ሀ ለ ሐ መ ሠ ረ ሰ ሸ ቀ በ ተ ቸ ኀ ነ ኘ አ ከ ኸ ወ ዐ ዘ ዠ የ ደ ጀ ገ ጠ ጨ ጰ ጸ ፀ ፈ ፐ
ተ [1] ፡ ተ፤ ደኃራይ ፊደል፤ ኻያ ኹለተኛ፤ መጨረሻና መደምደሚያ፤ በግእዝ አልፍ ቤት በአበገደ፤ ስሙ ታዊ፤ ታው፤ ቍጥሩ አራት መቶ፤ አኃዝ ሲኾን ተ ፡ (፬፻) አርባዕቱ ምእት ይባላል።
[2] ፡ ተ፤ የርባታ ተውሳክ፤ የመደረግና የመደራረግ ልማድ። ቀተለ፤ ተቀትለ፤ ተቃተለ። ከፈለ፤ ተከፍለ፤ ተካፈለ። ፈለጠ፤ ተፈልጠ ፣ ተፋለጠ፤ የመሰለው ኹሉ። ኹለተኛም፤ በ፮ ፊደላት ፡ (ተደዘጠጸሰ) ከሚነሡ በቀር፤ በግስ ኹሉ ላ፭ ሰራዊት ለሩቅ ሴትና ላራቱ ቅርቦች የትንቢት አንቀጽ ሥርው ይኾናል። ይህም፤ ቀተለት ልከ ኪ ክሙ ን ብሎ፤ ትቀትል ሊ ሉ ላ እያለ ሌላውን ኹሉ ያሳያል። ተደዘጠጸሰን መሠረት አድርገው በሚነሡ ግን ሥርውነት የለውም፤ ንቁል ነው። ይህም፤ ተተክለ ይተከል፤ ተደመረ ይዴመር፤ ተዘርዐ ይዘራዕ፤ ተጠውመ ይጠወም፤ ተጸውዐ ይጼዋዕ፤ ተሰብሐ ይሴባሕ ማለቱን ያሳያል። ሦስተኛም፤ አብዢና ምእላድ እየኾነ በመጨረሻ ቃል በዘር በነባር በአርእስትና በሳቢ ዘር ባንዲትና በብዙ ሴት ቅጽል ይገባል። በጥሬ ሲገባ፤ ወሀበ ብሎ ሀብት፤ ሐመየ ሐሜት፤ ፈነወ ፍኖት። በማብዛት ሲገባ፤ ብዕል ብዕላት፤ ገድላት፤ ገድላት፤ ኀይል ኀይላት። በነባር ሲገባ፤ ማይ ማያት፤ ሰማይ ሰማያት፤ ኮከብ ከዋክብት ይላል። በአርእስት ሲገባ፤ ቀቲል ቀቲሎት፤ ቀዊሞት ገቢሮት። በሳቢ ዘር ሲገባ፤ ቅትለት ቁሙት ግብረት ይላል። በሴቶች ቅጽል ሲገባ፤ ላንዲቱ ቀታሊት ገባሪት ሠናይት ክብርት፤ ለብዙዎች ቀታልያት ገባርያት ሠናያት ክቡራት ይላል። ትእምርት ትዕግሥት ትውክልት፤ ይህን የመሰለ፤ ባዕድ ከምእላድ ይባላል። ተ ከባዕዶችም ከምእላዶችም ይቈጠራል፤ እንደ ወ ክኹል ገብ ነው።
ተኃለቀ ፡ ተላለቀ፤ ተጫረሰ፤ ተለያየ ተበታተነ። ይትኃለቁ በበይናቲሆሙ። ተኃለቁ በበይናቲሆሙ ፡ (፪ዜና ፡ ፳ ፡ ፳፫። ኢዮ፬ ፡ ፲፩)።
ተኈለቈ ፡ ተቈጠረ፤ ከቍጥር ገባ። ተኈለቈ ምስለ ኃጥኣን ፡ (ኢሳ፶፫ ፡ ፲፪)።
ተኀለየ ፡ ታሰበ ነቃ። ውስተ ልበ ሰብው ዘኢተኀለየ። ሶበ ተኀለየት ውስቴትከ ኅሊና ዝሙት። ይትሐሰብ ሊተ ወይትኄለይ ፡ (ኪዳ። ፊልክ ፡ ፻፷፩። ስንክ ፡ ጥር፳፮)።
ተኀለደ ፡ ተጨረሰ ተፈጸመ፤ ተቈረጠ። ባለቅኔዎች ግን፤ ቈራጭነት ተሾመ ይሉታል። ወተኀልዶቱሰ ለሞት መጠውዎ። እመ አበይነ ይትኄለድ ብነ ቃለ አረጋዊ ፡ (ድጓ ፡ አዋል)።
ተሓለፈ ፡ ተማማለ፤ ተካየደ።
ተኃለፈ ፡ ተላለፈ ተሸጋገረ፤ ዕልፍ ዕልፍ አለ፤ የእግር የነገር። ተመላለሰ፤ ወዲያ ወዲህ አለ ተዛወረ። እንግዳ እለ ይትኃለፉ እምብሔር ለብሔር። ተኃለፍኩ በኵሉ እስራኤል። ሞፃእቱ ትትኃለፍ በሐይቀ ባሕር ፡ (ኪዳ። ፩ ፡ ፲፯ ፡ ፮። ክብ ፡ ነገ )።
ተሓሊ ፡ መትሕል፤ ፡ (ልት ላን ላት) የሚዞር የሚቀላውጥ፤ ዘዋሪ ቀላዋጭ፤ አውታታ ከርታታ፤ ተለል ተለል የሚል፤ እብድ እንዝህሉል። ወይከውኑ መትሕላነ ውስተ አሕዛብ። አንሰ ረከብኩ ነገረ እንዘ ኣነብብ መጻሕፍቲከ ዘፈኖከ ሊተ ምስለ ሰብእ መትሕላን እለ ኢኮኑ ፍጹማነ ወአልቦሙ አእምሮ ጥዩቀ ፡ (ሆሴ፱ ፡ ፲፯። ሃይ ፡ አበ ፡ ብንያ)።
ተሐልመ ፡ ታለመ፤ በሕልም ታየ።
ተሐልበ ፡ ታለበ፤ ወተቱን ሰጠ።
ተሐልየ ተሐለየ ፡ ተጐብ ተማለደ፤ ጕቦ ተቀበለ። ወመኰንንኒ ይትሐለይ ሕልያነ። ወብዙኀ ተሐልዮሙ እምኀበ ኢያሶን ወእምኀበ ቢጹ ኀደግዎሙ ፡ (ዕን፩ ፡ ፫። ግብ፲፯ ፡ ፱)።
ተኀልፈ ፡ ታለፈ ተዘለለ፤ ታለፈበት በላዩ።
ተሓመመ ፡ ተቃና ተመቀኛኘ። ትሓምሞ ወተቃንኦ። አኮ በተሓምሞ ፡ (፩ጢሞ ፡ ፮ ፡ ፬። ሮሜ፲፫ ፡ ፲፫)።
ተኀመሰ ፤ ዐምስት ኾነ ፤ ዐምስት ተባለ ፤ ካምስት ተከፈለ።
ተሓመወ ፡ ተማመቸ፤ ዐማችና ዐማት ተኳዃነ፤ ተጋባ ተዛመደ። ምንት አነ ከመ እትሓመዎ ለንጉሥ። እስመ ተሓመውነ ምስለ አሕዛብ። ኢትትሓመውዎሙ። እምእለ ይትሓመዉነ ውእቱ ፡ (፩ነገ ፡ ፲፰ ፡ ፲፰። ዕዝ፱ ፡ ፲፬። ዘዳ፯ ፡ ፫። ሩት፪ ፡ ፳)።
ተሓመየ ፡ ተማማ፤ ተነቃቀፈ፤ ተቀናና ተመቀኛኘ።ኢትትሓመዩ በበይናቲክሙ። ተሓምዮ ፡ (ያዕ፬ ፡ ፲፩። ገላ፭ ፡ ፳፮። ፩ጴጥ ፡ ፪ ፡ ፩)።
ተኀመየ ፡ ታሰረ ተጋዘ፤ እጅ እግሩን ተያዘ።
ተሐምየ ፡ ታማ ተነቀፈ፤ ተሰደበ። ለሊከ ዘትትሔመይ ወአኮ ውእቱ ፡ (አፈ ፡ ተ1፲፩)።
ተሐምደ ፡ ታመደ፤ ተበላ ጠፋ፤ ሐመድ ኾነ። ሰማያት ይጠበለሉ ወምድር ትትሐመድ ፡ (ኪዳ)።
ተሐምገ ፡ ታመገ፤ ተበላሸ፤ ደፈረሰ ፈዘዘ። አልቦ ተሐምጎ ውስተ ጽርየታ። ተሐምጉ ማያቲሆሙ። ረሥአ ወተሐምጋ አዕይንቲሁ ወኢይሬኢ ፡ (አፈ ፡ ተ፳፫። መዝ ፡ ፵፭። ዘፍ፳፯ ፡ ፩። ፩ነገ ፡ ፬ ፡ ፲፭)።
ተኀሠ ፡ ታሠሠ። ተሻ ተፈለገ፤ ተመረመረ። ጥበብ ተኀሠት በኀበ ኵሎሙ ቀደምት። እትኀሠሥ ለቤተ አስራኤል። ለእመ አነ ቀተልኩከ እትኀሠሥ በቅትለትከ ፡ (ሢራ፴፬ ፡ ፩። ሕዝ፴፮ ፡ ፴፯። ዮሴፍ)።
ተኃሠሠ ፡ ተፈላለገ ተመራመረ፤ ተከራከረ። ኢይትኃሠሱ በበይናቲሆሙ። አኀዙ ይትኃሠሥዎ። ወኮነ ትኃሥሦ ፡ (ኢሳ፴፬ ፡ ፲፮። ማር፰ ፡ ፲፩። ዮሐ፫ ፡ ፳፭)።
ተሐሰበ ፡ ታሰበ፤ ተቈጠረ ተገመገመ። እለ ኢይትሐሰቡ በሐሳበ ዓመት። ይትሐሰብ ሎቱ ጥበበ። ዘከመ ዝ እምኢተሐሰበ ምስለ ኃጥኣን። ዘኢተወክፈ ንስሓሁ ለኃጥእ ኀጢአተ ዚኣሁ ይትሐሰብ ላዕሌሁ ፡ (ሔኖ፸፭ ፡ ፩። ምሳ፲፯ ፡ ፳፰። ቄር ፡ ጰላ። ቀሌ)።
ተሓሰበ ፡ ተሳሰበ ተቈጣጠረ ተገማገመ፤ ተመራመረ። ወሶበ አኀዘ ተሓስቦቶሙ። ሶበ ትትሓሰብ ምስለ ሱታፌከ በእንተ ተግባርከ። ወዘሰ እንዘ ቦ ይነሥእ ፡ (ማቴ፲፰ ፡ ፳፬። ሢራሣ፪ ፡ ፫። ዲድ ፡ ፲፱)።
ተሐሰወ ፡ ተዋሸ፤ ታበለ ሐሰት ኾነ ፤ ተለወጠ። ኢተሐሰወ ቃለ እግዚ። በዘኢይትሔሰው ተስፋከ። ወለእመ ኮነ ነገሩ ከመ ዝ ወኢይትሔሰው ፡ (ሮሜ፱ ፡ ፮። ግንዘ። ዮሴፍ)።
ተሐሠየ ተሐሥየ ፡ ተደሰተ፤ ዕሠይ አለ። ይትፌሣሕ ሰማይ ወትትሐሠይ ምድር። ይትሐሠዩ ብከ። እንዘ ትትሐሠይ ፡ (ድጓ። ኩፋ ፡ ፳፭። ሢራ፴፪ ፡ ፲፩)።
ተሐስለ ፡ ተለበበ ተሸበበ፤ ተከተተ ተሰበሰበ። በሕሳለ ኀጢአቱ ኵሉ ይትሐሰል ፡ (ምሳ፭ ፡ ፳፪)
ተሐስየ ፡ ታሸ፤ ለፋ ተለፋ፤ ተረገጠ።
ተኀሥፈ ፡ ታከከ ቈሰለ፤ ተላጠ ተነካ።
ተሓረመ ፡ ተራረመ፤ ተለያየ ተገዛዘተ።
ተኀረሰ ፡ ታረሰ ተቀለበ፤ ተመገበ፤ ሳይጥር ሳያስብ። እስመ መጠነ ዝ መዋዕል ይነብራ እንዘ ይትኄረሳ ወይሤንያ ፡ (አስቴ፪ ፡ ፲፪)።
ተሓረደ ፡ ተራረደ፤ ተቀራደደ።
ተሐርመ ፡ ታረመ፤ ተተወ ሕርም ተባለ። ተለየ ተቀደሰ፤ ተከለከለ። ተገዝሩ ወተሐርሙ በእንተ ፍርሀቶሙ ለአይሁድ።ዘይትሔረም ለእግዚ። ዘከመ መሀርኩክሙ ትትሐረሙ ከማሁ ተዐቀቡ ፡ (አስቴ፰ ፡ ፲፯። ያዕ፩ ፡ ፳፮። ፩ቆሮ ፡ ፲፩ ፡ ፪)።
ተሐርሰ ፡ ታረሰ ተቈፈረ፤ ተሠራ። መብእስ ዘኢተሐርሰ ወኢተዘርዐ ፡ (ዘዳ፳፩ ፡ ፬)።
ተኀርወ ፡ ተበሳ ተነደለ፤ ተፈለፈለ። እብን ዘይትኀሮ። አእባን ዘይትኀረዉ ፡ (ዘፀ፳፭ ፡ ፯። ፴፭ ፡ ፰)።
ተኀርየ ፡ ተመረጠ፤ ተለየ ተወደደ።
ተሐርደ ፡ ታረደ፤ ተሠዋ። ተሐርደ በእንቲኣነ በግዐ መሥዋዕት ክርስቶስ ፡ (ቄር ፡ ጰላ)።
ተሐርጸ ፡ ተፈጨ ተደቈሰ፤ ደቀቀ ዐመድ ኾነ። ተሐርጸ በምዕር ፡ (ዳን፪ ፡ ፴፭)።
ተሓቀየ ፡ ተፋጨ ተፈጫጨ፤ ተፋተገ ተፈጋፈገ፤ እሳት ስለት ዘር ለማውጣት፤ የንጨት የብረት የሕያው ፍጥረት የተባት የንስት።
ተሓቀፈ ፡ ተቃቀፈ፤ ተያያዘ ተጣመረ። ጊዜ ለተሓቅፎ፤ ወጊዜ ለተራሕቆ እምተሓቅፎ። ተሓቀፉ በበይናቲሆሙ። ተኣምኁ ወተሓቀፉ ፡ (መክ፫ ፡ ፭። ፩ነገ ፡ ፳ ፡ ፵፩። ዕዝ፬ ፡ ፵፯)።
ተሐቅረ ፡ ተቈፈረ፤ ተመረመረ። ተናቀ ተነቀፈ፤ ተቃለለ።
ተሐቅየ ፡ ተፋጨ ተጋጨ፤ ጥርሱ። ተፈጨ ተቈረጠመ፤ ቈሎው።
ተሐቅፈ ፡ ታቀፈ ተያዘ፤ ዕቅፍ ኾነ። ተሐቅፈ በአብራክ ፡ (መጽ ፡ ምስ)።
ተሐበ ተሐበበ ፡ ተወደደ፤ ውድ ኾነ።
ተኀበለ ፡ ተደፈረ፤ ተናቀ ተጠቃ። ልማዱ ግን አድራጊ ነው። ተኀባሊ ፡ (አፈ ፡ ተ፬)።
ተኃበለ ፡ ተደፋፈረ ተጨካከነ።
ተሓበረ ፡ ቀለም ገባ ተነከረ፤ ተጌጠ ተሸለመ።
ተኃበረ ፡ ተባበረ ተነባበረ፤ ተጫፈረ ተጨማመረ። ኢይትኃበር ውስተ ማኅበሮሙ ዘደም። ወኢይትኃበር ምስለ ኅሩያኒሆሙ። ምስለ ጻድቃን ኢይትኃበር። ይከልኦሙ እምዐቂበ ልብ ተኃብሮቶሙ ምስለ ሰብእ ወተናግሮቶሙ ምስሌሆሙ። ተኃባሪ ውስተ ግዕዙ ለቅዱስ ፡ (መዝ ፡ ፲፭። ፻፵። ምሳ፫ ፡ ፴፪። ፊልክ ፡ ፺፩። ገድ ፡ ኪሮ)።
ተሐበየ ፡ ተሾመ፤ ተወከለ። ተዋሰ፤ ዋስ መድን ተያዥ አበ ልጅ ኾነ። ገብርከ ተሐበዮ ለዝ ሕፃን እምኀበ አቡሁ። ኢትትሐበዮ ለዘይጸንዐከ። መኑ ይትሐበዮ ለሰራቂ። ተሐበየኒ ከመ ኢይወፅእ እኩይ እምኔየ። ዘሂ ተሐበየ ወዘሂ ተሐበይዎ ኢይትዋሰቡ ፡ (ዘፍ፵፬ ፡ ፴፭። ሢራ፰ ፡ ፲፫። ፴፮ ፡ ፴፩። ኩፋ ፡ ፴፮። ፍ ፡ ነ ፡ ፳፬)።
፡ ተስፋ ሰጠ አማኰተ፤ አይዞኽ አለ። ምስጢሩ ከዚያው ከመዋዕለ ይገባል። ተሐበየ ሎቱ ብዙኀ ንዋየ። ተሐበየ ሎቱ ከመ ዮናናውያን ኢይትመየጡ ዳግመ ፡ (ዮሴፍ)።
ተሐባዪ ፡ የሚዋስ፤ የዕዳና የክርስትና የምንኵስና ዋስ የሚኾን። እስመ ተሐባይያን እለ ተወክፉነ በጥምቀት ናሁ ኮኑነ አበወ ወእማተ። ተሐበይት ፡ (ፈ ፡ መ ፡ ፭። ፍ ፡ ነ ፡ ፳፬ ፡ ፪)።
ተሐብለ ፡ ተዋሸ ታበለ፤ ተገመደ ተፈተለ፤ ታሰረ ተሰፈረ።
ተሐብለየ ፡ ተበዘበዘ፤ ተዘረፈ ተቀማ፤ ተማረከ። ገንዘቡንም ባለገንዘቡንም ያሳያል።
ተሓብለየ ፡ ተበዛበዘ፤ ተዘረፈ ተቀማ፤ ተቃማ፤ ተናጠቀ።
ተሐብሰ ፡ ታበሰ ታሰረ፤ ከግዞት ቤት ገባ።
ተሐብረተ ፡ ተወለወለ። ተሰነገለ፤ ታደሰ ተኰላ ፡ (ሕዝ፳፩ ፡ ፱)።
ተሐብቀቀ ፡ አደፈ ረከሰ፤ ተበላሸ ደፈረሰ፤ ታወከ ተሸበረ። ለ ይትሐበቀቁ ውስተ ብዙኅ ትካዝ። ይትሀወኩ አሕዛብ ወይትሐበቀቁ ሕዝብ ፡ (ሄርማ። ሱቱ፱ ፡ ፫)።
ተኀብአ ፡ ታባ ተሸሸገ፤ ተደበቀ ተሰወረ፤ ራቀ ረቀቀ። ተኀብኡ ውስተ ግበበ ምድር። ተኀቢኦሙ ታሕተ ዖም። ተኀብአት እምአዕዋፈ ሰማይ። አልቦ ምንትኒ ዘይትኀበ እምኔሁ ፡ (ኢሳ፪ ፡ ፲። ኩፋ ፡ ፴፬። ኢዮ፳፰ ፡ ፳፩። ፴፬ ፡ ፳፩)።
ተኀብዘ ፡ ታበዘ ተጋገረ፤ በሰለ ተዘጋጀ። ኅብዝት ዘተኀብዘት በዕለቱ ፡ (ፈ ፡ መ ፡ ፳፮ ፡ ፩)።
ተሐተ ፡ (ይትሐተት) ተመረመረ፤ ተጠየቀ።
ተሓተተ ፡ ተመራመረ፤ ተጠያየቀ።
ተሓቲ ፡ (ቲት ትያን ያት) ታች ታች የሚል፤ የሚዋረድ፤ ተዋራጅ፤ የትቢት ጠላት የትሕትና ወዳጅ።
ተኀትመ ፡ ታተመ፤ ተመለከተ፤ ተዘጋ ተጨረሰ፤ ተቀባ። ይትኀተሙ ውስተ ፍጽሞሙ። ይትኀተሙ አግብርት በመላኪሆሙ። ተሠጥቀት ምድር በአምሳለ ኆኅት ወመሠጠቶ ለውእቱ ሥጋ ፡ (አዳም) ወተኀትመት ከመ ቀዳሚ። ከመ ትትኀተም ጌጋይ። ምሥዋዕ ዘተኀትመ በሜሮን ፡ (ራእ፯ ፡ ፫። ፍ ፡ ነ ፡ ፶፩። ቀሌ። ዳን፱ ፡ ፳፬። ፈ ፡ መ ፡ ፲፱ ፡ ፩)።
ተኀንቀ ፡ ታነቀ ታንቆ ሞተ፤ በሌላ እጅ ወይም በገዛ እጁ። እንዘ ይትኀነቁ አምታትኪ። እስከ ትፈቱ ትትኀነቅ። ተኀንቀ ወሞተ። ፈቀደ ይትኀነቅ በእዴሁ ፡ (ጦቢ፫ ፡ ፰ ፡ ፲። ማቴ፳፯ ፡ ፭። ገድ ፡ ተክ)።
ተሐንጸ ፤ ታነጠ ተሠራ ፤ ተዘጋጀ። አመ ትትሐነጽ ኢየሩሳሌም። ተሐነጽክሙ ጊበ መሠረተ ሐዋርያት። ለክሙ ተሠርዐ ወተሐንጸ ትፍሥሕት (ድጓ። ኤፌ፪ ፡ ፳። ሱቱ ፡ ዕዝ፰ ፡ ፷፪)።
ተኀንጸጸ ፡ ተጠረጠረ፤ ተንጠረጠረ። ይትኀነጸጹ ከመ ዐለስ ፡ (ስንክ ፡ ጳጉ፭)።
ተኀንፈጠ ፡ ተሣለ ተቀረጸ። ክልኤቱ ማኅተም፤ አሐዱ እምኔሆሙ ዘወርቅ፤ ወካልኡ ዘኀጺን፤ ዘተኀንፈጠ ውስቴቶሙ አርኣያ አሐዱ ንጉሥ ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፱)።
ተሐንፈጸ ፡ ተነፈሰ ተበጠረ፤ ተለየ ተንጓለለ። ዘርዐ ሐለሰ አመ ተሐንፈጸ ይበውእ ኀበ ዘርዑ ሶበ ዘርዕዎ ፡ (አዋል)።
ተሐከ ተሐከከ ፡ ታከከ ተፈገፈገ፤ ተላገ ተሞረደ።
ተሀከከ ፡ (ተሀውከ) ታወከ ተሸበረ፤ ዐዘነ ተቈረቈረ። እስመ አኀው ሶበ ዘርከይዎ ለአባ ሙሴ ተብህለ ሎቱ ኢተሀከከኑ ልብከ፤ ወይቤ ተሀከኩ ወባሕቱ ኢተናገርኩ ፡ (ፊልክ ፡ ፶፱)።
ተሃከየ ፤ (ይትሃከይ) ፤ ተሳነፈ ፤ ተሰናንፈ ፤ ተደራራጊ።
ተሓወለ ፡ ተቀላቀለ ተደባለቀ፤ ተሳተፈ ተባበረ። ይደሉ ንዕቀብ ርእሰነ ወኢንትሓወል ምስለ ኃጥኣን። ኢትትሓወል ምስለ ብእሲ ደም። ኢትትሓወሉ ዕልዋነ ሃይማኖት። ይትፈለጥ ወኢትትሓወልዎ ፡ (ዲድ ፡ ፬ ፡ ፮። ቀሌ። ፪ተሰ ፡ ፫ ፡ ፲፬)።
ተሓወረ ፡ ተኺያኺያደ፤ ተካኺያደ።
ተሓወዘ ፡ ተጣጣመ፤ ተጠፋፈጠ ተመሳሰለ፤ ተከነዋወነ፤ የሥራ።
ተሐወጸ ፡ ተጐበኘ ታየ። ተሰለለ፤ ተፈቀደ ተቈጠረ። ከመ ትትሐወጽ እመንፈስ ቅዱስ። እለ የሐውሩ ከመ ይትሐወጹ ፡ (ኪዳ። ዘፀ፴ ፡ ፲፫)።
ተሐዋሲ ፡ (ሲት ስያን ያት) የሚንቀሳቀስ ተንቀሳቃሽ፤ ደመ ነፍስ ያለው፤ ያሙስና ያርብ ፍጥረት። ኢይሢጥ ምንተኒ እምተሐዋስያን አው እምእለ ኢይትሐወሱ። ነሶሳወ ተሐዋስያን ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፴፫ ፡ ፬። ጥበ፲፯ ፡ ፱)።
ተሐውለ ፡ ተጨመረ ተዘነቀ፤ ተደባለቀ። ኢይዴመሮ መርድእ ወኢይትሐወሎ ጻማ ወድካም ፡ (ዮሴፍ)።
ተኀውሠ ፡ ተቀላቀለ፤ ተደባለቀ። ሶበ ይትፌሣሕ ኢይትኀወሦ ጸልዕ። ተኀዊሦኑ እንጋ ወተቶሲሖ ክልኤሆሙ ኮኑ አሐደ ህላዌ ፡ (ምሳ፲፬ ፡ ፲። ቄር ፡ ጰላ)።
ተሀውከ ፡ ታወከ፤ ተናወጠ ተነዋወጠ፤ ተነሣሣ። ወተሀውከት ኵላ ሀገር። ባሕርሰ ይትሀወክ። ተሀውኩ ከመ ዕፀ ገዳም። ተሀውከ ልቡ ላዕሌሃ። ኢይኩን ተሀዋኬ ወኢሰካሬ ወኢቍጧኣ ፡ (ማቴ፳፩ ፡ ፲። ዮሐ፮ ፡ ፲፰። ኢሳ፯ ፡ ፪። ዮዲ፲፪ ፡ ፲፮። ፍ ፡ ነ ፡ ፭)።
ተሐውዘ ፡ ተደሰተ፤ ደስ ፈቅ አለው፤ ተድላ አገኘ። ተሐውዞ ወተደልዎ ፡ (ስንክ ፡ ኅጻ፲)።
ተሓዘለ ፡ ተዛዘለ፤ ተደራረበ፤ ተነባበረ።
ተሐዘበ ፡ ታዘበ፤ ተሰበለበ፤ ታሰበ ታማ፤ ተጠረጠረ። ባማርኛ ግን ናቀ መሰከረ ይኾናል፤ እገሌ ታዘበኝ እንዲሉ።
ተሓዘበ ፡ ተዛዘበ ተሳሰበ፤ ተጠራጠረ።
ተሐዝለ ፡ ታዘለ ተጫነ፤ ሸክም ኾነ ተለጠፈ። ተሐዚሎ በዘባንኪ ፡ (አርጋ)።
ተሀየ ተሀየየ ፡ ቸል ተባል፤ ተተወ ተጣለ። ብእሲ ዐማፂ ይትሄየይ ፡ (ምሳ፲፪ ፡ ፪)።
ተኀየለ ፡ ተበረታበት፤ ተደፈረ ተሸነፈ፤ ተጠቃ በታች ኾነ።
ተኃየለ ፡ ተበራታ ተበረታታ፤ ተጠናከረ ተጠነካከረ፤ አይዞኽ አይዞኽ ተባባለ። ተጋፋ ተዳፈረ፤ ተደፋፈረ። መኑ ይክል ምስሌሁ ተኃይሎ። ኢይትኃየሉ ዐሪገ። ኢትትኃየል ውሒዘ ፈለግ ፡ (ኢዮ፴፮ ፡ ፳፪። ዘፀ፲፱ ፡ ፳፬። ሢራ፬ ፡ ፳፮)።
ተሓየሰ ፡ ተነቃቀፈ፤ ተጣላ ተካሰሰ። ኅድጉ ለቢጽክሙ ዘተሓየስክምዎ እመ ቦ ዘትሓየሰ ምስለ ቢጹ ይኅድግ ሎቱ ፡ (ማር፲፩ ፡ ፳፭። ቅዳ። ቆላ፫ ፡ ፲፫)።
ተኃየሰ ፡ ተሻሻለ፤ ተበላለጠ ተላላቀ።
ተሃየደ ፡ ተቃማ ተሻማ፤ ተነጣጠቀ፤ ርስ በርሱ።
ተኃያሊ ፡ ተጋፊ ግፈኛ፤ ኀይለኛ። ለእመ ኮነ ተኃያሊ ባዕለ ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፴፭)።
ተሐይሰ ፡ ተነቀፈ፤ ተሰደበ ተነወረ። ከመ ኢትትሐየስ አንተ በእበደ ዚኣሁ። ከመ ኢትርፍቁ ለኵነኔ ወኢትትሐየሱ ፡ (ሢራ፳፪ ፡ ፲፫። ፩ቆሮ ፡ ፲፩ ፡ ፴፬)።
ተሐይከ ፡ ተላመጠ፤ ተለነቀጠ። ጽኑዕ ውእቱ ዘኢይትሐየክ ፡ (ቅዳ ፡ ሕር)።
ተሀይደ ፡ ተቀማ ተነጠቀ፤ ተማረከ፤ ገንዘቡ ወይም ርሱ ራሱ። ዘያስተጋብእ ብዕሎ በዐመፃ ይትሀየድ ብዕሉ እምኔሁ። ዘእንበለ ትትሀየድ ብእሲቱ እምኔሁ። ሰማይ ይትሀየድ። ተሀይዱ ደቂቅነ ፡ (ዲድ ፡ ፲፱። ኩፋ ፡ ፲፫። ሔኖ፹፫ ፡ ፫። ሱቱ ዕዝ፲ ፡ ፴፭)።
ተኀይጠ ፡ ተሸንገለ ተታለለ። አዳም ተኀይጠ እምሰይጣን። ኢተሀውከ ወኢደንገፀ ወኢተኀይጠ ፡ (ፈ ፡ መ ፡ ፫ ፡ ፪። አፈ ፡ ድ፳፭)።
ተሀይጰ ፡ ተነደፈ ተወረወረ፤ ተወጋ ተገመሰ። ከመ ሀየል ዘተነድፈ ወተሀይጰ ከብዶ። ኢተሀይጳ ውስተ ሕማም። ተሀይጳ በሐጸ ቃሉ ለጳውሎስ ፡ (ምሳ ፡ ፯ ፡ ፳፫። ተረ ፡ ቄር፲፮። ገድ ፡ ተክ)።
ተሐደሰ ፡ ታደሰ፤ ተለወጠ ዐዲስ ኾነ። ወናሁ ተሐደሱ ኵሎሙ። ተሐደሰት ወሐይወት መንፈሱ። ተሐደሰት ሕገ መንግሥት ፡ (ራእ፳፩ ፡ ፭። ኩፋ ፡ ፵፫። ክብ ፡ ነገ)። አርመመ ዝኅነ በማለት ፈነታ ተሐደሰ ይላል፤ ጸና ረጋ ለማለት። ተሐደሳ መንገሌየ ደስያት። ወአመ በሕፅኑ ተጸውረ ማዕቀበ አልፋ ሕፃን፤ ተሐደሰ ኢያሪኮ ብሉየ መዋዕል ወአዝማን ፡ (ኢሳ፵፩ ፡ ፩። ቅኔ)።
ተኃደረ ፡ ተዳደረ፤ ተጣጋ ተቃረበ፤ ተጎራበተ። አውፅኦሙ እምኔከ ወኢትትኃደሮሙ። ቦ እለ ኢተኃደራ ምስለ ካልኣቲሆን ፡ (ዘፀ፳፫ ፡ ፴፪። ሄርማ ፡ ገ፹)።
ተኃደገ ፡ ተፋታ ተላቀቀ፤ ተለያየ። ብእሲት ኢትትኃደግ ምስለ ምታ። ኢትፍቅድ ተኃድጎ ምስሌሃ። ኢያብዝኁ ተኃድጎ ምስለ አንስቲያሆሙ ፡ (፩ቆሮ ፡ ፯ ፡ ፲ ፡ ፳፯። ቀሌ)።
ተኀደፈ ፡ ታደፈ፤ተወለወ ተቀዘፈ፤ ታዘዘ ተጠበቀ። ተኀዲፎ በእደ ዚኣከ ፡ (ጥበ፲፬ ፡ ፮)።
ተሀድየ ፡ በሰለ ሟከከ፤ ዝንግልግል አለ። ባለብሉዮች ግን ተፋጨ ይሉታል። ተቀሎኩ ወተሀድያ ለአዕፅምትየ ፡ (ኢዮ፴ ፡ ፴)።
ተኀድገ ፡ ተተወ ተጣለ፤ ተፈታ ተለቀቀ፤ ቀረ ኖረ፤ ተከለከለ። ተኀድገ ይሁዳ። አህጉር እለ ተኀድጋ። ብእሲት ዘተኀድገት በዝሙት። ተኀድጉ ሰይጣናት ላዕሌነ። ኢይትኀደግ ዝየ እብን ዲበ እብን። ኢንትኀደግ እምለአቦ ቍርባን ፡ (ሚል፪ ፡ ፲፩። ሕዝ፴፮ ፡ ፬። ፈ ፡ መ ፡ ፭ ፡ ፲፮። ፊልክ ፡ ፺፮። ማቴ፳፬ ፡ ፪። ዘኍ፱ ፡ ፯)።
ተሓገዘ ፡ ተጋገዘ፤ ተረዳዳ። ወእምዝ ተሓገዝነ ወአጽናዕናሃ በሐብል ፡ (ግብ፳፯ ፡ ፲፯)።
ተሐገገ ፡ ታገገ ተወሰነ፤ ተጣፈ። ዝንቱ ሕግ ዘተሐገገ በዛቲ መጽሐፍ። ዕድሜ ዘተሐገገ ፡ (ፈ ፡ መ ፡ ፭ ፡ ፬። ፍ ፡ ነ ፡ ፵፩)።
ተሀጕለ ፡ ታጐለ ቀረ ተዳፈነ፤ የቅዳሴ የግብር። ጠፋ ተበላሸ፤ሞተ ታጣ፤ ተጐዳ። ተሀጕለት ግብጽ። ይትሀጐል አሐዱ እምነ አባልከ። አባግዕ ዘተሀጕላ። ተሀጕሉ እማእከለ ትዕይንት። ኢትፍቅድ ተሀጕኑሎቶሙ ፡ (ዘፀ፲ ፡ ፯። ማቴ፭ ፡ ፳፱። ፲ ፡ ፮። ዘኍ፲፮ ፡ ፴፫። ሱቱ ፡ ዕዝ፱ ፡ ፴፬)። በተሀጕለ ፈንታ ሀጕለ ይላል፤ የጣፊ ስሕተት ነው። ተሀጕል ሀጕለ ዐቢየ። ከመ ኢትህጐሉ። ወናሁ ሀጕሉ እሙንቱ ወዓለምኒ ፡ (ሔኖ፹፫ ፡ ፯። ኩፋ ፡ ፴፮። ሱቱ ፡ ዕዝ፬ ፡ ፳፪)።
ተሐግ ትሐግ ፡ ለምለም ሣር፤ ሰርዶ፤ የሰርዶ ዐይነት ጨሌ፤ አበቃቀሉ ችግ ችፍግ ያለ። ከመ አባግዕ ውስተ ተሐግ። በኀዲገ መርዔት ውስተ ተሐግ ፡ (ሚል፭ ፡ ፮። ስንክ ፡ ግን፲፰)።
ተሐግዘ ፡ ተገታ ቆመ፤ ተከለከለ። ታገዘ ተረዳ፤ ተደገፈ።
ተሃጐለ ፡ (ይትሃጐል) ተጓጐለ፤ ተጣፋ ተጣጣ።
ተኀጥአ ፤ ታጣ ጠፋ ፤ ሸሸ ኰበለለ። ተኀጥአ ሲሳይ። በተኀጥኦተ መምህር። በእንተ ዘይትረከብ እምዘተኀጥአ።ተኀጥአ ወአምሠጠ። አግብርት እለ ተኀጥኡ እምአጋዕዝቲሆሙ (ዮሴፍ። ምሳ፳፱ ፡ ፲፰። ፍ ፡ ነ ፡ ፵። ፩ነገ ፡ ፲፱ ፡ ፲፪። ፳፭ ፡ ፩ )።
ተሓጸ ተሓጸጸ ፡ ተካፈለ ተከፋፈለ፤ ተናነሰ ተቀናነስ።
ተሓጸረ ፡ ተጣጠረ ተካበበ፤ ርስ በርሱ። እስመ ተሓጸራ ምስለ ቢጾን ፡ (ሄርማ ፡ ገ፱)።
ተሓፀየ ፡ ተጫጨ፤ የጋብቻ ውል ተዋዋለ።
ተሐጽረ ፡ ታጠረ ተከበበ፤ ተዘጋ ተጠበቀ። በወላትወ ነኪር ተሐጺረከ። ፍኖትየ ተሐጽረ በሦክ። ከመ ትትሐጸር በመስቀልከ ፡ (ተረ ፡ ቄር፰። ስንክ ፡ ኅዳ፲፯። ቅዳ)።
ተኀፅበ ፡ ታጠበ ጠራ፤ ከርስሐት ተለየ። ተኀርፅበት ሥጋሃ በማይ። ዘይትኀፀብ እምድኅረ ገሰሰ በድነ፤ ምንት ይበቍዕ ተኀፅቦ። ተኀፂቦ ውእቱ ልብስ ፡ (ዮዲ፲ ፡ ፫። ሢራ፴፩ ፡ ፴። ዘሌ፲፫ ፡ ፶፰)።
ተሐፅነ ፡ ጠባ ጠጣ፤ አደገ፤ ታቀፈ ዕቅፍ ኾነ። ተሐፀንኩ በጥብ። ትትሐፀኒ ሐሊበ አሕዛብ። ደቂቅ እለ ተሐፅኑ ምስሌሁ። ተሐፅነ በኵሉ ምግባረ ሠናይ። ዘከመ ተሐፀንኪ ውስተ እዴየ ፡ (ኢዮ፫ ፡ ፲፪። ኢሳ፰ ፡ ፲፮። ፪ዜና ፡ ፲ ፡ ፰። ስንክ ፡ ጥቅ፲፫። አስቴ፬ ፡ ፰)።
ተሐፅየ ፡ ታጨ፤ ማጫ ወሰደ ተቀበለ። ድንግል እንተ ተሐፀየት ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፵፭ ፡ ፵፰)።
ተኃፈረ ፡ ተፋፈረ፤ ተፋራ ተፋዘዘ። ወይም ኀፍረት ለኀፍረት ተጋለጠ ተገላለጠ፤ ተደፋፈረ፤ የሩካቤ።
ተኀፍረ ፡ (ተደራጊ) ታፈረ ተፈራ፤ ከበረ።
ተኀጽወ ፡ ተሰለበ፤ ተሰነጋ፤ እስኪቱን ተቀማ። ለእመ ተኀጽወ እምሰብእ በትዕግልት ፡ (ቀኖ ፡ ፲፭)።
ተሖሰ ፡ ተሐውሰ፤ ተነቃነቀ፤ ተናወጠ ተንቀሳቀሰ፤ ተወዛወዘ ወዲያ ወዲህ አለ፤ ዐለፈ። ኢይትሐወስ እንከ እመንበሩ። ዘመደ እንስሳ ወዘይትሐወስ። ብርዕ ዘይትሐወስ እምነፋስ ይትሐወስ ጽላሎት ፡ (ኢሳ፵፮ ፡ ፯። ዘፍ፩ ፡ ፳፬። ማቴ፲፩ ፡ ፯። ማሕ፬ ፡ ፮)። ታወሰ አስታወሰ ማለት ዐማርኛው ከዚህ ወጥቷል።
ተሖረ ፡ ተሐው(ወ) ረ፤ ተኼደ፤ ተኼደበት። ተሠራ፤ ተደረገ።
ተለምደ ፡ ተለመደ፤ ታወቀ ተጠና፤ ልማድ ኾነ፤ ትምርቱ ሥራው።
ተለምጸ ፡ ተለመጠ፤ ተላመጠ፤ ተለማመጠ።
ተለሰነ ፡ በቁሙ፤ ተመረገ፤ ጭቃው ቤቱ።
ተለቃሒ ፡ ልቆኛ፤ ተማሪ ፥ ተበዳሪ። ለቃሒ ወተለቃሒ ፡ (ምሳ፳፱ ፡ ፲፫)።
ተለቅሐ ፡ ተለቃ ተበደረ፤ ወስደ ተቀበለ፤ የገንዘብ የትምርት። እፈዲ እሎንተ ዘተለቃሕኩ፤ ትምርት ፡ (አረጋ ፡ መል፴፭)። ዘይትሌቃሕ ከመ ዘይሌቅሕ። ኢትትለቃሕ እንዘ ነዳይ አንተ። ዘይትሌቃሕ ሥርናየ ውስተ ክምሩ ፡ (ኢሳ፳፬ ፡ ፪። ሢራ፲፰ ፡ ፴፫። ምሳ፳ ፡ ፬)። ዐለፈ ተሰጠ፤ ተሰጭ ኾነ ገንዘቡ ፥ ካበዳሪ ወደ ተበዳሪ።
ተለቅሰ ፡ ተለቀለ፤ ልቅሶው ሐዘንተኛው። ተለቀሰለት፤ ሟቹ።
ተለበወ ፡ ታወቀ፤ ተረዳ። ወሰማያዊሰ ብእሲ ይትሌቦ ክርስቶስ ፡ (ቄር ፡ ጰላ)። ተለበመ፤ ተዘጋጀ ተሰናዳ። የመሧዕትን ዶቄት ልብም ማለት ፥ ዐማርኛው ከዚህ ወጥቷል።
ተለብሰ ፡ ተለበሰ፤ ልብስ ኾነ።
ተለብጠ ፡ ተለበጠ፤ ተሸፈነ። ከመ ወርቅ ዘተለብጠ ዲበ እብነ ያክንት ፡ (አርጋ)።
ተለትመ ፡ ተለተመ፤ ኅፅቦ ጕርዶ ወጣ፤ ታሸ ታበቀ።
ተለኣኪ ፡ የሚላክ ተላኪ፤ አገልጋይ። ተለኣክያን ለምሥዋዕ ፡ (ፈ ፡ መ ፡ ፲ ፡ ፭)።
ተለክፈ ፡ ተለከፈ፤ ተነካ። እግዚ ዘኢይትለከፍ። እሳት ዘኢይትለከፍ ፡ (ድጓ። ቅዳ)።
ተለክአ ፡ ተለካ፤ ተሰፈረ። ተጣበቀ፤ ተቀረቀረ፤ ተቸነከረ። ወተለካአት ሐመር ማእከለ አእባን ልዑላት። እስከ ተለክአ ውስተ ልቡ። አእጋሪከ በቅንዋት እለ ተለኩ ፡ (ግብ፳፯ ፡ ፵፩። ዮሴፍ። ደራሲ)።
፡ ተጣፈ ታተመ፤ ተቀረጸ። ተለክአ ዲብዲቆን ዘማኅበረ ነቢያት። ዲናር ዘተለክአ በስሙ ለቄሳር ፡ (አርጋ ፡ ፫። መጽ ፡ ምስ)።
ተለጕመ ፤ ተለጐመ ፥ ተዘጋ ፤ ዝም አለ ፥ ተገታ። ናሁ ተለጕመ ዜማ መሰንቆ ጥዑም። ተለጕሞ ልሳን። ይትለጐም ጸላኢ (ግንዘ። አፈ ፡ ተ፳፬። ማር ፡ ይሥ፮ ፡ ፪)።
ተለፍጸ ፡ ተለፈጠ፤ ታሸ ታበቀ ተለወሰ። ሊጥ ማለት የዚህ ዘር ነው።
ተሊም ሞት ፡ (ተለመ ይተልም ይትልም። ዕብ ታሌም) መትለም፤ መሠንጠቅ፤ ዕርሻ መዠመር ማረስ፤ በፈር ላይ ፈር እየጨመሩ መኼድ መመላለስ።
ተሊው ዎት ፡ (ተለወ ይተሉ ይትሉ። ዕብ ታላ። ሱር ትላ፤ ሰቀለ። ዐረ ተላ፤ ተጋ) መከተል መምሰል፤ መውደድ፤ ተከትሎ መኼድ፤ ልብን ሐሳብን ባንድ ነገር ላይ መስቀል ማንጠልጠል፤ ማሰር ማቈራኘት ርሱን መጠበቅ፤ ተግቶ ማየት መመልከት፤ የሎሌ የተማሪ የሕዝብ። ንዑ ትልዉኒ፤ ወተለውዎ ብዙኃን አሕዛብ። ሠናይ ተሊዎቱ ለእግዚ። ኀደግነ ተሊዎቶ ለአምላክነ። ይሢሙ ህየንቴሁ ካልአ ዘይተልዎ። ዘይተልዋ ለዘማ። ተለወ ነፍሱ ኀቤሃ ጥቀ። እመ ተለወ ልብየ ብእሲተ ብእሲ። ተለወት ነፍሶሙ ኀበ ጣዖት ፡ (ማቴ፬ ፡ ፳ ፡ ፳፭። ሢራ፵፮ ፡ ፲። ኢሳ፶፱ ፡ ፲፫። ፍ ፡ ነ ፡ ፬። ሢራ፲፱ ፡ ፪። ጦቢ፮ ፡ ፲፰። ኢዮ፴፩ ፡ ፱። ኩፋ ፡ ፲፪)። ዴገነ ለክፉ ብቻ ነው፤ ተለወ ግን ለክፉም ለበጎም ይኾናል፤ የዴገነን ፍች ተመልከት። ዴገኖሙ ወተለዎሙ። ኢተለውዎሙ ድኅሬሆሙ። ሑሩ ፍጡነ ወትልውዎሙ፤ የክፉ ፡ (ዘፍ፲፬ ፡ ፲፬። ፴፭ ፡ ፭። ኢያ፪ ፡ ፭)። ተሎ ቶሎ ማለት ከዚህ ወጥቷል።
ተላሀቀ ፡ (ይትላሀቅ) ተላላቀ ፥ ተበላለጠ፤ እኔ እበልጥ ተባባለ።
ተላሃዪ ፡ ተጫዋች ፥ ተጨዋዋች፤ ጨዋተኛ፤ ጨዎታ ዐዋቂ። ሰካሪ ወተላሃዪ ወነፋኄ እንዚራ ፡ (ፈ ፡ መ ፡ ፴፬ ፡ ፩)።
ተላሀየ ፡ (ተደራጊና ተደራራጊ) ተጨወተ፤ ተጨዋወተ። ወአኀዝኩ እትላሀይ ምስሌሆን። ከመ ዘይትላሀይ። ኦ ድንግል አኮ በተላሆዮ ዘልህቂ ከመ አዋልደ ዕብራውያን። ተላህዮሰ እንተ ይእቲ ተላህዮ በዕፅ ወእንዚራ ወአርጋኖን፤ ወተረፈ ንዋያተ ማሕሌት ዘተውኔት ሕሩም ውእቱ ፡ (ሄርማ። ገድ ፡ ተክ። ቅዳ ፡ ሕር። ፈ ፡ መ ፡ ፴፪)። ዝሙት ወተላህዮት። ለእመ ተረክበት ብእሲት ምስለ ካልእታ ይትላሀያ በበይናቲሆን ፡ (ሲጻፉ ሲጋጩ)። ለእመ ተላሀየ ካህን በነፍስተ ሥጋሁ ፡ (ገድ ፡ አዳ። ቄድር)።
ተላህያ ፡ ተላህዮታ፤ ተከውሶታ ወተሀውኮታ፤ ሞገዳ ወማዕበላ ፡ (መዝ ፡ ፺፪)።
ተላመደ ፡ በቁሙ፤ ተለማመደ፤ ተዋወቀ።
ተላቀሰ ፡ በቁሙ፤ ተለቃቀሰ ተዛዘነ።
ተላበሰ ፡ (ተደራራጊ) በቁሙ፤ ተለባበሰ፤ ርስ በርሱ። ባማርኛ ግን አደግድግ ሲል ተላበስ ይላል፤ መላበስ የካህናት፤ መታጠቅ ማሸንፈጥ የሕዝብ የሰራዊት።
ተላብ ተላቤ ፡ ተልባ፤ ክታን። ተላቤ ዘኢነሥኡ ፍሬሁ። እመ ዘራዕከ ከሙነ ተእርርኑ ተላቤ። ተላቤ ወሰገም ማሰነ ፡ (ስንክ ፡ ሐም፭። መቃ ፡ ገ፭። ዘፀ፱ ፡ ፴፩)።
ተላዐለ ፡ ተናሣ ተነሣሣ፤ ተከባበረ፤ ተበላለጠ ፥ እኔ እበልጥ ፥ እኔ እበልጥ ተባባለ። ግእዝና ራብዕ ካለመለየት የተነሣ በተላዐለና በለዐለ ፈንታ ተለዐለ ይላል፤ የመምርና የጣፊ ስሕተት ነው።
ተላዕ ፡ (ዓት) ደረት፤ ፍርንባ፤ ካንገት እስከ ሆድ ያለ ክፍል ፡ (ዘፀ ፡ ፳፱ ፡ ፳፮ ፡ ፳፯። ዘሌ፯ ፡ ፴)።
ተላከፈ ፡ ተላከፈ፤ በቁሙ፤ ተቃመሰ። ተለካከፈ ተነካካ፤ ተጋጠመ ተገናኘ። ክነፊሆሙ ስፉሓን ወርቡባን፤ ወይትላከፉ በበይናቲሆሙ ፡ (፪ዜና ፡ ፫ ፡ ፲፫)።
ተላክአ ፡ ተለካካ። ተጋጠመ ተያያዘ ፥ ተጣመረ። ይትላካእ ብእሲ ምስለ እኍሁ፤ ወይጣበቁ ወኢይትፋትሑ ፡ (ኢዮ፵፩ ፡ ፰)። አንዳንድ መጣፍ ግን ያስተላክእ ይላል ፥ ስሕተት ነው፤ ይትላካእ ያለውን ይጣበቁ ብሎ ተርጕሞታል።
ተላኰየ ፡ ተለጐጠ፤ ተላጐጠ ተጣላ፤ ተዘባዘበ ተወዛገበ፤ ተሟገተ ተከራከረ። ኢትትላኰይ ምስለ ብእሲ ነባቢ። ትትላኰዩኒ ወኢተኀፍሩ። ወተላኰይዎሙ ለዐበይቶሙ። ኢትትላኰይ በግብር ዘኢይበቍዕ ፡ (ሢራ፰ ፡ ፫። ኢዮ፲፱ ፡ ፫። ነሐ፲፯ ፡ ፲፯። ፪ጢሞ ፡ ፪ ፡ ፲፬)።
ተላወሰ ፡ በቁሙ፤ ተለዋወሰ ፥ ተንቀሳቀሰ ፥ ታወከ ተነሣሣ። እስመ ትትላወስ ኅሊናሆሙ ፡ (ምሳ፳፮ ፡ ፲)።
ተላዊ ፡ (ዊት ውያን ያት፤ ለውት) የሚከተል፤ የሚመስል፤ መሳይ ተከታይ፤ ተማሪ ተባባሪ፤ ተሰማሚ። ተላዊሆሙ ለሐዋርያት። ተላውያን ለኀበ ቃሉ። ተለውተ አሠሮሙ ለተንባላት። ዝንቱ ግብር ኢኮነ ተላዌ ለሕገ ጠባይዕ ፡ (ሃይ ፡ አበ። ፊልክ ፡ ፫። መጽ ፡ ምስ። አፈ ፡ ድ፳፯)።
ተላጸቀ ፡ ተላጠቀ ፥ ተለጣጠፈ፤ ተጣጋ ተያያዘ፤ ተጣመረ፤ ተቃረበ። እለ ይትላጸቃ በበይኖን። ነፍስ እንተ ትትላጸቅ ምስለ እግዚ። እመ ቦ ብእሲ ዘተላጸቀ ወሰከበ ምስለ ብእሲቱ በእሎን መዋዕል። ተላጽቆተ ስኢል ፡ (ዘፀ፳፰ ፡ ፯። አፈ ፡ ተ፳፰። ፈ ፡ መ ፡ ፲ ፡ ፫። አፈ ፡ ተ፳፯)። በቀርበና በለጸቀም ፈንታ ተላጸቀ ይላል። ሶበ ይትላጸቆ ብእሲ ወየሐውር በገቦሁ ይረግዞ። ይትላጸቅ ረድእ ለመምህሩ። ጎሩ ዘይትላጸቅ ፡ (ዮሴፍ። ቄር ፡ ጰላ። ፍ ፡ ነ ፡ ፴፯)።
ተላጸየ ፡ ተላጨ፤ ተለጫጨ ፡ (ዘሌ፲፫ ፡ ፴፫። ፲፬ ፡ ፰ ፡ ፱። ሚክ፩ ፡ ፲፮)። ተላጸየ ርእሶ። ለትትላጸይ ወእመ አኮ ለትትቀረፅ ፡ (ግብ፲፰ ፡ ፲፰። ፩ቆሮ ፡ ፲፩ ፡ ፮)።
ተሌለየ ፡ ተለየ፤ ተለያየ። ተሌለይ እምኔየ። ናሁ እትሌለይ እምኵሎሙ አዝማድየ። እፎ ተሌለዩ ፡ (ዘፍ፲፫ ፡ ፬። ግንዘ። ሔኖ፰ ፡ ፲፬)።
ተልኈሰሰ ፡ ተሾከሾከ፤ ሰውዮው ሹክሹክታ ሰማ፤ ወይም ሹክሹክታው በዦሮ ተሰማ። በእንተ ዝሙት ዘተልኈሰሱ ፡ (ማር ፡ ይሥ፰)። ተደገመ ተልከሰከሰ፤ አስማቱ ጸሎቱ።
ተልሓፍ ፡ ሐዘን፤ ጭንቅ። ወምንት ተልሓፍየ ለዘአፍኣ እኴንኖ ፡ (፩ቆሮ ፡ ፭ ፡ ፲፪)።
ተልህቀ ፡ (ይትለሀቅ) ተላቀ ተበለጠ፤ ላቂያና ብልጫ ዐጣ፤ አነሰ።
ተልሕኰ ፡ ተሠራ፤ ተፈጠረ። ዘተልሕኰ ቅድመ። እምድር ተልሕኰ ብእሲ። ተልሕኮተ ሥጋ ቀደመ እምንፍኀተ ነፍስ። ዛቲ ነፍስ እንተ ተልሕኰት በአምሳሊከ ፡ (ጥበ፯ ፡ ፩። ኪዳ። ማር ፡ ይሥ፳፰ ፡ ፬። ግንዘ)።
ተልሕየ ፡ ተጌጠ፤ ተሸለመ፤ ተኳለ ተቀባ፤ ለማማር መልክ ለመጨመር። ወአኀዙ አይሁድ በዝ በዓል ይትለሐዩ በአዕጹቀ በቀልት። ወኅሩያን በቅድሜሁ ይትለሐዩ ከመ ብርሃነ እሳት ፡ (ዮሴፍ። ሔኖ፴፱ ፡ ፯)።
ተልሕጸ ፡ ተላጠ፤ ተመለጠ። ገጹ ሥጋሁ ተልሕጸ ፡ (ገድ ፡ አዳ)።
ተልኋሰሰ ፡ ተሾካሾከ፤ ርስ በርሱ። ዘተልኋሰሱ በእዝን ፡ (ሉቃ፲፪ ፡ ፫)። አብነቱ ግን፤ ዘኒ አልኈሰስክሙ ነው።
ተልሚድ [1] ፡ (ዕብ ታልሚድ። ሱር ታልሚዳ። ዐረ ተልሚዝ-ድ)። ተማሪ፤ ደቀ መዝሙር። ዘነገሮ ጴጥሮስ ለቀሌምንጦስ ተልሚዱ ፡ (ቀሌ። ስንክ ፡ ሐም፭)።
[2] ፡ ተማሪ፤–ለመደ።
ተልዕለ ተለዐለ ፡ ልዒል፤ ልዒሎት፤ ለዐለ።
ተልእከ ፡ ተላከ፤ አገለገለ። ተልኢኮሙ ኀቤሁ። ተንሥአት ወተልእከቶሙ። ወተልእኩ ውስተ ደብተራሁ ፡ (ቀኖ። ማር፩ ፡ ፴፩። ሢራ፳፬ ፡ ፩)።
ተልፍዮስ ፡ (ጽር ታልፒዎስ። ዕብ ታልፊዮት) የዘበኞች ቤት፤ የሰልፍ መሣሪያ፤ ጋሻ ጦር ሰይፍ ቀስት የሚሰቀልበት ፡ (ማሕ ፡ ፬ ፡ ፬)።
ተሎሰ ፡ ተቦካ፤ ተለወሰ። ናእት ዘኢተሎሰ በብሒእ ፡ (መጽ ፡ ምስ)።
ተመሃሪ ፡ ተመሃሪ፤ ተማሪ ፥ ረድእ ደቀ መዝሙር። ተመሃርያን ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፲)።
ተመላለሰ ፡ (የተመለሰ ድርብ) በቁሙ ፥ ዞረ ወዲያ ወዲህ አለ የእግር። ባሕታዊ እኩይ ዘይትመላለስ ውስተ አድዋል ፡ (ፊልክ ፡ ፭)። አንሶሰወን እይ።
ተመላትሐ ፡ ጕንጮቹን ያዘ፤ ፊቶቹን ጸፋ በ፪ እጁ፤ የሐዘን የአንክሮ። ባለቅኔዎች ግን አገና ተጣፋ ይሉታል፤ በጥፊ ተማታ ቢያሰኝ እንጂ አገና አያሰኝም፤ እውነተኛ ፍችው ጕንጭንና ፊትን አይለቅም።
ተመልሐ ፡ ተጨወየ፤ ጨው ኾነ፤ በጨው ተጣፈጠ። ኵሉ በጼው ይትሜላሕ ፡ (ቀሌ። ስንክ ፡ ሐም፯። ማር፱ ፡ ፵፱። ሕዝ፲፮ ፡ ፬)።
ተመልኀ ፡ ተነቀለ፤ ተመዘዘ። ወበኀይለ ነፋስ ይትመላኅ።እምቅድመ ይትመልኁ መባርቅት። ሰይፍ እንተ ተመልኀት ፡ (ጥበ፬ ፡ ፬። ቅዳ ፡ አፈ። ሕዝ፳፩ ፡ ፳፰)። ታረመ ተነጨ ተመለጠ፤ ምስጢሩ ያው መነቀል ነው። ተመልኀ ክነፊሃ። ይበኪ አስከ ተመልኁ ሥዕርተ አዕይንቲሁ ፡ (ዳን፯ ፡ ፬። ፊልክ ፡ ፶፭)።
ተመልሰ ፡ ተመለሰ፤ ተወለወለ ተሰነገል።
ተመልአ ፡ ተመላ፤ ጠገበ ውስጡ ኹሉ ያዘ፤ ተመላበት ፥ በዝቶ ዐደረበት፤ ኀዳሪው። ተመልአት ደብተራ ስብሐተ እግዚ። ኢያሱ ተመልአ መንፈሰ ጥበብ። ተመልአት አየር እምነ መላእክት ፡ (ዘፀ ፡ ፳፰። ዘዳ፴፬ ፡ ፱። ስንክ ፡ ኅዳ፳፯)።
ተመልከ ፡ ተመለከ፤ ተገዛ። ዘኢይትመለክ ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፴፱ ፡ ፫)።
፡ አምላክ
ኾነ ፤ አምላክ ተባለ። በተመልከ ፈንታ ተአምለከ ይላል ፤
ስሕተት ነው። አምላክ ዘተሰብአ ፤ ዕጓለ መሕያው ዘተአምለከ። ለይሰባሕ ስሙ ለእግዚ
ስቡሕ ፤ ወይትአምለክ ስሙ ለእግዚ አምላክ (መጽ
፡ ምስ)።
ተመልከተ ፡ ተመለከተ፤ ባለምልክት ኾነ ለራሱ። ጠበቀ ፥ አስተዋለ፤ ሌላውን። ወበእንተ ብዝኀ በዋእያን ወወፃእያን ኀደገ ተመልክቶ ሎሙ፤ ከመ ኢያእምር አኩይያነ እምኔሆሙ ፡ (ፊልክ ፡ ፻፮)።
ተመልጠ ፡ ተመለጠ ፥ ተመላለጠ ፥ ምልጥልጥ አለ፤ ተላጠ ተገጠበ። ተመልጠ ርእሱ። ወተመልጠ ኵሉ መትከፍት ፡ (ዘሌ፲፫ ፡ ፵ ፡ ፵፩። ሕዝ፳፱ ፡ ፲፰)።
ተመሰለ ፡ በቁሙ፤ ሠሙ በወርቅ ወርቁ በሠም፤ ምሳሌው ተረቱ ተነገረ፤ ሥዕሉ ምስሉ ጣዖቱ ተሠራ። ኵሉ ዘይትዔበይ ይትሜሰል በሰይጣን። ዘእንዘ ቦ ንዋይ ይትሜሰል ከመ ነዳይ። ሰይጣን ይትሜሰል በኵሉ አራዊት። ወዳራኒ ውእቱ ዘተመሰለ በበግዕ ፡ (ፈ ፡ መ ፡ ፫ ፡ ፩። አፈ ፡ ተ፲፩። ቀሌ። ዮሴፍ)። ተመሰለ ብሎ ከመና በ ካልተከተሉት ተደራጊ አይኾንም፤ ግእዝም ቢስብ አድራጊ ኹኖ ከመሰለ መንገድ ይገባና ተ ጸያፍ ይኾናል። ዳግመኛም በኮነ ፈንታ፤ ተመሰልኪ ብእሲተ ዘማ። ተመሰለ ከመ ብእሲ። ወተማሰለ ሙሴ ከመ ሊቀ ጳጳሳት ይላል ፡ (ሕዝ፲፮ ፡ ፴፪። ፊልጵ፪ ፡ ፯። ቀሌ)። ይህ ኹሉ የጣፊና የመላሽ ስሕተት ነው።
ተመሳጠረ ፡ በቁሙ፤ ተራቀቀ፤ በስውር በምስጢር ተናገረ፤ ተነጋገረ። ተመሳጠረ ምስሌየ። እትመሳጠር ምስለ ፍቁራንየ። በተመሳጥሮ እትናገር ምስሌከ ፡ (አረጋ ፡ መል፴፪ ፡ ፵፫)።
ተመስሐ ፡ ተቀባ። ተመሳ፤ ተበላ ፥ ምሳ ኾነ፤ ምግቡ ፡ (መጽ ፡ ምስ)።
ተመሥረተ ፡ (ተሣረረ) ተመሠረተ፤ መሠረት ኾነ፤ ታነጸ ተሠራ፤ ጸና። ዓዲሁ ኢተመሥረተ ፡ (ሃይማኖትክሙ) እስመ ዘይትመሠረት ይደልዎ ይኩን ጽኑዐ ፡ (አፈ ፡ ድ፱)።
ተመስወ ፡ ቀለጠ ሟሟ፤ ዘለ ደከመ፤ ጠፋ ፈሰሰ። ከመ ይትመሶ መዓረ ግራ እምገጸ እሳት። ተመስወት ነፍስየ ወኀጣእኩ ኀይለ። ወይትመሰዋ አዕይንተ ረሲዓን ፡ (ኢሳ፷፬ ፡ ፪። ዳን፲ ፡ ፲፫። ኢዮ፲፩ ፡ ፳)።
ተመሥጠ ፡ ተመሠጠ፤ ተነጠቀ ተቀማ፤ ተማረከ ተዘረፈ፤ ጠፋ ታጣ። ተመሠጥኩ በነኰርኳረ ንቅሳት። ንትመሠጥ በደመና። ኢትትመሠጥ በቀራንብቲሃ። ተመሥጦ ንዋም እምአዕይንቲሆሙ ፡ (ሔኖ፶፪ ፡ ፩። ፩ተሰ ፡ ፬ ፡ ፲፯። ምሳ፮ ፡ ፳፭። ፬ ፡ ፲፮)።
ተመስጠረ ፡ (ተሰጥረ) ምስጢር ኾነ፤ ተሰወረ ተደበቀ፤ ጠለቀ ረቀቀ። እምልብኒ ተመስጠረ ወእምኅሊናኒ ተሰወረ ፡ (መጽ ፡ ምስ)።
ተመረደ ፡ ተሞረደ፤ ተወረረ።
ተመርገ ፡ ተመረገ፤ ተለሰነ ተለቀለቀ።
ተመርሐ ፡ ተመራ፤ ተከተለ። ተመራሕነ ውስተ ዛቲ ጸጋሁ። ተመሪሐነኬ ውስተ ጽድቅ። ከመ ንትመራሕ በትእዛዙ። ይደልወነ ከመ ንትመራሕ በምግባራቲሆሙ ወንትመሰል ቦሙ ፡ (ሮሜ፭ ፡ ፪። ቄር። ፊልክ። ዮሴፍ)።
ተመርሰ ፡ ተነከረ ተዘፈዘፈ፤ በሰበስ ገማ ፥ ተበላሸ ዘጼኣ ወተመርሳ እምአባላት ይትመተራ፤ ወሲሲተ ዕፄ ይከውና ፡ (ተረ ፡ ቄር፯)።
ተመርዐወ ፡ ተጋባ፤ ተሞሸረ፤ ተከለለ፤ ከጮኛው ጋራ ተካየደ፤ በሕግ ቀንበር ተጠመደ፤ ከጫጕላ ገባ ተዋሐደ። ጽርሕ ንጽሕት እንተ ባቲ ተመርዐወ ቃል። ተመርዐወነ። ዘተመርዐዋ ፡ (ተረ ፡ ቄር፲፰። መጽ ፡ ምስ። አርጋ)።
ተመርጐዘ ፡ ተመረ(ኰ) ጐዘ በትር ያዘ፤ ተደገፈ። ተመርጐዘ ባቲ። አእዳዊከ እለ ይትመረጐዛ በትረ ወርቅ። ዘእንበለ በትር ወተመርጕዞ። እንዘ ይትመረጐዙ ሕገ ኦሪት ዘሙሴ ፡ (፬ነገ ፡ ፲፰ ፡ ፳፩። ደራሲ። ቀሌ። ተረ ፡ ቄር፳፪)።
ተመቈሰ ፡ ተቈረጠ ተለየ፤ ተከለከለ ፥ ዐጣ ተቸገረ። ኵሎ ዘሰአላ አዕይንትየ ኢተመቈስኩ። ስእለተ ዚኣነ አብአ ኀበ አቡሁ ምእመን ወኢይትሜቈስ ፡ (መክ፪ ፡ ፲። ተረ ፡ ቄር፲፰)።
ተመቈረ ፡ ታጀለ ፥ ተነከረ፤ ተጣፈጠ።
ተመትሀ ፡ ተመታ ተጠቃ፤ ምትሀት ኾነ፤ ታባ ታይቶ ጠፋ። መጽሐፍ ግን ተመትሀተ ይላል፤ ስሕተት ነው ፡ (ገድ ፡ አዳ። መጽ ፡ ምስ)።
ተመትረ ፡ ተመተረ ፥ ተቈረጠ፤ ተለየ ተሻረ፤ ተጨርሶ ጠፋ። ተመትሩ አርእስቲሆሙ። ሊተ ሠላሳ ዓመት እምዘተመተርኩ እመፃምርትየ። ለይትመተር እመዓርጊሁ። ኢይትመተር ብእሲ ፡ (ቀሌ። ፊልክ ፡ ፫። ፈ ፡ መ ፡ ፮ ፡ ፩። ኤር፴፫ ፡ ፵፯)።
ተመነነ ፡ ተናቀ፤ ተነቀፈ ተጠላ ፥ ረከሰ። እምጽቡር ይትሜነን ንብረቱ። ተትሕትኩ ወተመነንኩ። አፈ አበዳን ይትሜነን ፡ (ጥበ፲፭ ፡ ፲። መዝ፹፯። ምሳ፲፪ ፡ ፰)።
ተመነየ [1] ፡ ምኞት ኾነ፤ ታሰበ ተከጀለ፤ ተሻ ተፈለገ። ልማዱ ግን ፥
[2] ፡ (ዐረ ተመነ። መነየ) ተመኘ ሻ ፈለገ፤ ወደደ ለመነ። ተመነየ ይርአይ ዕለትየ፤ ርእየሂ ወተፈሥሐ። ብሔር እንተ ትትሜነይ ነፍስክሙ። አብጻሕክዎ ኀበ ዘተመነየ፤ ጸልኡ ሕይወተ ወተመነዩ መዊተ። ከመ ይትመነይ እምኔሁ ዘፈቀደ ፡ (ዮሐ፰ ፡ ፶፮። ኤር፳፪ ፡ ፳፯። ዮሴፍ። ስንክ ፡ ታኅ፭)።
ተመናሰወ ፡ ተፋተነ ፥ ተፈታተነ፤ ተሟከረ ተጣፋ።
ተመናት አትማን ፡ እባቦች፤ ዘንዶዎች። ተመናት ወአናብስት ፡ (ስንክ ፡ ግን፲፱)።
ተመን ፡ (ዕብ ታኒን። ሱር ታኔን። ዐረ ቲኒን) እባብ ዘንዶ፤ አርጃኖ፤ የባሕር የየብስ። ተመን ዐቢይ። በአምሳለ ተመን ወአራዊት ፡ (ስንክ ፡ መስ፲፱። ኪዳ። ገድ ፡ ተክ። አቡሻ ፡ ፶)።
ተመንሰወ ፡ (ተነስወ) ተፈተነ ተመረመረ፤ ተጨነቀ ተሣቀየ፤ ጠፋ ተጐዳ፤ ድል ኾነ። ኢየኀድገክሙ ትትመንሰዉ። ኃጥእ ይትመነሶ በሕቢት። ኢትትመንሰዉ በፍትወት ፡ (፩ቆሮ ፡ ፲ ፡ ፲፫። ሢራ፳፱ ፡ ፳፱። ፩ተሰ ፡ ፬ ፡ ፭)።
ተመንዘዘ ፡ ተመነቸከ፤ ተጨነቀ ተቸገረ፤ በጽኑ ተያዘ።
ተመንደበ ፡ ተመነደበ፤ ተጨነቀ ተጠበበ። ተመንደብኩ እምኵለሄ። ይትመነደቡ ከመ ዘይመውት። ዘብዙኀ ተመንደበ ብዙኀ ይትሜየን ፡ (፪ነገ ፡ ፳፬ ፡ ፲፬። ኢሳ፶፱ ፡ ፲። ሢራ፴፩ ፡ ፲፩)።
ተመንገነ ፡ ተዘወረ ፥ ተጠመደ፤ መኪናው ወጥመዱ። ተተነኰለ፤ ተንኰል ሠራ ፥ አታለለ፤ ሰውዮው። ኢብክሡት ወኢበተመንግኖ፤ ወተመንገነት ኢልዛቤል ለቀቲሎቱ። እልው ይትመነገኑ በጕሕሎቶሙ ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፵፬ ፡ ፬። ኤፌ፬ ፡ ፲፬)።
ተመዓኒ ፡ (ዕብ ቴማኒ) ቴማናዊ፤ ደቡባዊ፤ ስመ ኮከብ፤ ካራቱ ዐበይት ከዋክብት አንዱ፤ ከፀሓይ ጋራ ያመት ርቦ ፺፩ ዕለት የሚመግብ። ምልክኤል ዘይሰመይ ስሙ ተመዓኒ ወፀሓየ ወኵሉ መዋዕል ዘበሥልጣነ ዚኣሁ ይመልክ ተስዓ ወአሐዱ ዕለት ፡ (ሔኖ ፡ ፷፬)።
ተመከረ ፡ ተሞከረ፤ ተፈተነ ተመረመረ። መኑ ተመከረ ቦቱ ወኢስሕተ። ተመከሩ ሰማዕት ከመ ወርቅ በእሳት። ተመኪሮ ይነሥእ አክሊለ። እምኀበ ዲያብሎስ ተመከረ ፡ (ሢራ፴፬ ፡ ፲። መዋሥ። ያዕ፩ ፡ ፲፪–፲፬። ቅዳ ፡ ዲዮ)።
ተመካነየ ፡ ተመከኛኘ፤ ርስ በርሱ።
ተመክሐ ፡ ተመካበት ፥ ተከበረበት፤ መመኪያ መከበሪያ ኾነ፤ ለሌላው።
ተመክረ ፡ ተመከረ፤ ምክር ሰማ ተቀበለ።
ተመክዐበ ፡ (ተክዕበ) ታጠፈ ተደረበ፤ ዕጥፍ ድርብ ኾነ። ወይትመክዐብ መዋዕለ ሕይወቱ። በህየ ይትመክዐብ ሎቱ። ከመ ይትመክዐብ ሀጕልክሙ ፡ (ሢራ፳፮ ፡ ፩። አፈ ፡ ተ፭። ፳፬)።
፡ በዛ ተራባ ፤ ፈደፈደ። ወተመክዐበ ለከ ቦ ዘምእት ወዘስሳ ወዘሠላሳ (ገድ ፡ ዮሐ ፡ ከማ)።
ተመዘነ ፡ በቁሙ፤ ተለካ ፥ ከሚዛን ገባ። ዘይሰፈር ወዘይትሜዘን ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፳፰)።
ተመዝመዘ ፡ ተመዘመዘ፤ ታሸ ተወለወለ። በከመ ይትመዘመዝ ጻሕል። እለ ተመዝመዙ በዐጌ ፡ (፬ነገ ፡ ፳፩ ፡ ፲፫። ኪዳ። አርጋ)።
ተመዝገነ ፡ ተመሰገነ፤ ምስጋና አገኘ። ይትመዘገን በዘይትከሀሎ። አልቦ ዘይትመዘገን ከመ ምግባረ ትሩፋት። ሰላም ለሖር ኀበ እግዚኡ ዘተመዝገነ ፡ (፪ቆሮ ፡ ፰ ፡ ፲፪። አፈ ፡ ድ፲። ስንክ ፡ ሐም፲፪)።
ተመየነ ፡ ተታለለ ተሸነገለ፤ ተንኰል ተሠራበት።
ተመያኒ ፡ ተመያኒ፤ ፡ (ኒት ንያን ያት) ተታላይ ተሸንጋይ፤ ተላላ። ልማዱ ግን መያኒ እንደ ማለት፤ የሚተነኰል፤ ተንኰለኛ፤ ሸንጋይ አታላይ። ትምይንተ ሐሰቶሙ ለተመያንያን ፡ (አቡሻ ፡ ፵፯)።
ተመያየጠ ፡ (የተመይጠ ድርብ) ተመላለሰ፤ ተዛወረ ተገላበጠ፤ ተለዋወጠ። ማእከለ አሠረ ጽድቅ እትመያየጥ። እንዘ ይትመያየጥ በዐራቱ። ሕማመ ፈፀንት ዘይትመያየጥ በበ ራብዕት፤ እስመ ግብር ዘልፈ ይትመያየጥ ወይትዌለጥ ፡ (ምሳ፰ ፡ ፳። ፍ ፡ ነ ፡ ፵፯። ዮሴፍ)።
ተመያጢ ተማያጢ ፡ የተመ(ማ) ለስ፤ የሚለወጥ ተለዋጭ፤ ተመላሽ ተመላላሽ። ተመያጥያን ኀበ እግዚ። ባሕታውያን ተመያጥያን ለኀበ ዓለም። አንሰ ከመ አሐዱ እምአርድእቲክሙ ወተመ(ማ) ያጢ ለነርክሙ ፡ (ፊልክ ፡ ፫ና ፡ ፭። ዮሴፍ)።
ተመይሰ ፡ ተመሸተ፤ ተጠጀ ተጣለ ተዘለለ። ተዘነበለ፤ ተመለሰ። ከመ ውሒዘ ማይ ከማሁ ልበ ንጉሥ ውስተ እደ እግዚ፤ ኀበ ፈቀደ ህየ ይመይሳ(ጣ) ወህየ ትትመየስ ፡ (ምሳ፳፩ ፡ ፩)።
ተመይጠ ፡ ተመለሰ፤ ታጠፈ ተቀለሰ፤ ዞረ ተገለበጠ። ተመየጡ ጎቤየ ወእትመየጥ ኀቤክሙ። ተመየጥ ድኅሬከ። ከመ ኢትትመየጥ እምገቦከ ኀበ ገቦከ ፡ (ዘካ፩ ፡ ፫። ቀሌ። ሕዝ፬ ፡ ፰)።
፡ ተለወጠ፤ ሌላ ኾነ። ተመይጠ ልቡ ለፈርዖን። ይትመየጥ ቈላቲሃ ወይከውን ፒሳ። ይመስሎሙ ከመ ህላዌ ቃል ተመይጠ ውስተ ዝንቱ ሥጋ። እስመ ኅበስት ይትመየጥ ለከዊነ ሥጋሁ ፡ (ዘፀ፲፬ ፡ ፭። ኢሳ፴፬ ፡ ፱። ቄር። መጽ ፡ ምስ)።
ተመገበ ፡ በቁሙ፤ በላ ጠጣ ተቀለበ፤ ተጠበቀ፤ ተሾመ። ነፍስ እንተ ትትሜገብ በመንፈስ አምላካዊት። ተመገበ ቦቱ። እለ ይትሜገብዎ ግብረ መወልጣን ፡ (አፈ ፡ ተ፴፬። ፍ ፡ ነ ፡ ፵። ፈ ፡ መ ፡ ፲፱)።
ተመጠነ ፡ በቁሙ፤ ተለካ ተመዘነ፤ ከልክ ገባ። ዘይትሜጠን በእመት። ክበደ ብዕሉ ዘኢይትሜጠን ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፴፫። መጽ ፡ ምስ)።
ተመጠወ ፡ ተሰጠ፤ ተሰጠው፤ ተቀበለ፤ ተመጠወተ ምጧተኛ ኾነ። ተመጠዋ እምነ ያማኑ፤ ወሶበ ተመጠዋ። ዘይትሜጦ ቍርባነ ምዕረ በበ ዓመት። ተመጠው አምኃየ እምእዴየ ፡ (ራእ፭ ፡ ፯ ፡ ፰። አፈ ፡ ተ፲፯። ዘፍ፴፫ ፡ ፲)።
ተመጣዊ ፡ የሚሰጥ ተሰጭ። ተቀባይ ተመጥዋች። ሙሴ ተመጣዌ ኦሪት። ተመጣዌ ቍርባን። ተመጣዌ ኅብስት ወማይ ፡ (መጽ ፡ ምስ። ፈ ፡ መ ፡ ፳፮ ፡ ፰። ደራሲ)።
ተመጥቀ ፡ ተነጠቀ ተመነጠቀ፤ ወደ ላይ ተሳበ፤ ከፍ ከፍ አለ። ዘተመጥቀ በደመና ሰማይ ፡ (ስንክ ፡ ጥቅ፲፪)።
ተመጽወተ ፡ ተመጠወተ፤ ምጧት ተቀበለ፤ ድኻው። ይትመጸወት በአንቀጸ ሀገር ፡ (ስንክ ፡ ጥቅ፱። ታኅ ፡ ፲)። ተሰጠ ዐለፈ፤ ተናኘ ታደለ፤ ገንዘቡ።
ተሙዝ ፡ (ዕብ ፡ ታሙዝ። ሱር ፡ ታሙዛ) ስመ ወርኅ ራብዕ፤ ሐምሌ። በራብዕ ወርኅ ዘውእቱ ወርኀ ተሙዝ ፡ (ዮሴፍ። መጽ ፡ ምስ)።
፡ ስመ ጣዖት፤ የአምልኮው ሥርዐት ሙሾና ልቅሶ የኾነ ፡ (ሕዝ፰ ፡ ፲፬)።
ተሚም ሞት ፡ (ተመ ይተምም ይትምም፤ ዐረ ወትግ። ዕብ ታም፤ ፈጸመ፤ ተፈጸመ፤ መላ ልክ ኾነ) መትመም፤ ፈጽሞ መጮኽ፤ መክለል ማስገምገም፤ ማግሣት ማጕረምረም፤ የሰማይ፤ የዝናም ያታሞ የነጋሪት ለሰውም ይኾናል። አታሞ ማለት ከዚህ ወጥቷል።
ተማሐለ ፡ ተማማለ፤ ተፈጣጠመ፤ ቃል ኪዳን ተጋባ። ተማሐልነ ክልኤነ። ተማሐልነ ምስለ ሲኦል። ዕደው እለ ተማሐልከ ፡ (፩ነገ ፡ ፳ ፡ ፳፬። ኢሳ፳፰ ፡ ፭። ዓብድ ፡ ፯)።
ተማሐዘ ፡ (ይትማሐዝ) ተጐላመሰ፤ ተዳራ ተቃበጠ፤ ተዋዛ ተጫወተ። ይትማሐዛ መራዕዊክሙ ፡ (ሆሴ፬ ፡ ፲፫ ፡ ፲፬)። ኢትትማሐዝ ምስለ ብእሲት። ኢትትማሐዝ ምስለ መኳንንት። ዘይትማሐዝ ምስለ ጸላእቱ ይፈቅድ ከሢተ ኀጢአቱ እስመ ተማሕዞሰ መራኁተ ተጻልኦ ለጸላእቱ ፡ (ፈላስ ፡ ገ፶፩። ፳፫። ፷)። ዋዛ ለቁም ነገር ብላቴን ጌታው ማለት ከዚህ የወጣ ነው።
ተማሕለለ ፡ (ተቀ ግ) ተማለለ፤ ለመነ ማለደ፤ አቤት አቤት አለ፤ መሐላና ኪዳን በማሳሰብ። ይትማሐለል አሮን በዲበ አቅርንቲሁ። እንዘ ይትማሐለል ቅድመ እግዚ በእንተ አበሳ። ወሰገደ ሎቱ እንዘ ይትማሐለል። ኀበ መኑ እትማሐለል ፡ (ዘፀ፴ ፡ ፲። ኩፋ ፡ ፵፩። ማቴ፲፯ ፡ ፲፬። አርጋ)።
ተማህረከ ፡ (ይትማሀረክ) ተማረከ፤ ተዘረፈ ፡ (ወይም ተመራረከ፤ ተዛረፈ)። አስዋር እለ ተማህረኩ። እስመ ተማህረካ አባግዕየ ፡ (ኢሳ፭ ፡ ፲፯። ሕዝ፴፬ ፡ ፰)።
ተማህከወ ፡ ፈራ ደነገጠ፤ ክው ክች አለ። ወሶበ ይወዲ ዲቤክሙ ቃሎ አኮኑ ትትማሀከዉ ወትፈርሁ፤ ወኵሎሙ ብርሃናት ይትሀወኩ በፍርሀት ዐቢይ። ወምድር ኵላ ትትማሀከው ወትርዕድ ወትጔጕእ ፡ (ሔኖ፻፪ ፡ ፩ ፡ ፪)።
ተማሕፀነ ፡ ተማጠነ፤ ይግባኝ አለ። ተማሕፀንኩ ሎሙ በቄሳር ፡ (ግብ፳፰ ፡ ፲፱)።
፡ ዐደራ አኖረ፤ ዐደራ ተባለ፤ ጠበቀ ተከናከነ፤ ዐደራውን። ኢይፈዲ ዘተማሕፀነ። ተለቃሒ ወተማሕፃኒ። ዘየዐቅብ አፉሁ ይትማሐፀን ነፍሶ። ይትማሕፀንከ እምኵሉ እኩይ ፡ (ዘፀ፳፪ ፡ ፲። ፍ ፡ ነ ፡ ፴፪። ምሳ፲፫ ፡ ፫። ኩፋ ፡ ፲፪)።
፡ ሸሸ ተጠጋ የሙጥኝ አለ፤ ራሱን ለሌላ ዐደራ ሰጠ። ፍና ኀበ ይትማሐፀን ቀታሊ። ኀበ መኑ ትትማሐፀኑ። ተማሕፀነ ኀበ ቤተ ክርስቲያን ፡ (ዘፀ፳፩ ፡ ፲፫። ኢሳ፲ ፡ ፫። ቀሌ)። ይትጋባእ ይረውጽ በማለት ፈንታ ይትማሐፀን ይላል ፡ (ኢሳ፶፬ ፡ ፲፭። ፶፭ ፡ ፭)።
ተማለሰ ፡ በቁሙ፤ ተመላለሰ፤ የገጽ የቃል።
ተማልኀ ፡ ተማዘዘ፤ የሰይፍ የበትር።
ተማልዐ ፡ ተማላ ፥ ወሰደ፤ ይዞ ኼደ። ዲያብሎስ ተማልዖሙ ለአዳም ወለሔዋን ውስተ ስሕተተ ዚኣሁ እንዘ የኀይጦሙ። ወእምኔሆሙ ተዐቀቡ ከመ ኢይትማልዑክሙ ምስሌሆሙ ውስተ ገሃነም። ተማልዒ ሊተ ምስሌኪ ፍተ ኅብስት ፡ (መቃ ፡ ገ፰። ቀሌ። ፫ነገ ፡ ፲፯ ፡ ፲፩)።
ተማም ፡ በቁሙ፤ ፍጹም፤ ልክ ምሉ፤ ሕጸጽ የሌለበት።
ተማሰለ ፡ በቁሙ፤ ተመሳሰለ ፥ ተነጻጸረ። ኢይትማሰላ ወርቅ። ወኢይትማሰል ምስለ ባዕድ ንብረቱ ፡ (ኢዮ፳፰ ፡ ፲፯። ጥበ፪ ፡ ፲፯)። ለወጥም ይኾናል።
ተማሠጠ ፡ ተናጠቀ ፥ ተነጣጠቀ፤ ተቃማ ተሻማ ፡ (መዝ ፡ ፵፫። ፹፰። ኢሳ፵፪ ፡ ፳፬። ሆሴ፲፫ ፡ ፰)። ኮኑ ይትማሠጡ እምሲሳይ፤ ለእመ ረከቡ ንስቲተ ይመሥጥ አብ እምወልዱ ወወልድኒ እምአቡሁ ፡ (ዮሴፍ)።
ተማረየ ፡ ተሟረተ ተጠነቈለ፤ ሟርቱ ጥንቈላው ተደረገ። ተደራራጊ ሲኾን ግን ፥ ተሞራረተ ተጠናቈለ ፥ ተጠነቋቈለ ያሰኛል።
ተማዐደ ፡ ተማከረ ተመካከረ። ተማዐዱ በበይናቲክሙ። ከንቱ ዘተማዐዱ ፡ (ኪዳ። ኢሳ፴ ፡ ፯)።
ተማዕለየ ፡ (ዲቃ ግ) ዐለየ፤ ዐለወ፤ ወነጀለ። ተማዕለዩ ሎቱ፤ ሖሩ ይትማዕለይዎሙ ፡ (መቃ)።
ተማዕተበ ፡ (ተዐትበ) ተማተበ፤ ተባረከ፤ ተመሳቀለ። በአምሳለ ከዋክብት በተትማዕትቦ ፡ (ስንክ ፡ ኅዳ፰። ቀሌ)።
ተማዕዐ ፡ ተጣላ ተቋጣ፤ ተበሰጫጨ። ተማዕዑ ወተፋለጡ ፡ (ግብ፲፭ ፡ ፴፱)።
ተማዕዘረ ፡ በራ፤ ብርሃን ኾነ፤ ፈለቀ፤ አንጸበረቀ። እስመ በሡራሔ ገጹ ለጰራቅሊጦስ ተማዕዘሩ ፡ (ገድ ፡ ተክ)።
ተማከረ ፡ በቁሙ፤ ተመካከረ፤ ምክር አዋጣ አሻሻለ። ኢትትማከር ምስለ አብድ። ወጸቢሖ ተማከሩ፤ ወተማኪሮሙ ፡ (ሢራ፰ ፡ ፲፯። ማቴ፳፯ ፡ ፩ ፡ ፯)።
ተማወቀ ፡ ተሟሟቀ። እስመ እመ ኖሙ ክልኤሆሙ ይትማወቁ፤ ወአሐዱሰ እፎ ይትማወቅ ፡ (መክ፬ ፡ ፲፩)።
ተማወጸ ፡ ተካካሰ፤ ተራረቀ።
ተማየጠ ፡ ተማለሰ ፥ ተላወጠ፤ ተዛወረ።
ተማጽአ ፡ ተማጣ ተመጣጣ፤ ተሳሳበ ተጓተተ።
ተሜርጋብ ፡ ሣጥን፤–ኤርጋብ።
ተምህረ ፡ ተማረ፤ ለመደ። ተምህረ መጽሐፈ። ተምህረ መሢጠ። እስከ ይትሜሀሩ ብዙኃን ፡ (ኩፉ ፡ ፬። ሕዝ፲፱ ፡ ፫።ዳን፲፬ ፡ ፬)። ነበበ ኀለየ በማለት ፈንታ ተምህረ ይላል፤ የመላሽ ስሕተት ነው። ኢትትመሀር ነፍስየ ኀጢአተ። ልበ ጻድቃን ይትሜሀር ሃይማኖተ። እስመ ሐሰተ ይትሜሀር ልቦሙ ፡ (ኢዮ፳፯ ፡ ፬። ምሳ፲፭ ፡ ፳፰። ፳፬ ፡ ፪)።
ተምሃር ፡ ትምርት፤ ልማድ። ሕግከ ተምሃርየ ውእቱ። እስመ እኩይ ተምሃሩ ፡ (መዝ ፡ ፻፲፰። ሄርማ ፡ ገ፴፬)።
ተምሕለ ፡ ተማለ፤ ተማለበት።
ተምሕረ ፡ ተማረ ፥ ይቅር ተባለ፤ ይቅርታ አገኘ። ዘይምሕር ይትመሐር። ብፁዓን መሓርያን፤ እስመ እሙንቱ ይትመሐሩ ፡ (ምሳ፲፯ ፡ ፭። ማቴ፭ ፡ ፯)።
ተምህከ ፡ ተማረ ይቅር ተባለ፤ ይቅርታ አገኘ።
ተምሕወ ፡ ጠፋ ተደመሰሰ፤ ተነቀለ። ወይትመሐዉ ምግባራቲክሙ። ሥርወ ጻድቃን ኢይትመሐዉ። ሣዕር ዘተምሕወ። ይቀድም ተምሒዎ እምነ ኵሉ ሣዕር ፡ (ሕዝ፮ ፡ ፮። ምሳ፲፪ ፡ ፫። ሄርማ ፡ ገ፶፬። ሢራ፵ ፡ ፲፮)።
ተምሕጸ ፡ ተመታ ተቈረጠ፤ ሞተ ጠፋ።
ተምላስ ፡ በቁሙ፤ ምላሽ ትፋት ቅርሻት፤ ባፍ ገብቶ ባፍ የሚወጣ።
ተምራት ተመርታት ፡ ተምሮች፤ የተምር ፍሬዎች።
ተምር ተመርት ፡ (ዐረ ተምር። ዕብ ታማር) በቁሙ፤ ሰሌን ዘንባባ፤ የሰሌን ፍሬ፤ ሕንባቡ ዛላው ዘለላው፤ የሚበላው። ወህየ ማይ ጥዑም ወኅለታት ወበቀልታት ወተምር ብዙኅ። ፍሬ በለስ ወተምር። ቂሐተ ተምር ወጽዕዳዌ ፀምር። እምነ ተመርተ ቈላ። በቀልተ ተመርት። ፀመርተ ተመርት ዘበቀልት ፡ (ስንክ ፡ ጥር፳፪። ሚያ፮። አፈ ፡ ተ፲፪። ኩፋ ፡ ፳፱። ዘኍ፴፫ ፡ ፱። ዮሐ፲፪ ፡ ፲፫)። ተምር ተመርት ፍሬውና ዛፉ፤ በቀልት ግንዱ፤ ፀመርት ቅጠሉ።
ተምኔት ፡ (ታት) ምኞት ፥ ፈቃድ፤ ልመና ፡ (መዝ ፡ ፰። ኢዮ፳፯)። አነ እሁበከ ተምኔተ ልብከ። ረከቡ ተምኔቶሙ ብነ ፡ (ቀሌ። ዮሴፍ)።
ተምዐ ፡ ተቈጣ ዐዘነ፤–መዕዐ።
ተምዕዘ ፡ ተሸተተ፤ ተጣፈጠ ተቀመመ ፥ ተነጠረ፤ ሽቱው። ሽቱ ተቀባ ዘገበ፤ ተረጨ ተረበረበ፤ ሰውየው ወይም ልብሱ። ዘተሰርገወት ሰርጓተ ወርቅ ወተምዕዘት አፈዋተ። በዊአ ቤተ ብለኔ ወተምዕዞ በዕፍረት። በመዐዛሁ ለክርስቶስ ተምዕዙ ሐዋርያት። ከመ እትመዐዝ በጼና አልባስኪ ፡ (ፈ ፡ መ ፡ ፴፬ ፡ ፰። አቡሻ ፡ ቀሌ። አርጋ ፡ ፫)።
ተምዕደ ፡ ተማረ፤ ተመከረ፤ ምክር ሰማ ፥ ተቀበለ። ይትመዐዱ። ወይጠናቀቁ በእንተ ግብራ ለቅድስት ቤተ ክር ፡ (ቀሌ)።
ተምያን ፡ ተንኰል፤ ውሸት፤ ግብዝነት። ተቀትለ በተምያነ ነገር ወትጓሕልዎ ፡ (ዮሴፍ)።
፡ ግብዝ ቅልቅል፤ ጥሩ ጠንካራ ያይዶለ የተንኰልና የማታለል ሥራ፤ ያንጥረኛ የመሸተኛ የሌላውም ኹሉ። ወርቅ ጽሩይ ወፍቱን ዘኢኮነ ተምያነ። ወርቅክሙ ተምያን። ብሩረ ተምያን። መዳልወ ተምያን። ጽሩይ ውእቱ። ዘእንበለ ተምያን ፡ (፩ዜና ፡ ፳፰ ፡ ፲፰። ኢሳ፩ ፡ ፳፪። ምሳ፳፮ ፡ ፲፫። ሚክ፮ ፡ ፲፩። ቅዳ ፡ ጎር)።
ተምያጥ ፡ መመላለስ፤ ምልልስ፤ ተለዋዋጭ ተገላባጭ መኾን፤ እንደ ኅሥሥት። የተምያጥና የተውላጥ ምስጢር ጥቂት ይለያየል። ተውላጥ እንደ ብእሲተ ሎጥ እንደ ማየ ቃና ተለውጦ አለመመለስ ነው። ተምያጥ ግን እንደ ማየ ግብጽ እንደ በትረ ሙሴ መመላለስ ነው። ተምያጠ ወተውላጠ ህላውያት። ዘእንበለ ተምያጥ ወተውላጥ ፡ (ሃይ ፡ አበ። ስንክ ፡ ኅዳ፲፮። አርጋ ፡ ፭ና ፡ ፯)።
ተሞቅሐ ፡ ታሰረ፤ ተጋዘ። እገሪከ ኢተሞቅሓ። ዘኢተሞቅሐ በማእሰራ። ተምቂሐከ። በተቀሥፎ ወበተሞቅሖ። ወለጦ ልብሰ ተሞቅሖቱ ፡ (፪ነገ ፡ ፫ ፡ ፳፬። ሢራ፳፰ ፡ ፲፱። ማቴ፳፭ ፡ ፵፬። ፪ቆሮ ፡ ፮። ኤር፮ ፡ ፭። ኤር፶፪ ፡ ፴፪)።
ተሞአ ፡ (ይትመዋእ) ተሸነፈ፤ ድል ኾነ፤ ተረታ። ሞት ተሞአ። ወሶበሂ ይትዋቀሥ ይፃእ ተመዊኦ ፡ (ድጓ። መዝ ፡ ፻፰)። በተሞአ ፈንታ ተመውአ ይላል፤ በሰብሐና በቀደሰ መንገድ ካልኾነ በቀር በቀተለ ቤት አያሰኝም። ተመውአ ቀትል በይእቲ ዕለት ፡ (፪ዜና ፡ ፲፰ ፡ ፴፬)።
ተሞገሰ ፡ ከበረ ተመሰገነ፤ ብፁዕ ተባለ፤ ባለሟል ኾነ፤ ልጅነት አገኘ። አባ ዮሐኒ ፈድፋደ ኀየሰ ተሞገሰ። የሐንስ ተፈሥሐ ወተሞገሰ። እመ በመንፈሱ ለኢየሱስ ንትሞገስ ወንጼውዖ ለእግዚ አቡነ ፡ (መዋሥ። ቄር ስምዓት)።
ተሞገደ ፡ ታወከ፤ ተማገደ።
ተሞጥሐ ፡ ለበሰ ተጐናጠፈ፤ ተሸለመ አጌጠ። ተሞጥሐ ሞጣሕተ ፍዳ። በጻሕኩ ኀበ ዘይለብስ ልብሰ ፍዳ ወይትሞጣሕ ሞጣሕተ በቀል። ንትሞጣሕ ሞጣሕተ ብርሃን ፡ (ኢሳ፶፱ ፡ ፲፯ ፡ ፲፰። ግንዘ። አፈ ፡ ተ፲፯። አርጋ ፡ ፬)።
ተሞጸ ፡ ተመውጸ፤ ተሟጨ፤ ተካሰ።
ተሟቅሐ ፡ (ይትሟቃሕ፤ አው ተም(መ) ዋቅሐ ይትመዋቃሕ) ተሳሰረ።
ተሟገደ ፡ (ይትሟገድ፤ አው ተምዋገደ፤ ተመዋገደ) ወቅሐን ተመልከት።
ተሠለሰ ፡ ተሦሰተ፤ ሦስት። ኾነ ፫ ተባለ ፫ኛ ኾነ። እግዚ ዘይሤለስ በአካሉ። በከመ አብ ወወልድ ይነብር ዲበ መንበሩ መንፈስ ቅዱስሂ ይሤለስ ዲበ መንበረ ስብሐቲሁ ፡ (ደራሲ። መጽ ፡ ምስ)።
ተሰለጠ ተሰልጠ ፡ ተፈጸመ፤ ተጨረሰ፤ መላ ልክ ኾነ። በዘይሴለጥ ሙስናሃ ለኢየሩሳሴም። ከመ ትሰለጥ ኀጢአት። ከመ ኢይሰለጡ ዘእንበሌነ። ዮም በጽሐ ወተሰልጠ ውስተ እዘኒክሙ ፡ (ዳን፱ ፡ ፪ ፡ ፳፬። ዕብ፲፩ ፡ ፵። ሉቃ፬ ፡ ፳፩)።
ተሠልቀ ፡ ተሠለቀ፤ መሣለቂያ ኾነ፤ በስድብ ተላጠ።
ተሰልበ ፡ ተሰለበ፤ ተገፈፈ፤ ተቀማ፤ ተማረከ። ወኢንፈቅድ ንሰለብ ዘእንበለ ከመ ንልበስ። ተሰልበ መንግሥቱ። ተሰልበ ልብ። ሰትየት ወይነ ወሶበ ተሰልበ ልባ እምስካረ ወይን ፡ (፪ቆሮ ፡ ፭ ፡ ፬። ቈስጠ። ገድ ፡ አዳ። ስንክ ፡ ሠኔ፬)።
ተሰመነ ፡ በቁሙ፤ ስምንት ኾነ፤ ተባለ።
ተሠምረ ፡ ተሠመረ፤ ተዘጋጀ። ተወደደ ተፈቀደ።
ተሰምዐ ፡ (ራት) በቁሙ፤ ማሥመሪያ ቀጥ ያለ የተካከለ ዘንግ አራት ገጽ ያለው፤ ወይም ጠፍጣፋ ባለኹለት ገጽ። መሥመር የወደቀበት የተጋደመበት፤ ወስፌው ርሳሱ የኼደበት መዛሪያው ትልሙ ፡ (አቡሻ ፡ ፵፮)። የመሥመር አሠራር ጥበቡ የመጣ ከሙዝ ቅጠልና ከንሰት ከኮባ ከጕናጕና ነው ይባላል።
ተሰምየ ፡ ተሰየመ፤ ስም ተቀበለ፤ ተጠራ ስሙ ተነሣ፤ ተወሣ እገሌ ተባለ፤ ስመ ጥር ኾነ። አሕዛብ እለ ተሰምዩ በስምከ። ተሰምየ ስሙ። ወተሰምየ ክርስቶስሀ በእንተ ዘተቀብዐ ምስሌነ ከመ ሰብእ። በምግባር ወበተሰምዮ ፡ (ሢራ፴፮ ፡ ፲፯። መክ፮ ፡ ፲። ሃይ ፡ አበ ፡ ቄር። ስንክ ፡ ሐም፳፩)።
ተሰረ ፡ ተሰረረ ተወጣበት፤ ተጠቃ በታች ኾነ። ፡ (ተረት) ዥብ ሊሰር ኺዶ ተሰሮ ገባ። ተጣደ፤ በጕልቻ ላይ ተቀመጠ። ማሰሮ ማለት ከዚህ ወጥቷል።
ተሠርሐ ፡ (ዕብ ጻላሕ። ሱር ጽላሕ። ዐረ ጸለሐ) ተበጀ፤ ተዘጋጀ፤ ተከናወነ፤ ሰላ ተሳላ፤ ተሳካ፤ ተሰናበተ። ወልድየ ተሠራሕ። ተሠርሐ ሕዝብ በኵሉ። ትሤራሕ በኵሉ ፍኖትከ ፡ (ኩፋ ፡ ፴፩። መዝ ፡ ፵፬። ፪ዜና ፡ ፴፪ ፡ ፴። ጦቢ፬ ፡ ፮)።
ተሠርመ ፡ ተዋጠ፤ ሰጠመ፤ ዘቀጠ፤ ከረግረግ ገባ። ወኢተሠርሙ ውስተ ባሕር ፡ (መቃ)።
ተሰርቀ ፡ ተሰረቀ፤ ተደበቀ፤ ጠፋ ኰበለለ፤ ተሰረቀበት ገንዘቡ። ተሰርቀ ንዋዩ እምቤቱ። ዘተሰርቀ ንዋዩ። ማኅደር ዘኢይሰረቅ ፡ (ፊልክ ፡ ፳፰። አፈ ፡ ተ፲፩። ቅዳ ፡ ዮሐ)።
ተሠርዐ ፡ ተሠራ፤ ተበጀ፤ ተዘጋጀ፤ ተሰናዳ፤ ተጣፈ ተወሰነ፤ ታገገ ተደነገገ። አኮ ለጻድቃን ዘይሠራዕ ሕግ። በከመ ተሠርዐ በአንቲኣሁ። እስመ ለዐሠርቱ ክፍል ወመንፈቅ ተሠርዐ ዓለም ፡ (፩ጢሞ ፡ ፩። ሉቃ፳፪ ፡ ፳፪። ሱቱ ፡ ዕዝ፲፬ ፡ ፬)። ተሰምየ ተብህለ ተጸውዐ በማለት ፈንታ ተሠርዐ ይላል፤ ተባለ ማለት ነው። ወተሠርዐ ወልደ እግዚ በኀይል ቅብዐ መንፈስ ቅዱስ ቄር)።
ተሠርወ ፡ ተተከለ፤ ተመሠረተ ሥር መሠረት ኾነ። ወተሠርዉ ኵሎሙ በሃይማኖት ፡ (ገድ ፡ ተክ)።
ተሠርወ ተሠረወ ፡ ተነቀለ፤ ጠፋ። ከመ ይሠረዉ ለዓለመ ዓለም። ረሲዓን እምሥርዎሙ እምድር ይሤረዉ። ለትሠሮ ይእቲ ነፍስ እምእስራኤል ፡ (መዝ ፡ ፺፩። ምሳ፲፭ ፡ ፮። ዘፀ፲፪ ፡ ፲፭)።
ተሰርየ ፡ ተሰረየ፤ ተፈታ ቀለለ፤ ይቅር ተባለ፤ ጠፋ ተፋቀ፤ ተደመሰሰ። ኢትሰረይ ለክሙ ዛቲ ኀጢአትክሙ። በምጽዋት ይሰረይ ኀጢአት። ዘእንበለ ይትነዛህ ደም ኢይሰረይ። ኢተሰርየ ሎቱ ኀጢአቱ ፡ (ኢሳ፳፪ ፡ ፲፬። ምሳ፲፭ ፡ ፳፯። ዕብ፱ ፡ ፳፪። መጽ ፡ ምስ)።
ተሰርገወ ፡ ተጌጠ፤ ተሸለመ፤ ጌጥ ሽልማት፤ ተቀበለ፤ ለበሰ፤ ተፀረረ። ተሰርገወት አውቃፋተ። ተሰርገወት አዕኑጊሃ። ብእሲት ዘተሰርገወት ሰርጓተ ወርቅ ወብሩር። አኮ በተሰርግዎ ወርቅ ወብሩር። ተሰርገወት ምድረ ገነት በሥነ ጽጌያት ፡ (ዮዲ፲ ፡ ፬። ሆሴ፪ ፡ ፲፭። ፈ ፡ መ ፡ ፴፬ ፡ ፰። ፩ጴጥ ፡ ፫ ፡ ፫። ቀሌ)።
ተሰቍረ ፡ ተሸነቈረ፤ ተሰረሰረ ፣ ተበሳ ተነደለ። ተሰቍረ እዱ ፡ (ስንክ ፡ ኅዳ፳፰)።
ተሰቈ ተሰቈቈ ፡ ተሻ ተፈለገ ተወደደ፤ ገንዘቡ።
ተሰቅለ ፡ ተሰቀለ ተመዘነ፤ ተያዘ ተንጠለጠለ። ተሰቅለ ዲበ ዕፅ። ምንትኒ ዘይሰቀል ቦቱ ኅሊናሁ። ይሰቀሉ በአጽምዖቱ። በእላ ክልኤ ትእዛዛት ተሰቅሉ ኦሪት ወነቢያት ፡ (፩ጴጥ ፡ ፪ ፡ ፳፬። ፊልክ ፡ ፪፻፬። ሉቃ፲፱ ፡ ፵፰። ማቴ፳፪ ፡ ፵)።
ተሠቅሠቀ ፡ ተሸከሸከ፤ ተታታ፤ ተበሳሳ ፥ ተነዳደለ፤ ሽክሽክ ኾነ፤ ሥራው።
ተሰቅየ ፡ ተጠጣ፤ ውሃው። ጠጣ ረካ ጠገበ። ወምድርሰ እምነ ዝናም ትሰቀይ ማየ ፡ (ዘዳ፲፩ ፡ ፲፩)።
ተሰበከ ፡ ቀለጠ፤ ፈሰሰ፤ ተሠራ። በከመ ይሰበክ ብሩር፤ ትሰበኩ በማእከላ ፡ (ሕዝ፳፪ ፡ ፳፪)።
ተሰብሐ ፡ ተመሰገነ፤ ከበረ፤ ተገለጠ፤ በራ ብሩህ ኾነ። ይሴቦሕ ስምየ በውስተ ኵሉ አሕዛብ። ጥቀ ተሰብሐ ስምከ። አመ ተሰብሐ ኢየሱስ። ወተሰብሐ ሕብረ ገጹ ፡ (ሚል፩ ፡ ፲፩። መዝ ፡ ፰። ዮሐ፲፪ ፡ ፲፮። ዘፀ፴፩ ፡ ፳፱)።
ተሰብረ ፡ ተሰበረ፤ ንሰባበረ፤ ነከተ ነኰተ፤ ተንቈጨቈጨ። ድል ኾነ ተመታ፤ ተሻረ፤ ፈረሰ ተናደ ሸሸ። ተሰብረ ጸወንክሙ። በተሰብሮ ቍጽ። ተመገደበ ሐመሮሙ ከመ ይሰበር። ተሰብሩ ሕዝብ በቅድመ ፀሮሙ። ተሰብሩ ሰብአ ኢትዮጵያ ወጐዩ። ወተሰብረ ሰራዊቶሙ ፡ (፪ዜና ፡ ፮ ፡ ፳፬። ፲፬ ፡ ፲፪። ፫ነገ ፡ ፳፪ ፡ ፴፭። ዘፍ፲፬ ፡ ፲)።
ተሰብአ ፡ ተጠገበ፤ ተረገዘ ሰው ኾነ፤ ሥጋ ለበሰ፤ ነፍስንና ሥጋን ነሣ፤ ተዋሐደ ገንዘብ አደረገ፤ ሰው ተባለ፤ በሰው ስም ተጠራ። ተሠገወ ወተሰብአ እምድንገል። ተሰብአ እምድንግል። ተሰብአ እማርያም። ውእቱ ይቤለኒ ከመ ቃሉ ይሰባእ በደኃሪ መዋዕል። ለልየ በእዴየ ለሐኵዋ ለድንግል እንተ እምኔሃ ተሰባእኩ። አምላክ ተሰባኢ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ፡ (ዲድ ፡ ፲፪። ቀሌ። ድጓ። ማር ፡ ይሥ)።
ተሰብዐ ፡ ተሰበተ፤ ሰባት ኾነ፤ ተባለ፤ በሰባት ክፍል ተከፈለ። ተሰብዖት ፡ (ኩፉ ፡ ፩)።
ተሰብኦ ኦት ፡ መፀነስ መረገዝ። ሰው መኾን፤ ሥጋ መልበስ፤ የአዳምን ባሕርይ መንሣት። ተሰብኦተከ እመ ቦ ዘያስተሐቅር መኒኖ ፡ (ደራሲ። አርጋ ፡ ፩)።
ተሰብከ ፡ ተሰበከ፤ ተነገረ። ወይሰበክ ዝ ወንጌለ መንግሥት። ዘበነቢያት አቅደመ ተዐውቆ ወበሐዋርያት ተሰብከ። ጥበብ ትሰበክ ፡ (ማቴ፳፬ ፡ ፲፬። ኪዳ። ምሳ፩ ፡ ፳፩)።
ተሠትረ ፡ ተሠነተረ፤ ተገረፈ፤ ተገጠበ።
ተሰትየ ፡ ተጠጣ፤ መጠጥ ኾነ። ዘተበልዐ ወተሰትየ ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፶፪። ኩፋ ፡ ፲። ቅዳ)።
ተሰነ ፡ ተሳለ ተሾለ ተሞረደ፤ ጥርሳም ኾነ። ተነከሰ፤ ተዘበተረ ተጋጠ ተገመጠ ተነጨ።
ተሠነየ ፡ ተጌጠ ተሸለመ፤ ተበጃጀ፤ ለማማር። ወይእቲሰ ተሠነየት በኵሉ። ተሠነየት ጥቀ። ለምንት ኢትሰረገው ውስተ ቤተ ክርስቲያን ወኢትሤነይ ፡ (አስቴ ፡ ፭። ዮዲ፲ ፡ ፬። ፲፪ ፡ ፲፭። ፬ነገ ፡ ፱ ፡ ፴። አፈ ፡ ተ፳፰)።
ተሰናሰለ ፡ ተሳሰረ፤ ተቈላለፈ፤ ተያያዘ፤ ተቈረኛኘ ተገጣጠመ። ይሰናሰላ በበይናቲሆን። ናሁኬ ተሰናሰላ ትእዛዛት አሐቲ በአሐቲ። እለ ይዘመዱ ወይሰናሰሉ ፡ (ዘፀ፳፮ ፡ ፫። መጽ ፡ ምስ። ፍ ፡ ነ ፡ ፳፬ ፡ ፪)።
ተሰናአለ ፡ ተሰነባበተ፤ ተመራረቀ፤ ከመሳሳም ጋራ ደኅና ኹን ደኅና ኹን ተባባለ። አኀዙ ይሳሕዉ ወይብክዩ ወይሰናአሉ በበይናቲሆሙ። ከመ ይሕቅፎሙ ለውሉዱ ወየአምኆሙ ወይሰናአሎሙ። ተሰናአለ ወላዲተ። ተሰናአልዎ በአስተርክቦ ፡ (ዮሴፍ። ስንክ ፡ ሐም፲። ግንዘ)።
ተሰናአወ ፡ (873) ፡ (ተሰንአ፤ ተሳንአ) ተሰማማ፤ ተጋጠመ፤ ተባበረ፤ አንድ ልብ አንድ ሐሳብ ኾነ። ጼወ ርከቡ ወተሰናአዉ። ተሰናአወ ዮሳፍጥ ምስለ ንጉሠ እስራኤል። ተሰናእዎ እሳት ወማይ በአሐዱ ህላዌ። ተሰናአዉ በዝ ምክር፤ ከመ ኢይሰናአዉ ላዕለ ወልጦ መጻሕፍት። በእንተ ተሰናእዎተ ክልኤሆሙ ለምንኵስና። ተሰናአዉ ምስሌሃ ከመ የሀብዋ ንዋየ ፡ (ማር፱ ፡ ፶። ፫ነገ ፡ ፵፪ ፡ ፵፭። አርጋ ፡ ፪። ዮሴፍ። ፈ ፡ መ ፡ ፲፪ ፡ ፫። ስንክ ፡ ግን፳፩)።
ተሰናኣዊ ፡ (ተሳናኢ) የሚሰማማ ተሰማሚ፤ ተባባሪ። ተሰናኣውያን ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፴፯)።
ተሰንሰለ ፡ ተያዘ ታሰረ፤ ተቈራኘ፤ ከሰንሰለት ገባ።
ተሰንቀወ ፡ ተሰነቃ፤ ተመታ ተደረደረ፤ ተከረከረ። ከመ ይሰንቀው ምዑዘ ፡ (አርጋ)።
ተሰንአለ ፡ ተሰናበተ፤ ተፈታ ተለቀቀ፤ የመኼድ ትእዛዝ ተቀበለ።
ተሰንጸ ፡ ተሰነጠ፤ ተፋቀ ለዘበ፤ ተነቀሰ ተጌጠ ተዋበ።
ተሰካተየ ፡ (ይሰካተይ) ተሰማማ ተባበረ፤ ተማማለ ሤራ ቈረጠ፤ አሤረ ክፉ መከረ፤ ዱለቱን ሤራውን በመሐላ አሰረ። ተሰካተዩ በማዕሌቶሙ፤ ወተሰካተዩ ምስለ እለ እምድኅሬሁ ፡ (መቃ ፡ ገ፲፬። መዝ ፡ ፹፪። ግብ፳፫ ፡ ፲፪ ፡ ፲፬)።
ተሰክመ ፡ ሸክም ኾነ፤ በራስ በጫንቃ ተያዘ፤ ታዘለ ተነገተ፤ ሸክሙ።
ተሠክረ ፡ ተገዛ፤ ለክራይ ተሰጠ።
ተሰክተተ ፡ ተጣደ፤ ተዋደደ፤ ተተከለ።
ተሰክዐ ፡ ተሰካ፤ ተደረደረ። ዘተሰክዐ በፈትለ ሜላት። አስናኒከ አያተ አዕናቍ እለ ተሰክዓ ፡ (አርጋ። ደራሲ)።
ተሰክየ ፡ ተከሰሰ፤ ተወቀሠ፤ በዳኛ ተያዘ። ዘባቲ ንሰከይ ፡ (ቅዳ ፡ ሕር)።
ተሰወረ ፡ በቁሙ፤ ተሸሸገ፤ ተደበቀ፤ ራቀ ረቀቀ፤ ታባ ጠፋ ዕልም አለ፤ የማይታይ የማይገኝ ኾነ። ለምንት ትሴወር እምኔየ። ኢይሴወር እምቅድመ አዕይንትየ ኀጢአቶሙ። ወተሰወረ እምአዕይንቲሆሙ ፡ (ኢዮ፲፫ ፡ ፳፬። ኤር፲፮ ፡ ፲፯። ግብ፩ ፡ ፱)።
ተሰውቀ ፡ ተደገፈ፤ ተሸራሸ፤ ከመውደቅ ዳነ።
ተሠውጠ ፡ ተመለሰ፤ ምልስ ቅልስ አለ፤ ፊቱን አዞረ ፥ ተመልሶ መጣ። እሠወጥ ወአሐውር ቤትየ። ይሠወጥ ብሔሮ። ይሠወጡ እሙንቱ ኀቤከ ፡ (ሆሴ፭ ፡ ፲፭። ኢሳ፴፯ ፡ ፯–፱። ኤር፲፭ ፡ ፲፱)።
ተሰውጠ ፡ ተጨመረ፤ ገባ፤ ተዋሐደ፤ ተቀላቀለ። ይሰወጥ ማይ ውስተ ሐመር እሞገድ። ዕፍረት ዘተሰውጠ ፡ (ማር፬ ፡ ፴፯። ማሕ፩ ፡ ፫)።
ተሠዝየ ፡ ተለየ ተነጠለ፤ ተወገዘ ከማኅበር ካንድነት ከጉባኤ ወጣ። እለ ተሠዝዩ ለዘበፁግ ይሜህር ወለዘተስዕረ ፡ (ተረ ፡ ቄር። ሲኖዶ)።
ተሠይመ ፡ ተሾመ ፥ ተቀመጠ፤ ቀረበ ተዘጋጀ። ተሠየምኩ ንጉሠ በላዕሌሆሙ። ተሠይመ ማሕጼ ዲበ ሥርወ ዕፀው ፡ (መዝ ፡ ፪። ማቴ፫ ፡ ፲)። ኮነ ተሰምየ ተጸውዐ በማለት ፈንታ ተሠይመ ይላል፤ የመላሽ ስሕተት ነው። ዘቱ ተሠየምኩ ዐዋዴ። ጳውሎስ ዘተሠይመ ሐዋርያሁ ፡ (ቆላ፩ ፡ ፳፫። ፩ቆሮ ፡ ፩ ፡ ፩)።
ተሠይመተ ፡ (ተሠይመ) ተሸመተ ተገዛ፤ እኽሉ። ሾመየ ሠለጠነ፤ ከበረ ተሾመ ሹም ኾነ፤ በገዛ እጁ የሾመውና የመረጠው ያከበረው ሳይኖር ፡ (ዕብ፭ ፡ ፬ ፡ ፭)። መምህራን ግን ቀና ተመቀኘ ይሉታል፤ ዘይቤው አይዶለም። አኮ ተሠይሚተነ ዲበ ብእሲ ዘንትናገር፤ እስመ መፍትው ንሕዝን፤ እስመ እኍ ማሰነ ፡ (ተረ ፡ ቄር፲፩)።
ተሠይጠ ፡ ተሼጠ ተለወጠ፤ ተገዛ ተዋጀ፤ ዐለፈ ተሰጠ፤ ለባለዋጋ። ተሠይጠ ዮሴፍ ወኮነ ገብረ። ጥበብ ኢትሠየጥ በወርቀ ኦፊር። ይሠየጥኑ ክቡር ለሠላሳ ብሩር ፡ (መዝ ፡ ፻፬። ኢዮ፳፰ ፡ ፲፮። ድጓ)።
ተሰይጠነ ፡ ሰይጣን ኾነ፤ ሰይጣን ተባለ። ኮከበ ጽባሕ ዘተሰይጠነ በትዕቢቱ ፡ (ማር ፡ ይሥ፪)።
ተሰደ ፡ ተሰደደ፤ ተበተነ ፣ ተባረረ፤ ተለየ፤ ተከለከለ፤ ጠፋ ታጣ። ዐማፅያን ይሰደዱ እምውስቴታ። ጊሜ እንተ ተሰደ። ይሴደድ እምቤተ ክርስቲያን። ይሰደዱ እምቍርባን። ተሰዱ በዝናም ወበበረድ ፡ (ምሳ፪ ፡ ፳፪። ጥበ፪ ፡ ፬። ፈ ፡ መ ፡ ፮ ፡ ፲፫። ፰ ፡ ፩። ጥበ፲፮ ፡ ፲፮)። ፈለሰን ተመልከት።
ተሰደሰ ፡ በቁሙ፤ ስድስት ኾነ፤ ስድስት ተባለ፤ በስድስት ክፍል ተከፈለ።
ተሰድቀ ፡ ተጨፈለቀ፤ ተሠነጠቀ። ሥላሴ እንተ ኢትሰደቅ ወኢትትፈለጥ በዕሪና ፡ (ተረ ፡ ቄር፲፱)። አካሏ እንደ ብረት የማይጨፈለቅ ፥ ባሕርይዋ እንደንጨት የማይሠነጠቅ፤ በአካል አንድ በባሕርይ ሦስት የማትባል፤ የባሕርይ ምንታዌ ያካል ርባዔ የሌለባት ማለት ነው። አዶናይንና ኤሎሄን መለኮትን እይ።
ተሰግመ ፡ ታሰረ፤ ተዘጋ፤ ተቈለፈ፤ ድዳ ኾነ፤ ደነቈረ።
ተሠግረ ፡ ተጠመደ፤ ከወጥመድ ገባ ፥ ተያዘ ታሰረ፤ ተዘጋ። ዘሠርፀ መሥገርተ ውእቱ ይሠገር ቦቱ። ይሠገሩ ብእሲ ምስለ ብእሲቱ። ኢትሠገር በአዕይንቲሃ ፡ (ሢራ፳፯ ፡ ፳፮። ኤር፮ ፡ ፲፩። ምሳ፮ ፡ ፳፭)።
ተሠግወ ተሠገወ ፡ ሥጋ ኾነ ፥ ሥጋ ለበሰ፤ ጐላ ገዘፈ። ተሠግዎቱ ለወልድ። ቃል ሶበ ይሤጎ በልሳን። ተሠጊዎ ነሥአ ቅብዐተ። እመኒ ዘአልቦሙ ልብ ኢይሌብዉ ዘ ኵሎ ልብ ለዘቦቱ ብሂለ ተሠገወ የአክሎ ፡ (አርጋ ፡ ፩። ያዕ ፡ ዘእል። ቄር። ቅኔ)።
ተሰግደ ፡ ተሰገደ፤ ተሰገደለት፤ ስግደት አምልኮት፤ ተቀበለ፤ አምላክ ተባለ። እመላእክት ይሰገድ። ለግሙራ ኢይወፅእ እምተሰግዶ እምኔነ ወእምቅዱሳን መላእክት ዋሕድ። አሐዱ ውእቱ ክርስቶስ ዘበትስብእቱ ይሰግድ ወበመለኮቱ ይሰገድ ፡ (ተረ ፡ ቄር ፡ እስት)።
ተሠጠ ፡ ተቀደደ፤ ተሠነጠቀ ተተረተረ። ኢይሠጠጥ ደመናሁ በታሕቴሁ። ወተሠጠ መንጦላዕተ ምኵራብ ፡ (ኢዮ፳፮ ፡ ፰። ማቴ፳፯ ፡ ፶፩)።
ተሰጣዊ ፡ (ዊት ውያን ያት) ጥያቄ፤ ተቀባይ፤ ተጠያቂ፤ ምላሽ ሰጪ፤ ተሰጦ አቅራቢ። ተሰጣዌ ስእለታት ፡ (አረጋ ፡ ድ፲፮)።
ተሰጥሐ ፡ ተሰጣ ተዘረጋ፤ ተገለጠ፤ ለፀሓይ ተሰጠ። ተነፅኀ ወተሰጥሐ ውስተ ምድር። አብድንት ይሰጥሓ ውስተ ገጸ ገዳም። ትሰጣሕ ኀጢአትነ በይእቲ ዕለት ፡ (ሄርማ ፡ ገ፳፩። መሳ ፡ ፳፩። ኤር፬ ፡ ፳፪። አፈ ፡ ተ፴፩)።
ተሠጥቀ ፡ ተሠነጠቀ ተተረተረ፤ ነቃ ፈነዳ ተቀደደ ተከፈለ። ጸዋልዕት ተሠጥቁ። ተሠጥቀ ገቦሁ። ተሠጥቀ ኵሉ ቀላይ። ሕዝብ ዘተሠጥቀ ሎሙ ባሕር። ነፋስ ተሠጥቀ በሐጽ ፡ (ቀሌ። ግብ፩ ፡ ፲፰። ዘፍ፯ ፡ ፲፩። ዮሴፍ። ጥበ፭ ፡ ፲፪)።
ተሰጥወ ተሰጠወ ፡ ተሰጠ፤ ተሰጠው፤ ተቀበለ። ኢይምሰልከ ዘይሰጠወከ በአብኦ ዐመፃ። ውዴተ ዘሐሰት ኢትሰጠው። ዘይሰጠወክሙ እግዚ በእደዊሁ ለኢየሱስ ክርስቶስ ፡ (ሢራ፴፪ ፡ ፲፭። ዘፀ፳፫ ፡ ፩። ፩ጴጥ ፡ ፪ ፡ ፭። ፫ዮሐ ፡ ፱)።
፡ መለሰ፤ ተናገረ፤ ምላሽ ሰጠ፤ ታዘዘ ሰማ እሺ በጎ አለ። ጸዋዕኩ ወአልቦ ዘተሰጥወኒ። ኢተሰጥውዎ ቃለ። ይጼውዐኒ ወእሰጠዎ። ኢንፈቅድ ንሰጠውከ በዝንቱ ነገ ር። ብጽሒ ፍጡነ ትሰጠዊዮ ዘይቤ ፡ (ኢሳ፶ ፡ ፪። ፴፮ ፡ ፳፩። መዝ ፡ ፺። ዳን፫። ፲፮። ደራሲ)። ሰማ ታዘዘ እሺ በጎ አለ ማለት፤ ምስጢሩ ከተቀበለ ይገባል።
ተሰጥዎ ፡ መሰጠት መቀበል፤ ተሰጭ ተቀባይ ታዳይ መኾን። መስማት መቀበል፤ ምላሽ መስጠት፤ መልሶ መናገር።
፡ በቁሙ፤ ተሰጦ፤ የቅዳሴ ጸሎት፤ ሕዝብ ለዲቆን ለቄስ የሚመልሱት ቃል፤ ተንሥኡና ሰላም ሲላቸው ፥ እግዚኦ ተሣህልነ፤ ምስለ መንፈስከ ማለት፤ ይህን የመሰለ። ተሰጦ ተቀባይ እንዲሉ።
ተሠጽረ ፡ ተሠነጠረ፤ ተሠነጠቀ፤ ተፈለጠ። ተሠጽረ ጕንደ ጣዖት ፡ (መጽ ፡ ምስ)።
ተሰፈወ ፡ ተስፋ አደረገ፤ ታመነ፤ ባለተስፋ ኾነ። እሴፎ ሕይወትየ። ምድር እንተ ትሴፎ ዝናመ። ኪያየ ይሴፈዉ አሕዛብ ፡ (ኢዮ፪ ፡ ፱። ፳፱ ፡ ፳፫። ኢሳ፶፩ ፡ ፭)።
ተሰፍሐ ፡ ተዘረጋ፤ ተንሰራፋ፤ ተነፋ ዐበጠ። ተሰፍሐ እደ እኩያን። የማኑ ለእግዚ ተሰፍሐት ውስተ ኵሉ ምድር። ተሰፍሐት ሃይማኖት ርትዕት ውስተ ኵሉ ብሔረ ግብጽ። ተጠምቀ ውስተ ዐዘቅተ ናጥራን ወተሰፍሐ ሥጋሁ ወኮነ ጸሊመ ፡ (ዮሴፍ። ቀሌ። ስንክ ፡ ግን፬። ጥቅ፲፫)።
ተሰፍረ ፡ ተሰፈረ፤ ተለካ። ኢይሰፈር ኆጻ ባሕር ፡ (ኤር፴፫ ፡ ፳፪)።
ተሰፍየ ፡ ተሰፋ ተጠቀመ፤ ተጋጠመ፤ ተያያዘ። ወበዳግም ንፍኀተ ቀርን ይሰፊያ አዕፅምት ምስለ ሥጋ ፡ (ቅዳ ፡ ያዕ)።
ተሰፍጠ ፡ ተታለለ፤ ተሸነገለ፤ ተሞኘ። ሄሮድስ ተሰፍጠ በምክንያተ ዝሙት። እስመ ይሰፈጥ እምሰይጣናት። ተሰፍጠ ለፍትወት ፡ (ስንክ ፡ ጥቅ፱። ፊልክ ፡ ፻፵። ፻፷፪)።
ተሱዕ ተሱዓት ፡ ዝኒ ከማሁ፤ ዘጠኝ፤ ዘጠንኛ። ሰላም እብል ዕደወ ተሱዐ፤ ወአምኣተኒ ሠላሳ ወሰብዓ። አመ ተሱዑ ለጽልመት። ሠርከ ወሌሊተ ወጊዜ ተሱዓት ሰዓት ፡ (ስንክ ፡ ሚያ፳፫። ሐጌ፪ ፡ ፩። ሥር ፡ ጳኵ። ማቴ፳፯ ፡ ፵፮። ግብ፫ ፡ ፩)።
ተሣሀለ ፡ ይቅር ተባለ፤ ተማረ ይቅርታ አገኘ። ይቅር ተባባለ፤ ተራረቀ። ልማዱ ግን ይቅር አለ ነው።
ተሳለመ ፡ ተሰላለመ፤ ተገናኘ፤ ተሳሰመ፤ ሰላም ሰላም ተባባለ፤ ተፋቀረ አንድ ኾነ። እምድኅረ ተሠይመ ኤጲስቆጶስ ይሳለምዎ ኵሉ ለለ አሐዱ። በተሳልሞ ዚኣሁ። በሓ በልዋ ተሳለምዋ። ተካየዱ ለተሳልሞ ወለተራድኦ ፡ (ሲኖዶ። ቀሌ። ኪዳ። ድጓ። ዮሴፍ)።
ተሣለቀ ፡ (ተደራራጊ) በቁሙ፤ ተሠላለቀ ተዘባበተ፤ ተጫወተ ርስ በርሱ። መጽሐፍ ግን ተደራራጊ አንቀጽ አድራጊነትም ስላለው በሠለቀ ፈንታ እንዳማርኛው ተሣለቀ ይላል፤ አብዝቶ መላልሶ ለማለት፤ ምስለና ላዕለ በ ይሰማሙታል። ኢትሣለቅ ምስለ አብድ። ኢይሣለቅ ግሙራ ምስለ ሕፃናት ወኢይዘፍን። ተሣሊቆሙ ላዕሌሁ ሰለብዎ። ኀለየ ሄሮድስ ከመ ውእቱ ይሣለቅ ቦቱ ፡ (ሢራ፰ ፡ ፬። ስንክ ፡ ጥር፳፪። ማቴ፳፯ ፡ ፴፩። ዮሴፍ)።
ተሣመረ ፡ ተዋደደ ተሰማማ፤ ተባበረ አንድ ፈቃድ ኾነ። ኢይኩን ተዋስቦ ዘእንበለ በተሣምሮቶሙ ለክልኤሆሙ። ወተሣመሩ በምክረ ዚኣሁ። ተሣሚረነ ምስለ አካኪዮስ ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፳፬ ፡ ፬። ፪ዜና ፡ ፴፪ ፡ ፫። ተረ ፡ ቄር፲፭)።
ተሳመከ ፡ ተጣጋ ተጠጋጋ፤ ተደጋገፈ፤ ተጠናና፤ ተጋጠመ ተባበረ። ተናበበ ተዛረፈ። አዕጻድ ይሳመካ ፡ (ዘፀ፳፮ ፡ ፫ ፡ ፲፯)
ተሳምዐ ፡ ተሳማ ተዳመጠ፤ ተሰማማ ተደማመጠ፤ የቋንቋ ፡ (ዘፍ፲፩ ፡ ፯)።
ተሣረረ ፡ ተመሠረተ፤ ተሠራ፤ ታነጸ። እስመ ዲበ ኰኵሕ ተሣረረ። ቤተ ክርስቲያን ዘተሣረረት ፡ (ማቴ፯ ፡ ፳፭። ዲድ ፡ ፰። ቆላ፪ ፡ ፯)።
ተሳረቀ ፡ በቁሙ፤ ተጣፋ፤ ተቀላቀለ፤ ተበላሸ።
ተሳረየ ፡ ተካካሰ፤ ተራረቀ፤ ይቅር ተባባለ።
ተሣቀየ ፡ በቁሙ፤ ሥቃይ ተቀበለ፤ ተጨነቀ፤ ባለመከራ ኾነ። ውስተ ኵነኔ ደይን ተሣቀዩ እስከ ለዓለም ፡ (መቃ ፡ ገ፳፪። መሳ፲ ፡ ፱። ዕብ፲፫ ፡ ፫)።
ተሳተፈ ፡ በቁሙ፤ ተገናኘ፤ ተባበረ፤ ተዋሐደ፤ አንድ ኾነ፤ በግብር በነገር። ለእመ ፈቀደ ተሳትፎታ ያውስባ በሰብሳብ ሕጋዊ። እመ ኮንኩ ምስሌክሙ እምተሳተፍኩክሙ በዐመፃክሙ። ወእምድኅረ ዝንቱ ይሳተፍ በጸሎት ባሕቲቱ ዘእንበለ ቍርባን። ተሳተፍነ ምስለ ወልድከ ወኮነ አሐደ ሥጋ። ወበዝ ተሳትፍክሙ ምስለ እለ ከመ ዝ ኮኑ ፡ (ፈ ፡ መ ፡ ፰ ፡ ፩። ዮሴፍ። ፈ ፡ መ ፡ ፬ ፡ ፬። ዝማሬ። ዕብ፲ ፡ ፴፫)።
ተሳታፊ ፡ የሚሳተፍ፤ የሚተባበር፤ ተባባሪ፤ ተካፋይ። ተሳታፍያን ውስቴቱ ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፴፯)።
ተሳነነ ፡ ተባላ ተናከሰ ተዘባተረ፤ ጥርስ ለጥርስ ገጠመ፤ ያራዊት የመኪና። ተጣላ ተሟገተ ተከራከረ። ኢትሳነን ምስለ መኰንን። ኢትሳነን በቅሥተ ሂጉይ። ብእሲ ዘይሳነን ወይትዋቀሥ። ኵሉ ለነፍሱ ይሳነን ፡ (ሢራ፰ ፡ ፲፬። ፲፩ ፡ ፱። ኤር፲፭ ፡ ፲። ሚክ፯ ፡ ፪)።
ተሳአለ ፡ (ተደራራጊ) ተለማመነ፤ ተጠያየቀ፤ ተመራመረ ፡ (ማቴ፲ ፡ ፲፩)።
ተሳዐመ ፡ ተሳሳመ፤ አፍ ላፍ ተገናኘ፤ ከንፈር ለከንፈር ተጋጠመ። ተሓቀፉ በበይናቲሆሙ ወተሳዐሙ። ጽድቅ ወሰላም ተሳዐማ ፡ (ስንክ ፡ ሚያ፲፰። መዝ ፡ ፹፬)።
ተሣአበ ፡ ተዳደፈ፤ ተራከሰ ፥ ተረካከሰ።
ተሣአነ ፡ ተሳካ፤ ተሰማማ ፥ ተዋደደ፤ ጫማውና እግሩ።
ተሳዒ መተስዕ ፡ የሚዘጥን ዘጣኝ፤ ዘጠኝ ባይ፤ ከዘጠኝ ከፋይ።
ተሳእሎ ፡ መጠያየቅ፤ መመራመር፤ ርስ በርሱ።
ተሳከረ ፡ (ዐማርኛ) በቁሙ፤ ተሳሳተ፤ የተራ የቍጥር።
ተሳወቀ ፡ ተደጋገፈ፤ ተጠናና፤ አይዞኽ አይዞኽ ተባባለ። እስመ ይሳወቃ በበይናቲሆን ወይጻንዓ በኀይሎን ፡ (ሄርማ ፡ ገ፲፭)።
ተሣየመ ፡ ተሿሿመ፤ ርስ በርሱ።
ተሣየጠ ፡ ተሻሻጠ፤ ተገበያየ ተወጃጀ፤ ርስ በርሱ። ዋጀ ገዛ ተቀበለ፤ ከሸያጭ እጅ። ተሣየጠ ብሎ ዋጀ ገዛ ማለት መላሽና ጣፊ በገዝአ ፈንታ ስላገቡት እንጂ ፍችው ኹኖ አይዶለም፤ ፍችውስ የመዠመሪያው ነው። ዘይሠይጥ ከመ ዘይሣየጥ። በእንተ ተሣይጦ ወሠዪጥ። በሤጥ ብዙኅ እሣየጠከ። ዘተሣየጠ ወዘሤጠ ፡ (ኢሳ፳፬ ፡ ፪። ፍ ፡ ነ ፡ ፴፫። ፩ዜና ፡ ፳፩ ፡ ፳፬። ሕዝ፯ ፡ ፲፪)።
ተሣያጢ ፡ የተሻሻጠ፤ የተወጃጀ። ፡ (ገዛኢ) የሚገዛ ገዥ፤ ዋጋ ሰጪ። ሠያጢ ወተሣያጢ። ሠያጢ ይሁዳ ወተሣያጢ ቀያፋ። ፍቅረ ሢመት አዖረት አዕይንተ ልቡ ለተሣያጢ። ተሣያጤ ሥጋ ሐኖት ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፴፫። ሲኖዶ። ፈ ፡ መ ፡ ፳፭ ፡ ፩። ምሳ፳፫ ፡ ፳)።
ተሣገረ ፡ ተሣገረ፤ ተሠጋገረ። ተሸጋገረ፤ ተረማመደ።
ተሳጠወ ፡ ተሟገተ፤ ተከራከረ፤ ተጠያየቀ፤ ተወዳደረ፤ እሰጥ እሰጥ ተባባለ፤ በዳኛ ፊት። ወይም ያለዳኛ በመጽሐፍ ቃል፤ እንደ ቄርሎስ እንደ ጰላድዮስ፤ እንደ አኀው እንደ ፊልክስዩስ።
ተሴሰየ ፡ በቁሙ፤ ተመገበ፤ ተቀበለ፤ በላ ጠጣ፤ ጠገበ፤ ተደሰተ። ዘኢይፈቅድ ይትቀነይ ኢይሴሰይ። እለ ይሴሰዩ እማእደ ንጉሥ። አንስት ይሴሰያ እምግብረ እደዊሆን። ተሴሰዩ እምጻማ እደዊሆሙ። እምነ ዘአምጻእኩ እሴሰይ ፡ (፪ተሰ ፡ ፫ ፡ ፲። ዳን፩ ፡ ፲፫። ቀሌ። ስንክ ፡ ጥር፲፯። ዮዲ፲፪ ፡ ፪። መዝ ፡ ፵)።
ተሤረየ ፡ ተሤረ፤ ተሤረበት። ታለለ ቀለም ገባ፤ ተነከረ። ኵሉ ክዳንየ ተሤረየ። ከመ ይሤረያ እገሪከ በደም። ተሤረየ ሥጋሁ እምጠለ ሰማይ። ግብር ዘበተሤርዮ ይዌልጥ ኅብሮሙ። እምድኅረ ተሤረያ ነፍሳቲነ በምግባረ ኀጢአት ፡ (ኢሳ፷፫ ፡ ፫። መዝ ፡ ፷፯። ዳን፬ ፡ ፴። ጥበ፲፭ ፡ ፬። አፈ ፡ ተ፲፪)።
ተስሕለ ፡ ተሳለ፤ ተሞረደ፤ ሾለ ስለታም ኾነ። እመ ተስሕለት መዐቱ ፡ (ምሳ፳፬ ፡ ፳፫)።
ተስሕበ ፡ ተሳበ፤ ቀረበ፤ ተማረከ፤ ተጐተተ። ተስሓቢ በሐብለ ፍቅሩ። ወይሰሐብ እንከ በልቡ። ተስሕበ ሰብእ በሥነ ላሕየ ምግባር። ጠቢብ ኢይትአኀዝ በአፍቅሮቱ ለሐሳዊ ወኢይስሕብ ሎቱ ፡ (ገድ ፡ ኪሮ። ፊልክ ፡ ፵፰። ጥበ፲፬ ፡ ፳። ፈላስ)።
ተስሕተ ፡ ተሳተ፤ አመለጠ፤ ሳይገኝ ቀረ፤ ጊጤው ዐላማው መንገዱ ዕውቀቱ።
ተስሕጠ ፡ ተነካ ተጐዳ፤ ተጐነጠ፤ ተቈነጠጠ።
ተሥላስ ፡ (ሳት) የደርብ ደርብ ፫ኛ ክፍል፤ ሰገነት መልዕልተ መልዕልት። እምተሥላሰ ቤታ። አኖኅዎ ጥቀ ሐኒጾሙ መልዕልቴሁ ተሥላሰ ልዑለ እምዕፅ። ጸድፈ እምተሥላስ ፡ (ስንክ ፡ መስ፳፯። ዮሴፍ። ግብ፳ ፡ ፱)።
ተስናን ፡ (ናት) ጠብ ክርክር፤ ሙግት ፍጅት፤ ንዝንዝ ጭቅጭቅ። ዐዘቅተ ተስናን። የዐስየከ ቅሥተ ወተስናነ። እመ ርኢክሙ ማእከለ አኀው ጋእዘ ወተስናነ። ተስናነ ድሜጥሮስ ፡ (ዘፍ፲፬ ፡ ፯። ሢራ፳፱ ፡ ፭። ዲድ ፡ ፲። ግብ፲፱ ፡ ፴፰)።
፡ ፍርድ፤ ቋንቋ፤ የነገር ዐይነት ርስ በርሱ የማይመሳሰል ተጣይ። በጐይየ ተስናን። ይስሕቡክሙ ውስተ ተስናናት። ወዘዘ ዚኣሁ ቃሎሙ ወተስናኖሙ ፡ (ቀኖ ፡ ኒቅ። ያዕ፪ ፡ ፮። ፩ቆሮ ፡ ፲፬ ፡ ፲)።
ተስዐቱ ት ፡ የወንዶች ድምር፤ ዘጠኝ። ተስዐቱ ቅዱሳን። ተስዐቱ በዓላት። ተስዐቱ እሙንቱ። ኀዲጎ ተስዓ ወተስዐት ነገደ ፡ (ታሪ ፡ ነገ። ድር ፡ መድ። ሢራ፳፭ ፡ ፯። ድጓ)።
ተስዑ ፤ የሴቶች ድምር ፤ (ጠ–፱) ዘጠኝ። ዕሥራ ወተስዑ አህጉር። ወጊዜ ተስዑ ሰዓት (ኢያ፲፭ ፡ ፴፪ ፡ ፶፬ ፡ ፶፯። ፳፩ ፡ ፲፮። ማቴ፳ ፡ ፭። ፳፯ ፡ ፴፭)።
ተስዓ ፡ ዘጠና፤ ፡ (ጸ–፺) ዘጠኝ ጊዜ ዐሥር፤ ወይም ዐሥር ጊዜ ዘጠኝ። ተስዓ ዓም ላቲ። ወዔሊሰ ወልደ ተስዓ ዓም። ሠለስቱ ምእት ወተስዓ ዕለት። ተስዓ ወተስዐቱ ፡ (ዘፍ፲፯ ፡ ፲፯ ፡ ፳፬። ፩ነገ ፡ ፬ ፡ ፲፭። ሕዝ፬ ፡ ፭። ማቴ፲፰ ፡ ፲፪ ፡ ፲፫)።
ተሥዕለ ፡ ተሣለ፤ ተቀረጸ፤ ተፈጠረ። አሠረ እዴሁ ውስተ ኰኵሕ ተሥዕለ። ከመ ዘተሥዕለ በእደ ኬንያ። በአርኣያ እግዚ ተሥዕለ ዕጓለ መሕያው። ተሥዕለ በማሕፀነ ሙላድ ፡ (ስንክ ፡ ሚያ፰። መጽ ፡ ምስ)።
ተስእለ ፡ (ተደራጊ) ተለመነ፤ ተጠየቀ፤ ተመረመረ፤ ተለማኝ ተጠያቂ ኾነ።
ተስእሎ ሎት ፡ (ጥ ለጠ) መለመን፤ መጠየቅ፤ ተለማኝ ተጠያቂ መኾን። ልማዱ ግን አድራጊነት ነው። ክፍል ቀዳሚ፤ እምትስእሎታተ ዜናሆሙ ለአበው መነኮሳት ፡ (ፊልክ ፡ ፩)።
ተስዕመ ፡ ተሳመ፤ ተጨመጨመ።
ተስዕረ ፡ ተሻረ ፈረሰ፤ ተሰበረ፤ ጠፋ፤ ተፈታ ተለቀቀ። ይሰዐር እምሢመቱ። ይሰዐር ተዋስቦ። ተስዕረ አርዑቶሙ። ባሕርኒ ተስዕረት እንከ። ተስዕርኪ እምደዌኪ ፡ (ቀሌ። ፍ ፡ ነ ፡ ፳፬ ፡ ፩። ኢሳ፱ ፡ ፬። ራእ፳፩ ፡ ፩። ሉቃ፲፫ ፡ ፲፪)።
ተሥእነ ፡ ተለበሰ፤ ተሰካ ገባ ፥ ተዋደደ፤ ጫማው።
ተስእነ ፡ ተሳነ ፤ አቃተ ፤ የማይቻል ኾነ ፤ ችሎቱ ታጣ። እፈቅድ እምጻእ ኀቤክሙ ወይሰአነኒ። ወሶበ ተስእኖ ለሕገ ኦሪት ፡ (ሮሜ፩ ፡ ፲፪። ፰ ፡ ፫)።
ተሥዕዐ ፡ ተገፈፈ፤ በነነ፤ ተበተነ። ተሥዕዐ እምአዕይንቲሁ ከመ ዘሣሬት። ወተሥዕዐ እምብንተ አዕይንቲሁ ዝኩ ጢስ ፡ (ግብ፱ ፡ ፲፰። ጦቢ፲፩ ፡ ፲፪። ስንክ ፡ መስ፲፮)።
ተስዖ ዖት ፡ (ተስዐ ይቴስዕ ይተስዕ። ዕብ ታሼዕ) መዘጠን፤ ዘጠኝ ማድረግ፤ ከዘጠኝ መክፈል፤ ዘጠኝ ማለት። ወይም ዘጠኝ መኾን መባል፤ ከዘጠኝ መከፈል።
ተስፋ [1] ፡ (ፋት) በቁሙ፤ አለኝታ፤ እምነት፤ አገኛለሁ ማለት ጸጋ ሀብት። ከመ ያጽንዓ ለተስፋ አበው። እለ ቀበጹ ተስፋሆሙ። እመ ቦ ተስፋ ለድኂን። ኢታስተኀፍረኒ እምተስፋየ። ይጽንሑ ተስፋሁ በአብ። እልክቱ ተስፋት ፡ (ሮሜ፲፭ ፡ ፰። ሢራ፲፯ ፡ ፳፬። ቀሌ። መዝ ፡ ፻፲፰። ግብ፩ ፡ ፬። አፈ ፡ ድ፳፫)።
[2] ፡ ተስፋ፤–በቁሙ፤–ሰፍዎ ሰፈወ ተሰፈወ።
ተሦዐ ፡ ተሠዋ ታረደ ፥ ነደደ ጤሰ ተጠበሰ። ክርስቶስ ዘተሦዐ በምዕር። እስመ ለሊሁ ምሥዋዕ ወለሊሁ ካህን ወለሊሁ ተሠዋዒ። ተሠውዖቱ። ሥጋከ ለለ ጊዜ ይሠዋዕ ፡ (አፈ ፡ ድ፲፰ ፡ ፲፯። ፳፭። ደራሲ)።
ተረመ ፡ ተራመመ፤ ብራናው። ዝም ተባለ፤ የዝም ብሎ ኾነ፤ ተረሳ፤ ቀረ፤ ተደበቀ፤ በምስጢርነት። ኢይትረመም ስምየ ወስምከ በታሕተ ሰማይ። ትትረመም መለኮቱ ፡ (ኩፋ ፡ ፳፩። ቄር)።
ተረምየ ፡ ተጣለ፤ ተወጋ፤ ቈሰለ። መለኮት ተቀሥፈ ወኢሐመ፤ ተቀነወ ወኢተሰቍረ፤ ተረግዘ ወኢተረምየ ፡ (መጽ ፡ ምስ)።
ተረሰየ ፡ ተደረገ ለበሰ አጌጠ ተሸለመ፤ ተጠረረ ታጠቀ ተሰለፈ፤ ተዘጋጀ። ተረሰይኩ ርትዐ ከመ ዐጽፍ። ተረሳዪተ ክብር በዑጻፌ። ዘይትሬሰይ በሰርጐ አንስት። መጽኡ ተረስዮሙ። እለ ተረሰዩ ለቀትል። መኑ ይትሬሰይ ለቀትል ፡ (ኢዮ፳፱ ፡ ፲፬። ስንክ ፡ ሐም፳፩። ቀሌ። ግብ፳፭ ፡ ፳፫። ዘኍ፴፩ ፡ ፭። ፩ቆሮ ፡ ፲፬ ፡ ፲)። ተሰምዕ ትከብር በማለት ፈንታ ትትሬሰይ ይላል፤ የመላሽ ስሕተት ነው። ዐይን እንተ ርእየተኒ ትትሬሰየኒ። ትትሬሰዩ በብዕሎሙ ፡ (ኢዮ፳፱ ፡ ፲፩። ኢሳ፷፩ ፡ ፮)።
ተረስዐ ፡ ተረሳ ተዘነጋ፤ ጠፋ ታባ ተሰወረ፤ ራቀ ተለየ ባዕድ ኾነ። ኵሉ ይትረሳዕ። ተረስዐኒ በሊዐ እክል። ተረስዐኒ ነገሩ። አልቦ ዘተረስዐከ። ተረስዐት እምኵሉ ሰበእ። ይትረሳዕ ልቦሙ እምጥበብ ፡ (መክ፪ ፡ ፲፮። መዝ ፻፩። ዳን፪ ፡ ፭። ኢሳ፵ ፡ ፳፮። ኢዮ፳፰ ፡ ፳፩። ሔኖ፺፫ ፡ ፰)።
ተረቅየ ፡ ተረጨ፤ ተረጨበት። ዲያቆን ያጥምቅ ዘተረቅየ። ይትረቀይ እምካህን ፡ (ኪዳ)።
ተረበ ፡ ተዘረጋ፤ ተዘረረ። እምቅድመ ይትረበባ ሰማያት ፡ (ቅዳ ፡ አፈ። ዲዮስ)።
ተረብሐ ፡ ተገኘ፤ ተወለደ፤ ትርፉ ጥቅሙ ዐራጣው። ዘተረብሐ ፡ (ቄር ፡ ጰላ)።
ተረብዐ ፡ አራት ኾነ፤ አራት ተባለ፤ ካራት ተከፈለ።
ተረትዐ ፡ ተረታ፤ ተሸነፈ፤ ድል ኾነ።
ተረከ ፡ (ዐረ ተረከ፤ ኀደገ) በቁሙ ታሪክ ተረከ፤ ጣፈ አወራ። ነተረከ ነትራካ ማለት ከዚህ ወጥቷል።
ተረክበ ፡ ተረከበ፤ ተቀበለ። ተገኘ፤ ተያዘ፤ ተመረመረ። እምአይቴ ተረክበት ጥበብ። ብእሲት እንተ ተረክበት በዝሙት። ለእመ ተረክበ ካህን በሰሪቅ። ስዉር ውእቱ ዘኢይረክብዎ በኅሊና ፡ (ኢዮ፳፰ ፡ ፲፪። ዮሐ፰ ፡ ፫። ቄድር። ቅዳ ፡ ኤጲ)። ቦ ሀሎ በማለት ፈንታ ተረክበ ይላል፤ ስሕተት ነው። ወተረክበ ለሰሎሞን አርባዕቱ ምእት አፍራስ ፡ (፪ዜና ፡ ፱ ፡ ፳፭)።
ተረውየ ፡ ተጠጣ፤ ተጠገበ፤ ዝናሙ ጠሉ ውሃው ጠበሉ።
ተረየፀ ፡ ተገራ፤ ተማረ፤ ተሠራ ተቀጣ፤ ለመደ፤ ገራም ኾነ። ፈረስ ዘኢተረየፀ። እልክቱ ኢተረየፁ ወኢተመከሩ ወኢያእመሩ ሠናየ እምነ እኩይ። እመሰ ተረየፀ ኅሊና ልብነ፤ በምንትኬ ይትረየፃ ኅሊናቲነ ፡ (ሢራ፴ ፡ ፰። አፈ ፡ ድ፰። ተግ፰)።
ተረዳዪ ፡ ተበዳሪ፤ ዐራጣ ከፋይ። ወይም ተቀባይ፤ ባላራጣ።
ተረድአ ፡ ተረዳ፤ ታገዘ፤ ተጦረ፤ ጡረተኛ ኾነ። ዘይትረዳእ በመኳንንተ ዝ ዓለም። እለ ይትረድኡ በክልኤ ፍና ፡ (ሲኖዶ። ማር ፡ ይሥ፮ ፡ ፪)።
፡ ተረዳ፤ የሞት፤ ወሬ ሰማ። ትምርት ገባው፤ ዘለቀው፤ ተረዳው፤ ፡ (ዐማርኛ)።
፡ ተረዳ፤ ታወቀ፤ ጐላ ተገለጠ፤ ርግጥ ኾነ፤ ወሬው ትምርቱ።
ተረድየ ፡ ባራጣ ወሰደ፤ ተበደረ። ወይም ዐራጣውን ተቀበለ፤ አበዳሪ። ኢትትረደይ እምኀበ ቢጽከ ኢርዴ ወርቅ ወኢርዴ እክል ፡ (ዘዳ፳፫ ፡ ፳ ፡ ፳፩)።
ተረግመ ፡ ተረገመ፤ ተሰደበ፤ ማለ ተገዘተ። ረገምኩ ወተረገምኩ። አፍቅሮ ወኢትትረገም ላዕሌሁ። ወአኀዘ ይትረገም ወይምሐል ፡ (አዋል። ቀሌ። ማር፲፬ ፡ ፸፩)። ተርጐመን እይ፤ የዚህ ዲቃላ ነው።
ተረግዘ ፡ ተወጋ። ነሥአ ሰይፈ ወተረግዘ ለሊሁ ፡ (፩ነገ ፡ ፴፩ ፡ ፬ ፡ ፭። ግብ፲፮ ፡ ፳፯)።
ተረግፀ ፡ ተረገጠ፤ በርግጫ ተመታ፤ ተናቀ ተጠቀጠቀ። እውነት ኾነ፤ ልኩ ተገኘ።
ተረጥበ ፡ (ዐማርኛ) ተረወበ፤ ተቀለተ፤ ርጥባን ቀለታ አገኘ።
ተረፍ [1] ፡ (ፋት) ዝኒ ከማሁ፤ ትራፊ፤ ትርፍ ቅሬታ፤ መጨረሻ። ተረፈ ቤተ ይሁዳ። ዘርዖሙ ወተረፎሙ። ዝንቱ ኀሠሣ ከመ ተረፍ ውእቱ። እምተረፈ ልብ ይነብብ አፍ። ተረፈ ነቢያት ሱቱኤል። ተረፈ ኤርምያስ። ተረፈ ቄርሎስ ፡ (ሶፎ፪ ፡ ፯። ኢሳ፲፬ ፡ ፳፪። አፈ ፡ ድ፳፪። ማቴ፲፪ ፡ ፴፬። ዮሐ፩ ፡ ፲፮። ስንክ ፡ ሐም፮)።
[2] ፡ (ዕብ ማሣእ) ክቡድ ቃል፤ ትንቢት ራእይ፤ በነቢያት አፍ የሚነገር፤ የፊተኛው ነቢይ ተናግሮለት ከዚያ የቀረ የተረፈ። ተረፈ ቃለ እግዚአብሔር ፡ (ሚል፩ ፡ ፩። ዕን፩ ፡ ፩ ፡ ፯)።
ተረፍአ ፡ ተፈወሰ፤ ተሰፋ፤ ታከመ፤ ተጠቀመ።
ተሪፍ ፎት ፡ (ተርፈ፤ ተረፈ ይተርፍ ይትርፍ። ዐረ ተሪፈ። ዕብ ያታር። ሱር ዬታር) መትረፍ፤ መትረፍረፍ፤ መብዛት መብለጥ፤ ከልክ ማለፍ፤ ተርፎ መቅረት መኖር፤ መዳን ማምለጥ፤ እልፍ ትርፍ ቀሪ ውዝፍ መኾን። ኖኅን ተመልከት፤ የዚህ ጎር ነው። አከሎሙ ወተርፎሙ። ወዘተርፈ እምዝ ይኩን ለመልአክ። አስተጋብኡ ዘተርፈ። አልቦ ዘይትርፍ እምኔሆሙ። ትርፍ ላዕለ ልማድከ። ወትተርፍ ምድሮሙ በድወ። እመ ሞተት ብእሲት ወተርፈ ምታ ፡ (ዘፀ፴፮ ፡ ፯። ሕዝ፵፰ ፡ ፳፩። ማቴ፲፬ ፡ ፳። ኤር፲፩ ፡ ፳፫። ፊልክ ፡ ፸፰። ኢሳ፮ ፡ ፲፩። ፍ ፡ ነ ፡ ፵፪ ፡ ፫)።
ተራሐቀ ፡ ተራራቀ፤ ተለያየ። ጊዜ ለተራሕቆ። ኢይትራሐቁ አሐዱ አሐዱ እምካልኡ። ተራሕቆ እምዓለም ፡ (መክ፫ ፡ ፭። ዮኤ፪ ፡ ፰። ፊልክ ፡ ፬)።
ተራመመ ፡ ዝም ተባባለ፤ ተፋዘዘ። ፡ (ተረት) ሰዉም ዝም መጣፉም ዝም።
ተራብሐ ፡ ተራባ፤ ተባዛ፤ ተጠቃቀመ፤ ተገበያየ፤ ተሻሻጠ። ንትራባሕ በትግብርተ እክልነ ፡ (ዓሞ፰ ፡ ፮)።
ተራትዐ ፡ ተረታታ፤ ተነጣጠረ። ተቀናና፤ ተዘገጃጀ፤ ተከነዋወነ፤ ተሳካ። እስከ አመ ይትራትዕ ፡ (ዕብ፱ ፡ ፲)።
ተራአየ ፡ ተያየ፤ ተማሰለ፤ ተመሳሰለ፤ ተነጻጸረ። ነዐ ንትራአይ ገጸ በገጽ። የሐውሩኑ ክልኤቱ ኅቡረ እንዘ ኢይትአዩ ፡ (፬ነገ ፡ ፲፬ ፡ ፰። ዓሞ፫ ፡ ፫)።
ተራከበ ፡ ተረካከበ፤ ተገናኘ፤ ተጋጠመ፤ ተሳሳመ፤ አንድ ኾነ። ባዕል ወነዳይ ይትራከቡ ኅቡረ። ተራከቡ ለቀትል። ጊዜ ተራክቦቱ ምስለ ብእሲቱ። ወይትራከብ ቃላቲሆሙ ምስለ ጽራሐ ብካየ ጸላእት ፡ (ምሳ፳፪ ፡ ፪። ፩ዜና ፡ ፲፱ ፡ ፱። ፈ ፡ መ ፡ ፲፩ ፡ ፪። ጥበ፲፰ ፡ ፲)።
ተራኰሰ ፡ ተራከሰ፤ ተረካከሰ፤ ተዳደፈ። ይትራኰሱ ይዜምዉ ፡ (ኩፋ ፡ ፲፮)።
ተራወጸ ፡ ተራወጠ፤ ተሯሯጠ፤ ተሽቀዳደመ። እምከመ መጽኦ ደምፀ ጸባኢት የኀድጉ ኵሎ ወይትራወጹ ለቀትል። ሕፃናት እለ ይትራወጹ ማእከለ ጉባኤ። ኦ አንስት ዕቀባ ውሉደክን ከመ ኢይትራወጹ ዝየ ወዝየ ፡ (አፈ ፡ ተ፭ና ፡ ፯። ቈስጠ። ማር፱ ፡ ፳፭)።
ተራደየ ፡ ተበዳደረ፤ ባራጣ በወለድ ተስማማ። ኢትትራደዮ ፡ (ዘፀ፳፪ ፡ ፳፬)።
ተራድአ ፡ ተራዳ፤ ተረዳዳ፤ ተጋገዘ። ተራድኡ በበይናቲሆሙ እኍ ምስለ እኍ ዘይትራዳእ። ትትራድኦ ለምታ። ከመ ይትራድኡ ኅቡረ በየብስ ወበባሕር፤ ወከመ ኢይትራድኡ ዘልፈ ፀረ ሮም ላዕሌሆሙ ፡ (ኦስቴ፱ ፡ ፲፮። ምሳ፲፰ ፡ ፲፱። ፳፱ ፡ ፴። ዮሴፍ)።
ተራገመ ፡ በቁሙ፤ ተረጋገመ፤ ተሳደበ፤ ተሰዳደበ፤ ተማማለ። ተራገሙ ወተማሐሉ ወቦኡ ኪዳነ ፡ (ነሐ፲ ፡ ፳፬)።
ተራገዘ ፡ ተዋጋ፤ ተዘራከተ፤ በሰይፍ ተማታ፤ ተራረደ፤ ተቀራደደ። ይትራገዙ ውሉዶሙ ፡ (ሔኖ፲ ፡ ፲፪። ዳን፱ ፡ ፳፮)።
ተራገፀ ፡ ተራገጠ፤ ተረጋገጠ፤ በርግጫ ተማታ። ፡ (ተረት) አህያ ላህያ ቢራገጥ ጥርስ አይሳበር።
፡ ተፈራገጠ፤ ፍርግጥግጥ አለ፤ የጻዕር ፡ (መሳ፬ ፡ ፳፩። ፭ ፡ ፳፯። አቡሻ ፡ ፵፯)።
ተራፊ ፡ (ፊት ፍያን ያት) በቁሙ የሚተርፍ፤ የሚቀር፤ ቀሪ፤ ነዋሪ። ሕዝብ ተራፍያን በምድር። ኵሎሙ ተራፍያነ ይሁዳ ፡ (ኤር፵፯ ፡ ፮። ፶ ፡ ፭)።
ተራፊን ፡ (ጽር ቴራፊን። ዕብ ትራፊም) ጣዖታት፤ አብያተ ጣዖት፤ ሥዕላተ ጣዖት፤ የሰው ምስሎች አሻንጕሊቶች፤ የሟርት መሣሪያ፤ ንዋያተ ሰገል፤ የቀድሞ ሰዎች የሚያመልኩት የሚያሟርቱበት ፡ (መሳ፲፯ ፡ ፭። ፲፰ ፡ ፲፬። ፲፯ ፡ ፳። ፬ነገ ፡ ፳፫ ፡ ፳፬። ፪ዜና ፡ ፴፭ ፡ ፲፱። ሕዝ፳፩ ፡ ፳፩)።
ተርሙስ ፡ (ጽር፤ ቴርሙስ። ዐረ ቱርሙስ) ግብጦ፤ አዳጕራ፤ የመኬ ዐይነት። አባ ቅፍሪ ኢይጥዕም ዘእንበለ ተርሙስ መሪር። ኮነ ይሴሰይ ሐሠረ ተርሙስ ኵሎ አሚረ። ወሶበ ፈቀደ ይትጋደል ነበረ ሰማንያ ዕለተ እንዘ ይበልዕ ሐመደ ምስለ ተርሙስ ፡ (ስንክ ፡ ኀዳ፰። መጋ፲፬። የካ፳፬)።
ተርሜን ፡ (ጽር ራትሜን። ዕብ ሮቴም) ስመ ዕፅ ዐቢይ፤ የዱር የበረሓ ዛፍ፤ ዐጽቃም ቅጠላም። ባለብሉዮች ግን ከትክታ ደደሆ ይሉታል። ሖረ ፍኖተ በድው ወነበረ ታሕተ ዕፀ ተርሜን ፡ (፫ነገ ፡ ፲፱ ፡ ፬)።
ተርሴስ ፡ (ጽር ታርሲስ። ዕብ ታርሺሽ) ስመ ዕንቍ፤ የብርሌና የመስታዮት ዐይነት፤ እንደ ውሃ የሚያጥበረብር ፡ (ማሕ፭ ፡ ፲፬። ዳን፲ ፡ ፮። ሕዝ፩ ፡ ፲፮)።
፡ ስመ ነገድ፤ ስመ ሀገር ፡ (ዘፍ፲ ፡ ፬። ዮና፩ ፡ ፫። ሕዝ፳፯ ፡ ፲፪)።
ተርቢዝ ፡ አተላ ሐሠር፤–ተብሪዝ፤ በረዘ።
ተርእሰ ፡ ተንተራሰ፤ ተጠጋ፤ ተደገፈ። መጽሐፍ ግን እንዳማርኛው ተተርአሰ ይላል፤ አያሰኝም። ተተርኢሶ ኖመ። ያዕቆብ ቅዳሴ ተተርአሰ እብነ ፡ (ማር፬ ፡ ፴፰። ቅኔ)።
ተርእየ ታየ ፡ ተገለጠ። ወተርእየት ማይ ርግዕተ። ኢትትረአይ ቅድሜየ ዕራቀከ። መፍትው ለአንስት ይትረአያ በአርኣያ ህድኦት ወበትሕትና ፍድፋድ ፡ (ጥበ፲፱ ፡ ፯። ዘፀ፳፫ ፡ ፯። ፈ ፡ መ ፡ ፴፬ ፡ ፰)። በተርእየ ፈንታ አስተርእየ ይላል፤ የስሕተት ስሕተት ነው፤ አያሰኝም። ገባሬ ሰማያት ወምድር ዘያስተርኢ ወዘኢያስተርኢ። አስተርአየ ዘኢያስተርኢ፤ እሙነ ኮነ አስተርእዮቱ ፡ (ጸሎ ፡ ሃይ። ድጓ)። በአርአየ ቦታ አስተርአየ ቢል ግን፤ ሥርወ ቀለሙ ሳድስ ስለ ኾነ፤ ርትዕ እንጂ ጸያፍ አይኾንም፤ ስሕተት አይባልም።
ተርዕየ ፡ ተረዐየ፤ ተጠበቀ፤ ተሰማራ ሣር በላ፤ ነጨ ጋጠ። ይትረዐዩ ከመ አስዋር ወከመ አባግዕ ሐቅለ። ተኵላት ወአባግዕ ይትረዐዩ ኅቡረ። አባሕኵ እለ ኀጥኡ ዘይትረዐዩ። ላሕም ዘይትረዐይ ሣዕረ። ትትረዐይ ሣዕረ ከመ ላሕም ፡ (ኢሳ፭ ፡ ፲፯። ፴ ፡ ፳፫። ፷፭ ፡ ፳፳። ሰቈ፩ ፡ ፮። መዝ ፡ ፻፭። ዳን፬ ፡ ፴)። በተርዕየ ፈንታ ተራዐየ ይላል፤ ስሕተት ነው። ይትራዐዩ ውስተ ቀርሜሎስ። ኵሉ ዘመደ እንስሳ ይትራዐዮ ለውእቱ ሣዕር፤ ይበልዖ ብሂል ፡ (ኤር፳፯ ፡ ፲፬። ሄርማ)።
ተርጐመ [1] ፡ በቁሙ፤–ተረጐ ተ።
[2] ፡ ተርጐመ፤ ፡ (ዲቃ ግ፤ ረገመ፤ ተረግመ። ዕብ ወሱር ታርጌም። ዐረ ተርገመ) ተረጐመ፤ ቃልን በቃል ለወጠ፤ ገለበጠ፤ መጽሐፍን ቀዳ መለሰ፤ ከቋንቋ ወደ ቋንቋ። ወይም በዚያው ባንዱ ቋንቋ፤ አንድም እያለ ፈታ ኣፍታታ ዘረዘረ፤ ቁሞ ሰበከ አስተማረ፤ ላንዱ ቅንጣት ቃል ብዙ ፍሬ ብዙ ፍካሬ ሰጠ። ወኮነ ዮሴፍ ይተረጕም ሎሙ ዘይትናገሮሙ ጢጦስ በልሳነ ሮም ወያየድዖሙ በልሳነ ዕብራውያን። በእንተ ተርጕሞቱ እምልሳነ ጽርእ ኀበ ዐረቢ። ተርጕሞ ቃለ መጻሕፍት። ተርጕም ለነ ፡ (ዮሴፍ። ፍ ፡ ነ ፡ መቅ። ቀሌ። ፊልክ ፡ ፴)።
ተርጓሚ ፡ (ሚት ምያን ያት) በቁሙ፤ የሚተረጕም፤ የሚፈታ፤ ፈች አስረጅ። አኮሰ ውዳሴ ለተርጓምያን ፡ (ፊልክ)።
ተሮሐ ፡ ተሮሐ፤ ተራገበ፤ ተርገበገበ፤ ተነሰነሰ፤ ተረጨ። መጽሐፍ ግን ተሮሐ ተረውሐ በማለት ፈንታ ተራውሐ ይላል፤ አያሰኝም። ዘተጸፍዐ መልታሕቱ ተለዐለ ወነበረ በየማነ አቡሁ እንዘ ይትራዋሕ ሎቱ አክናፈ እሳት ዘሐራ ሰማይ ፡ (መጽ ፡ ምስ)።
ተሮደ ተረውደ ፡ ተያዘ፤ ተከበበ፤ ተወረረ ተዘረፈ፤ ተዘመተበት።
ተቀልመ ፡ ተቀለመ፤ ተጣፈ፤ ከቀለም ገባ፤ አደፈ ተበከለ፤ ተኵለፈለፈ።
ተቀልሰ ፡ ተቀለሰ፤ ተጐነበሰ፤ ታጠፈ ዞረ ተመለሰ፤ ምልስ ቅልስ አለ።
ተቀልዐ ፡ ተቀላ፤ ተገለጠ። ይትቀላዕ መንጦላዕት ዘቅድመ ገጹ ፡ (ቅዳ ፡ ያዕ)።
ተቀልወ ፡ ተቈላ፤ ተንደገደገ። ተቀሎኩ ወተሀድየ አዕፅምትየ። ትትቀሎ ነፍሱ ውሰተ አፍቅሮ እግዚ። ሶበ ለብሰ ባሕታዊ አስኬማ ይነሥእ እምጸጋ መንፈስ ቅዱስ ተቀልዎተ መንፈሳዊተ ፡ (ኢዮ፴ ፡ ፴። ፊልክ ፡ ፻፮ና ፡ ፸፬)።
ተቀመረ ፡ በቁሙ፤ ተዘጋጀ፤ ተጋረደ ተዘረጋ፤ ተቈጠረ፤ ተከፈለ። ይትቄመር ውስተ ሰማይ ወየዐውዶ ስብሐቲሁ ፡ (ሢራ፵፫ ፡ ፲፪)።
ተቀመጠ ፡ በቁሙ፤ ቍጭ አለ፤ ጕልበቱን ጭኑን ዐጠፈ፤ ምድር ያዘ፤ ተንዘራፈጠ። ተቈመጠ፤ ቈማጣ ኾነ። በጽሐ ኀበ ምኔት ወተቀመጠ ኀበ ዴዴ ወበከየ። ኀበ እቀውም ወኀ እትቀመጥ ፡ (ፊልክ ፡ ፳፰። ደራሲ)።
ተቀሥመ ፡ ተለቀመ፤ ተቈረጠ። እንበለ ይትቀሠም ወይን ፡ (ዘኍ፲፫ ፡ ፳)።
ተቀስመ ተቀሰመ ፡ ተጣፈጠ፤ ተቀመመ። በምንት ይትቄሰም ፡ (ማቴ፭ ፡ ፲፫)።
ተቀሥፈ ፡ ተቀሠፈ፤ ተመታ ተቀጣ፤ ተገረፈ። ሕቡል እንዘ ይትቀሠፍ። በተቀሥፎ ወበተሞቅሖ። ወኢተሥፉ ምስለ ሰብእ። ተቀሥፈት ፀሓይ፤ ተመታች ፡ (ሢራ፲፱ ፡ ፳፭። ፪ቆሮ ፡ ፮ ፡ ፭። መዝ ፡ ፸፪። ራእ፰ ፡ ፲፪)።
ተቀርጸ ፡ ተቀረጠ፤ ተነጠጠ፤ ተጣፈ ተነደፈ። ናሁ ተአዘዘ ወተቀርጸ። ወከመ ዝ ተጽሕፈ ወተቀርጸ በእንቲኣሁ። ሰንበተ አይሁድ እንተ ተቀርጸት በጽላተ ሰማይ። ወሀበ ሙሴ በሰሌዳተ አብላቅ እለ ተቀርጻ በሆህያተ ዕብራይስጢ ፡ (ኩፋ ፡ ፲፮። ፳፬። መጽ ፡ ምስ)።
ተቀርመ ፡ ተቃረመ፤ ተለቀመ፤ እልፉ እንቡጡ ዛላው።
ተቀርፀ ፡ (ተቀረጠ) ተቈረጠ፤ ተሸለተ። እስከ ተቀርፀ ሥጋሁ። መራዕይ እለ ተቀርፃ። ተቀርፆ ሥዕርት። አልቦ ዘይትቀረፅ ርእሶ ዘእንበለ ያእምር አባስ ፡ (ስንክ ፡ ግን፳፰። ማሕ፬ ፡ ፪። ስንክ ፡ ሐም፳፩። ሥር ፡ ጳኵ)።
ተቀበለ ፡ በቁሙ፤ ወሰደ፤ እጅ አደረገ፤ ያዘ ጨበጠ፤ ተረከበ፤ የሰጡትን ወይም ወደ ርሱ የመጣውን የተቃጣውን። ለይትቀበል ቍርባነከ። ፈኒውየ እትቄበለከ። ፃእ ተቀበሎ ለአካዝ። ኢትርስዑ ተቀብሎ ነግድ ፡ (፩ነገ ፡ ፳፮ ፡ ፲፱። ኩፉ ፡ ፳፯። ኢሳ፯ ፡ ፫። ዕብ፲፫ ፡ ፪)።
፡ ሰማ፤ አመነ፤ ተስፋ አደረገ፤ ራራ፤ ታገሠ ይቅር አለ። ምስጢሩ እንደ ተወክፈ ነው፤ ቅበላን አይለቅም። ዘኢተቀበላ ለመንግሥተ እግዚ። ወበየውሀት ተቀበልዎ ለቃል። ከመ ይትቀበሎ ለገጽየ በዳኅን። ተቀበል አበሳየ ፡ (ማር፲ ፡ ፲፭። ያዕ፩ ፡ ፳፩። ዘፍ፴፪ ፡ ፳፩። ዘፀ፲ ፡ ፲፯)።
፡ ተሰጠ፤ ተሰጭ ኾነ፤ ተቀበሉት፤ ከሰጭ ወደ ተቀባይ እጅ ዐለፈ፤ ተወሰደ።
ተቀባሊ ፡ (ሊት ልያን ያት) የሚቀበል፤ ተቀባይ፤ ወሳጅ። አኀው ተቀባልያን ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፵፪ ፡ ፮)።
ተቀብረ ፡ ተቀበረ፤ ከጕድጓድ ገባ፤ ተከተተ፤ ዐፈር ለበሰ። ፡ (ሙሾ) የሺዋ መኳንንት እንግዴህ አትልፉ፤ ተመዞ የነበር ተከተተ ሰይፉ። ሐመ ወሞተ ወተቀብረ ፡ (ጸሎ ፡ ሃይ)።
ተቀብዐ ፡ ተቀባ።ተቀብዐት ገጻ ዕፍረተ። ሳኦልሂ ተቀብዐ ለነጊሥ ፡ (ዮዲ፲፮ ፡ ፯። ቄር)።
ተቀብወ ፡ ተነፋ፤ ተቀበተተ፤ ሆዱ ቂብ አለ፤ እንቅብ መሰለ፤ የደዌ የማውቄ።
ተቀብየ ፡ ተዘጋጀ። ወተቀብየት ቀትል ፡ (ሕዝ፳፩ ፡ ፲፭)።
ተቀትለ ፡ ተገደለ፤ ሞተ፤ ተመታ፤ ታረደ፤ ተወጋ ቈሰለ፤ ጠፋ ተበላሸ፤ ረከስ። ረሰይከነ ለተቀትሎ። ተቀትለት ሀገር። እስመ ተቀተልከ። ወተቀትለት ምድር በደም ፡ (ጦቢ፫ ፡ ፬። ሕዝ፴፫ ፡ ፳፩። ራእ፭ ፡ ፱። መዝ ፡ ፻፭)።
ተቀትረ ተቀተረ ፡ ተዘጋ፤ ተሸጐረ፤ ተወጋ ተቸነከረ። ታጠነ ጤሰ፤ ሸተተ፤ መሧዕት ኾነ። ዘበዮርዳኖስ ተጠምቀ ወዘበመስቀል ተቀትረ ፡ (መጽ ፡ ምስ)።
ተቀነነ ፡ ቀኖና ያዘ፤ ተቀበለ። ተቈነነ፤ መቍነን፤ አገኘ፤ ታደለ።
ተቀነወ ፡ ተቸነከረ፤ ተበሳ ተነደለ። እንዘ ይትቀሠፍ ወይትቄኖ በቅንዋት። ተቀነወ እደዊሁ። በቀኖተ ኀጺን ተቀነወ እግሩ ፡ (ሃይ ፡ አበ። ቀሌ። ስንክ ፡ ሠኔ፳፭)።
ተቀንየ ፡ ተገዛ፤ አገለገለ፤ ተገዥ አገልጋይ ኾነ፤ ተሠራ ተፈጠረ። ተቀነዩ ለእግዚ በፍርሀት። እስመ ለከንቱ ተቀንየ ዓለም። ነባሪ ዘበጽድቅ ይትቀነይ ለከ። ከመ ይትቀነያ ለገነት ፡ (መዝ ፡ ፪። ሮሜ፰ ፡ ፳። ሢራ፯ ፡ ፳። ኩፋ ፡ ፫)።
ተቀየመ ፡ ቂም ተያዘበት፤ ለክፉ ታሰበ፤ ተመደበ።
ተቀይአ ፡ ተተፋ፤ ወጣ፤ ተለየ፤ ተመለሰ። የተነቅበ ፍች መለየት መውጣት ስለ ኾነ፤ በተነቅበ ፈንታ ተቄአ ይላል፤ ምስጢሩ አንድ ነው ፡ (ሕዝ፳፫ ፡ ፲፰)።
ተቀደሰ ፡ በቁሙ፤ ተባረከ፤ ተመሰገነ፤ ተለየ፤ ተመረጠ፤ ከበረ፤ ተሾመ፤ ነጻ ጥሩ ኾነ። ቤተ ክርስቲያን ዘተቀደሰት። ሶበ ተቀደስኩ በላዕሌክሙ። ካህናት እለ ተቀደሱ። እምከርሠ እሙ ተቀደሰ ከመ ይኩን ነቢየ። ትትቄደስ ምድር እምኵሉ አበሳ ፡ (ስንክ ፡ ሚያ፲፭። ሕዝ፴፮ ፡ ፳፫። ፵፰ ፡ ፲፩። ኩፋ ፡ ፬)።
ተቀድሐ ፡ ተቀዳ፤ ተገለበጠ። ማይ ዘኢተቀድሐ። መጽሐፈ ሰዋስው ዘተቀድሐ እምሰማንያ ወአሐዱ መጻሕፍት ፡ (መጽ ፡ ምስ። ግስ)።
ተቀድመ ፡ ተቀደመ፤ ታለፈ፤ ቅድምናውን ብኵርናውን ጣ፤ እንደ ዔሳው።
ተቀጥቀጠ ፡ ተቀጠቀጠ፤ ደቀቀ፤ ነከተ፤ ተሰበረ፤ ተመራ ተደበደ። መሥገርትሰ ተቀጥቀጠት። ይትቀጠቀጥ ከመ ዕፅ ብኍብኍ። አመኒ በኀጺን ኀጺን ይትቀጠቀጥ፤ እሳት ዘያመውቆ እምተቀጥቅጦ ኢያመሥጥ ፡ (መዝ ፡ ፻፳፫ ፡ ኢዮ፳፬ ፡ ፳። ቅኔ)።
ተቀጥፈ ፡ ተቀጠፈ፤ ተቀጨ፤ ባጭር ቀረ፤ አለዕድሜው ሞተ፤ ተቀሠፈ።
ተቀጸለ ፡ ተቀጠለ፤ ተጨመረ ተቀጥላ ኾነ፤ በሰው ራስ ላይ፤ ያበባ ያክሊል። ተቀዳጀ፤ ሰውዮው በራሱ ደፋ ለበሰ ተሸከመ፤ ጠመጠመ። እንዘ ይትቄጸል አክሊለ ዘሦክ። ንትቀጸል ጽጌ ረዳ። ንትቀጸል አሕባለ ውስተ አርእስቲነ ፡ (ዮሐ፲፱ ፡ ፭። ጥበ፪ ፡ ፰። ፫ነገ ፡ ፳ ፡ ፴፩)።
ተቀጽረ ፡ ተቀጠረ፤ ታጠረ፤ ተከበበ።
ተቀጽዐ ፡ ተቀጨ፤ ተሠራ ተቀጣ፤ ጐበጠ፤ ፈራ ደነገጠ። ወትትቀጻዕ ኵሳ ነፍስ። አረጋዊ ዘተቀጽዐ ዘባኑ። ተቀጽዑ ወኢተርፈት ነፍሶሙ በላዕሌሆሙ ፡ (ሕዝ፳፩ ፡ ፯። አፈ ፡ ተ፳፫። ነሐ፮ ፡ ፩። ኢሳ፲፫ ፡ ፰)።
ተቀፍለ ፡ ተለበጠ፤ ተሸለመ፤ ለበሰ አጌጠ። ይትቀፈሉ ወርቀ ፡ (ዘፀ፳፮ ፡ ፳፱። ፳፯ ፡ ፲፩)።
ተቀፍጸ ፡ ተገለጠ፤ ተገፈፈ፤ ተከፈተ። ወይትቀፈጽ ኀፍረቶሙ ለግብጽ። ተቀፈጽኪ እምድኅሬኪ። ይትቀፈጽ ኆኅት ፡ (ኢሳ፳ ፡ ፬። ኤር፲፫ ፡ ፳፪። ቅዳ)።
ተቃሐወ ፡ ተፈካከረ፤ ተቃወመ ተወዳደረ፤ ተሟገተ ተከራከረ። ይትቃሐዉ በምግባረ ትሩፋት። አላ ከመ ይትቃሐዎሙ ለነሀብተ ብሩር። ኢትትቃሐው ምስለ ዘይብዕለከ። ለእመ ተቃሐወ በዝንቱ። ተቃሕዎት ፡ (አፈ ፡ ድ፳፪። ጥበ፲፭ ፡ ፱። ሢራ፰ ፡ ፪። አብጥ ፡ ፬። ፊልጵ፩ ፡ ፲፭)።
ተቃለሰ ፡ ታገለ፤ ተያያዘ፤ ተጠማዘዘ ፣ ተናነቀ። ይትቃለስ ምስሌሁ ፡ (ስንክ ፡ ጥቅ፳፱)።
ተቃረመ ፡ ተቀራመተ፤ ተቀረማመተ፤ የሥጋ ፡ (ዐማርኛ)።
ተቃረበ ፡ በቁሙ፤ ተቀራረበ፤ ተጣጋ ተጠጋጋ፤ ተሳለፈ ተሰላለፈ። ኢይትቃረብ ወኢይኑም ምስለ ብእሲቱ። እለ ይትቃረቡኒ። እምተራክቦ ወተኣምኆ እንዘ ይትቃረቡ። እንበለ ይትቃረቡ ፡ (ፈ ፡ መ ፡ ፲፬ ፡ ፱። መዝ ፡ ፶፬። ቄድር። ማቴ፩ ፡ ፲፰)። ቀሪብ፤ ቀርበ በማለት ፈንታ ተቃረበ ይላል፤ ስሕተት ነው። ኀፍረት ተቃርቦ ለበሊዐ እክለ ባዕድ። አው ይትቃረብ ኀበ ሃይማኖት ርትዕት ፡ (ሢራ፵፩ ፡ ፲፱። ፈ ፡ መ ፡ ፳፯ ፡ ፰)።
ተቃረነ ፡ ተዋጋ፤ ተተማተመ፤ ተቀራሸመ፤ ተጣላ ተቃወመ፤ ተከራከረ፤ የሰው የእንስሳ። ተገሐሡ እምኵሉ ዘይትቃረን ተቃርኖ ምስለ ሕግ። ቀዳሚ ዘይትቃረነከ ተቃረነ ምስሌነ። ይትቃረኑ ምስለ ኵሉ ሰብእ ፡ (ዲድ ፡ ፴፫። ቀሌ። ፩ተሰ ፡ ፪ ፡ ፲፭)።
ተቃራሚ ፡ የሚቀራመት፤ ተቀራማች፤ ዐራጅ በጋማች።
ተቃራኒ ፡ (ኒት ንያን ያት) ተዋጊ፤ ተጣይ፤ ወደረኛ፤ ባለጋራ። ዲያብሎስ ተቃራኔ። ኵሉ ሕሡም ተቃራኒሁ ለሠናይ። እስመ ፈውሰ ኵሉ ኀጢአት ይደሉ ከመ ይኩን ተቃራኔ ለኀጢአት። ፀር ተቃራንያን ፡ (ስንክ ፡ ኅዳ፳፮። ፈላስ። ፈ ፡ መ ፡ ፫ ፡ ፫። ጥበ፲፰ ፡ ፯)።
ተቃበለ ፡ ተቀባበለ፤ ተሰጣጠ። ቀበሎ፤ ቀበሌ ማለት ከዚህ የወጣ ነው። ተቀበለ በማለት ፈንታ ተቃበለ ይላል፤ ስሕተት ነው። ተቃበል ነግደ፤ ተቃብሎ ነግድ ፡ (ሄርማ)።
ተቃተለ ፡ ተጋደለ፤ ተገዳደለ፤ ተዋጋ፤ ተላለፈ፤ ተጋጠመ። ይጻልኡ በበይናቲሆሙ ወይትቃተሉ። ይትቃተልዎ ለይሁዳ። ተቃተሎ ለመነኮስ ኅሊና ዝሙት። ንትቃተል ክልኤነ በባሕቲትነ ፡ (ማቴ፳፬ ፡ ፲። ኢሳ፱ ፡ ፳፩። ገድ ፡ ዳን። ፩ነገ ፡ ፲፯ ፡ ፲)።
ተቃነጸ ፡ ተዛለለ ተፈናጨ ተሯሯጠ።
ተቃንአ ፡ ተቃና፤ ተቀናና፤ ተፈካከረ። ትትቃንኡ ዝንቱ ምስለ ዝንቱ። አሰስልዋ ለተሒምዮ ወለተቃንኦ። እስመ ኀበ ሀለወ ተቃንኦ ህየ ሀሎ ሀውከ ፡ (ኩፋ ፡ ፯። ፩ጴጥ ፡ ፪ ፡ ፩። ያዕ፫ ፡ ፲፬)።
ተቃዐነ ፡ ተጫነቀ፤ ተጨናነቀ፤ ተጣበበ ፡ (ሉቃ፰ ፡ ፵፭)።
ተቃወመ ፡ በቁሙ፤ ተቋቋመ፤ ተሟገተ ተከራከረ፤ ተወዳደረ ተፈካከ። መኑ ይትቃወማ ለኵነኔሁ። አልቦ ዘይትቃወሞ ለቃልኪ። ለእመ ተቃወሞ ዲያቆን ለቀሲስ። ምስለ ብርሃን እንዘ ትትቃወም ትትረከብ ከመ ቀዳማዊት ይእቲ ፡ (ኢዮ፱ ፡ ፲፱። ዮዲ፰ ፡ ፳፰። ፍ ፡ ነ ፡ ፱። ቅዳ ፡ ኤጲ)።
ተቃዋሚ ፡ (ሚት ምያን ያት) በቁሙ፤ ተጣይ፤ ከሳሽ፤ ቁሞ የሚያቆም፤ የሚቋቋም። ብእሲት ተቃዋሚት። ኰነንከ ተቃዋምያነ ፡ (ፈላስ። ጥበ፲፩ ፡ ፱)።
ተቃደመ ፡ ተቀዳደመ፤ ተከታተለ፤ ተጋጠመ ተሰላለፈ፤ ፊት ለፊት። ተቃደማ ሰይጣን ወተራከባ። ተቃደምዎሙ ወተቃተልዎሙ ፡ (ግንዘ። ፪ነገ ፡ ፲ ፡ ፲)።
ተቃጸበ ፡ ተጣቀሰ፤ ተጠቃቀሰ። የሐውራ እንዘ ይትቃጸባ በአዕይንቲሆን። ዘይትቃጸብ በአዕይንቲሁ። ይሬእይዎ ወይትቃጸቡ ቦቱ ፡ (ኢሳ፫ ፡ ፲፮። ምሳ፲ ፡ ፲። ጥበ፬ ፡ ፲፰)።
ተቈልቈለ ፡ ተቈለቈለ፤ ተደፋ፤ ወረደ፤ ተዘቀዘቀ። እስመ ተቈልቈለ ፀሓይ ፡ (ኤር፮ ፡ ፬። ሉቃ፱ ፡ ፲፪። ፳፬ ፡ ፳፱)። ይርሕቅ ይሴስል በማለት ፈንታ ይትቈለቈል ይላል፤ የመላሽ ስሕተት ነው ፡ (ዘካ፲፬ ፡ ፬)።
ተቈልፈ ፡ ተቈለፈ፤ በቍልፍ ተዘጋ።
ተቈርቈረ ፡ በቁሙ፤ ተቈረቈረ፤ ዐዘነ፤ ተቈጣ፤ ተናወጠ፤ ተንቀጠቀጠ፤ ከሐዘን ከቍጣ የተነሣ። ተመሠረተ ተዠመረ፤ ሀገሩ ከተማው።
ተቈናደየ ፡ ተቈናዳ፤ ተዛለለ፤ ተቃበጠ፤ ተዳራ። ፍሒልን ይመስላል።
ተቈጽረ ፡ ተቈጠረ፤ ተቋጠረ፤ ተሰበሰበ። በከመ ይትዐወቅ ንዋየ ለብሓ ዘተሰብረ እምነ ዘኢተሰብረ በተቈጽሮ፤ ከማሁ ብእሲኒ በንባቡ ፡ (ፈላስ)።
ተቅማጥ ፡ በቁሙ፤ ቅዘን፤ ቀጭን ዐይነ ምድር።
ተቅሣም ፡ (ማት) ለቀማ፤ ቈረጣ፤ አዝመራ፤ ዐጽቅ ዘለላ። ወተቅሣመ ፍሬሃ ፡ (አርጋ ፡ ፬)።
ተቅራም ፡ ተቅራም፤ ፡ (ማት) ቀርም፤ ቃርሚያ። ከመ ተቅራም አመ ቀሥም። ተቅራመ ማእረር። ዐቀብተ መቃብር አረሩ ኅጠተ ብሩር ጸዐዳ፤ ወተቅራመ ብሩር መቃብረ አትረፉ ለእንግዳ ፡ (ሚክ፯ ፡ ፩። ስንክ ፡ መስ፲፩። ቅኔ)።
ተቅዋም [1] ፡ (ማት) መቅረዝ፤ ማብሪያ፤ የመብራት ዕቃ፤ የቀንዲል የፋና ማኖሪያ፤ የሚቆም የሚተከል ወይም የሚሰቀል የሚንጠለጠል፤ ባለብዙ ዐጽቅ። ርኢኩ ተቅዋመ ማኅቶት ዘኵለንታሃ ውርቅ። ማኅቶት እንተ ታበርህ ዲበ ተቅዋማ። ወትገብር ሊተ ተቅዋመ ወርቅ ጽሩይ ፡ (ዘካ፬ ፡ ፪። ሢራ፳፮ ፡ ፲፯። ዘፀ፳፭ ፡ ፴፩)።
[2] ፡ ተቅዋም፤–መቅረዝ፤–ቀዊም ቆመ።
ተቅዳ ፡ (ዐረ ተቅደት። ዕብ ጋድ) ድንብላል፤ የድንብላል ፍሬ፤ ታናናሽ ድንብልብል፤ ቅመም የሚኾን። ድቁቅ ከመ ተቅዳ። ወከመ ፍሬ ተቅዳ ፡ (ዘፀ፲፮ ፡ ፲፬ ፡ ፴፩። ዘኍ፲፩ ፡ ፯)።
ተቅጺል ፡ ተቀጥላ የንጨት ዲቃላ።
ተቋጸረ ፡ ተቋጠረ፤ ተቈጣጠረ፤ ተሸናገለ፤ ተሸነጋገለ። ዘይከውን በውስቴቱ ተቋጽሮ። ተቋጻርያን ምስለ እሊኣሁ ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፴)።
፡ ተባበረ፤ አንድ ልብ አንድ ሐሳብ ኾነ፤ ሤራ ቈረጠ ተማማለ፤ ለመግደል ለመወንጀል። መጽሐፍ ግን ተቋጸረ በማለት ፈንታ አስተቋጸረ ይላል፤ የጣፊ ስሕተት ነው። አስተቋጸሩ ሎቱ በኵለሄ ማዕሌተ ፡ (፬ነገ ፡ ፲፪ ፡ ፳)።
ተበሕብሐ ፡ (ይትበሐባሕ ይትባሕባሕ) ተሣለ ተመሰለ፤ ተፈጠረ።
ተበለተ ፡ በቁሙ፤ ተለየ ተነጠለ፤ ደኸየ ብቸኛ ኾነ፤ ብቻውን ቀረ እንደ ኖሓሚን ፡ (ሩት፩ ፡ ፭)።
ተበልዐ ፡ ተበላ፤ ተበላላ፤ ተዋጠ፤ ተቃጠለ። ይትበላዕ እክል። ልብስ ዘተበልዐ እምቍንቍኔ። ተበልዑ እምዓሣት። በእሳት ይትበላዕ ፡ (ኢዮ፮ ፡ ፮። ፲፫ ፡ ፳፰። ሔኖ፷፩ ፡ ፭። ስንክ ፡ ሠኔ፳)።
ተበስለ ፡ ተቀቀለ ተጋገረ፤ ተቈላ ተነፈረ። ሰላም ለአሮን ዕጓላተ ርግብ ዘአስረረ በእሳት ወማይ ድኅረ ተበስሉ ኅቡረ ፡ (ስንክ ፡ ግን፳፩)።
ተበሥረ ፡ በቁሙ፤ ምሥራች ሰማ፤ ሐዲስ ወሬ አገኘ፤ ሰውዮው። ተወራ ተባለ ተነገረ፤ ተሰበከ፤ ወሬው ትንቢቱ የምሥራቹ። ስምዖን ዘተበሥረ ፅንሱ በአፈ ዮሐንስ መጥምቅ። በከመ ተበሥረ አምአፈ ማርቆስ ፡ (ስንክ ፡ ግን፳፱። ሚያ፳፪። መጋ፳)።
ተበረ ፡ (ይትበረር) ተለቀመ፤ ጠራ ጥሩ ኾነ። ብርትና ብረት የዚህ ዘር ነው።
ተበርበረ ፡ በቁሙ፤ ተበረበረ ተበዘበዘ፤ ተወረረ ተዘረፈ። ይትበረበር አብያቲሆሙ። እለ በርበሩከ ይትበረበሩ። ተፄወዉ ሕዝብ ወተበርበሩ። ረሰይከነ ለተበርብሮ። ተበርበረት ታቦተ ሕግነ ፡ (ሶፎ፩ ፡ ፫። ኤር፴፯ ፡ ፲፮። ኢሳ፵፪ ፡ ፳፪። ጦቢ፫ ፡ ፬። ሱቱ ፡ ዕዝ ፡ ፲ ፡ ፴)።
ተበርዘ ፡ ተበረዘ፤ ተበጠበጠ ማሩ ድፍድፉ። ተለየ ተጣለ ሐሠሩ ጕድፉ።
ተበቀለ ፡ ተጠየቀ ተመረመረ፤ ተሠራ ተቀጣ፤ ፍርድ ለበሰ።
ተበቍዐ ፡ ተጠቀመ ጥቅም አገኘ፤ ተረባ። ተማለደ፤ ተለመነ። ዘይትበቋዕ ቦቱ ሎቱ። ትሩፋት ዘይትበቍዑ ባቲ እለ ይትመርሑ ቦቱ ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፴፱ ፡ ፪። ፊልክ ፡ ፲፭)።
ተበቍጸ ፡ ፋመ መረተ፤ ተጫረ ታፈሠ።
ተበትከ ፡ ተበተከ፤ ተቈረጠ፤ ተበጠሰ፤ ተነቀለ ተፈነቀለ። ይትበተክ ፈትል። ኢይትበተክ ቶታነ አሣእኒሆሙ። ይትበትክ መሣግሪሆሙ። ተበትከ እብን እምደብር ፡ (መሳ፲፮ ፡ ፱። ኤር፭ ፡ ፳፯። ሉቃ፭ ፡ ፮። ዳን፪ ፡ ፴፬ ፡ ፵፭)።
ተበኵረ ፡ ተበኰረ፤ በኵር ኾነ በኵር ተባለ፤ የበኵርነት ክብር ተቀበለ። ዮሐንስ እምከርሠ መካን ዘተበኵረ ፡ (ድጓ)።
፡ ታጐለ፤ ቀረ። እምትበኰር በዓሉ ለቅዱስ ሚካኤል ፡ (ድር ፡ ሚካ)።
ተበውሐ ፡ (ይትበዋሕ) ሠለጠነ፤ ሥልጣን አገኘ ተቀበለ፤ ባለመብት ኾነ። ኢይትበውሑ ላዕለ ውሉደ ጻድቃን። አሜሃ ተበውሐ ጢጦስ በኵሉ አህጉር። እስመ ተበዋሕኩ እትናገር። ሥርዐት ቅድስት ዘተበዋሕክሙ፤ የተቀበላችኋት ፡ (ኩፋ ፡ ፲። ዮሴፍ። ዘፍ፲፰ ፡ ፴፩። ቀሌ)።
ተበዘተ ፡ ተባዘተ፤ ተፍታታ፤ ተነቀሰ።
ተበየነ ፡ ተለየ፤ ታወቀ ተረዳ፤ ታየ ተገለጠ። በከመ ተበየነ፤ ወበእንተ ተበይኖ። ውእቱኬ ይትቤየን እምግባረ ማርታ ወማርያም። ናሁ ተበየነ ለከ ጥያቄ ነገርየ። ተበየነ ንዝህላልከ ፡ (ፊልክ ፡ ፫። ፶፬። ዮሴፍ)።
ተበይጸ ፡ ተለየ፤ ተመረጠ፤ ተገለለ።
ተበድረ ፡ ተቀደመ። ተወደደ፤ ተመረጠ፤ ከበረ በለጠ። ይትበደር ቃል ሠናይ እምውሂብ። ኢይትበደር ብዕል እምነቢረ ጥዑይ። ይትበደር ሰብእ እምዕንቈ ሰንፔር ክቡር፤ እምወርቅ ወእምብሩር ይትበደሩ ጻድቃን። ጥበብ ትትበደር እምወርቅ ፡ (ሢራ፲፰ ፡ ፲፯። ፴ ፡ ፲፮። ድጓ። ፈላስ)።
፡ በቁሙ፤ ተበደረ ተለቃ። ተበድሬ ተቀድሜ እንዲሉ።
ተበጥሐ ፡ ተበጣ ተፈቃ፤ ተተፈተፈ፤ እንደ ሱዳን።
ተበጥረ ፡ ተበጠረ፤ ተንጠረጠረ፤ ተነፈሰ፤ ተነቀሰ ጥሩ ኾነ።
ተበጽለ ፡ ተላጠ ተመለጠ ፤ ተበጨቀ ተቈረጠ። ተቀሥፈ እስከ ተበጽለ አነጻ ማእሱ። ይትቤጸል ማእስየ ምስለ ሥጋየ። ሰሐብዎ ዲበ አእባን በሊኃት እስከ ይትቤጸል ሥጋሁ (ስንክ ፡ ሠኔ። ሐም፳፭። ኢዮ፲፱ ፡ ፳። መጽ ፡ ምስ)።
ተበፅዐ ፡ ተቈረጠ፤ ተገመገመ። ተለየ ተቀደሰ፤ ከበረ ተመሰገነ፤ ተመረቀ ብፁዕ ተባለ። ተበዕፀ ኢዮብ።ዝንቱ ውእቱ ዘይትዌደስ ወይትበፃዕ። እምካልኣኒሁ ዘተበፅዐ። ሰላም ለአእጋሪከ ዘተወደሳ ወተበፅዓ ፡ (አፈ ፡ ተ፳። ፈላስ። ስንክ ፡ ሐም፳፭። ጥር፭። ደራሲ)። በተበፅዐ ፈንታ አብፅዐ ይላል፤ የመላሽ ስሕተት ነው። አይቴኑ አብፅዖትክሙ ፡ (ገላ፬ ፡ ፲፭)።
ተቢዕ ዖት ፡ (ተብዐ ይተብዕ ይትባዕ፤ ጠብዐ። ዐረ ተቢዐ፤ ተለወ። ዕብ ታባዕ፤ ሻ ፈለገ) መትባት መጨከን፤ ጨካኝ ቈራጥ ወንድ መኾን፤ መድፈር፤ አለመፍራት፤ አለማመንታት። ጽናዕ ወትባዕ። ትብቡ ወጽንዑ። ከመ ኢይትባዕ ላዕሌከ ፡ (ኢያ፩ ፡ ፮። ፲ ፡ ፳፭። ሢራ፰ ፡ ፲፭)። መትባት ለብረት ላንደበት ይነገራል። አፉ የተባ ነው፤ ብረቱን አትባው፤ ውሃ ብረት ያጠናል እንዲሉ። የብረት ትባት ሥራው ካለቀለት በኋላ በእሳት ግሞ ከውሃ መግባት ነው፤ አለዚያ አይጠነክርም ይባላል።
ተባሀለ ፡ ተባባለ ተማከረ፤ ተነጋገረ፤ ተሟገተ ተከራከረ። ተባሀሉ አሐዱ ምስለ ካልኡ። ተባሀሉ በበይናቲሆሙ ከመ የሀቦ። እሉ እሙንቱ እለ ተባሀልዎ ለፈርዖን። ወእፎ እክል ባሕቲትየ ተባህሎትሙ። አመ ይትባሀሎ ለሰይጣን ፡ (ዘፍ፲፩ ፡ ፫። ኩፋ ፡ ፳፰። ዘፀ፮ ፡ ፳፯። ዘዳ፩ ፡ ፲፪። ይሁ ፡ ፱)።
ተባሐተ ፡ ተባባተ፤ ተሳለፈ ተዋጋ፤ ታገለ፤ ተጋደለ። ይትባሐቱ አጋንንት ምስለ ሰብእ ወይወድዩ፤ ውስተ ልቦሙ ኅሊና እኩየ። ዕቀበነ እግዚኦ በዛቲ ሰዓት እምእለ ይትባሐቱ አጋንንት ፡ (ቈስጠ ፡ ፭። ደራሲ)።
ተባሕተወ ፡ (ተደራራጊ) ተለያየ፤ ተነጣጠለ፤ እየብቻው ኾነ።
ተባሕአ ፡ ተቧካ፤ ተቦካካ ርስ በርሱ፤ የዱቄት የነገር።
ተባልሐ ፡ ዳነ፤ ወጣ አመለጠ። ኢይትባላሕ ዘተመንደበ። ዘይትባላሕ እምኔሃ። ሠለስቱ ደቂቅ እለ ተባልሑ እምእቶነ እሳት ፡ (ኢሳ፰ ፡ ፳፪። መክ፯ ፡ ፳፮። መዋሥ)።
ተባልዐ ፡ ተባላ፤ ተናከሰ፤ ተቃማ ፡ (ገላ፭ ፡ ፲፭። ኩፋ ፡ ፭)። አኀዙ ይትባልዑ ሥጋሆሙ በበይናቲሆሙ ፡ (ሔኖ፯ ፡ ፭)።
ተባረከ ፡ (ተደራጊና ተደራራጊ) በቁሙ፤ ተመሰገነ ተመረቀ፤ ቡራኬ ምስጋና ተቀበለ፤ በዛ በረከተ። ይትባረክ እግዚ። ሰገደ ሎቱ ወተባረከ እምኔሁ ፡ (ሩት፬ ፡ ፲፬።መዋሥ)። ተበራረከ ተመራረቀ፤ ተመሰጋገነ ፥ ርስ በርሱ። ይትባረኩ ቦቱ አሕዛበ ምድር። ተባረኩ በበይናቲሆሙ ፡ (መዝ ፡ ፸፩ ፡ ፲፰። ስንክ ፡ የካ፱)።
ተባረዘ ፡ በቁሙ፤ ተቀላቀለ። ተናፈሰ ተናጻ፤ ተቃለለ ፡ (ገድ ፡ አዳ ፡ ገ፸፮)።
ተባረየ ፡ ተለዋወጠ፤ ተፈራረቀ ተጋገዘ፤ ተራረፈ። ዘእንበለ ይኩን ተባርዮ ሌሊት ወመዓልት። ወእምዝ ተባረዩ ፀሓይ ወወርኅ ወከዋክብት። ኅቡረ በተባርዮ። ዘበጥዎ በአብትር እንዘ ይትባረዩ ፡ (መቃ ፡ ገ፲። ፳፫። ስንክ ፡ ጥቅ፬። ሐም፳)። ተገዛ፤ ባሪያ ኾነ፤ ባሪያ ተባለ፤ ተሼጠ ተለወጠ።
ተባረጸ ፡ ተብለጨለጨ፤ ብልጭልጭ ቍልጭልጭ አለ። እምቅድመ ይትባረጹ ከዋክብት ፡ (ቅዳ ፡ አፈ)።
ተባአሰ ፡ ተጣላ፤ ተጠላላ፤ ታገለ ተጋደለ፤ ተሟገተ ተከራከረ። ደቂቀ እምየ ተባአሱ በእንቲኣየ። ተባአሰ በእንተ ጽድቅ። ወተባአሱ ይትመየጡ መንገለ ምድር። ተባአሰ ያድኅኖ ፡ (ማሕ፩ ፡ ፮። ሢራ፬ ፡ ፳፰። ዮና፩ ፡ ፲፫። ዳን፮ ፡ ፲፬)። አገበረ በማለት ፈንታ ተባአሰ ይላል። ተባአሳ ወአድከማ ፡ (፪ነገ ፡ ፲፫ ፡ ፲፬)።
ተባዐደ ፡ ተለያየ ተራራቀ። ምስጢሩ ተብዕደ ተበዐደ ካለው ይገባል፤ መለያየት የጋራ ነውና። ገበርኩ ከመ አንቲ ትኩኒ እንቲኣየ ወአንቲሰ ትትባዐዲ እምኔየ፤ በከመ ተባዐዱ ሰዶም ወገሞራ። ዘአልቦ ተባዕይ ፡ (መቃ ፡ ገ፮። ስንክ ፡ ጥር፰)።
ተባዒ ፡ (ዒት ዕያን ያት፤ ዕት) የሚጨክን፤ ጨካኝ፤ ደፋር ቈራጥ። ብእሲ ተባዕ። ተባዕያን ምስሌሆሙ። ዕደው ስሙያን ወተባዕት ፡ (ኢሳ፰ ፡ ፰። ፴፬ ፡ ፯። ፩ዜና ፡ ፲፪ ፡ ፴)።
ተባዕ ፡ (ዕት ዓን ዓት) ዝኒ ከማሁ። ብእሲ መስተቃትል ወተባዕ። ጽኑዕ ወተባዕ። ሐራዊ ተባዕ። ከመ ዕደው ተባዓን ፡ (ሢራ፳፮ ፡ ፳፰። ፩ዜና ፡ ፲፩ ፡ ፳፭። ስንክ ፡ ሐም፳፪። ዮኤ፪ ፡ ፯)።
ተባዕታዊ ይ ፡ ወንድ፤ ወንዳዊ፤ ወንድማ፤ ወንዳወንድ፤ ብርቱ። ሕፃን ተባዕታዊ። ዐንበሪ ተባዕታይ። መንፈሰ ባሕር ተባዕታይ ፡ (ፈ ፡ መ ፡ ፳፯ ፡ ፭። ሔኖ፰ ፡ ፰ ፡ ፲፮)።
ተባዕት ፡ (ብ አትቡዕ) በቁሙ ተባት፤ ወንድ፤ አውራ፤ አለሌ። ተባዕተ ወእንስተ ገብሮሙ። ወለደት ተባዕተ። ዶርሆ ተባዕት። አፍራስ አትቡዕ። አባግዕ አትቡዕ። ደቂቅ አትቡዕ ፡ (ዘፍ፩ ፡ ፳፯። ኢሳ፷፮ ፡ ፯። ፪ዜና ፡ ፱ ፡ ፳፭። ፲፯ ፡ ፲፩። ፴፩ ፡ ፲፮)።
ተባከየ ፡ ተላቀሰ፤ ተለቃቀሰ፤ ተፋጀ። ሶበ ተኣምኑ ወተባከዩ በበይናቲሆሙ ወተሳዐሙ ፡ (ተረ ፡ ባሮ)።
ተባውአ ፡ ተጋባ፤ ተገባባ፤ ባልና ሚስት ኾነ።
ተባዝኀ ፡ ተባዛ ተራባ፤ ተዋለደ። ወይትባዝኃ በሙፋሪሆን ፡ (መዝ ፡ ፻፵፫ ፡ ዘፍ፩ ፡ ፳፪)። በበዝኀ ፈንታ ተባዝኀ ይላል፤ ፈጽሞ ለማለት። ከመ ትትባዛኅ በሕይወትከ። ወትትባዛኅ በረከቱ ለጻድቅ። ተባዝኁ በእግዚእነ ፡ (ሢራ፪ ፡ ፫። ፲፩ ፡ ፳፪። ፪ጴጥ ፡ ፫ ፡ ፲፰)።
ተባየተ ፡ ተዳደረ፤ ተዋገነ፤ ተጎራበተ፤ ተከታተመ።
ተባየጸ ፡ ባልንጀራ ኾነ፤ ተመሳሰለ፤ ተካከለ፤ ተዋደደ፤ ተሰማማ፤ ተሳተፈ። ውእቱ መነኮስ ዘተባየጸከ። ይትባየጾሙ ለልዑላን። ዘይትባየጾ በማእድ። በእንተ ዘኀሠሠ ተባይጾተ ፡ (ስንክ ፡ ሐም፳፰። አፈ ፡ ድ፩። ፈ ፡ መ ፡ ፪ ፡ ፲፩። ፍ ፡ ነ ፡ ፬)።
ተባደረ ፡ ተሯሯጠ፤ ተሽቀዳደመ፤ ተፈካከረ። እስመ ይትባደሩ ውስተ ርእሰ ምርፋቅ። ተባደሩ ለሠናይ። ዘንተ ስምዑ ወተባደሩ ከመ ትግበሩ። እለ ፈጸሙ ረዊጸ ወተባድሮ ፡ (ሉቃ፲፬ ፡ ፯። ፩ተሰ ፡ ፭ ፡ ፲፭። ቀሌ። ስንክ ፡ ታኅ፲፪)።
ተባደወ ፡ ተለያየ፤ ተበታተነ፤ ተዘራ ተረጨ፤ በየበረሓው ተሠራጨ። እምኀየሰነ ተባድዎ እምነ ተጋብኦ በእንግልጋ፤ እስመ ተዘርዎ ቀጥቀጠ አልባቢነ፤ ወሶበ አድኀነነ እግዚ እምተባድዎ ወአግብአነ ውስተ ምድርነ ዐመፅናሁ። ይበኪ ላዕለ ሙስናሆሙ ወተባድዎቶሙ ፡ (ዮሴፍ)።
ተባጽሐ ፡ ተዳረሰ ተጋጠመ ተገናኘ፤ አንድ ኾነ። እስከ ይትባጽሖሙ ወይዳደቆሙ መዐተ እግዚ። ተባጽሖታ ለልብ ምስለ እግዚ ፡ (ፈ ፡ መ ፡ ፲፯ ፡ ፪። ፊልክ ፡ ፻፲)።
፡ ተካሰሰ ተቈራኘ፤ ተማላ፤ ይዞ ተያይዞ ኼደ፤ ከዳኛ ወሰደ፤ አደረሰ። ተረታታ ተነጣጠረ። ወተባጽሕዎ አይሁድ ለጳውሎስ ኀበ ጋልዮስ ፡ (ግብ፲፰ ፡ ፲፪። ፲፱ ፡ ፴፯። ማር፲፫ ፡ ፱። ሉቃ፲፪ ፡ ፶፰)።
ተቤሳ [1] ፡ ተቤስ። ፡ (ዕብ አፌር። ጽር ቴላሞን) ግልባቤ ገጽ፤ ሠርመዲ ቀጸላ፤ የፊት መሸፈኛ። ወአሰረ ተቤሳ ውስተ አዕይንቲሁ ፡ (፫ነገ ፡ ፳። ፴፰ ፡ ፵፩)።
[2] ፡ (ዕብ ኤፌር። ዐረ ቲብን) ትቢያ ዐቧራ፤ ደቃቅ ዐፈር፤ ዐመድ፤ እብቅ። ሐራሲ ትጉህ ቴዎድሮስ ዘኵለንታሁ ተመልአ ቀኖተ ኀጺን ተቤሳ ፡ (ቅኔ)።
[3] ፡ ግልባቤ፤ ጸበል፤–ተብየሰ።
ተቤዝወ ተቤዘወ ፡ ተዋጀ ተገዛ፤ ቤዛ አገኘ፤ ዳነ ነጻ ወጣ። በደሙ ትትቤዘው ነፍስ። እለ ተቤዘዉ እምነ ምድረ ግብጽ፤ እለ ቀደሙ ተቤዝዎ። እስመ እምኢተቤዘውነ እመ ኢኮነ ከመ ዝ ፡ (ዘሌ፲፯ ፡ ፲፩። ራእ፲፬ ፡ ፫ ፡ ፲፬። ቄር)።
ተብህለ ፡ ተባለ ተተነባ፤ ተወራ ተነገረ፤ ተጠራ ተሰየመ። ተብህለ ለቀደምት። ዘተብህለ በዳንኤል ነቢይ። ብፅዓን እንተ ተብህለት ለብዙኃን። መጽሐፍ ዘይትበሀል ፈውስ መንፈሳዊ። ዘሀሎ ውስተ ይትበሀል ውስተ ዓለም ወልድ። እስመ ኅሊና ፅቡስ ምኑነ ይትበሀል ፡ (ማቴ፭ ፡ ፳፩። ፳፬ ፡ ፲፭። ፊልክ ፡ ፸፱። ፈ ፡ መ። ዕር ፡ ኢሳ፰ ፡ ፳፭። ጥበ፪ ፡ ፲፩)።
ተብሕአ ፡ ተቦካ ተለወሰ፤ ሊጥ ኾነ።
ተብሲል [1] ፡ ንፍሮ፤ የኽል ወጥ። ተብሲለ ብርስን ፡ (ዘፍ፳፭ ፡ ፳፱። ዳን፲፫ ፡ ፴፫)።
[2] ፡ ንፍሮ፤–በሰለ።
ተብሪዝ ፡ አተላ አንብላ፤ ዝቃጭ ተራዋጭ ሐሠር፤ ሽንት ቅዘን ዐይነ ምድር። ቀጥቀጥዎሙ ለመርገማት ወኢረከብዎሙ ተብሪዝ ወእልተግቢጥ ፡ (አዋል)። ገብጥን እይ።
ተብዕደ ተበዐደ ፡ ተለየ ተነጠለ፤ ራቀ ወገደ፤ ባዕድ ኾነ፤ ዝምድና ዐጣ። ወረደ እንዘ ኢይትፈለጥ እምህላዌሁ፤ ነገደ እንዘ ኢይትበዐድ እምሥላሴሁ። ኢተበዐደ ወኢተፈልጠ በኵሉ ግብሩ ወልድ ዋሕድ ፡ (ቅዳ ፡ አፈ። ድጓ። ኤፍ ፡ ፩)።
፡ ተሻረ፤ ተለወጠ ተቀየረ፤ ሌላ ኾነ ሌላ ተባለ። ኢይትበዐድ እምሢመቱ ውስተ ካልእ ሢመት። ኢተበዐደ እመለኮቱ ዘእግዚ ቃል። እስመ ኢይትበዐድ ዘእግዚ ቃል፤ አላ ለዝሉፉ ውእቱ ይሄሉ ፡ (ቀሌ። ድጓ። ቄር ፡ ጰላ። እስት)።
(ጥ) ተብዖ ዖት ፡ (ተብዐ ይቴብዕ ይተብዕ) ዝኒ ከማሁ፤ ሲጠብቅ የስብሐ፤ ሲላላ የገብረ።
ተብያስ ፡ ስመ ሀገር። ሌባ ሲሶይ ተብያሳዊ ፡ (ፊልክ)።
ተተርጐመ ፡ ተተረጐመ፤ ተቀዳ ተገለበጠ፤ ተመለሰ። ተፈታ፤ ምስጢሩ ታወቀ ተገለጠ። ዛቲ መጽሐፍ ተተርጐመት እምልሳነ ዐረቢ ለግእዝ በአፈ ዕንባቆም ወሚካኤል ግብጻዊ። ዘኢያብቈለ ቀርነ ወጽፍረ፤ ይተረጐም ዘአልቦ ትዕግልት።
ተተክለ ፡ ተተከለ፤ ተቀሰቀሰ : ተሠራ፤ ተሙ ሠረተ ፡ ( ቆመ 1 ተወስነ ፡ ይእቲ መላጺ ፡ ተተከለት፤ ዲበ፣ክሣዱ ወሞተ። ተመልዒ ፡ እምሥርውኪ ፡ ወተጎሊ ፡ ውስተ ፡ ባሕር ፡ ተተከለ ፡ ደብተራሁ። ቤተ ፡ ጸሎት ፡ እንተ፣ተተካለት፤ ለምስጋድ። ተተ ከሰት፤ፍትወት በጠባይዕ እንስሳዊት ተተከለ ፡ ብርሃን፣በአምሳለ ፡ 0ምዽ። በተተከለ ዕድሜ፤ ፡ (ገድ' ኪሮ። ሉቃ፲፯: ፮ " ኩፋ ፡ ፲፪ " ድጓ። ፍ ነ ፷፬ ፡ ፩ " ስንኳ ፡ የካ፬ = ተረ - ቈር) "
ተታለወ ፡ ተከታተለ፤ ተራደፈ፤ ተከታታይ ኾነ። እንዘ ይታለዉ አሐዱ ድኅረ አሐዱ። ይታለዎ ዝንቱ መርገም። መከራ ብዙኅ እንተ ተታለወት። ዘእንበለ ቀዲም ወተታልዎ ፡ (ስንክ ፡ ታኅ፳፫። ዘዳ፳፱ ፡ ፲፱። አፈ ፡ ድ፳፯። አዋል)።
ተታብዐ ፡ ተጨካከነ፤ ተጸናና፤ አይዞኽ አይዞኽ ተባባለ። ተታቢዖሙ ፡ (ዘፍ፴፬ ፡ ፳፭)።
ተቶስሐ ፡ ተቀለቀለ፤ በረዘ፤ ተጨመረ፤ ተዘነቀ፤ ተደበለቀ። ወይን ዘኢተቶስሐ ከመ ንጉሥ ዐማፂ፤ ወዘተቶስሐሰ ከመ ንጉሥ ራትዕ። ውሒዛተ ሊቃንያ በደም ይቶሳሕ። ተቶስሐ ደሞሙ በደመ መባእ። ወተቶስሐ አብድንተ ካህናት ምስለ አብድንት ነኪራን ፡ (ፈላስ። ኪዳ። ዮሴፍ)።
ተቷስሐ ተተዋስሐ ፡ ተቀላቀለ፤ ተደበላለቀ፤ ተበራረዘ፤ ተጨማመረ፤ ተዛነቀ ተዘናነቀ። ከመ ኢይትዋስሑ ፡ (ቈስጠ ፡ ፶፪)።
ተነስቀ ፡ ተሰደረ ተደረደረ፤ ተላለፈ ተጋጠመ።
ተነሥተ ፡ (ተነሠተ ፥ ተነቀለ፤ እንስቱ) ፈረሰ ፥ ፈራረሰ። ተነሥተ መቅደስ። ከመ ሀለዋ ትትነሠት። ወኢይትነሠት እንከ ፡ (ሱቱ ፡ ዕዝ፲ ፡ ፳፰። ጦቢ፲፬ ፡ ፬። ኤር፴፰ ፡ ፵)።
ተነስነሰ ፡ ተነሰነሰ፤ ተረጨ ተረበረበ፤ ሽቱው በልብስ ፥ ልብሱ በሽቱ።
ተነሥአ ፡ ተወሰደ፤ ተመረጠ። አመ ይትነሣእ እምኔሆሙ። ለዘተነሥአ እምኔሁ ብእሲ ፡ (ማቴ፱ ፡ ፲፭። ቄር ፡ ጰላ)።
ተነስከ ፡ ተነከሰ። ዘእምአርዌ ምድር ተነስከ ፡ (ስንክ ፡ መስ፰። ዘኍ፳፩ ፡ ፰)።
ተነሥገ ፡ ተዕነገ፤ ተዘጋ ተቈለፈ።
ተነቅለ ፡ ተነቀለ፤ ተመዘዘ። በእንተ ዘተነቅለ ዐፅመ ገቦሁ ፡ (ቅዳ ፡ ቄር)።
ተነቅበ ፡ ተነቀበ፤ ተወጋ ተበሳ፤ ተነደለ። ተለየ ራቀ፤ ወጣ ለቀቀ፤ ቦታውን። ሰላም ለፀአተ ነፍስኪ በመዐዛ ክርስቶስ ዘተነቅበ፤ መሰንቆ ማሕሌት ሐዋዝ ከመ ያሰርር አልባበ ፡ (ስንክ ፡ ጥር፳፩)። በተነቅበ ፈንታ ነቀበ ይላል፤ ስሕተት ነው፤ ዳግመኛም በተነቅበ ፈንታ ተቄአ ይላል፤ እንደ ተነቅበ አያጠግብም። ነቀበተኒ ነፍስየ እምኔሃ፤ በከመ ነቀበታ ነፍስየ ለእኅታ ፡ (ሕዝ፳፫ ፡ ፲፰)።
ተነቅፈ ፡ ተነቀፈ፤ ተመታ ተላጠ ተቀረፈ።
ተነበ ፡ ተነበበ ተደገመ፤ ተነገረ ፥ ተጮኸ ተዜመ። መጽሐፍ ዘተነበ ቅድመ ንጉሥ። በእንተ ጸሎት ዘይትነበብ ዲበ ማይ። ዘኢይትነበብ ኅቡእ። እምነግህ ይትነበብ ቅድሳቱ ፡ (፪ዜና ፡ ፴፬ ፡ ፳፬። ዲድ ፡ ፵። መዝ ፡ ፶። ሢራ፵፯ ፡ ፲)።
ተነበየ ፡ ተተነባ ፥ ተነገረ፤ ትንቢቱ ከነቢዩ አፍ ወጣ ተሰማ።
ተነትነ ፡ ተሰጠ፤ ተናኘ ተሰጭ ኾነ።
ተነትፈ ፤ ነተበ ፤ ተነጨ ተበጨቀ ፥ ተበጫጨቀ። አብድ ኢይሣየጥ አሣእነ እስከ ይትነተፍ እገሪሁ። ወተነትፈ ሥጋሆሙ (ፈላስ ፡ ገ፵። ስንክ ፡ ሐም፭)።
ተነክየ ፡ ተነካ ፥ ተጐዳ፤ ጐደለ ፥ ታጐለ። ኢተነክየ ወኢምንተኒ። አልቦ ዘትትነከይ አንተ በእበደ ዚኣሁ። ወኢይትነከይ መለኮቱ። ፈርሀ ከመ ኢትፀራዕ አው ከመ ኢትትነከይ ተፀምዶ ፡ (ዳን፮ ፡ ፳፫። ሢራ፳፪ ፡ ፲፫። ቄር ፡ ጰላ። ፊልክ ፡ ፲፭)።
ተነክረ ፡ ተነከረ፤ ተዘፈቀ። ተለየ፤ ተደነቀ ተመሰገነ። ተነክሩ ኃጥኣን እማሕፀን። ተነከርኩ በአዕይንተ ኀያላን። ይትነከር እምኀበ መላእክት ፡ (መዝ ፡ ፶፯። ጥበ፰ ፡ ፲፩። አርጋ ፡ ፫)። ተደነቀ ማለት ዐማርኛው አድናቂነትንም ያሳያል፤ ለግእዙ ግን አይስማማም።
ተነክነከ ፡ ተነቀ(ቃ) ነቀ፤ ተወዘ(ዛ) ወዘ ተናጠ ተናወጠ። ዐምደ ሃይማኖት ዘኢይትነከነክ እምኀይለ ነፋሳት ፡ (መጽ ፡ ምስ። አርጋ ፡ ፩)።
ተነውረ ፡ ተነወረ ፥ ነውረኛ ኾነ፤ ተነቀፈ ተሰደበ። ይትነወሩ እምከመ ነትዑ። የኀስሩ ወይትነወሩ ፡ (ፊልክ ፡ ፬። ፴፩)።
ተነዝሀ ፡ ተነዛ ተረጨ፤ ተበተነ ተፈነጠቀ። ተነዝሀ ደማ ኀበ አረፍት። ተነዝሀ ደሞሙ ውስተ አልባስየ። ደም እንተ ባቲ ተነዝሃ ነፍሳቲነ ፡ (፬ነገ ፡ ፱ ፡ ፴፫። ኢሳ፷፫ ፡ ፫። አፈ ፡ ድ፳፯)። በተነዝሀ ፈንታ አንዝሀ ይላል፤ ስሕተት ነው። ኢያንዝሀ ላዕሌሁ ማየ ምንዛህ ፡ (ዘኍ፲፱ ፡ ፲፫)።
ተነዝረ ፡ ተነከስ፤ ተነደፈ። እንዘ ይትነተፍ ወይትኔዘር ፡ (ኪዳ)።
ተነዝነዘ ፡ በቁሙ ፥ ተነዘነዘ ተሣቀየ። በእኩይ እንዘ ይትነዘነዝ ፡ (ኪዳ)።
ተነዝፈ ፡ ተጣፋ ፥ ተወነዘፈ፤ ነዚፋው ልብሱ። ተነጽፈ ተገድፈ፤ በማለት ፈንታ ተነዝፈ ይላል፤ የጣፊ ስሕተት ነው። ተነግፈ ወተነዝፈ ፡ (ናሖ፪ ፡ ፲)። ዕብራይስጡ ግን ቡቃህ ይላል፤ ባዶ ባደማ ማለት ነው።
ተነድለ ፡ ተነደለ ፥ ተበሳ ተሸነቈረ፤ ነዳላ ኾነ።
ተነድቀ ፡ ተነደቀ ፥ ተገነባ፤ ታነጠ ተሠራ። ኬብሮን ተነድቀት። ሶበ ተነድቃ እልኩ አእባን። ደብር ዘላዕሌሁ ተነድቀት ሀገሮሙ ፡ (ዘኍ፲፫ ፡ ፳፪። ሄርማ ፡ ገ፸፰። ሉቃ፬ ፡ ፳፱)።
ተነድአ ፡ ተነዳ፤ ተነድቶ ኼደ። ኵሉ ዘይትዳእ በበትር። ወበኀይለ ነፋስ ይትነድኣ። ቦ እለ በፍትወተ ዝሙት ይትነድኡ ፡ (ዘሌ፳፮ ፡ ፴፪። ያዕ፫ ፡ ፬። ተረ ፡ ቄር፲፱)።
ተነድፈ ፡ ተነደፈ፤ ተወረወረ ፥ ተወጋ። ይጔጕእ ዘተነድፈ ይምላኅ ሐጸ። ሀየል ዘተነድፈ ወተሀይጰ ከብዶ። ተነዲፎሙ በፍቅራ። አውፅአኒ እምውስተ ቀትል እስመ ተነደፍኩ ፡ (ሢራ ፡ ፲፱ ፡ ፲፪። ምሳ፯ ፡ ፳፫። ዮሴፍ። ፫ነገ ፡ ፳፪ ፡ ፴፬። ማሕ፪ ፡ ፭)።
ተነግረ ፡ ተነገረ ፥ ተወራ ተባለ ፥ ተተነባ። በቀኖና ዘተነግረ ቀዳሚ። በከመ ተነግረ። ዝንቱ ባህል ቀደመ ተነግሮ ፡ (ቀሌ። ኪዳ። አፈ ፡ ድ፭)።
ተነግደ ፡ ተነገደ፤ ንግዱ ተደረገ ፡ (መንገዱ ተኼደ ፥ ታለፈ ተረገጠ)። በመጽአ ፈንታ ተነግደ ይላል፤ ስሕተት ነው። ሥራዌ ረሲዓን ይትነገድ እምርሑቅ ፡ (ምሳ፳፩ ፡ ፯)።
ተነግፈ ፡ ተነገፈ፤ ተንገፈገፈ። ረገፈ፤ ደረቀ ወደቀ። ቈጽል ዘይትነገፍ እምነፋስ። ዘቀዳሚ ይትነገፍ ወዘደኃሪ ይሠርጽ። ዕፀው ዘኢይትነገፉ ፡ (ኢዮ፲፫ ፡ ፳፭። ሢራ፲፬ ፡ ፲፰። ሔኖ ፡ ፫)።
ተነጥፈ ፡ ጠራ ነጠረ፤ ተኰላ ጥሩ ኾነ። ኢዮብ ተፈተነ ወተነጥፈ ከመ ወርቅ ፡ (አርጋ ፡ ፫)።
ተነጸረ ፡ ታየ ተገለጠ፤ ጐላ ተረዳ ፥ ግልጥ ኾነ።
ተነፅኀ ፡ ተጣለ ተወረወረ፤ ወደቀ ተዋረደ። ተነፅኀት ለሊሃ እመካን ልዑል ዲበ ምድር ከመ ትሙት ወኢሞተት። ረከቦ ለአቡሁ ተነፂኆ ፡ (ዮሴፍ)። ዲበ ምድር ትትነፃኅ። ወመብዝኅቶሙ ተነፅኀ በገዳም። እሜሃ ተነፅኀ አበ ሕፃን ወሰገደ ታሕተ እግረ አባ ዘይኑን ፡ (ኪዳ። ፩ቆሮ ፡ ፲ ፡ ፭። ስንክ ፡ የካ፫)።
ተነጽለ ፡ ተነጠለ፤ ተለየ ወለቀ። እንዘ ይገሽም ሠርዌ ተነጽለ ማሕጼሁ ወወድቀ ውስተ ማይ ፡ (፬ነገ ፡ ፮ ፡ ፭)።
ተነጽየ ፡ ተነጨ፤ ተነቀለ። ዲዮስቆሮስ ቀናኢ በእንተ ሃይማኖት ዘትመልኀ ጥረሲሁ ወተነጽየ መብዝኅተ ጽሕሙ ፡ (ስንክ ፡ መስ፯)።
ተነጽፈ ፡ ተነጠፈ ፥ ተዘረጋ፤ ተበጀ ተዘጋጀ። ውስተ ጽልመት ተነጽፈ ምስካብ። ኀበ ተነጽፈ ዕረፍት። ተነጽፈ ምስሓግ በታሕቴከ ፡ (ኢዮ፲፯ ፡ ፲፫። ቀሌ። ኢሳ፲፬ ፡ ፲፩)። ተጸንተቀ በማለት ፈንታ ተነጽፈ ይላል ፡ (ዮዲ፱ ፡ ፫)።
ተነፍኀ ፡ ተነፋ፤ ዐበጠ ታበየ፤ ተቈጣ አኰረፈ። ዘተነፍኀ ከርሡ። እንዘ ትትነፋኅ ላዕሌነ። ተነፍኆ ልብ ፡ (መ ፡ ፈ። ተረ ፡ ቄር፰። ዮሴፍ)።
፡ ተነፋ፤ ተመታ ጮኸ። ኢየአምን እስከ ይትነፋኅ ቀርን። ወይትነፋኅ ቀርን ሠለስተ ጊዜ በአፈ ሚካኤል ፡ (ኢዮ፴፱ ፡ ፳፬። ቀሌ)።
፡ ተነፈሰ ፥ እፍ እፍ ተባለ ፥ ነፋስና ትንፋሽ ተቀበለ። ተተንፈሰ ፥ ትንፋሹ፤ ተተነፈሰበት ፥ ተቀባዩ። ተነፍኀ ላዕሌሁ መንፈሰ እግዚ ፡ (መቃ ፡ ገ፳)።
ተነፍረ ፡ ተነፈረ፤ ተቀቀለ። ቸነፈር የዚህ ዘር ነው።
ተነፍቀ ፡ ተነፈቀ፤ ተለየ ተከፈለ። ይትነፈቅ እስራኤል ለክልኤ። ተነፍቀት ሥዕርታ ፡ (፩ነገ ፡ ፲፭ ፡ ፳፱። ዮዲ፲ ፡ ፫)። በተነፍቀ ፈንታ ተናፈቀ ይላል፤ አያሰኝም። ቦኑ ተናፈቀ ክርስቶስ። ተናፈቀ ልቦሙ። ኢይትናፈቁ እንከ ለክልኤ። ተናፈቀ ምኵናነኒከ ፡ (፩ቆሮ ፡ ፩ ፡ ፲፫። ሆሴ፲ ፡ ፪። ሕዝ፴፯ ፡ ፳፪። ሢራ፵፯ ፡ ፳፩)።
ተነፍገ ተንፈገ ፡ (ፈጊግ ፈገ ፈገገ) ተነፈገ፤ ገማ ከረፋ ትንፋጋም ኾነ።
ተኒን ኖት ፡ (ተነ ይተንን ይትንን። ዕብ ወሱር ትናን) መትነን፤ መብነን፤ መጤስ መትጐልጐል፤ ብን ትን ማለት። መስፋት መዘርጋት፤ ሰፊ ወርዳም ቁመታም መኾን።
ተናኀለ ፡ ተፋረሰ ፥ ተፈራረሰ፤ የዋጋ የውል።
ተናሰከ ፤ ተናከሰ ተነካከሰ ተባላ። አኀዙ ይትናሰኵ በበይናቲሆሙ። ትትባልዑ ወትትናሰኵ (ሔኖ፹፱ ፡ ፲፩። ገላ፭ ፡ ፲፭)።
ተናሥአ ፡ ተናሣ ተነሣሣ፤ ተቃወመ ተቋቋመ። ጽኑዕ ውእቱ ዘኢይትናሥእዎ ነገሥት ፡ (ቅዳ ፡ ኤጲ)። በተንሥአ ፈንታ ተናሥአ ይላል፤ የተደራጊ ተደራራጊ ነው፤ ተፋለስ እንደ ማለት።
ተናበረ ፡ ተነባበረ ፥ ተቀማመጠ፤ ንብብር ኾነ። አነባበሮ እንዲሉ።
ተናበበ ፡ በቁሙ፤ ተነጋገረ። መላእክት ተናበቡ ምስለ አይሁድ። ኢይትናበቡ በበይናቲሆሙ በነገረ ሥላቅ ወኀፍረት ፡ (አፈ ፡ ድ፩። ፍ ፡ ነ ፡ ፲)።
ተናአሰ ፡ ተናነስ፤ እንስንስ አለ። የንእሰ ድርብ።
ተናከረ ፡ ተለየ ተለያየ፤ ተላቀቀ ተፈራቀቀ፤ እየብቻው ኾነ፤ ተካዳ ተካካደ። ተናከራ ለዛቲ ዓለም። ተናከርዎ ለዝንቱ ቤት። ተናክሮ እትናከሮሙ ፡ (ስንክ ፡ ጥር፲፩። ኤር፲፱ ፡ ፬። ሆሴ፩ ፡ ፮)። ተዳነቀ ፥ ተደናነቀ፤ ርስ በርሱ።
ተናውኀ ፡ ተራረፈ፤ ተራዘመ ተባዛ ፥ ተጋነነ። ወበጊዜ ተናውኆታ የሀድእ ልብ። ገሥጾ ለዐርክከ እንበለ ይትናዋኅ መዐት ፡ (ማር ፡ ይሥ፲፮ ፡ ፫። ሢራ፲፱ ፡ ፲፯)።
ተናዘዘ ፡ በቁሙ፤ ንስሓ ገባ። ተጸናና ተረጋጋ፤ ሐዘኑን ተወ ተደሰተ። ሶበ ይላሕዉ ይትናዘዙ ብየ። ወይትናዘዛ ክልኤሆን እምቃለ መጻሕፍት። አላ ይትናዘዙ ምስሌሁ ፡ (ኢዮ፳፱ ፡ ፳፭። ነገረ ፡ ማር። ስንክ ፡ ጳጕ፩)።
ተናደደ ፡ በቁሙ፤ ተያያዘ ተቀጣጠለ ፥ ተሟሟቀ። ትትናደድ ሐሩረ አፍቅሮ ውስተ ነፍሱ። ወትቈርር ተናድዶቶሙ ፡ (ፊልክ ፡ ፻፮። ፭)።
ተናደፈ ፡ ተወራወረ ፥ ተዋጋ፤ ተቋሰለ። ተመዪጠከ መንጸረ ትትናደፈነ ለእለ ሞእነ ወበአሕጻ ቅንአትከ ትፈቱ ታቍስለነ ፡ (ተረ ፡ ቄር፰)።
ተናድአ ፡ ተናዳ ፥ ተነዳዳ፤ ተያይዞ ኼደ ነጐደ።
ተናገሠ ፡ በቁሙ፤ ተነጋገሠ ፥ ርስ በርሱ ወይም በዘመን። ንግሥተ አዜብ ትትናገሦ ለዳዊት አሐደ ዓመተ ፡ (ታሪ ፡ ነገ)። ክብረ ነገሥቱ ግን ፳፱ ይላል፤ ስሕተት ነው።
ተናገረ ፡ (ተደራራጊ) ተነጋገረ ፥ ተባባለ፤ ተጨዋወተ ተወያየ። ኢይኩን ተናግሮ እንዘ ይበልዑ። ኢትትናገር ምስለ ብእሲት በዘታቀንኣ። ተናገረ ምስሌሆሙ ምስጢረ ምክሩ። ኢተናገሩ በበይናቲሆሙ ዘውስተ ልቦሙ ፡ (ሥር ፡ ጳኵ። ሢራ፴፯ ፡ ፲፩። ዮዲ፪ ፡ ፪። ዳን፩ ፡ ፲)።
ተናገደ ፡ በቁሙ ፥ ተነጋገደ፤ ተመላለሰ አገር ላገር ዞረ፤ እንግዳ ኾነ በንግድ በስደት። ሥርዐተ ተናግዶ ወረባሕ። ሠየጥ እለ ይትናገዱ ወያመጽኡ ሎቱ። ምጽዋት ተናግዶ አምላካዊት። ተናግድዶቱ ለአብርሃም። እለ ይትናገዱ አኀው ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ መቅ። ፪ዜና ፡ ፱ ፡ ፲፬። ፍ ፡ ነ ፡ ፲፮። ቅዳ ፡ ሕር። ቀኖ ፡ ፴፱)።
ተናገፈ ፡ ተራገፈ ፥ ተረጋገፈ፤ ተለያየ። ተናገፋ ለመዋቲት ሕይወት። ሕይወተ ዓለም በተናግፎ ፡ (ሱቱ ፡ ዕዝ፻፬ ፡ ፲። ስንክ ፡ ታኅ፩)።
ተናጸረ ፡ ተያየ ተነጻጸረ፤ ተመሳሰለ። ወእምዝ ተናጸሩ ንጉሥ ወመገብቱ በበይናቲሆሙ። ወተናጸሩ ገጸ በገጽ። አንቀጸ ዐጸድ ውሳጢ ይትናጸር ምስለ አንቀጽ ሰሜናዊ። ሲናሰ ደብር ይእቲ በብሔረ ዐረብ ወትትናጸር ምስለ ኢየሩሳሌም። ቃሎሙ ጽዱቅ ዘኢይትናጸሮ ሕሳዌ ወጽልሔት ፡ (ዕዝ፬ ፡ ፴፫። ቅዳ ፡ ሕር። ሕዝ፵ ፡ ፳፫። ገላ፬ ፡ ፳፭። አዋል)።
ተናጸየ ፡ ተናጨ፤ ተነጫጨ። ተነጫነጨ፤ ናጫ ነጭናጫ ኾነ፤ ጠባዩ።
ተናጽሐ ፡ ተናጻ ተጣጠበ፤ ርስ በርሱ ወይም በገዛ እጁ። ተናጻሕ እምኀጣይኢከ ፡ (ሄርማ ፡ ገ፰)።
ተናፈረ ፡ ተነፋፈረ፤ ተዛዛተ።
ተናፈቀ [1] ፡ ተለያየ ፥ ተከፋፈለ። ወፅኡ ተናፊቆሙ ውስተ መርብዕተ ማኅፈድ። መንግሥት እንተ ትትናፈቅ በበይናቲሃ ፡ (ኩፋ ፡ ፴፰። ማቴ፲፪ ፡ ፳፭)።
[2] ፡ በቁሙ፤ ተሻ ተፈለገ። ተጠረጠረ፤ ተጠራጠረ ፡ (ተነፋፈቀ)።
ተን ፡ በቁሙ፤ ተንታ፤ ጢስ ብናኝ። ዲበ አርእስተ አድባር ለተነ ጊሜ ዘያጠይሶ። ተነ ጢስ ለእሳት ይቀድሞ ተነ ጢሱ። ዘእንበለ ይደመር ለብርሃነ እሳት ተን ፡ (መጽ ፡ ምስ። ዮኤ፫ ፡ ፫። ሢራ፳፪ ፡ ፳፬። ፊልክ ፡ ፪፻፴፮)።
ተንህበ ፡ ተናበ፤ ተሠራ ተቀጠቀጠ፤ ፈሰሰ ቀለጠ።
ተንሥአ ፡ ተነሣ ፥ ነቃ፤ ቦታ ለቀቀ፤ አፍ አፈፍ በማድረግ አለ ፥ ቆመ፤ በእግር በነገር። ተንሥአ ከመ ዘንቃህ እምንዋም። ኢይክል ተንሥኦ ቅድሜከ። እለ ይትነሥኡ ላዕሌየ። እመሰ ይክሕዱ ምስጢረ ትሥጉት ይትነሥእዎሙ ሐዋርያት ፡ (መዝ ፡ ፸፯። ዘፍ፴፩ ፡ ፴፭። ኢዮ፳፯ ፡ ፯። ቄር ፡ ጰላ)። ነቅሀንና ቆመን እይ፤ የዚህ ጎሮች ናቸው።
ተንበል ባል ፡ (ብ ተናብል፤ ልት) ዝኒ ዓዲ ከማሁ፤ አማላጅ፤ አስታራቂ። አኮ በተንባል ወአኮ በመልአክ። ይምጽኡ ተናብልት እምግብጽ። ፈነዉ ተናብልተ ድኅሬሁ ፡ (ኢሳ፷፫ ፡ ፱። መዝ ፡ ፷፯። ሉቃ፲፱ ፡ ፲፬)።
ተንባሊ ፡ (ሊት ልያን ያት፤ በልት) የሚለምን የሚጸልይ፤ ማላጅ አማላጅ፤ አቈላማጭ። ምጽዋት ተንባሊት ይእቲ። ማርያም ተንባሊተ ኵሎሙ ሕዝብ ፡ (አፈ ፡ ተ፴፪። ስንክ ፡ ሚያ፮)።
ተንባላታዊ ይ ፡ እስላም፤ የከሊፋ ወገን፤ ሙሐመዳዊ። ውእቱ ተንባላታዊ። ብእሲት ተንባላታዊት አው አረማዊት። ዘይከውን ተንባላታየ ፡ (ስንክ ፡ ኅዳ፬። መጋ፳፯። ሲኖዶ)።
ተንባል ፡ (ብ ተንባላት) ከመ ነገድ እስላማዊ፤ ከሊፋ የሙሐመድ ተከታይ፤ ተፊናዊ ፍንው ማለት ነው። ተንባለ አምላክ ሲል፤ ረሱል አላህ እንዲል ፡ (ዐረብ)። እምቅድመ ይንገሡ ተንባላት በግብጽ። እምሥጋዌ እስከ ተንባላት ስድስቱ ምእት ዐሠርቱ ወአርባዕቱ ዓመት። እምሰማዕታት እስከ ተንባላት ሠለስቱ ምእት ሠላሳ ወሰመንቱ። ሐላበ ተንባላት። ምስለ ተንባላት ወአይሁድ። ለእመ ዘመወ ማእምን አው ማእምንት በተንባላት። ነቢየ ተንባላት ፡ (ስንክ ፡ ጥር፰። መር ፡ ዕዉ። አቡሻ ፡ ፬። ቄድር። ገድ ፡ ተክ)።
ተንብሎ ሎት ፡ (ተንበለ ይተነብል ይተንብል፤ ነበ፤ ነበየ፤ ብህለ) መለመን፤ መጸለይ፤ መማለድ፤ ማማለድ፤ ማላጅ አማላጅ መኾን፤ ዕርቅ ፍቅር ይቅርታ መፈለግ፤ ማረኝ ማርልኝ ማለት። ወንሕነሰ ንተነብል በአምሳለ ክርስቶስ። ዘበእንቲኣሁ እተነብል ሙቁሕየ። ወይተነብል ሎሙ። ሰአሎ ለጊዮርጊስ ከመ ይተንብል በእንቲኣሁ ኀበ እግዚ። ማርያም ትተነብል ለደቂቀ ዕጓለ መሕያው ኀበ ወልዳ። ተንብሊ በእንቲኣነ ፡ (፪ቆሮ ፡ ፭ ፡ ፳። ኤፌ፮ ፡ ፳። ዕብ፯ ፡ ፳፭። ስንክ
፡ ኅዳ፯። ሚያ፳፩። ድጓ)።
ተንተነ [1] ፡ ተፍገመገመ፤–ተኒን ተነ።
[2] ፡ ተነተነ ከፋፈለ፤ ለመስጠት ለማደል። ነተነንና አስተንተነን እይ፤ የዚህ ጎር ነው። ተፍገመገመ፤ ተንገደገደ፤ ተወዘወዘ፤ ተጨነቀ። ተንተንኩ ለወዲቅ። ትተነትን ከመ ስኩር ወትጸንን። ባዕል ለእመ ተንተነ ይሰውቅዎ አዕርክቲሁ። እምቀትለ ወለተ ሕዝብየ ተንተንኩ። አሐዝን ለሞትከ ወእተነትን ለድክትምናየ ፡ (መዝ ፡ ፻፲፯። ኢሳ፳፬ ፡ ፳። ሢራ፲፫ ፡ ፳፩። ኤር፰ ፡ ፷፩። ዮሴፍ)።
ተንተገ ፡ ተተገ፤ ተኰሰ ለኰሰ ፥ ቈሰቈሰ ተረኰሰ፤ በክፋይ መታ። ተቈጣ ቱግ ትንትግ አለ ፥ ተቃጠለ፤ እሳቱ ወይም ስዉ።
ተንእደ ፡ ከበረ ተመሰገነ፤ ተደነቀ። ኢይኩን አሐዱሂ ቀሲሰ ዘኢተንእደ በስምዐ ኀምስቱ ዕደው። ዘተንእዱ በበ አስማቲሆሙ። ሥዕርተ ርእስኪ ዘተንእደ ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፮። ስንክ ፡ ኅዳ፳፪። ደራሲ)።
ተንዕወ ፡ ታደነ፤ ተያዘ ፥ ከወጥመድ ገባ። መዋኢ ተሞአ ወነዓዊ ተንዕወ። ይትነዐዉ እመንገለ ሐዘን ፡ (መጽ ፡ ምስ። ማር ፡ ይሥ፪ ፡ ፲፩)። ተጠራ ና ወዴህ ተባለ፤ ተሳበ ቀረበ፤ ተጠርቶ መጣ።
ተንከራ ር ፡ (ዐረ ተንከር። ዕብ ፒፕዳ። ጽር ቶፓዚዮን) ጥሩ ጠንካራ ዕንቍ፤ ዐይነቱ ሐመልሚል፤ ቅጠልያ አረንጓዴ፤ ወይም ብጫቴ፤ የወራ የበሰለ ቅጠል የሚመስል። ወኢይትዔረያ ተንከራ ዘኢትዮጵያ ፡ (ኢዮ፳፰ ፡ ፲፱)።
፡ ሙሻዘር ፤ የማዕደናት መጣብቅ። ጠነከረ
ቸነከረ ችንካር ማለት ከዚህ ወጥቷል።
ተንከተም [1] ፡ ታንኳ፤ ድልድይ፤–ከተመ።
[2] ፡ (ታንኳ) መሸጋገሪያ ድልድይ፤ በታላቅ ወንዝ ላይ የሚጋደም ፥ ጫፍና ጫፉ ከማዶ እስከ ማዶ የሚገጥም፤ ዕንጨትና ብረት ግንብ፤ ን ስሯጽ ነው። ወገብረ ተንከተመ ዲበ ባሕር። ተበትከት ተንከተም ዘውስተ ባሕር። ማርያም ተንከተመ ኵሉ ስእለታት ፡ (ስንክ ፡ መጋ፳፰። ነሐ፲፪። ግንዘ)።
ተኖለወ ፡ ተጠበቀ፤ ተነዳ ፥ ተሰማራ።
ተዐ(ሥ)ሠረ ፡ ተጠራ፤ ታደመ፤ ተቀጠረ። እለ ተዐሥሩ ለመርዓ። እለ ተዐሠሩ ውስተ ከብካብ ፡ (ስንክ ፡ ጥቅ፲፬። ማቴ፳፪ ፡ ፫)።
ተዐ(ስ)ሰበ ፡ ተለራየ፤ ክራይ ኾነ፤ ለክራይ ተሰጠ።
ተአኃ [1] ፡ ወንድምነት፤ ወዳጅነት፤ ፍቅር ዝምድና፤ ወንድሜ ወንድሜ ማለት። ሰዐረ ተአኃሁ። ተአኃሆሙ ለአዕርክት። ያረትዕ ተአኃሁ ፡ (ሢራ፳፪ ፡ ፳። ፳፭ ፡ ፩። ፳፯ ፡ ፲፰። ፮ ፡ ፲፯)።
[2] ፡ ወንድም ፥ የወንድም ወገን፤ ዘር ልጅ፤ ዘመድ ወዳጅ። ቦኑ ብከ ተአኃ በዝየ። ታበዝኅ ተአኃሁ። ለምስኪኖሙ ወለተአኃሆሙ ፡ (ዘፍ፲፱ ፡ ፲፪። ሢራ፮ ፡ ፭። አስቴ፱ ፡ ፳፪)።
[3] ፡ ወንድምነት፤–አኀወ።
ተዐለለ ፡ (ተዐለ) ታለለ፤ ቀለየ፤ ተጐለተ። እጼሊ ከመ አነ እትዐለል እምክርስቶስ ፡ (ሮሜ፱ ፡ ፫)።
ተዐለመ ፡ ተመለከተ፤ ባለምልክት ኾነ። ተጣፈ ተነገረ፤ ትምርቱ። ተማረ፤ ትምርት ገባው፤ መዐልም ኾነ፤ ሰውዮው።
ተአለደ ፡ ተለቀመ ተሰበሰበ፤ ተከማቸ፤ ተወሰነ አንድ ቦታ ያዘ። ውስተ አሐተኔ ኀበ ተአለዱ። እንዘ ትትኤለዱ። ይትአለዱ፤ ወይትጋብኡ ኵሎሙ እስራኤል። ወአንትሙሰ ናሁ ተአለደ ውስቴትክሙ ኵሉ ነውር። ኢይትአመር እምኀበ ይወፅእ መለኮትከ ወኀበ ይትኤለድ ህላዌከ ፡ (ስንክ ፡ ግን፲፰። ሚያ፩። ፪ነገ ፡ ፲፯ ፡ ፲፩። ዮሴፍ። ቅዳ ፡ አት)።
ተዐልመ ፡ (ዕብ ሄዓሌም) ዕልም አለ፤ ታባ ተሰወረ፤ ከመታየትና ከመታወቅ።
ተዐልወ ፡ ተከዳ፤ ተካደ፤ ተጣለ። አመ ይትዐለዉ ሰብእ ኀያላን ፡ (መክ፲፪ ፡ ፫)።
፡ ተለወጠ
፤ ሌላ ኾነ። እምነግህ እስከ ሠርክ ትትዐለው መንበርት (ሢራ፲፰ ፡ ፳፮)።
፡ ተቀበለ ፤ የሀብት የትምርት። ወተዐልዉ ነቢያት እምኔሁ። ትምህርት ዘመሀርኵክሙ ፤ ዘከመ ተዐሎክሙ (ሢራ፵፰ ፡ ፰። ፩ቆሮ ፡ ፲፭ ፡ ፩)።
፡ ተቀዳ ፤ ተመለሰ ፤ ተተረጐመ። እምነ ዐረቢ ለግእዝ መጻሕፍት ተዐልዋ። ወመክብበ መጻሕፍትሰ ዘብሉይ ተዐልዋ እምዕብራይስጢ ኀበ ግእዝ (ስንክ ፡ ነሐ፳። መጽ ፡ ምስ)። የግእዝ ብሉያት በዘመነ ብሉይ ከዕብራይስጥ ተቀድተዋል ማለት ፤ ሳይከካና ሳይቦካ ፤ ሳይጋገር ምጣድ ሳይነካ ፤ እምኀበ አልቦ የተገኘ የሕልም እንጀራ ነው ፤ ትምርት ቀስቅሶት ከንዋመ ሀኬት ለነቃው ለዛሬ ዘመን ልጅ አያጠግብም።
ተአልፈ ፡ ተቈጠረ፤ በዛ፤ እልፍ ኾነ፤ እልፍ ተባለ።
ተአመረ ፡ ተመለከተ፤ ታየ፤ ታለመ፤ ምልክት ዐላማ ኾነ፤ ተነፋ ፥ መለከቱ። አንብሮ ኀበ ይትኤመሩ። ተአመሩ በቃለ ቀርን። እትኤመሮሙ ፡ (ዘኍ፳፩ ፡ ፰። ኤር፬ ፡ ፭። ዘካ፲ ፡ ፰)። በአመረ ፈንታ ተአመረ ይላል፤ ጠነቈለ ሲል። ዘይትኤመር በአጻብዕ አው በአሕጻ። ተአማርያን ፡ (ቄድር። ፍ ፡ ነ ፡ ፵፭)።
ተአመተ ፡ ታመተ፤ ተገመተ፤ ተከነዳ።
ተዐመፀ ፡ ተገፋ፤ ተበደለ፤ ግፍ ተቀበለ። ይትዔመፅ ከመ ሐሳዊ ፡ (ተረ ፡ ቄር)።
ተአማኒ ፡ የሚታመን ታማኝ፤ የማይጠረጠር። ኢይትከሀሎ ለሰብእ ይኩን ተአማኔ እመ ኢይግሐሠ ርእሶ እምግዕዘ ልማድ። ተአማንያን ፡ (አፈ ፡ ድ፳፪። ፍ ፡ ነ ፡ ፳)።
ተአምኀ ፡ እጅ ተነሣ፤ እጅ እግሩ ተሳመ፤ እጅ መንሻ ተሰጠው፤ ተቀበለ።
ተአምረ ፡ ታወቀ፤ የታወቀ የተረዳ ኾነ። አራዊት እለ ይትአመሩ። ውስተ ልበ አብድ ኢትትአመር ጽድቅ። ልበ ጠቢብ ይትአመር እምአፉሁ። ኀይላት ዘኢተአምሩ ፡ (ጥበ፲፩ ፡ ፲፱። ምሳ፲፬ ፡ ፴፫። ፲፮ ፡ ፳፫። ኤር፵ ፡ ፫)።
ተአምነ ፡ ታመነ፤ ታመነበት፤ የታመነ ኾነ፤ ለሌሎች። ተዘለነ ተዘለለ፤ ሐሳቡን ጣለ፤ ምን አለብኝ አለ። ተወከለን እይ፤ የዚህ ጎር ነው። ሰበክዎ ውስተ አሕዛብ ወተአምነ ውስተ ዓለም። ወንጌል ዘአነ ተአመንኩ ቦቱ። በእንተ ተአምኖ ኤጲስቆጶስ ላዕለ ንዋየ ቤተ ክርስቲያን። ሰላም ለመቃርዮስ በእስክንድርያ ዘተአምነ መርዔተ ክርስቶስ ይዕቀብ። ይነብር ተአሚኖ። ፡ (፩ጢሞ ፡ ፲፫ ፡ ፲፮። ፩ ፡ ፲፩። ቀኖና ፡ ፴፩። ስንክ ፡ መስ፬። ሢራ፬ ፡ ፲፭)።
ተዐሠረ ፡ ዐሥር ኾነ፤ ዐሥር ተባለ፤ ካሥር ተከፈለ፤ ዐሥራት ወጣለት፤ ታሸረ።
ተዐሰቀ ፡ ታሰቀ፤ ተሠራ፤ ተጠለፈ፤ ተዥጐረጐረ።
ተአስረ ፡ ታሰረ፤ ተቈራኘ፤ አንድ ኾነ። ከመ ከልብ ዘየሐውር ለተአስሮ። ተአስረ ለሊሁ እደዊሁ ወእገሪሁ። ተአስረት ነፍስ በሥጋ። ነፍሰ ዮናታን ተአስረት በነፍሰ ዳዊት ፡ (ምሳ፯ ፡ ፳፪። ግብ፳፩ ፡ ፲፩። ዮሴፍ። ፩ነገ ፡ ፲፰ ፡ ፩)።
ተዐስየ ተዐሰየ ፡ ተሰጠው፤ ተቀበለ፤ ዋጋውን አገኘ። ዋጋው ገንዘቡ ተሰጠ፤ ከሰጭ ወደ ተቀባይ ዐለፈ። ትትዐሰይ አመ የሕይዉ ጻድቃን። ይትዐሰይ ብዙኀ። ተዐስየ ምሕረተ በዝንቱ። ተዐስየ ዕሴተ ሠዋዒ ፡ (ሉቃ፲፬ ፡ ፲፬። መዝ ፡ ፲፰። ቄር። አፈ ፡ ተ፴፬)።
ተአረ ፡ ተማረረ፤ ታጨደ፤ ተሰበሰበ፤ ተለቀመ ተቈረጠ ፡ (ድጓ)።
ተዐረዘ ፡ ለበሰ፤ ልብስ አገኘ፤ ተቀበለ። ልብሰ ዚኣነ ንትዔረዝ። ሀበኒ ዘእበይት ወእትዔረዝ። ተዐሪዞ ሃይማኖተ ክርስቶስ ፡ (ኢሳ፬ ፡ ፩። ቀሌ። አርጋ ፡ ፩። ስንክ ፡ ሠኔ፲፩)።
ተዐረየ ፡ (ዐረየ፤ ተገብሮ) ተካከለ፤ ተመሳሰለ። በይእቲ ዕለት ይትዔረይ መዓልት ምስለ ሌሊት። አልቦ ዘይትዔረዮ ለቅንአት። ወኢይትዔረዮ ዕፀ ቄጵርስስ ፡ (ሔኖ፸፪ ፡ ፳። ምሳ፳፯ ፡ ፬። ሕዝ፴፩ ፡ ፰)። ኹለተኛም፤ ታከለ፤ ተመሰለ፤ ሌላው እኩያው አከለው መሰለው ያሰኛል፤ መተካከል የጋራ ነውና።
ተዐርቀ ፡ ታረቀ፤ ጐበጠ፤ ቀና ረታ፤ ዕንጨቱ።
ተአርወየ ፡ (አርወየ) አውሬ ኾነ። ገሠጾ በተአርውዮ ወአንበሮ በተአንስሶ። ይትአረወዩ ከመ አናብስት። ኖላዊ ዘይትአረወይ። እመኒ ተአርወየ ላዕሌከ ከመ ነምር አክሞስስ አንተ። ለነሳሒ ኢይደልዎ ይትመዐዕ ወኢይትአርወይ። ቀነየ ኵሎ አሕዛበ እለ ኮኑ ይትአረወይዎሙ ለአይሁድ ፡ (መጽ ፡ ምስ። ኤር፳፰ ፡ ፴፰። ሄርማ። አፈ ፡ ተ፳፪ ፡ ፴፩። ዮሴፍ)።
ተዐርዘ ፡ ታረዘ፤ ዕርዝተኛ ኾነ፤ ተራቈተ፤ ልብስ ምግብ ዐጣ፤ ተቸገረ።
ተአርየ ፡ ተለቀመ ተቃረመ፤ ታረመ ተመረጠ።
ተዐቀመ ፡ ተወሰነ፤ ተገታ። ኢይትዔቀም ባሕረ ጸጋኪ ፡ (ስንክ ፡ ሠኔ፳፩)።
ተዐቍረረ ፡ ታቈረ፤ ተቋጠረ፤ ተፀነሰ፤ ተወሰነ። ፈጠርከ በንስቲት ነጠብጣበ ዘርዕ ዘይትዐቈር ውስተ ማሕፀን። በእንተ ተዐቍሮ ዘርዕ በማሕፀና። ተፀንሰ በከርሥ እንዘ ኢይትዐቈር ፡ (ዲድ ፡ ፴፰። አፈ ፡ ድ፳፫። ቅዳ ፡ ዮሐ)።
ተዐቃቢ ፡ ተጠባቂ፤ ተጠንቃቂ፤ ጠንቃቃ። ዮሐንስ ተዐቃቢ፤ ሦስት አምላክ የሚል ፡ (ሃይ ፡ አበ ፡ ኪራ)።
ተዐቅበ ፡ ተጠበቀ፤ ተጠነቀቀ፤ ተለከከለ፤ ራቀ። ተዐቀብ እምነ እኩይ። ተዐቀብ ኢያስሕትከ። ይትዐቀቡ እምነ ኵሉ ዝሙት ወርኵስ ፡ (ሢራ፲፩ ፡ ፴፫። ፲፫ ፡ ፰። ኩፋ ፡ ፳)።
ተዐቅደ ፡ ታቀደ፤ ተቀየደ፤ ተኰደኰደ።
ተዐቅጸ ፡ ተሰነ(ና) ከለ፤ እግሩ ታሰረ ተቀየደ። ኩኑ ንቁሃነ ወኢትትዐቀጹ በምንትኒ። እሙንቱሰ ተዐቅጹ ወወድቁ ፡ (ዮሴፍ። መዝ ፡ ፲፱)።
ተዐቅፈ ፡ ተነቀፈ፤ ዕንቅፋት መታው፤ አገኘው፤ ተሰናከለ። ዘእንበለ ይትዐቀፉ እገሪክሙ። ከመ ኢትትዐቀፍ በእብን እግርከ። ይትዐቀፉ ደቂቅ በልሂቅ። ኢይትዐቀፍ በኀጢአት ፡ (ኤር፲፫ ፡ ፲፮። መዝ ፡ ፺። ኢሳ፫ ፡ ፭። ሢራ፳፫ ፡ ፲፪)።
ተዐበየ ፡ (ጥ) ታበየ፤ ትቢተኛ ኾነ፤ ኰራ ተጓደደ፤ ተነፋ ዐበጠ፤ ልቡ ሐሳቡ። ለምንት ይትዔበይ መሬት ወሐመድ። ኢትትዐበይ በመዋዕለ ተጽናስከ። ከመ ኢይትዐበይ ንኡስ ላዕለ ዐቢይ። ዲያቆናት ኢይትዐበዩ ለተልእኮ ጽኑሳን። ተዐባዪ ላዕለ ነዳያን። እስመ ተዐበየ ልብከ ፡ (ሢራ፲ ፡ ፱ና ፡ ፳፮። ቀሌ። ዲድ ፡ ፲፯። ፍ ፡ ነ ፡ ፲፮። ሕዝ፳፰ ፡ ፪)።
ተአብየ ፡ እንቢ ተባለ፤ ተጠላ፤ ተሰለቸ ፥ ተጠገበ፤ ፍቅሩ ለእግዚእነ ኢይትአበይ ፡ (አዋል)።
ተዐትበ ፡ ታተበ፤ ተቄረጠ። ተባረከ፤ ታታመ። ሀባ ናህየ ለዛቲ ነፍስ ዘተዐትበት በጥምቀትከ ወተቀደሰት በደምከ። ተዐትበት በዕፀ መስቀሉ። ከመ ይትዐተብ ራእየ ነቢያት ፡ (ግንዘ። ድጓ። ዳን፱ ፡ ፳፬)።
ተአንመ ፡ ተሠራ፤ ተሰፋ፤ ተጠለፈ። ወኢትልበስ ልብሰ ዘተአንመ በፀምር ወበዐጌ። ልብስ ዘኢተአንመ ወክዳን ወኢተፈትለ ፡ (ዘዳ፳፪ ፡ ፲፩። ዲድ ፡ ፩። ቅዳ ፡ ዮሐ)።
ተአንሰሰ ፡ እንስሳ ኾነ፤ ተሞኘ፤ ከእንስሳት ማኅበር ገባ፤ አንድ ኾነ፤ በግብር። እለ ይትአነሰሱ ምስለ እንስሳ ዘውእቱ ዝሙት። ተአንሰሱ ከመ እንስሳ። ረሰዮ ከመ አርዌ ገዳም፤ ገሠጾ በተአርውዮ ወአንበሮ በተአንስሶ ፡ (ዲድ ፡ ፴፫። ቀሌ። መጽ ፡ ምስ)።
ተአንሰረ ፡ ንስር ኾነ፤ ንስር ተባለ። ተአንስሮትየ ፡ (አዋል)።
ተአንተለ ፡ ተጠላ፤ ተሰለቸ፤ ቸል ተባለ።
ተአንገደ ፡ (የተናገደ ድርብ) ተስተናገደ፤ እንግዳ ኾነ ፥ እንግድነት ኼደ ተሰደደ። እለ ሖሩ ወተአንገዱ። ጥበብ ዐርክ ይእቲ በውስተ ተአንግዶ። ተአንገደ ምስለ ያዕቆብ ፡ (ቅዳ። ፈላስ። ሃይ ፡ አበ፪)።
ተአኵተ ፡ ተመሰገነ፤ ተባረከ ተመረቀ። እምኀበ መላእክት ተአኵተ። ትትአኰቱ በኀቤሁ። ብእሲ ኄር ብዙኀ ይትአኰት ፡ (ኪዳ። ዮዲ፲፪ ፡ ፲፫። ምሳ፳፰ ፡ ፳)።
ተአኪያሃ ፡ (ጽር ቴዎቶኮስ) ወላዲተ አምላክ። ሰመዮ ለድርሳኑ ድርሳነ ተአኪያሃ ማርያም፤ ዘውእቱ ወላዲተ አምላክ ብሂል ፡ (ያዕ ዘእል)።
ተአክለ ተአከለ ፡ ተበላ፤ ምግብ ኾነ ተወሰነ፤ ቆመ ጸና። ኀደግነ በብዕለ ቃላቲሆሙ ለአበው ተአኪለነ። መፍትውሰ ተአኪለነ በእለ ቀደሙነ መምህራን ትምህርት ወዘቅዱሳን ማየ ተረዊየነ ናክብር በአርምሞ ፡ (ተረ ፡ ቄር፫ና ፡ ፮)።
ተዐወረ ፡ (ይትዔወር) ዐይኑን ጨፈነ፤ ቸል አለ፤ ናቀ፤ ዕውር መሰለ፤ እያየ እንዳላየ ኾነ፤ ደፈረ። ይትዔወር ነፍሶ። ይትዔወር ቢጾ። ኀፍረት ተዐውሮቱ ለቢጽከ። ኢይባእ ውስተ ምሥዋዕ፤ ወእመሰ ተዐወረ ከመ ይባእ ፡ (ሢራ፲፬ ፡ ፰። ፳፱ ፡ ፲፬። ፵፩ ፡ ፳፩። ቀሌ)።
ተዐወገ ፡ (ይትዔወግ) አላገጠ፤ አለመጠ፤ ተሣለቀ፤ አፉን ከንፈሩን በማጣመም፤ ዐይኑን በማጨንቈር በማሳወር፤ ይህን በመሰለ ነገር። ወተዐዊጎሙ አይሁድ በክርስቶስ። ተዐዊጎሙ ይነግሩ ፡ (ቄር ፡ እስት። ጰላ)።
ተዐዋሪ ፡ ቸል ባይ፤ ቸልተኛ። አይቴ ለተናስሖ ተዐዋርያን ፡ (ግንዘ)።
ተዐውቀ ፡ ታወቀ፤ ተረዳ፤ ጐላ ተገለጠ። ይትዐወቅ እምርሑቅ ዘይክል ነቢበ። ሕልመ ሌሊት ዘኢይትዐወቅ። ከመ ይትዐወቅ ጽድቁ። ተዐውቀ እግዚ በይሁዳ። ዘተዐውቀ አበሳሁ በውስተ ፍትሕ ፡ (ሢራ፳፩ ፡ ፯። ኢዮ፳ ፡ ፰። ሚክ፮ ፡ ፭። መዝ ፡ ፸፭። ዲድ ፡ ፲)።
ተዐውደ ፡ ታወደ፤ ተዞረ፤ ዐዋጅ ተነገረ። በዖደ ፈንታ ተዐውደ ይላል፤ የተሳሳተ ነው። አኮኑ ፍጡነ ይረውጽ ፀሓይ፤ ተዐዊዶ ሰማየ ፡ (፩ዕዝ ፡ ፬ ፡ ፴፬)።
ተዐውገ ፡ ተጋገረ፤ ተነጐተ፤ ተጠቤተ።
ተአዘዘ ፡ ታዘዘ፤ ሰማ ተቀበለ፤ ዕሺ በጎ አለ፤ ተገዛ አገለገለ። ወተአዘዘ ውእቱ ዐንበሪ የኀጦ ለዮናስ። ኀሊ ዳእሙ ዘተአዘዝከ። አልቦ ዘይትኤዘዝ ለቃልከ። ልህቀ እንዘ ይትኤዘዝ ለአዝማዲሁ። ተአዘዛ ለአምታቲክን ፡ (ዮና፪ ፡ ፲፩። ሢራ፫ ፡ ፳፪። ዮዲ፲፮ ፡ ፲፬። ድጓ። ዲድ ፡ ፫)።
ተአዛዚ ፡ የሚታዘዝ ታዛዥ፤ ተለኣኪ አገልጋይ፤ ዕሺ ባይ ፈቃደኛ። ተአዛዚ ዲበ ሰብእ። ተአዛዚ ለትፍሥሕት ወለኑዛዜ። ረድኡ ወተአዛዚሁ። ወትከውን ለከ ተአዛዚተ ፡ (ሔኖ፳ ፡ ፭። ስንክ ፡ የካ፲፪። ጥቅ፲፱። ፈላስ)።
ተዐዝረ ፡ ተበተነ፤ ተዘራ ተረጨ፤ ተሠራጨ፤ ተናኘ ተወራኘ፤ የጮራ የጭፍራ። ወተዐዝሩ ላዕለ ሌሒ ፡ (መሳ፲፭ ፡ ፱)።
ተዐየረ ፡ (ተደራጊ) ተሰደበ፤ ተዋረደ፤ ተናቀ፤ ተጠቃ፤ ተግዳሮት ሰማ።
ተአየነ ፡ (ዐረ አእነ) ተከበከበ፤ ደላው ተመቸው፤ ባለጤና ኾነ፤ ዕረፍት አገኘ።
ተዐየነ [1] ፡ ተጐበኘ፤ ተሰለለ፤ ተመረመረ፤ ምንጩ ቦታው። ተገመገመ፤ ዋጋው።
[2] ፡ ተዐየነ፤ ከተመ፤ ምንጭ ይዞ ሰፈረ፤ ጐዦ ሠራ፤ ድንኳን ተከለ፤ ሕዝቡ። እለ ይቀድሙ ተዐይኖ። ወተዐየኑ ውስተ አቤኔዜር ፡ (ዘኍ፪ ፡ ፫። ፩ነገ ፡ ፬ ፡ ፩)።
፡ ከበበ፤ ዐጠረ፤ ዙሪያውን ያዘ፤ በዙሪያ ሰፈረ። ሶበ ኖኀ ተዐይኖ ላዕለ ሀገር። ወተዐየና ለሀገር ወዐገታ። ወይትዐየኑኪ ፡ (ዮሴፍ። ሉቃ፲፱ ፡ ፵፫)።
ተዐደመ ፡ ታደመ፤ ተቀጠረ፤ ተወሰነ። በመዋዕል ዘተዐደመ። ዐስብ ዘተዐደመት ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፳፬ ፡ ፪። ፴፮)።
ተአደወ ፡ ተጠረገ፤ ተኰሰተረ፤ ተከወነ፤ ቤቱ ጕድፉ።
ተዐድወ ፡ ፣ ታለፈ፤ ተዘዕለ፤ ወንዙ ሕጉ ትእዛዙ።
ተዐገለ ፡ (ተደራጊ) ተቀማ፤ ተነጠቀ፤ ተገፋ፤ ተበደለ።
ተዐገሠ ፡ ታገሠ፤ ተገታ፤ ቈየ፤ ጠበቀ፤ ደጅ ጠና፤ ቻለ ተሸከመ። ደናግል ወመዓስብ ይትዐገሣ፤ ወእመሰ ኢክህላ ተዐግሦ ለያውስባ። ተዐገሡ ዓዲ ኀሙሰ መዋዕለ። ዘይትዔገሦ ለእግዚ። እለ ይትዔገሡ ሐዘናተ ወጻዕቃተ ፡ (ቀሌ። ዮዲ፯ ፡ ፴። ሢራ፳፰ ፡ ፩። ማር ፡ ይሥ፲፫)።
፡ ተቻለ የሚቻል ተቻይ
ኾነ ፤ መከራው ሸክሙ።
ተዐጋሢ ፡ (ሢት ሥያን ያት) የሚታገሥ፤ ታጋሽ፤ ቻይ፤ ልበ ሰፊ ነገር ዐላፊ። ተዐጋሢ እምፅርፈት። ኩኑ ጽኑዓነ ወኀያላነ ወተዐጋሥያነ ወማእምራነ። ተዐጋሥያን ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፲። ዮሴፍ። አፈ ፡ ተ፴)።
ተዐግተ ፡ ታገተ፤ ተያዘ ታሰረ። ተከበበ፤ ተዘጋ፤ ታጠረ። ተዐግተት ሀገር። ዝንቱ መዓር ተዐግተ በንህብ ፡ (፫ነገ ፡ ፲፮ ፡ ፲፰። ስንክ ፡ ሠኔ፲፪)።
ተዐጥነ ፡ ታጠነ፤ ተጤሰ። ዐጠኑት ዐጤሱለት።
ተዐጥፈ ፡ ተሠራ፤ ታጠፈ፤ ተጠቀለለ፤ ዝሓው ልብሱ።
ተዐጽረ ፡ ተጠመቀ፤ ተዘለለ። ዘተዐጽረ እምአስካለ ወይን ፡ (ፈ ፡ መ ፡ ፳፮ ፡ ፩። መቃ)።
ተዐጽወ ፡ ተዘጋ፤ ዝግ ኾነ፤ ተዘጋበት። ተዐጽዉ አብያት። ተዐጽዉ አህጉር። ባእ ተዐጸው ማእከለ ቤትከ። ወሶበ ተዐጽዉ ክልኤሆሙ ፡ (ኢሳ፳፬ ፡ ፲። ኤር፲፫ ፡ ፲፱። ሕዝ፫ ፡ ፳፬። ጦቢ፰ ፡ ፬)።
ተዐጽደ ፡ ታጨደ፤ ተቈረጠ፤ ተከፈለ፤ ተወሰነ። እመ ኢተዐጽደ ዘተዘርዐ። ወተዐጽደት ምድር ፡ (ሱቱ ፡ ዕዝ፪ ፡ ፳፯። ራእ፲፬ ፡ ፲፮። ያዕ፭ ፡ ፯)።
ተዐጽፈ ፡ ታጠፈ፤ ተደረበ፤ ልብሱ። ለበሰ፤ ተጐናጠፈ፤ ሰዉ። ተዐጸፍኬ ልብሰከ። ልብስ ቀጢን ዘይትዐጸፍ ካህን። ትትዐጸፍ አልባሲሃ። ንትዐጸፍኬ ኦ አኀውየ በዝንቱ ፡ (ግብ፲፪ ፡ ፰። ሢራ፶ ፡ ፪። ዮዲ፲ ፡ ፯። አፈ ፡ ተ፴፬)።
ተአፍየ ፡ ተጋገረ፤ በሰለ፤ በእቶን በምጣድ ወይም በፍሕም።
ተኣሐደ ፡ ተዋሐደ፤ ተወሓሐደ፤ አንድ ተኳዃነ፤ ተባበረ።
ተኣኅወ ፡ ተወናደመ፤ ወንድማማች ኾነ፤ ተዋደደ ተዛመደ፤ ተስማማ አንድ ኾነ። አትናቴዎስ ወኢራኒ ዘተኣኀዉ። ኢፈቀደ ይትኣኀዎሙ ለኪሩቤል። ተኣኅዎት መንፈሳዊት። አልቦ ገቢር ምስሌከ ተኣኅዎ። በከመ ተኣኀውከ ምስለ አካዝያስ። ምስለ ኵሉ ሰብእ ተኣኀዉ ፡ (ስንክ ፡ ኅዳ፫። አርጋ ፡ ፮። ፍ ፡ ነ ፡ ፲ ፡ ፮። ኩፋ ፡ ፴፯። ፪ዜና ፡ ፳ ፡ ፴፯። ሮሜ፲፪ ፡ ፲፰)።
ተኣኀዘ ፡ ተያያዘ ተሳሰረ፤ ተከራከረ፤ ተካሰሰ ተዋዋሰ፤ ተዣመረ። ይትኣኀዝ ምስለ ቤተ ራባ። ተኣኀዝዎ ለጳውሎስ። ተኣኀዙ ይትቃተሉ ፡ (ኢያ፲፱ ፡ ፲፩። ግብ፲፯ ፡ ፲፰። ፪ነገ ፡ ፲ ፡ ፰)።
ተኣመረ ፡ ተዋወቀ፤ ተወዳጀ፤ ተዋደደ።
ተዓመቀ ተዐማመቀ ፡ ተማመቀ፤ ተናነቀ፤ ተጫቈነ፤ ተጋፋ ታገለ፤ ለመጣል ለማውደቅ፤ በታች ለማድረግ። ኢትትዐማመቅ ምስለ ሰይጠናት፤ ደረት ለደረት አትጋፋ ፡ (ፊልክ ፡ ፳)።
ተኣመነ ፡ ተማመነ፤ ተማማለ።
ተዓመፀ ፡ ተጋፋ፤ ተገፋፋ፤ ተጣላ፤ ግፍ ተሣራ፤ ተበዳደለ። ለምንት ትትዓመፁ በበይናቲክሙ። ኀፍረት ተዓምፆ ምስለ ዐርክከ ፡ (ግብ፯ ፡ ፳፮። ሢራ፵፩ ፡ ፲፰)።
ተኣምኀ ፡ እጅ ተነሣሣ፤ ተሳሳመ፤ እጅ ለእጅ ተያያዘ፤ ተገናኘ ወይም ተሰነባበተ። ተኣምኁ በበይናቲክሙ በአምኃ ቅድሳት። ወተኣምኆሙ በአምኃ መንፈሳዊት። ዘይፈቱ ድንግልና ይትኣማኅ ፡ (ይሰናበት) ኵሎ ጥሪቶ ውሂቦ ለምስኪናን ፡ (ቅዳ። ገድ ፡ ተክ። ኪዳ)።
ተኣምር ፡ (ራት) በቁሙ፤ ታምር ታምራት፤ ድንቅ ምልክት፤ እንደ ነቢያት እንደ ሐዋርያት በእግዜር ኀይል በክርስቶስ ስም ካልኾነ በቀር ማንም ሰው ሊሠራው የማይችል ልዩ ድንቅ ጕድ ብርቅ የኾነ አምላካዊ ሥራ ፡ (ዮሐ፲፬ ፡ ፲፪። ዘፀ፬ ፡ ፰ ፡ ፱)።
፡ ፀሓይ
ጨረቃ ኮከብ።
ሰገደ ለኵሉ
ተኣምረ ሰማይ።
ፀሓይ ወተኣምር
(፪ዜና ፡ ፴፫ ፡
፫።
ኤር፲ ፡ ፪።
ሔኖ፵፰ ፡ ፫።
ኵፋ ፡ ፬)።
ተኣሰረ ፡ ተሳሰረ፤ ተቈራኘ፤ ተቈላለፈ።
ተዓረቀ ፡ ታረቀ፤ ተራረቀ፤ ተሰማማ፤ አንድ ልብ ኾነ። ፡ (ተረት) ሲታጠቡ ከክንድ፤ ሲታረቁ ከሆድ። ኢይትዓረቅ በብዙኅ ሀብት። ይትዓረቅ ምስለ ቢጹ። ለእመ አበየት ተዓርቆ ምስለ ምታ ፡ (ምሳ፮ ፡ ፴፭። ዲድ ፡ ፲፩። ፈ ፡ መ ፡ ፲፪ ፡ ፪)።
ተዓረከ ፡ ተወዳጀ፤ ተዛመደ፤ ተቀናጀ፤ ተጣመደ፤ ተባበረ ተመሳሰለ፤ በመልክ በግብር። እመ ትትዓረክ ዐርከ፤ ተዓረክ በመዋዕለ ተጽናስከ። ዘተዓረኮ ለዕቡይ ይከውን ከማሁ። በአይቴ ይትዓረክ መቅፁት ምስለ ጽህርት ተኵላ ምስለ በግዕ ፡ (ሢራ፮ ፡ ፯። ፲፫ ፡ ፩–፪፤ ፲፯)።
ተዓቀበ ፡ ተጠባበቀ። ከመ ይትራድኡ ኅቡረ በባሕር ወበየብስ ወይትዓቀቡ በበይናቲሆሙ ፡ (ዮሴፍ)።
ተዓቀፈ ፡ ተነቃቀፈ፤ ተሰነካከለ። ኢትትዓቀፉ በትሕዝብት ፡ (ገድ ፡ ዮሐ ፡ ከማ)።
ተኣበየ ፡ እንቢ ተባባለ፤ በፈቃድ በግብር ተለያየ፤ ተጣላ፤ ተፈራቀቀ አንድነት ስምምነት ዐጣ። እስመ ሥጋኒ ይፈቱ ዘኢይፈቱ መንፈስ፤ ወመንፈስኒ ይፈቱ ዘኢይፈቱ ሥጋ ፥ ወይትኣበዩ በበይናቲሆሙ ከመ ኢትግበሩ ዘትፈቅዱ ፡ (ገላ፭ ፡ ፲፯)።
(ላ) ተዓበየ ፡ ተበላለጠ፤ ተላላቀ፤ ተወዳደረ፤ እኔ እበልጥ እኔ እበልጥ ተባባለ።
ተኣተተ ፡ ተራራቀ፤ ተለያየ፤ እየብቻው ኾነ። አተተ፤ የጠፈረና የዐሰየ ቤት እንደ ኾነ የቀደሰ ቤት እንዳይዶለ አስተውል።
ተኣከለ ፡ ተባላ ተናከሰ፤ ተካከለ፤ ተወዳደረ። ኢትትኣከል እንዘ ነዳይ አንተ ምስለ ባዕል ፡ (ምሳ፳፫ ፡ ፬)።
ተኣከየ ፡ (ተደራራጊ) ተከፋፋ ተጠላላ፤ ሆድ ተባባሰ ተናናቀ።
ተኣኰተ ፡ (ይትኣኰት ይትኣኰት) ተመሰጋገነ፤ ፡ (ተደራራጊ)።
ተኣኳቲ ፡ ተመሰጋጋኝ።
ተዓወቀ ፡ ተዋወቀ፤ ተላመደ፤ ተወዳጀ ተዛመደ።
ተኣዘዘ ፡ ተዛዘዘ፤ ተደራራጊ።
ተዓየነ ፡ ተሳፈረ፤ ተሰፋፈረ፤ ጐን ለጐን ወይም ፊት ለፊት።
ተኣየየ ፡ ተመሳሰለ፤ ተነጻጻረ። ዘመንገለ ሰብእ ክቡር ወልዑል፤ ወኢይትኣየይ ምስለ ካልእ በልዕልናሁ። እምክልኤቱ እለ ኢይትኣየያ ዘውእቱ መለኮት ወትስብእት። አማንኑ ከመ ለብሂል መርገመ ኮነ ወኀጢተ ከማሁ ይትኣየይ ነገር ዘይብል ኮነ ሥጋ ፡ (ቄር ፡ እስት ፡ ጰላ)።
ተዓይን ፡ ሰፈሮች፤ ድንኳኖች፤ ከተሞች። ሰራዊቶች፤ ጭፍሮች፤ ማኅበሮች። ተዓይኒሆሙ ለኤዶምያስ። እምኵሉ ተዓይኒሁ ለያዕቆብ። ወርእየ ያዕቆብ ተዓይነ እግዚ። እመኒ ጸብአኒ ተዓይን። ተዓይነ ክርስቶስ ፡ (መዝ ፡ ፹፪ና ፡ ፹፮። ዘፍ፴፪ ፡ ፩–፪። መዝ ፡ ፳፮። ስንክ ፡ ሐም፲፪)።
ተዓደመ ፡ ተቃጠረ፤ ተቀጣጠረ፤ ተዋዋለ፤ ተስማማ። ተዓደሙ እስከ ሠርቀ ወርኅ፤ ይግበሩ ከመ ዝ። በከመ ተደመርከ ወተዓደምከ ምስለ አካዝያስ ፡ (፩ዕዝ ፡ ፱ ፡ ፲፮። ፪ዜና ፡ ፳ ፡ ፴፯)።
ተዓደወ ፡ (ተደራራጊ) ተሸጋገረ፤ ተላለፈ፤ ርስ በርሱ።
ተዓገለ ፡ (ተደራራጊ) ታገለ፤ተጋገለ፤ ተቃማ ተናጠቀ፤ ተሳረቀ። ፡ (ግጥም) እግዜር ከኔ ጋራ እንታገል አለኝ፤ ረ እንዴት ፈጥሮ ሊጥለኝ፤ አለመጣሉም ታውቋል፤ በያዕቆብ ትግል። ፡ (ዘፍ፴፪ ፡ ፳፬–፳፱)።
ተዓገሠ ፡ ተጋገሠ ተቻቻለ፤ ርስ በርሱ።
ተዓፀወ ፡ ዕፃ ተጣጣለ፤ ተካፈለ። ንዑ ንትዓፀው፤ ወተዓፀዉ። መፍትው ከመ ንትፃፀው በበ ክልኤ እምኔነ፤ ወዘወፅአ ቦቱ ዕፃ ለቀቲል፤ ይቅትል ካልኦ። ወተዓፀዉ ዲበ ዐራዝየ ፡ (ዮና፩ ፡ ፯። ዮሴፍ። መዝ ፡ ፳፩)።
ተኤኀ ተአይኅ ፡ ጠፋ ሰጠመ፤ ተደፈነ ውሃ ለበሰ። ወከማሁ ሶበ ተአይኅ ምድር አድኀነቶ ጥበብ። አመ ተአይኀ ዓለም ፡ (ጥበ፲ ፡ ፬። ደራሲ)።
ተእኅዘ [1] ፡ ተያዘ ተጨበጠ፤ ታሰረ፤ ተጣበቀ፤ ተገታ፤ ተከለከለ፤ ተወረሰ ርስት ኾነ። እመ ተእኅዞ ተእኅዘ ሰራቂ። ተእኅዘ በመሥገርት። ዘገሰሰ ፒሳ ይትአኀዝ ቦቱ። አስራበ ሰማይ ተእኅዘ። ወተእኅዛ አዕይንቲሆሙ ከመ ኢ። ተእኅዘ ልማደ እብስት ወርስዐት ፡ (ምሳ፮ ፡ ፴። ኤር፴፩ ፡ ፵፬። ሢራ፲፫ ፡ ፩። ዘፍ፰ ፡ ፪። ሉቃ፳፬ ፡ ፲፮ ፡ ጥበ፲፬ ፡ ፲፮)
[2] ፡ ተያዘ ተዋሰ ተዳነ፤ ተያዥ ዋስ መድን ኾነ፤ ዋስ በራሴ አለ። ታገተ ተያዘ በውስትና በዕዳ። አብ ኢይትአኀዝ በዕዳ ልቃሐ ወልዱ ለእመ ኢኮነ ዘተለቅሐ በትእዛዘ ዚኣሁ
፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፳፯)። በአኀዘ ፈንታ ተአኀዘ ይላል፤ ስሕተት ነው። ኢትትአኀዝ ማሕረጸ ፡ (ዘዳ፳፬ ፡ ፮ ፡ ፲)።
ተእሕደ ፡ አንድ ኾነ፤ አንድ ተባለ።
ተከለለ ፡ በቁሙ፤ ተጋረደ ለበሰ፤ ተቀዳጀ። ተከለሉ በፍኖቶሙ ደመና። ተከለለ ገጹ ብርሃነ። ክብረ ወስብሐት ዘተከለለ ፡ (ዮሴፍ። ስንክ ፡ የካ፳፩። ዕብ፪ ፡ ፱)።
ተከልሰሰ ፡ ተላሰሰ፤ ታጨደ ታሰረ፤ ተሰበሰበ።
ተከልአ ፡ ተከለከለ፤ ተገታ ቆመ። ተከልአኒ ገቢር ዘእፈቅድ። ተከልአ ዝናመ ሰማይ። ተከልአ ጸብእ ኀምስተ ዕለተ ፡ (ኪዳ። ፫ነገ ፡ ፰ ፡ ፴፭። ዮሴፍ)።
ተከልከለ ፡ ተክለክልለ፤ ክልክል ኾነ። ጺሕ ፍኖቶ ዘእንበለ ክልአት ወኢተከልክሎ። ኢይትከለከል ፡ (ግንዘ። ገድ ፡ ኪሮ)።
ተከስበ ፡ ተገዘረ፤ ተከረከመ። ዘኢተከስበ ሥጋ ነፍስቱ። ኢኀፈረ ከሢተ ዕርቃን ለተከስቦ ፡ (ኩፋ ፡ ፲፭። መጽ ፡ ምስ)።
ተከሥተ ፡ ተገለጠ፤ ተከፈተ። አልቦ ክዱን ዘኢይትከሠት። ወተከሥቱ መቃብራት ፡ (ማር፬ ፡ ፳፪። ማቴ፳፯ ፡ ፶፪)።
ተከርየ ፡ ተቈፈረ፤ ተማሰ። እስከ ይትከረይ ግብ ለኃጥኣን ፡ (መዝ ፡ ፺፫)።
ተከበ ፡ ተከበበ፤ ተሰበሰበ፤ ተኮበ ተኳሰ፤ ተንከበከበ ክብ እንክብል ኾነ።
ተከብሰ ፡ ተከበሰ፤ ተክበሰበሰ፤ በራሱ ላይ ጌጥ ተሸከመ፤ ተሸለመ። ፀፈረት ርእሳ ወተከብሰት ፡ (ዮዲ፲፮ ፡ ፰)።
ተከብተ ፡ ተሸሸገ ተደበቀ፤ ታባ ተሰወረ፤ ከቦታው ታጣ። ተከብተ ሔኖክ። ከመ ትትከበት መንፈስየ። ስእነ ተከብቶ ፡ (ሔኖ፲፪ ፡ ፩። ፸፩ ፡ ፩። ማር፯ ፡ ፳፬)።
ተከትመ ፡ ተከተበ፤ ተጠቈረ፤ ተበጣ ተተኰሰ። ዘይትሜሰል በአርኣያ ዘኢኮነ አርኣያሁ ከመ ካህን ዘይትከተም አው ዘይለብስ አልባሰ ሐራ ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፵፫ ፡ ፲፪)።
ተከትፈ ፡ ታሰረ ተጣመረ፤ ተኰረኰመ። ተከተፈ።
ተከነ(ን)ሰ ፡ ተሰበሰበ፤ ተከማቸ ፥ አንድ ኾነ፤ ተቀላቀለ። ተቀበለቶ እንዘ ትትኬነስ ደሴተ ቆጵሮስ ለኤዎስጣቴዎስ። ይባእ ወይትከነስ ወይቅረብ። አልባ ተከንሶ ወተደምሮ ምስለ ሕዝብ ፡ (ደራሲ። ኪዳ። ቀሌ)።
፡ ታዘዘ ፤ ተገዛ። ዘሆባይ ይትኬነስ ሎቱ ፥ ወወይጠል ይሰግድ ሎቱ (ድጓ)።
ተከወለ ፡ ወደ ኋላ አለ፤ አፈገፈገ። ደጀን ኾነ፤ በኋላ ኼደ ተከተለ፤ የሰልፍ የጕዞ። ይትኬወል እምኔነ። እለ ይትኬወሉ ድኅረ መስቀል። ወእለሂ ይትኬወሉ ድኅረ ታቦት የሐውሩ እንዘ ይነፍኁ ቀርነ ፡ (መጽ ፡ ምስ። ኢያ፮ ፡ ፱)። ደኀረንና ተድኅረን እይ።
ተከወነ ፡ (ኮነ) በቁሙ፤ ተፈጸመ ሥራው ዐለቀለት።
ተከውሰ ፡ ተካወሰ፤ ተናወጠ ተነዋወጠ፤ ታወከ ተደረጠ።
ተከዚ ፡ ፈሳሽ ጐርፍ፤ ወራጅ: ውሃ፤ ስመ ፈለግ። ገርዎ ፡ ውስተ ፡ ትከዚ። ተከዜ ግብጽ ው ሐዘ ፡ ማይ ፡ ዘይወፅእ ፡ እም ፡ -ተከዚ ተከዜ፣ ጤ ግሮስ። ተከዜ ፡ ኤፍራጥስ። አመ : በሡሩ፣ ወረ ሱዑ ለሐምሌ፣ በይእቲ ፡ ዕለት ፡ ገብረ ፡ ሎቱ እ 2ዚ:ተኣምረ ለንጉሥ ፡ ልብ ፡ -ድንል፣ ወዐድዎ፣ ለተክዚ ፡ በእግር፣ እምድኅረ ጉቡኣን ሐዋርያት፣ ፡ (ዝብ፩ ፡ ፳፪። ፪ዜና ፡ ፯ ፡ ፰ = ሢራ፳፬ ፡ ። ጦቢ፮: ፪። ፩ዜና ፡ ፭ ፡ ፬። ታሪ ፡ ግራ)
ተከይደ ፡ ተረገጠ ተጠቀጠቀ፤ ተናቀ ተጠቃ ተጨቈነ። ውስተ መካን እንተ ኢተከይደት። መቅደስ ወኀይል ተከይደ። አርዌ ተከይደ ወከይሲ ተቀትለ ፡ (ጥበ፲፩ ፡ ፪። ዳን፰ ፡ ፲፫። ኪዳ)።
ተከድነ ፡ ተከደነ ለበሰ ተሰወረ ተሸፈነ። ትትከደኑ ወኢትመውቁ። ከመ ትትከደኑ በዕለተ መዐቱ ለእግዚ። ተከድነት ገጻ ፡ (ሐጌ፩ ፡ ፮። ሶፎ፪ ፡ ፫። ዘፍ፳፬ ፡ ፷፭)።
ተከፈ ፡ (ዕብ ካታፍ) ተሸከመ፤ ሸክምን በትከሻ ያዘ፤ አኖረ አስቀመጠ፤ ትከሻውን ለሸክም ሰጠ።
ተከፍለ ፡ ተከፈለ፤ ከኹለት ከሦስት ወይም ከብዙ። በጽሑ ውስተ ፈለገ ጤግሮስ ወተከፍለ ሎሙ ማይ ወዐደዉ። ተደምሮ ዘመድ ይትከፈል ኀበ ክልኤ ክፍል። ዝንቱ ጾታ ይትከፈል ለኀበ ብዙኅ ክፍል ፡ (ስንክ ፡ የካ፲፩። ፈ ፡ መ ፡ ፭ ፡ ፪። ፳፭ ፡ ፩)።
፡ ታደለ ተቀበለ ፤ ተቀባይ ኾነ አገኘ ፤ ብድሩን ዋጋዉን (ዐማርኛ)።
ተከፍአ ፡ ተከፋ ዐዘነ ተቈረቈረ ፡ (ዐማርኛ)።
ተኵሕለ ፡ ተኳለ ተቀባ፤ ተተኰሰ። ተኵሕሎት ወአሠንዮ ቀራንብት። በተኵሕሎትን። ተኵሕለት አዕይንቲሃ ፡ (ሔኖ፰ ፡ ፩። ፈ ፡ መ ፡ ፴፬ ፡ ፰። ፬ነገ ፡ ፱ ፡ ፴)።
ተኵላ [1] ፡ (ዕብ ሹዓል። ሱር ታዓል። ዐረ ሸዕላብ) በቁሙ፤ የበረሓ ውሻ፤ የቀበሮ ወንድም፤ ተንኰለኛ ርጉም። የቍንጽልን ፍች ተመልከት። የግእዝ መጽሐፍ ግን በተኵላ ፈንታ ቍንጽል እንዲል፤ በዝእበ ፈንታ ተኵላ ይላል፤ የመላሽ ስሕተት ነው። ሶበ ርእየ ተኵላ፤ ይመሥጦን ተኵላ ፡ (ዮሐ፲ ፡ ፲፪)። የዝእብን አፈታት ተመልከት፤ ስለ ቍንጽል የጠቀስነው ቃል ተኵላ እንደ ኾነ፤ ስለ ተኵላም የጠቀስነውና ያልጠቀስነው ተኵላ የሚል ኹሉ ዝእብ ነው እንጂ፤ በቁሙ ተኵላ እንዳይመስልኽ ያማርኛውን ቅዱስ መጽሐፍ እይ።
[2] ፡ (ዕብ ሻሓል) አንበሳ፤ ስመ አንበሳ። ላዕለ ተኵላ ወከይሲ ትጼዐን ፡ (መዝ ፡ ፺)።
ተኵላት ተኳሉት ፡ ተኵሎች የበረሓ ውሾች። ይትረዐዩ ተኵላት ምስለ አባግዕ። ከመ አባግዕ ማእከለ ተኳሉት ፡ (ኢሳ፲፩ ፡ ፮። ማቴ፲ ፡ ፲፮)።
ተኪል ሎት ፡ (ተከለ ይተክል ይ ትክል። ሱር ትካል። ዕብ ፡ ሻታል። ዐረ ፡ ወከለ ፡ ተኪለ) መትከል፤ መቀስቀብ ፡ መትከል፤ የካስማ " ከመሬት ፡ መሻጥ፤ መወተፍ : መሽጉጥ : ማቆም ፡ ማጽናት፤ የተክል። ተክሉ ፡ ደባትሪሆሙ ፡ ተ ክለት፤መትከለ።ተከሉ ፡ ወይህ።ትከሉ ፡ አቅማሐ ፡ (ጥበ፲፩ ፡ ፪። ሙሳ፬ ፡ ፳፭። ሙን ፡ ፻፮ " ኤር፴፮፥፭)።
—፤ መከፈል ፡ ( መተካት፤ ምትክ ፡ ማቆም ፡ መስጠት፤ የስው " የከብት = ዘስረቀ ላሕመ እው ፡ በግዐ ይት ካል ፡ ህየንተ ፡ ሕዱ ትዓምስት ፡ እወ ፡ ወግእ ፡ ሕም ላሕመ ፡ ወሞተ ፡ ይትከል ፡ ላሕም ፡ ህየንተ ፡ ላሕም፤(ዘፀ፳፪ ፡ ፩። ፳፭። ጥሩ)።
—፤ መወስን ፡ መቍረጥ ፣ ማገግ ፣ መደንገግ ፣ ሕግ ፡ ማቆም " ሥርዐተ ፡ ይትከል ፡ (ቅዱ ፡ ሐዋ)።
—፤ መግፋት፤ መድፋት ፡ ማዳፋት፤ መወርወር : መገ ፍቀር ፣ መጣል ፣ በግንባር ፣ መትከል፤ መንዳት ፡ መጐስጐስ ማስቸኰል፤ ያጋፋሪ ፡ የዘበኛ " መጽሐፍ : ግን : በተከለ ፡ ፈንታ ፡ እትከል ፡ ይላል፤ እያሰኝም። ነዳይ ፥ እመ፣ተዐቅፈ፣ ያቴከልዎ :: ታቴሱ ፡ ሃዳየ ፡ ሰው ስተ፤ኆኅት : ያቴከልዎ ፡ ለመስቀል ፡ እውፅእዎ ፡ እንዘ ፡ ድቴከልዎ ፡ (ሢራ፲- ፳፫። ዓሞ፩ ፡ ፲፪ ፡ ቁር። ባሮ)።
ተኪት ቶት ፡ (ተከተ ይተክት ይትክት) መታከት፤ መድከም፤ የጕልበት ፡ (ዐማርኛ)።
፡ ማለፍ
መቅደም ፤
ኀላፊ መኾን
፤ መቈየት
፤ መዘግየት
፤ የጊዜ የዘመን።
፡ መድማት ፤ ደም መኾን ፤ ደም ማየት ፤ በዚሁ እስከ ሰባት ቀን መቈየት ፤ የሴቶች። ዛቲ መጽሐፍ ኢትቅረብ ኀበ ይወልዳ ይተክታ (አዋል)።
ተካሀለ ፡ ተቻቻለ፤ ተሰማማ ተዋደደ፤ ተዋዋለ ተቋረጠ፤ የዋጋ። ተካሀለ ምስለ ገባእት በበ ዲናር ለዕለት። አኮኑ በዲናር ተካሀልኩከ መኑ ውእቱ ዘተካሀለኪ ፡ (ማቴ፳ ፡ ፪ ፡ ፲፫። ማር ፡ ይሥ፲፫ ፡ ፪)።
ተካሐደ ፡ ተካካደ ተከራከረ፤ ተሟገተ ፡ (ግብ፲፰ ፡ ፲፭። ፩ቆሮ ፡ ፩ ፡ ፲፩። ፪ጴጥ ፪ ፡ ፫)። ትፈቅድኑ ንትካሐዶሙ ለቃላቲከ በነገራቶሙ ለዕልዋን እስመ በተካሕዶ ይትወለድ ለነ ባቍዕ። ቦኑ እንከ ዘትትካሐደኒ በዝ ነገርየ። ኢትትካሐድ በእንተ ጽድቅ ፡ (ቄር ፡ ጰላ ፡ ገ፷፰። ፸። ሢራ፬ ፡ ፳፭)።
ተካሊ ፡ (ሊት ፡ ልያን ፡ ያት) የሚተ ክል ፡ ተካይ፤ ተክል ፡ ፀጋይ " አቡየ ፡ ተካሊሁ ፡ (ዮሐ ፲፭ ፥ ፩)
ተካልሐ ፡ ተጯጯኸ፤ ተፋጀ ተዋካ፤ ተዚያዚያመ።
ተካወነ ፡ ተኳኳነ፤ ተከዋወነ ተከነዋወነ፤ ተቃና ተሳካ።
ተካየደ [1] ፡ ተራገጠ፤ ተረጋገጠ። እስከ ይትካየዱ በበይናቲሆሙ ፡ (ሉቃ፳፩ ፡ ፩)። በኬደ ፈንታ ተካየደ ይላል፤ ስሕተት ነው። ይትካየድዋ አሕዛብ ፡ (ራእ፲፩ ፡ ፪)።
[2] ፡ ተዋዋለ፤ ተጣጣፈ፤ ቃል ኪዳን ተጋባ ተማማለ፤ ነገር ተቋረጠ። ተካየዶሙ በእደ ነቢያት። ተካየዱ ዮናታን ወዳዊት ኪዳነ። ተካየድነ ምስለ ሞት። ተካየዶ ከመ ያውስብ ወለቶ ፡ (፬ነገ ፡ ፲፯ ፡ ፲፫። ፩ነገ ፡ ፲፰ ፡ ፫። ኢሳ፳፰ ፡ ፲፭። ስንክ ፡ ሚያ፳፫)።
ተካፈለ ፡ በቁሙ፤ ተከፋፈለ ተተናተነ። ኵሎ ተግባረከ ይትካፈሉ መዋርስቲከ። ተካፈሉ ምድርየ። ተካፈሉ አልባስየ። እለ ይትካፈሉ በርበረ። ዘይትካፈል ምስለ ሰራቂ ፡ (ሢራ፲፬ ፡ ፲፭። ዮኤ፬ ፡ ፪። መዝ ፡ ፳፩። ኢሳ፱ ፡ ፫። ምሳ፳፱ ፡ ፳፬)።
ተኬሳ ፡ (ብ ፡ ተካይስ) ትክሻ ፡ ብራኳ። ወደፎ ፡ ማእከለ ፡ ተኤሳሁ :: ሳዊሮስ ፣ ለጓሳ ፡ እ ገዳ ዕልዋን ፡ ዘይሰብር ፡ ወዘመናፍቃን ፡ ተኬላ :: ወይጸውርዎ ፡ በተኍሳሆሙ:(፬ነገ ፡ ፬ ፡ ፳፬። ስንክ ፡ የካ፲፬ " አረጋ ፡ ( መ፴፮)።
ተክህለ ፡ ተቻለ፤ ተመቸ። ኵሉ ይትከሀል። እምእደ ዚኣሁ ጐይይ ኢይትከሀል ወኢይደሉ። ኢይከሀል ለኈልቆ። ኤይትከሀል ከመ ዝ ይኩን። በከመ ይትከሀለከ። እስመ ቅኔ መዝሙርሰ ተከሃሊት በኵሉ ጊዜ ፡ (ማቴ፲፱ ፡ ፳፮። ጥበ፲፮ ፡ ፲፭። መክ፫ ፡ ፲፬። ዘፀ፰ ፡ ፳፪። ሢራ፴፰ ፡ ፲፩። ፊልክ ፡ ፪፻፴፰)።
ተክህነ ፡ ተካነ፤ ክህነት ተሾመ ተቀበለ፤ ካህን ኾነ ካህን ተባለ፤ ለማገልገል። ክሂን ከሹመት በኋላ ማገልገልን ፣ ተክህኖ ከማገልገል በፊት መሾምን የሹመትን ጊዜ የተቀቡበትን ዕለትና ሰዓት ያሻያል። መጽሐፍ ግን ኹለቱንም ጾታ አንድ አድርጎ ተክህነ ይላል፤ አያሰኝም። ይርዐይ መርዔተ ወይትከሀን። እስመ አንተ አዘዝከነ ንቁም ቅድሜከ ወለከ ንትከሀን። እፎ ተኀረይከ ለተክህኖ ፡ (ኪዳ። ቅዳ። መጽ ፡ ምስ)።
ተክሕደ ፡ ተካደ ተጣለ ተተወ፤ ተከዳ ዐሎ ተባለ። እለ ኵሎሙ ይትከሐዱ ወይትሀጐሉ ፡ (ሔኖ፶፪ ፡ ፰)።
ተክሊል ፡ በቁሙ፤ የግቢ ሥርዐት ቃል ኪዳን፤ ካህናት በመርዓዊና በመርዓት ላይ የሚፈጽሙት፤ የሕግ ጋብቻ ሊፈርስ የማይቻል። ቃል ኪዳኑን ተክሊል ያሰኘው የሙሽሮቹ ልብስ ጌጡ ሽልማቱ ፈርጡ ቀለበቱ ያበባው አክሊል ነው። ሶበ ተዋሰቡ በጸሎተ ተክሊል። እምቅድመ ይግበሩ ሎቱ ተክሊለ፤ ወእምድኅረ ተክሊል። አውስቦሰ ዳግሚት ተሐጽጽ እምቀዳሚት፤ ወለዛቲ ተሠርዐ በቀኖናት ከመ ኢይኩን ላቲ በረከተ ተክሊል፤ አላ ይግበሩ ጸሎተ አስተስርዮ ፡ (ፈ ፡ መ ፡ ፭ ፡ ፲፯። ፲፪ ፡ ፭። ፍ ፡ ነ ፡ ፳፬ ፡ ፩)።
ተክል ፡ (ላት፤አትክልት) በቁሙ፤ፍሬያም ዕንጨት፤ ዛፍ፤ ቅመም፤ ቅጠላቅጠል የሚበላ : የሚሸተት፤ ገነታዊ ፡ ዕፅ፤ ሕግ፣ ሥርዕት = ከመ ፡ ትት ከሱ ፡ ኵሎ ፡ ተከለ ፡ ወኵሎ ፡ ዕፀ። እኩይ ፡ ተክል ፡ ገብረ ፡ ሥርወ ላዕሌሆሙ። ኢበልዐ ፡ ፍሬያት ፡ እ ትክልት ፡ ኵላ ፡ ተካል ፡ አንተ ፡ እተክሳ ፡ ሕቡየ ፡ ት ሠሮ ፡ (ኩፋ ፡ ፯ ፡ ሢራ፫ ፡ ፳፰። ስንክ ፡ ግን፲፰። ማቴ ፲፭ - ፲፫)።
—፤ ችግኝ፤ ፍል : የተክል : ቡቃያ፤ ግልግል ፡ ገና ፡ እየ ፈለስ ፡ የሚተከል፤ ወይም ፡ ተተክሎ ፡ የጸደቀ፤ ከጽጌ: ከፍሬ ፡ ያልደረስ = ልጅ፣ አማኒ ፡ ምእመን = ሐዲስ ፡ ተከል። ተከሰ ፡ ስም። ወኢይኩን ፡ ዘእምሐዲስ ፡ ተከል ፡ ነወ ፡ ኢይትዐበይ። ተከለ ፡ ርትዕ ፡ ተክለ ፡ ጽድቅ ፡ (ኢዮ፲፬ ፥ ፬። ሕዝ፴፬ ' ፳፱ " ፩ጢሞ ፡ ፫ ፡ 7። ኩፋ ፡ ፩ና ፡ ፲፮)።
፡ ምትክ። ይፍዲ ላሕመ ተክለ ላሕሙ። ሢም ተክሎሙ። ተወልደ ሴት ተክለ አቤል ፡ (ዘፀ፳፩ ፡ ፴፮። ፫ነገ ፡ ፳ ፡ ፳፭። ዘረፋ)። ባላገባቦች ግን ስለ ፈንታ ይሉታል።
ተክዕበ ፡ ተካበ፤ ታጠፈ ተደረበ። ካባ ካቡት ማለት የዚህ ዘር ነው።
ተክዕወ ፡ ፈሰሰ ተጨመረ ፥ ተጨለጠ ፥ ተገኝቶ ኼደ። ይትከዐው ዝናም እምውስተ ደመና። ፈለግ ይትከዐው ውስተ ባሕር። ሶበ ተክዕዉ አሕዛብ ውስተ ሕብረ እከይ ወፁግ ፡ (ኢዮ፴፮ ፡ ፳፯። ሔኖ፲፯ ፡ ፭። ጥበ፲ ፡ ፲፭)።
(ጥ) ተክዞ ዞት ፡ (ተከዘ ፡ ይቴክዝ'ይተ ክዝ) መተከዝ መወዝወዝ፣እህህ ማለት፤እጥብቆ ፡ ማዘን ፣ መትከንከን፤ መጨነቅ ፡ ማስብ : ተከዘት ነፍ ስየ ፡ እስከ ፡ ለሞት ፡ ተክዘ፣ ዮናስ፣ ዐቢየ ፡ ትሓዘ። በእሱ፣ሠለስቱ ፡ ተከዘ ፡ ልብየ። ኢይቴክዝ ፡ በእ ንተ ፡ ቤቱ ፡ አልቦ ፡ ዘይቴክዝ ፡ በእንቲኣ ፡ ተከዘ ፡ እግዚአብሔር ፡ ስእለቶሙ ፡ ዐሰበ ፡ (ማር፲፬ ' ፴፬ " የኖ፬ ' ፩ " ሢራ፳፮ ፳፰ " ምሳ፳፫ - ፴፬። ኤር፲፩ ፡ ሽ - ስንጎ ፡ ሚያ፲፬ )።
—፤ መፍስስ ፡ መጕረፍ፤ መውረድ፣መኼድ፤ አለመታ ገድ፤ የውሃ ፡ የእንብ ፡ የኅሊና።
ተኰሰ ፡ (ዐማርኛ) በቁሙ፤ አቃጠለ፤ በእሳት ወይም በጋለ ብረት። ዕደውኒ ይፈቅዱ ይተኵሱ ቤተ ንግሥት ፡ (ድር ፡ ሚካ። መ ፡ ፈ)።
ተኰስተረ ፡ ተጠረገ፤ ተጠራረገ፤ ተቈጠቈጠ። ቤት ዘኢተኰስተረ። እስመ በቍላት ይትኰሰተሩ በእደ መስተገብራን ፡ (መጽ ፡ ምስ። አፈ ፡ ድ፲፪)።
ተኰስየ ፡ ተለየ ተነጠለ፤ ጠፋ ተበላሸ፤ ተነቀፈ። እስመ ኢንትዌከፍ ዘይክል ተኰስዮ። ባቍዕ ወመፍቀሬ ሰብእ ዘኢይትኰሰይ ፡ (ቄር ፡ እስት። ተረ)።
ተኰርዐ ፡ ተመታ፤ ተቈረመ። ወንትኰራዕ። በበትረ ኅለት ተኰራዕከ ፡ (፩ቆሮ ፡ ፬ ፡ ፲፩። ቅዳ ፡ ያዕ)።
ተኰነነ ፡ በቁሙ፤ ተፈረደበት፤ ተቀጣ ተሣቀየ፤ ተገዛ ዜጋ ኾነ። ዘየአምን ቦቱ ኢይትኴነን፤ ወዘሰ ኢአምነ ቦቱ ወድአ ተኰነነ። ይትኰነኑ በሰይፍ። ኅዳጠ ተኰኒኖሙ። ለኵሉ ነፍሰ መኰንን ተኰነኑ ፡ (ዮሐ፫ ፡ ፲፰። ፍ ፡ ነ ፡ ፵፯። ጥበ፫ ፡ ፭።ሮሜ፲፫ ፡ ፩)።
ተኳነነ ፡ ተፋረደ፤ ተፈራረደ። ተዋቀሠ ተወቃቀሠ ለመታረቅ። ትኳነኑ ሄሮድስ ወጲላጦስ፤ እስመ ጋእዝ ቦሙ እምቅድም። ተደመሩ ክልኤሆሙ ወተኳነኑ ወገብሩ ሰላመ በበይናቲሆሙ ፡ (ሉቃ፳፪ ፡ ፲፪። ዮሴፍ)።
ተወሀውሀ [1] ፡ (ይትወሀዋህ ይትዋህዋህ) ጠራ በራ ጸደለ፤ ውሃ መሰለ፤ በረቀ አሸበረቀ፤ አማረ ተዋበ፤ የመልክ የኅብር። ጸጋ ክበር አገኘ፤ ተደሰተ በደስታ ኖረ፤ ተመላለሰ፤ ምስጢሩ ግን ጥምቀትና ሀብተ ልደት ነው። ጻድቃንኒ ትፍሥሐተ ይትፌሥሑ ወይትወሀውሁ በአዝማን ዘአልቦ ኍልቍ፤ ደቂቃ ለቤተ ክርስቲያን ይዕቀቡ ሥርዐታ ወይትዋህውሁ ውስቴታ ወያሠንዩ ግበሪሃ። ይትወሀውሁ በኵሉ ክብር ወፍሥሓ ዘእንበለ ጻማ ወሕማም ፡ (ድጓ። ቃሌ)። እለ ቀዲሙ የዐይሉ ገዳመ ወአድባረ ወድኅረ ይትወሀውሁ በአዕጻደ ነገሥት። ይሰግዱ ላቲ ወይትወሀውሁ በቅድሜሃ ፡ (መጽ ፡ ምስ። ስንክ ፡ ነሐ፳፩)።
[2] ፡ በራ ተመላለሰ፤–ወህውሀ።
ተወለጠ ፡ ተለወጠ ተተካ፤ ሌላ ኾነ። ተወለጠ ርእየተ ገጹ። ተወለጠ ወኮነ ከመ መልአክ ያንሶሱ ማእከለ ሰብእ ተወሲጦ ፡ (ዳን፫ ፡ ፲፱። ዕር ፡ ኢሳ፱ ፡ ፴። ዮሴፍ)።
ተወላተወ ፡ ተመካከተ፤ ተሳለፈ።
ተወላዲ ፡ የተወለደ ተወላጅ ልጅ። አይቴኬ ሀሎ ዝየ ፍቁር ወላዲ፤ ወአይቴ ሀሎ ዘመድ ወላድያን ወተወላዲ። አብ ወላዲ ወኢተወላዲ፤ ወልድ ተወላዲ ወኢወላዲ ፡ (ግንዘ። አትና)።
ተወልተወ ፡ ተለበሰ፤ ተመከተ ተነገበ፤ ጌጡ። ጋሻው።
ተወልወለ ፡ ተወለወለ ተሰነገለ፤ ጠራ ፡ (ዐማርኛ)።
ተወልደ ፡ ተወለደ፤ ካባት ከናት ወጣ ተከፈለ። ዘተወልደ ወአኮ ዘተገብረ። ሕፃን ተወልደ ለነ። ወተወሊዶ ፡ (ኒቅ። ኢሳ፱ ፡ ፯። ማቴ፪ ፡ ፩)
፡ ልጅ ኾነ ተባለ፤ በልጅ ስም ተጠራ፤ ታደሰ። እምአግዚአብሔር ተወልዱ። ዘኢተወልደ ዳግመ
፡ (ዮሐ፩ ፡ ፲፫ ፡ ፫ ፡ ፫)።
፡ ተገኘ መጣ ተፈጠረ። ይትወለድ ብሩር እምጸበለ ምድር። በተካሕዶ ይትወለድ ለነ ባቍዕ። እምስካር ይትወለድ ምርዓት ወዝሙት። እምልብ ይትወለድ ኀጢአት። እምዛቲ ግብር ይትወለድ ቀትል። ሰዓል ይትወለድ እምነ ቍር ፡ (ሔኖ፷፭ ፡ ፯። ቄር ፡ ጰላ። ቀሌ። ፈ ፡ መ ፡ ፪ : ፲፩። ፳፬ ፡ ፩። አዋል)።
ተወሠረ ፡ ተቈረጠ፤ ተሠነጠቀ። እስከ ተወሠረ ለክልኤ። እለ በሞሠርት ተወሥሩ ፡ (ዕር ፡ ኢሳ፭ ፡ ፲፬። ስንክ ፡ ጥቅ፲፯)።
ተወሰቀ ፡ ታለበ ተደገነ ተዘጋጀ።
ተወሰነ ፡ በቁሙ፤ ታገገ ተደነገገ፤ ተቈረጠ። መካን ዘተወሰነ፤ ዕድሜ ዘተወሰነ። መጠን ዘተወሰነ። ተወሰነ ወተፈትሐ ላዕለ ኵሎሙ ምእመናን ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፳፰። ፴፮። ፈ ፡ መ ፡ ፲ ፡ ፫)።
ተወሰከ ፡ ተጨመረ፤ ፡ (ለት በት) በዛ። ይትዌሰኩ ዲበ ፀርነ። ወይትዌሰኩ ውስቴቶሙ ፈላስያን። ወተወሰከ ውስተ እስራኤል። ወኮኑ ሰራዊተ ሮም ይትዌሰኩ ለለ ኵሉ ዕለት ፡ (ዘፀ፩ ፡ ፲። ኢሳ፲፬ ፡ ፩። ዮዲ፲፬ ፡ ፲። ዮሴፍ)።
ተወስበ ፡ ተዳረ፤ ለሚስት ተሰጠ፤ ገቢ ኾነ። ወተወስበት ለመርቅያን። ለእመ ተወስበት ለብእሲ ፡ (ዮሐ ፡ መደ። ፈ ፡ መ ፡ ፭ ፡ ፲፪። ፍ ፡ ነ ፡ ፳፬ ፡ ፩)።
ተወሥአ ፡ ተወሣ ታሰበ፤ ተባለ ተነገረ፤ ተሰጠ፤ ቃሉ ምላሹ።
ተወስደ ፤ ተወሰደ ተይዞ ኼደ ፤ በግድ።
ተወርሰ ፡ ተወረሰ፤ ርስቱን ገንዘቡን ተቀማ፤ ሰውዮው። ወይም ርስቱ ለሌላ ዐለፈ፤ እንደ ከነዓን። ከመ ኢትትወረስ ለካልኣን ፡ (ስንክ ፡ ሠኔ፲፮)።
ተወርወ ፡ ተወረወረ ተጣለ፤ ተምዘገዘገ፤ ዘለለ መር ቸር ዱብ አለ፤ ወረደ ወደቀ። ተወረው ታሕተ። ተወርዉ ላዕሌሆሙ ውስተ እሳት። ፈቃዱ ተወርወት ኀበ ዐጸደ ወይን። ተጋብኡ ውስተ አህጉር ጽኑዓት ወንትወሮ ፡ (ማቴ፬ ፡ ፯። ፳፩ ፡ ፳፩። ዮሴፍ። ስንክ ፡ ታኅ፩። ኤር ፡ ፲፬)።
ተወርደ ፡ (ዐማርኛ) ፤ ተወረደ ፤ ዕዳውን ግብሩን ተወጣ። ውርዴ ኾነ ፤ ቂጥኝ ወጣለት።
ተወቅሠ ፡ ተወቀሠ ተመከረ፤ ተገሠጸ። ይትወቀሥ እምሰብአ ሀገር እስከ ኦሆ ይቤ ወይትመየጥ ኀበ መንበሩ ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፭)።
ተወቅረ ፡ ተወቀረ ተጠረበ፤ ተቈፈረ፤ ተዋቀረ። እብን ዘኢተወቅረ። ጽኑዓት እማንቱ ለተወቅሮ ፡ (ኢያ፰ ፡ ፴፫። ሄርማ ፡ ገ፹፩)።
ተወቅዐ ፡ ተወቃ ተመታ፤ ተገፈፈ።
ተወቅየ ፡ ተቈረጠ፤ ተቈራረጠ፤ ተገዘረ ተቀረጠፈ። በሰይፍ ተወቅየ። ጕንደ ሃይማኖት ዘኢይትወቀይ። ኢፈርሀ ሕማመ ተወቅዮ ቍልፈተ ነፍስቱ ፡ (ስንክ ፡ ሚያ፳፯። መጽ ፡ ምስ)።
ተወተ ፡ ታታ፤ ጐነጐነ፤ አዋሰበ፤ አሰረ ዐዘበ፤ የጥራዝ የድጕስ፤ የጫማ ያፎት። ሠረከን እይ፤ የዚህ መንትያ ነው።
ተወትረ ፡ ተወተረ ተገተረ፤ ተዘወተረ።
ተወነ ፡ በለገ፤ ዘነመ፤ በልግ ኾነ።
ተወን ፡ በልግ፤ ዘመነ በልግ ጸደይ፤ የበጋ የብላጊ ዝናም። ዘመነ ሐጋይ ወተወን። ዝናመ ተወን ወመፀው። ተከልአ ጠል ወተወን። ይሁብ ዝናመ ተወን ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፭። ኤር፭ ፡ ፳፬። ፫ ፡ ፫። ዘካ፲ ፡ ፩። ድጓ)
ተወከለ ፡ በቁሙ ወኪል ኾነ፤ ታመነ፤ ለሿሚው፤ ለወካዩ። አመነ ታመነ እምነቱን ጣለ በወኪሉ፤ ተስፋ አደረገ፤ ወካዩ ወኪሉን። ታመነ ማለት ባማርኛ እንደ ሳቢ ዘር ነው፤ ኹለት ያሳያል፤ ለሌላ መታመንንና በሌላ ማመን። ኪያከ ተወከልኩ እግዚኦ። ሀሉ ተወኪለከ በእግዚ። ንሕነ ተወከልናሆሙ። በተወክሎተ መጻሕፍት ፡ (መዝ ፡ ፴። ምሳ፫ ፡ ፭። ኢሳ፳ ፡ ፮። ሮሜ፲፭ ፡ ፬)
ተወካፊ ፡ የሚቀበል፤ ተቀባይ። ተወካፌ ነግድ። ተወካፌ ንስሓ
፡ (ዲድ ፡ ፲። ፈ ፡ መ ፡ ፩ ፡ ፮)።
ተወክፈ ፡ ተሰጠ ቀረበ፤ ተሰጠው ተቀበለ። ተሰጭውን መደብ አድርጎ ተቀባዩንም ያሳያል። መዐዛ ሠናይ ዘይትዌከፍ ቅድሜሁ። ተወከፍነ እምእዴሁ ቍርባነ። ዘኪያክሙ ተወክፈ ኪያየ ተወክፈ፤ ወዘኪያየ ተወክፈ ተወክፎ ለዘፈነወኒ ፡ (ኩፋ ፡ ፬ ፡ ፬። ማቴ፲ L ፵ ፡ ፵፩)።
o ወደደ ዐቀፈ ፤ ታቀፈ። ተወክፈቶ ነፍስየ። ዕድ ኢይትወከፍ
ወለተ በጥምቀት
(ኢሳ፵፪ ፡ ፩። ፈ ፡ መ ፡ ፭ ፡ ፪)።
፤ ሰማ ፤ አመነ ፤ ዕሺ አለ ፤ ታገሠ። ምስጢሩ ያው መቀበል ነው ፤ አይለወጥም። ይትወከፍ እዝንክሙ ቃለ አፉሁ። ተወከፍ ቃለ አመትከ። እለ ይትዌከፍዎ ለአርጌንስ። እኪተ ኢንትዌከፍ። ተወከፍ ኵሎ ዘመጽአከ (ኤር፱ ፡ ፳። ዮዲ፲፩ ፡ ፭። ቄር ፡ እስት። ኢዮ፪ ፡ ፲። ሢራ፪ ፡ ፬)።
ተወደ ፡ ተወደደ ተፈቀረ። ተሰካ፤ ተጨመረ፤ ፡ (ዘፀ፳፭ ፡ ፲፭)።
ተወደሰ ፡ በቁሙ፤ ተሞገሰ፤ ተመሰገነ፤ አቦ አቦ ተባለ። አብደሩ በኀበ ሰብእ ተወድሶ፤ ወለኮ በኀበ እግዚ። እስመ ይትዌደስ ኃጥእ በፍትወተ ነፍሱ ፡ (ዲድ ፡ ፳፭። መዝ ፡ ፱)።
ተወድአ ፡ ተጨረሰ፤ ተፈጸመ፤ ተፈጀ ዐለቀ። ይትዌዳእ ኵሉ እኩይ። መዛግብተ እክል ወሥርናይ ይትዌዳእ በፄፄ ወበነቀዝ። ተወድአ ወርቅነ። ፍሥሓ ዘኢይትዌዳእ ፡ (ሔኖ። መቃ። ዘፍ፵፯ ፡ ፲፰። ኪዳ)።
ተወድየ ፡ ተጨመረ ገባ፤ ተጣለ ተጫነ። ይነሥእ እምዘይትወደይ ውስቴቱ። ተወድየ ውስተ ቤተ ሞቅሕ፤ ገሪፍ እንተ ተወድየት ውስተ ባሕር። ኢተወድየ ላዕሌሃ አርዑት ፡ (ዮሐ፲፪ ፡ ፮። ዕር ፡ ኢሳ፪ ፡ ፲፫። ማቴ፲፫ ፡ ፵፯። ዘኍ፲፱ ፡ ፪)።
ተወግረ ፡ በቁሙ፤ በደንጊያ ተመታ፤ ተደበደብ ፡ (ዘፀ፲፱ ፡ ፲፫። ፳፩ ፡ ፴፪)። ለተወግሮቱ በእብን። ወበሕግነሰ ሠርዐ ሙሴ ከመ ትትወገር በእብን ፡ (ኩፉ ፡ ፴፫። ዮሐ፰ ፡ ፭)።
ተወግዐ ፡ ተጋተ፤ ገጭ ጕርጕጭ አደረገ። መጠጡንና ወጉንም ያሳያል። እለ ከልእዎሙ ኢይትወግዑ ሐሊበ። እስመ ኵሉ ዘይትወጋዕ ሐሊበ ሕፃን ውእቱ ፡ (ኢሳ፳፰ ፡ ፱። ዕብ፭ ፡ ፲፫)።
ተወግአ ፡ ተወጋ፤ ተወገጠ። ፡ (ተረት) ያወቀ ተጠነቀቀ፤ የዘነጋ ተወጋ። ሰላም ለገበዋቱከ በቅትራተ ኀጺን እለ ተወግኡ ፡ (ደራሲ)።
ተወግዘ ፡ ተወገዘ ተገዘተ፤ በግዝት ተለየ። ካህን ዘተወግዘ ፡ (አብጥ ፡ ፲)።
ተወጥሐ ፤ ተከመረ ተቈለለ። ወተወጥሐ ካዕበ እመት (ዘኍ፲፩ ፡ ፴፩)።
ተወጥነ ፤
በቁሙ ፤ ተወጠነ ተዠመረ ፤
ተበገረ። ግብአተ ሀገር
በእደ ፀር
ተወጥነ በመንግሥተ ልብነ ድንግል። ተግሣጽ ትትዌጠን እምአስተሐምሞ። ሐሳብ ይትዌጠን እምጥንተ ተውት (ታሪ ፡ ግራ። አፈ ፡ ድ፴። አቡሻ ፡ ፵፯)።
ተወጽሐ ፡ ፈሰሰ ተቀዳ፤ ገባ ተጨመረ። እስመ ተወጻሕከ በምግባር እኩይ ፡ (ሄርማ ፡ ገ፮)። በተወጽሐ ፈንታ ተዋጽሐ ይላል፤ አያሰኝም።
ተወፅኀ ፡ አማጠ፤ በምጥ ተያዘ ተጨነቀ፤ ተፈጨ ተቈላ። ወይትዌፃኅ ከመ ማሕምም እንተ ትወልድ ሕፃነ። ፡ (ሢራ፲፱ ፡ ፲፩። አፈ ፡ ተ፳፩። አርጋ ፡ ፩)።
ተወጽአ ፡ ተሸነፈ ድል ኾነ፤ ተረታ።
ተወፅፈ ፡ ተወነጨፈ ተጣለ፤ ተወረወረ። ወነፍስ ጸላእትከሰ ተወፅፈት በማእከለ ሞፀፍ። ለይትወፀፉ ፡ (፩ነገ ፡ ፳፭ ፡ ፳፱። ዘፀ፲፱ ፡ ፲፫)።
ተወፈየ ፡ ተሰጠ፤ ተሰጭ ኾነ። ተቀበለ፤ እጅ አደረገ። ሃይማኖት አንተ እምትካት ተወፈየት፤ ተሰጠች ፡ (ቄር ፡ እስ)። ተወፈያ ለርብቃ። አመ ተወፈየ መንግሥቶ። ምድረ ጽጌ ተወፈየ ዐስበ፤ ተቀበለ ፡ (ዘፍ፳፬ ፡ ፷፩። ፩ቆሮ ፡ ፲፭ ፡ ፳፬። ስንክ ፡ ጥቅ፬)።
ተዋሐሰ ፡ ተዋዋሰ ተሰጣጠ፤ ዋስ ተጣራ።
ተዋሀበ ፡ ተሰጣጠ፤ ተቀባበለ። ሕዝብ ይትዋሀቡ ሰላመ በበይናቲሆሙ፤ ብእሲ ለብእሲ ወአንስት ለአንስት ፡ (ኪዳ)
ተዋሐየ ፡ ተጐበኘ፤ ተጐበኛኘ።
ተዋሐደ ፡ (ተደራራጊ) በቁሙ፤ ተወሓሐደ ተገናዘበ፤ አንድ ኾነ፤ ምንታዌ ዐጣ። መዋሐድ ለኹለት ለሦስት ከዚያም ለሚበዛ ይነገራል። ወተዋሕዶሂ ውእቱ ዘክልኤሆሙ። ወኢኮነነ ክርስቶስ እኅወ በግብር ሐዲስ፤ አላ ለቢሶ ሥጋ ዚኣነ በተዋሕዶ ዘኢይትነገር። እስመ ተዋሕዶ አእተታ ለምንታዌ። ይሤለሱ በአካላት ወይትዋሐዱ በመለኮት ፡ (ሃይ ፡ አበ)። ግስነቱ ዐጕልና ሐውልት የባረከ ቤት እንደ ኾነ አስተውል።
ተዋሕዶ ፡ መዋሐድ አንድ መኾን፤ ኅብረት አንድነት። እግዚ ዘይሤለስ በአካሉ፤ እንዘ ተዋሕዶ ያጸንዕ በመለኮቱ ወኀይሉ። ተዋሕዶ አምላክ ወሰብእ ለክልኤ ነፈቀ። አሚነ ተዋሕዶት አምላካዊት። በእንተ ተዋሕዶ ፡ (ደራሲ። ስንክ ፡ መስ፯። ፍ ፡ ነ ፡ ፵፮። አቡሻ ፡ ፶)።
፡ ስመ ጉባኤ፤ የኤፌሶን ማኅበር ኹለቱ መቶ ጳጳሳት። ኦርቶዶክስ የኒቅያ ስም እንደ ኾነ ተዋሕዶም የኤፌሶን ስም ነው፤ የንስጥሮስን። ባህል ኅድረት ማለትን ነቅፈው አጸይፈው ስላወገዙ፤ ባህላቸውና ስማቸው በኅድረት አንጻር ተዋሕዶ ተብሏል። የኦርቶዶክስና የተዋሕዶም ባህል ባጭር ቃል ይህ ነው፤ ቃልና ሥጋ በተዋሕዶ ወልድ ዋሕድ፤ አንድ አካል አንድ ልጅ፤ ፍጹም አምላክና ፍጹም ሰብእ፤ በተዐቅቦ ኹለት ባሕርያት፤ ኹለት የባሕርይ ልደታት፤ ኹለት ግብራት። መንፈስ ቅዱስ ቅብዕ፤ በቅብዐተ መንፈስ መሲሕ ወበኵር፤ ዳግማይ አዳም ንጉሥ ካህን፤ ነቢይ ሐዋርያ ማለት ነው። የኢትዮጵያም እምነትና ትምርት ከአብርሀ አጽብሐ እስካፄ ሱስንዮስ ይህ ብቻ ነበረ፤ በሱስንዮስና በፋሲል ዘመን ግን ካራና ቅባት የሚባሉ እናዛዥ ዘድንግል እነዘኢየሱስ ኹለት ወገኖች ተነሥተው የተዋሕዶን ስም ቀምተው፤ ተዋሕዶና ኦርቶዶክስ እኛ ነን ብለው እውነተኛውን ተዋሕዶ ጸጋ የሚሉ ስም ቀብተውታል። ከነዚሁ ደግሞ ካራው እስካምስት፤ ቅባቱ እስከ ሦስት ተከፍሎ፤ ባህላቸው ፰ ዐይነት ነው። ዐሥራ ስድስትም የሚሉ አሉ፤ መጥባሕትንና ቅብዐትን ተመልከት። ፡ (መወድስ ዘኦርቶተዶክሳዊ ክፍለ ዮሐንስ) ሃይማኖተ ቄርሎስ ኮነት ግማዳተ አብድ ወኍልቈ ተመትሮ አብዝኀት ኀበ ኢሀሎ ንጉሥ፤ ካህነ ደብረ ኤፍሬም ቅድመ እምዘመተራ ነኣስ። ወአመ ኢዮርብዓም ለምሳሌ በእደ ነቢይ ዘተሠጠት ልብስ ፡ (መሳ፲፱ ፡ ፳፱ ፡ ፴። ፫ነገ ፡ ፲፩ ፡ ፴ ፡ ፴፩)።
ተዋለደ ፡ በቁሙ፤ ተራባ ተባዛ። ይትባዝኁ ወይትዋለዱ። ኢይትዋለዱ ፡ (ኢዮ፴፬ ፡ ፬። ገድ ፡ ተክ)። በወለደ ፈንታ ተዋለደ ይላል፤ ስሕተት ነው። ንኡሳትሂ ያውስባ ወይትዋለዳ። ወእትዋለድ እምኔሃ ፡ (፩ጢሞ ፡ ፭ ፡ ፲፬። ዘፍ፴ ፡ ፫)።
ተዋለጠ ፡ ተላወጠ ተለዋወጠ፤ ተወጃጀ። በእንተ ተዋልጦ። እስመ እግዚ ተዋለጠ ዓለመ በክርስቶስ፤ ቦቱ ተዋለጠነ ፡ (ሩት፬ ፡ ፯። ፪ቆሮ ፡ ፭ ፡ ፲፱። ቄር ጰላ)።
ተዋልጦ ፡ መለዋወጥ መቀያየር፤ መፈራረቅ። በእንተ ምክንያተ ተዋልጦ ጠባይዐ ዕጓለ መሕያው ፡ (ፈ ፡ መ ፡ ፩ ፡ ፫)።
ተዋሠረ ፡ ተሳሰበ ተገዛገዘ፤ አንዱን መጋዝ ለኹለት ይዞ።
ተዋሰበ ፡ በቁሙ፤ ተወሳሰበ፤ ተጋባ ተዛመደ ተገናዘበ። ትትዋሰቡ ምስሌሆሙ። ኢያወስቡ ወኢይትዋሰቡ። እመ ኮነ አሐዱ እምተዋሳብያን ድንግለ። እሎን ተዋስቦታት ፡ (ኢያ፳፫ ፡ ፲፪። ማቴ፳፪ ፡ ፴። ፈ ፡ መ ፡ ፭ ፡ ፲፯)። በተዋስቦ ፈንታ አውስቦ ይላል፤ አያሰኝም። ክቡር አውስቦ በኵለሄ ፡ (ዕብ፲፫ ፡ ፬)።
ተዋሰነ ፡ በቁሙ፤ ተወሳሰነ ተዳካ፤ ተካለለ ተደናበረ። ኤማት እንተ ትትዋሰና ፡ (ዘካ፱ ፡ ፪)።
ተዋሲማ ፡ (ዐረ ታሱም፤ ብ ተዋሲም) ጫማ መጫሚያ፤ ወይም የኮከብ ስም፤ ኹለቶ እንደ ማለት ፡ (አቡሻ ፡ ፶)።
ተዋሣኢ ፡ ተሟጋች ተከራካሪ። ሶበ ይትዋሣእ ተዋሣኢ ፡ (አፈ ፡ ድ፳፯)።
ተዋሥአ ፡ ተመላለሰ ተከራከረ፤ ተሟገተ ተባባለ። አልቦ ዘይትዋሥአኒ። ኢትትዋሣእ በኀበ ጸዓሊ። ወተዋሥኦ እለእስክንድሮስ ፡ (ኢሳ፲ ፡ ፲፬። ሢራ፰ ፡ ፲፩። ፍ ፡ ነ ፡ መቅ)።
ተዋረሰ ፡ ተወራረሰ፤ ተካፈለ ተለፋፈለ፤ ተተናተነ። ኢይባኡ ውስተ ተዋርሶ። ለተዋርሶ ዘኢይበለ። ተዋረሱ ኵሎ ደወሎሙ። ወሱቱፋኒሁ በተዋርሶ ፡ (ፈ ፡ መ ፡ ፭ ፡ ፫። ፩ጴጥ ፡ ፩ ፡ ፲፭። ዮዲ፭ ፡ ፲፭። አፈ ፡ ድ፮)።
ተዋረደ ፡ (ወረደ) በቁሙ፤ ወረደን እይ። ተወራረደ እሰጥ አገባ ተባባለ፤ ውርድ ተናዛ።
ተዋራሲ ሞረስ ፡ (ብ መዋርስት) የሚዋረስ የሚመራረስ፤ ተዋራሽ ተወራራሽ፤ ድፍን አቋራሽ ርቢት አጋማሽ፤ ተካፋይ ባላንጣ ባለጢንጦ፤ አለቃና ምንዝር ተከታይና በኵር። ተዋራሴ ስሙ። ኵሎ ተግባረከ ይትካፈሉ መዋርስቲከ። እሁብ ገራውሂሆሙ ለመዋርስት። ወእምከመሰ ውሉደ እግዚ ንሕነ፤ ወራስያኒሁ ንሕነ፤ ወእምከመሂ ወራስያነ እግዚ ንሕነ መዋርስቲሁ ለክርስቶስ ንሕነ፤ ወእምከመ ዐረይነ ሕማመ ንዔሪ ክብረ ምስሌሁ ፡ (ስንክ ፡ ጥቅ፲፫። ሢራ፲፬ ፡ ፲፭። ኤር፰ ፡ ፲። ሮሜ፰ ፡ ፲፯። ኤፌ፫ ፡ ፮)።
ተዋቀሠ ፡ በቁሙ፤ ተሟገተ ተከራከረ። ንዑ ንትዋቀሥ። ኵሉ ይትዋቀሥ ለእኁሁ። ኢክህለት ተዋቅሦተክሙ ፡ (ኢሳ፩ ፡ ፲፰። ፵፩ ፡ ፮። ዳን፩ ፡ ፶፯)። በወቀሠ ፈንታ ተዋቀሠ ይላል፤ አያሰኝም። ተዋቀሥዋ ለእምክሙ። መኑ ይትዋቀሦሙ ፡ (ሆሴ፪ ፡ ፬። ሮሜ፰ ፡ ፴፫)።
ተዋነየ [1] ፡ ተጫወተ፤ ተጨዋወተ፤ ተነጋገረ። ደቅ ወአዋልድ ዘይትዋነዩ። እንዘ ይትዋነያ በመሰንቆ። እምከመ ተዋነይከ ምስሌሁ ፡ (ዘካ፰ ፡ ፭። መሳ፳፩ ፡ ፳፩። ሢራ ፡ ፴፱)።
[2] ፡ ተጨዋወተ፤–ዋነየ።
ተዋናዪ ፡ የሚጫወት፤ ተጫዋች ጨዎታ ዐዋቂ።
ተዋዐለ ፡ ተዋዋለ፤ ተሰማማ። ተካሀለን እይ።
ተዋከተ ፡ ተጪጯኸ፤ ተዋካ ተተራመሰ። ኢትትዋከት ምስለ ሰብእ። ኢትትዋከቱ እስከ ንሠወጥ ኀቤክሙ ፡ (አረጋ ፡ ድ፩። ዘፀ፳፬ ፡ ፲፬)።
ተዋከፈ ፡ ተቀባበለ ተሰጣጠ።
ተዋክሐ ፡ ተዋካ ተደናፋ፤ ተጪጯኸ ተሟገተ፤ ተከራከረ ተወዳደረ። ማኅበረ አጋንንት እለ ይትዋክሑ። ወተዋክሑ በበይናቲሆሙ። መኑ እንከ ተረፈ ተዋካሒ። ይትዋክሖኑ ማኅቶት ለፀሓይ ፡ (ገድ ፡ ተክ። ሉቃ ፡ ፳፪ ፡ ፳፬። ቄር)።
ተዋደየ ፡ ነገር ተሣራ፤ ተማማ ተካሰስ፤ ተጣላ።
ተዋደደ ፡ በቁሙ፤ ተገባ ተመቸ ተሰማማ፤ ተሳካ ተዛመደ፤ ጸና ተደላደለ። ፡ (ምሳ፲፯ ፡ ፯። ፲፱ ፡ ፲፬)። አላ ተዋደደ ወተደለወ ዝንቱ ስም ለዘበሥጋ ተወልደ። ዘቦቱ የኀድር ኵሉ ሥጋ ወይትዋደድ በአሥራው ወመሌሊት። ሠነየ ንብረተቶሙ ወተዋደደ፤ ሶበ ተዋደደ ትእዛዙ። ተዋደደ ነገርነ ወረትዐ መንግሥትነ ፡ (ቄር ፡ ጰላ። ቆላ፪ ፡ ፲፬። ዮሴፍ)።
ተዋድዶ ፡ መዋደድ መሰማማት፤ በፍቅር በችንካር አንድ መኾን።
ተዋገረ ፡ ተማታ ተወራወረ፤ ደንጊያ ተጣጣለ ፡ (ግብ ፡ ፲፬ ፡ ፭)።
ተዋገዘ ፡ በቁሙ፤ ተገዛዘተ ተማማለ፤ ተለያየ፤ ተከራከረ ፡ (ሔኖ፮ ፡ ፬)። ከመ እትዋገዞ ለልብየ ወእሬስዮ መልአከ በማለት ፈንታ ግዘተ እትዋገዞ ይላል ፡ (፫ነገ ፡ ፲፩ ፡ ፴፬)።
ተዋግአ ፡ ተዋጋ፤ ተተማተመ። ይትዋግኡ በኵናት ፡ (አዋል)።
ተዋጥሐ ፡ ተካመረ ተከማመረ፤ ተነባበረ። አሐቲ ውስተ ካልእት ይትዋጣሕ ፡ (መጽ ፡ ምስ)።
ተዋፀፈ ፡ ተወናጨፈ፤ ተወነጫጨፈ ተወራወረ።
ተዋፅአ ፡ ተዋጣ፤ ተወጣጣ፤ የድግስ የገንዘብ የቃል።
ተዋፈረ ፡ ተሰማራ ተሰመራራ፤ እየብቻው ኼደ ተሠራጨ፤ ዕዳሪ ለመውጣት ወገብ ለመምከር። ወቦአ ይትዋፈር ፡ (፩ነገ ፡ ፳፬ ፡ ፬)።
ተውህበ ፤ ተሰጠ ታደለ ፤ ዐለፈ። ወልድ ተውህበ ለነ። ዝናም አበየ ተውሀቦ ለምድር። ተውህበ መብልዐ ለአንስርት። ተውህቦ ትትወሀብ ዛ ሀገር (ኢሳ፱ ፡ ፮። ኵፋ ፡ ፵፪። ኢዮ፲፭ ፡ ፲፫። ኤር፵፩ ፡ ፪)።
፡
ኾነ ፤ ተደረገ። ተውህቡ
ታሕተ እደዊሁ (ኵፋ ፡ ፲፩)። ተዋበ አማረ ውበት አገኘ።
ተውሕሰ ተወሐሰ ፡ ተዋሰ፤ ዋስ ኾ እዋሳለኹ አለ። አልቦ ዘይትወሐሰክሙ። ኢይደልዎ ለካህን ከመ ይትወሐስ አሐደሂ ወየአኀዝ ንዋየ ፡ (ቀሌ። ፍ ፡ ነ ፡ ፳፯)።
፡ አውሱኝ አለ፤ ተዋሰ ወሰደ። ተወሐሲ ለኪ ንዋየ ልሕኵት እምኀበ ጎርኪ። ዕሴተ ተወሓሲ። ለእመ ተውሕሰ ብእሲ እምቢጹ እንስሳ ፡ (፬ነገ ፡ ፬ ፡ ፫። ፍ ፡ ነ ፡ ፳፱። ፵፭)።
፡ ተሰጠ፤ ካዋሽ ወደ ተዋሽ ኼደ ዐለፈ፤ ዕቃው ከብቱ። ንዋይ ዘይትወሐስ ለእመ ነበረ ውስተ እደ አሐዱ ሠላሳ ዓመተ ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፴፯)። ዳግመኛም፤ በወሐሰ ፈንታ አውሐሰ እንዲል፤ በተውሕሰም ፈንታ አስተውሐሰ ይላል፤ ኹሉም ስሕተት ነው። ወአስተውሐሱ እምግብጽ ንዋየ ብሩር ወወርቅ ወልብስ ፡ (ዘፀ፲፪ ፡ ፴፭)።
ተውኅጠ ፡ ተዋጠ፤ ሰጠመ ዘቀጠ። ዘኢይትወኀጥ ፡ (ኢዮ፳ ፡ ፲፰። ሔኖ፹፫ ፡ ፬)።
ተውላጠ ፡ (ዐቢይና ደቂቅ አገባብ) ስለ፤ ምስጢሩ ለውጥን አይለቅም። ተውላጠ ሴሰይዎ፤ ስለ መገቡት ፡ (ስንክ ፡ መጋ፰)። ደቂቅ ሲኾን በብትን ይገባል። ተለዐለ ሞገሰ ስሙ ተውላጠ ጻማሁ ወሕማሙ። ተውላጠ ዝ ፡ (ስንክ ፡ ነሐ፲፮። ዮሴፍ። ፡ (ዕር፲፱ ፡ ቍ፷፱)።
ተውላጥ ፡ (ጣት) መለወጥ መለዋወጥ፤ ውላጤ ፡ (ያዕ፩ ፡ ፲፯)። ከመ ተውላጥ ዘረከባ። ተውላጣት። አልቦቱ ቱስሕት ወኢተውላጥ ግሙራ ፡ (አፈ ፡ ተ፲፮። ፴፪። ሃይ ፡ አበ ፡ ብን)።
፡ ለውጥ ዋጋ፤ ቤዛ። ለዐርክ ምእመን አልቦቱ ተውላጥ። ኢወርቅ ሤጡ ወኢብሩር ተውላጡ። ረሰይኩ ለከ ተውላጥከ ግብጸ። ተውላጠ ዓለም ፡ (ሢራ፮ ፡ ፲፭። ድጓ። ኢሳ፵፫ ፡ ፫። ሔኖ፰ ፡ ፩)።
ተውሳክ ፡ (ካት) ጭማሪ፤ ተጨማሪ የስፍር የቍጥር ማማያ ማስተካከያ። ዘእንበለ ተውሳክ ወኢሕጸት። ወተውሳክክሙ ሰመንቱ። ተውሳካት ፡ (ዮሴፍ። ስንክ ፡ መጋ፬። ፍ ፡ ነ ፡ ፴፬)።
፡ ትርፍ ተረፍ ቀሪ፤ ከስፍር ከቍጥር ያልገባ። እነግሥኑ ዐሠርተ ዓመታተ፤ ወይቤሎ እወ ዕሥራ ዓመተ ወሠላሳ ዓመተ ወተውሳከ፤ ወይቤሎ ሚ መጠን ተውሳኩ ፡ (ዮሴፍ)።
፡ ብዛት፤ ብዙነት። በእንተ ተውሳክ መብልዕ ወመስቴ።ለእመ ፈቀደ ፈጽሞ ጽድቅ ወተውሳከ ትሩፋት ፡ (ፈ ፡ መ ፡ ፲፬ ፡ ፩። ፴፫ ፡ ፮)። ባማርኛ ግን በሽታ ማለት ነው፤ ተውሳካም እንዲሉ።
ተውር ፡ (ዐረ ሰውር፤ ተውር) ስመ ኮከብ ኔላናዊ፤ ካሥራ ኹለቱ መናዝሎች አንዱ። ፍችው በሬ ማለት ነው፤ ከፀሓይ ጋራ በሚያዝያ ወር ፴፩ ዕለት ካ፲፪ ኬክሮስ ይመግባል። እልተውር ፡ (አቡሻ)።
ተውት ፡ (ቅብጥ) ስመ ወርኅ፤ መዠመሪያ ወር፤ መስከረም ፡ (አቡሻ ፡ ፰)።
ተውኔት ፡ ጨዎታ ዘፈን፤ ብዙ ስምና ስልት መሣሪያ ያለው። ቃለ ተውኔት። ንዋየ ተውኔት። ቤተ ተውኔት። መካነ ተውኔት። ዘከመ ተውኔቶሙ። ወኀያላን ተውኔቱ
፡ (ኤር፴፯ ፡ ፲፱። ዳን፫ ፡ ፯። ዲድ ፡ ፳፯። ግብ፲፱ ፡ ፳፱። ጥበ፲፪ ፡ ፳፭። ዕንባ፩ ፡ ፲)።
ተውዕረ ፡ ተደነቀ፤ ዕጹብ ተባለ።
ተውዳስ ፡ (ሳት) ውዳሴ ምስጋና፤ የሚገባ የማይገባ።
ተዘልፈ ፡ ተዘወተረ፤ ተለመደ። በቁሙ፤ ተዘለፈ ተሰደበ በገዛ አፉ፤ ተጸጸተ ተወቀሠ በኅሊናው። እመ ተዘከርኩ ተዘለፍኩ።ወባሕቱ በዘተዘለፍኩ ተመሰውኩ። ቦ እለ ይዘለፉ ወይትመውኡ ፡ (ኢዮ፳፩ ፡ ፮። ፵፪ ፡ ፮። ቄር)።
ተዘመረ ፡ በቁሙ፤ ተዘራ ታጨደ። ምስክር ተጠራ፤ ተጠቀሰ። ተመስገነ ተወደሰ። ተዜመ ተቃኘ ተደረደረ። ልማዱ ግን አድራጊ ነው።
ተዘምደ ፡ ተዘመደ፤ ዘመድ ኾነ ተሰማማ። እሉ እለ ይዘመዱ ወይሰናሰሉ፤ እስመ ተወልዱ እምአበው ወእምሔዋን። ለእመ ዘመወ ምስለ ካልእት ዘትዘመድ ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፳፬ ፡ ፪። ፈ ፡ መ ፡ ፭ ፡ ፫)።
ተዘርዐ ፡ ተዘራ ፡ ተበተነ፤ ዘሩ። ተዘራበት ተተከለበት፤ ርሻው። ኅቡረ ተዘራዕነ ማእከለ ከርሥኪ። ዘርዕ ዘይዘራዕ። ምድር ዘኢይዘራዕ ፡ (ኩፋ ፡ ፴፭። ዘሌ፲፩ ፡ ፴፯። ኤር ፡ ፪ ፡ ፪)።
ተዘርከየ ፡ ተዘርከየ፤ ተሰደበ፤ ስሙ ጠፋ፤ ወሬው ከፋ።
ተዘርወ ፡ ተዘራ ተበተነ፤ ተበታተነ። እምህየ ተዘርዉ ውስተ ኵሉ አህጉር። ኵልክሙ ትዘረዉ ለለ አሐዱ ውስተ መካኑ።እስመ ጽሑፍ እቀትሎ ለኖላዊ ወይዘረዉ አባግዕ ፡ (ኩፋ ፡ ፲። ዮሐ፲፮ ፡ ፴፪። ማቴ፳፮ ፡ ፴፩)።
ተዘርዘረ ፡ ተዘረዘረ ተፍታታ፤ ተለያየ ተበታተነ፤ ጠፋ ከንቱ ኾነ። ይትከሀልኑ ይሕየው ዘማሰነ ወዘተዘርዘረ። አዘዘ ይሥትርዎሙ በአጽፋረ ኀጺን ከመ ይዘርዘር ሥጋሆሙ። ወይዘርዘር ኵሉ ዘፍጥረታተ ሕምዝ። ጸለየ ቅዱስ ማእከለ እሳት ወተዘርዘረ ውእቱ አሳት ወወፅኦ ቅዱስ እምኔሁ ፡ (ኪዳ። ስንክ ፡ ታኅ፲፪። ቅዳ። ስንክ ፡ ኅዳ፲፱)።
ተዘብጠ ፡ ተዘበጠ፤ ለጥ አለ ተካከለ። ተመታ ተወቃ፤ ተደበደበ። ሥልሰ ተዘበጥኩ በአብትር። ሰገም ተዘብጦ። ከበሮ ዘይዘበጥ ፡ (ተረ ፡ ቄር። ዘፀ፱ ፡ ፴፩። ፩ቆሮ ፡ ፲፫ ፡ ፩)።
ተዘንግዐ ፡ ተዘነጋ ተረሳ፤ ጠፋ ቀረ።
ተዘንጐጐ ፡ ተሽሟጠጠ፤ ተሰደበ ተነቀፈ፤ ማላገጫ ኾነ። ወተዘንግየጉ በኀበ ሀለዉ ፡ (ዘዳ፴፪ ፡ ፴፮)።
ተዘክረ ተዘከረ ፡ ታሰበ፤ ትዝ አለ ተወሣ፤ ተጠራ፤ ተነገረ። ልማዱ ግን እንደ ዘከረ አድራጊነት ነው። ወተዘከረ ሣህሎ። ተዘከረኒ በመንግሥትከ። ተዘከርኩ በሌሊት ስመከ እያለ፤ ገንዘቡን ተገብሮነትን ትቶ አለገንዘቡ ይነገራል።
ተዘወ(ው)ረ ፡ ተዞረ ተከበበ ተጠበቀ። ይዜውሩ ከመ አባግዕ። ነፍስ ዝልፍት ኢትዜወር ፡ (አዮ፳፩ ፡ ፲፩። ሢራ፲፬ ፡ ፲፫)።
ተዘውገ ፡ ተዘወገ ተጠመደ፤ ዘውግ ኾነ ተባለ።
ተዘግሐ ፡ ተዘጋ፤ ተዘጋበት። ተዘግሖ ውስተ ቤተ ሞቅሕ። ሶበ ወፅኡ እምተዘግሖቶሙ። ፍኖተ ተዘግሖ በውስተ ገዳም ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፳። ፊልክ ፡ ፻፷፬። ገድ ፡ ኪሮ)።
ተዘግበ ፡ ተዘገበ ተሰበሰበ፤ ደለበ ተጠበቀ። በኀቤከ ተዘግበት ጥበብ። ብዕል ዘይዘገብ በዐመፃ። ይዘገብ ለጻድቃን ብዕለ ረሲዓን ፡ (ኢዮ፲፭ ፡ ፰። ፳ ፡ ፲፭። ምሳ፲፫ ፡ ፳፪)።
ተዘግዐ ፡ ተዘጋ፤ ተሰነገ ተወተፈ። ዘግሐን እይ፤ የዚህ መንቲያ ነው።
ተዘግደየ ተዘጋደየ ፡ ተዘጋጀ፤ ተዘገጃጀ። ተሰካተዩ ወተዘጋደዩ ለመዊት ፡ (ነግሥ)።
ተዛለፈ ፡ ተዘዋተረ፤ ተዘወታተረ። በቁሙ፤ ተሳደበ ተሰዳደበ፤ ተሟገተ ተከራከረ። መደቡ መደራረግ ሲኾን ማድረግም አለበት። ኢትዛለፍ በማእከለ ሊቃውንት። ለማርያም እኅተ ሙሴ ሶበ ተዛለፈት እውፅእዋ እምትዕይንት። እምድኅረ ተዛለፉ በስምዕ ከመ ቀታሌ ነፍስ ውእቱ። ይዛለፎሙ ለብዙኃን አሕዛብ ፡ (ሢራ፯ ፡ ፲፬። ዲድ ፡ ፴፩። ቀሌ። ኢሳ፪ ፡ ፬)።
ተዛመደ ፡ በቁሙ፤ ተዘማመደ፤ ተሰማማ። መዛመድ በ፪ ወገን ነው፤ በሥጋ በነፍስ፤ ለኹለቱም ብዙ ስልት አለው።
ተዛበጠ ፡ ተማታ ተደባደበ፤ ተቀናደበ። እለ ይትላሀዩ ወይዛበጡ ወይትጋደሉ። ኅሊናት እለ ይዛበጡ በበይናቲሆሙ ፡ (አፈ ፡ ተ፲፱። አረጋ)።
ተዛነፈ ፡ በቁሙ ተዛነፈ። ፡ (ግጥም፤ ስለ ሳውልና ስለ ኬፋ ሞት) ጳውሎስ ታርዶ በኔሮን ሰይፍ፤ ኹለቱ ዓመት ፈርጅ ሳይዛነፍ፤ ሰቅሎ ለመግደል በመጨረሻ፤ ወሰዱት እንጂ ከምሥራቅ ዋሻ፤ ጴጥሮስን ማርካ ከባቢሎን፤ ሮም እንድትከብር እንድትገን።
ተዛወገ ፡ በቁሙ፤ ተጋባ ተጣመደ፤ ተዛመደ ተመሳሰለ፤ ተካከለ ተዋገነ። ዘይሬእያ ለዘማ ይዛወጋ ለሙስና። ዛቲ ኀጢአት ትዛወግ ምስለ ዘይክዑ። በዘይዛወጎ ለግብር። ሰላም ለአስናንኪ ሐሊበ ዕጐልት ዘተዛወጋ ፡ (ምሳ፳፰ ፡ ፯። ፈ ፡ መ ፡ ፲፫። አፈ ፡ ተ፲፫። ደራሲ)።
ተዛውዐ ፡ ተጫወተ፤ ተጨዋወተ፤ ተናገረ ተከራከረ፤ በጨዎታ ቃል። ኢትዛዋዕ ምስለ መሰንቃዊት። በከ ይዛዋዕ። ተዛውዖ ደቂቅ። ዘፈቀድኩ እምእሉ ኵሎሙ ይዛወዕ ምስሌየ ወእዛዋዕ ምስሌሁ፤ ተዛውዖ ምስለ አኀው በቃለ መጻሕፍት ትጠዕሞሙ ለለባውያን እምኵሉ ጣዕማት ፡ (ሤራ፱ ፡ ፬። ፬ነገ ፡ ፱ ፡ ፲፩። አፈ ፡ ተ፲፩። ፈላስ ፡ ገ፴፭)።
ተዜነወ ፡ (ይዜኖ) ተወራ ተነገረ፤ ቃሉ። ተረዳ ተማረ ተበሠረ፤ ሰውዮው። ዕበየ ዝንቱ ጻድቅ ሶበ ተዜነወ። ወነዳያን ይዜነዉ ፡ (ስንክ ፡ ሚያ፯። ማቴ፲፩ ፡ ፭)።
ተዝኅረ ተዘኀረ ፡ ተዣረ ታጀረ፤ ተጓደደ ተጐላመመ፤ ያካኼድ ያለባበስ። ተዝኅአ አዋልደ ጽዮን ወየሐውራ እንዘ ያገዝፋ ክሣዶን። ኢትዘኀር በሥነ አልባሲከ ፡ (ኢሳ፫ ፡ ፲፮። ሢራ፲፩ ፡ ፬)። ታበየ ኰራ ተመካ፤ የግብር ያነጋገር። ተዘኀረት ልብከ። ተዘኀሩ ፀርየ። ተዘኀሩ ላዕለ ብሔርየ። ለምንት ይዜኀር ኀያል በእከዩ ፡ (ዐብድ ፡ ፫ ፡ ። ሰቈ፩ ፡ ፫። ዘካ፪ ፡ ፰። መዝ ፡ ፶፩)።
ተዝሕቀ ፡ ተዛቀ። ተገፈፈ፤ ተላጠ። ተዝሕቀ አነዳሆሙ ፡ (ስንክ ፡ ሐም፭። ገድ ፡ አዳ)።
ተዝኪር ፡ (ዐረብ) ገዳም፤ የመነኵሴ ቦታ ቤት በኣት ፡ (ስንክ ፡ የካ፱)። አንዳንድ መጣፍ። በተዝኪር ፈንታ ተክዚር ይላል፤ የተሳሳተ ነው።
ተዝካር ፡ በቁሙ፤ ዝኒ ከማሁ፤ መታሰቢያ በዓል መሥዋዕት ጸሎት፤ ንባብ ቃል ነገር። ወከመ ዝ ግበሩ ተዝካርየ። ግብር ሎቱ ተዝካሮ። ዘይሁብ ስኂኒ ለተዝካርየ። ተዝካረ ስእለት ፡ (ሉቃ፳፪ : ፲፱። ሢራ፴፰ ፡ ፳፫። ኢሳ፷፮ ፡ ፫። ጦቢ፲፪ ፡ ፲፪)።
፡ ወግ ታሪክ ዜና። መጽሐፈ ተዝካር። ተዝካረ ኖብያት። ጸሓፌ ተዝካር ፡ (ሚል፫ ፡ ፲፮። አስቴ ፡ ፩። ኢሳ፴፮ ፡ ፫)። የዝክርና የተዝካር ዘይቤ በማናቸውም ስልት ቢነገር ምስጢሩ ከመታሰቢያነት አይወጣም።
ተዝያነወ ፡ (ይዝያነው ይዝያነው) ተነጋገረ፤ ተጨዋወተ። እንዘ ይዝያነዉ ዕበያቲሁ ለእግዚ። ሶበ ንዝያነው በእንተ አሐዱ ብእሲ። ዜና ይነብር ለዓለም ወይዝያነዉ ቦቱ ትውልድ እምድኅረ ትውልድ። ወተዝያነዉ ዳኅናሃ ለኢየሩሳሌም ፡ (ስንክ ፡ የካ፫። አፈ ፡ ድ፩። ዮሴፍ። መዝ ፡ ፻፳፩)።
ተየውሀ ፡ (ተገብሮ) የዋህ ኾነ፤ ቀና ለዘበ፤ ተገራ ለመደ፤ የወይፈን የበቅሎ ላውሬም ይኾናል። ተሞኘ ተታለለ ተሸነገለ። አኮ ከመ ሰብእ ዘይትዬዋህ እግዚአብሔር። በተየውሆ ፡ (ዘኍ፳፫ ፡ ፲፱። ሮሜ፲፮ ፡ ፲፰)።
ተየድዐ ፡ ታወቀ ተረዳ፤ ተሰማ ተባለ ተነገረ። ከመ ይትየዳዕ ስምየ ውስተ ኵሉ ምድር። ተየድዐ ነገሩ ውስተ ሀገር። በከመ ተየድዐ ወተነግረ በዐሠርቱ ወክልኤቱ አንቀጽ ፡ (ዘፀ፱ ፡ ፲፮። ዮሴፍ። አቡሻ ፡ ፴፱)።
ተዪህ ሆት ፡ ተዪህ ሆት ፡ (ቴህ ይተይሀይቲህ። ዐረ ፡ ተሀ። ዕብ ፡ ታህህ) መዞር ፡ መቀላውጥ | ፡ ። ፡ መዞር ፡ መቀላውጥ፤ ከሰው ፡ ደጅ ፡ መቀመጥ፣ ሊበሉ ማየት ፣ ማፍጠጥ፤ እ ንድ፣ ውሻ ፡ መኾን። ትሕለን ተመልከት፤ የዚህ ጎሮ) ነው።(ተረት) ፣አጐንብሶ በላን ተኝተኽ ፡ ቀላውጠው።
— ማዕር ፡ ችቦ ማድረግ፣ የቅጥቅጥ ፡ የጭራሮ "
ተያሂ ፡ (ሂት ፡ ህያን ፡
ያት) የሚቀ
ውጥ : ቀላዋጭ፤
እፍጣጭ።
ተያፍን ትያፍን ፡ ወይፋፍን፣ወይፈኖች' ወይፋፍኖች ፡ ኵሉ ፡ ሃገሩ ተደፍን ፡ ወብዕራ፣ እስክ ፡ ያገርር ፡ ትድፍ ፡ ሁ ፡ ከመ ፡ ተደፍን ፡ ወብዕራ፣(ሚ ራ፴፰ ፡ ፳፭ ፡ ፳፮ ▪ ስንዝ ፡ ግን፲፩)።
ተይ ፡ (ጽር ፡ ቲዮን) |ዲን ፡ ድኝ፥ ዳራ፣ ክብራት ፡ እሳት፣ወተይ ፡ (መዝ ፡ ፩ = ዘፍ፲፬ ፡ ፳፬። ራእ፬ ፡ ፲፯)።
ተይህደ ፡ ይሁዲ ኾነ፤ በኦሪት በግዝረት አመነ። ቦኑ ለዐይነ ሰብእ ይትየሀዱ። አኮኑ በክዱን ይትየሀዱ። ምንት ረባሁ ለተይህዶ። እለ ይትየሀዱ ምጽአተ ዚኣሁ ፡ (ሮሜ፪ ፡ ፳፰ ፡ ፳፱። ፫ ፡ ፩። ገላ፪ ፡ ፲፬)።
ተደለ ተደለለ ፡ በቁሙ ተከፈከፈ ተበጠረ፤ ተቈነደለ።
ተደለወ ፡ ተዘጋጀ ተደራጀ፤ ተሰናዳ። ተደላደለ ተቀማጠለ፤ ተድላ አደረገ በተድላ ኖረ፤ ተደሰተ። ተደለዉ አሕዛብ ለጸብእ። ተደለው ከመ ትሑር። ወመጽአ ሳኦል ተደሊዎ። ባዕድ ይዴሎ በንዋየ ዚኣሁ። ከመ ትደሎ አመ ተድላሁ። እምትደለው ወትትፈጋዕ በንዋየ ነኪር ፡ (አስቴ፩ ፡ ፮። ጦቢ፭ ፡ ፲፯። ፩ነገ ፡ ፳፮ ፡ ፬። ኢዮ፲፰ ፡ ፳። ሢራ ፡ ፳፱ ፡ ፪ ፡ ፳፪)።
ተደልወ ፡ ተመዘነ፤ ተካከለ ፡ (ሔኖ፵፩ ፡ ፩። ፵፫ ፡ ፪)። እስመ በመዳልው ተደልወ ዓለም። ሶበ ተደልወት ምስለ ብርሃን ፡ (ሱቱ ፡ ዕዝ፪ ፡ ፵፮። ጥበ፯ ፡ ፳፱)።
ተደመረ ፡ በቁሙ፤ ገባ ተጨመረ፤ አንድ ኾነ ተዋሐደ፤ ገጠመ ተገናኘ። ኢይዴመር ኀጺን ምስለ ልሕኵት። ኤፍሬም ተደመረ ምስለ አሕዛብ። እምክልኤቱ ህላዌ ተደመረ አሐዱ ክርስቶስ። አኀዙ ይደመሩ ምስለ አዋልደ ሰብእ ፡ (ዳን፪ ፡ ፵፫። ሆሴ፯ ፡ ፰። ቄር። ኩፋ ፡ ፬)።
ተደምሰሰ ፡ ተደመሰሰ፤ ተፋቀ ጠፋ፤ እንዳልንበረ ኾነ። ይደመሰሱ እመጽሐፈ ሕያዋን። ኢይደመሰስ ነገርየ እምልብክሙ። ብፅል ዘይዘገብ በዐመፃ ይደመሰስ በእንተ ተደምስሶቱ ለዝ ዓለም ፡ (ኩፋ ፡ ፴። ሔኖ፺፬ ፡ ፭። ኢዮ፳ ፡ ፲፭። ዕር ፡ ኢሳ፩ ፡ ፭)። ተቃተሉ ተጻብኡ ተጣፍኡ በማለት ፈንታ ተደምሰሱ ይላል፤ ስሕተት ነው። ተደምሰሱ በበይናቲሆሙ ፡ (ዮሴፍ)።
ተደረ ፡ (ይዴረር ይደረር) ታረተ፤ እራት በላ ተጋበዘ። እምድኅረ ተደሩ። እንዘ ይዴረሩ። ሶበ አኅለቁ ተደሮ። ኖመ ዘእንበለ ይደረር። ምንተ ተደረርከ ፡ (ሉቃ፳፪ ፡ ፳። ዮሐ፲፫ ፡ ፪። ጦቢ፰ ፡ ፩። ዳን፮ ፡ ፲፰። ሄርማ)።
ተደራበየ ፡ ተወራወረ፤ ተዋጋ ተማታ። ወራዙትኒ ተደራበይዎሙ። ይደራበዩ ዕደው በአሕጻት ፡ (ዮዲ፲፮ ፡ ፲፪። ፊልክ ፡ ፻)።
ተደርሰ ፡ ተደረሰ፤ ተጣፈ ተተረጐመ። ወለእመ ተደርሰ ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፵፭)።
ተደርገ ፡ ተሠራ ተደረገ፤ ተደራጀ፤ ገጠመ አንድ ኾነ። ይደረጉ ክልኤቱ ፡ (ሕዝ፩ ፡ ፲፩)።
ተደበ ፡ ተደበበ፤ ተዘረጋ፤ ተዋቀረ።
ተደብተረ ፡ ተደበተረ፤ ተተከለ ተዘረጋ ተወጠረ እንደ ድንኳን ኾነ። ወተደብተረት ሎሙ ይእቲ እብን ፡ (ገድ ፡ አዳ። መጽ ፡ ምስ)።
ተደናገፀ ፡ ተደናገጠ ተደነጋገጠ፤ ርስ በርሱ ፡ (ዐማርኛ)።
ተደናጸወ ፡ ተናፈገ፤ ተጣላ ተቃና፤ ተጯጯኸ። ይደናጻዉ ከመ አክልብት። አሐዱ ለካልኡ ይደናጸዉ ፡ (ገድ ፡ ተክ። ዕር ፡ ኢሳ፯ ፡ ፱)።
ተደንገለ ፡ ተደነገለ ድንግል ኾን፤ ተጠበቀ ተጠነቀቀ። ወለነፍሳትኒ እለ ተደንገላ። ተደንግሎ ሥጋ ወነፍስ ለመኑ ተውህበ ፡ (አፈ ፡ ተ፳፰። ደራሲ)።
ተደንገገ ፡ ተደነገገ፤ ተወሰነ ተወደበ። ስፍሕት በኵሉሄ ዘኢትደነገግ ፡ (አትና)።
ተደየነ ፡ ተዳኘ ተቀጣ፤ ተፈረደበት፤ ፍርድ ለበሰ፤ ቅጣት ተቀበለ። ወዘሰ ኢአምነ ይዴየን። ከመ ይደየኑ መዓልተ ወሌሊተ። ዘከመ ይዴየኑ ኃጥኣን በኵነኔ እሳት ፡ (ማር፲፮ ፡ ፲፮። ራእ፳ ፡ ፲። ቀሌ)።
ተደጕጸ ፡ ተወጋ ተነካ ተጐነጠ፤ ተደጐሰ ተሠመረ።
ተደግመ ፡ ተደገመ፤ መጣፉ። ፪ኛ ጊዜ ተደረገ፤ ሥራው። ዘኢኮነ ከማሁ እምፍጥረተ ዓለም ወኢይደገም እንከ እምድኅሬሁ ፡ (ዮኤ፪ ፡ ፪)።
ተደፍረ ፡ በቁሙ፤ ተደፈረ ተናቀ። ግሩም ውእቱ ዘኢይደፈር። ኦ ዘኢትደፈር ይሁዳ ደፈረከ ፡ (ቅዳ ፡ ሕር። ያዕ)።
ተደፍነ ፡ ተደፈነ ተዘጋ፤ ተቀበረ ዐፈር ለበሰ። ተደፍኑ ውስተ ምድር። ዐይንየ ተደፍነት። ማይ ይደፈን በማእከለ ምድር። ንደፈንኑ ኅቡረ ውስተ መሬት። እስከ ኅቡረ ተደፍኑ ፡ (ሰቈ፪ ፡ ፱። ፫ ፡ ፵፰። ኢዮ፲፬ ፡ ፲፱። ፲፯ ፡ ፲፮። ስንክ ፡ ጥቅ፲፱)።
ተዳለወ ፡ (ይዳለው) ተደራራጊ፤ ተዘገጃጀ ተሰነዳዳ ተመቻቸ።
ተዳለገ ፡ ተወራወረ ተመካከተ። ዕደው ኀያላን ወእለሂ ይዳለጉ ጠፍኡ ፡ (ኩፉ ፡ ፵፰)።
ተዳመረ ፡ ተገናኘ ተጣመረ። በተዳመረ ፈንታ ተደማመረ ይላል፤ አያስኝም። ተባዕት ወአንስት ዘይደማመሩ ፡ (ፊልክ ፡ ፻፶፭)።
ተዳረገ ፡ በቁሙ፤ ተደራረገ ተጋጠመ፤ ተዋደደ ተሰማማ። ዘይዳረግ፤ ተዳርጎ ፡ (ፍ ፡ ነ)።
ተዳበለ ፡ በቁሙ፤ ተባበረ ተጨፋፈረ፤ ተሸረበ ተደራረበ። ተዳበለ ፀራዊ ወተመዊኦ ጐየ ፡ (ተረ ፡ ቄር፲)። .
ተዳወለ ፡ ተዋሰነ፤ ተወሳሰነ ተዳካ። እለ ይዳወልዎ እለ ዐውዱ ፡ (፫ነገ ፡ ፴ ፡ ፲፯)።
ተዳደቀ ፡ ተገናኘ ተገነኛኘ፤ ተጋጠመ። ተዳደቁ ኵሎሙ ውስተ ጸብእ። ኢይደሉ ንዳደቃ ለጸብእ ዘእንበለ በትእዛዘ እግዚ፤ አላ በተዳድቆ ግብት ፡ (ዮሴፍ። ፈ ፡ መ ፡ ፬ ፡ ፲፪)።
ተዳጐጸ ፡ ተጣለ ተጓነጠ፤ ተጐናነጠ።
ተድሕረ ፡ ተዳረ፤ ተፈታ ተለቀቀ።
ተድኅረ ፡ ተመረቀ፤ ተባረከ፤ ተመሰገነ።
ተድኅነ ፡ ተዳነ ተዋሰ፤ መድን ተያዥ ኾነ፤ እዳናለኹ አለ። ወመድኅነ ነፍስኒ ይደልዎ ከመ ያምጽእ ዘተድኅነ፤ ወይኩን ቃለ ዛቲ ተድኅኖ ከመ ይበል ተድኅንኩ ለአብጽሖተ እገሌ ለእገሌ፤ አው ተድኅንኩ ለእገሌ ገጸ እገሌ፤ አው ተድኅኖተ እገሌ ላዕሌየ። ኢይደሉ ተድኅኖቱ ለዘይደሉ ላዕሌሁ ቀትል ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፳፯)።
ተድኅየ ፡ ተቈፈረ ተማሰ፤ ጠለቀ፤ ጐደጐደ።
ተድላ ፡ በቁሙ፤ ደስታ ድሎት ምቾት፤ ምቹ ፍራሽ ፈርሽ የዙፋን የኮር። ኢያፍቱከ ተድላሆሙ ለረሲዓን። ገነተ ተድላ ርእስየ። ፍትሕ ወርትዕ ተድላ መንበሩ ፡ (ሢራ፱ ፡ ፲፪። ዘፍ፫ ፡ ፳፫። ፩ቆሮ ፡ ፲ ፡ ፴፫። መዝ ፡ ፺፮)።
፡ አገባብ ፤ ክብር
ገንዘብ። እስመ
ከመ ዝ
ተድላ ለነ። ተድላ መለኮት። መዛግብቲሆሙ ከመ እምላእ
ተድላ (ማቴ፫ ፡ ፲፭። ቄር። ምሳ፰ ፡ ፳፩)።
ተድባብ [1] ፡ (ባት) ጣራ ባጥ፤ ጠፈር መዋቅር፤ መክደኛ ክዳን፤ ጥላ ከለላ ዳስ ጐዦ። ተሞቅሑ መትሕተ ተድባበ ቤት።ወትገብር ላቲ መልዕልቴሃ ተድባበ ዘወርቅ። ይትዔገሥ ቍረ ክረምት ወሐሩረ ሐጋይ ታሕተ ሰማይ ዘእንበለ ተድባብ ፡ (ጥበ፲፯–፪። ዘፀ፳፭ ፡ ፲፯–፳፪። ስንክ ፡ ሐም፳፭)። የማእዝን ራስ ጫፍ፤ የቤት የቅጽር መስኮት ቅስት፤ ዝንቦ ቀጸላ፤ ደርብ ዕንቍላል ግንብ፤ ሰገነት፤ ዘውድ አክሊል ጕልላት፤ የመርከብ ዕንጨት በኋላና በፊት በማእዝኑ ራስ የሚኾን። በስተላይ ለሚኾን ኹሉ ይነገራል። አውረድዎ እንተ ተድባበ ቅጽር። ተድባበ ቤተ መቅደስ። ወይደንን እንተ ተድባብ። ወለእመ ሐነጽከ ቤተ ሐዲሰ ትገብር ሎቱ ትድባበ ለናሕስከ። ለእመ አረፍት ይእቲ ንሕንጽ ዲቤሃ ተድባበ ዘብሩር። ተምህሩ ይግበሩ ተድባበ አሕማር። ወኮኑ ይገብሩ ተድባበ አሕማር ፡ (ግብ፱ ፡ ፳፭። ማቴ፬ ፡ ፭። ማሕ፪ ፡ ፱። ዘዳ፳፪ ፡ ፰። ማሕ፰ ፡ ፱። ስንክ ፡ ጥር፲፯። የካ፪)።
[2] ፡ ባጥ ፥ ጣራ፤–ደበበ።
ተገለ ፡ ተለየ ተገለለ ተንጓለለ፤ ተንጋለለ። ፡ (ተረት) ተንጋሎ ቢተፉ ተመልሶ ታፉ።
ተገለደ ፡ ተቈረበተ፤ ቈርበት ለበሰ፤ ተደጐሰ።
ተገልበበ ፡ ተሸፈነ፤ ተከናነበ፤ ተሰወረ ተደበቀ፤ በልብስ ባለባበስ። ተገገልበበት ገጻ። ክዳን በዘይትገለበቡ እምጣል። አንስት ደናግል ኢይትገልበባ ርእሶን በቤተ ክር አላ ሥዕርቶን ያንኃ። ወይቤሎ ንጉሥ እትገልበብ ወእባእ ውስተ ቀትል ፡ (ዘፍ፴፰ ፡ ፲፭። ኢሳ፬ ፡ ፮። ኪዳ። ፫ነገ ፡ ፳፪ ፡ ፴)።
ተገልወ ፡ ተሸፈነ፤ ተጋረደ። ዘበሠቀ ጽልመት ተገልወ ፡ (መጽ ፡ ምስ)።
ተገልየ ፡ ተቈረጠ፤ ተገለጠ።
ተገልገለ ፡ (ዕብ ጋላህ) ተማረከ ተዘረፈ፤ ተበረበረ። እስመ ገልገላ ተገልግሎ ትትገለገል ፡ (ዓሞ፭ ፡ ፭)። ተፄውዎ፤ ፈሊስ ትፈልስ፤ ጠፊአ ትጠፍእ ማለት ነው።
ተገልጸ ፡ ተገለጠ ግልጥ ኾነ፤ ታየ ተረዳ። ፡ (ሙሴ) ሶበ ይትገለበብ ይትረአይ ወሶበ ይትገለጽ ይሴወር ወኢይትዐወቅ ፡ (አዋል)።
ተገልፈ ፡ ተቀረጸ፤ ተሣለ ተመለለ። ይትገለፋ አናቅጽኪ። ዘተገልፈ በሰሌዳ። ውስተ ከርሠ እምየ ተገለፍኩ ሥጋ ፡ (ኢሳ፰ ፡ ፲፰። ስንክ ፡ መስ፳፮። ጥበ፯ ፡ ፩)።
ተገመነ ፡ ዐረረ ገመነ ተከነ አደፈ ረከሰ፤ ሴሰነ። ኢተገመነት ነፍስየ በርኵስ። ተገመንኩ ለከ እምኔከ። ወተገመነ ሕዝብ ፡ (ሕዝ፬ ፡ ፲፬። ኩፋ ፡ ፴፫። ዘኍ፳ ፡ ፩)።
ተገምሰ ፡ ተገመሰ፤ ተከፈለ ተገመደለ።
ተገምረ ፡ ተጨረሰ ተከተተ ተካተተ፤ ተቻለ ተወሰነ። እስከ ተገምረ ኵሉ ሕዝብ ወዐደወ። ፀርሰ ተገምሩ በኵናት። ውስተ ከርሥ ይትገመር። ተገምረ በማሕፀነ ድንግል። መለኮት ኢይትገመር በምንትኒ። እፎ አግመርኪዮ ለዘኢይትገመር ተገምሮ ፡ (ኢያ፫ ፡ ፲፯። መዝ ፡ ፱። ማቴ፲፭ ፡ ፲፯። ኪዳ። ቄር። ድጓ)።
ተገምዐ ፡ ተላጨ ተቈረጠ፤ ተፋቀ ፡ ለዘበ። ከመ ይትገምዑ ፡ (ኤር፳፰ ፡ ፴፱)።
ተገምደ ተገመደ ፡ ታረደ ተጐመደ፤ ተጐማመደ፤ ታጨደ ተቈረጠ። በሰይፍ ተገምዱ ሕፃናት ንጹሓን። ዘተገምደ በመጥባሕት። ሐረገ ወይን እንተ ትትገመድ ወትትአረር። ሰሐብዎ ወኮነ ሥጋሁ ይትጌመድ ፡ (ስንክ ፡ ታኅ፴። መጋ፲፭። ድጓ። አቡሻ ፡ ፶)።
ተገምጸ ተገመጸ ፡ ተገመጠ፤ ተቀለስ ተጐነበሰ፤ ጐበጠ፤ ወትትገመጽ እምህየ መንገለ ሰሜን ፡ (ኩፋ ፡ ፰)።
ተገሰ ፡ ተዳሰሰ ተዳበሰ፤ ተነካ ተያዘ። ተገሰ እምቶማስ።እሳት ሕይወት ዘኢይትገሰስ ፡ (ኪዳ። ሳታት። ቄር)።
ተገሠጸ ፡ በቁሙ፤ ተመከረ፤ ተሠራ ተቀጣ፤ ምክር ሰማ፤ ቅጣት ተቀበለ። ገሠጽከኒ ወተገሠጽኩ። ዘእምንእስከ ኢተገሠጽከ። ወልድ ዘኢተገሠጸ። ገሠጾ ወኢተገሠጸ። ከመ ይትገሠጽ። ዘይትጌሠጹ በሥርዐታ ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን ፡ (ኤር፴፰ ፡ ፲፰። ሢራ፳፭ ፡ ፫።፴ ፡ ፰። ስንክ ፡ ታኅ፲፪። ቀሌ)።
ተገርመ ተገረመ ፡ ታበየ ኰራ፤ ገረመመ፤ ተገራመመ። ኢይምጽኡ በተገርሞ። ኢይሰምዕ ድምፀ ዘይትጌረም። ኢትትገረመነ ኦ ፀረ እግዚ በኵነኔከ። ተገረሞሙ ወፀረፎሙ ፡ (ገድ ፡ ተክ። ቀሌ። ኢዮ፴፱ ፡ ፯። ዮሴፍ)።
ተገበረ ፡ (ይትጌበር) ዝኒ ከማሁ፤ በግድ ተሠራ፤ ተደረገ ታረሰ ተነገደ። ልማዱ ግን አድራጊነት ነው ፥ በጣም ተሳስቷል፤ መዠመሪያውን እይ። ተገባሬ ምድር ፡ (ዘካ፲፫ ፡ ፭። ፍ ፡ ነ ፡ ፴፰)።
ተገብሰሰ ፡ ተመረገ ተለሰነ፤ ተካከለ የተላሰ ነገር መሰለ፤ ኖራ ተቀባ።
ተገብረ ፡ (ይትገበር) ተሠራ ተደረገ፤ ተፈጠረ፤ ተበጀ ተዘጋጀ። እንተ ተገብረት በወርቅ ወበዕንቍ። ይትገበር ሎቱ በዓል ዐቢይ። ተገቢሮ ሠሐቅዎ መላእክት። ዘበአማን ተወልደ ወኢተገብረ። ተገብረ ዝንቱ ኵሉ በእዴኪ ፡ (ራእ፲፰ ፡ ፲፮። ስንክ ፡ ሚያ፳፬። ኢዮ፵ ፡ ፲፬። ቄር። ዮዲ፲ ፡ ፲)።
ተገተ ፡ ተጐተተ፤ ዐለቀ አረጀ፤ ግትቻ ኾነ።
ተገነ ፡ ተተከለ፤ ታጠረ ተቀጠረ፤ ተክሉ ቦታው።
ተገንበ ፡ ተሠራ ተገነባ፤ ገንቦው ግንቡ።
ተገንዘ ፡ ተገነዘ ተከፈነ፤ ተሰወረ ተቀበረ። ተገንዙ በእደ መላእክት። ሞተሂ ወተገንዘ ፡ (ገድ ፡ ዘሚ። ቄር)።
ተገንጰለ ፡ ተለወጠ ተገለበጠ፤ ተገነበለ፤ ግንብል ግንብል አለ። ወተገንጰለ በኵሉ ወተመይጠ ዘትሥጉት ምስጢር ፡ (ቄር ፡ ጰላ)።
ተገዝመ ፡ ተቈረጠ ተቈራረጠ፤ ተጨፈጨፈ። ዕፀው ነዊኃን ይትገዘሙ። ዕፅ እንተ ተገዝመት። ተገዚሞ ዳግመ ይፈሪ ፡ (ሔኖ፹፫ ፡ ፬። ዲድ ፡ ፳፭። ኢዮ፲፬ ፡ ፯። ማቴ፯ ፡ ፲)።
ተገዝረ ፡ ተገዘረ፤ ተቈረጠ፤ ተከረከመ ፡ (ዘፍ ፡ ፲፯ ፡ ፲፬ ፡ ፳፬–፳፯)። ተገዘሩ ፡ ለአምላክክሙ። ዘተገዝረ በምክንያተ ደዌ ወአዘዝዎ ዐቀብተ ሥራይ ፡ (ኤር፬ ፡ ፬። ፈ ፡ መ ፡ ፴፫ ፡ ፪)።
ተገዝአ ፡ ተገዛ፤ ተገዥ ኾነ። ታደለ ተሰጠ፤ ምግቡ።
ተገየረ ፡ (ዕብ ሂትጋየር) ወደ አይሁድ መጣ ተጠጋ፤ ይሁዲ ኾነ በኦሪት አመነ፤ የሀደንና ተይህደን እይ። ተለሰነ ተቀባ፤ ተለቀለቀ።
ተገድለ ፡ ተገደለ ታረደ በሰው እጅ ሞተ፤ ተጣለ ወደቀ ገደል ገባ።
ተገድፈ ፡ ተገደፈ፤ ተጣለ ወደቀ፤ ተተወ ተረሳ፤ ቀረ፤ ጠፋ ታጣ። ትትገደፍ ኦሪት እምካእህን። ይትገደፍ አብድንቲሆሙ። ከመ አባግዕ ተገደፍነ። ተገድፈ ወአልቦ ዘተረክበ። በእንተ ረኪበ ዘተገድፈ ፡ (ሕዝ፯ ፡ ፳፮። ኢሳ፴፬ ፡ ፫። ፶፫ ፡ ፮። ኩፋ ፡ ፵፫። ፍ ፡ ነ ፡ ፵)።
ተገፍትዐ ፡ ተገለበጠ ተደፋ፤ ተለወጠ፤ ልውጥ ግልብጥ ሌላ ኾነ፤ ፈረሰ። ከመ ተገፍትዐት ሰዶም ወገሞራ። ትትገፈታዕ ነነዌ። ወተገፍትዐ ዝሙትኪ። ኢይጐነዲ ተገፍትዖ ቤቱ ፡ (ኤር፳፱ ፡ ፲፱። ዮና፫ ፡ ፬። ሕዝ፲፮ ፡ ፴፬። ሢራ፳፯ ፡ ፫)።
ተገፍዐ ፡ ተገፋ ተበደለ፤ ግፍ ተቀበለ፤ ተጠቃ። እትገፋዕ እምኔከ ፣ ናሁ ይትገፍዑ ደቂቅነ። ተገፍዐ በዐውደ ምኵናን ፡ (ዘፀ፲፮ ፡ ፭። ነሐ፭ ፡ ፭። አፈ ፡ ተ፲፩)።
ተጊህ ሆት ፡ (ተግሀ ይተግህ ይትጋህ) መትጋት፤ መንቃት፤ መጠበቅ ማስተዋል፤ እንቅልፍን ሀኬትን መተው፤ ማድባት ማሸመቅ። ዘይትግህ ውስተ አናቅጽየ። ትግሁ እንከ። ነምር ይተግህ ላዕለ አህጉሪክሙ ፡ (ምሳ፰ ፡ ፴፬። ማቴ፳፬ ፡ ፵፪። ኤር፭ ፡ ፮)።
፡ ማሰብ ማስተንተን፤ መውደድ መፍቀድ፤ መቸኰል ማረበድ። እስመ እሙንቱ ይተግሁ ለነፍስክሙ። ይተግህ ለሠናይትክሙ። ትግሂ ለመፍቅድየ በከመ ትተግህ እም ለውሉዳ። ይተግሁ በሌሊት ወበመዓልት አንብቦ መጻሕፍት። እተግህ አነ ከመ እግበር ዘነበብኩ። ተጋህኩ ለአፅርዖ ፈቃዱ ፡ (ዕብ፲፫ ፡ ፲፯። አፈ ፡ ድ፳፱። አርጋ። ስንክ ፡ ኅዳ፳፮። ኤር፩ ፡ ፲፪። ዮሴፍ)።
ተጉሕለ ፡ (ይትጐሐል) ተደራጊ፤ የጕሕለ ተገብሮ።
ተጊር ሮት ፡ (ተገረ ይተግር ይትግር። ዐረ ታጀረ። ዕብ ታጌር) መነገድ፤ ርቆ መኼድ፤ ነጋዴ መኾን። መንቀል መትከል፤ መሳብ መገተር፤ የእግር የድንኳን የካስማ የአውታር።
ተጋሂ ፡ (ሂት ሀያን ያት) የሚተጋ፤ ተጊ፤ ዐሳቢ። ጳጳስ ይኩን ተጋሄ። ተጋህያን ለኵሉ ርኵስ ወእከይ ፡ (ኪዳ። ቀሌ)።
ተጋብአ [1] ፡ ተመላለሰ፤ ወጣ ገባ ምልስ ቅልስ አለ። መጽሐፍ ግን በተጋብኦ ፈንታ ተገባባአ ይላል፤ አያሰኝም። ወተገባብአ ኀበ አረጋዊ ፡ (ፊልክ ፡ ፻፳፰)።
[2] ፡ ተሰበሰበ፤ ተሰባሰበ፤ ተከማቸ ተከመቻቸ፤ ተወሰነ ተጨበጠ ተኰረኰመ። ተጋብኡ ኵሎሙ አሕዛብ ኅቡረ። ህየ ይትጋብኡ አንስርት። ፀነስኪዮ እንዘ ኢይትጋባእ ፡ (ኢሳ፵፫ ፡ ፱። ማቴ፳፬ ፡ ፳፰። ቅዳ)። በገብአ ፈንታ ተጋብአ ይላል፤ አያሰኝም። ማይ እምከመ ተክዕወ ኢይትጋባእ። ይትጋባእ ማይ ዲበ ግብጽ። ትትጋባእኑ መሥገርት ዘእንበለ ተአኀዘ ፡ (፪ነገ ፡ ፲፬ ፡ ፲፬። ዘፀ፲፬ ፡ ፳፮። ዓሞ፫ ፡ ፲፭)።
ተጋነየ ፡ (ገነየ) ተገዛ ታዘዘ፤ ተለማመጠ። ተገናኘ፤ እጅ ነሣ ሰገደ፤ ጫማ ሳመ። ተገናኘ ከማለት በቀር ሌላው አፈታት ለገነየ እንጂ ለተጋነየ አይስማማም።
ተጋአዘ ፡ ተነቃቀፈ ተጣላ ተከራከረ። አልቦ ዘትትጋአዙ በፍኖት። ደናግለ ቀተለ ዮልያኖስ በተጋእዞ። እለ ይትጋአዙ። ተጋአዝኩ ምስሌሃ። ኢይክል ተጋእዞ ምስለ ዘይጸንዕ ፡ (ዘፍ፵፭ ፡ ፳፬። ስንክ ኅዳ፲። ምሳ፲ ፡ ፲፪። ጦቢ፪ ፡ ፲፬። መክ፮ ፡ ፲)።
ተጋዐዘ ፡ ተጓጓዘ፤ ተከታተለ ተግተለተለ።
ተጋኣዚ ፡ ተጣይ ተፃራሪ፤ ተሟጋች ተከራካሪ፤ ባለጋራ። ዘይፈትሕ፤ ማእከለ ተጋኣዝያን። ኮኑ ተጋኣዝያነ ምስለ ሐዋርያት ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፵፫ ፡ ፪። አቡሻ ፡ ፲፪)።
ተጋወረ ፡ ተጎራበተ፤ ተቃረበ ተቀራረበ። ኢይትጋወርዎን ለአንስት። ጸልአ ተጋውሮ እኁሁ። ወአርሐቆ እምተጋውሮ መላእእክት። በሓውርት እለ ይትጋወራ ምስል ከተታ ፡ (ፍ። ነ ፡ ፲ ፡ ፮። ዮሴፍ። ፈ ፡ መ ፡ ፫ ፡ ፪። ገድ ፡ ተክ)።
ተጋውሐ ፡ ተገለጠ፤ ተጋለጠ፤ በራ አበራ፤ የብርሃን። እምቅድመ ይትጋውሑ ብርሃናት። ይሬኢ ደመናተ ብርሃን እንዘ ይትጋውሑ። ጸዳለ መባርቅት እንዘ ይትጋዋሕ ፡ (ቅዳ ፡ አፈ። አረጋ ፡ መል፴፪። መጽ ፡ ምስ)። ሸሸ ጠፋ፤ ራቀ ወገደ፤ ተሰደደ፤ የጽልመት። ዘያቀድም ውሂበ ምጽዋት አንዘ ሀሎ በሕይወቱ ይትጋዋሕ ሎቱ ጽልመተ ኀጣውኢሁ በብርሃነ ማኅቶት ዘውሂበ ምጽዋት ፡ (መጽ ፡ ምስ)።
ተጋየጸ ፡ (ተደራጊና ተደራራጊ) ተነቀፈ፤ ተናቀ። ተነቃቀፈ ተናናቀ ተገዳደረ። ተጊያጊያጠ ተሸላለመ። ርስ በርስ ወይም በገዛ እጅ።
ተጋደለ ፡ በቁሙ፤ ታገለ ተናንቀ፤ ተማታ ተቋሰለ፤ ተጋ ተዋጋ ተሳለፈ፤ ተቃወመ ተከራከረ ተደባደበ፤ በጕልበት ባንደበት፤ በመሰለው ኹሉ። ወተጋደሎ ብእሲ እስከ ጸብሐ። ረከበ ክልኤተ ዕደወ እንዘ ይትጋደሉ። ንትጋደል ለጸቢኦቶሙ እስከ ንመውት። ይትጋደል አበ ምኔት ለአድኅኖቱ። ተጋድሎታ ለፍትወት። ተጋደልዋ ለኀጢአት። ተጋደለ በንስሓ። ተጋደሊ ሰማዕት በጻማ ወበምንዳቤ ፡ (ዘፍ፴፪ ፡ ፳፬ ፡ ፳፭። ዘፀ፪ ፡ ፲፫። ዮሴፍ። ፍ ፡ ነ ፡ ፲። ፳፬ ፡ ፭። ዕብ፲፪ ፡ ፬። መቃ ፡ ገ፲፭። መዋሥ)።
ተጋዳሊ ፡ የሚጋደል፤ ተጋዳይ። ፡ (ተረት) አልሞት ባይ ተጋዳይ። ገድለኛ፤ መንፈሳዊ ዐርበኛ። ይቤ አሐዱ እምተጋዳልያን ክቡር ሞቶሙ ለሰማዕታት ፡ (ፈላስ ፡ ገ፸፬)።
ተጋፍዐ ፡ ተጋፋ ተጫነቀ፤ ተጨቋቈነ ተሳደበ። ወኮኑ ሰብእ ይትጋፍዑ ከመ ይልክፉ ዘፈረ ልብሱ። ዘይትጋፋዕ ፡ (ስንክ ፡ ነሐ፲፬። ቀሌ)።
ተግሕፈ ፡ ተጋፈ ተጠረገ።
ተግሊድ ፡ (ዐረ ተጅሊድ) ድጕስ ድጕስት፤ አደጓጐስ፤ አጠራረዝ፤ የድጕስ ሥራ።
ተግሣጽ ፡ (ጻት) በቁሙ፤ ስብከት ትምርት፤ ብርቱ ምክር ምዕዳን፤ ቍጣ ዘለፋ ኀይለ ቃል፤ ከበትር የሚበልጥ የሚሻል የምስጢሩ ስሜት ልብ የሚሰብር የሚነካ። ተግሣጸ ሰሎሞን። በእንተ ተግሣጸ ካህናት። በእንተ ተግሣጸ ሕዝባውያን። ዕቀብ ተግሣጾሙ ለአእሩግ። አባ ሲኖዳ ደረሰ ድርሳናተ ብዙኃተ ወተግሣጻተ ወቃላተ በቍዔት ፡ (ምሳ፳፭–፳፱። ፈ ፡ መ ፡ ፴፪። ፴፬። ሢራ፰ ፡ ፱። ስንክ ፡ ሐም፯)።
ተግቢጥ [1] ፡ ሻታ፤ ሽንት ቅዘን፤ ቀጭን ዐይነ ምድር። በረዘንና ተብሪዝን እይ።
[2] ፡ (ዐረብ) ሽንት ቅዘን። ገብጥንና ተርቢዝን እይ።
ተግባር ፡ በቁሙ፤ ፍጥረት ሥራ፤ ዕርሻ ቍፋሮ ንግድ፤ ጥበበ እድ በየስሙና በያይነቱ። ኵሉ ተግባረ እግዚ ሠናይ ወአልቦ ግዱፍ። ተግባረ ምድር። ወሰምረ ሎቱ ተግባሩ። በንዋየ ብርት ረሰዩ ተግባረኪ። ሤጥ ወተግባር። ተግባረ እደው። ምንት ተግባርክሙ ፡ (፩ጢሞ ፡ ፬ ፡ ፬። ኤር ፡ ፲፬ ፡ ፬። ሉቃ፲፪ ፡ ፲፮። ሕዝ፳፯ ፡ ፲፫። ሢራ፳፯ ፡ ፪። ፯ ፡ ፲፮። ዘፍ፵፮ ፡ ፴፫)።
፡ ጕዳይ ግዳጅ ባሕርያዊ ሥራ። ኀይል ብዕል የንግድ ዕቃ መናገጃ። እምብዝኀ ተግባርኪ። አምጽኡ ዓሣኒ ወባዕደኒ ብዙኀ ተግባሮሙ ፡ (ሕዝ፳፯ ፡ ፲፰። ነሐ፲፫ ፡ ፲፮)።
ተግእዘ ፡ ተጠላ ተነቀፈ፤ ተጋዘ።
ተጐለተ ፡ በቁሙ፤ ጕልት ኾነ ተሰጠ ተወረሰ። ዘተጐለተ ሎቱ ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፲፰)።
ተጐርዐየ ፡ ታነቀ፤ ጕረሮው ተያዘ ተሰቀዘ፤ በገዛ እጁ ወይም። በጠላት እጅ። እምፈተውኩ ለልየ እትጐርዐይ ፡ (ኢዮ፴ ፡ ፳፬)።
ተጐነኰ ፡ ተከመረ ተቈለለ። ተጐነኰ ክምረ ሥርናይ። ይዌግርዎ እስከ ይትጔንኵ እብን ዲበ እብን ፡ (መጽ ፡ ምስ)።
ተጐድዐ ፡ ተጐዳ ተመታ፤ ተነካ ተጐነጠ ተሰበረ፤ ተፈተነ። ተጐድዐ ብረኪሁ። መጽአ ድምፅ ከመ ዘጽኑዕ ነፋስ ወመሰሎሙ ከመ ዘተጐድዐ ገበዋቲሁ ለቤት። ይትጐድዑ አዕማዲክሙ። ብእሲ ዘበኵሉ ተጐድዐ። ወዘሰ ኢተጐድዐ አልቦ ዘየአምር ፡ (ዳን፭ ፡ ፮። ሕዝ፮ ፡ ፮። መጽ ምስ። ሢራ፳፩ ፡ ፳፪። ፴፩ ፡ ፲)።
ተጓሀነ ተጓህነወ ፡ ተጓጓነ፤ ተጯጯኸ ተዚያዚያመ ተናናረ።
ተጓሕለወ ፡ (ተደራጊና ተደራራጊ) ተሸነገለ፤ ተሞኘ ተታለለ። ተቀትለ በተምያነ ነገር ወበተጓሕልዎ። ይትጓሐለዉ በፍቅሮሙ ፡ (ዮሴፍ። ፪ጴጥ ፡ ፪ ፡ ፲፫)። ተሸናገለ ተሸነጋገለ፤ ተተናኰለ ተተነኳኰለ፤ ተካዳ ተከዳዳ። ከመ ኢይትጓሕለውክሙ። ተጓሕለወነ እዩ ፡ (፳ነገ ፡ ፳፫ ፡ ፳፪። ፪ነገ ፡ ፱ ፡ ፳፫)።
ተጓልሐ ፡ ተዳራ ተቃበጠ፤ ተዳለቀ ተዳሰቀ፤ በግልጥ። ወይም በስውር፤ ኀፍረት ለኀፍረት ተጋለጠ፤ ተገላለጠ። ኀፍረት ተናግሮ ብእሲተ ባዕድ ወኢትትጓልሓ ላቲ፤ ወኢትኂጣ ለወለታ፤ ወኢትቅረብ ኀበ ምስካባ ፡ (ሢራ፵፩ ፡ ፳፪)።
ተጓድዐ ፡ ተጓዳ፤ ተማታ ተጋጨ ተጻፋ(ተዋጋ ተሳበረ ተቀራሸመ፤ የበሬ)። እንዘ ይትጓድዑ ምስለ ክንፍ ክንፈ። ይደነግፁ ሠረገላት ወይትጓድዑ በፍኖት ፡ (ስንክ ፡ ግን፲፱። ናሖ፪ ፡ ፭)።
ተጠምቀ ፡ ተጠመቀ፤ ተነከረ፤ ታጠበ ተጣጠባ በገዛ እጁ፤ወይም በሰው እጅ፤ ስርየት ልጅነት ለማግኘት። ሑር ተጠመቅ ውስተ ተከዜ ዮርዳኖስ።ትወፅእ በሌሊት ወትጠመቅ ወስተ ነቅዐ ማይ። ወተጠምቀ ውስተ ይእቲ ዐዘቅት ዘናጥራን። ተጠምቀ ህየ በማይ ፡ (፬ነገ ፡ ፭ ፡ ፲ ፡ ፲፬። ዮዲ፲፪ ፡ ፯። ስንክ ፡ ጥቅ፲፫። ኅዳ፲፭)። ወእምድኅረ ተጠምቁ ሕዝብ ተጠምቀ ኢየሱስኒ። አኮ ፈቂዶ ለተጠምቆ፤ አላ ጽሕቀ ያብርህ ማያተ ወያኀይል መካናተ ለእለ ሀለዎሙ ይጠመቁ ውስቴቱ። ወተጠሚቆ ወፅአ እማይ። እለ ተጠመቅነ በእግዚእነ ውስተ ሞቱ። ተጠመቅነ በአሚነ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፡ (ሉቃ፫ ፡ ፳፩። ሃይ ፡ አበ ፡ ሳዊ። ተረ ፡ ቄር፲፮። ማቴ፫ ፡ ፲፮። ሮሜ፮ ፡ ፫። ቀሌ)።
ተጠምዐ ፡ ተነከረ ተዘፈቀ፤ ገባ ጠለቀ። በከመ ይዴመር ሠርዮ ምስለ ፀምር ተጠሚዖ። አጽፋረ እግርከ በደመ ቅንዋት እለ ተጠምዓ። ለእመ ተጠምዐት ነፍስከ ውስተ ኅሊናት እኪት ትከውን ጸሎትከ ዘኢንጽሕት ፡ (ቄር ፡ እስት። ፊልክ ፡ ፻፷፩)።
ተጠስየ ፡ ጠፋ ተደመሰሰ፤ ተፋቀ ተጣሰ። ተመስወ ልቦሙ ወተጠስየ፤ ወኀጥኡ ዘይኄልዩ፤ ጠፋ ፡ (ኢያ፭ ፡ ፩)።
ተጠርቀ ፡ ተጠረቀ፤ ተቀጠቀጠ ተኰላሸ።
ተጠርዘዘ ፡ ተንጠረዘዘ፤ ጠርዛዛ ኾነ።
ተጠርየ ፡ ተገዛ ተዋጀ፤ ተገኘ ተሰጠ፤ ጥሩ ገንዘብ ኾነ። አንተ ኀለይከ ከመ ጸጋ እግዚ ትጠረይ በብሩር። ንዋይ ዘይጠረይ እምግብር። ሃይማኖት እንተ ትጠረይ እምተምህሮ። ትሩፋት እንተ እምኔሃ ትጠረይ ንጽሐ ልብ። ጸጋ መንፈስ ቅዱስ እንተ ትጠረይ በጥምቀት ፡ (ፈ ፡ መ ፡ ፳፭ ፡ ፩። ፍ ፡ ነ ፡ ፴፬። ማር ፡ ይሥ። ፊልክ ፡ ፬ ፡ ፳)።
ተጠቅለለ ፡ ተጠቀለለ፤ ተሸበለለ።
ተጠቅመ ፡ ተጠቀመ ተሠራ፤ ታጠረ ተከበበ፤ ጥቅም አገኘ። ከመ ትጠቀብ ባለው ትጠቀም እንዲል ፡ (ቅዳ ፡ ዮሐ)።
ተጠቅበ ፡ ተሰፋ ተጠቀመ፤ ተጣፈ ተለገበ፤ ታደሰ ተጠገነ። ከመ ትትሐጸር በመስቀልከ ወትጠቀብ በመጽለብትከ እማእከለ መንሱት ፡ (ቅዳ ፡ ዮሐ)። ምስጢሩ መራቅ መጠበቅ ነው፤ አንዳንድ መጣፍ ትጠበቅ ትጠቀም ይላል።
ተጠቅዐ ፡ ተመታ ተነፋ፤ ተጠቃ፤ ተጠጋ።
ተጠብሐ ፡ ታረደ፤ ተጠባ ተበለተ ተገፈፈ። መጽአ ይጠባሕ ከመ በግዕ። ከመ ላሕም ዘየሐውር ለተጠብሖ ፡ (ኢሳ፶፫ ፡ ፯። ምሳ፯ ፡ ፳፪። ዘኍ፲፩ ፡ ፳፪)።
፡ ተበጣ፤ ተተፈተፈ፤ ተፈቃ። ይጠባሕ ገጾሙ ፡ (ሕዝ፮ ፡ ፱)።
ተጠብለለ ፡ ተጠቀለለ ተሸፈነ፤ ተጠመጠመ። ሰማያት ይጠበለሉ። በአጽርቅት ተጠብለለ። ከይሲ ተጠብለለ ውስተ ክሣዱ ፡ (ኪዳ። ድጓ። ስንክ ፡ ሐም፳፬)።
ተጠብሰ ፡ ተጠበሰ፤ ለእሳት ተሰጠ ተረመጠ እስኪበስል።
ተጠብጠበ ፡ ተገረፈ፤ ተጠበጠበ። ሰላም ለጳውሎስ ቅሡፈ ዘባን ወገቦ፤ በመኃትወ ነድ ወተጠብጥቦ ፡ (ስንክ ፡ የካ፱)።
ተጠናቀቀ ፤ ተራቀቀ ፤ መራቀቅ አበዛ። ሀለወ ዘይጠበብ ወይጠናቀቅ እንዘ ይዔምፅ። ተጠናቀቀ ለገቢረ አምሳሉ በዘይሤኒ ወይኄይስ። በተጠናቅቆ (ሢራ፲፱ ፡ ፳፭። ጥበ፲፬ ፡ ፲፱። ቀሌ)
ተጠንቀቀ ፡ ተጠነቀቀ ፤
ሥራው ወይም ሠሪው። ሶበሰ ኢተዐውቀት ወኢተጠንቀቀት ዛቲ። ዝንቱ ተጠንቀቀ በብዙኅ ቀኖናት (ፈ ፡ መ ፡ ፪ ፡ ፲። ፵፩ ፡ ፬)።
ተጠው(ወ)ቀ ፡ ተጨነቀ፤ ተጠበበ በቦታ፤ በሐሳብ በመከራ። ተጠውቀት በጸቈን። ትጠወቅ ነፍስየ። ኢይጠወቅ አሐዱ ምስለ ካልኡ። ወተጠወቀ በሕቁ እስከ ይደዊ። ተጠወቀ ወተዐጽበ ፡ (ዘኍ፳፪ ፡ ፳፭። ኢዮ፲ ፡ ፩። ሢራ፲፮ ፡ ፳፰። ፪ነገ ፡ ፲፫ ፡ ፪። ፊልክ ፡ ፷፫)።
ተጠውመ ፡ ታጠፈ ተጣጠፈ፤ ዕጥፍጥፍ አለ ተጠቀለለ። ትጠወም ሰማይ ከመ መጽሐፍ። ወሰማይኒ ተጠውመት ከመ ክርታስ ፡ (ኢሳ፴፬ ፡ ፬። ራእ፮ ፡ ፲፬። ሔኖ፺ ፡ ፳፰)።
ተጠየረ ፡ (ዐረብ። ዕብ ጣዬር) ተነባ፤ ጠነቈለ፤ አሟረተ፤ በወፍ ጩኸት በድምፀ አራዊት በሌላውም ፍጥረት። ከሟርቱና ከጥንቈላው ጋራ አምልኮትንም ያሳያል። ኢትጠየሩ በዖፍ። ዘይጤየሩ በሐሳበ ፀሓይ ወወርኅ ፡ (ዘሌ፲፱ ፡ ፳፮። አርጋ ፡ ፪)። ዘይጤየር በዖፍ ወበማይ ወበእሳት። እመ ቦ ዘተጠየረ በአዕዋፍ፤ አው በአራዊት አው በካልእ፤ አው በዘኮነ ከዊኖ ፡ (ቀሌ)።
ተጠየቀ ፡ በቁሙ፤ ተመረመረ፤ ታወቀ ተረዳ ተረገጠ፤ ታየ ተገለጠ። በዝ ተዐውቀ ወተጠየቀ ከመ ፡ (አቡሻ ፡ ፲፪)። ወበዝ ተዐውቀ ሕልመ አቡሆሙ። ለእመ ተጠየቀ ሞተ ንጉሥ። ወተጠየቀ ሶቤሃ ነገረ አረጋዊ ፡ (ዮሴፍ)።
ተጠየተ ፡ በቁሙ፤ ተመረጠ ተዘጋጀ።
ተጠያሪ ፡ (ሪት ርያን ያት) የሚያሟርት ሟርተኛ፤ ጠንቋይ፤ወፍ ጠያቂ፤ እንዳገውና እንዳርማጭሖ ሰው የወፍ ቋንቋ የሚያውቅ። ኢትኩን ተጠያሬ በዖፍ። ተጠያሪ በመሬት ወበሐመድ ወበፍሬ ዕፀው። ተጠያርያን ፡ (መጽ ፡ ምስ። ሲኖዶ። ቄድር)።
ተጠፈረ ፡ በቁሙ። አጥፈረ ተጠፍረ ቢል ግን የቀተለ ቤት ነው።
ተጣሀረ ፡ ተናጻ ተጣራ፤ ተጣጠበ ተጠማመቀ። ኢትትኀፃቡ ኵሎ ጊዜ ወኢተግበሩ ዘከመ ያለምዱ ተጣህሮ ፡ (ዲድ ፡ ፴፫)።
ተጣቀበ ፡ ተጣቀመ ተጠቃቀመ፤ ተሰፋፋ።
ተጣበቀ ፡ በቁሙ፤ ተጠባበቀ፤ ተያያዘ ተጣመረ። አሐዱ ምስለ ካልኡ ተጣበቁ፤ ይጣበቁ ወኢይትፋትሑ። ኵናት ተጣበቀት ምስለ እራኁ ፡ (ኢዮ፵፩ ፡ ፯ ፡ ፰። ገድ ፡ ተክ)።
ተጣበበ ፡ በቁሙ፤ ተራቀቀ፤ ተተናኰለ ተተነኳኰለ።
ተጣዐመ ፡ ተጣጣመ፤ ተቃመሰ።
ተጣእጥአ ፡ ተዘጋጀ ተሰናዳ፤ ተከናወነ ተከነዋወነ። እንበለ ይጣእጥኡ አድባር። እምቅድመ ይጣእጥኣ መሠረታተ አውግር። እምድኅረ ጸንዐት መንግሥቱ ወተጣእጥእ። ኢተጣእጥኦ ለአግሪጳስ ንብረት። ወኢይጣአጣእ ተግባሮሙ ፡ (ዲድ ፡ ፴። መጽ ፡ ምስ። ፪ዜና ፡ ፲፪ ፡ ፩። ዮሴፍ)።
ተጣወቀ ፡ ተጫነቀ ተጨናነቀ፤ ተጣበበ። ይጣወቅኑ ዓለም ፡ (ሱቱ ፡ ዕዝ፫)። በጦቀ ፈንታ ጠውቀየ ካለ ዘንድ፤ ይጣወቅኑ ባለው ይጠዋቀይኑ ይላል።
ተጣጋዒ ጥጉዕ ፡ የተጣጋ የተጠጋጋ፤ ስግስግ ንብብር።
ተጣግዐ ፡ ተጣጋ ተጠጋጋ፤ ተነባበረ።
ተጣፍሐ ፡ ተጣፋ፤ እጅ ለጅ ተማታ፤ ያገና የገባያ። ሸያጭና ገዥ በዋጋ ተስማምተው ነገር ሲጨርሱ እንደ መማል እንደ መፈጣጠም ይጣፋሉ።
ተጣፍአ ፡ ተጣፋ፤ ተጠፋፋ፤ ተጋደለ።
ተጤዐ ፡ (ይጠያዕ) ተመረገ ተለሰነ፤ ተደፈነ ተቀባ።
ተጤገነ ፡ በሰለ፤ ተቈላ ተጋገረ። ታደሰ ተጠገነ።
ተጥሕለ ፡ ተጣለ፤ ወደቀ፤ ተጠጀ ተጠመቀ። ዘቀጠ አተላ ኾነ፤ ተሰበሰበ ተከማቸ። ውስተ መንጠፍት ይጠሐል ሐሠር ፡ (ሢራ፳፯ ፡ ፬)።
ተጥላስ ፡ (ሳት። ሮማይ ፡ ቲቱሊስ።፤ ዐረ እተጥላሳት) አንቀጽ፣ምዕራፍ፤ ክፍል-መስ እከት፤የጉባኤ ፡ የማኅበር፣መጽሐፍ፤ቀኖና፤የመጽሐፍ፣ ስምና ፡ እርእስት፤ ማስታወቂያ። ጠስ ፡ ዘውእቱ ፡ ተጥ ላሳት፣(ፍ ነ ፡ መቅ)። ተጥላስና ፡ ( አብጥሊስ ፡ አንድ፤ ሶም ፡ ነው፤ ኹለት ፡ እይደለም፤ እብጥሊስን ፡ እይ። ፍካሬ ፡ አብጥሊስ ፡ አው ፡ ተጥላላት ፡ ቀኖና ው እቱ ፡ በልሳኝ ፡ ጽርእ ፡ (ሲኖዶ)። ጽርኡ ፡ ከሮማይስጥ ፡ ስስ ' ወስደው ጽርእ ፡ ይላል ፡ እንጂ ፡ ቃሉ ፡ የላቲን ፡ ነው።
ተጥባብ ፡ ተንኰል፤ ክፉ ምክር፤ የፑሊቲክ ነገር። ወኮነ ውስቴቱ ዐቢይ እከይ ወተጓሕልዎ ወተጥባብ ወተምያን ፡ (ዮሴፍ)።
ተጥዕመ ፡ ተቀመሰ፤ ተጣፈጠ።
ተጰጰሰ ፡ በቁሙ፤ ጳጳስ ኾነ፤ ተሾመ፤ ጳጳስ ተባለ። ሰላም ለጳውሎስ በቍስጥንጥንያ ዘተጰጰሰ። እስከ ተኀርየ ለተጰጵሶ ፡ (ስንክ ፡ ግን፳፯)።
ተጸለለ ፡ ተጋረደ፤ ተሸፈነ፤ ታወረ። ተጸለለ አዕይንትየ። ወተጸለለ ልቦሙ ከመ ኢያእምርዎ ፡ (ግብ፲፫ ፡ ፲፩። ፳፪ ፡ ፲፩። ቅዳ ፡ ግሩ)።
ተጸለየ ፡ በቁሙ፤ ተጸለየለት፤ ተጸለየበት፤ ተለመነ ተመሰገነ፤ ጸሎት ምስጋና ቀረበለት። ዘአሐደ ይሰገድ ወአሐደ ይሴባሕ ወአሐደ ይጼለይ ፡ (መጽ ፡ ምስ)።
ተጸልሐወ ፡ ተቃለለ፤ ተሸነገለ፤ ተሞኘ፤ ተበለጠ።
ተጸልበ ፡ ተሰቀለ፤ ተንጠለጠለ፤ ከምድር ከፍ አለ። ተጸልበ ምስለ ኵሉ ቤቱ። ኀበ ተጸልበ እግዚኦሙ ፡ (አስቴ፰ ፡ ፲፫። ራእ፲፩ ፡ ፰)።
ተጸልአ ፡ ተጠላ፤ ተነቀፈ። ርእየ ከመ ትጸላእ ልያ። ዘተጸልኡ በኀበ እግዚ። እስመ ዕሩየ ተጸልኡ ፡ (ኩፋ ፡ ፳፰። ዘፍ፳፱ ፡ ፴፩። ምሳ፳፪ ፡ ፴፩። ጥበ፲፬ ፡ ፱)።
ተፀመረ ፡ ተጨመረ፤ ተደረበ፤ ተጣበቀ፤ ተዋሐደ፤ ፩ ኾነ። ተፀመረ ፅምረት ህላዌ ፡ (ተረ ፡ ቄር)።
ተፀምደ ፡ ተጠመደ፤ ጥንድ ኾነ፤ ከወጥመድ ከወስኮ ገባ፤ ተያዘ፤ አገለገለ። ተፀምደ ምስሌሁ በአሐዱ አርዑት። ተፀመድ መኳንንቲከ። ዘይፈቅድ ይፀመደኒ ፡ (ኩፋ ፡ ፴፯። ሢራ፳፫ ፡ ፲፬። ማር፰ ፡ ፴፬። ማቴ፲፫ ፡ ፶፪)።
፡ ነቃ ተጋ እንቅልፍ ዐጣ ፤ ወደደ አፈቀረ ፤ አዘወተረ ፤ ሥራውን አገልግሎቱን። ተፀምዶ ለተድላ ዝ ዓለም ያማስን ነፍሰ። ይፀመዱ ጸሎተ። ይፀመድ ጸሎታተ ወአጽዋመ። ሐና ነቢይት እንተ ተፀምደት ጾመ ወጸሎተ (አፈ ፡ ተ፳፰። ግብ፩ ፡ ፲፬። ፊልክ ፡ ፯ና ፡ ፶፬)።
ተጸርበ ፡ ተጠረበ፤ ተጠራረበ፤ ተላገ።
ተፀርዐ ፡ ተፈታ፤ ቀረ፤ ታጐለ፤ ተቋረጠ፤ ቆመ፤ ጠፋ ተበላሸ ከንቱ ኾነ፤ ሥራው። አውስቦ ይፀራዕ ለእመ መንኰሱ ብእሲ ወብእሲት። ወእምቅድመ ይፍጥር መላእክተ ለቅዳሴ አኮ ስብሐቲሁ ዘተፀርዐ። ወተፀርዐ ጽድቅ ወርትዕ እምዓለም። ወእምዝ ተፀርዐ ሕንጻ ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፳፬ ፡ ፯። ቅዳ ፡ ግሩ። ዮሴፍ። ዕዝ፬ ፡ ፳፬)።
ተፀርፈ ፡ ተሰደበ፤ የስድብ ቃል ስማ፤ ስድብ ተቀበለ።
ተጸብረ ፡ ጨቀየ፤ ጭቃ ኾነ፤ ላቈጠ፤ ተረገጠ፤ ተቈለለ።
ተጸብአ ፡ ተወጋ፤ ቈሰለ፤ ተዘመተበት። ተግሣሻጽ ይሬስዮ ለመስተጋድል ይጽናዕ ወኢይትመዋእ በውስተ ገድል ወይጸባእ በውስተ ጸብእ ፡ (አፈ ፡ ድ፴)።
ተፀብጠ ፡ ተጨበጠ ተያዘ።
ተጸትመ ፡ ተሰበረ፤ ተቀጠቀጠ፤ ተሰነጋ፤ ተሞከተ።
ተፀንሰ ፡ ተፀነስ፤ ተረገዘ። ተፀንሰ በከርሥ። ዕለት እንተ ባቲ ተፀነስከ። ተፀንሶቱ እንበለ ዘርዕ ፡ (ቅዳ። መጽ ፡ ምስ። ሃይ ፡ አበ)።
ተጸንቀቀ ፡ ተነከረ፤ ተጨማለቀ፤ ፈጽሞ አደፈ።
ተጸንዐ ፡ ተጠና፤ ተያዘ፤ ከልብ ገባ፤ ተረዳ፤ ትምርቱ ቀለሙ።
ተጸንጰወ ፡ ተጨቈነ፤ ተቀጠቀጠ፤ ተጠመዘዘ።
ተጸንጸለ ፡ ተመታ፤ ተቃጨለ። አንቲ ተጸንጻሊ ፡ (አርጋ ፡ ፩)።
ተጸወነ ፡ ተጠበቀ፤ ተጠጋ፤ ጥግ ያዘ፤ ተማጠነ፤ የሙጥኝ አለ፤ ደወለ። ተጸወነ ህየ። ተጸወኑ ውስተ በኣታት። ፈለጠ ስድስተ አህጕረ ከመ ይጸወን ውስቴቶሙ ኵሉ ዘቀተለ ነፍሰ ፡ (ዮሴፍ። ኤር፬ ፡ ፳፱። ስንክ ፡ ሠኔ፳፮)።
፡ ታጠረ ተቀጠረ፤ አንባ ኾነ። ተከበበ፤ ዙሪያው ተያዘ። ወተጸወነት ሀገር እስከ ዐሠርቱ ወአሐዱ ዓመት ፡ (፬ነገ ፡ ፳፬ ፡ ፲። ፳፭ ፡ ፩)።
ተጸውረ ፤ ተያዘ
፤ ተረገዘ ፤ ተጫነ ፤
ሸክም ኾነ።
ተጸውረ በከርሥ።
እፎ ጾርኪዮ ለዘኢይጸወር ተጸውሮ። ውስተ ዕፅ ተጸዊሮ
(ቅዳ። ድጓ። ጥበ፲፬ ፡ ፮)።
ተጸውዐ ፡ ተጠራ፤ ታደመ፤ ተባለ። ዘሎቱ ተጸዋዕከ። ብፁዓን እለ ተጸውዑ ውስተ በዓለ መርዓ በግዑ። ተጸውዐ ስሞሙ ዐረብ ፡ (፩ጢሞ ፡ ፮ ፡ ፲፪። ራእ፲፱ ፡ ፱። ኩፋ ፡ ፳)።
ተጸገወ ፡ ተሰጠ፤ ተሰጠው፤ ተቀበለ፤ አገኘ፤ ታደለ ተመጸወተ። አእምር ዘተጸጎከ። ከመ ትጸገዉ ሕይወተ በኀበ እግዚ። ዘተጸጎኩ ዘንተ ኵሎ እምኔከ። ተጸገዉ ዘንተ ወልደ። ዘንተ ኵሎ ተጸጊዎ ፡ (ዲድ ፱። ዮሴፍ። ስንክ ፡ ሠኔ፬። አርጋ ፡ ፬)።
ተጸግበ ፡ ተጠገበ፤ ተሰለቸ፤ ተጠላ፤ ተነቀፈ።
ተጸፍረ ፡ ተጣፈረ፤ ጥፍሩን ቈረጠ ከረከመ። ኢተጸፍረ ወኢተላጸየ ፡ (፪ነገ ፡ ፲፱ ፡ ፳፬)። ዕብራይስጡ ግን፤ ወኢገበረ ጽሕሞ ይላል፤ አላበጀም አላዘጋጀም፤ አልነቀስም አላበጠረም ማለት ነው፤ ከዚህ በቀር ጥፍር መቍረጥን ራስ መላጨትን አያሳይም። ጐጽፈረን ተመልከት፤ የዚህ ዲቃላ ነው።
ተፀፍረ ተፀፈረ ፡ ተታታ፤ ተሠራ፤ ተጐነጐነ፤ ተሸረበ ተደረበ አንድ ኾነ። በተፀፍሮ ሥዕርቶን። አክሊለ ስብሐት ዘተፀፍረ። ወኵሉ አብድ ዘከመ ዝ ይፀፈር። ተፀፈርነ በህላዌነ እምእለ ኢይትጸየያ ፡ (፩ጴጥ ፡ ፫ ፡ ፫። ኢሳ፳፰ ፡ ፭። ምሳ፳ ፡ ፩። ቄር)። በተፀፍረ ፈንታ ተፃፈረ ይላል፤ ስሕተት ነው። አሕባለ ኃጥኣን ተፃፈራ ላዕሌየ ፡ (መዝ ፡ ፻፲፰)።
ተጸፍቀ ፡ ተጨፈቀ፤ ጭፍቅ አለ፤ በዛ፤ ጽፍቅ ኾነ፤ ተዘጋ ተወተፈ፤ ተጀጐለ። ነዋ ተጸፍቁ ቦቱ ምንዳቤያት ብዙኃት። ማሕፀነ ራሔል ተጸፍቀ ፡ (አፈ ፡ ድ፳፯። ኩፋ ፡ ፳፰)።
ተጸፍነ ፡ ተጨፈነ፤ ተደበቀ፤ ተከተተ።
ተጸፍዐ ፡ ተጸፋ፤ በጥፊ ተመታ፤ ሰውዮው ከበሮው። መዝሙሩ በከበሮና በጸናጽል በጠፊሐ እድ ተዜመ ተባለ። ይጸፋዕ ወይጼዐል። በእደ ገብር ተጸፋዕከ። እንተ አንተ በእንቲኣሃ ተጸፋዕከ በውስተ ዐውድ ከመ ታግዕዛ ፡ (ተረ ፡ ቄር፬። ቅዳ ፡ ያዕ። ዮሐ)።
ተጸፍጸፈ ፡ ተነጠፈ፤ ተለጠፈ፤ ተጸፈጸፈ፤ ደንጊያው። ተሸፈነ ተለበጠ፤ ደንጊያ ለበሰ።
ተጻሕየየ ፡ ታረመ፤ ተነቀለ፤ ተለየ፤ ዐረሙ። ታረመለት፤ ዐረም ጠፋለት፤ እኽሉ ተክሉ መጽሐፉ፤ ባለመስታዮቱ።
ተጻልአ ፡ ተጣላ፤ ተጠላላ፤ ተነቃቀፈ። ኢትፍቅድ ተጻልኦ ምስለ ሰብእ ፡ (ምሳ፫ ፡ ፴)።
ተፃመረ ፡ ተጋባ፤ ተጣመረ፤ ተባበረ፤ ተጫፈረ፤ ተሰማማ፤ ተዋደደ፤ አንድ ኾነ። ብእሲ ይፃመር ምስለ ብእሲቱ። እስመ ትፃመር ነፍስ ምስለ ሰይጣን፤ ከመ ተፃምሮታ ለብእሲት ምስለ ብእሲ። ዘይፃመር ምስለ ጠቢብ ፡ (ኩፉ ፡ ፫። ፊልክ ፡ ፻፲። ምሳ፲፫ ፡ ፳)።
ተፃመደ ፡ ተጣመደ፤ ተጠማመደ፤ ተቈራኘ፤ አጣማጅ ወደረኛ ኾነ፤ ተወዳደረ።
ተፃረረ ፡ ተጣላ ተጠላላ፤ ጠላት ተኳዃነ ተሰላለፈ፤ ለመዋጋት ለመጋደል። ፍችው ከፀረረ ፍች ይገጥማል፤ ባማርኛው የማድረግም ምስጢር አለበት። እለ ይፃረሩኒ በከንቱ። ተፃረርዋ ኵሎሙ ፍቁራኒሃ። አንተ ተፃረርካሁ እምትካት። ቀተለ ኵሎ ዘኮነ ይፃረሮ ፡ (መዝ ፡ ፫። ሰቈ፩ ፡ ፪። መቃ። ዮሴፍ)።
ተፃረፈ ፡ ተሳደበ፤ ተሰዳደበ፤ ተደራራጊ ነው። ባማርኛ ግን ተሳደበ ማለት አድራጊም ይኾናል። መታ ተማታ ተማች፤ እንደ ማለት። ኢተፃረፍክሙ ፡ (አዋል)።
ተጻብሐ ፡ ተሰላለመ፤ የጧት ሰላምታ ተሰጣጠ፤ ጽባሕከ ኄር ወይም እንዴት ዐደርኽ ተባባለ። ወእመ ቦ ዘተጻብሐከ ኢትጻብሖ ፡ (፬ነገ ፡ ፬ ፡ ፳፱)።
ተጻብአ ፡ ተጣላ፤ ተዋጋ፤ ተሳለፈ። ወተጻብኦሙ ውእቱ አርዌ። ወይጻብኡ ምስለ በግዑ። እጻባእ ኅሊናትየ። ወትጻብኡሂ ፡ (ራእ፲፪ ፡ ፯። ፲፯ ፡ ፲፬። ፊልክ። ያዕ፬ ፡ ፪)።
ተጻንሐ ፡ ተጠባበቀ፤ ተቈያየ። ተጻንሑ ቢጸክሙ ፡ (፩ቆሮ ፡ ፲፩ ፡ ፴፫)።
ተጻንዐ ፡ (ጸንዐ) ተጣና፤ ተበራታ ተጠናከረ፤ በገዛ እጁ ወይም ርስ በርሱ። ተደራጊና ተደራራጊ ነው፤ እንደ ተባረከ ኹለት ያሳያል። ተደራጊ ሲኾን የጸንዐ ድርብ ነው። ተደራጊም ቢኾን ተደራራጊነት አይቀርም፤ የሕዋሳትን ርስ በርስ ይሻል። ጊዜ ተጻንዖተ ተቃትሎተ ሰይጣናት ምስሌሆሙ ፡ (ፊልክ ፡ ፹፭)።
ተጻዐለ ፡ ተሳደበ፤ ተሰዳደበ። ይጻዐሉ ወይትዋገሩ ፡ (ግብ፲፬ ፡ ፭)።
ተጻዐቀ ፡ ተጫነቀ፤ ተጣበበ፤ ተጋፋ፤ ተነባበረ ጽፍቅ ኾነ። አኮኑ ይጣወቅ ሰብእ ወይጻዐቀከ ፡ (ሉቃ፰ ፡ ፵፭)።
ተጻዐነ ፡ ተጫጫነ ተሸካከመ፤ ተነባበረ፤ አንዱ ባንዱ ላይ።
ተጻዓቂ ፡ የሚጫነቅ፤ የሚጣበብ፤ የሚጋፋ የሚፋተግ፤ ተጨናናቂ። መዛሕም፤ ዘበትርጓሜሁ ትጻ(ጸ) ዓቂ ፡ (ስንክ ፡ ሠኔ፲፱)። መዛሕምን ተመልከት።
ተፃእፅአ ተፀአፅአ ፡ አነሰ ተቀነሰ እንስንስ አለ፤ ጭንጋፍ ኾነ። ሰገደ ተዋረደ፤ ለጣዖት ተገዛ። ወተፀአፅኡ ተግባሮ ፡ (ሮሜ፩ ፡ ፳፭)። ፍጡር ኹኖ ፈጣሪ አለኝ ማለት እንደ መፅነስና እንደ መፀነስ ነው፤ በፈጣሪ ፈንታ ፍጥረትን ማምለክ ግን እንደ መውረድ እንደ ማሶረድ፤ ዘርቶ እንዳለመቃም ወልዶ እንዳለመሳም ነውና፤ ምስጢሩ የውቀትን ሕጸጽ፤ ተፀንሶ በቅሎ አለማደግን ባጭር መቀጨትን በዝርዝር መቅረትን ያሳያል።
ተጻወረ ፡ ተሸካከመ ፤ ተቻቻለ፤ ተነባበረ። ተጻወራ በበይናቲሆን፤ በበ አሐቲ እብን ጾራ ኅቡረ ፡ (ሄርማ)።
ተጻውዐ ፡ ተጣራ፤ ተጠራራ። ቀላይ ለቀላይ ተጻውዓ በቃለ አስራብ ፡ (መዝ ፡ ፵፩)።
ተጻገበ ፡ ተጣገበ፤ ተሰላቸ፤ ተሰለቻቸ።
ተጻገወ ፡ ተሰጣጠ፤ ተቀባበለ፤ ተቻቻረ፤ ይቅር ተባባለ ፡ (ራእ፲፩ ፡ ፲። ኤፌ፬ ፡ ፴፪። ቆላ፫ ፡ ፲፫)።
ተፃፈረ ፡ ተጫፈረ፤ ተባበረ፤ በዋዌ። አነ ወአብ አሐዱ ንሕነ ፡ (ዮሐ፲ ፡ ፴፩)።
ተጻፈቀ ፡ ተጫፈቀ፤ ተጨፋፈቀ፤ ተጠጋጋ። ኢንጻፈቅ አላ ንትራሐቅ፤ ብእሲ ብእሲ እምካልኡ። እስመ ገብኡ ወተጻፈቁ ብዙኃን ኀቤሁ ፡ (፪ዕዝ ፡ ፲፬ ፡ ፲፱። ፪ዜና ፡ ፲፭ ፡ ፱)።
ተጼሐ ፡ ተጠረገ፤ ተደለደለ፤ ተበጀ ተዘጋጀ፤ ተከናወነ። ትጸያሕ ፍኖተ ራትዓን። ይጸያሕ ዐውዱ ለማኅፈድ። ይጸያሕ ሎቱ ኵሉ ግብር ፡ (ኤር፳፮ ፡ ፯። ሄርማ። አፈ ፡ ተ፳፮)።
ተፄወወ ፡ ተማረከ፤ ተወሰደ፤ ፈለሰ። ከመ ኢይፄወዋ አንስቲያሆሙ። ተፄወዉ ሕዝብየ። እስከ ተፄወዉ እምነ ብሔሮሙ ፡ (ዮዲ፬ ፡ ፲፪። ኢሳ፭ ፡ ፲፫። ሢራ፵፰ ፡ ፲፭)።
ተጽሕፈ ፡ ተጣፈ፤ ተቈጠረ፤ ተጣፈበት። ተጽሕፈ ዐርከ እግዚ ውስተ ጽላተ ሰማይ። ለተጽሕፎ፤ ሀገረ ዳዊት ዐርገ። ጽላት እለ ተጽሕፋ በአጻብዒሁ ለእግዚ ፡ (ኩፋ ፡ ፲፬። ስንክ ፡ ታኅ፳፰። ዘዳ፱ ፡ ፲)።
ተጽራሕ ፡ (ሓት) ደርብ፤ ኹለተኛ ክፍል። ተጽራሕ ወተሥላስ ፡ (ዘፍ፮ ፡ ፲፮)።
ተጽናስ ፡ ዝኒ ከማሁ፤ ችግር፤ ችጋር ቀጠና፤ ረኃብ ዕርዝና፤ ፍጹም ድኽነት። ተጽናስከ ይሰድዶሙ ለአዕርክቲከ። ዘይፈቅዱ ለተጽናሶሙ። ብዕልሰ እመ በጽድቅ ወበኀጢአት ተጽናስ፤ አክአብ እንዘ ሀሎ እምኢተጸነሰ ኤልያስ ፡ (ሢራ፲፪ ፡ ፱። ያዕ፪ ፡ ፲፮። ቅኔ)።
ተጽዕለ ፡ ተጣለ፤ ተሰደበ፤ ተዋረደ። ተጽዕልኩ በኀበ ኵሎሙ ጾላእትየ። ንሰርሕ ወንጼዐል። ወተጽዕልክሙ ፡ (መዝ ፡ ፴። ፩ጢሞ ፡ ፬ ፡ ፲። ዕብ፲ ፡ ፴፫)።
ተጽዕቀ ፡ ተጨነቀ፤ ተጠበበ፤ በቦታ በመከራ። አንዘ ይጸዐቁ አሐዱ ምስለ ካልኡ። ባልሖሙ እምነ ገዐር ወተጽዕቆተ ግብር ዘነበሩ ባቲ ፡ (መቃ። አፈ ፡ ድ፳፯)።
ተጽዕነ ፡ ተጫነ፤ ተቀመጠ፤ ሸክም ኾነ፤ በላይ። ተጫነበት፤ ተሸከመ፤ ተደበለለ፤ ጸዋሪ ኾነ። ተጽዕነ ላዕለ ኪሩቤል። እስመ ተጽዕንከ ዲበ አፍራሲከ። ናሁ ፈረስ ጸዐዳ ወዘይጼዐኖ ቀስተ ያጸንዕ። ተጽዕነ ላዕሌዑ ሰይጣን ፡ (መዝ ፡ ፲፯። ዕን፫ ፡ ፰። ራእ፮ ፡ ፪። ስንክ ፡ መስ፲፱)።
ተጽዕደ ፡ ተጣደ፤ ምድር ለቀቀ፤ ከጕልቻ ላቀ፤ በላይ ኾነ፤ ጕልቾች የሳንሳ ያዙት፤ ተሸከሙት።
ተጽዕጠ ፡ ተቀመመ፤ ተጣፈጠ፤ ተነጠረ፤ ተዘጋጀ። ተቀባ ተረጨ ተረበረበ፤ ሽቱው ስዉ ልብሱ።
ተጽፋቅ ፡ (ቃት) ጽፍቅነት፤ ጨፈቃ፤ ጀጐል፤ ሽምጥ፤ ውታፍ። ይትዐጸው ሙላድ በተጽፋቀ ማሕፀን። ሥብ ወፍር ፡ (መጽ ፡ ምስ)።
፡ ምልአት፤ ምሉነት፤ ልባጥ ልብጣት። ዕንቍ ዘተጽፋቅ ለዐጽፍ ፡ (ዘፀ፴፭ ፡ ፳፯)።
ተፈልየ ፡ ተለየ፤ ተመረጠ፤ ምራጭ ኾነ። ፡ (ተረት) መራጭ ይወድቃል ከምራጭ። በኢተፈልዮ። እንዘ አልብኪ ተፈልዮ ፡ (ስንክ ፡ ሠኔ፪። ደራሲ)።
ተፈልጠ ፡ ተለየ፤ ተመረጠ፤ ተበተነ፤ ታወቀ። ዘይፈቅድ ይትፈለጥ እምአዕርክት። ዘተጸውዐ ወተፈልጠ። ተፈልጡ አርድእት እስከ አጽናፈ ዓለም ከመ ይስብኩ ዜና ወንጌል። ባቲ ይትፈለጥ መዋዕል ፡ (ምሳ፲፰ ፡ ፩። ሮሜ፩ ፡ ፩። ቀሌ። ሢራ፵፫ ፡ ፮)።
ተፈልጸ ፡ (ዕብ ሂትፋሌጽ፤ ደንገፀ ተሰብረ) ተፈለጠ፤ ተሠነጠቀ፤ ነከተ ደቀቀ። እምከመ ረግዐ አስሐትያ ይትፈለጽ ከመ ስባራት ማህው በሊኃት ፡ (ሢራ፵፫ ፡ ፲፱)።
ተፈሥሐ ፡ ተደሰተ፤ ደስ አለው፤ ደስ ተሰኘ። ተፈሥሐ ወሰትየ። ተፈሥሐ ልቡ። እለ ይትፌሥሑ በድቀቱ ለጻድቅ ፡ (ኩፉ ፡ ፯። ሩት፫ ፡ ፯። ሢራ፲ ፡ ፳)።
ተፈርሀ ፡ ተፈራ፤ ተፈሪ ኾነ። ዘይትፈራህ በእንቲኣሁ ሞት። ይትፈቀር እስመ መሓሪ፤ ይትፈራህ እስመ እግዚ ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፲፭። መዋሥ)።
ተፈርቀ ፡ ተከፈለ፤ ዳነ ተለቀቀ፤ ወጣ፤ አመለጠ።
ተፈርነሰ ፡ በቁሙ፤ ተፈረነሰ፤ በላ ጠገበ፤ ተመገበ፤ ተኛ ተጋደመ፤ ደስ አለው፤ ከዚህ የተነሣ ልቡ ታበየ፤ ክፉ ዐሰበ። ለእመ መጠውከ ርእሰከ ለተፈርንሶ ፡ (ምሳ፳፬ ፡ ፳፯)።
ተፈርዘዘ ፡ ተንፈረዘዘ፤ ፈካ ፈነዳ፤ ወለደ ዘረዘረ። ይትፈረዘዝ ቍልሕ ፡ (መክ፲፪ ፡ ፭። አርጋ ፡ ፮)።
፡ ተደሰተ
፤ ደላው ደስ አለው ፤ ሣቀ ፈነደቀ ፤ አወካ ተሽካካ። አኮ ከመ ንንበር ዘልፈ በሠሐቅ ወተፈርዝዞ። አንበሳ ምኵሕ ልሙደ ደም ለተፈርዝዞ (አፈ ፡
ተ፲፭። አዋል)።
፡ ተበተነ
ተበታተነ ፤
ተዘራ በነነ
፤ ጠፋ
እንደሌለ ኾነ። ይትፈረዘዝ ከመ
ጊሜ (ጥበ፪ ፡
፬)
ተፈርደ ፡ ተፈረደ፤ ተለየ ተነጠለ፤ ነጠላ ኾነ።
ተፈቅረ ፡ ተወደደ፤ ተሳበ ቀረበ፤ ባለሟል ኾነ። ይትፈቀሩ በእንቲኣኪ ጽሉኣን። ኮንኩ እትፈቀር በገጸ እምየ። ተፈቀር በኀበ ብዙኃን። ፈቀደ ይግበር ግብረ ዘይትፈቀር ቦቱ በኀበ ቄሳር ፡ (ጦቢ፲፫ ፡ ፲። ምሳ፬ ፡ ፫። ሢራ፬ ፡ ፯። ዮሴፍ)።
ተፈቅዐ ፡ ተገመሰ፤ ተፈነከተ፤ ቈሰለ።
ተፈቅደ ፡ ተፈቀደ፤ ተጐበኘ፤ ተቈጠረ፤ ተወደደ፤ ተፈለገ። ሰላም ለሚልክያስ እንተ አድምዐ ተፈቅዶ፤ ምስለ ንኡሳን ነቢያት። ዘኢይትፈቀድ ነገር። እንተ ትትፈቀድ በኵሉ። ዘይትፈቀድ ለነፍስቶሙ ፡ (ስንክ ፡ ጥር፰። ሢራ፳፩ ፡ ፲፰። ምሳ፮ ፡ ፰። ሮሜ፲፭ ፡ ፳፯)። በተፈቅደ ፈንታ ተፋቀደ ይላል፤ ስሕተት ነው። ኵልክሙ እለ ተፋቀድክሙ ፡ (ዘኍ፲፬ ፡ ፳፱)።
ተፈተተ ፡ በቁሙ፤ ተቈረሰ፤ ተገመሰ። ወይትፌተት እብነ በረድ። ዝ ውእቱ ሥጋየ ዘበእንቲኣክሙ ይትፌተት ለኅድገተ ኀጢአት ፡ (ሢራ፵፫ ፡ ፲፭። ቅዳ ፡ እግዚ)።
ተፈትሐ ፡ ተከፈተ፤ ተፈታ፤ ቀለጠ፤ ፈረሰ፤ ተለየ ተከፈለ። ተፈትሑ መዓምቅት። ተፈትሐ ማኅሜሁ እምነ መዝራዕቱ። ተፈትሐ ማይ ዘረግዐ። ወይትፈታሕ ማእሰረ ተዋስቦ። ተፈትሐ መሌሊተ ሐቌሁ ፡ (ሔኖ። መሳ፲፭ ፡ ፲፬። ስንክ ፡ ሚያ፳፭። ፈ ፡ መ ፡ ፲፪ ፡ ፭። ዳን፭ ፡ ፮)። ተፈታሕ በማለት ፈንታ ኤፍታሔ ሕ ይላል፤ የተሳሳተ ነው ፡ (ማር፯ ፡ ፴፬)።
፡ ተፈታ፤ ፍትሐት ዘወልድ ተደገመለት፤ ግንዘት መዋሥዕት ደረሰለት፤ ኀጢአቱ ይቅር ተባለለት፤ የተናዛዥ የሙት። ተፈትሐት ኀጢአታ። እምዝኒ ኵሉ ነገር ታሐዝነኒ ይሉኝታ፤ አምጣነ ካህናት ቀተልዋ ወተቀብረት ሳትፈታ ፡ (ኢሳ፵ ፡ ፪። ቅኔ)።
፡ ተፈረደ ፡ (ለት፤ በት)። ታዘዘ፤ ተሠራ። ተፈትሐ ላዕሌሁ ፍትሐ ሞት። ተወሰነ ወተፈትሐ ላእለ ኵሎም ምእመናን ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፴፬። ፈ ፡ መ ፡ ፲ ፡ ፫)።
ተፈትለ ፡ ተፈተለ፤ ተከረረ። ልብስ ዘኢተፈትለ ወኢተአንመ በእደው ፡ (ሲኖዶ። ሳታ)።
ተፈትነ ፡ ተፈተነ፤ ተሞከረ፤ ተመረመረ፤ ፈሰሰ ቀለጠ። እለ ተመከሩ ወተፈትኑ። መንፈስ ሕያው ወቅዱስ ዘኢይትፈተን። ወርቅ ይትፈተን በምንሃብ ፡ (አፈ ፡ ተ፰። ቅዳ ፡ ዮሐ። ጥበ፫ ፡ ፮)።
ተፈትወ ፡ ተወደደ፤ በለጠ ከበረ። መክፈልት ዘይትፈቶ። ወይትፈቶ እምወርቅ ወእምዕንቍ ፡ (ጥበ፫ ፡ ፲፬። መዝ ፡ ፲፰)። ወሰደ ተማለደ በማለት ፈንታ ተፈትወ ይላል፤ የተሳሳተ ነው። ተፈቲዎ። ተፈቲውየ ፡ (ዘፀ፳፪ ፡ ፲፩። ዘኍ፲፮ ፡ ፲፭)።
ተፈነወ ፡ ተላከ፤ መጣ፤ ቀረበ፤ ተወረወረ፤ ተሸኘ። ተፈነወ ኀቤየ አሐዱ እምሱራፌን። ጸሎት እንተ ትትፌኖ ውስተ ዝንቱ መካን። ወለከ ይትፌኖ ጸሎት በኢየሩሳሌም። ተፈነወ ኵናት ኀቤሁ። ወእምኀቤክሙ እትፌኖ ህየ ፡ (ኢሳ፮ ፡ ፮። ፪ዜና ፡ ፯ ፡ ፲፭። መዝ ፡ ፷፬። አፈ ፡ ተ፳፪። ሮሜ፲፭ ፡ ፳፬)።
ተፈከረ ፡ ተተረጐመ፤ ተፈታ፤ ተመረመረ። ዕጹብ ዝ ነገር ወኢይትፌከር። ኦ ዝንቱ ምስጢር ዘኢይትፌከር ወዘኢይተረጐም ፡ (ቄር ፡ ጰላ። ቅዳ ፡ አፈ)።
ተፈወሰ ፡ በቁሙ፤ ዳነ፤ ሻረ፤ ታከመ፤ መድኀኒት ተደረገለት። ወለእለሂ ይፈቅዱ ይትፈወሱ አሕየዎሙ። ከመ ይትፈወስ እምቍስሉ። ተፈወሰ ውእቱ ማይ። ሀለወ ይትፌወስ ንድፈቶ። እንበለ ትሕምም ተፈወስ ፡ (ሉቃ፱ ፡ ፲፩። ፪ዜና ፡ ፳፪ ፡ ፮። ፬ነገ ፡ ፪ ፣ ፳፪። ፱ ፡ ፲፮። ሢራ፲፱ ፡ ፲፱)።
ተፈየ ፡ (ሰፈወ፤ ተሰፈወ) አመነ፤ ታመነ፤ ተስፋ አደረገ። አነ እተፊ ከመ ለእመ ነበርከ ውስተ በኣትከ በስመ እግዚ፤ ትትረከብ ውስተ መካነ እንጦንዮስ። ተኀድግኑ ግብረከ ወትተፊ ላዕሌሁ። እተፊ ላዕሌክሙ። በሃይማኖትከ እስመ ነፍስየ ትተፊ ፡ (ፊልክ ፡ ፶፬። ኢዮ፴፱ ፡ ፲፩። ፪ቆሮ ፡ ፲ ፡ ፲፩። ስንክ ፡ ጥቅ፲፯)።
ተፈየተ ፡ ተቀማ፤ ተሰረቀ። ተፈይቶ በኅቡእ ፡ (ሲኖዶ)።
ተፈድየ ፡ ተከፈለ፤ ተቀበለ። ዮም ለእመ ወሀበከ ጌሠመ ይትፈደየከ። ትትፈደዩ ዕዳክሙ ወትሰክዩ ፡ (ሢራ፳ ፡ ፲፭። ኢሳ፶፰ ፡ ፫)።
፡ ተቀጣ፤ ቅጣት ተቀበለ። ይትፈደይ በከመ ገብረ። ተፈድየት እምእደ እግዚ ካዕበተ ኀጢአታ። በእፎ ኢይትፈደይ ወልድ በኀጢአተ አቡሁ ፡ (ኢዮ፳፬ ፡ ፳። ኢሳ፵ ፡ ፪። ሕዝ፲፰ ፡ ፲፱። ሉቃ፳፫ ፡ ፵፩)።
ተፈጥረ ፡ ተፈጠረ፤ ተገኘ፤ ተሠራ። እምቅድመ ይትፈጠር ዓለም። ኵሉ እምነ ምድር ተፈጥረ። ሰንበትሰ ተፈጥረት በእንተ ሰብእ ፡ (ቅዳ። ሢራ፵፩ ፡ ፲። ማር፪ ፡ ፳፯)።
ተፈጸመ ፡ በቁሙ፤ መላ፤ ተጨረሰ፤ ዐለቀ፤ በቃ ፍጹም ኾነ። ከመ ይትፈጸም ዘተብህለ። ኢተፈጸመ ኀጢአቶሙ እስከ ይእዜ። እምኢተፈጸመ ሎሙ ዝ። ወበዝንቱ ትትፌጸም ተፋቅሮ ፡ (ማቴ፩ ፡ ፳፪። ኩፋ ፡ ፲፬። ዮሴፍ። ፩ዮሐ ፡ ፬ ፡ ፲፯)።
ተፈጽሐ ፡ ተገመሰ፤ ተፈለጠ፤ ተፈነከተ። ኰኵሕ ኢይትፈጻሕ በጕድብ ወበማሕጼ ከመ ዕፀው። በከመ እብነ አድማስ ዘኢይትፈጻሕ ፡ (መጽ ፡ ምስ። አፈ ፡ ተ፳፪)።
ተፈፅመ ፡ ተዘጋ፤ ታፈነ፤ ተደፈነ፤ ተከለከለ፤ ምላሽ ዐጣ፤ ዝም አለ። ተፈፅመ አንቅዕተ ቀላይ። ተፈፅመ አፈ ኵሉ አራዊት። እምነቢብ ይትፈፀም አፉሁ ለዐማፂ። ኀያላን ይትፌፀሙ ወኢይነብቡ ፡ (ኩፋ ፡ ፫ና ፡ ፭። ኢዮ፭ ፡ ፲፮። ፳፬ ፡ ፱)።
ተፉሕ ፡ (ሓት። ዐረ በጣጣ) ድንች፤ ትፋሕማ የምድር ትፋሕ፤ ወጥ የሚኾን።
ተፊእ ኦት ፡ (ተፍአ ይተፍእ ይትፋእ። ዕብ ቱፍ። ዐረ ተፈፈ፤ ተፈለ) መትፋት፤ ምራቅን አክ እንትፍ ጢቅ ማለት፤ መቀርሸት ማስመለስ። አዘዘ ከመ ይትፍኡ ምራቀ። ተፍአት ቅድመ ገጽ። እንዘ ይተፍእ ሕምዞ ላዕሌነ ፡ (መጽ ፡ ምስ። ቀሌ። ተረ ፡ ቄር)።
ተፋለሰ ፡ (ተገብሮ ወተጋብሮ፤ በተገብሮነቱ የፈለሰ ድርብ) በቁሙ፤ ተዛወረ፤ ተዘዋወረ፤ ተገላበጠ፤ ተለዋወጠ፤ ተወራረሰ። እለ ይትፋለሱ ውስተ ገዳማት። ዘይትፋለስ ውስተ ምስካቢሁ። ተፋልሶተ ጊዜያት። ዝንቱ መጽሐፍ እንዘ ይትፋለስ እምትውልድ ውስተ ትውልድ በጽሐ ኀበ እግዝእትነ ማርያም ፡ (አፈ ፡ ድ፳፰። ሢራ፳፰ ፡ ፲፰። ስንክ ፡ ሚያ፮)።
ተፋለየ ፡ ተለያየ፤ ተከፋፈለ፤ እየብቻው ኾነ። ተጋብኡ ኀበ ቍድስ ሰብእ ብዙኃን ወተፋለየ ነገሮሙ ወበዝኀ ቀትል ማእከሌሆሙ። ወሶበ አእመሩ ሮም ተፋልዮተ ነገሮሙ ለአይሁድ ቀርቡ ኀበ ቅጽር። ዐብየ ክላሕ ወተሀውከት ሀገር በእንተ ተፋልዮቶሙ ለሰብእ ፡ (ዮሴፍ)።
ተፋለጠ ፡ ተለያየ፤ ተከፋፈለ። ተማዕዑ ወተፋለጡ ዘዘ ዚኣሆሙ ፡ (ግብ፲፭ ፡ ፴፱። ፫ነገ ፡ ፲፮ ፡ ፮)።
ተፋሰሰ ፡ ተዓፀወ፤ ዕፃ ተጣጣለ፤ ተሻኰተ፤ እንሻኰት አለ፤ በጣት። ኢንግምድ ወኢንሥጥጥ፤ አላ ንትፋሰስ ላዕሌሁ ለዘረክቦ ይርከቦ ፡ (ዮሐ፲፱ ፡ ፳፬)።
ተፋረቀ ፡ ተካፈለ፤ ተከፋፈለ፤ ተፈራረቀ፤ ተጋገዘ። ባረየን ተመልከት።
ተፋረደ ፡ በቁሙ፤ ተፈራረደ፤ ተለያየ፤ ተነጣጠለ። አልቦ ፍዳ በዘይትፋረዱ ወይመጽኡ ውስተ ሲኦል ፡ (መጽ ፡ ምስ)።
ተፋርሀ ፤ ተፋራ
፤ ተፈራራ።
ተፋቀረ ፡ በቁሙ፤ ተዋደደ፤ ተሰማማ፤ አንድ ኾነ። ተፋቀሩ በበይናቲክሙ። ከመ ይትፋቀር ምስለ ውሉዱ። ተፋቀር ምስለ ብእሲትከ ፡ (ኩፋ ፡ ፴፭። ዮሴፍ። ምሳ፭ ፡ ፲፱)።
ተፋቀደ ፡ ተቋጠረ፤ ተቈጣጠረ፤ ተጐበኛኘ፤ ተፈላለገ፤ ተመራመረ። ተፋቀዱ ወአእምሩ መኑ ዘሖረ እምኔክሙ። ወተፋቀዱ ሕዝብ ፡ (፩ነገ ፡ ፲፬ ፡ ፲፯። መሳ፳፩ ፡ ፱)።
ተፋተነ ፡ በቁሙ፤ ተፈታተነ፤ ተሟከረ። ዘእንበለ ይትፋተን ምስለ እግዚ ፡ (ገድ ፡ ኪሮ)።
ተፋትሐ ፡ ተፋታ፤ ተፍታታ፤ ተለያየ፤ ተላቀቀ፤ ተሟገተ፤ ተፋረደ ተካሰሰ። ይጣበቁ ወኢይትፋትሑ። ኢትትፋታሕ ምስለ ኤጲስቆጶሳት። ኢይትፋትሑ ምእመናን በኀበ እለ ኢየአምኑ። ይትፋትሑ በበይናቲሆሙ ሥርዐተ ሠናይ አምልኮ ፡ (ኢዮ፵፩ ፡ ፰። ዲድ ፡ ፱። ፍ ፡ ነ ፡ ፵፫ ፡ ፱። ቀኖና)።
ተፋነወ ፡ ተላላከ፤ ተሸኛኘ፤ ተሰናበተ። ወእምዝ ተፋነውዎ። አንሰ እትፋነወክሙ። ሑር ተፋነዎሙ ለአዝማዲከ ፡ (ስንክ ፡ ጥቅ፱። የካ፫። ነሐ፲፬)።
ተፋአመ ፡ ተጓረሠ፤ ተጐራረሠ።
ተፋኢ ፡ (ኢት እያን ያት) የሚተፋ፤ ትፋታም፤ ቅርሻታም። ተፋእያነ ሕምዘ ከይሲ ወአርዌ ምድር ፡ (ኪዳ)።
ተፋወለ ፡ ጠነቈለ፤ አሟረተ። መሠርይ ወዘይትፋወል በፍሬ ዕፀው ወዛጐል ዲበ ሐመድ። ኢትኩን እምእለ የዐቅቡ ሰዓታተ ወኀራይያነ ዕለታት፤ ወኢረዩኣዩ ከዋክብት፤ ወኢእምእለ ይትፋወሉ ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፲፩ ፡ ፩ና ፡ ፫)።
ተፋጠነ ፡ በቁሙ፤ ተቻኰለ፤ ተቸኳኰለ። ኢይትፋጠነኒ ፡ (፪ቆሮ ፡ ፲፪ ፡ ፲፬)።
ተፋጸየ ፡ ተፏጨ፤ ተፎጫጨ፤ በፉጨት ተጣራ።
ተፍሕሰ ፡ ታሸ፤ ተዋሐደ፤ ቀላ ታለለ፤ ቀይ ቀለም ገባ፤ ልብሱ ፈትሉ።
ተፍኅረ ፡ ታጨ፤ ተፈለገ፤ ዕጮኛ ኾነ፤ ለግቢ ተስጠ። ድንግል እንተ ይእቲ ሕፅይት፤ አው ተፍኅረት ለብእሲ ፡ (ፈ ፡ መ ፡ ፮ ፡ ፰። ማቴ፩ ፡ ፲፰። ሉቃ፩ ፡ ፳፯)።
ተፍሕቀ ፡ ተፋቀ፤ ለዘበ፤ ተነጠጠ።
ተፍእመ ፡ ተጐረሠ፤ ምግቡ። ጐረሠ፤ ካፉ አገባ። አባ አጋቶን ተፍእመ እብነ ከመ ኢይትናገር ነገረ ፅሩዐ። ዘየአክሎ ለተፍእሞቱ። ከመ ኢይትፈአምዎ ክልኤ ጊዜ። አይ አፍ ዘይትፈአም ዘንተ ኅብስተ። ይመሥጡ ኅብስተ ወይትፈአምዎ እንበለ አእምሮ፤ ወእምድኅረ ዝ ይመውቱ። በተፍእሞ ሣዕር ልምሉም ፡ (ስንክ ፡ መስ፲፮። ፈ ፡ መ ፡ ፳፮ ፡ ፮–፯። ቅዳ ፡ ሕር። ዮሴፍ። ስንክ ፡ የካ፲፮)።
ተፍጻሜት ፡ ዝኒ ዓዲ ከማሁ። ተፍጻሜተ ዓመት። ተፍጻሜተ ሰማዕት። ተፍጻሜቱ ለዝ ዓለም። እስከ ተፍጻሜቱ። ወእምተፍጻሜተ ዚኣሁ ለኵሉ ይሁብ ፡ (ኩፋ ፡ ፬። ስንክ ፡ ኅዳ፳፱። ዕር ፡ ኢሳ፲፩ ፡ ፴፯። መክ፫ ፡ ፲፩። ተረ ፡ ቄር)።
ተፍጻም ፡ ዝኒ ከማሁ፤ መጨረሻ፤ መደምደሚያ፤ ምላት። አመ ተፍጻመ ወርኅ አዕረፈ። እፎ ፈቀደ ኅሊናየ ለውዳሴኪ ተፍጻሞ ፡ (ስንክ ፡ ግን፴። ደራሲ)።
(ጥ) ቱማ ፡ (ሱር ቱማእ) ሶመት፤ ነጭ ሽንኵርት። ኢይባርኩ ላዕለ ሰግላ ወኢላዕለ በጸል ወኢላዕለ ቱማ ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፲፯። ሲኖዶ)።
ቱሱሕ ፡ (ሓን ሓት ስሕት) የተቀላቀለ፤ ቅልቅል፤ ድብልቅ፤ ዝንጕርጕር፤ አንድ ዐይነት ብቻ ያይዶለ። ወይን ምስለ ከርቤ ቱሱሕ። ወትካትሰ ሰማያት ቱሱሕ ምስለ ማይ ወምድርኒ ሀለወት ምስለ ማይ። ሠናይ ዘይረክብ ሰብእ በዝ ዓለም ቱሱሕ በጻማ ወድካም። እስመ ቱስሕት በቍር ወሞቅ ፡ (ማር፲፭ ፡ ፳፫። ቀሌ። ዮሴፍ። ኩፋ ፡ ፰)።
፡ተጣይ ርባ ፤
ቶማሳዊ ግስ ፤ በመጥበቅና በመላላት በመንታ መንገድ የሚኼድ ፤ ሲጠብቅ
ቀደሰን ሲላላ ቀተለን
የሚመስል። (ማስረጃ) ፤ አሚር ፤ አመረ የአምር ይእምር። መሲል ፤ መሰለ ይመስል ይምስል። ተቢዕ ፤ ተብዐ ይተብዕ
ይትባዕ ፤ የቀተለ። አምሮ አመረ ይኤምር
የአምር። መስሎ መሰለ ይሜስል ይመስል። ተብዖ ተብዐ ይቴብዕ ይተብዕ ፤ የቀደሰ። ይህን የመሰለ ኹሉ።
ቱሳሔ ፡ (ሕያት) ዝኒ ከማሁ፤ መቀላቀል፤ ፡ (ጥቀ) መቀላቀል፤ አቀላቀል፤ ቅልቅልነት፤ ቅልቅል መኾን፤ እንደ ማርና እንደ ወተት፤ እንደ ውሃና እንደ መሬት፤ ወይም እንደ ዶቄትና እንደ ዶቄት። ቅልቀላ፤ ድብለቃ፤ ጭመራ፤ ብረዛ፤ ክለሳ፤ ጭማሪ ተውሳክ። ቍረተ ቱሳሔ ዘርዕ። አሕላም ይትወለዱ እምቱሳሕያተ ጠባይዓት አርባዕቱ። ሕንብርትከ ሕንብርተ መንፈስ ረቂቅ ዘቱሳሔሁ መብረቅ ፡ (ፈ ፡ መ ፡ ፲፪ ፡ ፭። ፈላስ። ደራሲ)።
ቱስሕት ፡ የተቀላቀለች፤ ቅልቅል። መቀላቀል፤ ቅልቅልነት፤ ቅልቀላ ድብለቃ። ጭማሪ ተውሳክ። እስመ ድኩም ቱስሕተ ነፍስትክሙ። ትድምረት ዘእንበለ ቱስሕት ወሚጠት። አክራጦን ዘአልቦቱ ቱስሕት። ሐሊብ ነባቢ ዘአልቦቱ ቱስሕት ፡ (፩ቆሮ ፡ ፯ ፡ ፭። ቄር ፡ ጰላ፤ ተረ። ፩ጴጥ ፡ ፪ ፡ ፪)።
ቱት ፡ (ዐረ ወዕብ) የዛፍ ስም፤ ቅጠሉን የሐር ትሎች የሚበሉት፤ ፍሬው ጥፍጥ ያጋም የእንዦሪ ዐይነት፤ ዐጽቃም ቅጠላም።
ቲሃ ፡ ችቦ ፡ ሽማ ፡ ዳቦት የጭራሮ ፡ መብራት።
ቲቶ [1] ፡ ተውት፤ ስመ ወርኅ፤ መስከረም። ተውትን ተመልከት፤ ከዚህ ጋራ አንድ ነው። ሠርቀቲቶ፤ የመስከረም መባቻ ፡ (መር ፡ ዕዉ)።
[2] ፡ የሰው ስም፤ የጳውሎስ ረድ ፡ (ገላ፪ ፡ ፩)።
ቲን ቴና ፡ —ርሕብ ግዘፍ፤—ተኒን
ቲግራ ፡ (ዕብራ) ቍጣ ብስጭት፤ ወፈፍታ ቅለት፤ ጠብ ጠበኝነት።
ታሕማ ፡ (ማት) ዐምቻ ጋብቻ፤ ዐማችነት። ገብረ ታሕማ ምስለ ነገሥተ አሕዛብ ፡ (አርጋ ፡ ፭)። ዐማች፤ የሴት ልጅ ባል። ወይቤልዎ ለሎጥ ብከኑ ታሕማ በዝየ። ወወፅአ ኀበ ታሕማቲሁ ፡ (ዘፍ፲፱ ፡ ፲፪ ፡ ፲፬)።
፡ ዐማት ፤ የባል ወይም የሚስት አባት እናት። አክብሪ ታሕማኪ። ወቀበሮሙ በክብር ለታሕማቲሁ (ጦቢ፲ ፡ ፲፪። ፲፬ ፡ ፲፫)።
ታኅማስ ፡ ዐምስት፤ ዐምስተኛ። ታኅማሰ ዓመታት ሠሰስቱ። ሰመንቱ ሰዓት ወአርባዕቱ ታኅማስ ሰዓት ፡ (ስንክ ፡ ታኅ፲፭። ሚያ፲፭። አቡሻ ፡ ፵፬)።
ታኅሣሥ [1] ፡ ምርምር ምርመራ፤ ፍላጎት ፍለጋ። በቁሙ ትሣሥ፤ የወር ስም፤ የመስከረም አራተኛ። ወርኀ ታኃሥሦ ማለት ነው ፡ (ማቴ፪ ፡ ፩–፯)።
[2] ፡ ወር ክትክታ፤ ኀሠሠ።
ታኅሦሥ ፡ (ትግሪኛ) ስመ ዕፅ፤ ክትክታ፤ ቅጠሉ ቀንበጡ ለሐዲስ ምጣድ ማሟሻ ማሠሻ የሚኾን። ዕንጨቱም እንደ ፍየለ ፈጅ ተቀጥቅጦ መብራት ይኾናል።
ታሕተ ፡ በታች፤ ወደ ታች። ንበር ታሕተ። ወረደ ታሕት። ተወረው ታሕተ።
ታሕታዊ ይ ፡ (ዊት ይት ቲት) የታች፤ ታችኛ፤ መጨረሻ፤ በታች ያለ። ከንፈሩ ታሕታይ የዐቢ። ታሕታይ ማኅደር። ሀገረ ታሕታይተ ወላዕላይተ። ሲኦል ታሕቲት። ግብ ታሕቲት ቀላይ ታሕቲት ፡ (ኪዳ። ቀሌ። ፩ዜና ፡ ፯ ፡ ፳፬። መዝ ፡ ፹፭። ሰቈ፫ ፡ ፶፬። ኩፋ ፡ ፭)።
ታሕት ቱ ፡ (ዕብ ታሐት። ሱር ታሕታ። ዐረ ተሕት) ደቂቅ አገባብ። ታች፤ ምድር፤ እግር ሥር፤ የላዕል የሰማይ የርእስ አንጻር። አኮ ዘቦቱ ለመለኮት ላዕል ወታሕት። በሰማይ በላዕሉ ወበምድር በታሕቱ። አንትሙሰ እምታሕቱ አንትሙ። እምሐቌሁ እስከ ታሕቱ። ጸወዑ ቢጸክሙ ታሕተ ወይንክሙ። እምታሕተ እደዊሆሙ ለሊቃነ ጳጳሳት ፡ (ቅዳ ፡ ሕር። ዮኤ፫ ፡ ፫። ዮሐ፰ ፡ ፳፫። ሕዝ፰ ፡ ፪። ዘካ፫ ፡ ፲። ፍ ፡ ነ ፡ ፬)።
ታሕጻጽ ታሕጻጺት ፡ ጕዳይ ሕጸጽ፤ ማነስ ታናሽነት። በአይኒ ታሕጻጽ ወእበድ ዘኮነ። እለ ይኄልዩ ድካመ ወታሕጻጸ ለወልደ እግዚ። አርጌንስ ይሜህር ታሕጻጸ ወልድ እምአብ። ታሕጻጺተ ደቂቃት ኀጣውእ፤ ፡ (ፊልክ ፡ ፻፸፩። ሃይ ፡ አበ። መጽ ፡ ምስ። ቀሌ)።
ታስሪ ፡ ታስሪን፤ ፡ (ዕብ ታሽሪ። ሱር ቴሽሪን) ስመ ወርኅ ሶርያዊ፤ ጥቅምትና ኅዳር። እሊህ ኹለቱ፤ ታስሪን ቀዳማይ ታስሪን ደኃራይ ይባላሉ። ወበወርኀ ታስሪ ፡ (ዮሴፍ)።
ታስዓዊ ይ ፡ (ዊት ዒት) ዝኒ ከማሁ፤ ዘጠንኛ ዘጠንኛው፤ ከዘጠኝ አንዱ።
ታስዕ ፡ (ዕት ዓን ዓት) ዘጠንኛ፤ ከዘጠኝ አንድ። በታስዕ ዓመት። አመ ዐሡሩ ወረቡዑ ለታስዕ ወርኅ። ወበታስዕት ዕለት ፡ (ሕዝ፳፬ ፡ ፩። ሐጌ፪ ፡ ፲። ዘኍ፯ ፡ ፰)።
ታሪክ ፡ (ካት። ዐረ ታእሪክ) በቁሙ፤ ያለፈ የተጣፈ ወሬ፤ አንቲካ ዜና፤ የዘመን ቍጥር ዓመተ ምሕረት። ዝንቱ መጽሐፈ ታሪክ። ውስተ ታሪክ ጉባኤ ሣልስ። ወእሙንቱ ይገብሩ ክልኤተ ታሪካተ፤ ታሪከ ሥጋዌ ወታሪከ ዲዮቅልጥያኖስ ፡ (ታሪ ፡ ነገ። ያዕ ፡ ዘእል። አቡሻ ፡ ፰)።
ታቦር ፡ (ዕብራ) የተራራ ስም፤ ታላቅ ረዥም ተራራ፤ በናዝሬት አጠገብ በስተምሥራቅ ያለ፤ ጌታ ምስጢረ መንግሥቱን ለነቢያት ለሐዋርያት የገለጸበት። ፡ (መሳ፬ ፡ ፮ ፡ ፲፪። መዝ ፡ ፹፰)። በዓለ ዕርገት ወበዓለ ኀምሳ ወበዓለ ታቦር ዘቦቱ ተወለጠ ወአእመሩ አርዳኢሁ ስብሐተ መለኮቱ። ወሪዶሙ እምደብር እምደብረ ታቦር አዘዞሙ ኢይንግሩ ዘርእዩ በደብር እስከ አመ ይትፌጸም በዕድሜሁ ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፲፱። ድጓ፤ ሠለ)።
ታቦት [1] ፡ (ታት። ቅብጥ ቴቢ። ዕብ ቴባ፤ ቴቡታ። ዐረ ታቡት) መርከብ፤ ሣጥን፤ ሙዳየ ምጽዋት ሙዳየ ምዉት ፡ (ኩፋ ፡ ፭። ዘፍ፮ ፡ ፲፬)። ንፍቀ ታቦት ፡ (ማቴ፳፬ ፡ ፴፰። ፩ጴጥ ፡ ፫ ፡ ፳)። ወሶበ ርእዩ ከመ ብዙኅ ወርቁ ዘተረክበ ውስተ ታቦት። ገነዞ ሴት ለአዳም ወአንበሮ ውስተ ታቦት በምሥራቀ ገነት ፡ (፬ነገ ፡ ፲፪ ፡ ፲። ቀሌ)። ምስጢሩ ቦታነትና ማኅደርነት ነው። አንትሙ ታቦት ለንጉሥ ፡ (፩ጴጥ ፡ ፪ ፡ ፱)። ባለቅኔዎች ግን የቤተ ጥሬ ነው ይላሉ።
[2] ፡ (ዕብ አሮን) የቁም ሣጥን፤ ዐሠርቱ ቃላት የተጣፉባቸው የኹለቱ ጽላት ማኅደር። ታቦት ዘመርጡል። ታቦተ ሕግ። ታቦተ እግዚአብሔር። ታቦት በወርቅ ልቡጥ እምኵለሄ ዘግቡር እምዕፅ ዘኢይነቅዝ ፡ (ዘፀ፳፭ ፡ ፲። ፴፰ ፡ ፩። ዘኍ፲፬ ፡ ፵፬። ፩ዜና ፡ ፲፫ ፡ ፫። ኤፍ ፡ ፩)።
[3] ፡ መንበር ምሥዋዕ፤ በመንበር ላይ የሚቀመጥ ጽላት። ጸሎት፤ እምቅድመ ያልብስ ታቦተ። ወይኩን ታቦት ዘይፈልስ እመካን ውስተ መካን ከመ እብነ ደቂቀ እስራኤል ፡ (ቅዳ። ፍ ፡ ነ ፡ ፩)።
(ጥኒ) ታኒን ፡ (ዕብራ) ስመ አራዊት ዐበይት እለ ውስተ ባሕር፤ መደበኛው ግን ዐዞ ነው፤ ለዘንዶና ላርጃኖም ይኾናል፤ ተመንን እይ።
ታናክ ቴናክ ፡ ስመ ዕፅ፤ አንድ ዐይነት ዕንጨት፤ እንደ ጥድና እንደ ወይራ መልካም ሽታ ያለው፤ ለመሥዋዕት ሙጋድ የሚኾን። ቡራቴ ወቴናክ ፡ (ኩፋ ፡ ፳፩)። ባለብሉዮች ግን ጠዶ ይሉታል።
ታዕካ ፡ (ካት) የንጉሥ ቤት፤ ቤተ መንግሥት፤ አዳራሽ ታላቅ ከፍተኛ፤ ከፍ ባለ ቦታ የተሠራ፤ ግቢ፤ ሰፈር፤ ከልካይ አስከልካይ ዘበኛ አጋፋሪ ያለበት። ታዕካ ንጉሥ። ጸግዎ ሰላመ ለንጉሥነ፤ ለታዕካሁ ወለሰራዊቱ። ቈስጠንጢኖስ ታዕካ ኀበ ዘሐነጸ ሎቱ። ማርያም ታዕካ በምድር ወታዕካ በሰማይ፤ ታዕካ መንግሥተ ሰማያት ፡ (አቡሻ ፡ ፶። ቅዳ። ስንክ ፡ ጥር፳፯። ድጓ። መቃ)።
ታእካ ፡ አዳራሽ፤–ዐከወ።
ታኦሎጎስ ፡ (ጽር ቴዎሎጉስ) ሎጎሰ ቴዎ፤ ነባቤ አምላክ፤ ነባቤ መለኮት። ጎርጎርዮስ ታኦሎጎስ፤ ዮሐንስ ታኦሎጎስ ፡ (ያዕ ዘእል)። በታኦሎጎስ ፈንታ ቴዎሎጎስ እንደ ማለት ኹሉ፤ አዛውሮ ቴዎጎሎስ ይላል፤ የጣፊ ስሕተት ነው፤ ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፬። ስንክ ፡ መስ፬። ድጓ)።
ታኦማጎሲስ ፡ (ጽር ቴዎማኾስ) ፀረ አምላክ፤ እንደ ማኒና እንደ ፍራማሶን ያለ ፍጹም ከሓዲ፤ ወይም እንደ አርዮስ እንደ መቅዶንዮስ ያለ ፍጹም መናፍቅ። ፡ (ሥላሴ ቅኔ) እልፍ ዐላውያን፤ ማኒሰ ኮነ የዐብዮሙ ምስለ መንፈስ ቅዱስ ወአብ እስከ አኅጥአነ ወልደ፤ እስመ ምስለ ባዕድ ተናገረ ባዕደ፤ ወእምዐላውያን ኀጥአ ዘይመስሎ አሐደ፤ ዐመፃ ካልአ ኀበ ፈቀደ፤ ሰባልዮስ በዝ እስመ ኢለመደ፤ ወከመ ዝ አርዮስ ኢክሕደ። ታኦማጎሲስ፤ ዘበትርጓሜሁ ፀረ እግዚአብሔር ፡ (ሃይ ፡ አበ)።
ታኦስ ፡ (ጽር ቴዎስ) አምላክ። ታዖስ ናይናን ኦ አምላክ መሐረነ ፡ (ግብ ፡ ሕማ)።
ታኦስክንድሳውያን ፡ (ጽርእ) ቀታልያነ አምላክ፤ ባምላክነቱ ታመመ ሞተ የሚሉ ፡ (ሃይ ፡ አበ)።
ታኦርያ ፡ (ጽርእ) ሠናይ መሠንይ፤ አው ሰማያዊ፤ ብርሃናዊ። ዘይሰመይ ታኦርያ ዘውእቱ ራእይ ልቡናዊ ፡ (ማር ፡ ይሥ፭ ፡ ፩)።
ታኦንትያ ፡ (ጽርእ) አምላክ ሐመ በህላዌሁ፤ ቱሳሔ ውላጤ አንድ ባሕርይ አንድ ግብር የሚሉ የመናፍቃን ባህል። ተሳረቀንና አስተሳረቀን እይ፤ ሰረቀ።
ታኦዶኮስ ፡ (ጽር ቴዎቶኮስ) ወላዲተ አምላክ፤ እመ አምላክ።
ታኦፊላ ፡ (ጽር ቴዎፊሌ) ቴዎፍሎስ፤ ፍቁረ አምላክ፤ መፍቀሬ አምላክ ፡ (ግብ፩ ፡ ፩)።
ታው [1] ፡ ስመ ፊደል፤ ካያ ኹለተኛ ተ፤ ምልክት ዐላማ ማለት ነው፤ መስቀል ትእምርተ መስቀል እንደ ማለት። ሔትዮትን እይ፤ ከዚህ ጋራ አንድ ነው ፡ (መዝ፻፲፰ ፡ ፻፷፱–፻፸፮። ሰቈ፩ ፡ ፳፪። ፪ ፡ ፳፪። ፫ ፡ ፷፬። ፬ ፡ ፳፪)።
[2] ፡ (ዐማርኛ፤ ትእዛዝ አንቀጽ) ተው፤ አትንካ፤ በቃ። ምስጢሩ ደኃራዊነት ነው፤ አዳም የፍጥረት ፍጻሜ እንደ ኾነ ታውም የፊደል ፍጻሜ ነውና ፥ መካተቾነቱን ያሳያል። ፡ (ተረት) መተው ነገሬን ከተተው።
ቴሀ ፡ ዞረ ቀላወጠ፤–ተየሀ።
ቴሌም [1] ፡ (ጽር'ቴሜን። ዕብ ፡ ኦብ) ማርተኛ : ጠንቋይ፤ ዛጐል ጣይ፤ ጋኔን 'ሳቢ ፡ ባላሾክ ፩፤ ምትዞታም መሠሪ ሙት ፡ ወሪ(ሬሳ ፡ እናጋሪ፣ መንቅሄ ፡ ምዉት፤ ካህነ : ወዖት " ባለብሎዮች ፡ ግን ፡ -የእባብ ፡ ምስል ፡ ጣዖት ፡ ይሉታል ፡ (፬ነን ፡ ፳፩ ፡ ፮)።
[2] ፡ ቴሌም፤–ሟርተኛ፤–ተየሌም።
ቴማን [1] ፡ (ዕብራ) የማእዝን ፡ ስም ፡ ናጌብ ፡ ደቡብ፤ የደቡብ ፡ ነፋስ፤ በደቡብ ፡ ያለ ፡ ሀገርና ፡ ሕዝብ፤ የመን፤ መላው » የዐረብ አገሮ ፡ የማን ፡ ተመልከት፤ ከዚህ ፡ ጋራ ፡ እንድ ፡ ነው ፡ ሚም ፡ ገጸከ ፡ መንገለ ፡ ቴማን። እግዚ ፡ ይመጽእ ፡ እምቴማን ፡ (ሕዝ፳፬ ፡ ሹ ፡ ዕንደ ፡ ፫)።
—፤ ስመ ፡ ነገድ ፣ የዔሳው ፡ የልጅ ልጅ ፣ የኤዶምያስ v ፲፩ # ኤሮ፱ ፡ ፯። ኢዮ፪ ፡ ፲፩)። ሕዝብና ፡ መዲና፤ ከዐረቦች ፡ ነገድ ፡ የተለየ ፡ (ዘፍ፴፮ ተነ።
[2] ፡ ደቡብ፤–ተየማን።
ቴቄል ፡ (ሱር ትቄል) ሰቀለ፤ ደለወ፤ መዘነ ፡ (ዳን፭ ፡ ፳፮)።
ቴቆሔ ፡ (ዕብ ትቆዕ) ከመ ሀገር፤ ዘይታም፤ የዘይት አገር፤ በይሁዳ ክፍል ያለች ፡ (፪ነገ ፡ ፲፬ ፡ ፪። ዓሞ፩ ፡ ፩። ፪ዜና ፡ ፳ ፡ ፳)። ባለቅኔዎች ግን የፈረስ አገር ይሏታል። በምቅዋመ አእዱግ ይቅብሩ አፍራሰ ቴቁሔ ፡ (ቅኔ)።
ቴአስ ፡ (ጽርእ) ስመ ሀገር፤ የቦታ ስም። አንስት እለ ትመጽኣ እምነ ቴአስ ንዓ ፡ (ኢሳ፳፯ ፡ ፲፩። ዕብራይስጡ ግን፤ ግእዙ እምነ ቴአስ ንዓ ባለው ምኢሮት ኦታ ይላል፤ ያውዕያሃ ያነድሃ ማለት ነው፤ ቦታንና አገርን አያሳይም።
ቴዎሎጊያ ፡ ሊቅ፤ መቶርጕም፤ የሊቃውንት መጽሐፍ፤ ብሉያትንና ሐዲሳትን፤ እየጠቀሰ የሚፈታ፤ ምስጢረ ሥላሴን ምስጢረ ሥጋዌን አምልቶ አስፍቶ የሚናገር፤ እንዳፈ ወርቅ እንደ ቄርሎስ ድርሳን ያለ የጉባኤ መጽሐፍ፤ ቤተ ክርስቲያን የምታምነው የምትቀበለው።
ቴዎሎጎስ ፡ ነባቤ መለኮት። ታኦሎጎስና ቴዎሎጎስ አንድ ስም ናቸው፤ ባለዜሞችና ባለሐዲሶች ግን ቴዎሎጎስን ነዊኀ እስኪት ይሉታል፤ የተሳሳተ ነው።
ቴዱ ፡ (ዕብ ቆዳ) ቡራኬ ፡ ምስጋኖ ግናይች እኰቴት ፡ አንቀጸ ፡ ቴዱ ፡ ( ነገ)።
ቴዱ ቴዳ ፡ ግናይ ፥ ትእምርት፤–ተየዱ ዳ።
ቴዳ ፡ (ብ'ቴዳት።ጽር'ቲታ) የስም: - ምልክት፤ እስክንድሮ ፡ በእስክንድርያ ፡ ቀበሮት ፡ በነበ ረው በወርቅ መዝገብ ፡ ላይ ፡ ተጥፎ ፡ እባ ፡ ቴዎፍሎስ ፡ ያገኘው» መዝገብ ፡ ዘጽሑፍ ፡ ውስቴቱ፣ሠለስቱ፣ ቴዳት። ወተርጐሞሙ ፡ ዝንቱ ፡ ሕብ ፡ ለሠለስቱ፤ቴ ዳት ፡ ወይቤ ፡ አሐዱ ፡ ቴዳ ፡ ዘቴዎስ ፡ ወአሐዱ ዘቴ ዎፍሎስ ፡ ወአሐዱ ፡ ዘቴዎዶስዮስ ወክፈሎ ፡ ዝ ጓቱ ፡ መዝገብ ፡ ግስ ፡ ሠለስቱ፤ከፍል ፡ (አቡሻ - ፶ ፡ ስንክ ፡ ጥቅ፲፰)።
ቴዳብ ፡ ዳቢት ፡ ጐን፤የጐን ፡ ሥጋ፣የጐድን ፡ ዘርፍ። ጐድን ተዳቢት እንዲሉ።(ይባቤ) ዲያብሎስ ፡ በትቢቱ ፡ ተወጋ ፡ ዳቢቱ "
ቴገን ፡ ጤገን፤ ምጣድ፤ እቶን
፡ (ዘሌ፮ ፡ ፲፬)።
ቴጉን ፡ ጤጉን፤ የበሰለ የተጋገረ። ኅብስተ ቴጉን ፡ (ዘሌ፪ ፡ ፭)። ጤገነን ተመልከት፤ ከዚህ ጋራ አንድ ነው፤ ሴማውያን ጠ የሚሉትን ያፌታውያን ተ ስላሉት ኹለት ይመስላል። ባለብሉዮች ጕልቻ ይሉታል።
ቴግሪ ፡ (ጽርእ) ጤግሮሳዊ፤ ክፉ ጨካኝ ነብር፤ ጤግሮስን እይ። ዲያብሎስም በተንኰሉና በመርዛምነቱ እባብ እንዲባል፤ በጨካኝነቱ ቲግር ይባላል ፡ (ሄርማ ፡ ገ፳፩)። የሰውን ጠባይ የሚመረምሩ ፈላስፎች የጣፉት ታሪክ ግን ትግሬና ትግራይ የሕዝብ ስም ሲኾን፤ ንባቡም ምስጢሩም ቲግር ቱግሪ ከማለት የወጣ የጠባይ ስም ነው፤ የግብር አይደለም ይላል።
ቴፈን ተይፈን ፡ (ዐረ
፡ የፈን) ወይፈን፤ ያደገ የደረሰ፤ ከሦስት ፡ ዓመት ፡ በላይ ፡ ያለ፤ የሚያፈ፤ ነፍን የሚንጠላጠል። ሐማሴኖች ፡ ዘራብዕ ፡ ይሉታል።
ትሑት ፡ (ታን ታት ሕት) በቁሙ፤ የተዋረደ፤ የተናቀ፤ ወራዳ ታናሽ፤ ድኻ ዜጋ፤ ታዛዥ ተገዥ ፈቃደኛ፤ እሺ ባይ፤ ዐፋራም ፈሪ። ትሑት ምስለ ዐቢይ። ወራእዩኒ ምኑን ወትሑት እምኵሉ ሰብእ። ሕዝብ ትሑታን። ከመ ይኩኑ ትሑታነ ወይትአዘዙ። ትሑታነ ልብ። ትሑታነ ገጽ። ወእለ ይደልዎ ለመለኮተ ክርስቶስ ንነግር ወትሑታተሰ ለትስብእቱ አወፈዩነ። ጠባብ ወትሕት
፡ (ኩፉ ፡ ፳፫። ኢሳ፶፫ ፡ ፫። ፲፰ ፡ ፯። ዲድ ፡ ፳፪። ዳን፫ ፡ ፷፬። ሔኖ፵፰ ፡ ፰። ቄር። ድጓ)።
ትሒል ሎት ፡ (ትሕለ ይትሕል ይትሐል። ዕብ ታሖል፤ ሀትሔል) መዠመር፤ መቅደም፤ ዠማሪ ቀዳማዊ መኾን፤ በሥራ ኹሉ። መዞር መንከርተት ለመቀላወጥ፤ ዘዋሪ ቀላዋጭ መኾን፤ በየድግሱ ቤት ከስው አስቀድሞ መገኘት። መጽሐፍ ግን በትሕለ ፈንታ ተትሕለ ተታሐለ ይላል፤ አያሰኝም። ወአነሂ አዐውድ ወእተሐል። እለ በተታሕሎ የሐይዉ። ከመ እለ ያንሶስዉ ወይቴሐሉ ፡ (ኢዮ፪ ፡ ፱። ፴ ፡ ፬። አፈ ፡ ተ፲፮)።
ትሒት ቶት ፡ (ተሐተ ይቴሕት ይትሐት) መተቸት፤ ታች ታች ማለት፤ ወደ ታች መውረድ መዋረድ፤ ዝቅ ዝቅ ማለት፤ ትሑት ታሕት ታችኛ ዝቅተኛ መኾን፤ ማነስ ንኡስ አነ ማለት ከትቢትና ከልዕልና መሸሽ መራቅ፤ ዐቅምን ማወቅ። ኵሉ ማዕምቅ ይምላእ ወኵሉ ደብር ወወግር ይትሐት ፡ (ኢሳ፵ ፡ ፬። ሉቃ፫ ፡ ፭)። መጻሕፍትና ባለቅኔዎች ግን በለዐለ ፈንታ ተለዐለ እንዲሉ በተሐተም ፈንታ ተትሕተ ይላሉ፤ አያሰኝም፤ ግስነቱ ወፅአንና መጽአን ጌሠን ፈለሳነ የመሰለ ዐጕል ነውና፤ እንደ ገቢር ግስ የመደረግ ልማድ ተን አይፈልግም። ተትሕትከ ሎቱ። ብእሲት ትትአዘዝ ወትተሐት ሰምታ። በከመ ወልድ ይቴሐት ለአቡሁ ከማሁ ዲያቆንሂ ይተሐት ለኤጲስቆጶስ። ተትሕተ እስከ ምድር። ተትሕተ እምዕበዩ። ዘይቴሐት እምኔከ ፡ (አስቴ፮ ፡ ፲፫። ዲድ ፡ ፫። ፬። ኢሳ፳፭ ፡ ፲፪። ኩፋ ፡ ፳፬። ዳን፪ ፡ ፴፱)።
ትሄ ፡ (ያት። ጽር ቴኤ ሄ። ዕብ ታእ) ታናሽ ዕልፍኝ፤ ዕቃ ቤት፤ እንደ ጕርጅ እንደ ጓዳ ያለ። ለቂንድና ለማር ሰፈፍ ሳይቀር ቤትነት ላለው ክፍል ለታናናሽ ኹሉ ይነገራል ፡ (ሕዝ፵ ፡ ፯ ፡ ፲ ፡ ፲፪ ፡ ፲፫)።
ትሕላፍ ፡ መሐላ፤ ቃል ኪዳን። አልቦሙ ትሕላፍ ምስለ ሶርያ ፡ (መሳ፲፰ ፡ ፯)።
ትኅላፍ ፡ መተላለፍ፤ ዕልፊት ዐለፌታ ዕላፊ፤ የገር። አልቦ ላዕሌየ ትኅላፍ ፡ (ቅዳ)።
ትኅምስት ፡ ዐምስትነት። ዐምስት እጅ፤ ዐምስት ዕጥፍ። ህየንተ አሐዱ ላሕም ይፈዲ ትኅምስተ። ሠለስቱ ትኅምስተ ብርሃን ፡ (ዘፀ፳፩ ፡ ፴፯። ሔኖ፸፰ ፡ ፯)።
ትሕስብት ፡ መተሳሰብ መቈጣጠር፤ ቍጥርጥር ምርምር።
ትሕርምት ፡ (ታት) በቁሙ፤ ጾም ተዐቅቦ፤ የትሩፋት ሕግ። ምስጢሩ ያው መከልከል ነው፤ ከሕርመት ይገባል። የብሰ ሥጋሁ እምብዝኀ ትሕርምት። ተፀራዕከ እምትሕርምትከ። ሶበ ይትሐረሙ እምትሕርምታቲሆሙ ፡ (ፊልክ ፡ ፲፮። ፹፮። መጽ ፡ ምስ። ቀሌ)።
ትሕቢት ፡ ዋስነት ዋስትና፤ ዋስ መኾን። ኢይባኡ ቀሳውስት ውስተ ትሕቢት ፡ (ቀኖ ፡ ኒቅ፳፰)። ተሓበየ አስተሓበየ ብሎ ተዋዋሰ አዋዋሰ ያሰኛል፤ ተደራራጊኖ አደራራጊ አንቀጽ።
ትሕትና ፡ በቁሙ፤ ትሑትነት፤ ዝቅታ፤ ውርደት፤ የልዕልና አንጻር ወደረኛ፤ የትቢት ደመኛ። ኦ ትሕትና ዘመጠነ ዝ ትሕትና። በትሕትና ረከበ ልዕልና። ኢትእመን ትሕትናሁ ፡ (ቅዳ ፡ አፈ። መዋሥ። ዮሴፍ)።
ትሕዝብት ፡ በቁሙ፤ ትዝብት። ጥርጣሬ ጥርጥር፤ የፍርሀት ሐሳብ። እምፍርሀት ወእምትሕዝብት ዘይመጽእ። እምትሕዝብተ ጸላኢ። በሰማይ ዘአልቦቱ ፍርሀት ወኢትሕዝብት። ፍርሀቱ ወትሕዝብቱ ፡ (ሉቃ፳፩ ፡ ፳፮። መዝ ፡ ፷፫። ግንዘ። ዮሴፍ)።
ትኅይልት ፡ መበራታት፤ ብርታት ብርቱነት ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፵፫ ፡ ፲፪። ግንዘ)።
ትሕጻጼ ፡ (ጽያት) መጕደል፤ መጓደል፤ ጕድለት ጐደሎነት። በእንተ ትሕጻጼ ራእዩ። ኮነ ሎቱ ትሕጻጼ ኅዳጥ ፡ (ፊልክ ፡ ፯። ፻፺፫)።
ትሕጽጽት ፡ ዝኒ ከማሁ። መዐት ምስለ ትሕጽጽተ ልቡና ይወልድ ጽዕለተ ወጽልአ ወቀቲለ ፡ (ፊልክ ፡ ፸፱)።
ትለም አትላም አትልምት ፡ አትልምት፤ ትልሞች፤ ፈሮች። አርውዮ ለትለሚሃ። ዘከመ የሐርስ ትለሚሁ። አውፅአ ሠለስተ አትላመ። ሐረሰ ሠላሳ አትልምተ ፡ (መዝ ፡ ፷፬። ሢራ፴፰ ፡ ፳፮። ገድለ ፡ ሕፃን ሞአ። ስንክ ፡ ኅዳ፳፩። ሐም፪)።
ትልሂት ፡ ጨዎታ ፥ ጭውውት፤ ዝሙት ፥ የፍትወት ሥራ። ትልሂት በነፍስተ ሥጋሁ ፡ (ቄድር)። ተላህያም ጥሬ ዘር ኹኖ በትልሂት አፈታት ይፈታል።
ትልም ፡ (ዕብ ቴሌም፤ ትላም። ዐረ ተለም) በቁሙ፤ ፈር፤ ስበት የኼደበት ሥንጥቅ። ትልመ ገራውሂከ። ኢትዝራዕ ውስተ ትልመ ኀጢአት። ኢንደንግፅ ወኢናጽንን ትልመነ ፡ (ኢዮ፴፱ ፡ ፲። ሢራ፯ ፡ ፫። አፈ ፡ ተ፭)።
ትልወት ትሎት ፡ (ታት) መከተል፤ አከታተል፤ ተከታይነት፤ ክተላ። በትልወተ ወልድ። ትልወተ ኤጲስቆጶስ ፡ (አዋል)።
፡ የሴት ልጅ ገንዘብ፤ ጫማ መዳሪያ ካባቷ ቤት ይዛው ነድታው አስከትላው የምትኼድ። እመ ፈቀደ ያስተዋስብ ወለቶ ይሁባ ትልወታ በአምጣነ ክሂሎቱ። ይደሉ እንከ አውስቦ ዘእንበለ ትልወት ወኢሕፄ። ትሎት ዘአምጽአቶ ኀቤሁ ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፳፬ ፡ ፩ ፡ ፫ ፡ ፯)።
ትልው መትልው ፡ (ዋን ዋት ሉት) ዝኒ ከማሁ፤ የመሰለ የተከተለ፤ ስምም፤ የሚከተል፤ ተከታይ፤ ምክትል። ሊቀ ጳጳሳት ዘሮሜ መትልወ ጴጥሮስ። ትኌልቁ እምቀዳሚት ዕለት በበ መትልው። ወመትልወ ዝንቱ። ስማዕ መትልወ ዝንቱ። ዝ ውእቱ ምዑዝ ለመትልወ ወይን። አናጕንስጢስ ያንብ ዘንተ ወዘመትልው ቀሰስ ፡ (ቀኖ ፡ ኒቅ። አቡሻ ፡ ፱። አፈ ፡ ድ፩። ፫። ምሳ፲፪ ፡ ፲፩። ኪዳ)።
ትማልም ፡ (ዕብ ትሞል፤ ኤትሞል። ሱር ኤትማል) ትላንት፤ ዓምና፤ ያለፈ ቀን ጊዜና ዘመን። በከመ ቀተልኮ ትማልም። ዘትማልም ወዮም ፡ (ዘፀ፪ ፡ ፲፬። ዕብ፲፫ ፡ ፰)።
ትምህርት ፡ (ታት) ዝኒ ከማሁ፤ በቁሙ ትምርት፤ ዕውቀት፤ ድርሳን ምዕዳን። ወልድ ዘእንበለ ትምህርት። ነፍሳት እለ አልቦን ትምህርት። በትምህርታቲሁ። ትምህርታት ወተግሣጻት ፡ (ምሳ፲፯ ፡ ፳፩። ጥበ፲፯ ፡ ፩። ቄር። ስንክ ፡ መስ፳)። ልማድና ባህል ይኾናል፤ ምስጢሩ ያው ትምርት ነው።
ትምልክት ፡ ተገዥነት፤ አገዛዝ ጭቈና። አውፃእኮሙ ለእስራኤል እምትምልክተ ፈርዖን ፡ (ዲድ ፡ ፴፰)።
ትምስውና ፡ ዝለት ድካም፤ ዝልፍልፍነት ፡ (ፊልክ ፻፹፩)።
ትምዕዕት ፡ ቍጣ ብስጭት፤ ብስጩነት። ትምዕዕት ፍጥረታዊት ፡ (ፊልክ ፡ ፻፵፩)።
ትምእክት ፡ ቍጣ ዛቻ፤ ፍጥጫ ግልምጫ፤ ጕራ ፍከራ፤ በትር ስንዘራ። ያሐዝን ትምእክት ልበ ጠቢባን። ኢያደንገፃ ትምእክቱ ፡ (ምሳ፲፯ ፡ ፲። ዮሴፍ)።
ትምክሕት ፡ በቁሙ፤ መመኪያ ክብር፤ ተመካሒነት፤ ትዕቢት ኵራት። ትምክሕተሙ ለረሲዓን ትጠፍእ። ተኀፈርክሙ በትምክሕትክሙ። ኵላ ትምክሕት እንተ ከመ ዝ እኪት ይእቲ ፡ (ምሳ፲፩ ፡ ፯። ኤር፲፪ ፡ ፲፫። ያዕ፬ ፡ ፲፮)።
ትምይንት ፡ ዝኒ ከማሁ። ኢንሑር በትምይንት። እለ የሐውሩ በትምይንት። ወአእመረ ትምይንቶሙ ፡ (፪ቆሮ ፡ ፬ ፡ ፪። ፪ተሰ ፡ ፫ ፡ ፮። ሉቃ፳ ፡ ፳፫)።
ትሱዕ ፡ (ዓን ዓት ስዕት) የዘጠነ ዘጠኝ የኾነ፤ የተባለ፤ የተከፈለ።
ትሳዔ ተሱዐት ፡ መዘጠን፤ ዘጠኝ ማድረግ፤ ዘጠኝ መኾን፤ አዘጣጠን፤ ዝጠና ዘጠኝነት።
ትሥልስት ፡ ሦስትነት፤ ሦስቲዮ ጕንጕን ሽርብ፤ ሦስት እጅ። ተዋሕዶትከኒ ኢይትነገር ወትሥልስትከኒ ኢይትሌቦ። እመ ቦ ዘይፈልጦ ለእግዚ እምትሥልስቱ ውጉዘ ለይኩን። ትርብዕተ ርቡዓን ኪሩቤል ወትሥልስተ አምላክ ዋሕድ ፡ (አረጋ ፡ ድ፳፪። ያዕ ፡ ዘእል። ደራሲ። ቅዳ ፡ ዲዮ)።
ትስባኤ ፡ ሰው መኾን፤ ሰውነት፤ የሰውነት ገላ፤ ባሕርይ። ስብእናን ተመልከት፤ ከዚህ ጋራ አንድ ነው። ዕሩቀ እመለኮት ረሰዩ ትስባኤ ፡ (ስንክ ፡ ጥቅ፲፱)።
ትስብእት ፡ ዝኒ ከማሁ፤ ስውነት፤ ሰው፤ ፍጹም የሰው ባሕርይ፤ ኵለንታ ሰብእ፤ ነፍስና ሥጋ፤ ወይም ነፍስ ያለው ሥጋ። ትስብእቱ ለዋሕድ። መለኮት ወትስብእት ፡ (አምላክነትና ሰውነት፤ አምላክና ሰው፤ ወይም ቃልና ሥጋ)። እመ ቦ ዘይቤ አየኬ ዘወለደት ድንግል ሚመ ትስብእተ ወሚመ መለኮተ። ኢትፍልጥ ሊተ እምድኅረ ትድምርት፤ እስመ ዘፈለጠ እንተ ባሕቲቱ ብእሴ ወእንተ ባሕቲቱ አምላክ ቃለ፤ ክልኤተ ይሬስዮ ለዐማኑኤል ፡ (ቄር ፡ እስት)።
ትስብዕት ፡ ሰባትነት፤ ስባተኛነት፤ ሰባት እጅ፤ ሰባት ዕጥፍ። ወበዝኀ መክፈልተ ብንያም እመክፈልተ ኵሎሙ ትስብዕተ ፡ (ኩፋ ፡ ፵፫)።
ትስዕ ፡ የልክ የጊዜ ቅጽል፤ ዘጠኝ። ትስዐ በእመት ኑኃ። ሰፈረ ትስዐ በበ ትስዕ ወበበ ዕሥር ፡ (ዘዳ፫ ፡ ፲፩። ዘረፋ)።
ትስድስት ፡ ዝኒ ከማሁ፣ ስድስትንት ስድስት መኾን።
ትሥጉት ፡ ዝኒ ከማሁ፤ ሥጋነት ፥ ሰውነት፤ ሰው መኾን ፥ ሥጋ መልበስ። ወእምቅድመ ትሥጉት አልቦ ዘይሰምዮ ለቃለ እግዚ ክርስቶስ። በእንተ ትሥጉቱ ለመድኀኒነ። አሚን በትሥጉት ወልድ ፡ (ቄር። ፈ ፡ መ ፡ ፳፯ ፡ ፰። አርጋ ፡ ፪)።
ትሩፍ ፡ (ፋን ፋት ርፍት) የቀረ የተረፈ፤ ቀሪ ትርፍ። በእንተ ትሩፋን። እሬስያ ትርፍተ። ሕገጋት ትሩፋት። ምግባራት ትሩፋት ፡ (መዝ ፡ ፭። ሚክ፬ ፡ ፯። ፈ ፡ መ ፡ ፩ ፡ ፩። አፈ ፡ ተ፫)።
፡ የበለጠ፤ የተሻለ፤ ብዙ ፍጹም፤ መንፈሳዊ። ግብር ትሩፍ ኢወሊድ ምስለ ኂሩት። አይ እምኔሆሙ ዘትሩፍ። ብእሲ ኄር ወጠቢብ ወትሩፍ። ትሩፈ ምግባር። አብ ቅዱስ ወትሩፍ ፡ (ጥበ፬ ፡ ፩። ፊልክ ፡ ፺፱። ዮሴፍ። ስንክ ፡ የካ፰። ፈ ፡ መ)።
፡ መንፈሳዊ ሥራ፤ ተውሳከ ምግባር፤ በሕግና በትእዛዝ ላይ የሚጨመር፤ ሰው በፈቃዱ ወዶ የሚሠራው፤ ካሥር አንድ አውጥቶ ደግሞ ከዘጠኝ መስጠት፤ ይህን የመሰለ ፡ (ማቴ፮ ፡ ፴፱–፵፩)። ገቢረ ትሩፋት። ምግባረ ትሩፋት። ተሰምዐ ዜና ትሩፋቲሁ ወአእምሮቱ ወቅድስናሁ። አግዕዞሰ እምግብረ ትሩፋት ይእቲ ፡ (ፈ ፡ መ ፡ ፪ ፡ ፪። ስንክ ፡ የካ፲፬። ጳጕ፭። ፍ ፡ ነ ፡ ፴፩)።
ትራፍ ፡ (ፋት) ትራፊ ትርፍ፤ ትርፍቻ፤ ብልጫ ላቂያ፤ ቅሬታ ቅሬት። ኀደጉ ትራፋቲሆሙ ለሕፃናቲሆሙ። ትራፋተ ነገር ነዋ ጽሑፋን እሙንቱ። ወናሁመ ተበየነ ውስተ ቃላተ እግዚእነ ትራፈ ገዳፍያን መምለክያን። ትራፋተ ነገሥት። ትራፋተ ዐውድ ፡ (መዝ ፡ ፲፮። ዕር ፡ ኢሳ፪ ፡ ፮። ፊልክ ፡ ፫። አብጥ ፡ ፴፩። መር ፡ ዕዉ)።
ትርሲት ፡ (ታት) [1] ፡ ጌጥ ሽልማት፤ መሣሪያ፤ የክብር ልብስ። ትርሴተ አብያት። ትርሲተ መርዓዊ ወመርዓት። እንተ ባቲ ትርሲተ ዝሙት። ለለብዋ ኵሎ ትርሲታ። ቅንቲ ሐቌኪ ወልበሲ ትርሲተ መንግሥትኪ ፡ (ሚክ፪ ፡ ፱። ኢሳ፷፩ ፡ ፲። ምሳ፯ ፡ ፲። ሰቈ፩ ፡ ፮። ድጓ)።
[2] ፡ ልጅነት፤ የልጅነት ክብር፤ ጸጋ ሀብት፤ ሕግ ሥርዐት፤ አባት ለልጁ የሚሰጠው። ትርሲተ ወልድ። እለ ሎሙ ትርሲተ ውሉድ ፡ (ሮሜ፰ ፡ ፲፭ ፡ ፳፫። ኤፌ፩ ፡ ፭። ገዳ፬ ፡ ፭)።
ትርሳ ፡ የባሕር አውሬ ዠርባው ጋሻ የሚመስል። ወለወልታኒ ገብርዎ እምነ ትርሳ ዘሀሎ ውስተ ባሕር፤ እስመ ዘባኑ ይመስል ከመ ወልታ ፡ (ጊ ፡ ወ ፡ ሐ ፡ ገ፳፫)።
ትርብዕት ፡ አራትነት፤ አራት እጅ፤ አራት ዕጥፍ፤ አራት ማእዝን። ትርብዕተ ርቡዓን ኪሩቤል ወትሥልስተ አምላክ ዋሕድ። ወሀበ ሎቱ ህየንተ አሐዱ ትርብዕተ። ውስተ ትርብዕተ ዓለም። በገበዋተ ጎል ዘበትርብዕት ፡ (ደራሲ። ፊልክ ፡ ፫። ቅዳ። አርጋ ፡ ፩)።
ትርአስ ፡ ትራስ ራስጌ፤–ርእሰ ትርኣስ።
ትርኣስ ፡ (ሳት) ትራስ፤ መከዳ፤ ራስጌ፤ የመከዳ ቦታ፤ የራስ በታች፤ ቅርብ አጠገብ። መንገለ ትርኣሲሁ። ሖረት ውስተ ምስካቡ መንገለ ትርኣሱ። ይነብሩ አሐዱ ትርኣሰ ወአሐዱ ትርጋፀ። ረከበ ትርአሶ ኅብስተ ፡ (፩ነገ ፡ ፳፮ ፡ ፯። ዮዲ፲፫ ፡ ፮። ዮሐ፳ ፡ ፲፪። ፫ነገ ፡ ፲፱ ፡ ፮)።
ትርያ ፡ (ዐረ ቱርያ) ጠራው፤ ጉቡኣን ከዋክብት። ዘገብሮ ለትርያ። ኅቡረ ትክልኑ ተአኀዛ ለትርያ ፡ (ኢዮ፱ ፡ ፬። ፴፰ ፡ ፴፩)። ጠራው ኪማ ሰኬላ፤ አንድ ወገን ናቸው።
ትርጕማን ፡ (ዐረ ተርጁማን። ሱር ታርግማና። ዕብ ሜሌጽ) በቁሙ፤ አስተርጓሚ፤ አምጃር፤ አነጋጋሪ፤ ማእከል ኹኖ ያንዱን ቃል ላንዱ የሚያሰማ ኹለት ቋንቋ ዐዋቂ፤ አፍ ጠበቃ አስታራቂ። ወእሙንቱሰ ኢያእመሩ ከመ ይሰምዖሙ ዮሴፍ፤ እስመ ትርጕማን ሀሎ ማእከሎሙ ፡ (ዘፍ፵፪ ፡ ፳፫)።
ትርጉም ፡ (ማን ማት ጕምት) በቁሙ፤ የተተረጐመ፤ የተፈታ።
ትርጋፅ ፡ እግርጌ፤ የእግር ቦታ፤ መዘርጊያ፤ መረጋገጫ። ትርኣሰ ወትርጋፀ። ግበሩ ሎሙ ቅድመ በድኖሙ አርባዕተ መሳቅለ፤ በትርኣስ ወበትርጋፅ በየማን ወበፀጋም ፡ (ዮሐ፳ ፡ ፲፪። ግንዘ)።
ትርጓሜ ፡ (ምያት) ሳቢና ጥሬ ዘር። መተርጐም፤ ፡ (ጥተ) መተርጐም፤ አተረጓጐም፤ አቀዳድ አመላለስ፤ ትርጐማ፤ አፈታት፤ ዘይቤ አወጣጥ፤ ምስጢር አገላለጥ። በቁሙ፤ ፍች፤ የንባብ ፍሬ፤ ምስጢሩ ስልቱ ውስጡ ሐሳቡ። ከመ ዝ ትርጓሜሁ እመጽሐፈ ሶርያ። በትርጓሜ መጻሕፍት ቅዱሳት። ትርጓሜ ስሙ። መምህረ ትርጓሜ። ይቤ ዮሐንስ አፈ ወርቅ በትርጓሜሁ ዘንተ ክፍለ ፡ (ኢዮ፵፪ ፡ ፲፰። ቀሌ። ዕብ፯ ፡ ፪። ስንክ ፡ ጥቅ፱። ፍ ፡ ነ ፡ ፵፬)።
ትቍጥዕት ፡ ዝኒ ከማሁ። ሰይጣነ ዝሙት ወሰይጣነ ትቍጥዕት ፡ (ፊልክ ፡ ፲፫)።
(ላ) ትቡዕ ፡ (ብዕት) የተባ ትብ፤ ጨካኝ፤ ቈራጥ። እመሰ ኮንክሙ ትቡዓነ ወጽኑዓነ
፡ (ዮሴፍ)።
ትቤ ፡ ትላለች፤–ብሂል።
ትብሌ ፡ ትብላይ፤ ትብልያ፤ ፡ (ሮማይ። ታቡላ፤ ገበታ። ዕብ ሖሼን) ልብሰ ተክህኖ፤ የደረት ሳንቃ፤ ሴደርያ። ትብልያ ዘመቅፈርት። ትብልያ ዘልብሰ መትከፍት ፡ (ዘፀ፳፰ ፡ ፮ ፡ ፰። ፴፮ ፡ ፲፪)። በትብልያ ፈንታ ኤፉድ፤ በኤፉድ ፈንታ ትብልያ ይላል፤ ፍችው እየቅል ነው።
ትብዐት ፡ (ዓት) መትባት፤ አተባብ፤ አጨካከን፤ ጨካኝነት፤ ወንድነት። እመ ትፈቅዱ ትክሥቱ ትብዐተክሙ ወጽንዐተክሙ ፃኡ አፍኣ ሀገር ፡ (ዮሴፍ)።
ትብዕ ፡ (ዓት) ትባት፤ ጭካኔ ጭከና፤ ድፍረት፤ ጕብዝና፤ የወንድነት ሥራ። ፈርሁ ሜዶን እምነ ትብዓ ፡ (ዮዲ፲፮ ፡ ፲። ስንክ ፡ መስ፲)።
ትብዕና ፡ ትብነት፤ ወንድነት፤ ጨካኝነት፤ ጭከና። ብዙኃን ወኀያላን በጽንዕ ወበትብዕና ወበአፍራስ ፡ (፪ዜና ፡ ፲፮ ፡ ፰)።
ትን ቲን ቴን ፡ ወርድ ስፋት፤ ቁመት፤ ወፍር። ኑኁ ወርሕቡ ወቲን1ፉ ፡ (ቆመዓ፣ ዕምራ በእመት። ወስዝር ቴና ፡ (ግዘፋ) ለይእቲ ባሕር እንተ ብርት ፡ (፪ዜና ፡ ፬ ፡ ፩ ፡ ፭)።
ትንሣኤ ፡ በቁሙ፤ መነሣት ፥ አነሣሥ ፥ መውጣት ብቅ ማለት፤ መታደስ መብቀል፤ ሐዲስ ሕይወት። ትንሣኤ ፀር። ትንሣኤ ፈያት። ትንሣኤ መዋግድ። ትንሣኤ ፀሓይ። ትንሣኤ ሙታን ትንሣኤሁ ገብረ በሰንበት ፡ (ቅዳ። ኪዳ። መጽ ፡ ምስ። ኩፋ ፡ ፫። ማቴ፳፪ ፡ ፳፫። ድጓ)።
ትንቢት ፡ (ብ ትንቢታት፤ አው ትንባያት) በቁሙ፤ ራእይ ንግር ፥ ገና ወደ ፊት የሚመጣ ነገር፤ አስቀድሞ የሚታይና የሚገለጥ ፥ ከመንፈስ ቅዱስ የሚሰጥ። መንፈሰ ትንቢት። ወይነግሩ በትንቢቶሙ። ሶበ ሰምዑ ዘንተ ትንቢተ ፡ (ኩፋ ፡ ፴፩። ሢራ፵፬ ፡ ፫። ፪ዜና ፡ ፲፭ ፡ ፰)። በእንተ እላ ራእያት ወትንቢታት። እንዘ ታነብቡ ወትጼልዩ እምነ መዝሙራት ወትንቢታት ወኦሪት። እግዚ ፈጸመ ትንባያተ ፡ (ዕር ፡ ኢሳ፲፩ ፡ ፵፩። ፍ ፡ ነ ፡ ፲፱። ደራሲ)።
ትንባሌ ል ፡ መለመን፤ አለማመን፤ ጸሎት ልመና፤ ምልጃ ቍልምጫ። አንግፍኒ በትንባሌ እምብኳይ ወወይሌ ፡ (ደራሲ። ስንክ ፡ መስ፩። ኅዳ፲፪። ጥር፴)።
ትንባክ ፡ (ትግ ወዐረ) ትንባኾ፤ የታወቀ ቅጠል፤ ጢሱና ዶቄቱ ባፍና ባፍንጫ የሚጠጣ፤ የሚጐረሥ፤ በቅብጠት፤ በቅንጦት የሚለመድ፤ ኹሉ የማይፈልገው።
ትንብልና ፡ ዝኒ ከማሁ፤ ልመና ምልጃ፤ አማላጅነት። በትንብልናሃ ለቤተ ክርስቲያን። በዐሠርቱ ወአርባዕቱ ትንብልናከ። በትንብልና ሣህልከ ፡ (ሳታት። ድጓ)።
ትንቱን ፡ (ናን ናት ትንት) የተፍገመገመ፤ የተገፋ የተደፋ፤ የተሰናከለ፤ ሊወድቅ የቀረበ። ከመ ትሱቁኒ ለትንቱን። የሀብከ ለትንቱን እግዚ ትንሣኤ ፡ (ስንክ ፡ መጋ፳፩። ደራሲ)
ትንታኔ ፡ መፍገምገም፤ መንገድገድ፤ ውዝወዛ፤ ጭንቅ፤ እወድቅ አልወድቅ ማለት፤ ጽነት። ቡቀኒ ጊዜ ትንታኔ። ወበጻሕኩ ድኅሬሆሙ ኀበ ትንታኔ ወሀጕል። ወአጽንዑ እንበለ ትንታኔ ሃይማኖተ ርትዕተ ፡ (ስንክ ፡ መጋ፩። ዮሴፍ። ተረ ፡ ቄር)።
ትንታግ [1] ፡ (ጋት) በቁሙ፤ ክፋይ ትኳሽ ፥ ትርኳሽ፤ ባንድ ወገኑ እሳት የበላው ያጐደለው የእሳት ትራፊ ዕንጨት። ከመ ትንታግ ዘአውፅእዎ እምእሳት። ትንታገ እሳት። በብዝኀ ትንታጉ ለእሳት ይበዝኅ ፍሕሙ። ትንታጋተ ዕፀው እለ ይጠይሱ ፡ (ዘካ፫ ፡ ፪። ዓሞ፬ ፡ ፲፩። ሢራ፲፩ ፡ ፴፪። ኢሳ፯ ፡ ፬)።
[2] ፡ ክፋይ ትርኳሽ፤–ነቲግ ነትገ።
ትንንያ ፡ (ዕብ ዐሮብ) ትንኝ፤ ቅማል፤ ጻጹት፤ ታናሽ ተናካሽ ፍጥረት። ዐኮትንና ጻጹትን ተመልከት። ሀኮት ወትንንያ። በትንንያ ወበጽንጽንያ። መራደ ትንንያ ፡ (መዝ ፡ ፻፬። ኩፋ ፡ ፵፰። ጥበ፲፪ ፡ ፰)።
ትእሕድ ትእሕዲት ፡ ትእሕድ፤ ትእሕዲት፤ አንድነት፤ አንድ መኾን፤ መዋሐድ መተባበር።
ትእልፊት ፡ ብዛት፤ ብዙ እልፍነት። ሺሕ እልፍ፤ ወይም እልፍ ጊዜ ሺሕ። ፡ (ቈእ–፲፻፻፻) ዐሥር ሚልዮን። ወናሁ መጽአ በትእልፊት ቅዱሳን። ትእልፊተ ትእልፊት። ወትእልፊተ አእላፋት ፡ (ሔኖ፩ ፡ ፱። ፲፬ ፡ ፳፪። ዳን፯ ፡ ፲)።
ትእምርት ፡ (ታት) ምልክት፤ አምሳል፤ አብነት፤ ዐላማ፤ ታምራት፤ ጕድ። ትእምርተ ኪዳንየ። ትእምርተ ተኀሥሥ ወትእምርትሰ ኢይትወሀባ ዘእንበለ ትእምርተ ዮናስ ነቢይ። ወይከውነክሙ ሕዝቅኤል ትእምርተ። ንሥኡ ትእምርተ። ወእሁብ ትእምርተ በሰማይ በላዕሉ። ወይትወለድ ትእምርት እምአንስት ፡ (ዘፍ፱ ፡ ፲፪። ማቴ፲፪ ፡ ፴፱። ሕዝ፳፬ ፡ ፳፬። ኤር፮ ፡ ፩። ግብ፪ ፡ ፲፱። ሱቱ ፡ ዕዝ፫ ፡ ፲፪)። ይትወለድ ትእምርት ያለው እባብ ዘንዶ አርዌ እንስሳ አሞራ ነው። የፍጻሜ ዘመን ምልክት። ሰውም ቢኾን ሸብቶ ጥርስ አውጥቶ ለዘር በቅቶ ማለት ነው፤ እንዲህም ኹኖ ተወልዶ ወዲያው ይናገራል። ወይትወለዱ አክይስት እምሰብእ፤ ወዓዲ አራዊት እኩያን፤ ወይትወለዱ ደቂቅ ዘይትናገሩ ነገሩ ነገረ ጽኑዐ በጊዜሃ፤ ወራእዮሙኒ ከመ ዘልሂቅ ወልደቶሙኒ ዘምስለ ሢበት። ወአንስት ይወልዳ ዘአርባዕቱ እግሩ፤ ወይትናገሩ ደቂቆን በውስተ ማሕፀን፤ ወብዙኅ ተኣምር ዘይከውን ፡ (ኪዳ፩)። ግናይን ተመልከት።
ትዕሲት ፡ ስጦታ፤ አስጣጥ፤ ጕርሻ በቅሽሽ።
ትዕሥርት ፡ ዐሥርነት፤ ዐሥር ዕጥፍ፤ ዐሥረኛ ክፍል፤ ያሥር ቤት፤ ባሥር ባሥር የሚበዛ ቍጥር፤ ካሥር እስከ ዘጠና ያለው። ረከበ ትዕሥርተ እምኵሉ። ወይከውኑ ትዕሥርተ። አእላፍ ወአምኣት ወትዕሥርት ወአሐዳት ፡ (ዳን፩ ፡ ፳። ኢሳ፮ ፡ ፲፫። አቡሻ ፡ ፲፩)።
ትእሪር ፡ ማረራ፤ ዐጨዳ ቈረጣ ስብሰባ ክመራ፤ ለቀማ፤ አለቃቀም። ውጤት፤ ምርት።
ትዕሪና ፡ ዝኒ ከማሁ። ትዕሪና ዕለታት ፡ (አቡሻ ፡ ፴፯)።
ትዕሪን ፡ ጌጥ ሽልማት፤ የወርቅ የብር መሣሪያ ፥ ሥራው ከምሳሌው የተካከለ። ኪራስን እይ።
ትዕርዝት ፡ ጥብቆ፤ ቀሚስ፤ የሚጠለቅ የሚቈለፍ። እስመ ኮነት ትዕርዝቱ ኅልቅተ። ኮነ ትዕርዝቶሙ እምአምእስተ አባግዕ ፡ (ፊልክ ፡ ፶፮ና ፡ ፹፱)።
ትዕቢት ፡ በቁሙ፤ ትቢት፤ ትቢተኛነት፤ ኵራት፤ የልብ እድገት ከፍታ። ኀበ ሀለወት ትዕቤት ህየ ሀሎ ኀሳር። ትዕቢትሰ ጥንተ ኀጢአት ይእቲ ዘቦአት ውስተ ፍጥረት፤ እስመ ባቲ ወድቀ ሰይጣን። ትዕቢት ልቦሙ። ዑቅ ኢትንብብ ነገረ ትዕቢት ፡ (ጦቢ፬ ፡ ፲፫። ፈ ፡ መ ፡ ፫ ፡ ፩። ሢራ፫ ፡ ፳፬። ፴፭ ፡ ፲፪)።
ትዕውርት ፡ ቸልታ፤ ቸልተኛነት፤ ንቀት፤ ድፍረት።
ትእዛዝ ፡ (ዛት) በቁሙ፤ እግዚኣዊ አምላካዊ ቃል፤ ከሥራ አስቀድሞ የሚሰጥ የሚጣፍ የሚነገር፤ ሕግ ሥርዐት አድርግ አድርግ የሚል፤ ፈቃድ ደንብ ዕድር፤ የሚገባ ነገር። እስመ በትእዛዝ ውእቱ ቃሉ። ወፅአ ትእዛዝ እምኀበ ንጉሥ። ይወፅኡ እምትእዛዝነ። በእንተ ትእዛዝ ወጽሕፈቱ። ታቦት እንተ ትእዛዝ። ዐቂበ ትእዛዛቲሁ ለእግዚ። ትእዛዛተ ሰብእ። ትእዛዘ አበዊነ ሐዋርያት ፡ (ሉቃ፬ ፡ ፴፪። ዳን፪ ፡ ፲፫። ዮሴፍ። ፍ ፡ ነ ፡ ፵፩ ፡ ፩። ዘፀ፴፱ ፡ ፲፭። ሢራ፳፫ ፡ ፳፯። ኢሳ ፳፱ ፡ ፲፫። ቅዳ)። ትእዛዝ አንቀጽ ትእዛዝ መባሉ ከላይ ወደ ታች ሲመጣ ነው፤ ከታች ወደ ላይ ሲወጣ ግን ልመና ጸሎት ይባላል።
ትዕይርት ፡ (ታት) ስድብ፤ ውርደት፤ ለግድ፤ ተግዳሮት፤ ጡር መስቃ። ትዕይርተ ይከውኖ። ከመ ኢይስማዕ ትዕይርተ። ትዕይርቱ ለክርስቶስ እንዘ ንጸውር ትዕይርቶ ፡ (ጦቢ፫ ፡ ፬ና ፡ ፲፫። ዕብ፲፩ ፡ ፳፮። ፲፫ ፡ ፲፫)።
ትዕይንት ፡ (ታት) ሰፈር፤ ከተማ፤ መንደር፤ ብዙ ድንኳን፤ ጐዦ ቤት፤ ዳስ በረት። ቀርበ ሙሴ ኀበ ትዕይንት፤ ወቆመ ውስተ አንቀጸ ትዕይንት ፡ (ዘፀ፴፪ ፡ ፲፱ና ፡ ፳፮)።
፡ ሰራዊት ጭፍራ ፤ ጓዝ
ወገን ፤ ሕዝብ ቤተ ሰብ። ጉባኤ ማኅበር
ሸንጎ ፤
የሰው መንጋ
፤ ባንድነት
የሚሰፍር የሚንጋጋ። መንግሥትን
ተመልከት። ወሰሰለ መልአከ እግዚ ዘየሐውር ቅድመ ትዕይንቶሙ ለደቂቀ እስራኤል። ወትዕይንቶሙሰ ለኢሎፍሊ ተዐየኑ ፈለገ። ትዕይንቶሙ ለእለ ቆሬ (ዘፀ፲፬ ፡ ፲፱–፳። ፩ዜና ፡
፲፩ ፡ ፲፭።
ሢራ፵፭ ፡ ፲፰)።
ትዕግልት ፡ (ታት) በቁሙ ፤ ትግል። ቅሚያ ፤ ስርቆት ፤ ግፍ በደል። ወይነ ትዕግልት። ዘይትዔገል ትዕግልተ እኩየ። ኵሉ ትዕግልት ውስቴታ ፡ (ዓሞ፪ ፡ ፰። ዕን፪ ፡ ፬። ኤር፮ ፡ ፮)።
ትዕግሥት ፡ (ታት) በቁሙ፤ መታገሥ፤ መቈየት፤ ታጋሽነት፤ አንኆ መንፈስ። ሰማዕክሙ ትዕግሥቶ ለኢዮብ። ዘይሰትያ ለትዕግሥት ከመ ማይ። ዕድሜ ዘትዕግሥት። በእንተ ትዕግሥታተ ነፍሳት ናስተበቍዕ ፡ (ያዕ፭ ፡ ፲፩። ኢዮ፴፬ ፡ ፯። ፍ ፡ ነ ፡ ፵። ኪዳ)።
ትኩል ፡ (ላን ፡ ላት ክልት) የተተከለ፤ ትክል፤ የቆመ ፡ (የተሠራ። ትኹል ፡ -ውስተ ፡ ቤተ ፡ ሐማ : ዕፅ ፡ ትከልት ፡ ኀበ፣ሙሓዘ ፡ ማይ ፡ ማዕ ርፖ፤ትክልት፣ውስተ ፡ ምድር።በዓባት ፡ ትኩላት። ዲያቆናት ትኩሳን፤ለመልእክተ ፡ ቤተ ፡ ክርስቲያን ፡ (አስቱ ' ፬ " መዝ ፡ ፩። ፋ ፡ ፳፯ " እብጥ ፡ ፭)።
ትኩት ፡ (ታን ታት ትክት) የታከተ፤ ታካታ። ደም የሚያይ፤ ደማም፤ መርገማም። ኢይክል ተንሥኦ ቅድሜከ፤ እስመ ትክት አነ። ሰከቡ ምስለ ትክት። ከመ ርኵሰ ትክት። ኀራስ ወትክት ፡ (ዘፍ፴፩ ፡ ፴፭። ሕዝ፳፪ ፡ ፲። ፴፮ ፡ ፲፯። ቀሌ)።
ትኩዝ ፡ (ዛን-ዛት ፡ ክዝት) ያነ'የተከዘ፤ በጽኑ ፡ ሐዘን ፣ የተያዘ ፣ የሚያስብ ፡ የሚጨነቅ፤ ሐሳብና ፣ ጭንቅ የያዘው ፡ የወዘወዘው። ሕሙም ፡ ወትኩዝ። ትኩዝየ ፡ ኣንሶሱ። ወሖረ ፡ ትኩዞ። ሕ ዘነ ፡ ወትኩዘ ፡ ልብ ፡ (ሮሜ፰ ፡ ፳፪። መዝ ፡ ፹፯ = ማ ር፲ ፡ ፳፪። ኤፍ ፡ ፪)።
ትካት ፡ ዱሮ፤ ጥንት ቀድሞ፤ ያለፈ የቈየ ጊዜ ዘመን። ኹለተኛም፤ ትላንት ከትላንት በስቲያ፤ ዓምና ሐች ዓምና፤ የወዲያኛው ያሰኛል። ሰብአ ትካት። መዋዕለ ትካት። ምትየ ዘትካት። እምትካት ወእስከ ለዓለም። ወስሙሰ ለውእቱ ብሔር ትካቲሁ ሉዝ። ቀዳሚየ ቃል አልብየ፤ ወትካትየ ፡ (ኢዮ፳፪ ፡ ፪። ሆሴ፪ ፡ ፱። መዝ ፡ ፺፪። ዘፍ፳፳ኛ ፲፪። ዘፀ፪ ፥ ፲)።
ትካዜ ፡ (ዝያት) በቁሙ ፣ መተከዝ፤ እተካ ክዝ፤ ትከዛ፤ ሐዘን › ጭንቅ፤ ሐሳብ፤ እህህታ።
ትካዝ ፡ (ዛት) ጭንቅ፣ ሐሳብ፤ ጕዳይ ፡ ሙ ፍቅድ፤ ዕጦት ችግር ፣ ንግድ ፡ ተግባረ ፡ እድዞ ዘእን በለ ፡ ሐዘን ፡ ወካዝ። ብዙኃት ፡ እማንቱ ፡ ትካ ዛተ ፡ ዓለም። ትካዝ ፡ ብየ ፡ ንኪ። ኢትንግር ቅ ድመ ፡ ኬር፣ ትካዘ ፡ ምስለ ፡ ማእምራን፤ ይ ኩኝ ፡ ትኣዝከ። ዘይንሊ ፡ ትካዘ ፡ ዝንቱ ፡ ዓለም! ፡ (ኢዮ፲፩ ፥ ፲፰። እፈተ፰ - ፫ነገ ፡ በ፲፬ ፡ ራሂ : ፲፰። ፱ ፡ ፲፭። ዲድ ፡ ፫)
ትክለት ፡ መትከል፤ መተከል ፣ እተካከል፤ ትክልነት
፡ ተከላ፤ ትክሎሽ።
፡ (ቅዳ " እርጋ - ፩)። ኢት ጸረ፣ሥርወ ትከሰትከ ፡ (መጽ ፡ ምስ)።
ትክቶ ፡ ደም፤ አደፍ፤ ግዳጅ፤ የሴቶች አበባ። ኀደጋ ለሳራ ትክቶ አንስት። መዋዕለ ትክቶሃ። ጸርቀ ትክቶ። ደመ ትክትሆን ፡ (ዘፍ፲፰ ፡ ፲፩። ዘሌ፲፪ ፡ ፪። ኢሳ፷፬ ፡ ፪። መጽ ፡ ምስ)።
ትኳን ፡ (ናት። ዐረ ተክዊን፤ ፍጥረት) በቁሙ፤ ትዃን ያልጋ ተባይ፤ ሲበላ የሚያተክን የሚያትከነክን፤ ግማታም ክርፋታም።
ትውሕስት ፡ (ታት) በቁሙ ትውስት፤ መዋስ ውሰት፤ ዋስትና ዋስነት። በእንተ ትውሕስታት ወሤጥ ወተዓስቦ ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፵፫ ፡ ፯)።
ትውልድ ፡ (ዳት) በቁሙ፤ ዘር ልጅ፤ ባላገር ተወላጅ። ኵሉ ትውልድ ዘሥጋ ወደም። ትውልደ ቃግስት። ትውልደ ሕርቱማን። ትውልደ ዘመድየ። ትውልደ ምድር ፡ (ሢራ፲፬ ፡ ፲፰። ኢሳ፲፬ ፡ ፳፱። ፶፯ ፡ ፬። ዘፍ፲፭ ፡ ፪ ፡ ፫። ዘፀ፲፪ ፡ ፵፰)።
፡ ወገን ነገድ፤ ሐረግ። በኵሉ ትውልዶሙ ፡ (፩ዜና ፡ ፯ ፡ ፪)።
፡ የሰው አወላለድ የዘር አወራረድ ሽቅብና ቍልቍል የሚቈጠር፤ በተራ የሚጣፍ የሚነገር፤ የሰው ዕድሜ ዘመን መዋዕል፤ ተወልዶ እስኪሞትና እስኪቀበር ተሹሞ እስኪሻር የሚኖረው። አስከ ሣልስ ወራብዕ ትውልድ። ትውልድ እንተ ትመጽእ። ለብዙኅ ትውልድ። ለትውልደ ትውልድ። ለትውልዳት እስከ ዓለም ፡ (ዘፀ፳ ፡ ፭። መዝ ፡ ፳፩። ኢሳ፳፬ ፡ ፳፪። ሢራ፴፱ ፡ ፱። ሔኖ፹፪ ፡ ፪)።
ትውዕርት ፡ ድንቂያ፤ ድንቅነት ልዩነት ልውጥነት። በትውዕርቱ ወበመንክሩ ለዘክርስቶስ ምስጢር ፡ (ቄር ፡ ጰላ)።
ትውክልት ቱክልት ፡ (ታት) በቁሙ፤ መታመን እምነት፤ ትምክሕት፤ ጽኑ ተስፋ አለኝታ፤ የማይታበል የማይጠረጠር የሃይማኖት ፍሬ። ትውክልተ ተስፋ። ትውክልተ ክብሮሙ። አኅደግዎ ትውክልቶ። ሃይማኖት ወቱክልት ወተፋቅሮ። እስመ ቱክልታ እግዚ ውእቱ። በእንተ ሕጸተ ቱክልቱ ላዕለ እግዚ ፡ (ግብ፳፮ ፡ ፮። ኢሳ፳፰ ፡ ፬። ሚክ፪ ፡ ፰። ፩ቆሮ ፡ ፲፫ ፡ ፲፫። ፩ጢሞ ፡ ፭ ፡ ፭። ዮሴፍ)።
ትውክልና ፡ ጥብቅና፤ ወኪልነት። ትክልነት ባለርስትነት፤ ባለሐዲሶች ግን ቍራኝነት ይሉታል። ወኀደጎሙ ለእኩያን ህየ ውስተ ትውክልና እዕከ ዕለተ ደይን ፡ (መቅ ፡ ወን)።
ትውዝፍት ፡ ትዕቢ ኵራት፤ ከልብስና ከጌጥ የተነሣ። የምንዝር ጌጥ መልክ የሚያድስ የሚለውጥ ፡ (ቀሌ)።
፡ ውዝፍነት ቀሪነት። ዛወፈን እይ፤ የዚህ ሞክሼ ነው። ትውዝፍት በማለት ፈንታ ትዝውፍት ይላል ፡ (ገላ፭ ፡ ፳)።
ትውፅኅት ፡ ምጥ ጭንቅ፤ እህታ የሆድ በሽታ ፡ (ቄድር ፡ ገ፶፱)።
ትውፊት ፡ ስጦታ፤ ልማድ ትምርት፤ ወግ ታሪክ፤ ሃይማኖት ሥርዐት፤ ከጥንት ከአበው ሲያያዝ ሲወርድ፤ ቃል በቃል ሲነገር የመጣ። ዘርትዕት ወእንተ ሐዋርያት ሃይማኖት ትውፊት። ትውፊተ ቅዱሳን መምህራን። ትውፊቶሙ ለቅዱሳን ሐዋርያት። ትውፊተ መጻሕፍቲሆሙ ፡ (ቄር ፡ እስ። ጰላ። መጽ ፡ ምስ)።
ትዝኅርት ፡ (ታት) በቁሙ፤ ትቢት ኵራት፤ ትምክሕት ተግዳሮት። ለብዙኃን አስሐቶሙ ትዝሕርቶሙ። ትምክሕት ወትዝኅርት ያማስንዎ ለባዕል ፡ (ሢራ፫ ፡ ፳፬። ፳፩ ፡ ፬)።
ትዝልፍት ፡ ዝወተራ አዘውታሪነት፤ ተሳዳቢነት። ክርክር ስድብ፤ ንዝንዝ ውዝግብ፤ ችክታ። በእንተ ትዝልፍቱ። አኮ በሀከክ ወበትዝልፍት። ትዝልፍተ ኅሊና ስኡን ፡ (ቀኖና። ግብ፲፱ ፡ ፴፮። ቄር ፡ ጰላ)።
ትዝምድ ፡ (ዳት) መዛመድ፤ ዝምድና። ዘመድ፤ ወገን ነገድ፤ ልጅ ቤተ ሰብ፤ ትውልድ። እምድርከ ወእምትዝምድከ፤ ወገን። እሉ ትዝምደ ያዕቆብ። ኂሩተ ትዝምድ። ኵሉ በበ ትዝምዱ ኵሎ መዋዕለ። በኵሉ ትዝምዶሙ ፡ (ኩፋ ፡ ፲፪። ፴፱። ጥበ፰ ፡ ፫። ኩፋ ፡ ፭። ፮)።
ትዝምድና ፡ ዝምድና ዘመድነት፤ ተወላጅነት። ትዝምድና ዘውሉድ ፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፵፪ ፡ ፮)።
ትያህ ፡ (ሃት) ዙረት፤ ቅልውጥ | ሳይጠሩ ፡ መሮጥ፤ኺደ ፡ ማፍጠጥ።
ትያጥራ ትያጥሮን ፡ (ጽር ቲአትራ) ስሙ ፡ ሀገር ፡ በታናሽ ፡ እስያ ያለች ፣(ራእ፩ ፲፩ = ፪ • ፲፰)።
ትያጥሮን ፡ (ጽር'ቴአትሮን) የሣቅ) የጨዎታ ፡ ቤት ፡ ብዙ ፡ ዐይነት ፡ የጥጋብ ፡ ጨዎት ምላ ሌና ፡ ተረት ፡ ምትሀትና ፡ ውሸት። Hትያጥሮን።ቤተ፥ ትያጥሮን፣(ኪዳ። ስንክ ፡ ሐም፭። ታነ፲፪። መጋ፲፯)።
ትይህድና ፡ ይሁዲነት፤ የአይሁድ እምነትና ሥርዐት፤ ለሐዲስ ኪዳን አምሳል መርገፍ ኹኖ የተሰጠ ፡ (መጽ ፡ ምስ። ስንክ ፡ ግን፲፯)።
ትድምርት ፡ ዝኒ ከማሁ፤ ጋብቻ ሩካቤ ፅምረት፤ ተዋሕዶ አንድነት፤ ፡ (ጥቀ) መቀላቀል፤ ቅልቅልነት። ለበጎም ለክፉም ይነገራል፤ ፅምረት ፥ እንደ ባልና ሚስት፤ ተዋሕዶ ፥ እንደ ነፍስና እንደ ሥጋ፤ እንደ መለኮት እንደ ትስብእት፤ አንድነት ለኹሉም ይኾናል። መቀላቀል እንደ ዶቄትና እንደ ዶቄት፤ እንደ ኖራና እንደ መሬት፤ ወይም እንደ መንጋና እንደ መንጋ። ትድምርተ ብእሲ ወብእሲት። ነፍሱ እንተ ለብሳ በትድምርት። ዘእንበለ ቱስሕት ወኢትድምርት። ይትዐቀቡ እምትድምርተ እኩያን ሰብእ። ይሰደዱ እምትድምርተ ምእመናን፤ አንድነት ሱታፌ ጉባኤ ፡ (ዲድ ፡ ፴፫። ቄር። ቅዳ። ዲድ። ፈ ፡ መ ፡ ፰ ፡ ፩)። ለቍጥርም ይኾናል ፡ (አቡሻ ፡ ፲፩)።
ትጉህ ፡ (ሃን ሃት ግህት) በቁሙ፤ የተጋ የነቃ፤ እንቅልፍ የሌለው። ትጉህ ለገቢረ ሠናይ። ውእቱሰ ትጉህ ለአሕሥሞትየ። ትጉሃን መላእክት እለ ኢይነውሙ። ትግህት ንብ ፡ (ዲድ ፡ ፬። ዮሴፍ። መዋሥ። ስንክ ፡ መስ፳፭)።
ትጋህ ፡ (ሃት) ትጋት ንቃት፤ የእንቅልፍ ዕጦት፤ ሐሳብ ፈቃድ። በጻሕቅ ብዙኅ ወበትጋህ ፍድፉድ። ኀሠሥዎ በትጋህ ዐቢይ። ወለት ትጋህ ኅቡእ ይእቲ ለአቡሃ። ትጋሁ ዘከመ ያቅሕም ብዕራይሁ። ትጋሆሙ ለገሥጾትነ ፡ (አፈ ፡ ድ፴፬። አቡሻ ፡ ፶። ሢራ፵፪ ፡ ፱። ፴፰ ፡ ፳፮። አፈ ፡ ድ፳፱)።
ትግሀት ፡ (ታት) መትጋት፤ አተጋግ፤ ትጉህነት፤ ትጋት፤ እንቅልፍ ማጣት። ሌሊተ ተኖልዎሙ ትግሀታተ ከንቱ ኢይምጽኦሙ። ቅዱስ ብሶይ መዓልተ ጸሎታተ ወሌለተ ትግሀታተ ፈጸመ ፡ (ቅዳ ፡ ያዕ። ድጓ)።
ትግምርት ፡ ቻይነት አቻቻል፤ ችሎት።
ትግምድ ፡ መቈረጥ ቈራጥነት፤ ቈራጣ መኾን። ትግምደ አልባሲሆሙ ፡ (ግንዘ)።
ትግራይ ፡ ትግሪኛ፤ የትግሬ ወገን፤ በትግሬና ባማርኛ ማኽል ያለ ቋንቋና ሕዝብ፤ ቋንቋነቱ ካማርኛ ይልቅ ለትግሬ ለግእዝ የሚቀርብ።
ትግሬ ተጋሪ ፡ (ዐረ ታጅር። ዕብ ታጋር) ነጋዴ ዐጣሪ፤ ሸያጭ ሸቃጭ ቸርቻሪ። የቋንቋ ስም፤ ሴማዊ ግእዛዊ ቋንቋ፤ ሐባቦች የሚናገሩበት፤ ከዐረብና ከዕብራይስጥ ሱታፌነት ያለው። ስመ ሀገር በመረብና በተከዚ በደንከልና በባዜን መካከል ያለ ክፍል።
ትግርምት ፡ ግርማ፤ አስፈሪነት፤ ተፈሪነት። እለሰ ኢይፈርሁ ትግርምቶ ለውእቱ ንጉሥ። ትግርምቱ ያወድቆ። ኢትፍርሁ ትግርምቶሙ ፡ (ቀሌ። ኢዮ፲፭ ፡ ፳፩። ኢሳ፰ ፡ ፲፪)።
ትግብርት ፡ ሥራነት፤ አሠራር አደራረግ። ሥራ፤ የሥራ ስልት መልክ። ትግብርቶሙ። ትግብርተ ንህብ ፡ (ኩፋ ፡ ፲፩። ምሳ፮ ፡ ፰)። ግርድ ዕንፋጭ በማለት ፈንታ ትግብርት ይላል ፡ (ዓሞ፰ ፡ ፮)።
ትግዕርት ፡ ጣር ጋር፤ ጣረኝነት ጋረኝነት። አማን ትግዕርታ ለኀጢልአ አስስለ ፡ (ቄር ፡ ጰላ)።
ትፅርርት ፡ ፀርነት፤ ተፃራሪነት፤ ጠላትነት ፡ (ፊልክ ፡ ፻፭)።
ትፊላ ፡ (ዕብራ) ጸሎት ፥ ልመና ፥ ምሕላ። ለጸሎት በማለት ፈንታ ላትፊላ እንዲል ፡ (ነሐ፲፩ ፡ ፲፯)።
ትፋሕ ፡ (ዕብ ታፉዋሕ። ዐረ ቱፋሕ) የተክል ዕንጨት ስም፤ ፍሬው ክብ እንክብል፤ ሥጋማ ጥፍጥ። ኮልን እይ፤ ተና ጠ ተወራራሾች ስለ ኾኑ በትፋሕ ፈንታ ጥፋሕ ይላል ፡ (ስንክ ፡ ሐም፰)። አዘዘ ያምጽኡ ሎቱ ትፋሐ፤ አነዳ ትፋሕ። ወፈነወ ንጉሥ ትፋሐ ሰብእሲቱ፤ ወይእቲኒ ፈነወት ውእተ ትፋሐ ለዩሊኑስ፤ እስመ ሕሙም ውእቱ፤ ወሶበ ሖረ ንጉሥ ከመ የሐውጾ ርእዮ ለውእቱ ትፋሕ፤ ወይቤላ ሀብኒ ትፋሐ ዘፈኖኩ ለኪ ወትቤሎ በላዕክዎ ፡ (ዮሴፍ። ዮሐ ፡ መደ)።
ትፋእ ፡ ትፋት፤ አክታ። ይመጽአኒ ትፋእ ከመ እቂእ ፡ (አረጋ ፡ መ፲)።
ትፍሥሕት ፡ (ታት) ዝኒ ከማሁ፤ ተድላ፤ ደስታ፤ ዕረፍት። አልቦ ትፍሥሕት ዘይኄይስ እምሐሤተ ልብ። ወይን ለትፍሥሕት ተፈጥረ። ለብሰት አልባሰ ትፍሥሕታ። ትፍሥሕታተ ሰማይ ፡ (ሢራ፴ ፡ ፲፮። ፴፬ ፡ ፳፯። ዮዲ፲ ፡ ፫። ስንክ ፡ ሐም፳፭)።
ትፍአት ፡ መትፋት፤ አተፋፍ፤ ትፋት፤ ምራቅ። ተፍኦ ትፍአቶ ፡ (ዘኍ፲፪ ፡ ፲፬)።
ትፍግዕት ፡ (ታት) ዝኒ ዓዲ ከማሁ። ትፍግዕት ያማስን ሥጋ ወፍሰ ኅቡረ። አፍቅሮ ትፍግዕታት። ትፍግዕታተ ሕዋሳት ፡ (አፈ ፡ ተ፳፱። ፊልክ ፡ ፵፬)።
ቶማስ [1] ፡ (ጽር። ዕብ ቶማእ) የሰው ስም፤ ካ፲፪ቱ ሐዋርያት አንዱ። መንታ፤ መንትያ ኹለትያ፤ ፅንሱና ልደቱ ከወንድም ጋራ የኾነ ብቻውን ያይዶለ ማለት ነው ፡ (ማቴ፲ ፡ ፫)።
[2] ፡ የሰው የፀሓይ ስም፤–ተወማስ።
ቶማስስ ፡ ስመ ፀሓይ፤ የኦርያሬስ ኹለተኛ። ወአስማቱ ለፀሓይ ከመ ዝ፤ አሐዱ ኦርያሬስ ወካልኡ ቶማስስ ፡ (ሔኖ፸፰ ፡ ፩)።
ቶሳሒ ፡ (ሒት ሕያን ያት) የሚቀላቅል የሚጨምር፤ ጨማሪ ደባላቂ።
ቶስሖ ሖት ፡ (ቶስሐ ይቶስሕ። ዕብ ታዌስ፤ ሤረየ) መቀላቀል፤ መደባለቅ፤ መበረዝ፤ መጨመር መከለስ፤ የፈሳሽ። መያስያንኪ ይቶስሑ ማየ ውስተ ወይን። ቶስሐ ሐሊበ ወንጌል ምስለ ጸቃውዐ ኦሪት። ኅዳጠ ወይነ ቶስሕ። እለ ይቶስሑ ላዕለ ወርቅ ብሩረ አው ንሓሰ ፡ (ኢሳ፩ ፡ ፳፪። መጽ ፡ ምስ። ፩ጢሞ ፡ ፭ ፡ ፳፫። ፈ ፡ መ ፡ ፲፱ ፡ ፪)።
፡ ማዋደድ ማሰማማት፤ መጨማመር። ቶስሖ ለነፍስትነ። ትቶስሕዋ ለጥበብ በንጹሕ ልብ። ቶስሐ ውዳሴ ውስተ ገሥጾቶሙ ፡ (፩ቆሮ ፡ ፲፪ ፡ ፳፬። ሄርማ። አፈ ፡ ድ፲)።
ቶራ [1] ፡ (ዕብራ) ሕግ ሥርዐት፤ ኦሪት፤ ዐሠርቱ ቃላት።
[2] ፡ ቶራ፤ ፡ (ሱር ታውራ፤ ሶር። ዕብ ያሕሙር) ቦኸር፤ የበረሓ እንስሳ፤ የፌቆና የዋሊያ ወገን፤ ቀንዱ ረዥም ዐጽቃም ባለብዙ ቅጥይ፤ ዥራቱ ዐጭር የሠሣ ዐይነት፤ ወተታም ፡ (ዘዳ፲፬ ፡ ፭)። ወይጠል ወቶራ ወሀየላት። ሐሊብ ቶራ ፡ (መቃ ፡ ገ፭። ስንክ ፡ መስ፲፱)።
ቶራት ፡ ቶሮች፤ ቶራዎች። ቶራት ወአልሕምተ ገዳም
፡ (ፍ ፡ ነ ፡ ፵፬ ፡ ፪። ስንክ
፡ ግን፳፰)።
ቶሬን [1] ፡ (ዕብራ) የመርከብ ምሰሶ ዐምድ ተራዳ፤ የሸራ ያላማ መስቀያ ፡ (ኢሳ፴ ፡ ፲፯)።
[2] ፡ ተራዳ፤–ተውር።
ቶርማን ፡ (ትግሬ) ጋድም፤ ሠረገላ።
ቶታን [1] ፡ (ናት) በቁሙ፤ ማዘቢያ፤ ሢር ጠፍር። ቶታነ አሣእን ፡ (ዘፍ፲፬ ፡ ፳፫። መሳ፱ ፡ ፫። ኢሳ፭ ፡ ፳፯። ማር፩ ፡ ፯)።
[2] ፡ ቶታን፤–በቁሙ፤–ተወተ።
ቶጳዝዮን ፡ (ጽር ቶፓዚዮን። ዕብ ፊ ፒፕዳ) ዕንቍ፤ የዕንቍ ስም፤ ብጫቴ። ተንከራን ተመልከት፤ ከዚህ ጋራ አንድ ነው ፡ (ዘፀ፳፰ ፡ ፲፯)።

No comments:
Post a Comment