ሀ ለ ሐ መ ሠ ረ ሰ ሸ ቀ በ ተ ቸ ኀ ነ ኘ አ ከ ኸ ወ ዐ ዘ ዠ የ ደ ጀ ገ ጠ ጨ ጰ ጸ ፀ ፈ ፐ
ኀ ፡-ዘጠንኛ ፊደል፤ የሆይ ሀ ሦስተኛ፤ የሐውት ሐ ኹለተኛ። ስሙ ኀርም፤ ጸሐፍት ግን ብዙኃን ይሉታል። ዘጠንኛነቱም በመልክ ብቻ እንጂ፤ እንደ ጤት በተራ በፊደልነት አይዶለም፤ ሦስተኛና ኹለተኛነቱም በድምጥና በቅርጥ
ባሠራረዝ ነው። ፀጰ ፀ የጸ ዲቃላ ስለ ኾነ ካባቱ ከጸደይ እንዲደረብ፤ ለብቻው እንዳይቈጠር፤ ኀርም ኀም የሐ ዲቃላ ስለ ኾነ ከሐ ቢደረብ እንጂ ለብቻው አይቈጠርም፤ እንደ ኻያ ኹለቱ ፊደላት መደበኛነት የለውም።
በፊደል ቍጥር ግን ከታው በኋላ ሲጣፍ ኀ ፡-(ሀቀ) ፭፻፤ ፀ ፡-(ወቀ) ፮፻
ይባላል፤ ጰና ፐም ከነዚህ ቀጥለው ይገባሉ። ፭፻ነቱም ኀመሰና ኀምስት ኀምሳ የሚጣፍ በኀርም ነውና፤ ያምስትነት ምስጢር ስላለው ነው። ዳግመኛም በመልክና በተራ ቍጥር ታስዓይ ፊደል ስለ ኾነ፤ ኈ ከፐ በኋላ የ፱፻ አኃዝ እየኾነ በታስዕነት ይጣፋል፤ ይህም
ጰ ፯፻፤ ፐ ፰፻፤ ኈ ፱፻ እያለ መኼዱን ያሳያል፤
አቡጊዳን እይ። በዐረብ ፊደል የኀና የፀ ድምፅ
ከሐና ከጸ ድምፅ ልዩ ሲኾን መልካቸው አንድ ነው፤
ከነቍጣ በቀር መለዮ የለውም፤ ገጐ ከኰ እንደ ማለት ነው። በግእዝ ፊደል ግን የመልክ እንጂ የድምፅ ልዩነት የላቸውም፤ በጥፈት ብቻ ምስጢርና ቃል የቋንቋ ሞክሼ ይለያሉ፤ ልዩነታቸውም የጠፋ ከፍሬ ምናጦስ ወዲህ ነው። ከዚያ በፊት
ግን የኀርም
ኀ ድምፅ እንደዚህ ነበረ
ይባላል፤ ኅኻ ኁኹ ኂኺ ፡-(ኃኻ) ኄኼ ኅኽ ኆኾ፤ ራብዑም ኃ እንደ መልኩ የድምጥና የምስጢር ልዩነት
አለው፤ አፍ ያስከፍታል፤ ዝርዝር ያሳያል።
ኑኅ ኑኃ። ብዝኅ ብዝኃ። በዐረብ ግን ግእዙ ኀ ኸ ይባላል። በዕብራይስጥም
እንደዚህ አኹን እንደ
ጣፍነው የካፍ ድርብ ኹኖ ይነገራል፤
ዕብራውያን ካፍን ነቍጣ ጨምረው ከ፤ ነቍጣውን ትተው ኸ ይሉታል፤ መልኩም ፪ ዐይነት ነው። ባማርኛና በትግሪኛ ካፍን እንደ
ኀርም ኀ፤ ኸ ማለት የዕብራይስጥ ሕግ ነው
እንጂ፤ የዐረብና የግእዝ አይዶለም።
ኀለየ ፡-ለዘበ፤ ዘፈነ፤–ሐልይ ሐለየ።
ኀለፈ ፡-ማለ ተረገመ፤–ሐሊፍ ሐለፈ።
ኀሊል ሎት ፡-(ኀለለ የኀልል ይኅልል። ዐረ ኃለ። ሱር ወዕብ ሓላል) መብሳት፤ መንደል መፈልፈል፤ ውስጠ ክፍት ባዶ ማድረግ፤ እንደ ከበሮ።
ኀሊቅ ቆት ፡-(ኀልቀ የኀልቅ ይኅልቅ። ዐረ ኀሊቀ። ዕብ ሐላቅ፤ ከፈለ) ማለቅ ማርጀት መጨረስ፤ ተካቶ መጥፋት። ኵሉ ግብር ይበሊ ወየኀልቅ ወገባሪሁ የኀልቅ ምስሌሁ። እስከ ኀልቀ ኵኩ ክርታስ በእሳት። ኀልቀ ወይኖሙ። ሐሊቀ የኀልቁ እምገጸ ምድር ፡-(ሢራ፲፬ ፡-፲፱። ኤር፵፫ ፡-፳፫። ዮሐ፪ ፡-፫። ሶፎ፩ ፡-፪)።
፡-ማነስ መጕደል፤ ሕጹጽ መኾን። የኀልቅ ክብሩ ለያዕቆብ። ኢየኀልቅ ወርኅኪ ፡-(ኢሳ፲፯ ፡-፬። ፰ ፡-፳)።
፡-መከፈል መከፋፈል፤ መለየት ልዩ ልዩ መኾን። ኢኀልቀ ሥጋ ዘተደመረ ፡-(ቄር)።
፡-መጨነቅ ለሞት መቅረብ፤ ነፍስ ከሥጋ ልለይ ልውጣ ማለት፤ መቈረጥ፤ የትንፋሽ የነገር። ሶበ ኀልቀት ነፍስየ። ይኅልቅ ነገሩ ፡-(ዮና፪ ፡-፰። መዝ፻፵፩። ጦቢ፯ ፡-፱)። ይባእ ነገረ ክልኤሆሙ ኀበ ፈታሕት በማለት ፈንታ፤ ይኅልቆሙ በበይናቲሆሙ ይላል፤ የመላሽ ስሕተት ነው ፡-(ዘፀ ፡-፳፪ ፡-፱)።
ኀሊው ዎት ፡-(ኀለወ ይኄሉ ይኅሉ) መጠበቅ፤ ዘበኛ የሌሊት። ሌሊተ ኅልዉ ወመዓልተ ተቀነዩ። ይተግሁ ወይኄልዉ። እምተግሀ ወእምኀለወ። ከንቶ ይተግሁ እለ ይኄልዉ። እለ ይኄልዋ ፡-(ነሐ፬ ፡-፳፪። ሉቃ፪ ፡-፰። ፲፪ ፡-፲፱። መዝ ፡-፻፳፮። ሰቈ፬ ፡-፲፬)።
ኀሊፍ ፎት ፡-(ኀለፈ የኀልፍ ይኅልፍ። ዕብ ወሱር፤ ሓላፍ። ዐረ ኀለፈ) ማለፍ ፈጥኖ መኼድ፤ መሻገር መራመድ፤ መራቅ መወገድ። ዘኒ ኀለፈ ወዘኒ ይመጽእ። ወእምድኀረ ኀለፉ እሉ። እምቅድመ ገጹ ኅልፍ ፡-(ሢራ፵፪ ፡-፲፱። ማቴ፪ ፡-፲፫። መክ፫ ፡-፰)።
፡-መሞት መለየት፤ መቅረት። ኀለፈ አሮን ወበከይዎ። አሌ ለነ፤ ካህነ አምላክ ኤርምያስ ኀለፈ እምኔነ። ለዘከመ ዝ የኀልፎ ብዙኅ ረባሕ ፡-(ዘኍ፳ ፡-፳፱። ተረ ፡-ኤር። ሢራ፴፯ ፡-፳)።
፡-መናፈቅ፤ መሻት መመኘት። ኀለሰፈት ነፍስየ ውስተ አድኅኖትከ ፡-(መዝ ፡-፻፲፳)። ደግ መልካም ሲሉ ማለፊያ ማለት ዐማርኛው ከዚህ የወጣ ነው፤ ምኅላፍን እይ። ባለመጣፎች ኀፈን ገባ ይሉና ምስክሩን፤ ኀለፈት ሰንበት። ወየኀልፍ ሐጽ ውስተ ሥጋሁ ይላሉ፤ የተሳሳተ ነው ፡-(ማር፲፮ ፡-፩። ኢዮ፳ ፡-፳፭)። ዳግመኛም በኀለፈ ፈንታ ተኀለፈ ይላል፤ ስሕተት ነው። ዑቅ አልቦ ዘይትኀለፈከ። ኢትትኀለፎ ለዘይስእለከ ፡-(ሄርማ። ሢራ፬ ፡-፫)።
ኀላዊ ፡-(ዊት ውያን ያት፤ ለውት) የሚጠብቅ፤ ጠባቂ። ዘበኛ እረኛ። ኖላዊ ዘመዓልት፤ ኀላዊ ዘሌሊት። ኀላዌ ብዕራይ ፡-(ድጓ። አዋል)።
ኀላዪ ፡-(ዪት ይያን ያት) የሚያስብ ዐሳቢ። ኀላዬ እኩይ ፡-(ሲኖዶ)።
ኀላፊ ፡-(ፊት ፍያን ያት፤ ኀለፍት) የሚያልፍ መንገደኛ፤ ዐላፊ ጠፊ፤ ሟች፤ ተለዋጭ፤ ወረተኛ። ኀላፌ ፍኖት። ኵሉ ኀላፍያን። ዐበጡ አሐደ እምኀለፍት። ዓለም ኀላፊ። መብልዕ ኀላፊ። ዐርክ ኀላፊ ፡-(መዝ ፡-፸፱። ሰቈ፩ ፡-፲፪። ቀሌ። ዮሐ፲፫ ፡-፲፪። ሢራ ፮ ፡-፰)። በኀለፍት ፈንታ ኀላፊት ይላል፤ የተሳሳተ ነው።
ኃል ፡-(ላን ልት ታት)። ፡-(ሐባብ ወ ዐረብ) አጎት፤ ፡-(ኃልት) አክሥት፤ ያባትና የናት ወንድም እኅት። ፡-(ተረት፤ በቅሎ አባቷን ስትክድ) ባዝራ እናቴ፤ ድንጕላ አጎቴ።
(ጥ) ኀልዮ ዮት ኖ ፡-(ኀለየ ይኄሊ የኀሊ። ትግ ሐባ ኀለነ) ማሰብ፤ ከልብ ማንቃት፤ ነገርን ሥራን ከነቢብ ከገቢር በፊት በሐሳብ በልብ መፍጠር ማስገኘት ማሰናዳት። መመርመር መፈለግ፤ ማውጣት ማውረድ። አልቦሙ ልብ ለኀልዮ። ልበ ወሀቦሙ በዘይኄልዩ። ኀለየ መጠነ አሐዱ ሰዓት። ኢተኀልዩ ወኢምንተኒ ፡-(ኩፋ ፡-፳፪። ሢራ፲፯ ፡- ፮። ዳን፬ ፡-፲፮። ፊልጵ፬ ፡-፮)።
ኀልዶ ዶት ፡-(ኀለደ ይኄልድ የኀልድ። ሱር ሕላድ፤ በልብ ተሳበ፤ እባብኛ ኼደ። ዕብ ሓላድ፤ ፋረ ቈፈረ። ዐረ ኀለደ፤ አረጀ) ብዙ ዘመን መኖር መቈየት፤ ዕድሜ ማግኘት። መጨረስ መፍጀት መክተት፤ ዕድሜን ሥራን። መቍረጥ መበጠስ፤ ምክርን ፍርድን። አለደን ተመልከት የዚህ ጎር ነው።
ኀመለ ፡-ለቀመ፤–ሐሚል ሐመለ።
ኀመሰ ፡-ዐመሰ፤ ዋኘ፤–ሐምሶ ሐመሰ።
ኀመየ ፡-ዐማ፤ ነቀፈ፤–ሐምይ ሐመየ።
ኀሙስ ፡-የዕለት ቅጽልና ስም፤ ዐምስት፤ ዐምስተኛ። ተዐገሡ ዓዲ ኀሙሰ መዋዕለ። ወእምድኅረ ኀሙስ መዋዕል። አመ ኀሙሱ ለሠርቅ፤ ቅጽል ፡-(ዮዲ፯ ፡-፴። ፰ ፡-፱። ሕዝ፴፫ ፡-፳፩)። ዕለተ ኀሙስ፤ ምሴተ ኀሙስ፤ ስም። ፡-(ግጥም ስላጤ ቴዎ ሞት) አምላክን መስሎ ቴዎድሮስ፤ ንዑና ሑሩ ሲል ዐሙስ፤ ሰኞ መቅደላ ተጨነቀ፤ ሰው መኾኑ ታወቀ።
ኀማሲ መኀምስ ፡-(ስት ሳን ሳት) ዐምስት የሚያደርግ፤ ካምስት የሚከፍል ከፋይ፤ ዐምስት ባይ።
ኀማዪ ፡-የሚያስር አሳሪ፤ ባለወግ።
ኃምሲት ፡-የኬክሮስ ዐምስቲያ ክፍል በራብዒትና በሳድሲት ማኽል ያለች። አንዲቱ ኃምሲት ስሳ ሳድሲት ትኾናለች፤ ኬክሮስን እይ። በመካነ ሳድሲት ኍልቈ ኃምሲት ፡-(አቡሻ ፡-፲፩)።
ኀምሳ ፡-(ነ–፶) በቁሙ፤ ዐምሳ፤ ፭ ጊዜ ዐሥር፤ ወይም ፲ ጊዜ ዐምስት። ኀምሳ ወኀምስተ መዋዕለ። ኀምሳ በእመት። በዓለ ኀምሳ። ወበኀምሳ ዕለት። ኀምሳ ዓመት አልብከ ፡-(ጦቢ፩ ፡-፳፩። ሕዝ፵ ፡-፲፭። ዲድ ፡-፴። ቅዳ። ዮሐ፰ ፡-፶፯)።
ኃምሳዊ ይ ፡-(ዊት ሲት) ዝኒ ከማሁ። ግዘት ኃምሳይ። ዘአውሰበ ራብዒት አው ኃምሲተ ፡-(ያዕ ፡-ዘእል። ፈ ፡-መ ፡-፭ ፡-፱)።
ኀምስ ፡-የቍጥር ስም በሴት አንቀጽ፤ ዐምስት ማለት ነው። ኀምስ አዋልድ። ኀምስ አህጉረ ግብጽ ይነብባ። ኀምስ ኅብስት። ዐሥሮን ደናግል፤ ወእምኔሆን ኀምስ አብዳት ወኀምስ ጠባባት ፡-(፩ነገ ፡-፳፭ ፡-፵፪። ኢሳ፲፱ ፡-፲፰። ማቴ፲፬ ፡-፲፯። ፳፭ ፡-፪)።
ኃምስ ፡-(ስት) ዐምስተኛ ካምስት አንድ፤ ዐምሾ። ወለደት ወልደ ኃምሰ። ወበኃምስ ትውልድ ዐርጉ እምግብጽ። ኢዮብ ኃምስ እምአብርሃም። በኃምስ ወርኅ ፡-(ዘፍ፴ ፡-፲፯። ዘፀ፲፫ ፡-፲፰። ታሪ ፡-ኢዮ። ኤር፩ ፡-፫)።
ኀምስት ቱ ፡-ዝኒ ከማሁ፤ በቁሙ በወንድ አንቀጽ። ወነበረ በዘከመ ዝ ግብር ኀምስተ ዓመተ። ኀምስቱ ዕደው ነበሩ ምስሌኪ። ኀምስቲነ ፡-(ፊልክ። ዮሐ፬ ፡-፲፰። ስንክ ፡-ሠኔ፲፱)። ቱ ባርቲክልነት ወይም ባጸፋነት ሲፈታ፤ ዐምስቱ፤ ዐምስተኛው፤ ካምስት አንዱ ያሰኛል። ውስተ ኀምስቱ ሰማይ ፡-(ዕር ፡-ኢሳ፰ ፡-፩)።
(ጥ) ኀምሶ ሶት ፡-(ኀመሰ ይኄምስ የኀምስ። ዐረ ኀመሰ። ሱር፤ ወዕብ፤ ሓሜሽ) ዐምስት ማድረግ፤ ካምስት መክፈል፤ እስካምስት ጊዜ መመላለስ። ዘይኄምሶን ለኬክሮሳተ ሰዓታት ከመ ይኩና መዓርገ ጸሎታት ፡-(መጽ ፡-ምስ)።
ኀምራዊ ፡-ዐይነቱ ወይም ቅላቱ የጥቍር ወይን ጠጅ የሚመስል። መሻች፤ መሸተኛ፤ ሸያጩና ገዢው።
ኀምር ፡-(ዐረ) የወይን ጠጅ፤ የጥቍር ቀይ፤ ደባባ።
ኀምዮ ዮት ፡-(ኀመየ ይኄሚ የኀሚ) ማሰር መቀፈድ። ኀመይዎ ለእግዚእነ። አዘዘ የኀምይዎሙ ውስተ ክሣውዲሆሙ ፡-(ማር፲፭ ፡-፩። ዮሐ፲፰ ፡-፲፪። ስንክ ፡-ሠኔ፲፱)።
ኀሠመ ፡-ከፋ፤–ሐሢም ሐሠመ።
ኀሰሰ ፡-ሻ ፈለገ፤–ኀሢሥ ኀሠ፤ ኀሠሠ።
ኀሠሣ ፡-(ሣት) ፍላጎት ፍለጋ፤ ጥያቄ ጥየቃ፤ ምርምር ምርመራ፤ ፈቃድ መፍቅድ፤ ሐሳብ ምኞት። ብየ ኀሠሣ። እምኂሩትክሙ። ንኄሊ በእንቲኣሁ በብዙኅ ኀሠሣ። ተተክለት ፍትወት በጠባይዕ እንስሳዊት፤ ከመ ይትፈጸም ኀሠሣ ተራክቦ ዘእምኔሁ ይከውን ዘርዕ። ይኩን ፈቃዱ ወኀሠሣሁ ከመ ይኩኑ ትሑታነ ፡-(ስንክ ፡-የካ፳፰። አፈ ፡-ድ፪። ፍ ፡-ነ ፡-፳፬ ፡-፩። ፲ ፡-፪)። ጐርፍን ዐሠሣ ማለት ዐማርኛው ከዚህ ወጥቷል።
ኀሠረ ፡-ሰበሰበ፤–ሐሢር ሐሠረ።
ኀሰር ፡-ገለባ ጕድፍ፤–ሐሢር ሐሠረ።
ኀሰት ፡-ውሸት፤–ሐስዎ ሐሰወ።
ኀሠወ ፡-ዋሸ ዐበለ፤–ሐስዎ ሐሰወ።
ኀሢሥ ሦት ፡-(ኀሠ፤ ኀሠሠ የኀሥሥ፤ ይኅሥሥ። ዕብ ሓሻሽ፤ ሐየጸ። ቤቄሽ፤ ፈለገ) ማሠሥ መሟሰስ፤ መጥረግ፤ ማበስ፤ ማደፍ መወልወል፤ የምጣድ። ኢትኅሥሥ አጽሕልተ ወኢትልሐስ መጻብኅተ። ውሒዘ አንብዓ ኀሠሠ በአጽባዕተ እዱ ልምሉም። ወኀሠሠት አንብዕየ በአጻብዒሃ ፡-(ሢራ፴፬ ፡-፲፪። ደራሲ። ድር ፡-መድ)።
፡-መሻት መፈለግ መለመን፤ ለማግኘት። ኅሡ አእዱጊነ።ተኀሥሦሙ ወኢትረክቦሙ። ኅሡ ወአስተብቍዑ ፡-(፩ነገ ፡-፬ ፡-፫። ኢሳ፵፩ ፡-፲፪። ቅዳ)።
፡-መጠየቅ መመርመር፤ ለማወቅ። እለ የኀሡ በእንተ ሕያዋን እምነ ሙታን። ኢትኅሥሥ እፎ ይትሁነኑ። ለኀሢሥ ወለፈቲን በጥበብ ፡-(ኢሳ፰ ፡-፲፱። ሱቱ ፡-ዕዝ፬ ፡-፲፬። መክ፩ ፡-፲፫)።
፡-መውደድ መፍቀድ፤ መከጀል መመኘት። ምስጢሩ ያው መፈለግ ነው፤ ከመሻት አይወጣም። ኅሥሥ ትግበር ኵሎ ዘያሠምሮ ለእግዚ። ኀሰሰ መኰንን ከመ ይክሐዶ ለክርስቶስ ፡-(ዲድ ፡-፩። ስንክ። መጋ፮)። በኀሠሠና በተኃሠሠ ፈንታ ተኀሠሠ ይላል፤ የጣፊና የመላሽ ስሕተት ነው። ኢይትኀሠሥ ሎቱ እኩየ ኵሎ መዋዕለ ሕይወትየ። እትኀሠሥ አባግዕየ እምእደ ኖሎት። እለ ይትኀንሠሡ በእንተ ፍልሰተ ሔኖክ ወኤልያስ ፡-(ኩፋ ፡-፴፭። ሕዝ፴፬ ፡-፲። አፈ ፡-ድ፳፪)።
ኀሲር ሮት ፡-(ኀስረ የኀስር ይኅሰር። ዕብ ሐሳር። ሱር ሕሳር። ዐረ ኀሰረ) መጕደል ማነስ መክሰር። መዋረድ መጐስቈል፤ አይቶ ዐጣ አድጎ አነሰ መኾን። ኀስረ ክብሮሙ። ኢታዕቢ ርእሰከ ከመ ኢትኅሰር። እስመ ኵሉ ዘአዕበየ ርእሶ የኀስር ፡-(ኢሳ፫ ፡-፰። ሢራ፩ ፡-፴። ሉቃ፲፬ ፡-፲፩)።
ኀሢዕ ዖት ፡-(ኀሥዐ የኀሥዕ ይኅሣዕ። ዐረ ኀሸዐ። ዕብ ሐሻህ) ማረፍ፤ ዝም ጸጥ ጫ ማለት፤ አለመታወክ። መብረድ መቀዝቀዝ፤ የቍጣ የጠብ። ኀበ ኢሀሎ መዐትም የኀሥዕ ጋእዝ። መዐት ይኅሣዕ ፡-(ምሳ፳፮ ፡-፳። ቅዳ ፡-ኪዳ)።
ኀሢፍ ፎት ፡-(ኀሠፈ የኀሥፍ ይኅሥፍ። ዐረ ኀሺፈ። ዕብ ሐሳፍ) ማከክ ማቍሰል፤ መላጥ መምለጥ፤ መቅረፍ መግፈፍ፤ መግለጥ።
ኀሣሢ ፡-(ሢት ሥያን ያት) የሚያሥሥ ዐሣሽ። ፈላጊ መርማሪ። ኀሣሤ ነቢብ። ሰካዪ ኀሣሤ ዕዳ ውእቱ። ኀሣሥያነ መንግሥተ ሰማያት። ኀሣሥያተ ንዋየ ባዕድ ፡-(ኢዮ፲፩ ፡-፲፪። ፍ ፡-ነ ፡-፵፫ ፡-፯። ግንዘ። ዲድ ፡-፲፬)።
ኀሳር ፡-(ራት) ሕጸጽ፤ ክ(ኅ) ሳራ፤ ውርደት መከራ፤ ዕጦት ጕዳት፤ ጕስቍልና። ኀሳር ዐቢይ። ኀሳርከኒ ወክብርከኒ እምቃልከ። መዋዕለ ኀሳራ። ጽኑሕ ሎቱ ኀሳር ዕጹብ። ፍትወት እሞን ለኀሳራት ወለድካማት፤ ፡-(ኩፋ ፡-፲፪። ሢራ፭ ፡-፲፫። ኢዮ፲፰ ፡-፲፪። ፍ ፡-ነ ፡-፳፬ ፡-፩)።
ኀሥል ፡-ዳውላ፤–ሐሲል ሐሰለ።
ኀስል ፡-ዳውላ፤–ሐሲል ሐሰለ።
ኀሥረ ፡-ጐሰቈለ፤–ኀሲር፤ ኀስረ።
ኀረመ [1]:-ተወ፤–ሐሪም ሐረመ።
[2]፡-ኀረመ፤ ፡-(ኀረወ) ጣፈ፤ ነደፈ በገረ፤ አመለከተ፤ ከመቅረጥና ከመፈልፈል በፊት። የኀረወን ፍች ተመልከት።
ኀረሠ [1]:-ዐረሰ፤–ሐሪስ ሐረሰ።
[2]:-ወለደ፤–ኀሪስ ኀረሰ።
ኀረወ ፡-ቈፈረ፤–ሐሪው ሐረወ።
ኀረደ ፡-ዐረደ፤–ሐሪድ ሐረደ።
ኀረፋ ፡-ዐረፋ፤–ሐረፋ።
ኀሪስ ሶት ፡-(ኀርሰ፤ ኀረሰ የኀርስ ይኅ(ረ) ርስ) መውለድ መጨቀል፤ ዐራስ እመጫት መኾን። ኢበፀኒስ ወኢበኀሪስ። አመ ዕለተ ኀሪሳ ለእምከ። እማቲሆሙ እለ ኀረሳሆሙ። አባግዕ ወዕጐላት የኀርሳ ፡-(ኦርጋ። መጽ ፡-ምስ። ኤር፲፮ ፡-፫። ዘፍ፴፫ ፡-፲፫)። መወለድ፤ ከማሕፀን መውጣት፤ ርጥብ ጨቅላ መኾን። ዐራስ ልጅ እንዲሉ።
ኀሪው ዎት ፡-(ኀረወ የኀሩ ይኅሩ። ዐረ ኀረተ። ዕብ ሓራት። ሱር ሕራት) መብሳት መንደል፤ መፈልፈል፤ መቅረጥ ማንጠጥ፤ ማስመጥ ማሳበጥ፤ የደንጊያና የንጨት የብረት።ዕርሻና ቁፋሮም ያሳያል። እለ ይገልፉ ወየኀርዉ ዐይነ ማኅተም፤ ኀሪወ ማኅተም። እብን ዘኀረዎ ኬንያ ፡-(ሢራ፴፰ ፡-፳፯። አዋል)። ኀረመንና ኀንፈጠን እይ፤ ኀረመ የዚህ መንቲያ ነው።
ኀሪፍ [1]፡-(ዐረብ። ዕብ ሖሬፍ) ጸደይ፤ ያመት ሩብ የዘመን ርቦ፤ በሐጋይና በክረምት መካከል ያለ ወራት። ፪ኛም ከክረምት ደርበው መንፈቀ ዓመት ይሉታል፤ ይኸውም ከጥቅምት እስከ ሚያዝያ ማለት ነው፤ ባገራችን ግን ከሚያዝያ እስከ ጥቅምት ይኾናል።
[2]፡-ኀሪፍ፤ ዘንድሮ ይህ ዓመት፤ መላው ፲፪ቱ ወር። ኅድጋ ኀሪፈኒ ፡-(ሉቃ፲፪ ፡-፰)። ገሪፍ ወኀሪፍ፤ ዓምናና ዘንድሮ።
ኀሪፍ ፎት ፡-(ኀርፈ የኀርፍ ይኅርፍ። ዐረ ኀረፈ። ዕብ ሓራፍ፤ ከረመ) መልቀም መሰብሰብ፤ የፍሬ። መክረም፤ ክረምት እስኪወጣ መቈየት።
ኀራሲ መኀርስ ፡-የሚያርስ ዐራሽ፤ ቀላቢ መጋቢ፤ ተከባካቢ።
ኀራስ ፡-(ሳት) በቁሙ፤ ዐራስ ወላድ፤ ትኵስ እመጫት፤ የጨቅላ እናት፤ የምታጠባ። ብእሲት ኀራስ። እምኀራስ ወትክት። ድብ ኀራስ። ወተመጠዎ እምድኅረ ኀራሳት ፡-(ቄድር። ቀሌ። ፪ነገ ፡-፲፯ ፡-፰። መዝ ፡-፸፯)።
፡-ጨቅላ ርጥብ ልጅ፤ ለጋ ቀንበጥ ቅቤ የሚውጥ፤ ጡት የሚመጥ የሚመጠምጥ። ባማርኛ ልማድ ለወንድም ለሴትም ይከታል፤ በግእዝ ግን ለሴት ብቻ ነው።
ኀራዊ ፡-(ዊት ውያን ያት፤ ረውት) የሚሥል፤ የሚቀርጥ። ኀራዌ ማኅተም ፡-(አዋል)።
ኀራውያ ፡-ሕሪያ፤–ሐረወ።
ኀራዪ ፡-(ዪት ይያን ያት) የሚመርጥ፤ መራጭ። ኀራዬ ሰዓት ወኀራዬ ዕለታት ፡-(ቈስጠ)።
ኀርም ፡-የፊደል ስም፤ ፫ኛ ኀ፤ ልዩ ብቸኛ፤ ኄር ኂሩት።
(ጥ) ኀርሶ ሶት ፡-(ኀረሰ፤ ይኄርስ፤ የኀርስ) ማረስ፤ መቀለብ፤ መመገብ፤ መከባከብ፤ ያራስ የመጫት የወይዛዝር። አዘዘ የኀርስዎሙ። እለ የኀርስዎሙ። ኀረስኩኪ በስንዳሌ ፡-(ዳን ፡-፩ ፡-፭። ኤር፳፮ ፡-፳፩። ሕዝ፲፮ ፡-፲፫)።
ኀርይ ዮት ፡-(ኀረየ፤ ኀርየ። ዐረ ኀረ። ዕብ ባሓር) መምረጥ ማሻሻል፤ መውደድ ማቅረብ፤ ለሹመት ለሥራ። ፡-(ተረት) ከሰው መርጦ ለሹመት፤ ከንጨት መርጦ ለታቦት። አኮ አንትሙ ዘኀረይክሙኒ፤ አላ አነ ኀረይኩክሙ ወሤምኩክሙ። ሕዝብ ዘኀረየ ሎቱ ለርስቱ። ዘበዳዊት ተነበየ ወበዮሐንስ ጥምቀተ ኀርየ ፡-(ዮሐ፲፭ ፡-፲፮። መዝ ፡-፴፪። ድጓ)። ኀረየ ባለው ዘንዱን ይኅሪ፤ ኀርየ ባለው ይኅረይ ይላል፤ የቀተለና የገብረ አካኼድ ነው።
ኀቀፈ ፡-ዐቀፈ፤–ሐቂፍ ሐቀፈ።
ኀበ ፡-(ዐቢይና ደቂቅ አገባብ) ዘንድ፤ የ፤ ቦዝና ከመ፤ እየ ሲ ይኾናል። ወኀበ በዝኀት ኀጢአት ህየ ፈድፈደት ጸጋሁ ለእግዚ፤ ኀጢአት ከበዛች ዘንድ። ኀበ ጸንዐ ክረምት ይበዝኁ አንቅዕት ፡-(ሮሜ፮ ፡-፳። ዘረፋ)። የ ሲኾን የቦታ ቅጽል ነው፤ በቂም ይኾናል። ወንሰግር ውስተ መካን ኀበ ቆመ እግረ እግዚእነ። ዘየኀድር ውስተ ብርሃን ኀበ አልቦ ዘይቀርቦ። ከመ ተሀልዉ ኀ ሀሎኩ አነ ፡-(መዝ ፡-፻፴፩። ውዳ ፡-፫። ዮሐ፲፬ ፡-፫)። የነቱን ፡-(መኾኑን) ደግሞ የቦታ ቅጽል ስለ ኾነ እምና እንተ በ ገብተውም ሳይገቡም ይበዘብዙታል፤ አንዳንድ ጊዜም አዳማቂ ኹነው ይቀራሉ። ቦ ብሔር እምኀበ ይወፅእ ብሩር፤ የሚወጣበት። ኢየአምር እንተ ኀበ አሐውር፤ የምኼድበትን። አልቦ በኀበ ኢይከብር ነቢይ፤ የማይከብርበት። ቦዝና ከመ ሲኾን በኀላፊ ይገባል ፡-(ማር፲፮ ፡-፬። ሉቃ፳፬ ፡-፪)። እየና ሲ ሲኾን በደጊም በትንቢት ይገባል። ቤተሳኦል ኀበ ኀበ ይትነሠት ሖረ፤ ወቤተ ዳዊትሰ ኀበ ኀበ ይጸንዕ ፤ እየ እየ። ኀበ ኀበ ይተብዕ ይትቃተል፤ ኀበ ኀበ ይፈርህ ይጐይይ፤ ኢ ሲ። በዚህ አፈታት መንገዱ የእንዘ ነውና፤ በሩቅ በሩቁ የተባለው በቅርብ በቅርቡ ስስ ሳሳ ይኾናል። ኀበ ኀበ እ(ት) ፈርህ፤ ስስ። ኀበ ኀበ እረብ ፡-(ኢት) ሳሳ። በ ግእዝ መኾኑ ሲናበብ ብቻ ነው፤ ሲረባና ሲዘረዘር ግን፤ ኀቤየ ፡-(ከ ኪ ሁ ሃ) እያለ ወደ ኃምስነት ይለወጣል። ደቂቅ ሲኾን ደግሞ በቦታ በአካል እየገባ ዘንድ ፥ አጠገብ ፥ ወደ ይኾናል፤ ዘንድና አጠገብ በምስጢር ፩ ነው። እንተ ሀለወት ኀበ አብ። ነበረ ኀበ ዐዘቅት። አሐውር ኀበ አብ ፡-(፩ዮሐ ፡-፩ ፡-፪። ዮሐ፬ ፡-፮። ፲፮ ፡-፲)። አንዳንድ ጊዜም ለና በ አዳማቂና በቁም ቀሪ ኹነው ያጋንኑታል። ባሕታውያን ተመያጥያን ለኀበ ዓለም፤ ወደ። ተላውያን ለኀበ ቃሉ፤ ቃሉን ወይም እንደቃሉ ያሰኛል። ይሠየም ለኀበ እግዚአብሔር፤ ወደግዜር ለሚደርስ ነገር። ብዕል ዘይትዐቀብ በኀበ ዘአጥረዮ፤ ዘንድ። ሠረገላ በኀበ ይጼዐን፤ አዳማቂ ፡-(ፊልክ ፡-፭። ፫። ዕብ፭ ፡-፩። መክ፭ ፡-፲፪። ሔኖ፸፫ ፡-፪)። ዳግመኛም እስከ፤ እም፤ ቅድም በማለት ፈንታ ለኀበ በኀበ ይላል፤ የመላሽ ስሕተት ነው። መርሕ ለኀበ ክርስቶስ። ኢትንሥኡ ቤዛ በኀበ ቀታሊ። ዘበኀበ ሰብእ ዐቢይ፤ በኀበ እግዚ ትሑት ወርኩስ ፡-(ገላ፫ ፡-፳፬። ዘኍ፴፭ ፡-፴፩። ሉቃ፲፮ ፡-፲፭)። ዕር፲፱ ፡-ቍ፸ ተመልከት።
ኀበበ [1]:-ሰደበ፤–ሀቢብ ሀበበ።
[2]:-ወደደ፤–ሐቢብ ሐበበ።
[3]፡-(ሐንበበ) ዐሸ ረገጠ፤ ጠመቀ፤ የወይን የዘይት። ኬደንና ዐጸረን እይ።
ኀበየ ፡-ኀበየ፤–ጠበቀ፤–ሐብይ ሐበየ።
ኀቢር ሮት ፡-(ኀበረ፤ ኀብረ የኀብር ይኅበር። ዕብ ሓቤር። ሱር ሓባር) ማበር፤ ማሤር አንዱ ካንዱ ጋራ መግጠም መዋደድ መሰማማት፤ መጨመር ዐብሮ መቈጠር፤ ፩ ልብ ፩ ሐሳብ መኾን። ኀበሩ ቃለ ነቢያት። ወአሶርሁ ኀብረ ምስሌሆሙ። ኢትኅበር ምስለ ኃጥኣን ለእመ በዝኁ። ሀበነ ንኅበር በዘዚኣከ መንፈስ። እለ የኀብሩ በሕጋ ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን ፡-(ድጓ። መዝ ፡-፹፪። ሢራ፯ ፡-፲፪። ቅጻ። ቀሌ)።
ኀቢን ኖት ፡-(ኀበነ የኀብን ይኅብን። ዐረ ኀበነ) መሸጐጥ መክተት፤ ከኪስ ከሴደርያ ማግባት፤ የስዓት የገንዘብ የማረሚያ። ማጥለቅ መልበስ፤ ሰውነትን በቀሚስ መክተት። ራስን ማሰር፤ መጠምጠም።
ኀቢእ ኦት ፡-(ኀብአ የኀብእ ይኅባእ፤ ከበተ። ዕብ ሓባእ፤ሐባሀ፤ ታባ። ዐረ ኀባ) ማባት መሰወር መደበቅ መሸሸግ፤ እንዳይታይና እንዳይገኝ እንዳይታወቅ ማድረግ፤ መሸጐጥ መቅበር። እግዚ ኀብኦ ለሔኖክ። ኀብአ ርእሶ። ኀብአ ለመለኮቱ። ኀብአ እዴሁ ሀካይ ውስተ ሕፅኑ። ኅብኦሙ ኅቡረ ውስተ ምድር ፡-(ሢራ፵፬ ፡-፲፮። ውዳ ፡-፯። ድጓ። ምሳ፳፮ ፡-፲፭። ኢዮ፵ ፡-፰)። ከበተንና ሰወረን እይ፤ የዚህ ጎሮች ናቸው።
ኀቢዝ ዞት ፡-(ኀበዘ የኀብዝ ይኅብዝ። ዐረ ኀ ኸበዘ) ማበዝ መጋገር፤ ሊጥን ወደ እቶ ማግባት፤ በምጣድ ላይ ማፍሰስ ማብሰል። ኀበዙ ኀሪጾሙ። እቶን ዘአንደዱ ለኀቢዘ ኅብዝት።ረሰየ ሄሮድስ ሰብአ ብዙኃነ ለኀቢዘ ኅብዝት ወአዘዞሙ ከመ ይኅብዙ ወትረ ፡-(ዘፀ፲፪ ፡-፴፱። ሆሴ፯ ፡-፬። ዮሴፍ)።
ኀባሊ ፡-(ሊት ልያን ያት) ደፋር ጨካኝ። ደፋሪ ወኀባሊ። እምሰብእ ዐማፂ ወኀባሊ ባልሐነ ፡-(ቄድር። ሊጦን)።
ኀባሪ ፡-(ሪት ርያን ያት) የሚያብር ዐባሪ፤ ሤረኛ ዐድመኛ፤ መሳይ።
ኀባኢ ፡-(ኢት እያን ያት) የሚያባ የሚሸሽግ ሸሻጊ፤ ታዳጊ።መንጦላዕት ኀባኢተ መለኮት ፡-(ቅዳ)።
ኀባዚ ፡-(ዚት ዝያን ያት፤ በዝት) የሚያብዝ፤ ዐበዛ ጋጋሪ።ሊቀ ኀባዝያን ፡-(ዘፍ፵ ፡-፩)።
ኀብለ ፡-ዐበለ፤–ሐቢል ሐብለ።
ኀብሎ ሎት ፡-(ኀበለ ይኄብል የኀብል። ዐረ ኀቢለ) መክፋት መጨከን፤ ማበድ መወግሸት፤ መድፈር አለማፈር፤ የማይገባውን መናገር መሥራት፤ ይገባኛል ማለት። መጽሐፍ ግን በኀበለ ፈንታ ተኀበለ ይላል ስሕተት ነው። እፎ እንከ ተኀበለ ልብከ። ተኀበሉ አግብርት ወወረዱ ላዕሌነ። ደንገፁ ፋርስ እምተኀብሎታ። ቀሲስ ዘተስዕረ በርትዕ በእንተ ኀጢአቱ ወእምዝ ተኀበለ ላዕለ ግብረ መልእክት። ዘተኀበለ ከመ ያውስብ ራብዓየ ፡-(ኢዮ፲፭ ፡-፲፪። ዮዲ፲፬ ፡-፲፫። ፲፮ ፡-፲። ፍ ፡-ነ ፡-፮። ፈ ፡-መ ፡-፭ ፡-፲)።
ኀብጠ ፡-ዐበጠ፤–ሐቢጥ ሐብጠ።
ኀተተ ፡-መረመረ፤–ሐተተ።
ኀቲም ሞት ፡-(ኀተመ የኀትም ይኅትም። ዕብ ሓታም። ሱር ሕታም። ዐረ ኀተመ) ማተም፤
መዝጋት መቈለፍ፤ ማሸግ። እመ ኀተምከ ወርቀከ ወብሩረከ። ሠናይ ኀቲም ላዕለ ብእሲት እኪት ፡-(ሢራ፳፰ ፡-፳፬። ፵፪ ፡-፮)።
፡-መጣፍ መቍጠር፤ ጥፎ ቈጥሮ
ማኖር። ኀተምከኑ ውስተ ቍናማቲከ ጌጋይየ ፡-(ኢዮ፲፬ ፡-፲፯)።
፡-መሸፈን ማልበስ መሰወር፤ መተው።
ወገጸ ከዋክብት የኀትም። ኅትሞ ለዝ ራእይ። ኅትም ወኢትጽሐፍ ዘንተ ፡-(ኢዮ፱ ፡-፯። ዳን፰ ፡-፳፮። ራእ፲ ፡-፬)።
፡-ስምን መጣፍ ማመልከት፤
በብርዕ በቀለም ወይም በማኅተም፤
ማኅተምም ባይኖር
የጥፈትና ያውራ ጣት
ምልክት ፊርማ ማድረግ። ኀተመ ንጉሥ በሕልቀቱ። ወኀተምዋ ለእብን ፡-(ዳን፮ ፡-፲፯። ማቴ፳፯ ፡-፳፮)።
፡-ማጥቈር መክተብ፤ ገላን ጥቍር
ቀለም ቀብቶ በመርፌ በሾኽ መንቀስ መጠቅጠቅ። ኢትኅትሙ አባለክሙ በመርፍእ ፡-(ፍ ፡-ነ ፡-፵፭)።
፡-መጨረስ መፈጸም። ኢይፃኡ እምቤተ ክርስቲያን ዘእንበለ ይኅትም ካህን። ይኅትሙ ጸሎቶሙ በጸሎተ እግዝእትነ ማርያም ፡-(ቀሌ። ፍ ፡-ነ ፡-፲፬)።
፡-መመስከር፤ ማስረዳት ማጽናት፤ የነገር። እስመ ለዝስ እግዚአብሔር ኀተሞ። አኀትም
ቃላትየ በጽድቅ ፡-(ዮሐ፮ ፡-፳፯። ቄር)።
፡-መቅባት መቀደስ ማክበር፤ በሜሮን። የኀትም አንፈ ወፍጽመ ልበ ወእዝነ። እመ ቦ ቀሲስ ዘኀተማ በቅብዕ ቅዱስ ፡-(ኪዳ። ፈ ፡-መ ፡-፭ ፡-፲፪)። የኀተመን ፍች ፲፱ ብለው የሚቈጥሩ አሉ፤ ምስክራቸው አያጠግብም። ከተመንና ዐተበን እይ፤ የዚህ ጎር ነው።
ኀቲው ዎት ፡-(ኀተወ የኀቱ ይኅቱ። ዕብ ያቃድ። ሱር ዪቃድ። ዐረ ወቀደ) መቃጠል መንደድ፤ ቦግ ቱግ ብልጭ ቍልጭ ማለት፤ መብራት ብርሃን መኾን ፡-(መዝ ፡-፲፯። ኢሳ፷፪ ፡-፩)። ቅድሜሁ የኀትዉ ሰብዑ መኃትው። ዕንቍ ዘየኀቱ። ርእየተ ገጽከ አምሳለ መብረቅ ኀተወ ፡-(ራእ፬ ፡-፭። ዘፍ፪ ፡-፲፪። ስንክ ፡-ነሐ፲፫)።
ኀታሚ ፡-(ሚት ምያን ያት) የሚያትም። ዐታሚ፤ ባለማኅተም። ዓለመ ኀታሚ። ፈጣሪ አስመሳይ፤ ፍጥረቱን በፍጥረት የሚያትም ፡-(ኪዳ)።
ኀነፊ ፡-ሐናፊ፤ ፡-(ዕብ ሐኔፍ። ሱር ሐንፋእ፤ ሐንፋያ) ዐላዊ ከሓዲ፤ ሸንጋይ አታላይ፤ ግብዝ አረመኔ፤ ስመ ነገድ ካራቱ ነገደ ተንባላት አንዱ፤ የቀሩትም ሦስቱ ሐንበሊ መለኪ ሸፍዒ ይባላሉ። ሃይማኖታቸውም እንደ ስማቸው አራት ነው፤ አይተባበርም። እምውሉደ ኀነፊ አረማውያን ፡-(ስንክ ፡-ግን፯)።
ኀነፋዊ ፡-(ዊት ውያን ያት) የኀነፊ ወገን፤ አረመኔ ተንባላታዊ። ወበመዋዕሊሁ አስተርአየት አሐቲ ብእሲት ኀነፋዊት። ንጉሠ ምስር ኀነፋዊ ፡-(ዮሐ ፡-መደ። ስንክ ፡-ጥቅ፳፩)።
ኀኒቅ ቆት ፡-(ኀነቀ የኀንቅ ይኅንቅ። ዐረ ኀነቀ። ሱር ሕናቅ። ዕብ ሐናቅ) ማነቅ ማስጨነቅ፤ ጕረሮን ዐንገትን አጥብቆ ሰቅስቆ መያዝ ማሰር ለመግደል፤ አፍን አፍንጫን ማፈን መድፈን፤ ትንፋሽ መከልከል። ዐነቀን እይ፤ የዚህ ጎር ነው፤ ለክፋም ለበጎም ይኾናል፤ ኀነቀ ግን ለክፉ ብቻ ነው ፡-(ማቴ፲፫ ፡-፯። ፲፰ ፡-፳፰። ፩ነገ፲፯ ፡-፴፭)። ኀነቀኒ አፈ መልስየ። ኀነቆ መንፈስ እኩይ። ወሰዶ እንዘ የኀንቆ ክሣዶ ወያረውጾ ጕጕአ። ንኅንቃ ለነፍስነ ወንለጕማ ከመ ፈረስ ኀያል ወድሩክ ፡-(ኢዮ፴ ፡-፲፰። ፩ነገ ፡-፲፮ ፡-፲፬። ገድ ፡-ተክ። አፈ ፡-ተ፴፩)።
ኀናቂ ፡-(ቂት ቅያን ያት፤ ነቅት) የሚያንቅ ዐናቂ፤ ዐንቆ ገዳይ።
ኀንቦ ፡-አንቦ፤–ነብዐ አንብዕ።
ኀንገረ ፡-ዐነከሰ ዐንካሳ ኾነ። ተሸከመ፤ እንኮኮ ወይም አሽኮኮ አለ። እግር ለሌለው እግር ኾነ ማለት ነው፤ በገድል በታምር በድርሰት ይገኛል።
ኀንገር ፡-(ዕብ ሒጌር) ዐንካሳ ልምሾ ጥምልምል፤ የሚድኽ የሚንፏቀቅ። ግሔ ሽኮኮ እግረ ኵንትሽ፤ ዐጫጭር። ገሐየን እይ።
ኀንጽጾ ጾት ፡-(ኀንጸጸ የኀነጽጽ የኀንጽጽ። ሐንፈጸ) መጠርጠር ማውለብ፤ በጥርስ። ማንጠርጠር ማበጠር ማንዘርዘር፤ በሰፌድ በወንፊት ፡-(ሉቃ፳፪ ፡-፴፩)። ማንጠጥ መቅረጥ፤ የቀንድና የንጨት።
ኀንፈጠ [1]:-ጫረ ጐፈጨረ፤–ሐንፈጠ።
[2]:-ቀረጠ፤–ኀፊጥ ኀፈጠ።
[3]፡-(ስሯጽ ግስ) ዐተመ፤ በማኅተም መታ ረገጠ፤ ፈረመ። ወይም ሣለ መሰለ፤ ነደፈ ቀረጸ፤ በማኅተም ላይ።
ኀንፈጸ ፡-አጐለበ፤–ነፍጸ ሐንፈጸ።
ኀወ ፡-ኀወወ፤ ፡-(ኀዊው። ከዊው ከወ፤ ከወወ) ከፈተ ከፋፈተ፤ ተከፈተ ክፍት ኾነ።
ኀወጸ ፡-ጐበኘ፤–ሐውጾ ሐወጸ።
ኀዊሥ ሦት ፡-(ኆሠ፤ ኀወሠ፤ የኀውሥ ይኁሥ) መቀላቀል መደባለቅ፤ አንዱን ካንዱ ጋራ መለወስ መቀመም፤ እንደ ውሃና እንደ መሬት እንደ መድኀኒት።
ኀውሥ ፡-ዝኒ ከማሁ። ቅልቀላ ድብለቃ፤ ቅልቅልነት፤የባሕርይ ፍልሰት። ዘእንበለ ኀውሥ ፡-(ቄር ፡-ገ፳)።
ኀዘለ ፡-ዐዘለ ተሸከመ፤–ሐዚል ሐዘለ።
ኀዘነ ፡-ዐዘነ፤–ሐዚን ሐዘነ።
ኀዘዘ ፡-ዐነቀ አስጨነቀ፤–ሐዚዝ ሐዘዘ።
ኀዝል ፡-(ዐረ እልኀዚል) ጣብ የጨዎታ ስም፤ በጠጠር ወይም በተነጠጠ ዕንጨት የሚጫወቱት ጨዎት፤ እንደ ገበጣና እንደ ሰንጠረዥ ያለ ፡-(ፍ ፡-ነ ፡-፵፫ ፡-፲፪)።
ኀዝዐ ፡-ነዳ አባረረ፤--ሐዚእ ሐዝአ።
ኀየል ፡-ዋሊያ፤–ሀየል።
ኀየሠ ፡-ተሻለ፤–ኀዪስ ኀየሰ።
ኀዪል ሎት ፡-(ኄለ የኀይል ይኂል። ዕብ ሓል ያሒል) መጮኽ ቡታ መስደድ፤ ድረሱልኝ ማለት፤ ከምጥና ከጭንቅ የተነሣ። ሕዝብን ሰራዊትን በጩኸት በቀንዳ መለከት መሰብስብ መጥራት፤ ወይም መጠራት ተካቶ መሰብሰብ። ወኄለ ኵሉ ሕዝብ ወተለውዎሙ ፡-(ኢያ፰ ፡-፲፮)።
ኀዪስ ሶት ፡-ኀየሰ ይኄይስ ይኂስ። ኄረወ) መሻል መብለጥ። ይኄይሰኒ መዊት እምሐዪው። ይኄይሰክሙ እሑር። ፈሪሀ እግዚ እምኵሉ ትኄይስ ፡-(ጦቢ፫ ፡-፮። ዮሐ፲፮ ፡-፯። ሢራ፳፭ ፡-፲፮)።
፡-ማማር መወፈር፤ ማሸብረቅ፤ ኀየሰት ነፍስቶሙ ወሠነየት ራእዮሙ ፡-(ዳን፩ ፡-፲፭)። በኀየሰ ፈንታ ተኀየሰ ይላል፤ ስሕተት ነው። ኢትፍቅድ ተኀይሶ እምኔሆሙ፤ አላ ኩን ዕሩየ ምስሌሆሙ ፡-(ሲኖዶ)።
ኀዪር ሮት ፡-(ኄረ፤ ኀየረ የኀይር ይኂር። ዐረ ኃረ) መቸር፤ መለገስ፤ ፊት ለፊት እያዩ እያሳዩ መስጠት ማቅረብ፤ ማደል ማሳለፍ።
ኀዪጥ ጦት ፡-(ኄጠ የኀይጥ ይኂጥ) መሸንገል መደለል ማባበል፤ በምክር በነገር ማሳት ማታለል። በመብልዑ የኀይጠከ። ኄጥዎሙ ለሕዝብ ወኦሆ አበልዎሙ። ዑቁ ኢይኂጡክሙ በተጥባበ ነገር። ኄጦሙ ለሰብእ በነገረ የውሀት ፡-(ሢራ፲፫ ፡-፯። ማር፲፭ ፡-፲፩። ቈላ፪ ፡-፰። ገድ ፡-ተክ)።
ኀያል ፡-(ላን ላት የልት) በቁሙ፤ ኀይለኛ ዐርበኛ፤ ጥኑ ብርቱ ጠንካራ፤ ጕልበታም። ኢይዘኀር ኀያል በኀይሉ። ነፋስ ኀያል። እብነ አድማስ ኀያል። እግዚአ ኀያላን። ሠለስቱ ኀየልት ፡-(ኤር፱ ፡-፳፫። ኢሳ፲፩ ፡-፲፭። ቅዳ። መዝ ፡-፵፯። ፩ዜና ፡-፲፩ ፡-፲፬። ፪ዜና ፡-፳፫ ፡-፳)።
፡-ዐያሌ ብዙ፤ እጅግ። ፡-(ግጥም፤ በራስ ዐሊ ጊዜ) አንድ ሰው ሞተ አሉ በጋሎች ከተማ፤ ዐያሌ አይሞትሞይ ደስ እንዲለኝማ ፡-(አያ ፡-ዐሊ)።
ኀያጢ ፡-(ጢት ጥያን ያት) የሚሸነግል፤ ሸንጋይ፤ አታላይ።
ኀይል ፡-(ላት) በቁሙ፤ ጕልበት ብርታት፤ ጥናት ጥንካሬ፤ ችሎት። እመ ደክመ ኀይሉ ወስእነ። በኵሉ ኀይልየ። ኀይላቲሁ ዘውስጥ ፡-(ሢራ ፡-፲፱ ፡-፳፰። ዘፍ፴፩ ፡-፮። ፍ ፡-ነ ፡-፵፭)።
፡-ታምራት ድንቅ ሥራ። ኀይላተ ብዙኀ ገበርነ። አህጉር እለ በውስቴቶን ገብረ ኀይለ ብዙኀ። በእንተ ኵሉ ዘርእዩ ኀይል ፡-(ማቴ፯ ፡-፳፪። ፲፩ ፡-፳። ሉቃ፲፱ ፡-፴፯)።
፡-ብዕል፤ ብዙ ገንዘብ፤ ጥሪት ድልብ። ኀይለ ደማስቆ። እለ በልዑ እምነ ኀይላ። በጽንዕየ ገበርኩ ሊተ ዘንተ ኀይለ ዐቢየ ፡-(ኢሳ፰ ፡-፬። ራእ፲፰ ፡-፫። ዘዳ፰ ፡-፲፯ ፡-፲፰)።
፡-ዕውቀት፤ ሰማያዊ ጸጋ፤ መንፈሳዊ ሀብት። ኀይል ታኄይል። እስከ ትለብሱ ኀይሰ ፡-(መክ፲ ፡-፲። ግብ፩ ፡-፰። ግብ፩ ፡-፰)።
፡-ሰራዊት ጭፍራ የጦር ሕዝብ፤ ጓዝ። ኢዮአብ መልአከ ኀይል። በኀይል ክቡድ። ኀይለ ሰማያት። ኀይላት ዘዝ ዓለም ፡-(፫ነገ ፡-፪ ፡-፳፪። ፲ ፡-፪። ማቴ፳፬ ፡-፳፱። ዕር ፡-ኢሳ፬ ፡-፬)።
ኀይሎ ሎት ፡-(ኀየለ ይኄይል የኀይል) ማየል መበርታት፤ መጐልበት ኀይለኛ መኾን፤ መድፈር፤ ማሸነፍ። ጽንዑ ወኀይሉ። በዘይኄይል ድካምየ። ወሬዛ ዘይኄይላ ለድንግል ፡-(፪ነገ ፡-፲ ፡-፲፪። አርጋ። ቀሌ)።
፡-መብዛት መበርከት፤ ዐያሌ መኾን። ድምፀ መጥቅዕ ይበልኅ ወይኄይል ጥቀ። ወኀየለ ቃሎሙ። እስከ ኀየሎሙ ደም ፡-(ዘፀ፲፱ ፡-፲፱። ሉቃ፳፫ ፡-፳፫። ፫ነገ ፡-፲፰ ፡-፳፰)። በገበረ ፈንታ ተገበረ እንዲል በኀየለም ፈንታ ተኀየለ ይላል፤ ስሕተት ነው። ተኀየሉ ከመ ትባኡ። ጽገዑ ወተኀየሉ። እለ ይትኄየሉ። በፈቃድ፤ አው በተኀይሎ። ተኀየሉ ንዋየ ቤተ ክርስቲያን ፡-(ሉቃ፲፫ ፡-፳፬። ፪ዜና ፡-፴፪ ፡-፯። ዘፀ ፡-፲፰። ቄድር ፡-ገ፴። ቀሌ)።
ኀይመት ፡-(ታት። ዐረ ኀይም፤ ኀይመት) ድንኳን፤ ማደሪያ ከፀምር ከክታን ከማእስ የሚሠራ፤ የጓዝ የሰፈር ቤት የሚነቀል። የሚተከል፤ የሚታጠፍ የሚዘረጋ ፡-(ዘፍ፲፰ ፡-፩ ፡-፮። ዕብ፲፩ ፡-፱። ማሕ፩ ፡-፭)። ጳውሎስ ኮነ መስተገብረ ኀይመት። ዐረብ እለ ይነብሩ በኀይመታት ፡-(አፈ ፡-ተ፳፮። ሲኖዶ)።
ኀደመ [1]:-አንቀላፋ፤–ሀዲም ሀደመ።
[2]፡-ኀደመ፤–ተረተ፤–ሐድሞ ሐደመ።
ኀደየ ፡-አበሰለ፤–ሀድይ ሀደየ።
ኀዲር ሮት ፡-(ኀደረ የኀድር ይኅድር፤ ቤተ። ዕብ ሓዳር። ዐረ ኀደረ) ማደር፤ ከሠርክ እስከ ነግህ ባንድ ቦታ መኖር፤ ተኝቶ ተጋድሞ ሌሊትን በንቅልፍ ማሳለፍ። ገሐሡ ቤተ ገብርክሙ ወኅድሩ፤ ወይቤልዎ ነኀድር ውስተ መርኅብ። ረቢ አይቴ ተኀድር፤ ወርእዩ ኀበ የኀድር ፡-(ዘፍ፲፱ ፡-፪። ዮሐ፩ ፡-፵)።
፡-መግባት መክተት፤ ወደ ውስጥ ማለፍ ውሳጣዊ መኾን። ኀደረ ቤተ ነዳይ፤ ኀደረ ውስተ ማኅፀን ፡-(ቅዳ ፡-ዮሐ)።
፡-ከሰው መጠጋ፤ አሽከር ሎሌ ዐማች መኾን። ኀደረ ኀበ አሐዱ ዐዱላማዊ ፡-(ዘፍ፴፰ ፡-፩)።
፡-መኖሮ መጽናት፤ መተባበር መሰማማት። ኢየኀድራ አእባን ውስተ ንድቅ። ዘቦቱ የኀድር ኵሉ ሕንጻ። ርእስ ዘቦቱ የኀድር ኵሉ ሥጋ ወይትዋደድ ፡-(ሄርማ ፡-ገ፱። ኤፌ፪ ፡-፳፩። ፬ ፡-፲፮። ቆላ፪ ፡-፲፱)። በኀደረ ፈንታ ተኀድረ ይላል፤ አያሰኝም። አጽናፍ ዘይትኀደር እምሰማይ ፡-(ምሳ፰ ፡-፳፮)።
ኀዲግ ጎት ፡-(ኀደገ የኀድግ ይኅድግ። ዕብ ሐዳል፤ ዐዛብ) መተው መጣል፤ ይቅር ማለት፤ መፍታት መልቀቅ፤ ማራቅ። ሰበቀን እይ፤ የዚህ ጎር ነው። ለምንት ኀደገኒ። ኅድግ ለነ አበሳነ። ኵሉ ዘየኀድግ ብእሲቶ። አኀዛ ወኢትኅድጋ። ኢትኅድግ ምሕረተከ እምነ ቤትየ ፡-(መዝ ፡-፳፩። ማቴ፮ ፡-፲፪። ሢራ፮ ፡-፳፯)።
ኀዳሪ ፡-(ሪት ርያን ያት ደርት) የሚያድር፤ ዐዳሪ፤ እንግዳ ጥገኛ፤ ደባል ሎሌ፤ አሽከር ቤተ ሰብ። ኀፍረት ለኀዳሪ ሰሪቀ ማኅደር። ኀዳሪ ዘአሐት ዕለተ ኀደረ። ኀደርቱ ለካህን። ኀዳሪ ወገባኢ። ባእ ኀዳሪነ፤ ፃእ ኀዳሪነ ፡-(ሢራ፵፩ ፡-፲፱። ጥበ፭ ፡-፲፭። ዘሌ፳፪ ፡-፲። ዘፀ፲፪ ፡-፵፭። ሢራ፳፱ ፡-፳፮ ፡-፳፯)።
ኀዳጊ ፡-(ጊት ግያን ያት) የሚተው፤ ይቅር ባይ። ኮነ ተሐራሜ ወኮነ ኀዳጌ። ክርስቶስ ኀዳጌ ኀጢአት ፡-(ስንክ ፡-የካ፳፭። ቄር። ፍ ፡-ነ ፡-፲)።
ኀዳፍ [1]:-ማዥራት፤–ሐዳፍ።
[2]፡-ኀዳፊ፤ ፡-(ፊት ፍያን ያት) የሚቀዝፍ ቀዛፊ፤ መሪ ጠባቂ መምር። ወኵሉ ዘኀዳፍ። ኀዳፍያንኪ። ኅዳፌ ነፍሳት። ኀዳፍያነ ክርስቲያን ፡-(ራእ፲፰ ፡-፲፯። ሕዝ፳፯ ፡-፰። ቅዳ ፡-ኪዳ)።
[3]፡-(ብ አኅዳፍ) መቅዘፊያ፤ ትርክዛ፤ መያዣው እንደርፍ ጫፉ እንደ ድግር ያለ ዝርግ ጠፍጣፋ፤ ቀላል፤ ዕንጨት ፡-(ሕዝ፳፯ ፡-፮)።
፡-የመርከብ ዥራት በስተኋላ ኹኖ የመርከቡን ፊት የሚመልስና የሚቀልስ፤ ወደ ወደዱበት የሚያስኼድ። ይመይጦን ብእሲ በኀዳፍ ንኡስ ወያበውኦን ውስተ መርሶ ኀበ ፈቀደ ፡-(ያዕ ፡-፬)።
፡-ዕውቀት ምክር፤ ሥልጣን። ዘሰ አጥረየ ኀዳፈ። እለ አልቦሙ ኀዳፍ። እንቲኣከ ኀዳፍ ኦ አብ ትሠርዕ ኵሎ ፡-(ምሳ፩ ፡-፭። ፲፩ ፡-፲፬። ጥበ፲፬ ፡-፫) )።
ኀድአ ፡-ጸጥ አለ፤–ሀዲእ ሀድአ።
(ጥ) ኀድፎ ፡-(ኀደፈ ይኄድፍ የኀድፍ። ቀ(ደ) ዘፈ) መቅዘፍ፤ ባሕርን በትርክዛ መክፈል መሠንጠቅ፤ ታንኳን መርከብን መምራት ማስኬድ፤ ማዘዝ መጠበቅ፤ እንዳይሰጥም። ከመ ዘየኀድፍ ውስተ ብዙኅ ሞገድ። ኀደፈቶ በንዋየ ዕፅ ምኑን። ኀድፈኒ እማዕበሰ ኀጢአት፤ ዘይኄድፎ ለዓለም እማዕበለ ኀጣውእ በራግናተ ወንጌሉ ቅዱስ ፡-(ምሳ፳፫ ፡-፴፬። ጥበ፲ ፡-፬። አርጋ)።
፡-መወልወል ማደስ ማጽናት። ከመ ነኀድፍ ልቦሙ ለመሀይምናን። ወመንፈስ ቅዱስ ይኄድፍ። ኀድፍ ልቦሙ በፈሪሆትከ። ለኀድፎ ነፍስ፤ ፡-(ቅዳ ፡-አት። ሕር። ቄድር ፡-ገ፲፩። ፶፫)።
፡-መምከር፤ ማስተማር። ምስጢሩ ከመምራትና ከማጽናት ይገባል። ወኃጥኣን ይኄድፉ ሕብለ ፡-(ምሳ፲፪ ፡-፭)።
ኀጕል ፡-ጥፋት፤–ሀጕል ሀጕለ።
ኀጢአት ፡-(ብ ኅጣውእ፤ ይእ) በቁሙ፤ በደል ዐመጥ፤ ግፍ ሕገ ወጥ ሥራ፤ በኀልዮና በነቢብ በገቢር የሚሠራ። ተኀድገ ለከ ኀጢአትከ። ወይስረይ ለነ ኀጣውኢነ። ክልኤቲ ኀጣይእ። አአምር ሕማምከ ወኀጣይአከ ፡-(ማር፪ ፡-፭። ቅዳ። ሢራ፯ ፡-፰። ራእ ፡-፪ ፡-፱)።
ኀጢእ ኦት ፡-(ኀጥአ የኀጥእ ይኅጣእ። ዕብ ሐጣእ። ሱር ሕጣእ። ዐረ ኀጢአ) ኀጢአት መሥራት፤ መበደል፤ ሕግ ያዘዘውን መተው ያላዘዘውን ማድረግ፤ ጽድቅን መቃወም። ኢትኅጣእ ፈድፋደ። ለኄር ወለዘሂ የኀጥእ። ከመ ይኅጣእ። ከመ ኢይኅጥኡ ለከ። ነፍስ እንተ ኀጥአት ይእቲ ትመውት ፡-(መክ፯ ፡-፲፯። ፱ ፡-፪ ፡-፲፰። ፪ዜና ፡-፳፪ ፡-፫። ኩፋ ፡-፩። ሕዝ፲፰ ፡-፬ ፡-፳)።
፡-ማጣት መቸገር፤ ፈልጎ አለማግኘት፤ ዕጦተኛ አይቶ ዐጣ መኾን። ይግዕሩ ወየኀጥኡ እክለ። ይመውቱ በኀጢአ ማይ። አርመሙ ወኀጥኡ ቃለ እንተ ያወሥኡ። ማሰነ ብሔር በኀጢአ ሰብእ ወእንስሳ ፡-(ሰቈ፩ ፡-፲፩። ኢሳ፶ ፡-፪። ነሐ፭ ፡-፰። ኤር፵ ፡-፲፩)።
ኀጢጥ ጦት ፡-(ኀጠ፤ ኀጠጠ የኀጥጥ ይኅጥጥ። ሐጸ። ዕብ ሓጣጥ፤ ወጋ በሳ ነቈረ) ማጠጥ ጥቃቅን መኾን ማነስ መቅጠን። ኀጢጥና ሐጺጽ አንድ ዘር ናቸው። ኆጻ ከነዚህ ወጥቷል።
ኀጣኢ ፡-(ኢት እያን ያት) ኀጢአት ሠሪ የሚሠራ፤ ኃጥእ ኀጢአተኛ። ያጣ የሚያጣ።
ኀጣጥ ፡-(ዕብ አጣድ) በቁሙ፤ ዐጣጥ፤ እሾኻም ዕንጨት እሾኹ ታናናሽ።
ኃጥኣዊ ፡-ኃጥኣዊ፤ ዝኒ ዓዲ ከማሁ። ለእመ ርኢከ ዘማዌ ወኃጥኣዌ ፡-(ፊልክ ፡-፴፭)።
ኃጥእ ፡-(እት ኣን ኣት) ዝኒ ከማሁ፤ በቁሙ ኀጢአተኛ፤ ሕግ አፍራሽ ተላላፊ ፡-(ዕጦተኛ፤ አይቶ ዐጣ)። ብእሲ ኃጥእ። ብእሲት ኃጥእት። ኃጥኣን ወመጸብሓን ፡-(ሉቃ፭ ፡-፰። ፯ ፡-፴፯። ማቴ፱ ፡-፲)። አነ ወወልድየ ሰሎሞን ንከውን ኃጥኣነ። ድኾች። አይቶ ዐጦች፤ ወይም በቁሙ ፡-(፫ነገ ፡-፩ ፡-፳፩)።
ኀጸረ ፡-ዐጠረ ቀጠረ፤–ሐጺር ሐጸረ።
ኀጸበ ፡-ዐጠበ፤–ኀፂብ ፡-ኀፀበ።
ኀጸነ ፡-አሳደገ፤–ሐፂን ሐፀነ።
ኀፀነ ፡-አሳደገ፤–ሐፂን ሐፀነ።
ኀፀየ ፤–ዐጨ ፤–ሐፅይ ሐፀየ።
(ጥ) ኀጺር ፡-(ራን ራት ጻር) ዐጭር ታናሽ፤ ድንክ ኵንትሽ። ኣነውኆ ለዕፅ ኀጺር። ዘበሕቁ ኀጺር። ኀጺራት አጻብዒሁ ፡-(ሕዝ፲፯ ፡-፳፬። ዘሌ፳፩ ፡-፰። ሄርማ)።
ኀጺር ሮት ፡-(ኀጽረ የኀጽር ይኅጽር። ዕብ ቃጻር። ዐረ ቀጸረ) ማጠር ማነስ፤ ዐጭር መኾን፤ የቁመት የጊዜ። አእባን እለ የኀጽራ። ሶበ አ ዘኀጽራ እማንቱ መዋዕል ፡-(ሄርማ ፡-ገ፰። ማቴ፳፬ ፡-፳፪)።
ኀፂብ ቦት ፡-(ኀፀበ የኀፅብ ይኅፅብ። ዐረ ኀፀበ፤ ቀለም አገባ) ማጠብ ማጥራት ማንጻት። ይኅፅቡ አልባሲሆሙ። ኀፀብኩኪ በማይ። ኀፀባ ለምድር እምኵሉ ርስሐት። የኀፅቦሙ እግዚ ለደቂቀ ጽዮን ፡-(ዘፀ፲፱ ፡-፲። ሕዝ፲፮ ፡-፱። መቃ ፡-ገ፯። ኢሳ፬ ፡-፬)። በኀፂብ ፈንታ ኀፅበት እንደ ማለት ኀፀባ ይላል። ኢታስትት ኀፀባ እገሪሆሙ ለአኀው ፡-(ሲኖዶ ፡-ኒቅ)። በኀፀበም ፈንታ አስተኀፀበ ይላል፤ ስሕተት ነው። ኢታአንግዱ በአስተኀ(ዐ) ፅ(ጽ) ቦ አላ በፍቅር ፡-(አፈ ፡-ተ፴፫)።
ኀጺን ፡-(ናት፤ ኀጻውንት) ብረት፤ የታወቀ ማዕደን፤ ከምድር የሚገኝ፤ ካፈር ከመሬት የሚወጣ፤ ብርቱ ከባድ ጥኑ ጠንካራ። ብርትንና ብሩርን ተመልከት፤ ብረት ማለት ከዚያ የወጣ ነው፤ ኀጺንም ከኀጸወና ከመሐጸ ከ፪ቱ ወጥቷል። ወኀጺንሂ እምውስተ ምድር ይትገበር። ምድር እንተ እበኒሃ ኀጺን። በምንሃብ ያሜክርዎ ለኀጺን ፡-(ኢዮ፳፰ ፡-፪። ዘዳ፰ ፡-፱። ሢራ፴፬ ፡-፳፮)።
፡-መቍረጫ መፍለጫ፤ የብረት መሣሪያ ማናቸውም ኹሉ፤በየስሙና በያይነቱ። አብልኀ ጸራቢ ኀጺነ። ወለኀጺናትሰ ገብሮሙ ሰንጐጐ። ተፈትሓ ኵሎን ኀጻውንት። ኀጻውንተ መስቀል ፡-(ኢሳ፵፬ ፡-፲፪። ገድ ፡-ተክ። ቄድር። አርጋ ፡-፪)።
ኀጺው ዎት ፡-(ኀጸወ የኀጹ ይኅጹ፤ ዐረ ኀጸ። ሱር ሕጻእ) መቍረጥ መሰንጋት ማኰላሸት፤ መስለብ መጕመድ፤ ጃን ደረባ ማድረግ፤ ራስን ወይም ሌላውን፤ መሐጸን እይ። ዘየኀጹ ርእሶ በፈቃዱ። ብእሲ ዘኀጸወ ኀፍረተ ሥጋሁ በፈቃደ ርእሱ፤ አው ጸላእቱ ኀጸውዎ ፡-(ቀሌ። ፈ ፡-መ ፡-፴፫ ፡-፪። ማቴ፲፱ ፡-፲፪)።
ኀፃቢ ፡-(ቢት ብያን ያት፤ ፀብት) የሚያጥብ ዐጣቢ፤ ቀለም አግቢ። ኀፃቤ ልብስ ፡-(ፍ ፡-ነ ፡-፴፮)።
ኀጻዊ ፡-(ዊት ውያን ያት፤ ጸውት) የሚሰልብ፤ ሰላቢ ቈራጭ።
ኀጽድ ዶት ፡-(ኀጸደ የኀጽድ ይኅጽድ። ዐረ ሐጸደ፤ ዐሰደ) ማጦ መጠምዘዝ፤ ማረቅ ማጕበጥ፤ መጠቅለል፤ የሐረግ የንጨት የሽቦ የብረት።
ኀፈሠ ፡-ዐፈሠ፤–ሐፊሥ ሐፈሠ።
ኀፈነ ፡-ዐፈነሩ፤–ሐፊን ሐፈነ።
ኀፈወ ፡-ወዛ፤–ሀፊው ሀፈወ።
ኀፊር ሮት ፡-(ኀፍረ፤ ኀፈረ የኀፍር ይኅፈር። ዐረ ኀፊረ። ዕብ ሓፌር። ሱር ሕፋር) ማፈር መፍራት፤ ከራቍትነት የተነሣ እንደ አዳም። መደንገጥ መለወጥ፤ ዐመድ መምሰል፤ ከኀፍረት ብዛት የተነሣ። ኀፍረትን ዕርቃንን መሰወር መክደን።ኀፊረ ኢኀፍሩ። ተዐቢ ኀፊሮትየ። ዘኢየኀፍር ገጸ ክቡር። ኢንኅፈር እምሢበተ ልሂቅ ፡-(ኤር፮ ፡-፲፭። ዘፀ፲ ፡-፫። ኢዮ፴፬ ፡-፲፱። ጥበ፪ ፡-፲)። በኀፍረ ፈንታ ተኀፍረ ይላል፤ ስሕተት ነው። ኢይግባእ ነዳይ ተኀፊሮ። መኑ ተአመነ በእግዚ ወተኀፍረ። ይሑሩ ተኀፊሮሙ። ተኀፍሩ ኵሉ ነሀብት በእንተ ግልፎሆሙ። ይእተ አሚረ ትትኀፈር እምጌጋይከ ፡-(መዝ ፡-፸፫። ሢራ፪ ፡-፲። ኢሳ፵፭ ፡-፲፮። ኤር፲ ፡-፲፬። ዘካ፫ ፡-፲፩)።
ኀፊድ ዶት ፡-(ኀፈደ የኀፍድ ይኅፍድ። ነደቀ፤ ሐነጸ፤ ሣረረ) መገንባት መናስ መንደቅ፤ ቤትን ግንብን፤ አስፍቶ አስረዝሞ አጠንክሮ መሥራት እንደ ባቢሎን ሕዝብ።
ኀፊጥ ጦት ፡-(ኀፈጠ የኀፍጥ ይኅፍጥ። ዐረ ኅበጠ። ዕብ ሓባጥ። ሱር ሕባጥ) መምታት መውቃት መደብደብ፤ የበትር። መደሰቅ መሰጐድ መጠፍጠፍ፤ የቡጢ የጥፊ። ኅፍጣ አጥባተክን ፡-(ኢሳ፴፪ ፡-፲፪)።
ኀፋሪ ፡-(ሪት ርያን ያት) ያፈረ የሚያፍር፤ ዐፋር። ደፋሪ ወኢኀፋሪ። ብእሲት ኀፋሪት ፡-(ግንዘ። ሢራ፳፮ ፡-፲፭)።
ኀፋጢ ፡-መኅፍጥ፤ የሚመታ ተማች፤ ደብዳቢ ወቂ ደሳቂ።
ኀፍረት ፡-(ታት) በቁሙ፤ ዕፍረት ፍራት። ከመ ኀፍረተ ሰራቂ ሶበ ይእኅዝዎ ከማሁ የኀፍሩ። ወከደነኒ ኀፍረት ገጽየ።ቦ ኀፍረት እንተ ታመጽእ ኀጢአተ፤ ወቦ ኀፍረት ለክብር። ዘአልቦ ኀፍረት ፡-(ኤር፪ ፡-፳፮። መዝ ፡-፵፯። ምሳ፳፮ ፡-፲፩። መክ፰ ፡-፩)።
፡-እድፍ ጕድፍ ገመና ነውር፤ ስድብ ስንፍና፤ የሚያሳፍር የሚያስነቅፍ ነገር። ኢሜጥኩ ገጽየ እምኀፍረተ ምራቅ። ተዐገሠ ኀፍረተ መስቀል። ኀፍረት ለነ እንተ ከመ ዛቲ ብእሲት ረኪበነ እመ ኢተናገርናሃ። ገብረ ኀፍረተ። ነገረ ኀፍረት ፡-(ኢሳ፶ ፡-፮። ዕብ፲፪ ፡-፪። ዮዲ፲፪ ፡-፲፪። ዘፍ፴፬ ፡-፯። ቆላ፫ ፡-፰)።
፡-ዕራቍት ዕርቃን፤ የወንድ የሴት ገላ፤ አባለ ዘር አፈ ማሕፀን። ኢትክሥት ኅፍረተ አቡከ ወእምከ። ከደንኩ ኀፍረተኪ። ከመ ኢይሑር ዕራቆ ወኢያስተርኢ ኀፍረቱ ፡-(ዘሌ፲፰ ፡-፯። ሕዝ፲፮ ፡-፰። ራእ፲፮ ፡-፲፭)።
ኁሠት ፡-(ላ ጥ ቀደ) መቀላቀል መደባለቅ፤ አቀላቀል ቅልቅልንት፤ ድብልቅነት። ኮነ ሰብአ ዘእንበለ ኁሠት። ቱስሕት ወኁሠት ፡-(ቄር ፡-ጰላ)።
ኁሣሤ ፡-ማሠሥ መታሠሥ። ፡-(ላ ጥ) መሻት መፈለግ፤ መመርመር አመራመር። ምርመራ፤ ምርማሪ፤ መላ ግምት፤ ጥንቈላ ሟርት። ፡-(ኩፋ ፡-፲፩)።
ኁባሬ ፡-ዝኒ ከማሁ። ድማሬ ወኁባሬ ፡-(ቅዳ)።
ኁጻድ አው ኆጻድ ፡-(ዳት። ዕብ ቄሬስ፤ ዋው) ሜንጦ፤ ቀለበት፤ ዘለበት የድንኳን መግጠሚያ ማያያዣ፤ ማቈላለፊያ። ወግበር ኆጻዳተ ኀምሳ ዘወርቅ፤ ወደምር አዕጻደ አሐተ ምስለ ካልእታ በኆጻዳት፤ ወይኩን ደብተራሁ አሐደ ፡-(ዘፀ፳፮ ፡-፮)።
ኁፋሬ ፡-ማፈር፤ ድል መኾን መሸነፍ፤ ዕፍረት ፍራት። ይዜከሮ እንከ ለኁፋሬሁ ፡-(ማር ፡-ይሥ፬ ፡-፮)።
ኍሉቍ ቅ ፡-(ቃን ቃት ልቀት) የተቈጠረ፤ ከቈጥር የገባ።እንዘ ኍሉቅ ምስሌነ። ወምስሌሆሙ ኍሉቍ። እለ ተርፉ ይከውኑ ኍሉቃን። ሥዕርተ ርእስክሙ ኵሎን ኍሉቃት እማንቱ ፡-(ግብ፩ ፡-፲፯። ቅዳ ፡-ሕር። ኢሳ፲ ፡-፲፱። ማቴ፲ ፡-፴። ሉቃ፲፪ ፡-፯)።
ኍላቌ ፡-(ቍያት) መቍጠር፤ መቈጠር አቈጣጠር ቈጠራ፤ ቍጥር፤ ያእምር ኍላቌሁ፤ ወኍላቌሁኒ ስድስቱ ምእት ስሳ ወስድስቱ ፡-(ራእ፲፫ ፡-፲፰)።
ኍልቍ ፡-ቍጥር ፤ ሒሳብ
፤ በየስሙና በያኃዙ ልክና መልክ ውሳኔ ያለው ፤ ካንድ እስከ ምእልፊት በየቤቱ በየመክብቡ የሚጣፍና የሚነገር። በዝኀ እምኍልቍ። አልቦ ኍልቍ ለጥበቢሁ። በአምጣነ ኍልቆሙ ለደቂቀ አስራኤል። በኍልቈ መዋዕል ዘሰከብከ። በኍልቈ አህጉሪከ አማልክቲከ (መዝ ፡ ፴፱። ፻፵፮። ሢራ፵፭ ፡ ፲፩። ሕዝ፬ ፡ ፬። ኤር፪ ፡ ፳፰)።
ኈልቆ ፡-ቆት ፤ (ኈለቈ ይኄልቍ ይኈልቍ። ዐረ ኀለቀ ፤ፈጠረ ለየ ፤ አስታወቀ ፤ በቍጥር። ዕብ ሐላቅ ፤ ከፈለ) ፤ መቍጠር ፤ መተርተር መደመር ፤
ማብዛት መክፈል። አኀዘንና ሐሰበን ተመልከት ፤
የዚህ አግዋር
ናቸው። ርኢ ከዋክብተ እመ
ትክል ኈልቆትሙ። አቡየሰ ይኄልቍ መዋዕለ። ኈለቍነ ሎሙ ኵሎ ወደለውነ። ብፁዕ ብእሲ ዘኢኈለቈ ሎቱ እግዚ ኀጢአቶ (ኵፋ ፡ ፲፬። ጦቢ፱ ፡ ፬። ዕዝ፰ ፡ ፴፬። መዝ ፡ ፴፩)።
ኈላቍ ፡-(ቍት ቍያን ያት) የማቈጥር ቈጣሪ፤ ቍጥር ዐዋቂ።
ኂሳን ፡-መሻል፤ ብልጫ ላቂያ። ኂሳነ ህላዌሁ። ብዙኅ ኂሳኑ ለእግዚ እምሰብእ ፡-(ቄር ፡-ጰላ)።
ኂረት ፡-መቸር መስጠት፤ ቸርነት ደግነት። ይኩን ኂረትኪ በሥነ ግዕዝ ወይዋሄ ፡-(አፈ ፡-ተ፳፰)።
ኂሩት ፡-(ታት) ቸርነት ደግነት፤ በጎነት። በኂሩተ ጻድቃን ትረትዕ ሀገር። አልቦ እኩይ ዘእንበለ ኂሩት። ይኄይስ እከዩ ለብእሲ እምነ ኂሩታ ለብእሲት። ርእስ ኂሩታት ፡-(ምሳ፲፩ ፡-፲። ኩፋ ፡-፴፭። ሢራ፵፭ ፡-፳፫። ፊልክ ፡-፫)።
ኂሩና ኂርውና ኄረውና ፡-ዝኒ ከማሁ ሩት። በኂሩና ነፍሱ። ምሕረት ወኂርውና። ኢበቍዖ ኂርውናሁ ፡-(ሢራ፵፭ ፡-፳፫። አፈ ፡-ተ፲፩። ፍ ፡-ነ ፡-፱)።
ኂጠት ፡-መታለል፤ ማታለል፤ መሸንገል አሸነጋገል፤ ሽንገላ።እምኂጠተ ጸላኢ ንትዐቀብ። አእመረ ከመ ውእቱ ኂጠት እምሰይጣን ፡-(ኪዳ። ስንክ ፡-መስ፳፩)።
ኂጣን ፡-ሽንገላ ድለላ፤ ጕሕሉት ተንኰል፤ ልዝብ ጥዑም ቃል፤ ንባበ ደግ ምስጢረ ክፉ፤ ፡-(ፑሊቲክ)። በኂጣነ ነገር ወበተየውሆ። አኮ በኂጣን ወተጥባበ ነገር። በትምይንት ወኂጣን። በኂጣን እኩይ ኄጦ ፡-(ሮሜ፲፮ ፡-፲፰። ፩ቆሮ ፡-፪ ፡-፩። አፈ ፡-ድ፳፮። ቄድር ፡-ገ፷፩)።
ኄላ ፡-የወይን ዘለላ፤–ሄላ።
ኄሰ [1]፡-ነቀፈ፤–ሐዪስ ሔሰ።
[2]፡-ነቀፈ፤–ሐዪስ ሔሰ።
ኄረወ [1]፡-(ይኄሩ ይኄሩ። ኄረ፤ ኀየረ) ወ ተቀጥላ ነው። ቸረ ለገሰ፤ ደግ ቅን መልካም ኾነ። ሶበ ኄረወ እግዚ ለደቂቀ እስራኤል። ኄርዎተ ነፍስ ይትሌዐል ላዕለ ኵሎን ኂሩታት። በኂሩቱ ለኖላዊ ይኄርዉ መርዔት ፡-(መጽ ፡-ምስ። ፈላስ ፡-ገ፴፪። አዋል)።
፡-በለጠ ተሻለ። ደቂቀ አቡከ እለ ይኄርዉ እምኔከ። ዕረፍተ ሞት ይኄሩ ሊተ እምግባራ ለዛቲ ሕይወት ፡-(፪ዜና ፡-፳፩ ፡-፲፫። ፊልክ ፡-፻፸፪)።
[2]፤–ቸረ ፤–ኀዪር ኄረ ኀየረ።
ኄር [1]፡-(ርት ራን ራት። ዐረ ኀይር። ዕብ ጦብ) ቸር ለጋስ፤ ደግ ቅን፤ በጎ ደኅና መልካም፤ ተንኰልና ክፋት ቢስነት የሌለው። ምንተ ትብለኒ ኄር በእንተ ኄር፤ አልቦ ኄር ዘእንበለ አሐዱ እግዚአብሔር። ጻድቅ ወኄር ለቤተ አስራሌል። ብአሲት ኄርት። እኩያን ወኄራን። የሐውር ፍናወ ዘኢኮና ኄርት ፡-(ማቴ፲፱ ፡-፲፮። ኢሳ፷፫ ፡-። ሣራ፯ ፡-፲፱። ማቴ፭ ፡-፵፭። ምሳ፮ ፡-፲፪)። ኄራን በማለት ፈንታ ኄራት ይላል፤ የመላሽ ስሕተት ነው ፡-(ግብ፲፫ ፡-፵፫። ፲፯ ፡-፬)።
[2]፡-ቸር፤–ኀዪር ኄረ ኀየረ።
(ጥ) ኅለት ፡-(ታት) ውስጠ ክፍት፤ ዘንግ፤ ብርዕ፤ አገዳ ቅልጥም ያለው የጐሽ መቃ ወይም ቀለም፤ ሸንበቆ ቀርክሓ፤የመሰለው ኹሉ። አራዊተ ኅለት። ኅለት ዘዐቅም። ዐቃቤ ኅለት። ብሔረ ኅለት። ውስተ ኅለት ዘውጡሕ ፡-(መዝ ፡-፷፯። ሕዝ፵ ፡-፫። ኢሳ፳፯ ፡-፬። ፴፭ ፡-፯። ኢያ፪ ፡-፮)።
ኅሉቅ ፡-(ቃን ቃት ልቅት) ያለቀ የተጨረሰ፤ ቍርጥ። ኅሉቀ ወምቱረ ነገረ ሰማዕኩ። ኅሉቀ እነግር ፡-(ኢሳ፳፰ ፡-፳፪። ፲ ፡-፳፪። ኤር፲፰ ፡-፯። ሮሜ፱ ፡-፳፰)።
ኅሉይ ፡-(ያን ያት ሊት) የታሰበ፤ ዕስብ።
ኅሉፍ ፡-(ፋን ፋት ልፍት) ያለፈ፤ የኼደ። እሴፎ አርአይክሙ ኅሉፈ። እስመ ኅሉፍ ገጾሙ ለኢየሩሳሌም። ካህናትሰ ኅሉፋነ ፍኖት ፡-(ሮሜ፲፭ ፡-፳፬። ሉቃ፬ ፡-፶፫። ሆሴ፮ ፡-፱)።
፡-የተለየ ልዩ ልውጥ። እስመ ኮነ ኅላዌሁ ኅሉፈ እምኔሆሙ ፡-(ገድ ፡-ኪሮ)። የታለፈ፤ የተዘለለ።
ኅሊ ኅልያ ፡-(ያት። ኀለየ) ኅሊና ሐሳብ፤ ምኞት ከልብ የሚነቃ ነቅዐ ልብ፤ ውሳጣዊ ሕዋስ። ጽርየት ኅሊሁ። ንጹሐ ሥጋ ወኅልያ። ጽዱላነ ልብ ወኅልያ ፡-(ፈ ፡-መ ፡-፮ ፡-፬። ስንክ ፡-ግን፲፱። የካ፮)።
ኅሊና ፡-(ናት። ኀለነ) በቁሙ፤ ዝኒ ከማሁ፤ ሐሳብ ምኞት። ኵሉ ኅሲናሁ ዘከመ የሐርስ ትለሚሁ። ልብ እንተ ትወልድ ኅሊና እኩየ። ኅሊናት ዘሥጋ ፡-(ሢራ፴፰ ፡-፳፮። ምሳ፮ ፡-፲፰። ይሁ ፡-፲)።
፡-የአፍኣ የውስጥ
ሕዋስ። ተነሣሽ
ተንቀሳቃሽ ማለት ነው ፤ ሖሰንና ሎሰን
እይ። በእንተ
ዐቂበ ኅሊናት ዘአፍኣ ወውስጥ። ወግብረ ኅሊናት ዘውእቶሙ
ነጽሮ
ወሰሚዕ (አረጋ ፡ ድ፲፭። ማር ፡ ይሥ፳፪ ፡ ፩)።
ኅሊናዊ ፡-የሐሳብ ሥራ፤ ኅቡእ ረቂቅ፤ ውሳጣዊ ድብቅ፤ ካሳቢው በቀር ለሌላ የማይታወቅ። ተውህበ ላቲ አእምሮ ግብራት ኅሊናውያት ፡-(ስንክ ፡-ሚያ፲፩)።
ኅላፍ ፡-(ፋት) (ፋት) በቁሙ፤ የብራና ስሯጽ፤ ቀንጃ ኹኖ ታጥፎ ተቀንፎ ባንድ ወገን፤ ወይም ተቀናጅቶና ተላልፎ በ፪ ወገን በጥራዝ መካከል የሚገባ ፪ ገጽ ያለው አንዳንድ ሉሕ ወይም ቅጠል። ቀንጃና ቅንጁም ባይኾን አንዱ ቅጠል ታጥፎ ወስፌ ያለፈበት ሰንበሩ ኅላፍ ይባላል። ሢራክን እይ።
ኅልቀት ፡-ኅልቀት፤ ማለቅ ተጨርሶ መጥፋት፤ መክሳት፤ ማነስ መጕደል። ዘተነበይከ በይሁዳ ኅልቀተ ኃጥኣን እምድር። እምብዝኀ ኅልቀተ ሥጋሁ በእንተ አጽዋም ፡-(ስንክ ፡-ሐም፬። ገድ ፡-ተክ)።
፡-ጫፍ መጨረሻ፤ ፍጻሜ። እስከ ኅልቀተ ዓለም ፡-(፲፪ ፡-፬)።
ኅልቅ [1]፡-ጕረሮ፤ ድሪም፤ሐሊቅ ሐለቀ።
[2]፡-ኅልቅ፤ ዕልቀት፤ ዕልቂት፤ ዕልቂያ ጥፋት። ቀርበ ዕለተ ኅልቆሙ ፡-(ዘዳ፴፪ ፡-፴፭)።
ኅልድ ፡-(ዳት። ዕብ ሔሌድ) ፋሮ፤ ታናሽ አውሬ ምድር የሚፍር የሚቈፍር።
ኅልፈት ፡-በቁሙ፤ ማለፍ፤ መኼድ፤ አስተላለፍ። በኅልፈተ ዐውሎ። የኀልፍ ንብረትነ ከመ አሠረ ኅልፈተ ደመና። ኅልፈቶሙ ውስተ ባሕረ ኤርትራ ፡-(ምሳ፲ ፡-፳፭። ጥበ፪ ፡-፬። አፈ ፡-ድ፮)።
፡-መሞት፤ መውጣት፤ ከዓለም ከሥጋ መለየት፤ መታጣት እንዳልነበረ መኾን። ከመ ትዘከርዋ እምድኅረ ኅልፈትየ። ኅልፈተ ዝንቱ ዓለም ፡-(፪ጴጥ ፡-፩ ፡-፲፭። ስንክ)።
፡-መውጫ መጨረሻ፤ ፍጻሜ። ኅልፈተ ጊዜያት ወዓመታት። ኅልፈተ መንግሥትከ። እምከመ ሰምዐ ኅልፈቶ ለጊዜ ምንዳቤ ፡-(ጥበ፰ ፡-፰። ዮሴፍ። አፈ ፡-ድ፩)። በኅልፈትና በፍልጠት ፈንታ ተኃልፎት ይላል፤ አያሰኝም። ኦ ነፍስ ናሁ በጽሐ ተኃልፎትኪ እምሥጋ ፡-(ማር ፡-ይሥ፲፫ ፡-፪)።
ኅሙስ ፡-(ሳን ሳት ምስት) ዐምስት የኾነ የተባለ፤ ካ፭ የተከፈለ ፭ነት ያለው።
ኅሙይ ፡-(ያን ያት ሚት) የታሰረ፤ እስር እስረኛ፤ ግዞተኛ። ወፈነዎ ሐና ኅሙዮ። ኢየሱስ ኅሙይ በእንቲኣነ ፡-(ዮሐ፲፰ ፡-፳፬። ደራሲ)።
ኅማሴ ፡-ዐምስት መኾን፤ ዐምስትነት።
ኅማዬ ፡-ማሰር፤ መታሰር፤ አስተሳሰር እስራት። በእንተ ኅማዬከ በእደ አይሁድ ከመ ሰራቂ ፡-(አዋል)።
ኅምስ [1]፡-ዐምስት። የልክና የጊዜ ቅጽል፤ በቂ። ዕሥር ወኅምስ በእመት። ኅምሰ ቀሠፋኒ አይሁድ ፡-(ዘፀ፴፯ ፡-፲፪። ፪ቆሮ ፡-፲፩ ፡-፳፬)።
[2]፡-(ዕብ ኤምጻእ፤ ውስጥ መካከል። ሖሜሽ። ሱር ሑምሻ፤ሆድ የወገብና የጭን መገናኛ ብሽሽት ጕያ) በቍሙ፤ ማሕፀን፤ አፈ ማሕፀን፤ የሴቶች ዐምስተኛ ሕዋስ። ፭ኛነቱም ካንገት በላይ ላሉት ላራቱ ነው። ኅምሳ ለወላዲትከ። ዘይፈትሕ ኵሎ ኅምስ ፡-(ኩፋ ፡-፳፭። ዘፀ፲፫ ፡-፪ ፡-፲፪ ፡-፲፫ ፡-፲፭)።
ኅምር ፡-ዝኒ ከማሁ ለኀምር፤ ቀይ ዐይነት።
ኅምዝ ፡-መርዝ፤–ሐሚዝ፤ ሐመዘ።
ኅሠፍ ፡-(ፋት) ዕከክ ብግር፤ ኪንታሮት ቍስል፤ የገላ ነውር።
ኅሡሥ ፡-(ሣን ሣት ሥሥት) የታሠሠ የተሻ የተፈለገ።
ኅሱር ፡-(ራን ራት ስርት) በቁሙ፤ ያነሰ የጐደለ፤ ሕጹጽ። የተዋረደ ትሑት ወራዳ፤ ጐስቋላ ምናምንቴ። በእንተ አልባሲሁ ኅሱር። ኅሱረ ነፍስ። ረሰይኩክሙ ኅሱራነ። ወለተ ባቢሎን ኅስርት ፡-(ስንክ ፡-ጥቅ፳፯። ፈ ፡-መ ፡-፳፮ ፡-፰። ሚል፪ ፡-፱። መዝ ፡-፻፴፮)።
ኅሡፍ ፡-(ፋን ፋት ሥፍት) ያከከ የታከከ፤ ቍስላም ዕከካም ፡-(ዘሌ፳፪ ፡-፳፪)።
ኅሳል ፡-ልባብ፤–ሐሲል ሐሰለ።
ኅሥሥት ፡-በቁሙ ዕሥሥት፤ የንሽላሊት ዐይነት፤ መልኳ እንደ ሌታ ቀን የሚለዋወጥ፤ ጠንቋዮች አጥበቀው የሚሿት።
ኅሩይ ፡-(ያን ያት ሪት) የተመረጠ ምርጥ፤ ዳኛ አስታራቂ። ንዋይ ኅሩይ። ወአልዐልኩ ኅሩይየ እምሕዝብየ። ኅሩይ ዘይፈትሕ ፡-(ቅዳ። መዝ ፡-፹፰። ኢዮ፱ ፡-፴፫)።
ኅሬ ፡-መረጣ ምርጫ፤ ምርጥነት። ስመ ነገድ፤ እስራኤል። ነገደ ኅሬ ፡-(ስንክ ፡-ኅዳ፫)። ዳግመኛም፤ ኅሩይ ኅርየት በማለት ፈንታ ኅሬ ይላል ፡-(ሮሜ፲፩ ፡-፭ ፡-፯ ፡-፳፰)።
ኅርመት ፡-የፊደል ቅንጣት፤ አንዳንዱ ቅርጽ፤ በየስሙና በየመልኩ ልዩ ልዩ ኹኖ የሚጣፍ፤ ብቻ ብቻውን የሚቈጠርና የሚነገር። አ ቡ ጊ ዳ ሄ ው ዞ፤ ይህን የመሰለ። የውጣ ፡-(የ-፲) እንተ አሐቲ ኅርመታ ወአሐቲ ቅርጸታ ፡-(ማቴ፭ ፡-፲፰። ድጓ)።
፡-ብቸኛ ቃል፤ ንባቡ ፊደሉ ከነቍጥ እስከ ነቍጥ የሚጣፍ በነቍጥ የሚወስን። አልፍ ቤት ገምል ድልት ሆይ ዋዌ ዛይ፤ አብ ወልድ መንፈስ ቅድስት ሥላሴ አሐዱ አምላክ፤ ይህን የመሰለ። ኢንኤዝዝ አሐተ ቃለ፤ አው አሐተ ኅርመተ ይትወለጥ እምዘሀሎ ህየ ፡-(ተረ ፡-ቄር፲፭)።
ኅርስ ፡-ዐራስነት፤ ወሊድ ወለዳ፤ የወሊድ ወራት ከርስሐት እስኪነጹ ድረስ ፵ ወይም ፹ ቀን፤ ፵ የወንድ ፥ ፹ የሴት ልጅ። በመዋዕለ ትክቶሃ ወኅርሳ ኢትቅረባ። እንዘ ውእቶን ኢንጹሓት አምኅርሶን። ፅኑሳቲሆሙ ኢይድኅፃ ወይድኅና በኅርሶን ፡-(ፍ ፡-ነ ፡-፵፪ ፡-፭። ፈ ፡-መ ፡-፲ ፡-፩። ኢዮ፳፩ ፡-፲)።
ኅርወት ፡-(ታት) መብሳት መበሳት፤ አበሳስ። ብስ ነዳላ፤ ፍልፍል ቅርጥ። አሰርዎሙ ውስተ ኅርወተ ጕንድ ክቡደ እስረት፤ ብስ። ኅርወተ ዐይነ ማኅተም፤ ቅርጥ ፡-(መቃ ፡-ገ፪። ስንክ ፡-ሠኔ፲፱። ዘፀ፳፰ ፡-፲፩)።
ኅርው ፡-(ዋን ዋት ሩት) የተበሳ፤ የተቀረጠ፤ ያበጠ የሰመጠ። ወኅርው ሰኰናሁ በአምሳለ ጕንድ። ኅርው ዐይነ ማኅተም ፡-(ስንክ ፡-ሠኔ፬። ሢራ፵፭። ፲፩)።
ኅርየት ፡-መምረጥ መመረጥ፤ አመራረጥ መረጣ፤ ምርጥነት፤ ፈቃድ። ሰብአ ኅርየት። ኅርየተ ሠያጢ፤ ዘቦቱ ኅርየት ፡-(ፍ ፡-ነ ፡-፬። ፴፫ ፡-፫)።
ኅሮ ፡-መብሻ መንደያ መፈልፈያ፤ መቅረጫ ማንጠጫ፤ መሮ አፈ ምሣር ወስፌ፤ የመሰለው ኹሉ። መጽሐፍ ግን በኅሮ ፈንታ ኅርወት ይላል። ጸቍር አንፎ በኅርወት ፡-(ኢዮ፵ ፡-፳፩)።
ኅቡል ፡-(ላን ላት ብልት) የተደፈረ የተናቀ፤ ጥቁ። ክፉ እብድ ደፋር ጨካኝ። ኅቡላን ወዝሉፋን ፡-(፪ጴጥ ፡-፪ ፡-፲)።
ኅቡረ ፡-(ደቂቅ አገባብ) ዐብሮ አንድ ኹኖ፤ ባንድነት አንድጋ። ዘበልዐ ኅቡረ ይመውት ኅቡረ። ምስሌሆሙ ኅቡረ። ሶበ ይሄልዉ አኀው ኅቡረ። ኢታድርግ ኅቡረ ፡-(አዋል። መዝ ፡-፪። ፻፴፪። ሢራ፯ ፡-፰)።
ኅቡር ፡-(ራን ራት ብርት) ያበረ፤ የተባበረ አንድ የኾነ፤ እኩያ ዐብሮ አደግ ባልንጀራ። ኅቡር ምስሌነ በዛቲ ጸጋ። ኅቡረ ህላዌ። ኅቡረ መንበር። ኅቡረ ካህንየ። ኅቡራነ ግዕዝ ፡-(ቄር ፡-ጰላ። ተረ። ስንክ ፡-ሚያ፳፰)።
ኅቡኣዊ ፡-የውስጥ የልቡና፤ ጥልቅ ረቂቅ። ኅሊና ኅቡኣዊት ፡-(ፊልክ ፡-፻፳፪)።
ኅቡእ ፡-(ኣን ኣት ብእት) በቁሙ፤ የታባ የተሸሸገ፤ ሽሽግ ድብቅ፤ ስውር ጥልቅ ረቂቅ። መዝገብ ኅቡእ ወክቡት። ኅቡእ እምዕጓለ መሕያው። ምእመናን ኅቡኣን፤ ትምህርተ ኅቡኣት። በእድ ኅብእት። በዐውሎ ኅቡእ ፡-(ዮሴፍ። ሢራ፲፩ ፡-፬። ኪዳ። ዘፀ፲፯ ፡-፲፮። መዝ ፡-፹)።
ኅቡዝ ፡-(ዛን ዛት ብዝት) የታበዘ የተጋገር ግግር።
(ጥ) ኅባኔ ፡-(ንያት) ቀሚስ፤ ያንገት የደረት ልብስ፤ የቀሚስ ተካሪስ። ኅባኔ ፀፈረ ውስተ ክሣድየ። ይኩን መልበሱ ለካህን ርሒብ ዘእንበለ ኅባኔ። ጽሕሙ ኮነ ነዊኀ ወይበጽሕ እስከ ኅባኔሁ፤ ትጥቅ ፡-(ኢዮ፴ ፡-፲፰። ሲኖዶ። ስንክ ፡-ግን፲፫። መዝ ፡-፻፴፪)። ልብሰ ምንኵስና፤ እንደ ሞጣሕት ያለ ባንገት ተጠልቆ ወደ ፊትና ወደ ኋላ እስከ ታች የሚወርድ። የራስ ማሰሪያ፤ ጥምጥም መጠምጠሚያ። የልብስ ዘርፍ፤ የኩታ ጫፍ፤ ጥለቱ ዕዳያቱ፤ ወይም ጥልፍ ዝምዝማት።
ኅባዝ አው ኅንባዝ ፡-አጣብቂኝ የሥቃይ መሣሪያ፤ እንደ ወፍጮና እንደ ምጣድ ያለ፤ ዐላውያን ሰማዕታትን የሚሣቅዩበት። አዘዘ ያዕርግዎሙ መልዕልተ ኅንባዝ እስከ ይውሕዝ ደሞሙ ዲበ ምድር። አዘዘ ያዕርግዎ ላዕለ ኅንባዝ ወየዐጽርዎ ሥጋሁ እስከ ውሕዘ ደሙ ከመ ማይ። አዘዘ ይስቅልዎ ዲበ ኅንባዝ ወየዐጽርዎ በመንኰራኵረ እሳት ዘኀጺን። ወሰበሮ መልአክ ለኅንባዝ ፡-(ስንክ ፡-ሚያ፲፰። ግን፲፱። ሠኔ፬ ፡-፭)። ን ስሯጽ ኹኖ ገብቷል፤ የግእዝ መላሾች ዐረቡ ሐብ ሕቡብ ያለውን ሕባብ በማለት ፈንታ ሕንባብ እንዳሉት ኅባዝንም ኅንባዝ ብለውታል።
ኅብል ፡-ድፍረት፤ ክፋት ጭካኔ።
ኅብስት ፡-የተጋገረች፤ እንጀራ፤–ኀቢዝ ኀበዘ።
ኅብረት ፡-(ታት) በቁሙ፤ አንድነት፤ ማበር መተባበር አንድ መኾን፤ መሰማማት። ኅብረተ ህላዌ። ኅብረተ ሥላሴ። ኅብረተ ዜማ። ኅብረተ ቃል። ኢይፈቅዱ ኅብረተ አበዊሆሙ ፡-(ቄር ፡-ጰላ። አርጋ። አዋል። ፍ ፡-ነ ፡-፳፬)።
ኅብር [1]፡-ቀለም፤ ዐይነት፤–ሓብሮ ሓበረ።
[2]፡-ኅብር፤ ፡-(ራት) ወገን ክፍል ዳርቻ፤ የቦታ የሰፈር። ውስተ አሐዱ ኅብር እምነ ገራህቱ። ውስተ አሐዱ ኅብረ ሀገር። ኅብረ በድው። ኅብር ዘባሕረ ኪኔሪውት። ኅብር ዘደብረ ኤፍሬም። ቁም መንገለ የማን አሐደ ኅብረ ፡-(ሩት፪ ፡-፫። ፩ነገ ፡-፱ ፡-፳፯። ዘኍ፴፫ ፡-፮። ኢያ፲፫ ፡-፳፯። መሳ፲፱ ፡-፮። ሱቱ ፡-ዕዝ፪ ፡-፶፬)።
ኅብአት ፡-ማባት መታባት፤ ሽሸጋ ድበቃ። ከመ ኢይትከሀሎ ኅብአተ አበሳ። ሰአሎ ኅብአተ ሀገር ፡-(ጥበ፲ ፡-፰። ዮሴፍ)።
ኅብዝ ፡-(ዛት፤ ኀባውዝ። ኅብ(ስ) ዝት፤ ታት። ዐረ ኍ ኹብዝ፤ ዛት) እንጌራ ዳቦ ጠቢታ። መጽሐፍ ግን በኅብዝና በኅብዝት ፈንታ ኅብስት ይላል፤ ስ በልማድና በጸሓፊ ስሕተት የገባ ነው፤ ደነባ ገነባ ብሎ ደምብ ግምብ እንደ ማለት። ኅብስተ ሰገም። ኅብስተ ስንዳሌ። ኅብስተ በረከት። ኀባውዘ ቍርባን ፡-(መሳ፯ ፡-፲፫። ዮዲ፲ ፡-፭። ሲኖዶ። ማቴ፲፪ ፡-፬)።
ኅቱም ፡-(ማን ማት ትምት) የታተመ ዕትም፤ የተጻፈ ጽሑፍ፤ የተዘጋ ዝግ፤ ስውር። መጽሐፍ ኅቱም። ዕዳ ዘኅቱም ላዕለ ዘመደ ዕጓለ መሕያው። ዐዘቅት ኅትምት። እስመ ዕጽው ወኅቱም ነገሩ ፡-(ኢሳ፳፱ ፡-፲፮። ስንክ ፡-መጋ፲፯። ማሕ፬ ፡-፲፪። ዳን፲፪ ፡-፰)።
ኅትመት ፡-ማተም፤ መታተም፤ አስተታተም ዕተማ፤ ዕትማት፤ ቡራኬ። ጸሎተ ኅትመት ፡-(ቅዳ። ስንክ ፡-የካ፯)።
ኅትው ፡-(ቱት ትውት፤ ዋን ዋት) የበራ የተቃጠለ ፡-(ሉቃ፲፪ ፡-፴፭)። አዕናቍ ኅትዋን ፡-(ስንክ ፡-ሠኔ፳፮)።
ኅኑቅ ፡-(ቃን ቃት ንቅት) የታነቀ የተጨነቀ፤ ታንቆ ታፍኖ የሞተ። ዘርዐ ትሩፋቲሆሙ ኅኑቅ በሦከ ዝ ዓለም። ምቱረ ልሳን በመጥባሕት ወኅኑቀ ጕርዔ በእድ። በሊዐ ደም ወኅኑቅ ፡-(ፊልክ ፡-፫። ስንክ ፡-ጥቅ፭ ፡-፲፰። ፍ ፡-ነ ፡-፳፫)።
ኅንቅርት [1]፡-በቁሙ፤ ዕንቅርት፤ ኵልኵልት ያንገት። የማንቍርት ተቀጥላ ጕረሮ የሚያንቅ የሚያስጨንቅ። ፡-(ተረት) የግፍ ግፍ በንቅርት ላይ ዦሮ ደግፍ። ኅንቅርት ዘወፅአ በክሣዱ ፡-(መ ፡-ፈ) ፣ ከኀነቀና ከነቀረ የተዴቀለ ስም ነውና ነቀረንና አንቀረን እይ።
[2]:-ከውር፤–ሕንቅርት ነቀረ።
ኅንቀት ፡-ማነቅ መታነቅ፤ አስተናነቅ፤ ዕንቂያ ዕንቂቅ፤ ድንገተኛ ሞት ፡-(ስንክ ፡-ሐም፪። መጽ ፡-ምስ)። ኅንቀተ ፍትወት ፡-(ግንዘ)።
ኅንባብ ፡-ፍሬ፤–ሐንበበ።
ኅንንት ፡-ዕንቅርት፤ ያንገት ደዌ።
ኅንጻጽ ፡-(ጻት) ጥርጣሪ፤ እንጥርጣሪ ንፋሽ ገለባ ልቃሚ ብጣሪ። ኑፋቄና ኅንጻጽ ባማርኛ ይተባበራሉ። ፡-(ግጥም፤ አቶ ሰይፉ ከድተዋል ተብለው ከታሙ በኋላ በፍቅር መጥተው ሲገናኙ) አለጊዜው ጊዜ ማን እሸት አምጥቷል፤ በዚህ በቤታችኹ ጥርጣሪ መልቷል። የእሳት ፍንጣሪ፤ የምጣድ ብልጭልጭታ። ቀለምጺጸን እይ።
ኅዋ ፡-(ብ ኅዋኅው። ዕብ ሖዋሕ፤ ሐዋሒም) ነቅ፤ ሥንጥቅ። በቁሙ፤ ክፍት ባዶ ወለል፤ የቤት የደጃፍ። አየር፤ የሰማይና የምድር መካከል፤ የርጉዕ ነፋስ ቦታ። መጣፍ ግን በኅዋ ፈንታ ኅዋኅው ይላል። ኅዋኅወ ሰማይ። ኅዋኅወ ፈለክ። ኅዋኅወ ቤተ ክርስቲያን ፡-(ሔኖ። አቡሻ። ቅዳ)።
ኅዉሥ ፡-(ሣን ሣት ውሥት) የተቀላቀለ ቅልቅል፤ ድብልቅ ቅይጥ። ኀጺን ወልሕኵት ኅዉሥ፤ ከማሁ ኅዉሣን በዘርዐ ዕጓለ መሕያው። አምጽአ ኅዉሠ ከርቤ ወዐልወ። አፈዋተ ከርቤ ኅዉሥ ፡-(ዳን፪ ፡-፵፫። ዮሐ፲፱ ፡-፴፱። ቅዳ ፡-አፈ)።
ኅዉር ፡-(ዐረ ኀዋር) ደካማ ድዉይ፤ ቀጭን ኰሳሳ። ወአነ ኅዉር እምሕል ለክሙ ፡-(ጦማር)።
ኅዩል ፡-ኅዩል፤ ፡-(ላን ላት ይልት) የበረታ ብርቱ፤ ብዙ ኀይለኛ። ኅዮለ ማየ፤ ኅዩል ውእቱ። ማዕበል ኅዩል ፡-(ጥበ፲፫ ፡-፪ ፡-፬። ፲፱ ፡-፯)።
ኅዩጥ ፡-(ጣን ጣት ይጥ) የተታለለ የተሸነገለ፤ ተላላ ሽንግል።
ኅዱር ፡-(ራን ራት ድርት) ያደረ፤ የኖረ የሰፈረ። ወኵሉ ምግባረ መንፈስ ኅዱር ውስተ ሥጋሁ። ኩን ምስሌሆሙ ኅዱረ። እለ ኅዱራን ዲበ ምድር ፡-(ኦፈ ፡-ድ፲፭። ፊልክ ፡-፻፹፩። መዝ ፡-፴፪)።
ኅዱግ ፡-(ጋን ጋት ድግት) የተተወ የተሰረየ፤ የተፈታ የተለቀቀ፤ ልቅ ስድ። ኀጣይኢሃ ኅድግት። ብእሲት ኅድግት። ወዘሰ ኅድግት አውሰበ ፡-(ፊልክ ፡-፴፭። ኢሳ፶፬ ፡-፮። ማቴ፭ ፡-፴፪)። ኅዱግ ስኩር በማለት ፈንታ ኅዳግ ይላል፤ አያሰኝም ፡-(መዝ ፡-፸፯። ኢሳ፳፬ ፡-፳)።
ኅዱፍ ፡-(ፋን ፋት ድፍት) የታደፈ፤ የተቀዘፈ፤ ጥብቅ።
ኅዳር ፡-(ዕብ አዳር፤ መጋቢት። ቅብጥ አቶር) በቁሙ፤ የወር ስም የመስከረም ሦስተኛ፤ ያዝመራ ወራት ጠባቆች ከዱር የሚያድሩበት። አመ ሰሙኑ ለኅዳር። መንፈቀ ኅዳር። ፡-(ስንክ ፡-ኅዳ፰። ፲፭)።
ኀዳሪ ፤ (ሪት ርያን ያት ደርት) ፤ የሚያድር ፤ ዐዳሪ ፤ እንግዳ ጥገኛ ፤ ደባል ሎሌ ፤ አሽከር ቤተ ሰብ። ኀፍረት ለኀዳሪ ሰሪቀ ማኅደር። ኀዳሪ ዘአሐት ዕለተ ኀደረ። ኀደርቱ ለካህን። ኀዳሪ ወገባኢ። ባእ ኀዳሪነ ፤ ፃእ ኀዳሪነ (ሢራ፵፩ ፡ ፲፱። ጥበ፭ ፡ ፲፭። ዘሌ፳፪ ፡ ፲። ዘፀ፲፪ ፡ ፵፭። ሢራ፳፱ ፡ ፳፮ ፡ ፳፯)።
ኅዳግ ፡-(ጋት) ፤ በቁሙ የመጽሐፍ እግር ፤ ከቀለሙ በታች እጅ የሚያርፍበት ባዶ ብራና ፤ ስፋቱ ከአርእስትና ከገጽ ከግልየት የሚበልጥ። ሥርው ፤ ጥንት። ንግባእኬ ኅበ ኅዳገ ነገር (መጽ ፡ ምስ)።
ኅዳጥ [1]፡-(ኅጣጥ፤ ጣን) ጥቂት፤ ትንሽ፤ ብዛት የሌለው።ማእረሩሰ ብዙኅ ወገባሩ ኅዳጥ ወኅዳጣን ኅሩያን። በእንተ ኅዳጥ ኀጢአት ፡-(ማቴ፱ ፡-፴፯። ፳ ፡-፲፮። ኢሳ፶፯ ፡-፲፯)። ዋሕድ ክልኤ በማለት ፈንታ ኅዳጥ ይላል፤ ፩ ፍሬ ፪ ፍሬ እንደ ማለት ነው። ኅዳጥ የአክል። በኅዳጥ ዓሣ ፡-(ሉቃ፲ ፡-፵፪። ቅኔ)።
[2]፡-ጥቂት፤–ኅጣጥ፤ ኀጠ ኀጠጠ።
ኅዳፌ ፡-መቅዘፍ፤ መቀዘፍ፤ አቀዛዘፍ ቀዘፋ። ትእዛዝ ዕውቀት፤ ፈሊጥ። በኅዳፌ ይከውን ጸብእ ፡-(ምሳ፳፬ ፡-፮)።
ኅድረት ፡-ማደር መኖር፤ አስተዳደር። ዐዳር፤ ትዳር ኑሮ። በእንተ ኅድረተ አኀው። ወኅድረቶሙ ለእስራኤል ፡-(ፊልክ ፡-፻፹፩። ዘፀ፲፪ ፡-፵)።
ኅድገት ፡-(ታት) (ላ ጥ) መተው መጣል፤ መፍታት መፈታት፤ አፈታት፤ ዕረፍት፤ ስሬት። የሥራ፤ የሴት፤የኀጢአት። ከመ ትጸውዕ ኅድገተ። ዓመተ ኅድገት። በእንተ ከሊአ ኅድገተ ብእሲት። ኅድገተ አበሳ ፡-(ኤር፵፩ ፡-፰። ዘሌ፳፯ ፡-፲፯። ፍ ፡-ነ ፡-፳፬። ቅዳ)። በኅድገት ፈንታ ኅዳጋቅ ይላል፤ ስሕተት ነው። ወገብረ ኅዳጋቲሃ ኵሎ ደወለ መንግሥቱ ፡-(አስቴ፪ ፡-፲፰)። በሚገዛው አገር ላለው ሕዝብ ኹሉ ዕረፍት ነጻነት ሰጠ፤ ግብር አቀለለ ማለት ነው።
ኅድጋን ኅድገት ፡-ፍች ልቅ፤ የባልና የሚስት መለያየት፤ የጋብቻቸው ውል መፍረስ። መጽሐፍ ግን ኅድጋን ገት በማለት ፈንታ ኅዳጋት ይላል፤ የተሳሳተ ነው። መጽሐፈ ኅዳጋት ፡-(ዘዳ፳፬ ፡-፩። ኢሳ፶ ፡-፩። ማቴ፭ ፡-፴፩። ማር፲ ፡-፬)። ፍልጣንን እይ፤ የዚህ ጎር ነው።
ኅጠት [1]፡-(ታት። ኆጻ፤ ኆጻት) ቅንጣት፤ ታናሽ ፍሬ፤ ያሸዋ የእኽል የሌላውም ኹሉ። ኅጠተ ኆጻ። ኅጠተ ጼው። ኅጠተ ዘርዕ እኩይ። ኅጠተ ስናፔ። ኅጠተ ሥርናይ ፡-(ሢራ፲፰ ፡-፲። ስንክ ፡-ሐም፯። ሱቱ ፡-ዕዝ፪ ፡-፴፰። ማቴ፲፫ ፡-፴፩። ዮሐ፲፪ ፡-፳፬)። ኅጠታተ ዕጣን፤ አንኳር ቈቀር። ኅጠታተ ዛጐል ፡-(ቅዳ። ፍ ፡-ነ ፡-፵፮)።
[2]፡-ቅንጣት፤–ኀጢጥ ኀጠ ኀጠጠ።
ኅጥሜ ፡-(ዐረ ኂጥሚይ) ሰላጣ ሥንቆ የወፍ ዘረር፤ ማናቸውም ቅጠላ ቅጠል፤ በጨው የሚጣፍጥ። ባለብሉዮች ግን የጐመን ዘር፤ ጥማቂ ይሉታል ፡-(ኢዮ፮ ፡-፮)።
ኅጥእና ፡-ኃጥእነት፤ አይቶ ዐጣነት ፡-(ፈላስ ፡-ገ፹፪)።
ኅጸር ኅጽረት ፡-ማጠር ዕጥረት ዐጭርነት ፡-(ሔኖ፸፪ ፡-፳፫። ፍ ፡-ነ ፡-፴፯)። በእንተ ኀጽረተ እደዊሆሙ ወበአንተ ዘአልቦሙ ክሂል። ይትዔረይ ሌሊት ምስለ መዓልት በኑኀት ወበኅጽረት ፡-(ዮሴፍ። አቡሻ ፡-፲፬)።
ኅጹር ፡-(ራን ራት ጽርት) ያጠረ ዐጭር፤ ታናሽ ጥቂት። ዘመን ኅጹር። ነገር ኅጹር። እስመ ኅጹር ዕለትየ። በኅጹር አዘዝኩክሙ። ኅጹረ እነግረከ ፡-(ፍ ፡-ነ ፡-፳። ፪ቆሮ ፡-፲ ፡-፲። ዕብ፲፩ ፡-፴፪። ግብ፳፬ ፡-፬)።
ኅፁብ ፡-(ባን ባት ፅብት) የታጠበ የጠራ፤ ንጹሕ ጥሩ። ወኅፁብ ሥጋነ በማይ ንጹሕ። አልባስ ኅፁብ ፡-(ዕብ፲ ፡-፳፪። ስንክ ፡-መጋ፫)።
ኅፃብ ፡-(ባት) ዕጣቢ፤ እድፍ። ማየ ኅፃቤሁ ኮኖን በቍዔተ ለአዋልደ ዮሴፍ። በኅፃበ እግሩ ፡-(አረጋ ፡-ድ፳፬። ስንክ ፡-ግን፰)።
ኅፅበት ፡-ማጠብ፤ መታጠብ፤ አስተጣጠብ፤ ዐጠባ ዕጥበት፤ ስርየት ጥምቀት። ኅፅበተ ሥጋ። ኅፅበተ እግር። ኅፅበተ ኀጢአት። ኅፅበት ዘዳግም ልደት ፡-(፩ጴጥ ፡-፫ ፡-፳፩። ፊልክ ፡-፻፲፬። ኪዳ። ቅዳ ፡-ኤጲ)።
ኅጽወት ፡-መስለብ፤ መሰለብ፤ ጃን ደረባ መኾን፤ ማድረግ። ዘፈቀደ ኅጽወት ፡-(ፊልክ ፡-፪፻፴)።
ኅጽው ፡-(ዋን) የተሰለበ ስልብ ጐማዳ፤ ጃን ደረባ። ከመ ኅጽው ሶበ የሐቅፋ ለድንግል። በእንተ ኅጽዋን ወግዙራን። እስመ ቦ ኅጽዋን ፡-(ሢራ፴ ፡-፳። ፈ ፡-መ ፡-፴፫። ማቴ፲፱ ፡-፲፪። ግብ፰ ፡-፳፯)።
ኅፉር ፡-(ራን ራት ፍርት) የታፈረ የተፈራ፤ ታፋሪ ተፈሪ። ያፈረ የፈራ፤ ኀፍረት የያዘው። እስመ ኅፉራን እሙንቱ። ሖሩ ኅፉራኒሆሙ። ዘኅፉር ገጻ ፡-(፪ነገ ፡-፲ ፡-፭። አፈ ፡-ተ፲፫። ኪዳ)።
ኅፍጠት ፡-የማኅተም ቅርጽ፤ ጥፈት መልክ። አልቦ ፍልጠት ውስተ ኅፍጠት ዘአርኣያ ንጉሣዊ ማእከለ ዘተኀትመ በማኅተመ ወርቅ ወማእከለ ዘተኀትመ በማኅተመ ኀጺን፤ ወኢይትዐወቅ አይ እምኔሆሙ ዘኅቱም በወርቅ እምዘኅቱም በኀጺን ፡-(ፍ ፡-ነ ፡-፱)።
ኆኄ ፡-ስመ ፊደል፤–ሆሄ ፡-ሀ።
ኆኅ ፡-(ብ ኆኃት። ዐረ ኀውኅ። ሱር ሓውሓ። ዕብ ሖዋሕ፤ሦክ) የባሕር ኰክ፤ እሾኻም ፍሬው ጥቍር፤ ዘይቶንና ዘቢብ የሚመስል፤ ተምር የሚያካክል። ቈጽለ ኆኃት። ከመ ቈጽለ ኆኃት። ፡-(ቀሌ። ግንዘ)።
ኆኅት ፡-(ብ ኆኃት፤ ኀዋኅው። ዐረ ኀውኀት፤ ታናሽ ጠባብ መስኮት ፉካ፤ ዐይን የሚያስልክ እጅ የሚያሾልክ፤ ነፋስና ብርሃን የሚያገባ። ደጃፍ በር፤ የቤት የቅጥር መውጫ መግቢያ፤ ባዶው ክፍቱ ሳንቃ የሚከድነው መዝጊያ የሚደፍነው። አንቀጽን እይ፤ የዚህ ጎር ነው፤ ነቅጾ። ኆኅተ አንቀጽ። ለኵሉ ዘመጽአ ርኅው ኆኅትየ። ባእ ቤተከ ወዕጹ ኆኅተከ። ይትረኀዋ ኆኃት እለ እምፍጥረት። አርኀወ ኆኃተ ሰማይ። እስመ ሰበረ ኆኃተ ብርት ፡-(ኪዳ። ኢዮ፴፩ ፡-፴፪። ኢሳ፳፮ ፡-፳። መዝ ፡-፳፫። ፸፯። ፻፮)።
ኆሠ ፡-ነቀነቀ፤–ሐዊስ ሖሰ።
ኆር ፡-(ዕብ ሖር) ብስ ነዳላ፤ ታናሽ ጠባብ መስኮት ፡-(ሕዝ፰ ፡-፯)።
ኆኖፌ ፡-መናፍቅ፤ ገበር ዐጓጕል ሕዝብ ሃይማኖቱ የተበላሸ፤ እንደ ቅማንት እንደ ተንባላት ያለ። ወደጐጾሙ በኅቡእ ፍኖት ለእለ ኆኖፌ ፡-(አፈ ፡-ድ፪። ተግ፬)።
ኆጻ [1]፡-፡-አሸዋ፤–ኀጠ ሐጸ፤ ኀወጸ።
[2]፡-(ኀጢጥ ኀጠ፤ ሐጸ። ዐረ ሐጸን። ሱር ሕጻጻ። ዕብ ሓጻጽ) ጠጠር፤ አሸዋ፤ ድቡሽት፤ ታናናሽ ጥቃቅን የደንጊያ ቅንጣት፤ እንደ ጤፍ ምርት እንደ ከርት ዶቄት ያለ፤ በወንዝ ዳር በባሕር ጠረፍ በምድረ በዳ የሚገኝ። ጥሬነቱ ከኀጢጥና ከሐጺጽ የተዴቀለ ነው፤ ኀጠንና ሐጸን ረመለን እይ። በዓለ አስፈሬዳት ወኆ ደራቅ። ኮነ ይወዲ ኆጻ ንስቲተ ውስተ አፉሁ። ከመ አህ፣እቲ ኅጠተ ኆጻ እምውስተ ኵሉ ኆጻ። ኆጻ ባሕር። ወደፈኖ ውስተ ኆጻ። ዘሐነጸ ቤቶ ዲበ ኆጻ ፡-(ፊልክ ፡-፴። ፷፱። ሢራ፲፰ ፡-፲። ፵፬ ፡-፳፩። ዘፀ፪ ፡-፲፪። ማቴ፯ ፡-፳፮)።
No comments:
Post a Comment