~ቀ~

                                 

-፲፱ኛ ፊደል በግእዝ አልፍ ቤት በአበገደ፤ ስሙ ቆፍ፤ ቍጥሩ መቶ፤ አኃዝ ሲኾ -() ምእት ይባላል። ዳግመኛም መቶነቱን ሳይለቅ ከኈ በኋላ ያ፲፻ አኃዝ እየኾነ ስለ ሺሕ  ይጣፋል። ይህም ኈ፱፻፤ ቈ፲፻ እ፻፻ እያለ መኼዱን ያሳያል ያቡጊዳን አኃዝ ተመልከት

ቀሓሚ -(ሚት ምያን ያት፤ ሐምት) የሚቅም፤ ቃሚ ገታሚ ጥሬ በል

ቀሕቅሖ ሖት -(788) -(ቀሕቅሐ ይቀሐቅሕ ይቀሕቅሕ። ዐረ ቀሕቀሐ ሱር ቃሕቃሕ) መቈርቈር፤ መቀብቀብ፤ መጠብጦብ፤ የሰደቃ የጣት ለመጥራት፤ ወይም እገሌ በማለት ፈንታ እህ ዕሽ ማለት በጣት ማመልከት፤ ውሰድ አምጣ ማለት፤ በጸሎት በማእድ ጊዜ ሥሩና ምንጩ ቆቅሐ ነው፤ ከቈቍዐም ጋራ ይሰማማል ዐና ይዋረሳሉ ወእመ ዘትፈቅድ በውስተ ማእድ ትንብብ ቀሕቅሕ። ልቦ ዘይትናገር፤ አላ ይቀሕቅሑ -(ሥር -ጳኩ)

ቀለም [1]-(ማት፤ አቅላም) በቁሙ፤ ሕብር፤ ፈሳሽ ዐይነት፤ መጣፊያ ማቅለሚያ። ጽሑf በቀይሕ ቀለም ወበጸሊም ቀለም ንበለ ቀለም። ጸሐፍ ስምየ በረቀ መርዓ ገቢረከ ሲለደስ ለዘኮንኩ ኃጥአ ደመከ ቀለመ ወዐፅመከ ብርዐ -(አቡሻ -፵፮። ስንክ -ታኅ፳፪። ድጓ)

[2]-(ዐረብ  ጽር ላሞስ ዕብ ቃኔ) ብርዕ የቀለም መንካ፤ መጥለቂያ ከዕ ከኀጺን የሚሠራ፤ ወይም ጸሓፊው የሚቀርጠው ውስጠ ክፍት መቃ ሸንበቆ ቀስተንቻ፤ የመሰለው ኹሉ ቀለመ ኀጺን። ከመ ቀለመ ጸሓፊ በማየ ሕመት ወበቀለም -(ኤር፲፯ - መዝ -፵፬። ዮሐ -፲፫)

[3]-(ዕብ ቄሤት) የቀለም ቀንድ፤ ቢልቃጥ፤ ሙዳየ ቀለም ቀለመ ጸሓፊ በሐቌሁ -(ሕዝ፱ -)

 -መልክአ ፊደል፤ የፊደል ቅንጣት፤ አንዳንዱ ኅርመት ግእዝ ቀለም ሳድስ ቀለም፤ ሰባት ቀለማት እንዲሉ -(ባላገባቦች)

 -ትምርት፤ ዕውቀት፤ ከመጽሐፍ ከመምር የሚገኝ -(ሙሾ፤ የተማሪ እናት፤ ልጇን ዳግም ግራኝ ስላቃጠለባት) ይማርልኝ ብዬ በጌ ምድር ሰድጄ ቀለም ገባው አሉ እሳት ኾነ ልጄ። -(የተማሪ እኅት ሊቅ ወንድሟ ሙቶ ሲቀበር) ዐፈር መልሱ እንጂ ደንጊያ ለምናችኹ የቀለም ቀንድ ነው ትሰብሩታላችኹ።

ቀለምጤዳ -(ጽር ክሊማቲዳ) የወይን ዕንጨት፤ ዐጽቁ ሐረጉ ተቈርጦ የወደቀውና የደረቀው ጭራሮው ጭራንፎው ባለብሉዮች ግን ቍልቋል ይሉታል -(ዳን፫ -፳፪ ስንክ -ሐም፭) ቀለምጤዳ በማለት ፈንታ አቅላሚዶን ይላል፤ ስሕተት ነው -(መጽ -ምስ)

ቀለምሲስ -ከፊለ ስም፤ አቡቀለምሲስ።

ቀለምጺጽ -(ጺጸ ቀለም) ጺጽ ከጻጹት መጥቷል። የእሳት ብራሪ፤ ፍንጣሪ። የምጣድ ቂጥ እሳት ብልጭልጭታ ጺጽ እሳቱ ብልጭታው ጣጣቴው፤ ቀለም ጥላቱ ሕመቱ ቃለ ቀለምጺጽ -(ጥበ፪  -፲፱)

ቀለንቶን -(ጽር ሌንዴ) መባቻ የወር መዠመሪያ ሠርቀ ወርኀ ወበወርኀ ሮሜ ቅድመ ዕሥራ ወሰመንቱ ቀለንቶን -(ተረ -ር፳፭)

ቀለጰ ቀልጰጰ -(ዐረ ቁለብ ቀለበ) ነከሰ ነደፈ ዋጠ፤ ሰለቀጠ፤ የአክይስት ነጠቀ ወስደ ጐፈጨረ፤ ሰበረ ዘበተረ፤ የአንስርት የአራዊት። በህየኒ እኤዝዞ ለከይሲ ወይቀልጶሙ። ወደይዎሙ ውስተ ግብ ወቀለጵዎሙ አናብስት ዘእንበለ ይብጽሑ ምድረ። በዘኢይክሉ ቀልጵጶቶ መስተቃርናነ ሠናይ -(ዓሞ፱ -፫። ገድ -ተክ መጽ -ምስ ቄድር)

ቀሊል -(ላን ላት ላል) በቁሙ የሚቀል ቀላል ከፊፍ ታናሽ ጥቂት ጾርየ ቀሊል ደለዎ ወኮነ ቀሊለ እምኵሉ ማያተ ፍራቅያ ቀሊልኑ በኀቤክሙ አስተፅብሶተ ሰብእ -(ማቴ፲፩ -፴። ዮሴፍ። ኢሳ፯ -፲፫)

 -ፈጣን፤ ቀልጣፋ ችኩል ደመና ቀሊል። አኮ ቀሊላን ረዊጽ ቀሊላት እገሪሁ ቀላለ ኮነት ሕይወትየ -(ኢሳ፲፱ -፩። መክ፱ -፲፩ ፪ነገ - -፲፰ ኢዮ፯ -)

ቀሊል ሎት -(ቀለ ይቀልል ይቅልል ዕብ ቃላል ሱር ቃል ዐረ ቀለ) መቅለል ማነስ ሚዛን ከአንጻር። ቂል ማለት ከዚህ ወጥቷል። አበሳ ዘኢይቀልል እምዝኩ። ምንት ይቀልል ምብሂል ትቀልል ሲኦል እምኔሃ -(አፈ -ተ፳፯ ማቴ፱ -፭። ሢራ፳፰ -፳፩) ቀልቀለን እይ፤ የዚህ ዲቃላ ነው።

 -መፍጠን፤ መቀልጠፍ፤ ፈጣን ሯጭ መኾን። ይቀሉ ምንስር ይቀልል ሩጸቶሙ ምነፋስ ኅሊና ይቀልል ወይሰርር እምኵሉ ክንፍ -(፪ነገ - -፳፫ ቀሌ። አፈ -ተ፳፪) በቀለ ፈንታ ተቀለለ ይላል፤ ስሕተት ነው ይትቀለሉ ምኀጢአቶሙ። ይትቀለሉ ምጻዕር -(ሱቱ -ዕዝ፯ ኪዳ)

ቀሊም ሞት -(ቀለመ ይቀልም ይቅልም) መቅለም ማቅለም መጣፍ፤ ማሳደፍ መበከል፤ ከቀለም ማግባት መንከር፤ ማለል ማግዘፍ የቃል የልብስ ሀበነ ከመ ንጽሐፍ ወጸግወነ ከመ ንቅልም -(አረጋ -ድ፩)

ቀሊስ ሶት -(ቀለሰ ይቀልስ ይቅልስ። ዕብ ቃሌስ፤ ሣቀ ተሣለቀ) መቀለስ፤ ማስጐንበስ፤ ማረቅ፤ ማጕበጥ።

ቀሊብ ቦት -(ቀለበ ይቀልብ ይቅልብ። ዐረብ) መቅለብ፤ እያጓኑ እያነጠሩ መልሶ መያዝ መቀበል፤ መገልበጥ ማፍሰስ መከንበል፤ ማሸነፍ ድል መንሣት፤ በላይ መኾን ቀለጰን እይ የዚህ መንቲያ ነው ምንት የዐጽብ ምዘይቀልብ ብዙኀ አስይፍተ -(አፈ -ተ፲፮) ቀለብ ማለት ከቀለበና ከቀለጰ ከ፪ ወጥቷል

ቀሊዕ ዖት -(ቀልዐ ይቀልዕ ይቅላዕ ዐረ ቀለዐ ዕብ ቃላዕ) መቅላት መክላት መግለጥ መግፈፍ ማውለቅ የልብስ የመጋረጃ የመጣፍ ብእሲቶ ለምንት ትቀልዒ ልባቤ ርእስኪ እንዘ ትሥሕቂ አዘዘ ይቅልዑ ልባቤ ገጻ ዘዘ ይቅላዕ ልብሶ ፍረት ቀሊዕ መጽሐፍ ለዘኢየአምር ሆህያተ -(አፈ -ተ፲፭ ስንክ -ኅዳ፲፮ ታኅ፲። መጽ -ምስ)

 -መምታት፤ መልጋት፤ ማጠንጋት፤ ለመወርወር የኳስ የጥንግ

 -ማወንጨፍ፤ መተኰስ፤ አርቆ መጣል፤ የደንጊያ ያረር

ቀሊው ዎት -(ቀለወ ይቀሉ ይቅሉ። ዕብ ቃላህ። ዐረ ቀላ) መቍላት፤ ማመስ መጥበስ፤ መለብለብ፤ ማንኰት። ቀሊወከ -( -) በቀለወ ፈንታ ቈለወ ይላል ያማርኛ ነው

ቀሊድ -(ቀለደ። ዐረብ) መቅዳት፤ ማከማቸት፤ የውሃ። መቀለድ ቀልደኛ መኾን። መቀንደብ፤ ቅንድብን መብጣት መፍቃት፤ ስላይን በሽታ

ቀላሚ -(ሚት ምያን ያት) የሚቀልም፤ የሚያቀልም፤ ጣፊ ታቢ፤ ቀለም አግቢ።

ቀላቂል -(ትግሬ) ቈላ ሜዳ፤ ዘብጥ ረባዳ፤ የገደል ሥር፤ የተራራ እግር።

ቀላዒ -(ዒት ዕያን ያት) የሚቀላ የሚያወልቅ፤ ገላጭ ገፋፊ እግዚ ብርሃነ ልብየ ቀላዔ ግላ -(ጥበ -ጠቢ)

ቀላውትሞኖስ -(ጽር ክላፍትሞኖስ) ብካይ፤ ልቅሶ ብራይስጡ ግን የቱት ዛፎች ይላል ቱት የሐር ዛፍ ነው -(፪ሳሙ - -፳፫) ቈላተ ብካይም እንደዚህ ነው። ባካ ብካኢም ዛፍ ብኪ ልቅሶ ይባላል፤ በዚህ ምክንያት ተሳሳቷል።

ቀላይ -(ያት) በቁሙ፤ ጥልቅ ጠሊቅ፤ ዕመቅ፤ የባሕር የፈለግ። ቀላየ ባሕር። ቀላያተ አፍላግ ቀላያተ ማያት -(ኢሳ፶፩ -፲። ኢዮ፳፰ -፲፩ መዝ -፸፮)

ቀልቀል -(ላት) ገደል፤ ተራራ፤ አንባ፤ የተራራ ዙሪያ ርእሰ ቀልቀል ከመ  ዘማእከለ ቀልቀል ታንሶሱ ኢትንበር ደወለ ቀልቀል ምስለ ጸላኢከ ከመ ኢያጽ ድፍከ -(፪ዜና -፳፭ -፲፪ -፪። ሢራ፱ -፲፫ መጽ -ምስ) ቍልቋል፤ ቈለቈል ማለት ከዚህ ወጥቷል፤ የቈላ የቍልቍለት ዛፍ ያሰኛል።

ቀልቅሎ ሎት -(ቀልቀለ ይቀለቅል ይቀልቅል። ዐረብ ዕብ ቂልቃል) መቀልቀል፤ መደብለቅ መደበላለቅ፤ ማማሰል መነቅነቅ፤ መናድ ማፍረስ ማውለቅለቅ፤ ማጥፋት ማበላሸት።

ቀልብ -ሐሳብ ምኞት፤ ውበት ደም ግባት፤ ባለሟልነት መወደድ መክበር፤ አቦ መባል ቀልባም ቀልበ ቢስ እንዲሉ

ቀልይ ዮት -(ቀለየ ይቀሊ ይቅሊ ቀለወ) መጥለቅ መጐድጐድ፤ ዕሙቅ ጥልቅ ኾን ይቀሊ እምቀላየ ቀላያት ወይትሌዐል መልዕልተ ሉዓሌ -(መጽ -ምስ)  

 -ጠልቆ ማወቅ፤ መዝለፍ መገሠጽ፤ መውቀሥ መክሰስ መፍረድ መመስከር፤ የልብ የኅሊና። ይቀልየከ ልብከ ሊተሰ ፈድፋደ ያሐዝነኒ ወያቴክዘኒ ወይቀልየኒ ልብየ -(፫ነገ - -፵፬። መቃ -፲፱ ሮሜ፪ -፲፭ ፩ዮሐ - -፳፩)

ቀልደድ -ቅንድብ፤ ሽፋል የዐይን ከንፈር ወይም ጕድጓዱ ሬው፤ ብሮንዶው እንደ ውሃ ኹኖ የመላበት። ፀይንኽ ይፍሰስ እንዲሉ። ቀልደደ ዐይን -(አርጋ -)

ቀልድ ቀላድ -(ዐማርኛ) በቁሙ ቀላጅ፤ ቀላድ ጣይ እንዲሉ።

ቀልፎንያ -(ሮማይ ኮሎፎንያ) ሙጫ እንደ ዕጣን ያለ፤ የሚሸት የሚቃጠል፤ መጣብቅ የሚኾን። ቃር ወፒሳ ወተይ ወቅጥራን ወሰብዐቱ ልጥር እምነ ቀልፎንያ -(ስንክ -ሐም፭)

ቀመራዊ -ወርኃዊ ዘወርኅ ወርኅ ቀመራዊ ልቍ ቀመራዊ ወፀሓያዊ -(አቡሻ - -፴፩)

ቀመር [1]-(ራት፤ አቅማር) መጋረጃ አጐበር፤ ጠፈር መዋቅር ዋልታ ገበታ ዘሰቀሎ ሰማይ ከመ ቀመር ዘእንበለ ዐምድ -(ቅዳ ኢሳ፵ -፳፪)

 [2]-ክፍል፤ ምዕራፍ፤ ጥር ሒሳብ፤ የቍጥር መደብ። አቅማር በእንተ አኅብሮ ቃላት ቀመር ቀዳማዊ። አንቲ ውእቱ ዳግሚት ቀመር። ቀመረ ዐረብ። ዐውደ ቀመሩ ለወርኅ። ናሁ ኀልቀ ቀመርነ ዘተውህቦ ለአዳም ፯፻ ዓመት -(መቅ -ወን ውዳ -ማር መጽ -ምስ አዋል)

[3]-(ዐረብ) ጨረቃ ዐውደ ቀመር የጨረቃ ዙሪያ ውደ ወርኅ ዐውደ ረቃ ወይም ዐውደ አበቅቴ ማለት ነው የዐውድን ፍች እይ

ቀሚሕ  ሖት -(ቀምሐ ይቀምሕ ይቅማሕ ሰምረ፤ ፈረየ) ማፍራት፤ መበጀት ፍሬ መያዝ መሸከም፤ ማንዠርገግ፤ ያዝመራ የተክል። መቀማት መመንተፍ መንጠቅ።

ቀሚል ሎት -(ቀመለ ይቀምል ይቅምል ዕብ ቃማል፤ የብሰ መጽለወ) መቅመል፤ መቀማመል፤ መላልሶ ማየት ማገላበጥ ወይቀምላ ለምድረ ግብጽ ከመ ይቀምል ኖላዊ ልባሲሁ ወረከበቶ እንዘ ይቀምል ጸጕሮ -(ኤር፵፫ -፲፪ ገድ -ተክ)

ቀሚስ -በቁሙ፤ ቀምየሰ

 -(ዐረ ቀሚጽ) በቁሙ የውስጥ የገላ ልብስ፤ ባንገት የሚጠለቅ፤ ታናሽ ወይም ታላቅ። እለ ቀሚሰ ይቀጽፁ። ወይለብስ ቀሲስ ልብሰ ቤተ ክርስቲያን ቀሚሰ ወምጣሕተ ወፊቃረ ወአክሊለ ወሶበ ፈቀደ ከመ ይልበስ ቀሚሰ፤ ይነጽር ለእ ኮነ ነዊኀ ኀጺረ -(ዮሴፍ። ቄድር። ቅዳ)

ቀማይስ -(ሳት) ቀሚሶች። ለብሱ ብሰ ጺን እምታሕተ ማይሳቲሆሙ -(ዮሴፍ። ገድ -አዳ)

ቀምሐ -ቃመ ገተመቀሐመ

ቀምሕ -(ዐረ ስንዴ ዕብ ቄማሕ ዶቄት) ፍሬ ቅንጣት ምርት ዛላ ዘለላ፤ ሕንባብ፤ በየስሙ በየነገዱ የማግሰኞ ፍጥረት የሚያፈራው ፍጡነ ትበልዕ ቀምሓ። ትጸግቡ እምነ ቀምሕየ። ይተክ ወይነ ወይበልዑ ምሖ -(ሢራ፮ -፲፱ ፳፬ -፲፱ ኢሳ፷፭ -፳፩)

 -ዘርዕ ተክል ቅመም፤ ዛፍ ዕንጨት የሚዘራና የሚተከል የሚያፈራ ኹሉ። ዐቃቢሁ ለቀምሕ ይሬኢ ፍሬሁ። ዕፀወ ቀምሕ። ልገተ ዐቃቤ ቀምሕ -(ሢራ፳፯ -፮። ነሐ፱ -፳፭ ኢሳ፩ -)

ቀምሮ  ሮት -(ቀመረ ይቄምር ይቀምር። ዕብ ቃማር ሸፈነ) መቀመር ማዘጋጀት፤ መቍጠር ማሰብ፤ መመደብ መዘርጋት መጋረድ፤ መለየት መክፈል፤ በስፍር በቍጥር ማደላደል ዘዐውደ ፀሓይ ወወርኅ ከመ እንተ መጽሔት ቀመረ እዴሁ ለልዑል ይቄምሮ። በዕፅ ትሰውቆን ወትቄምሮን -(መጽ -ምስ። ሢራ፵፫ -፲፪ ገድ -ላሊ)

ቀምጠራ -(ዐረ ቀመጥር ዕብ ምጣር) ሣጥን፤ ቍናማት፤ ረጢት፤ የልብስ የገንዘብ። ያስክሬንን ፍች ተመልከት፤ ከዚህ ጋራ ንድ ነው በእንተ ስክሬን ወቀምጠራ ዘሙዳየ ምጿት ወኮነ ሰራቄ ብሩር ዘውስተ ቀምጠራ ዘአስክሬነ እግዚኡ -(ዮሐ፲፫ -፳፱ መጽ -ምስ )

ቀምጠራት ቀማጥር -ሣጥኖች፤ ቍናማቶች እለ ይትፌሥሑ በብዝኀ ዕንቆሙ ክቡር ወኪያሁ ዕንቈ የዐቅቡ ውስተ ቀምጠራት ዝጊሖሙ ጽኑዐ -(ተረ -ቄር፳፪)

ቀምጠወ -(ተቀ ) አስተካከለ፤ አለሰለሰ ቀበቀበ አንቀረቀበ መላልሶ ዐርሶ ሉን መኰላውን ሰብሮ ስክሶ። መጽሐፍ ግን አቀምጠወ ይላል፤ አያሰኝም። አኮኑ አቀምጢዎ ገራህቶ ሶቤሃ ይዘርዕ -(ኢሳ፳፰ -፳፭) ባለብሉዮች ተለመ ይሉታል።

()          ቀምጦ ጦት -() ቀምጦ፤ ጦት፤ -(ቀመጠ ይቄምጥ ይቀምጥ። ዕብ ቃማጥ ዐረ ቀመጠ ሱር ቅማጥ) አጥብቆ መያዝ፤ ማሰር መሸንከፍ ማጠፍ ማጣመር። ማስቀመጥ ማኖር፤ መጐቸት፤ ቍጭ ማድረግ። መቍመጥ መቍረጥ መበጠስ።

ቀሠመ -አጣፈጠ፤ቀሰመ።

ቀሰመ [1]:-ለቀመቀሢ ቀሠመ

[2]-() ቀሰመ፤ -(ዕብ ቃሳም ሱር ቅሳም) አሟረተ ጠነቈለ፤ ገመተ መላ ጣለ መጽሐፍ ግን በቀሰመ ፈንታ አስተቃሰመ ይላል፤ አድራጊውን ባደራራጊ፤ የመላሽ ስሕተት ነው። በከመ ሐሰበ ወአስተቃሰመ ለአማስኖቶሙ አስተቃስሚ ሊተ -(አስቴ፱ -፳፬ ፩ነገ -፳፰ -)

ቀሠፋይ -አፍኣዊ፤ ዘአፍኣ ይፍልጥ መንጦላዕት ውሳጤ ወቀሠፋየ -(ዘፀ፳፮ -፴፫)

ቀሡታት -ቀሣውት፤ ማድጎች ቀሡታተ ይጽዐን በአንበሳ ቀሣውቲሆሙ -(ደራሲ። ኤር፲፬ -)

ቀሡት [1]-(ዕብ ቄሤት) የቀለም ዕቃ ቢልቃጥ፤ ሙዳየ ቀለም የገንቦና የማድጋ ዐይነት ገንቦ፤ ማድጋ፤ እንስራ፤ የውሃ ዕቃ ሸክላ ቀሡተ ጸሓፊ። ቀሡተ ልሕኵት። ስተይ ማየ ምቀሡትከ -(ሕዝ፱ - ኤር፲፱ -፩። ምሳ፭ -፲፭)

[2]-ማድጋ፤ቀሠወ።

ቀሢም ሞት -(ቀሠመ ይቀሥም ይቅሥም። ቀጠፈ) መቅሠም፤ መልቀም መቃረም መቍረጥ ማጨድ፤ መጨርገድ ማርገፍ መሰብሰብ ያታክልት በከመ ይቀሥምዎ ዘይት ማሁ ይቀሥምዎሙ ከመ ዘየአርር ድኅረ ዘይቀሥም ቅሥም አስካሎ ለዐጸደ ወይን ቀሠምነ ለከ ስምዐ እመጻሕፍት -(ኢሳ፳፬ -፲፫ ራ፴ -፳፭ ራእ፲፬ -፲፱ መጽ -ምስ)

ቀሲሳን ቀሳውስት -ቄሶች፤ ቀሳውስቶች ትሢም ቀሲሳነ ይጸውዕ ቀሳውስተ -(ቲቶ፩ -፭። ያዕ፭ -፲፬) ኤጲስቆጶስ በማለት ፈንታ ቀሲስ ይላል፤ የመላሽ ስሕተት ነው ምስለ ቀሳውስት ወዲያቆናት -(ፊልጵ፩ -)

ቀሲስ -ቀሲስ -(ዐረ ቀሲስ ሱር ቃሺሻ) ስ፤ ካህን፤ ሽማግሌ። ቀሲስ ወዲያቆን። እምነ ቀሲስ -(ቅዳ። ፪ዮሐ -)

ቀሲስ ሶት -(ቀሰ፤ ቀሰሰ ይቀስስ ይቅስስ። ዕብ ቅሻሽ። ሱር ቃሽ) ማርጀት፤ መሸምገል፤ መቈሸሽ፤ ቈሻሻ መኾን፤ ቈሻሻ መልቀም፤ ማጋበስ መሰብሰብ። መቅሰስ ካህን ቄስ መኾን ቅስና መሾም። ምሥዋዒሆሙ በኀበ ቀሰሱ ወዛቆኑ -(ቀኖ -ኒቅ -፸፱)

ቀሢጥ ጦት -(ቀሠጠ ይቀሥጥ ይቅሥጥ ዐረቀሸ ) መቅሠጥ፤ ማንሣት ማነሣሣት፤ ከፍሎ መስረቅ መደበቅ፤ ማታለል መቅጠፍ። ቀሢጠ ዋየ ባዕድ ዘይቀሥጥ እምቤተ እግዚ ቀሠጡ መንፈቀ ሤጡ ከመ ትቅሥጦሙ በተሳልሞ ፀሮሙ -(መቃ። ቀሌ። ግብ፭ -፪። የሴፍ)

ቀሢፍ ፎት -(ቀሠፈ ይቀሥፍ ይቅሥፍ ቀጠፈ ዐረ ቀጸፈ) መቅሠፍ፤ መቅጠፍ መዘንጠፍ፤ መቍረጥ መቅጨት ባጭር ማስቀረት የተክል የሰብል የሕፃን። መግፈፍ መግለጥ፤ ማስራቈት፤ ዕራቍት ማስጣል፤ ለመግረፍ።

 -መግረፍ፤ መጠብጠብ፤ መምታት፤ መቅጣት መዝለፍ መገሠጽ። ዘይቀሥፍ ብዕራይሁ ይቀሥፎሙ ለአሕዛብ። ቀሠፍከኒ ወተቀሠፍኩ እግዚኦ በመዐትከ ትቅሥፈኒ -(ሢራ፴፰ -፳፭ ራእ፲፱ -፲፭ ኤር፳ -፮። መዝ -፮። ኢሳ፲፩ -)

ቀሣሚ -(ሚት ምያን ያት ሣም ሠምት) የሚቀሥም የሚለቅም፤ ለቃሚ ራጭ ድኅነኒ ምቀሣሜ ወይን ያሌዕል ማዕጸዶ ሶበ ቦኡ ቀሣም ላዕሌከ -(ደራሲ። ዐብድ -)

ቀሳሚ -(ሚት ምያን ያት) የሚያጣፍጥ አጣፋጭ፤ ቀማሚ ወጥ ቤት

ቀሣጢ -(ጢት ጥያን ያት፤ ሠጥ) በቁሙ፤ ሌባ ቀጣፊ፤ አታላይ። ሰራቂ ወቀሣጢ ዘአንበሩ ብየ -(አዋል)

ቀሣፊ -(ፊት ፍያን ያት) የሚገርፍ፤ ገራፊ ቀጪ ኀበ ቀሣፌሁ -(ኢሳ፱ -፲፫)

ቀስ [1]-ቀሲስ ቀሰ።

 [2]-ቀይስ፤ -(ትግ ቀሽ) ዝኒ ከማሁ ቀሲስ። አባ ገሪማ ቀስ ዘመደራ። ወይቤልዎ ወመኳንንት ለአባ ሊባኖስ ለእመ ሰረቀ ክሊሮስ ዘውእቱ ቀይሰ ገበዝ ንዋያተ ምሥዋዕ -(መዋሥ - -፲፯ -)

ቀሥም -( አቅሣም) የተክል መከር አዝመራ ፍሬው የሚለቀምበት፤ የለቀማና የቈረጣ  ወራት የኀብር ቀሥም ምስለ ማእረር -(ዓሞ፱ -፲፫ ዘሌ፳፮ - መሳ፰ -)

 -ፍሬ፤ ሕንባብ አስካል፤ ተለቅሞ ተቈርጦ ያለ በመዋዕለ ማእረረ ቀሥም። ቅሣመ ዐጸድ ይሴፈዉ ቀሥሞ -(ሢራ፳፬ -፳፯ ሥር ጳኵ። ማር -ይሥ፲፭ -)

ቀስም -ቅስም፤ -(ማት) ሟርት፤ ጥንቈላ ነሲብ ግምት፤ መላ ትንቢተ ሐሰት። መጽሐፍ ግን በቀስም ፈንታ መቅስም መቅሰም መቃስም ይላል፤ ኹሉም ስሕተት ነው፤ አያሰኝም። ሰብአ መቅስም በለዐም ዘመቅስም። ሕልም ወሰገል ወመቃስም ከንቱ ሎሙ -(፩ነገ - ኢያ፲፫ -፳፪። ራ፴፩ -)

ቀስም ቅስም -ቀመመን፤ ጣዕም፤ ጥፍጥነት፤ አጠፋፈጥ፤ የቅመም የወጥ ዘእንበለ ቀስም። ወኢይብላዕ ቀስመ -(ቀሌ። ቄድር)

ቀስሞ ሞት -(ጥስ) ቀስሞ፤ ሞት፤ -(ቀሰመ ይቄስም ይቀስም አው ቀሲም ቀሰመ ይቀስም ይቅስም ዐረ ቀሰመ፤ ከፈለ) ማጣፈጥ ማጠፋፈጥ፤ መመጠን መቀመም፤ ሰብስቦ ማዋሐድ ማዛመድ ለማጣፈጥ በምንት ይቄስምዎ ለቀሲመ ልሳንየ -(ማር፬ - አርጋ) ሲጠብቅ የቀደሰ፤ ሲላላ የቀተለ ቤት ነው ስለዚህ በ፪ ዳል

ቀስተወ -ቀሰተ፤ ቀስት ሠራ፤ ቀስት አስመሰለ፤ አጐበጠ። ዐለበ፤ ደገነ፤ ሳበ ጠጠ፤ ነደፈ ፍላጻውን በቀስት። ወቦአ ወቀስተወ ፍጽመ፤ ኢዮአ -(፩ዜና -፲፩ -)

ቀስታም -(ማት) መንደርቶ ሎታ መድ ዱላ ቀስት ጋራ የሚያዝ። በቀስታመ ይሉ ድከሞ ለአርዌ ርኩስ በትርከ ወቀስታምከ ገሠጽኮ ለዮናስ በቀስታመ ባሕር -(ድጓ መዝ -፳፪ ቅኔ)

ቀስታዊ -ቀስት ሠሪ፤ ቀስተኛ ባለቀስት፤ ነዳፊ፤ ወርዋሪ።

ቀሥት -በቁሙ፤ቀስት።

ቀስት -(ዕብ ቄሼት ሱር ቂሽታ ዐረ ቀውስ) በቁሙ፤ ደጋን፤ ጐባባ፤ ጐባጣ የጦር መሣሪያ። ቀስት ጠዋይ። ቀስተ ብርት ቀስተ ደመና። ቀስተ እግዚአብሔር -(ሆሴ፯ -፲፭ መዝ -፲፯ ሕዝ፩ -፳፰ ኩፋ -)

ቀሥፍ ቅሥፍ አፍኣ ዕዳሪ ገጠር ከከተማ ውጭ ያለ አገር ከቤት ውጭ ያለ ዐዘቅተ ኵስ ሜዳ ይቁሙ ቅሥፈ እቱተ ይሁድ እለ ተዘርዉ ውስተ ኵሉ በሓውርተ ቀሥፍ ይነብ ጽመ ቅሥፈ (ቀሌ። አስቴ፱ ፲፱ መሳ፫ ፳፬)

ቀረብ -( አቅራብ) የደጋ የቈላ እንቧይ እሾኻም ፍሬው ክብ እንክብል ሎሚ የማ ያካክል። ምስክር የለውም ባለሐዲሶች ግን -(ሉቃ፲፩ -፲፪) ወእመኒ እንቆቅሖ ስአሎ ዐቅራበኑ ይሁቦ ያለውን፤ እንቧይ ይሉታል፤ ስሕተት ነው እውነተኛ ፍችው አይዶለም። የጽርኡ አብነት ከጽርእም የተቀዳው ኹሉ፤ እመኒ ዓሣ ሰአሎ አርዌ ምድርኑ ይሁቦ ባለው አንጻር ጊንጥ እንደ ማለት በዐይን ዐቅራበኑ ይላል እንጂ፤ እንቧዮች እንደ ማለት በአልፍ አቅራብ አይልም

ቀረፀ -(ዐረ ቀረፀ። ሱር ቅራጥ) ቀረጠ፤ ቀረጥ ተቀበለ -(ዐማርኛ) ቈረጠ ሸለተ ላጨ ረከመ የሕዋስ የጠጕር የጥፍር። ቀረፀ ዝኖ ዘፀጋም። ኢትቅርፅ እምኔከ ባለ ርዕ። ይደሉ ምድኅረ ተመጥዎ ቍርባን ቀሪፀ አጽፋር ወተላጽዮ ጸጕር ኢይቅርፅ ጽፈሪሁ። ታንኅ ሥዕርተ ርእስከ ዳእሙ ቅርፅ ሖረ ይቀርፅ ባግዒሁ ከመ በግዕ ዘኢይነብብ በቅድመ ዘይቀርፆ ምነ ቀዳሚ ዘቀረፅኩ -(ፊልክ -፯። ፪፻፴ ቅዳ ቄድር ዲድ -፩። ፍ፴፩ -፲፱ ኢሳ፶፫ -፯። ጦቢ፩ -)

ቀረፅ -በቁሙ፤ ቀረጥ ነጋዴ ለመንግሥት የሚያቀርጠው ገንዘብ። ስመ ዕፅ

ቀሪም ሞት -(ቀረመ ይቀርም ይቅርም። ዐረ ቀረመ ዕብ ቃራም፤ ቍርበት ሸፈነ፤ ቍርበታም ኾነ) መቃረም መልቀም ካጫጅ የቀረውን የወደቀውን እልፍ እንቡጥ ዛላ ዘለላ መማረር ሀብኒ ክፍልየ ምዘቀረምኪ፤ አኀዘት ትቅርም -(ድር -ሚካ) ብዙው መጽሐፍ ግን በቀረመ ፈንታ ተቀረመ ይላል፤ ስሕተት ነው። ትትቄረሞሙ ዘከመ ተቀረምከ ኪያየ ተቅራመ ይትቄረምዎሙ ከመ ወይን ለተረፈ እስራኤል። ትትቀረም ሕንባባተ ወይንከ -(ሰቈ፩ -፳፪ ኤር፮ -፱። ዘሌ፲፱ -)

ቀሪብ ቦት -(ቀርበ ይቀርብ ይቅረብ ዕብ ቃሬብ ሱር ቅሪብ ዐረ ቀሪበ) መቅረብ፤ መጠጋት፤ መድረስ መንካት፤ መለጠቅ መጣበቅ ልጥፍ ማለት እንደ ሥጋና እንደ ርበት፤ ወዳጅ ዘመድ ባለሟል መኾን። ቅረብ ዝየ ወአልቦ ዘይክል ቀሪበ ኀቤሁ ይቀርቡኒ በከናፍሪሆሙ ዘመድ ዘይቀርብ ምኔየ -(ሔኖ፲፭ - ሃይ -አበ። ኢሳ፳፱ -፲፫ ሩት፫ -፲፪)

 -መቍረብ፤ መቀበል፤ መሳተፍ እለ ትቀርቡ ፃኡ። ይባእ ወይትከነስ ወይቅረብ። ይቅረቡ ቍርባነ ቅድመ ይቅረቡ ጳጳሳት ወእምድኅሬሁ ቀሳውስት -(ኪዳ ቀሌ - - - ቅዳ) ቀርበ ይቀርብ ይቅረብ በማለት ፈንታ ቀረበ ይቄርብ ይቅርብ ይላል የጸዐለና የገረመ ቤት ነው እለ ይቄርቡ እግዚ እስመ ሙንቱ ይቄርቡ መሥዋዕቶ እንዘ ይቄርብ ረበ ቍርባኖሙ -(ዘፀ፲፱ -፳፪ ዘሌ፳፩ - -፰። ኪዳ ሲኖዶ) ዳግመኛም በቀርበና በቀረበ ፈንታ ተቀረበ ይላል፤ ስሕተት ነው ለእ ፈቀደ ይትቀረብ ቍርባነ እምዘይትቄረብ -( - -፲፬ -፱። - -፲፮) ሦስተኛ ደግሞ እንዳማርኛው ቈረበ አቍረበ ይላል፤ ስሕተት ነው፤ አያሰኝም። ለምንት ኢትቈርቢ ቍርባነ ፍርንጅ -(ስንክ -ኅዳ፲፯)

ቀሪን ኖት -(ቀረነ ይቀርን ይቅርን። ዕብ ቃራን) -(መቀርናት) ቀንድ ማብቀል ማውጣት፤ ቀንዳም ቀንደኛ ባለቀንድ መኾን። መውጋት ማናፈር፤ በቀንድ መቈፈር የበሬ ማሰር ማቈራኘት ማጣመር ማቀናጀት፤ የገበሬ ቅራና ቍራኛ ማለት የዚህ ዘር ነው ቀንድ መምሰል ቀንድ መኾን ቀንድ መባል ያገር ቀንድ እንዲሉ። ማየል መበርታት፤ መንገሥ መሠልጠን በላይ መኾን። ቈንደየን ተመልከት።

ቀሪዕ ዖት -(ቀርዐ ይቀርዕ ይቅራዕ ዐረ ቀረዐ። ዕብ ቃራዕ ቀደደ) ሪዕ መቍራት መቈረም፤ መኰርኰም መምታት ራስን በበትር ማድረግ ኰርዐን ተመልከት የዚህ መንቲያ ነው

ቀሪጽ ጾት -(ቀረጸ ይቀርጽ ይቅርጽ ዐረ ቀረጸ። ዕብ ሐራጽ) መቅረጥ ማነጥ፤ ማንጠጥ፤ ምስል መሥራት መልክ ማውጣት ማስጌጥ፤ መብጣት መክተፍ መተፍተፍ። በዕፅ ኀጺን በሰሌዳ እብን መጣፍ መፈደል፤ መንደፍ መፈልፈል፤ ፊደሉን ማስመጥ ወይም ማሳበጥ። ኵሎሙ አሕዛብ ሀለዎሙ ምግባራት ዘልማድ ዘትሤኒ በኀቤሆሙ ወቦ ዘትከውን ሳረ በኀበ ካልኣኒሃ ከመ ቀሪጸ ገጽ በጎበ ትዮጵያ ወኖባ፤ ወከመ ተላጽዮ ጽሕም በኀበ ፍርንጅ። ወረከበ መጽሐፈ ዘቀረጹ ቀደምት ውስተ ኰኵሕ -( - -፶፩። ኩፋ -)

ቀሪፍ ፎት -(ቀረፈ ይቀርፍ ይቅርፍ። ዐረ ቀለፈ። ሱር ቅላፍ) መቅረፍ፤ መላጥ። ቈለፈን እይ ተወራርዋል፤ ቀረፈ ማርኛ ነው ቀረፈ ኵሎ ቅርፍቶ ቅርፍ ጸልዐ ዘኀጢአት -(ጥበ፲፫ -፲፩ ደራሲ)

(ጥራ) ቀራሕ የሚነጭ የሚጨልጥ ጨላጭ አንቃሪ። ልጩ ምልጥ መላጣ በራ ቡሓ

ቀራሚ -(ሚት ምያን ያት ረምት) የሚቃርም፤ ቃራሚ፤ ለቃሚ። በቀራሚ ፈንታ ተቀራሚ ይላል፤ ስሕተት ነው  ተቀራሜ በለስ አነ -(ዓሞ፯ -፲፫)

ቀራቢ -(ቢት ብያን ያት ረብት) የሚቀርብ፤ የሚጠጋ፤ ቀራቢ፤ ቈራቢ።

ቀራቢብ -(ዐረብ) ያልተሰፋ ልብስ ፈርጅ መዳ ጣቃ ቁማስን እይ፤ ከዚህ ጋራ አንድ ነው

ቀራኒ መቅርን -( መቃርንት) ቀንዳም የሚወጋ የሚቃወም፤ ጠላት ደመኛ ወደረኛ እስመ እሉ እለ ይነሥኡ ርዴ መቃርንቲሁ ለእግ -(ዲድ -፳፩)

ቀራንዮ -(ጽር ክራኒዩ) ርእሳዊ፤ ድማ ኃዊ መካነ ድማኅ ጎልጎታ ዘበትርጓሜሁ ቀራንዮ -(ማቴ፳፯ -፴፫። ማር፲፭ -፳፪ ዮሐ፲፱ -፲፯) ድማኅንና ጎልጎታን እይ።

ቀራዪ -(ዪት ይያን ያት) ሟርተኛ አስማት ደጋሚ ጋኔን ጠሪ፤ ባላሾክሿኪ።

ቀራዲን -(ናት) ዝንጀሮች፤ ጭላዶች። ሆባይን ተመልከት።

ቀራፂ -(ፂት ፅያን ያት) የሚቈርጥ ራጭ፤ ቀራጭ፤ ሸላች ላጭታ ጸውዐት ቀራፄ ወቀረፀቶ መላጼ ቀራፂ -(መሳ፲፮ -፲፱። ሕዝ፭ -)

ቀሬናዊ [1]-(ሱር ቁርያና ዐረ ቀሪይ) ቍርጩ ድኻ፤ ባለጌ፤ ባላገር። እፎ እትለአኮ ለዝንቱ ቀሬናዊ -( - -)

[2]-(ቀሬን፤ ቄሬን፤ ስመ ሀገር) የቀሬን ሰው አገሩ ቀሬን የሚባል፤ የግብጽ አውራጃ የልብያ ቅርብ አጠገብ። ብእሲ ቀሬናዊ ዘስሙ ስምዖን -(ማቴ፳፯ -)

ቀርሖ ሖት -(ቀርሐ ይቄርሕ ይቀርሕ ዕብ ቃራሕ) መንጨት መላጨት መምለጥ፤ የጠጕር። ይቄርሑ ርእሶሙ በእንቲኣኪ ወይቀንቱ ሠቀ -(ሕዝ፳፯ -፴፩) በርሐን እይ

 -መጨለጥ፤ ማንቀር፤ የውሃ። ጸወበን ተመልከት የዚህ ወንድም ነው።

ቀርመዝ (ዐረ ቂርሚዝ) ቀይ ግምጃ እንድኪ ጃዊ ኳኳን ተመልከት (ኢሳ፩ ፲፰)

ቀርሜሎስ -(ጽር ርሚሎን ዕብ ርሜል) የተራራ ስም ተራራ በባሕር ዳር ያለ ኤልያስ የጸለየበት -(፫ነገ -፲፰ -፵፪)

ቀርም -(ማት፤ አቅራም) በቁሙ፤ ቃርሚያ፤ ቅራሚ፤ ካጫጆች የቀረ ቅሬታ። -(ተረት) ሰው እንዳቅሙ፤ እኽል እንደ ቀርሙ። ወይተርፍ ርሙ ውስቴቱ ዘያስተጋብእ ርመ በማእረር -(ኢሳ፲፯ -፮። ሚክ፯ -) በቀርም ፈንታ ቀሪም ይላል፤ የጣፊ ስሕተት ነው ሠዊት ዘይወድቅ እምነ ቀሪሙ -(ኢዮ፳፬ -፳፬)

ቀርቀር -(ዕብ ቃርቆር) ስመ ገር ዮርዳኖስ ማዶ ያለ። ባለብሉዮች ግን ገዎቻ ቋጥኝ ይሉታል -(መሳ፰ -)

ቀርቂሳዊ -ገበጣ ዐዋቂ፤ ተጫዋች። ቀርቂሳዊ ዘይትዋነይ ቀርቂሰ -(መጽ -ቈስ -)

ቀርቂስ -(ዕብ ቃርቃሽ፤ ሻኵራ የቃጭል ቍላ) መካነ ተውኔት፤ ብዙ ዐይነት ሥጋዊ ጨዎታ ያለበት ለእመ ኮነ ሐዱ ዘየሐውር ኀበ ቀርቂስ፤ ለይኅድግ ለይሰደድ -(መጽ - -፳፯)

 -ገበጣ፤ ስንጠረዥ። ካህን ዘአዝለፈ ተዋንዮ ርቂስ -( - -)

ቀርብ -(ዕብ ሬብ) ቀርበታ፤ ውስጥ፤ ውሳጣዊ ሆድ፤ መላው ኹለንተናው፤ በእግርና በራስ መካከል ያለው፤ የንዋያተ ውስጥ ሣጥን አቅማዳ። ግራብን ተመልከት የዚህ መንቲያ ነው

ቀርነብ -(ዐረ፤ አርነብ። ሱር አርንባ ዕብ አርኔቤት) ጥንቸል ሮዋ እንደ ቀንድ የኾነ፤ ቀንድ የሚመስል፤ ረዣዥም ሣር የምትበላ፤ የምታመስኳ ያሽኮኮ ወገን

ቀርነናእ -(ዕብ ቅርናን) ቀንዳም ትል፤ ተሳቦ ዛጐል ልብሱ ቀንዱ ብርንዶ የኾነ ልሕሉሕ ልጋጋም። ሐለዚዝንና ናእትን ተመልከት

ቀርነው ቀርነለው -ቀርናዊ ቀርነ ላዊ ቀንዳም ቀንደ ቈልማማ፤ ላዊን እይ

 -ቀርነ ቅብዕ ወይም ቅብዐ ቀርን። ከሌዊና ይሁዳ ወገን ካህንና ንጉሥ የሚቀቡት። ባለቅኔዎች ግን ሽቱ ይሉታል -(ጥሬ -ሰዋ)  

ቀርኔን -ቀሬን ስመ ሀገር ወእለሂ እምቀርኔን -(ግብ፪ -)

ቀርን -( አቅርንት። ዕብ ቄሬን። ሱር ቃርና። ዐረ ቀርን) ቀንድ ጥኑ ንካራ ደረቅ እንደ ዐጽቅ ኹኖ በእንስሳት ራስ የሚወጣ የሚያድግ የሚረዝም፤ ጠማማ ቈልማማ የቀንድ መሣሪያ ቱልቱላ ዋንጫ የቀንድ ዐይነት ቀንድ የሚመስል፤ ቀንዳ መለከት፤ የዝኆን ጥርስ የመሰለው ኹሉ ሕም ዘኢይትኄየል በቀርኑ ክቡዳነ ቅርንት ንፍኁ ቀርነ ቀርነ ዝብጦ ቀርነ ጌ። ቀርነ ቅብዕ ንፍኀተ ቀርን ቃለ ቀርን -(ቅዳ። መዝ -፵፬። ፺፯ ዓሞ፫ -፲፭ ፩ነገ -፲፮ -፩። ፩ተሰ - -፲፮ ኢሳ፲፰ -) ባለቅኔዎች ግን ነጋሪት ይሉታል፤ ፍችው አይዶለም ትንፍኁ ቀርነ ዘእንበለ በሆሳዕና -(ድጓ) ጥፍርም የጣት ቀንድ ይባላል ሰላም ለአጽፋረ ግርኪ አቅርንተ አጻብዕ ዐሠርቱ -(ደራሲ)

 -ጮራ ምዕዛር የፀሓይ እግር፤ ለጋ ረቃ፤ ማእዝን። ቀርነ ወርኅ። ስክንድር ይሰመይ ዘክልኤ አቅርንቲሁ እስመ ውእቱ ነግ በአቅርንተ ፀሓይ ምሥራቂሃ ስከ ምዕራቢሃ -(አዋል። አቡሻ -፵፰)

 -ኀይል፤ ጽንዕ ሥልጣን፤ ንጉሥ መስፍን ኣበቍል ቀርነ ለዳዊት ወያሌዕል ቀርነ መሲሑ። አንሥአ ለነ ቀርነ መድኀኒት ይእተ ሚረ ይበቍል ቀርን ቤተ አስራኤል። ተሰብረ ቀርነ  ሞአብ -(መዝ -፻፳፩ ፩ነገ - -፲። ሉቃ፩ -፷፱። ሕዝ፳፱ -፳፩ ኤር፴፩ -፳፭) ዘአሐዱ ቀርኑ ውራሪሥ ቀርነ ኅብስት፤ ቍርማሚ ሾለቅ -(መዝ -፳፩። ሕዝ፲፫ -፲፱)

ቀርአ -ረመ፤ መታቀርዐ።

ቀርያሲም -(ጽር ካሪሲም) ጣዖት፤ ስመ ጣዖት -(፪ዜና -፴፭ -፲፱)

ቀርይ ዮት -(ቀረየ ይቀሪ ይቅሪ ቃራእ) ማሟረት መጠንቈል፤ አስማት መድገም፤ ጋኔን አሾክሿኪ መጥራት፤ ቅኔ ተመሪ ባለቅኔው አፍ እየሰማ እንዲጮኽ ወይም እንዳስተርጓሚ ካሾክሿኪው አፍ እየሰሙ ማውራት መለፍለፍ መቀባጠር። ለምንት ሰረቅሙ ገይበ ብሩር ዘይሰቲ ወይቀሪ ቦቱ እግዚእየ -(ዘፍ፵፬ -)

 -መቅረት መትረፍ ቀሪ ትርፍ ውዝፍ መኾን -(ዐማርኛ)

ቀርዱ -የተራራ ስም፤ ታላቅ ተራራ፤ ከአራራት ተራሮች አንዱ።

ቀርድ ቅርድ -(ዐረ ቂርድ) ዝንጀሮ፤ ጭላዳ፤ ነጨው ጥቍሬው -(ገድ -ተክ)

ቀርጣሎን -(ጽር ካርታሎስ። ቃርጢል። ሱር ቃርጣላ። ዐረ ቂርጠለት) ቅርጫት የሪቅ የጐታ ዐይነት፤ የወይን መልቀሚያ፤ ዘለላውን በርሱ እየከተቱ የሚጭኑበት የሚሸከሙበት፤ እንደ ስፌት ብዙ ዐይነት ያለው፤ ጉብ መሶብ እንቅብ አገልግል ቅንብቻ የሚመስል። ከፈርንና መሥየምትን አስፈሬድንና ረቦን እይ ትነሥእ እምፍሬ ምድር ወትወዲ ውስተ ቀርጣሎን። ወሤሙ ርእስቲሆሙ ውስተ ቀርጣሎስ -(ዘዳ፳፮ - -፬። ፬ነገ - -)

ቀቀበ -(ነቀበ) ገበ፤ ሰፋ፤ ሸፈፈ ደጐሰ አለበሰ የሰይፍ የጐራዴ የሳንጃ የጦር

ቀቀብ -(ባት ዕብ ንዳን ታዓር) ገባ አፎት፤ ሽፋፍ ድርቄ የሰይፍ ቤት ማኅደር ወፅኣ መጥባሕትየ ምነ ቀቀባ። አግብኣ መጥባሕትከ ውስተ ቀቀባ። በልዑ ማእሰ ቀቀበ ስይፍቲሆሙ -(ሕዝ፳፩ - -፴። መጽ -ምስ -ዮሴፍ)

ቀቀኖ -(ጽር ኪክኖስ ዕብ ቃአት ቂቅ ሱር ቃታእ ዐረ ቁቅ) ርኩም -(ዘሌ፲፩ -፲፱ ዘዳ፲፬ -፲፯) ጕንባሕንና አበ ንባሕን፤ ድገ መረብን እይ። ብዥው ቀቃንው፤ በሴት አንቀጽ ሲኾን ቀቀኑት፤ ቀቃኑት ያሰኛል።

ቀበላ -(ቅባሌ) ማቀበል፤ መቀበል፤ አቀባበል፤ ቅበላ፤ ተቀባይነት። ወፃ ቀበላ ለቀበላሆሙ ለኢሎፍሊ ቀበላ መርዓዊ -(፪ዜና -፲፭ - ፩ዜና -፲፬ -፰። ማቴ፳፭ -)

 -ዋዜማ፤ ድራር መያዣ መቀበያ ቀበላ ጾም -(አቡሻ -፳፯)

ቀበር -ቀበራ አቀባበር ግንዛት፤ አገናነዝ የሬ ሕግ ሽቱ መቅባት ማጠን ማጤስ መፍታት ማልቀስ፤ ርግዶ ሙሾ የመሰለው ኹሉ። ገብሩ ሎቱ ሙፃአ ቆበር ዐቢየ ጥቀ ወኢገብረ ሕዝብ ፀአተ ቀበረ ዚኣሁ በላዕሌሁ -(፪ዜና -፲፮ -፲፬ ፳፩ -፲፱)

 - በድን አስከሬን፤ ሬሳነት የሬሳ ጓዝ ዐጀብ፤ ልቅሶኛ፤ ከሬሳው ጋራ የሚንጋጋ ዘአማዕቀብኮ ቀበረ አዳም ለመልከ ዴቅ። ቀበርየ ገብረት እስመ ተዐቅቦ ለዕለተ ቀበርየ። ወረከበ ቀበረ ዘወልደ መበለት -(ጥበ - ማቴ፳፮ -፲፪። ማር፲፬ -፰። ዮሐ፲፪ -፯። ሉቃ፯ -፲፪)

ቀበሮ -በቁሙ፤ ቍንጽል፤ እንደ ሬሳ በጕድጓድ የሚኖር የሚከተት።

ቀበየ -(ዐረ ቀባ) አበጀ፤ አዘጋጀ፤ አሰናዳ

ቀበያወበጠ -(የቧልተኛ ግስ) ቀላወጠ አፉን ከንፈሩን ለማመጠ፤ አቀለማመጠ፤ ሲበላ ውጥ ወይም ሲቀላውጥ። አቈለጳጰሰ እንደ ማለት ነው ምስክር ሳይኖረው እንዲያው በልማድ ይገሰሳል፤ መምህራንም የ፮ ፊደል ግስ ብለው ግስ አርእስት ይቈጥሩታል።

ቀቢል ሎት -(ቀብለ ይቀብል ይቅበል። ነትገ ሐጸ) ማነስ መጕደል መክፈል ቅምጥል ማለት፤ ከቍጥር ከምልአት። ይቀብላ እምልቍ ውራኂሁ ባሕርኒ ሶበ ይቀብል። ትሁብ ለኵሉ እንዘ ትቀብል። አሐዱ በመለኮት ዘኢይትከፈል ምሉእ በኵለሄ ዘኢይቀብል -(ኢዮ፲፬ -፲፩ ፳፩ -፳፩ ቅዳ -ዮሐ ገድ -ኪሮ)

ቀቢር ሮት -(ቀበረ ይቀብር ይቅብር ዕብ ቃባር ሱር ቅባር ዐረ ቀበረ) መቈፈር ማጥለቅ፤ መቅበር መሰወር መደበቅ፤ መክተት ከጕድጓድ ማግባት፤ መዝጋት መድፈን በመሬት፤ የሬሳ የገንዘብ። ደፈነን ተመልከት እቅብሮ ለአቡ ይቅብሩ ምዉታኒሆሙ ወኢያበውሑ ይቅብርዎሙ ወነበሩ እንዘ ይቀበሩ ርእሶሙ ወቀበራ ታሕተ ዕፀ ሕይወት፤ ሰወራ፤ -(ማቴ፰ -፳፩ -፳፪ ራእ፲፩ -፱። አዋል)

 -ፈን መሸፈን፤ መቆበር፤ ጋግ መኾን መብነን መትነን የትቢያ ያቧራ የጉም።

ቀቢዕ ዖት -(ቀብዐ ይቀብዕ ይቅባዕ ዕብ ቃባዕ፤ ሐገገ ዐደመ መልአ ) መቅባት መቀባት፤ መላከክ፤ መለቅለቅ፤ ለመሾም ለማክበር ለማሳመር፤ ለመፈወስ ቀብዖ ቅብዐ ቅድሳት። ቀብዖ በሕጕሬ። ቀብዖ ወርቀ ንጹሐ። ትቅብዖ ዕፍረተ ገብረ ጽቡረ በምራቁ ወቀብዖ አዕይንቲሁ -(ሢራ፵፭ -፲፭ ጥበ፲፫ -፲፬ ፫ነገ - -፲፰። - -፶፩። ዮሐ፱ -) ልብስና ቀለም፤ ሽቱና ተቀቢው ልዩ ልዮች ኾኑ መጋጠማቸው ለተዋሕዶ ምሳሌ እየኾነ ይነገራል። ከመ  ፀምር ውስተ ሠርዮ ከማሁ ተቀቢዖ ትስብእተ በመለኮቱ። ዕፍረትሰ ሥጋ ዚኣኪ ወተቀባዒሁ ቃል ውእቱ -(ኤጲ -አክሲ። አርጋ) እንዲህ ያለው ንባብ፤ ግስ ሠም ለበስ ይባላል፤ ካሮች ግን ሠሙን ወርቅ ምሳሌውን ጽድቅ አድርገው ቀብዐን አዋሐደ ተቀብዐ ተዋሐደ እያሉ፤ አለቋንቋው አለንባቡ፤ አለስልቱ አላገባቡ፤ አላንጻሩ አለምስጢሩ ይፈቱታል። የተቀብዐ ፍች ተዋሐደ ማለት ከኾነ ቄርሎስ አፈ ወርቅ ይጽሕቅ ቅብዐተ በህላዌሁ ወመለኮቱሰ ኢይትቀባዕ ይላሉና፤ ይህ ንባብ ሳይወዱ በግድ ባሕርዩ ተዋሕዶ አይሻም፤ መለኮቱ አይዋሐድም ያሰኝባቸዋል። ተማሪ ፣፤ ሳይኾኑ መምህር መኾን፤ እውነቱን ሐሰት ሐሰቱን እውነት እያሰኘ እንዲህ ፈራሽ ነገር ያናግራል። የተሰብአንና የተቀብዐን ምስጢር ስንኳን ልቡን ርባውን አላገኙትም፤ ቅባቶችም እንዲሁ ናቸው።

ቀቢው ዎት -(ቀበወ ይቀቡ ይቅቡ) መንፋት፤ መቀብተት፤ ማሳበጥ። ቀብተተን እይ የዚህ ፊል ነው

ቀቢጽ ጾት -(ቀብጸ ይቀብጽ ይቅበጽ ዕብ ቃባጽ ሰበሰበ) መቅበጥ መቅበጥበጥ፤ መውደቅ መደንገጥ፤ መቸገር ማጣት ተስፋ መቍረጥ ተዐገሡ ወኢትቅበጹ። ቀብጸተኒ ነፍስየ። አቡየ ወእምየ ቀብጹኒ ወኢይሴፈዉ ንከ ይርአዩኒ -(ሄርማ። መዝ -፻፵፪። ጦቢ፲ -) በቀብጸ ፈንታ ተቀብጸ ይላል ስሕተት ነው እለ ቀብጹ። ትትቀበጽ -(ኪዳ። ሢራ፳፪ -፳፪)

ቀባሪ -(ሪት ርያን ያት፤ በርት) ቁሙ፤ የሚቀብር ማሽ ቈፋሪ -(ተረት) ቀባሪ ፈጣሪ፤ ጠዋሪ ቀባሪ

ቀባዒ -(ዒት ዕያን ያት) የሚቀባ ቀቢ ሠያሚ አብ ባዒ ወልድ ተቀባዒ መንፈስ ቅዱስ ቅብዕ -(አዕ -ምስ)

()          ቀብሎ ሎት -(ቀበለ ይቄብል ይቀብል። ዕብ ቃባል። ሱር ቅባል። ዐረ ቀበለ ተቀበለ) ማቀበል መስጠት ማጕረሥ ማዋጥ፤ ማሲያዝ ማስጨበጥ በተቀበለ ፈንታ ቀበለ ይላል፤ ስሕተት ነው -(ዘፍ፳፯ -፵፭)

ቀብቀሊስ -(ዐረ እልቀብቀሊስ) ሊቀ ጳጳስ። ርግጡ አልተገኘም -(ማር -ይሥ)

ቀብቀበ -(ትግሬ) ሐቀየ በቁሙ፤ ቀበቀበ፤ ቅብቃብ ተከለ ቈረቈረ ቀብ ቀብ አደረገ መላልሶ መታ ዐረሰ አለሰለሰ -(ዐማርኛ) መጽሐፍ ግን በቀብቀበ ፈንታ አቀብቀበ ይላል፤ ስሕተት ሐራሲ ያቀድም ቀብቅቦታ ወአስተዳልዎታ -(ግብ -ሕማ)

ቀብተተ -በቁሙ ቀበተተ ነፋ አሳበጠ። ቀበወን እይ

ቀብአ -ቀባ ላከከ፤ቀቢዕ ቀብዐ

ቀተተ -ቈተቸ፤ቀተወ

ቀቲል ሎት -(ቀተለ ይቀትል ይቅትል። ዕብ ቃጣል። ሱር ቅጣል። ዐረ ቀተለ) መግደል፤ መውጋት ማቍሰል መቍረጥ፤ ማጥፋት ማድከም መጕዳት። ይመክሩ ቀቲል። ቀተለ ርእሶ ለሊሁ ዕፄ ቀተሎ ለዝኩ ሐምሐም በጾም ሰብእናሆሙ ቀተሉ -(ኢሳ፶፱ -፯። ዮሴፍ ዮና፬ -፯። ድጓ)

ቀቲው ዎት -(ቀተወ ይቀቱ ይቅቱ። ዐረ ወቀተ፤ ጊዜ ወሰነ) መገበር ግብር መስጠት፤ ገባር ተገዥ መኾን። ጋላ በሬ ገበሬ ል፤ ቆቲዮ ቆቱ የሚለው ከዚህ ይሰማማል። መቈታቸት ቍትቻ ማድረግ፤ መወራረድ የቍትቻን ውርርድን መክፈል። በቀተወ ፈንታ ቀተተ ይልና ጥሬውን ደግሞ ቀቶት እንደ ማለት ቀተት ይላል የመላሽና የጣፊ ስሕተት ነው። ከመ  ይግበር ቀተተ ምስሌሁ። ወእለ ይሰትዩ በቀተት -(ዳን፲፩ -፮። - -፲፩)

ቀታ -(ዐረ ቂሻእ) ቈስያ የዱባ ወገን አልቀታ ወሐምሐም -( - -፲፯)

ቀታሊ -(ሊት ልያን ያት ተልት) የሚገድል፤ ገዳይ፤ አጥፊ ቀታሌ ፍስ። ኮነተኒ ቀታሊተ ኖሎት ቀታልያን ቀተልተ በዊሆሙ -(ሢራ፴፩ -፳፭ ሮሜ፯ - ኤር፳፫ -፩። ፩ጢ - -) በቅቱል ፈንታ ቀታሊ ይላል፤ ስሕተት ነው ኢትግበርዋ ቀታሊተ ለምድርክሙ -(ዘኍ፴፭ -፴፫)

ቀትል -(ላት) ግድያ፤ ሰልፍ፤ ውጊት ጦርነት ቀትል በመጥባሕት ገብሩ ቀትለ ጸብእ ወቀትል። በሕገ ቀትል። ቀትላተ ሰይጣናት -(ዮሴፍ። ፩ዜና - -፩። ያዕ፬ -፩። ዮዲ፯ -፲፩ ፊልክ)

ቀትር -በቁሙ መንፈቀ መዓልት፤ እኩለ ቀን፤ ፮ኛ ዓት፤ የፀሓይ አፍሬ ቀርኑ ምዕዛሩ ምድርን ፊት ለፊት የሚወጋበት። ይጼልለከ ምፀሓየ ቀትር ቀትረ መዓልት። ቀትር። ብርሃነ ቀትር ጋኔነ ቀትር -(ሢራ፴፩ -፲፱ ፴፭ -፲፮። ማር፲፭ -፴፫። ኢሳ፲፰ -፬። መዝ -)

()          ቀትሮ ሮት -(ቀተረ ይቄትር ይቀትር። አው ቀቲር ቀተረ ይቀትር ይቅትር። ዐረ ቀተረ) ማዋደድ ማዛመድ መቸንከር መቀርቀር፤ መደንቀር የንጨት የብረት መዝጋት መቈለፍ ማጐር፤ መወርወር መሸጐር የመዝጊያ። ዐጸወ ኅተ ወቀተረ ዕጽዉ ኆኅተ ወቀትሩ። ወዳእነ ቀተርነ ኅተ -(መሳ፫ -፳፫ ፬ነገ - - ሉቃ፲፩ -)

 -በቁሙ፤ መቀተር ማሾል፤ ሹል ማድረግ ለማዋደድ ቀትር መኾን፤ የጊዜ ወቀቲሮ ስሱ ሰዓት -(ሉቃ፳፫ -፵፬)

 -ማጠን፤ ማጤስ፤ ማሽተት -(ዕብ ወሱር ቃጣር ቅጣር፤ ቋጠረ፤ ዐጠነ) በእንተ ዕጣኑ ለአሮን እንተ ቍረረ መዐተ ሞት ሶበ ቀተረ -(አዋል)

ቀቶት -ገባርነት ግብር ቍትቻ ውርርድ፤ ውሽንብር፤ የማጉስ የቍትቻ ዕዳ የውርርድ ገንዘብ። በእንተ ከመ መፍትው ይስተዩ በቀቶት አስተዋፂኦሙ። ወአንበሩ ቀቶተ በዝንቱ -(ቀኖ -ሎዶ -፶፩። ገድ -ተክ)

ቀነነ -ዐገገ፤ ሠራ፤ ደነባ ሕግ ሥራት ደንብ አቆመ፤ ቀኖና ሰጠ ቀንኑ ላዕለ ብእሲት ዝግዕት እመ ዘቀነነ ርእሶ በፈቃዱ -(ሲኖዶ ቄድር)

 -ቈነ መቍነን ሰጠ ዐደለ ረሰ ከፈለ ተነተነ፤ ዘገነ ታፈነ፤ የምግብ።

ቀነጠ -(ዕብ ቃኖጥ፤ ሀቅኔጥ) አስጮኸ አስቈጣ፤ አስወገሸ።

ቀኒት ቶት -(ቀነተ ይቀንት ይቅንት ዐረ ነጠቀ) መቀነት፤ መታጠቅ፤ ወገብን ማሰር ማጥበቅ፤ ማገልደም ማሸረጥ ማሸንፈጥ፤ ማሸንቀጥ፤ በትጥቅ ማጌጥ ቅንት ሐቌከ ከመ ብእሲ ቅንት ሰይፈከ ያል ውስተ ሐቌከ ቀነተት ሠቀ ውስተ ሐቌሃ ቅንት በልብሰ ዐጌ ወቀነትኩ። ህየንተ ቅናትኪ ዘወርቅ ሐብለ ቅንቲ -(ኢዮ፴፰ - መዝ - ዮዲ፰ -፭። ሄርማ ኢሳ፫ -)

ቀኒእ -(ረቲእ) በቁሙ፤ መቅናት፤ ቀጥ ማለት፤ ቅን እውነተኛ መኾን፤ መመቸት መፋጠን መከናወን፤ የሥራ አበያ ቢቀና ቤት ያቀና እንዲሉ ኢትቅንኡ መዊት -(ጥበ፩ -፲፪)

ቀኒእ ኦት -(ቀንአ ይቀንእ ይቅናእ። ዐረ ቀነአ። ዕብ ቃኔእ) መቅናት፤ መመቅኘት፤ ማዘን መቈጣት መበሳጨት፤ በሌላው ድልና ሀብት ወይም እንደ ርሱ ለመኾን መንቃት መትጋት፤ ርሱን አብነት ማድረግ ምን ፈቀረኝ ማለት። ኢትቅናእ ላዕለ አኩያን። ተመየጥ ኀበ ቃሕም ወቅናእ ርእየከ ፍናዊሁ። ቅናእ ለንስሓ -(መዝ -፴፮። ምሳ፮ -፮። ራእ፫ -፲፱)

ቀኒጽ ጾት -(ቀነጸ ይቀንጽ ይቅንጽ) መነሣት መቆም አፈፍ በርደግ ማለት መዝለል፤ መፈንጨት፤ መቅበጥ መቈጣት መቀናጣት፤ መር ቸር ባጥ ፊናጥ ማለት፤ መንጠቅ መሸሽ መሮጥ መፈርጠጥ ቀነጸ ምዲበ ሠረገላ ቀነጸ ላዕሌ ወቀተሎ በሰይፍ ቀነጹ ዕለ ሰራዊተ ዮናናውያን። ቀነጸ ምኔሃ ወወፅአ መጽአ ንዘ ይቀንጽ -(መጽ -ምስ። ዮሴፍ። ማሕ፪ -)

ቀናቲ -(ቲት ትያን ያት) የሚቀንት የሚያጠብቅ የሚታጠቅ ታጣቂ።

ቀናኢ -(ኢት እያን ያት) የሚቀና ቀናተኛ ምቀኛ። አነ እግዚ ቀናኢ ስምዖን ቀናኢ በዝኁ ቀናእያኒሁ ጸላእያንየ ወቀናእያንየ መበለታት እኩያት ቀናእያት ወመስተዋድያት -(ዘፀ፳ -፭። ሉቃ፮ -፲፭ ፈላስ ዮሴፍ ዲድ -)

ቀናዊ -(ዊት ውያን ያት) የሚቸነክር፤ የሚጠርቅ፤ ቸንካሪ።

ቀናዪ -(ዪት ይያን ያት፤ ነይት) የሚገዛ፤ የሚነዳ ገዥ አዛዥ ጌታ በዓልከ ኵሉ ባሪ ወቀናዪ ረፍት ውእቱ ናይያኒሆሙ ይቴ ሀለዉ ቀነይት ወቅኑያን -(ድጓ። መዋሥ አፈ -ተ፳፮ ግንዘ)

ቀንሞን -(ዕብ ቂናሞን ጽር ኪናሞን ዐረ ቂርፈት) ሽቱ የሽቱ ዕነጨት ስም፤ ቀረፋ። በቀንሞን ፈንታ ቀንሞስ ቀናንሞስ ወይም ኹሉን ጐርዶ ቀንሞ ቀናንሞ ይላል የጣፊ ስሕተት ነው -(ዘፀ፴ -፳፫ ራእ፲፰ -፲፫ ማሕ፬ -፲፬ ሔኖ፴ -፫። ፴፪ -)

ቀንዐ -ቀናቀኒእ ቀንአ።

()          ቀንአት [1]-(ዐረ ቂነት። ዕብ ሔልባና። ጽር ኻልባኒ) የሽቱ ዕንጨት ስም ከዕፀ ጣን አንዱ፤ በሶርያና በኢትዮጵያ የሚበቅል -(ዘፀ፴ -፴፬)

[2]-(ዐረ ዑድ ዕብ አሀሎት ጽር ስታክቲ) ሽቱ የሽቱ ስም፤ ዕጣን ስኂን ወቀንአት ወማየ ልብን ወሰንበልት -(ኩፋ -፫። መዝ -ጋዘ። ቅዳ)

ቀንዎ  ዎት -(ቀነወ ይቄኑ ይቀኑ መረ) መቸነከር፤ ማጣመር በችንካር ማጣበቅ መጠረቅ፤ መጓጐጥ መጠቅጠቅ መውጋት ማቍሰል መብሳት መንደል ቀኑ ፍቅረከ ውስተ ልብየ ነዉኒ ደውየ ወእገርየ በቅንዋቲከ ቀነውኮ ለሞ -(ያዕ -እል። መዝ -፳፩። ግንዘ)

ቀንይ ዮት [1]-(ቀንየ ይቀኒ ይቅነይ ዕብ ቆኔን) ጩኾ ማልቀስ መቈዘም፤ ማሞሽ መግጠም፤ ማዜም ማጕረምረም፤ መቀንቀን መዝፈን፤ መምራት መቀኘት፤ መሪ ቀንቃኝ፤ ባለቅኔ መኾን። መጽሐፍ ግን በቀንየ ፈንታ ተቀንየ ይላል፤ አያሰኝም፤ ያማርኛ ነው። ረከብዎ ለአ የሴፍ እንዘ ይትቀነይ ምስለ ሐዱ መነኮስ። ካህናት ይትቀነዩ ዘንተ መዝሙረ በዜማ ሐዘንዚን። ወእምዝ በል ወተቀነይ ሃሌ ወአኀዘ ይትቀነይ በሠለስቱ ዜማ -(ስንክ -ጥቅ፳፫ ግንዘ ድጓ። ታምር)

 [2]-(ቀነየ ይቀኒ ይቅኒ። ቃናህ ሱር ቅናእ። ዐረ ቀነይ) መግዛት መዋጀት፤ መቤዠት፤ መውሰድ ገንዘብ ማድረግ በዋጋ፤ ጠረየን ተመልከት። መፍጠር መሥራት፤ መግዛት መጌትየት፤ ገዥ አዛዥ ጌታ መኾን ግድ ማሠራት ማስገበር ማሳረስ ማስቈፈር ባሪያ ማድረግ። ውእቱ ይቅኒኪ ወይቀንይዎሙ አርባዕተ ምእተ ዓመተ። እለ እኩየ ቅኔ ይቀንይዎሙ ንቅንዮ ነዳይ በዕዳነ -(ዘፍ፫ -፲፮። ፲፭ -፲፫ ኢሳ፲፱ -፬። ዓሞ፰ -)

ቀንዲላት ቀናዲል -ቀንዲሎች፤ መብራቶች፤ ማብሪያዎች -(ስንክ -መስ፲። ጥር፴) ቈንዳላ ማለት ዐማርኛው ከዚህ የወጣ ነው።

ቀንዲል -(ዐረ ቂንዲል) መብራት፤ ማብሪያ፤ የዘይት የሠም፤ መደበኛው ግን ዘይት ነው ለእመ ልቀ ቅብዐ ዘይት አምቀንዲል ወኢይቀድሱ በአሐዱ ሠምዕ አላ በክልኤቱ በገበዋተ ምሥዋዕ በቀንዲል ህየንተ ሠለስቱ ሠምዕ -(መጽ -ምስ። ሥር -ቅዳ) መጽሐፈ ቀንዲል፤ መጽሐፈ ዘይት ጸሎተ ዘይት ቅብዐ ድዉያን፤ በዘይት ላይ የሚነበብ የሚጸለይ።

ቀንጠሰ -(798) -(ቀንጠበ) ቀነጠስ፤ ቈረጠ በጠሰ፤ ለቀመ፤ የጐመን የሥንቆ። አልቦሙ ዘይበልዑ ዘእንበለ ሐምለ ገዳም ይቀነጥሱ ምአድባር ወይሴሰዩ -(ዕር -ኢሳ)

ቀንጠወ -ቈነጠነ አሰከረ፤ አቀናጣ፤ ጤና ነሣ፤ ልብ አሳጣ፤ አብዝቶ የበሉት የጠጡት።

ቀንጦስጤ -(ጽር አኮንቲስቴ) ወራውያን፤ ነዳፍያን፤ ቀስተኞች -(፩ነገ -፴፩ -)

ቀኖት -(ታት) ችንካር ምስማር እኾኽ ጋሬጣ፤ የብረት የንጨት። በቀኖት ጽንዕዎ። አይቴ ውእቱ ቀኖትከ ሞት ይከውኑክሙ መሥገርተ ወዕቅፍተ ወቀኖታተ -(ኤር፲ -፬። ሆሴ፲፫ -፲፬ ኢያ፳፫ -፲፫)

ቀኖና -(ናት ጽር ካኖን) ሕግ ሥርዐት ደንብ ፍርድ ቅጣት ቀኖና ብሂል ሥርዐት ቀኖናተ ነገሥት። እመ ብእሲ ዘዘመወ ምስለ ወለተ ብእሲቱ ቀኖናሁ ዐሠርቱ ወኀምስቱ ዓመት። ዘዘመወ ምዕረ አሐተ ያጹርዎ ቀኖና ቀሊለ ወለእመ ተመይጠ ያክብዱ ላዕሌሁ ቆኖና። ወሀቦ ቆኖናተ ክቡዳተ -( - - -፫። -፮። ስንክ -ነሐ፲፭)

ቀዊል ሎት -(ቆለ፤ ቀወለ ይቀውል ይቁል። ዐረ ቃለ) ብሂል፤ ነቢብ፤ ደሚፅ፤ ማለት መናገር፤ መጮኽ ቃል መስጠት ማሰማት ከጥሬው በቀር አንቀጹ አይገኝም። ቆሌ ቀውላላ ቃቂል ቃጭል ማለት ከዚህ የወጣ ነው

ቀዊም ሞት -(ቆመ ይቀውም ይቁም ዕብ ቁም ሱር ቃም ዐረ ቃመ) መቆም መነሣት፤ አፈፍ በርደግ ቀጥ ማለት፤ እንደ ምድ መኾን፤ መጽናት መበርታት መሸራሸት ቁሙ ወአጽምዑ ወንጌለ ብዙኃን ቆሙ ላዕሌ ቁም በእገሪከ አእጋሪከ እለ ጠብዓ ለቀዊም -(ቅዳ። መዝ - ሕዝ፪ - ደራሲ)

 -መገታት፤ መከልከል፤ ቁሞ መቈየት፤ መጽናት ጸንቶ መኖር ቀዋሚ መኾን፤ መተካት መውረስ ያባትን ወይም የሌላውን ሥራና ስፍራ መያዝ ቆመ ዝናም እምሰማይ ቆመ ውሕዘተ ደማ ቁመኒ ቁመኒ በእንተ አግዚ ይቀውም መንግሥቱ ወኵሉ ቦቱ ቆመ ሃይማኖትሰ ትቀውም ለዓለም ይቀውም ትእዛዙ ወኢይቀውም ዘርዑ -(ዘፍ፰ - ሉቃ፰ -፵። ገድ -ተክ ሉቃ፲፩ -፲፰ ቆላ፩ -፲፯ ራ፵ -፪። - -፵፩። ኤር) ተወልደ ተፈጥረ ተሣረረ በማለት ፈንታ ቆመ ይላል፤ የመላሽ ስሕተት ነው። ዘእንበለ ትቁም ምድር ንበለ ይቁሙ አድባር -(ሱቱ -ዕዝ፩ -፮። መዝ -፹፱)

ቀዊዕ ዖት -(ቆዐ ይቀውዕ ይቃዕ ይቅዋዕ) መዘርዘር መውለድ፤ መጨቋት፤ መዠመር መቋጠር። የአዝርዕት የአትክልት። መልቀም መቃረም፤ መቀዋት መቅሠም። ቈዐለን እይ፤ የዚህ ዲቃላ ነው

ቀዋሚ -ቀዋሚ -(ሚት ምያን ያት) በቁሙ የሚቆም ቋሚ ጸንቶ የሚኖር ጠበቃ የነገር አባት መጋቢ ሹም ሱራፈል ወኪሩቤል ቀዋምያን ዐውደ መንበሩ ጽርሕ ቀዋሚት እንተ ትወድቅ። ቀዋሚ ይረክብ ስብሐተ ዋሚሃ ለመዐስብ። ቀዋሚ ለመበለት ወለዕጓለ ማውታ ወይርአይ ሊቀ ምኔት ምአኀው ኀበ ዘሎቱ ምግባር ሠናይ ወይረስዮ ቀዋሜ ላዕለ ምኔት ወላዕለ መዛግብቲሁ -(ግንዘ። ርጋ -፫። ፪ቆሮ - -፲፩ ድጓ ኪዳ - -)

ቀዋም -ቀዋሚ፤ ጠንካራ፤ ቁመታም ረዥም ኵሉ አረፍት ቀዋም -(ኢሳ፪ -፲፭)

ቀዋብዕ -(ቀዋብዕት፤ ቆብዓት) ቆቦች የራስ ልብሶች ሥራዕ ሎሙ ቀዋብዕተ ዘአልቦ ዝዕላ -(ሥር -ጳኵ)

ቀውስ [1]-(ዐረብ) ቀስት፤ ደጋን -(ገድ -አዳ)

[2]-(እልቀውስ) ኮከብ፤ የኮከብ ስም መልኩ ቀስተኛ ባለቀስት የሚመስል ኮከብነቱም የኅዳር ነው፤ ከፀሓይ ጋራ ፳፱ ዕለ ፳፰ ኬክሮስ ይመግባል -(አቡሻ -)

ቀውዕ ቆዕ -ጨርቋ፤ እንጭጭ፤ ቃሪያ። መከር አዝመራ -(ትግሬ) በጽሐ ጊዜ ውዕ ቆዐ ትጼኑ ቆዐ ጽጌ ወይን። አበው በልዑ ቆዐ ከመ ቆዐ ቀምሕ ፍሬሆሙ ቆዕ ከንቱ -(መጽ -ምስ ድጓ ሕዝ፲፰ -፪። ሢራ፶፩ -፲፭ ጥበ፬ -) ኮል ዕንጐት በማለት ፈንታ ቆዕ ይላል ሕተት ነው። ምስለ ናርዶስ -(ማሕ፬ -፲፫)

 -ቅላ፤ ሕፃን፤ ለጋ ቀንባጥ፤ ዝርዝረ ቀጭ ዐመደ ፈጭ እንዘ ተመሥጠ ሕፃነ -(ጥበ፲፬ -፲፭። ምሳ፲፫ -)

ቀዘፈ -(ዐረብ) በቁሙ ዐረቦች ዳሌጥን ቍጣ እየጨመሩ ይሉታልና፤ ስለዚህ ቀዘፈ ቀደፈ እያለ በኹለት ይጥፋል። ቀያፈንና ኀደፈን እይ

ቀየሰ -ቀየሰ -(ትግሬ ወዐረብ) ለካ፤ ፈረ ገመተ

(ጥዪ)        ቀዪሕ ሖት -(ሕት ሓን ሓት ያሕ) ቀይ፤ እሳት የሚመስል። አርዌ ቀይሕ ከመ ጽጌ ረዳ ቀይሕት። ዕጐልት ቀያሕ አፍራስ ቀይሓን። ሕብራት ቀይሓት -(ራእ፲፯ -፫። ስንክ -ሠኔ፩ ዘኍ፲፱ - ዘካ፩ -፰። ፈላስ)

ቀዪሕ ቀይሕ -(ቄሐ ይቀይሕ ይቂሕ ዕብ አዳም የኤዳም) መቅላት ቀይ መኾን ደም መምሰል ለምንት ቄሐ አልባሲከ ቄሐ ከመ ደም ውእቱ ማይ። ይቀይሕ እምጽጌ ረዳ -(ኢሳ፩ -፲፰ ፷፮ - ፬ነገ - -፳፪ ሔኖ)

ቀዪእ ኦት -(ቄአ ይቀይእ ይቂእ ቃእ። ዐረ ቃአ) ቋቅ ማለት ማስታ ወክ ማስመለስ፤ መትፋት መቀርሸት፤ ባፍ የገባውን መልሶ ባፍ ማውጣት፤ የሰው ነገር ትምርት ክር አለመቀበል። ብላዕ በዐቅም ከመ ኢትቂእ። ቄአ እምአፉሁ ደመ ብዙኀ። ቄእከ ሕምዘ እማፉከ ላዕለ ሔዋን። እምከመ ሰምዐ ይቀይኦ ወያገብኦ ድኅረ ዘባኑ -(ምሳ፳፭ -፲፮። ዮሴፍ። መቃ። ሢራ፳፩ -፲፭)

ቀያሕይት -(ዕብ አዳምዳሜት) ያቀይ ቀያቴ ዳማ ጥቂት ቀይ ፈገግ ያለች በጣም ያልፈካች፤ ያልፈነዳች የለምጽ አበባ፤ ቡቃያ -(ዘሌ፲፫ -፳፬ -፵፱። ፲፬ -፴፯)

ቀያሚ -(ሚት ምያን ያት) የሚቀየም፤ ተቀያሚ፤ ቂመኛ -( - -)

ቀያኢ -(ኢት እያን ያት) የሚተፋ፤ ትፋታም፤ ቅርሻታም።

()          ቀይሞ  ሞት -(ቀየመ ይም ይቀይም ናቃም ሱር ንቃም። ዐረ ቀመ) መቀየም፤ መበቀል፤ ቂም በቀል መያዝ ክፉ ማሰብ መመኘት፤ ለክፉ የክፋቱን ዋጋ ለመመለስ ማድባት ማሸመቅ፤ ጊዜና ቦታ መፈለግ። መጽሐፍ ግን በቀየመ ፈንታ ተቀየመ ይላል፤ ያሰኝም ያማርኛ እንጂ የግእዝ አይዶለም። ቂመኑ ትትቄየማኒ ትትቀየም ቢጸከ ተቀያሚ ወመፍቀሬ ንዋይ። ኢኮነ ከመ ዕጓለ መሕያው ዘይትቄየም -(ዮኤ፫ -፬። ሢራ፳፰ -፯። ማር -ይሥ፪ -፲፫ ዮዲ፰ -፲፮) በቀለን ተመልከት።

ቀይስ -ቄስቀሰሰ

ቀይጡን -(ዐረብ) ጓዳ፤ ጐድጓዳ፤ ሰግዳዳ በቤት ውስጥ ያለ ክፍል፤ የዕቃ ማኖሪያ፤ መሰወሪያ፤ የቁም ሣጥን። ቀይጡነ አውታን ዘውእቱ ብሂል ቤተ ጣዖት -(አቡሻ -)

ቀዲሕ ሖት -(ቀድሐ ይቀድሕ ይቅዳሕ። ዐረ ቀደሐ። ዕብ ቃዳሕ፤ ነደ ውዕየ) መቅዳት፤ መጥለቅ፤ መደንበቅ፤ መጨለፍ መጨመር፤ መገልበጥ ማሳለፍ መሰብሰብ  መልቀም ማጠራቀም። የፈሳሽ የቃል የመጣፍ፤ የእሳት የመብራት የጧፍ ለቀዲሐ ማይ። እለ ይቀድሕዎ ለሜስ ወይን ዘቀዳሕኩ ለክሙ። መጽሐፈ ስንክሳር ዘበትርጓሜሁ ጉባኤ ዘቀድሕዎ በዊነ ምኵሎን ገድላት -(ኩፋ -፪። ኢሳ፭ -፳፪። ምሳ፱ -፭። ስንክ -መስ፩)

 -መብሳት መንደል። መታመም መተኰስ መላብ መውዛት ውሃ መኾን፤ መቅለጥ መቅዘን

ቀዲሙ -(አገባብ) ቀድሞ፤ አስቀድሞ፤ ፊት ጥንት ዱሮ መዠመሪያ እለ የአምርዎ ቀዲሙ ቀዲሙ ዜነወነ እምቀዲሙ ወቀዲሙሰ ነገርኩክሙ ቀደሙኒ እምቅድመ መዋዕል -(ኢዮ፵፪ -፲፩ ኤፍ -፩። ዮሐ፩ - ፲፮ -፬። ግብ፭ -፴፮)

ቀዲም -(ቀደመ ይቀድም ይቅድም። ዕብ ቃዳም። ሱር ቅዳም ዐረ ቀደመ) መቅደም፤ ፊተኛ፤ መዠመሪያ መኾንመላቅ መብለጥ መዠመር መወጠን ለደም ይቀድሞ ኳ። ይቀድመኒ ወሪደ ምኵሉ ዘይቀድም። ቀደመት ማርያም ወትቤ። ቅድሙ እምቅዱሳንየ -(ሢራ፳፪ -፳፬ ዮሐ፭ - ያዕ፭ -፲፪። ዘፀ፲፭ -፳፩ ሕዝ፱ -)

 -ቅድምና፤ በኵርነት። ቀዲም ዘኮነ ሎቱ በውስተ ርስት -( - -)

ቀዲው ዎት -(ቀደወ ይቀዱ ይቅዱ ዕብ ቂዳ ሽቱ ቀረፋ) ማማር፤ መሽተት፤ መጣፈጥ፤ መንጻት መጥራት፤ ንጹሕ ብሩህ ጸዐዳ መኾን፤ ከዚህ የተነሣ መወደድ መክበር ቀደወ ኅሊናሁ አላ ከመ ዛሕለ ብርት ኮነ -(መጽ -ምስ)

ቀዲድ ዶት -(ቀደ ይቀድድ ይቅድድ ዕብ ቃዴድ) መቅደድ መሠንጠቅ ማረስ መግመስ፤ የመሬት የልብስ። -(ተረት) ከቀዳዳ ይሻላል ጠምዳዳ መቃድ ቅድ ቃዳ ቈዳ ማለት ዚህ የወጣ ነው

ቀዲፍ ፎት -(ቀደፈ ይቀድፍ ይቅድፍ ዐረ ቀዘፈ) መቅዘፍ ባሕርን መቅደድ ታንኳን መርከብን መምራት መውሰድ፤ ማስኬድ ኀደፈን ተመልከት፤ የዚህ ጎረ ቤት ነው እለ ይቀድፉ -(ሕዝ፳፯ - -፳፯ -፳፱ -፴፭)

ቀዳሒ -(ሒት ሕያን ያት ሕት) የሚቀዳ፤ ቀጂ፤ አሳላፊ። ሐጣብያነ ዕፀው ወቀዳሕያነ ማይ። ወቀዳሕቶኒ ሊቀ ቀዳሕያን -(መቃ። ነገ - -፭። ዘፍ፵ -)

ቀዳሚ [1]-(ሚት ምያን ያት ደምት) በቁሙ፤ የሚቀድም የሚበልጥ ታላቅ ደገኛ፤ ፊተኛ ዠማሪ ቀዳሚ ወደኃሪ ትእዛዝ ቀዳሚት። ቀዳሜ ጽላት ከመ ቀዳምያት በው ቀደምት። ነቢያት ቀደምት -(ቅዳ። ማር፲፪ -፳፰ ሊጦ። ዘፀ፴፬ -፩። ሔኖ ዘካ፩ -)

[2]-(አገባብ) ቀድሞ ዱሮ ጥንት ፊት፤ መዠመሪያ። እምቀዳሚ መዋዕልኪ። ዘቀዳሚ ወዘደኃሪ። ቀዳሚ ጸሐፍኩ በቀዳሚ ገብረ እግዚ -(ዮዲ፰ -፲፬ መዝ -፻፴፫ -፩። ዘፍ፩ -)

ቀዳማዊ -(ዊት ውያን ያት) አው ቀዳማይ፤ -(ይያን ያት ይት ) የቀዳም፤ የቅዳሜ። በቁሙ፤ ፊተኛ የፊት የዱሮ መዠመሪያ ተቀዳሚ፤ ታላቅ በኵር ግንባር ቀደም  መስተጽዕነ መስቀል ፈረስ መድኀኔ ዓለም ዘቀዳማይሁ ጽፍዐት ወደኃራይሁ ቀሥፎ ህርቃኖስ ቀዳማዊ። ቀዳማየ አውራኅ ወተወልደ ውእቱ ቀዳማይ እመንፈስ ቅዱስ -(ቅኔ። ዮሴፍ ዘፀ፲፪ - ቄር -)

ቀዳማይ (ይያን ያት ይት ) የቀዳም የቅዳሜ። በቁሙ ፊተኛ የፊት የዱሮ መዠመሪያ ተቀዳሚ ታላቅ በኵር ግንባር ቀደም  መስተጽዕነ መስቀል ፈረስ መድኀኔ ዓለም ዘቀዳማይሁ ጽፍዐት ወደኃራይሁ ቀሥፎ ህርቃኖስ ቀዳማዊ። ቀዳማየ አውራኅ ወተወልደ ውእቱ ቀዳማይ እመንፈስ ቅዱስ (ቅኔ። ዮሴፍ ዘፀ፲፪ ቄር )

ቀዳም -መዠመሪያ፤ ቅዳሜ፤ ሰንበተ አይሁድ የእሑድ ምሳሌ መንገደ ቀዳም። ሺሕ ክንድ ማለት ነው -(ግብ፲ -፲፪)

ቀዳሲ -(ሲት ስያን ያት) የሚቀድስ ቀዳሽ አክባሪ ምላክ ዘውእቱ ሐዋጺሆሙ ወቀዳሲሆሙ -(አቡሻ -)

ቀዳዊ -(ዊት ውያን ያት ደውት) የሚያምር ደስ የሚያሰኝ አልባስ ቀደውት -(ሉቃ፲፭ -፳፪)

ቀዴሚን -(ጽር ዴሚን። ዕብ ቅዱሚም) አዝማን ቀደምት መዋዕለ ትካት አዕዋደ ቀትል -(መሳ፭ -፳፩)

ቀድሀ -ቀዳ፤ቀዲሕ ቀድሐ

ቀድሕ ቅድሕ -ቀዳ፤ቀዲሕ ቀድሐ

()          ቀድሞ ሞት -(ቀደመ ይቄድም፤ ይቀድም። አቅደመ) መቀደም፤ ማስቀደም፤ ቀዳማይ ማድረግ ቀዳማይ ማግባት ማንጠልጠል -(ግጥም፤ ዘራፊ የመርቆሬዎስን ጽላት በኮርቻው ራስ በቀዳማይ ሰቅሎ ስለ ወሰደው) ፈረሰኛ አላምንም እኔ ምን ቢኾን፤ ቀደሙት ይሉኛል መርቆሬዎስን።

ቀድሶ ሶት -(ቀደሰ ይቄድስ ይቀድስ። ዕብ ቂዳሽ ሱር ቃዲሽ ዐረ ቀደሰ) መቀደስ፤ መባረክ ማመስገን፤ ማክበር ማግነን፤ ማንጻት ማጥራት መለየት፤ ለእግዜር መስጠት የእግዜር ገንዘብ ማድረግ ለቀሲስ ሎቱ ሐዱ ሥልጣን፤ ወውእቱ ከመ ይምሀር ወያጥምቅ ወይቀድስ ወይባርክ ሕዝበ ቀድሱ ኵሎ አብያተ ክርስቲያናት ዘሐነጽክምዎሙ ወኅትምዎሙ በማኅተመ እግዚ ዘውእቱ ቅብዐ ሜሮን ቅዱስ። ቀድስዎ ለእግዚ ባረካ ወቀደሳ ያነጽሕ ወይቄድስ እምኵሉ ርኵስ። ቄድሶሙ ሕዝብ ሊተ -( - -፮። - -፳፰ -፩። ኢሳ፰ -፲፫ ዘፍ፪ -፫። ዘሌ፲፮ -፲፱ ኩፋ -)

ቀጋ -(ጋት) በቁሙ ስመ ዕፅ እሾኻም አበባው የሚሸት ፍሬው የሚጥም -(ተረት) የቤት ቀጋ የሜዳ ዐልጋ እንተ ትሰመይ ባሕረ ቀጋ -(ገድ -ተክ)

ቀጠራቅጢን -(ጽር ካታራክቲስ) የባሕር ወፍ፤ እንደ ዝይ እንደ ሶረን ያለ ባለብሉዮች ግን ድንቢጥ ይሉታል -(ዘሌ፲፩ -፲፯ ዳ፲፬ -፲፯)

ቀጢብ ቦት -(ቀጠበ ይቀጥብ ይቅጥብ። ዕብ ቃጣብ) መቃጠብ ማለብ፤ ማመልከት፤ ለመቍረጥ ለመበጠስ፤ የዝሓ የልብስ። መቈጠብ መንፈግ ቀንጠበን እይ፤ የዚህ ስሯጽ ነው

ቀጢን ናት [1]-(ቀጠነ ይቀጥን ይቅጥን ሱር ቅጢን ዕብ ቃጦን) መቅጠን ማነስ ቀጭን መኾን

[2]-(ጥጢ) ቀጢን፤ -(ናን ናት ጣን፤ ጠንት) የቀጠነ፤ ቀጭን ሥሥ ረቂቅ ልብስ ቀጢን ዘይትዐጸፍ ካህን። ሰብዐቱ ሠዊት ቀጢናን። አስናኒሁ ቀጢናት። በቀጣን ዐይነ ልብ። በቀጠንት ገለድኩ ምስካብየ ብእሲ ዘርሱይ በቀጠንት ልባስ እለ ቀጠንተ ይለብሱ ውስተ አብያተ ገሥት ሀለዉ -(ሢራ፶ - ዘፍ፵፩ -፮። ዜና -እስ ቄር - ምሳ - -፲፮ ማቴ፲፩ -)

ቀጢፍ ፎት -(ቀጠፈ ይቀጥፍ ይቅጥፍ። ዕብ ቃጣፍ) መቅጠፍ መዘንጠፍ መቀንዘፍ፤ መቅጨት፤ መቀንባት፤ መሸምጠጥ፤ መቍረጥ፤ መንቀል መላሰስ፤ የቅጠል የሠዊት። ንትፈሣሕ በዕፀዊሃ ወአኮ ዘንቀጥፍ እምፍሬሃ -(ቅዳ -አት። ሕዝ፲፯ -)

 -መዋሸት፤ ነገር ማበላሸት፤ -(ዐማርኛ) ሌብነትንም ያሳያል

ቀጣ -(ዕብ ቃጥ፤ ጥቀ) ታናሽ የወርቅ ገንዘብ፤ የወቄት ኻያኛ ተሣየጠ በኀምሳ ቀጣ -(አዋል)

ቀጣፊ -(ፊት ፍያን ያት) በቁሙ የሚቀጥፍ፤ የሚዋሽ፤ ዋሾ ሌባ ላዩ ጣፊ ውስጡ ቀጣፊ እንዲሉ።

ቀጥቃጢ -(ጢት ጥያን ያት) የሚቀጠቅጥ፤ ቀጥቃጭ፤ አንጥረኛ።

ቀጥቅጦ  ጦት -(ቀጥቀጠ ይቀጠቅጥ ይቀጥቅጥ። ዕብ ቃጥቄጥ) መቀጥቀጥ፤ መጨፍለቅ፤ መውገጥ ማድቀቅ፤ መላልሶ መምታት፤ መሰባበር፤ ማንከት፤ ማጥፋት። ሥሩና ምንጩ ቈጢ ቈጠ ጠጠ ነው ቀጥቅጥ መዝራዕቶ መፍጽሐ ጺን ዐፅመ እገሪሁ ቀጥቀጡ። ቀጥቅጦ ለፀራዊ እግ ይቀጠቅጥ ጸብአ ወቀጥቀጦሙ እግዚ ዐቢየ ቅጥቃጤ ንቀጥቅጦ እምድረ ሕያዋን -(መዝ -፱። ስንክ -ነሐ፳፭ ሢራ፴፫ -፱። ዘፀ፲፭ -፫። ኢያ፲ - ኤር፲፩ -፲፱)

ቀጸለ -(ይቄጽል ይቀጽል ቀጽሎ) ቀጠለ ቀጣጠለ፤ መረ የቁመት የፍሬ የትምርት

ቀጸላ -(ላት) [1]-በቁሙ፤ የራስ ልብስ ጌጥ ሽልማት፤ ታናሹም ታላቁም፤ ማናቸውም ኹሉ በየስሙና በያይነቱ ወገሮ ሥልሶ ሠርመዲ ከሎታ አክሊል ዘውድ ሜትራ፤ ፌት ቆብ መጠምጠሚያ ጠርቡሽ ባርኔጣ፤ የመሰለው ኹሉ። ዕጨጌዎችና አበ ምኔቶች በቆባቸው ላይ የሚለብሱት የሚከናነቡት ሻሽ ነጠላ። ወህየንተ ዘወርቅ ቀጸላሃ ብርሐት ወፅአ ላዕሌ ወድማኅ ኢኮነት ድማኀ ወዲበ ርእሶሙ ቦሙ ጸላ በአምሳለ ወርቅ ሰብዐቱ ቀጸላት። ወተቀጸሊ ቀጸላኪ ዲበ ርእስኪ ዘስብሐቲሁ ቅዱስ። ቀጸላቲሆን ወባሕርያቲሆን -(ቅኔ። ራእ፱ -፯። ፲፪ -፫። ባሮ፭ -፪። ኢሳ፫ -፲፱)

[2]-ቅጽል በስምና በግብር የሚጨመር ቃል፤፲ የአካልንና የግብርን አኳኾኀ ጠባዩን መልኩን የሚገልጥና የሚያስረዳ። ነዊኅ ሠናይ ጸዐዳ እንደ ማለት

ቀጸወ -ጣደ አበሰለቀፀወ

ቀጺመት -(ታት። ዕብ ቅጺዓህ፤ ቃኔ ዐረ ቀጸብ) ሽቱ የሽቱ ዕንጨት ስም ውስጠ ክፍት፤ የመቃ የሸንበቆ ዐይነት ቀጺመት ወቀናንሞ -(ስንክ -ነሐ፳፯ ዘፀ፴ -፳፫ ማሕ፬ -፲፬)

ቀጺር ሮት -(ቀጸረ ይቀጽር ይቅጽር። ዐረ ቀጸረ። ዕብ ቃጻር ዐጨደ፤ አነሰ) መቅጠር ማጠር መጀጐል፤ ማረድ መመሸግ፤ በቤት በከተማ ዙሪያ ዐጥር ቅጥር መሥራት፤ መክበብ፤ ዙሪያውን መያዝ። ወቀጸሩ ላዕለ ህጉር -(ዮዲ፬ -) ሐጸረን ተመልከት

 -ቀጠሮ ማድረግ፤ ቀን መቍረጥ፤ መወሰን -(ዐማርኛ) ዐደመን እይ

ቀጺብ ቦት -(ቀጸበ ይቀጽብ ይቅጽብ ዐረ ቀጸበ። ዕብ ቃጻብ፤ ረጠ ወሰነ) መቅጸብ፤ ዐይንን መክፈትና መክደን መጥቀስ በዐይንና በእጅ መጥራት ማመልከት ከንፈርን መንከስ። -(ተረት) ባይን ጥቅሻ በከንፈር ክሻ ይቀጽብ በዐይን ይቀጽብ በእዴሁ አንበስብሶ በቀራንበት ወቀጺብ በአዕይንት ዘእንበለ ፍረት ወቀጸባ ከመ ታምጽእ -(ምሳ፮ -፲፫ ኪዳ - -፴፬ -፰። ገድ -ተክ)

 -መመሰል፤ መተረት፤ ምሳሌ መስጠት። መፍጠን መቀልጠፍ ማፌዝ ማላገጥ

ቀጺዕ ዖት -ቀጺዕ፤ ዖት -(ቀጽዐ ይቀጽዕ ይቅጻዕ ዕብ ቃጻዕ። ዐረ ቀጠዐ) መቅጨት መቅጻት፤ እየለኩ፤ እያስተካከሉ መቍረጥ ማጠፍ ማጕበጥ ማረቅ፤ ማስጐንበስ፤ ማስጨነቅ። የጫማ የብራና የማኅደር የልብስ፤ የወገብ የደጋን እለ ይቀጽዑ ቀሚሰ ጽዕዋ ለነፍስየ። ይቀጽዕ ኵሎ ሐቌ ያደነግፁ ወይቀጽዑ ከመ ማሕምም -(ገድ -አዳ። መዝ -፶፮። ናሖ፪ -፲። ሢራ፴፩ -)

 -ማወቅ ዐውቆ መሥራት መቅጣት፤ መደልደል ማስተካከል መጥረግ መመድመድ የሰው የቦታ የመንገድ። አሠር ዘቀጻዕነ ፍኖትየ ወአሠርየ አንተ ቀጻዕከ ወቀጻዕክዋ በጾም ለነፍስየ -(ኢዮ፭ -፳፯ መዝ -፻፴፰ -፷፰) ዘቀጻዕነ  በማለት ፈንታ ዘአቅጻዕነ ይላል፤ ስሕተት ነው። ባለብሉዮችም ያሶጋነው ወግ ያስተረክነው ታሪክ ብለው ይፈቱታል።

ቀፂው ዎት -(ቀፀወ ይቀፁ ይቅፁ ዕብ ቃጻህ፤ ቈረጠ ለየ) መጣድ ማስረር መቀቀል ማንፈር

ቀጻሪ -(ሪት ርያን ያት፤ ጸርት) የሚያጥር የሚቀጥር ቀጣሪ፤ ቅጥር ሠሪ

ቀጻዕ ቀጻ -( ቀጻት) የእሳት እራት ባሕርይ ፈቃዱ የሚቀጣ የሚቃጠል፤ ቅጣት የሚቀበል፤ ኋላም ታድሶ የሚነሣ የትንሣኤ ሙታን ምሳል ዖፍ ዘይሰመይ ቀጻ -(ሃይ -አበ -ኤጲ)

ቀጻጴ -(ቀጻቢ ቀጸበ) ገበሎ በና እንቃቅላ የዕሥሥት ዐይነት -(አዋል)

ቀጽቀጸ -(ቀጥቀጠ) አንቈጨቈጨ ፈጨ ረጠመ፤ ወዘወዘ፤ አራደ አንቀጠቀጠ፤ የደዌ የሐዘን የፍርሀት። በእንተ ዝንቱ ይቀጸቅጸኒ ሐቌየ -(ኢሳ፳፩ -)

ቀጽበ -(ትግ ዕብ ቃጸፍ) ተቈጣ ተናደደ፤ ወገሽ አበደ ቱግ አለ እሳት ኾነ

ቀፈር ቅፍር -ክርክር፤ ፍልቅ፤ ፍልፍል፤ የዥማት መግቢያ የንጨት መጋጠሚያ። ቀፈረ ሐጽ። ቀፈረ ዐምድ -(ማር፲ -፳፭ ዘፀ፳፮ -፳፬)

ቀፈት [1]-ጫንቃ ደንደስ ጥናት፤ ድርቅና ጭካኔ፤ ትዕቢት ግዘፍ ድንዳኔ። ቀፈቶሙ ጸኒኖሙ ይወዲ ርእሶ ብረኪሁ ወያደንን ቀፈቶ ወያቴሕት ኅሊናሁ ኢያትሐትከ ቀፈተ ልብከ ፈተ ልብ ዘሥጋ -(ቄር። ቄድር። መቃ ቅዳ)

[2]:-ደንደስ፤ቀፊፍ።

ቀፈዋት -ቀፎዎች ክልኤ ቀፈዋተ -(ገድ -ተክ)

(ጥፊ)        ቀፊል ሎት -(ቀፈለ ይቀፍል ይቅፍል። ዕብ ቃፋል) ማጠፍ መደረብ፤ ዕጥፍ ድርብ ማድረግ፤ መጠምጠም፤ ማልበስ መሸፈን፤ መለበጥ ማስጌጥ። በዐረብ ግን ቀፈለ ብሎ ለፈ ዘጋ ያሰኛል። ከመ ብሩረ ተምያን ዘቀፈልዎ ዕለ ንዋየ ብሓ ዘቀፈሎን ብሩር። ቀፊልየ በዐረር -(ምሳ፳፮ -፳፫ ዘፀ፴፰ -፲፱ ድር -ሚካ)

ቀፊር ሮት -(ቀፈረ ይቀፍር ይቅፍር) መቈፈር መፈልፈል፤ መፈለቅ፤ መከርከር፤ የመሬት የንጨት፤ የደጋን የሚዛን። መቀፈር መቀቀር ማለብ መደገን፤ የዦሮ የቀስት የነፍጥ መጠየቅ መመርመር ትንቢት መፈለግ፤ ከነቢይ ከካህን

ቀፊጽ ጾት -(ቀፈጸ ይቀፍጽ ይቅፍጽ። ዕብ ቃፋጽ፤ ቀነጸ) መግለጥ፤ መክፈት መግፈፍ፤ ማስራቈት። ቀልዐን ተመልከት የዚህ መንቲያ ነው። ቀፈጽኪ አቍያጸኪ። ቀፈጽኪ ኀፍረተኪ መኑ ይቀፍጽ ግልባቤ ገጹ ይቀፍጾን ግዚ ልባሲሆን -(ሕዝ፲፮ -፳፭ -፴፮። ኢዮ፵፬ -፬። ኢሳ፫ -፲፯)

ቀፊፍ -(ቀፈ ዐረብ ሱር ቃፊፍ ዕብ ቃፋእ) መርጋት፤ መጽናት፤ እንደ ዳቦና እንደ ደንጊያ መኾን፤ የፈሳሽ ነገር፤ የሠም የውርጭ የመሰለው ኹሉ። መጨከን ልበ ደንጊያ መኾን፤ አለመራራት አለማዘን፤ መወፈር መግዘፍ መታበይ። በቁሙ፤ መቅፈፍ መከርከም ማስተካከል። -(ዐማርኛ)

ቀፋዲት -(ጽር ኻፉሪ። ዕብ ክፎሬይ) ምንዛህ፤ ምዝራቅ የውሃ የጠበል መርጫ ነዝሀንና ዘረቀን ተመልከት -(፩ዕዝ - -፳፯) ባለብሉዮች ጻሕል ጽዋ ይሉታል)

ቀፋጺ -(ጺት ጽያን ያት) የሚገልጥ ገላጭ ገፋፊ።

ቀፎ -(ዐረ ቁፈት ዕብ ቁፋህ) እንቅብ ቅርጫት አገልግል፤ ፈር በቁሙ የንቦች ቤት፤ ሣጥ ኹለት አፍ ያለው፤ ወይም ጕድጓድ ማጓ ቀባ ሰው ያልሠራው ንባም ማራም ቦታ ዛፍ ቀፎ ዘመዓር -(፩ነገ -፲፬ -፳፭)

ቁላቤ -መቅለብ፤ አቀላለብ፤ ቀለባ ቅልቦሽ ገላባጭነት፤ ሕሉት ጽልሑት ዋዛ ፈዛዛ እፌኑ ዕሌሆሙ ቁላቤ አፍ -(ፍካ -እየ)

ቍልሕ -(ሐት) ጓሚያ፤ ያበባ የጥጥ እንቡጥ ድብድብ እርጉዝ ገና ያልፈካ ያልፈነዳ፤ ያበጠ የሞጠሞጠ ያጐመጐመ፤ ወይም መፍካት መፈንዳት የዠመረ -(መክ፲፪ -፭። አርጋ -)

 -ቍላ፤ ቈለጥ፤ ታችኛው ቅሉ፤ እንጥልጥሉ ፍሬው ዕንቍላሉ፤ የተባትነት ምልክት። እስኪትን እይ ወዓዲ ይወርድ ዲበ ስኪት ወቍልሕ -(አረጋ -ድ፯)

ቍልቍሊተ -ወደ ታች ወደ ምድር አቈልቍሎ ተደፍቶ ተዘቅዝቆ ተሰቅለ ቍልቍሊተ መልዕልተ የር። ተሰቅለ ልዑለ አገሪሁ ወቍልቍሊተ ድማኁ ወአስተብቍዖሙ ከመ ይስቅልዎ ቍልቍሊተ -(ገድ -ተክ ስንክ -መጋ፲፬ ሐም፭ ጥቅ፲)

ቍልቍሊት -በቁሙ፤ ቍልቍል፤ ዝቅዝቆሽ፤ የዝቅዝቂት።

-(ላን ላት ልት) ያቈለቈለ፤ የተቈለቈለ፤ ወደ ታች ያለ፤ የተዘቀዘቀ፤ ዝቅዝቅ ማይ ይውሕዝ ቍልቁለ አላ ዐቀበ -(ፍካሬ -እየ)

ቍልቋስ -የንጨት ስም በውሃ ዳር የሚበቅል፤ ፍሬው የሚበላ እሾኻም ወተታም፤ እንደ ቍልቋል ቶሎ የሚጸድቅ ሥር የሚሰድ ረከቡ በውእቱ መካን ማየ ጽሩየ እንዘ የዐውዶ ቍልቋስ -(ስንክ -ኅዳ፲፯)

ቍልዔ -(ዕብ ቁላእ ቀላል፤ ታናሽ ናዐር) ልደ ቤት ብላቴና የቤት ልጅ ቤተ የተወለደ፤ ታናሽ ደቦል ለጋ ወጣት አሽከር ሎሌ ገልጋይ፤ ሲጠሩት አቤት ሲልኩት ወዴት የሚል ፈጣን ቀልጣፋ፤ እግረ ቀላል። ወሀቦ ለቍልዔሁ ወአፍጠነ ገቢሮቶ ረድ አንተ ወቍልዔከ ናሁ ልዔየ ዘኀረይኩ ወተወክፎ ለእስራኤል ቍልዔዕሁ -(ዘፍ፲፰ - መሳ፯ -፲። ኢሳ፵፪ -፩። ሉቃ፩ -፶፬)

ቍልዔት -( ቍልዕያት) ገረድ፤ ሴት አሽከር አመትከ ወቍልዔትከ እወፅእ አነ ምስለ ልዔትየ -(፩ነገ -፳፭ -፵፩። ዮዲ፰ -፴፫። -)

ቍልዕውና -ብላቴንነት፤ የቤት ልጅነት ባለሟልነት -(አርጋ)

ቍልዝ -(ዛት) ቍጥቋጦ፤ ቍጥቋጭ፤ ጭፍጫፊ

ቍልዝም -ስመ ሀገር ዘበሶርያ ሚልኪ ቍልዝማዊ -(ስንክ)

ቍልፈት -(ታት) መቈለፍ፤ -(ጥቈ) መቈለፍ አቈላለፍ፤ ቍለፋ፤ ቍልፍነት። ቍልፋት፤ ቈለፈት ሸንኰፍ፤ ግልባቤ ነፍስት፤ የመሌሊት ሽፋን ቍልፈተ ነፍስቶሙ ዝረትከ ቍልፈተ ትከውነከ -(፩ነገ -፲፰ -፳፯ ሮሜ፪ -፳፭፳፯)

ቍልፍ -(ፋት) በቁሙ፤ መቈለፊያ፤ ባለመክፈቻ እለ ያርኅዉ ቍልፈ ጸኒሖሙ ጊዜ የሐውር በዓለ ቤት ቀቲሮ ወነሢጎ እለ ይሰብሩ ቍልፋተ -( - -፲፯ -፯። - -፵፱)

ቁመት -መቆም፤ አቋቋም፤ በቁሙ ቀጥታ ዘለግታ፤ ምጥቀት፤ ርዝመት። ተዘከር ቁሙትየ ቅድሜከ ወይትሀጐል ቁመቶሙ በምንዳቤ -(ኤር፲፰ ኩፋ -፳፫)

 -አናዎር፤ ኑሮ፤ ጽንዐት፤ ልዩነት። እለ ይከውኑ ውስተ ቁመት ፍጽምት። ሥርዐተ ቁመተ ዓለም። ቁመት ወሕርመት -(ፊልክ -፵፭። ጥበ፯ -፲፯ ቀሌ)

ቁማስ -(ዐረ ቁማሽ) መዳ፤ ጣቃ፤ የልብስ ነዶ። ቁማስ ቀራቢብ -( - -፴፫ -)

ቁማር -ዝኒ ከማሁ፤ አንድ ዐይነት ጨዎታ ጥቅምና ጕዳት ያለበት

ቁምስና -ቆሞስነት፤ ቆሞስ መኾን፤ የቆሞስ ማዕርግ

ቍሱል -(ላን ላት ስልት) የቈሰለ፤ የተነካ፤ ንክ ውግ ምት። ቍሱላነ ልብ -(ኢሳ፶፯ -፲፭። ፷፩ -)

ቍስለት -መቍሰል፤ አቈሳሰል፤ ቍስልነት ድካም ሐዘን፤ ጭቅጭቅ -(ዐማርኛ)

ቍስል -(ላት ቍሰል) በቁሙ፤ የተነካ ገላ ደዌ በትር ያረፈበት፤ ግርፋት ውግታት፤ መከራ፤ ቂም፤ ሐዘን፤ ኀጢአት ከመ ይትፈወስ ምቍስል ዘአቍሰልዎ ቍስለ ሕዝቡ ቍስል ከመ ቍስልየ። ቍስለ ሞት፤ -(የሚገድል፤ ለሞት የሚያበቃ) እምኵሉ ቍስል የአ ቍስለ ልብ። ወቍስለ ማዑት -(፪ዜና -፳፪ -፮። ኢሳ፴ -፳፮ ሰቈ፩ -፲፪። ራእ፲፫ -፫። ሢራ፳፭ -፲፫ - -)

ቍስጥ -(ዐረ ቁስጥ ዕብ ቆሽጥ) ሽቱ፤ የሽቱ ስም። ባለቅኔዎች ቀበርቾ ይሉታል ዝክረ ስምኪ ሐዋዝ ምነ ልበኔ ወቍስጥ ወእምነ ሰንበልት ምዑዝ -(ደራሲ)

ቍረት -በቁሙ፤ መቀዝቀዝ፤ መብረድ፤ አቀዛቀዝ አበራረድ ቅዝቃዜ፤ ብርድ፤ ቈፈን። ቍረተ ቱሳሔ ዘርዕ። ቍረተ ሥጋሁ ያጥፍኦ እሳተ መለኮቱ። ቍረተ ኅሊና -( - -፲፪ -፭። ያዕ -ዘእል አርጋ -)

ቍር [1]-በቁሙ፤ ብርድ፤ ቈፈን፤ ቅዝቃዜ ይመውት በቍር ይርዕዱ በእንተ ቍር ስመ ክረምት ውእቱ። ቍር ወበረድ። እስመ ብዙኅ ቍራ ይእቲ ሌሊት -(ኢዮ፴፩ -፲፰። ፩ዕዝ - -፮። ዘካ፲፬ -፮። ዮሐ፲፰ -፲፰)

[2]ብርድ ሪር ረ።

ቍርቁር -የተቈረቈረ ያዘነ የተቈጣ ቍጡ

ቍርቍር -ቍርቈራ ሐዘን፤ ቍጣ ብስጭት፤ ክርክር ሙግት፤ ጩኸ ፍጅት። ኢኀፊር፤ ካሕድ ቍርቍር መዐት ሁከት -(ኪዳ)

ቍርበት -(ዐማርኛ) በቁሙ፤ ማእስ የሥጋ ልብስ፤ ሥጋን ናጥንቱ ከነዥማቱ ሰብስቦ የሚይዝ የሚገንዝ።

ቍርባን -(ናት ዕብ ቆርባን ሱር ቁርባና። ዐረ ቁርባን) በቁሙ፤ መንፈሳዊ አምኃ፤ ስለት፤ መሥዋዕት፤ መባእ፤ ለአምላክ የሚቀርብ የሚሰጥ ገንዘብ፤ ማናቸውም ኹሉ። የመሥዋዕትን ፍች ተመልከት። መሥዋዕተ ወቍርባነ ፈቀድኩ አምጽኡ ቍርባኖሙ ቅድመ ምሥዋዕ መንፈቁ ዲድርክም ቍርባን እግዚ -(መዝ -፴፬። ዘኍ -፲። ዘፀ፴ -፲፫ -፲፬)

 -መሥዋዕተ ወንጌል፤ ጥሩ ስንዴና ወይን ውሃ በቀር ሌላ ጭማሪ የሌለበት፤ በቍርባንነቱ ዕሙቅ ጥልቅ ረቂቅ ምስጢር ያለበት በእንተ ሥርዐተ ቍርባን አኰቴተ ቍርባን ርአዮሙ ሥርዐተ ምስጢር ዘቍርባን። አንቀጽ በአንተ ቍርባን ወኢያዕርጉ ላዕለ ምሥዋዕ ዘእንበለ ኅብስተ ሥርናይ ንጹሕ ወማየ ወይን ንጹሕ -(ኪዳ። ቅዳ - -፲፫)

ቍርኣን -የሕግ መጽሐፍ፤ መሐመድ ለወገኖቹ የጣፈው ርሱን ነቢይ ሐዋርያ ብለው የሚያምኑ እስላሞች ከሰማይ ወርዷል የሚሉት ፍችው ንባብ ድጋም ማለት ነው ዋነኛ ግን ፉርቃን ነው ፈረቀን እይ

ቍርእ -በቁሙ ቍር፤ርዕ

ቍርዕ -(ዓት) የራስ ቍር ቦርቦርቲ የብረት ቆብ1 ጌራ -(አዋል)

ቍናማት -ቍናማት ቍናማቶች፤ የበግ የፍየል ስልቾች።

ቍናምት -ቍናምት -(ዐረ ቀነም በግ መንጋ) በቁሙ፤ ኰረጆ ኪስ ረጢት አቅማዳ፤ ቀምጠራ ተረንተራ። መጽሐፍ ግን በቍናምት ፈንታ ቍናማት ይላል ያንዱን በብዙ ሐዱ ቍናማት ይኩን ለኵልነ አእባነ ቍናማት። ኀተምከ ውስተ ቍናማቲከ ጌጋይየ -(ምሳ፩ -፲፬ ፲፮ -፲፩ ኢዮ፲፬ -፲፯)

ቍንቍኔ -ቍንቍን፤ ጥንጣን፤ ግንደ ቈርቍር ነቀዝ፤ ብል፤ ትል፤ የዕፅና የእክል የልብስ ተባይ ፃፄ ወቍንቍኔ ከመ ብላዐ ቍንቍኔ ልብስ ዘተበልዐ እምቍንቍኔ -(ኢሳ፶፩ -፰። ማቴ፰ -፲፱ -)

 -ቅንቅን፤ የዶሮ ቅማል፤ ጤፍ የሚያካክል።

ቍንዝዕ -ቋንዣ ባት ቃንዛ የበትር የቍስል ስሜት። ንዳላ ሥዕርት። ሥሩና ምንጩ ዝዐ ነው

ቍንዝዕት -ቈንዦ ሳዱላ፤ ባለቈንዳላ፤ ልጃ ገረድ ጐበዝ እንደ ዥብ የሚነጥቃት ነዝዐን ተመልከት

ቍንጽ -(ጻት) ቍንጫ ፈርዐጽ የሚዘል የሚፈናጠር -(፩ነገ -፳፬ -፲፭)

 -ቍንጮ፤ የቤት የሰው -(ዐማርኛ)

ቍንጽል -(ዕብ ሹዓል) ቀበሮ፤ ይም፤ ተኵላ፤ ነጣቂ የበረሓ ውሻ ክፉ ተንኰለኛ የመኳንንትና የሰይጣናት ምሳል። ቀበሮና ተኵላ እንደ ነጭና እንደ ጥቍር ዝንጀር ይመሳሰላሉ ዘመዳሞች ናቸው፤ ከጥቍሬ ዝንጀር ነጨው እንዲከፋ ቀበሮ ተኵላ ይከፋል። ነገዳቸውና ጠባያቸው አንድ ስለ ኾነ በተኵላ ፈንታ ንጽል ይላል ሑሩ በልዋ ዛቲ ቍንጽል ይበውእኑ ንበሳ ውስተ ግበ ቍንጽል አው ቍንጽል ንበሳ ሰይጣንሰ ቍንጽል ጓሕላዊ -(ሉቃ፲፫ -፴፫። አዋል። ቄድር)

ቍየጽ አቍያጽ -ጭኖች ቍየጺሁ ዕማድ ዘበጦ ላዕለ ቍየጹ ልባሰ ቍያጽ ቆፈጽኪ አቍያጸኪ -(ማሕ፭ -፲፭ ዮሴፍ። ዳን፫ -፳፩ ሕዝ፲፮ -፳፭)

ቍይጽ ቍጽ (ሱር ሹቃ። ዕብ ሾቅ ዐረ ሳቅ) ጭን ከጕልበት እስከ ሙሓይት እስከ ታፋ ያለው ክፍል ወሰበሩ ቍይጾ ቀዳማዊ (ዮሐ፲፱ ) 

ቍድስ -(ዐረብ) መቅደስ፤ መካነ መቅደስ ኢየሩሳሌም። ሀገረ ቍድስ -(ዮሴፍ)

ቍጠጥ -ቀጫጭነት ቀጭንነት፤ አቀጣጠን ቀጠና ቅጥነት ቅጠንየ ባለው ቍጠጥየ ይገዝፍ ምሐቌ ቡየ እንዲል -(፫ነገ -፲፪ -) ባለብሉዮች ግን አውራ ጣት ይሉታል።

ቍጡዕ -(ዓን ዓት ጥዕት) የተቈጣ ቍጡ፤ ብስጩ፤ ወፈፍተኛ። ብእሲ ቍጡዕ ለእመ ንሥአሂ ምዉተ ትእመንዎ -(ፊልክ -፻፵፭ ምሳ፳፯ -)

ቍጣጥ -የግልገል በጠጥ ቍጫጭ ጭጫን ታናሽ ፍጥረት

() ቍጥ ምዝራጥ ዐንካሴ ሽብዳ ጅንፎ በጅንፎነቱ ላይ ምዝራጥነት ያለው። ወረገዞ በቍጠ ኲናቱ (፪ነገ ፳፫)ቍጥን -(ዐረ ቁጥን) ጥጥ ሲፈትሉት የሚቀጥን። ጡጥንና ጥጥን ተመልከት። ጠብለላ በቍጥን ወበአልባስ ንጹሕ -(ስንክ -መስ፲) ባለቅኔዎች ግን ግምጃ ይሉታል

ቍጥዓ -ቍጣ፤ ብስጭት፤ ወፈፍታ፤ እብደት። ዕለተ መዐት ወቍጥዓ መዐትኒ ወቍጥዓ ርኩሳን እሙንቱ። በእንተ መዐት ወቍጥዓ -(ኩፋ -፳፬ ሢራ፳፯ -፴። - -፳፩)

ቍጹል -(ላን ላት ጽልት) ያጀፈጀፈ፤ ቅጠላም፤ ባለቅጠል። ጽለ ዕፅ ጹል ለገቢረ ምጽላል -(ነሐ፰ -፲፭)

ቍጹር -(ራን ራት ጽርት) የታሰረ የተቋጠረ፤ ቍጥርጥር። ጹር ውስተ አሥዋክ። እንተ ቍጽርት ውስቴታ። ቍጹረ ገጽ -(ፊልክ -፻፲፯ ክብ -ነገ። ገድ -አዳ)

ቍጽረት -መቋጠር መፅ() ነስ፤ አቈጣጠር እስራት፤ ጥራት ቍጥርጥርነት መጋጠሚያ አመ ሰቡዑ ለነሐሴ ጽረታ መካነ ጽረቱ ቍጽረቱ ከመ እብነ ኰኵሕ። ቍጽረተ ዐራዙ -(አዋል። ኢዮ፵፩ -፯። ዘፀ፳፰ -፴፭)

ቍጽር -(ራት) በቁሙ፤ ቍጥር እስራት ግርፋት ዐለንጋ ጅራፍ፤ ጢጢ ሳንባ ጠለፍ ክፉ ምክር፤ ሽንገላ ተንኰል። ኢታጽንፁ ቍጽረክሙ። እለ ይጸብእዎ በቍጽር ይመክሩ በቍጽር ያመንስዉኒ -(ኢሳ፳፰ -፳፪። - መዝ -፴፬። ፴፯)

ቍጽሮ -ጥልፍ፤ ግብረ መርፌ መልበስተ ቍጽሮ -(ዘፀ፳፰ -)

 -ቋጠሮ፤ ቋጨራ፤ የታሰረ የሣር የቅጠል ነዶ ችቦ። ቍጣሮ አቍጣሮ፤ የመቍጠሪያ ጸሎት።

ቂሐት -መቅላት፤ አቀላል፤ ቅላት፤ ቀይነት። ንበይነ ቂሐተ ደሞሙ። ቂሐተ ተምር ወጽዕዳዌ ፀምር ዘእምፍጥረቶሙ ውእቱ ወአኮ ዘተሤረዩ -(መጽ -ምስ። አፈ -ተ፲፪)

ቂላኖስ -(ጽር ፌሎኒስ። ዐረ ) ክቡር ልብስ፤ በላይ የሚደረብ ፌሎንን ተመልከት፤ ከዚህ ጋራ አንድ ነው ዐረቦች ፈን ኹለተኛ ነቍጣ ጨምረው ይሉታልና፤ ስለዚህ ቂላኖስ ይላል። ኹለተኛም በቂላኖስ ፈንታ ሄላንሳን ይላል ሰፍሐ ቂላኖሰ ዲበ ምድር ወወረደት ጦማር ማእከለ ሄላንሳን -(ጦማ -ሃይ -) መምህራን ግን ሄላንሳንን ክቡር ምንጣፍ ርፍ ወላንሳ ይሉታል።

ቂም -በቁሙ ክፉ ሐሳብ፤ የልብ ቍስል ቂሙን ቀረፈብኝ እንዲሉ አልቦ ዘየአኪ እምቂመ ጸላእት። ቂም ወቅንአት። ኩን ጻድቀ ወመሓሬ ዘእንበለ ጽልሑት ወቂም -(ሢራ፳፭ -፲፭ ቀሌ ዲድ -)

ቂሳርያ -ስመ ሀገር፤ ቄሳራዊት፤ ሄሮድስ ስለ ቄሳር ክብር ባሕር አጠገብ በፍልስጥኤም የሠራት ልጁ ፊልጶስ ሔርሞን አጠገብ ሌላ ኹለተኛ ከተማ ሠርቶ ቂሳርያ ዘፊል አሰኝቷታል -(ግብ፲ -፩። ማር፰ -፳፯)

ቂራዲስ -(ጽር ኪራዳስ ዕብ ቂርሔሬስ) ስመ ሀገር፤ የሞአብ ክፍል፤ ከሞአብ አገሮች አንዲቱ። ዕደወ ቂራዲስ -(ኤር፵፰ -፴፩። ኢሳ፲፮ -፲፩)

ቂራጥ -(ዐረብ። ጽር ኬራቲዎን) የሚዛን ስም፤ ታናሽ ልክ፤ ክብደቱ አራት የወይራ ፍሬ የሚያነሣ፤ ወይም ከዚያ የሚያንስ የገንዘብ ም፤ ታናሽ ገንዘብ ሳንቲም ተሩብ፤ ወይም ሳንቲም ብቻ የሚኾን። ጸባሕት ዕለ ኵሉ ክርስቲያን ለለ ራጥ በበ ዓመት። ብእሲ ዘይወቅር አእባነ በቂራጠ ወርቅ ኵሎ ዕለተ ስተዋፂኦሙ ዘበበ ክልኤቱ ቂራጥ -(አቡሻ -፶። ስንክ -ግን፰ ሠኔ፲፭)

ቂርቆስ -የሰው ስም ሰማዕት፤ ከነናቱ እሳት የገባ አንጌቤንን እይ። ቂርቆስ አንቆቅሖ ተሠርዐ ምስለ -(ቅኔ። ስንክ -ጥር፲፭ ሐም፲፱)

ቂቁይ -(ያን ያት ቅይት) በቁሙ፤ ቅቅታም፤ ቀብቃባ ንፉግ ቢስ ጨባጭ አኀ ይዝክሩ መሓርያነ ወቂቁያነ -(ስንክ -መስ፳፯)

ቂቅየት -መቀቀት፤ መንፈግ፤ ቅቅት ንፍገት፤ ንፋግነት -(ፈላስ)

ቃህም -ብረ ንዳንቃሕም

ቃሕም -(ማት) አግዝ፤ ገብረ ንዳን ፍሬ እክልን፤ እንደ ገበሬ የሚዘግብ፤ የሚሰበስብ። ቃሕም ሀካይ። ንሬእዮ ለሰብእ ከመ ቃሕም ወዕፄያት። ዘጊበ መዛግብት ዘቃሕም ወተመይኖ ብር ዘሣሬት። ትጋሆሙ ፅብስት ንህብ ወሀካይ ቃሕም -(ምሳ፮ -፮። -ተ፲፮ ፈላስ። ስንክ -መስ፳፭)

 -ቃሚያ ጕርሻ፤ አንድ ጊዜ የሚቃም የሚቋት የሚጐረሥ። ኵሉ ይትኀጣእ ኀሠሥዎ እምነ ፍተ ቃሕም ኅብስት ስከ ነጥበ ማይ ሪር -(ቅኔ)

-ቃሞ ተረር ፍሬው የማሽላ ዐይነት ታሽቶ የሚቃም።

ቃሕዋ -(ዐረብ) ቡና የቡና ፍሬ ልቶ ፈጭቆ አፍልቶ ሲጠጡት የሚያነቃ።

ቃሕው -(ዋት) ፍክክር፤ ሙግት ክርክር፤ ንዝንዝ ጭቅጭቅ፤ ቍትቻ፤ ውርርድ ቅንአት ወቃሕው ወሚን ወአፍቅሮ መዊእ። ፈጸምዋ ዐመፃ በቃሕዎሙ ቃሕወ ገብረ ምስለ -(ፊልክ -፶፮። ዘፍ፵፱ -፭። አርጋ -)

ቃሊ -(ትግሬ ወዐረብ) ውድ ቡር በርካሽ ዋጋ የማይገኝ ዕቃ ጣቃ።

ቃል [1]-(ላት ቆል ሱር ቃላ ዐረ ቃል ቀውል) በቁሙ፤ ፍሬ ነገር ድምጥ ጽራሕ፤ ክላሕ፤ ንባሕ፤ ለኈሳስ ከጯኺውና ተናጋሪው አፍ በዦሮ የሚሰማ ኹሉ መጽአ ቃል እምሰማይ አንሥኡ ቃለክሙ ቃለ ወሀቡ ደመናት፤ ቃለ ነጐድጓድከ በሠረገላት ቃል ተሰምዐ በራማ -(ዳን፬ -፳፰ ኢሳ፲፫ - መዝ -፸፯። ኤር፴፰ -፲፭)

 -ሕግ ትእዛዝ፤ ትምርት ዐዋጅ ኢይትገሐሡ ምነ ቃሉ ዐሥሩ ቃላት። ቃላተ እግዚእነ -(ሢራ፲፮ -፳፰ ዘፀ፴፬ -፳፰ ዘዳ፬ -፲፫ ፊልክ -)

 -የአካል ስም፤ መለኮታዊ አካል፤ ወልድ። ወለዝንቱ ስም ዘውእቱ ቃል ንሌብዎ እምሠለስቱ ቃላት፤ አተርጋን ብርፎሪኮን አአትሪኮን ወኢታምስልዎ ለዝ ቃል ከመ ቃላት እለ ዘከርናሙ ዘእንበለ ህላዌ ወአካል። ቃል ዘኮነ ሥጋ በአካሱ -(ሃይ -አበ -ጎር ብንያ)

 [2]-በቁሙ፤ቀዊል ቀወለ

ቃማ -(ሱር ምኒካ። ዕብ ርቢድ) ቀምሓዊ፤ ዝርግፍ የወርቅ የብር ማርዳ ድሪ ያንገት ጌጥ ሽልማት፤ ባዝግናን ተመልከት፤ ከዚህ ጋራ አንድ ነው ቃማ ፍሬነቱን ባዝግና ዝግኝነቱን ያሳያል። ሰላም ለክሣድኪ ቃማ ንጽሕ ዐነቀ። ስኬማ አምሳለ ባዝግና ወቃማ -(ደራሲ። ዳን፭ -፲፮ -፳፱)

ቃስ -(ዐረ ቂያስ ልክ መለኪያ) ላ፤ የገላ ልብስ፤ ሱሪ ቀሚስ፤ ልከኛ፤ በልክ የተሰፋ ረዘመ ዐጠረ የማይሉት፤ ድርማንቅ ልብሰ ቃስ -(ዘፀ፴፮ -፴፬። ዘሌ፲፮ -)

 -የላይ ልብስ፤ ጀባ ካባ መጐናጠፊያ ዘይትሞጣሕ ቃሰ። አስኬማ፤ ልብሰ ቃስ አኮ ለአሮን ሰርጐ ዘባኑ -(ደራሲ)

ቃሩራ -(ዐረ ቃሩረት ትግ ቈራረት) በቁሙ ቅዛዝ ጠርሙዝ፤ የብርሌ የብርጭቆ ይነት፤ ሥራው ቈሪር ውሃ የኾነ ክብረት ልሕኵት፤ ያይዶለ -(ዮሴፍ)

ቃር -(ዐረ ቂር ቃር) ሙጫ የዛፍ ደም። ቃር ወፒሳ ተይ -(ስንክ -ሐም፭)

ቃርሐ -(ዲቃ ) አቃረ ተኰሰ ፈላ -(ዐማርኛ)  

ቃርሕ ቃር -ትኵሳት፤ የምግብ አለመስማማት።

ቃቂል -ቃቂል፤ ቃጭል፤ ታናሽ መረዋ። ዘሩ ቀዊል

ቃቄር -(ራት። ቁርቁር) እንቍራሪት ትል አሙኝት ሌሊት የሚጮኽ የሚንጫጫ ወይነቅዉ ከመ ቃቄራት -(ገድ -ተክ)

ቃቡ [1]:-ድርጎ፤ቀበወ።

[2]-(ጽር ካቡ ዕብ ቃብ) የመስፈሪያ ስም ታናሽ ልክ ድርጎ ልቢጥ ለምሸሽ። የኢፍን ፲፰ኛ እጅ የምቲዝ። ሀሎ ውስተ ስፈሬዳ ኅዳጥ ሥርናይ ዘየአክል መጠነ መስፈርተ ቃቡ። ወራብዕተ አዴሃ ለመስፈርተ ቃቡ ስሐ ርግብ ምስቱ ብሩር -(ገድ -ተክ ነገ - -፳፭)

ቃባ -የበግ ደዌ ዐንገት የሚያሳብጥ -(ዐማርኛ)

ቃቤላ -ማሽላ፤ ያገዳ እኽል

ቃነየ -(ዕብ ጌን) ቃኘ ደረደረ፤ የመዝሙር የበገና። ትቃኒ ውታሪሃ ኀበ አሳፍ ይቃኒ ወኀበ ደቂቀ ቆሬ ይሴብሑ -(ናሖ፫ -፰። መጽ -ምስ)

ቃና [1]-ዜማ ድምፅ፤ የዜማ ስልት ጣዕም ቀናን፤ አቀናቀን። አውታረ መሰንቆ ፍሉጥ ወሊሉየ ቃና። መስፍነ ትዕይንት፤ ቃና ወኢሥርዐት -(ፈላስ። አፈ -ድ፴፬)

[2]-ስመ ሀገር፤ በናዝሬት አጠገብ ያለች -(ዮሐ፪ -)

ቃዕደወ -(ዐደወ ቀደወ ዐረ ቀዐደ፤ ተቀመጠ) አሻግሮ አየ ተመለከተ፤ ዐይኑን አርቆ ጣለ አራመደ ፊት ለፊት ማዶ ለማዶ ቀደወ መጥቶ በፀደወ ተደርቧል

ቃውም -(ምት ማን ማት) የሚቆም፤ አለቃ፤ ጠበቃ፤ የነገር አባት ወይም ወደረኛ፤ ከሳሽ ባለጋራ። አነ ቃእምከ ወዐስብከ ጥቀ ንጉሥ ብው ቃውመ ሕዝብ -(ኩፋ -፲፬። ጥበ፮ -፳፮ አርጋ)

ቃይጽ -(ዕብራ) በጋ ወርኀ ማእረር የሙቀት ወራት

ቃዲ -(ዐረ ቃፂን። ዕብ ቃጺን) ፈራጅ፤ ዳኛ፤ ባለፍትሐ ነገሥት፤ ገዥ መስፍን -(ዐማርኛ)

ቃዴስ -(ዕብ ቃዴሽ) ሲና፤ ደብረ ሲና፤ የሲና በረሓ ምድረ በዳ ጌታ እስራኤልን የቀደሰበት፤ ርሱም በሕዝቡ አፍ የተቀደሰበት፤ ቅዱሳነ ኩኑ እስመ አነሂ ቅዱስ አነ ብሎ ቅዳሴውን ቅድስናውን ዘመን ያስተማረበት። ምስጢሩ ዐቢይ ወግሩም ማለት ነው ጽኑዕ ማለትም ይሰማማዋል። ወያድለቀልቆ እግዚ ሐቅለ ቃዴስ -(መዝ -፳፰)

ቃዴስም -(ጽር ካዲሲም ዕብ ቅዴሽም) አብያተ ጣዖት፤ በቅዱስ ቦታ ላይ መቅደስ አጠገብ የተሠሩ የጣዖታት ቤቶች። አምላክ መቅደስ የተለዩ ልዩዎች ማለት ነው። ወነሠተ አብያተ ቃዴስም -(፬ነገ -፳፫ -)

ቃግስት -(ታት) የባብ ስም፤ ክፉ እባብ እፍኝት ጕበና። ትውልደ ቃግስት -(ኢሳ፲፬ -፳፱ ምሳ፳፫ -)

ቃፍ [1]-(ዕብ ማጣራ) ጊጤ፤ ዐላማ መጋፊያ፤ ብራኳ። የመጠራን ፍች ተመልከት፤ ከዚህ ጋራ ንድ ነው ከመ ቃፍ -(ኢዮ፲፮ -፲፪)

[2]-(ዐረብ) ስመ ፊደል ቀ። ጋፍ፤ ወንቃፍ ማለት ዚህ ወጥቷል።

ቄሳር [1]-(ጽር ኬሳር) ስመ ንጉሥ ፍችው ሠጣጤ ከርሥ እናቱ በምጥ ጊዜ ሙታ፤ አዋላጆች ሆዷን ሠንጥቀው ስላወጡት ሀቡ ዘቄሳር ለቄሳር። ወፅአ ትእዛዝ እምኀበ ሳር ንጉሥ ኮንከ ዐርኮ ለቄሳር -(ቀሌ ሉቃ፳ -፳፭። -፩። ዮሐ፲፱ -፲፪)

 [2]-ስመ ንጉሥ፤ቀይሳር።

ቄሣር ቂሣርያ -የሰው ያገር ስም፤ቄሳር።

ቄር -(ዕብ ቂር) ስመ ሀገር። ወይፄወዉ ቂረ ሕዝቦሙ ሶርያ ወአፍለሶሙ ውስተ ቂር -(ዓሞ፩ -፭። ፬ነገ -፲፮ -) ባለብሉዮች ግን ቄረ ሕዝቦሙ ብለው ያነቡና ፍችውን ኀያላን መኳንንት ደቦሎች ይሉታል። ባለሊቃውንትም፤ ቄርሎስ ብሂል ኀያል ይሉና ምስክር ይህን ይጠቅሳሉ፤ ስሕተት ነው

ቄርኔን ቂሪን -(ጽር ክሪኒ ዕብ ብሬካ) ኵሬ የውሃ መቋሚያ፤ ጐድጓዳ ቦታ -(፪ነገ - -፲፫ ፬ነገ - -)

ቄቀየ -ቀቀተ፤ቀይቀየ።

ቄቅሐ [1]-አጠራ፤ ጥሩ አደረገ፤ ዐጠበ ፈተገ ለቀመ አበጠረ፤ ነፋ፤ የእክል

 [2]--አጠራቀይቅሐ።

ቄቅሕ ቄቃሕ -ጥሩ ነገር፤ እድፍ ድፍ ንፋሽ ገለባ የሌለው ልቅም፤ ፍትግ ክክ ኅፅቦ፤ የተነፋ ዶቄት። ቄቅሐ ሥርናይ -(ዘዳ፴፪ -፲፬ መዝ -፻፵፯ ዮሴፍ። መቃ)

ቄቅዮ ዮት -(ቄቀየ ይቄቂ) መቀቀት መንቀብቀብ፤ መሠሠት፤ መንፈግ መቤስ መቈጠብ፤ ገንዘብን አጥብቆ መያዝ መጨበጥ ዘይቄቂ ውፅኦ እምንዋዩ ዘይደሉ ይሁብ ምክዕቢተ በከንቱ። ዘይቄቂ ለርእሱ ይዘግብ ለባዕድ ዘቦቱ ንዋይ ወይቄቂ -(ፈላስ። ትእ -ጴጥ። አፈ -ተ፴፪)

ቄአ -ተፋ ቀረሸ፤ቀዪእ 

ቄዐ -ተፋ ቀረሸ፤ቀዪእ ቄአ

ቄዳር -ስመ ነገድ፤ ዐረባዊ፤ ኹለተኛው የይስማኤል ልጅ ዘላን የዘላኖች አባት -(ዘፍ፳፭ -፲፬ መዝ -፻፲፱ ማሕ፩ -)

ቄዳርስ -(ጽር ኪዳሪስ) ጥቍር ቆብ ፌት ጠምጠሚያ ጥምጥም፤ የካህናት -(ዘፀ፴፮ -፴፬። ዘሌ፰ -፲፫ ፲፮ -) በቄዳርስ ፈንታ ቄድራን ይላል -(ሢራ፵፭ -፲፪)

ቄዴም -(ዕብራ) ቅድም፤ ምሥራቅ። ደቂቀ ዴም -(ሕዝ፳፬ -)

ቄድር -(ዐረ ቀድር እድፍ ርኵስ) ጥምቀተ ዮሐንስ፤ የንስሓ ጥምቀት። መጽሐፈ ቄድር ዘአንበሩ መምህራን በእንተ ዘክሕደ ሃይማኖቶ አው ርኰሰ ሥጋሁ ምስለ ዘኢምእመናን ተባዕት ንስት መነኮስ መነኮሳይት

ቄድሮስ [1]-(ጽር ኬድሮስ። ዕብ ኤሬዝ) አርዝ፤ ስመ አርዝ፤ የሊባኖስ ዛፍ፤ ወፍራም ረዥም፤ ታላቅ ምጡቅ፤ ናና ባለብዙ ዐጽቅ ባለብሉዮች ግን ዋንዛ ይሉታል። ኅሩይ ከመ ቄድሮስ -(ማሕ፭ -፲፭ -፱። ሢራ፳፬ -፲፫። ፫ነገ - -፱። -፲፫) በቄድሮስ ፈንታ ቄዳር ይላል ስሕተት ነው ቄዳር ዘስሙ ዐርቦት -(ኩፋ -፳፩)

[2]--ቄድሮስ፤ -(ጽር ኬድሮን። ዕብ ቂድሮን) የቦታ ስም፤ በደብረ ዘይትና በኢየሩሳሌም መካከል ያለ ቈላ ሸለቆ፤ ዛፋም ዘይታም አታክልታም፤ ፀሓ የማይደርሰው፤ ቢደርሰውም ቶሎ የሚያልፈው መካነ ጽልመት ወጽላሎት፤ ጥላማ፤ ጽልሙት ማለት ነው ፈለገ ቄድሮስ ማዕዶተ ቄድሮስ ፈለገ አርዝ -(፪ነገ -፳፫ -፮። ዮሐ፲፰ -) በቄድሮን ፈንታ ቄድሮስ ማለት የጣፊ ስሕተት ነው።

ቄጵርስስ -( ኪፓሪሶስ። ዕብ ብሮሽ) የዛፍ ስም፤ ጥድ፤ የጥድ የዘግባ ዐይነት፤ ግንዱ ነጭ፤ ዶቅማ የሚመስል። ቄጵርስስ ወኵሉ ዕፀወ ገዳም -(ኩፋ -፲፫። ሕዝ፳፯ -፭። ፴፩ -)

ቄጼሩት -(ዕብ ቅጹሮት) ዐጫጭሮች፤ ታናናሾች፤ ጠባቦች -(ሕዝ፵፪ -)

ቄፋዝ [1]-(ጽር ኬፋዝ። ዕብ ፋዝ) ጥሩ ወርቅ፤ የኡፋዝ ወርቅ ኡፋዝ ሚባል ምድር የሚወጣ ፎዘንና አፌዝን ተመልከት ርእሱ ወርቀ ቄፋዝ -(ማሕ፭ -፲፩)

 [2]-(ጽር ኬፋዝ) አፌዝ፤ ጥሩ ወርቅ ምዝምዝ። ርእሱ ወርቀ ቄፋዝ -(ማሕ፭ -፲፩) ፎዘን ተመልከት

ቈሀልት -(ዕብ ቈሄሌት) አፈ ጉባኤ ስለ ጉባኤ በጉባኤ ላይ የሚናገር፤ ሰሎሞን፤ የሰሎሞን መጽሐፍ ፪ኛው ክፍል መክብብ -( - -)

ቈሊፍ ፎት -(ቈለፈ ይቈልፍ ይቍልፍ ሱር ቅላፍ። ዕብ ቃላፍ ዐረ ቀለፈ) መቅረፍ፤ መላጥ፤ መምለጥ፤ መሸልቀቅ መግፈፍ፤ ማሸት፤ መፈልፈል፤ የውስጡን ማውጣት

 -መቈለፍ መዝጋት መግጠም ማተም ማንቀላፋት።

ቈላ -( ላት) በቁሙ፤ ሞቃት የሙቀት ቦታ፤ ጐድጓዳ ሸለቆ፤ ፀሓያም ሐሩራም ቈላ ዕሙቅ እስመ መካነ ብሔሩ ቈላ ውእቱ ቈላ ብካይ -(ሔኖ አዋል። መዝ -፹፫)

ቈላዕይ -ብላቴኖች፤ የቤት ልጆች። መጣፍ ግን ልዔያት ይላል -(ዮሴፍ)

ቈላፍ -(ፋን ፋት) የተቈለፈ፤ ቍልፍ ላፋ። ያልተገዘረ ሽፍን ልፈታም፤ ቈለፈታም። ወኵሉ ቈላፍ ኢይብላዕ እምኔሁ ዕልገተ ቈላፋ -(ዘፀ፲፪ -፵፰። ፩ነገ -፲፰ -፳፭)

ቈልቈለ -ቈለቈለ፤ ደፋ፤ ዘቀዘቀ፤ ቃጣ ሰበቀ ወረወረ የጦር የዘገር ሶበ ልቈለ ናቶ ዕለ ህጉሪሆሙ -(ሢራ፵፮ -) በቈልቈለ ፈንታ አቈልቈለ ይላል፤ ስሕተት ነው። አስተጻንዐ መዝራዕቶ ወአቈልቈለ ናቶ ወረገዞ -(ገድ -ተክ)

ቈልዞ ዞት -(ቈለዘ ይቌልዝ ይቈልዝ) መቍረጥ፤ መቈጥቈጥ፤ መጨፍጨፍ መመልመል -(አርጋ -)

ቈሲል ሎት -(ቈስለ ይቈስል ይቍሰል። ዕብ ካሻል ተሰናከለ) መቍሰል መንካት፤ መመታት፤ ቍስለኛ ቍስላም መኾን በደዌ በበትር በሥራ በሐዘን። አነ ጠቢብ ወእፌውሶሙ ድዉያን እለ ቈስሉ በደዌ። ቈሰልኩ በቤተ ዐርክየ። ወናሁ በዊነ ቈስሉ በኀጺን -(ስንክ -ግን፳፮ ዘካ፲፫ -፮። ፪ዜና -፳፱ -)

ቈስቈስ -( ቈሳቍስ፤ ሳት) የቤት ቃ፤ ታናናሽ፤ ሰባራ ሥንጥር ደጅ አፍ የመለሰው ማጀት የጐረሠው፤ ማናቸውም ኹሉ፤ በየስሙና ያይነቱ። ኵሎ ንዋዮ ወቈስቈሶ ማህረኩ። ወብዙኀ ቈሳቍሳተ ወቈሳቍሳቲሁኒ ወበህየ ርኢኩ ፀወ ኵነ ፈድፋደ ቈስቈሰ መዐዛ -(መቃ ገድ -ተክ። ዘፍ፴፩ -፲፰ ሔኖ፳፱ -) ቈሰቈሰ ቀሰቀሰ ማለት ከዚህ የወጣ ነው። ቀና ተወራራሾች ስለ ኾኑ፤ በቈሳቍስ ፈንታ ኰሳኵስ ይላል ራታተ ወኰሳኵሳተ ወአጽሕልተ -(ዲድ -፴፩)

ቈስያ ያት -(ዐረ ቁሻእ። ዕብ ቂሹእ) የቅል የዱባ ወገን፤ ያቦሬ ያንኰላ የሽክና ዐይነት፤ ሞላላ ወጥ የሚኾን የሚቀቀል ቶሎ። የሚበስል -(ዘኍ፲፩ -) ባለብሉዮች ግን ቈሽት የበለስ ቋንጣ ይሉታል

ቈሥጤ -(ዕብ ቄባህ) ቈሽት፤ ሽንፍላ ጓራ -(ዘዳ፲፰ -)

ቈስጤ -ቈሽት ጨጓራ፤ቀሠጠ

ቈረቈር በቁሙ ነጭ የራስ ቋቍሻ። (ተረት) በቡሓ ላይ ቈረቈር

ቈሪር -(ራን ራት ራር) የቈረረ የቀዘቀዘ፤ ቀዝቃዛ፤ በራዳ ፋስ ቈሪር ማይ ቈሪር ሓይ ጥዒና ቈሪራን አዝርዕት። ራር ወሙስንት ምክር -(ሢራ፵፫ - ምሳ፳፭ -፳፭ ስንክ -ሐም፲፪ ቄር -)

ቈሪር ሮት -(ቈረ ይቈርር ይቍርር ዕብ ቃራር ሱር ቃር ዐረ ቀረ) መቍረር መብረድ፤ መቀዝቀዝ፤ ከሙቀት መለየት፤ በራድ ቀዝቃዛ መኾን። ወናሁ አብርሃም ቈረ ከመ  በረድ -(ኩፋ -፳፫) ተመይጠ ተፈጸመ በማለት ፈንታ ቈረ ይላል፤ የመላሽ ስሕተት ነው። ስከ ይቈርር መዐተ እኍከ -(ዘፍ፳፯ -፵፬። ኢዮ፲፬ -፲፫ ኢሳ፩ -፳፬ -፳፭)

ቈሪፍ -(ዐማርኛ) ዦሯማ ሯም ሮው ታላላቅ የኾነ፤ ልክ ያለፈ። ቀርፋፋ ከርፋፋ ማለት ዚህ የወጣ ነው

ቈርቍሮ  ሮት -(ቈርቈረ ይቈረቍር ይቈርቍር። ዐረ ቀርቀረ። ዕብ ቃርቄር) መቈርቈር፤ መቀብቀብ፤ የጥሪ፤ ቃሕቅሐን ተመልከት። መጮኽ ማስካካት፤ ቍርቍሩ ማለት፤ የደሮ የንቍራሪት፤ ቃቂርንና ቈርነናዕን እይ ዘሩ ቈሪር ቈረ ነው

 -በቁሙ መቈርቈር መጐርበጥ አለመመቸት ማሳዘን ማስቈጣት። የሐዘነን ፍች ተመልከት። መመሥረት፤ መዠመር ለማቅናት ለመሥራት፤ ያገር የከተማ -(ዐማርኛ)

ቈርቈሮ -በቁሙ፤ ጯኺ ፈሳሽ።

ቈርነናዕ -ናዓት፤ -(ዕብ ጽፋርዴዕ ዐረ ፀፋዲዕ ሱር ዑርድዓናያ) ጓጉንቸር እንቍራሪት። ጯኺ አቅራሪ ፋሪ ነጨሬ ማለት ነው ቃቄርን እይ ይቀይእ ተከዚ ቈርነናዓተ -(ዘፀ፰ -፲፫)

ቈርኔን -(ጽር ኮሪኒ። ዕብ ሐዳሻ) ሐዲስ መሣሪያ የጦር ልብስ። ባለብሉዮች ግን ለይተው ቋዝመን ይሉታል፤ ይኸውም እንደ ያለ ጋፋቾች የሚታጠቁት ታናሽ ካራ ነው -(፪ነገ -፳፩ -፲፮)

ቈቀወ -ቍቁ አለ -(ዐማርኛ)

ቈቍዖ ዖት -(ቈቍዐ ይቌቍዕ ይቈቍዕ። ዕብ ቃዕቄዕ፤ ወጋ በሳ ነቀለ) መንቋቋት ማለት፤ ያጥንት መጕረብ ማጐብጐብ፤ መላጥ መመለ መብለዝ መዝጐን፤ መካከም መጣመን፤ የእጅና የእግር። መክሳት መድረቅ መጣጋት፤ መጐስቈል ሬሳ መምሰል የሰውነት ይቌቍዕ ኵሉ ዕፅምቲሁ ቈቍዓ ወቈስላ አጻብዒሆሙ። ቈቍ በሐዊረ ኖት መከየደ እግርኪ ቈቍዐ ማእሶሙ ዲበ ዕፅምቲሆሙ -(ኢዮ፴፫ -፲፱ ድር -መድ ደራሲ። ሰቈ፬ -)

ቈናዝዓት -ብርንጎዎች። ኢትግበሩ ቈናዝዓት እምሥዕርተ ርእስክሙ -( - -፵፭። ዘሌ፲፱ -፳፯)

ቈናዝዕ -(ዐረ ቁዘዐት ቁንዙዐት) ብርንጎ የራስ ጠጕ ሥራ ነዶው ፈትሉ ገመዱ ንጕኑ እንጥልጥሉ። ንጮ ጋሜ ሳዱላ የዙሪያ ልጭታት። ቈናዝዒሃ ፍቱል። ሰብዑ ቈናዝዐ ርእስየ -(ገድ -ተክ። መሳ፲፮ -፲፫)

ቈናዝዕት -ቈነዣዥት፤ ሳዱሎች፤ ደናግሎች

ቈናጽል -ተኵሎች፤ ቀበሮዎች ቀበራርት። ሥግሃ ለነ ናጽለ ንኡሳነ ወአኀዘ ሠለስተ ምእተ ቁናጽለ ለቈናጽል በብ ቦሙ -(ማሕ፪ -፲፭ መሳ፲፭ -፬። ማቴ፰ -)

ቈንቈነ -በቁሙ፤ ነቀዘ፤ ጠነጠነ ተላ ረጀ አፈጀ ወአልባሲክሙኒ ቈንቈነ ዘኢይበሊ ወዘኢይማስን፤ ወዘኢይቈነቍን -(ዕ፭ - ቄድር)

ቈንደየ -(ጐንደየ) ተጓደደ ታበየ ተንጠራራ፤ ቀንድ አወጣ፤ ወይም ቀንድ ኾነ ንድ ተባለ ያገር ቀንድ እንዲሉ -(መዝ -፻፴፩። ሉቃ፩ -፷፱። ሕዝ፳፱ -፳፩) መጽሐፍ ግን በቈንደየ ፈንታ ተቈናደየ ይላል፤ አያሰኝም። ትትቈናደዩ ብየ ወትዘረክዩኒ -(ኢዮ፲፱ -) ጐንደየን ተመልከት፤ የዚህ ሥር ነው

 -ቈነዳ፤ ዘለለ፤ ቈንዳ ቈንዳ አለ። የቍጣ የኵራት ወይም የደስታ።

ቈዐለ -(ይቍዕል ይቍዐል ቀዊዕ ቆዐ) ሠባ ወፈረ፤ ጮማ ኾነ፤ አደገ አፈረጠመ

ቈጠጠ -(ዕብ ቃጻጽ) ቀጠጠ ረጠ ቈጠቈጠ፤ የሣር የቅጠል። ቍጥቋጦ ማለት የዚህ ዘር ነው በቁሙ ቈጠጠ ጣጥ ጣለ

ቈጢጥ -(ጣን ጣት ጣጥ) ቀጫጫ ሻዋ ቀጭን መጽሐፍ ግን በገዚፍ ፈንታ ጢጥ ይላል ወዔግሎንሰ ቈጢጥ ብእሲ ውእቱ ጥቀ -(መሳ፫ -፲፯) ቀጠጦ ቀጠጥና ማለት ከዚህ ወጥቷል። ቀጠጦ፤ የማሽላ ስም ፍሬው ቀጫጫ

ቈጢጥ ጦት -(ቈጠ፤ ጠጠ ይቈጥጥ ይቍጥጥ ቀጠነ) መቀጨጭ መቅጠን፤ ቀጫጫ ቀጭን መኾን፤ መክሳት መመንመን። ቀጥቀጠን እይ የዚህ ዲቃላ ነው አንቀጥቀጠም ሳይቀር

ቈጥዖ ዖት -(ቈጥዐ ይቌጥዕ ይቈጥዕ ዐረ ቀዐጠ ዕብ ቁጥ ናቀ፤ ጠላ) መቈጣት፤ መወግሸት፤ ቍጡ ብስጩ መኾን መጥላት መሰልቸት። መጽሐፍ ግን በቈጥዐ ፈንታ ተቈጥዐ ይላል፤ ያማርኛ ነው መዕዐን ተመልከት። ኢትቈጥዐ ልቡ ይትቌጣዕ ዲበ ሰብእ ትትቈጣዕ ነባሪከ ዘያበዝኅ ቢበ ይትቌጥዕዎ -(ሰቈ፪ -፳፪ ፊልክ -፵፰። ሢራ፬ -፬። -)

ቈጸራ -ሽንገላ ስርቆት ቅጥፈት አግብእ ሎቱ ንዋዮ ወሀቦ ዘእንበለ ጸራ ወርዴ -(ቀሌ)

ቈጺል ሎት -(ቈጸለ ይቈጽል ይቍጽል። ሐመለ፤ ለምለመ) ማቍጸል ቅጠል ማውጣት፤ መለምለም፤ ማቀጠል፤ ማጀፍጀፍ፤ ዐጽቃም ቅጠላም መኾን። መጽሐፍ ግን በቈጽለ ፈንታ አቍጸለ ይላል፤ ስሕተት ነው -(አርጋ -)

ቈጺር ሮት -(ቈጸረ ይቈጽር ይቍጽር። ዕብ ቃሻር ቃጣር ሱር ቅጣር) መቋጠር መቀጠል፤ አንዱን ካንዱ ጋራ፤ ወይም አንዱን ባንዱ ማሰር ማቈር፤ ማጽናት ማጠንከር መሰገጥ መኰፍተር መጨምደድ፤ የፊት። ነሥኦ ዲናረ ወርቅ ወቈጸሮ በጸርቅ። ጸርዎ በልብሶሙ ጸሩ ማዑቶሙ ሐብል መንፈሳዊ ዘያዐርግ ልበ ምድር ወይቈጽሮ ውስተ ሰማይ ኢትቍጽሩ ገጸክሙ እፎ ከመ ይቈጽር ገጾ ትካዝ ወቈጺረ ገጽ -(ስንክ -ታኀ፲ መጽ -ምስ መዝ -፲፮ ፊልክ -፻፳፭ - -፵፭። አፈ -ተ፳፱)

 -ክፉ ማሰብ፤ መፅነስ መተንኰል ማታለል መሸንገል። እመ ዘቈጸረ ከመ ይቅትል። አንተሰ ትቈጽር በዘትትሜጠዋ ለነፍስየ ለመጋቢ ይደልዎ ከመ ይቍጽር ለአመጋቢሁ ውስተ ሠዪጥ ወተሣይጦ -(ዘፀ፳፩ -፲፬ ፩ነገ -፳፬ -፲፪። - -)

 -መቍጠር፤ ቍጥር ሒሳብ ማድረግ አንድ ኹለት ሦስት ማለት። ኈለቈ ሐሰበ አኀዘ ብሎ ቈጠ ማለት፤ ዐማርኛው ከዚህ የወጣ ነው።

ቈጻሪ -(ሪት ርያን ያት) የሚቈጥር የሚቋጥር፤ አሳሪ ቋጣሪ ዐሳቢ ቈጣሪ

ቈጽል -(ላት፤ አቀጽል) ቅጠል ቅጠላቅጠል፤ የዛፍ የመጣፍ የወርቅ የብር። ልጥ ሐረግ ከመ ጽለ ዕፅ ዘጽፉቅ ጽሉ በኅብስት ወማይ ወቈጽል ቈጽለ ወርቅ ረቃቅ ቈጽለ ሥርቆ -(ሢራ፲፬ -፲፰ ቀሌ። ዘፀ፳፰ -፴፮። ራ፲፩ -)

ቅሒም ሞት -(ቀሐመ ይቅሕም ይቅሐም። ቀምሐ) መቃም፤ መገተም፤ የፍሬ የበሶ የፍርፋሪ። -(ግጥም፤ ትግሬ ስለ ነጮች) አዒንቶም ዚመስሉ ዒንት ደማሙ ስናኖም ዚመስሉ ብርስን ዘቀሐሙ። መጽሐፍ ግን በቀሐመ ፈንታ ቀምሐ ላል፤ ስሕተት ነው ይቀምሕ አንበሳ ሐሠረ ከመ ላሕም። ይረክቡ አልሕምት ዘይቁምሑ። ሐመደ ይቀምሑ። ሐመደ ከመ ክል ቀማሕኩ። ይቀምሕ መሬተ ውስተ አፉሁ። ወይቀምሑ ሐሪጸ -(ኢሳ፲፩ -፯። ዕን፫ -፲፯ መዝ -፸፩። ፻፩ አፈ -ድ፰ ዮሴፍ)

ቅሒው ዎት -(ቀሐወ ይቅሑ ይቅሐው ወቅሐ አሰረ) ማየል መበርታት መንቃት መትጋት፤ አለኹ አለኹ ማለት፤ ማፈል መገንፈል፤ ዐፍለኛ መኾን፤ መፈካከር መወዳደር፤ እኔ እበልጥ እኔ እበልጥ ወይም እታከል እታከል ማለት በቀሐወ ፈንታ ተቀሐወ ይላል፤ ስሕተት ነው

ቅሕቃሔ -ቍርቈራ፤ ጥብጠባ የምልክት ጥሪ ትእዛዝ

ቅለት -በቁሙ፤ መቅለል፤ ቀላለል፤ ቀላልነት፤ ችኰላ ፍጥነት።

ቅሉም -(ማን ማት ልምት) የተቀለመ፤ የተጣፈ፤ ያደፈ እድፋም።

ቅሉዕ -(ዓን ዓት ልዕት) የተቀላ፤ የተገለጠ ግልጥ ብእሲት ትኅድግ ሥዕርታ ከመ ይኩን ቅሉዐ ውስተ ቤተ ርስቲያን -( - -፲፩)

ቅሉይ -(ያን ያት ሊት) የጠለቀ፤ ጥልቅ፤ ዕሙቅ -(አርጋ)

ቅልመት -ማደፍ ማሳደፍ አስተዳደፍ እድፍ፤ እድፈት እድፋምነት ኅፅብ ኵሎ ቅልመታ -(አርጋ)

ቅልንብትራ -ቅልንብትራ፤ -(ጽር ሊምቢትራ) ምዕቃል፤ መታጠቢያ መጠመቂያ -(ዮሐ፭ -)

ቅልዓ -(ዐረ ልዐት) ዕርድ ምሽግ መታኰሻ፤ መወራወሪያ -(ዮሴፍ)

ቅልው -(ዋን ዋት ሉት፤ የተቈላ እንኵቶ ጥብስ -(ዘሌ፪ -፲፬። ፳፫ -፲፬)

ቅሙር -(ራን ራት ምርት) የተቀመረ ቅምር፤ የተቈጠረ የተከፈለ። ወቅሙር ዐዘቅተ ጠፈሩ መሥልስተ -(፫ነገ - -፵፩)

ቅማል ቍማል -(ላት) በቁሙ የልብስ የጠጕር ተባይ፤ እጅግ ታናሽ፤ ባለ፮ እግር ደም የሚመጥ። በአንቃል ዘውእቱ ማል -(አዋል)

ቅምሖ -በቁሙ፤ የጕረሮ በሽታ፤ እንደ ፍሬ የሚያብጥ የሚፈርጥ።

()           ቅምጥ -ያይን ዐር ጭንቅ ጦት ችጋር ምጥና -(ዐማርኛ)

ቅሡም -(ማን ማት ሥምት) የተቀሠመ፤ የተለቀመ፤ ልቅም ቍርጥ።

( )        ቅሱም -(ማን ማት ስምት) የተጣፈጠ፤ ጥፍጥ ቅምም ነገሩ ቅሱም በጼወ መለኮት። ተግሣጽ ጥዑም ወዜና ቅሱም ከመ ቅሱም ማእድ -(ድጓ ፈላስ ስንክ -ጥር፲)

ቅሡፍ -(ፋን ፋት ሥፍት) የተቀሠፈ፤ የተገረፈ፤ የተመታ -(መዝ - ኢሳ፶፫ - -)

ቅሳሜ -ማጠፈጥ፤ መጣፈጥ መቀመም፤ አቀማመም፤ ቅመማ፤ ቅመምነት። እምጽቡር ብሕባሔከ ወእምኔሁ ቅሳሜነ -(ኢዮ፴፫ -)

ቅሣር -(ራት። ዐረ ቂሽረት ዕብ ቃሽቄሼት) ገለፈት የዓሣ ቅርፍት ክንፍ ወቅሣር -(ዘሌ፲፩ -፲፪ ዳ፲፬ - - ሕዝ፳፱ -)

ቅሥመት -መልቀም መቍረጥ መቈረጥ አቈራረጥ፤ ቈረጣ ለቀማ። ቅብዐ ዘይት ዘቀዳሚ ቅሥመታ -(ዘፀ፳፯ -)

»ቅሥት -(ታት) [1]-ወቀሣ ከሰሳ ጠብ ክርክር ሙግት ፍርድ። ቅሥተ ጊጉይ ማየ ቅሥት ቅሥተከ መፍትው ትግበሩ ቅሥተ በሰንበተ ክርስቲያን ልቦ ዘይከውን ቅሥት -(ሢራ፲፩ -፱። ዘኍ -፲፫ ግብ፳፮ -፩። ዲድ - መክ፰ -፲፩)

[2]:-ክርክር፤ወቀሠ።

ቅስና [1]:-ቄስነት፤ቀሲስ ቀሰ።

[2]-ቄስነት፤ ቄስ መኾን፤ የቄስ ማዕርግ የሹመቱ ስም። ዘተሠይመ ሢመ ቅስና ይነሥእ መተ ቅስና በሕልያን -( - - -፫። - - -)

ቅሥፈት -(ታት) መግረፍ፤ መገረፍ ገራረፍ፤ ግርፊያ፤ ግርፋት፤ ቍስል፤ ደዌ መከራ ወኀፀቦሙ እምቅሥፈቶሙ በቅሥፈታቲሁ። ወሐይወ ዮብ ምድኅረ ቅሥፈቱ -(ግብ፲፮ -፴፫። ደራሲ ኢዮ፵፪ -፲፮)

 -መውጫ ውጭ፤ ዕዳሪ። ወቅሥፈቱ ብሔረ ምድያም -(ክብ -ነገ)

ቅሩም -(ማን ማት ርምት) የተቃረመ፤ የተለቀመ፤ ቃርሞሽ።

ቅሩብ -(ባን ባት ርብት) የቀረበ የቈረበ ቅርብ፤ አጠገብ፤ ዘመድ፤ ዐጭር ጥቂት እለ ቅሩባን ኀበ ንጉሥ። ቅሩብ ውእቱ ረኪቦታ ዘየኀድር ቅሩበ ቤታ ለቅሩበ ምናሴ ምታ ስመ ቅሩብ ዘመኑ ፍሥሓ ዝንቱ ዓለም ቅሩብ ወኅዳጥ -(አስቴ፩ -፲፪። ሢራ፶፩ -፳፮ ፲፬ -፳፬ ዮዲ፲፮ -፳፬ ዮሴፍ። ቀሌ)

ቅሩጽ -(ጻን ጻት ርጽት) የተቀረጠ የተጣፈ፤ ያበጠ የሰመጠ መልክ ያለው። ወረከብናሁ በትር ጽሩበ በንባብ ወቅሩጸ በትርጓሜ -(ቅኔ። ሃይ -አበ -ሳዊ)

ቅሩፅ -(ፃን ፃት ፅት) የተቈረጠ ርጥ ሽልት ድኅረ ወድቀ መልዕልተ ምድር ርእሱ ቅሩፅ መራዕይ ቅሩፃት -(ስንክ -ሚያ፲፰ ደራሲ)

ቅራስያ -(ዐረ እልቅራስያ) ዕፅ ፍሬ ፅ፤ ፍሬነቱ እንደ እንኰይ ያለ፤ ታናናሽ ጥንታም -( - -፲፯)

ቅራፍ -(ፋት) ቅራፊ ልጥ። ኤልሳዕ ፈወሰ በጣዕመ ጼው ማየ ያሪኮ ሕሙመ፤ ወበቅራፈ ዕፅ ውፅአ ማሕጼ ስጡመ -(ስንክ -ጥቅ፳)

ቅርሐት -ልጭታት፤ ንጭታት በራነት በራ መኾን። እንቃሪ፤ ጭላጭ -(አዋል)

ቅርመት መቃረም (ጥቃ) መቃረም አቀራረም ቅርሚያ  ለቀማ።

o መቀራመት ቅርምቻ ቀረመት ቅርምት አንዱን ፍሪዳ ብዙ ኹኖ መግዛት ማረድ ሥጋውን ፋፍሎ በዕፃ መውሰድ

ቅርበት -መቅረብ፤ አቀራረብ፤ ቅርቢያ ቀረቤታ፤ ቅርብነት -(ቄር -)

ቅርንብ -( ቀራንብት) ቅርንው ቀርናዊ ምርቅ ቂንድ። ቅንድብ፤ ሸፋሽፍት፤ ከሽፋል በታች ያለው ያይን መክደኛ ክንፈሩ ላዩና ታቹ ቅንድብ ርበቱ ንቃው፤ ሸፋሽፍት ጠጕ ፈቃው ምርቁ እንደ ቀንድ ኹኖ የበቀለው፤ አፍሬውን ወደ ላይ ወደ ታች ያሾተለው ቈጽለ ወብርዐ ወሐሠረ ወቅርንበ ምርቅ ቂንድ -(መቃ -ገ፭) ሰላም ለቀራንብቲከ ከመ ክልኤ ክንፈ ኪሩብ እለ ይጼልላ ወትረ ዕይንቲከ ዘርግብ ጸጕረ ቀራንብቲሁ። በስባሰ ቀራንብት። ወቀራንብቲሁኒ የሐቶ ዕጓለ መሕያው ቀራንብት ኀቤሁ ዐይን እንዘ ቅሩባን ቀራንብተ ይኔጽር ዐይን -(ደራሲ ስንክ -ግን፲፫ መጽ -ምስ መዝ -፲። ቅኔ) ሽፋልም ሸፋሽፍት ጋራ ባንድነት ቅንድብ ይባላል። ብራይስጡ ንፈር ከናፍር ሲል ሳፋ ስፋታይም ስፋቶት ይላልና ሸፋሽፍት ዚህ ወጥቷል፤ ፍችው ከንፈራዊ ሥዕርተ ከንፈር ማለት ነው፤ ለአፍም ይኾናል፤ ጽሕምን ተመልከት። ሽፋልም የዕብራይስጥ ነው፤ -(ሻፋል) ጭር ቀጭን ሳሳ ደካማ ልም ልዝብ ማለት ነው የጠጕሩን ባይ ባሕርያዊ ሕጉን አለማደጉን ያሳያል።

ቅርዳን -(ዐረ ጊርደውን) ያይጥ ገመር፤ ታላቅ ዐይጥ፤ ፍልፈል -(አዋል)

ቅርጥብ -(ዐረ ቀርፀብ) የሚነክስ የሚግጥ የሚያበላሽ፤ በልቶ የማይጠግብ እንዳይጥ እንደ ምሥጥ ያለ አጥፊ ዘራፊ ሌባ ቀጣፊ ባለመጽሐፎች ግን ጊንጥ ዳሞትራ ሸሽላ ይሉታል። ወቅሪስኒ ሰመዮ እልቅርጥበ እስመ ይነስክ ምኵሉ ገቦ -(ፊልክ -፶፮)

ቅርጸት -መቅረጽ፤ መቀረጽ፤ አቀራረጽ፤ ቅርጽ፤ ጥፈት፤ የፊደል መልክ፤ እጅ እግር ኅርመት ቅንጣት ወጸሐፉ ላዕሌሁ በቅርጸተ ማኅተም የውጣ እንተ አሐቲ ቅርጸታ -(ዘፀ፴፮ -፴፱። ማቴ፭ -፲፰። ቀሌ)

ቅርፍት -(ታት) በቁሙ፤ ቅርፊት ልጥ እንቡጥ፤ ቂንድ፤ ገለባ ንፋሽ ቍርበት ጐለፈት። ቅርፍተ ዕፅ ቅርፍተ ብስት ቅርፍተ ሮማን ቅርፍተ ተርሙስ ቅርፍተ ሥጋ -(፬ነገ - -፮። ዋል። ማሕ፬ -፫። ስንክ -የካ፳፬ ቅዳ -ያዕ። ሕዝ፳፱ -)

ቅቡል [1]-(ላን ላት ብልት) ያነሰ የጐደለ፤ ጐደሎ፤ ባዶ ጽሕብት ቅቡላን -(ሄርማ)

[2]-ቅቡል፤ -(ላን ላት ብል) የተቀበለ የተቀበሉት፤ ቅብል፤ ተሰጭ።

ቅቡር -(ራን ራት ብርት) የተቀባረ ፈር የለበሰ ተቀብረ ከመ ያንሥኦሙ ለቅቡራን -(ቅዳ)

ቅቡዕ -(ዓን ዓት ብዕት) የተቀባ ክርስቶስንና መሲሕን ተመልከት። ቅቡዕ በቅብዕ ቅቡዓኒከ ዋኅወ ቅቡዓተ ወርቅ -(ዘሌ፪ -፬። ን፫ -፲፫ ፪ዜና - -)

ቅቡጽ -(ጻን ጻት ብጽት) የቀበጠ ቅብጢ ቀበጥ። ያጣ የነጣ፤ ተስፋ የቈረጠ አለኝታ ሌለው። ስማዕ ቃሎሙ ለቅቡጻን ሰብእ ቅቡጻን እለ ቅቡጻን ተስፋሆሙ -(አስቴ፬ -፲፯ ኢሳ፳፱ -፲፱ ፩ተሰ - -፲፫)

ቅብለት -መጕደል፤ አጐዳደል፤ ጐደሎነት ሕጸጽ። በቅብለት ፈንታ ቅላሌ ቅላሌ ይላል፤ ስሕተት ነው በእንተ ስካር ወቅባሌ -( - -፵፫ -)

ቅብቅብ -በቁሙ፤ የለሰለሰ ዕርሻ።

ቅብዐት [1]-መቅባት፤ መቀባት፤ አቀባብ፤ ቅብነት፤ ቅባት። ቅብዐተ በለሳን። በቅብዐተ ዝን ዘይት ቅዱስ -(ኪዳ። ዲድ -፴፱) ቅቡዕ መሲሕ በማለት ፈንታ ቅብዐት ይላል፤ የመላሽ ሕተት ነው ይጠፍዕ ቅብዐት። ዝንቱ ክርስቶስ ወፍካሬሁ ቅብዐት ወገሃደ ይሰመይ ቅብዐተ፤ ስመ በዘተሰብአ ተቀብዐ -(ዳን፱ -፳፮ ቄር -)

[2]-የሃይማኖት ስም፤ ዕውር ዘኢየሱስ ባፄ ፋሲል መን ያወጣው፤ አዛዥ ድንግል የካራን ባህልና ካራ መባልን በሱስንዮስ ዘመን እንዳወጣ። የቅባት ባህል ክፍል ነው መዠመሪያ በፋሲል ዘመን የተነሠት እነዘኢየሱስ መጽሐፍ አንደየ ርእሶ ይላልና ቃል በተዋሕዶ ዜገ ከሥጋ ሲዋሐድ የባሕርይ ክብሩን ዐጣ ቀቀ፤ ሲቀባ ወደ ጥንተ ክብሩ ተመልሶ በሰውነቱም ባምላክነቱም አንድ ወገን በቅባት የባሕርይ ልጅ ኾነ ብለዋል። ምስጢሩ እንደ በትረ ሙሴ ማለት ነው ሚጠትንና ውላጤን ባንድነት ያሳያል

፪ኛ ባንደኛው ዮሐንስ የተነሡ እናካለ ክርስቶስ ዜገ ማለትን ነቅፈው አጸይፈው መጽሐፍ እስመ ተዋሕዶ አእተታ ለምንታዌ ይላልና ሥጋ በተዋሕዶ አንድ አካል ኾነ እንጂ የአምላክነት ክብር አላገኘም ሲቀባ ግን ክብር ተላልፎለት፤ ተፈጥሮ ተገብሮ ፍቶለት በቅባት የባሕርይ ልጅ የባሕርይ አምላክ ኾነ ብለዋል። ምስጢሩ መቀባቅትንና መለወጥን ለሥጋ ብቻ መስጠት ነው -(ተረት) አልሸሹም ዘወር አሉ በቴዎድሮስ ዘመን የነበሩት እናለቃ ጐሹ በቅባት ብቻ ማለትን ነቅፈው መጽሐፍ በኹለቱም ኹሉ በተዋሕዶ ባረ በቅባት ከበረ ይላልና ቅባት ያለተዋሕዶ ተዋሕዶም ያለቅባት ብቻ ብቻውን አያከብርም፤ በተዋሕዶና በቅባት ባንድነት የአምላክነት ክብር ክብሮ የባሕርይ ልጅ ኾነ ብለዋል ሦስቱ ኹሉ ፍጹም ውላጤ ነው፤ ሥጋን ፍጡርነት ቃልን ከመሲሕነት ያወጣል። ተቀብዐ ማለት ግን ንቀጹ የቃል ስለ ኾነ ካራና ቅባት እንደሚሉት ሥጋ አካለ ቃል ያገኘውን የወረሰውን ሉዓላዊ ሥርዐት የባሕርይ ክብር የባሕርይ ልደት ወልድየ አንተን ያይዶለ ቄርሎስ አፈ ወርቅ እንደሚሉት ቃል በሥጋ ርስት በሥጋ ባሕርይ እንደ ሰሎሞን እንደ ይሥሐቅ ወልደ ዳዊት ወልደ ብርሃም፤ ወልደ አዳም ወልደ ማርያም በተባለበት በሰውነቱ በሰው ልጅነቱ ቀዳማይ አዳም ያሶለደውን ሀብት ከአብ ተቀብሎ ዮም ወለድኩከ የተባለበትን ታሕታዊውን ሥርዐት፤ ዳግማይ ዳም በኵረ ምእመናን ንጉሥ ካህን የኾነበትን፤ ነቢይ ሐዋርያ መልአክ ያሰኘውን የሰውነቱን ክብር ፍጹም ሀብቱን ፍጹም ሹመቱን የግብር ልደቱን ቢያሳይ እንጂ የባሕርይ ልደትን የአምላክነትን አያሳይም። በብሉይ በሐዲስ በሊቃውንት እንደ ተጻፈ እንደ ተነገረ -(መወድስ ዘክፍለ ዮሐንስ) ይማኖተ ርሎስ ኮነት ማዳተ ብድ ወኍልቈ ተመትሮ አብዝኀት ኀበ ኢሀሎ ጉሥ ካህነ ደብረ ፍሬም ቅድመ ምዘመተራ ነኣስ፤ ወአመ ኢዮርብዓም ምሳሌ በእደ ቢይ ዘተሠጠት ልብስ። እን እምኵሉሰ ያጠይስ ወዘያነድድ ልቡና ኢትበሊ ዶምያስ ተቀበዐ ቅብዐ ውላጤ ሕሩመ ተውላጥ ክርስቶስ፤ ወአኮ በተቀብዖቱ በኵረ ውሉዳ ለዮርዳኖስ። ወእንዘ ትትናገሪ ዘንተ በአድንኖ ክሣድ ወርእስ፤ ከመ አነ ሰማዕኩኪ ኢይስማዕኪ ጳውሎስ

ቅብዕ -(ዓት) በቁሙ፤ ቅቤ፤ ቅባት ሽቱ የሚበላ የሚቀባ የሚበራ፤ እንስሳትና ዕፀዋት ምድር የሚገኝ ፈሳሽ። ቅብዐ ዕጉልት። ቅብዐ ዘይት። ቅብዐ ዕፍረት። ቅብዐ ማኅቶት ምንትኒ ምዘመደ ቅብዓት -(ዘዳ፴፪ -፲፬ ዘፀ፳፯ - አስቴ፪ -፲፪ አርጋ -፩። - -፳፮ -)

 -ዘይት ወይራ የቅባት ንጨት ደብረ ቅብዕ ዐጸደ ቅብዕ -(፪ነገ -፲፭ -፴። ፬ነገ -፲፭ -)

ቅብው -(ዋን ዋት ውት ቡት) የተነፋ ንፍ እንቅብ ሆድ ደዌ የነፋው ሆዱ የቀደመው ብእሲ ቅብው ቅድሜሁ -(ሉቃ፲፬ -)

ቅብጢ -(ዐማርኛ ቀበጥ) ግብጻዊ፤ የግብጥ ሰው፤ ቋንቋ ጽርእ ጋራ የሚቃረብ። ዛሬ ግን ቋንቋነቱ ጠፍቶ ፊደሉ ብቻ አለ ያነኑም ዐረብ ወርሶታል፤ የሚማረው የለም። በእንተ ብዝኀ ተደምሮቶሙ ምስለ ተንባላት እስመ ጠፍአ ልሳኖሙ ቅብጥ ዘእምኔሁ የአምሩ ጽድቀ ሃይማኖቶሙ -(ሳዊ -) ግብጽን ተመልከት

ቅብጥ -ግብጽ ግብጥ የሚጽራይም ቋንቋ ትውልድና ዘር ርስትና ምድር፤ ምጽ() ር።

ቅብጸት -ማጣት፤ ጦት ተስፋ መቍረጥ። ቅብጸተ ተስፋ ቅብጸተ ሰላም ቅብጸተ ዕድሜ፤ ቅብጸተ መት -(ስንክ -የካ፫ - -፵፬ -)

ቅቱል -(ላን ላት፤ ትልት) በሰው እጅ የሞተ የተገደለ፤ የተወጋ የቈሰለ ቍስለኛ፤ ግዳይ ሬሳ ወለእመ ተረክበ ቅቱል በውስተ ምድር። ቅቱላን በኵናት -(ዘዳ፩ -፩። ሶፎ፪ -፲፪) ጉት በማለት ፈንታ ቅቱል ይላል ስሕተት ነው ሀገር ትልት -(ኢሳ፩ -)

ቅቱር -(ራን ራት ትርት) የተዘጋ ዝግ ሽጕር ቅርቅር ቤተ ሞቅሕ ዝጉሕ ወቅቱር -(ግብ፭ -፳፫)

ቅታሬ ቅታር -መጤስ መሽተት። ሽቱ ጣን፤ የተቀመመ የተጣፈጠ፤ የደቀቀ የተወገጠ። የዕጣን ሽታ መዐዛ ዕጣን ዘቅታሬ ደቂቅ ዕጣን ዘካልእ ቅታሬሁ -(ዘፀ፴ - - -፴፬ -፴፰)

ቅትለት -(ታት) መግደል፤ መገደል፤ አገዳደል፤ ግድያ፤ ትግል ትግያ ጦርነት። ወኢነስሑ ዓዲ እምነ ቅትለቶሙ። ዜና ቅትለቱ ለአልዓዛር ካህን ስፍጠታተ ሰይጣን ልባዊት ወቅትለታቲሁ ኅቡኣት -(ራእ፱ -፳፩ ዮሴፍ ፊልክ -)

ቅትር -(ራት) ችንካር፤ ቀኖት ምስማር ወስፌ አፈ ምሣር፤ ካስማ ችካል፤ ማናቸውም ሹል የኾነ ኹሉ ጺን ብዙኅ ለቅትራተ ዋኅው ቅንው በቅትራተ ጻውንት ቅትራት ርሱን ከመ ቅትራት ለአድግ -(፩ዜና -፳፪ - መጽ -ምስ መክ፲፪ -፲፩ ምሳ፳፮ -)

ቅኑም -(ሱር ቅኑማ ዐረ አቅኑም) አካል፤ ህላዌ፤ ፍጹም ገጽ ፍጹም መልክ ያለው፤ እኔየሚል አካልንና ጠባይዕን ህላዌን ተመልከት

ቅኑት -(ታን ታት ንት) የታጠቀ የተቀነተ፤ ቅንት፤ ዝግጁ ልባም። ቅኑት ሐቌሁ በወርቅ። ቅኑታነ ስቅ። ቅኑታነ ስይፍት -(ዳን፲ -፭። ሕዝ፳፫ -፲፭ -፲፭ ኩፋ -፴፯)

ቅኑይ -(ያን ያት ኒት) የተገዛ ግዝ፤ ተገዥ ባሪያ ፍጡር ግቡር ሥጋ ቅኑይ ለኀጢአት። ነባሪ ወቅኑይ ያግዕዝ ቅኑያነ ሠርዐ ሰንበተ ዕረፍት ለቅኑያን -(ጥበ፩ -፬። ፪ጴጥ - -፲፱ ፩ጢሞ - -፩። ፊልክ -፫። ድጓ)

ቅናት -(ታት ቅናውት) በቁሙ መቀነቻ መታጠቂያ ትጥቅ የወገብ ማሰሪያ፤ ቀበቶ ዝናር መቀነት። በቅናቱ ዘአዲም በቅናት ዘወርቅ አልባሰ ወቅናታተ። ወኢይፍትሑ ቅናውቲሆሙ -(ማቴ፫ -፬። ራእ፩ -፲፫ ዘፀ፳፰ -፵። ኢሳ፭ -፳፯)

ቅናዌ -መቸንከር፤ -(ጥቸ) መቸንከር፤ አቸነካከር ችንከራ የችንካር ውግ ቍስል ቅናዌ ወርግዘተ ናት -(መጽ -ምስ)

ቅናው ቅናዋት -ችንካሮች የችንካር ቍስሎች፤ ውግታቶች ውስተ ዘነቦሙ ቦሙ ቅናዋት። ማስ ርእየ አሠሮሙ ለቅናዋት ርግዘተ ገቦሁ ወቅናዋተ እደዊሁ ምስቱ ቅናዋት -(ራእ፱ - ስንክ -ሚያ፮ ግንዘ። አዋል)

ቅኔ [1]-(ዕብ ቂና) በቁሙ፤ ሙሾ ግጥም ቅንቀና፤ ቍዘማ፤ የፍታት የልቅሶ ዜማ፤ ማሕሌት ጉማ። መጽሐፈ ቅኔ። አህ ድምፀ ቅኔሆሙ ለካህናት በቤተ ክርስቲያን ስመ ናሁ ተለጕመ ዜማ መሰንቆ ጥዑም በውስተ መዝሙር ወጸሎት -(አዋል። ግንዘ)

 [2]-የዜማ የቅኔ ቦታ፤ ሦስተኛ ክፍል ከመቅደስ። ቅኔ ማሕሌት።

 [1]-ቅኔ፤ አገዛዝ፤ ባርነት። ቅኔ እኩይ። በዝኀ ኔሃ ርዑተ ቅኔ -(ኢሳ፲፬ -፫። ሰቈ፩ -፫። ገላ፭ -)

 -ንግድ፤ ተግባረ እድ፤ አገልግሎት ቅኔ እደዊነ ናፅርዕ ምቅኔ እደዊሃ ትሁብ ለነዳያን ሥርዐተ ቅኔ ቤተ ክርስቲያን -(ዲድ -፲፫ና -፬። ኪዳ) መዓልትን ቀን ማለት ዐማርኛው ከዚህ ወጥቷል የሥራ ጊዜ ማለት ነው።

ቅንአት -መቅናት፤ መመቅኘት ቅናት ምቀኝነት፤ ቍጣ ብስጭት ቀናኢነት። ቅንአት እግዚ ይገብር ዘንተ። በቅንአተ ዲያብሎስ መጽአ ሞት በከመ ኮነ ውስቴቱ ቅንአት በሕገ ሪት ማሁ ተመክዐበ ውስቴቱ ቅንአት በሕገ ኢየሲስ -(ኢሳ፱ -፯። ጥብበ፪ -፳፬ ስንክ -ሐም፭) ቅንአትና የቀነተ ዘር ቅናት ባማርኛ ይተባበራሉ -(ግጥም) ባፋ በጐራዴ ትደነቃላችኹ፤ ወገብ ቈርጦ እሚጥል ቅናት ሳለላችኹ። ለመነኵሴ ብቻ ማን ሰጠው ቅናቱን፤ ለዓለማዊ ነው የተሠራው ጥንቱን። እስራኤል በጣዖት ስላመነዘሩ፤ ፈጣሪም ታጥቆታል እንኳን ሰው ፍጡሩ።

ቅንእ -ዝኒ ከማሁ። ቅንኡ ብእሲ እምኀበ ቢጹ -(መክ፬ -)

ቅንው -(ዋን ዋት ኑት) የተቸነከረ የተጣመረ፤ አንድ የኾነ ኢየሱስ ክርስቶስ ቅንወ አእጋር ወእድ እሑድ ሱር ወቅንው በሰንበት -(ደራሲ። ሲኖዶ)

ቅንየት ቅኔት -መግዛት መገዛት አገዛዝ ግዛት፤ ግዙነት ባርነት። ወእምቅንየቶሙ ድኅነክሙ እስከ ትቀንይዋ ሀገር እስመ ቀርበ ቅንየታ ወፅአ እምእዴሁ ኀበ ቅንየተ ካልኡ ተበርብሮ ወለቅንየት -(ዘፀ፮ -፮። ዮሴፍ - ፳፯ አስቴ - -)

 -መፍጠር፤ አፈጣጠር ፈጠራ እስመ ቅንየትከ ወምልክናከ ይሬስየከ ትሣሀል ላዕለ ኵሉ -(ጥበ፲፪ -፲፮)

ቅንጣብ -(ባት) ቅንጣቢ ንጣቢ ቍራጭ ብጣሽ፤ ራፊ፤ ቅፋፊ። ወይእዜሰ ግማዳተ አብድ ወቅንጣባተ ረሰይከኒ -(ኢዮ፲፮ -)

ቅንጣዌ -ቍንጣን፤ የጥጋብ ብዛት፤ የሆዳም በሽታ ሰብእሲ ሥሡዕ ዘኢይጸግብ ደዌሁ ቅንጣዌ ወገብጥ። ጽጋብ ጸዋዔ ቅንጣዌ ውእቱ ወቅንጣዌ ጸዋዔ ደዌ ወደዌ ጸዋዔ ሞት -(ሢራ፴፬ - ፈላስ) ቄንጥ መቂናጥ ማለት ከዚህ ወጥቷል

ቅንፍዛት ቀናፍዝ -ዣርቶች፤ ጠጕ ክፉዎች ባለሾኽ ጠጕሮች

ቅንፍዝ -(ዕብ ቂፎድ ሱር ቂፉዳ ዐረ ቁንፉድ ) ዣርት እሾኻም አውሬ፤ ጠጕሩ እንደ ጋሬጣ እንደ ምስማር ያለ ሽመልመሌ ዐይነት -(ኢሳ፲፬ -፳፫ ፴፬ -፲፩)

ቅዒን ኖት -(ቀዐነ ይቅዕን ይቅዐን። ቀነየ) ማስጨነቅ ማስጠበብ፤ ማጣበቅ መጨነቅ መጠበብ መጣበቅ፤ የቦታ።

ቅዉም -(ማን ማት ውምት) የቆመ የጸና የተለመደ የተለየ እሙንቱ ቅዉማን ዕለ ቅጽር። ወውእቱ ቅዉም በኀበ ግብጻውያን ወመለካውያን ሕሩም ወቅዉም እምቤተ ክርስቲያን -(ዮሴፍ - -መቅ። ቀሌ)

ቅያሔ -ዝኒ ከማሁ። ይሰወጥ ውስተ ገጽየ ንተ ገጽከ ቅያሔ -(ደራሲ)

ቅያሜ -መቀየም፤ አቀያየም፤ ቅየማ፤ ቂመኛነት። ፍቅርሰ ጥአተ ሚን ወቅያሜ -(ኦዋል)

ቅያእ -ቋቅታ፤ ምላሽ፤ ትፋት፤ ቅርሻት። ልብ ይገብእ ዲበ ያኡ -(ምሳ፳፮ -፲፩)

ቅዱሕ -(ሓን ሓት ድሕት) የተቀዳ ቅድ ዘቅዱሕ ውስተ ጽዋዐ መዐቱ -(ራእ፲፬ -)

ቅዱም -(ማን ማት ድምት) የተቀደመ፤ የታለፈ፤ ቅድምናውን ያጣ

ቅዱስ -(ሳን ሳት ድስት) በቁሙ የተቀደሰ ክቡር፤ ምስጉን ልዩ ምርጥ፤ ንጹሕ ጽሩይ ቅዱሰ ቅዱሳን ስሙ። ቅዱሳነ ልዑል። መጻሕፍት ቅዱሳት ሀገር ቅድስት -(ኢሳ፶፯ -፲፭። ዳን፯ -፳፯። ሮሜ፩ - ማቴ፬ -)

ቅዳሴ -(ሳን ሳት ድስት) በቁሙ የተቀደሰ ክቡር፤ ምስጉን ልዩ ምርጥ፤ ንጹሕ ጽሩይ ቅዱሰ ቅዱሳን ስሙ። ቅዱሳነ ልዑል። መጻሕፍት ቅዱሳት ሀገር ቅድስት -(ኢሳ፶፯ -፲፭። ዳን፯ -፳፯። ሮሜ፩ - ማቴ፬ -)

ቅድሐት -መቅዳት፤ መቀዳት፤ አቀዳድ፤ ቅድነት ዘምሉእ ቅድሐቱ -(መዝ -፸፬)

ቅድመ -ቀድሞ፤ አስቀድሞ፤ በፊት፤ ወደ ፊት ፊት ለፊ ቅድመ ጠይቅ ቅድመ ውፅእ ሠርዌ እምዐይንከ ደኃርት ይከውኑ ቅድመ። ሑሩ ቅድመ። እስመ ተሐውር ቅድመ እግዚ -(ሢራ፲፩ -፯። ማቴ፯ -፭። ፲፯ - ፲፱ -፴። ዘፀ፴፪ -፲፮ ሉቃ፩ -፸፮) ድሜየ እያለ ይዘረዝራል ሲኾን እም እያዳመቀው፤ ሳያዳምቀውም፤ በሣልሳይ አንቀጽ ይገባል። በሰማይኒ ቅድመ ይትፈጠር ኪሩብ እምቅድመ ይትፈጠር ዓለም -(ደራሲ። ጸሎ -ሃይ)

ቅድመት -መቅደም፤ መቀደም፤ አቀዳደም ቀደማ፤ ቅድሚያ ቀዳማዊነት፤ ሥልጣን። አልቦ ቅድመት ሀለዎቶሙ ወቅድመት ኮነ ዲበ መትከፍቱ አሐቲ ቅድመት ወአሐቲ ስፍነት -(አዋል ኢሳ፱ -፮። ደራሲ)

ቅድም -ፊት ገጽ ቀድሞ ዱሮ ጥን መዠመሪያ። እምቅድም ወአምድኅር። መንገለ ቅድም። ዘሀሎ እምቅድም እከያቲሁ ዘቅድም -(ራእ፬ -፮። ዘፀ፳፰ -፲፬ ፩ዮሐ -፩። ስንክ -ጥቅ፮)

ቅድምና -ቀዳማዊነት ቅድሚያ ብልጫ ላቂያ ልቅና ብኵርና። አልቦ ጥንት ለቅድምናከ አኀ የአምር ቅድምናሁ -( - -መቅ አፈ -ድ፫)

ቅድሳት -ቅድስና፤ ክብር ንጽሕ ጸጋ ብፅዓን፤ መሥዋዕት ቍርባን። ከመርክብ ቅድሳቲሁ ፈነውኩ ቅድሳቲከ ፍቁርየ ቅድሳት ለቅዱሳን ቅድሳቶ ነሢአነ ንዋየ ቅድሳት -(ዕብ፲፪ - ተረ -ቄር፲፭ ቅዳ)

ቅድስተ ቅዱሳን -(ዕብ ቆዴሽ ቆዳሽም) በቁሙ፤ መቅደስ ኦሪት፤ መካነ ታቦት፤ ባርባው ክንድ ፊት ያለ ኻያው ክንድ -(ዕብ፱ -፳፭ ፲፫ -፲፩) ዳቤርን ተመልከት።

ቅድስና -ቅዱስነት፤ ክቡርነት፤ ንጽሕና፤ ከበሬታ ኰነነ ሴት ሕዝቦ በጽድቅ ወበንጽሕ ወበቅድስና። መንፈሰ ቅድስና። ነኀሥሥ ምነ ቅድስናከ -(ቀሌ። ኪዳ። ስንክ -ጥቅ፲፪)

ቅድው -(ዋን ዋት ዱት) ያማረ የተዋበ ውብ ምዑዝ ጥዑም ንጹሕ ጽሩይ ውድ ክቡር። ሕሡም ወቦ ቅድው ዘአርኣያከ ቅድው ዕፍረት ቅድው መዓር ቅድው። በግዕ ቅድው ልብስ ቅድው -(መጽ -ምስ። ዐርኬ ዓሞ፮ -) ሕዝ፳፯ -፲፯ ፩ጴጥ - -፲፱ ፩ጢሞ - -)

ቅጠን -ቅጥነት፤ ቀጭንነት፤ ቀጠና። ቅጠንየ ይገዝፍ እምሐቌ ቡየ -(፫ነገ -፲፪ -)

ቅጡሮት -(ዕብራ) ሳሞች ጠቀራሞች ጢስና ጠቀራ ያለባቸው ቤቶች። -(ሕዝ፵፮ -፳፪)

ቅጡፍ -(ፋን ፋት ጥፍት) የተቀጠፈ፤ የተዘነጠፈ፤ የተቈረጠ የተቀጨ።

(ጥጣ)        ቅጣፍ -(ፋት። ዐረብ) ቅጣፊ፤ ዝንጣፊ፤ ቍራጭ፤ ብጣሽ፤ ዛላ ዘለላ ዐጽቅ ሙሽራ ለቅኔም ይኾናል፤ ቀጠፋ ቅኔ እንዲሉ።

ቅጥራን -(ዐረ ቀጥራን) በቁሙ የሙጫ ቅመም፤ ከዛፍ የሚገኝ የሚወጣ፤ እንደ ዝፍት የሚነድ የሚቃጠል። አፍልሕዎ ውስተ ጻሕል በዝፍት ወበቅጥራን። ቃር ወፒሳ ወተይ ወቅጥራን -(ስንክ -ጥር፳፯ ሐም፭)

ቅጥቁጥ -(ጣን ጣት ቅጥ) የተቀጠቀጠ፤ የደቀቀ፤ ቅጥቅጥ፤ ደቃቅ፤ ያዘነ የተከዘ። በትረ ብርዕ ቅጥቁጥ። ዘያነሥኦ ለውዱቅ ወይፌውሶ ቅጥቁጥ። ቅጥቁጠ ልቡ ቅጥቁጣንኪ -(ኢሳ፴፮ -፮። ቀሌ። አፈ -ተ፴፩ ሶፎ፫ -፲፰)

ቅጥቃጤ -በቁሙ፤ መቀጥቀጥ፤ -(ጥቀ) መቀጥቀጥ፤ አቀጣቀጥ ቅጥቀጣ፤ ስብራት፤ ሐዘን ትካዜ ጥቃጤ ጻሕብ። ቅጥቃጤ ነፍስ። ቅጥቃጤ ልብ -(ኢሳ፴ -፲፬ ፷፭ -፲፬ ዮሴፍ)

ቅጥነት -ቅጥነት፤ በቁሙ መቅጠን፤ አቀጣጠን፤ ቀጭንነት፤ መርቀቅ መራቀቅ። ርኢከኑ ቅጥነተ ልቡ ሐዋርያ። ቅጥነተ ጥበብ -(አፈ -ድ፩ ፲፬ - -፵፫)

ቅጥፈት -በቁሙ፤ መቅጠፍ፤ መቀጠፍ፤ ቀጣጠፍ፤ ቀጠፋ፤ ውሸት ኵሸት።

ቅጹል -(ላን ላት ጽልት) የተቀጠለ ቅጥል። የተቀዳጀ ቅድጁ።

ቅጹር -(ራን ራት ጽርት) የታጠረ የተቀጠረ። ሀገር ቅጽርት -(ኢሳ፩ -)

(ራት)        ቅጽር -በቁሙ፤ ቅጥር፤ ዐጥር፤ መካበቢያ፤ የቤት የከተማ። ለእመ ፈቀደ ይሕንጽ ብእሲ ቅጽረ ይርሐቅ እምቢጹ ሐተ ምሥጋረ እግር ገር እን ባቲ ቅጽር ይጠቅሙ ርእሶሙ ቅጽረ። ኢያሪኮ እንተ የዐውዳ ሰብዐቱ ቅጽራት -( - -፴፯። ዘሌ፳፭ -፳፱ ምሳ፳፰ -፬። ስንክ -ሠኔ፳፮)

ቅጽቃጼ -(ቅጥቃጤ) መፍጨት፤ መፈጨት መወዝወዝ፤ መቈርጠም። ቍርጥማት፤ ቃንዛ፤ የደዌ የሐዘን ስሜት። ፈውስ ዘያሴስል ቅጽቃጼ ሕማም -(አፈ -ድ፳፩)

ቅጽበት -መጥቀስ፤ መጠቀስ፤ አጠቃቀስ፤ ጥቅሻ፤ ንክሻ። በቁሙ፤ ፍጥነት፤ ችኰላ ቅልጠፋ፤ ወዲያው ቶሎ ድንገት፤ ጥቂት ሳይቈይ ሳይዘገይ ይኤምር በቅጽበተ አጻብዕ ዘነበበ በጊዜሁ ይገብሮ ወዘኀለየ በቅጽበት ይከውኖ። በመጠነ አሐቲ ቅጽበት ኢተፈልጠ መለኮት እምትስብእት፤ ወኢከመ  ቅጽበተ ዐይን። ወበሣልስ ንፍኅተ ቀርን ይትነሥኡ ሙታን ከመ  ቅጽበተ ዐይን -(ምሳ፮ -፲፫ ቅዳ -ግሩ። ጥበ፲፰ - ሃይ -በ። ቅዳ -ያዕ)

 -ጥቅስ፤ ምሳሌ ተረት፤ አንጻር ነገረ ጠቢባን ቅጽበት ፈክሮ ቅጽበት -(ምሳ፩ -፮። ጥበ፰ -)

ቅፉል -(ላን ላት ፍልት) የተለበጠ ልብጥ ቅፉለ ወርቅ። እለ ቅፉላን በብሩር -(አርጋ -፬። ኢሳ፴ -፳፪። ዘፀ፳፮ -፴፪። ፴፯ - -፲፭)

ቅፉጽ -(ጻን ጻት ፍጽት) የተገለጠ የተገፈፈ ግልጥ ክፍት፤ ባዶ

ቅፍሎ -( ቀፋልው ሉት) ቈጽለ ወርቅ፤ ሥሥ ረቂቅ፤ ልብጣት፤ ቅባት ቅፍሎ ወርቅ -(ዘፀ፳፭ -፲፰ - -)

ቆሎንያ -(ጽር ኮሎኒኣ) ግዛት፤ ቅኝ፤ አውራጃ ክፍል ጭማሪ፤ ያንድ ሹም አገር -(ግብ፲፮ -፲፪)

ቆመሰ አው ተቆመሰ -ቆሞስ ኾነ ተባለ ቁምስና ተሾመ ተቀበለ

ቆም -( ቆማት) ቁመት ርዝመት የሕንጻ የገላ መጠን ምድር ወደ ላይ ወደ ሰማይ ከእግር እስከ ራስ ከሥር እስከ ያለ ወኖኀ ቆማ። ይትዐወቅ ኑኃ ወግድማ ወኢቆማ በአምጣነ ቆሙ ለሰብእ ኀይሉ ቆመ ረፍት ወደምስስ ቆሞሙ በእደ ብእሲት -(ሕዝ፲፱ -፲፩ ቀሌ። ሢራ፳፰ -፲። ዮዲ፩ - -)

ቆሞስ [1]-(ሳት ዐረብ) በቁሙ የማዕርግ ስም፤ የኤጴስቆጶስ ምክትል፤ ተወራጅ። -(ሙሾ ስለ ቄስና ስለ ቆሞስ) እኔን ፍረድ ቢሉኝ ሞት በደለኛ ነው ቄስ ለፍታት ቆሞስ ቢቀር ምነው። ኤጲስቆጶሳት ወአልቆሞሳት -(ገድ -ተክ)

 [2]--ቁማስበቁሙ መዳቀውመሰ።

ቆራህ -(ጽር ኩራ) ገነት፤ ያታክልት ቦታ ቆራሁ ለንጉሥ -(ነሐ፫ -፲፭)

ቆራሕ -ገነት፤ቀወራህ።

ቆሮስ [1]-(ጽር ኮሮስ። ዕብ ኮር) የመስፈሪያ ስም፤ ዐሥር ኢፍ የሚይዝ፤ ዐሥረ ፈጅ ሖሜርን ተመልከት ከዚህ ጋራ ንድ ነው በመስፈርተ ቆሮስ -(ዘሌ፳፯ -፲፮ ዘኍ፲፩ - ሉቃ፲፮ -)

 [2]--መስፈሪያ፤ቀወሮስ።

ቆቃሕ -( ቀዋቅሕ ዕብ ቆሬእ) ተባት ቆቅ። ቆቃሕ ይነቁ ወያስተጋብእ ዘኢወለደ ቆቃሕ ተሠግረ -(ፊሳሎ። ሢራ፲፩ -)

ቆቅሕ -(ሓት ዕብ ቁቂያ፤ ቆቅማ ወፍ) አንስት ቆቅ። ነቀወት ቆቅሕ ወኢወለደት። መቃርዮስ ዘተሴሰይከ ቅሐ -(ኤር፲፯ -፲፩ ስንክ -ታኅ፲፫)

ቆቅሖ  ሖት -(ቆቅሐ ይቆቅሕ ዐረ ቀውቀ ዕብ ቃዕቄዐ) ማሽካካት ማስካካት፤ ቃቃቃ ማለት፤ የዶሮ ያሞራ፤ ለመውለድ ዕንቍላል ለመጣል። ቀሕቅሐን እይ፤ የዚህ ዲቃላ ነው

ቆባር -(ራት) ዐቧራ ትቢያ በቁም የሚቀብር የሚደፍን፤ እንደ ስሓራ በረሓ በነፋስ ጊዜ -(ዘዳ፳፰ -፳፬) ጭጋግ፤ ጉም ጢስ ጥቍር ደመና፤ የሚያፍን የሚሸፍን፤ የሚያጨልም ወቆባር ታሕተ እገሪሁ። ዕለተ ጽልመት ወቆባር ድባረ ቆባራት እለ ክረምት -(መዝ -፲፯ ሶፎ፩ -፲፭ ሕዝ፴፬ -፲፪ ሔና፲፯ -) ቆበር ቆበራም ማለት ከዚህ የመጣ ነው

ቆብዕ [1]-በቁሙ ቆብቀወብዕ።

 [2]-(ዕብ ቆባዕ ባዕ ሚግባዓ ሱር ቁባዓ ዐረ ቁበት) የራስ ልብስ፤ ጌጥ ቆብ፤ ኵፌት፤ ባርኔጣ ቦርቦርቲ ጠርቡሽ ረዥም ላቅ፤ በራስ የሚደፋ። ቂብ ቂብ ቆበብ የሚል ቄዳርስንና ማዕፈርትን እይ ቆብዑ ውሩት ዲበ መታክፍቲሁ። ነሥአ ቆብዐ ወአስኬማ። ይቤ ጳውሎስ ቆብዐ ሰላም ደገኒ ዴማስ መነኮሰ ሕልም፤ ወአፍቀሮ ዝንቱ ዓለም -(ፊልክ -፶፮። -ተክ። ቅኔ)

ቆንደራጢስ -(ጽር ኮድራንቲስ) የአሶርዮን ሩብ፤ ታናሽ ወራዳ፤ መጨረሻ ገንዘብ የጸሪቅን ፍች ተመልከት -(ማር፲፪ -)

ቆዓት ቃውዕ አቅዋዕ -ጨርቋዎች፤ ቅሎች ሕፃናት።

ቆጰረ [1]-(ልብ ወለድ ግስ) ቈረጠመ ረጣጠመ፤ ፈጨ አንቀጫቀጨ።

 [2]--ረጠመ፤ቀውጰረ

ቆጵሮስ [1]-(ጽር ኪፕሮስ ዕብ ቂፍሮስ ዐረ ቁብሩስ) ስመ ሀገር፤ ደሴት፤ ወይናም ዘይታም ሌዋዊ ዘምድረ ቆጵሮስ -(ግብ፬ -፴፮)

 [2]-(ጽር ኮፕሮስ) ፍግ ንድያ፤ በጠጥ፤ ዐዛባ እበት በት። አላዳስን እይ -(ሉቃ፲፬ -፴፭)

 [3]--ስመ ሀገር፤ ደሴት፤ቀውጵሮስ።

[1]-(ናት ቆብዕ ዓት) ኵፍ ገንባሌ እስከ ልበት ድረስ የሚገባ። ቆጶናቲሁ። ቆጶናት። ቆጶናተ ያክንት -(ሢራ፵፭ -፰። አፈ -ተ፪ አረጋ) ጋላ ስንዱ ዝግጁ ልባም ጠፍተኛ ፈጣን ቀልጣፋ ሲል ቆጴ የሚለው፤ ከቆጶን ጋራ በጣም ይሰማማል።

 [2]- ጫማ፤ቀወጶን።

ቆፋዊ -ዝንጀሯም፤ ዝንጀርማ የዝንጀሮ ይነት፤ ቆፍቋፋ ሥሡ ንፉግ

ቆፍ -(ዕብ) ስመ ፊደል ቀ፤ ዝንጀሮ ማለት ነው -(መዝ -፻፲፰ -፻፵፭፻፶፪ ሰቈ፩ -፲፱ -፲፱ -፶፬። -፲፱)

ቋረፈ -ቈረፈ፤ ቈራረፈ፤ ቈራረጠ በጣጠሰ። ይቋርፍ ራዊት -(አዋል)

ቋርፍ -የዋልድቦች ምግብ፤ ሥራሥር፤ እንደ ድንችና እንደ ሽንኵርት የሚላጥ፤ የሚቀረፍ።

ቋንቋ -በቁሙ፤ ልሳን የቃል የነገር ልት -(ዐማርኛ)

ቋእ -ራ፤ቋዕ ቀዊዕ

ቋዕ [1]-( ቋዓት። ዕብ ዖሬብ ዐረ ቁራብ ጽር ኮራክስ) ጥቍር ሞራ ቀዋዒ የሚቀዋ ቀሣሚ ለቃሚ። ፈነዎ ቋዕ ጸሊም ከመ ቋዕ ርእዩ ቋዓተ -(ዘፍ፰ -፯። ማሕ፭ -፲፩ ሉቃ፲፪ -፳፬) ቍራ ከርኩም ይልቅ እንደ ዝኆን ዕድሚያም ነው ይባላል። ገላግልቱም ሲፈለፈሉ እንደ ራዛ ነጫጮች ወይም እንደ ሕጕሬ እንደ በርበሬ ቀያዮች ኹነው ይወጡና በኋላ ሲያድጉ ይጠቍራሉ እናታቸውም ስለ ንጣታቸው ፈርታ ደንግጣ እስኪጠቍሩ ድረስ ከዚያው ጥላቸው ወደ ሌላ ቦታ ትኼዳለች። የፍጥረቱ አባት እግዜር ግን ፈትፍቶ እንደ ማጕረሥ ተሐዋስያን ታናናሹን ዝንብና ትንኝ እስካፋቸው እያቀረበ ይመግባቸዋል። ዘይሁቦሙ ሴሳዮሙ ለእንስሳ ወለዕጕልው ቋዓት እለ ይጼውዕዎ -(መዝ -፻፵፮)

[2]--ቍራ፤ዊዕ ቆዐ


No comments:

Post a Comment

ማውጫ

ሀ   ለ   ሐ   መ   ሠ   ረ   ሰ   ሸ   ቀ   በ   ተ   ቸ   ኀ   ነ   ኘ   አ   ከ   ኸ   ወ   ዐ   ዘ   ዠ   የ   ደ   ጀ   ገ   ጠ   ጨ   ጰ   ጸ   ፀ   ፈ   ፐ