ሀ ለ ሐ መ ሠ ረ ሰ ሸ ቀ በ ተ ቸ ኀ ነ ኘ አ ከ ኸ ወ ዐ ዘ ዠ የ ደ ጀ ገ ጠ ጨ ጰ ጸ ፀ ፈ ፐ
መ [1] ፡ ፲፫ ፊደል በግእዝ አልፍ ቤት በአበገደ፤ ስሙ ማይ ፥ ቍጥሩ አርባ፤ አኃዝ ሲኾን ፡ (መ–፵) አርብዓ ይባላል።
[2] ፡ የቃል አጐላማሽ፤ አጋናኝና አዳማቂ። መድረሻ እየኾነ በአንቀጽ ሳይቀር በኹሉ ይገባል። መኑመ፤ ምንተኑመ፤ እስኩመ፤ እአፎመ። ውእቱመ ፡ (ርሱማ) ካልእመ፤ ባዕድመ። መጽአመ ዘይመጽእ። ፍችው ራብዕ ማድረግ ፥ ወይም ራብዕ መኾን ነው፤ ሳይፈታም አዳማቂ ኹኖ ይቀራል።
፡ (ዕር፳ ፡ ቍ፺፩)።
[3] ፡ ባዕድ ዘር። በዘመድ ዘር ላይ እየተጨመረ መነሻ ይኾናል፤ ግእዙ ብቻ ስለ ተነገረ ካዕቡ ፥ ራብዑ ፥ ሳድሱ ሳብዑ አይቀሩም። ይህም ሰፈነ መስፍን፤ ወደየ ሙዳይ፤ ሔበ ማሕየብ፤ ኀለፈ ምኅላፍ፤ ወፀፈ ሞፀፍ እያለ መኼዱን ያሳያል። ሙና ሞ ጐራጆች ናቸው፤ በወ ከሚነሣ ከወ ግስ በቀር በሌላ አይገኙም።
መኈ(ኆ)ሥሥ ፡ (ሣት፤ አው መኋሥሥት) ሹካ መንካ ጭልፋ፤ የሥጋ ማውጫ። ጕጠት የጥርስ መንቀያ። መኈሥሥ ዘሠለስቱ ስነኒሁ። መኋሥሥት ወፍያላት። መኈሥሠ ስነን ፡ (፩ነገ ፡ ፪ ፡ ፲፫። ዘኍ፬ ፡ ፲፬። ስንክ
፡ ጥር፲፭)።
መሐለ ፡ (ብሂል ብህለ። ዐረ በሀለ) ማለ ተረገመ፤ ተፈጠመ፤ ነገርን ለማጽደቅ ለማጽናት። ኢትምሐሉ ግሙራ። እለ ይምሕሉ በጽድቅ አው በሐሰት። መሐልኩ በርእስየ። ዘብዙኀ ይምሕል ፡ (ማቴ፭ ፡ ፴፫። ፈ ፡ መ ፡ ፳፪። ኤር፳፪ ፡ ፭። ሢራ፳፯ ፡ ፲፬)። ተሳለ፤ ብፅዐት ገባ፤ ውል አደረገ። በፅዐንና ኬደን ብህለን ተመልከት።
መሓሊ ፡ (ሊት ልያን ያት) የማለ ፥ የሚምል፤ ማይ ማለኛ። ብእሲ መሓሊ። ለእመ አእመረ መሓሊ። ሐሳዊ ወመሓሊ በሐሰት ፡ (ሢራ፳፫ ፡ ፲፩። ፍ ፡ ነ ፡ ፵፫ ፡ ፭። ቀሌ)።
መሐላ ፡ በቁሙ፤ ማላ ፥ ፍጥም፤ የውል ነገር ማጽደቂያ፤ በፈጣሪ ወይም በፍጡር ስም በሚወዱትና በሚያከብሩት ነገር የሚደረግ። መሐላ በሐሰት። መሐላ ጽድቅ። ከመ ኣቅም መሐላየ ፡ (ቀሌ። ኩፋ
፡ ፴፭። ኤር፲፩ ፡ ፭)።
፡ ስለት ብፅዐት፤ ወይም የስለትና የብፅዐት ቃል፤ ውል ኪዳን። በመሐላሆሙ ለማርያም ወለወልዳ ፡ (ስንክ ፡ ጥቅ፱)።
መሐልል ማሕልል ፡ የሚያሳርር የሚያቃጥል። ሽቱ የሚያበጅ የሚያወጣ፤ ቀማሚ አንጣሪ፤ የሚያቀልጥ የሚያጣፍጥ። ውእቱ ዘገብረ አፈዋተ ዕጣን በንጹሕ ግብረ መሐልል ፡ (ዘፀ፴፰ ፡ ፳፬)። ሐረረን እይ።
መኈልቍ ፡ (ቍት ቋን ቋት) ዝኒ ከማሁ። መኈልቍ ከአኈለቈም ሊወጣ ይችላል፤ መስም ቅጽል ካድራጊና ካስደራጊ አንቀጽ ወጥቶ በማድረግም፤ በማስደረግም በ፪ ስልት ይፈታል።
መሐልቅ ፡ ክብ ሥራ፤ ምእዙን ሞላላ ያይዶለ፤ እንደ ሰፌድ እንደ ምጣድ ያለ። ሀሎ በአኵስም ሥዕለ ምትረተ ርእሱ ለዮሐንስ መጥምቅ ሥዑለ በመሐልቀ ብርት ፡ (ታሪ ፡ አኵ)። በቁሙ፤ ግርሽ የብር ገንዘብ ክብነት ያላት፤ ዐይነቷ የብር መጠኗ የዝራር። በኀርም ኀ ሲጣፍ ግን፤ መኀልቅ ማለት ታናሽ ክፍል የብር ካያኛ ማለት ነው፤ ማነሷንና መከፈሏን እንጂ ክብነቷን አይሻም።
መሐስብ ፡ (ብት ባን ባት) ዝኒ ከማሁ ፡ (መጽ
፡ ምስ)።
መሐስዕ ፡ ጠቦት፤–ሐሲዕ ሐስዐ።
መሐረ ፡ አስተማረ፤–ምሂር መሀረ።
መሐረም [1] ፡ (ዐረ እልሙሐረም) ያረቦች መዠመሪያ ወር የካቲት፤ በጨረቃ መንገድ ፡ (አቡሻ)።
[2] ፡ መሐረም፤–ያረቦች መዠመሪያ ወር፤–ሐረመ።
መሃሪ ፡ (ሪት ርያን ያት፤ ሀርት) በቁሙ ፥ ማሪ መሪ፤ መካሪ አስተማሪ።
መሓሪ ፡ (ሪት ርያን ያት) በቁሙ፤ የሚምር ማሪ፤ ይቅር ባይ ዐዛኝ ርሩ፤ ሰጭ መጿች፤ ለጋስ ሰው ወዳጅ። መሓሬ ብዙኃን እምዕዳ። መሓሪ ለዕጓለ መሕያው። ዐይንከ መሓሪት። ወኩኑ መሓርያነ ቢጽክሙ። አንስት መሓርያት
፡ (ስንክ ፡ ጥቅ፱። ኅዳ፲፬። አርጋ። ኤፌ፬ ፡ ፴፪። ሰቈ፬
፡ ፲)። መሐርና መዓር ባማርኛ ይተባበራሉ። ፡ (ግጥም፤ ልጅ ኢያሱ በተያዙ ጊዜ ታስረው ከነበሩት ሰዎቻቸው አንዱ) ጠጅም አልቀመስነ ከተለየናችኹ፤ አውራው ከተያዘ። ማሩን እባካችኹ።
መኀብል ፤ መስተኀብል ፡ (ልት ላን ላት) የሚያስደፍር፤ የሚያስጨክን። ምስለ መስተኀብ(ይ) ል ኢትኅበር መንገደ ፡ (ሢራ ፡ ፲ ፡ ፲፭)።
መሐትት ፡ (ታን ታት) የሚመረምር፤ የሚያስመረምር፤መርማሪ አስመርማሪ።
መሀነ ፡ ፈገፈገ፤–ምሒን መሐነ።
መሀና ፡ እጅ መንሻ፤–መሐና።
መሐና ፡ (ዕብ ሚንሓህ) እጅ መንሻ ፥ በረከት፤ የፍቅር ስጦታ። ንሣእ መሐና። ወአብአ ሎቱ መሐና ፡ (፬ነገ ፡ ፰ ፡ ፰። ፲፯ ፡ ፫ ፡ ፬። ፳ ፡ ፲፪)።
መሓን ፡ ማሻ ማልፊያ፤ ወይም አልፊ ዐሽታ፤ ዐራቢ። ማእሰ በግዕ ሕሱይ ግቡረ መሓን ፡ (ዘፀ፴፭ ፡ ፯ ፡ ፳፫)።
መሐከ ፡ ራራ ዐዘነ፤–ምሂክ መሀከ።
መሀከ ምህከ ፡ (መሐረ፤ ምሕረ) ራራ ፥ ዐዘነ ፥ ማረ፤ ይቅር አለ። ኢመሀተኪ ዐይን። ወልዶ ጥቀ ኢምህከ እምኔነ። አንተሰ ትምህክ ሐምሐመ። መሀክ ሕዝበከ። መሀኩ ሊተ ወልድየ። ዘእንበለ ምሂክ። ምሂኮትየ ፡ (ሕዝ፲፮ ፡ ፭። ሮሜ፰ ፡ ፴፪። ዮና፬ ፡ ፲። ዮኤ፪ ፡ ፲፮። ፪ነገ
፡ ፲፰ ፡ ፭። ስንክ። አርጋ)።
፡ ገመገመ ፥ ሣሣ ፥ ቈጠበ። ዘይምህክ በትሮ። ዘይምህክ ነገረ። ኢትምሀኩ ገሥጾቶሙ ፡ (ምሳ፲፫ ፡ ፳፬። ኢዮ፵፪ ፡ ፫። ዲድ ፡ ፳፪)።
፡ አዳነ ተቤዠ፤ ጠበቀ። ይምህክ ነፍሰ እሞት። እምእደ ሳኦል መሀኮ። ወእምነኪር መሀኮ ለገብርከ ፡ (ኢዮ፴፫ ፡ ፲፰። አርጋ ፡ ፬። መዝ ፡ ፲፰)።
መሃኪ ፡ (ኪት ክያን ያት) የሚራራ፤ መሓሪ ዐዛኝ፤ ይቅር ባይ፤ አዳኝ ፈዋሽ። አብ መሃኪ ዘይምህክ ወልዶ። እግዚ መሃኪከ ፡ (አፈ ፡ ተ፬። ዘፀ፲፭ ፡ ፳፮)።
መሐወ [1] ፡ (ዕብ መሓህ። ዐረ መሓ) አጠፋ ደመሰሰ ፥ በውሃ በምራቅ፤ የርስሐት የጥፈት። ምህወና መሐወ መሰወ እነዚህ ሦስቱ ፩ ዘር ናቸው።
[2] ፡ ነቀለ መዘዘ፤ ከሥሩ አፈለሰ፤ ቀጨ ዐሸ፤ ያታክልት የሸት። እግዚ ይተክል ወይምሑ። መሐወኒ እንተ ኵለሄ። ይየብስ ዘእንበለ ይምሐውዎ። አኀዙ ይምሐዉ ሠዊተ። ወመሐዋ ለእዴሁ ፡ (ቀሌ። ኢዮ፲፱ ፡ ፲። መዝ ፡ ፻፳፰። ማቴ፲፪ ፡ ፩። ስንክ)።
መሓዊ ፡ (ዊት ውያን ያት፤ ሐውት) የሚያጠፋ፤ ነቃይ አጥፊ።
መሐውር ፡ (ርት ራን ራት) የሚኼድ ኸያጅ ዘዋሪ፤ የሚያስኼድ፤ ነጅ ወሳጅ።
መሀውክ ፡ (ክት ካን ካት) ዝኒ ከማሁ፤ እኪት ይእቲ ሐሜት ወመሀውክት። ቍጥዓ ወፍርሀት መሀውካን ፡ (ሄርማ። ፍ ፡ ነ ፡ ፵፫ ፡ ፬)።
መሐውጽ ፡ (ጽት ጻን ጻት) ዝኒ ከማሁ፤ ጕበኛ ሰላይ፤ ፈላስፋ ጠንቋይ። መሐውጻነ ኮከብ ፡ (ኪዳ ፡ ገ፳፮)።
መሐዘ ፡ (ምዒዝ ምዕዘ) ጐለመሰ፤ ጐበዘ አደገ፤ ሚዝት ፈለገ፤ ወሸመ ውሽማ ያዘ። ሚዜ ሚዝ(ስ) ት ሚያዝያ ማለት ከዚህ ወጥቷል።
መሓዛ ፡ ጕልማስነት ልጅነት፤ ዐፍላ ጕብዝና ፥ ቍንዥና። ተሐራሚት እምወይነ መሓዛ ወእምእክለ ውርዙት ፡ (ስንክ ፡ ጥቅ፳፬)።
መሓዝ ፡ (ዛን ዛት) ደጐባ ጕልማሳ ጐበዝ፤ ውሽማ የሰው ሴት የሚሰርቅ የሚያማግጥ። ለቃናትኒ ወመሓዛት፤ ተንሥኡ መሓዛት። ወመሓዝሰ በንዴተ አእምሮ ሀጕለ ነፍሱ ይገብር። ብእሲት እንተ ተኀድግ ምታ ወትወልድ ወራሴ እምዲበ መሓዛ። መሓዛንኪ እለ ይሰክቡ ምስሌኪ ፡ (መዝ
፡ ፻፵፰። ግብ፭ ፡ ፮። ምሳ፮ ፡ ፴፪። ሢራ፳፫
፡ ፳፪። ኢሳ፶፯ ፡ ፰)።
መሀይምን ፡ (ንት ናን ናት) ዝኒ ከማሁ፤ ምእመን፤ ያመነ የታመነ፤ አማኒ እሙን የማይጠረጠር። መሀይምን ውእቱ በኵሉ። ስምዕ መሀይምን። ክርስቲያናዊት መሀይምንት። ማሕየዊ ለኵሉ ሰበእ ወፈድፋደሰ ለመሀይምናን ፡ (ኩፋ ፡ ፲፯። ራእ፩ ፡ ፭። ኪዳ። ፩ጢሞ ፡ ፬ ፡ ፲)። በቁሙ ማይምን፤ ያልተማረ ያልተካነ ሕዝባዊ ጨዋ።
፡ (ተረት) ከማይምን ባለጌ የተማሪ አሮጌ።
መሐደምት ፡ (ታት) ተረት ምሳሌ፤ ጨዎታ ቧልት፤ ለግጥ ፡ (፩ጢሞ ፡ ፩ ፡ ፬። ፬ ፡ ፯። ፪ጢሞ ፡ ፬ ፡ ፬። ቲቶ፩ ፡ ፲፬። ፪ጴጥ ፡ ፩ ፡ ፲፮)። ዝንቱ ወቱ ነገረ መሐደምት ወተዛውዖ ደቂቅ፤ እስመ ደቂቅ ይሰምዑ ብዙኀ ነገረ መሐደምት እምኀበ ሐፃኒት። መሐደምት ስኡን። አነ መሐደምቶሙ ፡ (አፈ ፡ ተ፲፩። ቄር። ኢዮ፴ ፡ ፱)።
መሐድም ፡ (ምት ማን ማት) ዝኒ ከማሁ፤ ተረታም።
መኀድፍ ፡ (ፍት
ፋን ፋት) ዝኒ ከማሁ፤ ቀዛፊ። መኀድፋነ ፍርሀት ፡
(ማር ፡ ይሥ፳፮)።
መሐጸ ፡ (ምሒጽ። ዐረ መሐጸ። ዕብ ማሐጽ) መታ፤ ፈለጠ ቈረጠ፤ ሰበረ አደቀቀ፤ ገደለ አጠፋ። የይፋት እስላም መታ አስመታ ሲል ማጠ አስማጠ ይላል። ፪ኛም ግእዙ አሐርጾሙ ከመ ጸበል ባለው፤ ዕብራይስጡ ኤምሐጼም ክዓፋር እንዲል ፡ (መዝ፲፯)። ከመ ይምሐጾሙ በሰይፍ። መሐጾሙ ወቀተሎሙ ፡ (ኩፋ ፡ ፭ና ፡ ፵፰)።
መሓጺ
፡ (ጺት ጽያን ያት) የሚመታ ተማች፤ ፈላጭ ቈራጭ፤ ገዳይ አጥፊ። ለሆሎፎርኒስ ግብተ በሰይፈ ዮዲት መሓጺሁ ፡ (ደራሲ)።
መሕልይ መሕለዪ መሐልይ ፡ ዝኒ ከማሁ፤ ዘፋኝ። መዝፈኛ፤ ጊዜ መሣሪያ ቦታ።
መኅምስት ፡ ዐምስት ወገን፤ ዐምስት ክፍል፤ ዐምስት እጅ
፡ (ዘፍ፵፫ ፡ ፴፬)።
መሕቅር መስተሐ(ሕ) ቅር ፡ (ርት ራን ራት) የሚያስተሐቅር፤ የሚነቅፍ የሚያቃልል)
ነቃፊ፤ አስነቃፊ። ብእሲ ነባቢ ወመስተሐቅር። ኖሎት ገፋዕያን ወመስተሐቅራን ፡ (ዕን፪ ፡ ፮። ኪዳ ፡ ገ፬። ቄር
፡ ጰላ)።
መሕቡብ ፡ (ዐረ) ዝኒ ከማሁ፤ የተወደደ ውድ፤ መውደድ መወደድ ያለው። መሕቡብ ኢጲስቆጶስ ዘመንበግ ፡ (አቡሻ ፡ ፵፯)።
መኅንቅ ፡ (ብ መኃንቅ) የሚያንቅ፤ ማነቂያ ማነቆ፤ ሸምቀቆ።
መሕያው ምሕያው ፡ መዳኛ መኗሪያ ቦታ፤ ምድር ዓለመ ሰብእ፤ ወይም እግዜር ዓለመ ኵሉ ፍጡር። ዕጓለ መሕያው፤የምድር ልጅ አዳም፤ ሥጋው ካፈር ከመሬተ ምድር፤ ነፍሱ ከሕያው ከግዜር የተገኘች፤ ነፍስና ሥጋ ፍጹም ሰብእ። የአዳምንና የዕጓልን ፍች ተመልከት። ፪ኛም መ መሬት፤ ም ምድር፤ ሕያው እግዜር፤ በተገናኝ መሬተ ሕያው፤ ምድረ ሕያው ማለት ነው፤ አምላክ እንደ ማለት።
መለለ ፡ (ዕብ ማላል፤ ዐሸ ፈለፈለ፤ ሳበ መዘዘ፤ አለ ተናገረ ፥ ቃል አወጣ) ገቢርና ዐጕል፤ መለመለ ላጠ ላገ ፥ መለሎ አደረገ፤ ዐረቀ አስተካከለ። መለል አለ፤ ረዘመ መለሎ ኾነ፤ የንጨት የፈትል ለሰውም ይኾናል። ፡ (የስድብ ግጥም) እየው መለል ብሎ የወንዝ ዳር ጕሎ፤ ቂል ነው የዝም ብሎ። ሰላላ መላላ ድርና ማግ ፈትላ ፥ ሸማኔ አስቸገረች ወይዘሮ ወንዲላ። ሜላትን እይ፤ የዚህ ዘር ነው።
መለምልም [1] ፡ (ምት ማን ማት) የሚያለመልም፤ አለምላሚ። የለመለመ ፥ ለምለም፤ ለስላሳ ርጥብ፤ ጥሉላት ፥ የብሎት ምግብ። ወኵሎ መለምልመ ፡ (ኪዳ)።
[2] ፡ ለስላሳ ርጥብ፤–ለምለመ።
መለቀ ፡ (መሊቅ። ዕብ ማላቅ) ቈረጠ ፥ ቀጨ ፥ ነጨ ፥ የራስና ያንገት የጠጕር። ለሣርና ለንጨት ለሸትም ይኾናል። መለጠን እይ፤ የዚህ ጎር ነው።
መለብው ፡ (ዋን) አለባዊ፤ የሚያለብም፤ አስተዋቂ አስረጅ። መለብው። ሐዋርያት መምህራኒክሙ ወመለብዋኒክሙ ፡ (ዮሴፍ። ቈስጠ)።
መለንስ ፡ (ጽር ሜላንሲዎን) ጥቍር ክሙን ፥ ኑግ የሚመስል ፡ (ኢሳ፳፰ ፡ ፳፭ ፡ ፳፭)።
፡ ኑግ መጭ ፥ የከሙን ዐይነት። ቅብዐ መለንስ፤ ኅብስተ መለንስ፤ ቅባኑግ ፥ የኑግ ልጥልጥ ፥ ቂጣ ጭፍቆ ፡ (ገድ ፡ ተክ) ከሙንን እይ።
መለከት ፡ በቁሙ፤ የመንግሥትና የሹመት ምልክት፤ ነገሥታት መኳንንት የሚያስነፉት። ቡቅንና መጥቅዕን እይ፤ ቀንዳ መለከት እንዲሉ።
መለካዊ ፡ (ዊት ውያን ያት) ንጉሣዊ፤ የንጉሥ ወገን፤ ንጉሥ የሾመው ራስ ደጃዝማች፤ ባለንቢልታ ባለመለከት፤ መልከኛ ፥ ከኳደሬ እስከ ንጉሥ ያለው ሹም ኹሉ። የጉባኤ ስም ፥ ማኅበረ ኬልቄዶን፤ ንጉሥ ያቆመው የሰበሰበው፤ የንጉሡን ፈቃድ የሚፈጽም። ወበስመ ንጉሥ ሰመዮሙ መለካውያነ፤ ፈጻምያነ ፈቃደ ንጉሥ ብሂል። ወተርጐምዎ ኀበ ዐረቢ መለካውያን ወንስጥሮሳውያን ፡ (ፈሀረ። ፍ ፡ ነ ፡ መቅ)።
መለክ አው መልክ ፡ (ብ መለካን፤ አው አምላክ፤ አማልክት። ዐረ መሊክ። ዕብ ሜሌኽ። ሱር ማልካ) ዝኒ ከማሁ፤ የመለከ መላኪ፤ ንጉሥ ባለዘውድ። መለክ ሰገድ። መልከ ጼዴቅ ፡ (ታሪ ፡ ነገ። ዕብ፯ ፡ ፩ ፡ ፪)።
መለኮታዊ ፡ በቁሙ፤ ባሕርያዊ አምላክነት ያለው ፥ የአምላክ የመለኮት። መለኮታዊ ክርስቶስ ዘለብሰ ትስብእተ። ዝንቱ ኅብስት መለኮታዊ። ትምህርታት መለኮታውያት
፡ (ስንክ። አርጋ። ቅዳ። ቄር)።
መለኮት [1] ፡ (ዐረ መለኩት። ዕብ ማልኩት። ሱር ማልኩታ) ግዛት ፥ መንግሥት ሥልጣን። ውስተ ኵሉ በሓውርት መለኮቱ። መለኮትከ ወመንግሥትከ ይነብር ለዓለም ፡ (መዝ ፡ ፻፪። ሔኖ፹፬ ፡ ፪)።
[2] ፡ (ዕብ ኤል፤ ኤሎሃ። ሱር ኤላሃ። ዐረ አላህ) በቁሙ፤ ልዩ ክቡር ስም፤ ከፈጣሪ በቀር ማንም ፍጡር የማይጠራባት ፥ እንደ እግዚአብሔር ያለ። የባሕርይ አምላክ፤ ባሕርያዊ ንጉሥ፤ ጥንትና ፍጻሜ የሌለው ዘላለማዊ ገዥ፤ ገባሬ ኵሉ ፥ መላኬ ኵሉ ፥ ምሉእ ውስተ ኵሉ ፥ ማለት ነው። ከባሕርይ ከግብር የሚወጣ ባሕርያዊ ስምና ቅጽል የአካልን ባለቤትነት ልኩንና መልኩን ግብሩንም እንደ መስታዮት ፊት ለፊት ያሳያል። መለኮት ስም ዘአልቦ ብዕድና ፡ (ተረ ፡ ቄር፲፭)። አኮ ዘቦቱ ለመኮት ክበብ ከመ ፀሓይ ወወርኅ ወዐቅም ከመ ሰበእ፤ አላ ምሉእ ውአቱ በኵለሄ፤ ወመለኮትሰ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡ (ቅዳ ሕር)። ስለ ሥጋዌም፤ ወተወልደ መለኮት በሥጋ። ክቡር አንተ ዕፀ መስቀል ወክቡር ዘቀደሰከ ደመ መለኮት ቃል። መልዕልተ ዝንቱ መስቀል አመ ሞተ መለኮት በትስብእቱ። እስመ እምንእስከ ልዮን መፍቀሬ ነገር አንተ፤ ከፈልከ ኀበ ክልኤ ሥግወ መለኮተ ቢል፤ ፍችው አምላክ ማለት ነው፤ አንዱን አካል ብቻ ያሳያል።
[3] ፡ (ዕብ ኤላሁት። ዐረ ላሁት። ጽር ቲዎቲስ። ሮማይ ዲዊኒታስ) አምላክነት፤ ፈጣሪነት፤ አምላክ መኾን ፥ ፈጣሪ መኾን፤ ወይም የአምላክ ባሕርይ ፥ ጠባዩ ኹነታው ፥ ቅድስት ሥላሴን የሚያዋሕድ የሚያስተባብር ፥ አንድ አምላክ የሚያሰኝ። ፈጥሮ መግዛትና መፍጠር ማስገኘት የባሕርያቸው ስለ ኾነ ባሕርያቸው በግብር ስሙ መለኮት ይባላል፤ እነትና መኾንም ፩ ወገን ናቸው፤ ትርጓሜያቸው ባሕርይ ከማለት ይገባል። ምስጢራተ መለኮትከ። ኢይደሉኬ ናስተማስል መለኮቶ። ይሤለሱ በአካላት ወይትዋሐዱ በመለኮት። መለኮትኒ ይትዐወቅ ከመ ውእቱ ያኀብር ቅድስተ ሥላሴ
፡ (ጥበ፲፪ ፡ ፭። ግብ፲፯ ፡ ፳፱። ሃይ ፡ አበ)። ዳግመኛም፤ ያካልና የግብር የስም መሠረት ፥ ያንድነትና የሦስትነት የነገር ኹሉ ጥንት ሥሩና ምንጩ ባሕርይ ስለ ኾነ ፥ ከዚህ ካንዱ ባሕርይ አንድ ስም ነሥተው ሦስቱ ኹሉ ህላዌ ህላዌ እንዲባሉ ፥ መለኮት መለኮት ይባላሉ፤ አምላክ ማለት ነው፤ ምስጢሩ ከ፪ኛው ፍች ይገባል። ቦሙ አአምን ወእትአመብ ከመ እሙንቱ መለኮት ወህላዌ ወእሙነ እብል ከመ እሙንቱ መለኮት፤ ወለለ አሐዱ አሐዱ እምአካላተ ቅድስት ሥላሴ ያበጽሕ ፍጹመ መለኮተ ምስለ ዘዚኣሁ አካል ወስም፤ ወዝኒ ዘመለኮተ ዚኣሁ ፡ (ሃይ ፡ አበ ፡ ባስ ፡ ጾክ)። ሦስተኛም፤ አካላት ከባሕርያቸው ከመለኮት ስምን የሚነሡ ስለ ኾነ ፥ ሊቃውንት ኹሉ በየድርሳናቸው አካል ሲሉ መለኮት ይላሉ። ወአልቦ ኀውሥ ውስተ መለኮቱ፤ አላ ሥላሴ ፍጽምት። እስመ ሠለስቱ ኍልቈ መለኮቱ። ትሥልስተ መለኮት ፡ (ተረ ፡ ቄር
፡ ኤጲ፲፯። ሳዊ፲፱። መጽ ፡ ምስ)። «ማስረጃ፤ ወልድ በተለየ አካሉ ሰው በኾነ ጊዜ ባሕርዩም ሰው ኹኗል ፩ ባሕርይ ወልድ ቅብ ለማለት ቅድስት ሥላሴን የብዕልና የባሕርይ አንድነት በሌላቸው በ፫ ባለጠጎች መስለው ፫ አካል በማለት ፈንታ ፫ መለኮት ፫ ልዩ አማልክት ስለሚሉ ስለ ሐዲስ ካሮች፤ ባህልና አፈታት።
መለየ ፡ (ሌለየ፤ መሰወ) መላ መታ፤ በመላ ዐወቀ፤ መለኛ ኾነ። ፡ (ተረት) ካጕል ጥንቈላ የሰው ልጅ መላ። አፈረሰ፤ ፈታ ለያየ አውለቀለቀ። አሟሟ አቀለጠ አፈሰሰ፤ ምስጢሩ ከማፍረስ ይገባል። ግስነቱ ከመሰወና ከሌለየ የተዴቀለ ስለ ኾነ የኹለቱንም ስልት ያሳያል። ፪ኛም በመሳዊ ፈንታ መላዪ፤ በመላዪ ፈንታ መሳዊ ይላል።
መለገ ፡ (ዕብ ማላግ፤ ነጨ መለጠ) ማለገ ምልግልግ አለ፤ ማላጋ ኾነ የፈሳሽ፤ ለሰውም ይኾናል። ታገሠ፤ ቻለ።
መለጎስ ፡ (ጽር ማላኮስ) ለምለም፤ ለስላሳ ፥ ዝልፍልፍ የሚል የሚተጣጠፍ፤ የለፋ ወይም የራሰ ርጥብ ትኵስ ፡ (ፈ ፡ መ ፡ ፲፫)።
መለጠ ፡ (መሊጥ። ዐረ መሊጠ። ዕብ ማራጥ። ሱር ምራጥ) በቁሙ፤ ላጠ ቀረፈ ገጠበ፤ ነጨ ላጨ፤ የቈርበት የጠጕር። ለሐጸንና ቀረፈን ነጸየን እይ። መለጠቶ እግሮ ለበዓለም ፡ (ዘኍ፳፪ ፡ ፳፭)። ሞለጨ ፥ ሙልጭ አለ፤ አመለጠ። ሟለጠ ፥ ሟላጣ ኾነ፤ ከመላጥና ከመመለጥ ብዛት።
መለጸ ፡ (መሊጽ። ዕብ ማሎጽ፤ ሂማሌጽ) ጣፈጠ፤ እጅ አስመጠጠ፤ ላመ ጣመ፤ ደስ አሰኘ፤ የምግብ ያንደበት የቃል። ጥዑመ ልሳን እንዲሉ። ለመጸን እይ፤ የዚህ ጎር ነው።
መሊኅ ኆት ፡ (መልኀ ይመልኅ ይምላኅ። ዐረ መለኀ) መንቀል መምዘዝ ማፍለስ ማውጣት፤ ማጥፋት ማራቅ ፥ ቦታ ማስለቀቅ፤ ነቀለንና ሠረወን እይ፤ የዚህ ጎሮች ናቸው። ጊዜ ለተኪል ወጊዜ ለመሊኅ ዘተከሉ። ሰይፎ ይመልኅ። እመልኆሙ እምድሮሙ። ከመ ይምላኅ እምኔሆሙ ዛተ ልማደ እኪተ ፡ (መክ፫ ፡ ፪። መዝ ፡ ፯። ኤር፲፪ ፡ ፲፬። ፈ ፡ መ ፡ ፳፪ ፡ ፩)። ባልሐ አውፅአ በማለት ፈንታ መልኅ ይላል፤ የጣፊና የመላሽ ስሕተት ነው፤ አያሰኝም። እግዚ መልኆሙ እምቅኔ መሪር ፡ (ሲኖዶ)።
መሊስ ሶት ፡ (መለሰ ይመልስ ይምልስ) መመለስ፤ መለወጥ፤ የቃል የነገር ፥ ለውሃና ለእግርም ይኾናል። ወመለሱ ቃሎሙ ፡ (ግብ፳፰ ፡ ፮)።
፡ መመላለስ መደጋገም፤ እየመላለሱ መወልወል መስንገል፤ መሞረድ መሳል፤ የግብር። ሰይፎ ይመልስ
፡ (መዝ ፡ ፯)።
፡ መፍለቅ ማንጸብረቅ፤ መንቦግቦግ መብራት መጽደል፤ ከውልወላና ከስንገላ ብዛት። ኵናት ዘይመልስ። ሰይፍ ተንሥኢ ወምልሲ። እንተ ትዌጥን ከመ ትብራህ ወትምልስ ፡ (ናሖ፫ ፡ ፫። ሕዝ፳፩ ፡ ፳፰። ፊልክ
፡ ፺፯)።
መሊእ ኦት ፡ (መልአ ይመልእ ይምላእ። ዕብ ማሌእ። ሱር ምላእ። ዐረ መለአ፤ መሊአ) ዐጕልና ገቢር፤ «ላዕለና ውስተ በ ግእዝ ይሰማሙታል»። መምላት፤ መንተርፈፍ ጢም ማለት፤ ማደር መከተት፤ የኀዳሪ ፡ (ማር፬ ፡ ፴፯። ሉቃ፩ ፡ ፲፭። ፬ ፡ ፩። ዮሐ፲፪ ፡ ፫)።
፡ መመላት፤ በውስጥና በሆድ እስካፍ እስከ ከንፈር መያዝ፤ ጐደሎ አለመኾን፤ የማኅደር። መልአት ምድር ደመ፤ ወመልአት ሀገር ዐመፃ። ይመልእ ወይነ ኵሉ ዝቅ። ኢይመልእ ዐይኑ ብዕለ። መልአ ደመና ዝናመ
፡ (ሕዝ፱ ፡ ፱። ኤር፲፫ ፡ ፲፪። መክ፬ ፡ ፰። ፲፩ ፡ ፫)።
፡ መምላት፤ እስከ ልኩ መድረስ፤ ማለቅ መፈጸም፤ መተካከል፤ አለማነስና አለመጕደል፤ ምሉእ ፍጹም ትክክል መኾን፤ የስፍር የቍጥር የሥራ የስፍራ። አመ መልአት ዓመት። መልአ ጽሕፈተ ዝንቱ መጽሐፍ። ኵሉ ማዕምቅ ይምላእ
፡ (ኤር፵፩ ፡ ፲፬። ፍ ፡ ነ። ኢሳ፵ ፡ ፬)።
፡ መብዛት መርባት፤ መበርከት መትረፍ፤ ዐያሌ እጅግ ብዙ መኾን ከልክ ማለፍ ፡ (ዘፍ፴ ፡ ፴። ፵፯ ፡ ፳፯። ፵፰ ፡ ፲፮። ዘፀ፩ ፡ ፯ ፡ ፳)። እስከዚህ ዐጕል ነው።
፡ ማግባት፤ መጨመር አብዝቶ መክተት፤ ኀዳሪውን በማኅደር መምላት፤ ገቢር። መልአ አሕስሊሆሙ ሥርናየ። ምልእዎንኬ ለእላ መሳብክት ማየ። መልእዎ ደመ ለዝንቱ ቤት። ከመ ናእክ መላእካሁ ለብሩር ፡ (ኩፋ ፡ ፵፪። ዮሐ፪ ፡ ፯። ኤር፲፱ ፡ ፬። ሢራ፵፯ ፡ ፲፰)።
መሊክ ኮት ፡ (መለከ ይመልክ ይምልክ። ዐረ መለከ። ዕብ ማላኽ። ሱር ምላኽ) መምለክ፤ ማሸነፍ መግዛት መያዝ፤ መውረስ ገንዘብ ማድረግ። ዘይመልክ ሀገረ። እለ ይመልክዋ ለየብስ። ዮሐናን ወእሊኣሁ ተጸወኑ ኀበ ቍድስ ወመለክዋ። ለዛቲ ምድር ከመ ይምልክዋ ለዓለም። ይሁቡ ኵሎ ዘይመልኩ ለነዳያን ፡ (ምሳ፲፮ ፡ ፴፪። ሔኖ፰፪ ፡ ፬። ዮሴፍ። ዘፍ፵፰ ፡ ፱። አፈ ፡ ተ፲፫)።
፡ መንገሥ መሠልጠን፤ ጌታ ዳኛ ሠሪ ቀጪ መሪ ጠባቂ መኾን። ይመልኮ እበድ። መለከ ላዕሌነ ሀኬት። ዘየዐቢ ብርሃን ከመ ይምልክ መዓልተ። አንሰ ኢይመልክ ለክሙ ወወልድየኒ፤ እግዚ ይመልክ ለክሙ። መለከ እምታሕቴሁ ለንጉሥ
፡ (ምሳ፲፰ ፡ ፪። አፈ ፡ ድ፳፬። ዘፍ፩ ፡ ፲፮። መሳ፰ ፡ ፳፫። አዋል)። ዘይክል ዘይእኅዝ ፥ እግዚእ በማለት ፈንታ ዘኵሎ ይመልክ ይላል፤ አያሰኝም ፡ (ኢዮ፲፭ ፡ ፳፭። ሚል፩ ፡ ፬። ዘካ፩ ፡ ፫)።
መሊጦ ፡ ዐጥፍ ሌጦ ዘብድው፤ ጠጕር የሌለው የላይ ልብስ። እስከ ኢኀደጉ መሊጦሁ ፡ (ገድ
፡ ኪሮ)።
መሊጦን ፡ (ዕብ ሜሌጥ፤ ምሰሶ ባላ፤ ጋድም ሠረገላ) የኪሩቤል ስም፤ ካርባዕቱ እንስሳ አንዱ። ዐምዳዊ ዘዐምድ ማለት ነው፤ መላጥነት ሳይቀር ተሸካሚነትትን ያሳያል። በራ መራ መሊጦን
፡ (መዋሥ)።
መላኂ ፡ (ኂት ኅያን ያት) የሚነቅል የሚመዝ፤ ነቃይ መዛዥ። ሳቦር ወልደ ሐርመዝ ዘይሰመይ መላኄ መትከፍት፤ እስመ ውእቱ ኮነ ሶበ ይመውኦ ለካልእ ንጉሥ የአስሮ ወይመልኅ መታክፍቲሁ ፡ (ስንክ ፡ ሚያ፲፱)።
መላልኤል ፡ (ዕብ ማሃላልኤል) የሰው ስም፤ ፭ኛው ትውልድ ከአዳም፤ ቀዳማዊ ፥ በኵረ አምላክ ፥ ስብሐተ አምላክ፤ ዘይሴብሕ አምላከ ፡ (ዘፍ፭ ፡ ፲፪)።
መላኢ ፡ (ኢት እያን ያት) የመላ የሚመላ፤ መዪ ተመዪ። መላኤ ንትጋ። መላኤ ኵሉ ዓለም ፡ (ጥበ ፡ ጠቢ። አርጋ ፡ ፩)። በመላኢ ፈንታ መምልእ ይላል፤ ፍችው አንድ ነው። መምልአ ዐሥር ፡ (አዋል)።
መላኪ ፡ (ኪት ክያን ያት) የመለከ ፥ የሚመልክ፤ ገዢ ሠራዒ መጋቢ፤ ነጋሢ ወራሲ፤ ባለቤት ጌታ፤ ባለሙሉ ሥልጣን ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፳፬ ፡ ፪። ፴፩ ፡ ፴፯። አፈ ፡ ተ፲፪)። እግዚ መላኬ ነፍሳቲነ ወፈጣሪሃ ውስተ ሥጋነ። እግዚ መላኬ ሰማያት ወምድር። ክርስቶስ መላኬ ኵሉ አጽናፍ። በኵረ መላኪ ፡ (ዮሴፍ። መቃ ፡ ገ፲። ስንክ ፡ መስ፪። ድጓ)።
መላዪ ፡ (ዪት ይያን ያት) መለኛ፤ መላ ዐዋቂ። የሚያፈርስ የሚለያይ፤ አቅላጭ አፍሳሽ። መሳዬ(ሳዌ) ኀጻውንት አድማስ ፡ (ስንክ ፡ ኅዳ፲፪)።
መላጺ ፡ (ጽያት) መላጫ መቍረጫ፤ ምላጭ ሰንጢ፤ ሰይፍ ካራ፤ ስለታም ብረት
፡ (ኢሳ፯ ፡ ፳። መዝ ፡ ፶፩። ዘኍ፮ ፡ ፭)። መላጺ ኢለከፈኒ ርእስየ፤ እስመ ናዝራዊ አነ። ከመ ጠቢብ ዐቃቤ ሥራይ ዘይጠብሕ በመላጺ። ከመ መላጺ በሊኅ ዘክልኤ አፉሁ
፡ (መሳ፲፮ ፡ ፲፯። ዲድ ፡ ፲። ሢራ፳፩ ፡ ፫)።
፡ ምላጭ፤–ላጽዮ ላጸየ።
መሌሊት ፡ (ብ መለያልይ ያት) ሕዋስ ፥ ብልት ፥ አባል ፥ ልዩ ልዩነት ያለው የሥጋ ዐጽቅ፤ በየስሙና በየክፍሉ በየማውዱ፤ ሥር ዥማት እስኪት። ገመዱ መሌሊቶሙ ከመ ሥጋ። ትጠብሖ በበ መሌሊቱ። መለያልየ አዕፅምቲሃ። መሌሊተ ሐቌሁ። መለያልያት ኅቡረ። ወብከ መለያልይ ዝኩ ዘታስተሐቅሮ
፡ (ሚክ፫ ፡ ፫። ዘፀ፳፬ ፡ ፲፯። መሳ፲፱ ፡ ፳፱። ዳን፭ ፡ ፮። አፈ
፡ ተ፭። ፩ቆሮ ፡ ፲፪ ፡ ፳፪–፳፬)።
መልሀቅ ፡ (ብ መላህቅት፤ ታት) ሊቅ ታላቅ የሚበልጥ፤ አለቃ ሹም፤ አሮጌ ሽማግሌ። መላህቅተ ሕዝብ። ኢይፍታሕ ሕዝባዊ ወኢመላህቅት፤ ዘእንበለ ዳእሙ ሥዩማነ ቤተ ክር። ደናግል ወመበለታት ወመላህቅታት
፡ (ባልቴቶች) ይቁማ ቅድመ ኵሎን አንስት ፡ (ዘፀ፲፯ ፡ ፭። ዲድ፲። ፲፪)። መልሀቅ ወንድና ሴት ያስተባብራል፤ ለሴት ሲነገር ቅ ይጠብቃል።
መልህቅ ፡ በቁሙ፤–ለሐቀ።
መልሕቅ [1] ፡ (ቃት፤ መላሕቅ) በቁሙ፤ የመርከብ ልጓም እንዳይኼድ እንዳይናወጥ የሚገታው፤ እንዳልጋ እግር አራት ኹኖ ፪ቱ በፊት ፪ቱ በኋላ ባራቱ ማእዝን የሚወርድ፤ ታላቅ ዘናና ብረት የጐዳ በቄ ቀንድ የሚመስል። ላትሮንስም ብረት ለድብልብሉ ይነገራል። ወረድኩ ውስተ ምድር ከመ መልሕቅ ታሕተ። አውረዱ አርባዕተ መልሕቃተ። ወመተሩ መላሕቀ ፡ (ዮና፪ ፡ ፯። ግብ፳፯ ፡ ፳፱ ፡ ፵። አፈ ፡ ድ፲፩)።
፡ መጽሐፍ፤ የመጽሐፍ ስም። አንክሮጦስን እይ፤ ከዚህ ጋራ አንድ ነው። ይቤ
፡ (ኤጴፋንዮስ) በውስተ መጽሐፉ ዘይሰመይ መልሕቅ ፡ (ሃይ ፡ አበ)።
[2]
፡ በቁሙ፤–ለሐቀ።
(ጥ) መልሖ ሖት
፡ (መልሐ ይሜልሕ ይመልሕ። ዐረ መለሐ። ዕብ ማላሕ። ሱር ምላሕ) ማጨውየት ጨው ማውጣት ፥ ውሃውን ጨው ማድረግ፤ ወይም ጨው መመር፤ በጨው ማጣፈጥ ፥ ማጀል፤ የምግብ የሕፃን የሥጋ የዓሣ የቈርበት። መቈረን እይ፤ የዚህ ጎር ነው።
መልስ ፡ በቁሙ ፥ ስጣዌ ቃል፤ ምላሽ የጥያቄ ፍሬ።
መልበስ መልበስት ፡ (ብ መላብስ ት) ዝኒ ከማሁ፤ ልብስ። አፈ መልበስየ። ኅባኔ መልበሱ። መልበስተ እንግድዓ። ዘመልበስቱ መዛግብተ ብርሃን። ወመላብሲሆሙ ፡ (ኢዮ፴ ፡ ፲፰። መዝ
፡ ፻፴፪። ዘፀ፳፰ ፡ ፬። ፪ዜና ፡ ፬)።
መልታሕት [1] ፡ (ብ መላትሕ። ዕብ ማልታዓ፤ ብ ማልታዖት) መንጋጋ ፥ ጕንጭ ፥ ፊት ፥ የግራ የቀኝ ፡ (ማቴ፭ ፡ ፴፬። ኢሳ፶ ፡ ፮። ፫ነገ ፡ ፳፪ ፡ ፳፬)። ሰላም ለመላትሒከ ተጸፍዖ ዘኢኀፈራ ፡ (ደራሲ)።
[2]
፡ ጕንጭ ፊት፤–ለትሐ።
መልትሐ ፡ (ዲቃ ግ) መለታ፤ እጁን ባፋና በጕንጩ አኖረ። መጽሐፍ ግን በመልትሐ ፈንታ ተመላትሐ ይላል። ትኔጽሩኒ ወታነክሩ ፥ ወትትመላትሑ በእደዊክሙ ፡ (ኢዮ፳፩ ፡ ፭)።
(ላ) መልዐ ፡ (ላ) መልዐ፤–መላ ተመላ፤–መሊእ መልአ።
(ጥ) መልአ ኦት ፡ (ጥ) መልአ፤–ያዘ ፥ ዠመረ፤–መልዖ መልዐ።
መልአከ አው ተመልአከ ፡ አለቃ ኾነ፤ ተሾመ። ከመ ትትመልአክ ለነ። ተመልአክ ለነ አንተ። ወተመልአከ አቤሜሌክ ለቤተ እስራኤል። ተመልአኩ ካህናት ላዕለ ደቂቀ እስራኤል ፡ (ዘኍ፲፮ ፡ ፲፫። መሳ፰ ፡ ፳፪። ፱ ፡ ፳፪። ክብ ነገ፲፯)።
መልአክ ፡ (ብ መላእክት። ዐረ መልአክ። ሱር ማልአካ። ዕብ ማልአኽ) በቁሙ ፥ የግዜር መልክተኛ ፥ ሰማያዊ ረቂቅ፤ የእሑድ ፍጥረት። ወአስተርአዮ መልአክ እምሰማይ። ፈነወ መልአኮ ወአድኀነኒ። ተሰዓ ወተስዐቱ ነገደ መላእክት ፡ (ሉቃ፳፪ ፡ ፵፫። ግብ፲፪ ፡ ፲፩። ግንዘ)።
፡ አለቃ ፥ ሹም ፥ አበጋዝ፤ ተሹሞ ከንጉሥ የተላከ። መልአከ አሕዛብ። ወንትልዎ ለፍጹም መልአክነ። መላእክት ረዋጽያን። ነገሥተ ምድር ወመላእክትኒ። ዘያወፅእ ነፍሶሙ ለመላእክት ፡ (ማቴ፳፯ ፡ ፲፩። ዕብ፲፪ ፡ ፪። መዝ ፡ ፪። ፸፭)። ልኢክና መልአክ ባማርኛ ይተባበራሉ። ፡ (ግጥም) ይድረስ አይድረስ ምን ዐውቃለኹ፤ መላኩን ልኬዋለኹ።
፡ በቁሙ ፥ መላክ፤–ልኢክ ለአከ።
መልአክና ምልእክና ፡ አለቅነት፤ መልአክነት፤ መልአክ መኾን፤ መባል። ኢይወፅእ ምስፍና ወምልክና እምአባሉ ባለው ምልእክና ይላል
፡ (ዘፍ፵፬ ፡ ፲)።
መልዕልት ፡ (ታት) መውጫ ፥ መረጋገጫ ዕርከን፤ መሰላል። ወመልዕልቴሁ ገጸ ፡ (ሕዝ፵፫ ፡ ፲፮)።
፡ ላይ፤ በላይ። ላዕልና ዲበን እይ፤ ከዚህ ጋራ አንድ ነው። ወጽልመት መልዕልተ ቀላይ። ለዘወረደ እመልዕልት። አልቦ ይትማሰለነ፤ እስመ መልዕልተ አምሳል ንሕነ ፡ (ዘፍ፩ ፡ ፪። ድጓ ፡ ቀሌ)።
መልእክት ፡ (ታት) በቁሙ መልክት፤ ደብዳቤ ክታብ። ወበጽሐ መልእክት ኀበ መልአከ ሰጲራ። በዘተርፉ መልእክታቲሁ ፡ (ግብ፳፩ ፡ ፴፩። አፈ ፡ ድ፴፬)።
(ጥ) መልዖ ዖት ፡ (መልዐ ይሜልዕ ይመልዕ። ዐረ መለዐ) መንገድ መዠመር፤ መምራት፤ ፈጥኖ መነሣት እግርን መንቀል፤ በችኰላ መኼድ መራመድ። መልዕ ንሑር። መልዕ ፍኖተከ። ቅድሜየ እሜልዕ ወድኅሬ እዴግን። ደመ ትዝምድክን እምትካት ዘመንግሥት ፥ ወይሜልዕሂ ዘእምይእዜ ፡ (፩ነገ ፡ ፳፮ ፡ ፲፩። ስንክ ፡ መስ፲። ፊልጵ፫ ፡ ፲፬። ቄር)። አንዳንድ መጣፍ በመልዐ ፈንታ አምልዐ አመልዐ ይላል፤ ስሕተት ነው። ገብኡ ድኅሬሆሙ ወኢያመልዑ ቅድሜሆሙ። ርቱዓን የሐውሩ ቦቱ ወያሜልዑ ቅድመ። ወዘንተ ብሂሎ አመልዐ ቅድመ ወዐርገ ኢየሩሳሌም ፡ (ኤር፯ ፡ ፳፬። ሚክ፪ ፡ ፯ ፡ ፰። ሉቃ ፡ ፲፱ ፡ ፳፰)።
መልከተ ፡ (ተቀ ግ) አመለከተ አሳየ፤ ምልክት ጣፈ አደረገ። መለከት ነፋ፤ አስጮኸ።
መልክእ [1] ፡ (ኣት) በቁሙ፤ መልክ ገጽ ፥ የፊት ቅርጽ፤ ሥዕል ምስል፤ ልክ ያለው በልክ የተሠራ። ዘመኑ መልክኡ ወመጽሐፉ። መልክአ ዲናር ይዌልጡ። መልክአ ገጹ ለኤልያብ። እመ በጽሑ መልክኣት ተርእዩ በልቡና ፡ (ማቴ፳፪ ፡ ፳። ቄር። ቅዳ ፡ ጎር። ፈላስ)።
፡ አካል ቁመት ፥ የአካል ህላዌ፤ ገላ ሕዋስ ፥ ከእግር እስከ ራስ። አርኣያ መልክእከ። ገጽ ወመልክእ። እሙንቱ ሠለስቱ አካላት ፍጹማነ መልክእ ወገጽ ፡ (ጥበ፲፮ ፡ ፳፩። ሃይ ፡ አበ፯ ፡ ፲፭)። እግዚ አክበሮ ለሰብእ በአስተሣንዮ ሥነ መልክእ ሰብኣዊ እምዘመደ ኵሉ ፍጥረት። እንዘ ውእቱ ፍጹመ መልክእ፤ በከመ ፈጠሮ እግዚ ፡ (ፈ ፡ መ ፡ ፩ ፡ ፩። ፴፫ ፡ ፬)።
፡ የድርሰት ስም፤ የመልክ ውዳሴና መዝሙር፤ ከራስ ጠጕር እስከ እግር ጥፍር የሚቈጥር። መልክአ ኢየሱስ
[2]
፡ መልክ ፊት፤–ለኪእ ለክአ።
መልጉ ፡ (ብ መላግው) ማላጋ፤ ምልግልግ። ዕጉሥ ፥ ታጋሽ ትዕግሥተኛ፤ ቻይ ልበ ሰፊ ፡ (ሲኖዶ ፡ ገ፫፻፺፬)።
መልጶጶን [1] ፡ (ዕብ ማልፖን፤ ምላፕፖን) ዱባ የባር ቅል፤ ታላቅ ክብ፤ ወይም ሞላላ ሳይቀቀል የማይበላ፤ ዐይነቱ ብጫ። ፡ (ተረት) ዱባና ቅል ዐብሮ ይበቅል፤ አበላሉ እየቅል።
[2] ፡ (ጽር ፖፖናስ። ዕብ አባጢሕ) በጢሕ፤ ብርጭቅ የዱባ ዐይነት፤ ጥሬው የሚበላ የማይቀቀል። ባለቅኔዎች ግን ጐመን ይሉታል፤ በጢሕን እይ። መልጶጶን ወስጕርንድ ፡ (ዘኍ፲፩ ፡ ፭)።
መልፉፍ ፡ (ዐረ) የተሸፈነ የተጠቀለለ፤ ሽፍን ጐመን ኵርንባ፤ ጭብጦና ኵብ ራስ የሚመስል ፥ ቶሎ የሚበስል።
መሎኬ ፡ (ጽር ማላኺ፤ ሞሎኺ። ዐረ ምሉኅያ፤ ምሉኅዪት) ሙሉክዬ፤ ጥሩ ሐምል የወጥ ቅጠል፤ ለግላጋ ጠውላጋ፤ እንደ ልቅና እንደ ሳማ የሚማልግ የሚምለገለግ፤ ለንጉሥ የሚገባ የንጉሥ ወጥ ማለት ነው፤ ባንዱራውን ያቡን ወጥ እንዲሉት። እንዳረቡ ግን በመልኀ ዘይብ ሲፈቱት የሚነቀልና የሚላሰስ ያሰኛል። ወይጸመሒ ከመ መሎኬ በውስተ ሐሩር። ውዕየ በነደ ቃሉ ከመ እርየተ ሐምለ መሎኬ ፡ (ኢዮ፳፬ ፡ ፳፬። ስነክ ፡ የካ፲፫። መጽ ፡ ምስ)። ባለብሉዮች ግን ሐመድማዶ ይሉታል፤ ፍችው አይዶለም።
መመስል ፡ (ልት ላን ላት) ተራች፤ ምስል አፍሳሽ።
መመተ ፡ (መምቶ። ዕብ ሁሜም) ጐደለ አነሰ፤ ሕጹጽ ኅሱር ነውረኛ ኾነ፤ የመልክ የሕዋስ የጠባይ የግብር። ባለቅኔዎች ግን እንደ መምዐ ተሸበረ ብለው ይፈቱታል፤ ከጥሬው በቀር አንቀጹ አይገኝም፤ ጎርነቱ የመምዐ ነው።
መምህር ፡ (ርት ራን ራት) ዝኒ ከማሁ፤ በቁሙ ፥ መምር የትምርት አባት። አሐዱ ውእቱ መምህርክሙ። መምህርት ይእቲ። መምህራነ ቤተ ክርስቲያን
፡ (ማቴ፳፫ ፡ ፰። ስንክ ፡ ሐም፳፭። ኅዳ፳፬)። ውርወት ድቀት ፍርሀት በማለት ፈንታ መምህረ ሕግ ይላል፤ የመላሽ ስሕተት ጎው ፡ (መዝ፱ ፡ ፳፩)።
መምሕፃን ፡ መማጠኛ፤
መሸሻ መጠጊያ የሙጥኝ መባያ፤ ገዳም። ድንቅ
ታምራት የረዴት ምልክት። ነደቀ ምሥዋዐ ወሰመየ ስሞ መምሕፃን ፡ (ዘፀ፲፯ ፡ ፲፭)። ሽቦሌት በማለት ፈንታ መምሕፃን ይላል፤
የተሳሳተ ነው፤ ሰብለን እይ ፡
(መሳ፲፪ ፡ ፮)።
መምሕፅን ፡ (ናት) ጠባቂ ባልደረባ፤ መልአከ ዑቃቤ
፡ (አርጋ)።
መምለኪ ፡ ያመለከ ፤ የሚያመልክ
፥ የሚያስመልክ ፤ አምላኪ አስመላኪ። መምለኬ እግዚ። መምለክያነ ጣዖት ፡ (ቄድር። ስንክ)።
ባሕታዊ መናኒ መነኵሴ ፤ ፈቃደ ሥጋውን የሚገዛ ፤ ነፍሱን ለግዜር ሥጋውን ለማኅበር የሚያስገዛ። መምለኪ ፍጹም መምለኪ ማእከላዊ ፤ መምለኪ ወጣኒ ፡ (ፊልክ ፡ ፬)።
መምሰ(ስ)ል ፡ መሰል አካል፤ አምሳያ እኩያ፤ ሱታፌ አንጻር። አልባቲ መምሰል እምአንስት። ሀገር እንተ አልባቲ መምሰል። እስመ መምስልከ ውእቱ
፡ (ዮሴፍ። መዋሥ። ኩፋ ፡ ፴፰)። ቅድም ጥቃ በማለት ፈንታ መንጸር እንደ ማለት መምሰል ይላል ፡ (መክ ፡ ፲፬)።
መምሠጥ ፡ (ብ መማሥጥ) መንጠቂያ ፥ መንጠቆ፤ መኆሥሥ ሜንጦ። የድንኳን ቍልፍ፤ ቀለበት ዘለበት፤ ወይም በየጠርዙና በየመጋጠሚያው ያለው ብስ ነዳላ ፥ ማያያዣው ገመዱና ቍልፉ የሚገባበት። ኆጻድን እይ፤ ከዚህ ጋራ አንድ ነው። ወግበር መምሠጢሆን ዘሕብረ ያክንት፤ ኀምሳ መማሥጠ። መማሥጠ መናግሥት ፡ (ዘፀ፳፮ ፡ ፬ ፡ ፭ ፡ ፳፱)። ገመዱና ፈትሉም መምሠጥ ይባላል።
መምተርት ፡ መምተሪያ፤ መቍረጫ ፡ (ዕር ፡ ኢሳ፬ ፡ ፳፩። ሔኖ፳፩ ፡ ፯)።
መምዐ ፡ (መዪዕ ሜዐ። ምዒው መዐወ) ፈራ ፥ ደነገጠ ፥ ከልብ ካንዠት፤ ታወከ ተሸበረ ሸሸ ደነበረ። ከመዐወና ከሜዐ ከኹለቱ የተዴቀለ ነው። መምዑ ወጐዩ። መምዑ መሳፍንተ ኤዶም። ኢትፍርሁ ወኢትመምዑ። ይሜምዑ ዐሥርቱ ምእት እምድምፀ አሐዱ
፡ (ዮዲ፲፭ ፡ ፫። ዘፀ፲፭ ፡ ፲፭። ዘዳ፳ ፡ ፫። ኢሳ፴ ፡ ፲፯)።
መምዕ ፡ የሚያሸብር ፥ አሸባሪ፤ ማሸበሪያ። ኢእቢድኑ ወኢመምዕ ዝንቱ ዘይነግሩ
፡ (ቄር ፡ እስት ፡ ገ፲)።
መምዕላይ ፡ ወንጀለኛ፤ ሽፍታ፤ ወያኔ አረመኔ ክፉ ጨካኝ። ንጉሥ ዘእንበለ ሕግ ኢንጉሥ ውእቱ፤ አላ መምዕላይ። ሰበርከ ስነኒሁ ለመምዕላይ ንጉሠ ገሃነም
፡ (መጽ ፡ አዳር ፡ ፶። ግንዘ)። መዐለን ተመልከት፤ የዚህ ወንድም ነው።
መምዕል [1] ፡ ወንጀለኛ፤–ምዒል መዐለ።
[2] ፡ መምዕል፤ ፡ (ልት ላን ላት) ዝኒ ከማሁ። አይቴ ሀለዉ ነገሥት መምዕላን ወመዋእያን። መምዕላን ነገሥት ፡ (ግንዘ። ቀሌ)። ለዐለንና ዐለወን ዐለየን እይ፤ የዚህ ጎሮች ናቸው፤ ባለቅኔዎች ግን በመዐለ ፈንታ መስሙን መምዐለ ብለው ይገሱታል፤ የተሳሳተ ነው።
መምክሕ መመክሕ ፡ መመኪያ፤ የሚያስመካ አስመኪ፤ አስከባሪ። ከመ ኢይበሉኒ ፀር አይቴኑ መምክሑ ፡ (አይቴኑመ ምክሑ)
፡ (ደራሲ)።
መምክር ፡ (ርት ራን ራት፤ መማክርት) ዝኒ ከማሁ። እሙ ኮነቶ መምክረ። እስመ መምክርት ይእቲ። መማክርቲሁ ለዳዊት
፡ (፪ዜና ፡ ፳፪ ፡ ፫። ጥበ፰ ፡ ፬። ፪ነገ ፡ ፲፭ ፡ ፲፪)።
መምክን ከኒ ፡ መምከኛ፤ የሚያመክን ፥ አምካኝ። መምከኒተ ሕዝብ ፡ (ሕዝ፴፮ ፡ ፲፪)።
መምጠቅ ፡ (ቅት) ኰረኮ ቍናማት የግልገል ስልቻ፤ ወይም ከነት ከቈርበት የሚሠራ የረኞች ኰፈዳ፤ ወንጭፍና ደንጊያ ሌላም ነገር የሚከቱበት። ኀረየ ኀምስተ አእባነ እምውስተ ፈለግ ወወደየ ውስተ መምጠቂሁ ፡ (፪ነገ ፡ ፲፯ ፡ ፵)።
መሞግስ ፡ (ስት ሳን ሳት) የሚወድ የሚያከብር፤ ወዶ የሚያሶድድ፤ ባለሟል የሚያደርግ፤ የሚያስደርግ። መሞግስት
፡ (አርጋ)።
መሠልስ ፡ (ስት ሳን ሳት) የሚሠልስ፤ የሚያሠልስ አሠላሽ።
መሠረት ፡ (ታት) በቁሙ፤ የሕንጻ ሥር፤ መብቀያ
፡ (፩ቆሮ ፡ ፲–፲፪። ሉቃ፮ ፡ ፵፰። መዝ ፡ ፹፰)።
መሰረት ፡ በቁሙ፤–ሣርሮ ሣረረ።
መሠርይ ፡ (ዪት ይት ያን ያት) ዝኒ ከማሁ፤ መሠሪ፤ ጠንቋይ፤ ሟርተኛ፤ ምትሀታም። ሲሞን መሠርይ። ጠባብ ይእቲ ወመሠርይት። ኢዮሎስ ሊቀ መሠርያን ፡ (ግብ፰ ፡ ፬። ዮሴፍ። ቀሌ)።
መሰንቃዊ ፡ ባለመሰንቆ፤ ዘፋኝ አዝማሪ። ኢትዛዋዕ ምስለ መሰንቃዊት
፡ (ሢራ፱ ፡ ፪። ፈላስ)።
መሰንቅው ፡ (ዋን ዋት ቁት) ዝኒ ከማሁ፤ አዝማሪ ዘማሪ፤ ዘፋኝ ቀንቃኝ መሪ።
መሰንቆ ፡ (ብ መሰናቅው፤ ቁት ንቆታት) በቁሙ፤ ሙዚቃ፤ ዜማ። መሰንቆ ወመዝሙር
፡ (ሢራ፵ ፡ ፳፩)። መሰናቅው። ቃለ መሰናቁት። መሰንቆታት
፡ (አርጋ ፡ ፫። ቅዳ። ራእ፲፬ ፡ ፪)። ከበሮ አታሞ ምሥጋር በማለት ፈንታ መሰንቆ ይላል፤ ስሕተት ነው ፡ (መሳ፲፩ ፡ ፴፬። ፳፩ ፡ ፳፩። ፪ነገ ፡ ፮ ፡ ፲፫)።
መሠንይ ፡ የሚያሳምር፤ የሚያበጅ፤ አስጊያጭ። መሠንያነ ሐተታ ፡ (አዋል)።
መሰከ ፡ አመሸከ ፥ እምሽክ አደረገ፤ ቈረጠ ዐጨደ። ነጨ ጋጠ አመሰኳ፤ ሰኵዐን እይ። ባለቅኔዎች ግን አቀጠነ ይሉታል፤ መስክ መሰክ ማሽንክ ማለት የዚህ ዘር ነው።
መሰውር ፡ (ርት ራን ራት) ዝኒ ከማሁ። መክደኛ ክዳን። ረዳኢ ወመሰውር
፡ (ዘፀ፲፭ ፡ ፪። ፳፯ ፡ ፫)።
መሰግል ፡ (ልት ላን ላት) ጠንቋይ፤ ሟርተኛ፤ ኮከብ ዐዋቂ፤ ፍልሱፍ፤ መለኛ። ለመርዓተ ፀርነ ሲኦል ኢሳይያስ መሰግላ እመ ተስእለቶ ቅድመ ወጠየቀቶ በቃላ፤ ዘመነ ሥጋዌ ማቴዎስ ያፈርሀኪ ይቤላ፤ ወይትባአሰኪ ደም ዘተክዕወ በመሐላ። መሰግለ ፀሓይ። መሰግላን በአዕዋፍ
፡ (ቅኔ። ሲኖዶ። ዲድ ፡ ፲፫። ማቴ፪ ፡ ፩)።
መሠግር ፡ አጥማጅ፤–ሠጊር ሠገረ።
መሰጠ ፡ ነጠቀ፤–መሢጥ መሠጠ።
መሲሓዊ ፡ (ዊት ውያን ያት) የመሲሕ፤ በመሲሕ የሚያምን ፥ መሲሕን የመሳ ክርስቲያን። ሕግ መሲሓዊት። በዓላት መሲሓውያት። ሕዝብ መሲሓውያን ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፬። ፳፫። አቡሻ። ስንክ ፡ መስ፬)።
መሢሕ ፡ በቁሙ ቅቡዕ፤–መሲሕ መስሐ።
መሲሕ ሖት ፡ (መስሐ ይመስሕ ይምሳሕ። ዕብ ማሻሕ። ሱር ምሻሕ። ዐረ መሰሐ፤ ቀባ) መቅባት፤ ቅባት መጨመር፤ በቅባቅ ማሸት ማጣፈጥ። ዘቀብዖ ባለው ዘመስሖ እንዲል ፡ (ግብ፲ ፡ ፴፰)።
፡ መምሳት፤ ምሳ መብላት። ፡ (ተረት) ታልመሱ እያነሡ። እምድኅረ አኅለቁ መሲሐ። ወቦኡ ንጉሥ ወሐማ ይምስሑ ምስለ ንግሥት። ንዑ ንምሳሕ። ወእምድኅረ መስሑ
፡ (፫ነገ ፡ ፩ ፡ ፵፩። አስቴ፯ ፡ ፩። ዮሐ፳፩ ፡ ፲፪
፡ ፲፭)።
መሲሕ ፡ (ሓን) ፡ (ዐረ። ዕብ ማሽያሕ። ሱር ምሺሓ) በቁሙ፤ ምሱሕ የተቀባ ቅቡዕ፤ ለሹመትና ለምግብነት የተዘጋጀ፤ ንጉሥ ታ ካህን ወይም ነቢይ፤ ሲቀባ ሀብታተ መንፈስ የመሉበት። የክርስቶስን ፍች እይ፤ ከዚህ ጋራ ፩ ነው። ለመሲሕየ ቂሮስ። ኢትግስሱ መሲሓንየ። መኑ ውእቱ ሐሳዌ ዘእንበለ ዘይክሕድ ወይብል፤ እስመ ኢየሱስ ኢኮነ መሲሐ፤ ወዝንቱ ውእቱ ሐሳዌ መሲሕ ፡ (ኢሳ፵፭ ፡ ፩። መዝ፻፬። ፩ዮሐ ፡ ፪ ፡ ፳፪)። መሲሕ ማለት በሦስቱ ቋንቆች በዐረብ በሱርስት በዕብራይስጥ ቅቡዕነት ብቻ ያሳያል፤ በግእዝ ግን ቅቡዕነትን መደብ አድርጎ ምሳሕነትንም ከነጊዜው ከናቀራረቡ ያሳያል ፡ (ዮሐ ፡ ፲፱ ፡ ፲፬። ማቴ ፡ ፳፯ ፡ ፵፭ ፡ ፵፮)።
መሲሕና ፡ መሲሕነት፤ መሲሕ መኾን።
መሲል ሎት ፡ (መሰለ ይመስል ይምስል። ዕብ ማሻል። ሱር ምታል። ዐረ መሰ(ተ) ለ) መምሰል፤ መስሎ መታየት ፥ ባሕርይ ሳይለወጥ ሌላ መባል፤ በውነት ወይም በሐሰት ፥ ያውም በመልክና በግብር በነገር ብቻ። ይመስሎ ዝንቱ ወልድ ለጦቢት። አርዌ ዘይመስል ድበ። ወይመስሎሙ ወልደ ዮሴፍ። ነገርየ ይመስል ሐሰተ። እመኒ ኅዳጠ ወዘሀበከ ብዙኀ ይመስሎ። ቦ ፍናው ዘይመስላሁ ለብእሲ ርቱዐተ ፡ (ጦቢ፯ ፡ ፪። ዳን፯ ፡ ፭። ሉቃ፫ ፡ ፳፫። ኢዮ፮ ፡ ፫። ሢራ፳ ፡ ፲፬። ምሳ፲፮ ፡ ፳፭)። በመሰለ ፈንታ ተመሰለ ተማሰለ ይላል፤ ስሕተት ነው። ተመስለ ከመ ብእሲ። ተመሰሉ ኪያየ በከመ አነ እትሜሰሎ። መነ ትሜሰል ፡ (ፊልጵ፪ ፡ ፯። ፩ቆሮ ፡ ፲፩ ፡ ፩። ሕዝ፴፩ ፡ ፪)። ከመ ዘኢይትማሰል ገጽ ገጸ። ይትማሰሎሙ ለገባርያነ ብርት። መኑ ይትማሰሎ ለጣዕመ ዚኣሁ ፡ (ምሳ፳፯ ፡ ፲፱። ጥበ፲፭ ፡ ፱። ቀሌ)። አርእስቱ የቀተለና የቀደሰ ቤት ነው፤ ስለዚህ በመላላትና በመጥበቅ በቱሱሕነት ይገሰሳል።
መሲና ፡ (ናት) በቁሙ፤ የማቶልድ ከብት ፥ መካን ሙስንተ ማሕፀን።
መሲክ ኮት ፡ (መሰከ ይመስክ ይምስክ። ዕብ ማሻኽ። ዐረ መሰከ) መያዝ መጨበጥ፤ መሳብ መጐተት፤ መለጠጥ መዘርጋት፤ ለመንደፍ የቀስት የፍላጻ። ምስክ አባ ቀስተከ ወፈኑ ሐጸከ። ወሰቀ ወመሰከ ቀስቶ። እስመ መሰኩከ መንገሌየ
፡ (ኩፋ ፡ ፴፰። ፬ነገ ፡ ፱ ፡ ፳፬። ዘካ፱ ፡ ፲፫)። ወሰቀ ማለብ መደገንን ፥ መሰከ አሰማምቶ ይዞ መሳብ መንደፍን ያሳያል፤ ነገር ግን ኹሉም በኹሉ አለ፤ ይወራረሳሉ። ወስቅ ቀስተከ ወምስክ አሕጻከ ፡ (፬ነገ ፡ ፲፫ ፡ ፲፮)።
መሲው ዎት ፡ ( መስወ፤ መሰወ ይመሱ ይምሱ። መለየ አምሀወ) ማቅለጥ ፥ ማፍሰስ፤ ውሃ ማድረግ፤ ማጥፋት ማፍረስ፤ የረጋውን። ከመ ይመስዎ ፀሓይ ለበረድ። ነደ እሳት ይመስዋ ለነፍሱ። መቅሠፍት ይመስዎሙ። ዝንቱ ማይ ይምሱ ኵሎ አባላተኪ
፡ (ሢራ፫ ፡ ፲፭። ፴፰ ፡ ፳፰። ፳፯ ፡ ፳፱። ፍ ፡ ነ ፡ ፳፬ ፡ ፮)። ኢከላእኩ ኢያጽለምኩ በማለት ፈንታ ኢመሰውኩ ዐይነ ዕቤር ይላል፤ የመላሽ ስሕተት ነው፤ ባለብሉዮች ግን አላስለቀስኩም ብለው ይፈቱታል ፡ (ኢዮ፴፩ ፡ ፲፮)።
መሢጥ ጦት ፡ (መሠጠ ይመሥጥ ይምሥጥ። መለጠ፤ መዘገ፤ መጠቀ) መንጠቅ፤ መቀማት በኀይል መውሰድ፤ መዝረፍ መግፈፍ። ትምህረ መሢጠ። መሠጡ ኖላዌ ምስለ መርዔቱ። ትመሥጥዎሙ አምእስቲሆሙ እምላዕሌሆሙ
፡ (ሕዝ፲፱ ፡ ፫። ኢዮ፳፬ ፡ ፪። ሚክ፫ ፡ ፪)።
፡ ሸሸ ሮጠ፤ ዳነ ወጣ አመለጠ፤ እንዳይያዝ ፥ ወይም ነጥቆ ፥ እንደ በቅሎ። መንጠቅ ፪ ያሳያል፤ ራስን ገንዘብን ከሌላው እጅ፤ መጽሐፍ ግን በመሠጠ ፈንታ አምሠጠ ይላል፤ ግስነቱ ገቢርና ዐጕል ነውና፤ አያሰኝም። አምሠጡ ውስተ ጽዮን። ወይጠል ዘያመሥጥ። አምሠጠ በፈረስ ረዋጺ። እመ ቦ ዘአምሠጠክሙ። ከመ ትክሀሉ አምሥጦ
፡ (ኢሳ፲፫ ፡ ፲፬። ፫ነገ ፡ ፳ ፡ ፳። ፬ነገ ፡ ፲ ፡ ፳፬። ሉቃ፳፩ ፡ ፴፮)።
መሳሒ ፡ (ሒት ሕያን ያት፤ ሕት) የመሳ የሚመሳ፤ ምሳ በል፤ ቀቢ።
(ላ ጥ) መሳሊ መምሰሊ ፡ (ሊት ልያን ያት) የሚመስል መሳይ ፥ ተራች፤ ሠዓሊ ምስል አፍሳሽ። ምድር መምሰሊተ ሕማምየ። ኩኑ መምሰልያነ እግዚ። መምሰሌ ርጢን ፡ (ጥበ፯ ፡ ፫። ቄር ፡ ጰላ። አዋል)። በመሳሊና በመምሰሊ ፈንታ ተመሳሊ ይላል፤ አያሰኝም። አፍቅሮተ ሰብእ ተመሳሊት ለአፍቅሮተ እግዚ። ተመሳልያን ቦሙ ውስተ ምግባራቲሆሙ። ይኩኑ ተመሳልያነ በምግባራቲሁ። ተመሳሌ ንኡስ ቀርን። ተመሳሌ አባ ይስሪን ፡ (ፊልክ ፡ ፻፲፬። ፻፹፬። ፍ ፡ ነ ፡ ፭ ፡ ፲፭። ጥበ ፡ ጠቢ። ደራሲ)።
መሣንቅ ፡ (ቅት) የሥንቅ መያዦች፤ አቅማዶች። አምጽአ ዝኰ መሣንቀ በማኅተሞን። ወጾሩ መሣንቀ ብሉየ። መሣንቂነ ፡ (ጦቢ፱ ፡ ፭። ኢያ፬ ፡ ፪። ፩ነገ ፡ ፱ ፡ ፯)። መሣንቅ ብሎ ዝኰ፤ ብሉየ ማለት፤ የጣፊ ስሕተት ነው። ዘእንበለ ይቁም አድባር
፡ (መዝ ፡ ፹፱)።
መሣዕርት ፡ ሚዶዎች፤ ብርኵማዎች።
መሳዊ ፡ (ዊት ውያን ያት) የሚያቀልጥ ፥ አቅላጭ አጥፊ ፡ (ስንክ ፡ ኅዳ)።
መሳውቃት ፡ የብዙ ብዙ። ድጋፎች፤ ደገፋዎች
፡ (፫ነገ ፡ ፲ ፡ ፲፪)።
መሳውብ ፡ መሶቦች፤ አገልግሎች። ምስጢራቸው ሣጥንነትና ክብነት ነው።
መሣጢ ፡ (ጢት ጥያን ያት፤ ሠጥ) የነጠቀ ፥ የሚነጥቅ፤ ነጣቂ ቀማኛ። አንበሳ መሣጢ። ተኵላ መሣጢ። አራዊት መሣጥያን። ተኵላት መሠጥ ፡ (ዮሴፍ። ቀሌ። ፍ ፡ ነ ፡ ፴፫ ፡ ፬። ማቴ፯ ፡ ፲፭)።
መሴስይ ፡ (ያን ያት ሲት) ዝኒ ከማሁ። አነ እግዚ ፈጣሪሁ ወለሓኵሁ መጋቢሁ ወዐቃቢሁ ወመሴስዩ ለኵሉ ዘሥጋ። እወ እግዚኦ መጋቤ ኵሉ እወ እግዚኦ መሴስየ ኵሉ መሴሲት ፡ (ቀሌ። ቅዳ ፡ ዲዮስ። አርጋ ፡ ፭)።
መሥሐቂ ፡ (ሕቅ ቅት ቃን ቃት) የሚሥቅ ሣቂ፤ የሚያሥቅ አሣቂ፤ አጫዋች ቀላጅ ቧልተኛ፤ ዘፋኝ አዝማሪ። መካነ መሥሕቃን
፡ (ሲኖዶ)።
መስሐብ ፡ (ብ መሳሕብ) መሳቢያ፤ የብረት መሣሪያ፤ ብዙ ጥርስ ያለው፤ ወይም እንዳካፋ ያለ። ወገብሩ ሎቱ መስሐበ ኀጺን ፡ (ስንክ ፡ የካ፳፩)።
መስሕብ ፡ (ብት ባን ባት) የሚስብ፤ የሚያስብ፤ ሳቢ አሳቢ አስጐታች፤ ማራኪ አስማራኪ።
መስሕት ፡ (ጥት) ፡ (ታን ታት) ዝኒ ከማሁ። የነፍስ ዕንቅፋት። ጋኔን መስሕት። ኀይል መስሕት። አጋንንት መስሕታን። መስሕታት ለካልኣን ፡ (ኢሳ፲፱ ፡ ፲፬። ፪ተሰ ፡ ፪ ፡ ፲፩። ፩ጢሞ ፡ ፬ ፡ ፩። ዲድ ፡ ፲፬)። ደብር መስሕት፤ የጣዖት ተራራ፤ ቤተ ጣዖት ምሥዋዐ ጣዖት ፡ (፬ነገ ፡ ፳፫ ፡ ፲፫)።
መስኅንት ፡ የማድ ቤት፤ ማብሰያ መቀቀያ። አልቦ ዘያመጽእ መብልዐ ድዉያን ውስተ መስኅንተ አኀው ሶበ ያበስሉ፤ አላ ይግበሩ ሎሙ ለድዉያን እንተ ባሕቲቶሙ ፡ (ሥር ፡ ጳኵ)።
መሥለስ ፡ (ብ መሣልስ) መሠለሻ፤ ሦስት ማድረጊያ ከሦስት መክፈያ፤ ወይም ሦስቱን እጅ አንድ የሚያደርግ፤ ሚዛን መስፈርት የሥልስ ወጭት ፡ (ዘፍ፲፰ ፡ ፮። ማቴ፲፫ ፡ ፴፫። ሉቃ፲፫ ፡ ፳፩)።
መስልማዊ ፡ (ዊት) የእስላም፤ እስላም የኾነ፤ ያሰለመ። መስልማዊት
፡ (ቄድር)።
መስልም [1] ፡ እስላም፤–ሰሊም ሰለመ።
[2] ፡ (ምት ማን ማት። ዐረ ሙስሊም) ያሰለመ፤ እስላም። ንስራኒ ኮነ መስልመ። መስልማን ፡ (ታምረ ፡ ማር። አዋል)።
መሥልስት ፡ ሦስት ወገን፤ ሦስት ክፍል፤ ታላቅ ሠረገላ ሦስት ፈረሶች የሚስቡት። ወትከፍል ደወለ ምድርከ መሥልስተ። መስተጽዕናን በመሥልስት ፡ (ዘዳ፲፱ ፡ ፫። ዘፀ፲፭ ፡ ፬)። ሲዘረዘርና ሲናበብ ግን ሦስተኛ ያሰኛል። ወመሥልስታ ለፀሓይ ያውዕዮሙ ለአድባር ፡ (ሢራ፵፫ ፡ ፬)። ሙቀቷ ቀትሯ በጋዋ ማለት ነው፤ ሦስተኛነቱም ከክበብ ከጸዳል፤ ከነግህ ከሠለስት፤ ከክረምት ከመፀው ይባላል።
መስሎ ሎት ፡ (መሰለ፤ ይሜስል ይመስል) መመሰል ፥ መተረት፤ ነገርን ከነገር ማስጠጋት፤ ማመሳሰልና ማነጻጸር፤ በቃል። መስል ምሳሌ። እሜስል ላዕሌክሙ አምሳለ። ውስተ መስሎ ነገር ኢይሄልዉ። ወመሰለ ሎሙ ወመሀሮሙ
፡ (ሕዝ፲፯ ፡ -፪። መሳ፲፬ ፡ ፲፪። ሢራ፴፰ ፡ ፴፫። ሉቃ፲፬ ፡ ፯)።
፡ መሣል መንደፍ መበገር ፥ መልክ ማውጣት፤ በቀለም በርሳስ። ምስል ማፍሰስ ፥ ጣዖት መሥራት፤ ማንጠጥ መቅረጥ፤ የሸክላ የማዕደን የዕፅ የቀርን፤ ምንም ስልቱ ቢለይ ምስጢሩ ከዚያው ከመስሎ አይወጣም። ገብሮ ወመሰሎ። ይሜስል ጽቡረ በእደዊሁ። ገለፎ ወመሰሎ በአምሳለ ሰብእ ፡ (ኢሳ፵ ፡ ፲፱። ፴፰ ፡ ፴። ጥበ፲፫ ፡ ፲፫)። ዳግመኛም በመሰለ ፈንታ አስተማሰለ ይላል፤ አያሰኝም። በመኑ ታስተማስልዎ ለእግዚ። በመኑ አስተማስላ ለዛቲ ትውልድ። አው አስተማሰሎ በእንስሳ። ከመ ታመክሮ በአስተማስሎ ፡ (ኢሳ፵ ፡ ፲፰። ማቴ፲፩ ፡ ፲፮። ጥበ፲፫ ፡ ፲፬። ፪ዜና ፡ ፱ ፡ ፩)። ሐቀረንና ዐገሠን እይ፤ ይህም እንደዚያ ነው።
መሥመሪ ፡ (ሪት ርያን ያት) የሚያሠምር፤ ደስ የሚያሰኝ አገልጋይ። መሥመሬ እግዚ። ይከውኑ መሥመርያነ ኀቤሁ። መሥመሪተ ቅዱሳን ፡ (ጥበ፬ ፡ ፲። ዮሴፍ። አዋል)።
መሥመር ፡ (ራት) በቁሙ፤ ማሥመሪያ ቀጥ ያለ የተካከለ ዘንግ አራት ገጽ ያለው፤ ወይም ጠፍጣፋ ባለኹለት ገጽ። መሥመር የወደቀበት የተጋደመበት፤ ወስፌው ርሳሱ የኼደበት መዛሪያው ትልሙ ፡ (አቡሻ ፡ ፵፮)። የመሥመር አሠራር ጥበቡ የመጣ ከሙዝ ቅጠልና ከንሰት ከኮባ ከጕናጕና ነው ይባላል።
መስመክ ት ፡ (ብ መሳምክ ት) ማስጠጊያ፤ አንድ ማድረጊያ፤ ጋድም፤ ቅርቃር፤ ችንካር መወርወሪያ፤ ቍልፍ። መስመክተ ሠርዌሁ ፡ (ዘፀ፳፮ ፡ ፲፯)።
፡ ጐን፤ ክፍል ማእዝን
፡ (ዘፀ፳፭ ፡ ፲፪ ፡ ፲፬ ፡ ፲፱)።
መስም [1] ፡ ባዕድ ዘር፤–ሰምይ ሰመየ።
[2] ፡ ስም የተጣፈበት ዕቃ ጥቅል። ስም የሚኾን ቅጽል፤ እንደ ተቀብዖ ስም ያለ፤ በባዕድ ፊደል የሚነሣ፤ እግዚእ መስፍን መተርጕም መፈክር፤ መምህር ማእምር፤ ይህን የመስለ ኹሉ። በባዕድ ዘርም ባይነሣ ስምና ቅጽል የሚኾን ማናቸውም ጥሬ ዘር ኹሉ በየራሱ ስምነት ስላለው፤ እንደዚሁ መስም ይባላል፤ ባለቅኔዎች ግን አይሉትም።
መስምዕ ፡ (ዕት ዓን ዓት) የሚያሰማ፤ አሰሚ፤ አስሚ አስመስካሪ።
መሥረብ ፡ መሳቢያ፤ መምጠጫ፤ ውስጠ ክፍት፤ እንደ ላስቲክ፤ እንደ ዋገምት፤ እንደ ውዥሞ ፡ (እንደ ዘነዘና) ያለ፤ የመጠጥ የትንባኾ፤ ለውሃም ይኾናል። ወመሥረበ ማይሂ ተስዓ ወአሐዱ
፡ (ታሪ አኵ)። መሽረብ መትረብ።
መሥረተ ፡ (ሣረረ) መሠረተ፤ አጸና፤ ሠራ። መጽሐፍ ግን አመሥረተ ይላል፤ ስሕተት ነው።
መስረፍ ፡ መብሻ። መስረፈ አንፍ
፡ (ስንክ ፡ ጥር፲፭)።
መሥሬ መሠርይ ፡ መጽሐፈ መድኀኒት፤ የጠንቋይ፤ ወይም የሐኪም። መሥሬ ውሉድ ፡ (ስንክ)።
መስርሕ ፡ (ሕት ሓን ሓት) የሚያደክም፤ አድካሚ። ምግባራት መስርሕ(ሓ) ት ፡ (ፊልክ ፡ ፺፰)።
መስቀለ ፡ (883) መስቀል ኾነ፤ መስቀል መሰለ ተመሳቀለ።
መስቀላት መሳቅል ፡ (883) መስቀሎች፤ መከራዎች
፡ (ስንክ ፡ ታኅ፮ ፡ ፲፯። መጋ፲። ግን፱። ዮሐ፲፱ ፡ ፴፩)።
መስቀላዊ ፡ መስቀላዊ፤ የመስቀል ወገን፤ ዐይነት፤ ምልክት፤ መስቀልኛ ማ ባለመስቀል፤ መስቀላም። አምላክ መስቀላዊ ፡ (መጽ ፡ ምስ)።
መስቀል [1] ፡ በቁሙ፤–ሰቂል ሰቀለ።
[2] ፡ (ዕብ ሚሽቃል፤ ሚዛን) በቁሙ፤ መስቀያ፤ መመዘኛ፤ መስቀያ፤ መንጠልጠያ፤ ለሞት የሚያበቃ መከራ። ይጹር መስቀለ ሞቱ። እምነት ዘመስቀለ ክርስቶስ። አስተርእዮቱ ለመስቀል። እስመ ነገረ መስቀሉስ እበድ ውእቱ በኀበ ህጉላ ፡ (ማር፰ ፡ ፴፬። ስንክ መስ፲፯። መጋ፲። ፩ቆሮ ፡ ፩ ፡ ፲፯)።
መስቀር [1] ፡ ታቦተ ኖኅ፤–ሰቍር ሰቈረ።
[2] ፡ መስቀር፤ ፡ (ዕብ ሚሽቃር) የተሳቦና የዔሊ ቤት፤ ዛጐሉ ልብሱ ፥ መደበቂያውና መሸንቀሪያው። መርከን፤ ታቦተ ኖኅ፤ ውስጠ ክፍት ባለመስኮት ማለት ነው። ጸረበ ሎቱ መስቀረ ዐቢየ ወነበረ ዲቤሃ ወሠለስቱ አልሕምት ነበሩ ምስሌሁ በይእቲ መስቀር። ወውእቱ መስቀር ይጸቢ ዲበ ማይ። መስቀረ ዕፅ። እትአመን ባቲ እስመ አርኣያ መስቀር ይእቲ ፡ (ገድ ፡ አዳ። ሔኖ፹፱ ፡ ፩ ፡ ፮ ፡ ፰። አርጋ ፡ ፫። ድጓ)።
መስቄ [1] ፡ ማጠጫ፤–ሰቅይ ሰቀየ።
[2] ፡ (ብ መሳቅይ) ማጠጫ፤ መጠጥ መስጫ፤ መቅጃ መገልበጫ። የሸማኔ ዕቃ መወርወሪያ፤ ማጉን ለድር ወይም ግራውን ለዝሓ የሚያጠጣበት። ቀናዲለ ወመሳቅየ መኃትወ ወመሳውረ። ንዋየ መስቄ
፡ (ክብ ፡ ነገ። ፍ ፡ ነ ፡ መቅ)።
መሥቄ ፡ መሣቀያ፤ መውጊያ፤ መጠቈሚያ፤ ሹል ዕንጨት፤ ምስማር። ተግሣጽ ውእቱ ከመ መሥቄ ለነፍስ ፡ (ፍ ፡ ነ)።
መስቄሎን ፡ (ጽር ሜስካሎን) የሸማኔ ዕንጨት መጠቅለያው፤ ደልዳላ ወፍራም ፥ ምእዙን ራሳም፤ አራት ብስ ያለው። ወዕፀ ኵናቱ ከመ መስቄሎነ አነምት ፡ (፩ነገ ፡ ፲፯ ፡ ፯)።
መስቈር ፡ (ብ መሳቍር) መሸንቈሪያ፤ መብሻ መሰርሰሪያ፤ ወስፌ አፈ ምሣር።
መስቈርር ፡ (ርት ራን ራት) የሚያስጠይፍ አስጠያፊ፤ አስቀያሚ። የሚጠየፍ ተጠያፊ ተቀያሚ፤ ተሰቃቂ። አሕላማት መስቈርርት፤ አስጠያፊ
፡ (ፊልክ ፡ ፻፷፪)።
መስቈቅው ፡ (ቍት ቅውት፤ ዋን ዋት) ጩኾ የሚያለቅስ፤ አልቃሽ ፥ አስለቃሽ፤ ገጣሚ ቀንቃኝ፤ ሙሾ አውጭ፤ ባለሙሾ። መስቈቅው ወቍጹር። ጸውዕዎን ለመስቈቅዋት። ኢይደሉ ተዓስቦተ ሕሩማት ዘከመ መስቈቅዋት ወሰብአ ሥራይ ፡ (ገድ ፡ አዳ። ኤር፱ ፡ ፲፯። ፍ ፡ ነ ፡ ፴፯)።
መስበልት ፡ የእሸት ፍሬ፤ ዛላ፤ እልፍ፤ ዝሪት አዝመራ። ዐዘቅት ዘእንበለ ማይ፤ ደመና ዘእንበለ ዝናም፤ ሠዊት ዘእንበለ መስበልት። አልቦሙ ኅጠት ለመስበልቶሙ። ኵሉ መስተገብረ ገራውህ ሐጹረ አሥዋክ ያዐውድ ውስተ መስበልቱ ፡ (መጽ ፡ ምስ ፡ ገ፴፩። ፪፻፴፪። ፪፻፺)።
መስበክ ት ፡ (ብ መሳብክ፤ ት) የሸክላ ዕቃ፤ እንስራ ማድጋ፤ ገንቦ፤ ማሰሮ ምንቸት። ይትቀጠቀጥ መስበክት ውስተ ዐዘቅት። መሳብክተ ማይ ፡ (መክ፲፪ ፡ ፮። መዋሥ። ዮሐ፪ ፡ ፮ ፡ ፯። መሳ፮ ፡ ፲፮። ፫ነገ ፡ ፲፰ ፡ ፴፬)።
፡ የብረት ዕቃ፤ መሣሪያ፤ ወይም ቦታ፤ መጥበሻ፤ ማፍሰሻ፤ ከውር። ይሰበኩ በመስበኩ። እለ ሰበክዎሙ ለአልሕምት በውስተ መስበክ። እምነ መሳብክተ ኀጺን። በመሳብክቲሁ ከመ ወርቅ በእሳት ፈተኖሙ ለቅዱሳን ፡ (፫ነገ ፡ ፯ ፡ ፲፩። ፰ ፡ ፶፩። ፪ዜና ፡ ፬ ፡ ፫። መዋሥ)።
መስበዒ ፡ ብዕ ፡ (ዕት ዓን ዓት) ዝኒ ከማሁ፤ አስማታም፤ ባላስማት። አሜዜራሕ መሀረ ኵሎ መስበዕያነ ወመታርያነ ሥርው
፡ (ሔኖ፰ ፡ ፫)።
መሥብሕት ፡ (ብ መሣብሕት) ሥብ ጮማ፤ የሥጋ ክፍል ፥ መክፈልት ዕድል ፥ መቍነን፤ ለዳቦና ለፍሬም ይኾናል። እለ ትበልዑ መሣብሕተ መሥዋዕቶሙ
፡ (ዘዳ፴፪ ፡ ፴፰)።
መስብር ፡ (ርት ራን ራት) የሚሰብር፤ ሰባሪ፤ መስበሪያ። መስብረ ርእስ፤ መስብረ ብረክ ፡ (ስንክ ፡ ጥር፲፭)።
መስተሐምም ፡ (ምት ማን ማት) የሚያስታምም አስታማሚ፤ ትጉህ ንቁህ፤ ዐሳቢ አስተንታኝ። መስትሐምማን ለግብረ ቅድስና ፡ (ቀሌ)።
መስተሓምም ፡ ክፉ መድኀኒት፤ የሚያም የሚገድል ሥራይ የሚኾን። ወይም ሰውዮው ባለመድኀኒቱ። ብእሲ መስተሓምም፤ አው ተጠያሪ ፡ (ቈስጠ)።
መስተሓምው ፡ (ውት ዋን ዋት) አማጭ፤ አስተጫጭ። ፡ (ተረት) አማጭን መጦር፤ አማጭን በጦር። የባል ወንድም፤ ዘመዱ ጐሣው፤ ርሱ ሲሞት ሚስቱን የሚወርስ፤ የሚያገባ። ክድንን ዐጽፈከ፤ እስመ መስተሓምው አንተ ፡ (ሩት፫ ፡ ፱። ፲፩ ፡ ፲፪። ፬ ፡ ፩–፰)። መስተሓምው ከማለት ይልቅ፤ ወራሲ መውርስ ቢል በቀና።
መስተኃሥሥ ፡ (ሥት ሣን ሣት) አመራማሪ፤ ተመራማሪ። መስተኀሥሥ ብሎ በግእዝ ኀ ሲጣፍ ግን አድራጊ ኹኖ፤ ኀሣሢ መኅሥሥ፤ ፈላጊ መርማሪ ያሰኛል። ለእመ ኮነ መስተኀሥሣነ በእንተ ንጽሐ ሥጋ ባሕቲቱ። መስተኀሥሣን ለእከይ ፡ (ፊልክ ፡ ፻፰። ሮሜ፩ ፡ ፴፩)።
መስተኃብል ፡ የሚያደፋፍር፤ አጨካካኝ።
መስተሃክይ ፡ የሚያሳንፍ አሳናፊ፤ አሰናናፊ።
መስተሓውር ፡ የሚያካኺድ፤ አዋሳጅ መናጆ። አሳባቂ፤ መስተዋድይ። ዓዲ መስተሓውራን ፡ (፪ተሰ ፡ ፫ ፡ ፲፩)።
መስተኃይል ፡ (ልት ላን ላት) የሚያበረታታ፤ በሉ በሉ የሚል ፡ (ሢራ፰ ፡ ፲፭)።
መስተላህይ ፡ የሚጨዋወት፤ ተጨዋዋች። የሚያጨዋውት፤ አጨዋዋች።
መስተመይን ፡ መስተመይን፤ ፡ (ንት ናን ናት። መመይን) ዝኒ ከማሁ ፡ (፪ቆሮ ፡ ፲፪ ፡ ፲፮። ሮሜ፩ ፡ ፳፱። አፈ ፡ ድ፴፫)።
መስተመይጥ ፡ (ተመይጠ ተመያየጠ) ተመያጢ፤ የተመለሰ የሚመለስ ምልስ፤ ገር የዋህ ኀዳጌ በቀል። ብዙኀ ሣህል ወመስተመይጥ ላዕለ ጌጋዮሙ ፡ (፪ዜና ፡ ፴፫። ነቢ ፡ ፮)።
መስተማይጥ ፡ (ተማየጠ፤ አስተማየጠ) ተማያጢ፤ አስተማያጢ፤ የተማለሰ፤ የሚያማልስ፤ ተማላሽ አማላሽ።
መስተምሕር ማሕር ፡ (ርት ራን ራት) የሚያስምር የሚያማልድ አማላጅ፤ አስተዛዛኝ። ኦ መስተምሕርት አስተምሕሪ ኀበ ወልድኪ
፡ (ቅዳ)።
መስተሰናእው ፡ የሚያሰማማ፤ የሚሰማማ፤ አስማሚ፤ ተሰማሚ። ፈቃዶሙ መስተሰናእውት ፡ (ፊልክ)።
መስተሣህል ፡ (ልት ላን ላት) መሥሀሊ ፥ መሥህል፤ ይቅር ባይ ፥ ይቅር የሚል ፥ ገር ኀዳጌ በቀል። ስምየኒ መሓሪ ወመስተሣህል ፡ (ዘፀ፴፬ ፡ ፮። መዝ
፡ ፹፭)። ይቅር የሚያሰኝ፤ አስማሪ አስታራቂ። አደራራጊም ይኾናል።
መስተሳልም ፡ የሚያፈፋቅር፤ የሚያስታርቅ፤ አሰማሚ፤ አሳላሚ። ዐራቄ ኩኑነ ወመስትሳልመ ቅድመ እግዚአብሔር ፡ (ስንክ
፡ ኅዳ፳፮)።
መስተሣልቅ ፡ (ቅት ቃን ቃት) የሚሣለቅ፤ የሚያሣልቅ፤ አላጋጭ ተሣላቂ። መስተሣልቅ ውእቱ ላዕለ ሰብእ። ወመስተሣልቃን ይኴንንዎሙ ፡ (ፈ ፡ መ ፡ ፱ ፡ ፪። ኢሳ፫ ፡ ፬። መዝ ፡ ፩)።
መስተሳትፍ ፡ (ፍት ፋን ፋት) የሚያሳትፍ አሳታፊ፤ የሚሳተፍ ተሳታፊ፤ ሱቱፍ።
መስተሳንን ፡ (ንንት ናን ናት) የሚያጣላ አጣይ፤ ተጣይ ፈራሽ።
መስተሣይም ፡ የሚሿሿም፤ ተሿሿሚ። የሚያሿሹም፤ አሿሿሚ።
መስተሣይጥ ፡ የሚያሻሽጥ አሻሻጭ፤ ተሻሻጭ። የሚገዛ ገዥ።
መስተስርይ ፡ (ያን ያት ሪት። ርዪት) የሚያስተሰርይ፤ አስተስራዪ፤ አማላጅ አስታራቂ። ከመ ትኩን መስተስርየ ኀጢአት። ገድለ ኵሎሙ ቅዱሳን መስተስርየ ኀጢአትየ። ኢየሱስ ክርስቶስ መስተስርየ ኵሉ ጌጋይ ፡ (ቀሌ። መጽ ፡ ምስ። ደራሲ)።
መስተራሕቅ ፡ የሚያራርቅ፤ የሚራራቅ፤ ተራራቂ በመራራቅ በልዩነት ያለ። በበዓላት አው በጊዜያት መስተራሕቃት
፡ (ፊልክ ፡ ፸፱)።
መስተራምም ፡ (አርማሚ መርምም) ዝኒ ዓዲ ከማሁ፤ ዝም የሚያሰኝ። ዘመስተራምም በእንቲኣሁ
፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፵፫ ፡ ፩)።
መስተራብሕ ፡ (ሒት ሓን ሓት) የሚያራባ፤ የሚያባዛ። ወኢመስትራብሒት
፡ (ዲድ ፡ ፲፬)።
መስተራትዕ ፡ (ዕት ዓን ዓት) የሚያቃና፤ ፈጣን ቀልጣፋ፤ ቁመታም ደረታም ኀይለኛ፤ የጭፍራ አለቃ፤ ባለወግ ጭፍራ ዘበኛ፤ ያዥ ጨባጭ፤ አሳሪ ቀጭ፤ ፈላጭ ቈራጭ፤ ሰያፊ ገራፊ፤ ሰቃይ ገዳይ። መስተራትዓነ ሐራ
፡ (ማቴ፳፯ ፡ ፳፯። ማር፮ ፡ ፳፯። ዲድ ፡ ፳፩። መቃ
፡ ገ፪)። መጽሐፍ ግን በመስተራትዓን ፈንታ መስተራትዓት ይላል፤ የጣፊ ስሕተት ነው።
መሥተር ፡ (ዐረብ) ማሥመሪያ፤ ተጋዳሚው፤ ዕንጨት፤ ወይም ብረት። ሚዶ ማበጠሪያ።
መሥተር ትር ፡ (ሣትር) መሠንተሪያ፤ መቅደጃ፤ የብረት መግረፊያ፤ ጫፉ የሚቈርጥ የሚከትፍ። መሥተረ ኀጺን። መሣትረ ዘኀጺን። ሠጠቁ ማእሰ ሥጋሆሙ በመጥባሕት ዘኀጺን ፡ (ስንክ ፡ ሚያ፬። ታኅ፯)።
መስተቀይም ፡ (ምት ማን ማት) የሚቀየም፤ የሚያስቀይም፤ ተቀያሚ አስቀያሚ፤ አሳዛኝ። መስተቀይም ወመዐትም። ኩኑ ኄራነ ወአኮ መስተቀይማነ ፡ (ቀኖ
፡ ኒቅ። ግንዘ)።
መስተቃስም ፡ የሚያጠናቍል፤ አጠናቋይ፤ አጠነቋቋይ።
መስተቃርን ፡ (ንት ናን ናት) የሚያጣላ፤ አጣይ። የሚጠላ፤ ተጣይ፤ ባለጋራ። ወእመሰ ተቃወመኒ መስተቃርን። ዲፓሁ ለመስተቃርን። ዘይከውን መስተቃርነ ለዝንቱ ፡ (አፈ ፡ ተ፴፩። ማር ፡ ይሥ፳ ፡ ፫። ስንክ ፡ መጋ፫)።
መስተቃትል ፡ (ልት ላን ላት) የሚጋደል፤ የሚያጋድል፤ አጋዳይ አገዳዳይ፤ ተጋዳይ፤ ዐርበኛ፤ ተዋጊ ሰልፈኛ። ብእሲ መስተቃትል ወተባዕ። እዴከ መስተቃትልት ወመዋኢት። አሕዛብ መስተቃትላን
፡ (ሢራ፳፮ ፡ ፳፰። ጥበ፲
፡ ፳። ኢሳ፲፫ ፡ ፬)።
መስተቃውም ፡ የሚቃወም፤ የሚያቀዋውም፤ አቃዋሚ። መስተቃውማን ፡ (አዋል)።
መስተበቅል ፡ ባለበቅሎ፤ በቅሎ የሚያረባ የሚሼጥ የሚያከራይ፤ ወይም ለጓሚ ባልደራስ በቅሎ ጠባቂ። አዘዘ ያምጽኡ አልባሰ ክህነት ምኩሐ ወመስተበቅለ ፥ ወበትረ ክህነት፤ ወአመ ሳኒታ አምጽአ በቅለ ወኵሎ ዘይትፈቀድ ለፍኖት ወአጽዐኖ ለአባ አትናቴዎስ ፡ (ስንክ ፡ ጥቅ፬)።
መስተባእስ ፡ (ሳን) የሚያጣላ፤ የሚጣላ፤ ተጣይ፤ ደመኛ፤ ተዋጊ ዐርበኛ። ኢይኩኑ መስተባእሳነ በእከይ። መስተባእሳነ ሃይማኖት። የዋሃን ይኩኑ መስተባእሳነ ፡ (ቀኖ
፡ ኒቅ፳፰። ቄር ገ፲፬። ዮኤ፫ ፡ ፲፩። ኩፋ ፡ ፴፯)።
መስተባዕድ ፡ የሚለያይ፤ የሚያራርቅ አራራቂ።
መስተባይት ፡ ተዳዳሪ፤ አስተዳዳሪ።
መስተባይጽ ፡ (ጽት ጻን ጻት) የሚያሰማማ፤ የሚሰማማ፤ ስምም፤ ፍቅረኛ። ለሐሱ ሰኰናሁ፤ ወኮኑ ሎቱ መስተባይጻነ በተጋንዮ ብዙኅ ፡ (ስንክ ፡ ታኅ፯)።
መስተብቍዕ [1] ፡ (ዕት ዓን ዓት) ዝኒ ከማሁ። ሣልስና መስም በፍች አንድ ናቸው። ገሞራውያን ይነብሩ በኵሉ ሕይወቶሙ ምስለ መስተብቍዓን ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፵፰)።
[2] ፡ (ጥሬ ዘር) ምልጃ ልመና ዝብዘባ፤ ጸሎት ጸዋት ሐዋርያት ለቄሶች የሠሩት፤ በእንተ በእንተ እያለ ኹሉን በየጾታው የሚጠራ። ይኸውም በቅዳሴ ጓዝ ይገኛል፤ መሠረቱ ግን ሲኖዶስ ነው። መስተብቍዕ ዘሐዋርያት ፡ (ቅዳ)።
መስተቲ መስትት ፡ (ታን) የሚንቅ፤ የሚያቃልል፤ የሚያስታጕል፤ ዕቡይ፤ ሀካይ። እመ ገብረ ዐመፃ ወኮነ ዕቅፍተ ወመስትተ ለእለ ነሥኡ ጥምቀተ። ከመ ኢንኩን መስትታነ ፡ (ሲኖዶ። ዲድ ፡ ፬። ፪ዕዝ ፡ ፲፪ ፡ ፲፯)።
መስተታልው ፡ የሚያራድፍ፤ የሚያከታትል፤ አከታታይ።
መስተናሥእ ፡ (እት ኣን ኣት) አስተናሣኢ፤ የሚያናሣ ፥ የሚያነሣሣ፤ አነሣሽ ጐስጓሽ። ሠርዑ መስተናሥኣነ ለግብረ ቤተ እግዚ ፡ (አቡሻ ፳)።
መስተናድእ ፡ (እት ኣን ኣት) የሚያናዳ አናጅ፤ መናጆ። ሱቱፋነ ሰረቅት መስተናድኣን
፡ (ኢሳ፩ ፡ ፳፫)።
መስተናግር ፡ የሚነጋገር ፥ የሚያነጋግር፤ አማላጅ አምጃር፤ ጠበቃ ወባት፤ ነገረ ፈጅ ፥ የነገር ኣባት። ይኩን መስተናግረ ምስሌከ። ዐርከ መሀይምናን መስተናግር ለጻድቃን ፡ (ኪዳ)።
መስተናጽሕ ፡ የሚያናጻ። የሚያቧካ፤ ጥሩ ርሾ።
መስተዐግሥ ፡ ዝኒ ከማሁ። ይኄይስ መስተዐግሥ። ነፍስ መስተዐግሥት። በእንተ መስተዐግሣን ፡ (መክ፯ ፡ ፱። ሢራ፳፮ ፡ ፲፭። ኪዳ)።
መስተኣብድ ፡ (ድት ዳን ዳት) ሰንፎ የሚያሰንፍ፤ የሚያሳንፍ ፥ አሳናፊ፤ ዋዘኛ፤ ፌዘኛ፤ ሕጹጸ አእምሮ። መስተኣብዳን ለአስተኣብዶ። ዕደው መስተኣብዳን
፡ (፪ጴጥ ፡ ፫ ፡ ፫። ሶፎ፫ ፡ ፬)።
መስተኣኵት ፡ የሚመሰጋገን የሚያመሰጋግን።
መስተኣዝዝ ፡ የሚያስተዛዝዝ አስተዛዛዥ።
መስተኣድ ፡ (ጽር ሜስታኣል) ዕቃ ቤት ፥ ገበዝ የአልባሳትና የንዋያት ሹም ጠባቂ ፡ (፬ነገ ፡ ፲ ፡ ፳፪)።
መስተዓግል ፡ የሚያቀማማ፤ የቀማኛ ዐጋዥ ረዳት፤ ዐብሮ የሚሰርቅ የሚቀማ።
መስተዓግሥ ፡ የሚያቻችል፤ የሚያስተጋግሥ፤ አቻቻይ።
መስተካህል ፡ (ልት ላን ላት) የሚያቻችል አቻቻይ፤ አሰማሚ።
መስተካሕድ ፡ (ዳን) የሚያሟግት የሚያከራክር፤ ዳኛ። ተሟጋች ተከራካሪ፤ መናፍቅ ከሓዲ። ለመስተካሕድ ብእሲ ፡ (ቲቶ፫ ፡ ፲። መጽ ፡ ምስ። አፈ ፡ ድ፲፫)።
መስተዋቅሥ ፡ የሚየዋቅሥ የሚያከራክር፤ ዳኛ። የሚዋቀሥ ተዋቃሽ ተከራካሪ፤ ባለጋራ። እስመ መስተዋቅሥ ጽኑዕ ውእቱ ፡ (ቅዳ)።
መስተዋክፍ ፡ (ፍት ፋን ፋት) የሚያቀባብል፤ አቀባባይ። የሚቀባበል ተቀባባይ
፡ (፩ዜና ፡ ፳፮ ፡ ፲፰)።
መስተዋድይ ፡ አሳባቂ ነገረ ሠሪ፤ ከሳሽ አሳጭ፤ ጠላት ባለጋራ፤ ወድቀ መስተዋድይ ዘአስተዋደዮሙ ለአኀዊነ። ጻድቅ መስተዋድየ ርእሱ። አዘዝክዎሙ ለመስተዋድያንሂ፤ ይምጽኡ ኀቤከ ፡ (ራእ፲፪ ፡ ፩። ምሳ፲፰ ፡ ፲፯። ግብ፳፫ ፡ ፫)።
መስተዛውዕ ፡ (ዕት ዓን ዓት) የሚጫወት የሚያጫውት፤ ተጫዋች አጫዋች። ኢተኀሊ ኅሊና መስተዛውዕተ ፡ (ኪዳ)።
መስተዳጕጽ ፡ የሚያጣላ አጣይ፤ አሳባቂ ነገረ ሠሪ። ልሳን መስተዳጕጽ ሆኮሙ ለብዙኃን። ኢይኩና መስተዳጕጻተ ፡ (ሢራ፳፰ ፡ ፲፬። ፍ ፡ ነ ፡ ፰ ፡ ፩)።
መስተገብራዊ ፡ ዝኒ ከማሁ፤ አሠሪ ባለሥራ። ሠሪ ሠራተኛ ፡ (ፊልክ ፡ ፻፮)። ተግባር ረባሕ በማለት ፈንታ ምስትግባር መስተገብር ይላል፤ ስሕተት ነው
፡ (ኢሳ፳፫ ፡ ፲፰)።
መስተገብር ፡ (ርት ራን ራት) አግባሪ አገባሪ መገብር፤ የሚያሠራ አሠሪ አስደራጊ። ልማዱ ግን እንደ ተገበረ አድራጊነት ነው፤ አስተገበረን አይመስልም። መስተገብር ውእቱ ዘይትጌበር ዘልፈ። ንህብ መስተገብርት ይእቲ። መስተገብራነ ማህው። መስተገብራነ ቤተ ክርስቲያን። መስተገብራነ ምድር ፡ (ፈ ፡ መ ፡ ፳፫ ፡ ፩። ምሳ፮ ፡ ፰። ገድ ላሊ። ዲድ ፡ ፲፫)።
መስተጋብእ ኢ ፡ ዝኒ ከማሁ፤ የሚሰበስስብ ሰብሳቢ፤መሰብሰቢያ ቦታ። መስተጋብአ ጾታ ተግሣጻት ውእቱ። ኦ ከርሥ መስተጋብኢተ ኵሉ ርስሐተ ኀጢአት
፡ (ፈላስ። ግንዘ)።
መስተጋእዝ ፡ የሚያጣላ የሚያሟግት፤ የሚሟገት ተሟጋች ተከራካሪ። ለእመ ይቤለከ አሐዱ መስተጋእዝ። መስተጋእዛን በበይናቲሆሙ
፡ (ፈ ፡ መ ፡ ፪ ፡ ፲። አፈ ፡ ድ፰ ፡ ፳፱)።
መስተጋድል ፡ (ልት ላን ላት) የሚጋደል የሚታገል፤ ተጋዳሊ። የሚያጋድል የሚያስታግል፤ አጋዳይ። ወእመኒ መስተጋድል ኢይከውኖ ምዝጋና እመ ዘበሕጉ ኢተጋደለ። መስተጋድልት ተሐራሚት ወንጽሕት ማርታ። ሰማዕት ወጻድቃን መስተጋድላን ለሠናይ ፡ (፪ጢሞ ፡ ፪ ፡ ፭። ስንክ ፡ ሠኔ፫። ቅዳ)።
መስተፃምር ፡ (ርት፤ ራን ራት) የሚያጣምር፤ የሚያጋባ፤ አማጭ፤ ነገር ቈራጭ።
መስተፃርር ፡ (ርት ራን ራት) የሚያጣላ፤ አጣይ። የሚጠላ፤ ተጣይ፤ ተቃዋሚ። ለትማስን ምክረ መስተፃርር። ኀጢአት መስተፃርርት ለእግዚ፤ አጣይ ፡ (ግንዘ። ፊልክ)። ለመስተፃርራን አስተሳልምዎሙ። ኢኮኑ ቃላተ አበው መስተፃርራት፤ ተጣይ ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፵፫ ፡ ። ፊልክ ፡ ፶)።
መስተፃርፍ ፡ የሚያሳድብ፤ የሚያሰዳድብ፤ አሳዳቢ፤ አጣይ።
መስተጻዕን ፡ የሚያጫጭን፤ የሚያሸካክም፤ አጫጫኝ።
መስተጽዕን ተጽዓኒ ፡ ተጸዓኒ፤ የሚጫን፤ ተጫኝ፤ ተቀማጭ። መስተጽዕነ ኪሩቤል። መስተጽዕናነ አፍራስ። ኅሩያነ ወመስተጽዕናነ በመሥልስት ፡ (አርጋ ፡ ፩። ኢዮ፩ ፡ ፲፯። ዘፀ፲፭ ፡ ፬)።
መስተፋቅር ፡ የሚያፋቅር የሚያዋድድ፤ ክታብ መድኀኒት፤ ጠንቋዮች ለሴቶች የሚሼጡት።
መስተፋጥን ኒ ፡ የሚያፋጥን፤ የሚፋጠን። በመስትፋጥኒት መልእክት። ወምስለ ዝ ኵሉ ሩጸቱ መስተፋጥኒ። አእጋር መስተፋጥኒት
፡ (ስንክ ፡ ጥቅ፱። ገድ
፡ ተክ። ግንዘ)።
መስቴ [1] ፡ መጠጥ ጫ፤–ሰትይ ሰትየ።
[2] ፡ መጠጫ፤ ብርሌ ዋንጫ። መሸታ መጠጥ፤ ተቀድቶ የሚሰጥ። መብልዕ ወመስቴ። መስቴ መኰንን ፡ (ቅዳ። ኪዳ። ሮሜ፲፬ ፡ ፲፯። ቆላ፪ ፡ ፲፮)።
መስቴማ ፡ (ዕብ ማስጤማህ፤ ሳጣም) ጠብ ጥል ቂም በቀል ጠላትነት፤ ወቀሣ ከሰሳ። ጠላት ጠበኛ፤ ከሳሽ አሳጭ ሰይጣን። ባለብሉዮች ግን የመየነ ዘር መስሏቸው፤ ተመያኒ መስተመይን ይሉታል
፡ (ኩፋ ፡ ፲። ፲፯። ፲፰)።
መሥነቂ ፡ (ንቅ) ሥንቅ የሚያሲዝ፤ የሚሰጥ።
መሥነቅ ፡ (ቅት) ሥንቅ መያዣ፤ መቋጠሪያ፤ መክተቻ፤ አቅማዳ ፥ ኪስ ፥ ከረጢት። ዘአልቦቱ መሥነቀ ኅብስት። መሥነቅት አሐቲ ትኩነነ ፡ (መጽ
፡ ምስ። ምሳ፩ ፡ ፲፬)።
መስኖ [1] ፡ በቁሙ፤–ሰኒው ሰነወ።
[2] ፡ (ብ መሳንው) በቁሙ፤ የቦይ ውሃ ወደ መሩት ወደ ወሰዱት የሚኼድ።
፡ (ተረት) ማየ ሰሊሖም ዕዉር፤ ኀበ ወሰድዎ የሐውር።
መሥዔ [1] ፡ መንሽ፤–ሥዕይ ሠዐየ።
[2] ፡ መሥዔ፤ ፡ (ብ መሣዕይ) ማዝሪያ፤ መበተኛ፤ መንሽ፤ ወይም መሽን፤ ላይዳ። መሥዔሆሙ ለረሲዓን፤ ንጉሥ ጠቢብ። ዘመሥዔ ውስተ እዴሁ ፡ (ምሳ፳ ፡ ፳፮። ማቴ፫ ፡ ፲፪)።
መስዕ ፡ (ዐረ ሚስዕ) የማእዝን ስም፤ ንኡስ ማእዝን፤ በሰሜንና በምሥራቅ መካከል ያለ፤ የሰሜን ምሥራቅ የአዜብ ትይዩና አንጻር አፋዛዥ። ባርክ መስዐ ወአዜበ ፡ (ቅዳ)። ማእዝንነቱ የሰሜን ወገን ስለ ኾነ ሰሜንም በርሱ ስም መስዕ ይባላል። እብሎ ለመስዕ። ሰፍሖ ለመስዕ ዲበ ወኢምንት። ገቦ መስዕ። ንጉሠ መስዕ ፡ (ኢሳ፵፫ ፡ ፭። መዝ ፡ ፵፯። ዳን፲፩ ፡ ፮)። ኹለተኛም በመላሾች ስሕተት፤ ምሥራቅን አዜብ፤ ደቡብን ጽላሎትን መስዕ ይላል። አንሥአ አዜበ እምሰማይ፤ ወአምጽአ መስዐ በኀይሉ። ዘይመይጦ ለብርሃን መንገለ መስዕ ፡ (መዝ ፡ ፸፯። ዓሞ፭ ፡ ፰)።
መሥዕ ፡ በቁሙ፤–መስዕ።
መሥዕል ፡ (ልት ላን ላት) የሚሥል፤ የሚያሥል፤ ሣይ አሣይ። መሥዕለ ሕፃናት። መሥዕል ዘትያጥሮን ፡ (መጽ ፡ ምስ። አዋል)።
መስእል ፡ (ልት ላን ላት) ጠንቋይ፤ ጋኔን ሳቢ፤ ሙት ጠሪ፤ ባለሰአልት። አስጠንቋይ፤ ጠንቋይ ጠያቂ ፡ (ሲኖዶ)።
መሥዕርት ፡ ሚዶ፤ የጠጕር መሣሪያ፤ ማበጠሪያ። ብርኵማ የንጨት ትራስ። የግንብ ልባጥ፤ ጥግ ጌጥ
፡ (ማሕ፩ ፡ ፲፯)።
መስዖዝዝ ፡ የሚያፈዝ፤ የሚያደነዝዝ፤ አፍዝ፤ አደንግዝ። ወይን መስዖዝዝ ፡ (አርጋ ፡ ፬)። አፍዝ አደንግዝ የዓሣ ስም ነው፤ መጠኗና መልኳ ታናሽ ኹኖ ግርማዋ የሚያስደነግጥ፤ ሲይዟት እጅ የምታፈዝ ፥ ሲበሏት የምታደነግዝ ፥ ዓሣ ወጋሮች ለይተው የሚያውቋት ከወንዝ ዓሣ ኹሉ የተለየች መርዛም ዓሣ አለች ይባላል።
መስከም ምስካም ፡ (ዕብ ሼኬም) መሸከሚያ መያዣ ማንሻ፤ ምቹ፤ ጫንቃ ትከሻ።
መስከረም ፡ (መስ ከረም። መዝከረም) በቁሙ፤ ስመ ወርኅ ቀዳማይ፤ የወርና ያመት መዠመሪያ በግብጽና በኢትዮጵያ ቍጥር። ጥንትም ከሥጋዌ በፊት ለዓለም ኹሉ መዠመሪያ ወር ነው፤ ይኸውም በአይሁድ ዐውዳመት በበዓለ መጥቅ ይታወቃል፤ አታኒም እይ። መስ ከመስየ መጥቶ በከረም ላይ ወድቋል፤ ስለዚህ መስየ ክረምት ፥ ምሴተ ክረምት ተብሎ ይፈታል፤ ምስጢሩ ፀአትና መሰስ ማለት ነው፤ የክረምት ጫፍ መካተቻ የመፀው መባቻ መኾኑን ያሳያል። በዓመት ዘይቤ ሲፈቱት ግን መቅድመ አውራኅ ርእሰ ክራማት ያሰኛል፤ ይኸውም መንና ስን እየብቻቸው ነጣጥሎ መቅድምና ርእስ ብሎ ነው። ፪ኛም፤ ዝና ስ በጣፊ ስሕተት ይዋረሳሉና ፡ (መሐዘ ሚዜ ሚስት፤ ኀበዘ ኅቡዝ ኅብስት) የዘከረ መስም መዝከርና ከረም፤ ተጋጥመው፤ መዝከረ ከረም በመባል ፈንታ አንዱን ከረ ጐርዶ መዝከረም መዝከረ ዓም እንደ መባል ኹሉ፤ ዝ ለስ ተለውጦ መስከረም ተብሏል፤ ያመት ማሰቢያ መታሰቢያ፤ ወይም ዐውደ ዓመት ማለት ነው። ውእቱ ርእሰ ዓመት ዘግብጽ ወኢትዮጵያ። አመ ዐሡሩ ለመስከረም ፡ (ስንክ ፡ መስ፩ ፡ ፲)።
፡ የወር ስም፤–ከሪም ከረመ።
መስከቢ መስክብ ፡ መስክብ፤ የሚያስተኛ የሚያጋድም፤ አስተኝ አጋዳሚ። ማስተኛ ማጋደሚያ፤ ምንጣፍ ዐልጋ ቦታ።
መስከነ ፡ ምስኪን ኾነ፤ ዓለምን ገንዘብን ናቀ፤ ተወ። ብፁዕ ዘመስከነ በእንተ ጽድቅ ፡ (ራእ ፡ ሲኖ)።
መሥኵዐ ፡ መሰኳ አመሰኳ፤–ሰኵዐ፤ መሰከ።
መስክይ ፡ ዝኒ ከማሁ። ዝንቱ ኅብስት መስክይ ወመኰንን ፡ (ቅዳ ፡ ሕር)።
መስኮት [1] ፡ በቁሙ፤–ሰኪው ሰከወ።
[2] ፡ (ብ መሳክው) በቁሙ ክፍት፤ ታናሽ ደጅ አፍ፤ በግድግዳ በናስ በቤት በቅጥር ግንብ የሚሠራ፤ የብርሃን የነፋስ መግቢያ፤ ያይን መላኪያ ማሾለኪያ። ዳንኤል ዘአርኀወ መስኮተ ቤቱ። ሐወጸ ንጉሥ እንትተ መስኮት ወርእዮ ለይሥሐቅ። ዘይሔውጽ እንተ መሳክዊሃ። መሳክው ለብርሃን፤ መሳክው ለንጻሬ
፡ (ሃይ ፡ አበ። ዳን፮ ፡ ፲። ዘፍ፳፮ ፡ ፰። ሢራ፲፬ ፡ ፳፫። ፍ ፡ ነ ፡ ፴፯)።
መስወቅ መሶቅ ፡ (ብ መሳውቅ) ዝኒ ከማሁ። ምክያደ መሳውቅ
፡ (ገድ ፡ ላሊ)።
መስወድ ፡ ብ መሳውድ) መጫሪያ መተርከሻ፤ ገል ብረት። እግር፤ መሠረት። መስወደ እሳት ፡ (ዘፀ፳፯ ፡ ፫። ፴፰ ፡ ፳፪ ፡ ፳፫። ኤር፶፪
፡ ፲፱)። መሳውድት፤ ወይም አእጋር በማለት ፈንታ መሳውልት ይላል፤ የጣፊ ስሕተት ነው።
፡ (ዘፀ፴፱ ፡ ፲። ፴፰ ፡ ፳፬)።
መሥዋዕት ፡ (ብ መሣውዕ፤ ዕት) ምሥዋዕ ፥ መሠዊያ ቦታ። ወግበር ላቲ ቀጸላ ለመሥዋዕት። ቤተ መሥዋዕት፤ ገበዋተ መሥዋዕት
፡ (ዘፀ፳፯ ፡ ፫ ፡ ፭–፯)።
፡ ማረጃ ፥ ወቅለምት፤ ማንደጃ ፥ ማቃጠያ እሳት። ወአምጽኡ ማሬ ዘድያስ ምስለ አልሕምት ወመሣውዕ
፡ (ግብ፲፬ ፡ ፲፫)። የጽርኡ አብነት ግን ወአክሊላት ይላል።
፡ በቁሙ፤ መንፈሳዊ አምኃ ፥ ሕርድ ቍርባን ፥ የእንስሳት፤ ያዝርዕትና ያትክልት የስንዴ የወይን ፥ የዘይት የዕጣን የመሰለው ኹሉ፤ ፍጡር ለፈጣሪው ከጸሎትና ከምስጋና ጋራ የሚያቀርበው የሚያቃጥለው። መሥዋዕተ ፋሲካሁ። መሥዋዕት ዘልዉስ በቅብዕ። መሥዋዕተ ወቍርባነ ኢፈቀድኩ። ኅብስተ መሥዋዕት ፡ (ዘፀ፲፪ ፡ ፳፯። ኩፋ
፡ ፮። መዝ ፡ ፴፰። ማር፪ ፡ ፳፮)። ከመ ያምጽይ መሣውዒሆሙ ኵሎ ዘይሠውዑ። ወባሕቱ ይትሀወኩ መሣውዕት
፡ (ዘሌ፲፯ ፡ ፭። ዳን፰ ፡ ፲፩)።
መሥየምት ፤ (ብ መሣይምት)
፤ መሾሚያ ፤ ማኖሪያ ማስቀመጫ መክተቻ ፤ ጋን ሣጥን ጐታ ፤
ቅርጫት ጋዘና እንቅብ አገልግል መሶብ ፤ የመሰለው ኹሉ። በድነ
ሕፃን በውስተ
መሥየምት (ስንክ ፡
የካ፫። ማር፮ ፡ ፵፫። ሉቃ፱ ፡ ፲፯)።
መሥየንት ፡ (ዐረ መሻነት) ፊኛ የሽንት ቋት ከረጢት፤ መታቈሪያው።
መስይ ዮት ፡ (መስየ፤ መሰየ ይመሲ ይምሰይ፤ ይምሲ) መምሸት፤ መሥረክ ሠርክ ማታ መኾን፤ የጊዜ። እፎ እንጋ ይመሲ። እምከመ መስየ። ዘኀበ መስዮ ይበይት። እስመ መስየነ ብሔር። ይውዕል ወይትቀነይ እስከ ይመሲ ፡ (ዘዳ፳፰ ፡ ፷፯። ማቴ፲፮ ፡ ፪። ሢራ፴፮ ፡ ፴፩። ገድ ፡ ተክ። መዝ ፡ ፻፫)።
መስደዲ ፡ ዝኒ ከማሁ። መስደዴ ፀር ፡ (አዋል)።
መስድስት ፡ ስድስት ወገን፤ እመም፤ ገዝም፤ ትልም፤ ዙር፤ መሥመር፤ የመሰለው ኹሉ።
መሥገርት ፡ (ታት፤ መሣግር፤ ርት) ወጥመድ፤ ከባቢ ጦር ፥ ክፉ ነገር፤ መያዣ ማሰሪያ፤ የግዞት ቤት ሐብስ ወህኒ፤ በደለኛ ታስሮ ተዘግቶ የሚቀመጥበት። መሥገርት ለአዕዋፍ። ትወርድ እግሩ ውስተ መሥገርት። መሥገርታተ ሰይጣን። ብትክ እምኔነ መሣግረ ዘአስተዳለዎ አሥጋሪ። መሣግርት ፡ (ምሳ፩ ፡ ፲፯። ኢዮ፲፰ ፡ ፰። ፊልክ። ግንዘ። አፈ ፡ ተ፴፬)።
መስገዲ ፡ የሚያሰግድ፤ አሰጋጅ። መስገዲ ለኵሉ
፡ (ቅዳ ፡ ሕር)።
መሥግው መሠግው ፡ ሠጋዊ ፡ (ሠገወ)። አሥጋዊ ፡ (ኦሥገወ)።
መስጠሚ ም ፡ ዝኒ ከማሁ፤ መስጠሚያ፤ ማስጠሚያ። የሚያሰጥም፤ አስጣሚ። ቦታ፤ አካል። ማየ አይኅ መስጠሜ ዘርዑ ለቃየል። ዮርዳኖስ መስጥመ አበሳ ሙሴ ወአሮን መስጥማነ ፈርዖን በኤርትራ፤ ባርቅሂ ወዲቦራ መስጥማነ ወልዱ ሲሳራ በፈለገ ቂሶን
፡ (ዘረፋ)።
መስጥሕ [1] ፡ (ብ መሳጥሕ) ማስጫ በመዘርጊያ፤ መዘረሪያ፤ መሰተሪያ፤ መሣሪያ ቦታ።
[2] ፡ ሒ፤ ፡ (ሰጣሒ) የሚያሰጣ፤ የሚዘረጋ፤ አስጭ፤ ገላጭ።
መስጥም ፡ (ምት ማን ማት) የሚያሰጥም፤ የሚያጠልቅ፤ የሚውጥ፤ የሚያሰጥ። ወረውዎ ውስተ ባሕር መስጥም። ልሳን መስጥም፤ ልጐት ዘዝንቱ ሕይወት መስጥም
፡ (ስንክ ፡ የካ፲፯። መዝ
፡ ፶፩። አፈ ፡ ተ፳፪)።
መስጦ ፡ እልመስጦ፤ ፡ (ጽር ፒስቲስ) እምነት፤ ሃይማኖት። እልመስጦ አግያ፤ ወይእቲ ሃይማኖት ቅድስት እንተ መሀሮሙ እግዚእነ ፡ (ሃይ ፡ አበ)። እል የዐረብ ተውሳክ ነው፤ መስጦ አግያ ያለውን ሃይማኖት ቅድስት ብሎ ተረጐመው፤ መምህራን ግን እልም ትምርት፤ ስጦ ምልአተ ንባብ፤ አግያ ፥ ኅቡእ ብለው፤ ሌላም ብዙ አፈታት ይፈቱታል። እንተ መሀሮሙ ያለውንም አንቀጸ ምኅላፍ ብሎታል፤ የፊት በር ፥ ቀዳማይ አንቀጽ ማለት ነው።
መስጴጦምያ ፡ (ጽር ሜሶፖታሚያ) ማእከለ አፍላግ፤ ሜሶ ፥ ማእከል፤ ፖታሚያ ፥ አፍላግ፤ ጤግሮስና ኤፍራጥስ ፡ (ግብ፪ ፡ ፱። ፯ ፡ ፪)።
መስፈርስ ፡ የበሽታ ስም፤–አስፋር
መስፈርት ፡ (ታት፤ መሳፍር ት) መስፈሪያ፤ መቍጠሪያ፤ ልክ መጠን ሚዛን። ንግበር መስፈርተ ንስቲት። መስፈርተ ኢፍ። መሳፍር ክልኤ። ወሀቦ ሤጦ ለውእቱ መካን በመስፈርተ ወርቅ ስድስቱ ምእት። ኢይግበሩ ዐመፃ በውስተ ሐሳበ አውራኆሙ ወኢበመሳፍረ ሚዛኖሙ ፡ (ዓሞ፷ ፡ ፭። ሩት፪
፡ ፲፯። ምሳ፳ ፡ ፲። ፩ዜና
፡ ፳፩ ፡ ፳፭። መቃ ፡ ገ፲)።
መስፌ ፡ (ብ መስፍያት መሳፍይ) መስፊያ መሳፍቻ፤ ወስፌ፤ መርፌ፤ የስፌት መኪና። እንዘ ይሰፊ በመስፌ ተሠጥቀ አጻብዒሁ። ወለለ ኵሉ ዐዲዎታ ለመስፌ። ንዋየ መስፌ
፡ (ስንክ ፡ ሚያ፴። ፊልክ
፡ ፻፶፯። አዋል)።
መስፌቶም ፡ (ጽር ሞስፌታም። ዕብ ሚሽፋታይም) ከንፈሮች፤ ዳር ደንበሮች። ለምንት ትነብር ማእከለ መስፌቶም ፡ (ምሳ፭ ፡ ፲፮)።
መስፍሕ [1] ፡ መስፍ፤–ሰፊሕ ሰፍሐ።
[2] ፡ (ብ መሳፍሕ) በቁሙ፤ መስፍ፤ የብረት ማስፊያ መቀጥቀጫ ታችኛው፤ ለመዶሻውም ይኾናል። አንበረት እደዊሁ ወእገሪሁ ዲበ መስፍሕ ወዘበጡ ሐራ። አዘዘ ያምጽኡ መስፍሐ ነሃቢ ወይስብሩ ቍየጺሆሙ ፡ (ስንክ ፡ ነሐ፳፭)።
መስፍን ት ፡ (ብ መሳፍን፤ ት) በቁሙ፤ ገዥ ፈራጅ፤ የወረዳ ሹም፤ ራስ ደጅ አዝማች፤ አበጋዝ አለቃ፤ ነገድ። ሤመ ሎሙ መሳፍንተ። መስፍነ ሶርያ። ወይእቲ መስፍኖን ለአንስት። መስፍነ ኀምሳ። ዐሠርቱ ወክልኤቱ መሳፍንት ፡ (ግብ፲፫ ፡ ፳። ሉቃ፪ ፡ ፪። ዮዲ፲፭ ፡ ፲፫። ኢሳ፫ ፡ ፫። ዘፍ፳፭ ፡ ፲፮)።
መሶር ፡ (ብ መሳውር) መሶጥ መሳውጥ፤ መጨመሪያ፤ ማፍሰሻ፤ ማንቈርቈሪያ ጡታም ዕቃ ማሰሮ። ሶጠን ተመልከት፤ ጠ በጸሓፊ ስሕተት ለረ ተለውጦ መሳውር ተብሏል፤ ምስጢሩ ግን የሶጠ ዘር ነው፤ ስዊጥን አይለቅም ፡ (ዘካ፬ ፡ ፪። ቀሌ። ድጓ)። በሰወረ አፈታት ሲፈቱት ግን፤ ማፈኛ መክደኛ መግላሊት ያሰኛል፤ ባለብሉዮችም እንዲሁ ይሉታል።
መሶቅት ፡ (መሳውቅት) የሴት አንቀጽ። ዝኒ ዓዲ ከማሁ።
መሶብ [1] ፡ በቁሙ፤–ሰዊብ ሶበ ሰወበ።
[2] ፡ (ዕብ ሞሻብ፤ ምንባር ቦታ ዕቃ) በቁሙ፤ የዳቦ ሣጥን፤ የንጀራ ታቦት፤ አገልግል ሌማት ቅንብቻ ጉብ፤ ሙዳየ ኅብስት። መሶበ ወርቅ እንተ መና። ስፋሕ የማነከ ላዕለ ዛቲ መሶብ። ንሣእ መሶበ ኅብስት ወጻሕበ ወይን ፡ (ዕብ፱ ፡ ፬። ቅዳ ፡ ጎር)።
መሶጥ ፡ (ብ መሳውጥ) ማፍሰሻ፤ መጨመሪያ ጡት፤ ወይም ጡታም ዕቃ። መጽሐፍ ግን በጥ ፈንታ መሶር መሳውር ይላል። ባለብሉዮችም የሰወረ ዘር መስሏቸው፤ ማፈኛ መክደኛ መግላሊት መሰወሪያ ይሉታል፤ የተሳሳተ ነው። ሰብዐቱ መሳውር በዘይሰቅይዋ ለመኃትዊሃ
፡ (ዘካ፬ ፡ ፪። መቃ ፡ ገ፲፰። ክብ ፡ ነገ። ቀሌ። ድጓ)።
መረስይ መስተረስይ ፡ መስተረስይ፤ የሚያስጠርር፤ አስጠራሪ፤ ሰልፍ አስተማሪ።
»መረቅ [1] ፡ (ዐረ። ዕብ ማራቅ) በቁሙ፤ የሥጋ ውሃ የበሰለበት የተቀቀለበት። ፡ (ተረት) ሠምና ወርቅ እንጀራና መረቅ። ከሥጋው ጦመኛ ነኝ ከመረቁ አውጡልኝ
፡ (መጽ ፡ ፈው)። መረቃ አመረቃ ማለት ከዚህ ወጥቷል፤ ፍችው ጣፈጠ ማለት ነው።
[2] ፡ በቁሙ፤–ወረቀ ምራቅ።
መረብ [1]
፡ በረሓ ፥ ወጥመድ፤–ረቢብ ረበ፤ ረበበ።
[2] ፡ (ዕብ ሚድባር) በረሓ፤ ምድረ በዳ፤ ያደን የወጥመድ ስፍራ፤ የእንስሳት የአራዊት ወጥመድ፤ አሽከላ። ወኮንኩ ከመ አድገ መረብ ዘገዳም ፡ (መዝ ፡ ፻፩)።
[3] ፡ (ዕብ ሙራኣ። ዐረ መሪእ) የአዕዋፍ ፊኛ፤ ያንገታቸው ኪስ ከረጢት በስተታች በደረት ያለው፤ ጥሬ መቋጠሪያው።
፡ በቁሙ፤ መረቦ የሚባል አምራ ባለታላቅ ፊኛ፤ መጠኑ የርኩም እግሩ የሽመላ፤ ላባው ክቡር በውድ የሚሼጥ። በቀቀኖ ፈንታ አድገ መረብ እንዲል ፡ (መዝ
፡ ፻፩)። አድግን እይ።
መረብዕ ፡ (ዕት ዓን ዓት) ዝኒ ከማሁ፤ ረባዒ።
መረውሕ ፡ (ብ መራውሕ፤ ሓት። ዐረ ሚርወሕ፤ ሚርወሐት። ሱር ማርዋሕታ) ማርገቢያ፤ ማናፈሻ፤ መነሳንስ፤ ጭራ፤ የጭራ ዐይነት ኹሉ። ይቁሙ ክልኤቱ ዲያቆናት በገበዋተ ምሧዕ ወየአኀዙ መራውሓተ ዘግቡራት እምግብር ልሙጽ ወይስድዱ ጽንጽንያተ ፡ (ፍ ፡ ነ
፡ ፲፪)።
መረየ ፡ (መርይ። ዕብ ያሞር፤ ሄሚር) ለወጠ ቀየረ፤ አስተላለፈ አሠገረ፤ የብተት የቀን ፥ የጊዜ የዘመን። መጽሐፍ ግን በመረየ ፈንታ አሜረየ አምረየ ይላል፤ አያሰኝም። ዛቲ ዕለት አሜረየት፤ እንዘ ታመሪ
፡ (መጽ ፡ ምስ ፡ ገ፪፻፷፭)። ሥሩና ምንጩ መሪሕ ነው።
መረግድ [1]:-በቁሙ፤ ርግዶ፤–ረገደ ፀ።
[2] ፡ መረግድ፤ ዘመረግድ፤ ፡ (ጽር ስማራግዶስ። ዕብ ባሬቄት፤ ዝማርጋድ። ሱር ዝማርግዳ። ዐረ ዘበርጀድ፤ ዙሙሩድ) ዕንቍ፤ የዕንቍ ስም፤ ሕብሩ ሐመልሚል፤ ወይም የባሕር ውሃ የሚመስል፤ የሚበርቅ የሚያብረቀርቅ። በዐረቡ ዘበርጀድና ዙሙሩድ ልዩዎች ናቸው፤ ዘበርጀድ ተርሴስና ክርስቲሎቤ ከርሴምቶን ካለው ይሰማማል። እብን ዘሕብረ መረግድ። ይመስል ሕብሩ ከመ መረግድ። ወንሣእ ክልኤ እብነ መረግድ ፡ (አስቴ፩ ፡ ፮። ራእ፬ ፡ ፫። ዘፀ፳፰ ፡ ፱ ፡ ፲፯)። ወገብሩ ኵሎ እብነ ዘመረግድ። ወራውሬ ወዘመረግድ። ወራብዕት በዘመረግድ ፡ (ዘፀ፴፮ ፡ ፲፫ ፡ ፲፯። ራእ፳፩ ፡ ፲፱)።
መረግፅ መረግድ ፡ ርግዶ፤ ረገዳ፤ ሽብሸባ፤ ውዝወዛ፤ ዳንኪራ እስክታ፤ ከበሮ ጭብጨባ ያለበት። የፀሓይ ፀ አጠራር በዐረብ እንደ ምድራዊ ድ ስለ ኾነ፤ መረግፅ በማለት ፈንታ መረግድ ይላል። ንኡስ መረግድ፤ ዐቢይ መረግድ። መረግድሰ አምሳለ ኪደተ ላሕም ፡ (ገድ ፡ አብርሀ)።
መረጠ ፡ (ዕብ ማራጥ) ሳለ ሰነገለ፤ ነጨ ነቀለ። በቁሙ ፥ ለየ ሾመ አከበረ።
፡ (ተረት) ከንጨት መርጦ ለታቦት፤ ከሰው መርጦ ለሹመት። ሙርጥ ማለት ከዚህ ወጥቷል።
መሪኅ ፡ (ዐረ እልምሪኅ) ኮከብ ፥ የኮከብ ስም፤ የፀሓይን ብርሃን ከሚነሡ ከስምንቱ ዐበይት ከዋክብት አንዱ።
መሪሕ ሖት ፡ (መርሐ ይመርሕ ይምራሕ። ዕብ ማራሕ፤ ቀባ መረገ ዐቨ) መምራት፤ ፊት ፊት መኼድ፤ መሳብ መውሰድ፤ የመንገድ የትምርት የዜማ የጸሎት። መረየን እይ፤ የዚህ ፣መምቲያ ነው። መሪሐ ይመርሖሙ። መልአክ ዘይመርሐኒ። እለ ይመርሑ ወእለ ይተልዉ። ዘመርሐነ ውስተ ብሔረ በድው ፡ (፬ነገ ፡ ፬ ፡ ፳። ዕር ፡ ኢሳ፯ ፡ ፲፯። ማር፲፩ ፡ ፱። ኤር፪ ፡ ፮)።
፡ ማሳየት ፥ ማስረዳት፤ መግለጥ ማስረገጥ፤ የነገር ፥ የምስጢር። ወይመርሕ ኀበ ዝንቱ ቃሉ ለልዑል። ተወክፎተ ሠያጢ ዐረቦነ እምእደ ተሣያጢ ይመርሕ ኀበ ፍጻሜ ሠዪጥ ወተሣይጦ ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፳፬ ፡ ፩። ፴፫)። በመርሐ ፈንታ አምርሐ ይላል፤ ስሕተት ነው። አንተ አምራሕከ ጽድቀ ወኀጢአተ ወፈለጥከ ብርሃነ ወጽልመተ እኩየ ወሠናየ ፡ (ኪዳ)።
መሪስ ፡ (መረሰ፤ ዐረ። ዕብ ማራስ) መንከር መዘፍዘፍ ማጀል፤ በጨው በውሃ በቅጠል ፥ ለማራስ ለማበስበስ።
መሪር ፡ (ራን ራት ራር) በቁሙ፤ መራራ ክፉ፤ ቍጡ ብስጩ፤ ዐመፀኛ። እለ ይብልዎ ለጥዑም መሪረ ወለመሪር ጥዑመ። መሪረ ኮነ ሜስ። ይኄይስ መዊት እመራር ሕይወት። ትውልድ ዕሉት ወመራር። መሪራነ ነፍስ። ሕዝብ መሪራን። ቤተ መሪራን ፡ (ኢሳ፭ ፡ ፳። ፳፬ ፡ ፱። ሢራ፴ ፡ ፲፯። መዝ ፡ ፸፯። መሳ፲፰ ፡ ፳፭። ዕን፩ ፡ ፮። ሕዝ፪ ፡ ፭)።
መሪር ሮት ፡ (መረ፤ መረረ ይመርር ይምርር። ዕብ፤ ማራር። ሱር ማር። ዐረ መረ) መምረር፤ መጐፍነን፤ ከጣፋጣና ከሖምጣጣ ልዩ ክፉ መኾን፤ የጣዕም የጠባይ። ይመርር ጣዕሙ ለመዓር በዕጕሥታር። ዘይመርር እምሐሞት። ለትምረራ ለከርሥከ። ወይመርሮሙ ምግባራ ለጽድቅ
፡ (ሄርማ ፡ ገ፴። ምሳ፭ ፡ ፬። ራእ፭ ፡ ፮። ቀሌ)።
፡ ማዘን መትከንከን፤ መቈጣት መበሳጨት፤ ዕርር ምርር ማለት። መሪረ መረርኩ። መረረተኒ ነፍስየ እምኔክን። ወምንትኑ ዘመደ መዋቲ ከመ ትምርር በእንቲኣሁ
፡ (ሰቈ፩ ፡ ፳። ሩት፩ ፡ ፲፫። ሱቱ ፡ ዕዝ፰ ፡ ፵)። መር ማለት መናር፤ ዘሎ ማለፍ። መረመርና መረመረ ማለት የዚህ ዘር ነው።
መሪት ቶት ፡ (መረተ ይመርት ይምርት) መምረት፤ ከገለባና ከአበቅ መለየት ፥ እንዳፈር መቈለል። መመረት መዛግ፤ ዐፈር መሬት መኾን ፥ ወዳፈርነት መመልስ፤ የማዕደናትና የሥጋ የንጨት።
መሪዕ ዖት ፡ (መርዐ ይመርዕ ይምራዕ። ዕብ ማራእ) መጐምዠት መሻፈድ ፥ መድራት መዳራት፤ የንስት። መዝለል መከመር፤ መስረር መውጣት ፊጥ ማለት፤ የተባት። ንባቡም ምስጢሩም ምዒር ነ ምዕረ ካለው የወጣ ነው፤ መዐረንና ፈሐለን እይ። ብእሲት እንተ ትመርዕ በብእሲት፤ አው ብእሲ ዘይመርዕ በደቂቅ። እመ ቦ ብእሲት ዘትመርዕ በሥጋሃ። እመ ቦ ብእሲ ዘያፈቅር ደቂቀ ከመ ይምራዕ ቦሙ ፡ (ቄድር)። ኰነነ ደየነ በማለት ፈንታ መርዐ ይላል፤ ስሕተት ነው። መራዕኪዮን ለአኃትኪ
፡ (ሕዝ፲፮ ፡ ፶፪)። አንዳንድ መጽሐፍ በመርዐ ፈንታ ተመርዐ ይላል፤ አያሰኝም። ዘይረኵስ በተመርዖ ውስተ ፍትወት። እስመ ይትመራዕ ነፍስቶሙ ፡ (መጽ
፡ ቈስጠ። ሄርማ
፡ ገ፲፮)።
መሪግ ጎት ፡ (መረገ ይመርግ ይምርግ። ዕብ ማራግ፤ ነቀለ አፈለሰ። ማራሕ፤ መረገ ለሰነ) መምረግ፤ መለጠፍ መለሰን፤ መዝጋት መድፈን፤ መቅባት መለቅለቅ፤ የጭቃ የበት የኖራ የሺሜንት። ይመርግዎ ለውእቱ ቤት፤ ወእምድኅረ መረግዎ። ጽቡር በዘይመርጉ ቦቱ። ወትመርጎ መሬተ ጸዐዳ ፡ (ዘሌ፲፬ ፡ ፳፪ ፡ ፳፫። ኩፋ ፡ ፲። ዘዳ፳፫ ፡ ፪ ፡ ፬)።
መራሒ ፡ (ሒት ሕያን ያት፤ ሕት) ዝኒ ከማሁ፤ መሪ አስተማሪ። መራሔ ሕይወት። መራሔ ኵሉ እኩይ። ዛቲ መጽሐፍ መራሒተ ልቡና ይእቲ። መራሕያነ ብርሃን ፡ (ኪዳ። ቀሌ። ፈላስ። ቅዳ ፡ መስተ)።
መራሕያን ፡ የርባታ መደቦች፤ ዐሥሩ ሰራዊት፤ አነ አንተ ቲ፤ ውእቱ ይእቲ፤ ንሕነ አንትሙ ን፤ ውእቶሙ ን። ቀተልኩ ከ ኪ ለ ለት፤ ቀተልነ ክሙ ክን ሉ ላ። የውእቱንና የሁን አፈታት እይ።
መራስው ፡ መልሕቆች፤ ወደቦች።
መራናታ ፡ ጌታ መጣ፤–ማር ማሪ ማራን።
መራናት ፤–ማብሪያ ፤–ነዊር ኖረ መናረት።
መራዕዋት ፡ መርዓውያት፤ ሙሽሮች፤ ልጃገረዶች፤ ምራቶች። እለ ውእቶን መራዕዋተ ክርስቶስ። ከመ እማንቱ ይኩና መርዓውያቲሁ ለክርስቶስ ፡ (ፈ ፡ መ ፡ ፮ ፡ ፲። ስንክ
፡ የካ፮)። መራዕዋት በማለት ፈንታ መራዕው እያለ የወንዶቹን ለሴቶች ያደርጋል፤ ስሕተት ነው። ቅዱሳት መራዕው። ክልኤሆን መራዕዊሃ ፡ (ቄር። ሩት፩ ፡ ፮ ፡ ፯። ሆሴ፬
፡ ፲፫)።
መራዕው ፡ መራዕው፤ መርዓውያን፤ ሙሽሮች፤ ባሎች፤ ወንዶች፤ ዐዲስ ያገቡ፤ ዓመት ያልሞላቸው።
መራዕይ ያት መርዔታት ፡ መርዔታት፤ መንጎች፤ መንጋዎች፤ የሚንጋጉ። መራዕየ አልሕምት ወመራዕየ አባግዕ። መራዕየ አሕርው። ኖሎት ወመራዕዪሆሙ ፡ (ኩፋ ፡ ፳። ማር፭ ፡ ፲፩። ኤር፮ ፡ ፫)።
፡ ሰራዊት፤ ወታደር፤ ጭፍራ። መጋቤ መራዕይ ፡ (ዘፍ፳፩ ፡ ፳፪። ፳፮ ፡ ፳፮)።
መራክብት ፡ (ዕብ ታኒም) አከይስት፤ ግሩማን አራዊት፤ የሚሰሩ የሚወረወሩ
፡ (ኢሳ፲፫ ፡ ፳፪)።
መራዲ ፡ (ዲት) አው መራድ ፡ (ያን ያት) የመረደ መራጅ፤ ሽፍታ ወራሪ፤ ጠብጣቢ ገሥጋሽ፤ ሰራዊት ጭፍራ ፥ የጦር ሕዝብ ፥ ዘማች። ፈኖከ መራደ ትንንያ ይቅድሙ ተዓይኒከ። በእንቲኣክሙ እፌኑ ባቢሎን መራደ። ወሰአሎ ለፍምፍምዮስ ከመ ይፈኑ ሎቱ መራደ መርድአ ላዕለ እኍሁ ፡ (ጥበ፲፪ ፡ ፰። ኢሳ፵፫ ፡ ፲፬። ዮሴፍ)። ሀጕል ቀትል መዐት ስደት በማለት ፈንታ መራድ ይላል፤ የመላሽ ስሕተት ነው። መራደ ረሲዓን። እለ ይትቃተሉ ውስተ መራድ። ወፀቀበ መራደ። አንሥኡ መራደ
፡ (ምሳ፫ ፡ ፳፭። ዮኤ፪ ፡ ፭። ዓሞ፩ ፡ ፲፩። ግብ፲፫ ፡ ፶)።
መራድ ፡ የሚሞርድ ሞራጅ፤ ሰው ወይም ሞረድ፤ መራጃ ታላቅ መዶሻ። የዕቡይ ሞረድ እንዲሉ። በረደንና በርደድን እይ። መና በ ይዋረሳሉ፤ ዝናም ብ።
መሬታዊ ፡ በቁሙ፤ ምድራዊ ግዙፍ፤ ካፈር ከመሬት የተገኘ ሟች ፈራሽ በስባሽ። በከመ ዝኩ መሬታዊ ከማሁ መሬታውያን ፡ (፩ቆሮ ፡ ፲፭ ፡ ፵፰)።
መሬት ፡ በቁሙ፤ ዐፈር ትቢያ ዐመድ እንደ ምርት የሚዛቅ የሚታፈሥ፤ የብስ ገራህት ጓል ጕሊት መኰላ ፥ የምድር ገላ ፥ የሚረጥብ የሚደርቅ ፥ የሚፈርስ የሚደቅ፤ ካራቱ ባሕርያት አንዱ፤ ጽልመትና ውዕየት ርጥበት ያለው፤ በጽልመቱ ከነፋስ ፥ በውዕየቱ ከእሳት ፥ በርጥበቱ ክውሃ የሚስማማ። ኩኵሕ ኀበ አልቦ መሬት። ወደዩ መሬተ ዲበ ርእሶሙ። መሬት አንተ ወትገብእ ውስተ መሬት። እለ ይነውሙ ውስተ መሬተ ምድር ፡ (ማቴ፲፫ ፡ ፭። ሰቈ፪ ፡ ፲። ዘፍ፫ ፡ ፲፱። ዳን፲፪
፡ ፪)። ጽቡር ኖራ ድኵዕ በማለት ፈንታ መሬት ይላል። አብያተ መሬት። መሬት ጸዐዳ። መሬተ ምድር ፡ (ኢዮ፬ ፡ ፲፱። ዘዳ፳፯ ፡ ፪። መዝ ፡ ፹፰)።
መርሐቂ መርሕቅ ፡ (ቅት ቃን ቃት) የሚያርቅ፤ የሚያሶግድ አራቂ። ትሕትና መርሕቅኒ ወመድኅንኒ እመሥገርተ ሰይጣን ፡ (ፊልክ
፡ ፻፶፪)። ኹለተኛም ማራቂያ ማስራቂያ ማሶገጃ ተብሎ በማድረጊያነት ይፈታል።
መርሕ መራሕ ፡ (ብ አምርሕት) የሚመራ መሪ፤ መምር አብነት። አንተ መርሖሙ ለዕዉራን። ኤጲስቆጶስ ውእቱ መርሖሙ ለሕዝብ። አንትሙሂ መርሐ ኩንዎሙ። እስመ ውእቱ መርሕ ውስተ ጥበብ ፡ (ሮሜ፪ ፡ ፲፱። ዲድ ፡ ፬። ኪዳ። ጥበ፯ ፡ ፲፭)። ንተሉ አምርሕተ ሠናይ ፍኖት። ዕዉራን አምርሕተ ዕዉራን
፡ (ቅዳ ፡ ሕር። ማቴ፲፭ ፡ ፲፬። ፳፫ ፡ ፲፮ ፡ ፳፬)።
መርሕብ ፡ (ብ መራሕብት) ሰፊ ቦታ፤ ሜዳ፤ ሰታታ፤ ገባያ ጉባይ፤ አደባባይ። ወአውፅአኒ ውስተ መርሕብ። ነኀድር ውስተ መርሕብ። መኣዝነ መራሕብት ፡ (መዝ ፡ ፲፯። ዘፍ፲፱ ፡ ፪። ማቴ፮ ፡ ፭)።
መርኅብ ፡ የሚያስርብ፤ አስራቢ።
መርሕፅ መርሐፂ ፡ መርሐፂ፤ የማያልብ፤ የሚያወዛ የሚያስወዛ።
መርኆ ፡ (ብ መራኀት፤ ታት) መክፈቻ፤ መከፈቻ፤ ማስከፈቻ። ነሥኡ መርኆ ወአርኀዉ። እሙንቱ እለ ይእኅዚ መራኁተ ቤተ እግዚ ፡ (መሳ፫ ፡ ፳፭። ፩ዜና
፡ ፱ ፡ ፳፯)።
መርመሌ ፡ (ዕብ፤ ታርሚል። ሱር ታርማላ) መክተቻ፤ ፊኛ ከረጢት፤ ቈርባብቻ፤ ኰረጆ፤ ቍናማት፤ ኩፋዳ። መምጠቅን ተመልከት፤ ከዚህ ጋራ አንድ ነው። በመርመሌ ፈንታ መርመሬ ይላል፤ የጣፊ ስሕተት ነው። ኀምስተ አእባነ ልሙጻተ ወክቡባተ ጸዊሮ በመርመሬ፤ እስመ ዘክርስቶስ መርመሬ እንተ በምድር ቤተ ክርስቲያን፤ ወባቲ አእባን ክቡራት
፡ (ተረ ፡ ቄር፰)።
መርመም ፡ (ብ መራምም) መራመሚያ፤ ዐይናማ ደንጊያ።
መርመሬ ፡ ኰፈዳ ኰረጆ፤–ረመለ መርመሌ።
መርመር ፡ (ዐረ) ነጭ ደንጊያ፤ እብነ በረድ። አዕማደ መርመር ፡ (ስንክ ፡ ታኅ)።
መርምም ፡ ዝኒ ከማሁ። መርምመ ልሳን እምጽዋዔክሙ።እስመ ጸላእትነ ሶበ ርእዩ ልሳነነ መርምመ እምእከይ ፡ (ግንዘ)።
መርሠሠ ፡ ዳሰሰ ዳበሰ፤–መርሰሰ።
መርሰሰ ፡ (ተቀ ግ) ዳሰሰ ዳበሰ ነካ ዐሻሸ የተነከረውን። ሻ ፈለገ ተም ተም አለ፤ ተደናበረ። ወትገብእ ትመርስስ መዓልተ ዘከመ ይመረስስ ዕዉር በውስተ ጽልመት
፡ (ዘዳ፳፰ ፡ ፳፱)። በመርሰሰ ፈንታ አመርሰሰ ይላል፤ ስሕተት ነው። ወያመረስሱ ውስተ አረፍት ከመ ዕዉር። ያመረስሱ ቀትረ ከመ ሌሊት ፡ (ኢሳ፶፱ ፡ ፲። ኢዮ፭ ፡ ፲፬)። ከዚህ ይልቅ ደግሞ ፊደል አዛውሮ ረምሰሰ አረምሰሰ ይላል፤ ቀሐመንና ዕጕሥታ(ዕጉትሣ) ርን እይ። ታረመስስ ዲበ አባላቲከ ፡ (አረጋ ፡ ድ፯)።
መርሰስ ፡ ዳሰሳ፤ ዳበሳ። ዕዉር ውእቱ ዘየሐውር በመርሰስ ፡ (፪ጴጥ ፡ ፩ ፡ ፱)።
መርሴ ፡ (ትግሬ) የበር መዝጊያ። ሲበዛ መርስያት፤ መራስይ ያሰኛል።
መርስ [1]
፡ ወደብ፤–ረሲው ረሰወ።
[2] ፡ (ሳት) ጸጥታ፤ ዝምታ፤ ፍጹም ዕረፍት፤ መርከብ ከወደብ ሲቆም የሚገኘው። ወይም የባሕሩ ጠረፍ፤ ወደቡ ገደቡ። መርስ ወዛኅን ጥዑይ። መካንር መርስ ለለ ኵሉ። ኀድፈኒ ውስተ ዛኅን ወመርስ ፡ (አፈ ፡ ተ፲፰። ስንክ
፡ ጥቅ፳። ኅዳ፲)።
መርስዒ ዕ ፡ (ዓን) የሚያስረሳ፤ አስረሽ፤ አረሳሽ። መርስዔ ሐዘን መሪር። ሐዘን ወፍሥሓ መርስዓን
፡ (ደራሲ። ፍ ፡ ነ ፡ ፵፫ ፡ ፬)።
መርሥእ ኢ ፡ የሚያስረጅ፤ እርጅና የሚስብ የሚያመጣ።
መርሶ [1] ፡ (ዐረ ሚርሳት) መልሕቅ፤ የመርከብ ልጓም። እስመ መርሶ ሶበ ይረስውዎ ይከልኦ ለሐመር ከመ ኢያንቀልቅል ለፌ ወለፌ ፡ (አፈ ፡ ድ፲፩። ዕብ፮ ፡ ፲፱)።
[2] ፡ (ዐረ ሙርስን) ወደብ፤ የመርከብ መቋሚያ፤ ጽንፈ ባሕር ከፈረ ባሕር፤ የባሕር ደጃፍ መውጫና መግቢያ፤ ወይም ዙሪያ። መርሶ አሕማር። መርሖሙ ውስተ መርሶ ኀበ ፈቀዱ መርሶ ሕይወት እሙስና ፡ (ዘፍ፵፱ ፡ ፲፫። መዝ
፡ ፻፮። ኪዳ)።
መርቄ [1] ፡
ቈላ በረሓ፤–ረቅይ ረቀየ።
[2] ፡ ሙቀት፤ ትኵሳት፤ ሐሩር፤ በጋ ድርቅ። ያጸልል እምነ መርቄ ታሕቴሃ። አኮኑ ዝናም ያቈርሮ ለመርቄ። መንፈሰ መርቄ። ዐውሎ መርቄ። ላህብ ወመርቄ ፡ (ሢራ፲፬ ፡ ፳፯። ፲፰ ፡ ፲፮። ኢሳ፬ ፡ ፬። ኤር፲፰ ፡ ፲፯። አርጋ)።
፡ ቈላ፤ በረሓ፤ ሙቀታም ሐሩራም። ብሔረ መርቄ። ምድረ ካምሰ መርቄ ይእቲ፤ ወምድረ ሴምሰ ኢመርቄ ወኢደደክ፤ ላ ቱስሕት ይእቲ በቍር ወበሞቅ። ይባርክዎ ደደክ ወመርቄ ፡ (ሢራ፴፪ ፡ ፳፮። ኩፋ ፡ ፰። ዳን፫ ፡ ፵፰)።
መርበብት ፡ (ብ መራብብት) በቁሙ፤ መረብ፤ መርበብ፤ ያሣ ወጥመድ፤ የሌላውም ኹሉ፤ ወስከምት፤ ማነቆ ሸምቀቆ። ይወድዩ መርበብተ ውስተ ባሕር። ተከለ መርበብተ ከመ ያሥግር ባቲ አራዊት። መርበብት ሕይወት
፡ (ማቴ፬ ፡ ፲፰። ስንክ ፡ ሚያ፲፰። ቅዳ ፡ ዮሐ)።
መርብዕት ፡ አራት ጐን ወገን፤ ገጽ ማእዝን፤ ላንድነቱ አራት ክፍል፤ ቅርጽ ገጽ ያለው። እንተ መርብዕት። መርብዕተ ማኅፈድ። መርብዕተ መኣዝኒሃ ለዓለም ያንቀለቅል። አሠረ ልቡ ለብእሲ መርብዕተ ያስተርኢ ፡ (፫ነገ ፡ ፮ ፡ ፴። ኩፋ ፡ ፴፰። ኪዳ። ሢራ፴፯ ፡ ፲፰)።
መርትዒ ዕ ፡ የሚያቀና፤ ቅን የሚያደርግ። መርትዐ ጠበብት
፡ (ጥበ፯ ፡ ፲፭)።
መርዐወ ፡ (ዲ ቃ ግ) አጋባ፤ አዛወገ፤ ከከከ፤ ሰረገ፤ ሞሸረ፤ ጨጐለ፤ የጋብቻ በዓል አደረገ።
መርዐይ መርዔት ፡ መንጋ፤ የእንስሳት ማኅበር፤ ጉባኤ ሸንጎ እንግልጋ፤ በየስሙ በየነገዱ። ሰኰናሆሙ ለመርዔት። መርዔተ አጣሊ። አባግዐ መርዔት። ኢትፍራህ ኦ ንኡስ መርዔት ፡ (ማሕ፩ ፡ ፯። ፬ ፡ ፩። ኤር፳፫ ፡ ፩። ሉቃ፲፪
፡ ፴፪)።
መርዓ ፡ ጋብቻ ግቢ፤ ተክሊል፤ ሰርግ፤ የደስታ በዓል። ሶበ ተፈጸመ መዋዕለ መርዓ። አዕበዮ ለመርዓ አስቴር። ልብሰ መርዓ። ቤተ መርዓ። መርዓ መንግሥት። ለመርዓ ስምከ ይትገበር ክብካብ
፡ (አስቴ፩ ፡ ፭። ፪ ፡ ፲፰። ማቴ፳፪ ፡ ፲፩። ሄርማ። ገድ ፡ ላሊ። ስንክ ፡ መጋ፫)።
መርዓ ት ዊ ፡ ሰርግ፤ ሙሽራ፤–ረዐወ።
መርዓት ፡ (ዊት) ሙሽሪት፤ ሴት ሙሽራ፤ የመርዓዊ ጣምራ፤ ልጃገረድ፤ ምራት፤ የወንድ ልጅ ሚስት። ዘቦቱ መርዓት መርዓዊ ውእቱ። ከመ መርዓት ስርጉት ለምታ። መርዓትኒ እምሐማታ ፡ (ዮሐ፫ ፡ ፳፱። ራእ፳፩ ፡ ፪። ማቴ፲ ፡ ፴፭)።
መርዓዊ ፡ (ዊት ውያን ያት) ሰርገኛ፤ ዕድመኛ። ሙሽራ፤ ባል፤ ወንድ፤ ዐማች። ደቂቀ መርዓዊ። መርዓዊ ሰማያዊ። ትብሎ መርዓት ለመርዓዊሃ። ኢይስክብ መርዓዊ ምስለ ሐማቱ ፡ (ማቴ፱ ፡ ፲፭። ቀሌ። ድጓ። ቄድር)።
መርዔት ፡ መንጋ፤–ርዕይ ረዐየ።
መርዕው ፡ (ዋን ዋት ዑት) ዝኒ ከማሁ፤ ጠማጅ፤ አቀናጅ።
መርዕድ ፡ (ድት ዳን ዳት) የሚያርድ የሚያንቀጠቅጥ፤ ድምጡና መልኩ የሚያስፈራ። ደባትሪሁ ዘነድ ወሠረገላሁ መርዕድ። ንጥረ መባርቅት መርዕድ ፡ (ሳታ። መጽ ፡ ምስ)።
፡ ግምጃ፤ ልብሰ መንግሥት፤ አርድ አንቀጥቅጥ የሚባል፤ ጠብደንን ተመልከት።
መርከብ [1] ፡ (ብ መራክብ። ዐረ መርከብ። ሱር ማርካብታ) በቁሙ፤ ሐመር፤ የባሕር ባቡር።
[2] ፡ (ዕብ ሜርካባ) ፤ ሠረገላ ፤ ፈረስ የሚያሮጠው ፤ ሰው የሚቀመጠው።
መርወይ ፡ (ብ መራውይ) የውሃ ዕቃ፤ መጠጫ፤ ማጠጫ፤ ቅል መንቀል። እምብዝኀ ንዋይ ዘአፍቀርከ፤ ሐወ ዘዐቈርከ በመርወይ ፡ (ድጓ)።
መርወጺ ፡ የሚያሮጥ፤ የሚያስሮጥ፤ አሯጭ አስሯጭ፤ ጋላቢ። መርወጼ አፍራስ
፡ (ቈስጠ)።
መርዋሕት ፡ (ታት። ቅብጥ) መረዋ፤ መረዋት፤ ቃጭል፤ ታላቅ ታናሽ መካከለኛ በያይነቱ። መርዋሕት ዘይሰማዕ ድምፁ እስከ ነዋኅ ፡ (አዋል)።
መርውሕ ፡ (ሕት ሓን ሓት) ዝኒ ከማሁ፤ አናፋሽ።
መርዘም ፡ ትዕቢት፤ ኵራት፤ ነቀጥቃጥ፤ እንባዜ፤ እስክታ፤ ፃሕስ፤ ሑሰተ ርእስ። እምስካር ይትወለድ ምርዓት ወዝሙት ወሥሥዕት ፅርፈት ወትዕቢት ወመሐላ በሐሰት ወኢያሠንዮ በዝንጋዔ ወመርዘመ ርእስ። ቅንአት ወፍትወተ አንስት ልበ ጠቢባን ያማስን፤ ወዓዲ ስካር ወዘፈን ወመርዘመ ርእስ
፡ (ቀሌ)።
መርደደ ፡ (ተቀ ግ) ደፈረ ጨከነ፤ ተጋ ፈጠነ።
መርድ ፡ የከበሬታ ስም፤ ከራሶች በላይ ክንጉሦች በታች መካከለኛ፤ የሺዋ ባላልጋ፤ ወይም ዐልጋ ወራሽ የነጋሢ ዘር የሚጠራበት። መርድ አምኃየስ፤ መርድ ኀይሌ እንዲሉ።
መርድእ ፡ (እት ኣን ኣት) ዝኒ ከማሁ። ንግበር ሎቱ መርድአ ዘከማሁ። ኢየኀሥሥ መርድአ። እስመ ዓለም መርድእ ውእቱ ለጻድቃን ፡ (ኩፋ ፡ ፫። ቅዳ ፡ ኢጲ። ጥበ፲፮ ፡ ፲፯)። ረድኤት በማለት ፈንታ መርድእ ይላል፤ ስሕተት ነው። በመርድአ አግዚአብሔር። አዘዘ ይኅድግ መርድአ ህርቃኖስ ፡ (ፊልክ ፡ ፮። ዮሴፍ)።
መርዶ ፤ ዶት ፤ (መረደ
ይሜርድ ይመርድ። ዕብ
ማራድ። ሱር ምራድ። ዐረ መሩደ) ፤ መሞረድ። መሸፈት ማመጥ ፤ መውረር መዝረፍ ፥ ማሸበር። መረደ ሀገሮሙ ለሳምራውያን ወአንኀለ መቅደሶሙ (ዮሴፍ)።
፡ መጠብጠብ ፥ መሮጥ መገሥገሥ ፥ ቶሎ ቶሎ መኼድ ፥ ቸኵሎ መራመድ። ዘይሜርድ ፍኖቶ። መረዱ ይዴግንዎሙ። ውስተ አርእስተ አድባር ይሜርዱ። ለእመ መረድነ ላዕሌሆሙ (መዝ ፡ ፲፰። ጥበ፲፱ ፡ ፪። ዮኤ፪ ፡ ፭። ዘፍ፴፫ ፡ ፲፫)። ሮደንና ዴገነን እይ ፤
የዚህ ጎሮች ናቸው።
መርገም ፡ (ማት) በቁሙ፤ ርግማን፤ ስድብ፤ ክቡድ ቃል። መጽአ መርገም ላዕሌነ ወመሐላ። መሪር አፉሆሙ ወምሉእ መርገመ። ኢይፃእ እምአፉሁ ቃለ መርገም። ቡራኬ ወመርገም ፡ (ዳን፬ ፡ ፲፩። ሮሜ፫ ፡ ፲፬። ዲድ ፡ ፲፯። ያዕ፫ ፡ ፲)።
መርገገ ፡ መረገገ ፥ ጐመዘዘ፤ መርጋጋ ኾነ አፍ ያዘ እንደ ጭቃ ፡ (ዐማርኛ)።
መርገፅ ፡ በቁሙ፤ መርገጥ፤ የበሬ ዕቃ ስም፤ የወገል ወይም የከርፈስ ጠፍር፤ ገበሬ ድግሩን ማረሻውን ከሞፈር ጋራ እየረገጠ የሚያስርበት።
፡ ርካብ፤ የርካብ፤ ጠፍር። ተጽዕነ ላዕለ ፈረስ፤ ወበጊዜሃ ተመትረ መርገፁ ፡ (ድር ፡ ሚካ)።
መርገፍ ፡ (ዐማርኛ) ቀጭን ልብስ፤ ጥሩ ግላስ፤ በብዙ ዐይነት ሐር የተሠራ፤ የተጠለፈ፤ ሻኵራ አጫዋች። ፡ (ግጥም) አባቶቻችን ለበቅሏቸው፤ ኮርቻ ነበር ዐሳባቸው የዛሬ፤ ልጆች እጅግ ኰሩ፤ ለመርገፉ ነው የሚጥሩ።
መርግሕ [1] ፡ መርግ፤–ረግሐ።
[2] ፡ (ሓት፤ መራግሕ) መርግ፤ ቋጥኝ፤ ናዳ ናደት፤ ታላቅ ደንጊያ። ወውእቱሂ መርግሐ እሳት ይወ ድቅ ዲቤሆሙ ፡ (ራእ ፡ ባሮ)።
መርግዕ ፡ መርግ ናደት፤–ረግሐ መርግሕ።
መርጡላዊ ፡ ኦሪታዊ ዘኦሪት፤ ስምዓዊ ዘስምዕ
፡ (መጽ ፡ ምስ)።
መርጡል ፡ (ዕብ ሞዔድ። ሱር ዚምና። ዐረ እሊጅቲማዕ) ዕድሜ ፥ የበዓልና የቀጠሮ ቀን፤ የጉባኤ ቦታ ፥ ዐውደ ስምዕ ፥ ሕዝብ ለጸሎትና ለመሧዕት ፥ ወይም ለክርክርና ለሙግት ለዘፈን ለጨዎት ለምስክርነት የሚሰበሰብበት። ደብተራ ዘመርጡል
፡ (ዘፀ፳፱ ፡ ፬ ፡ ፲። ፴ ፡ ፲፰። ፳፮ ፡ ፴፮)። በዕብራይስጡ ዔዱትና ሞዔድ ልዩ ሲኾን ጽርኡ አንድ አድርጎታል። ባለቅኔዎችም መርጡልን ተራዳ ድንኳን አዳራሽ ይሉታል። ባለብሉዮች ግን ዘመርጡል ያለውን ዘዘመን ዘብዑድ ዘስምዕ ይሉታል። አዳራሽ ከተባለ ዘንድ መቅደስ ቤተ ክር በማለት ፈንታ መርጡል ይላል ፡ (ስንክ ፡ ጥቅ፮ና ፡ ፳፭)። እምኔታት በውስተ አሐቲ መርጡል
፡ (ስንክ ፡ ጥር፩ና ፡ ፲፪። ገድ ፡ ተክ)። መርጡለ ማርያም ሥዕርተ ርእስ በመልዕልተ ድማኅ ዘበቈለት ፡ (ቅኔ)።
መርጡር ል ፡ (ጽር ማርቲሪዮን፤ ማርቲሪዩ። ዕብ ዔዱት። ሱር ሳሀዱታ። ዐረ ሸሀደት) ኦሪት ሕግ፤ ጽላት፤ ስምዕ። ታቦት ዘመርጡር ል
፡ (ዘፀ፳፭ ፡ ፳፪። ፳፮ ፡ ፴፫)። መካነ መርጡል። በቅድመ መርጡል
፡ (፪ዜና ፡ ፳፬ ፡ ፮። ዘፀ፲፮ ፡ ፴፬)።
መርፈቅ ፡ መድረክ። ወተለዐለ መርፈቀ ኆኅት ፡ (ኢሳ፮ ፡ ፬)።
መርፍእ እት ፡ (ብ መራፍእት) መርፌ፤ መስፌ፤ የመርፌ ዐይነት ችንካር የብረት እሾኽ። ስቍረተ መርፍእ። ግብረ መርፍእ። ዘበመርፍእ። አዘዘ ይቀንውዋ እደዊሃ ወእገሪሃ በመራፍእት በሊኃት። ዘየኀትም እደዊሁ ወእገሪሁ በመርፍእ። ኢትኅትሙ አባለክሙ በመርፍእ ፡ (ማቴ፲፱ ፡ ፳፬። ዘፀ፳፯ ፡ ፲፮። ፴፯ ፡ ፳፩። ስንክ ፡ ጥር፴። ቈስጠ ፡ ፷፪)።
መሽተሪ ፡ (ዐረ እልሙሽተሪ) ኮከብ፤ የኮከብ ስም
፡ (አፈ ፡ ተ፳፮)።
መቀቀ ፡ (መቂቅ መቀ። ዕብ ማቆቅ ሂሞቅ) ማቀቀ፤ ማቅ ለበሰ ባለመከራ ኾነ፤ ቀለጠ ሟሟ፤ አነሰ ኰሰሰ፤ አረጀ ተበላሸ። ጣጣ አንጣጣ፤ የጕረሮ። ወመቀቆ ጕርዔሁ
፡ (ታም ፡ ማር ፡ የካ፲፮)።
መቍለዝ ፡ መቈጥቈጫ፤ ፋስ፤ መጥረቢያ። ሲበዛ፤ መቋልዝ።
መቍረሪ ፡ (ሪት ርያን ያት) የሚያበርድ፤ አብራጅ፤ አቀዝቃዥ።
መቍረር ርት ፡ ማቍረሪያ፤ ማብረጃ፤ ማቀዝቀዣ፤ ማቅረሪያ፤ ማንቈርቈሪያ፤ ኵስኵስት፤ ጡታም ብርት፤ ልሕኵት። ማየ መቍረር፤ የኵስኵስት ውሃ፤ የቅዳሴ ጠበል። ወማየ መቍረርኒ ኢይንጥብ ምንትኒ እምአፍ ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፲፫)።
መቍጸርት ፡ ጕንጕን ሽርብ፤ ቋድ ጥብጣብ፤ የልብስ ማስጌጫ መዘምዘሚያ፤ ዝምዝማት፤ ቍልፍ ተካሪስ። ወመቍጸርቱ ወርቅ ዘግቡር በዕንቍ ፡ (ሢራ፵፭ ፡ ፲፩)።
፡ መቍጠሪያ፤ መቋጠሪያ፤ መቈጣጠሪያ፤ የቍጥር መሣሪያ።
መቍሶ ሶት ፡ (መቈሰ ይሜቍስ ይመቍስ) መቍረጥ፤ መለየት ማጥፋት። መቀስ ማለት ከዚህ ወጥቷል። ፡ (ተረት) ቀስ በመቀስ። ይሜቍሶ እግዚ እምሀብቱ እንተ አሰፈወ ለኄራን ሥዩማነ ቤተ ክር ፡ (ቀሌ። መቃ
፡ ገ፭)።
፡ ማበል ፥ መክዳት፤ ቃልን መለወጥ። ኢይሜቍስ እግዚ ዘወፅአ እምአፉሁ። ኢይሜቍሰከ ፡ (መዋሥ። ሄርማ ፡ ገ፴፯)።
መቍዐል [1] ፡ ሥብ ጮማ ፥ ወረሞ፤–ቈዐለ።
[2]
፡ መቍዐል፤ ፡ (ብ መቋዕል ልት። ዐረ ሙካል፤ ሙቅለት) ሥብ ወፍር ጮማ። የሠባ የወፈረ ያፈረጠመ፤ ወረሞ አውላዶ፤ መሐስዕ። መቍዐለ ጠሊ ወላሕም። እለ ይሴሰዬ መቋዕለ። ቍርባናተ ወመቋዕልተ ፡ (ዘዳ፴፪ ፡ ፲፬። ዓሞ፯ ፡ ፬። ፪ዜና ፡ ፯ ፡ ፯)።
መቃምር ፡ የጨዎታ ስም፤ ቅልሞሽ፤ ቍጥር ያለበት ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፵፫ ፡ ፲፪)።
መቃብር ፡ (ራት) መቅበሪያዎች፤ መቃብሮች። መቃብር ብዙ፤ መቃብራት የብዙ ብዙ። መቃብረ አበዊከ። መቃብር ገብሱሳን። ነቅዐ ኰኵሕ ወተከሥቱ መቃብራት ፡ (ኩፋ ፡ ፴፪። ማቴ፳፫ ፡ ፳፯። ፳፯ ፡ ፶፬)። መቅበር መቅበርት በማለት ፈንታ መቃብር እያለ ይጥፋል፤ ስሕተት ነው። መቃብር ክሡት። መቃብረ ራሔል። ውስተ አሐዱ መቃብር ፡ (ሮሜ፫ ፡ ፲፫። ኩፋ
፡ ፴፪። ጦቢ፬ ፡ ፬) አንዱን ጕድጓድ መቃብር ማለት ያማርኛ ነው፤ የግእዝ አይዶለም። አንድ መኳንንት እንዲሉ።
መቃኒት ፡ (ታት) የሥቃይ መሣሪያ፤ መቅጫ፤ ማሽቈጥቈጫ፤ በየስሙና በያይነቱ። አዘዘ ሳቦር ንጉሥ ያምጽኡ መቃኒተ ሥቃይ ከመ ያፍርሆ ለቅዱስ። አርአዮ ኵሎ መቃኒታተ ሥቃያት
፡ (ስንክ ፡ ታኅ፲። መጋ፯)።
መቃይጽ [1] ፡ የጭን ብረት፤–ቍይጽ።
[2]
፡ የሥቃይ መሣሪያ፤ መንቈር ዛንጅር፤ የጭን እግር ብረት። ለገብር እኩይ ሰውጥ ወመቃይጽ
፡ (ሢራ፴ ፡ ፴፭)።
መቈረ ፡ (ይሜቍር ይመቍር፤ መቍሮ። ዐረ መቀረ) ዐጀለ ፥ ነከረ ዘፈዘፈ ፥ አጣፈጠ ፥ በጨው በመጣጣ፤ የዓሣ የዘይት የቃሪያ የልፍት የመሰለው ኹሉ።
መቅለድ [1] ፡ ዳካ ኵስኵስት፤–ቀለደ።
[2] ፡ (ብ መቃልድ) የውሃ ዕቃ፤ መቅጃ፤ መገልበጫ፤ ለገን ሰንና ብርት ኵስኵስት። ነሥአ ማየ ወወደየ ውስተ መቅለድ፤ ወኀፀበ እግረ አርዳኢሁ
፡ (መዋሥ። ዘፀ፳፬ ፡ ፮)። ንብቲራን እይ።
መቅልዕ ፡ (ብ መቃልዕ) በድል ነጐድ፤ ወንጭፍ፤ ነፍጥ መድፍ፤ ዱላ መንዶ፤ የጥንግ መልጊያ
፡ (ገድ ፡ አዳ)።
መቅሠም ፡ መልቀሚያ፤ መቍረጫ፤ አኀዘ መቅሠሞ
፡ (ሆሴ፮ ፡ ፲)።
መቅሰምት ፡ (ብ መቃስምት) የሟርት መሣሪያ፤ በየስሙና በያይነቱ። ወነሥኡ መቃስምቲሆሙ ምስሌሆሙ ፡ (ዘኍ፳፪ ፡ ፯)።
መቅሠፍት ፡ (ታት) መግረፊያ፤ ጅራፍ ዐለንጋ ከዘራ ጨንገር፤ የመሰለው ኹሉ። መቅሠፍት ወተግሣጽ። ቍስለ መቅሠፍት ይገበር አምግልተ። ድምፀ መቅሠፍት። ወገብረ መቅሠፍተ ጥብጣቤ ዘሐብል ፡ (ሢራ፳፪ ፡ ፮። ፳፰ ፡ ፲፯። ኖሖ፫ ፡ ፩። ዮሐ፪
፡ ፲፭)።
፡ ግርፋት፤ ቍስል፤ ሰንበር፤ በትር፤ ቅጣት። መጠውኩ ዘባንየ ለመቅሠፍት። ምንትኑ ዝ መቅሠፍት ዘማእከለ እደዊከ። ዘየአምር ፈቃደ እግዚኡ ወኢይገብር ብዙኅ መቅሠፍቱ ፡ (ኢሳ፶ ፡ ፮። ዘካ፲፫ ፡ ፮። ሉቃ፲፪
፡ ፵፯)።
፡ በቁሙ፤ የእግዜር ዐለንጋ፤ መቻያ፤ ፍርድ ቅጣት፤ መከራ ሥጋ። ዓዲ አሐተ መቅሠፍተ ኣመጽእ ዲበ ፈርዖን ወዲበ ኵሉ ግብጽ። ሰብዐቱ መላእክት እለ ይጸውሩ ሰብዐተ መቅሠፍተ። አርባዕቱ መቅሠፍት እኩያት
፡ (ዘፀ፲፩ ፡ ፩። ራእ፲፭ ፡ ፩። ሕዝ፲፬ ፡ ፳፩)።
መቅስም [1] ፡ (ምት ማን ማት) ጠንቋይ፤ ሟርተኛ፤ መለኛ፤ ነቢየ ሐሰት። በመቅስም ፈንታ መስተቃስም ይላል፤ አያሰኝም። መስተቃስማን
፡ (አርጋ ፡ ፫። ቀሌ። ገድ
፡ ተክ)። መስተቅስም ቢል ግን አስጠንቋይ ያሰኛል፤ ከአስተቅሰመ ይሰማማል።
[2] : መቅስም መቅሰም ፡ (ብ መቃስም፤ ማት) ማጣፈጫ፤ ጨው፤ ቅመም፤ እንደ ማር ከብዙ ተቀሥሞ አንድ የኾነ፤ ብዙ ዐይነት ወጥ፤ በብዙ ቅመም የተሠራ፤ ሽታውና ጣዕሙ ልብ የሚመሥጥ፤ እጅ የሚያስመጥጥ። ይትዐቀብ እመቃስማተ መብልዕ ወመስቴ። እመ ቦ ዘጥዕመ ዘኮነ እመቃስማት። ይኅድግ ኵሎ መቃስማተ። ኢይብልዑ መቃስማተ
፡ (ቄድር። ፍ ፡ ነ
፡ ፲፭)።
መቅረቢ ርብ ፡ ርብ፤ የሚቀርብ፤ የሚያቀርብ፤ የሚያስቀርብ፤ አቅራቢ። ሎቱ ናቄርብ ዘውእቱ መቅርብ ፡ (ቅዳ ፡ አት)።
መቅረብ ፡ (ብት) ቀራቢ፤ ዘመድ፤ ወዳጅ። አሐዱ እምአግዋሪሁ ወመቅረቡ ፡ (ሲኖዶ)።
መቅረፅ ፡ (ብ መቃርፅ። ዐረ ሚቅራፅ) መቅረጭት፤ መቍረጫ፤ መላጫ፤ መቀስ ምላጭ፤ የመሰለው ኹሉ። ይቤሎ ለረድኡ ሀበኒ መጥባሕተ አው መቅረፀ ወመተረ ባቲ ልሳኖ ፡ (ስንክ ፡ ጳጕ፭)። ሙዳየ ዔረግ በማለት ፈንታ መቅረፅ እንደ ማለት ቄረፅ ይቄርፅ ይላል፤ የተሳሳተ ነው ፡ (ዓሞ፰ ፡ ፩)።
መቅርዕ ፡ (ብ መቃርዕ። ዐረ ሚቅረዐት) መቍሪያ፤ መቈረሚያ በትር፤ የራስጌ ዱላ፤ ወይም የራስ በሽታ፤ የራስ ምታት። በቅሥፈተ መቃርዕ ፡ (አቡሻ ፡ ፶)።
መቅበር ፡ (ርት) መቅበሪያ፤ መቀበሪያ፤ የሬሳ ጉድጓድ። ህየንተ መቅበርቱ
፡ (ኢሳ፶፫ ፡ ፬)።
መቅትል ተል ፡ መቅትል፤ ተል፤ ፡ (ብ መቃትል) መግደያ፤ መሣሪያ። ገዳይ፤ ባለመሣሪያ።
መቅነዪ ፡ የሚገዛ፤ የሚያስገዛ፤ ገዥ አስገዥ። ለከ ንትቀነይ ዘአንተ መቅነዪ ለኵሉ ፡ (ቅዳ)።
መቅንእ መቃንእ ፡ መቃንእ፤ መቃን፤ መቃኖች የግራና የቀኝ። ራግዛትን እይ።
መቅዐን ፡ (ብ መቃዕን) የሚያስጨንቅ፤ የሚያስጠብብ፤ ጠባብ። ጭንቅ ጥብ፤ አጣብቂኝ። ፍኖት እንተ ትወስድ ውስተ ሕይወት፤ ጽዕቅት ወመቅዐን ይእቲ። እስመ መቅዐን ወጠዋይ ምሕዋራ
፡ (አፈ ፡ ተ፳፰። ደራሲ)።
መቅዓን ፡ (ናት) የሥቃይ መሣሪያ፤ የሚያጣብቅ፤ የሚጠረቅቅ፤ የሚያጦዝ የሚጠመዝዝ። አዘዘ ንጉሥ ይደይዎ ውስተ መቅዐን እስከ ይነቅዕ መለያልዪሁ ወይጠወይ ሥጋሁ በእኩይ ፡ (ስንክ ፡ መጋ፲፯)።
መቅደስ ፡ (ብ መቃድስ) በቁሙ፤ መቀደሻ፤ ማመስገኛ፤ መሥዋዕትና፤ ጸሎት ማቅረቢያ የአምልኮት ቤት፤ ሦስት ክፍል ያለው፤ ለብሉዩ ኡላም ሀይከል ዳቤር ወይም ቅድስተ ቅዱሳን፤ ለሐዲሱ ቅኔ ማሕሌት ቅድስት መቅደስ ማለት ነው። ጽርሐ መቅደስ። ቤተ መቅደስ። ሀገረ መቅደስከ። ወያረኵሱ መቃድሲሆሙ
፡ (መዝ ፡ ፭። ኩፋ ፡ ፵፱። ኢሳ፷፬ ፡ ፲። ሕዝ፯ ፡ ፳፬። አፈ ፡ ድ፲፯)። በመቅደስ ፈንታ ምቅዳስ ይላል፤ የጣፊ ስሕተት ነው ፡ (ዘፀ፳፭ ፡ ፰። ፳፮ ፡ ፴፫። ፳፰ ፡ ፫)።
መቅደፍ ፡ (ብ መቃድፍ) መቅዘፊያ፤ ትርክዛ፤ ኀዳፍ። አነ ጸራቢ ወነዳቂ ወእገብር መዋፍርተ ወአርዑተ ወመዳልወ ወመንኰራኵረ ወአሕማረ ወመቃድፈ ወታዕካ ነገሥት ፡ (ስንክ ፡ ጥቅ፱። መጽ
፡ ምስ)። ኹለተኛም መቅደፍት መቃድፍት ይላል በሴት አንቀጽ፤ ፍችው አንድ ነው።
መቅድሕ ፡ (ብ መቃድሕ) መብሻ፤ መንደያ፤ መሰርሰሪያ። መቅድሐ እዝን
፡ (ስንክ ፡ ጥር፲፭)።
መቅድሕት ፡ (ሓት) መቅጃ፤ መጥለቂያ፤ የውሃ ዕቃ፤ የፍም መጫሪያ፤ መዛቂያ፤ ማጠኛ ማጤሻ። መቅድሕተ እሳት ይክዑ ላዕሌሆሙ ፡ (ቀሌ መቃ)።
መቅድመ ፡ ቀድሞ፤ አስቀድሞ፤ በፊት። ውእቱ መቅድመ ተቀበረ። ወውእቱ መቅድመ ገብረ በዓለ መጸለት። መቅድመ ፈድፋደ ፡ (ኩፋ ፡ ፬። ፲፮። ቅዳ ፡ ሕር)።
መቅድም ፡ (ብ መቃድም) መዠመሪያ፤ ታላቅ። መቅድመ ቃሉ ለእግዚ። መቅድመ ዕፍረታት ፡ (ዕብ፭ ፡ ፲፪። ማሕ፬ ፡ ፲፬)።
: በቁሙ ፤ የመጽሐፍ መግቢያ ፤ በር ደጅ አፍ ፤ አስቀድሞ የመጽሐፉን ጠባይ
፤ የተጣፈበትን
ምክንያት ገልጦ የሚነግር የሚያስረዳ። መቅድመ ወንጌል።
መቅድመ ጳውሎስ። መቅድመ ጉባኤ። መቅድመ ተኣምር።
መቅጠን ፡ (ብ መቃጥን። ዐረ ሚቅጠን) በቁሙ፤ የዓሣ ወጥመድ፤ ቀጭን ሜንጦ፤ መንጠቆ። ይውሩ መቃጥነ መሥገርተ አንቃር ውስተ ልጐት ወያውፅእ ዓሣ ፡ (ኪዳ። ማቴ፲፯ ፡ ፳፯)።
መቅፁት [1] ፡ ድስት፤–ቀፂው ቀፀወ።
[2] ፡ (ታት፤ መቃፅው) ሸክላ፤ ድስት ምንቸት፤ ማሰሮ፤ የሸክላ የብረት። በአይቴ ይትዐረክ መቅፁት ምስለ ጽህርት። መቅፁተ ብርት ዐቢይ። ብሱል በመቅፁት። ምንባረ መቅፁት ፡ (ሢራ፲፫ ፡ ፪። ዮሴፍ። ዘሌ፪ ፡ ፯። ፲፩ ፡ ፴፭)።
መቅፈል ልት ፡ (ብ መቃፍልት) መለበጫ፤ ልባጥ፤ ሽልማት ጌጥ። ወትገብር መቃፍልቲሃ ለታቦት በወርቅ ጽሩይ
፡ (ክብ ፡ ነገ)።
መቅፈርት ፡ (ዕብ ኤፎድ። ጽር ሄፖሚዳ) ልብሰ ኤፉድ፤ ከአልባሰ ክህነት አንዱ፤ ትንቢት ማወቂያ፤ መጠየቂያ መመርመሪያ። አፈደን ተመልከት። ትብልያ ዘመቅፈርት
፡ (ዘፀ፳፰ ፡ ፬)።
መቋሲ መመቍስ ፡ መመቍስ፤ የሚቈርጥ የሚለይ አጥፊ፤ ዐባይ ዋሾ ቀጣፊ።
መበለ ፡ (ዐበለ፤ ማዕበል) ጌታየ ፥ ሠለጠነ፤ ደፈረ። በሐኵ እንዘ ይሜብል ላዕለ መርዔት። ገብር ጠቢብ ይሜብል አጋዕዝተ አብዳነ። ወብእሲትሰ ትምሀር ኢናበውሕ፤ ኢትመብል ላዕለ ብእሲ ፡ (ምሳ፳፬ ፡ ፷፮። ፲፯ ፡ ፪። ፩ጢሞ ፡ ፪ ፡ ፲፪)።
መበለት [1] ፡ በቁሙ ድኻ ሴት፤–በልቶ በለተ።
- [2]
መበለት ፤ (ታት) ፤ ድኻ ብቸኛ ሴት ፤ ባልቴት ባሏ የሞተባት ፤ በጋማች ሥጋን ከሥጋ እንዲለይ ሞት ከባሏ የለያት የነጠላት። መነኵሲ (ዘፍ፪ ፡
፳፬። ማቴ፲፱ ፡ ፭
፡ ፮)። ኢይከውን መበለተ ወኢይሬኢ ላሐ። ለብሰት አልባሰ መበለታ። ወነበረት መበለተ። መበለት ዕቤር። ወለንኡሳትሰ
መበለታት ተገሐሦን። መነኮሳት ወመበለታት (ራእ፲፰ ፡ ፯። ዘፍ፴፰ ፡ ፲፱። ፪ነገ ፡ ፲፫ ፡ ፳። ፈ ፡ መ ፡ ፭ ፡ ፯። ፩ጢሞ ፡ ፭ ፡ ፲፩። ስንክ ፡ መጋ፳፯)።
መበቅል መስተበቅል ፡ የሚበቀል የሚያስበቅል፤ ተበቃይ አስበቃይ። እግዚ ቀናኢ ወመስተበቅል ፡ (ናሖ፩ ፡ ፪። መዝ ፡ ፺፫። ፩ተሰ ፡ ፬ ፡ ፮። ዲድ ፡ ፬)።
መበይን ፡ (ንት ናን ናት) ዝኒ ከማሁ። ኢነሣኤ ገጽ መበይን ፡ (ዲድ
፡ ፬)።
መባሕት [1] ፡ ሥልጣን መበት፤ ሹመት፤ ትእዛዝ፤ ፈቃድ። ተውህበ ሎቱ መባሕት። በመባሕተ መኑ ትገብር ዘንተ። ወሰአሰ መጽሐፈ መባሕት። ዲያቆን ኢይግበር ምንተኒ ዘእንበለ መባሕተ ኤጲስቆጶስ አቡሁ። እስከ ይረክብ መባሕተ ቃልየ። ይጽሐፍ መባሕተ ፡ (ዳን፯ ፡ ፮። ማቴ፳፩ ፡ ፳፫። ግብ፬ ፡ ፪። ዲድ ፡ ፪። ቀሌ። ሲኖዶ)
[2] ፡ መብት፤–በዊሕ፤ ቦሐ ተበውሐ።
መባእ ፡ (ኣት) በቁሙ፤ መባ እጅ መንሻ፤ በረከት፤ ቍርባን፤ መሥዋዕት። ጸሎተ መባእ። ወርቀ መባእ ዘሣጹን። ኢትበል በብዝኀ መባእየ ይሰሪ ሊተ። አብእ መባአ ለእግዚ ፡ (ቅዳ። ፈ ፡ መ ፡ ፲፮ ፡ ፩። ሢራ ፡ ፯ ፡ ፱። ፲፬ ፡ ፲፩። ማቴ፭ ፡ ፳፬)።
መቤዝዊ ው ፡ ዝኒ ከማሁ። መድኀኒት መቤዝዊተ እሞ ቅድስተ። ወልደከ መድኅነ ወመቤዝወ። መቤዝወ ዓለም ፡ (ድጓ። ስንክ ፡ ታኅ፯። ቅዳ ፡ ሐዋ፤ ኤጲ። ደራሲ)።
መብሕት ፡ ፍጹም ጥሩ፤ እድፍ ጕድፍ እንከን የሌለበት፤ ያልተንካ ድፍን። ምሥዋዕ ዘእብን መብሕት ዘኢተወቅረ ፡ (ኢያ፰ ፡ ፴፫)።
መብልኂ ኅ ፡ (ኂት ኅያን ያት) የሚስል የሚያሾል፤ ሳይ አሿይ።
መብልኅ ት ፡ (ብ መባልኅት) የብረት መሣሪያ፤ ስለትና ሹለት ጥርስ ሌላም ብዙ ዐይነት ያለው። ካራን ቢላዎ ማለት ከዚህ የወጣ ነው። ወእምዝ አዘዞ ንጉሥ ለሃቤ ኀጺን ከመ ይግበር መባልኅተ ኵነኔ ግሩም፤ መላጺያተ ዘእመት፤ ሙቃዓተ መስበረ ርእስ፤ መጥወዬ ክሣድ፤ መኈሠሥ ስነን መውፅኤ ዐይን መስረፈ አንፍ መቅድሐ እዝን፤ ፈታሔ መለያልይ ምፍሓቀ ገበዋት ወመስብረ ብረክ ወመዋቅየ አምትንት ወሥርው ፡ (ስንክ
፡ ጥር፲፭)።
መብልዕ [1] ፡ መብል ምግብ፤–በሊዕ በልዐ።
[2] ፡ (ብ
መባልዕት) ፤ በቁሙ ፤ መብል ፤ ምግብ ሲሳይ ፤
አፍን መንገድ አድርጎ ወደ ሆድ የሚገባ ኹሉ። ለክሙ ውእቱ መብልዕ። ወሀቡ ፍትወቶሙ ለመብልዕ። ግበር መባልዕተ ቅብዕ።
መባልዕት ጥዑማት (ዘፍ፩ ፡ ፳፱። ሰቈ፩ ፡ ፲፩። ኵፋ ፡ ፳፮።
ቀሌ። ፪ዜና ፡ ፱ ፡ ፳፬)።
መብልዕ መባልዕት በማለት ፈንታ ብልዕ ብልዓት ይላል ፤ ፍችው አንድ ነው።
መብሰል ፡ (ላት) ማብሰያ መቀቀያ። መብሰለ ብርት ዘውዑይ ፍልሐቱ። በመብሰለ ብርት ርሱን ፡ (ስንክ ፡ ነሐ፰። ጥበ ፡ ጠቢ)።
መብስል ፡ የበሰለ ምግብ፤ ትኩስ ለስላሳ፤ የላመ የጣመ። ኢይብልዑ መብስላተ አላ ኅብስተ ይቡሰ ወጼወ ወማየ ፡ (ቄድር)።
መብረቅ ፡ (ብ መባርቅት) በቁሙ፤ የእሳት ሰይፍ የእሳት ፍላጻ በዝናም ጊዜ ከደመና አፎት የሚመዘዝ የሚወረወር። ብልኀተ መብረቅ። መብረቅ ወፀዓዕ ወነጐድጓድ። ይረውጽ መብረቅ ቅድመ ነጐድጓድ። ገብረ መባርቅተ ለዝናም ፡ (ቅዳ ፡ ኤጲ። ራእ፬ ፡ ፭። ሢራ፴፭ ፡ ፲። ኤር፲ ፡ ፲፫)።
፡ የክብር ብርሃን፤ ጮራ ምዕዛር። ሰላም ለሥንኪ ዘአዋከየ መብረቃ ለብሔረ ጽልመት ወጣቃ። መብረቅ ለሥጋሁ ከለላ ፡ (ስንክ ፡ መጋ፳። ሚያ፴)።
መብረድ ፡ (ዐረ መብረድ፤ ሞረድ) ማብረጃ፤ ማቀዝቀዣ። መሞረጃ ሞረድ፤ መዶሻ። ልሳኖሙ በሊኅ ከመ መብረደ ኀጺን፤ ሞረድ ፡ (ዜና ፡ እስ)።
መብርሂ ፡ (ሂት ህያን ያት) የሚያበራ አብሪ ገላጭ፤ አስረጅ። ዕንቍ ፈርጥ የልብሰ አሮን ጌጥ። ፀሓይ መብርሂ። መብርሄ ኵሉ። መብርህያት ወማኅተማት ፡ (ደራሲ። አዋል። ዘፀ፳፰
፡ ፳፮)።
መብርህ ፡ (ብ መባርህት) መብራት፤ የፋና የቀንዲል። ሶበ ቦኡ በመባርህት ያጠፍኦ ነፋስ። ፡ (ሥር ፡ አኵ)።
መብዐለ ሜኮኖት ፤ መክደኛ ፤ እንደ ዙሓ ያለ የብረት መግላሊት (፬ነገ ፡ ፲፮ ፡ ፲፯)።
መብዐሊ ዕል ፡ የሚያከብር፤ አክባሪ። መብዐሊት ፡ (አርጋ ፡ ፬)።
መብዐል [1] ፡ (ብ መባዕላት ልት) ዙሓ ጠገራ፤ ምዝምዝ ጥፍጥፍ፤ የወርቅ የብር የንሓስ የብረት የማዕደናት ኹሉ፤ ዛንጅር መንቈር፤ ሰንሰለት እግር ብረት። ወያስተዳልዉ ኵሎ መባዕላተ ሰይጣን
፡ (ሔኖ ፡ ፵)።
[2]
፡ መክደኛ፤–ብዒል ብዕለ።
መብዕል ፡ ምብዓል፤
፡ (ላት) መክበሪያ፤ ገንዘብ ማግኛ፤ የብረት የዕንጨት የደንጊያ መሣሪያ እንደ ወፍጮ ያለ። ኢትትአኀዝ ማሕረጸ ወኢመድሔ፤ እስመ መብዕለ ነፍስ ውእቱ። አዕይንቲሁ ይጤይቅ ኵሎ አምሳለ ምብዓል፤ ወትጋሁኒ ከመ ያስተሣኒ ምብዓሎ ወምንሃቦ ፡ (ዘዳ፳ ፡ ፮። ሢራ
፡ ፴፰ ፡ ፳፰)።
መብእስ [1] ፡ (ስት ሳን ሳት) የሚያብስ፤ የሚያከፋ። ክፋ መንገድ፤ ወጥ ገብ፤ ሸካራ ሰንከልካላ፤ ድንጉር። ይኩን ኵሉ መብእስ መጽያሕተ ርቱዐ። ኮነ ፍናዊሁ መብእሰ። የሐውሩ መብእሰ። መብእስ እበኒሃ ለፍኖተ ኃጥኣን። ሀበኒ ርእሶ ለዮሐንስ ጸያሔ መብእስ ፡ (ኢሳ፵ ፡ ፬። ሱቱ ፡ ዕዝ፭ ፡ ፲፩። ኤር፮ ፡ ፳፰። ሢራ፳፩ ፡ ፲። ድጓ)።
[2] ፡ ወጥ ገብ ድንጕር፤–ብኢስ ብእሰ።
መብዕር ፡ (ብ መባዕር) ዐራሽ ቈፋሪ። የበሬ ዕቃ፤ ማረሻ መቈፈሪ መደንጐሪያ።
መብኵሕ ፡ (ሕት ሓን ሓት) ቅጽልና ጥሬ። የሚያናፋ፤ አናፊ። ማናፊያ ወናፍ።
መብክይ ፡ ዝኒ ከማሁ፤ አልቃሽ፤ ወይም አስለቃሽ። ወበዊኦ ቤተ ርእየ መብክያነ ፡ (ማቴ፬ ፡ ፳፫። መጽ ፡ ምስ)።
መብዝኂ ፡ ዝኒ ከማሁ። መብዝኅያነ ነገር። መብዝኄ ነቢብ። ወንሕነ በኀቤክሙ ከመ መብዝኄ ነገር ፡ (ኪዳ ፡ ገ፬። ፈ ፡ መ ፳፩ ፡ ፫። አፈ ፡ ተ፳፫)።
መብዝኅት ፡ የተከፍሎ ብዛት፤ ላቂያ፤ ብልጫ። ሲነበብና ሲዘረዘር የቅጽል አፈታት ይፈታል። መብዝኅተ መዋዕሊሆሙ። መብዝኅተ ሕዝብ
፡ (ኩፋ ፡ ፳፫ ፡ አርጋ)። የሚበዛው የሚልቀው የሚበልጠው፤ ብዙው ያሰኛል። መብዝኅቶሙ ተነፅኁ በገዳም። ወመብዝኅቶሙ ሀለዉ እስከ ዮም ፡ (፩ቆሮ ፡ ፲ ፡ ፭። ፲፭ ፡ ፮)።
መብዝኅቶ ፡ ብዙዉን፤ ይልቁን፤ ብዙ ጊዜ። መብዝኅቶ ይወድቅ ውስተ እሳት። ወአንተሰ መብዝኅቶ ትትሜሰል ከመ ኃጥእ ፡ (ማቴ፲፯ ፡ ፲፭። ሱቱ ፡ ዕዝ፰ ፡ ፶፯። ጦቢ፩ ፡ ፮)።
መተሬ ፡ አንድ ዐይነት ቅጠል ፥ ፍሬው እንደ ሙስና ኮሶ የሚያመክን።
መተርእስ ፡ የራስጌ ሰይፍ፤–ርኢስ ርእሰ።
መተርእስት ፡ መንተራሻ፤ ማንተራሻ፤ ትራስ፤ ብርኵማ። የራስጌ ሰይፍ፤ ዱላ ሽጕጥ፤ የመሰለው ኹሉ። መተርእስቱ እንተ በዲቤሃ ያሰምክ። መልኀት መተርእስቶ ወዘበጠት ክሣዶ ወመተረት ርእሶ እምኔሁ ፡ (ዮዲ፲፫ ፡ ፮ና ፡ ፰ ፡ ፲፭)።
መተርጕም ፡ (ምት ማን ማት። ዕብ ምታርጌም) የሚተረጕም፤ የሚያስተረጕም፤ ተርጓሚ፤ አስተርጓሚ፤ ሊቅ መፈክር፤ ትርጁማን አምጃር። አባ ሰላማ መተርጕም። ይቤ መተርጕም። ለብዙኃን እመተርጕማን። መተርጕመ አሕላማት። መተርጕመ ልሳኖሙ ፡ (ስንክ ፡ ነሐ፳። ፊልክ። ፍ ፡ ነ ፡ ፶፩። ፲፩። አዋል)።
መተቀ ፡ (መቲቅ። ዕብ ማታቅ) ጣፈጠ ፥ ጥፍጥ ኾነ፤ ማር ማር አለ ፥ ደስ አሰኘ፤ ያታክልት ያገዳ የፍሬ፤ ለወሬም ይኾናል።
መተነ [1] ፡ (ከሠደ። ዐረ መተነ፤ ረዘመ) ተሳበ ተገተረ፤ ጸና ጠነከረ ፥ ዠመተ።
[2] ፡ (ዕብ ማታን ይምቶን) ለዘበ፤ ራሰ ረጠበ።
መተንብል ፡ (ልት ላን ላት) ዝኒ ከማሁ። ልሳን መተንብልት ዘይረክብ ሰብእ መፍቅዶ። ኄራን መተንብላን እለ ይስእለ ምሕረተ ለውሉደ ሰብእ። መተንብላን ለኵሉ ሰብእ። ደንግል ሠናያት ወመተብላት
፡ (ፈላስ። ድጓ። ስንክ። ኅዳ፲፫። መዋሥ)።
መተክዝ ፡ (ዝት ፡ ዛን'ዛት) የሚያሳ ዝን፤ የሚያስተክዝ፤ እስተካዥ።
መቲህ ሆት ፡ (መትሀ ይመትህ፤ ይምታህ። ዐረ መቲሀ) መሳት፤ ማሳት ፥ ምትሀት ማድረግ ማሳየት። እለ ይመትሁ ፡ (አርጋ)። መምታት ፥ መማታት፤ ያለሌ የበትር የቸነፈር። መሣሣት መንፈግ፤ የሆዳም።
መቲር ሮት ፡ (መተረ ይመትር ይምትር። ዕብ ባታር) መምተር፤ መቍረጥ መቈራረጥ መበጠስ፤ መለየት መሻር፤ ጨርሶ ማጥፋት። እመትር ርእሰከ እምኔከ። ወመተራ ዐሠርተ ወክልኤተ ክፍለ። መቲረ ሥርው። ምትራ እምኔከ። ይመትርዎ እመዓርጊሃ ለቤተ ክር። ክልአታት ወመቲሮታት እምነ። መተረ እግዚ እምእስራኤል ርእሰ ወዘነበ ፡ (፩ነገ ፡ ፲፯ ፡ ፵፮። መሳ፲፬ ፡ ፳፱። ሔኖ፯። ሢራ፳፭ ፡ ፳፮። ቀሌ። ፊልክ ፡ ፶፭። ኢሳ፱ ፡ ፲፬)። በቀጥቀጠና በረሰየ ፈንታ መተረ ይላል፤ ስሕተት ነው ፡ (ኢሳ፪ ፡ ፬ ፡ ሚክ፬ ፡ ፫)።
መታሂ ፡ (ሂት ህያን ያት) ስሑት መስሐቲ፤ ምታታም ምታተኛ። ተማች አጥቂ፤ አለሌ ዱለኛ። ሥሡ ንፉግ፤ ሆዳም በላተኛ። ኢትደረር ምስለ ብእሲ መታሂ
፡ (ምሳ፳፫ ፡ ፮)።
መታሪ ፡ (ሪት ርያን ያት፤ ተርት) በቁሙ፤ የሚመትር፤ ቈራጭ ፥ በጣሽ። ሰይፍ መታሪ። መታርያነ ሥርዋት ፡ (ጥበ፭ ፡ ፳፩። አቡሻ ፡ ፶። ሔኖ፰ ፡ ፫። ፳፩ ፡ ፯)።
መታግር [1] ፡ ገመድ አውታር፤–ተጊር ተገረ።
[2] ፡ መታግር፤ ምሰሶዎች፤ ወጋግራ ባላ፤ ዋልታ ሠረገላ። ለኅዋኅዊሃ ወለመሳክዊሃ ወለመታግሪሃ ወለአዕማድኒ ፡ (ገድ ፡ ተክ)።
መታግርት ፡ (ዕብ ፍቃዒም) ስንበሮች፤ ቅርጾች የታነጡ የተነጠጡ፤ ያበጡ የሰመጡ፤ ፈቅዐን ተመልከት። ወመታግርተ ገብረ ላቲ ፡ (፫ነገ ፡ ፯ ፡ ፳፬)።
መትህ ፡ (ሃት) ምትሀት፤ ምትሀትነት፤ ሳይኾኑ መስሎ መታየት። እስመ መልአክ ዘበመትህ ፡ (ሐኪም መስሎ) ሠጠጠ ከርሦ ለፈላሲ ወአርአዮ ሕማመ ልቡ፤ ወአግብኦ በከመ ሀሎ። ተርእዩ ሎሙ ሰይጣናት ዘበመትህ መንክር ፡ (ምድርን እንደ ሰፌድ እያነቀረቀቡ)። ፈቃድ ዘይወልድ መትሀ
፡ (ፊልክ ፡ ፳፭ና ፡ ፳፱። ማር ፡ ይሥ፲፱ ፡ ፪)።
መትሕተ ታሕቲት ፡ የታች ታች፤ መጨረሻ ታች፤ እንጦርጦስ ፡ (ቀሌ)።
መትሕታዊ ፡ ታሕታዊ፤ ዘታሕት፤ ታችና የታች። ልዑላዊ ወመትሕታዊ ፡ (ፊልክ ፡ ፻፸፭)።
መትሕት ፡ (ጥሬና ቅጽል) ታሕት፤ ትሑት። ታች፤ ጕድጓድ፤ ሸለቆ፤ ጥልቅ ዕሙቅ ሲኦል ገሃነም። በመትሕተ ምድር። ውስተ መትሕተ እሳት። ነበረ ውስተ መካን ልዑል ወዮሐናኒ ወእሊኣሁ ውስተ መካን መትሕት። ባሕር መትሕት
፡ (መዝ ፡ ፻፴፰። ሔኖ፲ ፡ ፲፫። ዮሴፍ)።
መትለው ልው ትሎ ፡ (ብ መታልው) ኋላ መጨረሻ፤ ቀጥሎ፤ ተከትሎ፤ ወዲያው። ዘበመትልወ በዓለ እግዚእከ ኮነ በዓልከ። መትልወ ሐጋይ። ወመትሎሁ ይበል። ለዝ መዋኢ እንዘ ይኔጽር አክሊሎ፤ በዕለተ ፈለሰ አዕረ መትሎ ፡ (መዋሥ፤ ድጓ። አዋል። ኪዳ። ስንክ ፡ ሐም፲፯)።
፡ ተራ፤ ረድፍ፤ ማዕርግ፤ ተከታታይነት ያለው። በበ መትልው። ሥዩማን በበ መትሎሆሙ። ሰላም ለአብርሃም ወለይሥሐቅ በመትሎ፤ ወለሣልሳይ ያዕቆብ። ስምዐነ አምላክነ ወሰላመከ ሀበነ እስመ ወሀብከነ ኵሎ፤ ስብሐተ ዚኣከ ንንግር እምትካት ዘሀሎ፤ በበ መዓርገ ወበበ መትሎ
፡ (ሉቃ፩ ፡ ፫። ሲኖዶ። ስንክ
፡ ሚያ፳፰። ደራሲ)።
መትር ፡ (ብ አምታር) የልክ ስም፤ ኹለቱን ክንድ አንድ የሚያደርግ በትር ወይም ዘንግ፤ በተረን እይ። ማተረ ማለት ከዚህ ወጥቷል፤ ሻ ፈለገ ጐበኘ ቈጠረ ገመተ ማለት ነው።
መትርፍ ፡ የሚያተርፍ፤ አትራፊ አስቀሪ። ይከውኑ መትርፋነ ውሉዶሙ
፡ (ኩፋ ፡ ፲፭)።
መትን ፡ (ብ አምትንት) ዥማት ፥ ክሥዳ። ከብዙ በቀር ባንድ አይገኝም። የአስር በአሥራው ወያጸንዕ በአምትንት። ነፍስ እስርት በሥጋ፤ ወሙቅሕት በዐፅም ወአምትንት ወአሥራው ፡ (ቅዳ ፡ ግሩ። ዮሴፍ)።
መትከል [1] ፡ ኵላብ፤–ተኪል ተከለ።
[2] ፡ (ብ ፡ መታክል) መትከያ ማስተከያ። ካስማ፤ ችካል፤ ኵላብ
፡ መንዞረር ፣ የዕቃ
፡ መስቀያ : የሰንጨት ፣ የብረት ፣ ምስማር። }ሥት : መ ትክለ። መትከል
፡ በዘይሰቅሉ
፡ ቦቱ ፡ ኵሎ ፡ ንዋየ። መታጠል
፡ ወወታግር
፡ (መሳ፬
፡ ፳፩። ሕዝ፲፰ ' ፫። ዘኍ፫ ፲ ፯) " በመትከል ፡ ፈንታ ፡ መትከልት ፡ መታ ክልት ፡ ይላል ፡ በሴት ፡ እንቀጽ፤ፍችው እንድ ፡ ነው።
መትከፍ ፡ ትከሻ ጫንቃ፤–ተከፈ።
መትከፍ ት ፡ (ብ መታክፍ ት። ዕብ ካቴፍ። ሱር ካትፋ። ዐረ ኪትፍ) ጫንቃ፤ የጡንቻ ራስ፤ የእጅ መብቀያ፤ የደንደስ ጫፍ፤ ያንገት የማዥራት ግራና ቀኝ። ማዥራትም ከመትከፍ ጋራ ጫንቃ ይባላል፤ ሐዳፍን ተመልከት። ሰላም ለመትከፍትከ ከመ ልብሰ ክህነት ሎግዮ ጊዜ ፀአተ ፍትሕ ዘጾረ አርዑተ መስቀል በቀራንዮ። ይጸውርዎን በመትከፍት። አትሕት መታክፍቲከ ወተሰከማ። ወሀባ ለአጋር ወአንበረ ዲበ መትከፍታ። ይጼዐን በመታክፉ ፡ (ደራሲ። ኢሳ፵፱ ፡ ፳፪። ሢራ፮ ፡ ፳፭። ዘፍ፳፩ ፡ ፲፬። ስንክ
፡ ሐም፳፮)።
መትገር ት ፡ (ብ መታግር ት) ወተር፤ አውታር፤ የድንኳን ገመድ። መታክሊሆን ወመታግሪሆን ፡ (ዘኍ፫ ፡ ፴፯። ፬ ፡ ፴፪)።
መነ መነሃ ፡ መነ፤ መነሃ፤ ማን፤ ማነን። መነ እፌኑ። መነ ትብል ርእስከ። መነሃ ትሳተፉ በቅድሳት ፡ (ኢሳ፮ ፡ ፰። ዮሐ፩ ፡ ፳፪። ኪዳ)።
መነሳንስት ፡ (ሳት) በቁሙ ፥ መነሳንስ፤ መራውሕ ፥ የሐር ፈትል እንደ ጭራ ኹኖ የተሠራ የተቈነነ ባለወርቅ እጀታ። በዛቲ ዕለት አዕረፈ አባ ኖብ በዓለ መነሳንስቲሁ ዘወርቅ፤ ሰላም ለኖብ መሳንስቲሁ ዘወርቅ፤ ሰዳዴ አራዊት ደቃቅ። ይትቀነዩ ሎቱ ከመ ነጋሢ፤ ወመነሳንሳተኒ ዘሐሪር ገብሩ ሎቱ ፡ (ስንክ ፡ የካ፭። ገድ ፡ ኪሮ)።
መነተ ፡ (ይመንት ይምንት፤ ጥያቄ) ምን ኾነ ፥ ምን ተባለ፤ ምን አ(ተ) ደረገ።
መነን ፡ (ዐማርኛ) የሴት ልጅ ስም፤ ቀጭን ፈታይ ፥ ባለሟያ፤ ወይም መልከ መልካም ትክክል ፍጽምት ፥ ሕጸድ የሌለባት ማለት ነው፤ እግዝእትን እይ
፡ (ገዝአ ፡ አግዝአ)።
መነኮሳዊ ዪ ይ ፡ (፤ ፡ (ውያን ይያን) የመነኵሴ ወገን፤ የገዳም ሰው ፥ ገና ቆብ ያልጫነ ረድ አመካሪ፤ አናኮ ደጐባ ፥ ወይም ቆብ የጫነ ተራ መነኵሴ፤ ብቻውን የሚኖር ባተሌ ፥ ድንግል።
መነኮሳዊት ፡ (ዪት ውያት ይያት) መነኮሳት፤ መነኵሲት የሴት መናኝ፤ መበለት ባሕታዊት ፡ (ፈ ፡ መ ፡ ፮ ፡ ፱። ቄድር። ገ፷፪)። በእንተ መነኮሳይያት ወመበለታት። እልፍ ባሕታውያን ወክልኤቱ እልፍ መነኮሳይያት ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፲። ፊልክ ፡ ፴፮።
መነኮስ ፡ (ስት ሳን ሳት። ጽር ሞናኾስ። ትግ ሐባ ሙንኩስ፤ ነዳይ) መነኵሴ መናኝ፤ ድኻ ለማኝ፤ ከዓለም ከዘመድ ከሕዝብ ከገንዘብ የተለየ። መጻሕፍትና መምራን ግን ወንድና ሴቱን አይለዩትም። መነኮስ ባሕታዊ። መነኮሳት ገዳማውያን። መነኮሳተ ምኔት። ወኮነት መነኮሰ ፡ (ስንክ ፡ መስ፲፫ ፡ ፲፰። ፍ ፡ ነ ፡ ፲። አዋል)።
መነየ ፡ (ይመኒ ይምኒ መንይ። ዕብ ማናዕ። ዐረ መነዐ) ለየ ከለለ ወሰነ፤ ዐጠረ ቀጠረ፤ ዙሪያዉን ዘጋ ከለከለ፤ የገዳም የቤተ ክሲያን።
መነጽር ፡ (ርት ራን ራት) ዝኒ ከማሁ፤ ነጻሪ። በቁሙ፤ ማያ መመልከቻ የዐይን ቤዛ ፥ ብርሃኑን ብሌኑን የሚጠብቅ ፥ አጐልቶ የሚያሳይ ታናሹ፤ ወይም ታላቁ አርስጣላብ።
መኑ ፡ (ሱር ማኑ። ዐረ ሚን፤ መን) መ ኑ፤ መ ፥ ማ ማን፤ ኑ ፥ ነው፤ በተገናኝ ማነው። በጥያቄነት ላይ ስምና አንቀጽ ኹኖ አካልን ሌላውንም ግብር ያሳያል፤ መና ሚ ፩ ወገን ኹነው ከኑ ጋራ ገጥመዋል፤ የሦስቱንም ፍች በየቦታው እይ። አንዳንድ መምህራን መጥበቁን ሲያዩ ደጊመ ቃል ያለበት መስሏቸው የመነነ ዘር ነው ይላሉ። መኑ የዐቢ መንግሥተ ሰማያትኑ ወሚመ ገነት። መኑ ወመኑ አንትሙ። መኑ ስሙ ወመኑ ስመ አቡሁ ፡ (ቀሌ። ዘፀ፲
፡ ፰። ቅዳ ፡ አፈ)። መኑና ምንት በወንድና በሴት ሲለዩ መኑ የወንድ ምንት የሴት ይኾናል። ሲበዙና ሲዘረዘሩም መኑ ምኖት ፥ ምኑ ምኖቱ፤ ምንት ምንታት ፥ ምንቱ ምንታቲሁ ያሰኛሉ። መጻሕፍትና መምህራን ግን ለይተው አብዝተው በርባታ አልጠነቀቁትም።
መኒን ኖት ፡ (መነ፤ መነነ ይመንን ይምንን) ማነስ መጕደል፤ መቅጠን መመንመን መናኛ ሞኝ መኾን፤ የትምርት የውቀት የገላ የናላ። ቅጥነት ለፈትልም ይኾናል፤ መነን ድር እንዲሉ።
መና ፡ (ጽር ማና። ዕብ ማን) በቁሙ፤ መኖ ምግብ ፥ ሰማያዊ ቀለብ፤ እግዜር ለእስራኤል ፵ ዘመን ምሉ ዕለት ዕለት ከሰማይ ጐተራው እያወጣ በሙሴ በመጋቢው እጅ እንደ ገዳም ንፍሮ ይሰፍረውና ይቈንነው ያድለው የነበር የድንብላል ዐይነት ፡ (ዘፀ፲፮ ፡ ፲፭ ፡ ፴፩። መዝ ፡ ፸፯)። ሙጫ ፥ እን ዶሮ ማር ያለ፤ በሲና በረሓ ከሚበቅሉ ዕንጨቶች የሚገኝ። የኹለቱም ፍች ሚ ምንት ማለት ነው፤ እንግድነቱን ፥ ሐዲስ ምግብነቱን ፥ በሌላ ቦታ አለመገኘቱን ያሳያል።
መናረት [1] ፡ ማብሪያ፤–ነዊር ኖረ ነወረ።
[2] ፡ መናረት፤ ፡ (ዐረ። ሱር ምናርታ። ዕብ ምኖራ) ምንዋር፤ ማብሪያ መቅረዝ፤ የፋና የቀንዲል ማኖሪያ የሚሰቀል ፥ ወይም የሚተከል፤ ተቅዋም። ወገብረ መናረተ
፡ (ዘፀ፴፰ ፡ ፲፫። ፵ ፡ ፬ ፡ ፳፪)። ዳግመኛም ፥ በመናረት ፈንታ አዛውሮ መራናት ይላል፤ የተሳሳተ ነው። ወዲበ መራናት አኅትዉ ፡ (ዘሌ፳፬ ፡ ፬። ዘኍ፫ ፡ ፴፩። ፰ ፡ ፪–፬። ዕብ፱ ፡ ፪። ድጓ)።
መናኒ ፡ (ኒት ንያን ያት) በቁሙ፤ የሚንቅ ናቂ መናኝ። መናኒተ ዓለም። መናኔ ዓለም። ልብሰ መናንያን ፡ (ስንክ ፡ ኅዳ፲፯ ፡ ፲፱። ፍ ፡ ነ ፲ ፡ ፮)።
መናዝል ፡ (ዕብ ምዚሎት፤ ማዛሮት) ያ፲፪ቱ ወር ኮከቦች፤ ከእልሐመል እስከ ሑት ያሉ ፥ በእንስሳት ስም የሚጠሩ መገብተ አውራኅ። ሐሳበ መናዝል፤ ስም ወስመ እም ፡ (የጥንቈላ መጣፍ)።
መናዝዝ ፡ (ዝዝት፤ ዝዚት ዛን ዛት) ዝኒ ከማሁ። መናህይ ወመናዝዝ። መናዝዛን ለእኪት። መናዝዚት ፡ (ግንዘ። ኢዮ፲፮ ፡ ፪። አርጋ)።
መናፍስት አው መንፈሳት ፡ ነፍሳት ፥ ነፋሳት፤ መላእክት ፥ ሰይጣናት። እግዚአ መናፍስት። መንፈሳቲሆሙ ለእለ ሞቱ። መናፍስት ንጹሓት ለባውያት ወቀጢናት። መናፍስት ርኩሳን ፡ (ሔኖ። ጥበ፯ ፡ ፳፫። ማቴ፲ ፡ ፩)።
መናፍቅ ፡ (ቅት ቃን ቃት) ናፋቂ ፥ አናፋቂ፤ የሚጠራጠር ፥ የሚያጠራጥር፤ ጠርጣሪ አጠራጣሪ፤ ሃይማኖቱ ሕጹጽ የኾነ ፥ ምሉእና ፍጹም ትክክል ያይዶለ፤ መንፈቁን አምኖ መንፈቁን የሚክድ። ዕልዋን ወመናፍቃን። በእንተ ዘይበውእ ውስተ ሕግነ እመናፍቃን
፡ (ቀሌ። ሲኖዶ)።
መንሀዪ ፡ (መንህይ፤ መናህይ) የሚያሳርፍ፤ አሳራፊ ፥ ዕረፍት ሰጪ ፥ አይዞኽ ባይ ፥ አጸናኝ አስተዛዛኝ። መንሂት ለስራሕየ። መናህየ ወመናዝዘ ለሰብኦሙ ከዊነከ፤ መንፈሰ ናዛዜ ወመናህየ ለሰብኦሙ ፈኑ
፡ (አርጋ ፡ ፬። ግንዘ)።
መንሰወ ፡ (ነሰወ) ፈተነ መረመረ፤ አስጨነቀ ጐዳ አጠፋ። መጽሐፍ ግን በመንሰወ ፈንታ አመንሰወ ይላል፤ አያሰኝም። ይመክሩ በቍጽር ያመንስዉኒ። መንሱተ ከመ ያመንስዎ ፡ (መዝ ፡ ፴፬። ፪ዜና ፡ ፮ ፡ ፳፪)።
መንሰክ ፡ (ብ መናስክ) መንከሻ፤ መንጋጋ ክራንቻ ጥርስ።
መንሠግ ፡ (ብ መናሥግት) መሰነጊያ ስናግ፤ መወርወሪያ ፥ መቈለፊያ ፥ ቍልፍ። እደ መንሠግ። ወመንሠግ ዘማእከለ ዐምድ። እመ ወደይከ ማዕጾ ወመንሠገ ላዕለ አፉከ። አቀመ ኆኅተ ወገብረ መናሥግተ። መዓጹት ወመናሥግት ፡ (ማሕ፭ ፡ ፭። ዘፀ፳፮ ፡ ፳፰። ሢራ፳፰ ፡ ፳፭። ፵፱ ፡ ፲፫። ኢዮ፴፰ ፡ ፲)።
፡ በር ደጃፍ፤ መዝጊያ ፥ ማኅተም። ይሞቅሐከ ወይወስደከ ውስተ መንሠገ ሲኦል። ዘድንግል መናሥግተ ኢያርኂዎ ፡ (ቀሌ። ድጓ)።
መንሱት [1] ፡ ፈተና፤–ነሲው ነሰወ።
[2] ፡ መንሱት፤ ፡ (ብ መናስው። ዕብ ኒሳዮን) ታላቅ ፈተና፤ ፍጹም መከራ፤ ያልታሰበ አደጋ። ኢታብአነ ውስተ መንሱት። ጸልዩ ከመ ኢትባኡ ውስተ መንሱት። መንሱት በባሕር ወበየብስ። ወተዐገሡ መናስወ ሰይጣናዊተ። መናስወ ዓለም ፡ (ማቴ፮ ፡ ፲፪። ፳፮ ፡ ፵፩። ዮሴፍ። ፊልክ ፡ ፫። አርጋ)። ዕቅፍት መሥገርት በማለት ፈንታ መንሱት ይላል
፡ (ማቴ፲፰ ፡ ፯)።
መንሶስው ፡ (ውት ሱት፤ ዋን ዋት) የሚያመላልስ፤ የሚመላለስ፤ አመላላሽ፤ ተመላላሽ።
መንቀልቅል ፡ (ልት ላን ላት) የሚያናውጥ፤ አናዋጭ ጐስጓሽ አነሣሽ። ሥነ ራእየ አንስት መንቀልቅልት ለፍትወት ፡ (ፊልክ ፡ ፻፮)።
መንቈር ፡ (ዕብ ማቆር) የአዕዋፍ ኵንቢ፤ ያፋቸው መጐጥ በጥርስና በከንፈር ቦታ የበቀለው መውጊያቸውና ማንቈሪያቸው መጠቅጠቂያቸው፤ እንደ ጥፍርና እንደ ማጕርጥ የሰላ የሾለ ያሾተለ። በቁሙ ፥ የሽፍታ ቀንበር ረዥም ባላ፤ ዐንገቱን እንደ ወይፈን ጠምደው በሥሩ ይዘው እየገፉና እያዳፉ የሚያመጡበት።
መንቅዕት ፡ (ብ መናቅዕ ት) ነቅ፤ ሥንጥቅ ፥ ንቃቃት። በመንቅዕተ ደብር
፡ (መቃ ፡ ገ፳፭)።
፡ ማውድ ዳሌ የወገብና የጭን መጋጠሚያ ወይም መለያያ። ሰይፉ ዲበ መንቅዕቱ። ንብረተ መናቅዕትኪ ፡ (ማሕ፫ ፡ ፰። ፯ ፡ ፪)። ባለብሉዮች ግን መታጠቂያ መቀነቻ ወገብ ብብት ላት ይሉታል። ፪ኛም በቍየጽ ፈንታ መናቅዕ ይላል፤ አያሰኝም። እምሐቌ እስከ መናቅዕ። ሥብሕ ዘዲበ መናቅዕ ወከብድ ፡ (ዘፀ፳፰ ፡ ፴፰። ኩፋ
፡ ፳፩)።
፡ ተቃዋሚ፤ ተቃራኒ ፥ ተፃራሪ። መናቅዕቲሃ ለእኪት ሠናይት፤ ወመናቅዕቲሁ ለሞት ሕይወት፤ ከማሁ መናቅዕቲሃ ለጽድቅ ኀጢአት
፡ (ሢራ፴፮ ፡ ፲፬)። መንቅዕታ በማለት ፈንታ ያንዱን በብዙ መናቅዕቲሃ ማለት የመላሽና የጣፊ ስሕተት ነው።
መንበሐብሕ አው ምንባሐብሕ ፡ (ሓት) የሚንቧቧ የገደል ውሃ ሿሿቴ ፏፏቴ፤ ጐርፍ ማዕበል፤ ተወርውሮ ከደንጊያ ላይ ሲያርፍ ፥ ወይም ርስ በርሱ ሲዋጋ ሲሳለፍ ፥ ሲጋጭ ሲተላለፍ ብዙ የሚጮኽ ከሩቅ የሚሰማ። ድምፀ ምንባሐብሓተ ማይ ዘየሐውር በኀይል። ውሒዝ ዐቢይ ዘይወርድ በኀይል እምውስተ ምንባሐብሓት። ጰራቅሊጦስ መንበሐብሓተ ጥምቀትነ። ክርስቶስ አምላኪየ ወተስፋየ፤ ወዕፀ መስቀሉ በትረ ሃይማኖትየ፤ ወርግዘተ ገቦሁ መንበሐብሓተ ጥምቀትየ ፡ (ጥበ፲፯ ፡ ፲፯። ኢሳ፲፯ ፡ ፲፫። መጽ ፡ ምስ)።
መንበር ፡ (ብ መናብርት) በቁሙ፤ ወንበር ግርንቡድ፤ መኖሪያ ፥ ማረፊያ መቀመጫ፤ ዙፋን አትሮንስ፤ ድንክ አረፍት መደብ፤ ለመቀመጫ የተለየ ከፍ ያለ ቦታ። ወናሁ መንበር ውስተ ሰማይ። ወበዐውዱ ለውእቱ መንበር ዕሥራ ወአርባዕቱ መናብርት። መናብርተ ቤተ ዳዊት። መንበረ ቀሳውስት
፡ (ራእ፬ ፡ ፪ ፡ ፬። መዝ ፡ ፻፳፩። ሲኖዶ)።
፡ ስመ ነገድ ፥ መልአክ፤ የኪሩብ ወገን ኪሩብ ጸዋሬ መንበር። መናብርት ወኀይላት ፡ (ቅዳ ፡ ባስ)።
መንበርት ፡ (ታት) ንብረት፤ አናዎር ኑሮ። እምነግህ እስከ ሠርክ ትትዐሎ መንበርት ፡ (ሢራ፲፰ ፡ ፳፮)።
፡ ዕድሜ ፥ ዘመን መዋዕል። እመኒ ኖኀ መንበርቶሙ ፡ (ጥበ፫ ፡ ፲፯)።
፡ ጥሪት ገንዘብ፤ ምግብ ፡ (ሉቃ፰ ፡ ፲፬። ፩ዮሐ ፡ ፪ ፡ ፲፮። ፫ ፡ ፲፯። ማር፲፪ ፡ ፵፬። ዲድ ፡ ፲፬)። ተሀየያ ለመንበርትከ ሥጋዊት ወአስተሐምም ለመንበርትከ መንፈሳዊት ፡ (ፊልክ ፡ ፸፮)።
መንተሌ ሊ ፡ (ሊት) ጥንቸል፤ የጥንቸል ወገን። ፈልፈል ወመንተሌ። መንተሊት ተቃሐወት ምስለ ምድር እንዘ ትብል፤ እበጽሕ ኀበ ኢሀሎኪ አንቲ
፡ (ፍካሬ ፡ እየ። ገድ ፡ ፊል ፡ ገ፪፻፵፫)።
መንተወ ፡ (ተቀ ግ፤ ምላሽ) መነታ፤ መንታ ኾነ፤ መንታ ወለደ። ኢመንተወ በግጻዌ ወኢተወሰከ በህላዌ። ኵሎን እለ ይመነትዋ ፡ (መጽ ፡ ምስ። ማሕ፬ ፡ ፪። ፮ ፡ ፮)። አንዳንድ መጣፍ በመንተወ ፈንታ ተመንተወ ይላል፤ ስሕተት ነው።
መንታ ፡ (ብ መናትው) በቁሙ፤ ኹለት ፥ ጥንድ ፥ ዘውግ፤ የተካከለ የተመሳሰለ። መንታ ሀለወ ውስተ ከርሣ። ከመ ክልኤ ዕጕለ መንታ ዘወይጠል። እንተ ወለደት መንታ። ወለደ እምርብቃ ክልኤ ደቂቀ መናትወ
፡ (ዘፍ፴፰ ፡ ፳፯። ማሕ፬ ፡ ፭። ፍ ፡ ነ ፡ ፵፩ ፡ ፫። መጽ ፡ ምስ)።
መንኖ ኖት ፡ (መነነ ይሜንን ይመንን) መመነን፤ መናቅ መጥላት፤ ማኰሰስ ማርከስ፤ መንቀፍ ማጸየፍ፤ መካድ መጣል ፥ ከሕጹጽነቱ የተነሣ። ሕጹጽነት ለመናኙም ለተመናኙም ይኾናል። ዔሳው መነነ ቀዲሙ ተወልዶ። ይሜንን እኩየ፤ ወየኀሪ ሠናየ። መንኖ መነንከነ። እግዚ መነኖሙ ፡ (ኩፋ
፡ ፳፬። ኢሳ፯ ፡ ፲፭። ሰቈ፭ ፡ ፳፪። ኤር፮ ፡ ፴)። መስፈር መቍጠር መመዘን፤ ሰቅሉን ምናን ፥ ምናኑን መክሊት ማድረግ፤ የገንዘብ። ማኒን ተመልከት፤ ከዚህ ጋራ አንድ ነው።
መንእስ ፡ (ስት ሳን ሳት) ያነሰ ታናሽ፤ አንስተኛ ፥ ሕጹጽ። አነ ጴጥሮስ መንእስ በሥጋ ወዐዚዝ በመንፈስ። ደቂቅክሙ መንእሳን ፡ (ቀሌ። ክብ ፡ ነገ)።
መንከስ [1] ፡ መንከሻ ጥርስ፤–ነከሰ።
[2] ፡
መንከሻ፤ የፊት ጥርስ ክራንቻ መንጋጋ። ዐፅመ መንከስ ፡ (መሳ፲፭ ፡ ፲፬–፲፯)። ተዐቀቡ እምልሳናቲክሙ፤ እስመ ተቃትሎቱ ለብእሲ ማእከለ መንከሱ ውእቱ ፡ (ፈላስ ፡ ገ፴፩)። ነሰከን እይ፤ ሱርስቱ ንካስ ያለውን ዕብራይስጡ ናሻኽ ይላል፤ ግእዝ ግን እንደ ፪ቱም ነከሰ ነሰከ ይላል።
መንካ [1] ፡ በቁሙ፤–ነክይ ነከየ።
[2] ፡ (ካት) በቁሙ፤ ማንካ የመብል የመጠጥ መሣሪያ ዕርፈ መስቀል። ወረስያ ኅሪተ ወንጽሕተ ለዛቲ መንካ ፡ (ሥር ፡ ቅዳ)።
መንክራዊ ፡ (ዊት) ታምራታም ፥ ባለታምራት፤ አስደናቂ። ጎርጎርዮስ መንክራዊ። ቅድስተ ቅዱሳን ኮነት መንክራዊተ። ዕንቍ መንክራዊ ፡ (ፊልክ ፡ ፪፻፴፬። አፈ ፡ ድ፴፪። አዋል)።
መንክር ፡ (ርት ራን ራት) ድንቅ ፥ ታምር፤ ልውጥ ነገር፤ የሚደንቅ የሚያስደንቅ መደነቂያ። ገበርከ መንክረ ግብረ። ናሁ እግዚ ይገብር መንክረ። መንክርት ልደት። ጎርጎርዮስ ገባሬ መንክራት ፡ (ኢሳ፳፭ ፡ ፩። ፷፪ ፡ ፲፩። መጽ ፡ ምስ። ስንክ ፡ ኅዳ፳፩)።
መንኰሰ ፡ (ትግ ሐባ መንከሰ፤ ነድየ) መነኰሰ፤ አስኬማ ለበሰ ፥ ቃል ኪዳን ገባ፤ ደኸየ ፥ ድኻ ኾነ። ብዉሕ ሎሙ ይመነኵሱ። ይመንኵስ በፈቃደ ርእሱ። ለእመ መንኰሱ ክልኤሆሙ። ይሑር ውስተ ገዳም ወይመንኩስ ፡ (ፈ ፡ መ ፡ ፭ ፡ ፪። ፲፪ ፡ ፬ ፡ ፭። ስንክ ፡ መስ፲፬)።
መንኰራኵር ፡ (ራት) በቁሙ፤ ሠረገላ፤ የሠረገላ እግር ተሽከርካሪው። ቃለ መንኰራኵር። በሠረገላ ወመንኰራኵር። መንኰራኵረ ሠረገላቲሆሙ
፡ (ናሖ፫ ፡ ፪። ሕዝ፳፫ ፡ ፳፬። ኢሳ፭ ፡ ፳፰)። ስሙ ፩ ሲኾን ዐይነቱና ክፍሉ ብዙ ነው፤ ያውድማና የሰልፍ የሥቃይ አለ፤ ያውድማዉን በኬደ ተራ እይ። አስይፍተ መንገን በሊኃት ዘመንኰራኵር። ሰብዐቱ ምእት ወሰማንያ መንኰራኵራት፤ የሰልፍ ፡ (ስንክ ፡ መስ፭። ታሪ ፡ አኵ)። ወእምዝ አምጽአ መኰንን መንኰራኵራተ ዘብርት ወአኬድዎ ለቅዱስ። ወደይዎ ውስተ መንኰራኵራት ዘርቡብ ታሕቴሆን አፍሓመ እሳት። አዘዘ ከመ ይስቅልዎ ውስተ መንኰራኵር ወይኰንንዎ ፡ (ስንክ ፡ የካ፲፫። ታኅ፲፪። ጥር፩)።
፡ መንገድ ጐዳና ቀጥ ያለ የተካከለ፤ ሠረገላ የሚኼድበት። ታረትዕ መንኰራኵረ ሠናይተ። መንኰራኵረ ርትዕ። ወግበሩ መንኰራኵረ ርቱዐ ለእገሪክሙ ፡ (ምሳ፪ ፡ ፱። ፬ ፡ ፲፩። ፬ ፡ ፲፪። ዕብ፲፪ ፡ ፲፫)።
መንኮብ ፡ አውራ ጣት፤–ነኪብ ነከበ።
መንኮብ መንኮብያ ፡ (ያት) ዐጽቅ ክንፍ፤ እጅና እግር፤ አውራ ጣት ፡ (ኵንቢ)። አሰረቶ መንኮብያቲሁ። ዘይበትክ ማእሰረ ኀጢአት መንኮብያቲሁ ተአስረ። እገሪሁ ጸፋሕት፤ መንኮብያቲሁ ጽንጵዋት። ዕተብ ገጸከ በዘይተልዎ ለመንኮብያ። መንኮብያቲሁ ጠበወ
፡ (ሉቃ፪ ፡ ፯ ፡ ፲፪። ቄር። ኪዳ። ሲኖዶ። ደራሲ)።
መንኮክት [1] ፡ እንዝርት፤–ኮክዎ ኮከወ።
[2] ፡ (ብ መናኩክት) እንዝርት፤ የመንኰራኵር ብረት ተጋዳሚው። ከመ መንኮክት እንተ ተዐውድ
፡ (ሢ፴፮ ፡ ፭)።
መንዘህልል መንዛህልል ፡ ዝኒ ዓዲ ከማሁ። ወልድ መንዘህልል ዘይዘብጥ ወላድያኒሁ ወይፀርፎሙ። ህዩይ ወመንዘህልል። በእንተ ሀካያን ወመንዛህልላን። ውስተ ቤተ ሐኖት ዘውእቱ ቤተ ዘማውያን ወመንዛህልላን። ኢይሑር ኀበ መካናት ዘይትጋብኡ ውስቴቶን መንዛህልላን ወእለ ይሰክቡ ተባዕተ ወአብዛኅያነ ሠሐቅ ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፵፪ ፡ ፲፫። ፊልክ
፡ ፻፴፫። አፈ ፡ ድ፫። ፈ ፡ መ ፡ ፴፪ ፡ ፩። ፴፬ ፡ ፪)።
መንዘለ ፡ ከበደ መነዘለ፤ ደፋ ወደ ታች አለ፤ የሚዛን ፡ (ዐማርኛ)።
መንዘረ ፡ (ዘረወ) መነዘረ ፥ በተነ፤ ለወጠ ፥ ሸረፈ፤ ወርቅን ለብር ብርን ላሞሌ ለመሐልቅ።
መንዘዘ ፡ መነቸከ፤ ችክ ምንችክ አለ፤ መንቻካ ኾነ።
መንዚር ፡ (ራን። ዕብ ማምዜር። ሱር ማምዚራ) ማንዘራሽ ፥ ዲቃላ፤ ያመንዝራ ልጅ አመንዝራ፤ ሴሰኛ ቅንዝረኛ። ሑር ዲቤሆሙ ለመንዚራን ወለምኑናን ወዲበ ውሉደ ዘማ ፡ (ሔኖ፲ ፡ ፱)።
መንዝ ፡ ስመ ሀገር፤ የሺዋ ክፍል። መኑ ዝ ማለት ነው። መንዜ፤ መን ዚ ፡ (ትግሪኛ)። ፪ኛም መንዝህ መንዝሃዊ ብሎ በነዝሀ ዘይቤ ሲፈቱት ከምንዛህ ጋራ ይሰማማልና፤ ነዝሀን እይ።
መንዝር ፡ አመንዝራ፤–ነዚር ነዘረ።
መንዝዝ ፡ የሚያነዝዝ፤ ንዛዥ ትንታ። ነዝናዛ ችኮ ፥ መንቻካ።
መንዮ ዮት ፡ ፣ ፡ (መነየ ይሜኒ ይመኒ) መመኘት ምኞት ማድረግ፤ መሻት መፈለግ። መጽሐፍ ግን በመነየ ፈንታ ተመነየ ይላል፤ አድራጊውን በተደራጊ፤ አያሰኝም።
መንደለ ፡ (ዲቃ ግ) መነደለ፤ ዐጠበ አጠራ ወለወለ ፥ አደረቀ፤ የወጭት የገላ።
መንደል ፡ መንደያ፤ መብሻ መሸንቈሪያ።
መንደቅ ፡ (ብ መናድቅ) ዐራዳ ሠንጣቃ፤ ብስ ሽንቍር ነዳላ፤ የተራራ የንጨት የደንጊያ የሸክላ ፥ ወይም የሌላ። አሴቦን ዘቦ መንደቅ። ዘይፌኑ እስኪቶ ውስተ መንደቅ። ወያወስብ ምድረ ነዲቆ ፡ (ዘዳ፬ ፡ ፵፱። ሲኖዶ። ታምር)። አንዳንድ መጽሐፍ በመንደቅ ፈንታ መንድቅ ይላል፤ ስሕተት ነው፤ አያሰኝም።
መንደበ ፡ መነደበ፤ ዐረደ ጐደበ፤ ጐነደበ ቈረጠ፤ የመሬት የዛፍ። ሰረቀ ቀማ ደበደበ፤ አስጨነቀ አስጠበበ። መጽሐፍ ግን በመንደበ ፈንታ አመንደበ ይላል፤ አያሰኝም። ኣመነድቦሙ ወኢይክሉ ቀዊመ። ያመነድብ ነፍሳተ። ሶበ አመንደብዎ ፀሩ ፡ (መዝ
፡ ፲፯። ምሳ፲፪ ፡ ፲፫። ሢራ፵፮ ፡ ፲፮)።
መንደብ ፡ ምንዳቤ፤ የምንዳቤ ቦታ ፥ የሚያስጨንቅ የሚያስጠብብ፤ ወንበዲያም። ዐረብ ፥ የጭነቅ የመከራ በር ሲል ፥ ባብ እልመንደብ እንዲል። ይኸውም በኦቦክና በዓደን መካከል ያለው ባሕር ነው፤ ቀድሞ በዘመነ ብሉይ ከእስክንድር በፊት እንደ ስዮስ ካናል ካፍሪቃ ወደ እስያ ክፍል በእግር የሚያሳልፍ የብስ ነበረ ይባላል።
መንዲል [1] ፡ በቁሙ፤–ነዲል ነደለ።
[2] ፡ (ላት፤ መናዲል) በቁሙ፤ መመንደያ ማጠቢያ ማበሻ መወልወያ ፥ ጨርቅ ቍራጭ ታላቅ ማረሚያ፤ የሥራ ልብስ ፊዶ። መክፌንና ለንጽን እይ። ቀነተ መንዲለ ወኀፀበ እግረ አርዳኢሁ። ትኩን ላዕለ መታክፍቲሆሙ መንዲል ስፍሕት። ይልበስ ካህን መንዲለ ዘቦቱ ትእምርተ መስቀል። ገብርሌል ዘጸዳለ ብርሃን መንዲሉ። መንዲላት ፡ (መጽ ፡ ምስ። ፈ ፡ ፴፩ ፡ ፭። ደራሲ። ስንክ
፡ ግን፳፩)።
መንዲያ ፡ (ጽር ማንዲያስ። ዕብ ማድ) ክቡር ልብስ። የማድዮን ፍች እይ፤ ከዚህ ጋራ አንድ ነው ፡ (፩ነገ ፡ ፲፰ ፡ ፭)።
መንዳእ አው መንዳእታ ፡ የደረትና የትከሻ ደዌ፤ የሚያጐብጥና የሚቀልስ የሚተረክስ።
መንድድ ፡ (ብ መናድድ) ማናደጃ ማቀቀጣጠያ፤ ቅባትነትና መጣብቅነት ያለው ፥ እሳትን የሚያገን የሚያስቈጣ፤ እንደ ጋዝ እንደ ዝፍት ያለ። አዘዘ ያንድዱ እቶነ ወይደዩ ውስቴቱ መናግገንተ ጽህርት ወመፍልሕተ እሳት፤ ፒሳ ወፓፒራ ወሥብሐ ወመዓረ ግራ ወአስፈሊጠ ወክብሪተ ወኵሎ መናድደ ጽህርት ፡ (መቃ ፡ ገ፪)።
መንገለ ፡ (ዐማርኛ) መነገለ፤ አነገለ ፥ ነቀለ አፈለሰ።
መንገለ መንግል ፡ መንግል፤–ወደ ፥ ጌጥ፤–ነገለ።
መንገል ፡ መታያ መተያያ ፥ አንጻር አፋዛዥ ፥ አቅጣጫ ፊት ለፊት፤ የቦታ። ዐቢይና ደቂቅ አገባብ ሲኾን እንደ ኀበ ፥ ወደ ፥ ወገን ፥ አጠገብ ፥ ዘንድ ፥ ቅጽል ይኾናል። መንገለ ምሥራቅ። እኅትየ ይእቲ እመንገለ አቡየ። ኢታቅሞ መንገሌከ ፡ (ደቂቅ)። አልቦ ማኅቶት መንገለ ተኀጥኡ ሠምዕ ወዘይት። መንገለ ፈለሱ። መንገለ ተግሕሠ። መንገለ ትፈቅድ ፍና
፡ (ስንክ ፡ ኅዳ፰። ግን፳)። አንዳንድ ጊዜም፤ ባወራረድ ፍች በ በስተ ረገድ ይኾናል፤ ምስጢሩ ከዘንድና ከወገን ካጠገብ ይገባል ፡ (ዕር፲፱ ፡ ቍ፸)።
መንገነ አው አመንገነ ፡ ዘወረ፤ መኪና አስኬደ። አጠመደ ፥ ወጥመድ አኖረ።
መንገኒቅ ፡ (ዐረ። ሱር ማንጋኒቃ) የዱሮ መድፍ ፥ የመዘውር ወንጭፍ እንዳንደርቢ ብዙ ታላላቅ ደንጊያ አርቆ የሚጥል የሚወረውር። ባለቅኔዎች ግን ነፍጥ ጠመንዣ ሽጕጥ ይሉታል ፡ (ታሪ ፡ ነገ)። መንገኒቅ ባለው አብዝቶ መናዝኒቅ ይላል፤ ወሠርዑ ሰብአ ፋርስ መናዝኒቀ ዘውእቱ መዋግረ እብን ፡ (ጊ ፡ ወ ፡ ሐ ፡ ገ፪፻፭)።
መንገን ፡ (ብ መናግንት። ጽር ማጋኖን። ሱር ማንጋኖን። ዐረ መንገኑን) መዘውር መኪና፤ የመዘውሩ ውስጥ ጥርሱና ሆዱ። ወገብረ ሠረገላ እለ በመንገን ይነድፉ ከመ ይኩና መልዕልተ ማኅፈድ ወማእዝን ወይነድፉ በሐጽ ወበእብን። መንገነ ሶበ ነጸረ ቅዱስ ጊዮርጊስ ለስምዐ መዊት ጥሕረ። መናግንተ ኀጺን ፡ (፪ዜና ፡ ፳፰ ፡ ፲፭። ድጓ። ገድ ፡ ኪሮ)።
፡ አሽክላ ፥ ወጥመድ፤ ተንኰል ክፉ ምክር። መናግንተ ሰይጣን
፡ (ኤፌ፮ ፡ ፲፩። ዲድ
፡ ፲፫ና ፡ ፲፬። ሄርማ ፡ ገ፳፰። ግንዘ)። ከንቱ በክ በማለቅ ፈንታ መንገን ይላል፤ የመላሽ ስሕተት ነው ፡ (፪ዜና ፡ ፳፰ ፡ ፲፭። ድጓ። ገድ ፡ ኪሮስ)።
መንገድ ፡ በቁሙ፤ ጥርጊያ ጐዳና ፥ መኼጃ መንጐጃ። ኢትሑሩ መንገደ። ኢጼሐ መንገደ። ወበመንገድሂ እትመነደብ ዘልፈ። ጥቃ መንገድ
፡ (ኤር፮ ፡ ፳፭። ፲
፡ ፳፫። ፪ቆሮ ፡ ፲፩ ፡ ፳፮። ማቴ፳ ፡ ፴)።
፡ አካኼድ ፥ ጕዞ ርምጃ፤ የመንገድ ሥራ። ምስለ መስተኀይል ኢትኅበር መንገደ። ምሯጸ ብእሲ እንተ ይእቲ መንገደ ቀዳም። ጸሎተ መንገደ ሰማይ ፡ (ሢራ፰ ፡ ፲፭። ግብ፩ ፡ ፲፪። ግንዘ)።
፡ ንግድ፤ የንግድ ሥራ ፥ ችርቻሮ። ስእነ ከመ ይሴሲ እሞ እመሂ በመንገድ ፥ ወእመሂ በግብር ዘይገብሩ ሰብአ ዓለም ፡ (ቀሌ)።
መንግል ፡ የሚታይ ገላ፤ ፊት ዐንገት ደረት ፥ ራስ ጠጕር እጅ እግር። እስመ ትወድዩ ሥት ላዕሌክሙ አንትሙ ዕደው ፈድፋደ እምአንስት፤ ወሕብረ ፈድፋደ እምድንግል በመንግል ፡ (ሔኖ ፡ ድጓ)። ባለብሉዮች ግን ጌጥና ሽልማት ይሉታል።
መንግሥት [1] ፡ በቁሙ፤–ነጊሥ ነግሠ።
[2] ፡ (ታት) በቁሙ፤ መንገሻ መሠልጠኛ ፥ ጌታ መኾኛ ግዛት፤ ያው ግን ካንድ ንጉሥ በታች ያለ ፥ ባንድ ሕግ ጸንቶ የሚኖር አገርና ሕዝብ፤ በውስጡ ብዙ ታላላቅ ክፍል ፥ ሰፋፊ አህጉር ልዩ ልዩ ነገድ ያለበት ማኅበረ ንጉሥ ፥ መርዔተ ንጉሥ እረኛውን መርጦ የሚያነግሥ። መንግሥት ትትፋለስ እምሕዝብ ለሕዝብ። ኵላ መንግሥት ዘትትናፈቅ በበይናቲሃ። ለኵሉ መንግሥታተ ምድር። መንግሥታት ዐበይት ፡ (ሢራ፲ ፡ ፰። ማቴ፲፪ ፡ ፳፭። ዘዳ፳፰ ፡ ፳፭። ፴፭ ፡ ፰)።
፡ የንጉሥ ማዕርግ ፥ ክብር ሥልጣን ጌትነት፤ የሕዝብና የሰራዊት ብዛት ፥ ኅብረት አንድነት፤ ምስጢሩ ከዚያው ይገባል። ፀረፍክሙ ላዕለ መንግሥትየ። ወመንግሥታኒ የሀብ ንጉሥ ለካልአት ብእሲት። አስቴር ሱታፌ መንግሥትነ። መንግሥት እንተ ኢጸውዐት ስመከ። ቅድመኒ መንግሥተ ምድር ወመንግሥተ ሰማይ ድኅረ ኢለዘሮጸ ወኢለዘበደረ
፡ (ታሪ ፡ ነገ። አስቴ፩ ፡ ፲፱። ፲፮ ፡ ፲፫። መዝ ፡ ፸፰። ቅኔ)። እምቅድመ ዓለም ወእስከ ለዓለም ሀሎ እግዚ በመንግሥቱ ፡ (ባንድነቱ) እግዚ በትሥልስቱ ፡ (በሦስትነቱ) እግዚ በመለኮቱ ፡ (በምልአቱና በስፋቱ)። እምቅድመ ጎሕ ወጽባሕ ወእምቅድመ መዓልት ወሌሊት እምቅድመ ይትፈጠሩ መላእክት ሀሎ እግዚ በመንግሥቱ ፡ (በሥልጣኑ በጌትነቱ)። የመንግሥት አፈታት እንደ መለኮት ባለብዙ ስልት ነው ፡ (ቅዳ ፡ ዲዮ)።
መንግር ፡ (ርት ራን ራት) ጪኺ፤ ለፋፊ፤ ነጋሪ። ፡ (መንገሪያ ያዋጅ መሣሪያ፤ ደበሎ ነጋሪት)። ኢበሐላምያን ወኢበመንግራን ፡ (፩ነገ ፡ ፳፰ ፡ ፮)።
መንግድ ፡ የሚነግድ፤ ነጋዲ። መኼጃ መነገጃ፤ መንገድ ገንዘብ። በዘኮነ መንግደ ይገብሩ ፡ (መስተ)።
መንጠፍት [1] ፡ ማጥሪያ፤–ነጢፍ ነጠፈ።
[2] ፡ ወንጠፍት የወንፊት ዐይነት፤ ማጥሪያ ማጥለያ መጥመቂያ፤ ማንጠፍጠፊያ ጠፍ ማድረጊያ። ውስተ መንጣፍት ይጠሐል ሐሠር ፡ (ሢራ፳፯ ፡ ፬)።
መንጢጥ [1] ፡ የወፍ ስም፤–ነጢጥ ነጠ።
[2] ፡ (ጣት፤ አው መናጢጥ) ዋኖስ ቡላል፤ ርግብ የርግብ ወገን ፥ መሧዕት የሚኾን አነጥናጭ ወፍ። ነሥአ መንጢጠ ወዕጕለ ርግብ። ዖፈ መንጢጥ ዘኢነባቢ ይትገሐሥ እምአውስቦ ዳግማዊ። ዖፈ ነበልባል ጽዕድወ እሰምየከ መንጢጠ። መንጢጣት
፡ (ኩፋ ፡ ፮። ፍ ፡ ነ ፡ ፳፬። ደራሲ። ስንክ ፡ ሠኔ፲፪)።
መንጥያዊ ፡ (ዊት ውያን ያት) ዝኒ ዓዲ ከማሁ። የችኮ የዘብዛባ ወገን፤ ጐስጓሽ አነሣሽ፤ አገባሪ አስቸጋሪ፤ አስቸኳይ በሉ በሉ ባይ። ወሶበ ተመውአ እምውስተ መዓርጋት መንጥያውያት፤ አድርጉን አድርጉን ከሚሉ ከታላላቁ ኀጣውእ ፡ (ፊልክ ፡ ፻)።
መንጥይ ፡ (ያን) ዝኒ ከማሁ፤ ወዓዲ። መዘብዘቢያ፤ ምክንያት።
መንጦላዕት ፡ (ብ መንጠዋልዕ ት፤ ዓት) መጋረጃ፤ ግርዶሽ ጥላ ከለላ፤ ልብስ ክዳን፤ ልባጥ ሽፋን
፡ (ዘፀ፳፮ ፡ ፴፩–፴፯)። ውሳጤ መንጦላዕት። ትከድኖሙ በመንጦላዕትከ። መንጠዋልዕ ዘወርቅ ፡ (ዕብ፮ ፡ ፲፱። መዝ
፡ ፴። ፫ነገ ፡ ፮ ፡ ፴፪)።
፡ ጕርጅ፤ መክዘን የዕቃና የልብስ የገንዘብ ቤት፤ ጐተራ። ዲበ መንጠዋልዕ ወዲበ ንጽሐ ቅድሳት። ቤተ መንጠዋልዕ ፡ (፩ዜና ፡ ፳፫ ፡ ፳፰። ፪ዜና ፡ ፴፩ ፡ ፲፩)።
መንጸረ ፡ ገሃደ፤ ታይቶ ተገልጦ ግልጥ ኹኖ፤ በግልጥ ፊት ለፊት። አስተርአየ መንጸረ። አውሥኦሙ መንጸረ። መንጸረኬ አበሳ ውእቱ ከፊል ለክልኤ ፡ (ቄር)። ኢሖረ መንጸረ ቅድሜሁ ዘኍ፳፬ ፡ ፩)። መነጠረ መነጨረ፤ ገላለጠ ፡ (ዐማርኛ)። መንጠር ምንጭር ፥ ምንጭራም ማለት የዚህ ዘር ነው።
መንጸር ፡ ዝኒ ከማሁ፤ አንጻር። ንሑር እንተ መንጸር። ኢሖረ መንጸረ። ዝንቱ መንጸረ ዝንቱ። መንጸረ ሙዳየ ምጿት። ዘይቀውም መንጸረ ፡ (ዘፍ፴፫ ፡ ፲፪። ዘኍ፳፬ ፡ ፩። ኩፋ ፡ ፰። ማር፲፪ ፡ ፵፩። ፲፭ ፡ ፴፱)።
መንጸፍ ፡ ምንጣፍ፤–ነጺፍ ነጸፈ።
መንጸፍ ምንጻፍ ፡ ምንጸፍ፤ ፡ (ፉት መናጽፍ) ምንጣፍ ዐልጋ፤ ማንጠፊያ መነጠፊያ ቦታ መኝታ። ነጸፈ ሠናየ መንጸፈ። ይሰክብ ውስተ ምድር ዘእንበለ መንጸፍ። መንጸፈ ድንግልናሃ። ሞሙ ይእቲ ምድር እምትካት፤ ወይእዜሰ ኮነት መንጸፈ ለአብድንቲሆሙ። ዐራታት ወመንጸፋት። ሠረገላት ወመናጽፍ ሠናያተ ፡ (አፈ ፡ ፳፭። ስንክ ፡ መስ፲፬። ዘዳሸ፳፪ ፡ ፲፭። ግንዘ። ፍ ፡ ነ ፡ ፲፯። አፈ
፡ ተ፪)።
፡ ዐዘቅት ጕድጓድ፤ ታች የታች ታች፤ እግርጌ መረጋገጫ መጠቃጠቂያ፤ አንጦርጦስ። ወድቀ ዲያብሎስ እምኑኀ አርያም ውስተ መንጸፈ ደይን በእንተ ትዕቢቱ ወኮነ መንጸፈ ለኵሉ፤ ወተመነነ እምቅዱሳን መላእክት። ደቂቀ ገሃነም ኮኑ ምጥዋነ ለምንጻፈ ደይን ፡ (ቀሌ። መጽ
፡ ምስ)።
መንጸፍት ፡ የራስ ልብስ ጌጥ፤–መጽነፍት፤ ጸነፈ።
መንጽሕ ምንጻሕ ፡ ምንጻሕ፤ ፡ (ሓት) መንጫ ማንጫ፤ ማጠቢያ መታጠቢያ።
መንፈሳዊ ፡ በቁሙ፤ የነፍስ የመንፈስ የመልአክ። ፍትሕ መንፈሳዊ። ኵነኔ መንፈሳዊ። ማሕሌት መንፈሳዊት
፡ (ፈ ፡ መ ፡ ፬ ፡ ፪። ረቂቅ፤ ንጹሕ ቅዱስ፤ ለነፍሱ ያደረ፤ የግዜር ወገን። አርባዕቱ እንስሳ መንፈሳውያን። አዋልድ መንፈሳውያት ፡ (ቅዳ። ፈ ፡ መ ፡ ፮ ፡ ፩)።
መንፈስ ፡ በቁሙ፤–ነፊስ ነፍሰ።
፡ (ዕብ ወሱር ወዐረ ሩሕ) ረቂቅ ነገር፤ ትንፋሽ እፍታ፤ ነፋስ። በመንፈሰ ከናፍሪሁ። ይሁቦሙ መንፈሰ ለሕዝብ። መንፈስ ኀበ ፈቀደ ይነፍኅ
፡ (ኢሳ፲፩ ፡ ፬። ፵፪ ፡ ፭። ዮሐ፫ ፡ ፰)።
፡ ነፍስ መልአክ፤ ሰይጣን ምትሀት። ወፅአት መንፈሱ ሶቤሃ። ኵሉ መንፈስ ዘይትለአክ። መንፈስ እኩይ። ወመስሎሙ ከመ ዘመንፈሰ ይሬእዩ ፡ (ማቴ፳፯ ፡ ፶። ኩፋ ፡ ፪። ጦቢ፮ ፡ ፰። ሉቃ፳፬ ፡ ፴፯)።
፡ ሰው፤ ሰውነት ፥ ገጽ መልክ፤ ልብ ልቡና ዕውቀት ትዕግሥት። ኵሉ መንፈስ ዘያዕቆብ ዘቦአ ውስተ ግብጽ ሰብዓ መንፈስ። መንፈሰ መራዕይከ። ሐመት መንፈስየ ጥቀ። እሁቦሙ መንፈሰ ሐዲሰ። አንኅ መንፈስከ ላዕሌየ ፡ (ኩፋ ፡ ፵፬። ምሳ፳፯ ፡ ፳፫። ሱቱ
፡ ዕዝ፲፪ ፡ ፰። ሕዝ፲፩ ፡ ፲፱። ፊልክ)።
፡ መምር ትምርት፤ ፈቃድ ምክር ሐሳብ፤ ሥልጣን ባሕርይ። ለኵላ መንፈስ ኢትእመንዋ። እስመ መንፈሱ ይእቲ ሥምረቱ። አይቴኑ አሐውር እመንፈስከ ፡ (፩ዮሐ ፡ ፬ ፡ ፩። ትር ፡ ወን። መዝ፻፴፰)።
፡ በቁሙ፤ መንፈስ ቅዱስ ባሕርያዊ አካላዊ ሕይወት፤ እንደ ነፍስ ፍጡር እንደ ነፋስ ዝርው ያይዶለ የሥላሴ ሦስተኛ አካል፤ ከአብ የሚሠርጽ ከወልድ የሚነሣ ፥ ለሰው ለመላእክት ጸጋ ሀብት ኹኖ የሚሰጥ። ወመንፈሰ እግዚ ይጼልል መልዕልተ ማይ። ወየዐርፍ ላዕሌሁ መንፈሰ እግዚ። ሀብትኬ ሠናይ መንፈስ ቅዱስ
፡ (ዘፍ፩ ፡ ፪። ኢሳ፲፩ ፡ ፪ ፡ ፫። ቄር)። የመንፈስ አፈታት ምንም ስልቱና ዐማርኛ ቢበዛ ዘይቤው ረቂቅ ርቀት ስለ ኾነ ለረቂቃን ኹሉ ይነገራል። እስመ እግዚ መንፈስ ውእቱ። አኮኑ ኵሎሙ መላእክት መንፈስ እሙንቱ። ለመንፈስሰ አልቦቱ ሥጋ ወዐፅም ፡ (ዮሐ፬ ፡ ፳፬። ዕብ፩ ፡ ፲፬። ሉቃ፳፬
፡ ፴፱)።
መንፈቅ ፡ ዝኒ ከማሁ፤ በቁሙ፤ እኩሌታ ፥ ግማሽ። መንፈቀ ነገደ ምናሴ። መንፈቀ ዓመት። መንፈቀ ወርኅ ፡ (ዘኍ፴፪ ፡ ፴፫። ዳን፯ ፡ ፳፭። ኩፋ ፡ ፲፬)።
መንፌ ፡ (ያት ያታት) መንፊያ ማጥሪያ ማንዘርዘሪያ፤ ወንፊት ወንጠፍት። ይጸውር ማየ በመንፌ። ዐቈሩ ማየ በመንፌ ወኢተክዕወ ማይ። ወይሠይጥ መንፌያታተ
፡ (ገድ ፡ ተክ። መጽ ፡ ምስ። ፊልክ ፡ ፻፹፱)።
መአኀዝት ፤
ዝኒ ከማሁ ፤
የከተማ ቦታ።
መአኀዝተ ሀገር
ትሁቡ (ሕዝ፵፭ ፡
፮)።
መዐለ ፡ (ይምዕል ይምዐል ምዒል። ዕብ ማዐል) ታበየ፤ ወነጀለ ፥ ካደ ከዳ ዐበለ። መሐለን እይ ፥ የዚህ መንቲያ ነው፤ መአከ የመሀከ ወንድም እንደ ኾነ።
መዐልም ፡ (ዐረ ሙዐሊም) መምህር፤ ሰባኪ፤ አስተማሪ፤ ሊቅ
፡ (አዋል)።
መዐምፅ ፡ (ፅት ፃን ፃት) ዝኒ ከማሁ። ኢትኩን መዐምፀ ፡ (ዘፀ፳፫ ፡ ፩። ምሳ፲፬ ፡ ፳፭)።
መአሰ ፡ (ዕብ ማአስ፤ ናቀ ነቀፈ) ገፈፈ አስራቈተ፤ ቈርበት አወጣ። ማሰ ቈፈረ፤ አጐደጐደ። ማሳ ማሽ ማለት ከዚህ ወጥቷል።
መዐስብ [1] ፡
ፈት ብቸኛ፤–ዐሰበ።
[2] ፡ (ብት ባን ባት) ፈት፤ ብቸኛ፤ ጋለሞታ፤ ሚስት የሌለችው። መዐስበ ናዝዝ። መዐስበ ሐውጽ። ረድኤት ለመዐስባን፤ ወኀይለ ትዕግሥት ለደናግል። ዘአውሰበ መዐስብተ
፡ (ኪዳ። ቅዳ። አርጋ ፡ ፯። ፍ ፡ ነ ፡ ፱ ፡ ፩)።
[3] ፡ መዐንስብ፤–ሟርተኛ፤–ዐንሰበ።
መዐርዒር ፡ መዓራዊ፤ የሚጣፍጥ ጣፋጭ ጥፍጥ፤ ማር ማር የሚል የማር ወገን። መሪር ወመዐርዒር። ማየ ሰርቅ መዐርዒረ ስተይ። ነገረ ገድሉ መዐርዒር ለተናግሮ ፡ (ሔኖ። ምሳ፱ ፡ ፲፯። ድጓ። ማሕ፭ ፡ ፲፮)።
መዐርይ ፡ (ዕሩይ) ትክክል፤ እኩያ፤ አምሳያ። በኅሊናሰ ኮኑ መዐርያነ። ዘይሜህር ዘእንበለ ይስአሎ፤ መዐርይ ውእቱ ምስለ ዘይዘልፎ። አንተ መሲሑ ወመዐርዩ ለእግዚ ፡ (ፊልክ ፡ ፩። ፪፻፳፱። ስንክ
፡ ታኅ፳፱)።
መአብስ ፡ (ስት ፡ ሳን ፡ ሳት) ዝኒ ከማሁ፤ በደለኛ። ዘይስሕት በአሐቲ ኮነ መአብስ በኵሉ። መአብስ ውእቱ ላዕለ እግዚእነ ፡ (ያዕ፪ ፡ ፲። ፍ ፡ ነ
፡ ፲፫)።
መአተ ፡ (መዐት ብዛት፤ ምዒዕ መዕፅዐ) በዛ ፈደፈደ፤ ዐሥር ዕጥፍ ፥ ወይም መቶ ኾነ ፥ መቶ ተባለ።
መዐት ፡ በቁሙ ፥ ቍጣ፤–ምዒዕ መዕዐ።
መዐት አው መዓት ፡ በቁሙ፤ መቈጣት መበሳጨት። ማት ቍጣ ተግሣጽ፤ ብስጭት፤ ንደት ጩኸት። ኢይቈርር መዓትየ ላዕለ ፀርየ። ወነዳይሰ ኢይሰምዕ መዐተ። በእንተ መዐት ወቍጥዓ። መዐትኒ ወቍጥዓኒ ርኩሳን እሙንቱ ፡ (ኢሳ፩ ፡ ፳፬። ምሳ፲፫ ፡ ፰። ፈ ፡ መ ፡ ፳፩። ሢራ፳፯ ፡ ፴)።
፡ ብዛት፤ ብዙነት ፥ እጅግነት።
፡ (ግጥም፤ መርድ አምኃየስ ወጥ ቤታቸውን አሽከራቸው ሲሳለማት አይተው) ዓሣ የምቲዙ መረብ የያዛችኹ ፥ ያሣማት ያሣማት እኔ ላሳያችኹ። ወሀቡ ህየ መዓተ ቍርባኖሙ ፡ (ሕዝ፳ ፡ ፳፰)።
መዐትም ፡ ቍጡ ክፉ፤–ዐተመ።
፡ (ምት ማን ማት) ቍጡ፤ ብስጩ፤ ተናዳጅ። ኢይኩን አሐዱ እምዘመደ ካህናት መዐትመ ወመፍጠኔ መዐት። ነፍስ መዐትም ዘይነድድ ከመ እሳት። ነባቢት ወመዐትምት። አናብስት መዐትማን ፡ (ፈ ፡ መ ፡ ፳፩ ፡ ፫። ሢራ፳፫ ፡ ፲፮። ምሳ፳፩ ፡ ፲፪። ጥበ፲፩ ፡ ፲፰)።
መአነ ፡ (ዐረ መአ። ዕብ ማኤን፤ እንቢ አለ) ዘረጋ አሰፋ፤ ሰፊ አደረገ፤ የቦታ የሕንጻ። እንደ ዕብራይስጡ ሲፈቱት ግን ዘጋ ከለከለ ያሰኛል።
መዐንስብ [1] ፡ ሟርተኛ፤–ዐሰበ፤ ዐንሰበ።
[2] ፡
(ብት ባን ባት) ሟርተኛ፤ መለኛ፤ በነሲብ በግምት የሚናገር። መዐንስበ አራዊት ወእመ አኮ ዐቃቢሆሙ። ማርያን ወመዐንስባን ፡ (ኪዳ። ዲድ ፡ ፲፫)።
መአከ ፡ (የመሀከ ዋርሳ) ተቈጣ ፥ ዛተ ገላመጠ፤ ቃጣ ሰነዘረ፤ አስፈራራ፤ በቃል በበትር። መጽሐፍ ግን በመአከ ፈንታ ተምእከ ተመአከ ይላል፤ ስሕተት ነው። ወዓዲ አፍርሆ እንዘ ይትሜአክ። ኢኮነ ከመ ሰብእ እግዚ ዘይትሜአክ ወኢኮነ ከመ ዕጓለ መሕያው ዘይትቄየም። ወይትሜአክ ዔሳው ያዕቆብሀ በእንተ በረከት ዘባረኮ አቡሁ ፡ (ዮሴፍ። ዮዲ፰ ፡ ፲፮። ኩፋ ፡ ፳፮)።
መዐከ ፡ ተቈጣ፤ ጨከነ፤–ምኢክ መአከ።
መአክ(ጥ)ል ፡ (ዕብ ፡ (ጥኮ) ማኮሌት) ተሰፍሮ ለቀለብተኛ የሚሰጥ እኽል። ወሀቦ ሥርናየ፤ መአክጠ ለቤቱ
፡ (፫ነገ ፡ ፰ ፡ ፲፩)። ዘይቤው ቀለብ ምግብ።
መአክጥ ፡ ምግብ ቀለብ፤–አኪል አከለ።
መዐወ ፡ (ሜዐ። ሜመየ፤ ምህወ) ረጠበ ራሰ፤ ለዘበ ለሰለሰ፤ ላመ ጣመ። ሰፈረ፤ ቦታ ያዘ። ጋላም ጣፈጠ ሲል ሚዐዌ ይላል፤ ከመላም ከመጣም ይሰማማል።
መዐዛ ፡ (ዛት) በቁሙ ሽታ፤ ሽቱ ፥ ሽቶ። ጥዕመ መዐዛየ ከመ ቀናንሞ። መዐዛ ሠናይ። መዐዛ እኩይ። ዕፀወ መዐዛ። ኢተቀብዐት መዐዛተ ፡ (ሢራ፳፬ ፡ ፲፭። ዘሌ፩ ፡ ፱። መጽ ፡ ምስ። ሔኖ፳፬ ፡ ፫። መቃ ፡ ገ፲፩)። መዐዛ ማይ፤ ሰትይ ረውይ ጠል
፡ (ኢዮ፲፬ ፡ ፱)።
መአዝል ፡ (ዕብ ምኡዛል) የሚኼድ ፥ ኻያጅ፤ ገሥጋሽ ተመላላሽ ፡ (ሕዝ፳፯ ፡ ፲፱)።
መአዝዝ መስተአዝዝ ፡ መአዝዝ፤ መስተአዝዝ፤ ፡ (ዝት ዛን ዛት) የሚያዝ፤ የሚያሳዝዝ፤ አዛዥ አሳዛዥ።
መአደ [1] ፡ መአደ፤–መከረ፤–ምዒድ መዐደ።
[2] ፡ (ዐረ ማድ። ዕብ ማዳድ) ሰፈረ ከነዳ፤ አስተካከለ ፥ ወርዱን ቁመቱን፤ የሕንጻ የንጨት የቦታ የመሬት።
መአድም ፡ (ምት ማን ማት) ዝኒ ከማሁ፤ የሚያምር። እለ ሠናይ ራእዮሙ ወመአድም ሥኖሙ። ብእሲ ቀይሕ መአድም ገጹ፤ መአድምት ብእሲት። መዐርዒር ነገር ወመአድም ንባብ ፡ (አፈ ፡ ተ፲፯። ገድ
፡ ተክ። ስንክ ፡ ኅዳ፳፯)።
መዐግል መስተዐግል ፡ የሚቀማ፤ የሚያስቀማ፤ አስቀሚ፤ ቀማኛ። ርኩስ ወመስተዐግል። እምብዝኆሙ ለመስተዐግላን የዐወይዉ ወይግዕሩ ፡ (ኤፌ፭ ፡ ፭። ኢዮ፴ ፡ ፱)።
መአግር ፡ (ርት ራን ራት) ዝኒ ዓዲ ከማሁ ለአጋር ወአጋሪ።
መዓሊ ፡ መምዐሊ፤ ፡ (ሊት ልያን ያት) የሚታበይ ወንጀለኛ፤ ዐባይ ክሓዲ ከዳተኛ ፡ (ስንክ ፡ ታኅ፲፪። ነሐ፳፭)።
መዓልታዊ ፡ የቀን የሙያ፤ ቀን የሚመግብ። ፀሓይ መዓልታዊ
፡ (ጥበ ፡ ጠቢ)።
መዓልት ፡ በቁሙ ቀን፤–ውዒል ወዐለ።
መዓምቅ ት ፡ ጥልቆች፤ ጕድጓደች፤ መዓምቅተ ሲኦል ፡ (ምሳ፲፬ ፡ ፲፪)።
መዓስባን ፡ (ባት) ዝኒ ከማሁ፤ የብዙ ብዙ። መነኮሳት መዓስባን። መበለታት ወመዓስባት
፡ (ኪዳ)።
መዓስብ ፡ መዓስብ፤ ፈቶች፤ ሚስት የሌላቸው።
መዓረ ዕፅ ፡ ሙጫ፤ የዶሮ ማር ፥ ወይም አዶሮማል ከንጨት የሚገኝ።
መዓረ ገዳም
፡ የ(ቀባ) ማጓ ማር በዱር በገደል በዛፍ ላይ የሚገኝ ፡ (ማቴ፫ ፡ ፬)።
መዓረ ግራ ፡ የንጀራ መዓር፤ እንጀራነት ያለው፤ ወይም ግራ መዓር፤ የማር እንጀራ። መዓር፤ ወለላው፤ ግራ እንጀራው ግግሩ ዐይኑ ጠቃጠቆው ፥ ሰፈፉ ሠሙ የተነጠረው የተጋገረው፤ ሲቀልጥ ወለላ መስሎ የሚፈሰው። ባለብሉዮች ግን ሙጫ አዶሮማል ብለው ይጨምሩበታል፤ ግራን እይ። ወይትመሰዉ ከመ መዓረ ግራ። በከመ መዓረ ግራ የኀትም ሰብእ በማኅተመ ወርቅ
፡ (ሔኖ፩ ፡ ፮። ቄር)።
መዓረ ጸደና ፡ የጣዝማ ማር ከምድር ውስጥ የሚገኝ ፡ (ማር፩ ፡ ፮)።
መዓር ፡ (ዕብ፤ ያዓር፤ ድባሽ) በቁሙ ፥ ማር የሚጣፍጥ ፥ እጅ የሚያስመጥጥት፤ የንህብ ሥራ። ምንት ይጥዕም ዕመዓር። ዐገቱኒ ከመ ንህብ መዓረ ፡ (መሳ፰ ፡ ፱። መዝ ፡ ፻፲፯)።
መዓቅብ ብት ፡ ዘበኞች፤ ጠባቆች። ረከብዋ መዓቅበ ፋርስ። መዓቅብት እለ የዐቅቡ ሀገረ። ከመ መዓቅበ ሐቅል ፡ (ዮዲ፲ ፡ ፲፩። ማሕ፫ ፡ ፫። ኤር፬ ፡ ፲፯)።
መዓብል ፡ (ልት) መሣሪያዎች፤ ፍላጾች፤ ሰይፎች፤ ሾተሎች። በመዓብል ፈንታ ማዕበል ይላል፤ የተሳሳተ ነው። እሙንቱሰ ማዕበል ያሰጥሙ ፡ (መዝ ፡ ፶፬ ፡ ፳፩)። ያሰጥሙ የመላሽ ስሕተት ነው፤ በጽርእና በዕብራይስጥ የለም።
መዓንቅ ፡ ዋኖሾች፤ ቡላሎች። ያመጽእ ክልኤተ መዓንቀ ፡ (ዘሌ፭ ፡ ፯)።
መዓክክት ፡ ታላላቅ ድስቶች፤ ጋኖች፤ መታጠቢያዎች። ወመዓክክተኒ ፡ (፪ነገ ፡ ፰ ፡ ፰)።
መዓዚ ፡ (ዚት ዝያን ያት) የሚሸት ሸታች፤ ምዑዘ ባሕርይ ፥ ዕዙዘ መዐዛ።
መዓዝር ፡ ብርሃኖች፤ የብርሃን ቀርኖች። መዓዝረ ፀሓይ፤ መዓዝረ ስብሐት
፡ (መጽ ፡ ምስ)።
መኣዝነ ሰብእ
፡ ፊቱ ኋላው ቀኙ ግራው።
መዓዲ ፡ (ዲት ድያን ያት) የሚመክር መካሪ፤ መጣፍ አሰሚ። ንሣእ መዓዴ። መዓድያኒሁ ፡ (ፊልክ ፡ ፻፪። ፪፻፴፩። ሥር
፡ ጳኵ)።
መዓድናት ፡ የብዙ ብዙ። ንጽሕፍ ነገረ ኀጻውንት ወመዓድናት ፡ (ጥሬ ፡ ሰዋ)።
መዓድው ፡ ማደዎች፤ አሻገሮች፤ ወንዝና ባሕር የለያቸው፤ የከፈላቸው።
መዓጽው ፡ (ጹት ጽዋት) መዝጎች፤ ሳንቆች። በበ ክልኤ መዓጽዊሁ። መዓጹት ወመናሥግት። መዓጹት ዘቅድመ ገጹ ፡ (ሕዝ፵፩ ፡ ፳፬። ኢዮ፴፰ ፡ ፲። ፵፩ ፡ ፭)።
መዓጽድ ፡ ማጭዶች። ይመትሩ ኵያንዊሆሙ ለመዓጽድ
፡ (ኢሳ፪ ፡ ፬)።
መእኅዝት [1] ፡ (ብ መኣኅዝት) መያዣ መጨበጫ፤ እጀታ ዦሮ፤ ቀለበት መኣኅዝት በዘይእኅዝዋ ፡ (ዘፀ፴፰ ፡ ፬ ፡ ፲ ፡ ፳፫)።
[2] ፡ የተቋም ጽዋ፤ ቀንዲሉ ዘይቱና ፈትሉ የሚኾንበት፤ ያገዳው ራስ
፡ (ዘፀ፳፭ ፡ ፴፩ ፡ ፴፫። ፴፯ ፡ ፲፯ ፡ ፲፱። ፴፰ ፡ ፲፮)።
[3] ፡ የወርቅ ኅርወት፤ መደቡ ስጕዱ ጕድጓዱ ዕንቍ ፈርጥ እንዳይን ኹኖ የሚሰካበት የሚያዝበት ፥ ዐይን መስሎ ጐርጦ ፍጥጥ ብሎ የሚታይበት ፡ (ዘፀ፳፰ ፡ ፲፩)።
[4] ፡ የሚይዝ የሚያያይዝ ቀለም መጣብቅ ፤ ከያዘ የማይለቅ። ጽቡር ለመኣኅዝቲሆን (ገድ ፡ ላሊ)።
መእሕድት ፡ አንድ ወገን፤ አንድ ፊት፤ ፩ እመም፤ ፩ ገዝም፤ ፩ አፍታ፤ ፩ ወረራ፤ ፩ ፈፋ፤ ፩ አውራጃ፤ ፩ ቃዳ፤ ፩ ተለላ፤ ፩ ትልም፤ ፩ መዛሪያ፤ ይህን የመሰለ ኹሉ።
መከሴና ፡ (ዕብ ምካሴ) መሸፈኛ መጋረጃ ልብስ። ወገብሩ ሕዝብ መክሴና ለምሥዋዕ ዘሐነጹ
፡ (ዮሴፍ)።
መከሴና ሜክሱት ፡ መሸፈኛ፤–ከሰየ።
መከራ ፡ (ራት) በቁሙ፤ ፈተና ጭንቅ። እብነ መከራ። መከራሆሙ ለወርቅ ወለብሩር ርስነት። መናስው ወመከራት። መከራተ ሰይጣናት ፡ (ሢራ፮ ፡ ፳፩። ምሳ፳፯ ፡ ፳፩። አፈ ፡ ተ፪። ፊልክ ፡ ፳፮)።
መከር ፡ በቁሙ፤ የእክልና የተክል አዝመራ፤ ምድር ለገበሬ የምትሰጠው ፍሬ፤ ተዘርቶ እስኪታጨድ እስኪመረትና እስኪከተት እንደ ሰማዕታት ብዙ መከራ ያለበት ፡ (ዐማርኛ)።
መከርክር [1] ፡ ወፍጮ ከነመጁ፤ እናትና ልጁ። ስነነ ሞሠረት ቦቱ፤ ወጥረሲሁ መከርክር ፡ (ምሳ፳፬ ፡ ፴፯)።
[2] ፡ መከርክር፤–ወፍጮ፤–ከርከረ።
መከየድ ፡ (ብ መካይድ) መርገጫ መኼጃ፤ ጫማ ውስጥ እግር ዝርጉ ጠፍጣፋው። መካነ መከየደ እገርየ። በማእከለ መከየደ እገሪሁ ወፅአ ቍስል። ፍቅርኪ ሠረጸ ውስተ ልብየ ወኮነ ሥረዊሁ እስከ መካይድየ። ሰላም ለመካይድኪ እለ ረከቦን መከራ፤ እንበለ አሳእን እመ ሖራ
፡ (ሕዝ፵፫ ፡ ፯። ገድ ፡ ተክ። አርጋ ፡ ፭። ደራሲ)።
፡ ድኳ ግርንቡድ፤ ሉሕ ምንጣፍ የእግር ድጋፍ ማረፊያ። ሰማይኒ መንበርየ ወምድርኒ መከየደ እገርየ። ወኢተዘከረ መከየደ እገሪሁ በዕለተ መዐቱ። ኣገብኦሙ ለጸላእትከ ታሕተ መከየደ እገሪከ ፡ (ኢሳ፷፮ ፡ ፩። ሰቈ፪ ፡ ፩። መዝ ፡ ፻፱)።
፡ የንጨት ሰገነት፤ ደርብ መረባርብ እንደ ቈጥና እንደ ማማ ኹኖ ለመስበኪያና ለማንበቢያ ላዋጅ መንገሪያ የተሠራ፤ ዕርከንና መሰላል ያለው። ወቆመ ዕዝራ ላዕለ መከየድ ዘዕፅ ፡ (ነሐ፰ ፡ ፬)።
፡ ጫማ ወይም መጫሚያ፤ የውስጥ እግር ቤዛ። ዲበ ኤዶምያስ እሰፍሕ መከየድየ
፡ (መዝ ፡ ፶፱። ፻፯)።
፡ የጫማ ልክ መጠን፤ ይፍሩ ወይም አሠሩ። ዐሠርቱ ወክልኤቱ መከየደ እግር ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፴፯)።
፡ ስክተት፤ የዐምድ ሥር መሠረት፤ መብቀያውና መተከያው። አዕማደ ወርቅ እለ ይቀውሙ ዲበ መከየደ ብሩር። ወመካይዲሆን ኀምስቱ ዘብርት
፡ (ሢራ፳፮ ፡ ፲፰። ዘፀ፴፯ ፡ ፮–፱)። በመከየድ ፈንታ ምክያድ ይላል፤ አያሰኝም። አሠረ ምክያደ ብእሴ ፡ (ስንክ ፡ ታኅ፲)።
መኵሰየ ተመኵሰየ ፡ (ኰሰየ) ሞከሸ፤ ተሞካሸ፤ ሞክሼ ኾነ፤ በስም ተባበረ። ተመኵሰዩ መልከ ጼዴቅ ወኢያሱ ምስለ ክርስቶስ በጸዊረ ስም፤ ወአኮ በአማን። ሰላም ለሱስንዮስ በምግባር ወተሰምዮ ለዕጓለ ጴጥሮስ ሱሲ ዘተመኵሰዮ ፡ (መጽ ፡ ምስ። ስንክ ፡ ሐም፳፩)።
መኵሲ ሴ ስይ ፡ (ብ መኵስያት፤ አው መኳስይ) ሞክሼ የስም ተባባሪ፤ ስም ዐበር። ሶፍያ አንጌቤናይት እስመ አነ መኵሲሃ። ዳንኤል ብፁዕ መኵሴ ዳንኤል ነቢይ። ወካልእሰ በመኵሴ ወልድ ተሰምየ ወልደ ፡ (ስንክ ፡ መስ፭። ታኅ፯። ቄር)።
መኵሴ ፡ ሞክሼ፤–ኰሰየ።
መኵረቢ ፡ ማረሻ ማፍረሻ፤ ዶማ ደንጐራ። ባለቅኔዎች ግን መጥረቢያ ይሉታል።
መኪር ሮት ፡ (መከረ ይመክር ይምክር። ዐረ መከረ፤ አታለለ። ዕብ ማካር፤ ሼጠ) መምከር፤ ማሰብ ማውጣት ማውረድ፤ ሐሳብን ማሻሻል መምረጥ ማበላለጥ፤ መወሰን መቍረጥ፤ ለማድረግ ለመተው። ምክሩ ምክረ ዘንገብር። ምንተ መከረ እግዚ ላዕለ ግብጽ። ምክር እምውስተ ሕዝብ ዕደወ ጻድቃነ፤ ምረጥ
፡ (፪ነገ ፡ ፲፮ ፡ ፳። ኢሳ፲፱ ፡ ፲፪። ዘፀ፲፰ ፡ ፳፩)።
፡ መስጠት ማቅረብ፤ የምክር የገንዘብ፤ ማስተማር ማመልከት ፥ ለሌላው፤ ምስጢሩ ከዚያው ከመምከር ይገባል፤ መጽሐፍ ግን በመከረ ፈንታ አምከረ ተማከረ ይላል፤ ስሕተት ነው። መኑ ከመ አምከረ ላዕለ ጢሮስ። መኑ መማክርቲሁ ዘአምከሮ። ኵሉ መምከር ያመክር ምክረ። ንዒ አምክርኪ ምክረ። እንዘ ያመክርዎ በግዐ ከመ ካህን፤ ወሐሊበ ከመ ሕፃን፤ ወርቀ ከመ ንጉሥ ፥ ወዕጣነ ከመ አምላክ
፡ (ኢሳ፳፫ ፡ ፰። ፵ ፡ ፲፫። ሢራ፴፯ ፡ ፯። ፫ነገ ፡ ፩ ፡ ፲፪። አዋል)። ተማከሩ ምክረ እኩየ ላዕሌከ። መኑ ተማከሮ ፡ (ኢሳ፯ ፡ ፭። ሮሜ፲፩ ፡ ፴፬)።
መኪና [1] ፡ (ጽር ሜካኔ) በቁሙ፤ መዘውር የጥበብና የብልኀት መሣሪያ፤ ሥራን ኹሉ በፍጥነት የሚያስኬድ።
[2]
፡ በቁሙ መዘውር፤–ከዪን ኬነ ኬነወ።
መኪን ኖት ፡ (መከነ፤ አው መክነ ይመክን ይምክን) መምከን፤ መካን መኾን፤ አለመውለድ ፥ አለማፍራት፤ ወይም ወልዶ መቅበር ልጅ ማጣት፤ መጨንገፍ ማሶረድ፤ አብቦ መቅረት። ርእየት ልያ ከመ መክነት። አንስት ይመክና። ትመክን ብሔረ ሃይማኖት። አልሕምቲሆሙ ኢይመክና ፡ (ኩፋ ፡ ፳፰። ፬ነገ
፡ ፪ ፡ ፱። ሱቱ ፡ ዕዝ፫ ፡ ፪። ኢዮ፳፩ ፡ ፲)። በመክነና በመከነ ፈንታ ተመክነ ይላል፤ ስሕተት ነው።
መካሒ መካሕ ፡ የሚመካ፤ ትምክሕተኛ ኵሩ፤ ተከባሪ። አይ ውእቱ ዝንቱ ብእሲ መካሕ ፡ (ኢሳ፷፫ ፡ ፩)።
መካሪ መምከሪ ፡ (ሪት ርያን ያት) በቁሙ፤ የሚመክር መካር። አስተዋይ፤ ምክር ዐዋቂ፤ አማካሪ። ልበ መካርያን። ኅሊና መካርያን። ልብ መካሪት። መምከሪሁ ለንጉሥ። መምከሬ ሠናይ ፡ (ምሳ፲፭ ፡ ፳፪። ቅዳ ፡ ኤጲ። ምሳ፳፬ ፡ ፮። ፩ዜና ፡ ፳፯ ፡ ፴፫። ዲድ)።
መካን [1] ፡ (ናት። ዐረ መከን። ዕብ ማቆም። ሱር አታር) ቦታ ሰፈር ስፍራ። መቆሚያ መቀመጫ፤ ቤት መሥሪያ ማደሪያ መኖሪያ፤ መሰብሰቢያና መከማቻ፤ ዐጸድ ወዠድ፤ አገር መንደር ከተማ ገጠር። ለይትጋባእ ማይ ዘመትሕተ ሰማይ ውስተ አሐዱ መካን። ከመ ኢይቁሙ ውስተ መካንከ እስመ አልቦሙ መካን። መካናት ብሩሃን። መካናት ሠርያት። ራሕብ መካናቲሆሙ ፡ (ዘፍ፩ ፡ ፱። ሢራ፲፪ ፡ ፲፪። ሉቃ፪ ፡ ፯። ሔኖ፲፯ ፡ ፫። ፳፪ ፡ ፩። ፵፫ ፡ ፪)።
፡ ማእዝን፤ የመጽሐፍ አንቀጽ ምዕራፍ ክፍል። እምአርባዕቱ መካን። ወከሢቶ መጽሐፈ ረከበ መካነ ዘይብል። በዝንቱ ገጸ መካን፤ ወበገጸ መካንኒ ፡ (ማቴ፳፬ ፡ ፴፩። ሉቃ፬ ፡ ፲፯። ሃይ ፡ አበ)።
፡ የቍጥር መደብ፤ የአኃዝ ጉባኤ በየረድፉና በየተራው በየተለላው የሚጣፍበት ፡ (አቡሻ ፡ ፲፩)። ምስጢሩ ከዚያው ከቦታነት አይወጣም።
[2] ፡ መካን፤–ቦታ ሰፈር፤–ከዊን ኮነ።
[3] ፡ (ጥ) መካን፤ (ናት) በቁሙ፤ የማዮ(ቶ) ልድ፤ የማያ(ታ) ፈራ፤ መሲና። ወሳራሰ መካን ይእቲ ወኢትወልድ። እስመ መካን ይእቲ ኤልሳቤጥ። ብፁዓት መካናት እለ ኢወለዳ ፡ (ዘፍ፲፩ ፡ ፴። ሉቃ፩ ፡ ፯። ፳፫ ፡ ፳፱)።
መክ ፡ የመጽሐፍ ስም፤ ፪ኛው ክፍል ፍትሐ ነገሥት። መ መለከ፤ ክ ካልእ ወይም ክልኤት ከማለት መጥቶ ፩ ስም ኹኗል። ዳግመኛም በዕብራይስጥ ፊደል ቤትና ካፍ
፡ (በ ከ) እንደ ፮ና እንደ ፯ ይማሰላሉና ፥ ዳግምና ካልእ ለማለት መብ በማለት ፈንታ መክ ማለት ስሕተት ነው ብለው የሚፈቱ አሉ። መክ ዘውእቱ ነገሥት ዳግም ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ መቅ)። መግና መጅም ፡ (ገ ፡ ደ) ዐረቡ ጋሜልን ጂም እያለ አጠራሩን ስለ ለወጠው በዚህ ምክንያት ተዛውረው አለቦታቸው ተጥፈዋል፤ ፍቻቸውን በየቦታቸው እይ።
መክሖ ሖት ፡ (መክሐ ይሜክሕ ይመክሕ) መመካት፤ መታበይ መኵራት፤ መክበር መከበር፤ ክቡር ምስጉን ተከባሪ መኾን፤ እኔ እገሌ ማለት። መጽሐፍ ግን በመየነ ፈንታ ተመየነ እንዲል በመክሐም ፈንታ ተመክሐ ይላል፤ ተ ያማርኛ ነው ፥ አያሰኝም። ትትሜካሕ በማእከለ አሕዛብ። መኑ ተመክሐ ከማከ። ወይትሜካሕ ከመ እግዚአብሔር አቡሁ። ኢትትመክሑ በቅትለትየ ፡ (ሢራ፳፬ ፡ ፩። ፵፰ ፡ ፬። ጥበ፪ ፡ ፲፮። ዮሴፍ)።
መክሊት ፡ የሚዛን ዐዋቂ፤–ከልይ ከለየ።
መክልእ መከልእ ፡ (እት ኣን ኣት) ዝኒ ከማሁ። ይቀውሙ ቅድመ ንጉሥ መከልኣን እለ ኦያበውሑ ከመ ይቅረቦ መኑሂ። ወባሕቱ ብዙኃን መከልኣን ፡ (መጽ ፡ ምስ። ፩ቆሮ ፡ ፲፮ ፡ ፱)።
መክልይ መክሊት ፡ (ብ መካልይ፤ መካልያት። መክሊታት) የሚዛን ዐዋቂ፤ ደንጊያ ወይም ብረት ርሳስ፤ መጠኑ ፫ ቪሕ ሰቀል የሚያነሣ። አንዱ መክሊት ስሳ ምናን፤ አንዱ ምናን ኀምሳ ሰቀል ይኾናል። የቤተ መቅደስ ሚዛን ግን ዕጥፍ ነው፤ መክሊቱ ቀከ–፻፳ ምናን፤ ምናኑ ቀ–፻ ስቅል ይኾናል። መክሊተ ወርቅ ትገብራ። መክሊተ ጥጥ፤ መክሊተ ኀጺን። መክሊተ ዐረር። ነሥአ ዐሠርተ ወክልኤተ መክሊተ ብሩር ፡ (ዘፀ፳፭ ፡ ፴፱። ፍ ፡ ነ ፡ ፴፮። ዘካ፭ ፡ ፯። ፬ነገ ፡ ፭ ፡ ፭)። ኵሉ ወርቅ ዘተገብረ ዕሥራ ወተስዐቱ መካልይ፤ ወብሩርኒ ዘመባእ ምእት መካልይ። ዘይፈዲ እልፈ መካልየ። በረድ ዘመጠነ መካልይ ፡ (ዘፀ፴፱ ፡ ፩። ማቴ
፡ ፲፰ ፡ ፳፬። ፳፭ ፡ ፲፭ ፡ ፳፰። ራእ፲፮ ፡ ፳፩)።
መክስብ ፡ ሸንኰ ዋሸላ፤ ቍልፈት ከተማ ነፍስት፤ በምላጭ ተቈርጦ የሚወድቀው ትርፉ። ወገዘረ ሥጋ መክስቦሙ
፡ (ኩፋ ፡ ፲፭)።
መክሥት ፡ (ታን ታት) ዝኒ ከማሁ፤ የሚገልጥ ገላጭ። መግለጫ፤ ግላጭ። መክሥተ አፉሁ ከመ መልአከ እግዚ። መክሥተ አፉሁ መዐዛ ዕጣን፤ አፉን የሚከፍትበት ፥ ወይም ካፉ የሚወጣ ቃል እስትንፋስ ፡ (ስንክ
፡ ጥቅ፳፩። መጽ ፡ ምስ)።
መክሪት ፡ (ብ መካርይ) አው መክርይ ፡ (ያት) መቈፈሪያ፤ መማሻ መኳቻ። አኀዘ መክርየ በእደዊሁ። ይክረዩ ውስተ ይእቲ በኣት በመክርይ ዘወርቅ። ሶበ ተኀጥአ መጥባሕት ለክሣዶሙ ይምትራ፤ መክርያቲሆሙ ወሀቡ ለሐራ ፡ (ስንክ ፡ ግን፳፰። አዋል። ስንክ ፡ መስ፲፩)።
(ጥ) መክሮ ሮት ፡ (ጥ) መክሮ፤ ሮት፤ ፡ (መከረ ይሜክር ይመክር። ነሰወ፤ ፈተነ) መሞከር፤ መፈተን፤ መመርመር ፥ ማስጨነቅ፤ ጠባዩንና ምስጢሩን ለማወቅ። መጽሐፍ ግን በመከረ ፈንታ አመከረ ይላል፤ ስሕተት ነው። በእሳት ያሜክርዎ ለወርቅ። በብዙኅ ነገር ያሜክረከ። አመክሮሙ ለአግብርቲከ ዐሡረ መዋዕለ። ወቀርበ ዘያሜክሮ
፡ (ሢራ፪ ፡ ፭። ፲፫ ፡ ፲፩። ዳን፩ ፡ ፲፪። ማቴ፬ ፡ ፫)።
መክብብ ፡ መክብብ፤
፡ (ብት ባን ባት) የሚከብ የሚያስከብብ፤ ከባቢ አስከባቢ፤ ሹም አለቃ ሰብሳቢ። ኩን መክብበ አሕዛብ። በመክብበ ማኅበሮሙ ለቅዱሳን ፡ (ኩፋ ፡ ፳፯። አርጋ ፡ ፬)።
፡ የቍጥር ድምር፤ ጅምላ ጠቅላላ ቍጥር። ሰመንቱ እልፍ ወሰብዓ ምእት ኮነ መክብበ ኍልቆሙ። ወኮነ መክብበ አጻብዒሁ ዕሥራ ወአርባዕቱ ፡ (፩ዜና ፡ ፯ ፡ ፭። ፳ ፡ ፮)። ዘመን መዋዕል በማለት ፈንታ መክብብ ይላል፤ ስሕተት ነው። ወኮነ መክብበ ንግሡ ለዳዊት አርብዓ ዓመተ
፡ (፩ዜኖ ፡ ፳፱ ፡ ፳፯)።
፡ ኵሉ ኵለንታ፤ መላው። መክብበ ሥጋ። መክብበ መጻሕፍት ዘብሉይ
፡ (ፊልክ ፡ ፲፪። መጽ ፡ ምስ)።
፡ መጨረሻ መደምደሚያ፤ ጕልላት። የሐንስ መክብበ ነቢያት። ጴጥሮስ መክብባ ለስምዐ ሃይማኖት ፡ (አዋል። ስንክ
፡ የካ፩)።
፡ ወገን ዐይነት። እብነ ሶም በበ መክብቡ ፡ (፩ዜና ፡ ፳፱ ፡ ፪)።
፡ የመጽሐፍ ስም፤ ከመጻሕፍተ ሰሎሞን አንዱ። ርሱው ራሱ ሰሎሞን፤ ሰባኪ መምህር መገሥጽ ማለት ነው፤ ቈሀልትን እይ። ቃለ መክብብ ወልደ ዳዊት ፡ (መክ፩ ፡ ፲፪። ፯ ፡ ፳፰። ፲፪ ፡ ፰ ፡ ፱)።
መክተፍ ፡ (ትግ ሐባ) መትከፍ ፥ ትከሻ ጫንቃ። መክተፊያ፤ መከሸኛ።
መክነስ ፡ (ብ መካንስ። ዐረብ) መጥረጊያ ፥ መኰስተሪያ ፥ የጕድፍ መሣሪያ።
መክነየ ፡ (ዲቃ ግ) መከኘ፤ ምክንያት ኾነ፤ የክፋ የበጎ።
መክኑን [1] ፡ ኅቡእ፤–ከኒን ከነ፤ እልመ።
[2] ፡
የተሰወረ ፥ ያልታወቀ፤ ስውር ኅቡእ። እልመክኑን ዝ ብሂል ኅቡእ ፡ (ስንክ ፡ ጥቅ፮። ግብ፲፯ ፡ ፳፫)።
መክደን ፡ (ብ መካድን) መክደኛ መሸፈኛ፤ ክዳን ልብስ። አልቦ ሣዕር ለመክደኖን። አምሳለ መክደን። መክደነ አርእስት ዘኀጺን፤ የራስ ቍር ፡ (ገድ ፡ ላሊ። ፊልክ ፡ ፻፴፮። ፪ዜና ፡ ፳፮ ፡ ፲፯)።
መክደንት ፡ (ታት) ዝኒ ከማሁ።
መክድን መክደኒ ፡ ዝኒ ከማሁ።
መክፈልት [1] ፡ (ታት) በቁሙ፤ ክፍል ልዩ ልዩነት ያለው። በብዙኅ መክፈልት። አርባዕቱ መክፈልተ ዓመታት። ዝንቱ ገጽ ይትከፈል ኀበ ሰመንቱ መክፈልታት ፡ (ዕብ፩ ፡ ፩። ሔኖ፹፪ ፡ ፲፩። ፍ ፡ ነ ፡ ፭)።
፡ ዕድል ፈንታ ድርሻ፤ ዕፃ። መክፈልትየ እምኵሉ ስራሕየ። ምስለ አራዊት መክፈልቱ። ዝ ውእቱ መክፈልቱ ለኃጥእ እምኀበ እግዚ ፡ (መክ፲ ፡ ፳፩። ዳን፬ ፡ ፲፪። ኢዮ፳ ፡ ፳፱)።
[2] ፡ ዕድል ፈንታ፤–ከፊል ከፈለ።
መክፈት ፡ ወገን ነገድ። መክፈተ እንስሳት መክፈተ ሰበእ ውእቱ፤ ወዘይሤኒ እመክፈተ ሰብእ ነቢያት እሙንቱ ፡ (ጊ ፡ ወ ፡ ሐ ፡ ገ፫)።
መክፌ [1] ፡ (አከፈ) ማጠቆ የልብስ ቤዛ፤ ታላቅ መንዲል እንደ ሞጣሕት ያለ ፥ ማበሻ መወልወያ። ከከፈየና ከአከፈ ከኹለቱ የተዴቀለ ነው። ነሥአ መክፌ ወቀነተ፤ ወመዝመዘ በውእቱ መክፌ ፡ (ዮሐ፲፫ ፡ ፬ ፡ ፭)
[2] ፡ ማበሻ ማጠቆ፤–ከፈየ።
መኰንን ፡ (ንንት) ዝኒ ከማሁ፤ በቁሙ። ኢትፍቅድ ከዊነ መኰንን። መኰንነ ጽድቅ። መኰንነ ምድር። መኰንና ለይሁዳ። እስመ መኰንንቶሙ ይእቲ ጥበብ ፡ (ሢራ፯ ፡ ፮። መዝ ፡ ፯። ኩፋ ፡ ፴። ኤር፳፪ ፡ ፴። ጥበ፯ ፡ ፲፪)።
(ጥ) መኰየ ፡ (ይሜኵ ይመኵ፤ መኵዮ፤ የመክሐ ቅጥይ። ዐረ መቀይ፤ መቃ፤ ዐቀበ) መከተ፤ ጠበቀ፤ ጋሸኛ ዘበኛ ኾነ። ተአዘዝኩ እፈኑ ሰብአ አፍራስ ወእግር እለ ያጸንዑ ብሔረ ወይሜኵዩ እምነ ፀርነ። አሕዛብ እለ ይሜኡ’ዩ ለእለ ውስተ ይሁዳ ፡ (፩ዕዝ ፡ ፭ ፡ ፷፱። ፰ ፡ ፶፩)። ሞከተ ሰነጋ፤ ሙክት አደረገ ፡ (ዐማርኛ)።
መኳንንት ፡ (ታት) በቁሙ፤ መኳንንቶች፤ ገዦች ፈራጆች፤ ሹማምት መምራን። መኳንንትሰ ኢኮኑ ግሩማነ ለዘይገብር ሠናየ። ተዘከሩ መኳንንቲክሙ ዘነገሩክሙ ቃለ እግዚ ፡ (ሮሜ፲፫ ፡ ፫። ዕብ፲፫ ፡ ፯)።
መወልድ ፡ (ድት ዲት፤ ዳን ዳት) የሚያስወልድ አሶላጅ፤ አዋላጅ ሐኪም
፡ (ዕር ፡ ኢሳ፲፩ ፡ ፲፬)። ሰሎሜ መወልዲት። መወልዳተ ዕብራውያት ፡ (ታም ፡ እየ። ዘፀ፩ ፡ ፲፭ ፡ ፳፩)።
መወልጥ ፡ (ጣን ጣት) ዝኒ ከማሁ፤ መንዛሪ፤ አንዱን ለብዙ ብዙውን ላንድ የሚለውጥ። ገፍትዐ ማእዳቲሆሙ ለመወልጣን ፡ (ማቴ፳፩ ፡ ፲፪። ማር፲፩ ፡ ፲፭። ዮሐ፪ ፡ ፲፬)።
መወድስ ፡ በቁሙ ማወደሻ ድርሰት መዝሙር ቅኔ ግጥም። ድርሰትየ ዘውእቱ መወድስ። ወመወድሱ ዕዝል ፡ (አዋል። ግንዘ)።
መዊቅ ቆት ፡ (ሞቀ ይመውቅ ይሙቅ። ሐመ፤ ረስነ) መሞቅ፤ መተኰስ ፥ ሙቀት መንሣት ማግኘት፤ ከፀሓይ ከእሳት ከልብስ ከደዌ፤ ማቅ ማለት ከዚህ ወጥቷል፤ ደመቀን እይ። ሶበ ሞቀ ፀሓይ። ወእምከመ ሞቀ ፀሓይ ይምሁ። ሐወዘኒ እስመ ሞቁ። ትትከደኑ ወኢትመውቁ። እምፀምረ አባግዕየ ሞቀ መታክፍቲሆሙ ፡ (፩ነገ ፡ ፲፩ ፡ ፱። ዘፀ፲፮ ፡ ፳፩። ኢሳ፵፬ ፡ ፲፮። ሐጌ፩ ፡ ፮። ኢዮ፴፩ ፡ ፳)። በሞቀ ፈንታ ተማወቀ ይላል፤ አያሰኝም
፡ (ኢሳ፵፬ ፡ ፲፮)።
መዊት ቶት ፡ (ሞተ ይመውት ይሙት። ዕብ ሜት። ሱር ሚት። ዐረ ማተ) መሞት መለየት፤ በነፍስ ከሥጋ በሥጋ ከነፍስ መራቅ ፥ እየብቻ መኾን ፥ መድረቅ መፍረስ መበስበስ፤ መነቀል መፍለስ፤ መጥፋት መታጣት። ሐዪውኒ ወመዊትኒ። ሞተ ዐማኑኤል ከመ ሞተ ዚኣነ ዘውእቱ ተፈልጦተ ነፍስ እምሥጋ። ሞትነ እምኀጢአት። ወሙት እምፍትወታቲሁ ለዝ ዓለም። እመ ሞተ አዕጹቂሁ። እለ ካዕበ ሞታ ወተሠረዋ። ሞተት ኅሊና እምኔሁ
፡ (ሢራ፲፩ ፡ ፲፬። ሃይ
፡ አበ። ሮሜ፮ ፡ ፪። ፊልክ ፡ ፫። ኢዮ፲፬ ፡ ፰። ይሁ
፡ ፲፪። ቄድር)።
መዊእ ኦት ፡ (ሞአ ይመውእ ይማእ) ማሸነፍ፤ መርታት፤ ድል መንሣት። ትእምርተ መዊእ። ወይን ይመውእ፤ አንስት ይመውኣ። ሞኦ ለሞት ወተንሥአ። ሞእክምዎ ለእኩይ ፡ (አፈ ፡ ተ፭። ዕዝ፫ ፡ ፲። ድጓ። ፩ዮሐ ፡ ፪ ፡ ፲፫)።
መዊጽ ጾት ፡ (ሞጸ ይመውጽ ይሙጽ። ዐረ ማጸ) መሟጨት መፋቅ፤ የጥርስ። መፈግፈግ መወልወል፤ መጥረግ ማጥራት፤ የድፍ የጕድፍ። መካስ ፥ ካሳ መስጠት፤ ቂምን በቀልን በካሳ ማጥፋት። ፡ (ተረት) ሲታረቁ ክሶ፤ ሲጸድቁ መነኵሶ።
መዋሕድ ፡ መስተዋሕድ፤ የሚያዋሕድ አዋሓጅ፤ አንድ አድራጊ።
መዋሥእት ፡ (ብዙ) መመለሾች። የዜማ መጽሐፍ ስም፤ ቃሉ በመዝሙር መካክል እየገባ የሚመላለስ፤ ግራና ቀኝ ኹነው መዘምራን የሚቀባበሉት፤ ለሙታን ለበዓል የተሠራ። መዋሥእት ዘፈላስያን ፡ (ግንዘ)።
መዋቲ ፡ (ቲት ትያን ያት) በቁሙ፤ የሞተ የሚሞት ሟች፤ ሥጋዊ ሰው። አንተ መዋቲ ዘከመ ዕሪናከ ምስሌነ፤ ወአንተ ኢመዋቲ ዘከመ ዕሪናከ ምስለ አብ። እመ ኮነ መዋቲ ካህነ። ተናገሮ በልሳነ መዋቲ ፡ (ሃይ ፡ አነ። ፍ ፡ ነ ፡ ፳፪። ቀሌ)።
መዋኢ ፡ (ኢት እያን ያት) ያሸነፈ ፥ የሚያሸንፍ፤ አሸናፊ። ሰላም ለከ አባዲር መዋኢ። ወኢሞኦ በኀይሊ መዋኢት። በእንተ ሰማዕታት መዋእያን ፡ (ስንክ ፡ መስ፳፰። መቅ ፡ ወን። ቅዳ)።
መዋዕልና ፡ ዘመንነት። ብሉየ መዋዕልና ፡ (ሃይ
፡ አበ)።
መዋጺ ፡ (ጺት ጽያን ያት) የማሟጭ ሟጪ፤ ካሽ ካሳ ሰጪ።
መውኀዲ መውኅድ ፡ የሚያጐድል አጕዳይ፤ አሳናሽ፤ ማጕደያ።
መውስድ ፡ (ብ መዋስድ) መውሰጃ፤ ዋስዳ፤ ዕቃ መሣሪያ።
መውዕይ ፡ (ያን ያት፤ ዪት ዒት) የሚያቃጥል አቃጣይ፤ ተኳሽ። እሳት መውዒት ፡ (ፊልክ ፡ ፻፸፫)።
መውፅኢ ፡ ዝኒ ከማሁ፤ የሚያወጣ፤ አውጭ። ማውጫ፤ መሣሪያ። መውፅኤ ዐይን ፡ (ስንክ ፡ ጥር፲፭)።
መዘምር ፡ (ርት ራን ራት) ዝኒ ከማሁ፤ ዘማሪ አዝማሪ፤ ባለበገና። በከመ ይቤ መዘምር። መዘምራን ወመዘምራት ፡ (መጽ ፡ ምስ። ዕዘ፪ ፡ ፷፭)።
መዘምው ፡ የሚያሴስን፤ ዝሙት የሚያስተምር፤ የሚያገብር።
መዘረ ፡ (መዚር፤ ሜሰ፤ ዐጸረ) ጠመቀ ዘለለ፤ ዐሸ አማሰለ፤ በጠበጠ ጣለ፤ የድፍድፍ የማር። መጸረን እይ፤ የዚህ መንቲያ ነው፤ መዘረ የጅ የመዳፍ ፥ መጸረ ያፍ።
መዘክር ፡ (ርት ራን ራት) የሚዘከር፤ የሚያዘክር አዘካሪ፤ ዐላቢ አሳሳቢ። ሹም፤ ቄላጤ፤ ምስክር። ኦ ድንግል አዘክሪ ኀበ መዘክር ዘኢይረስዕ ኵሎ ፡ (ቅዳ ፡ ሕር)። ጸሓፊ በማለት ፈንታ ጸሓፌ ታሪክ እንደ ማለት መዘክር ይላል፤ ምንም ምስጢሩ ቢገጥም ንባቡ ልዩ ነው
፡ (፪ነገ ፡ ፰ ፡ ፲፮። ፳ ፡ ፳፬። ፬ነገ ፡ ፲፰ ፡ ፲፰። ፴፯)።
መዘውር ፡ (ርት ራን ራት) ዝኒ ከማሁ፤ ዘዋሪ። በቁሙ፤ መኪና የሚዘወር።
መዘዝ ፡ ክፉ ነገር ፥ ያንደበት መርዝ ሰይፍና ዱላ የሚያማዝዝ ፡ (ዐማርኛ)።
መዘገ ፡ (ዐረ መዘጀ፤ አጋጨ። ዕብ ማዛግ፤ ቀዳ ቀላቀለ) አስቀና፤ አፈካከረ። በማሕዘ ዚኣከሙ ምዝጉ ኵልክሙ ፡ (፪ቆሮ ፬ ፡ ፪)።
፡ ነጠቀ መነጠቀ፤ ነቀለ ሳበ፤ በኀይል ወሰደ። ጸሎቱ ለኤልያስ ሰማየ መዘገ። ረድኤትከ ወለተ ከለባት መዘገ ፡ (ድጓ። ስንክ ፡ ታኅ፲፪)። መሠጠንና መጠቀን እይ፤ የዚህ ጎሮች ናቸው።
መዚዝ ዞት ፡ (መዘ፤ መዘዘ ይመዝዝ ይምዝዝ) መምዘዝ መንቀል፤ መንጠቅ፤ የሰይፍ የዱላ፤ ለሥርም ይኾናል፤ መልኀን እይ፤ ከዚህ ጋራ አንድ ነው። መዝመዘም ከዚህ ወጥቷል።
መዛሕም ፡ (ዐረ መዛሒም) ጹፉቅ ፥ ጽፍቀት ማለት ነው የሰውን ብዛት የቦታን ጥበት መላፋትንና መፋተግንም ያሳያል ፡ (ስንክ ፡ ሠኔ፲፱)።
መዛሪ ፡ (ሪት ርያን ያት፤ ዘርት) የጠመቀ የሚጠምቅ ፥ ጠማቂ ፥ ጠላ ቤት ፥ ጠጅ ቤት፤ መሻት መሸተኛ፤ ቀጅ ጂ ፥ አሳላፊ። መዛርያን ወመዛርያት። ሊቀ መዘርት
፡ (መክ፪ ፡ ፰። ኩፋ ፡ ፴፱)።
መዜንው ፡ (ውት ኑት ዋን ዋት) ዝኒ ከማሁ። ዛቲ መጽሐፍ መዜንወ ዘያስተፌሥሕ ትከውን ለከ። ከመ ንኩን መዜንዋነ ኄራነ ፡ (ፈላስ። ኪዳ)።
መዝሐ ፡ (ዐረ መዘሐ) ተላፋ ተዳራ፤ ተቃበጠ ፥ ተቀማጠለ። መሐዘንና ሐንቀቀን እይ፤ የዚህ ጎሮች ናቸው። መጽሐፍ ግን በመዝሐ ፈንታ አስተማዝሐ ይላል፤ አያሰኝም። እምከመ አስተማዛሕኮ ለወልድከ ፡ (ሢራ፴ ፡ ፬)።
መዝለል ምዝላል ፡ መሎጊያ፤ ደጓሳ ዕንጨት የሳንሳ የሚይዙበት። ድንባዝን እይ፤ ከዚህ ጋራ አንድ ነው፤ ባለብሉዮች ግን ቀፎ ባጥይ ይሉታል። ወጾርዎ ክልኤቱ በምዝላል ፡ (ዘኍ፲፫ ፡ ፳፬)።
መዝለፊ ፡ ዝኒ ከማሁ፤ አዘውታሪ። መዝለፌ ስካር ወእከይ። መዝለፊተ ተፀምዶ። ኩኑ ለጸሎት መዝለፍያነ ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፭። ፲ ፡ ፰። ፲፬)። የሚያዘልፍ የሚነቅፍ፤ ዘላፊ፤ አዘላፊ። ኮነነ መዝለፌ ኅሊናነ
፡ (ጥበ፪ ፡ ፲፬)።
መዝመዘ ፡ (መዚዝ መዘ። ዕብ ማዝሜዝ) መዘመዘ፤ ዐሸ አለፋ አለሰለሰ፤ ዐደፈ ወለወለ
፡ (ዮሐ፲፩ ፡ ፪። ፲፪ ፡ ፫። ፲፫ ፡ ፭)። ይመዘምዝዎሙ እምጸበለ ቤት። መዝመዙ ሥጋሆሙ በአጽርቅት
፡ (ተረ ፡ ኤር፲፪። ስንክ ፡ ኅዳ፩። ታኅ፲፪)።
መዝሙር [1] ፡ (ራት፤ መዛሙርት። ዕብ ሚዝሞር። ሱር ማዝሙራ። ዐረ መዝሙር) በቁሙ፤ ምስጋና ውዳሴ ጸሎት፤ መጽሐፈ ዳዊት፤ ከ፻፶ው ክፍላት አንዱም አንዱም ክፍል። መዝሙረ ዳዊት ትመስል ገነተ፤ መዝሙረ ድንግል፤መዝሙረ ክርስቶስ። በከመ ይቤ በውስተ መዝሙር ዘክልኤቱ ፡ (ደራሲ። ግብ፲፫ ፡ ፴፫)። ማመስገኛ ንዋየ ማሕሌት በገና ክራር ከበሮ ጸናጽል፤ የመሰለው ኹሉ። ንሥኡ መዝሙረ ወሀቡ ከበሮ፤ መዝሙር ሐዋዝ ዘምስከ መሰንቆ። በከበሮ ወበመዝሙር ይዜምሩ ሎቱ ፡ (መዝ ፡ ፹። ፻፵፰)። ዜማ ድምፅ ከሰው ከበገና የሚወጣ። ደረሰ ያሬድ መጽሐፈ መዝሙር። ትረክብ መዝሙረ ነቢያት። ወኢያጸምዕ መዝሙረ መሰንቆክሙ ፡ (ታሪ ፡ ነገ። ፩ነገ ፡ ፲ ፡ ፭ ፡ ፲። ዓሞ፭ ፡ ፳፫)።
[2] ፡ መዝሙር፤–ምስጋና በገና፤–ዘምሮ ዘመረ።
መዝረብ ፡ መምቻ፤ መቀጥቀጫ፤ ድሕንጻ መዶሻ። ነሥአት መትከለ ወመዝረበ። በሰፌልያ ወበመዝረብ አዕፅምቲከ ስቡር ፡ (አቡሻ ፡ ፵፯። ደራሲ)።
መዝራዕት [1] ፡ (ብ መዛርዕ። ዕብ ዝሮዐ። ሱር ዝራዕ። ዐረ ዚራዕ) ጡንቻ፤ ከመትከፍት እስከ ኵርናዕ ያለው መዠመሪያው ክፍል፤ አገዳው ቅልጥሙ። ፪ኛም የክንድ መሠረት ስለ ኾነ ክንድ ወርች ይባላል። እግዚኦ ልዑለ መዝራዕትከ ኢያእምረ። ተመጠውክዎ ዲበ መዝራዕትየ። ምዕራፈ መዛርዕ። መዛርዕ እለ ሥጋ። እገዳ ወመዝራዕተ ፡ (ኢሳ፳፮ ፡ ፲፩። ሆሴ፲፩ ፡ ፫። ፪ዜና ፡ ፬ ፡ ፲፰። ፴፪ ፡ ፰። ሕዝ፳፬ ፡ ፬)። እጅጌ፤ የቀሚስ እጀታ። መዛርዐ ቀሚሱ ፡ (ፈ ፡ መ ፡ ፴፩ ፡ ፭)።
[2] ፡ ክንድ ጡንቻ፤–ዘሪዕ ዘርዐ።
መዝርዕ [1] ፡ (ብ መዛርዕ) ቁፋ ቅርጫት፤ ላዳን ታላቅ የቤት ቍና። ቤዶ ቀረዋ፤ እንቅብ ጕርዝኝ ጕብ፤ ገበሬ ዘር የሚሰፍርበት የሚያኖርበት፤ ወይም በርሱ ይዞ የሚዘራበት የዘር መሣሪያ፤ ለሌላም ይኾናል። አግሐሡ ዘተርፈ ፍተታተ ዐሠርተ ወክልኤተ መዛርዐ ምሉአ ፡ (ማቴ፲፬ ፡ ፳። ፲፮)።
[2] ፡ (ብ መዛርዕ፤ ዓት። መሥርዕ፤ ሥራዕ ዓት። ዐረ ሺራዕ) የመርከብ ሸራ ከፈትለ ክታን የሚሠራ፤ ወፍራም ጥቅጥቅ ጥሩ ጠንካራ ረዥም ሰፊ ታላቅ መጋረጃ፤ ነፋስ እየሳበ መርከብ የሚያስኬድ። ዘሩ ሠርዐ ነው፤ ሥራዕን ተመልከት፤ ጣፊና መላሽ ሠን በዘ ለውጠው ዘርዐ ብለውታል። ወናሁ መዝርዐ ሐመርነ ሠናይት ወጽሪት። ንስፋሕ እንከ መዝርዐ ሐመርነ እንተ ይእቲ ኅሊናነ። ለትኩን እንከ መዝርዕነ ንጽሕተ ወጽሪተ ፡ (አፈ
፡ ተ፴፬)።
መዝበል ፡ (ልት፤ ታት) ፍግ ማፈሻ ግትቻ፤ ወይም መጣያ መቈለያ።
መዝበረ ፡ (ዲቃ ፡ ግ) ፈረሰ ተናደ፤ ተበተነ። መዝበረ ኵሉ አህጉር። መዝበርኪ ወወደቂ ወማሰንኪ። አሕየወ ምሥዋዐ ዘመዝበረ ፡ (ኢሳ፳፬ ፡ ፲። ፵፱ ፡ ፲፱። ፫ነገ
፡ ፲፪ ፡ ፴፪)። በመዝበ ፈንታ ተመዝበረ ይላል፤ አያሰኝም። ወተሐንጻ አብያተ ክርስቲያናት ዘተመዝበራ ፡ (ስንክ ፡ መጋ፳፯)።
መዝበር [1] ፡ (ራት፤ መዛብርት) ባድማ ባዶ፤ ፍራሽ ጠፍ፤ የተፈታና የፈረሰ አገር መንደር። ይትሐነጽ መዝበርከ። ንሕንጽ መዝበራ። እገብሮን ለአህጉሪክሙ መዝበረ
፡ (ኢሳ፶፰ ፡ ፲፪። ሚል፩ ፡ ፬። ዘሌ፳፮ ፡ ፴፩)።
[2] ፡ ፍራሽ፤–ዘቢር ዘበረ።
መዝበጥ ፡ (ብ መዛብጥ) መዝበጫ፤ መምቻ መነረቻ፤ በትር፤ ቅጣት ፡ (ገድ ፡ አዳ)።
መዝብሕ ፡ መዝብሕ፤ ፡ (ብ መዛብሕ) ማረጃ፤ ስለት የብረት መሣሪያ። የሚያርድ፤ ዐራጅ። የታረደ ዕርድ፤ ፍሪዳ መሥዋዕት። ወብሂሉቱሰ ስጡሕ አምጽአ ዘንተ እምሥርዐተ መዛብሕ ዘመሥዋዕት ፡ (አፈ ፡ ድ፯)።
መዝኖ ኖት ፡ (መዘነ ይሜዝን ይመዝን። ዐረ ወዘነ። ዕብ አዜን) መመዘን መለካት፤ ነገርን መሞከር፤ በሚዛን ዕውቀት ማነጻጸር፤ ደለወን እይ። መዝኖት ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፴፫)።
መዝከር ምዝካር ፡ ማሰቢያ፤ ማሳሰቢያ፤ ጊዜ ቦታ ምክንያት። መስ(ዝ) ከረምን እይ።
መዝገበ ቃላት ፡ መዝገበ ቃላት፤ የቋንቋ መጽሐፍ፤ ግስና ነባር።
መዝገብ ፡ (ብ መዛግብት) መዝገቢያ መክተቻ ማከማቻ፤ ዕቃ ቤት ሣጥን ጐታ ጐተራ ጕርጅ፤ ደልገን ድብኝት ጕስጕሻ፤ ማድጋ ፊቀን ገንቦ ጋን፤ የመሰለው ኹሉ። መዝገበ ንጉሥ። አርኀዉ መዛግብቲሆሙ። ያስተጋብእ ሥርናዮ ወስተ መዝገቡ። ወአባእክሙ ኵሎ ማእረረክሙ ውስተ መዛግብት። ምእት መዛግብተ ወይን ወመዛግብተ ቅብዕ ፡ (አስቴ፫ ፡ ፬። ማቴ፪ ፡ ፲፪። ሚል፫ ፡ ፲። ዕዝ፯
፡ ፳፪)።
፡ ድልብ፤ ቅምጥ ገንዘብ፤ የተደበቀ የተጠበቀ። ብከ መዝገብ ዘሥዩም ለከ ኀበ ልዑል። ረከበ መዝገበ። መዝገብ ኅቡእ ወክቡት ፡ (ሱቱ ፡ ዕዝ፮ ፡ ፶። ሢራ፮ ፡ ፲፬። ኢሳ፵፭ ፡ ፫)።
፡ በቁሙ፤ ደብተር የገንዘብ ወጪና ገቢ የሚጣፍበት። መዝገብ ይታይ እንዲሉ።
፡ የመጽሐፍ ስም፤ ታላቅ መጽሐፍ፤ ብዙ ነገር የተጣፈበት እንደ ድጓ ያለ። ይቤ ቄርሎስ በውስተ መጽሐፉ ዘይሰመይ መዝገብ ፡ (ሃይ ፡ አበ)።
መዝገነ ፡ (ዲቃ ፡ ግ) አመሰገነ፤ አሸገነ አዠገነ፤ ዠግና አደረገ፤ በቃል። መጽሐፍ ግን በመዝገነ ፈንታ አመዝገነ ይላል፤ አ ያማርኛ ነው። ንጉሥ ዐማፂ እመ ገበርከ ሠናየ ኢያመዘግነከ፤ ወለእመ አበስከ ይቀትለከ። ሑር ሐበ ካህን፤ ወአመዝገኖ። ኢያመዝገነ ጽጋዌነ ላዕሌሁ ፡ (ፈላስ ፡ ገ፹። ዮሴፍ)። ዘና ሰ ተወራራሾች ስለ ኾኑ ዐማርኛው ሰ ይላል። ሚዝትንና ኅብዝ(ስ) ትን ሰገነንኖ መስገነን እይ።
መዝገነ ምዝጋና ፡ ዘጊን ዘገነ።
መዝገን ፡ (ብ መዛግን ት) መዝገኛ ማፈሻ፤ ዕፍኝ ጥርኝ ውስጥ እጅ።
መዝግሕ ፡ (ብ መዛግሕ ት) መዝጊያ መቈለፊያ። ኀበ ብዙኅ በዋኢቱ በመዝግሕ አንብር። ይዘግሑ መዛግሐ። መዛግሕተ ድንግልና ኢበተከ ፡ (ሢራ፵፪ ፡ ፮። ኪዳ ፡ ገ፬። ተረ ፡ ቄር ፡ ፲፰)።
፡ ቢተዋ ማልደያ የጅ ቦራ። መዝግሕ ዘበመዝራዕቱ ፡ (፪ነገ ፡ ፩ ፡ ፲)።
፡ ጋሻ፤ አግሬ። መዛግሕተ ወርቅ
፡ (፪ነገ ፡ ፰ ፡ ፯)።
መዝጐለ ፡ ተመዝጐ፤ ተዘናጐለ፤ ተዘነጓጐለ። ተቃወመ ተከራከረ፤ ፍቅር አንድነት ዐጣ። ይቤ ለአርድእት እንዘ ይምዕድ ሰላመ እንቲኣየ አኀድግ ለክሙ፤ ከመ ወኢመኑሂ ኀበ ካልኡ ኢይትመዝጐል በሥርዐት ሠናየ አምልኮ አላ ዕሩየ ዘበአማን ያርእዩ ስብሐተ። ወኵሉ ይትመዘጐል ቃለ በበይናቲሁ በሃይማኖት ፡ (መጽ ፡ ምስ)።
መዝጐል [1]
፡ ዛጐልማ ዝንጕርጕር። ዛጐልማ ዶሮ እንዲሉ።
[2] ፡ ዛጐልማ፤–ዛጐል ዘጐለ።
መዠስጢ ፡ (ጽር ሜጊስቲ) የልዕልና የከበሬታ ስም፤ ልዑል ዐቢይ ክቡር ራስ ቢቶደድ ይህን የመሰለ ፡ (አቡሻ ፡ ፰)። ዖሜጋ እንዲል ታላቅ ዖ ሲል።
መዪስ ሶት ፡ (ሜሰ ይመይስ ይሚስ፤ ሜጠ። ዐረ ማሰ) መመሸት፤ መለወስ ማሸት፤ መበጥበጥ ማማሰል፤ መጠጀት መዘለል፤ የወይን የማር የድፍድፍ የቡሖ። ማዘንበል ማስጐንበስ፤ መመለስ፤ የጋን የመስኖ፤ ለሐሳብና ለልብም ይኾናል። መለሰን እይ፤ የዚህ ጎር ነው።
መዪን ኖት ፡ (ሜነ ይመይን ይሚን። ዐረ ማነ) አው መይኖ፤ ኖት፤ ፡ (መየነ ይሜይን ይመይን። መነየ) መተንኰል ፥ መጠበብ፤ ማወቅ መራቀቅ፤ ለግብር ለነገር መልክ ማውጣት ፥ ምሳሌ መስጠት። መክዳት ፥ መዋሸት ማበል፤ ማታለል መሸንገል። መተንኰል ለክፉም ለበጎም ይኾናል፤ ማእከላዊ ነው። መጽሐፍ ግን በመየነ ፈንታ እንዳማርኛው ተመየነ ይላል፤ ስሕተት ነው፤ ተ አለቦታው ገብቷል። ቦ ሰብእ ዘበኵሉ ይትሜየን ወብዙኀ የአምር። ተመይኖ ግብር፤ ተተነኰለ ተጠበበ ፡ (ሢራ፴፯ ፡ ፲፱። ፈላስ ፡ ገ፲፯)። ይትሜየኑ ወይገብሩ ትምይንተ። ከመ አልቦ ዘይትሜየን ላዕለ ዳንኤል። ተመየኖሙ ከመ ይቅትሎሙ። በብዙኀ ተመይኖ። እለ ይትሜየንዎ ለቃለ እግዚ፤ ከዳ ሸነገለ ፡ (ኤር፱ ፡ ፯። ዳን፮ ፡ ፲፯። ፬ነገ ፡ ፲ ፡ ፲፱። አስቴ፰ ፡ ፲፫። ቀሌ)።
መዪጥ ጦት ፡ (ሜጠ ይመይጥ ይሚጥ። ሦጠ፤ ሜሰ፤ ወለጠ) መመለስ ፥ መቀለስ፤ ማዞር። ኢትሚጥ ገጸከ እምኔየ። ሜጡ ዘባኖሙ ኀቤየ። ሚጥ ሎቱ ካልእታሂ
፡ (ጦቢ፫ ፡ ፮። ኤር፪ ፡ ፳፯። ማቴ፭ ፡ ፴፱)።
፡ መለወጥ መገልበጥ
፤ ሌላ ማድረግ ፤ የባሕርይ የግብር። ኢትሚጥ ብፅዐተከ። ኢትሚጥ
ፍትሐ። እመሂ መከርክሙ ምክረ ይመይጦ እግዚ። ዘሜጦ ሰማይ ወረሰዮ ጼወ።
ሚጦ ለዝንቱ ኅብስት ከመ ይኵን ሥጋከ (ሢራ፯ ፡ ፲፬። ዘፀ ፡ ፳፫ ፡ ፮። ኢሳ፰ ፡ ፲። ሢራ፴፬ ፡ ፴፫። ቅዳ)። ይመውእ ያደክም በማለት ፈንታ ይመይጥ
ይላል ፤ የመላሽ ስሕተት ነው
(ዘፀ፲፯ ፡ ፲፫)።
መያሲ ፡ (ሲት ስያን ያት) መሻት መሸተኛ፤ የሚጠጅ የሚጠምቅ የሚዘልል፤ በጥባጭ ዐረቂ አውጭ። እለ ይገይሡ በጽባሕ ቤተ መያሲ። ወኢይጸድቅ መያሲ እምዐመፃ። መያስያን እለ ይቶስሑ ማየ በወይን። ለብሰ ልብሰ መያስያን ፡ (ኢሳ፭ ፡ ፲፩። ሢራ፳፮ ፡ ፳፱። ፈ ፡ መ ፡ ፳፮ ፡ ፪። ዮሴፍ)። መይሳ፤ መላሽ አስመላሽ።
መያጢ ፡ (ጢት ጥያን ያት) የመለሰ ፥ የሚለውጥ፤ መላሽ ለዋጭ፤ ገልባጭ። መያጢሃ ለነፍስ። መያጢሆሙ ለፂውዋን። መያጤ ልሳን ፡ (ኪዳ። ሃይ ፡ አበ። ምሳ፲፯ ፡ ፳)።
መይኖ ኖት ፡ (መየነ ይሜይን ይመይን። መነየ) መተንኰል ፥ መጠበብ፤ ማወቅ መራቀቅ፤ ለግብር ለነገር መልክ ማውጣት ፥ ምሳሌ መስጠት። መክዳት ፥ መዋሸት ማበል፤ ማታለል መሸንገል። መተንኰል ለክፉም ለበጎም ይኾናል፤ ማእከላዊ ነው። መጽሐፍ ግን በመየነ ፈንታ እንዳማርኛው ተመየነ ይላል፤ ስሕተት ነው፤ ተ አለቦታው ገብቷል። ቦ ሰብእ ዘበኵሉ ይትሜየን ወብዙኀ የአምር። ተመይኖ ግብር፤ ተተነኰለ ተጠበበ ፡ (ሢራ፴፯ ፡ ፲፱። ፈላስ ፡ ገ፲፯)። ይትሜየኑ ወይገብሩ ትምይንተ። ከመ አልቦ ዘይትሜየን ላዕለ ዳንኤል። ተመየኖሙ ከመ ይቅትሎሙ። በብዙኀ ተመይኖ። እለ ይትሜየንዎ ለቃለ እግዚ፤ ከዳ ሸነገለ ፡ (ኤር፱ ፡ ፯። ዳን፮ ፡ ፲፯። ፬ነገ ፡ ፲ ፡ ፲፱። አስቴ፰ ፡ ፲፫። ቀሌ)።
መደምም ፡ (ምት ማን ማት) የሚያስደምም የሚያስገርም፤ አስደናቂ። ከርሠ መቃብር ታችኛው ውስጡ የሬሳው ቤት። ሺዎች ግን መደንን ይሉታል፤ ራስ የሚያስደንን፤ ቀባሮችና አስቀባሮች በአድንኖተ ርእስ የሚያዩት ማለት ነው ፡ (ዐማርኛ)።
መደረ [1] ፡ (ይመድር ይምድር። ዐረ መዲረ) ሰፋ፤ ረዘመ፤ ወፈረ። ስፋት የወርድ ፥ ርዝማን የቁመት ፥ ወፍር የወል የመካከል። ብሕረን ተመልከት ፥ የዚህ መንቲያ ነው፤ ብሕረ የባሕር ፥ መደረ የየብስ።
[2] ፡ መደረ፤ ፡ (ዐረ ረከዘ) በቁሙ፤ ወጋ ቸከለ፤ ምድር ያዘ ተመረኰዘ፤ ከምድር ወረደ ተጠጋ፤ የብስ ረገጠ፤ የቀዛፊና የመርከብ የባለታንኳ።
መደባዊ ይ ፡ መደበኛ፤ መደባም ባለመደብ፤ የመደብ። ባላባት ዋና ደቀ መደባይ
፡ (ገድ ፡ ተክ)።
መደቤና ፡ (ዕብ ማድሜና) ስመ ሀገር የብንያም ክፍል ፡ (ኢሳ፲ ፡ ፴፩)።
መደብ [1] ፡ (ዕብ ዐሩጋ፤ ዐዛራ) በቁሙ፤ ዕርከን ምዕራግ፤ መውጫ መወጣጫ ስፋትና ከፍታ ያለው፤ ላታክልትም ይነገራል ፡ (ሕዝ፲፯ ፡ ፲። ፵፫ ፡ ፲፬ ፡ ፲፯ ፡ ፳)። ደመ ቅሥፈቱ ያርሕስ መደበ። ተፈትሑ ኵሉ አራዊት ወበልዑ ስጕርንደ ሰማንያ መደበ ፡ (ስንክ ፡ ጳግ፬። ገድ ፡ ተክ)።
፡ የርባታ ክፍል ዐሥሩ ሰራዊት ወይም መራሕያን።
[2] ፡ በቁሙ ዕርከን፤–ደይቦ ደየበ።
መደንግፅ ፡ (ቅጽልና ጥሬ) የሚያስደነግጥ የሚያስፈራ፤ አስፈሪ አስደንጋጭ። ወይን መደንገፅ። መብረቅ መደገንፅ ፣ ፀዓዕ መደንገፅ። መኳንንተ ምድር መደንግፃን ፡ (መዝ ፡ ፶፱።ዮሴፍ። ኢዮ፴፯ ፡ ፬። ጥበ፰ ፡ ፲፬። ማሕ፮ ፡ ፬ ፡ ፲)።
፡ ማደንገጫ ማስደንገጫ፤ ማስፈሪያ ማስፈራሪያ። በመደንገፅ ዐቢይ ፡ (ዘዳ፬ ፡ ፴፬)።
መደደ ፡ መደ፤ ፡ (ትግ ወዐረ) ዘረጋ፤ መደመደ አስተካከለ፤ ያውድማ የቤት። ሜዳ መደዳ ማለት ከዚህ ወጥቷል። መአደን እይ፤ የዚህ ጎር ነው።
መዲና [1] ፡ (ናት) በቁሙ፤ ታላቅ ከተማ መናገሻ፤ ፍርድ የሚቈረጥበት፤ በይግባኝ የሚኬድበት። ቆሮንቶስ ልህቅተ አካይያ እንተ ይእቲ መዲና። ወገብረ መዲናሁ በጐንደር። ወኢወፅአ እመዲናሁ
፡ (አዋል። ታሪ ፡ ነገ)።
[2] ፡ መዲና፤–በቁሙ ከተማ፤–ደይኖ ደየነ።
መድኀፂ ኅፅ ፡ የሚያድጥ የሚያሰናክል አሰናካይ። እሬኢ መድኀፂነ ፡ (ሱቱ ፡ ዕዝ፰ ፡ ፳፪)።
መድሔ ፡ (ብ መዳሕይ) መፍጫ፤ መጅ፤ የወፍጮ ልጅ፤ ወይም ግልገል። መድሔ ማሕረጽ። እመ ኮነ ሰማይ መድሔ ወምድርኒ ማሕረጸ
፡ (ዘዳ፳፬ ፡ ፮። አርጋ ፡ ፫)።
መድኅር ፡ (ርት ራን ራት) ቅጽልና ጥሬ። የሚመርቅ መራቂ፤ የሚያቈይ የሚያዘገይ፤ ቅጽል። ምርቃት ፥ በረከት ምስጋና ብፅዓን፤ ጥሬ። መድኅረ አብ። መርገመ ወመድኅር። አቅረብነ ለክሙ መርገመ ወመድኅረ ፡ (ሢራ፫ ፡ ፱። ፪ቆሮ ፡ ፮ ፡ ፰። ቀሌ)።
መድኀኒት ፡ (ታት) በቁሙ፤ መዳኛ ማዳኛ መዳኒት ፈውስ፤ የሚያድን። መድኀኒት በዘይትፌወስ ቍስል። ጸሎትሰ መድኀኒት ይእቲ። መድኀኒተ ዓለም ኮነ ደመ ጽጌኪ ክርስቶስ። ጌራ መድኀኒት። መድኀኒታት
፡ (አርጋ። አፈ ፡ ተ፳፯። ደራሲ።ኢሳ፶፱ ፡ ፲፯። ግንዘ)። ድኂን ድኅነት በማለት ፈንታ መድኀኒት ይላል ፡ (፩ነገ ፡ ፲፩ ፡ ፱። ፩ጴጥ ፡ ፱)። መሥዋዕተ መድኀኒት። ዘይፈቅድ መድኀኒት እምኀጣውኢሁ
፡ (ዓሞ፭ ፡ ፳፪። ፈ ፡ መ ፡ ፪ ፡ ፭)።
መድኅን ፡ ዝኒ ከማሁ፤ የሚያድን አዳኝ፤ በቁሙ መድን ዋስ ተያዥ ቤዛ ነጻ አውጭ። እምጽዮን ይወፅእ መድኅን። መድኅነ ዓለም። ተወልደ ለክሙ ዮም መድኅን። ውስተ ዘመድኅን መርሶ። ወልቃሕሰ ይደሉ ከመ ይኩን በአኀዝ አው በትሕቢት አው በመድኅን፤ አው በመጽሐፍ እንተ ውስቴታ ሰማዕት። መድኅነ ኮነ ሎቱ። ወለብእሲት ኢይትወከፉ እምኔሃ መድኅነ ወኢተሐብዮ
፡ (ሮሜ ፲፩ ፡ ፳፮። ዮሐ፬ ፡ ፵፪። ሉቃ፪ ፡ ፲፩። ስንክ
፡ ፲፩። ስንክ
፡ ጳግ፩። ፍ ፡ ነ ፡ ፳፯)።
መድለው ፡ (ብ መዳልው) አው መድሎት፤ ፡ (ታት) መመዘኛ ማስተካከያ፤ ሚዛን ደንጊያ ልክ፤ ብዙ ስምና ክፍል ያለው። መድሎተ ሰቅል። መድሎተ ልጥር። ወተረክበ መድሎተ ውእቱ አክሊል መክሊተ። መዳልው ዐቢይ ወንኡስ። መዳልወ አልባብ። መዳልወ ፀሓይ
፡ (ዘፀ፴፱ ፡ ፪። ስንክ ፡ ሚያ፫። ፩ዜና ፡ ፳ ፡ ፪። ምሳ፳ ፡ ፫። ስንክ ፡ ጥቅ፩። ክብ ፡ ነገ)።
መድመፅ ፡ በቁሙ፤ መዳመጫ መራመሚያ፤ የደንጊያ የገል፤ ሲዳምጥ ድምጥ የሚሰጥ።
መድምሕ ሕት ፡ (ብ መዳምሕ፤ ሕት) መጥለቂያ መቅጃ መጨለፊያ፤ ማጥሪያ፤ ታናሽ ጻሕል፤ መንካ ዕርፈ መስቀል የማእድና የምሧዕ መሣሪያ። ወገብረ ንዋየ ማእድ አጽሕለ ወመዳምሐ። መዳምሕት ዘቤተ ምሥዋዕ። መጥዎተ ደሙ ለክርስቶስ በመዳምሐ ወይን ዘውእቱ መንካ
፡ (ዘፀ፴፰ ፡ ፲፪። ፪ዜና ፡ ፬ ፡ ፲፩። መጽ ፡ ምስ)።
መድምም ፡ (ማት) ዝኒ ከማሁ፤ ቅጽልና ጥሬ። እጅግ የሚድንቅ፤ የሚደነቅ፤ የሚያስደንቅ ታላቅ ድንቅ ግሩም፤ ታምር አምላካዊ ግብር። መድምም ውእቱ ሥና ፈድፋደ ቅድሜሆሙ። መድምም ኀይሉ። እስመ መድምም አንተ እግዚኦ። ገበርከ ኵሎ መድምመ ዘመትሕተ ሰማይ። በኵሉ መድምምየ ዘእገብር። ዝኩ ተኣምር ወመድምም ዐቢይ። መድምማት ፡ (ዮዲ፲ ፡ ፲፬። መሳ፲፮ ፡ ፲፫። አስቴ፭ ፡ ፪። ፬ ፡ ፲። ዘፀ፫
፡ ፳። ዘዳ፳፱ ፡ ፪። ቅዳ ፡ ኤጲ)።
መድረክ ፡ (ብ መዳርክ) በቁሙ፤ መረጋገጫ ከመዝጊያ በታች የሚጋደም። መድረከ ኆኅቱ። ኀበ መድረከ ኆኅትክሙ። መዳርክ ወመሳክው ፡ (ሢራ፮ ፡ ፴፮። ያዕ፭ ፡ ፱። ሕዝ፵፩ ፡ ፲፮)።
መድረወ ፡ ከምድር አገባ፤ ከተተ ቀበረ፤ ፈጸመ ጨረሰ ፥ አከናወነ፤ ያዝመራ የሥራ። ገመረን እይ፤ የዚህ ጎር ነው።
መድቀቅ ት ፡ ማድቀቂያ፤ ማላሚያ መደቈሻ። ወያደቅቅዎ በመድቀቅ ፡ (ዘኍ፲፩ ፡ ፰)።
መድቅሕ ፡ (ብ መዳቅሕ) መድቂያ መደሰቂያ መምቻ፤ መዶሻ መብሻ። ማደሻ መቀደሻ መመረቂያ፤ ቅዳሴ በዓል
፡ (ዘኍ፯ ፡ ፲። ዘዳ፳ ፡ ፭። ዳን፫ ፡ ፪። ፫ነገ ፰ ፡ ፷፮)። ወገብሩ መድቅሐ ቤተ እግዚ በትፍሥሕት። ወአብኡ ለመድቅሐ ቤት ምእተ አልሕምተ ፡ (ዕዝ፮ ፡ ፲፮ ፡ ፲፯)።
መድበል [1] ፡ ማከማቻ መከማቻ፤ መሰብሰቢያ መዶለቻ፤ ሸንጎ ጉባኤ የሰው መንጋ። መድበለ ማኅበር። መድበለ ቅዱሳን አኀው። አዘዙ ይግበሩ መድበለ። ለእለ ምስሌሁ መድበል ፡ (ማሕ፯ ፡ ፩። ስንክ ፡ ሠኔ፲፮። ሚያ፲፯። መስ፱)። የቅጽል ስም ወንዶችና ሴቶች የሚያስተባብር፤ ቀደምት፤ ደኀርት፤ ገበርት፤ ቀተልት፤ ይህን የመሰለ።
[2] ፡ ክምቹ፤–ደቢል ደበለ።
መድበራ [1] ፡ (ዕብ ሚድባር) ዱር የከብት መስምሪያ፤ ብዙ ሣር ቅጠል ውሃ ያለበት። ወይም በጭራሽ ምናምን የሌለው ደረቅ በረሓ፤ ምድረ በዳ። ገዳም ዘመድበራ። ማእከላ ለደብረ መድበራ ፡ (ኢያ፭፤ ፮። ሔኖ፳፱ ፡ ፩)።
፡ መድበል ማኅበር፤ ጉባኤ አንድነት። ይገብሩ መድበራ ፡ (ሔኖ፸፯ ፡ ፯)።
[2] ፡ መድበራ፤–ዱር በረሓ፤–ደቢር ደበረ ፥ ደብር።
መድብራይጥስ ፡ (ጽር ማብዳሪቲስ። ዕብ ሚድባራ) ጠፍ ባዶ ባድማ፤ የዱሮ ከተማ፤ የተፈታ አገር፤ ዱር ጣሻ፤ በረሓ የኾነ። መድብራይ ጥስ ዘቤቶን ፡ (ኢያ፲፰ ፡ ፲፪)።
መድክም ፡ (ምት ማን ማት) የሚያደክም፤ አድካሚ። ዛቲ ግብር መድክምት ጥቀ ፡ (ፊልክ ፡ ፳፫)።
መድጐጽ ፡ (ብ መዳጕጽ) መውጊያ መጓጐጫ አርቃሾ ችንካር፤ የእንስሶች መንኪያ መጠቈሚያ። ነገረ ጠቢባን ከመ መድጐጸ ላሕም ፡ (መክ፲፪ ፡ ፲፩)።
፡ በቁሙ፤ ማሥመሪያ፤ ማሰንበሪያ አፈ ዱልዱም ወስፌ፤ መድጐስ የድጕስ መሣሪያ በየስሙና በያይነቱ። መግለድን ተመልከት።
መድፍን ፡ (ብ ፡ መዳፍንት) የተቀበረ ወርቅ፤ ገንዘብ። ከመ መድፍን ክቡት። ረኪበ መድፍን። መድፍን ኅቡእ ውስተ ገራህት ፡ (ሢራ፳ ፡ ፴። ፵ ፡ ፲፰። ማቴ፲፫ ፡ ፵፬)።
መድፍዕ ፡ (ብ ፡ መዳፍዕ) በቁሙ፤ መድፍ ታላቅ ዕውቅ የጦር መሣሪያ፤ ሲተኰስ እንደ መብረቅ የሚጮኽ የሚነጕድ፤ ዐረሩ ርቆ የሚኼድ። ወተንሥአ ግራኝ በእግረ ትዕቢት እንዘ ይትአመን በመድፍዕ ወበቱርክ ፡ (ታሪ ፡ ነገ)። የምጣድ ሞግድ፤ አክንባሎ መክደኛው።
፡ መዳና የእጅ ተረከዝ።
፡ (ተረት) አፈኛ ባፉ፤ ኀይለኛ በመዳፋ።
መጅ ፡ ፫ኛ ክፍል ፍትሐ ነገሥት። መጅ ዘውእቱ ነገሥት ሣልስ ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ መቅ)። በቁሙ የወፍጮ ግልገል ፡ (ዐማርኛ)።
መገሥጽ ፡ (ጽት ጻን ጻት) ዝኒ ከማሁ፤ ገሣጺ
፡ (፩ጢሞ ፡ ፫ ፡ ፪። ሆሴ፭ ፡ ፪)። አብ መገሥጽ። መምህር ወመገሥጽ ዘአልሀቀ ደቂቆ በንጽሕ ፡ (ጥበ፲፩ ፡ ፲፩። ዲድ ፡ ፬)።
መገን ፡ (ብ አምጋን። ዕብ ማጌን) ጋሻ ፥ አግሬ። በዳዊት ጋሻ አምሳል የተሠራ የአይሁድ ንሻን፤ ማኅተመ ሰሎሞን። የኢትዮጵያም ሽልማትና ትእምርተ መንግሥት ከዚህ ጋራ አንድ ነው።
መጕረጽ [1] ፡ (ጻት፤ መጓርጽ) መብጫ መጋረጫ፤ ጋሬጣ ሥንጥር። ማጕርጥ የጥፍር ዐይነት ሹል ስል፤ መውጊያ ቸክ ጠቅ ማድረጊያ። አራዊት መሣጥያን እለ ቦሙ ጽፍራት ወመጕረጽ ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፳፫)።
[2] ፡ ማጕርጥ፤–ጐሪጽ ጐረጸ።
መጋቢ ፡ (ቢት ብያን ያት፤ ገብት) በቁሙ፤ የሚመግብ የሚጠብቅ፤ ጠባቂ ሹም፤ አዛዥ ቤታባት፤ ምስለኔ እንደራሴ፤ ወኪል ሞግዚት፤ መሪ አስተማሪ። መጋቤ ቤተ ንጉሥ። መጋቤ ሀገር። መጋብያነ ሕግ። መጋቤ ኵሉ። መጋቢት ፡ (ኢሳ፳፪ ፡ ፲፭። ሮሜ፲፮ ፡ ፳፫። ዳን፲፩ ፡ ፳፪። ቅዳ። ስንክ ፡ መጋ፳፮)። መገብተ አብያተ ንጉሥ። ተሠይሙ መገብተ ላዕለ ኵሉ ጥሪቱ። መገብተ ምኵራብ [ዕዝ፰ ፡ ፷፬። ፩ዜና ፡ ፳፯ ፡ ፴፬። ግብ፬ ፡ ፩)።
መጋቢት ፡ በቁሙ፤ ስመ ወርኀ ሳብዕት እመስከረም፤ የመዓልትና የሌሊት ምግብና እንደ መስከረም ትክክል የሚኾንባት ወርኀ ዕሪና ማለት ነው። እስመ ይዔሪ መዓልት ወሌሊት አመ ዕሥራ ወኀሙሱ ለወርኀ መጋቢት ፡ (ዲድ ፡ ፴)። ካያ ዐምስት ያለው የዱሮውን ነው፤ ዛሬ ግን በደቃይቅ ቍጥር ፬ ቀን ወደ ታች ወርዶ አመ ዕሥራ ወአሚሩ ኹኗል። በኛም ብተት አመ ዐሡሩ ወሠሉሱ፤ ወይም ወረቡዑ ይኾናል።
መግ ፡ የመጽሐፍ ስም፤ ፬ኛው ክፍል ፍትሐ ነገሥት። መግ ዘውእቱ ነገሥት ራብዕ ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ መቅ)።
መግለ አው መገለ ፡ (ዐረ መጀለ። ዕብ ማጌል) መግል ያዘ፤ ዐበጠ። መገለ፤ ፈረጠ። ጸልዕ ዘይመግል ፡ (ኢሳ፩ ፡ ፮)።
መግለድ ፡ (ብ መጋልድ) መድጐስ፤ መደጐሻ፤ የድጕስት ዕቃ መሣሪያ፤ ፱ ዐይነት። ርእሰ መድጐስ ፫። መሳቢያ የድጕሱ ኹሉ መከፈፊያ ፩። ዐይነ ርግብ ትንሽና ትልቅ ፪። ቀርነ በግዕ ፩። የውሃ እናት ፩። ፍየል ፈለግ ፩። ድሙር ፬። በነዚህ ላይ ደግሞ ፮። ጨምረው ፲፭ የሚሉ አሉ፤ መደበኞቹ ግን ዘጠኝ ናቸው፤ የቀረው ትርፍ ነው።
መግል ፡ (ብ አምግልት) በቁሙ፤ ካበጠ ከቈሰለ ገላ የሚፈስ ነጭ እድፍ። ለእመ ኮነ ቍስል ዕሙቀ ወምሉአ መግል ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፭። ስንክ
፡ ነሐ፫)። ቍስለ መቅሠፍት ይገብር አምግልተ ፡ (ሢራ፳፰ ፡ ፲፯)።
መግረምት ፡ ማስፈሪያ ማስፈራሪያ፤ መስፈራርቾ። ወይከውኖሙ ለእግብጽ መግረምቶሙ ብሔረ ይሁዳ ፡ (ኢሳ፲፱ ፡ ፲፯)።
መግበር ት ፡ (ብ መጋብርት) መሥሪያ መሣሪያ፤ ዕቃ። ኵሉ ግብሩ ወኵሉ መጋብርቲሁ። ለመጋብርት ፡ (ዘፀ፳፯ ፡ ፲፱። ፴፱ ፡ ፲ ፡ ፳፩። ሕዝ፲፭ ፡ ፫)።
መግቦ ቦት ፡ (መገበ ይሜግብ ይመግብ) መመገብ ፥ መቀለብ፤ ማብላት ማጠጣት፤ ምግብ መስጠት ፡ (ዐማርኛ)። መጠበቅ ፥ መከናከን፤ መክበብ ፥ ለመጠበቅ። ይሜግቡ በጽድቅ መንበሮ። ኢይክል ሠሪዐ መንግሥት ወመግቦታ። ዘይሜግብ ንዋያ ለድክትምት። ይሜግብዋ ወየዐውድዋ። ሣህል ይሜግቦሙ። ይሜግብ ሕዝቦ ፡ (ምሳ፳ ፡ ፳፰። ዮሴፍ። ፍ ፡ ነ ፡ ፳፬ ፡ ፫። ፪ዜና ፡ ፬ ፡ ፫። መዝ ፡ ፴፩። ፻፳፬። ዘዳ፴፪ ፡ ፲)።
፡ መምራት ማስተማር፤ በሥራት ማስኬድ። ምስጢሩ ከዚያው ከመጠበቅ ይገባል። ነፍስ እስርት በሥጋ ከመ ትመግቦ ወትሥራዕ ሕይወቶ። ይሜግባ ለሐመር
፡ (ዮሌፍ። መጽ ፡ ምስ)።
መግነዝ ፡ (ብ ፡ መጋንዝ) በቁሙ፤ መገነዣ የውስጥ የአፍኣ ልብስ ፈትል፤ ሽቱ ሣጥን ለሬሳ የሚገባ ኹሉ። አዘዘ እስክንድር ከመ ይግንዝዎ ለዳራ በሠናይ መግነዝ። ኢሠነቀ እምንዋይከ ዘእንበለ መግነዝ። ኵሉ መፍቅዶ መግነዝ። ገነዘቶ በለልባስ ሠናያት ወገብረት ሎቱ መልዕልተ መግነዙ ልብሰ ዘወርቅ ወአንበረቶ በሣጹን። ጠብለለ ልደቶ በመግነዘ ኅቡኣቲሁ ከመ ኢያእምርዎ ፍጡራን ፡ (ዮሴፍ። ግንዝ። ገድ ፡ ላሊ። ስንክ ፡ ሐም፳፪። መጽ ፡ ምስ)።
መግእዝ ፡ (ዝት ፡ ዛን ዛት) ዝኒ ከማሁ፤ ነዝናዛ ዘብዛባ፤ ጓረኛ ነገረኛ። ጕጉእ ወመግእዝ፤ ዐርክ መግእዝ። ብእሲት መግእዝት ፡ (ምሳ፳፩ ፡ ፳፬። ፱ ፡ ፲፫። ዲድ ፡ ፫)።
መግዌ [1] ፡ (ዕብ ግዊያ፤ ገላ በድን ሬሳ) ጥራዝ የመጽሐፍ ነዶ ገና ያልተሰፋ ያልጠረዘ። በውኁድ መግዌ ፡ (አዋል)።
[2] ፡
ጥራዝ የመጣፍ ነዶ፤–ጎግዎ ጎገወ።
መግዘዝ ት ፡ (ብ መጋዝዝ) መጋረጃ ዐጥር ቅጥር፤ ከለላ ጀጐል፤ ጋራ ተራራ ገመገም። መገዘዝ ማለት ከዚህ የወጣ ነው። ፡ (ግጥም) ጣርማ በር ኹኜ ታየኝ መገዘዝ፤ ልቤ ለቡልጋ ዐደር ሲጋበዝ።
መግዘፊ ዝፍ ፡ የሚያገዝፍ አግዛፊ፤ አሥቢ አወፋሪ።
መግዘፍ ፡ መግዘፊያ ማግዘፊያ፤ ማወፈሪያ። ግዘፍ፤ ወፍር። ሲናበብ የቅጽል አፈታት ይፈታል። በመግዘፈ ምድር፤ ከመ ግዝፈ ምድር፤ ግዙፍ ፡ (፪ዜና ፡ ፬፤ ፲፯)።
መግዝም ፡ መቍረጫ ገዝሞ ጕድብ። ገዛሚም ይኾናል።
መግዝእ [1] ፡ (እት ኣን ኣት) ዝኒ ከማሁ፤ ገዥ ዐዳይ ቀላቢ፤ ሐፃኒ መጋቢ ሞግዚት።
[2] ፡ እት፤ ፡ (ብ መጋዝእ ኣት፤ መጋዝእት ታት) ፍሪዳ፤ ሰንጋ ድልብ ቅልብ፤ ኰርማ ገች ሙክት፤ የሥጋ ከብት። አምጽኡ መግዝአ ላሕም ወጥብሑ። አልሕምት መጋዝእ ወመጋዝአ ደዋርህ። ጠባሕኩ መጋዝ እትየ ፡ (ሉቃ፲፭ ፡ ፳፫። ፫ነገ ፡ ፬ ፡ ፳፫። ማቴ፳፪ ፡ ፬)።
[3] ፡ መግዝእ፤–ገች ፍሪዳ፤–ገዚእ ገዝአ።
መግዝዕ ፡ (ብ መጋዝዕ ዓት) መጋዝ፤ መገዝገዣ መቍረጫ መተርተሪያ። አዘዘ ይሥትርዋ በመጋዝዕ ወተሰብረ መጋዝዕ ፡ (ስንክ ፡ ጥር፳)።
መግድም ፡ (ምት ማን ማት) የሚያገድም አግድሞ የሚያይ፤ ጠማማ ፀዋግ፤ አግድሞ አደግ። ወሶበ ተናገረ ምስሌሆሙ ረከቦሙ ዓለማውያነ መግድማነ ፡ (ፊልክ ፡ ፸፱)።
መጐጸ ፡ (ደጐጸ መድጐጽ) ተቈጣ ዘለፈ፤ ነጠበ ነቀፈ። መጽሐፍ ግን በመጐጸ ፈንታ አመጐጸ ይላል፤ አያሰኝም። ሊቃናተ ኢታመጕጽ። ዘይመጕጽ ሊቃናተ
፡ (፩ጢሞ ፡ ፩። ቀሌ)።
መጠራ ፡ (ዕብ ማጣራ) ማንጠሪያ ማነጣጠሪያ የቀስተኛና የነፍጠኛ ዐላማ ፥ ወይም ይላማ፤ ፍላጻው ዐረሩ ሲነደፍ ሲተኰስ የሚያርፍበት፤ እንደ ጊጤ ያለ በሩቅ በአንጻር ፊት ለፊት የቆመ የተተከለ። ባለብሉዮች ግን ለይተው ትከሻ ብራኳ መጋፊያ ይሉታል። እነድፍ አሕጻ ኀበ መጠራ ፡ (፩ነገ ፡ ፳ ፡ ፳። ሰቈ፫ ፡ ፲፪። ኢዮ፲፯ ፡ ፲፪)።
መጠር ፡ (ዐረ። ዕብ ማጣር። ሱር ምጣር) ዝናብ የውሃ ሕንባብ ፥ ነጠብጣብ፤ ከላይ ከአየር ከቀስተ ደመና የሚነደፍ የሚወነጨፍ።
መጠቀ [1] ፡ (መጢቅ። ዐርገ ለዐለ፤ ኖኀ) በቁሙ፤ ምድር ለቀቀ ፥ ከምድር ራቀ፤ ረዘመ። ምድር መልቀቅ ያሞራ የወፍ፤ መርዘም የሕንጻ የዛፍ።
[2] ፡ (መዘገ፤ መሠጠ) ነጠቀ መነጠቀ፤ ከፍ አደረገ አነሣ፤ ሳበ ጐተተ፤ አዳነ አወጣ፤ ራሱን ወይም ሌላውን። ምስጢሩ ከዚያው ከፊተኛው ይገባል። ከመ ኢይረድ ታሕቲተ ምጥቅኒ ላዕለ። እምግበ ሙስና ምጥቀኒ ፡ (ደራሲ)። እግዚ መጠቀኒ። ዘይመጥቃ ወያሌዕላ። ይመጥቆ እምነ ዝንቱ መከራ
፡ (ዘፍ፴ ፡ ፰። ፫ነገ
፡ ፯ ፡ ፳፬። ማር ፡ ይሥ፲፪ ፡ ፪)።
[3]:-ጣፈጠ ጥፍጥ ኾነ፤–መተቀ።
መጠን ፡ (ብ አምጣን፤ ናት) በቁሙ፤ ልክ ስፍር ቍጥር፤ ሚዛን ገመድ፤ ዐቅም ማዕርግ። መጠኑ ለረድእ ከመ ሊቁ። ለእሳትሰ ቦቱ መጠን። ወኵሉ ክብር ኢመጠና። ክቡራተ መጠን ፡ (ማቴ፲ ፡ ፳፭። ቅዳ። ምሳ፰ ፡ ፲፩። ማር ፡ ይሥ፮ ፡ ፬)። መኑ ሠርዐ አምጣኒሃ። በከመ አምጣኒሁ ለዝኩ። ወእሉ አምጣናተ ምሥዋዕ በእመታት ፡ (ኢዮ፴፰ ፡ ፭። ሕዝ፵ ፡ ፳፬። ፵፫ ፡ ፲፫)። ፈትል ሐብል በማለት ፈንታ አምጣን ይላል፤ ምስጢሩ እንጂ ፥ ዘይቤው አይዶለም። ሰሐበ አምጣነ። አምጣን ዘየዐውዶ ፡ (ሰቈ፪ ፡ ፰። ኤር፶፪ ፡ ፳፩)።
መጠን አምጣን ፡ አምጣን፤ ዐቢይ አገባብ፤ የ ፥ እንደ ያኽል፤ ጊዜ ዘመን፤ ሳ ይኾናል፤ ጊዜና ሳ ፩ ወገን ነው። መጠነ ገብረ ላቲ ለነፍስየ። ተአምር መጠነ ተልእከኒ። መጠነ ብከ የ ፡ (መዝ ፡ ፷፭)። ፈለግየ ኮነኒ መጠነ ባሕር። ኢትሬኢኑ መጠነ ይበልዕ ወይሰቲ። ወአምጣነ ገፍዐት ወሣቀየት፤ ከማሁ፤ እንደ ፡ (ሢራ፳፬ ፡ ፴፩። ዳን፲፫ ፡ ፮። ራእ፲፰ ፡ ፯)። ሚ መጠን ኑኃ ፥ ወሚ መጠን ርሕባ። መጠነ አሐቲ ሰዓት። መጠነ ዝ መዋዕል፤ ያኽል ፡ (ዘካ፪ ፡ ፪። ዳን፬ ፡ ፲፮። አስቴ፪ ፡ ፲፪)። አምጣነ ትበልዕዎ ለዝንቱ ኅብስት። አምጣነ ሕያው ውእቱ። አምጣነሰ ሕፃን ውእቱ ወራሲ። አምጣነ ሀሎ መርዓዊ ምስሌሆሙ፤ ጊዜ ሳለ ፡ (፩ቆሮ ፡ ፲፩ ፡ ፳፮። ሮሜ፯ ፡ ፩። ገላ፬ ፡ ፩። ማቴ፱ ፡ ፲፭)። አምጣን ለብቻው ተለይቶ እንደ እስመ ና ስለ ይኾናል። እፈርህ ሞተ፤ አምጣነ ደወይኩ፤ ታምሚያለኹና ፥ ስለ። መጠንና አምጣን ስፍር ቍጥር ሲኾኑ ውስጠ ብዙነት ባለው ነገር ይገባሉ፤ ልክና ሚዛን ሲኾኑ ግን ውስጠ ብዙነት ኣያሳዩም። አምጣን የመጠን ብዢ ነው፤ አምሳል የምስል ብዢ እንደ ኾነ። አምጣንና አምሳል ላንድ መነገሩ በልማድ እንጂ በሰዋስው ሕግ አይዶለም ፡ (ዕር፲፱ ፡ ፸፪)።
መጠንቍል ፡ (ልት ላን ላት) ዝኒ ከማሁ። እመሂ ዘያጣዑ፤ እመሂ መጠንቍል፤ እመሂ ዘማዊ ወሐሳዊ ፡ (ቄድር ፡ ገ፳፯)።
መጠንጢን ፡ መጠነኛ፤ ታናሽ ልክ መተንተኛ፤ ወይም ጢንጦ የክፍል ክፍል ሢሶ ርቢት ዐምሾ ትሙን፤ ይህን የመሰለ ፡ (ሄርማ)።
መጠይት ፡ (ታን) የሚያስጠይት አስጠያች፤ ወይም ጠያች።
መጢማ [1] ፡
ምጥማዕ፤ መንከሪያ፤ ጢቆሽ የውሃ መርጫ መፈንጠቂያ። ንሣእ መጢማ ዘማይ ወንፋኅ ውስተ ሰማይ ፡ (ሄርማ
፡ ገ፵፬)።
[2] ፡ ጢቆሽ፤–ጠሚዕ ጠምዐ።
መጣቂ መምጠቂ ፡ (ቂት ቅያን ያት) የሚነጥቅ፤ ነጣቂ።
መጣኒ ፡ (ኒት ንያን ያት) የሚመጥን መጣኝ፤ ሰፋሪ ልክ ዐዋቂ። ወኢኅሊና መጣንያን ፡ (ያዕ ፡ ዘእል)።
መጣዊ ፡ (ዊት ውያን ያት) የሚሰጥ የሚያድል የሚያቀብል፤ በአፍ በእጅ። መጣዌ ኦሪት
፡ (መጽ ፡ ምስ)።
መጥለሊ መጥልል ፡ የሚያጠል የሚያለመልም፤ የሚያረካ።አስትየኒ ዘንተ ወይነ ኀይል መጥለሌ ፡ (ጥበ
፡ ጠቢ)።
መጥለል ፡ ማጥለያ ማጥሪያ፤ ወንጠፍት። ከመ ዘመጥለል ሙሓዝ
፡ (ስንክ ፡ ግን፳)።
መጥለውዝ ፡ መጥረቢያ፤–ጸለወ መጽለውዝ።
መጥምቃዊ ፡ ዝኒ ከማሁ፤ ያጥማቂ የጠማቂ ወገን፤ አጥማቂነት ያለው። ዮሐንስ መጥምቃዊ ፡ (ፊልክ
፡ ፻፲፪)።
መጥሪት ፡ (ብ መጥርያት ታት) ጥሪት ማጥሪያ፤ ዕቃ መሣሪያ፤ ወፍጮ መኪና፤ ወይም የሚከራይ ገመል አህያ ፈረስ በቅሎ ባሪያ የመሰለው ኹሉ። በእንተ አንስቲያሆሙ ወውሉዶሙ ወመጥርያታቲሆሙ ወኪነታቲሆሙ ፡ (ፊልክ
፡ ፫)።
መጥሮጶሊስ [1] ፡ (ጽር ሚትሮፖሊስ) እመ አህጉር፤ ታላቅ መዲና ፥ ከተማ መናገሻ። ዮሐንስ ኤጲስቆጶስ ዘቍስጥንጥንያ መጥሮጶሊስ ፡ (ራእ ፡ ፩)።
[2] ፡ (ጽር ሚትሮፖሊቲስ) ዐቢይ ጳጳስ ፥ ወይም ሊቀ ጳጳስ በታላቅ መዲና የተሾመ። መጥሮጶሊስ ዘውእቱ ጳጳስ ፡ (ሲኖዶ። ፍ ፡ ነ ፡ ፬)።
መጥቀብት ፡ (ብ መጣቅብት) መጥቀሚያ መጠቃቀሚያ፤ የስፌት መሣሪያ።
መጥቍል ፡ (ልት ላን ላት) ዝኒ ከማሁ። የሰው ስም፤ ምትሀታም አስማታም፤ ጠንቋይ መሠሪ፤ ጋኔን ጠሪ ሙት አናጋሪ ማለት ነው ፡ (ነገ ፡ ማር)።
መጥቅዕ ፡ (ብ መጣቅዕት) በቁሙ፤ መጥቅ ድወል ቃጭል፤ መረዋ ነጋሪት፤ ቱልቱላ ዋሽንት፤ እንቢልታ መለከት። መጥቅዕሰ ተወጥነ በኖኅ፤ ወገብረ መጥቅዐ እምዕፀወ አብኖስ ዘኑኁ ሠለስቱ በእመት ወግድሙ አሐዱ በእመት፤ ወሶበ አኀዘ ይግበር ታቦተ ይጠቅዕ ሎሙ ኵሎ ዕለተ ሠለስተ ጊዜ። ድምፀ መጥቅዕ። ቃለ መጥቅዕ። ሰብዐቱ መላእክት እለ ያጸንዑ ሰብዐተ መጣቅዕተ። ግበር ለከ ክልኤተ መጣቅዕተ ዘብሩር ፡ (ቀሌ። ዕብ፲፪ ፡ ፲፱። ሪእ፬ ፡ ፩። ፰ ፡ ፮። ዘኍ፲ ፡ ፪)።
፡ በዓል የበዓል ስም፤ የዕብራውያን ዐውዳመት ቱልቱላ መለከት የሚነፋበት፤ በ፯ኛው ወር የጥቅምት ጨረቃ በምትበቅልበት ቀን የሚውል። አታሚንን እይ፤ ከዚህ ጋራ አንድ ነው ፡ (ዘሌ፳፫ ፡ ፳፬)።
መጥበስ [1] ፡ መጥበሻ፤–ጠቢስ ጠበሰ።
[2] ፡
መጥበስ ት፤ መጥበሻ፤ መጠበሻ የብረት ሠቅሠቅ፤ ምሧዐ ብርት። መጥበስ ለአፍሓም ወዕፀው ለእሳት። ወትገብር መጥበሰቶ ሠቅሠቀ ዘብርት ከመ መሥገርተ ዓሣ። ወአግብር ላቲ ለመጥበስት አርባዕተ ሕልቀታተ ፡ (ምሳ፳፮ ፡ ፳፩። ዘፀ፳፯ ፡ ፬ ፡ ፭)።
መጥበቅ ት ፡ (ብ መጣብቅ ት) ማጥበቂያ፤ ማጣበቂያ መጣብቅ፤ ሙጫ ችንካር። መጥበቅተ አዕማዲሆን ፡ (ዘፀ፴፯ ፡ ፲፭። ኢሳ፵፩ ፡ ፯)።
መጥባሕታዊ ፡ የካራ ወገን፤ የካራ ዐይነት ስለታም። ባለካራ፤ ባለሾተል፤ ወይም ሃይማኖቱ ካራ የሚባል። እሉሰ መጥባሕታውያን ይትናገሩ ፈጠራ
፡ (ምእላድ)። የካራ ባህል ስልቱ ፭ ነው። ፩ኛው፤ መንፈስ ቅዱስ ቃል የነሣውን ሥጋ አለዘር ቢከፍልና ቢፈጥር ቅብዕ ተባለ ይላል። ፪ኛው፤ ከአዳም ፍዳ ስላነጻው ቅብዕ ተባለ ብሎ መጣፍ ይጠቅሳል ፡ (ሮሜ፲፬ ፡ ፲፭)። ፫ኛው፤ የብሉዩ ሊቀ ካህናት ፬ቱን ሽቱ ባ፭ኛ ዘይት ያዋሕዳቸው ነበረና፤ መንፈስ ቅዱስም አዋሓጅ ስለ ኾነ ቅብዕ ተባለ ይላል። ፬ኛው፤ በሰውነቱ ለኛ አብነት ሊኾን ተቀባ እንጂ፤ መቀባቱ ለርሱ አልጠቀመውም ይላል። እንዚህ አራቱ ኹሉ መንፈስ ቅዱስ ቅብዕ የሚሉ ናቸው፤ ባህላቸው ግን ገባሪ፤ መንጽሒ፤ ደማሪ፤ ዘኢይረብሕ ቢያሰኝ እንጂ፤ ቅብዕ አያሰኘውም። ፭ኛው፤ ወልድ ቅብዕ፤ በሰውነቱ አምላክ፤ ሥጋውን በተዋሕዶ ስላከበረ ቅብዕ ተባለ፤ ተቀብዐ ማለትም ተዋሐደ ማለት ነው እንጂ፤ አንደኛ በመንፈስ ቅዱስ ከበረ ተሾመ ማለት አይዶለም ይላል። ከኹሉ አስቀድሞ በሱስንዮስ ዘመን የበቀለው፤ ኋላም በቴዎድሮስ የተሳለው ይህ ፭ኛው ነው፤ ያነቁትም ሰዎች ፥ አዛዥ ዘድንግል አአ ክርስቶስ ይባላሉ፤ የተሳለበትም ምክንያት ይህ ነው። ፡ (ታሪክ) የጐንደሮች መንግሥት ዘውዱ ብቻ ሲቀር ግዛቱ ኹሉ ባ፲፯፻፸፯ ዓመት ወደ መሳፍንት ከኼደ በኋላ ራስ ወልደ ሥላሴ ትግሬን ለብቻቸው ሲገዙ በርሳቸው ዘመን፤ ከተንቤን ከደብረ ዳሞ ካባ ገሪማ ከነዚህ ከሦስቱ አህጉር አባ ኪኑ ፥ ደብተራ በትሩ ፥ አለቃ ዐምደ መንሱት የሚባሉ ሦስት ሐሳውያን ተነሥተው ፲፪ ክሕደት ፈጥረው ጥፈው በኢትዮጵያ እንደዚህ የሚሉ ብዙ መናፍቃን ተነሥተው አስቸግረውናል፤ የሊህም መረቻ አፋቸው የሚዘጋበት ወልድ ቅብዕ ማለት ነው፤ ያለዚህ አይረቱምና ይህን ሃይማኖት አጽኑልን፤ የተላከ ካ፵፬ቱ አድባራት ከጐንደር ብለው ወደ ግብጽ ላኩ። ፡ (ተረት) የገባያ ግርግርታ ለቀጣፊ ተመቸው። ግብጦችም ያባቶቻቸው ትምርትና ቋንቋ በተንባላት ዘመን ዕልም ድርግም ብሎ ስለ ጠፋ እውነት መስሏቸው ተቀበሉት። «በአንተ ብዝኀ ተደምሮቶሙ ምስለ ተንባላት እስመ ጠፍአ ልሳኖሙ ቅብጥ ዘእምኔሁ የአምሩ ጽድቀ ሃይማኖቶሙ፤ ወኮኑ ዘኢይሰምዑ ዝክረ ሥሉስ ቅዱስ ማእከሌሆሙ ዘእንበለ ኅዳጣን፤ ወኢለወልደ እግዚ ተዘከርዎ» ፡ (ሳዊ ፡ ዘእስ ፡ ድ፲)። ከለማበት የተጋባበት እንደሚሉት ኹሉ፤ ከዚያ ወዲህ የመጡት ጳጳሳት እናባ ኢዮሳብ፤ ይልቁንም ጥንተ ስማቸው ሚናስ እንድራዎስ የነበረ ቄርሎስ ሰላማ ወልድ ቅብ በማለት ጸንተው ሲሰዱና ሲያሰድዱ ሲያሳስሩና ሲያስገርፉ ሲያሰይፉ ኖሩ፤ ከዚህ የተነሣ የግብጦች ሃይማኖት ተብሎ ባዋጅ በግዝት የማርቆስን ስም ተቀብቶ እስከ ዛሬ ነግሧል፤ የትርጓሜውን መጥፎነት ወልድ ዋሕድ ማለትን እንዲያፈርስ በክርስቶስ ፍች ተመልከት። ምድራዊ ፡ አንጥረኛ፤የሠራውን መስቀል ግብዞችና አታላዮች ከሰማይ ወርዷል እንደሚሉት ይህም እንደዚያ ነው። ፡ (ተረት፤ ስለ ቅርናታም ሴት) ወይዘሮ ስመኝ ለማያውቁሽ ታጠኝ። ቀድሞም በ፱፻ ዓመት ፥ የሽፍቶች እናት የፈላሾች እኅት ከምትኾን ከዚያች ካመንዝራ ከጕዲት በፊት እንደነዚሁ ሚናስ እንድራዎስ የሚባሉ ፪ ሐሳውያን ያውጣኪ ወገኖች መጥተው ጳጳጳት ሳይኾኑ ጳጳሳት ነን ብለው፤ ኢትዮጵያን በሐሰት በስሕተት በክለዋታል፤ በሰውነቱ አምላክ ፥ ፩ ባሕርይ ፥ ፩ ግብር ማለትና ልደትን በ፳፰ ማክበር በነሱ ጊዜ ተዠምሯል። በመጨረሻውም ሐሰታቸው ታውቆ በሰይፍ ስለ ተቀጡና ወዲያው ያ ጕደኛ የጕዲት መንግሥት ስለ ተዠመረ በዚህ ምክንያት ፥ ከልጆቿ ይልቅ ባዕድ የንጀራ ልጅ የምቶደው እናታችን ኢትዮጵያ ፸ ዘመን ያኽል ያለጳጳስ ያለኤጲስቆጶስ ኑራለች
፡ (ስንክ ፡ መጋ፫)። ፊተኞቹንና ኋለኞቹን የሚያስተባብር ሥላሴ፤ ዘሺዬ ወልደ ሥላሴ፤ የደብረ ሊባኖስ መነኵሴ፤ ዘዖደ ኵሎ አድያማተ ግብጽ ወጽርእ ወሶርያ። ሂሮድስ ወጲላጦስ ተንሥኡ ቅድመ እንበለ ፍትሕ ላዕለ አቡሁ ቀባዒ ወላዕለ ወልዱ ቅቡዕ። ከማሆሙ ዓዲ ተንሥኡ በግፍዕ፤ ዘእምግብጽ ሚናስ ሐሳዊ ወእንድራዎስ ጽሉእ። ወበከመ ተኵላት እምአባግዕ፤ ይትኀንጥኡ እሉ እምይትኀጣእ ሰብእ፤ እስመ ኮኑ አርኣያ ለጸብእ።
መጥባሕት ፡ (ብ መጣብሕ ት) ማረጃ መቍረጫ፤ ካራ ቢላዎ ሰንጢ፤ ስለታም ብረት፤ ጐራዴ ስለቱ ባንድ ወገን ብቻ የኾነ፤ወይም ፪ አፍ ያለው፤ ሰይፍ ሾተል፤ አፋ ጩቤ፤ ጕዶ ዱቢት፤ ቀጭኔ ዋልሴ፤ ዐጥንት አይመልሴ። መጥባሕት ዘእብን፤
፡ (ሱፋጭ ቡልጭት)። መጥባሕት ዘጠባሕያነ አልሕምት። መጥባሕተ ጸሓፊ። አነዳ ድማሁ በመጥባሕት ጠብሑ። መጥባሕት ዘክልኤ አፉሁ። ይጸውሩ መጥባሕተ ንኡሳነ ወበሊኃነ ወየኀብእዎሙ ውስተ ልብሶሙ። ነሥኡ መጣብሒሆሙ ፡ (ኢያ፭ ፡ ፪። አዋል። ኤር፵፫ ፡ ፳፫። ስንክ ፡ ሐም፲፫። ምሳ፭ ፡ ፬። ዮሴፍ። ዘፍ፴፬ ፡ ፳፭)።
መጥኖ ኖት ፡ (መጠነ ይሜጥን ይመጥን። መአደ) መመጠን መለካት፤ መስፈር መከንዳት፤ ልክ ማወቅ መገመት፤ ይኽን ያኽል ማለት፤ መወሰን ማስተካከል። ዐቀመንና ወሰነን እይ፤ የዚህ መንደር ናቸው። ይሜጥንዋ በሐብለ መስፈርት። ወመጠነ ርሕበ ሕንጻ አሐደ ኅለተ። አሜሃ ይሜጥን ድካመ ዚኣሁ። ይፈቅድ ይትአመንዎ ወአኮ ከመ ይመጥንዎ፤ ወእስመ ኢይትከሀሎ ለኅሊና ይመጥን ባሕርየ ዚኣሁ ፡ (ኢሳ፴፬ ፡ ፲፩። ሕዝ፵ ፡ ፭። ማር ፡ ይሥ፯ ፡ ፩። አፈ ፡ ድ፳፪)።
መጥዐዊ ፡ ዝኒ ዓዲ ከማሁ። መጥዐዊ ወመጸብሓዊ። አረሚ መጥዐውያን ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፭። ቅዳ ፡ ሕር)። በመጣዕውና በመጥዐዊ ፈንታ መጣዓዊ ይላል አያሰኝም። ፡ (ቀሌ)።
መጥዕው ፡ መጣዕው፤
፡ (ዋን ዋት ዑት) ዝኒ ከማሁ። መጣዕዋን ፡ (ዲድ)።
መጥዕይ ፡ (ያን ያት ዒት) ዝኒ ከማሁ።
መጥወይ ፡ (ያት፤ መጣውይ) ማጥመሚያ መቈልመሚያ፤ መጠምዘዣ ማስጠምዘዣ። ኰነንዎ በመጥወይ ወበመጥባሕት። እንዘ ውእቱ ሀሎ በመጥወይ ቍሱለ ፡ (ስንክ ፡ ግን፫። ሐም፳፭)። በመጥወይ ፈንታ መጥመይ ይላል፤ የጣፊ ስሕተት ነው። ግበር መጥመየ ወመዋሥርተ ፡ (ስንክ ፡ ጥር፲፭)።
መጥዎ ዎት ፡ (መጠወ ይሜጡ ይመጡ። ሰጠወ፤ ወሀበ ወከፈ ወፈየ። ዐረ አዕጣ) መመጥወት፤ ምጧት መስጠት ማደል፤ ማጕረሥ ማቀበል፤ ማሳለፍ ማቅረብ፤ ማሲያዝ ማስጨበጥ ማስረከብ። ዘመጠወ ርእሶ በእንቲኣነ። መጠዎ ቍርባነ። ከመ ይመጥውዋ ጽዋዐ። መጥወኒ እሜጥወከ ፡ (ቲቶ፪ ፡ ፲፬። ቀሌ። ራእ፲፮ ፡ ፲፱። አዋል)።
መጥፍኢ እ ፡ የሚያጠፋ አጥፊ፤ አስጠፊ ፡ (አቡሻ ፡ ፲፫)። መጥፊያ ማጥፊያ፤ ማስጠፊያ፤ መሣሪያ ምክንያት።
መፀ መፀፀ ፡ መጠጠ፤ ሖመጠጠ፤ መጣጣ። ኾነ ያበባው ፍሬ ቃሪያው። ፡ (የገና ስድብ) ሳይነኩኝ አልነካም ፥ ሲነኩኝ አልሸሽም፤ እኮማጠጣለኹ እንደ ቃሪያ ኰሽም። ቦካ በሰለ፤ ሟከከ ተንደረከከ፤ የርሾና የመጠጥ የፍሬ፤ መብሰል ለኹሉ ይኾናል።
መጸለት [1] ፡ (ዕብ ማጾት) ፍጹም ናእት፤ ቂጣ፤ ወዲያው ተለውሶ የሚጋገር፤ የፋሲካ ምግብ፤ አይሁድ እስከ ሰባት ቀን የሚበሉት። ናእትንና ፍሥሕን ተመልከት። ወቀርበ በዓለ መጸለት ዘስሙ ፋሲካ። ወበጽሐት ዕለተ መጸለት አመ ይጠብሑ ፍሥሐ። አስትዓ ዘመጸለት ፡ (ሉቃ፳፪ ፡ ፩ና ፡ ፮። ማር፲፬ ፡ ፩ና ፡ ፲፪። ሲኖዶ)።
[2] ፡ መጸለት፤–ቂጣ፤–ጸለየ ጽሌ ጽላት ጸለተ።
መጸልይ ፡ ዝኒ ከማሁ። ረከቦ ጽዉመ ወጽምወ ወመጸልየ ፡ (ፊልክ
፡ ፻፴፯)።
መጸረ ፡ ዐኘከ አላመጠ አመሰኳ ቈረጠመ በጥር ስ፤ ለመምጠጥ ወይም ለመዋጥ፤ ያገዳ የምግብ። መጸና መጸረ ፩ ዘር ናቸው፤ ጸና ረ ስለ ተዋረሱ መንታ ኹነዋል። ኢትልሳሕ እንዘ ትሜጽር። እለ ሥርወ ዕፀ ይሜጽሩ እምዐቢይ ረኃብ። እስከ ይሜጽሩ ልሳናቲሆሙ ፡ (ሢራ፴፬ ፡ ፲፮። ኢዮ፴ ፡ ፬። ራእ፲፮ ፡ ፲)።
መጸብሓዊ ፡ ዝኒ ከማሁ። ማቴዎስ መጸብሓዊ
፡ (ማቴ፲ ፡ ፫። ፲፰ ፡ ፲፯። ፳፩ ፡ ፴፩)።
መጸብሕ ፡ (ሕት ሓን ሓት) የሚያስገብር፤ አስገባሪ፤ ቀራጭ፤ ግብር ተቀባይ ፡ (ማቴ፱ ፡ ፲–፲፩)።
መፀወ ፡ (ጸገየ፤ ጼነወ፤ መጠወ) አበበ ፥ አበባ ያዘ፤ አረገዘ ፥ ደበደበ፤ ለማፍራትና ለመውለድ ለመዘርዘር። ምስጢሩ መዐዛ መስጠት፤ እንቡጥና ፍሬ ማሳየት ነው፤ ከጥሬው በቀር አንቀጹ አይገኝም።
መፀው ፡ የክፍለ ዓመት ስም፤ ያመት ርቦ ፥ ወይም ሩብ ጸአ=፺፩ ቀን ከመስከረም ፳፮ እስከ ታኅሣሥ ፳፮። ወርኅ ጽጌ ዘመነ ጽጌ ማለት ነው። ክረምት ወመፀው ማእረር ወሐጋይ። ያዘንም ለክሙ ጸደየ ወመፀወ። ይሁበነ ዝናመ ተወን ወመፀው ፡ (ኩፋ ፡ ፪። ዮኤ፪ ፡ ፳፫። ኤር፭ ፡ ፳፬)።
መጸግው ፡ ዝኒ ከማሁ
፡ (አርጋ ፡ ፬)።
መጺእ ኦት ፡ (መጽእ ይመጽእ ይምጻእ። ዕብ ማጻእ። ሱር ምጻእ፤ ረከበ) መምጣት፤ መገኘት ፥ መኾን። ዘመጽአ ወካዕበ ይመጽእ። እምአይቴ መጻእነ ፥ ወመኑ ፈጠረነ። ወመጽአ ረኀብ ውስተ ብሔር ፡ (ውዳ ፡ ማር፪። አክሲማ። ሩት፩ ፡ ፩)።
መፂፅ ፡ (ፃን ፃት ፃፅ) መጣጣ ሖምጣጣ፤ ቃሪያ እንጭጭ ጨርቋ፤ ወይም የቦካ የበሰለ ብስል። ቃሪያንና ብስልን መሖምጠጥ ያገናኛቸዋል። ብሒእ ወመፂፅ። ተኵላት መሪራን ወመፂፃን። ወይፈሪ ፍሬ መፂፀ፤ ብስል ፡ (ቅዳ ፡ አፈ። ቄር ፡ ጰላ። ኢሳ፲፰ ፡ ፭)።
መጺጽ ጾት ፡ (መጸ ይመጽጽ፤ ይምጽጽ። ዕብ ማጻጽ። ሱር ማጽ። ዐረ መጸ) መምጠጥ ፥ መመጥመጥ፤ መጥባት በከንፈር መሳብ፤ በውስጡ ያለውን መጠጣት መጐንጨት። ሰትየ ብሎ ጠጣ ማለት ዐማርኛው ከዚህ ወጥቷል። መፀን እይ፤ የዚህ ጎር ነው።
መጻርብት ፡ መጥረቦች፤ መጥረቢያዎች።
መጻብኅ ፡ (ኅት) ድስቶች፤ ሳሕኖች። ኢያጥረየ ምንተኒ ዘእንበለ አሐዱ ዐጽፍ ወሠቅ ወመጻብኅ ወምስሓግ። ኢትኅሥሥ አጽሕልተ ወኢትልሐሰ መጻብኅተ። መጻብኅቲሃ ወአጽሕልቲሃ ፡ (ስንክ ፡ ነሐ፭። ሢራ፴፬ ፡ ፲፬። ዘኍ፬ ፡ ፯)።
መጻኢ ፡ (ኢት እያን ያት) የሚመጣ የሚገኝ፤ መጪ ዃኝ፤ መጤ መጣተኛ። ንዋየ መጻኢ ዓለም። ኅሊናት ወጠባይዓት ወመጻእያት ዘውስጥ ፡ (ደራሲ። ፍ ፡ ነ ፡ መቅ። አፈ ፡ ድ፲)።
መጻዕር ፡ (ርት) የሚሣቅዩ፤ ሣቃዮች፤ ሥቃዮች፤ የሥቃይ መሣሮች። አዘዘ ስደተ ላዕለ ኤጲስቆጶሳት ወመጻዕርተ ኵነኔ ዕጹበ ላዕለ መሀይምናን ፡ (መጽ
፡ ምስ)።
መጻዕን ፡ (ናት) መጫኞች፤ ቅራኖች፤ የጭነት መሣሪያዎች።
መጻውዕ ፡ (ዓት) መረዋ፤ ቃጭል፤ ቱልቱላ፤ ነጋሪት፤ መጥቅ ድወል የመሰለው ኹሉ። ሶበ ይመውት ሰብእ ትገንዝ ወታመጽእ መጥቅዐ ወመጻውዐ ወማኅቶተ ሠለስተ ወታነሥኦ ለበድን
፡ (ግንዘ)።
መፃጕዕ [1] ፡ በቁሙ ጐባጣ፤–ፀጊዕ ፀግዐ።
[2] ፡ (ዕት ዓን ዓት) ባለብዙ መጨጊያ፤ ድውይ፤ ባልጋ በምንጣፍ የወደቀ፤ የተጨነቀ፤ የጐበጠ፤ የተጨበጠ፤ የስለለ የሰለሰለ፤ መነሣት መቀመጥ፤ መዞር መገላበጥ የማይችል፤ ሽባ ጐባጣ፤ ተርካሳ። ትቤ ዐራት ጊዜ ተባርዮ አልጸቀ፤ መፃጕዕ ከማየ ከመ ትጹረኒ ሕቀ። ወኮነ መፃጕዐ እደዊሁ ወእገሪሁ ፡ (ቅኔ። ስንክ ፡ መጋ፪። ማቴ፬ ፡ ፳፬። ፰ ፡ ፮ ፡ ፱ ፡ ፪። ማር፪ ፡ ፫። ሉቃ፭ ፡ ፲፰)።
መጼንው ፡ የሚያሸት፤ የሚያነፈንፍ፤ አሽታች።
መፄፂት ፡ (ዕብ ተሓሽ። ዐረ ቱኀሽ) ያውሬ ስም፤ አንድ ዐይነት አውሬ እንደ ተኵላና እንደ ነብር ያለ ነጣቂ፤ ጠጕረ ልም ቈርበተ መልካም። መጣጤ ሖምጣጤ ማለት ነው፤ ስሙ የጠባዩን ክፋት ያሳያል፤ ተሓሽ ያለውም በሖሰ ዘይቤ ሲፈቱት፤ ተሐዋሲ ቀበጥ ቅብጥብጥ ያሰኛል። ቈርበቱ እጅግ ያማረ የከበረ ጥኑ ጠንካራ ስለ ኾነ ሙሴ ለድንኳኑና ለመሣሪያ ኹሉ ልብስና ክዳን አድርጎታል፤ የግእዝ ኦሪት መፄፂት ማእሰ መፄፂት የሚለው ኹሉ ይህን አውሬ ነው። ባለብሉዮች ግን ሰማያዊ፤ ጥቍር ይሉታል
፡ (ዘፀ፴፭ ፡ ፯ ፡ ፳፫። ፴፱ ፡ ፲፰። ዘኍ፬ ፡ ፮ ፡ ፰–፲፬ ፡ ፳፭)።
መፅ(መ)ምርት ፡ (ብ መፃምርት) ሴት፤ ሚስት፤ የወንድ ጣምራ፤ ኹለተኛ። መጽሐፍ ግን ያንዱን በብዙ፤ መፃምርት ይላል፤ አያሰኝም። እስመ ሊተ ሠላሳ ዓመት እምአመ ተመተርኩ እምነ መፃምርትየ። ዘይፈቅድ ይዘሙ ምስለ መፃምርተ ካልኡ ፡ (ፊልክ ፡ ፫። ፴፩)።
መጽ(ጥ)ለውዝ ፡ መጥረቢያ መዘለፊያ፤ ወይም ወቅለምት።
መጽሐፍ ፡ (ብ መጻሕፍት፤ ታት) በቁሙ፤ መጣፍ፤ በላዩ ቃል ነገር የተጣፈበት ብራና፤ ወረቀት፤ ነዶው ባንድነት የታሰረና የተያዘ፤ የተሰፋ የተጠረዘ፤ የታፈፈ የተደጐሰ፤ ቅዱስ ክታብ፤ አምላካዊ ንባብ፤ ብሉይ ሐዲስ፤ ሌላውም ኹሉ፤ ደብዳቤ ሳይቀር። በከመ ይቤ መጽሐፍ። ቅዱሳት መጻሕፍት። መጻሕፍታቲሁ ወመጻሕፍተ አበዊሁ። ይምሀርዎሙ መጽሐፈ ወነገረ ፋርስ። መጽሐፈ መልእከት
፡ (ዮሐ፯ ፡ ፴፰። ሮሜ፩ ፡ ፪። ኩፋ
፡ ፵፭። ዳን፩ ፡ ፬። ግብ፱ ፡ ፪)።
፡ ወግ ታሪክ፤ ትምርት ዕውቀት፤ ስፍር ቍጥር፤ ተርትሮ ደምሮ የሚጥፉት። ስማ ለዳቤር ሀገረ መጽሐፍ። አብዝኆ መጻሕፍት ያዘነግዕ ልበ። መጽሐፈ ልደቱ ለኢየሱስ
፡ (ኢያ፲፭ ፡ ፲፭። ግብ፳፮ ፡ ፳፬። ማቴ፩ ፡ ፩)። መጽሐፍ በስምና በግብር እየተናበበ እንዳወራረዱ ይፈታል፤ ምስጢሩ ግን ከመጽሐፍነት አይወጣም።
መጽሔት [1] ፡ መስታዮት፤–ጸሐየ።
[2] ፡ (ታት፤ መጻሕይ) መስታዮት ንጹሕ ብሩህ ጽሩይ፤ መልክ የሚያሳይ፤ ማይ ሰማይ የሚመስል። መጽሔት ዝሕልት። መጽሔት ብረህት። ከመ ዘሬኢ ፍጥረተ ገጹ በመጽሔት
፡ (ሢራ፲፪ ፡ ፲፩። ቀሌ። ያዕ፩ ፡ ፳፫)።
መፅሕስ ፡ (ስት ሳን ሳት) አስረጋጭ፤ አሸብሻቢ፤ ዳንኪራ መቺ።
መጽለብት ፡ (ታት) ዝኒ ከማሁ። ከመ ትጠቀም መጽለብትከ እማእከለ መንሱት ፡ (ቅዳ ፡ ዮሐ)።
መጽለወ [1] ፡ መጽለወ፤–ጠወለገ፤–ጸሊው ጸለወ መጽልው።
[2] ፡ መጽለወ፤ ፡ (ዲቃ ግ። ዐረ መዘለ) ጠወለገ፤ ደከመ ዛለ፤ ዝልፍልፍ አለ። ዕፀ ሕይወት እንተ ኢትመጸሉ። ፈርሀት ንግሥት ወመጽለወት ወተንተነት። ወኢይፈቅድ እፈንዎሙ ጽዉማነ፤ ከመ ኢይመጽልዉ በፍኖት ፡ (አርጋ። አስቴ ፡ ፭። ማቴ፲፭። ፴፪) በመጽለወ ፈንታ ተመጽለወ ይላል፤ ስሕተት ነው። ይትመጸለዉ ወይቈጽሩ ገጾሙ። ትመጽለዉ በድንጋፄ እንዘ ይዴመሙ ጥቀ
፡ (ማቴ፮ ፡ ፲፮። ጥበ፲፯ ፡ ፫)።
መጽልም ፡ (ምት ማን ማት) የሚያጨልም፤ የሚያጠቍር፤ አጥቋሪ።
፡ የጨለመ፤ የጠቈረ፤ ጽሉም፤ ጸሊም። በውስተ መጽልም መካን። ኢትኅሥሥ ርእየተ ገጽየ ፥ እስመ ገጽየ መጽልም ከመ ኀጣውእየ። አንሰ መጽልመ ገጽ ወብዙኀ አበሳት ፡ (ኩፋ ፡ ፭። ስንክ ፡ ሐም። ታኅ፲፬)።
መጽልእ ፡ የሚጠላ፤ የሚያስጠላ፤ ተጠይ አስጠይ፤ አስቀያሚ። መጽልእ ዘከመ ዝ ብእሲ ፡ (ሢራ፳ ፡ ፲፭)።
መፅመ(ም)ድ ፡ (ብ መፃምድ) መጥመጃ፤ ማጥመጃ፤ ማስጠመጃ፤ መቀርቀቢያ፤ ማቈራኛ፤ ኹለቱን ነገር አንድ የሚያደርግ፤ ቀንበር ምራን ማነቆ ቅራና መጫኛ ሰንሰለት፤ የመሰለው ኹሉ።
መጽመሚ ፡ ዦሮ የሚደፍን፤ የሚያስደፍን፤ ከመስማት የሚከለክል። አፍ የሚያሲዝ፤ ዝም የሚያሰኝ። መስም ቅጽል ከኹለት አዕማድ እንዲወጣ አስተውል።
መፅመር መፅምር ፡ (ብ መፃምር) ዐባሪ ተባባሪ ተጫፋሪ፤ ጓደኛ ወዳጅ ባልንጀራ፤ ዕጮኛ ባል ሙሽራ፤ የብእሲት። ጣምራ። መጨመሪያ ማጣመሪያ፤ መጣብቅ ችንካር፤ የመሰለው ኹሉ። መጣምር ማለት ከዚህ የወጣ ነው። ኢትኩን መፅመሮ ለብእሲ መዐትም። ምስለ ዐርክከ ወመፅመርከ ፡ (ምሳ፳፪ ፡ ፳፬። አዋል)። በመፅመር ፈንታ መፃምርት ይላል፤ ስሕተት ነው። እኁየ ወመፃምርትየ። ይኩን መፃምርተ ምስለ ማኅበረ ቅዱሳን። ወረስዮ መፃምርተ ምስለ ሰማያውያን ፡ (ፊልጵ፬ ፡ ፫። ግንዘ)።
መጽረብ ፡ (ብት) መጥረቢያ፤ መላጊያ፤ መሸለቻ። ዘረበን፤ ተመልከት።
መፅርር ፡ (ብ መፃርርት) የሚፃረር፤ ተፃራሪ፤ የሚያስጠርር፤ አስጠራሪ፤ ጥሩር አልባሽ፤ የሰልፍ መምር። መሣሪያውንም ያሳያል።
መጽርይ [1] ፡ ጥሩ አበባ፤–ጸርይ ጸርየ።
[2] ፡ (ዕብ ካርኮም። ዐረ ኩርኩም) የሽቱ ቅጠል፤ ጥሩ ሽቱ፤ አበባው ብጫቴ፤ ዐደይ የሚመስል፤ ሽታው ብርቱ፤ የሚሰነፍጥ። ባለብሉዮች ግን ቀጋ ይሉታል። ናርዶስ ወመጽርይ። ነስነስኩ ምስካብየ መጽርየ። ይለብስ ዘሕብረ መጽርይ ፡ (ማሕ፬ ፡ ፲፬። ምሳ፯ ፡ ፲፯። ሄርማ)።
መጽብኅ ፡ (ኅት) የወጥ ዕቃ፤ መሣሪያ፤ ድስት ሳሕን ጭልፋ ማማሰያ የመሰለው ኹሉ ውስተ መጽብኅ
፡ (ማቴ፳፮ ፡ ፳፫)።
መጽብብ ፡ የማያጠብ፤ አጥባቢ። ጠባብ፤ ታናሽ፤ ቀጭን። መጽብበ ቦእኩ። ከመ አባግዕ ውስተ መጽብብ። ወእንተ መጽብብ ሙባኢሁ ፡ (ኢዮ፴ ፡ ፳፰። ሚክ፪ ፡ ፲፪። ሱቱ ፡ ዕዝ፲፫ ፡ ፵፬)።
፡ አንባ ኰረብታ፤ ዕርድ ምሽግ፤ ጠላት የማይደፍረው። ወነበረ ዳዊት ውስተ መጽብብ ፡ (፩ነገ ፡ ፳፫ ፡ ፲፬)።
መጽብኢት ፡ ዝኒ ዓዲ ከማሁ። መጽብኢቶሙ ፡ (፩ዜና ፡ ፲፬ ፡ ፲፭)። ዕብራይስጡ ግን ብካኢም ይላል፤ የቱት ዐይነት ዛፎች ማለት ነው። ቱት ዐጽቃም ቅጠላም፤ የሐር ዛፍ ነው፤ ቅጠሉን የሐር ትሎች ይበሉታል፤ ፍሬውም እንዦሪ ይመስላል።
መጽነፍት ፡ (ዕብ ሚጽኔፌት) የራስ ልብስ፤ ጌጥ መሸፈኛ፤ ሰበን፤ ጥምጥም ከነቆቡ፤ ካህናተ ኦሪት የሚለብሱት
፡ (ሕዝ፳፩ ፡ ፳፮)።
መጽንሕ ፡ መጥን፤ መቈያ፤ መስተንግዶ፤ መተያያ። አውገዘ ከመ ኢየሀቡ ግብረ ወመጽንሐ በኀይል ዘእንበለ ፈቃዶሙ ሶበ የአቱ ንጉሥ ፡ (ሥር ፡ አኵ)።
መጽንዕ ዒ
፡ መጥኛ፤ ማጥኛ። የሚያጠና፤ መጥኔ፤ አጥኝ፤ ደጋፊ። መጥኔ ይስጥኽ እንዲሉ። ረዳኤ ወዐቃቤ ወመጽንዔ። ኅረይ መዝሙረ መጽንዔ ወመድኀኔ ፡ (ግንዘ። ፊልክ ፡ ፻፷፫)።
መጽአሞ [1] ፡ ድምፅ ጩኸት፤–ጽኢም ጸአመ።
[2] ፡ ጩኽት፤ የናደት ድምጥ፤ የገደል ማሚቶ፤ ተራራ ገደል ዋሻ እያስተጋባ የሚጮኸው፤ ጩኸት። ወሰምዑ መጽአሞሁ። ወይዌውዑ ማእከለ መጽአሞ
፡ (ፊልክ። ኢዮ፴ ፡ ፯)። ዕብራይስጡ ግን ሲሒም ይላል፤ ቍጥቋጦ ማለት ነው።
፡ ደስክ፤ ቅዠት፤ ምትሀት፤ በእንቅልፍ ልብ የሚታይና የሚደብት፤ የሚጫን የሚያስጮኽ፤ የሚያስጨንቅ፤ የሚያስለፈልፍ፤ የአጋንንት መልክ፤ ለስው የሚታዩበት አርኣያና አምሳል። ወይመልእ ውስተ አብያቲሃ መጽአሞ ፡ (ኢሳ፲፫ ፡ ፳፩)። ዕብራይስጡ ኦሒም ይላል፤ አሥዋክ ፥ አራዊት ፥ አዕዋፍ ርኩሳን ብለው፤ ይፈቱታል፤ ዖፍ ማለት ከአቡቀለምሲስ ይሰማማል ፡ (ራእ፲፰ ፡ ፪)።
መጽዕል ፡ (ልት ላን ላት) የሚሰድብ፤ የሚያሰድብ፤ አሰዳቢ አስነቃፊ። መሰደቢያ ማሰደቢያ።
መጽዕር ፡ (ርት ራን ራት) የሚያጥር፤ የሚያስቸግር፤ የሚሣቅይ፤ አስጨናቂ። መሣቀያ፤ ማስጨነቂያ፤ የሥቃይ መሣሪያ።
መጽዕቅ ፡ (ቅት ቃን ቃት) የሚያስጨንቅ አስጨናቂ። ሕማም ወጽንዐ ንዴት መጽዕቅ
፡ (ጥበ ፡ ጠቢ)።
መጽዕን ፡ (ንት ናን ናት፤ ዐኒ) የሚጭን፤ ጫኝ። መጫኛ፤ ቅራና፤ ማሸከሚያ።
መጽዕጥ ፡ (ጣን ጣት። መጻዕጥ ጣት) ዝኒ ከማሁ፤ የሴት ሲኾን ጥ ይጠብቃል። ይነሥእ አዋልዲክሙ ለመጽዕጣት ፡ (፩ነገ ፡ ፰ ፡ ፲፫)።
መጽወተ ፡ (መጠወ) ሰጠ ፥ መጠ(ጸ) ወተ፤ ትእዛዝ ፈጸመ። ይምሕሩ ወይመጸውቱ። ኢትበል እምፈተውኩ ይኩን ሊተ ብዙኀ ንዋይ ከመ እመጽውት ላዕለ ነዳያን። ይኩን መሓሬ ወመጽዋቴ
፡ (ምሳ፲፫ ፡ ፱። አፈ ፡ ተ፫። ዲድ ፡ ፬)።
መጽያሕት ፡ ዝኒ ከማሁ። ፍኖተ ጽኑዓን መጽያሕት። ይኩን ኵሉ መብእስ መጽያሕተ ርቱዐ። ስእኑ ሐዊረ መጽያሕት ፡ (ምሳ፲፭ ፡ ፲፱። ኢሳ፵ ፡ ፬። ፶፱ ፡ ፲፬)። ፍኖትን ተመልከት።
መጽደቂ ፡ የሚያጸድቅ፤ አጽዳቂ። ሃይማኖተ ክርስቶስ መጽደቂ ፡ (ስንክ ፡ መጋ፳፪)።
መፅፈርት ፡ ወጥመድ፤ ጕንጕን፤ አበታ ገመድ። መፅፈርተ ሲኦል
፡ (ምሳ፱ ፡ ፲፰)። ዕብራይስጡ ግን መዓምቅተ ሲኦል ይላላል።
መጾር [1] ፡ መጽወርት፤ (ብ መጻውር፤ ርት) መሸከሚያ፤ መቀመጫ፤ ዐልጋ፤ ወንበር፤ መሎጊያ፤ ቀላጥም፤ ዐንገት፤ ዦሮ፤ እጀታ፤ ማንጠልጠያ፤ የመሰለው ኹሎ። መጾረ ገብረ ለርእሱ። ወግበር መጻውርተ እምዕፅ ዘኢይነቅዝ
፡ (ማሕ፫ ፡ ፬። ዘፀ፳፯ ፡ ፮ና ፡ ፯)።
[2] ፡ መጾር ፤–መሸከሚያ ፤–ጸዊር ጾረ።
መፈክር ፡ (ርት ራን ራት) ዝኒ ከማሁ፤ መተርጕም፤ ጠንቋይ። ልሳን መፈክርት ዘትዜኑ ዘውስተ ኅሊና መፈክራነ ሕልም። መፈክር በሰዓታት ፡ (ፊልክ ፡ ፱። ኩፋ ፡ ፵። ዘፍ፵ ፡ ፰። ሲኖዶ)።
መፈውስ ፡ (ስት ሳን ሳት) ዝኒ ከማሁ። መፈውሰ ልብ። መፈውስ፤ ልሳን፤ ዕፀ ሕይወት። መፈውሰ ነፍስ ወመፈውሰ ሥጋ። ካህናትኒ ለነፍስ መፈውሳን ፡ (ምሳ፲፬ ፡ ፴። ፲፭ ፡ ፬። ቅዳ ፡ መስተ። ተረ
፡ ቄር፩)።
መፈድፍድ ፡ የሚያበዛ፤ አብዢ። ብዙ እጅግ፤ ዐያሌ። ወመፈድፍዶሙ የዐቅቡ ዕቅበተ ቤተ ሳኦል ፡ (፩ዜና ፡ ፲፪ ፡ ፳፱)።
መፈጽም ፡ የሚፈጽም፤ የሚያስፈጽም፤ ፈጻሚ አስፈጻሚ። መፈጽመ ተስፋ ለዘአሰፈወ ፡ (ፈላስ ፡ ገ፲፫)።
መፍሐቅ ፡ የሚፍቅ፤ ፋቂ፤ መፋቂያ መሣሪያ። መፍሐቀ ገበዋት ፡ (ስንክ
፡ ጥር፲፭)
መፍልሕ ፡ መፍሊያ፤ ማፍሊያ፤ ማስፈሊያ። ሲያበዛ መፋልሕት ይላል። መናግንተ ጽህርት ወመፋልሕተ እሳት
፡ (መቃ ፡ ገ፪)።
መፍልስ ፡ የሚያፈልስ፤ አፍላሽ። የበረሓ ዐሣማ፤ ሕሪያ፤ ሲያበዛ መፋልስ ይላል። ከመ መፍልስ ዘይመጽእ ውስተ ረምሕ። ሐራውያ ዘውእቱ መፍልስ ፡ (ኩፋ ፡ ፴፯። አዋል)።
መፍልስት ፡ ስርቆሽ በር፤ መሿለኪያ። ወፅኣ እንተ መፍልስት። ወቦኡ እንተ መፍልስት ፡ (ዳን፩ ፡ ፲፰ና
፡ ፳፮። ስንክ ፡ መስ፳፰)። ባለብሉዮች ግን ሥርጥ ጐዳና፤ ስላች መንገድ ይሉታል።
መፍረዪ ፡ መፍርይ፤ ፡ (ይት ያን) ዝኒ ከማሁ። መፍርይት ለእንተ ይትበላዕ ፡ (ቅዳ ፡ ሕር)።
መፍርሂ ፡ ዝኒ ከማሁ፤ አስፈሪ።
መፍርህ ፡ (ህት ሃን ሃት) የሚያስፈራ፤ አስፈሪ፤ አስገራሚ። ባሕር መፍርህ። መንበርከ መፍርህ። ወኮነት መፍርህተ። መፍርሃን ፡ (ጥበ፲
፡ ፲፰። ቅዳ። መቃ። አርጋ
፡ ፮)።
መፍርያን ፡ (ሱር ማፍርያና) የሰው ስም፤ የሚያፈራ፤ የሚያስፈራ፤ ፍሬያማ ፍሬያም። እልመፍርያን ሊቀ ጳጳሳት ዘሀገረ ሠርቅ
፡ (ስንክ ፡ ጥቅ፱)።
መፍቀሪ ፡ (ሪት ርያን ያት) ዝኒ ዓዲ ከማሁ። መፍቀሬ ሰብእ። መፍቀሪተ ዝሙት። ወመፍቀርያነ ዐመፃ። አኃት ክቡራት ወመፍቀርያተ እግዚ ፡ (ጥበ፩ ፡ ፮። ፈ ፡ መ ፡ ፰ ፡ ፯። ሮሜ፪ ፡ ፰። ቄር)።
መፍቅዳዊ ፡ የሚፈልግ፤ ፈላጊ። ድኻ ለማኝ። ያዐርፎሙ ለመፍቅዳውያን ፡ (ፊልክ ፡ ፪)።
፡ የሚፈለግ፤ ተፈላጊ። ግብር መፍቅዳዊት
፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፴፪)።
መፍቅር ፡ (ርት ራን ራት) ዝኒ ከማሁ። መፍቅረ ወርቅ፤ መፍቅራነ ክብር ዘዝ ዓለም ፡ (ዕር ፡ ኢሳ፫ ፡ ፳፭)።
መፍቅድ [1] ፡ ቀዲ፤ የሚወድ የሚፈቅድ፤ ወዳጅ ፈቃጅ። ፈቃዲን ተመልከት፤ ከዚህ ጋራ አንድ ነው።
[2] ፡ (ዳት) ግብር፤ ነገር፤ ጕዳይ፤ ባሕርያዊ ሥራ፤ በግድ የሚፈለግ፤ ለባሕርይ የሚያሻ፤ ጋብቻ ምግብ ልብስ የመሰለው ኹሉ። ወሀባ ኵሎ መፍቅዳ ዘሰአለቶ። ይቤሎሙ አይድዑኒ መፍቅደክሙ። ይፈጽም ለክሙ ኵሎ መፍቅደክሙ። መፍቅደ ሥጋሁ ረከበ። ቀዳሜ ኵሉ መፍቅዱ ለሰብእ ማይ ወእሳት። ዝንቱ ላዕለ ክልኤቱ መፍቅዳት ፡ (፪ዜና ፡ ፱ ፡ ፲፪። ዮሴፍ። ፊልጵ፬ ፡ ፲፱። ስንክ ፡ መጋ፴። ሢራ፴፱ ፡ ፳፮። ፍ ፡ ነ ፡ ፴፪)።
መፍተኒ ፡ ዝኒ ከማሁ። መፍተኔ አዕርክት ፡ (ፈላስ)።
መፍትሒ ፡ ዝኒ ከማሁ፤ የሚሽር፤ የሚያፈርስ። ስቴ ሰላም መፍትሔ ሕማምነ፤ ዘውእቱ ደመ ኢየሱስ ክርስቶስ። መፍትሔ ሥራይ ፡ (ተረ ፡ ቄር። አዋል)።
መፍትሕ ፡ (ዐረ ምፍታሕ) መክፈቻ፤ መሻሪያ፤ ማፍረሻ። መፍትሐ ሥራይ ፡ (አዋል)።
መፍትው ፡ ፍትው፤ ያማረ፤ የተወደደ፤ ደስ የሚያሰኝ፤ የሚያስጐመዥ፤ የሚያስመኝ፤ የሚያሻ የሚያስፈልግ። ኵሉ ግብሩ ለእግዚአብሔር ሠናይ ወመፍትው። መፍትው ለዐይን ሰርጕ። ወይን መፍትው። በእንተ ምድረ ሕዝብየ መፍትው። አስተዳሎኩ ለዝንቱ ሕንጻ ኵሎ ዘመፍትው ፡ (ሢራ፵፪ ፡ ፳፪። ፵፭ ፡ ፲፪። ዓሞ፭ ፡ ፲፩። ኢሳ፴፪
፡ ፲፪። ፩ዜና ፡ ፳፰ ፡ ፪)።
፡ የተገባ፤ የሚገባ፤ አገባብ፤ ርትዕ ተድላ ድልወት። መፍትው ያንሶሱ ቀሲስ ኀበ አብያተ ድዉያን። መፍትው ይሕየው ይስማኤል ቅድሜከ። እመ ገብረ ዘኢመፍትው። አኮ መፍትው ፡ (ኪዳ። ኩፋ ፡ ፲፭። ቀሌ። ማቴ፲፬ ፡ ፲፮)።
መፍዴ ፡ (ዐረ ፊደት። ዕብ ኬሴፍ) ጥሩ ብር፤ ወርቅ፤ ገንዘብ፤ የሚያበድሩት የሚከፍሉት። መፍዴ ዘኢኮነ ተምያነ። አመ ይነሥኡ ረባሐ መክሊት መፍዴ፤ እለ ያረብሑ ወርቆሙ በርዴ ፡ (ዘፍ፳፫ ፡ ፲፮። ስንክ ፡ ታኅ፫)።
መፍጠኒ ፡ የሚያፈጥን፤ የሚያስፈጥን፤ አፍጣኝ፤ አስፈጣኝ። ፡ (ተረት) አፍጣኝና አቅጣኝ፤ ከመዳሮ እንገናኝ። መፍጠኔ መዐት። ሞት መፍጠኒ ፡ (ፈ ፡ መ ፡ ፳፩ ፡ ፫። ቄድር)።
መፍጽሕ ፡ (ሕት። መፋጽሕ፤ ሕት) መፍጫ፤ መፍለጫ፤ መቀጥቀጫ፤ መጅ ፋስ፤ መዶሻ፤ ድጅኖ፤ ደንጐራ፤ በትረ ቃቃን፤ መሮ፤ ሽብልቅ፤ ውሻል። መፍጽሕ ዘይፈጽሕ ኰኵሐ። ስመ ፍጽሐ ኀጺን ዐፅመ እገሪሁ ቀጥቀጡ። ማሕጼ ወመፍጽሕ። ብርዐ ይመስሎ መፍጽሕ
፡ (ኤር፳፫ ፡ ፳፱። ስንክ
፡ ነሐ፳፭። መዝ ፡ ፸፫። ኢዮ፵፩
፡ ፳)።
ሙ ፡ የወንዶች አብዢ ምእላድ፤ በሩቆችና በቅርቦች ዝርዝር የሚገባ። ለሊሆሙ ፥ ለሊክሙ፤ ሎሙ ፥ ለክሙ፤ ጸውዖሙ ፥ ጸውዐክሙ።
ሙ(ሞ)ሓዪት ፡ መጐብኛ፤ መሰለያ። በቁሙ፤ ታፋ ሙላ ማውድ ዳሌ።
ሙሓዝ ፡ (ዛት) መፍሰሻ ማፍሰሻ ማስፈሰሻ፤ ወንዝ ቦይ መትረብ፤ አሸንዳ። ኢትግበር ሎቱ ሙሓዘ ሰማይ። ሙሓዘ ማየ ግብጽ። የኀድሩ ውስተ ሙሓዛተ ማይ። ዕፅ ዘበቈለት ኀበ ሙሓዘ ማይ
፡ (ሢራ፳፭ ፡ ፳፭። ኩፋ ፡ ፲። ኤር፴፰ ፡ ፱። ድጓ)።
ሙሓድ ምስትውሓድ ፡ መዋሐጃ፤ ማዋሐጃ፤ ቦታ መሣሪያ።
ሙላድ ፡ (ዳት) መውለጃ ማሶለጃ ማዋለጃ፤ መወለጃ፤ መገኛ መውጫ ቦታ፤ ማሕፀን፤ መዠመሪያ ካባት፤ ኹለተኛ ከናት የሚወለዱበት። ብሔረ ሙላድኪ። ምድረ ሙላዱ። ዘርዐ ሙላድ። ሙላዳት ፡ (ሩት፪ ፡ ፲፩። ኤር፳፪ ፡ ፲። ቅዳ ፡ ቄር። ሔኖ፪ ፡ ፩)።
ሙሱን ፡ (ናን ናት ስንት) የማሳነ፤ ጥፉ መጥፎ ብልሹ፤ ግም ድፍርስ። ዐጽቀ በለስ ሙሱን ጥቀ። ሙሱናነ ልብ። ማይ ሙሱን። ሙሱነ ይሰትዩ ፡ (ኤር፳፬ ፡ ፪። ፪ጢሞ
፡ ፫ ፡ ፰። መጽ ፡ ምስ። ሕዝ፬ ፡ ፲፮)።
ሙሲቂ ፡ (ዐረብ) ሞዛቂ፤ ባለሙዚቃ። ዝ ውእቱ ሠራዕያነ ዜማ ፡ (ጊ ፡ ወ ፡ ሐ ፡ ገ፲፯)።
ሙስና ፡ (ናት) ጥፉነት ፥ ጥፋት፤ መፍረስ መበስበስ፤ መከራ መቅሠፍት። ሙስናሃ ለነነዌ። ተዘከሮ ለሞት ወለሙስና። ወተጋብኡ አርባዕቱ ሙስናት፤ ዘውእቶሙ ቀትል ወዋዕይ ወጸብእ ወረኀብ ፡ (ጦቢ፲፬ ፡ ፲፭። ሢራ፲፰ ፡ ፮። ዮሴፍ)። የንጨት ስም ፥ ፩ ዐይነት ዕንጨት፤ ቅርፍቱን ድቍሶ በበሶ ሲበሉት ኮሶ የሚያመክን የትግሮች መዳኒት።
ሙራድ ፡ (ዳት) መውረጃ ቍልቍለት፤ ዕርከን መዓርግ። ሙራደ ደብር። ሙራደ ዐቀብ ዘደብረ ዘይት። ይውሕዝ ከመ ማይ ውስተ ሙራድ። በበ ሙራድዶሙ
፡ (ኢያ፰ ፡ ፳፬። ሉቃ፲፱ ፡ ፴፯። ኢሳ፴ ፡ ፳፰። ፍ ፡ ነ ፡ ፶፪)።
ሙቀት ፡ በቁሙ፤ መሞቅ አሟሟቅ፤ ትኵሳት ትኵስነት። እስከ ሙቀት ፀሓይ። ሙቀተ ሐሩር። እንዘ ሀሎ ሙቀት ላዕሌሁ። አስሐትያ ዘአልቦ ሙቀት
፡ (ነሐ፯ ፡ ፫። ሔኖ ፡ ፬። ቅዳ። ቀሌ)።
ሙቁሕ ፡ (ሓን ሓት ቅሕት) የታሰረ የተጋዘ፤ እስር ግዞተኛ። እግር ሙቁሕ። ሙቁሓን እደዊሆሙ። እለ ሙቅሕታ ትነበር ነፍሶሙ ፡ (ሢራ፳፩ ፡ ፲፱። ኢሳ፵፭ ፡ ፲፬። ፩ጴጥ ፡ ፫ ፡ ፲፱)።
ሙቃሔ ፡ (ሕያት) ማሰር መታሰር አስተሳሰር። እስራት ግዞት፤ የግዞት ቤት። እመ ሙቃሔሁ። ሙቃሔ ጽኑዕ። ኦ ዘፈታሕኮ እሙቃሔ እግሩ ወእዱ። ውስተ ሙቃሔሁ ኢኀደገቶ ፡ (ስንክ ፡ ግን፲፱። መስ፮። ጥበ
፡ ጠቢ። ጥበ፲ ፡ ፲፬)።
ሙቃሥ ፡ (ሣት) መውቀሻ መወቀሻ መዋቀሻ መካሰሻ ቦታ። በአሐዱ ዐውድ ወበአሐቲ ሙቃሥ፤ ዐውደ ሙቃሥ። አሐዱ ክብር ወመንግሥት ወምኵናን ወሙቃሥ ፡ (መጽ ፡ ምስ።ደራሲ)።
ሙቃዕ ሞቅዕ ፡ (ብ ሙቃዓት፤ መዋቅዕ። ዐረ ሚቀዐት፤መዶሻ) መውቂያ መግፈፊያ፤ ፍሬን ከገለባ ሥጋን ከቈርበት ዕንጨትን ከቅርፍት የሚለዩበት መሣሪያ ቦታ።
ሙባኒም [1] ፡ (ዕብ ሙካኒም) ቅዉማን፤ ርቱዓን፤ ወይም ቅልብሶች ቅንፎች ማለት ነው። በዕብራይስጡ በና ከ ፡ (ቤት ካፍ) ይማሰላሉና በዚህ ምክንያት ተሳስቶ ሙካ በማለት ፈንታ ሙባ ብሎታል። ወከናፍሪሆሙ አሐዱ ጥፍሕ ሙባ(ካ) ኒም እንተ ውስጥ ፡ (ሕዝ፵ ፡ ፵፫)።
[2] ፡ ቅዉማን ርቱዓን፤–መው።
ሙባእ ፡ (ኣት) መግቢያ፤ ማግቢያ፤ ማስገቢያ፤ በር፤ ደጃፍ። ኢየአምር ሙባእየ ወሙፃእየ። እስመ እንተ ህየ ቦቱ ሙባእ ላዕለ ይሁዳ። ሙባአ ግብጽ። ሙባአ ባቢሎን። ሙባኣቲሁ ፡ (፫ነገ ፡ ፫ ፡ ፯። ዮዲ፬ ፡ ፯። ኩፋ ፡ ፲። ፳። ሕዝ፵፫ ፡ ፲፩)።
ሙተት ፡ መሞት፤ አማወት። ይሬእዩ ሙተተ ጻድቅ። ወሙተቶሂ ምኑነ። በእንተ ሙተቱ ለብልጣሶር
፡ (ጥበ፬ ፡ ፲፯። ፭ ፡ ፬። ዮሴፍ)።
ሙናሕ ፡ ማረፊያ፤–ነዊኅ ኖኅ።
ሙአት ፡ ማሸነፍ፤ መሸነፍ፤ አሸናፊነት፤ ድል ርታታ። እፎ ትኄልዩ አንትሙ ሙአቶሙ። እምድኅረ ሙአተ ኵሎሙ ሰይጣናት። እምኀቤከ ሙአት። ተሰጥመ ሞት ውስተ ሙአት ፡ (ዮሴፍ። ፊልክ ፡ ፴፱። ዕዝ፬ ፡ ፶፱። ፩ቆሮ ፡ ፲፭ ፡ ፶፬)።
ሙዓል ፡ (ላት) መዋያ ውሎ ማድረጊያ ቦታ፤ የቀን ሐበስ፤ ወይም ቍርጥ ፍርድ እስኪፈረድበት በደለኛ የሚውልበትና የሚያድርበት። ምስክሩ ቀድሞ ተነግሯል።
፡ በቁሙ ሙያ፤ ጥሩ ሥራ ተግባረ እድ። ባለሙያ እንዲሉ ፡ (ዐማርኛ)።
ሙዓይ ፡ (ያት፤ መዋዕይ) መቃጠያ ማቃጠያ፤ መተኰሻ።
ሙክፍ ፡ (ፋት) መስጫ ማቅረቢያ ማቀበያ፤ መቀበያ። ሙካፈ ስእለቱ
ለኢዮብ ፡ (ደራሲ። አርጋ ፡ ፫)።
ሙዝ ፡ (ብ አሟዝ፤ አምዋዝ። ዐረ መውዝ። ሱር ሙዛ) በቁሙ፤ የታወቀ ተክል የንሰትና የኮባ የጕናጕና ወገን፤ ፍሪው ጥፍጥ ፡ (አዋል)።
ሙዳቅ ፡ (ቃት) መውደቂያ መዘቅዘቂያ፤ ማረፊያ ቦታ ፡ (ሔኖ፰ ፡ ፲፫ ፡ ፻
፡ ፮)።
ሙዳየ ቀለም ፡ የቀለም ቀንድ፤ ወይም ቢልቃጥ ፡ (ሕዝ፱ ፡ ፪)።
ሙዳየ ቀርጠሎን ፡ የወይን እሸት ቅርችጫት፤ ዘለላውን የሚሸከሙበት ፡ (ዘዳ፳፮ ፡ ፬)።
ሙዳየ በለስ ፡ የበለስ መልቀሚያ ታናሽ እንቅብ ቅርጫት
፡ (ተረ ፡ ባሮ)።
ሙዳየ ዕጣን ፡ በቁሙ፤ ታናሽ ስፌት ወይም ቧት የዕጣን ማቅረቢያ ፡ (ቅዳ)።
ሙዳየ ዕፍረት ፡ የሽቱ ዕቃ፤ ስፌት ናርጅ፤ ቢልቃጥ።
ሙዳየ ማይ ፡ የውሃ ዕቃ፤ እንስራ ፊቀን፤ በርሚል ጋን፤ቀርበታ ፡ (ዮዲ፯ ፡ ፳)።
ሙዳየ ምጽዋት ፡ የገንዘብ ሣጥን፤ ምእመናን አምኃቸውን የሚያገቡበት፤ አፈ ጠባብ ሆደ ሰፊ፤ ገንዘብ የሚያስገባ፤ እጅ የማያስገባ፤ ገንዘቡ ሲመላ ተከፍቶ እንደ ንፍሮ የሚዘረገፍ ፡ (፪ዜና
፡ ፳፬ ፡ ፲፩። ማር፲፪ ፡ ፵፩)።
ሙዳየ ዘቢብ ፡ አገልግል ቅንብቻ፤ ቧት፤ ኪስ ከረጢት
፡ (፩ነገ ፡ ፳፭ ፡ ፲፰)።
ሙዳየ ዔረግ ፡ የበጋ እንቅብ፤ የመከር ቅርጫት ፍሬ የተመላ ፡ (ዓሞ፰ ፡ ፩)።
ሙዳይ ፡ (ያት) በቁሙ፤ ማኖሪያ መጨመሪያ፤ መክተቻ ዕቃ። ዕፍረት ዘተሰውጠ እሙዳይ ውስተ ሙዳይ
፡ (ቀሌ)። ለንዋያት ኹሉ ይነገራል፤ ዋዲያት ማለት ከዚህ ወጥቷል።
ሙዳድ ሞዳድ ፡ (ብ መዋድድ) ማዋደጃ ማሰማሚያ፤ ዛቢያ። ችንካር ቍልፍ፤ የመሰለው ኹሉ። ወመዋድዲሆን ዘብሩር ፡ (ዘፀ፴፯ ፡ ፲፯። ፴፰ ፡ ፲፯)። የሰው ስም፤ ሙሴ ከመረጣቸው ከሰባ ኹለቱ አንዱ ፡ (ዘኍ፲፩ ፡ ፳፮)።
ሙጋር ፡ መውገሪያ፤ መወገሪያ፤ መጣያ መወርወሪያ ቦታ። ተአተተ ሕቀ እምኔሆሙ መጠነ ሙጋረ እብን ፡ (ሉቃ፳፪ ፡ ፵፩። ስንክ ፡ ነሐ፲፬)።
ሙጋድ ፡ (ዕብ ሞቄድ፤ ሞቅዳ) ማገዶ፤ የመሥዋዕት ዕንጨት ጥሩ ፍልጥ፤ መልካም ሽታ ያለው።
ሙጣሔ ፡ መልበስ መጐናጠፍ፤ መደረብ መከናነብ፤ አለባበስ፤ ልብሳት፤ ልባሰ ሽፋን።
ሙጥራን ፡ (ዐረብ) ጳጳስ ሜጥራ የሚለብስ።
ሙፃእ ፡ (ኣት) መውጫ ቀዳዳ፤ በር ደጃፍ መስኮት፤ ዳገት ሥርጥ፤ መሿለኪያ ስርቆሽ ሠገራ፤ ምንጭ። አልቦ ሙፃእ እማእክሎሙ። እንተ አልባቲ ሙፃእ እስከ ለዓለም። ሙባኣቲሁ ወሙፃኣቲሁ። ሙፃአ ኵስሕ። ከመ ዘይደፍን ዐዘቅተ ወያማስን ሙፃአ ማይ። አስተርአዩ ሙፃኣተ ማያት
፡ (ዮዲ፯ ፡ ፲፫። ቀሌ። ሕዝ፵፫ ፡ ፲፩። ስንክ ፡ ነሐ፲፰። ምሳ፳፭ ፡ ፳፮። ፪ነገ፳፪ ፡ ፲፮)።
ሙጻእ ፡ –መውጫ ቀዳዳ ፤–ወፂእ ወፅአ።
ሙጽ ፡ ሙጭ፤ ቈላፋ በትር የጤፍና የማሽላ መውቂያ። ቈላፋም ባይኾን ማናቸውም የራቻ መውቂያ ሙጭ ይባላል።
ሙፋር ፡ (ራት) መሰምሪያ፤ ማሰምሪያ ቦታ። በምድሮሙ ወበሙፋሮሙ። ሚጥ ልበከ ለመርዔትከ ወለሙፋረ ዚኣከ ፡ (ሔኖ፹ ፡ ፪። ምሳ፳፯ ፡ ፳፫። መዝ ፡ ፻፵፫)።
ሚ ፡ (ዕብ ሚ፤ ማ፤ ሜ) የጥያቄና የምርመራ፤ የአንክሮ አገባብ። ማ ማን፤ ምን ምንድር። ሚ የዐቢ እምረኀብ ወሚ ያሐምም እምነ ቍር። ምንት አነ ወሚ ዘመድየ። ሚ ትርጓሜሁ ለቃል ፡ (አፈ ፡ ተ፳፰። ዮዲ፲፪ ፡ ፲፬። ፊልክ ፡ ፷፭)።
፡ ምንኛ፤ ምን ያኽል፤ ስንት። ሚ አዳም። ሚ በዝኁ። ሚ መጠን ፡ (ማሕ፬ ፡ ፲። መዝ ፡ ፫። ቅዳ)። ሚ ወሚ ቢል፤ ምንና ምን፤ ማንና ማን ያሰኛል። በጠጠትና በምኞት ላይ ሲወድቅ ምነው ይኾናል። ሚ እሞትነ በግብጽ። መጽሐፍ ግን ሶበ ሞትነ ይላል፤ አያሰኝም ፡ (ዘፀ፲፮ ፡ ፫)። ፡ (ዕር፳ ፡ ቍ፺፩)።
ሚ(ም)ልኤል ፡ ስመ ኮክብ ዐቢይ፤ መጋቤ ጸደይ ፡ (ሔኖ)።
ሚል ፡ (ላቲን) የመንገድ ስፍር በቁሙት፤ ሺሕ ርምጃ፤ ሺሕ መትር ወይም ፪ ሺሕ ክንድ ማለት ነው፤ ፩ ምዕራፍ እንደ ማለት። ርምጃ የዱሮ፤ መትር የዛሬ ነው። ፡ (ሚልዮን፤ ሺ ጊዜ ሺ፤ መቶ ፻፻)። የወስኑም ደንጊያ በሺሕ በሺሑ መትር የሚቆመው ሚል ይባላል።
ሚመ ፡ (ሚ፤ መ) ንኡስ አገባብ፤ የማሻሻልና የማማረጥ ፥ የጥያቄ ቃል። ወይ ፥ ወይስ። ሚና መ ተጋጥመው አንድ ወገን ኹነዋል፤ አውንና ዮጊን ሚንና መን እይ። እምሰማይኑ ወሚመ እምሰብእ። ምንት እምንኀሶሙ ለእለ ተፈጥሩ፤ ሚመ ተፈጥሮ ወሚመ ኢተፈጥሮ። አየኬ ዘወለደት ድንግል፤ ሚመ ትስብእተ ወሚመ መለኮተ ፡ (ማቴ፳፩ ፡ ፳፭። ቄር እስት)። ፡ (ዕር፳ ፡ ቍ፻፩)።
ሚሶር ፡ (ዕብ ሚሾር) ሜዳ፤ ለጥ ቀጥ ያለ የተካከለ፤ እንዳውድማ ያለ፤ ርቱዕ ማለት ነው። ፡ (ተረት) ሰፊ ሜዳ እንደ ወግዳ ፡ (ኢያ፲፫ ፡ ፲፮)።
ሚሻሑ ፡ (ዕብ ሜይ ሳሑ) ሚ ማይ፤ ሻሑ ላሑ ዋነተኛ፤ በተገናኝ ማየ ሐማሊ። እግረኛ የማይደፍረው ፥ ዋነተኛ የሚሻገረው ዕሙቅ ጥልቅ ማለት ነው ፡ (ሕዝ፵፯ ፡ ፭)።
ሚበዝኁ ፡ የቅኔ ስም፤ በ፫ኛው መዝሙር የሚገባ ፥ ፫ ቤት ያለው።
ሚን ፡ ክዳት ክፋት ተንኰል፤ ክፉ ምክር ሽንገላ ፡ (ፑሊቲክ)። ቅንአት ወቃሕው ወሚን። ሰይጣነ ስብሐት ብጡል ብዙኀ ሚን ወእከይ ፡ (ፊልክ ፡ ፶፮)። አይቴ ሀሎ ኀይልከ ወሚንከ ዘትገብሮ በላዕለ ሰብእ ፡ (ገድ ፡ ተክ)።
ሚዓ ሜዓ ፡ (ብ ሜዓት፤ አምያዕ) ጥሩ ሽቱ የነጠረ የቀለጠ የተጣፈጠ። ከርቤ ሰሊክ ሚዓ። ማርያም ገነተ ሚዓ ወሰሊክ። ስኂን ወሚዐ ወሰሊኆት ፡ (ገድ ፡ አዳ። ስንክ ፡ ጥቅ፳፩። አርጋ ፡ ፯)።
ሚካኤል ፡ (ዕብ) የመልአክ ስም፤ ሊቀ መላእክት፤ ሚ መኑ፤ ካ ከመ፤ ኤል አምላክ፤ በተገናኝ መኑ ከመ አምላክ ማለት ነው። ሚክያስ ፡ (ጽር። ዕብ ሚካህ) ማለት መኑ ከመ እግዚአብሔር ማለት እንደ ኾነ ፡ (ሔኖ። ዳን ፡ ፲፪ ፡ ፩። ይሁ ፡ ፱። ራእ፲፪ ፡ ፯)።
ሚክሎል [1] ፡ (ዕብራ) ክቡር ልብስ፤ ፍጹም ጌጥ ፍጹም ሽልማት ፡ (ሕዝ፳፫ ፡ ፲፪)።
[2] ፡ ፍጹም ጌጥ፤–ከልሎ ከለለ።
ሚዘብ ፡ (ሐባብ) ቦይ፤ መትረብ፤ አሸንዳ።
ሚዛን ፡ (ዐረ እልሚዛን) በቁሙ፤ መድሎት ፥ መመዘኛ ልክ። ዘይሰርቁ በሚዛን። እለ ይዔምፁ በሚዛን ፡ (ፈ ፡ መ ፡ ፲፯ ፡ ፯። ፳፮ ፡ ፫። መቃ ፡ ገ፲)።
፡ የኮከብ ስም፤ መልኩ ሚዛን የሚመስል የመስከረም ኮከብ። ከፀሓይ ጋራ ፴ ዕለት ፲ ኬክሮስ ይመግባል ፡ (አቡሻ ፡ ፬)። ሚዛን ያሰኘው መልኩ ብቻ አይደለም ፥ ግብሩም ተጨምሯል፤ በርሱ ምግብና ውስጥ በመስከረም ባ፲፩ኛ ቀን መዓልትና ሌሊት ይተካከላሉ።
ሚዜ ፡ (ትግ ማዛይ። ዕብ ሚይ ዜ፤ መኑ ዝ) በቁሙ፤ ዐማርኛ። ዐርከ መርዓዊ፤ ግልገል ሙሽራ፤ የመርዓዊ አሳሳች እኩያው አምሳያው፤ ከማሳሳቱም የተነሣ የመርዓት ወገኖች መኑ ዝንቱ ብለው የሚያደንቁት የሚጠይቁት
፡ (ዮሐ፩ ፡ ፲፱። ፫ ፡ ፳፱)።
ሚዝት ፡ በቁሙ፤ ሴት ሙሽራ ፥ የመርዓዊ ጣምራ ፥ ሚዝ(ስ) ቱ። መሐዘን እይ፤ የሚዜና የሚዝት ሥር መሠረት ርሱ ነው። አንዳንድ ሰዎች ግን ስን ተከትለው ሚስት ማለት የሜሰ ዘር ነው ይላሉና፤ በኅብዝ(ስ) ት ንባብ ይረታሉ።
ሚያዝያ ፡ በቁሙ ፥ ማዚያ፤ ስመ ወርኅ ሳምን እመስከረም፤ የሚዛዝትና የሙሽሮች ወር መኑ መኑ የሚባሉበት ፡ (መዝ
፡ ፳፫። ኪዳ)። በግንቦት ወር ከጥንት ዠምሮ ባገራችን ልማድ ጋብቻና ሰርግ የለምና፤ ሚያዝያን የሚዛዝት ወር ማለት ስለዚህ ነው። ግንቦት ግን የዛር የቡዳ የደበል አንሣ ወር ይባላል፤ ይኸውም የመባቻው ለት በሚሠራው ሥራ ይታወቃል፤ አቢብንና ኔዎንን እይ። በወርኀ ሚያዝያ። በቀዳሚ ወርኅ ብሩህ ዘውእቱ ሚያዝያ
፡ (ዘፀ፴፬ ፡ ፲፰። ዲድ
፡ ፳፬)።
ሚጠት [1] ፡ መመለስ፤–መዪጥ ሜጠ።
[2] ፡ (ታት) መመለስ፤ መዞር። እሬስያ ኅቡረ ለሚጠቶሙ። ሚጠተ ብርሃናተ ሰማይ። እምቅድመ ሚጠታት ዘብርሃናት። በሚጠተ ገጸ እግዚ እምኔነ ፡ (ሚክ፪ ፡ ፲፪። ሔኖ፸፪ ፡ ፩። ቅዳ ፡ ዲዮ። ዮሴፍ)።
፡ መለወጥ፤ ውላጤ። ሚጠተ የአምኑ ላዕሌሁ ለዘኢየአምር ሚጠተ። ዘእንበለ ሚጠት
፡ (ቄር። ቅዳ)።
፡ መልስ ፥ ምላሽ የጥያቄና የወረቀት። ሰድ መጽሐፈ ኀበ ንጉሠ ምዕራብ፤ ወለእመ ነሣእከ ሚጠተ እምኔሁ ተመየጥ ኀቤየ ፡ (ዮሴፍ)።
ሚጣን ፡ ዝኒ ዓዲ ከማሁ፤ መለወጥ ፥ ልውጥነት። ጽዱቅ ወክቡር ነገረ እግዚ፤ ወአልቦ ወኢምንትኒ ሚጣን በኀበ እለ ቦሙ አእምሮ ፡ (መቃ
፡ ገ፲)።
ማሄለክ ፡ (ዕብ ማሃላኽ) መኼጃ መመላለሻ፤ መንገድ ወልወል ፡ (ሕዝ፵፪ ፡ ፬)።
ማኅለቅት ፡ ማለቂያ መጨረሻ፤ ዳርቻ ፍጻሜ። ጥንት፤ወማኅለቅት። ይርአይ ማኅለቅቶ ለነገር። ወማኅለቅቱሰ ለጽድቀ አሪት። ወአልቦ ማኅለቅት ለመንግሥቱ ፡ (ኢሳ፲፱ ፡ ፲፭። ማቴ፳፮ ፡ ፶፯። ሮሜ፲
፡ ፬። ሉቃ፩ ፡ ፴፯)።
ማሕለብ ፡ (ብ መሓልብ) ማለቢያ ቄጆ፤ የወተት ዕቃ መሣሪያ።
ማኅለፍት ፡ (ታት) ዝኒ ከማሁ። ጸሎተ ማኅለፍተ ነፍስ። ማኅለፍታተ ነፍሶሙ ግዑዘ ዘእንለ ክልአት ፡ (ግንዘ)። መንገደ ሰማይ ማለት ነው።
ማሕሌታዊ ፡ (ታይ) የማሕሌት ሰው፤ ደብተራ አወዳሽ፤ መርቶ የሚቀኝ ራሱን የቻለ። ድምጣም ድምጠ መልካም፤ ማሕሌት የሚያሞቅ የሚያደምቅ፤ መዝፈን መቀንቀን መወረብ ማስረገጥ ከበሮ መዝበጥ የሚያውቅ። ማሕሌታይ ሚካኤል መዐርዒረ ዜማ። ያሬድ ማሕሌታይ
፡ (ደራሲ። ስንክ ፡ ግን፲፩። አፈ ፡ ተ፳፬)።
ማሕሌት [1] ፡ (ታት። አው ማሕልይ፤ ብ መሓልይ) ዘፈን ምስጋና፤ ወረብ ለዘብ፤ ቅዳሴ ውዳሴ፤ ቅኔ ግጥም፤ ጉማ ተመማ የብዙ ሰው ዜማ። ማሕሌተ አብድ። አዋልደ ማሕሌት። አልቦ ዘይክል አእምሮታ ለይእቲ ማሕሌት ዘእንበለ እልክቱ። ያስምዕክሙ ቃለ መሰናቁት ዘሕፃናት ወማሕሌተ ዘመላእክት። ተስእሉነ ነገረ ማሕሌት ወይቤኡነ ሕልዮ ለነ እማሕልዪሃ ለጽዮን፤ እፎ ነሐሊ ማሕሌተ እግዚ በምድር ነኪር። ማሕልየ መሓልይ ዘሰሎሞን
፡ (መክ፯ ፡ ፭። ፲፪ ፡ ፬። ራእ፲፬ ፡ ፫። ቅዳ
፡ ሕር። መዝ ፡ ፻፴፮። ማሕ ፡ ፩)።
[2] ፡ ማሕሌት፤–በቁሙ ምስጋና፤–ሐልይ ሐለየ።
ማሕመሚ ፡ ዝኒ ከማሁ። ዝብጠት ማሕመሚ ፡ (ፈ ፡ መ ፡ ፰ ፡ ፫)።
ማኅሜ ፡ (ያት) ማሰሪያ፤ መታሰሪያ። ፈትሐ ማኅሜሁ እመዝራዕቱ። ወፈትሕዎ እማኅሜሁ እመዝራዕቱ። ወፈትሕዎ እማኅሜሁ ለአክዮር። እበትክ ማኅሜከ ፡ (መሳ፲፭ ፡ ፲፬። ዮዲ፮ ፡ ፲፫። ናሖ፩ ፡ ፲፫)።
ማሕምም ማሕመም ፡ (ጥሬና ቅጽል) ምጥ ጭንቅ። አኀዞሙ ማሕምም
፡ (ዘፀ፲፭ ፡ ፲፬)። የሚያሳምም የሚጐዳ፤ የሚያስጨንቅ። ዘበጥዎ ዝብጠተ ዐቢየ ወማሕምመ ፡ (ስንክ ፡ መጋ፳፯)።
ማኅሠሥ ፡ (ማሠሻ) ዝኒ ከማሁ። ብዙኅ ጻሕቁ ወፍድፉድ ማኅሠሡ። እንዘ ይትለአክዎ ዘልፈ መላእክት ለማኅሠሡ። ሶበ አናኅከ ማኅሠሠ። ማኅሠሥ ዘላዕለ እምልብ ፡ (ስንክ ፡ መስ፰። ግን፳፱። ሐም፮። ቄር
፡ እስት)።
ማሕስዕ ዕት ፡ አው መሐስዕ፤ ፡ (ብ መሓስዕ ዓት) ጠቦት፤ ጡት የተወ፤ ዓመት የኾነው ግልገል ወጠጤ። ማሕስዐ በግዕ። ማሕስዐ ጠሊ። መሐስዐ በግዕ አሐዱ። እምአይቴ ዛቲ መሐስዕት ፡ (ዘፍ፴፩ ፡ ፴፰። ፩ነገ ፡ ፲፮ ፡ ፳። ፯ ፡ ፱። ጦቢ፪ ፡ ፲፫)። መሓስዐ አባግዕ። መሓስዐ አጣሊ። ሰረሩ ዲበ እልኩ መሓስዕ ፡ (መዝ ፡ ፻፲፫። ሢራ፵፯ ፡ ፫። ማሕ፩ ፡ ፰። ሔኖ ፡ ፸፩ክ)።
ማሕረስ ፡ (ብ መሓርስ) ማረሻ፤ ማሳረሻ፤ ብረት ለብቻው እንደ ጦር ተሠርቶ ከዕርፍ የሚዋደድ። ወማሕረሰክሙ አግብሩ ኵያንወ። ወይመትሩ ኵያንዊሆሙ ለማሕረስ። ግብረ ማሕረስ፤ ዕርሻ ቍፋሮ ፡ (ዮኤ፫ ፡ ፲። ሚክ፬ ፡ ፫። ዘኍ፳፰ ፡ ፲፰)።
ማህረከ ፡ (ይማሀርክ፤ ይማህርክ፤ ተቀ ግ፤ ወይም የመሀከ ስሯጽ) ማረከ ፥ ዘርፎ ወሰደ ነጻ፤ ወደ ርሱ ላበ አቀረበ፤ በትምርት በታምራት፤ ወይም በጦርነት። ይማሀርኮሙ ለጽኑዓን። ማህረኩ ወቀተሉ ደቀከ። ወማህረከ እንስሳሆሙ። ማህረክዎሙ ምህርካ ብዙኀ ፡ (ኢሳ፶፫ ፡ ፲፪። ኢዮ፩ ፡ ፲፯። ዮዲ፪ ፡ ፳፫። ፪ዜና ፡ ፲፬ ፡ ፲፫)።
ማሕረከ ፡ ማረከ፤–ምሂር መሀረ ማህረከ።
ማሕረጽ ፡ (ጻን ት፤ መሓርጽ) መፍጫ ማስፈጫ፤ ወፍጮ የቅምጥ የመዘውር፤ ደንጊያው ፪ ኹኖ የተካከለ፤ እንደ ምጎጎ(ጣድ) ና እንደ ሞግድ፤ እንደ ሰፌድና እንደ ሰፌድ ገጥሞ ላይኛው ብቻ የሚዞር የሚሽከረከር። ወይም የቁም ወፍጮ ማላሚያ መደቈሻ፤ እናቱም ግልገሉም ሞላላ የኾነ፤ ሴቶች በ፪ እጃቸው የሚገፋት የሚያመላልሱት። አመት እንተ ትነብር ዲበ ማሕረጽ። ንሥኢ ማሕረጸ ወሕርጺ ሐሪጸ። የሐርጽዎ በማሕረጽ። ቃለ ማሕረጽ። በአሐቲ ማሕረጽ ፡ (ዘፀ፲፩ ፡ ፭። ኢሳ፵፯ ፡ ፪። ዘኍ፲፩ ፡ ፰። ዮሴፍ። ሉቃ፲፯ ፡ ፴፮)። የወፍጮ መጅ፤ ግልገል ላይኛው ብቻ። ማሕረጸ አድግ። እብን ዐቢይ ከመ ማሕረጽ። ስባረ ማሕረጽ ፡ (ማቴ፲፰ ፡ ፮። ራእ፲፰ ፡ ፳፩። መሳ፱ ፡ ፶፫)።
ማህር ፡ (ብ አምህርት) ዝኒ ዓዲ ከማሁ። አእላፍ አምህርት ፡ (፩ቆሮ ፡ ፬ ፡ ፲፭)።
ማኅበራዊ ፡ የማኅበር፤ ማኅበረተኛ፤ ማኅበርነት ያለው። አኀው ማኅበራውያን፤ መነኮሳት ማኅበራውያን ፡ (ሥር ፡ ጳኵ)።
ማኅበር ፡ (ራን) በቁሙ፤ አንድነት፤ ጉባኤ ሸንጎ ብዙ ሰው፤ ቤተ ክርስቲያን። ሥርዐተ ማኅበር። ዕቀብ ማኅበረነ። ማኅበሮሙ ለነቢያት። ማኅበረ ሕዝብ። ማኅበረ ሠለስቱ አስማት ፡ (ስንክ ፡ መስ፳፬። ቅዳ። ፩ነገ ፡ ፲፱ ፡ ፳። ኤር፴፫ ፡ ፲፯። አርጋ)።
፡ ወገን ነገድ፤ ቤተ ሰብ ጭፍራ፤ ሰራዊት። ሰራዊተ ገብርኤል በበ ማኅበሮሙ። ዳታን ወአቤሮን ወማኅበራኒሆሙ። ማኅበሩ ለዲዮቅልጥያኖስ ፡ (ቅዳ ፡ ያዕ። ፈ ፡ መ ፡ ፫ ፡ ፫። ስንክ ፡ ሐም፩)።
ማኅበርት ፡ (ታት) ዕጥፍ ድርብ፤ ንብብር። መኑ ይበውእ ውስተ ማኅበርተ እንግድዓሁ
፡ (ኢዮ፵፩ ፡ ፬)።
፡ የልብስ መጋጠሚያ፤ ስፌት ዝራር ተካሪስ። ወውስተ ክልኤሆን ማኅበርቱ። ፡ (ዘፀ፴፮ ፡ ፳፭)።
ማኅበብ ት ፡ (ታት። መኃብብ) የወይን መርገጫ፤ ምክያድ ምዕጻር። ወይነ ማኅበብትከ። በእንተ ማኅበብት ፡ (ምሳ፫ ፡ ፲። መዝ
፡ ፰)።
ማኅበዝ ምኅባዝ ፡ መጋሪያ፤ እቶን ማድ ቤት። ጢሰ ማኅበዝ። ቦ ዘይትቀነይ ምድረ ወየሐርስ፤ ቦ ዘገነት ወቦ ዘዐጸደ ሐምል፤ ቦ ዘይጸርብ ወቦ ዘይገልፍ ወቦ ዘምኅባዝ፤ አልቦ ዘይትናገር ውስተ ምኅባዝ እንዘ ይገብሩ ኅብዝተ ፡ (አዋል። ሥር
፡ ጳኵ)። በምኅባዝ ፈንታ ምኅማዝ ይላል፤ ስሕተት ነው። ኢውዕየት ቀዊማ ማእከለ ውዑይ ወርሱን ምኅማዝ ፡ (ስንክ ፡ ግን፳)።
ማኅተም ፡ (ማት፤ መኃትም። ዐረ ኅትም። ዕብ ሖታም) በቁሙ፤ ማተሚያ መታተሚያ፤ የበር የነገር መዝጊያ፤ የጣት የጥፈት ምልክት፤ ኀቲም ቀለበት ፈርጡ ማኅተም የኾነ፤ ስምና መልክ የተቀረጠበት፤ ቀለበትነት ከማኅተምነት ያለው ፡ (ዳን፮ ፡ ፲፯። አስቴ፰ ፡ ፰)። እንዘ ኢያርኁ ማኅተመ ድንግልናሃ። ምጽዋቱ ለሰብእ ከመ ማኅተም ምስሌሁ። ዘኀተመኪ በሰብዐቱ መኃትም ፡ (ቅዳ። ሢራ፲፯ ፡ ፳፪። ራእ ፡ ባሮ)።
፡ ማኅተም የወደቀበት፤ ሥዕሉና ምስሉ ጥፈቱ፤ የማኅተሙ ቅጅ። ዳኅንኑ ማኅትም። ወማኅተማት ፡ (ዳን፲፫ ፡ ፲፯። ዘፀ፳፰ ፡ ፳፮)።
፡ ጥምቀትና ሜሮን፤ ቍርባን። ማኅተመ እግዚ፤ ዘውእቱ ቅብዐ ሜሮን ቅዱስ። ኢያፍርሁኒ ቀታልያኒሃ ለነፍስ፤ እስመ ማኅተምየ ደምከ ቅዱስ ፡ (ፈ ፡ መ። ፳፰ ፡ ፩። ስንክ ፡ መጋ፳፯)።
፡ የጥፈት መሣሪያ፤ መጻሕፍት የሚታተሙበት፤ መኪና ፊደል በየስሙና በየመልኩ ከብረት ከርሳስ የሚሠራ። ንሕነ ገበርነ ዘንተ ማኅተመ ወኀተምነ መጻሕፍተ ፡ (አዋል)። የማኅተምሥራ የተዠመረ ባ፲፬፻፴፮ ዓ.ም. ነው ይባላል፤ የዠመሩትም ጕተንቤርግ፤ ፎስት የሚባሉ ፪ የጀርመን ሊቃውንት ናቸው።
፡ የቀመር ስም ማእከላይ ቀመር፤ ቍጥሩ ፸፮ ዓመት። በዚህ አበቅቴና ወንጌላዊ ይገናኙበታል፤ አበቅቴው አልቦ ወንጌላዊው ማቴዎስ። ዐውደ ማኅተም ፡ (መር ፡ ዕዉ)።
ማሕተት ፡ (ብ መሓትት) ምስክር፤ እማኝ ነባሪ ሽማግሌ። ስምዕ አሐዱ ኢይከውን ማሕተተ ለአቅትሎ መንፈስ። አነ ማሕተቶሙ። ከናፍሪከ ማሕተትከ። ማሕተቶሙ ለኃጥኣን ሞት። መጽሐፈ ማሕተትየ ዝኩ ኅቱም። ፡ (ዘኍ፴፭ ፡ ፴። ሮሜ፲ ፡ ፪። ኢዮ፲፭ ፡ ፮ ፡ ፴፬። ኤር፴፱ ፡ ፲፩ ፡ ፲፪)። በመሓትት ፈንታ ማሕተት ይላል፤ ስሕተት ነው። ዘኢዘለፍዎ ማሕተት በገጽ ፡ (ግብ፳፭ ፡ ፲፮)።
ማኅትው ፡ (ዋት፤ አው መኃትው) ማብሪያ፤ መቅረዝ ቀንዲል ፋኖስ የመሰለው ኹሉ። ሰብዑ መኃትዉ ዘወርቅ።ወክልኤቱ መኃትው ፡ (ራእ፩ ፡ ፲፪ ፡ ፲፫። ፲፩ ፡ ፬)።
፡ ዋዜማ ንኡስ በዓል እንደ ቀዳም ያለ፤ መብራት የሚበራበት። ኢትስግድ በዕለተ እሑድ ወኢበማኅትዊሃ። ሰንበት ማኅትወ ፋሲካ ፡ (ኒቅ። ዲድ ፡ ፴)። መዠመሪያ መዝሙር ከዋዜማ በፊት የሚጣፍ፤ የዋዜማው ለት ጧት በነግህ የሚባል ፡ (ድጓ)።
ማኅቶት ማኅ(ተ) ትው ፡ (ብ መኃትው ዋት) ፋና መብራት፤ የሠም የዘይት፤ የሌላውም ኹሉ። ወማኅቶት ውስተ እደዊሆሙ። ማኅቶት ዘየ(ያ) ኀቱ። መኃትወ ጽጕ ፡ (ኩፋ ፡ ፳፫። ዮሐ፭ ፡ ፴፭። ፲፰ ፡ ፫)።
ማሕነክ ፡ (ብ መሓንክ) ማኘኪያ መንጋጋ፤ የመኪና ጥርስ፤ የሥጋ መምተሪያ፤ የሰው ወጥመድ፤ ሥጋን ከናጥንቱ የሚፈጭ የሚያልም የሚደቍስ የሚቈርጥ የሚበጣጥስ። መንሰክ ወማሕነክ። ወአንተሰ እስክንድር ንጉሥ ተዐቀብ፤ እስመ አልቦ ዘይወፅእ እምድኅረ ቦአ ውስተ ዛቲ ሀገር እምነጋድያን ከመ ይንግር ዜና ለእለ ይመጽኡ፤ ወአዝዞሙ ለሰራዊትከ ይትዐቀቡ፤ እስመ
ኀበ ኆኅትሂ ወማእከለ ቤትሂ ወማዕገትሂ ሀሎ ማሕነክ ወሠርም
ወማዕምቅ፤ ወእምድኅረ ወድቀ
አልቦ ዘይትነሣእ፤ አላ ይትከዐው አማዑቱ ወይትቀጠቀጥ አዕፅምቱ ፡ (አዋል። ዜና ፡ እስ)።
ማህከወ ፡ (ተቀ ግ። መሀከ) አስፈራ፤ አስደነገጠ።
ማህው ፡ (ብ ማህዋት፤ አምሃው። ዐረ መሃት) የብርሌና የብርጭቆ የቅዛዝ የመስታዮት ጭቃ ዐፈሩ ደንጊያው እንደ ኖራ ፈልቶና ቀልጦ የሚሠራ፤ ወይም የተሠራው። መስተገብራነ ማህው። አምጽኡ ሎሙ እምህየ ሕምዘ በማህው። ጽዋዐ ማህው። እለ ይሰትዩ ወይነ በማህው ወቢረሌ። ማህው ለእመ ተሰብረ አልቦ ዘያስተጣግዖ ዘእንበለ ገባሪሁ። ስባራተ ማህው በሊኃት ፡ (ስንክ
፡ ኅዳ፳፩። ዮሴፍ። አርጋ። ዓሞ፮ ፡ ፮። ያዕ ፡ ዘእል። ሢራ፵፫ ፡ ፲፱)።
ማሕዘል ልት ፡ (ብ መሓዝል፤ ላት) ማዘያ
መሸከሚያ፤ አንቀልባ።
ማሕዘኒ ማሕዝን ፡ (440) ፡ (ቅጽልና ጥሬ) የሚያሳዝን፤ አሳዛኝ። ማዘኛ፤ ማሳዘኛ። ሞት ማሕዘኒ። ቃል ማሕዘኒ። ማሕዘነ ኮኖ ዝ ቃል። ኅዳጥ ውእቱ ንብረትነ ወማሕዝን። በአርኣያ ማሕዘን ፡ (አዋል። ስንክ
፡ ጥቅ፳፭። ኩፋ ፡ ፲፯። ጥበ፪
፡ ፩። አፈ ፡ ተ፲፩)።
ማሕየብ [1] ፡ (ባት) መቅጃ መጥለቂያ፤ የውሃ ዕቃ። ማሕየብኒ አልብከ። ከመ ነጠብጣበ ማሕየብ። ማሕየበ ዐዘቅት። ምልኢዮን ለኵሎን ማሕየባት
፡ (ዮሐ፬ ፡ ፲፩። ኢሳ፵ ፡ ፲፭። ፍ ፡ ነ ፡ ፴፮። ስንክ ፡ ሠኔ፳)።
[2] ፡ መቅጃ፤–ሐዪብ ሔበ።
ማሕይው ማሕየዊ ፡ (ዊት ውያን ያት) የሚያድን፤ ዐዳሽ ፈዋሽ፤ ሕያው አድራጊ። ማሕይዉ ለኵሉ ሰብእ። እግዚእ ማሕየዊ። ሕማማቲሁ መድኀኒት ወማሕየዊት ፡ (፩ጢሞ ፡ ፬ ፡ ፲። ቅዳ)።
ማኅደር ፡ (ራት፤ መኃድር። ዐረ ኂድር። ዕብ ሔዴር) ማደሪያ ሰፈር ቤት በኣት፤ የመኝታ ቦታ ዕልፍኝ፤ በታላላቅ ቤት ውስጥ የሚሠራ ልዩ ልዩ ክፍል ደጃፍና መስኮት ያለው፤ ደንኳን መቃብር። ማደሪያነት ላለው ለቦታ ኹሉ ይነገራል። ማኅደረ እንግዳ። አተዉ ማኅደሪሆሙ። እንታክቲ ማኅደር። በእንተ ማኅደራት። ሲሳይ ወዐራዝ ማኅደር። ተከለ ማኅደረ። ማኅደሩ ለኵሉ ዘሞተ ምድር ፡ (ኪዳ። ዮዲ፲፫ ፡ ፩። አፈ ፡ ተ፳፰። ፍ ፡ ነ ፡ ፳፫ ፡ ፴፪። ዘፍ፴፭ ፡ ፲፮። ኢዮ፴ ፡ ፳፫)።
፡ ቀመር፤ የቀመር ስም፤ ዐውደ ፀሓይ ፳፰ ዓመት፤ ዕለት ወንጌላዊ ረቡና ማቴዎስ የሚገናኙበት። የጨረቃም ነገር አለበት
፡ (አቡሻ ፡ ፬)።
ማኅደፍ [1] ፡ (ብ መኃድፍ) መቅዘፊያ። ማደፊያ መወልወያ፤ መንዲል ማሠሻ ማበሻ። በማኅደፍ ፈንታ ማኅፈድ ይላል፤ የተሳሳተ ነው። ወእምዝ ይትመጦ ንፍቅ በማኅፈድ። ጸሎት ላዕለ ማኅፈዳት
፡ (ሥር ፡ ቅዳ)
[2] ፡ ማኅደፍ፤–ማደፊያ መወልወያ፤–ኀድፎ ኀደፈ።
ማህጕል ፡ (ላን) ዝኒ ከማሁ፤ አጥፊ መጥፎ። እሉ እሙንቱ ማህጕላን ጸላእያነ ሠናይ። እኩያን ወማህጕላን ኖሎት ፡ (ዲድ፲፤ ፵፩)።
ማኅጣእ ፡ ኀጢአት የሚያሠራ፤ ማመጫ መሸፈቻ ቦታ። ወማኅጣአ አግብርት ማእከላ እምትካት ፡ (ዕዝ፬ ፡ ፲፭)።
ማኅፀብ ፡ (ባት፤ አው መኃፅብ። ማኅፀብት፤ ብ መኃፅብት) ማጠቢያ ማስታጠቢያ፤ የጥበት መሣሪያ። ነሥአ ማኅፀበ ወአስተዮን ለእሱ አባግዕ። ማኅፀበ አልባስ
፡ (ቀሌ። ስንክ ፡ ሐም፲፰)።
ማሕፀን ፡ (ናት፤ መሓፅን) በቁሙ፤ የሴት ሆድ ከዚያውም ለብቻው የተለየ የፅንስ የሽል ቦታ፤ ልጅ ተፀንሶ አስኪወለድ የሚኖርበት። ዕትብት እየጠባ የሚያድግበት። ተዐቍረ ውስተ ማሕፀን። ዘእንበለ ትፃእ እማሕፀን። እንዘ ባ ውስተ ማሕፀና። ተሀውከ ማሕፀና በእንተ ወልዳ ፡ (ቅዳ። ኤር፩ ፡ ፭። ማቴ፩ ፡ ፲፰። ፫ነገ ፡ ፫ ፡ ፳፮)።
ማሕጸን ፡ በቁሙ ማጠን፤–ሐፂን ሐፀነ።
ማሕፀንት ፡ (ታት) ዐደራ፤ ያደራ ገንዘብ፤ እንደ ፅንስ እንደ ሽል በፍጹም ጥንቃቄ የሚጠበቅ። ፡ (ተረት) ዐደራ ጥብቅ፤ ሰማይ ሩቅ። ታገብእ ምድር ማሕፀንታ። ዕቀብ ማሕፀንተከ። ኀፍረት ሰሪቅ እምንዋየ ማሕፀንት(ሔኖ፶፩ ፡ ፩። ፩ጢሞ ፡ ፮ ፡ ፳። ሢራ፵፩ ፡ ፲፱)።
ማሕጼ ፡ ማጤ ፥ ምሣር መቍረጫ መፍለጫ፤ መምቻ መከትከቻ
፡ (መዝ ፡ ፸፫ ፡ ፯። ማቴ፫ ፡ ፲። ፬ነገ ፡ ፮ ፡ ፭ ፡ ፮)።
ማኅፅ ፡ ማጥ ረግረግ፤ አረንቋ የሚያሰ(ስ) ምጥ የሚያስጨንቅ።
ማኅፈሪት ፡ ኵፌት፤ እንደ ዘውድ ያለ ቆብ፤ የቀድሞ ነገሥታት ሊቃነ ካህናት ዛሬም ጳጳሳት ኤጲስቆጶሳት በራሳቸው ላይ የሚደፉት የሚቀዳጁት። በከይዎ ሕዝብ ለጴጥሮስ ተቀጺሎሙ ማኅፈሪተ ልብሶ፤ ጋላት ሶበ መተሩ ክብርተ ርእሶ ፡ (ድጓ)። በማኅፈሪት ፈንታ ማዕፈርት ይላል፤ ፍችው አንድ ነው፤ ዐፈረን ተመልከት።
ማኅፈር [1] ፡ (ርት ራን ራት) የታመነ ወዳጅ ባልንጀራ፤ ዘመድ ጎረቤት ቤተ ሰብ፤ ቄስ ሐኪም፤ ገመናን ኀፍረትን ገልጦ የሚነግሩትና የሚያሳዩት። ዐርክ ወማኅፈር። ንግር ለማኅፈርከ ወለማኅፈረ ሕዝብከ። አመ ኮነ አንበሳ ማኅፈሮ ለላሕም
፡ (ሢራ፵ ፡ ፳፫። ፵፪ ፡ ፲፩። ኩፋ ፡ ፴፯)። ዐማች፤ ያማችና የምራት ወገን፤ የጋብቻ ዘመድ። የወንድ ወገን ለሴት የሴት ወገን ለወንድ ማኅፈር ይባላል።
[2] ፡
ማኅፈር፤–እሙን ወዳጅ –ኀፊር ኀፍረ።
ማሕፈር ፡ ወዳጅ፤–ኀፊር ኀፍረ።
ማኅፈድ ፡ (ዳት፤ አው መኃፍድ። ዕብ አፔዴን። ዐረ ፈደን) ግንብ፤ አዳራሽ ቤተ መንግሥት፤ ኑኅ ርሕብ ምጥቀት ርዝመት ያለው። ዕርድ ምሽግ፤ አንባ ኰረብታ፤ ከጠላት የሚጠበቁበት የሰላይና የጕበኛ የዘበኛ ቤት፤ በከተማ ዙሪያ ዐልፎ ዐልፎ በየበሩ በየማእዝኑ እንደ ሐውልት እንደ ደወል ቤት እንደስላም መጮኺያ ረዥም ኹኖ የሚሠራ፤ ጠላት ወዳጅ ከሩቅ ሲመጣ የሚያዩበት
፡ (ዘፍ፲፩ ፡ ፬ ፡ ፭። ኩፋ ፡ ፲)። ማኅፈድ ጽኑዕ ቅድመ ገጸ ጸላኢ። ዲበ ኵሉ ማኅፈድ ጽኑዕ ነዋኅ። ማኅፈደ ኖሎት ፡ (መዝ ፡ ፰። ኢሳ፪ ፡ ፲፭። ሚክ፬ ፡ ፰)። ማኅፈደ ጢስ፤ ዐምድ። ማኅፈደ ሥጋ፤ ሰውነት ግዘፍ
፡ (መሳ፳ ፡ ፵። መጽ ፡ ምስ)። በማኅደፍ ፈንታ ማኅፈድ ይላል፤ የተሳሳተ ነው፤ ኀደፈን እይ። ጸሎት ላዕለ ማኅፈዳት
፡ (ቅዳ)።
[2] ፡ ግንብ፤–ኀፊድ ኀፈደ።
ማሕፈድ ፡ ግንብ፤–ኀፊድ ኀፈደ።
ማልሕ ፡ (ዐረ ማሊሕ) ጨዋም ፥ ጨው ጨው የሚል ፥ የጨው ውሃ። ባሕረ ማልሕ
፡ (ኦቡሻ ፡ ፶)። ባሕረ ጼው ማለት ነው።
ማሞን ፡ (ጽር ማሞና) ገንዘብ፤ ጥሪት ፥ ብዕል። ጣዖት አሻንጕሊት ከወርቅና ከብር የተሠራ ፡ (ማቴ፮ ፡ ፳፬) ወለንዋይ ባለው ወለማሞን ይላል። ሕፃናትን ማሞ ማሚት ማለት ከዚህ የወጣ ስም ይመስላል።
ማሰረ ፡ (ዕብ ማሳር) እጅ በጅ ሰጠ፤ አስጨበጠ፤ አሲያዘ አስረከበ። ሙሽራ ማለት ከዚህ ወጥቷል፤ በሕግ የተሰጠ ለጋ ቀንበጥ ወጣት ማለት ነው፤ ለሰሌንና ለኮባም ይኾናል።
ማሳኒ ፡ (ኒት ንያን ያት) ማሳኝ፤ የሚጠፋ ጠፊ፤ ፈራሽ በስባሽ። መብልዕ ማሳኒ። ጥሪት ማሳኒ ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፱። ስንክ ፡ ጥቅ፴)።
ማሴው ፡ (ጽር ሜሶ) ማእከል፤ ማእከላይ። አንቀጸ ማሴው ፡ (ኤር፴፱ ፡ ፫)። መስጴጦምያን እይ፤ ከዚህ ጋራ አንድ ነው።
ማሴጌሬት [1] ፡ ሰንበር፤–ሠገረ።
[2] ፡ ማሴጌሬት ፡ (ዕብ ሚስጌሬት) ሰንበር ፥ ዝናር፤ እንደ ወጥመድና እንደ ማገር ዙሮ የሚገጥም የሕንጻ ጌጥ
፡ (፫ነገ ፡ ፯ ፡ ፴፩)።
ማስኖ ኖት ፡ (ማሰነ ይማስን ይማስን። መንሰወ፤ ነሰወ። ዕብ ናሻም፤ ሕቅ አለ) መማሰን፤ መድከም መልፋት ፡ (ዐማርኛ)። መጥፋት መሞት ፥ መበላሸት፤ መፍረስ መበስበስ። ማሕፀንት ዘማሰነት ማስኖ ፍጥረታዌ። ዘማሰነ ልቡ። ወርቅ ዘይማስን። ለብሰ ሥጋ ዘይማስን ወረሰዮ ዘኢይማስን። ይማስን ቤቶሙ ለዕቡያን ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፳፱ ፡ ፫። ፴፪። ፩ጴጥ ፡ ፩ ፡ ፯። ቅዳ። ሢራ፳፩ ፡ ፬)
ማስያስ ፡ (ዕብ ማሽያሕ) መሲሕ ፥ ምሱሕ፤ ቅቡዕ። ማስያስ ዘይሰመይ ክርስቶስ። ማስያስ ናይናን ፡ (ስንክ ፡ ጥር፮። ግብ ፡ ሕማ)።
ማረየ ፡ (ይማሪ፤ ማርዮ) ሟረተ አሟረተ፤ ጠነቈለ ወር አጓደለ፤ በፊደል ቍጥር በግድፈት። መጽሐፍ ግን በማረየ ፈንታ ተመርየ ተማረየ ተማረተ ይላል ፥ ኹሉም ስሕተት ነው፤ አያሰኝም። ለተመርዮ ወለተሰግሎ። ዘያሰግል ወዘይትሜረይ። ዘይትማረይ ወዘያበውኦሙ ውስተ ቤቱ ለማርያን። ኵሉ ተማርዮ እምኀይለ አጋንንት ወኵሉ ተነብዮ እምኀይለ መንፈስ ቅዱስ። ብእሲት ዘትትማረት አው ለካልእታ ትብል ትትማረት በእንተ ፍቅረ ምታ፤ አው በእንተ ፍቅረ ካልእ ፡ (ኩፋ ፡ ፲፩። ቀሌ። ፍ ፡ ነ ፡ ፲፩። መጽ ፡ ምስ። ሲኖዶ)።
ማሪት ፡ ሟርተኛ፤–መረየ ማረየ።
ማራ [1] ፡ የኪሩቤል ስም፤ ዝኒ ዓዲ ከማሁ፤ እግዚእ፤ እግዚኣዊ ዘእግዚእ። ምስጢሩ ገጸ ሰብእን ያያል፤ መደበኛው ርሱ ነውና። በራ ማራ ፡ (መዋሥ)።
[2] ፡ (ዕብ ማራህ፤ ማራታ) የቦታ ስም መራራ ውሃ ያለበት። ኢረከቡ ማየ ከመ ይስተዩ በማራ። ወግዕዙ እምነ ማራ ፡ (ዘፀ፲፭ ፡ ፳፫። ዘኍ፴፫ ፡ ፱)። ዳግመኛም በማራ ፈንታ ምረት ይላል፤ ስሕተት ነው።
ማራን ማራና ፡ ማራና፤ እግዚእነ ፥ ጌታችን። በምራን ዘይቤ ሲፈቱት ግን የሚማርን ማራኝ ፥ የሚያስር የሚያቈራኝ ኹሉን የሚዳኝ፤ ሰው አይፈሬ መልአክ አይፍሬ የፍርድ ገበሬ ያሰኛል። ፡ (ማቴ፲፫ ፡ ፬ ፡ ፴፪–፵፪)።
ማራን አታ ፡ (እግዚእ መጽአ) የሐዲስ መላሽ ፡ (፩ቆሮ ፡ ፲፮ ፡ ፳፪) እስከ ምጽአቱ ለእግዚእነ ያለውን ፥ የቄርሎስ መላሽ እንደ ጽርኡና እንዳረቡ ሐዲስ ፥ ማራን አታ በማለት ፈንታ ፩ ቃል አድርጎ መራናታ ይላል። ባለሐዲሶች ግን ባለሊቃውንትም ሳይቀሩ የቄርሎስ ቃል መስሏቸው ለርሱ ሰጥተው ይፈታሉ፤ ፍችውንም መቅረዟ ሙበራቷ ይሉታል። ባለቅኔዎችም መረነ አበራ ብለው ይገሱታል፤ የኹሉም ስሕተት ነው፤ ያማርኛውን ሐዲስና መናረትን እይ፤ ነዊር ኖረ ፡ (ዕብ፱ ፡ ፪)።
ማር ማሪ ፡ (ሱር) እግዚእ፤ ጌታ። ለግዜርም ለሰውም ይነገራል፤ ስምነቱ ግን ያምላክ ነው። ማር ኤፍሬም ሶርያዊ ፥ ማሪ ያዕቆብ ዘስሩግ ቢል፤ የኔታ ፡ (የኔ ጌታ) እገሌ፤ ጌታዬ እገሌ እንደ ማለት ነው
፡ (ሃይ ፡ አበ)። ማርታም ማለት እንደዚሁ እግዝእት እመቤት ማለት ነው።
ማርቲሪ ፡ (ጽር። ዕብ ሄዒድ። ዐረ ሸሂደ) ሰምዐ ፥ መሰከረ፤ ሰማዕት ኾነ ፡ (ዮሐ፩ ፡ ፲፭)።
ማርዪ ማሪ ማሬ ፡ (ዪት ሪት፤ ርያን ያት፤ ረይት) የሚያሟርት የሚጠነቍል፤ ማርተኛ ጠንቋይ፤ ነቢየ ሐሰት ካህነ ጣዖት። ጲጥፋራ ማሪ ዘሀገረ ሔልዩ። ዮቶር ማሬ ምድያም። ወአምጽኡ ማሬ ዘድዮስ
፡ (ዘፍ፵፩ ፡ ፵፭። ዘፀ፪ ፡ ፲፮። ግብ፲፬ ፡ ፲፫)። እመ ቦ ዘሐተተ ማሪተ። ማርያን ወሰብአ ሰገል። ውእቱ ይገብር ግብረ ሥራይ ወዘማርያት ፡ (ቀሌ። ዳን፮ ፡ ፭። ፪ዜና ፡ ፴፫ ፡ ፮)። በማረይት ፈንታ ማሪታት ይላል ፥ አያሰኝም፤ ማረይት ቅጽልነቱ መድበል ስለ ኾነ ብዙዎችን ወንዶችና ሴቶች ያስተባብራል፤ ማሪታት ግን ለሴቶች ብቻ ነው። ሐሳውያን ማሪታት ፡ (ቄር ፡ ገ፩)።
ማርያም [1] ፡ መራረ መዋዕል፤–መሪር መረ።
[2] ፡ (ዕብ ሚርያም) ነቢይት ፥ የሙሴና የአሮን እኅት ፡ (ዘፀ፲፭ ፡ ፳)። ቃሉ ፪ ነው ፥ ማር ሚር ፩ ወገን፤ መራራ መራር። ያም ፥ ዮም ዕለት ዘመን መዋዕል፤ በተገናኝ ምርርተ ዮም ወይም መራረ መዋዕል ፥ ዘመሪር መዋዕሊሃ። ዘመኗ ዘመነ ልደቷ ማሩር የተባለእ ማሉል ፈርዖን በእስራኤል ላይ ክፉ ምክር መክሮ ወንድ ወንዱ ለሞት ሴት ሴቱ ለትሎት ብሎ መራራ ዐዋጅ ያስነገረበት፤ እስራኤልም ዕርር ምርር ብለው ያዘኑበት ያለቀሱበት የሐዘን የመከራ ወራት ስለኾነ አባት እናቷ፤ ዘበመዋዕሊሃ አምረሩ ግብጽ ሕይወተ እስራኤል ሲሉ እንደዚህ ያለ ስም ሰጥተዋታል
፡ (ዘፀ፩ ፡ ፰–፲፮)። ፪ኛም፤ ኮከብ ዐቢይ ወረደ እምሰማይ ወስሙ ለውእቱ ኮከብ ዕጕሥታር ይላልና ፡ (ራእ፰ ፡ ፲ ፡ ፲፩)። ማር ሚር ፥ ሬቶ ሐሞቶ የሚባል ኮከብ፤ ያም ፥ ባሕር ይኾናል፤ ያም ሱፍ እንዲል ባሕረ ኤርትራ ሲል ፡ (ዕብራ)። በተገናኝ ፥ ኮከበ ባሕር፤ መራሒት ለእለ ውስተ ባሕር ማለት ነው። ባሕርም የዘመን ምሳሌ ነውና ፥ የባሕሩና የኮከቡ ስም ጣዕም ምረት ስለ ኾነ ምስጢሩ ከዚያው ከፊተኛው ይገባል፤ የመርሐ ዕዉር አርእስት ኍልቈ ዘመን ሲል ሐሳበ ባሕር በማለት ፈንታ ባሕረ ሐሳብ እንዲል። ስላዲሱም ዘመን ቡራኬ እንኳን ከዘመን ወደ ዘመን አሻገረኽ ማለት ዘመንን በባሕርና በወንዝ መስሎ ነው፤ መመሳሰል የጋራ ነውና ፡ (ሕዝ፳፯ ፡ ፪–፭)። በፈርዖን ዐዋጅ ከባሕር ከጀጀባ ሥር ለሚወድቁ ለእስራኤል ልጆች፤ ናሁ ወልድ ይትወለድ ለነ፤ ቤዛ ወመድኅን እምግብጽ ያወፅአነ እያለች በደረቅ ትንቢቷ እንደ ኮከብ የምታበራ ኋላም በኤርትራ ከበሮዋን ነጥቃ ስብሕዎ እያለች የምትቀነቅን የምትመራ ነቢዪት ማሕሌታዊት ልዕልተ ቃል አርኣያ ድንግል ስለ ኾነች አስቃድሞ ይህ ሊዓላዊ ስም ኮከበ ባሕርነት ተሰጥቷታል፤ ትንቢቷም በአይሁድ ኩፋሌ ይገኛል። ኖትያዊ ይኔጽር ኀበ ከዋክብት
፡ (እለ ሰሜን) አመ የሐውር ውስተ ባሕር ዘከመ ይመርሓ ወያከይዳ ለሐመሩ እስከ ይበጽሕ ኀበ መርሶ ፡ (ማር ፡ ይሥ፳፰)። ማርያም ብሎ ዘበዕብራይስጢ ሚርያም በማለት ፈንታ ማሪሃም ማለት የተሳሳተ ነው ፡ (አርጋ። ታምረ ፡ ማር)። በዚህም ስም ብዙ ሴቶች ተጠርተውበታል፤ እስከዚህ ሠምና ብሉይ ነው። ለወርቁና ለሐዲሱ ግን የኮከብ ልጅ ኮከብ ነውና ፥ በርሷ ኮከብነት የርሱን ኮከብነት መናገር ነው ፡ (ዘኍ፳፬ ፡ ፲፯። ፪ጴጥ ፡ ፩ ፡ ፲፱)። ብሊት ማርያም የብሉይ ኪዳን ጥንት እንደ ኾነች ሐዳስ ማርያምም የሐዲስ ኪዳን ጥንት ናትና፤ አስቀድሞ በማርያም ዘመን የኾነው ግፍና መከራ ድንቅ ሥራ ኹሉ ኋላ በድንግል ማርያም ለሚኾነው አምሳል መርገፍ ኹኖ ተጥፏል ፡ (ዕብ፲ ፡ ፩)። ማርያሞች እንዲነጻጸሩ ፥ ፈርዖንና ሄሮድስ ፥ ሙሴና ክርስቶስ ፥ ንሴብሖና ታዐብዮ ይነጻጸራሉ ፡ (ዘፀ፲፭ ፡ ፩ ፡ ፳፩። ሉቃ፩ ፡ ፴፮–፵፭)። ብሊት ማርያም በልደተ ሥጋ እኅተ ሙሴ እንደ ተባለች ፥ ሐዳስ ማርያምም ለሥግው ቃል ልጇ በልደተ ነፍስ እኅት ትባላለች። ማስተባበር ልማዷ እንጂ ነው፤ ድንግልናን ከወሊድ እንዳስተባበረች ፥ እኅትነትንም ከናትነት አስተባብራለች፤ በሰንበት ላይ ደብረ ዘይት እንዲሉ። ይኸውም ዮም ወለድኩከ በተባለበት በበኵርነቱ በግብር ልደቱ ነውና፤ የበኵዮን ፍች እይ። የጐንደሩም ሊቅ አዋልደ ሎጥን ከኦሪት ጠቅሶ በሚበዝኁ ቅኔው እንዲህ ይላል ፡ (ዘፀ፲፱ ፡ ፴፮–፴፰)። በዘርዐ አቡሆን ኮና አኃተ ውሉዶን አኃት አመ ወርኀ ሕጸጽ ወንትጋ፤ ለከሰ አምላክ ክርስቶስ ቀዳሜ ጸጋ ወለተ ሐና ጠባብ በመንፈስ ቅዱስ አኅትከ እንዘ እምከ በሥጋ።
ማቂፊም ፡ (ዕብራ) የሚያቅፉ የሚከቡ፤ ዙሪያዎች። ዘሩ ሐቀረ ነው
፡ (፫ነገ ፡ ፯ ፡ ፳፬)።
ማኒ [1] ፡ (ጽር። ሱር ምኔእ ምናህ። ዕብ ማናህ) ሰፈረ ቈጠረ ፈጸመ ፡ (ዳን፭ ፡ ፳፮)። ባለቅኔዎች ግን መስፈሪያ ድርጎ ይሉታል። ዐይንየሂ ሶበ ተሰፍረ በጽልመተ ሌሊት ማኒ እስከ ኤዶምያስ ሀገርየ መኑ ይመርሐኒ ፡ (የውር ፡ ቅኔ)።
[2] ፡ የሰው ስም፤ ፩ኛው በዘመነ ብሉይ የነበረ ይሁዲ ፍጹም ከሓዲ፤ ሠራዒ መጋቢ ፈጣሪ የለም የሚል የፍራማሶኖች አባት። እልፍ ዐላውያን፤ ማኒሰ ኮነ የዐብዮሙ ፡ (ቅኔ)። ፪ኛው በዘመነ ሐዲስ የተነሣ፤ ቃል ሥጋ ኮነን ምትሀት ጽላሎት የሚል ፡ (ቄር እስት)።
ማንቍርት ፡ በቁሙ፤ ያንገትና ያገጭ መገናኛ ጕጡ ፡ (ዐማርኛ)።
ማንጦን ፡ (ጽር ፕኔፍማቶን) የተሳሳተ ከፊለ ስም፤ መንፈስ ማለት ነው። አግያስ ማንጦን ፡ (አጊዮስ ፕኔፍማቶስ) ቅዱስ መንፈስ ፡ (ቅዳ)።
ማዔጌላህ ፡ (ዕብ ማዕጋላህ፤ ማዕጋል) የሠረገላ መንገድ ፥ የሰራዊት ሰፈር፤ ክቢ ከባቢ ፥ መካበቢያ። ወበጽሐ ውስተ ማዔጌላህ ፡ (፩ነገ ፡ ፲፯ ፡ ፳)።
ማዕለል ፡ ዐለላ፤ ማለያ፤ ቀለም፤ ብዙ ዐይነት ያለው። ኢትሠአን አሣእነ ዕሉለ በማዕለል፤ ወኢሕልቀተ ወርቅ ውስተ አጻብዒከ ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፲፩)።
ማዕለልት ፡ ጕልት፤ ገንዘብ፤ ምሎ ተፈጥሞ ሕርም ይኹንብኝ ብሎ የሰጡት። ወሰመዩ ስም ለውእቱ መካን ማዕለልት ፡ (ዘኍ፳፩ ፡ ፫)።
ማዕሌት [1] ፡ ወንጀል ዐመፅ፤–ዐለየ።
[2] ፡ ወንጀል፤ ግፍ በደል፤ አሉታ፤ እንቢታ፤ ኀጢአት፤ ክፋት። ማዕሌተ ሀገር። በማዕሌቶሙ ዘዐለዉከ። መልአከ ማዕሌት። ከመ ይኅበር ማዕሌቶሙ። ማዕሌተ ይገብር ላዕሌከ ዓምጽ ፡ (ሢራ፳፮ ፡ ፭። ዳን፱ ፡ ፯። ፫ነገ ፡ ፲፩ ፡ ፲፬። ሆሴ፯ ፡ ፪። ዓሞ፯ ፡ ፲፩)።
ማእምር ፡ (ርት ራን ራት) ዝኒ ከማሁ። ማእምር ወዐውቅ። ማእምረ ኅቡኣት። ማእምራን ለገቢረ ሠናይ። ማእምራነ ቃል ፡ (መዝ ፡ ፶፬። አርጋ። መክ፬ ፡ ፲፯። ሢራ፲፰ ፡ ፳፱)።
ማዕምቅ ፡ ጥልቅ ዐዘቅት፤–ዐሚቅ ዐመቀ።
፡ ማዕምቅ ት፤ ፡ (ቃት) ጥልቅ ቦታ፤ ጕድጓድ፤ ዐዘቅት፤ የምድር ቤት፤ ገደል፤ ዋሻ ቈላ፤ መቀራቅርት፤ ዘብጥ ዘቅዛቃ ወዳቃ። ማዕምቀ ባሕር። ማዕምቅቲሃ ለምድር። ወአውደቆ ውስተ ማዕምቅ። ኵሉ ማዕምቅ ይምላእ ፡ (መዝ ፡ ፷፰። ኩፋ ፡ ፭። ራእ፳ ፡ ፫። ኢሳ፵ ፡ ፬። ባሮ፭ ፡ ፯)።
ማእሰረ ልሳን ፡ ድዳነት፤ ዝምታ
፡ (ማር ፡ ፯ ፡ ፴፭)።
ማእሰረ ሰላም ፡ ፍቅር፤ አንድነት ፡ (ኤፌ፬ ፡ ፫)።
ማእሰረ ተዋስቦ ፡ የግቢ ሥርዐት፤ ተክሊል ቃል ኪዳን ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፳፬ ፡ ፬)። በነገር ኹሉ እየተናበበ እንደ ስልቱና እንዳወራረዱ ይፈታል።
ማእሰረ ዐመፃ ፡ ኀጢአት፤ ክህደት ፡ (ቅዳ)።
ማእሰረ ግዘት ፡ የግዝት ቃል፤ ውጉዝ ማለት ፡ (አፈ ፡ ተ፬)።
ማእሰር ፡ (ራት፤ መኣስር። ማእሰርት፤ መኣስርት፤ ታት) ማሰሪያ፤ መታሰሪያ፤ የእስራት ቦታ፤ መሣሪያ። ታወፅኦሙ ለሙቁሓን እማእሰር። ማእሰርተ ኀጺን። መኣስርቲሃኒ ሰርጐ ያክንት ፡ (ኢሳ፵፪ ፡ ፯። ሔኖ፷፩ ፡ ፫። ሢራ፮ ፡ ፴)።
፡ ልባጥ ልብጣት፤ የናስና የግንብ። ወማእሰሩ በዕፀ ብሔር
፡ (፩ዕዝ ፡ ፮ ፡ ፳፬)።
ማዕሰበ ፡ (ዐሰበ) ፈት ኾነ፤ ገለሞተ፤ ብቻውን ኖረ፤ ሚስቱ ሙታ፤ ወይም በነውር ወጥታ። ሐና ወለተ ፋኑኤል ማዕሰበት ሰማንያ ወአርባዕተ ክራምተ ፡ (ስንክ ፡ የካ፰። ኢሳ፶፬ ፡ ፬)። በማዕሰበ ፈንታ ተማዕሰበ ይላል፤ አንድ ወገን ነው። እንዘ ትትማዐሰቢ ፡ (ኩፋ ፡ ፵፩)።
ማእስ ፡ (ብ አምእስት) በቁሙ፤ ማስ ቈርበት፤ ጠፍር ፥ ቈዳ አነዳ። ማእሰ በግዕ ሕሱይ። ማእሰ ዘባኑ። ኢይቅንቱ ማእሰ ፡ (ዘፀ፳፭ ፡ ፭። ኢዮ፵ ፡ ፳፭። ሕዝ፵፬ ፡ ፲፰)። ትመሥጥዎሙ አምእስቲሆሙ እምላዕሌሆሙ። በልዑ አምእስተ ሠረገላቲሆሙ ወማእሰ ቀቀበ አስይፍቲሆሙ ፡ (ሚክ፫ ፡ ፪። ዮሴፍ። ዘፍ፳፯ ፡ ፲፮)።
ማዕስ [1] ፡ (ብ አምእስት) በቁሙ፤ ማስ ቈርበት፤ ጠፍር ፥ ቈዳ አነዳ። ማእሰ በግዕ ሕሱይ። ማእሰ ዘባኑ። ኢይቅንቱ ማእሰ ፡ (ዘፀ፳፭ ፡ ፭። ኢዮ፵ ፡ ፳፭። ሕዝ፵፬ ፡ ፲፰)። ትመሥጥዎሙ አምእስቲሆሙ እምላዕሌሆሙ። በልዑ አምእስተ ሠረገላቲሆሙ ወማእሰ ቀቀበ አስይፍቲሆሙ ፡ (ሚክ፫ ፡ ፪። ዮሴፍ። ዘፍ፳፯ ፡ ፲፮)።
[2] ፡ ማዕስ ፤–ማስ ቈርበት ፤–መአሰ ማእስ።
ማእረር ፡ (ራት) መከር፤ አዝመራ፤ ፍሬ የልታጨደ ያልተሰበሰበ። ይበልዑ ማእረረከ። መዋዕለ ማእረር። ማእረሩሰ ብዙኅ። ወምድር ትሁብ ማእረራ። ማእረረ ምግባሮሙ
፡ (ኤር፭ ፡ ፲፮። ሢራ፳፬ ፡ ፳፮። ማቴ፱ ፡ ፴፯። ዘካ፰ ፡ ፲፪። ኢሳ፫ ፡ ፲)።
ማዕረብት ፡ (ዕብ ማዐራብ) መናገጃ፤ ገባያ፤ መደብር። የንግድ ዕቃ፤ ሸቀጥ። ነጋድያን ሠየጥ በማለት ፈንታ ማዕረብት ይላል፤ የተሳሳተ ነው። ተርሴስ እሙንቱ ማዕረብትኪ። አራም ማዕረብትኪ
፡ (ሕዝ፳፯ ፡ ፲፪ና
፡ ፲፮)።
ማዕርግ መዓርግ ፡ (ጋት) ማረጊያ፤ መውጫ፤ መረጋገጫ፤ መሰላል፤ ዕርከን፤ ደረጃ፤ እንደ ጣት መቀዳደምና መከታተል መበላለጥ ያለው፤ ውስጠ ብዙ፤ ሥራው የመሥመር ዐይነት፤ርስ በርሱ የተያያዘ፤ ደረገን ተመልከት። ማዕርግ ትከልት ውስተ ምድር። መዓርግ ዘያወርድ እምሀገረ ዳዊት። መዓርግ ምሥዋዕ። ዐሠርቱ መዓርጋት ፡ (ኩፋ ፡ ፳፯። ነሐ፫ ፡ ፲፭። ሢራ፶ ፡ ፲፩። ፬ነገ ፡ ፳
፡ ፱–፲፩)። ለፀሓይና ለጨረቃም መንገድ ይነገራል። ሠለስቱ ምእት ወስሳ መዓርጋት፤ ለአሐቲ ኆኅት ሠላሳ መዓርግ ዕሩያን ፡ (አቡሻ ፡ ፬)። በመድረክ ፈንታ ማዕርግ ይላል፤ ስሕተት ነው። ማዕርገ ዳጎን ፡ (፩ነገ ፡ ፭ ፡ ፭)።
፡ በቁሙ፤ ሹመት፤ ክብር፤ ሥልጣን፤ ከኳደሬ እስከ ንጉሥ፤ ከአናጕንስጢስ እስከ ሊቀ ጳጳስ ያለ። ወተጋብኡ ለህርቃኖስ መዓርገ መንግሥት ወመዓርገ ክህነት። ይትመተር እማዕርጊሁ። አቡሊናርዮስ ተአመነ ከመ መንፈስ ቅዱስ የሐጽጽ እምአብ ወወልድ በማዕርገ አምላክና
፡ (ዮሴፍ። ቀሌ። ፈ ፡ መ ፡ ፮ ፡ ፩)።
፡ ክፍል፤ ወገን፤ ተራ፤ ረድፍ። ወካዕበ ሠርዐ ፍድፋዴ ባሕታውያን ውስተ ሠለስቱ መዓርጋት። ስፉይ በሠላስ መዓርገ ስፍየት ፡ (ፊልክ ፡ ፬። ፈ ፡ መ ፡ ፴፩ ፡ ፭)።
ማዕቀቢ ፡ አስጠባቂ፤ ዐደራ አኗሪ። ካዕበተ ይፈዲ ለማዕቀቢሁ ፡ (ዘፀ፳፪ ፡ ፱)።
ማዕቀብ ፡ (ቅብ) (ቅብ) ዝኒ ከማሁ ለዐቃቢ፤ ዘበኛ፤ ወታደር፤ እረኛ፤ ጠባቂ። ማረፊያ መጠበቂያ ቦታ። እቀውም ውስተ ማዕቀብየ ፡ (ዕን፪ ፡ ፩)።
ማዕቀፍ ፡ (ቅፍ፤ ቅፍት) ዕንቅፋት፤ መሰናክል፤ ወጥመድ። ሲያበዛ መዓቅፍ ያላል። ፍኖት መጽያሕት ዘእንበለ ማዕቀፍ። እስመ ማዕቀፍየ ሊተ። ወእማዕቀፎሙ። ያመጽኡ ማዕቅፍተ ፡ (ቅዳ ፡ ኤጲ። ማቴ፲፮ ፡ ፳፫። መዝ
፡ ፻፵። ኢሳ፳፱ ፡ ፳፩)።
ማዕቅድ ፡ ዐቃድ ፣ ቀስተ ደመና፤ ጕበን፤ ጣራ፤ ባጥ፤ መዋቅር። ሲያበዛ መዓቅድ ይላል። አልቦ ጠፈር ለመዓቅዶን፤ ወአልቦ ሣዕር ለመክደኖን፤ ኢይፈቅድ አሕባለ ለመዓቅዶን ፡ (ገድ ፡ ላሊ)።
ማዕበል [1] ፡ በቁሙ፤ ብልጭታ፤–ዐበለ።
[2] ፡ (ልት። ዐረ ሚዕበለት) የብረት መሣሪያ፤ ማረሻ ማጭድ፤ ፍላጻ ጦር፤ ሰይፍ ሳንጃ፤ የመሰለው ኹሉ። ይፋቶች ሰይፉን ዐበሌ እንዲሉት። ማዕበሉ። ማዕበለ ኀጺን ማዕበል በሊኅ ልሳኖሙ። ትወፅእ ማዕበልት ከመ መብረቅ ፡ (፩ነገ ፡ ፲፫ ፡ ፳፩። ፫ነገ ፡ ፮ ፡ ፲፩። ኤር፱ ፡ ፰። ዘካ፱ ፡ ፲፪። ዕን፫ ፡ ፲፩)። የብዕለን ጥሬ ምብዓልን ተመልከት።
[3] ፡ (ላት) ፤
በቁሙ ፤
የውሃ ሁከት ፤ ሞገድ ፤
ፈረሰኛ ፤ ጐርፍ ፤ የሚወስድ
የሚያሰጥም ፤
የሚያማታ የሚያንገላታ።
ወደፈኖሙ ማዕበል። ማዕበለ ባሕር። ማዕበል
ዐቢይ። ማዕበለ ማይ። ማዕበላተ ውሒዛተ መናፍስት ፡ (ዘፀ፲፭ ፡ ፭። ኢዮ፴፮ ፡ ፴። ዮና፩ ፡ ፲፩። ኢሳ፷፮ ፡ ፲፪። ኪዳ)።
ማዕተበ ረስን ፡ መስቀላዊ የተኵስ ምልክት፤ ጠባሳ፤ ዕትራት። ቀይ የመስቀል ምልክት፤ ከልብስ ላይ በቀይ ፈትል የሚጣፍ፤ የሚሰፋና የሚጠለፍ ፡ (ሥር ጳኵ)።
፡ አብነት፤ ምሳሌ፤ ጠንክ። ኀደገ ለነ ማዕተቦ ፡ (ድጓ። ፩ጴጥ ፡ ፪ ፡ ፳፩)።
ማዕተብ [1] ፡
ምልክት፤–ዐቲብ ዐተበ።
[2] ፡ (ዕብ ሖታም) ኅቲም ቀለበት፤ ፈርጡ ማኅተም የኾነ። ኀቲምን ተመልከት። ሕልቀተ ማዕተብ። ከመ ማዕተብ ፡ (ሢራ፵፱ ፡ ፲፩። ሐጌ፪ ፡ ፳፪። ኤር፳፪ ፡ ፳፬)።
፡ ትእምርተ መስቀል። ዐጽፍ ጸሊም ዘምሉእ ማዕተበ። ረሰየ ዐውደ በኣቱ ማዕተበ መስቀል ዐውዶ ፡ (ገድ ፡ ዳን። ፊልክ ፡ ፳፮)።
፡ በቁሙ፤ ማተብ፤ ምልክት፤ ዕልባት። ማዕተበ ሐሪር ዘሀሎ በክሣዱ። ወግዝረትሰ ማዕተበ ጽድቅ። ማዕተባ ፡ (ማኅተማ) ለመጽሐፍየ ፡ (ስንክ ፡ ሐም፲፱። ሮሜ፬ ፡ ፲፩። ፩ቆሮ፱ ፡ ፪)።
[3] ፡ አንባር፤ ማልደያ፤ ቢተዋ፤ ጩፋ፤ የጅቦራ፤ የልካ። ኹሉም የእጅ ጌጥ ነው፤ ቢተዋ ይበልጣል፤ የሚያደርገውም ዐሥር ገዳይ ነው፤ እገሌ ቢተዋ መልቷል እንዲሉ። አንብረኒ ከመ ሕልቀት ውስተ ልብከ፤ ወከመ ማዕተብ በመዝራዕትከ ፡ (ማሕ፰ ፡ ፮)።
ማእነም ፡ (ማት) መሥሪያ፤ መሣሪያ፤ የሰፊ የጠላፊ የሸማኔ ዕቃ። ግብረ ማእነም። ይትአነም በማእነም። ኬነውት ዘማእነም ፡ (ዘፀ፳፮ ፡ ፩። ፳፰ ፡ ፲፯። ፴፯ ፡ ፳፩)።
ማዕነቅ [1] ፡
ቡላል፤–ዐኒቅ ዐነቀ።
[2] ፡ ዋኖስ፤ ቡላል፤ የርግብ ዐይነት ወፍ፤ ዐንገቷ ሐር የታሰረበት የሚመስል
፡ (ዘፍ፲፭ ፡ ፱። ማሕ፩ ፡ ፲)።
ማእነፍ ፡ (ብ መኣንፍት) የሥልስ ወጭት፤ ጻሕለ ኀጺን ወብርት፤ ማኅተመ ኅብስት ኅብስተ ገጽ የሚጋገርበት። ሊጡን ወይም ቡሖውን በርሱ እያደረጉ ከእቶን አግብተው ሲያወጡት፤ ኅብስቱ ርሱን መስሎ የርሱን መልክ ነሥቶ ይወጣልና፤ ጻሕሉን ማእነፍ ያሰኘው የኅብስቱና የሥልሱ ሽታ ነው። ወትገብር መኣንፍቲሃ
፡ (ዘፀ፳፭ ፡ ፳፱)። ዳግመኛም፤ መኣንፍት በማለት ፈንታ መኣፍንት ይላል፤ መጋገሪያ ማለት ነው። አፈየን ተመልከት።
ማዕነፍ ፡ የሥልስ ወጭት፤–አኒፍ አነፈ።
ማእን ፡ ስፋት፤ ወርድ። ባለብሉዮች ግን መማቻ መታኰሻ ቅጥር ይሉታል። ወገብረ ቆመ አረፍቱ ሰብዓ በእመት፤ ወማእኖ ዘኀምሳ በእመት ፡ (ዮዲ፩ ፡ ፪)።
ማዕኖ ፡ ዐዛባ ጭቃ፤–ምኢን መአነ።
ማእከለ ፡ (ደቂቅ አገባብ) በመካከል፤ ወደ መካከል፤ በውስጥ ወደ ውስጥ። ቁም ማእከለ። ባእ ማእከለ። ሐነጽኩ ማኅፈደ ማእከሎ
፡ (ሉቃ፮ ፡ ፰። ሕዝ፲ ፡ ፪። ኢሳ፭ ፡ ፪)።
ማእከላዊ ይ [1] ፡ መካከለኛ፤ የማናይ ፀጋማይ ወይም ቀዳማይ ደኃራይ ላዕላይ ታሕታይ ያለው። ወልዱ ማእከላዊ። ፍኖት ማእከላይ። ማኅደር ማእከላይ። አበው ማእከላውያን። ይቤለከ ከመ ትፀመድ ወትትጋደል በገድል ማእከላይ፤ ከመ ኢይድክም ሥጋከ። እስመ ማእከላይ አንተ
፡ (ፈ ፡ መ ፡ ፲፩ ፡ ፪። አፈ ፡ ድ፪። ቀሌ። ያዕ ዘእል። ስንክ ፡ ግን፲፰ ፡ ራእ፫ ፡ ፲፮)።
[2] ፡ ማእከላዊ፤ ዳኛ ጠባቂ፤ አማላጅ አስታራቂ።
፡ (ተረት) ዳኛ የወል፤ ምሰሶ የመካከል። ማእከላይሁ ለእግዚአብሔር ወለሰብእ ፡ (ቄር)።
ማእከል [1] ፡ መካከል፤–አኪል አከለ።
[2] ፡ ማእከል ፤ መካከል ፤
ወገብ ጕንድ ፤
ሕንብርት ሆድ ፤
ውስጥ ማኅደር ፤
ኅዋ አየር ፤
ወሰን ደንበር ፤ እኵሌታ እኵል። አዕማድ
እለ ማእከል።
ምትሮሙ እማእከሎሙ።
ያንቅዕከ እማእከልከ።
ዝንቱ መካን
ማእከለ ምድር።
ፃኡ እማእከላ።
ይሰርር ማእከለ
ሰማይ ወምድር።
ማእከለ ሌሊት
(መሳ፲፮ ፡
፳፱። ዘፍ፲፭
፡ ፲።
ዳን፩ ፡
፶፭። ቀሌ።
ኢሳ፶፪ ፡
፲፩። ራእ፰
፡ ፲፫።
ማቴ፳፭ ፡
፮)።
ማዕከል ፡ መካከል፤–አኪል አከለ ማእከል።
ማእከልና ፡ ማእከላዊነት። ለእመ ሞተ ፍጹም በእርግናሁ ወማእከላዊኒ በማእከልናሁ ወወጣኒ በውርዝውናሁ
፡ (ፊልክ ፡ ፬)።
ማዕከክ [1] ፡ ድስት ማሰሮ፤–ዐኪክ ዐከከ።
[2] ፡ ማዕከክ፤ ፡ (ዕብ ኪዮር) ድስት፤ ማሰሮ ምንቸት፤ የሚጣድ። ገንቦ ማድጋ፤ እንስራ ጋን ዝንግሪር፤ ዋዲያት ለገን፤ ማጠቢያ መታጠቢያ፤ የውሃ ዕቃ ኹሉ፤ ክብነት ያለው። ጣሳ ኵባያ ዋንጫ ጽዋዕ ሳይቀር መቅጃውን ኹሉ ያሳያል። ኬጥሮጋውሎስን፤ ንብቲራን መቅለድን ተመልከት፤ ከዚህ ጋራ አንድ ነው። ዘገብረ ማዕከከ ብርት፤ ወገብሮ ለውእቱ ማዕከክ ከመ ይትኀፀቡ ውስቴቱ። ሕንበርትኪ ከመ ማዕከክ፤ ጽዋ ፡ (ዘፀ፴፰ ፡ ፳፮–፳፯። ማሕ፯ ፡ ፫)።
ማእኰት [1] ፡ ጸጋ ሀብት ስርየት በጥምቀት በቍርባን በንስሓ የሚሰጥ። ሀቦ እግዚኦ ማእኰተ መንፈስ ቅዱስ በዕበየ ሣህልከ ወምሕረትከ
፡ (ግንዘ)።
[2] ፡ ማኵታ፤ እጅ መንሻ፤ በረከት፤ ጕቦ ማማለጃ፤ አመስግኖና ተመስግኖ የሚሰጡት የሚቀበሉት። ነገሥታት ወመኳንንት እለ ይበልዑ ማእኰት። ወመኳንንቲሆሙ በላዕያነ ማእኰት
፡ (ቀሌ። መቃ ፡ ገ፱)።
[3] ፡ ምልጃ ተስፋ ደጅ ጥናት። መሐላ ኪዳን ብፅዐት። ወብየ ማእኰት እምኀበ ዘፈጠረኒ ከመ እለ አስሐትክዎሙ ይትወደዩ ምስሌየ ውስተ እሳት። ወወሀቦ ማእኰተ ለቅዱስ ሚካኤል ለዘገብረ ተዝካሮ
፡ (መቃ ፡ ገ፳፪። ድር ፡ ሚካ)።
ማዕው ማዑት ፡ (ብ አማዑት። ዕብ ሜዒም፤ ሜዖት። ሱር ምዓያ። ዐረ መዕይ፤ ብ አምዓእ) አንዠት፤ ሆድ ፥ የሆድ ዕቃ የመብል መሣሪያ፤ ካንዠት ጋራ ዐብሮ ተያይዞና ተገንዞ ያለው ንዋየ ውስጥ። ማዕውና ማዑት ስላልተለመዱ አማዑት ብቻ እንደ ሰብእ ውስጠ ብዙ ኹኖ ላንድም ይነገራል። እስከ ይወፅእ አማዑትከ። ቦአት ከመ ማይ ውስተ አማዑቱ። ሥብሕ ዘውስተ አማዑቱ። ሕማመ አማዑት። እምብካዮሙ ይትመሰዉ አማዑቲከ ፡ (፪ዜና ፡ ፳፩ ፡ ፲፭። መዝ
፡ ፻፰። ዘሌ፬ ፡ ፰። ግብ፳፰ ፡ ፰። ሢራ፴ ፡ ፯)። የብዙ ብዙ ሲኾን አማዕዋት ያሰኛል ፡ (ዘፍ፵፫ ፡ ፴)።
ማዕዘር ፡ ብርሃን፤ የጮራ እግር፤ ቀርኑ፤ ጦሩ፤ የሚዋጋው። እንተ ሠረቀ ማዕዘሩ ፡ (ስንክ ፡ መጋ፭)።
ማእዜ ፡ (ዕብ ማታይ። ሱር ኤምታይ። ዐረ መተ) የጊዜና የጥያቄ አገባብ፤ መቼ ምን ጊዜ ፥ በምን ሰዓት። ለ እም እስከ ይሰማሙታል። ኈለቈኑ አውራኂሁ ማእዜ ይትወለድ። ማአዜ እበጽሕ። ለአይ ወለማእዜ መዋዕል። ዘኢይብልዎ እማእዜ። አስከ ማእዜኑ ትላሕዎ ፡ (ኢዮ፴፱ ፡ ፪። መዝ
፡ ፵። ፩ጴጥ ፡ ፩ ፡ ፲፩። ቅዳ ፡ ኤጲ። ፩ነገ ፡ ፲፮)። ኢ ወኢ ትርጋፅ፤ ኒ ትርኣስ ሲኾኑት መቼም መች ከቶ ይኾናል። ኢማእዜ ኢኮኑ ሕያዋነ። ወኢማእዜ። ኢለከፎን ፀሓይ ማእዜኒ ፡ (መቃ ፡ ገ፩። ቄር። ስንክ ፡ ኅዳ፳፮)።
ማእዝን ማእዘን ት [1] ፡ (ብ መኣዝን ት፤ ማእዝናት፤ ማእዘንታት) በቁሙ፤ የቦታ ክፍል ለብቻው አንድ ወገን የተለየ፤ እንደ ዦሮ ተመሳሳይ አንጻር ኹለተኛ ያለው። መዠመሪያውን ምሥራቅ ቢሉ አንጻሩ ምዕራብ፤ ሰሜን ቢሉ አንጻሩ ደቡብ፤ መስዕ ቢሉ አንጻሩ አዜብ፤ ሊባ ቢሉ አንጻሩ ባሕር። ይቁሙ ውስተ አሐቲ ማእዝን እመኣዝኒሃ ለቤተ ክርስቲያን። በማእዝነ ቤት። እማእዘንት እስከ ማእዘንት። ርእሰ ማእዘንት። አርባዕቱ መኣዝነ ዓለም። መኣዝኒሃ ለምድር። መኣዝኒሆሙ ለእስራኤል
፡ (ፈ ፡ መ ፡ ፮ ፡ ፲፬። አፈ ፡ ተ፴፩። ዮዲ፩ ፡ ፫። መዝ ፡ ፻፲፯። ዘፍ፪
፡ ፲። ራእ፯ ፡ ፩። ፩ነገ ፡ ፲፬
፡ ፴፰)።
[2] ፡ በቁሙ፤–አዚን አዘነ።
ማዕደን ፡ (ብ መዓድን፤ አው ማዕደናት) በቁሙ፤ የብረት ወገን የሚጠበስና የሚቀልጥ የሚቀጠቀጥ፤ ከወርቅ እስከ ርሳስ ፯ ዐይነትና ፯ ስም ያለው።
ማእድ ፡ (ዳት። ዐረ ማይዳ፤ ማይደት) በቁሙ፤ ማድ ገበታ፤ ሰደቃ አውራጅ፤ የምግብ ማቅረቢያ ፥ መብሊያ መጠጫ፤ ወይም መሼጫ መለወጫ፤ ሰፊ ዝርግ ሞላላ ፥ ወርዳም ቁመታም፤ ወይም ክብ እንዳውድማ ያለ እግራም። አስትዳለወት ዘዚኣሃ ማእደ። ማእደ መኳንንት። ኢበልዐት አመትከ እማእደ ሐማ። ወገፍትዐ ማእዳቲሆሙ ለመወልጣን ፡ (ምሳ፱ ፡ ፪። ፳፫ ፡ ፩። አስቴ፬ ፡ ፲፯። ማቴ፳፩ ፡ ፲፪። ፳፭ ፡ ፳፯)።
፡ ምሧዕ መንበር፤ የግዜር ማእድ ዕጣንና ቍርባን ማቅረቢያ። ማእደ ክህነት ዘሥሩዕ ቅድሜከ ፡ (ቅዳ
፡ ያዕ)። ማእዳት ዘምሥያም ፡ (፩ዜና ፡ ፳፰ ፡ ፲፮። ኩፋ ፡ ፴፩። ሚል፩ ፡ ፯)።
፡ ምሳ ፥ ድግስ፤ መብልና መጠጥ እንጀራና ወጥ። ወገብረ ማእደ ዐቢየ። ባርኮ ማእድ። ጸሎተ ማእድ ፡ (ዘፍ፳፩ ፡ ፷። ግብ፳ ፡ ፯። ሥር ፡ ጳኵ)።
ማዕድ ፡ ማድ ሰደቃ፤–መአደ፤ ማእድ።
ማእድው ፡ (ብ መኣድው ዋት) መጥረጊያ፤ የጕድፍ መሣሪያ ማስገለያ።
ማዕዶ ማዕዶት ፡ (ማዕዶት) ማዶ፤ አሻገር ከወንዝ ወዲያ ወይም ወዲህ ያለ ቦታ፤ ትይዩ አንጻር፤ ፊት ለፊት፤ አቅጣጫ አፍዛዣ። የፋሲካ ሰኞ። ማዕዶተ ዮርዳኖስ። ነገሥት እለ ማዕዶተ ባሕር። ወበጺሖ ማዕዶተ። ዋዜማ ዘማዕዶት ፡ (ኢሳ፰ ፡ ፳፰። ኤር፴፪ ፡ ፰። ማቴ፰ ፡ ፳፰። ድጓ)።
ማዕገት ፡ ከባቢ ጦር፤ ደበቅ ሰራዊት፤ ወጥመድ፤ አሽክላ። አንበሩ ማዕገተ። ወማዕገቶሙ ለእስራኤል። ወይሠገር በማዕገትየ ፡ (መሳ፱ ፡ ፳፭። ፳
፡ ፴፫። ሕዝ፲፪ ፡ ፲፫)።
፡ ዕርድ፤ ምሽግ፤ አንባ፤ ከተማ፤ መክበቢያ፤ መከበቢያ፤ የተወስነ ቦታ። ይትከወሱ በውስተ ማዕገቶሙ። ወእማዕገት ከሃክ ውእቱ መለኮት ፡ (ሚክ፯ ፡ ፲፯። ቄር)።
ማዕጠንት ፡ (ታት) ማጠኛ፤ ማጤሻ፤ ጥና። ማዕጠንተ ወርቅ። ወማዕጠንታተሂ ፡ (ራእ፰ ፡ ፫። ዘኍ፬ ፡ ፲፬)።
ማዕጸድ ፡ (ዕብ ማዓጻድ፤ ገዠሞ፤ መጥረቢያ፤ መላጊያ) ማጭድ፤ ማጨጃ፤ መቍረጫ። ማዕጸድ በሊኅ ውስተ እዴሁ ፡ (ራእ፲፬ ፡ ፲፬–፲፱)።
ማዕጸፍ ፡ (ፍት) ዝኒ ከማሁ፤ ዐጽፍ። ሲያበዛ መዓጽፍት ይላል
፡ (መጽ ፡ ምስ)።
ማዕጾ ፡ መዝጊያ፤ ላንቃ። ከመ ማዕጾ እንተ ተዐውድ። ድርኵኵተ ማዕጾ። ወማዕጾ ዘዐቅም ፡ (ምሳ፳፮ ፡ ፲፬። ዘካ፲፪ ፡ ፪። መዝ ፡ ፻፵)።
፡ ዐጥር ቅጥር ሽምጥ። ሰበረ ማዕጾ ወጐየ። ንግበር ላቲ ማዕጾ ዘቄድሮስ ፡ (ኩፋ ፡ ፴፱። ማሕ፰ ፡ ፱)።
ማዕፈርት ፡ ማዕፈርት፤ ፡ (ሱር ማዕፍራእ፤ ኩፋር። ዕብ ሚጽኔፌት) የራስ ልብስ፤ መሸፈኛ፤ ቆብ፤ ኵፌት፤ መጠምጠሚያ። ማኅፈሪትን ተመልከት። ትወዲ ዲቤሆሙ ማዕፈርቶሙ ፡ (ዘፀ፳፱ ፡ ፱)።
ማዖን ፡ ማዖን፤ ፡ (ዕብራ) ቤት ቦታ፤ የቤት ማእዝን ፥ ግራና ቀኝ፤ ጐን ጥግ ፥ አጠገብ ስብሳብ።
ማኹን ፡ ማኹን፤ ፡ (ቅብጥ) ስመ ወርኅ፤ ታኅሣሥ፤ ግንቦት። ኪያህክንና በሽንስን እይ፤ ለኹለቱ ወሮች ፪ ፪ ስም አላቸው ፡ (አቡሻ ፡ ፰)።
ማውታ ፡ ማውታ፤ ሙት ፥ በክት ሳያርዱት ታሞ ወይም ገደል ገብቶ የሞተ የከብት ሬሳ። ማውታ ወደም ወብትክ። ዘረኵሰ በበሊዐ ማውታ። ጽዩእ ሥጋ ማውታ ፡ (ቀሌ። ፈ ፡ መ ፡ ፮ ፡ ፬። ዲድ ፡ ፮)። ለስው ሬሳም ይኾናል። ዕጓለ ማውታ፤ የሙት ልድ። በደክታም ፈንታ ዕጓለ ማውታ ይላል፤ የትርጓሜ ቃል ነው። አብ ለዕጓለ ማውታ። ኀደገኒ አቡየ ዕጓለ ማውታ። ኢየኀድገክሙ ዕጓለ ማውታ ትኩኑ ፡ (መዝ
፡ ፷፯። ጦቢ፩ ፡ ፰። ዮሐ፲፬ ፡ ፲፰)። ማውቻ ደካማ ኰሳሳ ፥ ዐቅመ ቢስ
፡ (ዐማርኛ)።
ማውትና ፡ ማውትና፤ ሙትነት በክትነት፤ ደካምነት። በእንተ ዕጓለ ማውትናሆሙ ወድክትምናሆሙ ፡ (ዮሴፍ)።
ማዙሮት ፡ ማዙሮት፤ ፡ (ጽር። ዕብ ማዛሎት) መናዝል፤ ከዋክብት መገብተ አውራኅ፤ የቀድሞ ሰዎች በየወሩ የሚያመልኳቸው ፥ ዛሬም ጠንቋዮች ለየሰዉ የሚያድሏቸዋ፤ ነዘለን እይ
፡ (፬ነገ ፡ ፳፫ ፡ ፭)።
ማዝግና ባዝግና ፡ (ናት) ዝርግፍ፤ የወርቅ የብር ዶቃ፤ ድባ ማርዳ ሰደፍ፤ የሚዘገን፤ በፈትል ተስክቶ ባንገት የሚታሰር ያንገት የደረት ጌጥ፤ የሴቶች የወንዶች ሽልማት። ቃማን ተመልከት፤ ክዚህ ጋራ አንድ ነው። ትረስዕኑ መርዓት ሰርጓ ወድንግል ባዝግናሃ። ወአዕነቆ ባዝግና ወርቅ ውስተ ከሣዱ። ባዝንግናት ዘውስተ ክሣደ አግማል
፡ (ኤር፪ ፴፪። ፵፩ ፡ ፵፪። መሳ፰ ፡ ፳፩ ፡ ፳፮)። መን በ ስለ ወረሰው በማዝግና ፈንታ ዝግና ይላል፤ ዘና ሰ እንደ ተዋረሱ ይህም እንደዚያ ነው።
ማያዊ ፡ (ዊት ውያን ያት) ውህማ፤ ውሃም ፥ ውሃማ፤ የውሃ። ጠባይዕ ማያዊ፤ ነፋሳዊ መሬታዊ እሳታዊ ፡ (ፈላስ ፡ ገ፲፮)።
ማይ ፡ (ብ ማያት። ዕብ ማይም። ሱር ማያእ። ዐረ ማእ) በቁሙ ፥ ውሃ የታወቀ ፈሳሽ ከምድር ሆድ የሚፈልቅ የሚወጣ፤ በባሕር በየብስ ፥ በጕድጓድ በዐዘቅት ፥ በአፍላግ በአንቅዕት ፥ በኹሉ የሚገኝ፤ ለባሕርዩና ለባሕርያነቱ የተለየ ሕብር ጣዕምና መዐዛ የሌለው ፥ ጽሩይ ንጹሕ ቈሪር ፥ ካራቱ ባሕርያት አንዱ፤ በርጥበቱ ከመሬት ፥ በጽርየቱ ከእሳት በቍረቱ ከነፋስ የሚስማማ፤ ለሚጠጣው ኹሉ ልምላሜ የሚሰጥ የሚያቀዘቅዝ የሚያረካ ባሕርያዊ መጠጥ ፥ ዝናም ጠል። ዘይቤው ምህው ማለት ነው፤ ምህወን እይ። ማይ ብዙኅ። አንቅዕተ ማያቲሆሙ። ማያተ አፍላግ። ኢትስተይ ማየ ዕራቆ። ስቁለ አመ ርእዩከ አርዳኢከ ኮኑ መዐዛ ማይ ፡ (ኢሳ፲፩ ፡ ፱። ዮዲ፯ ፡ ፲፪። ቅዳ። ፩ጢሞ ፡ ፭ ፡ ፳፫። ቅኔ)። ማይ መሪር ጥዑም ምዉቅ ቢል፤ ምረቱና ጣዕሙ ሙቀቱ ከመሬት እንጂ ከባሕርዩ አይዶለም። ከሥጋ ባሕርይም የሚወጣ እንብ ደም ዘር ሌላውም ኹሉ ማይ ይባላል፤ ፈሳሽ ማለት ነው። ይውሕዝ አንብዕ ከመ ማይ። ከዐዉ ደሞሙ ከመ ማይ። ወእንዘ ማይ ውእቱ ታረግዖ በጥበብከ ፡ (ቅዳ ፡ ያዕ። መዝ
፡ ፸፰። ቅዳ ፡ አት)። ስመ ፊደል መ፤ የአልፍ ፲፫ኛ።
ማዳይ ፡ ምድያም፤ ስመ ነገድ ፡ (ዘፍ፲ ፡ ፪። ፳፭ ፡ ፪)።
ማድዮ ፡ (ዕብ ማድ፤ ማድያው። ጽር ማንዲያስ) የላይ ልብስ። የክብር ልብስ፤ ነገሥታት መኳንንት ልጆቻቸውም የሚለብሱት። ዮና ው ዝርዝሮች ናቸው፤ ልብሰ ዕበዩ እንደ ማለት። ወሀቦ ዐጽፈ ዘላዕሌሁ ወማድዮሂ ፡ (፩ነገ ፡ ፲፰ ፡ ፭)። ባለብሉዮች ግን ጩፋ ይሉታል። ፪ኛ ደግሞ እንደ ጽርኡ ቃል በማድዮ ፈንታ መንድያ ይላል፤ ይህነንም የጦር ልብስ እንደ ፀሓየ ፊሳ ያለ፤ ዘየሀይድ ዐይነ ብለው ይፈቱታል።
ማድጋ ፡ በቁሙ እንስራ፤–ደጊግ ደገ።
ማጎግ ፡ ጎጋዊ የጎግ ወገን። ወያስተጋብኦሙ ለጎግ ወለማጎግ ፡ (ራእ፳ ፡ ፰)።
ማጣ ፡ (ዕብ ሚጣ) ዐልጋ ዙፋን። እግረ ማጣ
፡ (ድጓ። መዋሥ)።
ሜሄኑህ ፡ (ዕብ ሜሄናህ) እምኔሆን ፡ (ሕዝ፵፪ ፡ ፭)።
ሜላቅ ፡ (ቃት) ቅርጫት፤ ታናሽ አስፈሬድ፤ ወይም እንቅብ ጕርዝኝ። ቦ ዘይፀፍር ሜላቃተ እለ እሙንቱ አስፈሬዳት ደቃቃት ፡ (ሥር ፡ ጳኩ)።
ሜላት ፡ (መለለ፤ ለትሐ። ዕብ ሚላት) ጥሩ ፀምር፤ ጥሩ ሐር፤ ጥሩ የክት ልብስ ፥ ግምጃ፤ ከፀምር ከሐር ከክታን ከጥጥ የሚሠራ። ስምነቱ ከመለለና ከለትሐ የተዴቀለ ነው፤ ሜላት ጽርየቱን ንጣቱን፤ ግምጃ ቀለሙን ዐይነቱን ያሳያል፤ እልታሕን እይ
፡ (ዘፍ፵፩ ፡ ፵፪። ዘፀ፳፭ ፡ ፬። ሉቃ፲፮ ፡ ፲፬)።
ሜላትራ ሮን ፡ (ጽርእ) ጸፍጸፍ ብላጥ፤ በቤት ዙሪያ የሚሠራ ጌጥ፤ እንደ ዐምድና እንደ ዝናር ያለ ሥረ ወጥ፤ ወይም የኋላ ቅጥል ፥ ልብጣት ፥ ልባጥ። ዳግመኛም ጌጥነቱን ሲያይ በከታር ፈንታ ሜላትራ ይላል፤ ባለብሉዮም ጸፍጸፍና ልባጥ በማለት ፈንታ መደብ፤ ልዝብ ጠርብ ይሉታል ፡ (፫ነገ ፡ ፯ ፡ ፱ ፡ ፵፩)። ሰሎሞን አስተቀጸላ ለመቅደስ በሜላትሮን
፡ (አርጋ)። ንባቡም ምስጢሩም ከሜላት ጋራ ይሰማማል።
ሜላንትራ ፡ ጸፍጸፍ፤–ሜላትራ።
ሜሎስ ፡ (ጽርእ) ዜማ ፥ ተሰጦ የዜማ ምስጋና፤ ግራና ቀኝ የሚመላለስ። እሳታዊ ዕንቍ ፥ የሚበርቅ የሚያንጸበርቅ። ከርሡ ወእንግድዓሁ ዘዕንቈ ኢያሰጲድ ወሰርዲኖ፤ ክሣዱ ብርሃን ዘለንጳስ ገጹ ዘሜሎስ ወአዕይንቲሁ ዘጳዝዮን ፡ (መጽ ፡ ምስ)።
ሜመየ ፡ (ምህወ፤ የመመ) ውሃ ኾነ፤ ሟሟ ቀለጠ፤ ውሃ መሰለ ፥ ውሳ ውሃ አለ። ባለቅኔዎች ግን ለየ ለያየ ይሉታል፤ ምስክር የለውም።
፡ ወኸየ ውሃ ኾነ፤–መይመየ።
ሜም ፡ (ዕብ) ስመ ፊደል መ፤ ማይ ማያት ማለት ነው። ደምፁ ወተሐምጉ ማያቲሆሙ ባለው፤ ዕብራይስጡ ዬሄሙ የሕምሩ ሜማው እንዲል ፡ (መዝ ፡ ፵፭)። ሜም ጥቀ አፍቀርኩ ሕገከ ፡ (መዝ ፡ ፻፲፰ ፡ ፺፯–፻፬። ሰቈ፩ ፡ ፲፫። ፪ ፡ ፲፫። ፫ ፡ ፴፰። ፬ ፡ ፲፫)።
፡ ስመ ፊደል ዕብራዊ መ–መየም።
ሜስ ፡ (ብ አምያስ) መሸታ፤ ጠጅ ዐረቂ፤ የወይን የማር የሌላውም ኹሉ፤ የሚያሰክር መጠጥ። ስታየ ሜሰ ወይን። ኢይሰተ ወይነ ወሜሰ። ጻዕፈ ወይን ወሜስ ወምዝር። አምያስ ዘግቡር በእሳት። ወኢምንትኒ እምዘመደ አምያስ ዘአጣእጥእዎ በመዓር አው በሶከር
፡ (ቀሌ። ሉቃ፩ ፡ ፲፭። ገድ ፡ ተክ። አብጥ ፡ ፪። ፈ ፡ መ ፡ ፳፮ ፡ ፩)።
ሜሩቃዕ ፡ (ዕብ ራቃዕ፤ ዘረጋ አሣሣ፤ ምሩቃዕ) ሥሥ ረቂቅ፤ ዝርግ ጠፍጣፋ፤ ልብስን ዕንጨትን ለማስጌጥና ለመለበጥ እንደ ቅጠል ኹኖ የተሠራ። ባለብሉዮች ግን ጽርየት ንጣት ይሉታል። ብሩር ሜሩቃዕ ፡ (ኤር፲ ፡ ፱)።
ሜሮን ፡ (ጽር ሚሮን) የከርቤ ሽቱ ፥ ወይም ሌላ ያልተቀደሰ ፥ ማንም የሚቀባው፤ ሥሩና ምንጩ መሪር መረ ነው። ዕጣነ ወሜሮነ ፡ (ራእ፲፰ ፡ ፲፫)።
፡ በቁሙ ፥ ቅብዐ ቅዱስ የተባረከ ሽቱ፤ ጳጳሳት ከበለሳንና ከዕፀወ ዕጣን ከአስጳዳቆስ ፥ ከሌላም ከብዙ ዐይነት ሽቱ የሚያወጡት። መደበኛው ግን በለሳን ነው፤ ፍችውን በቦታው ተመልከት። በለሳነ ኮነ ሀፈ ሥጋሁ በቍሎ፤ ሜሮነ ቅብዑ ዘይቄድስ ኵሎ ለትእምርት በኀቤነ እስከ ዮም ሀሎ። ወይኅትም ኪያሃ በሜሮን፤ እስመ ማኅተመ እግዚ ውእቱ ፡ (ደራሲ። ፍ ፡ ነ ፡ ፩)።
ሜትራይቁይ ፡ የጭፍራ ስም። ጋላትን እይ፤ ከዚህ ጋራ አንድ ነው ፡ (መጽ ፡ ምስ)።
ሜዐ ፡ (መዪዕ። ዐረ መዐ ማዐ፤ ደከመ ፈሰሰ) ቀለጠ ፥ ውሃ ኾነ፤ ነጠረ ተጣፈጠ። ምህወንና መስወን ጸዐጠን እይ፤ የዚህ ጎሮች ናቸው።
ሜዓ ፡ ጥሩ ሽቱ፤–መዪዕ ሜዐ።
ሜኤፌሳይም ፡ (ዕብ ሜይ አፍሳይም) ጥቂት ውሆች ጫማ የሚያለብሱ ፥ እስከ ቍርጭምጭሚት የሚደርሱ ፥ ወንዙ ባዶ ኹኖ ከማነሳቸው የተነሣ እያሉ የሉም የሚባሉ ፡ (ሕዝ፵፯ ፡ ፫)።
ሜኪር ፡ (ቅብጥ ሜኺር) ስመ ወርኅ፤ የካቲት ፡ (አቡሻ)።
ሜክሱት ፡ (ዕብ ምኩሶት) የተሸፈኑ ፥ የተዘጉ የተደፈኑ፤ መስኮቶች ፡ (ሕዝ፵፩ ፡ ፲፯)።
ሜኮኖት ፡ (ጽር። ዕብ ምኮኖት) ድጋፎች፤ ተሸካሞች መሠረቶች፤ ወይም ስክተቶች ጕልቾች። አንዲቱን ምኮና ይላል፤ ኹሉም የሴት አንቀጽ ነው። ለለ አሐቲ ሜኮኖት አሐዱ ኬጥሮጋውሉስ፤ ወከማሁ ለዐሠርቱ ሜኮኖት
፡ (፫ነገ ፡ ፯ ፡ ፴፰)።
ሜጥራ ፡ (ጽር ሚትራ። ዕብ ኔዜር) የተቀደሰ አክሊል ዘውድ፤ ሥራውና ጌጡ ከነገሥታት ዘውድ የተለየ፤ ቀድሞ በብሉይ ሊቃነ ካህናት ዛሬም በሐዲስ ሊቃነ ጳጳሳት የሚለብሱት። ኢያዜርን እይ፤ ከዚህ ጋራ አንድ ነው ፡ (ዘፀ፴፮ ፡ ፴፬ ፡ ፴፰)። በዕብራይስጥ ግን ም፴፱ ቍ፴ና ፴፩ ነው፤ ዐማርኛውን እይ።
ሜፌቲ ፡ (ዕብ ሚፌ(ፔ) ቲ) ሜ እም ፌቲ ሞኝ የዋህ፤ ሕጹጸ አእምሮ ስሑት፤ ፈታዊ። እምብእሴ ሾጌ ወሜፌቲ ፡ (ሕዝ፵፭ ፡ ፳)።
ምሁር ፡ (ራን ራት ህርት) በቁሙ፤ የተማረ ፥ ትምርት የጠገበ፤ ዐዋቂ ሊቅ፤ ልባም አስተዋይ። ምሁር በኵሉ ጥበብ። ምሁራን በኀበ እግዚ። ነገሩ ኢኮነ ከመ ምሁር። ብእሲ ምሁር ፡ (ቀሌ። ኢሳ፶፬ ፡ ፲፫። ኢዮ፴፬ ፡ ፴፭። ሢራ፴፩ ፡ ፱)።
ምሑር ፡ (ራን ራት ሕርት) የተማረ፤ ይቅር የተባለ። ኢኮንክሙ ምሑራነ ፡ (፩ጴጥ ፡ ፪ ፡ ፲)።
ምሁክ ፡ (ካን ካት ሀክት) የተማረ፤ ይቅርታ ያገኘ።
ምሑጽ ፡ (ጻን ጻት ሕጽት) የተመታ የተቈረጠ፤ የሞተ የጠፋ። ወትከውን ምሑጸ በምርኣየ አዕይንቲከ
፡ (ዘዳ፳፰ ፡ ፴፬)። ዕብራይስጡ ግን ምሹጋዕ ይላል፤ እብድ እንቡዝ ቅብዝብዝ ማለት ነው። ባለብሉዮችም ዐይንን ተከትለው፤ ዕውር ጨምጫማ ይሉታል፤ ፪ኛም ምሕጸ ሸሸ ብለው ምሑጽ የሸሸ ይላሉ። ዘይቤው አይዶለም። ፫ኛም በምሑጽ ፈንታ ምሑስ ይላል፤ ስሕተት ነው። ከመ አይሁድ ምሑሳን
፡ (ሲኖዶ)።
ምሂር ሮት ፡ (መሀረ ይሜህር ይምሀር። ዕብ ማሀር፤ ፈጠነ ቸኰለ) መማር፤ መምህር መኾን ፥ መምራት ማሳየት፤ መምከር ማስተማር፤ ማልመድ ማስለመድ። መሀሮ አቡሁ መጽሐፈ። ዘሰ ይሜህር ወይገብር። ትሜህር እገሪሃ ሐዊረ ፡ (ኩፋ ፡ ፯። ማቴ፭ ፡ ፲፱። ዘዳ፳፰ ፡ ፶፮)።
፡ መቅጣት ፥ መግረፍ፤ መቈጣት ፥ መዝለፍ። መሀር ወልደከ። መሀረኒ እግዚኦ። ገሠጸ ወመሀረ ፡ (ምሳ፳፱ ፡ ፲፯። ኤር፲ ፡ ፳፬። ሢራ፯ ፡ ፳፫)። መርሐን እይ፤ የዚህ መንቲያ ነው።
ምሒር ሮት ፡ (ምሕረ፤ መሐረ ይምሕር ይምሐር። ዕበ ማሐል፤ ራሐም። ሱር ርሔም። ዐረ ረሒመ) መማር ፥ ይቅር ማለት፤ ዕዳን በደልን መተው። ለዘሂ መሐርክዎ እምሕሮ። መፍትው አንተሂ ትምሐር ቢጸከ በከመ አነ መሐርኩከ። አሐዱ ዘመሐሮ መንፈቀ ዕዳሁ ፡ (ሮሜ፱ ፡ ፲፭። ማቴ፲፰ ፡ ፴፫። ፈ ፡ መ ፡ ፪ ፡ ፲፩)።
፡ መውደድ ማፍቀር፤ ከፍቅር የተነሣ ማዘን መራራት፤ መስጠት መመጽወት። በከመ ይምሕር አብ ውሉዶ ከማሁ ይምሕሮሙ እግዚ ለእለ ይፈርህዎ። ሶበ መጽወትነ ወመሐርነ። ርእዮ ወምሕሮ። ደቀቅ ዘምሕሮ እግዚ ለገብርከ። በምሒረ ነዳይ ፡ (መዝ ፡ ፻፪። አፈ ፡ ተ፴፬። ሉቃ፲ ፡ ፴፫። ዘፍ፴፫ ፡ ፭። ዳን፬ ፡ ፳፬)። በምሕረ ፈንታ አስተምሐረ ይላል፤ ስሕተት ነው። ነጽር ላዕሌየ ወአስተምሕረኒ። አስተምሕር ሕማሞሙ ለዘመድነ ፡ (ጦቢ፫ ፡ ፲፭። ዮዲ፮ ፡ ፲፱)።
ምሒን ኖት ፡ (መሐነ ይምሕን ይምሐን። ዐረ መሐነ) መፈግፈግ፤ ማሸት ማልፋት፤ ማለስለስ፤ ቈርበት፤ ለልብስና ለፈትልም ይኾናል። መስጠት ማስረከብ እንሆ ማለት።
ምኂፅ ፆት ፡ (መኅፀ ይምኅፅ፤ ይምኀፅ። ዐረ መኂፀ) ማማጥ መጨነቅ፤ በምጥ መያዝ፤ ለመውለድ፤ የሆድን ለማውጣት። መጽሐፍ ግን በምኅፀ ፈንታ እንዳማርኛው አምኀፀ ይላል፤ ስሕተት ነው። ጊዜ ታምኅፅ ትኬልሕ ፡ (አዋል)።
ምህላ ፡ ልመና ምልጃ፤–ምሒል መሐለ።
ምሕላ ምሕላል ፡ በቁሙ፤ ልመና ምልጃ፤ የማኅበር የሕዝብ ጸሎት እግዚኦታ። እመኒ አብዛኅክሙ ምሕላክሙ። ቀድሱ ጾመ ወስብኩ ምሕላ። በኵሉ ምሕላ ወበኵሉ ጸሎት። ተወከፍ ምሕላነ ፡ (ኢሳ፩ ፡ ፲፭። ዮኤ፩ ፡ ፲፬። ፫ነገ ፡ ፰ ፡ ፴፰። ድጓ)። መሐለ ከብህለ የወጣ ስለ ኾነ ተማህለለ ምህላ እያለ በሆይ ሀ ይጥፋል፤ ገንዘቡ ኣይዶለም።
ምህላው ፡ መኖሪያ፤ ቦታ ሀገር። ነፍስ እመ ትፈልጠት እምሥጋ በሞት ገብአት ኀበ ብርሃን፤ ዘውእቱ ማኅደራ ወምህላዋ ወፍግዓሃ ወተድላሃ። ነሥኣ ለሀገረ ባቢሎን ወተወፈየ ምህላወ ብልጣሶር
፡ (ዮሴፍ)።
ምሕላይ ፡ መዝፈኛ ቦታ፤ ቅኔ ማሕሌት የሰርግ ቤት፤ የመሰለው ኹሉ።
ምኅላፍ ፡ (ፋት) ማለፊያ ማሳለፊያ፤ መግቢያ መውጫ በር መንገድ፤ ቦታ። ኢወሀቦ ምኅላፈ እንተ ደወሉ። አልቦ ምኅላፍ። ዳእሙ ምኅላፈ ክልኤቱ ዕደው ኵለንታሁ። ተኀጥእ ምኅላፈ። ትገብር ለከ ምኅላፈ እንተ ደማስቆ ፡ (ዘኍ፳ ፡ ፳፩። ኢዮ፲፱ ፡ ፰። ዮዲ፬ ፡ ፯። ፫ነገ ፡ ፳ ፡ ፴፬። ሆሴ፪ ፡ ፰)።
ምሕረት [1] ፡ (ታት) በቁሙ፤ ይቅር ማለት ፥ መባል። ይቅርታ ቸርነት፤ ርኅራኄ ፍቅር ምጿት። እለ ትፈርህዎ ለእግዚ ጽንሕዋ ለምሕረቱ፤ እስመ በከመ ዕበዩ ከማሁ ዕበየ ምሕረቱ። አበ ምሕረታት። የዐጹ ምሕረቶ። እለ አልቦሙ ምሕረት። ምሕረተ ነዳያን ፡ (ሢራ፪ ፡ ፯ ፡ ፳፫። ኪዳ። ፪ጢሞ ፡ ፫ ፡ ፫። ሮሜ ፡ ፩ ፡ ፴፩። ፍ ፡ ነ ፡ ፲፪)።
፡ ልብ ሆድ አንዠት፤ የርኅራኄ ምንጭ። ተፈሥሐ ምሕረቱ ወልቡ ላዕሌሁ። ምሕረትየ ይባርከከ። አሕዘኑ ምሕረተ አቡሆሙ
፡ (ኩፋ ፡ ፳፪። ፳፭። ፴፬)።
[2] ፡ ምሕረት፤ ፡ (ዕብ ሬሔም፤ ራሓም) ማሕፀን ፥ አፈ ማሕፀን፤ የፅንስ የሽል ቦታ። ምስጢሩ ከሆድ ይገባል። ኅቡረ ተዘራዕነ በውስተ ከርሥኪ ወኅቡረ ወፃእነ እምሕረትኪ ፡ (ኩፋ ፡ ፳፭)።
ምሕራም ፡ (ማት) መቅደስ ምኵራብ መስጊድ፤ ለግዜር ወይም ለጣዖት የተሠራ ቤት። ኢትትነበይ አንከ በቤቴል፤ እስመ ምሕራመ ነገሥት ይእቲ
፡ (ዓሞ፯ ፡ ፲፫። ሔኖ፺፱ ፡ ፯)።
፡ ጣዖት፤ ግዘፈ ጣዖት፤ የጣዖት ዐምድ ሐውልት፤ ወይም ዐጸድ አታክልት በጣዖቱ ዙሪያ የሚበቅልና የሚተከል። ለቤተ ክሲያንም ዛፍ ይስማማል፤ ምስጢሩ ክልክልነትና ቅድስና ነው። እገዝም ምሕራማቲከ። ሐውልተ ምሕራማቲሆሙ። ምሕራነ ዖም። ምሕራማተ ጣዖት ተገዝመ ፡ (ሚክ፭ ፡ ፲፫። ፫ነገ ፡ ፲፬ ፡ ፳፫። ፲፭ ፡ ፲፫። ኢሳ፳፯ ፡ ፱)።
ምህርካ ፡ (ካት) ምህሩክ፤ የተማረከ ፥ ምርኮ፤ ምርኮኛ። ፄዋ ወምህርካ። ተካፈልነ ምህርካ። እንዘ ትሰመይ መምህረ ወካቶሊካ፤ አባእከ ሎቱ ለክርስቶስ ምህርካ
፡ (ዘኍ፴፩ ፡ ፲፩። መዝ ፡ ፷፯። ስንክ ፡ ግን፳፮)።
ምህርክና ፡ ምርኮነት፤ ምርኮ መኾን። በምህርካ ፈንታ ምህርክና ይላል፤ ስሕተት ነው ፡ (፪ዜና ፡ ፳፰ ፡ ፭ ፡ ፰ ፡ ፲፫)።
ምሕቃፍ ፡ (ፋት) ማቀፊያ መታቀፊያ፤ እጅ ክንፍ ቦታ።
ምኅባእ ፡ (ኣት) ማቢያ መታቢያ ፡ (ላ ጥ) መሸሸጊያ መደበቂያ፤ መሰወሪያ። ወሰወረኒ በምኅባአ ጽላሎቱ። ከመ ያንብራ ውስተ ምኅባእ ፡ (መዝ
፡ ፳፮። ሉቃ፲፩ ፡ ፴፫። ፪ነገ
፡ ፳፩ ፡ ፲፪። ሔኖ)።
ምሕን ፡ በቁሙ፤ መን የሸማ መሥሪያ፤ ርስ በርሱ የሚፋተግ የሚፈጋፈግ። አነመን እይ። ወምሕኑሂ ዘእምላዕሉ ጽላሎተ እግዚ ፡ (ቅዳ ፡ ሕር። ተረ ፡ ቄር)።
ምህከት ፡ መራራት፤ ይቅር ማለት። ይቅር መባል፤ ይቅርታ ማግኘት። ይቅርታ ፥ ስርየት፤ ርኅራኄ። ምህከት ወምሕረት ፡ (ዮሴፍ)።
ምህወ ፡ (ይምሁ ይምሀው፤ ምሂው። መስወ መሰወ) ሟሟ ቀለጠ፤ ውሃ ኾነ፤ ዛለ ደከመ ወዛ ፡ (ዘፀ፲፮ ፡ ፳፩)። ሥጋሁ ከመ ማይ ምህወ። ባሕር እንተ ኢተዐዱ አምወሰና ወምድርኒ እንተ ኢትምሁ እምዝብጠተ መዋግዲሃ። ይምሁ ወይትመሰው ኵሉ አባል ፡ (ስንክ። አትና። ግንዘ)። ማይ ውሃ ማለት ኹለቱም ከዚህ የወጣ ነው። በምህወ ፈንታ ተምህወ ይላል፤ ስሕተት ነው። ትትመሀው አባሉ ፡ (ግንዘ)።
ምሕወ ፡ ሟሟ ቀለጠ፤–ምህወ።
ምሕዋጽ ፡ (ጻት) መጐብኛ መመልከቻ፤ መስኮት። ምሥሃል፤ የታቦተ ሙሴ መክደኛ በላዩ ኪሩቤል የተሣሉበት፤ እግዜር እስራኤልን የሚጐበኝበት ቃሉን የሚያሰማበት ፡ (ዘፀ፴፩ ፡ ፯)። ሣህለን እይ።
ምሕው ፡ (ዋን ዋት ሑት) የጠፋ የተነቀለ፤ ጥፉ ንቁል።
ምሕዛል ምስትሕዛል ፡ ማስተዛዛያ፤ የሚያስተዛዝሉት ዜማ ድጋም
፡ (ድጓ)።
ምኅዳፍ ፡ (ፋት) የቀዛፊና የመቅዘፊያ የትርከዛ ቦታ።
ምሕጸ መሐጸ ፡ አማጠ ተጨነቀ፤––ምኅፅ መኀፀ።
ምሕጸት ፡ መምታት መቍረጥ፤ መመታት መቈረጥ፤ ሞት ጥፋት። ኢመጽኦሙ መቅሠፍት ለቀቲል ወለምሕጸት ፡ (ኩፋ ፡ ፵፱)።
ምሕፁን ፡ (ናን ናት ፅንት) የተማጠነ ሙጥኝ የሙጥኝ ያለ፤ የደወለ።
ምኅፃብ ፡ (ባት) ማጠቢያ፤ መታጠቢያ ቦታ መሣሪያ። መራዕይ እለ ወፅኣ እምኅፃብ። ቤተ ምኅፃብ። ወደየ ማየ ውስተ ምኅፃብ ፡ (ማሕ፬ ፡ ፪። ፮ ፡ ፮። ፍ ፡ ነ ፡ ፲፩። ዲድ ፡ ፲፯)።
ምኅፅ ፡ ምጥ ጭንቅ፤ እሕታ። ሐመመን እይ፤ የዚህ ጎር ነው። ፡ (ተረት) ምጡን ርሺው፤ ልጁን አንሺው። የልጅ ደፋር ምጥ ለናቷ ታስተምር።
ምሕፅና ፡ ምጥንታ ዐደራ። ቀሲሳን እለ ዐቀቡ ምሕፅናሆሙ በጽድቅ
፡ (ቅዳ ፡ ዮሐ)።
ምኅፋር ፡ (ራት) ማፈሪያ፤ ኀፍረት። ኢይትከሠት ምኅፋሪከ ፡ (ዘፀ፳ ፡ ፳፮)።
ምሖር ምሕዋር ፡ (ራን) ምሖር፤ ምሕዋር፤(ራን) መኼጃ ማስኼጃ፤ መንገድ ጐዳና። ምሕዋረ ሠሉስ ዕለት። ምሕዋረ ሰቡዕ መዋዕል። ወብሔሩሰ ምሕዋረ ዓመት ወመንፈቅ
፡ (ዘፀ፫ ፡ ፲፰። ዘፍ፴፩ ፡ ፳፫። ሱቱ ፡ ዕዝ፲፩)። ምሕዋራተ ማያት፤ መስኖ ቦይ መትረብ
፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፴፯ ፡ ፫)። ዕሥራ ምእት፤ ወይም ካዕበተ ዐሠርቱ ምእት በማለት ፈንታ ዐሠርተ ምእተ ምሕዋረ ዓመት ይላል፤ የመላሽ ስሕተት ነው፤ መተርጕማን ግን ሺሕ ዘመን ቀጥሎ ቀጥሎ ቢኖር ብለው ይፈቱታል ፡ (መክ ፡ ፮ ፡ ፮)።
ምሉኅ ፡ (ኃን ኃት ልኅት) የተነቀለ የተመዘዘ፤ ንቁል። ሰይፍ ምሉኅ ውስተ እዴሁ። ምሉኀ አጽፋር። ሕዝብ ትሑታን ወምሉኃን። ከመ ዐቃብ ምልኅት ፡ (ዘኍ፳፪ ፡ ፳፫። ስንክ ፡ የካ፲፫። ኢሳ፲፰ ፡ ፯። ፪ነገ ፡ ፳፫ ፡ ፮)።
ምሉስ ፡ (ሳን ሳት ልስት) የተመለሰ ፥ ምልስ፤ ቅልስ። የተሳለ የተሰነገለ፤ ብሩህ ጽዱል መፍርህ ዘያንበለብል። መጽሐፍ ግን በምሉስ ፈንታ ሜሎስ ይላል። ወይትፌኖ ሜሎስ ሰይፈ እሳት። ገጽከ ሜሎስ፤ እሳት ዘይነድድ ፡ (ቅዳ ፡ ያዕ። ቄር። ዘፍ፫ ፡ ፳፬)።
ምሉእ ፡ (ኣን ኣት ልእት) የመላ፤ የተመላ፤ ምሉ ፍጹም ትክክል። ወርኅ ምሉአ ብርሃን። ዕደው ምሉኣነ ጥበብ። አኮ በምልእት ልብ
፡ (አቡሻ ፡ ፲፫። ስንክ ፡ ጥቅ፳፮። ፪ዜና ፡ ፳፭ ፡ ፪)።
ምሉክ ፡ (ካን ካት ክት) የተመለከ ምልክ፤ የተገዛ ግዝ፤ እጅ ዐደር። ከመ ይኩን ምሉከ ለተአማኒ ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፴፱ ፡ ፫)።
፡ የመልከ፤ የነገሠ ንጉሥ፤ ሥሉጥ ሥልጡን፤ ባለምሉ ሥልጣን። በትእዛዞሙ ለምሉካን ነገሥት። ዛቲ ክብርት ወምልክት ማኅበረ ቤተ ክርስቲያን ፡ (ተረ ፡ ቄር፲፬ ፡ ፫)።
ምሉጥ ፡ (ጣን ጣት ልጥ) የተመለጠ፤ ምልጥ መላጣ፤ በራ ቡሓ፤ ገጣባ ንክ፤ የዳነ ያመለጠ፤ ሙላጭ ሟላጣ።
ምላጺ ጼ ፡ (ብ ምላጽያን። ዕብ ሜሊጽ፤ አምጃር) የንብ እንጀራ ፥ ሰፈፉ ጠቃጠቆው፤ ወይም ቀፎው ፥ ማጓው የንቡ መዝገብ። ወለላውንም ያሳያል። ኀበ ምላጽያኒሁ ውስተ ገዳም ፡ (አዋል። ገድ ፡ ላሊ)። በምላጺ ፈንታ የላጸየ ዘር መስሎት መላጺ ይላል፤ ስሕተት ነው።
ምልሓስ ፡ ምላስ፤ ልሳን ፥ አንደበት፤ መላሻ መቅመሻ መናገሪያ። ለስላሳ ልስልስ ማለት ከዚህ የወጣ ነው። ፡ (ተረት) በለምለም ምላሱ፤ በሠላሳ ጥርሱ።
ምልኀት ፡ መምዘዝ፤ መንቀል፤ አነቃቀል ነቀላ።
ምልሕ ምልሐ ፡ (ዐረ ሚልሕ) ጨው፤ ጨውነት። አልቦሙ ምክር ወኢለብዎ በማለት ፈንታ፤ አልቦሙ ምልሕ ወኢሃይማኖት ይላል፤ የመላሽ ስሕተት ነው ፡ (ዘዳ፴፪ ፡ ፳፰)። ባለብሉዮችም ከሃይማኖት ስለ ተጫፈረ ምግባር ይሉታል፤ ባለቅኔዎችም መልሐ ምግባር ሠራ ብለው ይገሱታል።
ምልአት ፡ መምላት ፥ መመላት፤ አመላል ምሉነት፤ ምላት ፍጻሜ። ወለለ ምልአቱ ለኮራ። ምልአተ ከርሥ ዘእንበለ ዐቅም። ወለምልአተ መንፈስ ቅዱስ ፡ (ቄድር። መቃ ፡ ገ፳፬። ቅዳ)።
ምልእ ፡ ምላት፤ ምሉ ፍጹም ክፍል፤ ልከኛ፤ ሕጸጽና ተውሳክ የሌለው። ንሥኡ ምልአ እደዊክሙ ሐመደ። ምልአ ሕፍኑ። ምልአ ቤት ወርቀ እመ ወሀበኒ። ኩሉ ዓለም በምልኡ ፡ (ዘፀ፱ ፡ ፰። ዘሌ፪ ፡ ፪። ዘኍ፳፪ ፡ ፲፰። መዝ ፡ ፵፱)።
ምልከት ፡ መምለክ መግዛት፤ መመለክ መገዛት አገዛዝ፤ አምላክ መኾን። ምልክ ግዛ፤ ርስት ጕልት፤ ድርሻ ይዘታ። እመ እገበርዎ ከመ ይትዐሰብ ምልከተ ካልኡ ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፴፭)።
ምልካእ ፡ መለኪያ ልክ፤ ማተሚያ ፥ ማጣበቂያ።
ምልክ ፡ በቁሙ፤ ምሉክ ግዝ፤ ርስት ቦታ፤ የተያዘ የተረዘዘ እጅ ዐደር።
ምልክት ፡ በቁሙ፤ የዜማ የንባብ፤ የትርጓሜ የስም የቍጥር፤ በፊደል በነቍጣ የሚደረግ። ወጠኑ አውፅኦ ምልክት ፡ (ታሪ ፡ ነገ)። ድጓን እይ።
ምልክና ፡ መልከኝነት፤ ገዥነት ጌትነት ሹመት አገዛዝ ግዛት ጥበቃ። ቅንየትከ ወምልክናከ ኵሎ። ፈጠርነ ዓለመ ከመ ይትዐወቅ ምልክናነ ወዕበየ ኀይልነ። ዘታሕተ ምልክናሁ። አሰስሎት ምልክናሁ ፡ (ጥበ፲ ፡ ፲፬። ቀሌ። ፍ ፡ ነ ፡ ፳፬)።
ምልክኤል [1] ፡ (ምሉከ ኤል) ስመ ኮከብ። ዐቢይ ፥ መጋቤ መፀው ካራቱ መራሕያን አንዱ ፡ (ሔኖ ፡ ፷፬)።
[2] ፡ ምልክ ኤል፤–መሊክ መለከ።
ምልዋይ ፡ መጠምጠሚያ፤ ጥምጥም ፥ ራስ ማሰሪያ ፥ መሸፈኛ።
ምልጣን [1] ፡ (ናት) በቁሙ፤ የዜማ ምልልስ ፥ ፊት መሪና ተመሪ ፥ ቀጥሎ ግራና ቀኝ አንሾች የሚሉት፤ ይልቁንም ባ፭ቱ ዐበይት በዓላት በልደት በጥምቀት በትንሣኤና በዕርገት በደብረ ታቦር ፡ (ድጓ)።
[2] ፡ በቁሙ፤–ለጢን ለጠነ።
ምሙዕ ፡ (ዓን ዓት ምዕት) የታወከ ፥ የተሸበረ፤ ፈሪ ድንጉጥ።
ምማቴ ፡ (ዕብ ወዐረ ሙም። ሱር ሙማ) ሕጸጽ ፥ ሕጹጽነት፤ ነውረ ሥጋ ፥ የሕዋሳት መጕደል፤ ወይም አለመስተካከል ፥ ዐንካሳ ጠንባሳ ፥ ወንካራ ሸውራራ ፥ ደፍጣጣ ገጣጣ ፥ ድንክ ጐባጣ፤ የመሰለው ኹሉ
፡ (ምሳ፳ ፡ ፴)።
፡ ቍጣ ብስጭት ፥ የጠባይ ክፋት፤ ዐመል ታናሽ መኾን። በእንተ ዘውስቴቶሙ ምማቴ ወጽነት ወውኅደተ አእምሮ ወድካመ ጠባይዕ ወብዝኀ ሕማማት
፡ (ፊልክ ፡ ፶፭)።
ምማዔ ፡ መሸበ መታወክ፤ ሽብር ሁክት። ፍርሀት ወምማዔ። እንበለ ምማዔ ፡ (ስንክ ፡ ጥር፲፫። ሐም፮። ነሐ፳፱)።
ምምሣጥ ፡ (ጣት) መቀሚያ፤ የቅሚያ ቦታ።
ምምባሬ ፡ (ጽር ማምብሬ። ዕብ ማምሬ) የመረ ጥሬ፤ የሰው ስም፤ የአብርሃም ወዳጅ ባለቃል ኪዳን፤ ሽፍታ እንቢተኛ አሳዛኝ ማለት ነው፤ መረንና አምረረን እይ። መሪርና ነቢር ልዩ ሲኾን መምረሪ መምርር፤ ወይም ማምሬ በማለት ፈንታ ምምባሬ ምንባሬ ማለት፤ የመላሽና የጣፊ ስሕተት ነው ፡ (ዘፍ፲፬ ፡ ፲፫ ፡ ፳፬። ፲፰ ፡ ፩። ቅዳ
፡ ጎር)።
ምምዓ ፡ ዝኒ ከማሁ፤ ሽብር ሁከት ፥ ጭንቅ። ዕለተ ምምዓ ወሙስና። ረዓድ ወምምዓ ፡ (ሶፎ፩ ፡ ፲፭። ኤር፲፭ ፡ ፰)።
ምምጻእ ፡ (ኣት) መምጫ፤ መገኛ ቦታ። ወምምጻአ አፍራሲሁ እምድረ ግብጽ። ይወፅኡ አርባዕቱ ዕደው ወኢይትአመር ምምጻኦሙ ፡ (፪ዜና ፡ ፩ ፡ ፲፮። ፱ ፡ ፳፰። ሳቤላ)።
ምሟት ምምዋት ፡ መሞቻ፤ ቦታ። ምሟቲሁ ለዖዛ ፡ (፪ነገ ፡ ፮ ፡ ፰)።
ምሟእ ፡ (ኣት) ማሸነፊያ ድል መንሻ፤ መርቻ መረቻ።
ምሱሕ ፡ የመሳ፤ ምሳ የበላ። የተመሳ ፥ የተበላ። የተቀባ ፥ ቅቡዕ።
(ላ ጥ) ምሱል ፡ (ላን ላት ስልት) የመሰለ፤ የተመሰለ፤ ፅንስ ሽል ፡ (ዘፀ፳፩ ፡ ፳፫)።
ምሱቅ ፡ ጥርብ፤–ነሲቅ ነሰቀ ንሱቅ።
ምሡጥ ፡ (ጣን ጣት፤ ሥጥ) የተመሠጠ፤ የተነጠቀ። ምሡጠ ልብ ወኅሊና። ንሕነሰ በዐይነ ሃይማኖት ምሡጥ ፍጹመ ሥጋዌከ ንሬኢ እምውስጥ ፡ (ስንክ ፡ ግን፳፰። ደራሲ)።
ምሳሕ ፡ (ሓት) ምሳ ፥ የቀን ምግብ ፥ ድግስ በቀትር በተሲያት የሚበላ፤ እንጀራው ወዛም ወጡ ቅባታም። ምስጢሩ ቅባትን አይለቅም። ገብሩ ሎቱ ምሳሐ። እስከ ጊዜ ምሳሕ። አው እምድኅረ ምሳሕ። በውስተ ምሳሓት ፡ (፪ነገ ፡ ፫ ፡ ፳። ፳፬ ፡ ፲፭። ሥር ፡ ጳኵ። ማቴ፳፫ ፡ ፮)።
ምሳሌ ፡ (ልያት) በቁሙ፤ ማስረጃ አንጻር ተረት፤ ፍሬ ነገር። ናመጽእ ምሳሌ ላዕለ ዝንቱ። ዝ ምሳሌ ይውኅድ እምአማን። ምሳልያተ ሰሎሞን። ወኮኑ ብየ ሠለስቱ ምሳልያት ፡ (አፈ ፡ ተ፪። ቄር ፡ ጰላ። ምሳ ፡ ፩። ሔኖ)።
ምሣር ፡ (ራት) በቁሙ፤ ፋስ መቍረጫ መፍለጫ መጥረቢያ። ከመ ምሣር ዘይሤጽር። ምሣረ ጸራቢ ዘጸረበ ግልፎ። ጸረቦሙ በምሣራተ ኀጺን ፡ (ዲድ ፡ ፲። ስንክ
፡ ሚያ፳፮። ፩ዜና ፡ ፳ ፡ ፫)። ሞሠርና ምሣር ይሞካሻሉና፤ በሞሠር ፈንታ ምሣር ይላል።
ምሳር ፡ በቁሙ፤–ወሥሮ ወሠረ ሞሠር።
ምሴት ፡ (ዐረ ፡ መሳ። ዕብ ኤሜሽ) ምሽት ማታ፤ ከሠርክ እስከ ንዋም። ምሴተ ኀሙስ ለጸቢሐ ዐርብ። በምሴት ይደምፅ ብካይ። በዐሡሩ ወሰቡዑ ምሴት። ደመና ምሴት ፡ (ቅዳ ኤጲ። መዝ ፡ ፳፱። ኩፋ ፡ ፳፫። ምሳ፲፮ ፡ ፲፭)።
ምሥሃል ፡ (ዕብ ካፎሬት። ጽር ይላስቲሪዎን) ይቅር መባያ ፥ ማስተስረያ፤ ይቅርታ ስርየት ማግኛ፤ የታቦተ ሙሴ ፥ መክደኛ ፥ ልባጥ መሸፈኛ ፥ ፪ቱ ኪሩቤል የተሣሉበት። አጐበር መጋረጃ ፥ የምሧዕ የመንበር ያልጋ የዙፋን። ወገብረ ምሥሃለ መልዕልተ ታቦት እምወርቅ ንጹሕ
፡ (ዘፀ፴፰ ፡ ፭–፰። ዕብ፱ ፡ ፭)።ኀጢአት ጣዖት በማለት ፈንታ ምሥሃል ይላል፤ ስሕተት ነው። ምሥሃለ ሰማርያ ፡ (ዓሞ፰ ፡ ፲፬)።
ምስሓል ፡ (ላት) መሳያ፤ መሳል ሰኰቴ፤ ልዝብ ደንጊያ።
ምሥሓቅ ፡ (ቃት) መሣቂያ፤ መጨዋቻ፤ ትያጥሮን። ሕገ ምሥሓቅ ፡ (አዋል)።
ምስሓብ ፡ (ባት) ምስሓብ፤ ፡ (ባት) መሳቢያ፤ ማሳቢያ ቦታ፤ ለኮ ገመድ ሰንስለት። ሐብለ ምስሓብከ ፡ (አዋል)።
፡ አስማት፤ ድጋም፤ የጠንቋይ ጸሎት፤ ዛርና ጋኔን የሚስብ፤ የሚያቀርብ። ምስሓበ ዛር፤ ጋኔን ሳቢ እንዲሉ
፡ (ዐማርኛ)።
ምስሓግ [1] ፡ ምሳግ፤–ስሒግ ሰሐገ።
[2] ፡ ምስሓግ፤ ፡ (ጋት፤ መሳሕግት፤ ታት) ሰቈቃው፤ ሙሾ ልቅሶ ዋይታ፤ የልቅሶ ግጥም። ወአስቈቀዎ ኤርምያስ ለኢዮስያስ፤ ወይቤሉ ኵሉ ሐለይት ወሐላይያት ምስሓጋቲሆሙ ላዕለ ኢዮስያስ እስከ ዛቲ ዕለት፤ ወሠርዕዋ ለይእቲ ምስሓግ በኵሉ እስራኤል፤ ወነያ ጽሕፍት ውስተ ምስሓግ ፡ (፪ዜና
፡ ፴፭ ፡ ፳፭)።
[3] ፡ ምስሓግ፤
፡ (ዕብ ሪማህ) ብዙ ትል፤ እንደ ሮማን ፍሬ ጽፍቅ የኾነ፤ መግነዝ የሬሳ ጕዝጓዝ፤ ሰሌን፤ ሣጥን። ተነጸፍከ ምስሓገ በታሕቴከ ፡ (ኢሳ፲፬ ፡ ፲፩)።
፡ ምሽግ፤ ምሳግ በረት። የሙሾ የልቅሶ ቦታ፤ ማርገጃ መቃብር፤ የሙት ቤት። ኢትባእ ምስሌሆሙ ውስተ ምስሓግ። ትግበር ላቲ ዳሰ ኀበ ትነብር ውስተ ምስሓግ ወትረ ፡ (ኤር፲፮ ፡ ፰። ኢሳ፲፮ ፡ ፫)።
፡ ምንጣፍ ዳውዣ ገሣ። ኅሱር ልብስ፤ ኰስኳሳ፤ ሸካራ ከሰሌን ጭረት የሚሠራ፤ ተሊስ፤ ማቅ ምንጣፍ፤ መናኒ መነኵሴ በረኸኛ ሐዘነተኛ የሚለብሰው። እኁ ለባሴ ምስሓግ ፡ (ፊልክ ፡ ፻፴፫)። ምስሓግ በማለት ፈንታ መሳግሕት መሳግሕታት ይላል፤ ስሕተት ነው
፡ (ፊልክ ፡ ፻፹፱)።
ምስሕ ፡ ምስ ዳረጎት፤ ጕርሻ ቅምሻ፤ ለዛር ለጋኔን ለቡዳ የሚሰጥ የሚፈነጠቅ። ለበቅርና ለጥፊም ይኾናል፤ ምሱን ስጠው እንዲሉ።
ምስለ ፡ (ደቂቅ አገ) ከ–ጋራ፤ ዐብሮ ፥ ከነ ፥ ቸልታ ፥ ሲ፤ እንደ። ኢታማስን ጻድቃነ ምስለ ኃጥኣን። መጽአ ምስለ ብእሲቱ ወውሉዱ፤ ከነ። ሰረረ ንስር ምስለ መጽሐፍ። ተለውዋ ዕደው ምስለ ንዋየ ሐቅሎሙ፤ ይዘው። በጽባሕ ምስለ ትንሣኤ ፀሓይ፤ ሲ። አበስነ ምስለ አበዊነ። ወኢተቀሥፉ ምስለ ሰብእ፤ እንደ ፡ (ዘፍ፲፰ ፡ ፳፫። አዋል። ተረ
፡ ባሮ። ዮዲ፲፭ ፡ ፲፫። መዝ ፡ ፻፭። ፸፪)። ምስሌሁ ሃ ከ ኪ የ እያለ ፥ እንደ ኀበ በኃምስ ይዘረዝራል። በወ ፈንታ ምስለ ይላል፤ ስሕተት ነው። ኣፈልሰከ ለከ ምስለ አኀዊከ ፡ (ኤር፳ ፡ ፬)። ፡ (ዕር፳፩ ፡ ቍ፻፲፬)።
ምስሌሁ ፡ ከርሱ ጋራ፤ እንደ ርሱ። ምስሉ ሥዕሉ፤ መልኩ።
ምስል ፡ (ብ ምሰል፤ ምስላት፤ አምሳል ላት) በቁሙ፤ ጣዖት ፥ መታሰቢያ፤ ግልፎ ቅርጽ ተመሳሳይ መልክ ያለው፤ የነገር ምሳሌ ተረት ዕንቈቅልኽ። ምስል ዐቢይ ርእሱ ዘወርቅ። ግነዩ ወስግዱ ለምስል። ምሰሊሆሙ ትሰብሩ። ወሰበረ ምስላቲሆሙ። እሤሩ ግልፎከ ወአምሳሊከ። አምሳላተ እንስሳ። ልበ ጠቢብ ይፌክር አምሳለ። ይፈትን ሰርጐ ምስል ፡ (ዳን፪ ፡ ፴፩። ፫ ፡ ፭። ዘፀ፴፬ ፡ ፲፫። ዮዲ፫ ፡ ፰። ሚክ፭ ፡ ፲፪። ጥበ፲፫ ፡ ፲። ሢራ፫ ፡ ፳፱። መክ፲፪ ፡ ፱)።
ምሥልስት ፡ (ዕብ ምሹላሾት) ሣልሳት ሣልሳውያት፤ ሦስተኞች ሦስተኛ ክፍሎች፤ ደርቦች ተሥላሶች። እስመ ምሥልስት እማንቱ ፡ (ሕዝ፵፪ ፡ ፮)።
ምስማዕ ፡ (ዓት) መስሚያ፤ ማሰማያ፤ የዦሮ ብሌን፤ ውስጠኛይቱ። ውስተ ምስማዐ እዝን። ዝኩ ቃል ሶበ ይደምፅ በምስማዓቲነ። ውስተ ጹዱቃት ምስማዓተ መንግሥት ኢይሰማዕ ሥሕጸት። ኢተሰጥዎ በምስማዐ ሥሕጸት ዘላዕለ እግዚ። ድኁነ ምስማዕ ወንጻሬ ፡ (መዝ ፡ ፲፯። አፈ ፡ ተ፲፯። ቄር ፡ ገ፯። ፍ
፡ ነ ፡ ፵፫)።
፡ ቦታ፤ ሸንጎ አደባባይ። እመ ቦእከ ውስተ ምስማዐ ሰማይ ፡ (አፈ ፡ ተ፳፰)። ጥቃት ውርደት ትሕትና በማለት ፈንታ ምስማዕ ይላል፤ አያሰኝም። አግብአ ኵሎ ኅሊና ውስተ ምስማዐ ክርስቶስ ፡ (ቄር ፡ ጰላ)።
ምስማክ ፡ (ካት) መጠጊያ፤ ድጋፍ፤ ዐልጋ፤ መከዳ። ምስማክ ርእስየ። ምስማኩ ዘወርቅ። ውስተ ምስማክ ዘኀበ አረፍት
፡ (መዝ ፡ ፶፬። ማሕ፫ ፡ ፲። ፩ነገ ፡ ፳ ፡ ፳፭)።
፡ ምሰሶ ተራዳ፤ ባላ ጫፍ። ዐውደ ምስማኩ ይእቲ። አትርፉ ምስማካቲሃ ፡ (ሢራ፴፮ ፡ ፳፱። ኤር፭ ፡ ፲)።
ምስራ ማሱራ ፡ (ቅብጥ ሜሱሪ) የወር ስም፤ ነሐሴ
፡ (አቡሻ)።
ምሥራቃዊ ፡ የምሥራቅ። ቴዎድሮስ ምሥራቃዊ። ምሥራቃውያን ፡ (ስንክ ፡ ጥር፲፪። ፍ ፡ ነ ፡ ፬)።
ምሥራቅ ፡ (ቃት) በቁሙ፤ የፀሓይ፤ መውጫ፤ መገለጫ፤ ማእዝን፤ ሀገር፤ የምዕራብ ትይዩና አንጻር። እምሥራቀ ፀሓይ እስከነ ዐረብ። ነገሥት እለ እምነ ምሥራቀ ፀሓይ። ምሥራቃት ፡ (መዝ
፡ ፻፲፪። ራእ፲፮ ፡ ፲፪። አቡሻ
፡ ፵፯)።
ምሥራብ ፡ መጠጫ፤ ብርሌ ዋንጫ፤ የመሰለው ኹሉ። ሰላም ለሰፍነግ፤ ለብሒአ ሐሞት ምሥራቡ ፡ (ስንክ ፡ መስ፲፱)። ለቦታም ይኾናል።
(ጥስ) ምስር [1] ፡ በቁሙ፤ ብርስን ፡ (መ ፡ ፈ)።
(ላስ) [2] ፡ምስር
፡ (ዐረ ሚጽር፤ መጽር) በቁሙ፤ ስመ ሀገር ፥ ግብጥ የሚጽራይም ክፍል ሚጽር። ሊጣፍ የሚገባው በጻዴ ነው እንጂ በሳት ሰ አይዶለም። ደወለ ምስር። ማዕልቃ ዘምስር።
ምስቁል ፡ (ላን ላት ቅልት) የተመሳቀለ፤ ምስቅል፤ መስቀልማ። ምስቁለ አእዳው። ይግበር መንዲለ ምስቁለ ላዕለ መታክፍቲሁ ፡ (ፈ ፡ መ ፡ ፳፮ ፡ ፰። ፴፩ ፡ ፭)።
ምስቃይ ፡ (ያት) ቦይ መትረብ፤ የመስኖ ውሃ የሚሳብ የሚጐተት። ዘቦቱ ምስቃይ ውስተ ምድር ይደልዎ ለረኪበ ፍኖት ኀበ በዊእ ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፴፯)።
ምሥባሕ ፡ (ሓት) መሥቢያ ማሥቢያ ፥ ማድለቢያ።
ምስባክ ፡ (ካት) መስበኪያ ቦታ፤ ከፍ ያለ። ዲያቆን ከወንጌል በፊት የሚያዜመው መዝሙር።
ምስብዒት ፡ ሰባት እጅ፤ ሰባት ዕጥፍ፤ ሰባት ጊዜ ሰባት፤ መጠ ፵፱። ይፈዲ ምስብዒተ። ይበርህ ምስብዒተ እምፀሓይ። የኀሥሥ ይረስዮ ምስብዒተ። ሰብዐቱ ዓመት ዘምስብዒት ፡ (ምሳ፮ ፡ ፴፩። ቀሌ። ሢራ፯ ፡ ፲፪። ዘሌ፳፭ ፡ ፰)።
ምስታይ ፡ ማጠጫ፤ መጠጫ ቦታ፤ ገንዳ፤ የመሸታ ቤት። ወሶጠት ቀሡታ ፍጡነ ውስተ ምስታይ። ገብላት ዘምስታየ ማይ። ምንባረ ምስታይ ፡ (ዘፍ፳፬ ፡ ፳። ፴ ፡ ፴፰። ዮሴፍ)።
ምስትስራይ ፡ (ያት) ማስተስረያ፤ ቦታ መሣሪያ። ምስኣል ወምስትስራየ ኀጢአት ፡ (ቀሌ። መቃ። ድጓ)። በምስትስራይ ፈንታ ስርየት ይላል፤ ስሕተት ነው። ወገብሮ ስርየተ ፡ (ሮሜ፫ ፡ ፳፭)።
ምስትቅታል ፡ መገደያ፤ መገዳደያ፤ ማገዳደያ፤ ቦታ።
ምስትብጻሕ ፡ መዳረሻ መገናኛ መጋጠሚያ፤ ጉባኤ ሸንጎ።
ምስትዕዳው ፡ መሸጋገሪያ መተላለፊያ፤ ማሸጋገሪያ ማስተላለፊያ።
ምስትጕባእ ፡ ዝኒ ከማሁ። ቤተ ምስትጕባአ ዚኣሁ። ምስፋሕ ወምስትጕባእ ፡ (ሔኖ፶፫ ፡ ፮)። አንዳንድ መጽሐፍ ግን ጥሬውን በቅጽል ለውጦ፤ ምስትጕቡእ ይላል፤ አያሰኝም ፡ (ቅዳ ፡ ሕር)።
ምሥናይ ፡ ማማሪያ፤ መዋቢያ፤ መልካም ቦታ፤ ምቹ ስፍራ። ጌሴም ምሥናይሃ ለምድረ ግብጽ። ንበር ዝየ ውስተ ምሥናይ ፡ (ኩፋ ፡ ፵፭። ያዕ፪ ፡ ፫)።
ምስኣል ፡ (ላት) መለመኛ፤ መማለጃ፤ መጠየቂያ ቦታ፤ ቤተ ክሲያን። ትኩን ምስኣለ ወምስጋደ ወምስትስራየ ኀጢአት ፡ (ቀሌ። ድጓ። አርጋ
፡ ፬)።
ምስኪነት ፡ ምስኪንነት፤ ንዴት፤ ምናኔ። ወምስኪነትየኒ። ኖኅሰ አምሳለ ምስኪነት ፡ (ቅዳ። ፊልክ
፡ ፪፻፰)።
ምስኪን [1] ፡ በቁሙ፤–ሰኪን ሰከነ።
[2] ፡ (ንት ናን
ናት። ዕብ ሚስኬን።
ሱር ሜስኪና። ዐረ መስኪን) ፤ በቁሙ ፤
ቍርጩ ድኻ ፤ ጦም ዐዳሪ ፤ ቤት ንብረት ገንዝብ ርስት መጠጊያ የሌለው ፤
ጥገኛ ለማኝ። ብፁዕ ዘይሌቡ ላዕለ ነዳይ ወምስኪን። ግዩር ወምስኪን። ጸውዕ ነዳያነ ወምስኪና። ዘለምስኪናን ወለልሕዋን
ይናዝዞሙ (መዝ
፡ ፴፱። ቅዳ ፡ ቄር። ሉቃ፲፬ ፡ ፲፫። ኪዳ)።
ምስካብ ፡ (ባት) መተኛ መጋደሚያ ቦታ ዐልጋ ምንጣፍ መቃብር መኝታ ቤት ጧ ዟ ብሎ ሬሳ መስሎ የሚተኙበት የሚዘረጉበት። ሐኖት፤ ቤተ ዝሙት። ወነበረ ዲበ ምስካቢሁ። ምስካበ ኀጺን። ወሀብዋ ምስካባቲሁ ወኵሎ ንዋዮ ህየ ነጸፍኪ ምስካበኪ። ውስተ ምስካበ ሲኦል ይነውሙ። ምስካቢነ ዘበሕቍ ፡ (ዘፍ፵፰ ፡ ፪። ስንክ
፡ ግን፲፱። ዮዲ፲፭ ፡ ፲፩። ኢሳ፶፯ ፡ ፯። ኢዮ፳፩ ፡ ፲፫። ማሕ፩ ፡ ፲፮)።
ምስካይ ፡ (ያት) መክሰሻ፤ መከሰሻ። መሸሻ መጠጊያ፤ መማጠኛ፤ የሙጥኝ መባያ፤ መደወያ፤ ገዳም ደብር። አህጉር ዘምስካይ። ምስካዮሙ ለግፉዓን። ማርያም ድንግል ለነፍስየ ደብረ ምስካያ ፡ (ዘኍ፴፭ ፡ ፮ ፡ ፲፩። ድጓ። ደራሲ)።
ምስክ ፡ (ፋርስ ሙሽክ። ዐረ ሚስክ። ሱር ሙሳክ። ዕብ ሙሻቅ። ጽር ሞስኮስ)። የሽቱ አውሬ፤ ዝባድ ወይም እንደ ዝባድ ያለ ሌላ። ጥሩ ሽቱ ከዚያው ካውሬው ገላ የሚገኝ። ምስክ ዘውስተ ቢረሌ። ጼናሁ ይምዕዝ እምስክ ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፴፰ ፡ -፪። አረጋ ፡ ድ፲፫)።
ምስዋር ፡ (ራት) መሰወሪያ፤ መደበቂያ ቦታ፤ ጓዳ ስግዳ፤ መቅደስ፤ መጋረጃ፤ አንባ ዋሻ፤ ዕርድ ምሽግ። ይትኀባእ በምስዋር ይትረሳዕ። ወረሰየ ጽልመተ ምስዋሮ። እምድኅረ አረፍተ ምስዋር። መንጦላዕተ ምስዋራቲሁ ለሕያው። ዝንቱ መካን ኮነኒ ምስዋረ ህየንተ አልባስየ። ምስዋር ረድኤት። ሐገፋ ወምስዋር
፡ (ጥበ፲፯ ፡ ፫። መዝ ፡ ፲፯። ነሐ፬ ፡ ፲፫። ቅዳ
፡ ሕር። ስንክ ፡ ግን፳፰። ኪዳ። አፈ
፡ ተ፭)።
ምሥዋን ፡ (ብ መሣውን፤ ምሥዋናት) ማልገጊያ መትፊያ፤ ልጋግ መጣያ መቀበያ፤ የድዉይ ፡ (አዋል)።
ምስው ፡ (ዋን ዋት ሱት) የቀለጠ ፥ የዛለ የደከመ የፈሰሰ። አብራክ ምስዋት
፡ (አፈ ፡ ድ፴)። ፅዉስ ሐንካስ ማለት ነው ፡ (ዕብ፲፪ ፡ ፲፪)።
ምሥያም ፡ (ማት) መሿሚያ፤ መኖሪያ ማኖሪያ፤ ቦታ ስፍራ። እለ ይትቀነዩ በውስተ ምሥያሞሙ። ምሥያመ አስሐትያ። መዝገበ ረድኤት። ወምሥያመ ትፍሥሕት
፡ (፩ዜና ፡ ፳፭ ፡ ፩። ኢዮ፴፰ ፡ ፳፪። ቅዳ
፡ ዮሐ)። በመሥየምት ፈንታ ምሥያም ይላል፤ ፍችው ፩ ነው። ኅብስተ ምሥያም። ማእዳት ዘምሥያም ዕጣነ። ዕጣነ ምሥያም። ኀብአቶ እሙ ለሕፃን ውስተ ምሥያም ወሰቀለዮ ላዕለ ዕፀ በለስ ፡ (፩ዜና ፡ ፳፫ ፡ ፳፱። ፳፰ ፡ ፲፮። ፪ዜና ፡ ፲፫ ፡ ፲፩። ስንክ ፡ ግን፲፭። ሠኔ፲፱)።
ምሥያጣዊ ፡ ገባያኛ ገባያተኛ፤ የገባያ ሰው ዐጣሪ ነጋዴ። ምሥያጣዊ ዘእንበለ ንዋይ ፡ (መጽ ፡ ምስ)።
ምሥያጥ ፡ (ጣት) መሼጫ መሸቀጫ ገባያ ሱቅ መደብር። ሰብአ ምሥያጥ። ህየ ይገብሩ ምሥያጠ። ተፀርዐ ሤጥ ወምሥያጥ። ዛቲ መጽሐፍ ትመስል ምሥያጠ፤ ወኵሎ ዘኀለይከ ትረክብ ውስቴታ። ተኣምኆ በውስተ ምሥያጣት ፡ (አፈ ፡ ድ፩። ነሐ፲፫ ፡ ፳። ዮሴፍ። ፊልክ። ማቴ፳፫ ፡ ፯)።
ምስድሲት ፡ ስድስት ዕጥፍ፤ ለወ–፴፮። ስድስት እጅ።
ምሥጋር ፡ (ራት) መሥ(ሻ) ገሪያ ፥ መራመጃ፤ እርምጃ። ዘይረውጽ ኢይኔጽር ኀበ ምሥጋሪሁ። ዘኢይክል ይትሐወስ ወኢየሐውር አሐተ ምሥጋረ። ወኢምሥጋረ እግር ፡ (አፈ ፡ ድ፯። ጥበ፲፫ ፡ ፲፰። ዘዳ፪ ፡ ፭)።
ምሥጋው ፡ መሥጊያ። መሠጊያ፤ ሰው መኾኛ ፥ ሥጋ መልበሻ። መንፈስ ቅዱስ ቀደሳ ለወለተ ሥጋውያን ከመ ትኩን ምሥጋወ ለአምላከ ኵሉ ዘሥጋ ፡ (መጽ ፡ ምስ)።
ምስጋድ ፡ (ዐረ መስጊድ) መስገጃ፤ ማሰገጃ፤ መቅደሰ ኦሪት፤ ቤተ ክሲያን፤ ቤተ ጣዖት። ቤተ ጸሎት እንተ ተተክለት ለምስጋድ። ምስጋደ አማልክት ፡ (ድጓ። አርጋ ፡ ፬። አብጥ ፡ ፷፮)።
ምሥጠት ፡ መንጠቅ ፥ መነጠቅ ፥ አነጣጠቅ፤ ንጥቂያ ቅሚያ፤ ሽሽት ሩጫ። አይድዖሙ ፍኖተ አስትሮብሎስ ወምሥጠቶ መንግሥተ ዘልሂቅ እኍሁ። ያፈጥን ፍጻሜ ኅልፈተ ምሥጠቶሙ ፡ (ዮሴፍ። ጥበ፲፬ ፡ ፲፬)።
ምስጢራዊ ፡ ምስጢራም፤ ምስጢረኛ ባለምስጢር፤ ምስጢር የኾነ፤ የምስጢር ሥራ፤ ኅቡእ ረቂቅ። ተዋሕዶተ መለኮት በሥጋ ተዋሕዶ ምስጢራዊ። ወበዛቲ ዕለት ገብረ ድራረ ምስጢራዊተ ፡ (ያዕ
፡ ዘእል። አቡሻ ፡ ፳፩)።
ምሥጢር ፡ በቁሙ፤–ሰጢር ሰጠረ።
ምስጢር [1] ፡ በቁሙ፤–ሰጢር ሰጠረ።
[2] ፡ (ራት። ጽር ሚስቲሪዮን) በቁሙ፤ ስጡር፤ ኅቡእ ስዉር፤ ሽሽግ ነገር ሐሳብና ምክር። በዓላት በጕሃን ወመሥዋዕት በምስጢር። ምስጢረ መንግሥት ሠናይ ለኀቢእ። ምስጢ ምክሩ። ዝንቱ ነገር ይኩን በምስጢር ፡ (ጥበ፲፬ ፡ ፲፭። ጦቢ፲፪
፡ ፯። ቀሌ)።
፡ አምላካዊ ግብር፤ መንፈሳዊ ረቂቅ፤ የማይታይ የማይታወቅ፤ የሚታመንና የሚደነቅ ብቻ። አዕማደ ምስጢር። በእንተ ትድምርተ ቃል ዘበምስጢር። ምስጢር ግሩም ምስጢር አምላካዊ። ሥርዐተ ምስጢ ዘቍርባን። ወይትመጦ እምስጢራት ቅዱሳት
፡ (ቄር። አፈ ፡ ተ፲፯። ቅዳ። ፍ ፡ ነ ፡ ፭)።
ምስጣሕ ፡ (ሓት) ማስጫ፤ መሰጫ፤ ቦታ መሣሪያ። ምስጣሐ መሥገርት ፡ (ሕዝ፳፮ ፡ ፲፬)።
ምሥጥ ፡ በቁሙ፤ ነጭ የቈላ ተባይ ፥ የጕንዳን ዐይነት፤ ውስጥ ውስጡን የሚኼድ መሣጢ፤ የክፉ ምሳሌ። እገሌ ምሥጥ ነው እንዲሉ። ፡ (ተረት) ምሥጥ ወደ ውስጥ።
ምስፋሕ ፡ መዘርጊያ፤ ፡ (ጥዘ) መዘርጊያ፤ ቦታ። ምስፋሕ ወምስትግባእ
፡ (ቅዳ)። መጽሐፍ ግን፤ ምስፋሕ ወምስትጉቡእ ይላል፤ አያሰኝም። ዳግመኛም በምስፋሕ ፈንታ ምስትስፋሕ ይላል፤ ፍችው አንድ ነው ፡ (መጽ ፡ ምስ)።
ምስፋር ፡ (ራት) መስፈሪያ መሳፈሪያ፤ ሰፈር ስፍራ ቦታ፤ ምዕራፍ።
ምስፋይ ፡ (ያት) መስፊያ፤ መሰፊያ፤ ማሰፊያ፤ ቦታ መሣሪያ።
ምስፋጥ ፡ (ጣት) ማታለያ መሸንገያ፤ ማሳቻ ማሳሳቻ።
ምስፍና ፡ መስፍንነት፤ ሹመት ግዛት፤ ሥልጣን፤ በትረ መንግሥት። አመ ምስፍና ባርቅ። ኢይወፅእ ምስፍና እምአባሉ። እግዚ አዕበየ ክብርየ ወምስፍናየ ላዕለ ኵሉ ዓለም
፡ (ጥበ ፡ ጦቢ። ዘፍ፵፬ ፡ ፲። ዮሴፍ)።
ምሧዕ ምሥዋዕ ፡ (ዓት) በቁሙ፤ መሠዊያ ፥ መሥዋዕት ማቅረቢያ፤ ማረጃ ማንደጃ ፥ ቦታ ምድጃ ፥ የብሉይ። ነደቀ ኖኅ ምሧዐ ወአዕረገ ቍርባነ ዲበ ምሥዋዕ። ጸርሐ ወይቤ። ምሧዕ ምሧዕ ከመ ዝ ይቤ እግዚ። ወይትነሠቱ ምሥዋዐቲክሙ ፡ (ዘፍ፰ ፡ ፳። ፫ነገ ፡ ፲፫ ፡ ፪። ሕዝ፮ ፡ ፬)።
፡ መንበረ ታቦት፤ ጽሌ ጽላት፤ የሐዲስ። ያንብሩ ዲበ ምሧዕ ወንጌለ ዮሐንስ፤ ወለእመ ተሰብረ ምሧዕ አው ፈለሰ ይቀድሱ ዳግመ። ክልኤቱ ምሧዓት አሐዱ ዘያፈልስዎ እመካን ውስተ መካን ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፩። ፈ ፡ መ ፡ ፳፱ ፡ ፪)።
ምረር (ራት) [1] ፡ በቁሙ፤ ምረት መራርነት፤ ሐዘን መከራ ቍጣ። ምረሩ ለማይ። ምረሩ ለሞት። እክሥት ምረረ ነፍስየ። እለ ተዐገሡ ምረራተ ብዙኃተ ፡ (ራእ፰ ፡ ፲፩። መቃ ፡ ገ፲፱። ኢዮ፯ ፡ ፲፩። አፈ ፡ ድ፴፩)።
[2] ፡ (ዕብ ምሬራ። ሱር ምሪራ። ዐረ መራረት) መሪር ፥ መራራ፤ በጠባዩ ምረት መራርነት ያለው፤ ሐሞት ከርቤ ሬት ኮሶ ፥ የመሰለው ኹሉ፤ መደበኛው ግን ሐሞት ነው። ጥዕምኩ ዕጕሥታረ ወኵሎ ምረራተ፤ ወኢረከብኩ ዘይመርር እምንዴት ፡ (ፈላስ
፡ ገ፷፭)። አንዳንድ መጣፍ በምረር ፈንታ መሪር እንደ ማለት ምረት ይላል ፡ (ዘዳ፳፱ ፡ ፲፰። ጥበ፰ ፡ ፲፮)።
ምረት ፡ በቁሙ፤ መምረር ፥ ማዘን፤ አመራረር ፥ መራርነት ክፋት። ምረተ ሕምዝየ። በምረተ ነፍሱ። አእመረ ምረቶሙ ፡ (ሰቈ፫ ፡ ፳። ሢራ፬ ፡ ፮። ኩፋ ፡ ፩)። ሬት ማለት ከዚህ የወጣ ነው።
ምረግ ፡ (ጋት አምራግ) ምርግ ፥ ምርጊት፤ ልስናት ልቅልቃት። ከመ ምረገ አረፍት። አይቴመ ምረግ ዘመረግሙ። ምረገ ኆጻ ውስተ አረፍት
፡ (ኢዮ፴፫ ፡ ፳፬። ሕዝ፲፫ ፡ ፲፪። ሢራ፳፪ ፡ ፲፯። ዳን፭ ፡ ፭)።
ምሩሕ ፡ (ሓን ሓት ርሕት) የተመራ፤ ተመሪ ተማሪ ፥ ተከታይ።
ምሩር ፡ (ራን ራት ርርት) የመረረ፤ የተመረረ፤ ያዘነ የተከፋ። ለምንት ወሀብኮሙ ብርሃነ ለምሩራን። ከማሁ ለምሩራን ፡ (ኢዮ፫ ፡ ፳። መዝ ፡ ፷፯)።
ምሩዕ ፡ (ዓን ዓት ርዕት) የሻፈደ ጕምዡ፤ ሴሰኛ ድራተኛ፤ ዘማዊ። ምሩዕ በፍትወተ ነፍሱ ምርዕት ይእቲ። ሰመይዋ ምርዕተ ፡ (ቀኖኒቅ። ምሳ፯ ፡ ፲፩። ቄድር)።
ምሩድ ፡ (ዳን ዳት ርድ) የተሞረደ ሙርድ፤ የተወረረ የተዘረፈ።
ምሩግ ፡ (ጋን ጋት ርግት) የተመረገ ምርግ፤ ልስን ልቅልቅ። ቤት ምሩግ። ይረክቦ ምሩገ ፡ (ምሳ፳፩ ፡ ፬። ማቴ፲፪ ፡ ፵፬)።
»ምራቅ ፡ በቁሙ፤ ትፋት ትፍታ፤ አክታ ጢቅታ። ኢሜጥኩ ገጽየ እምኀፍረተ ምራቅ። ለእመ መጽኦ ምራቅ። ጽቡረ ገብረ በምራቁ ፡ (ኢሳ፶ ፡ ፮። ፊልክ ፡ ፲። ዮሐ፱ ፡ ፮)። በምራቅ ፈንታ ረቅ ይላል። በረቀ አፉሆሙ
፡ (አዋል)። መረቀ ማለት ከምራቅ ወጥቷል፤ መርቀኝ ሲል እንትፍትፍ በልብኝ እንዲል ፡ (ባላገር)።
ምርሓስ ፡ ማራሻ፤ መንከሪያ፤ ዕቃ ቦታ።
ምርሐት ፡ መምራት፤ መመራት፤ መሪነት ፥ ተመሪነት፤ አመራር ምራት ምሪት። ዘወሀቦ ጥበበ ምርሐት ፡ (ፊልክ ፡ ፻፱)።
ምርስኔ ፡ (ጽር ሚርሲኒ) የሽቱ ዕንጨት፤ ባርሰነት ወይም አደስ። አዴሸምን እይ፤ ከዚህ ጋራ ፩ ነው። ዕፀ ጲቅሶን መምርስኔ ፡ (ኢሳ፵፩ ፡ ፲፱። ኩፋ ፡ ፳፩)።
ምርቃይ ፡ መድገሚያ፤ መርጫ፤ የጠበል ቦታ ፡ (ኪዳ)።
ምርት ፡ በቁሙ፤ የመረተ የተመረተ ፥ ባውድማ መካከል የተሾመ የተሸለመ ቍልል ጥሩ እኽል።
ምርዐት ፡ መጐምዠት፤ መዳራት መቃበጥ፤ መቄናጠጥ፤ በውስጥ በአፍኣ መታወክ መቅበጥበጥ። ዝሙት ወምርዐት።ፈቲው ፥ ምርዐት ወዝሙት። ገብረ ዝሙተ ወምርዐተ። ኩፋ ፡ ፳፭። ኪዳ ፡ ገ፬። ፈ ፡ መ ፡ ፮ ፡ ፲፩)።
ምርኣይ ፡ (ያት) ማያ፤ ማሳያ፤ መተያ፤ ቦታ፤ መስታዮት፤ መነጽር። ርእይ፤ ራእይ፤ ርእየት በማለት ፈንታ ምርኣይ ይላል፤ የተሳሳተ ነው። ምርኣየ አዕይንቲከ ፡ (ዘዳ፳፰ ፡ ፴፬)። ሞራ ማለት ከዚህ ወጥቷል፤ ማያ መጠንቈያ ማለት ነው ፡ (ሕዝ፳፩ ፡ ፳፩)።
ምርዕ ምርዓ ምርዓት ፡ (ታት) ሴሰን ድራት፤ እንስሳዊ ጭዎት፤ ልፊያ ቍልመማ ፥ የዝሙት ዋዜማ። እምስካር ይትወለድ ምርዓት። ርኵስ ወምርዓት። ዘኢያስተዋድይዎሙ በምርዓት
፡ (ቀሌ። ገላ፭ ፡ ፲፱። ቲቶ፩ ፡ ፮)።
ምርዕውና ፡ ሙሽርነት፤ ጋብቻ፤ ሰርግ። ለዝንቱ ብእሲ ኢያጽሐቆ ዲበ ምድር ምርዕውና
፡ (መዋሥ)።
ምርካብ ፡ (ባት) ማግኛ፤ መገኛ፤ ማስገኛ ቦታ። ደመ ወዝ፤ ምንዳ፤ የሙያ፤ የጕልበት ዋጋ፤ ጥቅም፤ ትርፍ፤ በሥራ የሚገኝ። ዘኒ የሐርስ እንዘ ይሴፎ ምርካቦ
፡ (፩ቆሮ ፡ ፱ ፡ ፲ ፡ ፲፬። ግብ፲፱ ፡ ፳፭)።
፡ ሐሳብ፤ ጥበብ፤ ነገር፤ ምስጢር፤ ከልብ የሚገኝ። ምርካብ ዘልብ ውፁእ ፡ (ቄር
፡ ጰላ)።
ምርዋሕ ፡ (ሓት) ምዝራቅ፤ ምንዛህ የውሃ መርጫ፤ መፈንጠቂያ። ይሰድዎ ኀበ ቤተ ክርስቲያን በመኃትው ወበመጻውዕት ወበምርዋሕ ወበድባብ። ወትረቂ መቃብሪሁ በማይ ፡ (ግንዘ)።
ምርዋጽ ፡ (ጻት) መሮጫ፤ ማስሮጫ፤ የሩጫ ቦታ፤ ሜዳ ስታታ። ምርዋጸ ብእሲ። ምርዋጸ ፈረስ። ሖሩ ኀበ ምርዋጻት ፡ (ግብ፩ ፡ ፲፪። ዲድ
፡ ፴፫። አፈ ፡ ተ፯)።
ምርያ ፡ ሠግር፤ የሱባዔ ቍጥር፤ ዐውደ ዕለት ፯ ቀን ብቻ ስለ ኾነ የአውራኅንና ያመታትን ብተትና በዓል ከቀን ወደ ቀን የሚያሻግር የሚያዘዋውር። ዕለተ ምርያ ዘያጠውዮን ለመዋዕለ ዓመታት ወያዐውዶን እምዝ ውስተ ዝ ፡ (መጽ ፡ ምስ)። ከፅንስ እስከ ልደት ያለውም የጌታችን መዋዕለ ፅንስ ፱ ወር ካ፭ ቀን ዮም ወለድኩከ የተባለበት ለብሉዩና ለሐዲሱ ዘመን ሠግር ስለ ኾነ ፥ እንደዚሁ ምርያ ይባላል፤ ዕለት ኀሪት ዕለተ መድኀኒት ማለት ነው ፡ (ኢሳ፵፱ ፡ ፩ ፡ ፭ ፡ ፮ ፡ ፰)።
ምርዱድ ፡ ደፋር ጨካኝ፤ ትጉ ፈጣን፤ ሥራዉን መንገዱን የማያቆም የማያቋርጥ ፡ (ሄርማ ፡ ገ፯ና
፡ ፲)።
ምርጉዝ ፡ (ዛን ዛት ጕዝት) በትር የያዘ፤ የተደገፈ፤ የተመረጐዘ፤ ባለምርጕዝ፤ ድውይ ዐንካሳ ደካማ።
ምርጕዝ ፡ (ብ መራጕዝ) በቁሙ፤ ደጓሳ በትር፤ እንደ ባላና እንደ መቃን ኹኖ የሚደግፍ። ምርጕዞሙ ውስተ እዴሆሙ። ምርጕዘ ጻድቃን። ምርጕዝ ለርሥኣንየ ፡ (ዘካ፰ ፡ ፬። ኪዳ። ድጓ)።
፡ በቁሙ፤–ረጊዝ ረገዘ።
ምርጋፅ ፡ መርገጫ፤ መረገጫ፤ ማስረገጫ፤ ማርገጃ፤ ማመርገጃ ቦታ።
ምርፋቅ ፡ (ቃት) መርፈቂያ፤ የሰደቃ ቤት፤ የምግብ ቦታ፤ ዳስ፤ ደጀ ሰላም፤ የመሽታ ቤት። ኢትርፍቅ ውስተ ርእሰ ምርፋቅ። ይርፍቁ በበ ምርፋቃቲሆሙ። የሐውር ኀበ ምርፋቃት ፡ (ሉቃ፲፬ ፡ ፯–፲። ማር፮ ፡ ፴፱። አፈ ፡ ተ፴። ቀሌ)።
፡ ጋሬዳ፤ የቍትቻ ድግስ። ኢይግበሩ ምርፋቀ ለስቴ
፡ (ቀኖ ፡ ሎዶቅ)።
ምርፋእ ፡ (ኣት) መስፊያ፤ ማሰፊያ፤ መሰፊያ ቦታ።
ምቁር ፡ (ራን ራት ቍርት) የታጀለ የተነከረ የተዘፈዘፈ። ምቁረ ኤልያስ ፡ (ምቁር ኤልያስ) የተጣፈጠ ዘይቶን የወይራ ፍሬ ፡ (ሥር ፡ ጳኵ)።
ምቅሓም ፡ መቃሚያ፤ ግርግም፤ የእንስሳት ማእድ፤ ቤት በረት ጋጥ። መጽሐፍ ግን በጣፎች ስሕተት ምቅማሕ ይላል ፡ (ኢሳ፩ ፡ ፫። ዕን፫ ፡ ፲፯። ሉቃ፲፫ ፡ ፲፭)።
ምቅማሕ ፡ መቃሚያ፤–ምቅሓም።
ምቅሳም ፡ (ማት) ማሟረቻ፤ መጠንቈያና ማስጠንቈያ፤ ቦታ።
ምቅሣፍ ቅሥፍ ፡ (ፋት) መግረፊያ፤ መገረፊያ፤ ማስገረፊያ ቦታ።
ምቅራብ [1] ፡ (ባት) መቅረቢያ፤ ማቅረቢያ፤ መቃረቢያ፤ አዳራሽ ወልወል፤ አይጸየፍ። ነበሩ ውስተ ምቅራቡ ወአንበብዋ ለይእቲ መጽሐፍ ፡ (ዕዝ ፡ ፲፬)።
[2] ፡ (ዕብ ሜልቃሐይም) የቀንዲል መጥቀሻ፤ መኰስተሪያ፤ መቀስ። ጽዋዓት ወምቅራባት ፡ (፪ዜና ፡ ፬ ፡ ፳፬)።
ምቅባዕ ፡ (ዓት) መቅቢያ፤ መቀቢያ፤ ቦታ። ከመ ዝ ይትቀብዑ እምቅዱስ ቅብዕ በኀበ ምቅባዕ
፡ (ቈስጠ ፡ ፴፱)።
ምቅታል ፡ (ላት) መግደያ፤ መገደያ፤ ማስገደያ ቦታ። መልዕልተ ምቅታል ፡ (፪ነገ ፡ ፭ ፡ ፳)።
ምቅናይ ፡ (ያት) [1] ፡ የድጓ ባህል፤ የምዕራፍ ቀለም ባደራረስ ጊዜ የሚዜም የሚዘመም።
[2] ፡ መግዣ፤ መገዣ፤ ማስገዣ፤ ቦታ ገባያ። ቤተ ምቅናይክሙ
፡ (ዘፀ፳ ፡ ፪)።
ምቅዋም ፡ (ማት) መቋሚያ፤ ቦታ ስፍራ፤ ጥግ ደገፋ። የመነኵሴ በትር፤ ፡ (ተረት) መቃዱን ታጥቆ፤ መቋሚያውን ነጥቆ። ምቅዋመ አጣሊ ርጉማን ወምቅዋመ አባግዕ ቡሩካን። ዐጸደ ምቅዋም ለካህናት። በበ ምቅዋማቲሆሙ ፡ (ግንዘ። ኪዳ። ፪ዜና ፡ ፯ ፡ ፮)።
፡ ኩሬ፤ ዐይግ፤ ምዕቃል። ምዕራፍ አንቀጽ፤ የመጽሐፍ ክፍል። ምቅዋመ ማይ። ወላዕለ ኵሉ ምቅዋም ኍልቍ ፡ (ዘፀ፯ ፡ ፲፱። ሲኖዶ
፡ ገ፩)።
ምቅዳሕ ፡ (ሓት) መቅጃ፤ መቀጃ፤ ቦታ ዕቃ። ምቅዳሐ ፈውስ ወዐዘቅተ በረከት። ገይበ ወርቅ ምቅዳሐ ስብሐት
፡ (አርጋ ፡ ፪)።
ምብሃል ፡ (ላት) መባያ መናገሪያ። ማሰኛ፤ ማናገሪያ።
ምብላኅ ፡ (ኃት) መሳያ ማሾያ፤ መሳል ሞረድ፤ የመሰለው ኹሉ።
ምብላዕ ፡ (ዓት) መብያ፤ ማብያ፤ መበያ፤ ቦታ ዕቃ ወጥ፤ አፍ።
ምብራህ ፡ (ሃት) መብሪያ ማብሪያ፤ ቦታ መቅረዝ።
ምብቋጽ ፡ (ጻት) ማንደጃ ምድጃ፤ መጫሪያ መተርከሻ መዝገኛ ማፈሻ፤ ብረት ገል።
ምብዓር ፡ (ራት) መቈፈሪያ፤ የርሻ የቍፋሮ መሣሪያ።
ምብኳሕ ፡ (ሓት) አጐዶ ማናፊያ፤ ወናፍ። ምብኳሐ ነሃቢ ሥጡቅ። በብዙኅ ምብኳሕ ፡ (ኢዮ ፡ ፴፪ ፡ ፲፱። አርጋ ፡ ፫)።
ምብያት ፡ ማደሪያ፤ ማሳደሪያ፤ መኖሪያ፤ ቦታ ቤት በረት። ከመ መርዔት ውስተ ምብያቲሁ። ምብያቲከ ፡ (ሚክ፪ ፡ ፲፪። ኢሳ፴፯ ፡ ፳፰)።
ምብጣር ፡ (ራት) ማበጠሪያ ማንጠርጠሪያ፤ ሚዶ፤ ስፌድ፤ ፍርድ ዳኛ ወይም ነቃሽ ምስክር ፍትሐ ነገሥት።
ምብጻሕ ፡ (ሓት) መድረሻ ማድረሻ፤ ጫፍ መጨረሻ፤ መግቢያ ማረፊያ መጠጊያ ፡ (ገድ ፡ ኪሮ። ሔኖ፸፬ ፡ ፲፩)።
ምብፃው ፡ መኝታ መተኛ ማስተኛ ቦታ፤ መደብ ዐልጋ። ለእመ ረከብከ ብእሲተ በውስተ ምብፃውከ ፡ (ፊልክ
፡ ፪፻፫)።
ምቱህ ፡ (ሃን ሃት ትህት) የተመታ፤ ምትሀት የኾነ።
ምቱር ፡ (ራን ራት ትርት) የተመተረ፤ የተቈረጠ ቍርጥ፤ የተሻረ ሽር። ምቱረ እድ። ምቱራን በሰይፍ አምሳለ ዕፀው። ምቱርኑ ዝ ነገር። ምቱር እመዓርጊሁ
፡ (ማር፱ ፡ ፵፫። ስንክ ፡ ጥቅ፳፪። ኪዳ። ቀሌ)።
ምቱቅ ፡ ጥዑም ፥ ጥፍጥ፤ መዐርዒር፤ ላይንና ለዦሮም ደስ የሚያሰኝ ነገር ምቱቅ ይባላል። ዘእምልደቱ ዕዉረ አሕየወ፤ ወምቱቀ ብርሃነ አብቈለ ሎቱ ወኵሎሙ አንክሩ
፡ (ቄር ፡ እስት)።
ምታር ፡ (ራት) ምታሪ ቍራጭ፤ ብጣሽ ክፍል። መተሩ ሥጋሃ በበ ምታር። ወመተርዎ ለቅዱስ ኀበ ሠለስቱ ምታራት። ምታር ዐቢይ ፡ (ስንክ ፡ መስ፳፪ና ፡ ፳፱። ዮሴፍ)። ምታሮ የሥጋ ንፍሮ፤ ዝግን ሥቅሥቆ።
ምት [1] ፡ (ብ አምታት። ዕብ ማታህ፤ ምቲም) ባል ዕጮኛ፤ ሚስት ያለችው ወንድ ፥ ጕልማሳ። ሥሡ ንፉግ ቀናኢ ተማች ማለት ነው። ፡ (ተረት) ንጉሥ በመንግሥቱ ፥ ጕልማሳ በሚስቱ። በሸንጎ ቢረታ ፥ ከቤት ሚስቱን መታ። ርእሳ ለብእሲት ምታ። ምትኪ ዘንእስኪ። እንተ ባቲ ምት። አንትንሂ አንስት ተኰነና ለአምታቲክን ፡ (፩ቆሮ ፡ ፲፩ ፡ ፫። ኤር፫ ፡ ፬። ኢሳ፶፬ ፡ ፩። ፩ጴጥ ፡ ፫ ፡ ፩)።
[2]:-ባል ወንድ፤–መቲህ መትሀ።
ምትሀታዊ ፡ ምትሀታም፤ የምትሀት ሥራ፤ ኀላፊ ጠፊ አታላይ። ፡ (ኦ አንስት) ኅድጋ ስርጋዌ ወፍኖተ ምትሀታዊው ፡ (አፈ ፡ ተ፳፰)።
ምትሀት ፡ (ታት) መምታት፤ መመታት፤ አመታት። ምታት ፥ ምች፤ ቸነፈር፤ በትሩና መችው የማይታይ ኅቡእ ረቂቅ ሕማም ፥ መቅሠፍት
፡ (፪ነገ ፡ ፳፬ ፡ ፲፭–፲፯። ዘፀ፲፪ ፡ ፳፱ ፡ ፴)።
፡ በቁሙ፤ ሳይኾን የኾነ መስሎ ግዘፍ ነሥቶ መልክ ገዝቶ የሚታይ ነገር፤ እንደ ሕልምና እንደ ጥላ እንደ ስኒማ ያለ፤ ሰይጣናዊ ሐሰት፤ ወይም መልአካዊ እውነት። ራእየ ምትሀት ፀዋግ። ምትሀት አሕላም። ምትሀት ዓለማዊ። ምትሀተ ዐይን። እለ ምትሀተ የአምኑ ፡ (ጥበ፲፯ ፡ ፬። ፲፰ ፡ ፲፯። እለ ፡ ተ፳፰። ዕን፪ ፡ ፲፰። ቄር)። ይቤሉ አኀው፤ እስመ ሠለስቱ ሰይጣናት ቦኡ ኀበ ማር ወቅሪስ በአምሳለ ሠለስቱ ቀሳውስት
፡ (አርዮስና ንስጥሮስ መቅዶንዮስ) ወተዋቀሡ ምስሌሁ። ወመላእክተኒ ሖሩ በአምሳለ ዓለማውያን ኀበ ሊቀ በኣታት በእንተ በዓለ አስፈሬዳት ወኆጻ፤ ወኮኑ ይሰግዱ ለመስቀል ወይኤምኅዎ ወይጼልዩ። ቦኑ ኮነ ውእቱ ጥዩቀ፤ አው አልቦ። ይቤ መተርጕም፤ ወመላእክትሰ ኮኑ ይሰግዱ ወይኤምኁ ወይጼልዩ በርእሶሙ፤ በከመ ይጼልያ ወይኤምኃ ወይሰግዳ ነፍሳቲሆሙ ለፍጹማን ምስለ ሥጋቲሆሙ። ወሰይጣናትሰ ኮኑ ይገብሩ ውእተ በምትሀታቲሆሙ ሕስውት፤ እስመ አልቦሙ ሥልጣን ለሰይጣናት ከመ ይግበሩ ምትሀተ ዘበአማን ዘእምጠባይዕ በከመ ይገብሩ መላእክት
፡ (ፊልክ ፡ ፴፫)።
ምትረት ፡ መቍ(ቈ) ረጥ፤ አቈራረጥ ቈረጣ ቍርጠት። ምትረተ ርእስ። ምትረተ ተስፋ። ምትረተ ኅሊና ፡ (አዋል። ፊልክ ፡ ፶፬። ስንክ ፡ ጥቅ፩)። በስብረትና በንሥተት ፈንታ ምትረት ይላል ጥፋት ማለት ነው። ምትረተ ዖዛ። ምትረተ ዋራሲን ፡ (፩ዜና ፡ ፲፫ ፡ ፲፩። ፲፬ ፡ ፲፩)።
ምትቀት ፡ መጣፈጥ፤ ጥፍጥነት። ይቤልዋ ዕፀው ለበለስ ፥ ንዒ ንግሢ ላዕሌነ፤ ወትቤሎሙ በለስ ፥ እኅድግኑ ምትቀትየ ወፍሬየ ቡሩከ ወእንግሥ ላዕለ ዕፀው
፡ (መሳ፱ ፡ ፲ ፡ ፲፩)። መጻሕፍት ግን በጣፎች ስሕተት ያነንም ይኸንም ምጡቅ ምጥቀት ይላሉ፤ መምህራንም ሥሩን ስላላገኙት በምጡቅ ዘይቤ ይፈቱታል።
ምኑን ፡ (ናን ናት ንንት) የተናቀ፤ የተጠላ የረከሰ ፥ ከንቱ። ወራእዩ ምኑን። ምኑነ ረሰይክሙ ትእዛዝየ። ምኑናነ ኮነ በኀቤሁ
፡ (ኢሳ፶፫ ፡ ፫። ምሳ፩ ፡ ፳፭። ጥበ፪ ፡ ፲፪)።
ምናኔ ፡ በቁሙ፤ ፡ (ላ ጥ) መመነን መናቅ፤ ምነና ንቀት አናናቅ። ወሎቱ ምናኔ። ርኵስ ወምናኔ። እመ ሖረ በትምይንት ወምናኔ ፡ (ምሳ፲፰ ፡ ፲፫። ኩፋ ፡ ፳፩። ዲድ ፡ ፬)።
ምናን ፡ (ብ ምናናት። ጽር ምና። ዐረ መናን። ዕብ ማኔ። ሱር ማንያ) በቁሙ፤ የሚዛንና የገንዘብ ስም፤ አንዱ ምናን ፶ ሰቅል ነው፤ ፷ው ምናን ፩ መክሊት ይኾናል፤ የመክሊትን ፍች እይ ፡ (ሕዝ፵፭ ፡ ፲፪። ፫ነገ ፡ ፲ ፡ ፲፯። ሉቃ፲፱ ፡ ፲፫)። እሁብከ ሠለስተ ምእተ ምናናቱ ወርቅ፤ ወድልወቱ ሠለስቱ ምእት ምናናት
፡ (ዮሴፍ)።
ምኔት ፡ ምኔት፤ ፡ (ታት) ገዳም፤ ልዩ ክል ክልክል ፥ የመነኮሳት ሀገርና መንደር ከነቤተ ክሲያኑ። ሐነጸ ምኔተ ወአስተጋብአ አኀወ። ምኔታተ መነኮሳት። ሊቀ ምኔት። አበ ምኔት። እመ ምኔት ፡ (ፊልክ ፡ ፩። ገድ ፡ ተክ። ፍ ፡ ነ ፡ ፲)።
ምንኃል ፡ (ላት) መፍረሻ፤ ማፍረሻ። ወማኀፈደኪ ያንኅል በምንኃሊሁ ፡ (ሕዝ፳፮ ፡ ፱)።
ምንሃር [1] ፡ መስኖ፤–ንሂር ነሀረ።
[2] ፡ መንሀር፤ መስኖ ፥ የመስኖ ውሃ ከወንዝ ተከፍሎ በቦይ በመትረብ ወደ ተክል ወደርሻ የሚገባ። ወከመ ምንሃር ቦእኩ ውስተ ገነት። ሰላም ለከሣድከ ዘተመሰለ ምንሃረ በአንቅዖ ሐሊብ ወማይ አመ በመጥባሕት ተመትረ ፡ (ሢራ፳፬ ፡ ፴። ደራሲ)።
፡ አሰጅ ፥ እንግዴ ሥጋ ፥ ልጅ ከማሕፀን በወጣ ጊዜ ከደምና ከዛሕል ከርስሐት ጋራ ዐብሮ የሚወርድ። ሰይልን ተመልከት።
ምንሃብ ፡ (ባት) መሥሪያ ከውር አጉዶ ምድጃ፤ ወይም መሣሪያ ፋብሪቃ። ነሃቢ ዘይነብር ኀበ ምንሃብ። ጠሰ ምንሃብ። ዘከመ ያስተሣኒ ምብዓሎ ወምንሃቦ። ከመ እሳተ ምንሃብ ዘአርሰንዎ በብዙኅ ምብኳሕ ፡ (ሢራ፴፰ ፡ ፳፰። አርጋ ፡ ፫)።
ምንሣእ ፡ መንሾ መነሾ፤ መውሰጃ መቀበያ። ጕቦ ማማለጃ። አሌ ሎሙ ለመደልዋን እለ ያጸድቅዎ ለኃጥእ በእንተ ምንሣእ ፡ (ኪዳ)።
ምንሳዌ ፡ መጥፋት፤ አጠፋፍ፤ ፈተና ጥፋት ጕዳት። አሰረ ከመ በግዕ ዘአልቦ ምንሳዌ፤ መራዕየ ደብር ዘይቀትል አርዌ ፡ (ስንክ ፡ ኅዳ፰)።
ምንስው ፡ (ዋን ዋት ሱት) የተፈተነ ፍቱን፤ ደካማ ፥ ክፉ ጥፉ። ይሬስዮ ለመስተጋድል ምንስወ። ከመ ምንስዋን። ነፍስ ምንሱት ፣ ጸላእትየ ምንስዋን ፡ (ፊልክ ፡ ፸፱። ፪ቆሮ ፡ ፮ ፡ ፱። ዘዳ፳፰ ፡ ፷፭። መዝ ፡ ፲፯።
ምንቃህ ፡ (ሃት) መንቂያ፤ ማንቂያ።
ምንባር ፡ (ራት) መኖሪያ መቀመጫ፤ ቦታ ስፍራ ፥ ጉባኤ ሸንጎ አደባባይ። እግዚ ዘተናገረ ምስለ አቡነ አብርሃም በላዕለ ዕፀ ምንባር። ኰኵሕ ይበሊ በውስተ ምንባሩ። ኢይትሐወስ እንከ እምንባሩ። ምንባራተ ንዋየ ሐቅል። ሄሮድስ በንእሱ የሐውር ኀበ ምንባረ ማእምራን ከመ ይትመሀር እምኔሆሙ ፡ (ቅዳ ፡ ጎር። ኢዮ፲፬ ፡ ፲፰። ኢሳ፵፮ ፡ ፯። ፪ዜና ፡ ፴፪ ፡ ፳፯። ዮሴፍ)። በምንባር ፈንታ መንበር ይላል፤ አያሰኝም። መንበረ መስተሣልቃን
፡ (መዝ ፡ ፩)።
ምንባብ ፡ (ባት) ማንበቢያ ፥ የንባብ ቦታ። ምንባበ መጻሕፍት ይኩን እቱት ሕቀ እምሥዋዕ። መጻሕፍተ ምንባብ ፡ (ኪዳ። ቅዳ)።
፡ የንባብ መጽሐፍ። ግጽው ስንክሳር፤ ገድል ታምር፤ በየውስጡ ያለው ምዕራፉ ክፍሉ። ተፈጸመ ምንባብ ዘወርኀ ሠኔ። አርእስተ ምንባብ ዘይትነበብ ላዕለ ሙታን
፡ (ስንክ ፡ ሠኔ፴። ግንዘ)።
ምንታዊ ፡ መንታነት፤ ኹለትነት። ተዋሕዶ ያግሕሥ ኵነኔሁ ለምንታዌ። ኅጡአ ምንታዌ ክርስቶስ ፡ (ሃይ ፡ አበ። ደራሲ)። ሚመንታት፤ ኹለት ልብ መኾን።
ምንት [1] ፡ ዝኒ ከማሁ፤ ጥያቄና የጥያቄ ስም፤ የባሕርይንና የግብርን የተጸውዖን ስም የሚያስጠይቅ የሚያስመረምር፤ ስም ላለው ኹሉ ይነገራል። ፡ (ማነች ፥ ማናት) ምን ፥ ምንድር ን፤ ምኖች ምንድሮ(ኖ) ች። ምንት አነ። ምንት ሕዝብከ። ምንትከ እሙንቱ። ምንት ብየ ምስሌኪ። ምንት ዕፁ በኀበ ረከብክሙ ፡ (ኢዮ፬ ፡ ፳፬። ዮና፩ ፡ ፰። ዘፍ፴፫ ፡ ፭። ዮሐ፪ ፡ ፬። ዳን፩ ፡ ፶፰)። ሂ ኒ ትራስ ሲኾኑት ፥ ምንም ምን አንዳች ከቶ ያሰኛል። ባለቤት ሲኖር ቅጽል ፥ ሳይኖር በቂ ይኾናል። ኢታንሥኡ ምንተኒ ጾረ። ምንትኒ ሐሰት። ኢነኀድግ ወኢምንተኒ ፡ (ኤር ፡ ፲፯ ፡ ፳፩። ምሳ፳፬ ፡ ፳፫። ዘፀ፲ ፡ ፳፮)። መንተወን እይ፤ የዚህ ዲቃላ ነው።
[2] ፡ ምን ምንድር፤– መኑ መ ኑ።
ምንትው ፡ (ዋን ዋት ቱት) የመነታ ፥ መንታ የኾነ፤ መንታ የወለደ። ምንትወ ልደት። ምንትዋት
፡ (ደራሲ። ገድ ፡ ተክ)።
ምንትውና ፡ ዝኒ ከማሁ፤ መንታነት።
ምንዓው ፡ ማደኛ ፥ መታደኛ፤ ደን ዱር በረሓ። ምንዓወ ሀየላት
፡ (፩ነገ ፡ ፳፬ ፡ ፫)።
ምንኵስና ፡ በቁሙ፤ መነኵሴነት፤ መነኵሴ መኾን። ኢይፃኡ እምንኵስና። በጊዜ ምንኵስናሆሙ። እምድኅረ ምንኵስናሁ። ሥርዐተ ምንኵስና። ለብሰት አልባሰ ምንኵስና ፈ ፡ መ ፡ ፭ ፡ ፪። ፲፪ ፡ ፬። ፍ ፡ ነ ፡ ፲። ፊልክ ፡ ፩። ስንክ ፡ ጥቅ፩)።
ምንኵስናዊ ፡ የምንኵስና ግብር፤ አናዎር። ሕይወት ምንኵስናዊት ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፶፪)።
ምንዋኅ አው ምኗኅ ሙናኅ ፡ ምንዋኅ፤ አው ምኗኅ፤ ሙናኅ፤ ፡ (ዕብ ሙናሕ) ማረፊያ መጠጊያ፤ ስብሳብ የቤት ዙሪያ ፡ (ሕዝ፵፩ ፡ ፲፩)።
ምንዙሕ ፡ ምዙሕ፤–መዝሐ።
ምንዙዝ [1] ፡ የተሣቀየ፤–ነዚዝ ነዘ።
[2] ፡ ምንዙዝ፤ ፡ (ዛን ዛት ዝዝት) የተጨነቀ፤ በጥኑ መከራ የተያዘ፤ የተጠላ የተነቀፈ። ይድኀኑ ምንዱባን ወያዕርፉ ምንዙዛን። ወኅሩያንየሂ ምንዙዛን በቅድሜሆሙ ፡ (ቅዳ ፡ ዮሐ። ኪዳ)።
ምንዛህ ፡ (ሃት) መርጫ፤ መረጫ። ምንዛሀ ደም። ማየ ምንዛህ ፡ (አርጋ። መጽ ፡ ምስ)።
ምንዱብ ፡ (ባን ባት ድብት) በቁሙ፤ የተጨነቀ የተጠበበ፤ ከተያዘበት ጭንቅ መውጫ ማምለጫ ያጣ ፥ ድኻ ችጕር። ኵሉ ምንዱብ። ምንዱበ ይነብር። ረዳኤ ምንዱባን። ነፍስ ምንድብት ወጥውቅት
፡ (፩ነገ ፡ ፳፪ ፡ ፪። ሢራ፴፮ ፡ ፴። ቅዳ ፡ መስተ)።
ምንዳቤ [1] ፡ በቁሙ ፥ ጭንቅ፤–ነዲብ ነደበ።
[2] ፡ (ያት) ጭንቅ ጥብ፤ ዐጸባ ችግር፤ መከራ ሥቃይ። ሀሎኩ ምስሌሁ አመ ምንዳቤሁ። ዕለተ ሕማም ወምንዳቤ። ተጻፈቁ ቦቱ ምንዳቤያት ብዙኃት ፡ (መዝ ፡ ፺። ሶፎ፩ ፡ ፲፭። አፈ
፡ ድ፳፮)።
ምንዳኣዊ ፡ ምንደኛ ፥ ባለምንዳ፤ እረኛ ሎሌ ፥ በሰጡኝ ዐርስ።
ምንዳእ ፡ (ኣት) መንጃ መነጃ በትር ጅራፍ መንገድ። በቁሙ ፥ ምንዳ፤ የረኛ ዋጋ ፥ ደመ ወዝ፤ ኖል ዐስበ ኖላዊ፤ ለገበሬም ይኾናል፤ ሲያርስ በሮች እየነዳ ነውና።
ምንዳድ ፡ መንደጃ ፥ ማንደጃ፤ የእሳት ቦታ እቶን ምድጃ። ወደይዎሙ ውስተ ምንዳደ እሳት ወአውዐይዎሙ። ኢይደልዎ ለአሐዱ ከመ ይግበር እቶነ አው ምንዳደ ብለኔ ኀበ ገቦ ሐጹር በዘይነክያ እሳቱ
፡ (ስንክ ፡ ኅዳ፳፪። ታኅ፭። የካ፲፫። ሠኔ፯። ፍ ፡ ነ ፡ ፴፯)።
ምንዳፍ ፡ (ፋት) መንደፊያ፤ መወርወሪያ ቦታ ፍላጻው ተነድፎ የሚያርፍበት። መጠነ አሐቲ ምንዳፈ ሐጽ
፡ (ኩፋ ፡ ፲፯። ዘፍ፳፩ ፡ ፲፮)።
ምንግላግ ፡ (ጋት) መሰብሰቢያ መከማቻ፤ ቦታ። ምንግላጊሆሙ ለኢሎፍሊ ፡ (፩ነገ ፡ ፲ ፡ ፭። ዮዲ፮ ፡ ፲፮)።
ምንጣብ ፡ መንጠቢያ፤ ማንጠቢያ።
ምንጽርና ፡ አንጻርነት፤ ተነጻጻሪነት ፥ ወደረኛነት ባላጋራነት። ወንሕነኒ ንትመየጦሙ በተስእሎ ውስተ ምንጽርና ፡ (ቄር ፡ ጰላ)።
ምንፋኅ ፡ (ኃት) መንፊያ ማናፊያ ፥ እፍ እፍ መባያ፤ አፍ ወናፍ ትንፋሽ።
ምዑዕ ፡ (ዓን ዓት ዕዕት) የተቈጣ ፥ ቍጡ ብስጩ፤ ተናዳጅ ጠበኛ። መፍትው ትትዐገሥዎሙ ለምዑዓን። ወገብረ ሰላመ ማእከለ ምዑዓን ፡ (ዲድ ፡ ፲። ፊልክ
፡ ፶፩)።
ምኡክ ፡ (ካን ካት እክት) ቍጡ ፥ ዐይነ ደረቅ፤ አፍጣጭ ገላማጭ። ርኩስ በኀበ እግዚ ምኡክ ዐይን። ኅብአኒ እምልሳን ድሩክ ወእምዐይን ምኡክ ፡ (ምሳ፳፯ ፡ ፳። ስንክ ፡ ኅዳ፭)።
ምዑዝ ፡ (ዛን ዛት ዕዝት) የሸተተ፤ የተሸተተ፤ የጣፈጠ ፥ የተጣፈጠ። ሽቱ የተቀባ ፥ ቅቡዕ። ዕፍረት ምዑዝ። ዘምዑዝ ጼናሁ። ጽጌ ገነት ምዕዝት። ዕፀዊሃ ምዑዛን
፡ (ቅዳ። ዮሴፍ። ፈላስ። ድጓ)። ሐዋዝ በማለት ፈንታ ወዝንቱ ምዑዝ ለመትልወ ወይን ይላል፤ ስሕተት ነው
፡ (ምሳ፲፪ ፡ ፲፩) በዕብራይስጥ ግን ዝንቱና ምዑዝ የለም፤ ለመትልወ ወይን ያለውም ፡ (ምራዴፍ ፊቂም) ዘይዴግን ከንቶ ነው እንጂ ፥ ወይን አያሰኝም።
ምዑድ ፡ (ዳን ዳት ዕድ) የተማረ የተመከረ፤ ምክር የገባው።
ምዒር ሮት ፡ (ምዕረ፤ መዐረ ይምዕር ይምዐር። ዐረ መረ) ፈጥኖ ማለፍ፤ መር ቸር ማለት ጊዜ ብቻ፤ ለማለፍና ለመሻገር። መጣፈጥ መምተቅ፤ ጥፍጥ መኾን ለጊዜው፤ አፍን ዐልፎ ከጕረሮ እስኪወርድ። ምስጢሩ ጊዜን አይለቅም። መርዐን እይ፤ የዚህ ጎር ነው።
ምዒዕ ዖት ፡ (መዕዐ ይምዕዕ ይምዐዕ። መዐወ፤ ማዑት) መቈጣት ፥ መበሳጨት፤ ማዘን ፥
መናደድ፤ ከልብ ካንዠት። ምዒውና ምዒዕ ሱቱፋን ናቸው። ፡ (ተረት) ካንዠት ካዘኑ እንብ አይጠፋም። መጽሐፍ ግን በመዕዐ ፈንታ ተምዐ ተምዕዐ ይላል፤ ስሕተት ነው። ባለቅኔዎችም ተምዐን ተቈጣ ፥ ተምዕዐን ተበሳጨ ብለው ብቻ ብቻውን ይገሱታል። ተምዐ እግዚ ዐቢየ መዐተ። ሶበ ትትመዐዕ ተዘከር ዕለተ ሞትከ። ወሶበ አነ ተማዕኩ
ኅዳጠ። ተምዒዐከ ፡ (ኢሳ፭ ፡ ፳፭። ሢራ፲፰ ፡ ፳፬። ዘካ፩ ፡ ፲፭። መዝ ፡
፳፮)።
ምዒዝ ዞት ፡ (ምዕዘ ይምዕዝ ይምዐዝ) መሽተት፤ መልካም ሽታ መስጠት፤ ላፍንጫ መጣፈጥ ፥ ጥሩ ሽቱ መኾን። ዘይምዕዝ እምኵሉ መዐዛ። ጸጌ ዘሠናየ መዐዛ ይምዕዝ። ቤተ ክር እንተ ትምዕዝ ቆዐ ጽጌ ዘዕፀ ወይን ፡ (ሔኖ፳፬ ፡ ፬። አንቀ ፡ ብር። ተረ ፡ ቄር ፡ ኤጲ፲፮)። ዐዘዘን እይ፤ የዚህ ጎር ነው፤ በመዐዛው የዕዘዝ ምስጢር አለበት።
ምዒድ ዶት ፡ (መዐደ፤ አው ምዕደ ይምዕድ ይምዐድ። ዕብ ያዐድ፤ መከረ። ሀምዔድ፤ አሰናከለ) መምከር ማስተማር፤ አብዝቶ መላልሶ ምክር መስጠት፤ ክፉውን ምክር በምክር መለወጥ፤ ማፍረስ ማሰናከል። መከረ ለክፉም ለበጎም ይኾናል፤ መዐደ ግን ለበጎ ብቻ ነው። መዐድዎ ለዘጌገየ ከመ ይኅድግ ኪያሃ ፍኖተ። ይምዐድዎሙ ወይግበሩ ንስሓ። እግዚ መዐዶ ለሰበእ ከመ ኢይዕልዎ። መዐደነ ነገረ ሕይወት። ምሂር ወምዒድ ፡ (ቅዳ ፡ አት። ፍ ፡ ነ ፡ ፵፮። ዮሴፍ። ገድ
፡ ተክ። አርጋ)።
ምእኃዝ ፡ (ዛት) መያያዣ፤ ቅርብ አጠገብ፤ ወሰን ደንበር፤ አፍዛዣ አንጻር። እስከ ምእኃዘ ኤዶም። ምእኃዘ ጎልጎል
፡ (ዘኍ፴፬ ፡ ፫። ዘዳ፲፩ ፡ ፴)። ዐይን ሙሓዝ በማለት ፈንታ ምእኃዝ ይላል ስሕተት ነው ፡ (፫ነገ ፡ ፩
፡ ፱)።
ምእሕዲት ፡ አንድ ዕጥፍ፤ አንድ እጅ፤ አንድ ክፍል።
ምእላድ (ዳት) [1] ፡ ማከማቻ፤ መከማቻ፤ መሰብሰቢያ ቦታ
፡ (ዘፍ፩ ፡ ፱)። ምእላዲሆሙ ለማያት። ምእላዳት። ወምእላደ ገበርክሙ ማእከለ ክልኤቱ አረፍት ፡ (ቄድር። ቀሌ። ኢሳ፳፪ ፡ ፲፩)።
[2] ፡ በቁሙ፤ የመጽሐፍ ስም፤ ዐጭር ቍርጭኝ ቅድ፤ ቃሉ ከብዙ መጻሕፍት ተለቅሞ ለብቻው የተጣፈ መጣፍ እንደ ፍትሐ ነገሥት እንደ ሃይማኖተ አበው ያለ፤ ከዚያም የሚያንስ ሥነ ፍጥረትን አዕማደ ምስጢርን የመሰለ፤ በቅርብ የሚገኝ የክርስቲያን ትምርት።
[3] ፡ ተጨማሪ ፊደል፤ ትራስ እየኾነ በመጨረሻ ቃል የሚገባ፤ ወንድና ሴት አንድና ብዙ የሚለይበት። እሊሁም አራት ናቸው፤ ት ናን ዊው ዩያይ፤ አገባባቸውን በየፊደላቸው ተመልከት።
ምእልፊት ፡ የእልፍ እልፍ፤ እልፍ ጊዜ እልፍ፤ ወይም መቶ እልፍ ጊዜ ሺሕ
፡ (እእ – ፻፻፻፻) መቶ ሚልዮን። ምእልፊተ አእላፍ። ምእልፊተ ትቀሥፍ ፡ (መዝ ፡ ፷፯። ጥበ፲፪ ፡ ፳፪)። ዳግመኛም በማሸጋሸግ ፥ ትእልፊታት ብሎ መቶ ሚልዮን፤ ምእልፊት ብሎ ሺሕ ሚልዮን፤ ምእልፊታት ብሎ እልፍ ሚልዮን ያሰኛል። ከእልፍ በላይ ያለ ቍጥር በውሳኔም ያለውሳኔም ይነገራል፤ ውሳኔው ይህ የተጻፈው ነው። ያለውሳኔ ግን ሲነገር፤ እልፍ አእላፍ፤ አእላፈ አእላፋት ወትእልፊተ አእላፋት ምእልፊት ይላል
፡ (አዋል)። ብዛቱ እንዳሸዋና እንደ ኮከብ ያለ፤ ሰፍሮ ቈጥሮ ሊያውቁችት የማይቻል፤ ስፍር ቍጥር ልክ መጠን የሌለው የብዙ ብዙ ማለት ነው ፡ (ዘፍ፲፫ ፡ ፲፮። ፲፭ ፡ ፭)። ረበዋትን እይ፤ ረቢብ ረበ፤ ረበበ።
ምእመን ማእምን ፡ (ንት ናት ናት) በቁሙ፤ ያመነ አማኒ፤ የታመነ እሙን፤ እውነተኛ ክርስቲያን፤ ማመኛ መታመኛ እግዜር፤ ዘመድ ወዳጅ ባልንጀር፤ የማይጠረጠር። ይትአመን ከመ ውእቱ ምእመን በአብ ወበወልድ ወበመንፈስ ቅዱስ። ብእሲት ማእምንት። ዘምእመን በስምከ። ምእመናን ወምእመናት። ዕደው ምእመናን በኀይሎሙ። አዋልድ ምእመናት። ውእቱ ምእመኑ። ወይከውኖ ምእመነ ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፫። ፳፬ ፡ ፭። ግንዘ። ቅዳ። ዮዲ፪ ፡ ፭። ኢሳ፴፪ ፡ ፱። ሢራ፴፩ ፡ ፲፰። ፴፮ ፡ ፫። መዝ ፡ ፲፯)።
ምእማር ፡ ማመልከቻ፤ መመልከቻ፤ ታምራት ምልክት ማድረጊያ፤ ቦታ መሣሪያ።
ምዕማድ ፡ (ዳት፤ መዓምድ) ማቆሚያ፤ የዐምድ እግር፤ ስክተት፤ መሠረት። ሰመንቱ አዕማድ፤ ወምዕማዶሙኒ ዘብሩር ዐሠርቱ ወስድስቱ፤ ወለለ አሐዱ ዐምድ በበ ክልኤ ምዕማዲሁ። ወበእንተ ዝ ፈቀደ ያስተጻንዕ ምዕማዲሁ ፡ (ዘፀ፳፮ ፡ ፳፭። አፈ ፡ ድ፫)።
ምዕስብና ፡ ግልሙትና፤ ፈትነት፤ ብቻነት። ኢይክሉ ምዕስብና። ከመ ሕማማተ ዘምዕስብና ይጠይቅ ፡ (ቀኖ ፡ ስርድ። ኪዳ። ቄድር)።
ምዕራብ ፡ (ዕብ ማዐራብ) ዝኒ ከማሁ፤ በቁሙ። ፀሓይኒ አእመረ ምዕራቢሁ። ምዕራበ ፀሓይ። ኮከበ ምዕራብ ፡ (መዝ ፡ ፻፫። ኢሳ፱ ፡ ፲፪። ስንክ ፡ የካ፪)።
ምዕራግ ፡ (ጋት) ዳገት፤ ዐቀበት፤ የተራራ መንገድ፤ ሽቅብ የሚወስድ። ምዕራገ ሀገር። እንተ ምዕራጋት እስመ አልቦ ምዕራግ ለአድባሆሙ
፡ (፪ዜና ፡ ፴፪
፡ ፭። ፩ዜና ፡ ፳፮ ፡ ፲፮። ዮዲ፯ ፡ ፲)።
፡ ታላቅ መሰላል፤ ባለሦስት ባላራት እግር፤ ብቻውን የሚቆም። ኦ ምዕራግ እምድር እስከ ሰማይ ፡ (ቅዳ ፡ ሕር)።
ምዕራፊት ፡ (ምዕፋሪት ማዕፈሪት፤ ዐፈረ) ሐሜለት፤ በርኖስ፤ የላይ ልብስ። ኤልሳዕ ሶበ ወረወ ላዕሌሁ ምዕራፊቶ ኤልያስ ኀደገ ዓለመ ወተለዎ ፡ (ፊልክ ፡ ፭። ፫ነገ ፡ ፲፱ ፡ ፲፫)። ዕራፊ ማለት ከዚሀ ወጥቷል።
ምዕራፍ (ፋት) [1] ፡ ማረፊያ፤ ማሳረፊያ፤ መኖሪያ፤ መቀመጫ፤ ቦታ ሰፈር። ወይከውን ክቡረ ምዕራፊሁ። ይእኅዝ ጽድቅ ምዕራፈ። ዛቲ ይእቲ ምዕራፍየ። ከመ ንኩን ምዕራፈ ስሙ ለሥሉስ ፡ (ኢሳ፲፩ ፡ ፲። ፴፪
፡ ፲፯። መዝ ፡ ፻፴፩። ቀሌ። ዘኍ፲
፡ ፴፫)።
፡ ገበዋተ መንበር፤ ክንድ የሚያርፍበት፤ የሚደገፍበት። ክልኤቱ ምዕራፈ መዛርዕ
፡ (፪ዜና ፡ ፱ ፡ ፲፰)።
[2] ፡ (ጽር ስታዲዎን። ዕብ ሪስ) የምድር ልክ፤ የርሕቀት መስፈሪያ፤ ፍላጻ ተነድፎ ደንጊያ ተወንጭፎ የሚያርፍበት፤ የፈረስ አፍታ የጕልማሳ ሩጫ፤ እስኪደክመው ቃታ እስኪይዘው የሚሮጥበት፤ ሴትና ወንድ የሚለይበት። በመትር ፻፹፬፤ በክንድ ፫፻፷፰ ይኾናል ይላሉ፤ ፬፻ ክንድ የሚሉም አሉ። ሀገር እንተ ርሕቅት እምኢየሩሳሌም መጠነ ስሳ ምዕራፍ። መጠነ ዕሥራ ወኀምስቱ ምዕራፍ አው ሠላሳ ፡ (ሉቃ፳፬ ፡ ፲፫። ዮሐ፮ ፡ ፲፱። ፲፩ ፡ ፲፰። ራእ፲፬ ፡ ፳)።
[3] ፡ (ጽር ሚሊዎን። ዕብ ሚል) ዝኒ ከማሁ፤ ታላቅ መስፈሪያ፤ ዐይነ ገመድ፤ ሺሕ መትር፤ ወይም ኹለት ሺሕ ክንድ። ወለዘሂ ዐበጠከ አሐደ ምዕራፈ፤ ሑር ምስሌሁ ክልኤተ። መጠነ ክልኤቱ ምዕራፍ። ወመጠነ ውእቱ ቅጽር አርብዓ ወኀምስቱ ምዕራፍ። ወኮነት በኣቱ ርሕቅተ መጠነ ዐሠርቱ ምዕራፍ ፡ (ማቴ፭ ፡ ፵፩። ገድ ፡ ተክ። ዮሴፍ። ፊልክ ፡ ፶፭)።
[4] ፡ (ዕብ ፌሬቅ) የመጽሐፍ ክፍል፤ አንቀጽ፤ በውስጡ ብዙ ቃል ያለበት። ኢትሌቡ እሎንተ ምዕራፋተ። ወከመ ዝ ገብረ ውስተ ብዙኅ ምዕራፍት ፡ (አፈ ፡ ተ፬። ድ፰)። ከነጥብ እስከ ነጥብ ያለውም።=። አንዳንዱ ቍጥር ንኡስ ምዕራፍ፤ ሠረዝ ደግሞ፤ የንኡስ ንኡስ ይባላል።
ምእር ፡ አንድ ጊዜ፤–ምዕር።
ምዕር ፡ (ብ ምዕራት፤ የብ ብ ምዕራታት። ዐረ መረት) ፩ ጊዜ ፥ ፊት መዠመሪያ፤ ጥቂት ጊዜ፤ ደቂቃ ቅጽበት፤ ቶሎ አኹን፤ ድንገት ወዲያው። ምዕረ ለለ ዓመት። ንጠይቅ ምዕረ። ምዕረ ወካዕበ። ብላዕ ወስተይ ምዕረ ወተፈሣሕ። ኵሉ ፍጡን በኀበ እግዜ ለእንተ ምዕር። ተኀባእ ኅዳጠ ምዕረ። ወይከውን በጊዜሃ ለምዕር። ይጢስ ምዕረ፤ አኹን ፡ (ዘፀ፴ ፡ ፲። ዮዲ፭ ፡ ፳። ቲቶ፫ ፡ ፲። ጦቢ፯ ፡ ፲። ሢራ፲፰ ፡ ፳፮። ኢሳ፳፮ ፡ ፳። ፳፱ ፡ ፭። ፩ነገ ፡ ፪ ፡ ፲፮)። በበ ምዕር። ምዕራተ ብዙኃተ። ምዕራትት ፡ (ኢያ፮ ፡ ፫። ፈ ፡ መ ፡ ፲፬ ፡ ፲። ፊልክ ፡ ፹፭)።
ምዕርዕርና ፡ ምዕርዕርና፤ ማርነት ጥፍጥነት፤ ማር ማር ማለት መጣፈጥ። ጣዕመ ምዕርዕርናከ ፡ (ጥበ፲፮ ፡ ፳፩)።
ምዕቃል ፡ (ላት) ኵሬ፤ የውሃ መቋሚያ፤ መጠራቀሚያ፤ ባታክልት ውስጥ፤ በቦይ በቦምባ ጫፍ፤ ወይም በዱር በበረሓ ያለ፤ ታናሽ ባሕር፤ መዋኛ መታጠቢያ። ሐነጸ ምዕቃለ ማይ። ለእመ አብሐከ አሐዱ ከመ ታስቲ እምዕቃለ ዚኣሁ። ኵሎ ምዕቃላተ ፡ (ሢራ፵፰ ፡ ፲፯። ፍ ፡ ነ ፡ ፴፯። ኩፋ ፡ ፪። መክ፪ ፡ ፮። ማሕ፭ ፡ ፲፪። ፯ ፡ ፭)።
ምዕቅብና ፡ ዐደራ፤ ጥበቃ፤ ምጥንታ። በእንተ ምዕቅብና ንዋይ። ወይእቲ እኅተ አቡየ በምዕቅብና ፡ (ፍ ፡ ነ
፡ ፳፱። ፳፬ ፡ ፪)።
ምእታው ፡ (ዋት) መግቢያ፤ ማግቢያ፤ መመለሻ፤ መምጫ፤ ቤት አገር። ከመ ይኩን ምእታዊክሙ ኀበ መላእክት። ምእታዊሆሙ ውስተ ፈለገ ሲኦል። ወምእታዉሰ አርማቴም። ምእታወ አፍራሲሁ እምነ ግብጽ
፡ (ሄርማ። ቀሌ። ፩ነገ ፡ ፯ ፡ ፲፯። ፫ነገ ፡ ፲ ፡ ፳፰)።
ምእት ፡ (ዕብ ሜኣ። ሱር ማኣ። ዐረ ሚአት) የቍጥር ስም ፥ መቶ፤ ዐሥር ጊዜ ዐሥር፤ ወይም መቶ ጊዜ አንድ። ምእት ክረምት። ምእት አባግዕ። ኀረዩ ምእተ ብእሴ ፡ (ሢራ፲፰ ፡ ፱። ዘፍ፴፫ ፡ ፲፱። ዮዲ፲ ፡ ፲፯። ከክልኤቱ እስከ እልፍ ተስዓ ወተስዐቱ ምእት እያለ በቅጽል ይዘምታል።
ምዕትዝላ ፡ (ዐረ እልመተዚለት) ሊሉያን፤ ፍለጣን። በባህል በትምርት ከፈሪሳውያን ተለይተው ለብቻቸው ማኅበር ያቆሙ ከስምንቱ ክፍል ቤተ አይሁድ አንዱ። ባለሐዲሶች ግን እልመተዕላን ይሏቸዋል ፡ (ዮሴፍ ፡ ገ፫፻)።
ምእናም ፡ መሥሪያ ቦታ፤ የሸማኔ ጕድጓድ፤ ዐርብ። ግብረ ምእናም። ማርያም ምእናም ግሩም። ምእናም አንቲ ዘእምኔኪ ለብሰ
፡ (አፈ ፡ ድ፪። ተረ ፡ ቄር፲፰። ቅዳ)።
ምእኖ አው ማእኖ ፡ ዐዛባ ፥ ጭቃ፤ ማጥ ረግረግ። አሕርው ዘውስተ ጽቡረ ማእኖ ያንገረግሩ ፡ (መጽ ፡ ምስ)።
ምእከት ፡ መቈጣት መዛት፤ መቃጣት ማስፈራራት።
ምዕዋን ፡ (ናት) ሰሜን ፥ ግራ፤ የደቡብ አንጻር። መንገለ ምዕዋን። መንጸረ ምዕዋን ፡ (ዘፀ፳፮ ፡ ፴፭። ፳፯ ፡ ፲፩)። ባለብሉዮች ግን መስዕ ይሉታል፤ የመስዕን ፍች እይ። ዳግመኛም በደቡብ ፈንታ ምዕዋን ይላል፤ ስሕተት ነው። ገጸ ምዕዋን ፡ (ዘፀ፳፮ ፡ ፲፰)።
ምዕዋድ ፡ (ዳት) ዝኒ ከማሁ፤ ዙሪያ ክበብ። መክበቢያ፤ መከበቢያ፤ መዞሪያ ማወጃ ቦታ፤ ወይም መዝሙር እያወዱ የሚዘምሩት። ምዕዋደ ቅጽራ እምአንቀጽ ለአንቀጽ። ሠናይ ምዕዋደ ቀስት። ወአዖደኒ ውስቴቶሙ ምዕዋዳተ። መዝሙር ዘምዕዋድ
፡ (ዮና፫ ፡ ፫። ጥበ፭ ፡ ፳፪። ሕዝ፴፯ ፡ ፪። ድጓ)።
ምእዙን ፡ (ናን ናት ዝንት) የተማዘነ፤ አራት ገጽ ያለው፤ ባላራት ማእዝን።
ምዕዛር [1] ፡
የብርሃን ጮራ፤–ዐዚር ዐዘረ።
[2] ፡ (ራት) የብርሃን ወንፊት፤ ብርሃን የሚነዛበት፤ ብሱ ነዳላው። ወክነፊሁ ዘምዕዛረ ፀሓይ ፡ (መጽ
፡ ምስ)። ያቡሻህር የመርሐ ዕዉር የሔኖክና የቍጥር መምራን ለፀሓይ ፭፻፲፭፤ ለጨረቃ ፻፭ ምዕዛር አላቸው ይላሉ። «የትርጓሜያቸውም ምክንያት፤ ንባቡ ምስጢሩ፤ ሥሩ አነጋገሩ ይህ ነው ፡ (ዘፍ፩ ፡ ፲፮)። ሙሴ፤ ወገብረ እግዚአብሔር ክልኤተ ብርሃናተ ዐበይተ፤ ዘየዐቢ ብርሃን ከመ ይምልክ መዓልተ፤ ወዘይንእስ ብርሃን ከመ ይምልክ ሌሊተ፤ ምስለ ከዋክብት ያለውን። ቅዱስ ጳውሎስ፤ ካልእ ክብሩ ለፀሓይ፤ ወካልእ ክብሩ ለወርኅ፤ ወካልእ ክብሮሙ ለከዋክብት ብሎ ነገረን ፡ (፩ቆሮ ፡ ፲፭ ፡ ፵፩)። ሊቃውንትም በቅዳሴያቸው፤ ወአመ ፈጠረ ፀሓየ ወወርኀ አኮ ከመ ያብርሁ ሎቱ ከመ ዘጸልሞ፤ አላ ጸገዎሙ ንስቲተ እምዘዚኣሁ ብርሃን፤ መጠነ ኅጠተ ሥርናይ፤ ወበእንት ዝ አብርሁ ዲበ ሰብእ ብለው አስተማሩን ፡ (ቅዳ ፡ ግሩ)። ይህነንም መጠነ ኅጠተ ሥርናይ የተባለውን ብርሃን፤ ከሺሕ መጠን ይከፍሉታል። ከዚህም ከሺሑ ፭፻፺፭ቱኡ ለፀሓይ ይደርሳታል በምዕዛሯ ልክ፤ ፬፻፭ ይተርፋል። ከዚህ ደግሞ ፻፭ቱ ለጨረቃ፤ ፻ው ለከዋክብት፤ ፻ው ለደመናት፤ ፻ው ለቀላያት ይደርሳቸዋል። ይህም ለፀሓይ የሚደርሳት፤ ፭፻፺፭ቱ በ፺፰ ቢቀምሩት ፮ ክፍል ኹኖ ፯ ይተርፋል፤ ይህም ፮ቱ ክፍል ከነግህ እስከ ቀትር በየሰዓቱ ይሰጣታል። እንዲህ ማለት የምዕዛሯን መክፈት መዘጋት መናገር ነው፤ ፯ቱ ምዕዛሮች ግን መቼም መች አይዘጉም። ከ፮ ሰዓት በኋላ ፺፰ቱ ይዘጋል፤ እስከ ፮ ሰዓት ኹሉም ፈጽሞ ይዘጋል። ባንድ ዕለት ስድስት ተውሳክ፤ ስድስት ሕጸጽ አላት። ለጨረቃ ይደርሳታል ያልነው ፻፭ቱ ደግሞ ፲፭ ሱባዔ ይኾናል፤ ይህም ከዕለተ ሠርቅ እስከ ዕለተ ገሀህ በየዕለቱ ይሰጣታል። ካ፲፭ ቀን በኋላ በየዕለቱ ፯ ፯ እጅ ይነሣታል፤ እስካ፲፭ ቀን። እንዲህ ማለት የምዕዛሯን መክፈት መዘጋት መናገር ነው እንጂ፤ ከአፍኣ የሚሰጣት ሌላ ብርሃን አለ ማለት አይዶለም። ለፀሓይ ምዕዛር እንዳላት፤ ለጨረቃም አላት ብለው ይተረጕማሉ»።
[3] ፡ (ዕብ አሖር) ድኅር፤ ኋላ ዠርባ። ትሬኢ ምዕዛርየ፤ ወገጽየሰ ኢያስተርኢ ለከ ፡ (ዘፀ፴፫ ፡ ፳፫)።
ምዕያም ፡ (ማት) በረት፤ ጎል፤ ምስሓግ፤ ብዙ መንጋ የሚያድርበት፤ የሚመሰግበት። አይቴ ኀለፈት እምዕያማ ማርያም ጣዕዋ ፡ (ደራሲ። ሔኖ፹፮ ፡ ፪)።
ምዕደት ፡ መምከር ፥ መመከር ፥ አመካከር፤ መካሪነት ፥ ተመካሪነት።
ምዕዳን ፡ (ናት) ምክር ተግሣጽ፤ ስብከት ትምርት፤ መንፈሳዊ ጨዎት። ሰሚዐ ነገረ ምዕዳን። ቃለ ምዕዳን። ምዕዳነ ጽድቅክሙ በሊኅ። ኢይመይጦን ለአልባቢክሙ ምዕዳን እምግዘፊሆን። መጻሕፍተ ምዕዳናት
፡ (ፊልክ ፡ ፵፮። ፍ ፡ ነ ፡ ፵፰። ስንክ ፡ ሠኔ፲፮። ዮሴፍ። ገድ ፡ ኪሮ። አፈ ፡ ድ፲)።
ምዕዳው ፡ (ዋት) መሻገሪያ፤ ሜዴ መልካ፤ ድልድይ፤ ታንኳ። አልብየ ምዕዳው ዘእንበለ በተንከተመ ሃይማኖት። ማርያም ምዕዳው እምሠርም፤ ዘጽድቅ ተንከተም ፡ (መጽ ፡ ምስ። ደራሲ)።
ምዕጣን ፡ ማጠኛ፤ ማጤሻ፤ ቦታ። ምሥዋዕ ዘምዕጣን
፡ (ዘሌ፬ ፡ ፯)።
ምኩሕ ፡ (ሓን ሓት ክሕት) በቁሙ፤ መካሕ፤ የተመካ ትምክሕተኛ፤ ተመኪና አስመኪ መመኪያ የኾነ፤ ክቡር ምስጉን። አልባሰ ክህነት ምኩሕ። አልባስ ክቡራት ወምኩሓት ፡ (ስንክ ፡ ጥቅ፱። አፈ ፡ ተ፳፰)።
ምኵሳሕ ፤ መኵሻ ፥ ኵስ መጣያ ፥ ዐዘቅት ዕዳሪ። ዐጸደ ምኵሳሕ (መጽ ፡
ምስ)።
ምኵስታር ፡ (ራት) መጥረጊያ ፥ መጠራረጊያ የጕድፍ መሣሪያ። ወይልሕሱ ምኵስታረ ቤት
፡ (አዋል)።
ምኵራብ ፡ (ብ ምኵራባት፤ መኳርብት) ታላቅ ሕንጻ ተራራ ኰረብታ የሚያኽል፤ መስጊድ ቤተ ጣዖት፤ የአደሁድ መቅደስ ቤተ ጸሎት፤ ጉባኤያቸውና ማኅበራቸው። ምኵራበ አይሁድ ወአረሚ። ሐነጸ ምኵራበ ዐቢየ ለዙሐል። ምኵራበ አማልክት። ወዐርጉ ምኵራበ ጴጥሮስ ወዮሐንስ። ሕፄሃ ለመርዓትከ ወኅዳጋቲሃ ለእንተ ኀደጋ ምኵራብ ፡ (ቀሌ። ዮሴፍ። ስንክ ፡ መጋ፳፰። ግብ፫ ፡ ፩ ፡ ፪ ፡ ፫። ቅዳ ፡ ዮሐ)። የዐወይዉ በምኵራባቲሆሙ። በመኳርብት ወበአስኳት ፡ (ዓሞቿ፰ ፡ ፫። ማቴ፮ ፡ ፪። ግብ፲፭ ፡ ፳፩)።
ምኩር [1] ፡ (ራን ራት ክርት) የተመከረ፤ ዕድሜና መጣፍ መከራ ፥ ወይም ባልንጀራ የመከረው።
[2] ፡ ምኩር፤ የተሞከረ ሙክር፤ ፍቱን። ምኩር በኵሉ ፡ (ዕብ፬ ፡ ፲፭። ዲድ ፡ ፬። ፍ ፡ ነ ፡ ፲)።
ምኵናን ፡ (ናት) መፍረጃ፤ ሸንጎ አደባባይ፤ የፍርድ የቅጣት ቦታ። ግሩም ዐውደ ምኵናንከ። መዋቅሕትየ በኀበ ኵሉ ምኵናን። በእንተ ሰማዕታት እለ ይወስድዎሙ ኀበ ምኵናን ፡ (ቀሌ። ፊልጵ፩ ፡ ፲፫። ዲድ ፡ ፳፭)።
፡ ግዛት ሥልጣን ጌትነት፤ የጌትነት ስፍራ። ደወለ ምኵናኑ። ምኵናነ ሄሮድስ። ተውህበ ሎቱ ምኵናን፤ ወምኵናኑኒ ምኵናን ዘለዓለም በኢየሩሳሌም ምኵናንየ፤ ኀበ አኰነኒ ፡ (፪ነገ ፡ ፬ ፡ ፪። ሉቃ ፡ ፳፫ ፡ ፯። ዳን፯ ፡ ፲፬። ሢራ፳፬ ፡ ፲፩)።
ምክሕ ፡ መመኪያ፤ ትምክሕት፤ ክብር ምስጋና፤ ሞገስ ልዕልና፤ ጌጥ ሽልማት፤ የሚያስመካ ነገር ማናቸውም ኹሉ። ኢይከውነከ ምክሐ። በፍርሀተ እግዚ ይኩን ምክሕከ። ምክሖሙ ፈሪሀ እግዚ። ይከውኖ ምክሐ በኀበ ማኅፈሩ። አክሊለ ምክሕ ፡ (ሢራ፫ ፡ ፲። ፯ ፡ ፲፮። ፳፭ ፡ ፮። ፴ ፡ ፪። ሕዝ፲፮ ፡ ፲፪)።
ምክላእ ፡ (ኣት) መከልከያ ኬላ በር፤ ዐጥር ቅጥር አጕራ።
ምክራም ፡ ምክራም፤ መክረሚያ ፥ ማክረሚያ፤ የክረምት ቦታ ሙቀት ያለው፤ ቈላ የምድር ቤት። ቤተ ምክራም ወቤተ ሐጋይ። ወንጉሥ ይነብር ውስተ ቤተ ምክራም። ወገብሩ ህየ ምክራመ ፡ (ዓሞ፫ ፡ ፲፭። ኤር፵፫ ፡ ፳፪። ታሪ ፡ ነገ)።
ምክር ፡ (ራት) በቁሙ፤ ቍርጥ ሐሳብ ፈቃድ፤ ትምርት ዕውቀት፤ ምስጢር ኅቡእ ነገር። መንፈሰ ኀይል ወምክር። ኢኮነ ምክርየ ከመ ምክርክሙ። ኀበ ክልኤቱ ምክራት። ምክሮሙ ለሊቃውንት። ዘያወፅእ ምክረ ቢጹ ፡ (ኢሳ፲፩ ፡ ፪። ፶፭ ፡ ፰። ፍ ፡ ነ ፡ ፳፬ ፡ ፪። ኢዮ፲፪ ፡ ፳። ሢራ፲፫ ፡ ፲፪)።
ምክነት ፡ መምከን፤ መካንነት። ምክነትሰ ኢትውህባ ለብእሲት ፡ (ሔኖ)።
ምክንያት ፡ (ታት) ምክንያት፤ ፡ (ታት) በቁሙ፤ ሽፍጥ አሉታ፤ ሐተታ የቃል መከታ። ሰበብ፤ መንሾ መነሾ፤ ከርከሬሻ የነገር ማንሻ። መገኛ ሥር ሥረ ነገር፤ ጥንት መሠረት። ሀቦ ዘመፍትው ወኢታብዝኅ ምክንያተ። ሐተቶሙ ምክንያተ ደዌሃ። ከመ ኢይርከብ ምክንያተ በዘይጸብኦን። ብሂሎቱሰ ጥንተ ሕይወቶሙ ምክንያተ ሕይወቶሙ ብሂል። አክብር አባከ ወእመከ፤ እስመ እሙንቱ ምክንያተ ልደትከ ፡ (አፈ ፡ ድ፲፩። ዮሴፍ። ፩ጢሞ ፡ ፭ ፡ ፲፬። አፈ ፡ ድ፬። ፍ ፡ ነ
፡ ፲፩)።
ምክዓው ፡ (ዋት) ማፍሰሻ፤ መገልበጫ። ምክዓወ ማይ ዘኵሉ ቀላይ። ምክዓወ ሐመድ ፡ (ሔኖ፲፯ ፡ ፯። ዘሌ፬ ፡ ፲፪)።
ምክዕቢት (ታት) [1] ፡ ዕጥፍ ድርብ ፤ ኹለት እጅ። ምክዕቢተ ክብር ይደልዎሙ። ምክዕቢት ውእቱ ኀይሎን። ትሠርዕዎ ምክዕቢተ። ኃጥእ ዘክልኤ ግዕዙ ወምክዕቢተ
የሐውር (፩ጢሞ ፡ ፭ ፡ ፲፯። ሄርማ ፡ ገ፴፪። ዘሌ፳፬ ፡ ፮። ሢራ፪ ፡ ፲፪)። ከአኃዝ ጋራ ሲነገር
እንዳወራረዱ ይፈታል። ኵሉ ምክዕቢት ፤ አሐዱ አሐዱ ቅድመ ካልኡ። ፍጥረት ኹሉ ፪ ፪ ነው ፤ ያውም ተባትና እንስት (ሢራ፵፪ ፡ ፳፬)። ብዙኀ ምክዕቢተ ፤ ፪ ዕጥፍ ፥ ፬ እጅ (ሉቃ፲፰ ፡ ፴)። ሰብዐቱ
ምክዕቢታተ ትምህርት ፤ ፯ ዕጥፍ ፥ ፵፱ (ሔኖ፺፫ ፡ ፲)።
[2] ፡ ምክዕቢት፤ የመስሪያ ስም፤ ታላቅ ያውድማ ልክ ፥ ዳውላ ቅርጫት፤ ፪ እጅ የሚይዝ የሚያነሣ ፡ (ዘፍ፳፮ ፡ ፲፪)። በትግሪኛም ካዕቦ የሚባል መስፈሪያ አለ፤ እንተላምን እይ። ባማርኛም ታላቁን ዋነጫ ካቦ ማለት የክዒብ ዘር ነው።
[3] ፡ ምክዕቢት፤–ዕጥፍ ድርብ፤–ክዒብ ከዐበ።
ምክያድ ፡ (ዳት) ዐውድማ ተረግጦ የጠበቀ መሬት፤ ያዝመራ መውቂያ ማበራያ፤ ፍሬን ከገለባ መለያ፤ ማምረቻ ማግረጃ። የወይን መርገጫ፤ የዘይት የሰሊጥ የቅባኑግ ማውጫ። ምክያደ እክል። ምክያደ ወይን። ትበውኡ ውስተ ምክያድ ትቅድሑ። ምክያዳቲሆሙ
፡ (፫ነገ ፡ ፳፩ ፡ ፩። ዘኍ፲፰ ፡ ፳፯። ሐጌ፪ ፡ ፲፮። ፍ ፡ ነ ፲፰)። መዛግብት በማለት ፈንታ ምክያዳት ይላል፤ ስሕተት ነው። ተነሥቱ ምክያዳት ፡ (ዮኤ ፡ ፲፯)።
ምክዳን ፡ ዝኒ ዓዲ ከማሁ፤ መክደኛ መከደኛ።
ምዋኤ ፡ ዝኒ ከማሁ። ብጡል እምዋኤክሙ ፡ (አዋል)።
ምውልታው ፡ መመከቻ መመካከቻ፤ መስላለፊያ፤
፡ (አርጋ ፡ ፭)።
ምዉእ ፡ (ኣን ኣት ውእት) የተሸነፈ፤ ድል የኾነ፤ የተረታ። ትከውን ምዉአ ሎቱ። ሕገ ጸብእ ወመዊእ ትሬስዮሙ ለምዉኣን አግብርተ ለመዋእያን ፡ (ፈላስ ፡ ገ፴፱። ፍ ፡ ነ ፡ ፴፩)።
ምውዳስ ፡ ማወደሻ መወደሻ፤ ቦታ መሣሪያ ጊዜ። ምክንያት ፡ (አዋል)።
ምዉቅ ፡ (ቃን ቃት ውቅት) የሞቀ፤ ሙቅ ቅኵስ። ለከሰ ምዉቅ ውእቱ አልባሲከ። ምዉቅ ከመ እሳት። ኅብስት ምዉቅ። ማይ ምዉቅ። ዐዚዝ ወምዉቅ በመንፈስ ቅዱስ ፡ (ኢዮ፴፯ ፡ ፲፮። ሔኖ፲፬ ፡ ፲፫። ፩ነገ ፡ ፳፩ ፡ ፮። ስንክ ፡ የካ፲፩። ራእ፫ ፡ ፲፭። ቀሌ)።
ምዉት ሙት ፡ (ታን ታት ውት) በቁሙ፤ የሞተ የተለየ፤ሬሳ በድን አስክሬን። ምዉተ ትካት። ምዉታን በኀጢአት። በእንተ ሙታን። ምውት ይእቲ ለሊሃ። ፡ (ሰቈ፫ ፡ ፮። ኤፌ፪ ፡ ፩። ፍ ፡ ነ ፡ ፳፪። ያዕ፪ ፡ ፲፯)።
ምዉጽ ፡ (ጻን ጻት ውጽት) የተሟጨ የተካሰ።
ምዙሕ ፡ (ሓን ሓት ዝሕት) ድልድል ቅምጥል፤ ቀለጤ ቀበጥ፤ ቅብጥብጥ። ከረዮ ጽጋብ ለምዙሕ ፡ (ዘዳ፴፪ ፡ ፲፭)። መጽሐፍ ግን በምዙሕ ፈንታ ምንዙሕ ይላል፤ ባለቅኔዎችም መንዝሐ ብለው ይገሳሉ፤ ነዝሀና መዝሐ ተዛንቆን ከነዝሀ መስም ከምንዛህ መጥቷል።
ምዙን ፡ (ናን ናት ዝንት) የተመዘነ የተለካ፤ ምዝን ምእዙን። እዝንና ማእዘንን በአዘነ ተራ ተመልከት፤ ከዚህ ጋራ አንድ ነው።
ምዙዛት ፡ (ዕብራ) ራግዛት፤ የግራና የቀኝ መቃኖች። አንዲቱን ምዙዛ ይላታል፤ ኹሉም የሴት አንቀጽ ነው
፡ (ሕዝ፵፩ ፡ ፳፩)።
ምዝሓቅ ፡ (ቃት) መዛቂያ፤ መግፈፊያ፤ ቦታ ወይም መሣሪያ። ውስተ አስኳተ ሀገር ወቦ በምዝሓቅ ወቦ እለ በመንኰራኵር ፡ (መጽ ምስ)።
ምዝላል ፡ መሎጊያ፤–ዘሊል ዘለ።
ምዝሙዝ ፤ የተመዘመዘ ምዝምዝ ፤ የታሸ የተወለወለ ፤ ጥሩ ደረቅ።
ምዝማር ፡ (ራት) ጥቅስ፤ የመጽሐፍ ቃል ምስክር የሚኾን። ብዙኅ ምዝማር ብየ። ዘእምቅዱሳት መጻሕፍት ምዝማር ፡ (መጽ ፡ ምስ። ቄር)።
ምዝራቅ ፡ (ዐረ ሚዝራቅ) ምዝራጥ ጦር ዘገር፤ የሚወረወር። ደርበዮ በምዝራቅ ውስተ ከርሡ ወቀተሎ ፡ (ዮሴፍ)።
ምዝራዕ ፡ (ዓት) መዝሪያ መዛሪያ፤ ቃዳ ተለላ፤ እመም ገዝም።
ምዝር ፡ ምዝር፤ ፡ (ዐረ ሚዝር መዘር) ዝልል ፥ ጥሩ ጠላ ከእኽል ከጌሾ የሚሠራ፤ ዐረቂ ጠጅ የሚያሰክር መጠጥ
፡ (ገድ ፡ ተክ)።
ምዝቡር ፡ (ራን ራት ብርት) የፈረሰ፤ የተናደ። ቤትየሰ ምዝቡር። አገኀለ ኵሎ አብያተ ጣዖታት ወረሰዮሙ ምዝቡራነ ፡ (ሐጌ፩ ፡ ፬። ስንክ ፡ ሠኔ፬)።
ምዝባሕ ፡ ማረጃ መሠዊያ ቦታ፤ ምሥዋዕ መንበረ ታቦት።
ምዝባሬ ፡ መፍረስ አፈራረስ፤ ፍርሻ፤ ጠፍነት። ምዝባሬ ዳግም ዘቤተ መቅደስ ፡ (አቡሻ)።
ምዝጉን ፡ (ናን ናት ግንት) የተመሰገነ፤ ምስጉን።
ምዝጋና ፡ (ናት) ምስጋና ክብር፤ ትምክሕት። ኢታፅርዕ ገቢረ ሠናይ፤ እስመ ገባሪሁ ኢየኀጥእ ምዝጋና በውስተ ዓለም። ከመ ይርከቡ ምዝጋና እምኀበ እግዚአብሔር በእንተ ዘአምንዎ። ምዝጋናየ። ኢይከውነኑ ምዝጋና። ወእመኒ መስተጋድል ኢይከውኖ ምዝጋና እመ ዘበሕጉ ኢተጋለ ፡ (ፈላስ ፡ ገ፶፯። መቃ
፡ ገ፲፱። ፩ቆሮ ፡ ፲፭ ፡ ፲፮። ፪ጢሞ ፡ ፪ ፡ ፭። ፪ነገ ፡ ፳፫ ፡ ፲፰)።
ምዝፋን ፡ (ናት) መዝፈኛ፤ ማዘፈኛ ቦታ መሣሪያ። ዘበልዐ በቤተ ምዝፋናት
፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፱)።
ምዩስ ፡ (ሳን ሳት ይስት) የተጠጀ የተጣለ፤ የተዘነበለ ዝንብል ምልስ።
ምዩን ፡ የተታለለ የተሸነገለ፤ ተላላ ሽንግል፤ ሌሎች ያታለሉት የተተነኰሉት። እስመ ውስተ ምይንት ነፍስ ኢትበውእ ጥበብ ፡ (ጥበ፩ ፡ ፬)።
ምዩጥ ፡ (ጣን፤ ጣት ይጥ) የተመለሰ፤ የተማለሰ፤ ምልስ ልውጥ። ምዩጠ ገጽ እምስእለትየ። እስመ ምዩጥ ገጾሙ። ሰበእ ምዩጣን ኀቤከ ፡ (አርጋ ፡ ፫። ሄርማ ፡ ገ፲፯። ዮሴፍ)።
ምያኔ ፡ መተንኰል፤ መተናኰል፤ ተንኰለኝነት ትንኰላ ሽንገላ። ምያኔ ወጕሕሉት
፡ (አዋል)።
ምያጤ ሙያጤ ፡ (መዊጥ ሞጠ ይመውጥ ይሙጥ) ዝኒ ከማሁ፤ መመለስ፤ ምለሳ። መለወጥ፤ መለዋወጥ መዛወር። ወና የ ተወራራሾች ስለ ኾኑ በምያጤ ፈንታ ሙያጤ ይላል። ዘእንበለ ሙያጤ። ሙያጤ ልደት። ሙያጤ መዋዕል ወተፋልሶ ጊዜያት
፡ (መጽ ፡ ምስ። ጥበ፯ ፡ ፲፰። ፲፬ ፡ ፳፮)።
ምዳቍ [1] ፡ ምዳቋ ሚዳቋ፤ የዱር እንስሳ የሠሣ ወገን፤ ቂጠ ወፍራም፤ እግረ ቀጭን ዐንገተ ረዥም፤ ምድርን በእግሯ የምትደቃ የምትደቀድቅ። አምሥጦተ ምዳቍ እማዕገት ፡ (ሢራ፳፯ ፡ ፳)።
[2] ፡ ምዳቍ፤–ምዳቋ፤–ደቂሕ ደቅሐ።
ምድሓክ ፡ መዳኺያ፤ ዴዴ ወልወል መርሕብ።
ምድኃፅ ፡ (ፃት) (ጥዳ) መዳጫ መሰናከያ፤ ቦታ ምክንያት።
ምድራስ ፡ (ሳት) ዝኒ ከማሁ፤ ድርሳን ድርሳት፤ ትርጓሜ ስብከት። ዛቲ መጽሐፈ ምድራስ ዘውእቱ ሥሉጥ ላዕለ ቀድሶ ቍርባን ወላዕለ ምህሮ ወላዕለ ምድራሳት። ወዘምድራሳት ፡ (መጽ ፡ ምስ። ፩ቆሮ ፡ ፲፬ ፡ ፳፮)።
፡ ቦታ፤ ድርሳን መድረሻ መተርጐሚያ፤ ቤተ ክሲያን ጉባኤ የተማሪ ቤት።
ምድራዊ ፡ (ዊት ውያን ያት) በቁሙ፤ የምድር ፥ ከምድር የተገኘ ፥ በምድር የሚኖር። ወልደ ምድራዊ። ሥጋ መሬት ምድራዊ። ንጉሥ ምድራዊ። ሕይወት ኀላፊት ምድራዊት ፡ (ጥበ፯ ፡ ፩። ዮሴፍ። ፊልክ ፡ ፻፺፪። መቃ)።
ምድር ፡ (ብ ምድራት፤ አምዳር፤ አምዳራት ፥ ሮት) በቁሙ፤ ሰፊ ዝርግ፤ ረዥም ፥ ወርዳም ቁመታም፤ ደንዳና ወፍራም፤ ከነባሕሩና ከነየብሱ ፥ ከነጕተናው ከነልብሱ ባንድንት። ዘገብረ ሰማየ ወምድረ። ገባሬ ሰማያት ወምድር። ሰማይ ወምድር የኀልፍ ፡ (ቅዳ)።
፡ የብስ የባሕር ርቦ፤ ከየብስ የተፈጠሩ የዐርብ ፍጥረቶች የሚኖሩበት። ወሰመዮ ለየብስ ምድረ ወለምእላደ ማይ ባሕረ። ለታብቍል ምድር ሐመልማለ ሣዕር። ለታውፅእ ምድር ዘመደ አንስሳ ወአራዊት ፡ (ዘፍ፩ ፡ ፲
፡ ፲፩። ፳፬)።
፡ የቦታ የርስት የመንግሥት ክፍል፤ ሀገር ብሔር ፥ አውራጃ መንደር ፥ ከተማ ገጠር ፥ በሕዝብ በነገድ ፥ በገመድ በቀላድ የተለየ፤ ከነሕዝቡ ከነባለቤቱ። ኵሉ ምድር። ምድራት ርሒባት። አድባር ወአምዳር። ውሳንያተ አምዳር። ይበውእ ውስተ አምዳራት። ወዘረውክዎሙ በአምዳሮት ፡ (ዮዲ፲፩ ፡ ፲፮። ፩ዜና ፡ ፬ ፡ ፵። ዘዳ፲፩ ፡ ፲፩። ፍ ፡ ነ ፡ ፳፯። ዳን፲፩ ፡ ፵። ሕዝ፲፩ ፡ ፲፮)።
፡ የሰው ባሕርይ፤ ሥጋ ዐፈር መሬት። ዘምድረ ለብሰ ፡ (ኪዳ)። ምድረ ግብ ፥ ምድረ ባሕር ቢል፤ ታሕት ውስጥ ልብ ማለት ነው ፡ (ዳን፮ ፡ ፳፬። ኢዮ፴፰ ፡ ፲፮)።
ምድቃስ ፡ ማንቀላፊያ መተኛ መኝታ፤ የንቅልፍ ቦታ። ኢይኑም ውስተ ሠናይ ምድቃስ አላ ውስተ ሐመድ ፡ (ቄድር)።
ምድናን ፡ (ናት) ማጐንባሻ፤ መጐንበሻ። አኮ ዘቦቱ ለመለኮት ምድናን ወአትሕቶ ርእስ ከመ ይንሣእ እምድር ዘኮነ ውስቴታ ፡ (ቅዳ ፡ ሕር)።
ምድጋም ፡ (ማት) መድገሚያ፤ ቦታ መጣፍ ጊዜ። ድጋም ንባብ፤ ዜማ የሌለው ቃል።
ምጉብ ፡ (ባን ባት ግብት) የተመገበ፤ የተጠበቀ፤ የተሾመ። ወውእቱሰ ምጉብ በኀይለ አምላኩ ፡ (ገድ ፡ ኪሮ)።
ምጉያይ ፡ መሸሻ መጠጊያ፤–ጐይይ ጐየ።
ምጕሕያ [1] ፡ ዐረም፤ እሾኻም ቅጠል፤ ኵርንችት ዐቃቅማ አሜከላ ሙጃ የመሰለው ኹሉ። ሦክ ወምጕሕያ ፡ (ኢሳ፯ ፡ ፳፫–፭። መቃ ፡ ገ፲፪)።
[2] ፡ ዐረም ቋያ፤–ጐሐየ።
ምጕባእ ፡ (ኣት) መሰብሰቢያ መከማቻ፤ መጠራቀሚያ ቦታ። ወበይእቲ ዕለት ፈጠረ ላቲ ልጐታተ ዘአብሕርት በበ ምጕባኣቲሆሙ ወኵሎ አፍላገ ወምጕባኣቲሆሙ ሰማያት ውስት አድባር ወውስተ ኵሉ ምድር ወኵሎ ምዕቃላተ ፡ (ኩፋ ፡ ፪)።
ምጕንጳ [1] ፡ ጐረንጐሬ፤–ገነጰ።
[2] ፡ (ጳት) ፤ ጐረንጐሬ የፍላጻ ቤት ፤ ባለቀስት ፍላጾቹን አክቦ ሰብስቦ የሚይዝበት እንደ ቍናማት እንደ ከረጢት ያለ። ዘያወፅእ አሕጻሁ እምጕንጳሁ። ንሥኡ ምጕንጳ። ምልኡ ምጕንጳክሙ። አሕጻቲሆሙ ውስተ ምጕንጳቲሆሙ ፡ (ሢራ፳፮ ፡ ፲፪።
ኢሳ፳፪ ፡ ፮። ኤር፳፰ ፡ ፲፩። መዝ ፡ ፲)።
ምጕያይ ፡ (ያት) መሸሻ መጠጊያ፤ መማጠኛ የሙጥኝ መባያ። ምጕያዮን ለግሔ። ኮንከነ ምጕያየ ፡ (መዝ ፡ ፻፫። ኪዳ)። ጕያ ጕየት በማለት ፈንታ ምጕያይ ይላል ፡ (ናሖ፫ ፡ ፱)።
ምጕጣይ [1] ፡ (ያት)
መውጊያ መጓጐጫ፤ መቈንጠጫ፤ አሽሙር ችንካር አርቃሾ። ይብእስከ ረጊፅ ውስተ ቀኖት ባለው፤ ጽኑዕ ለከ ምጕጣይ ወተረግፆ እንዲል ፡ (ግብ፳፮ ፡ ፲፬)።
[2] ፡ መጓጐጫ፤–ጐጥይ ጐጠየ።
ምግሓሥ ፡ (ሣት) መግቢያ ማግቢያ፤ ማግለያ ማስገለያ፤ ቦታ ዐዘቅተ ኵስሕ። ኀበ አልቦ ምግሓሥ። ምግሓሠ ጽርሑ ፡ (ዘኍ፳፪ ፡ ፳፮። መሳ፫ ፡ ፳፬)።
፡ መሣሪያ፤ መዛቂያ ማፈሻ፤ መውሰጃ ማንሻ እንዳካፋና እንደ ላይዳ እንዳስፈሬዳ ያለ። ኢያሚንና ኰከም መስወድ የዚህ ዘውጎች ናቸው። ምግሓሣት ፡ (ዘፀ፳፯ ፡ ፫። ፴፰ ፡ ፫)።
ምግሃድ ፡ መግለጫ፤ መገለጫ፤ ማስረጃ ፡ (ቦታ መሣሪያ ቃል)።
ምግሓፍ ፡ (ፋት) ዝኒ ከማሁ መጋፊያ ማፈሻ፤ መጥረጊያ።
ምግራፍ ፡ (ፋት) መግረፊያ ቦታ ወይም ጅራፍ ሳንባ ጠለፍ። መጅረፋ አካፋ የብረት ላይዳ፤ መጋፊያ መጥረጊያ።
ምግባር ፡ (ራት) [1] ፡ በቁሙ፤ ሥራ፤ የሚገባ የማይገባ፤ በሕግ የታዘዘ ወይም ያልታዘዘ ማናቸውም ኹሉ። ለኵሉ ሰብእ ይፈድዮ በከመ ምግባሩ። ምግባረ ወሀብናሁ። ኵሉ ምግባሮሙ ርኩስ። ንጹሕ አነ በምግባርየ። ሶበሰ አብርሃም በምግባሩ ጸድቀ። ዘይበቍዕ ለምግበ ምግባራቲሁ ወንዋዩ። ፡ (ሢራ፴፪ ፡ ፳፬። ኩፋ ፡ ፫። ፳፩። ኢዮ፲፩ ፡ ፬። ሮሜ፬ ፡ ፪። ፍ ፡ ነ ፡ ፴፪)።
[2] ፡ መሥሪያ ማድረጊያ ቦታ መሣሪያ፤ ወይም ባሕርይ፤ አካል ሥራውን የሚፈጽምበት። ምግባር ይመርሕ ኀበ ጥያቄ አስማት ወምግባርኒ ይትፌጸም በህላዌ ፡ (ሃይ
፡ አበ)።
ምግባእ ፡ (ኣት) መግቢያ መመለሻ፤ ተመልሶ መምጫ ቦታ። ኀቤየ ምግባኢሁ። ውስተ ምድር ምግባኢሆሙ።የሐውር ውስተ ፍኖት እንተ አልባቲ ምግባእ ለዓለም ፡ (ማሕ፯ ፡ ፲፩። ሢራ፲፮ ፡ ፴። ግንዘ። ዘፍ፫ ፡ ፬ ፡ ፯)።
ምግብ ፡ በቁሙ፤ ቀለብ ፥ መብል መጠጥ ፥ እንጀራና ወጥ። ማርያም ሀብኒ ምግበ ዕለት፤ እስመ ተማሕፀንኩ አንሰ በዘዚኣኪ ስደት ፡ (ቅኔ)።
፡ ጥበቃ ፥ ሹመት ፥ የሹመት ሥራ ፥ አስተዳደር። መገቦሙ ምግበ እኩየ። ዘሀለወት ታሕተ ምግቡ። ከመ ይፈጽም ምግቦ። ትሰዐር እምግብከ። በምግቡ ለቈስጠንጢኖስ
፡ (አፈ ፡ ድ፴፬። ፍ ፡ ነ ፳፬ ፡ ፫። ተረ ባሮ። ኢሳ፳፪ ፡ ፲፱። ስንክ ፡ መስ፳፩። ሉቃ፲፮ ፡ ፪–፬)።
ምግብና ፡ መጋቢነት፤ ጥበቃ ሹመት። በእንተ ምግብና ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፴)። ምግብ ምግብና ፥ ወይም ምጋቤ በማለት ፈንታ ምግበት ይላል፤ ቤቱ የቀደሰ ነውና ፥ አያሰኝም። ሥልጣነ ምግበት ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፳፬ ፡ ፫)።
ምግዓዝ ፡ መጓዣ፤ ማጓዣ፤ መዝመቻ መስደጃ። ምግዓዞሙ ለእስራኤል ፡ (አዋል)።
ምጡቅ ፡ (ቃን ቃት ጥቅት) በቁሙ፤ የመጠቀ ከምድር የራቀ፤ ከፍተኛ ረዥም፤ ሩቅ ረቂቅ። እግዚ ዘዲበ ልዑል ወምጡቅ የኀድር። መንበር ልዑል ወምጡቅ። ሰማይ ምጡቅ፤ ደመና ምጡቅ። ምጡቃነ ስረት ፡ (ቄድር። ቄር። አዋል)።
ምጡን ፡ (ናን ናት ጥንት) የተመጠነ የተለካ፤ ምጥን ልከኛ ፡ (መጽ ፡ ምስ)።
ምጣኔ ፡ (ገቢር ወተገ) መመጠን መለካት፤ አመጣጠን አለካክ ምጠና ግምገማ፤ ልክ መጠን ፥ ስፍር ቍጥር፤ የወርድ የቁመት የስፋት። ወእምነ ምጣኔ ልቡና። አምጽአ ሥርዐተ ምጣኔ እምርሑቅ። ሄሮድስ አስተናደፈ መሠረታቲሁ፤ ኑኆ ወግድሞ በምጣኔ ቀዳማዊ። ይሬስኡ ዕድሜ ወርኆሙ በምጣኔ ምሕዋረ ፀሓይ ወስተ አሐቲ ኆኅት። ውፁኣን እምጣኔ ፡ (ፊልክ ፡ ፮። አፈ ፡ ድ፰። ዮሴፍ። አቡሻ
፡ ፲፪። አዋል)።
ምጣዌ ፡ አሰጣጥ፤ አቀባበል፤ ስጦታ ምጧት።
ምጥማቅ ፡ (ቃት) መጥመቂያ ማጥመቂያ፤ መጠመቂያ መታጠቢያ፤ ቦታ። ቤተ ምጥማቅ። ዋዜማ ዘደብረ ምጥማቅ። ወረደ ወልድ እምሰማያት ውስተ ምጥማቃት። በኀበ ምጥማቃት እንተ ላዕላይ ፍኖት። ምጥማቃት ሰሊሖም ፡ (ኪዳ ፡ ድጓ። ኢሳ፯ ፡ ፫። ዮሐ፱ ፡ ፯)።
ምጥቀት ፡ ምጡቅነት ፥ ርዝማን ርዝመት፤ ዘለግታ ቁመት።
ምጥቅ ፡ ርቀት ፥ አራራቅ፤ ልዕልና ከፍታ። ምጥቆሙ ለአየራት ፡ (አርጋ)።
ምጥባሕ ፡ ማረጃ ቦታ፤ ምሧዕ መንበረ ታቦት። ምጥባሐ ሥጋሁ ወምቅዳሐ፤ ደሙ ለክርስቶስ
፡ (አርጋ ፡ ፯)።
ምጥዓይ ፡ (ያት) መዳኛ፤ ጤና ማግኛ መፈወሻ ቦታ መድኀኒት።
ምጥው ፡ (ውት ጡት፤ ዋን ዋት) የተሰጠ፤ የተሰጠው፤ ተሰጭ ገንዘብ ወይም ተቀባይ ሰው። ሶበ ነጸረ ርእሶ ምጥወ ለኵሉ መከራ ፡ (ፈ ፡ መ ፡ ፬ ፡ ፩)።
ምጥጋዕ ፡ (ዓት) መጠጊያ ማስጠጊያ ቦታ። መጪጊያ መከዳ፤ ድጋፍ። ፅጋዕንና ምፅጋዕን እይ፤ ከዚህ ጋራ አንድ ነው።
ምጥፋእ ፡ መጥፊያ ማጥፊያ ስፍራ፤ የጥፋት ቦታ።
ምፀት ፡ መጣጥነት ፣ መጣጣ ሖምጣጣ መኾን። በቁሙ፤ የተሣልቆ ቃል ፥ ሰሚውን የሚያሥቅና የሚያሰደንቅ፤ ተቀባዩን ግን የሚያሳዝን የሚያኮማጥጥ ልውጥና ግልብጥ አነጋገር። ጋን ታረደ ፥ ሙክት ተዘነበለ፤ ጊዮርጊስ ሊቀ መላእክት፤ ሚካኤል፤ ሊቀ ሰማዕታት፤ ይህን የመሰለ። ለዳዊት ወሬዛ ፋሲለደስ፤ ፈረሱ ቀዋሚ ከመ ነፋስ ወፈረሰ ፀሩ ረዋጺ ከመ አድማስ
፡ (ቅኔ)።
ምጹእ ፡ ምጹእ፤ ፡ (ኣን ኣት ጽእት) የመጣ፤ የተገኘ የኾነ፤ መጥቶ ያለ።
ምጽሓል ፡ ምጽሓል፤
፡ (ዕብ ዔጥ) ብርዕ፤ አፈ ምሣር፤ መጣፊያ፤ መቅረጫ። ባለብሉዮች ግን ሰሌዳ ይሉታል። በምጽሓለ ኀጺን ወዐረር እመ ጸሐፎ ውስተ ኰኵሕ ፡ (ኢዮ፲፱ ፡ ፳፬)። ብረቱን ብርዕ፤ ርሳሱን ቀለም አድርጎ ማለት ነው።
ምጽሓፍ ፡ ምጽሓፍ፤
፡ (ፋት) መጣፊያ፤ መቍጠሪያ፤ መማሪያ፤ የጥፈት የትምርት ቤት።
ምጽላል (ላት) [1] ፡ ማጥለያ፤ ማጥሪያ። መጠጊያ ማስጠጊያ፤ ጥላማ ቦታ፤ የዛፍ ሥር፤ ዳስ፤ ድንኳን፤ ጐዦ፤ ቤት፤ ማኅደርነት ያለው ኹሉ። ወሐነጸ ምጽላላተ ሎቱ ወለአግብርቲሁ። ወይተክሉ ምላሳሎሙ። ከመ ምጽላላተ ቄዳር። ለአዕዋፍኒ ምጽላል ቦሙ። ምጽላላቲሆሙ ዘለዓለማዊት ፡ (ኩፋ ፡ ፲፮። ኤር፮ ፡ ፫። ማሕ፩ ፡ ፭። ማቴ፰ ፡ ፳። ፊልክ ፡ ፫)።
[2] ፡ (ዕብ ሱኮት) ዳስ፤ ጥላ፤ ከለላ፤ ለበዓል ለድግስ የሚሠራ። የአይሁድ በዓል፤ በጥቅምት እኩሌታ የሚውል። በምጽላል ፈንታ መጸለት ይላል፤ የመላሽና የጣፊ ስሕተት ነው። ከመ ይንበሩ ደቂቀ እስራኤል በመጸለት። ወውእቱ መቅድመ ገብረ በዓለ መጸለት። ወቀርበ በዓለ መጸለቶሙ ለአይሁድ ፡ (ዕዝ ፡ ነሐ፰ ፡ ፲፬። ኩፋ ፡ ፲፮። ዮሐ፯ ፡ ፪)።
ምጽላይ ፡ (ያት) መጸለያ፤ የጸሎት ቦታ፤ ቤተ ክሲያን፤ ምኵራብ፤ መስጊድ። ምጽላየ መሀይምናን። ዘይጼሊ ኀበ ምጽላየ አይሁድ ወአረሚ ፡ (ቅዳ ፡ ጎር። ቀሌ)።
ምጽልው ፡ (ዋን ዋት ሉት) የጠለገ፤ ጠውላጋ፤ ደካማ፤ ዝልፍልፍ። ሣዕር ልምሉም ወአኮ ምጽልው። ወነበርነ ውዱቃኒነ ውስተ ምድር ከመ እንተ ሰብእ ምጽልዋን ፡ (ስንክ ፡ የካ፲፮። ኪዳ
፡ ፩)።
ምጽማእ ፡ መጠሚያ፤ ማስጠሚያ፤ ደረቅ በረሓ። ወረሰየ ምጽማአ ሙሓዘ ማይ
፡ (መዝ ፡ ፻፮)።
ምጽራብ ፡ (ባት) መጥረቢያ ቦታ፤ የጥርበት ቤት። ዘያወፅኡ መሬተ እምጽራበ ቤተ ክርስቲያን ፡ (ገድ ፡ ላሊ)።
ምጽባሕ ፡ መገበሪያ፤ ማስገበሪያ፤ ግብር መስጫ መቀበያ፤ ቦታ ጉምሩክ ገባያ፤ በር። እንዘ ይነበር ውስተ ምጽባሕ ፡ (ስንክ ፡ ጥር፳፭። ማቴ፱ ፡ ፱)።
ምጽባኅ ፡ (ኃት) የወጥ ቤት፤ ምድጃ፤ ቦታ።
ምጽባእ ፡ (ኣት) ፡ (፤ መውጊያ፤ መዋጊያ፤ መሳለፊያ። ማደሪያ፤ መሳፈሪያ፤ ጐዦ መሥሪያ፤ ድንኳን መትክያ። ዘይሰመይ ምጽባአ ዳዊት
፡ (አቡሻ ፡ ፵፯)።
ምጽናዕ ፡ (ዓት) መጥኛ፤ መጠንክሪያ፤ ማጥኛ ማበርቻ። ሰማይ፤ ጠፈረ ሰማይ፤ ከሀኖስ ጋራ ርስ በርሱ የተጠናና። ሀኖስን ተመልከት። ወበዕለት ሳኒት ገብረ ምጽናዓተ ማእከለ ማይ። እፎኬ ዘኢንኅሉ ምጽናዓተ ሰማይ። ለዘመጽአ ወልድ በአፈ ነቢያት ተሰቢኮ፤ ከመ ያስተፋኑ ሐራ መልአኮ እስከ ምጽንዓት ኀምስ ሚካኤል ተለውኮ ፡ (ኩፋ ፡ ፪። መጽ ፡ ምስ። ስንክ
፡ ታኅ፲፪)።
ምፅንጋዕ ፡ (ምፅጋዕ) መጠጊያ ቦታ፤ ጋጥ በረት፤ ግርግም። ወእደ አልቦ አልሕምት ምፅንጋዕ ንጹሕ። ዲበ ዕፀ መስቀል ተቀነወ ወዲበ ምፅንጋዕ ተጠብለለ። ነደቀ ውስተ ጾላዕቱ በአምሳለ ምፅንጋዕ ፡ (ምሳ፲፬ ፡ ፬። ድጓ። ገድ ፡ ተክ)።
ምጽአታዊ ፡ የምጽአት። ምጣታም ፥ ምጣተኛ ፥ ሆዳም ፡ (ዐማርኛ)።
ምጽአት ፡ መምጣት፤ አመጣጥ። አሐቲ ይእቲ ምጽአቱ ለኵሉ ውስተ ዓለም። በምጽአትየ ካዕበ ኀቤክሙ። ሠናይ ምጽአትከ ፡ (ጥበ፯ ፡ ፭። ፊልጵ፩ ፡ ፳፮። ገድ ፡ ተክ)።
፡ በቁሙ ፥ ምጣት፤ ድንገተኛ ነገር ፥ አደጋ መቅሠፍት ፥ ራብ ችጋር
፡ (ዐማርኛ)። ምጣት ያምጣብኽ እንዲሉ።
ምጽዓድ ፡ መጣጃ፤ ምድጃ፤ ጕልቻ፤ የምጣድ ቤት፤ በቁሙ ምጣድ፤ ምጎጎ ፡ (ዐማርኛ)።
ምጽዋት [1] ፡ በቁሙ፤–ጸዊት ጾተ።
[2] ፡ ምጽዋት፤ ምጿት፤ ፡ (ታት። ዕብ ሚጽዋህ፤ ትእዛዝ። ሱር ማጡታእ፤ ልመና ፍላጎት) በቁሙ ፥ ምጧት ለድኻ ለግዜር የሚሰጥ ገንዘብ ስጦታ፤ በብሉይ በሐዲስ የታዘዘ። ሌላውም የፍቅርና የርኅራኄ ሥራ ምክርን ርዳታን የመሰለው ኹሉ የግዜር ትእዛዝ ስለ ኾነ ምጿት ይባላል። ስኢለ ምጽዋት። ውሂበ ምጽዋት። ብዙኀ ምጿተ ገበርኩ ለአኀውየ። ሢጡ ንዋየክሙ ወሀቡ ምጿተ ለነዳያን፤ ደዮ ውስተ ሙዳየ ምጽዋት። ምጿታት ፡ (ሢራ፴፩ ፳፭። ፴፯ ፡ ፲፩። ጦቢ፩ ፡ ፫። ፍ ፡ ነ ፡ ፲፮። ስንክ ፡ ኅዳ፲፪)።
ምጽዋን ፡ (ናት) መጠጊያ፤ ማስጠጊያ ቦታ፤ ከለላ መከታ ያለው።
ምጽዋዕ ፡ መጥሪያ፤ መጮኺያ፤ የእስላም ፕራሚድ። የደሴት ስም፤ የሐማሴን በር።
ምፅጋዕ ፡ (ዓት) መጠጊያ ማረፊያ ቦታ፤ ዐልጋ መኝታ። ፀንግዐን ተመልከት።
ምፍሓቅ ፡ መፋቂያ፤ ማንጠጫ፤ ቦታ ስፍራ።
ምፍዋስ ፡ መካነ ፈውስ፤ ቤተ ድዉያን፤ ቤተ ክሲያን፤ ጠበል፤ ማዎት፤ ፍል ውሃ። ቦ እለ መጽኡ ውስተ ምፍዋስ ዘቤተ ክርስቲያን። ከመ ይስአሉ ዘእምኀቤከ ርቅየተ ወሕይወተ። ወቦ ውስተ እየሩሳሌም ምጥማቃት
፡ (ተረ ፡ ቄር፲፱። ሊጦን። ዮሐ፭ ፡ ፪–፬)።
ምፍያት ፡ መቀሚያ፤ የወንበዴ ቦታ። ምፍያተ አክይስት ፡ (አዋል)።
ምፍዳይ ፡ መክፈያ፤ ሚዛን ቍና ላዳን። ወኀጢአቱ ምፍዳዩ ፡ (ተረ
፡ ቄር፲፰)።
ምፍጣር ፡ መፍጠሪያ፤ መፈጠሪያ፤ ቦታ ማሕፀን። ምፍጣረ ጸቃውዕ
፡ (አርጋ ፡ ፭)።
ሞሎሕ ፡ ስመ ጣዖት፤–ሞሎኽ መሊክ መለከ።
ሞሎክ ፡ (ጽር ሞሎኽ። ዕብ ሞሌኽ) የደቂቀ ዓሞን ጣዖት ፥ እስራኤል ያመልኩት የነበረ፤ ፊቱ የጥጃ ፥ እጁና ግንዱ የሰው፤ እጆቹ ሕፃን ለመቀበል የተዘረጉ፤ በስተፊቱና በአንጻሩ ወደ ምሥራቅ ወገን በሰባቱ ሰማያት አምሳል ፯ ቅጥርና ፯ ደጃፍ ያለው። መላኪ መሪ መሪ ጠባቂ ንጉሥ ማለት ነው
፡ (ዘሌ፲፰ ፡ ፳፩። ፳ ፡ ፪ ፡ ፬። ግብ፯ ፡ ፵፫)። ያምልኮቱም ሥራት፤ ሰንዳሌና ዘይት ለሚያቀርብ ፩ኛው በር፤ ርግብና ዋኖስ ለሚያቀርብ ፪ኛው፤ በግ ለሚያቀርብ ፫ኛው፤ ፍየል ለሚያቀርብ ፬ኛው፤ ጥጃ ለሚያቀርብ ፭ኛው፤ በሬ ለሚያቀርብ ፮ኛው ይከፈትለታል፤ ልጁን ለሚያቀርብ ግን ፯ቱ ኹሉ ተከፍቶለት ለጣዖቱ እጅ በጅ ይሰጣል። ከዚያ በኋላ ካህናቱ ሕፃኑን ከሞሎኽ እጆች ተቀብለው በ፪ ወገን እሳት ያነዱና ከማኽል አግብተው ተወከፍ ለነ እያሉ ያሳልፉታል፤ ከዚህ የቀረውን ሐተታና ታሪክ በጣፌጥና በገሃነም ፍች ተመልከት።
ሞሠር ት ፡ (ብ መዋሥር ት) መጋዝ፤ ጥርሳም ብረት መቍረጫ መሠንጠቂያ። ይትሌዐልኑ ሞሠርት። መዋሥረ ኀጺን። መዋሥርተ ዕፅ
፡ (ኢሳ፲ ፡ ፲፭። ስንክ ፡ ሐም፳፭። ሲኖዶ)።
ሞሳሕ ፡ ስመ ነገድ፤–መሰከ ሞሳኽ።
ሞሣእ ት ፡ መመለሻ ምላሽ መስጫ፤ መነጋገሪያ፤ ቦታ መጽሐፍ።
ሞሳኽ ፡ (ጽር ሜሴኽ። ዕብ ሜሼኽ) ስመ ነገድ፤ ከሰባቱ ደቂቀ ያፌት አንዱ ፮ኛው፤ የመስኮቦች አባት
፡ (ዘፍ፲ ፡ ፪። ፩ዜና ፡ ፩ ፡ ፭። ሕዝ፴፰ ፡ ፪)። ሳቢ ጐታች መሪ፤ ወይም የታደመ የተቀጠረ ፥ ዕድመኛ ባለቀጠሮ ማለት ነው፤ ጎግ ማጎግን እይ ፡ (ሕዝ፴፰ ፡ ፯–፲ ፡ ፲፯–፲፱)።
ሞራእ [1] ፡ (ብ መዋርእት) ፤ ግልድም፤ ሽርጥ፤ ማጠቆ፤ መታጠቂያ። ተሣየጥ ለከ ሞራአ። ሰፈዩ ቈጽለ በለስ ወገብሩ ሎሙ መዋርእተ ፡ (ኤር፲፫ ፡ ፩። ዘፍ፫ ፡ ፯። ኩፋ ፡ ፫)።
፡ በቁሙ ሞራ፤ የንዋየ ውስጥ ልብስ የሆድ ዕቃ ሽፋን፤ ሥሥ እንደ ክርታስ ያለ፤ጋሎች የሚያሟርቱበት
፡ (ዐማርኛ)።
[2] ፡ ግልድም ፥ ሞራ፤–ወሪእ ወርአ።
ሞቀ ፡ በቁሙ፤–መዊቅ ቆት።
ሞቀር ርት ፡ (ብ መዋቅር) መውቀሪያ መጥረቢያ፤ የደንጊያ መሣሪያ የነጠረ ብረት። መዋቅረ እብን ፡ (አዋል)።
ሞቀይ ት ፡ (ብ መዋቅይ) መቍረጫ መቀርጠፊያ፤ መዘለፊያ። መዋቅየ አምትንት ወሥርው
፡ (ስንክ ፡ ጥር፲፭)።
ሞቃሒ ፡ (ሒት ሕያን ያት) የሚያስር አሳሪ፤ እስር ጠባቂ ዘበኛ። ሰገደ ሞቃሒ ለሙቁሓን ፡ (አፈ ፡ ተ፳፮)።
ሞቅ ፡ ሙቀት፤ ትኵሳት ፡ (ሔኖ፸፭ ፡ ፬ ፡ ፯)። ነፋሰ ሞቅ። እሳተ መለኮት
ዘይቄድስ ነፍሰ ወያጥዒ ሞቁ ፡ (ሔኖ፸፮ ፡ ፭ ፡ ፯። ደራሲ)።
ሞቅሐ [1] ፡ (ወቅሐ) ያዘ አሰረ አጋዘ፤ አቈራኘ ከወህኒ አገባ። መኑ ውእቱ ዘይሞቅሖ ለአዴየ። ሞቅሕዎ በኀጺን። አዘዘ ይደዮ ጋጋ ውስተ ክሣዱ ወይሞቅሕዎ እደዊሁ ወእገሪሁ። ዕደው እለ ሞቃሕክምዎሙ
፡ (ኢዮ፲፯ ፡ ፫። ስንክ ፡ ሚያ፳። ኅዳ፳፮። ግብ፭ ፡ ፳፭)።
[2] ፡ አሰረ፤–ወቂሕ ወቅሐ።
ሞቅሕ ፡ (ብ መዋቅሕት) ማሰሪያ ማቈራኛ፤ ሰንሰለት እግረ ሙቅ ወይም እግር ብረት፤ ቀንበር መንቈር፤ ዛንጅር የመሰለው ኹሉ። ወድቃ መዋቅሕት እምእደዊሁ። ሰበርኩ መዋቅሕቲክሙ። መዋቅሕቲሃ ዘብርት። አሕመምዎሙ በመዋቅሕት
፡ (ግብ፲፪ ፡ ፯። ዘሌ፳፮ ፡ ፲፫። ሢራ፳፰ ፡ ፳። ኢሳ፳፪ ፡ ፫)።
፡ ግዞት እስራት፤ የግዞት ቤት፤ ሐብስ፤ ወህኒ። ቤተ ሞቅሕ። ሀለወ ውስተ ሞቅሕ። ወደዮሙ ውስተ ሞቅሕ ፡ (ማቴ፲፩ ፡ ፪። ኩፋ ፡ ፴፱። ዘፍ፵ ፡ ፫)።
ሞት ፡ በቁሙ፤ የሥጋዊና የደማዊ ሕይወት ፍጻሜ፤ በአዳም ኀጢአት የመጣ ጠባይዓዊ ዕዳ፤ ባሕርያዊ ፍዳ። ፡ (ግጥም) ከጐዣምና ከዳሞት ማን ይበልጣለ በስፋት፤ ተዉት አየነው ለየነው ታላቁ ዳሞት ነው። መኑ ሰብእ ዘየሐዩ ወኢይሬእዮ ለሞት። ወሞተ መብዝኅቶሙኒ እስመ ይከውን በፍናው ብዙኃት። ሞተ ግብት። ሞት ጠባይዓዊ፤ ሞተ ፈቃድ። አግዚአብሔርሰ ኢገብረ ሞት ወኢይኤድሞ ሀጕሎሙ ለሕያዋን። ኮነኖሙ ሞት እምአዳም እስከ ሙሴ ለእለሂ ኢአበሱ ከመ አበሳሁ ለአዳም ፡ (መዝ
፡ ፹፰። ፊልክ። ፍ ፡ ነ ፡ ፶። ፈላስ። ጥበ፩ ፡ ፲፫። ሮሜ፭ ፡ ፲፬)።
ሞአ ፡ አሸነፈ፤–መዊእ፤ መዊኦት።
ሞዐልት መዓልት ፡ (ብ መዋዕል ላት) በቁሙ ቀን፤ ፀሓይ ወጥቶ እስኪገባ ያለ የሥራ ጊዜ ፲፪ ሰዓት። ዘሌሊት መዓልተ ይከውኖ። አርብዓ መዋዕለ ወአርብዓ ለያልየ ፡ (ሢራ፴፰ ፡ ፳፰።ማቴ፬ ፡ ፪)።
፡ ጊዜ ዘመን ወራት። ተዘከር መዋዕለ ረኃብ አመ መዋዕለ ጽጋብ። መዋዕል ወአዝማን። በእማንቱ መዋዕል ፡ (ሢራ፲፰ ፡ ፳፭። ግብ፩ ፡ ፯። ዘፍ፴፰ ፡ ፩)። መዋዕል በዕለትና በዕለታት ፈንታ እየገባ ውስጠ ብዙ ኹኖ ላንድም ለብዙም ይነገራል። በዝ መዋዕል፤ በኵሉ መዋዕል፤ በእማንቱ መዋዕል፤ ስዱሰ መዋዕለ። መዋዕል እኩያት፤ መዋዕል ሠናያት። በአንቀጽ ሲገባ እንደ ዕለት ዐቢይ አገባብ ይኾናል። በመዋዕለ ተወልደ ዮሴፍ። በመዋዕለ ትኤብስ ፡ (ኩፋ ፡ ፳፰። ሢራ፲፰ ፡ ፳፯)።
ሞገስ [1] ፡ በቁሙ፤ ሞጋሳ ውድ ውዴታ፤ ባለሟልነት፤ ጸጋ ክብር ውዳሴ ብፅዓን፤ ግርማ ውበት ደም ግባት ጣዕም ሥን። ቦሙ ሞገስ በኀበ ኵሉ ሕዝብ። እንተ ተዐቢ ሞገሰ ይሁበነ። ረከብኪ ሞገሰ። ገጽከ ምሉእ ሞገሰ። ሞገሳ ለብእሲት ያስተፌሥሖ ለምታ ፡ (ግብ፪ ፡ ፵፯። ያዕ፬ ፡ ፮። ሉቃ፩ ፡ ፴። አስቴ፭ ፡ ፪። ሢራ፳፮ ፡ ፲፫)።
[2] ፡ ባለሟልነት፤–ወጊስ ወገሰ።
[3] ፡ ውድ ውዴታ፤–ወጊስ ወገሰ።
ሞገር ፡ ጥና፤ የዕጣን መውገሪያ። ዕጣነ ሞገር እንዲሉ፤ ቅኔው በዕጣን ፈንታ ስለ ገባ።
ሞገርት ፡ ውርወራ ጥሎሽ፤ እንዝግዝጎሽ። ዘበሞገርተ እብን ወዕፀወ ገዳም ፡ (፩ነገ ፡ ፲፬ ፡ ፲፬)።
ሞገት [1] ፡ ሞገድ፤–ወጊድ ወገደ።
[2] ፡ ሞገድ፤–ወጊድ ወገደ።
ሞገደ ፡ (ይሞግድ) በቁሙ፤ አወከ ደረጠ በጠበጠ። ማገደ ዠገደ፤ የዕንጨት
ሞገዳዊ ፡ ሞገደኛ ሞገዳም ባለሞገድ። ሞጋች ተሟጋች፤ ሸፋጭ።
ሞገድ [1] ፡ (ዳት፤ መዋግድ፤ ዳት። ዐረ መውጅ) በቁሙ፤ ማዕበል የባሕር ጐርፍ የውሃ ተራራ ፈረሰኛ፤ እንደ ገመገም እየኾነ ከማኽል ወደ ዳር፤ ከዳር ወደ ማኽል የሚኼድ የሚነጕድ፤ ነፋሳት የሚክቡትና የሚንዱት የሚያወጡትና የሚያወርዱት። የእሳት ላንቃ ነበልባል። ሞገደ ባሕር እንተ ይዘብጣ ነፋስ ወያነውኃ። ወይትሀወክ እሞገዳት። እምአፉሁ መዋግደ እሳት ወፅአ። መዋግዳት
፡ (ያዕ፩ ፡ ፮። ማቴ፲፬ ፡ ፳፬። ሱቱ
፡ ዕዝ፲፫ ፡ ፲፩። ቀሌ)። በሞገድ ፈንታ ሞገት ይላል፤ ሙግት ማለት ከዚሀ ወጥቷል። ዐረቡ በመውጅ ፈንታ መውጀት ይላልና ይህም እንደዚያ ነው ፡ (አስቴ፫ ፡ ፪። ሱቱ ፡ ዕዝ፪ ፡ ፶)።
፡ ሞገድ ልክ ያለው የበጋ ሁከት፤ ማዕበል ከልክ ያለፈ የክረምት፤ ጐርፉ ወደብ የሚያፈርስ ወደ የብስ የሚፈስ ፡ (መዝ ፡ ፵፩)።
[2] ፡ በቁሙ ማዕበል፤–ወጊድ ወገደ።
ሞግእ መውግእ ሙጋእ ፡ (ብ መዋግእ) መውጊያ መውገጫ፤ ማፍረሻ፤ ቀንድ ዘገር፤ ሙገጫ የሙገጫ ግልገል፤ ድጅኖ ደንጐራ። ተወግኦ በአሐዱ ሙጋእ። ይጐድዕዎ ውስተ ሞግእ። ከመ ይትክሉ ምግአ ኀጺን ላዕለ ቅጽር። ተክለ መዋግአ ዘነፍጥ ፡ (ሥር ፡ አኵ። አዋል። ዮሴፍ)።
ሞጣሕት ፡ በቁሙ፤–ወዋሖ ወጥሐ።
ሞጥሐ ፡ (ይሞጥሕ) (ይሞጥሕ) አለበሰ አጐናጠፈ፤ ሸፈነ ደረበ፤ አከናነበ።
ሞጥሕ ሞጣሕት ፡ (ታት፤ መዋጥሕ) የክምር ቍንጮ ክዳን፤ የላይ ልብስ መደረቢያ። በቁሙ ልብሰ ተክህኖ ዝናር፤ ካባ ላንቃ፤ መጐናጠፊያ፤ ሠርመዲ ቀጸላ ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፰ ፡ ፫)። መዋጥሕየ። መዋጥሕ ዘሰንዱናት። ወከመ ሞጣሕት ትዌልጦሙ ፡ (ሆሴ፪ ፡ ፯። ሉቃ፳፬ ፡ ፲፪። መዝ ፡ ፻፩)።
ሞፀፍ ት ፡ (ብ መዋፅፍ ት) ማወንጨፊያ፤ በድል ነጐድ ወንጭፍ። ነፍጥ፤ መድፍ። ዘይወዲ እብነ ዲበ ዋፀፍ። እብነ ሞፀፍ። ሰብአ ሞፀፍ። ሞፀፍተ እብን። መዋፅፍተ እብን ፡ (ምሳ፳፮ ፡ ፰። ዘካ፱ ፡ ፲፭። ዮዲ፮ ፡ ፲፪። መሳ፳ ፡ ፲፮። ፪ዜና ፡ ፳፮ ፡ ፲፬)። መዋጽሕት በማለት ፈንታ የወጽሐን ጥሬ ለወፀፈ ሰጥቶ መዋጽፍት ይላል፤ የተሳሳተ ነው። አኮ በአሕባል ዘይጠፍሮን ወአኮ በመዋጽፍት ወበሣዕር ዘይከድኖን። ዘእንበለ ዕፅ ወመሬት ወዘእንበለ አሕባለ ጠፈር ወመዋጽፍት። መዋጽፍት ዘዕፅ ፡ (ገድ ፡ ላሊ)።
ሞጻ ፡ (ጻት) ካሳ፤ የበደል ዋጋ፤ ሤጠ ደም መሧዕተ ኀጢአት
፡ (፩ነገ ፡ ፯ ፡ ፫ ፡ ፬ ፡ ፰ ፡ ፲፯)። መሟጫ መፋቂያ፤ ርጥብ ዕንጨት ወይም ጭራ።
ሞጻሕ ት ፡ (ብ መዋጽሕ፤ ት) የመጠጥ መሥዋዕት፤ ወይን ሥልስ፤ ስለ ክብረ አምላክ የሚረጭ የሚፈስ። ወአውጽሖ ሞጻሕተ። አንሥኦ እዴሁ በሞጻሕት። መሥዋዕት ወቍርባን ወሞጻሕት ፡ (፪ነገ ፡ ፳፫ ፡ ፲፮። ሢራ፶ ፡ ፲፭። ሕዝ፵፭ ፡ ፲፯)።
፡ ማፍሰሻ መቅጃ፤ ዋንጫ ጻሕል ጽዋ ፍንጃል፤ የሥልስ ወጭት። መዋጽሕ በዘያወጽሑ ቦቱ። ቤተ መዋጽሕት
፡ (ዘፀ፴፰ ፡ ፲፪። ፳፭ ፡ ፳፬)።
፡ መዋቅር፤ የጣራ የባጥ ዕንጨት፤ ክርክራ። ወመዋጽሕተ ቤትነ ዘአርዝ ፡ (ማሕ፩ ፡ ፲፯)።
ሞፃእት ፡ ዝኒ ከማሁ፤ መውጫ መዝለቂያ ብቅ መባያ፤ ጫፍ መጨረሻ ፍጻሜ
፡ (ዘኍ፴፬
፡ ፬)። መብእስ እበኒሃ ለፍኖተ ኃጥኣን ወጸድፍ ሞፃእታ። ሞፃእቱ ለቅሥት የኀልቅ በመሐላ ፡ (ሢራ፳፩ ፡ ፲። ዕብ፮ ፡ ፲፮)።
ሞጽ ፡ (ዕብ) ትቢያ እብቅ፤ ቀንድ እድፍ ጕድፍ ደቃቅ ነገር።
ሞፈር ፡ በቁሙ፤–ወፊር ወፈረ።
ሞፈር ት ፡ (ብ መዋፍር ት) በቁሙ፤ የርሻ የስምሪት ዕቃ ገበሬ ይዞት የሚሰመር፤ ወፍራም ረዥም። አነ ጸራቢ ወእጸርብ መዋፍረ ወመናብርተ ወካልኣነ። መዋፍርት ዘየሐርሱ ወይመልኁ አሥዋከ ፡ (ስንክ ፡ ግን፳፮። ጥቅ፱)።
ሞፍጥ [1] ፡ (ብ መዋፍጥ) መተኰሻ ማብሰያ፤ ምድጃ እቶን። ዘከመ ያዐውድ ሞፍጦ ፡ (ሢራ፴፰ ፡ ፴)
[2] ፡ መተኰሻ፤–ወፊጥ ወፈጠ።
ሟል ፡ (ዕብ ሙል) ትይዩ አንጻር ፊት ለፊት፤ አኳያ እኩያ አምሳያ። ወዳጅን ባለሟል እንዲሉ፤ በዐረብ ግን ማል ብሎ ገንዘብ ይላል።
No comments:
Post a Comment