ሀ ለ ሐ መ ሠ ረ ሰ ሸ ቀ በ ተ ቸ ኀ ነ ኘ አ ከ ኸ ወ ዐ ዘ ዠ የ ደ ጀ ገ ጠ ጨ ጰ ጸ ፀ ፈ ፐ
ጰ ፡-ትርፍ ዲቃላ ፊደል፤ በመልክ በተራ ፳፭ኛ፤ መልኩ ከጸ ድምፁ ከበ የተዴቀለ፤ ስሙ ጴት ጰይት፤ ይኸውም ቤት በይት እንደ ማለት ነው። ቍጥሩ ፯፻፤ አኃዝ ሲኾን ጰ ሰብዐቱ ምእት ይባላል፤ ያቡጊዳን አኃዝ ተመልከት። የኋላ ሰዎች በራሱ ላይ ነቍጣ ጨምረው ጸን ጰ ብለውታል፤ ከግእዝ በፊት በነበረው በሳባ ፊደል ግን ዲቃልነቱና ድርብነቱ በመልክም በድምፅም የበ ብቻ ነበር፤ የቀድሞ ቅርጹ አሠራረዙ እንዴት እንደ ኾነ፤ ፀንና የዐጰ ዐን ፍች ተመልከት። ጰና ፐ ምንም ኹለት ዐይነት ቢኾኑ በምስጢር አንድ ኅርመት ናቸው፤ ጰ ሲላላ ፐ፤ ፐ ሲጠብቅ ደግሞ ጰ ይባል ነበረ ይባላል። ይኸውም ሊታወቅ በጰና በፐ የሚጣፍ ቃል ኹሉ፤ በጽርእና በቅብጥ በሮማይስጥ በዕብራይስጥም ፐ ኹኖ ይገኛል። ጰና ፐ ለግእዝ ቋንቋ በውድ እንጂ በግድ አይፈለጉም፤ እንሆ ዐረቦች ጴጥሮስ ጳውሎስ ጲላጦስ፤ ወይም ፔትሮስ ፓውሎስ ፒላቶስ በማለት ፈንታ ቡጥሩስ ቡሉስ ቢላጦስ ይላሉና፤ ዕብራውያንም ፌጥሮስ ፎሉስ ፊላጦስ ይላሉና፤ ለግእዝም በጰና በፐ ፈንታ በ፤ ወይም ፈ ይበቃው ነበር። ከጽርእና ከቅብጥ ከሮማይስጥ ቃል የመጣ የውጭ አገር ቋንቋ ያልተተረጐመ ፍጹም ጥሬና ነባር ስም፤ ወይም ጋላና ወላሞ ካልኾነ በቀር ለግእዝና ላማርኛ ለትግሬም ለትግሪኛም ጰንና ፐን የሚያስፈልግ ቃል የለም፤ አይገኝም። ከጥንቅ የነበረ የግእዝ ፊደል አለመኾኑ ፥ የኋላ ቅጥል መኾኑ ዲቃልነቱ በዚህ ይታወቃል። ጰ በጋልኛ ተርፏል፤ ፐም በወላምኛ ይገኛል፤ ጋልኛ ግን ሴማዊና ሳባዊ ይመስላል።
ጰላሞን ፡-ስመ ሰብእ።
ጰላጢኖስ ፡-(ጽር፤ ፕላታኖስ) የዛፍ ስም፤ አንድ ዐይነት ዛፍ፤ ታላቅ ገናና እንደ ዋርካና እንደ ዘግባ ያለ። ባለብሉዮች ግን ለይተው ሾላ ብሳና ለውዝ ገውዝ ይሉታል። ኖኅኩ ከመ በቀልት፤ ወዐበይኩ ከመ ጰላጢኖስ ፡-(ሢራ፳፬ ፡-፲፬)።
ጰራልያ ፡-(ጽር ፓራሊዮስ) የባሕር ዳር፤ ጽንፍ ጠረፍ፤ ወደብ ገደብ፤ አጠገብ ጎረ ቤት። ጰራልያ ዘምድረ ከነዓን። ሰብአ ጰራልያ ፡-(ዘዳ፩ ፡-፯። ኢያ፲፩ ፡-፫። ሕዝ፳፭ ፡-፲፮)።
ጰራቅሊጦስ ፡-(ጽር ፓራክሊቶስ። ዕብ ፕራቅሊጥ) አማላጅ አስታራቂ፤ አፍ ጠበቃ፤ ትርጁማን አምጃር፤ እያጣፈጠ የሚናገር፤ ስብቅል ካፉ ማር ጠብ የሚል። ወእመኒ ቦ ዘአበሰ ብነ ኀበ አብ ጰራቅሊጦስ ኢየሱስ ክርስቶስ ጻድቅ። ወአፉየ ሙሴ ለእመ ኮነ ጸያፈ፤ ጰራቅሊጦስ አሮን ይኩነኒ አፈ ፡-(፩ዮሐ ፡-፪ ፡-፩። ደራሲ)።
፡-ናዛዚ መጽንዒ፤ መስተፍሥሒ፤ መንፈስ ቅዱስ። በዓለ ኀምሳ፤ የትንሣኤ ዐምሳኛ የዕርገት ዐሥረኛ፤ እሑድ ቀን የሚውል። እስእሎ ለአብ ይፈኑ ለክሙ ጰራቅሊጦስሀ ካልአ። ወቡሩክ መንፈስ ቅዱስ ጰራቅሊጦስ መጽንዔ ኵልነ። ዕለተ ጰራቅሊጦስ ዘውእቱ ተፍጻሜተ ኀምሳ ፡-(ዮሐ፲፬ ፡-፲፮። ቅዳ። አቡሻ ፡-፴፰)።
ጰንገለ [1]፡-(ጽር አፓንጌሊን፤ ገንጰለ) ቀዳ፤ መለሰ፤ ተረጐመ፤ ገለበጠ፤ ጣፈ። አነበበ፤ አየ አስተዋለ፤ ተመለከተ፤ የመጽሐፍ። መጽሐፍ ግን በጰንገለ ፈንታ እንደ ጽርኡ አጰንገለ ይላል፤ አያሰኝም። ዘያጰነግል መጻሕፍተ እግዚ ዘብሉይ ወዘሐዲስ። ይደልዎ ለኤጲስቆጶስ የኀሊ ተሓሥሦ ወአጰንግሎ መጻሕፍት በበ መትልው። ፈከረ ሐዲሰ ወአጰንገለ ብሉየ። አጰንገለ ሎሙ መጻሕፍተ በነገረ ብሔሮሙ፤ መለሰ ፡-(ቀሌ። ዲድ ፡-፬። ስንክ ፡-ኅዳ፮። አዋል)። ያጰነግሉ መጻሕፍተ። ውስተ ጸሎታቲሆሙ ወአጰንግሎቶሙ። ይደሉ ለውጡናን ከመ ያብዝኁ አጰንግሎ ውስተ ትእዛዛት ወውስተ ትሩፋት፤ ተመለከተ ፡-(ሥር ፡-ጳኵ። ፊልክ ፡-፸፫። ፻፵፯)።
[2]፡-(ፈንገለ) ፈነገለ፤ ፈንጋይ ኾነ። ገንጰለን እይ።
ጰንጋሊ መጵንግል ፡-የሚቀዳ የሚመልስ፤ አንባቢ ተመልካች። መጰንግል ዘይቤ ተርጓሚ ወአንባቤ መጽሐፍ በቃል ፡-(ጥሬ ፡-ሰዋ)።
ጰንጠቆስጤ ቴ ፡-(ጽር ፔንቲኮስቲ) በዓለ ኀምሳ፤ የፋሲካ ዐምሳኛ፤ በዓለ ሠዊት፤ ጰራቅሊጦስ። በዓለ ጰንጠቆስጤ ቅድስት። መዋዕለ ጰንጠቆስጤ። ሰላም ለድሜጥሮስ ሐጋጌ አጽዋም እምስቴ፤ ወሠራዔ መብልዕ በጰንጠቆስቴ ፡-(ጦቢ፪ ፡-፩። ግብ፪ ፡-፩። ፳ ፡-፲፮። ስንክ ፡-ጥቅ፲፪)።
ጰንጤን ጳንጦስ ፡-(ጽር ፖንቶን) ስመ ሀገር፤ በእስያ ውስጥ ያለች ፡-(ማቴ፳፯ ፡-፪። ፩ጴጥ ፡-፩ ፡-፩)።
ጰይት ጴት ፡-ስመ ፊደል፤ ጰ። በዪት ቤት ማለት ነው፤ ጰና በ አንድ ወገን ናቸው። ጰንጠቆስቴ ጰራቅሊጦስ ብለውም የሚፈቱ አሉ።
ጲላጦስ ፡-ስመ ሰብእ።
ጲክሶን ፡-(ጽር ፒክሶስ) እሾኻም ዛፍ፤ ግራር፤ የግራር ዐይነት። ሰጢንን ተመልከት፤ ከዚህ ጋራ አንድ ነው። ብሔረ አርዝ ወዕፀ ጲቅሶን ፡-(ኢሳ፵፩ ፡-፲፱)።
ጳሒን ፡-( ቅብጥ ፓዖኒ) ስመ ወርኅ፤ ሠኔ። በኡናህን እይ፤ ከዚህ ጋራ አንድ ነው ፡-(ስንክ ፡-ሠኔ፲፱)። ዳግመኛም በጳሒን ፈንታ ጵዮን ይላል፤ ፍችው አንድ ነው ፡-(መጽ ፡-ምስ)።
ጳልቃን ፡-(ጽር ፔሌካን) ርኩም። ቀቀኖን ተመልከት፤ ከዚህ ጋራ አንድ ነው። መምህራን ግን የከራድዮንንዕ ለጳልቃን ሰጥተው ይፈታሉ። ከራድዮንን እይ።
ጳሲካ ፡-(ጽር ፓስኻ) ፍሥሕ፤ ፋሲካ። ወይገብሩ ጳሲካ ፡-(ኩፋ ፡-፵፱። ፶)።
ጳስጦፎርያ ፡-(ጽር ፓስቶርዮን) የዕቃ ቤት፤ ቤተ መዛግብት ፡-(ኤር፴፭ ፡-፬)።
ጳሬኑ ፡-(ጽር ፓሪኑ) ፡-(907) ፡-(ጽር ፓሪኑ) ጥሩ ደንጊያ፤ ፍጹም ነጭ፤ የእብነ በረድ ዐይነት። ዕንቍ፤ የዕንቍ ስም።
ጳኵሚስ ፡-(ቅብጥ ፓኹም) ስመ ሰብእ፤ ዐቢይ መንኮስ፤ የእንጦንስ ሦስተኛ፤ እንጦንስ መቃርስንና ጰላሞንን፤ ጰላሞን ጳኵሚስን፤ ጳኵሚስ ቴዎድሮስን፤ ቴዎድሮስ አረጋዊ ዘደብረ ዳሞን ይወልዳል። ጳኵሚስ ፵ ዘመን ምሉ አበ ማኅበር ኹኖ የኖረ ነው። ራእይ ዘአባ ጳኵሚስ። ሥርዐተ ጳኵሚስ።
ጳኵምስ ፡-(ቅብጥ ፓኾን፤ ፓሾንስ) ስመ ወርኅ፤ ግንቦት ፡-(ስንክ ፡-ሠኔ፲፱)።
ጳኵሲማ ፡-(ጽር ፓክሳማስ። ዕብ ፓክሳም) ደረቅ ዳቦ፤ ኵርኵሪት፤ የለከት የብስኩት ዐይነት፤ እንዳይነቅዝና እንዳይሻግት ታምሶ ተጠብሶ ብዙ ቀን የሚኖር የመነኮሳት ምግብ። ክልኤቱ አእሩግ ዐደዉ ፈለገ ወነበሩ ይብልዑ፤ ወጠምዐ አሐዱ እምኔሆሙ ጳኵሲማሁ፤ ወይቤሎ ካልኡ ለምንት ታርሕሳ ወታስተፌሥሖ ለልብከ። በዕለተ ሰንበት ይበልዕ አሐደ ጳኵሲማ። ወይትሜጦ አሐደ ጳኵሲማ እምኅብስት ወሐምል ፡-(ፊልክ ፡-፸፰። ስንክ ፡-ታኅ፲፭። ፲፯)።
ጳውሎስ ፡-(ጽር ፓፍሎስ። ሮማይ ፓውሉስ) ንኡስ፤ ትንሽ።
ጳውቄና ፡-(ጽር ዝፍኪና) ዕንጨት፤ ሉሕ ጠርብ የሚኾን፤ የሚቃነጥ የሚቀረጥ፤ እንደ ጥድ እንደ ዘግባ ያለ። ባለብሉዮች ግን ለይተው ጥድ ኵሓ ይሉታል ፡-(፫ነገ ፡-፭ ፡-፱። ፮ ፡-፲፭ ፡-፴። ፱ ፡-፲፩። ፪ዜና ፡-፪ ፡-፰)።
ጳዝዮን [1]፡-(ጽር ቶፓዚዎን) ብጫቴ ዕንቍ፤ ወራውሬ ፡-(ዘፀ፳፰ ፡-፲፯። ፴፮ ፡-፲፯። ሕዝ፳፰ ፡-፲፫)። በወራውሬ ፈንታ ጳዝዮን በጳዝዮን ፈንታ ወራውሬ ይላል ፡-(ራእ፳፩ ፡-፩)።
[2]፡-(ዕብ ፓዝ። ጽር ቶፓዚዮን) ፋዝ፤ የአፌዝ ወርቅ፤ ጥሩ ወርቅ። ፎዘን ተመልከት። እምወርቅ ወእምጳዝዮን ፡-(መዝ ፡-፻፲፰)።
ጳጕሜን ፡-(ጽር ሄፓጎሜኔ) በቁሙ፤ ቈግሜ፤ ጭማሪ ተውሳክ፤ ፭ ቀን ተሩብ። ኹለተኛም ከፀውደ ወርኅ ስለ ተረፈና ባመት መጨረሻ ስለ ተገኘ ተረፍ ይባላል። ሩቡ ደግሞ ባራተኛ ዓመት ይመላና ፭ የነበረው ፮ ይባላል፤ ይህም ስድስተኛ ጳግሜ አራቱ ወንጌላውያን በሰዓትና በኬክሮስ ካራት አድርገው ስለ ተካፈሉት፤ እንዳምስተኛው ከአበቅቴ ገብቶ አይቈጠርም። ስድስተኛነቱም ላለፈው ለሉቃስ ጳግሜ ነው እንጂ፤ ገና ወደ ፊት ለሚመጣው ለዮሐንስ ጳግሜ አይዶለምና፤ ዮሐንስም በመስከረም አንድ ባተ እንጂ በጳግሜ አልባተምና፤ በዮሐንስ ዘመን በዓለ ልደትን በጳግሜ ምክንያት ማፋለስ ታላቅ ስሕተት ነው። ይህም ስሕተት የተዠመረ ባፄ ዐምደ ጽዮን ዘመን ነው። ማውረድና ማፋለስ ከኾነም በልደት ብቻ ምን መጥቷል፤ ኹሉን ካመት እስካመት መናድ ያስፈልጋል፤ ትንሣኤም ቅዳሜ ይውላል።
ጳጦስ ፤ (ጽር ባቶስ) ፤ ባጦስ ፤ የሾኽ ቍጥቋጦ ፤ ሐመልማል። ባጦስንና ሳቤቅን ተመልከት። በኀበ ዕፀ ጳጦስ (ሱቱ
፡ ዕዝ፬ ፡ ፫። ማር፲፪ ፡ ፳፮። ግብ፯ ፡ ፴፭። ዲድ ፡ ፴፮። ድጓ)።
ጳጲራ ፡-ፓፒራ።
ጳጳስ ፡-(ሳት። ጽር ፓፓስ) ቄስ፤ ቆሞስ፤ ዐርከ ኤጲስቆጶስ። ሢመተ እዴሆሙ ለጳጳሳት ፡-(፩ጢሞ ፡-፬ ፡-፲፬)። ቄሱ ጳጳስ እንዲባል ጳጳሱ ደግሞ ቄስ ይባላል ፡-(፪ዮሐ ፡-፩። ፊልጵ፩ ፡-፩)።
፡-ኤጲስቆጶስ፤ ሠያሜ ቀሳውስት ወዲያቆናት። ዘይፈቅድ ይሠየም ጳጳሰ ፡-(፩ጢሞ ፡-፫ ፡-፩። ቲቶ፩ ፡-፯። ግብ፳ ፡-፳፰። ኪዳ)። ክልኤቱ ምእት ጳጳሳት ፡-(ስንክ ፡-መስ፲፪)።
፡-በቁሙ፤ ጳጳስ፤ መጥሮጶሊስ፤ የኤጲስቆጶሳት አለቃ፤ ሿሚ፤ አዛዥ። ወለእመ ሤመ ጳጳስ አሐደ ኤጲስቆጶሰ እምኤጲስቆጶሳት ፡-(ፍ ፡-ነ ፡-፬)።
ጴጥራ ፡-(ጽር ፔትራ) ኰኵሕ፤ ንጥፍ ደንጊያ፤ ጭንጫ።
ጴጥሮስ ፡-(ጽር ፔትሮስ) ኰኵሓዊ፤ ዘኰኵሕ፤ ብእሴ ኰኵሕ። የግእዝ መላሽ ግን በጴጥሮስ ፈንታ ኰኵሓዊ እንደ ማለት ኰኵሕ ይላል፤ የተሳሳተ ነው፤ አያሰኝም። ጴጥሮስ ልዩ እንደ ኾኑ ኰኵሓዊና ኰኵሕም ልዩ ናቸው። ወኰኵሕሰ ክርስቶስ ሃይማኖተ ጴጥሮስ ዘተብህለ በአፈ ጴጥሮስ፤ አንተ ውእቱ ክርስቶስ ወልደ እግዚአብሔር፤ እስመ ይቤ ወዲበ ዛቲ ኰኵሕ አሐንጻ ለቤተ ክርስቲያንየ፤ ከመ ዘይቤ ወዲበ ዛቲ ሃይማኖትከ ፡-(ትር ፡-ወን። ማቴ፲፮ ፡-፲፰። ፩ቆሮ ፡-፫ ፡-፲–፲፫። ፲ ፡-፬)።
ጴጥያስ ጲጦን ፡-ጲጦን፤ ፡-(ጽር ፒቲስ፤ ፒቲዬስ) ጥሩ የተክል ዕንጨት ዛፍ፤ ምዑዝ ገናና። ጢጤንን ተመልከት፤ የዚህ ጎር ነው። ዕፀ ጴጥያስ ፡-(ሕዝ፴፩ ፡-፰። ኩፋ ፡-፳፩)።
ጵልንትዩ ፡-(ጽር ፕሊንቲዩ። ዕብ ማልኬን) የጣዖት ቦታ፤ ምሥዋዐ ጣዖት፤ ደቂቀ አሞን ሞሎኽ ለሚባል ጣዖት ልጆቻቸውን የሚጠብሱብት የሚያቃጥሉበት፤ የሞሎኽን ፍች ተመልከት። ባለብሉዮች ግን ግዞት የግዞት ቤት ይሉታል ፡-(፪ነገ ፡-፲፪ ፡-፴፩)።
ጵስጥቂስ ፡-(ጽር ፒስቲኪስ) ጥሩ ሽቱ፤ ውድ ክቡር ፡-(ዮሐ፲፪ ፡-፫)።
ጵሩጳጣ ፡-(ጽር ፕሮባታ) አባግዕ፤ በጎች፤ የበግ መንጎች።
ጵሩጳጥቄ ፡-(ጽር ፕሮባቲክ) አባግዓዊ፤ ዘአባግዕ፤ የበጎች። አንቀጸ ጵሩጳጥቄ ፡-(ነሐ፫ ፡-፩ ፡-፴፩። ዮሐ፭ ፡-፪)። ባለሐዲሶች ግን ዘብዙኃን ዘፈውስ ዘበዓል ይሉታል።
ጵርስፎራ ፡-(ጽር ፕሮስፎራ) መባአ ኅብስት፤ ሰንበቴ እንደ ዛቲና እንደ ተስፋ ያለ፤ ወይም ኅብስተ አኰቴት፤ ምእመናን የሚያቀርቡት ቍርባን። ጵርስፎራ ዘሰንበት። ወያብኡ አርባዕተ ጵርስፎራ በዕለተ እሑድ ወሠለስተ በካልኣን ዕለታት። ፡-(ኪዳ። ሥር ፡-ቅዳ)።
ጵርንሶ ፡-ጵርንሶ፤ ፡-(ጽር ፓሪኒስ) ዝኒ ከማሁ፤ ዕንቍ ፡-(አስቴ፩ ፡-፮)።
ጵርዮን ኒ ዮኖ ስ ፡-(ጽር ፕሪዮን) የሰው ወጥመድ፤ መጋዝ፤ ጥርሳም ብረት፤ መኪና የሚቈርጥ የሚበጣጥስ። አንበሮሙ ውስተ ጵርዮን ፡-(፪ነገ ፡-፲፪ ፡-፴፩። ዮዲ፫ ፡-፱)።
ጵርድክይሴ ፡-(ጽር ፔርዲክስ) ድርንቅ የባሕር ቆቅ፤ ወይም ሶረን ፡-(ገድ ፡-ላሊ)።
ጵርጵግ ፡-(ጽርእ) ስመ ብእሲት፤ መበለት፤ ኤልያስን ያስተናገደች ፡-(ሉቃ፬ ፡-፳፮)። ይህ ስም የተገኘ ካንኮበሮች መምህር ከየኔታ ወልደ ሥሉስ ቃል ነው፤ ርሳቸው ከመምህራቸው አፍ ወይም ከአዋልድ መጽሐፍ አግኝተው እንዲህ ይሉ ነበር ይባላል።
ጵርፍርዮና ፡-(ጽር ፖርፊሪዮና) የባሕር ዶሮ፤ የማይበላ ፡-(ዘዳ፲፬ ፡-፲፰)።
ጵኒኖ ፡-(ጽር ፒኒኑ። ዕብ ፍኒኒም) ዕንቍ፤ የዕንቍ ስም፤ ሰደፍ ወይም ሌላ ፡-(አስቴ፩ ፡-፮)።
ጵንጋሌ ፡-መቅዳት መገልበጥ፤ አገለባበጥ፤ ግልበጣ ምለሳ፤ ንባብ ምልከታ።
ጵዮን ፡-ሠኔ፤–ጳሒን።
ጵጱስ ፡-(ሳን) የጰጰሰ፤ የተጰጰሰ፤ ጳጳስ የኾነ፤ የተሾመ ፡-(መጽ ፡-ምስ)።
ጵጳሴ ፡-መጰጰስ፤ አጰጳጰስ ጳጳስ መኾን፤ ጵጰሳ ጳጳስነት። ሢመተ ጵጳሴ ፡-(ስንክ ፡-መስ፬)።
ጵጵስና ፡-ጳጳስነት፤ ከዊነ ጳጳስ ማዕርግ። ወሶበ ተሠይመ ጵጵስና ዝንቱ ዘዝኩር በስመ ሊቃናት ፡-(ፍ ፡-ነ ፡-፬)።
ጶሊስ ፡-(ጽር ፖሊስ) መዲና፤ ታላቅ ከተማ። ሊቀ ጳጳሳት ስምዖን ዘእስክንድርያ ጶሲስ ፡-(ስንክ ፡-ሐም፳፯)።
ጶዴሬ ፡-(ጽር ፖዲሪስ) የላይ ልብስ፤ ጥሩ ክቡር በርኖስ፤ ጀባ ካባ መጐናጠፊያ፤ ነገሥታት ካህናት የሚለብሱት። ልብሰ እንግድዓ፤ የደረት ልብስ ሳንቃ፤ ከአልባሰ ክህነት አንዱ። ዘይለብስ ጶዴረ። ልብሰ ጶዴር ፡-(ሕዝ፱ ፡-፪። ሢራ፳፯ ፡-፰። ራእ፩ ፡-፲፫። ዘፀ፳፭ ፡-፯)።
No comments:
Post a Comment