~ወ~

                                 

[1]- ፊደል፤ በግእዝ አልፍ ቤት በአበገደ ስሙ ዋዌ ጥሩ ስድስት አኃዝ ሲኾን ድስት ድስት ይባላል ዕብራውያን ግን ስድስትን መደብ አድርገው በራሱ ላይ ነቍጣ እየጨመሩ ስድስት እልፍ ይሉታል ፮ኛ ማለት ምስጢሩ ዐርብንና የዐርብን ፍጥረት መደብ አድርጎ፤ ዳግማይ አዳም ሥግው ቃልን ምስጢረ መስቀልን ያሳያል፤ የዋዌን ፍች ተመልከት

[2]-( - -ዓዲ) ንኡስ አገባብ። አጫፋሪ ማሰሪያ ፋይ፤ አጋናኝ ም፤ ቸልታ ዘተረስዐ፤ ውጥን ራሽ የአኃዝ ቅላይ ጊዜ፤ ስንኳ ግን ሰ፤ ፈጽሞ አዳማቂ ይኾናል ሲኾን በኹሉ ይገባል በልዐ ወሰትየ ሰምዐ ወርእየ ሲኾን በስም ይገባል፤ ጴጥሮስ ወጳውሎስ፤ ያዕቆብ ወዮሐንስ በሦስት ስሞች ሲገባ መዠመሪያው ኹለተኛው ይኾናል፤ ጳውሎስ ወስልዋኖስ ወጢሞቴዎስ በብዙ ስሞች ሲገባ ጭራሽ ይኾናል ወይም ጠቅላይ ኹኖ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ያሰኛል ተንሥአ ወኀደገ ልብሶ፤ ተጠምቀ ወአድነነ ርእሶ፤ ቸልታ ልብሱን ጥሎ ራሱን አድንኖ ዘተረስዐ ሲኾን የኋሊት ይፈታል የወደቀበት ማሰሪያ ያልወደቀበት ቸልታ ይኾናል ይባእ ወይርአይ፤ ብቶ ሐመ ወሞተ፤ ታሞ ሖረ ወመጽአ ኺዶ መጣ። ተሰቅለ ጴጥሮስ ማሁ እንድርያስ ተውህበ ጳውሎስ ሙቁሕ ወካልኣንሂ ሙቁሓን ውጥን ይህ የፊቱን በኋላ ሲጨርስ ነው የኋላውን በፊት ሲጨርስ፤ ሰማይ ወምድር የኀልፍ ይላል ማይም ያልፋል፤ ምድርም ታልፋለች ያሰኛል፤ ሰማይ ምድር ያልፋል ተብሎም በጠቅይነት ሊፈታ ይቻላል፤ ባላገባቦች ግን ጋራ ይሉታል። ዐሠርቱ ወክልኤቱ ሰበዓ ወኀምስቱ ሠለስቱ ምእት ዐሠርቱ ወሰመንቱ ቅላይ ልፍ ወዕሥራ ምእት ወተወሊዶ ወጸቢሖ ጊዜ። ኢወሀቦ ርስተ ወኢመጠነ ምክያደ እግር ንኳ። ጸድቀ ቄርሎስ ወኢጸድቀ ንስጥሮስ፤ ግን። እንጂም ይኾናል ምስጢሩ ያው ነው ልዐ ወኢሰትየ ብሎ አልጠጣም እንጂ ያሰኛል። ምንተ ንበልዕ ወምንተ ንሰቲ ስ። ሖረ ወኀለፈ፤ ተበ ወጸሐፈ ፈጽሞ። ፈጽሞ ያሰኘው ያናቅጽ ኅብረት የፍች አንድነት ነው እንጂ ምስጢሩና ሙያው ካጫፋሪነት አይወጣም አዳማቂ ሲኾን እንደ በሣልሳይ አንቀጽ ስምዐኒ ወእንግርከ፤ ቅረበኒ ወእግስስከ፤ ኢትግበራ ለእኪ ወኢይር እኩይ እያለ ይገባል ሲኾን ምንተ ትሁበኒ ወአነ ኣገብኦ ክሙ ይላል እኹል ገብ ፊደል ስለ ኾነ ስልቱና አፈታቱ ብዙ ነውና የቀረውን በግስ መልና በፊደል ታሪክ በንኡስ አገባብ ተመልከት። ኹለተኛም የግስ ዐመል ኹኖ ፊደልን ኹሉ ካዕብና ብዕ ያደርጋል የካዕብ የሳብዕ ሥረያቸው ነው፤ ሥረይነቱ እንዴት እንደ ኾነ በፊደል ሪክ እይ። ባማርኛም እንደ ባዕድ ዘር ይኾናል መደ፤ ጥመድ። ነበረ፤ ወንበር ወስፌ ነፋ ወንፊት ገመ፤ ዋገምት፤ የመሰለው ኹሉ

ወሓሲ -(ሲት ስያን ያት ሐስት) የሚያውስ አዋሽ፤ ሰጭ ባለገንዘብ ወኢሀሎ ወሓሲ ግዚአ ንዋይ -(ዘፀ፳፪ -፲፫)

ወሃቢ -(ቢት ብያን ያት) ሚሰጥ ዳይ አሳላፊ፤ ለጋስ እጀ ሰፊ ወሃቢሃ ለሕግ ወሃቤ ሕይወት። እግዚ ወሃቤ ዕሴት ወመክፈልት ለዘገብረ ፈቃዶ ብእሲ ፍሡሕ ወወሃቢ -(ያዕ፬ -፲፪ ኪዳ ዮሴፍ ምሳ፳፪ -)

ወሀብት -ወሃብያን ወሃብያት።

ወሓኪ -(ኪት ክያን ያት) የሚያነሣሣ፤ አነሣሽ ጐስጓሽ።

ወሓዚ -(ዚት ዝያን ያት ሐዝት) የሚፈስ ፈሳሽ፤ የሚያፈስ አፍሳሽ።

ወኀየ -ጐበኘ፤ዋሕዮ ዋሐየ

ወኃጢ -(ጢት ጥያን ያት ኀጥ) የሚውጥ፤ ዋጭ። ጠብቆ ቀለም የሚያስቀር ፊደል በርባታ ጊዜ ደገ ባረከ ዖቀ ንተ ኰነነ ሕነ 

ወሒዝ ውሒዝ -ወሒዝ ውሒዝ -(ዛት ወሓይዝት) ወንዝ፤ የወንዝ ውሃ ፈሳሽ ጐርፍ። ውሒዝ ዐቢይ ውሒዝ ኀያል ከመ ውሒዛተ ማይ ውሕዙ ወሓይዝት ወሓይዝተ አፍላግ ቅኑያቲኹ -(ኢሳ፲፯ -፲፫ ፶፱ -፲፱ ምሳ፳፩ -፩። ማቴ፯ -፳፭ ቅዳ -ኤጲ)

ወህውሀ -(ይወሀውህ ይዋህውህ ወህውሆ ተቀ -) ውሃ ውሃ አለ የጣዕም የሕሙም

ወሕውሐ -በራ፤ ተመላለሰውሂህ ወህሀ ወህውሀ።

ወሕዝ -(ዕብ ዚዓ) ወዝ ላበት ሀፍ ራሕፅ ከገላ የሚፈልቅ የሚፈስ

ወለበ -(ትግ ዞረ ተመለሰ) በቁሙ ተፈለፈለ፤ ውልብኝ ኾነ፤ ተጠረጠረ የእሸት ያሹቅ ውልብ አለ ልም አለ ይቶ ፋ፤ ተውለበለበ የጨርቅ የምላስ የገለባ -(ዐማርኛ)

ወለባ -(ዐማርኛ) በቁሙ፤ የእሸት ገለባ ፍልፋይ ጥርጣሪ ረቈንዳ።

 -የራስ ጌጥ፤ ማከኪያ -(ተረት) ራስ ተላጭቶ ወለባ፤ ልባልባ ታጥቆ ዐዛባ

ወለት -ብንት ሴት ልጅወሊድ ወለደ ወለድት።

ወለድ ወለት -( አዋልድ) ልጅ ልጃገረድ፤ ወይም የተዳረች። በከመ እም ከማሁ ወለታ። ወለተ ወልድከ አው ወለት ወለትከ አዋልደ አዋልዲሁ -(ሕዝ፲፮ -፵፬። ዘሌ፲፰ - ዘፍ፵፮ -)

(ጥጥ)        ወለጥ -ቀስት፤ ወስፈንጠር የሚለጠጥ ወለጠ ወመቅልዐ -(ገድ -አዳ)

ወሊል ሎት -(ወለ ወለለ ይወልል፤ ይለል) መውለል መዋለል ወለል ወለል ማለት፤ ወለላ ማለት ከዚህ ወጥቷል፤ ወልወለ የዚህ ዲቃላ ነው

ወሊድ ዶት -(ወለደ ይወልድ ይለድ። ዕብ ያላድ ሱር ሌድ ዐረ ወለደ) መውለድ ማውጣት መፍጠር ማምጣት ማስገኘት በባሕርይ በግብር ለፀኒስ ወጊዜ ወሊድ ምድር ትወልድ ሣዕረ። ጥዓ ወመዐት ይወልዱ ካሕደ -(መክ፫ - ዕብ፮ -፯። አፈ -ድ፮)

ወሊግ ጎት -(ወለገ ይወልግ ይለግ ዐረ ወለጀ) መውለግ ማውለግ መሹለክለክ ሹልክ ብሎ መግባት ዋልጋ ዋልጌ ውላጋ ማለት ከዚህ ወጥቷል።

ወላዲ -(ዲት ድያን ያት) የሚወልድ ወላጅ አስገኝ አባት፤ ፈጣሪ። ወላዲሃ። ወላዴ ሕይወት። ወላዴ ሥን ወላዲትክሙ ወላዲተ አምላክ እናት ወላድያን -(ሢራ፳፪ -፬። ኪዳ ጥበ፲፫ -፫። ኤር፳፯ -፲፪ ቄር ዘዳ፳፬ -፲፮)

ወላድ -(ዳት) ቁሙ የምትወልድ ሴት መካን ያይዶለች ወላድ ስእነት ወለደ ወላድ ተቀሥፎቱ ዘትነብር በምንዳቤ -(፩ነገ - -፭። ቅኔ)

ወላጢ -(ጢት ጥያን ያት) የሚለውጥ ለዋጭ መንዛሪ ቸርቻሪ

ወልብ -ውልብኝ የእሸት ፍሬ ታሽቶ ተፈልፍሎ የሚቃወም የሚጠረጠር። የአዕዋፍ ዘር ዕንቍላል ከዚያውም ውስጡ ፍሬው አስካሉ። ከመ አንቆቅሖ ባለው ከመ ተረፈ ወልብ እንዲል -(ኢሳ -፲፪)

ወልተወ -አጌጠ ለበሰ ተጠረረ መከተ ከለለ ጋረደ መጽሐፍ ግን በወልተወ ፈንታ ተወልተወ ይላል ንትወልተው በንዋየ ሐቅል ዘሃይማኖት ንትወልተው ሃይማኖቶሙ ተወልተዉ በይእቲ ኅሊና -(አፈ -ተ፳፪ መዋሥ ፩ጴጥ - -)

ወልታ -(ታት ወላትው ወልወለ) ላቅ ጋሻ አላባሽ አግሬ ክብ ወይም ሞላላ ከጐሽ ካውራሪሥ ከዝኆን ቍርበት የሚሠራ ፍችው የወል የመካከል ማለት ነው ዋልታ እንደ ማለት ዋልታ ቅሉ ከዚህ ወጥቷል ከመ ወልታ ሥሙር ከለልከነ ወልታ ብርሃን ወልታት ይጸውሩ ወላትወ -(መዝ -፭። ሮሜ፲፫ -፲፪ ዮሴፍ። ኩፋ -፴፯)

ወልታዊ -የሚመከት መካች፤ ጋሸኛ ባለጋሻ ጋሻ ያዥ ጋሻ ዣግሬ

ወልዋሊ -ወልዋይ፤ ወላዋይ፤ ወለብላባ

ወልውሎ -(ወልወለ ይወለውል ይወልውል ወሊል ወለ ወለለ) ቁሙ፤ መወልወል ሰንገል -(ዐማርኛ) ወልወል ወለል፤ ወልታ ማለት የዚህ ዘር ነው

 -መዋለል መገፋት መናጥ፤ መወዛወዝ፤ ውል ውል ሽው ሽው ማለት፤ የውሃ የዛፍ የነፋስ መወላወል መጠራጠር ምልስ ቅልስ ማለት ውለብለብ፤ የኅሊና የእግር የምላስ ሎለወን እይ መጽሐፍ ግን በወልወለ ፈንታ ተወላወለ ይላል፤ ማርኛ ረጠረና ተጠራጠረ ስለ ኾነ ግእዙን እንዳማርኛው አስኪዶታል። ዝንጉዓን እለ ትወላወሉ ኅሲና ዘይትወላወል እጋር እለ ይትወላወላ ለገቢረ እከይ። ላህበ ነድ እን ይትወላወል ወያንሶሱ ውስቴቶሙ -(አፈ -ተ፳፫ አርጋ ምሳ፮ -፲፰ ጥበ፲፱ -)

ወልደ ኀይል -ኀይለኛ ዐዋቂ፤ ባለአእምሮ የጦር ሰው -(፩ነገ -፲፰ -፲፯)

ወልደ ሀጕል -ጥፋት የሚገባው ለጥፋት የተገባ መጥፎ ርጉም -(ዮሐ፲፯ -፲፪)

ወልደ ሞት -ሞት የሚገባው ይሞት በቃ የተፈረደበት -(፩ነገ - -፴፩)

ወልደ እግዚ -ሥግው ቃል ክርስቶስ መልአክ -(ማቴ፬ -፫። ዳን፫ -፳፭)

ወልደ እጓለ መሕያው -የሰው ልጅ ው፤ የአዳም ዘር ኹሉ -(ሕዝ፪ -)

ወልድ -( አውላድ ውሉድ ደቂቅ) ልጅ፤ ተባት ወንድ ድንግል ትፀንስ ወትወልድ ወልደ። ኢያእመራ እስከ ወለደት ወልደ ዘበኵራ በኒ ውሉደ፤ ወእመ እመውት -(ማቴ፩ -፳፫ -፳፭ ዘፍ፴ -) ስምነቱ ማእከላዊ ነው ላደገውም ላላደገውም ይነገራል። ወልድ መባል ግን በኹለት ወገን ነው በባሕርይ በግብር ወይም በጸጋ፤ ግብርና ጸጋ አንድ ወገን ናቸው እንዳረቡ ውላድ አውላድ በማለት ፈንታ፤ ውሉድ ብሎ ልጆች ማለት እንደ ደቂቅ በልማድ ነው እንጂ፤ንባቡም ፍችውም ስሕተት ነው አያሰኝም፤ አንስትን ቢጽና ፀርን እይ ይህም እንደዚያ ነው

ወልድና -ልጅነት፤ ልጅ መኾን ዝምደት አብና ወወልድና -( - -፳፬ -፮። አፈ -ድ፪ -)

ወልጦ ጦት -(ወለጠ ይዌልጥ ይወልጥ) መለወጥ መተካት አንዱን በሌላ ወይም ሌላ ማድረግ። ኢትወልጥ ዐርከ ትወልጥ ግዕዘከ። ወልጡ አልባሲክሙ እመ ይዌልጥ ሐራውያ ማእሶ ወጸጕሮሂ ከመ ፀምር -(ሢራ፯ -፲፰ -፳፱። ዘፍ፴፭ - ኩፋ -፴፯)

ወማይ -ጥቋቍር ወፍ ረንጓዴ መሳይ የማሽ ተባይ -(ዐማርኛ)

ወሰረ -ገዘገዘወሥሮ ወሠረ።

ወሠቀ -ዐለበ ደከረወስቆ ወሰቀ

ወሰን -(ናት ነታት) ቁሙ፤ ዳርቻ ዳር ደንበር ምልክት ወደብ ገደብ፤ ፍጻሜ ያነብር ወሰነ ለባሕር። ገበርኩ ላቲ ወሰነ። እስከ ወሰንከ ሰደዱከ ወሰን ሰሜናዊ። ዘይትዐዶ ወሰነ አልቦ ለዝ ሕግ ወሰነ መዋዕል -(ምሳ፰ -፳፱ ኢዮ፴፰ - ዓብድ -፯። ሕዝ፵፰ -፩። ሆሴ፭ -፲። ኩፋ -፲፮)

ወሲስ ሶት -(ወሰ ይወስስ ይሰስ) መወሰስ ማነስ መኰስስ ሥሥ ወሰስ መኾን የከብት የቅንጣት። ፪ኛም፤ ወስወሰ ብሎ ወሰወሰ፤ ተወሳወሰ ውስወሳ ወስዋሳ ማለት ከዚህ ይወጣል -(ዐማርኛ)

ወሲብ -(ወሰበ ይወስብ ይሰብ። ዕብ ያሻብ ተቀመጠ) መዳበል ደረብ ካንድ ከሌላ መጠጋት ደባል ድልባን ኹኖ መቀመጥ መወሰብ ጥለፍ መቈለፍ የፈትል ያረግ ምስጢሩ ያው ነው ደባልነት አይወጣም ወሸባ ማለት ከዚህ ወጥቷል

ወሢእ ኦት -(ወሥአ ይወሥእ ይሣእ ጐሥዐ) ማውሣት ማሰብ መናገር መጠየቅ መመለስ ምላሽ መስጠት መጽሐፍ ግን በወሥአ ፈንታ አውሥአ ይላል አያሰኝም። ታውሥእ ሕሡመ በአፉከ ሙሴ ያወሥእ ወእግዚ ይሰጠዎ። ወአውሥኡ ኵሉ ሕዝብ በይእቲ ስብሐት። ከመ ታወሥእዎሙ ቃለ ለእለ ይሴአሉክሙ በእንተ ዛቲ -(ኢሳ፶፰ -፲፫ አርጋ - ዮዲ፲፭ -፲፬ ፩ጴጥ - -፲፭)

ወሲድ ዶት -(ወሰደ ይወስድ ይሰድ። ዕብ ያሳድ፤ መሠረተ) መውሰድ ይዞ መኼድ፤ ከቦታ ወደ ቦታ ወሰደኒ የሩሳሌም ወሰደኒ መንፈስ ገዳመ። ወሰደኒ ውስተ አየር ዘሳበዕ ሰማይ ፍኖት እንተ ትወስድ ውስተ ሀጕ -(ሕዝ፰ - ራእ፲፮ - -ኢሳ፱ -፩። ማቴ፯ -፲፫)

ወሲጥ ጦት -(ወሰጠ ይወስጥ ይሰጥ፤ ይውስጥ ዐረብ) መወሰጥ በውስጥ ኾን ውስጥ መግባት፤ ወደ ውስጥ ማግባት መክበብ ማማከል። ሦጠን እይ፤ የዚህ መንቲያ ነው

ወሣሪ መወሥር -የሚቈርጥ፤ የሚሠነጥቅ፤ ባለመጋዝ

ወሳኒ -(ኒት ንያን ያት) የሚወስን ወሳኝ፤ ሐጋጊ ደንጋጊ። ፈጣሬ አዝማን ወወሳኔ ዓመታት ወሳኔ ሀልዎታት ከመ ኢይትዐደዉ እምዘአዘዘ -(መጽ -ምስ አፈ -ድ፪)

ወሳይድ -(ዐረ ወሳኢድ) የራስ ድጋፍ ትራስ ብርኵማ መክዳ መጨጊያ። በወሳይድ ሜላት -(ዮሴፍ) ሥሩና ምንጩ ደየና ሰዐ ናቸው ኹለቱንም እይ

ወሳዲ -(ዲት ድያን ያት) የሚወስድ ወሳጅ ይዞ -() ኸያጅ።

ወሳጢ -ውሳጢ -(ጢት ያን ያት) የውስጥ፤ ውስጠኛ። አንቀጽ ውሳጢ። ዐጸድ ውሳጢ። ወውስተ ውሳጢትሰ። ውሳጢተ ጽርሕ መዛግብት ውሳጥያን አዕይንተ ልብነ ውሳጥያት -(ሕዝ፰ - -፫። ዕብ፱ - ፬ነገ - - ዜና -፳፰ -፲፩ ቅዳ -ኪዳ)

ወሥሮ ወሢር ሮት -(ወሠረ ይዌሥር ይወሥር ዕብ ናሣር ዐረ ነሸረ ወሸረ) መወሠር፤ መገዝገዝ መከርከር መቍረጥ፤ መሠንጠቅ መተርተር፤ በመጋዝ። ወሠረ ዕፀ ወሠርዎን በሞሠርተ ኀጺን ለፅኑሳት። ወሠሮ ለኢሳይያስ በምሠርተ ፅ። ወቦ እለ ወሠርዎሙ በሞሠርት -(ጥበ፲፫ -፲፩ ዓሞ፩ -፫። ዕር -ኢሳ፭ -፩። ዕብ፲፩ -፴፯)

ወስቆ ቆት -(ወሰቀ ይዌስቅ ይወስቅ፤ ዐሰቀ ዕብ ናሻቅ) መወሰቅ መለጠጥ መቀፈር፤ መሳብ መገተር ማለብ መደከር መደገን ማከናወን የቀስት የንዋየ ሐቅል መሰከን እይ የዚህ ወንድም ነው ወሰቀ ቀስቶ እለ ወሰቁ ቅስስቲሆሙ ወሰቁ ልሳኖሙ ከመ ቀስት ለሐሰት። ወይዌስቅ ቀስቶ -(ኩፉ -፴፰። ኤር፬ -፳፱ -፫። መዝ -፶፯ -)

ወስኖ ኖት -(ወሰነ ይዌስን ይወስን ዐረ ወዘነ መዘነ) መወሰን መደንገግ መቈረን መከለል፤ ማመልከት ምልክት ማድረግ የቦቃ የሕግ ወስን ሊተ መካነ ዘአኀድር ውስቴቱ ይዋስን በኆጻ። አኮ ጻሕቅከ ወትጋህከ በዓለም ዘይዌስከከ ምዘወሰነ ለከ ፈጣሪከ ወኢተሀክዮትከ ዘያሐጽጸከ እምዘዐቀመ ለከ። ሠርሁ ወወሰኑ በቀኖናሆሙ -(ስንክ -መጋ፳፯ ቅዳ -ግሩ ፈላስ -ገ፳፯ - -መቅ)

ወስኮ ኮት -(ወሰከ ይዌስክ ይወስክ ዐረ ወሸቀ ከመረ) መጨመር መደመር ማብዛት ትዌስኩ ኀጢአት በዲበ ጢአት። ጠቢብ ይዌስክ ጥበበ ባዕል ይዌስክ አዕርክተ ወወሰከ ዓዲ ፈሪሆቶ ለእግዚ -(ኢሳ፩ -፭። ምሳ፩ -፭። ፲፬ -፬። ጦቢ፲፬ -) ወሸቀ ወሰካ ወስኮ ወስከምት ማለት ከዚህ የወጣ ነው

ወረኃ በቁሙ እግረ ወንካራ ወይም እግረ ማጭድ እግሩ ለጋ ረቃ የሚመስል ቆም በመካከሉ ልጅ የሚያሾልክ (ዐማርኛ)

ወረስ ወረት -ገነዘብ ጥሪት ረጃት። ግብ ፍቅር እንደ ገንዘብ ንዱ ወዳንዱ ፈጥኖ የሚያልፍ። ወረታም ባለወረት ወረተኛ እንዲሉ

ወረረ -(ትግ ወዐም። ወሪር ወረ) በቁሙ፤ ዘረፈ በዘበዘ አደጋ ጣለ። -(ተረት) ጭር ምከር፤ ረዥም ውረር የቀን ወራሪ፤ የሌት ሰባሪ

ወረቀት -(ዐረ ወረቅ። ዕብ የሬቅ ቅጠል) ቁሙ ክርታስ መጣፊያ ሥሥ ደካማ ማርኛ በቀር በግእዝ ቃል ውስጥ አይገኝም

ወረየ -(ይወሪ ይረይ) አወራ አሳየ ገለጠ የነገር የምስጢር

ወሪስ ሶት -(ወረሰ ይወርስ ይረስ ዕብ ያራሽ ሱር ሬት ዐረ ወሪሰ ) መውረስ መውረት እጅ ማድረግ የሙትን ይዘታ ርስትና ገንዘብ በሟቹ ፈቃድ መውሰድ መያዝ ወይም ሳይሞት በግድ መቀማት፤ እንደ እስራኤል በእንተ ዘይወርስ ብእሲ እምብእሲቱ ወብእሲት እምብእሲሃ ንዋይ ብዙኅ ዘወረሰት እምታ ከመ ይረሳ ለምድርይወርስ ኵሎ መንግሥተ ምድር -( - -፵፪ -፫። ስንክ -ጳጕ፫ ቀሌ) በወረሰ ፈንታ ተወርሰ ይላል ሕተት ነው -(ኢያ፲፰ -)

ወሪቅ ቆት -(ወረቀ ይወርቅ ይረቅ ዕብ ያራቅ) መትፋት ትፍ ማለት፤ አፍ ምራቅ ማውጣት። ኢይትሀከዩ ወሪቀ ውስተ ገጽየ ኢይውርቅ ምራቆ። ምንት ዘኢወረቀ አባ መቃራ -(ኢዮ፴ - - -፲፪ ፊልክ -)

 -ቅጠል መኾን መርቀቅ መሣሣት፤ መወረቅ መወየብ ወርቅ የበሰለ ቅጠል መምሰል ረቀቀን እይ የዚህ ጎር ነው

ወሪእ ኦት -(ወርአ ይወርእ ይራእ ዐረ ወረ) መሰወር መደበቅ፤ መሸፈን መጋረድ የኀፍረት፤ ለሌላም ይኾናል

ወሪው ዎት -(ወረወ ይዌሩ ይውሩ። ዕብ ያራህ) መወርወር መጣል ማሽቀንጠር ወሪወ እብን ይዌርዉ አልባሲሆሙ ትዌርዎሙ ማእከለ ሳት። እዌሩ ላዕሌሆሙ መሥገርትየ ወረወ ነፍሶ እመልዕልተ ዓሌ ወሞተ -(መኮ፫ -፭። ግብ፳፪ -፳፫። ሕዝ፭ -፬። ሆሴ፯ -፲፪ ዮሴፍ)

ወሪዝ ዞት -(ወረዘ ይወርዝ ይረዝ) መወርዛት መርጠብ የሸክላ የግንብ።

ወሪድ ዶት -(ወረደ ይወርድ ረድ ዐረብ። ዕብ ያራድ) መውረድ መቈልቈል፤ ከላይ ወደ ታች መውደቅ ዝነም መፍሰስ እምና ውስተ ዲበ ላዕለ ይሰማሙታል። ጐንደየ ወሪደ እምደብር ወረደ እምሰማይ። ረድ መስቀልከ አኀ ማይ ይረድ ውስተ ቀላይ። ወረደ ዕፃ ላዕለ ዮናስ። ፍርሀት ወረዓድ ወረደ ላዕሌሁ -(ዘፀ፴፪ -፩። ማቴ፳፰ -፪። ማር፲፭ -፴። -፭። ዮና፩ -፯። ሉቃ፩ -፲፪)

 -መዋረድ፤ ትሑት መኾን መጽሐፍ ግን በወረደ ፈንታ ተወርደ ተወረደ ተዋረደ ይላል አያሰኝም ያማርኛ ነው ተወርዶቱ ለእግዚ ዊነ ሰብእ ቀሲስ ብዉሕ ሎቱ ከመ ይትወረድ መልእክተ ካህናት እለ ምታሕቴሁ። ነቢያትኒ ይትዌረዱ በዓል። ፍትወተ ነፍላ ትትዌረድ ጽርኬ ዘከመ እፎ ይትዋረድ ርኢከኑ ዝንቱ ሕገ ተዋርዶ ወለት እን ይትዋረዳ ጋኔን -(መጽ -ምስ ኤር፪ - -፳፬ አፈ -ድ፪ -፰። ግብ፲፮ -፲፯) እንደ ዘንመ ዐጕ ስለ ኾነ ሌላ ተገብሮ የለውም

ወራሲ -(ሲት ስያን ያት) የሚወርስ ወራሽ ዋርሳ ዘረሰዮ ወራሴ ለኵሉ ወራሲ ጠባይዓዊ ብእሲት ዘትወልድ ወራሴ ወራስያኒሃ ምድረ ሕያዋን ወራስያነ ክብር -(ዕብ፩ -፪። - -፵፪ -፫። ሢራ፳፫ - ቀሌ ዮሴፍ) በወራሲ ፈንታ ዋርስ ይላል -(ማቴ፳፩ -፴፰። ስንክ -ኀዳ፴)

ወራዊ -(ዊት ውያን ያት ረውት) የሚወረውር ወርዋሪወራዌ ረምሕ -(ፊልክ -፪፻፰)

ወራውሬ -እብነ በረድ፤ ነጭ ደንጊያ። ብነ ክቡረ ወዕንቈ ወራውሬ ብዙኀ -(፩ዜና -፳፱ -)

ወራውር -ውርወራ የወንጭፍ ደንጊያ፤ መርግ ናደት

ወራዪ -ወሬኛ አውሪ ወሬ ነጋሪ

ወራዲ -(ዲት ድያን ያት) ሚወርድ ወራጅ ፈሳሽ፤ የሚዋረድ ተዋራጅ።

ወሬ -በቁሙ -(ዐማርኛ)

ወሬዛ -( ወራዝው ወራዙት) ልማሳ ጐበዝ ለጋ ወጣት ሶባ ሦታ ካሥራምስት ዓመት በላይ ያለ ለዘር የበቃ ለማልሞ ሪዘ ቀምቀሞ  ወሬዛ ወሕፃን ልሂቅ ወወሬዛ ወልድ ወሬዛ ወሬዛ ሀየል ወራዙትኒ ወደናግል -(፩ዜና -፳፬ -፩። ሕዝ፬ -፮። ዳን፩ -፵፭። ማሕ፪ -፱። መዝ -፻፵፰)

ወሬዛዊ -ዝኒ ከማሁ። ወሬዛዊት ድንግል -( - -)

ወርኃዊ -ወረኛ ወራተኛ ወረተኛ የሚያልፍ። በየወሩ ጨረቃ ሲወጣ የሚጥል ጋኔን ወርኃውያን -(ማቴ፬ -፳፬) የጨረቃ ቍጥር። ወርኅ ወርኃዊ። ዓመት ወርኃዊ -(አቡሻ)

ወርኅ -( አውራኅ ኃት። ዕብ ያሬሐ ዬራሕ ሱር ያርሓ) ጨረቃ የፀሓይ ታናሽ ፀሓይኒ ይጸልም ወወርኅኒ ይሁብ ብርሃኖ የሐጽጽ ልቡ ከመ ወርኅ ወርኅ ምልእት ሠርቀ ወርኅ -(ማቴ፳፬ -፳፱ ሢራ፳፯ -፲፩ -፮። ኢሳ፩ -፲፬)

 -በቁሙ፤ የጨረቃ ወር ተወልዳ ጠፍ እስክትኾን የምታበራው ፳፱ ቀን ፲፪ ሰዓት ፯፻፺፫ ክፍል። የክፍሉ መጠን እጅግ ስላነሰ ክፍል ሴኮንድ ፲፰ ክፍል ደቂቃ ነው ፻፺፫ቱ ፍል ፵፬  ደቃይቅ ኹኖ ክፍል ይተርፋል ከ፹ው ክፍል ደቂቃ ወይም ዓት ይኾናል። የፀሓይ ወር ሲኾን ቀን ነው ሕጸጽ የለበትም። ዝንቱ ወርኅ ይኩንክሙ ቀዳማየ አውራኅ። ዐሠርቱ ወክልኤቱ ወርኅ በአውራኅ እሙራት ወርኅ ወርኃዊ ወርኅ ፀሓያዊ። ኵሎን ውራኅ -(ዘፀ፲፪  ፪። ዳን፬ -፳፮። ሔኖ፸፰ -፱። አቡሻ -፫። - -፴፮)

 -ጊዜ ዘመን ወራት። ወበጽሐ ወርኃ ለኤልሳቤጥ በወርኀ ቀላውዴዎስ። ዘመነ መንሱት ወወርኀ ተከውሶ። በወርኀ ምግቡ ለያሬድ -(ሉቃ፩ -፶፯። ስንክ -ሚያ፲፭ -፳፪ ጥበ -)

ወርቃዊ -ወርቃም ባለወርቅ፤ ወርቅማ ወርቅ የሚመስል የወርቅ ዐይነት ጥር ሚዛን። ልቍ ወርቃዊ -(አዋል)

ወርቅ -በቁሙ ከማዕደን ኹሉ የሚበልጥ ልዩ ክቡር ገንዘብ ሕብሩ ብጫ ቀይ ሐመልሚል አንጥረኞችና ጃን ሸላሞች ሌሎች ንዋያትን ርሱ ለማስጌጥ ለመለበጥ እንደ ቀለም በላይ የሚቀቡትና የሚያፈሱት፤ እንደ ወረቀት የሚያሣሡት ስለ መልኩና ስለ ግብሩ ስሙን ቅጠል ወስዷል። ወረቅ የገንዘብ ኹሉ ራስ ስለ ኾነ ማኅተመ ንጉሥ ያለበ መዳቡም ብሩም ማናቸውም ኹሉ በርሱ  በመክብቡ ስም ወርቅ ይባላል ወርቀ ጥ። ደፈነ ወርቀ እግዚኡ ወሀብዎሙ ብዙኀ ወርቀ ሠገራት ብር ገንዘብ ማለት ነው -(ዘሌ፳፭ -፶። ማቴ፳፭ -፲፰ ፳፰ -፲፪)

ወርዘወ -(ተቀ ) ጐለ() መሰ አደገ ጐበዘ ሪዝ አወጣ አቀመቀመ ጸና በረታ ልሕቀ በበ ሕቅ ወወርዘወ በአምጣነ ብእሲ ወርዘውኩሂ ወረሣእኩ። አመ ወርዘወ። ጽናዕ ወውርዚ በእንተ ሕዝበ ዚኣነ -(መጽ -ምስ መዝ -፴፮። ገድ -ሊ። ፩ዜና -፲፱ -፲፫) በመርዘወ ፈንታ ተወርዘወ ይላል፤ አያሰኝም። ላዕለ ሞት ተወርዘወ ንዘ ይትወረዘው በኀይለ መንፈስ ቅዱስ -(ድጓ ገድ -ተክ)

ወርድ -(ዐረ ዐርድ) በቁሙ፤ ስፋ ርሕብ ጐን ወይኩን ዐጽፍ ዘእመት ኑኁ ወእመት ወርዱ -(ዘፀ፳፰ -፲፮ - -፴፩ -) ወረዳ አውራጃ -(ዐማርኛ)

ወቀሰ -ቁሙወቂሥ ወቀሠ

ወቀፈ -(ዐረ) ቆመ የሐቀፈ ሞክሼና መንቲያ ሐቀፈን እይ

ወቂሕ ሖት -(ወቅሐ ይወቅሕ ይቃሕ ዐረ ) ማጥበቅ ማስተሳሰር ራኘት፤ ማቋለፍ ላለፍ። መጽሐፍ በወቅሐ ፈንታ ሞቅሐ ይላል ወገደንና ወገሰን ወን እይ አካዳቸው ከዚህ ጋራ ነው

ወቂሥ ሦት -(ወቀሠ ይወቅሥ ይውቅሥ፤ አው ይቀሥ) መውቀሥ መክ መንቀፍ መዝለፍ መገሠጽ መምከር፤ መንገር መናገር ቃልን ማፍሰስ መዘርዘር ምንተ ንብል ወምንተ ንወቅሥ አኀዘ ይውቅሣ -(ይቀሣ) ልብነ በዘንወቅሥ በእንተ ሀከክ ፈቀደ ይውቅሥ ለዐውድ። እወቅሥ ጽድቀኪ ወተግባረኪ -(ኩፋ -፵፫። ዮሴፍ ግብ፲፱ - -፴፫ - ኢሳ፶፯ -፲፪)

ወቂር ሮት -(ወቀረ ይወቀር ይቀር። ዐረብ) መውቀር ማለዘብ፤ መቈፈር ጥረብ የደንጊያ የገደል የዋሻ የጕድጓድ። ወቀረ ውስተ ኰኵሕ ግበበ ብዙኃነ ዘይወቅርሂ ወዘይጸርብ ንዘ ይወቅር ረከበ አእባነ ወርቅ ርእይዋ ለኰኵሕ እንተ ወቀርክሙ መካን ዘወቀረ ሎቱ። ቀር ለከ ክልኤ ጽላተ ዘእብን -(፪ዜና -፳፮ - ገድ ላሊ። ስንክ -ግን፰ ኢሳ፶፩ -፩። ጥበ፲፫ -፲፭። ዘፀ፴፬ -) ማዋቀር መቋጠር በግንብ በግድግዳ ጣራ ባጥ መሥራት

ወቂዕ ዖት -(ወቅዐ ይወቅዕ ይቃዕ ዐረ ወቀዐ) መውቃት መምታት መደብደብ በሙቃዕ ይወቅዕዎ -(ኢሳ፳፰ -፳፯)

 -መግፈፍ መላጥ ወይወቅዕዎ ወይፈልጡ መለያልዮ ዘዘ ዚኣሁ -(ዘሌ፩ -) ቈርበቱን ከሥጋው ለመለየት እግሩን ሠንብጠው በታናሽ ሸንበቆ እየነፉ ይመቱታልና፤ ዘይቤው ውቂያን አይለቅም አንዳንድ መጣፍ ወይወቅይዎ ይላል ማረድ ማወራረድን መቍረጥ መከትከትን ያሳያል፤ ምስጢሩ ዚያው አይወጣም።

ወቃሢ -(ሢት ሥያን ያት) የሚወቅሥ ወቃሽ ከሳሽወቃሥያን ንበለ ፍትሕ ዕለ ወቃሢ ደሉ አቅሞተ ሰማዕት -(መቃ -ገ፬ - -፵፱)

ወቃሪ -(ሪት ርያን ያት ቀርት) በቁሙ የሚወቅር የሚያዋቅር ራቢ ወቀርተ እእብን ወፈሐቅት -(፩ዜና -፳፪ - ፪ነገ - -፲፩)

ወቃዒ -(ዒት ዕያን ያት፤ ) የሚወቃ ወቂ ነፊ ገፋፊ

ወቄት -( አውቅያት ዐረ ወቂየት) በቁሙ፤ የሚዛን ስም የልጥር ፲፪ኛ ንዱ ወቄት ድሪም፤ አላዱ ወይም እኩሌታው ድሪም ይኾናል ልጥርን እይ ወኮነ ሕልቅ ሠላሳ አሞሌ ወወቄት ለአሐዱ ብዕራይ ወብየ አውቅያተ ወርቅ -(ሥር -አኵ። ፈላስ)

ወቅት -( አውቃት ዐረብ) ጊዜ ወራት ዓመታት ወአውቃት -(ስንክ -ግን፳፫)

ወቅይ ዮት -(ወቀየ ይወቂ ይቀይ ዐረ ወቀይ) መጠበቅ፤ መወባበቅ ድውይን በጊዜ ሞት። ከመ ይናዝዝዎ ወይወቅይዎ ፍልሰቶ -(ስንክ -ጥቅ፳)

 -መቍረጥ መቀርጠፍ፤ መቅጨት መዘለፍ  ወቅዐን እይ የዚህ ጎር ነው። መጽሐፍ ግን በወቀየ ፈንታ አውቀየ ይላል አያሰኝም። ኢያወቅዮ ርእሶ ወቂ ቍልፈተ ልቦሙ ውቀዮ ሣዶ በአሐቲ ዝበጠት። አዘዘ ያውቅዩ ልሳና ምጕንዱ -(ዘሌ፭ -፰። -፩። መቃ -ገ፯ ስንክ -መስ፯ ሮሜ፲፩ -፳፪)

ወቅፍ -( አውቃፍ ፋት ዐረብ) አንባር ቀለበት እጅን ጣትን ዐቅፎና ከቦ የሚይዝ ቀዋሚ የእጅ ጌጥ ኢኀሠሣ ውቃፈ ብሩር ወወርቅ ለስርጋዌሆን ወደይኩ አውቃፋተ ውስተ እደውኪ። ርባዕቱ አውቃፋት -(ደራሲ ሕዝ፲፮ -፲፩  ዘፀ፴፯ -፲፫)

ወባ -(ዐረ ወባእ) የበሽታ ም፤ ክፉ ሽታ የሚመጣ በሽታ ምክንያት የሚጋባ እንደ ጕንፋን ያለ በቁሙ ወባ፤ ንዳድ። ሕማመ ወባ -(ዮሴፍ)

ወቦ [1]-ስመ ስመ ጭፍራ። ወቦና በቾ እንዲሉ

[2]-( ) ወቦ -(ወቢብ ወበ፤ ነጠቀ) ያውሬ የነብርና ያንበሳ ዲቃላ ወቦ ሸማኔ እንዲሉ። ኹሉም ዐማርኛ ነው

ወተር -( አውታር ዕብ የቴር ሱር ያትራ ዐረ ወተር) ቁሙ፤ ዥማት መድ የክራር የበገና የደጋን የድንኳን። ቃለ ውታረ መሰንቆ መዝሙር ዘዐሠርቱ አውታሪሁ ሰሩኒ በሰብዐቱ አውታር ሐዳሳት እለ ልቦሙ ብትከት -(ቀሌ። መዝ - መሳ፲፮ -)

ወተት -(ዐማርኛ) ቁሙ ሊብ -(ተረት) የረጋ ወተት ቅቤ ይወጣዋል።

ወተን አውታን -(ዐረብ) ጣዖት የጣዖት ስም ቀይጡነ ውታን -(አቡሻ -)

()          ወተገ -(ይዌትግ ይወትግ፤ ወትጎ ነትገ) ሸሸ በለለ ተሰደደ እለ ወተጉ እም ሞአብ ወተገ ኵሉ በሓውርት -(ኢሳ፲ -፬። ኤር፬ -፳፱) ባለቅኔዎች ግን ቀማ ይሉታል

ወተፈ -(ትግ -ወዐም) በቁሙ ዘጋ ደፈነ አጐረሠ

ወቲር ሮት -(ወተረ ይወትር ይተር) መወ() ተር መገተር፤ ሳብ መዘርጋት። ወተረ ቀስቶ -(ዕን፫ -፱። መዝ -)

 -መትኰር፤ ማዘውተር የዐይን የኅሊና ማብዛት መደጋገም፤ መመላለስ። መውደድ ማሰብ። መጽሐፍ ግን በወተረ ፈንታ አውተረ ይላል፤ አያሰኝም። ታውትር እዴከ ዘኢኮነት እንቲኣከ፤ ዘረጋ -(ምሳ፭ -) ወትር አዕይንትየ ላዕሌሆሙ። ኢታውትር ይነከ ቤሃ። ዘያወትር አዕይንቲሁ ይኄሊ ጠዋየ እመ አውተርከ ዐይነከ ቤሁ ተኰረ -(ዓሞ፱ -፬። ምሳ፱ -፲፰ ፲፮ -፴። ፳፫ -) ውተረ ጸልዮ ውትሮ ጸሎት ጳውሎስ ኢያውተረ ነጊረ ትሕትናሁ፤ አበዛ -(ሉቃ፳፪ -፵፬። አፈ -ተ፱ ድ፪) ኤልያስ ኮነ ያወትር ህድአተ ወብሕታዌ ንዘ ያወትራ ይሕየዋ በንጽሕ ታውትር ስማዔ ወደደ -(ፊልክ -፩። ፲፩ ፪፻፵፪)

ወቲት ቶት -(ወተ ወተተ ይወትት ይተት) ማውተት መዋተት፤ አውታታ ከርታታ መኾን ወተተ ማለት ከወተትና ውሃ ካገፋፉ ካጐራረፉ የወጣ ነው ፪ኛም ወትወተ ብሎ ወተወተ ማለት ከዚህ ይወጣል፤ ኹሉም ዐማርኛ ነው

ወትር ወትረ -ዘልፍ ዘልፈ ወትሮ ዘወትር፤ ዕለት ዕለት በየቀኑ። ፍርየታ ዘወትር። ሀበነ ዘወትር ጸሎተነ ዘወትረ ይሴብሑ። በከመ ልማድ ዘወትር ወትረ ይጌሥጽ ወትረ በኵሉ ወበኵሉ ሰዓት -(ዘፀ፳፱ -፴፰። ኪዳ አፈ -ድ፲፮ ምሳ፲፫ -፳፬ ድጓ)

ወናግ -(ሐረር) አንበሳ ወናን ሰገድ ዘውእቱ ሚናስ -(ታሪ -ነገ) ስምነቱ፤ ወንጎ ወነገ ከማለት ከሩዛቤ ሥጋ ካራዊት እሮት የወጣ ነው

ወንጌላዊ [1]-የወንጌል መምር፤ ባኪ ጸሓፊ እማኒ፤ ክርስቲያን ማቴዎስ ወንጌላዊ። ርባዕቱ ወንጌላውያን ዘወንጌላውያን ትምህርት። ሃይማኖት ወንጌላዊት። ጸሎት ወንጌላዊት -(ቅዳ ቄር አፈ -ድ፴፩ ፊልክ -፻፸፩)

[2]-ወንጀለኛ ባለወንጀል። ወንገለ ወነጀለ።

ወንጌል [1]-(ትግሬ) ወንጀል ልወት በደል ጥፋት ክፋት ነውር

[2]-ወንጌል፤ -(ላት ጽር ሄዋንጌሊዎን ዐረ ኢንጂል) በቁሙ፤ብሥራት ምሥራች ዲስ ዜና መልካም ወሬ፤ ደስ የሚያሰኝ ስብከት አምላካዊ ሰማያዊ ነገር፤ ምስጢረ ሥላሴ ምስጢረ ሥጋዌ ወንጌል ብሂል በልሳነ ጽርእ ወትርጓሜሁ ስብከት ወይሰበክ ወንጌለ መንግሥት ውስተ ኵሉ ጽናፈ ዓለም -(መቅ -ወን ማቴ፳፬ -፲፬)

 -መጽሐፍ የመጽሐፍ ስም፤ የሐዲስ ኪዳን መጽሐፍ፤ እንደ ነገሥት ክፍል ያለው ሰዎች የጣፉት፤ ፍችው ያው ብሥራት ነው በከመ ይቤ ወንጌል ቅዱስ። አርባዕቱ መጻሕፍተ ወንጌል ዘሊየአምር ገረ መጻሕፍት ወፈድፋደሰ ርባዕተ ወንጌላተ -(ስንክ -ኔ፳፬ - - -፬። )

ወዓሊ -(ሊት ልያን ያት ዐልት) የሚውል ሙያተኛ ሎሌ አሽክር ወታደር ወዓሊ ዘምስሌየ እምተባአሱ ሊተ ወዓልያንየ ይጸውርዎ ወዐልት -(ፊልጵ፪ -፳፭ ዮሐ፲፰ -፴፮። ግብ፳፩ -፴፭)

ወዓሪ መውዕር -የሚሻክ ሸካራ። ድናቂ አዳናቂ።

ወዓዪ -(ዪት ይያን ያት) የሚነድ የሚቃጠል፤ ተቃጣይ

ወዕር -(ዐረ ያዓር) ዱር ገደል ደንጊያማ ድን ሰንከልካ ቦታ የማይደርበት። መጽሐፍ በወ ፈንታ ወር ይላል ወእምዝ ፅኡ በሌ ምይ ደብር እን ምሩ ፍኖ ወበጽሑ ውስተ ወርዕ፤ እን ፍኖተ -(ገድ -ኪሮ)

ወዕደ -ወደ ዘንድወእደ።

ወእደ ውእደ -(እድ ወእድ) ዐቢይና ደቂቅ አገባብ። ዘንድ ቅጽል ወእደ አልቦ አልሕምት ምፅንጋዕ ንጹሕ ላሞች ሌሉ፤ ተሌሉ ዘንድ ወይም ተሌሉበት ዘንድ ምኔት ውእደ ለሊ ይነብር የሚኖርበት ወመጽኦ ቤሃ አሐዱ ወሬዛ እምወእደ ይትኀባእ ተደበቀበት -(ምሳ፲፬ - ሥር -ጳኵ ዳን፩ -፴፯። -(ዕር፲፱ -ቍ፸)

 -ደቂቅ ሲኾን ወደ አጠገብ ይኾናል ወደ ወዴት ማለት ዐማርኛው ዚህ ወጥቷል እቱ ውእደ ሕዝብከ ወደ። በውእደ ማየ ባሕር አጠገ -(ኩፋ -) ኀበና መንገለም እንደዚሁ ናቸው አደወ ነውና የእድን አፈታት ተመል

ወከተ -(ወክሐ) ጮኸ ተንጫጫ አወካ ውካታ አደረገ፤ ግር ግር አለ። መጽሐፍ ግን በወከተ ፈንታ አውከተ ይላል ወአዘዞሙ ለሕዝብ ከመ ኢያውክቱ -(ኢያ፮ -)

ወኪብ ቦት -(ወከበ ይወክብ ይከብ ዐረ ወከበ) መትጋት መቸኰል፤ ማዘውተር፤ መሩት እስኪፈጸም ድረስ አለማቋረጥ ወይም ሌላ ሥራ ጣልቃ አለማግባት። በኢወኪቦቶሙ -(ዕር -ኢሳ፫ -፳፬)

ወኪዕ ዖት -(ወክዐ ይወክዕ ይካዕ ዕብ ያጋዕ) መድከም መታከት፤ በሥራ ብዛት ከዐወን እይ የዚህ ጎር ነው

ወኪክ ኮት -(ወከ፤ ወከከ ይወክክ ይውክክ ይከክ) መውከክ ወከክ ማለት ደንገጥ መፍራት፤ ማፈግፈግ መራቅ ወደ ኋላ ማለት። መሳት መሳሳት፤ የማያውቁትን ደፍሮ መናገር መቀባጠር። መጽሐፍ ግን በወከከ ፈንታ አውከከ ይላል ውከኩ እምሃይማኖት ውከኩ ምጽድቅ -(፩ጢሞ - -፮። ፪ጢሞ - -፲፰)

ወኪፍ ፎት -(ወከፈ ይዌክፍ ይከፍ) ማውከፍ እጅ በጅ መስጠት ማቀበል ማሲያዝ ማስጨበጥ፤ ማቅረብ ማስረከብ። መጽሐፍ ግን በወከፈ ፈንታ አውከፈ ይላል ያሰኝም ልዕ በዘያወክፉ ኅዳጠ አውከፉ አይሁድ ላዕሌሆሙ ወለዘርዖሙ ኢይፍልሱ ወአውከፈት አንብዐ ወለታ -(ኢሳ፴ -፲፬ አስቴ፬ -፳፯ -፲፮) ካፍን እይ የዚህ ዘር ነው።

ወክሕ -ወክሕ፤ ውካታ ድንፋታ፤ ጩኸት ፍጅት ክርክር ሙግት ወክሕ ብዙኅ። መሐደምት ወወክሕ -(ዕር -ኢሳ፫ -፳፪ ቲቶ፫ -)

 -ተግሣጽ ስብከት ኀይለ ቃል። ዮሐንስ አህድአ እምካልኣኒሁ አንኀ ወክሐ፤ እን ይብል ምላዕሉ ወረደ ቃለ -(ድጓ)

()          ወክሖ ሖት -(ወክሐ ይዌክሕ ይወክሕ። ዕብ ያካሕ) ማውካት ወካዎ ወኮ ማለት ማቅራራት መደንፋት፤ መጮኽ መድረቅረቅ መፈከር መንደቅደቅ። ይዌክሑ ወይዌውዑ ኵሉ ሰራዊተ መንግሥት -(ሥር -አኵ) ወከተን እይ የዚህ መንቲያ ነው

ወክሎ ሎት -(ወከለ ይዌክል ይወክል። ዐረ ወከለ) መወከል ወኪል ጠበቃ ማድረግ ምኖ መሾም እንደራሴ ማለት ተከለን እይ የዚህ ጎር ነው

ወክአ -ደከመወኪዕ ወክዐ

ወውዖ ዖት -(ወውዐ ይዌውዕ ይወውዕ ዐረ ወዕውዐ) መጮኽ ማውካት መደንፋት፤ እልል ማለት። ወውዐ በዐቢይ ቃል ወውዑ ዕሌሁ። ይዌውዕ ዲበ ፀሩ። ወውዐ ሎቱ ቢሳ ወውዑ ኵሉ ሕዝብ -(ዳን፲፫ -፲፰ ኤር፪ -፲፭ ኢሳ፵፪ -፲፫ ፪ነገ -፳፩ -፲፯። ዮዲ፲፬ -)

ወዎ -(ዐማርኛ) ደጀን የኋላ ጦር የፊታውራሪ አንጻር። ወዎነት ሾመ እንዲሉ።

ወዘረ -(ዐረብ) ለበጠ ሸለመ አስጌጠ የሕንጻ ወወዘሩ ድቀ ማኅፈድ በዕፅ

 -ወየዘረ ሾመ አከበረ ራስ ቢትወደድ አደረገ መጽሐፍ ግን በወዘረ ፈንታ አስተውዘረ ይላል ስመ አክሳይሮስ ስተውዘረ ብእሴ ዘይብልዎ ሀማን -(ዮሴፍ)

ወዘነ -መዘነሚዛን መዝኖ መዘነ

ወዚር -ወይዘር ታላቅ መኰንን ራስ ትወደድ ባለሟል። ሶበ ትሠይመ ሀማን ወዚረ ለአክሳይሮስ -(ዮሴፍ) ተወዘረ ማለት ከዚህ ወጥቷል

ወዚዝ -(ወዘ ወዘዘ ወዝወዘ) ቁሙ ዐማርኛ

ወዚፍ ፎት -(ወዘፈ ይወዝፍ ይዘፍ ሱር ያዛፍ፤ ተለወጠ) ማጌጥ፤ መለወጥ ሌላ መልክ ማውጣት። መጽሐፍ ግን በወዘፈ ፈንታ ተወዝፈ ይላል። እምተወዝፎቱኒ -(አዋል) በቁሙ መወዘፍ ማስቀመጥ ማስቀረት ውዝፍ እንዲሉ።

ወዜመ -(ይወዘይም ይወዚም) ወዘመ ዋዜማ ቆመ ዜማ መረ ከዋይ የመጣ ዕድ ዘር ነው ነቀወ ብሎ በአንቀወ ፈንታ ንቀወ እንዲል፤ ይህም እንደዚያ ነው

ወይ [1]-(ዐረ -ዋእ ወይ ሱር ዋይ ዕብ ኦይ) ንኡስ አገባብ። በቁሙ ወዮ ወየው፤ ዋይ ውይ አወይ የልቅሶ የሐዘን የቍጣ የንደት የብስጭት ቃል ነው ወይ ሊተ ወይ ልየ ወይ ለከ እያለ እንደ አሌ በለ ይዘምታል። ኢይብልዎ ወይ አግዚእየ ወይ እኁየ -(ኤር፳፪ -፲፰) አሌንና ሰይን ተመልከት የዚህ ጎሮች ናቸው

[2]-ወይ -(ዐማርኛ) በቁሙ -(ዋዌ አው) የማማረጥ ቃል አውን እይ -(ግጥም ሐፄ ባሏን የሰቀሉባት) ወይ አልተቀደሰ የባረኩት ሰው ንጉሥ መስቀልዎን ቢተዉት ምነው ፪ኛም የምኞትና የፍላጎት የአንክሮ ቃል ይኾናል፤ -(ግጥምና ሙሾ ስለ ጐንደር ጥፋት) ቴዎድሮስ መጣ ዐይኑን አፍጦ፤ ወይ መሸሸጊያ ታናሽ ቍጥቋጦ። ተከተለኝ ብዬ ዙሬ ዙሬ ሳይ ወይ ጥጋብ ወይ ራት ጐንደር ቀረ ወይ ኛም ያቤቱታ ቃል የጥሪ ተሰጦ ይኾናል -(ግጥም፤ የበለው እኅት ተማርካ በመተማ ሳለች) ጐዣም አፋፉ ላይ የሚጣራው ማነው ወንድሜ እንደ ኾነ ወይ በለው ወይ በለው ምስጢሩ እንደ ላይኛው ነው ኛም የጥያቄ ቃል ይኾናል ኼደ ወይ መጣ ወይ

ወይለየ -ጩኾ አለቀሰ ዋይ ዋይ ውይ ውይ ወይለይ ወይ ልየ አለ

ወይሌ -(ዐረ ወይል። ሮማ ዋየል ድምፅ) ወይ ሊተ አደጋ መቅሠፍት ድንገተኛ ሞት ሐዘን መርዶ ልቅሶ ዋይታ ዋይ ዋይ ማለት የልቅሶ ጩኸት። ወይሌ በዲበ ወይሌ ወይሌ ዕለ ናባው ለመኑ ወይሌ ወለመኑ ሀከክ ኢሳይያስ ነቢይ ይሁቦሙ ወይሌ ሰካርያን ወይቤ አሌ ሎሙ -(ሕዝ፯ -፳፮ ኤር፴፩ -፩። ምሳ፳፫ -፳፬። - -)

ወይል -ስመ ዕፅ፤ ሕፃናት የጠመንዣ ዕንጨት የሚሉት ርበቱብ እንደ ጅና አውጥተው ንጨቱ ጫፍ ቈርጠው እንደ ቡሽ ወቅፈው ባንድ ወገን ሲገፋት እንደ ቢራና እንደ ሻፓኝ ቅዛዝ የሚል የሚፈነዳ

ወይን -( አውያን ዕብ ያይን ዐረ ወይን ጠጅ) በቁሙ የተክል ዕንጨት ሐረጋም፤ ፍሬው ከንጨት ኹሉ ፍሬ የሚከብር ጠጅና ዐረቂ የሚኾን በግእዝና ባማርኛ ከሥር እስከ ጫፉ ዕንጨቱም ፍሬውም ሳይቀር ኹለንተናው ኹሉ ወይን ተብሎ ባንድ ስም ይጠራል በዐረብና በዕብራይስጥ ግን ወይን የሚባል ብቻ ነው። ተከሉ ወይነ ልቦ ስካል ውስተ ወይን አውያን ጸገዩ። ገብረ ወይነ ምፍሬ። ወይን ዘግቡር በእሳት፤ -(መዝ -፻፮ ኤር፰ - ማሕ፪ -፲፫ ኩፋ -፯። ብጥ -) ወያኔ ማለት ከዚህ የወጣ ስም ይመስላል።

ወይጠል -(ላት) ፌቆ የፌቆ ወገን የበረሓ እንስሳ።ዶርቃስንና ጣቢታን እይ ከዚህ ጋራ አንድ ነው። ወይጠል ወቶራ ወሀየላት። ወይጣላት -(መቃ -ገ፭ ሥር ጳኵ)

ወይጦ -ስመ ነገድ፤ በጣና ዙሪያ የሚኖር ጕማሬ የባሕር አውሬ የሚያድን

ወደብ -(ዐማርኛ) ቁሙ የባሕር ጠረፍ በር መግቢያ የመርከብ መቋሚያ

ወደፈ -(ወፀፈ) ጣለ ወረወረ አሽቀነጠረ የማይረባን ነገር

ወዲር -(ወደረ ይወድር ይደር) መወደር፤ መወዳደር -(ዐማርኛ)

ወዲቅ ቆት -(ወድቀ ይወድቅ ይደቅ። ዐረ -ወደቀ) መውደቅ -(ጥጣ) መጣል፤ ድንገት ከላይ ወደ ታች መውረድ እንደ ዝናም ወይም ከቁም በምድር ላይ መደፋት፤ ፍግም ማለት ወዲቅ እመካናት ልዑላት። ወድቀ ምሰማይ። ዳይ ለእ ወድቀ ይከይድዎ ቢጹ። ወድቁ በገጾሙ -(ፊልክ -፻፸፪። ኢሳ፲፬ -፲፪ ራ፲፫ -፳፩። ማቴ፲፯ -)

 -መግባት መያዝ። ይወድቁ ውስተ ግብ። ከመ ትደቅ ውስተ መሥገርታ በኵሉ ወደቀ ኢትደቅ ውስተ እደ ጸላእትከ -(ማቴ፲፭ -፲፬ ራ፬ -፫። ፳፭ -፲፬)

 -መፍረስ መናድ ድል መኾን በጦርነት መሞት ጥቅም ወአረፍት ዘወድቀ ወወድቁ ምደቂቀ ብንያም ልፍ ወሰማንያ ምእት ሣልስትኪ ይወድቁ በኵናት -(ኩፋ -፵፮። መሳ፳ -፵፬። ሕዝ፭ -፲፪)

 -መተኛት መጋደም፤ መጣመር ወይም መከመር የዝሙት ዘወድቀ ዐርክ ምስለ ዐርክቱ ዘይወድቅ ምስለ ብእሲት። ብእሲ ዘቦቱ ብእሲት ወወድቀ ዕለ ብእሲ ተባዕት ዘወድቀ በእንስሳ -(ቄድር። ሲኖዶ)

 -መስገድ መንበርከክ፤ በግንባር መተክል ምድርን በአፍ መሳም ወድቀ አብራም በገጹ ወድቁ ወሰገዱ ሎቱ ወድቀ ወአስተብቍዖ -(ዘፍ፲፰ ፬። ማቴ፪ -፲፩ ፲፰ -፳፮)

 -ማዘን መፍራት ማቀርቀር ዐንገትን መድፋት ምንት ይወድቅ ገጽከ ኢይደቅ ልቡ ለእግዚእየ -(ዘፍ፬ -፮። ፩ነገ -፲፯ -፴፪)

 -መሻር መዋረድ ከሹመት ከክብር መውጣት መለየት። ይደቅ እምሢመቱ ይደቅ እማዕርጊሁ። ወድቀት እምክብራ። ወደቅሙ እምጸጋሁ -(አብጥ -፭። - - -፩። ቀሌ ገላ፭ -) በወድቀ ፈንታ ተወድቀ ተዋደቀ ይላል ሕተት ቈጽለ ኃት ኢይትወደቅ ዘእንበለ ፈቃድየ ሶበ ቀሠፍዎ ሥጋሁ ተበጽለ እስከ ተዋደቀ በበ ክፍል ክፍለ -(ቀሌ ነክ -ሐም፳፭)

ወዲድ ዶት -(ወደ ወደደ ይወድድ ይደድ) መውደድ ማፍቀር ማግባት መጨመር አንዱን ባንዱ ውስጥ ወይም በመካከል እንደ ሳጋ እንደ ሽብልቅ እንደ ስሯጽና እንደ ዚቅ ወደየን ተመልከት የዚህ መንቲያ ነው

ወዲፈት -( ወዲፋት) ዕላቂ ውዳቂ ርቅ ረንጮ ቅርንጥስ ባለብሉዮች ግን ያልተከለሰ ማቅ ዳውዣ ይሉታል። ወይጠበልልዎ በወዲፈት። ዘእንበለ ወዲፈት ወአነዳ ላሕም -(ኤር፳፪ -፲፱ ገድ -ተክ)

ወዳሲ መወድስ -የሚያወድስ አወዳሽ አመስጋኝ ገጣሚ ባለቅኔ

ወዳኢ መወድእ -የሚርስ ራሽ ፈጻሚ ከታች

ወዳዪ -(ዪት ይያን ያት፤ ደይት) ጨማሪ ነገረ ሠሪ፤ ክፉ አድራጊ ወዳዬ እከይ ወጽልእ ማእከለ ሰብእ -(ሲኖዶ)

ወድሶ ሶት -(ወደሰ ይዌድስ ይወድስ ዕብ ሆዳህ) ማወደስ ማሞገስ ማመስገን በምስጋና ደስ ማሰኘት ጥበብ ትዌድስ እሳ ብዙኃን ይዌድስዎ እንበይነ ጥበቢሁ። ንወድሶሙ ለዕደው ከቡራን ይወድስከ ነኪር -(ሢራ፳፬ -፩። ፴፱ -፱። ምሳ፳፯ -)

ወድአ -(ንኡስ አገባብ) ቀድሞ ኦስቀድሞ፤ አካቶ ፈጽሞ፤ ጭራሽ በጭራሽ። እለ ወድኡ ሞቱ። ወድአ ተሠይመ ወዳእነ እዝናሆሙ ወዳእነ ሞትነ። ወዳእነ ቀተርነ ኅተ -(መክ፬ - ማቴ፫ - ሮሜ - -፱። - ሉቃ፲፩ -)

ወድኦ ኦት -(ወድአ ይዌድእ ይወድእ ዐረ ወደዐ አደረገ ላክ) መጨረስ፤ መፍጀት መፈጸም መክተት፤ የግብር የነገር ትዌድእዎ ወኢታተርፉ ምኔሁ። ሳት ዘይዌድእ ሕያው ፍስ ኢትወድእ አመት ዘሀለወ ምስሌሃ ነጸረ ንጉሥ በዘወድኡ ማእደ -(ዘፀ፲፪ - - ዘዳ፱ -፫። ዮዲ፲፪ -፬። ን፲፫ -፲፰)

ወድይ ዮት -(ወደየ ይወዲ ይደይ። ወደደ) መጨመር መዶል ማግባት ማኖር ማድረግ መወርወር መጣል ወደዩ ሐሞተ ውስተ መብልዕየ። ይወዲ እዴሁ ውስተ ርዌ ምድር ደይ ቃሎ ውስተ ልብከ። እወዲ እዴየ ዲበ አፉየ ትደዩ ባሕርየክሙ ቅድመ አሕርው ወደይዎ ውስተ ግበ ናብስት ወደየት አዕይንቲሃ ላዕለ ሴፍ። ዘወደየ እሳተ ውስተ አህጉር -(መዝ -፷፰ ኢሳ፲፩ -፰። ኢዮ፳፪ -፳፪ ፴፱ -፴፬። ማቴ፯ -፮። ዳን፲፫ -፴፩። ዘፍ፴፱ -፯። - - -)

ወገል -(ዐረ ሸንገል) ቁሙ፤ ከርፈስ ዕርፍን ከሞፈር ከድግር የሚያያይዝ ስበትን እይ

ወገሬ -የማሽላ ስም የይፋት ማሽላ ራሱ ምንቸት የሚያካክል ፍችው ደኅኔ መልካሜ ማለት ነው። -(ወገሬት) ወገር ዕደር እንዲል፤ ደኅና ደር ሲል -(ጕራጌና እስላም) ፪ኛም የወገራ ማለትን ያሰማል፤ ወገራ በጐንደርና በስሜን መካክል ያለ አገር ነው -(ግጥም) ወገራ እግዚእ ዘኢፈትጠራ፤ ከቤት ቢገቡ ጢሱ ደጅ ቢወጡ ፋሱ እኽሉን ቢበሉት ፈሱ

ወገብ -(ዐማርኛ) ቁሙ ሕቌ ገቦ ንድ። -(ተረት) በሰማይ ቢዞር ዘመዱ አንበጣ በምድር ወገቡን ይይዛል ፌንጣ

ወገን -(ዐማርኛ) ቁሙ መንጋ ዘመድ ወገን ጠባቂ ባለወገን እንዲሉ።

ወገዝ -( አውጋዝ) በቁሙ፤ ያደገ ጥጃ ታናሽ ወይፈን ጊደር በመብል ጊዜ ከበሬ የሚለይ ማለት ነው -(ዐማርኛ)

ወገግ - ሀገር፤ ዐሰቦት። ሳሙኤል ዘወገግ ደብረ ወገግ -(ገድ -ተክ)

ወጊስ ሶት -(ወገሰ ይወግስ ይገስ ትግ ሐገሸ ፈሥሐ) መወግሸት፤ መቈጣት ወጌሻ ሐኪም መኾን መፈወስ ማዳን  ማፀን መጠገን ዚህ የተነሣ መወደድ መክበር። መዋብ ማማር ደስ ማሰኘት፤ የመልክ የግብር መጽሐፍ ግን በወገሰ ፈንታ ሞገሰ ይላል ወገደንና ወቅሐን እይ የዚህ አምሳል ናቸው ለብፁዕ ቂርቆስ አልቦ ዘይምግሶ፤ በክብር የሚበልጠው -(መዋሥ ድጓ)

ወጊር ሮት -(ወገረ ይዌግር ይውግር አው ይወግር ይገር) መወርወር ማጓን መጣል። ውርወራ የወል ኖሽ ወደ ላይ ጥሎሽ ወደ ወይም ፊት ለፊት። ዘገር ማለት ከዚህ ወጥቷል፤ ዘይትወገር ያሰኛል። ዘይወግር እብነ ላዕሌ ትወርድ ዲበ ርእሱ ንሣእ እብነ ወገር ዕለ ጓነ -(ሢራ፳፯ -፳፭ሄርማ) ገርዎ ውስተ ተከዚ ወገሩ አብትሮሙ ዘያስተሐይጻ ድንግል ወይወግር ይኖ ከመ ያርኵሳ ጣለ -(ዘፀ፩ -፳፪ -)

 -መውገር በደንጊያ መምታት መግመስ መፈንከት፤ መስበር መቀጥቀጥ ድንጊያን መቈለል መክመር ወገረቶ በስባረ ማሕረጽ ወገሮሙ እግዚ በእብነ በረድ ለይገራ በእብን ወነሥኡ ብነ ከመ ይውግርዎ -(መሳ፱ -፶፫። ኢያ፲ -፲፩። ዮሐ፰ -፯። -፴፩)

 -ማጠን ማጤስ ማቃጠል የዕጣንን ቀር ከፍሕም ላይ መጣል መኰንን ሠሠ ከመ ክሕዶ ክርስቶስ ወይውግር ዕጣነ ጣዖታት። ወእምዝ ይውግር ዕጣነ -(ስንክ -መጋ፮ ቅዳ) የወገረ ምስጢር በትግርኛ አለሌው ባዝራይቱን መታት እንደ ማለት ነው

ወጊብ ቦት -(ወገበ ይወግብ ይገብ ይውግብ ዐረ -ወጀበ) መወገብ፤ ድንገት መምጣት መውደቅ ያደጋ አመጣጥ ደደቀን እይ፤ የዚህ ጎር ነው ወገብ መያዝ፤ እስ ወገብ መድረስ የውሃ

ወጊእ ኦት -(ወግአ ይወግእ ይጋእ አው ይውጋእ ዕብ ናጋሕ ዐረ ወጀአ) መውጋት መደደቅ መደንጐር መዘር መቸብለክ መቸክቸክ። መውገጥ። ለእመ ወግአ ሕም ብእሴ ወጋእክሙ አስዋር። በሐኵ ይወግእ በአቅርንሁ ወግአኒ በኵያንው ወግኦኒ ሦክ እለ ወግእዎ -(ዘፀ፳፩ -፳፰ ኤር፳፯ -፲፩ ዳን፰ -፬። ኢዮ፲፮ -፲፫ መዝ -፴፩። ራእ፩ -) ድል ማድረግ። ማሸነፍ መግደል የሸሸውን ማሳደድ ተል። ንወግ ለኵሎሙ ፀርነ -(መዝ -፵፫። ኢያ፲ - ፲፮ -፲። ዘዳ፩ -፵፬። ዮዲ፲፮ -፲፬) ዋግ ማለት ዚህ ወጥቷል

ወጊዝ ዞት -(ወገዘ ይወግዝ ይገዝ) መውገዝ መገዘት መለየት መካድ መርገም። መጽሐፍ ግን በወገዘ ፈንታ አውገዘ ይላል። ወኪያሁኒ ያወግዝዎ እምነ ማኅበሩ። ውገዝዎሙ እስከ ዛቲ ዕለት። ብእሲ ዘአውገዘ ኤጲስቆጶስ ለየ -(ዕዝ፲ -) እለ ታወግዙ ግዘታተ ከመ ኢይፍትሑ ዘይፈቅድ  ይጠመቅ ይምሀርዎ ያውግዝ ሰይጣነ ወይእመን በክርስቶስ ወግዘከ ሰይጣን ወኵሎ ምግባራቲከ ውገዞ ለከይሲ ካደ ረገመ -(ሔኖ፺፭ -፬። ዲድ -፴፱ -ስንክ -የካ፪)

ወጊድ ዶት -(ወገደ ይወግድ ይገድ) መወገድ መራቅ፤ መፍሰስ መጕረፍ ላይ ላዩን ማለፍ።

ወጊግ ጎት -(ወገ ወገገ ይወግግ ይገግ ይውግግ) መውገግ ወገግ ማለት የንጋት

ወጋሪ -(ሪት ርያን ያት ገርት) የሚወረውር የሚጥል ጣይ ወገርተ እብን -(ገድ -ኪሮ)

 -በቁሙ ዓሣ አጥማጅ፤ መረቡን ወደ ባሕር ዓሣውን ወደ የብስ የሚጥል። ዓሣ ወጋሪ እንዲሉ

ወጋኢ -(ኢት እያን ያት) የሚወጋ የሚወግጥ ወጊ ተዋጊ -(ዘፀ፳፩ -፴፮። - -፵፭)

ወግር -( አውግር ራት ዕብ ይጋር ጋል ሱር ያግራ) የደንጊያ ክምር ልል፤ እንደ ኰረብታ ያለ። አለዱ ብነ ወገብሩ ወግረ ወሰመያ ሳባ ወግረ ስምዕ ወያዕቆብኒ ሰመያ ክማሁ። ዛቲ ወግር ወዛቲ ሐውልት -(ዘፍ፴፩ -፵፮ -፵፯ -፶፪)

 -ቁሙ፤ ኰረብታ ሊልታ ተሬ ጕባ ጐባታ አዳጋ ፍተኛ ቦታ ደፈር ሸንተረር ከተራራ የሚያንስ እቀውም ዲበ ርእሰ ወግር ርጉ ውስተ ርእሳ ለወግር። ወኮነ ወግረ ዐቢየ ውእቱ ድፍ። ወግረ ኃጥኣን ውግር ልዑላት ወባቲ አውግራትኒ ወአድባራት -(ዘፀ፲፯ - -፲። ንክ -መጋ፲ ኢሳ፳፰ -፴፩። -፳፭። አፈ -ተ፴፬)

ወግአ -ጋተ አገነፋወጊዕ ወግዐ

ወግዐ [1]:-በቁሙ ወጋ፤ወጊእ ወግአ።

[2]-(ገዐተ) ጋተ አስጐነጨ አስጐረጐጨ በጥርኝ። -(አወጋ ተረከ) ወትፈቅዱ ሐሊበ ይውግዑክሙ ሐሊበ ወጋዕኩክሙ -(ዕብ፭ -፲፪ ቆሮ - -)

ወግዓዊ -ወገኛ ወጋም፤ ባለወግ።

ወግዕ -ቁሙ፤ ወግ ታሪክ ንቲካ ወሬ ከሽማግሎች አፍ የሚገኝ። ዜና ወግዕ ዘመንግሥተ ሺዋ ዘሰማዕናሁ እምእለ ይዛውዑ ዜና ወግዕ -(ታሪ -ነገ) ልማድ ደንብ አበል ለሹም ወይም ለሌላ የሚገባ -(ዐማርኛ)

ወግዝ -(ዛት) ሕርም ልዩ ክልክል፤ የግዜር ገንዘብ። ዘዐለወ በወግዝ -(፩ዜና - -)

ወጠሰ -(ጤሰ፤ ጠየሰ) አቃጠለ ነደደ፤ ለኰሰ ነደደ ተቃጠለ፤ ቦግ ቱግ አለ -(ገድ -አዳ -ገ፻፴፰ና -)

ወጢን ኖት -(ወጠነ ይዌጥን ይውጥን፤ አው ይወጥን ይጠን ዐረ በደአ) መወጠን መዠመር፤ አኀዘን እይ ወወጠነ ጸውዖ ስመ እግዚ እምቅድመ ትውጥኑ ዐሊወ ንዌጥን በጽሒፈ መጽሐፍ። ንጥንኬ ዘለፋ ብዉሕ ሎቱ ከመ ይውጥን ጸሎተ ቤተ ክር -(ኩፋ - ዮሴፍ ፈላስ -ገ፩ መጽ -ምስ - -፴፩ -)

ወጢጥ ጦት -(ወጠ ወጠጠ ይወጥጥ ይጠጥ) መወጠጥ -(ጥወ) መወጠጥ፤ ወጠጤ መኾን

ወጣኒ -(ኒት ንያን ያት ጠንት) በቁሙ የሚዠምር ማሪ ወጣኒ ወፈጻሚ መምለኪ ወጣኒ ወጠንት -(መዋሥ። ቅዳ። ፊልክ -፬። ደራሲ) በወጣኒ ፈንታ ውጡን ይላል አያሰኝም -(ፊልክ - -)

()          ወጥሖ ሖት -(ወጥሐ ይዌጥሕ ይወጥሕ። ዐረ ጠሐ) መከመር መቈለል ማስተካከል፤ መሰደር መደርደር፤ ማነባበር አንዱን ባንዱ ላይ ማኖር ማድረግ ወጣሕከ ፀወ ዲበ ሳት ይዌጥሑ ዝክተ ዘገመዱ ወርእሰኒ ወሥብሐኒ ላዕለ ዕፀው ወጥሕዎሙ ምክዕቢተ ይዌጥሕ ሎሙ ፍዳሆሙ ቅድሜሆሙ ትዌጥሕ ተድባበ ዲበ ታቦት -(ሢራ፰ -፫። ዘሌ፩ - -፰።፬ነገ - -፰። ሱቱ -ዕዝ፲፪ -፴፰። ፀ፳፭ -፳፩)

ወጥስ -(ዐረ ወጢስ) ምድጃ እቶን ፋርን

ወጥወጠ -በቁሙ ወጠወጠ ወጥዋጣ ለግላጋ ነ። ወጥ ሠራ ወጥ አወጣ አሳለፈ ጠለቀ ኹሉም ዐማርኛ ነው -(ተረት) ወጡ ሳይወጠወጥ ወዝከንባዩ ቂጥ

ወጸፈ -ወጨ ወነ ወፀፈ

ወጺሕ ሖት -(ወጽሐ ይወጽሕ ይጻሕ ዕብ ያጻቅ) ማፍ ማፍለቅ፤ መቅዳት መር ማድረግ። መጽሐፍ ግን በወጽሐ ፈን አውጽሐ ይላል ውጻሕ ወይነ። ውጽሐ ደመ ስካል። ሶበ ውጽሖ ሞጻሕት ይወድቅ ናሕስ ወያወጽሕ ቤት -(ሚክ፪ -፲፩። ራ፶ -፲፭ ኤር፶፩ -፲፭ መክ፲ -፲፰) ማዋቀር መማገር፤ጣ ባጥ መሥራት።

ወጺብ ቦት -(ወጸበ ይወጽብ ይውጽብ ዐረ ዐጸበ) መሥራ መቀልበት ማፍ ማቅለጥ ቀጥቀጥ፤ የወርቅ የብር። ዐነገን ዐጸበን እይ ነው፤ በሥራው ነቅና መደነቅ ት።

ወፂእ ኦት -(ወፅአ ይወፅእ ይፃእ ዕብ ያጻእ) መውጣት፤ ውስጥ ወደ ፍኣ ካሉበት ወደ ላ። መብቀል፤ መወለድ፤፤ ለቅ መገኘት። እም ኀበ ግእዝ ማሙታል ፃእ ርሠ ምየ። ወፅ አኀዊሁ ፃእ ሐቅለ። ዘይወፅ አ። ምኔኪ ይወፅእ ጉሥ ፅአ ምኔሁ ደም ወማይ -(ኢዮ፩ -፳፩ ዘፀ፪ -፲፩። ማሕ፯ -፲፪ ፳፮ - - -፩። ዮሐ፲፱ -፴፭። መሳ፲፬ -፲፬)

 -መዳን መራቅ፤ መለየት። ይወፅ እምኵሉ። ዘይወፅእ ምዓም። ወፅ እምኵሉ ጥበብ -(ክ፯ -፲፰ ፊልክ ራ፴፯ -፳፩)

 -መጥፋ ጣት። ምስ መራቅ መለየ ካለው ባል ትርሳ ነገ ምልብከ። ኢታንብር የ፤ እስመ ዛሁ -(ዳ፬ -፬። ኩፋ -) በኮነ ፈንታ ወፅ ል፤ ኝም። ፈረስ ተረየፀ ይወፅእ እኩየ፤ ወልድ ሠጸ ይወፅ -(ራ፴ -)

ወፂፍ ፎት -() (ወፀፈ ይዌፅፍ ይውፅፍ፤ አው ይወፅፍ ይፀፍ) መወ መርት፤ የዝናም። መወን ማወን መወርወር መምታት፤ የደንጊያ -(፩ነገ -፲፯ -፵፱) ትዌ ሥረሃ። ወፀፎ ብን ሄጶ ውስተ ፍጽሙ -(ገድ -ክ። ራ፵፯ -፬። መዝ -፻፶፩)

ወፃኢ -(ኢት እያን ያት) የሚወጣ፤ ወጭ እን ብዝ በዋእያን ወወፃእያን -(ፊልክ -፻፳፪)

ወጻኢ መወጽእ -የሚያሸን አሸናፊ፤ ኀይኛ።

ወፃፊ -(ፊት ፍያን ያት ፀፍት) የሚጭፍ የሚወነጭፍ፤ ወን ወርዋሪ ባለወንጭፍ። ወፃፍያን በሞፀፍተ ብን። ወፀፍት ደፍት -(፩ዜና -፲፪ - ፪ዜና -፲፬ -)

ወጽሐ -አስማጠወፅ ፅኀ።

()          ወፅኆ ኆት -(ወፅኀ ይዌፅኅ ይወኅ። ) ስማ ማስነቅ፤ መፍ ቍላ የሆድ። መኀፀን ወፅአን እይ የዚህ ጎሮች ናቸው።

ወጽብ ውጽብ ውጽቦ -( አውጻብ ባት) ቀለበት ጕትቻ፤ ወይም ያፍንጫ ጌጥ ውስተ ውጽቦ ወርቅ ሰርን። ውጽቦ ወርቅ ውስተ አን ሐራውያ ምጽ ውጻበ። እን ባት ወባዝግና -(፲፩ -፳፪ ፳፭ -፲፪ ዘፀ፴፭ -፳፪ ሳ፰ -፳፮)

ወጽአ -ወጣ፤

()          ወጽኦ ኦት -(ወጽአ ይዌጽእ ይወጽእ ፅኀ) ማየል ት፤ ማሸነፍ ድል መንሣት። ነፅንና ወድ እይ። ሶበ ዕል ሙሴ ዴሁ ይዌ ስራል፤ ወሶበ ያቴሕት ዴሁ ይዌጽ ዐማ -(ፀ፲፯ -፲፩)

ወፅፍ ወፀፍ - በረድ ውሽንፍር የወንጭፍ ጊያ፤ ጥይት ረር

ወፊር ሮት -(ወፈረ ይወፍር ይፈር) መወፈር መደንደን፤ መስፋት መዘርጋት። ይወፍር ዕጹቂሁ -(ሆሴ፲፬ -)

 -መሰምረት ዳሪ መውጣት ወደ ዱር ወደ ተግባር ድ፤ ማለፍ። በረዘን እይ የዚህ ጎር ነው ወፈረ ሐቅለ። ወፈረ ቡሁ ውስ ረር። ይወፍር ውስተ ባሩ ኑፈር ንእቱ። ፈር ቤሃ ዘየሐርስ ወፈረ በሰበት -(ዳን፲፫ -፴፫። ፬ነ - -፲፰ መዝ -፻፫ ጓ። ራ፮ -፲፱ ሉቃ፮ -)

ወፊጥ ጦት -(ወፈጠ ይወፍጥ ይፈጥ) መተኰስ ማብሰል የልብስ የሸክላ፤ ለነፍጥም ይኾናል ወበሱባ ራብዕ ወፈጡ ሳት፤ ወኮኖሙ ንፋ ከመ -(ኩፋ -)

ወፊፍ ፎት -(ወፈ ወፈፈ ይወፍፍ ይፈፍ) ወፈፍ ወፈፍ፤ አፈ አፈፍ ማለት መነሣሣት ወፈፍ መኾን -(ማርኛ) ተመልከት

ወፋሪ -(ሪት ርያን ያት፤ ፈርት) የሚሰመር ተሰምሪ ራሽ ፋሪ ሣር ዐጫ ሰባሪ ወፋርያ ዕፀው -(ኢያ፬ -፳፭)

ወፋጢ -(ጢት ጥያን ያት ፈጥ) የሚተ ተኳሽ ዐዋቂ

ወፍር -ወፍራም ዕርሻ ብት መሰምሪያ ዱር መስክ። ዘይትቀ ወፍረ ፍረ ሐረስት ዐጸደ ወፍር ዐብ ኵሉ ወፍር ዘውስተ ገዳም። አዕጻዳት ወፍር -(ኩፋ -፶። መክ፭ -፰። - -፮። ኤር፳፫ -፲። ዮዲ፫ -)

 -ዳይ ተግባር መፍቅድ ገንዘ የሚያስፈልግ። ዘይዘሩ ዋየ ቤተ ክርስቲያ ለወፍረ ቤቱ -(ቀሌ)

ወፍይ -(ወፈየ ይወፊ ይወፊ ዐረ ወፈይ) ልና ገቢር፤ ፈረ ቤት። ጥዑይ መኾን፤ አለመደል አለመነካት። መስ ማሲያዝ ማስበጥ፤ ዐደራ ማለት፤ ዐደራን ዕዳን መመለስ መክፈል። መጽሐፍ በወፈየ ፈንታ ወፈየ ይላል፤ አያኝም። ወፈ ውስተ እዴሁ ወፈይዋ ዮሴፍ። ጔጕ ምድር ታውፊ ማሕፀ ወፈየት ዕዳ ምታ -(ዮሐ፫ -፴፮። -ማር ሱቱ -ዕዝ -፶፩ ስንክ -ሠኔ፳) ዳግመኛም በአዘዘ ፈንታ አወፈየ ይላል ምስጢሩ ዐደራ ካለው ይገባል። ወፈዮ ይሕ ቤተ -(፩ዜና -፳፪ - -፲፯)

-() ወገን ቅጽል ምድራዊ ሰማያዊ እያለ እንደ ምእላድ በጫፍ በትራስ ይገባል። ፪ኛም ግብረ ሰብእ ያለውን ግብር ሰብኣዊ ይላልና በዚህ ምክንያት የሙሻዘር ውስጠ ይባላል ዊና ንድ ወገን ናቸው

-() የራብዕ ሥረይ -(ዋየል) ላራቱ ዲቃሎች ጉዋ በነዚህ ንጻር ለሚገኙም ለራብዖች ኹሉ ላማርኛ ፊደል ሥረይ ይኾናል ቡዋ ባማርኛም የሐዘንና የነቀፌታ ቃል ይኾናል

ዋሓዪ -(ዪት ይያን ያት) የሚጐበኝ፤ ፈቃጅ ጠባቂ ከሃሊ ኵሉ ወዋሓዬ ኵሉ -(ቄር)

ዋኀደ -ተዋሐደዋሕዶ ዋሐደ

ዋሕስ -ቁሙ ዋስ መድን ተያዥ ተጠሪ ገባሪ። ነሣኤ ዋሕስ ወበዋሕስ -( - -፳፯ ፴፪)

ዋሕይ ዮት -(ዋሐየ ይዋሒ ይዋሒ ዐረ ወሐይ) መጐብኘት መፍቀድ መላልሶ ተመላልሶ ማየት፤ እየዞሩ መሰለል መጠበቅ። ዋሐይኩ ኆኅተ ቤታ የሐውር ይሥሐቅ ወይዋሒ ጥሪቶ -( ኤጲስቆጶስ) ዋሕዮሙ ለኃጥኣን መዓልተ ወሌሊተ። እስመ ይዋሒ ጸዓዕ ወበድልቅልቅ ዋሕያ በበትር ለኀጢአቶሙ -(ኢዮ፴፩ -፬። ኩፋ -፳፪ ቀሌ ኢሳ፳፱ -፮። መዝ -፹፰) ሐወጸን ተመልከት፤ የዚህ ጎር ነው

ዋህድ -አንድ ብቻዋሕዶ ዋሐደ ዋሕድ።

ዋሕድ -ዉሑድ -(ዳን ዳት ሕድ ድት፤ ውሕድ። ዕብ -ያሒድ። ዐረ -ዋሒድ) የተዋሐደ አንድ የኾነ፤ የተባበረ አንድ ወጣት አንድ ቅንጣት ምንታዌ መንቲያ ወይም ተቀዳሚና ተከታይ የሌለው ፍጹም አንድ ውኅደን እይ። ትቀትል ወልዳ ዋሕደ። ወቦቱ ወለት ዋሕድ ወልድ ዋሕድ ዘሀሎ ውስተ ሕፅነ ቡሁ ክርስቶስ ዋሕድ -(ዮሴፍ። ሉቃ፰ -፵፪። ዮሐ፩ -፲፰ ስንክ -የካ፬)

ዋሕድ ወበኵር -ሥግው ቃል የሥግው ቃል ስም ይሰመይ ዋሕደሂ ወበኵረሂ -(ቄር) ዋሕድ፤ በወዲያኛው በአምላክነት በባሕርይ ልደት ወልድየ አንተ በተባለበት። ወበኵር በወዲህኛው በሰውነት ሰው ኹኖ ነሣው በቅባት በግብር  ልደት ወአነ ዮም ወለድኩከ አነ እከውኖ አባሁ ወውእቱ ይከውነኒ ወልድየ በተባለበት። ውእቱ ይብለኒ ቡየ አን ወአነሂ በኵርየ እሬስዮ። በኵረ ልደት ለኵሉ ፍጥረት በኵረ ልደተ ተግባሩ -(መዝ፹፰ ሃይ -አበ ኄሬ። ቄር)

ዋሕድና -ንድነት፤ አንድ ልጅነት አንድ ብቻ መኾን

ዋሕዶ ዶት -(ዋሐደ ይዋሕድ ይዋሕድ። ዕብ ያሐድ) መዋሐድ አንድ መኾን መተባበር፤ አንዱ ካነዱ ጋራ እሒድን እይ መጽሐፍ ግን በዋሐደ ፈንታ ተውሕደ ተወሐደ ይላል ይትወሐዱ ክልኤሆሙ ይኩኑ አሐደ ሥጋ ናሁ ተዋሐደ ወተሰውጠ ቦቱ -( - - -፬። - -፳፮ -)

ዋኔ ዋኖስ -በቁሙ ተጫዋች ወፍ ማዕነቅ -(ዐማርኛ)

ዋንይ ዮት -(ዋነየ ይዋኒ ይዋኒ ትግ ወነሰ ተጫወተ) መዋኘት፤ -(ጥና) ዋና ዋነኛ ዋነተኛ መኾን፤ መጫዎት መዝፈን መወሳወስ። ጸበተ መስፈፍ መንካፈፍን ዋነየ ውስወሳን ያሳያል ዘፈንና ዋና አንድ ወገን ናቸው ወኒ ወና ዋኖስ ማለት የዚህ ነው

ዋዕይ -ቃጠሎ ሙቀት ትኵሳት ሐሩር ድርቅ በጋ ከመ ዋዕየ እሳት ዋዕየ ፀሓይ ዋዕየ ፍትወት -(ኢሳ፱ -፲፱ ሔኖ -፬። - - -)

ዋካ -ብርሃን ውጋጋን ወገግታ ቦግታ ዳል ምዕዛር ስመ ፈድፋደ  ሠናይ ዋካሁ ጸዳል ወኢዋካ ብርሃን ዘያንጸበርቅ ዋካሁ ርእየ ዋካ ወኢርእየ ማኅቶተ ስመ ዋካ ይእቲ ብርሃን ዘቀዳሚ -(ሢራ፵፫ -፲፩ ሱቱ -ዕዝ፮ -፲፬። ፈላስ -ገ፷፰ አርጋ -፬። ጥበ፯ -፳፮) ስመ ሀገር በመንዝ ውስጥ ያለ

ዋክዮ ዮት -(ዋከየ ይዋኪ ይዋኪ ወህውሀ) መብራት መጽደል ማለት እምብዝኀ ብርሃኑ ዋከየት ሀገር -(ገድ -ተክ)

ዋዌ -ስመ ፊደል ሳድስ ኛው የግእዝ ፊደል ወ፤ በአበገደ ወገል ሸንገል ሜንጦ ቈላፋ ብረት ልፍ ዘለበት ማለት ነው ሸንገል እንደ ሜንጦ ያለ የመስኮት ስናግ ነው ቍል ማእከል ኹኖ ግራና ቀኙን እንዲያያዝ፤ አጫፋሪነቱን ያሳያል ዘለበት ማለትም በግብሩ ላይ መልኩን ምሮ ያስረዳል። ሆህያተ ቤት ወዋዌ -(አፈ -ድ፩)

ዋው -(ዕብ ወሱር ወዐረ) ዝኒ ከማሁ። ዋው ይምጻእ ምሕረትከ -(መዝ -፻፲፰ -፵፩ -፵፰። ሰቈ፩ -፮። - -፲፭ -)

ዋዜማ [1]-በቁሙዜመ ወዝየመ

 [2]-በቁሙ መዠመሪያ ዜማ ከበዓሉ በፊት ማታዉን የሚዜምና የሚመራ መዝሙር፤ ቅኔ። ዋዜማ ዘሠርክ። እምድኅረ ፍጻሜ ዋዜማ -(ድጓ ገድ -) ውዥሞ ውዥምዥም ማለት ከዚህ ይሰማማል።

 -ድራር፤ ንኡስ በዓል፤ ማኅትው የሚቆምበት ዋዜማ የሚመራበት ቀን ማኅትው የነግህ መዝሙር ነው ዋይ ዜማ ሲል ግን ቃል ነውና ዋይን ተመልከት

ዋየየ -ዋየ አስተዛዘነ አጫወተ።

ዋይ -በቁሙ፤ ጕዳይ ግዳጅ ዋይ የለሽ እንዲሉ። በግእዝ ግን አንክሮና አጋኖ ምኞት ይኾናል። ዋይ ዜማ ዘሰማዕኩ በሰማይ መላእክት -(ድጓ)

ዋግራ -የሬት ሽቱ፤ ወይም ወገርት። ሣዕሮን ተመልከት

ዌቦርኮኤቦት -(ጽር ዌባርካቦት። ዕብ ኢካቦድ) የሰው ስም ስብሐት ወኢክብር ክብር የለውም ማለት ነው ባለብሉዮች ግን በር ኹኖ ትሾም ኹኖ በስደት ይሉታል አባቱና አጎቱ ሙተው እስራኤል ድል ኹነው ታቦተ ጽዮን ወደ ኢሎፍሊ የተማረ ለት ስለ ተወለደ ኢካቦድ ተብሏል -(፩ነገ - -፳፩)

[1]-ብዥ ምእላድ ሰግላ ሰጋልው፤ ሰላድው ወላትው፤የመሰለው ኹሉ የወዲያኛው ትግሬም፤ ቀርቡ መጽኡ ፈርሁ ንገፁ ሲል ቀርበው። መጽአው ፈርሀው ደንገፀው ይላል

[2]-ያማርኛና የጥንታዊ ግእዝ ዝርዝር ግእ ቀተለው ቀተል ገደለው ገደ ውን ጐርዶ ቀተሎ ልኮ ማለት የሐዲስ ግእዝ ነው

ውሑስ -(ሳን ሳት ሕስት) የተዋሰ ዊስ የኾነ ውሰት የተወሰደ የተሰጠ።

ውሁብ -(ባን ባት ህብት) የተሰጠ ተሰጭ የኾነ። ውሁባን -(ዘኍ፫ -) የተሰጠው የታደለ፤ ሀብታም ዕድላም። ውብ መልከ መልካም ደመ ግቡ ደማም ውበት  ደም ግባት  የተሰጠው በተፈጥሮ

ውሑዝ -(ዛን ዛት ሕዝት) የፈለቀ የሚፈልቅ ፈሳሽ ወራጅ አንብዕ ውሕዝት -(ፊልክ -፻፲)

ውኁደ -ጥቂት፤ በጥቂት። ውኁደ ጻመውኩ። ክአብ ውኁደ ተቀንየ ለበዓል ወኢዩሰ ብዙኀ ይትቀነይ ሎቱ ዘበ ውኁደ አፍቀረኒ ውኁደ ይትኀደግ ሎቱ -(ሢራ፶፩ -፳፯። ነገ - -፲፰ ሉቃ፯ -፵፯) በውኁድ ፈንታ ዋኅድ ይላል ፍችው አንድ ነው -(ሄርማ)

ውኁድ -(ዳን ዳት ኅድ) ያነሰ የጐደለ፤ ታናሽ ጐደሎ፤ ጥቂት። ውኁድ አነ በኁልቍየ ውኁድ መዋዕለ ሕይወትየ ጥሪትከ እመኒ ብዙኅ ወእመኒ ውኁድ። ውኁዳነ ምድር ዘእንበለ ውኁዳት መካናት ውኅድ ንቲ -(ዘፍ፴፬ -፴። ኢዮ፲ - ሢራ፵፪ -፬። መዝ -፲፮ ኩፋ -፴፭። ሚክ፭ -)

ውኁጥ -(ጣን ጣት ኅጥ) የተዋጠ የሰጠመ፤ የተጐረሠ የተበላ።

ውሂህ -(ወህሀ ይወህህ የሀህ ምህወ መየ) መወህየት፤ውሃ ውህማ ውሃማ መኾን፤ መቅለጥ፤ የምህወንና የመየን አፈታት ተመልክት

ውሒስ ሶት -(ወሐሰ ይዌሕስ የሐስ ዐረ ወሰ) ማዋስ ዋስ ጠበቃ፤ ተመላሽ መስጠት እገሌ ተዋሰኝ፤ ዕንካ ውሰድ ማለት ምስጢሩ መስጠት ነው። መጽሐፍ ግን በወሐሰ ፈንታ አውሐሰ ይላል ያማርኛ ነው ይደልዎ ከመ ያውሕስ ንዋዮ -( - -፳፰)

ውሂብ ቦት -(ወሀበ ይውሀብ የሀብ ዕብ ያሀብ ሱር ይሃብ ዐረ ወሀበ) ይውህብ ፈንታ ይሁብ ይላል የተሳሳተ ነው ሆበን እይ። መስጠት መናኘት ማደል ማሳለፍ የያዙትን ከሌላ እጅ ማግባት፤ ማሲያዝ ማስጨበጥ ማስረከብ፤ ዕንካ ተቀበል ማለት፤ ማቅረብ እጅ በቃል ቃል ሠናይ ይኄይስ እምውሂብ በእንተ ሀብት ወወሃቢ ወዘይሁብዎ ቱ፤ ወንዋይ ዘይሁቡ ኪያሁ አኰቴተ ለእግዚ -(ሢራ፲፰ -፲፮ - -፳፮ መዝ ፷፯)

 -ማዘዝ ማሰናበት፤ ምስጢሩ ያው መስጠት ነው ለአዳም ባሕቲቱ ወሀቦ ይክድን ፍረቶ ወኢወሀቦ ከመ ይትመየጥ ቤተ አቡሁ -(ኩፋ -፫። ነገ -፲፰ -)

 -ማድረግ ማኖር ማሳደር ምስጢሩ የረሰየና የሤመ ነው ዕብራይስጥም ታን ብሎ ሀበ ረሰየ ሤመ ይላል ረሰየን እይ እሁብ ኪዳነ ምስሌክሙ ቀስቶ ወሀበ ውስተ ደመና ፍርሀተክሙ ሁብ ኀበ ኵሉ ዘውስተ ምድር ዘሕያው የሀብ ሠናየ ውስተ ልቡ ወእሁብ መንፈስየ ውስቴትክሙ -(ዘፍ፱ -፱። ኩፋ -፮። መክ፯ -፫። ሕዝ፴፮ L ፳፯) ማስዋብ ማሳመር ማስጌጥ ውብ ማድረግ -(ዐማርኛ)

ውሒክ ኮት -(ወሐከ ይዌሕክ የሐክ) ማወክ ማነሣሣት መነዝነዝ መጐትጐት በግብር በነገር ማስቸገር ዕንቅፋት የክፉ አብነት መኾን ሆከን እይ የዚህ ጎር ነው ወሐኮ ዐርክከ ዘተሐበይኮ። ይዌሕኮ ለፈጣሪሁ ወሐኮ ኃጥእ ለእግዚ ውሒከ ወሐኮሙ ለፀረ እግዚአብሔር። አነ አአምር ውሒኮተከ -(ምሳ፮ -፫። ፲፬ -፴፩። መዝ -፱። ፪ነገ -፲፪ -፲፬ ዘዳ፴፩ -፳፯)

ውሒዝ ዞት -(ውሕዘ ይውሕዝ የሐዝ ዐረ ወዘዐ ዕብ ያዛዕ ወዛ) መፍለቅ መፍሰስ መውረድ መጕረፍ ይውሕዝ ማይ። ፈለግ ዘይውሕዝ የሐዝ ማየ ቀራንብቲክሙ ብእሲት እን ደም ይውሕዛ -(ኢሳ፴ -፳፭ ፴፫ - ኤር፬ -፲፰ ማር፭ -፳፭)

 -ማፍለቅ ማፍሰስ ማውረድ ማጕረፍ እደውየ ይውሕዛ ርቤ ምድር እንተ ትውሕዝ ሐሊበ ወመዓረ። ይንየ ውሕዘት ማየ -(ማሕ፭ -፭። ዘፀ፫ -፰። ሰቈ፩ -፲፮) ግስነቱ ዐጕልና ገቢር እንደ ኾነ አስተውል።

ውኂድ -(ውኅደ ይውኅድ ይውኅድ፤ የኀድ) መጕደል ማነስ መቀነስ አንዳንድ እያሉ ጥቂት መኾን ብቻ መቅረት፤ ማጠር መቅጠን። ዋሐደን እይ፤ የዚህ ጎር ነው ብዝኁ ወኢትውኀዱ እለ ይውኅዱ የአክሉ እልፈ ዓመተ ረሲዓን ይውኅድ መተ ክህነቱ ይውኅድ እምዓመት ውዳሴ ይውኅድ እምክብርክን ተኵላ ይንእስ እምነ ሐርጌ፤ ወአንበሳ ይውኅድ እምነጌ -(ኤር፴፱ -፮። ኢሳ፷ -፳፪ ምሳ፲ -፳፯ ዮሴፍ ቄር ቅኔ)

ውኂድ ዶት -(ውኅደ ይውኅድ ይውኅድ፤ የኀድ) መጕደል ማነስ መቀነስ አንዳንድ እያሉ ጥቂት መኾን ብቻ መቅረት፤ ማጠር መቅጠን። ዋሐደን እይ፤ የዚህ ጎር ነው ብዝኁ ወኢትውኀዱ እለ ይውኅዱ የአክሉ እልፈ ዓመተ ረሲዓን ይውኅድ መተ ክህነቱ ይውኅድ እምዓመት ውዳሴ ይውኅድ እምክብርክን ተኵላ ይንእስ እምነ ሐርጌ፤ ወአንበሳ ይውኅድ እምነጌ -(ኤር፴፱ -፮። ኢሳ፷ -፳፪ ምሳ፲ -፳፯ ዮሴፍ ቄር ቅኔ)

ውኂጥ ጦት -(ውኅጠ ወኀጠ ይውኅጥ የኀጥ። ዐረ ሐጠ) መዋጥ መሰልቀጥ ወደ ሆድ መሳብ በጕረሮ መቅለብ ማግባት መክተት መጕረሥ መብላት ከመ ያለምድ ውኂጠ ብቅው ለውኂጥ። ዘዘ ዐንበሬ የኀጦ ዮናስ ወውኂጦ ቅዐ ነኀ ሕያዎ እለ ይውኅጥዎሙ ለሕዝብየ -(ኪዳ። አርጋ -፩። ዮና፪ -፩። ዳን፲፫ -፳፯ ምሳ፩ -፲፪ መዝ -፲፫)

ውሕሰት -ማዋስ መዋስ አዋዋስ ውሰት ዋስትና ዋስነት፤ ውሰትነት። አው በአኅዝ፤ በውሕሰት -( - -፴፱)

ውህዋሄ -የመልክና የክብር ብርሃን ሥን ላሕይ፤ ጸጋ ዕበይ። ባለብሉዮች ግን የዋሐየ ዘር ድርገው -(ውሕየት) መጐብኘት ይሉታል። ዘረከበ ብእሲተ ርተ ረከበ ሞገሰ፤ ወነሥአ ምኀበ እግዚ ውህዋሄ -(ምሳ፲፰ -፳፪)

ውሕዘት -ፍሰስ፤ አፈሳሰስ፤ ፈሳሽነት። ውሕዘቱ መንገለ ሰሜን በውሕዘተ አንብዕ ወቆመ ሶቤሃ ውሕዘተ ደማ -(ሔኖ፳፮ - ሥር -ጳኵ ሉቃ፰ -፵፬)

ውሕደ -አነሰ ጐደለውኂድ ውኅደ።

ውኅደት -መጕደል ማነስ አጐዳደል ጐደሎነት ውኅደተ ሕዝብ በውኅደተ ጥርዮ -(ምሳ፲፬ -፳፰ ፊልክ -፳፬) በውኅደት ፈንታ ውኂድ እንደ ማለት ውኅድ ይላል፤ አያሰኝም -(መዝ -፻፩)

ውሕጠ -ዋጠውኂጥ ውኅጠ

ውኅጠት -( ) መዋጥ አዋዋጥ ውጦሽ

ውሉደ ሕይወት -ሙተው በክብር የሚነሡ ዳግመኛ ሊሞቱ የማይችሉ -(ሉቃ፳ -፴፮)

ውሉደ መንግሥት -ከበርቴዎች ላባቶች፤ መደበኞች -(ማቴ፰ -፲፪)

ውሉደ ቤት - ሰቦች አሽከሮች ገልጋዮች የቤት ውልዶች

ውሉደ ብርሃን -ዐዋቆች ጻድቃን መናንያን -(ሉቃ፲፮ -)

ውሉደ አርጤምስ -መምለክያነ ጣዖት አርጤምስን ብቻ የሚያመልኩ።

ውሉደ አቡነ ተክ ሃይ -መነኮሳት አርድእት በቆብ በትምርት የተወለዱ -(ስንክ -ሐም፲፱)

ውሉደ አዳም -ዎች ኹሉ ወንዱም ሴቱም -(ሢራ፵ -)

ውሉደ እግዚ -መላእክት፤ ጻድቃን ምእመናን -(ኢዮ፩ -፮። ሮሜ፰ -፲፬)

ውሉደ ጥምቀት -ውሉደ ጥምቀት፤ ክርስቲያኖች ሀብተ ወልድና ስመ ክርስትና ያላቸው -(አርጋ)

ውሉድ -(ዳን ዳት ልድ) የተወለደ ውልድ ልጅ ውላጅ ከባሕርይ የተከፈል። እሁባ ውሉደ እምነከ ትረክብ ሳራ ውሉደ። መኑ ውሉድ ዘኢይጌሥጾ ቡሁ ውሉዳነ ልሂቃነ ሰብእ። ወትከውን ከመ ውሉደ ልዑል ዘያፈቅር ውሉዶ ልጁን -(ዘፍ፲፯ -፲፮ ፲፰ -፲። ዕብ፲፪ -፮። ስንክ -ኔ፫ ራ፬ -፲። -) ልዑል ምጡቅ ረዥም ታላቅ በማለት ፈንታ ውሉድ እምአእላፍ ይላል -(ማሕ፭ -) ባለቅኔዎችም ባለብሉዮችም ንባቡን እንደ ቀደሰ ቤት አጥብቀው ፍችውን ኅሩይ ይሉታል ብራይስስጡ ግን ዳጉል ሜርባባ ዐረቡም ሙዕሊሞን በይነ ሪብወቲን ይላል፤ እንደ ባንዲራና እንዳላማ በብዙ ራዊት መካከል በተራዳ ላይ የቆመ የተንጠለጠለ ወይም ከፍ ያለ የተሰቀለ ስቁል ማለት ነው ኔስታሊን እይ

ውሉጥ -(ጣን ጣት ልጥየተለወጠ ልውጥ ልዩ ሌላ ውሉጥ እምኔነ ዘእንበለ ኀጢአ በቀኖናት ውሉጣት -(ተረ - - - -)

ውላጤ -( ) መለወጥ አለዋወጥ ልወጣ፤ ልውጥነት ውፁእ ሚጠት ወእምውላጤ። ንሕነ ከሃልያን ለውላጤሁ -(ቄር። ዮሴፍ)

ውልታዌ -መመከት አመካከት፤ ምከታ -(አፈ -ተ፭)

ውልትው -የመከተ የተመከተ ምክት

ውልዋሌ -ውልወላ መዋለል፤ መወላወል ጥርጥር ውዝወዛ ውዝውዝታ፤ ፍርሀት ፍጥነት። ውልዋሌ ወሑሰተ ፍስ። ስመ ለዛቲ በዓል በውልዋሌ ገበርክምዋ። በደመ በግዕ ዘበልዕዎ ደቂቀ እስራኤል በውልዋሌ ሌሊተ ፀአቶሙ -(ፊልክ -፶፬። ኩፋ -፵፱። መጽ -ምስ ዘፀ፲፪ -፲፩)

ውልዉል -የተወለወለ የሚዋልል፤ ወዲያ ወዲህ የሚል ቅብዝብዝ ውልዉለ ነፋስ -(አዋል)

ውሡር -ውሡር -(ራን ራት ሥርት) የተቈረጠ ቍርጥ፤ ሥንጥቅ ትርትር

ውሱቅ -(ቃን ቃት ስቅት) የታለበ የተደገነ፤ ድግን። ሐጽ ውሱቅ በአንጻረ ጸላኢ ውሱቃን አቅሰስቲሆሙ -(ማር -ይሥ፯ -፩። ኢሳ፭ -፳፰ ፳፩ -፲፭)

ውሱብ -(ባን ባት ስብት) ያገባ ተገባ የተዳረ ጐዦ ወጥ ትከውብ ምኍልቈ በለታት ውሱባት ንስት ውሱባት። ማእከለ ውሱባን ወደናግል ሀሎ ፍልጠት ክሡት -( - - -፲፪ - -)

ውሱን -(ናን ናት ስንት) በቁሙ የተወሰነ የተቈረጠ ርጥ ወሰን ደንበር ልክ መጠን ያለው። መካን ውሱን ሥሩዐ ወዕቁመ ወውሱነ በሩ እግዚ ረሰየ ለክሙ ውስተ ዓለም መዋዕለ ውሱነ መዓርጋት ዘውሱን ሎቱ ጊዜ ዘውሱን ሎቱ -( - -፳፰ ቆሮ -፲፬ -፵። ዮሴፍ - - -፪። -)

ውሱክ -(ካን ካት ስክት) የተጨመረ ጭምር፤ ብዙ። ዐፅም ውሱክ። አስተብቍዖት ውሱክ -( - -፲፪ -፳፩ ስንክ -ሐም፩)

ውሣሬ -መቍረጥ መቈረጥ አቈራረጥ፤ ቈረ ግዝገዛ ርተራ ሥንጠቃ

ውሳኔ -(ንያት) መወሰን -(ጥወ) መወሰን አወሳሰን ውሰና ዝንቱ ውሳኔ ሕግ ይደሉ ላዕለ ኵሉ። ውሳንያት ሕግ። ውሳንያ እንተ ወሰንዋ አበው ቀደምት -( - - -፭። ገድ -ኪሮ ያዕ -ዘእል)

 -በቁሙ ፍጻሜ ወሰን ደንበር። በእንተ ውሳኔ አውስቦ ውሳንያተ አምዳር ሕገ ኦሪት ቦቱ ወሰን ወለዛቲሰ አልባቲ ውሳኔ። በጽሐት በምዕር ኀበ ውሳኔ -( - -፳፬ -፬። መቅ። አፈ -ድ፲፱ ፲፫)

ውሳኬ ውሳክ -(ካት) መጨመር -(ጥጨ) መጨመር አጨማመር፤ ጭመራ፤ ጭማሪ ሰላም ለኅሊናከ ዘኮነ መምለኬ ሥሳሴ ዕሩየ እንበለ ውሳኬ ውሳኬ መልእክቱ ወዝንቱ ውእቱ ሥርዐተ ውሳኬ። ጠፈሮንሂ ቀመሮንሂ ውሳካቲሆንሂ እብን -(ደራሲ ስንክ -ጥቅ፱ አፈ -ተ፰ ገድ -ላሊ)

ውሳጤ -(ጥያት) ውስጥ ውሳጥ የውስጥ ውስጥ፤ ዋሻ ጕስጕ ውስጥነት ያለው ኹሉ በውሳጤ ሀገር ወአፍኣሃ ምውሳጤሁ ወአፍኣሁ ኵሉ ውሳጥያቲሁ ለደቡብ። ቦአ ውስተ ውሳጥያተ ርሑ ውስተ አብያት ወውስተ ውሳጥያት ልቦሙ መዛግብት ወኢውሳጥያት -(ዮሴፍ ፀ፳፭ -፲፩። ኩፋ -፱። ፫ነ - -፴። ኢሳ፵፪ -፳፩ ሉቃ፲፪ -፳፬)

ውሥተ -ወደውስተ።

ውስተ -ወደ ወሲጥ ወሰጠ

ውስት ውስቴት ውስተ -(ውስጥ ውሳጤ ውስጠ) ደቂቅ አገባብ ውስጥ ማኽል ጋራ ወደ ይኾናል ፍችው በን ምስጢሩ ውስጥን አይለቅም እም እንተ ይሰማሙታል ውስተ ባሕር እምውስተ አፍ የኀልፍ እንተ ውስቴታ እያለ ይገባል ምስክሩን እንደ ተራው እይ ይነብሩ ውስተ ጽልመት ከመ አንበሳ ውስተ እንሰሳ ኢይትኌለቍ ውስተ ሕዛብ ሚጥዎ ውስተ ላሕ ወአግብእዎ ውስተ ትካዝ -(ማቴ፬ -፲፮ ሚክ፭ -፰። ዘኍ፳፫ -፱። ያዕ፬ -) ዲበ ላዕለ በማለት ፈንታ ውስተ ይላል የመላሽ ስሕተት ነው፤ ውስጥነት ማእከልነት እንጂ ላዕልነት አይስማማውም። መሥዔ ውስተ ዴሁ ኢሀ ውስተ መካኑ ይኩኑ ውስተ ጠፈረ ሰማይ -(ማቴ፫ -፲፪ ፩ነገ - -፳፭ ፍ፩ -፲፬) ወረደት እምውስተ ገመላ ያሴስል ሐመደ እምውስተ ምሥዋዕ ወድቀ እምውስተ መንበሩ። ይሰክቡ ውስተ ዐራታት ዲበ ዕለ -(ዘፍ፳፬ -፷፬። ዘሌ፮ -፫። ፩ነገ - -፲፰። ዓሞ፮ -) ዳግመኛም በግእዝ ፈንታ ገቢር ለማድረግ ውስተ ይላል ይህም ስሕተት ነው አያሰኝም። እሬስየከ ውስተ ሕዝብ ዐቢይ  ይእቲ ኮነት ውስተ ርእሰ ማእዘንት ዘበጠት ውስተ ክሣዱ ንብብ ውስተ ወንጌል -(ዘፀ፴፪ -፲። መዝ -፻፲፯ ዮዲ፲፫ -፰። ማር -ይሥ) በውሳጢት አንጻር ውስቴቱ እያለ ይዘረዝራል፤ ወና እንዲወራረሱ ጠና ተም ይዋረሳሉና፤ ውስጠ የነበረው ውስተ መባሉ ስለዚህ ነው

ውስኪ -የመጠጥ ስም ውሱከ መቃስም ጽሩይ ወጥዑም የንግሊዞች መጠጥ ዋጋው ድኻ የሚጐንጥ፤ ልብስ የሚያሼጥ። -(ተረት) ዛሬም ውስኪ ነገም ውስኪ ተነጎዲያ እስኪ

ውስጠ -በውስጥ ወደ ውስጥ ወደ ግቢ ወደ ማኽል። ወደየዮን ውስጠ ይኔጽር ውስጠ ወቦኡ ውስጠ ኀበ ንጉሥ ውስጠ እምነ መንጦላዕት -(ዘፀ፵ -፲፰ ፪ዜና - -፬። ፳፱ -፲፰ ሌ፲፮ -፲፪)

ውስጠ ወይራ -የቅኔ መንገድ ም፤ በዘና በተናባቢና በዝርዝር በአኃዝ ውስጥ የሚሰማ ቃል ናዝሬት ዘገሊላ የገሊላ ክፍል። ኢየሱስ ናዝራዊ የናዝሬት ሰው። ብእሲተ ዮርጊስ ወለደት ሠለስተ -(ክሣደ ጊዮርጊድ ውሐዘት ደመ ወማየ ወሐሊበ) ጳውሎስ እሳተ ወንጌል -(ሐዋርያ ) ምኵራበ ይሁድ አውዐየ በነበልባቡ -(በስብከቱ)

ውስጠ -የቅጽል ስም በውስጡ የሚሰማበት ቀታሊ ቅቱል፤ አዳም፤ ሠናይ ይህን የመሰለ

ውስጣዊ ውሳጣዊ -ዝኒ ማሁ ለውሳጢ። እንተ ውሳጣይ ኅት ሕዋሳት ውሳጣውያት አእምሮተ መጻሕፍት ውሳጣዊት ዘትሰመይ መንፈሳዊተ -(፪ዜና -፳፫ - ፈሳስ -ገ፶፫ ፊልክ ፪፻፴፬)

ውስጥ ውሳጥ -( ውሰጣት ውሳጣት) በቁሙ ሆድ ልብ መካከል ጓዳ ማጀት ዝንቱሰ ውስጡ ጽቡር ወሞቀኒ ብየ በውስጥየ ንዋየ ውስጥ ትበውእ ምውስጥ ለውስጥ -(ዳን፲፫ -፯። መዝ -፴፰። ዘሌ፩ -፲፫ ዜና -፲፰ -፳፪)

ውሩድ -(ዳን ዳት ርድ) የወረደ ተዋረደ ወደ ታች ያለ ወራዳ ሑት ውሩድ ልባቤሃ ውስተ ገጻ -(ሄርማ -፳፩)

ውርው -(ዋን ዋት ሩት) የተወረወረ የተጣለ የወደቀ። ወቆብዑ ውሩት ዲበ መታክፍቲሁ። ውርዋት -(ፊልክ -፶፮። አዋል)

ውርዙት -ንእስ ሕፃንነት፤ ጕልማስነት፤ ብዝና ዐፍላ። ኀሠሥክዋ እምነ ውርዙትየ ኀለ ውርዙቱ። መዋዕለ ውርዙቶሙ ንዘ ሀለዋ በኀይለ ውርዙቶን -(ጥበ፰ - ሱቱ -ዝ፲፬ -፰። ሔኖ፲ -፲፯ ዲድ -፲፬

ውርዛዌ - ዝኒ ከማሁ መዋዕለ ውርዛዌ ልቦ ርሥኣን ውርዛዌሁ -(ጥበ፪ -፮። ቅዳ) ፪ኛም፤ መጐልመስ አጐለማመስ፤ ልመሳ ይኾናል

ውርዝው -(ውት ዙት ዋን ዋት) ያደገ የጐለመሰ ብርቱ ብእሲት ውር(ዝው) ዙት ውርዝዋት አንስት  ደናግል ርሱያት ወስርግዋት ወውርዝዋት በሃይማኖት -(ስንክ -ግን፳ ዲድ -፲፬ መዋሥ)

ውርዝውና -ዝኒ ዓዲ ከማሁ፤ ጕልማስነት፤ -(አፈ -ተ፯ ፊልክ -፬። - -)

ውቁሥ -(ሣን ሣት ቅሥት) የተወቀሠ፤ የተነቀፈ የተዘለፈ።

ውቁር -(ራን ራት ቅርት) የተወቀረ የተዋቀረ፤ ውቅር፤ ጥርብ ልዝብ። እብን ውቁር በን እለ ኮና ውቁራተ -(፬ነገ -፲፪ -፲፪ ዘዳ፳፯ -)

ውቁዕ -(ዓን ዓት ቅዕት) የተወቃ የተገፈፈ የተላጠ

ውቁይ -ውቁይ -(ያን ያት ቅይት ቂት) የተቈረጠ፤ ቍርጥ አርዮስ ውቁይ በሰይፈ መር7 -(ስንክ -ነሐ፲፰)

ውቅሮ -ዋሻ ፍርኵታ ድጓድ መቃብር ተጠርቦ ተወቅሮ ንጾ ተቈፍሮ የተሠራ ዐዘቅት ውቅሮ። ቤት ዘውቅሮ ርእስ ዘውቅሮ ብነ ውቅሮ -(ነሐ፱ -፳፭ ጥበ፲፫ -፲፭ ዘዳ፫ -፳፯። ፬ነገ -፳፪ -)

 -ጥርብ ደንጊያ ገንቢዎች በየረድፉ የሚሰድሩት የሚደረድሩት አረፍት ዘኢኮነ በውቅሮ። ወበዐውዱ ሠለስቱ ጾታ ዘኢኮነ ውቅሮ፤ ወአርባዕቱ ጾታ በውቅሮ አቢያተ ዘውቅሮ መኒነከ -(፫ነገ - -፴፫። -፵፱። ድጓ) በውቁር ፈንታ ውቅሮ ይላል አያሰኝም። ማእዳት ዘእብን ውቅሮ -(ሕዝ፵ -፵፪)

ውቅየት -(ታት) መቍረጥ መቈረጥ አቁርራረጥ ረጣ ቅርጠፋ ዐጭር ቈራጣ ሰናፊል ምጣ ሱሪ፤ ግልድም ሽርጥ የወንድ የሴት ክቡራተ ቀማይሳተ ወውቅየታተ ሠናያተ ወገብሩ ውቅየተ ኀጺን ዘአምሳለ ግላ -(አዋል ስንክ -ሐም፭)

ውቅያኖስ -(ጽር ዖኬያኖስ) በቁሙ ለመ ማይ፤ ቢይ ባሕር ሰፊ ጥልቅ ዕሙቅ ባራቱ ማእዘን የመላ፤ ከየብስ እጅ የሚበልጥ እንደ የብስ ክፍል ያለው ባሕር ለታላቅ ብቻ ይኾናል ውቅያኖስ ግን ለታላቅ ብቻ ነው ባሕረ ውቅያኖስ -(ዮሴፍ። አርጋ -)

ውቱረ -ወትሮ አዘውትሮ በኹሉ ወገን በውስጥ በአፍኣ። ውቱረ ይዋሕየኒ ፆራር። ይከድንዋ በወርቅ ውቱረ -(ኢዮ፴ -፲፭። ዕብ፱ -)

ውቱር -(ራን ራት ትርት) የተወተረ የተዘወተረ፤ የዘወትር።

ውዑል -(ላን ላት ዕልት) የዋለ ባለውለታ ሙያተኛ። ጥቃ ገቦከ ዘልፈ ሰእኩን ውዑለ -(ደራሲ)

ውዑር ዋዕር -ዕጹብ ልዩ ልውጥ፤ አስቸጋሪ ጥልቅ ረቂቅ፤ ሊያምኑት እንጂ ደርሶ ሊያውቁት ሊመረምሩት የማይቻል ማን ነኪር ወዋዕር ርስ ምስ ውስተ ቅድስት ወመንክርት ወዋዕር ማን ልደት ዋዕረ ነከ -( -ጰላ)

ውዑይ -(ያን ያት ዒት) የነደደ የተቃጠለ ሙቅ ትኵስ የሚፋጅ ውዑየ ድ። ውዑይ ፍቅር ንብዕ ውዑይ ፋስ ውዑይ ይከወኑ ውዑያነ። ውዒት በእሳት -(ስንክ -ነሐ፳፬ አርጋ -፩። አፈ -ተ፴፩ ሕዝ፲፯ -፲። ኢሳ፴፫ -፲፪ መዝ -፸፬)

ውዒል ሎት -(ውዕለ ወዐለ ይውዕል የዐል) መዋል፤ ውሎ ውለታ ማድረግ፤ ንድ ቦታ ባንድ ሥራ ጧት እስከ ማታ መኖር መቈየት፤ ወይም መዋልና ማደር መሰንበት። እለ ይውዕሉ በስታይ ዘኀቤሁ ወዐልኩ ዮም ወዐሉ ኀቤሁ ይእተ ዕለተ። ይውዕል ወይትቀነይ አስከ ይመሲ ንውዕል ውስተ ፍኖት እንዘ ሐውር በረ ትዕይንት ወውዕለ እስከ ሐይዉ -(ኢሳ፭ -፲፩ ሩት፪ -፲፱። ዮሐ፩ -፵። መዝ -፻፫። ዘፍ፴፫ -፲፬። ኢያ፭ -) ለበወ ብሎ ስተዋለ ማለት ዐማርኛው ከዚህ ወጥቷል

ውዒር ሮት -(ወዐረ ይዌዕር የዐር ይውዐር ዐረ ወዐረ) ከር ማስቸገር ሸካራ ዋይ መኾን የግብር የነገር ማድነቅ ማን ዕጹብ ዕጹብ ማለት። መጽሐፍ ግን ፈን ተወ ይላል። አን እትዐር ጥበቦ -( -ቄር)

ውዕላ -(ዕብ ያዔል። ሱር ያዕላ ዐረ ወዕል፤ የበዳ ፍየል) ዋሊያ፤ የዋሊያ ወገን ቦኸር፤ ተባት ወይጠል። ሀየልን እይ -(ዘዳ፲፬ -)

ውዕል -(ላት) በቁሙ፤ ውል ዳን፤ የታ ነገር። -(ተረ) ውል አያወላውል -(ማርኛ)

ውእቱ -(ዕብ ወሱር ሁ። ዐረ ሁወ) ነባር ቅጽልና ነባር አንቀጽ የወጣ፤ ያኛው ርሱ ቅጽልና ዐጸፋ ለሩቅ ወንድ ይእቲ፤ ውእቶሙ። እሙንቱ፤ ውእቶን እማንቱ አንተ ንቲ ትሙ ትን፤ ንሕነ እያለ እስካሥር ይረባል፤ የሁን አፈታት እይ ውእቱ ብእሲ፤ ይእቲ ብእሲት። ለውእቶሙ ሕዛብ፤ በውእቶን መዋዕል ቅጽል ውእቱ ይጸንዕ እምኔየ ጸፋ ዝኩንና ዝስኩን ዝክቱን ተመልት፤ የዚህ አንጻር ናቸው አንቀጽ ሲኾን ደግሞ ነው አለ ኖረ ነበረ ኾነ፤ እስ ንሕነ ድረስ ኹሉ እንዲህ ውእቱና ኮነና ሀሎ ሱቱፋን ናቸው ይወራረሳሉ፤ ይኸውም ቀዳሚሁ ቃል ውእቱ ወውእቱ ቃል ኀበ እግዚእ ውአቱ ባለው ይታወቃል። ውእቱ ባንድ ጸፋና አንቀጽ ይኾናል ዘወረደሂ ውእቱ ወዘዐርገሂ ውእቱ። ፪ኛም በግብር ለውጥ ሩቁን በቅርብ ቅርቡን ሩቅ፤ አንዱን በብዙ፤ ብዙውን ባንድ፤ ወንዱን በሴት ሴቱን በወንድ ያናገራል። አን ውእቱ ዘይገብር ኵሎ፤ አምላክ ውእቱ ዘለብሰ ማርያም ይእቲ ኪሩቤል፤ ወኪሩቤል ሙንቱ ማርያም እምጸዊረ አምሳክ የፊተኛው ኹለቱ አካልን ያመጣል የኋለኛውም ኹለቱ ግብርን ይገልጣል። በአካል ለውጥ ግን በየራሱ ያናግራል ወይም ተለዋጭ ይኾናል ምላክ ማርያም ይእቲ፤ ማርያም እመ ምላክ ይእቲ ድንግል ዘተናገራ ኢሳይያስ ማርያም ይእቲ ማርያም ዘተናገራ ኢሳይያስ ድንግል ይእቲ እብን ዘወሀቦ ሰይጣን ለእግዚእነ ኅብስት ውእቱ ኅብስት ዘወሀቦ ሰይጣን ለእግዚእነ ብን ውእቱ። ቅጽል ባለቤት ሲርቅ ተለዋጭ ይባላል ተለዋጭ ደግሞ ግብር ነገር ባሕርይ ይተረጕማል አካል ያመጣል አስቀድመን እንደ ተናገርነ አካልም ኹኖ ቅጽልም ኹኖ ማሰሪያ ወደቀበት ተለዋጭ ይኾናል ኛም በሰዋስው ኹሉ በጥሬ በቅጽል በሚስማማው ቃል ይጣፍና ሳይነገር ተደብቆ ያስራል፤ ይልቁንም በቅኔ ንባብ ተሠግዎቱ ቃል ወተጸልቦቱ በሥጋ ያድኅን ዓለመ ወይቤዙ ሰብአ ዘተሰቅለ በቀራንዮ ሥግው አምላ ጽድቅ ወአኮ ብእሲ ዕሩቅ፤ የውእቱ መመርመሪያ ያድኅንና ይቤዙ ምላክ ጽድቅ ናቸው

ውዕየት ዕየት -መቃጠል መሞቅ መተኰስ መናደድ። ውዕየተ ሀገር። ውዕየተ ቤተ እግ ውዕየት ዘፍትወት በውዕየተ ልብ ልባዌ ወበውዕየተ ፍስ -(ራእ፲፰ -፲፰ አቡሻ - - -፳፬ -፩። ስንክ -ሐም፮ ፊልክ -፻፷፫)

ውዕይ -(ውዕየ፤ ወዐየ ይውዒ የዐይ) መንደድ መቃጠል  መጋም መጋል መሞቅ፤ መተኰስ መፋጀት፤ መቈጣት ማዘን እስከ በሕቁ ይውዒ ኢይውዕያ አልባሲሁ። ከመ ኢተዐይ በነዶሙ። ምድር ትውዒ እሙቀተ ፀሓይ ውዕየ ልብየ -(ዳን፫ -፲፱ ምሳ፮ -፳፯ ሢራ፰ - ሔኖ -፬። መዝ -፸፪) መጮኽ ዋይ ማለት፤ ቡታ መስደድ -(ትግሬ)

ውኩል -(ላን ላት ክልት) የተወከለ የታመነ እሙን ሥልጡን ሹም ወኪል ባለቤት አከ ውኩላነ ሀገመላእክት እለ ውኩላን ብነ -(ሕዝ፬ አፈ -ተ፳፫)

 -ያመነ አማኒ፤ ተአማኒ ተዘላይ፤ ምን አለብኝ ባይ፤ ተሰፋዊ ባለፍጹም ተስፋ ጻድቅ ከመ አንበሳ ውኩል። ውኩላነ ይረሲክሙ በእላንቱ ቃላት። ሰይጣን ውኩል በዝንቱ ግብር ውእቱ ኮነ ውኩለ ዲበ ምግባሩ -(ምሳ፳፰ - ፪ዜና - -፲፭ ቀኖ -ኒቅ፬ ፊልክ -፻፶፬)

ውኩይ -(ያን ያት ኪት፤ ክይት) የበራ ብሩህ ጽዱልልብሰ ብርሃን ውኩይ -(ገድ -ተክ)

ውኩፍ -(ፋን ፋት ክፍት) የተሰጠው የተቀበለ ተቀባይ የተሰጠ የተወደደ ወደው አሜን ብለው የሚቀበሉት ተሰጭ አእመርነ ውኩፍ ስእለትከ ኢይኩን ውኩፈ ርባኖሙ በእንተ ኍልቈ መጻሕፍት ውኩፋት ጉባእያት ውኩፋት -( - - -፶፩)

ውካታ -(ዐማርኛ) በቁሙ የብዙ ድምፅ ቱማታ ጩኸት።

ውካፌ -መቀበል አቀባበል ቅበላ የአምሩ ውካፌ ነገሩ ብዙኀ ዜያተ -(ዮሴፍ)

ውዋዔ -መጮኽ፤ አጪጪኽ ጩኸት ሰላም እብል በቃለ ስብሐት ወውዋዔ -(ስንክ -ታኅ፮)

ውውዓ -ጩኸት ውካታ፤ እልልታ ድንፋታ ቡታ ዋይታ ውውዓ ቀትል። ውውዓሆሙ ሰብአ ፍራስ። ውውዓ ኮነ ውውዓ ምውስጥ -(ኤር፬ -፲፱ -፳፱ ማቴ፳፭ -፮። ሶፎ፩ -)

ውዱስ -(ሳን ሳት ድስት) የተወደሰ የተመሰገነ ምስጉን። ንበር ምስለ ራን ከመ ትኩን ውዱሰ በኀበ እግዚ ኮነ ነሃቤ ወርቅ ወብሩር ወውዱስ ውእቱ በግብረ እደዊሁ ወዛ እምግባሩ ውድስት ዘዘከርናሃ ዛቲ ይእቲ መሥዋዕት ውድስት -(ፈላስ -ገ፵፰ ስንክ -ሐም፲። ዮሴፍ። አፈ -ተ፲፩)

ውዱቅ -(ቃን ቃት ድቅት) የወደቀ፤ የፈረሰ ውዳቂ ውድቃን ወዳቃ ዘቅዛቃ ውድቅ ናሁ ሆሎፎርኒስ ውዱቅ ውስተ ምድር በድኑ ረከብዎ ውዱቀ ወምዉተ። ያነሥኦሙ ለውዱቃን አረፍት ውድቅት ውዱቅ እማዕርግ የተሻረ ሽር -(ዮዲ፲፬ -፲፰ ተረ - ራ፵፱ -፲፫ ቀሌ)

ውዱይ -(ያን ያት ዲት) የተጨመረ ጭምር ቅልቅል።

ውዱድ [1]-(ዳን ዳት ድድ) የተወደደ ውድ፤ የተዋደደ። የተስማማ የማይወልቅ የማይነቃነቅ። ውስተ ውጽቦ ወርቅ ዕንቈ ሰርድዮን ውዱድ ድባር እለ ውዱዳን እለ ውዱዳት ማንቱ -(ምሳ፳፭ -፲፪። ዘፍ፵፱ -፳፮ ደራሲ)

[2]-ውዱድ የሰማይ ስምና ቅጽል መጨረሻ ሰማይ -(ሕዝ፩ -፳፫ -፳፬) በቀዳሚ ገብረ እግ ሰማየ ወምድረ፤ ወመልዕልተ ሰማይ ውዱድ አስተዳለወ መንበረ -(ደራሲ)

ውዳሴ -(ስያት) በቁሙ፤ ማወደስ መወደስ አወዳደስ ውደሳ ምስጋና። ኵሉ ዘነገርነ ውዳሴ ይውኅድ አምክብርክን ዝክረ ጻድቃን ምስለ ውዳሴ ፍቅረ ውዳሴ ከንቱ ውዳስያት -(ቄር ምሳ፲ -፯። -ተ፳፯)

ውዳሴ ማሪያም -ዝኒ ከማሁ ፍሬም ስለ ክብረ ድንግል የደረሰው የ፯ ድርሰት በ፯ቱ ዕለታት የሚደገምና የሚዜም የዜማ ትምርት መዠመሪያ

ውዳሴ አምላክ -የመጽሐፍ ከብዙ ድርሳናት የተለቀመ የሊቃውንት ቃል ባለ፯ ክፍል፤ ከሰኞ እስከ እሑድ የሚነበብ

ውዳኤ -መጨረስ -(ጥጨ) መጨረስ አጨራረስ ጭረሳ ጭራሽ ክታች፤ ፍጻሜ -(ፊልክ)

ውዳይ -(ትግሬ) ግብር ሥራ። ውዳይ ሐዋርያት -(ግብ -)

ውዴት -ዝኒ ከማሁ ነገር መሥራት ማሳበቅ ያንዱን ነውር ለሌላው መንገር በዦሮው ማግባት በልቡ መሰንቀር። ሰብቅ ክስ ሐሜት ውዴት እኪት ውዴት ዘሐሰት ኢይስማዕ ውዴተ ሐሰት ላዕለ ካልእ። መጽሐፈ ውዴት። በዓለ ውዴት። -(ዘፍ፴፯ -፪። ዘፀ፳፫ -፩። ዲድ -፬። ነሐ፬ -፰። - -)

ውድየት -መጨመር -(ጥጨ) መጨመር አጨመማመር ጭመራ፤ ጭምርነት ከመ ውድየት ወይን ሐዲስ በሐዲስ ዝቅ -(ስንክ -ኅዳ፲፯)

ውጉር -(ራን ራት ግርት) የተወገረ የተደበደበ ደንጊያ የተጐራበት የተመረበት ከቦሙ ለጣዖታት ውጉራነ ወስቡራነ -(ስንክ -መጋ፲፯)

ውጉእ -(ኣን ኣት ግእት) የተወጋ ውግ፤ የተወገጠ ውግጥ እለ ውጉኣን በኵናት። ቅብዐ ዘይት ውጉእ -(ዘፀ፳፯ - ዘሌ፳፬ -)

ውጉዝ -(ዛን ዛት ግዝት) በቁሙ የተወገዘ የተለየ ርጉም ውጉዘ ለይኩን ኢትከውን ውግዝተ -(ገላ፩ -፰። ዘካ፲፬ -፲፩)

 -ሕርም የተባለ የተከለከለ፤ ሕግ የነቀፈው ያጸየፈው ሥራ፤ ማናቸውም ኹሉ ቀቲልሰ እኍልቈ በይት ኀጣውእ ክሉኣ ወውጉዛት በልብ ወበሕግ -( - -፵፯)

ውጋጋን -(ዐማርኛ) ቁሙ፤ ወገግታ የፀሓይ የእሳት ጸዳል፤ፈገገን ጎሕንና ነግህን እይ

ውግረት -መውገር መወገር አወጋገር ውግራት ውርወራ ደንጊያ አጣጣል አወራወር የደንጊያ ሰልፍ ጦርነት፤  እንዳንደርቢና እንደ በረድ ያለ ተኰነነ ምዕረ በውግረት ወምዕረ በንድፈተ አሕጻ ኮነ ጸብእ ማእከሌሆሙ በንዋየ ሐቅል ወበውግረተ አእባን ወበሞፀፍ ቀተለ በውግረተ እብን ወበኀጺን -(ስንክ -ሐም፭ ዮሴፍ ቀሌ - - -)

 -ማጠን መታጠን፤ አስተጣጠን ተደመረ በውግረተ ዕጣን ለአማልክት -(ስንክ -ኅዳ፳፭)

ውግአት -መውጋኃት መወጋት አወጋግ ውጊ ውጊያ፤ ውግታት፤ በቁሙ ውጋት ውግ ሦክ -(ስንክ -ጥር፫)

ውግዘት -መውገዝ፤ መወገዝ አወጋገዝ በቁሙ ግዝት፤ ውጉዝነት ዘከልእዎ ቍርባነ በእንተ ውግዘት። ኢይፍታሕ እምኔሁ ግዘቶ -(አብጥ -፱። ቀኖ -ኒቅ፮)

ውጡሕ -(ሓን ሓት ጥሕት) የተከመረ፤ ክምር ልል ድርድር ድርብርብ ንብብር -(ኢያ፪ -፮። መሳ፲፭ -) ፀው ውጡሓን ርቡዕ ውጡሕ -(ኢሳ፴ -፴፫። ዘፀ፴፮ -፲፮)

ውጡን (ናን ናት ጥንት) የተወጠነ የተዠመረ ዥምር ውጥን

ውጥነት -መወጠን መዠመር -(ጥወዠ) መወጠን መዠመር፤ አወጣጠን አዠማመር ዥመራ፤ ማሪነት፤ ዥምርነት። ለእመ ሊፈጸሙ ውጥነቶሙ በሠናይ። ውጥነተ አጽባእ ኮነ ሞቱ በውጥነቱ -(አፈ -ተ፳፬ ፊልክ -፵፬። )

ውጣኔ -ዝኒ ከማሁ ዥመራ አዠማመር -(ሙጣን) መዠመሪያ። ውጣኔሁ ለጾም -(አቡሻ -፴፰)

ውፁእ -(ኣን ኣት ፅእት) የወ የራቀ የተለየ ልዩ ትርፍ ውፁኣን ምጽድቅ ውፁ ምጸጋሁ ውፁእ እም -( - -፱። መቃ -ገ፭ መዝ -፻፶፩)

ውፁፍ -(ፋን ፋት ፅፍት) የተወነፈ፤ የተጣለ የተወረወረ

ውፉይ -(ያን ያት ፊት) የተ ጭ፤ የተጠው ተቀባይ

ውፋዬ ወፍየት -(397) መስት፤ መቀበል ሰጣጥ አቀባበል ስጦ ቅበ -( - -፴፬)

ውፍረት -በቁሙ፤ መወፈር አወፋፈር ውፋ ግዘፍ፤ ወፍራምነት። መሰምረት መራር ምሪት። ቡሩ ይኩን ውፍረትክሙ ትወክሙ -()

ዉሓዬ ዋሕ ሕየት -መጐብኘት -(ጥጐ) መጐብኘት አጐበኛኘት፤ ጕብኘታ ጥየቃ ስለላ ጥበቃ እለ ይፈቅዱ ዋሕየ ዋሕይ ወሐተታ -(አፈ -ተ፳፬ ጥበ፲፬ -፲፬)

ዉሑይ -(ያን ያት ሒት) የተጐበኘ ብኙ ጥበቅ


 

No comments:

Post a Comment

ማውጫ

ሀ   ለ   ሐ   መ   ሠ   ረ   ሰ   ሸ   ቀ   በ   ተ   ቸ   ኀ   ነ   ኘ   አ   ከ   ኸ   ወ   ዐ   ዘ   ዠ   የ   ደ   ጀ   ገ   ጠ   ጨ   ጰ   ጸ   ፀ   ፈ   ፐ