ሀ ለ ሐ መ ሠ ረ ሰ ሸ ቀ በ ተ ቸ ኀ ነ ኘ አ ከ ኸ ወ ዐ ዘ ዠ የ ደ ጀ ገ ጠ ጨ ጰ ጸ ፀ ፈ ፐ
ፐ ፤ የጰ ኹለተኛ ፤
ትርፍ ዲቃላ ፤ ጽርኣዊ ፊደል
፤ በመልክ በተራ ፳፮ኛ
፤ የፈ
ድርብ ፤
ስሙ ፒ
፤ ፔ
፤ ይኸውም ፊ ፌ ማለት ነው
፤ ከፈ
ቀጥሎ መጻፉም የፈ ድርብ ስለ ኾነ ነው። ፐ መባሉ በግእዝ ነው እንጂ በጽርእና በቅብጥ
በላቲን ታው ቴ ይባላል ፤ መጨረሻ ፊደል መኾኑም ተ ስለ ኾነ ነው ይባላል። ጰን ጰንጠቆስቴና ጰራቅሊጦስ ብለው የሚፈቱ ግን ይህነንም ፓኖስ ፕኔፍማቶስ ይሉታል ፤ ፋኖስ
መንፈስ ማለት
ነው። ሰማንያ የምንለው አኃዝ (፹) በጽርእና
በቅብጥ ፐ ይባላል ፤ ፈ ማለት ነው
፤ ዕብራውያንም ነቍጣ እየጨመሩ ፈን ፐ ይሉታል። ፐ ድርብነቱ የፈ ስለ ኾነ ስምንትነትን ሳይለቅ የስምንት
መቶ አኃዝ ይኾናል ፤ ይህም ጰ ፯፻ ፤ ፐ ፰፻ ፤ ኈ ፱፻ ፤ ቈ ፲፻ ፤ እ እ እልፍ እያለ መኼዱን ያሳያል
፤ ያቡጊዳን
አኃዝ ተመልከት። በዕብራይስጥም ኹለት ዐይነት ፈ አለ አባትና ልጅ
፤ አባቱ
፹ ፤ ልጁ ፰፻ ይባላል።
ፐፒረለይ ፡-(ጽር ፖርፊራ፤ ኮኪኖስ) ቀይ ሐር፤ ዝኅንን ፀምር፤ ቀይ ቀለም የገባ የሐር ፈትል፤ ጐፍላ ፡-(ዘፀ፴፭ ፡-፮። ዕብ፱ ፡-፲፱። አፈ ፡-ድ፲፮)። አዝዝ ሎሙ ማዕተበ ረስን ዘመስቀል ዘፒፒራ ውስቴቱ ፡-(ሥር ፡-
ፐፒራ ፐፒር ፡-(ጽር ፖርፊራ። ዕብ አርጋማን) የቀለም ስም፤ ዝኅንን ቀይ ቀለም፤ ደባባ፤ ቅላቱ በጣም ያልደመቀ። ሠያጢተ ፐፒራ ፡-(ግብ፲፮ ፡-፲፬)። ባለሐዲሶች ግን እንዶድ ይሉታል።
ፒሉፓዴር ፡-ፒሉፓዴር፤ የሰው ስም፤ መርቆሬዎስ ፡-(ድጓ)።
ፒላስ ሳ ፡-(ጽርእ) (ጽርእ) ደጅ አፍ በር፤ አጐበር። የፊላስን ፍች ተመልከት፤ ከዚህ ጋራ አንድ ነው። ማርያም ፒላሰ መለኮት። ይጠባሕ መርዓዊ ለምሳሐ መሀይምናን በውስተ ፒላሳሃ ለመርዓት። አብአተኪ ውስተ ፒላሳሁ ለወልድ ፡-(አርጋ ፡-፫። መጽ ፡-ምስ)።
ፒሳ ፡-(ጽርእ) ዝፍት፤ ሙጫ፤ የሙጫ ቅጥራን። አስፈሊጥን እይ፤ የዚህ ጎር ነው። ወትቀብዓ በፒሳ። ወወደዩ ውስተ እሳቱ ተየ ወፒሳ። ዘገሰሰ ፒሳ ይትአኀዝ ቦቱ ፡-(ዘፍ፮ ፡-፲፬። ዳን፫ ፡-፳፪። ሢራ፲፫ ፡-፩)።
ፒርልዩ ፡-(ጽርእ) ባለቅኔዎች ቀንጠፋ ይሉታል፤ እንጃ። ወልድ ለእመ ተሰቅለ ፒርልዩ ፡-(ቅኔ)።
ፓሲካ ፡-ፓሲካ፤ ፡-(ጽር ፓስኻ) ዝኒ ከማሁ፤ ፍሥሕ፤ ፋሲካ። የፋሲካን ፍች ተመልከት። ጽዋዐ ፓሲካ ምሉአ ድኅረ ሰለጥከ ስትየ ፡-(ደራሲ)።
ፓሳ ፡-(ዕብ ፓሳሕ፤ ፔሳሕ) ፋሲካ፤ መሥዋዕት። ዘተወከፍኮ ለኢዮስያስ በፓሳ ፡-(አዋል። ጥበ ፡-ጠቢ)።
ፓና ፡-(ብ ፓናት። ጽር ፓኖስ፤ ፋኖስ) ፋና፤ ፋኖስ፤ ከውጭ ሲወጡ የሚያበሩት፤ ባለቅዛዝ ባለመስታዮት። ዘሩም ምስጢሩም የፈነወ ነው። አመ የአኀዙከ መጽኡ በመኃትወ ጽጕ ወፓና። ወበፓናት ፡-(ደራሲ። ዮሐ፲፰ ፡-፫)።
ፓንዋማንጦን ፡-(ጽር ፕኔፍማቶን) መንፈስ ፡-(ቅዱስ) ማለት ነው ፡-(ቅዳሴ)።
ፓፒራ ፡-(ጽር ፓፒሮስ) መንድደ እሳት፤ የጋዝና የዝፍት የክብሪት ወገን። እሳተ ወፖፒራ ፡-(መቃ ፡-ገ፪)። ነደን ተመልከት።
ፔካ ፡-(ዕብ ፑኽ፤ ኵል፤ ክቡር ደንጊያ) ነጭ ደንጊያ፤ እብነ በረድ። ማርያም ድንግል መንበር ዘእብነ ፔካ ፡-(ደራሲ። ሔኖ፲፰ ፡-፰)።
ፕስልቴ ፡-(ጽር ፕሳልቲሪዮን) መዝሙር፤ ግናይ፤ ማሕልይ፤ የሚያዜሙት፤ የሚያስተዛዝሉት ምስጋና ጸሎት። ወያንብቡ እንከ መዝሙረ ወማሕሌተ አርባዕተ፤ አሐዱ ዘሙሴ ወአሐዱ ዘሰሎሞን ወዘባዕዳንሂ ነቢያት ከመ ዘፕስልቴ፤ ወክልኤቱ ፕስልቴ ፡-(ኪዳ)።
ፕሬዝቢጤር ፡-(ጽር ፕሬስቢቴሮስ) ቆሞስ ካህን ቄስ፤ ወይም የተሾመበት ቦታውና ደብሩ ቤቱ ማኅደሩ። በፕ ፈንታ ጠርዝቤጤር ጤርዜቤጤር ይላል፤ የጣፊ ስሕተት ነው ፡-(መጽ ፡-ምስ)።
ፕንትዮን ፡-(ጽር ፕሊንቲዮን) አበቅቴ ፀሓይ። መጽሐፍ ግን በፐንት ፈንታ ጥንት ይላል፤ ፕና ጥ ተመሳሳዮች ስለ ኾኑ ፣ ጥ በስሕተት ገብቷል። መምህራንም የወጠነ ዘር መስሏቸው ጥንተ ፀሓይ ዕለተ ፀሓይ እያሉ በጥንት ዘይቤ ይፈቱታል። ጥንትዮን ብሂል ጥንተ ብርሃን ፡-(መጽ ፡-ምስ)።
ፕፕሬ ፡-(ጽር ፔፔሪ። ዐረ ባባሪ) በርበሬ፤ በየመልኩና በያይነቱ፤ ይልቁንም ቍንዶው። ዕፀ መዐዛ ወቀናንም ወፕፕሬ ፡-(ሔኖ፴፪ ፡-፩)።
No comments:
Post a Comment