንያቱም የባረከ ቤት ተደራጊው ከተደራራጊው እንዲደረብ፤ አስደራጊውም ካደራራጊው ይደረባልና፤ ስለዚህ ነው። መደረቡም ሥርወ ቀለሙ ራበዕ ስለ ኾነለት ነው፤ ተቃተለ አስተቃተለ እንደ ማለት፤ አስተን እይ።
አስተባአሰ ፡ አባባሰ፤ አጣላ አጠላላ፤ አሟገተ አከራከረ። አባባሰ ማለት ዐማርኛው መነኵሴ ይነካል። አስተባአሶሙ በጽልእ። ዘያስተባእስ ወዘያስተሳልም በምንትኒ ግብር ኢይደልዎ ከመ ይኩን ስምዐ በውአቱ ግብር ፡ (ዮሴፍ። ፍ ፡ ነ ፡ ፵፫ ፡ ፲፪)።
አስተባዐደ ፡ አለያየ፤ አራራቀ፤ ነጣጠለ ከፉፈለ። ያስተባዕድ ሥላሴ፤ እፎ ያስተባዕዶ ለዘኢይትባዐድ ፡ (መጽ ፡ ምስ)። .
አስተባከየ ፡ አላቀሰ፤ አለቃቀስ። ስሕልት ሰይፍከ ብእሲ ልዑል፤ ለሰበአ ሞረት ወመርሐ ቤቴ አምኃ ኢየሱስ መስተጋድል። የተሳለች ሰይፍኽ ታላቅ ሰው
፡ (ያማርኛ ግእዝ)።
አስተባውአ ፡ አጋባ፤ አገባባ፤ አዛወገ።
አስተባዝኀ ፡ አባዛ አራባ፤ አዋለደ አበራከተ። ኣስተባዝኀከ ጥቀ ፡ (ዘፍ፲፯ ፡ ፮ ፡ ፳)።
አስተባየተ ፡ አስተዳደረ፤ አዋገነ፤ አጎራበተ።
አስተባየጸ ፡ አመሳሰለ፤ አወዳጀ፤ አቀናጀ፤ አሰማማ። እንዘ ያስተባይጾሙ ምስሌሁ ፡ (መጽ ፡ ምስ)።
አስተባደረ ፡ አቀዳደመ፤ አሽቀዳደመ፤ አፈራረቀ፤ የፈረስ የእግር። አምጣነ ጊዜ ሠርክ ንረውጽ እንዘ ናስተባድር እግረ እክል ኀበ ሀሎ ወላሕም ኀበ ሖረ ፡ (ቅኔ)።
አስተባጽሐ ፡ አዳረሰ አገናኘ አጋጠመ፤ አረታታ አነጣጠረ።
አስተብቍዐ ፡ ለመነ ማለደ፤ ማላጅ አማላጅ ኾነ፤ ዘበዘበ ማረኝ ማርልኝ አለ። አሐተ ስእለተ ኣስተበቍዕ በኀቤከ። በእንተ ምንት ታስተበቍዕኒ። ወካዕበ ናስተበቍዖ ለአምላከ ምሕረት። ጊዜ ጸሎትነ ወአስተብቍዖትነ ፡ (ኩፋ
፡ ፴፭። አስቴ፭ ፡ ፫። ቅዳ)።
፡ ናዘዘ አጽናና፤ ደስ አሰኘ፤ አትዘን አታልቅስ አለ። ምስጢሩ ያው ልመና ነው። ኢታብዝኈ አስተብቍዖትየ። ያጽንዕክሙ ወያስተብቍዕክሙ በእንተ ሃይማኖትክሙ ፡ (ኢሳ፳፪ ፡ ፬። ፩ተስ ፡ ፫ ፡ ፪። ዘፍ፴፯ ፡ ፴፭። ፪ነገ ፡ ፲ ፡ ፫)።
አስተብቋዒ ፡ የሚማልድ የሚያማልድ፤ ማላጅ አማላጅ፤ አስታራቂ። አስተብቋዕያን ለክሙ ኀበ እግዚ ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፭።ቅዳ ሕር)።
አስተብፅዐ ፡ (አድራጊ) አከበረ አመሰገነ አደነቀ። ጥቅስ እንዳለፈው ነው። አስተብፅዑ ነፍስተ ዓሣ ፡ (ቅኔ)።
አስተተ ፡ አዋረደ አዋደቀ አጣጣለ፤ ናቀ አቃለለ፤ ተወ ቸል አለ፤ አስታጐለ። እለ አስተትዎ ለጻድቅ። ዘያሰትት ግብረ እግዚ ውእቱኒ ያሰትቶ። ኢታስትት ቃሎ ለአክዮር። አስቲተነ ሕይወተ። ኢታስትት ገቢረ ምጽዋት። ኢታስትት ተግባረ እደዊከ ፡ (ጥበ፫ ፡ ፲። ምሳ፲፫ ፡ ፲፫። ዮዲ፲፩ ፡ ፲። ዕብ፪ ፡ ፫። ሢራ፯
፡ ፲። ፲፭)።
አስተታለወ ፡ አከታተለ፤ አራደፈ። እንዘ ያስተታልዎን ለአሐቲ ድኅረ አሐቲ። በአስተታልዎ። እለ ያስትታልዎሙ ፡ (ስንክ ፡ መስ፭። አቡሻ ፡ ፱። ዮዲ፫ ፡ ፮)።
አስተታብዐ ፡ አጨካከነ፤ አጸናና። ለአስተታብዖ በቅድመ ጸባኢት ፡ (መጽ ፡ ምስ)።
አስተናሰከ ፡ አናከሰ፤ አባላ አጣላ። ከመ ያስትናስኮሙ ለደቂቃ ፡ (መጽ
፡ ምስ)።
አስተናሥአ ፡ አናሣ፤አነሣሣ አወከ። አድራጊና አደራራጊ ነው፤ ባድራጊነቱ የአንሥአ ድርብ። ጸላእቶ ያስተናሥእ። ረድኤቱ ወአስተናሥኦቱ። ዝንቱ ግብር አስተናሥኣ ለይእቲ ብእሲት። ያስትናሥእ ኅሊና ወየሀውክ
፡ (ኢሳ፱ ፡ ፲፩። ፈ ፡ መ ፡ ፫ ፡ ፮። አፈ ፡ ድ፳፮። ፈላስ ፡ ገ፶፮)።
አስተናበረ ፡ በቁሙ፤ አነባበረ ፥ አቀማመጠ፤ አበጀ አዘጋጀ አሰናዳ፤ ሰደረ ደረደረ። አስተናበረ ዕፀወ። ቅዳሕ ወይኖ ወአስተናብር። አስተናበረ አድባረ ወአውግረ። አበው አስተናበሩ ቀኖናሆሙ። ወአስተናበረ ምዕራፋተ ፡ (፫ነገ ፡ ፲፰ ፡ ፴፫። ዳን፲፫ ፡ ፲። ቅዳ። ፈ ፡ መ ፡ ፲፫። አቡሻ ፡ ፪)።
አስተናበበ ፡ አናበበ፤ አነጋገረ፤ አዛረፈ ዘርፍና ባለቤት አደረገ፤ መጽሐፍን ከመጽሐፍ ፥ ሰውን ከስው፤ ስምን ከስም።
አስተናአሰ ፡ አስተናነሰ። የአንአሰ ድርብ።
አስተናከረ ፡ አናከረ አነካከረ። አለያየ፤ አዳነቀ አደናነቀ። አንከረ ማድረግንና ማስደረግን ፪ቱን እንዲያሳይ ፥ አስተናከረም ማድረግን ጨምሮ ያሳያል፤ አዳነቀ ማለት ገቢር ነውና፤ አስተጋብሮም ይኾናል። ያስተናክሩ ሥነ ባህሎሙ። ዘአስተናከራ ለመለኮተ ወልድ
፡ (ቄር ፡ ጰላ። መጽ ፡ ምስ)።
አስተናደፈ ፡ አናደፈ፤ አሰማማ አመሳሰለ አስተካክለ ፥ ሕንጻውን ከንድፉ ከቢጋሩ ጋራ። አንኀለ ሄሮድስ መቅደሰ እስከ መሠረቱ ወአስተናደፈ መሠረታቲሁ በምጣኔ ሕንጻ ቀዳማዊ ፡ (ዮሴፍ)። በሣረረና በመሥረተ ፈንታ አስተናደፍኩ መሠረተ ይላል፤ የመላሽ ስሕተት ነው፤ አያሰኝም ፡ (፩ቆሮ ፡ ፫ ፡ ፲)።
አስተናድአ ፡ አናዳ ፥ አነዳዳ፤ አዋሰደ። ያስተናድኡ ዘስርቅ ፡ (ዲድ ፡ ፭። ሕዝ፲፰ ፡ ፲፫ ፡ ፲፮)።
አስተናገሠ ፡ አናዳ ፥ አነዳዳ፤ አዋሰደ። ያስተናድኡ ዘስርቅ ፡ (ዲድ ፡ ፭። ሕዝ፲፰ ፡ ፲፫ ፡ ፲፮)።
አስተናገረ ፡ (አደራራጊ) አነጋገረ፤ አጨዋወተ።
አስተናግር ፡ (አስተንገረ) በቁሙ፤ አብሾ ዕፀ ፋርስ
፡ (ጫት፤ መጠጥ) የሚያሳብድ የሚያስለፈልፍ ፥ ርጥብ ደረቁን የሚያናግር የሚያስቀባጥር
፡ (ዐማርኛ)።
አስተናጸረ ፡ አስተያየ፤ አናጸረ አነጻጸረ።
አስተናጸየ ፡ አናጨ አነጫጨ፤ አነጫነጨ ፥ አበሳጨ።
አስተናጽሐ ፡ አናጻ አጣራ፤ አስተጣጠበ።
አስተንተነ [1] ፡ አስተነተነ፤ ይህ ለዚህ አለ፤ ዐሰበ ተጋ ተወዘወዘ ፥ በሐሳብ ተያዘ፤ ለመስጠት ለመርዳት ለማገልገል። ባርክ ዲበ እለ ያስተነትኑ በዕጣን ወቍርባን። ለተልእኮ ምሥዋዕ ዘጽሕቀ ወዘአስተንተነ። እንዘ ያስተነትኑ ኩነቶሙ ዘኀለፈ ወለዘኒ ይመጽእ ፡ (ቅዳ። ስንክ
፡ ሠኔ፲፰። ገድ ፡ ኪሮ)።
፡ አሳሰበ፤ አተጋ አገበረ፤ ራሱን ወይም ሌላውን። እለ ይገብሩ ትርፍተ በሥጋቲሆሙ ባሕቲቱ ወኢያስተንተኑ ነፍሳቲሆሙ ውስተ ተጋድሎተ ኅሊናት ኢይበጽሑ ኀበ ንጽሐ ልብ ፡ (ፊልክ ፡ ፻፹፮)።
[2] ፡ ዐሰበ ተጋ፤–ነቲን ነተነ።
አስተንፈሰ ፡ ተነፈሰ፤ እፍ አለ ትንፋሽ አወጣ፤ ተናገረ። እግዚ ዘአስተንፈሰ ቦቱ ነፍሰ። መጻሕፍተ ሐሰት ዘአስተንፈሰ ሰይጣን ውስተ አፉሆሙ
፡ (ጥበ፲፭ ፡ ፲፩። መጽ ፡ ምስ)።
፡ አነፈነፈ፤ ሳበ ማገ አሸተተ። አስተንፈሰ ወአጼነወ። ከመ ይክሀል አጼንዎ ዘያስተነፍስ
፡ (ቅዳ ፡ ሕር። ቀሌ)።
አስተዐመፀ ፡ (አዐመፀ) አሳመጠ፤ አሸፈተ፤ ግፍ አሠራ።
አስተዐረየ ፡ ዝኒ ከማሁ። አስተዐረይኮሙ ምስሌነ። ያስተዔርዮ ለአብ በወልዱ ፡ (ማቴ፳ ፡ ፲፪። አፈ
፡ ድ፬)።
አስተዐቀበ ፡ (አዕቀበ) አስጠበቀ፤ አስጠነቀቀ፤ ተጠበቁ ፥ ተጠንቀቁ አለ። ወታስተዐቅቦሙ እምኔየ። አእምር ከመ እግዚ አስተዐቀበ እምበዓለ ዕዳ ፡ (ሕዝ፴፫ ፡ ፯። ፍ ፡ ነ ፡ ፳፯)።
አስተኣበደ ፡ (አደራራጊ) አሳነፈ አስናነፈ፤ አቋጣ አቈጣጣ ፥ አናናቀ።
አስተአከየ ፡ (አድራጊ) ዝኒ ከማሁ፤ አከፋ አክፋፋ፤ አጥላላ፤ ናቀ ነቀፈ አቃለለ፤ ቢያክ ቢያክ አለ፤ አብዝቶ መላልሶ ፈጽሞ። ኢታስተአክዮ ለሰብእ በርሥአቱ። ኢታስተአክዮ ለሰብእ እንበይነ ሕሠሚሁ። ያስተአኪ ተግሣጸ አብ። ወአስተአከዮ ሄሮድስ
፡ (ሢራ፰ ፡ ፮። ፲፩ ፡ ፪። ምሳ፲፭ ፡ ፭። ሉቃ፳፫ ፡ ፲፩)።
አስተዐጸበ ፡ አከበደ፤ አገነነ፤ አስተባሰ፤ አደነቀ፤ ዕጹብ ዕጹብ አለ፤ የክፉ የበጎ። አስተዐጸቡ ሮም ዘገብሩ አይሁድ። ኢያስተዐጸበ ንትፈተ ሥጋሁ። አፍቅሩ ነግደ እንዘ ኢታስተዐጽቡ፤ የክፉ
፡ (ዮሴፍ። ስንክ ፡ መጋ፮። ፩ጴጥ ፡ ፬ ፡ ፱)። ከመ ይትናጸሩ በበይናቲሆሙ ወያስተዐጽቡ ፍጥረቶሙ። ነበሩ እንዘ ያስተዐጽቡ ግብረ እግዚ። ኣነክር ወኣስተዐጽብ እምኔክሙ፤ የበጎ
፡ (ቀሌ። ገድ
፡ ተክ። አቡሻ ፡ ፳)።
አስተኣኀወ ፡ አወናደመ፤ ወንድማማች አደረገ፤ አቀናጀ። ለየ ከፈለ አመነታ፤ መንታ አደረገ፤ አጫፈረ። እፎ ከፈልካሁ ወእፎ አመንተውካሁ ለዋሕድ ወአስተኣኀውካሁ ለአሐዱ አካል
፡ (መጽ ፡ ምስ)።
አስተኣኀዘ ፡ አያያዘ፤ አቀጣጠለ፤ አዠማመረ። ከመ ዝ አስተኣኀዘ ኀምስተ አብያተ ክርስቲያናት እምአሐቲ ኰኵሕ። ለእመ ዐርጉ ሮም መልዕልተ ማኅፈድ አስተኣኅዝ እሳተ ውስቴቱ። አሌ ሎሙ ለእለ ያስተኣኅዙ ቤተ ምስለ ቤት። መኑ ያስተኣኅዝ ቀትለ
፡ (ገድ ፡ ላሊ። ዮሴፍ። ኢሳ፭ ፡ ፰። ፫ነገ ፡ ፳ ፡ ፲፬)።
አስተኣመረ ፡ አስተዋወቀ፤ አወዳጀ።
አስተኣመነ ፡ አስተማመነ፤ አማማለ አገዛዘተ።
አስተዓመፀ ፡ አባደለ፤ አበዳደለ፤ አጋፈ፤ ግፍ አሣራ።
አስተኣምኀ ፡ አሳለመ፤ አሳሳመ፤ አገናኘ። አስተኣሚኀከ ቤተ ክርስቲያን ትብል ጸዋተ
፡ (ግንዘ)።
አስተኣሰረ ፡ አስተሳሰረ፤ አያያዘ፤ አዋሰበ፤ አቈረኛኘ።
አስተዓረቀ ፡ አስተራረቀ፤ አስማማ። እለ ያስተሳልሙ ወያስተዓርቁ
፡ (ቀሌ)።
አስተዓረከ ፡ አወዳጀ፤ አዛመደ፤ አመሳሰለ፤ አስተካከለ። መኑ ያስተዓርኮ ለነዳይ ምስለ ባዕል
፡ (ሢራ፲፫ ፡ ፲፰)።
አስተዓቀበ ፡ (አደራራጊ) አጠባበቀ፤ ተጠባበቁ አለ።
አስተዓበየ ፡ አበላለጠ፤ አላላቀ፤ አመዛዘነ። ወአስተዓበየ አምጣነ ይፈድዮ ለወልደ እግዚ፤ ከመ ሰማይ ወዘውስቴቱ፤ ወምድር ወዘዲቤሃ ፡ (መቅ ፡ ወን)።
አስተኣከለ ፡ አስተካከለ፤ አወዳደረ፤ አነጻጸረ።
አስተኣከየ ፡ (አደራራጊ) አከፋፋ አጠላላ፤ አናናቀ መስተጻልእ ኾነ።
አስተኣኰተ ፡ (ያስተኣኵት ፡ ያስተኣኵት) አመሰጋገነ፤
፡ (አደራራጊ)።
አስተኣኳቲ ፡ አመሰጋጋኝ።
አስተዓወቀ ፡ አስተዋወቀ፤ አላመደ፤ አለማመደ።
አስተኣዘዘ ፡ አስተዛዘዘ፤ ተዛዘዙ አለ፤ አደራራጊ።
አስተዓደወ ፡ አሸጋገረ፤ አስተላለፈ።
አስተዓገለ ፡ (አደራራጊ) አስተጋገለ፤ አቀማማ፤ አነጣጠቀ።
አስተዓገሠ ፡ አቻቻለ አስተጋገሠ፤ መዠመሪያውን ዐግሦን ተመልከት። እሞን ታስተዔግሦን፤ ወትብሎን ጽንዓ
፡ (ስንክ ፡ መስ፯)።
አስተዓፀወ ፡ ዕፃ አጣጣለ። ዕፀው ዘቦቱ ያስተዓፁ። ወአስተዓፀወ ዕለተ እምዕለተ ወወርኀ እምወርኅ
፡ (ዘሌ፲፮ ፡ ፰። አስቴ፫ ፡ ፯)።
አስተእኰተ አስተአኰተ ፡ ዝኒ ከማሁ፤
፡ (አስደራጊ)።
አስተካሀለ ፡ አቻቻለ፤ አሰማማ አዋደደ።
አስተካሐደ ፡ አካካደ፤ አሟገተ፤ አከራከረ።
አስተካልሐ ፡ ኣጯጯኸ፤ አዳመቀ፤ ጩኸት አስተማረ። ወአስተካልሐ ደቂቃ በዜማ ሐዲስ ለሀገረ አዜብ
፡ (ገድ ፡ ዘሚ)።
አስተካበደ ፡ አካበደ፤ አከባበደ፤ አስተባሰ፤ የመጥላትና የመሰቀቅ። ግስነቱ ዐጕልና ሐውልት ስለ ኾነ ፍችው እንደ አክበደ አድራጊ ነው። ለእመ አስተዐጸበ ወአስተካበደ ንስሓሁ ዘወሀብዎ ካህናት
፡ (ቀሌ)። ይቴክዝ ወያስተካበድ ፍና መንሱት። አስተካበደ ሐሚመ ፡ (ቄር ፡ ጰላ)።
አስተካየደ ፡ አዋዋለ አማማለ፤ ቃል ኪዳን አጋባ። ወአስተካየደ ዮዳሄ ኪዳነ ማእከለ ቤተ እግዚ ወማእከለ ቤተ ንጉሥ ወማእከለ ሕዝብ ከመ ይኩኑ ሕዝበ እግዚ። አስተካየድዎ ከመ ኢ ፡ (፬ነገ ፡ ፲፩ ፡ ፲፯። ስንክ ፡ ሠኔ)።
አስተካፈለ ፡ አካፈለ፤ አከፋፈለ። ኖኅ አስተካፈሎሙ ኵሎ ምድረ ለደቂቁ። ዛቲ ምድር ዘታስተካፍልዋ ርስተ ለአንጋደ እስሬኤል ፡ (ስንክ ፡ ጥር፮። ሕዝ፵፰ ፡ ፳፱)።
አስተወከለ ፡ (አወከለ) አሳመነ አስታመነ፤ በተስፋ አጸና፤ አቈራኘ። ተፋቅሮ በኵሉ ያስተአምን ወበኵሉ ያስተዌክል ፡ (፩ቆሮ ፡ ፲፫ ፡ ፯)።
አስተዋሐሰ ፡ አዋዋሰ፤ ዋስ አጣራ አካሰሰ።
አስተዋሀበ ፡ አሰጣጠ፤ አቀባበለ አስተላለፈ ፡ (ዘፀ፳፩ ፡ ፴፩)።
አስተዋሐየ ፡ አስጐበኘ፤ አጐበኛኘ። ዘያስተዋ(ዕ) ሕያ ለእከይ ይትሀጐል ባቲ ፡ (ምሳ፲፱ ፡ ፱)።
አስተዋለደ ፡ አዋልደ አወላላደ፤ አባዛ አራባ። ወያስተዋልዶ ለእንስሳከ
፡ (ዘዳ፳፰ ፡ ፲፩። ፴ ፡ ፱)።
አስተዋሰበ ፡ አዋሰበ፤ አወሳሰበ። አጋባ አዛመደ፤ አጣመረ አጣመደ፤ አቀናጀ አራከበ፤ የወንድና የሴት። ወአስተዋሰቡ ደቂቆሙ። ለብእሲ ጠቢብ አስተዋስባ። አስተዋሰብዋ ለሰብዐቱ ዕደው። አነ ፈቀድኩ ከመ ኣስተዋስብ ወለተከ ለወልደ እስክንድር። ፈቀዱ አበዊሁ ከመ ያስትዋስብዎ ሎቱ ብእሲት ፡ (ዕዝ፱ ፡ ፪። ሢራ፯ ፡ ፳፭። ጦቢ፫ ፡ ፰። ዮሴፍ። ስንክ
፡ መጋ፳፯)።
አስተዋሰነ ፡ አዋሰነ አወሳሰነ፤ አካፈለ አካለለ።
አስተዋረሰ ፡ አዋረሰ አወራረሰ፤ አከፋፈለ። አድራጊና አደራራጊ ነው፤ አስተዋረደን እይ። አመ ያስትዋርሶሙ ንዋዮ ለደቂቁ። እምርስቱ ያስተዋርስ ለውሉዱ። አስተዋርስ ንዋየከ። መባሕት ለአቡሁ ከመ ኢያስተዋርሶ ርስተ ዚኣሁ። እዴሁ አስተዋረሰቶሙ ፡ (ዘዳ፳፩ ፡ ፲፮። ሕዝ፵፮ ፡ ፲፰። ሢራ፴ ፡ ፴፪። ፈ ፡ መ ፡ ፳ ፡ ፬። ኢሳ፴፬ ፡ ፲፯)።
አስተዋረደ ፡ (አድራጊና አደራራጊ፤ ባድራጊነቱ የአውረደ ድርብ) አዋረደ፤ አወራረደ። አፍለሰ አስተፋለሰ እንደ ማለት ነው። ያስተዋርድዎ ውስተ አምጣነ ገብር ለመንፈስ ቅዱስ ፡ (ተረ ፡ ቄር)።
አስተዋቀሠ ፡ አዋቀሠ አወቃቀሠ፤ ኦሟገተ አከራከረ። ሶበሁ ያስተዋቅሥዎ ለሰብእ ምስለ እግዚ። ኣስተዋቅሦሙ ለኵሉ አሕዛብ ፡ (ኢዮ፲፮ ፡ ፳፩። ዮኤ፬ ፡ ፲፪)።
አስተዋናዪ መስተዋንይ ፡ የሚያጫውት፤ አጫዋች አጨዋዋች። መስተዋንያን ፡ (ሲኖዶ)።
አስተዋዐየ ፡ አቀጣጠለ፤ አያያዘ፤ እሳቱን። ዘያስተዋዕያ ለእከይ ፡ (ምሳ፲፱ ፡ ፱)።
አስተዋከለ ፡ አዋከለ ፥ አወካከለ፤ አስተማመነ፤ አጸናና።
አስተዋከፈ ፡ አወካከፈ አሰጣጠ፤ አቀባበለ አረካከበ።
አስተዋደየ ፡ አሳበቀ፤ ነገር ሠራ፤ ከሰሰ አካሰሰ አወናጀለ፤ አሳጣ። ሐሰተ አስተዋደዩኒ። ኢኀደጉ አስተዋድዮቶሙ። ዮጊ በጽልእ አስተዋደይዎ። አስትዋደዩኒ ኀበ ንጉሥ። ኣስተዋዲ ርእስየ ኀበ እግዚ ፡ (ዳን፩ ፡ ፵፫። ፫ ፡ ፳፪። ሢራ፲፱ ፡ ፲፭። ጦቢ፩ ፡ ፲፱። መዝ ፡ ፴፩)።
አስተዋፅአ ፡ ኣዋጣ፤ አወጣጣ። ንባቡ የማደራረግ ሲኾን ፍችው እንደ አውፅአ ነው፤ ማድረግና ማስደረግ አለበት። አስተዋፅኡ ወገደፉ ውስተ ባሕር ንዋዮሙ። አስተዋፅኦ ኪን ወተግባር። ከመ ያስተዋፅኡ መጽሐፈ ፍትሕ እምብሉይ ወሐዲስ። ዘአስተዋፃእከ ሎቱ
፡ (ዮና፩ ፡ ፭። መጽ ፡ ምስ። ፍ ፡ ነ ፡ መቅ። ሉቃ፲ ፡ ፴፭)። ወአሐውር። ኣስተዋፅእ ምጽዋተ። አስተዋፅኦ ለመድፍንከ በእንተ ትእዛዙ ለልዑል። እለ ያስተዋፅኡ ብዕሎሙ በሠናይ፤ ለእመ ቦ ምንትኒ ዘአጥረይነ ናስትዋፅእ በዘይደሉ። ወአስተዋፅአት ኵሎ ንዋያ ወአኅለቀት ፡ (ጦቢ፩ ፡ ፯። ሢራ፳፬
፡ ፲፩። አፈ ፡ ተ፪። ማር፭ ፡ ፳፮)። ይህ የተጠቀሰ ጥቅስ ኹሉ በአውፅአ ፈንታ የገባ ነው፤ መላሾች አበላሽተውታል።
አስተዛመደ ፡ (ዘመደ) አዛመደ አዘማመደ፤ አሰማማ። አድራጊና አደራራጊ ብዙ ጊዜ በፍች ይተባበራል። ተሰምዮት በመንፈስ ዘያስተዛምድ ምስለ መንፈስ ቅዱስ፤ ከመ ተዘምዶት ሥጋዊ ያስተሳትፍ ምስለ ሥጋ ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፶፩)።
አስተዛበጠ ፡ አማታ አጋጨ አዋጋ አናከሰ። ያስተዛብጡ አባግዕ ወዶርሆ ምስለ ካልኡ ፡ (ቈስጠ ፡ ፲፫)።
አስተዛወገ ፡ (ዞገ፤ ዘወገ) አዋገነ አዛመደ አሰማማ፤ አንድ አደረገ። አድራጊና አደራራጊ ነው። ወያስተዛውጎ በቃለ ተስፋ። ዕለት ብሂል ዘያስተዛውጎሙ ለሌሊት ወለመዓልት ፡ (አፈ ፡ ድ፰። አዋል)።
አስተዛውዐ ፡ አዋዛ አጫወተ፤ አጨዋወተ። ፊልሞን መአንዝር ያስተዛውዖ ለአርያኖስ መኰንን
፡ (ስንክ ፡ የካ፳)።
አስተዝያነወ ፡ (ያስተዝያኑ) አዋራ አጨዋወተ።
አስተየ ፡ አጠጣ፤ አስጠጣ፤ ጠጡልኝ አጠጡልኝ አለ። ከመ ኣስትዮሙ ለሕዝብየ። ለዘይላሑ አስትዮ ወይነ። አዘዘ ያስትይዋ እምነ ወይኑ። ዘያሰትዮ ለቢጹ በዘይመውት ፡ (ኢሳ፵፫ ፡ ፳። ሢራ፴፬ ፡ ፳፱። ዮዲ፲፪ ፡ ፩። ዕን፪ ፡ ፲፭)።
አስተደለወ ፡ (ያስተዴሉ ያስተደሉ፤ አው አስተዳለወ ያስተዳሉ ያስተዳሉ) የደለወና የአድለወ ድርብ፤ አድራጊና አስደራጊ። አዘጋጀ አሰናዳ። አደላደለ አስመቸ አመቻቸ። ያስተዴሉ ለዓለም መፍቅዶ። ወያስትዴሉ ክረምተ ለምድር። አስትዳለወ መንበሮ። አስተዳለወ ሀገረ ፡ (ሢራ፴፱ ፡ ፴፩። መዝ ፡ ፻፵፮። ፻፪። ዕብ፲፩ ፡ ፲፮)።
አስተዳኀረ ፡ አከታተለ፤ አራደፈ። አስተዳኀረ መኣዝኒሃ
፡ (ቅዳ ፡ ኤጲ)።
አስተዳጐጸ ፡ አጣላ አነካካ፤ አጓነጦ። ያስተዳጕጽ ማእከለ አዕርክት። ልሳን ዐማፂ ዘያስተዳጕጽ ኀበ ገጉሥ። እለ ኢያስተዳጕጻ
፡ (ሢራ፳፰ ፡ ፬። ፶፩ ፡ ፮። ፩ጢሞ ፡ ፫ ፡ ፲፩)።
አስተገበረ ፡ (አግበረ አገበረ) አሠራ አስደረገ፤ አሳረሰ አስነገደ። ነፍስነ ትፈቅድ ረድኤተ ጽኑዐ ዘያስተጌብራ ለኅሊናነ። ኢያስተገበረ ኅሊናሁ በምንትኒ ዘይከልእ አብጽሖ ኀበ እግዚ። ወያስተጌብሮሙ ለኬነውት። መጺእየ እምአስተገበርክዎ ፡ (አፈ ፡ ተ፴፬። ፊልክ ፡ ፩። ግብ፲፱ ፡ ፳፬። ማቴ፳፭ ፡ ፳፯። ሉቃ፲፱ ፡ ፳፫)።
አስተጋባኢ መስተጋብኢ ፡ የሚያሰበስብ አሰብሳቢ፤ አሰባሳቢ። ልማዱ ግን ሰብሳቢ ነው። ይቤ አስተጋባኤ መጽሐፍ። መስተጋብኤ ነፍሳት ፡ (ፈላስ። ሲኖዶ)።
አስተጋብአ [1] ፡ በቁሙ አስተጋባ፤ የገደል የተራራ ፡ (ዐማርኛ)።
[2] ፡ አስተጋብአ፤ አሰበሰበ፤ አሰባሰበ ፡ (አስደራጊና አደራራጊ)። ልማዱ ግን፤ ሰበሰበ ነው።
አስተጋነየ ፡ አገናኘ፤ አገነኛኘ።
አስተጋአዘ ፡ አጣላ፤ አሟገተ
፡ አከራከረ።
አስተጋየደ ፡ አፋጠነ አሯሯጠ ፡ (ሽምጥ አስጋለበ)። አስተጋይድ ፈረሰከ ፡ (ደራሲ)።
አስተጋደለ ፡ አጋደለ፤ አስታገለ፤ አስተጋገለ።
አስተጋፍዐ ፡ አጋፋ አጫነቀ፤ ግፍ አሣራ።
አስተጓሕለወ ፡ አካዳ አከዳዳ። አስተጓሕለውኪ ፡ (ኢሳ፶፯ ፡ ፱)።
አስተጓህነወ ፡ አጓጓነ አጯጯኸ፤ አዚያዚያመ። ጸዋዕክዎሙ ለነቢያት ከመ ያስተጓህንዉኒ በቃለ ትንቢቶሙ
፡ (መጽ ፡ ምስ)።
አስተጠንቀቀ ፡ ዝኒ ከማሁ። አስተጠንቀቀ ሎቱ ወነገሮ ዘከመ ይገብራ ፡ (ቀሌ)።
አስተጠናቀቀ ፤
አጠናቀቀ ፤ አራቀቀ ፤ አታጋ። ጠባዩ ማደራረግና ማስደረግ ነው ፤ ባስደራጊነቱ
ከአጠንቀቀና አስተጠንቀቀ ይሰማማል
፤ ተደራራጎቹ ግብራት ሕዋሳት ሲኾኑ ምስጢሩ ከማድረግና ከማስደረግ ከኹለቱ ኹሉ
ይገባል። ፈድፋደ ናስተጠናቅቅ ኅሊናነ ፤ አልቦ ዘይክል አስተጠናቅቆ። ያስተጠናቅቁነ ለገቢረ ሠናይ (ቄር ፡ ጰላ። ቀሌ)።
አስተጣሐረ ፡ አጯጯኸ፤ አጋሣ አገሣሣ። ያስተጣሕር ነገሥተ ከመ አንበሳ ፡ (መጽ ፡ ምስ)።
አስተጣቀበ ፡ አጣቀመ፤ አጠቃቀመ፤ የጨርቅና የጨርቅ፤ ለነገርና ለሰውም ይኾናል።
አስተጣበቀ ፡ አጣበቀ አያያዘ አጋጠመ፤ አገጣጠመ። ከመ ዘያስተጣብቅ አግልዕተ። አስተጣበቅዋ ከመ እብነ ኰኵሕ። ግብር ዘያስተጣብቅዎ ፡ (ሢራ፳፪
፡ ፯። ኢዮ፴፰ ፡ ፴፰። ኤር ፡ ፲ ፡ ፲፭)።
አስተጣበበ ፡ አራቀቀ፤ ጥበብ አዋጣ አሻሻለ፤ ከራሱ ወይም ከሌላው። አሌ ሎሙ ለመናፍቃን እለ ያስተጣብቡ ርእሶሙ ፡ (ዲድ ፡ ፴፫)። ምስጢሩ አድራጊነት ካደራራጊነት ያሳያል፤ ባድራጊነቱ ያጥበበ ድርብ ነው።
አስተጣዐመ ፡ (ያስተጣዕም) አቃመሰ አቀማመሰ፤ አጠፋፈጠ፤ አሰነዳዳ። ኢናስተጣዕም ለከርሣነ፤ አላ ናስተጣዕም ትምህርተ መንፈሳዌ ፡ (አዋል)።
አስተጣወቀ ፡ አጫነቀ፤ አጨናነቀ፤ አጋፋ አጣበበ። ፡ (ተረት) ይጸድቅ አይጸድቅ አይታወቅ፤ ቤተ ክሲያን ያጫንቅ። አስተጣወቀ ባለውም አስተጠዋቀየ ይላል፤ ፍችው አንድ ነው።
አስተጣግዐ ፡ አጣጋ አጠጋጋ፤ ሰገሰገ ጽፍቅ አደረገ፤ አያያዘ አጣበቀ። ኣስተጣግዖሙ ለዓሣተ ፈለግከ በቅሣርከ። ማህው ለእመ ተሰብረ አልቦ ዘያስተጣግዖ ዘእንበለ ገባሪሁ። ከመ እብነ ጳዝዮን ዘአስተጣግዕዎ በወርቅ ጽሩይ። አስተጣግዑ አባላቲሆሙ ምስለ ሥጋ በግዕ። ያስተጣግዕ በኵላ ፡ (ሕዝ፳፱ ፡ ፬። ያዕ ፡ ዘእል። መጽ
፡ ምስ። አቡሻ ፡ ፶። ኢሳ፵፬ ፡ ፲፫)።
አስተጣፍሐ ፡ አጣፋ፤ አማታ ኦጋጨ። ይስፍሑ ወያስተጣፍሑ እደዊሆሙ። እንዘ ያስተጣፍሕ ክነፊሁ ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፭። ገድ ፡ ተክ)።
አስተጥዐመ ፡ አስተጠዐመ፤ ፡ (ያስተጥዕም) ዝኒ ከማሁ፤ አጣፈጠ አሰናዳ፤ አደነቀ። ዘኅቡረ አስተጠዐምከ ሊተ መባልዕተ። በከናፍሪሁ ያስተጥዕም ለከ ቃሎ። እመ አስተጣዐምከ ሎቱ ምግባሮ ቀተልኮ ለእኁከ። ሥጋ ያስተጥዕም ለነፍስ ምግባረ ሕሡመ
፡ (መዝ ፡ ፶፬። ሢራ፲፪ ፡ ፲፮። ዲድ ፡ ፮። ዮሴፍ)።
፡ ደስ ፈቅ አሰኘ፤ አስጐመዠ። ሰይጣን ያስተኮጥዕም ሎሙ በኅዳጥ ወይኴንን ሎሙ በብዙኅ ፡ (ቀሌ)።
አስተጻልአ ፡ አጣላ፤ አጠላላ። ዘያስተጻልእ ብእሴ ምስለ ብእሲቱ ፡ (ቄድር)።
አስተፃመረ ፡ አጋባ፤ አጣመረ፤ አዋደደ፤ አዋሐደ፤ አንድ አደረገ፤ የባልና የሚስት። አንቀጹ የማደራረግ ነው፤ ፍችው ግን ማድረግ ኹኖ ከፀመረ ፍች ይገጥማል። ዘእግዚ አስተፃመረ ሰብእ ኢይፍልጥ። ደናግል ዘኢያስተፃመርዎን አቡሆን ወእሞን በሕገ ሰብሳብ
፡ (ማር፲ ፡ ፱። መጽ ፡ ምስ)።
አስተፃመደ ፡ አጣመደ፤ አጠማመደ፤ ተቈራኙ አለ።
አስተፃረረ ፡ አጣላ፤ አጠላላ፤ አሳለፈ አሰላለፈ።
አስተፃረፈ ፡ አሳደበ፤ አሰዳደበ፤ አነቃቀፈ።
አስተጻብአ ፡ አጣላ፤ አዋጋ። ምንት ያስተጻብእክሙ እንዘ አኀው አንትሙ ፡ (ግብ፯ ፡ ፳፯)።
አስተጻንዐ ፡ (አጽንዐ) አጣና፤ አራታ፤ አጠናና አበረታታ፤ አይዞኽ አይዞኽ አለ። አድራጊና አደራራጊ ነው፤ ባድራጊነቱ የአጽንዐ ድርብ። በምስጢር ግን አደራራጊነት አይቀርም። አስተጻንዐ መዝራዕቶ ወአቈልቈለ ኵናቶ። ፈቀደ ያስተጻንዕ ምዕማዲሁ። ዘንተ ይቤ ከመ ያስተጻንዖሙ። ያስተጻንዑ ፍኅረተ በቅድመ ክልኤቱ ካህናት በአንብሮተ እድ ወበመስቀል ወበሕልቀት ፡ (ገድ ፡ ተክ። አፈ ፡ ድ፫። ፍ ፡ ነ ፡ ፳፬ ፡ ፫)።
አስተጻዐነ ፡ አጫጫነ አሸካከመ፤ አነባበረ፤ አደራረበ።
አስተጻደለ ፡ አጐላ፤ አስረዳ፤ አስታወቀ፤ የመነጽር የምሳሌ። ወዝንቱ አስተጻደለ ራእዮ ለፍና ትስብእት ፡ (ቄር ፡ ጰላ)።
አስተፃፈረ ፡ (ፀፈረ) አጫፈረ፤ አጨፋፈረ፤ ሌላውን ከራሱ፤ ራሱን ከሌላ፤ ወይም ሌላውን ከሌላ። አቡየ ወአነ ወመንፈስ ቅዱስ፤ ፀሓይ ወብርሃን ወዋዕይ
፡ (ቅዳ ፡ ግሩ)።
አስተፈግዐ ፡ (አፈግዐ) አስመቸ፤ ደስ አሰኘ። ዘያስትፌግዕ ልቦ
፡ (ሢራ፲፬ ፡ ፭)።
አስተፋለሰ ፡ (አድራጊና አደራራጊ፤ ባድራጊነቱ የአፍለሰ ድርብ) አፋለሰ፤ አፈናቀለ፤ አዛወረ፤ አገላበጠ፤ አሳረገ ወደ ላይ አወጣ። ዘያስተፋልስ አእባነ። ከመ ያስተፋልሶሙ በበ ንስቲት። ያስተፋልስዎ ውስተ መዓርገ ክህነት በመዓርግ እምድኅረ መዓርግ በበ መዓርጉ ፡ (ሢራ፲ ፡ ፱። አፈ ፡ ድ፩። ፍ ፡ ነ ፡ ፭)።
አስተፋለጠ ፡ (ፈለጠ) አለያየ፤ አፋታ። እምድኅረ አስተፋለጦሙ መኰንን በበይናቲሆሙ ፡ (ስንክ ፡ ግን፲፩)። ንባቡ ነው እንጂ ፍችው አደራራጊነት የለውም፤ አድራጊ ብቻ ነው።
አስተፋርሀ ፡ አፋራ፤ አፈራራ፤ እንዲፋሩ እንዲፈራሩ አደረገ።
አስተፋቀረ ፡ አፋቀረ፤ አፈቃቀረ፤ አዋደደ፤ አሰማማ። ሰይጣን ቀንአ ላዕሌሃ ወአስተፋቀራ ምስለ አሐዱ መነኮስ እስከ አማሰነት ድንግልናሃ ፡ (ስንክ ፡ ነሐ፭)።
አስተፋቀደ ፡ አፋቀደ፤ አቋጦረ፤ አፋለገ፤ አመራመረ። አደራራጊ ነው።
አስተፋተነ ፡ አፋተነ፤ አፈታተነ፤ አሟከረ፤ አሞካከረ።
አስተፋትሐ ፡ አፋታ፤ አለያየ፤ አሟገተ፤ አፋረደ አፈራረደ።
አስተፋነወ ፡ አላላከ፤ አሸኛኘ፤ አሰነባበተ።
አስተፋአመ ፡ አጓረሠ፤ አጐራረሠ፤ ተጓረሡ አለ።
አስተፋጠነ ፡ ኦፋጠነ፤ አፈጣጠነ፤ አቻኰለ፤ ኣቸኳኰለ፤ እጅ እግሩን ሕዋሳቱን፤ ወይም ሌላውን። እግዚአብሔር አስተፋጠኖ በሞት ለገባሬ ዝንቱ ግብር፤ ዘእንበለ ይብጻሕ ጊዜሁ ፡ (ፈ ፡ መ ፡ ፲፩ ፡ ፪)።
አስተፍአመ ፡ ለመነ፤ ቀላወጠ፤ አጕርሡኝ መጽውቱኝ አለ። ይፍልሱ ወያስተፍእሙ
፡ (መዝ ፡ ፻፰። ኢዮ፳፯ ፡ ፲፬። ፴ ፡ ፫ ፡ ፬)።
አስቲር ፡ (ትግሬ) ሰማይ፤ ጠፈር፤ አየር፤ ፈለክ።
አስታር [1] ፡ (ዕብራ) ሰማያዊ ጠፈራዊ ኮከብ፤ ኮከበ ሠርክ ፀሓይ ስትገባ ወዲያው ታይቶ ወዲያው የሚጠፋ፤ ከዚህ የተነሣ አስታር ቦሸሽ፤ ወይም አስታርቦ ሸሽ የሚባል። ኮከባዊ ዕንቍ፤ አበባ፤ የባሕር እንስሳ፤ መልኩና ቅርጹ ኮከብ የሚመስል የኮከብ ዐይነት። እስመ ኢይሁቦ እግዚ አስታረ ሞገስ
፡ (ሢራ፴፯ ፡ ፳፩)። ጽርኡ ግን ኢተውህቦ ጸጋ እግዚ ይላል።
[2] ፡ (ዐረ ኢስታር) ስጢጥራ። የስጢጥራን ፍች ተመልከት፤ ከዚህ ጋራ አንድ ነው። አስታር ዘይቤ ፲፪ ወቄት ይላል፤ የግምት አፈታት ፡ (ጥሬ ፡ ሰዋ)።
አስታዪ መስተዪ ፡ የሚያጠጣ የሚያስጠጣ፤ አጠጭ አስጠጭ፤ ዐዳይ ሰጭ
አስቴር ፡ (ዕብ ኤስቴር) ኅብእት፤ ስውርት። ወለት ዘስማ አስቴር
፡ (አስቴ፪ ፡ ፯)።
አስት ፡ በቁሙ፤ አስቴ፤ አስታ፤ እሳታም ዕንጨት።
አስትሮን ፡ (ጽርእ) ግዘፈ ብርሃን፤ ሰሌዳ፤ ክበብ፤ ወይም ግዙፋን ብርሃናት፤ ፀሓይ ጨረቃ ኮከብ።
አስትዐ ፡ አስፈራ፤ አስገበረ፤ ግብር አምጡ አለ።
አስትዓ [1] ፡ ግብር፤–ሰቲዕ ሰትዐ።
[2] ፡ ግብር፤ እጅ መንሻ፤ በረከት፤ በውድም በግድም የሚሰጥ። አስትዓ መንፈሳዊት። ናሁ አስትዓክሙ። ወዝንቱ ውእቱ ክብሩ ወአስትዓሁ እምዐበይተ ሀገር
፡ (ቄር። ፩ነገ ፡ ፴ ፡ ፳፮። ሔኖ፶፫ ፡ ፩። ፪ዜና ፡ ፩ ፡ ፲፮። ድጓ)። ሲበዛ አስትዓት፤ አስታዕ ያሰኛል።
አሥነቀ ፡ (ጥሠ) ሥንቅ ሰጠ፤ አሲያዘ። ሥንቀ ታሠንቆ። ወአሥነቀ ለኵሉ ሰብኡ። አሥነቁነ
፡ (ዘዳ፲፭ ፡ ፲፬። ዮዲ፪ ፡ ፲፰። ግብ፳፰ ፡ ፲)።
አሥዐለ ፡ አሣለ፤ ሥዕል አሠራ። ሄሮድስ አሥዐለ ውስተ ቤቱ ሥዕሎ፤ ወሥዕለ ኵሎሙ ነገሥት እለ ሞኦሙ። በእደ ማርያም አሥዐለ ሥዕለ ማርያም ወሥዕለ ኢየሱስ በእደ አፍርንጅ ፡ (ዮሴፍ። ታሪ ፡ ነገ)።
አስአለ ፡ አስለመነ፤ አስጠየቀ፤ አስማለደ አማላጅ ላከ። ዐቢየ ነቢየ ዮሐንስሀ አስአልነ፤ ያስተምሕር በእንቲኣነ፤ ሣህልከ ወትረ ይብጽሐነ ፡ (መዋሥ)።
አስዐረ ፡ አሻረ፤ አስፈረስ፤ አስጠፋ።
አሥአነ ፡ አስተሥ(ሠ) አነ፤ አጫማ፤ ጫማ አለበሰ፤ አስለበሰ። አልበስዎሙ ወአሥአንዎሙ እምበርበረ ዚኣሆሙ። አግበረ ሎቱ አሣእነ ዘኀጺን ወአስተሥአንዎ ለቅዱስ። ገብሩ ሎቱ ቅትራት ዘብርት ወአስተሠአንዎ እስከ በረረ ቅትራት ውስተ እገሪሁ ፡ (፪ዜና ፡ ፳፰ ፡ ፲፭። ድጓ። ስንክ ፡ ነሐ፲፬)።
አስዐዘዘ አስዖ ዘዘ ፡ አፈዘዘ፤ አደነዘዘ። አስከሮ ወአስዖዘዞ። ወአስዖዘዞ ጸኮ
፡ (ስንክ ፡ የካ፪። ነሐ፳፰። ዘፍ፴፪
፡ ፴፩ና ፡ ፴፪)።
፡ አስቈጣ፤ አስፈዘዘ፤ አሳዘነ፤ አሳፈረ፤ አስቀጠጠ። ልሳን ኅቡእ ያስዖዝዝ ገጸ ፡ (ምሳ፳፭ ፡ ፳፫)።
፡ ተከተለ፤ ሻ ፥ ፈለገ፤ አፈነፈነ። ዘያስዖዝዝ ነገረ ኢይድኅን ፡ (ምሳ፲፱ ፡ ፯)።
አሥዕርት ፡ ሣሮች፤ ቡቃዮች፤ የምድር ጠጕሮች
፡ (አፈ ፡ ተ፳፯)።
አስከመ ፡ አሸከመ፤ አሲያዘ፤ ጠመደ ጫነ፤ አስደበለለ፤ አስነገተ። አስከማ ለአጋር። ነሥአ ዕፀወ ወአስከሞ ለይሥሐቅ። ያሰክምዎ ለሰብእ ዲበ መትከፍቱ ፡ (ኩፋ
፡ ፲፯ና ፡ ፲፰። ማቴ፳፫ ፡ ፬። ግብ፲፭ ፡ ፲)።
አስከረ ፡ አሰከረ፤ ልብ አጠፋ፤ አረካ አጠገበ። ስቴ ዘያሰክር። ጽዋዕ ዘያሰክር። ስተዩ ደመ እስከ ያሰክረክሙ። ታሰክራ ለኵላ ምድር። ኣስክሮን በደሞሙ ለአሕጻየ ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፶። ቅዳ ፡ ሕር። ሕዝ፴፱ ፡ ፲፱። ኤር፳፰ ፡ ፯። ዘዳ፴፪ ፡ ፵፪)።
አስከሬን ፡ (ናት። ሮማይ ስክሪኒዉም) የገንዘብ መያዣ፤ ታናሽ ማፋዳ ኰረጆ፤ ቍናማት ከረጢት፤ ኪስ ሙዳይ፤ ተረንተራ። የወርቅ የብር የገንዘብ ሣጥን፤ የልብስ የጌጥ የሽልማት መዝገብ፤ ግምጃ ቤት ቤተ መዛግብት
፡ (ዮሐ፲፪ ፡ ፮። ፲፫ ፡ ፳፱)። መባአ አስከሬን ይሁዳ የዐቅብ። መጋቤ አስከሬን። ይላሕዉ አስከሬናተ ሰርጕኪ ፡ (ዲድ ፡ ፳፱። ሲኖዶ። ኢሳ፫
፡ ፳፮)።
፡ መቃብር፤ የሬሳ ሣጥን፤ ርጥብ ሬሳ ወይም ደረቁ የፈረሰው የበሰበሰው። ይህ ደግሞ የነፋስ ሣጥን ማለት ነው። ምስጢሩ ከዚያው አይወጣም።
አስከበ ፡ አተኛ አስተኛ፤ አጋደመ፤ አሰጣ ዘረጋ። አስከቦ በከብዱ ላዕለ ምሥዋዕ። አስከቡኪ ውስተ መሬት። አስከበቶ ውስተ ዐራት። አስከበቶ ውስተ ጎል። በአረፍተ ቤተ ክርስቲያን ታሰክቦ ለበድን። አስከብዎሙ ለአእሩግ ፡ (ዘፍ፳፪ ፡ ፱። ኢሳ፶፩ ፡ ፳፪። ፩ነገ ፡ ፲፱ ፡ ፲፫። ሉቃ፪ ፡ ፯። ግንዘ። ሰቈ፪
፡ ፳፩)።
አስከወ ፡ አሳየ፤ አስመለከተ፤ ማያ መመልከቻ ኾነ።
አስከየ ፡ አስከሰሰ፤ አስወቀሠ፤ ከሳሽ አስነሣ።
አስካል [1] ፡ ዘለላ ፍሬ፤–ሰኪል ሰከለ፤ ሰክል።
[2] ፡ አስካል፤ ፡ (ላት። ዕብ ኤሽኮል። ዐረ ኢሽካል። ሱር አትካላ) የወይን ዐጽቅ፤ ዛላ ዘለላ፤ እንደ ማሽላ ራስ ያለው የሕንባቡ መውጫ መወለጃ ቂንዱ ቈረቈንዳው ከፍሬው ጋራ ፡ (ዘፍ፵ ፡ ፲–፲፪)። ጸናሕክዎ ለወይንየ ይፍረይ አስካለ። አልቦ አስካል በውስተ ወይን። ወደመ አስካል ሰትዩ ወይነ። ይቀሥሙሁ እምአሥዋክ አስካለ። አስካለ በቀልት
፡ (ኢሳ፭ ፡ ፪። ኤር፰ ፡ ፲፫። ዘዳ፴፪ ፡ ፲፬ ፡ ፴፪። ማቴ፯ ፡ ፲፮። ሔኖ፳፬ ፡ ፬)። አበባና ፍሬ ላለው። ለዕንቍላል ሳይቀር ለርጉዝና ለድብድብ ኹሉ ይነገራል። አስካል ዘጸገየ። አስካለ አእምሮ እንተ ታሠርጽ ጥበበ። አንቆቅሖ አስካለ ዶርሆ
፡ (ማሕ፩ ፡ ፲፬። አዋል)።
አስኬማ [1] ፡ (ጽር ስኺማ) ልብስ፤ መልክ፤ ቅርጽ ገጽ። ነሥአ አርኣያ ገብር ወኮነ በአምሳለ ሰብእ በአስኬማሁ። ወበአስኬማሁ አስተርአየ ከመ ሰብእ
፡ (ቄር ፡ ጰላ)።
[2] ፡ (ሱር ኤስኪማ) በቁሙ፤ ልብሰ ምንኵስና፤ ከቀሚስ ከቅናት ከቆብ በኋላ በመጨረሻ የሚለበስ፤ የፍጻሜ ምንኵስና ምልክት። ይኸውም ከነት ካንቀልባ እንደ እንቢያጕሥ ኹኖ የሚሠራ ፲፪ ትእምርተ መስቀል ያለበት ነው። ካስኬማ በኋላ ባሕታዊ መኾን መዝጋት አጽንዖ በኣት ነው እንጂ ፥ ከገዳም መውጣት ወደ ዓለም መግባት ክልከል ነው። መልአኩ ለእንጦንዮስ ስለ ሰጠውና ምንኵስና ሕገ መላእክት ስለ ኾነ፤ ልብሱም አስኬማ መላእክት ይባላል። አልበስዎ አስኬማ ዘመላእክት። ዳንኤል አስኬማ መላእክት ዘለብሰ። አስኬማከኒ አልባቲ ሙስና ፡ (ስንክ ፡ መስ፲፰። ኅዳ፲፮። ድጓ)።
አሥወነ ፡ አስለገገ፤ ቈበር አስደፈቀ። አሥወና ለብእሲት። ወያሤውኖ ፡ (ስንክ ፡ መስ፩። ማር፱ ፡ ፲፰ ፡ ፳። ሉቃ፱ ፡ ፴፱)።
አሥወየ ፡ አሸተ ፥ እሸት አደረገ፤ እሸት አበላ። አሠየ አስጐመዠ፤ ብሉኝ ብሉኝ አለ፤ እሸቱ ፍሬው ፥ እንደ ዕፀ ገነት፤ ሐሠየን እይ
፡ (ዘፍ፫ ፡ ፮)።
አሥየመ ፡ አሤመ፤ አሾመ፤ ሹመት፤ አሰጠ።
አስያፍ አስይፍት ፡ ሰይፎች። ለበዓለ አስይፍትኒ ይረድኦሙ ፡ (ፊልክ)።
አስደደ ፡ አስደደ፤ ካገር አሶጡ አለ፤ ባዋጅ በትእዛዝ ፡ (ግብ፲፰ ፡ ፪)።
አስገለ ፡ አስጠነቈለ፤ ጠንቋይ ጠየቀ፤ አስጠየቀ።
አሥገረ [1] ፡ አሠገረ፤ አሻገረ አራመደ አሳለፈ፤ የቀን የብተት፤ አዳርን እይ። ወለለ ሠለስቱ ዓም ያሠግሩ አሐደ ወርኀ ወትከውኖሙ ይእቲ ዓመት ዐሠርተ ወሠለስተ ወርኀ ፡ (አቡሻ ፡ ፫)።
[2] ፡ አሥገረ፤ አስጠመደ ፥ በወጥመድ አሲያዘ፤ አሳሰረ።
አሥገወ አሠገወ አስተሠገወ ፡ አገዘፈ፤ አጐላ። ሶበ ይፈቅድ ሰብእ ይክሥት ነገረ ኅሊናሁ ያሠግዎ በልሳኑ ፡ (ያዕ ፡ ዘእል)።
አስገደ ፡ አሰገደ፤ አንበረከከ። ሥጋ እንተ ነሥአ እምኔነ አስገዶሙ ለመላእክት ፡ (አፈ ፡ ድ፭)።
አሥጋሪ ፡ (ሪት) መሥገሪ፥ግር፤ የሚያሠግር፤ የሚያሻግር። ወትሰመይ ይእቲ ዓመት አሥጋሪተ ወርኅ ፡ (አቡሻ ፡ ፴)።
አስጠመ ፡ አሰጠመ፤ ከባሕር አገባ ጣለ፤ አጠለቀ፤ ደፈነ ቀበረ፤ ዋጠ አሰመጠ፤ አለበሰ። ያሰጥሞን ለኀጣውኢነ። አስጥም ጽንዖሙ። ያሰጥም መራዕየ አሕርው። አስጠሞሙ ወይን። አፍላግ ኢያሰጥሙከ። ያሰጥም ሐዝሐዘ ፈለግ። ውሒዝ ዘይደፍና ወያሰጥማ ለምድር ፡ (ሚክ፯
፡ ፲፱። ዮዲ፱ ፡ ፰። ቅዳ ፡ ዮሐ። ኢሳ፳፰ ፡ ፯። ፵፫ ፡ ፪። ኢዮ፳፩ ፡ ፴፫። ኤር፳፱ ፡ ፪)።
አስጣሮት ፡ (ዕብ ዐሽታሮት። ጽር አስታርቲ) ጣዖታት፤ የበግ መንጋ የሚመስሉ፤ በበጎች አምሳል የተቀረጡና የተሣሉ የበግ ምስሎች። ባለብሉዮች ግን ከዋክብት ሦስቶ ስድስቶ ይሏቸዋል
፡ (መሳ፪ ፡ ፲፫)። ፪ኛም በአስጣሮት ፈንታ አስጦራጢ፤ አስጥርጥዮን ይላል፤ ፍችው አንድ ነው ፡ (፩ነገ ፡ ፴፩
፡ ፲)።
አስጥሐ ፡ (ጥሰ) አሰጣ፤ አስገለጠ፤ አስጡ ግለጡ አለ።
አስጳዳቶስ ፡ (ጽር አስፓላቶስ) የሽቱ ዕንጨት፤ እሾኻም፤ ሥሩ ከሽቱ ጋራ የሚቀመም የሚነጠር። ባለብሉዮች ዶርሶኒ ይሉታል ፡ (ሢራ፳፬ ፡ ፲፭። አርጋ ፡ ፮)።
አስፈሊጦስ ፡ (ጽር አስፋሊቶስ) የጡብ የሸክላ ጭቃ፤ የሙጫ ቅጥራን ለጡብ ለሸክላ የሚቀባ፤ የሚለቀለቅ። ባለብሉዮች ግን ሰሊጥ የባሕር ዐረፋ ይሉታል ፡ (ዘፀ፪ ፡ ፫። ኩፋ ፡ ፲። ፵፯። መቃ ፡ ገ፪። ስንክ ፡ ታኅ፪)።
አስፈረ ፡ አሰፈረ አስቈጠረ፤ ስፈሩ ቍጠሩ አለ። ያሰፍር ሥርናየ ፡ (ኩፉ
፡ ፵፫)።
አስፈሬድ ፡ (ዳት። ጽር ስፒሪዶስ)። ቅርጫት፤ እንቅብ፤ ወራንታ፤ የእንቅብ የቀፎ የጐታ ዐይነት፤ ከቀጫጭን ሐረግ ከለበቅ ከሸንበቆና ከቀርካሓ የሚሠራ
፡ (ማቴ፲፭ ፡ ፴፯። ማር፰ ፡ ፰። ግብ፱ ፡ ፳፭። ገድ ፡ ተክ። ዳን፲፫ ፡ ፴፫)።
አስፈር ፡ (ጽር ሪጎስ። ዕብ ዳሌቄት) ብርቱ ትኵሳት ከልክ ከመጠን ያለፈ። የሆድ በሽታ፤ ብጫ የሚያደርግ፤ የሚያጠወልግ። ይቀሥፈከ እግዚ፤ በደዌ ሲሕ ወበፈፀንት ወበአስፈር ፡ (ዘዳ፳፰ ፡ ፳፪)።
አስፈነ ፡ አሰፋ አበዛ፤ አስፈነ አሠለጠነ ፡ (አርጋ)።
አስፋር ፡ (ዐረ አጽፈር) ያይነት ስም፤ ብጫ፤ ወርቅ የሚመስል። አክደር ወአስፋር ፡ (መቃ ፡ ገ፫)።
አስፋርስ ፡ (አው መስፈርስ) የወፍ በሽታ፤ ሰውነት ወይባ የሚያስመስል ብጫ የሚያደርግ። ወየሐምም ሕማመ መስፈርስ
፡ (ስንክ ፡ ሐም፰)።
አስፌም ፡ (ጽር ሄሴፊም። ዕብ አሱፊም) የቦታ ስም፤ መካነ ጉባኤ፤ መሰብሰቢያ መከማቻ፤ ወይም ክምቹዎች ማለት ነው። ባለብሉዮች ግን ዐጥረ ገጥ ይሉታል፤ ለቤተ መቅደስ መቅረቡን ያሳያል
፡ (፩ዜና ፡ ፳፮ ፡ ፲፯)።
አስፌር [1] ፡ ዓምና፤–ሰፊር
፡ ሰፈረ።
[2] ፡ ዓምና፤ ያለፈው ዓመት፤ ስፍሩና ቍጥሩ የመላለት። ምስክር ሳይኖረው ባላገባቦች ይሉታል፤ አሚርን ተመልከት
፡ (ደቂቅ አገባብ)።
አሶ ፡ ወባ ንዳድ ትኵሳት፤ ሐኪምና ፈውስ የሚያስፈልግ
፡ (ትግሬ)።
አሶር ፡ (ዕብ አሹር) ስመ ነገድ፤ ስመ ሀገር፤ ታችኛው ሶርያ ነነዌ
፡ (ዘፍ፲ ፡ ፲፩ ፡ ፳፪)።
አሶርዮን ፡ (ጽር አሳሪዎን። ዕብ ኢሳር) ታናሽ ገንዘብ፤ የገንዘብ ክፍል፤ እንደ ሶልድና እንደ ቤሳ ያለች መዳብ፤ ንሓስ ፡ (ማቴ፲ ፡ ፲፱። ሉቃ፲፪ ፡ ፮)።
አሶቀ ፡ አስደገፈ፤ ደጋፊ ሰጠ።
አሶት ፡ ፈውስ፤ ሀብተ ፈውስ፤ መንፈሳዊ ሥልጣን
፡ (፩ቆሮ ፡ ፲፪ ፡ ፱ ፡ ፳፰ ፡ ፴)። ኀለይኩ ቅድስና ዘነቢያት ወአሶተ ዘሐዋርያት። እመንፈስ ቅዱስ ነሢኦ አሶተ ፡ (አርጋ ፡ ፯። ድጓ)።
አሶንያ ፡ ጨረቃ፤ የጨረቃ ስም። እብላንና ኤራስን ተመልከት
፡ (ሔኖ፸፰ ፡ ፪)።
አሦጠ ፡ አስመለሰ ፥ አስቀለሰ፤ አግባ መልስ አለ።
አሶጠ ፡ አስጨመረ፤ አስገረፈ።
አረሚ [1] ፡ (ሚት ማያን ያት) የአራም ወገን፤ የአራም ቋንቋ ሱርስት። አራማዊ ፥ ሶርያዊ ሕዝብ፤ ኦሪታውያንን እንደ ጋላ ኹኖ ይወርና ይዘርፍ ይማርክ የነበረ የእስራኤል ጠላት።
[2] ፡ አረመኔ፤ አሕዛብ፤ በኦሪት በወንጌል የማያምን። አሕዛብ ሥርዐት ያለው፤ አረመኔ ሥርዐት የሌለው። አእምንዎ ለአረሚ። አረሚ እለ ኢየአምርዎ ለእግዚ
፡ (ቀሌ። ፩ተሰ ፡ ፬ ፡ ፭። ሮሜ፱ ፡ ፳፬ ፡ ፴)።
[3] ፡ ጽርኣዊ፤ ግሪክ፤ ዮናን። ብሔረ አረሚኑ የሐውር ወይሜህሮሙ ለአረሚ። እለ እምአረሚ
፡ (ዮሐ፯ ፡ ፴፭። ፲፪ ፡ ፳። ሮሜ፩ ፡ ፲፬። ፩ቆሮ ፡ ፩
፡ ፳፪–፳፬)።
አረማዊ ዪ ፡ (ዊት ዪት ውያን ያት) የአራም የግሬክ ወገን፤ አሕዛብ፤ አረመኔ፤ ክፉ ጨካኝ፤ እምነት ርኅራኄ የሌለው። ለአይሁዳዊ ወለአረማዊ። ብእሲት ተንባላታዊት አው አረማዊት። ኢትትመሀሩ ፍኖተ አረማውያን ፡ (ሮሜ፩ ፡ ፲፮። ሲኖዶ። ኤር፲ ፡ ፪)።
አረሰየ አስተረሰየ ፡ አስደረገ፤ አስጠረረ፤ አሰለፈ፤ አስታጠቀ። አስተረሰይኮኑ ለቀትል በንዋየ ሐቅል። አስተረስዩ እምውስቴትክሙ ዕደወ ወተቃተሉ። ለምንት ታስተሬሲ አፍራሰ ውስተ ብሔረ ስንእ። አስተረስያ አንጻረ መንፈሰ ፀሪፍ ፡ (ኢዮ፴፱ ፡ ፳። ዘኍ፴፩ ፡ ፫። ኤር፲፪ ፡ ፭። ማር ፡ ይሥ፩ ፡ ፰)።
አረቦናት ፡ (ጽር አራቦት። ዕብ ሀሪፎት) የስንዴ ክክ፤ ወይም ፍትግ፤ ደረቈት። ስንዴውን ቀቅለው አድርቀው ይከኩና እንደ እንቀት እንደ ሩዝ በቅቤ አጣፍጠው ይበሉታል። ወሰጥሐት ቦሙ አረቦናተ
፡ (፪ነገ ፡ ፲፯ ፡ ፲፱)።
አረቦን ፡ መያዣ ፈለማ፤–ዐረቦን።
አረወ አው አርወየ ፡ (የአረዊ የአርዊ) አውሬ ኾነ፤ አውሬ ተባለ፤ በባሕርይ በግብር። ተቈጣ ተነሣሣ። መጽሐፍ ግን በአርወየ ፈንታ ተአርወየ ይላል፤ ፍችው አንድ ነው።
አረየ ፡ ተካከለ፤–ዐርይ ዐረየ።
አረየፀ ፡ አስተረየፀ፤ አስለፈ፤ አስጠረረ። ያስትረይፆሙ ለመስተጋድላኒሁ
፡ (አፈ ፡ ድ፳፭)።
አረጋዊ ይ ፡ (ዊት ዪት ውያን ያት) ያሮጌ ወገን መካከለኛ፤ መዋዕለ ውርዙቱ ያለፈ፤ ዕድሜው ካርባና ካምሳ የተረፈ፤ ጠጕሩ የጨበረ የርጅና መንገድ የዠመረ። አረጋዊ ዘበሥርዐቱ ይተሉ ዝሙተ። ናሁ አቡነ አረጋይ ውእቱ። አረጋዪት መበለት። መነኮሳት አረጋውያን ፡ (ሢራ፵፪ ፡ ፰። ዘፍ፲፱ ፡ ፴፩። ስንክ ፡ ኅዳ፳፪። ታኅ፰)።
፡ ባሕታዊ፤ መነኵሴ፤ መምህር፤ አበ ማኅበር። አረጋዊ መንፈሳዊ። ይቤሎ እኍ ለአረጋይ። ወይቤ አረጋዊ
፡ (አረጋ። ፊልክ)።
አረግ ፡ (ጊት፤
፡ (ብ አእሩግ ጋት) ) አሮጌ፤ ሽማግሌ፤ ታላቅ፤ ልሂቅ፤ ፸ ዓመት ያለፈው፤ ዕድሜ የጠገበ ለሞት የቀረበ። ሴት ብትኾን ከ፷ ዓመት በላይ ያለች፤ አሮጊት ባልቴት። አረጊት ዘድክምት ፈድፋደ። አእሩግ ወሊቃውንት
፡ (ፈላስ። ስንክ ፡ ታኅ፲፭)።
አረፈ ፡ (ዐረብ) ጨረሰ አበቃ፤ ፈጸመ፤ ደመደመ።
አረፍት ፡ (ፋት)
ግድግዳ፤ ዐጥር ቅጥር፤ ካብ ግንብ፤ ሥራው ያለቀለት። አረፍት ይሴውረኒ። አረፍት በይምን ወአረፍት በፅግም። አረፋቲሃ ለኢየሩሳሌም ፡ (ሢራ፳፫ ፡ ፲፰። ዘፀ፲፭ ፡ ፲፱። መዝ ፡ ፶)።
አሩራን ፡ (ጽር። ዕብ ኤሼል) ታላቅ ዛፍ ቅጠሉ ጽፍቅ ቁመቱ ምጡቅ የኾነ፤ ስሙ ያልታወቀ፤ ባለብሉዮች ግን ሮማን ይሉታል። ወቀበርዎ ታሕተ አሩራን
፡ (፩ነገ ፡ ፴፩ ፡ ፲፫)። ታላቅነቱም ሊታወቅ በዜና መዋዕል፤ ግእዙ ዘግባ ፥ ዐማርኛው ሰሌን ይለዋል ፡ (፩ዜና ፡ ፲
፡ ፲፪)።
አሪር ሮት ፡ (አረ፤ አረረ የአርር ይእርር ይእ። አረየ) መማረር፤ ማጨድ መቍረጥ መንቀል፤ መልቀም መቃረም፤ መሰብሰብ ማስር፤ መጐቸት፤ መከመር፤ ወቅቶ ማምረት፤ በጐታ መክተት፤ ያዝመራ። ዘዘርዐ ሰብእ የአርር። ትዘርዑ ወተአርሩ። ካልእ ዘይዘርዕ ወካልእ ዘየአርር። ወአንሰ ፈነውኩክሙ ትእርሩ። አረርኩ ከርቤ
፡ (ገላ፮ ፡ ፯። ኢሳ፴፯ ፡ ፴። ዮሐ፬ ፡ ፴፯ ፡ ፴፰። ማሕ፭ ፡ ፩)።
፡ መጮኽ እሪ ማለት፤ መጥራት ማቅራራት፤ ታላቅ ድምጥ መስጠት የሐዘን የዘፈን
፡ (ዐረብ)።
አሪግ ጎት ፡ (አረገ የአርግ ይእርግ። ዕብ አራግ አነመ፤ ሰፈየ። አራኽ፤ ኖኀ። ዐረ አርጃእ፤ ጸንሐ) ማርጀት፤ መሸምገል፤ አሮጌ ሽማግሌ መኾን፤ ከዕድሜ ርዝመት ከብዙ መቈየት የተነሣ። ልህቀን ተመልከት። አረገት ሳራ ፡ (ስንክ ፡ ነሐ፳፮)።
አራኅርኀ ፡ አራራ፤ አስራራ፤ አግራራ፤ አለዛዘበ፤ መከረ አስተማረ፤ ገር አደረገ። ዛቲ መጽሐፍ ታራኀርኅ ጠባይዒከ ወታሤኒ ግዕዘከ። ከመ ያራኅርኅ ልበ እግዚኡ። ታራኅርኅ ልቦ ላዕሌየ ፡ (ፈላስ። መቃ። ዮሴፍ)።
አራም ፡ ስመ ነገድ፤ ስመ ሀገር፤ ላይኛው ሶርያ፤ ደማስቆ
፡ (ዘፍ፲ ፡ ፳፪። ኢሳ፯
፡ ፩ ፡ ፰)።
አራሪ ፡ (ሪት ርያት ያት) የሚማርር ማራሪ፤ ዐጫጅ ሰብሳቢ ለቃሚ፤ ቃራሚ።
፡ (ተረት) አራሪ ለማራሪ ለበራሪ ይተው።
አራራት ፡ የኖኅ ተራራ ስም። አራራተ ነበረት ታቦት
፡ (ድጓ)።
አራራይ ፡ እሪታ፤ ቅርርት ታላቅ ጩኸት። የዜማ ስም፤ የዜማ ስልት። ሦስተኛ ዜማ የመንፈስ ቅዱስ አምሳል። ሠለስቱ ዜማ፤ ዘውእቱ ግእዝ ወዕዝል ወአራራይ
፡ (ስንክ ፡ ግን፲፩)።
አራቦት ፡ ሜዳ በረሓ፤–ዐራቦት።
አራዝ ዛት ፡ ልብስ፤–ዐርዞ ዐረዘ።
አራዪ ፡ (ዪት ይያን ያት፤ አረይት) የሚለቅም የሚቃርም፤ ቃራሚ መራጭ።
አራጊ ፡ (ጊት ግያን ያት) የሚያረጅ፤ የሚሸመግል፤ ሸምጋይ።
አርሐሰ ፡ አራሰ፤ አስራሰ፤ ነከረ፤ አረጠበ፤ አረካ አጠገበ። ያርሕሶሙ ነፍኒፍ ወጠለ ገዳም። እስከ ይውሕዝ ሀፉ ከመ ማይ ወያርሕስ ምድረ ኀበ ቆመ። ወበአንብዕየ አርሐስኩ ምስካብየ።
፡ (ኢዮ፳፱ ፡ ፰። ገድ ፡ ተክ። መዝ ፡ ፮። ሉቃ፯ ፡ ፴፰)።
አርሓሲ መርሕስ ፡ የሚያርስ፤ የሚያረጥብ፤ ነካሪ።
አርሐቀ ፡ አራቀ፤ አስራቀ አሶገደ፤ ለየ፤ ቈረጠ። ከመ ያርሕቁኒ እመቅደስየ። አርሕቅ መዐተ እምልብከ። አርሕቃ ለሐዘን እምኔከ። ጌጋይክሙ አርሐቀ ሠናይተ እምኔክሙ። አርሐቀኒ እምሕይወትየ
፡ (ሕዝ፰ ፡ ፮። መክ፲፩ ፡ ፲። ሢራ፴፰ ፡ ፳። ኤር፭ ፡ ፳፭። ኢዮ፴ ፡ ፳፪)። በአርሐቀ ፈንታ አስተርሐቀ ይላል፤ ፍችው አንድ ነው። እፎ ታስትርሕቀ ለዘኢይትረሐቅ። እምደሪሰ ድርሳን አስተርሐቆ። ወአስትርሐቅዋ ለኀጢአቶሙ ፡ (መጽ ፡ ምስ። ስንክ
፡ ታኅ፰። መዝ ፡ ፻፳፰)።
አርሐበ ፡ አሰፋ፤ ዘረጋ፤ ሰፊ አደረገ፤ አበዛ። ለያርሕብ ብሔረ። አርሐበ ለከ ደወለከ። አርሕቢ መታክለ ዘደብተራኪ። ከመ ያርሕቡ ንኅለተ። አርሐበት ሎቱ ብሰሎ እምጻማሁ ፡ (ዘፍ፱ ፡ ፳፯። ዘዳ፴፪ ፡ ፳። ኢሳ፶፬ ፡ ፪። ዮሴፍ። ጥበ፲ ፡ ፲)።
አርኀበ ፡ አስራበ፤ ምግብ ነሣ፤ ረኀብ አመጣ። ምግብ አስፈለገ፤ ልብላ ልብላ አሰኘ፤ ረኀቡ። አርኀበከ ወእምዝ መና ሴሰየከ። አርኅብዎ ወአጽምእዎ ፡ (ዘዳ፰ ፡ ፫። ፫ነገ ፡ ፳፪ ፡ ፳፯)።
አርሓቢ መርሐቢ ፡ (ሕብ) የሚያሰፋ፤ አስፊ፤ ሰፊ አድራጊ።
አርኀወ ፡ ከፈተ፤ አስከፈተ፤ ገለጠ፤ ሰበረ ድል አደረገ። አርኀወት ኆኅተ። አርኀዋ ለታቦት። አርኀውከ ሰማየ። አርኀወ ሀገረ ፡ (ጦቢ፰ ፡ ፲፫። ኩፋ ፡ ፭። ኢሳ፷፬ ፡ ፩። ዮሴፍ)።
አርሐፀ ፡ አወዛ፤ አስወዛ፤ አቅለጠለጠ።
አርኀ ፡ (የአርኅ ይእራኅ። ዕብ አራኽ፤ ኖኀ) ሰፋ ተዘረጋ ጠፈጠፈ፤ ሰፊ ዝርግ ጠፍጣፋ ኾነ።
አርመመ [1] ፡ አስረመመ፤–ረሚም ረመ፤ ረመመ።
[2] ፡ አርመመ፤ ፡ (አስደራጊ) አስራመመ፤ አስረመመ፤ ዝም አሰኘ፤ ጸጥ አደረገ፤ አፍ አሲያዘ ዕሻ ዝም በሉ አለ፤ ዝምታ አስተማረ። አርመሞሙ ለሰብእ። አርምም አፉከ። ኦ አፍ አመ ያረምመኪ ሞት እፎ ትከውኒ። ያርምም ልሳኖ እምእኪት። አንተ ትኴንን ኀይለ ባሕር ወታረምሞ ለድምፀ ማዕበላ ፡ (ዮሴፍ። ሢራ፴፭ ፡ ፰። ግንዘ። ፩ጴጥ ፡ ፫ ፡ ፲። መዝ ፡ ፹፰)። በአርመመ ፈንታ አስተራመመ ይላል፤ ስሕተት ነው። ወሌዋውያን ያስትራምሙ። አስትራመመ ሁከታ ለነፍስ። ባሕረ እምነ ተሀውኮ አስተራመመ። ወናስተራምሞ ለዝሉፉ
፡ (ነሐ፰ ፡ ፲፩። ፍ ፡ ነ ፡ ፵፫ ፡ ፲፪። ስንክ
፡ ታኅ፲፭። አፈ ፡ ተ፭)።
አርመስመሰ ፡ (ረምሰ። ዕብ ራማሽ) አርመስመሰ፤ ተርመስመሰ፤ በጁና በግሩ፤ ምስጢሩ ሐዊርና ኀሢሥ ገሲስ ናቸው፤ ከረሚስና ከመሪስ ከኹለቱ ዘር ተዴቅሏል። ወእንዘ ታርመሰምስ ጽዮን ብእሲት ኀባል፤ ሰበረቶ ለአጵሎን ጻሕል ፡ (ቅኔ። ሲኖዶ)።
አርማሕ (ሓት) [1] ፡ ዘገሮች ሠላጢኖች። እለ አርማሕ
፡ (፩ዜና ፡ ፲፪
፡ ፳፬)።
[2] ፡ አርማሕ፤ የሰው ስም፤ ጦረኛ ሐርበኛ፤ የኢትዮጵያ ንጉሥ፤ በሙሐመድ ዘመን የነበረ ፡ (ታሪ ፡ ነገ)።
አርማሚ ፡ (ሚት ምያን ያት) ዝም የሚያሰኝ፤ አፍ የሚያሲዝ። ዝም የሚል፤ ዝም ባይ፤ ዝምተኛ። ባለብሉዮች ግን ሚዛን፤ ዳኛ ብለው ይጨምሩበታል። ካሕደ የኀድግ አርማሚ። እንዘ ተናጋሪ አርማሚ። ብእሲት አርማሚት ወዐቃቢተ ልሳን ፡ (ምሳ፲፰ ፡ ፲፰። ፊልክ ፡ ፻፳። ፈላስ)።
አርማስ [1] ፡ ታንኮች፤–ረሚስ ረሚሰ፤ ረምስ።
[2] ፡ አርማስ፤ ታንኮች የዕቃ መርከቦች፤ ፡ (አሙኝቶች)። ናመጽኦሙ ወንገብሮሙ ከመ አርማስ እንተ ባሕር
፡ (፪ዜና ፡ ፪ ፡ ፲፮። ፫ነገ ፡ ፭ ፡ ፱። ጥበ፲፬ ፡ ፭። ስንክ ፡ መስ፲፰)።
፡ መጽሐፍ፤ የመጽሐፍ ስም፤ ውስጠ ብዙነት ያለው፤ ትርጓሜው የጐላ የተገለጠ፤ ዕፍን ሽፍን ያይዶለ። ይቤ በውስተ መጽሐፉ ዘሰመዮ አርማስ ፡ (ሃይ ፡ አበ)።
አርማስቆስ ፡ (ጽር አርሚስኮስ) ድሪ፤ ሰደፍ፤ ቀህረማን፤ እንደ ጨሌ እንደ መቍጥሪያ ያለ ያንገት ጌጥ። ባለብሉዮች ግን ግንብ መንቀል፤ የብር ዘንግ ዞሪት ይሉታል። ኤፎትን ተመልከት
፡ (ማሕ፩ ፡ ፲)። ቀህረማን ብጫ የንቍላል አስኳል የሚመስል፤ ዕጣን ዕጣን የሚሸት ነው፤ ፪ኛ ስሙ ቈርበት ካሪም።
አርማጌዶን ፡ (ዕብ ሀር ምጊዶን) የሀገር የቦታ ስም፤ የንፍታሌም ዕፃ
፡ (ራእ፲፮ ፡ ፲፯)።
አርምሞ ፡ ዝም ማሰኘት፤ ዝም ማለት። ዝምታ፤ ዕረፍት፤ ህድአት። በአርምሞ ወበተሐክሞ። ተናግሮ ብሩር ውእቱ አርምሞሰ ወርቅ ይእቲ ፡ (ምሳ፲፯ ፡ ፳፰። ፈላስ)።
አርሞን ኤርሞን ፡ (ዕብ ሔርሞን) የተራራ ስም፤ ጉማም በረዷም፤ የዮርዳኖስ ራስ። ፍችው ልዑል ነዋኅ፤ ቅዱስ። የግእዝ መጽሐፍ ከጽርእ ስለ ተቀዳና በጽርእ ፊደል ሀ ሐ ኤ ዒ የሚባሉ ስለ ኾነ፤ በሔርሞን ፈንታ ኤርሞን አርሞን ይላል
፡ (ዘዳ፫ ፡ ፰። ማሕ፬ ፡ ፭። ሔኖ ፡ ፮። ፲፫)።
አርሰነ ፡ አጋለ አጋመ፤ አስጋለ አስጋመ፤ ጠበሰ ተኰሰ፤ አሞቀ አናደደ፤ አቃጠለ። ኣረስኖሙ ወእፈትኖሙ። ከመ ብርት ዘአርሰንዎ በእሳት። አርሰንዎ ለቅዱስ በሰናስለ እሳት። ያረስን ልቦ በእንተ አፍቅሮ እግዚ
፡ (ኤሮ፱ ፡ ፯። ራእ፩ ፡ ፲፭። ስንክ ፡ ታኅ፰። ፊልክ
፡ ፩)።
አርሰየ ፡ ወደበ፤ አስጠጋ፤–አርሰወ፤ ረሰወ።
አርሲመርቲዳስ ፡ (ጽር አርኺማንድሪታስ) ዝኒ ከማሁ፤ የካህናት አለቃ፤ አበ ምኔት፤ አበ ማኅበር፤ ርእሰ ባሕታውያን
፡ (ስንክ ፡ ሐም፯)።
አርሲስ ፡ (ሳን። ጽር ኤሬሲስ፤ ኑፋቄ፤ ዕልወት) መናፍቅ፤ ዐላዊ፤ ባህሉና ትርጓሜው እንደ ካራና እንደ ቅባት ከሰው ከመጣፍ የማይገጥም ዕልዋን ዘይሰመዩ አርሲሰ በነገረ ጽርእ። ኢትጸሊ ምስለ አርሲሳን ዘውእቶሙ ዐላውያን ፡ (አብጥ ፡ ፵፫። ሃይ ፡ አበ። ስንክ ፡ ሠኔ፲፰)።
አርሳሕስሐ አርሰሐስሐ ፡ አጥብቆ አሳደፈ፤ አረከሰ፤ ፈጽሞ አነወረ፤ አስነወረ፤ ወቀሠ ፈረደ መሰከረ፤ ነቀፈ ዘለፈ። እንዘ ኢያርሳሐስሖሙ ዝንቱ ዓለም። ወያርሰሐስሖሙ ልቦሙ። ወእመሰ ያርሰሐስሐነ ልብነ። ኢይትረከብ በላዕሌሆሙ ወኢምንትኒ ዘያርሰሐስሖሙ እምእግዚ አምላኮሙ ፡ (ኪዳ። ሮሜ፪ ፡ ፲፭። ፩ዮሐ ፡ ፫ ፡ ፳። ቀሌ)።
አርሳኒ መርሰኒ ስን ፡ የሚያግል፤ የሚያግም፤ የሚጠብስ የሚተኵስ ፡ (አዋል)።
አርሳኒ አርሳንዮስ ፡ የሰው ስም፤ ሮማዊ ቅዱስ፤ ያስቄጥስ መነኵሴ። ዛ ጽፍዐት ዘአርሳኒ ፡ (ፊልክ)።
አርሳይሮስ ፡ (ጽር አርኺሄሬፍስ) የገዳም አባት፤ ሹም
፡ (መጽ ፡ ምስ)።
አርስሐ ፡ አሳደፈ፤ አኵለፈለፈ፤ እድፋም ጕድፋም ነውረኛ አደረገ። በፍርድ። አሌ ሎቱ ለዘአርስሕ ሥጋሁ በፍትወተ ዝሙት። መብዝኅቶሙ ለሰብአ ያረስሑ ነፍሶሙ። ታረስሕ አፉከ በኵስሕ። አርስሖሙ ዳንኤል እምቃሎሙ። ወሶበ ርእየ ከመ አርስሕዎ
፡ (ቀሌ። አፈ ፡ ድ፲፪። ተግ፲፯። ዳን፩ ፡ ፷፩። ማቴ፳፯ ፡ ፫)።
አርሥአ ፡ አስረጀ፤ አሸበተ፤ አሸመገለ። ዘእንበለ ይብጻሕ ጊዜሁ ያረሥእ ትካዝ። ብእሲት ነባቢት ታረሥእ ውርዝውና ምታ ፡ (ሢራ፴ ፡ ፳፬። ፈላስ)።
አርስዐ ፡ አስረሳ፤ አስዘነጋ፤ አረሳሳ። አርሳዕክሙኒ ዘእፈቅድ እበሎ። ያረስዖ ለሕዙን ሐዘኖ። አርስዓ ዐቲበ ርእሳ። ሐዘና ለልብ ያረስዕ ወይን ፡ (ዮሴፍ። ገድ ፡ ዘሚ። ቀሌ። ሢራ፴፬ ፡ ፳፱)።
፡ አሳተ፤ አስካደ፤ ኀጢአት አሠራ። አርስዖ ምናሴ ለይሁዳ ፡ (ዲድ)።
አርስጣላብ ፡ (ጽር አስትሮላቦስ) የፀሓይና የጨረቃ የኮከብ መነጽር መልካቸውን አቅርቦ የሚያሳይ የሚያስመረምር። ወይም መንገዳቸውን የሚናገርና የሚያስተምር የፍልስፍና መጽሐፍ። ወነሥአ አርስጣላበ ወነጸረ ውስቴቱ ዘይብል እልመክኑን። ቃይናን ወልደ አርፋክስድ ወጠነ ጽሒፈ አርስጣላብ እምድኅረ አይኅ፤ ወእምድኅሬሁ ጸሐፉ ህንዳውያን
፡ (ስንክ ፡ ጥቅ፯። ዮሐ ፡ መደ ፡ ክ፬)።
አርሶን ፡ (ጽር አርሲን። ዕብ ማሣእ፤ ሳባል) ጭነት፤ ሸክም የሚከብድ የሚያስጨንቅ። ባለብሉዮች ግን ጠርብ ይሉታል
፡ (፫ነገ ፡ ፭ ፡ ነ፭። ፬ነገ ፡ ፰ ፡ ፱)።
አርሺ ፡ (ቅብጥ) ሊቅ፤ አለቃ። አርሲመርቲዳስን እይ፤ ከዚህ ጋራ ፩ ነው። አርሺ፤ ዲያቆን
፡ (አቡሻ ፡ ፶)።
አርቀቀ ፡ አረቀቀ፤ አስረቀቀ፤ አሣሣ አቀጠነ፤ አስቀጠነ፤ ፋቀ ፈቀፈቀ፤ ራመመ።
አርቀየ ፡ አስደገመ፤ አስረጨ፤ አስሞቀ አስፈላ፤ አስነጠረ ዐረቂ አሶጣ።
አርቆሚን ፡ (ጽር አርኪኒም። ዕብ ባርቃኒም) እሾኾች፤ እሾኻም ዕንጨቶች፤ እሾኻቸውና ቅጠላቸው ነጫጭ የኾነ፤ በረቅ የሚመስል፤ ኰሸሽሎች ፡ (መሳ፰ ፡ ፯ ፡ ፲፮)። ባለብሉዮች ግን ግራር ይሉታል።
አርበበ ፡ (ሱር ራውርባ) አበዛ፤ አረባ፤ አከበረ። ረበበ፤ ቈለለ ከመረ፤ አላቀ ታላቅ አደረገ።
አርባብ [1] ፡ ጌቶች፤–ረቢብ ረበ ረብ።
[2] ፡ የኪሩቤል ስም፤ ጌቶች አለቆች፤ ደምሳሾች። አርባብ ኪሩቤል። ንበር ዲበ ሳሬል ወዲበ አርባዕቱ አርባብ ፡ (ቀሌ። አርጋ ፡ ፫። ማሕ፪ ፡ ፲፯)።
አርባዕ [1] ፡ አራት፤–ረብዖ ረብዐ።
[2] ፡ (የሴቶች) አራት። አርባዕ አዋልድ ደናግል። አርባዕ አህጉር። ዘየሐውር በአርባዕ
፡ (ግብ፳፩ ፡ ፱። ኢያ፳፩ ፡ ፲፰። ዘሌ፲፩ ፡ ፳)። በራብዕ ፈንታ አርባዕ ይላል፤ አያሰኝም። ወበእንተ አርባዕሰ
፡ (ዓሞ፩ ፡ ፫)።
አርባዕቱ ት ፡ (የወንዶች) አራት፤ አራቱ፤ ኦራተኛው። ቱ አርቲክል ነው። አርባዕቱ መኣዝነ ዓለም። አርባዕቱ ነፋሳት። አርባዕቱ አፍላጋት። አርባዕቱ ጠባይዓት። አርባዕቱ ወንጌላውያን ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፬)። በአኃዝ ብቻ ወይም እያቀናጀ፤ ፬ ፬ቱ እያለ ይጥፋል፤ አይገባም፤ የጣፊ ስሕተት ነው። ኹለተኛም አርባዕት በማለት ፈንታ አርባዕቱ ይላል። አርባዕቱ እንስሳት፤ አርባዕቱ ገጻት። አርባዕቱ ምእት
፡ (ሕዝ፩ ፡ ፭ ፡ ፮። ዘፍ፳፫ ፡ ፲፮)። ከአሐዱ እስከ ዐሠርቱ ያለ ቍጥር፤ ኹሉ እንደዚህ ነው፤ በገቢር ጊዜ ግን ካዕብነቱን ግእዝ ይወርሰዋል። ይነብሩ ፈላስያነ አርባዕተ ምእተ ዓመተ። ወርኢኩ አርባዕተ አቅርንተ ፡ (ዘፍ፲፭ ፡ ፲፫። ዘካ፩ ፡ ፲፰)።
አርባዕት ፡ የዜማ ቃል ትምርት፤ አራተኛ ክፍል፤ ከውዳሴ ማርያም
፡ (ድጓ)።
አርብሐ ፡ አስገዛ፤ አረባ፤ አስረባ፤ አበዛ፤ አስጠቀመ። እግዚአብሔር ዘአርባሕከነ ኵሎ ፍጥረተ ዘዘ ዚኣሁ ፍሬ። አርባሕከ ትምክሕተ በርእስከ ወበሰብእከ ኀሳረ ወዝንጓጔ። ሐዘን በእንተ እግዚ ያረብሕ ሕይወተ፤ ወሐዘን በእንተ ዓለም ያረብሕ ሞተ። በሊዕኒ ኢያረብሐነ ፡ (ቈስጠ። ዮሴፍ። ፍ ፡ ነ ፡ ፳፪። ፩ቆሮ ፡ ፰ ፡ ፰)።
አርብዓ ፡ (፵፤ መ) የቍጥር ስም፤ አርባ፤ አራት ዐሥር ወይም ዐሥር ጊዜ አራት። አርብዓ መዋዕለ ወአርብዓ ለያልየ አርብዓ ምእት። አርብዓ ዓመት
፡ (ማቴ፬ ፡ ፪። ፲፭ ፡ ፴፰። መዝ
፡ ፺፬)።
አርብዓዊ ፡ አርባኛ፤ ካርባ አንድ።
አርቦቅ ፡ ኵሓ፤ ችባሓ፤–ዐርቦት።
አርቲክል ፡ (ሮማይ አርቲኩሉስ) የስም ተውሳክ፤ ለ ላ ወንድና ሴት የሚለይበት። እልንና አሐዱን ተመልከት።
አርቴውቂኖን ፡ (ጽር አርኬፍቲኖን። ዕብ ሻሜን) ዘይት፤ ወይራ፤ ዕፀ ቅብዕ። ባላብሉዮች ግን ዋንዛ ዘግባ ይሉታል
፡ (፫ነገ ፡ ፮ ፡ ፴፩)።
አርትዐ ፡ አስረታ። አቀና፤ አጠና፤ አበጀ አዘጋጀ፤ ቅን አደረገ፤ አስደረገ። አርታዕል ነገረ። ከመ ያርትዕ እገሪነ። ኣረትዕ መንበረ መንግሥቱ። እግዚ አርትዐ ዓለመ በጥበቡ። አርትዕ ኵሎ ጠዋየ። አርትዕ ልበከ። አርታዕኩ ነፍስየ ፡ (ቄር ፡ ጰላ። ሉቃ፩ ፡ ፸፱። ፩ዜና ፡ ፳፪
፡ ፲። ኤር፲ ፡ ፲፪። ኢሳ፶፰ ፡ ፮። ሢራ፪ ፡ ፪። ፶፩ ፡ ፳)። በአርትዐ ፈንታ አስተራትዐ ይላል፤ ስሕተት ነው። እግዚ ዘይገብር ኵሎ ወያስትራትዕ። ከመ ያስተራትዕ ፍትሐ ለማኅፈሩ። ኤልያስ ይቀድም መጺአ ወያስተራትዕ ኵሎ። ከመ ታስተራትዕ ዘተርፈ። ናስተራትዕ ሃይማኖተ ፡ (ዓሞ፭ ፡ ፰። ሢራ፲፱ ፡ ፳፭። ማቴ፲፯ ፡ ፲፩። ቲቶ፩ ፡ ፭። ገድ
፡ ተክ)።
አርአሰ [1] ፡ ሾመ አሳደገ፤ ራስ አደረገ፤ አላቀ አበለጠ፤ በላይ አስቀመጠ። ካህነ እግዚ ዘአርአሶ ህየንቴሁ። ወአርአሶ ላዕለ ኵሉ ፡ (ፈ ፡ መ ፡ ፲፮ ፡ ፩። ኤፌ፩ ፡ ፲)።
[2] ፡ አንተራሰ፤ አቀና፤ ደገፈ፤ የድውይ።
አርዐወ ፡ አስጠመደ፤ ጥመዱ አለ።
አርዐየ ፡ አስጠበቀ፤ ጠባቂ ሾመ፤ ጠብቅልኝ አለ፤ ዐደራ ሰጠ።
አርአየ አስተርአየ ፡ አሳየ፤ ገለጠ፤ አበራ፤ ነገረ፤ አስተማረ፤ አሳወቀ፤ አስረዳ። አርአዮሙ እኪተኒ ወሠናይኒ። ከመ ኣርኢ ኀይልየ ላዕሌከ። እግዚ ያርኢ ገጾ ላዕሌከ። ነገር ዘአርአይኩከ። አርእየኒ ወአእምር። ምንተ ይቤሎ ዘአስተርአዮ። ዕፀ ዘያሬኢ ወያሌቡ ሠናየ ወእኩየ ፡ (ሢራ፲፯ ፡ ፯። ሮሜ፱ ፡ ፲፫። ዘኍ፮ ፡ ፳፮። ኤር፲፩ ፡ ፲፯። ፴፯ ፡ ፪። ሮሜ፲፩ ፡ ፬። ዘፍ፪ ፡ ፱)።
አርዐደ ፡ አራደ፤ አስፈራ፤ አናወጠ፤ አንቀጠቀጠ፤ አብረከረከ። አርዐድካ ለቀላይ። ዘበላዕሉ አንጐድጐደ ወዘበታሕቱ አርዐደ ፡ (ሱቱ
፡ ዕዝ፩ ፡ ፲፱። ቅዳ ፡ ግሩ)።
አርዑት [1] ፡ ቀንበር፤–ርዒው ረዐወ።
[2] ፡ (ዐረ አርዑወት) መጥመጃ፤ መጠመጃ፤ ማስጠመጃ፤ ቀንበር፤ ሕግ ሥርዐት፤ አገዛዝ፤ እግር ብረት። አርዑተ ብዕራ። ትወዲ አርዑተ ዲበ ክሣዱ። ንሥኡ አርዑትየ። አርዑት ዘሠርዑ ሳዕሌሆሙ። አርዑተ ግብጽ። አብእ እገሪከ ውስተ አርዑታ ፡ (ኢሳ፭ ፡ ፲፰። ኢዮ፴፱ ፡ ፲። ማቴ፲፩ ፡ ፳፬ ፡ ፴። ኩፋ ፡ ፴፬ ፡ ፵፬። ሢራ
፡ ፳፬)።
አርኣያ [1] ፡ በቁሙ፤–ርእይ ርእየ፤ አርአየ።
[2] ፡ በቁሙ፤ ሥዕል፤ አምሳል፤ ዐይነት፤ መልክ፤ አካል፤ አብነት መምር። ንግበር ሰብአ በአርኣያነ። በበ አርኣያሁ። አርኣያሁ ለእግዚ። ታሤኒ ገጻ ወታሰረጉ አርኣያሃ። ብርሃነ ስብሐቲሁ ወአምሳለ አራአያሁ። ኮነ አርኣያ ለዓለም ከመ ይነስሑ። እስመ አራኣያየ ወሀብኩክሙ
፡ (ዘፍ፩ ፡ ፲፪ና ፡ ፳፮። ፪ቆሮ ፡ ፬ ፡ ፬። ስንክ
፡ ጳጕ፭። ዕብ፩ ፡ ፫። ሢራ ፡ ፵፩ ፡ ፲፮። ዮሐ፲፫ ፡ ፲፭)።
፡ ዐቢይና ደቂቅ አገባብ፤ እንደ። አርኣያ ይነውም ዘልፈ። አርኣያ ብዙኅ ዝናም። አርኣያ ከመዝ ሰረረ
፡ (ስንክ ፡ ጥር፳፩። ጥቅ፳፭። ደራሲ)።
አርኤል ፡ (ዕብ አሪኤል) ምሥዋዕ የምሥዋዕ ስም። አሪ አንበሳ፤ ኤል አምላክ፤ በተገናኝ አንበሳ አምላክ ማለት ነው፤ ሥራውና ቅርጡ አቀማመጡ እንደ አንበሳ ስለ ኾነ፤ ኹለተኛም ለኣዕርጎ መሥዋዕት የወረደው እሳት በአንበሳ አምሳል ስለ ታየበት ፥ አንበሳ ተብሏል
፡ (ሕዝ፵፫ ፡ ፲፭ ፡ ፲፮)። ምስጢሩ ግን ሞአ አንበሳ ያለውን ያሳያል
፡ (ራእ፭ ፡ ፭)። በአርኤል ፈንታ አርያል ይላል፤ የጣፊ ስሕተት ነው ፡ (ኢሳ፳፱ ፡ ፩ ፡ ፪)። ሀሀርኤልን እይ፤ የዚህ ሞክሼ ነው።
አርእስት ፡ (ታት) ራሶች፤ ጫፎች፤ መዠመሪያዎች፤ አለቆች። ቀጥቀጥከ አርእስቲሁ ለከይሲ። መካን ዘይመትሩ ውስቴቱ አርእስታተ። አርእስተ ጥቅም። አርእስተ ነገር። አርእስተ ምንባብ። አርእስተ ዐሠርቱ ምእት። አርእስተ መላእክት
፡ (መዝ ፡ ፸፫። ስንክ ፡ ሐም፭። ምሳ፬ ፡ ፳፬። መቅ ፡ ወን። ግንዘ። ሔኖ። ኪዳ)።
አርከበ ፡ ጫነ፤ አስጫነ፤ አስቀመጠ፤ አፈናጠጠ። አስገኘ፤ አስረከበ፤ ሰጠ፤ አስጨበጠ። ትሕትና ዘምስለ ትዕግሥት ታረክብ ንጻርያተ። ብዝኀ ስታይ ኢያረክብ ኀይለ ወኢያኀጥእ ቍስለ። ታረክቦሙ ሕይወተ
፡ (ማር፩ ፡ ፭። ሢራ፴፬ ፡ ፴። ሄርማ)።
አርክ ፡ ወዳጅ፤–ዐሪክ ዐረከ፤ ዐርክ።
አርኰሰ ፡ አረከሰ፤ አስረከሰ፤ አሳደፈ፤ ሰደበ ነቀፈ፤ ርኩስ አለ፤ አሰኘ፤ አሰደበ አስነቀፈ፤ ሻረ አነወረ አስነወረ። አርኰስኮ ለውእቱ ምስካብ። ኢታርኵሱ ርእሰክሙ በዝንቱ ኵሉ። አርኰስክሙ ስምየ። አርኰሱ ሰንበታትየ። አርኰሱ ድንግለ ፡ (ዘፍ፱ ፡ ፬። ዘሌ፲፰ ፡ ፳፬። ሚል፩ ፡ ፮። ሕዝ፳ ፡ ፲፫። ዮዲ፱ ፡ ፪)። በአርኰሰ ፈንታ አስተራኰሰ ይላል፤ ስሕተት ነው። ያስተራኵስዎ አሕዛብ። ዘእግዚ አንጽሐ አንተ ኢታስተራኵስ። ዘተከልአ እምተዋስቦ እንዘ ያስተራኵስ። ብእሲት ዘአስተራኰሰት ምታ ወከአቶ ሰኪበ ምስሌሃ ኀልያ ከመ ርኩስ ውእቱ ግብረ ተዋስቦ ፡ (ኢሳ፵፱ ፡ ፯። ግብ፲ ፡ ፲፭። ፈ ፡ መ ፡ ፱ ፡ ፪ና ፡ ፬)።
አርወየ [1] ፡ አረካ፤–ረውይ ረወየ።
[2] ፡ አርወየ፤ አረካ፤ አብዝቶ አጠጣ፤ አጠገበ፤ አራሰ አረሰረሰ፤ አጨቀየ፤ ነከረ። ጽዋዕከኒ ጽኑዕ ወያረዊ። ሐወጽካ ለምድር ወአርወይካ፤ አርውዮ ለትለሚሃ። ያረዊ ነፍሶ እምቃለ እግዚ። ፈትለ አርዊ
፡ (መዝ ፡ ፳፪። ፷፬። ስንክ
፡ ጥቅ፲፮)።
አርዌ [1] ፡ (ዕብ አሪ፤ አርዬ፤ ብ አራዮት) አንበሳ፤ ዕጓለ አንበሳ፤ ያንበሳ ወገን ሥዕሉ ምስሉ፤ ቡችላው ግልገሉ፤ ደቦሉ።
[2] ፡ (ብ አራዊት) በቁሙ፤ አውሬ ነገዱ ከእንስሳ ከዖፍ የተለየ፤ ቍጡ ጠባየ ክፉ፤ ደም ልሶ ብርንዶ ጐርሦ ዐጥንት ከስክሶ የሚኖር፤ የሚያድንና የሚታደን በረኸኛ፤ የሰው የእንስሳ ደመኛ፤ በየስሙና በያይነቱ በየነገዱ። አርዌ ፀዋግ። አርዌ እኩይ። አራዊተ ሐቅል። አራዊተ ገዳም
፡ (ኩፋ ፡ ፴፬። ዘፍ፴፯ ፡ ፴፫። ኢዮ፭ ፡ ፳፪። ዳን፬ ፡ ፳፪)።
አርዌ ሐሪሥ ፡ አውራሪሥ። ሐርማዝንና ሐሪሥን ተመልከት ፡ (ኢዮ፴፱ ፡ ፱ ፡ ፲)።
አርዌ ባሕር ፡ የባሕር አውሬ፤ ዐዞ ጕማሬ ደራጎን ዐንበሪ፤ የመሰለው ኹሉ። እምቅድመ አራዊት ዘባሕር ፡ (ቅዳ ፡ ዲዮ። ራእ፲፩ ፡ ፯)።
አርዌ ብርት ፡ የእባብ ምስል ፡ (ዘኍ፳፩ ፡ ፰ ፡ ፱)።
አርዌ ምድር ፡ (ዐረ ሐየት። ሱር ሔውያ። ዕብ ናሓሽ። ጽር ዖፊስ) ከይሲ፤ እባብ፤ ዘንዶ፤ እግር ስለሌለው ከምድር ተጣብቆ በልቡ የሚሳብ፤ መርዛም ተንኰለኛ
፡ (ዘፍ ፫ ፡ ፩። ማቴ ፮ ፡ ፲)።
አርዌ ቤት ፡ ውሻ፤ ድመት።
አርዘመ ፡ አረዘመ፤ አስረዘመ፤ ረዥም ምጡቅ አደረገ፤ አስደረገ። ርዝመት፤ ለቁመትም ለሞላልነትም ይነገራል፤ ምጥቀት ግን ለቁመት ብቻ ነው።
አርዛት ፡ አእሩዝ፤ ዛፎች፤ መጽሐፍ ግን በአርዛትና በአእሩዝ ፈንታ ዕፀወ አርዝ ይላል
፡ (፫ነገ ፡ ፬ ፡ ፳፱። ፩ዜና ፡ ፲፬
፡ ፩)። አእሩዝ ዘገነተ አምላክ ፡ (ሕዝ፴፩ ፡ ፰)።
አርዝ ፡ (ዕብ ኤሬዝ። ሱር አርዛ። ዐረ አርዝ)። ታላቅ ዛፍ፤ ወፍራም ደንዳና፤ ረዥም ገናና፤ እንደ ጥድና እንደ ዘግባ ያለ። ላዕለ ኵሉ አርዘ ሊባኖስ ነዋኅ ወልዑል።ዐብየ ወተለዐለ ከመ አርዝ። አርዝ ዐቢይ
፡ (ኢሳ፪ ፡ ፲፫። መዝ ፡ ፴፮። ሕዝ፲፯
፡ ፳፫)።
አርያል ፡ ምሧዋዕ፤–አሪኤል።
አርያማዊ ፡ ላዕላዊ፤ ሰማያዊ፤ ዘሰማይ። ፀሓየ ጽድቅ አርያማዊ። አርያማዊት መቅደስ ፡ (ሳታ። ደራሲ)።
አርያም [1] ፡ ልዕልና፤–ረይም ሬመ ረየመ።
[2] ፡ አርያም፤ ፡ (ማት) የራማ ብዥ፤ ራማት አርያም አንድ ወገን፤ አርያማት የብዙ ብዙ። መጽሐፍ ግን አርያምን እንደ ራማ ላንድ ብቻ አድርጎ ይናገራል።
፡
ልዕልና
፤
ምጥቀት
፤
ላዕል ፤ መልዕልት። ሐነጸ መቅደሶ በአርያም። እለ ይነብሩ ውስተ አርያም። ከመ ያስርር ውስተ አርያም ዕጐሊሁ (መዝ ፡ ፸፯። ኢሳ፳፮ ፡ ፬። ዕን፪ ፡ ፬)።
፡ ሰማይ፤ ሰማየ ሰማያት፤ መጨረሻ ሰማይ። ዐረገ ውስተ አርያም ፄዊወከ ፄዋ። እስከ ትለብሱ ኀይለ እምአርያም። ወለከ ንፌኑ አኰቴት እስከ አርያም። እምቅድመ ይሕንጽ አየራት ወአርያማተ
፡ (መዝ ፡ ፷፮። ሉቃ፳፬ ፡ ፵፱። ቅዳ ፡ ግሩ)።
፡ የድጓ ቃል ትምርት፤ ኹለተኛ ክፍል ከውዳሴ ማርያም ፡ (ስንክ ፡ ግን፲፩)።
አርይ ዮት ፡ (አረየ የአሪ ይእሪ። ዕብ አራህ) መልቀም፤ መቃረም፤ መሰብሰብ፤ መምረጥ፤ ማረም መንቀል፤ መለየት መጣል
፡ (ዘሌ፲፱ ፡ ፱። ፳፫ ፡ ፳፪)። እሑርኑ ውስተ ገራህት እእሪ እክለ። ወሖረት ወአረየት። ንሑር ወንእርዮን። እንዘ ተአርዩ ክርዳደ። ወነቢሮሙ አረዩ ሠናዮ ፡ (ሩት፪ ፡ ፪ ፡ ፫። ማቴ፲፫ ፡ ፳፰ ፡ ፳፱ ፡ ፵፰)። አረረንና ኀረየን ተመልከት።
አርዮሳዊ ፡ (ዊት፤ ውያን ያት) የአርዮስ ወገን፤ በአርዮስ ሃይማኖት የሚያምን። አርዮሳዌ አውገዘ። አርዮሳውያን
፡ (ዝማሬ። ሃይ ፡ አበ ፡ ብንያሚ)።
አርዮስ ፡ (ጽር አሪዉስ) የሰው ስም፤ ጽርኣዊ መናፍቅ፤ ወልድን ከአብ የሚለይ የሚከፍል፤ በመለኮቱ ፍጡር የሚል፤ የሰውነቱን ለአምላክነቱ የሚናገር፤ ከዚህ የተነሣ ጉባኤ ኒቅያ፤ አምላከ ጽድቅ ዘእምአምላከ ጽድቅ ዘተወልደ ወአኮ ዘተገብረ፤ ኅቡረ ህላዌ ምስለ አብ ብላ፤ ረግማ አውግዛ የለየችው። ወሶበ ሰምዑ ቃሎ ርኩሰ ለአርዮስ ደንገፁ ሰራዊተ ሰማያት
፡ (ሃይ ፡ አበ)።
አርዮስፋጎስ ፡ (ጽር አሪዎስ ፓጎስ) የፈላስፎች ሸንጎ፤ የጥበበኞች አደባባይ፤ የፍየሎች ምሳግ፤ የሕፃናት መራወጫ መፈንደቂያ፤ የአእሩግ ፀሓይ መፙቂያ። ቤተ ምኵናን ዘስሙ አርዮስፋጎስ
፡ (ግብ፲፯ ፡ ፲፱)።
አርዮብ [1] ፡ (ጽር ኦሬዎን። ዕብ ክሲል)። ጉቡኣን ከዋክብት፤ ዘወትር ባንድነት ኹነው ችፍግ ብለው የሚታዩ፤ እንደነሦስቶ እንደነስድስቶ ያሉ
፡ (ኢሳ፲፫ ፡ ፲)። ጸዳሎሙ ለአብያዝ ወለአርዮብ ፡ (አርጋ ፡ ፯)።
[2] ፡ አርዮብ፤ ታላቅ ኮከብ እንደ ፀሓይ ያለ፤ ካራቱ ዐበይት ከዋክብት አንዱ። ጽዱል ኮከብ በጣም የሚያበራ የሚያሸበርቅ። እስመ ይቤ ኣነብር መንበርየ መልዕልተ አርዮብ ወአዐርግ ውስተ ምጽንዓት። ትጸድል እምሥነ አርዮብ
፡ (መጽ ፡ ምስ። ኢሳ፲፬ ፡ ፲፫። አርጋ ፡ ፬)።
አርዮጳጌጤስ ፡ (ጽር አሬዎፓጊቲስ) አርዮስፋጎስ ካለው ጋራ አንድ ነው
፡ (ግብ፲፯ ፡ ፴፬)።
አርደብ ፡ (ዐረ ኢርደብ። ቅብጥ ሄርቶብ። ጽር አርታቢ) የመስፈሪያ ስም፤ እንደ ቆሮስ ያለ ታላቅ መስፈሪያ፤ ሚዛን
፡ (አቡሻ ፡ ፶)።
አርደፈ ፡ አራደፈ፤ አከታተለ።
አርዳሚስ ፡ የሰሎሞን ልጅ፤ የምኒልክ ታናሽ፤ የሮብዓም ታላቅ፤ በነገሥትና በዜና መዋዕል ያለተጣፈ፤ ባለሐዲሶች የሚተርኩት
፡ (ሮሜ ፡ ፩)። ሰሎሞን ወለዶ ለምኒልክ ወለአርዳሚስ ፡ (ክብ ፡ ነገ)።
አርዳሚስ አርዴምስ ፡ አርጤምስ፤ ስመ ጣዖት
፡ (ስንክ ፡ ጥር፳፯። ግን፳፭። ሠኔ፬)።
አርዳኢ ፡ አርጂ፤ አርጅ፤ አስረጅ።
አርዳእ አርድአት ፡ ረዶች፤ ረዳቶች፤ አገልጋዮች፤ ተማሮች፤ ደቀ መዛሙርት፤ ምእመናን። ይቤልዎ አርዳኢሁ፤ ወይቤሎሙ ለቢጹ አርዳእ። ሰብዓ ወክልኤቱ አርድእት። ወተሰምዩ አርድእት ክርስቲያነ ፡ (ዮሐ፲፩ ፡ ፲፪
፡ ፲፮። ቅዳ። ግብ፲፩ ፡ ፳፮)። በአግብርት ፈንታ አርድእት ይላል፤ ስሕተት ነው። ወቀሪቦሙ አርዳኢሁ ለበዓለ ገራህት ፡ (ማቴ፲፫ ፡ ፳፯)።
አርድአ ፡ አረዳ፤ አማጠነ፤ ርዱኝ አለ፤ ረዳት ለመነ፤ ቡታ ሰደደ። ነሃቢ አርድአ ነሀብተ ብሩር
፡ (ስንክ ፡ ጥር፲፭)
፡ አስረዳ፤ ረዳት ሰጠ፤ ርዱ አለ፤ አስደራጊ።
፡ አረዳ፤ አስረዳ፤ ገልጦ ነገረ፤ አድራጊ። ጠየቀን ተመልከት።
አርገ ፡ ዐረገ ወጣ፤–ዐርገ።
አርገዘ ፡ (ዐማርኛ) አረገዘ፤ ተነፋ ዐበጠ፤ ተንዘረጠጠ።
አርገፀ ፡ (ዐማርኛ) አስረገጠ፤ መላልሶ ጠየቀ፤ ወይም ተናገረ፤ እውነቱን።
አርጋኖን ፡ (ጽር ኦርጋኖን። ዐረ አርቀኑን። ዕብ ዑጋብ) ኪታራ ሙዚቃ፤ የዘፈን የማሕሌት ዕቃ፤ መዝሙር በገና፤ ውዳሴ ምስጋና። መልካም ዜማ ለዦሮ ለልብ የሚጣፍጥ፤ ደስ የሚያሰኝ ድምጥ ፡ (፩ዜና ፡ ፮
፡ ፴፪)። አጽንዐ አውታረ አርጋኖን። አርጋኖን ወብዕዛ። አርጋኖነ ማርያም ድንግል ፡ (አዋል። ስንክ ፡ መስ፲፰። አርጋ ፡ ፩)።
አርግዐ ፡ አረጋ፤ አስረጋ፤ አጸና። አርጋዕከኒ ከመ ግብነት። የዐቍር ማየ በማሕፀን ወያረግዕ ከመ ይኩን ሥጋ። ናረግዖሙ ለማያት በውስተ ደመናት ወንፌኑ በረደ ወአስሐትያ ዲበ ምድር ፡ (ኢዮ፲ ፡ ፲። ቅዳ
፡ ግሩ። ቀሌ)።
አርጠበ ፡ አረጠበ፤ አስረጠበ፤ ርጥብ አደረገ። ኣረጥብ ዕፀ ይቡሰ
፡ (ሕዝ፲፯ ፡ ፳፬)።
አርጣባስ ፡ (ጽር አርታቢ) የርጥብ ሚዛን፤ የርጥብ መስፈሪያ፤ ለእኽልም ይኾናል፤ መስፈሪያነቱ ከአርደብ ጋራ ትክክል ነው፤ አርጣባስ ቅሉ አርደብ ከማለት የወጣ ስም ነው። ወያስተዋፅኡ ሎቱ ሲሳዮ ኵሎ አሚረ ስንዳሌ፤ ዕሥረ ወካዕበ በመስፈርተ አርጣባስ
፡ (ዳን፲፫ ፡ ፫)።
አርጤምስ ፡ (ጽር አርቴሚስ) ስመ ጣዖት፤ አርጤምስ በሚሏት በመልካም ሴት አምሳል የተሠራ የሴት ዐይነት ጣዖት። ስሙንና መልኩን ከሴቲቱ ወርሷል። ሰንበት ዕበያ ለአርጤምስ ፡ (ግብ፲፱ ፡ ፴፬ ፡ ፴፭)።
አርፈቀ ፡ አስቀመጣ፤ አስጠጋ፤ ስፍራ ሰጠ። አርፍቅዎሙ በበ ኀምሳ። ውስተ ሕፅኑ አንበረከ፤ ዲበ እንግድዓሁ አርፈቀከ።ያርፍቀነ ውስተ ሕፀኑ ለመርዓዊ ፡ (ሉቃ፱ ፡ ፲፬። ድጓ። መዋሥ)።
፡ አስረፈቀ፤ ዝም አሰኘ፤ አስታገሠ
፡ (ዐማርኛ) ምስጢሩ ከዚያው ይገባል።
አርፈደ ፡ በቁሙ፤ አረፈደ፤ አስረፈደ፤ አቈየ አዘገየ፤ ጊዜ አሳለፈ፤ ለወጠ፤ የጎሑን በጽባሕ የጽባሑን በነግህ የነግሁን በሠለስት። ፡ (ተረት) ገባያ ላርፋጅ ቤተ ክሲያን ለማላጅ። አልቦ ዘያመጽእ መብልዐ ድዉያን ውስተ መስኅንተ አኀው ኀበ ያበስሉ ሎሙ፤ አላ ይግበሩ ሎሙ ለድዉያን እንተ ባሕቲቶሙ፤ ወኢያርፍዱ ውሂቦቶሙ ለእለ ደወዩ ፡ (ሥር
፡ ጳኵ)። ፈረደንና ረደፈን እይ፤ የዚህ ጎሮች ናቸው።
አርፍአ ፡ አስፈወሰ አሳከመ፤ አሰፋ አስጠቀመ።
አሮድዮን [1] ፡ (ጽር ሄሮዲዎስ) ያሞራ ስም፤ ሽመላ፤ ሄሮድያኖስ
፡ (ዘሌ፲፩ ፡ ፲፱። ዘዳ፲፬ ፡ ፲፮)። አሮድዮን ሽመላ መባሉ በሽመላ ፈንታ ስለ ተጣፈ እንጂ ፍችው አይዶለም፤ መላሽ አበላሽቶታል፤ ሄሮድያኖስን ተመልከት።
[2] ፡ ዖፈ ያሬድ፤ በአምሳለ ዖፍ ታይቶ ዜማ ያስተማረው ምስጢር ያናገረው መልአክ፤ ወይም መንፈስ ቅዱስ፤ ስንክሳር ግን ፫ ወፎች ይላል
፡ (ግን ፡ ፲፩)። ስሙ ቅሉ ያሬድ የተባለ በአሮድዮን ነው ይባላል። ድምፁን እንደ ነሣ ስሙንም ነሥቷል። ዖፍ ዘይብልዎ አሮድዮን ከመ ቃለ ጠቢባን ይትፌሣሕ ወይትሐሠይ ሶበ ይትፈለጥ እምኀበ የኀድሩ ሰብአ ዓለም፤ ወየሐውር ኀበ መካነ በድው ወይነብር ውስቴቱ። ወተብህለ በእንተ ውእቱ ዖፍ ዘእሙር በክልኤ ሑረታት፤ ከመ ኵሉ ዘሰምዐ ቃናሁ ወንቃወ ዜማሁ ይትአሰር ድኅሬሁ በሑረቱ ውስተ ገዳም፤ እስከ ውእቱኒ እምጣዕመ ቃናሁ ይረስዕ ሕይወቶ ወይደክም ወይመውት ፡ (ማር ፡ ይሥ፳፰ ፡ ፫)።
አሮጸ ፡ አሮጠ፤ አስሮጠ፤ አስቸኰለ፤ አጣደፈ፤ ነዳ አባረረ። አሮጹ አፍራሴሆሙ። ያረውጾ ጋኔኑ። ያረውጾሙ ለሐንካሳን። ይትራድኡ ለአርውጾ ሐመር ፡ (፩ዕዝ ፡ ፪ ፡ ፴። ሉቃ፳፱። ቀሌ። መጽ
፡ ምስ)።
አቀመ ፡ (ቦአ፤ አብአ። ኖኀ አንኀ) አቆመ፤ አስቆመ፤ ተከለ፤ መሠረተ፤ አጸና፤ አስነሣ። አቀመኒ በእገርየ። ያቀውም ደብትራሁ። መኑ አቀሞሙ ለአድባር። ያቀውም ቃለ ገብሩ። አቅም ነቢያተ ለስምከ ፡ (ሕዝ፪ ፡ ፪። ኢሳ፲፬ ፡ ፳፭። ፵ ፡ ፲፫። ፵፬ ፡ ፳፮። ሢራ፴፮ ፡ ፳)። ቆመ ብሎ በአቆመ ፈንታ አቀመ ማለት የስሕተት ርባ ነው፤ ቦአና ኖኀ አብአ አንኀ ቢሉ፤ ወና አኀ ኹለት ዐመሎች ስላሉባቸው ነው። ቆመ ግን ከወ በቀር ሌላ ድርብ ዐመል የለውምና፤ አቆመ እንጂ አቀመ አያሰኝም። አቆመና ዐቀመ ይሞካከሻሉና በዚህ ምክንያት ተሳስቷል፤ ዐቀመን እይ።
፡ ገታ፤ መለሰ፤ ተወ። አዘዘ ያቅሙ ሠረገላሁ። አቅም እዴከ። ወአቀመት ወሊደ
፡ (ግብ፰ ፡ ፴፰። ፩ዜና
፡ ፳፩ ፡ ፲፭። ዘፍ፳፱ ፡ ፴፭)።
አቀበለ ፡ (አስደራጊ) አስቀበለ፤ አስጠ።
አቀደሰ ፡ አስቀደሰ፤ አስባረከ፤ አስመሰገነ።
አቀጸለ አስቀጸለ ፡ አስቀጠለ። አቀዳጀ፤ ጫነ አሸከመ፤ አስጌጠ ሸለመ። አክሊለ ትፍሥሕት ታስተቈጽለከ። ትገብር አክሊላተ ወታስተቄጽሎ ለዮሳዕ። አስተቀጸለ አረፍቶ በሜላትራ
፡ (ሢራ፮ ፡ ፴፩። ዘካ ፡ ፲፩። ፫ነገ ፡ ፮ ፡ ፱። ፯ ፡ ፵)።
አቍሰለ ፡ አቈሰለ፤ አስቈሰለ አሳዘነ። ነደፍዎ ወአቍሰልዎ። ትፍሥሕትከ ያቈስሎሙ ለጸላእትከ። አነ አቍሰልኩ ነፍስየ ፡ (፪ዜና
፡ ፳፪ ፡ ፭። ሢራ፲፪ ፡ ፰። ዮሴፍ)።
አቍለፈ ፡ አስቈለፈ፤ አስለበጠ። በአቅፈለ ፈንታ አቍለፈ ይላል
፡ (፫ነገ ፡ ፮ ፡ ፳፰)። አቍላፊሁ ወአቍፋሊሁ የሚሉት ልብ ወለድ ንባብ ከዚህ ወጥቷል
፡ (ማሕ ፡ ፫)። ፍችውም፤ መሳቢያው መለበቢያው፤ ትቱ ወንፊቱ ገመዱ ማለት ነው፤ ዝርዝሩ ዐራትን ያያል።
አቍላፍ ፡ ያልጋ ጠፍር፤–ቈሊፍ ቈለፈ፤ ቍልፍ።
አቍሳሊ መቍሰሊ ፡ (ሊት ልያን ያት) የሚያቈስል፤ የሚያስቈስል፤ አቍሳይ፤ አስቈሳይ፤ አሳዛኝ አስቀያሚ። ትካዝ መቍሰሌ ልብ ውእቱ በከመ ደዌ ያቈስል ሥጋ ፡ (ፈላስ)።
አቍረረ ፡ አቀዘቀዘ፤ አስቀዘቀዘ፤ አበረደ፤ አስበረደ፤ አስታገሠ። ሰትየ ማይ ያቈርር ላህበ ጽምእ። ዝናም ያቈርሮ ለመርቄ። አቍረረ ሙቀቶ። አቍርር መዐተከ ፡ (አፈ
፡ ተ፪። ሢራ፲፰ ፡ ፲፮። ፊልክ
፡ ፶። ዘፀ፴፪ ፡ ፲፪)።
፡ አቀረረ፤ ቀዳ፤ ጨመረ፤ አንቈረቈረ፤ ባፉ ወይም በሌላ። አቍረሩ ማየ በመንፌ ወኢቱክዕወ ማይ። ኢያቍርርሂ ወኢይክድን ቍርባኖ በኀብስት እቅድመ ሠርሖት
፡ (ገድ ፡ ዘሚ።ፍ ፡ ነ ፡ ፲፫)።
አቍጠጠ ፡ አቀጠነ፤ አመነመነ፤ አሰለሰለ። እመ አቍጠጠ ክሣዶ ከመ ሕልቅት
፡ (ኢሳ፶፰ ፡ ፭። ፊልክ)።
አቍጸለ ፡ አለመለመ፤ ዐደሰ አረጠበ፤ ዐጽቃም ቅጠላም አደረገ። ዐምደ ቤትየ ዘአቍጸልከ ፡ (ድጓ)።
አቍጸረ ፡ አስቈጠረ፤ አስቋጠረ። አስተነኰለ፤ አሳተ አባበለ፤ ሐሰት ሽንገላ አስተማረ። አቍጸሩ ሎቱ ዕደወ። ያቈጽሩ ሎቱ ሰማዕተ ሐሰት ፡ (ግብ፮ ፡ ፲፩። መጽ ፡ ምስ)።
አቃረየ [1] ፡ ሠዋ፤–ቀረየ።
[2] ፡ መሥዋዕት ሠዋ፤ አቀረበ፤ አምኃ ሰጠ። የእግዜርን ቃል ከነቢይ ከካህን ለመጠየቅ። ኢየአክል ሊባኖስ ለአንድዶ ወኵሉ እንስሳ ለአቃርዮ
፡ (ኢሳ፵ ፡ ፲፮)።
አቃኒ ፡ (ጽር አካን) የደጋ እሾኽ፤ እንቧይ ዝንኪላ፤ ኰሸሽላ። ባለብሉዮች ግን፤ ችፍርግ ቅርሽንባ ፡ (እንደኋኍላ) እንዳኍላ ይሉታል ፡ (፬ነገ ፡ ፲፬
፡ ፱)።
አቃኒም [1] ፡ አካላት፤–ቅኑም።
[2] ፡ አቃኒም፤ ፡ (ማት) አካላት፤ አካሎች፤ አካላቶች። አቃኒመ እግዚአብሔር እሙንቱ አስማት፤ ወአስማትሂ እሙንቱ አቃኒም፤ እስመ ትርጓሜሁ ለአቃኒም አካላት ጽኑዓን ቀዋምያን ፍጹማነ ገጽ ወመልክእ ብሂል ፡ (ሃይ ፡ አበ)።
አቃጥን ፡ ኵብኵባ፤–አጣቃን።
አቄአ ፡ አስተፋ። ኣቀይኣ እምአፋሃ ዘውኅጠት ፡ (ኤር፳፰ ፡ ፵፬)።
አቈቍዐ ፡ አንቋቋ፤ አቈሰለ፤ አከሳ፤ አደረቀ። እከየ ልቡ ያቌቍዕ አዕፅምቲሁ። ትጋሁ ለብዕል ያቌቍዕ አዕፅምተ ፡ (ሢራ፲፬ ፡ ፱። ፴፬ ፡ ፩)።
አቅሐመ ፡ አቅሐመ፤ አቃመ፤ አስቃመ። መጽሐፍ ግን አቅምሐ ይላል። ለአድግከሰ አቅምሖ። ዘከመ ያቀምሕ ብዕራይሁ። አቅምሐኒ ሐመደ ፡ (ሢራ፴ ፡ ፴፫። ፴፰ ፡ ፳፮። ሰቈ፫ ፡ ፲፮)።
አቅሐወ ፡ አነቃ፤ አተጋ፤ አበረታ፤ አፈካለረ።
አቅለለ ፡ አቀለለ፤ አስቀለለ፤ ከፈለ ቀነሰ አሳነሰ፤ ቀላል አደረገ። ከመ ያቅልል እዴሁ እምላዕሌክሙ። አቅለሉ ሐመሮሙ። ከመ ያቅልሉ ንስሓ ለእለ አበሱ። አቅልል ለነ እምነ ግብርናት። አቅለልኩ ዘንተ ምንዳቤ በእንተ ሥምረትከ ፡ (፩ነገ ፡ ፮ ፡ ፭። ዮና፩ ፡ ፭። ቀሌ። ፫ነገ ፡ ፲፪ ፡ ፬። ዮሴፍ)።
፡ አፈጠነ አቀለጠፈ፤ ፈጣን አደረገ። አቅለሉ ክነፊሆሙ
፡ (ቅዳ። ሳታት)።
፡ ናቀ፤ አቃለለ፤ ሰደበ አዋረደ፤ አኰሰሰ። ውሉድ እለ ያቀልሉ አበዊሆሙ። ዘያቀልል ማኅበረ ቤተ ክርስቲያን። ዘመሀረ አቅልሎ ቤተ ክር ፡ (ቀኖ ግንግ ፭ና ፡ ፲፮። ኒቅ ፡ ፳፱)። በአቅለለ ፈንታ አስተቃለለ ይላል፤ አድራጊውን ባደራራጊ፤ ስሕተት ነው። ያስተቃልሉ ተዋሕሶቶ። ታስተቃልልኑ ዘንተ ኀጢአቶሙ። እመ ቦ ዘያስተቃልል ምሥዋዐ። ኢታስተቃልሎ ለጸላኢከ ወበዝንቱ ትከውን ምዉአ ሎቱ ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፳፯። ሕዝ፰ ፡ ፲፯። ፈ ፡ መ ፡ ፳፱ ፡ ፬። ፈላስ)። የአቅለለ ፍች አቃለለ ማለት ስለ ኾነ፤ ግእዙን እንዳማርኛው አስኪዶታል፤ አስተቅለለ ቢል ግን አድራጊ ኹኖ በአቅለለ መንገድ ይኼዳል።
አቅለየ ፡ አጠለቀ፤ አስጠለቀ፤ ጥልቅ አደረገ፤ አስደረገ። አስወደደ፤ በውድ ሼጠ።
አቅሌለየ ፡ ጠየቀ ቈፈረ፤ አጥብቆ አጥልቆ መረመረ። ባለብሉዮች ግን አለዛዘበ ይሉታል። ነዳይ ማእምር ያቅሌልዮ ፡ (ምሳ፳፰ ፡ ፲፩)።
አቅሌስያ ፡ (ጽር ሄክሊሲያ) ቤተ ክርስቲያን፤ ጉባኤ ምእመናን
፡ (ድጓ)።
አቅማሕ ፡ (ሓት) ፍሬዎች፤ ቅንጣቶች፤ ቅመሞች፤ አዝርዕት አትክልት ዕፀዋት። አቅማሐ አዝርዕት። አቅማሐ አትክልት። አቅማሐ አፈዋት። ኵሉ አቅማሐ ገዳም። ትክሉ አቅማሓተ። አስተጋብእ ውስተ ልብየ አቅማሓተ ኵሉ ጥበብ
፡ (አርጋ። ዮኤ፩ ፡ ፲፪። ኤር፴፮ ፡ ፭። ደራሲ። ራእ፲፰ ፡ ፲፬)።
አቅሞንስ ፡ (ጽር ሄጉሜኖስ) አበ ማኅበር፤ ሊቀ ቀሳውስት። ኮሬ ኤጲስቆጶስ፤ ዘውእቱ አቅሞንስ
፡ (መጽ ፡ ምስ)።
አቅሠመ ፡ አስለቀመ ፣ አስቈረጠ። ወያቀሥሞሙ ቀሥሞ ፡ (፩ነገ ፡ ፰ ፡ ፲፪)።
አቅሰመ አስተቅሰመ ፡ አስሟረተ፤ አስጠነቈለ፤ መላ አስመታ፤ ጨሌ ጠጠር አስጣለ።
አቅሰሰ ፡ አቀሰሰ፤ አስቀሰሰ፤ ቅስና ሾመ፤ አሾመ፤ ቄስ አደረገ፤ አስደረገ።
አቅሠፈ ፡ አስቀሠፈ፤ አስገፈፈ፤ አስገረፈ፤ አስቀጣ።
አቅሳሚ መቅሰሚ ፡ አስጠንቋይ፤ ጠንቋይ ጠያቂ።
አቅረነ ፡ አቀረና፤ ቀንድ አስመሰለ፤ ቀንዳም አደረገ፤ አስወጋ።
አቅረየ ፡ አስሟረተ፤ ጋኔን አስጠራ፤ አስማት፤ አስደገመ።
አቅረፀ ፡ አስቈረጠ፤ አስቀረጠ፤ ቀረጥ አሰጠ አስቀበለ። አቀረጠ፤ ቀረጥ ሰጠ።
አቅረበ ፡ (ያቀርብ፤ ያቄርብ) አቀረበ፤ አስቀረበ፤ አስጠጋ፤ አሳጠረ። አቅርቦ መሥዋዕት። ናቄርብ ለከ ዘንተ ኅብስተ ወዘንተ ጽዋዐ። አቅረቡ ሎቱ አምኃሁ። ጠይቅ ኵሎ ዘአቅረቡ ለከ። አቅረብክዎሙ ለቤተ እስራኤል ኀቤየ። ወአቅረብኪ መዋዕለኪ ፡ (አፈ ፡ ድ፲፬። ኩፋ
፡ ፵፪። ሢራ፴፩ ፡ ፲፭። ኤር፲፫ ፡ ፲፩። ሕዝ፳፪ ፡ ፬)።
፡ ማቍረብ፤ ቍርባን መስጠት፤ ማቀበል። ኢታቅርብዎሙ። ወያቅርብዎ ቍርባነ ፡ (ቀሌ። ፈ ፡ መ ፡ ፬ ፡ ፪)። በአቅረበ ፈንታ አስተቅረበ ይላል፤ አንድ ወገን ነው። ዘጠቢብ በርእሱ ያስተቄርብ ርእሶ ፡ (ሢራ፳ ፡ ፲፫)።
አቅራብ ፡ ጊንጥ፤–ዐቅራብ።
አቅበረ ፡ አስቀበረ። ታቅብሩኒ በድንየ ፡ (ዘፍ፳፫ ፡ ፰)።
፡ አቀበረ፤ አቄመ፤ ለገመ፤ የቍስል
፡ (ዐማርኛ)። ኵሕስን ተመልከት።
አቅበጸ ፡ አቀበጠ፤ አቅበጠበጠ፤ አስቀበጠ። አሳጣ ነሣ፤ ተስፋ አስቈረጠ። አቅበጸኪ እግዚአብሔር ተስፋኪ። ዘኢያቅበጸከ ተስፋከ ፡ (ኤር፪
፡ ፴፮። ስንክ
፡ ሐም፭)።
አቅብዐ ፡ አስቀባ፤ አስለቀስቀ።
አቅተለ ፡ አስገደለ፤ አስፈጀ። በአቅትሎትከ ጽኑዓኒነ ፡ (ዮሴፍ)።
አቅተወ ፡ አስገበረ፤ ገባር አደረገ፤ አስጨነቀ። አቈታቸ፤ አወራረደ፤ ቍትቻ አስከፈለ። ሜጡ በትረ እለ ይትፈደዩ ወዐለውዎሙ ለእለ ያቀትዉ። እፎ ተስዕረ ዘያቀቱ። አልቦ ምንትኒ ዘያቀትውዎ፤ አስገበረ ፡ (ኢሳ፱ ፡ ፬። ፲፬ ፡ ፬። ዘዳ፳፬ ፡ ፭)።
አቅነተ ፡ አስቀነተ፤ አስታጠቀ፤ አሰለፈ። ባዕድ ያቀንተከ። አቀንተክሙ ብልባሌ። ዘያቀንቶ ለሰማይ በደመና ፡ (ዮሐ፳፩ ፡ ፲፰። ዓሞ፰ ፡ ፲። መዋሥ)።
አቅነየ ፡ አስገዛ። አቅነይክሙ ርእሰክሙ ለኀጢአት ፡ (ሮሜ፮ ፡ ፲፱። ፩ቆሮ ፡ ፱ ፡ ፲፱። ፪ቆሮ ፡ ፬ ፡ ፭)።
አቅነጸ ፡ አዘለለ፤ አስፈነጨ አቀናጣ። ፍቅር እንተ አቅነጸቶ እምዲበ ሐመር ፡ (መጽ ፡ ምስ)።
አቅንአ ፡ አቀና፤ አመራ፤ አስቀና፤ ቅናት አስነሣ፤ አሳደረ። ሑር ወልድየ ወአቅንእ ሀገረ። ወያቀኑ ለሐዊር መንገሌሆን። ኢያቅንእከ ብዕሎሙ ለኃጥኣን። ኢትትናገር ምስለ ብእሲት በዘታቀንኣ ፡ (ዜና ፡ ወግ። ማር ፡ ይሥ፬ ፡ ፭። ሢራ፱ ፡ ፩። ፴፯ ፡ ፲፩)።
አቅየሐይሐ ፡ (የቄሐና የአቄሐ ድርብ) ቀላ፤ ተቅላላ፤ ቀያቀይ ኾነ፤ ወደ ቀይነት ተለወጠ። ያቅየሐይሕ ሰማይ። ሕብር እንተ ታቅየሐይሕ
፡ (ማቴ፲፮ ፡ ፪። ዘሌ፲፫ ፡ ፳፬ ፡ ፵፱)።
፡ አቀላ
፤ አቅላላ
፤ ቀይ
ቀያይ ቀያቀይ
አደረገ ፤ ቀይ ቀለም ቀባ። አቅየሐይሐ
ሕብሮ (ጥበ፲፫ ፡ ፲፬)።
አቅደመ ፡ አስቀደመ፤ በፊት አደረገ፤ ዠመረ። አቅድሙኬ ምጽዋተ ከመ ይኩንክሙ ሥንቀ። በከመ አቅደምኩ ነጊረ። አቅደመ ስምዐ ከዊነ ፡ (ቀሌ። ቄር ፡ ጰላ። ድጓ)።
አቅደወ ፡ አሳመረ፤ አስጌጠ፤ አከበረ፤ አላቀ አበለጠ። ለህላዌ ሰብእ ያቀድዋ በርእሱ ወይሬስያ ሱታፌ መለኮት
፡ (ቄር ፡ ጰላ)።
አቅዲሙ ፡ አስቀድሞ፤ ፊት፤ መዠመሪያ። አቅዲሙ ነገረ ሙሴ በኦሪት
፡ (ድጓ)።
አቅዳሕ ፡ (ሓት) ኵባዮች፤ ብርጭቆች፤ ሽጕጦች። ይስተዩ ሠለስተ አቅዳሐ ወይን። ወይሰተይ ሠለስተ አቅዳሐ በበዓላተ እግዚእነ ባሕቲቱ ፡ (ፊልክ
፡ ፸፱። ቄድር)።
አቅድሐ ፡ አስቀዳ፤ አስገለበጠ። አተኰሰ አወዛ አላበ፤ አስቀመጠ።
አቅጠነ ፡ አቀጠነ፤ አስቀጠነ፤ ቀጭን አደረገ፤ አስደረገ፤ አረቀቀ። ያቀጥኖ ለልብ
፡ (ማር ፡ ይሥ፲፭ ፡ ፩)።
አቅጣኒ መቅጠኒ ፡ የሚያቀጥን የሚያስቀጥን፤ አቅጣኝ አስቀጣኝ። ፡ (ተረት) አፍጣኝና አቅጣኝ ከመዳሮ እንገናኝ።
አቅጸረ ፡ አስቀጠረ፤ ቅጥር አሠራ አስከበበ።
አቅጽዐ ፡ አስቀጨ፤ አስቀጣ፤ አስጐበጠ።
አቅፈለ ፡ አስለበጠ፤ አስለበሰ። እሌኒ አቅፈለት
፡ (መስቀለ) በወርቅ ወበዕንቍ ክቡር ፡ (ድጓ)።
አቆመ ፡ (ሖረ አሖረ፤ አኖመ፤ አዖቀ፤ አሮጸ) በቁሙ፤ እውነተኛው ጥርጊያ ይህ ነው።
አበ ላሕም ፡ አቢ ላም ፥ ዘላን ባለብዙ ላም፤ የላሞች ሐፃኒ መጋቢ። ወይም የላም ጌታ ፥ የከብት በሽታ።
አበ ምኔት ፡ የገዳም አባት፤ ባለገዳም።
አበ ደም ፡ ደመኛ ባለደም ደም አፍሳሽ ወይም የፙች ወገን ደም ፈላጊ። አድኅንኒ እምአበ ደም
፡ (ደራሲ)።
አበ ጉንባሕ ፡ (ትግሪኛ አባ ጉንባሕ) ርኩም፤ ጐንባሳ፤ የጩኸት ባለቤት። ጉንባሕን እይ። አበ ጉንባሕ ወከራድዮን ፡ (ዘዳ፲፬ ፡ ፲፰)።
(ጥ) አበለ [1]:-አሰኘ፤–ብህለ ፡ አብሀለ።
[2]:-በቁሙ ፥ ዐማርኛ፤–ሐቢል ሐብለ።
አበሞ አበሜ ፡ (ጽር አሞሞን። ዕብ ቂዳ) ሽቱ፤ የሽቱ ስም፤ ቅመም፤ ቀረፋ፤ የጢስ ዕንጨት ቅጠላም ያይዶለ። ቀረፋ ኹለት ዐይነት ነው፤ ቅመምና ሽቱ የሚኾን
፡ (ራእ፲፰ ፡ ፲፫። ዘፀ፴፤ ፳፬። ሕዝ፳፯ ፡ ፲፱)። ቀንሞስን እይ፤ ከዚህ ጋር አንድ ነው።
አበሳ ፡ (ሳት) በቁሙ፤ ዕዳ በደል፤ ኀጢአት፤ ክሕደት። አልብየ አበሳ። አበሳ ዘኢኮነ ለሞት፤ እስመ ቦ አበሳ ዘለሞት። ኅድግ ለነ አበሳነ። ወዘይመስሎ ለዝንቱ እምአበሳት። ገባርያነ አበሳት
፡ (ኢዮ፴፬ ፡ ፮። ፩ዮሐ ፡ ፭
፡ ፲፮። ፈ ፡ መ ፡ ፮ ፡ ፩። ፍ ፡ ነ መቅ)።
አበርበረ ፡ አስበረበረ፤ አዘረፈ አሶረረ።
አበርባራ ፡ ዶቢ፤–በሪር
፡ አበርባራ፤ ዶቢ የሳማ ዐይነት ቅጠል፤ በድብድባ ቦታ የሚበቅል፤ እንደ በርበሬ የሚለበልብ የሚያነገበግብ፤ ተኳሳ ኰስኳሳ፤ ጭረቱ እንደ ናጫና እንደ ቃጫ ገመድ የሚኾን ፡ (አዋል)
አበርጊላ ፡ ገበጣ፤ የገበጣ ጨዎት
፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፵፫
፡ ፲፪)።
አበቀ ፡ ታመመ ተደወየ፤ ዐከከ፤ ነጣ ገረጣ፤ ቈሸሸ ተበላሸ። አበቅ ለበሰ፤ አበቅ መሰለ፤ ኾነ።
አበቀለ አስተበቀለ ፡ አስተበቀለ፤ አስበቀለ፤ በቀል አስመለሰ፤ እንዲበቀሉ አደረገ።
አበቅ [1] ፡ (ዕብ
፡ አባቅ) በቁሙ፤ ጸበል ትቢያ ዐቧራ፤ ቅንቅን፤ በነፋስ የሚበን ደቃቅ ነገር ኹሉ።
[2] ፡ አበቅ፤ ፡ (ዕብ ሻሐፍ። ጽር እብሶራን) ደዌ ሥጋ፤ ዕከክ፤ ፈረሳቤት እንዳበቅ የሚያለብስ አበቅ የሚመስል ፥ ሰውነት የሚፍቅ የሚያሰለስል። አበቅ እኩይ። ደዌ ሲሕ ወአበቅ። ኢዮብ አመ አኀዞ አበቅ። ኦ ፈታኔ ኢዮብ በደዌ ወአበቅ። ፡ (ዘዳ፳፰ ፡ ፳፯። መቃ። ስንክ ፡ መስ፩። ጥበ
፡ ጠቢ)።
አበቅቴ ፡ (ትያት። ጽር ሄፓክቴ) ጭማሪ ተውሳክ፤ የቍጥር ማማያ ማስተካከያ። ተረፈ ዓመት ፥ የቀመር ትራፊ፤ ትርፍ ፍድፋጅ። አበቅቴ ፀሓይ። አበቅቴ ወርኅ። አበቅትያት። ሠርዐ ሐሳበ አበቅቴ፤ ፡ (አቡሻ ፡ ፳፫። ፳፭። ፴፩። ስንክ ፡ ጥቅ፲፪)።
አበነ ፡ ደነገየ፤ ደንጊያ ኾነ፤ ወደ ደንጊያነት ተለወጠ፤ ደረቀ ከረረ ፈዘዘ።
አበወ ፡ (ገቢር) ቃለ መሐላ፤ ምጥንታም ይኾናል። አበውን አበውና ፥ መሐላ፤ በአበው ፥ ምጥንታ። ሌላውም ስም ኹሉ በመሐላ ጊዜ መድረሻው ግእዝ ሲኾንለት ፥ ወይም የግእዝ ወራሽ ሀ ሲገባበት እንደዚህ ይፈታል። ጊዮርጊስሀ ማርያምሃ፤ የመሰለው ኹሉ።
አበው ፡ ዝኒ ከማሁ፤ አባቶችነት ፥ ከዊነ አበው። ኢይኩን ሎሙ ላዕሌሁ ማዕርገ አበውና
፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፲ ፡ ፮)።
አበውና ፡ ዝኒ ከማሁ፤ አባቶችነት ፥ ከዊነ አበው። ኢይኩን ሎሙ ላዕሌሁ ማዕርገ አበውና
፡ (ፍ ፡ ነ
፡ ፲ ፡ ፮)።
አበየነ ፡ አስበየነ አስፈረደ፤ አስለየ። አስረዳ፤ አስታወቀ። ንፈቅድ ከመ ታበይን ለነ ስምዓታተ። ያቤይን ሎሙ ክሕደቶ። ከመ ታበይን ዐመፃየ አበይኖት(ፊልክ ፡ ፫። ስንክ ፡ ሠኔ፮። ዮሴፍ። ገድ ፡ አዳ)።
አበደን ፡ (ዐረብ) ግሙራ፤ መቼም መች፤ ፈጽሞ ጭራሽ።
አበድበደ ፡ አዛገ አሳደፈ፤ ገደለ ቀሠፈ።
አበድቢድ [1] ፡ (ድት ዳን ዳት) እብድ ሞኝ፤ ሰነፍ አላዋቂ፤ ዕውቀቱ ትምርቱ ያጠረ፤ ወደ ስንፍና የሚያደላ፤ ጥበብና ምስጢር የማይገባው የማይሰማማው።
፡ ከሰነፍ ሰው አፍ የሚወጣ ተርታ ነገር ዐልጫ ቃል ጣዕምና ምስጢር የሌለው። ወበአበድቢዳት ቃላት ይትቃሐዉ
፡ (ቄር ፡ ጰላ፩)። መምህራን ግን የበድበደ ዘር አድርገው ፍችውን የሚያዝግ ይሉታል፤ ስሕተት ነው።
[2] ፡ አበድቢድ፤–ሞኝ ሰነፍ፤–አቢድ አበደ።
አበገደ ፡ (ዐረ አብጀድ) የፊደላተ ሴም የ፳፪ቱ አሌፋት ስምና አርእስት የግእዝና የዕብራይስጥ የሱርስት የዐረብ ሥርና ምንጭ ዘሩን እንደዚህ መጽሐፍ አካኼድ በአልፍ ዠምሮ በታው የሚጨርስ። ፪ኛም የግእዙ ተራ ሳይፋለስ ከካዕብ እስከ ሳብዕ ያሉት ፮ ፮ቱ እየተዛነቁ ሲጣፉ ስሙ አቡጊዳ ይባላል። ፡ (ተረት) አቡጊዳ የተማሪ ዕዳ።
አበጠ ፡ ሳበ ጐተተ፤–ዐበጠ።
አቡ ሻህር ፡ (ዐረብ) ታላቅ ስመ ጥር የቍጥር መጽሐፍ ብዙ ወግ ታሪክ ያለበት። አበ ወርኅ በዓለ ወርኅ፤ የጨረቃ ቍጥር ባለቤት። መጽሐፉ የጸሓፊውን ቃል ስለ ያዘ በጸሓፊው ስም ይጠራል።
አቡ ፈረጅ ፡ (ዐረብ) የመጽሐፍ ስም፤ ባለጸጋ ሀብታም ዕድላም፤ በተገናኝ ፬ቱን ፈርጅ ወንጌል እንደ ኩታ ገጥሞና አያይዞ የሚፈታ ፥ ዘርፍና ቅጽሉን የሚቋጭ ፥ ዐይነ ምስጢሩን የሚገልጥ የሚያቍለጨልጭ ሊቅ መተርጕም።
አቡሻህር ፡ መጽሐፍ፤–አብ ፥ አቡ ሻህር።
አቡቀለምሲስ [1] ፡ (ጽር አፖካሊፕሲስ) መጽሐፍ የመጽሐፍ ስም። ቃሉ ኹለት ነው፤ ቅጽልና ባለቤት። አፖ ሩቅ ረቂቅ ስውር ድብቅ ኅቡእ ክቡት፤ ካሊፕሲስ ራእይ ትንቢት። ራእየ ዮሐንስ አቡቀለምሲስ። ዮሐንስ ጸሐፈ ወንጌለ ወአቡቀለምሲስ ዘርእየ ውስተ ደሴተ ፍጥሞ
፡ (ስንክ ፡ ታኅ፩። ጥር፬)። እንዳረቡ ቃል በአብ ዘይቤ ሲፈታ ግን ለባለመጽሐፉ ስምና ቅጽል ይኾናል።
[2] ፡ አበ ራእይ፤ አበ ትንቢት፤ የሕልም ጌታ የራእይ ባለቤት፤ በዓለ ራእይ። ዮሐንስ ቴዎሎጎስ ዮሐንስ አቡቀለምሲስ ዮሐንስ ዘረፈቀ ውስተ ሕፅኑ ለኢየሱስ። ወንጌለ መለኮት ሰበከ ስምዐ ጽድቅ ኮንከ ወበእንተ ዝ አቡቀለምሲስ ተሰመይከ
፡ (ድጓ)።
አቡን [1] ፡ (ዐማርኛ) የቤተ ክሲያን አባት ፥ ጳጳስ ኤጴስቆጶስ፤ ምእመናን አባታችን ብለው የሚጠሩትና የሚያከብሩት አቦ አቦ የሚሉት። ፡ (ተረት) ያቡን የጨጌ ከብት በየወገኑ ይከተት። ከመ ዝ ይቤሉ አቡን
፡ (ታሪክ ፡ ጐንደር)።
[2] ፡ የድጓ መዝሙር ሰንበት ነክ ያይዶለ ሌጣ የዘወትር። መሪውን ባምጃር ተመሪውን ባቡን ሲመስሉት መተባበሩ እንደ ጌሾና እንደ ብቅል ኹኖ ሺሕ ፯፻ ዓመት ሆድ ያባውን የግብጦችን ምስጢር ያወጣዋል። ፡ (ታሪከኛ ግጥም) በከሣቴ ብርሃን ሰላማ አንጻር ብርሃነ አዜብ ከተባለው ከካልእ ሰላማ ዠምሮ ፥ በሰላማና በሰላማ በ፪ቱ የቀናች ሃይማኖት፤ ኋላ በሣልስ ሰላማ በቀን ጨለማ ትጠፋለች ትለወጣለች ተብሎ ቃል በቃል ሲነገር የመጣውን ንግርና ትንቢት ለመፈጻም፤ ፫ኛው ሰላማ ደጃች ውቤንና ራስ ዐሊን ካዋጋ በኋላ ፥ ሣልሳይነቱን ቀዳማይ ትንቢት እየመራው ፥ ከፋሲል ከተማ ጐንደር ገብቶ በተንቤኖች ቋንቋ ፥ አፉን ባልፈታ አምጃር ባስተርጓሚ ፥ የመናፍቃንን ትፋትና ቅርሻት ማር እያስመሰለ መንፈስ ቅዱስን ዐሎ ብሎ ፥ ፩ ባሕርይ ወልድ ቅብ ፥ በሰውነቱ አምላክ እያለ ለውጦ ገልብጦ ስለ ሰበከ ፥ ወደ ሺዋም የግዝት ወረቀት ስለ ላከ ፥ በዚህ ምክንያት ፥ የሺዎች አፈ ጉባኤ አለቃ ዐሥራት ከሣህለ ሥላሴ ተልከው ፥ ፬፻ ሰው አስከትለው እስከ ጐንደር ወርደው ፥ በሃይማኖት ዜማ ፥ በሥግው ቃል ትምርት አምላክ ወሰብእ መንፈስ ቅዱስ ቅብዕ በማለት ከጐንደር ሊቃውንት ተስማምተው ፥ አቡኑንም ድርስ ቍርጥ ባለው አነጋገር ፥ በክርክር ቃኝተው ወደ ትግሬ መርተው ሲመለሱ ያንኮበሩ ደብተራ ጕልቴ የገጠመው። እንዳሥራት ማን አለ የሚያውቀው ድጓውን፤ ትግሬ መርቶት መጣ ያን ረዥም አቡን።
[3] ፡ ጳጳስ፤–አብ።
አቢል ሎት ፡ (አበለ የአብል ይእብል። ዕብ አቤር፤ አጸና) መጽናት መበርታት፤ ማደግ እየጨመሩ መኼድ።
አቢሳ [1] ፡ (ዕብ አቢሻይ) አበ ጋዳ በዓለ ጋዳ እጅ መንሻ የሚሰጥ ወይም የሚቀበል።
[2] ፡ በዓለ ጋዳ፤–አቢብ አብ።
አቢስ ፡ (አቢሲን ፥ አቢሲኔ ፥ አቢሲኒያ) ስመ ነገድ ፥ የኵሽ ልጅ የሳባ ሳብዓይ የናምሩድ ተከታይ። ፪ኛ ስሙ ከለው ይባላል፤ ፪ቱም በታሪክ እንጂ በቅዱስ መጽሐፍ አይገኙም። የሳባ ክፍል ሳባ እንደ ተባለች የአቢስም ክፍል አቢሲንያ ተብላለች። አቢሲን ፥ አቢሳውያን፤ አቢሲኔ ፥ አቢሳዊ፤ አቢሲኒያ ፥ ሀገረ አቢስ ማለት ነው፤ እስክንድርያ እንደ ማለት። ስምነቱም ከዛፍና ከተክል የወጣ ገነታዊ ስም ነው። ቢሲን ቢሲና የሚባል ፍሬው የወይን ፍሬ የሚያካክል ጥሩ ተክል አለ፤ ሕብሩ እጅግ ፍጹም ቍጥር እጅግ ፍጹም ቀይ ሳይኾን ደበብ ያለ ማእከላዊ ነው፤ ጣዕሙና መልኩ ደም ግባቱ ከመዐዛው ጋራ ደስ ያሰኛል። አቢሲንም ማለት እንደ ቢሲን ፍሬ የሚያምር የቢሲና ፍሬ የሚመስል ማእከላዊ ሕብር ያለው ጥሩ ደመ ግቡ ማለት ነው። ስኒጋል የሚባለው ነገድ የሱዳን ቍራጭ እንደ ኾነ ፥ መደገዝካርም የአቢስ ቍራጭ ነው ይባላል፤ ይኸውም በቅርጹና በመልክአ ገጹ ይታወቃል
፡ (ጽርኣዊ ፡ ታሪክ)።
አቢብ [1] ፡ (ዐረብ። ቅብጥ ኤፒፕ) የግብጻውያን ወር ሐምሌ የመስከረም ፲፩ኛ
፡ (አቡሻ)።
[2] ፡ አቢብ፤
፡ (ዕብራ) መፀው፤ ዘመነ መፀው ከክረምት ቀጥሎ የሚብት፤ የጽጌ የፍሬ የልምላሜ ወራት፤ በዓለ ፋሲካ የሚውልበት ወርኀ ትፍሥሕት ወርኀ ተሐድሶ። ይኸውም ሚያዝያ ነው
፡ (ዘፀ፳፫ ፡ ፲፭)።
[3] ፡ አቢብ፤ የሰው ስም፤ በትንቢትና በምሳሌ ቡላ ለሚባል መነኵሴ ከግዜር የተሰጠ፤ ብዙኀ ዐጽቅ መፍርየ ጽድቅ። ተዘኪረከ ክርስቶስ ሥቃያተ አቢብ ገብርከ
፡ (ነግሥ። ስንክ ፡ ጥቅ፳፭)።
አቢብ ቦት ፡ (ጥ አበ የአብብ ይእብብ) ማበብ ማፍራት፤ የዕፀዋት። አበባ መልበስ መቀዳጀት፤ የመርዓዊና የመርዓት። አባት መኾን ዘር መስጠት፤ ወልዶ ማሶለድ፤ የወንድ የተባት።
አቢት ቶት ፡ (አበተ የአብት ይእብት) ማበት ሸብ ማድረግ፤ ወይም መማገር አጥብቆ ማሰር፤ አብታረግ እንዲሉ፤ ኹሉም ዐማርኛ ነው።
አቢድ ዶት ፡ (አብደ የአብድ ይእበድ። ዕብ አባድ) ማበድ፤ መቈጣት፤ አእመሮ ማጣት ፥ መወግሸት መነሣሣት ፥ አፈፍ አፈፍ ወፈፍ ወፈፍ ማለት ፥ መስነፍ፤ ሞኝ አላዋቂ መኾን፤ መጥፋት መበላሸት ፥ የልብ የናላ። ተአብዲኑ። ተአብድኑ ጳውሎስ። ወአብደ መራዕይ። የአብዱ ኵሎሙ እለ ነሰኮሙ ኅቡረ ምስሌሁ፤ በቁሙ
፡ (ግብ ፲፪ ፡ ፲፭። ፳፮
፡ ፳፬። ማር፭ ፡ ፲፫። ዲድ ፡ ፮)። ወእንዘ ይፈቅዱ ይጥብቡ አብዱ። እስመ አብዱ ኖሎት። ኢየአብድ እምኔክሙ፤ ሰነፈ ፡ (ሮሜ፩ ፡ ፳፪። ኤር ፲ ፡ ፳፩። ኢዮ፲፫ ፡ ፪)።
(ጥላ) አባ አብ [1] ፡ (ብ አበው) ወላጅ አባት ፥ ወንድ ተባት በዘር በሩካቤ የሚወልድና የሚያሶልድ። አክብር አባከ ወእመከ እስመ እሙንቱ ምክንያተ ፍጥረትከ
፡ (ዲድ)።
[2] ፡ አባ፤ አብ፤ የግብርና የክብር የማዕርግ ስም። አባት መባል በብዙ ወገን ስለ ኾነ ፥ ከግዜር ዠምሮ ያባትነት ሥራ ለሚሠሩ ለመንፈሳውያን አባቶች ፥ ለቄስ ለመነኵሴ ለአእሩግና ለሊቃውንት ለመምህራን ኹሉ ይነገራል። አቡነ ዘበሰማያት ኢታብአነ ውስተ መንሱት። ትእዛዘ አበዊነ ሐዋርያት። ብፁዕ አባ አቡነ ተክለ ሃይማኖት፤ የመሰለው ኹሉ ፥ ፡ (ቅዳ ፡ ድጓ)።
አባሕረረ ፡ አባነነ አስደነበረ፤ ከባሕር አገባ አሰጠመ። እንበለ ያደንግፆ ሞት ወኢያባሕርሮ ፡ (ስንክ ፡ ኅዳ፪። ጥር፳፩። ማቴ፰
፡ ፴፪)።
አባል ፡ (ላት። ዕብ ኤቤር፤ ኤባር፤ ብ ኤባሪም) ብልት የገላ ክፍል፤ በየስሙና በያንጻሩ እኩያ አምሳያ ያለው፤ ከራስ ጠጕር እስከ እግር ጥፍር በየክፍሉና በያንዳንዱ በየማውዱ ያለ ሥጋ፤ ሕዋስ ፥ አካል ገላ። አከለንና ሌለየን ተመልከት፤ የዚህ ጎር ነው። ከመ አባል ውስተ መቅፁት። መተሮ ለበግዕ በበ አባላቱ። እንዘ ንስቲት አባል አንቲ። ወተዐጽፈ አባለ ፥ መንፈስ ረቂቅ። ለእመ ሐመ አሐዱ አባል የሐምም ምስሌሁ ኵሉ ነፍስትነ። ዘፈወሰ አባለ ሙሱነ። አባለ ዘርዕ። ኢይኩን ዕሩቀ አባል ቅድመ መኑሂ። ብእሲት አባሉ ለብእሲ
፡ (ሚክ፫ ፡ ፫። ዘሌ፰ ፡ ፳። ቅዳ
፡ ሕር። ዮሐ። ፩ቆሮ ፡ ፲፪ ፡ ፳፮። ዲድ ፡ ፳፭። ፊልክ ፡ ፯። ፈ ፡ መ ፡ ፴፪ ፡ ፫። ዲድ ፲)። አባሎ የሚሉት ብርቱ የቈላ ዕንጨት ስሙ ከዚህ የወጣ ነው።
አባሲ ፡ (ሲት ስያት ያት) የሚያብስ የሚበድል፤ በዳይ በደለኛ፤ ያዋቂ አጥፊ፤ ደፋር፤ ጥጋበኛ። ኃጥእ ወአባሲ። አባሲ ዝንቱ ሕዝብ አበሳ ዐቢየ ፡ (አርጋ። ዘፀ፴፪ ፡ ፴፩)።
(ጥ) አባስ ፡ (ሱርስት) መምህር፤ አበ ማኅበር፤ አበ ምኔት ፥ የገዳም አባት ፡ (ሥር ጳኵ)። አባስ ካህነ ሮሜ ፡ (ታምረ ፡ ማር)።
አባረከ ፡ አስባረከ አስመረቀ፤ አስመሰገነ ቡሩክ አሰኘ።
አባር ፡ ድርቅ፤–ዐቢር
አባበለ ፡ ቀላቀለ፤ ደባለቀ፤ ዘባረቀ። በቁሙ አባበለ አሽበለበለ፤ አቈላመጠ። መጽሐፍ ግን በአ ፈንታ ሀ ይላል። ሀባባሊ ለዝሙት ፡ (ፈ ፡ መ ፡ ፳፬ ፡ ፩)።
አባት ፡ (ዕብ አቦት) አባቶች። አብ ሲበዛ አበው እንዳሰኘ ፥ አባም ሲበዛ በግድ አባት ያሰኛል፤ ባማርኛ ግን ውስጠ ብዙነቱ ሳይታወቅ ፥ ፩ መስሎ ፩ ተብሎ ስላንድ አካል ብቻ ይነገራል። አምላክ የመለክ ብዢ ሲኾን ስላንድ እንዲነገር ፥ ይህም እንደዚያ ነው፤ መለከን ተመልከት። ፡ (ሐተታ) አብ በጥሬነቱ ዘርፍ ይዞ ሲቀጸል ወይም በቂ ኹኖ እንደ ዘርፉ ስልት ሲፈታ ፥ ምስጢሩ ካባትነትና ከጌትነት ከባለቤትነት አይወጣም። አባም ባማርኛ ለሥጋዊ ሐርበኛ የፈረስ ስም ኹኖ ሲነገር እንደዚሁ ነው። አባ ጠቅል ብሎ ፥ የጠቅል ጌታ ወይም ባለቤት ያሰኛል። አብ የግእዝ የዐረብ የዕብራይስጥ፤ አባ የሱርስት ነው። አባ ገቢር ተገብሮ ይከታል ፥ ጕልት ቀለም ነው፤ አብም በገቢር ጊዜ አባ ይባላል። አክብር አባከ።
አባኢ መብእ ፡ (እት ኣን ኣት) የሚያገባ፤ አግቢ፤ መላሽ። ሰጭ አቅራቢ ፡ (ቅዳ ፡ ሕር)።
አባዕር ፡ በሮች፤ እንስሶች፤ ሞኞች አላዋቆች። አባዕር እለ ይወግኡ ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፵፯)።
(ላ) አባዊ [1] ፡ አበዋዊ፤
፡ (ዊት ውያን ያት) ወገን ቅጽል ወይም ሙሻዘር ውስጠ ዘ፤ ዘአበው እንተ አበው። በጽሐ ጊዜ ተራኅርኆ ሣህል አባዊት ላዕለ ልሕኵት አዳማዊት
፡ (ያዕ ፡ ዘእል። ገድ ፡ አዳ)። ተዓድዎ አበዋዊት ፡ (ማር
፡ ይሥ፳፪)።
[2] ፡ (ጥ) ስመ ፈለግ፤ ነጭ አባይና ጥቍር አባይ፤ ታላቅ ፈሳሽ ጐርፍ ማዕበል ማለት ነው። ተለይቶ ግን ለጥቍሩ አባይ ብቻ ሲነገር፤ አበ አፍላግ፤ በኵረ አፍላግ፤ ቀዳማይ ፈለግ ማለት ነው፤ አብ ከርሱ ለሚገቡ ለታናናሾቹ፤ በኵር ቀዳማይ ለወንድሞቹ ለሦስቱ ዐበይት አፍላጋት። ኤፌሶንንና ግዮንን ተመልከት። ፈለገ አባዊ
፡ (ታሪ ፡ ነገ)።
[3] ፡ የመነኵሴ ወገን
ረድ አመካሪ
ጥቍር ራስ ፤
ወንጌል በምናኔ
ወተት ላሳደጋት
ለወለተ እንጦንስ
ለምንኵስና የታጨ።
አባዪ ፡ (ዪት ይያን ያት) እንቢ ባይ፤ እንቢተኛ፤ ተጓዳጅ፤ አበያ።
አባዲ ፡ (ዲት ድያን ያት) የሚያብድ ፥ የሚሰንፍ፤ ሰናፊ ሰነፍ፤ አላዋቂ። ማርያም መጥበቢተ ዓለም አባዲ። ልቡ አባዲ
፡ (ደራሲ። ስንክ ፡ ታኅ፮)።
አባግዕ ፡ (ዕት ዓት) በቁሙ፤ በጎች፤ የበግ መንጎች ተባቱም እንስቱም፤ ወይም ተባቶች ብቻ። አባግዕ ወአጣሊ። አባግዕ ወአባግዕት ፡ (አዋል)። አባግዓት የብዙ ብዙ። አባግዕ አትቡዕ። አባግዕ አንስት። በግዕት አንስት እያለ ይጥፋል የተሳሳተ ነው ፡ (፪ዜና ፡ ፲፯ ፡ ፲፩። ዘኍ፯ ፡ ፲፯። ዘሌ፭ ፡ ፮)። ምእመናንም በኵራቸውና ኖላዊያቸው ሳይቀር በምሳሌ በጎች ይባላሉ ፡ (ዮሐ፩ ፡ ፳፱ ፡ ፴፮። ፲ ፡ ፯ ፡ ፰። ፳፩ ፡ ፲፯። ማቴ፲ ፡ ፮። ፲፭ ፡ ፳፬)። መላእክትም በኵራቸው ዳግማይ አዳም ስለ ኾነ እንደ ምእመናን በጎች ይባላሉ
፡ (ማቴ፲፰ ፡ ፲፪። ሉቃ፲፭ ፡ ፬)።
አቤል ፡ (ዕብ ሀቤል) የሰው ስም፤ ወልደ አዳም ፡ (ዘፍ፬ ፡ ፪)። አቤል መስክ ጨፌ፤ አልቃሽ። ሀቤል ከንቱ ብላሽ ማለት ነው።
አቤሜሌክ ፡ (ዕብ አቢሜሌኽ) አበ ንጉሥ፤ የንጉሥ አባት።
አቤሴሎም ፡ (ዕብ አብ ሻሎም) አበ ሰላም፤ በዓለ ሰላም፤ ሰላማዊ።
አቤተ ፡ ፥ አሳደረ፤ እስከ ነግህ አቈየ፤ አኖረ፤ አስጠጋ። ወኢያሠነዮ ማኅቶቶሙ ለአቢቶ። ወለብዙኃን ዕሩቃን አቤትዎሙ ዘእንበለ ልብስ። ወኢያቤተ ምንተኒ። ተኵላተ ዐረብ እለ ኢያበይቱ ለነግህ ፡ (፩ነገ ፡ ፫ ፡ ፫። ኢዮ፳፬ ፡ ፯። ሶፎ፫ ፡ ፫)።
አቤኔዜር ፡ (ዕብ ኤቤን ሃዓዜር) እብነ ረድኤት፤ የረድኤት ደንጊያ።
፡ (፩ነገ ፡ ፯ ፡ ፲፪)።
አቤዘወ ፡ አስቤዠ፤ ቤዛ አሰጠ፤ አስለወጠ፤ አስያዘ። ታቤዝዉ ምድረ ፡ (ዘሌ፳፭ ፡ ፳፬)።
አብ ፡ (ጥ) አብ፤
፡ (ዕብራ) የዕብራውያን ወር ነሐሴ የሚያዝያ ፭ኛ። በ፱ኛው ቀን ያውም በጨረቃ ቍጥር ፥ ፊተኛውና ኋላኛው ፪ቱ መቅደሶች በዘመን ሩጫ ተከታትለው የፈረሱበት የተቃጠሉበት ስለ ኾነ ፥ ዕለቱን ፳፬ ሰዓት ይጾሙታል፤ ወርኁኀም ወርኀ ምዝባሬ ይሉታል። መጥበቁም ስለ ደጊመ ቃል ነውና ፥ የደጊሙ ምስጢር ፪ቱን ምዝባሬ ያሳያል። አብ ዘውእቱ ወርኅ ኃምስ
፡ (ዮሴፍ)።
አብሐ [1] ፡ አሠለጠነ፤–በዊሕ ቦሐ።
[2] ፡ (ያበውሕ ያብሕ) አሠለጠነ፤ ፈቀደ አሰናበተ፤ ሾመ፤ ሥልጣን ሰጠ። ኢያብሖ አቡሁ። ወዘንተኒ እምገበርነ ሶበ ያበውሕ እግዚ። ንብብ ለእመ አብሑከ። ወአብሖሙ ላዕለ አጋንንት ፡ (ኩፋ
፡ ፴፩። ዕብ ፡ ፮ ፡ ፫። ሢራ፴፭ ፡ ፯። ማር ፡ ፮ ፡ ፯)።
አብሀለ ፡ አብሀለ፤ ፡ (ያብህል) አው አበለ ፡ (ያብል) አሰኘ፤ አናገረ ፡ (ማቴ፳፯ ፡ ፳። ግብ፭
፡ ፵)። ኦሆ በልኒ ወኦሆ አብሊዮ። ስእነ ኦሆ አብሎቶ። ኀለየ ከመ እሙ ኦሆ አበለቶ ለተወክፎ ትእዛዝ። አንጠይዎ ከመ ኦሆ ያብልዎ ፡ (አርጋ። ስንክ ፡ ታኅ፭። ዮሴፍ)።
አብሃሊ ፡ አብሃሊ፤ መብሃሊ፤ መብህል፤ የሚያሰኝ የሚያናግር፤ አሰኝ አናጋሪ።
አብሀመ ፡ አብሀመ፤ ድዳ አደረገ፤ አፍ አስያዘ፤ ዝም አሰኘ።
አብሃሚ መብህም ፡ ድዳ የሚያደርግ ፥ አፍ የሚዘጋ የሚለጕም።
አብሐተ ፡ አባተ፤ ሾመ አሠለጠነ። አሸነፈ ፥ በላይ ኾነ ፡ (ዐማርኛ)።
አብሕአ ፡ አቦካ፤ አስቦካ፤ በርሾ ለወሰ፤ አስለወሰ፤ አሖመጠጠ፤ ሖምጣጣ አደረገ፤ አስደረገ። አፍጥኒ ወአብሕኢ ሠለስተ መሣልሰ ወግበሪ ጻፍንተ ፡ (ዘፍ፲፰ ፡ ፮። ማቴ፲፫ ፡ ፴፫። ሉቃ፲፫ ፡ ፳፩)።
አብለለ ፡ ዝኒ ከማሁ አበለለ፤ ከንቱ አደረገ። በለለ ዐጕልና ገቢር ስለ ኾነ በበለለ ፈንታ አብለለ። እንደ ማለት ከዐወ ይላል፤ ስሕተት ነው ፡ (ዘፍ፲፩ ፡ ፯። ኩፋ ፡ ፲)።
አብለየ ፡ አስረጀ፤ አሳለፈ፤ አንቲካ አደረገ። አብለይከኒ ከመ ዝቅ። እፎ ትሬእያ ለዓለም ይቤ፤ እንዘ ታበሊ ነፍሳተ ወትሔድስ ሥጋተ ወታኀልፍ መዋዕላተ። ሐዳስ አብለየታ ለቀዳሚት ፡ (ኢዮ፲፫ ፡ ፳፰። ፈላስ ፡ ገ፷፯። ዕብ፰ ፡ ፲፫)።
አብላሊት [1] ፡ አለብላቢት፤–በሊል በለ።
[2] ፡ (ዐማርኛ) በቁሙ፤ ወይም አለብላቢት፤ ታናሽ ቅጠል ሐረጋም፤ እንደ ሳማና እንደ ዶቢ የምትለበልብ የምታንገበግብ። ሥርወ አብላሊት ፡ (መጽ ፡ ፈው። ትእ ፡ ጴጥ)።
አብላዪ መብለዪ ልይ ፡ ልይ፤ የሚያስረጅ፤ የሚያደገድግ፤ አሮጌ የሚያደርግ።
አብልኀ ፡ አበላ፤ አሰላ ኣሾለ፤ አፈጠነ፤ አስፈጠነ ብልኅ አደረገ። ኀጺን ለኀጺን ያበልኆ። አብልኀ ጸራቢ ኀጺነ። ያበልኅ መዐቶ ሰይፈ መታሬ። አብልኁ ልሳኖሙ። ፡ (ምሳ፳፯ ፡ ፲፯። ኢሳ፵፬ ፡ ፲፪። ዘካ፩ ፡ ፳፩። ጥበ፭ ፡ ፳፩። መዝ ፡ ፷፫)።
አብልዐ ፡ አበላ፤ አስበላ፤ አጐረሠ፤ አዋጠ አስዋጠ። ለእመ ርኅበ ጸላኢከ አብልዖ። አነ ኣበልዖሙ ጻዕረ። አብልዐኒያ ለይእቲ መጽሐፍ። ለእመ አብልዐ ገራህተ ሰብእ እንስሳሁ ፡ (ምሳ፳፭ ፡ ፳፩። ኤር፱ ፡ ፲፭። ሕዝ፫ ፡ ፪። ዘፀ፳፪ ፡ ፬)።
አብሰለ ፡ አበሰለ፤ አስበሰለ፤ ተኰሰ ጠበሰ። ያበስሉክሙ በጽህርት። ያበስሉ ሥጋ። ንጥፋሕ ግንፋለ ወናብስሎ በእሳት ፡ (ዓሞ፬ ፡ ፪። ፩ነገ ፡ ፪ ፡ ፲፫። ዘፍ፲፩ ፡ ፫)።
አብሰረ ፡ አበሠረ፤–በሠረ።
አብሠረ አስተብሠረ ፡ አስበሠረ፤ ደግ ወሬ አሰማ አስነገረ፤ ወሬኛ ላከ።
አብሲማዳኮስ
፡ (ጽርእ) ከኹለት አንድ የኾነ አምላክና ሰው ፩ አካል።
አብሳሊ መብሰሊ መበስል ፡ (ላን ላት) የሚያበስል አብሳይ፤ ጋጋሪ ቀቃይ፤ ሊጥ አፍሳሽ ወጭት ጠባሽ፤ ዐበዛ ወጥ ቤት። ሊቀ መበስላን። ለመበስላት። ወለኀባዝያት። ይቤሎ ለመበስል ፡ (ዘፍ፴፯ ፡ ፴፮። ፩ነገ ፡ ፰ ፡ ፲፫። ፱ ፡ ፳፫)።
አብሣሪ መስተብሥር ፡ የሚያስበሥር አስበሣሪ፤ ወሬ አስነጋሪ።
አብስሊዲስ ፡ (ጽር እብሳልቲስ) መዘምር ዘማሪ፤ አወዳሽ ደብተራ
፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፱)።
አብስልዋጥስ ፡ (ሮማይ ፡ አብሶሉቲዮኒስ) የፍታት ቃል የፍታት ሥርዐት ናዛዥ ለተናዛዥ የሚያሰማው ቃል፤ እፈትሐከ፤ ኩን ፍቱሐ፤ ፍትሐት ዘወልድ ፥ ይህን የመሰለ። የፍታት ዜማ ፥ ለሙታን የሚጸለይ ጸሎት፤ በግንዘት ያለ ቃል፤ ፍትሕት ወንጽሕተ ረስያ፤ የመሰለው ኹሉ። አብስልዋጥስ ይትበሀል በዜማ ግንዘት ፡ (ግንዘ)።
(ጥ) አብሶ ሶት ፡ (አበሰ ይኤብስ የአብስ። ዕብ አባስ) ማብላት ማጥገብ ፥ መቀለብ መመገብ ፥ ማሥባት ማወፈር፤ ከብትን ሰውነትን። ወይም በቁሙ ማበስ መጥረግ፤ አብዝቶ መብላት መጋፈፍ፤ እንደ እንስሳ መቀለብ፤ መሥባት መወፈር። ከዚህ የተነሣ ማበስ መበደል፤ ኀጢአት መሥራት፤ ዐውቆ ደፍሮ ኾነ ብሎ። አብሶ አበሰት። ኢይደግሙ አብሶ። ዘይገብር ኀጢአተ ይኤብስ ላዕለ ነፍሱ። ኢተአብስ በቃልከ። መላእክት አበሱ ምስለ አዋልደ ሰብእ። ዳዊት አመ አበሰ በብእሲተ ኦርዮ
፡ (ሰቈ፩ ፡ ፰። ሔኖ፭ ፡ ፰። ሢራ፲፱ ፡ ፬። ፴፭ ፡ ፲፪። ኩፋ ፡ ፬። ዲድ ፡ ፲)።
አብረቀ ፡ አበረቀ አባረቀ፤ አብረቀረቀ፤ መብረቅ ጣለ ወረወረ፤ አበራ ገለጠ፤ ብልጭ አደረገ። እግዚ አብረቀ መብረቀ። አብርቅ መባርቅቲከ። ፀሓየ ጽድቅ ዘሞኦ ለሞት ያበርቅ ጸዳሎ ላዕሌነ። አራዊት እለ እምውስተ ዐይኖሙ ፀዋገ ቀለምጺጸ ያበርቁ ፡ (፪ነገ ፡ ፳፪ ፡ ፲፭። መዝ
፡ ፻፲፫።አፈ ፡ ድ፬። ጥበ፲፩ ፡ ፲፱)።
አብረከ ፡ አበረከ አብረከረከ፤ አንበረከከ አሰገደ በጕልበት አቆመ፤ ራሱን ሰውነቱን ወይም ሌላውን። መጽሐፍ ግን በበረከና በአብረከ ቦታ፤ ይልቁንም በበረከ ፈንታ አስተብረከ ይላል፤ አያሰኝም። አስተብረከ በብረኪሁ ከመ ይስተይ። አስተብረከ ወአስተብቍዖ። ሰገደ ሎቱ ወአስተብረከ። አስተብርኮ እለ መነና ፡ (መላ፯ ፡ ፭። ማር፩ ፡ ፵። ቀሌ። ደራሲ)። ዳግመኛም በአብረከ ፈንታ አቤተ ይላል ስሕተት ነው ፡ (ዘፍ፳፬ ፡ ፲፩)።
አብረክሲስ ፡ (ዐረ አብርክሲስ። ጽር ፕራክሲስ) መጽሐፍ፤ የመጽሐፍ ስም፤ ግብረ ሐዋርያት፤ የሐዋርያት ሥራ፤ ዜና፤ ታሪክ። መጽሐፈ አብረክሲስ
፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፪)።
አብረደ ፡ አበረደ አስበረደ፤ አቀዘቀዘ፤ በረዶ አደረገ፤ አዘነመ። ዘእንበለ እሳት አንደደ ወዘእንበለ ማይ አብረደ ፡ (ቅዳ ፡ ግሩ)።
አብሪል ፡ (ሮማይ አፕሪል) የወር ስም ፥ ሚያዝያ።
አብሬክ ፡ (ዕብ አብሬኽ። ጽር ኪሪክስ) ትእዛዝ አንቀጽ፤ ብርክ አስተብርክ፤ ስግድ አምኅ፤ ግነይ ባርክ። ዮሴፍ በተሾመ ጊዜ ለሰብአ ግብጽ የተነገረ የፈርዖን ዐዋጅ ነው ፡ (ዘፍ፵፩ ፡ ፵፫)። ዳግመኛም ረበናት አብሬኽን አብ ራኽ ብለው ፪ ቃል አድርገው ይፈቱታል፤ አብ በቁሙ፤ ራኽ ለጋ ቀንበጥ ፎጠና ወጣት። ወጣት። አብ
የተባለ ዮሴፍ ነው ፤
ራኽ በተሾመ
ጊዜ የ፴
ዓመት ልጅ
ነበረና የድሜውን
ማነስ ፤ አብ
የአእምሮውን መጐልመስ
የሰውነቱን መሾምና
መንገሥ ፤ ለነፈርዖን
እንዳባት መኾኑን
ያሳያል ፤ ለወንድሞቹም
ለነሮቤል በመጋቢነቱ
እንደ ያዕቆብ
አባት ይባላል።
ረሰየኒ አበ
ለፈርዖን። ለደቂቀ
ያዕቆብ ወዮሴፍ
(ዘፍ፵፭ ፡
፰። መዝ፸፮)። የግእዝ
ኦሪት ግን
ወልዶ ይላል። አብሬኽንም
ኤር አብሬር ፤
ኤል አብሬል
ይላል። ባለብሉዮችም ፍችውን
ዐዋጅ ዐዋጅ
ገብር ኮነ
እግዚአ ፤ ባላገባቦችም
ይደልዎ ፤ ይበጅ
ያድርግ ይሉታል ፤
ኹሉም ስሕተት
ነው።
አብር ፡ (ብ አባር። ዐረ ኢብረት፤ ብ ኢባር) እሾኽ ቀጭን ሹል፤ መርፌ የሚመስል። ዕፀ ግረት እንዘ ቈጽለ ዕፁ አይትነገፍ ወአባሪሁኒ አይጸድፉ ፡ (መጽ ፡ ምስ)።
አብርሀ ፡ አበራ፤ አስበራ፤ አሳየ ገለጠ፤ አስረዳ። አንደዱ እሳተ ወአብርሁ። አብርሀ አዕይንትየ። አብርሃ ለጥበብ ከመ ጎሕ። እግዚ ያበርህ ሊተ ፡ (ዮዲ፲፫ ፡ ፲፫። ስንክ
፡ ነሐ፲፭። ሢራ፳፬ ፡ ፴፪። መዝ ፡ ፳፮። ዮሐ፩ ፡ ፭)።
አብሮጥስ ፡ (ጽር ፔሪዎዴፍቲስ) ታላቅ ቆሞስ የኤጲስቆጶስ ተከታይ
፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፭)።
አብቀወ [1] ፡ ከፈተ፤–በቂው በቀወ።
[2] ፡ ከፈተ፤ ለቀቀ። አስከፈተ፤ ክፈት አለ። አብቁ አፉከ ወብላዕ። ወመብዝኅቶሙ ኢክህሉ ያብቅዉ አፉሆሙ ለበሊዕ። አብቀዉ አፉሆሙ ላዕሌየ። ነዳይ ሶበ ይስእል ያበቁ አፉሁ እስከ እዘኒሁ። አብቀዉ ውስተ ነፋስ። አብቅዋ ለገዳም ፡ (ሕዝ፪ ፡ ፰። ዮሴፍ። መዝ
፡ ፳፩። ሢራ፳፩ ፡ ፭። ኤር፲፬ ፡ ፮። ሔኖ፲ ፡ ፬)።
አብቍልታ ፡ የሰው ስም፤ ሐረጉ ዐጽቁ። በዛቲ ዕለት ስምዐ ኮነ ብፁዕ አብቍልታ፤ ወኮነ እምዘመደ ክቡራን ዘሀገረ እንጽና ፡ (ስንክ ፡ ግን፳፬)።
አብቍልት ፡ (ታት) ሐረግ ዐጽቅ ለበቅ የማይሰበር፤ እንደ ሽቦ የሚተጣጠፍ። ፍትሓ ለመንፈስየ አቡየ አብቍልታ፤ በማእሰረ ጌጋይ አብቍልት ኢትንበር ሙቅሕታ።
አብቍዐ ፡ አበቃ አብቃቃ፤ አስበቃ አስጠቀመ።
አብቃው ፡ አፎች ላይኛውና ታችኛው ክፍል፤ ብቃውና አብቃው ከንፈር ከናፍር እንደ ማለት ነው። ትከሥት አብቃዊሁ ወታኬልሖ ፡ (ቅዳ ፡ አት)።
አብቈለ [1] ፡ አጸደቀ፤ ቡቃያ አወጣ፤ አቀጠለ፤ በራሱ በጐኑ። ለታብቍል ምድር ሐመልማለ ሣዕር። አብቈልኩ ሥርውየ። አብቍሉ ጽጌክሙ ከመ ጽጌ ረዳ። ዘኢያብቈለ ቀርነ ወጽፍረ ፡ (ዘፍ፩ ፡ ፲፩። ሢራ፳፬ ፡ ፲፪። ፴ ፡ ፲፬። መዝ ፡ ፷፰)።
[2] ፡ (አስደራጊ) አስበቀለ፤ እንዲያበቅል እንዲያጸድቅ አደረገ፤ ተክለ፤ ለይኩን በማለት ዝናምና ዘር በመስጠት፤ የፈጣሪና የቈፋሪ ፡ (ዘፍ፪ ፡ ፱። መዝ ፡ ፻፫)።ዘርዕ ዘያበቍል ፈጣሪከ። ኣበቍል ዖመ። ዕፅ ዘእግዚ አብቈለ። ይበልዕ ኵሎ ዕፀ ዘአብቈልክሙ ፡ (ሢራ፯ ፡ ፲፭። ኢሳ፵፩ ፡ ፲፰። ፵፬ ፡ ፲፬። ዘፀ፲ ፡ ፭)።
አብቅል ፡ (ልት) በቅሎች፤ አባቅልቶች አጋሰሶች። ፈነወ ዐሠርተ አብቅለ ፡ (ዘፍ፵፭ ፡ ፳፪)።
አብተከ ፡ አበተከ አብተከተከ፤ አስበተከ አስቈረጠ አስበጠሰ።
አብና ፡ አብነት፤ አባትነት፤ አባት መኾን። እስመ አብ ይሰመይ አበ በእንተ አብናሁ። ለአብ ቦቱ ስብሐት አብና
፡ (አፈ ፡ ድ፪። ሃይ ፡ አበ)።
አብኖስ ፡ (ዐረ አብኑስ። ጽር ሄቤኖስ) ዞጲ፤ ጥሩ ጠንካራ ዕንጨት፤ መልኩ ጥቍር ዋጋው ክቡር፤ በህንድና በሱዳን አገር በኢትዮጵያ የሚገኝ ፥ ከክቡርነቱም የተነሣ በሚዛን የሚሼጥ። ወገብረ መጥቅዐ እምዕፀወ አብኖስ ፡ (ቀሌ። ገድ ፡ አዳ)። ዞጲን ተመልከት።
አብአ ፡ አገባ፤ አስገባ፤ መለስ። አባእናሁ ውስተ ገነት። ኢታብእ ኵሎ ሰብአ ዘረከብከ ውስተ ቤትከ። ዘያወፅኦሙ ወዘያበውኦሙ። አብኦሙ ውስተ አእምሮ እግዚአብሔር ፡ (ኩፋ ፡ ፫። ሢራ፲፩ ፡ ፳፱። ዘኍ፳፯ ፡ ፲፯። ስንክ ፡ ግን፯)።
፡ ሰጠ፤ አቀረበ። እምከመ አባእኩ ለእግዚ። ካህን ዘያበውእ መሥዋዕተ። አነ አባእኩ ተዝካረ ስእለትክሙ ቅድሜሁ
፡ (ሢራ፯ ፡ ፱። ዘሌ፯ ፡ ፰። ጦቢ፲፪ ፡ ፲፪)።
አብዐለ ፡ አከበረ፤ አስከበረ፤ አበለጠገ፤ ሰውን ባዕል ዕለትን በዓል አደረገ። ቀሊል በኀበ እግዚ ያብዕሎ ለነዳይ። እድ ጽኑዕ ብእሴ ያብዕል። ቦ እለ ያብዕሉ ርእሶሙ ፡ (ሢራ፲፩ ፡ ፳፩። ምሳ፲ ፡ ፬። ፲፫ ፡ ፯)። ተጋብኡ አይሁድ ከመ ያብዕሉ፤ ወአብዐሉ ሰሙነ ዕለተ። ዕለት ዘያብዕሉ ቦቱ ትንሣኤ ቅድስተ። ባቲ ያብዕሉ ሮም በዓሎ ለእስጢፋኖስ። ተዝካረ ዕረፍቱ ያብዕሉ ሶርያ ፡ (ዮሴፍ። አቡሻ ፡ ፵። ስንክ ፡ መስ፲፪። ጥር፲፭)። በአብዐለ ፈንታ አስተብዐለ ይላል፤ ፍችው አንድ ነው። እለ ያስተብዕሉ ፡ (ይሁ
፡ ፲፮)።
አብአሰ ፡ አባሰ አከፋ፤ አስከፋ፤ አስጠላ።
አብዐደ ፡ አስለየ አስነጠለ፤ አስራቀ፤ ባዕድ አስደረገ።
አብዕልተ ኅጣውእ ንኡሳት ፡ ብዙ ጥቃቅን ኀጢአት የሚሠሩ ፡ (፩ ፡ ፭)።
አብዕልተ ነውራት ፡ ነውረኞች፤ ነውራሞች ባለብዙ ነውሮች ፡ (ፈ ፡ መ ፡ ፳ ፡ ፭)።
አብዕልተ ጉባኤ ቅድስት ፡ የጉባኤ ጌቶች ባለቤቶች፤ ቅዱሳን አበው፤ ሊቃውንት።
አብከየ ፡ አስለቀሰ፤ አሳዘነ፤ አስጮኸ ዋይ አሰኘ፤ እንብ አስፈሰሰ። በከየ ብካየ መሪረ እስከ አብከየ እለ ሀለዉ ህየ።ለእመ ኢበከይነ በፈቃድነ በዝየ ያበክዩነ በህየ ዘእንበለ ፈቃድነ። እለ አብከዩ ዕቤረ ወዕጓለ ማውታ። ምንት ያበክየኪ ፡ (ዮሴፍ። መቃ። ግንዘ። ፩ነገ ፡ ፩ ፡ ፰)።
አብኵሐ ፡ አናፋ አስነፋ፤ አስተነፈሰ፤ እፍ እፍ አሰኘ። ዘያበኵሕ ምብኳሐ እሳት ፡ (ኤር፮ ፡ ፳፱)
አብኰረ ፡ አአበከረ፤ በካር በኵር አስደረገ፤ አስተወ፤ ከለከለ።
አብዛኂ ፡ አብዛኂ፤ ፡ (ኂት ኅያን ያት) የሚያበዛ፤ የሚያስበዛ፤ አብዥ አስበዥ። ኢይኩን አብዛኄ ነገር። አብዛኅያነ ሠሐቅ ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፰ ፡ ፩። ፈ ፡ መ ፡ ፴፬ ፡ ፪)።
አብዝኀ ፡ አበዛ አረባ፤ አበረከተ። አስበዛ አስረባ፤ አስበረከተ። አብዝኆ ኣበዝኆ ለሕማምኪ። ዘአብዝኀ ብዕለ። ዘአብዝኀ ጥበበ አብዝኀ ሐዘነ ፡ (ዘፍ፫ ፡ ፲፮። መክ፭ ፡ ፲፩። ፩ ፡ ፲፪)።
አብየ ፡ ወፈረ ላቀ፤–ዐብየ።
አብያጽ ፡ ባልንጀሮች ፡ (ዳን፯ ፡ ፳። ማቴ፲፩ ፡ ፲፮። ዘካ፫ ፡ ፰)። ኢይትፈለጥ እምአብያጽየ። አጥሪ አግዋረ እምቅድመ ትሕንጽ አብያተ፤ ወአብያጸ እምቅድመ ትሑር ፍኖተ። አብያጺከ እለ መርቆራ
፡ (አፈ ፡ ድ፳፯። ፈላስ። ደራሲ)። በአብያጽ ፈንታ፤ ይከይድዎ ቢጹ፤ ለቢጹ አርዳእ፤ ቢጽ ወራዙት፤ ቢጽ እኩያን፤ ቢጽ ሐሳውያን፤ ኀምስቱ ምእት ቢጽ እያለ ይገኛል፤ የጣፊና የመላሽ ስሕተት ነው። እሬኢ በለሳተ ቢጸ፤ ኹለት፤ ዐይነት በለስ ክፋና መልካም ፡ (ኤር፳፬ ፡ ፫)። ቢጽ የግእዝ ተውሳክ ነው፤ በሌላ አይገኝም።
አብይ ዮት ፡ (አበየ
፡ የአቢ ፡ ይእበይ። ዐረ አበይ) እንቢ ማለት፤ አበያ ፥ እንቢተኛ መኾን ፥ መጓደድ፤ የሰጡትንና ያዘዙትን የለመኑትን አለመቀበል፤ አለመስማት ፥ አለማድረግ ፥ ዕሺ በጎ ይኹን አለማለት። እንብየን ተመልከት ፥ የዚህ ዘር ነው፤ ን ስሯጽ ኹኖ ስለ ገባበት ወደዚያ ኺዷል። ተአብዩ ትእዛዝየ ሰሚዐ ወሕግየ። አበየት ሰሚዖቶ። አበዩ ኵሎሙ ትእዛዘ ንጉሥ። ኢየአቢ ስእለተኪ። አበየ ዝናም ተውህቦ ለምድር። ኢይእበይ ባዕል ከመ ኢይጠመቅ ምስለ ነዳይ። እመ ጸውዐከ ኢትእበዮ
፡ (ዘፀ፲፮ ፡ ፳፰። አስቴ፩ ፡ ፲፪። ዮዲ፩ ፡ ፲፩። ኩፋ ፡ ፴፭። ፵፪። ፍ ፡ ነ ፡ ፫። ሢራ፲፫ ፡ ፱)።
አብደረ [1] ፡ አስቀደመ፤–በዲር
፡ በደረ።
[2] ፡ (አስደራጊ) አስሮጠ አስቀደመ። አስተጋይድ ፈረሰከ ወአብድር እምዐውሎ ፡ (ደራሲ)። አሶደደ አስመረጠ አስከበረ አስበለጠ። ልማዱ ግን አድራጊነት ነው፤ መንገዱ እንደ አእመረ ተሳስቷል።
አብደሬናን ቱቂኢም ፡ (ጽር አቤዲሪን አቱኪዪም) ቃሉ የዕብራይስጥ ነው፤ ዕብራይስጡ ወሀድባሪም አቲቂም ያለውን፤ ጽርኡ እንዳለ በጥሬው ወስዶታል። ወእሉ ዜናት ቀደምት፤ ነገራት ቀደምት ማለት ነው፤ አንቲካ ወሬ እንደ ማለት ፡ (፩ዜና ፡ ፬ ፡ ፳፪)። ዜናት ያላቸውም በኦሪት ዘኍልቍ ይገኛሉ ፡ (ም፳፭ ፡ ፩--፱)።
አብደነ ፡ አበደነ አፈዘዘ፤ ሬሳ አደረገ።
አብደወ ፡ አጠፋ፤ አስጠፋ፤ አወደመ ባዶ አደረገ። አብደወ ሀገሮሙ። ኣበዱ ፍኖቶሙ። እሁቦን ለአብድዎ ከመ አልቦ ዘይነብሮን ፡ (ዮሴፍ። ሶፎ፫ ፡ ፮። ኤር፵፩ ፡ ፳፪)።
አብድ [1]:-ባሪያ፤–ዐብድ።
[2] ፡ (ዳን ዳት ባድ) ዝኒ ከማሁ፤ እብድ፤ ቍጡ፤ ሰነፍ ሞኝ አላዋቂ። እመኒ በምክንያተ ጋኔን ዘያጌብሮ ዝንቱ አብድ ውእቱ። አብድ ከልብ ዘነሰኮ። ከመ አብድ ሐራውያ። አብዳነ አጥብብ። ኀምስ አብዳት ወኀምስ ጠባባት
፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፴፪። መ ፡ ፈ። ስንክ ፡ ነሐ፳፫። ኪዳ። ማቴ፳፭ ፡ ፪)።
አብዶን ፡ (ዕብ አባዶን) ፍጹም ጥፋት፤ መፍረስ ፥ መደምሰስ ፥ ባዶ ባድማ ምድረ በዳ መኾን፤ ሲኦል መቃብር። ወስሙ በዕብራይስጥ አብዶን
፡ (ራእ፱ ፡ ፲፩)። ባለብሉዮች በኤርምያስ ፡ (ም፰ ፡ ፯)። ሄሮድያኖስን ሽመላ እንደ ማለት ዖፈ ፊንክስ ብለው ሲተርኩ፤ አብዱ የዲን ጭቃ የሚሉት ከዚህ የወጣ ነው።
አብጠለ ፡ አባጠለ፤ አብጠለጠለ፤ አበጠለለ፤ አባጨ ነቀፈ፤ አጸየፈ ፡ (ዐማርኛ)። አጠፋ አበላሸ፤ ከንቱ አደረገ፤ አስቀረ፤ ከለከለ፤ አስተጓጐለ፤ ዐሎ አለ። አብጠለ ተቃትሎትሙ። አብጠልከ ነገረከ። አብጠለ ነሢአ ሕልያን በእንተ ሢመተ ክህነት። ሶበ ኮኑ ሰይጣናት የሐውሩ ኀበ ብሑታን ከመ ያስሕትዎሙ ወያብጥልዎሙ እምተግባሮሙ መንፈሳዊ። እለ ያበጥሉ ልደቶ እምአብ እምቅድመ ኵሉ ፍጥረት ፡ (ዮሴፍ። አቡሻ ፡ ፶። ፊልክ ፡ ፬። ዲድ ፡ ፴፫)። በአብጠለ ፈንታ በጠለ ይላል፤ አያሰኝም። ኦሪተ ንቤጥልኑ በሃይማኖት። ይቤጥሎሙ ጠቢብ ጳውሎስ። በጠለ እግዚ እምኔሆሙ መንግሥተ ፡ (ቄር)።
አብጠረ ፡ አስበጠረ፤ አስነፈሰ አስነንቀሰ።
አብጣሊ መብጠሊ ፡ የሚያጠፋ አጥፊ፤ አስጠፊ። ከመ ይኩን ዝንቱ መብጠሌ ሀጕሎሙ ለግብጽ ፡ (አፈ ፡ ድ፳፯)።
አብጥሊስ ፡ (ሳት። ዐረ እተጥላሳት) የመጽሐፍ ስም፤ ሦስተኛው የሐዋርያት ሲኖዶስ። ፍችው ቀኖና ማለት ነው፤ ተጥላስን እይ። ግጽው ወሥርዐት ወአብጢሊስ። ረስጠጅ ዘውእቱ ቀሌምንጦስ ሣልስ። ከመ ዝ መሀሩነ ሐዋርያት በአብጥሊሶሙ
፡ (ፍ ፡ ነ ፡ መቅ። ቅዳ)።
አብጻሒ መብጽሒ ሕ ፡ የሚያደርስ አድራሽ፤ ወሳጅ። ምግባር ዘመብጽሒት ኀቤሃ ፡ (ፊልክ ፡ ፳፬)።
አብጽሐ ፡ አደረሰ፤ አመጣ አቀረበ። ወሰደኒ ኢየሩሳሌም ወአብጽሐኒ ኀበ አንቀጽ። ያበጽሕዎ እስከ ደመና። አብጻሕክዎ ኀበ ዘተመነየ ፡ (ሕዝ፰ ፡ ፫። ሢራ፲፫ ፡ ፳፫። ዮሴፍ)።
፡ አስረዳ ገለጠ፤ አስታወቀ። ለእመ አብጻሕክሙ ሊተ ከመ ቤል ይበልዕ። ወያበጽድሕ ሎሙ ከመ ውእቱ ክርስቶስ ፡ (ዳን፲፫ ፡ ፬። ግብ፱ ፡ ፳፪። ፲፯ ፡ ፫። ፲፰ ፡ ፳፰)። በአብጽሐ ፈንታ አስተብጽሐ ይላል፤ ፍችው አንድ ነው። የኀሥሠኒ ወያስተበጽሕ ተስእሎተ በእንቲኣየ ፡ (አፈ ፡ ድ፳፮)። ኹለተኛም አስተባጽሖ ይላል ባደራራጊ፤ አያሰኝም። ይከልእ አስተባጽሖ ኀበ እግዚ። አስትባጽሖሙ ኀቤሁ ፡ (ፊልክ ፡ ፩። ስንክ ፡ ሚያ፲፰)።
አብፅዐ [1] ፡ (አድራጊ) አከበረ አመሰገነ መረቀ፤ አደነቀ፤ ደስ አሰኘ በብዕዐት ሥራ። ያበፅዖ ዲበ ምድር። አብፅዖ በሠናይ ሰርጕ። በዘያበፅዕ ሰባ ፡ (መዝ ፡ ፵። ሢራ፵፭ ፡ ፯። ሮሜ፬ ፡ ፮–፱)።
[2] ፡ (አስደራጊ) አስከበረ አስመሰገነ፤ አስመረቀ አስደነቀ ብፁዕ አስኘ ራሱን። አብፃዕኩ አነኒ። እመኒ ብዙኀ አብፃዕኩ ርእስየ በኀቤከ ወዐርገት ጸሎትየ ቅድሜከ ፡ (ዘፍ፴ ፡ ፲፩። ሱቱ ፡ ዕዝ፲
፡ ፲፪)። በአብፅዐ ፈንታ አስተብፅዐ ይላል ፥ ፍችው አድራጊነት ነው፤ እንደ ላይኛው። ተስዐቱ እሙንቱ እለ አስተብፃዕክዎሙ። ያስተበፅዕ ደኃሪቶሙ ለጻድቃን። ያስተበፅዑኒ ኵሉ ትውልድ። ናስተበፅዖሙ ለእለ ተዐገሡ ፡ (ሢራ፳፭ ፡ ፯። ጥበ፪ ፡ ፲፮። ሉቃ፩ ፡ ፵፰። ያዕ፭ ፡ ፲፩)።
(ጥ) አቦ ፡ (ጋልኛ) አባቶ ፥ አባት ሆይ ፥ አንተ። ትግሮች አባ ጋብር ፥ ዐማሮች አቡየ የሚሏቸውን ጻድቅና ቅዱስ ጋሎች አቦ ይሏቸዋል። ፡ (ግጥም፤ አቦን የምትዘክር ያምሳ ዓመት ሴት በመካንነቷ እንደነኤልሳቤጥ ስላዘነች) ልጅ ታሰጡኝ እንደኹ ልምጣ በመጋቢት፤ የዝቋላው አቦ የምድረ ከብዱ አባት። ኋላም ልጅ አግኝታ ደስፈቅ ስላላት፤ ያቦን ገድል ዐዝለው እሽርር ከሚሉ ፥ ከቶ እነማናቸው ወልደው ያላዘሉ።
አቦሊ ፡ (ጽር አቦሎስ) የገንዘብ ስም፤ ታናሽ ገንዘብ ፭ ሳንቲም፤ የዲድርክም ኻያኛ ፥ በዕብራይስጥ ጌራ ይባላል፤ ኻያው ጌራ ፩ ሰቅል እንዲኾን፤ ኻያው አቦሊ አንድ ዲድርክም ነው። ዕሥራ አቦሊ ለአሐቲ ዲድርክም
፡ (ዘሌ፳፯ ፡ ፳፭። ዘኍ፫ ፡ ፵፯። ዘፀ፴ ፡ ፲፫። ፩ነገ ፡ ፪ ፡ ፴፮)።
አተርጋዎን ፡ (ጽርእ) ቃል ድምፅ፤ ቃለ መላእክት፤ ፍሬ ነገር የሚሰማበት፤ አአትሪኮንን የመሰለ
፡ (ሃይ ፡ አበ)።
አተርጐመ ፡ አስተረጐመ፤ አስቀዳ፤ አስገለበጠ፤ አስበመለሰ። ዜናሁ ለብልማይ ፡ (በጥሊሞስ) ንጉሥ ዘከመ አተርጐመ ኦሪተ፤ ዕሥራ ወአርባዕተ መጻሕፍተ እምልሳነ ዕብራይስጥ ኀበ ልሳነ ዮናናውያን
፡ (ዮሴፍ)።
አተንተነ ፡ አፍገመገመ፤ ገፋ አዳፋ፤ ወዘወዘ፤ ነቀነቀ፤ አስጨነቀ። ብእሲ ዘያተነትኖ ስካረ ወይን። ሶበ አተንተኖ ሰይጣነ ዝሙት። አተከዘኒ ወአተንተነኒ ፡ (ኤር፳፫ ፡ ፱። ፊልክ ፡ ፯። ዮሴፍ)።
አተከዘ ፡ በቁሙ፤ አሳዘነ ፡ እስተከክ ፣ እስጪ ነቀ፤ አሳስበ። ኢታተከዞ ፡ እንዘ ፡ ፍሡሕ ውእቱ። ተሠፍኮሙ ፡ ወአተከዝ።ምንተ እተከዝኩከ ፡ - ፡ (ሢራ፴፬ ፡ ፵፩። ጥበ፲፩ ፡ ፲፪። ሚ፺፮፲፪)"
አቱር ፡ (ቅብጥ አቶር) ስመ ወርኅ፤ ኅዳር
፡ (አቡሻ ፡ ፰)።
አቲቅ ፡ (ዕብራ) የግንብ ዐምድ ፬ ማእዝን ያለው። ኹለተኛም የዕቃ ቤት ዐምድ ስለ ኾነ ዕቃ ቤት ብለው ይፈቱታል፤ እትዌቄህን እይ
፡ (ሕዝ፵፪ ፡ ፫)።
(ጥ) አቲት ቶት ፡ (አተተ የአትት ይእትት። ዕብ አቴት፤ አመለከተ) መራቅ ማግለል፤ መለየት፤ መነጠል፤ ገለል ፈቀቅ ማለት። ከመ ይእትት እመኔክሙ። የአትት ኵሉ ግላ። የአትቱ ኵሎሙ በሞት
፡ (፩ቆሮ ፡ ፭ ፡ ፪። ፪ቆሮ ፡ ፫
፡ ፲፮። ኩፋ ፡ ፯)።
፡ መሻር መቅረት፤ መጥፋት መበላሸት፤ ምስጢሩ ከዚያው ይገባል። ወይእትት ሥልጣኖሙ እምኵሉ መካናት። አእምሮ ዘኢየአትት። ተአትት ኵላ አእምሮቶሙ
፡ (ቄድር። ቅዳ። ኩፋ ፡ ፳፫)። ኹለተኛም በቀደሰ ቤት በአተተ ፈንታ ተአተተ ይላል፤ አያሰኝም። ኢትትኤተቱ ወርሑቀ ኢተሐውሩ። ተአተተ ሕቀ እምህየ። ኢይትአተቱ እምኔሁ። ይትአተት በትረ ግብጽ ፡ (ዘፀ፰ ፡ ፳፬። ማቴ፳፮
፡ ፴፱። ሔኖ፲፬ ፡ ፳፫። ዘካ፲ ፡ ፲፩)።
አቲው ዎት ፡ ( አተወ፤ አቶ የአቱ ይእቱ። ዕብ አታህ። ሱር አታእ። ዐረ አታ) መግባት፤ መመለስ፤ መምጣት፤ አቶ መባል ከሰው ቍጥር መግባት፤ አቻ መኾን መተካከል፤ ከሚስት ከባልንጀራ። ተአቱ መቃብሪከ። እቱ ኀበ ሕዝብከ። ወአተወ እምኀበ መዝበር። ለእመ ዳኅነ አቶክሙ። ይጐነዲ አቲወ
፡ (ኢዮ፭ ፡ ፳፮። ዘዳ፴፪ ፡ ፶። ኤር፲፱
፡ ፲፬። ጦቢ፭ ፡ ፲፮። ማቴ፳፬ ፡ ፵፰)።
አታሚን አታኒም ፡ (ጽር አታኒን። ዕብ ኤታኒም) ስመ ወርኅ፤ የዕብራውያን ፯ኛ ወር ጥቅምት፤ ፯ኛቱ ለሚያዝያ
፡ (፫ነገ ፡ ፰ ፡ ፪)። ኤታን፤ ጥንት መሠረት፤ ጥንተ ወርኅ ጥንተ ዓመት፤ ጥንተ ዓለም ጥንተ ፍጥረት። ኤታኒም ውስጠ ብዙ ነው ፍጥረትን ያሳያል፤ ዓለም የተፈጠረ በጥቅምት ነውና፤ በፀሓይ ቍጥር ግን የመስከረም ጫፍ ይኾናል። ይኸውም አመ ርእሰ ሳብዕ ሠርቀ ወርኅ ግብሩ መጥቅዐ ባለው ይታወቃል ፡ (ዘሌ፳፫ ፡ ፳፬)። የግእዝና የቅብጥም ዐውደ ዓመት በመስከረም ራስ መኾኑ መጥቅዕን መሠረት ይዞ ነው። ከአዳም ዠምሮ እስከ ሙሴ ቀዳማይ ወርኅ ኤታኒም ነበረ፤ ኋላ ግን ከግብጽ የወጡበት ኔሳን ስለ ኾነ፤ የፋሲካው በግ የክርስቶስ አምሳል ነውና፤ ምሳሌውን ከአማናዊው፤ ሥጋዊውን ከመንፈሳዊው አያይዞ ዛሬ በዚህ ወር ከገሃነም ትወጣላችኹ ሲል፤ ዓመ ከመ ዮም እንደ ማለት ዝንቱ ወርኅ ይኩንክሙ ቀዳማየ አውራኅ ብሎ የጥቅምትን ቅድምና ለሚያዚያ የሚያዝያን ፯ኛነት ለጥቅምት አዋርሶታል
፡ (ዘፀ፲፪ ፡ ፪)። ዐውደ ዓመት ግን ምንም የወር ቍጥር ቢፋለስ ከዚያው ከጥንቱ ከጥቅምት አልወጣም። ፍጥረተ ዓለም በሚያዝያ ነው እንጂ በጥቅምት አይዶለም ብሎ የሚያፈችል ቢኖር ፥ ባህሉ፤ ይኩንክሙ ቀዳማየ አውራኅ ባለው ቶሎ ይፈርሳል፤ ቀዳማዩ ቀዳማይ ይኹን አይባልምና። አቡ ሻህርም ጥንተ ፍጥረት መስከረም መኾኑን ለማስታወቅ የጨረቃን ቍጥር ለመጠንቀቅ ከሚያዝያ በታች ፯ ወሮች ተውሳክ ይጨምራል ፡ (አቡሻ ፡ ፴፮)።
አታቲ ፡ (ቲት ትያን ያት) የሚርቅ የሚያገል፤ አግላይ ፈቀቅ ባይ።
አታዊ ፡ (ዊት ውያን ያት፤ አተውት) የሚገባ ገቢ፤ ተመላሽ፤ መጪ፤ አቻ እኩያ።
አትሐተ ፡ አዋረደ፤ ዝቅ አደረገ፤ አስጐነበሰ። ትዕቢት ብእሴ ያቴሕት። አትሐቱ ርእሶሙ ወሰገዱ።ያቴሕት ርእሶ ታሕተ ሰኰናከ ፡ (ምሳ፳፱ ፡ ፳፫። ዘፍ፵፫ ፡ ፳፰። ሢራ፲፫ ፡ ፲፯)። አርትዐ ሠርሐ በማለት ፈንታ አትሐተ ይላል፤ የመላሽ ስሕተት ነው
፡ (ኢሳ፵፭ ፡ ፪)።
አትሓቲ መትሐቲ ፡ የሚያዋርድ፤ አዋራጅ። ለከ ናቴሕት ዘአንተ መትሐቲ ለኵሉ ፡ (ቅዳ ፡ ሕር)።
አትለወ ፡ አስከተለ፤ ትልዉኒ አለ፤ ተከታይ ሰጠ፤ አሶደደ። ከመ ኢያትልዉክሙ ድኅረ አማልክቲሆሙ። ኣተሉ መጥባሕትየ ድኅሬሆሙ። ብፁዕ ዘኢያትለወ ልቦ ድኅሪ ንዋይ ፡ (፫ነገ ፡ ፲፩ ፡ ፪ ፡ ፬። ሕዝ፭ ፡ ፪ ፡ ፲፪። ሢራ፴፬ ፡ ፰)።
፡ ጨመረ፤ ቀጠለ። ወእመሰ አትለወ አብሶ። ወእምዝ አትለወ ወይቤ። ወእምዝ ታተሉ እስመ ለዓለም ምሕረቱ። ዳንኤል ዘፈከረ ሕልመ ንጉሥ በቃሉ፤ ወተርጕሞቶ ፍጡነ ያተሉ ፡ (ሄርማ። አፈ ፡ ድ፪። ግንዘ። ስንክ
፡ መጋ፳፫)።
አትረፈ ፡ አተረፈ፤ አዳነ አስቀረ፤ ተወ፤ አበዛ ትርፍ አገኘ። አትረፈ እነ ዘርዐ። ወአትረፈ ሰማኒተ ነፍሳተ። እመ ቦ ዘሞተ ወአትረፈ ውሉደ። ወታተርፍዎ ለኵሉ። እለ ያተርፍዎ ለእክል ፡ (ኢሳ፩ ፡ ፯። ቅዳ ፡ ግሩ። ፍ ፡ ነ ፡ ፶፪። ፪ቆሮ ፡ ፱ ፡ ፰። ሉቃ፲፭ ፡ ፲፯)።
አትራኮስ ፡ (ጽር አንትራክስ) የዕንቍ ስም፤ ዕንቍ ፈርጥ ከደንጊያ ከሰል የሚገኝ
፡ (ጦቢ፲፫ ፡ ፲፯። ስንክ ፡ መስ፲፮)።
አትሮንስ ፡ (ጽር ትሮኖስ) የንጉሥ ዙፋን፤ የጳጳስ ወንበር ታላቅ ምጡቅ፤ የሰባኪ የአንባቢ ስፍራ በቤተ ክሲያን ውስጥ የሚሠራ፤ የመጽሐፍ ወንበር ታጥፎ የሚቀመጥበት ተዘርግቶ የሚነበብበት
፡ (፫ነገ ፡ ፲ ፡ ፱ ፡ ፲፰። ስንክ ፡ ኅዳ ፰ ፡ ፴። መጋ፲፫። ፍ ፡ ነ ፡ ፰ ፡ ፬)።
አትብዐ ፡ አተባ፤ አስተባ፤ አጨከነ፤ አስጨከነ፤ ወንድ አደረገ።
አትነነ ፡ አተነነ፤ አበነነ፤ አጤስ አስጤሰ።
አትከለ ፡ ኦስተከለ፤ እስተካ ፡ እስከፈለ። እስ ደፋ ፡ እስገፋ፤ እስገፈተረ።
አትከተ ፡ አታክተ፤ አሳለፈ አቈየ፤ አደማ ደም አሳየ። ያተክት ወያስተኀልፍ ዕድሜሁ፤ አቈየ ፡ (ሢራ፳፱ ፡ ፳፭)።
አትግሀ ፡ አተጋ፤ አነቃ፤ እንቅልፍ አሳጣ። አትግሀነ ለስብሐቲከ። እፎኑመ ፈድፋደ ሕማማተ እግዚእነ ክርስቶስ ያትግሀነ። ክቡድ ሕማም ያተግህ ወአልቦ ንዋም
፡ (ስንክ ፡ መስ፳፭። አፈ ፡ ድ፳፰። ሢራ፴፬ ፡ ፪)።
አትፍአ ፡ አስተፋ፤ አስቀረሸ፤ ጢቅ ጢቅ አሰኘ።
አነ ፡ (ዕብ አኒ። ሱር ወዐረ አና) ነባቢ ወነባቢት፤ ወይም አካላዊ ቃል፤ ነባቢነት ካለው ከፍጹም አካል የሚወጣ፤ በስምና በአካል ፈንታ የሚነገር፤ በቂና ቅጽል፤ ነባር አንቀጽ። እኔ፤ ራሴ፤ ቅሌ፤ ባለቤቴ፤ ነኝ። ዘሩ አኒስ፤ አነሰ ነው። አነና ንሕነ ወንድና ሴት ያስተባብራሉ፤ ንሕነ የአነ ብዢ ነው። አነ ወአብ በቂ። አነ ዮሐንስ፤ ቅጽል። ወለተ ባቱኤል አነ፤ አንቀጽ፤ ነኝ። ወንሕነ ምንት ንሕነ፤ እኛ ምንድር ነን፤ ነነ። አነ ኄር አነ፤ እኔ ቸር ነኝ፤ በቂና አንቀጽ። አንሰ አንተ ቲ ትሙ ትን፤ ንሕነ፤ ፮ቱ ኹሉ የውእቱ ርባ ነው። አነና አንሰ አንድ ወገን፤ ሰ አፍራሽና አጋናኝ አዳማቂ ነው፤ ማድነቅም ይኾናል፤ የሰን አፈታት ተመልከት። እኔስ እኔሳ እኔማ እኔ ግን እያሰኘ እንዳወራረዱ ይፈታል፤ ሰ ሲጨመርበት አንሰ ቢል እንጂ አነሰ አይልም። አንሰ አረማዊ እንዘ ክርስቲያናዊ በስም። ወአንሰ በጽድቅከ እሬኢ ገጸከ። አንሰ ነዳይ ወምስኪን አነ
፡ (ቅኔ። መዝ : ፲፮። ፴፱)። አንቀጽ ሲኾን አፈታቱ እንደ ውእቱ ነው፤ አነ፤ ነኝ ኾንኹ አለኹ ነበርኹ ያሰኛል፤ እንደ ውእቱም መረባቱ የውእቱ ጭፍራ ስለ ኾነ ነው፤ የቀሩትም እስከ ንሕነ ያሉት እንደ አነ ናቸው። ውእቱን እይ።
አነስሐ
፤ አላዘነ አስቈጨ ፤ አስጠጠተ። ኢያኔስሕ (፪ቆሮ ፡ ፯ ፡ ፰)።
አነበየ ፡ አስነበየ ፥ አስተነባ፤ ትንቢት አናገረ፤ ነቢይ አደረገ። ኪያሁ አመነየት ወአነሰየት ፡ (ቅዳ ፡ አትና)።
አነዳ ፡ (ዳት) ቈርበት፤ ቈዳ፤ ዳባ፤ ጠፍር፤ ዥራፍ። አነዳ ላሕም ርጡብ። አነዳ ዘመልዕልተ ሥጋነ ልብሰ ሐዘን ወሕማም። ይኩን ልብሰቱ እምአነዳ ማእስ ዘእንስሳ። በሐብለ አነዳ ተአስሩ። ዘቀሠፈ አሐደ እምአግብርቲሁ በአነዳ አው በበትር። እንዘ ይቀሥፍዎ በይቡስ አነዳ
፡ (ገድ ፡ ተክ። ቀሌ። ስንክ ፡ ጥቅ፲፯። ፍ ፡ ነ ፡ ፵፯። ስንክ ፡ መጋ፯)።
አነጸረ ፡ አው አንጸረ፤ አሳየ አመለክተ፤ በጣት ባንደበት። አንጸረ ወይቤ ንሥኡ ስትዩ ፡ (ቅዳ ፡ ሕር)።
፡ ፊቱን መለሰ፤ አቀና አመራ፤ ለመኼድ። አንጸሩ መንገለ ሰዶም። ኀበ አንጸረ ቀዳማዊ የሐውሩ ፡ (ዘፍ፲፰ ፡ ፲፮። ድጓ)።
አኒም ሞት ፡ (አነመ የአንም ይእንም። ነዊም ኖመ፤ አኖመ) መዘርጋት፤ ማጋደም፤ ድሩን ዝሓውን በቁመት በኑኅ፤ ማጉን ግራዉን በወርድ። መሥራት መታታት ማቈላለፍ መስፋት፤ መጥለፍ፤ የፈትል የልብስ። ፈትለ ሣሬት ተእንሙ። የአንማ አንስት። ይክል አኒመ ሜላት። አኒም ወሰፍየ አልባስ
፡ (ኢሳ፶፱ ፡ ፭። ፬ነገ ፡ ፳፫
፡ ፯። ፪ዜና ፡ ፪
፡ ፲፬። ፍነ ፡ ፳፫)።
አኒስ ሶት ፡ (አነሰ የአንስ ይእንስ) ሰው መኾን፤ አካል መግዛት፤ እንደ አዳምና እንደ ሔዋን ወንድ ተባት ፥ ሴት እንስት ኹኖ መፈጠር መገኘት። መፀነስ መወለድ። ፪ኛም ቁሙ ፥ ማነስ ታናሽ መኾን
፡ (ዐማርኛ)። ማን ማን አንሶ እንዲሉ። ንእሰንና ሰንአን ተመልከት የዚህ አግዋር ናቸው።
አኒቅ ቆት ፡ (አነቀ የአንቅ ይእንቅ። ዕብ አናቅ። ሱር ኤናቅ) መጮኽ ማኖቅኖቅ፤ መንሰቅሰቅ፤ የልቅሶ የጭንቅ። መንጠቅ መመንጠቅ፤ መቀማት መመንተፍ።
አኒቆንጦን ፡ (ጽር አኒኮንቶን) ስመ አህጉር፤ በተራው ያሉ፤ ከዳዊት በፊት ተወግተው ተዘርፈው የማያውቁ
፡ (፩ነገ ፡ ፳፯ ፡ ፰ ፡ ፱)።
አኒን ፡ አባለ ዘርዕ፤–ዐኒን።
አኒፍ ፎት
፡ አነፈ የአንፍ ይእንፍ። ዕብ አናፍ፤ ተቈጣ)። ማናፋት፤ ባፍንጫ መጮኽ፤ እንፍ ማለት መናፈጥ፤ አፍንጫን መንፋት መቀብተት፤ የጠብ የቍጣ። መነፋነፍ፤ ነፍናፋ መኾን። ማነፍነፍ ማሽተት፤ መማግ፤ የሽቱ የትንባኾ።
አናሕሰየ [1] ፡ ይቅር አለ ፥ ናቀ አቀለለ፤ ቂምን በቀልን ዕዳ በደልን ተወ ማረ አሳለፈ። ኢይደግም እንከ አናሕስየ ሎሙ። አናሕሰይኮ ለመሲሕኮ። ለዘትፈቅዱ አናሕስዮ አናሕስዮ ሎሙ። ስረይ ሎቱ ወአናሕሲ። አናሕሲ አበሳሆሙ ፡ (ዓሞ፯ ፡ ፰። መዝ ፡ ፹፰። ቀሌ። ግንዘ። ቅዳ)። ነስሐ፤ ትሕትና ልብ በማለት ፈንታ አናሕሰየ ዲበ እኪት። ተናሕስዮ ርእስ ይላል ፡ (፩ዜና ፡ ፳፩ ፡ ፲፭። ቆላ፪ ፡ ፲፰)።
[2] ፡ (አስደራጊ) ይቅር አሰኘ፤ አስናቀ አስረሳ፤ አስተወ አስማረ።
አናሕንሐ ፡ አናና ፥ አበዛ፤ አተረፈ አትረፈረፈ፤ የጥጋብ የስፍር።
አናሚ ፡ (ሚት ምያን ያት፤ አነምት) የሚሠራ ሠሪ፤ ሸማኔ፤ ሰፊ፤ ጠላፊ፤ ፡ (፩ነገ ፡ ፲፯ ፡ ፯። ፩ዜና ፡ ፲፩
፡ ፳፫። ፳ ፡ ፭)። ኮነ አናሜ አልባሳት ቀጠንት ወሰንዱናት ክቡራት። ወአናሚሁኒ መንፈስ ቅዱስ ፡ (ስንክ ፡ ግን፲፬። ቅዳ ፡ ሕር)።
አናኵዕ ፡ ኵብኵባ፤–ነክይ ነከየ፤ ነክዐ።
አናጕንስጢሳዊ ፡ (ዊት ውያን ያት) ዝኒ ከማሁ። አናጕንስጢስ ዘውእቱ አንባቢ። አናጕንስጢሳውያን ወመዘምራን። አናጕንስጢሳዊት
፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፰ ፡ ፭። ቈስጠ ፡ ፶፫)።
አናጕንስጢስ ፡ (ሳን። ጽር አናግኖስቲስ) አንባቢ፤ የንፍቀ ዲያቆን ምክትል።
አናፈቀ ፡ በቁሙ፤ አስናፈቀ፤ አነፋፈቀ። አስጠረጠረ፤ አጠራጠረ። አናፈቆ እንከ ወአህጐልካሁ ፡ (ፊልክ ፡ ፶፮)።
አን ፡ የማድረግና የመደረግ ልማድ። አ የግእዝ፤ ነ የዕብራይስጥ ነው፤ የአ ጠባይ በመዠመሪያ ገጽ ተነግሯል። ነ በዕብራይስጥ እንደ ተ ኹኖ የመደረግ ልማድ ይባላል።(ማስረጃ) በተገብሮ አንቀጽ፤ ተአስረ ተቀትለ ተጸልበ ሲል፤ ኒቅሻር ኒቅጣል ኒጽላብ እንዲል። አና ነ በየራሳቸው ኹለት ልማዶች ስለ ኾኑ እንደ ባልና ሚስት ገጥመው አንዱን ግስ በማድረግና በመደረግ በኹለት ጾታ ያስፈታሉ። ግሱም ከደጊመ ቃል ግስ የሚዴቀል ባላራት ፊደል ነው፤ ይህም ፥ በሊል በለ፤ በልበለ ብሎ፤ አንበልበለ፤ አንቦገቦገ ተንቦገቦገ።
፡ (ጐድጐደ) አንጐድጐደ፤ አሰማ ተሰማ። ፡ (ቀልቀለ፤ ኰርኰረ) አንቀልቀለ፤ አንኰርኰረ፤ አነዋወጠ አገለባበጠ፤ ተነዋወጠ ተገለባበጠ እያሰኘ ሌላውን ኹሉ ያሳያል። ርባ ቅምር ፫ኛ ዕርከን ፴፬ ቍጥር ተመልከት።
አንኀ አኖኀ ፡ (ያነውኅ ያንኅ፤ ያኑኅ) አሳረፈ፤ አተረፈ። አሰፋ አበዛ፤ አረዘመ ፥ አስረዘመ ፥ አሳደገ፤ ዘረጋ ላከ ሰደደ። ኣነውኅ መንፈስየ ላዕሌሆሙ። ትዕግሥት ወአንኆ መንፈስ። አንኅ ነገረ። ኣነውኆ ለዕፀ ኀጺር። ኢታንኅ ሥዕርተከ፤ አላ ቅርጽ። አንኅ እዴከ ወአውፅኦ ሎቱ፤ አንኅ ኀቤሁ ምርጕዘከ፤ ወኢታንኅ ሎቱ እዴክ
፡ (ስንክ ፡ ጳጕ፫። አፈ ፡ ተ፴። ግብ፳
፡ ፰። ሕዝ፲፯ ፡ ፳፬። ዲድ ፡ ፩። ፊልክ ፡ ፻፲፫)። ያርሕቆ በማለት ፈንታ ያነውኆ ይላል፤ የመላሽ ስሕተት ነው
፡ (ኢሳ፮ ፡ ፲፪)።
አንኀለ ፡ አፈረሰ ፥ አስፈረሰ፤ ናደ አስናደ። ኦ ዘአንኀልከ ጥቅማ ለኢያሪኮ። አብያተ ጸዓልያን ያንኅል እግዚ። ፈቀደ ጢጦስ ይሑር ኀበ ቅጽር ከመ ያንኅሎ ፡ (ቅዳ። ምሳ፲፭ ፡ ፳፭። ዮሴፍ)።
አንኃሊ መንኀሊ ኅል ፡ የሚያፈርስ ፥ የሚንድ፤ አፍራሽ ፥ አስፈራሽ። ወይም ማፍረሻ ፥ ማስፈረሻ ነገር መሣሪያ።
አንሀበ ፡ አስናበ፤ አሠራ አስቀጠቀጠ። ማሕረሰክሙ አንህቡ ለመጥባሕት ወማዕጸደክሙ አግብሩ ረምሐ። ኵናት ዘሎቱ አንሀቡ ፡ (መጽ ፡ ምስ። ቅዳ ፡ ግሩ)።
አንሀከ ፡ አሳዘነ አስተከዘ። ሰላም ለከርሥከ ምንዳቤ ረኀብ ዘኢያንሀኮ ፡ (ደራሲ)።
አንሀየ ፡ አሳረፈ ፥ ዕረፍት ሰጠ፤ እፎይ አሰኘ። አንሂ ሎሙ፤ አንሂ ለኵላ ነፍስ ፅብስት። አልቦ ዘያንህየኒ አንህዮ
፡ (ቅዳ። ሰቈ፩ ፡ ፳፩። አርጋ ፡ ፩)።
አንኀ ፡ አረዘመ፤–ነዊኅ ኖኀ።
አንሰረ ፡ አነስረ ፤ አስነሰረ ፤ ንስር አደረገ ፤ ንስር አሰኘ።
አንሠተ ፡ አነሠተ፤ አስነሠተ። እንሰት ማለት ከዚህ ወጥቷል ፡ (ጕራጌ)።
አንሳሕለለ ፡ (ዲቃ ግ) አመላለሰ፤ ተመላለሰ፤ ምልስ ቅልስ አለ። ስለት በመሳል ላይ ሞረድ በብረት ላይ እንዲመላለስ፤ እንደዚያ ማለት ነው። ለእመ ርኢከ ጠቢበ ጊሥ ኀቤሁ ወመድረከ ቤቱ ያንሳሕልል እገሪከ
፡ (ሢራ፮ ፡ ፴፮)። ባለብሉዮች ግን አደከመ ብለው ይጨምራሉ።
አንሳሕሳሒ ፡ (ሒት ሕያን ያት) የሚያነሣሣ፤ ነቅናቂ፤ አነሣሽ፤ ተነሣሽ ተንቀሳቃሽ። እምከመ ተገሠጸ አንሳሕሳሒ ወኮነ ፍጹመ ይትጌሠጻ ምግባራቲሁ እለ ይትገበራ በዚያንሳሐስሕ ዘውእቱ ሥጋ፤ እስመ ውእቱ ከመ ንዋየ መሥቄ ለነፍስ ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ መቅ)።
አንሳሕስሐ ፡ አነሣሣ፤ ቀሰቀሰ፤ ወዘወዘ፤ ነቀነቀ። ተነሣሣ፤ ተላወሰ፤ ተንቀሳቀሰ፤ ተነቃነቀ፤ ተወሳወሰ። ነፍስ ይእቲ እንተ ታንሳሐስሖ ለሥጋ። አልቦ ምንትኒ ግብር እምግብራት ዘያንሳሐስሖሙ ለከሓድያን ኀበ አንክሮ። አሠንዮትከ ለአግአዚ ያንሳሐስሖ ለፍዳ፤ ወአሠንዮትከ ለቂቁይ ያንሳሐስሖ ለተመይጦ ኀቤከ ለስኢል። ተስፍሁ ለከልብ ያንሳሐስሕ ዘነቦ ወእዘኒሁ። ሥጋ ያንሳሐስሕ ኀበ ፍትወቱ ወያስተጥዕም ለነፍስ ምግባራተ ሕሡማት። ዘያንሳሐስሕ ሥጋሁ በእዴሁ እመሂ ተባዕት አው አንስት፤ አነሣሣ ፡ (ፍ ፡ ነ
፡ መቅ። አፈ ፡ ተ፴፪። ፈላስ ፡ ገ፷፪ና ፡ ሮ፬። ዮሴፍ። ቄድር)። ሞተ ወተገንዘ ዘእንበለ እስትንፋስ ወዘእንበለ አንሳሕስሖ። ወአንሳሕስሐ ሥጋሁ ለምዉት። እመ ከሠትክሙ ዐሊወ ሮም ወአንሳሕሳሕክሙ። እመ አርሐቁ ኅሊናተ እምቀዳሚሁ ለአንሳሕስሖቶሙ፤ ተነሣሣ ፡ (ተረ ፡ ቄር። ቀሌ። ዮሴፍ። ፊልክ ፡ ፴፩)። አንሳሕስሖሰ ዘአርባዕቱ ጠባይዓት፤ ሶበ ያንሳሐስሕ ደም በውስተ ሥጋ ዘውእቱ ጠባይዕ ማያዊ፤ ይሬኢ ሰብእ በንዋሙ ግብረ ሠናየ ወመስትፍሥሔ፤ ወዓዲ ይሬኢ ሕብራተ ቀይሓተ ወፀአተ ደምሂ። ወለእመ አንሳሕስሐ ሳፍራ ዘውእቱ ጠባይዕ ነፋሳዊ፤ ይሬኢ ተጋእዞት ወአጽባእተ ወእሳተ ወሕብራተ ብዙኀ ወመኃትዋተ ወመባርቅተ፤ ወይመስሎ ዓዲ ከመ ዘሀሎ ውስተ ብለኔ ወውስተ ፀሓይ። ወሶበሂ ያንሳሐስሕ በልቀም ዘውእቱ ጠባይዕ መሬታዊ፤ ይሬኢ አብሕርተ ወአፍላጋተ በረደ ወዝናማተ ወአስሐትያ ወሕብራተ ጸዐድዒዳነ ወከመ ዘይሰቲ ማየ ይመስሎ። ወለእመ አንሳሕስሐ ሳውዳ ዘውእቱ ጠባይዕ እሳታዊ፤ ይሬኢ ጽልመተ ወመቃብራተ ወሙታነ ወሥርዐተ ሕዘን ወለቢሰ ልብስ ጸሊም፤ ወይበውኡ ኀቤሁ ፍርሀት ወረዓድ፤ ተነሣሣ ፡ (ፈላስ ፡ ገ፲፮)። ሐለመን ተመልከት፤ የዚህ ጎር ነው።
አንሣኢ መንሥኢ ፡ የሚያነሣ የሚያስነሣ፤ አንሽ አስነሽ። መንሥኤ ነዳያን እምድር። መንሥኤ ውዱቃን። መንሥኢሆሙ ለምዉታን ፡ (ስንክ ፡ ሠኔ፳፰። መቃ
፡ ገ፲፯። ግንዘ)።
አንሳዕስዐ ፡ አፈላ አገነፈለ፤ አፍለቀለቀ። ፈላ ገነፈለ ተፍለቀለቀ። ወያንሳዐስዓ ለሲኦል ከመ ጽህርት
፡ (ኢዮ፵፩ ፡ ፳፫)።
አንስ ፡ (ትግሬ እናስ። ዕብ ኤኖሽ ዐረ ኢንሳን) ሰው፤ ወንድ፤ ተባት፤ ጕልማሳ አነ አንሰ ማለት ከዚህ ወጥቷል፤ አነን ተመልከት።
አንስቲ(ት)ያዊት ፡ የሴቶች ወገን ሴት፤ እንስት የተባት ጓደኛ ኹለተኛ
፡ (ሔኖ፶፬ ፡ ፰። ፰ ፡ ፯። ፹፭ ፡ ፫)።
አንስቲያ አንስትያ ፡ (ያት። ዕብ ናሽም፤ ንሼይ) ሴቶች፤ ሚስቶች። ያ መጨመሩ ለማብዛትና ለማዛረፍ፤ ለመዘርዘር ነው፤ አንስትያ ብዙ፤ ያት የብዙ ብዙ። ደቂቅየ ወአንስቲያየ። ሰብዐቱ ምእት አንስትያሁ ለሰሎሞን። ወአንስቲያሆሙኒ ኀደጋ ፍጥረቶን። ዕደውኒ ያፍቅሩ አንስቲያሆሙ
፡ (ዘፍ፴ ፡ ፳፮። ፫ነገ ፡ ፲፩
፡ ፩። ሮሜ፩ ፡ ፳፮። ኤፌ፭ ፡ ፳፭)።
አንስታይ ዊ ፡ ሴታም ባለሴት፤ ሴት ወዳድ፤ ሴት አውል፤ ጠባቂ ጐማዳ፤ ስልብ ጃን ደረብ። ሴትማ የሴት ዐይነት፤ ፈናፍንት፤ ወንዳገረድ። ፈሪ ወንድ፤ ጐጋ አንበልጋ።
አንስት ፡ ሴት፤ ሔዋናዊት ኹለተኛ ዐይነት ሰው፤ ነፍስና ሥጋ ያላት፤ ብእሲት፤ ሚስት፤ ሲጫፈር፤ አንስ ወአንስት፤ አእኑስ ወአእንስት፤ ወይም ዕድ ወአንስት፤ ዕደው ወአእንስት ያሰኛል። የግእዝ መጽሐፍ ግን በመላሾች ስሕተት አንስትን እንደ ፀርና እንደ ቢጽ ላንድም ለብዙም ያደርጋል፤ በአእኑስ ፍች እንደ ተነገረ። ዘይትወለድ እምአንስት። ኢተንሥአ እምትውልደ አንስት። ብእሲ ወአንስት። ዕድ ወአንስት። ወእመሰ አልብከ ብእሲት ኢትፍቅድ አንስተ፤ ሴት
፡ (ሢራ፲ ፡ ፲፰። ማቴ፲፩ ፡ ፲፩። ኪዳ። ቅዳ። ፩ቆሮ ፡ ፯
፡ ፳፯)። ጠባባት አንስት ሐነጻ አብያተ። አንስት ሞአባውያት። ይበልዓኑ አንስት ፍሬ ከርሦን። ወይእኅዛሁ ሰብዑ አንስት። አንትንሂ አንስት። ወአንስትኒ ይበክያሁ፤ ሴቶች ፡ (ምሳ፲፬ ፡ ፩። ሩት፩ ፡ ፬። ሰቈ፪ ፡ ፳። ኢሳ፬ ፡ ፩። ፩ጴ ፡ ፫ ፡ ፩። ሉቃ፳፫ ፡ ፳፯)። የቀረውን ፭ኛ ክፍል፤ በሳቢና በተሳቢ አርእስት ተመልከት።
አንሥአ ፡ አነሣ አቀና፤ አስነሣ። አንሥአት ገጻ ውስተ ሰማይ። አንሥአ እገሪሁ ወሖረ። ኣንሥኦሙ ላዕሌክሙ ለፋርስ። ንጉሦሙ ዘኣሥነእ ሎሙ ፡ (ኩፋ ፡ ፳፭። ፳፯። ኢሳ፲፫ ፡ ፲፯። ኤር፴ ፡ ፯)። በአንሥአ ፈንታ አስተናሥአ መኳንንተ። ያስተናሥእ ጽልአ ወሀከከ ይላል፤ አስትናሥአን እይ።
አንሶሰወ ፡ አመላለሰ፤ ተመላለሰ፤ ኼደ ተራመደ፤ ዞረ ባከነ፤ ምልስ ቅልስ ወዲያ ወዲህ አለ፤ ታች ታቹን አገር ላገር መንደር ለመንደር። ተላወሰ፤ ተንቀሳቀሰ። ኢረከቡ ማየ ዘይጸውር ሐመሮሙ ወጻመዉ ወኢተመክነዩ ከመ ያንሶስዉ ሐመረ፤ አመላለሰ ፡ (ስንክ ፡ ታኅ፲)። አንሶሰውከኑ ውስተ አሠረ ቀላይ። አንሶሰወ እስከ ሰኪሞን። ቀሲስ መፍትው ያንሶሱ ኀበ አብያተ ድዉያን። ወአልቦ ዘያንሶሱ ፡ (ኢዮ፴፰ ፡ ፲፮። ኩፋ
፡ ፲፫። ኪዳ። ኤር፬ ፡ ፲)።
አንሦጠጠ ፡ (ዲቃ ግ፤ ከሠዊጥና ከሠጢጥ የወጣ) ተሰቀጠጠ ፥ ስቅጥጥ አለ፤ ገላው ተቈጣ ፥ ጠጕሩ ቆመ ተንጨፈረረ፤ እንደ ዣርትና እንደ ዶሮ እንደ ነብር እንደ ግስላ። አንሦጠጠኒ ኵለንታየ። ወአንሦጠጠኒ ሥዕርትየ ፡ (ሄርማ
፡ ገ፪ና ፡ ፯። ኢዮ፬ ፡ ፲፭። ኤር፪
፡ ፲፪። ሱቱ ፡ ዕዝ፫ ፡ ፳፪። ገድ
፡ ተክ)።
፡ አሰቀጠጠ ፥ ስቅጥጥ አደረገ፤ አቆመ አንጨፈረረ። ድምፀ ቃል ልዑል ዘያንሦጥጥ ድምፀ ንባቡ። ነገሩ ለዘብዙኀ ይምሕል ያንሦጥጥ ሥዕርተ። አንሦጠጦ ለሥዕርትየ ፡ (ጥበ፲፯ ፡ ፬። ሢራ፳፯ ፡ ፲፬። መጽ ፡ ምስ)።
አንሶጠጠ ፡ አሰቀጠጠ፤–ሠዊጥ ሦጠ።
አንቀልቀለ ፡ አነዋወጠ፤ ተነዋወጠ ተነቃነቀ፤ ተውለቀለቀ። ስእኑ አንቀልቅሎቶ። አብያቲሃ ዘኢያንቀለቅላ። ያንቀለቅል ለፌ ወለፌ። አርዑተ ብዕራ ዘያንቀለቅል ፡ (ሉቃ፮ ፡ ፵፰። ኢሳ፴፫ ፡ ፳። አፈ ፡ ድ፲፩። ሢራ፳፮ ፡ ፯)።
፡ ወጣ፤ ራቀ፤ ሸሸ
፡ (ዘፀ፳፭ ፡ ፲፭። ምሳ፲፯ ፡ ፲፫። ማሕ፪ ፡ ፲፯)።
አንቀሰ ፡ አሳደፈ አረከሰ፤ አጨማለቀ። አስነቀሰ፤ አስጠቈረ።
አንቀር ፡ አንቃር፤–ነቍር ነቈ አንቈረ።
፡ አንቃር ፥ እንጥል የላይኛው ክፍል፤ የጕረሮ ደጃፍ። መቃጥን ዘይሰቍር አንቀሮ ፡ (መጽ ፡ ምስ)። ሕንቅርትንና ኅንቅርትን እይ፤ ከዚህ የወጣ ነው፤ አዐና ሀሐኀ ተወራራሾች ስለ ኾኑ ወደዚያ ኺዷል።
አንቀበ ፡ አስነቀበ፤ እንቅብ አሰፋ፤ በእንቅብ ሰፈረ ፥ አሰፈረ።
አንቀተ ፡ አነቀተ አነከተ፤ አስነቀተ።
አንቀወ ፡ አስጮኸ፤ ደወለ መታ። ሰንቀወን እይ፤ የዚህ መንቲያ ነው።
አንቀጥቀጠ ፡ አንቀጠቀጠ፤ ተንቀጠቀጠ፤ ተንዘፈዘፈ፤ የደዌ የብርድ የፍርሀት። ዕጥፍ ዕጥፍ አለ፤ ተብረከረከ፤ የድካም። ያንቀጠቅጥ በእንተ ልምላሜ እገሪሁ
፡ (ማር ፡ ይሥ፮ ፡ ፪)።
አንቀጥቃጢ ፡ የሚያንቀጠቅጥ፤ የሚንቀጠቀጥ፤ አንቀጥቃጭ። የዜማ ምልክት።
አንቀጸ ፡ አደረቀ፤ አጐደለ አሳነሰ፤ አነቃ ሠነጠቀ ፥ ክፍት አደረገ፤ ለየ ከፈለ። አጸና አበረታ፤ ምስጢሩ ከማድረቅ ይገባል።
አንቀጽ ፡ በር ደጅ አፍ፤–ነቂጽ ነቀጸ፤ አንቀጸ።
፡ (ብ አናቅጽ) በር ደጃፍ፤ መውጫ መግቢያ፤ ክፍት ጐደሎ ቦታ። ኆኅትን እይ፤ ኀዊው ኀወ። ጸባብ አንቀጽ። ረሓብ አንቀጽ። አናቅጺሃ ለወለተ ጽዮን ፡ (ማቴ፯ ፡ ፲፫ ፡ ፲፬። መዝ
፡ ፱)።
፡ የመጽሐፍ ክፍል፤ ምዕራፍ። አንቀጽ ቀዳማዊ በእንተ ቤተ ክርስቲያን። እምአናኅኩ ነገረ በዝንቱ አንቀጽ ፡ (ፍ ፡ ነ
፡ ፩። አፈ ፡ ተ፴፪)።
፡ ዘማች ቃል ፥ የነገር ማሰሪያ ከዘር ከነባር የሚገኝ፤ ኀላፊና ትንቢት ትእዛዝ የሚለዩበት፤ ከፊል ከፈለ ይከፍል ይክፍል፤ ቦ ሎ አኮ ይህን የመሰለ።
፡ የዜማ ሥረይ፤ ብዙ ድርብና ዐመል ያለው። አንቀጽ ሃሌታ ፡ (ድጓ)።
፡ በረኛ አጋፋሪ፤ ጭፍራ ወታደር ፥ ሰራዊት። አናቅጸ ሲኦል ኢይኄይልዋ
፡ (ማቴ፲፮ ፡ ፲፰)።
አንቀፈ ፡ አስነቀፈ፤ ዕንቅፋት አስመታ።
አንቃሂ መንቅሂ ህ
፡ የሚያነቃ የሚያስነሣ፤ አንቂ አስነሽ። መንቅሄ ሙታን። መንቅህያነ ምዉት ፡ (ቅዳ ፡ ያዕ። ፍ ፡ ነ ፡ ፵፮። ዲድ ፡ ፲፫)።
አንቃዒ መንቅዒ ዕ ት ፡ የሚያነቃ ፥ አንቂ፤ ሠንጣቂ ፥ አፍላቂ። መንቅዒት ለእንተ ይሰተይ
፡ (ቅዳ ፡ ሕር)።
አንቃዕደወ ፡ አንጋጠጠ፤ አሻቀበ፤ ተንጋጠጠ፤ ወደ ላይ ወደ ሰማይ አየ፤ ዐይኑን ሰካ፤ ጸለየ ለመነ። ፡ (ተረት) ከመሮጥ፤ ማንጋጠጥ። ይትፌሣሕ በሰርጐ ሰማያት ሶበ ያንቃዐዱ። ጐዩ ኀበ ታቦት ወአንቃዕደዉ ኅበ ኖኅ ከመ ይንሥኦሙ ኀቤሁ። ላዕለ ላዕለ እንዘ ያንቃዐዱ፤ በነጽሮ ተሰብረ ክሣዱ። አንቃዕደወ ሰማየ ኀቤከ ኀበ አቡሁ። አልዐለ እደዊሁ ወአንቃዕደወ አዕይንቲሁ ወኅሊናቲሁ
፡ (መጽ ፡ ምስ። ቀሌ። ቅኔ። ቅዳ። ፊልክ
፡ ፳፫)።
አንቄ ፡ (ብ ኦናቅይ) ነጣቂ አሞራ፤ ጭላት፤ ጭልፊት፤ ሲላ ገዲ፤ የዶሮ ጠላት። ሾተሌ አሞራ ጅብሪ የሚባል፤ ምጡቅ ድምጠ ትልቅ፤ ክንፋም ረዥም፤ ውዥምዥም፤ ጥላው ለሰው ለእንስሳ ደዌ የሚኾን፤ ርጉዝ የሚያስወርድ የሚያስጨነግፍ፤ ወፍራም የሚያቀጥን የሚያመነምን፤ የሚያሰለስል። ሾተላይ ጋኔን ሕፃናትን እንደ ሄሮድስ ሰይፍ የሚፈጅ የሴቶች በሽታ። ሾተላይ መባልን ከሾተል ወስዷል፤ የግብር ስሙ ነው። ፍራህ ዕጓለ ዶርሆ ኑፋቄ፤ እስመ በርእስከ ዖደ መልአከ ሐሰት አንቄ። አንቄ ብሂል ሾተላይ፤ መናፍቅ
፡ (ቅኔ። ጥሬ ፡ ሰዋ። ስንክ
፡ ኅዳ፳፱። ጥር፴። መጋ፳፪)።
አንቈረ ፡ አነቈረ፤ አስነቈረ ፥ አስቈፈረ። አወጣ ጨለጠ አነቀረ፤ አጠፋ አስጠፋ አሳወረ። አንቈረቶሙ እከዮሙ። አው አንቈረ ዐይኖ
፡ (ጥበ፪ ፡ ፳፩። ገድ ፡ ተክ)።
አንቈርቈረ ፡ (ዐማርኛ) አንቈረቈረ፤ ተንቈረቈረ፤ የውሃ የጥሬ፤ ለዜማም ይኾናል።
አንቈጠ ፡ አነቈጠ፤ አስነቈጠ፤ ነቍጣ አደረገ።
አንቈጥቈጠ ፡ አንቈጠቄጠ፤ ሸለመ አስጌጠ፤ ተንቈጠቈጠ፤ በቀለም በልብስ። ስላውዳመት በዓል ግጫና አበባ ይዞ እንቍጣጣሽ ማለት ከዚህ ወጥቷል፤ ምስጢሩ የምሥራች ነው፤ ኀለፈ ክረምት ቆመ በረከት ተሰርገወት ምድር በሥነ ጽጌያት እያሰኘ ርግበ ኖኅን ያሳስባል።
አንቅሀ ፡ አነቃ አነቃቃ፤ ቀሰቀሰ አስነሣ፤ አተጋ አነሣሣ። አንቅሆ እምዐቢይ ንዋም ለዘይነውም። እለ ያነቅሁ ምዉተ። ከመ ያንቅህ ልቦሙ። ከመ ኣንቅህክሙ በዘክሮ ፡ (ሢራ፳፪ ፡ ፯። ፩ነገ ፡ ፳፰ ፡ ፫ ፡ ፯ ፡ ፲፩። ቀሌ። ፪ጴጥ
፡ ፩ ፡ ፲፫)።
አንቅዐ ፡ አነቃ ሠነጠቀ፤ ለየ ከፈለ። ይመትሮሙ ወያነቅዖሙ። ተአዘዘ ያንቅዕከ እማእከልከ። አንቅዕዎን ለፅኑሳት። ዐውሎ ኀያል ያነቅዓ ፡ (ጥበ፬ ፡ ፲፱። ዳን፩ ፡ ፲፫። ዓሞ፩ ፡ ፲፫። ሕዝ፲፫ ፡ ፲፩)።
፡ አመነጨ፤ አፈለቀ አወጣ አስገኘ። ኣነቅዕ አፍላገ ውስተ አድባር። ዐዘቃተ ምድር አንቅዑ ማያተ ብዙኀ። ዐይን ዘታነቅዕ ነፍጠ። ዘአንቅዓ ለጥበብ እምልቡ ፡ (ኢሳ፵፩ ፡ ፲፰። አቡሻ ፡ ፵፯። ዮሴፍ። ሢራ፶ ፡ ፳፯)። ሐቀፈ አንቆቅሖ በማለት ፈንታ አንቅዐ ይላል፤ አያሰኝም። አንቆቅሖ አርዌ ምድር ያነቅዑ ፡ (ኢሳ፶፱ ፡ ፭)።
አንቆቅሐ ፡ (ያንቆቅሕ) አፈራ ወለደ፤ ዕንቍላል ጣለ። ቋቋ ቀፈቀፈ ፈለፈለ፤ ወይም ተቋቋ ተቀፈቀፈ ተፈለፈለ፤ ዕንቍላሉ ፍሬው ጫጩቱ።
አንቆቅሖ ፡ ዕንቍላል፤–ቆቅሕ ቆቅሐ።
አንበ(ቦ)ጣ ፡ በቁሙ፤–ነበጠ።
አንበሐብሐ ፡ አንቧቧ፤–ነብሐ።
አንበልበለ ፡ አንቦገቦገ፤ ተንቦገቦገ፤ ቦግ ቦግ ቢል ቢል አለ፤ ነደደ ተቃጠለ። አንበልብል ልሳኖ ለገብርከ። እንተ ሠረቀ ዲቤኪ ወአንበልበለ ዋዕዩ። ዘያንበለብል ነዱ። እሳት ዘያንበለብል። አፍሓም ዘያንበለብል ፡ (ደራሲ። ስንክ ፡ ጥቅ፳፩። ሆሴ፯ ፡ ፬። ዘፀ፲፬ ፡ ፲፯። ዳን፯ ፡ ፱)። ደገመ አነበበ ሲሉ አንበለበለ ማለት ዐማርኛው ከዚህ የወጣ ነው፤ ትባትን ፍጥነትን ሙቀትን ያሳያል።
አንበሰ አው ተአንበሰ ፡ አንበሳ ኾነ፤ አንበሳ ተባለ በጠባይ በግብር።
አንበሳ [1] ፡ በቁሙ፤–በሲስ በሰ፤ በስበሰ፤ አንበስበሰ።
[2] ፡ (ብ አናብስት) በቁሙ፤ ግርማ ያለው አውሬ፤ ኀይለኛ ተፈሪ፤ ነጣቂ ሰባሪ፤ ዘላይ ተወርዋሪ፤ ዐዳኝ ግሩመ ዐይን የድመት ወገን። ድመትን ብስ ማለት ከዚህ የወጣ ነው። አንበሳ ዘጽኑሕ ለመሢጥ። ረከቦ አንበሳ በፍኖት ወቀተሎ። ፈነወ አናብስተ ወበልዕዎሙ። ግበ አናብስት ፡ (መዝ ፡ ፲፮። ፫ነገ ፡ ፲፫ ፡ ፳፬። ፬ነገ ፡ ፲፯ ፡ ፳፭። ዳን፮ ፡ ፯)።
አንበሳ ዕጓለ አንበሳ ፡ ታላቅ የታላቅ ልጅ፤ ንጉሥ ወልደ ንጉሥ፤ ኀያል ወልደ ኀያል።
አንበሳዊ ፡ (ዊት ውያን ያት) ያንበሳ ወገን ዐይነት፤ አንበስማ፤ አንበሳም ባላንበሳ። ሰላም እብል ለአንበሳዊ አውሎግ ፡ (ስንክ ፡ የካ፲፩)።
አንበሳዊት ፡ አንበሲት፤ እንስት አንበሳ። ጣሕረ አንበሳ ወንቃወ አንበሳዊት። እምከ አንበሳዊት። ከመ አንበሳዊት ፡ (ኢዮ፬ ፡ ፲። ሕዝ፲፱ ፡ ፪። ዳን፯ ፡ ፬)።
አንበስበሰ ፡ አገለባበጠ፤ ተገለባበጠ፤ አርገበገበ፤ተርገበገበ፤ የዐይን የቅንድብ፤ ለእጅም ይኾናል። አንበስብሶ ዐይን። አንበስብሶ ቀራንብቲሆን ፡ (ቀሌ። ፈ ፡ መ ፡ ፴፬ ፡ ፰)።
፡ አራመደ አሻገረ ወረወረ፤ ተራመደ ተወረወረ፤ የዐይን የእግር የመብረቅ። ያንበሰብስ ዲበ አውግር። እምቅድመ ያንበስብስ ፀዓዕ። ያንበሰብሱ መባርቅት እምፀአተ ቃሉ ፡ (ማሕ፪ ፡ ፰። ቅዳ ፡ አፈ። አርጋ)።
፡ አመላለሰ ተመላለሰ፤ ብልጭ ድርግም ክፍት ክድን አለ፤ የሰማይ የዐይን። ወከመ ፀሓይ አንበስበሰት፤ ተመላለሰች
፡ (ቅዳ ፡ አት)።
አንበረ ፡ አኖረ ፥ አስቀመጠ፤ አቈየ አዘገየ። ታነብሮ ዲበ ገሐፍት። ያነብሮሙ ለነገሥት ዲበ መናብርት። አብ እግዚአ ኵሉ እምአባግዒሁ አሐደ ኤልያስሀ አንበረ ለሞት እንግዳ ዘይመጽእ ድኅረ ፡ (ዘፀ፳፬ ፡ ፫። ኢዮ፲፪ ፡ ፲፰። ቅኔ)።
፡ ጣፈ ደረሰ፤ ጥፎ አኖረ። አንባርያነ ቃል። እመ ቦ ዘነሥአ እመጻሕፍተ ሐሰት እንተ አንበርዋ ከሓድያን ወአብኦ ኀበ ቤተ ክር ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ መቅ ፡ ፪)።
አንበቅበቀ ፡ አንበቀበቀ፤ ተንበቀበቀ፤ የፈሳሽ። ባቅቡቅን ተመልከት።
አንበበ ፡ አነበበ ፥ አስነበበ፤ አስጮኸ አናገረ። ከመ ይዘምሩ ያንብቡ። ያነብቡ ደቂቀ አሮን ወይነፍኍ በቀርነ ዝብጦ። ስእኑ አንብቦታ ለይእቲ መጽሐፍ። ለበሃማን ያነብቦሙ። ዘአንበበክሙ ሶቤሃ ንቡ ፡ (፩ዜና ፡ ፮ ፡ ፴፩። ሢራ፶ ፡ ፲፮። ዳን፭ ፡ ፰። ማር፯ ፡ ፴፩። ፲፫ ፡ ፲፩)።
አንበዘ [1] ፡ አስደራጊ አንቀጽ፤–ነቢዝ ነበዘ።
[2] ፡ አንበዘ፤ አስነበ፤ አሶለደ ፥ ልብ አሳጣ ፥ አቅበዘበዘ። ተነበዘ ፥ ተቅበዘበዘ፤ ዕውቀቱ ጕልበቱ አነሰ ጐደለ ተከፈለ፤ ተስፋ ቈረጠ። አንበዘ ልቡ። ያነብዝ አብድ እስከ ይነግር ቃለ ዘሰምዐ። አንባዙ ሶበ ርኅቡ። አንበዙ እምሥቃይ። አንበዘት ነፍስየ በላዕሌና። አንበዘት ነፍሶሙ፤ እስመ ዐገትዎሙ
፡ (ገድ ፡ ተክ። ሢራ፲፬ ፡ ፲፩። መሳ፰ ፡ ፬። ፲ ፡ ፲፮። ሰቈ፫ ፡ ፳። ዮዲ፯ ፡ ፲፱)። መጣፍ ግን ዐንበዘ የዐነብዝ ዕንቡዝ ዕንባዜ እያለ በዐይን ይጥፋል፤ የጣፊ ስሕተት ነው፤ ነዘረንና አንዘረን እይ።
አንበድበደ ፡ በቁሙ አስፈራ፤ አንቀጠቀጠ። ፈራ ተንበደበደ።
አንበጠ ፡ አፈላ አወጣ፤ አበቀለ።
አንበጣ ፡ (ብ አናብጥ) በቁሙ፤ ከምድር የሚፈላ ፪ እግርና ፬ ክንፍ ያለው፤ የሣር የቅጠል ያዝመራ ጠላት። ይቤ ወመጽአ አንበጣ። ወራእዮሙ ለእልክቱ አናብጥ ፡ (መዝ ፡ ፻፬። ራእ ፡ ፱ ፡ ፯)።
አንባሕቀወ [1] ፡ አፋሸገ፤–በቀወ።
[2] ፡ አብቀወ፤ በሕቁ አዛጋ አፋሸገ፤ አፉን አለልክ ከፈተ። ወይም ተከፈተ ተለቀቀ፤ በግድ በቀስመን በውድና በፈቃድ ሳይኾን። ሕ ከሕቀ መጥቶ ስሯጽ ኹኗል፤ ስለዚህ የበሕቁ ምስጢር አለበት።
አንባሕብሐ አው አንበሐብሐ ፡ አንቧቧ፤ ተንቧቧ ተንፏፏ ተንሿሿ፤ የፈሳሽ ውሃ። እምቅድመ ያንበሐብሑ ወሓይዝተ አፍላግ። ወሓይዝት እለ ያንበሐብሑ ፡ (ቅዳ ፡ አፈ። መጽ ፡ ምስ)።
አንባቢ ፡ በቁሙ፤ አናጋሪ አስጯኺ፤ አስነባቢ። በቍዔተ አንባቢ ወሰማዒ። አንባብያኒሁ ለዝንቱ መጽሐፍ ፡ (ፊልክ። አዋል)።
አንብሐ ፡ አጮኸ፤ አስጮኸ። ጕንባሕን እይ፤ የዚህ ዘር ነው፤ ግንባር የነበረ ዘር እንደ ኾነ።
አንብሮ እድ ፡ የቡራኬ ጸሎት ከቍርባን በኋላ ሕዝቡን ሲያሰናብት ቄስ የሚደግመው። ይኸውም በየቅዳሴው ጫፍ ባ፲፬ቱ ኹሉ ይገኛል።
አንብዐ ፡ አነባ አለቀሰ፤ አፈለቀ አፈሰሰ። ኣነብዕ እመ ርኢኩ ሰብአ ሕሙመ። አንብዐ ታነብዕ ዐይንየ። ያነበዓ አዕይንቲክሙ ፡ (ኢዮ፴ ፡ ፳፭። ዮሴፍ። ኤር፱ ፡ ፲፰)።
አንብዕ ፡ (ብ አናብዕ) እንብ እንባ የልቅሶ ፍሬ የሐዘን ጠበል ካይን የሚፈልቅ የሚፈለፍል፤ የሚፈላ የሚገነፍል። እንብ ፪ ወገን ነው፤ አንብዐ ሥጋ ፥ አንብዐ ጸጋ፤ ወይም ሥጋዊና መንፈሳዊ። ፈልፈለ አንብዕ። ይውሕዝ አንብዕ ከመ ማየ ክረምት። ዘደጐጸ ዐይኖ ያወርድ አንብዐ። በአንብዕ ውዑይ። ነገር በእንተ ፍልጠተ አናብዕ። እስመ አንብዐ አእሩግ ፍጹማን ሀበት እምግዚ በጸጋ፤ ወኢኮነት እምፍጥረት ፡ (ኤር፬ ፡ ፩። ቅዳ ፡ ያዕ። ሢራ፳፪ ፡ ፲፬። አፈ ፡ ተ፴፩። ማር
፡ ይሥ፬። ፊልክ ፡ ፸፯)።
አንቦ ፡ በቁሙ፤ ኮራ ኾራ እንብ እንብ የሚል፤ የጨው ዐፈር፤ ወይም ውሃ። መጽሐፍ ግን ኀምቦ ይላል፤ ስሕተት ነው። ዐዘቅተ ናጥራን ዘውእቱ ኀምቦ
፡ (ስንክ ፡ ጥቅ፲፫)።
አንተ ፡ (ቲ ትሙ ትን) በቁሙ፤ የአነ ርባታ፤ የቅርብ ወንድ፤ በቂና ቅጽል፤ ነባር አንቀጽ፤ ነኽ። የአነን አፈታት ተመልከት፤ መሪው ርሱ ነው። አንተ ትቤ። አንቲኒ ዓዲ እምሰአልኪዮ። አንትሙ ትሰግዱ ለዘኢተአምሩ። ኢትፍርሃ አንትንሰ፤ በቂ
፡ (ማቴ፳፮ ፡ ፳፭። ፳፰ ፡ ፭። ዮሐ፬ ፡ ፲ ፡ ፳፪)። አንተ ወልደ ዕጓለ መሕያው። ወአንቲኒ ቤተ ልሔም። አንትሙ ዕደው። አንትን አንስት፤ ቅጽል ፡ (ሕዝ፪ ፡ ፫። ማቴ፪ ፡ ፮። ፩ጴ ፡ ፫ ፡ ፩ ፡ ፯)። ዕራቅከ አንተ። አንቲ መኑ አንቲ። አንትሙ ኢለባውያን አንትሙ። አንትንሰ ጠባባት አንትን፤ አንቀጽ ፡ (ዘፍ፫ ፡ ፲፩። ዮዲ፲ ፡ ፲፪። ማቴ፲፭ ፡ ፲፮። ዘረፋ)። ደቂቅ ርባታ ፲፩ኛ ዕርከን ፹፬ቍ። ደቂቅ ቅጽል ፻፲፰ ቍጥር ተመልከት።
አንተለ ፡ (አቲል አተለ። ዕብ ዓጼል። ሱር ዐጤል። ዐረ ዐጠለ) ሰነፈ፤ ታከተ፤ ቦዘነ። አተለ አተላ ኾነ። ጠላ፤ ሰለቸ፤ ተሰቀቀ፤ ናቀ አቃለለ፤ ተወ ቸል አለ። መጽሐፍ ግን በአንተለ ፈንታ ተአንተለ ይላል፤ አያሰኝም። ኢተአንተለት ሎቱ ነፍሱ። ከመ ኢይትአንተሉ ወኢይበሉ ከብደነ። ጸምአ ወኢተአንተለ፤ ኢይኩን ምዩጠ ገጽ እምስእለትየ፤ እንዘ ይትአነተል በእንተ ኀጣውእየ። አንጐርጐሩ ወተአንተሉ። ኢትትአንተል ተግሣጸ እግዚ። ያፈጥን ለረድኤትየ ወኢይትአነተለኒ። በእበድ ወበተአንትሎ
፡ (ኩፋ ፡ ፲፯። ቀሌ። አርጋ ፡ ፬። ጥበ፲፪
፡ ፳፯። ምሳ፫ ፡ ፲፩። ዮሴፍ። ማር ፡ ፮
፡ ፬)።
አንተገ ፡ አሳነሰ አጐደለ፤ አስቀረ አስታጐለ፤ ቈረጠ አቋረጠ፤ አቆመ። ያነትጉ ወይዌስኩ። ኢታንትግ እምኔሁ ቃለ። አንተጉ ሐኒጸ ሀገር። ኢያንተጉ እንዘ ይሴብሑ ፡ (ኪዳ። ኤር፴፫ ፡ ፪። ኩፋ ፡ ፲። ኪዳ)።
አንቲካ ፡ (ዐረብ) በቁሙ፤ እንተ ከሃ፤ የዱሮ፤ የቀድሞ፤ የጥንት፤ ብዙ ዓመት የኖረ አሮጌ፤ ብሉይ።
አንታሊ መአንትል ፡ ታካታ ሰነፍ ቸልተኛ ስልቹ።
አንትዐ ፡ አሸሸ አሸነፈ፤ ነዳ አባረረ። አሐዱ ያነትዖሙ ለዐሠርቱ ምእት። አንትዐ አፅራረ። አንትዕዎሙ ወተለውዎሙ ፡ (ዘዳ፴፪ ፡ ፴። አፈ
፡ ተ፳፯። ዮሴፍ)። ተከለ ዘረጋ፤ ወጠረ ገተረ። አቀላ ዘኸነነ አነተ ፥ ነት አገባ።
አንአሰ ፡ አሳነሰ፤ አዋረደ ፥ ታናሽ አደረገ። አኮ ከመ ዘንክሕድ ወዘናንእስ። ወለእመኒ አንዕስኮ ዐቢይ ውእቱ። አመ ቦ ዘያንእስ አካለ ወልድ በእንተ ተሠግዎቱ ፡ (ኪዳ። ፈላስ። ያዕ ፡ ዘእል)። በአንአሰ ፈንታ አስተንአሰ ይላል፤ ፍችው አንድ ነው። ቦኑ እምኔነ ዘያስተንእሶ ለወልድ እምኂሩተ አብ። እንዘ ታስተንእስ ርእሰከ። ያስተንእስ ሲሳዮ
፡ (ቄር ፡ ጰላ። አፈ
፡ ተ፴። አረጋ ፡ ፩)።
አንአደ ፡ አስከበረ፤ አስመሰገነ።
አንኣሲ መንአሲ እስ ፡ የሚያሳንስ አሳናሽ፤ አቃላይ አዋራጅ።
አንከሐክሐ [1] ፡ ፈተፈተ፤–ከሕክሐ።
[2] ፡ ፈተፈተ ተፈተፈተ።
አንከረ ፡ አደነቀ፤–ነኪር ነከረ።
አንከብከበ ፡ አንከበከበ፤ ተንከበከበ፤ የፍትፍት ፡ (ዐማርኛ)።
አንከየ ፡ አስነካ ፥ አስጐዳ፤ ጕዳት አመጣ። ኢያነክየነ ፡ (፩ቆሮ ፡ ፰ ፡ ፰)። በሐነከ ፈንታ ሐንከየ እንደ ማለት አንከየ ይላል፤ ስሕተት ነው። እመ አንከይኮ እምሲሳይከ ወአፍአምኮ ለነዳይ
፡ (ኢሳ፶፰ ፡ ፲)።
አንኵዕ ፡ (ብ አናኵዕ) አንኮ አናኮ ደጐባ፤ ኵብኵባ፤ ችግኝ ፥ ፌንጣ፤ ግልገል አንበጣ ፥ የሚዘል የሚፈናጠር። የገዳም ረድ ፥ አመካሪ ዕንጨት ስባሪ። አንኮ ፥ በተለይ ዝንጀሮ ይኾናል፤ አንኮ በር እንዲሉ። መጽሐፍ ግን ፥ በአንኩዕ ፈንታ አናኵዕ ይላል፤ አንኵዕና አንበጣ ውስጠ ብዙ ናቸው፤ አናኵዕ ግን የብዙ ብዙ ነው፤ ከአናብጥ ጋራ ይሰማማል። ወወሀበ ለአናኵዕ ፍሬሆሙ። አናኵዕ ወአንበጣ። ይበልዖ አናኵዕ ለርስቶሙ
፡ (መዝ ፡ ፸፯። ፪ዜና ፡ ፮ ፡ ፳፰። ሆሴ፭ ፡ ፯)።
አንካሪ መንከሪ መንከር ፡ የሚያደንቅ ፥ የሚያስደንቅ፤ አድናቂ ፥ አስደናቂ።
አንክሶ ፡ (ጽር ኦኒክስ። ዕብ ሽሔሌት) የሽቱ ቅጠል፤ የባሕር ዛጐል መልካም ሽታ ያለው፤ እንደ ዕጣን እያደቀቁ የሚያጤሱት። ወይም የሽቱ ዕቃ ባሕረ ወጥ የደንጊያ የሰደፍ የዛጐል ቢልቃጥ። ባለብሉዮች ግን ጥርኝ ይሉታል። ማርያም ድንግል ምዕዝተ ምግባር ዘእምአንክሶ
፡ (ደራሲ። አርጋ ፡ ፫። ሢራ፳፬ ፡ ፲፭)።
አንክሮጦስ ፡ (ጽር አግኪሮቶስ) የመጽሐፍ ስም፤ ኢጲፋንዮስ የጻፈው። መልሕቅ መልሕቃዊ ማለት ነው፤ ለሐቀን እይ
፡ (ሃይ ፡ አበ)።
አንክዮን ፡ (ጽር ኦኒኺዮን) ዕንቍ፤ የዕንቍ ስም
፡ (ዘፀ፴፮ ፡ ፳። ሕዝ፳፰ ፡ ፲፫)።
አንኮለለ ፡ (ነኆለለ፤ አነኆለለ) ዞረ፤ አዞረ አሰከረ። ሐመር እንተ ታንኮልል ማእከለ ዐውሎ፤ ዞረ
፡ (ሢራ፴፮ ፡ ፪)። ዘአንኮለሎ ደም። ብፃው ክቡድ ዘያብኮልሎ ለድማኅ ስቴ ክርዳድ ፡ (ኢሳ፲፱ ፡ ፲፬። መጽ ፡ ምስ)።
አንኰርኰረ [1] ፡ ገለበጠ፤–ኰርኰረ።
[2] ፡ ገለበጠ ፈነቀለ፤ አገለባበጠ። ዘያንኰረኵር እብነ ፡ (ምሳ፳፮ ፡ ፳፯። ማቴ፳፯ ፡ ፰። ፳፰ ፡ ፪)።
፡ ጨቈነ፤ ዳጠ ደፈጠጠ። ናሁ አነ ኣንኰረኵረክሙ ዘከመ ያንኰረኵር ሠረገላ ብርዐ ፡ (ዓሞ፪ ፡ ፲፫)።
፡ ተገለበጠ፤ ተገለባበጠ ተንከባለለ፤ ኼደ ወይም መጣ፤ ቦታውን ለቀቀ ፡ (ማር፲፮ ፡ ፬። ሉቃ፳፬ ፡ ፪)። አእባን ክቡራት ያንኰረኵራ። ያንኰረኵር መንኰራኵር ውስተ ዐዘቅት። ኦ እኪት ፍትወት እምአይቴ አንኰርኰርኪ
፡ (ዘካ፱ ፡ ፲፮። መክ፲፪ ፡ ፮። ሢራ፴፯ ፡ ፫)።
አንኮከወ ፡ ነዘረ አዞረ አሽከረከረ፤ ተሽከረከረ።
አንወረ ፡ አነወረ፤ አስነወረ፤ ነቀፈ አጸየፈ፤ አስነቀፈ ፥ ነውረኛ አሰኘ። ኢትሕሚ ወኢታንውር። ለምንት ያነውር አረጋዊ ለብሑታን እለ ያነውኁ ሥዕርተ። መተረ እዝኖ እስከ አንወሮ። ወአንወርከ ክብረከ ፡ (አፈ ፡ ተ፲፫። ፊልክ ፡ ፵። ዮሴፍ። ሢራ፵፯ ፡ ፳። ፪ቆሮ ፡ ፮ ፡ ፫። ፰ ፡ ፳)። አኖረ አስኖረ።
አንዘረ ፡ አነዘረ፤ አስነዘረ፤ መታ ነፋ፤ ደረደረ አስጮኸ። ዘፈነ አዘመረ ፥ ቀነቀነ ዐብሮ ጮኸ። አንዘርነ ለክሙ ወኢዘፈንክሙ። ያነዝሩ ወይሰነቅዉ። ዳዊት ያነዝር በእንዚራ። በብዕዛ ያነዝሩ። አይቴ ሀሎ ልሳንከ አንዛሪ
፡ (ማቴ፲፩ ፡ ፲፯። ኢዮ፳፩ ፡ ፲፪። ፪ነገ ፡ ፮ ፲፩። ፩ዜና ፡ ፳፭ ፡ ፫ ፡ ፭። ግንዘ)። መጽሐፍ ግን አንዘረ ያነዝር በማለት ፈንታ ዐንዘረ የዐነዝር ፥ ዕንዚራ መዐንዝር እያለ በዐይነ ይጥፋል፤ የስሕተት ስሕተት ነው።
አንዘፍዘፈ ፡ በቁሙ፤ ዘረጋ አራገበ፤ አርገበገበ። ኪሩቤል እንዘ ያንዘፈዝፉ ክነፊሆሙ ዲበ ምሥሃል። መላእክተ እግዚ ያንዘፈዝፉ ክነፊሆሙ ላዕሌሁ ፡ (መጽ
፡ ምስ። ስንክ ፡ ጥቅ፳)።
አንዛህለለ ፡ አለል ዘለል አለ፤ ዞረ ባከነ ደከመ፤ በሴስን በቍንጣን። ታበየ ኰራ። ዘያንዛሀልል ምስለ አብዳን።አንዛህለሉ በአብዝኆ መብልዕ። አልባሰ ቀጠንት ይመስዋ ለነፈስ ሬስያ ታንዛህልል። ኢታንዛህልል ሶበ ገሠጸከ። አንዛህልሎታ ለነፍስ ፡ (ምሳ፲፫ ፡ ፳። አፈ ፡ ተ፳፱። ድ፳፬)። ገቢርም ይኾናል። መፍትው ለነ ኢንረስዮ ለሥጋ ዘእንበለ ረባሕ ወኢናንዛህልሎ በተፈግዖ ፡ (አፈ ፡ ተ፳፱)።
አንዛሪ መአንዝር ፡ (ርት ራን ራት) ፈታይ ባለእንዝርት፤ ባለመሰንቆ ፥ ባለክራር፤ ዘፋኝ አዝማሪ ፥ በገና ደርዳሪ። ፈያታዊ መአንዝር። ፊልሞን መአንዝር። ተዋናዪት ፥ አው መአንዝርት ፥ አው ዘፋኒት ፡ (ፊልክ ፡ ፵፪። ስንክ ፡ የካ፳። መስ፲፰)።
አንዝሀ ፡ አስነዛ አስረጨ፤ አስበተነ አስፈነጠቀ።
አንደር ፤
(ብ አናዲር።
ትግሬ) ፤
ዋሽንት የእንቢልታ
ዐይነት።
አንደቅደቀ ፡ አንደቀደቀ ተንደቀደቀ፤ የመሣሪያ የዦሮ።
አንደበራ ፡ ዲቃላ፤–ደቢር ደበረ፤ ደብረወ።
አንደበራ አንደባራ ፡ (ርው) ዲቃላ፤ በዝሙት የተወለደ ያመንዝራ ልጅ፤ ያልተሠራ ያልተቀጣ፤ ሕገ ወጥ፤ መረን አግድሞ አደግ፤ ደፋር ዳንዴ፤ ጣፎርዴ። ወእመሰ ኢገሠጹክሙ አንደበራ አንትሙ። ወልድ ዘኢተገሠጸ፤ ፈረስ ዘኢተረየፀ አንደባራ
፡ (ዕብ፲፪ ፡ ፰። አዋል)።
አንደብደበ ፡ አንደበደበ፤ ተንደበደበ፤ ደባደቦ ኾነ መሰለ፤ የገላ
፡ (ዐማርኛ)።
አንደየ ፡ አደኸየ ፥ አስቸገረ፤ አዋረደ። አንደየ ርእሶ እንዘ ባዕል። እግዚ ያነዲ ወያብዕል። ዘርክዮቶሙ ወአንድዮቶሙ። አፍቅሮ ንዋይ ውእቱ አንዳዪሁ ለብእሲ
፡ (፪ቆሮ ፡ ፰ ፡ ፱። ፩ነገ ፡ ፪
፡ ፯። ፊልክ ፡ ፻፵፩። ፈላስ)።
አንደደ ፡ አነደደ ፥ አስነደደ ፥ አቃጠለ፤ ለኰሰ አያያዘ። ወያነድዶሙ ወይን። ኢየአክል ሊባኖስ ለአንድዶ። ነበልባል ዘአንደድክሙ ፡ (ኢሳ፭ ፡ ፲፩። ፵ ፡ ፲፮። ፶ ፡ ፲፩)። እንዶድ ማለት ከዚህ ወጥቷል፤ እሳት የማዕደናትን ዛሕል እንዲያሶግድና እንዲያጠራ ፥ ርሱም መንጽሔ አልባስ ነውና፤ ምስጢሩ ይህን ያሳያል።
አንደግደገ ፡ (ዲቃ ግ) በቁሙ፤ ኦንደገደገ፤ ተንደገደገ ፡ (ዐማርኛ)።
አንደፈ ፡ አስነደፈ፤ አሶጋ ፡ (ስንክ ፡ ሐም፳፭)።
አንደፍደፈ ፡ አንደፈደፈ፤ ተንደፋደፈ ደፍ ደፍ አለ ፡ (ዐማርኛ)።
አንድ ፡ በቁሙ፤ ፡ (ዐማርኛ) አንድ አይነድ ፥ አንድ አይፈርድ እንዲሉ።
አንገለገ ፡ (ያንጌልግ ያንገልግ) ሰበሰበ አከማቸ ጉባኤ አቆመ። ተሰበሰበ ተከማቸ፤ ሸነጓ ከተመ፤ ተጠራቀመ፤ ዶለተ መከረ። አንገለግነ ዐቢየ እንግልጋ። አንገለጉ ኵሉ ሕዝብ ላዕለ ኤርምያስ። ለምንት አንገለጉ አሕዝብ ፡ (ነሐ፭ ፡ ፯። ኤር፴ ፡ ፱። መዝ ፡ ፪። ዘኍ፲፮ ፡ ፲፩። ግብ፲፭ ፡ ፮። ፩ቆሮ ፡ ፭ ፡ ፬)።
አንገሠ ፡ አነገሠ ፥ አስነገሠ፤ ሾመ አሠለጠነ። አንግሥ ሎሙ ንጉሠ። ይምሥጥዎ ወያንግሥዎ። ዘአንገሥኩከ ላዕሌሆሙ። አንገሠቶ ኀጢአት ለምት ፡ (፩ነገ ፡ ፰ ፡ ፳፪። ዮሐ፮ ፡ ፲፭። ፪ዜና ፡ ፩ ፡ ፲፩። ሮሜ፭ ፡ ፲፯)።
አንገሥገሠ ፡ አወከ ነቀነቀ፤ ታወከ ተደረጦ። እመ ኢታንገሠግሣ ነፋስ ለዕፅ ፡ (አዋል)። አንገሸገሸ ተንገሸገሸ ማለት ዐማርኛው ከዚህ የወጣ ነው።
አንገረ ፡ አናገረ ፥ አስለፈለፈ፤ አስነገረ፤ አሶራ አስለፈፈ ፥ አስተነባ። በነገረ ፈንታ ተናገረ እንዲል፤ በአንገረም ፈንታ አስተንገረ እንደ ማለት ኹሉ አስተናገረ ይላል፤ ስሕተት ነው። መንፈሰ እግዚ ዘያስተናግረኒ። አስተናገረ በሃማነ። አስተናገሩ ምዉተ
፡ (ኢዮ፳፯ ፡ ፫። ሲኖዶ። መጽ ፡ ምስ)። ወተትና ቅቤን አነገረ አነጐረ ፥ እንገር ንጕር ግራ እንጀራ ሙጌራ ማለት ከዚህ ወጥቷል። ምስጢሩ መፍሰስና መቅለጥ ፥ መርጋት መጋገር፤ ነው፤ ግራን ተመልከት። ሊጥ አፍሳሽ ወጭት ጠባሽ እንዲሉ።
አንገርገረ [1] ፡ አፍገመገመ፤ ጣለ አንከባለለ፤ አንደባለለ፤ አንፈራፈረ አፈራገጠ፤ የባሪያ የጋኔን አጣጣል። እኩይ ጋኔን አኀዞ ወያንገረግሮ። አውደቃ ወአንገርገራ። አንገርገሮሙ ውስተ ውእቱ መሬት ፡ (ማቴ፲፯ ፡ ፲፭። ስንክ
፡ የካ፫። ሠኔ፯ ፡ ፲፭)።
[2] ፡ ተፍገመገመ፤ ወደቀ ተንከባለለ፤ ተንደባለለ፤ ከብለል ደብለል አለ፤ ተንፈራፈረ። ከመ ሐራውያ ዘይኔጽር ታሕተ ወያጸንን እመንገለ ከርሡ ወያንገረግር ውስተ ጸብር። ወድቀ ውስተ ምድር ወአንገርገረ እንዘ ይበኪ። አንገርገረ ታሕተ እገሪሁ። ናንገርግር በተፋቅሮ ፡ (አፈ ፡ ተ፲፪። ስንክ ፡ መስ፫። ገድ ፡ ተክ። ምሳ፲፰ ፡ ፯)።
አንገርጋሪ ፡ (ሪት ርያን ያት) የሚያፍገመግም፤ የሚፍገመገም፤ ጣይ አንከባላይ፤ ተንከባላይ ደብለል ከብለል ባይ። በቁሙ፤ የመዝሙር ስም ምልጣን፤ ከ፳፪ቱ የድጓ አርእስቶች አንዱ ፮ኛው ርእስ፤ መሪ ከወንጌል በኋላ መስቀል ይዞ ሃሌ ሉያ ብሎ የሚመራው፤ ተቀባዮችም በዝማሜና በተሐውሶ፤ በአንገርግሮ የሚሉት።
አንገበ ፡ አነገበ ፥ ተሸክመ፤ በጐኑ በትከሻው። አቃሰተ፤ በሸክም ብዛት።
አንገብ ፡ (ትግሬ) መቀመጫ ቂጥ፤ ሙርጥ፤ ፊንጥጣ።
አንገደ ፡ አስኬደ፤ አስነገደ። ጠማማ ሲሉ አንጋዳ ማለት ከዚህ ወጥቷል።
አንገፈ ፡ አስረገፈ፤ አስተወ አስጣለ አዳነ። ናሁ አነ ኣነግፈክሙ ንዋየ ሐቅልክሙ። አንገፍዎ ላሐ። በከመ ያነግፍ ኖላዊ እምአፈ አንበሳ እግረ። ያነግፈኪ እምእደ ፀርኪ። አንገፍኒ በትንባሌ እምብካይ ወወይሌ ፡ (ኤር፳፩ ፡ ፬። ዘፍ፳፬ ፡ ፷፯። ዓሞ፫ ፡ ፲፪። ሚክ፬ ፡ ፲። ደራሲ)።
አንጕዐ ፡ አነጓ አጮኸ ፥ አአጮኸ፤ አናጋ ሰበረ ቀለጠመ። ይበልዕ ሥጋ ዘሠብሐ ወያነጕዕ አገዳሆን። የሐርጽ ወያነጕዕ፤ ወዘተርፈ ይከይድ በእግሩ
፡ (ዘካ፲፩ ፡ ፲፮። መቃ
፡ ገ፲፮)። በአንጕዐ ፈንታ አስተናጕዐ ይላል፤ አያሰኝም። መሪር ንጽሐ ሥጋ ለዘማዊ እስመ ያስተናጕዖ ፍትወተ ዝሙት ፡ (መጽ ፡ ምስ)።
አንጕዕ [1] ፡ (ብ አናጕዕ) አንጓ፤ አገዳ ቅልጥም ዐጥቅ። ባንጓው ውስጥ ያለ የቅልጥሙ ፍሬ ፥ ሥቡ ቅባቱ አንጎሉ። አዕፅምቲሁ ይመልእ አንጕዐ። ወይትከዐው አንጕዑ። ዝሙት ዘይትገበር ውስተ አንጕዕክሙ። ትበልዑ አንጕዓ ለምድር
፡ (ኢዮ፴፫ ፡ ፳፬። ፳፩ ፡ ፳፬። ያዕ፬ ፡ ፩። ዘፍ፵፭ ፡ ፲፰። መዝ ፡ ፷፪)።
[2] ፡
አንጓ፤–ነጕዕ ነጕዐ።
አንጉግ ፡ አርጃኖ፤–ዐንጉግ።
አንጋፊ መንገፊ ፡ የሚያስረግፍ፤ የሚያስጥል የሚያስተው ፥ የሚያስረሳ። መንገፌ ሐዘን። መንገፊ ለላሕየ
፡ (ዮሴፍ። አርጋ ፡ ፬)።
አንጌቤናይ ፡ (ዊ ዪት ዊት) ወይዘርማ፤ ወይዘር፤ የወይዛዝር ወገን። ሕፃን ንኡስ አንጌቤናይ ወልደ አንጌቤናዊት። ሶፍያ አንጌቤናይት። አፎምያ ባዕልት ወአንጌቤናዊት
፡ (ድጓ። ስንክ ፡ መስ፭። ግን፲፩። ሠኔ፲፪)።
አንጌቤን ፡ ወይዘር፤ የወይዘሮ ልጅ፤ በናቱ ከቤተ መንግሥት የሚወለድ፤ የነገሥታት ወገን፤ ተቀማጭ ሥራ ፈት፤ ድልድል ቅምጥል። ቂጣም ርጥጥ፤ ዘፍጣጣ፤ ቅምጥ።
አንጌገየ [1] ፡ ዝኒ ከማሁ፤–ጌግይ ጌገየ።
[2] ፡ (አንጎገወ) አዞረ አባከነ አቅበዘበዘ። ዞረ ባከነ ተቅበዘበዘ። ታንጌጊ በገዳም። እንዘ ኣንጌጊ ውስተ መራዕይ። አንጌገዩ ውስተ አድባር። አንጌገዩ ፍኖተ በዳ። ኢያንጌግዩ ለፌ ወለፌ ከመ ሐመር ዘይዘብጥዋ መዋግድ ፡ (ኩፋ
፡ ፲፯። ማሕ ፡ ፯። ዲድ
፡ ፲፪። ስንክ ፡ ጥር፪። ቀሌ)።
አንግሀ ፡ (አሌለየ) አነጋ ማለደ ተጋ፤ ሌሊት ተነሣ። ሖሩ በኑኀ ሌሊት ወአንግሁ ላዕለ ቂሳርያ። ወአንግሀ ጥቀ ሐዊረ። ለምንት አንጋህከ ገዪሠ ዝየ። ያንግሁ ሌሊተ ፡ (ዮሴፍ። ማር፲፮ ፡ ፪። ሄርማ። ኪዳ)። አስነጋ አስማለደ፤ ማለዳ አስነሣ ፡ (አስደራጊ)።
አንጐርጐረ ፡ (ነገረ አንገረ) አጕረመረመ፤ ተጕረመረመ፤ አንጐራጐረ ተናገረ፤ ነቀፈ ተቈጣ፤ ክፉ ቃል አወጣ፤ ቋቅ አክሽ እንደ ማለት፤ ለክፉም ለበጎም ይኾናል። ጐሥዐን ተመልከት። ለምንት ያገጐረጕር ሰብእ። ኢታንጐርጕር ላዕለ ጸጋ ዘወሀበከ። ወአንጐርጐሩ ጸሐፍት ወፈሪሳውያን። ወብዙኀ አንጐርጐሩ በእንቲኣሁ። ወሰምዑ ፈሪሳውያን ከመ አንጐርጐሩ ሕዝብ ፡ (ሰቈ ፡ ፴፰። ፈላስ። ሉቃ፲፭ ፡ ፪። ዮሐ ፡ ፯ ፡ ፲፪ ፡ ፴፪)።
አንጐርጓሪ መንጐርጕር ፡ (ርት ራን ራት) የሚያጕረመርም፤ ተቈጭ ተናጋሪ፤ ሐሜተኛ እንቢተኛ። ኢትኩን መንጐርጕረ ፡ (ቈስጠ ፡ ፰)።
አንጐድጐደ ፡ አንጐደጐደ አሰማ፤ ተንጐደጐደ ተሰማ ፡ (፩ነገ ፡ ፯ ፡ ፲፬። መዝ ፲፯)። ያንጐደጕድ ኀያል በፀዓዕ መደንግፅ። ዘበላዕሉ አንጐድጐደ ፡ (ኢዮ ፡ ፴፯ ፡ ፫ ፡ ፬። ቅዳ ፡ ግሩ)።
አንጎገወ [1] ፡ ዞረ ባከነ፤–ጎግዎ ጎገወ።
[2] ፡ አባከነ አባዘነ፤ አዞረ አንክረተተ፤ አናወዘ አቅበዘበዘ፤ የዐይን የእግር የኅሊና። አነ አንጎግዋ። አንጎግወከ ምስለ ሰራዊትከ። እንዘ ታሐምሙ ልበክሙ ወታንጎግዉ። አንጎግዎሙ ውስተ አድባር ፡ (ሆሴ፪ ፡ ፲፮። ሕዝበ፴፰ ፡ ፬። ኤር፰ ፡ ፲፰። ፳፯ ፡ ፮)። ባከነ ባዘነ ዞረ ተንከረተተ። ያንጎግዉ በካልእ ሥርዐት። አንጎግዎ ዘስሒት። የዐቅቡ አልባቢሆሙ እምአንጎግዎት ውስተ ኅሊናት እኪት። ያንጎጉ አልባቢሆሙ እምሀገር ኀበ ሀገር ፡ (ጥበ፲፬ ፡ ፳፫። ሃይ ፡ አበ። ፊልክ ፡ ፺፩ ፡ ፻፪)።
አንጎጋዊ ፡ መንጎግው፤ ፡ (ውት ጉት፤ ዋን ዋት) የሚያባክን የሚባክን በካና በከንካና ዘዋሪ ቀላዋጭ። ፍልጠት ማእከለ ፈላሲ ወመንጎግው፤ እስመ ፈላሲ የዐውድ ውስተ ምኔታት ከመ ይርባሕ ወያርብሕ ግብራተ መንፈሳውያት፤ ወመንጎግውሰኬ ይረብሕ ግብራተ ሥጋውያተ
፡ (ፊልክ ፡ ፳፩)።
አንጠልጠለ ፡ በቁሙ፤ እንጠለጠለ አነሣ ያዘ፤ ለመውሰድ ለመጣል፤ ወይም ለማኖር። ተያዘ ተንጠለጠለ፤ ተወዛወዘ፤ ለመውደቅ። ተቀሥፈ አባለ፤ እስከ ሥጋሁ አንጠልጠለ ፡ (ስንክ ፡ መጋ፲፯)።
አንጠረ ፡ አነጠረ ፥ አስነጠረ፤ አፈሰሰ አቀለጠ፤ አጠራ።
አንጠበ ፡ አነጠበ ፥ አስነጠበ፤ ጠብ አደረገ ፥ አስደረገ።
አንጠብጠበ [1] ፡ አንጠባጠበ፤–ነጢብ ነጥበ።
[2] ፡ አንጠበ(ባ) ጠበ፤ ጠብ ጠብ አደረገ ፥ አንጠፈጠፈ። ደመናት አንጠብጣቡ ማየ። ደመናት አንጠብጠቡ ዓሣ። ትሬእየነ ናንጠበጥብ ሀፈ ዘእምባእስ። ወሰማይኒ አንጠብጠበ ፡ (መሳ፭ ፡ ፬። ስንክ ፡ ሠኔ፳፬። ተረ ፡ ቄር፰። መዝ ፡ ፷፯)።
፡ ተንጠበ(ባ) ጠበ፤ ጠብ ጠብ አለ ፥ ፈሰስ ተንጠፈጠፈ
፡ (መዝ ፡ ፸፩። ፪ነገ ፡ ፳፩ ፡ ፲)። ወኢያንጠበጥብ መዐትየ ላዕለ ኢየሩሳሌም። ዘያንጠበጥብ እምላዕሉ ይሰቍራ ለእብን ፡ (፪ዜና ፡ ፲፪ ፡ ፯። ሄርማ ፡ ገ፵፬) ጸፍጸፈንና አንጸፍጸፈን እይ።
አንጠየ ፡ አስናጠ፤ አስገፋ ፥ አሶዘወዘ። ዘበዘበ ነዘነዘ፤ አስጨነቀ አስቸገረ፤ በነገር በልመና። አመንዘዘን እይ፤ የዚህ ጎር ነው
፡ (ሉቃ፲፩ ፡ ፯። ፲፰ ፡ ፭። ገላ፮ ፡ ፲፮)። ኢታንጥዮሙ ለቤተ ያዕቆብ። አንጠይዎ ከመ አሆ ያብልዎ። ፈድፋደ አንጠየኒ፤ እስመ ከልአኒ ሲሳይየ ወዐራዝየ። ዘያነጥዮሙ በኵሉ ፡ (ዓሞ፯ ፡ ፲፮። ዮሴፍ። ቀሌ። መቃ ፡ ገ፪)።
አንጠፈ ፡ አስነጠረ፤ አስኰላ።
አንጢዲቁ ማርያጦስ ፡ (ሮማይ አንቲዲኮ ማሪያኒቴ) አፅራረ ማርያም፤ በማርያም ድንግልና ላይ እንደ አይሁድ ክፉ የሚያወሩ የሚናገሩ። እሊሁም ባራተኛው መቶ ዓመተ ሥጋዌ ከኒቅያ በፊት ወይም በኋላ በዚያ ወራት የተነሡ ናቸው፤ ፡ (መጽ ፡ ምስ)።
አንጣሪ ፡ በቁሙ፤ አንጥረኛ ፥ ብር አፍሳሽ፤ ጃን ሸላሚ።
አንጣሪያ ፡ (ዐማርኛ) በቁሙ፤ የሥንቆ ቅጠል፤ ከማሽላ ውስጥ የሚበቅል ማላጋ፤ እንደ ሰርዶ ግድም የሚኼድ የሚዘረጋ። ፡ (ተረት) አንጣሪያ ላንጣሪያ ቢደጋገፍ ተያይዞ ዘፍ።
አንጣእጥአ ፡ (ዲቃ ግ) ፈራ ደነገጠ፤ ተንቀጠቀጠ፤ ተናወጠ ተነዋወጠ። ተንጣጣ ተፈናጠረ፤ ጣእ ጣእ ፍንጥር ፍንጥር አለ። አንጣጣ፤ አፈናጠረ። ለምንት ታንጣአጥእ
፡ (ሱቱ ፡ ዕዝ፭ ፡ ፲፭)።
አንጣዪ መንጠዪ ፡ (ዪት ይያን ያት) የሚዘበዝብ፤ ዘብዛባ ፥ ነዝናዛ፤ ችኮ መንቻካ መናጢ። በእንተ ፍርፋራተ ኅብዝት ትሰምዮኑ አንጣዬ ለእኍከ። መንጠዪ አንተ ፡ (አፈ ፡ ተ፲፩። ሄርማ
፡ ገ፶፭)።
አንጦለለ ፡ ነጠለ፤ ተረተረ። ተነጠለ፤ ተተረተረ። ለታጠፈ ለተጠቀለለ ይነገራል፤ ቤትን ገራህትን ሰፊ ቦታን ኹሉ ጠላላ ማለት ከዚህ የወጣ ነው። ከመ ኢያንጦልል ልብሰ ሎግዮን ፡ (ዘፀ፴፮ ፡ ፳፯)።
አንጦልዐ ፡ ዘረጋ ጋረደ፤ ሸፈነ። ተዘረጋ ተጋረደ፤ ተሸፈነ። አርሕቢ መታክለኪ ወአንጦልዒ ደባትረኪ። አንጦልዐ ውስተ ገጽየ ጽልመተ። አንጦልዐ ደመና ወሰወሮሙ። ሶበ ርእዮ አቡሁ አንጦልዐ ገጾ እምኔሁ፤ ወይቤሎ ረሐቅ እምኔየ ፡ (ስንክ ፡ መጋ፳፪። ኢዮ፲፱ ፡ ፰። መዝ፻፬። ዮሴፍ)። አንጐድጐደ ፥አንበልበለ ፥ አንሶስወ ብሎ በአን ልማድነት የሚገሰስ ኹሉ በማድረግና በመደረግ በ፪ ጾታ ቢፈታ እንጂ፤ ተንጐድጐደ ተንበልበለ ተንሶስወ እንዳይል ተንጦልዐ አይልም። አንዳንድ መጽሐፍ ግን በደራሲና በጸሓፊ ስሕተት ተንጦልዐ ይላል፤ አያስኝም። ሶበ ተንጦልዐ ሥጋሁ ለኢየሱስ። በመብረቀ ስብሐት ተገልበበ ወበደመና እሳት ተንጦልዐ። በከመ ተንጦልዐ ሥጋከ ዲበ ዕፀ መስቀል። ተንጦልዐ ኀጢአትየ ማእከሌየ ወማእከለ እግዚ ፡ (መጽ ፡ ምስ። ቅዳ ፡ ያዕ። አርጋ ፡ ፩)።.
አንጦርጦስ ፡ (ጽር። ዕብ አንጥሪ፤ ታላቅ ዋሻ) የታች ታች መጨረሻ ታች፤ ሲኦል ገሃነም። በርባሮስን እይ፤ ከዚህ ጋራ አንድ ነው። ወቦ ዘወድቀ ውስተ አንጦርጦስ ዘውእቱ መታሕተ ታሕቲት
፡ (አዋል)።
አንጸብረቀ ፡ (አብረቀ) በቁሙ፤ አንጸበረቀ፤ አብረቀረቀ፤ በራ ፈለቀ፤ ተብለጨለጨ፤ ቦግ ቦግ ፥ ብልጭ ብልጭ አለ፤ ታየ ተገለጠ፤ ጽሩይ ኾነ። ሰይፍ ውስተ እዴሁ ያንጸበርቅ ከመ መብረቅ። ወለእመኒ አንጸብረቀ ወልታ ንጉሥ። ዘበላዕሌሆን ያንጸበርቅ ብዑድ ሥነ ላሕይ። ስኂን ዘያንጸበርቅ ፡ (ዮሴፍ። ቄር። ዘፀ፴ ፡ ፴፬)።
አንፀወ ፡ አደረቀ አከረረ፤ አስደረቀ።
አንጸየ ፡ አስነጨ፤ አጋጠ አስጋጠ።
አንጸፈ ፡ አስነጠፈ፤ አስጐዘጐዘ።
አንፀፈ ፡ አደረቀ፤ አስደረቀ። ያነፅፍ እግዚ ባሕረ ግብጽ። አንፀፍኩ ማየ። ያነፅፍ ዐዘቃቲሁ። ያነፅፎሙ ለኵሉ አፍላግ ፡ (ኢሳ፲፩ ፡ ፲፭። ፴፯ ፡ ፳፭። ሆሴ፲፫ ፡ ፲፭። ናሖ፩ ፡ ፬)።
አንጸፍጸፈ ፡ አንጠፈጠፈ፤ ተንጠፈጠፈ፤ ፈሰሰ ጐረፈ። ነጥበን ተመልከት። ታንጸፍጽፍ ዐይንየ ቅድሜሁ። ዓዲ ሐሊቦሙ ያንጸፈጽፉ፤ ፡ (ገቢር)። ያንጸፈጽፍ መዓር እምአድባር። ወያንጸፈጽፍ ሐሊቦን
፡ (ኢዮ፲፮ ፡ ፳። ዮኤ፫ ፡ ፲፰። ዓሞ፱ ፡ ፲፫። ሱቱ ፡ ዕዝ፫ ፡ ፯። ተረ ፡ ባሮ)።
አንጻሒ መንጽሒ ፡ (ሒት ሕያን ያት) የሚያነጻ ፥ የሚያጠራ አጥሪ። ማይ መንጽሔ ዚኣነ። ሥጋ ወደም መንጽሔ ኀጢአት። ንስሓ እንተ ይእቲ መንጽሒቶሙ ለኃጥኣን ፡ (ኪዳ። ስንክ ፡ መጋ፲፬። ፊልክ
፡ ፻፷፮)።
አንጻሪ መንጽር መነጽር ፡ የሚያሳይ፤ አመልካች ጠቋሚ።
አንጻር [1] ፡ በቁሙ፤–ነጽሮ ነጸረ።
[2] ፡ አንጻር፤ ፡ (ራት) በቁሙ፤ አኳያ አቅጣጫ አፍዛዣ፤ ፊት ለፊት ትይዩ፤ ፊት ገጽ። አንጻረ ኢየሩሳሌም። ኀደረ አንጻረ ኬብሮን። አንበሮሙ አንጻራቲሆሙ በበ ገጾሙ። ሚጢ አዕይንተኪ እምአንጻርየ ፡ (ዳን፮ ፡ ፲። ኩፋ ፡ ፲፬ና ፡ ፲፮። ማሕ፮ ፡ ፭)።
አንጻፊ መንጸፊ ጽፍ ፡ የሚያስነጥፍ ፥ አንጣፊ፤ አስጐዝጓዥ።
አንጼዋ [1] ፡ ዐይጥ፤–ነጽይ ነጸየ።
[2] ፡ (ብ አናጹት) ዐይጥ ፥ ታናሽ አውሬ አፈ ሹል ጥርሰ ስል የሚግጥ የሚቈርጥ አጥፊ፤ በዱር በቤት በቈላ በደጋ የሚገኝ። ለእመ አማሰነ አንጼዋ ምንተኒ። አውፅአት ምድሮሙ አናጹተ ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፴፮። ፩ነገ ፡ ፮ ፡ ፩)።
አንጽሐ ፡ አነጻ አጠራ፤ ንጹሕ አደረገ፤ አስደረገ። አንጻሕኩ እደውየ። ትክል አንጽሖትየ። በአንጽሖ ርእሶን እምዝሙት ፡ (ኢዮ፱ ፡ ፴። ማቴ፰ ፡ ፪። ፩ጢሞ
፡ ፪ ፡ ፱)። በአንጽሐ ፈንታ አስተናጽሐ ይላል፤ አያሰኝም። ያሜክርዎ ወያስተናጽሕዎ እምአበሳሁ። ወአስተናጽሐ ርስሐተ ሰኳንዊሆሙ። ከመ ታስተናጽሕ ቀሢመ። ብእሲ ጠቢብ ዘያስተናጽሕ ሦከ እምገራህቱ
፡ (ክብ ፡ ነገ። መጽ
፡ ምስ። ዘዳ፳፬ ፡ ፳። ዲድ ፡ ፴፱)።
አንፅኀ ፡ አስጣለ፤ ጣለው አለ።
አንፆረረ ፡ አንሸዋረረ፤ ተንሸዋረረ፤ ዐይኑ ዘዋራ ሸውራራ ሸንዳራ ኾነ፤ ብጭርቅርቅ ወይም ጭብርቅርቅ አለ። ምስክር የለውም።
አንፈሰ ፡ አነፈሰ፤ አስነፈሰ ፥ እፍ እፍ አሰኘ። አሳረፈ አስተነፈሰ፤ ደስ አሰኘ። አስተብቍዖ ለሕፃን ከመ ያንፍሶ እምዝ ዓለም። አንፈስክምዎ ለእግዚ። አንፍሶ ፡ (መጽ ፡ ምስ። ዘፀ፴፪ ፡ ፳፱። ቅዳ ፡ ዮሐ)።
አንፈረ ፡ አነፈሰ፤ አስነፈሰ ፥ እፍ እፍ አሰኘ። አሳረፈ አስተነፈሰ፤ ደስ አሰኘ። አስተብቍዖ ለሕፃን ከመ ያንፍሶ እምዝ ዓለም። አንፈስክምዎ ለእግዚ። አንፍሶ ፡ (መጽ
፡ ምስ። ዘፀ፴፪ ፡ ፳፱። ቅዳ ፡ ዮሐ)።
አንፈርፈረ ፡ አንፈረፈረ፤ ተንፈረፈረ። አንፈራፈረ፤ ተንፈራፈረ፤ ፍር ፍር አለ።
አንፈቀ ፡ አስነፈቀ ፥ አስከፈለ፤ መንፈቅ አሰኘ።
አንፈጸ ፡ አሸሸ አራቀ፤ አባረረ በተነ። ወአንፈጸ እግዚ ንዋመ እምኔሁ። ሰደዶሙ ወአንፈጾሙ። ብርሃኑ ያነፍጾሙ ለአጋንንት ፡ (አስቴ፮ ፡ ፩። ጥበ፲፯ ፡ ፱። ገድ ፡ ኪሮ)።
፡ አዘራ ፥ አነፈሰ። ሜጠት ገጻ ወአንፈጸት በአጻብዒሃ ፡ (ስንክ ፡ ኅዳ፲፯)። ሐንፈጸን እይ፤ የዚህ ድርብ ነው፤ አን ሐ ከማለት በቀር ሌላ ልዩነት የለውም፤ ነቀወንና ሰንቀወን ይመስላል።
አንፍ ፡ (ዐረ አንፍ። ዕብ አፍ) አፍንጫ የአፍ ጎረ ቤት ፪ኛ፤ አፈ ሕንጻ፤ የራስ ቅል ደጃፍ፤ ማሽተቻ፤ ማነፍነፊያ፤ ካምስቱ ሕዋሳት አንዱ።
፡ (ማሕ፯ ፡ ፭ ፡ ፱። ኢሳ፴፯ ፡ ፳፱። መዝ ፡ ፻፲፫)። ለእመ ዐጸርከ አንፈከ
፡ (ምሳ፳፬ ፡ ፷፰)።
አንፍኀ ፡ አስነፋ፤ አስመታ። ወአንፍኀ ቀርነ ኢዮአብ ፡ (፪ነገ ፡ ፲፰ ፡ ፲፮። ፳ ፡ ፩)።
፡ አነፈሰ፤ ነፋስ አመጣ፤ እፍ እፍ አሰኘ፤ አስነፈሰ። መጽሐፍ ግን በአንፍኀ ፈንታ ነፍኀ ይላል፤ የመላሽ ስሕተት ነው። ይነፍኅ መንፈሶ ፡ (መዝ ፡ ፻፵፯)።
አኖመ ፡ አተኛ አስተኛ ፥ እንቅልፍ አሶስደ፤ አሳደረ። ምንት ያነውመከ። አኖሞሙ ለኵሎሙ ነገሥት። አኑም ውስቴትየ አፍቅሮተከ። አኑመነ በሰላም ፡ (ዮና፩ ፡ ፮። ኢሳ፲፬ ፡ ፲፰። ማር
፡ ይሥ፲፱ ፡ ፪። ድጓ)። አነመን እይ፤ የዚህ መንቲያ ነው፤ አቀመ የአቆመ ተውላጥ እንደ ኾነ።
አዐ(ዕ)ሰበ ፡ አከራየ፤ ለክራይ ሰጠ፤ ቤቱን ከብቱን፤ ወይም ጕልበቱን። እመ አገበርዎ ለብእሲ ከመ ያዐስብ ዘይመልኮ፤ አው ይትዐሰብ ምልከተ ካልኡ
፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፴፭)። አዐሰበ በማለት ፈንታ አስተዐሰበ ይላል፤ አንድ ወገን ነው። ለእመ ፈቀደ ከመ ይሢጥ ክፍለ ዚኣሁ፤ አው ያስተዐስቦ ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፴፯)።
አአመረ ፡ አስመለከተ፤ አስጠቈመ፤ አስጠነቈለ፤ ምልክት ታምራት አስደረገ።
አአምኀ ፡ እጅ አስነሣ፤ አሰገደ፤ እጅ መንሻ አሰጠ።
አዐሠረ ፡ ዐሥር አስደረገ፤ ዐሥራት አሶጣ፤ ግብር ቀረጥ አስከፈለ። ወአዕጻደ ወፍርክሙ ያዔሥረክሙ
፡ (፩ነገ ፡ ፰ ፡ ፲፯)።
አአርወየ ፡ አውሬ አደረገ፤ አሰኘ፤ አስቈጣ አነሣሣ። ያአርውዮ ለየዋህ ከመ ድብ ኀራስ ወይሬስዮ ከመ ሐራውያ ሐቅል
፡ (መጽ ፡ ምስ)።
አአበሰ ፡ አሳበሰ ፥ አስበደለ ፥ ኀጢአት አሠራ። እንተ ታኤብስ ምድረ
፡ (ኩፋ ፡ ፳፫)።
አአባሲ መአብስ ፡ የሚያሳብስ፤ የሚያስበድል፤ አገባሪ ኀጢአት አሠሪ።
አአትሪኮን ፤ (ጽር ቱሎጉ) ፤ ዝርው
ቃል ፤
ድምፅ ሰብኣዊ ፤ ፍሬ ነገር
የሚሰማበት። አአትሪኮን ውእቱ
ቃልነ ዘይትከዐው
ውስተ አየር
ወእምኔሁ ይትፌኖ
ንባብ (ሃይ ፡ አበ ፡ ጎር ፡ ገባ)።
አአንሰሰ ፡ እንስሳ ኦደረገ፤ አሞኘ ኦታለለ።
አአንገደ ፡ (የአንገደ ድርብ) አስተናገደ፤ እንግዳ አሳደረ ተቀበለ። ወበእንቲኣሃ አአንገዱ ሰብእ መላእክተ እንዘ ኢየአምሩ ፡ (አፈ ፡ ድ፴፪)።
አዐውየወ ፡ አስጮኸ፤ አስጨነቀ፤ አስለቀሰ። እንዘ ታግዕሩ ወታዐወይዉ ነዳየ ፡ (ኢሳ፶፰ ፡ ፬)።
አአዘበ አስተአዘበ ፡ ሸነ ሸና፤ አጨረቀ፤ ረጨ ፈነጠቀ። ባለብሉዮች ግን ሰለለ ጐበኘ ይሉታል። ዘያስተአዝብ ኀበ አረፍት። ቅጥር ተጠግቶ የሚሸን ውሻ፤ ወንድ ልጅ ቤተ ሰብ
፡ (፩ነገ ፡ ፳፭ ፡ ፳፪ ፡ ፴፬። ፫ነገ ፡ ፳፩
፡ ፳፩። ፬ነገ ፡ ፱
፡ ፰)።
አአዘዘ አስተአዘዘ ፡ አሳዘዘ፤ እዘዝ ናዝ አለ፤ አዛዥነት ሾመ፤ ወከለ።
አአደመ ፡ (ያኤድም ያአድም) አው አስተአደመ፤ ያስተኤድም ያስተአድም፤ አሳመረ፤ አሰማመረ፤ አደነቀ፤ አመሰገነ፤ አጣጣመ፤ ደስ ብሎት ሠራ አዘጋጀ። ኀፍረት አስተአድሞ ብእሲተ ባዕድ። አየ እምክልኤቱ ግብራት ትዌድስ ወታስተኤድም። ኢያስተአደምኩ ስቴሁ ለንጉሥ። ወባዕድኒ ዘአስተአደሙ በሕይወቶሙ
፡ (ሢራ፵፩ ፡ ፳። አፈ ፡ ድ፳፯። አስቴ፬። ፪ዕዝ ፡ ፩ ፡ ፮)።
አዐገለ አስተዐገለ ፡ አስቀማ፤ አስበደለ፤ ግፍ አሠራ።
አኢ [1] ፡ (አአይከ ተአኢ ተአኢ አኢ) ትእዛዝ አንቀጽ፤ ግባእ ተመየጥ። አኢ ወሑር ብሔረ ግብጽ
፡ (ዘፀ፬ ፡ ፲፱)።
[2] ፡ ያዋጅ ቃል፤ ስማ ስማ። በጽሐ ጊዜ ዘይትበሀል አኢ ዘውእቱ ስማዕ ብሂል
፡ (ገድ ፡ ተክ)።
አዔለ ፡ አዞረ፤ አባከነ፤ አንከረተተ። አዔሎሙ ውስተ ገዳም። አዔልዎ ውስተ ይእቲ ሀገር ፡ (ዘኍ፴፪
፡ ፲፫። ኢዮ፲፪ ፡ ፳፬። ስንክ ፡ መጋ፲፩)።
አኤል ፡ (ዕብ ኤል ኤላው) የግንብ ዐምድ፤ ውስጡ ግንብ ኹኖ አፍኣው በሉሕ የተጌጠ በልዝብ ጠርብ የተለበጠ። ኤልንና ኤላውን ተመልከት፤ ከዚህ ጋራ አንድ ነው። ወአኤል ዘኆኆት
፡ (ሕዝ፵ ፡ ፱)።
አኤናዖን ፡ (ጽር። ዕብ ዖላም) ለዓለም፤ ዘለዓለም ፡ (ዘዳ፴፫ ፡ ፲፭ ፡ ፳፯)።
አእኀረ ፡ አድኀረ፤ አቈየ አዘገየ፤ ለወጠ ሌላ አደረገ። ከተማ ዐውድከ ኢታእኅር፤ በኵራቱን ቀዳምያቱን አታዘግይ አትለውጥ ማለት ነው
፡ (ዘፀ፳፪ ፡ ፳፱)። ባለብሉዮች ግን ዐውድማኽን አጥርተኽ አትጥረግ ይሉታል።
አእኀዘ ፡ አስያዘ አስጨበጠ፤ አሳልፎ ሰጠ፤ ዐደራ አለ፤ አስጠጋ፤ አስደገፈ። ወአእኀዝዎ ኅለተ
፡ (ማቴ፳፯ ፡ ፳፱)። በአእኀዘ ፈንታ አስተእኀዘ አስተአኀዘ ይላል፤ ፍችው አንድ ነው፤ ካስደራጊነት አይወጣም። ለእመ አስተአኀዘ ብእሲ ንዋየ ብእሲቱ ዘእንበለ ምክራ ኢይደሉ እኂዝ። ወአስተአኀዘ ኢዮአዳ ኵሎ ቤተ እግዚ በእደ ካህናት። ዕፀ ሳቤቅ ዘያስተእኅዝ በግዐ ምስለ አቅርንቲሁ ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፳፬ ፡ ፭። ፪ዜና ፡ ፳፫
፡ ፲፰። መጽ ፡ ምስ)።
አእለፈ ፡ አስተማረ፤ ፊደል አስቈጠረ፤ አሌፍ እልፍ አሰኘ።
አዕለወ ፤ (አስደራጊ) ፤ አስወነጀለ ፤ አስከዳ ፤ አስካደ ዐሎ አሰኘ አስለወጠ።
ዘአዕለዎሙ ለሕዝብ በምክሩ።
ያዐልዎሙ ለሕዝብነ። ሶበ አዕለውዎ
ለሃይማኖት (ሢራ፵፯ ፡ ፳፫። ሉቃ፳፫ ፡ ፪። ክብ ፡ ነገ)
፡ አስፈጸመ ፤ አስተወ። አስቀዳ ፤ አስመለስ። ምስክሩን በዐሊው ተራ ተመልከት።
አዕላዊ ፡ የሚያስክድ፤ የሚያስከዳ። የሚያስተረጕም የሚያስቀዳ።
አእላፋት ፡ ብዙ እልፎች፤ የብዙ ብዙዎች። መቶ እልፍ፤ ወይም ሺሕ ጊዜ ሺሕ
፡ (ቀእ–፻፻፻) አንድ ሚልዮን። አእላፈ አእላፋት። ርኡሳነ አእላፋት ፡ (ዳን፯ ፡ ፲። ፩ዜና ፡ ፲፫
፡ ፩)።
አእላፍ ፡ ብዙ እልፍና ሺሕ፤ ዐሥር እልፍ፤ ወይም መቶ ሺሕ
፡ (የእ–፲፻፻) አእላፍ ወርቅ ወብሩር። ላዕለ አእላፍ። ይቀትል ብዙኀ አእላፈ ፡ (መዝ ፡ ፻፲፰። ዘፀ፴፬
፡ ፯። ዳን፲፩ ፡ ፲፪)።
አእመረ ፡ (ያአምር ያእ) አሳወቀ፤ አስረዳ። ልማዱ ግን አድራጊነት ነው፤ ዐወቀ ተረዳ፤ ወደደ። በቀተለ ፈንታ አቅተለ ብሎ ገደለ ማለት አላዋቂና ዘባራቂ እንዲያሰኝ ፥ ይህም እንደዚያ ነው፤ ጥሩ ዕውቀት ባላቸው ሰዎች ዘንድ ትምርትና መምር ያስነቅፋል።
፡ (ምሳሌ) ሰፌድና ወንፊት ያላት ሴት ያልተነፋ ዶቄት አታቦካም። አእመረ ዳዊት ከመ መጽአ ሳኦል። አአምር ርእስየ ከመ መሬት ወሐመድ አነ። ታአምርኑ ዘታነብብ። አእመራ ለብእሲቱ። እስመ እግዚ ያአምሮሙ ለመናንያን ፡ (፩ነገ ፡ ፳፮
፡ ፫። ኢዮ፵፪ ፡ ፮። ግብ፰ ፡ ፴። ዘፍ፬ ፡ ፩። ማር ፡ ይሥ፬ ፡ ፬።
አዕመቀ ፡ አጠለቀ፤ አስጠለቀ፤ ጥልቅ አደረገ፤ አስደረገ። አዕምቁ ለክሙ ኀበ ትነብሩ። ጥቀ አዕመቀ ከርየ ግብ። ኢይክል አዕሚቆ ኀልዮ ፡ (ኤር፳፱ ፡ ፱። ፴ ፡ ፰። ሉቃ፮ ፡ ፵፰። ቅዳ ፡ አፈ። ዮሐ። ግሩ)። አዕምቅ
፡ (አሙቅ) ላሕዎቶ ፡ (ሢራ፴፰ ፡ ፲፯)።
አእመነ ፡ አሳመነ፤ ወደ እምነት ሳበ፤ አስረዳ፤ ሰበከ ነገረ አስተማረ። ንሕነ ናአምኖ። ዘብዙኀ አሕዛበ አእመነ። አእመኖ በስመ ኢየሱስ። አእመኖሙ ለዕደው እለ ፈነዎሙ
፡ (ማቴ፳፰ ፡ ፲፬። ድጓ። ስንክ ፡ ኅዳ፲፬። ዮሴፍ)። በአእመነ ፈንታ አስተአመነ ይላል፤ ፍችው አንድ ነው። እንዘ ያስተአምነነ ዮሐንስ ይጽሕፍ። ወበግብሩ ያስተአምን ዝንቱ ከመ አማን። ወያስተአምን ዘንተ እንዘ ይብል። ሰይጣን ያስተአምን ሎሙ በግብሩ ፡ (ቄር ፡ እስት። ጰላ። ቀሌ)።
አዕማድ [1] ፡ ዐምዶች፤ ድጋፎች፤ ቋሞች ተሸካሞች፤ የእግር አገዶች። አዕማድ ዘንድቅ ወአዕማድ ዘእብን። አዕማደ ወርቅ እለ ይቀውሙ። ጳጳሳት ኄራን ዘይብልዎሙ አዕማድ። አዕማደ እግር ፡ (ሥር ፡ አኵ። ሢራ፳፮ ፡ ፲፰። ስንክ
፡ ጥር፮። ፩ነገ ፡ ፲፯ ፡ ፮)።
[2] ፡ የግስ ነገዶች፤ ወይም ጸዋትወ ግስ። እሊሁም አድራጊ አስደራጊ ተደራጊ ተደራራጊ፤ አደራራጊ ናቸው፤ ቀተለን ተመልከት።
አእምሮ ሮት ፡ ማሳወቅ፤ ማስረዳት። ልማዱ ግን፤ ማወቅ መረዳት። አእምሮ አእምር። ኢክህሉ አእምሮቶ። ነቢያት ቀደሙ አእምሮ ፡ (ምሳ፳፯ ፡ ፳፫። ኩፋ ፡ ፵። ድጓ)።
አእምሮ ፡ (እምሮ። ትግ አምር) ዕውቀት፤ ማስተዋል፤ ከጠባይ ከትምርት የሚገኝ። አእምሮ ታጌብረከ ለምህሮ። ጥበብ ወአእምሮ። ወተአተተት ኵላ አእምሮቶሙ። እለ አልቦሙ አእመሮ
፡ (ድጓ። ኪዳ። ኩፋ ፡ ፳፫። ሃይ ፡ አበ)። ስለ ተለመደ ነው እንጂ አእመሮ ጥሬ ዘር አይኾንም፤ አርእስት ነው።
አእሰረ ፡ አሳሰረ፤ አስጋዘ።
አእረረ ፡ አሳጫደ፤ አሰበሰበ፤ አስከተተ። ያአርሮሙ ማእረሬ
፡ (፩ነገ ፡ ፰ ፡ ፲፪)።
አዕረቀ ፡ አስራቈተ፤ ገፈፈ፤ ባዶ አደረገ። አዘዘ ያዕርቅዎ አልባሲሁ። ኢታዕርቆ እግዚኦ ለእኁነ እገሌ እምልብሰ ጥምቀት። እቤሎሙ ያዕርቁ ኵሎ መዛግብተ ፡ (ስንክ ፡ የካ፱። ግንዘ። ፪ዕዝ ፡ ፲፫ ፡ ፱)።
አዕረበ ፡ አስመሸ፤ ፀሓይ አገባ። ኢታዕርብ ፀሓየ በሰንበት እንዘ ትጸውም
፡ (ሲኖዶ)።
አዕረየ አዐረየ አዔረየ ፡ (ዐረየ፤ ገቢር) አሳከለ፤ አስመሰለ፤ ወይም አስተካከለ፤ አመሳሰለ፤ ኹሉም አድራጊ ነው። አዔረየ እንደ አሜረየ በጸያፍ ገብቷል፤ አያሰኝም። ያዔሪ ርእሶ ምስለ እግዚ። ጳውሎስ አዔረየ ርእሶ ምስለ ሐዋርያት። አዔረዮ ምስለ አቡሁ ፡ (ዮሐ፭ ፡ ፲፰። አፈ
፡ ድ፩። ፪)።
አእረገ ፡ አስረጀ፤ አሸመገለ፤ አሮጌ አሰኘ።
አዕረገ ፡ አሳረገ፤ ወደ ላይ አወጣ፤ ከፍ ከፍ አደረገ። አይቴ ታዐርገኒ። አዕረጎሙ ደብረ ነዋኀ። አዕረግዎ ለቅዱስ ውስተ ሐመር። ወሶበ መልአት አዕረግዋ ውስተ ሐይቅ ፡ (ዕር ፡ ኢሳ። ማር፱ ፡ ፪። ስንክ ፡ ኅዳ፳፰። ማቴ፲፫ ፡ ፵፰)።
፡ አኮረበ፤ ሰጠ፤ አበረክተ፤ የመሥዋዕት የጸሎት የምስጋና። አዕረጎ ለይሥሐቅ ወልዱ ውስተ ምሥዋዕ። እለ ያዐርጉ ጸሎትሙ ለቅዱሳን። ኪያከ ይሴብሕ፤ ወለከ ያዐርጉ ስብሐተ ፡ (ያዕ፪
፡ ፳፩። ጦቢ፲፪
፡ ፲፭። መዋሥ)።
አዕረፈ ፡ አሳረፈ፤ ዕረፍት ሰጠ፤ ቦታ አዘጋጀ። ያረውጾን ወኢያዐርፎን። አዕርፋ ለነፍስየ። ያዐርፋ ለእሙ። ወአዕረፈ ሊተ ፈጣሪየ መንበርየ ፡ (ሄርማ። ፊልሞ
፡ ፳። ሢራ፫ ፡ ፮። ፳፬ ፡ ፰)።
አዕራፍ ፡ ዕርፈ መስቀሎች፤ ዕርፎት።
አዕርክት ፡ ወዳጆች፤ ባልንጀሮች። ብዙኃን ይኩኑከ አዕርክተ። ጸላእትኒ አዕርክተ ይከውኑ። ህየንተ አዕርክቲሁ
፡ (ሢራ፮ ፡ ፮። ምሳ፲፭ ፡ ፳፰። ዮሐ፲፭ ፡ ፲፫)።
አዕቀበ ፡ አስጠበቀ፤ ዘበኛ አቆመ፤ ዐደራ አለ፤ ሰጠ፤ አኖረ። ወአዕቀበ አህጉሪሆሙ። የዐቅቡ ሕገ፤ እስመ ህርቃኖስ አዕቀቦሙ ዘንተ። ዘአዕቀቦ ንጉሥ። አዕቀብክዎ ለጋብኤል ዐሠርተ መካልየ ብሩር። ለዘአዕቀብዎ ብዙኀ፤ ይትኃሠሥዎ ብዙኀ ፡ (ዮዲ፫ ፡ ፮። ዮሴፍ። ኤር፴፪ ፡ ፫። ጦቢ፩ ፡ ፲፬። ዲድ
፡ ፮)።
አዕቀጸ ፡ አሰነከለ፤ አሳሰረ፤ አስቀየደ።
አዕቀፈ ፡ አስነቀፈ፤ ዐነቀፈ አሰናከለ፤ ዕንቅፋት አኖረ።
አዕበረ ፡ አሳለፈ፤ አሻገረ። አደረቀ አመከነ።
አእበነ ፡ አደነገየ፤ ደንጊያ አደረገ። እግዚ አእበና ወሜጠ ህላዌሃ ለከዊነ ሐውልት
፡ (መጽ ፡ ምስ። ዘፍ፲፬ ፡ ፳፮)።
አእበየ ፡ እንቢ አሰኘ ፥ እንቢታ አስተማረ፤ እንቢ በል አለ።
አዕበየ ፡ አሳደገ፤ ከፍ አደረገ፤ አላቀ፤ አበለጠ፤ አከበረ፤ አገነነ፤ አኰራ አጓደደ አስታበየ። አበዛ አጸና። ጥበብ አዕበየቶሙ ለደቂቃ። አዕበዮ እግዚ ለሰሎሞን። ኢታዕቢ ርእሰከ። ታዐብዮ እምነ ቢጹ። አዕበየ ምግባረ። መጠነ አዕበየ አፉሁ
፡ (ሢራ፬ ፡ ፲፩። ፩ዜና ፡ ፳፱ ፡ ፳፭። ሢራ፩ ፡ ፴። ፲፭ ፡ ፭። መክ፪ ፡ ፬። ዮዲ፮ ፡ ፲፯)። በአዕበየ ፈንታ አስተዐበየ ይላል እንዳማርኛው፤ አያሰኝም። ዘአስተዐበይኮሙ በኀጢአቶሙ። አእምሮሰ ያስተዔቢ። ወኢያስተዔቢ ልበ ፡ (፩ቆሮ ፡ ፰ ፡ ፩። ፲፫ ፡ ፬። ገድ ፡ ኪሮ)።
አእበደ ፡ አሳበደ፤ እብድ አደረገ። አሰነፈ፤ አሞኘ አታለለ ሸነገለ፤ ናቀ አቃለለ። ለምንት ታአብድ ሰብአ ኦ ሰይጣን። ያአብድዎሙ አጋንንት፤ በቁሙ
፡ (ገድ ፡ ተክ። ኩፋ ፡ ፲)። ኢታእብደኒ። አኮኑ አእበዳ እግዚ ለጥበበ ዝ ዓለም። አእብዳ ለነፍስከ
፡ (ጦቢ፲ ፡ ፯። ፩ቆሮ ፡ ፩ ፡ ፯። ማር ፡ ይሥ፪ ፡ ፲፩)። በአእበደ ፈንታ አስተእበደ እንደ ማለት አስተአበደ ይላል። ትክልኑ ታስተአብዶ ለእግዚ። አልቦ ዘያስተአብዳ ለውርዙትከ። ኢያስተአብዱ ወኢያስተአክዩ ትእዛዘ እግዚ
፡ (ሮሜ፪ ፡ ፬። ፩ጢሞ ፡ ፬ ፡ ፲፪። ቀሌ)።
አእባዲ ማእበዲ መስተአብድ ፡ የሚያሳብድ፤ የሚያሰንፍ፤ አስናፊ፤ አጥፊ። ቀታሌ ሰብእ ማእበዲ
፡ (ኪዳ ፡ ፩)።
አእተተ ፡ አራቀ፤ አስራቀ፤ አስወገደ፤ አሰደደ፤ አስጣለ አሶለቀ። ናአትቶ ለልጹቅ ወናቄርቦ ለርሑቅ። አእትቱ እምፍኖት እብነ። ታእትቶ ለዝሉፉ። አእትት አልባሰ ርሱሐ እምላዕሌሁ
፡ (ቅዳ ፡ ግሩ። ኢሳ፷፪ ፡ ፲። ኢዮ፲፬ ፡ ፳። ዘካ፫ ፡ ፬)።
፡ ገደለ፤ አጠፋ፤ በቁሙ፤ አተተ ከቍጥር አወጣ። ከመ ያእትቶሙ። ኢያእተተ ዘርዖሙ። ወእምዘተርፈከ አሐደ አእትት
፡ (ኩፋ ፡ ፲፮። ሢራ፵፯ ፡ ፳፪። መር ፡ ዕዉ)።
አእተወ ፡ አገባ፤ አስገባ፤ መለሰ፤ አመጣ። ኵሎ ጾረ ያአትዉ ኢየሩሳሌም። ያአትዎሙ ብሔሮሙ። ያአትዉ ጸባሕተ ለንጉሥ
፡ (ነሐ፲፫ ፡ ፲፭። ኢሳ፲፬ ፡ ፪። ፩ዕዝ ፡ ፬
፡ ፮)።
አእነመ ፡ አሠረ፤ አሰፋ፤ አስጠለፈ። አእነመ ላዕሌሁ አምሳለ ኪሩቤል
፡ (፪ዜና ፡ ፫ ፡ ፲፬)።
አዕነቀ ፡ አሸከመ፤ ጫነ፤ አስነገተ፤ አሳሰረ። አቡየ አዕነቀክሙ ጋጋ ክቡደ። ኣዐንቆ ባዝግና ወርቅ ውስተ ክሣዱ። አዕነቅዋ ባዝግና ወርቅ ፡ (፫ነገ
፡ ፲፪ ፡ ፲፩። ዳን፭ ፡ ፯። ገድ ፡ ተክ)።
አእኑስ ፡ (ዕብ አናሽም) ሰዎች፤ ወንዶች፤ ተባቶች። የግእዝ መጽሐፍ ግን አንስ አኑስ በማለት ፈንታ ተባዕት፤ ሰብእ፤ ዕደው ይላል ፪ኛም አንስት ብሎ ፥ ብዥውን አእንስት በማለት ፈንታ መልሶ አንስት አንስትያ ፥ አእኑስ ይላል፤ ተሳሳተ ነው። ተባዕተ ወአንስተ ፈጠሮሙ። አልቦ ተባዕት ወአልቦ አንስት። ኢያሕየዉ ኢተባዕተ ወኢአንስተ። ሤጡ ለተባዕት ኀምሳ፤ ወለአንስትሰ ሤጣ ሠላሳ። አፍራስ አንስት። ቡርክት እምአእኑስ። አፍራስ አእኑስ። አእዱግ አእኑስ
፡ (ዘፍ፩ ፡ ፳፯። ገላ፫ ፡ ፳፰። ፩ነገ ፡ ፳፯
፡ ፱። ዘሌ፳፯ ፡ ፫። ፫ነገ ፡ ፲
፡ ፳፮። ደራሲ። ፪ዜና ፡ ፱
፡ ፳፭። ኢዮ፩ ፡ ፫ ፡ ፲፬)። አእኑስ የአንስ ብዥ እንደ ኾነ አስተውል።
አዕኑግ ፡ ጕትቾች፤ ቀለበቶች፤ ንፎዎች፤ መንደልቶች
፡ (ዘፍ፳፬ ፡ ፳፪። ኢሳ፫ ፡ ፳። ሕዝ፲፮ ፡ ፲፪)።
አዕናቍ ፡ ዕንቆች፤ የከበሩ ደንጎች። ሰሐባ ለጥበብ እምአጸዕናቍ ፡ (ኢዮ፳፰ ፡ ፲፰)።
አእናፍ ፡ (ፋት) አፍንጮች። አንፍ ተረተር መስሎ የወረደው፤ በመካከል የተሰነደደው፤ ተረተሩ ርሱው ራሱ፤ አእናፍ መስኮቱ ብሱ። ሰላም ለአእናፍኪ መሳክወ ሠናይ መዐዛ። ይትመተሩ አእናፊሆሙ። እስከ ይወፅእ እምውስተ አእናፋቲክሙ
፡ (ደራሲ። ፍ ፡ ነ ፡ ፵፰። ዘኍ፲፩ ፡ ፳)።
አእከለ ፡ አቡላ፤ አስበላ፤ አበቃ አብቃቃ ጠገበ በቃኝ አለ፤ ፈጸመ ጨረሰ፤ አስጨረሰ። ወአእከልኩ። ከመ አእኪልየ ኢይኩን ሐሳዌ። ወኀበኒ ኢያእከልኩ። ወአእከሉ በርእይ። አእከለ ለቤዝዎቱ። ሶበ አእከለ ተምህሮ መዝሙረ ዳዊት
፡ (ሢራ፲፩ ፡ ፲፱። ምሳ፳፬ ፡ ፴፪። ፪ቆሮ ፡ ፲፩
፡ ፱። ጥበ፲፫ ፡ ፯። ዘሌ፳፭ ፡ ፳፮። ገድ ፡ ኪሮ)። በአእከለ ፈንታ አስተአከለ ይላል፤ አብቃቃ ለማለት፤ ፍችው አንድ ነው። ምድር እንተ ኢኮነት በአስተአክሎ ዘትበልዖ ፡ (ዘዳ፰ ፡ ፱)።
አእከየ ፡ አከፋ፤ አባሰ አስከፋ አስባሰ፤ ክፉ አደረገ አስደረገ፤ አስተነኰለ። ሰይጣን አእከየ ልበ አይሁድ ላዕለ ክርስቶስ። አእከዩ ልቦሙ። አብዝኀ አእክዮ ምግባሪሁ። ያአኪ ዐይኖ ላዕሌከ
፡ (አርጋ ፡ ፪። ሢራ፲፮ ፡ ፲። ኩፋ ፡ ፴፭)።
አእኰተ ፡ (ያአኵት ፡ ያእኵት) አስመሰገነ፤ አስመረቀ። ባለቅኔዎች ግን አእመረን ዐወቀ አሳወቀ እንዲሉ አእኰተንም በኹለት ጾታ ይፈቱታል፤ ከማስደረግ በቀር አድራጊነት አይስማማውም፤ የአን አፈታት ተመልከት።
አእኳቲ ፡ አስመስጋኝ። ይህነንም አመስጋኝ ይሉታል።
አዕወረ አዖረ ፡ (ያዐውር ያዑር) ዐወረ፤ አሳወረ፤ ዐይን አወጣ፤ አሶጣ ዕውር አደረገ፤ አስደረገ። ወአዕይንቲሁ፤ ለሴዴቅያስ አዖረ። አዑሮሙ አዕይንቲሆሙ ወአዖሮሙ። ሕልያን ያዐውር ዐዕይንተ ፡ (ኤር፵፮ ፡ ፯። ፬ነገ ፡ ፮ ፡ ፲፰። ዘፀ፳፫ ፡ ፰)።
አዕዋም ፡ ዝኒ ከማሁ። ነዋኃት አዕዋም። ውስተ አዕዋሚሃ ፡ (ኢሳ፴፯ ፡ ፳፬። ኤር፳፩ ፡ ፲፬)።
አዕዋድ ፡ (ዳት) ዙሪያዎች፤ ዐውድሞች፤ ሸንጎዎች። አውራጆች፤ ቀበሌዎች። ያገብኡክሙ ውስተ አዕዋድ። ነቢረ ፍጽም በውስተ አዕዋዳት። ምኔታት ዘአዕዋደ እለእስክንድርያ ፡ (ማቴ፲ ፡ ፲፯። ፳፫ ፡ ፮። ፊልክ ፡ ፲፰)።
አዕዋፍ ፡ (ፋት) ወፎች፤ በራሮች። ነጽሩ አዕዋፈ ሰማይ። እምኵሉ አዕዋፍ ትንእስ ንህብ። ዘወገሮን አዕዋፍ
፡ (ማቴ፮ ፡ ፳፮። ሢራ፲፩ ፡ ፫። ፳፪ ፡ ፳)።
አዕያግ ፡ (ጋት) ኵሬዎች፤ የውሃ መቋሞች። አዕያጊሆሙ። አዕያጋተ ማይ። ዝናም መልአ ኵሎ አዕያጋተ ዘሀሎ ኀቤሆሙ ፡ (ዘፀ፯ ፡ ፲፱። ዘሌ፲፩ ፡ ፴፮። ዮሴፍ)።
አእይ ዮት ፡ (አአየ የአኢ የአኢ) ወደ ወጡበት መመለስ፤ መግባት። መስማት፤ እህ ማለት።
አዕይንት ፡ ዐይኖች፤ የሥጋ መብራቶች። ይኔጽራ አዕይንቲሁ። ጠፍኣ አዕይንቲነ ፡ (ኢሳ፲፯ ፡ ፯። ሰቈ፬ ፡ ፲፯)።
አዕደወ ፡ አሻገረ፤ አሳለፈ። አዕድዎ አዕደዎሙ ገብርከ። አዕደዎቶሙ ባሕረ መፍርሀ። ወአዕደወኒ ውስተ ማይ
፡ (ኢያ፯ ፡ ፯። ጥበ፲ ፡ ፲፰። ሕዝ፵፯ ፡ ፫)።
አዕዳል ፡ (ዕብ ካትኖት። ጽር ኺቶኔስ) ኪቶች፤ ቀሚሶች፤ ኮቶች፤ ኵታዎች። ወገብረ ሎሙ አዕዳለ ማእስ፤ ወአልበሶሙ ፡ (ዘፍ፫ ፡ ፳፩)። ማእስ የሚያሞቅ የሚለሰልስ፤። ጠጕራም የደበሎ ቀሚስ ማለት ነው፤ ትርጓሜ ኦሪት የጥንቸል ቈርበት ነው ይላል። አልበሶሙ ማለት፤ ልብሱ ሳይቀር ፍርዱንም ያሳያል፤ ፍርድ ልበስ እንዲሉ።
አዕገተ ፡ አሳገተ፤ አስከበበ፤ አሳጠረ፤ ወጥመድ አኖረ።
አእጋር ፡ (ራት) ዝኒ ከማሁ ፥ እግሮች። አእጋራት፤ የብዙ። ኦ አእጋር እለ አንሶሰዋ ውስተ ገነት ተቀነዋ በቅንዋት። ሰላም ለአእጋሪከ እለ ጠባዓ ለቀዊም ፡ (ቅዳ ፡ አፈ። ደራሲ)
አዕጠቀ ፡ አስታጠቀ። አዕጥቁኒ ኀይላቲክሙ ወአቅንቱኒ ለጸብእ
፡ (ስንክ ፡ ታኅ፲፬)።
አዕጸበ ፡ አስጨነቀ፤ አባሰ፤ አጸና አበረታ። ወለዘፈቀደ ያዐጽብ። አዕጸቡ ተቃትሎ
፡ (ሮሜ፱ ፡ ፲፰። ፊልክ)።
አዕጹቅ ፡ (ቃት) ቅጥዮች፤ ጫፎች፤ ፍሬዎች። አዕጹቂሃ ኢይፈርዩ። ኖኃ አዕጹቅየ። ክልኤ አዕጹቀ በለስ። አዕጹቃተ ወይን ፡ (ሢራ፳፫ ፡ ፳፭። ፳፬ ፡ ፲፮። ኤር፳፬ ፡ ፩። ስንክ ፡ መስ፩)። አዕጹቀ ተቅዋም ቢል አገዶች ማለት ነው፤ ምስጢሩ ግን ከዚያው ከዐጽቅነቱ አይወጣም ፡ (ዘፀ፴፰ ፡ ፲፬–፲፭)።
አዕጻድ ፡ (ዳት) ቦቶች፤ ወዠዶች፤ ገጠሮች። አዕጻዳቲሆሙ ለኖሎት። ተስዑ አህጉር ወአዕጻዳቲሆን
፡ (ማሕ፩ ፡ ፯። ኢያ፲፭ ፡ ፴፪። ማቴ፲ ፡ ፲፩)።
አዕፅምት ፡ ዐጥንቶች፤ የገላ ክፍሎች። ኵሉ አዕፅምት፤ የብሱ አዕፅምቲነ ፡ (ሕዝ፴፯ ፡ ፲፩)።
አዕጽፍት ፡ ዐጽፎች፤ መጐናጠፊያዎች። ወልቡሳን አዕጽፍተ ፡ (፪ዜና ፡ ፲፰ ፡ ፱)።
አዖቀ ፡ አሳወቀ፤ አስታወቀ፤ ገለጠ፤ አስረዳ። ነገርከ ያዐውቀከ። ናሁ አዖቁክሙ ከመ ኢይፈቅድ ንሥተተ ወአዖቁ ዕልወቶሙ። ኢያዖቀ ፍድፋዴ ክብሮሙ
፡ (ማር፲፬ ፡ ፸። ዮሴፍ። አፈ
፡ ድ፩ጃ)።
አዖደ ፡ አዞረ፤ አሳወደ፤ ዐዋጅ አስነገረ። ያዐውድ መንኰራኵሪሁ። ከመ ያዑድ ዐዋዴ ቅድሜሁ። አዖደ ውስተ መርሕበ ሀገር
፡ (ሢራ፴፰ ፡ ፳፱። ዮሴፍ። አስቴ፮ ፡ ፲፩)።
አከለለ አስተከለለ ፡ (533) አስተከለለ፤ አስከለለ፤ ተክሊል አስደረገ፤ አክሊል አሠራ፤ አስደፋ።
አከፈ [1] ፡ አበሰ ጠረገ፤–ካፍ ወኪፍ ወከፈ።
[2] ፡ (የአክፍ ይእክፍ። አውከፈ) አበሰ ጠረገ። ወአከፈት አንብዐ ወለታ። ዐፈሠ ዛቀ፤ ጋፈ ጠረገ፤ የምርት የመሬት። አካፋ ማለት ከዚህ ወጥቷል።
አኵስሐ ፡ አስኰሳ፤ አሳራ አስቀዘነ።
አኵስም ፡ (ዕብ አ ኵሽም) አ ጥንት ቀዳማዊ ርእስ፤ ኵሽም ኵሻውያን የኵሽ ልጆች፤ ሕዝበ ኵሽ ነገደ ኵሽ። አኵሽም፤ ጥንታዊት ቀዳማዊት የነገደ ኵሽ መዲና የአህጉረ ኵሽ ራስ፤ እሞን ለአህጉረ ኵሽ። ወዲበ ርእሰ ሀገረ አበዊነ
፡ (ቅዳ ፡ ሕር)። ኵሳ አኵስም ማለት በሐዲስ ግእዝ ነው፤ በሳባና በጥንታዊ ግእዝ በዐረብ በሱርስት በዕብራይስጥ በሴም ቋንቋ ኹሉ ኵሽ እንጂ ኵሳ አይባልም ፡ (ዘፍ፲ ፡ ፯)። ዐማሮች አኵስም የሚሉትን ትግሮች አክሱም ይሉታል፤ ይኸውም ዐብይ ነብይ ጸም መገስ ሞጎስ በቱ ለቱ እንደሚሉት ያለ ነው እንጂ ፥ እውነተኛ አጠራር አይዶለም፤ እውነተኛውስ አኵስም ነው። ፪ኛም ቦ ዘይቤ ታሪክ፤ አኵስም ማለት ኰሰኰሰ ኰተኰተ ከማለት ካትክልት ሥራ የመጣ ነው፤ ትርጓሜውም የተክል ቦታ ማለት ነው ይላል፤ በዙሪያዋ ያሉት አህጉር ግን ጎረ ቤቶቿና አቅራቦቿ፤ አክሱም ዐድ ሕሡም ይሏታል።
አኪል [1] ፡ ማከል፤ መተካከል እኩያ አምሳያ መኾን ለሌላው። ወመለኮትሰ ኢይትበሀል ዘንተ የአክል ወዘንተ ይመስል ፡ (ቅዳ ፡ ሕር)።
[2] ፡ አኪል፤
፡ (ጥገ) መገመት መታሰብ መቈጠር ይህን ያኽል መባል፤ መኾን። ምስጢሩ ከዚያው ይገባል። እለ ይውኅዱ የአክሉ እልፈ። ወየአክሉ ገነውቱ ለቤል ሰብዓ። ወኵሉ ሕዝብ የአክሉ እልፈ ብእሴ። ወነበሩ ህየ ዘየአክል ዐሥርተ ዓመተ። ወየአክል ሠላሳ ክረምቱ ፡ (ኢሳ፷ ፡ ፳፪። ዳን፲፫ ፡ ፲። ፩ነገ ፡ ፲፬ ፡ ፳፪። ሩት፩ ፡ ፬። ሉቃ፫ ፡ ፳፫)።
[3] ፡ ማደግ፤ መጨመር፤ አካለ መጠን ማድረስ፤ ምሉእ ፍጹም አካላዊ መኾን ለራሱ፤ ቡቃያ ከዘረዘረና ከሸተ በኋላ ያው ያበስላል እንጂ ፥ ቁመት እንዳይጨምር እንደዚያ ማለት ነው። እስከ ይበጽሕ ወሬዛ ለመጠነ አካል። ለእመ ኢበጽሐ አካለ ፍጻሜሃ ፍጻሜ መጠነ አካል
፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፳፬)።
[4] ፡ መብቃት፤ መብቃቃት፤ በቂ ልከኛ መኾን አለማነስና አለመትረፍ። ኢየአክል ኵሉ መሥዋዕት ለመዐዛ ሠናይ። ኢየአክል ሊባኖስ ለአንድዶ። ኢአከሎሙ ስሕተት። እመ ኢየአክል ለሤጠ በግዕ። ዘኅዳጥ የአክሎ። አከሎሙ ወተርፎሙ
፡ (ዮዲ፲፮ ፡ ፲፮። ኢሳ፵ ፡ ፲፮። ጥበ፲፬ ፡ ፳፪። ዘሌ፭ ፡ ፯። ሢራ፴፬ ፡ ፲፱። ዘፀ፴፮ ፡ ፯)።
[5] መወሰን መደንገግ፤ ሕግ። ማግመር መክተት፤ መቻል፤ የቦታ። ምስጢሩ መብቃት ነው። ዘሰማይ ኢየአክሎ። ወኢአከሎሙ ምድር ፡ (፫ነገ ፡ ፰
፡ ፳፯። ዘፍ፲፫ ፡ ፮)።
አኪል ሎት ፡ (አከለ የአክል ይእክል። ዕብ አካል። ሱር ኤካል። ዐረ አከለ) መብላት መመገብ፤ መጕረሥ መቃም፤ ማላመጥ መዋጥ፤ ምግብን ወደ ሆድ ጐተራ ማግባት መክተት። ባለቅኔዎች ግን በአከለ ፈንታ አከጠ ብለው ይገሳሉ፤ የተሳሳተ ነው።
አኲት
ቶት ፡ (አኰተ የአኵት ይእኵት) ማመስገን፤ መባረክ መመረቅ፤ መየበብ ምስጋና ማቅረብ፤ ማገልገል በእጅ በቃል። መጽሐፍ ግን በአኰተ ፈንታ አእኰተ ይላል፤ የተሳሳተ ነው። አእኰተ ባረከ ወፈተተ። አእኵትዎ ጥቀ። አአኵተከ እግዚኦ። አእኵቶ ለዘጸገወከ። ብእሲት እንተ ኢተአኵቶ ለምታ
፡ (ቅዳ። ዮዲ፮ ፡ ፳። ኢሳ፲፪ ፡ ፩። ፈላስ። ሢራ፳፭ ፡ ፳፫)።
አኪው ዎት ፡ (አከወ የአኩ ይእኩ) መሸፈጥ ፥ ዐሎ ማለት ፥ ጽድቁን ባሉታ መለወጥ። አከየን ተመልከት የዚህ መንቲያ ነው።
አካሊ ፡ (ሊት ልያን ያት) የሚበቃ በቂ ልከኛ። ለእመ ኮኑ ሰማዕታቲሁ ኢአካልያነ ይትኃሠሥዎ ከመ ይወስክ ለአጠይቆ
፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፵፫ ፡ ፯)።
አካል ፡ (ላት)
[1] ፡ በቁሙ፤ ፍጹም ገጽ ፍጹም መልክ ያለው፤ ራሱን የቻለ ለራሱ የበቃ፤ እኔ የሚል ህላዌ ፥ ነባቢ፤ ቁመት ቁመና፤ የባሕርይ የግብር የስም ባለቤት፤ እገሌ የሚባል። እኔ ማለትም የሚገባ ዕውቀት ቀዋሚነት ላላቸው ለማይሞቱና ለማይጠፉ ለሦስት ብቻ ነው፤ ለአምላክ ለመልአክ ለነፍስ። በከመ አብ ህልው በአካሉ ወወልድኒ ከማሁ። ዘኢየአምን ከመ ውእቱ አሐዱ አካል እምሠለስቱ አካላት። እስመ ህላዌሁ ለቃል አው አካሉ ኢይትበሀል ካልአ ዘእንበለ አካለ ርእሱ ባቲቱ ዘውእቱ ቃል
፡ (አፈ ፡ ድ፪። ሃይ ፡ አበ)። አካል ያለባሕርይ ብቻውን አይቆምም፤ ባሕርይም ያላካል አይፈጸምም። ባሕርይና አካል እንደ ሥርና እንዳጽቅ፤ እንደ ነቅና እንደ መትረብ፤ እንደ ቅንጣትና እንዳገዳ ናቸው። በከመ ሠዊት ይትወለድ እምነ ዕራቁ ኅጠት ፡ (ማር ፡ ይሥ ፩)። ከዚህ ምሳሌም የተነሣ፤ ሥራ የባሕርይ ፍሬ ይባላል። ዳግመኛም ከራስ ጠጕር እስከ እግር ጥፍር ባጥነት በዥማት በሥጋ በቈርበት ተያይዞና ተሸፍኖ ያለው ባንድነት አካል ይባላል። አካለ ጐደሎ እንዲሉ። ኵሉ መሌሊት ይትበሀል አካለ። አካል በዘየአክል
፡ (አዋል)። አካል መባሉም በነፍስ ዕውቀትና በነፍስ አካልነት ነው እንጂ ፥ በራሱ በገንዘቡ አይዶለም፤ በገንዘቡስ የነፍስ መሣሪያ እንደ መኾኑ ፥ ሥጋ ገላ ይባላል፤ ይኸውም ገልዓዊ ገልዕ ጕልሕ ግልጥ ግዙፍ፤ የሚታይ የሚያዝ የሚዳሰስ፤ አፍኣዊ መሬታዊ ሕዋስ፤ እንስሳዊ ባሕርይ ማለት ነው። ፡ (ተረት) ልብስን ዐጥቦ ለገላ፤ ብርሌን ዐጥቦ ለጠላ። የሰው ገላ ርጥብ ሸክላ፤ ያልተተኰሰ ያልተኰላ። ፡ (ግጥም) ከዚያ ቤት ያለች ሸክላ ሠሪ ፥ ድኻ ናት አሉ ጦም ዐዳሪ፤ ማን አስተማራት ጥበቡን ገል ዐፈር መኾኑን
፡ (ገላ)። መሣሪያነቱም በዚህ ይታወቃል፤ ርሷ ስትለቀው በመውደቁ። ወአካልየኒ ወኢከመ ምንት በቅድሜከ። ወኢአካልየ በመትሕተ ምድር ፡ (መዝ ፡ ፴፰። ፻፴፰)። የህላዌንና የጠባይዕን ፍች ተመልከት፤ የዚህ ዘውግ ነው።
[2] ፡ ልክ፤ ዐቅም፤ መጠን። ለእሳትሰ ቦቱ መጠን ወቦቱ አካል። ዕፅ ዘይፈሪ ዕሩየኑ ይሁብ ፍሬሁ አኮኑ በበ አካሉ
፡ (በያቅሙ በየመጠኑ)። ሥጋ ዘነሥአ በአካለ ህላዌነ፤ በባሕርያችን መጠን ማለት ነው ፡ (ቅዳ። ኪዳ። ሃይ ፡ አበ)።
[3] ፡ አካል፤ ግዘፍ ወፍር ድንዳኔ፤ ታላቅነት። አሕማር ዘመጠነ ዝ አካሎሙ
፡ (ያዕ፫ ፡ ፬)።
አካዕ ፡ (ጽር አካይዖ) ስመ አምላክ፤ በመሐላ ጊዜ የሚጠራ። አ አልፋ፤ ካ ካይ ዋዌ፤ ዕ ዖሜጋ፤ አካዕ አወዖ፤ አልፋ ወዖ፤ ቀዳማዊ ወደኃራዊ፤ ርእስ ወማኅለቅት፤ ጥንት ወተፍጻሜት ማለት ነው። ባለብሉዮች ግን አምላክ ከሃሊ ይሉታል። ወአንበሮ ለዝ መሐላ አካዕ በእዴሁ ለሚካኤል። ሰላም ለእራኅከ ስመ መሐላ ዘፀበጠ
፡ (ሔኖ። ደራሲ)።
አካጥስ ፡ (ጽር አካቲስ፤ ዕብ ሽቦ) ዕንቍ፤ የዕንቍ ስም፤ ካ፲፪ አዕናቍ አንዱ
፡ (ዘፀ፳፰ ፡ ፲፱። ፴፮ ፡ ፲፱)።
አኬደ ፡ አስረገጠ፤ አበራየ። ኢትፍፅሞ አፉሁ ለላሕም ሶበ ታከይድ አክለከ። ወዘኒ ያከይድ እክለ ፡ (፩ጢሞ ፡ ፭ ፡ ፲፰። ፩ቆሮ ፡ ፱ ፡ ፱ ፡ ፲)።
፡ አስኬደ፤ አስሮጠ፤ ነዳ። አኬድከ ውስተ ባሕር አፍራሲከ። ወያከይዳ ለሐመሩ ፡ (ዕን፫ ፡ ፲፭። ማር ፡ ይሥ፳፰)። በዐጸደ ፈንታ አኬደ ይላል፤ የመላሽ ስሕተት ነው፤ ለእመ አኬድከ እክለ ገራህትከ። ያከይድ ዘርዐ ሠዊት ፡ (ዘዳ፳፬ ፡ ፲፱። ኢሳ፲፯ ፡ ፭)።
አክ(ቅ)ደር ፡ (ጽር ወዕብ) ጥቍር ጠቋራ ክሰልማ። ጽልመት ጽላሎት፤ ጨለማ። ቄዳርስንና ቄድሮስን እይ፤ ከዚህ ጋራ ፩ ነው፤ ቀና ከ ተወራርሰዋል።
አክሀለ ፡ አስቻለ አበረታ፤ አበቃ መብት ሰጠ አሰናበተ። ኵሎ እክል በዘውእቱ አክሀለኒ። እግዚ አክሀለነ በኵሉ ዘንፈቅድ። ያክህልክሙ እግዚ ለገቢረ ኵሉ ፈቃዱ። ወኢያክሀሎ ከመ ይቅረብ ኀቤሆሙ
፡ (ፊልጵ፬ ፡ ፲፫። ዮሴፍ። ግንዘ። ማር ፡ ይሥ፮ ፡ ፪)።
አክሃሊ መክህል ፡ የሚያስችል፤ አስቻይ።
አክሀነ ፡ አስካነ፤ ክህነት ሰጠ ሾመ፤ ካህን አደረገ። ያክህኖሙ ፡ (ቀኖ ፡ ኒቅ ፡ ፷፮)። ክህነት አሰጠ አሾመ፤ ካህን አስደረገ።
አክሐደ ፡ አስካደ፤ አስከዳ ዐሎ አሰኘ፤ አሳበለ፤ ከሓዲ አደረገ። አኀዊክሙ አክሐድዎሙ ለልብክሙ። አክሐድዎሙ ወይቤልዎሙ ንዑ ናምልክ ባዕደ
፡ (ዘዳ፩ ፡ ፳፰። ፲፫ ፡ ፲፫)። በክሕደና በአርሐቀ ፈንታ አክሐደ ይላል፤ የመላሽና የጣፊ ስሕተት ነው። ኢአምንዎን ወአክሐድዎን። አይድዐተነ ወአክሐድናሃ። ይቤ፤ መኑ አክሐደከ
፡ (ሉቃ፳፬ ፡ ፲፩። ኪዳ። ቄር ጰላ)። እስመ ያክሕዶ ለወልድከ እምኔየ፤ ወያመልክ ባዕደ። ትዕቢት ታክሕዶ እምነ ፈጣሪሁ ፡ (ዘዳ፯ ፡ ፬። ሢራ፲ ፡ ፲፪)። በአክሐደ ፈንቃ አስተክሐደ አስተከሐደ ይላል፤ ፍችው አንድ ነው። ከመ ያስተክሕዶ ጸጋ እግዚ እንተ ነበረት ላዕሌሁ። ቶማስ አስተከሐዶሙ ለአኀዊሁ ፡ (ቀሌ ፡ ገ፭። መጽ
፡ ምስ ፡ ገ፷፰)።
አክሓዲ ፡ መክሐዲ፤ መክሕድ፤ የሚያስክድ አስካጅ፤ አስከጅ።
አክሊል [1] ፡ በቁሙ፤–ከልሎ ከለለ።
[2] ፡ (ላት። ዐረ ኢክሊል። ሱር ክሊላ) ይቁሙ፤ ዘውድ፤ የራስ ጌጥ ሽልማት፤ የክብር ጕልላት። ወድቀ አክሊለ ርእስነ። አክሊለ ጽጌ። አክሊል ዘሦክ። ንሣእ ወርቀ ወብሩረ ወግበር አክሊላተ። አክሊለ ክህነት ወመንግሥት። አክሊል ዘእምዕንቍ ክቡር ፡ (ሰቈ፭ ፡ ፲፮። ደራሲ። ማር፲፭ ፡ ፲፯። ዘካ፮ ፡ ፲፩። ሳታት። መዝ ፡ ፳)።
፡ ኵፌት ቆብ ጥምጥም፤ የራስ ልብስ ቀጸላ መሸፈኛ ጌጥነት ያለው ፡ (ዘሌ፰ ፡ ፱)። መጽነፍትንና ቄዳርስን እይ፤ ከዚህ ጋራ አንድ ነው።
አክሊሮስ ፡ (ጽር ክሊሮስ፤ ክሊሪኮስ) ቄሰ ገበዝ፤ የቤተ ክሲያን ሹም፤ አስተንታኝ። ለእመ ሰረቀ አክሊሮስ ዘውእቱ ቀይሰ ገበዝ ንዋያተ ምሥዋዕ ፡ (ፈ ፡ መ ፡ ፲፯ ፡ ፮)።
አክማም ፡ የክንድ ልብሶች፤–ከሚም ከመ፤ ከመመ፤ ክማም።
አክሞሰሰ
፤ በጥቂቱ ሣቀ ፤
ከንፈሩን ገለጠ ፤ ጥርሱን ፍግግ ፊቱን ወገግ አደረገ። ሶበ
ይሥሕቅ አብድ ያዐቢ
ቃሎ ፤ ጠቢብሰ እምዕጹብ ያክሞስስ
ከናፍሪሁ። ወያክሞስሶሙ በየውሀት ለአብዳን።
አክሞስስ በኅቡእ
(ሢራ፳፩ ፡ ፳። ክብ
፡ ነገ፳፪። አፈ ፡ ድ፳፪)።
አክሰበ ፡ አስቈረጠ፤ አስገዘረ። ለአክስቦ ፡ (መጽ
፡ ምስ)።
አክሲማሮስ ፡ (ጽር፤ ሄክሳኢሜሮን) ስድስት ቀን ማለት ነው
፡ (አቡሻ ፡ ፲፬)። የመጽሐፍ ስም፤ የ፮ቱን ቀን ሥነ ፍጥረት አምልቶ አስፍቶ የሚናገር፤ ካያ ኹለት ብሎ የሚቈጥር፤ የኤጲፋንዮስ መጽሐፍ።
አክሲጦስ አው አግሲጦስ ፡ ያልታወቀ ጥሬ ትርፍ ቃል፤ በጽርኡም በዕንራይስጡም የሌለ። ባለብሉዮች ጉባኤ ነቢያት ጉባኤ ካህናት ይሉታል። ወትቤ አክሲጦስ አይቴ ሖረ ወልድ እኁኪ ፡ (ማሕ፭ ፡ ፲፯)። በማሕልይ ውስጥ ዐልፎ ዐልፎ እንደዚህ ያለ ይህን የመሰለ፤ እንደ ዚቅና እንደ ስሯጽ ከያሬድ በኋላ የገባ መዘምራን የማያዜሙት መምህራን የሚተረጕሙት ጥሬነት የሌለው ብዙ ትርፍ ንባብ አለ፤ ስሙንም ከጽርኡ ምላሽ ለይተው ዕብራይስጥ ይሉታል። ርሱ ግን ከግእዝ በቀር እንደ ሌላው ጥሬ በዕብራይስጥ አይገኝምና ግእዝ እንጂ ዕብራይስጥ ሊሉት አይገባም፤ ዕብራይስጥ ብሎ ስም የሰጠው ከማኽል አግብቶ ያስቀመጠው ከቶ ማን እንደ ኾነ አልታወቀም።
አክሳስ ፡ (ጽርእ) የእንስሳ ስም፤ ትንሣኤ ሙታንን የሚያስረዳ። ባለመጽሐፎች ግን ሺ እግር ፥ ቅንቡርስ ፥ የእበት ትል ይሉታል፤ እንጃ። ወእንስሳሂ ዘይሰመይ አክሳስ
፡ (ሃይ ፡ አበ ፡ ኤጲ)።
አክሶስያ ፡ (ጽር ኤክሱሲያ) ሥልጣን፤ ክሂል፤ ጌትነት። አክሶስያ ዘይደሉ ለመለኮት
፡ (ቄር ፡ ስምዓት)።
አክረመ ፡ አዘነመ፤ አከረመ አኖረ። ያከርም በበ ዓመት ፡ (ግብ፲፬ ፡ ፲፯)። አክርማ ማለት የዚህ ዘር ነው፤ እርጋሄን እይ።
አክረረ ፡ አከረረ፤ አስከረረ፤ አደረቀ ፥ በድንገት ገደለ። ፡ (ግጥም፤ ድኻ ገበሬ በራስ ዐሊ ጊዜ) ዐርሼ በበላኹ በቀንጃ በሬዬ፤ የዘንድሮን ዐሊ አክርሞት ጌታዬ። ኦ ሞት እግዚእየ አክርሮ ለዐሊ ማለት ነው።
አክረየ ፡ (አከራየ) አስኳተ አስቈፈረ። አክረይኩ ሎቱ ምክያዶ። ወደዩ ሥጋሁ ውስተ ገራውህ ዘአበው አክረዩ ፡ (ኢሳ፭ ፡ ፪። ስንክ ፡ ጥር፲፭)።
አክራጦን ፡ (ጽር አክራቶን) ጥሩ የወይን ጠጅ። አክራጦን ዘአልቦቱ ቱስሕት
፡ (ተረ ፡ ቄር። ኤጲ። አጋር)።
አክበረ ፡ አከበረ፤ አላቀ አበለጠ፤ አስከበረ አሶደደ። አክብር አባከ ወእመከ። አክበረ እግዚ አበ ላዕለ ውሉዱ። እግዚ አክበረከ ፡ (ዘፀ፳ ፡ ፲፪። ሢራ፫ ፡ ፪። ኢሳ፶፭ ፡ ፭)።
አክበበ ፡ አስከበበ፤ ጉባኤ አስደረገ።
አክበተ ፡ አስከበተ፤ አስደበቀ፤ አስጠበቀ።
አክበደ ፡ አከበደ፤ አስከበደ፤ አባዛ አጸና። አክበድኪ አርዑቶሙ ፈድፋደ። በኢያእምሮ ያከብድ ነገሮ። አክበደ ሙሴ ተክዞ ጥቀ። እለ ያከብዱ ዲበ አግብርቲሆሙ ቅኔ እኩየ። አክበድክሙ ላዕሌየ ነገረክሙ ፡ (ኢሳ፵፯ ፡ ፮። ኢዮ፴፭ ፡ ፲፮። ዘኍ፲፮ ፡ ፲፭። ዲድ ፡ ፳፩። ሚል፫ ፡ ፲፫)።
፡ ጫነ ጨቈነ አሸከመ፤ ምስጢሩ ያው ማክበድ ነው። ኢታክብድ ላዕሌሁ ጾረ ክቡደ። ይደሉ ከመ ያክብዱ ቀኖና ላዕሌሁ ፡ (ቀሌ። ፈ ፡ መ
፡ ፲፮ ፡ ፬)። በአክበደ ፈንታ አስተከበደ ይላል፤ ፍችው ፩ ነው። አስተክብዶ። ኢያስተክብድ ላዕሌሆሙ ፡ (ዲድ
፡ ፴፬ ፡ ፵፩)።
አክባሪ ፡ (ሪት ርያን ያት) በቁሙ፤ የሚያከብር የሚያስከብር። እስመ እሙንቱ መልክአ እግዚ አክባሪት እኵሎሙ ሰብእ ፡ (ፊልክ ፡ ፹፯)።
አክዐወ ፡ አስፈሰሰ። ያክዑ ደመ ላኳሆሙ ለአብዳን ፡ (ሢራ፳፯ ፡ ፲፭)።
አክዋል ዘዐርሞን ፡ ያርሞን ፍሬዎች፤ እንደ ትፋሕ ደስ የሚያሰኙ ፡ (መቃ ፡ ገ፫። ድጓ)። ዐርሞንንና ኤላጤን እይ። አክዋል ዘአርሞን ተብሎ በአልፍ ሲጣፍ ግን አርሞን በዕብራይስጥ ቃል ታላቅ ቤት ምኵራብ ነውና፤ የቤት ዙሪያ ጌጥ የጕልላት ሻኹራ መርገፍና አጫዋች ያሰኛል፤ ሕንባብን እይ።
አክይ [1] ፡ መስፋት፤ መግነን፤ የለምጽ የቍስል የክፉ ነገር። አክየት ይእቲ ሕብር
፡ (ዘሌ፲፰ ፡ ፰)።
[2] ፡ አክይ፤ መብዛት፤ ካሥር ማለፍ፤ ካያ መኾን መባል፤ ከኻያ መከፈል
፡ (ዐማርኛ)።
አክይ ዮት ፡ (አክየ፤ አከየ የአኪ ይእከይ ኪ) መክፋት፤ መባስ፤ ክፉ መጥፎ መኾን፤ የጠባይ የደዌ የመልክ። ፈድፋደ አክዩ። አልቦ ዘየአኪ እምርእሰ አርዌ ምድር። እምኵሉ ቍስል የአኪ ቍስለ ልብ። እምኵሉ አዕዋፍ ተአኪ ንህብ ፡ (ሄርማ። ሢራ፳፭ ፡ ፲፫ ፡ ፲፭። ፲፩ ፡ ፫)።
አክዮስ ፡ (ጽር አክሲዮስ) የምስጋና ቃል ጳጳስ ኤጲስቆጶስ ሲሾም የሚባል። ዕሦ ዕሦ ይበጅ ያድርግ፤ ሹመት ያዳብር እንደ ማለት። ወዓዲ ይበሉ አክዮስ፤ ይደልዎ ይደልዎ
፡ (ኪዳ። ስንክ ፡ ጥቅ፱
፡ ፳)።
አክደር ፡ (ዐረ አኅደር) የቅጠል ዐይነት ቅጠሊያ፤ አረንጓዴ። ወንጹፍ ጸፍጸፉ በሕብረ ወርቅ ወብሩር ወያክንት ወአክደር ወአስፋር
፡ (መቃ ፡ ገ፫)።
አክደነ ፡ አስከደነ አስለበሰ።
አክፈለ ፡ አስከፈለ፤ ኹለት አስደረገ።
አክፍአ ፡ አከፋ፤ አስከፋ፤ አፈዘዘ አሳወረ፤ አበላሸ አጣመመ። ነጽሮ ብርሃኑ ያከፍእ ዐይነ። መብረቅ ዘበአንበልብሎቱ ያከፍእ ዐይኖ ለዘይኔጽሮ። ያከፍእ ነገረ አምሳለ ወአርኣያ ፡ (ሢራ፵፫ ፡ ፬። መጽ ፡ ምስ። ተረ ፡ ቄር፳፪)።
አኮ ፡ (ጽር ኡኽ። ዕብ አኽ፤ ባሕቱ) ነባር፤ አሉታ አንቀጽ፤ እንኳን፤ አይዶለም አይኾንም፤ አይኹን፤ አይደረግ። ዳግመኛም ኑ ሲጨመርበት ጥያቄና አስረጅ እየኾነ በኹለት ይፈታል፤ አስረጅ ሲኾን ዐቢይ አገባብ ነው። አኮ ከመ ዝ ኃጥኣንሰ አኮ ከመ ዝ። አኮ አኮ በቅብዐ ደነስ። አኮ ሊተ ዘሦዕከ አባግዒከ። አኮሁ አነ ዘኣወልድ። አኮኑ ዛቲ ባቢሎን። አኮኑ ሰማርያ። አኮኑ ነዳያን እሙንቱ
፡ (መዝ ፡ ፩። ደራሲ። ኢሳ፵፫ ፡ ፳፫። ፷፮ ፡ ፱። ዳን፬ ፡ ፳፯። ሚክ፩ ፡ ፭። ኤር፭ ፡ ፬)።
አኮሰ ፡ አስደረጠ፤ አስበጠበጠ አስነቀነቀ።
አኰቴት [1] ፡ ምስጋና፤ አገልግሎት፤ መሥዋዕት። ከመ ተሀቡ አኰቴተ ለስምየ። ወሀበት ለእግዚአብሔር አኰቴተ ለቤተ እግዚአብሔር
፡ (ሚል ፪ ፡ ፪። ኩፋ ፳፭። ኤር ፲፯ ፡ ፳፮)። ምስጋናነቱም ባለፈ በተደረገ ነው፤ ሐሳብና ምኞት ሲፈጸም ለዚያ ለፈጻሚው በደስታ ቃል የሚቀርብና የሚነበብ የሚዜም ዜማ ነው፤ ንሴብሖ እንደ ማለት።
[2] ፡ አኰቴት፤ ቍርባን፤ ኅብስተ ቍርባን፤ የቍርባን ጸሎት ፍሬ ቅዳሴ፤ ነአኵቶ ነአኵተከ ብሎ የሚዠምር። እምድኅረ ተመጠዉ አኰቴተ። አኰቴተ ቍርባን ዘአበዊነ ሐዋርያት
፡ (ኪዳ። ቅዳ)።
አኮት ፡ ተናካሽ፤–ዐኪው ዐከወ።
አኰነነ ፡ አስፈረደ፤ አስገዛ አሠለጠነ፤ ፈራጅ አደረገ። ኣሜግቦ ምግበከ ወኣኴንኖ ምኵናኒከ። ለወልድከ ወለብእሲትከ ኢታኰንኖሙ ንዋየከ። በከመ አኰነንኮ ላዕለ ኵሉ ዘሥጋ ወነፍስ። አኰነኖሙ ለኵሎሙ አይሁድ ፡ (ኢሳ፳፪ ፡ ፳፩። ሢራ፴ ፡ ፳፰። ዮሐ፲፯ ፡ ፪። ዳን፫ ፡ ፴)።
አኮኑ ፡ (ዐቢይ አገባብ) አስረጅ፤ ና፤ እንደ ባሕቱ በፊትም በኋላም ይገባል። አገባብነቱን በቦታው ተመልከት
፡ (ዕር፲፱ ፡ ቍ፷፯)።
፡ ና፤–አኮ ኑ።
አኳቲ ፡ (ቲት ትያን ያት) የሚያመሰግን፤ አመስጋኝ፤ አገልጋይ። መጽሐፍ ግን አእኳቲ ይላል፤ አያሰኝም። ኮነ ብእሴ ትሑተ ወአእኳቴ እግዚ
፡ (አፈ ፡ ተ፳፮)።
አወልተወ ፡ አስጌጠ አስመከተ፤ አሰለፈ አስጠረረ፤ ጋሻ አለበሰ፤ አስለበሰ። ይደልወነ ከመ ናወልቱ ነፍሳቲነ ፡ (አፈ ፡ ተ፭)።
አወልወለ ፡ አሶለወለ፤ አስጠረጠረ። አወላወለ አጠራጠረ፤ አወጣ አወረደ አመላለሰ። መጽሐፍ ግን በአወልወለ ፈንታ አስተወላወለ ይላል። ያስተወላውላ ለምክረ ልቡ። ወውእቱ ገጾ አስተወላወለ ፡ (ሢራ፵ ፡ ፮። መክ፲ ፡ ፲)።
አወልዋሊ መወላውል ፡ (ልት ላን ላት) የሚያወላውል አወላዋይ፤ አጠራጣሪ። ኢይሑር ውስተ ሀገር ወኢይባእ ውስተ አብያት፤ ከመ ኢይምላእ ራእዩ ወእዘኒሁ እምነ መወላውላተ ዝንቱ ዓለም ፡ (ፊልክ ፡ ፻፲፫)።
አወሰነ ፡ አሶሰነ አስደነገገ፤ ወሰን አስደረገ።
አወርዘወ ፡ አላቀ አሳደገ፤ ጐበዝ አደረገ። ኢያወርዘውኩ ፡ (ኢሳ፳፫ ፡ ፬)።
አወተ ፡ (ሐባብ) ተለቃ ተበደረ፤ ታደለ ተቀበለ።
አወት ፡ ልቃሕ፤ ጸጋ ዕድል።
አወከለ ፡ አሶከለ፤ ወኪል አስደረገ።
አወደሰ ፡ አስወደሰ አስመሰገነ፤ ብፁዕ አሰኘ።
አወጥሐ ፡ አስከመረ፤ አስቈለለ።
አወፈየ ፡ (ባጕልነቱ አድራጊ፤ በገቢርነቱ አስደራጊ) አሰጠ፤ አሰጭ ኾነ። ልማዱ ግን ሰጠ፤ ሰጭ ኾነ ነው። እመ ፈቀደ ያወፊ ነፍሶ። ያወፍይዎን ለኅጽወ ንጉሥ። አወፈዮ ምሕፅና ፡ (ቀሌ። አስቴ፪ ፡ ፫። ስንክ ፡ መስ፭)።
አዊት ፡ ( ዕብ ኦት) ምልክት ፊደል፤ ታምራት ገቢረ ኀይል። የዮሐንስ መጥምቅ ስምና በዓል፤ ምልክታም ባለምልክት ማለት ነው። ባለቅኔዎች ግን ያገር ስም ፥ የወይን እሸት ጊዜ ይሉታል። በዓል ዘስሙይ ውእቱ ዮሐንስ አዊት። ዘአዊት ዮሐንስ
፡ (አብጥሊ። አዋል)።
አዊው ዎት ፡ (አወ፤ አወወ የአውው ይእ(ው) ወው) ማወው ዥብኛ መጮኽ፤ አዉ አዉ ማለት። ማያያዝ ማጫፈር ማከታተል፤ ያነኑ ደግሞ ማሻሻል ማማረጥ ማበላለጥ። እውዋ ፥ ዋዌ ፥ ዋው ማለት ከዚህ የወጣ ነው፤ እውዋ የሕፃናት ንዋየ ተውኔት፤ ዋዌንና ዋውን በቦታው ተመልከት።
አዋሐየ አውሐየ አስተውሐየ ፡ ኣስጐበኘ አስጠበቀ፤ አስጠየቀ።
አዋሐደ አስተዋደ ፡ በቁሙ፤ አዋሐደ አወሓሐደ፤ አሰማማ አንድ አደረገ። በበ አሐዱ ታዋሕድ። ዘያስተዋሕደከ ምስለ እግዚ። ወአስተዋሐደ ሥጋ እንተ ነሥአ ቃል እምኔሃ ፡ (አዋል። አረጋ ፡ ድ፩። ሃይ ፡ አበ ፡ ጎር)።
አዋልድ ፡ የሊቃውንት መጽሐፍ ድርሳናት ተግሣጻት፤ ንባባቸውና ምስጢራቸው እንደ ዐጽቅ ኹኖ ከብሉይ ከሐዲስ የወጣ
፡ (ማሕ፮ ፡ ፰)።
አዋነየ አስተዋነየ ፡ አጫወተ፤ አጨዋወተ።
አዋከየ ፡ አበራ አስበራ፤ አጸደለ። በራ ብሩህ ኾነ። ከዋክብት ዘአዋከዩ አድያማተ። ሰላም ለሥንኪ ዘአዋከየ መብረቃ ለብሔረ ጽልመት ወጣቃ። ዘበሥነ ስብከቱ ገዳም ታዋኪ ፡ (ገድ ፡ ተክ። ደራሲ። ድጓ)።
(ላ) አው ፡ (ዕብ ኦ። ሱር ወዐረ አው) ንኡስ አገባብ። አጫፋሪ አነጻጻሪ ቃል፤ ዋዌ፤ ወይ ወይም፤ በጥያቄ ጊዜ ወይስ። አንዳንድ ጊዜ ከሚመ ጋራ፤ አው ውእቱ ወሚመ አንተ ንዑ ሊተ እያለ፤ አንዳንድ ጊዜም ዋዌ ስለ ኾነ ብቻውን በመከታተል ይገባል። ለእመ አበስነ ለከ በአእምሮ አው በኢያእምሮ አው በጽልሑት አው በእከየ ልብ አው በገቢር አው በተናግሮ አው በናእሰ ልብ። ዕሥራ ወኀምስቱ አው ሠላሳ። አው ሠምዕ አው ዘይት። ቦኑ አው አልቦ። ንግሩኒ፤ አው ትሠውዑ አው ኣነሥእ ላዕሌክሙ ጥብጣቤ ሐብል ፡ (ቅዳ። ዮሐ፮ ፡ ፲፱። ፈ
፡ መ ፡ ፲፯ ፡ ፮። መቃ ፡ ገ፪)። ዋዌነት ስላለው አው ወአው አይልም፤ ምስጢሩ ማማረጥና ማሻሻል ነው።
አውሐሰ ፡ አስዋሰ፤ ዋስ አስጠራ፤ ውሰት አሰጠ።
አውሓሲ መውሐሲ መውሕስ የሚያስውስ ዋስ የሚያስጠራ፤ ዋስ የሚል። ከአውሓሲ በቀር መውሐሲና መውሕስ ፪ኛ እንደ ወሓሲ ባድራጊነት፤ ይፈታል። መጽሐፍ ግን አውሓሲንም በወሓሲ ፈንታ ይጥፋል። የሀብ ለአውሓሲ በከመ ቃሉ ለአውሓሲ
፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፳፰)።
አውሀበ ፡ አሰጠ አስቀበለ። ኢያውሀበከ እግዚ ክብረ፤ ፡ (ዘኍ፳፬ ፡ ፲፩)።
አውሐዘ ፡ አፈለቀ አፈሰሰ፤ አስፈሰሰ፤ አዘነመ። ኣውሕዝ ማየ በብሔረ ጽምእ። ደመናት ያውሕዙ ጠላተ። ለእመ አውሐዘ እግዚ አስራበ እክል እምሰማይ። ጴጥሮስ ወጳውሎስ አውሐዙ ምህሮ ወንጌል
፡ (ኢሳ፵፩ ፡ ፲፰። ምሳ፫ ፡ ፳። ፬ነገ ፡ ፯ ፡ ፪። አርጋ)።
አውሓዚ መውሐዚ መውሕዝ ፡ (ዝት ዛን ዛት) የሚያፈስ፤ የሚያስፈስስ።
አውኀደ ፡ አጐደለ፤ አስጐደለ፤ አሳነሰ ከፈለ፤ ጥቂት አደረገ። ታውኅዶን ለኀጣውኢከ። ቅንአት ወመዐት ያውኅዱ መዋዕለ ሕይወት። አውኅዶ ጥሪት። አኮ በአብዝኆ አላ በአውኅዶ። ሰአልዎ ያውኅድ እምነ ብዙኅ ሥቃዩ። አዘዘ ያውኅዱ አንድዶ እምታሕተ መቅፁት
፡ (ሢራ፳፰ ፡ ፰። ፴ ፡ ፳፬። ፊልክ ፡ ፳፱። ቅዳ። ስንክ
፡ ሐም፲፮። ዮሴፍ)።
አውለበ ፡ አወለበ፤ ዐሸ ፈለፈለ። አሳሸ አስፈለፈለ።
አውለደ ፡ አስወለደ፤ አዋለደ፤ እርጉዚቱን ዐገዘ ረዳ። አኮሁ ዘኣወልድ። ሶበ ታወልዳሆን ለዕበራውያት፤ ወእመሰ አንስት አውልዳሃ። ኢመፍትው ውስተ ጻዕረ ወላዲት ናውልዶ ለእግዚ ቃል። አዳም አውለደ ሴትሀ ፡ (ኢሳ፷፮ ፡ ፬። ዘፀ፩ ፡ ፲፮። ቄር። ዮሴፍ)።
አውል ፡ (ዐረ አል) ጊሜ የምድር ላቦት እንፏለት፤ የጉም ሽንት እንደ ጤፍ ቅንጣት ያለ፤ ባለቅኔዎች ግን ጤዛ ይሉታል። ይባርክዎ ጠል ወአውል። ወትተርፍ ምድር ባሕቲታ ዘእንበለ ጠል ወአውል። ኮነኒ አውለ
፡ (ዳን፫ ፡ ፵፭። ቀሌ። አዋል)።
አውልዕ [1] ፡ (ዕብ ኤሎን አሎን) ጥኑ ጠንካራ ዕንጨት፤ ብርቱ ዛፍ በሉጥ
፡ (ዘፍ፲፰ ፡ ፩)።
[2] ፡ አውልዕ፤
፡ (ዐረ ወለዐ፤ አበራ ለኰሰ) የበረሓ ዘይት ወይራ፤ መራራ ጠንካራ፤ ጥንካሬው እንደ በሉጥ ያለ። አውልዐ ገዳም። ወጽንዑ ከመ ጽንዐ አውልዕ። ዕፀ አውልዕ ፡ (ሮሜ፲፩ ፡ ፲፯ ፡ ፳፬። ዓሞ፪ ፡ ፱። መጽ ፡ ምስ)።
አውሎ ፡ ጥቅል ነፋስ፤–ዐዊል ዖለ፤ ዐውሎ።
አውሎኒ ን ና ፡ (ጽር አፍሎኒ) ዘብጥ ቈላ፤ ሜዳ ረባዳ ፡ (ዮዲ፯ ፡ ፫ ፡ ፲፯ ፡ ፲ ፡ ፲)።
አውሎግሶን ፡ (ጽር ኤፍሎጊሶን) ትእዛዝ አንቀጽ፤ ባርክ። መነኮሳት ግን ቃለ ጽዋዔ ይሉታል፤ ቤቶች ባለቤቶች እገሌ እንተኔ በማለት ፈንታ አውሎግሶን ብለው ይጠራሉ፤ ፍችውንም ክፈት ማለት ነው ይላሉ፤ አንዳንዶች ደግሞ አረጋዊ ዘይደልዎ ክብር ይሉታል
፡ (ገድ ፡ ዮሐ)።
አውሎግያ ፡ (ጽር ኤፍሎጊኣ) ቡሩክ ኅብስት፤ ተረፈ መሥዋዕት ከቍርባን በኋላ በቡራኬ ጊዜ የሚሰጥ። እንዘ ይሜጡ አውሎግያ። ኅብስተ አውሎግያ
፡ (ቅዳ። ኪዳ)።
አውሎግዮስ ጌርዮስ ፡ (ጽር ኤፍሎጊቶስ ኪሪዮስ) ቡሩክ እግዚአብሔር ፡ (ቅዳ)።
አውሰበ ፡ አስጠጋ አዳበለ ሰበሰበ፤ ከቤቱ አስቀመጠ። ሚስት አገባ፤ ቈበተ ገረድ ቀጠረ። ኢታውስብ ብእሲተ። ዘአውሰበ ብእሲተ ኄርተ። እለ ያወስቡ ዳግመ ይከውኑ ውፁኣነ እምሕግ ፡ (ኤር፲፪ ፳። ሚራጃ5ሄ ጽሸዘ። ዲድ ፲8)።
፡ ወደ ሴት ገባ ቀረበ፤ ተራከበ። አውስቦ በአሐዱ ሌሊት ሠለስተ ጊዜ፤ አውስቦ እንስሳ፤ አውስቦ አውናን ፡ (አንቀጸ ንስሓ)። ለሴትም ይነገራል። አውሰበት ካልአ ብእሴ። እምድኅረ አውስበት። እንተ ኢያውሰት ፡ (ኤር፫ ፡ ፩። ፵፪ ፡ ፬። ፩ቆሮ ፡ ፯ ፡ ፴፬)።
አውሣኢ ፡ (ኢት እያን ያት) የሚያሶሣ፤ መላሽ ምላሽ ሰጭ፤ ጠበቃ አፈ ጉባኤ። አንትሙ አውሣእያን በእንቲኣሆሙ
፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፭)።
አውስት ፡ (ጽር ጊብስ) ንስር የጥንብ አሞራ፤ አስቀድሞ ዐይን የሚያነቍር ፊት የሚፙጭር የሚጐፈጭር፤ ዐይን ሳያወጣ የማይበላ።
፡ (ሙሾ) ዘምቶ የሞተ ሰው ያዝንለት አያጣ፤ አሞራ እንኳ ወርዶ ፊቱን ነጭቶ ወጣ። አውስትኒ ሐቂፎ ዕጐሊሁ ይበይት ፡ (ኢዮ፴፱ ፡ ፳፯። ሔኖ፹፱ ፡ ፲። ፺ ፡ ፪ ፡ ፲፩ ፡ ፲፫ ፡ ፲፮)።
አውሥአ [1] ፡ አስደራጊ፤–ወሢእ ወሥአ።
[2] ፡ አውሥአ፤ አሶሣ አናገረ፤ አስጠየቀ አስመለሰ፤ አሳሰበ አስታወሰ። የልማድ ፍችው ግን አድራጊ ነው፤ እንደ አእመረ ተበላሽቷል።
አውረሰ ፡ አወረሰ፤ አስወረሰ። ያወርሶ እግዚ ለይሁዳ መክፈልቶ። ሕገ ዘያሐይዎሙ አውረሶሙ። ከመ ትረሱ ምድረ ወእም ድኅሬ ክሙኒ ታውርሱ ለደቂቅክሙ እስከ ለዓለም ፡ (ዘካ፪ ፡ ፲፪። ሢራ፲፯ ፡ ፲፩። ፩ዜና ፡ ፳፰ ፡ ፰)።
አውረደ ፡ አወረደ አዋረደ፤ ሻረ፤ አሶረደ። ኣወርዶሙ ቈላተ ዮሳፍጥ። አውረደቶሙ በሐብል እንተ መስኮት። አውረዶሙ ለነገሥት ውስተ ሞት ወለክቡራን እምነ ዐራታቲሆሙ። አውረድዎሙ ውስተ ምድር ለመሳፍንት
፡ (ዮኤ፫ ፡ ፪። ኢያ፪ ፡ ፲፭። ሢራ፵፰ ፡ ፮። ሰቈ፪ ፡ ፲)።
፡ አዘነመ፤ አፈሰሰ። እግዚ ያወርድ ጠለ ወዝናመ ላዕለ ምድር። አውረደት አንብዐ። አውረደ እሳት እምሰማይ
፡ (ኩፋ ፡ ፲፪። ሢራ፴፪ ፡ ፲፰። ፵፰ ፡ ፫)።
፡ ዘረጋ ላከ ሰደደ፤ የእጅ። አውረደ እዴሁ ወነሥኦ። ኢትቅድም አውርዶ እዴከ። ደይዎ ውስተ ዐዘቅት ወእዴክሙ ባሕቱ ኢታውርዱ ላዕሌሁ ፡ (፬ነገ ፡ ፮ ፡ ፯። ሢራ፴፬ ፡ ፲፰። ዘፍ፴፯ ፡ ፳፪)።
፡ ከላ አወጣ፤ አወለቀ አሰለበ፤ አራገፈ አሳረፈ፤ የልብስ የጭነት። የሸክም። ወአውረደ ዮናታን ዐጽፈ ዘላዕሌሁ ወወሀቦ ለዳዊት። ያውርዱ አልባሲሆሙ ዘተልእኩ ቦሙ። ወአውረዱ ኵሎ ዘውስተ ሐመር ፡ (፩ነገ ፡ ፲፰ ፡ ፬። ሕዝ፵፬ ፡ ፲፱። ግብ፳፩ ፡ ፫)። ምንም ያማርኛው ስልት ቢበዛ ምስጢሩ ከዚያው ከማውረድ አይወጣም።
አውራስ ፡ ( ጽርእ) ጸዳል ብርሃን፤ ነጸብራቅ ውጋጋን
፡ (ሕዝ፰ ፡ ፪)።
አውራቂስ ፡ (ጽር ሄውሮክሊዶን) ብርቱ ነፋስ ባሕር የሚደርጥ የሚያናውጥ፤ መርከብ የሚንጥ የሚገለብጥ። ጥፉንቂስን እይ፤ ከዚህ ጋራ አንድ ነው
፡ (ግብ፳፯ ፡ ፲፬)።
አውርዮን ፡ (ጽር አውሪዮን) ጌሰም፤ ሳኒታ
፡ (ዘኍ፲፬ ፡ ፳፭)።
አውቀረ ፡ አሶቀረ አስቈፈረ፤ አስጠረበ፤ ውቅር አሠራ። አውቀረ ኰኵሐ በኀጺን። አውቀርከ ለከ ዝኅረ ውስተ ኰኵሕ። አውቀረ ላቲ መንፈስ ቅዱስ ጥምቀተ መቃብረ ነፍስ፤ ወኀተማ በአእባን ሠላስ ፡ (ሢራ፵፰ ፡ ፲፯። ኢሳ፳፪ ፡ ፲፮። ቅኔ)።
አውቀየ ፡ አስቈረጠ፤ አስቀረጠፈ፤ ልማዱ ግን አድራጊነት ነው።
አውቃፍ ፡ አንባሮች፤–ወቀፈ።
አውተረ [1] ፡ አስደራጊ፤–ወቲር ወተረ።
[2] ፡ (አስደራጊ) አስወተረ አስገተረ፤ አዘወተረ። ልማዱ ግን አድራጊ ነው።
አውታሪ መውተሪ ፡ (ሪት ርያን ያት) የሚያዘወትር አዘውታሪ፤ ተኳር። እስመ ኮነ ውእቱ ጻድቀ ወመውተሬ ለህድአት ፡ (ፊልክ ፡ ፲፭)።
አውታይ ን ፡ (ዐረ አውታን) ታላቅ ሰፊ ቤት፤ ወይም ድንኳን
፡ (አቡሻ ፡ ፮)።
አውቴ ፡ (ጽር ናዋት። ዕብ ናዮት) የቦታ ስም፤ የጸሎት የትምርት ቤት፤ መጋቢያ መሰብሰቢያ፤ መካነ ጉባኤ። አውቴ ዘራማ
፡ (፩ነገ ፡ ፲ ፡ ፱
፡ ፲፱ ፡ ፳፫)።
አውናን ፡ (ጽር አፍናን። ዕብ ኦናን)። የሰው ስም፤ ፪ኛው የይሁዳ ልጅ
፡ (ዘፍ፴፰ ፡ ፱)። አውስቦ አውናን፤ የአውናን ፅምረት ሩካቤ፤ አውናናዊ ሥራ፤ ፈቃድን ፈጽሞ ዘር አለመስጠት ከውጭ ማፍሰስ ፡ (አንቀጸ ንስሓ፤ ወይም መጽሐፈ ኑዛዜ ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፳፬ ፡ ፭)።
አውዐለ ፡ አዋለ፤ ጠበቀ። ዘአውዐልከነ ኵሎ ኑኀ ዕለት። አውዐልዎሙ ውስተ ቤተ ሞቅሕ። ወአውዐሉ አፍራሲሆሙ ፡ (ድጓ። ግብ፭ ፡ ፲፰። ፳፫ ፡ ፴፪)።
፡ አስዋለ፤ አስጠበቀ። እስመ እፈቅድ ኣውዕል፤ ምንት ውእቱ አውዕሎ ፡ (ሄርማ ፡
ገ፶፪ ፡ ፶፫)።
፡ አዋለ፤ አሰረ፤ አጠበቀ ከግዞት አገባ።
አውዐልዎ ውስተ ሙዓል። አውዐልዎሙ ሙዓለ ፡ (ዘኍ፲፭ ፡ ፴፬። ግብ፬ ፡ ፫)።
አውዐረ ፡ አስደነቀ፤ ዕጹብ አሰኘ።
አውዐየ ፡ አቃጠለ ተኰሰ፤ ለበለበ። አዋዐይናሃ በእሳት። ከልኦሙ አውዕዮተ መቅደስ። ዐቀብተ ሥራይ ሶበ ይፈቅዱ በጢሐ ወአውዕዮ በእሳት። ፀሓይ ኢያውዒከ። ኅጠተ ስናፔ ሶበ ጥዕማ ብእሲ ታውዕዮ ፡ (ዘ፩ነገ ፡ ፴ ፡ ፲፬። ዮሴፍ። አፈ ፡ ተ፴። ዲድ ፡ ፲፬)።
አውዓሊ መውዐሊ ዕል ፡ የሚያውል አዋይ ጠባቂ፤ አሳሪ፤ ባለውል።
አውከተ ፡ አስጮኸ አሸበረ፤ ግር ግር አሰኘ።
አውከበ ፡ አዋከበ፤ አተጋ አተጋ፤ አስቸኰለ አቻኰለ።
አውከከ [1] ፡ አወከ አስፈራ፤–ወኪክ ወከ፤ ወከከ።
[2] ፡ አስፈራ አስጨነቀ፤ መከራ አሳየ። ያወክኮሙ ለአሕዛብ ፡ (ኢዮ፲፪ ፡ ፳፫)።
፡ አስቀረ፤ አስታጐለ፤ አስትዓሁ እለ አውከኩ ፡ (ድጓ)።
አውከፈ ፡ አስተውከፈ፤ አሰጠ፤ አስቀበለ።
አውክሐ ፡ አስደነፋ፤ ውካታ አስደረገ።
አውክሞዲስ ፡ (ጽር አውክሞዱስ። ዕብ ጊብዓት) ታናሽ ተራራ ጕባ ባማ፤ የሳኦል ከተማ
፡ (፩ነገ ፡ ፲፩ ፡ ፬። ፳፮ ፡ ፩)። ጽኑ በረሓ ምድረ በዳ ተራራ ኰረብታ ዋሻ ፍርኵታ ያለበት፤ ድኵላ ሠሣ አጋዘን ድፋሳ ሌላውም ኹሉ አውሬና እንስሳ የሚታደንበት ፡ (፩ነገ ፡ ፳፫ ፡ ፲፬ና ፡ ፲፭ ፡ ፲፱)።
አውክዐ [1] ፡ አደከመ
፡ አሰለቸ፤–ወኪዕ ወክዐ።
[2] ፡ አደከመ አታከተ፤ አስቸገረ አሰለቸ። አወክዑኒ እሉ መስሕታን ፡ (መቃ
፡ ገ፪)።
አውየነ ፡ ጠጀ ጠመቀ ረገጠ፤ ወይን አደረገ ዘለላውን፤ ወይም በታምራት ውሃዉን። ከመ ታውይን ማየ ፡ (ስንክ ፡ ጥር፲፫። ዮሐ፪ ፡ ፯–፱)።
አውያት ፡ ጩኸት ቡታ፤–ዐወየ ዐውየወ።
አውደቀ ፡ ጣለ አወደቀ፤ አዋረደ አሻረ። አሳዘነ፤ መታ ገደለ። አውደቀት በድኖ እምነ ምስካቡ። ወአውደቆ ውስተ ማዕምቅ። ለብዙኃን አውደቆሙ ትዕቢተ ልቦሙ። በእንተ ምክንያት እንተ ታወድቆ ለቀሲስ እማዕርጊሁ። ኢታውድቁ ልበክሙ። ለምንት አውደቀነ። አውደቅዎ በሰይፍ
፡ (ዮዲ፲፫ ፡ ፬። ራእ፳ ፡ ፫። ሢራ፫ ፡ ፳፬። ፍ ፡ ነ ፮ ፡ ፭። ነሐ፰ ፡ ፲። ኤር፲፬ ፡ ፲፱። ፪ዜና ፡ ፴፪ ፡ ፳፩)። ደደቀንና ደነቀን እይ፤ የወድቀ አግዋር ናቸው።
አውደደ ፡ አሶደደ። አዋደደ አስማማ፤ ሰካ አሳካ፤ ቸነከረ አንድ አደረገ፤ የግብር የነገር። አግበረ አርባዕተ ምእተ ጸናጽለ ወአውደዶን ዲበ መሣግር። አውደድዎ ውስተ ወርቅ። አውድድ ውስተ ሥጋየ ፈሪሆተከ ፡ (፪ዜና ፡ ፬ ፡ ፲፫። ዘፀ፴፮ ፡ ፲፫። መዝ፻፲፰ ፡ ፻፳)።
፡ ሸፈነ ለበጠ፤ በልባጥ አስጌጠ፤ ምስጢሩ ያው ማዋደድ ነው። ወለቤት ዐቢይ አውደዶ ወአጽንዖ በዕፀወ ዘግባት
፡ (፪ዜና ፡ ፫ ፡ ፭)። በአውደደ ፈንታ አስተዋደደ ይላል፤ ፍችው አንድ ነው ፥ ካድራጊነት በቀር አደራራጊነት የለውም
፡ (ዘኁ፬ ፡ ፮ ፡ ፰ ፡ ፲ ፡ ፲፩። ምሳ፰ ፡ ፴)። ዘእንበለ ያስተዋድድ እግዚ ምቋመ አድባር ወአውግር። አሠነየ ለነ ወአስተፍሥሐ መንግሥተነ ወአስተዋደደ አህጉሪነ ወሥልጣነነ ላዕለ ብዙኃን አሕዛብ። አስተዋድዶ መዝሙረ ማሕሌት። አስተዋደደ መዝሙራተ። ወአጻብዕየ ያስተዋድዳ መዝሙረ ፡ (መቃ ፡ ገ፳፫። ዮሴፍ። ስንክ ፡ የካ፰። ቀሌ። መዝ
፡ ፻፶፩)።
አውገረ ፡ አሶገረ አስመታ አስጣል።
አውገበ ፡ አደነገተ፤ ሥራውን በድንገት ሠራ፤ አደጋ ጣለ። አውገብዎሙ ወወረዱ ላዕሌሆሙ። ያወግቦ ወይነፅኆ። ዕለት እኪት አውገበተኒ። ወታወግቦሙ ዕለት እኪት
፡ (ትበጽሖሙ ግብተ)። እለ ይፈቅዱ ያውግቡ ፡ (ኢያ፲፩ ፡ ፯። ሉቃ፱ ፡ ፳፱። ሱቱ ዕዝ፲ ፡ ፴፱። ሚክ፪ ፡ ፫። ቄር)። ባለብሉዮች ግን፤ አፍርሀ አደንገፀ ይሉታል፤ ባለቅኔዎችም አኰረፈ ይሉታል።
አውገዘ ፡ አሶገዘ አስገዘተ፤ አስለየ። ልማዱ ግን አወገዘ ነው።
አውገደ ፡ አሶገደ፤ ወግድ አለ፤ አራቀ። ወግዳ ውጋዴ ማለት ከዚህ የወጣ ስም ይመስላል።
አውግሥጦስ ፡ የሮማውያን ወር ነሐሴ አውግሥቱስ የነገሠበት
፡ (ገድ ፡ ተክ)።
አውጠነ ፡ አሶጠነ፤ አዠመረ። ተአምኖ ያዌጥን ወተወክሎ ያፌጽም
፡ (አርጋ ፡ ፫)።
አውፃኢ ፡ የሚያወጣ አውጭ አሶጭ፤ አስገኝ። አውፃኢሁ ለዘእንተ ውስጥ። አውፃኢሃ ለዛቲ መጽሐፍ
፡ (ቅዳ ፡ ሕር። ፈላስ ፡ ገ፶፬)።
አውጽሐ ፡ (አስደራጊ) አስፈሰሰ፤ ባጥ አሠራ። ልማዱ ግን አድራጊ ነው።
አውፅአ ፡ አወጣ አሶጣ ሰደደ። አዳነ፤ እግዜር አወጣኝ እንዲሉ። አውፅኦሙ ኀቤነ። ተፋቅሮ ታወፅኣ ለፍርሀት። አውፃእኮን ዕራቆን ለዕቤራት ፡ (ዘፍ፲፱ ፡ ፭። ፩ዮሐ ፡ ፬ ፡ ፲፰። ኢ፳፪ ፡ ፱)።
፡ ገፈፈ፤ አፈሰሰ። አውፅኡ አምእስቲሆሙ። ኢያወፅእ ደመ
፡ (ሚክ፫ ፡ ፫። ጦማ)።
አውፈረ ፡ አሰማራ፤ ነዳ ወሰደ። ይገብር ነግሀ ወያወፍሮ ለሰብእ ውስተ ተግባሩ። ዘያወፍር እክለ ውስተ መቃብር
፡ (ቀሌ። ሢራ፴ ፡ ፲፰)።
አዘለ ፡ (ዐረ። ዕብ አዛል) ኼደ ነቀለ፤ ጓዙን ዕቃውን አነሣ ወሰደ፤ የነጋዴ የባለክራይ።
አዘመወ ፡ አሴሰነ፤ ዘማዊ አደረገ፤ አገለሞተ፤ አስገለሞተ። አዘመውካ ለብእሲተ ካልእከ። ወያዜምወኒ ዘእንበለ ፈቃድየ ፡ (ዲድ ፡ ፩። ገድ ፡ ተክ)።
አዘረ ፡ በተነ፤–ዐዚር ዐዘረ።
አዘርከየ ፡ አሰደበ፤ ተሳዳቡ አስነሣ።
አዘብዘበ ፡ አዘበዘበ፤ አረገዘ ተንጠረዘዘ፤ ሊናድ ቀረበ፤ የካብ የግንብ።
አዘንግዐ ፡ አዘነጋ፤ ዝንጉ አደረገ፤ አስረሳ ልብ አጠፋ። አብዝኆ መጻሕፍት ያዘነግዕ ልበ። ናሁ አነ አንጐግዋ ወኣዘነግዓ ልባ
፡ (ግብ ፡ ፳፮ ፡ ፳፬። ሆሴ፪ ፡ ፲፮)።
አዘንጐጐ ፡ አሰደበ፤ አስነቀፈ። አዘንጐግሙ ጎፍሳቲክሙ። ቦ እለ ይክሕዱ ወያዘነጕጉ ህሉተ ሥርዐተ
፡ (ዮሴፍ። መጽ ፡ ምስ)።
አዘከረ ፡ አሳሰበ፤ አስወሣ አስታወሰ። በዘአዘከረ ሎቱ መሐላ አበው። አዘክሪ ድንግል ልደቶ እምኔኪ። አዘከራ እሳተ ገሃነም። ወነዋ አዘከረ ዮሴፍ ወልደ ኮርዮን ከመ። አዘክሮ ለፈርዖን በእንቲኣየ ፡ (ጥበ ፡ ፲፰ ፡ ፳፪። ቅዳ። ስንክ ፡ የካ፫። ዮሴፍ። ዘፍ፵ ፡ ፲፬)። ዳግመኛም በአዘከረ ፈንታ ዘከረ ይላል፤ የጣፊ ስሕተት ነው። አነ እዜከረከ ኵሎ። ከመ ኣንቅህክሙ በዘክሮ። ዘክሮሙ ከመ ይትአዘዙ ፡ (ኩፋ ፡ ፴፪። ፪ጴጥ ፡ ፲ ፡ ፲፫። ፫ ፡ ፩። ቲቶ፫ ፡ ፩። ፪ጢሞ ፡ ፪ ፡ ፲፬)።
አዚኅ ኆት ፡ (አዝኀ የአዝኅ ይእዛኅ። ዐረ አዘ፤ ዐዘ) መብጣት መቍረጥ ፥ መሰንዘር መሠንበጥ በቅዛዝ በጠርሙዝ በሱፋጭ በምላጭ። ማዠት ማፍሰስ፤ ማንዛት መወርዛት። ጸወበን ተመልከት።
አዚብ ቦት ፡ (አዘበ። ዐረ ወሱር ዛብ። ዕብ ዙብ) መፍሰስ መንዣረር መንፎክፎክ፤ ፊር ፊር ጭርቅ ጭርቅ ጠብ ጠብ ማለት፤ የሽንት የዘር የወተት የደም የፈሳሽ ኹሉ።
አዚን ኖት ፡ (አዘነ የአዝን ይእዝን። ዕብ አዜን) መቀቀር መቀፈር፤ ዦሮ መስጠት ማቅረብ ለመስማት።
አዛል ፡ ጐበዝ ጕልማሳ፤ ብርቱ ጠንካራ። በሓ ኦ አዛል ዘኢይፈርህ ሞተ በቅድመ ቀታልያን። አባ ኖብ ድንግል ወአዛል መስተጋድል
፡ (ስንክ ፡ ሐም፰። ቅዳ)።
አዛምር ፡ የዳቦ ቅጠል፤ ዐይነቱ አረንጓዴ ብጫቴ ፡ (ዐማርኛ)።
(ጥዛ) አዛብ ፡ (ዕብ ኤዞብ። ጽር ሒሶፖስ) መርጫ የቀንበጥ ችቦ፤ ታናናሽ ቀጫጭን ቀንበጥ ሐረግ መልካም ሽታ ያለው ላይን ላፍንጫ ደስ የሚያሰኝ፤ ናዕናዕ አዩባን ነጭ ሽቱ ሪሓን፤ ዐጡንባር የጠጅ ሣር ይህን የመሰለ። ቅጥይ የገቦ በጐን የሚወጣ የሚያፈጠፍጥ፤ በቤት በግንብ ላይ ሳይዘሩት የሚበቅል ሣር ቅጠል፤ እንዳሸክትና እንደ ሙጃ ያለ። ሁስጱን ተመልከት፤ ከዚህ ጋራ አንድ ነው። ባለመጽሐፎች ግን ያነንም ይኽንም፤ የተጐነጐነ ሐር አዩባን ስምዛ አሸክት ይሉታል
፡ (ዘፀ፲፪ ፡ ፳፪። መዝ : ፶)። አንዳንድ ጊዜም ለናዕናዕ ብቻ ይነገራል፤ መደበኛው ርሱ ስለ ኾነ ፡ (ማቴ፳፫ ፡ ፳፫። ሉቃ፲፩ ፡ ፵፪)።
አዛኒ መአዝን ፡ ቀቃሪ ቀፋሪ፤ ሸምጣጭ፤ አድማጭ።
አዛዚ ፡ ( ዚት ዝያን ያት) የሚያዝ የሚናዝዝ፤ አዛዥ ናዛዥ፤ ሠራዒ መጋቢ። እለ አልቦሙ አብ ወኢእም ወኢአዛዚ። ረስየከ እግዚአብሔር አዛዜ ለኵነኔየ
፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፳፬ ፡ ፫። ዮሴፍ)።
አዜራህ ፡ ዕርከን፤–ዐዘረ።
አዜቈነ ፡ (ያዜቍን ያዜቍን) አዛቈነ ዲቁና፤ ሾመ። ፡ (ተረት) ያዛቈነ ሳያቀስ አይለቅም።
አዜብ [1] ፡ ደቡብ በረሓ፤–አዝየብ።
[2] ፡ አዜብ፤ አዝያብ
፡ (ዐረ አዝየብ) የማእዝን ስም፤ ንኡስ ማእዝን፤ የአፍሪቃ ወገን፤ በምዕራብና በደቡብ መካከል ያለ የደቡብ ግራ ፥ ምዕራብ፤ የመስዕ ትይዩና አንጻር ፊት ለፊት። ባለብሉዮች ቈላ በረሓ ይሉታል። ባርክ መስዐ ወአዜበ። ነፋሰ አዜብ። ንግሥተ አዜብ። ከመ ውሒዝ ውስተ አዜብ
፡ (ቅዳ። ሉቃ፲፪ ፡ ፶፭። ማቴ፲፪ ፡ ፵፪። መዝ ፡ ፻፳፭)። ጽባሕ ምሥራቅ በማለት ፈንታ አዜብ ይላል የመላሽና የጣፊ ስሕተት ነው። ነፋሰ አዜብ። አንሥአ አዜበ ፡ (ዘፀ፲ ፡ ፲፫። ኢዮ፴፰ ፡ ፳፬። መዝ ፡ ፸፯። ሔኖ፴፮
፡ ፩)።
አዝሐለ ፡ አዛገ አሳደፈ። አዛለ አደከመ።
አዝሓሊ መዝሕል ፡ የሚያዝግ፤ የሚያዝል አድካሚ።
አዝኀረ ፡ አሰፋ ዘረጋ፤ ነፋ። አዘረጋ፤ አሳበጠ አስነፋ። አኰራ አስታበየ፤ አስመካ።
አዝኃሪ መዝኅር ፡ (ርት ራን ራት) የሚያኰራ የሚያስታብይ አስመኪ። በዞጲ ፈንታ መዝኅርት ይላል ፡ (አዋል)።
አዝኀነ ፡ አዘና፤ ዝም አሰኘ ጸጥ አደረገ፤ አረጋ አረጋጋ። አዝኀና ለባሕር በተግሣጸ ነፋሳት። ዘአዝኀንከ እምኔነ ማዕበላተ ውሒዛተ መናፍስት ፡ (መጽ
፡ ምስ። ኪዳ)። በአዝኀነ ፈንታ አስተዝኀነ ይላል፤ ፍችው አንድ ነው። ውስተ ዘመድኅን መርሶ እንዘ ታስተዝኅኑ ንግዳ ለሐመርየ ፡ (ስንክ ፡ ጳጕ፩)። ዳግመኛም በግልብጮ አጣጣፍ ቀሐመን ቀምሐ እንደሚለው፤ ዝኅነ አዝኀነ በማለቅ ፈንታ ነዝሐ አንዝኀ ይላል፤ የጣፊ ስሕተት ነው። ጸጋ እንተ ታነዝኆሙ ለቅዱሳን። አልቦ ዘየሐውር ውስተ ምኔተ አንስት ከመ ያንዝኅ አኃተ
፡ (ፊልክ ፡ ፹፱። ሥር ፡ ጳኵ)።
አዝኃኒ መዝኀኒ ኅን ፡ የሚዘና የሚያጸና የሚያጸናና፤ የሚያረጋጋ፤ ጸጥ የሚያደርግ ዝም የሚያሰኝ ፡ (አርጋ ፡ ፫)።
አዝለፈ ፡ አዘወተረ፤ አራደፈ አከታተለ፤ እበዛ፤ መላለሰ። ወተረን እይ። ዘአዝለፈ ትዕግሥቶ። ሶበ አዝለፈ ጸሎተ። ከመ ያዝልፍ ገቢረ ትሩፋት
፡ (ማቴ፲ ፡ ፳፪። ፊልክ ፡ ፶፩። ፈ ፡ መ ፡ ፪ ፡ ፪)። አ(ስ) ዘለፈ አሰደበ፤ አስነቀፈ።
አዝላፊ ፡ የሚያዘወትር፤ አዘውታሪ። ለእመ ኮነ አዝላፌ ለገቢር። ይኩኑ አዝላፍያነ ጾም ወጸሎት ፡ (ፊልክ ፡ ፪፻፳፮። ፍ ፡ ነ ፡ ፲ ፡ ፮)። አስዳቢ፤ አስነቃፊ።
(ጥ) አዝሎ ሎት ፡ (አዘለ ይኤዝል የአዝል። ዐረ አዘረ። ዕብ አዛር፤ ቀነተ) ማደግ መጐልመስ ለጌጥ ለመሣሪያ መድረስ፤ መጐልበት መግነን፤ ኀይለኛ መኾን።
አዝመራ ፡ (ዐማርኛ) በቁሙ፤ ዐጨዳ ስብሰባ፤ ወይም ዝሪት።
አዝመረ አዘመረ ፡ አስቈረጠ፤ አሳጨደ። አ(ስ) ዠመረ፤ አስመሰገነ።
አዝመር [1] ፡ ደባባ ደባሳ፤–ዘመረ።
[2] ፡ (ዐረ አስመር) ያይነት ስም፤ ደባባ ደባሳ፤ የበሰለ የሟከከ ፍሬ የሚመስል፤ ፍጹም ቀይ ወይም ፍጹም ጥቍር ያይዶለ ማእከላዊ ሕብር ፡ (ራእ፲፰ ፡ ፲፪ ፡ ፲፮)።
አዝመደ ፡ አዘመደ፤ አስጠመደ።
አዝሙድ ፡ (ዳት) የቅመም ስም፤ አበሱዳ፤ አቡሱዳን ነጭና ጥቍር ዐይነት ፡ (ዐማርኛ)።
አዝረቅ [1] ፡ ኒል፤–ዘረቀ።
[2] ፡ (ዐረ አዝረቁ) ጥቍር የኒል ዐይነት፤ ጥቍረቱ ሰማይ የሚመስል። ብንተ አዕይንቲሁ አዝረቅ ከመ ኒል። አልባስ ዘሕብረ አዝረቅ ፡ (ስንክ ፡ ሐም፰። አቡሻ ፡ ፶)።
አዝረወ
፡ አስበተነ፤ አስጠፋ አስፈረሰ።
አዝርዐ ፡ አ(ስ) ዘራ አስተከለ፤ አስበተነ።
አዝበጠ ፡ አስመታ፤ አስደበደበ።
አዝነመ ፡ አዘነመ አወረደ፤ ረጨ አፈሰሰ። አስደራጊነትም አለበት። እኤዝዝ ደመናተ ከመ ኢያዝንሙ ላዕሌሃ። አዘዘ ደመና ወአዝነመ መና። ኣዘንም በረደ። ወአዝነመ እግዚ እሳተ ወተየ እምሰማይ ፡ (ኢሳ፭ ፡ ፮። መዝ ፡ ፸፯። ዘፀ፱ ፡ ፲፰። ዘፍ፲፱ ፡ ፳፬)።
አዝወገ አዞገ ፡ (ጥዘ) አዘወገ አስጠመደ፤ ጥንድ ዘውግ አስደረገ።
(ጥ) አዝዞ ዞት ፡ (አዘዘ። ዕብ ጻዌህ) ማዘዝ፤ መናዘዝ፤
፡ (ጥና) መናዘዝ፤ በሥራ ላይ ወይም በገንዘብ በርስት ቍርጥ ቃል መስጠት፤ አድርግ አታድርግ ይኹን አይኹን ማለት፤ በቃል በጥፈት፤ የሹም የቄስ ያባት የባለቤት። ፡ (ተረት) ያልተሾመ አያዝ፤ ያልቀሰሰ አይናዝዝ። ላይሞቱ መናዘዝ፤ ላይመቱ መጋበዝ። አዝዞ ይኩን በጽሒፍ። ወዘእንበለ ጽሒፍ ፈታሒ የአዝዝ ለላእካኒሁ በፈሪሀ እግዚ። አዘዘ ያብእዋ። አንተ ውእቱ ዘትኤዝዝ ለበዊእ ወለወፂእ። መኑ አዘዘክሙ ትሕንጹ። አዘዘ በእንተ ቤቱ ወሞተ። የአዝዝ እምቅድመ ምንኵስናሁ በእንተ ንዋዩ ዘከመ ፈቀደ
፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፵፩ ፡ ፩። ፵፫ ፡ ፫። ዮዲ፲፪ ፡ ፩። ፩ዜና ፡ ፲፩ ፡ ፪። ዕዝ፭ ፡ ፫። ፪ነገ ፡ ፲፯ ፡ ፳፫። ፍ ፡ ነ ፡ ፲)።
አዝግሐ ፡ አ(ስ) ዘጋ፤ አሲያዘ አስጨበጠ። መጽሐፍ ግን በአዝግሐ ፈንታ ዘግሐ ይላል። ወኢዘጋሕከኒ ውስተ እደ ፀርየ ፡ (መዝ ፡ ፴)።
አዝፈነ ፡ አዘፈነ፤ አዘለለ፤ ዘፈን አስተማረ። ያዘፍን አፍራሰ እንዘ ያነዝር በእንዚራ ፡ (ስንክ ፡ ጥቅ፬)።
አየረ ፡ ሰደበ፤–ዐይሮ አየረ።
አየራዊ ፡ ላዕላዊ፤ ነፋሳዊ። መብረቅ አየራዊ
፡ (ጥበ ፡ ጠቢ)።
አየር
፤ (ራት። ጽር አኢር) ፤ በቁሙ
፤ ኅዋ
፤ ክፍት
ከምድር በላይ
ከጠፈር በታች
ባዶው መካከሉ።
ርጉዕ ነፋስ
በአየር የመላ
፤ የተመላ።
ሠጢቆ አየረ።
በአየረ ሰማይ።
አዕዋፍ ዘውስተ
አየር ይሰርሩ።
መልዕልተ አየር።
ተመልአት አየር
እምነ መላእክት።
አየር ጽሕወ
ኮነ። ዐርገ
ውስተ አየራት።
ይኔጽር አየራተ
(ሃይ ፡ አበ።
ዮሴፍ። ፈላስ።
ምሳ፱ ፡ ፲፪።
ስንክ ፡ ግን፲፱። አፈ ፡
ድ፳፫።
መጽ ፡ ምስ።
ድጓ)።
አይሮፕላን ማለት
ከዚህ የወጣ
ነው ፤
ጠየረን ተመልከት።
አየነ ፡ አየ ገመተ፤–ዐይኖ ዐየነ።
አየየ ፡ ዞረ ባከነ፤–ዐየየ።
አዪኅ ኆት ፡ (ኤኀ፤ አይኀ የአይኅ ይኢኅ፤ ይእያኅ) ማጥፋት፤ መደምሰስ፤ መድፈን መቅበር ማስጠም፤ የጐርፍ የዝናም የማዕበል።
አዪስ ሶት ፡ (ኤሰ የአይስ ይኢስ። ዐረ አዪሰ። ዕብ ያአሽ) መዛበር፤ መጨነቅ መዋለል፤ መስነፍ መድከም መዛል፤ ተስፋ መቍረጥ፤ የበሽተኛ የሐዘንተኛ። አአይስ በሕማም ወትረ። ነፍስየ ተአነብዝ ወተአይስ ልብየ
፡ (ኢዮ፴ ፡ ፲፬። ኤር፬ ፡ ፲፱)።
(ጥዪ) አዪት ፡ በቁሙ፤ የወንድም ያጎት ሚስት፤ የእኅትና ያክሥት ምሳሌ፤ ባሏ አይዋ አያ የሚባል።
(ጥያ) አያር ፡ (ዕብ ኢያር) የዕብራውያን ኹለተኛ ወር፤ ግንቦት ፡ (ጥሬ ፡ ሰዋ)።
አያተ መዓር ፡ የማር እንጀራ አምሳል ዕንጐቻ፤ በማር በስኳር የሚሠራ። የማር አምሳል፤ ማር ማር የሚል በለስ ወይን ተምር ስኳር፤ የመሰለው ኹሉ። ወጣዕሙ ከመ አያተ መዓር። ይፈደፍድ ጣዕሙ እምኵሉ አያያተ መዓር ዘበምድር
፡ (ዘፀ፲፮ ፡ ፴፩። ገድ ፡ ተክ። ቀሌ)።
አያት [1] ፡ ምኖች፤ ምንድሮች፤ ማናቸውች የትኞች፤ እኔቶች፤ እነማን፤ እንዴት ያሉ። አያቶሙ ይኄይሱ። ዕቀብ ትእዛዛቲሁ፤ ወይቤሎ አያተ። አያተ ሥሕጸታተ ዘነበበ ፡ (ፊልክ ፡ ፩። ማቴ፲፱
፡ ፲፰። ቄር ፡ ጰላ)። ፡ (ዕር፳ ፡ ቍ፺) ተመልከት።
[2] ፡ (ታት፤ አያያት) በቁሙ፤ አያት እሚታ፤ ያባትና የናት ወላጆች አምሳዮች።
አያዪ ፡ (ዪት ይያን ያት) የሚመስል፤ መሳይ እኩያ አምሳያ።
አያይ ፡ (ያት) አምሳል አምሳያ፤ አንጻር እኩያ፤ አብነት መምህር፤ መልክ ግብር። ሰላም ለጎርጎርዮስ ወለአብድራጦስ አያዩ። ወቦ ላዕሌሁ ዘሕብረ በረድ አያይ። ወተወለጠ አያዩ። ኮነ ሐዋርያዌ በኵሉ አያዩ
፡ (ስንክ ፡ መስ፳፬። ጥር፩። ሐም፲፮። ፳፯። ግን፯)። በአያይ ፈንታ አያያት እንደ ማለት ኹሉ ጐርዶ አሳጥሮ አያት ይላል፤ አምሳል ማለት ነው። አያተ አዕናቍ እለ ተሰክዓ። አልቦ አያተ ግብራት ውስቴቱ። በዝኬ አያት ንለቡ። አላ በካልእ አያት። በአያተ እላንቱ። ወአያቶሙሰ ንነግር ፡ (ደራሲ። ቄር ፡ እስት ፡ ጰላ)።
አይ ፡ (ዐረ አይ። ዕብ ኤይ) ምን ምንድር ፥ ማን ማነኛው፤ ማናቸው፤ የቱ የትኛው። ለወንድም ለሴትም ፥ ለሩቅም ለቅርብም ይከታል፤ ንባቡ ጥያቄ ምስጢሩ አሉታና አንክሮ ፥ በጥያቄነቱ ስምን ቦታን ጊዜን ይፈልጋል፤ ሁ ኑ ያጋንኑታል፤ መኑንና ምንትን አይቴን ተመልከት። አይ ፥ ባለቤት ሲጠራ ቅጽል ፥ ባለቤት ሲቀር በቂ ይኾናል። አይ ልቡና ወአይ ነቢብ ወአይ ሰሚዕ ዘይክል አእምሮ። አይ አፍ ወአይ አስናን ወአይ ከርሥ ዘያገምር። አይ ይእቲ ዛቲ፤ አይ ውእቱ ዝንቱ
፡ (ውዳ። ቅዳ። ድጓ)። አይኑ ውእቱ መዋቲ ዘይነጽሕ። አየኑ ቤተ ተሐንጹ ሊተ። በአይ እምእላንቱ እሣሀሎሙ። በታሕተ አይ ዕፅ ፡ (ኢዮ፬ ፡ ፲፯። ኢሳ፷፮ ፡ ፩። ኤር፭ ፡ ፯)። እምዮም እምይእዜ በማለት ፈንታ ወአይ ይላል፤ መቼም መች ማለት ነው ፡ (ዘፀ፬ ፡ ፲)። አየየን ተመልከት፤ የዚህ ዘር ነው።
አይሁዳዊ ፡ (ዪ–ይ) በቁሙ፤ የአይሁድ ወገን ይሁዲ እስራኤላዊ፤ ወይም ፈላሻ ግዙር። ወነገርዎ ከመ መርዶኬዎስ አይሁዳዊ ውእቱ። ቦኑ አነ አይሁዳዊ። አይሁዳይ። አይሁዳውያን። ወእሙሰ አይሁዳዊት ፡ (አስቴ፫ ፡ ፬። ዮሐ፲፰ ፡ ፴፭። ሲኖዶ። ስንክ
፡ ኅዳ፳፩። ግብ፲፮ ፡ ፩)።
አይሁድ ፡ በቁሙ፤ ይሁዶች የይሁዳ ዘሮች። ይህ ስም እስከ ባቢሎን ምርኮ ድረስ የይሁዳ ብቻ ነበረ፤ ከምርኮ በኋላ እስከ ክርስቶስ ድረስ ለእስራኤል ኹሉ ተሰጥቷል። ፈላሻና እስራኤል። ሕዝብና አሕዛብ ሲኾኑ በይሁዳ ስም አይሁድ መባላቸው፤ ኋላ ከይሁዳ ወገን በሚመጣው በክርስቶስ ክርስቲያን ለመባል ምሳሌ ነው ፡ (ግብ፲፩ ፡ ፳፮)። ወፈቀደ ያጥፍኦሙ ለኵሎሙ አይሁድ ዘውስተ ደወለ መንግሥቱ ለአርጤክስስ። ቦኑ ለባሕቲቶሙ ለአይሁድ እግዚ አኮኑ ለአሕዛብኒ። እስመ መድኀኒት እምነ አይሁድ ፡ (አስቴ፫ ፡ ፮። ሮሜ፫ ፡ ፱። ዮሐ፬ ፡ ፳፪)። ከክርስቶስ ወዲህ ግን በክሕደታቸው ስለ ተነቀፉ አይሁድነታቸው ወዳረመኔነት ተለውጧል። ጉባኤ አይሁድ እለ ይሰመዩ በከንቱ አይሁደ። ፅርፈቶሙ ለእለ ይብሉ አይሁድ ንሕነ ወኢኮኑ፤ አላ ማኅበሩ በሰይጣን ፡ (ዲድ ፡ ፲፪። ራእ፪ ፡ ፱)።
አይኅ ፡ ጥፋት ስጥመት፤ የዝናም የጐርፍ የባሕር አደጋ፤ ታላቅ ብርቱ ዝናም፤ ዝናመ መዐት ከልክ ያለፈ የተረፈ፤ ዝናመ ኖኅ። ማየ አይኅ። እምነ ማይ ዘአመ አይኅ። ይመጽእ ዝናም ከመ አይኅ። አይኅ ዘነፋስ። ጸለየ ጸሎተ ጊዮርጊስ ወአውረደ እምሰማይ አይኀ እሳት ላዕለ ኵሎሙ ሰብዓ ነገሥት
፡ (ዘፍ፮ ፡ ፲፯። ኢሳ፶፬ ፡ ፱። ሕዝ፲፫ ፡ ፲፩። ቀሌ። መዋሥ)። ውሒዝ በማለት ፈንታ አይኅ ይላል ፡ (ዳን፱ ፡ ፳፮። ናሖ፩ ፡ ፰)።
አይኅአ ፡ (አ ተቀጥላ ነው) ወረደ፤ ከላይ ከሰማይ መጣ፤ ዘነመ ፈሰሰ። አይኅአ ቃል እምሰማይ። እምሰማያት እምኀበ አብ አይኅአ
፡ (ድጓ። ኪዳ)።
አይሉል ፡ (ዕብ ወጽር ኤሉል) ስመ ሳድስ ወርኅ ዕብራዊ፤ የዕብራውያን ስድስተኛ ወር ከሚያዝያ፤ ይኸውም መስከረም። አመ ዐሡሩ ወኀሙሱ ለጽልመተ አይሉል
፡ (ነሐ፮ ፡ ፲፭)።
አይመነ ፡ አቀና፤ ቀኝ አደረገ፤ ወደ ቀኝ መራ አስተማረ። ሀይመነንና አእመነን እይ፤ የዚህ አግዋር ናቸው።
አይቆና ፡ (ጽር ኢኮን፤ ኢኮና) ሥዕል፤ መልክአ ሥዕል በእጅ የተሣለ የተመሰለ። እምአይቆናሃ ወፂኣ ፡ (ስንክ ፡ ታኅ፳፩)። ባለቅኔዎች ግን የሥዕል ቤት ይሉታል።
አይበሰ ፡ አደረቀ፤ አስደረቀ። ኣየብሶሙ ለአፍላግ። ለሥርዉሂ ያየብሶ ነፋስ። ኣየብስ ዕፀ ርጡበ። ያረጥባ ለምድር ወያየብሳ ለባሕር። ያየብስዎ በፀሓይ ፡ (ኢሳ፶ ፡ ፪። ኢዮ፲፭ ፡ ፴። ሕዝ፲፯ ፡ ፳፬። ሳታት። መ ፡ ፈ)።
አይቴ ፡ (ዐረ አይነ። ዕብ አዪን፤ አና) ቃለ ጥያቄ፤ ንኡስ አገባብ፤ አገባብነቱም የቦታ። ፍችው ሔት፤ ዬት፤ ወዴት፤ ወደዜት። ቦታን የቦታን ስም ይሻል፤ ኑ መ እያጋነኑት ሳያጋንኑትም፤ ሂ ኒ ትራስ እየኾኑት ትራስ ሳይኾኑትም ይነገራል። አይቴኑ አሐውር። አይቴመ ምረግ ዘመረግሙ። አይቴኑመ ቃለ እግዚ። ወኢበአይቴኒ። አይቴ ሀሎከ። አይቴ ቀበርክምዎ። አይቴ ብሔራ፤ ወአይቴ ማኅደራ፤ አይቴ ደወላ፤ ወበአይቴ ተረክበ አሠረ ፍኖታ
፡ (መዝ ፡ ፻፴፰። ሕዝ፲፫ ፡ ፲፪። ኤር፲፯ ፡ ፲፭። ፫ነገ ፡ ፲ ፡ ፲፪። ኢዮ፴፰
፡ ፬። ዮሐ፲፩ ፡ ፴፬። ቅዳ ፡ ኤጲ)። የቦታ አገባቦች በ ኀበ እንተ እም እስከ ይሰማሙታል። የቀረውን በቦታው ተመልከት
፡ (ዕር፳ ፡ ቍ፺)።
(ጥ) አይኖ ኖት ፡ (አየነ
፡ ይኤይን የአይን) መከባክብ፤ ማደላደል ማቀማጠል፤ ማስመቸት። መጽሐፍ ግን በአየነ ፈንታ ተአየነ ይላል፤ አድራጊውን በተደራጊ። ወእመ ትቤለኒ ምንት ውእቱ ተድላ እብለከ ተአይኖ ሥጋ ፈድፋደ ወሴስዮቱ ሐሊበ ወመዓረ ወአዕርፎቱ እምጻማ ፡ (አፈ ፡ ድ ፲፫)።
አይይ ዮት ፡ (አየ፤ አየየ የአይይ ይእየይ፤ ይእይይ። አይ)። መምሰል፤ መተካከል፤ አምሳል መርገርፍ መኾን። ኪያን ተመልከት፤ የዚህ ዘር ነው።
አይድዐ ፡ (ብሀለ፤ ነበበ) አለ ነገረ አስተማረ፤ አመለከተ፤ አሳወቀ አስታወቀ፤ አስረዳ። ወአነ ኣየድዕ ግብርየ ለንጉሥ። መፍትወ ኣየድዕ። አይድዕ ከመ ኣሐይዋ ለምድር። ኢያይድዐት ብሔራ። ይእቲ አይድዐቶ ለንጉሥ ምክሮሙ ፡ (መዝ
፡ ፵፬። ምሳ፰ ፡ ፮። ሔኖ፲ ፡ ፲፩። አስቴ፪ ፡ ፳ ፡ ፳፪)።
አይጥ ፡ በቁሙ፤–ዐይጥ።
አደመነ ፡ አጨለመ አጠቈረ አሳዘነ። እፎ አደመና እግዚ ለወለተ ጽዮን። ያዴምኖ ለገጽ ከመ ጸለሎ መቅፁት። ብእሲት መንጐርጕርት ታዴምን ገጸ ምታ ፡ (ሰቈ፪ ፡ ፳። አርጋ ፡ ፪ ፡ ፈላስ)።
አደሳን ፡ (ሳት። ሱር ሀዳሲን። ዕብ ሀዳሲም) አደሶች የሽነት የባርሰነት ዛፎች። ማእከለ አዕዋም ዘአደሳን
፡ (ዘካ፩ ፡ ፰)። አንዳንድ መጣፍ ዘአዴሼም ይላል፤ አንዳንዱም አዴሼምን ትቶ ፥ በአዕዋም ፈንታ ማእከለ ክልኤ አድባር ይላል፤ ኹሉም ስሕተት ነው።
አደስ ፡ (ዕብ ወሱር ሀዳስ) በቁሙ፤ የሽቱ ዕንጨት፤ ሽነት ባርሰነት። ምርስኔን ተመልከት፤ ከዚህ ጋራ አንድ ነው።
አደር ፡ እሾኻም ዕንጨት ጋሬጣ፤ እሾኹ እንደ ችንካር ያለ መርዛም።
አደብደበ ፡ አስደበደበ። አስጨነቀ፤ አፈዘዘ አደከመ። ለእመ አደብደበታ ኀጢአት ለነፍስ ፡ (ፊልክ ፺፭)።
አደነ ፡ በቁሙ፤ ሻ ፈለገ፤–ዐደነ።
አደንቀወ ፡ አደነቈረ ደንቈሮ አደረገ፤ አሰኘ።
አደንገፀ ፡ አስደነገጠ፤ አስፈራ አሳዘነ። ምንት ያደነግፀኪ። ሕልም ያደግፆ ለእብድ። እበድከ አደንገፀኒ
፡ (ዕር ፡ ኢሳ፲፩ ፡ ፲። ሢራ፴፩ ፡ ፩። ፵፯ ፡ ፳)።
አደክተመ ፡ አደኸየ ድኻ አደረገ፤ አባት እናት አሳጣ። አደክተመኒ እምአቡየ ወእምየ ፡ (ዮሴፍ)።
አደየ ፡ ከፈለ፤–ዐድይ ዐደየ፤ ዕዳ።
አደግደገ ፡ አከሳ አቀጠነ አጐሰቈለ። አማለደ አአማለደ፤ አስገሠገሠ። አስታጠቀ፤ አስደገደገ። ደዌ አደግደገ ሥጋሁ ሥጋሁ። ወያደገድጎ ከመ ላሕም። አርባዕቱ ግብራት ያደገድጉ አባለ፤ ሐዊረ ፍኖት ወትጋህ ዘልፈ ወጸዊም ወጽምእ በሐሩር፤ አክሳ
፡ (ዮሴፍ። መዝ ፡ ፳፰። ፈላስ) ምንት ከመ ዝ ያደገድገከ፤ አማለደ ፡ (፪ነገ ፡ ፲፫ ፡ ፬)።
አደፋዊ ፡ (ዊት ውያን ያት) እድፋም ጕድፋም ጭቅቅታም።
አደፍ [1] ፡ (ብ አእዳፍ) በቁሙ እድፍ ጕድፍ፤ ርስሐት እዳው። ግብ ዘምሉእ አደፈ ወዕፄ
፡ (ስንክ ፡ ሐም፩)።
[2] ፡ የሴቶች ግዳጅ ፥ ትክቶ። ተርታ መናኛ እኽል ንፋሽ ገለባ ሐሠር ያለው። ጥሩና አደፍ እንዲሉ
፡ (ዐማርኛ)።
አዲም ፡ (ብ አድያም) ቅጽልና ጥሬ። ቀይሕ ቀይሓዊ፤ ደምማ፤ ዐረብ አንቀልባ፤ ነት የገባ ቈርበት። ማእሰ በግዕ ግቡረ አዲም። ቅናት ዘአዲም። ቅናታቲሆሙ አዲም ፡ (ዘፀ፴፱ ፡ ፳፩። ፬ነገ ፡ ፩
፡ ፰። ማቴ፫ ፡ ፬። ማር፩ ፡ ፮። ሥር ፡ ጳኵ)።
(ላ) አዲም ሞት ፡ (አደመ የአድም ይእድም። ዕብ አዳም። ዐረ አዲመ) መቅላት ፥ ቀይ መኾን ፥ ደም መምሰል ፥ ዐለላ እንሶስላ መግባት በቀይ ስባቅ መነከር መታለል፤ የነት የልብስ።
አዲር ፡ (ብ አዲሪም ዕብራ) ክቡር ምስጉን ታላቅ ገናና። ጥቀ ተሰብሐ ባለው ፥ ማህ አዲር ሽምኻ እንዲል ፡ (መዝ ፡ ፰)።
አዲው ፡ እጃም ባለእጅ መኾን፤ እጀ ሥራ ማወቅ፤ በተግባረ እድ መሠልጥን መራቀቅ። መያዝ መጨበጥ፤ እጅ ማድረግ፤ ከእጅ ማግባት።
አዲው ዎት ፡ (አደወ የአዱ ይእዱ። ዕብ ያዳህ) መጥረግ መጋፍ፤ መግፋት ማስገለል ፥ መኰስተር መሰብሰብ ዐፍሦ መጣል፤ መወርወር ማሽቀንጠር፤ የጕድፍ። ወነሥኣ ደናግል ማእድወ ወአደዋ ወአውፅኣ ኵሎ መሬተ እምዐውደ ማኅፈድ
፡ (ሄርማ)።
አዲግ ጎት ፡ (አደገ የአድግ ይእድግ። ዐረ ሐደጀ) መሸከም፤ መጫን፤ ማንገት ማዘል መደብለል፤ ተሸካሚ መኾን፤ በዠርባ። በቁሙ፤ ማደግ መመንደግ፤ ቁመትና ጐን መጨመር፤ ለሸክም ለጭነት መብቃት ፥ የሰው የከብት።
አዲፍ ፎት ፡ (አደፈ የአድፍ ይእድፍ) ማደፍ መኵለፍለፍ፤ እድፋም ጕድፋም መኾን።
አዳማ
፤
(ዕብራ)
፤
ምድር የብስ ገራህት ፤ ቀይ መሬት ፤ መረሬ ፤ ቅላቱ
ሸክላ ሕጕሬ ፤ ብስል በርበሬ የሚመስል ፤ ያፈር ወይዘሮ። አዳማ በሴት አንቀጽ ነው ፤ ሲያበዛ አዳሞት ይላል። ጋላም ቀይ ሲል ዲማ ዳማ ይላል።
አዳማዊ ፡ የአዳም ዘር ሰው፤ ወይም ባሕርዩና ግብሩ ተፈጥሮው። ልሕኵት አዳማዊት
፡ (ያዕ ፡ ዘእል)።
(ጥዳ) አዳም [1] ፡ በቁሙ፤ መዠመሪያ ሰው የሰው ኹሉ አባት፤ ጐበዝ ጕልማሳ ወንድ ተባት። የሥጋው ተፈጥሮ ካፈር ከመሬት ስለ ኾነ አዳም መባልን ከአዳማ ወስዷል። ሥግው እምድር ዘተሠገወ እመሬት፤ ጽቡር ልሕኵት፤ ቀይሐ ሥን ብጹሐ አምጣን ማለት ነው
፡ (ዘፍ፪ ፡ ፲፮ ፡ ፲፱–፳፫)። ኹለተኛም እንስሳዊና መልአካዊ ፪ ባሕርያት ስላሉት፤ በሥጋው መዋቲ ድኩም ፈራሽ በስባሽ፤ በነፍሱ ነባቢ ለባዊ ሕያው ባለአእምሮ ይባላል
፡ (ዘፍ፪ ፡ ፯)። አዳም በ፮ኛ ቀን መዠመሪያ ከምድር የፈለቀ የሰው ኹሉ ምንጭ ስለ ኾነ በዘር በሩካቤ ከርሱ እየተቀዳ ሞትና መቃብር የሚጠጡት ምድራዊ ሰው ኹሉ በርሱ በምንጩ ስም አዳም ይባላል ፡ (ዘፍ፫ ፡ ፲፱)። ግእዝ ግን ዕብራይስጥና ዐረብ ትግሬና ዐማርኛም ሳይቀሩ አዳም የሚሉትን ለውጦ ዕጓለ መሕያው ይላል፤ ፍችውን በቦታው ተመልከት።
[2] ፡ የሚያምር፤ ደስ የሚያሰኝ፤ ውብ ደግ መልካም፤ መልከ መልካም። እንደዚህ ያለው ውስጠ ዘ፤ ነቋር ጸጓር ፀዋግ ጸያፍ፤ የዋህ መካሕ፤ ሀካይ ይህን የመሰለ ዐጓጕል ቃል ኹሉ ፥ ቅጽልነቱ ፈናፍንታም ነው፤ ለወንድም ለሴትም ይኾናል። ወራዙት ዘአዳም አርኣያሆሙ። አዳም አጥባትኪ እምወይን። ከመ ማይ ቈሪር አዳም ለነፍስ ጽምእት። አዳም ወሠናይት። አዳመ ዝክር ወዜና። ወኮነ አዳመ ዝንቱ ነገር በቅድመ ንጉሥ
፡ (ዮሴፍ። ማሕ፩ ፡ ፪። ምሳ፳፭ ፡ ፳፭። ድጓ። ስንክ ፡ ሐም፲፬። ፪ዜና ፡ ፴ ፡ ፬)።
አዳር ፡ (ራት። ዕብራ) የዕብራውያን ወር መጋቢት የጥቅምት ፮ኛ የሚያዝያ ፲፪ኛ፤ በሠግር ጊዜ ፲፫ኛ
፡ (አስቴ፫ ፡ ፯። ዕዝ፮ ፡ ፲፭)። ፍችው ዕበይ ርሕብ ልዕልና ማለት ነው፤ ኅዳርን ተመልከት። ፡ (ታሪክ) በ፫ በ፫ ዓመት አንዳንድ ወር ሠግር እየጨመረ ዓመታቸው ፲፫ ወር ይኾናል፤ ስለዚህ መጋቢት ካለቀ በኋላ እንደ ገና መጋቢት ይላሉ። ይኸውም ፀሓይ ከጨረቃ የምታተርፈው ፲ ፲ ቀን አለና ያ ተሰብስቦ ነው። ወለለ ሠለስቱ ዓመት ያሠግሩ አሐደ ወርኀ ወይከውኑ አዳራት ክልኤተ
፡ (አቡሻ ፡ ፳)።
አዳዊ ፡ (ዊት ውያን ያት፤ አደውት) የሚጠርግ ጠራጊ፤ ባለወግ፤ የከተማ የቤተ ክሲያን።
አዴራ ፡ አደርማ፤ ቀኖት የቀኖት ስም፤ አራተኛ ቀኖት የቀኝ እግሩ። ሳዶር አላዶር ዳናት አዴራ ሮዳስ፤ ኀምስቱ ቅንዋተ መስቀል
፡ (አዋልድ የጸሎት መጽሐፍ)። ቀኖት ማለትም ችንካሩን ብቻ አያሳይም ስቍረቱንም እንጂ፤ ዐምስተኛው ቀኖና ኵናት ነው።
አዴሮት ፡ (ዕብ አዴሬት፤ ብ አዳሮት) የላይ ልብስ ታላቅ ሰፊ፤ ጀባ ካባ መጐናጠፊያ፤ ኀይል ጽንዕ። ባለቅኔዎች ግን ሥርጥ መንገድ ዕዳሪ ሸንጎ ይሉታል ፡ (ጥሬ ፡ ሰዋ)።
አዴገነ ፡ አስደገነ፤ አስከተለ ተከታይ ላከ። ወአዴገንዎ ውስተ ለኪስ ወቀተልዎ
፡ (፬ነገ ፡ ፲፬ ፡ ፲፱)።
አድኀረ ፡ (አስመረቀ አስመሰገነ) አቈየ፤ አስቈየ፤ አዘገየ። አስከተለ፤ በኋላ አደረገ። አድኀሩ ፍትሐ ላዕሌሁ። እመ አድኀርከኒ። አድኀርክዋ እምተበኵሮ፤ አቈየ
፡ (ዮሴፍ። አዋል)። ሞተ በሃይማኖት ወአድኀረ ሰብአ ድኅሬሁ። አድኀረ መብዝኅተ ሰብኡ ምስለ እኍሁ። ኦ አብዳን እፎ አድኀርክምዎ ለመለኮተ አምላክነ ጰራቅሊጦስ እምጥንተ ህላዌሆሙ ለፍጡራን
፡ (ዮሴፍ። መጽ ፡ ምስ)። በአድኀረ ፈንታ አስተደ(ድ) ኀረ ይላል፤ ፍችው አድራጊና አስደራጊ ነው፤ ዳ ካላለ አደራራጊነት የለውም። ለእመ አንተ አስተደኀርከ ቀቲሎታ። አስተድኀረ ወልዶ ጢጦስ ይዕግታ ለሀገር። ኢታስተድኅሮ እስከ ጌሠም። ወያስተድኅሩ መብልዖሙ እስከ ይመሲ
፡ (ዮሴፍ። ፍ ፡ ነ ፡ ፫።አቡሻ ፡ ፲፪። ዮሐ፪ ፡ ፲)።
አድኀነ ፡ አዳነ፤ አስዳነ፤ ታደገ አወጣ፤ ረዳ ዐገዘ። ያድኅን በዕለተ ምንዳቤ። ስእኑ አድኅኖ። አድኅኑ ግፉዐ። አድኅን ርእሰከ ፡ (ሢራ፪ ፡ ፲፩። ኢዮ፬ ፡ ፳። ኢሳ፩ ፡ ፲፯። ማቴ፳፯ ፡ ፵)።
አድኃኒ መድኀኒ ፡ (ኒት ንያን ያት) የሚያድን የሚቤዥ የሚታደግ፤ ታዳጊ። የሰው ስም። መድኀኔ ኵሉ። መድኀንየ። መድኀኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ። መድኀኔ ዓለም። መድኀኒት መቤዝዊት። አባ አድኃኒ
፡ (ጥበ፲፮ ፡ ፯። መዝ
፡ ፲፯። ፊልጵ፫ ፡ ፳። ቀሌ። ድጓ። ስንክ ፡ ጥር፫)።
አድሐከ ፡ አዳከ አስዳኸ መዳኽ አስተማረ። በበ ንስቲት ያድሕኮ ፡ (አፈ ፡ ድ፩)።
አድኀፀ ፡ አዳጠ፤ አስዳጠ፤ ዐነቀፈ አሰናከለ፤ ሰረጀ ዘረጠጠ፤ ለመጣል። አድኀፆ ለላእክ። ኢይደግም አድኅፆተ እግሮሙ። ተዐቀባ ኢታድኅፅከ ልሳንከ። ኰኵሕ ዚያድኅፅ። አድኀፅክዎ ለዲያብሎስ ወነሠትክዎ እመንበሩ ፡ (ዮሴፍ። ፬ነገ ፡ ፳፩ ፡ ፰። ሢራ፳፰ ፡ ፳፮። ኢሳ፰ ፡ ፲፬። ቀሌ)።
፡ ጨነገፈ ፡ አስጨነገፈ አሶረደ፤ ከመ ፃእፃእ ዘአድኀፀቶ ማሕፀነ እሙ። ብእሲት ዘትሰቲ ፈውሰ ከመ ታድኅፅ ፃእፃእ እማሕፀና
፡ (ኢዮ፫ ፡ ፲፮። ፈ ፡ መ ፡ ፬ ፡ ፬። ዘፀ፳፩ ፡ ፳፪ ፡ ፳፫። ፍ ፡ ነ ፡ ፵፰)። በአድኀፀ ፈንታ ድኅፀ ይላል፤ አያስኝም ፡ (ኢዮ ፡ ፳፩ ፡ ፲)።
አድኅኖ ት ፡ ማዳን፤ መታደግ መቤዠት፤ ነጻ ማውጣት፤ ትድግና። በእንተ ሕቢት ወአድኅኖ፤ አድኅኖሰ ዘነፍስ ውእቱ ወተሐብዮ ዘንዋይ። ዘእግንዚ አድኅኖ። ወንትፌሣሕ በአድኅኖትከ ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፳፯። መዝ
፡ ፫። ፱)።
አድለቀ ፡ አወከ አናወጠ፤ አስመታ አስደለቀ። መጽሐፍ ግን በደለቀና በአድለቀ ፈንታ ኹለቱን አዕማድ ደርቦ አድለቅለቀ ይላል።
አድለቅለቀ ፡ አነዋወጠ፤ ተነዋወጠ ፡ (መዝ ፡ ፳፰። ፶፱። ፺፰)። አነ ኣድለቀልቃ ለምድር። ወኣድለቀልቆን ለአህጉር። ዘያድለቀልቃ እመሠረታ፤ ገቢር
፡ (ዕብ፲፪ ፡ ፳፮። ኢሳ ፲ ፡ ፲፬። ኢዮ፬ ፡ ፮)። ያድለቀልቅ ሰማይ ወምድር። አድለቅለቁ አድባር እምኔሁ። ርዕደት ወአድለቅለቀት ምድር ያተገብሮ ፡ (ዮኤ፬ ፡ ፲፮። ናሖ፩ ፡ ፭። መዝ ፡ ፲፮)።
አድለወ ፡ አስመዘነ። አደላ፤ አስደላ፤ አስመቸ ደስ አለኘ፤ ግቡ አደረገ አበቃ። ታደሉ ሊተ መክሊተ ብሩር። ኢታድሉ ለሰብእ እንበይነ ላሕዩ። ለእግዚ አድልዎ ኢይክሉ። ዘንተ ሕዝበ አድሉ ለነሢአ ምስጢርከ ፡ (፫ነገ ፡ ፳ ፡ ፴፱። ሢራ፲፩ ፡ ፪። ሮሜ፰ ፡ ፰። ቅዳ ፡ ሕር)።
አድላዊ መድልው መደልው ፡ (ዋን) (ዋን) የሚያስመዝን፤ አስመዛኝ። በቁሙ፤ የሚያደላ፤ የሚያስመች። ግብዝ ሰነፍ፤ ሞኝ ዋሾ። ብእሲ መደልው። ኦ መደልው። ፈሪሳውያን መደልዋን። ረበናት መደልዋን ፡ (ኢዮ፴፬ ፡ ፴። ማቴ፯ ፡ ፭። ፳፫ ፡ ፲፫። ዳን፩ ፡ ፭)። ባለቅኔዎች ግን አመድለወ ብለው ይገሱና፤ መደልውን ከዚህ ያወጣሉ።
አድመመ ፡ አስደመመ፤ አስደነቀ አስገረመ፤ ዝም አሰኘ። አድመሞሙ ግብሩ። ፈድፋደ ያደምመኒ። በርእየ መንክራት ዘታደምም
፡ (ዮሴፍ። አፈ ፡ ተ፲፭። አረጋ ፡ ድ፮)።
አድመወ ፡ አደማ አስደማ፤ ደም አደረገ፤ በደም በከለ። ኦ ሔዋን ናሁ ይበክያ ኵሎን አዋልድኪ፤ ወይዴምዋ በከመ አድመውኪያ አንቲ ለአንትኩ ዕፅ ፡ (ቅዳ ፡ አት)።
አድመፀ ፡ አልጮኸ አሰማ፤ አስደመጠ። ፡ (አስዳመጠ አስራመመ)። አነ እግዚ ዘኣደምፆ ለማዕበላ። እማት ያደምፃ ቃለ ሰቈቃው። ለብሔረ አግዓዚ አድያሚሃ አድመፅከ ፡ (ኢሳ፶፩ ፡ ፲፭። ጥበ፲፰ ፡ ፲። ድጓ)።
አድማስ [1] ፡ (ጽር አዳማስ። ዕብ አናኽ። ዐረ ዚጅ) ናእክ፤ ርሳስ፤ ወይም ብረት፤ የሐዲስ ሕንጻና የማእዝን ልክ፤ መመዘኛ ማስተካከያ፤ ነደቅት በቀጭን ገመድ ጫፍ አስረው እንደ መልሕቅ ከላይ ወደ ታች የሚሰዱት። የደንጊያው ተራ የማእዝኑ ሥራ አለአድማስ አይቃናም፤ ማእዝኑ ደግሞ ከርሱ ስም ነሥቶ አድማስ ይባላል። ወናሁ ብእሲ ይቀውም ዲበ አረፍተ አድማስ፤ ወውስተ እዴሁ አድማስ። ከመ ቅጽረ አድማስ
፡ (ዓሞ፯ ፡ ፰። ራእ ፡ ባሮ)። አድማስ የልክ የሚዛን የማእዝን ስም ስለ ኾነ ባለቅኔዎች የምድር ዳር ዙሪያዋ ክበቧ ቅጥሯ ዳር ድንበሯ ይሉታል።
ወተሀውከት ኵላ ሀገር ኢየሩሳሌም፤ ፍኖተ አድማስ መከራሃ አኮኑ ኢይትፌጸም። ወእንዘ ዳዊት ያስቈቁ በተፈልጦ አምኖን ነፍስ ካዕበ አደንገፆ ርሕቀት አቤሴሎም አድማስ
፡ (ቅኔ)።
[2] ፡ (ዐረ አልማስ። ዕብ ሐላሚሽ) የደንጊያ ንጉሥ፤ አልማዝ ዕንቍ ፈርጥ። ጥኑ ጠንካራ ደንጊያ፤ ኰኵሕ አለት የማይሰበር የማይፈነከት። የነጠረ ብረት፤ ደንጊያ የሚጠርብ ኰኵሕ የሚነድል፤ የሚበሳ የሚሰረስር። እብነ አድማስ ሠራዊ ወደምሳሴ ኵሉ። ጽኑዕ ውእቱ ዘኢይትሔየክ፤ ዘውእቱ እብነ አድማስ ኀያል። መላዬ ኀጻውንት አድማስ
፡ (መቃ ፡ ገ፳፭። ቅዳ ፡ ሕር። ስንክ ፡ ኅዳ፲፪)።
አድምዐ ፡ አስገኘ አስመረመረ በቶሎ እንዲገኝ አደረገ።
(ጥ) አድሞ ሞት ፡ (አደመ ይኤድም ፡ የአ ድም) ማማር ፡ መዋብ፤ ደማም ፡ ደመ ግቡ ፡ መኾን ፡ ማስጐምዠት ደስ : ማስኘት፤ በባሕርይ ፡ በመልክ ፡ አዳምን ፡ መምስል፤ ከርሱ ፡ መተካከል። ሥን፤ወላ ሕይ ፡ ይኤድማ ፡ ለሀይን ፡ እንተ ፡ አደመቶ ፡ እም ኦሆን ፡ ብእሲት። ሶበ ፡ ተፈሥሑ ፡ በአድሞ ፡ ሥነ ፡ ላሕዮሙ ፡ -ቍርባንከሙ ፡ ኢይኤድመኒ። አደሞ ፡ ቃላ ፡ በቅድሜሁ ፡ በከመ ይኤድመከ ፡ ግበር ፡ ም ስሌየ ፡ ኵሎ ፡ ዘንሰየ ፡ ወአደሞ ሰስሎሞን ፡ በነፍሱ ፡ ከመ ፡ ይግበር ፡ (ሢራ፵ ፡ ፳፪። አስቴ፪ ፡ ፬። ጥበ፲፫ - ፫። ኤር፮ : ፳። ዮዲ፲፩ ፡ ፳። ጦቢ፫ ፡ ፮። ፪ዜና ▪ ፯ ፲፩)። በአደመ ፡ ፈንታ ፡ አስተኣደመ ፡ ይላል፤ ስሕተት ፡ ነው። ኢያስተኤድሞ ፡ ሀጕሎሙ ፡ ለሕያዋን ፡ (ጥበ፩ ፡ ፲፫)።
አድረሰ ፡ አደረሰ አስደረሰ፤ ጨረሰ አስጨረሰ፤ የቦታ የሥራ የድጋም የዜማ።
አድረከ ፡ (አድረገ) አጠና አበረታ፤ መድረክ ሠራ አጋጠመ።
አድረገ ፡ አስደረገ፤ ደረጃ አሠራ። በቁሙ፤ ሠራ አደረገ ፡ (ዐማርኛ)።
አድርያ አድርያቲክ ፡ የባሕር ስም፤ በኢጣልያና በግሬክ መካከል ያለች
፡ (ግብ፳፯ ፡ ፳፯)።
አድሮሄም ፡ (ዕብ አዲሬሄም። ጽር አዶሪም) ዐበይቶሙ፤ ጽኑዓኒሆሙ፤ ክቡራኒሆሙ፤ መላእክ(ህቅ) ቲሆሙ ማለት ነው። ባለብሉዮች ግን ገባሮች ይሉታል
፡ (ነሐ፫ ፡ ፭)።
አድቀቀ ፡ አደቀቀ፤ አስደቀቀ፤ ፈጨ ደቈሰ። ያደቅቆ ለኵሉ ፡ (ዳን፪ ፡ ፵። ዘፀ፴፪ ፡ ፳)።
አድነነ ፡ አደነነ አስደነነ፤ አጐነበለ አስጐነበሰ፤ ሰገደ አሰገደ።አድነነ ርእሶ ከመ ያጥምቆ እደ ገብር። አድንኑ አርእስቲክሙ። ፀሚደ አርዑት ያደንኖ ለክሣድ። አድነኑ አርእስቲሆሙ ወሰገዱ ለአዳም ፡ (ቅዳ። ሢራ፴ ፡ ፴፭። ቀሌ)።
አድናኒ መድነኒ ፡ የሚያጐነብስ የሚያስጐነብስ፤ አጐንባሽ አስጐንባሽ። ፡ (ተረት) ዐፋሽ አጐንባሽ። መንኰራኵረ ሠረገላ መድነኔ ክሣድ ፡ (ስንክ ፡ ጥር፲፭)።
አድከመ ፡ አደከመ፤ አለፋ አታከተ አሰለቸ፤ አሰነፈ። ያደክም ቃሎ ወይዬውሀከ። ያድክም ኀይሎ እንዘ ይትቀነይ። ስካር ያደክም ኅሊና ፡ (ሢራ፳፱ ፡ ፭። ፴፰ ፡ ፴። ቀሌ)።
አድወየ ፡ አደወየ ድውይ አደረገ፤ ደዌ አሳደረ። መጽአ ላዕለ ርእሱ ሐሩር ወአድወዮ ወሞተ። ለእሉ አድወዮሙ ፍርሀት። እንተ አድወያ ጋኔን። መከራት እለ ያደውያ። ምርዓይ ማዩ ዘያደዊ
፡ (ዮዲ፰ ፡ ፫። ጥበ፲፯ ፡ ፰። ሉቃ፲፫ ፡ ፲፩። ማር ፡ ይሥ፪ ፡ ፲፩። ፍ ፡ ነ ፡ ፴፮)።
አድያማ ፡ ስመ ሀገር፤ ካምስቱ አህጉረ ሰዶም አንዲቱ።
አድያም ፡ (ማት) ደወል ዙሪያ አውራጃ፤ ሰበካ ገጠር ታናናሽ አገር፤ ጕልት ግዛት። አህጉር ወአድያሚሆን። በኵሉ አድያሚነ። አድያማተ ትግሬ ፡ (ዘኍ፴፭ ፡ ፪። ዳን፱ ፡ ፲፮። ገድ ፡ ተክ)። አድያም የአዲም ብዢ ፥ ውስጠ ብዙ ነው። አድያማም የወጣው አዲም አዲሞት ፥ አዳማ አዳሞት ከማለት ነው።
አድገ መረብ ፡ (ዕብ ቃኣት ሚድባር። ጽር ፔሊካን) ዖፈ መረብ፤ የበዳ ርኩም፤ ቀቀኖ ፥ ወይም የርኩም ዐይነት መረቦ ፥ ጋጋኖ የባሕር ዶሮ። እሊህ ኹሉ አንድ ወገን ናቸው ፥ ይመሳሰላሉ፤ ቀቀኖንና መረብን ተመልከት፤ አድግ ማለት ግን የመላሽ ስሕተት ነው
፡ (መዝ፻፩ ፡ ፯። ዘሌ፲፩ ፡ ፲፰)። ማሕረጸ አድግ ቢል ፥ የወፍጮ ግልገል ማለት ነው፤ አድግ ታችኛው እናቱ ተሸካሚው ፥ ማሕረጽ ላይኛው ልጁ መጁ። ባለሐዲሶች ግን አህያ የሚያዞረው የመዘውር ወፍጮ ይሉታል
፡ (ማቴ፲፰ ፡ ፮)።
አድገ ገዳም ፡ የዱር የበዳ አህያ ሠጋር ጠጕረ መልካም፤ ነብርማ ሽልምልም፤ ሽመልመሌ ዐይነት። ሐለስትዮን እይ። ወኮንኩ ከመ አድገ ገዳም። በበዓሎሙ ለአእዱገ ገዳም ፡ (ኢዮ፳፬ ፡ ፭። ኢሳ፴፪ ፡ ፲፬። ሔኖ፹፱ ፡ ፲፩)።
አድገመ ፡ አስደገመ፤ አስነበበ፤ ድጋም አስተማረ።
አድግ ፡ (ብ አእዱግ፤ ጋት) ተሸካሚ፤ የጭን የጭነት የኮርቻ ከብት፤ አህያ አጋስስ በቅሎ ፈረስ ገመል ዝኆን። ስምነቱ የግብር ነውና ፥ ለኹሉም ይሆናል፤ ልማዱ ግን ላህያ ብቻ ነው። አድግ ወላሕም። አድገ ጸላኢከ። ወተገድፉ አእዱጊሁ ለቂስ። አእዱግ ፍኖቶሙ
፡ (ቅዳ። ዘፀ፳፫ ፡ ፭። ፩ነገ ፡ ፱
፡ ፫። ቅኔ)።
አድግት ፡ እድግት፤ ፡ (ብ አእድግት፤ እድግታት) እንስት አህያ፤ አህዩት፤ አህዪት፤ ወላድ እመጫት። ይጼዐን ዲበ እድግቱ። ዲበ እድግት ወዲበ ዕዋል ዕጓለ እድግት
፡ (ዘኍ፳፪ ፡ ፳፪። ማቴ፳፩ ፡ ፭)። እድግታት በማለት ፈንታ አእዱግ አእኑስ ይላል፤ አያሰኝም
፡ (ኢዮ፩ ፡ ፫)። ፈረስን ተመልከት።
አድፈረ ፡ አስደፈረ፤ ድፍረት አስተማረ።
አድፈነ ፡ አስደፈነ አስቀበረ፤ የድፍነት አበላ።
አዶናይ አዶናይ [1] ፡
(አዶናውያን አዶናይያን) እግዚኣዊ፤ ወልደ እግዚእ፤ ዘቦቱ እግዚእና። ዓለመኛ ባላዱኛ፤ ዘመናይ። ንትቀበል መርዓዌ አዶናይ ፡ (ድጓ)። እዱኛ አዱኛ ማለት ቅሉ አዶን ከማለት የወጣ ነው።
[2] ፡ አዶናይ፤
፡ (ዕብ አዶን፤ ጌታ። አዶኒ፤ ጌታዬ። አዶኒም ጌቶች) ስመ አምላክ፤ ይ ዝርዝር ነው፤ እግዚእየ ፥ አጋዕዝትየ፤ ወይም ጌታዬ ጌቶቼ። ላንድም ለብዙም ይኾናል፤ ዐዋጁ ግን የብዙ ወንዶች ነው
፡ (ሕዝ፪ ፡ ፬)። ከመ ዝ ይቤ አዶናይ እግዚአብሔር ተብሎ ለአምላክ ሲቀጠልና የአምላክ ስም ሲኾን ምስጢሩ ምስጢረ ሥላሴ ነውና ፥ አንድነትን መደብ አድርጎ ሦስትነትን ያሳያል፤ ዘይቤውም ጌቶቼ እግዚአብሔር እንዲህ አለ ያሰኛል። ይቤ አንድነቱን ፥ እግዚአብሔር ባሕርዩን መለኮቱን ፥ አዶናይ አካላቱን ያመለክታል። ይኸውም ሊታወቅ ኢሳይያስ የሱራፌልን ምስጋና ፫ ቅዱስ ከተናገረ በኋላ፤ ወሰማዕኩ ቃሎ ለአዶናይ እንዘ ይብል መነ እፌኑ ወመኑ የሐውር ለነ ኀበ ዝ ሕዝብ። ወእቤ ናሁ አነ ፈንወኒ ይላል። ለነ ዝርዝሩ ለአዶናይ ነው፤ ንግበር ሰብአ በአርኣያነ፤ ንዑ ንረድ ያለውን ይመስላል። አይሁድ ግን አንድ ገጽ ባዮች ስለ ኾኑ ራሱን ከሱራፌል አግብቶ ይላሉ። በኦሪትና በነቢያት ይህን የመሰለ ብዙ አለ፤ ኤሎሄን ተመልከት። አዶናይ በቋንቋ ኹሉ ለአምላክ ሲቀጸል እግዚእ፤ ለሰው ሲቀጸል አጋዕዝት ይባላል፤ ያውም ቢኾን ለብዙዎች ብቻ እንጂ ላንድ ሰው ብቻ አይቀጸልም። ዕብራይስጡ አዶናይ ሱሩና ኤል ቤት ዐብዴኼም ባለው ግእዙና ዐረቡ ሌላውም ኹሉ። አጋዕዝትየ ገሐሡ ቤተ ገብርክሙ እንዲል
፡ (ዘፍ ፡ ፲፱ ፡ ፪)። እግዚእ አጋዕዝት የሚያሰኘው አንቀጹ እንደ ኾነ አስተውል፤ ይቤ አዶናይ፤ ገሐሡ አዶናይ።
(ጥ) አገለ ፡ ተአገለ፤–ቀማ፤–ዐግሎ ዐገለ።
አገልገለ ፡ (ዐማርኛ) በቁሙ። አገልግል ግልጋሎ ጕልጓሎ ማለት ከዚህ ወጥቷል።
አገምዐ ፡ አስላጨ አስቈረጠ፤ አስለዘበ።
አገበረ ፡ በቁሙ፤ ግድ አለ አስገደደ በግድ አሠራ። መዐቱ ለብእሲ ጽድቀ እግዚ ኢያጌብሮ። ዛቲ መጽሐፍ ኢታጌብረከ ግብረ ዘኢትክል። ሰብእ እኩያን ያጌብሩኒ ዘንተ። ምንትኑ ዘአገበረከ ላዕለ ዝ። አገበሩነ ንግበር። እመኒ አገበሩከ ትብላዕ። ኢያገበርኩከ ከመ ትሡዕ ፡ (ያዕ፩ ፡ ፳። ፈላስ። ስንክ ፡ ሠኔ፳፰። ዮሴፍ። ዮዲ፰ ፡ ፵። ሢራ፴፬ ፡ ፳። ኢሳ፵፫ ፡ ፳፫)።
አገባሪ ፡ በቁሙ፤ የሚያስገድድ አስገዳጅ ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፴፭)።
አገተ ፡ ከበበ፤–ዐጊት
፡ ዐገተ።
አገን ፡ ንፍጥ ያፍንጫ እድፍ
፡ (ሐባብ)።
አገዳ ፡ (ዳት) እግር ዛል፤ ጭን ማኽል አገዳ ቅልጥም የእጅና የእግር፤ መደበኛ ዐጥንት። ዘቦ አገዳ መልዕልተ እገሪሁ። አገዳሁ ዘየማን። ያነጕዕ አገዳሆን። ተሰብረት አሐቲ አገዳ እግሩ። ሌዊ እኅወ ይሁዳ ዘሀብተ ክህነቱ አገዳ
፡ (ዘሌ፲፩ ፡ ፳፩። ፯ ፡ ፴፪። ዘካ፲፩ ፡ ፲፮። ገድ ፡ ተክ። ደራሲ)።
፡ ዐጥቅ አንጓ ክፍል፤ የሽመልና የቀርካሓ የመቃ የሸንበቆ የሸንኰር፤ የጥንቅሽ ያገዳ እኽል ኹሉ።
፡ (ቅኔ ፥ ራስ መኰንን ዐዷ ሳሉ) ጣሊያንንሂ የማሽላ እሸት እንድታበላው ጠብሰኽ፤ ምኒልክ ያ ደገኛ ይመጣልና ወደ ቤትኽ፤ አምጥተኽ ቈየው በፊት ራስ ራሱን ቈርጠኽ፤ አገዳውንስ ይመጡታል እየሰባበሩ አሽከሮችኽ።
አገገጸ ፡ አስፈገፈገ፤ አስፈራ አሳፈረ፤ ተግ አሰኘ አስታገሠ።
አገጸወ ፡ ፊት አሳየ ገለጠ፤ አጐላ አስረዳ፤ ጸላእያንየ ክህሉኒ በተጥባበ ነገረ ሐሰት ለሀጕልየ ወአገጸዉ ኀቤከ ፅሩዐ በገጸ ጽድቅ። ወያጌጹ በእንቲኣሁ ከዊነ አፍቅሮ ክርስቶስ ለዮሐንስ ፈድፋደ እምጴጥሮስ። ለእመ ጐንደየ ኅሊና ውስተ ልቡ ያጌጹ ላዕለ ብእሲ ከመ ያፈቅሮ ሎቱ
፡ (ዮሴፍ። ፊልክ ፡ ፰። ፸፩)። ያጌጹ በማለት ፈንታ ገጽዎት ይላል፤ አያሰኝም። ተጋብኦትነ ለግንዘቶሙ ለምዉታን ወሐዊር ቅድሜሆሙ ውእቱኬ ገጽዎተ አለስተፋንዎቶሙ ለእለ ይነግዱ፤ ወጠብልሎቶሙ በአልባስ ሐዲስ ገጽዎት በእንቲኣሆሙ ከመ ውእቶሙ ናሁ ይትነሥኡ በአልባስ ሐዲስ ዘኢይማስን
፡ (ግንዘ)።
አጉል ፡ በቁሙ፤ ክብ እንክብል፤–ዐጉል።
አጕሐቈ ፡ አጐበጠ፤ አስጐበጠ፤ ጐባጣ አደረገ ዐረቀ ቀለሰ፤ አስጐነበሰ። ፍርግያ ታጕሕቍ ዘባና። ትካዝ ያጕሕቍ አባለ ወያዐውር አዕይንተ ፡ (ኪዳ። ፈላስ ፡ ገ፵፯)።
አጕልሐ ፡ አጐላ፤ አገዘፈ አስገለጠ፤ አስረዳ።
አጕሥዐ ፡ አስገሣ፤ አናገረ። ዘያጐሥዕ ጥበበ ወይሁብ ሕይወተ ፡ (ቅዳ
፡ ሕር)።
አጊን ኖት ፡ (አገነ የአግን ይእግን። ዐረ ዐጀነ፤ አቦካ) መቍረጥ መክፈል ማሥመር፤ የሊጥ። መገመት ይህን ያኽል ማለት የዋጋ። አገና፤ ዋጋ ገዥና ሸያጭ የሚስማሙበት
፡ (ዐማርኛ)።
አጕየየ ፡ (ገባሪና አግባሪ) አሸሸ፤ አራቀ። ፡ (ጥሸ) አሸሸ አሰደደ፤ አሳደደ አባረረ። አመ ንእሱ አጕየየቶ እሙ እስከ ምድረ ግብፅ። ኢትንሥኡ ቤዛ ከመ ታጕይይዎ ውስተ ሀገረ ምስካይ። እቁም ላዕሌሁ ወአጕይዮሙ ለሕዝብ እለ ምስሴሁ። አጕየዮ ለንዋም። ወአጕየዮሙ ከመ ሩጸተ ሀየል ፡ (አፈ ፡ ድ፳፰። ዘኍ፴፭
፡ ፴፪። ፪ነገ ፡ ፲፯ ፡ ፪። ስንክ
፡ የካ፳፬። መጽ ፡ ምስ)።
አጕያዪ መጕይይ ፡ የሚያሸሽ የሚያርቅ፤ የሚያስርቅ።
አጕደለ ፡ በቁሙ፤ አጐደለ፤ አሳነሰ፤ አስጐደለ አስቀነሰ።
አጊድ ዶት ፡ (አገደ የአግድ ይእግድ። ዕብ አጋድ፤ አሰረ የነዶ የችቦ) በቁሙ ማገድ መከልከል መግታት። መስበር መቀልጠም፤ መክፈል መለየት፤ የሥጋና ያጥንት።
አጋም ፡ (ዕብራ፤ የውሃ ቦታ፤ ወንዝ ኩሬ) በቁሙ ፥ አጋም፤ ያጋም ፍሬ ጣዕሙና መልኩ ከማነሱ በቀር የጥቍር ወይን እሸት የሚመስል ጥፍጥ ፥ ዕንጨቱ እሾኻም ዐጥር የሚኾን።
አጋራዊ ፡ (ዊት ውያን ያት) ያርበኛ ወገን ዐርበኛ፤ የጦር ሰው። የአጋር ልጅ የይስማኤል ዘር። ወሰብአ ኢትዮጵያ ጸሊማን ወአጋራውያን፤ ዐርበኛ። ሞአብ ወአጋራውን፤ ይስማኤላዊ
፡ (ገድ ፡ ፊቅ። መዝ ፡ ፹፪)።
አጋር [1] ፡ (ራን ራት። አጋሪ ሪት ርያን ያት) እግረኛ ሯጭ ገሥጋሽ፤ ኻያጅ ተራማጅ፤ ዕድሜው ኻያ ዓመት የመላ፤ ከዚያም በላይ እስካርባ ዓመት ያለ ጐበዝ ጕልማሳ ፥ ወታደር ሰልፈኛ ዘማች ፥ ባዋጅ በቱልቱላ የተጠራ የተሰበሰበ። ስሳ እልፍ አጋር። አጋሮሙ። አጋርያን። ዐሠርቱ ምእት አጋር ብእሲ ፡ (ዘፀ፲፪ ፡ ፴፯። ዘኍ፲፩ ፡ ፳፩። ዮዲ፯ ፡ ፳። ፪ ፡ ፲፱። ፬ነገ ፡ ፲፫
፡ ፯)።
[2] ፡ አጋር፤
፡ (ዕብ ሀጋር) ስመ ብእሲት፤ የፈርዖን ዲቃላ ከገረድ የተወለደች፤ ኋላም ለአብርሃም ሚስት ለሳራ ገረድ ትኹንሽ ብሎ የሰጣት፤ የይስማኤል እናት። ፍችው ፥ ግይርት ፈላሲት ኰብላይ ማለት ነው፤ የመኼድና የመራመድ የሩጫ የግሥገሣ ምስጢር አለበት ፡ (ዘፍ፲፮ ፡ ፩–፲፮)።
አጋብአ ፡ አሰበሰበ፤ ሰብስቡ አለ ፡ (አስደራጊ)።
አጋዕዝት ፡ ስመ ነገድ መላእክጥ መላእክተ አጋዕዝት፥ ፡ (ሔኖ 61፥10። ኤፌ 1፥21። ቆላ1፥16)
አጋዘን አጋዜን ፡ በቁሙ፤ የዱር የበረሓ ላም፤ ቀንዳም ቀንደ ረዥም
፡ (አዋል)።
አጌሠ ፡ አገሠገሠ፤ አስገሠገሠ፤ አማለደ አስማለደ፤ ማለዳ ወሰደ። አመ ያገይሥዋ ለታቦት ካህናት አግብእዋ ውስተ መካና። እስከ አመ ያገይሥዎ ኀበ አስራኤል። ኢርኩስ ኀሪስኪ፤ ለምንትኬ አጌሥኪዮ ለፍሬ ቅድሳት ውስተ ቤተ መቅደስ ፡ (ድጓ። ሉቃ፩ ፡ ፹። መጽ ፡ ምስ)።
አጌገየ ፡ እሳተ ኀጢአት አሠራ። ያስሕት ወያጌጊ ፡ (ቲቆ፫ ፡ ፲፩)።
አግሐሠ ፡ አገዛባ፤ አስገባ። አራቀ አስራቀ አስገለለ፤ አሶገደ ለየ። አግሕሥ እገሪከ እምአሠሮሙ። ፍናወ ሕይወት ያግሕሣ እምአኩይ። አግሐሦሙ እንተ ባሕቲቶሙ። አስተፋጠኑ ወአግሐሡ ፡ (ምሳ፩ ፡ ፲፭። ፲፮ ፡ ፲፯። ጦቢ፲፪ ፡ ፮። ዮዲ፲፫ ፡ ፩)። ዳግመኛም በአግሐሠ ፈንታ አስተግሐሰ ይላል፤ ፍችው አንድ ነው። መጽብበ ቦእኩ ወአልቦ ዘያስተግሕሥ ሊተ። ፈቀድኩ ኣስተግሕሥ ዝኩ መጽብበ ፡ (ኢዮ፴ ፡ ፳፰። ሄርማ)። አስተጋሐሠ ቢል ግን አደራራጊ ኹኖ ፥ አራራቀ አለያየ ያሰኛል፤ አስተን ተመልከት።
አግሓሢ መግሕሥ ፡ የሚያገባ አግቢ፤ አራቂ አስገላይ፤ አጋፋሪ ከልካይ።
አግሀደ ፡ አግሀደ፤ አጋደ ገለጠ፤ አስገለጠ፤ አሳየ አስረዳ፤ ገልጦ ነገረ። አግህድ ሎቱ ፍጻሜ ዘይመጽእ። እስመ በዛቲ ዕለት አግሀደ እግዚእነ ኢየ ክር ርእሶ፤ እስመ ውእቱ ኢያግሀደ ርእሶ ለመኑሂ መጠነ ሠላሳ ዓም። ጳውሎስ ያግህድ ለነ ምስጢረ። ወይእዜሰ አግሀደ በብሂሎቱ። ስመ ክርስቶስ አግሀዱ ፡ (ሔኖ፲ ፡ ፪። ስንክ ፡ ጥር፲፩። ቄር ፡ ጰላ። አፈ ፡ ድ፫። ስንክ ፡ መስ፳፰)።
አግሃዲ መግሀዲ ህድ ፡ የሚያግድ የሚገልጥ፤ ገላጭ አስረጅ።
አግሐፈ ፡ አስጋፈ አስጠረገ፤ አስነሣ።
አግለበ ፡ አሸሸ አባረረ። ገለባ አወጣ ኣጓለበ አንጓለለ። አስገለበ አስገለጠ።
አግለየ ፡ አስቈረጠ አስገለጠ፤ አስለየ አስታወቀ፤ እገሌ አሰኘ፤ ራሱን ወይም ሌላውን።
አግለፈ ፡ አስቀረጸ፤ ምስል አሠራ አስፈሰሰ ፡ (፫ነገ ፡ ፮ ፡ ፳፱)።
አግላቢ መገልብ ፡ (ብት ባን ባት) የሚያሸሽ አባራሪ፤ ዓሣ ወጋሪ። መግለቦ ሠሪ ገለባ አውጭ። መጸብሓዊ ወመገልብ
፡ (መቅ ፡ ወን)።
አግል ፡ ዝኒ ከማሁ፤–ዐግል።
አግመሰ ፡ አስገመሰ አስቈረሰ፤ አሳረሰ።
አግመረ [1] ፡ (አስደራጊ) ገሚር ገመረ፤ ግሙራ።
[2] ፡ አስጨረሰ አስፈጸመ፤ አስቻለ ኦስወሰነ፤ አስደፈረ።
አግመደ አገመደ ፡ አስጐመደ ፡ (አስገመደ) አስቈረጠ አሳጨደ።
አግሙስ ፡ (ብዙ) ገሚስ ገመሰ፤ ገመስ ገሙስ።
አግሰሰ ፡ አስገሰሰ አስዳሰሰ፤ አስያዘ አስጨበጠ። አግስሰኒ አዕማደ እለ ዲቤሆን ይቀውም ዝንቱ ቤት ፡ (መሳ፲፮ ፡ ፳፮)።
አግረረ ፡ ገዛ፤ ዜጋ አደረገ። አስገዛ አስደራጊ። ይመውእ ወያገርር ኵሎ መንግሥተ። ወኵሎ በሓውርተ አግሪርየ። አልቦ ዘይክል አግርሮታ ለልሳን፤ ገዛ ፡ (ዳን፪ ፡ ፵፬። አስቴ ፡ ፫። ያዕ ፫ ፡ ፯)። ወኵሎ አግረርከ ሎቱ ታሕተ እገሪሁ። አግርር ርእሰከ ለጽድቅ፤ አስገዛ ፡ (መዝ ፡ ፰። ፩ጢሞ ፡ ፬ ፡ ፯)።
አግሪም [1] ፡ (ዕብ ሀግሪም፤ ሀግሪኢም) አጋራውያን የይስማኤል ልጆች በዮርዳኖስ ማዶ ያሉት። ፈለገ አግሪም
፡ (፩ዜና ፡ ፭ ፡ ፲፱። ፪ዜና ፡ ፳፭
፡ ፲፩)። ጽርኡና ዕብራይስጡ ግን ፈለገ ጼው ይላል፤ የባሕረ ጼው ዱሓ ፥ ሸለቆ፤ ወደ ባሕረ ጼው የሚፈስ ወንዝ ማለት ነው።
[2] ፡ (ዕብ ጊር፤ ኖራ) መገይራን፤ ኖራ አውጮች፤ ሸያጮች ቀቦች ለቅላቆች። እሊሁም ሰብአ ሰዶም ናቸው፤ የጊርንና የሰዶምን ፍች ተመልከት።
አግሪጳስ ፡ ፬ እግር ያለው አሞራ። ወሀሎ ዖፍ ዘይሰመይ አግሪጳስ በሀገረ ቃራት ወቦ አርባዕቱ አእጋር፤ ይመሥጥ ሶረ ወይሰርር መልዕልተ አየር እንበይነ ጽንዑ
፡ (ጊ ፡ ወ ፡ ሐ ፡ ገ፳፪)። ፪ኛም የሰው ስም ይኾናል ፡ (ግብ፳፭ ፡ ፲፫)።
አግራሪ ፡ መግረሪ፤ መግረር ርር፤ የሚገዛ፤ የሚያስገዛ፤ ገዥ አስገዥ። መግረሬ ፀርየ። መግረሬ አናብስት ፡ (ግንዘ። አርጋ
፡ ፬)።
(ላ) አግሬ ፡ በቁሙ፤ አላባሽ ጋሻ
፡ (ዐማርኛ)።
(ጥ) አግሮ ሮት ፡ (አገረ ይኤግር የአግር። ትግ ሐባብ አግረ። ዐረ ጀራህ። ዕብ አጋር፤ ሰበሰበ) መኼድ መራመድ፤ መሮጥ መፈርጠጥ፤ እግራም እግረኛ መኾን። በቁሙ ፥ ማገር መገርገር ማወክ መከልከል ፥ ከመንገድ ከሥራ ማስተጓጐል።
አግበረ ፡ አሠራ፤ አስደረገ። አግበሩነ ዕጹበ ግብረ። እለ ይቀውሙ ወያገብሩ ወያስተፋጥኑ ግብረ እግዚ። ፍቅር ኢታገብር እኩየ ወኢታኄሊ ሕሡመ ላዕለ ቢጽ። አግቢሮ ኀጻውንተ። ማሕረሰክሙ አግብሩ ኵያንወ ወማዕጸደክሙ አግብሩ ረምሐ
፡ (ዘዳ፳ ፡ ፮ ፡ ፮። ፩ዜና ፡ ፳፫ ፡ ፬። አፈ ፡ ተ፲፱። ገድ ላሊ። ዮኤ፬ ፡ ፲)።
አግባሪ ፡ አሠሪ አስደራጊ፤ አዛዥ።
አግብአ ፡ አገባ ከተተ አስገባ፤ መለሰ አስመለስ፤ አግባ መልስ አለ። አግብኣ ለመጥባሕትከ ውስተ ቤታ። ያገብኦሙ ድሕሬሆሙ ለጠቢባን። ወያገብኦ ድኅረ ዘባኑ። እመ አእተተ መኑ ያገብእ። ወአግብአት ባሕርኒ ኵሎ ሙታነ ፡ (ሜቴ፳፮ ፡ ፶፪። ኢሳ፵፬ ፡ ፳፭። ሢራ፳፩ ፡ ፲፭። ኢዮ፱ ፡ ፲፪። ራእ፳ ፡ ፲፫)።
፡ አሳልፎ ሰጠ ፤ ከተቀባይ እጅ አገባ ፤ አስያዘ አስጨበጠ ፤ አመጣ አቀረበ አስረከበ ፤ ፈረደ ፍርድ አቀና። ወኢያገብኦ ውስተ እደ ጸላሊኢሁ። ይሁዳ ዘአግቦ። እለ አግብኡ ነፍሶሙ ለከ። አግብኡ ቀርኖሙ ለባዕድ ወክብሮሙኒ ለካልእ። እለ ያገብኡ ጸባሕተ። አግብአ ፍትሐ ለዘሩባቤል (መዝ ፴፱። ማቴ፲ ፡ ፬። ቅዳ ፡ ዮሐ። ሢራ፵፱ ፡ ፭። ፪ነገ ፡ ፰ ፡ ፪። አርጋ)።
አግቦ ፡ (ዐማርኛ) ሸውራራ ስድብ፤ በራሱ እኔ እንዲህ አይዶለኹ ብሎ ፥ ወይም በሌላ አስመስሎ ጠላትን ለመንካት የሚነገር። ፡ (ተረት) ወይኖን ግረፈው ፈንዞን እንዲሰማው።
አግነነ ፡ (ያገንን ያግንን) አገነነ፤ አጋነነ፤ አጋናኝ ኾነ፤ ቃለ አጋኖ እንዲሉ። አስተከለ፤ አሳጠረ፤ አስቀጠረ፤ አስጠበቀ።
አግነዘ ፡ አስገነዘ አስከፈነ፤ አስከተተ። ለዕሩቅ ኢያልበሶ ወነዳያን እመ ይመውቱ ኢያግነዘ ወኢያቅበረ ፡ (ራእ
፡ ማር)።
አግነየ ፡ አስገዛ አሳመነ፤ አሰገደ አስመሰገነ። ፡ (አገኘ አስገኘ)። አግነዮሙ ለትእዛዘ ሮም። ወልድኒ ይገኒ ለዘአግነየ ሎቱ ኵሎ። ዘአናብስተ ታገኒ ወአራዊተ ትቀኒ ፡ (ዮሴፍ። ፩ቆሮ ፡ ፲፭ ፡ ፳፰። ስንክ ፡ መጋ፭)። መጽሐፍ ግን በአግነየ ፈንታ አስተጋነየ ይላል። ምሉአ ሞገስ ዮሐንስ እንተ ታስተጋኒ ድበ ፡ (ደራሲ)።
አግናሒ መግንሒ ሕ ፡ የሚያስጮኽ የሚያስቈጣ፤ አስቈጪ አናጋሪ።
አግን ፡ ቡሖ ሊጥ።
አግንሐ ፡ አስጮኸ አስቈጣ፤ እናገረ።
አግዐረ ፡ አስጮኸ አስጨነቀ፤ ዋይ አሰኘ፤ አስለቀሰ። አግዐሩ ነፍሰ ሕፃናት። እለ ታግዕሩ ነዳየ። ዕቤረ ብእሲት እመ ቦ ዘአግዐራ ፡ (ኢዮ ፡ ፳፬ ፡ ፲፬። ዓሞ፰ ፡ ፬። ሢራ፴፪ ፡ ፲፯)።
አግአዘ ፡ አስጠላ አስነቀፈ፤ አስጋዘ አስጐተተ፤ ከግዞት አስገባ፤ ግእዝ አስተማረ።
አግዐዘ ፡ አጓዘ፤ አስጓዘ፤ አሸሸ። ነጻ አወጣ፤ አስወጣ። ዐገዘ ረዳ፤ አጸና አበረታ፤ አዳነ። ወእምዝ አግዐዙ ተዓይኒሆሙ ወንዋዮሙኒ። አጋኣዘ ዮሴፍ ሥጋሁ ለያዕቆብ፤ ወአብጽሖ ኀበ መቃብረ አብርሃም፤ አጓዘ ፡ (ዮዲ፯ ፡ ፲፰። ቀሌ። ዘኍ፴፪ ፡ ፴)። በእንተ አግዕዞ ገብር። ኢይደሉ ከመ ትትወሰብ ብእሲት ለገብር ዘአግዐዞ ምታ። ንጉሥ ዘኢይሠይምዎ እግዚእ ዘኢያግዕዝዎ። አግዐዘነ እምኀጢአት ወሞት ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፴፩። ፈ ፡ መ ፡ ፭ ፡ ፲፭። ቅዳ ፡ ዮሐ። ሮሜ፰ ፡ ፪)።
አግዓሪ መግዐሪ ዕር ፡ የሚያስጮኽ የሚያስጨንቅ፤ አስለቃሽ፤
፡ (ግፈኛ ጨካኝ)።
አግዓዚ ፡ (ዚት ዝያን ያት፤ ጋዕዝት) አጓዥ፤ እግዚእ ጌታ ባለቤት፤ ነጻ አውጪ፤ አሰናባች፤ ጥሩ የሰው ልጅ። ወኵሉ ገብር ወአግዓዚ። ዘዘ እልፍ አግዓዚ። ግብርናተ ዘካልኡ መድኀኔ ዓለም አግዓዚ ዲበ ግዕዛኑ ወሰከ። ለአከት ኀበ አጋዕዝቲሃ። እግዚአ አጋዕዝ። አኀው አጋዕዝት ኪነት ፡ (ራእ፮ ፡ ፲፭። ፭ ፡ ፲፩። ቅኔ። ጦቢ፪ ፡ ፲፪። መዝ
፡ ፻፴፭። ፊልክ ፡ ፻፹፱)። ግዑዝ በማለት ፈንታ አግዓዚ አግዓዛይ ይላል፤ የተሳሳተ ነው። ትፌንዎ አግዓዜ። ትፌንዋ አግዓዚተ። ኢየሩሳሴም አግዓዚት። ወረሰይካ ለሔዋን አግዓዚተ እምጻዕረ ሞት። ወኩኑ ከመ አግዓዝያን። ጸጋ አግዓዝያን ዘነሥኡ። አግዓዝያንኑ እሙንቱ። እፎ ከመ ይረሲ ርእሶ አግዓዛየ። አግዓዛይት ፡ (ኤር፵፩ ፡ ፲፬። ዘዳ፳፩ ፡ ፲፬። ቀሌ። ውዳ ፡ ፪። ጴጥ ፡ ፪ ፡ ፲፮። ስንክ ፡ ሚያ፲፰። ማቴ፲፰ ፡ ፳፮። ቄር ፡ ጰላ። ፩ቆሮ ፡ ፯ ፡ ፳፪ ፡ ፴፱)።
፡ ስመ ነገድ ሴማዊ፤ የዮቅጣን ትውልድ፤ ከየመን ፈልሶ ተጕዞ ወደ ኵሽ ክፍል ወዳፍሪቃ የመጣ፤ ራሱን ለኵሽ ከመገዛት ነጻ ያወጣ፤ የኵሽን አገር ብሔረ አግዓዚ ያሰኘ። ለብሔረ አግዓዚ ሰበከ አባ ሰላማ ዜናሁ ፡ (ድጓ)። በአግዓዚ ፈንታ ግዕዝ ይላል፤ ምስጢሩ ጕዞና ስደት። ነጻነት ነው። ብሔረ ግዕዝ። ሰላም ለከ ቆመ በቀልት ወአርዝ ዘፈረየትከ ግዕዝ ይሥሕቅ ጥቡዕ ሰማዕተ ዐዚዝ። እስከ ዮም ትትፌሣሕ ግዕዝ ፡ (ስንክ ፡ መስ፳፭። ሐም፭። ታኅ፲፰)። ዐምሐራን ተመልከት፤ የዚህ ጎር ነው።
አግዋል ፡ ዘለለ፤–ዐግዋል።
አግዋር ፡ (ራት) ጎረ ቤቶች፤ ቅርቦች አጠገቦች። አክብር አግዋሪከ ወአኀዊከ። ግዕዙ እምአግዋሪሁ ለእግዚ ወመላእክቲሁ ኀበ አግዋሪሆሙ ለአጋንንት። እስመ ግዕዝነ እምአግዋሪሁ ለገነት ወገባእነ ውስተ ምድር ርግምት ፡ (ፈላስ ፡ ገ፳፪። ቀሌ
፡ ገ፲፯። ፳፫)።
አግዘመ ፡ አስገዘመ፤ አስቈረጠ። አግዘመ አዕዋመ። በአፈ መጥባሕት ክሣዶ አግዘመ ፡ (፪ዜና ፡ ፴፬ ፡ ፬። ፫ነገ ፡ ፲፭ ፡ ፲፫። ስንክ የካ፲፩)።
አግዘረ ፡ አስገዘረ፤ አስገረዘ። እም ድኅረ ሰቡዕ መዋዕል ታገዝር ወልዳ ፡ (ፈ ፡ መ ፡ ፲ ፡ ፩። ዘሌ፲፪ ፡ ፫)።
አግዘዘ ፡ አስቈረጠ፤ አስጀጐለ ጀጐል አሠራ።
አግዘፈ ፡ አገዘፈ አወፈረ፤ አደነደነ።
አግዝአ ፡ አስገዛ አጌተየ፤ ጌታ አደረን፤ ሾመ አሠለጠነ፤ ራሱን ወይም ሌላውን።
አግያ ፡ (አጊያ) ቅድስት። አግያ ሶፍያ። እልመስጦ አግያ
፡ (አዋል። ሃይ ፡ አበ)።
አግያስማንጦን ፡ (ጽር አጊዩ ፕኔፍማቶስ) ቅዱስ መንፈስ
፡ (ቅዳ)።
አግዮስ ፡ (ጽር አጊዎስ) ቅዱስ፤ ክቡር ምስጉን
፡ (ቅዳ። ግንዘ)።
አግደለ ፡ አስገደለ፤ ገደል አስጣለ።
አግደመ ፡ አጋደመ አስተኛ፤ አግድሞ ወሰደ። ያጸንንዎሙ ለፍጹማን እምዘክሮ እግዚ ኀበ ኀልዮ ፍጥረቱ ከመ ያግድምዎሙ እመልዕልት ኀበ ርኵሰት ፡ (ፊልክ
፡ ፹፭)።
አግደምደመ ፡ አፋተለ፤ አጣመረ። ኢታግደምድም እገሪከ ሶበ ትቀውም ለጸሎት። ወታግደመድም እገሪከ ፡ (አዋል። አረጋ)።
አግደፈ ፡ አስገደፈ አስጣለ፤ አስተወ አስረገፈ። ኣገድፈከ ቀስተከ። ያገድፎሙ ኵያንዊሆሙ ፡ (ሕዝ፴፱ ፡ ፫። ኢሳ፵፩ ፡ ፪)።
አግፍዐ ፡ አስገፋ አስበደለ፤ ግፍ አሠራ፤ ግፈኛ አደረገ፤ ገፋዒ አሰኘ። መጽሐፍ ግን በአግፍዐ ፈንታ አስተጋፍዐ ይላል፤ አያሰኝም። ለእግዚአብሔር ያስትጋፍዖ በልቡ ፡ (ምሳ፲፬ ፡ ፫)።
አጐንደየ ፡ አቈየ አዘገየ፤ አስቀረ። ያጐነዲ ከመ ዘኢይሁብ። አበያ ወአጐንደያ። አንከርኩ አጐንድዮተክሙ ትእዛዘ ንጉሥ። ኢያጐነዲ እግዚ ቃለ ዘነበበ ፡ (ቅዳ ፡ ግሩ። ሉቃ፲፰ ፡ ፬። ዮሴፍ። ፪ጴጥ ፡ ፫ ፡ ፱)። በአጐንደየ ፈንታ አስተጐናደየ ይላል፤ አያሰኝም ፡ (ገድ ፡ አዳ)።
አጐንዳዪ መጐንድይ ፡ የሚያቈይ የሚያዘገይ፤ ዙሪያ ጠማማ። እለ የሐውሩ ጕንዱየ ውስተ ፍኖት መጐንድይ ፡ (ፊልክ ፡ ፲፬)።
አጐጕአ ፡ አስቸኰለ፤ አቻኰለ፤ አጣደፈ፤ አስደነንጠ ፡ (ዘፍ፲፱ ፡ ፲፭። ዘፀ፭ ፡ ፲፫። ሔኖ፲፬ ፡ ፰)። ያጔጕእዎ ለሐማ ውስተ በዓል። መላእክት ያጔጕኡኒ። እግዚ አጐጕአኒ ፡ (አስቴ፮ ፡ ፲፬። ሔኖ፷፪ ፡ ፲። ኢዮ፳፫ ፡ ፲፮)።
አጐጓኢ መጐጕእ ፡ የሚያጓጓ፤ የሚያስቸኵል አስቸኳይ፤ መደንግፅ።
አጠረ ፡ (ዕብ አጣር) በቁሙ፤ ቀጠረ፤ ጀጐለ፤ከበበ ዙሪያውን ዘጋ። ሐጸረን እይ።
፡ (ተረት) እሾኽ ዐጣሪውን ነገር ፈጣሪውን።
አጠቀ ፡ ታጠቀ፤–ዐጢቅአጠቅለለ፤ አስተጠቅለለ፤ አስጠቀለለ፤ አስጠመጠመ።
አጠቅለለ አስተጠቅለለ ፡ አስጠቀለለ፤ አስጠመጠመ።
አጠነ ፡ በቁሙ፤–ዐጢን ዐጠነ።
አጠንቀቀ ፡ አስጠነቀቀ፤ አስለበመ፤ ሠሪን በሥራ ላይ።
አጠየረ አስተጠየረ ፡ አበረረ አስበረረ፤ አከነፈ አክንፈነፈ። አስጠነቈለ፤ ወፍ አስጠየቀ፤ አስመለከ። አድራጊና አስደራጊ ነው።
አጠየቀ ፡ አስጠየቀ፤ አስመረመረ። አስረዳ፤ አሳወቀ አስታወቀ፤ ነገረ አሰማ አስተማረ። አጠይቁኒ ኍልቆሙ። ወአጠይቅኦ ለንጉሥ ቃላተ። ተጋብኡ ኀበ ዕዝራ ከመ ያጠይቆሙ ኵሎ ቃለ ኦሪት ፡ (፩ዜና ፡ ፳፩ ፡ ፪። ፪ዜና ፡ ፴፬ ፡ ፳፰። ዕዝ፰ ፡ ፲፫)።
አጠየተ ፡ አስጠየተ፤ ጥይት አሠራ።
አጠያሪ መጠይር መስተጠይር ፡ አስጠንቋይ፤ ወፍ አስጠያቂ ፡ (ሲኖዶ)።
አጠያቂ መጠይቅ ፡ (ቅት ቃን ቃት) የሚያስጠይቅ፤ አስጠያቂ አስመርማሪ። የሚያስረዳ አስረጅ፤ መምር አስተማሪ። ወሌዋውያን መጠይቃን ለሕዝብ መጽሐፈ ፡ (ነሐ፰ ፡ ፯)።
አጠፈረ አስተጠፈረ ፡ አስጠፈረ አስማገረ፤ ጠፈር መዋቅር አሠራ
አጣርቆን ፡ (ጽር አፖርኾን። ዕብ ትሩሞት) መባእ መሥዋዕት፤ መንፈሳዊ አምኃ ፥ ቀዳምያት። አጶርጌን ተመልከት፤ ከዚህ ጋራ አንድ ነው
፡ (፪ነገ ፡ ፩ ፡ ፳፩)።
አጣቃን ፡ (ጽር አታኪን። ዕብ ሳልዓም ) ያንበጣ ወገን፤ ኵብኵባ፤ ፌንጣ
፡ (ዘሌ፲፩ ፡ ፳፪)።
አጣእጣኢ ፡ መጣእጥኢ፤ የሚያበጅ የሚያዘጋጅ አጣፋጭ፤ አሳማሪ አስጊያጭ። አጣእጣኢሆሙ ለፍጡራን፤
፡ (መጽ ፡ ምስ። አርጋ ፡ ፪)።
አጣእጥአ [1] ፡ (አስደራጊ) አስጠረገ አስከወነ፤ ንጹሕ አስደረገ።
[2] ፡ አጣእጥአ፤ ፡ (አድራጊ) አበጀ አዘጋጀ አሰናዳ፤ አሳመረ አስጌጠ አጣፈጠ፤ ፈጸመ ጨረሰ አከናወነ። ያጣአጥእ በከመ ፈቀደ። እንዘ ያጣአጥእ ቃለ። አምያስ ዘአጣእጥእዎ በሶከር። አጣእጥኡ ንብረተክሙ። ኢተክህሎሙ ያጣእጥኡ ሕንጸተ ፡ (ቅዳ ፡ ኢጲ። ስንክ ፡ ታኅ፲፭። ፈ ፡ መ
፡ ፳፮ ፡ ፩። ዮሴፍ)። ዳግመኛም አጣእጥአ በማለት ፈንታ አስተጣእጥአ ይላል፤ ፍችው ከማድረግ አይወጣም። ወቀደመ አስተጣእጥኦ፤ ወኮነ ውእቱ ፍኖተ ሕይወት ለነ ፡ (ቄር ፡ ጰላ)። ጣእጥአ የማህረከ ቤት ስለ ኾነ አስተ ሲገባበት ማድረግንና ማስደረግን መደብ አድርጎ ማደራረግንም ያሳያል፤ ማህረከንና ባረከን እይ።
አጤሰ ፡ በቁሙ፤ አጨሰ አበነነ ዐጠነ። አጤሰ ልቦ ወሐሞቶ ለዓሣ። ሰቀላ ቍልቍሊተ ወአጤሰ መትሕቴሃ እሳተ። ለተነ ጊሜ ዘያጤይሶ። አጢስ ቦቱ ፡ (ስንክ ፡ መስ፲፮። ጥቅ፲። መጽ ፡ ምስ። ጦቢ፮
፡ ፲፯)።
አጥሐለ ፡ አስጣለ፤ አስጠመቀ አስበጠበጠ።
አጥሀረ ፡ አነጻ አጠራ፤ ዐጠበ አጠመቀ። በዘያጥህሩ አይሁድ። በእንተ አጥህሮ ፡ (ዮሐ፪ ፡ ፮። ፫ ፡ ፳፭። መጽ
፡ ምስ)።
አጥሐረ አስተጥሐረ ፡ አስጮኸ፤ አስገሣ።
አጥሃሪ መጥህር ፡ የሚያነጻ የሚያጠራ፤ ዐጣቢ አጥማቂ፤ ወይም ውሃ።
አጥለለ ፡ አጠለለ አወረደ፤ የጠላ የጠል። አራሰ አረጠበ አለመለመ፤ አረካ። ያጠልል አዕፅምተ እምብዝኀ ጣዕሙ። መሥዋዕቱ ለጻድቅ ያጠልሎ ለምሥዋዕ። ያጥልል ለከ ቍርባነከ። በማየ ጸሎቱ ጽምአ ነጋድያን አጥለለ። በጠለ ምሕረቱ እግዚ ያጥልል ነፍሳቲክሙ ፡ (ቅዳ ፡ ሕር። ሢራ፴፪ ፡ ፰። መዝ ፡ ፲፱። ስንክ ፡ ኅዳ፲፱። ግንዘ)። በሰትየ ፈንታ አጥለለ ይላል፤ ስሕተት ነው። እንበለ ይብልዑ፤ እክለ ወማየ ያጥልሉ ፡ (ስንክ ፡ ሠኔ፲፱)።
አጥለሰ ፡ አጠለሰ፤ አጠቈረ አከሰለ፤ አጠላ አጨለመ።
አጥለቀ ፡ አጠለቀ፤ አስጠለቀ፤ የቀሚስ የሱሪ። አጥለቀለቀ አሳደፈ፤ አረከሰ። ርኩሱ ለብእሲ ቀታሊ ያጠልቆ ፡ (ምሳ፳፬ ፡ ፲)።
አጥላስ ፡ (ሳት) በቁሙ፤ ጥቍር የሐዘን ልብስ፤ ከል እማሎሚ፤ የጠለስና የጥላ የጨለማ ዐይነት።
አጥመቀ ፡ አጥመቀ፤ አስጠመቀ፤ አስነከረ። ሶበ ተወልደ ሕፃን ጥዑየ ይትዐገሡ አጥምቆተ። እናቅ አባቱ ርሱን ከማስጠመቅ
፡ (ፈ ፡ መ ፡ ፳፯ ፡ ፯)። ለካህናት ግን፤ ጠሚቅሁ ጠሚቆቶ እንጂ፤ አጥምቆቶ አያሰኝም።
አጥማቂ መጥምቅ ፡ የሚያስጠምቅ፤ አስጠማቂ። መጥምቅ ከጠመቀና ከአጥመቀ ከኹለቱ አዕማድ። እንደ ወጣ፤ ሌላውም መስም እንዲህ እንዲወጣ አስተውል።
አጥረስካ ፡ (ጽር ኤንስሮኒስቲኪ) የመጽሐፍ ስም፤ የሃይማኖት መጽሐፍ። ባለሊቃውንቶች ፥ መጽሐፈ ክፍል ወተዋሕዶ፤ ዘትሥልስት ወዘተዋሕዶ፤ ክምቹ ማለት ነው ይላሉ። ባለቅኔዎችም ተዝካር ይሉታል። እምአጥረስካ ዘዕሥራ ወአሐዱ
፡ (ሃይ ፡ አበ)።
አጥረቀ ፡ አስጠረቀ፤ አስመታ አስቀጠቀጠ፤ እስኪቀዝን ድረስ።
አጥረየ ፡ ጥሪት አስገዛ፤ አሷጀ ገንዘብ አስደረገ።
አጥራቂ ፡ የሚያስሞክት፤ የሚያሰነጋ። ባለብሉዮች ግን ጡርቂያም እንደ ማለት ቅዘናም ይሉታል፤ ፍችው አይዶለም።
አጥቀበ ፡ አስጠቀመ አስለገበ፤ አስደረተ፤ ልቭሱን ጫማውን አስጠገነ።
አጥቅዐ ፡ አስመቃ አስነፋ፤ አስጠቃ ጋ።
አጥበቀ ፡ አጠበቀ፤ አስጠበቀ። አጣበቀ ጣፈ ለጠፈ፤ቸነከረ አጣመረ። አጥበቃ ለምትርት የማኑ። አጥበቃ በምድር። ውስተ አረፍት አጥበቆ ወጸንዖ በኀጺን ፡ (ስንክ ፡ ጥቅ፳፪። ሰቈ፪ ፡ ፪። ጥበ፲፫ ፡ ፲፭)።
አጥበበ ፡ አለበመ አስተማረ፤ ብልኅ አደረገ። አብዳነ አጥብብ። መቅሠፍት ወተግሣጽ በኵለሄ ያጠብብ። እግዚ ያጠብቦሙ ለዕዉራን። አፍቅራ ወታጠብበከ ፡ (ኪዳ። ሢራ፳፪ ፡ ፮። መዝ ፡ ፻፵፭። ፊልክ)።
አጥበወ ፡ አጠባ አስጠባ፤ ጡት አጐረሠ፤ አስጐረሠ መገበ። ከመ ኣጥቡ ሕፃንየ። አክይስት አጥበዉ ዕጐሊሆሙ። አጥበውኩከ ወሐፀንኩከ። ያጠብዎ እግዚ ለሥረዊሃ እምክልኤቱ አጥባት እማይ ወእመሬት
፡ (፫ነገ ፡ ፮ ፡ ፳፩። ሰቈ፬ ፡ ፫። ዮሴፍ። መቃ
፡ ገ፭)።
አጥባቂ መጥብቅ ፡ በቁሙ፤ የሚያጠብቅ፤ የሚያጣብቅ አጣባቂ።
አጥባቢ መጥበቢ ፡ የሚያለብም አለባሚ፤ ብልኅ አድራጊ የጥበብ መሪ፤ ጥበብ አስተማሪ። መጥበቢሆሙ ለአብዳን። መምህሮሙ ወመጥበቢሆሙ ለእለ ይትቀነዩ ለእግዚ። መጥበቤ ሕፃናት በስምዑ
፡ (ሮሜ፪ ፡ ፳። ዲድ ፡ ፰። ስንክ
፡ ግን፫)።
አጥባዊ ፡ (ዊት ውያን ያት) የሚያጠባ አጥቢ፤ እመጫት ሞግዚት። ሐፃንያት ወአጥባውያት
፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፵፪
፡ ፲፫)።
አጥብሐ ፡ አሳረደ አስጠባ፤ አስበጣ አስገፈፈ።
አጥብዐ ፡ አሶደደ፤ አስጨከነ አስደፈረ፤ አጸና አበረታ። አጥብዐ አልባቢሆሙ። መንፈስ ቅዱስ አጥብዓ ከመ ትኩን ስምዐ። ቀድሳ ወአጥብዓ። አጥብዖው ለመዋእያን ሰማዕት። አጥብዑ ልቦሙ ፡ (፪ዜና ፡ ፴፪። ስንክ
፡ መስ፮። ኪዳ። አርጋ ፡ ፩። ቀሌ)።
አጥነፈ ፡ አያያዘ፤ አዋደደ። ወታጠንፎ በጥንገፍ ፡ (ዘፀ፴ ፡ ፬)።
አጥናን [1] ፡ ቅድስት ሥላሴ፤ ወይም ሰባቱ ሀብታት ፡ (ኢሳ፲፩ ፡ ፪)። በኀይለ አጥናን ዘሞኦ ለሰይጣን። ኀይልከ ኀይለ አጥናን። ኀይል ዘአጥናን ፡ (ድጓ። ስንክ
፡ ኅዳ፲፫። አርጋ ፡ ፮)። አንዳንድ ሰዎች፤ ትጋት ትጉህነት ሙቀት፤ መንፈሳዊ ቅንአት ይሉታል፤ ምስጢሩ ከሀብታት ይገባል።
[2] ፡
ትጋት፤–ጠኒን ጠነ።
አጥዐመ ፡ አበላ አቀመሰ፤ አስበላ አስቀመሰ። አጥዐመ ሥጋ ለአኀው። ወአጥዐሞ ሞተ። እግዚ አጥዐሞሙ በከመ አጥዐሙ ለሰብእ ረኃበ ፡ (ፊልክ ፡ ፪፻፵፫። ቄር
፡ ድ፸፬። ዮሴፍ)።
፡ አጣመ አጣፈጠ፤ ጣፋጭ አደረገ። ጼው ዘአጥዐሞ ለልሱሕ። አጥዕሙ መዐዛክሙ። አጥዕማ ለማሕሌትየ ውስተ አፈ ኵሉ ፡ (ቅዳ ፡ ዮሐ። ሢራ ፡ ፴፱ ፡ ፲፬። ስንክ
፡ ታኅ፭)።
አጥዐወ ፡ አጣዐወ፤ እሳተ አሳሳተ፤ ጣዖት አስመለከ። ልማዱ ግን አድራጊነት ነው። እመ ቦ እምአኀው ዘያጥዑ። እለ ያሰግሉ ወእለ ያጣዕዉ። ተምዐ መንፈሱ ሶበ ርእየ ያጣዕጢ ኵሉ ሀገር ልሄቆሮ 3፳» ቀሌ። ግብ፲5› ፲፪)።
አጥዐየ ፡ አጤነ፤ ልብ አደረገ ዐሰበ አስተዋለ ፡ (ዐማርኛ)። አዳን፤ አሻረ ፈወሰ፤ ጤነኛ አደረገ። አጥዐየ መፃጕዐ። ፈውሳት እለ ያጥዕያ ቍስላተ። ዝንቱ ደዌ ይከውን ዕጹበ ፈውሶቱ ወአጥዕዮቱ። ሕጸጸ ቅንአት ያጥዒ ሥጋ ፡ (ግንዘ። ፈ ፡ መ ፡ ፫ ፡ ፫ ፡ ፯። ፈላስ)።
አጥዓዊ ፡ መጥዐዊ፤ መጥዕው፤ መጣዕው) የሚያስት አሳች፤ ጣዖት አስመላኪ። ከአጥዓዊ በቀር ሦስቱ እንደ ፊተኛው ባድራጊነትም ይፈታል።
አጥዓዪ መጥዐዪ ፡ (ዪት ይያን ያት) የሚያሽር አዳኝ፤ ፈዋሽ።
አጥወየ ፡ (አስደራጊ) አስከረረ አስጠመዘዘ፤ አስጠመመ፤ አስቀለሰ አስጐነበሰ። ልማዱ ግን አድራጊነት ነው።
አጥዋዪ መጥወዪ ፡ የሚያስጠምም የሚያስቈለምም፤ ጠምዛዥ ቈልማሚ። መጥወዪ ከጠወየና ከአጥወየ ከኹለቱ ዐምዶች ስለ ወጣ በ፪ ስልት ይፈታል። መጥወዬ ክሣድ
፡ (ስንክ ፡ ጥር፲፭)።
አጥግዐ ፡ አስጠጋ አስደገፈ አጣበቀ አጸና። ያጥግዕ ላዕሌከ ወላዕለ ዘርዕከ፤ በከመ መዋዕለ ሰማይ ዲበ ምድር
፡ (ኩፋ ፡ ፲፱)።
አጥፍአ ፡ አጠፋ አስጠፋ፤ አወደመ ጠፍ አደረገ። ለእሳት እንተ ትነድድ ያጠፍኣ ማይ። ከመ ኣጥፍእ እምኔሃ ሰብአ ወእንስሳ። እብነ በረድ አጥፍአ ኵሎ ዘይሠርጽ ፡ (ሢራ፫ ፡ ፴። ሕዝ፲፬ ፡ ፲፱። ኩፋ ፡ ፵፰)።
አጰንገለ ፡ (አስደራጊ) አስቀዳ ፣ አስመለሰ አስተረጐመ፤ አሳየ አስነበበ፤ አስመለከተ።
አጰይዶን ፡ (ጽር ሄፓይዶን። ዕብ ሐርጡሚም) መሰግላን፤ ፙርተኞች ኮከብ ቈጣሮች፤ በፊደል በሥዕል በግብጻዊ ሰገል በሐረግ በጠልሰም የሚጠነቍሉ
፡ (ዳን፬ ፡ ፮)።
አጰጰሰ ፡ ጳጳስ አደረገ፤ ጵጵስና ሾመ፤ ጳጳስ አለ፤ ጳጳስ ኤጲስቆጶስ አሰኘ ብውሕ ሎቱ ከመ ያጳጳስ ጳጳሳተ በከመ ያጰጵሱ ሊቃነ ጳጳሳት ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፬)።
አጰጳሲ መጰጵስ ፡ የሚያጰጵስ፤ አጰጳሽ፤ ጳጳስ ሿሚ፤ ሊቀ ጳጳስ።
አጴልዮጤን
፡ (ጽር አፒልዎቲስ) የቦታ የማእዝን ስም፤ ወደ ምሥራቅ ያለ፤ ወይም መቅሠፍትነት ያለው የምሥራቅ ነፋስ ፡ (ዮዲ፯ ፡ ፲፰)።
አጵልዮን ፡ (ጽር አፖልዮን) አጥፊ፤ ጥፋት፤ ምዝባሬ ፍርሰት። አብዶንን እይ፤ ከዚህ ጋራ አንድ ነው ፡ (ራእ፱ ፡ ፲፩)።
አጵሎን ፡ (ጽር አፖሎ) ጣዖት፤ የጣዖት ስም
፡ (ስንክ ፡ ኅዳ፲፰። የካ፳፫። ነሐ ፲)።
አጶሊጹ ፡ (ጽር አፖሊፑ) በቤት ዙሪያ ያለ የውስጥ ወልወል፤ የተለየ ክፍል
፡ (ሕዝ፵፩ ፡ ፲፪)።
አጶርጌ ፡ (ጽር አፖርኺ) የእሸት በኵራት፤ በኵረ ወይን፤ በኵረ በለስ፤ በኵረ ኅብስት፤ የመሰለው ኹሉ። ናቄርብ ለከ አጶርጌ ቀዳምያተ ፍሬ ዚኣከ። አጶርጌ ባሕቲቱ ይበልዕ
፡ (መጽ ፡ ኪዳ። ራእ ፡ ማር። ሕዝ፵፬ ፡ ፴)። ተረፈ መሥዋዕትም አጶርጌ ይባላል።
አጶሮግዮን ፡ በኵርነት፤ ቀዳማዊነት፤ መዋዕለ ሠዊት። እመድኅረ ዕርገቱ ለእግዚእነ ዘበአጶሮግዮን ለኀበ ሰማይ
፡ (ማቴ፳፰ ፡ ፳፩)። ባለሐዲሶች ግን ሥጋ ይሉታል።
፡ ዕንቍ የዕንቍ ፈርጥ፤ ፍሬው ቅንጣቱ
፡ (ድጓ ፡ መስ፲፭። አርጋ ፡ ፮)።
አጸልመተ ፡ (አጽለመ) አጨለመ፤ አጠቈረ፤ ጨለማ አለበሰ።
አጸምሐየ ፡ አጠወለገ፤ አሳረረ፤ አቃጠለ፤ አጠፋ፤ ለወጠ። ላህበ ነድሂ ኢያጸምሐየ ሥጋ እንስሳ። ፍርሀተ እግዚ እምከመ ኀደረት ውስተ ብእሲ ታየብስ ሥጋሁ ወታጸመሒ አዕፅምቲሁ። ሐሜቶሙ ታጸምሕያ ለሃይማኖቶሙ። ኢያውሥአት ለአሐቲ እምኔሆን ወኢያጸምሐየት ገጻ ወኢተሀውከ ልባ
፡ (ጥበ፲፱ ፡ ፳። ፊልክ
፡ ፲፮። ሄርማ። ዮሴፍ)።
አጸብሐ ፡ አስገበረ፤ ግብር አስከፈለ፤ ገብሩ ግብር አምጡ አለ። ወያጼብሐክሙ ዐሥራተ እደ
፡ (፩ነገ ፡ ፰ ፡ ፲፭–፲፮)።
አጸነሰ አስተጸነሰ ፡ አስቸገረ፤ ችጋር አመጣ፤ ነሣ አሳጣ። ኢያስተጼንስ እግዚ ነፍሰ ጻድቅተ። ኢያስተጼንሶሙ እምበረከቱ ፡ (ምሳ፲ ፡ ፫። መቃ። መዝ ፡ ፹፫)።
አጸንሓሒ ፡ የሚያጤስ የሚያቃጥል፤ አሻታች። ሚካኤል ሣውዕ አጸንሓሔ ሠናይ ጼና መዐዛ
፡ (ደራሲ)።
አጸንሕሐ ፡ አጸንሕሐ፤ ሠዋ፤ መሥዋዕት አቀረበ፤ አጤሰ፤ አቃጠለ፤ አሻተተ። አጸንሕሐ ጽንሓሐ። ለአጸንሕሖ ቍርባን። ወኢኀበ ያጸነሕሑ ዕጣነ ፡ (ስንክ
፡ ሚያ፲፯። መጽ ፡ ምስ። ዳን፫ ፡ ፲፬)።
አጸየፈ ፡ (አስደራጊ) አስጠየፈ፤ አስነቀፈ፤ ጸያፍ አሰኘ።
አጸፍጸፈ ፡ አስጠፈጠፈ፤ አስለበጠ፤ አስነጠፈ።
አጻመተ ፡ አጣመተ፤ ፈጀ ጨረሰ፤ አጠፋ ደመሰሰ። ያጻምቶሙ መጥባሕት ፡ (ዘዳ፴፪ ፡ ፳፭)።
አጻመወ ፡ አደከመ፤ አታከተ፤ ሣቀየ፤ መከራ አሳየ። ኢታጻምዎ ለሊቅ። አጻመወት ሥጋሃ በተፀምዶ ጾም ወጸሎት። ነበረ በጾም ወበጸሎት ወአጻመወ ሥጋሁ ፈድፋደ ፡ (ማር፭ ፡ ፴፭። ስንክ ፡ ጥቅ፩። ግን፲፩)።
አጻብዕ ፡ (ዓት) ጣቶች፤ ዐምስቱ፤ ዐሥሩ፤ ወይም ካያው ኹሉ። ላምስቱ ጣት ስም ስም አላቸው፤ መዠመሪያው አውራ፤ ኹለተኛው ሌባ ወይም ማመልከቻ፤ ማማተቢያና መባረኪያ። ዕተብ ገጸከ በዘይተልዎ ለመንኮብያ
፡ (ሲኖዶ)። ሦስተኛው ረዥም ወይም መካከለኛ፤ አራተኛው ተከታይ ወይም የቀለበት ጣት፤ ዐምስተኛው ታናሽ ወይም መጨረሻ ይባላል። የነዚህ ያምስቱ ስም ለኹሉ ይኾናል። ሰላም ለአጻብዒከ አጻብዐ አዳም ዘተኬነዋ ፡ (ደራሲ)።
አጻዕደወ ፡ አነጣ አጠራ፤ ነጭ አደረገ። ኣጻዐድዎ ከመ በረድ። በዘአጻዕደወት አዕጹቂሃ። ኢትክል አጻዕድዎ አሐተ ሥዕርተ ርእስከ ፡ (ኢሳ፩ ፡ ፲፰። ዮኤ፩ ፡ ፯። ሲኖዶ)።
አፃእፅአ ፡ አስጨነገፈ። አብቃቃ አከፋፈለ። ወእምኔሁ ያፃአፅኡ ለነደቅት ወለጸረብት ፡ (፪ዜና ፡ ፳፬ ፡ ፲፪)።
አጼነወ ፡ (ዐረ ሸመ) አሸተተ፤ አነፈነፈ። ወአጼነወ እግዚ መዐዛ ሠናየ። ኢአንፎሙ ለአጼንዎ ነፋስ። እምርሑቅ ያጼንዎ ለቀትል። ፈትል ሶበ ያጼኑ እሳት ፡ (ዘፍ፰ ፡ ፳፩። ጥበ፲፭ ፡ ፲፭። ኢዮ፴፱ ፡ ፳፭። መሳ፲፮ ፡ ፱)።
አጼንዎ ፡ ማሽተት፤ ያፍንጫ ሥራ። ሕዋስን ተመልከት።
አፅሐሰ ፡ (አስደራጊ) ዳንኪራ አስመታ፤ አስጨፈረ፤ ርገጡ ዝለሉ አሸብሽቡ አለ፤ ወያም ርግጫ ሽብሸባ ርግዶ አስተማረ፤ እንደነጕኔ መኰንን።
አጽሐቀ ፡ አስመኘ አስፈለገ፤ አተጋ፤ አሳሰበ፤ አሳዘነ። ለዝንቱ ብእሲ ኢያጽሐቆ ምርዕውና ዲበ ምድር። ወከመ ዝ አጽሐቆ ኅሊናሁ ለሐዋርያ ወአገበሮ፤ ከመ ይጽሐፍ። ላሕምኑ አጽሐቆ ለእግዚ። ወአጽሐቀቶ ለጳውሎስ
፡ (መዋሥ። አፈ ፡ ወር ፡ መቅ። ፩ቆሮ ፡ ፱ ፡ ፱። ግብ፲፮ ፡ ፲፯)።
አጽሐበ ፡ አደከመ፤ አሰለቸ፤ ዘበዘበ፤ ነዘነዘ፤ ስጠኝ አድርግልኝ ብሎ። አጽሐበያ ነፍሶ በጾም ወበጸሎት። ምንተ አጽሐብኩከ። ከማ ኢያጽሕብዎ ለንጉሥ። ኢታጽሕቦ ወኢትስአሎ ፡ (ስንክ ፡ ግን፲። ሚክ፮ ፡ ፫። ዳን፮ ፡ ፪። ሢራ፴፬ ፡ ፴፩)።
አጽሐደ ፡ አጠዳ፤ አለዘበ፤ አለሰለሰ፤ ቀባ፤ ሾመ። ርጢናት እለ ይፈትሓ ሕብጠተ ወያጽሕዳ ቍስላተ። ያጽሕደኒ እምስሕከትየ። ወአጽሐድከ በቅብዕ ርእስየ። አጽሕዶሙ እደዊሆሙ(ፈ ፡ መ ፡ ፫ ፡ ፫። ስንክ ፡ ሚያ፲፮። መዝ
፡ ፳፪። ዘፀ፳፰ ፡ ፵፩)።
አጽሐፈ ፡ አስጣፈ፤ አስቈጠረ። ለዘጸሐፎ ወለዘአጽሐፎ ለዝንቱ መጽሐፍ። አጽሐፈ ኵሎ ብሔሮ ከመ የሀቡ ጸባሕት። ዘአጽሐፉ ሎቱ ትእዛዝ ፡ (ቀሌ። ፬ነገ ፡ ፳፫ ፡ ፴፭። ፍ ፡ ነ ፡ ፴፫ ፡ ፬)።
አጽለለ ፡ አጠራ፤ አጠለለ፤ አሰፈፈ አንጓለለ። ለኀጺነ ማሕጼ አጽለሎ ዲበ ማይ ፡ (አርጋ ፡ ፬)።
፡ አስጠጋ፤ አስጠለለ፤ ከጥላ አሳረፈ፤ ራሱን ወይም ሌላውን። ታጽልሉ ታሕተ ዕፅ። መኑ ያጸልል። ወአጽለለ ህየ ፡ (ዘፍ፲፰ ፡ ፬። መዝ
፡ ፲፬። ማቴ፳፩ ፡ ፲፯)።
አጽለመ ፡ አጨለመ፤ ጨለማ እደረገ፤ አጠቈረ፤ ከሰል አስመሰለ፤ አጠፋ ለወጠ። ያጸልም መዓልተ ከመ ሌሊት። ኣጸልም ደመና ላዕለ ምድር እከዪሃ ያጸልሞ ከመ ርእየተ ድብ ለገጻ። ቅንአተ እከይ ያጸልም ሠናያተ። ስካር ያጸልም ልበ። ገልዓት ዘአጽለምዎሙ በፍሕም ፡ (ዓሞ፭ ፡ ፰። ዘፍ፱ ፡ ፲፬። ሢራ፳፭ ፡ ፲፯። ጥበ፬ ፡ ፲፪። ቀሌ። ስንክ
፡ መጋ፳፯)።
አጽልአ ፡ አስጠላ፤ አስነቀፈ፤ አስቀየመ። አጽላእክሙኒ በኀበ ኵሎሙ። ቦ ዘያጸልእ ርእሶ በብዝኀ ነቢቡ። ከመ ኢታጽልኦ ለቢጽከ ፡ (ዘፍ፴፬ ፡ ፴። ሢራ፳ ፡ ፭። ፴፬ ፡ ፲፮)።
አጽልዕት ፡ ቍስሎች፤ መቅሠፍቶች። ኢየሱስ ክርስቶስ ዘአጽልዕቲሁ ምስሌሁ፤ ወመስቀለ ሞቱ ቅድሜሁ። አጽልዕት ዘይፈልሕ ዲበ ሰብእ ወእንስሳ። ሕማመ አጽልዕቲሆሙ ፡ (ደራሲ። ዘፀ፱ ፡ ፱–፲፩። ራእ፲፮ ፡ ፲፩)።
አጽመመ ፡ አጋ፤ ደፈነ፤ አደነቈረ። አጽመሙ እዘኒሆሙ ከመ ኢይስምዑ። ዘያጸምም እዘኒሁ ከመ ኢይስማዕ ዐውያተ ነዳይ። ላኳሆሙ ለአብዳን ያጸምም እዝነ። ድምፀ ሰፌልያ ያጸምም እዘኒሁ
፡ (ኢሳ፮ ፡ ፲። ዲድ ፡ ፲፬። ሢራ፳፯ ፡ ፲፬። ፴፯ ፡ ፳፰)።
አፅመደ ፡ አስጠመደ፤ ጥመዱ አጥምዱ አለ፤ በወጥመድ አሲያዘ፤ አሳረሰ። ፡ (ተረት) ምንም ቢያስጠምዱ በዘጠና፤ ቤቱን አይስትም ቀጠና።
አጽማዒ መጽምዕ ዒ ፡ የሚያደምጥ፤ አድማጭ፤ ሰሚ፤ አስማታም፤ ባላሾክሿኪ። የተማረ ሊቅ፤ መጽሐፍ የሚያሰማ፤ ተርጓሚ ሰባኪ። መጽምዔ ነገር ፡ (ኢሳ፫ ፡ ፫)።
አጽምአ ፡ አስጠማ፤ ውሃ ነሣ፤ ከለከለ፤ ውሃ ውሃ አሰኘ፤ የደዌ የምግብ። አጽማእካሁ እምስታየ ገነት። አርኅብዎ ወአጽምእዎ ፡ (መቃ። ፫ነገ ፡ ፳፪
፡ ፳፯)።
አጽምዐ ፡ ቀቀረ ቀፈረ፤ አዘነበለ፤ ዦሮውን ሰጠ፤ አቀረበ፤ ለመስማት። ሰማ፤ አደመጠ። አሰማ አስደመጠ፤ አስደራጊ። ጸለወንና አዘነን ተመልከት። አጽምዕ እዝነከ ወስምዐኒ። አጽምዑኒ ፍትሐ ከናፍርየ። አጽማዕኩ ሕቀ በእዝንየ። እዝን ያጸምዕ ኵሎ ምሳሌ ፡ (፬ነገ ፡ ፲፱ ፡ ፲፮። ኢዮ፲፫ ፡ ፮። ሢራ፶፩ ፡ ፲፮። ምሳ፲፪ ፡ ፱)።
አፅምዐ ፡ አደመጠ ፥ ሰማ፤–ጸምዐ።
አፅረሰ ፡ ኦጠረሰ፤ አደነዘ፤ ጥርስ ሰበረ አበለዘ። ያፀርሰከ አስናኒከ ፡ (ሢራ፴ ፡ ፲)።
አፅረረ ፡ አስከዳ፤ አሸፈተ፤ አስጠረረ፤ አሰለፈ፤ ጥሩር አለበሰ ፤ አስለበሰ።
አጽረበ ፡ አስጠረበ፤ አሳነጠ።
አጽረየ ፡ አጠራ፤ ንጹሕ አደረገ፤ ዐደሰ ኰላ፤ ፈጸመ። ወኢያጸሪ ርስሐቶ። አጽረይኩክሙ እምኀጢአትክሙ። አጽርዮ ለብሩር ዘኢኮነ ፍቱነ። ከመ ያርስንዎሙ ወያጽርይዎሙ። ለእመ አጽረየ ንስሓሁ በጽኑዕ ውዕየት
፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፲፩። ሕዝ፴፮ ፡ ፴፫። ምሳ፳፭ ፡ ፬። ዳን፲፩ ፡ ፳፭። ቄድር)።
አፅረፈ ፡ አሰደበ፤ አስነቀፈ፤ ስደቡ አለ።
አጽራሕ አጽርሕት ፡ አዳራሾች፤ ታላላቅ ቤቶች፤ ደርቦች። አጽራሐ ዴዴያት። ምሥዋዓት ዘውስተ አንሕስት ዘአጽራሐ አካዝ። አጽርሕት ፡ (፬ነገ ፡ ፳፫ ፡ ፰ና
፡ ፲፪። ስንክ ፡ መጋ፳፮)።
አፅራር ፡ ፀሮች፤ ዝግጁ ጠላቶች። ዐቀበቶ እምአፅራሪሁ። አፅራርየ እለ ተንሥኡ በነገረ ከንቱ ወበክ
፡ (ጥበ፲ ፡ ፲፪። ደራሲ)።
አፅርዐ ፡ (አስደራጊ) አቦዘነ፤ ሥራ አስፈታ፤ አስቀረ ከለከለ፤ አስተጓጐለ። ኢየሱስ አፅርዐ ምሒለ። አፅርዕ ትእዛዘ ፡ (ፈ ፡ መ ፡ ፳፪ ፡ ፩። አቡሻ ፡ ፶)።
አፅርዕት ፡ ቦዘኖች ሀኬቶች። ይትሜሀራ አፅርዕተ ፡ (፩ጢሞ ፡ ፭ ፡ ፲፫)።
አፅበሰ ፡ አደከመ፤ አዛለ፤ አሰነፈ፤ ናቀ፤ አቃለለ። ሕምዝ እንተ ታፀብስ አባለ። አፅበሰ ኅሊናሁ በኀይለ ወይን ፡ (ዲድ ፡ ፳፭። መጽ ፡ ምስ)። በአፅበሰ ፈንታ አስተፅበሰ ይላል፤ ፍችው፤ አንድ ነው። ቀሊልኑ በኀቤክሙ አስተፅብሶተ ሰብእ ወለእግዚአሔር ታስተፅብስዎ ፡ (ኢሳ፯ ፡ ፲፫። ሉቃ፲፪ ፡ ፴፪)። ዳግመኛም አፅበሰ አስተፅበሰ በማለት ፈንታ አስተፃበሰ ይላል፤ አያሰኝም፤ ፍጹም ጸያፍ ነው ፡ (ሉቃ፲፪ ፡ ፴፪)።
አጽበበ ፡ አጠበበ፤ አስጠበበ፤ አስጨነቀ፤ ትዕግሥት ዐጣ። ያንብሮ ውስተ መርሕብ ወኢያጽብብ ላዕሌሁ። አጽበቡ ላዕሌሆሙ በዐመፃ። ወያጸብብ እንግድዓሁ
፡ (ግብ፳፬ ፡ ፳፫። ፊልክ
፡ ፹፬። አፈ
፡ ድ፭)።
አጽበተ ፡ አስዋኘ፤ ቀዘፈ። ወረውዋ ውስተ ማዕምቀ ማይ ዘቦቱ አራዊት፤ ወጾርዋ ወአጽበትዋ መልዕልተ ማይ ወአውፅእዋ። አጽበቶ ለሐመርነ ውስተ ቀላየ ሃይማኖት
፡ (ስንክ ፡ ግን፲፩። መጽ
፡ ምስ)።
አጽባዕት [1] ፡ ጣት፤–ጸቢዕ ጸብዐ።
[2] ፡ (ዕብ ኤጽባዕ። ሱር ጺብዓእ። ዐረ ኢጽበዕ) ጣት፤ የእጆችና የእግሮች ዐጽቅ፤ ካምስቱ ክፍል አንዱ። ወፅአት አጽባዕተ እደ ሰብእ። ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ፤ አኮኑ አጽባዕት እምነ አጽባዕት የዐቢ ፡ (ዳን፭ ፡ ፭። ቅኔ)።
አጽባእት ፡ ጣት፤–አጽባዕት፤ ጸብዐ።
አጽብሐ ፡ አነጋ፤ አስነጋ፤ አማለደ፤ አስማለደ። የስው ስም። አብርሀ ወአጽብሐ ፡ (ታሪ ፡ ነገ)።
አፅነሰ ፡ አስፀነሰ፤ አሲያዘ፤ አስረገዘ። ብእሲሰ ይክል አፅንሶ ወአቅሞ ዘርዕ እምድኅረ ስሳ ዓመት። ኢይክል ተራክቦ ምስለ ብእሲቱ ወኢአፀንሶ ፡ (ፈ ፡ መ ፡ ፭ ፡ ፯። ፲፪ ፡ ፭። ቄድር)።
አጽነነ ፡ አጠነነ፤ አጠመመ፤ አዘነበለ፤ አስጐነበሰ፤ አዋረደ። አጽነነ ርእሶ። ሕልያን ያዐውር ወያጸንን ነገረ ርትዕ። መኑ አጽነኖ ለሰማይ ዲበ ምድር። አጽንኒ ቀሡተኪ። አጽንን እዝነከ ለርእየ ሕልመ አቡከ። አጽነነ እንዘ ኢይዘሮ እምድማሬሁ ፡ (ዮሐ፲፱ ፡ ፴። ዲድ ፡ ፬። ኢዮ፴፰ ፡ ፴፱። ዘፍ፳፬ ፡ ፲፬። ሔኖ፹ ፡ ፪። ቅዳ
፡ አፈ)።
አጽናሒ መጽንሒ ፡ የሚያቈይ፤ የሚያዘጋጅ። አጽናሔ ፍዳ ፡ (ጥበ ፡ ጠቢ)።
አጽናሕንሐ ፡ (የቅጥይ ቅጥይ) ወዘወዘ፤ አወዛወዘ፤ ለማጠን፤ የጥና የማጠንት።
አጽናዒ ፡ የሚያጠና፤ አጥኝ
፡ (ፈላስ)።
አጽንሐ ፡ አቈየ፤ አስቈየ፤ ደጅ አስጠና፤ አዘጋጀ። አጽናሕኮሙ ወነፃኅኮሙ። ሰማዕተ ባልሐ ዐስቦሙ አጽንሐ። ይቤሎሙ ያጽንሑ ሎቱ ሐመረ
፡ (መዝ ፡ ሮ፪። መዋሥ። ማር፫ ፡ ፱)።
አጽንዐ ፡ አጠና፤ አበረታ፤ አጠነከረ፤ መሠረተ፤ አጠበቀ ጠረነቀ፤ ሳበ ገተረ፤ ዘረጋ አከረረ፤ ያዘ ጨበጠ። አጽንዑ ገጾሙ እምኰኵሕ። አመ ያጸንዕ መንበሮ ላዕለ ነፋሳት። ወአጽንዐ እገሪሆሙ ውስተ ጕንድ። አጽንዐ አውታረ አርጋኖን። እመታ ታጸንዕ ለፈቲል። ዘያጸንዕ ሰብዐተ ኮከበ በየማኑ። ወያጸንዑ ውስተ እደዊሆሙ ፀበርተ ፡ (ኤር፭ ፡ ፫። ምሳ፰ ፡ ፳፯። ግብ፲፮ ፡ ፳፬። ዘርዐ ፡ ያዕ። ምሳ፳፱ ፡ ፴፯። ራእ፪ ፡ ፩። ፯ ፡ ፱)። ያዘ ጨበጠ ማለት ጣፊና መላሽ በእኁዝና በአኀዘ ፈንታ ያጸንዕ እያሉ ስለ ጣፉት እንጂ ዘይቤው አይዶለም።
፡ ጠበቀ፤ አጠና፤ ያዘ፤ የሕግ የትምርት። አጽንዕ ዘብከ። አጽንዖ ሃይማኖት። ሶበ ያነብቦ ለመጽሐፍ አሐዴ ጊዜ ያጸንዖ ፡ (ራእ፫ ፡ ፲፩። ቅዳ። ስንክ ፡ ሐም፫)።
አጽዐለ ፡ አሰደበ፤ አስነቀፈ፤ አስናቀ፤ ወልድ አብድ ያጼዕል አባሁ። ወዘኢያጽዐለ አዝማዲሁ። ከመ ኢያጽዕላ ርእሶን። እስመ ተዋርዶ ኢያጼዕል ፡ (ምሳ፳፰ ፡ ፯። መዝ ፡ ፲፬። ፩ጢሞ ፡ ፭ ፡ ፲፬። ተረ
፡ ቄር፩)።
አጽዐረ ፡ አጣረ፤ አደከመ፤ አስጣረ፤ አስጨነቀ፤ ሣቀየ፤ መከራ አሳየ፤ አስመረረ፤ አሳዘነ። አጽዐርዋ ለነፍሶሙ። ያጼዕረኒ ዘያወፅኣ ለነፍስየ። እስከ ምንትኑ ታጼዕርዋ ለነፍስየ። እስመ ጥቀ ያጽዕሮን። ወፈቀደ ያጽዕራ
፡ (ግብ፲፬ ፡ ፪። ኢዮ፲፯ ፡ ፩። ፲፱ ፡ ፪። ሄርማ። ስንክ
፡ ኅዳ፯)።
አጽዐቀ ፡ (ጠዊቅ ጦቀ) አስጨነቀ፤ አስጠበበ፤ አጣበቀ አጣብቆ ያዘ፤ መከራ አጸና ሣቀየ፤ አስገደደ። ኢያገምራ ርሕበ ዓለም ወኢያጽዕቃ መጽብብ ዘመቅዐን። ዘከርሥ ኢያጽዐቆ። ሶበ አጽዐቆ ምንዳቤ። እለ ያጽዕቁ ላዕለ ዕቤራት ፡ (አርጋ ፡ ፩። ድጓ። ፈ ፡ መ ፡ ፲፮ ፡ ። ፍ ፡ ነ ፡ ፲፪)።
አጽዐነ ፡ አስጫነ፤ ጫኑ፤ አሸክሙ አለ። በአጽዐነ ፈንታ አስተጽዐነ ይላል፤ ፍችው ፩ ነው።
አጽዐጠ ፡ አስቀመመ፤ አስጣፈጠ፤ አስነጠረ፤ ቀምሙ አጣፍጡ፤ አንጥሩ አቅልጡ አለ።
አጽዓብ አጽዕብት ፡ ነጣቆች አራዊት፤ ማሾች ሬሳ አውጭዎች፤ ከብዙ በቀር ባንድ አይገኝም። አዝእብተ ወአክልብተ ወአጽዕብተ ፡ (ሔኖ ፡ ክ፸)።
አጽዓጢ መጽዐጢ ዕጥ ፡ የሚያስቀምም፤ የሚያስነጥር፤ ሽቱ የሚያስበጅ።
አጽዕብት ፡ ሬሳ አውጮች፤–ጽዕብ።
አፅወሰ ፡ ሽባ አደረገ፤ አካል አጐደለ። እመ ቦ ዘአቍሰለ ዐይነ ገብሩ ወአፅወሰ
፡ (ዘፀ፳፩ ፡ ፳፮)።
አጽዋም ፡ (ማት) ጦሞች፤ የጦም ቀኖች፤ ወራቶች። አጽዋምሰ እለ ሥሩዓን ስድስቱ እሙንቱ፤ ጾመ አርድእት፤ ጾመ ረቡዕ ወዐርብ፤ ጾመ ልደት፤ ጾመ ዕለት ዘጽባሒሁ ዕለተ ጥምቀት፤ ጾመ አርብዓ፤ ጾመ ሰሙነ ሕማማት። አጽዋማት ፡ (አቡሻ
፡ ፴፰። ስንክ ፡ ሠኔ፲፯)።
አጽዋን ፡ (ናት) አንቦች፤ ዕርዶች፤ ምሽጎች። አጽዋኒሆሙ ወአድባሪሆሙ። አጽዋናት ውስተ አድባር። ይነሥት አጽዋናተ ፡ (ዮዲ፯ ፡ ፲። መሳ፮ ፡ ፪። ፪ቆሮ ፡ ፲ ፡ ፬)።
አጽደለ ፡ አበራ፤ አስበራ። ጸዳለ መብረቅ ቅድሜሃ አጽደለ። ኦርያሬስ እንተ ታጸድል ዲበ ርእሶሙ። ከመ ኢያጽድሉ ብርሃኖ ለወንጌለ ስብሐት። ወያጸድል እንተ ውስጣ ከመ ማህው ፡ (ስንክ ፡ ነሐ፲፮። አርጋ ፡ ፪። መጽ ፡ ምስ። ራእ፳፩ ፡ ፳፩)።
አጽደልደለ ፡ አብረቀረቀ፤ አጥበረበረ፤ ቦግ ቦግ አለ። ወሓይዝተ ብርሃን ወሥን እለ ያጽደለድሉ ፡ (መጽ
፡ ምስ)።
አጽደቀ ፡ አጸደቀ፤ ጻድቅ አደረገ፤ አመጻደቀ፤ ራሱን ወይም ሌላውን። እለ ያጸድቁ ርእሶሙ በዝን ዓለም ኃጥኣን እሙንቱ በቅድመ እግዚ። እለ ያጸድቅዎ ለኃጥእ። ወአጽድቁ ግፉዐ ወምስኪነ ፡ (ቀሌ። ኢሳ፭ ፡ ፳፫። መዝ ፡ ፹፩)።
፡ አጸና፤ አስረዳ። ያጸድቅ ምክረ መላእክቲሁ። ለአጽድቆተ ቃል ዘንቤ
፡ (ኢሳ፵፬ ፡ ፳፮። አቡሻ ፡ ፴፩)።
አጽደፈ ፡ ገፋ፤ ጣለ፤ ወረወረ፤ ገደል አገባ፤ ሰደደ፤ አወረደ። ከመ ያጽድፍዎ ታሕተ። አጽደፍዎሙ እምርእሰ ውእቱ ቀልቀል። አጽደፍዎ ውስተ ሲኦል። ወታጸድፎሙ ለአሕዛብ በመዐትከ ፡ (ሉቃ፬ ፡ ፳፱። ፪ዜና ፡ ፳፭ ፡ ፲፪። ሕዝ፴፩ ፡ ፲፰። መዝ ፡ ፶፬)።
፡ አጠደፈ፤ አጣደፈ፤ አስቸኰለ፤ አስሮጠ
፡ (ዐማርኛ)።
አጽገበ ፡ አጠገበ፤ አረካ፤ አብዝቶ ሰጠ። ዘበላዕኩ ያጸግበኒ። በክልኤ ዓሣ ወበኀምስቱ ኅብስት አጽገቦሙ ኢየሱስ ለኀምሳ ምእት። ወአጽገቦሙ እምበረከቱ ለርኁባን። አጽግቦ ለርኁብ እምእክልከ ፡ (ሱቱ ፡ ዕዝ፬ ፡ ፳፰። ዝማሬ። ሉቃ፩ ፡ ፶፫። ኢሳ፶፰ ፡ ፯)።
አጽገየ ፡ አላበበ፤ አበባ አስመሰለ፤ ባበባ አስጌጠ፤ አበባን ሣለ ቀረጠ። ጠበብተ እስራኤል በልብሰ አሮን ካህን ደርከኖ አጽገዩ፤ ወሮማናተ ወርቅ በዐውዳ አፍረዩ። አጽገዩ ሕዝብ መሀይምናን ፡ (ስንክ ፡ ጥቅ፳፩። ድጓ)።
አፅግዐ ፡ አስጠጋ፤ አስደገፈ፤ አስተኛ፤ አንተራሰ። መጽሐፍ ግን በአፅግዐ ፈንታ አስተፃግዐ ይላል፤ ስሕተት ነው። አንበርዎ ዲበ ዐራት ወአስተፃግዕዎ በወለድ ዘሜላት ፡ (ዮሴፍ)።
አጽፈቀ ፡ አስጨፈቀ፤ አስጀጐለ፤ ጽፍቅ አስደረገ።
አጽፋር ፡ (ዐረ አጽፈር) የዐይነት ስም፤ ብጫ፤ ወይባ ዐደይ አበባ የሚመስል ሕብር። አስፋርን ተመልከት፤ ከዚህ ጋራ ፩ ነው። ወአቅየሐይሐ ሕብሮ በአጽፋር ፡ (ጥበ፲፫ ፡ ፲፬)።
አፅፋር ፡ ቅጥሎች፤ ቅጥልጥሎች፤ ሹጦች የሆድ ውስጥ ትሎች። ኀምሳ አፅፋር
፡ (ገድ ፡ ላሊ)።
አጾመ ፡ አጦመ፤ አስጦመ፤ አስከለከለ። ያጸውም አፉሁ እምነገረ ዘርቅ
፡ (ስንክ ፡ መስ፳፰)።
አጾረ ፡ አሸከመ፤ አሲያዘ፤ ጫነ። ዘእጾርከኒ እጸውር። አጾርዎ መስቀሎ። ያጹርዎ ቀኖና ዘማውያን ፡ (፬ነገ ፡ ፲፰ ፡ ፲፬። ቅዳ ፡ ግሩ። ፈ ፡ መ ፡ ፭ ፡ ፰)።
አፈ መልበስ ፡ ራስጌ ዐንገትጌ፤ እጅጌ፤ እግርጌ፤ የቆብ የባርኔጣ ፥ የካባ የጀባ ፥ የቀሚስ የሱሪ ፥ የሹራብ የመጫሚያ ፡ (ኢዮ፴ ፡ ፲፰። ዘፀ፳፰ ፡ ፴፪)።
አፈ እቶን ፡ የምድጃ አፍ ዕንጨቱና ልጡ እየተቈረጠ የሚገባበት፤ ባንድ ወገን እሳቱ ባንድ ወገን ኅብስቱ የሚነድበት የሚጋገርበት፤ ወይም የጢስ መውጫው መትጐልጐያው፤ እንደ ባቡር ጋን ያለው። ከመ ጢስ ዘይወፅእ እምአፈ እቶን
፡ (መቃ ፡ ገ፳፬)።
አፈ ወርቅ ፡ የሰው የመጽሐፍ ስም፤ ጽሩየ ቃል፤ ነባቤ ቃል ጽሩይ። ቃሉ እንደ ወርቅ የጠራ የከበረ፤ እድፍ ጕድፍ ጸያፍ የሌለበት። ዮሐንስ አፈ ወርቅ
፡ (ስንክ ፡ ግን፲፪)።
አፈ ጽባሕ ፡ የመዓልት ደጅ አፍ፤ መግቢያው መባቻው፤ የፀሓይ ውጋጋን የሚታይበት፤ መዠመሪያ ጊዜ፤ ጎሕ ጎሐ ጽባሕ። የጧት ጧት ማለዳ፤ ጎሕ ሲቀድ ፥ ወፍ ሲጮኽ፤ ጎሐን ተመልከት። ባልቴቶች የጧት ምስጋና ሲያቀርቡ ስትዘጋው አይሰማብኽ ስትከፍተው ኰሽ አይልብኽ እንዲሉ። ዕቅበተ ሌሊት እንተ አፈ ጽባሕ
፡ (ዘፀ፲፬ ፡ ፳፬። ዘፍ፲፱ ፡ ፲፭። ፫ነገ ፡ ፲፯
፡ ፮)።
አፈልፈለ ፡ አመነጨ ፥ አፈለቀ፤ አፈሰሰ። አፈለፍል ማእከለ ገዳም ፡ (ኢሳ፵፩ ፡ ፲፰)።
አፈር ፡ በቁሙ፤–ዐፊር ዐፈረ።
አፈወሰ ፡ አስፈወሰ፤ መድኀኒት አስደረገ። አፈውሶ እምለምጹ ፡ (፬ነገ ፡ ፭ ፡ ፮)።
አፈዋት [1] ፡ ሽታዎች፤ ሽቱዎች፤ የሽቱ ቅመሞች። ንሣእ አፈዋተ። አግማል እለ ይጸውሩ አፈዋተ። ወአምጽኡ አፈዋተ ከርቤ
፡ (ዘፀ፴ ፡ ፳፫። ፫ነገ ፡ ፲
፡ ፪ ፡ ፳፭። ቅዳ)።
[2] ፡ አመንዝሮች፤ የሚያስቱ ልብ የሚሰልቡ፤ ሽቱ የሚዘግቡ፤ አፈኞች አፈ ዋሾች። አፈውን ተመልከት።
አፈው ፡ (ዋት) ሽታ መዐዛ፤ የሽቱ ትንፋሽ፤ ሙዳዩ ቢልቃጡ ሲከፈት ካፉ የሚወጣ ረቂቅ እስትንፋስ። ሽቱ፤ የሽቱ ስም፤ የሽቱ ቅመም። አፈው እንደ ሰብእ ውስጠ ብዙ ነው፤ ሽታውም ሽቱውም ከብዙ ዕንጨት ከብዙ አበባ እንደ ተቀመመ ያሳያል። አፈወ ቅብዕ ጥዑም። ኵሉ አፈው። እሉ አፈው። ተሣየጣ አፈወ
፡ (መክ፲ ፡ ፩። ሔኖ፴፩ ፡ ፫። ፴፪ ፡ ፩። ማር፲፮ ፡ ፩)።
አፈድፈደ ፡ አበዛ፤ አበለጠ፤ አጠና፤ አበረታ። ኢታፈድፍድ ምስሌሁ ተናግሮ። አፈድፈድኪ ኀጢአተኪ እምኔሆን። ጻመውኩ ለአፈድፍዶ ፍቅረ አውግስጦስ። ወአፈድፈዱ ጸሊኦቶ
፡ (ሢራ፲፫ ፡ ፲፩። ሕዝ፲፮ ፡ ፶፩። ዮሴፍ። ዘፍ፴፯ ፡ ፰)።
አፈጸመ ፡ አስፈጸመ፤ አስመላ፤ እስጨረሰ። ለአፈጽሞተ ምግባራት። ስብሐት ለእግዚ ዘአፈጸመኒ ዘወጠንኩ በጸጋሁ ፍድፉድ ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፵፭። ሃይ ፡ አበ)።
አፈፈ ፡ (ዕብ አፋፍ፤ ከበበ ዐቀፈ) በቁሙ፤ ቈረጠ፤ ዐረደ ቀረደደ አስተካከለ። አፈፍ በድረግ አለ፤ ፈጥኖ ተነሣ፤ ወይም አነሣ ያዘ፤ አፈፍ አደረገ። አፋ ፥ አፍታ አፈፋ አፋፍ ማለት አፈወና እፎም ሳይቀሩ የዚህ ዘር ናቸው፤ እፈፎን እይ።
አፋዪ ፡ (ዪት ይያን ያት) የሚጋግር ጋጋሪ፤ ዐበዛ፤ በዓለ እቶን።
አፊር አፌር ፡ (ዕብ ኦፊር) ስመ ነገድ፤ ስመ ሀገር፤ በእስያ ክፍል በደቡብ ዐረብ በባሕረ ፋርስ ወይም በህንድ ውቅያኖስ ዳር ያለች፤ በቀድሞ ዘመን ወርቅ እንዳፈር እንዳሸዋና እንደ ጠጠር ይታፈሥባት የነበረች
፡ (ዘፍ፲ ፡ ፳፱። ፫ነገ ፡ ፱ ፡ ፳፰። በአፊር ፈንታ ሶፎር አዝፋር ይላል ፡ (ኢዮ፳፰ ፡ ፲፮። መዝ፵፬ ፡ ፲፩)።
አፊው ዎት ፡ (አፈወ የአፉ ይእፉ። አፈየ። አፈፈ) መተንፈስ፤ እፍ ፥ እፎይ ማለት፤ መናገር፤ አፍን መልቀቅ መክፈት፤ ማፋሸግ ማዛጋት። ነፍኀንና ነፍሰን በቀወን ተመልከት።
አፊድ ፡ (አፈደ። ዕብ አፋድ) መታጠቅ፤ መልበስ፤ ማሸረጥ፤ ማሸንቀጥ።
አፋዊ ፡ (ዊት ውያን ያት) የሚተነፍስ፤ አፈኛ አፋም፤ ለፍላፊ፤ አፈ ሰፊ። ወገን ቅጽል ሲኾን ፥ የአፍ ያሰኛል።
አፌዝ ፡ (ዐረ አውፋዝ። ጽር ዖፋዝ፤ ዑፋዝ። ዕብ ፓዝ) የወርቅ ወርቅ፤ መዠመሪያ ወርቅ፤ የማዕድናት ራስ በኵራቸው፤ ጥራቱና ዋጋው ከወርቅ የሚበልጥ፤ ተርታው ወርቅ ለ፴ና ላ፵ ሲሸጥ ርሱ ፷ና ፹ የሚያወጣ። ቃሉ ፎዘ ከማለት የወጣ ነው፤ ፋዝን ተመልከት። ወርቀ አፌዝ
፡ (ዳን፲ ፡ ፭። በአፌዝ ፈንታ ቄፋዝ ይላል፤ አፌዝና ፋዝ ቄፋዝ አንድ ስም ነው ፡ (ማሕ፭ ፡ ፲፩)። ሰላም ለርእስከ በወርቀ አፌዝ ጽሩይ፤ ዘአስተማሰለቶ መርዓት ሠናይት ላሕይ ፡ (ደራሲ)። ባለብሉዮች ግን ኹሉንም የወርቅ አገር ብለው ይፈቱታል።
አፍ [1] ፡ (ብ አፈው ዋት። ዕብ ፌህ። ዐረ ፉህ፤ ፋህ፤ ፊህ፤ ፈም፤ ፉም። ሱር ፉማ) በቁሙ፤ በከንፈርና በከንፈር መካከል ያለ ክፍት ኅዋ፤ መተንፈሻና መናገሪያ፤ የቃል የትንፋሽ የመብል የመጠጥ የነገር ኹሉ መውጫ መግቢያ ደጅ፤ የሚከፈትና የሚዘጋ የሕዋሳት በር። አፍ አንድ፤ አፈው አፎት ኹለት ወይም ብዙ፤ አፈዋት የብዙ ብዙ። አፉየ ከ ኪ ሁ ሃ፤ አፉነ ክሙ እያለ ይዘረዝራል፤ ለታተመ ለተመረገ ለጕድጓድ ለመቃብር ሳይቀር አፍ ላለው ኹሉ ይነገራል። እምተረፈ ልብ ይነብብ አፍ። ይትናገሮ አፈ በአፍ። ያበቁ አፉሁ እስከ እዘኒሁ። ይወድሰከ አፈ ነኪር ወአኮ አፈ ዚኣከ። ተፈፅመ አፈ ኵሉ አራዊት። አፍ ቦሙ ወኢይነቡ፤ ወአልቦ መንፈስ ውስተ አፉሆሙ። አፈወ አንቅዕተ ቀላይ ዐቢይ፤ በሰብዑ አፈው፤ አፈወ ማዕምቅት ምድር። አፈዋት አፎች
፡ (ማቴ፲፪ ፡ ፴፬። ኤር፴፱ ፡ ፬። ሢራ፳፩ ፡ ፭። ፳፯ ፡ ፪። ኩፋ ፡ ፫። መዝ
፡ ፻፴፬። ኩፋ ፡ ፭። ገድ ፡ ተክ)።
፡ ቃል፤ ነገር። ትርጁማን፤ አምጃር፤ ጠበቃ ወኪል የነገር አባት። በአፈ ክልኤቱ ወሠለስቱ ሰማዕት። ኵሉ ይቁም በአፈ ዚኣሆሙ። እምአፈ ዐሠርቱ ወኀምስቱ ነቢያት፤ እምአፈ ዐሠርቱ ወክልኤቱ ሐዋርያት፤ እምአፈ ሠለስቱ ምእት፤ ቃል ፡ (ማቴ፲፰ ፡ ፲፮። ቀሌ። ቅዳ)። ይኩንከ አፈ። ትከውን ከመ አፉየ፤ ፡ (ባፌ ፡ አፈ ፡ ንጉሥ)። ወኮነ አፈ ጉባኤሆሙ አባ ኒቆላዎስ
፡ (ዘፀ፬ ፡ ፲፮። ኤር፲፭ ፡ ፲፱። ታሪ ፡ ነገ)።
፡ ወደብ ጠረፍ፤ ጫፍ አፋፍ። መንገለ አፉሃ ለባሕር። አፈ ሞት
፡ (ኩፋ ፡ ፰። አዋል)።
፡ ስለት፤ አንደበት። አፈ ሰይፍ፤ አፈ ኵናት አፈ ኀጺን። ሰይፍ ዘክልኤ አፉሁ
፡ (ኩፋ ፡ ፴፬። ዕብ፲፩ ፡ ፴፬። ዮዲ፪ ፡ ፳፯። መዝ ፡ ፻፵፱)።
[2] ፡ አፍኣ
፡ በቁሙ፤–አፈወ።
አፍሐመ ፡ አጋለ፤ አጋመ፤ አፋመ፤ አከሰለ፤ ፍሙን ከስል፤ ከስሉን ፍም አደረገ።
አፍሓም ፡ ፍሞች፤ ከሰሎች። አፍሓመ እሳት ቅድሜሁ፤ ወወገሮ ውስተ እሳት ዘአፍሓም። መፍርህኬ አብቅዎ ከናፍር ለውሒጠ አፍሓም ርሱን። አፍሓም ዘያንበለብል
፡ (ኤር፵፬ ፡ ፳፪–፳፫። ቅዳ ፡ ቄር። ዳን፯ ፡ ፱)።
አፍኅርት [1] ፡ ጫጩቶች፤–ፈርኀ።
[2] ፡ ጫጩት፤–አፍርኅት፤ ፈርኀ።
አፍለሰ ፡ አፈለሰ፤ አስፈለስ፤ ነቀለ አስነቀለ፤ ማረከ አስማረከ፤ አሰደደ፤ አራቀ፤ ካገር አሶጣ አስለቀቀ። ወአፈልሰክሙ ውስተ ባቢሎን። ኢይደግም አፍልሶተ እግረ እስራኤል እምዛቲ ምድር። ወአፍለሶ እምድረ ግብጽ ፡ (ግብ፯ ፡ ፵፫። ፪ዜና
፡ ፴፫ ፡ ፰። ኩፋ ፡ ፲፫)።
፡ ለወጠ፤ ገለበጠ። ፈነቀለ፤ አንከባለለ፤ ገፋ አስፈገፈገ። አዞረ አዛወረ። ያፈልስ ልበ የዋሃን። ያፈልስዋ ለጸጋ እግዚ ውስተ ዝሙት። ናሁ አፍለስኩ ኰኵሐ ወጾርኩ ኆጻ ወኢረከበኩ ዘይከብድ እምነቢር በቤተ አብዳን። ኢታፍልስ ደወለ ገራህት። እስክንድር አፍለሰ ጥንተ ዓመቶሙ ኀበ ጥንተ ዓመተ መንግሥቱ ዘውእቱ ታስሪን ቀዳማይ ፡ (ጥበ፬ ፡ ፲፪። ይሁ ፡ ፬። ፈላስ። ምሳ፳፫ ፡ ፲። አቡሻ ፡ ፴፱)።
አፍለቀ ፡ አፈለቀ፤ አስፈለቀ፤ አመነጨ፤ አፈሰሰ፤ ፍልቅ አደረገ፤ የጠበል የመጠጥ።
አፍለጠ ፡ አስፈለጠ፤ አስለየ አስረዳ፤ አሳወቀ አስታወቀ። ለሊሁ ጳውሎስ አፍለ ወአርአየ ከመ በአምሳሉ ወበአርኣያ ክህነቱ ለክርስቶስ ውእቱ መልከ ጼዴቅ። አፍለጦሙ ዮሴፍ ለአኀዊሁ በነፍስቱ ፡ (ተረ ፡ ቄር። ግብ፯ ፡ ፲፫)።
አፍላክ ፡ አየሮች፤ የአየር ክፍሎች፤ ማዕርጎች። ወይብሉ ዘበአፍላክ ፡ (ፊልክ)።
አፍላግ ፡ (ጋት) ወንዞች፤ ፈሳሾች። አፍላግ የሐውሩ ዐውደ ተክሉ። ወይዘብጥ ሰብዐተ አፍላጋተ
፡ (ሕዝ፴፩ ፡ ፬። ኢሳ፲፩ ፡ ፲፭)።
አፍልሐ ፡ አፈላ፤ አስፈላ፤ አቀለጠ። በዛቲ ዕለት ኮነ አፍልሖተ ሜሮን። ዘአፍልሕዎ በእሳት። አዘዘ ያፍልሑ ናእከ ወይክዐዉ ውስተ አፉሁ ፡ (ስንክ ፡ ሠኔ፳፩። ፈ ፡ መ ፡ ፳፮ ፡ ፩። ስንክ ፡ ጥቅ፭)።
አፍሶት ፡ የድዉያን ቤት፤–ሐፍሦት፤ ሐፈሠ።
አፍረሰ ፡ አፈረሰ፤ አስፈረሰ፤ ሻረ፤ ድል ነሣ። ዘሐነጸ ቤተ ወያፈርስ። ሶበ ኢያፍረስኩ ርእስየ እምኢክህልኩ እሕንጻ ለነፍስየ። ያፈርሱ ኅሊናተ ሰይጣናት ፡ (ፊልክ ፡ ፻፷፭። ፪፻፳። ፴፩)።
አፍረቀ ፡ አስከፈለ። አፈራረቀ፤ አከታተለ።
አፍረየ ፡
አሳበበ፤ አስፈራ፤ አሶለደ፤ እንዲያብብ እንዲያፈራ አደረገ። ኣፈርዮ ከመ ዘይት ስሙር። ያፈሪ ወያሰምር ፡ (ሆሴ፲፬ ፡ ፰። ግብ፲፬ ፡ ፲፯)።
አፍራቅያ [1] ፡ አፍሪቃ፤–ፈሪቅ ፈረቀ፤ አፍረቀ።
[2] ፡ አፍሪቃ፤ አንድ እጅ የዓለም ክፍል፤ ካምስት አንድ፤ ኢትዮጵያ ያለችባት ዓለም፤ ዙሪያዋ ዳር ደንበሯ ኹሉ በባሕር የታጠረ የተከበበ እንደ ደሴት ያለች፤ ሥዕሏና ምስሏ፤ ወይም ቅርጧ አቀማመጧ የወይን ዘለላ የሚመስል። ዮም ትዌድሶ አፍራቅያ ፡ (ድጓ)።
አፍሬጥልስ ፡ ዕንቍ፤ የዕንቍ ስም
፡ (አረጋ ፡ መል፵፮)።
አፍርሀ ፡ አስፈራ፤ አስፈራራ፤ አስከበረ። አኮኑ ኀይሉ ያፈርሀክሙ። ቃለ ፀዓዑ ያፈርሃ ለምድር። ጥበብ ለዘረከባ ታአምኖ ወታፈርሆ ፡ (ኢዮ፲፫ ፡ ፲፩። ሢራ፵፫ ፡ ፲፯። ፲፰ ፡ ፳፰)። በአፍርሀ ፈንታ አስተፋርሀ ይላል፤ አያሰኝም። እፈፎ ያስትፋርሆ በሙቱ ፡ (ቄር ጰላ)።
አፍርኅት [1] ፡ ጫጩቶች፤–ፈርኀ።
[2] ፡ አፍርኅት፤
፡ (ዐረ አፍሪኀት። ዕብ ኤፍሮሒም) ጫጩቶች፤ የወፍ ገላግልቶች። መጽሐፍ ግን በአፍርኅት ፈንታ አፍኅርት ይላል፤ የተሳሳተ ነው። ዖፍ ምስለ አፍኅርቲሃ። ከመ ይለድ አፍኅርተ። ከመ ዖፍ አፍኅርቲሃ ትሴውር በክንፋ
፡ (መቃ። ማር ፡ ይሥ፳፰ ፡ ፪። ደራሲ)።
አፍቀረ ፡ ወደደ፤ ተቀበለ፤ አከበረ፤ አሶደደ፤ አስከበረ። ጊዜ ለአፍቅሮ ወጊዜ ለጸሊእ። አፍቅሮ ነገድ። አፍቅሮ ለእግዚ አምላክከ፤ አፍቅር ቢጸከ ከመ ነፍስከ። አፍቅሩ ጸላእተክሙ። ኢታፍቅርዎ ለዓለም
፡ (መክ፫ ፡ ፰። ሮሜ፲፪
፡ ፲፫። ማቴ፳፪ ፡ ፴፯–፴፰። ፭ ፡ ፵፬። ፩ዮሐ ፡ ፪ ፡ ፲፭)።
አፍቀደ ፡ አስፈቀደ፤ አሶደደ፤ ፍቀዱልኝ አለ። አገበረ፤ አስገደደ፤ ግድ አለ። ዘአፍቀደ ሄሮድስ ለአስተዋስቦ። ዘአፍቀደኒ ለቀቲሎትከ ፡ (ዮሴፍ)። በአፍቀደ ፈንታ አስተፋቀደ ይላል፤ ስሕተት ነው። አስተፋቅድዎሙ ምስለ ኀይሎሙ ፡ (ዘኍ፩ ፡ ፫)።
አፍቃሪ ፡ የሚወድ፤ የሚያሶድድ፤ ወዳጅ፤ አሶዳጅ። አፍቃሪ ወናዛዚ
፡ (ግንዘ)።
አፍቃድ ፡ ፈቃዶች። እንደ ድርኡ ሄርጋብ፤ ቤርሴክታን፤ ወይም እንደ ግእዝ፤ መዝገብ ሣጹን በማለት ፈንታ አፍቃደ አርጋብ ይላል፤ የጣፊ ስሕተት ነው። አርጋብን ተመልከት ፡ (፪ነገ ፡ ፮ ፡ ፰ና ፲፩)።
አፍተነ ፡ አስፈተነ፤ አስመረመረ፤ ራሱን ወይም ሌላውን። አፍትን ርእሰከ ለካህን። ኀፍረት ብእሲት ከመ ታፍትን ኀጢአታ ገሃደ ለቅዱስ ባስልዮስ
፡ (ማር፩ ፡ ፵፬። ስንክ ፡ ሐም፲፭)።
አፍተወ ፡ አስመኘ፤ አስጐመዠ፤ ደስ አሰኘ፤ ኣስወደደ፤ አስፈለገ። ኢያፍቱከ ሥና ለብእሲተ ባዕድ። ኢያፍቱከ ተድላሆሙ ለረሲዓን። ወአፍተዋ ከመ ትብላዕ። ዘያፈትዎሙ ለመላእክት ከመ የሐውጽዎ
፡ (ሢራ፱ ፡ ፰ ፡ ፲፪። መቅ ፡ ወን። ፩ጴጥ ፡ ፩ ፡ ፲፪)።
አፍታል ፡ (ትልት) ፈትሎች፤ ክሮች። አፍታል። በበ አፍትልት
፡ (ዘፀ፴፮ ፡ ፲። አዋል)።
አፍትሐ ፡ አስከፈተ፤ አስፈረደ። ለእመ ብእሲ አፍትሐ ደመ እምድኅረ ቍርባን። ኢያፈትሕዎሙ ፍትሐ ኵነኔ ፡ (ቄድር። ሢራ፴፰ ፡ ፴፫)።
አፍኒን ፡ (ዕብ ኦፋኒም) መንኰራኵራት፤ ተሸከርካሮች፤ የሠረገላ እግሮች። አንዱ ኦፋን ይባላል
፡ (ሕዝ፩ ፡ ፲፭ ፡ ፲፮)። ጌልጌልን ተመልከት፤ ከዚህ ጋራ አንድ ነው። ወየዐውድዎ ለውእቱ ቤት ሱራፌን ወኪሩቤን ወአፍኒን ፡ (ሔኖ ፡ ፷፩ ፡ ፲)። በፋኑኤል ፈንታ አፍኒን፤ በአፍኒን ፈንታ ፋኑኤል ይላል፤ የተሳሳተ ነው። አፍኒን ሊቀ መላእክት አሐዱ እምተስዐቱ ሊቃናት ፡ (ስንክ ፡ ኅዳ፰)።
አፍአመ ፡ አስጐረሠ፤ ጕረሥ አጕርሥ አለ፤ አስደራጊ።
አፍአምት ፡ ዝኒ ከማሁ። ሄድከ አፍአምቶ ለርኁብ። ሄድዎሙ ለርኁባን አፍአምቶሙ። ወተሰፈወ የሀብዎ አፍአምተ
፡ (ኢዮ፳፪ ፡ ፯። ፳፬ ፡ ፲። ግብ፫ ፡ ፭)።
አፍኣ ፡ (ዕብ ሑጽ) በቁሙ፤ ውጭ ዕዳሪ፤ ደጅ፤ ወልወል፤ ከቤት ከቅጥር ከሀገር ከመንደር ከወሰን ከደንበር በውጭ ያለ በውስጥ ያይደለ፤ ነኪር ባዕድ ልዩ ቦታ። አልብነ ውሳጤ ወኢአፍኣ። ይቀውም አፍኣ። ዐጸወ ደብተራ እንተ አፍኣ። ዝንቱሰ ውስጡ ጽቡር ወአፍኣሁ ብርት። ተሰቅለ አፍኣ እምትዕይንት። በአፍኣሃ ለኢየሩሳሌም
፡ (ቀሌ። ሢራ፳፩ ፡ ፳፫። ዮዲ፲፫ ፡ ፩። ዳን፲፫ ፡ ፯። ዕብ፲፫ ፡ ፲፪። ኤር፲፩ ፡ ፮)።
አፍኣዊ ፡ (ዊት ውያን ያት) የአፍኣ የውጭ የደጅ፤ ግልጥ ገሃድ። ቅጽር አፍኣዊ። ጽልመት አፍኣዊ። ኢይሰርገዋ አንስት ሰርጐ አፍኣዌ። ኢትጽንኑ መንገለ ፍኖተ ሕገጋት አፍኣዊት
፡ (፪ዜና ፡ ፴፪ ፡ ፭። ፊልክ ፡ ፹፰። ፈ
፡ መ ፡ ፴፬ ፡ ፰። ፲፰ ፡ ፩)።
፡ ሥጋዊ ዓለማዊ፤ መናፍቅ፤ ኢጥሙቅ። አፍኣውያን ዓለማውያን። ምስለ ሰብእ አፍኣውያን። እመ ቦ ዘኮነ ውጉዘ ምስለ አፍኣውያን
፡ (ፊልክ ፡ ፭። ፈ ፡ መ ፡ ፴፪ ፡ ፩። ፍ ፡ ነ ፡ ፲፫)።
አፍዖታት አፋዕው ፡ እፍኝቶች።
አፍዖት [1] ፡ እፍኝት፤–ፈዐወ።
[2] ፡ (ዕብ ኤፍዔ። ዐረ አፍዐን) እፍኝት እባብ ኰርፋፊያ ዐጭር ዥራተ ጐንዳ፤ ትንፋሹና መርዙ ቶሎ የሚናኝ የሚጐዳ። ወፅአት አፍዖት። ሕምዘ አፍዖት። ልሳነ አፍዖት
፡ (ግብ፳፰ ፡ ፫። ዘዳ፴፪ ፡ ፴፫። ኢዮ፳ ፡ ፲፮)።
አፍከ ፡ (ዐረ አፈከ። ዕብ ሀፋኽ) ገለበጠ፤ ተገለበጠ፤ ዞረ ተዛወረ፤ ከቀኝ ወደ ግራ ከፊት ወደ ኋላ። መልኩን ሃይማኖቱን ለወጠ፤ ተለወጠ ሌላ ኾነ፤ ወደ ሌላ ሕዝብ ተጠጋ፤ የክፉ የበጎ። ሸሸ አፈገፈገ፤ ወደ ኋላ አለ።
አፍክያ ፡ (ጽር ዲአቲኒያ። ዕብ ቄሬስ) ኆጻድ፤ ሜንጦ፤ ዘለበት፤ ቀለበት፤ የድንኳን የመጋረጃ ቍልፍ፤ ማያያዣ
፡ (ዘፀ፴፭ ፡ ፲፩። ኀጸደንና ኆጻድን ተመልከት።
አፍይ ዮት ፡ (አፈየ የአፊ ይእፈይ። ዕብ አፋህ። ሱር ኤፋእ) ኀቢዝ፤ መጋገር፤ ማብሰል፤ መረመጥ፤ የሊጥ የብርኵታ።
አፍዮማክን ፡ (ጽር፤ ዖፊዮማኪስ) ሐሴን፤ ዐሸን፤ የአንበጣ ዐይነት፤ ከምድር የሚፈላ
፡ (ዘሌ፲፩ ፡ ፳፪)።
አፍደየ ፡ አስከፈለ፤ አስመለሰ። ይዝብጥዎው ወያፍድይዎሙ ፡ (ፈ ፡ መ ፡ ፲፯ ፡ ፯)።
አፍጠነ ፡ አፈጠነ፤ አስፈጠነ፤ አስቸኰለ፤ ቶሎ አደረገ፤ አስደረገ። አፍጥን ረዲኦትየ። ወአፍጠኑ ረሲዐ ምግባሩ። አፍጠነ ውሂቦታ ቅበዐ። ዘኢያፈጥን እዴሁ ለዘቢጥ
፡ (መዝ ፡ ፷፱ ፡ ፻፭። አስቴ፪ ፡ ፬። ፩ጢሞ
፡ ፫ ፡ ፫)። በአፍጠነ ፈንታ አስተፋጠነ ይላል፤ ስሕተት ነው፤ አያሰኝም። አስተፋጥን ትምጻእ ኀቤየ። ናስተፋጥን ከመ ንባእ። አስተፋጠኑ ወአግሐሡ ፡ (፪ጢሞ ፡ ፬ ፡ ፱። ዕብ፬ ፡ ፲፩። ዮዲ፲፫ ፡ ፩)።
አፎት ፡ (ዕብ ፊዮት) ኹለት አፍ ያለው ሰይፍ፤ አፋ፤ ሾተል፤ ጕዶ፤ ጩቤ። በቁሙ ሰገባ፤ ድርቄ የሰይፍ ማኅደር፤ ሽፋፍ። በስመ ኀዳሪ ይጼዋዕ ማኅደር።
ኡ ፡ ኡኡ፤ ፡ (ዐማርኛ) ኡኡታ፤ ኦ ኦኦ።
ኡባል ፡ (ዕብራ) ታናሽ ወንዝ፤ ፈፋ በዱር በዛፍ ውስጥ ያለ። የግንብ ደጃፍ የድልድይ በር። ወሀሎኩ አነ በኡባል ኡላይ
፡ (ዳን፰ ፡ ፪)። ኡላይ የወንዙ ስም ነው።
ኢ ፡ አሉታ፤ ነባር አንቀጽና ንኡስ አገባብ፤ ነባር አንቀጽ ሲኾን ፍችው እንደ አኮና እንደ ሐሰ እንደ አልቦ ነው
፡ (ዕር፲፩ ፡ ቍ፺፮)። ንኡስ አገባብ ሲኾን ፥ አል አ እንዳ ላ ሳ ያል የማ ይኾናል። ኢጸሐፈ ፥ አል፤ ኢይጽሕፍ ፥ አ፤ ኢይጽሐፍ ፥ እንዳ ላ ሳ። ኢጽሒፎ ፥ ሳ፤ ኢጸሓፊ ያልጣፈ የማይጥፍ። ትራስ እየኾነም በእፎ ሲገባ ኤ ይኾናል ፥ እፎኢ፤ ምስጢሩም ያሉታ አንክሮ ነው። ደቂቅ አገባብም ሲኾን እንደ እንበለ ነው፤ አለ ያለ ይኾናል። ኢ ወኢ እያለ ሲጫፈርና ሲደጋገም ኹኖ ፥ ቢኾን ያሰኛል። ፍችው አለ ሲኾን ከይቤ ዐማርኛ ይሰማማል፤ ፡ (ግጥም) ትሰሙ እንደኾን የወንጌል ቃል አለ–መስጠት ያጸድቃል። ባማርኛም ኢ አዪ ፥ አዬ ተብሎ ሲነገር ቃለ አኅስሮ ሐዘንና አንክሮ ይኾናል። ምስጢሩ አሉታና አፍራሽ ሲኾን ያማርኛው ስልት በዝቷልና ፥ ኹሉንም በንኡስ አገባብ ተመልከት ፡ (ዕር፳ ፡ ቍ፻)።
ኢሎፍሊ ፡ (ጽር አሎፍሊ) ስመ ነገድ ስመ ሀገር፤ ፍሌስት፤ ፍልስጥኤም፤ ፈለሰን ተመለከት። ይችውም ሜዲተራኒ በሚባለው በታላቁ ባሕር አጠገብ በዳር በደንበሩ በወደቡ ያለች የምድረ እስራኤል ጎረ ቤት ናት። ተጋብኡ ኢሎፍሊ ላዕለ እስራኤል። ወነሥእዋ ኢሎፍሊ ለታቦተ እግዚ። ኀምስቱ አሕዛበ ኢሎፍሊ
፡ (፩ነገ ፡ ፬ ፡ ፩። ፭ ፡ ፩። መሳ፫ ፡ ፫)።
ኢሎፍላዊ ፡ (ዊት ውያን ያት) ፍሌስታዊ፤ የፍሌስት ሰው፤ ወገን ዘር። ናሴብ ኢሎፍላዊ። አነ ውእቱ ኢሎፍላዊ
፡ (፩ነገ ፡ ፲ ፡ ፭። ፲፯ ፡ ፰ ፡ ፲)።
ኢም ፡ (ዕብ ፡ ኢይም) ቀብራርት አንበሳ የሚፈራቸው፤ የተኵላ ወገኖች፤ የበረሓ ውሾች። አንዱን ኢይ ይለዋል። ጺም ምስለ ኢም
፡ (ኤር፶ ፡ ፴፱)። ባለቅኔዎች ቀኝ ይሉታል።
ኢምንት ፡ በቁሙ ፥ ባዶ የሌለ ያልነበረ ያልተፈጠረ፤ ወይም የተናቀ ከንቱ ብላሽ ፥ እያለ መኖሩ የማይታሰብ። ወ በር ከፋችና አዳማቂ ይኾንለታል። ሰፍሖ ለመስዕ ዲበ ወኢምንት። ከመ ወኢምንት እሙንቱ
፡ (ኢዮ፳፮ ፡ ፯። ኢሳ፵ ፡ ፲፭)።
ኢብን ፡ (ጽር ይቢስ) የወንዝ አሞራ በወንዝ ዳር በባሕር ጠረፍ የሚኖር፤ ነጭ አፈ ረዥም፤ ትሎችን ተሐዋስያንን የሚለቅም፤ ከዚህ የተነሣ ግብጻውያን ያመልኩት ነበረ ይባላል
፡ (ዘሌ፲፩ ፡ ፲፯። ዘዳ፲፬ ፡ ፲፮)። ዕብራስጡ ግን ያንሹፍ ይላል፤ ጕጕት ማለት ነው።
ኢትዮጳዊ ኢትዮጵያዊ ፡ የኢትዮጵያ፤ አፍሪቃዊ፤ ኖባዊ ሱዳናዊ፤ ወይም አፍሪቄ ኖቤ ሱዳኔ። ምስጢሩ ጥቍረትና ቈለኛነት ነው። ይዌልጥኑ ኢትዮጵያዊ ማእሶ ወነምር ሕንብርብሬሁ። ወረከበ ኢትዮጵያዌ ንኡሰ፤ ደቦል ሻንቅላ
፡ (ኤር፲፫ ፡ ፳፫። ፊልክ ፡ ፴፬)።
ኢትዮጵያ ፡ (ጽር ኢትዖፒኣ። ዐረ ሱዳን። ዕብ ኵሽ፤ ስመ ነገድ) የመልክና የሕብር የሀገር ስም፤ የሱዳኖች አገር መላው ጠቅላላው፤ ከግብጽ ቀጥሎ ያለው። ጥቍር ጠቋራ ክሰልማ፤ የጥቍሮች አገር ማለት ነው። ኢትዮጵያ ታበጽሕ እደዊሃ ኀበ እግዚ። ኵሎሙ ኢትዮጵያ ዘጸሊም ሥጋሆሙ። ወቦ ዘትከውን ኀሳረ በኀበ ካልኣኒሃ ከመ ቀሪጸ ገጽ በኀ ኢትዮጵያ ወኖባ። ኖባ የነገድ የሀገር፤ ኢትዮጵያ የመልክ የሕብር ስም
፡ (መዝ : ፷፯። ቀሌ። ፍ ፡ ነ ፡ ፶፩)። ዕብራይስጡ ኵሽ የሚለውን የኵሽን ስም ኹሉ ፥ ጽርኡ ኢትዎፕስ ይለዋል፤ ከዚህ የተነሣ ታሪክ ጣፎች ኹሉ ኵሽን የኢትዎፕስ አባት፤ ወይም የአክሁናስ ልጅ አንደኛ ኢቶጲስ ይሉታል፤ አክሁናስ ያሉትም ኵሽን ነው። ኹለተኛም የኵሽ አገር ኹሉ በልጁ በኢትዮጲስ ስም ኢትዮጵያ ተባለች ይላሉ፤ የመላ የግምት አነጋገር ነው፤ ዕብራይስጥና ጽርእ ላላየ ግን እውነት ይመስለዋል። በጽርእ ቋንቋ ኢትዮጲስ የተባለው ያው በዕብራይስጥ ኵሽ የተባለው ዋነኛውና መደበኛው ርሱው ራሱ በኵሩ ግንባሩ ቀደሙ የካም ልጅ ነው እንጂ ፥ ሌላ ፪ኛ አካል የኵሽ ልጅ አይዶለም። ለኵሽ በኦሪትና በዜና መዋዕል ከተጻፉት ሳባ ሐዊላ ሰብታ ረዕማ ሰብተቃ ናምሩድ ከሚባሉት ከ፮ቱ ሌላ ፳፪ ልጆች እንዳሉት ዮናናዊ ታሪክ ይናገራል። ከዚሁ ከዮናን የተቀዳው የሞሪዬም ታሪክ፤ የካም ልጅ ኵሽ አርባ ፥ አልቤዎን ፥ ኪሬኔ ከሚባሉ ከ፫ቱ እኅቶቹ ፳፰ ወልዷል፤ ዕድሜውም ፬፻፸፰ ነው፤ መዲናውና መቃብሩ አኵስም ናት ይላል። ፳፰ ያላቸውንም በየስማቸው ጥፏቸዋል፤ የ፮ቱ ስም በኦሪት እንደ ተጣፈው ነው
፡ (ዘፍ፲ ፡ ፯ ፡ ፰)። ከቀሩትም ከ፳፪ቱ ነገድ አቢስ እንጂ ኢትዮጲስ የተባለ የለም፤ አቢስን ግን የሳባ ሳብዓይ የናምሩድ ተከታይ ከአልቤዎን የተወለደ የኵሽ ፯ኛ ልጁ ብሎ እናቱ ሳትቀር ስሙንም ቍጥሩንም ጥፎለታል፤ አቢስን ተመልከት። ኢትዎፕስ ማለት በጽርእ ኹለት ያሳያል፤ የሰው ስም ሲኾን ጥቍር ጠቋራ ከሰልማ፤ የሀገር ስም ሲኾን ቈላ በረሓ ምድረ በዳ። ስምነቱም ከኵሽ ሞት በኋላ በ፪ ሺሕ ካ፬፻፶ ዓመት ፸ ሊቃናት ያወጡት ከ፸ ሊቃናት የተገኘ ሐዲስ እንግዳ ደኃራዊ ስም ነው። በሱዳን ዙሪያ ያለችውም መላይቱ አፍሪቃ፤ ይልቁንም ከነጭ አባይ ወዲህ ያለችው ክፍል፤ የጥቍሮች የኵሽ ልጆች አገር ስለ ኾነች በዚህ ባዲሱ ስም ኢትዮጵያ ትባላለች ፡ (ዘፍ፪ ፡ ፲፫)። በብሉይ በሐዲስ የተጣፈው ዋነኛውና መደበኛው ኢትዮጵያ ግን ታላቁን በረሓ ሰሐራን ጨምሮ የኖባ ክፍል ነው ፡ (፪ዜና ፡ ፲፬
፡ ፱ ፡ ፲፪ ፡ ፲፫። ፲፮ ፡ ፰። ፬ነገ ፡ ፲፱
፡ ፱። ኢሳ፴፯ ፡ ፱። ሕዝ፴ ፡ ፬ ፡ ፭ ፡ ፱። ግብ፰ ፡ ፳፯)። ወዲያ ማዶም በእስያ ክፍል ያለው ያረቦች አገር ቃዴስ በርኔና ሐቅለ ሲና ሌላውም ኹሉ፤ ቈላ በረሓ ፍጹም ምድረ በዳ ስለ ኾነ፤ በዕብራይስጥ ፡ (ጺያ) ጺይም ይባላል እንጂ ፥ ኵሽ አይባልም፤ በጽርእ ግን እንዳፍሪቃ ክፍል እንደ ኖባ ኢትዮጵያ ይባላል። ይገንዩ ቅድሜሁ ኢትዮጵያ። ወወሀብኮሙ ሲሳዮሙ ለሕዝበ ኢትዮጵያ ፡ (መዝ ፡ ፸፩። ፸፫)። የቀረውን በሰፊው ታሪክ ተመልከት፤ ፡ (ክፍል ፩)።
ኢን ፡ (ዕብ ሂን) የልክ ስም፤ ታናሽ ገንቦ፤ የርጥብ መስፈሪያ፤ መሣሪያ፤ ፲፪ ሉግ የምቲዝ። ያንዱ ሉግ መጠን ፮ ዕንቍላል ይኾናል
፡ (ሕዝ፬ ፡ ፲፩)።
ኢየሱስ ፡ (ጽር፤ ይሱስ። ዐረ የሱዕ። ዕብ የሹዕ) ስመ ተጸውዖ ዐማኑኤልን የመሰለ። መድኅን መድኅኒ፤ መድኀኒት፤ ቤዛ መቤዝው
፡ (ማቴ፩ ፡ ፳፩። ዮሐ፬ ፡ ፳፪)። ኢና ይ አንድ ወገን ናቸው፤ የሱስ ማለት ይበቃ ነበር፤ ኢ እንዲያው በከንቱ ተጨምሯል ፥ ምስጢር የለውም፤ ኢያሱ ኢዮስያስ እንደ ማለት ነው። ባለሐዲሶች ግን ኢን አኮ መድኀኒት ሲሉ አይሁድ ጨምረውታል ብለው ያወራሉ፤ ውሸት ነው። ስምነቱም ብቻ የቃል ብቻ የሥጋ ስም አይዶለም፤ ቃልና ሥጋ ተውሕደው አንድ የኾኑበት ያንድ አካል የሥግው ቃል ስም ስለ ኾነ ፪ ባሕርይና ፪ ግብር፤ አምላክ ወሰብእነት ያሳያል፤ እንዳማኑኤል ነው። ሶበሰ አምላክ ውእቱ ባሕቲቱ እፎመ እምሐመ ሶበ ሰቀልዎ፤ ወሶበሂ ሰብእ ውእቱ በሕቲቱ እፎመ እምአድኀነ ፍጡራነ ፡ (ሃይ ፡ አበ)። ቤዛ ኹኖ መሰቀል መሞት ፥ ምግብ ኹኖ መበላት መጠጣት የሰውነት፤ ማዳን የአምላክነት ፡ (ዮሐ፮ ፡ ፷፮ ፡ ግብ፬
፡ ፲፪)። ከሥጋዌም በፊት የርሱ ምሳሌ ሊኾኑ የሱስ የተባሉ ብዙ ናቸው፤ ፡ (፩ዜና ፡ ፳፬ ፡ ፲፩። ነሐ፲፪ ፡ ፰)። ኢያሱና ሆሴዕም የዚህ ጭምር ናቸው።
ኢየሩሳሌም ፡ (ዕብ ይሩሻሌም) ስመ ሀገር፤ የዳዊት መዲና፤ የልጆቹ ኹሉ መናገሻ፤ በምድረ ይሁዳ ያለች ጥንታዊት ከተማ። ኢ የግእዝ ተውሳክ ነው፤ የሩ ሀገር፤ ሳሌም ሰላም፤ በተገናኝ ሀገረ ሰላም ማለት ነው። ሳሌም ከመባል በፊት ሴዱ ስላቀናት ሳይዳ ቤተ ሳይዳ ትባል ነበር፤ ቤተ ጸጋ ወሣህል ማለት ነው
፡ (ዮሐ፭ ፡ ፪)። ከሴዱ በኋላ ልጁ ሳሌም ስለ ነገሠባት ፥ ሳሌም የሩሳሌም ተብላለች፤ ከዚያ ወዲህ ስፙ አልተለወጠም ፡ (መዝ ፡ ፸፭
፡ ፫። ኢያ፲ ፡ ፩)። ‹‹እመጽሐፈ ዮሐንስ መደብር፤ ክፍል ራብዕ። መልከ ጼዴቅ ውእቱ ዘወፅአ እምነገደ ሴዱ ወልደ ንጉሠ ምስር ወኖባ፤ ወውእቱ ሴዱ ዘነግሠ በከነዓን ወውእቱ እምነገደ ጽኑዓን። ወውእቱ ተጻብኦሙ ወተቀንዩ ሎቱ፤ ወሶበ አስተፍሥሕዎ ነበረ ውስቴታ ወሐነጸ ሀገረ ወሰመያ በስመ ዚኣሁ ሳይዳ፤ ወእስከ ዮም ትሰመይ ሳይዳ፤ ወአቡሁ ለመልከ ጼዴቅ ወፅአ እምነ ሳይዳ›› ጊዮርጊስ ወልደ ሐሚድ ግን፤ መልከ ጼዴቅ ወልደ ፋሌቅ ብሎ ፥ የራግው ታናሽ ወንድም ሴማዊ ይለዋል። ወሐይወ ፋሌቅ እምድኅረ ወለዶ ለራግው ክልኤተ ምእተ ስሳ ወተስዐተ ፡ (፪፻፷፱) ዓመተ ወእምዝ ወለዶ ለመልከ ጼዴቅ ካህን ፡ (ጊ ፡ ወ ፡ ሐ ፡ ገ፳፬)። ወሶበ ቀርበ ዕለተ ሞቱ ለኖኅ አማሕፀኖ ለሴም ወልዱ ከመ ያፍልስ ሥጋሁ ለአዳም ወይቅብሮ ማእከለ ምድር ወይሢሞ ለመልከ ጼዴቅ ወልደ ፋሌቅ ኀበ መቃብሩ ከመ ይትለአኮ እስመ ካህኑ ለእግዚ ውእቱ ፡ (ጊ ፡ ወ ፡ ሐ ፡ ገ ፲፩)። ቀሌምንጦስኒ ወአቡ ሻህር ይቤሎ ከማሁ። ከሳሌም በኋላ የነገሡም ንጉሠ ሳሌም በመባል ላይ መልከ ጼዴቅ አዶን ጼዴቅ እየተባሉ በምሳሌ ስም ተጠርተዋል፤ ይኸውም ንጉሠ ጽድቅ እግዚአ ጽድቅ ማለት ነው። አማናዊው ንጉሠ ጽድቅና እግዚአ ጽድቅ ኢየሱስ ናዝራዊ እንደ ሰውነቱ ንጉሠ አይሁድ ተብሎ በመካከሏ ተሰቅሎ፤ ደቂቀ አዳምን ከአብ ፥ ሕዝብን ከአሕዛብ ፥ ሰውን ከመላእክት ፥ ነፍሳትን ከሥጋት የሚያስታርቅባት ስለ ኾነች፤ ስፙ እንደ ትንቢት ኹኖ ከነቢያት በፊት በዘመነ አበው ተነግሯል ፡ (ሉቃ፲፫ ፡ ፴፫። ኤፌ፪ ፡ ፲፫–፲፰። ቈላ፩ ፡ ፳–፳፪)። ነቢያት ግን በእስራኤል ክፋት ሰዶም ገሞራ ብለዋታል፤ ከሰዶምም ያከፏትና ያበለጧት አሉ ፡ (ኢሳ፩ ፡ ፲። ሕዝ፲፮ ፡ ፵፰)።
ኢየሩሳሌም ሰማያዊት ፡ ዐምስተኛ ሰማይ ከጠፈር፤ ዲያብሎስ የተፈጠረባት፤ ርሱ ከሸፈተ በኋላ ለአዳም ልጆች የተሰጠች ፡ (ዕብ፲፪ ፡ ፳፪ ፡ ፳፫። ራእ፳፩ ፡ ፪)።
ኢያሚን ፡ (ጽር ያሚን። ዕብ ያዔህ) የመሣሪያ ስም፤ ኮከም ከብርት ከብረት የሚሠራ፤ የፍም መጫሪያ መተርከሻ፤ ያመድ የጕድፍ መጋፊያ፤ መዛቂያ ማፈሻ፤ ሥራው እንደ መንካና እንደ ላይድ እንዳካፋ ያለ
፡ (፬ነገ ፡ ፳፭ ፡ ፲፬)።
ኢያሰጲስ ድ ፡ (ጽር ያስፒስ። ዕብ ያሽፌ) ዕንቍ፤ የዕንቍ ስም፤ ሕብሩ ሕብረ ሰማይ ጽሩይ፤ ቅዛዝ መስታዮት የሚመስል ፡ (ራእ፬ ፡ ፫። ፳፩ ፡ ፲፰ ፡ ፲፱። ሕዝ፳፰ ፡ ፲፫)።
ኢያዜር [1] ፡ (ጽር ያዚር። ዕብ ያዕዜር) ስመ ሀገር፤ የጋድ ርስት ሮቤልና ጋድ ሲማረኩ ሞአብ የወረሳት። ባለብሉዮች ግን ሔለይ የሊ ይሉታል። ባለቅኔዎችም አልቃሽ ይሉታል። እስከ ኢያዜር፤ ብካየ ኢያዜር
፡ (ኢሳ፲፮ ፡ ፰ና ፡ ፱። ዘኍ ፳፩ ፡ ፴፪)።
[2] ፡ (ጽር ወዕብ ኔዜር) ዘውድ አክሊል፤ ጋሜ ጐፈር፤ አንፋሮ ፥ የብፅዐት ጠጕር የማይላጭ። ባለብሉዮች ግን ዘውድ አክሊል በማለት ፈንታ ልብሰ መንግሥት አርድ አንቀጥቅጥ ይሉታል። ወአልበሶ ልብሰ ኢያዜር ፡ (፬ነገ ፡ ፲፩
፡ ፲፪)። ያዕዜርና ኔዜር ኹለት ልዩ ቃሎች ሲኾኑ የግእዝ መላሽ አንድ አድርጓቸዋል።
ኢዮር [1] ፡ (ጽር አኢር። ዐረ ኢያር) ሰማይ፤ ከጠፈር እስከ መንበር ያለው ሰባቱ ኹሉ፤ ጠፈርና ኅዋም ሳይቀሩ። ዘዲበ ኢዮር መንበሩ። ከመ ከዋክብት ዘኢዮር ይበዝኅ ኀጢአትየ። ተራወጸ በኢዮር ደመና ፡ (መዋሥ። መጽ ፡ ኑዛ። ደራሲ)።
[2] ፡ መካከለኛ ሰማይ የጠፈር
አራተኛ ፤
ከበላዩ ኢየሩሳሌም
ሰማያዊት ፥
ሰማይ ውዱድ
፤ ጽርሐ
አርያም ያሉበት
(ሥነ ፡ ፍጥ)።
ኢዮቤል ፡ (ጽር ዮቢል። ዕብ ዮቤል) የበግ ጠቦት፤ ወጠጤ ተባት፤ ቀንዳ መለከት፤ በዓለ ኀምሳ፤ ከ፯ ሱባዔ ወይም ካ፵፱ ዓመት በኋላ ዐምሳኛው ዓመት ብዙ ጠቦት የሚሠዋበት ቀንዳ መለከት የሚነፋበት
፡ (ዘሌ፳፭ ፡ ፩–፲፫)። ሲያበዛ ኢዮቤላት ኢዮቤልዮን ኢዮቤልዉ ኢዮቤልዎሳት ይላል ፡ (ኩፋ)።
ኢጥያ ፡ (ጽር ይቴያ) ስመ ዕፅ ተክላዊ። ዕፅ ዘስሙ ኢጥያ
፡ (ሄርማ ፡ ገ፷፩ና ፡ ፬)።
ኢፍ ኤፍ ፡ (ዕብ ኤፋ) የመስፈሪያ ስም፤ ታላቅ ቍና፤ ቤዶ፤ ላዳን፤ የሖሜር ዐሥረኛ። አንዱ ኢፍ ፫ ስኣ ይይዛል፤ ስኣ እንደ መሸመቻ ያለች ታናሽ ቍና ነች፤ መሥለስን እይ። መስፈርተ ኢፍ
፡ (ዘሌ፭ ፡ ፲፩። ዘኍ፭ ፡ ፲፭። ሩት፪ ፡ ፲፯። ሕዝ፵፭ ፡ ፲)።
ኣ ፡ (የቅጽል በር ከፋች) በዝርዝር ጊዜ፤ ቅጽሎቹም ዘ እንተ እለ ናቸው። ዚኣሁ እንቲኣሁ እሊኣሁ፤ ሃ ሆሙ ሆን፤ ዚኣከ፤ እንቲኣከ እሊኣከ ኪ ክሙ ክን የ ነ።
ኣሐድ ፡ (ኣሐት) አንደኛ አንደኛው
፡ (ዕር፲፭ ፡ ቍ፻፳፮) ተመልከት።
ኤ ፡ ስመ ፊደል፤–ዐ ዔ።
ኤለ ፡ ዞረ ባከነ፤–ዐዪል ዔለ።
ኤሉል ፡ ስመ ወርኅ፤–አይሉል።
ኤሊማስ ፡ (ጽር ሄሊማስ። ዐረ ዐሊሞን) የፙርተኛ ስም፤ እንደነኢያኔስ ያለ። መሠርይ። ምሁረ ሥራይ፤ መሰግል መዐልመ ሰገል ወምትሀት ጽጉበ ትምህርት ማለት ነው፤ ስምነቱ ዐለመ ከማለት የወጣ ነው፤ ጽርኡ ከዐረብ ወስዶታል፤ ሊጣፍ የሚገባው በዐይን ዐ እንጂ በአልፍ አልነበረም። ወይትዋቀሦሙ ውእቱ ዘሥራይ ዘይብልዎ ኤሊማስ፤ እስመ ከመ ዝ ትርጓሜ ስሙ
፡ (ግብ፲፫ ፡ ፰)።
ኤሊሳ ፡ ስመ ነገድ፤ ስመ ሀገር፤ መዲና ብዙ ደሴት ያለው
፡ (ዘፍ፲ ፡ ፬። ሕዝ፳፯ ፡ ፯)።
ኤላ ፡ ዐዘቅተ ማይ፤–ዐዪል፤–ዔለ።
ኤላማው ፡ በረንዳው፤ ደጀ ሰላሙ፤ ው ዝርዝር ነው
፡ (ሕዝ፵ ፡ ፳፩)።
ኤላም ፡ (ጽር። ዕብ ኡላም) በረንዳ፤ ደጀ ሰላም በታላቅ ቤት ደጃፍ ወይም በቅጥሩ በር የሚሠራ
፡ (ሕዝ፰ ፡ ፲፮። ፵ ፡ ፮። ፫ነገ ፡ ፮
፡ ፯)።
ኤላው ፡ (ዕብራ) አዕማዲሁ፤ አረፋቲሁ፤ ው ዝርዝር ነው። ወኤላው ካዕበ እመት
፡ (ሕዝ፵ ፡ ፱)። ኤልን ተመልከት፤ ኤላው ከኤል የወጣ ነው።
ኤላጢኑስ ፡ (ጽር ኤላቲኖስ። ዕብ ቶሬን) የመርከብ ዐምድ፤ ምሰሶ ወፍራም ረዥም የሸራና ያላማ መስቀያ
፡ (ሕዝ፳፯ ፡ ፭)።
ኤላጤ ፡ (ጽር ኤላቲ። ዕብ ዐርሞን) የተክል ዛፍ ስም፤ ቁመቱ ረዥም ቅጠሉ ሰፋፊ፤ ፍሬው መድኀኒት የሚኾን
፡ (ሕዝ፴፩ ፡ ፰)።
ኤሌዎን ፡ (ጽር ሄሌዎን) ዘይታም መካነ ዘይት። ድብር ዘስሙ ኤሌዎን
፡ (ሉቃ፲፱ ፡ ፳፱። ፳፩ ፡ ፴፯)። ኤልያስን እይ።
ኤል ፡ (ዕብራ) ናስ፤ ግንብ፤ ዐምድ
፡ (ሕዝ፵ ፡ ፰ና ፡ ፲፮)። አምላክ ፥ ፈጣሪ፤ ኤሎሄን ተመልከት።
ኤልማስ
፡ (ጽር ሔሊሙ፤ ቴሄሙ) ኤሎሄ፤ አምላኪየ። ኦ ወልድ ክላሕ ከመ ዘሐመ ወበል ኤልማስ ላማ ሰበቅታኒ ፡ (ቅዳ ፡ አት)።
ኤልዩ ፡ (ጽር ሄሊውድ) ረዐይታዊ፤ ረዥም ወፍራም፤ ኀይለኛ ጕልበታም። ባለብሉዮች ግን የድኩም ድኩም፤ ዐጭር ኰሳሳ ይሉታል
፡ (ኩፋ ፡ ፯)።
ኤልያስ [1] ፡ ኤልያስ፤ ፡ (ጽር ሄሊያስ) ዕፀ ዘይት ፍሬ ዘይት፤ ቅብዐ ዘይት። ወገደፈቶ ታሕተ አሐቲ ኤልያስ። ወአሐቲ መስፈርተ ኤልያስ ትገብር ዐሠርተ ምክያደ ዘይት ፡ (ኩፋ፲፯። ሔኖ፲ ፡ ፲፱)።
[2] ፡ (ጽር ሔሊያስ።
ዕብ ኤሊያህ)
ነቢይ፤ ስመ
ነቢይ፤ ፍችው
ኀይለ እግዚአብሔር ፡ (፫ነገ ፡ ፲፰ ፡ ፴፮)።
ኤልዳ ፡ ስመ ሀገር፤ አዳምና ሔዋን የተፈጠሩበት ማእከለ ምድር፤ ጉባኤ ኵሉ ምእላደ ኵሉ ማለት ነው። ወኀደሩ ውስተ ምድረ ኤልዳ ምድረ ፍጥረቶሙ
፡ (ኩፋ ፡ ፫)።
ኤልግ ፡ ስመ ነገድ፤ ለብቻቸው ፊደልና ቋንቋ ያላቸው መጣፋቸውን ለሌላ ሕዝብ የማያሳዩ፤ ተደብቀው የሚጥፉና የሚማሩ፤ አምልኳቸው ከስላም ከክርስቲያን የተለየ፤ ሌላ ፩ ዐይነት ሕዝብ። እሊህም በትግሬ በሐማሴን ጫፍ በመረብ አውራጃ በባሪያ ጸሊም ውስጥ ይኖራሉ።
ኤሎሃ ፡ ሱር። ኢላህ፤ ዐረ። ኤል፤ ዕብ። በተገናኝ፤ አምላክ ማለት ነው።
ኤሎሂም ፡ (ዕብ ወሱር። ዐረ ኢላሃት) አማልክት፤ አምላኮች ዳኞች ፈራጆች፤ መላእክት። ለፈጣሪ ሲቀጠልና የፈጣሪ ስም ሲኾን፤ በቋንቋ ኹሉ አምላክ ይባላል እንጂ ፥እንደ ዘይቤው ቃል በቃል አማልክት አይባልም፤ አለመባሉም
፡ (ባራእ ኤሎሂም፤ ፈጠረ አምላክ) እያለ አንቀጹ ያንድ ብቻ ስለ ኾነ ነው፤ አምላክም የመለክ ብዢ ነውና ፥ እንደ ኤሎሂም ብዙ ወንድ ያሳያል፤ መለከን እይ። ንባርኮ ለአብ ወወልድ ወመንፈስ፤ እንዘ አሐዱ ሠለስቱ ወእንዘ ሠለስቱ አሐዱ ማለት ኤሎሂም አዶናይ ከማለት ይሰማማል። ለፍጡራን ግን ለሰዎችና ለመላእክት ለጣዖታትም ሲነገር አንቀጹን መስሎ ተከትሎ አማልክት ይባላል፤ ከአንቀጽ በቀር ሌላ መለዮ የለውም። አንሰ እቤ አማልክት አንትሙ። ግበር ለነ አማልክተ ዘየሐውሩ ቅድሜነ ፡ (መዝ ፡ ፹፩። ዘፀ፴፪
፡ ፩ ፡ ፬)። መዝገበ ፊደል ገጽ ፶፱–፷፫ ተመልከት።
ኤሎሄ ፡ (ዐረ ኢላሂ። ዕብ ኤሊ) አምላኪየ፤ ፈጣሪየ፤ ለሓኵየ
፡ (፩ነገ ፡ ፩ ፡ ፲፩። ማቴ፳፯ ፡ ፵፮። ማር፲፭ ፡ ፴፬)። ሰላም ለዓሞጽ ነባቤ ቃሉ ለኤሎሄ። ኦ ዘትቤ ኤሎሄ ኤሎሄ፤ ኢየሱስ አምላከ ርኅራኄ
፡ (ስንክ ፡ ጳግ፭። ደራሲ)።
ኤሎቄ ፡ (ጽር ኤሊክስ፤ ኢሊኪ) ዐጽቀ ወይን፤ ሐረገ ወይን። ግእዝ ግን ዕፀ ዘይት ይላል፤ የተሳሳተ ነው
፡ (ዘፍ፵፱ ፡ ፲፩)።
ኤመ ፡ አፈገ ፡ መሰገ፤–ዐዪም
፡ ዔመ።
ኤሲሳህ ፡ (ዕብ አሺሻህ) የወይን የበለስ ቋንጣ፤ የመጠጥ ዕቃ፤ ብርጭቆ ጠርሙዝ ፥ የመሰለው ኹሉ፤ በመሣሪያው ጠጁን መናገር ነው፤ ባለብሉዮችም የወይን ጠጅ የዘቢብ ጕድጓድ ይሉታል። ምስጢሩ ግን ስሱንና ስድስን ያሳያል፤ የኢን፤ ፮ኛ እጅ ፮ኛ ክፍል ወይም ከ፮ ፩ ማለት ነው። የኢንንና የኤስፋርን ፍች እይ ፡ (፩ዜና ፡ ፲፮ ፡ ፫)።
ኤስታዎስ ፡ (ጽር ኤስ ቴዎስ) አሐዱ አምላክ
፡ (ስንክ ፡ ኅዳ፲፱። ሚያ፴)።
ኤስቴኤኪራን ፡ (ጽር ኢኽሲኢራን) ዓሣት፤ ዓሦች፤ ዓሣዎች። ባለብሉዮች ግን ዓሣ ወጋሮች ይሉታል
፡ (ነሐ፲፪ ፡ ፴፱)።
ኤስኬዴሬ ፡ (ጽር ኤክሴድሬ) የዕቃ ቤት፤ ዕልፍኝ
፡ (ሕዝ፵ ፡ ፵፬)።
ኤስፋር ፡ (ዕብ ኤሽፋር) ክፍል ዕድል፤ የሥጋ መቍነን፤ አንድ ሙዳ፤ ጉማ፤ የልጃገረድ ጡት የሚያኽል። ፋር የሚዛኑ ስም፤ ልኩ ፮ ጉማ የሚያነሣ፤ ኤስፋር የፋር ፮ኛ እጅ፤ ከ፮ አንድ
፡ (፩ዜና ፡ ፲፮ ፡ ፫)።
ኤረር [1] ፡ ብሩህ ሰማይ፤ ከጠፈር በላይ ከራማ በታች ያለ። ኤረር ፥ ራማ ፥ ኢዮር ፥ እሊህ ሦስቱ ዓለመ መላእክት ይባላሉ። የዘጠኙ ነገድ ከተማ የሦስት የሦስቱ፤ በነዚህ በሦስቱ ሰማያት ተከፍሏል፤ የሰማይን ፍች ተመልከት። እሊህም ከጠፈር እስከ ጽርሐ አርያም ያሉት፤ ጕልላት ሰገነት ፥ ላይ ደርብ ፥ ታች ደርብ ፥ መካከለኛ ደርብ ፥ ምድር ቤት ፥ መሠረት እንደ ማለት ናቸው። አየራቸውም ትክክል ነው፤ የርሕቀቱና የምጥቀቱ መጠን ካንዱ እስካንዱ ሺሕ ዓመት ያስኬዳል ይባላል። ዙሪያ ቅጥራቸውም አፍኣው የሚፋጅ ፥ ውስጡ የማይፋጅ የእሳት ቅጥር ነው፤ ቀሌምንጦስ ከጠፈር በላይ ያሉትን መንበረ መንግሥትን ጨምሮ ሰብዐቱ ሰማያተ ብርሃን ይላቸዋል
፡ (ሥነ ፡ ፍጥ)።
[2] ፡ ሰማይ፤–አየር ኢዮር።
ኤረግ ፡ ቀፎ ቅርጫት፤–ሐረገ፤ ዐየረ፤
ኤራስ ፡ (ኀራስ፤ ለጋ ጨቅላ) ጨረቃ፤ የጨረቃ ስም፤ አራተኛ ስፙ። እብላን ተመልከት።
ኤር ፡ መልአክ፤–ዔር፤ ዐየረ።
ኤርትራ ፡ (ጽር ፡ ኤሪትራ) የባሕር ስም፤ ከብርቱ ሰይድ እስከ ባሕረ ህንድ፤ ወይም ከስዮስ ወደብ እስከ ባብ እልመንደብ ያለ ባሕር፤ ቀይሕ ቀይሓዊ ማለት ነው። ባሕረ ኤርትራ
፡ (ባሕረ ሕምያር) የቀይ ሕዝብ ባሕር፤ ነጮችና ጥቍሮች ያይዶሉ ቀያዮች የመንና ሳባ የሚገዙት፤ ወይም ለራሱ ቅላት ቀይነት ያለው ባሕር። መሬቱ ቀይ ስለ ኾነ ቀይ ስልባቦት ይንሳፈፍበታል፤ ቀያይ ዓሣ ይወለድበታል፤ በዙሪያውም ቀያይ ሣር ቅጠል ያበቅላልና፤ ቀይ ያሰኘው ይህ ነው። ባሕርነቱም ከሜዲተራኒ እስከ ህንድ ውቅያኖስ ገጥሞ ተያይዞ በስተምሥራቅ እስያንና አፍሪቃን ይለያል ፡ (ዘፀ፲ ፡ ፲፱። ፲፫ ፡ ፲፰። ፲፭ ፡ ፬)።
ኤርዌት ፡ (ብ ኤረው) እንስት ዝኆን
፡ (ትግሬ)።
ኤርጋብ ፡ (ጽር ሄርጋብ። ዕብ አርጋዝ) ሣጥን፤ የሣጥን ስም
፡ (፩ነገ ፡ ፮ ፡ ፰ ፡ ፲፩)። ግእዙ ተሜርጋብ አፍቃዴ አርጋብ እያለ ያልነበረ ቃል ይጨምራል፤ ጽርኡም በ፰ኛው ቍጥር ቤርሴከታን ያለውን ባ፲፩ኛው ሄርጋብ ይላል፤ ዕብራይስጡ ግን አይለውጥም። ዳግመኛም በአርጋዝ ፈንታ አሪጓዝ ይላል፤ ባለብሉዮችም ድባብ ኮርቻ ይሉታል።
፡ ታላቅ ደንጊያ፤ ቋጥኝ ገዎቻ ዋሻነት ያለው፤ መንገደኞች የሚያርፉበትና የሚያድሩበት
፡ (፩ነገ ፡ ፳
፡ ፲፱ ፡ ፵፩)። ኤርጋብ ያሰኘው ዋሻው ነው።
ኤቄስዮም ፡ (ጽር ኢኬሲዮን) ቅድም፤ ጥንት
፡ (፬ነገ ፡ ፲፱ ፡ ፳፭)። ባለብሉዮች ግን ኀያላን ይሉታል።
ኤቲ ፡ (ጽርእ) ንጥፍ ደንጊያ፤ ሰፊ ታላቅ ልሙጽ
፡ (፫ነገ ፡ ፩ ፡ ፱)።
ኤውላጦን ፡ (ጽር ሄዊላት። ዕብ ሐዊላ) ስመ ነገድ፤ የሰው ስም፤ የካም የልጅ ልጅ፤ የኵሽ ኹለተኛ ልጁ የሳባ ታናሽ። ኆጻ ኆጻዊ ማለት ነው
፡ (ዘፍ፲ ፡ ፯)። ምድረ ኤውላጦን፤ ፡ (ዕብ ፡ ኤሬጵ ፡ ሐዊላ) የሐዊላ መሬት የወርቅ አሸዋ ድቡሽት፤ ወርቅ እንዳሸዋ የሚታፈሥበት ካባይ በመለስ ያለ ቈላ፤ ዳንግላ ምድረ ሻንቅላ፤ ወዲያ ማዶም ባባይና ባባይ መካከል ከላይ እስከ ታች እስከ ከርቱም ያለው ሸናጣ ሾጣጣ ዠላላ ሞላላ ፥ ሾገሌ የሱዳን ቀበሌ ሳይቀር
፡ (ዘፍ፪ ፡ ፲፩ ፡ ፲፪)። ሙሴ ፵ ዘመን በሱዳን አገር ስለ ኖረ የሐዊላን ብዕል ወርቋን ወርቃማነቷን የወርቋን ጥራትና ብዛት ባየው ባወቀው ተናግሯል ፡ (ዮሴፍ)። ባገራችንም አፈ ታሪክ፤ ሙሴ በትግሬ እስካኵስም እስከ ሽሚዛና፤ በጐንደርም እስከ ደንቢያና እስከ ጣና መጥቶ ነበረ ይባላል። ርሱም ራሱ ሱዳናዊት ሴት እንዳገባ በኦሪቱ ያመለክታል ፡ (ዘኍ፲፪ ፡ ፩)። ጊዮርጊስ ጽሩይ ወርቀ ኤውላጦን ፡ (ደራሲ)።
ኤዶማዊ ፡ የዔሳው ዘር የኤዶምያስ ሰው። ዔዴንን እይ።
ኤዶም ኤዶምያስ ፡ የዔሳው ስምና ሀገር፤ ቀይሕ ማለት ነው
፡ (ዘፍ፳፭ ፡ ፴። ኢሳ፷፫ ፡ ፩። መዝ፶፱)።
ኤጎንጤ ፡ (ጽር ጎኒኤ) ውስጥ፤ ውሳጢት
፡ (ሕዝ፵፩ ፡ ፲፭)።
ኤጲስቆጶስ ፡ (ሳት። ጽር
ሄፒስኮፖስ) ፤
ጠባቂ ፤ መምህር ፤
የጳጳስ ኹለተኛ ፤
የሊቀ ጳጳስ
ሦስተኛ። በእንተ
ኤጲስቆጶሳት። ወይሢም ኤጲስቆጶስ ባሕቲቱ ፤
እስመ ሣልሳይ
ማዕርጊሁ (ፍ
፡ ነ
፡ ፭።
፮)።
ሲኖዶስ ትእዛዘ
ጴጥሮስ ፤ ሊቃናት
ሠለስቱ ጾታ ፤ ወሠለስቲሆሙ አሐቲ
ፍና ይላቸዋልና ፤
እሊህ ሦስቱ
በመሾም በመሻር
አንድ ስለ
ኾኑ ፤ ኹሉም
በኤጲስቆጶስ ስም
ይጠራሉ። ኤጲስቆጶስ
ኵሉ ፍጥረት
ወልደ እግዚ
ዐቢይ ሊቀ
ካህናት። አትናቴዎስ
ዘኮነ ቅድመ
ኤጲስቆጶሰ ላዕለ
ሀገረ እስክንድርያ።
በከመ ይቤ
ፊልክስ ኤጲስቆጶስ
ዘሮሜ። (ፍ
፡ ነ
፡ ፱።
ቄር። ሃይ
፡ አበ)። ጳጳስን
ተመልከት።
ኤጲስቆጶስና ፡ ኤጴስቆጶስነት፤ ኤጲስቆጶስ መኾን፤ የኤጲስቆጶስ ሹመት ማዕርግ። እምድኅረ ኤጲስቆጶስናሁ
፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፵፪ ፡ ፲፩። ፭። ፊልክ ፡ ፲፭)።
ኤጲፋንያ ፡ (ጽር ሄፒፋኒያ) አስተርእዮ፤ መታየት መገለጽ፤ ዕለተ ጥምቀት። በዓለ ኤጲፋንያ በዘቦቱ አርአየ እግዚ ስብሐተ መለኮቱ በውስተ ጥምቀት በቅድመ ዮሐንስ በፈለገ ዮርዳኖስ። ኤጲፋንያ ሣልሲት ዘተጠምቁ ባቲ ዘኢተጠምቁ ትካት
፡ (ዲድ ፡ ፳፱። ስንክ ፡ ጥር፲፩
፡ ፲፫)።
ኤጲፋንዮስ ፡ (ጽር ሄፒፋኒዉስ) ዝኒ ከማሁ፤ የሰው ስም። ይኸውም ብዙ ድርሳናት የጣፈ የቆጵሮስ ኤጲስቆጶስ ነው፤ እንደ ጳውሎስ ምሁረ ኦሪት አይሁዳዊ ነበር፤ ጌታ በታምራት ማርኮ መምህረ ወንጌል አድርጎታል
፡ (ስንክ ፡ ግን፲፯። ሃይ ፡ አበ። ቅዳ)።
ኤጳውሎስ ፡ (ጽር ሄፓፍሌዎስ። ዕብ ፊሀሒሮት) ስመ ሀገር፤ እስራኤል ለፈርዖን የሠሩለት፤ ይኸውም ፊቶም ነው፤ መንቶቹ ረዣዥሞች ኹለት ጣዖታት የቆሙበት
፡ (ዘፀ፲፬ ፡ ፪። ፩ ፡ ፲፩)።
ኤጴሜዳስ ፡ (ጽር ኤፖሜዴስ) መትከፈ አንቀጽ፤ ደጃፉን ገብቶ ግራና ቀኝ ያለው የመዝጊያው ኋላ። ባለቅኔዎች ግን እብነ በረድ ይሉታል
፡ (ሕዝ፵ ፡ ፵፰። ፵፩ ፡ ፪)።
ኤጴሞስ ፡ (ጽር ኤፖሜዴስ) ዝኒ ከማሁ፤ መትከፍ፤ ልብሰ መትከፍ። ባለብሉዮች ግን ቀሚስ ዘይበጽሕ እስከ እግር እምርእስ ይሉታል
፡ (ዘፀ፳፰ ፡ ፯)።
ኤፉድ ፡ (ጽር ሄፉድ። ዕብ ኤፉድ) ልብሰ ተክህኖ ካህናተ ኦሪት በተልእኮ ጊዜ የሚለብሱት የሚታጠቁት፤ ቀሚስ። ልብሰ እንግድዓ ሴደርያ
፡ (፩ነገ ፡ ፪ ፡ ፲፰ ፡ ፳፰። ፲፬ ፡ ፫። ፴ ፡ ፯። ዘፀ፳፰ ፡ ፬)። ኤፉደ ጸሎት ወዕጣን ፡ (ጥበ፲፰ ፡ ፳፩)።
፡ ፊዶ፤ ማጠቆ፤ ዐጭር ሱሪ፤ ቍምጣ፤ ቈራጣ፤ የሥራ ልብስ፤ ማናቸውም።
ኤፌሶን [1] ፡ (ጽር ሄፍሶስ) ስመ ሀገር፤ በታናሽ እስያ ውስጥ ያለች፤ ጳውሎስ ዮሐንስ ያስተማሩባት፤ ሦስተኛው ጉባኤ የቆመባት፤ ንስጥሮስ እነታዎድሪጦስ የተወገዙባት።
፡ (፩ቆሮ ፡ ፲፭ ፡ ፴፪። ፩ጢሞ ፡ ፩ ፡ ፫። ኤፌ ፡ ፩
፡ ፩። ራእ፩ ፡ ፲፩። ፪ ፡ ፩)።
[2] ፡ (ጽር ፊሶን፤ ዕብ ፊሾን) ስመ ፈለግ፤ ካራቱ አፍላጋት አንደኛው መዠመሪያው ወንዝ፤ ጐዣምን የሚከብ ጥቍር አባይ፤ ጥቍር መባሉም የውሃው መልክ ዐይነቱና ኅበሩ ጥቍር ኒል ስለ መሰለ ነው ፡ (ዘፍ፪ ፡ ፲፩)። ኤ የመላሽ ተውሳክ ነው፤ የሱስን ኢየሱስ እንዳለው፤ ፊሶንንም ኤፌሶን ብሎታል። ዕብራውያን ተልባ የተልባ እግር ሲሉ ፊሽታን ይላሉና ፊሾን ማለት ከዚህ ወጥቷል፤ ርሱ የሚያጠጣት ምድረ ግብጽ ብዙ ተልባ የሚዘራባት፤ ከዚህ የተነሣ ብዙ ፈትልና ልብስ የምታስገኝ ፡ (የክታን) የፊሽታን አገር ስለ ኾነች፤ በሚያበቅለውና በሚያፋፋው ንጣትና ጥራት በሚሰጠው በፊሽታኑ ፊሾን ተብሏል። ይኸውም ፈለገ ግብጽ ሀገሪተ ፊሽታን ማለት ነው፤ ምንም ወንዝነቱ የኵሽ ቢኾን ሥራ የሚሠራ በሚጽራይም ክፍል ነውና፤ ስለዚህ የግብጽ ወንዝ ይባላል ፡ (ኢሳ፲፱ ፡ ፱። ሕዝ፳፯ ፡ ፯። ፳፱ ፡ ፫ ፡ ፬)። ባለመጽሐፎች ግን ፈለገ ኒል በማለት ፈንታ ፈለገ ሐሊብ ይሉታል። ወእንዘ ስሙ ኤፌሶን ፈለገ ጸዐዳ ሐሊብ ፡ (ቅኔ። ድጓ)።
ኤፍራጥስ ፡ (ጽር ሄፍራቲስ። ዕብ ፍራት) ስመ ፈለግ ዐቢይ፤ ራብዓይ ወንዝ
፡ (ዘፍ፪ ፡ ፲፬)። ምንጩ ከአርማንያ ተነሥቶ በአሶር ምድር ላይ ወደ ባቢሎን የሚጐርፍ። ካራቱ ዐበይት አፍላጋት ኹለቱ በአፍሪቃ ክፍል ኹለቱ በእስያ ክፍል ስለ ኾኑ ፥ ግዮን ከርቱም ሲደርስ ከኤፌሶን ገጥሞ አንድ ወንዝ ኹኖ ሜዲተራኒ እንዲገባ፤ ኤፍራጥስም ባቢሎን ሲደርስ ከጤግሮስ ጋር ይገጥምና አንድ ወንዝ ኹኖ ወደ ባሕረ ፋርስ ይገባል። ፍራት ፈረየ ከማለት ወጥቷል፤ ዘይቤው ፍሩይ መፍርይ ፥ ፍሬያማ ማለት ነው፤ ርሱ የሚያጠጣት ምድር ኹሉ ከላይ እስከ ታች ባለብዙ ፍሬ መኾኗን፤ የፍሬዋንና የመንጋዋን መብዛት መፈድፈድ፤ መርባት መዋለድ ያሳያል።
ኤፎት ፡ (ዕብ ንጢፎት) ያንገት ጌጥ፤ እንደ ድሪና እንደ ማርዳ ያለ፤ ጥሩ የወርቅ መሣሪያ። ባዝግና ዘኤፎት
፡ (መሳ፰ ፡ ፳፮)።
እ ፡ እልፍ ፥ ፲ ሺሕ፤ መቶ ጊዜ መቶ።
እኁዝ ፡ (ዛን ዛት ኅዝት) የያዘ ፥ የጨበጠ ፥ የተያዘ ፥ የታሰረ ፥ የተያያዘ። ኵሎሙ እኁዛነ አስይፍት። ሱራፊ እኁዘ ሰይፍ። ሊቃናት እኁዛነ መዓጥን፤ የያዘ
፡ (ማሕ፫ ፡ ፰። አርጋ ፡ ፭ና ፡ ፫)። እስመ ዓለም ወኵሉ ዘውስቴቱ እኁዝ ውስተ እዴሁ ለእግዚ። ቤተ ሞቅሕ ኀበ ሀሎ ዮሴፍ እኁዝ ህየ። እኁዛነ አጋንንት፤ የተያዘ ፡ (ዲድ ፡ ፳፭። ቅዳ። ኩፋ ፡ ፴፱። ማር፫ ፡ ፲፩)። እኁዝ ክነፊሆሙ ለለ አሐዱ። ከመ ይኩኑ እኁዛነ። እኁዛን በበይናቲሆሙ፤ የተያያዘ ፡ (ሕዝ፩ ፡ ፰። ፵፩ ፡ ፮። አዋል)።
እሑድ ፡ (ዳን ዳት ሕድ) አንድ የኾነ ፥ አንድ አንደኛ፤ መዠመሪያ፤ የዕለት ስም። በዕለተ እሑድ። በበ እሑድ። ለጸቢሐ እሑድ። ወበእሑድ ሰንበት። ናክብር እሑደ ሰንበተ። በለያልየ እሑዳት
፡ (ግብ ፳ ፡ ፯። ፩ ቆሮ ፲፯ ፡ ፪። ማቴ ፳፰ ፡ ፩። ማር ፲፯ ፡ ፪። ዲድ ፴፰። ፊልክ ፹፫)።
እኂል እኄላ ፡ (ዕብ ዒጉል ድቤላ፤ ስክ በለስ። ዐረ ሐለዋት፤ ጥፍጥ) ጥዑም ምቱቅ፤ የበለስ ቋንጣ እንደ ድባና እንደ ማርዳ እንደ መቍጠሪያ ፶ ፶ው ፻ ፻ው በረዣዥም ክር የሚሰካ። የሰሌን ፍሬ እንደ ሠምና እንደ ዳቦ የሚረጋ የሚረጋጋ ፥ ሲበሉት የሚጥም የሚጣፍጥ ማር ማር የሚል። ክልኤተ ምእተ እኄላ በለስ። ወወሀብዎ ስባረ እኄላ ተመርት
፡ (፩ነገ ፡ ፳፭ ፡ ፲፰። ፴ ፡ ፲፪)። ደበለን ተመልከት።
እኂር ሮት ፡ (አኀረ ይእኅር ይእኀር፤ ዐረ። ዕብ ኤሓር። ሱር አውሓር) ወደ ኋላ ማለት፤ መቈየት መዘግየት ፥ መትመክመክ
፡ (ጥለ) መለወጥ ሌላ መኾን። ደኀረን ተመልከት፤ የዚህ ጎር ነው።
እኂው ዎት ፡ (አኀወ ይእኁ ይእኀው) መወንደም ፥ ወንድም ማድረግ ፥ መሳብ ማቅረብ ፥ ወንድሜ ወንድሜ ማለት
፡ (ዮሐ፳ ፡ ፲፯። ማቴ፳፭ ፡ ፵)።
እኂዝ [1] ፡ መማረክ፤ መውሰድ፤ ማሰር መቈራኘት፤ የጠላት የደዌ የጋኔን። አኀዝዎ ለአጋግ ሕያዎ። አልቦ ዘአኀዝነ። አኀዞ ለኢዮብ ዝልጋሴ። ዘአኀዞ ጋኔን ፡ (፩ነገ ፡ ፲፭ ፡ ፰። ሉቃ፭ ፡ ፭። ኢዮ፪ ፡ ፯። ቀሌ)።
[2] ፡ መግታት፤ ማቆም መገድ፤ ማገር መገርገር፤ መጋበዝ ቈይ ዋል ዕደር ሰንብት ማለት። ኢይእኅዙ ልሳኖሙ። አኀዝ እግዚኦ መዋግደ ጸጋከ። ኢተአኀዙኒ፤ ፈንዉኒ እሑር። ትክልኑ ተአኀዛ ለትርያ ከመ ኢትሑር
፡ (ምሳ፳፯ ፡ ፳። አዋል። ዘፍ፳፬ ፡ ፶፮። ኢዮ፴፰ ፡ ፴፩)።
[3] ፡ መግዛት መውረስ፤ ገዥ ወራሽ መኾን። እለ ይእኅዝዋ ለምድር። ባቲ መኳንንት ይእኅዙ ምድረ። መኑ አኀዘ ኵሎ አጽናፈ ምድር። እግዚአብሔር ዘኵሎ ይእኅዝ
፡ (ሔኖ፴፰ ፡ ፬። ምሳ፰ ፡ ፲፮። ፳፬ ፡ ፳፯። ቅዳ)።
[4] መደገፍ መጠበቅ እንዳይወድቅ። መዠመር መወጠን፤ መሰብሰብ መቍጠር፤ የቍጥር ምልክት መጣፍ ፥ ማኖር። አኀዚዮ ለሕፃን በእደውኪ። አኀዝኩከ በእዴየ። ዘይእኅዝ ኵሎ ፍጥረተ፤ ጠበቀ
፡ (ኩፋ ፡ ፲፯። ኢሳ፵፪ ፡ ፮። ጥበ፩ ፡ ፯)። በዝንቱ ዓመት አኀዘ ዐባር ውስተ ምድር። አኀዙ ጸብአ። አኀዘ ይስብክ ወይምሀር። አዘኀ ይሕንጽ ወስእነ ፈጽሞ፤ ዠመረ ፡ (ኩፋ ፡ ፳፬። ዮሴፍ። ማቴ፬ ፡ ፲፯። ሉቃ፲፬ ፡ ፴)። አኀዘ ኵሉ ተዓይኒሆሙ ለደቂቀ እስራኤል፤ ቈጠረ ፡ (ዘኍ፳፮ ፡ ፪)።
[5] መጽናት መበርታት መጠንከር፤ ሥር መስደድ ካፈር ከመሬት መዋሐድ ፥ የማይነቀል መኾን፤ የዛፍ የደንጊያ። ለሰው ሲኾን ግን ምስጢሩ መግዛትና መውረስ ካለው ይገባል። ዘእንበለ የአኀዝ ሥርወ ወኀይለ። አኀዘ ሥርወ
፡ (ኩፋ ፡ ፴፯። ሄርማ)።
[6] ፡ (ጥሬ ዘር) አያያዝ አገዛዝ፤ ኀይል ዕዘዝ፤ ግዛት ሥልጣን፤ የጌትነት ሥራ። ስብሐት ወእኂዝ፤ እስመ ለከ እኂዝ
፡ (ቅዳ)።
እኂዝ ዞት ፡ (አኀዘ፤ ይእኅዝ የአኀዝ። ዕብ አሐዝ። ሱር ኤሐዝ። ዐረ አኀዘ) መያዝ መጨበጥ፤ እጅ ማድረግ፤ መቀበል፤ ያረቦን የመያዣ የዋስ የመድን። አኀዝዎ ለአኃዜ ኵሉ። አኀዞ ለውእቱ ዓሣ። በእኂዘ ሥጋሁ ወደሙ ለክርስቶስ
፡ (ቅዳ። ጦቢ፮ ፡ ፬። ቀሌ)።
እሒድ ዶት ፡ (አሐደ ይእሕድ የአሐድ። ዕብ አሔድ) አንድ ማድረግ፤ ማዋደድ ማስማማት፤ አንዱን ካንዱ ጋራ ማዛመድ ማዋሐድ፤ ምንታዌን ማጥፋት። ወይም አንድ መኾን፤ በተዋሕዶ አንድ መባል፤ ዋሐደን ተመልከት።
እኅት [1] ፡ (ዕብ አሖት። ሱር አሓታ። ዐረ ኡኅት) በቁሙ፤ እት የናት ያባት ልጅ፤ እንደ ወንድም ያለች፤ የናት አምሳያ፤ የቅርብ ዘመድ፤ ወዳጅ እኩያ ሚስት፤ ዐብሮ አደግ። መነኵሲት። ወቦ እኅት ሠናይት ለአቤሴሎም። እሙ ወእኅታ ለእሙ። ሰሎሜ እኅታ ለማርያም። እኅትየ መርዓት። ኢትትኃለፊ እኅትየ። ተንሥኢ እኅትየ ንጸሊ። እኍየ ወእኅትየ። ፌቤን እኅትነ
፡ (፪ነገ ፡ ፲፫ ፡ ፩። ዮሐ፲፱ ፡ ፳፭። ስንክ ፡ ግን፳፭። ማሕ፬
፡ ፱። ጦቢ፭ ፡ ፳፩። ፰ ፡ ፳፬። ማቴ፲፪ ፡ ፶። ሮሜ፲፮ ፡ ፩)።
[2] ፡ እኅት፤–በቁሙ፤–እኅው።
እኅዋ እኋ ፡ (እኅወ እኈ) ወንድምን። ገደፉ እኅዋሆሙ ከመ በድን። እኍኒ ኢያድኅን እኋሁ። ወአምጽኡ እኋክሙኒ ዘይንእስ ኀቤየ። ኵሉ ዘያምዕዕ እኅዋሁ
፡ (መዝ ፡ ፴፯ና ፡ ፵፰። ዘፍ፵፪
፡ ፳። ማቴ፭
፡ ፳፪)።
እኅው እኁ እኍ ፡ (ዕብ አሕ። ሱር አሓእ። ዐረ አኅ) ወንድም ፥ ወልደ እም ፥ የናት ያባት ልጅ ባባትና በናት የሚገጥም፤ በተዘሩበት ተዘርቶ በበቀሉበት የበቀለ፤ ወይም ያባት ልጅ ብቻ ፥ የናት ልጅ ብቻ፤ እኩል ወንድም። የቅርብ ዘመድ፤ ወገን ነገድ፤ ባልንጀራ ወዳጅ ፥ ዐብሮ አደግ ያገር ልጅ። መናኒ ረድእ፤ ባሕታዊ መነኵሴ። ወሶበ ተስእሎ እኍ ለአባ ይስሪን
፡ (ፊልክ ፡ ፩)። እኅወ
፡ (እኈ) አቡሁ። እኁሁ ለእግዚእነ። እኁሃ ለርብቃ። እኁከ፤ ኪ፤ የ። እኍሆሙ፤ ሆን፤ እኍክሙ፤ ክን፤ እኍነ እኁነ እያለ በሳድስ በካዕብ ይኼዳል፤ ይህም አሐድ አሐዱ ክልኤት ክልኤቱ እንደ ማለት ነው። ካዕቡ ገቢር ይከታል። ይቀትል ብእሲ እኁሁ
፡ (ኢሳ፲፱ ፡ ፪)።
እኅውና ፡ (እኅትና) ወንድምነት፤ ከዊነ እኍ፤ ዝምድና፤ ዕሪና፤ ሱታፌነት።
እኅዘት [1] ፡ መያዝ፤ ፡ (ጥያ) መያዝ፤ አያያዝ፤ ይዞታ፤ ያዥነት ጌትነት አገዛዝ። እኅዘትከ በመጣብሕ ወበአብትር። በእኅዘት ወሥልጣን
፡ (አዋል። አፈ ፡ ድ፪)።
[2] ፡ እኅዘት፤
፡ (ዕብ አሑዛት) ርስት ጕልት ግዛት፤ ይዞታ፤ እጅ ዐደር ቦታ። ወእኅዘቶሙ ይእቲ በመክፈልት ፡ (ሕዝ፵፮ ፡ ፲፮)።
እሕድ ፡ የጊዜ ቅጽል። እሕደ፤ አንድ ጊዜ። ባላገር ግን አንደዜ ፥ አንደዬ ይላል።
እለ ፡ (ዘ)
ቅጽልና በቂ አብዢ፤ የ እነ። ወቦ እለ ወረዱ። ወእምዝ ኀለፉ እለ ጳውሎስ እምነ ጳፉ ፡ (ግብ፲፭ ፡ ፩። ፲፫ ፡ ፲፫)። እለ የዘ ብዢ ነው፤ ቅጽልነቱ ለብዙ ብቻ እንጂ እንደ ዘ ላንድም ለብዙም አይኾንም፤ አብዢ ሲኾን ባንድ አካል ላይ ብቻ ይወድቃል። ሲዘረዘርም አን በር ከፋች አድርጎ እሊኣየ ከ ኪ ሁ ሃ፤ እሊኣነ ክሙ ክን ሆሙ ሆን እያለ ባሥሩ ሰራዊት ይረባል። ፡ (ዕር፲፱ ፡ ቍ፹)።
እለሌ ፡ አለሌ፤ የፈረስ ያህያ። ምልአተ ከርሥ ዘእንበለ ዐቅም ከመ እለሌ ፈረስ ወከመ ሐራውያ ገዳም
፡ (መቃ ፡ ገ፳፬)። ከአላ እስከ አሌ እልኩም ሳይቀር የአለለ ዘር ነው።
እለቄጥሩ ፡ (ጽር ኤሌክትሮን) ዘይበርቅ ዘያንጸባርቅ፤ የብርሃኑ ጽርየትና ብዛት ዐይን የሚያፈዝ የሚበዘብዝ፤ ኤሌትሪክ እንደ ማለት ነው። ባለቅኔዎች ግን ዖፍ ዘራብዕ ርእሱ ይሉታል፤ የተሳሳተ ነው። ከመ ርእየተ እለቄጥሩ
፡ (ሕዝ፩ ፡ ፬ ፡ ፳፯። ፰ ፡ ፪። ድጓ)።
እሉ እሎንቱ ፡ (ዝ ንቱ። ዕብ ኤሌህ) የብዙ ወንዶች ቅጽልና ዐጸፋ፤ እሊህ እኒህ፤ እነዚህ፤ እሊሆች፤ እሊኸኞች። ባለቤት ሲኖር ጭብጥ ቅጽል፤ ሲቀር ዐጸፋና በቂ ይኾናል። እሉ ሰብእ። አሐዱ እምእሉ። ሠራዔ ሕገጋት እሎንቱ። ይኅፅቦሙ ለእሎንቱ። ወእሎንቱ ተፈወሱ ምዕረ
፡ (ሕዝ፲፩ ፡ ፪። ቅኔያት)። እሉና እሎንቱ በገቢር ጊዜ አንድ ናቸው። ወሰሚዕየ እሎንተ ቃላተ።
እሉድ ፡ (ዳን ዳት ልድ) የተሰበሰበ፤ የተጐቸ የተከማቸ፤ ክምር ቍልል። ዕፀው እሉዳን
፡ (ገድ ፡ ተክ)።
እሉፍ ፡ (ፋን ፋት እልፍት) የበዛ የረባ፤ እልፍ የኾነ የተባለ።
እላ እላንቱ እሎን ፡ (ዛ ዛቲ) ዝኒ ከማሁ፤ የብዙ ሴቶች ቅጽልና ዐጸፋ፤ ወንዶቹም ሴቶቹም ቅርቦች ናቸው። ተዘመርነ እላ ክልኤ ቃላተ። በእላ ክልኤ ትእዛዛት። እላንቱ አእባን ይኬልሓ። እስመ እሎን ሠላስ ይትሜሰላ ፡ (ቄር። ማቴ፳፪ ፡ ፵። ሉቃ፲፱ ፡ ፵። ፊልክ ፡ ፺፱)።
እላንቱ ፡ እሊህ ሴ፤–እላ።
እላዴ ፡ መሰብሰብ፤ አሰባሰብ፤ ስብሰባ፤ ቍለላ ክመራ። እላዴ ብርዕ
፡ (አዋል)።
እል ፡ (ዐረብ) የስም ተውሳክ፤ ከስም ጋራ የሚጨመር ቃል። እልሐመል፤ እልሑት። እልቆሞሳት
፡ (አቡሻ ፡ ፬። ገድ ፡ ተክ)።
እልሐመል ፡ ኮከብ፤–ሐሚል
፡ ሐመለ።
እልሐዝል ፡ የጨዎታ ስም፤–ኀዝል።
እልሑት ፡ ኮከብ፤–ሑት ሐውት።
እልመስጦ ፡ እምነት ሃይማኖት፤–መስጦ።
እልመቃምር ፡ ቅልሞሽ፤–ቀምሮ ቀመረ።
እልመክኑን ፡ ኅቡእ፤–ከነ፤ ከነነ መክኑን።
እልሚዛን ፡ በቁሙ ኮከብ፤–መዝኖ መዘነ ሚዛን።
እልቀታ ፡ የዱባ ወገን፤–ቀታ።
እልቅርጥብ ፡ ነካሽ ጋጭ፤–ቅርጥብ።
እልባልተሪቦን ፡ (ጽር ፓቴር ኢሞን) እል የዐረብ ተውሳክ፤ ፓቴር አብ፤ ኢሞን ነ፤ በተገናኝ አቡነ ማለት ነው። ወጸለየ በቅድሜሆሙ እልባልተሪቦነ፤ ዘውእቱ አቡነ ዘበሰማያት
፡ (ስንክ ፡ መጋ፳፯)።
እልታሕ [1] ፡ ሥረ ወጥ፤–ለቲሕ ለትሐ።
[2] ፡ (ሓት። ዕብ ሜልታሓ) የልብስ ሣጥን፤ ወይም የክት ልብስ ፥ የጋን ሸማ ፥ በሣጥን በጋን የሚከተት። ሥረ ወጥ ልብስ ፥ ያልተሰፋ ትት ጥልፍ፤ መርፌና መቀስ፤ ያልዞረበት የሴቶች ሥራ። አልታሐ መንፈስ ተዐጽፈ። ወክዳኑሂ እልታሕ ፡ (ስንክ ፡ ጥቅ፲፬። ዮሐ፲፱ ፡ ፳፫)።
እልኩ ኵ እልክቱ ፡ (ዝኩ ዝስኩ፤ ዝኵ ዝስኵ) ቅጽልና ዐጸፋ፤ ለቅርብ ሩቆች ወንዶችና ሴቶች። እሊያ፤ እሊያኞች፤ እሊያኞቹ። እልኩ አብዳት። እልክቱ ደናግል። እልክቱ ይከድኑ ገጾሙ ፡ (ማቴ፳፭ ፡ ፰ ፡ ፲፩)። ዝኩን ተመልከት።
እልፍ [1] ፡ (ዕብ ኤሌፍ። ሱር አሌፍ። ዐረ አልፍ፤ ሺሕ) ዐሥር ሺሕ፤ ወይም መቶ ጊዜ መቶ
፡ (ቀቀ–፻፻። እ–፻፻። ዕብራይስጥና ሱርስት ግን ሺሑን እልፍ ብለው እልፉን ሪቦ ይላሉ፤ ዐረብና ትግሬም እንዲሁ ናቸው። ይኸውም ሊታወቅ አራተኛ ነገሥት ፡ (፲፱ ፡ ፴፭) ወቀተለ እምተዓይኒሆሙ ለአሶር ዐሠርተ ወሰመንተ እልፈ ወኀምሳ ምእተ ያለውን፤ ከዐረብ ቋንቋ የተቀዳው መጽሐፈ ቄርሎስ በመዠመሪያው ክፍል፤ ምእተ ወሰማንያ ወኀምስተ እልፈ ይላል። ፊልክስዩስም ፡ (ተስ፴፮ ፡ መተ) ወታሕተ ሥልጣኑ እልፍ ባሕታውያን ወክልኤቱ እልፍ መነኮሳይያት ይላል። ጥንታዊውም ያሮጌው ግእዝ እልፍ እንደዚህ ነበረ ይባላል፤ የሺሕን አፈታት ተመልከት።
[2] ፡ ብዙ፤ እጅግ ዐያሌ። እስከ እልፍ ትውልድ። አሐዱ እምእልፍ። እልፍ መዛግብተ ወርቅ ዐበይት
፡ (ዘዳ፭ ፡ ፲። ሢራ፮ ፡ ፮። ፵፩ ፡ ፲፪። የስንዴና የገብስ ዛላም ከፍሬው ብዛት የተነሣ አንዳንዱ ራስ እልፍ ይባላል። ፡ (ተረት) የስንዴው ዛላ ዕፍኝ ይመላ።
እሎን ፡ እሊህ ሴ፤–እላ።
እሎንቱ ፡ እሊህ ወ፤–እሉ።
እመ
፤ (እም።
ዕብ ኢም።
ሱር ኤ።
ዐረ ኢን)
ዐቢይ አገባብ።
ቢ ባ
ብ ከ
ካ ፤
እንደ እንደኾን
፤ ምንም
፤ ምን
አልባት። እመ
ቦ
ዘይቤ። ለእመ
ኵሎ ዓለመ
ረብሐ። እመ
አኮ። እመ
ፈተውከ። እመሰ
ነቢያት እሙንቱ።
እመ እግዚ
ኢሐነጸ ቤተ።
እመ አንተሁ
ክርስቶስ ንግረነ።
እመኒ ኵሎሙ
ዐለዉከ። እመ
ትፈሪ ለዓሙ።
የእመ አፈታት
ስልቱ ስለ
በዛ በያወራረዱ
ማቅኛ ትርፍ
ዐማርኛ ይሻልና
ምንም ፥ ምን አልባት ማለት
ስለዚህ ነው።
የቀረውን በዐቢይ
አገባብ ተመልከት
(ዕር፲፱ ፡ ቍ፸፮)።
እመ ሕያው ፡ ሔዋን፤ የሰው ኹሉ እናት
፡ (ዘፍ፫ ፡ ፳)። ዕጓለ መሕያውን እይ።
እመ ምኔት ፡ የገዳም እናት፤ የመነኮሳይያት አለቃ
፡ (ስንክ ፡ መስ፲፯ ፡ ኅዳ፲)።
እመ ቤት ፡ በቁሙ፤ ባልተ ቤት፤ የቤት ንግሥት የቤተ ሰብ እናት፤ መሪ አሳዳሪ፤ ራስና ራስነት ያላት። ርእሳ ለብእሲት ምታ
፡ (፪ቆሮ ፡ ፲፩ ፡ ፫)።
እመ አህጉር ፡ መዲና፤ ታላቅ ከተማ
፡ (መጽ ፡ ምስ)።
እመ ኵሉ ፡ መቃብር፤ የኹሉ ከታች
፡ (ሢራ፵ ፡ ፩)።
እመም ፡ (ዐረ አማም፤ ቅድም) በቁሙ፤ ፈፋ አፍታ፤ ወረራ፤ ፊት ለፊት አቅንቶ የሚሠራ።
እመት ፡ (ታት። ዕብ
፡ ወሱ፤ አማ። ቅብጥ ማቲ) ክንድ ከክርን እስከ ታላቅ ጣት ፡ ጫፍ ያለው ኹለቱ ክፍል። ዕፅ ዘኀምሳ በእመት። እመተ ሰብእ ወእመተ መልአክ። እደዊሃ ትሰፍሕ ዲበ ዘይበቍዕ፤ ወእመታ ታጸንዕ ለፈቲል። ሰላም ለእመታቲከ እለ ጸንዓ ይፍትላ ፡ (አስቴ፭ ፡ ፲፬። ራእ፳፩ ፡ ፲፯። ምሳ፳፱ ፡ ፴፯። ደራሲ)።
እሙኅ ፡ (ኃን ኃት እምኅት) እጅ የተነሣ፤ የተሳመ፤ ሰላም የተባለ።
እሙር [1] ፡ (ራን ራት ምርት) የተመለከተ፤ ምልክታም፤ ባለምልክት፤ ባለታምራት።
[2] ፡ (ራን ራት ምርት) የታወቀ፤ ዕውቅ፤ ግልጥ። እሙረ ይከውን ለክሙ። መቃብረ ጴጥሮስ ወጳውሎስ ወዮሐንስ ወቶማስ እሙራን ወክሡታን። በበዓላት እሙራት። በእምርት ዕለት በዓልነ ፡ (ሔኖ፺፯ ፡ ፪። አፈ ፡ ድ፳፮። ፈ ፡ መ ፡ ፲ ፡ ፲፫። ድጓ)። አምሮና አሚር በውስጠ ዘ ቱሱሓን ናቸው፤ ኹሉም ይጠብቃሉ፤ ይኸውም በመምህራን ልማድ ነው እንጂ ፥ በሰዋስው መንገድ አይዶለም።
እሙት ፡ የተገመተ፤ የተከነዳ።
እሙነ ፡ በውነት፤ በሚገባ። አማን ተወልደ እግዚእነ ኢየሱስ፤ እሙነ ልህቀ ፥ ወእሙነ በልዐ ፥ ወእሙነ ሐመ
፡ (ሃይ ፡ አበ)። የሐውር እሙነ፤ ታምኖ፤ ዐርፎ ተዘልሎ ፥ ምን አለብኝ ብሎ፤ ሳይሠጋ ሳይፈር፤ ሳይጠራጠር ፡ (ምሳ፲ ፡ ፱)።
እሙን ፡ (ናት ናት እምንት) በቁሙ፤ የታመነ የተረዳ፤ ርግጥ እውነት፤ የተገባ። ስምዑ ለእግዚ እሙን። እሙነ ኮነ ምክረ ትካት። እሙን ቃል ዘሰማዕኩ። እሙን ሕልሙ
፡ (መዝ ፡ ፲፰። ኢሳ፳፭ ፡ ፩። ፪ዜና ፡ ፱
፡ ፭። ዳን፪ ፡ ፵፭)።
እሙንቱ ፡ (ዐረ ሁም። ዕብ ሄማህ) የውእቱ ርባ፤ ውእቶሙና እሙንቱ አንድ ወገን ናቸው። እሊያ፤ ርሳቸው፤ እሊያኞች፤ ወይም ናቸው ነነ ያሰኛል፤ ቅጽልና በቂ ዐጸፋና አንቀጽ ይኾናል፤ የውእቱን ፍች ተመልከት። እሙንቱሰ ኢያእመሩ፤ እሊያ። እሉ ደናግል እለ መኑ እሙንቱ፤ ናቸው። ንሕነ እሙንቱ፤ ነን ነነ
፡ (ሄርማ። ቅዳ)።
እማኄ ፡ (ኅያት) እጅ መንሣት፤ እጅ አነሣሥ፤ ሰላምታ አሰጣጥ፤ አድንኖ፤ ሰላምታ ከበሬታ። ለዝክረ ስምኪ አቅረብኩ እማኄ
፡ (ደራሲ)።
እማሬ ፡ (ርያት) ማመልከት፤ መመልከት አመለካከት፤ ምልከታ፤ ምልክት። ኢያስተርእዩ ለንጻሬ ወኢይትሌበዉ ለእማሬ። ዕንባቆም ነቢይ ወልደ ዳኮር ነገደ ኅሬ፤ ሥራዌ ዘሕዝበ አይሁድ እንዘ ይኤምር እማሬ። ይጽሐፍ ውስቴታ እማሬ ዕለታት። አላ እማሬ ባሕቲቱ ወምሳሌ ዘኵነኔ። ዜና እማሬ ዘአስተርአየ በእንተ ንሥተተ መቅደስ
፡ (መጽ ፡ ምስ። ስንክ ፡ ኅዳ፫። ፍ
፡ ነ ፡ ፵፩ ፡ ፩። ዮሴፍ)።
እማቴ ፡ መከንዳት፤ መስፈር፤ አከነዳድ፤ ክንዳታ።
እማት ፡ እናቶች። ይቤልዎን ለእማቲሆሙ። እማቲነ ኮና ከመ መበለታት
፡ (ሰቆ፪፤ ፲፪። ፭ ፡ ፫)።
እማንቱ ፡ (ውእቶሙ) ዝኒ ከማሁ፤ የሴቶች። እማንቱሰ ይትሀጐላ
፡ (መዝ ፡ ፻፩)።
(ላ) እም [1] ፡ (እመ) ንኡስ አገባብ። ከ ካ ኪ ክ፤ በ ባ፤ ኋላ፤ ገና። አገባብነቱ የመነሻ የተከፋይ የተወላጅ ነው። መደበኛ ፍችው ከ ወይም ተ፤ የቀረው ተውሳክ። ወረደ እምሰማይ፤ ከሰማይ፤ ተሰማይ። መጽአ እምላዕሉ፤ ከላይ፤ ተላይ። ከና ተ አንድ ወገን ናቸው። ካ ሲኾን ከመን በር ከፋች አድርጎ አሉታ ባለበት በቀዳማይ አንቀጽ ይገባል። እምከመ ኢሞትኩ ዮም ኢየዐርፍ እምጻማ ዝንቱ ዓለም፤ ካልሞትኹ፤ ካ ያሰኘችውም ኢ ናት፤ በቦዝና በዘንድ በእመና በእም በሶበ እየገቡ ባ ካ እንዳ የሚያሰኙ ራብዕ አድራጎች አኮና ኢ አልቦ ናቸው። የቀረውን በንኡስ አገባብ ተመልከት ፡ (ዕር፳ ፡ ቍ፹፱)።
[2] ፡ (ጥ) ፤ ፡ (ዕብ ኤም። ሱር ኤማ። ዐረ ኡም) እናት ወላጅ መገኛ፤ ያባት ኹለተኛ፤ ወላድ ሴት፤ የጡት የክርስትና እናት፤ አሳዳጊ ሞግዚት፤ መነኵሲት፤ ያገር ባልቴት፤ እማሆይ እመ እንዲሉ። አክብር አባከ ወእመከ። እሙ ወእኅታ ለእሙ። እሙ መንፈሳዊት እንተ ተወክፈቶ በጥምቀት ፡ (ዘፀ፳ ፡ ፲፪። ዮሐ፲፱ ፡ ፳፭። ቀኖ ፡ ኒቅ)።
[3] ፡ ምንጭ ነቅ፤ ያባት የናት አገር። ፍትወተ ሥሥዕት ዘብዕል እመ ኵሎን ኀጣውእ እኩያት። እምነ ጽዮን ይብል ሰብእ
፡ (ፈ ፡ መ ፡ ፲፰ ፡ ፩። መዝ ፡ ፹፮)።
እምረት ፡ ማወቅ መታወቅ፤ አስተዋወቅ፤ ዕውቂያ፤ ዕውቀት፤ ዐዋቂነት።
እም(ብ)ኖዲ ፡ (ቅብጥ ፕኖቲ) አምላክ።
እምነ ፡ እም ነ፤–እም።
እምነት ፡ (ታት) በቁሙ፤ ሃይማኖት፤ ማመን መታመን፤ አስተማመን፤ እሙንነት። ዘወለጠ እምነተ ክርስቲያን። እምነት ዘመስቀለ ክርስቶስ። ሊቀ ካህናት ዘእምነትነ። እምነታት
፡ (ቀኖ ፡ አንጾ። ስንክ ፡ መስ፲፯። ቄር ፡ ጰላ። አፈ
፡ ተ፰)።
እምዘ ፡ እምዝ፤–እም ዘ ዝ፤
፡ (ዕር፲፱ ፡ ቍ፸፬)።
እምድሩ [1] ፡ አካቶ ፈጽሞ፤–መድረወ።
[2] ፡ አካቶ ፈጽሞ ጭራሽ፤ ካንዱ ዘንዱ። ግሙራን እይ። እመሰ እምድሩ ትኰሲ ሕማማቶ ትክሕድ ትስብእቶ
፡ (ተረ ፡ ቄር፩)።
እሱር ፡ (ራን ራት ስርት) የታሰረ፤ የተሳሰረ፤ የተቈራኘ፤ አንድ የኾነ፤ እስር፤ እስርስር። ንዋይ ዘኢኮነ እሱረ ማእሰር ላዕሌሁ። እሱራን ውስተ ፈለገ ኤፍራጥስ። እመ ኮንከ እሱረ ምስለ ብእሲትከ። ብእሲት ዘእስርት በሕግ። ዘአሰርከ በምድር ይኩን እሱረ በሰማያት
፡ (ዘኍ፲፱ ፡ ፲፭። ራእ፱ ፡ ፲፬። ፍ ፡ ነ ፡ ፳፬ ፡ ፭። ፳፭። ማቴ ፡ ፲፮
፡ ፲፱)።
እሳተ ሕይወት ፡ መንፈስ ቅዱስ
፡ (ማቴ፫ ፡ ፲፩)።
እሳተ መለኮት ፡ ባሕርይ፤ አካል፤ ወይም እሳትነት
፡ (ቅዳ)።
እሳተ እሳት ፡ የሰማይ እሳት፤ እሳተ ገሞራ፤ ከዚህ ዓለም እሳት ፯ እጅ የሚበልጥ
፡ (ሔኖ፲፬ ፡ ፳፪)።
እሳተ ገሃነም
፡ ብርቱ ቅጣት፤ እስራኤል ልጆቻቸውን ለሞሎኽ ሠውተው ያቃጥሉበት የነበረ የሰማያዊ እሳት ምሳሌ
፡ (ማቴ፭ ፡ ፳፪)።
እሳታዊ ፡ የእሳት፤ እሳታም፤ እሳትማ ቀይ፤ ውዑይ፤ ተፈጥሮው ከእሳት የኾነ፤ እሳትነት ያለው። ሳውዳ ዘውእቱ ጠባይዕ እሳታዊ። እሳታውያን እለ ነደ እሳት እሙንቱ ኪሩቤል
፡ (ፈላስ። ቅዳ ፡ ሕር)።
እሳት [1] ፡ (ብ እሳውት። ሱር ኤሽታ። ዕብ ኤሽ) በቁሙ፤ የሚነድ የሚበራ፤ የሚያቃጥል የሚበላ፤ የሚፋጅ የሚልጥ፤ የሚለመጥጥ። ይቡስ ውዑይ ብሩህ፤ ካራቱ ባሕርያት አንዱ በኹሉ የሚገኝ፤ በይብሰቱ ከነፋስ፤ በውዕየቱ ከመሬት፤ በብርሃኑ ከውሃ የሚሰማማ። በአምጣነ ዕፁ ለእሳት የዐቢ ነዱ። እሳት በላዒ። ደብረ ሚካኤል ወለደት ሊቃውንተ እለ ኮኑ እሳተ እሳተ
፡ (ሢራ፳፰ ፡ ፲። ፴ ፡ ፴። ቅኔ)።
[2] ፡ በቁሙ፤–አሲው አሰወ።
እሳት ዘለዓለም ፡ የማይጠልስ የማይጠፋ የማያልፍ ሥቃይ
፡ (ማቴ፲፰ ፡ ፰)።
እስ ፡ ያገባብ ልማድ እንደ እን ያለ፤ እንን የመሰለ። ሦስተኛ ፊደል ከኩመ ሲጨመር፤ እስከ እስኩ እስመ እያለ ርሱ ራሱ ፫ አገባብ ይኾናል፤ ልማድነቱም ከአስተና ከእስት የወጣ ነው።
እስላም [1] ፡ በቁሙ፤–ሰሊም ሰለመ፤ አስለመ።
[2] ፡ (ዐረ ኢስላም) በቁሙ፤ የሙሐመድ ወገን፤ በቍርኣ በፉርቃን የማያምን። ሃይማኖተ እስላም። አመ ነግሡ እስላም ፡ (አቡሻ ፡ ፶። ስንክ
፡ ታኅ፳፫)። ኀነፊን እይ። ፡ (ግጥም፤ በጋሎች ዘመን ከጋሎች መጋባት የፈለገ ዐምሐራ) ፍየሎቹን እላንት ከተካፈላችኹ፤ ይችን ላም ለኔ ስጡኝ እባካችኹ።
እስመ ፡ (እስ መ) ዐቢይና ንኡስ አገባብ። ና ፥ ስለ ፥ እንደ ፥ ብሎ ሲል ፥ እኮ ፥ ቢያ ይኾናል። አኀዘ ይሒሶን፤ እስመ ኢነስሓ። ምንትኑ ዝ ነገር፤ እስመ ይኤዝዞሙ። ንእዶ፤ እስመ ከመ ጠቢብ ገብረ፤ ና
፡ (ማቴ፲፩ ፡ ፳። ሉቃ፬ ፡ ፴፮። ፲፮ ፡ ፰)። ሞተ እስመ ሐመ፤ ተርፈ እስመ ደክመ፤ መጽለወ እስመ ጾመ፤ ስለ። ናና ስለ አንድ ወገን ናቸው፤ ና በገባበት ስለ፤ ስለ በገባበት ና ይገባል። ዘይክሕድ ወይብል እስመ ኢየሱስ ኢኮነ መሲሐ። እሙን ነገር እስመ ክርስቶስ መጽአ ውስተ ዓለም። ጽሑፍ እስመ አሐዱ እምአኀው መጽአ፤ እንደ
፡ (፩ዮሐ ፡ ፪ ፡ ፳፪። ፩ጢሞ ፡ ፩
፡ ፲፭። ፊልክ ፡ ፶፱)። አምጽኡ ወርቀ እስመ ንጉሥ ውእቱ። ንጉሥ ነውና፤ ንጉሥ ስለ ኾነ፤ ንጉሥ እንደ መኾኑ፤ ንጉሥ ነው ብለው፤ ንጉሥ ነኽ ሲሉ ያሰኛል። ብለውና ሲሉ የውእቱ ማቅኛ ትርፍ ዐማርኛ ነው እንጂ፤ የእስመ ዘይቤ አይዶለም። ጸዐሎ እስመ ገብር፤ አልዐሎ እስመ ኄር፤ ባሪያ ብሎ፤ ለጋስ ብሎ እያሰኘ በሚሰማማው ቃል ይፈታል። አንዳንድ ጊዜም ናሁ ይኾናል፤ ናሁ ደግሞ እስመ ይኾናል። እኮና ቢያ ሲኾን ንኡስ አገባብ ነው። እስመ ብዙኃን እለ አኀዙ፤ ብዙ ናቸው እኮ ፥ እኮን። እስመ ርኢከኒሁ አመንከኒ፤ አይተኽ ቢያ፤ ስለ ተብሎም ይፈታል። እስመ እንዘ ትሰምዕ ተጸመምከኒ፤ ሰምተኽ ቢያ፤ እየሰማኽ ቢያ ያሰኛል። የቀረውን ባገባብ ተመልከት ፡ (ዕር፲፱ ፡ ቍ፷፮)።
እስረት ፡ ማሰር፤ መታሰር፤ አስተሳሰር፤ እስራት፤ እስርነት። ውሂብ እምድኅረ ስኢል እስርተ እድ ውእቱ፤ ወውሂብሰ ዘእንበለ ይስአል ፈቲሐ እድ ውእቱ። በእንተ እስረቱ በሐብል። ለዘይደልዎ እስረት። አሰርዎሙ ክቡደ እስረተ
፡ (ፈላስ። አዋል። ፈ ፡ መ ፡ ፪ ፡ ፲፩። መቃ ፡ ገ፪)።
እስቁፍ ፡ (ዐረ ኡስቁፍ) ኤጲስ ቆጶስ፤ ሲያበዛ አስቃፍ ይላል
፡ (ስንክ ፡ ጥቅ፳፫። ነሐ፳፱)።
እስትርኩብ ፡ ዝግጁ፤ የነቃ፤ የተጋ፤ ትጉህ፤ ለሥራ ከኹሉ አስቀድሞ የሚገኝ። ጳጳስ ይኩን እስትርኩበ ለምሥዋዕ ወለጸሎት። ወውእቱ እስትርኩብ በጸሎት ወጾም
፡ (ኪዳ ፡ ቄድር)።
እስትንፋስ ፡ በቁሙ፤ ነፍስ ትንፋሽ ሕቅታ። እስትንፋሱ ሀለወት ላዕሌሁ። እስትንፋሰ አፉሁ። እስከ እስትንፋስ ደኃሪት ፡ (ዕር ፡ ኢሳ፮ ፡ ፲፩። መዝ ፡ ፴፪። ቅዳ)። ረቂቅ ነገር፤ ጥልቅ ምስጢር። እነግረክሙ እስትንፋሰ ቃልየ ፡ (ምሳ፩ ፡ ፳፫)።
እስትጉቡእ ፡ ክምቹ፤–ገብአ አስተጋብአ።
እስከ ፡ (እስ ከ። ዐቢይና ደቂቅ አገባብ) በቁሙ፤ በቅርብና በሩቅ ሲገባ፤ እስከ እስኪ፤ በትርፍ ዐማርኛ ድረስ ይኾናል። አመ ሶበ ጊዜ ኀበ ለ ነ ያዳምቁታል ፥ በር ይከፍቱለታል፤ ሳይከፍቱለትም እስከ እልህቅ ወእረሥእ፤ እስከ ይመሲ፤ እስከ ይጸብሕ እያለ ብቻውን ይገባል። ሲዘረዝር ግን ነን በር ከፋች አድርጎ እስከኔየ፤ ኔከ ኔኪ ኔሁ ኔሃ ኔነ እያለ በነ ይዘምታል። የቦታን የጊዜን የስፍርን የቍጥርን የሥራን ኹሉ ፍጻሜ መድረሻውን መካተቻውን ያሳያል። እስከ ሶበ እመጽእ። እስከ ጊዜ ይሠርቅ ፀሓይ። በጽሐ እስከ ኀበ ልጓመ ፈረስ። ተከዘት ነፍስየ እስከ ለሞት። እስከነ ዐረብ፤ የመሰለው ኹሉ። አንዳንድ ጊዜም ፍጻሜና ጭራሽ በሌለው፤ ኢወለደት እስከ አመ ሞተት። ኢያእመራ እስከ አመ ወለደት እያለ ይገባል ፡ (ዕር፲፱ ፡ ቍ፸፰)።
እስከ ለዓለም ፡ ዝኒ ዓዲ ከማሁ፤ እስከና ለ አንድ ወገን ናቸው፤ የሚመጣን ጊዜ ያሳያሉ። እስከ ዘላለም፤ እስከ ወትሮው፤ እስከ መቼም መች። እምቅድመ ዓለም ወእስከ ለዓለም አንተ ክመ ፡ (መዝ ፡ ፹፱። ቅዳ ፡ ዲዮ)።
እስከ እስኩ ፡ ዐቢይና ንኡስ አገባብ። ፍቻቸውን በአልፍ ተራ ተመልከት።
እስኩ ፡ (እስ ኩ) የጥያቄና የምክር የልመና ቃል፤ እስኪ ፥ እባክኽ። ንግርኒ እስኩ። እስኩ ፍታሕ ለሊከ። እስኩ ስምዐነ። እስኩ ሀበነ እያለ በኋላም በፊትም ይገባል። አንዳንድ ጊዜም፤ ተምኔት ተግዳሮት ፥ ዛቻ ፥ ግን ይኾናል። እስኩ ንርአያ እስኩኬ ንርአያ። ይዜንዉኮ እስኩ ወይንግሩከ። እስኩ እመ ኢትገንዩ ለምስል ወኢትሰግዱ
፡ (ድጓ። ኢሳ፲፱ ፡ ፲፪። ዳን፫ ፡ ፲፭)።
እስኪት [1] ፡ (ብ እስኪታት፤ አሰክት። ዕብ ኤሼኽ። ሱር አሽካ) ቍላ፤ የቍላ ፍሬ፤ ቈለጥ አስካሉ ዕንቍላሉ። ቍልሕን ተመልከት። ዘአሐቲ እስኪቱ። አልዐለት እዴሃ ወአኀዘቶ በክልኤሆን አሰክቲሁ ፡ (ዘሌ፳፩ ፡ ፳። ዘዳ ፳፭ ፡ ፲፩)።
[2] ፡ አባለ ዘርዕ፤ ላይኛው ዘንጉ፤ መድረሻ ማለት ነው። ዘሞተ እስኪቱ በሥራይ። ሠጠቁ መላእክት እስኪቶ ለማር ኤልያስ ሊቀ ምኔተ መነኮሳይያት ሶበ ኮነ ምስሌሁ በህየ ፍትወት። ለእለ ይዜምዉ በእንስሳ ይትመተር እስኪቶሙ። ብእሲ ዘይፌኑ እስኪቶ ውስተ መንደቅ፤ አው ውስተ ስቍረት፤ አው ውስተ እዴሁ ወይወፅእ እምኔሁ ፍትወት
፡ (መጽ ፡ ፈ። ፊልክ ፡ ፳፭። ፈ
፡ መ ፡ ፯ ፡ ፭። ፍ ፡ ነ ፡ ፵፰። ሲኖዶ)። አንዳንድ መምህራን ሰከየ አስከየ ብለው ይገሱና እስኪትን ከዚህ ያወጣሉ፤ ፍችውንም አሶቃሽ አስከሳሽ እስከ ሞት አድራሽ ይሉታል። ዘየዐቅብ እስኪቶ የዐቅብ ሕይወቶ ፡ (ፈላስ)።
[3] ፡ እስከ፤–አሰከ።
[4] ፡ አባለ ዘርዕ። ፍችውን በእስከ ተመልከት።
እስያ ፡ (ጽር አሲያ) ስመ ክፍለ ምድር፤ ስመ ብሔር፤ ካምስቱ የዓለም ክፍሎች አንዲቱ ታላቂቱ ክፍል፤ የኤውሮፓ ምሥራቅ። የቱርክ አገር ደግሞ ለብቻዋ ታናሽ እስያ ትባላለች
፡ (ራእ፩ ፡ ፲፩)።
እስፍንቱ [1] ፡ ስንት፤ ምን ያኽል፤–ሰፊን ሰፈነ ስፍን፤ እስፍንት።
[2] ፡ እስፍንቱ፤ ስንቱ ስንቶቹ፤ ስንቶች፤ ምን ያኽሎች። በእስፍንቱ ዕለታት። አስፍንቱ ዓመታት ዘነበርከ ውስተ ዛቲ ሀገር። እስፍነተ ይደልዎ ለእኍ ከመ ይንበር ውስተ ማኅበር። እስፍንተ ነፍሳተ ሰበእ ኀይለ ተኣምርኪ ዘመሠጠ ፡ (ስንክ ፡ ሐም፰። ፊልክ ፡ ፵፭። ደራሲ)።
እስፍንቶፎኔሕ ፡ (ጽር፤ ቅብጥ አብሶንቶምፋኔኽ) የፍልስፍና ስም ፈርዖን ለዮሴፍ ያወጣለት፤ ከሣቴ ኅቡእ፤ ማእምረ ኅቡኣት። ጸፈነን ተመልከት።
፡ (ዘፍ፵፩ ፡ ፵፭)።
እረፍት ፡ በቁሙ፤–ዐሪፍ ዐረፈ፤ አዕረፈ።
እሩር ፡ (ራን ራት ርርት) የታጨደ፤ የተሰበሰበ፤ ነዶ ክምር ቃርሚያ። ጥንግ።
እሩይ ፡ የተለቀመ ልቅም፤ ምርጥ፤ ዕርም።
እራኅ ፡ (ኃት) ጋልማ፤ ማኽል እጅ፤ ውስጥ እጅ ከመዳፍ እስከ ጣቶች ጫፍ ያለው፤ ዝርጉ ጠፍጣፋው፤ ለእግርም ይኾናል። እራኅ ዘይምን። ትሰፍሕ እደዊሃ ወእራኃ ለውሂብ። ኵሉ ውስተ እራኅነ። አንሥኦተ እደዊነ እንዘ ስፉሓት እራኃቲሆን። እራኃተ እደዊሁ። ኢገብረ አሣእነ ለእራኀ እግሩ ፡ (ስንክ ፡ መስ፲፬። ቀሌ
፡ ገ፻፺። ፵፱። ፍ ፡ ነ ፡ ፲፬። ፩ነገ ፡ ፭
፡ ፬። ስንክ ፡ ግን ፡ ፲፬)።
እራዛ ፡ በቁሙ፤–ራዛ፤ ሩዝ ረወዘ።
እርሳስ ፡ በቁሙ፤–ርሳስ።
እርዉይ ፡ (ዊት ዉያን ያት) አውሬ የኾነ ቍጡ ብስጩ፤ ክፉ ጨካኝ
፡ (መጽ ፡ ምስ)።
እርጋሄ ፡ አክርማ ስንደዶ፤ ግራምጣ የስፌት ሣር። ይሥጥቅሙ ከመ እርጋሄ
፡ (ድር ፡ ሚካ)።
እርግና ፡ በቁሙ፤ እርጅና፤ አሮጌነት።
፡ (ተረት) እርጅና ብቻኽን ና። ለእመ ሞተ በእርግናሁ ፡ (ፊልክ ፡ ፬። ፍ ፡ ነ ፡ ፲፮)።
(ጥ) እሮት ፡ (ዐማርኛ) በቁሙ፤ የአራዊት ስሪያ።
እበን አእባን ፡ (ናት) ደንጎች፤ ደንጊያዎች፤ ድንጋዮች፤ አዕናቍ። እስመ ሠምሩ እበኒሃ። አእባን ዐበይት። አእባናት። አእባነ ወርቅ። አእባነ ህንደኬ። አእባን ክቡራት በበ ሕበሪሆሙ
፡ (መዝ ፡ ፻፩። ኤር፶ ፡ ፱። ስንክ ፡ የካ፱ ፡ ግን፰። መቃ ፡ ገ፳፭። ፩ዜና ፡ ፳፱ ፡ ፪)። እበን ኹለት ወይም ጥቂት፤ አእባን ብዙ፤ አእባናት የብዙ ብዙ ይባላል፤ ባለቅኔዎች ግን እበንን የብዙ ብዙ ይሉታል ፥ አያሰኝም፤ እደውንና እገርን ተመልከት።
እበይ ፡ (ያት)
እንቢታ፤ እንቢተኝነት።
እበድ ፤
(ዳት) ፤ ማበድ ፥ እብደት ፤ እብድነት ፤ ቍጣ ፤
ስንፍና ድንቍርና ፤
ሞኝነት ፤ አለውቀት ፤
አላዋቂነት ፤ ልጅነት ጅልነት።
እበድከ አደንገፀኒ። እበድሰ
አልብየ። ዝንቱ አሚን
እበድ ውእቱ ፤
እበደ ደቂቅ። በመዋዕለ
እበድ። ፈድፈደት እበዶሙ
(ሢራ፵፩ ፡ ፲፭። ግብ፳፮ ፡ ፳፬። ቄር ፡
እስት።
አቡሻ ፡ ፪። ፪ጢሞ ፡ ፫ ፡ ፱)።
እቡስ ፡ (ሳን ሳት ብስት) ያበሰ ፥ የበደለ ፥ አበሰኛ፤ ኃጥእ ፥ ወንጀለኛ። እቡስ ትሬስዮሙ። እቡሳነ ልብ። ተሰቅለ ከመ እቡስ
፡ (ምሳ፲፫ ፡ ፮። መጽ ፡ ምስ። ስንክ ፡ መጋ፳፯)።
እቡቅ ፡ (ቃን ቃት ብቅት) ያከከ፤ ዕከካም፤ ቈሻሻ ቋቍሻም ድውይ
፡ (ዘሌ፳፩ ፡ ፳። ፳፪ ፡ ፳፪)።
እቡድ ፡ (ዳን ዳት ብድ) ያበደ የሰከረ የወገሸ፤ እብድ ቍጡ ብስጩ ጯኺ፤ ደረቅ። ከልብ እቡድ። ኮነ እቡደ ከመ ሐራውያ፤ እቡድ ወእሱር በሰናስል። ሞገዳተ ባሕር እቡዳት ፡ (የሚጮኹ የሚተሙ)። ወለት እብድ። ብእሲት እብድ ፡ (ዲድ ፡ ፮። ገድ
፡ ተክ። ይሁ ፡ ፲፫። ሢራ፳፪ ፡ ፫። ምሳ፱ ፡ ፲፫)። በአብድ ፈንታ እቡድ ይላል አያሰኝም። እምንጉሥ እቡድ ይኄይስ ገብር ጠቢብ ፡ (አዋል)። ጠባቢና ጠቢብ ፩ እንደ ኾኑ፤ አባዲና አብድም ፩ ናቸው።
እባብ ፡ (ዐማርኛ። ዐረ ኡባብ፤ ማዕበል) በቁሙ ፥ ውህኛ ማዕበልኛ የሚኼድ የሚዘል የሚወረወር ፥ በልቡ የሚሳብ የሚጐተት መርዛም ምላሰ መንታ የሰይጣን አርኣያ የክፉ ሰው አምሳል፤ እገሌ እባብ ነው እንዲሉ። ፡ (ተረት) እባብ ግደል፤ ከነበትሩ ገደል።
እቤር ፡ ባልቴት፤–ዐቢር ዐበረ።
እብላ ፡ ጨረቃ፤ የጨረቃ ስም። ወቦቱ ለወርኅ አርባዕቱ አስማት፤ አሶንያ ፥ እብላ ፥ ብናሌ ፥ ኤራስ
፡ (ሔኖ ፸፰ ፡ ፪። ስንክ ፡ ነሐ ፲፯)።
እብሰት ፡ ማበስ፤ መበደል አበዳደል፤ በደላ በደል፤ ኀጢአት ክሕደት። ወእምዝ በርሕቀተ መዋዕል ተእኅዘ ልማደ እብሰት ወርስዐት
፡ (ጥበ፲፬ ፡ ፲፮)።
እብነ መከራ ፡ የፈተና ደንጊያ፤ ታላቅ ከባድ፤ ክብ እንክብል ድንብልብል፤ ጐበዛዝት ርሱን በማንሣት በመሸከም ጕልበታቸውን የሚፈትኑበት
፡ (ሢራ፮ ፡ ፳፪)።
እብነ መዳልው ፡ የሚዛን ደንጊያ፤ ልክነት ያለው፤ ሌላውን በርሱ መመዘኛ ማስተካከያ
፡ (ሕዝ፭ ፡ ፩)።
እብነ ማእዘንት ፡ የማእዝን ደንጊያ ማጠፊያውና መቀነፊያው ኹለቱን ማእዘን የሚይዝና የሚያያይዝ፤ ኹለት ክንፍ ያለው
፡ (፩ጴጥ ፡ ፪ ፡ ፮)።
እብነ ሞፀፍ ፡ የወንጭፍ ደንጊያ፤ ታናናሽ ኵረት ፥ እንደ ፍላጻና እንደ ጥይት ርቆ የሚኼድ የሚወረወር
፡ (ዘካ፱ ፡ ፲)።
እብነ
ሰንፔር ፤ ሰንፔር
የሚባል ዕንቍ ፤
ክቡር ደንጊያ
(ኢዮ፳፰ ፡ ፮።
፩ቆሮ ፡ ፫ ፡ ፲፪)።
እብነ ቍናማት ፡ የሚዛን ደንጊያ፤ ታላቁም ታናሹም በየስሙና በያይነቱ ተሰብስቦ በኪስ በከረጢት የሚከተት
፡ (ምሳ፲፮ ፡ ፲፩)።
እብነ በረድ [1] ፡ በቁሙ የበረዶ ደንጊያ እንዳረር እንደ ጠጠር ያለ ከዚያም የሚበልጥ፤ ራስ የሚሰብር የሚቀጠቅጥ
፡ (ኢያ፲ ፡ ፲፩። ሢራ፵፫ ፡ ፲፮። ፵፮ ፡ ፭። ሕዝ፴፰ ፡ ፳፪። ሔኖ፲፬
፡ ፱)።
[2] ፡ እብነ በረድ፤ ነጭ ደንጊያ፤ በረድ የሚመስል፤ የበረዶ ዐይነት
፡ (ዐማርኛ)።
እብነ አስሐትያ ፡ የውርጭ ደንጊያ፤ የረጋው ግግሩ። ወይም ውርጭ የሚመስል ጽሩይ የብርሌ ጡብ፤ ብርሌ ዐይነት ደንጊያ
፡ (ሔኖ፸፩ ፡ ፭)።
እብነ አድማስ ፡ ርሳስ፤ ገንቢዎች ሕንጻ የሚለኩበት፤ ብረትና ደንጊያም ይኾናል
፡ (ቅዳ ፡ ሕር)።
እብነ እዝኅ ፡ ብልጩት ደንጊያም ይኾናል ፡ (ቅዳ ፡ ሕር)።
እብነ ኰኵሕ ፡ ጥኑ ጠንካራ ኀይለኛ ደንጊያ፤ የማይሰበር የማይፈነከት፤ አልማስ፤ አለት
፡ (ዘዳ፰ ፡ ፲፭። ሮሜ፱ ፡ ፴፫። ኢዮ፵፩ ፡ ፲፱። ሕዝ፫ ፡ ፰)።
እብን ክቡር
፡ ዕንቍ የዕንቍ ወገን፤ ሕብርና መልክእ ያለው።
እብን [1] ፡ (ዐረ ኢብን። ዕብ ቤን) ወንድ ልጅ ተባት፤ ሲያበዛ አብናእ ይላል። እብን እልሐኪም
፡ (ክብ ፡ ነገ)።
[2] ፡ (ዕብ ኤቤን። ሱር አብናእ) ደንጊያ፤ ድንጋይ በአፍኣ በውስጥ ከምድር የሚገኝ፤ የምድር ዐጥንት፤ ዕንቍ። ለዕንጨት ብዙ ዐይነት እንዳለው ለደንጊያም ብዙ ዐይነት አለው፤ ክቡርና ኅሱር ግብዝና ብርቱ። እብን ዐቢይ። ጽላት ዘእብን። ንሕንጽ በእብን
፡ (፩ነገ ፡ ፮ ፡ ፲፬። ዘፀ፴፪ ፡ ፲፭። ኢሳ፱
፡ ፲)።
እቱተ ፡ የራቀ ኹኖ፤ ርቆ ፈቀቅ ብሎ፤ ተለይቶ ብቻውን። ትነብር ምስሌየ እቱተ። እለ ይነብሩ እቱተ ምስለ ንጉሥ። ይኑም እቱተ እምነ ብእሲቱ
፡ (፩ዕዝ ፡ ፬ ፡ ፲፪። አስቴ፩ ፡ ፲፬። ፈ ፡ መ ፡ ፲፬ ፡ ፱)።
(ላጥ) እቱት ፡ (ታን ታት ትት) የራቀ ያገለለ፤ የተነቀለ የተፈነቀለ፤ ፈቅ ፈቀቅ ያለ፤ ገለልተኛ። ወእቱት አረፍተ ቤቱ። ረከበት እብነ እቱተ እምአፈ መቃብር። ምንባበ መጻሕፍት ይኩን እቱተ ሕቀ እምነ ምሥዋዕ
፡ (ሕዝ፵፩ ፡ ፮። ዮሐ፳ ፡ ፩። ኪዳ)።
እታቴ ፡ መራቅ፤ አራራቅ፤ ርቀት፤ ሩቅነት።
እትወት ፡ መግባት፤ መመለስ፤ ምለሳ፤ አመጣጥ። በንግደትከ ወበእትወትከ። ቡሩከ ይኩን። ውፍረትክሙ ወእትወትክሙ
፡ (መዝ ፡ ፻፳። ግንዘ)። እንዘ የአቱ በማለት ፈንታ እትወቶ ይላል፤ የመላሽ ስሕተት ነው ፡ (ማር፲፭ ፡ ፳፩። ሉቃ፳፫ ፡ ፳፮)።
፡ ምርት፤ ውጤት፤ የምድር ዐላባ፤ ፍሬ። በአምጣነ እትወተ እክለ ገራህቱ። ወይከውን እትወቱ ለእለ ይነድቁ ሀገረ። በእትወተ አክማሪሁ። እንበለ ዘርዕ እምድር እትወተ
፡ (ዘሌ፳፯ ፡ ፲፮። ሕዝ፵፰ ፡ ፲፰። መቃ ፡ ገ፱። ድጓ)።
እትዌቄህ ፡ (ዕብ አቴቄይሃእ) የግንብ ዐምድ፤ ሕንጻውን ለማጽናት ዐብሮ የተሠራ፤ ዐልፎ ዐልፎ የቆመ፤ ከላይ በቀስተ ደመና የተያያዘ
፡ (ሕዝ፵፩ ፡ ፭)።
እቶን ፡ (ናት። ሱር አቱና። ዐረ አቱን) የማድ ቤት፤ ፉርን፤ ማብሰያ መጋገሪያ፤ ምድጃ፤ የእሳት ጕድጓድ፤ አጐዶ ኖራ ክሰል የሚያወጡበት፤ ጡብ ሸክላ የሚተኵሱበት። ብሱል በእቶን። ከመ እቶን ዘአንደዱ ለኀቢዘ ኅብዝት። ለእመ ገብረ አሐዱ እቶነ ዘየዐርግ እምኔሁ ጢስ። በዓለ እቶን። እቶነ ገሃነም። እቶነ ኀጺን
፡ (ዘሌ፪ ፡ ፬። ሆሴ፯ ፡ ፬። ፍ ፡ ነ ፡ ፴፯። ፳፫። ሱቱ ፡ ዕዝ፮ ፡ ፩። ዘዳ፬ ፡ ፳)።
እኑም ፡ (ማን ማት ንምት) የተሠራ ሥር፤ ሥረ ወጥ፤ ጥልፍ፤ ዝምዝም። ሜላት ዘእኑም በወርቅ። እኑም ኵለንታሁ። መንጦላዕት ዘሜላት እኑም በፈትለ ወርቅ ፡ (ገድ ፡ ተክ። ዮሐ፲፱ ፡ ፳፫። ዮሴፍ። ዘፀ፳፮ ፡ ፴፩)።
እኑስ ፡ (ሳን ሳት ንስት) ያነሰ ንኡስ ተከታይ።
አኒድ ፤ ዶት ፤ (አነደ የአንድ ይእንድ። ዕብ
ዐናድ) ፤ ማሰር ማጥበቅ ፤
አንድ ማድረግ ፤
ነዶ ማለት
ከዚህ ወጥቷል።
መጠፈር ፤ መጐለብ
ቈርበት ማልበስ ፤
መደጐስ ፤ መሸለም
ማስጌጥ ፤ የከበሮና
የመጣፍ ፤ የመሰለው
ኹሉ። እሒድን
ተመልከት።
እን ፡ የአገባብ ልማድ፤ የጥሬ ዘር ባዕድ። ሌላ ፊደል አንድም ኹለትም ሦስትም ሲጨመርበት እሱ ራሱ አገባብ ይኾናል፤ ብቻውን ግን ቃልነት የለውም፤ አገባብነቱም በየፊደሉ ይለወጣል፤ አገባቡና መለወጡም ከዚህ ቀጥሎ እንደ ተጣፈው ነው።
እንመት ፡ መሥራት፤ መሠራት፤ አሠራር፤ የልብስ ሥራ። ልብስ ግሩም ዘቀጢን ፍትለቱ ወሠናይ እንመቱ። እንመተ ሣሬት። ዘእምላዕሉ እንመቱ፤
፡ (ዕር ፡ ኢሳ። አፈ ፡ ተ፴፬። ቅዳ)።
እንሞ ፡ የልብስ የፈትል ሥራ፤ ትት ስፌት፤ ጥልፍ ዝምዝማት፤ ያንገትጌ የእጅጌ፤ ወይም በጭራሽ ሥረ ወጥ። ወድማሬሁ እንሞ
፡ (ዘፀ፳፰ ፡ ፴፪)።
እንሰይ ፡ (ዐረ እንሲ) ጳግሜ፤ የነሐሴ ጫፍ ተቀጥላ። እንሰይ ዘውእቱ ለዋሕቅ
፡ (አቡሻ ፡ ፰)።
እንሱስ ፡ (ሳን ሳት ስስት) እንስሳ የኾነ፤ ሞኝ አላዋቂ። ከመ ኢይኩን እንሱሰ በኢልባዌ ነፍኀ ውስተ ገጹ መንፈሰ ሕይወት ፡ (መጽ ፡ ምስ)።
እንስሳ [2] ፡ በቁሙ፤–ሶስዎ ሶሰወ፤ አንሶሰወ።
[2] ፡ እንስሳ፤ ፡ (ሳት) በቁሙ፤ የቤት የዱር ከብት፤ ባላራት እግር፤ ሣር ነጭቶ ውሃ ተጐንጭቶ የሚኖር፤ የሚበላ የማይበላ። ለታውፅእ ምድር ዘመደ እንስሳ። ኵሉ እንስሳ ያፈቅር ዘመዶ። እንስሳ ገዳም። ይባርክዎ ኵሉ አራዊት ወእንስሳ። አርባዕቱ እንስሳ
፡ (ዘፍ፬ ፡ ፳፬። ሢራ፲፫ ፡ ፲፭። መዝ ፡ ፸፱። ዳን፫ ፡ ፹፩። ሕዝ፩ ፡ ፭)።
እንስሳዊ ፡ የእንስሳ፤ በእንስሳ ጠባይ ያለ ሥራ፤ እንሰስማ፤ እንሰስኛ። ጠባይዕ እንስሳዊት። ፍትወት እንስሳዊት። ይተልዉ ፍኖተ እንስሳዊተ ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፳፬ ፡ ፩። ፈላስ። ፈ ፡ መ ፡ ፲፩ ፡ ፩)።
እንስት ፡ (ታት) ዝኒ ከማሁ፤ በቁሙ፤ ሴት። አንስትና ብእሲት ለሰው ፍጥረት ብቻ፤ እንስት ለሰውም ለእንስሳም ለሣር ለንጨት ሳይቀር ለፍጥረት ኹሉ ይነገራል፤ መጣፍ ግን በእንስት ፈንታ ኹሉን አንስት ይላል። ተባዕተ ወአንስተ ገብረ እግዚ። ወእምነ ኵሉ ዘሥጋ ታበውእ ውስተ ታቦት በበ ክልኤቱ ተባዕተ ወአንስተ
፡ (ማር፲ ፡ ፮። ዘፍ፮ ፡ ፲፱ ፡ ፳። ፯ ፡ ፪ ፡ ፫)።
እንቀት ፡ በቁሙ፤ የገብስ ክክ የበሶ ዶቄት ከርቱ እንደ ሩዝ ያለው። እንቀት አንቅቼ ገንፎ አገንፍቼ እንዲሉ ፡ (ዐማርኛ)።
እንቁር ፡ እንቁራ፤ ጥንግ ዕሩር ፡ (ዐማርኛ)።
እንቃስ [1] ፡ ዐዛባ ጭቃ፤–ነቂስ ነቀሰ።
[2] ፡ ዐዛባ ጭቃ ጭቅቅት፤ እድፍ ጕድፍ ንቃሽ። ይገብእ ከልብ ዲበ ቅያኡ፤ ወሐራውያኒ ተኀፂባ ዲበ እንቃሳ ፡ (ቄር ፡ ጰላ። ፪ጴጥ
፡ ፪ ፡ ፳፪)።
እንቈራ [1] ፡ የንብ እንጀራ፤–ነቈ።
[2] እንቈራ፤ የንብ እንጀራ ፥ ጠቃጠቆው ክፍቱ ዐይኑ ሰፈፋ፤ ዕጩና ጐመጩ ወለላው የሚታቈርበት አንዳንዱ ጕድጓድ። እንቈራ ዘይትወለድ ቦቱ ንህብ፤ ወጸቃውዕኒ ይትዐቈር ቦቱ ፡ (ጥሬ ፡ ሰዋ። አርጋ ፡ ፭)።
[3] ፡ (ጽር አንኪራ) እንቍራ፤ ስመ ሀገር። ቴዎዶጦስ ዘእንቈራ ፡ (ተረ ፡ ቄር)።
እንቅዕድው ፡ (ዋን ዋት ዱት) ያንጋጠጠ፤ የተንጋጠጠ፤ ዐይኑ ልቡ የተመሠጠ፤ ሰማይ ሰማይ የሚያይ
፡ (አርጋ)።
እንቆራ ፡ (ጽር አንኮራ) ስመ ሀገር ቴዎዶጦስ ዘእንቆራ
፡ (ተረ ፡ ቄር፩። ሃይ ፡ አበ)።
እንቆቅሖ አንቆቅሖ ፡ (ሓት) ዕንቍላል፤ የአዕዋፍ አስካል፤ ወልደው ከማያጠቡ ከሌሎቹም ፍጥረት የሚገኝ ባሕርያዊ ፍሬ። ይበልዑ አንቆቅሖ ወግብነተ። ዖፍ እንተ ተሐቅፍ አንቆቅሖ። ወይነፅኁ አንቆቅሖሙ። አንቆቅሖ አርዌ ምድር
፡ (ቄድር። ዲድ ፡ ፮። ኢሳ፳፰ ፡ ፮። ፶፱ ፡ ፭)። እንቆቆ፤ እንቆቅልኽ ማለት ከዚህ ወጥቷል። ዕንቍላል ማለት ግን ዕንቈ ሉል ማለት ነው፤ ሉል የሚመስል የሉል ዐይነት። ዕንቍ ከዐነቀ፤ ላል ከሉል መጥቶ ተገናኝቶ አንድ ስም ኹኗል፤ ብሕረንና ዐነቀን ተመልከት።
እንቋዕ [1] ፡ ዕሦ ዕሠይ፤–እን ቋዕ።
[2] ፡ (እን ቋዕ። ዕብ ሄአሕ። ዐረ ሀይ) ንኡስ አገባብ። የደስታ ቃል፤ እንኳ እንኳዕ፤ ዕሦ ዕሠይ፤ ወሰው ውሽን፤ ይበል። እንቋዕ ተሰብረት ማዕጾ አሕዛብ። እለ ይብሉኒ እንቋዕ እንቋዕ
፡ (ሕዝ፳፮ ፡ ፪። ፴፮ ፡ ፪። መዝ ፡ ፴፬። ፴፱)። ስንኳንና እንኳን ልዩ ልዩዎች እንደ ኾኑ፤ እንኳዕም ከነዚህ ልዩ ነው። ስንኳን የማላላቅና የማበላለጥ ነው፤ እንኳን ግን የማዋረድና የማሳነስ ያሉታና የነቀፌታ ነው፤ ወ ሂ ኒ ጥቀን አኮን ተመልከት።
እንበለ [1]:-ያለ አለ፤–እን በለ።
[2] ፡ (እን በለ። ዕብ ባል፤ ብሊ) እን ፥ ተውሳክ ምልአተ ንባብ፤ በለ ፥ አሉታ። በተገናኝ ዐቢይና ንኡስ ደቂቅ አገባብ ነው። እንጂ ሳ አለ ያለ ከ–በቀር ይኾናል፤ ዘ እያዳመቀው ሳያዳምቀውም ብቻውን ይገባል። አገባብነቱን ፲፱ኛ ዕርከን ፹፩ ቍጥር ተመልከት።
እንበይነ [1]:-ስለ፤–እን በይነ።
[2]:-ስለ፤–በይነ።
[3] ፡ (እን በይነ) ዝኒ ከማሁ፤ ስለ። እን ትርፍና ተውሳክ አዳማቂ ነው፤ ፍች የለውም። እንበይነ ዘኢበልዑ። እንበይነ መኑ ይብል። እንበይነ ምጽዋት። ላሕም ዘእንበይነ ኀጢአት። እንበይነ ዝንቱ ፡ (ስንክ ፡ ሚያ፱። ዮሐ፲፫ ፡ ፳፪። ሢራ፳፬ ፡ ፬። ዘፀ፳፱ ፡ ፴፮። ቲቶ፩ ፡ ፭)።
እንቡዝ ፡ (ዛን ዛት ብዝት) በቁሙ፤ ልቡ የጠፋ፤ የተነበዘ ነባዛ፤ ንብዝ ቅብዝብዝ፤ ስካር እብድ። ሰብእ እንቡዛን። ብእሲት እንብዝት። እንቡዛነ ልብ ወድንቅዋነ እዝን ፡ (ኢሳ፳፭ ፡ ፭። ፶፬ ፡ ፮። መጽ ፡ ምስ)። ዕንቍ ፥ ወይም ለይቶ ብሉር በማለት ፈንታ እንቡዝ ይላል፤ የመላሽ ስሕተት ነው፤ ዝሉፍን እይ
፡ (ኢዮ፳፰ ፡ ፲፰)።
እንቡጥ ፡ በቁሙ፤ ያበባ እኽል ዛላ ከነፍሬው።
እንቢልታ ፡ (ዕብ ሐሊል) በቁሙ ታላቅ ዋሽንት፤ ውስጠ ክፍት፤ ነገሥታት መኳንንት ሲጓዙ ግብር ሲያገቡ ከመለከት ጋራ የሚያስነፉት፤ ከደጃዝማች በቀር ማንም ሹም የማያስነፋው።
እንባዜ ፡ መ(ን) ነባዝ፤ መቅበዝበዝ ፥ ድካም ሕጸጽ ስካር እብደት ልብ ማጣት። ሕማመ እንባዜሃ። እንባዜ ነፍስ። እንባዜ ስካር። እንባዜ ልብ። ጠበ እምእንባዜሁ ፡ (ኪዳ። መዝ ፡ ፶፬። መጽ ፡ ምስ። ፍ ፡ ነ ፡ ፵፫ ፡ ፲። ገድ ፡ ተክ)።
እንብልቡል ፡ (ላን ላት ብልት) የሚንበለበል የሚቃጠል፤ ቦግ ቦግ የሚል። ከመ እሳት እንብልብልት
፡ (ፊልክ ፡ ፻፶፫)።
እንብዝና ፡ ልበ ቢስነት፤ ጭንቀት ጥበት። እንብዝና ነፍሶሙ ፡ (ዘፀ ፡ ፱)። ድንባዝን እይ፤ የዚህ ጥሬ ነው፤ ድሕንጻ የሐነጸ ጥሬ እንደ
እንብየ ፡ የሐዘን የጸጸት የቍጣ የብስጭት ቃል፤ እንቢልኝ ወዲያልኝ፤ ይብላኝልኝ።
፡ (ግጥም) እንቢልኝ ወዲያልኝ ሰው መኾን ሰለቸኝ፤ ከላይ ቤት አልሠራኹ በምድር አልተመቸኝ።
እንብየ እንቢ ፡ (ዕብ ኤን ቢ፤ አልብየ) ነባር አንቀጽ፤ እንቢታና አሉታ፤ እንቢዮ፤ እንቢኝ፤ በቁሙ እንቢ፤ አሻፈረኝ፤ አልሰማም፤ አልቀበልም፤ አይኾንም፤ አይኹን። አበየና እንብየ አንድ ዘር ናቸው፤ አኮና አከየ ሐሰና ሐሰወ አንድ እንደ ኾኑ። ኦሆ በልዎ ለእግዚ፤ ወእንብየ በልዎ ለጋኔን። እንብየ ኢይሰምዕ
፡ (ያዕ፬ ፡ ፯። ኤር፳፪ ፡ ፳፩። ማቴ፳፩ ፡ ፳፱)። እንቢከ፤ ኪ ሁ ሃ፤ እንቢነ፤ ክሙ ክን ሆሙ ሆን እያለ ይዘረዝራል። ይቤሉ እንቢከ፤ ኢትበሎ ኦሆ። እንቢክሙ ደቂቅየ
፡ (፫ነገ ፡ ፳ ፡ ፰። ፩ ፡ ፪ ፡ ፳፬)።
እንብድቡድ ፡ ፈሪ በድባዳ።
እንቦሳ ፡ (ዐማርኛ) በቁሙ፤ ጥጃ የሚዘል የሚፈነጭ። ፡ (ተረትና ምርቃት) ወተት ለንቦሳ፤ ሥጋ ላንበሳ። ቤት ለንቦሳ፤ እሰር እንቦሳ።
እንተ [1] ፡ የ በ ወደ፤–እን ተ። ባዕድ ዘር ሲኾን፤ አን በገባበት ግስ፤ አንገለገ እንግልጋ ይላል። አን በሌለበትም ጐድዐ እንግድዓ እያለ ይገኛል።
[2] ፡ (እን ተ ዘ) ዐቢይ አገባብ። የሴት ቅጽል፤ የ፤ ቅጽልነቱም ላንድ ብቻ እንጂ እንደ ዘ ላንድም ለብዙም አይኾንም። ሀገር እንተ ተሐንጸት መልዕልተ ደብር። ደብተራ እንተ ኢገብራ እደ ሰብእ። ድንግል እንተ ተፍኅረት ለብእሲ ፡ (ማቴ፭ ፡ ፲፬። ዕብ፱ ፡ ፲፩። ሉቃ፩ ፡ ፳፯)። እንቲኣየ ከ ኪ ሁ ሃ፤ እንቲኣነ እያለ እስካሥር ይረባል። እም ብሎ እናት ማለት ዐማርኛው ከዚህ የወጣ ነው።
[3] ፡ ደቂቅ አገባብ። በ ፥ ወደ ፥ ለ ፥ ን ፥ አዳማቂ ፥ እየ ፥ ደጊመ ቃል። ኀለፉ እንተ የብስ። ሖሩ እንተ እግር። ይበውኡ እንተ መስኮት፤ በ
፡ (ዘፀ፲፭ ፡ ፲፮። ማር፮ ፡ ፴፫። ዮኤ፪ ፡ ፱)። ሖረት እንተ አውሎና ርቱዐ። ሮጸ እንተ መርሕበ ሀገር። ንሑር እንተ የማን አው እንተ ፀጋም፤ ወደ
፡ (ዮዲ፲ ፡ ፲፩። አስቴ፩ ፡ ፩። ዘረፋ)። ለና ን ሲኾን በባሕቲት ይገባል። እንተ ባሕቲቱ ብቻውን ለብቻው
፡ (ማቴ፲፬ ፡ ፲፫ ፡ ፳፫። ዮሐ፳ ፡ ፯)። እንተ ሶበ ጸዋዕክዎ ለእግዚ። እንተ ጊዜ ተንሥአ ሰብእ። ዘእንበለ ይቅረብዋ እንተ ከመ ብእሲ ወብእሲት፤ አዳማቂ ፡ (መዝ ፡ ፲፯። ፻፳፫። ጦቢ፫ ፡ ፰)። እየና ደጊመ ቃል ሲኾን በጊዜ ይገባል፤ እንተ ጽባሕ፤ እንተ ጽብሐት ይላል፤ ጸብሐን ተመልከት። ደቂቅነቱንም ባቢይ አገባብ ውስጥ ፹ቍ ተመልከት።
እንተ ጽብሐት ፡ በነጋ ቍጥር፤ እየነጋ፤ እየጠባ፤ ማለዳ ማለዳ፤ ነገም ነገም፤ ጧት ጧት፤ ዕለት ዕለት፤
ዘወትር፤ በየቀኑ። ወትትናገሮ ለዮፍ እንተ
ጸብሐት። እንተ ጸብሐት ኢትወልጥ ዐርከ። ወእንተ ጸብሐት ይበዝኁ ሕዝብ ፡ (ዘፍ፴፬ ፡ ፲። ሢራ፯ ፡ ፲፰። ግብ፲፮ ፡ ፭)።
እንተላም ፡ (ትግሪኛ) ታላቅ መስፈሪያ ፴፪ ካዕቦ የሚይዝ። አንዱ ካዕቦ ፰ ክፋሎ፤ ወይም ፰ ምኒልክ
፡ (አዋል)። ይኸውም የምኒልክ መልክ የተሣለበት ዋንጫ ኵባያ ማለት ነው።
እንታሌ ፡ ቸልታ፤ ስልቹነት፤ ስንፍና ቦዘን።
እንታክቲ ፡ (ዝክቱ) ዝኒ ከማሁ። እንታክቲ ዕጐልት ቀዳማዊት። እስመ ዛቲ ትትወለድ እምእንታክቲ። ለእንታክቲ ሌሊት አእመርዋ
፡ (ሔኖ። ማር ፡ ይሥ፩። ጥበ፲፰
፡ ፮)።
እንትኩ ፡ (ዝኩ) እንተ ከሃ፤ የሩቅ ሴት ዐጸፋና ቅጽል፤ ያች፤ ያችው፤ ያችኛይቱ፤ ያችኛዋ። እንትኩ ዕፅ ዘውስተ ገነት። እንትኩ ጣዕዋ አንስትያዊት
፡ (ቅዳ ፡ አት። ሔኖ ፡ ፷፯)። ገቢር ሲኾን በዝኩ አንጻር እንትኰ ይላል።
እንከ [1] ፡ (እን ከ) ንኡስ አገባብ። እንኪያ እንኪያው፤ እንግዲያው፤ እንግዴህ፤ ከዚያ ወዲያ፤ ከእንግዴህ ወዲህ። ሰኬ ትራስ እየኾኑት ሳይኾኑትም በኋላና በፊት ይገባል። አገባቡን ከነምስክሩ ፳ኛ ዕርከን ፺፰ ቍጥር ተመልከት።
[2] ፡ እንግዴህ እንግዴህ፤–እን ከ።
እንዘ [1] ፡ ሲ ሳ ስ፤–እን ዘ።
፡ (ዕር፲፱ ፡ ቍ፸፩)።
[2] ፡ እንዘ፤
፡ (እን ዘ) ዐቢይ አገባብ። ሲ ሳ ስ ቸልታ እየ ይኾናል። እንዘ ይጼዕልዎ ኢጸዐለ፤ ሲ። እንዘ አልቦ ዘያድኅን እንዘ ኢየሐጽጽ በላዕሉ ሳ። እመኒ እንዘ ትነውም ወእመኒ እንዘ ትነቅህ ስ። ረከቦሙ እንዘ ይነውም፤ ቸልታ። አንሶሰወ ውስተ ኵሉ ገሊላ እንዘ ይሰብክ በምኵራባቲሆሙ፤ እየ። እንዘ ከሀለወ በቀር በቀዳማይ አንቀጽ አይገባም። እንዘ ሀለዉ ኵሎሙ ኅቡረ
፡ (ግብ፪ ፡ ፩)። ዳግመኛም ፲፱ኛ ዕርከን ፸፩ ቍጥር ተመልከት።
እንዚራ ፡ (ራት) ንዋየ ማሕሌት፤ የሚነፋ የሚመታ የሚደረደር፤ ክራር በገና ሙዚቃ፤ የመሰለው ኹሉ። በከበሮ ወእንዚራ። እንዚራሁ ለበኵርኪ። እለ ይነፍኁ እንዚራተ ፡ (ኢሳ፭ ፡ ፲፪። ሳታት። ፍ ፡ ነ ፡ ፳፫)።
[2] ፡ (ላን ላት ልልት) አለል ዘለል የሚል፤ አውታታ ሥራ ፈት፤ ሊል ዘሊል፤ ስካር ሞኝ ዞላ፤ ተላላ ዘላላ። እመ ኮነ እንዝህሉለ በግብሩ ዝንቱ እንዝህሉል ውእቱ በሥርዐቱ ወንዋዩ፤ ወይትዐቀብ በጽኑዕ ከመ ካዕበ እንዝህሉለ ኢይኩን በሃይማኖቱ፤ ወዜናሁሰ ለእንዝህሉል ይትናጸር ምስለ ዜናሁ ለልብው
፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፵፪)። በእንዝህሉል ፈንታ ኅዝህሉል ነዘህሊል ይላል፤ ፍችው አንድ ነው። ተደመረ ምስለ አኀው ንዝህሉላን። ነዘህሊል ብእሲ እምንእሱ ገብረ ይከውን ፡ (ፊልክ ፡ ፻፬። ምሳ፳፱ ፡ ፳፩)።
እንዝርት ፡ በቁሙ፤ የፈትል መሣሪያ መፍተያ ማንዘሪያ፤ መንኮክት ባለ፫ ዐይነት፤ ዘንጉ ከሽመልና ከቀርካሓ ፥ ራሱ ከቀንድ ወይም ከወፍራም ቅል ፥ ቋንጣው ከቀጭን ሽቦ የሚሠራ።
እንዳዒ [1] ፡ እንጃ፤–እን ዳዒ።
[2] ፡ እንጃ፤–የዲዕ የድዐ፤ አይድዐ።
[3] ፡ (ዕብ ኤን ዴዒ፤ አልቦ ዑቀት) አሉታ፤ አላውቅም አላወቅኹም፤ አላስተዋልኹም። ወይም ጥርጥር፤ እንጃ፤ምናልባት። እንጋን እይ፤ የዚህ መንቲያ ነው። እንዳዒ፤ እግዚ የአምር። እንዳዒ፤ ኢያእመርነ ከመ ይመልእ ኵሉ ዝቅ ወይነ። እንዳዒ፤ እመ ቦ ዘኀለይከ ፡ (፪ቆሮ ፡ ፲፪ ፡ ፪ ፡ ፫። ኤር ፡ ፲፫ ፡ ፲፪። ሄርማ
፡ ገ፫)። ከማሁ በማለት ፈንታ እንዲሁ እንደ ማለት እንዳዒ ይላል በሌላም በብዙ ቦታ፤ እንዳዒ እንጋ። እፈርሀክሙ እንዳዒ እያለ አለ ስልቱ ገብቶ ይገኛል፤ የመላሽ ስሕተት ነው ፡ (፪ቆሮ ፡ ፲፩ ፡ ፫። ሮሜ፭ ፡ ፯። ገላ፬ ፡ ፲፩)።
እንድቅትዮን ፡ (ሮማይ ኢንዲክሲዎ) ተውሳክ ጭማሪ፤ የተባለ ግልጥ ነገር፤ ወይም ያተባለ ስውር። የተወሰነ ቀመር፤ ፲፭ ዓመት
፡ (አቡሻ)። ባለመርሐ ዕውሮች ግን የነደቀ ጥሬ መስሏቸው ዕለተ ንድቆሙ ለፍጡራን፤ ዕለተ ንድቁ ለአዳም ይሉታል።
እንጉጋዌ ፡ መባከን ብክነት፤ በካንነት፤ የልቡና ሁከት። እንጉጋዌ በእንተ ቃል ንእስት ፡ (ፊልክ ፡ ፻፫)።
እንጉግው ፡ የባከነ ብኩን፤ ዝርው እንቡዝ ቅብዝብዝ። እስመ እምርእይ ወሰሚዐ ነገር ብዙኅ ትከውን እንጎግወ ኅሊና። ኅሊናቲ ሆሙ እንጉግውት ድኅረ ዘይረክዎ ፡ (ፊልክ
፡ ፵፰። ፺፩)።
እንጊጉይ [1] ፡ የባከነ ብኩን ብክንክን በካና፤ እንቡዝ ቅብዝብዝ።
እንጋ [1]፡ እንጃ፤–እን ጋ።
[2] ፡ (እን ጋ) ፡ (ንኡስ ፡ አገባብ) የጥያቄና የጥርጥር የአንክሮ ቃል። እንጃ፤ ይኾን፤ እንከ ናሁ ይኾናል፤ እፎ መኑ፤ ሁ ኑ እየቀደሙለት ሳይቀድሙለትም ይገባል። ናሁ መኾኑ መላሶች በናሁ ፈንታ ስላገቡት እንጂ ፍችው ኹኖ አይዶለም። አገባቡንና ምስክሩን ፳ኛ ዕርከን ፺፮ ቍጥር ተመልከት።
እንጌግይ ፡ (ያት) ብክነት ዙረት፤ እንባዜ ቅብዝብዝታ፤ ቅብዝብዝነት። ጸሎት ዘእንበለ ፅርዐት ወኢእንጌግይ ፡ (ፊልክ ፡ ፬። ፲፫)።
እንግልጋ [1] ፡ ሸንጎ፤–ገልጎ ገለገ፤ አንገለገለ።
[2] ፡ መሰብሰብ መከማቸት፤ አስባሰብ ስብሰባ ክምቸታ፤ ክምቹነት። ሸንጎ ጉባኤ ማኅበር፤ ብዙ ሰው፤ የሰው መንጋ የሚንጋጋ። ልቅሶኛ ሰርገኛ ገበያተኛ ቤተ ክሲያን ሳሚ፤ የመሰለው ኹሉ። እንግልጋ አሕዛብ። ማእከለ ማኅበር ወእንግልጋ። ሰላም ለክሙ ቅዱሳን እንግልጋ። ምስለ ብዙኃን እንግልጋ፤ ሀገረ ዳዊት ማርያም ዐሪጋ ፡ (ሢራ፳፮ ፡ ፭። ምሳ፭ ፡ ፲፬። ስንክ ፡ መስ፫ ፡ ታኅ፳፰)።
እንግዳ [1] ፡ እንግዳ፤–በቁሙ፤–ነገደ።
[2] ፡ (ብ አናግድ) በቁሙ፤ ነግድ መንገደኛ ስደተኛ፤ መጤ ባይተዋር። ዝ እንግዳ አምአይቴ ዘመጽአ። ማኅደረ እንግዳ። መቃብረ እንገዳ። ዑቀኒ እስመ እንግዳ አነ ፡ (ድጓ። ቀኖ ፡ ኒቅ፸፯። ማቴ፳፯ ፡ ፯። ሩት፪ ፡ ፲)። ጸሊአ አናግድ። አክብሮ አናግድ ፡ (ጥበ፲፱ ፡ ፲፫። ፈላስ)።
እንግድዓ [1] ፡ ደረት፤–ጐዲዕ ጐድዐ።
[2] ፡ «እንግድዓ፤–ደረት፤–ጐዲዕ ጐድዐ»።
እንጐት ፡ የሽቱ ቅጠል፤–ዕንጐት።
እንጡሉዕ ፡ የተሸፈነ የተጋረደ፤ ሽፍን። አንጡሉዓን በመብረቀ ስብሐት ወግልቡባን በነደ እሳት። እንጡሉዕ በደመና እሳት ፡ (መጽ ፡ ምስ)።
እንጡላዔ ፡ (ላ ጥ)
መዘርጋት መጋረድ፤ አዘረጋግ
አገራረድ፤ ግርዶሽ። ክዱናን በስዋሬ ወኅቡኣን በእንጡላዔ ፡ (መጽ ፡ ምስ)።
እንጣእጤ ፡ ተልባ፤ የሚንጣጣ የሚፈናጠር ፡ (ትግሪኛ)።
እንጳጴ እንጳንጼ ፡ (ዕብ አባዕቡዓ) የገላ የቈርበት በሽታ፤ ደዌ ሥጋ፤ ዕበጥ፤ ዕከክ፤ ፈንጣጣ፤ ቍስል መግል የያዘ ያረገዘ። ጸውብ ወእንጳንጴ ፡ (ኢዮ፯ ፡ ፭። ኩፋ ፡ ፵፰)።
እከይ ፡ (ያት) (ያት) ክፋት፤ ክፉነት፤ መጥፎነት ልግም ተንኰል፤ የተንኰል ሥራ። እከየ ልብ። እከዪሃ የዐልዎ ለራእያ። ይኄይስ እከዩ ለብእሲ እምነ ኂሩታ ለብእሲት። ዘኢይትበላዕ በእከዩ። ሔኖክ ይጽሕፍ ኵሎ እከዮሙ። ምግባረ እከይ
፡ (መክ፯ ፡ ፬። ሢራ፳፭ ፡ ፲፯። ፵፪ ፡ ፲፬። ኤር፳፬ ፡ ፪። ኩፋ ፡ ፬። ዕብ፲ ፡ ፳፪)።
እኩል ፡ (ላን ላት ክልት) ያከለ፤ የበቃ ብቁ። እንዘ ጥቀ እኩል ዕድሜ መዋዕል ለበጺሕ
፡ (ተረ ፡ ቄር፲፪)። በቁሙ፤ እኩል እኩሌታ፤ ግማሽ፤ መንፈቅ ፡ (ዐማርኛ)።
እኩት ፡ (ታን ታት ኵት) የተመሰገነ፤ ምስጉን ምሩቅ። እኩት እንተ ወእኩት ስምከ። ክቡር ወእኩት። እኩት ወስቡሕ
፡ (ድጓ። ኩፋ ፡ ፴፭። ቅዳ)።
እኩይ ፡ (ያን ያት ኪት) የከፋ ክፉ፤ መጥፎ። ጋኔን እኩይ። ዘእኩይ ምግባሩ። እኩያነ ልማድ ወግዕዝ። እስመ ክልኤተ እኩያተ ገብሩ ሕዝብየ። ኢትግበራ ለእኪት ወኢይርከብከ እኩይ
፡ (መሳ፱ ፡ ፳፫። ዮሐ፫ ፡ ፳። ሮሜ፩ ፡ ፳፱። ኤር፪ ፡ ፲፫። ሢራ፯ ፡ ፩)።
እክል [1] ፡ (ላት፤ ዕብ ኦኬል። ዐረ ኡክል፤ አክል) መብል ምግብ ሲሳይ፤ የበሰለ የተዘጋጀ ወጥ። ኀጢአ እክል። ጕርዔ ይጥዕም እክለ። ብልዒ እክለኪ። እክል ወማይ። ዘይሴሰይ እክልየ
፡ (አርጋ ፡ ፩። ኢዮ፲፪ ፡ ፲፩። ሩት፪ ፡ ፲፬። ሢራ፳፱ ፡ ፳፩። መዝ ፡ ፵)።
[2] ፡ (ዕብ ዳጋን) በቁሙ፤ ያዝመራ እኽል በያይነቱ፤ ያልተፈጨ ጥሬ፤ ያገዳ ያበባ የሣር የብር ፍሬ፤ ተዘርቶ የሚበቅል፤ ታጭዶ የሚከመር፤ ተወቅቶ ተመርቶ የሚሰፈር፤ ተፈጭቶ ተቦክቶ የሚጋገር ማናቸውም ኹሉ። አይቴ እክል ወወይን። ሀሎ ውስተ ዐውደ እክል። ወሰምዐ ያዕቆብ ከመ ቦ እክል። ወጸዐኑ እክሎሙ። ቀዳሜ እክል። እክላት
፡ (ሰቈ፪ ፡ ፲፪። ፩ዜና ፡ ፳፩
፡ ፳። ግብ፯ ፡ ፲፪። ዘፍ፵፪ ፡ ፳፮። ዘፀ፳፫ ፡ ፲፮። አቡሻ ፡ ፵፮)።
እኳቴ ፡ ማመስገን፤ መመስገን፤ አመሰጋገን፤ ምስጋና ብፅዓን ቡራኬ። እንተ ደለዎ እኳቴ
፡ (ደራሲ)።
እወ ፡ (ዐረ ኢይ፤ ነዐም። ዕብ ሄን) ነባር አንቀጽና ንኡስ አገባብ። ያዎንታ ቃል፤ ፍችው አወን፤ እውነት፤ በውነት። ቦኑ ቃል እም እግዚአብሔር፤ ወይቤሎ እወ ቦ። እወ እኍየ። እወ እግዚኦ ፍትሖሙ። እወ እግዚኦ አምላከ ኵሉ እወ እግዚኦ አኃዜ ኵሉ እወ እግዚኦ ፈጣሬ ኵሉ። ወይኩን ነገርክሙ እመኒ እወ እወ፤ ወእመኒ አልቦ አልቦ
፡ (ኤር፵፬ ፡ ፲፯። ፊልሞ ፡ ፳። ግንዘ። ቅዳ። ማቴ፭ ፡ ፴፯)። የቀረውን በደቂቅ ርባታ ተመልከት ፡ (ዕር፲፩ ፡ ቍ፺፬)።
እውክክና ፡ ስሕተት፤ ድፍረት፤ ደፋርነት። እስመ በደኃሪ አዝማን ይርሕቁ አሐዱ አሐዱ እምሃይማኖት ወየሐውሩ ድኅረ መንፈሰ እውክክና ወድኅረ ትምህርተ ሰይጣናት ፡ (ፊልክ ፡ ፪፻፵፫)።
እዙዝ ፡ (ዛን ዛት ዝዝት) በቁሙ፤ የታዘዘ፤ የተገባ፤ የተሠራ የተወሰነ፤ የተጣፈ የተነገረ። እዙዝ ውእቱ ከመ ያጥፍእ። ሀቦ ክፍሎ ዘእዙዝ ለከ። በከመ እዙዝ በእንቲኣሆሙ፤ ወዓዲ እዙዝ ውስተ ሕግ። ዘኢእዙዝ በውስተ ሕግ
፡ (ዮዲ፫ ፡ ፰። ሢራ፯ ፡ ፴፩። ኩፋ ፡ ፭። ዲድ
፡ ፲። ቀሌ)።
እዝኅ ፡ (ኃት) [1] ፡ ሻፎ ብልጩት ደንጊያ፤ ቦረቦጭ፤ ሲሰብሩት ስለታም ሱፋጭ ራስ የሚላጭ። እብነ እዝኅ። መጣብሕ ዘእዝኅ። አንሥአ እዴሁ በእዝኅ። ኰኵሐ እዝኅ። ለኰኵሕ ወለእዝኅ
፡ (ኢያ፭ ፡ ፪። ፳፩ ፡ ፵። ኢዮ፳፰ ፡ ፱። ጥበ፲፩ ፡ ፬። መዝ ፡ ፻፲፫)።
[2] ፡ እዝኅ፤
፡ (ኃት) በቁሙ፤ እዥ፤ የደም ውሃ ቅራሪ ጥንፋፊ፤ የመግል ትራፊ ከተበጣ ወይም እሳት ከፈጀው ካበጠ ከቈሰለ ገላ ፥ ከሐዲስና ከሰባራ ሸክላ የሚፈስ።
እዝል ፡ የዜማ ስም፤–ዕዝል፤
እዝናዊ ፡ ዦሯም፤ ዦሯማ፤ ቈሪፍ ባለዦሮ፤ ዦሮ ወዳድ።
እዝን ፡ (ብ እዘን፤ አእዛን። ዕብ ኦዜን። ሱር ኣዝና። ዐረ ኡዝን) ዦሮ፤ መስሚያ ማድመጫ፤ መያዣ መጨበጫ የመሣሪያ።
፡ (ተረት) የነገር ጣዕም በዦሮ የእኽል ጣዕም በጕረሮ። እዝን ይፈልጥ ነገረ ወጕርዔ ይጥዕም እክለ። ሰማዕነ በእዘኒነ። አጽምሙ አእዛኒክሙ
፡ (ኢዮ፲፪ ፡ ፲፩። መዝ ፡ ፵፫። ኪዳ)።
እዝዝ ፤–ጽንዕ ፡ ኀይል
፤–ዕዘዝ
ዐዘዘ።
እዩኅ ፡ (ኃን ኃት ይኅት) ዝናም ያጠፋው ያሰጠመው፤ ውሃ የበላው።
እዩይ ፡ (ያን ያት ይይት) የተመሳሰለ፤ የተካከለ፤ የተነጻጸረ፤ ልኩና መልኩ አንድ የኾነ፤ ብልጫ ልዩነት የሌለው። እዩየ ግጻዌ ዘእንበለ ፍልጠት ወዕሩየ መለኮት። ዕሩያን በአካል ወእዩያን በሡራኄ ወበጸዳል
፡ (አርጋ ፡ ፫። ቅዳ። ቄር)።
እደ ኀጺን [1] ፡ የብረት እጅ። በሰው እጅ አምሳል የተሠራ ብረት፤ የሰማዕታት መሣቀያ። ገብሩ አምሳለ እድ ወአጻብዕ ዘኀጺን። በእደወ ኀጺን እንዘ ይጸፍዕ ገጾ
፡ (ስንክ ፡ ሐም፭። ግን፳፭)።
[2] ፡ የሐኪም መሣሪያ፤ መመርመሪያ። የፙርት የጥንቈላ ብረት መሰግላን የሚያፙርቱበት። እድ ዘኀጺን ዘየሐትት ዘውስተ ከርሥ
፡ (ስንክ ፡ ጥር፲፭)።
እደ መንሠግ ፡ የመዝጊያ እጀታ፤ ወይም የመወርወሪያው፤ ለመክፈት ለመዝጋት የሚያዘው
፡ (ማሕ፭ ፡ ፭)።
እደ ሰናስል ፡ ፍንጅ፤ የሰንሰለት እጅ፤ እስርና ቍራኛ በየክንዳቸው የሚያገቡት
፡ (መዝ፻፵፱)።
እደ ሰይፍ ፡ አፈ ሰይፍ፤ ስለት አንደበት፤ ወይም ውላጋ እጀታ መክድ
፡ (መዝ ፡ ፷፪)።
እደ አቤሴሎም ፡ ታላቅ ሐውልት፤ አቤሴሎም ለስሙ ማስጠሪያ ያቆመው፤ ኋላም የተቀበረበት። ምስጢሩ ቦታ ማለት ነው
፡ (፪ነገ ፡ ፲፰ ፡ ፲፰)።
እደ አትሮንስ ፡ ድጋፍ መከዳ፤ የመንበረ መንግሥት ጌጥ፤ የንጉሡ እጆች የሚረክዙት የሚመረኰዙት። ለመጽሐፍ ሲኾን ግን መልሕቅ ያሰኛል፤ አትሮንስን እይ
፡ (፫ነገ ፡ ፲ ፡ ፲፱)።
እደ ኲናት ፡ የጦር አንደበት፤ ቅጠሉ ጫፉ ሹሉ ውልብልቢቱ፤ ወይም ዛቢያው ሶማያው።
፡ (ተረት) በጋሻው ዕንብርት በጦሩ አንደበት በፈረሱ ዐንገት ፡ (ኤር፲፰ ፡ ፳፩)።
እደ የማን ፡ የቀኝ እጅ፤ የቀኝ ወርች በግራ አንጻር ያለ
፡ (ሢራ፳፩ ፡ ፳፩)።
እደው አእዳው ፡ (ዋት) እጆች፤ የገላ ቅጥዮች፤ ዐጽቆችና ክንፎች። እደው ኹለት ፥ አእዳው ብዙ ፥ አእዳዋት የብዙ ብዙ። እበን ዕፀው ቍየጽ እገር ዕየን እዘን፤ እንደዚህ ያለ ይህን የመሰለ ስም ኹሉ ፥ መነሻው መድረሻው ሳድስ ኹኖ መካከሉ ግእዝ፤ ዘውግ ይባላል። ኹለትም አራትም ቢኾኑ ከዚያም ቢበዙ ፥ ተባብረው ተጫፍረው ተነጻጽረው ባንድ ቦታና ባንድ ገላ ብቻ ያሉትን ያሳያል። ቀነዉኒ እደውየ ወእገርየ። ሰፍሐ እደዊሁ ለሕማም። ኦ አእዳው እለ ለሐኳሁ ለአዳም ተቀነዋ በቅንዋት
፡ (መዝ ፡ ፳፩። ቅዳ ፡ ዲዮ። አፈ)።
እዱም ፡ (ማን ማት ድምት) ያማረ ያጌጠ የተዋበ ውብ፤ መልካም፤ ደመ ግቡ። ሶበ ሖረ በፍኖት ርእየ እዱመ ብእሴ ለቢሶ አልባሰ ጸዐዳ። እዱመ ዜና። እድምተ ሥን
፡ (ዮሴፍ። አዋል)።
(ጥ) እዳው ፡ (ዋት) ጕድፍ፤ ጥራጊ፤ ሐመድ፤ ርካሽ ሣር ገለባ፤ ፍግ ዐዛባ። ገደፍኩ ኵሎ ወረሰይክዎ ከመ እዳው። ይከውን ኵሉ ዓለም በኀቤሁ ከመ እዳዋት ወከመ ኵስሕ። ኢይገሩ እዳዋተ
፡ (ፊልክ፫ ፡ ፰። አፈ ፡ ተ፲፰። ፍ ፡ ነ ፡ ፴፯። ኢሳ፴ ፡ ፳፪)።
እድ [1] ፡ (ዕብ፤ ሱር፤ ያድ። ዐረ የድ) እጅ፤ የገላ ክንፍ፤ መሥሪያው መሣሪያው፤ ከመትከፍት እስከ አጽባዕት፤ እንደ እግር ፫ ክፍል ያለው፤ ጡንቻ ክንድ መዳፍ። እዴየ ከ ኪ ሁ ሃ፤ እዴነ፤ ክሙ፤ ክን ሆሙ ሆን እያለ እንደ ኀበ በኃምስ ይዘረዝራል። ምስጢሩ ሥራን መደብ አድርጎ ኀይልና ሥልጣንን ያሳያል። አትሕቲ ርእስኪ ታሕተ እዴሃ። በእድ ጽንዕት። እድ ፅቡስ። ኵሉ እድ ይደክም። እድ ቦሙ ወኢይገሱ። ደይ እዴከ ላዕለ እዴየ። መጥወኒ እዴከ፤ ወመጠዎ እዴሁ። ከለባት ይበልዕዋ ለበትረ እዴነ ኤልዛቤል ፡ (ዘፍ፲፮ ፡ ፬። ዘፀ፮ ፡ ፩። ሢራ፳፭ ፡ ፳፫። ኢሳ፲፫ ፡ ፯። መዝ ፡ ፻፲፫። ዘፍ፳፬ ፡ ፪። ፬ነገ ፡ ፲ ፡ ፲፭። ቅኔ)።
[2] ፡ ቃል፤ አፍ፤ አንደበት። ወገብረ እግዚ ላዕሌከ በከመ ነበበ በእዴየ። ዘነበበ በእደ ኤርምያስ ነቢይ። ወኮነ ቃለ እግዚ በእደ ሐጌ ነቢይ። አምኑ በእደዊሃ
፡ (፩ነገ ፡ ፳፰ ፡ ፲፯። ኤር፵፬ ፡ ፪። ሐጌ፩ ፡ ፩። ስንክ ፡ መስ፳፯)። እድ ቃል መባሉ አፍ ሲናገር እጅም እንደ ምላስ ይሠራልና ከቃል ጋራ ተባባሪነት ስላለው ነው። አንሥአ እዴሁ ጳውሎስ
፡ (ግብ፳፮ ፡ ፩)።
[3] ፡ ወርች፤ የፊት እግር፤ የእንስሳትና የአራዊት።
፡ (ተረት) ወርች የረገጠው እግር አይስታው። ዘየሐውር በእደዊሁ። ላጽቂት ዘበእደዊሁ የሐውር ፡ (ዘሌ፲፩ ፡ ፳፯። ምሳ፳፬ ፡ ፳፫)።
[4]እድ
፤ ጐን
ሕፅን ፤
ቅርብ አጠገብ
የቦታ አዋሳኝ
ጎረ ቤት
ድንበረተኛ ፤
ቀበሌ አውራጃ
ግድም ገደማ።
ኀበ እደ
ኤማት። መንገለ
እደ ማየ
ባሕር። በእደ
ባሕር (ሕዝ፵፰ ፡
፩።
ኵፋ ፡ ፰ና ፡
፲።)።
[5]እድ
፤ ክፍል
፤ የክፍል
ስም። የኀልቅ
ክልኤ እድ
፤ ወይተርፍ
ሣልስተ እዴሃ። ራብዕተ እዴሃ
ለምድር። ትሰቲ
ሳድስተ እዴሃ
ለኢን። ብርሃነ
ዚኣሁ ሰብዐተ
እደ ያበርህ
እምዘወርኅ። ለዝኵ
ሳብዕተ እድ
(ዘካ፲፫ ፡ ፰ ፡
፱።
ራእ፮ ፡ ፰።
ሕዝ፬ ፡ ፲፩።
ሔኖ፸፪ ፡ ፴፯።
ሱቱ፶፬ ፡ ፶፰)።
[6]እድ ፤–እጅ ፥ እጀታ ፤–አዲው አደወ።
እድ ወእድ ፡ ዐቢይና ደቂቅ አገባብ። ፍችውን በወእድ ተራ ተመልከት፤ ሊጣፍ የሚገባው ከዚህ ነበረ፤ ወ በዋዌነት ገብቶ ማርኮ ስለ ወሰደው የወ ጭፍራ ኹኗል።
እድሜ ፡ ቀጠሮ፤–ዐደመ።እድ
፡ ወእድ፤ ዐቢይና ደቂቅ አገባብ። ፍችውን በወእድ ተራ ተመልከት፤ ሊጣፍ የሚገባው ከዚህ ነበረ፤ ወ በዋዌነት ገብቶ ማርኮ ስለ ወሰደው የወ ጭፍራ ኹኗል።
እድሞ ፡ (ዐማርኛ) ያፈር ቤት፤ ግድግዳው የግንብ ፥ ጣራው የንጨት ኹኖ ክዳኑ ዐፈር መሬት፤ እንደ ትግሬና እንዳደሬ ሥራ። የግንብ ዐጥር ቅጥር መካበቢያ፤ ወይም ዐፈር ቃም ካብ።
እድው [1] ፡ ደመኛ ባለጋራ፤–ዐደወ።
[2] ፡ (ዋን ዋት ዱት) የተጠረገ፤ የተኰሰተረ፤ ጕድፍ የሌለበት። ይረክቦ ዕሩቀ ወእድወ ወስርግወ ፡ (ማቴ፲፪ ፡ ፵፬። ሉቃ፲፩ ፡ ፳፭። ሄርማ)።
እገሌ [1] ፡ በቁሙ፤–ገልይ ገለየ፤ አግለየ።
[2] ፡ (ሊት። ዕብ ፍሎኒ። ሱር ፍላን። ዐረ ፉላን) የስም ለውጥና ምትክ፤ ህየንተ ስም፤ በስም ፈንታ የሚነገር ቃል። እከሌ፤ እንቶ(ተ) ኔ፤ እንተን፤ ያ ርሱ፤ አንድ ሰው፤ አንተ፤ ሰውዬ፤ ሰዌ። አካሉ ታውቆ ስሙ ላልታወቀ ለተደበቀ ዐጸፋና በቂ እየኾነ ለሩቅም ለቅርብም ይነገራል፤አከለ በቃ ይላልና፤ እክሌ ቅሉ አካሉን አካላዊነቱን ያሳያል። ሰውዮውን ዐውቆ ስሙን ባለማወቅ ፥ ወይም በመደበቅ ስሙን ሳይጠሩ ግብሩን ለመግለጥ፤ ሰውዮው ሴትዮይቱ፤ አንድ ሰውዬ አንዲት ሴትዮ እንደ ማለት ነው። ሑሩ ኀበ እገሌ። እገሌ እምቤተ እገሌ ውእቱ። አይቴ ሀለዉ እገሌ ወእገሊት። ሤጥኩ በሤጠ እገሌ። ረሳዕነ ግብረ እገሌ ፡ (ማቴ፳፮ ፡ ፲፰። አፈ ፡ ድ፭። ግንዘ። ፍ ፡ ነ ፡ ፴፫ ፡ ፫። ገድ ፡ አዳ)። ሰማዕከኑ ኦ እገሊ። ኢትትአመን ኦ እገሌ ትሕትናሁ። አንተ ሆይ፤ ሰውዬ ሆይ፤ እንተኔ ማለት ነው ፡ (ዮሴፍ)። ጸውዑ ሊተ እገሌሀ ወእገሊተ ቢል፤ ያነንም ያችንም፤ ርሱንም ርሷንም፤ ወንዱንም ሴቷንም ፥ ሴቲቱንም፤ ወይም ባልና ሚስቱን ያሰኛል ፡ (ሱቱ ፡ ዕዝ፮ ፡ ፶፩)። አንዳንድ ጊዜም ቅጽል ይኾናል። እንገት አገሌ። ፈለጥከኒ እምአመትየ እገሊት። ሑር ኀበ እገሊት ሀገር ፡ (ኪዳ። ዮሴፍ። ፊልክ ፡ ፫)። ለሥራና ለመሣሪያ ሲኾን፤ እንትን፤ አንዳች አንድ ነገር ያሰኛል።
እገሌያዊ ፡ (ዐረ ፉላኒ) የእከሌ፤ የእንቶ፤ የርሱ የዚያ፤ ያንድ ሰው። አዘዘ ከመ ኢያንብራ ውስተ መካን እገሌያዊ ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፳፱)።
እገር ፡ እግሮች ለብዙም ለጥቂትም ባንድ ገላ ላሉ ላራትም ለኹለትም ብቻ ከዚያም ለሚበዙ ላምሳና ለሺሕ ይነገራል። ሺ እግር፤ ዐምሳ እግር እንዲሉ። ወይቀውማ እገሪሁ። እገሪሆሙ ይረውጻ። ወድቀ ውስተ እገሪሃ ለዮዲት። ርቱዕ እገሪሆሙ። ዘብዙኅ እገሪሁ
፡ (ዘካ፲፬ ፡ ፬። ምሳ፩ ፡ ፲፮። ዮዲ፲፬ ፡ ፯። ሕዝ፩ ፡ ፯። ዘሌ፲፩ ፡ ፵፪)።
እጉሥታር ፡ ሬት፤–ዕጉሥታር። ዕጉትሣር ፥ ዐገተ።
እግረ መራኁት ፡ የመክፈቾች እግር መያዣቸው መንጠልጠያቸው ቀለበቱ፤ ወይም ሳንቆች የሚቆሙበት መድረክ፤ የመዝጊያ ቍላ ፥ ወንዴው
፡ (አዋል)።
እግረ ማጣ ፡ (ዕብ ሬጌል ሚጣ) የኪሩቤል ስም ፥ ያራቱ ኹሉ። ዘይቤው ያልጋ ሸንኰር የዙፋን እግር ፥ ምስጢሩ ጸወርተ መንበር
፡ (ድጓ። መዋሥ)። ቅዱስ ያሬድ እንዲህ ማለቱ፤ ጌታን በንጉሥ ፥ መንበረ መንግሥትን በኮር በግላስ ፥ ሰማይ ውዱድን ባልጋ በፈረስ፤ ኪሩቤልን ባራት እግሮቹ መስሎ ነው።
፡ (ሕዝ፩ ፡ ፳፮። መዝ፲፯ ፡ ፲፩)።
እግረ ደቂቅ ፡ የሕፃናት መንገድ፤ የልጆች አካኼድ አረማመድ፤ አቱ ሥግራ ታቱ ሥግራ ማለት ፥ ምስጢሩ ጕዞና ማዝገም ነው
፡ (ዘፍ፴፫ ፡ ፲፬)።
እግራዊ ፡ እግራም እግረኛ፤ ዘዋሪ፤ እግረ ብዙ፤ ሺ እግር ዐምሳ እግር የሚሉት ጥቍር ትል።
እግር [1] ፡ (ዕብ ሬጌል። ሱር ሬግላ። ዐረ ሪግል) በቁሙ፤ መቆሚያ መርገጫ፤ መኼጃ መራመጃ፤ ከጭን እስከ ሰኰና፤ እንደ እጅ ፫ ክፍል ያለው። ኪደተ እግረ ብእሲ። ከመ እግር ሙቁሕ። እግር ቦሙ ወኢየሐውሩ። እግረ ሰብእ ወእንስሳ። ክልኤ እግር። ዘአርባእቱ እግሩ ፡ (ሱቱ ፡ ዕዝ፭
፡ ፯። ሢራ፳፩ ፡ ፲፱። መዝ ፡ ፻፲፫። ሕዝ፳፱
፡ ፲፩። ዓሞ፫ ፡ ፲፪። ዘፀ፱ ፡ ፱ )።
[2] ፡ ታች ፥ ታችኛ ሥር። ታሰክቦ ለግኑዝ ኀበ እግረ ታቦት ፡ (ግንዘ)።
[3] ፡ ጫማ ፥ ውስጥ እግር፤ የጥላ መስፈሪያ፤ ከተረከዝ እስካውራ ጣት ጫፍ። ጽላሎት በግንቦት ዕሥራ ወአሐዱ እግር ወመንፈቀ እግር ፡ (አዋል። ቄር)። ግልያን ተመልከት።
[4] ጮራ፤ ጨረር፤ ቀረን ምዕዛር። እግረ አሚር። እገሪሃ ለፀሕይ። በረቀ ሥጋሆሙ ከመ እግረ ፀሓይ ፡ (ጥበ፪ ፡ ፬። ሔኖ፸፭ ፡ ፬። መቃ ፡ ገ፪)።
እግዚአብሔራዊ ፡ የግዜር፤ ግብር ባሕርይ ወይም ወገን እግዜራም ባለግዜር። ገቢረ መንክራት እግዚአብሔራዊ። ሐውጽዎሙ በሕዋጼ እግዚአብሔራዊት በዓላት አግዚአብሔራውያት ፡ (መጽ ምስ። ፍ ፡ ነ ፡ ፮። አቡሻ ፡ ፩)።
እግዚአብሔር ፡ (ዕብ ይሆዋ። ሱር ይያ። ዐረ ረብ። ጽር ወቅብ ኪሪዖስ። ሮማይ ዶሚኑስ) ስመ አምላክ፤ እግዚአ ብሔር፤ እግዚእ ጌታ፤ ብሔር ዓለም፤ በተገናኝ የዓለም ገዥ የዓለም ጌታ፤ ዓለም ሳይፈጠር የነበረ፤ ዓለምን ፈጥሮ የሚገዛ፤ ርሱ ኹሉን ቢያስገኝ ኹሉን ቢገዛ እንጂ ፥ ለርሱ አስገኝና ጌታ የሌለው፤ አበ ዓለም ንጉሠ ዓለም ፥ ወይም እግዚአ ኵሉ ንጉሠ ኵሉ ማለት ነው፤ ባማርኛ እግዜር ተብሎ በ፫ ቅንጣት ፊደል ይጣፋል፤ የአልፋ ምስጢር አለበት፤ ብሔርን እይ። እግዚእ እንደ አዶናይ ማእከላይ ስም ነው፤ ለኹሉ ይኾናል፤ ብሔር ሲጨመር ግን እንደ ይሆዋና እንደ መለኮት ነው፤ ከፈጣሪ በቀር ለማንም ፍጡር አይሰጥም፤ ፍጡር ምንም ቢነግሥ ምንም ቢጌተይ በታናናሽ ክፍል ነውና፤ ያው ቅሉ የፈጣሪ ገንዘብ ነውና ፥ የዓለም ጌታ ሊኾን ወይም እግዜር ሊባል አይቻልም። ጸባኦት በሚልበት ግን ዕብራይስጡ ይሆዋ ጽባኦት እንደሚለው እግዚአ ጸባኦት ቢያሰኝ እንጂ ፥ እግዚአብሔር ጸባኦት አያሰኝም፤ ፍጹም ጸያፍ ነው። የጸባኦት ፍች ኀይላት ሰራዊት ነውና ፥ ከዘርፍ በቀር ቅጽል አይኾንም። ዳግመኛም ዕብራይስጥና ዐረብ ጽርእ፤ አምላክ አምላክ የሚሉትን ኹሉ ግእዝ በብዙ ቦታ እግዚአብሔር ይላል ፡ (ዘፍ፩ ፡ ፩–፲፩። ዮሐ፩ ፡ ፪ ፡ ፮ ፡ ፲፪ ፡ ፲፫)። ይህን የመሰለ ብዙ አለ፤ ይህም ጥንቱን ሲመለስ ቃል በቃል አለመተርጐሙን፤ ኋላም አለመታረሙን ያስረዳል።
እግዚአብሔርና ፡ እግዜርነት አምላክነት፤ እግዜር መኾን።አመ ጽሕቀ ለከዊነ ዕጓለ መሕያው ኢኀደገ እግዚአብሔርናሁ ፡ (መጽ ምስ)።
እግዚኣዊ ፡ (ዝእታዊ ይ) የጌታ የግዜር፤ ጌትኛ።አምሳላት እግዚኣውያት ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፲፬)።
እግዚእ [1] ፡ ጌታ፤–ገዚእ ገዝአ፤ አግዝአ።
[2] ፡ (ኣን ኣት ዝእት) ቅጽልና ጥሬ። የግብርና የክብር የማዕርግ ስም፤ ጌታ ገዥ አዛዥ ሹም ባለቤት መምህር አያት፤ ታላቅ ወንድም። ጎይታይ እንዲል ፡ (ትግሬ)። ገብር ከመ እግዚአ። መኑ ውእቱ እግዚእነ። እግዚአ አጋዕዝት ፡ (ኢሳ፳፬ ፡ ፪። መዝ ፲፩። ፻፵፭)። እግዚእ ብሎ በአልፍ አጋእዝት ማለት ስሕተት እንደ ኾነ አስተውል። አጋዕዝት የአግዓዚ ብዥ ነው እንጂ ፥ የአግዚእ ብዥ እንዳይመስልኽ ግዕዘንና አግዐዘን ተመልክት። የእግዚእስ ብዥ ቢኾን አጋዝእት ይልልኽ ነበር።
እግዚእና ፡ ሥልጣን ሹመት መብት። በቁሙ፤ ገዥነት ጌትነት እግዜርነት። መንግሥት ወእግዚእና። ወይትአመን በእግዚእናሁ። እግዚእናሁ ላዕሌሃ ፡ (ቄር። ፍ ፡ ነ ፡ ፲፬። ፶፩)።
እግዚኦ ፡ የጩኸትና ያቤቱታ የምልጃ የልመና ቃል፤ በቅርብ ባጠገብ ፊት ለፊት ላለ ለሚያይ ለሚሰማ የሚነገር፤ አቤቱ ቶ፤ እግዜር ሆይ ጌታ ሆይ ጌቶ። እግዚኦ መሐረነ ክርስቶ። ሙያው እንደ እግዚእ ነው፤ ቅጽልና በቂ ይኾናል። እግዚአብሔር እግዚኦ። እግዚኦ ኢየሱስ ክር፤ ቅጽል።ስምዐኒ እግዚኦ ጸሎትየ፤ እግዚኦ ጸራሕኩ ኀቤከ፤ በቂ።
እግዝእተ ጌ ፡ እተጌ፤ የንጉሥ ሚስት ንግሥተ ምድር፤ ሐፄጌን እይ።
፡ (ግጥም ስለ ራስ ዐሊ እናት) እኛስ እንላለን እተጌ መነን፤ ዐሊ ማን ይላታል ሲጠራ እናቱን።
እግዝእት ፡ (ታት) እመቤት ወይዘሮ፤ ሴት አያት ታላቅ እኅት። እመይተይ እንዲል ፡ (ትግሬ)። አዘዘ ኢይስምይዋ ለረሲስ እግዝእተ። አመት ለእመ አውፅአት እግዝእታ። ለኅሪት ወለእግዝእት ፡ (ዮሴፍ። ምሳ፳፬ ፡ ፶፰። ፪ዮሐ ፡ ፩)።
እጓል ፡ ልጅ፤–ዕጓል።
እጠስ ፡ ንጥሻ፤–ዐጠሰ።
እፉይ ፡ (ያን ያት ፊት) የተጋገረ፤ የበሰለ፤ ትኵስ። ኅብስት እፉይ ዘእንበለ ግማኔ
፡ (መጽ ፡ መስ)።
እፎ ፡ (ዐረ ከይፈ። ዕብ ኤካ፤ ኤኽ) ንኡስ አገባብ። እንዴት ፥ እንደ ምን
፡ ምን ምንኛ፤ ምን ያኽል ስንት፤ ለምን ስለ ምን ፥ ምነው ፥ ረግ ይኾናል፤ የአንክሮና የጥያቄ ቃል ነው። በ ኬ መ ኑ እንጋ እያጋነኑት፤ ሳያጋንኑትም ብቻውን ፥ አንዳንድ ጊዜም በደጊመ ቃል ይነገራል። እፎ ኮነት ዘማ ሀገረ ጽዮን። እፎ ኀደጋሁ ለአቡከ። ኦ ሞት እፎ ዝክርከ መሪር። እፎ ተሰባሕከ ኤልያስ። ጽልመትከ እፎ። እፎ ኢተአምሩ፤ ለምን ፡ (ኢሳ፩ ፡ ፳፩። ጦቢ፲፩ ፡ ፩። ሢራ፵፩ ፡ ፩። ፵፰ ፡ ፬። ማቴ፮ ፡ ፳፫። ሉቃ፲፪ ፡ ፶፮)። ምነው ፥ ረግ ሲኾን ድንጋፄና ሐዘን ያሳያል። እፎ ምንተ ኮንከ፤ እስመ ሕዙነ እሬእየከ፤ ምነው ምን ኹነኻል። እፎ ሞተኑ ዝኩ ሕፃን፤ ረግ፤ ያ ብላቴና ሞተን እያሰኘ ጥያቄን ሳይለቅ ይነገራል። ካጋናኞችና ካዳማቆች ጋር ሲነገር፤ በእፎ ኢዐቀብከ፤ እፎኬ እፎኢ፤ እፎመ፤ እፎኑመ፤ እፎ እንጋ፤ እፎ እንከ ፈድፋደ እያለ ይገባል።
እፎ እፎ እፈፎ እፎ ፡ (ዕብ ኤካካህ) እንዴት እንዴት፤ ምን፤ ምን ምንኛ። እፎ ትቤ። በል እፈ እፎ
፡ (ቄር ፡ ጰላ)።
እፎያዊ ፡ (ዊት። ሱር አይፋናዩታ። ዕብ ኤኩት። ዐረ ከይፊየት) ጥሬና ቅጽል፤ እንዴት ያለ፤ እንደ ምን ያለ፤ ምን የመሰለ፤ የሚያስፈራ የሚያስጨንቅ፤ ወይም የሚያስደንቅ። ወእፎያዊት ተቃትሎት
፡ (ፊልክ ፡ ፺፭። ፻፲)።
ኦ [1]:-ስመ አምላክ፤–ዖ አልፋ ወዖ።
[2] ፡ (ንኡስ አገባብ) ሆይ፤ ወዮ ወየው፤ ምን፤ ይብላኝ። በምስጢር ቃለ ጽዋዔ ወአንክሮ፤ ቃለ አክብሮ ወአፍቅሮ፤ ቃለ ብካይ ወስቈቃው፤ ቃለ አኅስሮ ወአፍርሆ፤ ቃለ አራኅርኆ ይኾናል። ፍችውንና ምስክሩን በቦታው ተመልከት
፡ (ዕር፳ ፡ ቍ፺፬)።
ኦሄል ፡ (ዕብራ) ድንኳን፤ የድንኳን ስም።
ኦሆ ፡ ነባር አንቀጽ፤ የትሕትና የተአዝዞ ቃል። ዕሺ በጎ፤ በጄ፤ ይኹን፤ አደርጋለኹ፤ ምስጢሩ እንደ መሐላ ነው። ወይቤሉ ኦሆ ናገብእ ሎሙ በከመ አዘዝከነ ከማሁ ንገብር። ኢትበልዎ ኦሆ ለፍትወቱ። ኦሆ ብሂልየ ለመማክርትየ። ኦሆ በሃሊት። ኦሆ በልነ። በእንተ ኦሆ ብሂሎቱ ወትሕትናሁ
፡ (ነሐ፭ ፡ ፲፪። ሮሜ፮ ፡ ፲፪። አስቴ ፡ ፫። ዳን፩ ፡ ፳። ያዕ፫ ፡ ፲፯። ፊልክ ፡ ፻፳፱)።
ኦሆሊባ ፡ ድንኳኔ በርሷ፤ ድንኳኔ። ኦን ትቶ ሀላ ወሀሊባ ይላል፤ ግድፈት ነው። ኦሆላ ሰማርያ፤ ኦሆሊባ ኢየሩሳሌም
፡ (ሕዝ፳፫ ፡ ፩–፬)።
ኦሆላ ፡ ድንኳኗ፤ ድንኳንነቷ።
ኦሪታዊ ፡ የኦሪት፤ ኦሪታም፤ ባለኦሪት፤ ይሁዲ ፈላሻ። ኦሪታዊት ጠረጴዛ
፡ (መጽ ፡ ምስ)።
ኦሪት [1] ፡ (ሱር ኦራይታ። ዕብ ቶራ። ዐረ ናሙስ። ጽር ኖሞስ) በቁሙ፤ ሕግ፤ ፍትሕ፤ ትእዛዝ፤ ዐሠርቱ ቃላት። ፍትሕ ፥ የወል የመካከል። ሕግ ፥ አታድርግ አታድርግ። ትእዛዝ ፥ አድርግ አድርግ የሚለው። ባለብሉዮች ግን ዜና ፥ ብርሃን ፥ ስምዕ ፥ ደብር ፥ መደብር ብለው ይጨምሩበታል። እስመ ኦሪት በሙሴ ተውህበት ለነ። ኦሪትነኑ ትኴንኖ ለሰብእ። ታቦት እንተ ውስቴታ ኦሪት
፡ (ዮሐ፩ ፡ ፲፯። ፯ ፡ ፶፩። ዕብ ፡ ፱
፡ ፬)።
፡ መጽሐፍ ፤
የመጽሐፍ ስም ፤
ሙሴ የጻፈው
ዐምስቱ ክፍል
ወይም ዐምስቱ
ብሔር። ኦሪት
ወነቢያት ሰበኵ
በክርስቶስ። መምህረ
ኦሪት። ብሔረ
ኦሪት (ሃይ
፡ አበ።
ግብ፭ ፡
፴፬። አብጥ)። ከኦሪት
ጋራ ዐብረው
የሚጣፉ ኢያሱ
መሳፍንት ሩት
እሊህ ሦስቱ
፥
መጽሐፍ እንጂ
ኦሪት አይባሉም ፤
በግእዝ ልማድ
ግን አለስማቸው
ኦሪት ይባላሉ።
ሰመንቱ በሓውርተ
ኦሪት። ኦሪት
ዘኢያሱ። ኦሪት
ዘመሳፍንት። ኦሪት
ዘሩት።
[2] ፡ በቁሙ፤–አረየ፤ ኦራይታ።
ኦሪጋ ፡ (ጽር። ዕብ አቆ። ሱር ያዕላ። ዐረ ወዕል) ሳላ፤ የቦኸር ወገን፤ ቀንዳም ቀንደ ረዥም፤ ብዕዛን ተመልከት፤ ከዚህ ጋራ አንድ ነው። ባለብሉዮች ግን ሠሥ ሠሣ ይሉታል። ውዕላ ወኦሪጋ
፡ (ዘዳ፲፬ ፡ ፭)። ወረጋ ወሪጋ ማለት ከዚህ ወጥቷል። ወረጋ፤ ሌጣ ያልተጫነ ከብት። ወሪጋ፤ ቈንዦ መልከ ቀና ሴት።
ኦርቶዶክሳዊ ፡ ዝኒ ከማሁ፤ የኦርቶዶክስ ወገን፤ ኒቅያዊ፤ እውነተኛ፤ ቅን፤ በሃይማኖቱ ሐሰትና ስሕተት ጽነት የሌለበት። ይኩን ምእመነ ኦርቶዶክሳዌ። ሃይማኖት ኦርቶዶክሳዊት
፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፵፫ ፡ ፪። ያዕ ፡ ዘእል)። ብዙ ሰዎች ይልቁንም ካራና ቅባት ባህላቸውና ትምርታቸው ከቅዱስ መጽሐፍ የሚጣላ ስሕተት የተመላ ክፉ ጥፉ ሲኾን ኦርቶዶክሶች ነነ ይላሉ። ፡ (ሥላሴ ዘድንቆ ማርቆስ ኦርቶዶክሳዊ)። አርዮስ ወመምህሩ ላዕለ ሐዋርያት አመክነዩ ብሂለ ፍጡር ወልድ በቀዳማዊ ልደቱ፤ ለአጽድቆ ሕልም ነገሮሙ ከንቱ። ዮምኒ ይፈጽም ዐመፃ በመስፈርተ እሉ ክልኤቱ ፥ እንዘ ፍናዊሃ በኍልቈ ቤቱ ፥ ሰብእ ኵሉ ለሃይማኖቱ ፥ ይቀብዓ ስመ ምእት ሠለስቱ። የኦርቶዶክስ ባህል እንዴት እንደ ኾነ በተዋሕዶ ፍች ተመልከት ፡ (ዋሕዶ ፡ ዋሐደ)።
ኦርቶዶክስ ፡ (ጽርእ) ስመ ጉባኤ፤ የኒቅያ ማኅበር፤ ኦርቶ ፥ ርቱዕ፤ ዶክስ ፥ ባህል ሐሳብ ኅሊና፤ ስብሐት ምስጋና ይኾናል፤ በተገናኝ ርቱዐ ሃይማኖት ማለት ነው፤ ደኩስበተሪን ተመልከት። መጽሐፍ ግን በኦርቶ ፈንታ አርቶ ይላል፤ የጣፊ ስሕተት ነው።
ኦርያ ፤
(ጽር ኦራያን) ፤ የሕንጻ
ስም ሠናይት ፤
ስርጉት ፤ ውብ
መልካም። የሐዲስ
መምራን እድምተ
ሥን ፤
ሠናይተ ሡራሬ
ይሉታል (ግብ፫ ፡
፪)።
ኦርያሬስ [1] ፡ (ዕብ ኦር ሔሬስ) ፀሓይ፤ ስመ ፀሓይ፤ ሥዕለ ፀሓይ፤ ኦር ጸዳሉ ብርሃኑ ቀርኑ ምዕዛሩ፤ ያሬስ ሰሌዳው ክበቡ። ቶማስን ተመልከት
፡ (ሔኖ፸፰ ፡ ፩)። ኦርያሬሰ ሰማይ ልብስኪ ወአሣእንኪ እብላ። ሰላም ለአንጣዎስ ለሃይማኖቱ ዘአጽደላ እምኦርያሬስ ወእብላ። እምታስግዱ ብርከ ለኦርያሬስ ፡ (ደራሲ። ስንክ ፡ ነሐ፲፯። ኅዳ፬)።
[2] ፡ ፀሓይ፤–አወር ኦር።
ኦኦ ፡ (ጽር ዖዖ። ዕብ ሆይ ሆይ። ዐረ ያያ) የጩኸት የቡታ የሪታ ቃል፤ በቁሙ ወይም ኡኡ ዎዎ ወዮ ወዮ፤ ሆይ ሆይ። ኦኦ ጕዩ እምብሔረ ሰሜን
፡ (ዘካ፪ ፡ ፮)። አንዳንድ መጣፍ ግን ከጣፊ ስሕተት የተነሣ አአ፤ ኦአ ወይም ኹሉን ትቶ ጕዩ ይላል። በኦኦ ፈንታ አአ ወይም ኦአ ማለት ስሕተት፤ ኹሉን መተው ግድፈት ይባላል።
No comments:
Post a Comment