ሀ ለ ሐ መ ሠ ረ ሰ ሸ ቀ በ ተ ቸ ኀ ነ ኘ አ ከ ኸ ወ ዐ ዘ ዠ የ ደ ጀ ገ ጠ ጨ ጰ ጸ ፀ ፈ ፐ
ሰ ፡-ኻያ አንደኛ ፊደል በግእዝ አልፍ ቤት በአበገደ፤ ስሙ ሳት፤ ሰዓት፤ ቍጥሩ ፫፻፤ አኃዝ ሲኾን ሰ ሠለስቱ ምእት፤ ሦስት መቶ ይባላል። ሠውት ሠና ሳት ሰ ተዛውረው ስለ ተጣፉና ሳቱ ሰ በሠውት ሠ ቦታ ስለ ገባ በራሱ ላይ የውጣ ሠረዝ ቀርናዊ ነቍጣ ሲኾንበት ሸ ይባላል። ከ በነቍጣ ምክንያት ኸ እንዲባል ይኸም እንደዚያ ነው፤ በጥንታዊው ባሮጌው ግእዝ ግን ሸ የሚባል ሠውት ሠ ነው እንጂ ሳቱ ሰ አልነበረም፤ የቀረውን በሠውት አፈታት ተመልከት።
ሰ ፤ (አገባብ) ፤ ሳ ፤ ስ ትች ፤ ማ ፤ ና ግን ይኾናል ፤
ምስጢሩና ስልቱ አፍራሽነት ነው። ሳ ሲኾን በጥያቄ ቃል ይገባል። ሊቅክሙሰ ኢይሁብኑ ጸባሕተ ፤ መምራችኹሳ (ማቴ፲፯ ፡ ፳፭)። ሲከታተል ግን ፊተኛው ስ ወይም ትች ፤ ኋለኛው ሳ ይኾናል። ጴጥሮስሰ ነስሐ በእንተ ዘክሕደ ፤ ይሁዳሰ ኢነስሐኑ። አንተሰ መጻእከ ፤ እኁከሰ ተርፈኑ። ይሁዳሳ ፤
ወንድምኽሳ። ጥያቄ በሌለው ሲገባ
እንዳወራረዱ ይፈታል ፤
ወልድየስ ምተ ፤ ልጄስ ሙቷል ፤ ልጄማ ሙቶ። ሕያው ውእቱሰ ፤ ርሱስ። አንትሰ አንተ ክመ ፤ አንተማ አንተ ግን አንተስ ፤ ያስኛል። ወእመሰ ታፈቅሩ ዘያፈቅረክሙ ፤ የሚወዳችኹንማ። ና ሲኾን ፤ ይጽናሕሰ ይትርፍሰ እያለ በትእዛዝ አንቀጽ ይገባል። ትችና ስ አንድ ወገን ናቸው ፤ ትች ሲኾን ወ ሂ ኒ ግን እየኾኑ ይከተሉታል። ይህም
፤ ለዕቡያንሰ ይትቃወሞሙ ወለትሑታን ይሁቦሙ ክብረ። ቃልሰ ቃለ ያዕቆብ ወእደው ዘዔሳው። ለአድግሰ አቅሕም ወለገብርኒ ገሥጾ
እያለ ሌላውን ኹሉ
ያሳያል። ስትፈታም ፤ ትቢተኞችን
ይቃወማቸዋል ፤
ለትሑታን ግን ክብር ይሰጣቸዋል በል። ግን ሲኾን ፤
አንሰ እብለክሙ። አንትሙሰ ሶበ ትጼልዩ። ዛፒሰ አብአት ኵሎ ዘባ እያለ በኹሉ ይገባል። አንዳንድ ጊዜም ስ
ለማለት ሰን
አለቦታው ያስቀድማል ፤ የመላሽና የጣፊ ስሕተት ነው
፤ በጽርእም በዕብራይስጥም አይገኝ። ይህም ፤ ሰብእሰ ገጸ ይሬኢ ወእግዚአብሔርሰ ልበ ይሬኢ። እሙንየሰ ተዐቅጹ ወወድቁ ወንሕነሰ ተንሣእነ ወረታዕነ። ቤትየሰ ቤተ ጸሎት ይሰመይ
ወአንትሙሰ ረሰይክምዎ በኣተ ፈያት እያለ ሌላውን ኹሉ ያሳያል። ዳግመኛም ፤ ተምኔትየ ፤ ስእለትየ። እስመ
እፈቱ በማለት ፈንታ ፤ ይረትዕሰ ይርታዕ ፍኖትየ። እፈቱሰ እፍልስ
እያለ አላገባቡ ተጽፎ ይገኛል (ዕር፳
፡ ቍ፹፰)።
ሰሓሊ ፡-(ሊት ልያን ያት፤ ሐልት) የሚስል፤ የሚያሾል፤ ሳይ፤ አሿይ።
ሰሓቢ ፡-(ቢት ብያን ያት፤ ሐብት) የሚስብ የሚጐትት፤ ሳቢ ጐታች። ሰሓብያነ አርዑት ፡-(አፈ ፡-ድ፳፭)።
ሰሓቲ ፡-(ቲት ትያን ያት) የሚስት፤ የሚሳሳት፤ ሳች፤ ተሳሳች። ዐማፅያን ወሰሓትያን ወኃጥኣን። ሰሓትያን ወአባስያን ንሕነ ፡-(ዲድ። ቄድር)።
ሰሓዊ ፡-(ዊት ውያን ያት፤ ሐውት) የሚሳብ የሚጐተት፤ ዋነተኛ፤ ጉም መርከብ።
ሰሐየ ፡-ፈሰሰ ቀለጠ፤–ሴሐ ሰየሐ።
ሰሓጊ ፡-(ጊት ግያን ያት፤ ሐግት) የሚጮኽ፤ የሚስግ፤ የሚያፍግ፤ ሸካራ።
ሰሓጢ ፡-(ጢት ጥያን ያት) የሚነካ፤ ጐናጭ፤ ቈንጣጭ። ያገር ስም፤ የምጥዋ አጠገብ።
ሰለቀ ፡-አፌዘ ዘበተ፤–ሠለቀ፤ ተሣለቀ።
ሰለባ ፡-በቁሙ፤ የግዳይ ምልክት፤ የቅሚያ የዘረፋ ገንዘብ፤ ምርኮ።
ሰለደ ፡-(ሰሊድ። ዕብ ሳላድ) የኋሊት ዘለለ፤ ወደ ኋላ ኼደ አፈገፈገ። በዠርባው ወደቀ ተንጋለለ ተዘረጋ። ሹልዳ ማለት ከሰለደ ወጥቷል።
ሰለጠ ፡-ሠለጠነ፤–ሠሊጥ ሠለጠ።
ሰለፈ ፡-(ዕብ ሻላፍ፤ መልኀ) በቁሙ፤ ሰለፈ ተሰለፈ፤ ተፀረረ ተዘጋጀ፤ ፊት ለፊት ቆመ፤ መዘዘ ነቀለ፤ ሰይፉን ጐራዴውን።
ሰሊሖም ፡-(ጽር ሲሎአም። ዐረ ሲሉዋም። ዕብ ሺሎዋሕ) ፍንው፤ ፈሳሽ ወራጅ፤ ውስጥ ለውስጥ ኸያጅ፤ መስኖ። ምጥማቃተ ሰሊሖም ፡-(ዮሐ፱ ፡-፯ ፡-፲፩። ሉቃ፲፫ ፡-፬)።
ሰሊኆት ፡-(ዐረ ሰሊኀት። ዕብ ቅጺዖት። ጽር ካሲያ) ጥሩ ሽቱ፤ የሽቱ ዕንጨት ስም፤ ቀረፋ ፡-(መዝ ፡-፵፬። ሕዝ፳፯ ፡-፲፯)። በጎበዘ ፈንታ ኮበዘ እንዲል በሰሊኆት ፈንታ ሰሊክ ይላል፤ የጣፊ ስሕተት ነው፤ አንዳንድ ሰዎች ግን ከሩቅ የሚሸት እያሉ በስልክ ዘይቤ ይፈቱታል። ገነተ ሜዓ ወሰሊክ። ከርቤ ወሜዓ ወሰሊክ ፡-(ስንክ ፡-ጥቅ፳፩። ገድ ፡-አዳ። አንቀ ፡-ብር)።
ሰሊል ሎት ፡-(ሰለ፤ ሰለለ ይሰልል ይስልል። ዕብ ሻላል፤ ሳላል) መስለል፤ መስለል፤ ሰለል ማለት። መሰላልና ሰንሰለ ከዚህ የወጣ ነው። መሸለል ሽለላ ማድረግ፤ የስፌት የቅርርት። መምላት ማስተካከል፤ ለጥ ቀጥ ማድረግ።
ሰሊም ሞት ፡-(ሰለመ ይሰልም ይስልም። ሱር ሽሌም። ዕብ ሻላም። ዐረ ሰሊመ) መስለም፤ ስላምታ መስጠት፤ በእጅና ባንገት በቃል፤ ሰላም ለከ፤ በሓ፤ ሐዊሳ፤ እንዴት ዋልክ እንዴት ዐደርክ ጤና 5 ይስጥኽ ማለት፤ ዕርቅ ፍቅር ማድረግ። መሸለም ማስጌጥ ማንቈጥቈጥ። መስለም፤ እስላም መኾን የሙሐመድን ሕግ መቀበል። መጽሐፍ ግን በሰለመ ፈንታ እንዳማርኛው አስለመ ይላል። እመ ቦ ዘአስለመ በፈቃዱ ቀኖናሁ ሠለስቱ ዓመት ፡-(ቄድር)።
ሰሊብ ቦት ፡-(ሰለበ ይሰልብ ይስልብ። ዐረ ሰለበ። ዕብ ሻላፍ። ሱር ሽላፍ) መስለብ መቍረጥ፤ የሥጋ። ስለባ እንዲሉ፤ ዐለገን ተመልከት። መግፈፍ ማውለቅ ማውጣት፤ የልብሰ የቈርበት። መዝረፍ መቀማት፤ መማረክ መንጠቅ፤ የገንዘብ የልብ። አሰልባ አልባሲሃ ወመዋጥሒሃ። ይሰልቡ አልባሰ ዐስቆሙ። ሰለብዎ አልባሲሁ፤ ገፈፈ ፡-(ሆሴ፪ ፡-፲፩። ሕዝ፳፮ ፡-፲፮። ማቴ፳፯ ፡-፴፩)። አዕኑግ ዘሰለቡ። ይሰልቦ ንዋየ ሐቅሉ። ሰለሶ ረምሐ እዴሁ። ሰለብዎ ኵናቶ። ተሀይ አዕይንተ ወትሰልብ ልበ ፡-(መሳ፰ ፡-፳፭። ሉቃ፲፩ ፡-፳፪። ፩ዜና ፡-፲፩ ፡-፳፫። ሚክ፪ ፡-፰። ክብ ፡-ነገ)።
ሰሊብ ፡-(ዐረ ጸሊብ። ሱር ጽሊባ) ጸልቦ፤ መስቀል። ጸለበን ተመልከት።
ሰሊክ ፡-ሽቱ፤–ሰሊኆት።
ሰሊጥ [1]፡-(ዐረ ሰሊጥ) ዘይት፤ ቅባኑግ፤ የዕንጨት ቅባት። ይሴስይዎ ስንዳሌ ብሱል ዘቱሱሕ በማይ ወበቅብዕ ወሰሊጥ ወመዓር ዘንህብ፤ ያሰትይዎ ሜሰ ወሰሊጠ። ሰብዐቱ ልጥረ ቅብዕ ዘሰሊጥ ፡-(ስንክ ፡-ጥር፲፮። ሐም፭)።
[2]፡-ሰሊጥ፤ ፡-(ዐረ ሱምሱም። ዕብ ሹምሾም) በቁሙ፤ የእዝርዕት ወገን፤ ፍሬው ታናናሽ፤ ተልባ የሚያካክል፤ ዘይታም፤ ቅባታም፤ ቅባኑግ የሚኾን፤ ጥፍጥ። ወፈነወ ዳራ ለእስክንድር ኵዕሶ ወሰሊጠ ወበልዓ እስክንድር ለሰሲጥ፤ ወይቤ በላዕክዋ ለሰሊጥ ጥዕምት ይእቲ፤ ከመ ዝ እበልዖሙ ለሰራዊትከ ፡-(ዜና ፡-እስ)።
ሰላማ ፡-መታረቂያና ማስታረቂያ ቦታ ምሥዋዕ፤ የዕርቅና የፍቅር ምልክት የወንጌል ዐላማ መስቀል ያለበት፤ ወይም ርሱ ራሱ መስቀል። በሰላማ ወበክቡር ደም እንተ በክርስቶስ ተገብረ ፡-(ቅዳ ፡-ሐዋ። ቆላ፩ ፡-፳)።
ሰላማ ሳሌም ፡-የሰው ስም፤ ሰላማዊ ፍጹም ብእሴ ሰላም። ሐተታውን በአስማት ተራ ተመልከት።
ሰላማዊ ፡-ፍቅረኛ፤ ሰላምተኛ፤ ባለሰላምታ፤ የሰላም። እንዘ ሰላማዊ አነ። ትኩን ምስለ ኵሉ ሰላማዊተ ፡-(መዝ ፡-፻፲፱። ኪዳ)።
ሰላም ፡-(ሱር ሽላም። ዕብ ሻሎም። ዐረ ሰላም) በቁሙ፤ ፍጹም ጤና ዕረፍት፤ ዕርቅ ፍቅር አንድነት፤ ደኅንነት፤ ተድላ ደስታ፤ ሰላምታ፤ የቡራኬ የምርቃት ቃል ሰው ሲገናኝ ሲለያይ የሚለው የሚናገረው፤ ወይም የሚጥፈው። በሰላም የሐውር ወበሰላም ይትመየጥ። ብዙኀ ሰላመ አድማዕነ በመዋዕሊከ። ብፁዓን ገባርያነ ሰላም። ሰላም በዲበ ሰላም። ከመ ያእምር ሰላሞሙ። ሰላሞሙ ለዐማፅያን። ያቅርቡ ሎቱ ሰላመ። ሰላመ ገብርኤል ፡-(ኩፋ ፡-፳፯። ግብ፳፬ ፡-፫። ማቴ፭ ፡-፱። ኢሳ፶፯ ፡-፲፱። ኩፋ ፡-፴፬። መዝ ፡-፸፪። ኪዳ)።
ሰላቢ ፡-(ቢት ብያን ያት፤ ለብት) በቁሙ፤ የሚሰልብ፤ የሚገፍ፤ ሌባ ቀጣፊ፤ ቀማኛ። ሰላጢ፤ መሰልጥ፤ የሚጨርስ፤ የሚፈጽም፤ ፈጻሚ። ቃለ ነገር መሰልጥ ፡-(ስንክ ፡-ኅዳ፳፩)።
ሰላቲ ፡-(ቲት ትያን ያት) የሚነፋ፤ የሚሸልት፤ ሰላች፤ አላጋጭ።
ሰላጢ መሰልጥ ፡-የሚጨርስ፤ የሚፈጽም፤ ፈጻሚ። ቃለ ነገር መሰልጥ ፡-(ስንክ ፡-ኅዳ፳፩)።
ሰሌዳ [1]፡-(ጽር ሴሊዳ) ሉሕ ለውሕ፤ ጽሌ ገበታ፤ ዝርግ ጠፍጣፋ፤ ብራና ወረቀት፤ ጠርብ ሳንቃ፤ የመሰለው ኹሉ። ሰለተንና ሰፈደን ሎሐን እይ፤ የሰሊድ ጎር ናቸው። ሰሌዳ ሥዕል። ሰሌዳ እብን። ሶበ አንበበ ሠለስተ ሰሌዳ። ፍሉገ ይኩን ሰሌዳሁ። ሰሌዳ መጽሔት። ሰሌዳ በረድ ጸፍጸፈ ዐውዱ ፡-(ስንክ ፡-መስ፲። ኤር፲፯ ፡-፩። ፵፫ ፡-፳፫። ዘፀ፳፯ ፡-፰። አዋል።ቅዳ ፡-ኤጲ)። ቀለም በማለት ፈንታ ሰሌዳ ይላል፤ ስሕተት ነው። ወቀብዖ በሰሌዳ ፡-(ኤር፳፪ ፡-፲፬)።
[2]፡-ሰሌዳ፤ ፡-(ዕብ ሼሌድ ፥ ሺሌዳ) ንድፍ ቢጋር፤ ዐጥንትና ቈርበት፤ ቅርጽ ቁመና ጭገሬታ ምልክት።
ሰሌዳት ፡-ሰላድው፤ ሰሌዶች፤ ሰሌዳዎች። ሰሌዳተ እብን ዘሕግ። ሰሌዳተ ኀጺን። ሰላድወ ዕፅ ፡-(አርጋ። ስንክ ፡-ሐም፭። ግብ፳፯ ፡-፵፬)።
ሰልሰለ ፡-አያያዘ፤–ሰንሰለ። ሰሊል ሰለ።
ሰልቢባ ፡-ክፉ የባሕር ነፋስ፤ አውራቂስ፤ ማዕበል ሞገድ የሚያስነሣ። ወይእቲ ነፋስ እንተ ስማ ሰልቢባ ፡-(ግብ፳፯ ፡-፲፬)። ባለቅኔዎች ግን ልክስክስ ይሉታል።
ሰልቶ ቶት ፡-(ሰለተ ይሴልት ይሰልት። ዕብ ሳሌት) መንፋት፤ በወንፊት መለየት፤ የሐሪጽ። መጥረብ መሸለት፤ መፍለጥ መሠንጠቅ መሰባበር ማድቀቅ፤ የዕፅ። በቁሙ፤ መሰለት መክደን ማልበስ፤ የቤት የጣራ። መድረቅ መቅጠን ማነስ መኰሰስ፤ ወስስ መኾን፤ የሰብል ያዝመራ። መዘበት ማላገጥ መሣቅ መሣለቅ፤ ማፌዝ መላጥ። መሰልቸት፤ ስልቹ መኾን፤ ስልቻ ማውጣት።
ሰልከ ሰለከ ፡-በቁሙ፤ ኼደ ሾለከ፤ ሹልክ አለ ፡-(ዐማርኛ)።
ሰልጦ ጦት ፡-(ሰለጠ ይሴልጥ ይሰልጥ፤ ፈጸመ። ዕብ ሻሌም) መጨረስ፤ መፈጸም፤ መምላት፤ ፍጹም ትክክል ማድረግ፤ ሕጸጽን ማጥፋት፤ የሥራ የነገር። ዕዳን ብድርን ጨርሶ መክፈል መስጠት። ዋጋን ገንዘብን ጨርሶ ማግኘት መቀበል መውሰድ፤ ጥቂት ሳይቀር። ሰሊጦሙ ግብሮሙ። ሰፈራ ለመንግሥትከ ወሰሰጣ። እሴልጥ መዐትየ ላዕሌሆሙ። ሰለጠ መዊተ፤ ጨረሰ ፡-(ሉቃ፪ ፡-፵፫። ዳን፭ ፡-፳፮። ሕዝ፭ ፡-፲፫። ዮሐ፲፱ ፡-፴፱)። ሰልጥ ዘትፈዲ። ሰለጡኒ ኵሎ ውስተ ሕፅንየ፤ ከፈለ ፡-(ማቴ፲፰ ፡-፳፰ ፡-፴፬። ኢዮ፲፱ ፡-፳፯። ሉቃ፲፪ ፡-፶፰ ፡-፶፱)። ሰለጡ ዐስቦሙ። ሰለጡ መክፈልቶሙ፤ አገኘ ፡-(ማቴ፮ ፡-፲፮። ሉቃ፮ ፡-፳፬። ዘኍ፴፬ ፡-፲፭)። መስለጥ፤ ሰላጣ ማበጀት፤ ሽልጦ መጋገር።
ሰልፍ ፡-(ቀትል) በቁሙ፤ ውጊት ጦርነት፤ ሰይፍ መማዘዝ፤ መተራረድና መቀራደድ፤ መዋጋት መዘራከት፤ መታኰስ መጣበስ። ወተጻብእዎ በጽኑዕ ሰልፍ ፡-(ሥር ፡-አኵ፤ ታሪ ፡-ነገ)።
ሰመንቱ ት ፡-የወንዶች ድምር፤ ስምንት። ሰመንቱ ሰራዊት። ዐሠርቱ ወሰመንቱ ዕደው። ተስዓ ወሰመንቱ ዓም ፡-(ሚክ፭ ፡-፬። ሉቃ፲፫ ፡-፬ ፡-፲፩። ፩ነገ ፡-፬ ፡-፲፭)።
ሰመክ ፡-(ዐረብ) ዓሣ፤ ዘመደ ዓሣ።
ሰሙን [1]፡-የዕለት ቅጽል፤ ሱባዔ፤ ሰሞን፤ ሳምንት፤ ሰንበት፤ ሰባት ቀን፤ ከእሑድ እስከ ቀዳም። ሰባቱን ዕለት ሰሙን ማለት ከእሑድ እስከ እሑድ ስምንት እያሉ ነው፤ አለዚያ ስሕተት ይኾናል። ለለ ሰሙኑ ትነግሥ ወለለ ሰሙኑ ትሰፍን፤ ወለለ ሰሙኑ ትትቄመር። ኦ ቅድስት ንዒ ኀቤነ ለለ ሰሙኑ። ሰሙነ ሕማማት ወሰሙነ ፍሥሕ። ሰሙነ ሕርቃል። ኀሙሰ መዋዕለ በበ ሰሙን ፡-(ቅዳ ፡-አቅ። አቡሻ ፡-፩። ፍ ፡-ነ ፡-፲፭። ሲኖዶ)።
[2]፡-ሰሙን፤ ስምንተኛ። አመ ሰሙን ዕለት ፡-(ሉቃ፩ ፡-፶፬። ፪ ፡-፳፩)። ሰሙንን ሰባትና ስምንት ስምንተኛ ማለት ፍችው ኹኖ አይዶለም፤ መላሽና ጣፊ ሰቡዕ ሳምን በማለት ፈንታ አለዘይቤው ሰሙን እያሉ ስላገቡት እንጂ።
ሰሚር ሮት ፡-(ሰምረ ይሰምር ይስመር። ዐረ ሰመረ) መስመር፤ ማማር፤ ማፍራት መበጀት፤ ደስ ማሰኘት፤ ያዝመራ ያታክልት። ይፈሪ ወይሰምር። በሰብዐቱ ዓመት ዘሰምረ። እመሂ ይሰምር ዘርዖሙ በቅድሜሆሙ። ሰምረ ፍሬሁ። ወሰምረ ሎቱ ተግባሩ። ከመ ይስመር በላዕሌክሙ ፍሬ ጽድቅ ፡-(ቆላ፩ ፡-፮ ፡-፲። ኩፋ ፡-፵፪። ኢዮ፳፩ ፡-፰። ሉቃ፲፪ ፡-፲፮። ፊልጵ፬ ፡-፲፯)።
ሰሚዕ ዖት ፡-(ሰምዐ ይሰምዕ ይስማዕ። ዕብ ሻማዕ። ሱር ሽማዕ። ዐረ ሰሚዐ) መስማት፤ ማድመጥ፤ ማስተዋል መቀበል፤ በዦሮ በልብ፤ የቃል የቋንቋ። ፈተዉ ይስምዑ አንትሙ ዘትሰምዑ ወኢሰምዑ። ሰምዑኒ ቃልየ እስመ ተክህለኒ። አልቦ ዘይሰምዖ። ላዕለ ልሂቅ ኢትስማዕ ውዴተ። ይሰምዖኑ ጸሎቶ። ንግረነ ሱርስተ እስመ ንሰምዕ ፡-(ማቴ፲፫ ፡-፲፮። መዝ ፡-፻፵። ፩ቆሮ ፡-፲፬ ፡-፪። ኢዮ፳፯ ፡-፱። ኢሳ፴፮ ፡-፲፩)።
፡-መመስከር፤ ምስክር መኾን፤ ያዩትን የሰሙትን መንገር፤ አየኹ ሰማኹ ማለት። ኢትስማዕ ለቢጽከ ስምዐ ሐሰት። ሰምዕዎ ኵሎሙ ወአንከርዎ። ጽድቅ ውእቱ ስምዑ ዘሰምዐ በእንቲኣየ። ወግብረ ሐዋርያትኒ ትሰምዕ ከመ ወረደ መንፈስ ቅዱስ በአምሳለ ልሳናተ እሳት ፡-(ዘፀ፳ ፡-፲፮። ሉቃ፬ ፡-፳፪። ዮሐ፭ ፡-፴፪። ፊልክ ፡-፶፰)።
ሰሚክ ኮት ፡-(ሰመክ ይሰምክ ይስምክ። ዕብ ሳማኽ። ሱር ስማኽ) መጠጋት መደገፍ፤ ጥግ ደገፋ መያዝ፤ ማመን መማጠን፤ ትውክልት ተስፋ ማድረግ፤ የሰው። መናበብ መዛረፍ፤ ዘርፍ ቅጽል መኾን፤ የቃል። መጽሐፍ ግን በሰመከ ፈንታ አስመከ ይላል። ላዕለ እግዚ ያሰምኩ። አስመኩ በስመ እግዚ። አስመኩ በቤተ ክርስቲያን። ቤተ መቅደስ ብነ ያሰምክ። ናሰምክ በኵሉ ግብር ኀበ ረድኤተ እግዚአብሔር። አስመከት ላዕለ ርእሰ ወለታ። ዝኩ ዘያሰምክ ንጉሥ ላዕለ እዴሁ ፡-(ሚክ፫ ፡-፲፩። ኢሳ፶ ፡-፲። ቀሌ። ዮዲ፰ ፡-፳፬። አፈ ፡-ተ፲፪። አስቴ ፡-፭ ፡-፩። ፬ነገ ፡-፯ ፡-፪)።
ሰማኒ [1]፡-(ኒት ንያን ያት፤ መንት) የሚሰምን፤ ሰማኝ፤ ስምንት አድራጊ። ሸማኔ።
[2]፡-(ላ) ሰማኒ፤ ፡-(ዕብ ሽሞኔ። ሱር ትማኔ። ዐረ ተማኒ) የሴቶች ድምር፤ ሐ–፰ ስምንት። ሰማኒ ክረምቱ። ዐሥሩ ወሰማኒ አንስተ ነሥአ። አርብዓ ወሰማኒ ፡-(፬ነገ ፡-፳፪ ፡-፩። ፪ዜና ፡-፲፩ ፡-፳፩። ዘኍ፴፭ ፡-፯)።
ሰማኒቱ ት ፡-ዝኒ ከማሁ። መጽሐፍ ለሴቶች ለወንዶች ያደርገዋል፤ ዐዋጁ ግን ለሴቶች ብቻ ነው። በሠላሳ ወሰማኒቱ ዓመተ መንግሥቱ። ወለደ ዕሥራ ወሰማኒተ አትቡዐ። ወአትረፈ ሰማኒተ ነፍሳት እለ ዐቀቡ ቃሎ ፡-(፪ዜና ፡-፲፮ ፡-፩። ፲፩ ፡-፳፩። ቅዳ ፡-ግሩ)።
ሰማንያ ፡-በቁሙ፤ የቍጥር ስም፤ ፈ–፹፤ ስምንት ጊዜ ዐሥር፤ ወይም ዐሥር ጊዜ ስምንት ፡-(መዝ ፡-፹፰። ማሕ፮ ፡-፰። መሳ፫ ፡-፳። ፳ ፡-፳፭። ሉቃ፪ ፡-፳፯። ፲፮ ፡-፯)።
ሰማዒ ፡-(ዒት ዕያን ያት ዕት) የሚሰማ የሚቀበል፤ ሰሚ መስካሪ፤ ምስክር። ለእለ በጽድቅ ይጼውዕዎ ሰማዒ። ሰማዔ ስብሐተ ማሕሌት። ሰማዔ ስእለቶሙ ሰማዕያን። ለሊክሙ ሰማዕትየ ከመ አነ እግዚ። ኦሪት ወነቢያት ኮንዎ ሰማዕተ ፡-(ኢሳ፵፪ ፡-፲፫። ፵፬ ፡-፰። ዮሐ፫ ፡-፳፰። ሮሜ፫ ፡-፳፩)።
ሰማዕት ፡-(ታት) በቁሙ፤ የሚመሰክሩ መስካሮች፤ ሰማዕቶች፤ ሃይማኖታቸውን መስክረው በሰማዕትነት የሚሞቱ። ሰማዕተ ሐሰት። አስጢፋኖስ ቀዳሜ ሰማዕት። በእንተ ሰማዕታት መዋዕያን። ዓመተ ሰማዕታት ፡-(ማር፲፬ ፡-፶፯። ቅዳ። አቡሻ)። ሰማዒ አንድ፤ ሰማዕት ብዙ፤ ሰማዕታት የብዙ ብዙ ነው፤ መጽሐፍ ግን ስምዕ ስምዓት ስምዓታት በማለት ፈንታ ሰማዕት ሰማዕታት ይላል፤ የጥሬውን ለውስጠ ዘ ሰጥቶ፤ አያሰኝም፤ አንዱን ሰማዕት ማለት ያማርኛ ነው። ሰማዕት ጕጕእ። በዛቲ ዕለት ሰማዕተ ኮነ። ያምጽኡ ሰማዕቶሙ። በእንተ ፈታሒ ወሰማዕታት ፡-(ምሳ፲፪ ፡-፲፱። ስንክ ፡-ጥር፲፮። ኢሳ፵፫ ፡-፱። ፍ ፡-ነ ፡-፵፫)።
ሰማኪ ፡-(ኪት ክያን ያት) የሚጠጋ፤ የሚደገፍ ፣ ተሰፋዊ፤ ተናባቢ።
ሰማዪ ፡-(ዪት ይያን ያት፤ መይት) የሚሰይም ሰያሚ፤ ስም አውጭ፤ ስመኛ።
ሰማያዊ ፡-(ዊት ውያን ያት) የሰማይ፤ በሰማይ ያለ፤ የሚኖር፤ ከሰማይ የመጣ፤ የሰማይ ሥራ የሚሠራ፤ ሰማያም፤ ሰማይማ፤ የሰማይ ዐይነት፤ ሰማይ የሚመስል። አቡክሙ ሰማያዊ። መርዓዊ ሰማያዊ። ጸጋ ሰማያዊት። በከመ ዝኩ ሰማያዊ ከማሁ ሰማያውያን ፡-(ማቴ፭ ፡-፵፰። ቀሌ። ቄድር። ፩ቆሮ ፡-፲፭ ፡-፵፯–፵፱)።
ሰማይ ፡-(ብ ሰማያት። ዕብ ሻማይም። ሱር ሼማያእ። ዐረ ሰማእ) በቁሙ፤ ስፉሕ ስጡሕ ዝርግ፤ ልዑል ምጡቅ፤ ጠፈር ከራሳችን በላይ ርቆ መጥቆ ኒል መስሎ የሚታይ፤ የማየት ፍጻሜ ወሰን ደንበር፤ ከርሱ በላይ ሌላ የማያሳይ ግዙፍ መጋረጃ፤ የምድር ባጥ፤ መዋቅር ጣራ፤ ከእሳት ከውሃ የተሠራ፤ በነፋሳት አዕማድ የቆመ፤ ከበላዩ የውቅያኖስ ውሃ ሀኖስ የሰፈረበት ከበታቹ ግዙፋን ብርሃናት እንደ ፋኖስ የተሰቀሉበት። ሰማይ ኹለት ቃል ነው፤ ሰ ማይ፤ ፍችው እሳት ወማይ። ልዑል ምጡቅ መባል የወል ኹኖ ለጠፈርም ለላይኞችም ሰማያተ ብርሃን ለተባሉት ለሰባቱ ኹሉ ይነገራል፤ እሳት ወማይ ግን ለጠፈር ብቻ ነው። ሰባቱ ሰማያት በዕብራይስጥ፤ ዊሎን፤ ርቂዕ፤ ሻሓቅ፤ ዝቡል፤ ምዖን፤ ምኮን፤ ዓርቦት ይባላሉ። በግእዝም ኤረር፤ ራማ፤ ኢዮር፤ ኢየሩሳሌም ሰማያዊት፤ ሰማይ ውዱድ፤ መንበረ መንግሥት፤ ጽርሐ አርያም ይባላሉ፤ በቀዳሚ ፈጠረ አምላክ ሰማያተ ያላቸው እሊህን ከጠፈር በላይ ያሉትን ነው፤ ጠፈር ግን ግዙፍ ስለ ኾነ ቍጥሩ ወምድረ ካለው ነው፤ ሰማይ የተባለ ሰኞ ነውና ፡-(ዘፍ፩ ፡-፮–፱ ፡-፲፬–፲፯) ሣልስ ሰማይ። ሳብዕ ሰማይ። ተርኅዉ ሰማያት ወርኢኩ ራእየ አምላክ። ሰማያት ይነግራ ስብሐተ እግዚ ወግብረ እደዊሁ ያየድዕ ጠፈር። ይሴብሕዎ ሰማየ ሰማያት ወማይኒ ዘመልዕልተ ሰማያት ፡-(፪ቆሮ ፡-፲፪ ፡-፪። ዕር ፡-ኢሳ፫ ፡-፲፫። ሕዝ፩ ፡-፩። መዝ ፡-፲፰። ፻፵፰)።
ሰሜናዊ ፡-የሰሜን ወገን፤ አጠገብ፤ በሰሜን ያለ፤ ከሰሜን የመጣ፤ ወደ ሰሜን የሚያይ ፡-(ራእ፳፩ ፡-፲፫። ሕዝ፵ ፡-፳፫ ፡-፴፭ ፡-፵። ፵፩ ፡-፲፩። ፵፮ ፡-፱። ምሳ፳፭ ፡-፳፫)።
ሰሜን ፡-(ዕብ ስሞል። ሱር ስማል። ዐረ ሺማል) በቁሙ፤ የማእዝን ስም፤ ግራ፤ የግራ ማእዝን፤ የየማን የቴማን የደቡብ የናጌብ ትይዩና አንጻር ፊት ለፊት፤ በመስዕና በዛሕር መካከል ያለ። ከባሕር ወይም ከመስዕ ተነሥቶ የኋሊት ቢቈጥሩ ሰሜን ስምንተኛ ክፍል ይኾናል፤ የዘይቤው ዐይን ግራነትን መደብ አድርጎ ሳምናይነትን ያሳያል። ዲልማን ግን ሰሜንና ቴማን አንድ ነው ብሎ፤ ጣፊና መላሽ ቴማን ደቡብ በማለት ፈንታ ሰሜን፤ በሰሜን ፈንታ ደቡብ እያሉ አላገባቡ የጣፋትን ምስክር አድርጎ ይጠቅሳል ፡-(ኤር፲፯ ፡-፳፮። ዘካ፲፬ ፡-፬። ኢሳ፲፬ ፡-፴፩)። ይመጽኡ እምሥራቅ ወእምዕራብ እምሰሜን ወእምደቡብ። ተንሥእ ሰሜን ወነዐ ደቡብ። እመኒ ደቡበ ወእመኒ ሰሜነ ፡-(ሉቃ፲፫ ፡-፲፱። ማሕ፬ ፡-፲፮። መክ፲፩ ፡-፫። ኤር፩ ፡-፲፫። ሕዝ፩ ፡-፬)።
ሰምረ ፡-ወደደ ፈቀደ፤–ሠሚር ሠምረ።
ሰምር ሰመር ፡-(ብ ሰምራት፤ አስማር) አዝመራ፤ ያዝመራ መበጀት፤ ብጀታ፤ ፍሬ ዛላ ዘለላ፤ እሸት ጐምር፤ ነዶ ክምር፤ ምርት ቍልል። በሰምረ ገራህቱ፤ በሰምረ ዐጸደ ወይኑ ይፈዲ፤ አስማሮ ይፈዲ ፡-(ዘፀ፳፪ ፡-፬። አርጋ ፡-፭)።
(ጥ) ሰምኖ ኖት ፡-(ሰመነ ይሴምን ይሰምን። ዕብ ሻሜን፤ ሠባ ወፈረ) መሰመን፤ ስምንት ማድረግ፤ ከስምንት መክፈል መተንተን፤ የስፍር የቍጥር የማእዝን። ሸማ መሥራት። መወፈር መሥባት።
ሰምአ ፡-ሰማ፤ መሰከረ፤–ሰሚዕ ሰምዐ።
ሰምዕ ፡-ሠም ጧፍ፤–ሠምዕ።
ሰምይ ዮት ፡-(ሰመየ ይሰሚ ይስሚ። ዐረ ሰመ) መሰየም፤ ስም መስጠት፤ ስም ማውጣት፤ በስም መጥራት፤ እገሌ ማለት። ጸውዐን ተመልከት፤ የዚህ ጎር ነው። ሰመያ በስመ ወልዱ። ስምዮ ስሞ ኢይዝራኤል። ዘእንበለ ያእምር ሕፃን ሰምየ አቡሁ ወእሙ። ኢይሰሚ እንከ ስመ እግዚአብሔር። ኢትስምያኒ ኖሔሜን ፡-(ዘፍ፬ ፡-፲፯። ሆሴ፩ ፡-፬። ኢሳ፰ ፡-፬። ኤር፳ ፡-፱። ሩት፩ ፡-፳)።
፡-መሰመይ፤ ሰማይ ማድረግ፤ እንደ ሰማይ ማራቅ ማምጠቅ። ሰመያ ለገነት ሰማየ በልዕልናሃ ፡-(ፊልክ ፡-፰)።
ሰሞን ፡-ተራ ፈረቃ፤ የሹመት የማዕርግ ሥራ። ወከመ ዝ ትገብር ሎሙ ለሌዋውያን በበ ሕቢቶሙ ፡-(ዘኍ፬ ፡-፳፯ ፡-፳፰ ፡-፴፩–፴፫። ፯ ፡-፱። ፰ ፡-፳፮)።
ሰሰን ፡-(ናት) ሴሰኝነት፤ ታላቅ ኀጢአት፤ ከልክ ያለፈ የተረፈ ዝሙት፤ አምልኮ ጣዖት። ዛቲሰ ኀጢአት ሰሰን እኪት ይእቲ ፡-(፩ነገ ፡-፲፭ ፡-፳፫። አርጋ ፡-፬)።
ሰሲን ፡-(ሰሰነ፤ ይሰስን) መሴሰን፤ ባልን ሚስትን መካድ፤ ሌላ መውደድ፤ ዐልፎ ተርፎ መኼድ። ማሟረት መጠንቈል፤ ጣዖት ማምለክ ለሰይጣን መስገድ።
ሰሳሊ ፡-(ሊት ልያን ያት) የሚሸሽ የሚርቅ የሚወገድ፤ ኀላፊ ጠፊ።
ሰሳኒ ፡-(ኒት ንያን ያት) የሚሴስን፤ ሴሳኝ፤ ሴሰኛ፤ ሟርተኛ፤ መምለኬ ጣዖት።
(ጥግ) ሰስሎ ሎት ፡-(ሰሰለ ይሴስል ይሰስል። ሰረረ፤ ኀለፈ) መሸሽ፤ መራቅ መወገድ፤ መለየት ተነጥሎ መኼድ። ዘኢይሴስል እምቅድመ ዐይንከ። ኢይሴስሉ ወትረ እመንበረ መርዓዊ። ሰሰለ ረድኤተ እግዚ እምኔሁ። ሰሰለ ዮሴፍ ወሖረ። ርኢኩ እበዶሙ ለአብዳን ወሰሰልኩ ፡-(ዘፀ፲፫ ፡-፲፮። መሞሥ። ፈ ፡-መ ፡-፬ ፡-፮። ዮሴፍ። ፈላስ)።
፡-ማለፍ መጥፋት፤ መሻር መቅረት፤ ከቦታው መታጣት፤ መልቀቅ። ወርኢኩ ሰማየ ሐዲሰ ወምድረ ሐዳሰ፤ እስመ ሰሰለ ሰማይ ቀዳማዊ ወምድርኒ ቀዳሚት። ይሴስላ ግብተ ነፍሳተ ዐማፅያን። መሥዋዕት ይሴስል ወይሰዐር። ወእምዝ ሰሰለ ጽልመት ወአስተርአየ ብርሃን ፡-(ራእ፳፩ ፡-፩። ፪ጴጥ ፡-፫ ፡-፲። ምሳ፲፩ ፡-፴። አፈ ፡-ድ፲፰ ፡-ዲድ ፡-፳፬)። በሰሰለ ፈንታ ተሰሰለ ይላል፤ ስሕተት ነው። ተሰሰልክዎ አነ ለሐናንያ ፡-(ቀሌ)።
ሰረሰር ፡-በቁሙ፤ የዠርባ ዐጥንት ፡-(ዐማርኛ)።
ሰረቀ ፡-ወጣ ባተ፤–ሠረቀ።
ሰረበ ፡-ማገ፤–ሠረበ።
(ጥረ) ሰረወ ፡-ነቀለ አጠፋ፤–ሠረወ።
ሰረዘ ፡-በቁሙ፤–ሠረዘ።
(ጥረ) ሰረየ ፡-መዳኒት ሰጠ፤–ሠረየ።
ሰረገላ ፡-በቁሙ፤–ሠርገለ።
ሰሪሕ ሖት ፡-(ሰርሐ ይሰርሕ ይስራሕ። ዕብ ጣራሕ) መስራት መጣር፤ መሸከም መደብለል፤ መድከም መዛል ከስራ ከሸክም የተነሣ። ሰሪሐ ወልታ ኀጺን። ኢትስራሕ ሎሙ ባሕቲትከ። እንተ ብዙኀ ሰርሐት ለክሙ። በእንተ እለ ይሰርሑ ከመ ትባርክ ፍሬ ተግባሮሙ። በኵሉ ስራሕየ ዘሰራሕኩ። ትረክብ ሰሪሐከ ፡-(አዋል። ዘኍ፲፩ ፡-፲፯። ሮሜ፲፮ ፡-፮። ቅዳ። መክ፪ ፡-፲፬። ሢራ፲፫ ፡-፳፮)። ሠርዐን ተመልከት፤ የዚህ ጎር ነው፤ ሠርዐ የብልኀት፤ ሰርሐ የጕልበት።
ሰሪር ሮት ፡-(ሰረ፤ ሰረረ ይሰርር ይስርር። ዐረ ሳረ። ዕብ ሳረር፤ መለከ) መስረር፤ በላይ መኾን፤ መከመር፤ መ ዘል፤ መሰቀል፤ ያለሌ ያውራ የጋላቢ። ፡-(ተረት) ቀንም ሰረሩ ግራም ሰረሩ መገናኛው ኮሩ። መርዘም ማደግ ወደ ላይ መውጣት፤ መንጠራራት፤ የቁመት።
፡-መዝለል መር ቸር ባጥ እንጣጥ ፊናጥ ማለት፤ መወርወር፤ ያንበሳ የነምር የተራጋጭ ከብት። ትሰርር ላዕሌሆሙ ከመ አንበሳ። ይሰርሩ ከመ ነምር። ሰረረ ላዕሌሆሙ ዓሣ። ሰረረ ራጉኤል ወሰዐም ፡-(ሢራ፳፰ ፡-፳፫። ዕን፩ ፡-፰። ጦቢ፮ ፡-፫። ፯ ፡-፮)።
፡-መክነፍ መብረር፤ ወዳየር መውጣት፤ ከምድር መራቅ መምጠቅ፤ ምድርን መተው መልቀቅ፤ ምድር ደኅና ዋይ ማለት፤ የአዕዋፍ። መኑ ይሁበኒ ክንፈ ከመ ርግብ እስርር ወአዕርፍ። ወበክልኤ ክንፍ ይሰሩ። ይሰርራ ደመናት ከመ አዕዋፍ። ሰረረት ታቦተ ኖኅ መልዕልተ ማያት በክነፈ ነፋስ። እምነ ምድር ይሰርር ኅሊናሁ ለጴጥሮስ እስከ ሳበዕ ሰማይ ፡-(መዝ ፡-፶፬። ኢሳ፮ ፡-፪። ሢራ፵፫ ፡-፲፬። ቀሌ)።
ሰሪቅ ቆት ፡-(ሰረቀ ይሰርቅ ይስርቅ። ዐረ ሰረቀ። ዕብ ሳራቅ) መስረቅ፤ መደበቅ፤ ሳይታዩ መውሰድ ማንሣት፤ መሳብ መጐተት፤ ማጥፋት ማበላሸት፤ የገንዘብ የነገር። ይኄይስ ሰሪቅ እምሐስዎ። ኀፍረት ሰሪቅ እምንዋየ ማሕፀንት። ዘይሰርቁ በሚዛን። ሰረቀቶ ወነሥአቶ ሰሪቃ። ሰረቀ ርእሶ። እለ ይሰርቁ ቃልየ ፡-(ሢራ፳ ፡-፳፭። ፵፩ ፡-፲፱። ፈ ፡-መ ፡-፲፯ ፡-፯። ፪ዜና ፡-፳፪ ፡-፲፩። አፈ ፡-ድ፳፮። ኤር፳፫ ፡-፴)። አንዳንድ መጣፍ በሰረቀ ፈንታ አስረቀ ይላል፤ አያሰኝም። እስመ ሃይማኖተ እንተ ተወፈይነ ያሰርቁ ፡-(ቄር ፡-ጰላ)።
ሰሪብ ቦት ፡-(ሰረበ ይሰርብ ይስርብ። ዐረ ሰሪበ) መፍሰስ መውረድ፤ መጕረፍ መንፏፏት፤ መንደልደል መንሿሿት፤ መንቧቧት የዝናም የውሃ። ከጥሬው በቀር አንቀጹ አይገኝም።
ሰሪው ዎት ፡-(ሰረወ ይሰሩ ይስሩ። ዕብ ሳራህ። ዐረ ሰረይ) መዋጋት መታገል፤ መበርታት ማየል፤ ማሸነፍ መጣል፤ ድል መንሣት፤ አሸንፎ መግዛት።
ሰሪግ ጎት ፡-(ሰረገ ይሰርግ ይስርግ፤ ሰርገወ። ዐረ ሰሪጀ። ዕብ ሳራግ። ሱር ስራግ) መሥራት መታታት፤ መጥለፍ ማቈላለፍ፤ ሥረ ወጥ ማድረግ፤ የሹራብ የቀሚስ የመርገፍ። መሰረግ፤ ሰርግ ማድረግ መደገስ፤ የሰርጉን ቤትና የሰርጉን ልብስ መሸለም ማስጌጥ፤ ማንቈጥቈጥ። ረቀመንና ረገፈን እይ፤ የዚህ ጎር ናቸው።
ሰሪፍ ፎት ፡-(ሰረፈ ይሰርፍ ይስርፍ። ዕብ ሳራፍ) ማንደድ ማቃጠል፤ ማጤስ ማጠን፤ የመሥዋዕት የቍርባን፤ የዕፅና የሣዕር የሌላውም ኹሉ። መብሳት መንደል መሰርሰር።
ሰራሒ ፡-(ሒት ሕያን ያት፤ ሕት) የሚሰራ የሚጥር፤ የሚደክም የሚሸከም፤ ሰራተኛ።
ሰራሴሮት ፡-(ጽር ሴርሴሮት። ዕብ ሻርሽሮት) ሰንሰለት፤ የሰንሰለት ዐይነት ፡-(፪ዜና ፡-፫ ፡-፲፮)።
ሰራሪ ፡-(ሪት ርያን ያት) የሚሰር የሚበር፤ በራሪ ዘላይ። ንስር ሰራሪ። ዖፍ ሰራሪት። ከመ አእዋፍ ዘይሰርራ ወሰራርያት። አግማልሰራርያን ፡-(ግንዘ። መቃ። ምሳ፳፮ ፡-፪። ፍ ፡-ነ ፡-፵፯)።
ሰራቂ ፡-(ቂት ቅያን ያት፤ ረቅት) በቁሙ፤ የሚሰርቅ፤ የሚደብቅ፤ ሌባ ቀጣፊ። ከመ ኀፍረተ ሰራቂ ሶበ ይአኅዝዎ። ሰረቅተ ሰብእ። ሱቱፋነ ሰረቅት። በእንተ ኵነኔ ሰረቅት ፡-(ኤር፪ ፡-፳፮። ፩ጢሞ ፡-፩ ፡-፲። ኢሳ፩ ፡-፳፫። ፍ ፡-ነ ፡-፵፱)።
ሰራዪ መስረዪ ፡-(ዪት ይያን ያት፤ ረይት) ይቅር ባይ፤ ዕዳን በደልን የሚተው የሚያቀል፤ ይቅር የሚል። መሓሬ እከውን ወሰራዬ ለአበሳሆሙ። እግዚ ሰራዬ ኀጢአትነ። ሰራይያን ኀጣውአ። ቍርባን ሰራዬ ኀጢአት ፡-(፪ዜና ፡-፯ ፡-፲፬። ቅዳ። ፍ ፡-ነ ፡-፭። ፈ ፡-መ ፡-፳፮ ፡-፬)።
ሰራጊ ሰርጋዊ ፡-የሚያስጌጥ የሚሸልም፤ አስጊያጭ ሸላሚ፤ ሰርገኛ። መጽሐፍ ግን በሰረገና በሰርገወ ፈንታ አስርገወ ይላል፤ አያሰኝም። አሰርገወ ዕበያ ለጥበቢሁ። አሰርጎኩኪ ሰርጐ። አሰርጎከ ሰማየ ፀሓየ ወወርኀ። አሰርጎካ ለምድር። አሰርግዎ ነገረ ፡-(ሢራ፵፪ ፡-፳፩። ሕዝ፲፮ ፡-፲፩። መዋሥ። ድጓ። ተረ ፡-ቄር)።
ሰራፊ [1]፡-(ዕብ ጾሬፍ) አንጥረኛ፤ ብር አፍሳሽ፤ ጃን ሸላሚ። ወልደ ሰራፊ ፡-(ነሐ፫ ፡-፴፩)።
[2]፡-ሰራፊ፤ ፡-(ፊት ፍያን ያት፤ ረፍት) የሚያነድ የሚያጤስ፤ የሚያጥን ዐጣኝ።
ሰር ፡-የሞፈር ቂጥ፤ ሻኛው ጐባባው ፡-(ዐማርኛ)።
ሰርሐ ፡-(ጥር) –አቀና አበጀ፤–ሠርሐ።
ሰርም ፡-ረግረግ፤–ሠረመ።
ሰርቅ ፡-ዝኒ ከማሁ፤ ስርቆት። ማየ ሰርቅ። ንዋየ ሰርቅ ፡-(ምሳ፱ ፡-፲፯። ፈ ፡-መ ፡-፲፯ ፡-፩)።
ሰርባ ፡-(ትግሬ) ቋንዣ ባት።
ሰርብ ሰረብ ፡-(ብ አስራብ) ሿሿቴ ፏፏቴ፤ የዝናም የገደል የማዕበል ውሃ፤ ምንጭ ዐዘቅት ወንዝ ፡-(ቦንቧ) አሸንዳ፤ መስኖ። አስራበ ሰማይ። አስራበ ማይ። አስራበ ቀላይ። ቃለ ነቢያት ዘይውሕዝ ከመ አስራበ ወርቅ ንጹሕ። ለእመ አውሐዘ እግዚ አስራበ እክል እምሰማይ ፡-(ዘፍ፯ ፡-፲፩። ጥበ፲፮ ፡-፲፮። አርጋ፫። መዝ ፡-፵፩። ፬ነገ ፡-፯ ፡-፪)።
ሰርን ፡-በቁሙ፤ ያፍንጫ ዐጥንት፤ ኰሽኰሽ ፡-(ዐማርኛ)።
ሰርክ ሲራክ ፡-ሲራክ፤–በቁሙ፤–ሠረከ።
ሰርዌ [1]፡-(ብ ስረው፤ ሰራዊት። ዕብ ጽባእ፤ ጽባኦት። ዐረ ሰሪየት፤ ብዙ ፈረሰኛ) ሰራዊት፤ ጭፍራ፤ ወታደር፤ ዘማች፤ የጦር ሕዝብ፤ ሰልፈኛ። ፋኮል መልአከ ሰርዌሁ። ሶቤክ መልአከ ሰርዌሆሙ ብእሲ ጽኑዕ ፡-(ዘፍ፳፩ ፡-፳፪ ፡-፴፬። ፩ዜና ፡-፲፱ ፡-፲፰። ዳን፰ ፡-፲፩)። ንእማን መልአከ ስርዊሆሙ ለሶርያ ፡-(፬ነገ ፡-፭ ፡-፩። ፳፭ ፡-፲፱)። መላእክተ ሰራዊት። ሰራዊት ብዙኃን ወጽኑዓን። ሰራዊተ አሕዛብ። ሰራዊተ መላእክት። ገብርኤል ሊቀ ሰራዊተ ሰማያት ፡-(አስቴ፩ ፡-፫። ዮኤ፪ ፡-፭። ሕዝ፳፫ ፡-፳፬። ቅዳ። ስንክ ፡-ሠኔ፲፫)።
፡-የሰራዊት ክፍል፤ ክቢ፤ ቍርጥ፤ በያበጋዙና በያለቃው የሚጓዝ የሚሰለፍ ፡-(ኢዮ፩ ፡-፲፯። ፩ነገ ፡-፲፩ ፡-፲፩። መሳ፱ ፡-፴፬ ፡-፴፯)።
[2]፡-ሰርዌ፤ ፡-(ብ ሰራው። ዕብ ሳር፤ ሳሪም) የጦር አበጋዝ፤ አዝማች አለቃ፤ ደምሳሽ ጠቅላይ፤ ገዥ አዛዥ።
ሰርይ ዮት ፡-፤ ፡-(ሰረየ ይሰሪ ይስሪ። ሱር ሽራእ። ዐረ ሰራእ) መስረይ፤ መፍታት፤ መተው መልቀቅ፤ ማንጻት ማውጣት፤ ከኀጢአት፤ ተኀድገ ለከ፤ ኩን ፍቱሐ፤ ይቅር ለእግዜር ማለት፤ ዕዳን በደልን ማቅለል፤ የቄስ የተበዳይ። ይሰሪ ለከ ኀጢአተከ። ከመ እስረይ ሎሙ ኀጢአቶሙ። እግዚ ሰረየ በእንተ እኪት። ስረይ ሊተ ለኃጥእ እግዚኦ ፡-(ሢራ፳፰ ፡-፪። ኢሳ፴፰ ፡-፴፬። ዘፀ፴፫ ፡-፲፬። ሉቃ፲፰ ፡-፲፫)።
ሰርዲኖ ፡-(ጽር ሳርዲኖን። ዕብ ኦዴም) ዝኒ ከማሁ፤ ዕንቍ ቀይሕ ፡-(ራእ፬ ፡-፫)።
ሰርድዮን ፡-(ጽር ሳርዲዎስ፤ ሳርዲዎን። ዕብ ሾህም) ዕንቍ፤ የዕንቍ ስም፤ ክቡር ደንጊያ። ሶምን ተመልከት፤ ከዚህ ጋራ አንድ ነው። እብነ ሰርድዮን። ዕንቈ ሰርድዮን። ወሳድስት በሰርድዮን ፡-(ዘፀ፳፭ ፡-፯። ምሳ፳፭ ፡-፲፪። ራእ፳፩ ፡-፳)።
ሰርዶ ፡-የሣር ስም፤ ጥሩ ሣር፤ ትሐግ።
ሰርዶንክስ ፡-(ጽር ሳርዶኒክስ። ዕብ ያሀሎም) ዝኒ ዓዲ ከማሁ፤ ዕንቍ፤ ብርቱ ጠንካራ፤ ሕብሩ ይህ የማይባል፤ ባለጮራ ባለምዕዛር ፡-(ራእ፳፩ ፡-፳)።
ሰርጕ ፡-(ጓት) ጌጥ ሽልማት የሰርግ የበዓል ልብስ፤ መርዓዊና መርዓት ዘመዶቻቸውም የሚለብሱት። ሰርጐ ወርቅ። ሰርጐ ያክንት። ሰርጐ መርዓት። ትረስዕኑ መርዓት ሰርጓ። ሰርጐ ቤት። ሰርጕሃ ለሰማይ። ሰርጓቲሆሙ ሰርጐ ወርቅ ወብሩር። ሰርጓት ሰማይ ፡-(ዘፀ፴፪ ፡-፪። ሢራ፮ ፡-፴። ኢሳ፷፩ ፡-፲። ኤር፫ ፡-፴፪። ፩ዜና ፡-፳፱ ፡-፲፱። ዘዳ፲፯ ፡-፫። መቅ ፡-ታም። ኤር፰ ፡-፪)።
ሰርግ ፡-በቁሙ፤ ከብካብ፤ መርዓ፤ የጋብቻ በዓል ድግስ፤ የሚያጌጡበት የሚሸለሙበት።
ሰርጣን ሸርጣን ፡-(ዐረ ሰረጣን። ዕብ ሳርጣን) ጐርምጥ፤ የጐርምጥ ዐይነት፤ እግራም፤ ታናሽ የውሃ እንስሳ። ኮከብ፤ ካ፲፪ቱ መናዝል አንዱ። ኮከብነቱም የሠኔ ነው፤ ከፀሓይ ጋራ ፴፩ ዕለት ፳፮ ኬክሮስ ይመግባል ፡-(አቡሻ ፡-፬)።
ሰሮጸ ሰርወጸ ፡-(ረዊጽ ሮጸ ሰ። ዕብ ራጻጽ) ሰረወጠ፤ ስርውጥ አለ፤ ወለም አለ፤ ዞረ፤ ወለቀ፤ ተሰበረ፤ የሥር የዥማት ያጥንት፤ ከሩጫ ብዛር የተነሣ። ዐሸ ጠገነ፤ ሸበለቀ አሰረ።
ሰቀላ ፡-(ብ፤ ሰቃልው) በቁሙ፤ ቤት ድንኳን ሞላላ ዠላላ፤ ክብና ምእዙን ያይዶለ። በአምሳለ ስቀላ። ገበርተ ሰቀላ። ቦአ ውስተ ሰቀላሁ ወሰከበ። ሠለስቱ ሰቃልው። በሰቃልው ወበአጐበር ፡-(ገድ ፡-ተክ። ግብ፲፰ ፡-፫። ኩፋ ፡-፯። ማቴ፲፯ ፡-፬። መቅ ፡-ታም)።
ሰቂል ሎት ፡-(ሰቀለ ይሰቅል ይስቅል። ዕብ ሻቃል። ሱር ሽቃል፤ ትቃል። ዐረ ተቀለ፤ ሸቀለ) መስቀል ማንጠልጠል፤ መመዘን ወደ ላይ ማንሣት፤ ማጓን። ዘገብረ ሰማየ ወሰቀሎ። ሰቆላ ለምድር ዲበ ዕራቃ። ንሕነ ሰቀልናሁ ለሰማይ ዘእንበለ ዐምድ። ሰቀለ መንጠዋልዐ ዘወርቅ። መትከል በዘይሰቅሉ ቦቱ ኵሎ ንዋየ። ሰቀሉ ምስሌሁ ክልኤተ ፈያተ። ሰቀልዎ መልዕልተ ዕፅ ነዊኅ ፡-(ኢሳ፵፬ ፡-፭። ኢዮ፳፮ ፡-፯። ቀሌ። አፈ ፡-ተ፳፭። ሕዝ፲፭ ፡-፫። ድጓ። ዮሐ፲፱ ፡-፲፰። ስንክ ፡-መጋ፬)።
ሰቂማ ሰቂሞን ፡-(ጽር ሲኪማ። ዕብ ሽኬም) ሴኬም፤ ስመ ሀገር ቦታ፤ ያዕቆብ ከሴኬም አባት ከኤሞር የገዛት፤ ኋላም ለዮሴፍ የሰጣት ፡-(ዘፍ፴፫ ፡-፲፯–፳። ፵፰ ፡-፳፪። መዝ ፡-፶፱። ፻፯)። ባለብሉዮች ግን ምርኮ ይሉታል፤ ባለቅኔዎችም ሰቀመ ማረከ ብለው ይገሳሉ፤ ኹሉም ስሕተት ነው። ኤሞር የሀገሪቱ ቀንድ ዋና ባላባት ገዥ ስለ ኾነ፤ በልጁ ስም ሴኬም አሰኝቷታል። ያዕቆብም ዳስና በረት ስለ ሠራባት ሱኮት ብሏታል። ሴኬም ህየ በዲና ተሀጕለ ወበሳራ አቤሜሌክ ቈስለ ፡-(ቅኔ። ዘፍ፴፬ ፡-፩–፬)። የግእዝ መላሾች ሴኬምን ሰቂማ ስላሉት ንባቡም ምስጢሩም ተሳስቷል፤ ሰቂማና ሴኬም ፩ ስም ነው እንጂ ኹለት አይዶለም።
ሰቍር ሮት ፡-(ሰቈረ ይሰቍር ይስቍር፤ ነቈረ። ዕብ ዳቃር፤ ወጋ ሰነቀረ) መሸንቈር፤ መሰርሰር መብሳት መንደል፤ መፋር መቈፈር፤ ለመብሳት። ለአእባን ኢይክል ይስቍሮሙ ማይ፤ ይሰቍሩ አብያተ። ኢይሰቍሮ ቀስተ ብርት። ትሰቍር አንፎ በኅርወት። ይስቍር እዝነ ጥይዕተ። ሰቈረ እዘኒሆሙ ፡-(ዮሴፍ። ኢዮ፵፩ ፡-፲፱ ፡-፳፮። ቅዳ ፡-ዮሐ። ቀሌ)።
ሰቍቍ ቆት ፡-(ሰቈቈ ይሰቍቍ ይስቍቍ። ዕብ ሻቃቅ፤ ሹቅ። ዐረ ሻቀ) መፈለግ መሻት፤ መመኘት መጐምዠት፤ መውደድ መሣሣት፤ ባንድ ነገር ላይ መውደቅ፤ ልሙትበት ማለት። መጽሐፍ ግን በሰቈቈ ፈንታ ተሰቈቈ ይላል። ኢተሰቈቍ ንዋየክሙ። ኀፍረት ተሰቍቆ ንዋየ ባዕድ። ዘኢይሰቈቍ ንዋየ ባዕድ በዐመፃ ፡-(ግብ፳ ፡-፴፫። ፪ቆሮ ፡-፲፩ ፡-፰። ቀሌ)።
ሰቃሊ ፡-(ሊት ልያን ያት፤ ቀልት) የሚሰቅል፤ የሚያንጠለጥል፤ መዛኝ ሰቃይ። አይሁድ ሰቃልያን ፡-(ቀሌ)።
ሰቃዪ ፡-መስቀዪ፤ ፡-(ዪት ይያን ያት፤ ቀይት) የሚያጠጣ አጠጭ ጪ፤ ዐዳይ ሰጪ። ሰቃዬ አትክልት። ሥሡዓን በሳዕያን ወሰቃይያን ወሰካርያን ፡-(አዋል። መቃ)።
ሰቈራር ፡-(ቅጽልና ጥሬ) የሚያስጠይፍ፤ የሚያሰቅቅ፤ ከባድ፤ ግም፤ ጽሉእ፤ ርኩስ፤ ቅጽል።
ሰቈቃው ፡-ጩኸት ዋይታ፤ ልቅሶ ሙሾ፤ የልቅሶ ግጥም፤ ኀይለ ቃል። ሰቈቃወ ኤርምያስ ነቢይ። ንሥኢ ሰቈቃወ በከናፍርኪ። ንሣእ ሰቈቃወ ላዕለ መላእክተ እስራኤል ፡-(ሰቈ ፡-፩። ኤር፯ ፡-፳፬። ዝሕ፲፱ ፡-፩። ማቴ፪ ፡-፲፰)።
፡-ጩኸት፤–ቈቀወ አስቈቀወ።
ሰቅ ፡-በቁሙ ማቅ፤–ሠቅ።
ሰቅል ሰቅሎስ ን ፡-(ጽር ሲክሎስ። ዕብ ሼቄል) የሚዛን ደንጊያ፤ ብረት ርሳስ፤ ኻያ አቦሊ ወይም አንድ ዲድርክም የሚያነሣ። የገንዘብ ስም፤ ወርቅ ብር እንደ ዲድርክም ያለ፤ እስራኤል ለቤተ መቅደስ የሚሰጡት፤ አንዱ ሰቅል ፪ ድሪም ወይም ፳ ጌራ፤ ጌራና አቦሊ ሰቅልና ዲድርክም ትክክል ናቸው፤ ፶ው ሰቅል ፩ ምናን ይኾናል ፡-(ዘፀ፴ ፡-፳፫ ፡-፳፬። ፴፱ ፡-፩ ፡-፪። መሳ፰ ፡-፳። ሕዝ፬ ፡-፲። ፵፭ ፡-፲፪)።
ሰቅይ ዮት ፡-(ሰቀየ ይሰቂ፤ ይስቂ። ዐረ ሰቀይ። ዕብ ሻቆህ። ሱር ሽቄይ ) ማጠጣት፤ ማርካት፤ መጠጥ መስጠት፤ መጨመር። እሰቅያ ለገነት። ይፈለፍል ነቅዕ ወይሰቂ። ዘይሰቅዮሙ ለአድባር። ሰቀየነ ማየ። ሰብዐቱ መሳውር በዘይስቅይዎን ለመኃትዊሃ ፡-(ሢራ፳፬ ፡-፴፩። ዮኤ፫ ፡-፲፰። መዝ ፡-፻፫። አፈ ፡-ድ፳። ዘካ፬ ፡-፪)።
ሰቆጵዮን ፡-(ጽር ስኮፒያን። ዕብ ሚጽፋ) ስመ ሀገር፤ መሴፋ፤ በብንያም ክፍል ያለች። ማያ መመልከቻ በር ዐንገት፤ ጕበኛ ዘበኛ የሚቆምበት ማለት ነው ፡-(፫ነገ ፡-፲፭ ፡-፳፪። ኢያ፲፰ ፡-፳፮)። መሴፋ ፡-(ሚጽፋ) ተብለው የሚጠሩ ብዙ አገሮች ናቸው ፡-(ኢያ፲፭ ፡-፴፰። መሳ፳ ፡-፩። ፩ነገ ፡-፯ ፡-፮)።
ሰቋሪ ፡-(ሪት ርያን ያት፤ ቈርት) የሚሸንቍር የሚበሳ፤ ሰርሳሪ ሸንቋሪ።
ሰበረ ፡-(ዕብ ሳባር። ዐረ ጸበረ) ጸንሐ፤ ቈየ፤ ታገሠ፤ ደጅ ጠና።
ሰበቅታኒ ፡-(ሱር ሽባቅታኒ። ጽር ሳባኽታኒ። ዕብ ዐዛብታኒ) ኀደገኒ፤ ገደፍከኒ፤ ተውኸኝ፤ ጣልኸኝ። ኦ ወልድ ክላሕ ከመ ዘሐመ ወበል ኤልማስ ላማ ሰበቅታኒ ፡-(ቅዳ ፡-አት። ማቴ፳፯ ፡-፵፮። ማር፲፭ ፡-፴፬)።
ሰበብ ፡-በቁሙ፤ ምክንያት፤ መነሻ፤ የነገር ዙሪያ፤ ከርከሬሻ። ፡-(ተረት) በሰበቡ መምሬ ተሳቡ።
፡-የጥርስ እድፍ፤ ችክ፤ ግርድ ሻክላ፤ ኖራ ፡-(ትግሬ)።
ሰበን [1]፡-(ጽር ሳባኖን። ዕብ ሳብና) ነጭ ጥሩ ልብስ፤ ስንዱን፤ በኅፅበት ጊዜ ከውሃ ሲወጡ የሚለበስ።
[2]፡-(ጽር ሱዳሪዎን። ዕብ ሱዳር) ያነገትና የራስ የትከሻ ልብስ፤ ሻል፤ ሞጣሕት፤ በላይ የሚለበስ፤ ታናሽ ወይም ታላቅ ፡-(ሉቃ፲፬ ፡-፳። ዮሐ፲፩ ፡-፵፬። ፳ ፡-፯። ግብ፲፱ ፡-፲፪)።
[3]፡-ሰበን፤ ፡-(ናት። ጽር ኪዳሪስ። ዕብ ፍኤር፤ ጻኒፍ) የራስ ልብስ፤ ጌጥ ሽልማት፤ ቆብ ጥምጥም፤ መጠምጠሚያ። ደዩ ሰበነ ንጹሐ ዲበ ርእሱ። ሰበን ዘዐጌ ይኩን ላዕለ ርእሶሙ። ሰበኖሙ ይኩን ዐሠርተ በእሙት ፡-(ዘካ፫ ፡-፭። ሕዝ፵፬ ፡-፲፰። አቡሻ ፡-፭። ገድ ፡-አዳ ፡-ገ፻፵፱)። ቄዳርን ተመልከት።
ሰበጠ ፡-ቀረበ፤ ተዘጋጀ፤–ሠቢጥ ሠበጠ።
ሰቡዑ ፡-ሰባቱ፤ ሰባተኛው። አመ ሰቡዑ ለነሐሴ ፡-(መቅ ፡-ታም)።
ሰቡዕ ፡-የዕለት ቅጽል፤ ሰባት፤ ሰባተኛ። እምድኅረ ሰቡዕ መዋዕል። ሰቡዐ መዋዕለ። አመ ሰቡዕ። በሰቡዕ ሠርቅ ፡-(ዘፍ፯ ፡-፲። ዘሌ፲፭ ፡-፲፫። ዘካ፯ ፡-፭። ባሮ፩ ፡-፪)።
ሰቢል ሎት ፡-(ሰብለ ይሰብል ይስብል። ዕብ ሳባል፤ ጾረ። ዐረ ሰቢለ፤ ሰንበለ) ሰብል መኾን፤ መዘርዘር መውለድ፤ መጨርቋት፤ መሸት፤ ማፍራት፤ ፍሬ መያዝ መሸከም። ሰገም እንበለ ይስብል ፡-(ዘፀ፱ ፡-፴፩)።
ሰቢር ሮት ፡-(ሰበረ ይሰብር ይስብር። ዕብ ሻባር። ሱር ትባር። ዐረ ተበረ) መስበር፤ መሰባበር፤ መቀጥቀጥ፤ ማንከት፤ ማድቀቅ፤ ማድከም፤ ፡-(ድል ማድረግ፤ ማሸነፍ)። እሰብር አናቅጸ ብርት። እለ ይሰብሩ ቍልፋተ። ልሳን ድክምት ትሰብር አዕፅምተ። ሐዘኑ ለልብ ይሰብሮ ለኀይል። ለምንት ትሰብሩ ልብየ ፡-(ኢሳ፵፭ ፡-፪። ፍ ፡-ነ ፡-፵፬። ምሳ፳፭ ፡-፲፭። ሢራ፴፰ ፡-፲፰። ግብ፳፩ ፡-፲፫)። ዘበረን ተመልከት፤ የዚህ ጎረ ቤት ነው።
ሰቢቅ ቆት ፡-(ሰበቀ ይሰብቅ ይስብቅ። ሱር ሻባቅ) መተው መልቀቅ መጣል፤ እንዲሞት እንዲጠፋ ማድረግ። መስበቅ፤ ማሳበቅ፤ የእጅ የነገር። መጨፈቅ መማገር፤ ማያያዝ ማስተሳሰር፤ የዕፅ የሐረግ።
ሰቢብ ቦት ፡-(ሰበ፤ ሰበበ ይሰብብ ይስብብ። ዕብ ሳባብ) መዞር፤ ማቀፍ፤ መክበብ፤ ዙሮ መግጠም፤ መጠምጠም። መፍስስ፤ መነዛት፤ መረጨት፤ መሠራጨት፤ የመርዝ የሰራዊት። ወደኃሪታ ከመ ንስከተ አርዌ ምድር ትሰፍሕ ወከመ ዘእምቃግስት ይሰብቦ ሕምዙ ፡-(ምሳ፳፫ ፡-፴፪)።
፡-መሸበብ፤ በሽባ መያዝ መሳብ። መሰበብ፤ ሰበብ መሻት፤ ምክንያት መፈለግ፤ በዙሪያ መኼድ፤ ነገርን ለማፍረስ። ሰወበን ተመልከት፤ የዚህ መንቲያ ነው።
ሰቢእ ኦት ፡-(ሰብአ ይሰብእ ይስባእ። ዕብ ወሱር ሻባዕ። ዐረ ሸቢዐ) ፈጽሞ መጥገብ፤ መርካት፤ አብዝቶ ማግኘት፤ የምግብ የገንዘብ። መፅነስ ማርገዝ፤ መንጠርዘዝ፤ የሰብልና የሴት። ሰብዐን እይ፤ የዚህ መንቲያ ነው።
ሰቢክ ኮት ፡-(ሰበከ ይሰብክ ይስብክ፤ ከረዘ። ዕብ ሳባኽ፤ ሰንሰለ ፀፈረ) መስበክ፤ ማብሠር፤ ማስተማር፤ በታላቅ ቃል መጮኽ ማሰማት፤ መልፈፍ፤ መለፍለፍ፤ ዐዋጅ መንገር፤ ማዜም መዘመር፤ ማውራት መመስከር። ፈነወኒ እስብክ ግዕዛነ ለፂውዋን። በከመ ሰበኩ ነቢያት። እፎኑ ይሰምዑ ዘኢሰበኩ ሎሙ፤ ወእፎኑ ይሰብኩ እንዘ ኢይትፌነዉ። ይስብክ ሎቱ ዐዋዲ ውስተ መርሕበ ሀገር። ይስብክ ዲያቆን ቅድመ ወንጌል እመዝሙረ ዳዊት። ሰበከ በህየ በወንጌለ ኢየሱስ ፡-(ኢሳ፷፩ ፡-፩። ቀሌ። ሮሜ፲ ፡-፲፬። አስቴ፮ ፡-፱ ፡-፲፩። ሥር ፡-ቅዳ። ስንክ ፡-መጋ፲፩። ሠኔ፳፯)።
ሰባሒ ፡-(ሒት ሕያን ያት) የሚያመሰግን፤ አመስጋኝ፤ ቀዳሽ አወዳሽ። ይንእስ ሰባሒ እምተሰባሒ። ሰባሕያን ወመተንብላን ፡-(አዋል። መዋሥ። አርጋ ፡-፪)።
ሰባሪ ፡-(ሪት ርያን ያት) በቁሙ፤ የሚሰብር፤ የሚሰባብር። ከይሲ አው አርዌ ሰባሪ ፡-(ፊልክ ፡-፻፭)።
ሰባቂ ፡-(ቂት ቅያን ያት) በቁሙ፤ የሚሰብቅ፤ የሚያሳበቅ፤ ሰብቀኛ፤ ሰብቃም።
ሰባቢ ፡-ከባቢ ጦር፤ ዘበኛ ነጡር፤ ጭፍራ ወታደር። ሰባቢ፤ ሰበብ ፈላጊ፤ ስበበኛ፤ ሰበባም።
ሰባዒ ፡-(ዒት ዕያን ያት) የሚሰብት፤ ሰባች፤ ሰባት አድራጊ።
ሰባኪ [1]፡-(ኪት ክያን ያት) በቁሙ፤ የማሰብክ፤ የሚያስተምር፤ ዐዋጅ ነጋሪ። ኮነ ሐዋርያ ወሰባኬ ወንጌል። ዮሐንስ ሰባኬ ጥምቀት። በአፈ ዐሠርቱ ወኀምስቱ ነቢያት ሰባክያን ፡-(ዲድ ፡-፲። መዋሥ። ግንዘ። ፊልክ ፡-፵፩)።
[2]፡-ሰባኪ፤ የሚያቀልጥ የሚያፈስ፤ አቅላጭ አፍሳሽ። ሰባኬ ብሩር ፡-(አፈ ፡-ተ፭)።
ሰብሐ ፡-ሠባ ወፈረ፤–ሠቢሕ ሠብሐ።
(ጥ) ሰብሖ ሖት ፡-(ሰብሐ ይሴብሕ ይሰብሕ። ዕብ ወሱር ሻባሕ። ዐረ ሰበሐ) ማመስገን፤ ማወደስ፤ ማክበር ማግነን፤ በክብርና በታምራት መግለጥ፤ ማብራት፤ የክብር ብርሃን መስጠት። ሰብሕዎ ለእግዚ ኵልክሙ አሕዛብ፤ ወይሴብሕዎ ኵሎሙ ሕዝብ። ሰብሐኒ በቅድመ ሊቃውንቲሆሙ ለእስራኤል። እመሰ ለልየ ሰባሕኩ ርእስየ ኢይበቍዐኒ ስብሐትየ። አባ በጽሐ ጊዜሁ ከመ ትሰብሖ ለወልድከ፤ ወወልድከኒ ከመ ይሰብሕከ። ሰብሖ ለምሕረትከ ፡-(መዝ ፡-፻፲፮። ፩ነገ ፡-፲፭ ፡-፴። ዮሐ፰ ፡-፶፬። ፲፯ ፡-፩። መዝ ፡-፲፮)።
ሰብል ፡-(ላት፤ ዕብ ሽቦሌት። ሱር ሺብላ። ዐረ ሰበል) በቁሙ፤ ዝርዝር፤ ወለዳ፤ ጨርቋ ቀጭን እሸት፤ ራስ ዛላ፤ ዘለላ፤ እልፍ ከነምርቁና ከነቂንዱ ፡-(ማር፬ ፡-፳፰)። ሰብለ ሥርናይ ወሰበለ እክል። ሀለዉ ውስተ እዴሁ ሰብዐቱ ሰብላት ዘሠዊት ዘሠረጹ እምአሐዱ ብርዕ። ወሰብሉኒ ይከውን ሠላሳ ኅጠተ ፡-(መቃ ፡-ገ፲፱። ዮሴፍ። ፊልክ ፡-፬)።
»ሰብሰበ ፡-(ዐማርኛ) ሰበሰበ። ስብሳብ ሰበሰብ የዚህ ዘር ነው። ባለቅኔዎች ግን አገባ ብለው እንደ አውሰበ ይፈቱታል፤ ወሥአን እይ።
»ሰብሳብ [1]፡-ጋብቻ ግቢ ተክሊል፤ ፅምረት ሩካቤ። ዝሙት ኢኮነ ሰብሳበ ወኢይትኌለቍ ብሰብሳብ። ቀዳሚ ሰብሳብ ንዱሕ በኀበ እግዚ። ሰብሳብ ዘሕግ። ቀኖና ሰብሳብ። እለ ውስተ ሰብሳብ ፡-(ፈ ፡-መ ፡-፭ ፡-፰። ዲድ ፡-፲፬። ቄድር። ቀሌ። መቃ ፡-ገ፲፯)።
[2]፡-ጋብቻ ግቢ፤–ወሰበ።
ሰብር ፡-ትዕግሥት፤ ደጅ ጥናት፤ ሬት።
ሰብአ ሐጽ ወቀስት ፡-ቀስተኞች፤ ባለቀስቶች ፡-(ኢሳ፳፩ ፡-፲፭)።
ሰብአ ምሥያጥ ፡-ገባያተኞች፤ ነጋዶች ዐጣሮች፤ ባለመደብሮች ፡-(ግብ፲፯ ፡-፭)።
ሰብአ ቤት ፡-ቤተ ሰብ፤ ዘመድ፤ ወገን ነገድ፤ ሎሌ ገረድ ፡-(ዘፍ፴፭ ፡-፪)።
ሰብአ አዝያዥ ፡-ኮከበኞች ኮከብ ቈጣሮች፤ የኮከብ ፈላስፎች፤ ስብአ ሰገል ፡-(አቡሻ ፡-፲፩)።
ሰብአ ዐይን ፡-ጕበኛ ስላይ፤ ተመልካች፤ አስተዋይ ፡-(ሕዝ፫ ፡-፲፯)።
ሰብአ አፍራስ ፡-ፈረሰኞች፤ ፈረስ ዐዋቆች፤ ለጓሞች ባልደራሶች ፡-(ኤር፬ ፡-፳፱)።
ሰብአ ዜና ፡-ወሬኞች ወሬያሞች፤ ወሬ ነጋሮች፤ ባለምሥራቾች፤ ታሪክ ዐዋቆች ፡-(ናሖ፪ ፡-፩)።
ሰብዐቱ ት ፡-የወንዶች ድምር፤ ፡-(ዘ ፯) ሰባት፤ ሰባቱ፤ ሰባተኛው፤ ሰባተኞቹ። ሰብዐቱ አልሕምት። ሰብዐቱ ኖሎት። ሰብዐቱ አዕይንት። ንድቅ ሊተ ሰብዐተ ምሥዋዓተ፤ ወአስተዳሉ ሰብዐተ አልሕምተ ወሰብዐተ አባግዐ ፡-(ዘፍ፵፩ ፡-፪። ሚክ፭ ፡-፬። ሸካ፫ ፡-፱። ዘኍ፳፫ ፡-፩)።
ሰብዑ ፡-(ዕብ ሼባዕ። ሱር ሽባዕ። ዐረ ሰብዕ) የሴቶች ድምር፤ ሰባት። ገቢርም ይከታል። ሰብዑ አንስት። ሰብዑ አዋልድ። ሰብዑ እከያት። ወነሥአ ሰበዑ ኅብስተ ፡-(ኢሳ፬ ፡-፩። አስቴ፪ ፡-፱። ምሳ፳፮ ፡-፳፭። ማቴ፲፭ ፡-፴፮። ዘፍ፴፩ ፡-፳፰–፴)። አንዳንድ ጊዜም በወንዶች ድምር፤ ሰብዑ ደቂቅ እያለ ይገኛል፤ የጣፊ ስሕተት ነው።
ሰብዓ ፡-የቍጥር ስም፤ በስድሳና በሰማኒያ ማኽል ያለ፤ ሰባ ፡-(ዐ ፸) ሰባት ጊዜ ዐሥር፤ ወይም ዐሥር ጊዜ ሰባት። ሰብዓ ብእሲ። ሰብዓ ዓም። ሰብዓ ክራማት። ኢይብለከ እስከ ስብዕ አላ እስከ ሰብዓ ወስብዕ። ሰብዓ ሰንበታት ፡-(ሕዝ፰ ፡-፲፩። ዘካ፩ ፡-፲፪። መዝ ፡-፹፱። ማቴ፲፰ ፡-፳፪)።
ሰብኣት ፡-ሰዎች፤ ወገኖች፤ የቅርብ ዘመዶች። ሰብኣቲሁ ፡-(ዘሌ፳፭ ፡-፵፰ ፡-፵፱)።
ሰብኣዊ ፡-(ዊት) የሰው፤ ሰዋም ባለሰው፤ ሰውማ፤ ሰውኛ፤ በሰው ያደረ የተጠጋ፤ ባሕርያዊ፤ ጠባይዓዊ። መፍትው ይሰመይ ሰብኣዌ ወአኮ ሰብአ፤ እስመ ዘኀደራ ለናዝሬት ተሰምየ ናዝራዌ ወኢተሰምየ ናዝሬተ። ግብር ሰብኣዊ። አሕጽጽ አእምሮተከ ሰብኣዊተ ፡-(ቄር ፡-ጰላ። አፈ ፡-ድ፴፫። ፊልክ ፡-፹፪)።
ሰብእ ፡-(ዕብ ሽባእ፤ ስባአ፤ ስመ ነገድ፤ ሳባ) ባሕርያዊ ስም፤ በቁሙ፤ ሰው፤ አዳም፤ የአዳም ዘር ኹሉ፤ ነፍስና ሥጋ ያለው፤ ከነፍስ ከሥጋ አንድ የኾነ፤ በነፍስ አካልነት የቆመ የተፈጸመ፤ ሥጋ ብቻ ወይም ነፍስ ብቻ ያይሶለ ፍጹመ ሥጋ ወነፍስ፤ ፍጹመ ጸጋ ምሉአ ጸጋ። ንግበር ሰብአ በአርኣያነ ፡-(ዘፍ፩ ፡-፳፮። ፪ ፡-፯)። ስምነቱ ጠቅላይ ስለ ኾነ ለወንድም ለሴትም፤ ላንድም ለብዙም ይነገራል፤ ውስጠ ብዙ ነው። ይህም፤ አንሰ ዕፄ ወአኮ ሰብእ፤ ምኑን በኀበ ሰብእ። ሰብአ ወእንስሳ ታድኅን። እሉ ሰብእ ኵሉ ሰብእ እያለ መኼዱን ያሳያል። ዳግመኛም በስምና በግብር በነገር ኹሉ እየተናበበ እንዳወራረዱ ይፈታል።
ሰብእና ፡-፤ ሰው መኾን፤ የሰው ባሕርይ፤ አካሉ ገላው፤ ኹለንተናው፤ ኹለመናው። ሶበ ተግህደ ሰብእናሁ። ተውህቦ በሰብእናሁ። በጾም ወበጸሎት ሰበእናሆሙ ቀተሉ። ሰብእና ዚኣየ እሙር ፡-(ቀሌ። ቄር ፡-ጰላ። ድጓ። አዋል)።
ሰብዖ ዖት ፡-(ሰብዐ ይሴብዕ ይሰብዕ። ዕብ ሻቤዕ) መሰበት፤ ሰባት ማድረግ፤ ከሰባት መክፈል። በስመ አብ ዘይሴብዖን ለምዕዋደ ሰንበታት ከመ ይኩና ለኩፋሌ መዋዕል ወለፍጻሜ ኢዮቤልዮሳት ፡-(መጽ ፡-ምስ)። የሞፈርን ቂጥ ከነኹለንተናው ስበት ማለት ከዚህ የወጣ ነው። ማረሻና ከርፈስ ፡-(ወገል) ጠፍሩና ሞፈሩ ዕርፉና ድግሮቹ ሲደመሩ ፯ ናቸውና፤ ስበት ይይህነን ያሳያል።
፡-ማዘም፤ አስማት መድገም፤ እየመላለሱ ማንበብ ማነብነብ፤ እስከ ፯ ጊዜ።
ሰብኮ ኮት ፡-(ሰበከ ይሴብክ ይሰብክ። ዕብ ሻፋኽ። ዐረ ሰፈከ) ማቅለጥ፤ ማፍሰስ፤መጨፍለቅ፤ እየመቱ እየጠፈጠፉ መሥራት መገብሰስ፤ የማዕደን የሸክላ። ወሀበት ክልኤተ ምእተ ብሩረ ለዘይሰብኮ ወይገብሮ ግልፎ ወሰበኮ ፡-(መሳ፲፯ ፡-፬። ሕዝ፳፪ ፡-፳። ሚል፫ ፡-፫)።
ሰብድዓት ፡-(844) ፡-(ብ ሰባድዕት። ዐረ ሽብዲዕ፤ ጊንጥ) እፍኝት፤ ክፉ እባብ። ትውልደ ሰባድዕት ፡-(ሉቃ፫ ፡-፯)።
፡-ስመ ነገድ፤ የሰውና የአራዊት መልክ ያላቸው። አጥፍኡ ሀገረ ሰባድዕት እለ ገጾሙ ሰብእ ወዘነበ አድግ ውስተ ሐቌሆሙ። ወበጽሐ እስክንድር ኀበ ሰብድዓት ዘይበልዑ ሰብአ ወእንስሳ ወአራዊት ዕፀወ ወአሥዕርተ፤ እለ የሐይኩ እብነ ወይሰትዩ እሳተ፤ ብሔሮሙ ጽኑዕ፤ ወቦሙ አሐቲ ሙፃእ መጠነ ዕሥራ ወክልኤቱ በእመት። ወጸለየ ኀበ እግዚ ....... ወአስተቃረበ ሎቱ ክልኤተ አድባረ እለ ይብልዎሙ ምድቅኤል ቅርፍቶሬን፤ እስከ ይተርፍ ማእከሌሆን መጠነ ዕሥራ ወሠለስቱ በእመት ወአንበሮን ህየ ለሐሰይተ ብርት ሰከመ ነበሩ በምድረ ደቂቀ ያፌት ከመ ኢይፃኡ ሰብድዓት ወኢያጥፍኡ ሰብአ፤ ወይጕየዩ ሶበ ሰምዑ ቃለ ቀርን ወእንዚራ ወከበሮ ፡-(ክብ ፡-ነገ። ዜና ፡-እስ። ራእ፱ ፡-፩–፲፩)።
ሰተረ ፡-ሠነተረ፤–ሠተረ።
ሰቲር ሮት ፡-(ሰተረ ይሰትር ይስትር። ዕብ ፋራሽ) መሰተር፤ መዘርጋት ማዘጋጀት፤ ማለብ መደገን፤ ሰውሮ ማኖር፤ መሰወር፤ የገመድ የወጥመድ። ስጠረን ሰፍሐንና ስጥሕን ተመልከት፤ የዚህ ጎር ናቸው። ኀብኡ ሊተ መሥገርተ፤ ወሰተሩ አሕባለ መሣግር ፡-(መዝ ፡-፻፵)። መሸተር ማስጌጥ ፡-(ዐማርኛ)።
ሰቲት ቶት ፡-(ሰተ፤ ሰተተ ይሰትት ይስትት። ዕብ ሻታት) መቅናት መንሳተት፤ ሰተት ማለት፤ መውደቅ መዘርጋት፤ እንደ ስክተት እንደ መሠረት መኾን፤ መዋረድ መረገጥ፤ መናቅ።
ሰቲዕ ዖት ፡-(ሰትዐ ይሰትዕ ይስታዕ። ዕብ ሻታዕ) መፍራት መጠውለግ፤ መሽመልመል መድረቅ፤ ከመጠጥ ዕጦት የተነሣ፤ የቡቃያ የተክል የምላስ ፡-(ኢሳ፵፩ ፡-፲፭)።
፡-ፈርቶ መገበር፤ መገዛት፤ ግብር እጅ መንሻ መስጠት።
ሰታሪ ፡-(ሪት ርያን ያት፤ ተርት) የሚሰትር፤ የሚዘርር፤ የሚዘረጋ ዘርጊ።
ሰታዪ ፡-(ዪት ይያን ያት፤ ተይት) የሚጠጣ ጠጭ፤ መጠጥ ወዳጅ። በላዔ ሥጋ ወሰታዬ ደም። ኢትኩን ሰታዬ። ኢትኩኑ ሰታይያነ ብዙኅ ወይን ፡-(ድጓ። ምሳ፳፫ ፡-፳። ዲድ ፡-፯)።
(ጥ) ሰት ፡-ፊላ፤ ቄጠማ፤ ግራምጣ። ውስተ ሰት ወስማዝ ፡-(ኢዮ፵ ፡-፲፮)።
ሰትይ ዮት ፡-(ሰትየ ይሰቲ ይሰተይ። ዕብ ሻታህ። ሱር ሼቲይ) መጠጣት፤ መጐንጨት፤ መጠጥን በአፍ መቀበል፤ መሳብ መጐተት፤ ወደ ሆድ ማግባት፤ ፉት ገጭ ጕርጕጭ ማድረግ። በሊዕ ወሰትይ። ንብላዕ ወንስተይ። ስትይ ማየ እምቀሠትከ። በኀበ ይሰትዩ ወይነ። ስተዪ ምስሌነ ፡-(ሩት፫ ፡-፫። ኢሳ፳፪ ፡-፲፫። ምሳ፭ ፡-፲፭። ሢራ፴፭ ፡-፭። ዮዲ፲፪ ፡-፲፯)።
ሰነየ ሰኔ ፡-ሰኔ፤–አማረ፤–ሠነየ ሠኔ።
ሰኑይ ፡-(ዕብ ኼኒ፤ የዕለት ስም፤ ኹለተኛ፤ ኹለት፤ ሰኞ የእሑድ ማግስት፤ ሳኒታ ነገታ። በሰኑይ ዕለት። አመ ሰኑዩ ለሠርቅ። አሐቲ ዕለት ሰኑየ መዋዕለ ኮነት። ነበረ ሰኑየ መዋዕለ። ዘሰኑይ፤ ዕለተ ሰኑይ ፡-(ሆሴ፮ ፡-፪። ፩ነገ ፡-፳ ፡-፴፬። ሢራ፵፮ ፡-፬። ዮሐ፲፩ ፡-፮። አዋል)።
ሰኒሕ ሖት ፡-(ሰንሐ ይሰንሕ ይስናሕ። ዕብ ሻናህ፤ ተወለጠ) መለዘብ፤ መሟለጥ፤ መመለጥ፤ መቦሕየት፤ በራ መላጣ መኾን፤ ነት ጕበት መምሰል፤ የማኽል ራስ። በርሐንና ቀርሐን ተመልከት፤ የዚህ ጎር ናቸው።
ሰኒም ሞት ፡-(ሰነመ ይሰንም ይስንም። ዐረ ሰኒመ) መርዘም፤ ሻኛ ማውጣት፤ እንደ ግመል መኾን።
ሰኒን ኖት ፡-(ሰነነ ይሰንን ይስንን። ዕብ ሻናን። ዐረ ሰነ) መሞረድ መሳል፤ ማሾል፤ መዘርዘር ጥርስ ማውጣት፤ ሹል ስል ጥርሳም ማድረግ፤ የማጭድ የመጋዝ የብረት ኹሉ። መንከስ መቀርጨጭ መዘብተር፤ በጥርስ መቃወም የአራዊት፤ ነዘረን እይ።
ሰኒእ ፡-(ሰንአ ይሰንእ ይስናእ። ዕብ ሳናእ፤ ጠላ ፥ ተጣላ) መግጠም፤ መጋጠም፤ መሳካት፤ መሰናኘት፤ መስማማት ልክክ ማለት፤ መታረቅ መሳሳም መገናኘት፤ ግጥም ስምም መኾን አለመጣላት፤ አለመብለጥ አለማፈንገጥ፤ የግብር የነገር የቅኔ የመኪና የልብስ የጫማ ማሰሪያ። ሥእነን እይ፤ የዚህ ጎር ነው። መጽሐፍ ግን በሰንአ ፈንታ ተሰንአወ፤ ተሰነአወ ይላል፤ ወገሰን ወቅሐን ነሰወን ተመልከት፤ የዚህ መሰል ናቸው።
ሰኒው ዎት ፡-(ሰነወ ይሰኑ ይስኑ። ዐረ ሰና) መመሰን መስኖ ማውጣት፤ ውሃን ገመልና በሬ በሚያዞረው። በታላቅ መዘውር ከጕድጓድ ከዐዘቅት እያወጡ ማፍሰስ ማጠጣት፤ ወደ ቡቃያና ወዳታክልት መውሰድ ማግባት፤ መሳብ መጐተት፤ እንደ ግብጦች።
ሰኒጽ ጾት ፡-(ሰነጸ ይሰንጽ ይስንጽ። ዕብ ሻኔጽ፤ አጣበቀ አዋደደ) መሰነጥ፤ መፋቅ መፈቅፈቅ፤ ለማዋደድ። ማለዘብ መንቀስ፤ መኵላት፤ ማደስ፤ ማሳመር ማስጌጥ፤ የዕፅ የሸክላ የብረት። ሰንጢ ስንጣ ማለት ከዚህ ወጥቷል። ሰንአወን ተመልከት፤ የዚህ ጎር ነው።
ሰናብት ሰንበታት ፡-ሰንበቶች፤ ቀዳሞች፤ ዓመተ ኅድገቶች፤ በሱባዔ የሚቈጠሩ በዓላት፤ ኢዮቤላት፤ ሱባዔያት። ሰንበተ ሰናብት። ወሀብክዎሙ ሰንበታትየ። ሰበዑ ሰንበታት። በዓለ ሰናብት። ሰንበታተ መዋዕል ኀምሳ ወክልኤቱ። ሰንበታተ ዓመታት። ሰብዓ ሰንበታት ፡-(ዘሌ፲፮ ፡-፴፩። ሕዝ፳ ፡-፲፰። ዘዳ፲፮ ፡-፱ ፡-፲። ኩፋ፮ ፡-፶። ዳን፱ ፡-፳፬–፳፯)።
ሰናኒ መስንን ፡-የሚስል የሚያሾል፤ ጥርስ የሚያወጣ፤ የጥርስ ሐኪም፤ ነካሽ ዘብታሪ።
ሰናጺ ፡-(ጺት ጽያን ያት) የሚስንጥ ሰናጭ፤ ነቃሽ አስጊያጭ።
ሰናፊል ፡-(ዐረ ስርዋል። ዕብ ሳርባል) በቁሙ፤ ሰፊ ሱሪ፤ የእግር ቀሚስ ከወገብ እስከ ቍርጭምጭሚት የሚደርስ፤ የወንደች ልባልማ፤ ድርማንቅ ፡-(አዋል)።
ሰንሰል [1]፡-(ብ ሰናስል፤ ላት። ዕብ ሻርሽራ፤ ሻልሼሌት። ሱር ሺሻልታ። ዐረ ሲልሲለት) ሰንስለት ባለ፪ ፍንጅ ባለ፰ ጠገግ፤ ማሰሪያ ማቈራኛ፤ መስቀያ ማንጠልጠያ። ሰናስል ዘኀጺን። አሰሮ በሰናስል። ሰናስለ ወርቅ። እለ ሙቁሓን እደዊሆሙ በሰናስል ፡-(ስንክ ፡-ኅዳ፯። ገድ ፡-ተክ። አፈ ፡-ተ፱። ኢዮ፴፮ ፡-፰)።
[2]፡-(ዐማርኛ) ስምዛ፤ የስምዛ ዕንጨት ቅጠል፤ ሥሩ እንደ ሰንሰለት እየተያያዘ የሚዘምት ዐጽቁ የሚቈላለፍ። ሁስጱን ተመልከት።
ሰንሰሪቍ ፡-(ቋት። ዕብ ሲሪቆን። ዐረ ሰረቅ) ጥሩ ሐር፤ የሐር ልብስ ዛፋም ቅጥላም፤ አበባ ሐረግ የተሣለበት። ስርግዋን በጽጌ ሰንሰሪቍ። ለይ ወሰንሰሪቋት። መዋጥሒሆን ዘሰንሰሪቍ ፡-(ስንክ ፡-ጥር፲፪። ራእ፲፰ ፡-፲፪። ኢሳ፫ ፡-፳፫)።
ሰንሳሊ ፡-(ሊት ልያን ያት፤ ሰልት) የሚያስር፤ የሚያይዝ፤ አባሪ ሰንሰለት ሠሪ።
ሰንስሎ ሎት ፡-(ሰንሰለ ይሰነስል ይሰንስል። ሰሊል ሰለ፤ ሰልሰለ። ዕብ ሻልሴል) ማሰር መስቀል ማንጠልጠል፤ ማያያዝ ማቈራኘት ማቈላለፍ። መጽሐፍ ግን በሰንሰለ ፈንታ አሰንሰለ ይላል፤ አያሰኝም። በከመ አሰንሰለ ወአስተኣኀዘ ወልደ እግዚ ህላዌ ዚኣሁ ምስለ አቡሁ፤ ከማሁ አሰንሰለ ወአስተኣኀዘ ጳውሎስ ህላዌ መንፈስ ቅዱስ ምስለ አብ ወወልድ ፡-(መጽ ፡-ምስ ፡-ገ፲፭)።
ሰንቀወ ፡-(ነቀወ፤ ሰ ባዕድ) ሰነቃ፤ ሞዘቀ፤ መታ አስጮኸ፤ ደረደረ ከረከረ፤ ከመሣሪያው ጋራ ጮኸ አዜመ፤ ዘመረ ገጠመ፤ አጕረመረመ። ያነዝሩ ወይሰነቅዉ። ሠናየ ሰንቅዊ። ከመ ዘይሰነቁ ውስተ ቤተ ላሕ። ሰንቅዉ ሎቱ በመዝሙር ፡-(ኦዮ፳፩ ፡-፲፪። ኢሳ፳፫ ፡-፲፮። ሢራ፳፪ ፡-፮። ዮዲ፲፮ ፡-፩)። ነቀወን እይ፤ የዚህ ሥር ነው።
ሰንቃዊ ፡-(ዊት ውያን ያት) የሚመታ የሚደረድር፤ የሚያስጮኽ የሚጮኽ የሚዘምር። አሳፍ ሰንቃዊ፤ ዳዊት ሰንቃዊ ፡-(መጽ ፡-ምስ)።
ሰንበለ ፡-ዐረብ ሰቢለ፤–ሰቢል ሰብለ።
ሰንበተ እሑድ ፡-ሰንበተ፤ ቀዳሚት፤ ሰንበተ አይሁድ፤ ቅዳሜ፤ የብሉይ ሰንበት፤ የእሑድ ምሳሌ፤ ዋዜማ ድሮ ማኅትው፤ ኀተወን ተመልከት። ኢይደልዎሙ ለክርስቲያን ከመ ያፅርዑ ተገብሮ በዕለተ ሰንበት ከመ አይሁድ፤ አላ ይትገበሩ ከመ ክርስቲያን። ወኢትትዐቀቡ ሰንበተ ከመ አይሁድ ፡-(ፍ ፡-ነ ፡-፲፱)።
ሰንበተ ፡-ሰነበተ ቀረ ቈየ። ሰንበት ኾነ፤ ተባለ፤ ከበረ፤ ተሾመ ተቀደሰ።
ሰንበተ ቀዳሚት ፡-ሰንበተ አይሁድ፤ ቅዳሜ፤ የብሉይ ሰንበት፤ የእሑድ ምሳሌ፤ ዋዜማ ድሮ ማኅትው፤ ኀተወን ተመልከት። ኢይደልዎሙ ለክርስቲያን ከመ ያፅርዑ ተገብሮ በዕለተ ሰንበት ከመ አይሁድ፤ አላ ይትገበሩ ከመ ክርስቲያን። ወኢትትዐቀቡ ሰንበተ ከመ አይሁድ ፡-(ፍ ፡-ነ ፡-፲፱)።
ሰንበታዊ ፡-ሰንበቴ፤ ሰንበት ነክ፤ የሰንበት መዝሙር፤ የሱባዔ ቍጥር፤ የፊደል ቀመር ፥ ከግእዝ እስከ ሳብዕ። ፊደላት ሰንበታውያን ፡-(አዋል)።
ሰንበት ፡-(ሰብዐ፤ ሰብዐት። ዕብ ሻባት። ሱር ሻብታ። ዐረ ሰብት) የዕለት ስም፤ ሰባት፤ ሰባተኛ ቀን፤ ሰባተኛ ዓመት ማረፊያ ዕረፍት፤ ቀዳም፤ ዓመተ ኅድገት፤ ሱባዔ፤ ሳምንት ፡-(ዘፍ፪ ፡-፪ ፡-፫። ዘፀ፲፮ ፡-፳፫–፳፱። ፳ ፡-፰። ማቴ፲፪ ፡-፪። ዕብ፬ ፡-፬። ሔኖ፺፩ ፡-፲፪–፲፯። ግብ፲፯ ፡-፪)።
ሰንቡላ ፡-(ዐረ እሰንቡለት) ኮከብ፤ የኮከብ ስም፤ ካሥራ ኹለቱ መናዝል አንዱ። ሽቱ የሽቱ ዛላ ሽቷም ማለት ነው፤ ኮከብነቱም የነሐሴ ነው፤ ከፀሓይ ጋራ ፴ ዕለት ፵፪ ኬክሮስ ይመግባል ፡-(አቡሻ ፡-፫)።
ሰንቡል ሰንበልት ፡-ስነቡል፤ ጥሩ ሽቱ፤ ናርዶሳዊ፤ ከፅፀወ ዕጣን አንዱ፤ ወይም ዛጐል፤ የባሕር ሽቱ ፡-(ዘፀ፴ ፡-፴፬)። ከልበኔ ወሰንቡል። ሰንበልት ምዑዝ። ሰንበልት ቅድው ፡-(አዋ። ደራሲ። ሔኖ፴፪ ፡-፩። ኩፋ ፫ና ፡-፲፮)።
ሰንቡዕ ሰንብዕ ፡-ሰንቡዕ፤ ሰንብዕ፤ ፡-(ነቢዕ ነብዐ። ዕብ ናሻብ፤ ነፍኀ) ሳንባ፤ የልብ ሥር፤ የትንፋሽ ምንጭ ፡-(፫ነገ ፡-፳፪ ፡-፴፬። ፪ዜና ፡-፲፰ ፡-፴፫)። አይቴ መካነ ጽንዐተ መንፈስ፤ ይቤ በሰንቡዕ። ረገዞ ውስተ ሰንብዑ። ወጠቢባንሰ ይብሉ በእንተ ዝንቱ ተነጽፈ ሥብሕ ወሰንቡዕ በታሕቴሁ ለልብ ከመ ያህድእዎ ወያስተናፍስዎ በጊዜ መዐቱ እንዘ ይሜግብዎ ከመ እንተ ሰፍነግ ልምሉም ፡-(ገድ ፡-ተክ። አፈ ፡-ተ፭)።
ሰንቢል ፡-የመጠጥ እሸት፤ ዝርዝር መጠጥ፤ ጻዕፍ፤ ጕሽ። ግፌዳ ማኅበራዊ ድግስ። እለ ይተልዉ አሠረ ወይን ወእደ ይከውን ሰንቢል ፡-(ምሳ፳፫ ፡-፴)።
ሰንቢል ሰንበልት ሰንቡላ ፡-ሰብለ።
ሰንብል ፡-(ዐረ ሱንቡለት) እሸት፤ የእሸት ዛላ፤ ነዶ፤ ጥይት። ቀዳሚ ነበሩ ያበውኡ ሰንብለ ወአስካለ ወይን፤ ወናሁ ተፀርዐ ሰንብል ወተርፈ ወይን ፡-(ፈ ፡-መ ፡-፳፮ ፡-፪)።
ሰንአለ ፡-(ሰአለ፤ ን ስሯጽ ነው) አሰናበተ፤ ለቀቀ ፈታ፤ ኺድልኝ አለ፤ ለመነ።
ሰንአወ ፡-(አስንአ) አጋጠመ አሰማማ፤ አሳካ አሰናኘ፤ አገናኘ።
ሰንዐወ ፡-አጋጠመ፤–ሰኒእ ሰንአ።
ሰንከሩር ፡-(ጽር ክሪኖን) አበባ፤ ጽጌ ደንጐላ። ወግልፈት ላዕሌሃ አምሳለ ሰንከሩር ፡-(፪ዜና ፡-፬ ፡-፭)። የደንጐላን ፍች ተመልከት።
ሰንኮሪስ ሰንኮሪሶን ፡-(ጽር ሲግኾሪሶን) ትእዛዝ አንቀጽ፤ መሐር ተሣሀል አናሕሲ፤ ወይም ቅጽል፤ መሓሪ መስተሣህል ኀዳጌ በቀል። ሰንኮሪሶን እግዚኦ እስመ አልቦ ሰብእ ዘየሐዩ እንበለ ኀጢአት። አስተምሕር ለነ ሰአልናከ፤ ዮሐንስ ሰንኮሪስ ፡-(ግንዘ። መዋሥ)።
ሰንይ ዮት ፡-(ሰነየ ይሰኒ ይስኒ። ዕብ ሻናህ። ሱር ትናእ። ዐረ ሰነይ) መሰንይ፤ መኾለት ኹለት ማድረግ፤ ማጠፍ መደረብ። በመልክ በባሕርይ መለወጥ፤ ሌላ መኾን መምሰል።
ሰንደል ፡-(ዐረብ) ከመ ዕፅ ክቡር፤ ሕቍ፤ ጥሩ ጠንካራ ምዑዝ ዐዚዝ፤ ሠናየ ጼና። ወኵሉ ዕፀው ክቡራን ከመ ዑድ ወሰንደል ፡-(ጊ ፡-ወ ፡-ሐ ፡-ገ፳፫)።
ሰንደሮስ ስንድሪስ ፡-(ፋርስ ሰንደሩስ። ዐረ ሲንደሩስ) ሙጫ፤ የዕጣን ዐይነት፤ ነጭ ዕጣን፤ መልካም ሽታ ያለው። ሰንደሮስ ምስለ ጵርስቅላ። ከርቤ፤ ሚዓ፤ ሎዛን፤ ስንድሪስ ከሚን ጥፋሕ ሠለስቱ ሰቅል ሰንደሮስ ፡-(ማሕ፬ ፡-፲፫። ስንክ ፡-ሐም፰። ቄድር)።
ሰንደቅ ፡-(ዕብ ሳንዳቅ፤ አስገዛሪ፤ ሕፃንን በጭኑ የሚይዝ) ዐላማ ባንዴራ፤ የባንዴራ ዕንጨት መስቀያው ማንጠልጠያው። ሰንደቅ ዐላማ እንዲሉ። ኀደገ ሰንደቀ ወነጋሪተ ፡-(ታሪ ፡-ነገ)።
ሰንዱን ፡-(ናት። ጽር ሲንዶን። ዕብ ሳዲን) ጥሩ ነጭ ልብስ፤ በፍታ ሻሽ፤ ልብሰ ክታን፤ መጐናጸፊያ። ባለብሉዮች ማማት ይሉታል። ወሬዛ ዘይትዐጸፍ ሰንዱነ። የኀፅብ በወይን ልብሶ ወበደመ አስካል ሰንዱኖ። ኮነ አናሜ አልባሳት ቀጠንት ወሰንዱናት ክቡራት ፡-(ማር፲፬ ፡-፶፩። ዘፍ፵፱ ፡-፲፩። ስንክ ፡-ግን፲፬)።
ሰንዶቅ ወመንዶቅ ፡-የዐረብ ተረት፤ ሳንዱቅ ወበንዱቅ፤ ሣጥንና ዲቃላ። ባለቅኔዎች ግን ማርና ዕጣን ይሉታል ፡-(ጥሬ ፡-ሰዋ)።
ሰንጕጎ ጎት ፡-(ሰንጐጐ ይሰነጕጕ ይሰንጕጕ፤ ሰኒጕ ሰነጐ) መሰነግ፤ ባፍንጫ በቀለበት ማግባት፤ መስቀል መትከል፤ ማጽናት ማበርታት፤ የኵላብ የዘንግ የመጋረጃ። መሸንጓት፤ ሸንጎ ማድረግ።
ሰንጐጕ ፡-(ብ ሰናጕጕ) ጽኑ ብርቱ የማይሰበር፤ ከኀጺን ከማዕደን የተሠራ ዕቃ። ስናጋ ስናግ፤ ኵላብ፤ የብረት ዘንግ። ዘብርት ሰንጐጕ። ንዋየ ብርት ቅድወ ወሰናጕጐ ዘከመ ወርቅ ፡-(፫ነገ ፡-፯ ፡-፴፩። ፩ዕዝ ፡-፰ ፡-፶፮)። ወለኀጺናትሰ ገብርዎሙ ሰንጐጐ በዘይሰቅሉ ቦቱ መንጠዋልዐ ፡-(ገድ ፡-ተክ)።
ሰንጠረዥ ፡-(ፋርስ ሸትረንክ። ዐረ ሺጥረንግ) በቁሙ፤ የጨዎታና የመጫወቻ ስም፤ መደቡ እንደ ጸፍጸፍ ያለ ጥቍርና ነጭ፤ መጫወቻው የታነጠ የተነጠጠ የተቀረጠ ዕንጨት ስድስት ዐይነት ያለው፤ ይኸውም ንጉሥ ንግሥት ፊት አውራሪ ፈረስ ግንብ አሽከር ይባላል፤ የጨዎታውም ሐሳብና ምስጢር ፍጹም ጦርነት ነው። ካህናት ኢይትላሀዩ ግብረ ሰንጠረዥ ወገበጣ ወኵሎ ዘይመስሎ ፡-(ፈ ፡-መ ፡-፴፫ ፡-፯)።
ሰንጢ ሰንጣ ፡-ዐማርኛ፤–ሰነጸ።
ሰንፔር ፡-(ጽር ሳፕፊሮስ። ዕብ ሳፊ(ፒ) ር) ዕንቍ የዕንቍ ስም፤ ሕብሩ ቀይ፤ ፍሕም የሚመስል ፡-(ዘፀ፳፬ ፡-፲። ሕዝ፩ ፡-፳፮። ራእ፳፩ ፡-፲፱)።
ሰኖባር ፡-(ዐረ ሰነወብር) የዛፍ ስም፤ መልካም ሽታ ያለው፤ የዘግባ ዐይነት ፡-(ስንክ ፡-ሐም፭)።
ሰአለ [1]:-ሣለ መሰለ፤–ሥዒል ሠዐለ።
[2]:-ሳለ ሳላም ኾነ፤–ሰዐለ።
ሰዐለ [1]:-ለመነ ጠየቀ፤–ሰአለ።
[2]:-ሣለ ፈጠረ፤–ሠዐለ።
[3]፡-(ዐረ ሰዐለ) ሳለ፤ ሳላም ኾነ፤ ኡሁ ኡሁ አለ፤ ዐነጠስ።
ሰአልት ፡-ለማኞች፤ ጠያቆች፤ መርማሮች። የመጽሐፍ ስም፤ መጽሐፈ ሰገል፤ የጥንቈላ መጽሐፍ፤ እንዳውደ ነገሥት ያለ።
ሰአመ ፡-ሳመ ለከፈ፤–ስዒም ሰዐመ።
ሰአረ ፡-ሻረ፤–ስዒር ሰዐረ።
ሰአበ ፡-ረከሰ፤–ሠአበ።
ሰዐታት ሰዓታት ፡-ሰዓቶች፤ ጊዜዎች የዕለት ክፍሎች፤ ዘመኖች ወራቶች። እለ ያሰግሉ ውስተ ሰዐታት ወዕለታት ወለያልይ። እምዕለት እኪት ወእምሰዓታተ መንሱት። ለምንት ይረስዖን እግዚ ለሰዓታትየ ፡-(ቀሌ። ሊጦ። ኢዮ፳፬ ፡-፩)። ሺሑ ዓመት ፩ ዕለት ተብሎ ሲቈጠር ግን አንዱ ሰዓት ፵፩ ዓመት ከ፰ ወር ይኾናል። እስመ ዐሠርቱ ምእት ዓመት ከመ አሐቲ ዕለት ውስተ ስምዐ ሰማያት ፡-(ኩፋ ፡-፬። መዝ ፡-፹፱። ፪ጴጥ ፡-፫ ፡-፰)።
ሰዐወ ፡-(ትግ ሐባ) ሮጠ ፈረጠጠ፤ ዐለፈ ኼደ፤ ተራመደ።
ሰዐደ ፡-(ዕብ ሳዐድ) ዐገዘ ረዳ ደገፈ። ሰደየን እይ።
ሰኣሊ ፡-(ሊት ልያን ያት፤ አልት) የሚለምን፤ የሚጠይቅ፤ ለማኝ ጠያቂ፤ ማላጅ። ሰኣሊተ ምሕረት ለኃጥኣን። ሰኣሊት ሕይወተ ለነፍሳቲነ ፡-(ግንዘ። ቅዳ። ኤፍ ፡-፩)።
ሰዓል ፡-(ሱር ሻዕላ። ዕብ ሺዑል) ሳል፤ ጕንፋን፤ ንጥሻ ዕንጥስታ። ወለእመ መጽኦ ሰዓል ለይሚጥ ገጾ ወይስዐል ፡-(አረጋ ፡-ድ፲፫)።
ሰዓሚ ፡-(ሚት ምያን ያት፤ ዐምት) የሚስም፤ ሳሚ። ቤተ ክሲያን ሳሚ እንዲሉ።
ሰዓሪ ፡-(ሪት ርያን ያት፤ ዐርት) የሚሽር ሻሪ፤ አፍራሽ፤ አጥፊ ደምሳሽ። ሰዓሬ ሕግ። ሰዓርያነ ሰንበት። ሰዐርተ ጾም ፡-(አዋል)።
ሰዓት ፡-በቁሙ፤–ሰዐወ።
ሰዖዛዝ [1]፡-መፍዘዝ፤ መስለል፤ ድንዛዜ፤ የዥማት ደዌ፤ የበሽታ ጠንክ። ቍጣ ሐዘን ኀፍረት፤ ስቅጥጥታ። ሕማም ወሰዖዛዝ ፡-(ኩፋ ፡-፳፫)።
[2]፡-ሰዖዛዝ፤–መፍዘዝ፤–ዐዘዘ፤ አስዖዘዘ።
ሰከሕካሕ ፡-ዐይነ ምድር፤–ከሕክሐ።
ሰከረ ፡-ተከራየ፤–ሠከረ።
ሰከወ ፡-(ሱር፤ ስካእ። ዕብ ሳካህ) አየ ተመለከተ፤ ዐይኑን ላከ አሾለከ፤ ሰካ፤ ትክ አደረገ።
ሰኵሶ ሶት ፡-(ሰኰሰ ይሴኵስ ይሰኵስ። ዕብ ፋግ፤ ሻሕ) ማነስ መጕደል፤ ጥቂት መኾን፤ ወይም በጭራሽ መጥፋት መቅረት መታጐል፤ መፍዘዝ መቀዝቀዝ። ወይሴኵሱ ሕቀ ከመ ይቅብዑ ንጉሠ። ይሴኵስ ፍቅር እምአኀው ፡-(ሆሴ፰ ፡-፲። ቀሌ። ማቴ፳፬ ፡-፲፪። ዲድ ፡-፴፫)።
ሰኵዐ ፡-ሰኵዐ፤ ፡-(መሰከ) ሳበ ጐተተ፤ አወጣ አገባ፤ ከሆድ ከጕድጓድ። ከካ፤ አመሰኳ አመነ(ዘ) ዠኸ። መጽሐፍ ግን በሰኵዐ ፈንታ እንዳማርኛው አመስኵዐ ተመስኵዐ ይላል፤ ስሕተት ነው። እምኵሉ እንስሳ ዘይትመሰኳ ኪያሁ ብልዑ ፡-(ዘሌ፲፩ ፡-፫–፯። ዘዳ፲፬ ፡-፮–፰)። ከዚህስ ይልቅ ትግሬው ፡-(ሐባብ) መስክዐ ይላልና ፥ ርሱ ይሻላል፤ መሰከን እይ፤ የዚህ ጎር ነው።
ሰኪል ሎት ፡-(ሰከለ ይሰክል ይስክል። ተኪል ተከለ፤ ሰገለ) ማበብ ማፍራት፤ አበባ መጣል ፍሬ መያዝ፤ መውለድ መሸከም፤ የወይን የተምር። ከመ ዐጸደ ወይን ዘሰከለ ፡-(መጽ ፡-ምስ)።
ሰኪም ሞት ፡-(ሰከመ ይሰክም ይስክም። ዕብ ሻኮም፤ ሀሽኬም) ጸዊር፤ መሸከም፤ በጫንቃ በትከሻ ላይ መያዝ፤ ማንሣት። ተሐዝሉ በገቦክሙ ወትሰክሙ በመታክፍቲክሙ። ረስዮ ለክሣድየ ያድንን ወይስክም አርዑተ ትእዛዝከ ፡-(ሕዝ፴፬ ፡-፳፩። ስንክ ፡-ሠኔ) በሰከመ ፈንታ ተሰከመ ተስክመ ይላል፤ ስሕተት ነው። ተሰከማ ለይእቲ ቀሡት ፡-(ስንክ ፡-ታኅ፲፩። መሳ፲፮ ፡-፫። ኢሳ፵፮ ፡-፯። ሢራ፮ ፡-፳፭። ፲፫ ፡-፪)።
ሰኪር ሮት ፡-(ሰክረ ይሰክር ይስክር። ዕብ ሻካር። ሱር ሽካር። ዐረ ሰኪረ) መስከር፤ መርካት አብዝቶ መጠጣት፤ ከሐዘን ከቍጣ ከመጠጥ ብዛት የተነሣ እንቡዝ ቅብዝብዝ መኾን፤ አእምሮ ማጣት። ትሰክር ምድር እምደም፤ ኢትስተይ ወይነ ለሰኪር። ኢትስክሩ ወይነ። እስመ ሰክሩ በዘእንበለ ወይን ፡-(ኢሳ፴፬ ፡-፯። ዮዲ፮ ፡-፬። ጦቢ፬ ፡-፲፭። ምሳ፳፫ ፡-፴፩። ኢሳ፳፰ ፡-፩)።
ሰኪብ ቦት ፡-(ሰከበ ይሰክብ ይስክብ። ዕብ ሻካብ። ሱር ሽኬብ) መተኛት፤ መጋደም፤ መሰጣት መዘርጋት፤ ዟ ዘግ ማለት፤ ወደ ሴት መግባት፤ ማንቀላፋት፤ መሞት መቀበር።ሰከበ ሰኪሮ። ሶበ ይሰክብ ዲበ ምስካቡ። ዘይሰክብ ብእሲተ። ወሰከበ ምስለ አበዊሁ ፡-(ኩፋ ፡-፯። ኢዮ፴፫ ፡-፲፭። ፍ ፡-ነ ፡-፭። አዋል)።
ሰኪት ቶት ፡-(ሰከተ ይሰክት ይስክት። ሱር ሽካት) መስፈር፤ ስፈር ማድረግ፤ ቦታ መያዝ፤ ማደር ማረፍ።
ሰኪን ኖት ፡-(ሰከነ ይሰክን ይስክን። ዕብ ሻካን። ሱር ሽኬን። ዐረ ሰከነ) ማረፍ፤ ቦታ መያዝ፤ መኖር መቀመጥ፤ መሸራሸት። ቦታ መፈለግ መለመን፤ አስጠጉኝ አሳድሩኝ ማለት፤ እንግዳ ድኻ ስደተኛ መኾን፤ ሲዞሩና ሲለምኑ ውሎ የትም ከመሸበት ማደር። ነድየን ተመልከት፤ የዚህ ጎር ነው።
ሰኪኖን ፡-(ጽር ስኺኖስ) የዛፍ ስም፤ እንደ ጥድ መልካም ሽታ ያለው። ታሕተ ዕፀ ሰኪኖን። መዐዛሁ ከመ ዘሰኪኖን ፡-(ዳን፩ ፡-፶፬። ሔኖ፴ ፡-፪)።
ሰኪዕ ዖት ፡-(ሰክዐ ይሰክዕ ይስካዕ፤ ሰጕዐ። ሱር ሻኬይ) መብላት፤ መስካት፤ መሰካት፤ መደርደር፤ ማግባት ማሳለፍ፤ መቀርቀር መወተፍ፤ የፈትል የመርፌ የዶቃ የፈርጥ።
ሰካሪ ፡-(ሪት ርያን ያት፤ ከርት) የሚሰክር፤ ስካር፤ መጠጥ ወዳጅ። እኩይ ወይን ለጸዓሊ ወለሰካሪ። ብእሲት ሰካሪት። ይሰቲ ምስለ ሰከርት ፡-(ምሳ፳ ፡-፩። ሢራ፳፮ ፡-፰። ማቴ፳፬ ፡-፵፱)። ሰካሪት በማለት ፈንታ ጠባብ እንደ ማለት ሰካር ይላል። እመሂ ዘማዊት ወእመሂ ሰካር ፡-(ኪዳ)።
ሰካቢ ፡-(ቢት ብያን ያት፤ ከብት) የሚተኛ የሚጋደም፤ ሰነፍ፤ እንቅልፋም፤ አበያ ድዉይ ደካማ።
ሰካዪ ፡-(ዪት ይያን ያት፤ ከይት) የሚከስ፤ ከሳሽ፤ ጠላት ባለጋራ። ለእመ ሰከየነ ሰካዪ ፡-(አፊ ፡-ተ፳፯። ፍ ፡-ነ ፡-፳፯። ፵፫ ፡-፮)።
ሰኬዛ ፡-(ጽር ስኺዛ) ፍላጻ፤ ጕብጭ፤ ሹል ፡-(፩ነገ ፡-፳ ፡-፳–፳፪፤ ፴፮–፴፰)።
ሰክም ፡-(ማት) [1]፡-ሸክም፤ ጭነት፤ ጓዝ እክት። ጾረን ተመልከት፤ የዚህ ጎር ነው።
[2]፡-ሰክም፤ ፡-(ትግሬ ሸክም) አገጭ፤ ሸንጎበት፤ የጽሕም ቦታ፤ ታችኛው ክፍል።
ሰክተተ ፡-ጐለተ ጣደ፤ ተከለ ሰካ አዋደደ፤ አሰረረ፤ የድስት የምጣድ የዐምድ። ሰክትት ጽህርተ ፡-(ሕዝ፳፬ ፡-፩)።
ሰክተየ ፡-(ይሰከቲ ይሰክቲ። ከሰከተና ከሰከየ ከኹለቱ የተዴቀለ) አሳደመ ሤራ አስቈረጠ፤ አማማለ።
ሰክአ ፡-ሰካ ደረደረ፤–ሰኪዕ ሰክዐ።
ሰክይ ዮት ፡-(ሰከየ ይሰኪ ይስኪ። ዐረ ሸካ፤ ሸከይ) መክሰስ፤ በዳኛ መያዝ፤ ማሳጣት፤ ግፈኛ ወንጀለኛ ማድረግ። ትሰክዩ ወትትዋቀሡ። እመ ቦ ዘሰከይዎ ኀበ ፈታሒ። ከመ ይሰክይዎ ኀበ ቄሳር። ይስክይዎሙ ለአርድእት በዘሐሰዉ ፡-(ኢሳ፶፰ ፡-፫። ፍ ፡-ነ ፡-፵፫ ፡-፱። ዮሴፍ። ቄር ፡-ጰላ)።
፡-መሸሽ፤ መጠጋት፤ የሙጥኝ ማለት፤ ከገዳም ከቤተ ክሲያን ገብቶ መማጠን መደወል መጮኽ መማለል፤ ለመዳን። ይሰኪ ህየ ቀታሊ። ከመ ይስኪ ህየ። ሰከይኩ ኀበ እግዚ ወሰአልክዎ። ተወከፍ ዘኵልነ ሰክዮተ ወበቍዔተ። ይሰክዩ ኀቤሁ ፡-(ዘኍ፴፭ ፡-፲፩ ፡-፲፭። ጥበ፰ ፡-፳፩። ሊጦን። ቀሌ)።
ሰኰት ፡-(ብ አስኳት) ሱቅ አደባባይ፤ መተላለፊያ። ጽጕ ጽጐጕ ማለት ነው፤ ጽጕን ተመልከት። እመ ሀሎ ማእከሌሁ ወማእከለ ቢጹ ሰኰት ወመርሕብ። ሑር ሰኰተ እንተ ይብልዋ ርትዕት። በውስተ አስኳቲሃ። አስኳተ ሀገር ፡-(ፍ ፡-ነ ፡-፴፯። ግብ፲፪ ፡-፲። ኢሳ፲፭ ፡-፫። ሉቃ፲፬ ፡-፳፩። ማቴ፮ ፡-፪)።
ሰኮና ሰኰና ፡-(ብ ሰኳንው) በቁሙ፤ መከየድ፤ ጫማ፤ ውስጥ እግር፤ ከተረክዝ እስካውራ ጣት ያለው፤ ዝርጉ ጠፍጣፋው። ውስጥ እጅም ይኾናል። ሰኰና እገሪሃ። አንሥአ ሰኰናሁ ላዕሌየ። ዕቀቢ ሰኰናሆሙ። እስመ ጽንፋ ሰኰናሁ ለሰብእ ወከተማሁ ለሰብእ በከመ ሰኰና እዴሁ ፡-(፬ነገ ፡-፱ ፡-፴፭። መዝ ፡-፵። ዘፍ፫ ፡-፲፭። ሱቱ ፡-ዕዝ፮ ፡-፲)። ለእንስሳት ሲኾን ጥፍር ይባላል። ሰኰና አፍራሲሆሙ። ሰኰና እንስሳ። ዘንፉቅ ሰኰናሁ ፡-(ኢሳ፭ ፡-፳፰። ሕዝ፴፪ ፡-፲፪። ዘሌ፲፩ ፡-፫==፯)።
ሰኳዒ ፡-(ዒት ዕያን ያት፤ ዕት) የሚከካ የሚያመሰኳ፤ እንስሳ፤ አግዝ፤ ገብረ ጕንዳን። ቃሕምን ተመልከት፤ ከዚህ ጋራ አንድ ነው። ሰኳዕት እለ አልቦሙ ኀይል ፡-(ምሳ፳፬ ፡-፰)።
ሰወነ ፡-ቆበረ አለገገ፤–ሠዊን ሠወነ።
ሰወየ ፡-በሰለ ሸተ፤–ሠወየ።
ሰዊቅ ቆት ፡-(ሶቀ ይሰውቅ ይሱቅ፤ ዐመደ። ዕብ ሾቄቅ፤ ፈተወ) መሶቅ መደገፍ፤ እንዳይወድቅ ማድረግ፤ ደግፎ መያዝ መጠበቅ፤ ማገዝ መርዳት፤ ማጥናት ማበርታት አይዞኽ ማለት፤ ማቆም መግታት። አኮ በዕፅ ዘትሰውቆን። ባዕል ለእመ ተንተነ ይሰውቅዎ አዕርክቲሁ። ሶቀነ ወአብጽሐነ እስከ ዛቲ ሰዓት። ሶቀቶ ረድኤቱ። ለሰዊቆትየ ሶበ እድኅፅ። ኢያሱ ወልደ ነዌ ሶቀ ሎሙ ማየ ዮርዳኖስ ወኀለፉ ፡-(ገድ ፡-ላሊ። ሢራ፲፫ ፡-፳፩። ሊጦን። ፈ ፡-መ ፡-፫ ፡-፮። አርጋ ፡-፬። ስንክ ፡-ሠኔ፳፮)።
ሰዊብ ቦት ፡-(ሶበ፤ ሰወበ ይሰውብ ይሱብ። ሰበበ) ማዞር፤ መጠምጠም፤ አዙሮ መግጠም፤ ዙሪያ ክብ ማድረግ፤ የማገር የስፌት፤ የመሰለው ኹሉ።
ሰዊድ ፡-(ሶደ ይሰውድ ይሱድ። ዕብ ሳድ፤ ሣረረ) መጫር፤ መተርከስ፤ መዛቅ ማፈስ፤ ማንደድ፤ መቈስቈስ፤ የፍሕም። መመሥረት፤ መሠረት መጣል የሕንጻ የምክር።
ሰዊጥ ጦት ፡-(ሶጠ ይሰውጥ ይሱጥ፤ ወደየ። ዕብ ሻጥ ያሹጥ) መዋኘት፤ መቅዘፍ፤ መሸንቈጥ መግረፍ፤ ሾጥ ማድረግ። መጨመር ማፍሰስ፤ መሻጥ፤ መሸጐጥ፤ ማዘንበል መቅዳት መገልበጥ። እሰውጥ እምነ መንፈስየ ዲበ ኵሉ ዘሥጋ። ሶጠ ቅብዐ ላዕለ ርእሳ። ኢትሱጥ እሳቶሙ ለኃጥኣን። ሶጠት ቀሠታ ውስተ ምስታይ። ሶጠ እምጻሕብ ውስተ ጻሕብ ፡-(ግብ፪ ፡-፲፭። ዘፍ፳፰ ፡-፲፰። ሢራ፰ ፡-፲። ዘፍ፳፬ ፡-፳። ኤር፴፩ ፡-፲፩።
ሰዋስዋዊ ፡-ባለሰዋስው፤ የሰዋስው መምር፤ አገባብ ዐዋቂ። የመሰላል ዐይነት፤ ዕርከናም፤ ባለማዕርግ። ጽማዌ ሰዋስዋዊ ፡-(ማር ፡-ይሥ፲)።
ሰዋስው ፡-በቁሙ፤ የቋንቋ መጽሐፍ፤ ግስ፤ መዝገበ ቃል። የቋንቋ ትምርት ሕግ ሥርዐት፤ ዐዋጅ አገባብ፤ አጣጣፉና አረባቡ አካኼዱ አነባቡ ተለይቶ የሚታወቅበት፤ እንደ መሰላል ብዙ ዕርከን ያለው። መጽሐፈ ሰዋስው። ሖርኩ ኀበ ካልእ መምህረ ቅኔ ወሰዋስው ፡-(አዋል)።
ሰዋሪ ፡-(ሪት ርያን ያት) በቁሙ፤ የሚሰውር፤ የሚደብቅ፤ የሚታደግ ታዳጊ። እግዚ ሰዋሪ ወከዳኒ። ኀባኢተ መለኮት ወሰዋሪተ ኵሉ ኅሊናት ፡-(አዋል። ቅዳ ፡-ጎር)።
ሰዋቂ ፡-(ቂት ቅያን ያት) የሚደግፍ ደጋፊ፤ አይዞኽ ባይ። ሰዋቄ ትንቱናን እምዳኅፅ። ኩነኒ ሰዋቄ ወምስማክ። ምርጕዝ ሰዋቄ አብራክ ፡-(ደራሲ። አዋል)።
ሰዋጢ ፡-(ጢት ጥያን ያት) የሚጨምር ጨማሪ፤ ቀዛፊ፤ ገራፊ።
ሰውር ፡-የኮከብ ስም፤–ተውር።
ሰውሮ ሮት ፡-(ሰወረ ይሴውር ይሰውር፤ ኀብአ። ዕብ ሻዌር፤ ሸመቀ ፥ አደባ) መሰወር መደበቅ፤ መሸሸግ ማራቅ፤ መክለል መጋረድ፤ ማልበስ መክደን፤ መሸፈን መቅበር፤ እንዳይታይና እንዳይገኝ ቢገኝም እንዳይታወቅ ማድረግ፤ ራስን ሰውነትን ወይም ሌላውን። ኀብአን ተመልከት፤ የዚህ ጎር ነው። ኢትሰውር ሎሙ ኀጢአቶሙ። ሰውሮቶ ለሀርክየ ኢየኀፍር። ወይሴውር ኅሩያነ በደመና። ኀፍረተ መስብእ ሰወርከ በዕርቃነ ልብስ ፡-(፪ዕዝ ፡-፲፬ ፡-፮። ሢራ፳፪ ፡-፳፭። ቅዳ ፡-ዮሐ። ቅኔ)።
ሰውተል ፡-(ብ ሰዋትል) ሾተል፤ አፋ፤ ጩቤ ዱቢት፤ ዐጭር ሰይፍ፤ ሹል ስለታም። ዙያንው ወሰዋትል ዘእሳት ፡-(ኦዋል)።
ሰውደት ፡-(ሐባብ) ለምጽ፤ የእሳት ብላቶ ዐመድና ሲድ ወይም ኖራ የሚመስል።
ሰውጣት ፡-አስዋጥ፤ ዐለንጎች፤ መግረፊያዎች። ይዝብጥዎ በአስዋጥ ፡-(ስንክ ፡-ኅዳ፲፮)።
ሰውጥ ፡-(ዕብ ሾጥ። ሱር ሻውጣ። ዐረ ሰውጥ) ዐለንጋ፤ ለበቅ፤ መሸንቈጫ፤ ሾጥ ማድረጊያ። ከመ ሰውጥ ለፈረስ። ለገብር እኩይ ሰውጥ ወመቃይጽ ፡-(ምሳ፳፮ ፡-፫። ሢራ፴ ፡-፴፭)።
ሰዘየ ፡-ለየ አደላ፤–ሠዘየ።
ሰዚር ሮት ፡-(ሰዘረ ይሰዝር ይስዝር። ጠፍሐ) መሰንዘር፤ በስንዝር መለካት፤ መቃጣት፤ መዘርጋት። ዘሰማየ ሰዘረ ወዘአድባረ ደለወ። ሰዘሮ ለሰማይ በሕፍኑ። ዘሰማየ ሰዘርከ ወምድረ ሣረርከ ፡-(አዋል። ስንክ ፡-ሚያ፯። ድጓ)።
ሰዪሕ ሖት ፡-(ሴሐ ይሰይሕ ይሲሕ። ዐረ ሰሐ። ሱር ሻሕ) ማፍስስ ማቅለጥ፤ መቀጥቀጥ፤ ወይም መፍሰስ መቅለጥ፤ የማዕደናት። መታመም፤ መሳል፤ መሰልሰል መመንመን፤ ድዉይ መኾን። ከመ ኢይሲሕ ወኢይንበር መፃጕዐ ወኢይፀራዕ ግብረ ቤተ ክርስቲያን ፡-(ኪዳ ፡-ገ፰)። ባለቅኔዎች ግን፤ ወገጠ ይሉታል። ባለብሉዮችም በሴሐ ፈንታ ሰሐየ አስሐየ ይሉና፤ ፍችውን አጠፋ አደረቀ ይሉታል። ያሴሕይዋ ለሕይወቶሙ መላእክት ፡-(ኢዮ፴፮ ፡-፲፬)።
(ጥያ) ሰያሕ [1]፡-(ሕት፤ ሰያሒ ሒት) ብር አፍሳሽ፤ ወርቅ አቅላጭ፤ አንጥረኛ ቀጥቃጭ። ወገብረ ፡-(ምናሴ) ሰያሕተ፤ ወማርያተ አብዝኀ ፡-(ዲድ ፡-፯)።
[2]፡-(ዐረብ) ቤተ ክሲያን ሳሚ፤ ጠበለተኛ፤ ጩኾ የሚዘምር፤ ዘፋኝ እልል ባይ።
ሰያፊ ሰያፍ ፡-(ፊት ፍያን ያት፤ የፍት) በቁሙ፤ የሚቈርጥ፤ የሚበጥስ፤ ሰይፋም ሰይፈኛ ባለሰይፍ፤ ፈላጭ ቈራጭ ባለወግ። ይቤሎሙ ንጉሥ ለሰያፍያን ፡-(ማር ፡-ይሥ፴፬። ዮሴፍ። ስንክ ፡-መስ፲፰)።
ሰይ ፡-(ወይ፤ አሌ። ዕብ ኦይ፤ ሆይ) ወዮ፤ ዋይ፤ የሐዘን ቃል፤ ከጭንቅና ከምጥ የተነሣ። ልየ ለከ ሎሙ እያለ እንደ ወይና እንደ አሌ በለ ይዘምታል። ሰይ ልየ ዘርሕቀ ማኅደርየ ፡-(መዝ ፡-፻፲፱)።
ሰይል [1]፡-መከራ መቅሠፍት፤ ፍርድ ቅጣት፤ ጭንቅ ፍርሀት፤ ይብላኝ ወዮልኝ የሚያሰኝ። ይረክቦሙ እምኀበ እግዚ ዳይን ወሰይል፤ ይረክብ ሰይለ። አመ አደንገፀከ ሞት ወሰዓተ ሰይል ፡-(ቀሌ። ስንክ ፡-ሐም፲፩)።
[2]፡-(ዐረ ሰሊል። ዕብ ሽሊል) ሽል ያደገ ፅንስ በሆድ ውስጥ ያለ፤ በጣም ያልበሰለ፤ ምጡ የሚያስጨንቅ፤ ሰይ ዋይ አሌ የሚያሰኝ። ኀለየት በነፍሳ ከመ ትቅትል ሰይላ ፡-(ቄድር)።
[3]፡-ሰይል፤ ፡-(ዐረ ሰላን። ዕብ ሺልያ) ምንሃር፤ ሽላዊ፤ አሰጅ፤ እንግዴ ሥጋ፤ ከልጅ በኋላ የሚወጣ።
[4]፡-ሰይል፤–መከራ ፥ ሽል፤–ሰይ ል።
ሰይእ [1]፡-(ዐረ ሸይእ። ዕብ ምኡማ) አንዳች፤ ጥቂት፤ ምናምን፤ ምንም ምን፤ አካቶ ፈጽሞ፤ ካንዱ ዘንዱ። ምስጢሩ ሕርም ማለት ነው፤ አንዳች ክፉ ነገር እንዳይኾን ክልክላን ምጥንታን ዐደራን፤ ወይም ችሎት ማጣትን አለመመቸትን ያሳያል ፡-(፪ነገ ፡-፲፫ ፡-፪። ፲፰ ፡-፲፫)።
[2]፡-(ዕብ ሻውእ) ከንቱ፤ ብላሽ፤ ውሸት፤ ባዶ፤ ፍሬ ቢስ፤ የማይረባ።
ሰይጣናት ሰያጥንት ፡-ሰይጣኖች፤ ባለጋሮች። አመረ ፈያተ ለኀበ ሰይጣናት። ከመ ኢይኩን ሲሳየ ለሰይጣናት። ሰያጥንትኒ ይፈርሁ ፡-(ፊልክ ፡-፳፭። አረጋ ፡-ድ፳፬)።
ሰይጣናዊ ፡-የሰይጣን የባለጋራ፤ ወገን ሥራ። መልአከ ሰይጣናዊ። ዝንቱ ልማድ ሰይጣናዊ። ፍትወት ሰይጣናዊት። መናስው ሰይጣናዊት ፡-(ስንክ ፡-ሠኔ፬። አፈ ፡-ተ፲፩። ፈ ፡-መ ፡-፲፫። ፊልክ ፡-፫)።
ሰይጣን ፡-(ዐረ ሸይጣን። ዕብ ሳጣን። ሱር ሳጣና) ባለጋራ፤ ጠላት፤ ወደረኛ፤ ከሳሽ አሳጭ። በቁሙ፤ መንፈስ ርኩስ፤ ሳጥናኤል፤ ዲያብሎስ፤ ርሱ ራሱ፤ ወይም ከሰራዊቱ አንዱ። ወአቀመ አዴርሀ ሰይጣነ ላዕለ ሰሎሞን። ሑር እምድኅሬየ ሰይጣን። ወሰይጣን ይቁም በየማኑ ፡-(፫ነገ ፡-፲፩ ፡-፲፬። ማቴ፲፮ ፡-፳፫። መዝ ፡-፻፰)። ወሚካኤልኒ ሊቀ መላእክት አመ ይትባሀሎ ለሰይጣን። ወአርዌሰ ዐቢይ ዘስሙ ሰይጣን። ርኢክዎ ለሰይጣን ወድዋ እምሰማይ ፡-(ይሁ ፡-፱። ራእ፲፪ ፡-፬። ሉቃ፲ ፡-፲፰)።
ሰይፍ ፡-(ዐረ ሰይፍ። ሱር ሳይፋ። ዕብ ሳይፍ፤ ሔሬብ) በቁሙ፤ መምቻ መቍረጫ፤ መግደያ፤ የሰልፍ መሣሪያ፤ ኹለት አፍ ያለው፤ አፋ። መተሩ ክሣዶ በሰይፍ። ሰይፍ በሊኅ ዘክልኤ አፉሁ። ቅንት ሰይፈከ ፡-(ስንክ ፡-ግን፳፭። ራእ፩ ፡-፲፮። መዝ ፡-፵፬)።
ሰይፎ ፎት ፡-(ሰየፈ ይሴይፍ ይሰይፍ። ዕብ ሳዬፍ) መሰየፍ፤ መምታት መቍረጥ፤ መበጠስ፤ መክፈል፤ መለየት። በመጥባሕት ሐራዊ በሊኅ አመ ለርእሱ ሰየፋ። ፀዓዕ ኀያል ዘይሰይፍ ወይከፍል። ወእፎኬ ኢሰየፉከ አስይፍተ እሳት ፡-(ስንክ ፡-ጥቅ፲። ቅዳ ፡-ያዕ። መጽ ፡-ምስ)።
ሰደቃ ፡-(ዐማርኛ) በቁሙ፤ ማእድ ገበታ፤ ጠረጴዛ፤ አውራጅ፤ እግር ያለው ዝርግ፤ ሰታታ።
ሰደፍ ፡-(ዐረብ) የባሕር እንስሳ፤ ዕንቍ የሚወልድ፤ ዐጥንቱ እንደ ቀንድ እንደ ዝኆን ጥርስ የሚነጠጥና የሚቀረጥ፤ መስቀል መቍጠሪያ፤ ያንገት ጌጥ መሣሪያ፤ ዝራር የሚኾን፤ እስመ ሰደፍ ይወልዶ ለዕንቍ ሶበ ይትዌከፍ ኀይለ ነፋስ ፡-(ማር ፡-ይሥ፳፰)።
፡-የነፍጥ ላት፤ የጠመንዣ ዕንጨት ፡-(ዐማርኛ)።
ሰዱስ ፡-የዕለት ቅጽል፤ ስድስት፤ ስድስተኛ። ሰዱሰ ዕለተ ተገበር ግብረከ እስመ በሰዱስ ዕለት ገብረ እግዚ። አኮኑ ሰዱስ መዋዕል ውእቱ በዘትገብሩ። በሰዱሱ ለጽልመት። ወአመ ሰዱስ ዕለት ፡-(ዘፀ፳ ፡-፲። ሉቃ፲፫ ፡-፲፬። ሐጌ፪ ፡-፩። ማር፱ ፡-፪። ድጓ)።
ሰዱቃዊ ፡-(ውያን። ዕብ ጽዱቂ፤ ጽዱቂም) የሳዶቅ ወገን፤ ተማሪው ደቀ መዝሙሩ፤ ባህሉ ከፈሪሳዊ የተለየ፤ ከኦሪት በቀር ነቢያትን የማይቀበል፤ መልአክ መንፈስ ትንሣኤ የለም የሚል፤ መንፈሳዊን ኹሉ የሚክድ ፡-(ማቴ፫ ፡-፯። ግብ፳፫ ፡-፮)።
ሰዲሞት ፡-(ጽር ሳዲሞት። ዕብ ሻድሞት) የስዴማ ብዥ፤አሕቃላት አሕቁል፤ ገራውሀ እክል፤ አዕጻደ ተክል። ሰዲሞተ ቄድሮን ፡-(፬ነገ ፡-፳፫ ፡-፬)።
ሰዲር ሮት ፡-(ሰደረ ይሰድር ይስድር። ዕብ ሳዳር) መሰደር፤ መደርደር፤ በተራ ማኖር፤ እንደ ጣት እንደ ደረት ዐጥንት። ሴደርያ ማለት ከዚህ የወጣ ነው። ዐረከን ተመልከት።
ሰዲቅ ቆት [1፤ ፡-(ሰደቀ ይሰድቅ ይስድቅ። ዕብ ራፋድ) መዘርጋት፤ ማንጠፍ፤ መነስነስ መጐዝጐዝ ማመቻቸት፤ የማእድ ያልጋ። ማጋደም ማስተኛት፤ የድዉይ የሕፃን የሬሳ። ባለብሉዮች ግን ቀባ ዐሸ አለዘበ ይሉታል። ሰደቁኒ በአክዋል እስመ ፡-(ሕምምተ ፍቅር አነ) ተነደፍኩ በፍቅሩ ፡-(ማሕ፪ ፡-፭)።
[2]፡-(ዐረ ሰደከ፤ ወደየ። ዕብ ሳዳቅ፤ ሠጠቀ) መጨፍለቅ፤ አንዱን ባንዱ ላይ ጨምሮ ኹለት ሦስቱን አንድ ማድረግ፤ የብረት። መክፈል መሠንጠቅ መተርተር መፍለጥ፤ ያክርማ የንጨት የመሰለው ኹሉ። ባለቅኔዎች ግን ኰላ ይሉታል፤ ደመቀን ተመልከት፤ የዚህ ጎር ነው።
፡-አብዝቶ መቅባት፤ በቅቤ መለወስ ማጨማለቅ ፡-(ዐማርኛ)።
ሰዲድ ዶት ፡-ሰዲድ፤ ዶት፤ ፡-(ሰደደ፤ ሰደ ይሰድድ ይስድድ። ዕብ ሻዳድ። ዐረ ሸደ) መስደድ፤ ማሳደድ፤ ማብረር፤ ማውጣት፤ ማሶጣት፤ ማሰናበት፤ መለየት፤ መላክ፤ ወስደኽ ስጥ፤ ኺደኽ አምጣ ተከተል ማለት፤ ፈነወን ተመልከት፤ የዚህ ጎር ነው። ይሰድዱከ እምሰብእ። ብፁዓን አንትሙ ሶበ ይሰድዱክሙ። እመ ሰደዳ ብእሲ ለብእሲቱ። አውጊዘክሙ ስድድዎሙ። ወሰደደት ኀቤሃ ብዙኀ አምኃ ፡-(ዳን፬ ፡-፳፪። ማቴ፭ ፡-፲፩። ኤር፫ ፡-፩። ቀሌ። ዮሴፍ)።
ሰዳሲ ፡-(ሲት ስያን ያት) የሚሰድስ፤ ሰዳሽ፤ ስድስት አድራጊ።
ሰዳዪ ይ ፡-ዐጋዥ ረዳት፤ አይዞኽ ባይ፤ ተስፋ የሚሰጥ የሚያማኵት።
ሰዳዲ ፡-(ዲት ድያን ያት) የሚሰድ፤ የሚያሳድድ፤ አባራሪ። ዝ አስማት ሰዳዲሆሙ ለአጋንንት። ፋኑኤል ሰዳዴ ሰይጣናት። ሰዳዲ ወጸዓሊ ፡-(ግንዘ። ደራሲ። ፩ጢሞ ፡-፩ ፡-፲፫)።
ሰድሶ ሶት ፡-(ሰደሰ ይሴድስ ይሰድስ። ዕብ ሻሼህ) መሰደስ፤ ስድስት ማድረግ፤ ከስድስት መክፈል።
ሰድይ ፡-ተስፋ አለኝታ። አምላካዊ ቃል፤ ከፈጣሪ በቀር ፍጡር ሊናገረው የማይቻል። ጥዑመ ከናፍር ክርስቶስ እንተ ትነብብ ሰድየ ፡-(ደራሲ። ዮሐ፲ ፡-፴፩። ፲፬ ፡-፱)። ባለቅኔዎች ግን ሰደየ አማረ ብለው ይገሱና፤ ሰድይን ያማረ ይሉታል። ሰዐደንና ወሳይድን እይ።
ሰድይ ዮት ፡-(ሰደየ ይሰዲ ይስዲ። ትግ ሰዴ) ማገዝ መርዳት፤ መደገፍ ማጥናት፤ አይዞኽ ማለት።
ሰዶማዊ ፡-የሰዶም፤ ሰዶምማ፤ አሲዳም፤ የሰዶምን ሥራ የሚሠራ፤ ነውረኛ፤ ወንዳገረድ ፡-(ቄድር)።
ሰዶም ፡-(ዕብ ስዶም) ስመ ሀገር፤ ጌታ በመዐት ከገለበጣቸው ካ፭ቱ አህጉር አንዲቱ፤ ታላቂቱ። ሲድ ፥ ኖራ፤ ም ፥ ዊ፤ ስዶም ፥ ሲዳዊት፤ ዘሲዳውያን፤ ኖራማ ኖራም ባለኖራ፤ የኖራ አውጮች አገር፤ ዐዘቅተ ሲድ ቈላተ ሲድ ማለት ነው ፡-(ዘፍ፲፫ ፡-፲። ፲፬ ፡-፲)። ኋላም ባሕረ ጼው ኹኖ ያሰጠማት ከኖራው ዐዘቅት የመጣ ውሃ ነው ይባላል።
ሰገላዊ ፡-የጥንቈላ ሰው፤ ጠንቋይ፤ አስጠንቋይ። ሰገላውያን ፡-(ስንክ ፡-ታኅ፳፱)።
ሰገል ፡-(ላት) ጥንቈላ ሟርት፤ መላ ግምት፤ ጥበብ ዕውቀት። ሰገለ ይሴአል። በኀይለ ሰገልኪ። ሰገል ውስተ አፈ ንጉሥ። ሰብአ ሰገል ፡-(ሆሴ፬ ፡-፲፪። ኢሳ፵፯ ፡-፱። ምሳ፲፮ ፡-፲። ዳን፩ ፡-፳)።
ሰገም ስገም ፡-ገብስ፤ ምርቃም የብር እኽል፤ ሰውም እንስሳም የሚበላው፤ ቅንጣቱ ባሠር የታፈነ የተሸፈነ። ማእረረ ሰገም መስፈርተ ሰገም። ኅብስተ ሰገም። ንሣእ ለከ ሥርናየ ወሰገመ ፡-(ሩት፩ ፡-፳፪። ፪ ፡-፲፯ ፡-፳፫። ራእ፮ ፡-፮። ዮሐ፮ ፡-፱ ፡-፲፫። ሕዝ፬ ፡-፱)።
ሰገነ ፡-(ዘገነ) ሸገነ አማረ፤ ተሾመ ተሸለመ አጌጠ፤ ከበረ በለጠ ምስጉን ኾነ።
ሰገነት ፡-በቁሙ፤ ተሥላስንና ገነትን እይ፤ ፡-(ዐማርኛ)።
ሰገኖ ፡-(ዕብ ሱጋ፤ ታናሽ ወፍ። ሳጋን፤ ሹም አለቃ) ሰጐን፤ ታላቅ አሞራ፤ ሰጋጋ፤ ዐንገተ ረዥም፤ ጠጉሩና ዕንቍላሉ በውድ የሚሼጥ ክቡር። ለወንድም ለሴትም ይከታል፤ እንደ ዶርሆ ነው። ዐጸደ ሰገኖ ፡-(ኢሳ፴፬ ፡-፲፫። ዘሌ፲፩ ፡-፲፮። ዘዳ፲፬ ፡-፲፭)። ሲያበዛ ሰጋንው፤ ሰገኖታት ይላል፤ ፡-(ገድ ፡-አዳ)።
ሰጊል ሎት ፡-(ሰገለ ይሰግል ይስግል። ዕብ ሻጋል፤ ዘመወ። ሳካል፤ ለበወ) መጠንቈል፤ ማሟረት፤ መላ መምታት፤ በመላ ማወቅ፤ መፈልሰፍ መራቀቅ፤ በውነት ወይም በሐሰት። መጽሐፍ ግን በሰገለ ፈንታ አስገለ አስተስገለ ተሰግለ ይላል፤ ኹሉም ስሕተት ነው። ያሰግሉ ለኪ ወይኔጽሩ ሰማየ። እለ ያሰግሉ በእሳት ወበማይ ወበአዕዋም ወበአእባን፤ በኮከብ ወበእሳት። ዘያስተሰግል በዖፍ። ተሰግሎ በትኣምረ ሰማይ። ዘይሴገል በበድን ርኩስ ፡-(ኢሳ፵፯ ፡-፲፫። ቀሌ። ዘዳ፲፰ ፡-፲፩። ኩፋ ፡-፲፩። ኪዳ)። መትከል መዝራት፤ ማፍራት። ተከለንና ሰከለን ሰግላን እይ።
ሰጊም ሞት ፡-(ሰገመ ይሰግም ይስግም። ዕብ ሻጌም። ሱር ሽጋም። ዐረ ሰገመ) ማሰር ማጣመር፤ መዝጋት መግጠም፤ መቈለፍ፤ የመዝጊያ ያንደበት።
ሰጕዐ ፡-(ሰክዐ) ሳገ ሰነገ፤ በሳ፤ ነደለ። ያአትቱ ይመትሩ በማለት ፈንታ ይሰጕዑ ይላል፤ የተሳሳተ ነው። ይሰጕዑ እዝነኪ ፡-(ሕዝ፳፫ ፡-፳፭)።
ሰጊድ ዶት ፡-(ሰገደ ይሰግድ ይስግድ። ዕብ ሳጋድ። ሱር ስጊድ። ዐረ ሰጀደ) መስገድ፤ መዋረድ፤ ማጐንበስ መንበርከክ፤ መደፋት፤ በግንባር መውደቅ፤ ግንባርን ምድር አስነክቶ መሬት ስሞ መመለስ፤ የአምልኮና የአክብሮ። ወይከውን ጸሎት በሰንበት ዘእንበለ ሰጊድ ውስተ ምድር አላ በደኒን ወአትሕቶ ርእስ። ከመ ለስሙ ይስግድ ኵሉ ብርክ። ሰገደ በብረኪሁ። ይሰግዱ በገጾሙ ውስተ ምድር። ሰገደት ታሕተ እገሪሁ። ወሶቤሃ ወድቀ ንጉሥ በገጹ ወሰገደ ለዳንኤል ፡-(ቀኖ ፡-ኒቅ። ቆላ፪ ፡-፲። ፪ዜና ፡-፮ ፡-፲፫። ሢራ፶ ፡-፲፯። አስቴ፰ ፡-፫። ዳን፪ ፡-፵፮)።
ሰጋልው ፡-ሾሎች፤ የሾላ ዛፎች፤ ዕንጨቶች። ላዕለ ሰጋልው። በከመ ሰጋልው ፡-(፩ዜና ፡-፳፯ ፡-፳፱። ፪ዜና ፡-፩ ፡-፲፭)።
ሰጋኒ መስገኒ ገን ግን ፡-የሸገነ፤ ሸገን፤ ክቡር ምስጉን። ዘገነንና መዝገነን እይ፤ የዚህ መንቲያ ነው።
ሰጋዲ ፡-(ዲት ድያን ያት) የሚሰግድ፤ ሰጋጅ። ሰጋዲ ከመ መላእክት። ሰጋድያን ለአምላከ ሰማይ። በአማን ሰጋድያን ፡-(ደራሲ። ስንክ ፡-መጋ፲፫። ዮሐ፬ ፡-፳፫)።
ሰግላ ፡-(ዕብ ሺቅማህ። ሱር ሺቅማእ) ሾላ፤ ባንባ፤ ዋርካ፤ የሾላ የበለስ ዐይነት፤ የዱር የበረሓ በለስ። ወትብልዋ ለዛቲ ሰግላ። ዐርገ ዲበ ሰግላ ፡-(ሉቃ፲፯ ፡-፮። ፲፱ ፡-፬)።
ሰግላጥ ፡-(ዐረ ስጂላጥ። ሱር ሲግላእ፤ ሽቱ) ጥሩ ልብስ፤ ዛፋም ቅጠላም፤ ባለሐረግና ባላበባ፤ ሐር ክታን። ጥሩ ሽቱ፤ የሽቱ ዕንጨት፤ ቅጠሉ አበባው ሐረጉ በጥሩ ልብስ ላይ የሚሣል። አልባሲሆን ዘሜላት ወዘሢራይ ወሰግላጥ። ኢይትዔረይዎ ለጼናክሙ ጥንቁቅ፤ ሰግላጥ ዘባሕር ወጽጌ ዘሐይቅ ፡-(ኢሳ፫ ፡-፳፩–፳፫። አርጋ ፡-፩። ስንክ። ጥቅ፮)።
ሰግም ፡-(ዐረ ሸህም) ፍላጻ፤ የቀስት ጦር፤ የሚነደፍ የሚወረወር፤ ጫፉ እንደ ገብስ ራስ ያለ ፡-(ገድ ፡-አዳ)።
ሰጠጠ ፡-ቀደደ፤–ሠጢጥ፤ ሠጠጠ።
ሰጠጵዮን ፡-(ጽር ስቲፒን። ዐረ አስጡበት) የተልባ እግር ጭረት፤ መናኛው። ገለባው ግርዱ ገፈፎው። ፡-(ዳን፫ ፡-፳፪። ስንክ ፡-ሐም፭)።
ሰጡቃጤ ፡-(ጽር ስታክቲ። ዕብ ናጣፍ) የሙጫ ሽቱ፤ የሚጤስ የሚታጠን፤ ከታወቁ የሽቱ ዛፎች ከዕፀወ ዕጣን እንደ ማር ወለላ የሚፈስ የሚንጠፈጠፍ ፡-(ሢራ፳፬ ፡-፲፭)።
ሰጢሕ ሖት ፡-(ሰጥሐ ይሰጥሕ ይስጣሕ። ዐረ ሰጠሐ። ዕብ ሻጣሕ። ሱር ሽጣሕ) ማስጣት መዘርጋት፤ መዘረር መሰተር፤ ለፀሓይ መስጠት። ሱጥሑ ወኢይበሱ። ወሰጥሐት ላዕሌሁ ዐረቦናተ። ይሰጥሕዎሙ ለፀሓይ ወለወርኅ ፡-(ዘኍ፲፩ ፡-፴፪። ፪ነገ ፡-፲፯ ፡-፲፱። ኤር፰ ፡-፪)።
ሰጢም ሞት ፡-(ሰጥመ ይሰጥም ይስጠም። ዐረ ሰጠመ። ዕብ ሳታም፤ ዘጋ) መዘጋት፤ መደፈን፤ መቀበር መሰወር። መስጠም ከባሕር ከረግረግ መግባት፤ መጥለቅ፤ መሥረግ፤ መዝገጥ፤ መዋጥ መስመጥ። መጽሐፍ ግን በሰጥመ ፈንታ ተሰጥመ ይላል፤ አያሰኝም፤ ተ ያማርኛ ነው። እመ ተሰጥሙ ውስተ ቀላየ ባሕር። ወረዉ ነፍሳቲሆሙ ውስተ ፈለግ ወተሰጥሙ። አልጸቀት ሐመር ለተሰጥሞ። ተሰጠምነ በኀጣውኢነ። ተሰጥሞ ውስተ ጣዕማት ፡-(ዓሞ፱ ፡-፫። ዮሴፍ። ስንክ ፡-ሚያ፳፭። ሱቱ ፡-ዕዝ፮ ፡-፵፫። ፈ ፡-መ ፡-፲፯ ፡-፬)።
ሰጢር ሮት ፡-(ሰጠረ ይሰጥር ይስጥር። ትግሬ ሰጥረ። ዕብ ሳታር። ሱር ስታር። ዐረ ሰተረ) መመስጠር፤ ማመስጠር፤ ማርቀቅ ማጥለቅ፤ መሰወር መደበቅ፤ ማልበስ መሸሸግ፤ እንዳይታይ ማድረግ።
ሰጢን ፡-(ዕብ ሺጣ፤ ሺጢም) የንጨት ስም፤ እሾኻም ግራርማ፤ የግራር ዐይነት፤ የማይነቅዝ የማይጠነጥን። መጽሐፍ ግን ዕፀ ሰጢን በማለት ፈንታ ዕፅ ዘኢይነቅዝ ይላል ፡-(ዘፀ፳፭ ፡-፭ ፡-፲። ፳፮ ፡-፲፭ ፡-፳፮ ፡-፴፪። ፳፯ ፡-፩። ፴ ፡-፩)።
ሰጢው ዎት ፡-(ሰጠወ ይሰጡ ይስጡ) አው፤
ሰጣሒ ፡-(ሒት ሕያን ያት) የሚያሰጣ፤ አስጭ፤ ገላጭ ገላላጭ። ኦ ሰጣሒሁ ለኅቡእ ወከባቲሁ ለኵሉ ክሡት ፡-(ቅዳ ፡-ሕር)።
ሰጣዊ መሰጥው ፡-የሚሰጥ ሰጪ፤ ጠሪ ጠያቂ፤ መላሽ ተየካሽ። ኪያከ መሰጥወ፤ ኪያከ ሰማዔ ፡-(ቅዳ ፡-ግሩ)።
ሰጥረጲሎን ፡-(ጽር ስትሮፒሎስ) የዛፍ ስም፤ አንድ ዐይነት ዛፍ፤ እንደ ጥድ መልካም ሽታ ያለው፤ ዕንጨቱ የመሥዋዕት ሙጋድ የሚኾን ፡-(ኩፋ ፡-፳፩)። ባለብሉዮች ግን ሽነት ይሉታል።
ሰጥዎ ዎት ፡-(ሰጠወ ይሴጡ ይሰጡ፤ መጠወ። ዕብ ያሻጥ) መስጠት፤ ዕንካ ውሰድ ማለት፤ እጅን መዘርጋት። መጥራት መጠየቅ።
ሰጰለክስ ፡-(ጽር ስፓላክስ። ዕብ ሀቲንሻሜት፤ ጤሌፍ) ፍልፈል፤ ያይጥ ገመር። ሰኰና፤ ጥፍር፤ መዳፍ ውስጥ እግር፤ የእንስሳትና የአራዊት። ለሰውም ይኾናል፤ ዥብ አይበላሽ እንዲሉ ፡-(ዘሌ፲፩ ፡-፴። ፬ነገ ፡-፱ ፡-፴፭)። ባለብሉዮች ግን እሥሥት ይሉታል፤ ፍችው አይዶለም።
ሰጲራ [1]፡-(ጽር ሳፕፊሪስ። ዕብ ሻፒራ) ስመ ብእሲት፤ ሶፎራዊት ሰንፔራዊት፤ ዕንቍት ውቢት ሉሊት። ባለሐዲሶች ግን ሽቱ ይሉታል፤ ሶፎርን እይ ፡-(ግብ፭ ፡-፩)።
[2]፡-(ጽር ስፒራ) መለዮ ምልክት፤ የባንዴራ ዐይነት፤ በወታደሮች ልብስ፤ ባንገትጌው በእጅጌው የሚደረግ። ሠገራተ ሰጲራ፤ ሕዝበ ሰጲራ። ምልክት ያላቸው፤ ምልክታሞች፤ ባለምልክቶች ፡-(ማር፲፭ ፡-፲፮። ዮሐ፲፰ ፡-፫። ግብ፲ ፡-፩)። ባለሐዲሶች ግን፤ የጭፍራ ስም ብለው ይፈቱታል። ሠገረን ተመልከት።
ሰፈለ ፡-(ትግሬ) አቋተ፤ ደቀነ፤ ለመፍጨት ለማድቀቅ፤ ለመቀጥቀጥ፤ የዶቄት የብረት።
ሰፈር ፡-በቁሙ፤ ስፍራ። ጫፍ ዳርቻ ፥ ዘርፍ። ዘፈርንና ዘርፍን ጽፍርንም እይ፤ ከዚህ ጋራ አንድ ነው።
ሰፈርጐል ፡-(ዐረ ሰፈጃል) የተክል ዕንጨት ስም፤ ፍሬው ብጫ የትርንጎ ዐይነት፤ መጠኑ ከትርንጎ የሚያንስ፤ ጥፍጥ ፡-(ቈስጠ ፡-፴፱። ሲኖዶ)።
ሰፈፍ ፡-(ዐማርኛ) በቁሙ፤ የማር ገለባ፤ የጠላ ሐሠር ገፈት።
ሰፊሕ ሖት ፡-(ሰፍሐ ይሰፍሕ ይስፋሕ። ዐጕል) መስፋት መንሰራፋት፤ መብዛት፤ ሰፊ ዝርግ መኾን ፡-(ዘፍ፳፱ ፡-፲፫። ምሳ፳፫ ፡-፴፪። ጥበ፯ ፡-፳፬። ፰ ፡-፩። ፫ነገ ፡-፪ ፡-፳፭)። እምቅድመ ይስፍሑ ደመናት ፡-(ቅዳ)።
፡-ማስፋት፤ መዘርጋት። ይሰፍሑ ኵርበታቲሆሙ፤ እግዚ ዘሰፍሐ ሰማየ። ሰፍሑ ሠቃቲሆሙ። ሰፍሐት ማእደ ቅድሜሆሙ። ሰፍሑ እደዊሆሙ ወነሥኡ ፡-(ማቴ፳፫ ፡-፭። ዘካ፲፪ ፡-፩። ዮዲ፬ ፡-፲፩። ዮሴፍ። ኩፋ ፡-፰)። በሰፍሐ ፈንታ አስፍሐ ይላል፤ ፍችው አንድ ነው። አስፊሖሙ ርእሶሙ ውስተ አስትቶ። ያስፍሕ እግዚ ለያፌት። አስፍሐ እግዚ እደ ኵርሽ ፡-(ቄር ፡-ጰላ። ኩፋ ፡-፯። ዮሴፍ)።
ሰፊር ሮት ፡-(ሰፈረ ይሰፍር ይስፍር። ዕብ ሳፋር) መስፈር መቍጠር፤ መጣፍ መነመር፤ መለካት መመጠን፤ ከልክ ከሚዛን ከቍና ከላዳን ከመዝገብ ማግባት፤ ይህን ያኽል ማለት። ስእኑ ኈልቆቶ ወሰፈረ እምነ ብዝኁ። በመስፈርት ዘሰፈርክሙ ይሰፍሩ ለክሙ። መኑ ዘሰፈሮ ሰማይ በሕፍኑ።ሰፈራ እግዚ ለመንግሥትከ። ከመ ይስፍራ ለኢየሩሳሌም ፡-(ኩፋ ፡-፵። ማቴ፯ ፡-፪። ኢሳ፵ ፡-፲፪። ዳን ፡-፭ ፡-፳፱። ዘካ፪ ፡-፪)።
፡-መስፈር፤ በቁሙ ቦታ መያዝ፤ ሲኼዱ ውሎ ማረፍ፤ መጠለል፤ ድንኳን መትከል፤ ለማደር። ግዕዘ እምነ አራራ ወሰፈረ ውስተ ዱቂ ፡-(ታሪ ፡-ነገ)።
ሰፊን ኖት ፡-(ሰፈነ ይሰፍን ይስፍን። ሰፍሐ፤ ሰፈፈ) መስፈን፤ መስፋት መብዛት፤ መምላት መሸፈን፤ ምሉእ ስፉሕ መኾን፤ ከኹሉ መድረስ፤ እንደ ነፋስና እንደ ብርሃን። እስመ ዓዲሁ ኢሰፈነ ስብከቱ በላዕለ ኵሉ። ዐብየ እከይ ወሰፈነ ጽልእ፤ ሰፈነት ኵለሄ እከይ ወዐመፃ ወዝሙት። ሶበ ሰፈነ አሚን ላዕለ ኵሉ አሕዛብ። ናሁ ሰፈነት ወሰፈፈት እንበለ ንትጋ ፡-(አፈ ፡-ድ፬። ዮሴፍ። ፍ ፡-ነ ፡-፵፭ ፡-፪። ደራሲ)።
፡-መሾም መንገሥ፤ መሠልጠን፤ በላይ መኾን፤ ተሹሞ መግዛት፤ ማዘዝ። መገብት እለ ይሰፍኑ ላዕለ ቅኔ። ሰፈነ ላዕለ ብዙኃን አሕዛብ። ሰፈነት ላዕሌሆሙ ድንጋፄ እንተ ኢተሐዘብዋ። ናሁ አማርያ ካህን ይሰፍነክሙ። ዘይሰፍን ምኔተ ፡-(፩ዜና ፡-፳፱ ፡-፮። ዮሴፍ። ጥበ፲፰ ፡-፲፯። ፪ዜና ፲፬ ፡-፲፩። ፊልክ ፡-፲፯)።
ሰፊድ ሰፈደ ፡-አው ሳፍዶ፤ ፡-(ሳፈደ። ዕብ ሻፋድ፤ በሳ ነደለ) መሻፈድ መጐምዠት መድራት፤ መንጋለል መዘርጋት እንደ ሰፌድ መኾን፤ የእንስት።
ሰፊጥ ጦት ፡-(ሰፈጠ ይሰፍጥ ይስፍጥ። ዐረ ሰፉጠ፤ ለገሰ። ዕብ ሻፉጥ፤ ዳኘ ፈረደ) መሸፈጥ ማበል፤ ማታለል መሸንገል፤ መደለል ማባበል፤ ማሞኘት ማቄል፤ ማሳት ከመንገድ ማውጣት። መጽሐፍ ግን በሰፈጠ ፈንታ አስፈጠ ይላል፤ አያሰኝም። አስፍጢዮ ለምትኪ። አስፍጣ ሊተ ለዛቲ ብእሲት። አርዌ ምድር አስፈጠተኒ። ያሰፍጡነ ውስተ ዘኢንክል ገቢረ ፡-(መሳ፲፬ ፡-፲፭። ዮዲ፲፪ ፡-፲፩። ዘፍ፫ ፡-፲፫። ቀሌ)።
ሰፊፍ ፎት ፡-ሰፈፈ ይሰፍፍ ይስፍፍ፤ ሰፈነ። ዕብ ሳፋፍ። ዐረ ሰፈ) መስፈፍ መንሳፈፍ፤ መስፋት መምላት መንተርፈፍ፤ መልቶ መትረፍ መትረፍረፍ፤ ከልክ ማለፍ፤ የፈሳሽ። ናሕንሐንና ዛሕዝሐን እይ፤ የዚህ ጎር ናቸው። ወለዝንቱ ግብርናሁ ንሬእዮ ኵሎ ዕለተ ይሰፍፍ በውስተ ኵሉ ዓለም። እምከመ ጸርየ ልቡና ወኅሊና ኢይትዐደው እምዐቅሙ፤ ወእምከመ ሰፈፈት ፍትወት ትከውን ሐጸ ቀታሌ። ከመ ይስፍፋ መዛግብቲከ ብዙኀ ሥርናየ ወወይነ ማሕበብትከ ይስፍፍ። ከመ እብነ ፈለግ ይሰፍፍ ፡-(አፈ ፡-ተ፳፩። ፈላስ። ምሳ፫ ፡-፲። ኢዮ፳፪ ፡-፳፬)።
፡-ማጥራት ማጥለል፤ የጠላ የጠጅ የማር የወተት።
ሰፋሪ ፡-(ሪት ርያን ያት) በቁሙ፤ የሚሰፍር፤ የሚቈጥር፤ ቈጣሪ ነማሪ።
ሰፋኒ ፡-(ኒት ንያን ያት) የሚገዛ ገዥ፤ ጌታ፤ ንጉሥ አለቃ። ኮነ ሰፋኔ ላዕለ ኵሉ ነገሥተ ምድር። አልቦሙ ሰፋኒ ፡-(፪ዜና ፡-፱ ፡-፳፮። ፯ ፡-፲፰። ፲፩ ፡-፳፪። ፲፰ ፡-፲፮)። ሐለይት መስቈቅዋት በማለት ፈንታ ሰፋንያት ይላል፤ ስሕተት ነው ፡-(፪ዜና ፡-፴፭ ፡-፳፭)።
ሰፋዊ መሰፍው ፡-መሰፍው፤ የሚያማኵት፤ አማኳች፤ ተስፋ ሰጭ፤ አይዞኽ ባይ።
ሰፋዪ ፡-(ዪት ይያን ያት) የሚሰፋ ሰፊ፤ ጠላፊ። ሰፋዬ አሣእን ፡-(ግብ፬ ፡-፵፫)።
ሰፋጢ ፡-(ጢት ጥያን ያት) የሚሸፍጥ፤ የሚያታልል፤ ሸፋጭ አታላይ። ይመውኦሙ ጻሕቀ ዝንቱ ዓለም ወሰፋጢት ብዕል ፡-(ፍ ፡-ነ ፡-፵፭)።
ሰፌልያ ፡-መዶሻ መራጃ፤ መድሔ፤ አሰሎ፤ ታችኛውንም ያሳያል። ነሃቢ ይዘብጥ በሰፌልያሁ። ድምፀ ሰፌልያ። ዘበጦ ነሃቢ በሰፌልያ ፡-(ኢሳ፵፩ ፡-፯። ኤር፲ ፡-፬። ሢራ፴፰ ፡-፳፰። ያዕ ፡-ዘእል)። በሰፊልያ ወበመዝረብ አባላቲከ እለ ተመትሩ ፡-(ደራሲ)።
ሰፌድ ፡-(ዐማርኛ) በቁሙ፤ ዝርግ፤ ሰታታ ስፌት።
ሰፍነግ ፡-(ብ ሰፋንግ። ጽር ስፖጎስ። ይብ ስፎግ። ዐረ ስፍንጅ) በቁሙ፤ የባሕር ቡቃያ፤ እንጕዳይ፤ ለስላሳ ዐይናማ የጨጓራ ዐይነት፤ የገላ ማጠቢያ መታጠቢያ፤ ውሃ የሚመጥ የሚያነሣ። ሰፍነግ ልምሉም። ምድር ተፈጥረት በአምሳለ ሰፍነግ እንተ ትነብር መልዕልተ ማይ ፡-(አፈ ፡-ተ፭። ቀሌ። ማቴ፳፯ ፡-፵፰። ማር፲፭ ፡-፴፮። ዮሐ፲፱ ፡-፳፱)።
ሰፍዎ ዎት ፡-(ሰፈወ ይሴፉ ይሰፉ። ዕብ ጻፋህ፤ ተነባ) ማማኰት፤ ተስፋ መስጠት በተስፋ ማጽናት፤ ወደ ፊት የሚኾነውን አስቀድሞ መንገር ማብሠር፤ አይዞኽ ማለት፤ ማስታመን። መጽሐፍ ግን በሰፈወ ፈንታ አሰፈወ አስተሰፈወ ይላል፤ አድራጊውን ባስደራጊ አንቀጽ፤ አያሰኝም። አሰፈዎሙ ብዙኀ ንዋየ። ለእመ ወሀቡ ወለእመ አሰፈዉ ለድኅር። አሰፈውኮሙ ለዝ ሕዝብ ሐሰተ። ብዙኀ ያስተሴፍወከ። ቦ ዘበኀፍረት ያስተሴፍዎ ለማኅፈሩ ፡-(ዮሴፍ። ፈ ፡-መ ፡-፳፭ ፡-፫። ኤር፴፭ ፡-፲፭። ሢራ፲፫ ፡-፮። ፳ ፡-፳፫)። ተፈየን ተመልከት፤ የዚህ ከፊል ነው።
ሰፍይ ዮት ፡-(ሰፈየ ይሰፊ ይስፊ፤ ረፍአ። ዐረ ሰፈ፤ ጐነጐነ። ሸፋ፤ ፈወሰ) መስፋት መጥቀም፤ ማያያዝ መሸለል፤ የልብስ የጫማ ያክርማ። አኒም ወሰፍየ አልባስ። ከመ ይስፊ ቶታነ አሣእን። ሰፍየ አስፈሬዳት ፡-(ፍ ፡-ነ ፡-፳፫። ስንክ ፡-ኅዳ፳። ገድ ፡-ኪሮ)።
ሰፍደል ፡-(ብ ሰፋድል) ሥሥ ረቂቅ የሥጋ ክርታስ፤ የፅንስና የሽል የሕፃን ልብስ፤ ልጅ ሲወለድ ከማሕፀን ለብሶት ተጠቅሎበት የሚወጣ። ኦ ዘታወፅኦ ለሕፃን እምሐቌ ብእሲ ወትፌንዎ ውስተ ክርሠ ብእሲት ወትጠበልሎ በሰፋድል ረቂቅ፤ ወእንዘ ማይ ውእቱ ታረግዖ በጥበብከ ወትነፍኅ ላዕሌሁ መንፈሰ ሕይወት። ለባሴ ሰፋድል ፡-(ቅዳ ፡-አት። አዋል)።
ሱላማጢስ [1]፡-ፍጽምት፤–ሰሊም ሰለመ።
[2]፡-(ዕብ ሹላሚት) ፍጽምት፤ ፍጽምተ ሥን፤ፍጽምተ አሚን። ባለብሉዮች ግን ሰላማዊት ወሃቢተ ሰላም ይሉታል ፡-(ማሕ፯ ፡-፩)። ኹለተኛም በሱላሚት ፈንታ ሱላማጢስ እንደ ማለት፤ ሰላመ ሰጣዊት ይላል፤ ስሕተት ነው።
ሱላሜ ፡-መሳለም፤ ሰላምታ፤ ፍቅር ጥዒና። መዋዕለ ፍሥሓ ወሱላሜ ፡-(ስንክ ፡-ነሐ፲፪)።
ሱም ሶመት ፡-(ዐረ ሱም። ዕብ ሹሚም። ሱር ቱማእ) ነጭ ሽንኵርት፤ ቱማ። ባለብሉዮች ግን እንዥቦ፤ አንደ በርበሬ ይሉታል፤ ስጕርድን ተመልክት። በጸለ ወሶመተ። ስጕርድ ወሶመት ፡-(ዘኍ፲፩ ፡-፭። ገድ ፡-ተክ)።
ሱራፊ ፡-መልአክ፤ ከካህናተ ሰማይ አንዱ። ዘውገ ሱራፊ። ሱራፊ ካህን ወኪሩብ ቀሲስ። አዝዚዮ ለሱራፊ ዘሰማይ ቀሲስ ፡-(ስንክ ፡-ጥቅ፲፯። ድጓ። ደራሲ)።
ሱራፌን ል ም ፡-(ጽር ሴራፊም። ዕብ ስራፊም) ከመ ነገድ፤ ልዑላን መላእክት፤ ሊቃናት፤ ዐጠንት፤ ካህናት፤ የሰማይ ቀሳውስት፤ ቀዳሾች። ሱራፌን ይቀውሙ ዐውዶ። ወተፈነወ ኀቤየ አሐዱ እምሱራፌል። ኪሩቤም ወሱራፌም ፡-(ራእ፬ ፡-፬። ኢሳ፮ ፡-፪ ፡-፮። ቅዳ)። በን ፈንታ ል ም ማለት የጣፊ ስሕተት ነው፤ አያሰኝም።
ሱርስት ፡-(ጽር ሲሪስቲ። ዕብ አራሚት) አራማዊ፤ የአራም ቋንቋ፤ ታችኛው፤ አሶራውያን ከለዳውያን የሚናገሩበት፤ የዐረብ የግእዝ የዕብራይስጥ ወንድም። ፈኑ ለነ እግዚኦ መንፈሰ ጰራቅሊጦስ ነድ አርኣየ አንበቦሙ በገሃድ ለሐዋርያት ኄራን ንቡራነ እድ ያነብበነ በሱርስት ወሜድ። ንግረነ ሱርስተ ፡-(ደራሲ። ኢሳ8፴፮ ፡-፲፩)።
ሱርትዮን [1]፡-(ዕብ ሼሩት፤ አገልግሎት። ምሻሬት፤ አገልጋይ) የኪሩቤል ስም፤ ፡-(ሳረተ፤ ሳራቲ) ሳራትያን፤ አገልጋዮች፤ የውስጥ አሽከሮች። በራ መራ መሊጦን ሱርትዮን ፡-(መዋሥ)።
[2]፡-(ዐረ ጹራ፤ ጹረት። ዕብ ጹራት፤ ሥዕል ፥ አርኣያና አምሳል) የኪሩቤል ስም። የሰው የእንስሳ የንስር የአንበሳ አምሳል ማለት ነው። ግምጃን ሶራ ማለት ከዚህ ወጥቷል፤ በላዩ የሚሣለውን ወፍና ዛፍ ያመለክታል፤ ጣዎስን እይ። በስረት ዘይቤ ሲፈቱት ግን ገጸ ንስርን መደብ አድርጎ ክንፋቸውን ብቻ ያሳያል።
ሱቅ ፡-(ዐረብ። ዕብ ሹቅ) መደብር፤ ገባያ መሼጫና መግዣ ቤት ቦታ፤ የከተማ ውስጥ፤ የወደዱትና የፈለጉት የተመኙት ኹሉ የሚገኝበት።
ሱባዔ ፡-(ዕያት) በቁሙ፤ ሰባት፤ ፍጹም ቍጥር፤ የዕለት የዓመት። ወይከውን ለምጽአቱ ውስተ ምድር ሠለስቱ ምእት ወሠላሳ ወሠለስቱ ሱባዔ ዕለታት። በሱባዔ ሳበዕ። ሱባዔ ዓመታት። ወይዜከር ሰብዐተ ሱባዕያተ ፡-(ተረ ፡-ኤር። ኩፋ ፡-፬)። ሰንበትን ተመልከት፤ የዚህ ከፊል ነው፤ ን ስለ ገባበት ተለይቷል።
ሱባዔያዊ ፡-የሱባዔ፤ ቀመር፤ ቍጥር፤ ባለሱባዔ ፡-(አቡሻ ፡-፴፫)።
ሱቱፍ ፡-(ፋን ፋት ትፍት) የተሳተፈ፤ የተባበረ፤ አንድ የኾነ፤ ሽሪክ። ሰላም ለእራኅከ መክፈልተ ሕማማት ሱትፍ። እመ ቦ ብእሲት ዘኮነት ሱትፍተ ምስለ ሰይጣን። ሱቱፋነ ሰረቅት። ሱቱፍነ ጻማ ወሕማም። ሱቱፋን ንሕነ በበይናቲነ። ሰላም ወርትዕ ሱቱፋነ ይከውኑ ፡-(ደራሲ። ፈ ፡-መ ፡-፭ ፡-፲፪። ኢሳ፩ ፡-፳፫። ስንክ ፡-ጥር፳፮። ፩ዮሐ ፡-፩ ፡-፯። ሔኖ፲፩ ፡-፪)።
ሱታፌ ፡-መሳተፍ፤ መተባበር፤ ማኅበርነት፤ ድርገት፤ አንድነት። ተባባሪ፤ ሽሪክ ጓደኛ፤ ባልንጀራ፤ ማኅበረተኛ። አባ ጳኵሚስ አብ ሱታፌ መንፈሳውያን አስተጋብአ ብዙኃነ ሰብአ ወሐነጸ አድባራተ ወሠርዐ ለኵሎሙ ሱታፌ በግብረ እደዊሆሙ ወሲሳዮሙ። ከመ አንትሙኒ ትኩኑ ሱታፌ ምስሌነ። አነ ሱታፌከ በኵሉ ግብርከ። እኁክሙ ወሱታፌክሙ። አስቴር ሱታፌ መንግሥትነ። ለእመ ትጻብኦ ካህን ምስለ ካህን ሱታፈሁ ፡-(ስንክ ፡-ግን፲፩። ፩ዮሐ ፡-፩ ፡-፫። ዮሴፍ። ራእ፩ ፡-፱። አስቴ፰ ፡-፲፫። ፍ ፡-ነ ፡-፱)።
ሱታፍ ፡-ዝኒ ከማሁ። ከመ ንኩን ሱታፎ ለጽድቅ። ሰላም ለሕፅንኪ ለጥበበ ሰማይ ምዕራፋ፤ ዘኢይትረከብ ሱታፋ። ጥዑመ ዜና ጊዮርጊስ ለሐሊበ ዕጐልት ሱታፉ ፡-(፫ዮሐ ፡-፰። ደራሲ። ፩ጴጥ ፡-፭ ፡-፩። ፩ቆሮ ፡-፱ ፡-፳፫)።
ሱዓሪም ፡-(ዕብ ሾዓሪም) ሰዓርያን፤ ሰዐርት፤ በረኞች የሚከፍቱና የሚዘጉ የሚጠብቁ ፡-(ኤር፴፮ ፡-፲፯)።
ሱዳን ፡-ጥቍር፤ ጠቋራ፤ ከሰልማ መልክ ሕብር። የጥቍሮች የኵሽ ልጆች አገር፤ የአፍሪቃ ክፍል፤ ከግብጽ ጋራ የተያያዘ፤ ግዮን ኤፌሶን የሚያጠጡት። በጽርእና በግእዝ መጽሐፍም ኢትዮጵያ ይባላል፤ ፍችው ጥቍር ማለት ነው። ጥቍሩን ቅመም አበሱድ፤ አበሱዳ እንዲሉት ፡-(ዐማርኛ)።
ሱጠት ፡-መጨመር፤ ማዋሐድ። ተጨማሪ መኾን። ሱጠተ ርእሱ ፡-(ቄር ፡-ጰላ)።
ሲሃት ፡-(ዐረ ሻሀት) ለማኝ፤ ምስኪን፤ ቍርጩ ድኻ። ገዳመ ሲሃት፤ ሙሴ ዘሲሃት ፡-(ስንክ ፡-መስ፩)።
ሲሕ ፡-(ዕብ ሽሔፌት) የሳንባ ደዌ፤ ታላቅ ሳል፤ ኰብሽ ደዌ ሥጋ፤ የሚያከሳ የሚያጠቍር፤ የሚነፋ የሚያሳብጥ፤ የሚያቈስል የሚያሳክክ። ደዌ ሲሕ ፡-(ዘሌ፳፮ ፡-፲፮። ዘዳ፳፰ ፡-፳፪)።
ሲላን ፡-(ዐረ ሺላን። ጽር ሴሊኖን) እንስላል፤ ፍሬው። የክሙን ዐይነት፤ ከዐረቂ ቅመም የሚገባ። ርሔ ሪሓን በማለት ፈንታ ሲላን ይላል ፡-(ማቴ፳፫ ፡-፳፫)።
ሲሱይ ፡-(ያን ያት ሲት) የተሴሰየ፤ የሚቀለብ፤ ቅልብ፤ ሲሳያም፤ ቀለብተኛ፤ ባለድርጎ ባለቀለብ።
ሲሲት ፡-ዝኒ ከማሁ፤ ሲሳይ። ወሀብኩክሙ አራዊተ ለሲሲት። ልብስ ወሲሲት። ሲሲተ ልብ ቃላቲሁ ለእግዚ ፡-(ኩፉ ፡-፮። ፳፱። ቄር ፡-ጰላ)።
ሲሳይ ፡-(ያት) በቁሙ፤ ምግብ ቀለብ፤ ድርጎ መኖ፤ መፍቅደ ዕለት ቍርስ ምሳና እራት። ሲሳየነ ዘለለ ዕለትነ። ዘኢይረክብ ሲሳዮ። እክል ለሲሳይ። ዘእንበለ ሲሳይ። ሲሳየ ቋዓት ፡-(ነሐ፭ ፡-፲፰። ሢራ፲ ፡-፳፯። ኢሳ፶፭ ፡-፲። ኢዮ፳፬ ፡-፯። ፴፰ ፡-፵፩)። ዐስብ፤ ረባሕ በማለት ፈንታ ሲሳይ ይላል፤ ስሕተት ነው ፡-(ሉቃ፫ ፡-፲፬። ፲፱ ፡-፳፫)።
ሲሴት ፡-ዘማች አሞራ፤ ተዋጊ ምግብ ፈላጊ፤ ወይም ነጣቂ አውሬ ዐድኖ ፈልጎ የሚሴስይ። ሲሴተ ወአውስተ። ዕጕለ አናብስት ይጥሕሩ ወይመሥጡ ወይስእሉ ኀበ እግዚ ሲሳዮሙ ፡-(ሔኖ፹፱ ፡-፲። መዝ ፡-፻፫)።
ሲራ ፡-ሢራይ፤–ሤረየ።
ሲርኖን ፡-(ጽር ሲሪኖን) ሰጐን፤ ሰገኖ። አዋልደ ሲርኖን ፡-(ሚል፩ ፡-፰)።
ሲቃርዮን ፡-(ጽር። ሲካሪዖን) ዕደወ ደም፤ መጥባሕታውያን፤ ሾተላሞች፤ ባለሾተሎች ሾተል ታጣቆች፤ ሽፍቶች ወንበዶች ፡-(ግብ፳፩ ፡-፴፰)። ሲካ የሾተል ስም ስም።
ሲናጎግ ፡-(ጽርእ) ምኵራብ፤ ቤተ ጸሎት፤ መሰብሰቢያ፤ ከኒሳ ቤተ ክሲያን፤ ጉባኤ ሸንጎ አደባባይ።
ሲኖዲቆን [1]፡-ሲኖዲቆን፤–ሲኖዶሳዊ፤–ሲኖዶስ።
[2]፡-(ጽር ሲኖዲኮን) ሲኖዶሳዊ ዘሲኖዶስ፤ ማኅበራዊ ጉባኤያዊ። መተርጕማን ግን ቆነሲኖዲ ብለው ሊቅ ወማኅበር ይሉታል። መልእክተ ሲኖዲቆን ፡-(ሃይ ፡-አበ)።
ሲኖዶስ ሳት ፡-(ጽርእ) ጉባኤ፤ ሸንጎ፤ የጳጳሳትና የሊቃውንት ማኅበር፤ እከባ ስብሰባ። መጽሐፈ ሲኖዶስ ዘጸሐፉ ኵሎሙ ጳጳሳት። ቅድስት እንተ እምኵሉ ዓለም ሲኖዶስ ጉባኤ ፡-(ዘኤፌሶን)። ካዕበ ለለ ዓመት ሴኖዶስ ይትገበር። ወለኵሉ ዘዐለወ ዘንተ ሕገ ሲኖዶስ ያወግዞ ፡-(ተረ ፡-ቄር፲፪። ቀኖ ፡-፳፭። ፍ ፡-ነ ፡-፬)።
ሲኢን ኖት ፡-(ስእነ ይስእን ይስአን። ዕብ ሻኤን፤ ንህየ። ያሼን፤ ኖመ) መሳን፤ መድከም፤ መታከት፤ ኀይል ክሂል ሥልጣን ማጣት፤ አለመቻል፤ የማይቻለው መኾን። ስእኑ አውሥኦቶ ለኢዮብ። አናብስት ስእኑ ይግስስዎ። ኀሠሥኩ አእምር ወስእንኩ። ለእመ ስእነ ብእሲ ሰኪበ ምስሰ ብእሲቱ ለአቅሞ ዘርዕ፤ ወዝንቱ ስኢን ይከውን እምሠለስቱ ምክንያት። ስኢነነ ተዐግሦ ፡-(ኢዮ፴፪ ፡-፫። ስንክ ፡-ጳጕ፩። ሱቱ ፡-ዕዝ፲፫ ፡-፰። ፈ ፡-መ ፡-፲፪ ፡-፭። ፩ተሰ ፡-፫ ፡-፩)።
ሲኦል ፡-(ዕብ ወሱር ሽኦል) በቁሙ፤ ታሕተ ምድር፤ ልበ ምድር፤ መቃብር፤ የግዞት ቦታ፤ መካነ ኃጥኣን፤ እስከ ዕለተ ዐርብ ነፍሳት ኹሉ የነበሩበት። አኮኑ ክሡት ሲኦል በቅድሜሁ። ሞትሂ ወሲኦል ይቤሉ። ወኢድኀንካ ለነፍስየ እምሲኦል ታሕቲት። መራኁተ ሞት ወሴኦል። አናቅጸ ሲኦል ፡-(ኢዮ፳፮ ፡-፮። ፳፰ ፡-፳፪። መዝ ፡-፹፭። ራእ፩ ፡-፲፰። ማቴ፲፮ ፡-፲፰)።
ሲፓራ ፡-(ዕብ ጺፖራ) ዝኒ ከማሁ፤ ስመ ብእሲት፤ ዖፍ ላሕዪት፤ የመስቀል ወፍ ፡-(ዘፀ፪ ፡-፳፩)።
ሳሕለለ ፡-(ተቀ ግ) ደረቀ፤ ከረረ፤ እንደ መሳልና እንደ ብረት ኾነ።
ሳሕል ፡-ይቅርታ፤–ሣህሎ ሣሀለ።
ሳሕሳሕ ፡-(ትግሪኛ) ምናምንቴ፤ ልክስክስ፤ ወስዋሳ። ወድ ሳሕሳሕ እንዲል።
ሳሕስሖ ሖት ፡-(ሳሕስሐ ይሳሐስሕ ይሳሕስሕ። ዕብ ሳሓህ፤ ዋኘ፤ ዛዕዛዕ። ዐረ ዘዕዘዐ) መታወክ መናወጥ፤ መራድ መንቀጥቀጥ፤ መላወስ መንቀሳቀስ። መጽሐፍ ግን በሳሕስሐ ፈንታ አንሳሕስሐ፤ አንሰሐስሐ ይላል፤ በሶስወ ፈንታ አንሶሰወ እንዲል።
ሳሕበበ ፡-ሻገተ፤–ሣህበበ።
ሳሕክ ፡-(ካት) ስሓ፤ እንክን፤ ምማቴ፤ የገላ ነውር፤ ዕከክ ብግር፤ ቋቍሻ ቈረቈር፤ የመሰለው ኹሉ። ሽካራ ጸጓር ቅርፍርፍ መኾን። መመተን እይ፤ ባላገር ግን ስሓ በማለት ፈንታ ሳካ ይላል። ሳካም የለሽ እንዲሉ ፡-(የሴት ልጅ ስም)። አጽሕድ በቅብዕከ ለነፍስየ ሳሕካ ፡-(ስንክ ፡-ግን፰)።
ሳሕው ፡-የጉም ሽንት፤ ተነ ጊሜ፤ ግዘፈ ደመና፤ የሚጐተት ሻ ብትን የሚል። መንፈስነ ይትከዐው ከመ ሳሕወ ደመና። ጉባኤሆሙ ለዐማፅያን ከመ ሳሕወ ደመና፤ ወፍሥሓሆሙ ከመ ዖፍ ሰራሪት። ከመ ሳሕወ ጊሜ በገጸ ምድር ፡-(ጥበ፪ ፡-፫። መቃ ፡-ገ፲። አርጋ ፡-፩)።
ሳሙን ፡-(ዐረ ሳቡን) ሳሙና፤ የልብስ የገላ ማጠቢያ ማጥሪያ፤ ከሥብ ከሞራ ከዘይት ካመድ ከእንዶድ ከሌላም ዐይነት የሚሠራ፤ ቅመሙ ስምንትነት ያለው።
ሳሜኅ ፡-(ዕብ ሳሜኽ) የፊደል ስም፤ ሳምኬት ሰ ፡-(ሰቈ፩ ፡-፲፭)።
ሳሜን ፡-(ዕብ ሼሜን) ሥብ ሞራ ጮማ፤ ቅቤ ዘይት ቅባኑግ፤ የመሰለው ኹሉ።
ሳምኒት ፡-(ዕብ ሽሚኒት) ንዋየ ማሕሌት፤ በገና ክራር፤ ባለ፰ ፡-አውታር። በእንተ ሳምኒት ፡-(መዝ ፡-፲፩)።
ሳምናዊ ይ ፡-(ዊት ዪት ኒት) ዝኒ ከማሁ፤ ስምንተኛ።
ሳምን ንት ፡-ስምንተኛ። በሳምን ወርኅ። አመ ሳምንት ዕለት። ሳምኖሙ ውእቱ ፡-(ዘካ፩ ፡-፩። ዘሌ፱ ፡-፩። ሉቃ፱ ፡-፳፰። ራእ፲፯ ፡-፲፩)።
ሳምኬት ፡-(ሱር ሴምካት። ዕብ ሳሜኽ) የፊደል ስም ሰ፤ ፲፭ኛ። ምስማክ፤ ዐጋዥ፤ ረዳት ማለት ነው ፡-(መዝ ፡-፻፲፰። ሰቈ፩ ፡-፲፭። ፪ ፡-፲፭። ፫ ፡-፵፪። ፬ ፡-፲፭)።
ሳረረ ፡-ሠራ መሠረተ፤–ሣረረ።
ሳሪራ ፡-የሽቱ ውሃ፤ ጥሩ ሽቱ ልብ የሚመሥጥ፤ ከሩቅ የሚሸት። ነቄጥሩን እይ። ከመ ሳሪራ ወከልበኔ ፡-(ሔኖ፴፩ ፡-፩)።
ሳራብ ፡-ሳማ ዶቢ፤–ሣራብ።
ሳሬት ፡-ሸረሪት፤–ሠረየ።
ሳርሐ ፡-በራ፤–ሣርኀ።
ሳሮን ፡-ስመ ሀገር፤–ሣሮን።
ሳቀየ ፡-በቁሙ፤–ሣቀየ።
ሳቢላኔስ ፡-(ዕብ አቢሊን) ስመ ሀገር ሶርያዊ፤ ወይናም በለሳም ፡-(ሉቃ፫ ፡-፩)።
ሳባጥ ፡-የወር ስም፤–ሠበጠ ሣባጥ።
ሳቤቅ [1]፡-(ሱር ሲብቃ) ረዥም ዐጽቅ፤ ሐረግ፤ ማናቸውም። ሐረግ ሬሳ፤ ቧሔ ዐረግ።
[2]፡-(ጽር ሳቤክ። ዕብ ስባኽ። ሱር ኢላና። ዐረ ዓበት) ጽፍቅ ዱር፤ ቀጫጭን ዕንጨት ሐረግና ዐጽቅ፤ ርስ በርሱ የተሳበቀ፤ የተዋሰበ፤ የተቈላለፈ። ርእዩ በግዐ እኁዝ አቅርንቲሁ በዕፀ ሳቤቅ፤ ዕፀ ሳቤቅ ብሂል ዕፀ ስርየት መስቀል ፡-(ድጓ። ዘፍ፳፪ ፡-፲፫)።
ሳብላንዮስ ፡-(ጽርእ። ዕብ ሳብላኒ) የሰይጣን ስም፤ ክቡደ ጾር፤ ብዙኀ ጾር፤ ዘይጸውር ወዘያጸውር ፡-(መቃ ፡-ገ፳፪)። ሳብላንዮስ በማለት ፈንታ ሰልብልያኖስ ይላል፤ የተሳሳተ ነው። ወትእኅዞሙ ቅንአት ከመ ሰልብልያኖስ ፡-(ማሕ፭ ፡-፩)።
ሳብዓዊ ይ ፡-(ዊት ዪት ዒት) ዝኒ ከማሁ፤ ሰባተኛ፤ ው፤ ፡-(ዋ ይቱ)።
ሳብዕ ፡-(ዕት ዓን ዓት) ሰባተኛ፤ ከሰባት አንድ። በሳብዕ ወርኅ። በሳብዕ ዓመት። ሰሳብዕት ዕለት። ሳብዕተ እዴሃ ለምድር ፡-(ዘሌ፳፫ ፡-፳፬። ሕዝ፳ ፡-፩። ዘፍ፪ ፡-፪። ሱቱ ፡-ዕዝ፬ ፡-፵፮)።
ሳታፊ ፡-(ፊት ፍያን ያት) የሚያሳትፍ አሳታፊ፤ የሚያገናኝ፤ የሚያስተባብር።
ሳት ፡-(ዕብ ስታው። ዐረ ሽታ) ስመ ፊደል ፳፩ኛ ሰ። ክረምት የዝናም ወራት ማለት ነው። ጸሐፍት ግን ሳት በማለት ፈንታ እሳት ይሉታል፤ ጥንተ ስሙ ሰን እንጂ እን አይሻምና፤ ሠውት ሠን ንጉሥ እንደሚሉት ይህም እንደዚያ ነው። ፪ኛ ስሙ ስዐት ይባላል፤ ምስጢሩ ከዚያው ይገባል።
ሳትፎ ፎት ፡-(ሳተፈ ይሳትፍ። ዕብ ሻታፍ። ሱር ሻውቴፍ። ዐረ ሸረከ) ማሳተፍ፤ ማጕረሥ መወተፍ። መግጠም ማጋጠም፤ ማገናኘት ማስተባበር፤ አንዱን ካንዱ ጋራ ማዛወግ፤ አንድ ማድረግ። መጽሐፍ ግን በሐቀረ ፈንታ አስተሐቀረ እንዲል፤ በሳተፈ ፈንታ አስተሳተፈ ይላል፤ አድራጊውን ባደራራጊ። ታስተሳትፍ ኅሊና መንግሥትክሙ። ኣስተሳትፈከ በመንግሥትየ። ተዘምዶ ሥጋዊ ያስተሳትፍ ምስለ ሥጋ። ያስተሳትፍዎሙ እምስጢር ቅዱስ ፡-(ቄር። ፈላስ። ፍ ፡-ነ ፡-፶፩። ፈ ፡-መ ፡-፮ ፡-፲፫)።
ሳኒታ ፡-ዝኒ ከማሁ፤ ማግስት፤ ነገታ ነገ፤ ኹለተኛ። በሳኒታ ፋሲካ። ኢተአምር ዘትወልድ ሳኒታ። ወበሳኒታ ኳዕበ። በሳኒታ ዕለት እምዘቀተለ ፡-(ዘኍ፴፫ ፡-፫። ምሳ፫ ፡-፳፰። ዮሐ፩ ፡-፴፭። ኤር፵፰ ፡-፬)።
ሳን ፡-(ዕብ ሢን ሺን) ስመ ፊደል ኻያ አንደኛ፤ ሠ፤ ሸ። ስን፤ ጥርስ ማለት ነው። ሳን መላእክት ሰደዱኒ በከንቱ ፡-(መዝ ፡-፻፲፰ ፡-፻፷፩–፻፷፰)።
ሳንይ ሳኒት ፡-(ዐረ ሳኒን) የዕለት ቅጽል፤ ኹለተኛ፤ ካዕብ፤ ካልኣይ መዓልት። በሳኒት ዕለት። በሳኒታ ለቀዳሚት። እምሳኒተ ሰንበት። ለለ ይጸብሕ ሳኒት ፡-(ዘኍ፯ ፡-፲፰። ዘሌ፳፫ ፡-፲፩ ፡-፲፭። ስንክ ፡-የካ፰)።
ሳዓር ፡-(ዕብ ሻዐር) ታላቅ በር፤ የከተማ የቤተ ክሲያን የቅጥር ደጅ አፍ።
ሳዕ ሰዐት ሰዓት ፡-(ዕብ ወሱር ሻዓ። ዐረ ሳዐት) ሰዓ፤ ሰዓት፤ ጊዜ፤ የዕለት ፳፬ኛ ክፍል፤ ፷ ደቂቃ፤ ከ፳፬ቱ ክፍል አንዱ፤ ዘመን ወራት። የሰዓት መሣሪያ ባላ፲፪ ክፍል። እምጊዜ ጽባሕ እስከ ሳዐ ዕለት ይመሲ። በኵልይ ጊዜ ወበኵሉ ሳዕ። ሰዓተ ስቅለቱ ስሱ ሳዕ። ሳዐ ሞቱ ርሑቅ። በኵሉ ሰዓት። መጠነ አሐቲ ሰዓት። መንፈቀ ሰዓት። በአይ ሰዓት። በስድስቱ ሰዓት ፡-(ስንክ ፡-ግን፪። አርጋ። መጽ ፡-ምስ። ስንክ ፡-ኅዳ፫። ዘሌ፲፮ ፡-፪። ዳን፬ ፡-፲፮። ራእ፰ ፡-፩። ፫ ፡-፫። ዕር ፡-ኢሳ፬ ፡-፭)። የፊደል ስም፤ ሳት ሰ። ሳትን ተመልከት፤ ይህ ፪ኛ ስም ነው።
ሳዕሳዕ ፡-የቃል ምላሽ፤–ሣእሣእ፤ ወሥአ።
ሳእር ፡-በቁሙ ሣር፤–ሥዒር ሥዕረ።
ሳዕር ፡-ሣር፤–ሣዕር፤ ሥዕረ።
ሳእን ፡-ጫማ መጫሚያ፤–ሣእን።
ሳዕን ፡-ጫማ፤–ሣእን።
ሳኵዮ ዮት ፡-(ሳኰየ ይላኵ። ዕብ ሻጋህ። ሱር ሽጋእ) መሳት፤ ከመንገድ መውጣት፤ መዞር መባከን መንከርተት፤ ከበረሓ መግባት፤ መቅበዝበዝ፤ አለመንገድ መኼድ። ሳኰየት ውስተ ገዳም። እንዘ የዐይል ወይሳኵ። ወሳኰዩ ውስተ በድው። ከመ አባግዕ ትሳኵዩ። ሥልሰ ሳኰየት ሐመርየ ፡-(ዘፍ፳፩ ፡-፲፬። ፴፯ ፡-፲፭። መዝ ፡-፻፮። ፩ጴጥ ፡-፪ ፡-፳፭። ፪ቆሮ ፡-፲፩ ፡-፳፭)። ይሰበር ይትቀጠቀጥ በማለት ፈንታ ሳኰየ ይላል፤ ስሕተት ነው ፡-(ሆሴ፰ ፡-፮)።
ሳውዳ ፡-(ዐረ ሰውዳኡ) የእሳት ጠባይ፤ እሳታዊ ባሕርይ፤ የሚያነድ የሚያሞቅ የሚያቃጥል። ሐዘን ይትወለድ እምነ ሳውዳ ፡-(ፈላስ ፡-ገ፴፩)።
ሳድሲት ፡-የቍጥር መደብ፤ ስድስተኛ ክፍል፤ የኃምሲት ስሳኛ። ኬክሮስን እይ።
ሳድሳዊ ይ ፡-(ዊት ሲት) ዝኒ ከማሁ፤ ስድስተኛ።
ሳድስ ፡-(ስት ሳን ሳት) የተራ ቅጽል፤ ስድስተኛ፤ ከስድስት አንድ። በሳድስ ዓመት። ወበሳድስ ወርኅ። ወኮነ ሳድስተ ዕለተ። ሳድስተ ኢፍ ፡-(ሕዝ፰ ፡-፩። ሉቃ፩ ፡-፳፮። ዘፍ፩ ፡-፴፩። ሕዝ፵ ፡-፭ ፡-፲፫)።
ሳዶር ፡-የቀኖት ስም፤ ችንካር ያይዶለ ሌላ ዐይነት፤ ደጋን ብረት፤ እንደ ዝናር ኹኖ ከጡቶቹ በታች ሰውነቱን ከቦ ዐቅፎ ደግፎ ከመስቀል ጋራ አንድ የሚያደርግ፤ ወይም ገመድ ሰንሰለት። ሳዶር፤ ዘበትርጓሜሁ ካልእ። ወፈትሑ ሐብለ እምሐቌሁ ዘተአስረ ቦቱ ምስለ መስቀል ፡-(መጽ ፡-ምስ። ድር ፡-ማሕ)። ሳዶር ከሌለ ባራት ችንካር ብቻ ከመስቀል ተጣብቆ ቀጥ ብሎ መቆም አይቻልምና፤ ካልእ ማለቱ ስለዚህ ነው። አላዶርንና ዳናትን አዴራንና ሮዳስን እይ።
ሳዶቅ ፡-(ዕብ ጻዶቅ) የሰው ስም፤ ጻድቅ፤ እውነተኛ ፡-(፪ነገ ፡-፲፭ ፡-፳፭)። የሰዱቃውያን መምር።
ሳጥና [1]፡-ሰይጣን፤–ሴጠነ።
[2]፡-ሰይጣን። ሳጥናኤል፤ ሰይጣነ ኤል፤ ፀረ አምላክ፤ ያምላክ ጠላት። ባለሐዲሶች ግን ፥ ሥሉጥ ባለሟል። ቅሩበ መንበር አኃዜ መንጦላዕት ይሉታል፤ የስሕተት ስሕተት ነው፤ ምጸት ይመስላል። ሴስዩነ ከመ መና ሥሉስ ቅዱስ ሰላመክሙ ዳኅና፤ እማኅበርነ ያሰስል ሙስና ስዒሮ በጥዒና ሁከቶ ለሳጥና። ሰራዊተ ሳጥናኤል ፡-(ደራሲ። ድር ፡-ሚካ። ቀሌ)።
ሳፍ ፡-(ዕብራ) መድረክ። ቅድመ ሳፍ ፡-(ሕዝ፵፩ ፡-፲፮)።
ሳፍራ ፡-(ዐረ ጸፍራ) የነፋስ ባሕርይ፤ ነፋሳዊ ጠባይ። ሳፍራ ዘውእቱ ጠባይዕ ነፋሳዊ። ፅንስ ይትወለድ አምኀይለ ሳፍራ። ሀኬት ይትወለድ እምነ ሳፍራ ፡-(ፈላስ ፡-ገ፲፮ ፡-፴ ፡-፹፰)።
ሴመ ፡-ሾመ፤–ሠዪም ሤመ።
ሴሰየ ፡-በቁሙ፤–ሰይሰየ።
ሴሳዪ ፡-(ዪት ይያን ያት፤ ሰይት) የሚሴስይ የሚመግብ፤ የሚቀልብ፤ መጋቢ ቀላቢ።
ሴስዮ ዮት ፡-(ሴሰየ ይሴሲ። ዕብ ሲስ፤ ተሐሥየ) መሴሰይ፤ መመገብ፤ መቀለብ፤ ምግብ መስጠት፤ ግብር አግብቶ ማብላት ማጠጣት፤ ደስ ማሰኘት። ሴሰይክዎሙ እክለ ወማየ። ከመ እሴሲክሙ። ሴሰይኮሙኑ ለደቂቁ። ሴሰዮሙ ለአቡሁ ወለአኀዊሁ ወለጥሪቶሙ ኀባውዘ። ኵሎ አሚረ ይሴስይዎሙ ፡-(ለአናብስት) ክልኤተ ሰብአ ወክልኤተ አባግዐ። አዘዘ ይሴስይዋ እምነ ዘይገብሩ ሎቱ ሲሳዮ ፡-(፫ነገ ፡-፲፰ ፡-፲፫። ዘፍ፵፭ ፡-፯። ኢዮ፴፱ ፡-፫። ኩፋ ፡-፵፭። ዳን፲፫ ፡-፴፪። ዮዲ፲፪ ፡-፩)።
ሴሬቅ ፡-ጥሩ ወይን፤–ሤሬቅ።
ሴርኒስ ፡-(ጽር ሲሪኔስ) ዝኒ ከማሁ፤ ሰጐን። ዕጕለ አዕዋፍ ወሴርኒስ ፡-(ኢሳ፵፫ ፡-፳)።
ሴበ ፡-ሸበተ፤–ሠዪብ ሤበ።
ሴነ ፡-ሸነ፤–ሠዪን ሤነ።
ሴኬሉ ሴክሎ ፡-የተሳሳተ ስም፤ ካሴል፤ ኪስሌው፤ ታኅሣሥ ፡-(ዕዝ፲፩ ፡-፩። ስንክ ፡-የካ፭)።
ሴኬቤቴናሆም ፡-ያልታወቀ ጥሬ፤ ባለቅኔዎች፤ ሕቅፍ ዶሮ፤ የዶሮ እመጫት ብለው ይፈቱታል። ሴኬቤቴ ስከብት፤ ናሆም ፥ ንዋም፤ ሰከብተ ንዋም ማለት ይመስላል፤ ፍችውም እንቅልፍ ያስተኛቸው፤ የወሰዳቸው ያሰኛል።
ሴክል ፡-(ሮማይ፤ ሴኩሉም) የቀመር ስም፤ አስካለ ዘመን፤ መቶውን ዓመት እንደ መቶ ቅንጣት ሰብስቦ የያዘ ምእታዊ፤ በዓለ ምእት። ባጭር ቃል ፻ ዓመት ማለት ነው።
ሴጠነ ፡-(862) ፡-(ይሴጥን ይሴጥን፤ ሴጥኖ። ዕብ ሳጣን) ከሰሰ አሳጣ፤ አሳተ በጦር በነገር ተከተለ።
ሴፌላ ሴፌል ፡-(ጽር ሴፊላ። ዕብ ሽፌላ) ቈላ ጕድጓዳ፤ ዘብጥ ረባዳ፤ ዘቅዛቃ ወዳቃ፤ ወንዛወንዝ ሸለቆ ፡-(ዓብድ ፡-፲፱። ፪ዜና ፡-፳፮ ፡-፲)።
ስሑል ፡-(ላን ላት ሕልት) የተሳለ፤ ስል ሹል፤ ስለታም። ስሑል ፈድፋደ እመጥባሕት። አሕጻከ ስሑል ፡-(ምሳ፭ ፡-፬። መዝ ፡-ሣ፬)።
ስሑብ ፡-(ባን ባት ሕብት) የተሳበ፤ የተጋደመ፤ የደነነ የጸነነ፤ ዝርግ። የውጣ ፡-(፲) ዘእንበለ ጥውየት፤ ኢድኑነ ርእስ ወኢስሑበ አእጋር ከመ በዕዳን ሆህያት ፡-(መጽ ፡-ምስ)።
ስሑት ፡-(ታን ታት ሕት) የሳተ፤ የተሳተ፤ የተሳሳተ፤ አላዋቂ። አብድ ስሑት ውእቱ ወጠቢብሂ ዘይትጌሠጽ እምካልኣኒሁ። ጥበበ ስሑታን ፡-(ፈላስ። ኪዳ)።
ስኁን ፡-(ናን ናት ኅንት) የሞቀ፤ የተኰሰ፤ ሙቀት የነሣ ትኵስ።
ስሑክ ፡-(ካን ካት ሕክት) የሻከረ፤ ሸካራ፤ ቅርፍርፍ። ለእመኒ ኮነ ሥጋሆሙ ይቡሰ ወስሑከ ፡-(ኦፈ ፡-ተ፳፱)።
ስሑጥ ፡-ስሑጥ፤ ፡-(ጣን ጣት ሕጥ) የተነካ ንክ፤ የተጐነጠ፤ የተቈነጠጠ። የተሠራ የተቀጣ በሥራት ያደገ ፡-(ዐማርኛ)።
ስሒል ሎት ፡-(ሰሐለ ይስሕል ይስሐል። ዐረ ሰሐለ፤ ሰሕገለ) መሳል መሰንገል፤ ማስላት ማሾል፤ መሞረድ መፈግፈግ፤ እንዲሰላና እንዲበላ እንዲሾል ማድረግ። ዘይስሕል ሰይፈ ለቢጹ ይትቀተል ቦቱ ለሊሁ። አዘዘ ከመ ይስሐሉ ኵናተ ፡-(ፈላስ። ገድ ፡-ተክ)።
ስሒብ ቦት ፡-(ሰሐበ ይስሕብ ይስሐብ። ዐረ ሰሐበ። ዕብ ሳሐብ) መሳብ መጐተት፤ መምዘዝ ማውጣት፤ ማቅረብ ማምጣት፤ መወጠር መገተር መለጠጥ ማስፋት፤ ማስረዘም ማብዛት። ይስሕቡ አንስቲያሆሙ። ሰሐብዎ በመዐት። እስሕብ ኵሎ ኀቤየ። እለ ይስሕብዋ ለኀጢአቶሙ ከመ ሐብል ነዋኅ። መገሥጽ ሶበ ያነውኅ ነገረ ወይስሕብ ቃለ ያንጌጊ ሰማዒ ፡-(ኢሳ፲፫ ፡-፲፮። ቅዳ ፡-አፈ። ዮሐ፲፪ ፡-፴፪። ኢሳ፭ ፡-፴፪። አፈ ፡-ድ፳፯)።
ስሒት ቶት ፡-(ስሕተ ይስሕት ይስሐት፤ ጌገየ። ዕብ ሻሔት። ዐረ ሰሐተ፤ ሰሐጠ) መሳት፤ አለማግኘት፤ ወርውሮ ተኵሶ። ፡-(ተረት) ተውነት የሚሻል ሐሰት፤ ከመውጋት የሚሻል፤ መሳት። የሀይጱ ሥዕርተ ወኢይስሕቱ ፡-(መሳ፳ ፡-፲፮)።
፡-መሳሳት ከመንገድ መውጣት፤ መታለል መሸንገል፤ መርሳት መዘንጋት፤ ሳያውቁ መበደል፤ ክፉ መሥራት፤ ወይም እያወቁ ማጥፋት ማበላሸት፤ አጥፊ መኾን፤ ስሕጠን ተመልከት፤ የዚህ ጎር ነው። ስሕቱ ግብጽ። ብእሲኒ ዘዘ ዚኣሁ ሖረ በፍኖቱ ወስሕት። ለስሒት መኑ ይሌብዋ። ስሕትነ እምፍኖተ ጽድቅ። ኢይስሕቱ ወኢይፈልሱ እምነ ዐቅሞሙ። ይስሕቱ ሠርቀ ወሰንበተ። ብዙኃን እለ ስሕቱ በሥነ ብእሲት። ቦ ዘይስሕት እንዘ ኢይፈቅድ ልቡ ፡-(ኢሳ፲፱ ፡-፲፫። ፶፫ ፡-፮። መዝ ፡-፲፰። ጥበ፭ ፡-፮። ሔኖ፵፫ ፡-፲። ኩፋ ፡-፩። ሢራ፱ ፡-፰። ፲፱ ፡-፲፮)።
ስኂን ፡-ልብን፤ ልባንጃ፤ ጥሩ ነጭ ዕጣን፤ የግራር ሙጫ የሚመስል፤ የልብኀን ፍች፤ ከዚህ ጋራ አንድ ነው። ከርቤ ወስኂን ፡-(ማሕ፫ ፡-፮። ዘፀ፴ ፡-፴፬። ዘሌ፪ ፡-፩)። ሴቶች ከእሳት አግብተው የሚሞቁትና የሚያጤሱት ሌላውም የጢስ ዕንጨት ኹሉ ስኂን ይባላል።
ስኂን ኖት ፡-(ሰኀነ ይስኅን ይስኀን። ዐረ ሰኂነ። ሱር ሽሔን) መሞቅ፤ መተኰስ፤ ሙቀት መንሣት፤ ከፀሓይ ከእሳት መቅረብ። ይነሥእ እምውስቴቱ ወይስኅን። ይበቍጹ አፍሓመ ወይስኅኑ። ከመ ንስኅን። እምጽንዐተ ቍር። መዐተ ሥላሴ ዘኮነ አረጋዌ ዕድሜ ድኅረ እማየ አይኅ ወፅአ እመ ኢክህለ ቍረቱ፤ በምድረ ገሞራ ተረክበ እንዘ ይስኅን እሳተ ፡-(ኢሳ፵፬ ፡-፲፭። ዮሐ፲፰ ፡-፲፳። ግብ፳፰ ፡-፪። ቅኔ)።
ስሒክ ኮት ፡-(ስሕከ ይስሕክ ይስሐክ። ዐረ ሐሲከ) መሻከር፤ መቅረፍረፍ፤ መቈጣት እንደ ሦክና እንደ ቅርፍት እንዳርጃኖ መኾን ፥ የገላ፤ እንዳፄ ፋሲል። ፡-(ዘፈን) ከኛ ኺደኽ አገኘኾይ ሌላ፤ አርጃኖ ገላ። ወስሕከ ሥጋየ በኀጢአ ቅብዕ። ትስሕክ እምሦክ ወአሜለላ፤ ወትጠዊ እምአቅርንቲሁ ለሀየል ፡-(መዝ ፡-፻፰። መጽ ፡-ምስ)።
፡-መድረቅ መንቃት፤ ማበጥ መዘጋት፤ መስለል መጐርነን፤ የጕረሮ የቃል፤ ከደዌ ከጩኸት የተነሣ። ስሕከኒ ጕርዔየ። ወክልሐ ጢጦስ በውእቱ ዕለት እስከ ስሕከ ጕርዔሁ ፡-(መዝ ፡-፷፰። ዮሴፍ)።
ስሒው ዎት ፡-(ስሕወ ይስሑ ይስሐው። ዕብ ሳሓህ። ሱር ስሓእ) መሳብ፤ መጐተት፤ እየተሳቡ መኼድ፤ የከይሲ የዋና የጉም የደመና። እምቅድመ ይስሐው ግዘፈ ደመናት ፡-(ቅዳ ፡-አፈ)።
፡-ሻ ማለት መበተን፤ መድከም መዛል፤ የልብ የአእምሮ። ስሕወ ልቡ።
ስሒግ ጎት ፡-(ሰሐገ ይስሕግ ይስሐግ፤ ቀነየ። ዕብ ሻአግ) መጮኽ መድረቅረቅ፤ ዋይ ብሎ ማልቀስ፤ ማሞሽ መንሰቅሰቅ፤ ከሐዘን ከጭንቅ የተነሣ። መሳግ መመሰግ፤ ማግባት መጨመር መቀጠል፤ የጣራ የጥላ የሰሌን የስፌት የመሰለው ኹሉ። መሻከር መቈርቈር፤ መኰስልኰስ ማስቀቅ፤ እንዳባ ጨጓሬ መኾን፤ የልብስ የምንጣፍ የጠባይ። መሰብሰብ፤ ማፈግ፤ ማስተኛት ማስመሰግ፤ የሰው የእንስሳ።
ስሒጥ ጦት ፡-(ሰሐጠ ይስሕጥ ይስሐጥ። ሱር ሻሔጥ። ዕብ ሻሔት። ዐረ ሰሐተ) መሻጥ፤ ሻጥ ማድረግ፤ መንካት፤ መጫር፤ መቈንጠጥ፤ መጕዳት፤ መጐነጥ፤ መግደል ማጥፋት ማበላሸት። ኢሰሐጥዎ ለዳንኤል። ወኢኀደገ ይስሐጦሙ ሰብእ። ኢትስሐጥ ብእሲተ ባዕድ። ኢትስሐጣ ለድንገል። አልቦ ዘይስሕጥ። ናሁ ይእዜ እሙንቱ ሰሐጡነ ወመጽኡ ያውፅኡነ እምርስትነ ፡-(ዳ፮ ፡-፲፰። መዝ ፡-፻፬። ሢራ፱ ፡-፫። ፫ነገ ፡-፭ ፡-፬። ፪ዜና ፡-፳ ፡-፲፮)።
፡-ማጫር፤ ጠብ መፈለግ፤ መቈስቈስ መቈራቈስ፤ የጦርነት። መኑ ይቀድም ስሒጠ ወመኑ ያስተአኅዝ ቀትለ ፡-(፫ነገ ፡-፳ ፡-፲፬)።
ስሕለት ፡-መሳል፤ ፡-(ጥሳ) መሳል፤ አሳሳል፤ ስሎሽ፤ ስልነት ሹልነት፤ ስለት፤ ሹለት።
ስሕበት ፡-መሳብ፤ መጐተት፤ አሳሳብ፤ ስቦሽ፤ ጉተታ። በእንተ ስሕበቱ ለማርቆስ ፡-(አዋል)።
ስሕተ ሰሐተ ፡-ዐረፈ፤–ሥኂት ሥኅተ።
ስሕተት ፡-(ታት) በቁሙ፤ መሳት፤ መሳሳት፤ አላዋቂነት፤ መጥፎ አካኼድና አነጋገር፤ ሕገ ወጥ ሥራ፤ ኀጢአት ክሕደት። ፍኖተ ስሕተት። ስሕተቶሙ እምአእምሮ እግዚ። ስሕተተ ልቦሙ። ስሕተት አሕዛብ። ዘእንበለ ስሕተት። ዘስሕተታት በጠላ በትእዛዝከ ፡-(ጥበ፲፪ ፡-፳፬። ፲፬ ፡-፳፬። ኩፋ ፡-፩። ፮። ስንክ ፡-ጳጕ፬። ኪዳ)።
ስሕከት ፡-መሻከር፤ አሸካከር፤ ሽክረት ሽካርነት።
ስሕጠት ፡-መቈንጠጥ፤ ፡-(ጥቈ) መቈንጠጥ፤ አቈነጣጠጥ፤ ቍንጠጣ፤ ቍንጥጫ፤ ቍንጢጥ።
ስሕጸ ፡-ደፈረ፤–ሥሕጸ።
ስሉብ ፡-(ባን ባት ልብት) የተሰለበ፤ የተገፈፈ፤ ጐማዳ ፥ ስልብ፤ ጃን ደረብ።
ስሉጥ ፡-(ጣን ጣት ልጥ) የተጨረሰ፤ ምሉእ ፍጹም። ዓመተ ስሉጠ ስሳ ወሰቡዑ ፡-(ስንክ ፡-ጥር፳)።
ስላት ፡-ዘበት፤ ለግጥ፤ ሣቅ ሥላቅ፤ ምክንያተ ትፍሥሕት። ከመ ኢትረሲከ ስላተ ጸላኢከ። ኢይከውን ስላተ ጸላኢየ ፡-(ሢራ፵፪ ፡-፲፩። ሚክ፯ ፡-፰። መዝ ፡-፳፱ ፡-፴፯)። ስላች፤ ቀጭን መንገድ፤ ሥርጥ ማቋረጫ፤ ለነገርም ይኾናል።
ስላጤ ፡-መጨረስ፤ ጭረሳ፤ ጭራሽ። ፍጻሜ፤ ፍጹምነት፤ ልመና ጸሎት፤ ትርፍ ጥቅም። ከመ ይትዐወቅ ስላጤከ። ተወክፈ ለክሙ ስላጤክሙ። ወተወከፍከ ስላጤሆሙ ከመ ተዐስዮሙ ዐስበ ጽድቆሙ። ምንትኑ ስላጤሃ ለግዝረት ፡-(፩ጢሞ ፡-፬ ፡-፲፭። ፪ቆሮ ፡-፰ ፡-፲፯። ቅዳ ፡-ዮሐ። ሮሜ፫ ፡-፩)።
ስልበት ፡-መስለብ፤ መሰለብ፤ ኦሰላለብ፤ ስልቦሽ፤ ገፈፋ ቈረጣ፤ ግዝረት። ስልበተ ነፍስተ ሥጋ ፡-(ቆላ፪ ፡-፲፩)።
ስልት ፡-በቁሙ፤ የነገር የምስጢር አካኼድ፤ ስላቹ ጐዳናው፤ ረድፉና ተራው፤ ልኩና መልኩ፤ ንባቡ ሐሳቡ፤ አጣጣፉ አነጋገሩ። ዘጸሐፈ በክልኤቱ ስልት ፡-(አዋል)።
ስልክ ፡-(ዐረብ) በቁሙ፤ ሽቦ።
ስመጥ ፡-ዠርባ፤ ሽንጥ፤ የዠርባ ወንዝ፤ ሠርጓዳው ጐድጓዳው፤ ከማዥራት እስከ መንበርት ያለው። ሐቌሁ ምስለ ስመጢሁ ፡-(ዘሌ፫ ፡-፱)።
ስሙር ፡-(ራን ራት ምርት) ያማረ የበጀ፤ ያፈራ ፍሬያም፤ ወፍራም። ፍሬ ገራህት ስሙር። ዕፀ ዘይት ስሙር። ከመ እክለ ማእረር ስሙር። ምድር ስምርት። ፂዖታት ስሙራት ፡-(ኢሳ፷፩ ፡-፲፩። ሆሴ፲፬ ፡-፮። ኢዮ፭ ፡-፳፮። ኩፋ ፡-፳፭። ፩ዜና ፡-፬ ፡-፵)።
ስሙን ፡-(ናን ናት ምንት) የሰመነ፤ ስምንት የኾነ፤ የተባለ።
ስሙዓ ዓት ፡-(ዕብ ሽሙዓ) ዜና፤ ወሬ፤ ስም ግብር። ወፅአ ስሙዓቱ ውስተ ኵሉ ሶርያ። ወሰምዑ ከለዳውያን ስሙዓቶሙ። እለ አልቦሙ ስሙዓት። ወኮነት ስሙዓተ አሐዱ እምኔሆሙ እኪተ ፡-(ማቴ፬ ፡-፳፬። ፱ ፡-፳፮። ኤር፵፬ ፡-፭። አፈ ፡-ድ፳፮። ፊልክ ፡-፻፳፭)።
ስሙዕ ፡-(ዓን ዓት ምዕት) የሰማ፤ የመሰከረ። የተሰማ፤ የታወቀ ዕውቅ፤ ስመ ጥር። በርባን ስሙዕ። ምኔት ስሙዕ። ክቡራን ወስሙዓን ፡-(ማቴ፳፯ ፡-፲፮። ፊልክ ፡-፻፳፭። አፈ ፡-ድ፳፮)።
ስሙክ ፡-(ካን ካት ምክት) የተጠጋ፤ የተደገፈ፤ ጥገኛ፤ ባለጥግ።
(ጥሙ) ስሙይ ፡-(ያን ያት ሚት) የተሰየመ፤ የተጠራ፤ ስመ ጥር ገናና፤ የታወቀ። ስሙይ በስመ ሚካኤል ሊቀ ኀይለ ሰማይ። ስሙያን ወጽዉዓን በኢየሱስ። ስሙይ በሥነ አምልኮ። እሬስዮሙ ስሙያነ በኵሉ ምድር። አበው ክቡራን ወዕደው ስሙያን ፡-(ስንክ ፡-መጋ፳። ይሁ ፡-፩። ቄር። ዘካ፫ ፡-፲፱። አፈ ፡-ድ፳፪)።
ስማኅ ፡-(ዕብ ሱማቅ) ጣፊያ የጥቍር ቀይ፤ ደባባ። ስማኅ ብሂል ጣፍያ ፡-(ጥሬ ሰዋ)።
ስማራግዶስ ፡-(ጽርእ) ዕንቍ፤ የዕንቍ ስም። መረግድንና ናርዶስን እይ።
(ጥማ) ስማዔ ፤ ስመ
ጥርነት ፤
አቦ እገሌ መባል። ይቤ አረጋይ ኢታውትር ስማዔ እምሰብእ (ፊልክ
፡ ፪፻፵፪)።
ስማዊ ፡-የስም፤ ስመኛ፤ ስም አውጭ፤ ስም ሰጭ፤ ስማም፤ ባለስም፤ ስመ ጥር። አስማታም ባለኅቡእ ስም፤ አስማት የሚደግም፤ የሚጥፍና የሚያነግት የሚያስነግት፤ ስም የሚጠይቅ፤ በስም የሚያሟርት፤ ጠንቋይ መሠሪ፤ ኮከብ ቈጣሪ።
ስማዝ ፡-ሸንበቆ፤ የጐሽ መቃ ቀለም፤ በወንዝ ዳር በባሕር ጠረፍ የሚበቅል። ስማዝ ወብርዕ ፡-(ኢዮ፵ ፡-፲፮)።
ስሜን ፡-(ዐማርኛ) ያገር ስም፤ የጐንደር ሰሜን፤ ፍጹም ደጋ፤ ጮቄ፤ እንደ ሔርሞን በረዶ የሚፈላበት፤ ተራራው ከተራራ ኹሉ የሚበልጥ። የተራራው ራስ፤ ጫፉ መጨረሻው በረዶና ውርጭ ሰፍሮበት የሚኖር ስለ ኾነ አሻግሮና አሻቅቦ ሲያዩት ጉም ያፈነው ጭጋግ የሸፈነው ይመስላል፤ ከዚህ የተነሣ ስሙ ቧሒት ይባላል፤ ጥንተ ስሙ ግን ዳሸን ነው። ባለጊዎግራፎች ቁመቱንና ከፍታውን ከባሕር ላይ ፭ ሺሕ ከ፰ ሜትር ነው ይሉታል። ፡-(ተረት) ወጥ ያጣ ጐመን፤ አገር ያጣ ስሜን።
ስም [1]፡-በቁሙ፤–ሰምይ ሰመየ።
[2]፡-(ብ አስማት። ዕብ ወሱር ሼም። ዐረ ኢስም) በቁሙ፤ ከባሕርይ ከግብር የሚወጣ፤ ቦታነትና አካልነት ህላዌና ሕይወት ያለው ማናቸውም ኹሉ በየክፍሉና በያካሉ በየራስ ቅሉ፤ በያይነቱና በየመልኩ በየነገዱ፤ በየዘሩና በያባቱ በየዘመዱ ተለይቶ የሚጠራበት፤ የሚታወቅበት። ወሰመዮሙ አዳም ለኵሎሙ በበ አስማቲሆሙ፤ ወበከመ ጸውዖሙ ከማሁ ኮነ ስሞሙ። አምኅ ቢጸነ በበ አስማቲሆሙ። መኑ ስሙ ወመኑ ስመ አቡሁ ፡-(ኩፋ ፡-፫። ምሳ፳፬ ፡-፳፯) ኹለተኛም ከዘር ከነባር ስለ ወጣ ጥሬ ይባላል፤ ጥሬ ማለት ደግሞ ዐማርኛው ጥሪ አጠራር ከማለት ይሰማማል። ጥሬነቱም ስመ ተጸውዖ፤ ስመ ተቀብዖ ተብሎ በኹለት ዐይነት ይከፈላል። ስመ ተጸውዖ ፍጥረት ኹሉ ከፈጣሪውና ከጌታው ከአዳም እንድር ተሰየመ፤ እንዲሁ ደግሞ ካባት ከናት ከጌታ ከመቤት ከካህን ከቤተ ክርስቲያን ተሰይሞ የሚጠራበት፤ ነው ፡-(ዘፍ፩ ፡-፩–፳፯። ፪ ፡-፲፱ ፡-፳)። ስመ ተቀብዖ ግን ከተጸውዖ ስም በኋላ በሹመት ጊዜ ከቀቢ ከሿሚ የሚሰጥ የማዕርግ ስም ነው፤ ጳጳስ ቄስ፤ ንጉሥ ራስ፤ ይህን የመሰለ። በሰዋስው ዐዋጅ ቅጽል ባለቤት አከል ስለ ኾነ በስም ተጠግቶ ስም ይባላል እንጂ፤ ምስጢሩና ሙያው ቅጽልነት ነው፤ የተቀብዖ ስም ለተጸውዖ ስም ቅጽል እንደ ኾነ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ። የተጸውዖ ስም ለተቀብዖ ስም ተናባቢና ዘርፍ ሲኾን የቅጽል አፈታት ያፈታል። ይህም ነቢየ ሙሴ፤ ካህነ አሮን፤ ንጉሠ ዳዊት ብሎ፤ ሙሴ የሚባል ነቢይ፤ አሮን የሚባል ካህን፤ ዳዊት የሚባል ንጉሥ እያሰኘ፤ ሌላውን ኹሉ ያሳያል። ክርስቶስ የኢየሱስ ቅጽል እንደ ኾነ አስተውል፤ ስምነቱና ባለቤትነቱ ኢየሱስ ሲቀር ነው፤ ሌላውን ኹሉ በዚህ አንጻር እየው፤ ቅጽል ባይኾን ግን ኢየሱስ ወክርስቶስ ያሰኝ ነበር። ውስጠ ብዙነት የሌለው ስመ ተጸውዖ ፡-(አብርሃም ይሥሐቅ ያዕቆብ) በሙሻ ዘር መንገድ ካልኾነ በራሱ አይበዛም ይላሉ፤ ይህም አብርሃማን ት በማለት ፈንታ አብርሃማውያን እያለ ሌላውን ኹሉ ያሳያል። ዳግመኛም መቃርስን ሲያበዛ መቃርሳት ብሎ ይገኛልና፤ ፡-(ይኸውም ብፁዕ፤ ብፁዓን ማለት ነው)። ባንዱ ስም ብዙ ሰዎች ከተጠሩበት በዚህ አንጻር አብርሃማት ማለት ይገባል፤ ስላልተለመደ ነው እንጂ የማይበዛ ስምና ጥሬ አይገኝም።
ስምን ፡-ስምንት፤ የጊዜ የልክ ቅጽል። ስምን በእመት ፡-(ኩፋ ፡-፳፱)።
ስምዐት ፡-(ታት) መስማት፤ መመስከር፤ አሰማም አመሰካከር፤ ስሞታ ምስከራ፤ ምስክርነት።
ስምዓት ፡-(ታት) ምስክሮች፤ ጥቅሶች፤ ቃሎች፤ ከየመጽሐፉ ተለቅመው ተቀሥመው ባንድ ምእላድ የሚጣፉ እንደ ቄርሎስ እንደ ፍትሐ ነገሥት ቃላት ያሉ። ንጽሕፍ ስምዓተ እመጽሐፈ ሊቃውንት። ንፈቅድ ከመ ታበይነ ለነ ስምዓታት ፡-(አዋል። ፊልክ ፡-፫)።
ስምዕ [1]፡-ስሞታ፤ ምስከራ፤ ምስክር፤ ምስክርነት። ሰማዕት፤ ሰማዕትነት። በከመ ስምዕ ዘሰማዕክሙ። ወንሕነኒ ንሰምዕ ሠናየ ስምዐ በላዕሌኪ። መኑ የአምነነ ስምዐነ። ቂርቆስ ዘኮነ ስምዐ ለክርስቶስ። ወከመ ዝ ፈጸሙ ስምዖሙ። ሕማመ ስምዕ ፡-(ዕር ፡-ኢሳ፯ ፡-፪። ጦቢ፲ ፡-፰። ኢሳ፶፫ ፡-፩። መዋሥ። ስንክ ፡-ታኅ፴። አርጋ ፡-፩)።
[2]፡-ስምዕ፤ ፡-(ዕብ ዔዱት) ሕግ ትእዛዝ፤ አምላካዊ ፍርድ አገዛዝ፤ የተጣፈ የተወሰነ፤ ጽላት ዐሠርቱ ቃላት፤ እግዜር ለሙሴ የሰጠው። ስምዑ ለእግዚ እሙን። ወእዕቀብ ስምዐ አፉከ። እስመ ስምዐከ ለበውኩ። ቤተ ስምዕ። ደብተራ ስምዕ ፡-(መዝ ፡-፲፰። ፻፲፰ ፡-፹፰ ፡-፺፭። ፩ዜና ፡-፮ ፡-፴፪። ግብ፯ ፡-፵፬)።
ስምከት ፡-መጠጋት መደገፍ፤ መዋደድ መሳካት፤ አለመውለቅ፤ አለመነቃነቅ። እስመ ስምከተ መለኮት ዘዲበ ህላዌሁ ሠናይ ፡-(ቄር ፡-እስት)።
ስሱ ፡-ስሳ፤–ስድስት ስድሳ፤–ሰደሰ።
ስሱል ፡-(ላን ላት ስልት) የራቀ የወገደ፤ ርቆ የኼደ፤ ልዩ ባዕድ።
ስሳሌ ፡-መራቅ መወገድ፤ አራራቅ፤ ርቀት ሽሽት፤ ኅልፈት ጥፋት፤ መለየት። ስሳሌሆሙ ለሰማይ ወምድር። ስሳሌሃ። በኢስሳሌ። ስሳሌ ዚኣየ እምኔክሙ ፡-(መጽ ፡-ምስ። አፈ ፡-ድ፲፰። ጥበ ፡-ጠቢ። ፪ጴጥ ፡-፩ ፡-፲፬)።
ስረት ፡-መስረር መብረር መወርወር፤ አወራወር፤ ውርወራ። ስረተ ደመናት፤ ተዳድቆተ ስረቱ ፡-(መቃ። አርጋ ፡-፩። ጥበ፭ ፡-፲፩)።
ስሩሕ ፡-(ሓን ሓት ርሕት) የጣረ የደከመ፤ ድኩም። ስሩሓን ወክቡዳነ ጾር። ስሩሓን ለገቢረ ፈቃዱ ፡-(ማቴ፲፩ ፡-፳፰። ዲድ ፡-፳፮)።
ስሩር ፡-(ራን ራት ርርት) የተሰረረ፤ የተጠቃ። የሰረረ፤ በላይ የኾነ፤ የታዘለ የተከመረ፤ ያረፈ የሰፈረ፤ የከነፈ የበረረ፤ ብር ብር የሚል ክንፋም እግረ ቀላል። መንፈሰ ክርስቶስ ዲቤሁ ስርርት። ስርርት ይእቲ ወምርዕት ፡-(ስንክ ፡-ጥቅ፭። ምሳ፯ ፡-፲፩)።
ስሩቅ ፡-(ቃን ቃት ርቅት) የተሰረቀ፤ የተደበቀ፤ የስርቆት ገንዘብ።
ስሩይ ፡-(ያን ያት ሪት) የተሰረየ፤ የተሰረየለት፤ ስርየት ያገኘ።
ስሪር ሰሪር ፡-(ዐረብ፤ ወጕራጌ) ዐልጋ፤ ቈጥ፤ ማማ ቄራ፤ የዛፍ ላይ ስፍራ።
ስራሕ ፡-(ሓት) ድካም ሸክም፤ ጣር ጋር፤ ሐሳብ ምኞት፤ መከራ ጭንቅ፤ ችጋር። ርኢ ሕማምየ ወስራሕየ። ዕለተ ስራሕ ወምንዳቤ። ስራሑ ለመንበርት። ስራሓቲሁ ለዝንቱ ዓለም። ስራሕ እኩይ። በጻማ ወበስራሕ ፡-(መዝ ፡-፳፬። ሔኖ፵፭ ፡-፪። ፩ዮሐ ፡-፪ ፡-፲፮። ድጓ። መክ፩ ፡-፲፫። ፪ቆሮ ፡-፲፰ ፡-፳፯)።
(ጥ) ስር ፡-ቆም፤ ቁመት፤ ርዝመት፤ ከፍታ፤ የቤት የመርከብ። ወሠላሳ እመት ስራ ፡-(ዘፍ፮ ፡-፲፭)።
ስርቀት ፡-መስረቅ፤ መሰረቅ፤ አሰራረቅ፤ ስርቆት፤ ሌብነት።
ስርቅ ፡-ስርቆት ሽ፤ ስርቂያ ቅጥፊያ፤ የሌባ ሥራ። ስርቅ ወሕብል። ዝሙት ወስርቅ። ነሥአ ዘስርቅ ፡-(ጥበ፲፬ ፡-፳፭። ማር፯ ፡-፳፪። ሕዝ፲፰ ፡-፲፫)።
ስርናይ ፡-ስንዴ፤–ሥዕረ።
ስርዋጽ ስሯጽ ፡-(ጻት) ማጥኛ መጠገኛ ማጥበቂያ፤ ሽብልቅ ውሻል፤ ስባሪ ሥንጣሪ ሥንጣቂ ሥንባጭ። ይበውእ ስርዋጽ ውስተ እዴሁ ወያቈስሎ ፡-(፬ነገ ፡-፲፰ ፡- ፳፩። ኢሳ፴፱ ፡-፮)።
፡-ማቅኛ፤ ማስረጃ ማስታወቂያ፤ እንደ ዚቅ እንደ ሽብልቅ በነገር መካከል የሚገባ ትርፍ ቃል። ስርዋጽ፤ እምቃለ መምህር ኅሩይ አላዲሁ ለዝንቱ መጽሐፍ ፡-(ፍ ፡-ነ ፡-፲፭)።
፡-ወለምታ፤ ውልቃት ስብራት፤ ቅጭታት፤ ጕስምት ፡-(ዐማርኛ)።
ስርየት ፡-በቁሙ፤ መስረይ፤ መሰረይ፤ ይቅርታ፤ ዕርቅ ፍቅር። ታቦት መንበር። ሰአሉ ለነ ስርየተ ኀጢአት። ቤተ ስርየት ፡-(መዋሥ። ሔኖ፲፫ ፡-፮። ኩፋ ፡-፲፭። አፈ ፡-ድ፳። ፩ዜና ፡-፳፰ ፡-፳)።
ስርጋዌ ፡-(ውያት) ማጌጥ፤ መጌጥ፤ አጊያጊያጥ። ጌጥ ሽልማት፤ ልብስ፤ መሣሪያ። አንስት ምእመናት ኢይትመክሓ በስርጋዌሆን። ስርጋዌሃ ለሰማይ። ተዐበዩ ብነ በስርጋዌሆሙ፤ ስርጋዌሰ ለአፍራስ ቦሙ ፡-(ፈ ፡-መ ፡-፴፬ ፡-፰። ሢራ፵፯ ፡-፱። ቅኔ)።
ስርግው ፡-(ዋን ዋት ጉት) ያጌጠ የተጌጠ፤ የተሸለመ ሽልም፤ ሽልምልም። ስርግው ንድቁ። ስርግዋን በወርቅ። ርሱያት ወስርግዋት። ቤተ ክርስቲያን ስርጉት ከመ መርዓት ፡-(ሉቃ፳፩ ፡-፭። ኢሳ፴ ፡-፳፪። መዋሥ። ቀሌ)።
ስርግውና ፡-ሽልምነት፤ ሰርገኝነት፤ ሙሽርነት።
ስቁል ፡-(ላን ላት ቅልት) የተሰቀለ የተንጠለጠለ፤ እንጥልጥል። ዲበ ምንት ስቁል ሕላቃቲሃ። ወይከውኑ ስቁላነ ቦቱ። ዘስቁል ዲበ ዕፅ። ነጸሩ ጦማረ ስቁለ ማእከለ ሰማይ ወምድር። ሕግ ወነቢያት ስቅልት ውስት ፍቅረ እግዚ ወፍቅረ ቢጽ። ተግባሮሙ ስቁል በእግዚአ መናፍስት። ስቁል በለጽሊጸ ሰቅል ፡-(ኢዮ፴፰ ፡-፮። ኢሳ፳፪ ፡-፳፬። ዘዳ፳፩ ፡-፳፫። መጽ ፡-ጦማ። ፊልክ ፡-፻፳፮። ሔኖ፴፰ ፡-፪)።
ስቍሩር ፡-የተጠላ የተነቀፈ፤ የረከሰ ያስጠየፈ። የተጠየፈ፤ ሸቍራራ፤ ጥይፍተኛ። አክአብ ንጉሥ ወብእሲቱ ስቍርርት፤ አስጠያፊ ፡-(ስንክ ፡-ጥር፮)።
፡-ሰቈራር ፡-የተጠላ፤ የሚያስጠይፍ፤–ቈሪር ቈረ አስቈረረ።
ስቁር ፡-(ራን ራት ቍርት) የተሸነቈረ ሽንቍር ብስ ነዳላ ሥንጥቅ። ጻሕብ ስቁር። ጽሕድ ስቍርት። እብን ስቁር ፡-(ሢራ፳፩ ፡-፲፬። ምሳ፳፫ ፡-፳፯። ስንክ ፡-መስ፩)።
ስቁይ ፡-(ያን ያት ቂት ቅይት) የጠጣ የረካ የጠገበ። ስቁይ እማይ ፡-(ኢዮ፲፩ ፡-፲፭)።
ስቍረት ፡-መሸንቈር፤ መብሳት፤ መበሳት፤ አበሳስ ብስ ነዳላ ሽንቍር፤ ሽንቍርነት። ረከብኩ ስቍረተ ውስተ አረፍት። ፈነወ እዴሁ እንተ ስቍረት። ስቍረተ መርፍእ። ስቍረተ ኰኵሕ። ሶበ አብአ መራኁተ ውስተ ስቍረቱ ለሣጹን ተርኅወ ፍጡነ። ደይ እዴከ ውስተ ስቍረተ እዴየ ፡-(ሕዝ፰ ፡-፯። ማሕ፭ ፡-፬። ማቴ፲፱ ፡-፳፬። ዘፀ፴፫ ፡-፳፪። ስንክ ፡-ሠኔ፲፪። ኪዳ)።
ስቅለት ፡-በቁሙ፤ መስቀል፤ መሰቀል፤ አሰቃቀል፤ ሰቀላ ስቅሎሽ፤ ስቁልነት። ስቅለቱ ለኢየሱስ። በእንተ ስቅለትከ ወሞትክ ፡-(ቃሌ። ግንዘ)።
ስቅየት ፡-መጠጣት ፡-(ጥጠ) መጠጣት፤ ማጠጣት፤ አጠጣጥ፤ ፡-(አርጋ ፡-፫)።
ስቡሕ ፡-(ሓን ሓት ብሕት) የተመሰገነ፤ ምስጉን፤ ክቡር፤ ክቡድ ልዑል፤ ብሩህ ጽዱል። ንሴብሖ ለእግዚ ስቡሐ ዘተሰብሐ። ቃል ስቡሕ። ወስቡሕ ራእዮሙ። ዕፀው ስቡሓን ፡-(ዘፀ፲፭ ፡-፩። ምሳ፳፭ ፡-፳፯። ሔኖ፳፬ ፡-፪። ፴፪ ፡-፫)።
ስቡር ፡-(ራን ራት ብርት) የተሰበረ፤ ሰባራ፤ ሠንጣቃ ንቅ፤ ንክ። ማዕጾ ስቡር። ዘስቡር እግሩ። ምስል ስቡር ፡-(ኩፋ ፡-፴፱። ዘሌ፳፩ ፡-፲፬። መሳ፮ ፡-፳፰)። ሐንካስ በማለት ፈንታ ስቡር ይላል፤ የመላሽ ስሕተት ነው። ፡-(፪ነገ ፡-፭ ፡-፮ ፡-፰። ኢዮ፳፱ ፡-፲፭። ሉቃ፯ ፡-፳፪። ፲፬ ፡-፳፩)።
ስቡዕ ፡-(ዓን ዓት ብዕት) የተሰበተ፤ ሰባት የኾነ፤ የተባለ፤ ሰባትነት ያለው።
ስቡእ ፡-(ኣን ኣት ብእት) ሰው የኾነ፤ ልቡሰ ሥጋ። ሰይጣን ሥግው ወጋኔን ስቡእ ፡-(መጽ ፡-ምስ)።
ስቡክ ፡-(ካን ካት ብክት) የቀለጠ የፈሰሰ ፍስ፤ ቅጥቅጥ። ወገብረ ባሕረ እንተ ብብርት ስብክት ፡-(፪ዜና ፡-፬ ፡-፪ና ፡-፬)።
ስባሔ ፡-(ሕያት) ማመስገን፤ መመስገን፤ አመሰጋገን። ውዳሴ ምስጋና፤ ክብር፤ ብርሃን። አብዝኁ ስባሔሁ። ርኢ ስባሔሆሙ። ወሀበት ለእግዚ አኰቴተ ወስባሔ። ዝማርያት ወስባሕያት ፡-(ዮሴፍ። ፊልክ ፡-፻፺፭። ኩፋ ፡-፳፭። ፈ ፡-መ ፡-፴፪ ፡-፯)።
ስባር ፡-(ራት) ስባሪ፤ ፍላጭ፤ ገል እንክትካች። ቍራሽ ብጣሽ፤ ፍንካች። ስባረ ማሕረጽ ስባራተ ማህው በሊኃት። ስባረ እኄላ ተመርት ፡-(መሳ፱ ፡-፶፫። ሢራ፵፫ ፡-፲፱)።
ስባክ ፡-(ዕብ ስባኻ። ዐረ ሽበከት) ዐይነ ርግብ፤ የመረብ የመግለቦ ዐይነት ፡-(፬ነገ ፡-፳፭ ፡-፲፯)። ሳቤቅን ተመልከት፤ የሰበከ ዘር ነው።
ስባዔ ፤ (ዕያት) ፤ መሰበት ፤ ሰባት ማድረግ ፤ ወይም ሰባት መኾን ፤ መባል
፤ ሰባትነት።
ስብሐት ፡-(ታት) ዝኒ ከማሁ፤ ውዳሴ ምስጋና፤ ክብር ጌትነት፤ አምላካዊ ብርሃን፤ ጸዳል ምዕዛር። ኢያረሙ እምስብሐቲነ፤ ስብሐተ ነግህ። ሎቱ ስብሐት። ወርኢነ ስብሐቲሁ ከመ ስብሐተ ወልድ ዋሕድ። ወሀብክዎሙ ስብሐተ ዘወሀበከኒ። አክሊለ ስብሐት። ወስብሐተ እግዚ በረቀ ላዕሌሆሙ። ወምድር በርሀት እምስብሐቲሁ ፡-(ቀሌ። ሮሜ፲፩ ፡-፴፮። ዮሐ፩ ፡-፲፬። ፲፯ ፡-፳፪። ሉቃ፪ ፡-፱። ሕዝ፵፫ ፡-፪። ራእ፲፰ ፡-፩)።
ስብረት ፡-መስበር፤ መሰበር፤ አሰባበር፤ ሰበራ፤ ስብራት፤ ሰባርነት፤ ጕዳት፤ ትሕትና ሐዘን። ሰበራ ፡-(ለበትር) ክልኤተ ስብረተ ወኮነት ሠለስተ በትረ። ስብረት ህየንተ ስብረት። ሀጕል ወኪደት ወስብረት እምኀበ እግዚ። ስብረተ ልብ ፡-(ክብ ፡-ነገ። ዘሌ፳፬ ፡-፳። ኢሳ፳፪ ፡-፭። አፈ ፡-ተ፳፴፩)።
ስብዕ ፡-የጊዜና የልክ ቅጽል፤ ሰባት። ስብዕ በእመት። ከማሁ ገብረ እስከ ስብዕ። ስብዐ ለዕለትየ ፡-(ኩፋ ፡-፳፱። ፬ነገ ፡-፬ ፡-፴፭። መዝ ፡-፻፲፰)።
ስብዕ ስብዐት ፡-(ታት። ዕብ ሽቡዓ፤ መሐላ) ዐዚም፤ ሥራይ፤ አስማት፤ የጠንቋይ ጸሎት፤ ፯ ፡-፯ ጊዜ የሚጣፍ፤ የሚደገም፤ ጨጨ ዠዠ፤ ራፎን ራፎን፤ ይህን የመሰለ። ዘይገብር ስብዐ ወመቅሰመ። አርማሮስ ፈትሐ ስብዐታተ ፡-(ቀሌ ፡-ገ፻፵፬። ሔኖ፯ ፡-፩)።
ስብከተ ጌና ፡-በዓለ ስብከት፤ የስብከት እሑድ፤ ከታኅሣሥ ፯ እስካ፲፫ የሚውል፤ ወደ ፮ና ወዳ፲፬ የማይወርድ የማይወጣ። ዋዜማ ዘስብከት ፡-(ድጓ)።
ስብከት ፡-(ታት) በቁሙ፤ መስበክ፤ መሰበክ፤ አሰባበክ፤ ሰበካ፤ ትምርት፤ ዐዋጅ፤ ወሬ ታሪክ። በነዋኅ ስብከት። ስብክ ሎሙ በከመ ቀዳሚ ስብከት። ንስማዕ ስብከተ ትንሣኤሁ። ስብከት ዘኢየሱስ ፡-(ምሳ፱ ፡-፫። ዮና፫ ፡-፪። ዲድ ፡-፲፪። ቄር)።
ስብኮ ፡-(ብ ስብክዋት) ጣዖት፤ ምስል፤ አቅልጠው አፍስሰው ቀጥቅጠው ገብስሰው የሚሠሩት። ስብኮ ወርቅ ግቡር በአምሳለ ዕፅ። አማልክት ዘስብኮ። እሤርዎ ለግልፎከ ወለስብኮከ። ከመ ኢትበል ስብኮየ አዘዘኒ ፡-(ዮሴፍ። ዘሌ፲፱ ፡-፬። ናሖ፩ ፡-፲፬። ኢሳ፵፰ ፡-፭)።
ስቱት ፡-(ታን ታት ትት) ሰተት ያለ፤ የቀና የተንሳተተ፤ ዝርግ ወዳቃ፤ የተናቀ የተጠቃ። በስቱት ፈንታ መስትት ይላል፤ አያሰኝም። ከመ ኢይኩን እግዚእየ መስትተ ወዘኢይበቍዕ ፡-(ዮዲ፲፩ ፡-፲፩)።
ስቱይ ፡-(ያን ያት ቲት፤ ትይት) የተጠጣ። የጠጣ፤ የረካ፤ መጠጥ የጠገበ። ኢትገሥጽ ቢጸከ እንዘ ስቱይ ወይነ ፡-(ሢራ፴፬ ፡-፴፩)።
ስቴ ስታይ ፡-(ያት) መጠጥ፤ ፈሳሽነት ያለው፤ የሚያረካ የሚያሰክር። ስቴ ወአብዝኆቱ ሙስና ልቦሙ ለጠቢባን። ንዋየ ስቴ። ዘወሀበ ስቴ ሕምዝ። ስታይ ወአንስት ያስሕታሁ ለጠቢብ። ዝሙት ወስታይ ወስካር። ዘይሠርባ ለኀጢአት ከመ ስታይ ፡-(ሲኖዶ። ዘሌ፲፩ ፡-፴፬። ፍ ፡-ነ ፡-፵፬። ሢራ፲፱ ፡-፪። ሆሴ፬ ፡-፲፩። ኢዮ፲፭ ፡-፲፮)።
ስትየት ፡-መጠጣት፤ አጠጣጥ፤ መጠጥ። ድዉይ ዘይኤዝዞ ጠቢብ ከመ ይትከላእ እምነዊም ወስትየት ወሲሲት ፡-(ፊልክ ፡-፳)።
ስትፍና ፡-ሱታፌነት፤
ተባባሪነት፤ ሽሪክነት። አልቦ ዘረብሐ እምስትፍና መለኮት ፡-(ቄር ፡-ጰላ)።
ስኑሕ ፡-(ሓን ሓት ንሕት) የለዘበ የሟለጠ፤ ሙልጭ ቍልጭ ያለ፤ በራ መላጣ።
ስኑን ፡-(ናን ናት ንንት። ዕብ ሻኑን) የሾለ የተሳለ፤ ጥርስ ያወጣ፤ ስል ሹል ጥርሳም፤ የተነከሰ።
ስኑጽ ፡-(ጻን ጻት ንጽት) የተሰነጠ ስንጥ፤ ውብ ልዝብ፤ ስምም። በስኑጽ ፈንታ ስንጸት ይላል፤ አያሰኝም፤ ዶለ ወርቅ ውስተ ድደ ብሩር ስንጸት ፡-(ምሳ፳፭ ፡-፲፩)።
(ላ) ስናም ፡-(ዐረ ሰናም) ሻኛ፤ ጕብል፤ በዠርባ በትከሻ ላይ የሚወጣ፤ የድንክ የጐባጣ የተርካሳ። ዘስናም ፡-(ዘሰናም) ሻኛማ ባለሻኛ ጐባጣ፤ ድንክ። ባለብሉዮች ግን የሰነነ ዘር መስሏቸው፤ ጥርሳም ገጣጣ መልከ ክፉ ይሉታል ፡-(ዘሌ፳፩ ፡-፳። ፫ነገ ፡-፳ ፡-፲፩)። በስናም ፈንታ ስንዓም ይላል፤ የጣፊ ስሕተት ነው ፡-(ቀሌ)።
ስናፔ ፡-(ጽር ሲናፒ) ስናፍጭ፤ ቅንጣቱ ታናናሽ፤ አገዳው ታላላቅ፤ ቅጠሉና ፍሬው የሚሰነፍጥ የሚያስለቅስ፤ መራራ ሖምጣጣ፤ መድኀኒት የሚኾን ፡-(ማቴ፲፫ ፡-፴፩። ፲፯ ፡-፳። ማር፬ ፡-፴፩)። ወናሁ ፈነውኩ ለከ አነሂ ስናፔ ጠዐማ፤ ወተመጠዋ ዳራ ለስናፔ ወበልዓ፤ ወአንብዓ አዕይንቲሁ፤ ወአውፅኣ እምአፉሁ ወገደፋ። ወአእመረ በዝንቱ ከመ ሰራዊቱ መሪራን ፡-(ዜና ፡-እስ)።
(ጥን) ስን [1]፡-(ብ ስነን፤ አስናን። ዕብ ወሱር ሼን። ዐረ ሲን) ጥርስ፤ ክራንቻ መንጋጋ። ስን ቤዛ ስን። ሐቀዩ ስነኒሆሙ። ስነነ አራዊተ ምድር።
[2] ፡- (ጥን)
ስን ፤–ጥርስ ፤–ሰኒን ሰነነ።
ስንሐት ፡-መለዘብ፤ በራ ቡሓ መኾን፤ በራነት። ርእሱ ዘስንሐት ፡-(ዘሌ፲፫ ፡-፵፩–፵፬)።
ስንሱል ፡-(ላን ላት ስልት) የተሳሰረ፤ የተቈራኘ፤ ቍርኙ። እሉ ክልኤቱ ግብራት ስንሱላን ወእኁዛን በበይናቲሆሙ ፡-(አፈ ፡-ተ፳፮)።
ስንሳሌ ፡-አስተሳሰር፤ እስራት፤ ቍራኝነት።
ስንቃዌ ፡-አመታት፤ አደራደር፤ ምት ድርደራ ክርከራ።
ስንኣ ፡-(ብ ስንኣን) ስምም ግጥም፤ ቅን ደኅና እውነተኛ፤ ብእሴ ሰላም። እሉ ዕደው ስናኣን እሙንቱ ምስሌነ። እመሰ ስንኣን አንትሙ። ጸብኡከ ስንኣኒከ ፡-(ዘፍ፴፬ ፡-፳፩። ፵፪ ፡-፲፬ ፡-፴፩ ፡-፴፫ ፡-፴፬። ዐብድ ፡-፯)። አንዳንድ መጽሐፍ በስንኣን ፈንታ ስንእ ስንኣ እያለ የብዙውን ባንድ ይጥፋል። ወኵሎሙ እለ ዐውዱ ስንእ ምስሌሁ። ጸውዐ ኀቤሁ ባዕዳነ ብዙኃነ ስንኣሁ ፡-(፫ነገ ፡-፬ ፡-፳፬። ሱቱ ፡-ዕዝ፲፫ ፡-፲፯ ፡-፵፪)።
ስንኣሌ ፡-መሰናበት፤ መሰነባበት፤ ስንብቻ፤ የስንብቻ ቃል፤ ቡራኬ ምርቃት።
ስንኣዌ ፡-(ስንእ) ሱላሜ ሰላም፤ መሰማማት፤ መጋጠም፤ መገጣጠም፤ ግጥምነት፤ ስምምነት። ተሰናአዉ ስንኣዌ። ለሕይወት ኅቡረ በስናኣዌ ፡-(ስንክ ፡-ጥቅ፲፬። ፍ ፡-ነ ፡-፳፬ ፡-፬)።
ስንእ ፡-ሰላም፤ ዕርቅ ፍቅር አንድነት፤ ስምምነት፤ ወዳጅ ባልንጀራ። ስንኝ፤ ቤት የቅኔ። በብሔረ ስንእ እንተ ትትአመን። ምስሌየ ግበሩ ስንአ። ኢይኩን ለከ ስንእ ምስሌሁ። ሰላም ለእለ ሞቱ ምስሌሁ በስንእ። ሰላም ለመርክያኖስ ወለመርቆሬዎስ ስንኡ ፡-(ኤር፲፪ ፡-፭። ፬ነገ ፡-፲፪ ፡-፴፩። ቀሌ። ስንክ ፡-ሚያ፪። ጥቅ፳፰)።
ስንእው ፡-(ስኑእ) የተስማማ፤ ስምም፤ ግጥም። ጊዜ ኮነት ሀገርክሙ ሕንጽተ ወሰራዊትክሙ ስንእዋን ወንብረትክሙ ርቱዕ። ስንእወ ምግባር ምስለ ስንእዋኒሁ ፡-(ዮሴፍ። ስንክ ፡-ነሐ፳፫)።
ስንክሳር ፡-(ዐረ ሲንክሳር። ጽር ሲናክሳሪያ) የመጽሐፍ ስም፤ ካመት እስካመት የሚነበብ የቅዱሳን ዜና፤ ከየገድላቸው ባጭር ባጭር ቃል የተሰበሰበ፤ እሉድ ምእላድ እስትጉቡእ ማለት ነው። ስንክሳር ዘበትርጓሜሁ ጉባኤ። ስንክሳር ወደሳ ወንእዳ ፡-(ስንክ ፡-መስ፩። ፳፫)።
ስንዳሌ ፡-(ጽርእ ሴሚዳሊስ) የስንዴ ዶቄት፤ ታጥቦ ተፈትጎ የተፈጨ፤ ከዚያውም ንጹሑና ጥሩው መዠመሪያው ዐይነት፤ መሥዋዕት የሚኾነው። የዶቄትን ክፍልና ማዕርግ ሠወስትነቱን የማያውቁ አንዳንድ ሰዎች ግን ስንዴ ይሉታል፤ ፡-(ዘፍ፲፰ ፡-፮። ዘፀ፳፱ ፡-፪። ዘሌ፪ ፡-፩)። ኀብስተ ስንዳሌ ፡-(ዮዲ፲ ፡-፭)።
ስንጸት ፡-ስንኣዌ፤ ስምምነት፤ አሰናነጥ፤ ስነጣ ልዘባ።
ስንጽ ሰንጽ ፡-ንቅስ ንጥ፤ መልክ ቅርጥ፤ ጌጥ ፈርጥ፤ የመሣሪያ። ሽንጥ ሻንጣ።
ስኡል ፡-(ላን ላት እልት) የተለመነ፤ የተጠየቀ፤ ልምን ጥይቅ።
ስዑር ፡-(ራን ራት ዕርት) የተሻረ ያለፈ የቀረ፤ ሽር ሹር። ስዑር እምክህነት። ስዑር ወውጉዝ ፡-(አብጥሊ)። የሹም ሽር። ዳም ስዑር፤ ቅዳሜ ሹር ፡-(ዐማርኛ)።
ስኡን ፡-(ናን ናት እንት) የተሳነው፤ ችሎት ያጣ፤ የማይችል፤ ደካማ ሕጹጽ። ኃጥእ ወስኡን ወእብድ። መሐደምት ስኡን። ብርከ ስሉናን። ድካምሙ ለስኡናን ፡-(ፊልክ ፡-፩። ቄር። ኢዮ፬ ፡-፬። ሮሜ፲፭ ፡-፩)።
፡-የሚሳን የሚያቅት፤ ተስኖ የሚቀር፤ የማይቻል ሥራ። አልቦ ስኡን በኀቤሁ ለዘኵሎ ይክል ፡-(ቄር)።
ስኢል ሎት ፡-(ሰአለ ይስእል ይስአል። ዕብ ሻአል። ሱር ሼእል። ዐረ ሰአለ) መለመን፤ መፈለግ፤ መሻት፤ እባክኽ ስጠኝ አድርግልኝ ማለት፤ መማለድ። መጠየቅ፤ መመርመር፤ ለማወቅ ለማግኘት። ሕይወቱ ለነዳይ ስኢለ ምጽዋት። ሰአሉ ወይትወሀበክሙ፤ እስመ ኵሉ ዘበአለ ይነሥእ፤ ሰአሊ ለነ፤ ልመነ ፡-(ሢራ፴፩ ፡-፳፭። ማቴ፯ ፡-፯)። ይስእልዎሙ ለአማልክት። ሖረት ትስአል ኀበ እግዚአብሔር። በእንተ መኑ ትስእል ወትጤይቅ ፡-(ኢሳ፲፱ ፡-፫። ዘፍ፳፭ ፡-፳፪። ሔኖ፳፩ ፡-፭)። ብዙው መጽሐፍ ግን በሰአለ ፈንታ ተሰእለ፤ ተሰአለ፤ ተስእሎት ይላል፤ ባለቅኔዎችም እንዲሁ ይላሉ፤ የስሕተት ልማድ ነው። የግስ ርባ አካኼድ የአዕማድ መንገድ ከአእመረ ዠምሮ እንደሚገባው አልታወቀም፤ አልተጠነቀቀም። ወእመሂ ተስእልክዎሙ ኢይሰጠዉኒ። ተሰአሎ ለአቡከ ወይነግረከ። ተስእሎት ዘተስእልዎ ካልኣን። ተሰአሎ እግዚ ለኢዮብ ፡-(ኢሳ፵፩ ፡-፳፰። ዘዳ፴፪ ፡-፯። ስንክ ፡-የካ፲። ድጓ)። ሰንአለን ተመልከት፤ የዚህ ስሯጽ ነው።
ስዒም ሞት ፡-(ሰዐመ ይስዕም ይስዐም። ዕብ ናሻቅ) መሳም፤ መሳለም፤ መጨምጨም፤ በአፍ በከንፈር መንካት መልከፍ። ዘእስዕሞ ውእቱ፤ በስዒምኑ ታገብኦ። አኀዘቶ ወሰዐመቶ። እስከ ይትሌቃሕ ይስዕመከ ርእሰከ። አዘዘ ከመ ይስዐም እግረ አቡሁ። አእጋረ ክርስቶስ ሎቱ እንዘ ትስዕሚ ፡-(ሉቃ፳፪ ፡-፵፯ና ፡-፰። ምሳ፯ ፡-፲፫። ሢራ፳፮ ፡-፭። ዮሴፍ። ስንክ ፡-ታኅ፯)።
ስዒር ሮት ፡-(ሰዐረ ይስዕር ይስዐር። ዕብ ሻዐር፤ ከፈተ ዘጋ) መሻር፤ ማዋረድ፤ ማፍረስ መናድ፤ ማሳለፍ መለወጥ፤ ማሸነፍ፤ ድል ማድረግ፤ ማጥፋት መደምሰስ፤ መፍታት ማሰናበት። ስዒረ ጾም። ሰዐረኒ እምግብየ። ያነብር ነገሥታተ ወይስዕር። ኢመጻእኩ እስዐሮሙ ለኦሪት ወለነቢያት። ስዒሮ ሞተ በሥጋ። ሰዐሮ ለጣዖት። ንስዐር ዝክሮ እምድር። ወትስዕር ዝክሮሙ ኅቡረ። ሰዐሮ ለገብርከ። ሰዐር ሰብአ ፡-(ቀሌ። ሉቃ፲፮ ፡-፬። ዳን፪ ፡-፳፩። ማቴ፭ ፡-፲፯። ድጓ። ቅዳ። ምሳ፩ ፡-፲፪። መዝ ፡-፱። ሉቃ፪ ፡-፳፱። ማር፮ ፡-፴፮)። በሰዐረ ፈንታ አስዐረ ይላል፤ የመላሽ ስሕተት ነው ፡-(ዘዳ፪ ፡-፳፪። ፳፱ ፡-፳፯። ኢያ፳፬ ፡-፲፪)።
ስዓ ፡-ሩጫ ጥድፊያ ችኰላ፤ ያካኼድ።
ስእለት ፡-(ታት) መለመን፤ አለማመን፤ ልመና፤ ፍላጎት፤ ምልጃ፤ ጸሎት፤ ጥየቃ። ኀፈርኩ ስእለቶ ለንጉሥ ኀይለ ወአፍራሰ። ስእለት ብየ እንተ እስእል እምኀቤከ። ምንት ውእቱ ስእለትኪ። ወኮነ እምድኅረ ዝንቱ ስእለት። አባእኩ ተዝካረ ስእለትክሙ። ወተስእሉኒ ከመ እጽሐፍ ተዝካረ ስእለት ፡-(ዕዝ፰ ፡-፳፪። ኩፋ ፡-፴፭። እስቴ፯ ፡-፪። ፩ዜና ፡-፲፰ ፡-፩። ጦቢ፲፪ ፡-፲፪። ሔኖ፲፫ ፡-፪። ፲፬ ፡-፯)።
ስዕመት ፡-መሳም፤ ፡-(ጥሳ) መሳም፤ መሳሳም፤ አሳሳም፤ ስሞሽ። ስዕመተ አፉሁ። ስዕመተ ጸላኢ። ወሀቦሙ ስዕመተ ትእምርት ፡-(ማሕ፩ ፡-፪። ምሳ፳፬፤ ፮። ዲድ ፡-፳፱)።
ሳዕስዐ ፡-(ዕብ ሻዕሴዐ) ደስ አሰኘ፤ ተደሰተ፤ ደስ አለው።
ስዕረት ፡-መሻር፤ ፡-(ጥሻ) መሻር፤ አሻሻር፤ ሽረት። ስዕረተ ጾም። ስዕረተ ሞት። ሠመርነ በስዕረቱ ለናስጣርዮስ። ስዕረተ ኪዳን፤ ስዕረት ካህን ፡-(ቀሌ። ተረ ፡-ቄር። ዮሴፍ)።
ስዕነ ፡-ተሳነ፤–ስእነ።
ስእነት ፡-መድከም፤ ችሎት ማጣት፤ ደካምነት፤ ኢከሃሊነት። ኢኮነት ምክንያተ ስእነት ላዕሌሁ ለነገር ፡-(ቄር ፡-ገ፳፭)። ዕቅጸቶሙ ድቀቶሙ በማለት ፈንታ ስእነቶሙ ይላል፤ የመላሽና የጣፊ ስሕተት ነው ፡-(ኤር፲፰ ፡-፳፫)።
ስኩም ፡-(ማን ማት ክምት) የተሸከመ፤ ተሸካሚ። ሸክም የኾነ፤ የተጫነ፤ በትክሻ ላይ የሚኼድ፤ ሬሳ ቀንበር የመሰለው ኹሉ።
ስኩር ፡-(ራን ራት ክርት) የሰክረ፤ ልቡ የጠፋ፤ አብዝቶ የጠጣ የጠገበ። እንዘ ስኩር ውእቱ። ጽጉባን ወስኩራን። ወአምሰላ ዔሊ ከመ ስክርት። ወስክርት ይእቲ እምደሞሙ ለቅዱሳን ፡-(ሢራ፴፬ ፡-፴፩። ፩ቆሮ ፡-፲፩ ፡-፳፩። ፩ነገ ፡-፩ ፡-፲፫። ራእ፲፯ ፡-፮)።
ስኩብ ፡-(ባን ባት ክብት) የተኛ የተጋደመ፤ ዝርግ፤ የሞተ፤ እንቅልፍ የወሰደው። ሕፃን ስኩብ ውስተ ጎል። ኮነ ዘስኩብ ውስተ መቃብር። ርእዩ ኀበ ዝንቱ እኁ ዘስኩብ ማእከሌክሙ በሃም ወጽሙም። ስኩብ ኮንኩ በቤተ መላልኤል እምሔውየ ፡-(ሉቃ፪ ፡-፲፪። ፍ ፡-ነ ፡-፲፭። ግንዘ። ሔኖ፹፫ ፡-፫)።
ስኩዕ ፡-(ዓን ዓት ክዕት) የተሰካ፤ ስክ፤ ድርድር። ዕንቍ ግሉፍ ወስኩዕ ፡-(፫ነገ ፡-፲ ፡-፳፪)።
ስኵየት ፡-መሳሳት፤ ከመንገድ መውጣት። እስመ ተዘከሩ በስኵየተ ምግባሮሙ ፡-(ጥበ፲፱ ፡-፲)። መጽሐፍ ግን በጸሓፊ ስሕተት፤ ስክየት ይላል። ባለብሉዮችም ማካሰስ ማማጠን ብለው በሰከየ አፈታት ይፈቱታል።
ስኩይ ፡-(ያን ያት ኪት ክይት) የተከሰሰ፤ የተማጠነ፤ የሙጥኝ ያለ።
ስካር ፡-በቁሙ፤ የመጠጥ ጥጋብ፤ ናላ የሚያዞር ልብ የሚያጠፋ፤ ሰውነትን የሚያዝል የሚያደክም፤ የሚያስተኛ። እለ ይሰትይዎ ለወይን ለስካር። ነቂሆ ኖኅ እምንዋመ ስካሩ። ብእሲ ሀካይ ዘአኅለቀ ኵሎ ንዋዮ በስካር ወበዝሙት። እመልኦሙ ስካረ ፡-(ዮኤ፩ ፡-፭። ቀሌ። ዲድ ፡-፫። ፍነ ፡-፶። ኤር፲፫ ፡-፲፫)።
ስክመት ፡-መሸከም፤ ማሸከም፤ አሸካከም፤ ሸከማ፤ ተሸካሚነት።
ስክረት ፡-መስከር፤ መጠጥ ማብዛት፤ ስካር፤ ሰካርነት። ስክረት ይከውን ምክንያተ ለመዐት ፡-(ፊልክ ፡-፸፱። ፩ጴጥ ፡-፬ ፡-፫። ገላ፭ ፡-፳፩)።
ስክር ፡-(ዕብ ሼካር) ዐረቂ፤ ጠጅ፤ የሚያሰክር መጠጥ። ጕራጌ ጠላ ሲል ሰኸር እንዲል።
ስክበት ፡-መኛት፤ መተኛት፤ መጋደም፤ መኝታ፤ አተኛኘት፤ አዘረጋግ ፡-(አርጋ ፡-፪)።
ስክተት ፡-(ታት) ምዕማድ፤ የዐምድ እግር፤ ጕልቻ ፡-(ዘፀ፳፮ ፡-፲፱–፳፩)። በዕብራይስጥ ግን ፡-(ዘፀ፴፯ ፡-፳፬–፳፯)።
ስክቱት ፡-የተጐለተ፤ የተጣደ፤ ጕልት።
ስክየት ፡-መክሰስ፤ መክሰስ፤ አከሳሰስ፤ ክስሻ ክስ፤ ምጥንታ፤ ጩኸት። ለእመ ሰከየ ስክየተ ዘጥዩቅ። ስክየት ዲበ ጸላኢ። በቃለ ስክየት ፡-(ፍ ፡-ነ ፡-፵፫ ፡-፮። ቅዳ ፡-ያዕ። ኪዳ)።
ስዋሬ ፡-መሰወር ፡-(ጥሰ) መሰወር፤ አሰዋወር፤ ስውርነት፤ ስወራ ድበቃ። በስዋሬከ። መካነ ስዋሬ ፡-(ቅዳ ፡-ዮሐ። ገድ ፡-ተክ)።
ስዋቅ ፡-(ቃት፤ አስዋቅ) ድጋፍ ፣ ደገፋ፤ ምርጕዝ ባላ ወጋግራ፤ ዐምድ ምሰሶ። ኤፍሬም ስዋቀ ርእስየ። ሣረራ ለምድር ዲበ ማይ ወአጽንዓ ዘእንበለ ስዋቅ። ስዋቀ አጽራሒሃ። አስዋቅ ፡-(መዝ ፡-፻፯። መቃ ፡-ገ፳፭። መጽ ፡-ምስ። ገድ ፡-ኪሮ)።
ስዉር ፡-(ራን ራት ውርት) በቁሙ፤ ሽሽግ ድብቅ፤ ጥልቅ ረቂቅ፤ የማይታወቅ። አኮ በስዉር። ስዉር ነገር። ስዉር እምኔሆሙ ፡-(ዘኍ፲፪ ፡-፰። ምሳ፩ ፡-፮። ሉቃ፲፰ ፡-፴፬)።
ስዉቅ ፡-(ቃን ቃት ውቅ) የተደገፈ፤ የተደጋገፈ፤ ድግፍ ድግፍግፍ፤ ንብብር።
ስዉጥ ፡-(ጣን ጣት ውጥ) የተጨመረ፤ የተጨማመረ፤ የተቀላቀለ፤ የተጨመረበት። መዓር ስዉጥ። ከርሥኪ ስዉጠ ሥርናይ ፡-(አዋል። ማሕ፯ ፡-፫)።
ስዝር ፡-(ዕብ ዜሬት። ሱር ዛርታ። ዐረ ሽብር) ስንዝር፤ ማኽል እጅ፤ የጋት ቁመት፤ ካውራ ጣት ጫፍ እስከ ታናሽቱ ወይም እስከ ታላቁ ጫፍ። መኑ ሰፈሮ ለማይ በሕፍኑ ወለሰማይኒ በስዝሩ። ኑኁ ስድስ በእመት ወስዝር። ወለሕፃንኪ አሮን ቁመተ ግዙፍ አካል፤ ስዝረ የዐብዮ ሙሴ ዕፀ መስቀል ፡-(ኢሳ፵ ፡-፲፪። ፩ነገ ፡-፲፯ ፡-፬። ቅኔ)። ክንድ፤ ልክ መጠን ጋት በማለት ፈንታ ስዝር ይላል፤ የመላሽ ስሕተት ነው ፡-(መሳ፲፫ ፡-፲፮። ፫ነገ ፡-፯ ፡-፲፩። ሕዝ፵ ፡-፭)።
ስያሕ ፡-(ሓት) አጐዶ፤ ከውር፤ የእሳት ጕድጓድ። ጽዋዕ፤ ጽንሓሕ፤ ለቃቃ አፈ ሰፊ። ቶስሐት ውስተ ስያሓ ዘዚኣሃ ወይነ። ይሰወጥ በስያሖሙ ቃለ ሰላምየ ዝንቱ፤ በአምሳለ ወይን ዘምሉእ ቅድሐቱ፤ ጽዋዕ ፡-(ምሳ፬ ፡-፪። ስንክ ፡-ሐም፲፪)። ስያሐ ወርቅ። ስያሐ ዕጣን። መዐዛ ዕጣን ይትቄረብ በስያሐ ወርቅ ፡-(ገድ ፡-ተክ። አርጋ ፡-፫። መጽ ፡-ምስ)።
ስያሳ ፡-(ዐረብ) ፑሊቲክ፤ የነገር አካኼድ።
ስይጣኔ ፡-ሰይጣንነት፤ ሰብቅ ክስ፤ የሰይጣን ሥራ፤ ክፉ ሥልጣኔ።
ስደት ፡-(ታት) ፡-በቁሙ፤ መሰደድ መሰደድ፤ መለየት፤ ቦታን መልቀቅ፤ ከሀገር ከዘመድ መራቅ፤ መፍለስ መነቀል። ስደተ ኅሊናተ ሕማማት። ይንበሩ ኵሎ መዋዕለ ሕይወቶትሙ በስደት። ምንዳቤ ወስደት ፡-(ፊልክ ፡-፻፯። ፈ ፡-መ ፡-፮ ፡-፲፫። ማቴ፲፫ ፡-፳፩)።
ስዱስ ፡-(ሳን ሳት ድስት) የተሰደሰ፤ ስድስት የኾነ፤ የተባለ፤ ከስድስት የተከፈለ።
ስዱቅ ፡-(ቃን ቃት ድቅት) የተዘረጋ ዝርግ፤ ጭፍልቅ፤ ሥንጥቅ፤ የተቀባ ቅቡዕ። ስዱቅ በአክዋል ፡-(ድጓ)።
ስዱድ ፡-(ዳን ዳት ድድ) የተለየ፤ የተሰደደ፤ ስደተኛ። ስዱድ እምቤተ ክርስቲያን። ተስፋሆሙ ለስዱዳን ፡-(ሲኖዶ። ፍ ፡-ነ ፡-፲፫። ኪዳ)።
ስዳሴ ፡-መሰደስ፤ ስደሳ፤ ስድስት ማድረግ፤ ስድስት መኾን መባል፤ ስድስትነት።
ስዴማ ፡-(ዕብ ሽዴማ፤ ሽዴፋ) የሰለተ የደረቀ የቧዘዘ፤ ብርድ ቀጭ ዋግ የመታው ሰብል፤ ገራህቶ እክል ዐጸደ ተክል ሣዕረ አንሕስት ወስዴማ ፡-(፬ነገ ፡-፲፱ ፡-፳፮)።
ስድሱ ስሱ ፡-(ዕብ ሼሽ። ሱር ሽታ። ዐረ ሲት) የቍጥር ስም፤ የሴቶች ድምር፤ ስድስት፤ ባምስትና በሰባት መካከል ያለ ቍጥር፤ ገቢርም ይከታል ፥ እንደ ሰብዑ ነው። አጻብዐ እደዊሁ ወእገሪሁ በበ ስሱ። ናሁ ስሱ ዘይጸልእ እግዚ። ወእምድኅረ ስሱ መዋዕል። ሰዓት ወርኢኩ ስሱ ኅዋኅወ በምሥራቅ ወስሱ ኅዋኅወ በምዕራብ ፡-(፪ነገ ፡-፳፩ ፡-፳። ምሳ፮ ፡-፲፯። ማቴ፲፯ ፡-፩። ፳ ፡-፭። ሔኖ ፡-፶፪)። አንዳንድ ጊዜም ስለ ጣፊ ስሕተት፤ በወንዶች አንቀጽ እየገባ ተጥፎ ይገኛል።
ስድሳ ስሳ ፡-የቍጥር ስም፤ ባምሳና በሰባ መካከል ያለ፤ ሠ–፷፤ ዐሥር ጊዜ ስድስት፤ ወይም ስድስት ጊዜ ዐሥር። ኑኁ ስሳ በእመት። ስሳ እማንቱ ንግሥታት። ቦ ዘምእት ወቦ ዘስሳ። ኅረይ እንተ ስሳ ፡-(ዳን፫ ፡-፩። ማሕ፮ ፡-፰። ማቴ፲፫ ፡-፰። ፩ጢሞ ፡-፭ ፡-፱)።
ስድስ ፡-(ዕብ ዜሬት። ሱር ዛርታ። ዐረ ሽብር) ስንዝር፤ ማኽል እጅ፤ የጋት ቁመት፤ ካውራ ጣት ጫፍ እስከ ታናሽቱ ወይም እስከ ታላቁ ጫፍ። መኑ ሰፈሮ ለማይ በሕፍኑ ወለሰማይኒ በስዝሩ። ኑኁ ስድስ በእመት ወስዝር። ወለሕፃንኪ አሮን ቁመተ ግዙፍ አካል፤ ስዝረ የዐብዮ ሙሴ ዕፀ መስቀል ፡-(ኢሳ፵ ፡-፲፪። ፩ነገ ፡-፲፯ ፡-፬። ቅኔ)። ክንድ፤ ልክ መጠን ጋት በማለት ፈንታ ስዝር ይላል፤ የመላሽ ስሕተት ነው ፡-(መሳ፲፫ ፡-፲፮። ፫ነገ ፡-፯ ፡-፲፩። ሕዝ፵ ፡-፭)።
ስድስቱ ት ፡-ዝኒ ከማሁ፤ የወንዶች ድምር፤ ቀው--። ስድስቱ ዕደው። ወለለ አሐዱ በበ ስድስቱ ክነፊሆሙ። ስድስቱ ተወልዱ ሎቱ በኬብሮን፤ ወነግሠ በህየ ሰብዐተ ዓመተ ወስድስተ አውራኀ። ወለድኩ ሎቱ ስድስተ ደቂቀ ፡-(ሕዝ፱ ፡-፪። ኢሳ፮ ፡-፪። ፩ዜና ፡-፫ ፡-፬። ዘፍ ፡-፴ ፡-፳)።
ስድቅ ፡-(ትግሬ ሽድቅ) የአፍ ማእዝን ግራና ቀኙ ማጠፊያው።
ስጉም ፡-(ማን ማት ግምት) የታሰረ፤ የተዘጋ፤ ዝግ ቍልፍ፤ ድዳ ደንቈሮ። ስጉማን በማለት ፈንታ ስግመት ይላል፤ ስሕተት ነው። እስመ ስግመት እሙንቱ ፡-(ኩፋ ፡-፲፪)።
ስጉድ ፡-(ዳን ዳት ግድ) የሰገደ፤ የተዋረደ፤ በግንባሩ የተተከለ። ረከቦ እንዘ ስጉድ በገጹ። ስጊድ ውእቱ ዲበ ምድር ፡-(ስንክ ፡-ጥቅ፳። መጋ፲፫)። ቂሐት፤ ቀይሓት በማለት ፈንታ ስጉዳት ይላል፤ የመላሽ ስሕተት ነው። ስጉዳት አዕይንቲሁ ፡-(ምሳ፳፫ ፡-፳፱)።
ስጕርድ ፡-(ጽር ስኮርዶን። ቅብጥ ስኮርቶን። ዕብ ሐጺር። ዐረ ኩረት) ሽንኵርታዊ፤ የነጭ ሽንኵርት ዐይነት፤ ሣልሳይ ሽንኵርት የሚበላ፤ ራሱ እጅግ የማያኰርት፤ ቅጠለ ወርዳም ረዣዥም፤ በሀገራችን የሌለ። ዛሬ ግን ይገኛል። ዐይነታቸው አንድ ስለ ኾነ ነጩንም ሽንኵርት ስጕርድ ስጕርንድ እያለ ይጥፋል፤ ሶመትን ተመልከት ፡-(ዘኍ፲፩ ፡-፭። ገድ ፡-ተክ። መ ፡-ፈ)።
ስጋድ [1]፡-(ትግሬ) ዐንገት፤ ሰጋጅ መስገጃ።
[2]፡-
(ዕብ ሲግዳ ፤
ሻቄድ። ሱር ሺግድታ) ፤ የንጨት ስም
፤ አንድ ዐይነት
ዕንጨት ፤
ፍሬው የሚበላ
፤ ለውዝ
፤ ሰገድ።ዲፍራን ወስጋድ (ኵፋ
፡ ፳፩)።
ስግመት ፡-ድዳ መኾን፤ መደንቈር፤ ድዳነት፤ ድንቍርና።
ስግደት ፡-(ታት) በቁሙ፤ አሰጋገድ፤ ሰገዳ፤ ስግዶሽ፤ መውደቅ መነሣት። ይስግድ ኀምሳ ስግደተ። ምስለ ስግደታት ብዙኃት ፡-(ፈ ፡-መ ፡-፲፬ ፡-፩። ፊልክ ፡-፪፻፯)።
ስጡሕ ፡-(ሓን ሓት ጥሕት) የተሰጣ፤ የተገለጠ፤ ስጥ ግልጥ፤ ዝርግ ሰታታ፤ ገልባጣ። እንዘ ስጡሕ ልብስ። ዳእሙ ስጡሓነ ውስተ ገጸ ምድር ይከውኑ። ወኵሉ ክሡት ወስጡሕ በቅድመ አዕይንቲሁ። እንዘ ስጡሕ ልቦሙ ፡-(ሥር ፡-ጳኵ። ኤር፴፪ ፡-፲፱። ዕብ፬ ፡-፲፫። ፪ጴጥ ፡-፪ ፡-፲፬)።
ስጡም ፡-(ማን ማት ጥምት) የሰጠመ፤ የተሰጠመ፤ ባሕር የዋጠው የሸፈነው፤ ማዕበል ሞገድ የደፈነው። ማሕጼ ስጡም። እለ ስጡማን በግብረ ዓለም። እለ ስጡማን ውስተ ዐምዓመ ኀጢአት ፡-(ስንክ ፡-ጥቅ፳። አፈ ፡-ተ፲፭። ግንዘ)።
ስጢጥራ ፡-(ጽር ስታቲር። ዕብ ኤስቲራ) የገንዘብ ስም፤ ፋርሳዊ ገንዘብ፤ አራት ድሪም። ብር ሲኾን ፫ ፍራንክ ከ፸፪ ሳንቲም። ወርቅ ሲኾን ፲፱ ፍራንክ ከ፸ ሳንቲም ፡-(ዲክሲ ፡-ላሩስ)። ትረክብ ስጢጥራ። ስጢጥራ ዘይቤ አርባዕቱ ድርህም ፡-(ማቴ፲፯ ፡-፳፯። ጥሬ ፡-ሰዋ)። ድርህምንና ሕፍንን ተመልከት።
ስጣዌ ፡-መስጠት፤ መሰጠት፤ አሰጣጥ፤ ስጦታ፤ ቅበላ። ምላሽ ፥ መልስ፤ አመላለስ፤ ምለሳ። ስጣዌ መልእክት። ስጣዌ ስጣዌያት ፡-(አረጋ። አዋል)።
ስጥሐት ፡-ማስጣት፤ መሰጣት፤ አሰጣጥ፤ ስጥነት፤ ዝርግነት፤ግልጥነት።
ስጥመት ፡-በቁሙ፤ መስጠም፤ መሰጠም፤ አስጣጠም፤ ውሃ መልበስ፤ በውሃ መቀበር። ከመ ሰብአ ኖኅ በስጥመት ውስተ ማይ። ድኅኑ እምስጥመት ዘሞትከ በስጥመተ ማይ። ውዕየተ እሳት አው ስጥመተ ሐመር ፡-(ፊልክ ፡-፻፸፪። ስንክ ፡-ኅዳ፳፱። ሠኔ፮። ፍ ፡-ነ ፡-፵፱)።
ስጥወት ፡-ዝኒ ከማሁ፤ መስጠት፤ መመለስ፤ ምላሽ ስጦታ ፡-(ኩፋ ፡-፲፮)።
ስጥው ፡-(ውት ዋን ዋት) ውኩፍ፤ የተሰጠ፤ ተሰጭ፤ ወይም ተቀባይ፤ ውድ ክቡር። ይኩን ውስተ ፍጽሙ ለአሮን ስጥወ። ያበውኦ ስጥወ ፡-(ዘፀ፳፰ ፡-፴፰። ዘሌ፩ ፡-፫)።
ስፉሕ ፡-(ሓን ሓት ፍሕት) የሰፋ ሰፊ፤ ዝርግ፤ ብዙ። ምድር ቡርክት ወስፍሕት። ክነፊሆሙ ስፉሓን። እግዚ ስፉሐ ሀብት ፡-(ኩፋ ፡-፰። ፪ዜና ፡-፫ ፡-፲፫። ግንዘ)።
ስፉር ፡-ራት ፍርት) የተሰፈረ፤ የተለካ። ኢምጡን ወኢስፉር ፡-(መጽ ፡-ምስ)።
ስፉን ፡-(ናን ናት ፍንት) የሰፈነ የመላ፤ ምሉእ ፍጹም። ህላዌሁ ስፉን። ስፍንት ከመ መንፈስ ቅዱስ ፡-(አዋል። ቅዳ ፡-አት)።
ስፉይ ፡-(ያን ያት ፊት ፍይት) የተስፋ ስፍ፤ ጥልፍ፤ ግብረ መርፌ።
ስፉጥ ፡-(ጣን ጣት ፍጥ) የተሞኘ፤ የተታለለ፤ ተላላ፤ ድልል ሽንግል፤ ስሑት። ኦ ድንግል አኮ ወራዙት ስፉጣን። ዘናዘዙኪ ፡-(ቅዳ ፡-ሕር)።
ስፉፍ ፡-(ፋን ፋት ፍፍት) የሰፈፈ፤ የመላ የተረፈ፤ የጠራ የጠለለ። ሳፊ እንዲል ጥሩ ሲል ፡-(ዐረብ)።
ስፊና ፡-(ዕብራ) የነፋስ መርከብ ባለሸራ፤ ነፋስ የሚነዳው።
ስፋሪዳ ፡-(ጽር ስፊሪዲያ) ክብ እንክብል ድንብልብል፤ እንደ ኳስ ያለ። ስፋሪዳ ዘኀጺን እለ ርሱናት ፡-(ስንኩ ፡-መጋ፳)።
ስፍሐት ፡-መዘርጋት፤ ፡-(ጥዘ) መዘርጋት፤ አዘረጋግ፤ ዝርግነት፤ ስፋት። በስፍሐተ እዴሁ ዲበ ዕፀ መስቀል። ስፍሐታ ለማኅደር ፡-(ቀሌ። ፍ ፡-ነ ፡-፳፫)።
ስፍሕ ፡-ስፋት ሰፊነት፤ የወርድ የኑኅ ያራቱ ማእዝን። ስፍሐ በሓውርት። ስፍሐ ምድር። ወይኩን ስፍሐ ምጣኔ ማእከለ ቤት ወቤት ዐሠርቱ ወክልኤቱ መከየድ ፡-(ኢሳ፰ ፡-፰። ዕን፩ ፡-፮። ፍ ፡-ነ ፡-፴፯ ፡-፪)። በስፍሕና በርሕብ ፈንታ ጽፍሕ ይላል፤ በጸሊብ ፈንታ ሰሊብ እንዲል። ጽፍሐ መሠረቱ ሠላሳ በእመት። ጽፍሑ ዕሥር በእመት ፡-(ዮዲ፩ ፡-፪። ዘካ፭ ፡-፪። ሕዝ፵፩ ፡-፮)።
ስፍረት ፡-መስፈር፤ መሰፈር፤ አሰፋፈር፤ ስፍሮሽ ሰፈራ፤ እርምጃ። እለ ያሰግሉ በስፍረተ እግር ወበመስፈርተ እድ ፡-(ቀሌ)።
ስፍራ ፡-(ትግ ወዐረ) በቁሙ፤ ማእድ ሰደቃ።
ስፍር ፡-በቁሙ፤ ልክ መጠን፤ ይህን ያኽል የሚባል፤ አኃዝ ቍጥር። የዐረብ ዜሮ።
ስፍነት ፡-ምላች ስፋት፤ ብዛት፤ ግዛት ሥልጣን፤ ጌትነት።
ስፍን ፡-(ዕብ ካማ። ዐረ ከም) ንኡስ አገባብ። የስፍር የቍጥር የልክ የመጠን ጥያቄ፤ ስንት፤ ምን ያኽል። ለቡ ስፍን ኍልቆሙ። ስፍን ቦቱ ዲናራት ዘለቅሐ። ስፍን እምኤጲስቆጶሳት። ስፍነ ጊዜ ዘነትዐ ምዉእ ውእቱ ተመይጠ ወኮነ መዋኤ። ስፍነ አህጉረ ጽኑዓን እለ አመዝበሮን ወስፍነ አብያተ እለ አንኀሎን፤ ወስፍነ ዕደወ ኀያላነ እለ ረሰየ ይትዋነይዎሙ ዕፄያት። ተአምር ስፍነ ነገሥተ ርኩሳነ እለ ዐለዉ ፡-(ቀሌ። አፈ ፡-ተ፲፩። ሲኖዶ። ዮሴፍ። ግንዘ። ዲድ ፡-፪)።
ስፍው ፡-(ዋን ዋት ፉት) የታመነ የተወከለ፤ በተስፋ ያለ፤ ባለተስፋ።
ስፍየት ፡-መስፋት፤ መሰፋት፤ አሰፋፍ፤ ስፍነት፤ ስፌት ጥቅማት፤ የስፌት ዕቃ። ስፉይ በሠላስ መዓርገ ስፍየት ፡-(ፊልክ ፡-፬። ፈ ፡-መ ፡-፴፩ ፡-፭)።
ስፍጠት ፡-መታለል ፣ ማታለል፤ አታላይነት፤ ተታላይነት። ስፍጠተ ብዕል። ስፍጠታተ ሰይጣን ፡-(ማቴ፲፫ ፡-፳፪። ፊልክ ፡-፬)።
ሶ ፡-(ዕብ ናእ) ትእምርተ ስኢል ዐቢይ፤ የምልጃ የልመና ቃል፤ እባክኽ፤ እባክኽ። ሲገባም በመጨረሻ ቃል፤ በሣልሳይ አንቀጽ ይገባል፤ ልመናው እጅግ ብርቱ ነው። የአን አፈታት ተመልከት፤ የዚህ ጎረ ቤት ነው። አምላከ ኀያላን ተመየጥሶ። ኦ እግዚኦ አድኅንሶ፤ ሠርሕሶ ፡-(መዝ ፡-፺፱። ፻፲፯)። ኹለተኛም እንደ ዕብራይስጡ ነ ኹኖ በንሕነ ዝርዝር ይፈታል። ይህም፤ ተመየጥሶ፤ ተመየጠነ፤ ተመየጥ ለነ። አድኅንሶ፤ አድኅነነ። ሠርሕሶ፤ ሠርሐነ፤ ሠርሕ ለነ እያለ መኼዱን ያሳያል። ፡-(ዕር፳ ፡-ቍ፺፱)።
ሶልላ [1]፡-ዐፈር ኵረት፤–ሰሊል ሰለ።
[2]፡-(ዕብ) ዐፈር ኵረት ደንጊያ፤ የሕንጻ የድልድል ማስተካከያ። ወከዐው ላዕሌሃ ሶልላ ፡-(ሕዝ፬ ፡-፪። ፳፩ ፡-፳፯)። ሶልላ ባለው መራድ ይላል፤ የመላሽና የጣፊ ስሕተት ነው፤ አንዳንድ መጣፍ ግን መሬት ይላል።
ሶልያና ፡-(ጽር ሴሊኒ) ጨረቃ፤ ድንግል ማርያም። ጊዜ ዕረፍታ ለሶልያና ፡-(ድጓ)።
ሶም ሳውም ፡-(ዕብ ሾሀም። ጽር ሰርድዮን) የዕንቍ ስም፤ ዕንቍ፤ ክቡር ደንጊያ። እብነ ሶም። ቢረሌ ወሳውም ፡-(፩ዜና ፡-፳፱ ፡-፪። ዘፀ፳፰ ፡-፳)።
ሶሰወ ፡-ወጣ ወረደ፤–ሰውሰወ።
ሶሰው ሰውሰው ፡-(ብ ሰዋስው) መሰላል፤ ዕርከን፤ ማዕርግ ምዕራግ ደረጃ፤ መውጫ መውረጃ። መጽሐፍ ግን በሶሰው ፈንታ ሰዋስው ይልና በሰዋስው ፈንታ ሰዋስዋት ይላል፤ ዋት የብዙ ብዙ ነው። ሶሰውም ቢኾን እንደ ሰው ነው፤ ውስጠ ብዙነትን ያሳያል። ይደልዎ ለአሐዱ ከመ ይትክል ሰዋስወ በኀበ ገቦ አረፍት ለእመ ኮነ ውእቱ ዘኢይነኪ ካልኦ። ተከሉ ሰዋስወ ወዐርጉ። አስተናበረ ውስተ ልቡ ሰዋስዋተ ፡-(ፍ ፡-ነ ፡-፴፯። ዮሴፍ። ዘፍ፳፰ ፡-፲፪። ማር ፡-ይሥ፳፫)።
ሶሳን [1]፡-(ዕብ ሾሻን) አበባ፤ ያበባ ዐይነት ቅርጽ ፡-(፫ነገ ፡-፯ ፡-፲፱)።
[2]፡-ሶሳን፤–አበባ፤–ሰውሳን።
ሶሳው ፡-ሰውሰው፤ ፡-(ብ ሰዋስው) መሰላል፤ ዕርከን፤ ማዕርግ ምዕራግ ደረጃ፤ መውጫ መውረጃ። መጽሐፍ ግን በሶሰው ፈንታ ሰዋስው ይልና በሰዋስው ፈንታ ሰዋስዋት ይላል፤ ዋት የብዙ ብዙ ነው። ሶሰውም ቢኾን እንደ ሰው ነው፤ ውስጠ ብዙነትን ያሳያል። ይደልዎ ለአሐዱ ከመ ይትክል ሰዋስወ በኀበ ገቦ አረፍት ለእመ ኮነ ውእቱ ዘኢይነኪ ካልኦ። ተከሉ ሰዋስወ ወዐርጉ። አስተናበረ ውስተ ልቡ ሰዋስዋተ ፡-(ፍ ፡-ነ ፡-፴፯። ዮሴፍ። ዘፍ፳፰ ፡-፲፪። ማር ፡-ይሥ፳፫)።
ሶስና ፡-ከመ ብእሲት፤ አበቡት፤ አበባ። ዘአድኀና ለሶስና እምእደ ረበናት ፡-(ድጓ። ሊጦን። ዳን)።
ሶስዊ ፡-(ዊት ውያን ያት) ዝግተኛ፤ አስተውሎ ኸያጅ፤ ወጭ ወራጅ፤ ሰው፤ ባለሰዋስው።
ሶስዎ ዎት ፡-(ሶሰወ ይሶሱ። ዕብ ሺሼእ፤ ሂዳዴ) መሰውሰው፤ አስተውሎ መርገጥ፤ ቀስ ብሎ መኼድ መራመድ፤ እያዘገሙ ወደ ላይ ወደ ታች መውጣት መውረድ፤ የዕርክን የመሰላል የዳገት የስገነት። መሰላል ዕርከን መሥራት፤ ምሰሶ ማቆም መትከል።
ሶር ፡-(ብ አስዋር። ዕብ ሾር፤ ብ ሽዋሪም) ተባት ላም፤ በሬ፤ አውራ ኰርማ፤ ሚል ገች። ሶር አሐዱ እምውስተ አልሕምት። ወወፅአ ሶር ጸዐዳ። አልሕምት ብዙኃን ወአስዋር ሥቡሓን። መጋዝእትናየ ወአስዋርየ ፡-(ዘኍ፳፱ ፡-፰። ሔኖ፹፭ ፡-፱። መዝ ፡-፳፩። ማቴ፳፬ ፡-፬)። ተውርን ተመልከት፤ ከዚህ ጋራ አንድ ነው።
ሶቅ ፡-(ዕብ ሾቅ። ሱር ሻቃ። ዐረ ሳቅ) እግር ባት፤ ከጕልበት እስከ ቍርጭምጭሚት።
ሶበ ፡-ጊዜ፤–ሰዊብ ሰወበ፤–ሶብ።
ሶበርት ኮሶ [1]፡-የሆድ ትል፤ ሹጥ፤ ከጠፋ በኋላ እስከ ኹለት ወር የሚቈይ በሦስተኛ ወር የሚታይ። የኮሶ መድኀኒት መራራ፤ የሚዋጥ የሚቃም የሚጠጣ። ለዘአበዮ ሶበርት። ሠያጢተ ሶበርት ፡-(መ ፡-ፈ። ታሪ ፡-ቴዎ)።
[2]፡-ኮሶ ሹጥ፤–ሰበረ።
ሶቤ ሶቤሃ ፡-ያን ጊዜ፤ ፈጥኖ፤ ወዲያው፤ ቶሎ። ረኪቦ መጽሐፈ ሶቤ። ይእተ ሶቤ። ወቀትር ሶቤሃ። ምዕረ አውሢአከ፤ ሶቤሃ ፈጽም ቃለከ ፡-(ስንክ ፡-ሚያ፮። ማቴ፯ ፡-፳፫። ዮሐ፬ ፡-፮። ሢራ፴፭ ፡-፰)። ለሶቤሃ፤ እምሶቤሃ፤ እስከ ሶቤሃ ቢል ፍችው ፩ ነው። ሶቤሁ ሃ ከ ኪ የ፤ ሶቤሆሙ ን ክሙ ን ነ እያለ እንደ አመ ይዘረዝራል።
ሶብ ሶበ ፡-(ዐቢይ አገባብ፤ እመ) ቢ ባ ብ፤ ከ ካ፤ ጊዜ። ባ ካ መኾኑ ባሉታ ላይ ነው። ብፁዓን አንትሙ ሶበ ይጸልኡክሙ ወይጼዕሉክሙ ወያወፅኡ ለክሙ ስመ እኩየ፤ ቢ። ሶበ አኮ እግዚአብሔር ምስሌነ። እምኀየሶ ሶበ ኢተወልደ፤ ባ። ሶበሰ ታፈቅሩኒ። ሶበሰ እምዓለም አንትሙ፤ ብ። ሶበ እምዕጹብ ይድኅን ጻድቅ። ሶበ እንዘ ሰብእ አንተ ትትቄየም ሰብአ፤ ከ። ወሶበ እንዘ ዘበምድር እነግረክሙ ኢተአምኑኒ፤ ካ። ወሶበ ፈጸመ እግዚእ ኢየሱስ ዘንተ ነገረ፤ ጊዜ። አንዳንድ ባላገባቦች ሲ ሳ ስ ምነው ይኾናል ይላሉ፤ ምስክራቸው አያጠግብም። ሲ ሳ ስ ያሉት፤ ቢ ባ ብ ካለው ይገባል። ምነው ያሉትም፤ ሚ እሞትነ በማለት ፈንታ ሶበ ሞትነ ብሎ ስላገኙት ነው። የሚን አፈታት ተመልከት። የሶበ ምስጢር ባፈታቱ ኹሉ ጊዜን አይለቅም ፡-(ዕር፲፱ ፡-ቍ፸፮ ፡-፸፯)።
ሶዐ ፡-ሠዋ አቃጠለ፤–ሠዊዕ ሦዐ።
ሶከር ፡-(ራት፤ ሰዋክር) ሸንኰር፤ የስኳር አገዳ፤ ማር ማር ጥንቅሽ ጥንቅሽ የሚል። ስኳር፤ ያገዳ ማር፤ የማር ወለላ። ይጥዕም ቃልየ እመዓር ወሶከር። እመዓር ወሶከር ጥዕመኒ ለአፉየ። ሜስ ዘአጣእጥእዎ በሶከር ፡-(ቀሌ። መዝ ፡-፻፲፰። ፈ ፡-መ ፡-፳፮ ፡-፩)።
ሶክ ፡-እሾኽ፤–ሦክ።
ሶጠ ፡-መለሰ፤–ሠዊጥ ሦጠ።
ሶፎር ፡-(ጽር ሶፊር። ዕብ ኦፊር) የወርቅ አገር። አፌርን ተመልከት፤ ከዚህ ጋራ አንድ ነው። እብነ ፈለገ ሶፎር ፡-(ኢዮ፳፪ ፡-፳፬)።
ሶፎር ፤ (ጽር ሳፕፊሮስ። ዕብ ሳፊር) ፤ ዕንቍ የዕንቍ ስም። ሰንፔርን ተመልክት ፤ ከዚህ ጋራ አንድ ነው ፤ ጣፊና መላሽ በሰንፔር ፈንታ ሶፎር እያሉ ኹለት ስም አድርገውታል (ስንክ ፡ መስ፲፮። የካ፱። ድጓ። አርጋ ፡ ፯)።
No comments:
Post a Comment