ሀ ለ ሐ መ ሠ ረ ሰ ሸ ቀ በ ተ ቸ ኀ ነ ኘ አ ከ ኸ ወ ዐ ዘ ዠ የ ደ ጀ ገ ጠ ጨ ጰ ጸ ፀ ፈ ፐ
ደ ፡-አራተኛ ፊደል በግእዝ አልፍ ቤት በአበገደ፤ ስሙ ድል(ን) ት፤ ቍጥሩ አራት፤ አኃዝ ሲኾን ደ አርባዕት ቱ ይባላል። ዕብራውያን ግን አራትን መደብ አድርገው በራሱ ላይ ነቍጣ እየጨመሩ አራት እልፍ ይሉታል። ምስጢሩ ረቡንና የረቡን ፍጥረት መደብ አድርጎ ምስጢረ ሥጋዌን ያሳያል። ፡-(ዘፍ፩ ፡-፲፬። ዮሐ፩ ፡-፫–፭)።
ደሀለ ፡-ሸሸ፤–ደሐለ።
ደሐሰ ፡-ዳሰ ፈጨ ረገጠ፤–ፅሒስ ፀሐሰ።
ደሐረ ፡-መረቀ ፤–ድኂር ደኀረ።
ደሓሪ ፡-(ሪት ርያን ያት፤ ሐርት) የሚድር፤ የሚፈታ፤ የሚሰድ የሚያባርር።
ደኃሪ ፡-(ሪት ርያን ያት፤ ኀርት) ኋላኛ የኋላ መጨረሻ፤ ታናሽ ተከታይ። አግሪጳስ ውእቱ ደኃሪ እምእለ ነገሡ በይሁዳ። ደኃሪ ጸላኢ። ደኃሪተ ገመስ። እሙንቱ ደኃርያን። ቀደምት ወደኀርት ፡-(ዮሴፍ። ፩ቆሮ ፡-፲፭ ፡-፳፮። ማቴ፭ ፡-፳፮። ዘኍ፪ ፡-፴፩። ፪ዜና ፡-፳፮ ፡-፳፪)።
ደኃራዊ ይ ፡-ዝኒ ከማሁ፤ ህርቃኖስ ደኃራዊ። ከመ ያቅም ደኃራየ ፡-(ዮሴፍ። ዕብ፲ ፡-፱)።
ደሐየ ፡-ቈፈረ፤–ደኀየ፤ ደኅኀ።
ደኀየ ፡-(ደኅኀ) ቈፈረ ማሰ፤ አወለቀ፤ የጕድጓድ። ግበ ከረየ ወደኀየ። ጸናሒ ግበ ዘይድኂ። ወይድኅይዎሙ ፡-(መዝ ፡-፯። ደራሲ። ዲድ ፡-፲፯)።
ደሓዪ መድሐዪ ሕይ ፡-የሚፈጭ ፈጭታ፤ ባለወፍጮ።
ደኃፂ ድኁፅ ፡-(ፃን ፃት ኅፅት) የዳጠ፤ የተሰናከለ። የተዳጠ የተደፈጠጠ። የሚድጥ ዳጭ ፡-(ገቢር)።
ደለወ ፡-(ዐጕል) ኾነ ተገባ፤ ደላ ተመቸ ተስማማ። ፡-(ገበዘ ተገበዘ ግብዝ ኾነ)። ዘይደሉ ለመልእክተ ኵሉ። ለከ ይደሉ ስብሐት። ወደለዎ ብሔር ፡-(ጥበ፲፭ ፡-፯። መዝ ፡-፷፬። ሉቃ፲፪ ፡-፲፮)።
ደለው ፡-(ዐረ እደለው) ስመ ኮከብ፤ ደላዌ ማይ፤ ሐያቢ በዓለ ማሕየብ ማለት ነው። መልኩ በሥዕል ሲያዩት ውሃ ቀጅ ይመስሳል፤ ኮከብነቱም የጥር ነው፤ ከፀሓይ ጋራ ፳፱ ዕለት ፵፩ ኬክሮስ ይመግባል ፡-(አቡሻ ፡-፬)።
ደሊላ ፡-(ዕብ ድሊላ) ፡-(350) ፡-(ዕብ ድሊላ) ቀጭነን ክር፤ ገመድ ፈትል፤ ወይም ሥሥ ረቂቅ መንዲል፤ የጠጕር ማሰሪያ መሸፈኛ። የሶምሶን ሚስት ፡-(መሳ፲፮ ፡-፬)። ስሟ እንደ ትንቢት ኹኖ ተነግሯል።
ደሊቅ ቆት ፡-(ደለቀ ይደልቅ ይድልቅ። ዐረ ደሊቀ። ዕብ ዳላቅ፤ ነደ) መታወክ መናወጥ፤ መጋለብ መውለብለብ፤ የባሕር የእሳት። በቁሙ፤ መደለቅ መምታት፤ የከበሮና የርግጫ።
ደሊው ዎት ፡-(ደለወ ይደሉ ይድሉ። ዐረ ደላ። ሱር ድላ። ዕብ ፡-ዳላህ፤ ሔበ) መጥለቅ መቅዳት፤ መሳብ መጐተት፤ ከጕድጓድ ከጥልቅ ከዐዘቅት ማውጣት። ማንሣት መስቀል ማንጠልጠል፤ መመዘን መለካት ማስተካከል። ፡-(ማዘጋጀት፤ ማሰናዳት)። ወደለዉ፤ ዐስብየ። ደለውኩ ሎቱ ወርቆ። ወደለውኩ ሎሙ ወርቀ ወብሩረ። እመ ደለውከ ቃለከ በመዳልው። ወትደልዎ ፡-(ዘካ፲፩ ፡-፲፪። ኤር፴፱ ፡-፲። ዕዝ፰ ፡-፳፭። ሢራ፳፰ ፡-፳፭። ሕዝ፭ ፡-፩)። ዳግመኛም በቀደሰ ቤት ደልዎ፤ ደለወ ይዴሉ እያለ በ፪ መንገድ ይኼዳል። ተደለወና መደልው የዚህ አንጻር ናቸው።
ደላዊ ፡-(ዊት ውያን ያት) የሚመዝን መዛኝ፤ ውሃ ቀጅ ባለማሕየብ።
ደልሎ ሎት ፡-(ደለለ ይዴልል ይደልል። ዕብ ዳላል፤ ታላል) መመየድ፤ መከፍከፍ፤ ጠጕርን በሚዶ ማበጠር ማጐፈር፤ መበተን ማጐተን፤ መንቀስ መከናከን፤ ለቤት ክዳንም ይኾናል። ወይም መሥራት መጣስ፤ መሸረብ መጐንጐን፤ መፍተል መቈንደል። በቁሙ መደለል ማታለል፤ መሸንገል። ፡-(ተረት) ዶሮን ሲደልሏት ፥ በመጫኛ ጣሏት። ደላል ደላላ፤ ድላል ደለል ማለት ከዚህ ወጥቷል።
ደልጎ ጎት ፡-(ደለገ ይዴልግ ይደልግ። ዕብ ዳላግ፤ ዳላቅ) መዝለል ፡-(ጥወ) መወርወር፤ ዘሎ ተራምዶ ማለፍ፤ መፍጠን መቀልጠፍ፤ መናር መጓን፤ ላም እንዳየ አንበሳ መኾን፤ ያርበኛ። ማዘለል መወርወር አርቆ መጣል፤ የፍላጻ የጦር። ንኅረይ ለርእስነ ኅሩያነ ሰብአ እለ ይዴልጉ ውስተ ቀትል ወንሑር ላዕሌሁ ወንትቃተል ምስሌሁ ፡-(ኩፋ ፡-፴፯)።
ደመ ሰማዕት ፡-ስለ ሃይማኖት በግፈኞች እጅ የሚፈስ የምእመናን ደም።
ደመ ትክቶ ፡-የሴቶች ግዳጅ፤ ባሕርያዊ ምንጭ አበባ፤ በየወሩ ፯ ፯ ቀን የሚታይ።
ደመ ነፍስ ፡-የሰው የንስሳ ደም፤ ከዕፀዋት ደም የተለየ። በደም የሚሣል እንስሳዊ አእምሮ።
ደመ ኪዳን ፡-የግዝረት የመሧዕት ደም፤ ኪዳን ስለ ማጥናት የሚፈስ።
(ጥ) ደመመ ፡-(ይዴምም ይደምም፤ ደምሞ፤ ዐማርኛ) ዘጋ መረገ፤ ደፈነ፤ መላ ቈለለ አስተካከለ፤ ደመደመ። የመቃብርና ያቀባበር፤ ደምመው እንዲሉ ድፈነው አስተካክለው ሲሉ። ፡-(ሙሾ፤ መነኵሲት በወሊድ ሙቃ ስትቀበር፤ እኅቷና አክሥቷ) አንቺ ሞኝ አንቺ ሞኝ አንቺ ሞኝ ተላላ፤ የኋላዉን በፊት የፊቱን በኋላ። ያማወቷን ነገር ምን አጠያይቋችኹ፤ እንዲያው ቅበሩ እንጂ እየደመማችኹ።
ደመራ ድምር ፡-(ዐማርኛ) በቁሙ፤ የበዓለ መስቀል ዋዜማ፤ ዕንጨቶች የሚደመሩበት።
ደመቅ ፡-ድቃቂ ስባሪ፤ እንክትካች። ወትገብር ደቃቀ ወደመቀ ፡-(ኢሳ፴ ፡-፳፪)።
ደመና ፡-(ናት) በቁሙ፤ ከርጥብ ምድር የሚወጣ ጢስ ላበት፤ ተሰብስቦ ከጠፈር በታች በኅዋ የሚታይ፤ ጠፈርን የሚሸፍንና የሚጋርድ። ደመና ዐቢይ። ደመና ሰማይ። ደመና ዝናም። ደመናት ያውሐዙ ጠላተ ፡-(ሕዝ ፡-፩ ፡-፬። ዳን፯ ፡-፲፫። ሢራ፴፪ ፡-፳፮። ምሳ፫ ፡-፳)።
፡-ብዙ፤ ብዛት መዐት። ደመና ቋዓት። ደመና ዘናቢር ወትንንያ ፡-(ኩፋ ፡-፲፩። ስንክ ፡-ጥር፲፰)።
ደመንሚን ፡-ጨለማ ድግዝታ፤ ምሼት ማታ፤ የጉም ያፈና ጊዜ ቦታ፤ የማይታይ። ዝ ነገር ደመንሚነ ይመስል ለብዙኃን ፡-(ተረ ፡-ቄር፲፱)።
ደሚሕ ሖት ፡-(ደምሐ ይደምሕ ይድማሕ። ዕብ ዳማህ፤መሰለ) መጥለቅ መስመጥ፤ ወደ ውስጥ መግባት፤ ጠልቆ ማወቅ መመርመር። መቅዳት መጨለፍ። ኢታአምርኑ እግዚኦ አልባበ ሰበእ ዘእንተ ትደምሕ ኅሊናነ ፡-(ተረ ቄር፲)። ደምዐን ተመልከት፤ የዚህ መንቲያ ነው።
ደሚም ሞት ፡-(ደመ፤ ደመመ ይደምም ይድምም። ዕብ ዳማም) መድመም ፡-(ጥደ) መደመም፤ መደነቅ መገረም፤ መደንገጥ መፍራት፤ ዝም ዕክም ጸጥ ማለት፤ መፍዘዝ አፍን መያዝ፤ የክፋ የበጎ። ፡-(ድም ማለት፤ መጮኽ መፈንዳት)። መጽሐፍ ግን በደመ ፈንታ ተደመ ይላል፤ ተ ያማርኛ ነው። አንክረ ወተደመ። ታነክር ወትዴመም። ተደሙ እምነ ሥና። እንዘ ይዴመሙ ጥቀ ፡-(ዮሴፍ። አፈ ፡-ተ፳፰። ዮዲ፲ ፡-፯። ጥበ፲፯ ፡-፫)።
ደሚስ ሶት ፡-(ደምሰ ይደምስ ይድምስ። ዐረ ፡-ደመሰ። የደመነ ሞክሼ) መጥቈር፤ መጨለም መክበድ።
ደሚቅ ቆት ፡-(ደመቀ ይደምቅ ይድምቅ። ዐረ ደመከ ቀ) መጨፍለቅ፤ መስበር ማድቀቅ፤ መቀጥቀጥ መፍጨት፤ መምታት መግጨት ፡-(ማቴ፳፩ ፡-፵፬። ኢሳ፵፩ ፡-፲፮)። ደመቀቶ መልታሕቶ። በውግረተ እብን ደመቁ ሥጋሁ። እብን ለእብን ሶበ ይደምቆ ይወፅእ እሳት ፡-(መሳ፭ ፡-፳፮። ስንክ ፡-ጥቅ፬። አፈ ፡-ድ፲፱)። በቁሙ፤ መድመቅ ማማር፤ የልብስ የግምጃ። ፡-(ተረት) ማቅ ይሞቃል፤ ሻሽ ይደምቃል፤ ገቢውን ባለቤት ያውቃል።
ደሚፅ ፆት ፡-(ደምፀ ይደምፅ ይድምፅ። ዕብ ሻሜጽ፤ ሰደበ አሽሟጠጠ) መድመፅ መጮኽ፤ ድምፅ መስጠት፤ መሰማት መደመጥ፤ ድምጣም መኾን። ፡-(መዳመጥ መርገጥ፤ መደፍጠጥ፤ መራመም መፈግፈግ)። ደደምፅ ማዕበሉ። ዘእንበለ ይድምፅ ነጐድጓድ። በቃለ አሚን ወበትፍሥሕት ደምፁ። ደምፀ ወተሰብከ ውስት ዓለም ፡-(ኤር፭ ፡-፳፪። ሱቱ ፡-ዕዝ፬ ፡-፭። መዝ ፵፩። ድጓ)።
ደማሊ ፡-(ጽር፤ ዳማሊስ) ጥጃ እንቦሳ፤ በጥጃ አምሳል የተሠራ ጣዖት። ባለብሉዮች ግን የእንቦሳ ምስል በማለት ፈንታ የአንበሳ ምስል ይሉታል። ወኵሉ ሕዝብ እለ ክሕዱ ሦዑ ለበዓል ወለደማሊ ፡-(ጦቢ፩ ፡-፭)።
ደማሚት ፡-(ደማሚ ምያን ያት) በቁሙ፤ የሚደም የሚጮኽ ድም የሚል ባሩድ። ደማሚት የሴት አንቀጽ ነው፤ ስዱስ ብሎ ስድስት እንደ ማለት ፡-(ዐማርኛ)።
ደማስቆ ፡-(ዕብ ዳሜሴቅ) ስመ ሀገር፤ የአራም መዲና፤ ደማስ ግምጃ የሚሠራበት የሐርና የፀምር የልብስ የፈትል አገር። አምሳለ ሠቅ ፥ በዓለ ሠቅ ማለት ነው። ማየ ደም ፥ አምሳለ ፍሕም የሚሉም አሉ ፡-(፩ነገ ፡-፲፩ ፡-፳፬)።
ደማሪ መደምር ፡-(ዊት ውያን ያት) በቁሙ፤ የሚደምር የሚጨምር፤ አዋሓጅ፤ ቀላቃይ።
ደማዊ ፡-የደም፤ ደማም ደመ ነፍስ ያለው ደም የሚወጣው፤ ደሙ ሲያልቅና ሲደርቅ የሚሞት፤ በባሕርና በየብስ የሚኖር ሕያው ሥግው፤ ተላዋሽ ተንቀሳቃሽ ያሙስና ያርብ ፍጥረት ለማግሰኞም ፍጥረት ይነገራል። ደመ አስካል። ደሙ በለስ። ደመ ዕጕሥታር ፡-(ዘፍ፵፱ ፡-፲፩። መጽ ፡-ምስ)።
ደም ፡-(ማት። ዕብ ዳም። ሱር ድማ። ዐረ ደም) በቁሙ፤ ቀይ ፈሳሽ ከሕያው ከሥግው የሚገኝ ፡-(ዝፍ፱ ፡-፬–፮)። ሥጋ ወደም። እምነ ዘደም። ደማቲሆሙ ወደምየ። በእንተ ክዒወ ደማቲሆሙ። ርቱዕ ንክዐው ደማቲነ በአንተ ክርስቶስ አምሳለ ማይ ፡-(ሢራ፲፬ ፡-፲፰። ዮሐ፩ ፡-፲፫። ዮሴፍ። ፊልክ ፡-፻፴። አፈ ፡-ተ፭)። ዘር፤ ወገን። ተደምሮ በደም። ዘተርፈ እምነ ደሞሙ ለእለ ያርብሕ ፡-(ፈ ፡-መ ፡-፭ ፡-፩። ኢያ፲፫ ፡-፲፪)።
ደምኀ ፡-(ዐረ ደመኀ፤ ኖኀ) አደገ ላቀ፤ ረዘመ። አነሣ አቀና፤ የጠጕር የራስ።
ደምሮ ሮት ፡-(ደመረ ይዴምር ይደምር፤ ፀመረ። ዐረ ደመረ፤ ገባ) መደመር፤ መጨመር ማግባት፤ መግጠም ማገናኘት፤ማዋሐድ አንድ ማድረግ፤ መቀላቀል መደባለቅ። ትዴምር ኆጻዳተ ውስተ መማሥጥ። ኢትደምሩ ዕጣነ ዘካልእ ቅታሬሁ። ደምር አዕጻደ አሐተ ምስለ ካልእታ። ደመረ ሥጋነ ምስለ መለኮቱ። ይዴምሩ ደመ ምስለ ደም። ኢትደምር ንዋየከ ምስለ ዘይኄይለከ። ሠላሳ ወአሐዱ ወዕሥራ ወተስዐቱ ለእመ ደመርከ፤ ክልኤሆሙ ይከውኑ ስሳ ፡-(ዘፀ፳፮ ፡-፲፩። ፴ ፡-፱። ፳፮ ፡-፮። ድጓ። ሆሴ፬ ፡-፪። ሢራ፲፫ ፡-፪። አቡሻ ፡-፲፩)።
ደምሰሰ ፡-(ተቀ ፡-ግ) በቁሙ፤ ደመሰሰ አጠፋ፤ አበላሸ ፋቀ ሠረዘ፤ ይቅር አለ፤ የጥፈት የሥዕል የማኅተም። ወደምሰሰ ኵሎ ዘጽሑፍ ውስቴታ ለይእቲ ክርታስ። አነኬ ዘእደመስሶን ለኀጣውኢከ። ወደምሰሰ ለነ መጽሐፈ ዕዳነ። ደምሰሰ አሠርየ ፡-(ስንክ ፡-ሠኔ፲፪። ኢሳ፵፫ ፡-፳፭። ቆላ፪ ፡-፲፬። ኢዮ፴ ፡-፲፫)።
ደምሳሲ መደምስስ ፡-የሚደመስስ፤ ደምሳሽ አጥፊ። እግዚ ደምሳሴ አበሳየ። መልአክ መደምስስ ፡-(ቄድር። ፩ዜና ፡-፳፩ ፲፭)።
ደምኖ ኖት ፡-(ደመነ ይዴምን ይደምን፤ ደምሰ። ዕብ ዳሜን፤ ዘበለ) መዳመን መጥቈር መጨለም፤ ደመና መምሰል፤ ደመና መልበስ፤ በጉም መታፈን መሸፈን። እምከመ ቦአ ውስተ እዝኑ ለሰብእ ነገረ ሕሠም ይዴምን ገጽ። ፀሓየ ጽድቅ ዘኢይዴምን። ጸዳል ዘኢይዴምን። መጽሔት እንተ ኢትዴምን ፡-(ቀሌ። ቄር። አፈ ፡-ተ፱። ጥበ፯ ፡-፳፮)።
ደምዐ ፡-(ደምዐ፤ ትግ በጨበጣ ወጋ። ዕብ ዳማዕ፤ አነባ) ቶሎ አገኘ፤ በቶሎ ዐወቀ የሰውን ልብ ምስጢርና ሐሳብ። ደምዐና ደምሐ አንድ ዘር ናቸው፤ መጽሐፍ ግን በደምዐ ፈንታ አድምዐ ይላል፤ ስሕተት ነው። ሲወጉና ሲያዝኑ ደምና እንባ በቶሎ እንዲገኝ፤ ይህም እንደዚያ ነው። ኢያደምዕ ፍትወቶ። በደኃሪ ያደምዑ ኀይለ እምጸጋ። እመሰ አድምዐተከ ኢታወፅአከ። ጽዕልት ብእሲት ለእመ አድምዐት ብእሴ ኄረ ፡-(ኢዮ፳ ፡-፳። ፊልክ ፡-፹፫። ሢራ፳፩ ፡-፪። ምሳ፳፬ ፡-፶፰)።
ደምዎ ዎት ፡-(ደመወ ይዴሙ ይደሙ) መድማት፤ ደም መኾን፤ ደም መልበስ፤ መምሰል።
ደሲስ ሶት ፡-(ደሰ፤ ደሰሰ ይደስስ ይድስስ። ዐረ ደሰ) መሰወር መደበቅ፤ መከለል መጋረድ። መዳሰስ መዳበስ፤ በእጅ
፡-መንዳሰስ ድስስ ማለት፤ ማጐንበስ፤ ደሳሳ መኾን፤ የቤት የጐዦ፤ ለፈስም ይኾናል።
ደሳ ፡-ዳውዣ፤ ምንጣፍ የሱማሌ ሥራ፤ ጭገራም።
ደሴት ፡-(ብ ደስያት) በቁሙ፤ በባሕር ውስጥ ያለ፤ ባሕር የከበበው የብስ፤ ሀገር ምድር ተራራ፤ እንደ ደቅ እንደ ሐይቅ እንደ ዟይ ያለ። እለ ይነብሩ ውስተ ዛቲ ደሴት። ደሴተ ኬጥኤም። አድለቅለቃ ደስያት። ደስያት ዐበይት ፡-(ኢሳ፳ ፡-፮። ኤር፪ ፡-፲። ሕዝ፳፮ ፡-፲፭። ኩፋ ፡-፰)።
ደስከን ኖ ፡-(ብ ደሳክን። ዕብ ዲሾን። ሱር ሬማእ። ዐረ ሪእም) የዱር የበረሓ እንስሳ፤ ቀንዳም ቀንደ ታላላቅ ባለብዙ ዐጽቅ፤ እንደ ርኤም ያለ የዋሊያና የፌቆ ወገን፤ ባለብሉዮች ግን ጐሽ ይሉታል። ቶራ ወደስከን ፡-(ዘዳ፲፬ ፡-፭)።
ደስክ ፡-ደስክ፤ ደባስ ጋኔን የሚጫን የሚጨቍን የሚደብት፤ ድራሞን ተመልከት።
ደስዮ ዮት ፡-(ደሰየ ይደሲ ይድሲ። ዕብ ዳሽ። ዐረ ዳሰ) መዳስ፤ መርገጥ መደፍጠጥ፤ ማበራየት፤ ኬደን እይ። ማስደሰት፤ ደስ ማሰኘት መጣድ ማስረር። ደስታ፤ ድስት ከዚህ ወጥቷል።
ደስጴዳ ፡-(ጽር ዳሲፑስ፤ ዳሲፖዳ) ጥንቸል የሽኮኮ ዐይነት ፡-(ዘሌ፲፩ ፡-፭። ዘዳ፲፬ ፡-፯)።
ደረመን ፡-ዕከክ ፎከት፤ ፈረሳቤት ፡-(ዐማርኛ)።
ደረት ፡-(ዐማርኛ) በቁሙ እንግድዓ። ደርግሐ ብሎ ደረተ ማለት ከዚህ ወጥቷል።
ደሪስ ሶት ፡-(ደረሰ ይደርስ ይድርስ። ዕብ ዳራሽ። ሱር ድራሽ። ዐረ ደረሰ) መድረስ በቁሙ፤ በጽሐንና ለጸቀን ተመልከት። ድርዳን መድረስ፤ እየደረሱ መጻፍ። ደረሱ በእንተ ዝ ወጸሐፉ። ደሪሰ ድርሳን። ዘደረሰ አባ ሕርያቀቆስ ፡-(ቄር። ስንክ ፡-ታኅ፰። ቅዳ)።
ደሪር ሮት ፡-(ደረ ደረረ ይደርር ይድርር) ማረት፤ እራት ማብላት መጋበዝ። መወዘም፤ ዋዜማ መቆም። የደረረ ምስጢር መደበኛው፤ ሰውን እንዳሞሌና እንደ ኵልኵል በሰደቃው ዙሪያ ሰድሮ ደርድሮ ማስቀመጥ ነው፤ ዶርን እይ።
ደሪብ ቦት ፡-(ደረበ ይደርብ ይድርብ። ከዐበ፤ ደበለ) መደረብ መደራረብ። ደርብ ደረባ ድርብ እንዲሉ ፡-(ዐማርኛ)።
ደሪክ ኮት ፡-(ደረከ ይደርክ ይድርክ። ዕብ ዳራኽ። ሱር ድራኽ፤ ኬደ ረገፀ) መጥናት መጠንከር፤ መድረቅ መሻከር፤ መክፋት መጨከን። ደረቅ ማለት ቅሉ ከዚህ ወጥቷል። ትፀወግ እምሕምዘ አፍዖት ወትደርክ እምተኵላ ፡-(መጽ ፡-ምስ)።
፡-መንደርከክ መብሰል፤ መቅላት፤ የፍሬ የፍሕም።
ደሪዞን ፡-(ጽር ዲዎርዞን) ንድቀ የግንብ ሥራ ፡-(ሕዝ፵፩ ፡-፲፪)። ጠቀመን እይ።
ደሪግ ጎት ፡-(ደረገ ይደርግ ይድርግ። ሱር ዳራግ) ማድረግ፤ ማደራጀት ደረጃ መሥራት፤ በደረጃ መውጣት፤ መግጠም ማዛወግ፤ አንድ ማድረግ። መጽሐፍ ግን በደረገ ፈንታ አድረገ ይላል፤ አያሰኝም። ኅቡረ ኢታድርግ። አድሪጎ በአልጓሚሁ ፡-(ሢራ፯ ፡-፰። ቄር)።
ደራሲ ፡-(ሲት ስያን ያት) የሚደርስ ደራሽ፤ ባለድርሳን፤ ተርጓሚ ስባኪ፤ ፍጹም ሊቅ። ጎርጎርዮስ በዓለ መንክራት ወደራሴ ቅዳስያት። ቤተ ደራስያን ፡-(አቡሻ ፡-፶። ስንክ ፡-ሚያ፳፩)።
ደራጎን ፡-የየብስና የባሕር ዘንዶ እግርና ክንፍ ዦሮና ቀንድ ያለው፤ ዐጓጕል ከኹሉ አለኹ የሚል። ምስጢሩ ድርገትና ባለድርጎነት ነው፤ ድሩግ እንደ ማለት ፡-(ገድ ፡-ጊዮ)።
ደርሰኔ ፡-(ዐረ ዳርሲን ኒ) የሽቱ ዛፍ ስም፤ ዕንጨቱ ብዙ ዐይነት ያለው፤ ቅመምና መድኀኒት የሚኾን፤ ቀናንሞን እይ። ምቱረ ልሳኖ ኀበ ህላዌሁ አግብአ ሶበ ደርሰኔ ወመዓረ ቀብዐ ፡-(ስንክ ፡-ጥር፭)።
ደርቀ ፡-(ትግ ገፋ ገፈተረ) ደረቀ ከረረ፤ ደረቅ ኾነ። ዘሩ ደረከ ነው ፡-(ዐማርኛ)።
ደርበየ ፡-(ተቀ ግ)። ዕብ ዳርቤን) ወረወረ፤ ወጋ መታ፤ ደራርቦ መላልሶ። ደርበያ ኵናቱ ውስተ አረፍት። ደርብዮ ኵያንው። ከመ ብእሲ ዘይደረቢ ኵናት ይወግዖ ለዘተፈነወ ኀቤሁ። ለደርብዮቱ። ይደረቢ በኵያንዊሁ ፡-(፩ነገ ፡-፲፱ ፡-፲። መቃ ፡-ገ፲፬። አፈ ፡-ተ፳፪። ስንክ ፡-ኅዳ፯። ሕዝ፳፮ ፡-፰)። አንደርቢ ማለት ከዚህ ወጥቷል። ዘረበን እይ፤ የዚህ ጎር ነው።
(ጥ) ደርዐ ፡-ተጠረረ፤ ጥሩር ለበሰ። ጨከነ፤ ታገሠ። ሰማዕት ረከቡ ተስፋሆሙ ደሪዖሙ ወተዐጊሦሙ ፡-(ድጓ)።
ደርከኖ :-ኀምራዊ፤–ደሪክ ደረከ።
ደርዝ ፡-(ዐማርኛ) ድርብ ስፌት እንደ መኪና ስፍ ያለ፤ ወይም የባብ ጥርስ የጥልፍና የጥራዝ ዐይነት።
ደርጉ ፡-(ብ ደራግው) ወረንጦ፤ መቈንጠጫና ማጣበቂያ። ሚደርጉ፤ ሚ ወረንጦው ሹሉ፤ ደርጉ መቈንጠጫው።
ደርግ ፡-አንድነት፤ አንድጋ፤ መጋጠሚያ። ሐውጹ ማኅበረነ ወባርኩነ በደርግ። በደርገ አንቀጸ ዐጸድ ፡-(ስንክ ፡-ታኅ፲፮። ዘፀ፴፯ ፡-፲፫)።
ደርግሐ ፡-(ተቀ ግ) ደረተ፤ ሰፋ ጠቀመ። ሠራ አማገ፤ ድርና ማጊን ኣዛወገ፤ አንድ አደረገ።
ደቀ መዝሙር ፡-(መዛሙርት) በቁሙ፤ ተማሪ ዳዊት ደጋሚ።
ደቀ ጽርሕ ፡-ዙፋን ጠባቆች፤ የልፍኝ አሽከሮች ፡-(ኢሳ ፡-፴፱ ፡-፯)።
ደቂቃ ፡-(ብ ደቃይቅ። ዐረ ደቂቀት) በቁሙ፤ ታናሽ የጊዜ ክፍል፤ የሰዓት ወይም የኬክሮስ ፰ኛ፤ ከሥልሳው አንዱ ክፍል ፡-(አቡሻ ፡-፶፬)።
ደቂቅ ፡-(ቅት ቃት። ደቃቅ ቃት) ቅጽልና ጥሬ። በቁሙ የደቀቀ ደቃቅ፤ አሸዋ እብቅ ዶቄት ውግጥ፤ የሚበን የሚተን የሚበተን። ዕጣን ዘቅታሬ ደቂቅ። ትገብር ደቃቀ። ጼው ደቃቅ ፡-(ዘፀ፴ ፡-፯። ኢሳ፴ ፡-፳፪። ስንክ ፡-ኅዳ፩)።
፡-ታናናሽ ጥቃቅን፤ ቀጫጫ ቀጫጭን። ክንፍ ደቃቅ። አስናኒሁ ደቃቅ ወበሊኃት ከመ አስናነ ከልብ። ይሣርር ዲበ ማይ ወየሐንጽ በደቃቅ። አንስሳ ዐበይት ምስለ ደቃቅ። አራዊት ደቃቅ። አብትር ደቃቅ፤ እለ ንቅዐቶሙ። እለ ይፌጽሙ ?ሕጻጺት ደቂቃት ኀጣውእ። አሕባለ ሥርው ፡-(ሱቱ ፡-ዕዝ፲፩ ፡-፬። ዮሴፍ። ቅዳ። መዝ ፡-፻፫። ስንክ የካ፭። ሄርማ። ቀሌ። መቃ ፡-ገ፳)።
፡-ልጅ ዕጓል፤ ሕፃን ደቦል፤ አሽከር ጕብል። ውስጠ ብዙነት ስላለው እንደ ሰብእ ላንድም ለብዙም ይኾናል። ወልድየ ዓዲሁ ደቂቅ። ደቂቅት ድንግል። ደቂቅ ድኩማን። አዳም ወደቂቁ።ወርእየ ኢዮብ ደቂቆ ወደቂቀ ደቂቁ ፡-(፩ዜና ፡-፳፪ ፡-፭። ፊልክ ፡-፶፰። ዘፍ፴፫ ፡-፲፫። አርጋ። ኢዮ፵፪ ፡-፲፮)።
፡-ሕዝብ ቤተ ሰብ፤ አሻክርት አርድእት ደቀ መዛሙርት፤ ምስጢሩ ታናሽነት ነው። ደቂቀ እስራኤል። ደቂቁ ለንጉሥ። ደቂቀ አቤሴሎም። ደቂቁ ለአቡነ ተክለ ሃይማኖት። ደቂቀ ነቢያት። ደቂቀ ጥበብ ፡-(ዘፀ፩ ፡-፩። አስቴ፪ ፡-፪። ፪ነገ ፡-፲፫ ፡-፳፱። ገድ ፡-ተክ። ፬ነገ ፡-፪ ፡-፫። ማቴ፲፩ ፡-፲፱)።
ደቂቅ ቆት ፡-(ደቀ፤ ደቀቀ ይደቅቅ ይድቅቅ። ዕብ ዳቃቅ) መድቀቅ መላም ዶቄት መኾን፤ መርቀቅ መቅጠን፤ ማነስ መኰሰስ ታናሽ መኾን። ደግደገን እይ፤ የዚህ ጎር ነው።
ደቂቅና ፡-ልጅነት፤ ታናሽነት። በደቂቅናሁ። ኢከልኣ ደቂቅናሃ ፡-(ፊልክ ፡-፴፭። ፶፬)።
ደቃውቅ ፡-(ቃት) ልጆች፤ ታናናሾች። ዕቀብ አንስቲያሆሙ ወትማሕፀን ደቃውቂሆሙ። ደቃውቃት ፡-(ቅዳ ፡-ያዕ። ኪዳ)።
ደቅ ፡-(ዝኒ ከማሁ) ልጆች አሽከሮች ወሸከሮች። አንስት ወደቅ። አምጽኡ ሎቱ ደቀ። ወረከበ ደቀ ንኡሳነ ፡-(ማቴ፲፬ ፡-፳፩። ፲፱ ፡-፲፫። ፬ነገ ፡-፪ ፡-፳፫)።
፡-ኀያላን ጐበዛዝት፤ ወጣቶች። ወጸውዐ ዳዊት አሐደ እምውስተ ደቁ ወይቤሎ ሑር ቅትሎ። ለይትነሥኡ ደቅነ። ደቀ ብንያም ወደቀ ዳዊት ፡-(፪ነገ ፡-፩ ፡-፲፭። ፪ ፡-፲፬ ፡-፲፭)።
፡-ስመ ሀገር፤ በጣና ውስጥ ያለ ታላቅ ደሴት። ስመ ልሕኵት፤ የደቅ ሰዎች የሚሠሩት ጥሩ ሸክላ። ፡-(ግጥም፤ ያጤ ቴ ገረድ ኰብልላ ደቅ ስትገባ ያያት አዝማሪ ላጤ ቴ ሲያወራ) እጇን ተሰብራ በሙሉ ፥ ኂሩት ደቃለች አሉ።
ደቅሐ ፡-ደቅሐ፤ ፡-(ቀድሐ) በቁሙ፤ ደቃ ደሰቀ መታ ቸነከረ፤ በሳ ነደለ ሰረሰረ፤ ጠገነ ዐደሰ፤ ባረከ መረቀ ቀደሰ። በመድቅሑ ደቅሖሙ ወበኀይለ መዝራዕቱ አጽንዖሙ ፡-(ኢሳ፵፬ ፡-፲፪)።
ደቅሶ ሶት ፡-(ደቀሰ ይዴቅስ ይደቅስ። ዐረ ዱከስ) ማንቀላፋት፤ በእንቅልፍ መያዝ መድቀስቀስ፤ እንደ ሬሳ መኾን። ደቀሰ ወኖመ። ደቀሱ ኖሎትኪ። ወኢይዴቅስ ዘየዐቅበከ ፡-(ግብ፳ ፡-፱። ናሖ፪ ፡-፲፰። መዝ ፡-፻፳)።
፡-መተኛት መጋደም፤ መጣመር። ደቀሱ ውስተ ምድር። ዘይዴቅስ ምስለ ብእሲቱ ወላዕሌሃ ትክቶ ፡-(አዋል ፡-ሲኖዶ)። መደቈስ መደቋቈስ፤ ገቢር። ወይም ዐጕል ተገብሮ፤ ፡-(ጥደ) መደቈስ፤ ተደቋሽ መኾን።
ደቅደቀ ፡-(ተቀ ግ) በቁሙ፤ ደቀደቀ ፡-(ዐማርኛ)።
ደበራ ፡-የብልግና ሥራ፤ ዝሙት ሴሰን፤ ቅንዝር ምንዝር።
ደበርቢር ፡-(ዐረ ዱብር፤ ዘባን ድኅር) ታናሽ ድንኳን አጐበር፤ ማረፊያ መጠጊያ፤ ወይም እንደ ወንበርና እንዳትሮንስ ያለ፤ ሲጠጉት ዠርባ የሚጐንጥ፤ የሚጐረብጥ፤ መነኮሳት በርሱ ላይ ዐርፈው ርሱን ተደግፈው እንቅልፋቸውን የሚያሳልፉበት። ይኑሙ እንዘ ኢይሰክቡ አላ ከመ እንተ አትራኖስ ዘንድቅ ይግበሩ ደበርቢረ ወቦቱ ይንጽፉ አልባሲሆሙ ወይስክቡ ንቡረ ፡-(ሥር ፡-ጳኵ)።
ደቡብ ፡-የማእዝን ስም፤ ዐቢይ ማእዝን የሰሜን ትይዩና አንጻር ፊት ለፊት በሊባና በአዜብ መካክል ያለ፤ የምዕራብ ቀኝ የምሥራቅ ግራ። ሰሜንን ተመልከት። ኵሉ ገጽ እምደቡብ እስከ ሰሜን ፡-(ሕዝ፳ ፡-፵፰)። ደቡብ የምሥራቅ ግራ እንደ ኾነ ሰሜንም የምዕራብ ግራ ነውና፤ በዚህ ምክንያት ተሳስቶ፤ በደቡብ ፈንታ ሰሜን በሰሜን ፈንታ ደቡብ እያለ በብዙ ቦታ ተጥፎ ይገኛል ፡-(ኢሳ፲፬ ፡-፲፫ ፡-፴፩። ፵፩ ፡-፳፭። ፵፱ ፡-፲፪)።
ደቢል ሎት ፡-(ደበለ ይደብል ይድብል) መደበል ማዳበል፤ መሸረብ መደረብ፤ የሐብል የፊደል። መሰካት ማሳካት፤ በፈትል ወይም ርስ በርሱ፤ የድባ የበለስ የዋንጫ።
፡-ማከብ መሰብሰብ ማከማቸት፤ የሸንጎ። መጽሐፍ ግን በደበለና በተደብለ ፈንታ አመድበለ መድበለ ይላል፤ የተሳሳተ ነው። ሰላም ሰላም ለእንድራኒቆስ እብሎ ውሒዘ መንፈስ ዘሰትየ ምስለ ሐዋርያት በአመድብሎ። በቍስጥንጥንያ ዘመድበሉ ፡-(ስንክ ፡-ግን፳፪። ጥር፲፭)።
ደቢር ሮት ፡-(ደበረ ይደብር ይድብር) መደበር መገደም፤ ደብር ገዳም መሥራት ማዘጋጀት፤ ለንግድ ዕቃም ሳይቀር ለታሪክ ለመጽሐፍ ይኾናል።
ደቢቅ ቆት ፡-(ደበቀ ይደብቅ ይድብቅ። ዕብ ዳባቅ፤ ለጠቀ ተጠጋ) መደበቅ መደባበቅ፤ መሸጐጥ ማስጠጋት ፡-(ዐማርኛ)።
ደቢብ ቦት ፡-(ደበቀ ይደብቅ ይድብቅ። ዕብ ዳባቅ፤ ለጠቀ ተጠጋ) መደበቅ መደባበቅ፤ መሸጐጥ ማስጠጋት ፡-(ዐማርኛ)።
ደቢው ዎ ት ፡-(ደበወ፤ ይደቡ ይድቡ። ደበየ፤ ዴፐ) ማድባት መሸመቅ፤ ቀስ ዝግ ማለት፤ መደበት መጫን መጨቈን መደቋቈስ፤ ያውሬ የጠላት የንቅልፍ።
ደባሪ መደብር ፡-ሠራዒ መጋቢ፤ ባለቤት። ዮሐንስ መደብር ዘውእቱ ሠራዒ ብሂል።
ደባዪ ፡-(ዪት ይያን ያት፤ በይት) ወራሪ ዘራፊ፤ ቀማኛ። ደባዬ አባግዕ ፡-(አዋል)።
ደብረወ ፡-(ተቀ ግ) ዳበረ አደገ ላቀ፤ ባለቀ፤ ለዘር በቃ፤ ባለ ማገጠ።
ደብራን ፡-(ዐረ እደበራን። ዕብ ክሲል) ጉቡኣን ከዋክብት ባንድነት የተደበሩ፤ በጐሽ ስም የሚጠሩ፤ ፈላስፎች ጐሽ የሚሏቸው እነኀምስቶ፤ ወይም ካምስቱ አንዱ ታላቁ በጣም የሚያበራው። ባለብሉዮች ዳተኛ ይሉታል። ወአስተጋብኦሙ ለደብራን። ርኢከኑ ፍኖቶ ለደብራን ወሙፃኦ ፡-(ኢዮ፱ ፡-፱። ፴፰ ፡-፴፩)።
ደብር ፡-(ብ አድባር፤ ራት) ተራራ፤ ጋራ ገመገም፤ የምድር ዕንብርት ጕብር ታላቅ ረዥም፤ ከወግር የሚበልጥ። ደብረ ሲና። ደብረ ዘይት። ደብረ ታቦር። አድባረ እስራኤል ፡-(ሕዝ፮ ፡-፪)።
የተራራ ተራራ፤ ከተራራ ኹሉ የሚበልጥ፤ በረዶ የሚፈላበት ሰው የማይደርስበት፤ እንደ ዳሸን እንደ ሄርሞን ያለ የሰማይ ጎረ ቤት። አድባረ አራራት። አድባር ነዋኃት ዘመትሕተ ሰማይ ፡-(ኩፋ ፡-፰። ዘፍ፯ ፡-፲፱። ፰ ፡-፬)።
፡-ወሰን ደንበር፤ መዲና ከተማ ታላቅ አገር። ወኮነ አድባሪሆሙ ለከነዓን እምነ ሲዶን እስከ ጌራራ። ደብረ አህጉር። ዲበ ኵሉ አድባሪከ አድባረ ግብጽ ፡-(ዘፍ፲ ፡-፲፬። ኢያ፲፬ ፡-፲፭። ዘፀ፲ ፡-፬–፲፬። ኢሳ፩ ፡-፳፮)።
፡-ገዳም ቤተ ክሲያን፤ ታላቁም ታናሹም። ደብረ ሊባኖስ። ደብረ ዐስቦ። አድባራት ወገዳማት። አባ መቃርስ ዘደብረ አስቄጥስ፤ መዳልወ አልባብ ተሰምየት እስከ ዮም ደብሩ ፡-(ገድ ፡-ተክ። ስንክ ፡-መጋ፳፯)። ደብር ማለት በተራራ ላይ የሚሠራ፤ተራራ የሚያኽል ታላቅ ማለት ነው፤ የምኵራብን ፍች ተመልከት። ፡-(ሙሾ ስለ ድምፀ መልካም ደብተራ) ካህን ሞተ ብሎ አይነግሩም ዐዋጅ፤ እንዲያው በየደብሩ መላክ ነበረ እንጅ።
ደብተረ ፡-ደበተረ፤ ዘረጋ ነጠለ፤ ወጠረ ገተረ፤ በደብተረ ፈንታ አደብተረ ይላል ፡-(ገድ ፡-አዳ)።
ደብተራ ፡-(ጽር ዲፍቴራ) የምሧዕ የሠረገላ ተድባብ፤ የመንበረ ታቦት አጐበር፤ በስተላይ እንደ ድባብ እንደ ጃን ጥላ ፥ እንደ ባጥና እንደ ጣራ ኹኖ የሚሠራ። ድንኳን መላጃን በዲፍቴራ አምሳል የተሠራ፤ እንደ ብራና የሚወጠርና የሚገተር፤ ቤተ መቅደስ። ጸሓፊ፤ ባለደብተር ባለብራና። ፡-(ተረት) አይጥፍ ደብተራ፤ ክንፍ የለው አሞራ። ተክለ አብራም ደብተራሁ።
መትሕተ ደብተራ ሠቅ። በውስተ ደብተራሁ ቅዱስ። ከመ ትትሐነጽ ደብተራሁ ፡-(ኩፋ ፡-፲፫። ፩ዜና ፡-፲፯ ፡-፩። ሢራ፳፬ ፡-፲። ጦቢ፲፫ ፡-፲)።
ደብተራት ደባትር ፡-ደብተሮች መዝገቦች፤ የሚጣፍባቸው፤ ወይም የሚጥፉ ጣፎች ባለደብተሮች። ድንኳኖች አጐበሮች። ኆኅተ ደባትሪሆሙ። ደባትር ዘነደ እሳት። ደብተራት ፡-(ዘፀ፴፫ ፡-፲። ቅዳ ፡-ሕር። መቃ ፡-ገ፩)።
ደብተራዊ ፡-ድንኳን ተካይ የድንኳን አገልጋይ፤ ባለድንኳን፤ ሌዋዊ ፡-(አፈ ተ፲፮)። መዘምርን ደብተራ ማለት ከሌዋውያን ስም የመጣ ነው።
ደብተር ፡-(ዕብ ዲፍታር። ዐረ ደፍተር) በቁሙ መጣፊያ መክተቢያ፤ የብራና የወረቀት መዝገብ፤ ነጋዶች ጠርዘው አፍፈው መጣፍ አስመስለው ለየጸሓፊው የሚሼጡት። የገንዘብ ቍጥር ዘወፅአ ዘገባ የሚጣፍበት። ደብተር ማለት ቃሉ የፋርስ ቋንቋ ነው ይባላል።
ደብይ ዮት ፡-(ደበየ ይደቢ ይድቢ። ደበወ) ማደባየት፤ ካፈር ከመሬት ከድቤ ላይ መጣል ማንከባለል፤ ደባ መሥራት፤ ሳይታሰቡ ወደ ሰው ቤት መግባት ዘው ጥልቅ ዠቅ ማለት፤ መውረር መዝረፍ፤ መቀማት መመንተፍ። ደበዩኒ እለ አልቦሙ ምሕረት። ሮዱኒ ወደበዩኒ። ይደቢ አብያተ ሰብእ። ከመ ኢይድብያ ለቤተ ክርስቲያን ፡-(ኢዮ፴ ፡-፳፩። መዝ ፡-፴፯። ግብ፰ ፡-፫። መጽ ፡-ምስ)።
ደብደበ ፡-(ደበ። ዐረ ፡-ዘበ፤ ዘብዘበ) ፈራ ዐሰበ ተጨነቀ፤ የሚመጣበትን ስላወቀ። የሐዝን ወይደበድብ ፡-(ፊልክ ፡-፻፷፭። ቀሌ)።
፡-ፈዘዘ፤ ተነፋ ፥ ዱባ መሰለ፤ የሆድ የሰውነት አብዝቶ ከመብላት የተነሣ። ወሶበ ይነቅህ ኢይደበድብ ነፍስቱ ፡-(ሢራ፴፬ ፡-፳)።
፡-በቁሙ፤ ደበደበ መላልሶ መታ ቀጠቀጠ፤ ደብዳቢ እንዲሉ። አረገዝ ድብድብ ኾነ፤ የሰብል፤ ምስጢሩ ማበጥ መንዘርጠጥ ነውና ተነፋ ካለው ይገባል።
ደነሳዊ ፡-(ዊት ውያን ያት) ዘማዊ ሴሰኛ፤ ያመንዝሮች ሲሳይ። ይትወደዩ ውስተ ኵነኔ ደነሳውያን በርኵሰ ዝሙት ፡-(ፍ ፡-ነ ፡-፳፬ ፡-፭)።
ደነስ ፡-(ሳት) እድፍ አደፍ ትክቶ፤ ዝሙት ኀጢአት፤ የዝሙት ሥራ ምኞት፤ ዐስበ ዝሙት። መዋዕለ ደነስ። አኮ በፍትወተ ደነስ ዘተፀነስኪ። አንጽሐነ እምኵሉ ደነስ ወእምኵሉ ርኵስ። ያነጽሕ ልቦ እምደነሳት ፡-(አዋል። ቅዳ። ፊልክ ፡-፻፷፩)። ሀበኒ ደነስየ። ደነሰ ዘማ። ደነሰ ዝሙት፤ዋጋ ፡-(ኩፋ ፡-፵፩። ዘዳ፳፫ ፡-፲፱። ሚክ፩ ፡-፯)።
ደነክ ፡-ዝልዝል ትልትል፤ ቋንጣ ያልጋ ጠፍር።
ደነፈ ፡-(ትግ ደንፈ) ወውዐ፤ ደነፋ ፈከረ፤ ተንደቀደቀ ፡-(ዐማርኛ)።
ደኒቅ ቆት ፡-(ደነቀ ይደንቅ ይድንቅ። ደደቀ) መድነቅ መደነቅ፤ ድንቅ መኾን፤ መደንገት። ደደቀና ወገበን እይ።
ደኒን ኖት ፡-(ደነ ደነነ ይደንን ይድንን። ዐረ ደኒነ) መድነን መጐንበስ፤ ራስን መቀለስ፤ ዐንገትን መድፋት መስበር፤ ማቀርቀር። እድንን ወእፍታሕ። ደነነ ሥዕል ከመ ኦሆ ዘይብል። ትደንኑ ወትሰግዱ ሎቱ። ድንኒ ወንትዐዶኪ ፡-(ማር፩ ፡-፯። ድጓ። ኢሳ፵፮ ፡-፯። ፶፩ ፡-፳፫)።
፡-መጕበጥ መታጠፍ፤ በጭራሽ እንደ ደጋን መኾን፤ የደዌ የርግና። ኮነ ነዊኀ በቆሙ አላ ውእቱ ይደንን በእንተ ርሥእናሁ ፡-(ስንክ ፡-ግን፲፫)።
ደኒክ ኮት ፡-(ደነከ ይደንክ ይድንክ) መዘልዘል መተልተል፤ የሥጋ የቈርበት።
ደኒዝ ዞት ፡-(ደንዘ ደነዘ ይደንዝ ይድንዝ። ፀሪስ ፀርሰ) መደነዝ መጥረስ፤ ደነዝ መኾን፤ የስለት። ደንገዘንና ደንጐዘን እይ፤ የዚህ ስሯጽ ነው። ደንዘ ያማርኛ፤ ፀርሰ የግእዝ።
ደኒጽ ጾት ፡-(ደነጸ ይደንጽ ይድንጽ) አጥብቆ መያዝ መጨበጥ መቀየም፤ የጠላት የገንዘብ።
ደናግል ፡-ድንግሎች ደናግሎች፤ የወንድ የሴት፤ ጐበዛዝት ቈነዣዥት ያልተዳሰሱ። ደናግል ወመነኮሳት። በእንተ ደናግል ዕደው። ደናግል ንጹሓን፤ ወንዶች ፡-(ቅዳ። ስንክ ፡-ጥቅ፲፮። አርጋ ፡-፭)። ደናግል አለፍቀራከ። አዋልድ ደናግል። ወራዙትኒ ወደናግል። ዐሥሮን ደናግል ፡-(ማሕ፩ ፡-፫። መሳ፳፩ ፡-፲፪። መዝ ፡-፻፵፰። ማቴ፳፭ ፡-፩)።
ደን ፡-(ጥ) ደን ፡-(ዐማርኛ) በቁሙ፤ ዱር ጫካ ብዙ ዛፍ ዛፋም፤ የዛፍ ቦታ። ደን ጠባቂ የደን ሹም እንዲሉ፤ ሊባኖስን እይ።
ደንሶ ሶት ፡-(ደነሰ ይዴንስ ይደንስ። ዐረ ደኒሰ) ማደፍ መርከስ። ማሳደፍ ማርከስ፤ ማባበል መለመን፤ ዐስበ ዝሙት መስጠት። እስመ ደነሱኪ ወኢደነሱኪ ፡-(ሕዝ ፡-፲፮ ፡-፴፬)። በደንሰ ፈንታ ተደነሰ ይላል፤ አያስኝም። ይረኵሱ ባቲ ወይዴነሱ። እመ ቦ ዘአበሰ ወተደነሰ በዛቲ ኀጢአት። እመሂ በቃል አበሱ ወእመሂ በገቢር ረኵሱ፤ ወእመሂ በክሡት ተደነሱ ፡-(አፈ ፡-ድ፴፩። ፈ ፡-መ ፡-፭ ፡-፪። ግንዘ)።
ደንቀወ ፡-(ተቀ ግ) ደነቈረ፤ ተደፈነ አልሰማ አለ፤ የዦሮ። ኦ ዘአሜሃ ትውልድ ደንቀዋ እዝዚሆሙ ከመ ኢይስምዕዎ ፡-(ቅዳ ፡-ግሩ)። ደነቀረ በግድ አገባ፤ ቀረቀረ ፡-(ዐማርኛ)።
ደንቃዊ ድንቅው ፡-(356) የደነቈረ ደንቈሮ የማይሰማ። ወይም መካከለኛ ጥቂት ጥቂት የሚሰማ። ነፍሳት ደንቃውያት። ኦ ድንቅው፤ ድንቅዋነ እዝን ፡-(ቄር ፡-ጰላ። መጽ ፡-ምስ)።
ደንበር ፡-(ትግ፤ ክንፍ ላባ ቍንጮ) በቁሙ፤ ወሰን ዳርቻ ጽንፍ፤ ጫፍ ፡-(ዐማርኛ)። ደነበረ ተደናበረ ደንባራ ማለት ከዚህ ወጥቷል።
ደንዘዘ ፡-(ተቀ ግ) በቁሙ፤ ፈዘዘ ዳተኛ ቸልተኛ ኾነ።
ደንደስ ፡-(ዐማርኛ) በቁሙ፤ ጫንቃ ትከሻ፤ ደንደሳም እንዲሉ።
ደንደር ፡-(ዕብ ዳርዳር) እሾኻም ቅጠል፤ የሱፍና የኰሸሽላ ዐይነት፤ ኹለንተናው እሾኽ ስለ ኾነ ሊያዝ ሲጨበጥ የማይቻል። በቁሙ ደንደሮ እሾኽ ጋሬጣ፤ ወይም በደንደር አምሳል የሚሠራ የስልክና የብረት እሾኽ፤ የዱሮ ሰዎች እግረኛ ፈረሰኛ ጠላት በሚመጣበት መንገድ ወጥመድ አድርገው የሚቀብሩት የሚሰውሩት፤ አውሬ የሚያጠምዱበት። ይቤ እንጦንዮስ፤ አንሰ ርኢኩ ኵሎ መሣግረ ሰይጣን ትክልተ ዲበ ምድር .... በከመ ተጽሕፈ እስመ ኀብኡ ሊተ በውስተ ፍኖተ ምሕዋርየ መሣግረ ወአሕባለ። ወሶበ ርእየ አንከረ እምብዝኀ አሥዋክ ወደንደር እንተ ቍጽርት ውስቴታ፤ ወአራዊት እንተ ትወድቅ ፡-(ፊልክ ፡-፻፲፮)።
ደንደነ ፡-(ተቀ ግ) በቁሙ፤ ወፈረ ገዘፈ ዛፉ፤ ለሰውም ይኾናል። ደንዳና ከዚህ ወጥቷል።
ደንዳና ፡-(ዕብ ዳንዳና) የቅጠል ስም፤ አንድ ዐይነት ቅጠል ጥሩ ሽታ ያለው መድኀኒት የሚኾን። በቁሙ ወፍራም ግዙፍ ፡-(ዐማርኛ)። ደኒን ደነ ደንደነ።
ደንገለ ፡-(ዐረ ደገለ፤ ሸሸገ ደበቀ) ደነገለ፤ አጥብቆ ጠበቀ፤ ከለከለ ከሴት አራቀ ራሱን ወይም ሌላውን። የደንጐላ ምስጢር አብቦ አለማፍራት ነውና፤ ደንገለም የደንጐላ ዘር ስለ ኾነ ይህን ያሳያል። እምአይቴ ረከብከ ዘከመ ዝ ብሥራተ፤ እንበለ ዘርዕ እምድር እትወተ ወእንበለ ምት እም ድንግል ፅንሰተ ፡-(ድጓ)።
ደንገዘ ፡-(ደነዘ፤ ደንዘዘ) አረጀ ደከመ፤ መሸ ጨለመ ፡-(ዐማርኛ)።
ደንገገ ፡-(ደገገ፤ ደግደገ) ደነገገ፤ ወሰነ ዐገገ፤ ገደበ ወደበ፤ የሕግ የፈለግ።
ደንገፀ ጸ ፡-(ደጐጸ ደነጸ) ደነገጠ ፈራ ተንቀጠቀጠ። ምስጢሩ፤ ልብን በፍርሀት መድጐጽ መነካት ነው፤ ከማየት ከመስማት የተነሣ። ኵሉ ነፍስ ይደነግፅ። ደንገፀኒ ነፍስየ። ይደነግፅ ልብኪ። ደንገፁ በበይነ ዘኮነ ፡-(ኢሳ፲፫ ፡-፯። ፳፩ ፡-፬። ፷ ፡-፭። ዮዲ፲፭ ፡-፩)።
፡-ጮኸ አስተጋባ፤ ተሠነጠቀ፤ የምድር የተራራ። ደንገፀት ምድር እምቃሎሙ። ወይደነግፁ አድባር ነዋኃት ፡-(፫ነገ ፡-፩ ፡-፵። ፩ነገ ፡-፬ ፡-፭። ሔኖ፩ ፡-፮)።
ደንጐላ ፡-(ላት። ዕብ ሐባጼሌት) የዱር የበረሓ ሽንኵርት፤ በቈላ በደጋ የሚበቅል የዥብ ሽንኵርት ዐይነት መልካም አበባ የሚሰጥ፤ አበባው መረዋ ቃጭል የሚመስል፤ ጥሩ ሽታ ያለው። ጽጌ ደንጐላት ዘውስተ ቈላት። ወከመ ጽጌ ደንጐላት በማእከለ አሥዋክ ፡-(ማሕ፪ ፡-፩ ፡-፪)። ባለብሉዮች ግን ማእከለ አሥዋክን ሲያዩ ሱፍ ይሉታል፤ ፍችው አይዶለም።
ደንጐዘ ፡-ሠራ ቈነነ፤ ጐቸ ጐነጐነ፤ ከፈለ ፈተለ ቈነጣጠረ።
ደንጸወ ፡-(ተቀ ግ) ነፈገ ቤስ፤ ሣሣ ቈጠበ፤ ጨባጭ ኾነ፤ ቀና ተመቀኘ። ኢትደንጹ ዐይንከ ሶበ ትገብር ምጽዋተ። ጸጋዊ ዘእንበለ ደንጽዎ። ይደነጹ ባቲ ላዕለ ነዳያን። ይደነጹ በውስተ ማእድ። ትደነጹ ዐይኑ በእኁሁ ፡-(ጦቢ፬ ፡-፯። ቅዳ ፡-ኤጲ። ፍ ፡-ነ ፡-፲። ሢራ፲፬ ፡-፲። ዘዳ፳፰ ፡-፶፬ ፡-፶፮)።
ደንጻዊ ድንጽው ፡-ንፉግ ጨባጭ፤ ሥሡ ሥሥታም ፡-(ሢራ፲፰ ፡-፲፰። ፳፭ ፡-፪)። ለደንጻዊ ደረግምዎ በእከየ ግዕዙ። ኢትትማከር ምስለ ደንጻዊ እንበይነ ውሂበ ምጽዋት ፡-(፴፬ ፡-፳፫። ፴፯ ፡-፲፩)። ድንቅው በማለት ፈንታ ድንጽው ይላል፤ ስሕተት ነው። ኢትኩኑ ድንጽዋነ ወድንዙዛነ ልብ ለአሚን ፡-(መቃ ፡-ገ፲፰)።
ደንጽ ፡-ቂም በቀል ትግል፤ ጠብ ክርክር ፍጅት። ምንት ውእቱ ዝ ደንጽ። በደንጽ ሀለዉ አሐዱ ለአሐዱ ይትቃተሉ። ደንጽ ዘበኅዳጥ ፡-(ዕር ፡-ኢሳ፯ ፡-፲፩። ፲ ፡-፳፬)።
ደዐት ፡-ማወቅ መታወቅ፤ ዕውቀት አነጋገር፤ ንግግር።
ደኵስበተሪ ፡-(ጽር ፡-ዶክሳ ፡-ፓቴሪ) ስብሐት ለአብ ማለት ነው። ኦርቶዶክስን እይ። ወትብል ደኵስበተሪ አርባዕተ ጊዜ ፡-(ግንዘ)።
ደኵዐ ፡-(ይደኵዕ ይድኳዕ፤ ደኩዕ) ወደቀ ተጣለ ተረሳ።
ደኪም ሞት ፡-(ደክመ ይደክም ይድክም) መድከም መታከት፤ መዛል መስነፍ መላም መለስለስ፤ ማነስ መኰሰስ። እገሪከ ይረውጻ ወይደክማከ። ወደኪሞ በሐዊረ ፍኖት ነበረ። ደክመት ነፍስየ ፡-(ኤር፲፪ ፡-፭። ዮሐ፬ ፡-፮። ሱቱ ፡-ዕዝ፲፪ ፡-፰)።
፡-መፍዘዝ፤ መስለል፤ የዐይን የቃል፤ ማርጀት መታመም፤ ምስጢሩ ያው ድካም ነው። ደክማ አዕይንትየ በአንብዕ። ቃለ ወለተ ጽዮን ደክመ። ኢደክመት እምኀይላ። ደክመ አቡከ። ዘእንበለ ትድክም ፡-(ስቈ፪ ፡-፲፩። ኤር፬ ፡-፴፩። ኩፋ ፡-፴፭። ዘፍ፵፰ ፡-፩። ሢራ፲፰ ፡-፳፩)። ደክተመን እይ፤ የዚህ ስሯጽ ነው።
ደክተመ ፡-(ደክመ፤ ተ ፡-ስሯጽ። ዕብ ፡-ያቴም) ደኸየ፤ የሙት ልጅ ኾነ። አባት እናት ዐጣ። ድኻ ማለት ቅሉ ከዚህ ወጥቷል፤ ዕብራይስጥም ድኻ ሲል ዳኽ ይላል። ደክተመት ቤተ ክርስቲያን። ለእለ ተርፉ ድኅሬሁ ርድኦሙ፤ ወለእለሂ ደክተሙ ሕፅኖሙ ፡-(አቡሻ ፡-፶። ግንዘ)።
ደክታም ፡-(ብ ደካትም) ድኻ አደግ፤ ድኻ የሙት ልጅ። እፎ ኢይፈደፍድ ሐዘንየ እንዘ እኔጽር አንስቲያሆሙ ከዊኖን ደክታመ ወውሉዶሙ ዕጓለ ማውታ። ደክታም ነፍስየ እምእማ ወአባ። ንዋየ ደካትም ፡-(ዮሴፍ። ስንክ ፡-ታኅ፳፬። ፍ ፡-ነ ፡-፴፫ ፡-፬)።
ደወል [1]፡-(ብ አድዋል) ዙሪያ ዳርቻ ጫፍ፤ ወሰን ደንበር፤ ቀበሌ አውራጃ። ኢታፍልስ ደወለ ገራህት ዘአንበሩ አበው። ኵሉ ደወሉ ዘዐውዱ። ደወለ ጢሮስ። ደወለ ፋርስ። ተጋብኡ እምአድዋለ ብሔሮሙ ፡-(ምሳ፳፫ ፡-፲። ሕዝ፵፭ ፡-፩። ዘካ፱ ፡-፪። ኢሳ፯ ፡-፲፰። ነሐ፲፪ ፡-፳፰)።
[2]፡-ደወል ፡-(ላት) በቁሙ፤ መጥቅ መረዋ ቃጭል፤ የደንጊያ የንጨት የብረት፤ ሲደወል በዙሪያው ባውራጃው የሚሰማ። ከመ ድምፀ ብርት ዘይነቁ ባለው ደወል እንዲል ፡-(፩ቆሮ ፡-፲፫ ፡-፩)።
ደዊል ሎት ፡-ደዊል፤ ሎት፤ ፡-(ዶለ፤ ደወለ፤ ይደውል ይዱል። ዕብ ዳዌል፤ አኮበ ደወረ ጠመጠመ፤ የፈትል) መወሰን መከለል፤ የቦታ። መደወል፤ ማቃጨል። መዶል ማግባት፤ መክተት። ዱላ ዳውላ ዶልዷላ ዱለት ማለት የዚህ ዘር ነው።
ደዊር ሮት ፡-(ዶረ ይደውር ይዱር። ዕብ ዳር) መማገድ መረብረብ፤ ማንደድ መቈስቈስ፤ እሳት መለኰስ።
ደዋ ፡-(ትግ ወዐረ) መድኀኒት የሚያም የሚገድል ደዌ የሚኾን፤ ወይም የሚያድን።
ደዌ ፡-(ያት) በቁሙ በሽታ ሕማም የቈየ የዘገየ ዐብሮ የሚኖር፤ ወይም ዐልፎ ኻያጅ፤ ኀጢአት ፍትወት፤ ደዌ ነፍስ። ደዌ መሪር ወእኩይ ደዌ ከርሥ። ለእመ አሐዩ እምዛቲ ደዌ። ሐይወ እምደዌሁ። ደዌ ሲሕ። ነበረት ይእቲ ደዌ ውስተ ልብ ፡-(፪ዜና ፡-፩ ፡-፲፭። ፬ነገ ፡-፩ ፡-፪። ኢሳ፴፰ ፡-፱። ሢራ፴ ፡-፲፯። ሱቱ ፡-ዕዝ፩ ፡-፳፪)።
ደውርሀ ፡-(ይደወርህ ይደውርህ ፥ ደውርሆ፤ አው ዶርሀወ ይዶርሁ ፥ ዶርህዎ፤ ተቀ ፡-ግ) በዛ ተባዛ፤ ረባ ተንሻሻ።
ደውይ ዮት ፡-(ደወየ ይደዊ ይድወይ። ዐረ ደዊየ። ዕብ ዳዋህ። ሱር ድዊይ) መደወይ መታመም መበሸት፤ ድውይ መኾን ጤና ማጣት፤ በደዌ ዳኛ ባልጋ ቍራኛ መያዝ። እመሂ ደወየ ኢይሴፎ ሐዪወ። ደወዩ ከመ አባግዕ። ደወየ ልብነ። ደወይኩ ወሐወጽክሙኒ ፡-(ኢዮ፳፬ ፡-፳፫። ዘካ፲ ፡-፪። ሰቈ፭ ፡-፲፯። ማቴ፳፭ ፡-፴፯)።
ደያኒ መደይን ፡-የሚዳኝ ዳኛ፤ ፈራጅ ቀጭ። ደያኔ ጽድቅ ፡-(ፊልክ ፡-፻፷፬)።
ደይቦ ቦት ፡-(ደየበ ይዴይብ ይደይብ። ትግሬ) ማረግ ወደ ላይ መውጣት፤ ከፍ ከፍ ማለት፤ በላይ መኾን። መመደብ፤ መደብ ዕርከን መሥራት። ዐርገንና ለዐለን እይ፤ የዚህ አግዋር ናቸው።
ደይን ፡-(ናት) ቍርጥ ፍርድ፤ የማይላጥ የማይለወጥ፤ የማይመለስ ቃል፤ ንዑ ኀቤየ ሑሩ እምኔየ፤ ይህን የመሰለ። ኢትግበር ዘንተ ደይነ። ትንሣኤ ዘለደይን ዕለተ ደይን ፡-(ዘፍ፲፰ ፡-፳፭። ዮሐ፭ ፡-፳፱። ማቴ፲ ፡-፲፭)።
፡-ፍጹም ቅጣት፤ መከራ ሥቃይ፤ የሥቃይ ቦታ። መካነ ደይን። ጢሰ ደይኖሙ። ዐዘቅተ ደይን። ይጼዐሩ ውስተ ደይን። አንቀጸ ደይን ፡-(ኩፋ ፡-፯። ራእ፲፬ ፡-፲፩። ሱቱ ፡-ዕዝ፮ ፡-፩ ፡-፱። አርጋ ፡-፬)። ዲን ድኝ ማለት ፥ ደይን ከማለት ወጥቷል፤ ክብሪትን እይ።
ደይኖ ኖት ፡-(ደየነ ይዴይን ይደይን፤ ዳነየ። ዕብ ወሱር ዳን። ዐረ ዳነ) መዳኘት፤ መፍረድ መቅጣት፤ መገሠጽ መቈጣት። ወይዴይኖሙ በዐቢይ ፡-(ሱቱ ፡-ዕዝ፲፫ ፡-፵፩)።
ደደክ ፡-(ደገ፤ ደግደገ) ደጋ ጮቄ፤ ጉማም ብርዳም፤ ውርጫም፤ ነፋሳም። ወምድረ ሴምሰ ኢመርቄ ወኢደደክ። ይባርክዎ ደደክ ወመርቄ። ገነት ዘኢያየብሳ ነፋሰ መርቄ ወደደክ ፡-(ኩፋ ፡-፰። ዳን፫ ፡-፵፰። ስንክ ፡-ጥቅ፳፩)።
፡-ቀቅ፤ ቈሪር ነፋስ፤ በደጋ የሚወርድ የብርድ ዐይነት ኹሉ። አስሐትያ ወቍር ወሐመዳ ወደደክ። ዘየዐርግ እምኔሁ ከመ ጢስ ውአቱ፤ ወስሙ ደደክ ፡-(ሔኖ፸፮ ፡-፲፪። ፰ ፡-፲፰)።
ደዲቅ ቆት ፡-(ደደቀ ይደድቅ ይደድቅ። ወድቀ፤ ወገበ) መደንገት፤ ድንገት መኾን መደረግ፤ የሥራ። ሳይታሰቡ መድረስ መምጣት፤ ከተፍ ማለት፤ በድንገት ማግኘት መገኘት፤ ግጭት መግጠም። ደደቀ በውእቱ አዝማን ባእስ ማእከለ አይሁድ ወማእከለ አርማንያ። እመ ደደቀ ብጽሐተ ነግድ። እመ ቦ ካህን ዘደደቆ በንዋም ዝንየት ፣ ጽኑዐ ልብ ኢይደድቅ ሠናየ። ወደደቆ ለአብ መምህረ ፡-(ዮሴፍ። ፊልክ ፡-፸፬። ቄድር። ምሳ፲፯። ተረ ፡-ቄር)።
፡-መደደቅ መውጋት፤ መደንጐር፤ መፈንቀል መገልበጥ፤ መቈፈር መመንቀር ፡-(ዐማርኛ)። አንዳንድ መጽሐፍ ግን በደደቀ ፈንታ ተዳደቀ ይላል፤ አያሰኝም። እንተ ኢኀለይኩ ተዳደቀተእኒ። በከመ ይዳደቆ ለአብድ ከማሁ ሊተኒ ይዳደቀኒ። ለአብዳን ይዳደቆሙ ሞት። አልቦ ዘይዳደቃ። ወተዳደቆ አሐዱ ካህን። ከመ ይዳደቅዋ ለሀገር ፡-(ኢዮ፫ ፡-፳፭። መክ፪ ፡-፲፭። ምሳ፳፬ ፡-፰። ጥበ፯ ፡-፳፭። ሉቃ፲ ፡-፴፩። ዮሴፍ)።
ደጊም ሞት ፡-(ደገመ ይደግም ይድግም) መድገም መደጋገም፤ ቀድሞ የሠሩትን ፪ኛ መሥራት። ገሥጾ ለዐርክከ ዮጊ ኢገብረ ወእመኒ ገብረ ከመ ኢይድግም። ለእመ ቦ ዘአበስከ ኢትድግም። ደገሙ ዓዲ ወአበሱ። ኢይደግሙ አበሳ ፡-(ሢራ፲፱ ፡-፲፫።፳፩ ፡-፩። መዝ ፡-፸፯። ሔኖ፭ ፡-፰)።
፡-ማንበብ፤ ማነብነብ መጸለይ መድገም፤ መናገር መለፍለፍ።ነሥአ መጻሕፍተ አበዊሁ ወደገሞን። ወትደግም ምእተ ወኀምሳ መዝሙረ ዳዊት። ኢይደግሙ ነገረ በዲበ ነገርየ ፡-(ኩፉ ፡-፲፪። ግንዘ። ኢዮ፳፱ ፡-፳፪)።
ደጕስ ፡-(ትግሬ) ዳጕሳ፤ የድግስ እኸል፤ የጤፍ ዐይነት፤ ዐረቂና ጠላ እንጀራ የሚኾን።
ደጕር ሮት ፡-(ደጐረ ይደጕር ይድጕር። ዕብ ዳጋር) ማሞቅ መታቀፍ፤ ማመስ መቀፍቀፍ፤ የንቍላል። መዘርጋት ማርገብገብ፤ የክንፍ፤ ለመብረር። ኹሉም የወፍ ሥራ ነው። መለካት ከልክ ማግባት፤ መስፈር መመዘን ማስተካከል።
ደጕር ፤ ድጕር ፤ (ዐረ ደጅር) ፤ ድግር ፤ የሞፈር ክንፍ በግራና በቀኝ የሚቀጠል ፤ ሰረረን እይ። በአንጻረ ድጕር
ዕርፈ ወበአንጻረ ዕርፍ ድጕረ። አርዑተ ብዕራ ወጸሪበ
ድጕር (ኩፉ ፲፩። አዋል)። ደንጐራ አዳጕራ ማለት ከዚህ ወጥቷል።
ደጕዓሌ ደጓዕሌ ፡-(ዕብ ዴቄል። ሱር ዴቅላ። ዐረ ደቀል) የሰሌን ዐይነት ዛፍ ተምር፤ ግንዱ ቁመቱ የበቀልት፤ ቅጠሉ ሌላ ዐይነት፤ እንደ ውስጥ እጅና እንደ ጣት ያለ፤ ዲቃላ ማለት ከዚህ ወጥቷል።
፡-ሰሌን የሰሌን ቅጠል ዘንባባውና ዝንጣፊው፤ ፀመርቱ ሙሽራው፤ የተሠራ ወይም ያልተሠራ። ወአንበረ በውሳጢታ ታቦት አንጦሊዖ ደጕዓሌ። ነጸፈ ውስተ ግብ ቈጽለ ደጕዓሌ። ነሥአ ኅዳጠ ደጓዕሌ ወሠጠቆ ወበዕለት ካልእ አርሐቦ። ፅፍረት ዘደጓዕሌ። ፀፊረ ደጓዕሌ ፡-(ገድ ፡-ተክ። ገድ ፡-ዮሐ። ፊልክ ፡-፵፰። ፻፫። ስንክ ፡-ኅዳ፲፮)።
ደጊግ ጎት ፡-(ደገ ይደግግ ይድግግ። ዕብ ዳጋህ፤ በዛ ረባ) መደገግ መኵራት፤ ማደግ መመንደግ፤ ደግ ደገኛ፤ ታላቅ ምጡቅ መኾን። ደጋ ፡-(ማድጋ) ደደክ ማለት ከዚህ ወጥቷል፤ አዳጋ ቍሊልታ ተራራ ኰረብታ ከፍ ያለ ቦታ ማለት ነው፤ ልዕልናውን መደብ አድርጎ ደግነቱን ጤናማነቱን ያሳያል። ደንገገን ተመልከት፤ የዚህ ስሯጽ ነው። በጋልኛም ዝኆንን ደጋጋ ማለት ከዚህ የወጣ ነው፤ ነጌን እይ።
ደጕጽ ጾት ፡-(ደጐጸ ይደጕጽ ይድጕጽ። ዕብ ዳጋሽ፤ አጠበቀ፤ የማጥበቅ ምልክት አደረገ፤ የፊደል) መውጋት መጠቈም ጠቅ ማድረግ፤ መጓጐጥ መንካት መጐነጥ፤ መጐሰም መደሰቅ፤ መምታት። መጐጸን እይ የዚህ መንቲያ ነው። አሜከላ ለእመ አኀዝኮ በእዴከ ይደጕጽ። አሕጻከ ደጐጻኒ። ዘደጐጸ ዐይኖ ያወርድ አንብዐ። ዘይደጕጸኒ ሥጋየ። ደጐጸ እንግድዓሁ። ወገረ አሐዱ እምኔሆሙ አሐደ ዐጽቀ ወደጐጸ ገጸ ንጉሥ ፡-(አፈ ፡-ድ፲። መዝ ፡-፴፯። ሢራ፳፪ ፡-፲፱። ፪ቆሮ ፡-፲፪ ፡-፯። ገድ ፡- ተክ። ዮሴፍ)።
፡-መደጐስ፤ መደገስ ማስናዳት፤ ማሥመር ማሳመር፤ ማሰንበር፤ ማስመጥ ማሳበጥ፤ መሸለም ማስጌጥ፤ መልክ ማውጣት፤ ያንቀልባ የብራና፤ ገለደን እይ።
፡-መዳጐስ፤ ደጓሳ መኾን፤ ወይም ማድረግ። ምስጢሩ ማሳበጥ ካለው ይገባል። ደንገፀን ተመልከት፤ የዚህ ዲቃላ ነው።
ደጊፍ ፎት ፡-(ደገፈ ይደግፍ ይድግፍ። ትግ ደግፈ) መደገፍ መደጋገፍ፤ ማጽናት ማበርታት፤ እንዳይወድቅ ማድረግ፤ አይዞኽ ማለት። ገደፈ ማለት ከዚህ ወጥቷል፤ የዚህ ግልባጭ ነው። ሶቀንና ዐመደን ተመልከት፤ ደገፈ ያማርኛና የትግሬ ነው። አንዳንድ ሰዎች ግን ብርዕ ሲሉ ብዕር እንደሚሉት፤ ደገፈ ሲሉ ገደፈ ይላሉ፤ ኹሉም ስሕተት ነው።
ደጋሚ ፡-(ሚት ምያን ያት) በቁሙ፤ የሚደግም፤ የሚያነብ አንባቢ። ዳዊት ደጋሚ እንዲሉ።
ደጋን ፡-በቁሙ፤–ዴግኖ ዴገነ።
ደግደገ ፡-(ዲቃ ግ። ዕብ ዳግዴግ፤ ነካ ዳሰሰ) ከሳ ቀጠነ፤ ደቀቀ ረቀቀ ሣሣ። ማለደ ገሠገሠ፤ ማለዳ ተነሣ፤ ታጠቀ ተጣጠቀ፤ ለበሰ ተላበሰ አደገደገ።
ደግደግ ደግዲግ ፡-ጎሕ ነግህ ጧት ማለዳ፤ ነገታ ሳኒታ ማግስት። እፎ ወድቀ እምሰማይ ኮከበ ጽባሕ ዘቢደግዲግ ይሠርቅ። ወኢታትርፉ እምኔሁ ለደግደግ ፡-(ተረ ፡-ቄር፯። ዘፀ፲፪ ፡-፲)።
ደጐብያ ፡-(ዕብ ጎባይ። ዐረ ጃቢእ) ደጐባ፤ አንበጣ፤ ያነበጣ ወገን ኵብኵባ ፌንጣ፤ ሌላውም ኹሉ፤ አናኵዕን እይ። ለሰው ሲኾን ጐበዝ ወጣት ሦታ ደቦል ፥ ረድ ማለት ነው፤ መሓዝን ተመ ፡-(ዮኤ፩ ፡-፬። ፪ ፡-፳፭። ናሖ፫ ፡-፲፭ ፡-፲፮)። እመ ቦ ዘበልዐ አንበጣ ወደጐብያ አው ገመለ ፡-(ቀሌ)።
ደጓጺ ፡-(ጺት ጽያን ያት) የሚወጋ የሚጐንጥ፤ ደጓሽ አሥማሪ።
ደፈር ፡-ተራራ ኰረብታ፤ ገመገም።
ደፊር ሮት ፡-(ደፈረ ይደፍር ይድፍር። ዐረ ደፈረ፤ ገፋ አራቀ፤ ወዲያ አለ) መድፈር መጨከን፤ አለመፍራት አለማፈር፤ መናቅ ማቃለል ማዋረድ። ደፈርከ ትስተይ በንዋየ ቅድሳት።ኢኮኑ አይሁድ ይደፍሩ ይስዐሩ ካህነ እምሢመቱ እስከ ይመውት። ወኢክህለ አሐዱሂ ደድፍር ላዕሌሁ ፡-(ዮሴፍ)። ኢይድፍር ወኢይትናገር መኑሂ። ይደፍር ለምህሮ። ዘንተ ደፈርከ በትዕቢትከ። ሐሰወ ወደፈረ መሐላ። ደፈሮ ለእግዚእ ፡-(ስንክ ፡-ጥር፰። ፊልክ ፡-፪፻፱፳። መቃ ፡-ገ፮። ቀሌ። ቄድር)።
ደፊን ኖት ፡-(ደፈነ ይደፍን ይድፍን። ዐረ ደፈነ። ዕብ ዳፋን፤ ገፋ ደፋ) መድፈን፤ መምረግ መዝጋት። ዘይደፍን ዐዘቅተ። አዘዞሙ ይድፍኑ ውእተ መቃብረ። አዘዘ ይድፍኑ ግበባተ ፡-(ምሳ፳፭ ፡-፳፮። ጦቢ፰ ፡-፲፰። ዮሴፍ)
፡-መቅበር፤ መሸሸግ መሰወር፤ ካፈር ከመሬት ውስጥ ማግባት መክተት፤ ከእሳት ከፍሕም መረመጥ መሸጐጥ። ድፍኑ ደመ። ይደፍንኑ ምሕረተ በመዐቱ። ቀተሎ ወደፈኖ ውስተ ኆጻ። እመ ደፈንኩ ወርቅየ ውስተ መሬት። ደፈነቶ ውስተ ሐሪጽ። ደፈነት ናእተ ፡-(ኩፋ ፡-፯። ዘፀ፪ ፡-፲፪። ኢዮ፴፩ ፡-፳፬። ሉቃ፲፫ ፡-፳፩። ፩ነገ ፡-፳፰ ፡-፳፬)።
፡-መሸፈን ማልበስ መክደን። ደፈነኒ ቆባር። ይደፍነኪ ጸበል። ደፈኖሙ ማዕበል። ደፈነነ ጽላሎተ ሞት ፡-(ኢዮ፳፫ ፡-፲፯። ሕዝ፳፮ ፡-፲። ዘፀ፲፭ ፡-፲። መዝ ፡-፵፫)። ማስታጐል ማስቀረት፤ የግብር የጸሎት። ምስጢሩ ከመዝጋት ይገባል።
ደፊዕ ዖት ፡-(ደፍዐ ይደፍዕ ይድፋዕ። ዐረ ደፈዐ። ዕብ ዳፋህ) መድፋት መከንበል፤ መግፋት መጣል፤ መገልበጥ። ደፍዐ ገጾ። ኦ ገባሬ ብርሃናት ዘደፍዖ ለጽልመት። አባ ታድራ ወአባ ሉቃ አዝለፉ ኀምሳ ዓመተ እንዘ ይደፍዑ ኅሊናቲሆሙ፤ እስመ ኮኑ ይፈቅዱ ፈሊሰ እመካኖሙ ወኮኑ ይብሉ እስከ ክረምት ነሐውር፤ ወሶበ ይበጽሕ ክረምት ይብሉ እስከ ሐጋይ ነሐውር ፡-(ገድ ፡-ተክ። ቅዳ፤ ያዕ። ፊልክ ፡-፷፫)።
ደፋሪ ፡-(ሪት ርያን ያት) በቁሙ፤ የሚደፍር ደፋር ጨካኝ፤ ትቢተኛ። ጽኑዕ ወደፋሪ እምንእሱ። ደፋሪ ወኢኀፋሪ። ደፍርያን ፡-(ዮሴፍ። ግንዘ። ፊልክ ፡-፪፻፫)።
ደፋኒ ፡-(ኒት ንያን ያት) የሚደፍን ደፋኝ፤ ቀባሪ ሸሻጊ። ገብር ደፋኔ ወርቀ እግዚኡ ፡-(ፍ ፡-ነ ፡-፬)።
ደፍተር ፡-በቁሙ፤–ደብተር።
ደፍዕ ፡-የመዝጊያ ደፍ፤ ጕበን በመቃኖች ላይ የሚኾን።
ደፍደፈ ፡-አጋደመ ረበረበ፤ ደፈደፈ፤ መረገ አለበሰ ደመደመ፤ ኹሉም የእድሞ ሥራ ነው፤ እድሞን እይ። ይደፈድፉ ናሕሰ ፡-(ታሪ ፡-አኵ)።
ደፍደፍ [1]፡-ክርክራ፤–ደፊዕ ደፍዐ።
[2]፡-ክርክራ የእድሞ ቤት ጣራ፤ ሉሕ ጠርብ መረባርብ። ደፍደፈ ናሕስ።
ዱር ፡-በቁሙ፤ ደን ጫካ፤ ዎማ ብዙ ዛፍና ዕንጨት ያለበት። ታሕተ ዱር ተኀባእኩ ፡-(አዋል)።
ዱብል ፡-(ላቲን) ደባል፤ ዕጥፍ ድርብ መንታ ፊደል፤ ደጊመ ቃል። የበበ ነበበ፤ ደለለ ከለለ፤ ሐተተ ፈተተ፤ ይህን የመሰለ። ደበሎ ዐጐዛ ለምድ በላይ የሚደረብ። ፡-(ተረት) ሀብታም ይኼዳል በበቅሎ፤ ድኻ ይለብሳል ደበሎ።
ዱድ ፡-ስመ ነገድ፤–ደዊድ ዶደ፤ ዶድ።
ዲሎሳን ፡-(ጽር ፡-ዲሎሲስ። ዕብ ኡሪም) የበዓል መብራቶች፤ ለደስታና ለክብር የሚበሩ። ቃላት ነገራት ከሊቀ ካህናት ልብስ የሚስሙ። አልባስ ተኳህኖ ሊቀ ካህናት ቃለ እግዚ ሲጠይቅ የሚለብላቸው። ካህን ዘይለብስ ዲሎሳነ። ልብሰ ዲሎሳን ፡-(ዕዝ፪ ፡-፰። ፭ ፡-፵)።
ዲቁና ፡-በቁሙ፤ ዲያቆንነት ዲያቆን መኾን፤ የዲያቆን ሹመት ማዕርግ። ሢመተ ዲቁና። መልእክተ ዲቁና። ግብረ ዲቁና ፡-(ፈ ፡-መ ፡-፮ ፡-፭። ፍ ፡-ነ ፡-፯ ፡-። ስንክ ፡-ጥቅ፱)።
ዲበ ፡-ላይ ወይዶ ደየበ ዲብ ፡-ዲበ፤–ላይ ወደ፤–ደይቦ ደየበ፤ ዲብ።
ዲባግ ፡-(ጋት። ዐረ ፡-ዲባጅ) ልብሰ ሐር፤ ዝንጕርጕር ባለብዙ ሕብር፤ ወርቀ ዘቦ ግምጃ። ሢራያት ወዲባጋት። አልባሰ ዲባጋት። ቀጠንት ወኢዲባጋት። ጸውዖ ብእሲ ባዕል ለዲዮጋንስ ጠቢብ ውስተ ቤቱ ወኮነ ስርግወ በዲባጋት፤ ወብእሲሁሰ ኢኮነ ግሡጸ ፡-(መቃ። ስንክ ፡-መስ፲፮። አፈ ፡-ተ፳፰። ፈላስ)።
ዲብ ዲበ ፡-(ደቂቅ አገባብ) ላይ በላይ፤ ወደ ፥ ስለ ይኾናል፤ ሳይናበብ ሳይዘረዘር እንደ ላዕለ ብቻውን አይነገርም። ዘሐነጸ ቤቶ ዲበ ኰኵሕ። ኢይትኀደግ እብን ዲበ እብን። ሀሎ ዲቤሁ ልብስ ጥቁብ። ከልብ ይገብእ ዲበ ቅያኡ። ዲበ ሀጕለ ውሉዶሙ ይግዕሩ ፡-(ማቴ፯ ፡-፳፬። ፳፬ ፡-፪። ፊልክ ፡-፻፴፮። ምሳ፳፮ ፡-፲፩። ሔኖ፲፪ ፡-፮)። ኀበና ዲበ ይወራረሳሉ፤ ስለዚህ በኀበ ፈንታ ዲበ ይላል። ነበረ ዲበ ዐዘቅት ፡-(ዘፀ፪ ፡-፲፭)። የወዲያኛው ትግሬም ወደ ሲል ዲብ ይላል። ባማርኛ ግን ጕባ ጐባታ ታናሽ ቍሊልታ አዳጋ ቦታ፤ እንዳርባጫ ያለ ማለት ነው። ፡-(ተረት) የወዳጅ ዥብ፤ ልጄን ከዲብ። ድብኝትም የዚሁ ዘር ነው።
ዲብዲቆን ፡-(ጽር ዲፕቲኮን) ሰሌዳ፤ መጽሐፈ ተዝካር፤ የሙታን ወይም የሕያዋን፤ የማኅበርና የመምህራን የጳጳሳትና የቅዱሳን ስም በተራ የሚጣፍበት፤ የባስልዮስን ቅዳሴና ወዕቀቦሙን በእንተ ብፁዕን የመሰለ መዝገበ አስማት። መጽሐፈ ዲብዲቆን ዘቅዱሳን። ኀበ ተለክአ ዲብዲቆን ዘማኅበረ ነቢያት ፡-(መጽ ፡-ምስ። አርጋ ፡-፬)።
ዲና ፡-(ዕብራ) ስመ ብእሲት፤ ወለተ ያዕቆብ፤ ፍርዷ ፥ ፍርዲቱ ማለት ነው። ወንድሞቿ ስምዖንና ሌዊ በርሷ ምክንያት የሴኬምን ሰዎች ስለ ዘረፋና ስለ ፈጁ፤ ሽፍታ ኹሉ በነዚህ አምሳል ዲና ይባላል፤ የዲና ወንድም ማለት ነው። ሌኬም ህየ በዲና ተሀጕለ፤ ወበሳራ አቤሜሌክ ቈስለ ፡-(ቅኔ። ዘፍ፴ ፡-፳፩። ፴ ፡-፳፩። ፴፬ ፡-፩–፯ ፡-፳፬–፴)።
ዲናር ፡-(ራት። ጽር ዲናሪዮን) የገንዘብ ስም፤ ጽርኣዊ ሮማዊ፤ ታናሽ የብር ገንዘብ፤ የሰቅል እኩሌታ የዲድርክም አላድ፤ ወርቅም ይኾናል ፡-(ማቴ፲፰ ፡-፳፰። ፳ ፡-፪። ፳፪ ፡-፲፱)። ዲናረ ብሩር ዲናረ ወርቅ። ዲናራተ ብሩር ወወርቅ። ዲናራት ወጠፋልሐ ብሩር። ዲናር ግብጻዊ፤ ዲናር ጢሮሳዊ ፡-(፪ዜና ፡-፩ ፡-፲፯። ስንክ ፡-ጥቅ፲፮። ጥር፲፩። ፍ ፡-ነ ፡-፳፰ ፡-፴፫)። ደናራ ማለት ዐማርኛው ከዚህ ይሰማማል።
ዲኖ ፡-(ትግሬ) ዐጐዛ ሌጦ፤ ደበሎ። ፍርድ ልበስ ማለት ከዚህ ወጥቷል፤ ዐድልን ተመልከት። ባማርኛ ግን ጅን ጅናም የባሕር ጐሽ የጋኔን በሬ ማለት ነው። ይኸውም ከባሕር እየወጣ ሣር ይበላል፤ ከየብስ እንስሳትም ይወልዳል፤ ከርሱ የሚወለድ ላም ኹሉ በጣም ብርቱ ነው፤ በገር አይያዝም አይጠመድም፤ ብሄሞትን እይ።
ዲያቆናይ ዊ ፡-(ይያን ፡-ውያን) ዝኒ ከማሁ። አስጢፋኖስ ዲያቆናይ ምእመን በሰማይ ፡-(ድጓ)።
ዲያቆናይት ፡-(ዊት፤ ይያት ፡-ውያት) ሴት ዲያቆን፤ የ፰ ዓመት ባልቴት፤ በሴቶች ወገን እንደ ዲያቆን ኹና የምትላክ የምታገለግል። ወዲያቆናዊት ትገሥጾን ለአንስት ወታዕርፎን ወትርድኦን። እለ ያወስቡ መነኮሳይያተ ወዲያቆናይያተ ፡-(፩ጢሞ ፡-፭ ፡-፱። ፍ ፡-ነ ፡-፯። ፵፰)።
ዲያቆን ፡-(ናት። ጽር ፡-ዲያኮኖስ) በቁሙ፤ አገልጋይ የቄስ ተወራጅ በአንብሮተ እድ የሚሾም። ሶበ ትሰይሞ ለዲያቆም አንብር እዴከ ላዕሌሁ። ሊቀ ዲያቆናት። ንፍቀ ዲያቆን፤ የዲያቆን ተወራጅ ምክትል ፡-(ፍ ፡-ነ ፡-፯። ፰)።
ዲያብሎስ ፡-(ጽር ፡-ዲያቦሎስ። ዐረ ፡-ኢብሊስ) በቁሙ፤ ሰይጣን ጋኔን ክፉ መልአክ፤ የሰይጣንን ፍች ተመልከት፤ ክዚህ ጋራ አንድ ነው። ባለመጣፎች ግን፤ ዐማፂ ገፋዒ ጸናኒ ፈታዊ፤ ኀሣሤ አምላክና፤ ነድ ውዑይ ዖፍ ሰራሪ ይሉታል፤ ዘይቤው ከደየበና ከደበወ፤ ምስጢሩ ከሰይጣን ይሰማማል ፡-(ጥበ፪ ፡-፳፬። ማቴ፬ ፡-፩። ፲፫ ፡-፴፱)።
ዲዮስቆሪዶስ ፡-(ጽር ፡-ዲዎስኩሮን) መንታ ጣዖት ወንድማማች፤ የድያስ ልጆች የሚባሉ። ባለሐዲሶች ግን መስቀል ይሉታል ፡-(ግብ፳፰ ፡-፲፩)።
ዲዮስቆሮስ ፡-(ጽር ፡-ወቅብጥ) የሰው ስም፤ በዳኬዎስና በመርቅያን ዘመን የነበረ ሰማዕት፤ ያምላክ ወገን ቤተ ሰብ፤ ልደ ቤት አገልጋይ ፡-(ቅዳ። ሃይ ፡-አበ)።
ዲዮስጶራ ፤ (ጽር ፡ ዲያስፖራ) ፤ ዝርዋን ዘበዝርወት ዘበስደት ዘበፍልሰት (ያዕ፩ ፡ ፩)።
ዲዲሞስ [1]፡-መንቲያ፤–ዴደየ።
[2]፡-(ጽርእ። ዕብ ቶማእ) መንታዊ፤ መንቲያ ማለት ነው፤ ቶማስን እይ ፡-(ዮሐ፲፩ ፡-፲፮)።
ዲድስቅልያ [1]፡-የመጣፍ ስም፤–ደይደስ።
[2]፡-(ጽር ፡-ዲዳስካሊያ) የመጽሐፍ ስም፤ ፫ኛው የሐዋርያት መጽሐፍ፤ ትምርት ማለት ነው። ወሣልስ መጽሐፍ ዲድስቅልያ ዘውእቱ ትምህርት፤ ወኍላቌሁ አርብዓ ወሠለስቱ አንቀጽ ፡-(ፍ ፡-ነ ፡-መቅ)።
ዲድርክም [1]፡-የገንዘብ ስም፤–ደይደር።
[2]፡-ዲድርክም ሜ፤ ፡-(ጽር፤ ዲድራኽሞን ) የገንዘብ ስም እንደ ሩብና እንደ ፈረንክ ያለ፤ አንዱ ዲድርክም ኻያ አቦሊ ነው። የአቦሊን ፍች ተመልከት ፡-(ዘሌ፳፯ ፡-፫–፯)።
ዲፍራን ፡-(ሱር ዳፍራና) ጥድ የጥድ ዐይነት ዛፍ። ባለብሉዮች ግን ቀረጥ ይሉታል ፡-(ኩፋ ፡-፳፩)።
ዲፓ ፡-(ዲባ) (347) ሸመቃ ሽመቃ፤ ደበቅ ጦር ደባ ተንኰል። ነበረ ዲፓ። ቆመ ዲፖ። ጸንሐቶ ዲፓ ለንጉሥ። ወይጸንሕዎ ሎቱ በዲፓ ፡-(፩ነገ ፡-፲፭ ፡-፭። መሳ፱ ፡-፵፬። ዮሴፍ)።
ዳሕል ፡-ድል ሽሽት ኵብለላ።
ዳሕመመ ፡-ቈፈረ፤–ዳህምሞ ዳህመመ።
ዳህምሞ ሞት ፡-(ዳህመመ ይዳሀምም ይዳህምም። ዕብ ዳሀም፤ ብህመ) መቈፈር መኰትኰት፤ ዐፈር ማስታቀፍ። መቈለል መደመም፤ መመደብ፤ መደብ መሥራት፤ ላታክልት። ደመመን እይ፤ የዚህ ጎር ነው።
ዳኅነ ድኁነ ፡-ይኅና በደኅና፤ ወደ ደኅና፤ ድኖ ደኅና ኹኖ። ዳኅነ ሀሉ። ዳኅነ ይትናገሩ ለቢጾሙ። ትነብር ዳኅነ። ለእመ ዳኅነ አቶክሙ። ይሬኢ ዳኅነ። ወርእየ ዳኅነ። መጽአ ድኁነ ፡-(ግብ፳፫ ፡-፴። ኤር፱ ፡-፰። ኢዮ፲፩ ፡-፲፰። ጦቢ፭ ፡-፲፮። ፲፩ ፡-፯። ማር፰ ፡-፳፭። ዘረፋ)።
ዳኅና ፡-ደኅንነት፤ ጤና ሰላም፤ ትንሣኤ ሕይወት። አልቦ ዘይስእል ዳኅናኪ። ተስእሎ በእንተ ዳኅናሁ። ይዜንዉከ ዳኅና ብሔር። እነግር ጽድቀከ በዳኅናየ። በእንተ መንክር ዳኅናሁ ፡-(ኤር፲፭ ፡-፭። ፪ነገ ፡-፲፩ ፡-፯። ፩ነገ ፡-፲ ፡-፬። ኢሳ፴፰ ፡-፳። ጥበ፭ ፡-፪)። በዳኅን ፈንታ ዳኅና ይላል፤ ስሕተት ነው። ነበረት ሀገር ዳኅና ፡-(፬ነገ ፡-፲፩ ፡-፳)።
ዳኅን ፡-(ንት ናን ናት) የዳነ፤ የሚድን፤ ደኅና ባለጤና፤ ንጹሕ ጽሩይ። ዳኅንኑ አባ፤ እወ ዳኅን። ዳኅንኑ ማኅተም።ርኢ ለእመ ዳኅናንኑ አኀዊከ ወአባግዒሆሙኒ ፡-(ገድ ፡-ተክ። ዳን፲፫ ፡-፲፯። ዘፍ፴፯ ፡-፲፬። ፵፫ ፡-፳፯። ማቴ፳፫ ፡-፲፮ ፡-፲፰)። በዳኅና ፈንታ ዳኅን ይላል። ወኮነ ሰላም ወዳኅን ላዕለ ኵሉ በሓውርት። ዳኅን ወሰላም ፡-(ገድ ፡-ተክ። ፩ ፡-ተሰ ፡-፭ ፡-፫። ቀሌ)።
ዳኅፅ ፡-(ፃት) ዳጥ ድጥ፤ መሰናክል ዕንቅፋት፤ ኀጢአት፤ ሕገ ወጥ ሥራ። ጭንጋፍ ውርጃ ሽል። ዳኅፅ ወጽልመት። ያመጽኡ ዳኅፀ ለሕዝብ። አበሳነ ስረይ፤ ወዳኅፃቲነ እምሕግ። ይኄይስ እምኔሁ ዳኅፅ ፡-(መዝ ፡-፴፬። ዳን፲፩ ፡-፴፪። መክ፮ ፡-፫)።
ዳሕፍ ፡-ዳፋ ግፍ ግፊ፤ ድቀት ፍዳ፤ ጡር የክፉ ብድር።(ተረት) የኃጥኡ ዳፋ ጻድቁን አዳፋ። ኢያመሥጥ ኃጥእ እምነ ዳሕፍ ፡-(ሢራ፤ ፲፮ ፡-፲፫)።
ዳሌጥ ፡-(ዕብ ዳሌት። ጽር ዴልታ። ግእ ድልት) ስመ ፊደል ራብዕ ደ፤ መዝጊያ ሳንቃ ማለት ነው ፡-(መዝ ፡-፻፲፰ ፡-፳፭–፴፪። ሰቈ፩ ፡-፬። ፪ ፡-፬። ፫ ፡-፱። ፬ ፡-፬)።
ዳልጋ ፡-(ዐማርኛ) የባሕር በሬ፤ ጅን። የበሬ ዐንገት ትርፉ እንጥልጥሉ ቈርበት፤ ደላጎ፤ የጤፍ ዛላ። ማናቸውም ትርፍ ነገር ኹሉ።
ዳስ ፡-በቁሙ፤ ጥላ ከለላ፤ የሣር የቅጠል ጐዦ ግርዶ ከሐሩር ከቍር የሚሰውር። ዳሰ ዐቃቤ ወይን። ከመ ትግበር ዳሰ ኀበ ትነብር ፡-(ኢሳ፩ ፡-፰። ፲፮ ፡-፫)።
ዳራጊ ፡-(ጊት ግያን ያት) በቁሙ፤ የሚዳርግ ሰጭ አሰጭ፤ ድርጎ አውጭ ባለገንዘብ።
ዳርባን ፡-(ዕብራ) መድጐጸ ላሕም፤ አርቃሾ መውጊያ መጓጐጫ፤ ህየንተ ጅራፍ።
ዳርጎ ጎት ፡-(ዳረገ ይዳርግ ይዳረግ) መዳረግ ማስተላለፍ፤ ሰጭን ከተቀባይ መግጠም፤ የገንዘብ የቀለብ። ለእመ ዳረገ ሠያጢ ላዕለ ተሣያጢ ብእሴ በንዋይ ፡-(ፍ ፡-ነ ፡-፴፫ ፡-፯)።
ዳሮም ፡-(ዕብራ) ደቡብ፤ የሰሜን አንጻር ፡-(ሕዝ፳ ፡-፵፮)።
ዳባር ፡-(ዕብራ) ነገር ቃል፤ ባህል ብሂል፤ አንዳች ጕዳይ መፍቅድ።
ዳቤላ ፡-(ላት) ደቦል፤ ታላቅ የፍየል አውራ፤ የሚደረብና የሚታዘል የሚንጠላጠል፤ የላም አውራ ኰርማ ወይፈን። ዳቤላ ዘጠሊ። ሰብዐቱ ዳቤላት። ንስሐቦ ለዳቤላ ዘላሕም ፡-(ዳን፰ ፡-፭። ኩፋ ፡-፲፮። መጽ ፡-ምስ)።
ዳቤላም ፡-(ዕብ ድቤሊም) የበለስ ቋንጦች ቍጥራቶች፤ እንደ መቍጠሪያ የተሰኩ። አንዱን ስክ ድቤላ ይለዋል፤ እኄላን ተመልከት፤ ከዚህ ጋራ አንድ ነው። ባለብሉዮች ግን ዕፅቦ ጕርዶ የወጣለት ዶቄት ይሉታል ፡-(፩ዜና ፡-፲፪ ፡-፵)።
ዳቤር ፡-(ጽር ዳቢር። ዕብ ድቢር) መቅደስ፤ ቅድስተ ቅዱሳን፤ ባርባው ክንድ ፊት ያለ ኻያው ክንድ፤ መካነ ታቦት፤ ቃለ እግዚ የሚሰማበት፤ የሚነገርበት ፡-(፫ነገ ፡-፮ ፡-፲፮ ፡-፲፱–፳፫። ፰ ፡-፮ ፡-፰። ዘፀ፳፭ ፡-፳፪)።
፡-ስመ ሀገር ታናሽ ከተማ፤ በይሁዳ ክፍል ያለች፤ ካሌብ የወረሳት። እለ ይነብሩ ውስተ ዳቤር፤ ወስማ ለዳቤር ሀገረ መጽሐፍ ፡-(ኢያ፲፭ ፡-፲፭)። ዳቤር ያለውን ነገር እንደ ማለት መጽሐፍ ብሎ ፈታው፤ መጽሐፍን ዳቤር ድቢር ማለት በፋርስ ቋንቋ ነው ይላሉ ፡-(ረበናት)።
ዳታን ፡-የሰው ስም፤ ሥርዐት ማለት ነው፤ ፪ኛም ነቅዓዊ ይሉታል ፡-(ዘኍ፲፮ ፡-፳፬)።
ዳነተ ፡-(ዐማርኛ) በቁሙ፤ ጮኸ ተቈጣ፤ ኀይለ ቃል አወጣ። ነገሩ ችንካር ነው እንዲሉ።
ዳነየ ፡-(ደየነ) (ደየነ) ዳኘ፤ ፈረደ። ኢይዳንየነ ንጉሥ ፡-(ታሪ ፡-ነገ ኢያ)።
ዳናት ፡-ስመ ቀኖት ሣልስ፤ የግራ እጅ። ዳናት ዘበትርጓሜሁ ሣልስ ፡-(መጽ ፡-ምስ)።
ዳናዪ ዳኒ ፡-ደያኒ፤ የሚዳኝ ዳኚ ዳኛ፤ እውነተኛ መካከለኛ የፍርድ ሚዛን። ፡-(ተረት) ዳኛ የወል፤ ምሰሶ የመካከል። ዳኛ ቢያደላ በዳኛ፤ አህያ ቢያጋድል በመጫኛ። ዳኒና ደኃኒ ባማርኛ ይተባበራሉ። ፡-(ግጥም ፡-በቴዎ ጊዜ) ይልማናና ዴንሳ ቁሞ ይሟገታል፤ ይህን በጌምድርን ማን ዳኛ(ኝ) አድርጎታል። ዳነየ ያማርኛ እንጂ የግእዝ አይዶለም።
ዳን ፡-የዲና ወንድም፤ ስመ ነገድ ስመ ሀገር፤ ፈረደ ማለት ነው። ሰመየእቶ ስሞ ዳን። ተለዎሙ እስከ ዳን። እምዳን እስከ ቤርሳቤሕ ፡-(ዘፍ፴ ፡-፮። ፲፬ ፡-፲፬። ፪ነገ ፡-፲፯ ፡-፲፩)።
፡-ስመ ገድ፤–ደይኖ ደየነ።
ዳንስ ፡-(ሮማይ) ዘፈን እስክታ፤ የዝሙት ዋዜማ። እንስሳውን ገራም ጭምት ሲሉ ደንሴ ማለት ዐማርኛው ከዚህ ይሰማማል።
ዳንኤል ፡-(ዕብ ዳኒኤል) ስመ ሰብእ፤ ጻድቅ ነቢይ ፈላስፋ። አምላክ ደያኒየ መደይንየ የሚፈርድል(ብ) ኝ ፈራጄ፤ ዳኛዬ ማለት ነው ፡-(ዳን፩ ፡-፮። ሕዝ፲፬ ፡-፲፬። ፳፰ ፡-፫)። ደየነን እይ።
ዳንዮት ፡-መዳኘት፤ ዳኝነት፤ የዳኝነት ሥራ።
ዳዒ ፡-(ዕብ ዴዒ፤ ዴዓ፤ ዳዐት) ዕውቀት ዕውቂያ፤ ማስተዋል።
ዳዕሙ ፡-እንጂ፤–ድኢም ደአመ፤ ዳእሙ።
ዳእሙ ፡-(ትግ ደአም) ዐቢይና ንኡስ አገባብ። እንጂ ግን፤ ብቻ ይልቅ ይኾናል፤ እንጂና ግን ብቻና ይልቅ አንዳንድ ወገን ናቸው፤ ሲገባም እንደ ባሕቱ በፊት በኋላ ይገባል፤ አላንና ባሕቱን ተመልከት። ኃጥኣንሰ አኮ ከመ ዝ ዳእሙ ከመ መሬት፤ እንጂ። ኵሎ ዘቦ መጠውኩከ፤ ዳእሙ ኪያሁ ኢትግስስ፤ ግን። እሉኑ ዳእሙ ደቂቅከ፤ ብቻ። ወይቤሎ አልቦ፤ ዳእሙ ፈንወኒ፤ ይልቅ፤ ብቻም ይኾናል ፡-(መዝ ፡-፩። ኢዮ፩ ፡-፲፪። ፩ነገ ፡-፲፮ ፡-፲፩። ጦቢ፲ ፡-፱)። ፡-(ዕር፲፱ ፡-ቍ፹፩)።
ዳዕሮ ፡-የዛፍ ስም፤ ወርካ ዋርካ የሾላ የባንባ ዐይነት፤ ወፍራም ደንዳና ታላቅ ግዙፍ፤ ዐጽቁ ግድም የሚኼድ ወደ ምድር የሚወርድ፤ የሚሰፋ የሚንሰራፋ። እንደ ወርካ ያስፋኽ እንዲሉ። ፡-(ግጥም፤ ስደተኛ ፥ ጠላቱ ሹም ስለ ተሻረና ስለ ሞተ) ወርካ ምድር ነካ ደረሰ ንግሪ፤ እንግዴህ ልመለስ ልግባ ወዳገሬ። ወይጼድሎ ዖመ ዳዕሮ ፡-(ኢዮ፵ ፡-፲፯)። ዕብራይስጡ ግን አርዘ ሊባኖስ ይላል።
ዳዊት [1]፡-(ዕብ ዳዊድ) የሰው ስም፤ የእስራኤል ንጉሥ፤ ፍቁር መፍቀሪ ፡-(፩ነገ ፡-፲፮ ፡-፲፫)።
[2]፡-(ዕብ ትሂሊም) የመጽሐፍ ስም፤ መጽሐፈ መዝሙር፤ ዳዊትና እንደ ዳዊት ያሉ፤ እነአሳፍን የመሰሉ የግዜር መዘምራን የደረሱት። ብዙው የዳዊት ስለ ኾነ በዳዊት ስም ተጠርቷል እንጂ ፻፶ው ኹሉ የርሱ አይዶለም፤ ይኸውም በያርእስቱ ይታወቃል፤ ከምርኮም በኋላ የተደረሰ አለ። ይልቁንም እግዚኦ ጻወነ ኮነከነ ካለው ዠምሮ ምሕረተ ወፍትሐ እስከሚለው ድረስ ፲፩ዱ መዝሙር የሙሴ ይባላል። ምእት ወኀምሳ ዳዊት። ጸሎት ዘእምዳዊት በዜማ ፡-(ግንዘ)።
(ጥ) »ዳዋ ፡-(ዐማርኛ)
ዝኒ ዓዲ ከማሁ፤ በቁሙ ዱር ጥሻ ጣሻ። ፡-(ተረት) ዐይጥ በበላ ዳዋ ተመታ።
ዳየር ፡-አንባ ኰረብታ፤ ዙሪያው ገደል፤ የግሼና የግሸን ተራራ፤ ምስጢሩ ገዳምነት ነው።
ዳይቅ ፡-(ዕብ ዳየቅ) መቃኰሻ ግንብ፤ የውጭ ጠላት በቅጥር ዠርባ የሚሠራው፤ ወይም በዚያ ላይ ኹኖ እንዳንደርቢ ወደ ከተማ የሚሰደው የሚወረውረው ደንጊያ። ከመ ይሕንጽ ዳይቀ ፡-(ሕዝ፳፩ ፡-፳፪)።
ዳግመ ፡-ደግሞ መልሶ፤ ተመልሶ፤ ዳግመኛ። እምከ ዳግመ። ዓዲ ዳግመ። ወካዕበ የሐውር የአብስ ዳግመ። ዳግመ ይመጽእ ፡-(ኤር፫ ፡-፩። መሳ ፡-፲፫ ፡-፱። ሢራ፴፩ ፡-፴፩። ቅዳ)።
ዳግማዊ ዳግማይ ፡-(ዊት ውያን ያት) (ዪት ሚት፤ ይያን ያት) በቁሙ፤ ኹለተኛ ታናሽ፤ ተከታይ ምክትል። አባ ማርቆስ ዳግማዊ። ወልደ ዳግማዊት ብእሲት። ዳግማይ አዳም። ሰማይ ዳግሚት ፡-(ስንክ ፡-ጥቅ፳፫። መስ፬። ውዳ ፡-፬። ቅዳ። ድጓ)።
ዳግም ፡-(ምት ማን ማት) ድጋሚ ዳግሞሽ፤ ዳግመኛ ኹለተኛ። ዳግም ልደት። ዳግም ሞት። ዳግም ኦሪት። ዳግም ብእሲ። አዕቀጸኒ ወናሁ ዳግሙ ዮም። ሰላም ለክልስትያኖስ ለዮናክንዲስ ዳግሙ ፡-(ማቴ፲፱ ፡-፳፰። ራእ፪ ፡-፲፩። ዘዳ፲፯ ፡-፲፰። ፩ቆሮ ፡-፲፭ ፡-፵፯። ዘፍ፳፯ ፡-፴፱። ስንክ ፡-ሐም፫)።
ዳጎን ፡-(ዕብራ) ስመ ጣዖት፤ የባሕር ዳር ሰዎች ኢሎፍላውያን የሚያመልኩት፤ ፊቱና ራሱ የሰው፤ ግንዱና ገላው መለመላው የደራጎን ያሣ፤ ዐይነቱ ሦርዞና ጐርዞ ወይም አንባዛና ዐዞ የሚመስል። ዳግ ፥ ዓሣ፤ ዳጎን ፥ ዓሣዊ ዓሥማ ዓሦ ማለት ነው፤ ዥቦ ነብሮ እንደ ማለት ፡-(፩ነገ ፡-፭ ፡-፪)።
ዳፈን ፡-(ዐማርኛ) ያዳፋኝ፤ መቀጮ።
ዳፍን ፡-(ጽር ዳፍኒ) የዛፍ ስም ሽቱነትና ቅመምነት ያለው፤ ቅጠሉን ስለ ከበሬታ ቄሳሮች የሚቀዳጁት። ባለብሉዮች ግን ጥድ ይሉታል ፡-(ኩፋ ፡-፳፩)።
ዳፍንት ፡-በቁሙ፤ የዐይን በሽታ ከማታ እስከ ጧት የሚያሳውር። ዳፍንታም እንዲሉ።
፡-ቂጣ ብርኵታ ርሚጠ፤ አንባሻ ሽልጦ፤ በረመጥ በፍሕም ቀብረው አዳፍነው የሚያበስሉት የባላገር ኅብስት ፡-(ዘፍ፲፰ ፡-፮። ፲፱ ፡-፫። ዘፀ፲፪ ፡-፴፱)። ግበሪ ዳፍንተ ወአምጽኢ ሊተ። ከመ ይግበራ ዳፍንተ ፡-(፫ነገ ፡-፲፯ ፡-፲፫። ኤር፯ ፡-፲፫)።
ዴር ፡-(ሱር ፡-ዳይራ። ዐረ ደይር) ገዳም ዱር፤ የመነኮሳት ቦታ ሰፈር። ዘሩ ደዊር ነው፤ ወና የ ተወራራሾች ስለ ኾኑ በየ ምክንያት ወደዚህ መጥቷል፤ ዱርና ዴር ፩ ስም ናቸው። ኀበ ተሐንጸ ተዝኪር ወኀበ ተሣረረ ዴር ፡-(ስንክ ፡-የካ፱)።
ዴቆነ ፡-(ይዴቁን ይዴቁን) ዲያቆነ፤ ዛቆነ፤ ዲያቆን ኾነ። ዜቆነን ተመልከት፤ የዚህ ሞክሼና መንቲያ ነው።
ዴዳን [1]፡-ስመ ነገድ፤–ደይዳን።
[2]፡-(ዕብ ድዳን) ስመ ነገድ፤ የኵሽ የልጅ ልጅ፤ የሽባእ ወንድም፤ ዐደንን ያቀና ያረቦች አባት ፡-(ዘፍ፲ ፡-፯። ሕዝ፳፯ ፡-፲፭)። የአብርሃም ልጅ ከኬጡራ የተወለደ ፡-(ዘፍ፳፭ ፡-፫)።
ዴዴ [1]፡-ደጅ፤–ደይደየ፤ ዴደየ።
[2]፡-(ብ ዴዴያት፤ ዴዳያት፤ ዴድያት) ደጃፍ በረንዳ ወልወል፤ የቤት መዠመሪያ ክፍል፤ ክበር ከቅጥር በውስጥ ያለ ቦታ፤ ወይም ታላቅ የውጭ በር፤ ደጀ ሰላም። ዴዴሁ ለባዕል። እለ ውስተ ዴዴ ቤተ ክር። በዴዴያተ አብያት። ዴድያተ አንቀጽ። ወዴዳያቲሃ ፡-(ሉቃ፲፮ ፡-፳። ቀሌ። ሕዝ፴፫ ፡-፴። ኤር፩ ፡-፲፭። ራእ፳፩ ፡-፳፩)።
ዴድዮ ዮት ፡-(ዴደየ ይዴዲ ይዴዲ። ዕብ ዳዴህ፤ ሂዳዴ) መዝለል መፈንጨት፤ እንጥር ፍንጥር ድቅ ድቅ ማለት የግልገል የጥጃ። አካኼድ አረማመድ መማር፤ ማስተማር፤ ዳዴ ዳዴ ወይም አቱ ሥግራ፤ ታቱ ሥግራ ማለት የሕፃን የሞግዚት።
ዴጋኒ ፡-(ኒት ንያን ያት፤ ዴገንት) ደጋኝ አጥማጅ ዐዳኝ። የሚከተል ተከታይ፤ ፈላጊ አባራሪ ዠግና፤ ሯጭ ገሥጋሽ። ኤዎስጣቴዎስ አሠረ ቶማስ ዴጋኒ። ዴጋኔ ፀሩ ፡-(ድጓ። ስንክ ፡-ሚያ፳፰)።
ዴጋን ደጋን ፡-(ናት) በቁሙ፤ ቀስት የንጨት የብረት፤ ጐባባ ጐባጣ፤ ጠማማ። ደጋን ያማርኛ ቀስት የግእዝ ነው። እለ ፍናዊሆሙ መብእስ ወደጋን መንኰራኵሮሙ ፡-(ምሳ፪ ፡-፲፭)።
ዴግሬ ፡-(ላቲን ግራዱስ) ደረጃ ዕርከን፤ ልክ ሚዛን እንደ ድግር የተካከለ።
ዴግኖ ኖት ፡-(ዴገነ ይዴግን ይዴግን። ትግ ዳገነ። ዕብ ዳዮግ፤ አሥግሮ ዓሣ) መከተል ማባረር፤ መሻት ማደን፤ ማጥመድ ማለብ መደገን፤ ለመያዝ ለመግደል ለመማረክ። ዴግንየ እአኅዞሙ። ዴግንዎ ወትእኅዝዎ። ይዴግንዋ ለኦሪቶሙ። ለእመ ዴገንካ ለጽድቅ ትረክባ። ይዴግን ኀበ ሐመልማል ፡-(ዘፀ፲፭ ፡-፱። መዝ ፡-፸። ሮሜ፱ ፡-፴፩። ሢራ፳፯ ፡-፰። ኢዮ፴፱ ፡-፰)።
ዴፐ ደየፕ [1]፡-(ደበወ፤ ደበየ) ሸመቀ አሸመቀ፤ አደባ ደፈጠ ተደበቀ፤ ለመግደል አደጋ ለመጣል። ዘዴፐ ለከ ይቅትልከ። ዴፑ በፍኖት ፡-(ዮሴፍ)።
፡-ጦር ወጥመድ፤ አኖረ፤ ደበቀ ሸሽገ። ዴፐ ሎቱ ዕደወ ከመ የኀይል ቦቱ ፡-(ዮሴፍ)።
ዴፐ ዲፓ ፡-ሸመቀ፤ ሽመቃ፤–ደየፐ።
ድኁኅ ፡-(ኃን ኃት ኅኅት) የተፋረ የተጠረበ፤ የተወቀረ፤ ጥርብ ውቅር። አድባር ድኁኃን ፡-(ድጓ። ማሕ፪ ፡-፲፯። ፰ ፡-፲፬)። ዋሻ ፍርኵታ አንባነት ዕርድነት ያላቸው፤ ደንጊያ የመላባቸው ማለት ነው። ባለብሉዮች ግን ጽኑዓን ይሉታል፤ ባለቅኔዎችም ደኅኀ ጸና ይላሉ።
ድሑር ፡-(ራን ራት ሕርት) የተዳረ፤ የተፈታ ገለሞታ። ዘአውሰበ ድሕርተ አርኰሰ ሥጋሁ ፡-(ዲድ ፡-፴፫)።
ድኁር [1]፡-(ራን ራት ኅርት) የተመረቀ ምሩቅ። የቈየ የዘገየ።
[2]፡-(ዐማርኛ) ዐጭር ግጭር፤ ድንክ ጐባጣ፤ ሕጹጽ ታናሽ። ግናይን ተመልከት።
ድኁን ፡-(ናን ናት ኅንት) የዳነ ያመለጠ፤ ደኅና የኾነ፤ የተፈወሰ፤ ጥዑይ፤ ንጹሕ ጽሩይ፤ ያልተነካ። ኢድኁን አንተ በሞተ ኢየሱስ። ይረስዮ ምስለ ድኁናን። ድኁነ ምስማዕ ወንጻሬ፤ ድኁን እምነውር። ድኁን አነ እምሐሜት። ክርስቶስ ድኁን ውእቱ አምኀንጣውእ። ነፍስ ድኅንት ፡-(መጽ ፡-ምስ። ግንዘ። ፍ ፡-ነ ፡-፵፫ ፡-፩። አፈ ፡-ድ፬። ፲፭። ድጓ)።
ድሑክ ፡-የዳኸ የሚድኽ፤ ታናሽ እግረ ኵንትሽ ደካማ፤ እንዳሽኮኮና እንደ ላጽቂት ያለ፤ ማናቸውም ፍጥረት።
ድኁይ ፡-የተቈፈረ የተማሰ፤ ጥልቅ። ተገድፈ ሥጋከ ውስተ ክርየት ግብ ድኁይ ፡-(ደራሲ)።
ድኂኅ ኆት ፡-(ደኅኀ ይድኅኅ ይድኀኅ) መፋር መፈርፈር፤ መጥረብ መውቀር፤ የዋሻ የጐሬ።
ድሒል ሎት ፡-(ድሕለ ይድሕል ይድሐል። ዐረ ደሐለ) ድል መኾን፤ መሸሽ መኰብለል፤ ማምለጥ መራቅ፤ መደበቅ። መጽሐፍ ግን በድሕለ ፈንታ ተድሕለ ይላል። አመ ተድሕሉ ወጐዩ። እምገጸ ሄሮድስ ዘተድሕለ። እመንግሥተ ዓለም ዘተድሕለ ፡-(አዋል። ስንክ ሚያ፰። መስ፱)።
ድሒር ሮት ፡-(ደሐረ ይድሕር ይድሐር። ዐረ ደሐረ) ማባረር መስደድ፤ መፍታት መልቀቅ፤ ከቤት ማሶጣት፤ ማሰናበት ፡-(ማቴ፲፱ ፡-፱። ማር፬ ፡-፭ ፡-፲፩። ሉቃ፲፮ ፡-፲፰) ዘይድሕር ብአሲቶ ዘእንበለ ትዘሙ። ኢይድሐር ብእሲ ብእሲቶ ፡-(ቀሌ። ዲድ ፡-፴፫)።
፡-መዳር ማጋባት፤ ሴት ልጅን በሕግ በሥርዐት ለጮኛዋ መስጠት፤ ምስጢሩ ያው ማሶጣት ነው። ለወንድ ልጅም ይነገራል። ፡-(ግጥም ልጃገረድ ስላባቷ ስርግ) እንዲህ ያለ ዘመን የተበላልጨ፤ አባቴ ተዳሩ እኔ ተቀምጨ።
፡-ማዘዝ መፍቀድ አድርግ ማለት፤ ምስጢሩ ከማሰናበት ይገባል፤ ሙሴሰ በከመ እከየ ልብክሙ ደሐረክሙ ትኅድጉ አንስቲያክሙ ፡-(ማቴ ፲፬ ፡-፰)።
ድኂር ሮት ፡-(ደኀረ ይድኅር ይድኀር። አኀረ። ዐረ ደኀረ፤ ንእሰ) መቈየት መዘግየት፤ ማፈግፈግ ወደ ኋላ ማለት በኋላ መቅረት፤ ኋለኛ መጨረሻ መኾን፤ በግብር በነገር በማናቸውም። ከመ ይትመየጥ ወኢይድኀር። ለእመ ነበረ ሕዝባዊ ሠለስተ ሰንበት ድኂሮ እምቤተ ክርስቲያን ይክልእዎ ትድምርተ ፡-(ዮሴፍ። ቀኖና ፡-ግንር)። ብዙ መጽሐፍ በደኀረ ፈንታ ተድኅረ ይላል፤ ስሕተት ነው። ተድኂሮ መጽአ። ኢይበድሩ ወኢይዴኀሩ አሐደ ዕለተ። በእንተ እለ ተድኅሩ። እመሂ ኤጲስቆጶስ ተድኅረ እምስብሐተ ነግህ። ወኢተድኅረ አሐዱ እምኔሆሙ ለገቢረ ዝንቱ። እንበለ ተድኅሮ ፡-(ኪዳ። ሔኖ፸፬ ፡-፲፪። ቅዳ። ቀሌ። ዮሴፍ። ስንክ ፡-ኅዳ፲)።
፡-መመረቅ፤ መባረክ፤ ማመስገን። ሶበ አሐዱ ይድኅር ወካልኡ ይረግም። ለጸጋዊ ይድኅርዎ በሥነ ምግባሩ። ደኀረኒ ዘይመውት። ይድኅሩኒ ስኡናን። ይድኅሩኒ አራዊተ ገዳም። ይረግሙነ ወንሕነ ንድኅሮሙ። በአፉሆሙ ይድኅሩ ወበልቦሙ ይረግሙ ፡-(ሢራ፴፩ ፡-፳፱። ፴፬ ፡-፳፫። ኢዮ፳፱ ፡-፲፫። ፴፩ ፡-፲፱። ኢሳ፵፫ ፡-፳። ፩ቆሮ ፡-፬ ፡-፲፪። መዝ ፡-፷፩። ፸፩)።
ድኂን ኖት ፡-(ድኅነ ይድኅን ይድኀን። ዕብ ያሾዕ፤ ሂዋሼዕ) መዳን ማምለጥ መውጣት፤ ከተያዙ በኋላ፤ ወይም ሳይያዙ መቅረት መትረፍ፤ እንዳይያዙ መኾን፤ መጠንቀቅ መጠበቅ፤ በሕይወት መኖር፤ መታደስ መለምለም። ፡-(ዐጋዥ ረዳት ጠበቃ ወባት ዋስና መድን ተያዥ ማግኘት) እንደ አዳም። ሐይወን ተመ፤ የዚህ መንቲያ ነው፤ ሐይወ የግእዝ ድኅነ ያማርኛ። አልቦ ድኂን። መዋዕለ ድኂን። ድኂኖ እምባሕር። ወድኅነ ጢጦስ በይእቲ ዕለት እምቀትል ሠለስተ ጊዜያተ። ወልደተ ዓለም ለድኂን። ይእቲ ዕፅ ድኅነት ፡-(ኩፋ ፡-፵፪። አስቴ፱ ፡-፳፱። ግብ፳፰ ፡-፬። ዮሴፍ። ጥበ፩ ፡-፲፬። ሄርማ)።
ድሒክ ኮት ፡-(ድሕከ፤ ደሐከ ይድሕክ ይድሐክ) መዳኽ፤አጐንብሶ በእጅና በእግር መኼድ፤ ወይም እጅን ተይዞ በእግር ብቻ መወናከር፤ አካኼድና አረማመድ መማር፤ ለፊደልም ይኾናል። በድሒክ ውስተ መርሕብ። ሐንካስ ድሕከ እስከ ይበጽሕ ኀበ አባ ሳሙኤል፤ ይድሕክ ወይስእል። ወድሕከ ዲበ ምድር። ይድሕክ በነቢበ ፊደላት ፡-(መጽ ፡-ምስ። ገድ ፡-ሳሙ። ስንክ ፡-ሐም፲። አፈ ፡-ተ፳፮)። ድኳ ዳክዬ፤ ድኻ ድኰት ማለት ከዚህ ወጥቷል።
ድኂፅ ፆት ፡-(ድኅፀ፤ ይድኅፅ፤ ይድኀፅ። ዐረ ደሐፀ) መዳጥ መሰናከል፤ መውደቅ፤ የእግር የቃል። ከመ ኢይድኀፅ ሰኰናየ። ይኄይስ ትድኀፅ ወትደቅ ውስተ ምድር እምትድኀፅ በአፉከ። ትድኅፅ ምክሩ። ኢንድኀፅ በኀጢአት። ከመ ኢንድኀፅ እምርትዕት ሃይማኖት ፡-(መዝ፲፮። ሢራ፳ ፡-፲፰። ኢዮ፲፰ ፡-፯። ዲድ ፡-፬። ፳፭)። ፡-(ጥጨ) መጨንገፍ መውረድ፤ ጭንጋፍ መኾን፤ የፅንስ የሽል። መዳጥ መደፍጠጥ፤ መርገጥ መዠለጥ ፡-(ዐማርኛ)።
ድሒፍ ፎት ፡-ድሒፍ፤ ፎት፤ ፡-(ደሐፈ ይድሕፍ ይድሐፍ። ዕብ ዳሐፍ) መግፋት ማዳፋት፤ መገፍተር፤ ማጣደፍ ማባረር።
ድኅረ ፡-(ዐቢይና ደቂቅ አገባብ) ኋላ በኋላ፤ ወደ ኋላ። ምስጢሩ ጊዜ ነው፤ እም በ እንተ ይሰማሙታል። ዐቢይ ሲኾን፤ አምድኅረ ተደሩ፤ ወእምድኅረ መስሑ እያለ በቀዳማይ ይገባል። ደቂቅ ሲኾን በቦታ በጊዜ ይገባል። ሰማዕኩ በድኅሬየ። ቆመት እንተ ድኅሬሁ። ድኅረ ማዕጾ። ፈረሱ ለፈርዖን ይቤ ድኅረ ድኅረ፤ እስመ እግሩ ኢለመደ ባሕረ፤ ቦታ ፡-(ሕዝ፫ ፡-፲፪። ሉቃ፰ ፡-፵፬። ኢሳ፶፯ ፡-፰። ቅኔ)። እምድኅረ ሕቅ። እምድኅረ ፍልሰተ ባቢሎን። ወድኅረ ኵሎሙ አስተርአየኒ ሊተ። ቅድመ ጠይቅ ወድኅረ ትጌሥጽ፤ ጊዜ ፡-(ማር፲፬ ፡-፯። ማቴ፩ ፡-፲፪። ፩ቆሮ ፡-፲፭ ፡-፰። ሢራ፲፩ ፡-፯)። ፡-(ዕር፲፱ ፡-ቍ፸፱)።
ድኅሪት ፡-ኋሊት፤ የኋሊት፤ ኋላ፤ እንግሊላ። የሐርስ ድኅሪተ። እሱራን ድኅሪተ። ኢገብኡ ድኅሪተ። ከመ ይደቁ ድኅሪተ ፡-(ሉቃ፱ ፡-፷፪። መዋሥ። ስንክ ፡-ሐም፳፭። ኢሳ፳፰ ፡-፲፫)።
ድሕር ፡-ኋላ፤–ድኅር።
ድኅር ፡-(ራት) ኋላ ዠርባ፤ ከማዥራት እስከ ተረክዝ። በዠርባ አንጻር ያለ ቦታ፤ የኋላ ኋላ፤ ጓሮ። ድኅሬሆሙ ለእልክቱ አልሕምት ይኔጽር ውስጠ። ገቦሃ ዘድኅር። ዘባን እንተ ድኅር ፡-(፪ዜና ፡-፬ ፡-፬። ግብ፳፯ ፡-፵፩። ቅዳ ፡-ሕር)።
ድኅርና ፡-ደኃራዊነት፤ ኋለኛ መጨረሻ መኾን። ለቅድምናከ ወለድኅርናከ ፡-(ፍ ፡-ነ ፡-መቅ)።
ድሕነ ፡-ዳነ፤–ድኂን ድኅነ።
ድኅነት ፡-መዳን መፈወስ፤ ደኅንነት ጤና። ወአንከሩ እምድኅነቱ። እምአይቴ ተሰፈዉ እሉ ድኅነት ሕፃን። ድኅነተ ልብ ወአባል። ድኅነት እምደዌያት። ጾመ ድኅነት፤ ምሕላ ድኅነት ፡-(ስንክ ፡-ሐም፳፬። አፈ ፡-ድ፳፮። ፍ ፡-ነ ፡-፬። መር ፡-ዕዉ። ድጓ)።
ድሕንጻ ፡-(ድ ሕንጻ) በቁሙ፤ እደ ሕንጻ፤ የክራርና የበገና የመሰንቆ መምቻ፤ እድ ፥ ልጁ፤ ሕንጻ ፥ እናቱ። ንባቡ ሐነጸን፤ ምስጢሩ ደጐጸንና ደነጸን ይመስላል፤ ጥሬነቱ ግን የሐነጸ ነው። እድ ውእድ ተብሎ ወደ ወ እንደ ኼደ፤ ሕንጻም ድሕንጻ ተብሎ ወደ ደ መጥቷል። በድሕንጻ መንፈስ ዝብጢ አውታረ መሰንቆሁ ለልብየ። እብል ሰላመ በልሳንየ ድሕንጻ። ኦ ፎጢኖስ ኮገከ እንዚራሁ ለመንፈሰ ሰይጣን ወመሰንቆሁ ለመንፈሰ ሐሰት፤ ወደጐጸከ በድሕንጻሁ ፡-(ሳታት። ስንክ ፡-ጥቅ፳፯። መጽ ፡-ምስ)።
ድኅንጻ ፡-በቁሙ፤–ድሕንጻ።
ድሕይ ዮት ፡-(ደሐየ ይድሒ ይድሐይ። ዐረ ደሐ። ሱር ዳሒሓ) መፍጨት ማድቀቅ፤ መገርደፍ መሰለቅ፤ ማዞር ማሽከርከር፤ መግፋት መመለስ የመጅ።
ድሕጸ ፡-ዳጠ፤–ድኂፅ ድኅፀ።
ድኅፀት ፡-መዳጥ ፡-(ጥዳ) መዳጥ አዳዳጥ ድጦሽ፤ መሰናክል ፡-(ፊልክ ፡-፻ሮ፩። ፈላስ)።
ድሉል ፡-(ላን ላት ልልት) የተመየደ የተከፈከፈ ክፍክፍ፤ ወይም ወደ ታች፤ የተጣሰ የተዝረፈረፈ፤ ግልስልስ ያለ፤ የተቈናዘለ፤ የተጋመደ የተመሳቀለ። ድምድማሁ ድሉል። ሥዕርት ርእስኪ ድሉላት። ላሕይት ይእቲ ብእሲት፤ ድምድማሃ ድሉል ፡-(ማሕ፭ ፡-፲፩። አርጋ ፡-፮። ገድ ፡-ተክ)።
ድላሌ ፡-(ላ ፡-ጥ። ከ) መከፍከፍ አከፋከፍ፤ ፍከፋ፤ ክፍክፋት፤ የጠጕር ሥራ፤ ዐይነቱ መልኩ፤ ጠባዩ ኣኳዃኑ።ርእሱ ወርቀ ቄፋዝ ወድላሌሁ ጸሊም ከመ ቋዕ። ለሥዕርትኪ ሰላም ዘድላሌሁ ጸሊም ፡-(መጽ ፡-ምስ። ደራሲ)።
ድላግ ፡-ዝላይ ውርወራ መከታ፤ የሰልፍ ሥራ። ከመ ያእትት እምላዕሌየ ዘቀትለ ፀራዊ ድላገ ውሒዘ ረድኤትከ ይኩን በዐውድየ ዐይገ ፡-(ደራሲ)።
ድልማኑታ ፡-ስመ ሀገር፤ የገሊላ ምዕራብ ፡-(ማር ፡-፰ ፡-፲)።
ድልቅልቅ (ቃት) ፡- ሁከት ንውጽውጽታ፤ ሽብር ድብልቅልቅ። አድለቅለቀ ዐቢይ ድልቅልቅ። ወናሁ ኮነ ዐቢይ ድልቅልቅ። ወይከውን ዐቢይ ድልቅልቅ ወረኀብ በበ ብሔሩ ፡-(ግብ፲፮ ፡-፳፮። ማቴ፳፰ ፡-፪። ሉቃ፳፩ ፡-፲፩)።
ድልት ፡-(ድንት) ስመ ፊደል ራብዕ፤ የግእዝ አራተኛ ፊደል ደ። ፍችውን በዳሌጥና በድንት ተመልከት።
ድልወት ፡-(ታት) መመዘን ፡-(ጥመ) መመዘን፤ መዛኝና ተመዛኝ መኾን፤ አመዛዘን ምዘና ሚዛን፤ ልክ መጠን ፡-(ዘፍ፳፬ ፡-፳፪። ዘፀ፴ ፡-፴፬። መሳ፰ ፡-፳፮)። ወድልወቱ ለኵሉ ብርት ወኀጺን ዘላዕሌሁ ኀምሳ ምእት ሰቅሎን ፡-(፩ነገ ፡-፲፯ ፡-፭። ፪ነገ ፡-፲፬ ፡-፳፮)።
፡-አገባብ ርትዕ፤ ፡-(እውነት፤ የተገባ የሚገባ። በጽድቅ ተኰነኑ ዘከመ ድልወተ እከዮሙ። እንዘ አኮ ድልወት ሊተ አድኀንከኒ፤ አኮ ድልወት ሊተ ኣንቃዕዱ። በብ ድልወታት። ነበብከ ድልወተ ፡-(ጥበ፲፱ ፡-፲፪። ዲድ ፡-፯። ፍ ፡-ነ ፡-፱ ፡-፪። ቄር ፡-ጰላ)።
(ላ) ድልው [1]፡-(ዋን ዋት ሉት) የተመዘነ የተካከለ ልከኛ፤ አነሰ በዛ የማይባል። ቃሎሙ ፡-ለጠቢባን ድልው በመዳልው። ድልወ ዕርየት ፡-(ሢራ፳፩ ፡-፲፭። ፊልክ ፡-፫)።
[2]፡-(ጥ) ድልው፤ የተገባ፤ የተዘጋጀ የተሰናዳ ዝግጁ። ዘድልው ለክብር። ድልው መንበርከ። በዓልየ ድልው። ድልዋኒክሙ ሀልዉ። እልኩ እለ ድልዋት። ወድሉት ይእቲ ፡-(ሢራ፵፱ ፡-፲፪። መዝ ፡-፺፪። ማቴ፳፪ ፡-፰። ፳፬ ፡-፵፬። ፳፭ ፡-፲። ራእ፳፩ ፡-፪)። ድልኽ ማለት ከዚህ ወጥቷል።
ድልጕማ ፡-(ዐረ ዱምሉጅ) የእጅ የጣት ጌጥ ጥምዝ የወርቅ አንባር፤ ኀቲም ቀለበት ወይም ባለዕንቍ ፈርጥ። ወከመ ድልጕማ ውስተ እደ የማን። ሕልቀትየ ዘአጽባዕትየ ወድልጕማየ፤ አንባር ፡-(ሢራ፳፩ ፡-፳፩። ኩፋ ፡-፵፩)። ከመ ባዝግና ወርቅ ውስተ ክሣድ ወከመ ድልጕማ ዘውስተ አጻብዕ ፡-(ፈላስ ፡-ገ፲፰። ደልገን ማለት ከዚህ ይሰማማል።
ድመት [1]፡-መደመም መደነቅ፤ አደናነቅ፤ ድንቂያ። ጪኸት ድምታ፤ ድም ማለት።
[2]፡-(ታት። ዐረ ፡-ዲመት። ጽር ፡-ኤሉሪ) በቁሙ፤ ብስ ብሴ፤ ውር ውሮ የሚባል፤ ታናሽ የቤት አውሬ ያይጦች ደመኛ፤ ግርማው የሚደም የሚያስደምም፤ ያንበሳ ወገን ዐዳኝ ወሮ በላ። የዱር የባሕር ድመት። ጸጕረ ድመት። አናብስት ኮኑ ከመ ድመታት። ወረውዎ ውስተ ማዕበለ ባሕር፤ ከመ ይብልዕዎ ዓሣት ወዐናብርት ወድመታት ፡-(መ ፡-ፈ። ስንክ ፡-መጋ፳፫። ጥቅ፯)።
[3]፡-በቁሙ፤–ደሚም ደመመ።
ድሙስ ፡-ጥቍር ጠቋራ፤ ጽዕዳዌና ቅላት የሌለው። በድሙስ ሰማይ፤ በብሩህ ሰማይ ፡-(ቄድር)።
ድሙር ፡-(ራን ራት ምርት) በቁሙ፤ የተደመረ ድምር፤ ጭምር ቅልቅል። ኀጺን ድሙር ምስለ ልሕኵት። ኢኮኑ ድሙራነ ዝንቱ ምስለ ዝንቱ። ባሕር ድምርት በእሳት ፡-(ዳን፪ ፡-፵፩ ፡-፵፫። ራእ፲፭ ፡-፪)።
፡-የቍጥር ስም፤ አንድነት ጅምላ። ወኮነ ኵሉ ድሙር። ወድሙር ኵሉ ንዋዮሙ ፡-(ነሐ፯ ፡-፷፮። ግብ፪ ፡-፵፬)።
ድሙቅ ፡-የደመቀ ደማቅ፤ ቀለሙ ዕዳያቱ ጽዕዳዌው ቅላቱ ከሩቅ የሚቃይ። ወይትኀጣእ ቅድው ወድሙቅ አልባስ ፡-(ፍካሬ እየስ)።
ድሙን ፡-(ናን ናት ምንት) የዳመነ፤ የጨለመ የጠቈረ፤ ጥቍር። ያቅየሐይሕ ሰማይ ድሙነ። ኮነ ገጹ ድሙነ ወሕብሩ ጽምሑየ ፡-(ማቴ፲፮ ፡-፫። ፊልክ ፡-፻፰፬)።
ድሙፅ ፡-(ፃን ፃት ምፅት) የተሰማ የተደመጠ፤ ጧኺ ድምጣም ፡-(ስንክ ፡-ሐም፲፭)።
ድማኅ ፡-(ኃት) ራስ ጭንቅላት፤ የራስ ቅል ቸብቸቦ፤ ካንገት በላይ ያለው። ፡-(ግጥም) ዋርሳ አታግቡ ብሎ የገዘተ ማነው፤ ዮሐንስ እንደኾን ካንገቱ በላይ ነው ፡-(መዝ ፡-፯። ኩፋ ፡-፳፪)። በከመ ሰካሪ እምሐሩረ ወይን እንተ ተዐርግ ዲበ ድማኁ ይሬኢ ኵሎ ወኢየአምራ ፡-(ፊልክ ፡-፻፮)።
፡-ዐናት ማኽል ራስ፤ የናላ ርግብግቢት ሜዳው ስጡሑ በስተላይ ያለው፤ ለተራራና ለዛፍም። ይኾናል ፡-(ሔኖ፮ ፡-፮። ፲፰ ፡-፰)። ሥዕርተ ድማኅ፤ ቍንጮ ብርንጎ ክብሶ በማኽል ራስ ላይ የሚበቅል የሚከበስ ፡-(ሕዝ ፡-፰ ፡-፫። ዳን፲፫ ፡-፴፮። ኢዮ፲፮ ፡-፲፪)።
ድማም ፡-ድንቅ፤ ድንቂያ ዝምታ፤ አንክሮ። ወተደመ ይሥሐቅ ዐቢየ ድማመ ፡-(ኩፋ ፡-፳፮)።
ድማሬ ፡-(ርያት) መደመር፤ ፡-(ጥደ) መደመር፤ አደማመር ድመራ፤ ደመራ። ኅብረት አንድነት፤ ተዋሕዶ። ሀበነ ለኵልን ድማሬ። እንዘ ኢይዘሮ እምድማሬሁ። ድማሬ ዘህላዌ ጽድቅ ፡-(ኪዳ። ቅዳ ፡-ዮሐ። ቄር)።
፡-1 መቀላቀል፤(ጥቀ) መቀላቀል፤ አቀላቀል ቅልቀላ ድብለቃ፤ ቅልቅልነት። ኢድማሬ ህላውያት፤ የባሕርያት አለመቀላቀል ፡-(ሃይ ፡-አበ)።
ድማኔ ፡-መደመን፤ አደማመን፤ ድመና ጥቍረት ጨለማ። ሰማይ ንጽሕት ይእቲ ወኢይረክባ ርስሐት ወኢድማኔ ፡-(አፈ ፡-ተ፲፮)።
ድምሱስ ፡-(ሳን ሳት ስስት) የጠፋ የተደመሰሰ፤ ድምስስ ያለ፤ ዐይን የሌለው።
ድምሳሴ ፡-ማጥፋት መደምሰስ። መጥፋት መደምሰስ፤ አጠፋፍ ጥፋት። ደመ ክርስቶስ ዘይትከዐው ለድምሳሴ ኀጣውአ ዓለም። ድምሳሴ እደመስሶሙ። ድምሳሴ ኃጥኣን ሰብእ። ማየ ድምሳሴ ፡-(መጽ ፡-ምስ። ዘፀ፲፯ ፡-፲፬። ፪ጴጥ ፡-፫ ፡-፯)።
ድምቀት ፡-መድመቅ፤ አደማመቅ፤ የማሕሌት የዘፈን። ምስጢሩ ልብስን አይለቅም፤ ሲዘምሩና ሲዘፍኑ ለብሰው አጊጠው ነውና።
ድምድማ [1]:-ጕተና፤–ደሚኅ ደምኀ።
[2]፡-ድምድማ፤ ፡-(ማት) ጕተና ጐፈሬ፤ የራስ ጠጕር ፡-(ማሕ፭ ፡-፪ ፲፩። ፩ቆሮ ፡-፲፩ ፡-፲፬)። ቈናዝዕ ወድምድማተ ርእስ ፡-(አዋል)። ጫፍ መጨረሻ መደምደሚያ፤ ክዳን ክፍክፋት፤ ቍንጮ ጕልላት። ድምድማት እንዲሉ ፡-(ዐማርኛ)።
ድምፅ ፡-(ፃት) በቁሙ፤ ድምጥ ጓታ ጩኸት አጧጯኽ፤ የጩኸት ቃል። ድምፅ ፥ ተሰሚው፤ ቃል ፥ ፍሬው። ሰማዕኩ ድምፀ ክነፊሆሙ ከመ ድምፀ ማይ ብዙኅ። ድምፀ አራዊት። ድምፀ ጸሎት ሐዋዝ። ድምፀ ንባቦሙ። ድምፃት መደንግፃት ፡-(ሕዝ፩ ፡-፳፬። ስንክ ፡-ሚያ፲፯። ጥቅ5፮። ጥበ፩ ፡-፱። ፊልክ ፡-፻፲፮)።
ድስቅን ፡-(ጽር ዲስኮስ) ታናሽ ክብ ጻሕል የቍርባን መሥሪያ መቀደሻ። ኢያቅርብ ቢድስቅን ወኢያቅርብ በጽዋዕ። ዲያቆኑ ለቄስ ማለት ነው ፡-(ቀኖ ፡-ኒቅ፲፫)።
ድስቡጣ ፡-(ጽር ዴስፖታ፤ ቴ) ሊቅ እግዚእ፤ ደግ ገዥ። ድስቡጣ ናይናን። ምንስቲቲሙ ድስቡጣ ፡-(ግብ ፡-ሕማ)።
ድሩስ ፡-(ሳን ሳት ርስት) የደረሰ፤ የተደረሰ፤ ድርስ ፍጹም።
ድሩክ ፡-(ካን ካት ርክት) የጠና ጥኑ፤ ብርቱ ጠንካራ፤ ደረቅ ሸካራ፤ ክፋ ጨካኝ። ፡-(የተንደረከከ ብስል ቀይ)። ማእሰር ድሩክ። ልሳን ድሩክ። ቃል ድሩክ። ወዔሳውሰ ውእቱ ብእሲ ድሩክ ወሐቃላዊ ወጸጓር ወኵሉ ግብሩ ድሩክ። ድርክት ከመ ሲኦል ቅንአት ፡-(ስንክ ፡-ጥቅ፳፩። ኅዳ፭። ኩፋ ፡-፲፱። ማሕ፰ ፡-፮)።
ድሩግ [1]፡-(ጋን ጋት ርግት) የተደረገ ድርግ፤ ድርጁ ዝግጁ፤ ቅንጁ።
[2]፡-የተዳረገ፤ ገንዘብ ሰው። ንዋየ ድሩግ ንዋይ ድሩግ ፡-(ፍ ፡-ነ)።
ድሪቆን ድርቲቆን ፡-(ዕብ ርቂዕ) የሰማይ ስም፤ ፪ኛ ሰማይ ኤረር፤ ፪ኛነቱ ለጠፈር ነው፤ ለላይኞቹ ግን ለሰባቱ አንደኛ ይባላል ፡-(አዋል። ቀሌ)።
ድራሞ ፡-ደስክ የንቅልፍ ጋኔን የሚጫን የሚደብት፤ ይልቁንም በጸሎትና በጉባኤ ጊዜ። የመነኮሳት ደረሞኛ ጋኔነ ዝሙት፤ የሚያሳክክ የሚያስፎክት ዕከካም። ያስሕኮ ለሥጋ ወይሬስዮ ለብእሲ ይዝሐቅ ሥጋሁ ዘእንበለ አፅርዖ ፡-(አረጋ ፡-ድ፯)።
ድራር ፡-(ራት) እራት፤ የማታ ምግብ። ምሳሕ አው ድራር። እመሂ በድራር ወእመሂ በምሳሕ። ዘአሕጸጸ ድራሮ ይበይት ጥዑየ ሥጋሁ። ይጸውም ድራረ ፡-(ሉቃ፲፬ ፡-፲፪። ኪዳ። ፈላስ። ስንክ መስ፴)።
፡-ድሮ ዋዜማ፤ ቅበላ። ጾመ ድራረ ልደት ወጾመ ድራረ ጥምቀት። ማኅትው ዘድራረ ጾም ፡-(ፍ ፡-ነ ፡-፲፭። ድጓ)። ዲቃላውን ደርደረ አንደርደረ ብሎ፤ ደረደረ አንደረደረ ተንደረደረ ማለት ከዚህ ይወጣል ፡-(ዐማርኛ)።
ድርህማት ደራህም ፡-ድሪሞች። መጠነ ዐሠርቱ ድርህማት። ደራህም ዘሕልያን ፡-(ፍ ፡-ነ ፡-፴፱። ፈ ፡-መ ፡-፳፭ ፡-፩)።
ድርህም ፡-(ጽር ድራኽሚ። ዐረ ዲርሀም) የገንዘብ ስም፤ ድሪም እንደ ዲናር ያለ የፋርስ ገንዘብ። ዲናርና ድርህም ትክክል ናቸው ፡-(ስንክ ፡-የካ፭። ግብ፲፱ ፡-፲፱። ቀሌ)።
ድርሙስ ፡-(ጽር ድሪሙ) ዱር ደን ሐቅል ብዙ ዛፍና ዕንጨት ያለበት። ሐነጸ ቤተ ድርሙስ ፡-(፫ነገ ፡-፯ ፡-፪)። ድርሙስ ባለው ደግሞ በገዳም ይላል።
ድርማንቅ ፡-(ቃት) የውስጥ የገላ ልብስ፤ ሱሪ ቀሚስ፤ ልብ አልባ ጥብቆ፤ ዐጭር ቍምጣ ወይም ረዥም ጠባብ የወንድ የሴት። ድርማንቅ ዘዐጌ። ድርማንቃቲሆሙ ፡-(ሕዝ፵፬ ፡-፲፰። ዳን፫ ፡-፳፩። ዘፀ፳፰ ፡-፬)።
፡-የመግነዝ ስም የቄስ የመነኵሴ ግንዛት አስተሳሰሩ እንዳስኬማ ያለ፤ ፯ ትእምርተ መስቀል ያለበት። ድርማንቅ ፪ ቃል ነው፤ ድርማ ንቅ ወይም ድር ማንቅ፤ ድርማ ንቅ ሲኾን ድርማ ከድራሞ፤ ንቅ ከነቅሀ የወጣ ይመስላ፤ የሚለበስ ሌት ተቀን ነውና። ድር ማንቅ ሲኾን ግን፤ አለጥርጥር ድር ከድርዕ፤ ማንቅ ከዐነቀ መጥቷል ያሰኛል። የመግነዙም ስም በቁሙ ድርን ማሰሪያን ያሳያል። ፡-(ተረት) ድር ቢያብር አንበሳ ያስር።
ድርሰት ፡-(ታት) መድረስ፤ መደረስ፤ አደራረስ ደረሳ ድርሻ። በቁሙ የምስጋና ቃል፤ ቅኔ መልከ ሰላምታ ግጥም። ነባቤ ዝንቱ ድርሰት አርብዓ ወክልኤ። ድርሰታተ ማሕሌት ፡-(ደራሲ። አርጋ)።
ድርሳን ፡-(ናት) በቁሙ የተደረሰ የተጣፈ ቃል ነገር፤ ሰፊ ንባብ ረዥም ስብከት፤ ትርጓሜ አፈታት፤ ጕሥዐተ ልብ ፡-(ዲዝኩር) መዝሙር፤ ምስጢሩ የሚያጠግብ ቃሉ የሚያረካ፤ አነጋገሩ የተሳካ፤ ጣዕመ ቃሉና ኀይለ ቃሉ ደስ የሚያሰኝ ልብ የሚነካ። ድርሳን በእንተ ሰንበት ዘደረሰ ርቱዐ ሃይማኖት። ድርሳን ዘአባ ያዕቆብ ዘስሩግ ዘደረሰ በእንተ እለ ኖሙ ካህናት ወዲያቆናት። አባ ኤፍሬም ሶርያዊ ደረሰ ድርሳናተ ብዙኃተ ፈድፋደ ፡-(አዋል። ግንዘ። ስንክ ፡-ሐም፲፭)። ድርሳነ ማርያም ፥ ድርሳነ ሚካኤል ቢል ወግ ታሪክ ዜና ማለት ነው። ምስጢሩ ነገር ከማለት ይገባል።
ድርስ ፡-(ዐማርኛ) ልክ እውነት፤ ርግጥ። ድርሱን አገኘኹት እንዲሉ። የምልክት ስም፤ የዜማ ምልክት፤ ፍጹም ማለት ነው።
ድርስ ድራይ ፡-(ጽር ድሪስ፤ ድሪይ፤ ድሪዮስ) የዛፍ ስም በሉጥ። ባለብሉዮች ግን ወይራ ይሉታል ፡-(ኩፋ ፡-፲፫። ፲፬። ፴፩)። ለአብርሃም አብ ቀዳሚ ዘአስተርአይኮ ክርስቶስ፤ ቀትረ ታሐተ ዕፀ ድርስ፤ ተሰቀልከ ከመ እቡስ ፡-(ደራሲ)።
ድርቲቆን ፡-፪ኛ ሰማይ፤–ድሪቆን።
ድርንቅ ፡-(ዕብ ስላው) የባሕር ቆቅ ድርጭት፤ ፍርፍርት በወንዝ ዳር በባሕር ጠረፍ የሚኖር፤ የሠባ ያፈረጠመ ዐንገቱ ከክንፋ የገጠመ። ድርንቅ ማለት ቃሉ ከዶቄት ስፍር ወጥቷል፤ ዐምቆ ደርንቆ እንዲሉ። ያንገቱን ማጠር የሥጋውን መጥበቅ ያሳያል። ወሶበ ሰአሉ መብልዐ ፍግዓ ወተድላ ዐርገ እምውስተ ባሕር ብዙኅ ድርንቅ ፡-(ጥበ፲፱ ፡-፲፪)። ፍርፍርትን እይ።
ድርዕ ፡-(ብ አድራዕ። ዐረ ዲርዕ) ጥሩር የብረት ቀሚስ ሴደርያ በሰልፍ ጊዜ የሚለበስ። ወልታ ወድርዐ እንግድዓ። ዘቦ ድርዕ። ይለብስ ድርዐ ጽድቅ። አልባሰ ድርዖሙ። አድራዕ ወአቅስስት ፡-(ሔኖ፰ ፡-፩። ነሐ፬ ፡-፲፮። ጥበ፭ ፡-፲፱። ፪ነገ ፡-፲ ፡-፬። ፪ዜና ፡-፳፮ ፡-፲፰)። በምስጢር፤ ጥብዐት ትዕግሥት ይኾናል። በድርዐ እንግድዓ ወበጽንዐ ሃይማኖት ወረሰ መን ሰማ ፡-(ድጓ)።
ድርኵኵት ፡-(ታት) የመዝጊያ ቍላ ወንዴ፤ በመድረኩ ላይ የሚቆም የሚተከል፤ ወይም ሴቴው የመድረኩ ፍልፍል መቋሚያውና መተከያው። ከመ ማዕጾ እንተ ተዐውድ ውስተ ድርኵኵታ ፡-(ምሳ፳፮ ፡-፲፬። ዘካ፲፪ ፡-፪። ፫ነገ ፡-፮ ፡-፴፩)።
ድርክሜ ፡-(ጽር ድራኽሚ። ዕብ ቤቃዕ) ድሪም ድርህም፤ የዲድርክም አላድ። ድርክሜ አሐቲ። ድርክሜኑ ለለ ዕለት ፡-(ዘፀ፴፱ ፡-፫። ጦቢ፭ ፡-፲፬)።
ድርያሚን ድብርያሚን ፡-(ዕብ ዲብሬይ ሀያሚም) የብሉይ መጽሐፍ ስም፤ እንደ ነገሥት ያለ፤ ዜና መዋዕል ማለት ነው። ሕጹጻንን እይ፤ ከዚህ ጋራ አንድ ነው ፡-(አቡሻ)።
ድርድር ፡-በቁሙ ዐማርኛ፤–ደሪር ደረ ደርደረ።
ድርገት ፡-(ታት) [1]፡-ማድረግ፤ መደረግ፤ አድርጎት አደራረግ፤ ድርጊያ ድርጊት። አንድነት፤ አንድ መኾን፤ ማኅበር ሸንጎ ጉባኤ። ከመ ያውርሶ መንግሥተ ወድርገተ ምስለ እለ ይነሥኡ አክሊለ። ድርገት ምስለ መላእክት። ድርገተ አኀው። ድርገቶሙ ለቅዱሳን። ኀፍረት ሰቈቃወ ብካይ ማእከለ ድርገተ ማሕሌት ፡-(ቀሌ። ቄር። ፊልክ ፡-፵፬። ተረ ፡-ቄር። መጽ ፡-ምስ)።
[2]፡-(ታት። ዐረ፤ ደረጀት። ሱር ዳርጋ) ደረጃ ዕርከን ማዕርግ፤ የቤት የሹመት። ዘይሴብሕዎ ድርገታተ ሐራ። ወኵሉ ድርገታት ፡-(ድጓ። ቅዳ ፡-ሕር)።
ድርጋሕ ፡-ድሪቶ ደባደቦ፤ ሦስቲዮና አራቲዮ ኹኖ የተሰፋ የተጠቃቀመ ቆብ አሮጌ ጋቢ። ዐዲስ ልብስ ዐርበ ወጥ ገና ያልተሰፋ። አልቦ ዘይጠቅብ ግምደ ድርጋሐ ልብስ ውስተ ሥጠተ ልብስ ብሉይ ፡-(ማቴ፱ ፡-፲፮። ማር፪ ፡-፳፩። ሉቃ፭ ፡-፴፮)።
ድርጎ ፡-በቁሙ፤ ጕርሻ ዳረጎት፤ ተዳራጊ የሚቀበለው። በእንተ ድርጎ ዘይዳረግዎ፤ ኢትከውን አማነ ተዳርጎ ዘእንበለ በሥምረተ ዳራጊ ወተዳራጊ ፡-(ፍ ፡-ነ ፡-፴፫ ፡-፯)።
»ድቀት ፡-(ታት) መውደቅ መሰናከል፤ አወዳደቅ፤ ውድቂያ፤ መከራ ሞት ኀጢአት። እለ ይትፌሥሑ በድቀቱ ለጻድቅ። ድቀት ትጸንሖ። ይከውኑ ለድቀት ኅሱር። ታጎሥኦ እምነ ድቀቱ ከመ ኢይማስን። እስመ መተረ ግብራተ ድቀታት እለ ያርሕቅዎ እምእግዚ ፡-(ሢራ፳፯ ፡-፳፱። ኢዮ፲፭ ፡-፳፫። ጥበ፬ ፡-፲፱። ዲድ ፡-፮። ፊልክ ፡-፩)። በድቀት ፈንታ ውድቀት ይላል፤ ፍችው አንድ ነው። በእንተ ውድቀቱ ለሳዶቅ ካህን ፡-(ክብ ፡-ነገ)። ፪ኛም በፃእፃእ ፈንታ ድቀት ይላል። ለእመ ድቀት ይወርስ አባሁ ፡-(ፊልክ)።
ድቁስ ፡-(ሳን ሳት ቅስት) ያንቀላፋ፤ እንቅልፍ የወስደው የደበተው። ዘይነግሮ ለድቁስ። ኢድቁስ ወኢንዉም ፡-(ሢራ፳፪ ፡-፰። መጽ ፡-ምስ)። በቁሙ ድቍስ፤ ብትን ድልኽ ፡-(ዐማርኛ)።
ድቁቅ ፡-(ቃን ቃት ቅቅት) የደቀቀ ደቃቅ፤ የተወገጠ የተቀጠቀጠ፤ የተደቈሰ የተፈጨ፤ ታናናሽ ቅንጣት። ዕጣን ዘድቁቅ። ተሐርጽ ድቁቀ። ወይከውኑ ድቁቀ አግልዕተ ፡-(ዘሌ፲፮ ፡-፲፪። ዘፀ፴ ፡-፴፮። ኢሳ፴ ፡-፲፬)። ድቁቅ ቃሉ፤ የደከመ የሰለለ ቀጭን ፡-(ስንክ ፡-ነሐ፲፭)።
ድቍንዱቅ
፡-ምድቃሕ፤ ፋስ ምሣር መጥረቢያ። መፍጽሕ ወድቍንዱቅ ፡-(፫ነገ ፡-፮ ፡-፯)።
ድቃል ፡-(ብ ደቃልው። ዕብ ዴቄል። ሱር ዴቅላ። ዐረ ደቀል፤ ተምር) ዲቃላ፤ የዝሙት ልጅ ከሚመሳሰል ከማይመሳሰል የተወለደ። በቅልን ተመልከት።
ድቃስ ፡-ክቡድ እንቅልፍ እንደ ሞት ያለ፤ ስልምታ ሽልብታ፤እንጕልቻ። ወፈነወ እግዚ ድቃለ ላዕለ አዳም ፡-(ዘፍ፪ ፡-፳፩። መዝ ፡-፻፴፩። ምሳ፮ ፡-፬። ሉቃ፱ ፡-፴፪)።
ድቡስ ድንቡስ ፡-ድንቡስ፤ ፡-(ሳት። ዐረ ደቡስ፤ ብ ደባቢስ) ራሳም ችነካር። የበረት በሎታ፤ ወይም ዘንግ ወፍራም ሽቦ ቋራም ስለታም። አዘዘ ይዝብጥዎ በድቡሳት ዘኀጺን ፡-(ስንክ ፡-ታኅ፰። ጥር፩። ሐም፰። ሠኔ፳፯)። ቀሠፍዎ በድንቡሳት በሊኃት እስከ ተሰብሩ ገበዋቲሁ ወቦኡ ውስተ ከርሡ። ድንቡስ ክቡድ፤ ድንቡሳት ዘብርት፤ ፡-(ስንክ ፡-ሚያ፲፪። ፳፮)።
ድቡብ ፡-(ባን ባት ብብት) የተደበበ የተዘረጋ፤ ዝርግ። ደባባ፤ መዳብማ።
ድቡተ ፡-ቀስ ብሎ በቀስታ፤ በሹልክታ፤ ሳይታይ ሳይሰማ። ዐርገ ድቡተ እንተ ካልዕ ገጽ። ወፅአ ድቡተ። ወሶበ ስእነ ሠጊረ ድቡተ ሖረ ፡-(ገድ ፡-ተክ። ድጓ)።
ድቡት ፡-ሽመቃ፤ ቀስታ ዝግታ፤ ድበታ አደባበት። ርቱዕ በድቡት ንገበሮ ለዝ። ከመ ዘበድቡት ወበቀሊል ያሐምመከ ፡-(ግብ፲፱ ፡-፴፮። ሄርማ። ፪ጢሞ ፡-፬ ፡-፪)።
፡-(ጥ) ድቡት፤–ሽመቃ ቀስታ፤–ደቢው ደበወ።
ድባብ ፡-በቁሙ፤ ጃን ጥላ፤ የሚደበብ የሚዘረጋ የሚታጠፍ የሚጠቀለል፤ ጌጥና ሽልማት መረሻት ያለው፤ ወይም ሌጣ። ጸዋሬ ድባብ ፡-(ታሪ ፡-አኵ)።
(ጥ) ድባን ፡-(ዐረ) ዝንብ፤ ደበነ አደበነ ድብን አለ ማለት ከዚህ ወጥቷል።
ድቤ ፡-(ዐማርኛ) ዐፈር መሬት፤ ትቢያ ዐቧራ። ደባ ደቦ ደባይ ደባያት ማለት የዚህ ዘር ነው።
ድብ [1]፡-በቁሙ፤–ደቢው ደበወ።
[2]፡-ድብ፤ ፡-(ባት። ዕብ ዶብ። ሱር ዴባ። ዐረ ዱብ፤ ዱበት) በቁሙ አውሬ የዥብ ወገን፤ የሚያደባና የሚያሸምቅ፤ አድብቶ የሚይዝ የሚነጥቅ፤ ጥላው የሚያፈዝ የሚደብት፤ ጠጕራም ዐመድማ፤ ፡-(ወና ሴ)። ድብ ኀራስ። ድብ ርኁብ። ድብ እንተ ትንዑ። ቤተ አናብስት ወድባት። ከመ ትፈኑ ድባተ ብዙኀ ፡-(፪ነገ ፡-፲፯ ፡-፰። ሆሴ፲፫ ፡-፰። ስቈ፫ ፡-፲። ስንክ ፡-መስ፳፯። ጥበ፲፩ ፡-፲፰)።
፡-ስመ ከዋክብት እነሰባቶ፤ ከመንፈቀ ሰማይ ወዲያ ወደ ሰሜን ወገን ጅብ ብለው ታፍገውና ተመስገው ድርገት ኹነው የሚታዩ፤ ባለመርከቦች የሚመሩባቸው። ኖትያዊ ይኔጽር ኀበ ከዋክብት አመ የሐውር ውስተ ባሕር ዘከመ ይመርሓ ወያከይዳ ለሐመሩ ፡-(ማር ፡-ይሥ፳፰)።
ድብል ፡-(ትግሬ) ልብሰ ዔሊ፤ የደንጊያና የቀንድ ያጥንት ዐይነት ከራራ ጠንካራ። ጥኑ ከባድ ሸክም፤ ጭነት ውድን ወዴላ። በቁሙ፤ ድበላ ያበባ እኽል ሲከኩት ፪ነት ያለው ፡-(ዐማርኛ)።
ድብቱር ፡-የተዘረጋ፤ የተተከለ። ኀበ ድብቱር ደባትረ እሳት ፡-(መጽ ፡-ምስ)።
ድብታሬ ፡-መተከል መዘርጋት፤ ድብትርና ደብተርነት።
ድብዕንኵል ፡-(ላት) ያንበሳ ወጥመድ እንደ ቀፎ ያለ ፡-(ሕዝ፲፱። ገድ ፡-ተክ)።
ድኑስ ፡-(ሳን ሳት ንስት) ያደፈ የረከስ፤ እድፋም። ኢበላዕኩ አነ ግሙራ ርኩሰ ወድኑስ። ንሕነሰ ንሬሲ ኵሎ ርኩሰ ወድኑሰ። ዘማዊ ወድኑስ። ኅሊና ድንስት ፡-(ፍ ፡-ነ ፡-፳፫። አፈ ፡-ድ፳፮። ፴፫። ፊልክ ፡-፻፷፩)።
ድኑን ፡-(ናን ናት ንንት) የደነነ ያደነነ፤ የተጐነበሰ፤ ጕንብስ ጐንባሳ ተርካሳ። ሰይጣን ጐየ በኀፍረት ወበኀሳር ድኑነ። ወርእየ ኵሎ ኀይላተ ሰማይ ድኑናነ በዐውደ መስቀል ቅዱስ ፡-(ስንክ ፡-የካ፬። መቅ ፡-ወን)።
ድናኔ ፡-ድናኔ፤ መጐንበስ አጐነባበስ፤ ጐንባሳነት፤ መቅለስለስ ፡-(ገድ ፡-አዳ)። አውሥኦ ወድናኔ ፡-(ማር ፡-ይሥ፮ ፡-፬)።
ድንቀተ ፡-(ግብተ) ድንገት በድንገት፤ ሳይታሰብ። ድንቀተ ግብተ እንዘ ኢተአምር። በጽሑ ኀበ ሰራዊተ ዳራ እምቅድመ ጽባሕ ድንቀተ። እለ ይነግሩ እምአፉሆሙ ድንቀተ ወኢቀደሙ ጽሒፈ ፡-(ቀሌ። ዮሴፍ። ተረ ፡-ቄር)።
ድንቀት [1]፡-ዝኒ ከማሁ፤ አደናንቅ ድንቂያ፤ ድንቅነት። ድንቅ ብርቅ፤ የሚያስደንቅ። እምአይቴ አምጽአት ዛቲ ብእሲት ዘከመ ዝ ድንቀተ ፡-(ገድ ፡-ተክ)።
[2]፡-(ድድቀት) ድንገት፤ ቆሎ ወዲያው። ምስጢሩ ድንቂያን አይለቅም።
ድንቃዌ ፡-መደንቈር፤ ድንቍርና ደንቈሮነት። ዐጸወ እዝና በድንቃዌ ፡-(መጽ ፡-ምስ)።
ድንቡስ ፡-ችንካር፤ ሽቦ፤–ድቡስ።
ድንባዝ ፡-(ዛት ፥ ድ ንባዝ፤ ነበዘ) መጾር ምዝላል፤ መሎጊያ ወፍራም ደጓሳ ደልዳላ፤ እንደ ዕርፍና እንዳልጋ ዘንግ እንደ ሸማኔ መጠቅለያ ያለ፤ የወሰካ ዕንጨት የሳንሳ የሚይዙበት፤ የታቦተ ጽዮን መሸከሚያ ፡-(ዘፀ፳፭ ፡-፲፫–፲፭)። የመሰንቆና የበገና የክራር ዕንጨት ፡-(፪ዜና ፡-፬ ፡-፲፩)። ዘሩ ነበዘ ነው፤ ሕንጻ ድሕንጻ እንደ ተባለ ንባዝም ድንባዝ ተብሎ ወደዚህ መጥቷል፤ ባለቅኔዎች ግን ደንበዘ ደገፈ ብለው ይገሱና ድንባዝ ባላ ድጋፍ ወጋግራ ይላሉ።
ድንብዕኵል ፡-ያንበሳ ቀፎ፤–ድብዕኵል።
ድንታር ዲንታሮ ፡-የሱሪ መሽቀቅ፤ ጥብጣብ። ማነቆ ሸምቀቆ ፡-(ጥሬ ሰዋ)። ምስጢሩ ዘልፋዊ ማለት ነው። ወከመ ቅናት ዘይቀንት ዘልፈ ፡-(መዝ ፡-፻፰)።
ድንት [1]፡-(ድልት) ስመ ፊደል ራብዕ ደ፤ ለዓለም ዘለዓለም። ድንት ያኑርኽ እንዲሉ። እውነተኛ ስሙ ድልት ነው እንጂ ፥ ድንት አይዶለም፤ ል በን ተለውጧል፤ ዳሌጥንና ድልትን እይ።
[2]፡-ድንት፤ ፡-(ታት) ድንች፤ ነዋሪ የምድር ፍሬ፤ ከተዘራበት የማይጠፋ የማይታጣ።
ድንክ ፡-በቁሙ፤ ታናሽ ዐጭር ዐልጋ። ለሰውም ይኾናል።
ድንዙዝ ፡-(ዛን ዛት ዝዝት) የፈዘዘ ፈዛዛ፤ ደንዛዛ ደብዛዛ፤ እንቅልፋም፤ ሰነፍ ታካታ ደካማ። ወሀቦሙ መንፈሰ ድንዙዘ ፡-(ሮሜ፲፩ ፡-፰። ዕብ፭ ፡-፲፩። ፮ ፡-፲፪)። ኢትኩኑ ድንጉፃነ ወድንዙዛነ። ድምዙዛነ ልብ። ፍካሬሁ ኢኮነ ቀሊለ ወፈድፋደሰ ለእለ ኢይሌብዉ ወኮኑ ድንኩዙዛነ ለሰሚዕ ፡-(ኪዳ። መቃ። ተረ ፡-ቄር፳፩)።
ድንዛዜ ፡-መደንዘዝ መፍዘዝ፤ ፈዛዝነት። ድንዛዜ ወሀኬት እምሰሚዕ። ሀኬት ወድንዛዜ ፡-(አፈ ፡-ድ፲ ፡-ቀሌ)።
ድንገት ፡-(ዐማርኛ) በቁሙ ድንቀት፤–ደኒቅ ደነቀ።
ድንጉል ፡-(ላን ላት ግልት) የደነገለ የተደነገለ፤ ድንግል ጥብቅ፤ ሴት የማያውቅ። ቅድስት ወብፅዕት ወድንግልት ኢዮጰራቅስያ። ነበርኪ ድንግልተ። ደቂቅት ድንግልት ፡-(ስንክ ፡-መጋ፳፮። አርጋ ፡-፬። ፊልክ ፡-፶፰)። ባማርኛ ግን ድንጉል ላ፤ የንብ ውሃ ቀጅ፤ ያልተሰነጋ ፈረስ ማለት ነው። ከበገና አውታርም አንዱ ድንጉል ይባላል።
ድንጉግ ፡-(ጋን ጋት ግግት) የተወሰነ የተደነገገ፤ ውሱን። ኢድንጉግ መለኮቱ በግብረተ ዓለም ፡-(መጽ ፡-ምስ)።
ድንጉፅ ፡-(ፃን ፃት ግፅት) የደነገጠ፤ ድንጉጥ ፈሪ፤ ፍራት የያዘው ያፈዘዘው። ሀሎኩ ድንጉፅየ። ኀለፉ ድንጉፃኒሆሙ። አህጉር ድንጉፃት። ንበሪ ድንግፅተኪ ፡-(ሱቱ ፡-ዕዝ፩። ኤር፱ ፡-፲። ኢሳ፲፬ ፡-፴፩። ፵፯ ፡-፭)።
ድንጕዝ
፡-(ዛት) የጭራ የጠጕር ሥራ፤ ቍንናት፤ ያሠራሩ ዐይነት፤ የሥራው ስም። ጕቾ ብርንጎ ቍንጥርጥር፤ እንደ ሣህለ ሥላሴ ጠጕር። ፡-(ግጥም፤ መጥፎ ተነሳሒ ጠጠቱ የይሁዳን ጠጠት የመሰለ) የወንድሜ ራሱ ጕተናው አማረ፤ እኔም ባልተሠራኹ ይሻለኝ ነበረ። ድንጕዛት ፡-(ፍ ፡-ነ ፡-፶፩)።
ድንጋሌ ፡-መደንገል፤ ድንገላ ጥበቃ፤ ድንግልና። ድንጋሌ ሥጋ። ኀይለ ድንጋሌሁ። መሀሮሙ ለደናግል ለእለ ኢያውስቡ ከመ ይዕቀቡ ድንጋሌሆሙ ከመ ብንተ ዐይን ፡-(አፈ ፡-ተ፳፰። ስንክ ፡-መጋ፲፪። ቀሌ)።
ድንጋጌ ፡-ውሳኔ አወሳስን ውስና። ወሰን ደንበር፤ አሸዋ ደንጊያ። ባሕረ ውቅያኖስ ውሱን በድንጋጌሁ ፡-(አርጋ ፡-)።
ድንጋግ ፡-ዳርቻ ዳር፤ ወሰን ደንበር፤ ወደብ ገደብ፤ አፋፍ ጠረፍ። ኆጻ ዘድንጋገ ባሕር። አልቦ ድንጋግ ለባሕረ ጥበቡ። ወሜጠኒ ኀበ ድንጋገ ፈለግ። ኀበ ድንጋገ ማይ ፡-(ዘፍ፳፪ ፡-፲፯። ቅዳ ኤጲ። ሕዝ፵፯ ፡-፮። ሢራ፳፬ ፡-፲፬)።
ድንጋፄ ፡-በቁሙ፤ መደንገጥ አደነጋገጥ፤ ድንጋጤ ፍራት። ድንጋፄ የልብ የልቡና፤ ፍራት ያንጎል የናላ። ያመጽእ ድንጋፄ ላዕለ አሕዛብ። ዐቢይ ድንጋፄ አኀዞሙ። ድንጋፄ ልብ ፡-(ኤር፵፩ ፡-፪። ዳን፲ ፡-፯። ናሖ፪ ፡-፲)።
፡-እንቅልፍ ራእይ፤ አንክሮ ተደሞ ተመሥጦ። ወድቀ ድንጋፄ ላዕለ አብራም። መጽኦ ድንጋፄ ላዕሌሁ ወርእየ ፡-(ኩፉ ፡-፲፬። ግብ፲ ፡-፲)
ድንግል ፡-(ብ ደናግል) በቁሙ፤ ጥሬ ቅጽል፤ ፍችው እንደ ድንጉል ነው።
ዮሐንስ ድንግል። አሞንዮስ ድንግል። አባ ኖብ
ድንግል ፡-(ድጓ። ፊልክ። ቅዳ)።
ቅጽልነቱና ስምነቱ
የወንድ ብቻ ነበረ፤ መጽሐፍ ግን በጣፎች
ስሕተት ለወንድም ለሴትም ያደርገዋል። ብእሲት
ድንግል። ወለት ድንግል። ወስማ ለይእቲ ድንግል ማርያም ፡-(ዘሌ፳፩ ፡-፲፫። ዘዳ፳፪ ፡-፳፫። ሉቃ፩ ፡-፳፯)።
አንዳንድ ጊዜም ብእሲ ድንግል ወብእሲት ድንግልት ብሎ ይለያል ፡-(ፍ ፡-ነ ፡-፳፬ ፡-፭)።
ድንግልና ፡-በቁሙ፤ ድንግልነት ድንግል መኾን፤ ክብርና፤ ማኅተመ ሥጋ፤ ንጽሐ ሥጋ። በእንተ ምታ ዘድንግልናሃ። አርኰሰ ድገንልናሃ። ዮሐንስ ቅኑት በድንግልና። ዐቀበ ኖኅ ርእሶ በድንግልና ኀምስተ ምእተ ዓመተ ፡-(ዮኤ፩ ፡-፰። ፈ ፡-መ ፡-፮ ፡-፰። ድጓ። ቀሌ)።
ድንግልናዊ ፡-ድንግላይነት፤ ድንግላይ፤ ባለድንግልና። በዓለ ልደት ድንግልናዊ። እም ድንግልናዊት ፡-(አቡሻ ፡-፴፬። አርጋ ፡-፪)።
ድኢም ሞት ፡-(ደአመ ይድእም ይድአም ዐረብ) መትከል ማቆም ማጥናት፤ ማሸራሸት ማጥበቅ፤ እንዳይወድቅ እንዳይነቃነቅ ማድረግ፤ መመሥረት፤ የግብር የነገር፤ ከጥሬው በቀር አንቀጹ አይገኝም።
ድኩም ፡-(ማን ማት ክምት) የደከመ ደካማ ኰሳሳ፤ ታናሽ ወራዳ፤ አሮጌ በሽተኛ፤ ልም ልምሉም፤ ርጥብ ለጋ ጨቅላ። ድኩም ወጽኑስ። መንግሥት ድኩም። ልደትኪ አማሕፀነ ድክምት ሥጋ። አዕይንቲሃ ድኩም። ልሳን ድክምት። ድኩማን ደቂቅ ፡-(ገላ፬ ፡-፱። ሕዝ፲፯ ፡-፲፬። ስንክ ፡-ግን፩። ኩፋ ፡-፳፰። ምሳ፳፭ ፡-፲፭። ዘፍ፴፫ ፡-፲፫)።
ድኵዕ ፡-(ዕብ ዳክእ ዐፈር ትቢያ)። ፍግ ፋንድያ በጠጥ፤ ዐዛባ። ይከይድዎሙ ከመ ድኵዕ። እክዑ ድኵዐ። ተግሣጽ ለሕፃን ያሤንዮ በከመ ያሤንዮ ድኵዕ ለምድር ፡-(ኤር፰ ፡-፪። ሉቃ፲፫ ፡-፰። ፈላስ ፡-ገ፰)።
ድካም ፡-(ማት) በቁሙ፤ ስንፍና ሀኬት፤ ልፋት ጥረት አገልግሎት። እንበለ ድካም። ከመ ያእምር ድካሞ። ድካመ ፍጥረቱ ወአእምሮቱ። ሑጻጼ ወድካም። ዕሴተ ገድላቲሆሙ ወድካማቲሆሙ ፡-(ስንክ ፡-ጳግ፪። ኢዮ፴፯ ፡-፮። ፊልክ ፡-፻፸።ዮሴፍ። ፈ ፡-መ ፡-፩ ፡-፪)።
ድክመት ፡-መድከም፤ አደካከም፤ ድካም ደካምነት። እምድኅረ ርሥኣኑ ወድክመቱ ፡-(ፊልክ ፡-፶፪)።
ድክምና ፡-ደካምነት፤ ድካም። እንዘ ሀለውክኒ አንቲ ለድክምና መጽንዒ ፡-(አዋል)።
ድክቱም ፡-(ማን ማት ትምት) የደኸየ የተጣለ፤ አባት እናቱ የሞቱበት። ድክትምት ይእቲ እምአቡሃ ወእማ። ድክእቱማን ፡-(ኦዋል። ፍ ፡-ነ ፡-፳፬ ፡-፫)።
ድክታሜ ፡-ድክትምና፤ ድኽነት አይቶ ዐጣነት፤ የሙት ልጅነት። በእንተ ዕጓለ ማውትናሆሙ ወድክትምናሆሙ ፡-(ዮሴፍ። ፍ ፡-ነ ፡-፲፮)።
ድዉይ ፡-(ያን ያት ዱያን፤ ድውይት ዊት) በቁሙ፤ የተደወየ፤ ደዌ ያደረበት፤ ታማሚ በሽተኛ። ኢትትሀከይ ሐውጾ ድዉይ።ዘድዉይ ሥጋሁ። በእንተ ድዉያን። መጋቤ ዱያን። ነፍስ ድውይት ፡-(ሢራ፯ ፡-፴፭። ፴ ፡-፲፬። ፍ ፡-ነ ፡-፳፩። ሲኖዶ)።
ድዩን ፡-(ናን ናት ይንት) የተዳኘ የተቀጣ፤ ፍርድ የለበሰ፤ የተፈረደበት።
ድያስ ድዮስ ድያ ፡-(ጽር ፡-ዲዎስ) ወፍራም ረዥም ጣዖት፤ አምላክ ዐቢይ ማለት ነው። ዜዉስን እይ ፡-(ግብ፲፬ ፡-፲፪ ፡-፲፫። ስንክ ፡-ኅዳ፲፬)።
ድድ [1]፡-መሠረት፤–ወዲድ ወደ።
[2]፡-»ድድ፤ ፡-(ዳት) በቁሙ፤ ማውድ መሠረት፤ ምዕማድ ስክተት። ድደ መሠረት። ዐምዳ ወድዳ ለጽድቅ። ይጸውር ድደ ወይነብር ጠፈረ ፡-(ቆላ፩ ፡-፳፫። ፩ጢሞ ፡-፫ ፡-፲፭። ቅዳ)።
ድድቅ ፡-(ቃት) ድንገት፤ ድንገተኛ ያልታሰበ፤ አደጋ ሞት ጥፋት፤ ክፉ ነገር ኹሉ። አሑዱ ድድቅ ይዳደቆሙ ለክልኤሆሙ። ተዳደቆ ድድቅ ለውእቱ ንዋይ። ምንዳቤያት ወድድቃት። እምኵሉ ድድቅ ዘይጸንሖ ለዕጓለ መሕያው። እምድድቅ ዘውስተ ማያት ፡-(መክ፪ ፡-፲፬። ፍ ፡-ነ ፡-፵፩ ፡-፭። መቃ ፡-ገ፳፬። አርጋ ፡-፫። ደራሲ። መዝ ፡-፺)።
ድጉም ፡-(ማን ማት ግምት) የተደገመ፤ የተደጋገመ፤ ዕጥፍ ድርብ። የተደገመበት።
ድጉጽ ፡-(ጻን ጻት ጕጽት) (ጻን ጻት ጕጽት) የተወጋ የተነካ፤ የተደጐሰ ፡-(ስንክ ፡-ሠኔ፲፮)።
ድጕዓ
፡-(ሐማሴን) አልቃሽ አሟሽ ገጣሚ። ቍዘማ የልቅሶ ዜማ፤ ሙሾ ግጥም። ድጓን ተመልከት፤ የዚህ ዘር ነው። ድጕዓ ደግሞ ከጐድዐ ወጥቷል።
ድጕጸት
፡-መውጋት፤ መወጋት መነካት፤ ንኪት ሰንበር ዕበጥ፤ ድጕስ ድጐስት። እንበለ ሕማም ወእንበለ ድጕጸት ፡-(መጽ ፡-ምስ)።
ድጋም ፡-በቁሙ፤ መድገም፤ መደገም አደጋገም ደገማ፤ ድግሚያ ጸሎት።
(ጥ) ድግ ፡-በቁሙ፤ መቀነት፤ የሆድ ካሳ የወገብ ምሳ፤ ወገብ የሚያጠና የሚደግፍ።
ድግዱግ ፡-(ጋን ጋት ድግት) የከሳ የቀጠነ፤ ቀጭን ደግዳጋ፤ ኰሳሳ ከሻዋ። ድግዱግ ሥጋሆሙ። ድግዱጋኒክሙ። እስክንድር ድግዱግ መልክኡ። ኮነ አባ ብሶይ ድግዱገ ፡-(ዘፍ፵፩ ፡-፫። ዳን፩ ፡-፲። ዮሴፍ። ስንክ ሐም፰)።
ድግዳጌ ፡-መክሳት መቅጠን፤ አከሳስ፤ ክሳት ደግዳግነት ፡-(ስንክ ፡-የካ፳፭)። መቃጥቅ መልበስ፤ አለባበስ አስተጣጠቅ፤ ትጥቅ ድግድጋት። ዱግ ዶግ ማለት ከዚህ ወጥቷል።
ድጓ [1]:-የዜማ መጽሐፍ፤–ደጊግ ደገ ደግደገ።
[2]፡-የዜማ መጽሐፍ ስም፤ ቅዱስ ያሬድ ባፄ ገብረ መስቀል ዘመን ያዜመውና የገጠመው። የኋላም ሰዎች በየጊዜው ጨምረውበታል፤ ፻፶ው መዝሙር የዳዊት ብቻ እንዳይዶለ፤ ድጓም የያሬድ ብቻ አይዶለም። ድግዱግ ድግዱግ ጽሕፈት፤ ጥፈቱ የከሳ የቀጠነ ደቂቅ ረቂቅ የኾነ፤ አሸዋ እብቅ፤ ወይም ዜማ ቍዘማ፤ ግጥምና ዜማ ማለት ነው። ድጕዓን ተመልከት። በደጎ ዘይቤ ሲፈቱት ግን፤ ደግ ደገኛ አሰኝቶ የመጽሐፉን መጠን ታላቅነቱን ያሳያል፤ በርቀቱ ላይ የመንፈቅ ስንክሳር ያኽላልና። ፪ኛም፤ ምእላድ መድበል እስትጉቡእ ብለው ይፈቱታል፤ ቃሉ ከገድል ከታምር ከአዋልድ ሳይቀር፤ ከብሉይ ከሐዲስ ከሊቃውንት ተለቅሞ ተቀሥሞ የወጣ ድርሳን ኅዉሥ መዝሙር ሐዲስ ማለት ነው። ፫ኛም፤ በፊደል ቍጥር ሲፈቱት ደ ፡-፬ ፡-ገ ፡-፫፤ ድጓ ፡-፯ ይኾናል፤ እስመ ኍልቈ ሳብዕ ፍጹም ውእቱ ይላልና ፡-(ሃይ ፡-አበ) ፯ ፍጹም ቍጥር ነው። ድጓ ማለትም እንደ ስንክሳር ካመት እስካመት የተሠራ በየሱባዔው ከሑድ እስከ ቀዳም ዕለት ዕለት ጧት ማታ የሚቀርብ ፍጹም ድርሰት መሧዕተ ስብሐት መኾኑን ያሳያል፤ ዋዜማ ዘሠርክ ዕዝል ዘነግህ ስብሐተ ነግህ ይላልና። እየብቻውም ነጥሎ ቢፈቱት፤ ድ የክፍሉን ትርብዕት፤ እንደ ወንጌል ባ፬ ዐቢይ ክፍል ተከፍሎ፤ ዮሐንስ ፥ አስተምሕሮ ፥ ጾም ፥ ፋሲካ መባሉን፤ ጓ ምዕራፍን ዝማሬንና መዋሥዕትን ሦስቱን ያሳያል። ዳግመኛም ዋይ ዜማ ዘሰማዕኩ በሰማይ እመላእክት ይላልና፤ ሰባትነትን ለዜማው ብቻ ቢሰጡት፤ ድ የስልቱን ትርብዕት ቁምን ዝማሜን መረግድን ጽፈትን ያሳያል፤ እሊህ አራቱ የኪሩቤል አምሳል ናቸውና። ቁም ከመ ኪደተ ብእሲ፤ ዝማሜ ከመ ኪደተ አንበሳ፤ መረግድ ከመ ኪደተ ላሕም፤ ጽፍዐት ከመ ኪደተ ንስር፤ወእሱ ይትሜሰሉ በአርባዕቱ እንስሳ ፡-(ገድለ አብርሀ ወአጽብሐ)። ጓ የዜማውን ትሥልስት ዜማው ግእዝና ዕዝል አራራይ መኾኑን ያሳያል። ዜማ ጠቅላይ ስም ነው ያንድነት፤ ስሙ የሦስትነት። ምልክቱ ግን የኋላ ሰዎች ያበጁት ነው፤ የያሬድ አይዶለም። ወበመዋዕሊሁ ለዝንቱ ንጉሥ ገላውዴዎስ ተንሥኡ አዛዥ ጌራ ወአዛዥ ራጉኤል ካህናት ማእምራነ ዜማ ወወጠኑ አውፅኦ ምልክት ዘድጓ ፡-(ታረ ፡-ነገ)። ከዚህ የቀረውን የድጓን ዘይቤ ምስጢርና አፈታት ከድጓ መምህራን ይጠይቋል።
ድፉር ፡-(ራን ራት ፍርት) የተደፈረ የተናቀ የተጠቃ ጥቁ።
ድፉን ፡-(ናን ናት ፍንት) የተደፈነ የተቀበረ፤ ስውር ድብቅ ፡-(ኢያ፯ ፡-፳፩ ፡-፳፪)። ያልተቈረሰ ያልተከፈተ፤ ድፍን ምሉ ፍጹም፤ እንጀራ ቅል፤ የመሰለው ኹሉ። ለሀገርና ለሕዝብም ይኾናል፤ ድፍን ዐማራ ፥ ድፍን ትግሬ፤ መላው ጠቅላላው፤ ፩ ሳይቀር። .
ድፍረት ፡-በቁሙ፤ መድፈር መደፈር አደፋፈር፤ የትቢትና የጭካኔ ሥራ። ዝንቱ ይከውን ድፍረተ ወተኀብሎ። ያሴስል ድፍረተ ዝኁራን። ይትናገሮ ለንጉሥ በድፍረት ዘእንበለ ፍርሀት። በድፍረትክሙ ለእመ ቀረብክሙ። ነሢአ ሥጋሁ በድፍረት። ወድፍረት ውስተ ሀርብዶ ፡-(አፋ ፡-ተ፭። ቈስጠ ፡-፶፩። ስንክ ፡-ሠኔ፲፩። ቅዳ። አፈ ፡-ወር። ማር ፡-ይሥ፳፰ ፡-፫)።
ድፍነት ፡-መድፈን፤ መደፈን፤ አደፋፈን አቀባበር። ድፍነተ ምዉት ውስተ ምድር ከመ ዘሪዐ ዘርዕ ውስቴታ። እምቅድመ ድፍነተ ምዉታን ፡-(ግንዘ)።
ድፍዕ ፡-ድፋት አደፋፍ፤ ድፎ።
ድፍድፍ ፡-ጭቃ፤ የጠላ ቡሖ። ተሰብረ ገንዕ ወኢተክዕወ ድፍድፍ ፡-(ገድ ፡-ተክ)።
ዶርከኖ ፡-(ዕብ አርጋማን) ኀምራዊ ቀይ ሕብር ደባባ የበሰለ ፍሬ ወይም የጥቍር ወይን ደም የሚመስል። በርሱ የታለለ ልብስ ፈትል። መጻሕፍት ግን በያክንት ፈንታ ደርከኖ ይላሉ፤ መምህራንም ሰማያይ ይሉታል ፡-(ራእ፱ ፡-፲፰)።
ዶሐን ፡-(ዕብ ወሱር።ዐረ ዱኅን) ስመ እክል፤ አንድ ዐይነት እኽል፤ አገዳው ላንፋው የማሽላ፤ ዐጫጭር ቀጫጭን ፍሬው የዳጕሳ ዐይነት ፡-(ሕዝ፬ ፡-፱)።
ዶር [1]፡-(ዐረ ዱር፤ ዶረ ጠራ በራ) ጥሩ ወርቅ፤ ዕንቍ ፈርጥ፤ በወርቅ ኅርወት የሚሰካ። ወማእከሌሆሙ ታቦተ ዶር ዘስርጉት በሡራኄ ጸዳል። ታቦት ዘዶር ፡-(መጽ ፡-ምስ። ቅዳ ፡-ሕር)።
[2]፡-(ዕብራ) ትውልድ፤ ዘመን፤ የትውልድን ፍች ተመልከት። በዶሮሙ ፡-(ዘፀ፴ ፡-፲)። በዐረብ ግን፤ ዶር ተራ፤ ዱራ ዑደት ይኾናል።
[3]፡-ጥሩ ወርቅ፤–ደዊር ዶረ ደወረ።
ዶርሆ ፡-(ብ ደዋርህ) ዶሮ፤ ብዙ የሚወልድ የሚዋለድ ለማዳ የቤት ወፍ። ምስጢሩ መርባት ነው፤ ወንድና ሴት ያስተባበራል። በድምፀ ክነፊሆሡ ለሱራፌል ይነቁ ዶርሆ። ዶርሆ ተባዕት። ከመ ዶርሆ እንተ ታስተጋብእ ዕጐሊሃ ታሕተ ክነፊሃ። መጋዝአ ደዋርህ። ክልኤተ እልፈ ደዋርሀ ፡-(ቀሌ። ምሳ፳፬ ፡-፷፮። ማቴ፳፫ ፡-፴፯። ፫ነገ ፡-፬ ፡-፳፫። ገድ ፡-ተክ)።
፡-በቁሙ ዶሮ፤–ዶር ደወር።
ዶርቃስ ፡-(ጽር ዶርካስ) ፌቆ፤ ወይጦ ልንና ጣቢቃን እይ፤ ከዚህ ጋራ አንድ ነው። ባለሐዲሶች ግን ድሪቶ ጁሕ ጀባ ይሉታል ፡-(ግብ፬ ፡-፴፮ ፡-፴፱)።
ዶርገ ፤ ባንድነት አንድ ኹኖ ፤ ዐብሮ። ደርገ ይፌውስ። ዐጠነ ደርገ ምስሌሆሙ። ከመ ታዕርፍ ነፍሶሙ ወይኵኑ ደርገ ምስለ ሊቃናት ሰማያውያን
(ቄር። ገድ ፡ ተክ። ግንዘ)።
ዶታይም ን ፡-ስመ ሀገር፤ የኢይዝራኤል ቅርብ አጠገብ ፡-(ዘፍ፴፯ ፡-፲፯)።
ዶዲ ፡-የሰው ስም፤ ወዳጄ ዘመዴ ማለት ነው ፡-(፪ነገ ፡-፳፫ ፡-፳፬)። አንዳንድ መጣፍ ግን ዱድ ዶዳኢ ይላል፤ ስሕተት ነው። ዱድ ፥ ታላቅ ድስት ቅርጫት፤ ዱዳኢም ፥ የሽቱ ቅጠል ነው፤ ዕንጐትን ተመልከት።
ዶድ ፡-(ዕብራ። ሱር ዶዳ) አጐት፤ ያባት የናት ወንድም፤ ያክሥት ባል። ወዳጅ ዘመድ ባልንጀራ፤ እኩያ አምሳያ፤ ዐብሮ አደግ ወንድም አከል።
ዶፎኒ ፡-(ሱር ፡-ዱፍና) የሬሳ ሣጥን፤ አስክሬን። ዶፎኒ ጸበተ ፡-(ስንክ ፡-መጋ፰)።
~ ጀ ~
ጀውዛ ፡-ስመ ኮከብ፤–ገውዛ።
ጀይብ ፡-(ዐረብ) የቀሚስ ሕፅን ሰላጤ፤ በሰላጤው ላይ የሚሰፋ ኪስ ከረጢት፤ ውስጠ ክፍት ኹኖ ማረሚያ ገንዘብ የሚከት ፡-(ፈ ፡-መ ፡-፴፩ ፡-፭)። ምስጢሩ የዲብና የድብኝት ነው።
No comments:
Post a Comment