ሀ ለ ሐ መ ሠ ረ ሰ ሸ ቀ በ ተ ቸ ኀ ነ ኘ አ ከ ኸ ወ ዐ ዘ ዠ የ ደ ጀ ገ ጠ ጨ ጰ ጸ ፀ ፈ ፐ
ከ [1]፡-፲፩ኛ ፊደል በግእዝ አልፍ ቤት በአበገደ፤ ስሙ ካፍ ቍጥሩ ካያ፤ አኃዝ ሲኾን ከ ዕሥራ ይባላል፤ ካያ ኻያ፤ ወይም ኹለት ዐሥር ማለት ነው፤ ካዕበተ የ እንደ ማለት።
[2]፡-(ኩ ኪ ክሙ ክን) የአካል ዝርዝር፤ ጠቃሽና አሰሚ፤ ወይም ምእላድ። አንተ አነ አንቲ አንትሙ
አንትን የሚባሉትን የቅርብ የቅርቦቹን ወንዶችና ሴቶች ፭ቱን ሰራዊት፤ ነበብከ ኩ ኪ ክሙ ክን እያለ ዘርዝሮና ጠቅሶ ለይቶ ያሳያል። አነ ለሚለው ግን ከቀዳማይ በቀር
በዝርዝር ኹሉ አይገባም፤ ኩ የነበረውን የ ይወርሰዋል፤ ነበብኩ ንባብየ።
ከሃ ፡-(ብ ከሃት) ወዲያ ወደዚያ፤ ከዚያ በዚያ፤ የቦታን ፈቀቅታ ጥቂት ርሕቀት ያሳያል፤ ፍችው እንደ ህየ፤ ስልቱ እንደ ለፌ ነው። እም እየተስማማው ከለፌና ከዝየ ጋራ፤ ሳይስማማውም ይነገራል። አሐዱ እምለፌ ድንጋገ ፈለግ፤ ወአሐዱ እምከሃ ድንጋገ ፈለግ። ፍልስ እምዝየ ኀበ ከሃ። አሐውር ከሃ ወእጼሊ። ዝርዎ ከሃ። ረሐቁ ከሃ። በዝ ዓለም ወበከሃ በኀበ እግዚ። ከሃ ከሃቲሆሙ ፡-(ዳን፲፪ ፡-፭። ማቴ፲፯ ፡-፳። ፳፮ ፡-፴፮። ዘኍ፲፯ ፡-፪። ፩ነገ ፡-፲፱ ፡-፱። ዲድ ፡-፲፬። ሔኖ፴፪ ፡-፫)። ከሃየ ከ ኪ ሁ ሃ፤ ከሃነ ክሙ ክን ሆሙ ሆን እያለ ይዘረዝራል። እምለፌሁ ፈለግ ወእምከሃሁ ዕፀ ሕይወት ፡-(ራእ፳፪ ፡-፪)። ፡-(ዕር፳፩ ፡-ቍ፻፲፰)። አንዳንድ መጣፍ ግን በከሃ ፈንታ ከሃክ ከሃከ ይላል፤ የጣፊ ስሕተት ነው። ነዋ ዝየ ወነዋ ከሃክ። አስከ እትመየጥ ለፌ ወከሃከ። ተኃሥሦት እምጥንቃቄ ከሃክ። ወዓዲ ዘእምዝ ከሃከ ፡-(ሉቃ፲፯ ፡-፳፫። ፫ነገ ፡-፳ ፡-፵። ቄር)።
ከሓ ፡-ወዲያ፤–ከህሀ ከሃ።
ከሃሊ ፡-(ሊት ልያን ያት) የሚችል ቻይ፤ ኀይለኛ ብርቱ፤ ሥሉጥ ዕጉሥ። ከሃሌ ኵሉ። ጽኑዕ ወከሃሊ። ዘኮነ ከሃሌ በቃሉ ወምግባሩ። መሥዋዕት ከሃሊ ከመ ታስተስሪ። ንሕነ ከሃልያን ለውላጤሁ። ከሃሊ አነ ተጽናሰሂ ወተደልዎሂ ፡-(ጥበ፯ ፡-፳፫። ሩት፪ ፡-፩። ሉቃ፳፬ ፡-፱። አፈ ፡-ድ፲፯። ዮሴፍ። ፊልጵ፬ ፡-፲፪)።
ከሓዲ ፡-ከሓዲ፤ ፡-(ዲት፤ ድያን ያት) በቁሙ፤ የሚክድ ከዳተኛ ፥ ሸፋጭ፤ ዐላዊ። ይዛለፈክሙ ሕግ ከመ ከሓዲ። ወልድ ከሓዲ። ኢትኩኑ ከሓድያነ በእግዚ። መላእክትኪ ከሓድያን ፡-(ያዕ፪ ፡-፰። ዘዳ፳፩ ፡-፳፰። ዘኍ፲፬ ፡-፬። ኢሳ፩ ፡-፳፫)።
ከሕክሐ ፡-(ክሂህ ከሀሀ። ዐረ ከዕከዐ) ቀላቀለ ደባለቀ፤ አንድ አደረገ ቀምሞ። ከካ ፈነከተ፤ ፈነካከተ፤ ፈጨ ደቈሰ ጨፈለቀ፤ የወፍጮ የናዳ የመርግ።
ከለሜዳ ፡-(ዳት። ጽር ክላሚዳ) ዐጭር ካባ፤ የክብርና የማዕርግ ልብስ ካንገት እስከ ወገብ ወይም እስከ ጕልበት የሚደርስ፤ ነገሥታት መኳንንት ልጆቻቸውም የሚለብሱት። ለምድ ለምደኛ፤ ያርበኞች ሽልማት ፡-(ማቴ፳፯ ፡-፳፰ ፡-፴፩)። ፀምር መንጸፍ በማለት ፈንታ ከለሜዳ ይላል፤ የመላሽ ስሕተት ነው። ክዑበ ከለሜዳ ፡-(ምሳ፴፩ ፡-፳፪። ዲድ ፡-፫)። ዘርቤትን እይ፤ ከዚህ ጋራ ፩ ነው። በያክንትም ፈንታ ቀይ ለማለት ከለሜዳ ይላል፤ ፍችው ኦይዶለም። ያለብስዎ ከለሜዳተ ወደርከኖ ፡-(ኤር፲ ፡-፱)።
ከሊሕ ሖት ፡-(ከልሐ ይከልሕ ይክላሕ) አው ከልሖ፤ ሖት፤ ፡-(ከልሐ ይኬልሕ ይከልሕ) መክለል መጮኽ፤ በታላቅ ቃል መስበክ መንገር፤ ማዜም ማጕረምረም። ቆመ ራፋስቂስ ወከልሐ በዐቢይ ቃል። ክላሕ በኀይልከ። ከልሑ ከመ ቀርን ፡-(ኢሳ፴፮ ፡-፲፫። ፶፰ ፡-፩። ቅዳ ፡-ዮሐ)። ሰራሕኩ በክልሖ። ይኬልሕ ላዕሌሆሙ። ይኬልሑ አሐዱ አሐዱ ምስለ ካልኡ። ኵላ ምድር ትኬልሕ። እንዘ ይኬልሓ መጻሕፍት ፡-(መዝ ፡-፷፰ ፡-ኩፋ ፡-፲፩። ኢሳ፮ ፡-፫። ፲፬ ፡-፮። ቄር)። መብጣት መፍቃት፤ መሠንጠቅ ፡-(ትግ ፡-ሐባ)።
ከሊብ ቦት ፡-(ከለበ ይከልብ ይክልብ። ዕብ ካሌብ፤ ሰፋ ጠቀመ) መክለብ መክለብለብ፤ መቅለል መቸኰል፤ መክለፍለፍ፤ ቀላል ችኵል ክልፍልፍ መኾን ፡-(ዐማርኛ)።
ከላሒ ፡-(ሒት ሕያን ያት) የሚከል የሚጮኽ፤ ጯኺ፤ ቍጡ ደረቅ። ብእሲት ከላሒት ወነባቢት ታነሥእ መዋግደ ጸብእ። ኢትቅረብ ኀበ ብእሲት መስተጋእዝት ወከላሒት ፡-(ፈላስ ፡-ገ፶፪ ፡-፷፬)።
ከላሊ መከልል ፡-የሚከልል ከላይ፤ ቈራጭ ከፋይ።
ከላል ፡-ከሎታ ወለባ፤ ሚዶ መሥዕርት ፡-(ትግ ሐባ)።
ከለላ ዐጥር፤ ግርዶሽ።
ከላኢ መክልኢ ፡-(ኢት እያን ያት) የሚከለክል ከልካይ፤ በረኛ ዘበኛ አጋፋሪ፤ ጠላት ምቀኛ። ፍና መክልኢት ፡-(ፊልክ ፡-፻፷፱)።
ከላዪ መክለዪ ፡-መክለዪ ፡-(ዪት ይያን ያት) የሚሰፍር፤ ሰፋሪ መዛኝ።
ከሌ ፡-(ትግ። ዕብ ክሊ ኬሊ) የቤት ዕቃ፤ መሣሪያ ቈሳቍስ፤ ንዋየ ሐቅል ልክና መልክ ልዩ ስም ያለው፤ እንትን የሚባል።
ከልሎ ሎት ፡-(ከለለ ይኬልል ይከልል። ዕብ ካላል። ሱር። ካሌል ዐረ ካለ) መከለል መጋረድ፤ ማጠር መክበብ ማጀብ፤ ማክበር ጩኾ ማመስገን። ግሩማን የዐውድዎ ወሱራፌል ይኬልልዎ። እግዚኦ ከመ ወልታ ሥሙር ከለልከነ። ተለውዋ እንዘ ይኬልልዋ ወይሴብሑ በአፉሆሙ። ሶበ ርእይዎ ተወሊዶ ከለልዎ እንዘ ይብሉ፤ ስብሐት በአርያም ፡-(መዋሥ። መዝ ፡-፭። ዮዲ፲፭ ፡-፲፫። ቄር ፡-ገ፰)።
፡-ፈጽሞ ማስጌጥ መሸለም፤ ዘውድ መድፋት አክሊል ማቀዳጀት፤ ለንጉሥ ለሙሽራ። ዘከለሎ ለሰማይ በከዋክብት፤ ምድረ በጽጌ ወበፍሬ ከለልከ። እምዕበየ ግርማሁ ዘከለሎ። ክብረ ወስብሐተ ከለልኮ ፡-(ድጓ። ቀሌ። መዝ ፡-፰)።
፡-መደምለል፤ መጠቅለል መሰብሰብ፤ ብዙዉን ባንድነት ማሰብ፤ ኵሉ ኵለንታ ማለት። መፈጸም መጨረስ ማከናወን፤ የሥራ። መቍረጥ መክፈል ያንገትየመሬት።
ከልሰስ ፡-ክልስስት፤ ፡-(ብ ከላስስት) ነዶ ቋጨራ፤ ስንድቅ ድንከን፤ የታሰረና ያልታሰረ። ታበውኡ ክልስስተ እምቀዳሜ ማእረርክሙ። እለ የአስሩ ከላስስተ። ዘወድቀ እምነ ከላስስት ወጾሩ ከላስስቲሆሙ ፡-(ዘሌ፳፫ ፡-፲–፲፪። ዮዲ፰ ፡-፫። ሩት፪ ፡-፯። መዝ ፡-፻፳፭)።
ከልሳሲ ፡-(ሲት ስያን ያት፤ ሰስት) የሚላስስ፤ ዐጫጅ አሳሪ፤ ሰብሳቢ ከማሪ።
ከልስሶ ሶት ፡-(ከልሰሰ ይከለስስ ይከልስስ። ዐረ ከለደ ከለዘ) መሰብሰብ፤ መላሰስ መንቀል፤ የሸት የሽንብራ። እያጨዱ ማሰር ፥ የታጨደውን መሰንደቅ፤ መጐቸት መከመር፤ የነዶ የሣር። አለደንና ቈለዘን እይ፤ የዚህ ጎሮች ናቸው።
ከልበኔ ፡-(ጽር ኻልባኒ) የሙጫ ሽቱ፤ እንደ ዕጣን ያለ። ባለብሉዮች ግን በልብን ዘይቤ ልባንጃ ይሉታል ፡-(ሔኖ፴፩ ፡-፩። ሢራ፳፬ ፡-፲፭)።
ከልባዊ ፡-ገጸ ከልብ፤ ውሽማ የውሻ ዐይነት፤ ውሻ ፊት፤ ጠባየ ውሻ፤ ዘማዊ ወሻሚ ልክስክስ። ፡-(ግጥም ስለ ውሽማ) ውሾ ናና ናና ዕንካ ጤፍ እንጀራ፤ ወዳጅ መስሎ ጠላት የሴት ባልንጀራ።
ከልብ ፡-(ብ ከለባት፤ አክላብ፤ አክልብት። ዕብ ኬሌብ። ሱር ካልባ። ዐረ ከልብ) ውሻ፤ የቤት አውሬ የዥብ ወገን፤ የክፉ ሰዎች ምሳሌ። ውሻ ማለት፤ ደግሞ ዋሻም ሳይቀር ወሐሽ ውሕሽ ከማለት ከዐረብ ቃል መጥቷል፤ ይኸውም አውሬ ያራዊት ጐሬ ማለት ነው። ከልብ ይገብእ ዲበ ቅያኡ። ዐገቱኒ ከለባት ብብዝኃን። ኀምስቱ አክላብ። አክልብት ወአዝእብት ፡-(፪ጴጥ ፡-፪ ፡-፳፪። መዝ ፡-፳፩። ራእ፳፪ ፡-፲፭። ሢራ፲፫ ፡-፲፰)። ያገዳ ድርቆሽ ደረቅ ላንፋ ነፋስ የሚያከበው።
ከልተፈ ፡-(ከተፈ) ኰለተፈ ተኰላተፈ፤ ኵልትፍትፍ አለ ታሰረ፤ ጐለደፈ፤ ያንደበት የስለት። ል ስሯጽ ነው፤ ከተፈን እይ።
ከልአ ፡-ከላ አወለቀ፤–ከልዐ፤ ቀልዐ።
ከልዐ [1]:-ከለከለ፤–ከሊእ ከልአ።
[2]፡-ከልዐ፤ ፡-(ቀልዐ) ከላ አወለቀ፤ አወጣ አሰለበ፤ የልብስ የቀሚስ የጫማ። ቀልዐን እይ፤ የዚህ መንቲያ ነው። ኢትክልዑ አልባስየ። ከላዕኩ ክዳንየ ዘእትዐጸፍ ወወገርኩ። ከልዐ አልባሲሁ ወለብሰ ሠቀ ፡-(ገድ ፡-ዳን)። ክላዕ አሣእኒከ እምእገሪከ ፡-(ቀሌ)።
(ጥ) ከልኦ ኦት ፡-(ከልአ ይኬልእ ይከልእ) አው ከሊእ፤ ኦት፤ ፡-(ከልአ ይከልእ ይክላእ። ዕብ ካላእ። ሱር ክላእ። ዐረ ከለአ) መከልከል መንሣት፤ ማገድ ማስቀረት፤ ማቆም መግታት፤ ከነቢብ ከገቢር ከሐዊር። ከሊአ መንፈስ። ክላእ ልሳነከ እምእኩይ። መኑ ይከልአኒ ተጠምቆ። አኀዞ ለንጉሥ ወከልኦ ኢይባእ። ኢይከልእ ምሕረቶ እምገብሩ ፡-(መክ፰ ፡-፰። መዝ ፡-፴፭። ግብ፷ ፡-፴፮። ዳን፲፫ ፡-፲፮። ኩፋ ፡-፵፭)።
፡-መኾለት፤ ኹለት ማድረግ ፥ ከኹለት መክፈል።
ከልከለ ፡-(ከልአ። ዕብ ካልኬል፤ አበላ ረኀብን ከላ) ከለከለ፤ ክላ ክላ አለ፤ አገረ አስተጓጐለ። ከልካይ እንዲሉ ፡-(ዐማርኛ)።
ከልይ ዮት ፡-፣ ፡-(ከለየ ይከሊ ይክሊ። ዕብ ካል። ዐረ ካለ) መስፈር፤ መመዘን መለካት፤ ከልክ ማግባት፤ የሥራ የምግብ የገንዘብ።
ከመ ፡-(ዕብ ክሞ። ሱር ክማእ። ዐረ ከማ) ዐቢይና ደቂቅ አገባብ፤ እንደ። በ ዘ እያዳመቁት ሳያዳምቁትም ይነገራል፤ በአንጻር በውጥን ይገባል፤ ምስጢሩ መጠንና ልክ አምሳል ነው። በከመ ፈነወኒ አቡየ ከማሁ አነሂ እፌንወክሙ። ዐገቱኒ ከመ ንህብ መዓረ። ፪ኛም፤ እንተ እለ ዘ ባሉበት አንቀጽና ጥሬ ሲገባ መሰለ ይኾናል። ከመ ዘበኀይልነ ወከመ ዘበጽድቅነ ረሰይናሁ፤ ያደረግነው ይመስል፤ ወይም እንዳደረግነው ኹሉ። ፫ኛም፤ መሰለ ሲቀድመውና ሲከተለውን ን ይኾናል። ሰብዐተ ዓመተ ዘኰነንዎ ኢመሰሎ ከመ አሐቲ ዕለት። ወከመ ገሞራ እመሰልነ። ፬ኛም፤ በዘንድ ላይ ኮ ሲወድቅ አዳማቂ ኹኖ ይቀራል። መኑ ውእቱ እግዚኦ ከመ እእመን ቦቱ። ፭ኛም፤ አንቀጽ እያስቀረ ባንቀጽ ሲሳብ ገቢር ተገብሮ ይኾናል። ተዘከር እግዚኦ ከመ መሬት ንሕነ። ርእየ ከመ በዝኀ። ሰምዐ ከመ ተፄወወ። ደቂቅ አገባብም ሲኾን በጥሬና በስም እየገባ አንጻር ይኾናል። ተሰብረ ከመ ዕፅ፤ ተክዕወ ከመ ማይ። ፮ኛም፤ እም ሲወድቅበት እንደ ዘ በር ከፋች ኹኖ በእምና በእመ በሶበ በድኅረ ዘይቤ ይፈታል፤ ምክንያቱም መላሾች በነዚህ ቦታ ስላገቡት ነው። እምከመ ገሰስኩ ጽንፈ ልብሱ አሐዩ፤ ከዳሰስኹ ፥ ብዳስስ ፥ የዳሰስኹ እንደኾን ነ። እምከመ ርእዩኪ ሰብአ ግብጽ፤ ቢያዩሽ ፥ ካዩሽ ፥ ያዩሽ እንደ ኾነ። እምከመ ቦአ ሙሴ ውስተ ደብተራ፤ በገባ ጊዜ ፥ ሲገባ። ወእምከመ ወፅአ መንፈስ ርኩስ እምሰብአ፤ ከወጣ በኋላ ፥ በወጣ ጊዜ እያሰኘ በየገንዘቡ በያወራረዱ ይፈታል፤ እምን ተመልከት ፡-(ዕር፲፱ ፡-ቍ፸፫)።
ከመሠ ፡-ቀመሰ፤–ከመሰ።
(ላ) ከመረ ፡-(ላ) ከመረ፤ ፡-(ቀመረ። አለደ) በቁሙ፤ ቈለለ አንድ ላይ አከበ፤ ሰበሰበ።
ከመዝ [1]፡-ከመዝ፤ ፡-(ከመ ዝ) እንዲህ እንደዚህ። ዘከመ ዝ፤ እንደዚህ ያለ ይህን የመሰለ፤ የዝን አፈታት እይ። ከመ ዝ ይቤ። ዘከመ ዝ ብሥራት።
[2]፡-(ዝን አትጫን) የውሃ እናት፤ ጥቍር ጠቋራ እንዝዝ የምትመስል፤ በቋሚ ውሃ ላይ እንደ እንዝርት ራስ የምትዞር የምትሽከረከር፤ ፊካትምን እይ። ዝ ከእንዝዝ ከእንዝርት መጥቶ ከከመ ጋራ ተቈራኝቷል፤ ዘይቤው ከመ እንዝዝ፤ ወይም ከመ እንዝርት ማለት ነው። አርኣያ ከመዝ ሰረረ በዘባነ ዐባይ ተርሴስ፤ ሐመርኑ እንተ ይነድኦ ነፋስ ፡-(ደራሲ)።
ከሙን [1]፡-(ዕብ ካሞን። ሱር ካሙና። ዐረ ከሙን። ጽር ኪሚኖን) በቁሙ፤ የቅመም ስም፤ ፍሬው ታናናሽ ያንስላል ዐይነት፤ ጣዕምና መዐዛ ስሳለው ከንጀራና ከወጥ የሚገባ። ባለቅኔዎች ግን ተልባ ፌጦ ይሉታል ፡-(ማቴ፳፫ ፡-፳፫። ኢሳ፳፰ ፡-፳፭ ፡-፳፯)። ወኮነ ኢይበልዕ ዘእንበለ ኅብስት ወጼው ምስለ ከሙን ወሐምል ዘኢያብሰልዎ በእሳት ፡-(ስንክ ፡-ሐም፳፬)። በከሙን ፈንታ ከሜን ፥ ከሚን ፥ ካሚን ይላል፤ የጣፊ ስሕተት ነው። ስንድሪስ ወከሜን። እመ ዘራዕከ ከሚነ ፡-(ስንክ ፡-ሐም፰። መቃ ፡-ገ፭)።
[2]፡-ከሙን፤–በቁሙ፤–ከመወ።
ከሚም ሞት ፡-(ከመ፤ ከመመ ይከምም ይክምም) መከምከም፤ ማስተካከል። መሸፈን ማልበስ።
ከሚስ ፡-(ከመሰ፤ ዐረ። ትግ ከምሸ። ዕብ ክማሽ፤ መጽለወ የብሰ) መቅመስ፤ ቀምሶ መተው ልጥገብለት አለማለት፤ ሰውነትን በራብና በጥም በችጋር መቅጣት።
ከሚው ዎት ፡-(ከመወ ይከሙ ይክሙ። ዕብ ካማህ) አጥብቆ መውደድ፤ መሳብ ማቅረብ፤ እኩያ አምሳያ ማድረግ፤ እንደ ራስ ማየት። መመዘን ማስተካከል ፥ አንዱን ባንዱ ልክ መወሰን።
ከማሁ ፡-(ሃ ሆሙ ሆን፤ ከማየ ከ ኪ፤ ነ ክሙ ክን) እንዴሁ፤ እንደ ርሱ።
ከማርም ፡-(ዕብ ክማሪም) ካህናተ ጣዖት፤ ጥምጥማቸው ክምር የሚያካክል፤ አንዱን ካማር ፥ ኮሜር ይላል። አውዐዮሙ ለከማርም ፡-(፬ነገ ፡-፳፫ ፡-፭)።
ከሜሌዎን ፡-(ጽር ኻሜሌዎን) ኅሥሥት፤ ዕሥሥት የንሽላሊት ዐይነት ፡-(ዘሌ፲፩ ፡-፴)። ባለብሉዮች ግን እንቃቅላ ይሉታል። ከሜሌምን በማለት ፈንታ ገላሜዎስ ይላል፤ ስሕተት ነው።
ከምሰሰ ፡-ዐፈረ ተሰቀጠጠ፤ ኵምሽሽ አለ።
ከሰበ ፡-(ይከ ይክስ) ቈረጠ ሸለተ ከረከመ፤ ገዘረ፤ ትርፉን ገላ፤ የጠጕር የጥፍር የዋሸላ። ትከስቡ ቍልፈተክሙ፤ ከሰበ ሥጋሁ። ከመ ይክስቡ ውሉዶሙ ፡-(ኩፋ ፡-፲፭። ፲፮። ፳)።
ከሰየ ፡-(ዕብ ኬሳህ) ሸፈነ ጋረደ አለበሰ።
ከሲብ ቦት ፡-(ከሰበ ይከስብ ይክሰብ) መክሰብ ማትረፍ፤ ትርፍ ጥቅም ማግኘት፤ በሥራ ፡-(ትግሬ ወዐረብ)።
ከሢት ቶት ፡-(ከሠተ ይከሥት ይክሥት። ገለየ፤ ቀልዐ፤ ቀፈጸ) መክሠት መግለጥ፤ መክፈት ማብራት፤ መንገር ማውጣት። ወከሢቶ መጽሐፈ ረከበ። ከሠተ አፉሁ ወመሀሮሙ ትከሥት አዕይገተ ዕዉራን። ኀፍረት ከሢተ ምክረ ዐርክከ ፡-(ሉቃ፬ ፡-፲፯። ማቴ፭ ፡-፪። ኢሳ፵፪ ፡-፯። ሢራ፵፩ ፡-፳፫)።
ከሣቲ ፡-(ቲት ትያን ያት) የሚገልጥ ገላጭ። ክርስቶስ ከሣቴ ብርሃን። ከሣቴ ጽድቅ። ከሣቴ መስቅል ፡-(ድጓ። ስንክ ፡-የካ፳፯። ጥር፯)።
ከስከሰ ፡-(ዕብ ካሽኬሽ) ከሰከሰ፤ ሰባበረ ከፋፈለ ፡-(ዐማርኛ)።
ከሥዶ ዶት ፡-ዶት፤ ፡-(ከሠደ ይኬሥድ ይከሥድ) መክሠድ፤ መዠመት ዥማት ማውጣት፤ መክሳት ዥማታም መኾን፤ ወይም እንደ ዥማት መጥናት፤ መተነን እይ።
ከረበ ፡-(ከሪም ከረመ) ለቀመ ሰበሰበ፤ ተሸከመ የሳንሳ ያዘ፤ የወይን የበለስ፤ የሬሳ የጠርብ የከባድ ነገር፤ ባለቅኔዎች ግን ሰቀለ ይሉታል። ከረመን እይ፤ በ የመ ለውጥ ነው፤ ከተበ ብሎ ከተመ እንዲል ይኽም እንደዚያ ነው።
ከረቦ ፡-ታናሽ ቅርጫት ፥ የወይን የበለስ መልቀሚያ። ታላቅም ይኾናል፤ ቀርጣሎስን እይ፤ ከዚህ ጋራ ፩ ነው። ከረቦ ወይን ከመ ይምላእ ቦቱ ማየ። ሚጥ እዴከ ከመ ዘይቀሥም ውስተ ከረቦ ፡-(ስንክ ፡-ታኅ፳፫። ኤር፮ ፡-፱)።
ከረተ ፡-(ቀረፀ። ዕብ ካራት) ቈረጠ ከተከተ ፥ አፈፈ ቀረጠፈ። ከካ ገረደፈ ፥ ከረተፈ፤ ክርት ሽርንክት አደረገ፤ የዶቄት።
ከረከንድ ፡-(ዐማርኛ) በቁሙ፤ ባላንድ ቀንድ አውሬ ፥ ቀንዱ እንደ ቤት ቍንጮ በማኽል ራሱ የበቀለ፤ መልኩ የፈረስ ቀንዱ ያውራሪሥ። አውራሪሥም ስለ ቀንዱ አንድነት ከረከንድ ይባላል። ወለኵናትኒ ገብርዎ እምነ ከረከንድ ዘቀርኑ መልዕልተ ድማኁ ፡-(ጊ ፡-ወ ፡-ሐ ፡-ገ፳፫)።
ከረዘ ፡-(ዐረብ። ዕብ ካራዝ። ሱር ክራዝ) ዐወጀ፤ ጩኾ ሰበከ አስተማረ። ሾመ ቀደሰ ባረከ፤ የክህነትና ያዲስ ቤተ ክሲያን። ባለቅኔዎች ግን ከረዘ ሰቀለ፤ ክሩዝ መስቀል ብለው ይፈታሉ፤ ምስክር የለውም።
ከሪም ሞት ፡-(ከረመ ይከርም ይክርም። ዕብ ካራም። ዐረ ከሩመ) ወይን መትከል፤ የተተከለውን ማገልገል። መዝነም መፍሰስ፤ ክረምት መኾን፤ የወራት የጊዜ። መክረም ፥ ክረምትን ማለፍ ፥ ማሳለፍ፤ ብዙ ዘመን መኖር ፥ መቈየት። ወውእቱ መርሶ ኢይደሉ ይክርሙ ውስቴቱ ክረምተ። ሐመር ዘከረመት በይእቲ ደሴት። አጥባዕኩ እክርም ህየ። እመ ከረመ ትሰትዮ በትፍሥሕት ፡-(ግብ፳፯ ፡-፲፪። ፳፰ ፡-፲፩። ቲቶ፫ ፡-፲፪። ሢራ፱ ፡-፲)።
ከሪሥ ሦት ፡-(ከረሠ ይከርሥ ይክርሥ) መክተት ማግባት፤ማኖር ማስቀመጥ፤ ቦታ ማሲያዝ። ወንበሩን ኵርሲ እንዲል ፡-(ዐረብ)።
ከሪር ፡-(ዕብ አፊቅ) የወንዝ ውሃ ፈሳሽ፤ የፈሳሹ ቦታ ደንጊያው አለቱ፤ አሸዋው ኵረቱ፤ ውሃ የሚመታው ፥ በላዩ የሚኼድበት፤ ፈሳሹ ባሕሩ ወይም ጐርፋ ያለበሰውና የሸፈነው ታችኛው ውስጡ። ከራራ ደረቅ፤ ንቁጽ ይቡስ፤ ከውሃ ጋር ሲኖር የማይርስ የማይለሰልስ ማለት ነው። ከሪር ከኮራ ፥ አፊቅም ከፊቀን ይሰማማል፤ ከወረንና ኮራን እይ። ለከሪር ወለቈላት ፡-(ሕዝ፫ ፡-፮። ፴፮ ፡-፬ ፡-፮)። ከሪር ባለው ደግሞ አፍላግ ፥ አንቅዕት ይላል።
ከሪር ሮት ፡-(ከረ፤ ከረረ ይከርር ይክርር) መክረር መድረቅ፟፤ ክራራ ደረቅ መኾን፤ በድንገት መሞት። ክር ክራር ማለት፤ ከርከረም ሳይቀር የዚህ ዘር ነው።
ከሪዕ ዖት ፡-(ከርዐ ይክርዕ ይክራዕ። ዕብ ካራዕ) መስገድ መንበርከክ፤ ጕልበትን ማጠፍ።
ከራሚ ፡-(ሚት ምያን ያት) በቁሙ፤ የሚከርም ፥ የከረመ የኖረ፤ ያምና ፥ የኻች ዓምና ፥ የወዲያኛው፤ የብዙ ዓመት። እክል ከራሚ። ትበልዑ ከራሜ ወከራሜ ከራሚ። ወይን ከራሚ ፥ ዐርክ ዘቀዳሚ። እስመ በመከራ ወተድላ ይፌጽምዎ ለዕድሜ ፥ ዘይስአል ማየ ወዘያተርፍ ከራሜ ፡-(ዘሌ፳፭ ፡-፳፪። ፳፮ ፡-፲። አዋል። ቅኔ)።
ከራዪ ፡-(ዪት፤ ይያን ያት፤ ረይት) የሚከራይ። የሚቈፍር ቈፋሪ። ከራይያን። ከረይተ መቃብር ፡-(ፍ ፡-ነ ፡-፵፩ ፡-፩። ሕዝ፴፱ ፡-፲፭)።
ከራድዮን ፡-ስመ ዖፍ፤ ጥሩ ነጭ መልከ መልካም ወፍ፤ የክርስቶስ አርኣያ ፥ የሰውነቱ አምሳል፤ ፊላሎጎስ መጽሐፍ ተመልከት። ለዘተወልደ እምድንግል ምንተ ንብሎ ናስተማስሎ አርዌ ገዳምኑ አንበሳ ወሚመ ከራድዮን ዖፍ ጸዐዳ ንጉሠ ይሁዳ እምዘርዐ ዳዊት ዘመጽኦ ፡-(ድጓ)።
ከርሜል ፡-(ዕብ ካርሜል) ዕርሻ ወዠድ ፥ የእክልና የተክል ቦታ ፥ ወፍራም መሬት፤ በያመቱ ፍሬ የሚሰጥ የማያቋርጥ። ስመ ሀገር በይሁዳ ክፍል ያለች ፡-(ኢያ፲፭ ፡-፳፭) ወይም መላይቱ ምድረ እስራኤል ፡-(ኤር፪ ፡-፯)። ባለቅኔዎች ግን ችፍርግ ይሉታል፤ ምስክር የለውም። ከና ቀ ተወራራሾች ስለ ኾኑ በከ ፈንታ ቀ ይላልና ፥ ቀርሜሎስን እይ፤ ከዚህ ጋራ ፩ ነው።
ከርም ፡-(ብ አክራም። ዐረብ። ዕብ ኬሬም) የወይን ቦታ ፥ ዐጸደ ወይን ፥ ሐረገ ወይን። ደወለ ዐይነ ከርም። አስተጋብኡ ዕፀወ ከርም ወአንደዱ እሳተ ፡-(ሉቃ ፡-፩ ፡-፴፱። ስንክ ፡-ነሐ፲። ሐም፭)። ዐይነ ከርም ትርፍ አብነት ነው፤ ከግእዝ በቀር በጽርእና ባረብ አይገኝም።
ከርሴምቶን ፡-(ጽር ኽሪሶሊቶስ) ዕንቍ፤ የዕንቍ ስም ፡-(ሕዝ፳፰ ፡-፲፫)። ከርሴምቶን ባለው ክርስቲሎቤ ይላል፤ በጽርእ ኹለቱም ፩ ነው፤ ኽሪሶሊቶስ ይባላል፤ ይኸውም ተርሴስ ነው፤ ሕብሩም ሕብረ ማይ። የግእዝ መላሽ ግን ፪ አድርጎታል።
ከርሥ ፡-(ሣት። ዕብ ክሬሽ። ሱር ክሬስ፤ ሆድ። ዐረ ኪርሽ፤ ጨጓራ) በቁሙ፤ ሆድ፤ ውስጥ፤ የመብል ቋት የምግብ ስልቻ፤ የንዋያተ ውስጥ መዝገብ መክተቻ። ኵሉ እክል ይትበላዕ ወይወርድ ውስተ ከርሥ። መብልዕኒ ለከርሥ ወከርሥኒ ለመብልዕ ፡-(ሢራ፴፮ ፡-፳፫። ፩ቆሮ ፡-፮ ፡-፲፫)። ከርሠ ታቦት ፥ ከርሠ ምሧዕ ፥ ከርሠ ሐመር ቢል ውስጥ ማለት ነው። ማሕፀን ፥ ሰፋድል፤ የፅንስ የሽል ቦታ። ከርሠ እም። ፍሬ ከርሥ። ብፁዓት ከርሣት እለ ጾራሆሙ ፡-(መክ፭ ፡-፲፬። ኩፋ ፡-፳፰። ስንክ ፡-ጥር፫)።
፡-ሰውነት ነፍስ፤ ውሳጣዊ ሕዋስ፤ አንዠት። መንፈሰ ርቱዐ ሐድስ ውስተ ከርሥየ። ከርሥየኒ ተሀውከት ላቲ ወኀሠሠታ። ከርሥየ ከርሥየ ወሥርወ ልብየ ፡-(መዝ ፡-፶። ሢራ፶፩ ፡-፳፩። ኤር፬ ፡-፲፱)። ቀርብንና ውስጥን ተመልከት።
ከርስ ፡-ሆድ ውስጥ፤–ከርሥ።
ከርቤ ፡-(ዕብ ሞር። ዐረ ሙር። ሱር ሜራእ) በቁሙ፤ ሽቱ፤ የሽቱ ዕንጨት ደም ፥ ወተት፤ ሲደርቅ እንደ ሙጫ የሚለቀም፤ ወይም በርጥቡ እንደ ቅንጭብና እንደ ቍልቋል ደም የሚቀዳ፤ ሽታው ጥፍጥ ፥ ጣዕሙ መራራ። መሪርን እይ ፡-(መዝ ፡-፵፬ ማሕ፫ ፡-፮። ፭ ፡-፩ ፡-፭። ማቴ፪ ፡-፲፩። ማር፲፭ ፡-፳፫)።
ከርተሰ ፡-ከረተሰ፤ በክርታስ ላይ ጣፈ፤ ሣለ መሰለ፤ ነደፈ በገረ ፥ አንሣ፤ የመልክ የጥፈት። ለካእኮ በመልክአ ጽሕፈት ወከርተስኮ በክርታስ ፡-(አዋል)።
ከርከረ ፡-(ዐረ። ከሪር ከረ) ፈጨ፤ አዞረ መጁን። በቁሙ፤ ከረከረ ገዘገዘ። ወሠረን እይ፤ ካራ ከርከሮ ክርክር ማለት የዚህ ዘር ነው።
ከርከንድ ፡-(ዐረብ። ዕብ ካድኮድ) ዝኒ ከማሁ፤ ከርከዴን የሚባል ዕንቍ፤ ወይም ሌላ ከርከዴናዊ። ከደዋን እይ ፡-(ሕዝ፳፰ ፡-፲፮)።
ከርከዴን ፡-(ዐረብ። ዕብ ካድኮድ) ዝኒ ከማሁ፤ ከርከዴን የሚባል ዕንቍ፤ ወይም ሌላ ከርከዴናዊ። ከደዋን እይ ፡-(ሕዝ፳፰ ፡-፲፮)።
ከርካዕ ፡-(ዕብ ሻቄድ። ዐረ ለውዝ) የተክል ዕንጨት ስም ፥ ለውዝ፤ ፍሬው እንደ ኮክ ያለ፤ ዐጥንታም አፍኣውና ውስጡ የሚጥም። ባለብሉዮች ግን ሎሚ ይሉታል ፡-(ዘፍ፴ ፡-፴፯። ፵፫ ፡-፲፩። ኤር፩ ፡-፲፩። መክ፲፪ ፡-፭)።
፡-ቀርካሓ ውስጠ ክፍቅ፤ ወይም ፍልፍል ዕንጨት የቀርካሓ ዐይነት። ወግዘፉ አርባዕቱ አጻብዕ ዘከርካዕ ፡-(ኤር፶፪ ፡-፳፩)። ዘውእቱ ከርካዕ ማለት ነው፤ ንቡብን እይ።
ከርይ ዮት ፡-(ከርየ፤ ከረየ ይከሪ ይክሪ። ዕብ ካራህ፤ ክራእ። ዐረ ከራ ካረ) መቈፈር መማስ፤ መሰርሰር መፈልፈል ፥ መብላት መንደል። ከረየ ዐዘቅተ። ዘይከሪ ግበ። ይቤለኒ ክሪ አረፍተ ወከረይኩ። እለ ይከርዩ አብያተ ፡-(ኩፋ ፡-፳፬። ምሳ፳፮ ፡-፳፯። ሕዝ፰ ፡-፰። ፈ ፡-መ ፡-፲፯ ፡-፯)።
፡-መፈለግ ማሰብ፤ መቈስቈስ መጫር ፥ ማጫር፤ የጠብ። ብእሲ አብድ ይከሪ ለርእሱ እከየ። ብእሲ መዐትም ይከሪ ጋእዘ ፡-(ምሳ፲፮ ፡-፳፯። ፳፱ ፡-፳፪)።
፡-መከራየት በቍርጥ መግዛት፤ የቤት የከብት። መንፋት ማቀናጣት፤ ከመንገድ ማውጣት፤ የጥጋብ የስካር። ፡-(ዘዳ፴፪ ፡-፲፭)። በእኪት ዕለት ይከሪ ጽጋብ። ፈሓል ኢይክርየኒ ፡-(ሢራ፲፩ ፡-፳፯። ፳፫ ፡-፮)።
ከርደል ፡-(ዐረ ኀርደል። ዕብ ሓርዳል፤ ሰናፍጭ) ዐጭር ድንክ ኵርንባጥ፤ ታናሽ ዝራጭ እጅግ የተናቀ፤ ቁመተ ዶሮ መልከ ዝንጀሮ ፡-(ዐማርኛ)።
ከርደደ ፡-(ገሪድ ገረደ) ከረደደ፤ ከርዳዳ ኾነ ሻከረ።
ከበለ ፡-(ዕብ ካቤል) አሰረ ዘንጀረ፤ በብረት። ከንበሎን እይ፤ የዚህ ዘር ነው።
ከበሎ ፡-(ዕብ ኬቤል) ማሰሪያ፤ የግር ብረትና የሰንሰለት ፍንጅ፤ የሣጥን ዦሮ ቀለበት ዙሪያው ክብ የኾነ ምእዙን ያይዶለ። ወትገብር ውስተ አርባዕቱ መሳምክቲሃ ለታቦት አርባዕተ ከበሎ ፡-(ክብ ፡-ነገ፲፯)። ፅብንን እይ፤ ከዚህ ጋራ አንድ ነው።
ከበሮ ፡-(ብ ከባርው) በቁሙ፤ ንዋየ ማሕሌት አታሞ ነጋሪት፤ ከማዕደን ከንጨት ከቈርበት የሚሠራ፤ ስለ ክበረ በዓል የሚመታ። ክብራዊ ትእምርተ ክብር ጯኺ ተሰሚ ማለት ነው። ሰብሕዎ በከበሮ። ንሥኢ ከበሮኪ። መሰንቆ ወከበሮ ፡-(መዝ ፡-፻፶። ኤር፴፰ ፡-፬። ዳን፫ ፡-፲)።
ከበታ ፡-ስዋሬ ስወራ፤ ስውርነት። በመንከራቲሁ ያርኢ ከበታሁ። ኢይነግር በእንተ ከበታየ፤ አላ በዘያስተርኢ ፡-(ተረ ፡-ቄር፩። ፲)።
ከበወ ፡-ስዋሬ ስወራ፤ ስውርነት። በመንከራቲሁ ያርኢ ከበታሁ። ኢይነግር በእንተ ከበታየ፤ አላ በዘያስተርኢ ፡-(ተረ ፡-ቄር፩። ፲)።
ከቢስ ሶት ፡-(ከበሰ ይከብስ ይክብስ። ዕብ ካባስ፤ ዐጠበ አጠራ ወለወለ። ካባሽ፤ ያዘ ገዛ ሣቀየ አጠቃ) መከበስ ማክበስበስ፤ ጠጕርን ሰብስቦ ጠምዞ በማኽል ራስ ላይ መጠቅለል ማሰር፤ በወለባና በሚዶ መያዝ መቸንከር። ራስን ጠጕር በሚታሰርና በሚደፋ በሚለበስ ነገር መሸለም ማስጌጥ ማንቈጥቈጥ።
ከቢር ሮት ፡-(ከብረ ይከብር ይክበር። ዐረ ከቡረ። ዕብ ክባር፤ ዱሮ ቀድሞ) መክበር መከበር፤ መወደድ፤ ማደግ መብለጥ፤ መግነን ታላቅ መኾን፤ የሀብት የዋጋ፤ የማዕርግ የድሜ፤ የወርድ የቁመት። ከቢር እንዲል ዐረብ፤ ታላቅ ሲል። በክብረ አቡሁ ይከብር ሰብእ። ቦ ዘይከብር በአትሕቶ ርእሱ። ዘይውኅድ ይከብር ወይቴሐት ዘይበዝኅ። ብክሙ ይክበር ዘርዐ አብርሃም። ውእቱ ይከብር እምኔሆሙ ፡-(ሢራ፫ ፡-፲፩። ፳ ፡-፲፩። ሱቱ ፡-ዕዝ፮ ፡-፴፫። ኩፋ ፡-፴፩። ዳን፩ ፡-፬)። በከብረ ፈንታ ተከበረ ይላል፤ ተ ያማርኛ ነው። ወአንስትኒ ይትከበራ። ተከባሪ ፡-(ተረ ፡-ቄር፲፰። ሲኖዶ)።
ከቢብ ቦት ፡-(ከበበ ይከብብ ይክብብ። ዐረ ከበ። ሱር ካባባ) መክበብ ማጠር፤ መሾም ማክበር፤ መጥራት ማደም፤ መሰብሰብ ማከብ፤ በዓል ሰርግ ጉባኤ ማድረግ። ከመ ይቁሙ ከቢቦሙ እሳተ ከመ አረፍት። ርእየቶ ለዳዊት ምስለ ኵሎሙ ማኅበረ ነቢያት ወነፍሳተ ጻድቃን ከቢቦሙ ከመ አረፍት። ሐዋርያቲሁ ከበበ፤ እግረ አርዳኢሁ ኀፀበ ፡-(ገድ ፡-ተክ። ስንክ ፡-የካ፲፮። ድጓ)። ማኮብ ማኳስ መጠምጠም፤ የፈትል። ማንከብከብ ማንከብለል፤ ክበ እንክብል ማድረግ፤ የርጥብ ነገር የመድኀኒት።
ከቢት ቶት ፡-(ከበተ ይከብት ይክብት። ኀብአ) መከበት፤ መሸሸግ ፣ መሰወር መደበቅ፤ እንዳይገኝ ማድረግ። ኢተረክበ እስመ ከበቶ እግዚ። ከበተት ርእሳ። ኢንክል ከቢቶቶ። ይኄይስ አብድ ዘየኀብእ እበዲሁ እምጠቢብ ዘይከብት ጥበቢሁ ፡-(ዕብ፲፩ ፡-፭። ሉቃ፩ ፡-፳፬። ግብ፬ ፡-፲፮። ሢራ፳ ፡-፴፩)።
፡-ማሳደር፤ ከቤት ከበረት ማግባት፤ መጠበቅ መመልከት፤ የንግዳ የከብት። ከብት ማለት ቅሉ ኵበትም ሳይቀር ዐማርኛው ከዚህ የወጣ ነው።
ከቢድ ዶት ፡-(ከብደ ይከብድ ይክበድ። ዕብ ካቤድ) መክበድ መመንዘል፤ መብለጥ መብዛት፤ በሚዛን በቍጥር። ምንት ይከብድ እምነ ዐረር። ይከብድ እምኆጻ ባሕር ፡-(ሢራ፳፪። ኢዮ፮ ፡-፫)።
፡-መጥናት፤ መበርታት፤ ማየል። ከብደ ልቡ ለፈርዖን። ወከብደ ቀትል ዲበ ሳኦል። ከብደዌሁ ፡-(ዘፀ፯ ፡-፲፬። ፩ዜና ፡-፲ ፡-፫። ፫ነገ ፡-፲፯ ፡-፲፯)።
ከባቢ ፡-በቁሙ፤ የማከብ፤ ሰብሳቢ።
ከባቲ ፡-(ቲት ትያን ያት) የሚከብት ከባች፤ ሸሻጊ ደባቂ። ከባቲሁ ለኵሉ ክሡት። አምላክ ከባቴ አበሳ ፡-(ቅዳ ፡-ሕር። ግንዘ)።
ከብረወ ፡-(ተቀ ግ። ዕብ ቶፌፍ) ጸፋ መታ ኰረኰረ፤ ጐሰመ።
ከብከበ ፡-(ተቀ ግ) አኰበኰበ ፣ ኵብ፤ ኵብ አለ፤ ያካኼድ የዘፈን፤ የዝላይ ፡-(ትግሬ)። ኵብኵባ ማለት ከዚህ ወጥቷል። ከበከበ ፣ ተከባከበ አከበረ ፡-(ዐማርኛ)።
ከብካብ ፡-ሰርግ፤ የመርዓዊና የመርዓት ጉባኤ፤ የዘፈን የደስታ በዓል ፡-(ዮሐ፪ ፡-፩። ሉቃ፲፪ ፡-፴፮። ማቴ፳፪ ፡-፪)። ገብረ ከብካበ። መዋዕለ ከብካብ። አመ ከብካብ። በከመ መርዓዊ ይትፌሣሕ በውስተ ከብካቡ ፡-(ዘፍ፳፱ ፡-፳፪። አስቴ፱ ፡-፳፪። ጦቢ፮ ፡-፲፬። ቀሌ)።
፡-ከብካብ፤–ሰርግ፤–ከቢብ ከበበ ከብከበ።
ከብድ ፡-(ዕብ ፡-ካቤድ። ሱር ፡-ካብዳ። ዐረ ፡-ኪብድ) ጕበት፤ ከንዋያተ ፥ ውስጥ አንዱ ፥የሐሞት፤ ምንጭ ፥ ዐይነቱ ዳማ። ምትሮ ላዝ ዐሣ ወንሣእ ልቦ ወከብዶ ወሐሞቶ። ሕብረ ከብድ ፡-(ጦቢ፮ ፡-፬። ዘኈ ፬ ፡-፯)
ከተመ ፡-(ኀተመ፤ ከተበ) ዘጋ አሸገ ዐተመ፤ እንዳይከፈት። አመለከተ ፥ ምልክት ጣፈ አደረገ፤ በቀለም በተኵስ ፥ ወይም በመብጣት ፥ እንደ ሣይንቶች፤ ተድባበ ማርያም ለማለት ተን ብቻ በየቀኝ ክንዳቸው ይበጣሉ ፡-(ራእ፲፫ ፡-፲፮ ፡-፲፯)። በቁሙ፤ ከተማ ሠራ ፤ መዲና አደረገ።
ከተማ ፡-(ማት) ጫፍ ራስ፤ ዳርቻ ጽንፍ፤ መጨረሻ። ከተማ ነፍስት። ከተማ በትሩ። ከተማሁ ለደብር። ጕጠት ዘሠላስ ከተማት። አዕይንቲሁ ለአብድ ውስተ ከተማ ምድር ፡-(ዘፍ፲፯ ፡-፲፪። ፵፯ ፡-፴፩። ዘፀ፲፱ ፡-፳። ፊልክ ፡-፭። ምሳ፲፯ ፡-፳፬)።
፡-የፍሬ በኵራት ቀዳምያት። ከተማ ዐውድከ ፡-(ዘፀ፳፪ ፡-፳፱)።
፡-በቁሙ፤ የንጉሥ መዲና መናገሻ፤ የአህጉር ራስ። ፡-(ተረት) የድኻ ልጅ ባውድማ፤ የመኰንን ልጅ በከተማ። ሰብአ ከተማ። ወገብሩ ከተማ በህየ ፡-(ታሪ ፡-ነገ)።
ከተማዊ ፡-የከተማ ፥ የመዲና፤ ከተምኛ።
ከተረ ፡-(ቀተረ) በቁሙ፤ ዘጋ አቆመ፤ አገደ ከለከለ። ከተረ መዐተ ፡-(ጥበ፲፰ ፡-፳፩)።
፡-ከበበ ዐጠረ፤ ዙሪያውን ያዘ። ቀተረን እይ፤ የዚህ መንቲያ ነው። ፡-(ተረት) ባጤ ሞት የተከተረ በስለት የተመተረ።
ከተበ ፡-(ዐረ። ሱር ክታብ። ዕብ ካታብ) በቁሙ ጣፈ ፥ ጻፈ። አጋባ አራከበ፤ ተባቱን ከንስት ፥ ደዌውን ከጥዑይ፤ የተክል የፈንጣጣ።
ከቲት ቶት ፡-(ከተ ይከትት ይክትት። ዕብ ካት) መከትከት ማድቀቅ፤ መውቃት ማምረት፤ መሰብሰብ መክተት፤ ያዝመራ። የካቲትን እይ፤ ከዚህ የወጣ ነው።
ከቲፍ ፎት ፡-(ከተፈ ይከትፍ ይክትፍ። ዕብ ካፋት) ማሰር ማጣመር፤ ማስተላለፍ ማቈላለፍ፤ የእጅና የጣት እስራት ፥ ወይም ያለሰርት በጸሎት ጊዜ፤ ለግር ተወርችም ይኾናል። በቁሙ፤ መክተፍ መከሸን፤ የሥጋ የሽንኵርት። ድንገት መድረስ፤ ከተፍ ማለት ፡-(ዐማርኛ)። ከልተፈን እይ፤ የዚህ ስሯጽ ነው።
ከታሪ ፡-(ሪት ርያን ያት፤ ተርት) በቁሙ፤ ከባቢ ወንበዴ። ኽልተ ኸተርቲ ፡-(ትግሪኛ ማቴ፳፯ ፡-፴፰)።
ከታር ፡-ኮታሪት፤ ፡-(ጽር ኾታር፤ ኾታሮት። ዕብ ኮቴሬት፤ ብ ኮታሮት) የዐምድ ጕልላት፤ እንደ ዘውድ ያለ። ባለብሉዮች ግን ዋልታ ገበታ ይሉታል ፡-(፬ነገ ፡-፳፭ ፡-፲፯። ፪ዜና ፡-፬ ፡-፲፪ ፡-፲፫)።
፡-ኩታራ ታናሽ ልጅ ፥ ከጨዎታና ከንጀራ በቀር ሌላ የማይሻ፤ ሰደቃ የሚያቅፍ የሚከብ።
ከታቢ ፡-(ቢት ብያን ያት፤ ተብት) በቁሙ፤ የሚጥፍ ጣፊ። ከታብያን ፡-(ስንክ ፡-የካ፰)።
ከነተ ፡-(ቀኒት ቀነተ) ዐገዘ ረዳ፤ አይዞኽ አለ። ረባ ጠቀመ ፥ አገለገለ።
ከነነ ፡-(ዐረ ከነ) ሰወረ ደበቀ፤ ሸፈነ ከደነ።
ከነዓን ፡-(ዕብ ክናዓን) ስመ ነገድ ፥ ስመ ትውልድ፤ ወልደ ካም ራብዕ፤ ስመ ሀገር የከነዓን ልጆች የወረሷት ከሲዶን በመለስ እስከ ሰዶም ድረስ ፡-(ዘፍ፲ ፡-፮ ፡-፲፭–፲፱)። ፍችው ነጋዴ ማለት ነው፤ ተገዥ አገልጋይ እንደ ማለት፤ የኹሉ ታናሽ ነውና። ከዚህ የተነሣ ንግድንና የንግድን ሥራ ያወጡ የከነዓን ልጆች ስለ ኾኑ ነጋዴ ኹሉ ከነዓን ይባላል፤ ፡-(ሕዝ፲፯ ፡-፬)። ነጋዴም ማለት ምስጢሩ ፥ ከነዓን ይኩን ገብረ አግብርት ለአኀዊሁ ካለው ከኖኅ ትንቢት ጋራ ይሰማማል ፡-(ዘፍ፱ ፡-፳፭ ፡-፳፮)።
ከኒሳ ፡-(ብ ከናይስ። ዕብ ክኒሳ፤ ክኔሴት። ሱር ክኒስታ። ዐረ ከኒሰት) ታላቅ ጉባኤ ፥ ማኅበር እንግልጋ ፥ የሕዝብ መንጋ። መካነ ጉባኤ ፥ ቤተ ክሲያን ፥ ምኵራበ አይሁድ፤ የተጠረገ የተጌጠ። ሰላም ለጉባኤክሙ ውስተ አሐቲ ከኒሳ። ቤተ ክርስቲያን ከኒሳ እንተ አልብኪ አበሳ ፡-(ስንክ ፡-ኅዳ፲፩። ታኅ፲፪። ደራሲ)።
ከኒፍ ፎት ፡-(ከንፈ ይከንፍ ይክንፍ። ዕብ ካናፍ) መክነፍ መብረር፤ መዘርጋት መርበብ፤ ማቀፍ መሰብሰብ፤ ያሞራ የሰው። ዐጽቅ ማውጣት፤ የዕፀው።
ከናሲ መከንስ ፡-የሚከንስ፤ ሰብሳቢ ጠራጊ ፥ አንድ አድራጊ።
ከናዪ መክነዪ መክንይ ፡-መክንይ፤ ጋራጅ፤ መካች ተሟጋች።
(ጥ) ከንሶ አው ከኒስ ፡-(ከነሰ ይኬንስ ይከንስ። ዕብ ካናስ። ሱር ክናስ። ዐረ ከነሰ፤ ጠረገ) መከነስ፤ መሰብሰበ ማከብ፤ አንድ ማድረግ። ማዘዝ፤ መግዛት። መጽሐፍ ግን በከነሰ ፈንታ አክነስ ይላል፤ አያሰኝም። ሆባየ አክነስከ ፡-(መዋሥ)።
ከንበለ ፡-(ተቀ ግ) ከነበለ፤ ደፋ አፈሰሰ። ከንበሌ ሆይ ፥ ከንበል ያርገኝ ፥ አከንባሎ ፡-(ሞገድ) ማለት የዚህ ዘር ነው።
ከንበሎ ፡-(ከበለ) ወለባ፤ የራስ ማከኪያ ፥ የጠጕር ችንካር እንደ ሚዶ ያለ። ወወሀበቶ ለዐጻዌ ቤታ ከንበሎሃ ዘወርቅ ፡-(ስንክ ፡-መስ፳፯)።
ከንተረ ፡-(ከነተ። ተቀ ግ) ከነተረ፤ በዱላ መታ፤ ከምድር ጣለ ፡-(ዐማርኛ)። ዱላን ከንተሮ ማለት፤ ከዚህ ወጥቷል። ግስነቱ የከነተ ቅጥይ፤ ወይም የከተረ ስሯጽ ይባላል፤ ቅጥዩ ረ ፥ ስሯጹ ን።
ከንተወ ፡-(ተቀ ግ) ከንቱ ኾነ፤ ጠፋ ታጣ፤ ዐበለ ዋሸ፤ ተበላሸ።
ከንቱ ፡-በቁሙ፤ ብላሽ፤ ያለዋጋ፤ የማይረባ የማይጠቅም፤ ፈጥኖ የሚያልፍ የሚጠፋ። እስመ በከንቱ መሀርኩክሙ። ሕልም ወሰገል ወመቅስም ከንቱ ኵሎሙ። ከንቱ ከንቱ ይቤ መክብብ፤ ኵሉ ከንቱ ፡-(፪ቆሮ ፡-፲፩ ፡-፯። ሢራ፴፩ ፡-፭። መክ፩ ፡-፪)።
፡-ውሸት ቧልት፤ ዋዛ ፈዛዛ። ነቢያት ርእዩ ከንቶ። እለ ይትናገሩ ከንቶ ፡-(ሰቈ፪ ፡-፲፬። ኢሳ፰ ፡-፲፱)።
፡-ክፉ ፥ መጥፎ። ከመ ቆዕ ከንቱ ለስነን። ከንቱ ላሕይከ ፡-(ምሳ፲ ፡-፳፮። ኤርያ፬ ፡-፴)።
ከንትሮስ ፡-(ሳት። ዐረ ሙቀንጠረት) ክፍለ ዘመን፤ የዓመት ርቦ ፥ ፺፩ ዕለት ካ፲፭ ኬክሮክ። ባለመርሐ ዕዉሮች ግን የሰዓት ፴ኛ ክፍል ይሉታል፤ አንዱን ሰዓት ፴ ከንትሮስ ለማስት። ዘያስተባሪ አክራመ በሐጋይ ወመፀወ በጸደይ ከንትሮሳቲሆሙ ዘገብረ በዘይትዔረይ ፡-(መጽ ፡-ምስ)።
ከንዐ ፡-(ዕብ ካኖዕ፤ ሂካኔዕ) ተገዛ ተዋረደ፤ ግብር ሰጠ ፥ አቀረጠ።
ከንይ ዮት ፡-(ከነየ ይከኒ ይክኒ። ዕብ ካናህ፤ ሰመየ) መጋረድ መመከት፤ እንዲህ ነው እንጂ ፥ እንዲህ አይዶለም ማለት፤ በውነት ወይም በሐሰት። ከየነን ተመልከት፤ የዚህ ጎር ነው።
ከንፈር ፡-(ብ ከናፍር) በቁሙ፤ የአፍ ዙሪያ ፥ ማእዝን እንደ ሳንቃ የሚከፈት የሚዘጋ የሚንቀሳቀስ አንዱ ክፍል። ዘሩና አንቀጹ ከኒፍ ከንፈ ሲኾን ር ከከፈር መጥቶ ተደርቧል፤ ከፈርን እይ። ከንፈሩ ታሕታይ። ሠናይ ሞገሶን ለከናፍረ ጠቢብ። ንሥኢ ሰቈቃወ በከናፍርኪ ፡-(ኪዳ ፡-ገ፭። ሢራ፳፩ ፡-፲፮። ኤር፯ ፡-፳፱)።
፡-ቋንቋ ፥ የቋንቋ ስልት አነጋገር ካፍና ከከንፈር የሚሰማው። ይትናገሩ አሐደ ከንፈረ ወአሐደ ልሳነ። ሕዝብ ዘዕሙቅ ከናፍሪሁ ወክቡድ ልሳኑ። በካልእ ልሳን ወበካልእ ከናፍር እትናገሮሙ ፡-(ኩፋ ፡-፫። ሕዝ፫ ፡-፭። ፩ቆሮ ፡-፲፬ ፡-፳፩)። ለአፈ ማሕፀን ሳይቀር ከንፈር ላለው ኹሉ ይነገራል። ወኢይምላእ ጽዋዐ እስከ ከንፈራ ፡-(ፍ ፡-ነ ፡-፲፫)።
፡-ጫፍ ፥ ጠርዝ ፥ መጋጠሚያ፤ የልብስ የድንኳን። ከንፈረ ዐጸድ። ከንፈረ ሠቅ ፡-(ዘፀ፳፮ ፡-፬ ፡-፲)።
፡-ዳር ደንበር፤ አፋፍ ጠረፍ፤ ወደብ፤ ገደብ። ከመ ኆጻ ዘውስተ ከንፈረ ባሕር ፡-(መሳ፯ ፡-፲፪። ኩፋ ፡-፰)።
ከአወ ፡-አፈሰሰ፤–ክዒው ከዐወ።
ከዓቢ ፡-መክዕብ፤ የሚክብ ካቢ፤ ዐጣፊ ደራቢ።
ከዓዊ ፡-(ዊት ውያን ያት፤ ዐውት) የሚያፈስ፤ አፍሳሽ ፡-(ዘሌ፲፯ ፡-፬። አፈ ፡-ድ፳፬)።
(ጥ) ከወረ ፡-(ይኬውር ይከውር። ዕብ ካዌር) ጠመደ አጠመደ፤ ጋፈፈ ያዘ፤ የዓሣ። ቀዘፈ ተረከዘ፤ መርከብን ነዳ በሥራት አስኬደ፤ በባሕር በመርከብ ሥሉጥ ኾነ። መጽሐፍ ግን በከወረ ፈንታ ተከወረ ይላል፤ ስሕተት ነው። ኖትያት እለ ይትኬወሩ ውስተ ባሕረ ዓለም ዐሠርቱ ወክልኤቱ ሐዋርያት። መዋግድ እለ ያሰጥሙ ሐመረ ልቡ ለዘሊኢክል ጸቢተ ውስተ ቀላየ መጻሕፍት ወለዘኢይትኬወር በመቃድፈ ኦሪት ወነቢያት ወበመቃድፈ ወንጌል ወሐዋርያት ፡-(መጽ ፡-ምስ ፡-ገ፳፩። ፻፰)።
ከዊል ሎት ፡-(ኮለ፤ ይከውል ይኩል) አው፤ ከውሎ፤ ሎት፤ ፡-(ከወለ ይኬውል ይከውል) መከወል፤ ወደ ኋላ ማድረግ፤ የኋሊት ማስኼድ ማስፈግፈግ፤ ወይም በኋላ ማስከተል፤ አስከታይ መኾን።
ከዊስ ሶት ፡-(ኮሰ ይከውስ ይኩስ። ሖሰ) ማካወስ መበጥበጥ ማወክ መድረጥ፤ መነቅነቅ ማናወጥ፤ የባሕር የኮሶ የፈሳሽ ነገር ኮሶም በምሳሌ ባሕር ይባላል። ፡-(ዕንቆቅልኽ) ታናሽ ባሕር ዐጤን ታስፈር)። ኮሶ ማለት ቅጠሉ የዚህ ዘር ነው። መጽሐፍ ግን በኮሰ ፈንታ አኮሰ ይላል፤ ስሕተት ነው። አነ እግዚ ዘኣከውሳ ለባሕር። አኮስካ ለባሕር። ሰይጣናት ያከውሱ ውስተ ልቡ ብዙኀ እኪያተ ፡-(ኢሳ፶፩ ፡-፲፭። ሱቱ ፡-ዕዝ፩ ፡-፲፱። ፊልክ ፡-፴ ፡-፴፯)። ኮሰና ሖሰ ኆሠ አንድ ዘር ናቸው፤ ስልታቸው ግን እንደ ፊደላቸው ልዩነው፤ ይኸውም በምስክራቸው ይታወቃል፤ ፍቻቸውን በየቦታቸው ተመልከት።
ከዊር ሮት ፡-(ኮረ ይከውር ይኩር። ዐረ ካረ) መሸከም ማሸከም፤ ፡-(ላ ጥ ጫ) መጫን ማንገት መቀዳጀት፤ የሸክም የጌጥ። ለጥምጥምና ለቆብም ይኾናል። ከረየን እይ፤ የዚህ ጎር ነው።
ከዊን [1]፡-መፈጠር መገኘት፤ መወለድ ከማሕፀን መውጣት፤ ከላይ ወደ ታች መውረድ መዝነም፤ መምጣት መሰማት መነገር። እስመ ውእቱ ይቤ ወኮኑ። ነገር በእንተ ከዊነ ዓለም። ኵሉ ኮነ እመሬት። ኢይኩን ፍሬ እምኔኪ። ወኮኑ ሊተ እምኔሃ ሠለስቱ ውሉድ። ወኮነ አይኅ ላዕለ ምድር አርብዓ ዕለተ። ወኮነ ቃል እመልዕልተ ጠፈር ፡-(መዝ ፡-፻፵፰። ጊ ፡-ወ ፡-ሐ ፡-ገ፪። መክ፫ ፡-፳። ማቴ፳፩ ፡-፲፱። ፊልክ ፡-፫። ዘፍ፯ ፡-፲፪። ሕዝ፩ ፡-፳፭)።
፡-መደረግ፤ መፈጸም መከናወን፤ የሥራ የትንቢት የትእዛዝ። ዝ ኵሉ ይከውን ፍጡነ። በከመ ነበብኩ ከማሁ ይከውን። እስመ በግብር ይከውን ዘነበበ ዮናስ ነቢይ ፡-(ኢሳ፲፬ ፡-፩ ፡-፳፬። ጦቢ፲፬ ፡-፰)።
፡-ማደር መኖር፤ ቦታ መያዝ፤ ምስጢሩ ከመቆምና ከመቀመጥ ጋራ ይሰማማል። ኮነ በማርያም ድንግል። ለይኩን ብርሃኑ ለእግዚ አምላክነ ላዕሌነ። ከመ እኩን ቦቱ ፡-(ውዳ ፡-ማር፫። መዝ ፡-፹፱። ፊልጵ፫ ፡-፱)።
፡-መገባት መመቸት፤ መሰማማት። ኢይከውነከ ትዕጥን። ኢይከውነነ ንደዮ ውስተ ቤተ መባእ። ዘኢይከውኖሙ ለበሊዕ ፡-(፪ዜና ፡-፳፮ ፡-፲፰። ማቴ፳፯ ፡-፮። ሉቃ፮ ፡-፬)።
፡-መብቃት፤ ልክ መኾን። ኮነክሙ ዐዊዶቶ ለዝንቱ ደብር። ኮነከ ወኢትድግም። ይከውነክሙ ዐሪግ ውስተ ኢየሩሳሌም ፡-(ዘዳ፪ ፡-፫። ፫ ፡-፳፮። ፫ነገ ፡-፲፪ ፡-፳፰)።
፡-መጥቀም መርባት፤ ማገልገል። ምንት ይከውን ዕፀ ወይን እምኵሉ ዕፅ ፡-(ሕዝ፲፭ ፡-፪)።
፡-መሼጥ፤ መለወጥ፤ መገዛት። ወኮነ ርእሰ አድግ ለኀምሳ ሰቅለ ብሩር። መስፈርተ ስንዳሌ በሰቅል ትከውን ፡-(፬ነገ ፡-፮ ፡-፳፭። ፯ ፡-፩)።
[2]፡-(ዘርና ጥሬ) መኾን ኹነታ፤ እነት ባሕርይ ጠባይ። እነትና መኾን አንድ ወገን ናቸው፤ ምስጢራቸውም ባሕርይ ነው። እመሰኬ ከዊነ እግዚአብሔር ዘኢይትዌለጥ በከመ ይትዌለጥ ህላዌሆሙ ለፍጡራን። እምከዊነ ካህን ይኄይስ ከዊነ ኖላዊ ፡-(ማር ፡-ይሥ፴፫ ፡-፫። ቅኔ)።
ከዊን ኖት ፡-(ኮነ ይከውን ይኩን። ዐረ ካነ፤ ሀሎ። ዕብ ካን፤ ሀያህ) መኾን፤ መባል፤ ሳይለወጡ በሱታፌና በምሳሌ በግብር ሌላ ስም መቀበል። ቃል ሥጋ ኮነ። ውእቱ አምላክ ዘኮነ ሰብአ ወውእቱ ሰብእ ዘኮነ አምላከ በተዋሕዶተ መለኮት ምስለ ትስብእት። ኮንኪ ዐጽቀ ንጹሐ። እግዚኦ ጸወነ ኮንከነ ለትውልደ ትውልድ። አነ እከውና ጥቅመ እሳት ዐውዳ ፡-(ዮሐ፩ ፡-፲፬። ሃይ ፡-አበ። ውዳ ማር፫። መዝ ፡-፹፬። ዘካ፪ ፡-፭)። ወይም በጭራሽ ወደ ሌላ ባሕርይ መለወጥ ሌላ ዐይነት መኾን፤ ተለውጦና ተገልብጦ በሌላ ባሕርይ ስም መጠራት፤ ያው ግን ጭገሬታውና ምልክቱ አሠሩ ቢጋሩ ህላዌው ሳይጠፋ ሳይታጣ። ነጸረት ብእሲተ ሎጥ ድኅሬሃ ወኮነት ሐውልተ ጼው። ወኮነት በትር አርዌ ምድር። ወኮነ ኵሉ ማይ ዘውስተ ተከዚ ደመ። ጥዒሞ አንከረ ሊቀ ምርፋቅ ውእተ ማየ ዘኮነ ወይነ ፡-(ዘፍ፲፱ ፡-፳፮። ዘፀ፬ ፡-፫። ፯ ፡-፳። ዮሐ፪ ፡-፱)። ቀጥ ብሎ መቆም መገተር፤ ባሉበት መጥናት አለመናወጥ የምሰሶ የዐምድ የሐውልት፤ ክዋኒትን እይ፤ ምስክሩ ርሱ ነው። በመቆም አንጻር መቀመጥንም ያሳያል፤ ና ከዚህ ኹን እንዲሉ ተቀመጥ ሲሉ።
ከዊው ፡-(ከወ፤ ከወወ ይከውው ይክውው) መቅለል፤ መፍጠን መቀልጠፍ ያካኼድ ያነጋገር። መዋሸት መቅጠፍ፤ መለፍለፍ። ኀወወን እይ፤ የዚህ ዘር ነው።
ከዋላ ፡-ኋላ ዠርባ፤ ድኅር ዘባን። ነዐቅብ ፍጽመ ወከዋላ። ዳዊትሰ ወሰብኡ የሐውሩ ከዋላ። መንገለ ከዋላ ሐመር ፡-(ነሐ፬ ፡-፲፮። ፩ነገ ፡-፳፱ ፡-፪። ማር፬ ፡-፴፰)።
ከዋኒ ፡-(ኒት ንያን ያት) የኾነ የሚኾን፤ ዃኝ፤ ተሰጭ ተለዋጭ።
ከዋኒም ፡-(ዕብ አዳርኮኒም) የገንዘብ ስም፤ ፋርሳዊ ገንዘብ። አዳርኮኒም የብዙ ነው። ላንድ ሲኾን አዳርኮን አዳርክሞን ይላል፤ ባለብሉዮች ግን ሥንቅ ልብሰ ተክህኖ ይሉታል ፡-(ዕዝ፰ ፡-፳፯)።
ከዋክብተ ናግራን ፡-ሰማዕታት ፡-(ስንክ ፡-ኅዳ፳፮)።
ከዋክብት ፡-እለ ጽኑዓን፤ የማይኼዱ፤ የማይናወጡ ፡-(አቡሻ ፡-፴፯)።
ከዋክብት ጽልሙታን ፡-ስሑታን፤ ስተው የሚያስቱ፤ ደቂቀ ሴት ፡-(ይሁ ፡-፲፫)።
ከዋው ፡-(ዋዋን ት) ቀላል ፈጣን፤ ቀልጣፋ። እበን ከዋዋት። አእጋሪሁ ከዋዋት ፡-(ኢያ፬ ፡-፫። ስንክ ፡-ጥቅ፲፭)።
ከውሎ ሎት ፡-(ከወለ ይኬውል ይከውል) መከወል፤ ወደ ኋላ ማድረግ፤ የኋሊት ማስኼድ ማስፈግፈግ፤ ወይም በኋላ ማስከተል፤ አስከታይ መኾን።
ከውስ ፡-(ዕብ ኮስ። ሱር ካሳ። ዐረ ካስ) ጽዋ ዋንጫ፤ የመጠጥ መሣሪያ፤ መቅጃ መጠጫ፤ ማደያ መስጫ። ኮሶ፤ የደጋ ዛፍ፤ የሹጥ መድኀኒት፤ ፍሬውን ደቍሶ በጥብጦ ሲጠጡት ሆድ እያካወሰ የሚያስቀምጥ። ድፍርስ ብጥብጥ መራራ መጠጥ ማለት ነው፤ ሹጡም ኮሶ የሚያስጠጣ ስለ ኾነ ኮሶ ይባላል፤ ኮሶ ታየኝ እንዲሉ።
ከውር ፡-(ዕብ ኩር። ሱር ኩራ። ዐረ ከውር) በቁሙ፤ አጐዶ የማዕደናት ኹሉ መጥበሻ፤ ማቅለጫ ማፍሰሻ። በከመ ይትፈተን በከውር ወርቅ ወብሩር። ማእከለ ከውር። ይትዌለጥ ወርቅ ውስተ ከውር ኀበ ብሩር ፡-(ምሳ፲፯ ፡-፫። ሕዝ፳፪ ፡-፳። ያዕ ፡-ዘእል)።
(ጥ) ከውኖ ፡-(ከወነ ይኬውን ይከውን። ዕብ ካዌን) መከወን፤ ማከናወን መፈጸም፤ ማበጀት ማዘጋጀት፤ ማሳመር ማስጌጥ፤ ማቅናት ማሳካት።
ከዪን ኖት ፡-(ኬነ፤ ከየነ ይከይን ይኪን) መሾል መስላት ሹል ስል መኾን፤ ለመውጋት ለመቍረጥ መዘጋጀት፤ የብረት። ብልኅ መኾን፤ ሥራ ማወቅ በሥራ መራቀቅ፤ ሐዲስ ነገር መፍጠር፤ መኪና ማውጣት። በልኀንና ጠበን ተመልከት፤ የዚህ ጎሮች ናቸው። መጽሐፍ ግን በኬነ ፈንታ ኬነወ፤ ተኬነወ ይላል፤ ተ ከንቱ ነው። ተኬነዉ ኵልክሙ እለ ትስሕቱ። በተኬንዎ ምግባር። ዘዐቢይ በተኬንዎቱ ወኀያል በምግባሩ። ልብስ ብሩህ ዘኢተኬነዎ እደ ፅጓለ መሕያው ፡-(ኢሳ፵፮ ፡-፭። ጥበ፲፫ ፡-፲። ቅዳ)።
ከዪድ ዶት ፡-(ኬደ ይከይድ ይኪድ። ረገፀ ሄደ) መኼድ፤ መርገጥ መዳጥ መደፍጠጥ፤ መጠቅጠቅ ማጥቃት፤ በእግር በጫማ በርግጫ መምታት፤ ያውድማ የነዶ የወይን የጭቃ የልብስ የሰው። ይከይድዋ ለሞአብ ከመ ዘይከይዱ እክለ በመንኰራኵር። ኬዱኒ ከመ ጽቡር። ነዳይ እመ ወድቀ ይከይድዎ ቢጹ። ወኬዱኒ ፀርየ። ከመ ትኪዶሙ ፡-(ኢሳ፳፭ ፡-፲። ኢዮ፴ ፡-፲፱። ሢራ፲፫ ፡-፳፩። መዝ ፡-፶፭። ኩፋ ፡-፴፩)።
፡-መሄድ መራመድ፤ እግሮችን እያፈራረቁ ማንሣትና መጣል መንቀልና መትከል፤ ምስጢሩ ከዚያው ከመርገጥ አይወጣም፤ ሀይድን እይ። ፍኖተ ረሲዓን ኢትኪድ። ለከይደ አሠሮሙ። ወኀበኒ ኬደ ይደምፅ እግሩ በቃለ ፀዓዕ ፡-(ምሳ፬ ፡-፲፬። ኩፋ ፡-፳፩። ሢራ፴፭ ፡-፱)። አንዳንድ መጣፍ በኬደ ፈንታ እንዳማርኛው አኬደ ይላል፤ አያሰኝም። ኢያከይዱ ወይነ ውስተ ምክያድ። ያከይዱ እክለ ወወይነ። ተንሥኢ አኪዲዮሙ። ላሕም ዘያከይድ ፡-(ኢሳ፲፮ ፡-፲። ነሐ፲፫ ፡-፲፭። ሚክ፬ ፡-፲፫። ዘዳ፳፭ ፡-፬)።
ከያኒ ኬንያ ፡-(ያት) ብልኅ ጠቢብ፤ ብልኀተኛ ጥበበኛ፤ ሥራ ዐዋቂ አንጥረኛ ባለመኪና፤ ፈጣሪ ሐኪም ወጌሻ፤ መሐንድዝ ፈላስፋ በፍጥረት በሥራ የሚራቀቅ፤ ጥሩ ዕውቀት ያለው ፡-(ማሕ፯ ፡-፪። ዕብ፲፩ ፡-፲። ጥበ፯ ፡-፳፩)። አንተ ኬንያሁ ለኵሉ ፍጥረት። ኬንያ ፍጥረትነ። ኬንያት ፡-(ድጓ። ቅዳ። ስንክ ፡-ኅዳ፲፮)።
ከያዲ ፡-(ዲት ድያን ያት) የሚረግጥ ረጋጭ፤ አጥቂ ጠቅጣቂ።
ከይሲ ፡-(ብ አክ(ካ) ይስት፤ አኪስት) እባብ፤ ዘንዶ። ከይሲ ተጠብለለ ውስተ ክሣዱ። ስነነ አክይስት ዘቦቱ ሕምዝ። ወሀሎ ከይሲ ዐቢይ ዘያመልክዎ ሰብአ ባቢሎን። ወትከይድ አንበሳ ወከይሴ። ወናሁ ክልኤቱ አክይስት ዐበይት ፡-(ስንክ ፡-ሐም፳፬። ጥበ፲፮ ፡- ፲። ዳን፲፫ ፡-፳፪። መዝ ፡-፺። አስቴ፩ ፡-፭)።
፡-ዐዞ ደራጎን፤ የባሕር ተመን። ሰበርከ ርእሰ ከይሲ በውስተ ማይ። ይቀትሎ ለከይሲ ዘውስተ ባሕር። አክይስትኒ ወኵሉ ቀላያት ፡-(መዝ ፡-፸፫። ኢሳ፳፯ ፡-፩። መዝ ፡-፻፵፰)።
፡-ዐንበሪ ሌዋታን፤ ዲያብሎስ ሰይጣን። ከይሲ ዘፈጠርከ ይሣለቅ ላዕሌሆሙ በምክረ ከይሲ ርጉም ፡-(መዝ ፡-፻፫። ቅዳ ፡-አፈ)። ስነነ አናብስት በማለት ፈንታ ግርማ አክይስት ይላል፤ የመላሽ ስሕተት ነው። ብሄሞትንና ሌዋታንን እይ ፡-(ኢዮ፬ ፡-፲)።
ከደዋ ፡-(ዕብ ካድኮድ) ዕንቍ ፥ የዕንቍ ስም፤ ሕብሩ የሮማን ዐይነት እንደ ቦረቦጭ ያለ፤ የሚፈልቅ የሚብጨለጭ። ሠለስቱ አዕናቍ ዘወርቅ ወብሩር ወከደዋ። ወርቅ ወከደዋ ወብሩር ወካልኣን አዕናቍ ሀለዉ ይትረከቡ እስከ ዮም ፡-(ታሪ ፡-አኵ ፡-ገ፺፭)።
ከዲን ኖት ፡-(ከደነ ይከድን ይክድን። ዕብ ካዳን፤ አሰረ አቈራኘ የፈረስ የሠረገላ) መክደን መግጠም፤ ማልበስ መሸፈን፤ መሰወር መጋረድ፤ እንዳይታይ ማድረግ። አምጽኡ እብነ ወከደኑ ዲበ አፈ ግብ። ከደነት ኀፍረታ በቈጽል። ፈጺሞሙ ከዲነ ዘቅድሳት። ዘይከድን አበሳሁ። ይከድኑ ገጾሙ ፡-(ዳን፮ ፡-፲፯። ኩፋ ፡-፫። ዘኍ፬ ፡-፲፰። ምሳ፳፰ ፡-፲፫። ኢሳ፮ ፡-፪)።
ከዳኒ ፡-(ከደነ ይከድን ይክድን። ዕብ ካዳን፤ አሰረ አቈራኘ የፈረስ የሠረገላ) መክደን መግጠም፤ ማልበስ መሸፈን፤ መሰወር መጋረድ፤ እንዳይታይ ማድረግ። አምጽኡ እብነ ወከደኑ ዲበ አፈ ግብ። ከደነት ኀፍረታ በቈጽል። ፈጺሞሙ ከዲነ ዘቅድሳት። ዘይከድን አበሳሁ። ይከድኑ ገጾሙ ፡-(ዳን፮ ፡-፲፯። ኩፋ ፡-፫። ዘኍ፬ ፡-፲፰። ምሳ፳፰ ፡-፲፫። ኢሳ፮ ፡-፪)።
ከፈረ ፡-(ዕብ ካፋር። ዐረ ከፈረ፤ ቀፈረ) ከደነ አለዐሰ፤ ካደ ከዳ እምነቱን ተወ አፈረሰ። ካፍር እንዲል ፥ ከሓዲ ሲል ፡-(እስላም)። ራራ፤ ይቅር አለ ተወ፤ ኀጢአትን ማረ። ሰረየንና ሠሀለን ኀደገን ተመልከት። ኔኪፉርን እይ።
ከፈር ፡-(ብ አክፋር። ዐረ ከፍር) መቃብር፤ ሞላላ ጕድጓድ ወይም የምድር ቤት የሬሳ መክተቻ። እለ ተከድኑ ታሕተ ከፈር ፡-(ቅዳ ፡-ግሩ)።
፡-ቅርጫት መሶብ፤ ላዳን እንቅብ፤ ባላገሮች ሠርተውና ሰፍተው ለከተማ ሰው የሚሼጡት። ወአንበረ ውእተ ሥጋ ውስተ ከፈር። ከመ ያንብርዋ ታሕተ ከፈር። እሬኢ ሠለስተ አክፋረ ዲበ ርእስየ ፡-(መሳ፮ ፡-፲፱። ማቴ፭ ፡-፲፭። ዘፍ፵ ፡-፲፮–፲፰)።
ከፈተ ፡-(ዐረ) በቁሙ ፥ ገለጠ፤ አስጠጋ፤ ቀደመ፤ ወገነ።
ከፈን [1]፡-በቁሙ፤ ልብሰ መግነዝ፤ የሬሳ መጐናጠፊያ ፥ የመቃብር ሸማ። ፡-(ተረት) አለ በለኝ ቀለቤን፤ ሞተ በለኝ ከፈኔን። ከፈን ሳይገዙ ፥ ሬሳ አያጕዙ።
[2]፡-በቁሙ ልብስ፤–ከፈየ።
ከፈየ ፡-(ዐረ ከፈ) ከፈነ፤ አጐናጠፈ ጠቀለለ፤ ደፋ ጠመጠመ።
ከፈይ ፡-በቁሙ፤ ጠጕራም ለስላሳ መዳ ለምድ ቆብ ካባ ቀሚስ የሚኾን።
ከፉር ፡-(ዐረ ካፉር) በቁሙ፤ የብል መድኀነት፤ የጨውና የስኳር ዐይነት፤ ልብስንና ማእስን ከብል የሚያድን የሚጠብቅ። ለሌላም ለብዙ ነገር፤ ይልቁንም ለዕበጥና ለወለምታ ከዘይትና ከስቢርቶ ጋራ ይፈውሳል ፡-(ዮሴፍ)።
ከፊል ሎት ፡-(ከፈለ ይከፍል ይክፍል፤ ቀፈለ። ዕብ ክፋል፤ ቃፋል) ማክፈል፤ ማጠፍ መደረብ ፥ ኹለቱን ቀን አንድ አድርጎ መጦም፤ ጌታ ከተያዘበት እስከ ተነሣበት። መክፈል ፥ መከፋፈል ፥ መለየት፤ አንዱን ኹለት ወይም ብዙ ማድረግ ፥ መተንተን። አበሳኬ ከፊል ለክልኤ፤ እስመ አሐዱ ውእቱ ኢየሱስ ክርስቶስ። ይከፍልዋ ለመዓልት ኀበ ሠለስቱ መክፈልት። ከፈለ ሰራዊቶ አርባዕተ ክፍለ። ትከፍሎ ለዝንቱ ኀበ ስሳ ፡-(ቄር። ፍ ፡-ነ ፡-፲ ፡-፮። ዮሴፍ። አቡሻ)።
፡-ብድር ወረታ መመለስ፤ ከፍሎ መጥኖ መስጠቅ፤ ቈርሶ ማደል፤ ማውረስ። ወከፈሎ አብርሃም ዐሥራተ እምኵሉ። ወኵሉ በከመ ከፈሎ እግዚ በመስፈርተ ሃይማኖቱ። መኑ እምከፈለኒ ከመ እኩን። ርስትየ ዘከፈልዋ ለሕዝብየ ፡-(ዕብ፯ ፡-፪። ሮሜ፲፪ ፡-፫። አርጋ ፡-፩። ኤር፲፪ ፡-፲፬)።
ከፊእ ኦት ፡-(ከፍአ ይከፍእ ይክፋእ። ሱር ካፋእ፤ ገፋ ደፋ ገለበጠ፤ አስገደደ) መክፋት ፥ ክፋ መኾን፤ የጠባይ። አከየንና ብእሰን ሐሠመን እይ። መበላሸት፤ መፍዘዝ፤ የመልክ፤ የዐይን። ከፍአ አርኣያሃ። ዘከፍኦ ርእየቱ። ወእመ ደረስዎ ግንጵሊተ ይከፍእ ጸጋሁ ለምስጢር። አዕይንትየ ከፍኣ ለርእይ ፡-(አረጋ ፡-ድ፰። አፈ ፡-ተ፲፬። ተረ ፡-ቄር፫። ኩፋ ፡-፳፮)።
፡-መጥረስ መደነዝ ፥ መቸምቸም፤ የስለት የሹል። ይክፋእ ስነነ አክይስት። እስመ ከፍኡ እሉ አቅርንት። ወይክፋእ ሦኩ ለዲያብሎስ ፡-(ግንዘ። ዘካ፩ ፡-፴፩። ተረ ፡-ቄር፲፭)። አንዳንድ መጣፍ በከፍአ ፈንታ ፡-(ተከፍአ) ወይትክፋእ ሦኩ ይላል፤ የጣፊ ስሕተት ነው።
ከፋሊ ፡-(ሊት ልያን ያት) የሚያከፍል፤ አክፉይ አክፍለተኛ ፥ ያ፶፭ ሰዓት ጦመኛ። የሚከፍል የሚያድል፤ ከፋይ ዐዳይ። መኑ ሤመኒ ከፋሌ ወመኰንን። ኮነ ከፋሌ ሕዝብ። ከፋሌ ንዋይ ፡-(ሉቃ፲፪ ፡-፲፬። ገድ ፡-ኪሮ። ስንክ ፡-ሚያ፳፰)።
ከፋቲ ፡-(ቲት ትያን ያት) የሚከፍት ከፋች፤ የሚገልጥ ገላጭ።
ከፍዐ ፡-ከፋ ባሰ፤–ከፍአ።
ኵሑል ፡-(ላን ላት ሕልት) የተኳለ፤ የተቀባ፤ ተኵሳም ምልክታም።
ኵሒል ሎት ፡-(ኰሐለ ይኵሕል ይኵሐል። ዕብ ካሐል። ሱር ክሓል። ዐረ ከሐለ) መኳል ማስነካት፤ ዐይንን በኵል ዶቄት በመድኀኒት መቅባት፤ ለጌጥና ለፈውስ። በእብነ ፈውስ ኵሐሉኒ ዐይነ። አንተሰ ኵሐሎ ዝኩ ሐሞተ ውስተ አዕይንቲሁ። ለዘተወልደ ዕዉር አሕየዎ ክርስቶስ ኵሒሎ አዕይንቲሁ ጽቡረ ፡-(ስንክ ፡-ታኅ፳፬። ጦቢ፲፩ ፡-፯። ሲኖዶ)።
፡-መተኰስ አመሳቅሎ መጥበስ፤ የሌባን ግንባር በጋለ ብረት ማመልከት፤ ለከብትም ይኾናል። እመ ቦ ብእሲ ዘይበውእ ውስተ ምሥዋዕ መዓልተ አው ሌሊተ ወይነሥእ እምውስቴታ ምንተኒ ይኵሐልዎ በኀጺን ርሱን። ወተአዘዙ መገብት አመ ሆሳዕና ተዐርቀ ጽልመተ ይኵሐልዎ ለፀሓይ ዘ(ሠ) ሰረቀ ፡-(ፍ ፡-ነ ፡-፵፱። ቅኔ)።
ኵሒስ ሶት ፡-(ኵሕሰ ይኵሕስ ይኵሐስ። ዕብ ካሐሽ) መክሳት መቅጠን፤ ማነስ መኰሰስ ከሻዋ መኾን፤ የገላ። ማቅበር መለገም፤ ሳይሽር የሻረ መምሰል፤ ወይም መስፋት መግነን፤ የቍስል። ኵሕሰ ጸልዕኪ። እምቅድመ ይጺኡ ወይኵሐሱ ቍስላተ ነፍስየ ፡-(ናሖ፫ ፡-፲፱። አረጋ ፡-ድ፴፮)።
ኵሕሊ ፡-(ዐረብ) ኵሕላዊ፤ ኵልማ የኵል ዐይነት፤ ጥቍረቱ ኵል የሚመስል።
ኵሕል ፡-(ላት) በቁሙ ኵል፤ ጥቍር ሰማያዊ የቀለም ደንጊያ፤ ተደቍሶ ላይን የሚቀባ የሚኳል፤ ጌጥነት ከመድኀኒትነት ስላለው በኹለት ወገን የሚፈለግ። አዕይንት እለ ስርግዋን በኵሕል። ብንተ አዕይንቲሁ ከመ ኵሕል ወጸሊም ጽሕሙ። ተኵሕልኪ ኵሕለ ፡-(ግንዘ። ስንክ ፡-ሐም፰። ኤር፬ ፡-፴)።
ኵሕስ ፡-ክሳት ኰሳስነት፤ የቍስል ስፋት። ኀፍረተ ብእሲት።
ኵለንታ [1]፡-ኹለንተና ፥ ኹለመና፤ መላው ጠቅላላው ፥ ዙሪያ ገባው ፥ አራቱ ማእዝን፤ የገላ የቦታ። እንተ ኵለንታሆሙ ምሉኣነ አዕይንት። ኵለንታኪ ሠናይት። ኵለንታየ ተመስወ። ወኵለንታሁ በወርቅ ወበዕንቍ። ተቋመ ማኅቶት ዘኵለንታሃ ወርቅ። ኵለንታሃ ለዛቲ ምድር ፡-(ራእ፬ ፡-፰። ማሕ፬ ፡-፯። ሔኖ፰ ፡-፫። አስቴ ፡-፭። ዘካ፬ ፡-፪። ዘፍ፲፫ ፡-፲፭)።
[2]:-ኹለንተና፤ ከልሎ ከለለ፤ ኵል ኵሉ።
ኵለንታዊ ፡-(ዊት) የውስጥ የአፍኣ ፥ የነፍስ የሥጋ ፥ ፍጹም ሰብእና ፥ ፍጹም ልቡና ፥ ፍጹም ኅሊና። ኀደገት ግብራቲሁ ለዝ ዓለም ወመጽአት ምስለ ኵለንታዊታ ለኀበ ዓለም ካልእ፤ ልብ ሳይቀራት ፡-(ፊልክ ፡-፫)።
ኵሉ ፡-ኹሉ፤–ከልሎ ከለለ።
፡-(ኵላ ኵሎሙ ኵሎን) ኹሉ መላው፤ ፍጹሙ ጠቅላላው፤ አንድ ሳይቀር። ኵሉ ዓለም፤ ኵላ ምድር፤ ኵሎሙ ዕደው፤ ኵሎን አንስት። ኵሉ ቀላያት፤ ኵሉ ዕፀው፤ ኵሉ አሕዛብ። ሉ የሩቅ ዐጸፋ ስለ ኾነ የኵሉ ርባታ ከሩቆች በቀር ለቅርቦች ሰራዊት አይስማማም፤ በገቢርም ጊዜ ከሉ በቀር ላና ሎ አይለወጡም። ዳግመኛም፤ ኵሉ ፥ ላ ፥ ሎሙ ፥ ሎን በማለት ፈንታ፤ ኵልሁ ልሃ ፥ ልሆሙ ሆን እያሉ ፥ ኵልን ብቻ እንደ አሐድ እስካሥር ማርባት ይቻላል። አሐዱና ኵሉ በምስጢር አንድ ስለ ኾኑ፤ አሐዱ አሐዱ በማለት ፈንታ፤ ኵሉ ኵሉ፤ ወይም እያቀናጀ ኵሉ አሐዱ ይላል፤ አንድ እንኳ ሳይቀር ማለት ነው ፡-(ስንክ ፡-ሐም፳፯)። ኵሉ ከተጸውዖ ስም በቀር ውስጠ ብዙነት ላለው ለብትን ሰዋስው ኹሉ ቅጽልና ዐጸፋ በቂ ይኾናል፤ ካንድ በላይ ላለ ላንዱም ሳይቀር ከኹልት እስከ ምእልፊት በተከፍሎም ያለተከፍሎም ለብዙም ለጥቂትም ይነገራል። ኵሉ ሕዝብ፤ ኵሉ ፍጥረት፤ ኵሉ ነፍስ ይሴብሖ፤ ቅጽል። ኵልክሙ ተዐልዉኒ፤ እመሂ ኵሎሙ ዐለዉከ፤ ወኵሎሙ ሰማዕተ ኮኑ፤ ዐጸፋ። ኵሉ ዐረየ፤ እግዚአ ኵሉ፤ ወኵሉ ከመ ልብስ ይበሊ፤ በቂ። ኵሉ ላንድ መነገሩ ባንድነቱ ውስጥ ብዙ ክፍላት ብዙ ሕዋሳት ስላሉ ነው፤ ኵሉ ሕንጻ፤ ኵሉ መሌሊት፤ ኵሉ ሥጋሁ፤ የመሰለው ኹሉ። የግእዝ መጽሐፍ ግን በመላሽ ስሕተት፤ ዘላዕሌሁ ኀደረ ኵሉ መለኮቱ በሥጋ ሰብእ ይላል ፡-(ቆላ፪ ፡-፱)። የጽርኡ አብነት፤ ከጽርእም የተቀዳው ኹሉ፤ እስመ ኵሉ ምልአ መለኮት ኀደረ ቦቱ በሥጋሁ ይላል እንጂ፤ ኵሉ መለኮቱ አይልም። ኵሉ በማንም ቋንቋ ውስጠ ብዙነት ለሌለውና መከፈል ለማይስማማው ላንድ ብቻ አይነገርም፤ ምልአ መለኮት ያለውም ፍጹም ጸጋ ነው። ይህም ንባብ ምሉአ ጸጋ ወጽድቅ ካለው ጋራ እንጂ፤ ቃል ሥጋ ኮነ ወኀደረ ላዕሌነ ካለው ጋራ አይገጥምም፤ በጣም ሩቅ ነው ፡-(ዮሐ፩ ፡-፲፬)።ከለሜዳ -ኬልቄዶን
ኵሊት ፡-(ብ ኵልያት። ዕብ ኪልያ። ሱር ኩሌይታ። ዐረ ኩልየት) በቁሙ፤ ኵላሊት የሆድ ዕቃ ንዋየ ውስጥ ከጕበትና ከጣፊያ በታች በግራና በቀኝ በ፪ ወገን የሚገኝ፤ ክብ እንክብል የባሕርይ ሚዛን፤ እንደ ቍላ ፍሬ ኹለትነትና ትክክልነት ያለው። የፍትወት ምንጭ የፈቃደ ሥጋ መነሻ። ወንድን በሴት ላይ የሚያሶግሽ የሚያቅበጠብጥ፤ ወገብ የሚንጥ የሚያናውጥ ርሱ ነው ይባላል። ክልኤ ኵልያቲሁ ወሥብሐ ኵሊቱ። ረገዘኒ ኵልያትየ ፡-(ዘፀ፳፬ ፡-፲፫ ፡-፳፪። ኢዮ፲፮ ፡-፲፫)።
፡-ዕውቀት ሐሳብ፤ ረቂቅ ምክር ውሳጣዊ ነገር፤ ኵላሊት የሚያጤሰው፤ ልብ የሚያመላልሰው፤ ናላ የሚወርሰው፤ እነዚህም ፫ቱ ባንድ ሚዛን ይመሰላሉ። ዘይፈትን ልበ ወኵልያተ። ርሑቅ አንተ እምነ ኵልያቲሆሙ። ገሠጻኒ ኵልያትየ። ይትሀወካ ኵልያቲሁ እምዛቲ ቃል ፡-(ኤር፲፩ ፡-፳። ፲፪ ፡-፪። መዝ ፡-፲፭። ሔኖ፷፰ ፡-፫)።
ኵላ ፡-(ጽር ኮሊ) ፤ ቀለም
፤
መጣብቅ ሙጫ ፤ ለሚታነጥ ዕንጨት መልክና ውበት አንድነት የሚሰጥ። ወያስተጣግዖ በኵላ (ኢሳ፵፬ ፡ ፲፫)።
ኵላዊ ፡-የኹሉ የመላው ፡-(ፊልክ ፡-፻፴፬)።
ኵል ፡-(ዕብ ኮል። ሱር ካል። ዐረ ኩል) ኹል፤ ፡-(ኹል ጊዜ፤ ኹል ቀን)። ምሉእ ፍጹም ነገር ደምላላ ጠቅላላ ውስጠ ብዙ፤ ባንድነት የቆመ የተወሰነ ሥራ ነገር ቍጥር ማኅበር፤ አንድ ያልቀረው ያልጐደለው ድምር፤ ፍጥረት ሕዋሳት እንደ ማለት። ኵልና ኵሉ አሐድ አሐዱ፤ ዐሠርት ዐሠርቱ እንደ ማለት ናቸው፤ ርባታቸውም እንዲህ ነው፤ ኵል ለስድስቱ ቅርቦች፤ ኵሉ ላራቱ ሩቆች ይነገራል። ኵልዮ ከ ኪ፤ ኵልነ ክሙ ክን። ኵሉ ላ ሎሙ ሎን። አብርሃም አበ ኵልነ። ኵልክሙ አሕዛብ ፡-(ሮሜ፬ ፡-፲፮። መዝ ፡-፵፮)። በገቢርም ጊዜ ኵልየ ካለው በቀር ባምስቱ ኹሉ ልን ለ ይወርሰዋል። ዕቀብ ኵልነ። ከመ ትቅትል ኵልነ ፡-(ሊጦም። ዘፀ፲፮ ፡-፫)።
ኵልሄ ኵለሄ ፡-(ኵል ሄ) ኹል ጊዜ፤ ኹለግዜ፤ ኹለዬ፤ ዘወትር። ቦታ ኹሉ፤ አገር ኹሉ፤ አራቱ ማእዝን፤ ዐውድ ዘውር። ል ከተገብሮ ለ ከገቢር ይሰማማል። ምሉእ እምኔሁ ኵልሄ። አዐቅበከ በኵልሄ። አንሶሰወ ውስተ ኵልሄ። መሐወኒ እንተ ኵልሄ ፡-(አዋል። ኩፋ ፡-፳፯። ስንክ ፡-ግን፳፮። ኢዮ፲፱ ፡-፲)። ተሐውር ኵለሄ ኀበ ፈነውኩከ። ኀበ ታንሶሱ ኵለሄ። መላእክት ወሰብእ ዘይነብሩ ኵለሄ ፡-(ኤር፩ ፡-፯። ስንክ ፡-ሐም፳፮። ደራሲ)። ብዙው መጽሐፍ ገቢር ተገበሮ ሳይለይ፤ በኵለሄ ፥ እንተ ኵለሄ ፥ ውስተ ኵለሄ ይላል፤ አንዳንድ ጊዜም ፥ ላዕለ ምድር ኵልሄ እያለ አለቦታም ገብቶ ይገኛል፤ የሄን አፈታት ተመልከት።
ኵስሕ ፡-በቁሙ፤ ኵስ ዐርነ ምድር ፥ ፋንድያ ከሆድ የሚወጣ የምግብ ሐሠር። ከመ ይብልዑ ኵስሖሙ። ኵስሐ ርግብ። ኵስሐ አፍራስ ወእንስሳ ፡-(ኢሳ፮ ፡-፲፪። ፬ነገ ፡-፮ ፡-፳፭። ዮሴፍ)።
ኵስቱር ፡-(ራን ራት ትርት) የተጠረገ ጥርግ ጥሩ ፡-(ሉቃ፲፩ ፡-፳፭)።
ኵስታር ፡-(ራት) ጥራጊ፤ ጕድፍ። የጧፍ ትርኳሽ፤ ኵስታሪ።
ኵስኵስ ፡-(ትግ ሐባ) ኰሸኰሽ፤ ያፍንጫ ዐጥንት፤ ሹሉ እንደ ጡት ያለው።
ኵስኵስት ፡-(ብ ኰሳኵሳት) በቁሙ፤ ጡታም መንቀል ፥ ገንቦ እንስራ ማድጋ፤ ዝንጕርጕርነት ያለው። ሲያዩት ደስ እንዲያሰኝ ቀለም እየቀቡ ፥ ሳይደርቅም በርጥቡ ሐረግ እየጣሉ ያስጌጡታልና፤ ኵስኵስት ያሰኘው ሕብሩ ነው። ቀና ከ ተወራራሾች ስለ ኾኑ በቈ ፈንታ ኰ ይላል ፥ የጣፊ ስሕተት ነው፤ ቈሳቍስን እይ።
ኵስየት ፡-መለየት መክፈል፤ መከፈል። ወኵስየት ዘቅዱሳት መጻሕፍት ፡-(ቄር ፡-ጰላ)።
ኵሩዕ ፡-(ዓን ዓት ርዕት) የኰራ ኵሩ፤ ትቢተኛ። በቡጢ በኵርኵም የተመታ። ቅንወ አእዳው ወእግር ስቁለ አይሁድ ክርስቶስ፤ ርጉዘ ገቦ ወኵሩዐ ርእስ ፡-(ደራሲ)።
ኵርያቍ ኪርያቅ ፡-(ቅብጥ ኺያክ) ስመ ወርኅ ራብዕ፤ ታኅሣሥ። ኪያህክን እይ፤ ከዚህ ጋራ አንድ ነው። ተወልደ በወርኀ ጽርእ ኵርያቍ። በወርኀ ፍሥሓ ኵርያቍ ፡-(ተረ ፡-ቄር፳፭። ደራሲ)።
ኵራፒታ ፡-(ጽር ግራፊዲ) መጣፊያ ብርዕ ፥ ወይም ቀለም መቅቢያ በጫፉ ጭራ ጭረት ያለው። ካርታ ሰሌዳ ብለውም የሚፈቱ አሉ፤ ዕብራይስጡ ግን ሻሻር ይላል፤ ቀይ ቀለም ማለት ነው። አርኣያ ከለዳውያን ሥዑላን በኵራፒታ ፡-(ሕዝ፳፫ ፡-፲፬)።
ኵርህ ፡-ግድ ግዴታ፤ ፈቃድና ዕሺታ የሌለበት ፡-(፩ጴጥ ፡-፭ ፡-፰። ፈ ፡-መ ፡-፩ ፡-፫)። ሐመ በፈቃዱ ወአኮ በኵርህ ፡-(አፈ ፡-ድ፴፫)።
ኵርበት ፡-(ታት) ወግር ኰረብታ፤ ጕባ ጐባታ፤ ተሬ ቍሊልታ፤ አዳጋ ከፍተኛ ቦታ ፡-(ትግሪኛ ፡-ሉቃ፳፫ ፡-፴)።
፡-ንዋየ ጸሎት፤ ጠፍር ቈርበት፤ አይሁድ በጸሎት ጊዜ ከዚያው ከምኵራቡ በጃቸውና በራሳቸው የሚያስሩት የሚጠመጥሙት ምኵራባዊና ቈርበታዊ ልብስ፤ ባገራችንም ፈላሾች በጠይቦች ገዳም ይገኛል።
፡-ታናሽ የጸሎት መጽሐፍ፤ እንደ ልፋፈ ጽድቅ ያለ ኹሉ። ይሰፍሑ ኵርበታቲሆሙ ወያነውኁ አዝፋሪሆሙ ፡-(ማቴ፳፫ ፡-፭)።
፡-የጠንቋዮች ክታብ ጨርጨቤ ፥ ዐይነ ጥላ ፥ መፍትሔ ሥራይ ፥ መንድግ መስተፋቅር ግርማ ፥ ሞገስ መግረሬ ፀር፤ ሌላም ይህን የመሰለ በቈርበት ተሰፍቶ ባንገትና በክንድ የሚያዝ። ቦ እምኔሆሙ ገባርያነ ኵርበት። ኵርበታተ ኢታንብር ውስተ ሥጋከ። ዘየአስር ላዕሌሁ ኵርበታተ። ገባርያንነ ኵርበታት ፡-(ገድ ፡-ተክ። ሲኖዶ። ፍ ፡-ነ ፡-፲፩ ፡-፵፮)።
ኵርናዕ ፡-ክርን፤–ከሪዕ ከርዐ።
ኵርዐት ፡-በቁሙ፤ መኵራት መታበይ መቈነን፤ ኵራት ፥ ትዕቢት። ኵርዐቶሙ ለደቂቀ ዓሞን ፡-(ሶፎ፪ ፡-፰)።
፡-መኰራት፤ ራስን መመታት። ፡-(ግጥም) የየሱስ ክርስቶስ ኵርዐቱ ባባቱ ነወይ በናቱ፤ በናቱ ነው እንጂ ካብነቱ በቀር ምን አለው ባባቱ። ዘመልታሕትከ ጽፍዐት ወዘርእስከ ኵርዐት ፡-(ስንክ ፡-ታኅ፳፯)።
ኵርጓኔ ፡-ዙሪያ ፥ ክበብ፤ ሸንጎ አደባባይ። በኵርጓኔ ትዕይንት። አዘዝዎ ይንበር በዴዴ ቅጽር ወበኵርጓኔ ንጉሥ። ሶበ ትበውእ ውስተ ኵርጓኔ ፡-(ዘፀ፲፮ ፡-፲፫። አፈ ፡-ተ፲፫። ፲፭)።
፡-ጉባኤ፤ ማኅበር ሸንጎኛ። አሐዱ እምውስተ ኵርጓኔሁ። ሰባኬ ሃይማኖት ውስተ ኵርጓኔ ፡-(አፈ ፡-ተ፬። ስንክ ፡-ጥቅ፳፭።ደራሲ)።
ኩትፈት ፡-(ታት) ማሰር፤ መታሰር ፥ አስተሳሰር፤ እስራት። ኩትፈተ እደዊሁ ክልኤቱ። ውስተ ኀሳር ዘኩትፈታተ መስቀል ፡-(ፈ ፡-መ ፡-፴፩ ፡-፭። ፊልክ)።
ኩነት ፡-(ታት) መኾን፤ አኳዃን ኹነታ፤ አናዎር። እግዝእ የአምር ኅሊና ሰበእ እምቅድመ ኩነታ። ኩነተ ብሔር ፡-(አፈ ፡-ድ፫። ገድ ፡-ኪሮ)።
፡-ፍጥረት፤ ሥነ ፍጥረት፤ ለይኩን በማለት የተገኘ። ገባሬ ኵሉ ኩነታት ፡-(ያዕ ፡-ዘእል)።
፡-የአካል ህላዌ፤ ወይም ስም። ህላዌ፤ ወላዲነትና ተወላዲነት ሠራጺነት። ስም፤ ወላዲ ተወላዲ ሠራጺ፤ ወይም አብ ወልድ መንፈስ መባል ነው። እግዚ ዘይሤለስ በኩነታት፤ ዘውእቱ ሠለስቱ አካላቲሁ። ዘይሤለስ በአካላት ወበኩነታት ፡-(ያዕ ፡-ዘእል። ፍ ፡-ነ ፡-፩)።
ኵነኔ ፡-(ያት) ፍርድ፤ ቅጣት ፥ መቅሠፍት፤ ግዛት አገዛዝ፤ ሕግ ትእዛዝ፤ ሥልጣን መብት። ይኰንኑ ኵነኔ ጽድቅ። ወተመጠዋ ኵነኔሆን። ዐሥሩ ኵነኔያት ዐበይት ወፀዋጋት። እግዚኦ ኵነኔከ ሀቦ ለንጉሥ። ስምዑ ኵነኔሁ ወፍትሖ። ተውህበ ሊተ ኵነኔ ሰማይ ወምድር ፡-(ዘዳ፲፮ ፡-፲፰። ይሁ ፡-፯። ኩፋ ፡-፵፯። መዝ ፡-፸፩። ዘዳ፬ ፡-፩። ማቴ፳፰ ፡-፲፰)።
ኵኑን ፡-(ናን ናት ንንት) የተኰነነ፤ የተፈረደበት የተቀጣ። ኢኮነ ርቱዐ ሃይማኖቱ፤ አላ ኵኑን እምቅዱሳት መጻሕፍት። ኵኑን በፍልሐተ ቅጥራን። በእንተ ኵኑናን ሰማዕታቲከ ፡-(ቄር። ስንክ ፡-ጥር፳፯። አዋል)።
ኵናት ፡-ጦር ዘገር፤–ከየነ።
ኵናኔ ፡-መፍረድ ፥ መግዛት፤ መገዛት ፥ አገዛዝ አቀጣጥ።
ኵዒስ ሶት [1]፡-(ኵዕሰ፤ ኰዐሰ ይኵዕስ ይኵዐስ። ዕብ ካዐስ፤ ተቈጣ) ማኳስ ማኮብ፤ ወይም መኳስ ኳስ መኾን፤ ኳስ ማኸል፤ በኳስ መጫወት፤ ማጓን ማንጠር መልጋት።
[2]፡-ኵዒስ፤ ፡-(ጽር ኾይስ። ዕብ ባት) ታላቅ ገንቦ ፥ እንስራ ማድጋ የውሃ ዕቃ፤ ክብ እንክብል የኳስ ዐይነት። ያገምር አርብዓ በመስፈርተ ኵዒስ ፡-(፫ነገ ፡-፯ ፡-፴፰)።
ኵኢስ ፡-ታላቅ ገንቦ፤–ኵዒስ ኰዐሰ።
ኵዒት ቶት ፡-(ኰዐተ ይኵዕት ይኵዐት) መኳት መቈፈር፤ለመንቀል ለማፍለስ ለመናድ ለማፍረስ፤ ወይም ለማረድ ለማጐድጐድ ፥ ምሽግ ለማድረግ። ወመጽኡ ኅቡረ ወኰዐትዋ ለሀገር፤ ወከዐው ደሞሙ ከመ ማይ ለእለ ይነብሩ ውድቴታ። ፈረንጂ ለጕራዕ ምስለ ጐዳጕዲ ኰዐትካያ ቅድመ ትኩን መቃብርካ ፡-(መቃ ፡-ገ፲፬። ትግሪኛ ቅኔ)።
፡-መኰትኰት፤ ዐፈርና ፍግ ማስታቀፍ፤ የእክልና የተክል።
ኵዕሶ ፡-(ብ ኰዓስው) ኳስ፤ ንዋየ ተውኔት ከጨርቅ ወይም ከላስቲክ የሚሠራ። ወፈነወ ዳራ ለእስክንድር ኵዕሶ ወሰሊጠ ፡-(ዜና ፡-እስ)።
ኵዕንት [1]፡-የሚበላ ሥር፤–ኰዐተ።
[2]፡-ቍፋሮ፤ ኵትኳቶ። ችግር ሐዘን። ዘእንበለ ጻማ ወኵዕንት ፡-(አዋል)።
፡-በቁሙ፤ የላም ጡት ፥ ወይም ሌላ እንደ ቋርፍና እንደ ድንች ያለ የሚበላ ሥር። ወበጽሐ ውስተ ደብር ዘአልቦ ዘይነብር ውስቴቱ ዘእንበለ ኵዕንት ወቆቅሕ ወማይ ብዙኅ፤ ወሶቤሃ ኀለየ ወይቤ፤ ሶበ እወፍር ኀበ ኵዕንት ይፀራዕ ግብርየ ወአልብየ ረድእ ዘያአቱ ሊተ ፡-(ስንክ ፡-ታኅ፲፫)።
ኩፋሌ ፡-ዝኒ ከማሁ፤ መክፈል መግመስ፤ መለየት። ኩፋሌ መዋዕል። ኩፋሌ ኅብስት። ለይኩን ዝንቱ ኩፋሌ ማእከሌክሙ ፡-(ኩፋ ፡-፮። ቄድር ፡-ገ፳፰። አቡሻ ፡-፵፯)።
፡-መጽሐፍ ፥ የመጽሐፍ ስም፤ ከኹለቱ ብሔረ ኦሪት ከዘፍጥረትና ከዘፀአት የተከፈለ ፥ የዘመንን ክፍል የሚናገር በኢዮቤልዩ የሚቈጥር። መጽሐፈ ኩፋሌ ፡-(አብጥ ፡-፹፩)።
ኵፋር ኩፋር ፡-(ራት) (544) ልብሰ ስርየት፤ የኤጲስቆጶስ ልብስ ባለራዎት ካባ፤ ለሕዝቡም ለራሱም ፍጹም ስርየት በሚለምንበት በጸሎትና በቅዳሴ ጊዜ የሚለብሰው። ሰፍሐ ኵፋሮ ወነሥአ በእዴሁ እምእሳት፤ ወረሰዮ ውስቴቱ። አንበራ ለእሳት ውስተ ኵፋሩ። ለጳጳስ ወለዕጨጌ አሰርገዎሙ ኵፋረ ወዝናረ ወልብሰ ቀጠንት ፡-(ስንክ ፡-ጥቅ፲፪። መጋ፲፪። ታሪ ፡-ነገ ፡-ገ፴፬)። ዐፈረንና ማዕፈርትን እይ።
ኵፌት ፡-(ዐረ ኵፈት) ቆብ ጠርቡሽ ባለሐር ጐፍላ።
ኵፍ ኩፍ ፡-(ብ አክፋፍ። ዐረ ኁፍ) ታላቅ መጫሚያ፤ ጫማና ገንባሌ እግርን ከጫማ እስከ ጕልበት የሚያለብስ የሚከት የሚሸፍን። እስመ እሉ ኅጽዋን ኮኑ ያስተሣእንዎ ለንጉሥ ኩፈ፤ ወወደዩ ውስቴቱ አክይስተ ከመ ይንስክዎ ለንጉሥ፤ ወነሥአ ንጉሥ አክፋፈ ወረከበ ውስቴቶሙ አክይስተ ፡-(ዮሴፍ)።
»ኵሓ ፡-(ሓት) እፍታ አክታ፤ ትንፋሽ የሚያነድ የሚያበርድ፤ ወይም ልምላሜ፤ ርጥበት ርጥብነት። ስመ ዕፅ ሓያ አሓያ የሚባል፤ በወንዝ ዳር በውሃማ ቦታ የሚበቅል። ከመ ኵሓ ዘኀበ ሙሓዘ ማይ። ውስተ ኵሓቲሃ ፡-(ኢሳ፵፬ ፡-፬። መዝ ፡-፻፴፮)።
፡-ሓያ አሓያ፤–በኵሕ በኵሐ።
ኪሎ ፡-የሚዛን ስም፤ ፍጹም ልክ ባለሺሕ ክፍል። ኪሎ ግራም፤ ኪሎ መትር እንዲሉ ሺ ሲሉ።
ኪማ [1]፡-(ዕብ ኪማህ) የ፮ቱ ከዋክብት ተራ፤ ጾታቸውና ምግብናቸው አካኼዳቸው። ኪማ ወኬሌላ ፡-(ዓሞ፭ ፡-፰)።
[2]፡-፯ ከዋክብት፤–ከየመ።
ኪስ ፡-(ብ አክያስ። ዕብ ወዐረ፤ ኪስ። ሱር ኪሳ) በቁሙ፤ ታናሽ ከረጢት ቍናማት የገንዝብ መያዣ፤ ማሰሪያና መቈለፊያ ያለው በጄብ የሚያዝ። ፈትሐ ኪሶ ወአውፅአ ወርቀ ፡-(ዮሴፍ)። ጄብ፤ በኮት በካቡት በቀሚስ በሴደርያ ላይ በውስጥ በአፍኣ የሚሰፋ የልብስ ጓዳ። ሐስል፤ ሠቅ፤ ጆንያ ኬሻ። ጆን ህንዲ ነው።
ኪሩባዊ ፡-የኪሩብ፤ ወገን ነገድ። መልአክ ኪሩባዊ። ኪሩባውያን አፍራሱ። መንበር ኪሩባዊ ፡-(ስንክ ፡-መጋ፲፫። ኅዳ፰። ቅዳ)።
ኪሩቤን ል ም ፡-(ጽር ኼሩቢም። ዕብ ክሩቢም) መላእክት፤ ኪሩቦች መንበር ተሸካሞች፤ በእንስሳት አምሳል የሚታዩ፤ ስመ ነገድ። በኪሩቤን ፈንታ ኪሩቤል ኪሩቤም ይላል፤ ል በጣፊና በመላሽ ስሕተት የገባ ነው፤ ሱራፌልን እይ። ም የዕብራይስጥና የትግሬ ነው፤ የግእዝ አይዶለም፤ ሐባቦች ጻድቃም እኩያም እያሉ እንደ ዕብራውያን በም ያበዛሉ። ወማእከሎሙ ኪሩቤን ዘእሳት። ይኩና ኪሩቤን እንዘ ይረብባ ክነፊሆን። ወአዘዞሙ ለኪሩቤል ፡-(ሔኖ፲፬ ፡-፲፩። ዘፀ፳፭ ፡-፳። ዘፍ፫ ፡-፳፬)።
ኪሩብ ፡-(ጽር ኼሩብ። ዕብ ክሩብ) መልአክ፤ የመልአክ ስም፤ ሥዕሉ ምስሉ ነገዱ፤ ፬ ፬ ገጽ ካላቸው ካራቱ ጸወርተ መንበር አንዱ ፡-(ዘፀ፳፭ ፡-፲፱። ፫ነገ ፡-፮ ፡-፳፫። ሕዝ፱ ፡-፫። ፲ ፡-፩ ፡-፪)። ፍችው ተሸካሚነት ነው፤ መሊጦንን እይ። በዕብራይስጥ ግን ክሩብ ክሩቢት ፥ ጐመን የጐመን አበባ ፥ መልፉፍ ኵርንባ ማለት ነው፤ አይደረቄ አባጀኸኝ እንደ ማለት። በዚህ ዘይቤ ሲፈቱት ነዊኀ ክንፍ ጽፉቀ አክናፍ ያሰኛል ፡-(ራእ፬ ፡-፰)።
ኪራስ ፡-(ጽር ኽሪሲዉ) ወረቅ። ኪራስ ትዕሪን። ትዕሪነ ኪራስ፤ የወርቅ ቀለበት፤ ሽልማትና ጌጥ፤ ባለዕንቍ ፈርጥ ፡-(ስንክ ፡-የካ፱)።
ኪርያ ፡-(ጽር ኪሪያ) እግዝእት፤ እመቤት ወይዘሮ።
ኪርያላይሶን ፡-ኪራላይሶን፤ ፡-(ጽር ኪሪዬ ኤሌይሶን) እግዚኦ ተሣሀል። ኪሪዬ፤ አቤቱ ፥ ጌታ ሆይ። ኤሌይሶን፤ ይቅር በል። ኤሌይሶንሜ፤ ተሠሀለኒ። ኤሌይሶን ኢማስ፤ ተሠሀለነ። ጌርዮስን እይ ፡-(ፍ ፡-ነ ፡-፵፬ ፡-፬። ቅዳ። ግንዘ)። በኪሪዬ ፈንታ ኪርያ ማለት ስሕተት ነው።
ኪሮግልዮን ፡-(ጽር ኺሮግሪሊዮስ) ግሔ፤ ሽኮኮ ፥ አሽኮኮ። ባለብሉዮች ግን ሐሣማ ይሉታል ፡-(ዘሌ፲፩ ፡-፮። ዘዳ፲፬ ፡-፯)።
ኪነት ፡-(ታት) መጠበብ፤ መራቀቅ፤ ጥበበኛነት። የእጅ ጥበብ፤ ተግባረ እድ። ኪነተ ንዋየ ጸብእ። ኪነታቲሆሙ ፡-(ዮሴፍ። ፊልክ ፡-፫)።
ኵናት ፡-(ታት፤ ኵያንው። ዕብ ሐኒት። ዐረ ሐርበት) ጦር ዘገር፤ መውጊያ መዘርከቻ፤ በብልኀት በጥበብ የተሠራ የሰላ የሾለ። ንሣእ ወልታ ወኵናተ። ኵናታተ ወአርማሐ። ወላትው ወኵያንው ፡-(መዝ ፡-፴፬። ፪ዜና ፡-፲፩ ፡-፲፪። ፳፫ ፡-፱)።
ኪን ፡-(ብ ኪናት) ጥበበ ብልኀት፤ ተንኰል ርቀት። ዘእንበለ ኪን። በሥነ ኪኑ። ኪነ ዕንቍ። ዘቦቱ ኪን በወርቅ። ኪን ዘሕንጸት። ኪነ ሥራይ። ርእዩ ኪኖ ወምግባሮ ለሰይጣን ፡-(ጥበ፲፬ ፡-፬። ፲፫ ፡-፲፩። ዘፀ፴፭ ፡-፴፫። ፩ዜና ፡-፳፫ ፡-፲፭። ዮሴፍ። ቀሌ። ዲድ ፡-፴፪)።
፡-ሥራ ተግባር በየስሙና በያይነቱ ማናቸውም ኹሉ። ኢትትማከር ምስለ አብድ እንበይነ ኪን። ከመ ይጥብቡ በኪኖሙ። ተምህረ ኪነ እድ ለሲሳየ ዕለቱ ፡-(ሢራ፴፯ ፡-፲፩። ፴፰ ፡-፴፬። ፊልክ ፡-፩)።
፡-መሣሪያ መኪና፤ ወይም ሥራ፤ ተደራጊና ተሠሪ። አውዐዩ ሞግኦ ኀጺን ወኵሎ ኪነ ዘንዋየ ጸብእ። ይብሎኑ ኪን ለኬንያሁ። ኵሉ ኬንያ ወኵሉ ኪን ኢይትረከብ ፡-(ዮሴፍ። ኢሳ፳፱ ፡-፲፮። ራእ፲፰ ፡-፳፪)።
ኪያ ፡-(ዐረ ኢያ። ዕብ ኤት፤ ኦት) የገቢር ዐጸፋና ቅጽል። ለልን ተመልከት፤ ይህም እንደዚያ ነው፤ አለዝርዝር ብቻውን አይገባም። ምንጩና ሥሩ አያየ ነው፤ አ በከ ተለውጦ ኢያ በመባል ፈንታ ኪያ ተብሏል፤ ይኸውም ባረቡ ይታወቃል።
ኪያህክ ኪያክ ፡-(ቅብጥ) ስመ ወርኅ ራብዕ፤ ታኅሣሥ። ወኪያህክ ይሰመይ ማኹን፤ ወዓዲ ይሰመይ ሰዋዋ ፡-(አቡሻ ፡-፰)።
ኪያየ ፡-(ከ ኪ ሁ ሃ። ነ ክሙ ክን ሆሙ ሆን) እኔን፤ ራሴን። ቦኑ ኪያየ ትፈርሁ። ኪያከ ንሴብሕ። እስመ ኪያኪ ሠምረ። ኪያሁ ኀረየ። ዘኪያሃ አፍቀረ ፡-(ኤር፭ ፡-፳፪። ኪዳ። ውዳ ፡-ማር፬። ሢራ፵፭ ፡-፬። ፬ ፡-፲፪)። እፎ እንከ ኪያነ ያድኅኑ። እፎ እንከ ፈድፋደ ኪያክሙ። ወኪያክንሂ። በእንተ ፈጢሮትየ ኪያሆሙ። ወኪያሆን ፡-(ኢሳ፳ ፡-፮። ማቴ፮ ፡-፴። ዘረፋ። ዘፍ፮ ፡-፴። ዘሌ፳ ፡-፲፬)። አንዳንድ ጊዜም በተገብሮ ዐጸፋ በለሊሁና በውእቱ በሎቱና በቦቱ ፈንታ ተጥፎ ይገኛል፤ የመላሽ ስሕተት ነው። እወ ውእቱ ኪያሁ። ወኵሎሙ ርቱዓነ ልብ እለ ኪያሃ ቦሙ። እለ ሀለዉ በኪያሆን መዋዕል። ጸውዖ ኪያሁኒ ውስተ በዓል። ነዋ አምላክነ ዘኪያሁ ተወከልነ ፡-(አፈ ፡-ድ፲፩። መዝ ፡-፺፫። ዮዲ፬ ፡-፮። ጦቢ፱ ፡-፪። ኢሳ፳፭ ፡-፱)። ቅጽል መኾኑም፤ በዝኩና በውእቱ ፈንታ ሲገባ ነው። ኪያሁ መንፈሰ ነሢኦሙ። ይሠውዕ ኪያሃ መሥዋዕተ። እሬኢኑ እንጋ ኪያሃ ዕለተ ቢል፤ ያነን መንፈስ ፥ ያችን መሧዕት ፥ ያችን ዕለት ያሰኛል እንጂ፤ ርሱን ርሷን ማለት አይስማማም ፡-(ስንክ ፡-ግን፲፰። ዕብ፲ ፡-፲፩። ተረ ፡-ቄር)። ፡-(ዕር፲፬ ፡-ቍ፻፲፱)።
ኪዮኪሉ ፡-(ዕብ ኪ ዮክሉ) እስመ ይንእሱ፤ ያንሳሉና ፡-(ሕዝ፵፪ ፡-፭)።
ኪደት ፡-መርገጥ፤ መረገጥ፤ አረጋገጥ፤ ርግጫ፤ መጫማ ሰኰና ፡-(ስንክ ፡-መጋ፲፩። ኢሳ፳፪ ፡-፭)። ወኢታገምር ፍኖታ ዘእንበለ አሐቲ ኪደተ እግረ ብእሲ ፡-(ሱቱ ፡-ዕዝ፭ ፡-፯)።
ኪዳነ ምሕረት ፡-የማርያም ስም፤ ወይም የኪዳኗ በዓል በየካቲትና በናሴ ባ፲፮ ቀን የሚውል፤ ትእምርተ ኪዳን ማለት ነው ፥ ቀስተ ደመና እንደ ማለት፤ ቀስቱም ቅሉ በሕፃናት አፍ የማሪያም መቀነት ይባላል። ፡-(የታቦት ዘፈን) ኪዳነ ምረት ዘላለም እመቤት። ሰላም ለኪ ኪዳነ ምሕረት እምነ ፡-(ደራሲ)።
ኪዳን ፡-ውል፤–ከዪድ ኬደ።
[1]፡-(ናት። ዐረ ዐህድ። ዕብ ብሪት። ሱር ቅያም) በቁሙ፤ ውል ቁም ነገር፤ የፍቅርና ያንድነት መሐላ፤ ሰላማዊ ሕግ ኹለቱን ወገን እንድ የሚያደርግ፤ ስለ ረብና ስለ ጥቅም በተስፋ የቆመ የተጣፈ ሥርዐት፤ ቢያፈርሱት ጕዳትና ጠብ የሚያመጣ ፥ ጥቅም የሚያሳጣ። ወኵሎ ኪዳነ ዘተካየዶሙ ኢዐቀቡ። ገበሩ በከመ ኪዳንክሙ። ወኢይፀራዕ ኪዳነ ጼው። ኪዳን ዘጽኑዕ። መጽሐፈ ኪዳን። ኪዳን ብሊት ወሐዳስ። አይሁድ እለ መነኑ ኪዳናተ ፡-(፬ነገ ፡-፲፯ ፡-፭። ስንክ ፡-ጥቅ፲፱። ኩፋ ፡-፳፩። ገላ፫ ፡-፲፭። ዮሴፍ። አርጋ ፡-፭። ዲድ ፡-፴፫)።
[2]፡-ኪዳን፤ የመጽሐፍ ስም፤ ተረፈ ወንጌል የጌታና የሐዋርያት ቃል፤ ከትንሣኤ እስከ ዕርገት ያስተማራቸው፤ እየጠየቁት የመለሰላቸው። ከዕርገት በኋላ ከወንጌል በፊት በጥንተ ስብከት ጥፈውታል፤ እንደ ሔኖክ ፪ ክፍል አለው፤ ማስተማሩንም ሉቃስ ይመሰክራል ፡-(ግብ፩ ፡-፪ ፡-፫)። መጽሐፈ ኪዳን ዘእግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ። ጸሐፍዎ ለዝ ኪዳን ዮሐንስ ወጴጥሮስ ወማቴዎስ እንዘ ያጽሕፎሙ እግዚእነ፤ ወፈነዉ በአርኣያ ዝ ግጽወ እምኢየሩሳሌም ፡-(ክፍል ፡-፩)።
ኪዳን ዘነግህ ፡-ከመጽሐፈ ኪዳን የወጣ የነግህ ጸሎት፤ ቀሳውስት ጧት ጧት የሚያደርሱት። ከዚህ ሌላ ደግሞ ፮ ክፍሎች አሉ፤ ኹሉም በቅዳሴ ውስጥ ይገኛሉ፤ ያንድነት ስማቸው ፯ቱ ኪዳናት ይባላል።
ካሂ አካሂ ፡-(ብ ካህያት፤ አካህያት) ጊደርና ጥገት። ካሂ ጊደር፤ እንስት ጥጃ። አካሂ ጥገት፤ እመጫት ላም። ምስጢራቸው ማነስና መድከም ሕጹጽነት ነው። በዕብራይስጥ ግን ካሂ ማለት ከማሃ ከመ ዛ ማለት ነውና፤ በዚህ ዘይቤ ሲፈቱት ካሂ የጥጃ ጐፍላ ወይም እንቡጣ ስልቻው ምስሉ፤ ሲሞት ከዥራቱ እስካፉ ሸልቅቀው በሥጋው ፈንታ ገለባ ጐስረው ጠቅጥቀው፤ በግሮቹ ፈንታ ፬ ዕንጨት ሰክተው ሕያው አስመስለው የጨው ውሃ ቀብተው የሚያቆሙት፤ አካሂ ያነን እያየች እየላሰች ወተቷን የምትስጥ ማለት ነው። ፡-(ሙሾ፤ ላምና ዐላቢ) ያለ እየመሰለኝ ልጄ ሙቶ ሳለ፤ እንቡጣውን ባየው ልቤ ተታለለ። እንኳን አንች ላሟ ቤተ እስራኤል፤ ታታለል ነበረች በጥጃ ምስል።
ካህን ፡-(ናት። ዕብ ኮሄን። ሱር ካህና። ዐረ ካሂን) በቁሙ፤ ቄስ ጳጳስ የግዜር አገልጋይ የሕዝብ መሪ አስተማሪ፤ መንፈሳዊ አባት። አንተ ካህኑ ለዓለም። ትቀብዖ ወትቄድሶ ወይከውነኒ ካህነ። ካህናት ወሊቃነ ካህናት። ዕሥራ ወአርባዕቱ ካህናተ ሰማይ ፡-(መዝ ፡-፻፱። ዘፀ፵ ፡-፲፩። ቅዳ ፡-ሕር። ስንክ ፡-ኅዳ፳፬)።
ካሕድ ፡-ጥርጥር አሉታ፤ ኑፋቄ ክሕደት፤ ክርክር ሙግት፤ የነገርና የትምርት ዕንቅፋት መሰናክል። እለ ይገብሩ ካሕደ በላዕለ ክርስቶስ። እስመ ኵሉ ካሕድ ምግባሪሆሙ። ዘእንበለ ካሕድ። አልቦ ካሕድ በዝንቱ። ያመጽኡ ካሕደ ላዕለ ትምህርትክሙ። እብነ ካሕድ ፡-(ስንክ ፡-የካ፰። ኩፋ ፡-፳፫። ዕብ፯ ፡-፯። ቄር። ሮሜ፲፮ ፡-፲፯። ፩ጴጥ ፡-፪ ፡-፰)።
ካሌብ ፡-(ዕብ። ዘኍ፲፫ ፡-፮) የሰው ስም፤ ካ ከመ፤ ሌብ ልብ፤ በተገናኝ ከመ ልብ ዘከመ ልብ ማለት ነው። ካሌብን አንቀጽ አድርጎ ሰፋ ጠቀመ ባለው ዐማርኛ ሲፈቱት ግን አንዳርጌ ያሰኛል። አንዳርጌ መባልም ባሕር ተሻግሮ የመንን ይገዛ ለነበረው ለትግሬው ካሌብ ይሰማማል። ከርሱም አስቀድሞ ብዙ ያበሻ ነገሥታት ፸፯ ዓመት ገዝተውታል ፡-(ታሪክ)።
ካልኢት ፡-፪ኛ ክፍል የቍጥር ቤት የኬክሮስ ፰ኛ። ኬክሮስን እይ ፡-(አቡሻ ፡-፲፩)።
ካልኣዊ ዪ ይ ፡-ኹለተኛ፤ የኹለተኛ የዳግመኛ።
ካልእ ፡-(እት ኣን ኣት) ሌላ ልዩ፤ ኹለተኛ ተከታይ፤ መሰል እኩያ መንቲያ፤ ጓደኛ ወዳጅ ባልንጀራ፤ ባለሟል። ካልእ ክብሩ ለዘበሰማይ፤ ወካልእ ክብሩ ለዘበምድር። ሕጎሙ ካልእ እምነ ኵሉ አሕዛብ። ሶበ አሐዱ ይድኅር ወካልኡ ይረግም። ካልኣኒሁ አርዳእ። ካልእየ ኢገፋዕኩከ። ኵሲ ካልኡ ለዳዊት ፡-(፩ቆሮ ፡-፲፭ ፡-፵። አስቴ፪ ፡-፰። ሢራ፴፬ ፡-፳፱። ዮሐ፳ ፡-፳፭። ማቴ፳ ፡-፲፫። ፪ነገ ፡-፲፭ ፡-፴፯)።
ካሚዎን ካሚዮን ፡-(ሮማይ) የእሳት ቦታ፤ እሳታዊ ማኅፈድ፤ በእሳት የሜኼድ ማለት ነው፤ ሠረገላ እሳት እንደ ማለት። የከመወ ዘር አድርጎ በከመ ዘይቤ ሲፈቱት ግን፤ ካሚዎን፤ ከመ ንስር። ካሚዮን፤ ፡-(ከመ ዮን) ከመ ርግብ ፥ አምሳለ ርግብ ያሰኛል፤ ዮንን እይ ፡-(ራእ፲፪ ፣ ፲፬። መዝ ፡-፶፬)።
ካሴል ፡-(ዕብ ኪስሌው። ጽር ኻስሌው) የዕብራውያን ፱ኛ ወር፤ ታኅሣሥ ፡-(ዘካ፯ ፡-፩)።
ካሪም ፡-(ዕብራ) ከረይት፤ መክርያት። የቅጥር ማፍረሻ ቀንዳም ብረት፤ ባለመዘውር ባለመንኰራኵር። ሞግእን እይ፤ ከዚህ ጋራ ፩ ነው ፡-(ሕዝ፬ ፡-፪)።
ካራድርዮን ፡-(ጽር ኻራድሪዮስ። ዕብ አናፋ) ታላቅ አሞራ፤ እግረ ሽመላ የሽመላ ወገን፤ ባዋሽ ወንዝ የሚገኝ። ይህ ደግሞ የክርስቶስ ምሳሌ ስለ ኾነ አንዳንድ ክርስቲያኖች ርሱን ከነልጆቹ በሬሳ ልብስ ላይ ከመስቀል ጋራ ይሥሉታል። የውዳሴ ማሪያም ተርጓሞች ግን ስሙን ጳልቃን ጣልቃን ይሉታል ፥ የተሳሳተ ነው፤ ጳልቃንን እይ። አሮድዮን ወካራድርዮን ፡-(ዘሌ፲፩ ፡-፲፱)። ከራድዮንና ካራድርዮን ስለ ተቃረቡ በካራድርዮን ፈንታ ከራድዮን ይላል ፡-(ዘዳ፲፬ ፡-፲፰)።
ካኑን ፡-(ሱር ወዐረ) ስመ ወርኅ፤ የሶርያ ወር ፥ ታኅሣሥና ጥር። ካኑን ዳግማይ ፡-(ስንክ ፡-ጥር፲)።
ካዕሴ ፡-ፈርስ፤ እበት ርስሐተ ከብድ፤ በእንስሳት ሆድ በጨጓራና በሽንፍላ ባንዠት ውስጥ የሚገኝ። ምስጢሩ የጨጓራውን ክብነት እንደ ማድጋ መኾኑን ያሳያል፤ ባለብሉዮች ግን ለይተው የጨጓራ ሰንበር ይሉታል፤ ፍችው አይዶለም። ኵሎ ሥጋሁ ምስለ ርእሱ ወሰኳንዊሁ ወከርሦ ወካዕሴሁ ፡-(ዘሌ፬ ፡-፲፩። ፰ ፡-፲፯። ፲፮ ፡-፳፯። ዘኍ፲፱ ፡-፭)። ዳግመኛም ሐመድ በማለት ፈንታ ካዕሴ ይላል፤ የመላሽ ስሕተት ነው። ካዕሴ ዕጐልት ፡-(ዕብ፱ ፡-፲፫)።
ካዕበ ፡-፪ ጊዜ፤ ዳግመኛ፤ ኹለተኛ። ምዕረ ወካዕበ። ካዕበ ወሥልሰ። ወካዕበ ናስተበቍዕ ፡-(ፊልጵ ፡-፲፮። ሢራ፲፫ ፡-፯። ቅዳ)።
ካዕበት ክዕበት ፡-መካብ፤ ፡-(ጥካ) መካብ፤ አካካብ ፥ ክቦሽ። ኹለትነት፤ ኹለት እጅ፤ ዕጥፍ ድርብ። በኣተ ካዕበት። ለይኩን ካዕበተ ላዕሌየ መንፈስ ቅዱስ ዘዲቤከ። ወሀቦ እግዚ ለኢዮብ ካዕበተ ንዋዩ እምቀዲሙ። ይፍዲ ህየንተ ዘሰረቀ ኀምስተ ካዕበተ ፡-(እጅ)። ካዕበተ ሱባዔ ፡-(፲፬)። ካዕበተ ዐሥሩ ፡-(፳)። ካዕበተ ዕሥራ ፡-(፵)። ካዕበተ ምክዕቢት፤ የዕጥፍ ዕጥፍ ፥ ባንድ አራት ፡-(ዘፍ፳፫ ፡-፱። ፬ነገ ፡-፪ ፡-፱። ኢዮ፵፪ ፡-፲። ፈ ፡-መ ፡-፲፯ ፡-፮። ስንክ ፡-ግን፲፬። ነሐ፩። ታኅ፲፬። ራእ፲፰ ፡-፮)።
ካዕባዊ ይ ፡-(ካዕቢት) ሌላ፤ ኹለተኛ ፡-(ፊልክ ፡-፵፰። ፷፭)።
ካእብ ፡-ኹለተኛ፤–ክዒብ ከዐበ።
ካዕብ ፡-ዕጽፍ ድርብ፤ ኹለት። ካዕበ እመት። ያስተዋፅኡ ሎቱ ሲሳዮ ስንዳሌ ዕሥረ ወካዕበ በመስፈርተ አርጣባስ ፡-(ዘፀ፳፭ ፡-፲ ፡-፲፯። ዳን፲፫ ፡-፫)።
፡-ሌላ ፪ኛ፤ ወዳጅ ባልንጀራ፤ እኩያ መንቲያ። እመቃብሪሁ ቀዳሚ ውስተ መቃበር ካዕብ፤ እንዘ ያፈልስዎ ሕዝብ። ሰላም ለአውጋንዮስ ወለአውጋንድሮስ ካዕቡ ፡-(ስንክ ፡-ጥቅ፮። መጋ፲፬)።
ካድኮድ ፡-ዝኒ ከማሁ፤ ከደዋና ካድኮድ አንድ ስም ነው። ረአሙት ወካድኮድ ፡-(ሕዝ፳፯ ፡-፲፮)። በካድኮድ ፈንታ ከርከንድ ይላል፟፤ ከርከዴን ማለት ነው፤ ፍችውን በቦታው ተመልከት።
ካፍ ፡-(ወከፈ) ስመ ፊደል ፲፩ኛ ከ፤ በግእዝ አልፍ ቤት በአበገደ ፡-(መዝ ፡-፻፲፰ ፡-፹፩–፹፰። ሰቈ፩ ፡-፲፩ ፡-፲፩። ፫ ፡-፴፩። ፬ ፡-፲፩። አፈ ፡-ድ፫)። ፍችው ፥ ውስጥ እጅ ፥ መስጫ ማቀበያ ማልት ነው፤ ለእግርና ለመንካም ይኾናል። ወቦሙ ካፍ ከመ ካፈ ላሕም ፡-(ሕዝ፩ ፡-፯)። ወከፈን እይ፤ ሥሩና ምንጩ ርሱ ነው።
ኬ ፡-(አ–መ–ሶ) የአንክሮና የአጋኖ የአስተብቍዖ ቃል፤ በመጨረሻ ቃል እየገባ መድረሻውን ራብዕ በማድረግ ቃል ያገነታል፤ እኮ እንኳን ይኾናል። ብዙ ጊዜም ትርጓሜና ፍች ሳይፈልግ እንደ ከመ አዳማቂና የንባብ ጌጥ ኹኖ ይቀራል። ምንትኬ ሰብእ ዘይጸንሖ እሳት። ምንትኬ ዘአሜሃ ዐውያት ፡-(አንክሮ)። ንግባእኬ ኀበ ጥ ነ። ውእቱኬ። አንትሙኬ። ዝኬ ውእቱ፤ ዝኬ እፎ፤ ይህ ነዋ፤ ይህሳ ፡-(አጋኖ)። ወይንኬ አልቦሙ፤ የላቸውም እኮ ፡-(ምልጃ)። ርእዩ እመ ይዌልጡ አሕዛብ አማልክቲሆሙ፤ እንዘኬ ኢኮኑ አማልክተ፤ እንኳን ፡-(ኤር፪ ፡-፲፪)። አንዳንድ ጊዜም በዋዌ ፈንታ፤ ኵሉኬ ዕፅ ዘኢይፈሪ። ዘኬ ፈትሐ አሐተ እምላ። ኦሪትሰኬ እያለ አለቦታው ገብቶ ይገኛል። አንዳንድ ጊዜም ማ ይኾናል፤ ይኸውም በነባርና በትእዛዝ አንቀጽ ሲገባ ነው። ነዐኬ በልኬ፤ ናማ በልማ ፡-(ዕር፳ ፡-ቍ፺፱)።
ኬልቄዶን ፡-(ጽር ኻልኪዶን። ዕብ ሽቦ) ነጭ ዕንቍ፤ በንጣቱ ሰማያዊነት ያለበት። አካጥስን እይ፤ ከዚህ ጋራ አንድ ነው። ወሣልስት በኬልቄዶን ፡-(ራእ፳፩ ፡-፲፱)።
፡-የመዲና ስም፤ በታናሽ እስያ በቱርክ አገር ውስጥ ያለ፤ የቍስጥንጥንያ ቅርብ አጠገብ፤ ከልደት በኋላ ባ፬፻፶፩ የግሬክ ንጉሥ መርቅያኖስና ሚስቱ ብርክልያ ስለ መንግሥታቸው ልዕልና በሠለስቱ ምእት ዕጥፍ ፮፻፴፮ ጳጳሳት ሰብስበው ከጉባኤ ኹሉ የሚበልጥ ታላቅ ጉባኤ ያቆሙበት፤ ቀድሞ በኤፌሶን ከንስጥሮስ ጋራ ዐብረው ተወግዘው የነበሩ ፥ ኋላም እንደ ገና ከሞቱ በኋላ በቍስጥንጥንያ ጉባኤ ቢጊሊዮስ ዘሮም ከነመጽሐፋቸው ረግሞ አውግዞ የለያቸው እነኤባስ እነታዎድሪጦስ የገቡበት፤ የእስክንድርያው ሊቀ ጳጳስ ዲዮስቆሮስና መቃርዮስ፤ ሌሎችም መምህራን ከሶርያና ከአርመን የመጡ አራት ጳጳሳት ተጨምረው እነዚህ ፮ቱ የተለዩበት። ምክንያቱን በቤተ ክሲያን ታሪክ ተመልከት፤ ታሪኩ ግብ ፪ ወገን ነው፤ ፩ኛው የግብጽ የሶርያ የአርማንያ፤ ፪ኛው የግሬክና የሮምያ። የግሬኮች ታሪክ በዲዮስቆሮስ እጅ ከተጣፈው ከቅዳሴውና ከድርሳኑ ቃል አይስማማም ፥ ዐይንና ዐፈር ነው፤ ይኸውም ሊታወቅ ፍሬ ቅዳሴውን የኢትዮጵያ ካቶሊኮች ከሮማ ሊቃውንት አስአመርምረው ፥ ከፓፓ አስፈቅደው ሐሰቅና ስሕተት ጸያፍ የሌለበት ስለ ኾነ ይቀድሱበታል። ስሙን ብቻ በአርእስቱ ፥ አኰቴተ ቍርባን ዘቅዱስ ዲዮስቆሮስ በማለት ፈንታ ዲዮናስዮስ ብለውታል፤ ይህም ቅዳሴ የተደረሰና የተጣፈ በጋግራ ሳለ ነው፤ በግእዝ ተጥፎ እንደሚገኝ በሌሎችም ቋንቋ በሶርያና በአርመን በጽርእ በላቲን ይገኛል። ከመስማት ማየት ይበልጣልና፤ ቅዳሴዉን ከሥር እስከ ጫፍ ተመልከት፤ ፩ አካል ፪ ባሕርይ ሲል ታገኛለኽ። ፪ኛም ሃይማኖተ አበው ዲዮስቆሮስ የተለየበትን ለማስረዳት ከገዛ መጽሐፉ ባጭር ቃል ጠቅሶ ያመጣው የድርሳኑ ቍርጭኝ ወይም መልእክቱ ስላካልና ስለ ባሕርይ ስለ ህላዌም ፍች የሚለውን ባባ ብንያሚ ድርሳን ውስጥ ወካዕበ ይቤ፤ ዲዮስቆሮስ ተአማኒ ርእሰ ኤጲስቆጶሳት ዘእለእስክንድርያ በመልእክቱ ዘጸሐፋ ኀበ በርጢር እንዘ ሀሎ በጋግራ። ይቤ፤ አንሰ ረከብኩ ነገረ እንዘ ኣነብብ መጻሕፍቲከ ዘፈኖከ ሊተ ምስለ ሰበእ መትሕላን እለ ኢኮነ ፍጹማነ ወአልቦሙ አእምሮ ጥዩቀ፤ ካለው ዠምረኽ እስከ መጨረሻው ተመልከት። መልእክቱም የተጣፈበት ምክንያት ግብጦች በኦርቶዶክስ ባህል ተጣልተ ፪ ወገን ኹነው የጣፉትን ክታብ፤ በርጢር የተባለው ሰውዬ የርሱንም ክታብ ጨምሮ ፪ መነኮሳት አሲዞ ስለ ሳከለት ነው ይባላል።
ኬልቲ ፡-(ጽር ኼሬቲ። ዕብ ክሬቲ) የጭፍራ ስም። ቀርጤሳዊ የቀርጤስ ሕዝብ ማለት ነው፤ ጐንደሬ እንደ ማለት ፡-(፫ነገ ፡-፩ ፡-፴፰)። ል በጣፊ ስሕተት ወይም በጸያፍ አንደበት የገባ ነው። በሐረረ ፈንታ ሐለለ እንዲል።
ኬሰ ፡-(ይከይስ ይኪስ፤ ከዪስ። ኰዐሰ፤ ለወየ፤ ጠወየ) ዐጠፈ ጠቀለለ፤ ሰበሰበ፤ የልብስ የገመድ የሽቦ። ታጠፈ ተጠቀለለ። ግስነቱ ከኰዐሰና ከለወየ የተዴቀለ ነው፤ የ ከለወየ መጥቶ በዐ ፈንታ ገብቷል። የኹሉንም ፍች በየቦታው። እይ።
ኬሴላ ፡-(ዕብ ክሲል) ጉቡኣን፤ ከዋክብት፤ አንድነት ያላቸው። ኬሴላ ባለው ሴኬላ ይላል የተዛወረ ነው፤ ሰከለን እይ ፡-(ዓሞ፭ ፡-፰)።
ኬነወ ተኬነወ ፡-ከዪን ኬነ ከየነ።
ኬናዊ ፡-(ዊት ውያን ያት፤ ነውት፤ ኬነወ) ዝኒ ከማሁ። ኬነውት ፡-(ስንክ ፡-መሰ፭)። አንዳንድ መጽሐፍ ግን በኬንያትና በኬነውት ፈንታ ኪነት ኬነት ይላል፤ የጣፊ ስሕተት ነው። ኪነተ ዕፅ። ኪነተ አሕማር። ያስተጌብሮሙ ለኪነት ወይሁቦሙ ብዙኀ ንዋየ። ወያስተጋብኦሙ ለኵሉ ኬነት። ኤልያብ ሊቀ ኬነት ዘማእነም ፡-(ኩፋ ፡-፲፩። ራእ፲፰ ፡-፲፯። ግብ፲፱ ፡-፳፬ ፡-፳፭። ዘፀ፴፯ ፡-፳፩)።
ኬክሮስ ፡-(ሳት። ጽር ኪርኮስ) የክፍለ ዕለት ስም፤ የዕለት ፷ኛ። ፩ዱ ዕለት ወይም ፳፬ቱ ሰዓት ፷ ኬክሮስ፤ አንዱ ኬ ፷ ካልኢት፤ አንዱ ካ ፷ ሣልሲት፤ አንዱ ሣ ራብዒት፤ አንዱ ራ ፷ ኃምሲት፤ አንዱ ኃ ፷ ሳድሲት ይኾናል፤ ይህ ሲዘረዘር ነው። ሲጠቀለለል ደግሞ፤ ስሳው ሳ ፩ ኃምሲት፤ ስሳው ኃ ፩ ራብዒት፤ ስሳው ራ ፩ ሣልሲት፤ ስሳው ሣ ፩ ካልኢት፤ስሳው ካ ፩ ኬክሮስ፤ ስሳው ኬ ፩ ዕለት ይኾናል። አኀዝ ዓመተ እልሑጅራ በስድስቱ መካናት፤ በመካነ ዕለት ኍልቈ ኬክሮስ ወበመካነ ኬክሮስ ኍልቈ ካልኢት። ዘይኄምሶን ለኬክሮሳተ ሰዓታት ከመ ይኩና መዓርገ ጸሎታት ፡-(አቡሻ ፡-፲፩። መጽ ፡-ምስ)።
ኬደ [1]፡-ረገጠ፤–ከዪድ ኬደ።
[2]፡-ከየደ፤ ፡-(ዐረ ዐሂደ። ዕብ ዐዌድ፤ ሄዒድ) አዋለ አሰረ፤ ውል አደረገ፤ ነገርን ቈረጠ አጠበቀ አጠና፤ በቃል በጥፈት፤ የሥራ የንግድ።
ኬጢኢም ፡-(ጽር ኼቲይም። ዕብ ባቲም) ቤቶች፤ ድንኳኖች፤ ወይም የድንኳን ቈርበቶች በስተላይ ጠፈር መዋቅር የሚኾኑ ፡-(፬ነገ ፡-፳፫ ፡-፯)።
ኬጥሮጋውሎስ ፡-(ጽር ኺትሮካፍሉስ። ዕብ ኪዮሮት) የብረት ጋኖች፤ ታላላቅ ድስቶች፤ ለማብሰያ ለመቀቀያ፤ ወይም ውሃ ለመምሊያ ለመታጠቢያ የተሠሩ፤ ለታናናሾችም ይነገራል ፡-(፫ነገ ፡-፯ ፡-፴፰)።
ኬፋ ኬፋስ ፡-ኰኵሕ፤–ከፊእ ከፍአ።
ኬፋ ኬፋእ ኬፋስ ፡-(ሱር ኬፋእ። ጽር ኪፋስ) ደንጊያ፤ ዕንቍ። እብነ ኬፋስ አንቲ ፡-(አርጋ ፡-፪)። የሰው ስም፤ ጴጥሮስ ፡-(ዮሐ፩ ፡-፵፫። ፩ቆሮ ፡-፩ ፡-፲፪። ፲፭ ፡-፭። እብንንና ኰኵሕን ጴጥራን ተመልከት። ምስጢሩ ጥንካሬና ብርታት ሸካርነት ነው።
ኬፌቴሔን ፡-(ዕብ ክፊትሔሄን) ክ ክመ፤ ፌታሕ ኆኅት፤ ሄን ሆን፤ በተገናኝ ከመ ኅዋኅዊሆን ማለት ነው ፡-(ሕዝ፵፪ ፡-፲፩)። ኤፍታሔና ፈትሐን ተመልከት።
ክሁል ፡-(ላን ላት ህልት) የተቻለ የተቻቻለ፤ የተስማማ ስምም።
ክሁን ፡-(ናን ናት ህንት) የተካነ፤ ክህነት የተሾመ የተቀበለ።
ክሑድ ፡-(ዳን ዳት ሕድ) የተካደ፤ የተካካደ።
ክሂህ ሆት ፡-(ከሀሀ ይክሀሀ ይክሀህ። ዕብ ካሃህ ይክሄህ) መድከም ማነስ፤ መጨለም መፍዘዝ፤ መደንገዝ፤ የኀይል የጕልበት የዐይን የብርሃን። ከበወንና ለከወን እይ፤ የዚህ ጎሮች ናቸው። ከሕክሐም የዚህ ዲቃላ ነው።
ክሂል ሎት ፡-(ክህለ ይክል ይክሀል። ዕብ ያኮል) መቻል መብቃት፤ ማግመር መወሰን፤ በሚሠሩት ሥራ ማየል መበርታት፤ መብት ማግኘት። ገቢረኒ ትገብር፤ ወክሂለኒ ትክል። ኵሎ ዘትክል እዴከ ለገቢር። መኑ አነ ከመ እክሀል ሐኒጸ ሎቱ ቤተ ፡-(፩ነገ ፡-፳፮ ፡-፳፭። መክ፬ ፡-፲። ፪ዜና ፡-፪ ፡-፮)።
፡-ችሎት አቻቻል፤ ኀይል ብርታት፤ ዐቅም ጕልበት፤ ሥልጣን መብት። ሰብሕዎ በክሂሎቱ። በከመ ክሂሎትነ። አልብየ ክሂል ላዕሌሁ። ከመ የሀቦ ክሂለ ላዕሌሁ ወላዕለ ንዋዩ ፡-(መዝ ፡-፻፶። ስንክ ፡-ሠኔ፲፪። ገድ ፡-ተክ። ስንክ ፡-ግን፪)።
ክሂን ፡-(ከሀነ ይክህን ይክሀን። ዕብ ካሄን) ካህን መኾን፤ ክህነት ተሹሞ በግዜር ፊት ቁሞ ማገልገል የአምልኮ ሥራ መሥራት ስለ ራስና ስለ ሕዝብ መሧዕትና ጸሎት ማቅረብ፤ መባረክ መቀደስ ማጥመቅ ማቍረብ።
ክሒድ ዶት ፡-(ክሕደ ይክሕድ ይክሐድ። ዕብ ካሖድ ሂክሔድ፤ ታባ ተካደ) መካድ፤ መክዳት፤ እምነትን ውልን መሐላን ማፍረስ፤ መሸፈጥ ቃልን መለወጥ፤ መዋሸት ዐሎ ማለት፤ ማበል መወንጀል። ክሒደ ትክሕዱኒ። ክሕደ ሃይማኖቶ። አምጽኡ ላዕሌነ መሐላ ዘኢንክል ክሒደ። አምነ ወኢክሕደ። ከመ ተዐልዎ ብእሲት ለምታ ከማሁ ክሕዱኒ ቤተ እስራኤል ፡-(ኢሳ፵፰ ፡-፰። ፩ጢሞ ፡-፭ ፡-፰። ዮዲ፰ ፡-፴። ዮሐ፩ ፡-፳። ኤር፫ ፡-፳)።
ክሕለ ፡-ቻለ፤–ክሂል ክህለ።
ክህነታዊ ፡-የክህነት፤ ክህነታም ባለክህነት። መልእክት ክህነታዊት። ሀብት ክህነታዊት ፡-(ፍ ፡-ነ ፡-፲ ፡-፮። ፊልክ ፡-፲፭)።
ክህነት ፡-መካን ማስካን፤ ካህንነት፤ ተክኖ ማገልገል። አገልግሎት፤ መንፈሳዊ ሹመት፤ ፯ ዕርከኖች ያሉት። ፫ቱ ላይኞች ጵጵስናና ቅስና ዲቁና። ፬ቱ ታችኞች ንፍቀ ዲያቆንና አንባቢ፤ መዘምርና በረኛ። ጳጳስንና ኤጲስቆጶስን እይ። ተኀርየ ዘርዐ ሌዊ ለክህነት። ለክህነት ቅድስት ወንጽሕት። ኢይንግበር ሕዝባዊ ግብረ ክህነት ፡-(ኩፋ ፡-፴። ፩ጴጥ ፡-፪ ፡-፭። ዲድ ፡-፲፮)።
ክሕደት ፡-(ላ ጥ) መካድ፤ መካካድ አካካድ። በቁሙ፤ ክዳት አሉታ፤ ሸፍጥ ዐመጥ፤ በደል ወንጀል። ዝንቱሰ ክሕደት፤ ወአኮ ሃይማኖት። መጽሐፈ ክሕደት። ክሕደቶሙ ዘክሕዱከ ፡-(ታሪ ፡-ነገ። ስንክ ፡-መስ፲፫። ፫ነገ ፡-፰ ፡-፶)።
ክሉል ፡-(ላን ላት ልልት) የተከለለ ከልል፤ የተጌጠ፤ ክቡር ምስጉን፤ ቅድጁ፤ ዝግጁ። ቤት ክሉል በአክዋል። በስብሐት ልዕልት ክሉል ውእቱ። ክሉል በትርሲተ ብርሃን። ክሉል በጌራ መዊእ ፡-(መቃ ፡-ገ፫። ቄር። ስንክ ፡-ታኅ፰። ጥር፳፫)።
፡-የተደፋ የተጐለለ፤ ጕልል ንቡር። አክሊሉኒ ይኩን ክሉለ መልዕልተ ርእሱ ፡-(ፈ ፡-መ ፡-፴፩ ፡-፭)።
ክሉእ ፡-(ኣን ኣት ልእት) የተከለከለ ክልክል። ቀቲልሰ እምኍልቈ ዐበይት ኀጣውእ። እለ ክቡኣት ወውጉዛት በልብ ወበሕግ ፡-(ፍ ፡-ነ ፡-፵፮)።
ክላሕ ፡-ጩኸት፤ አጯጯኽ ዜማ፤ ፍጅት ውካታ። ሰምዐ ክላሐ ሰብእ። ክላሖሙ ለሰይጣናት። ያፈደፍዱ ክላሐ ዘእንበለ ኀፍረት ፡-(ዮሴፍ። ስንክ ፡-መስ፲፫። አፈ ፡-ድ፬)።
ክላሌ ፡-(ልያት) መከለል፤ ፡-(ጥከ) መከለል፤ መቈረጥ መቀዳጀት። ከለላ ቈረጣ ቅድጅት፤ ምስጋና ፍጻሜ፤ ፍጹም ክብር። ዮም ተጽሕፈ እምነገሥት ክላሌ በመጥባሕት ለጊዮርጊስ ሰማዕት። ኀይለ ክላሌሆሙ። ክላሌ ክብር ወስብሐት ይደሉ ለባሕቲቱ ፡-(ድጓ። ስንክ ፡-ኅዳ፯። አፈ ፡-ድ፬)። ክላሌሁ በመጥባሕት ያለው፤ የሰማዕታት ሞት እንደ ጌታ ሞት ስለ ኾነ ነፍሳቸውም ሙሽራው ናትና፤ ሥጋዋ ሲሰየፍ ገድሏ መፈጸሙን፤ የተፍኀሮን ሥራ ጨርሳ አክሊለ ብርሃን መቀበሏንና መቀዳጀቷንም ቢያሳይ እንጂ፤ መቈረጥን ብቻ አያሳይም።
ክልሱስ ፡-(ሳን ሳት ስስት) የተላሰሰ፤ የታጨደ የተሰበሰበ።
ክልአት ፡-(ታት) መከልከል ፡-(ጥ ከ) መከልከል መቅረት፤ አከላከል ክልከላ። ወሃቢ ዘእንበለ ክልአት። አልቦ ክልአት ለሞትነ። ዘእንበለ ምሕረት ወኢክልአት። ክልአታት ፡-(ቅዳ ፡-ኤጲ። ጥበ፪ ፡-፭። ፲፮ ፡-፲፮። ፊልክ ፡-፶፭)።
ክልኤ ፡-(ዕብ ኪል አዪም) ዝኒ ከማሁ፤ ኹለት፤ ጥንድ ጣምራ፤ የተቈራኙ የተመሳሰሉ፤ እንደ መቀስና እንደ ጕጠት እንደ ሚዛንና እንደ ጡት ያሉ፤ ቅጽልነቱ ሴትና ወንድ ያስተባብራል። ክልኤ አጥባትኪ። ምስለ ክልኤ አዋልዲሃ። ወፅኣ ክልኤሆን ኅቡረ። ተወልዱ ሎቱ ክልኤ ደቂቅ። ወነሥአ ክልኤ ደቂቆ። ይመጽኡ እሉ ክልኤሆሙ ላዕሌኪ ፡-(ማሕ፯ ፡-፬። ዳን፩ ፡-፲፭። ዮዲ፲፫ ፡-፲። ዘፍ፲ ፡-፳፭። ፵፰ ፡-፩። ኢሳ፵፯ ፡-፱)።
ክልኤቲ ክልኤ ፡-(ሴቶች) ዝኒ ከማሁ፤ ኹለት። በገቢር ጊዜ ክልኤ ቢል እንጂ ክልኤተ አይልም። ክልኤቲ አንስት። ክልኤቲ ኀጣይእ ፡-(ዘካ፭ ፡-፱። ሢራ፯ ፡-፰)። ነሥአ ክልኤ አንስትያ፤ ወወለዳ ሎቱ ክልኤ አዋልደ።
ክልኤት ክልኤቱ ፡-(ወንዶች) ኹለት ኹለቱ። ክልኤቱ ዕደው ዐርጉ ቤተ መቅደስ። ክልኤቱ እምኔክሙ። ትረክብ ክልኤተ ፅደወ ፡-(ሉቃ፲፰ ፡-፲። ማቴ፲፰ ፡-፲፱። ፩ነገ ፡-፲ ፡-፪)።
ክልእ ፡-(ዕብ ኬሌእ) ክልክል፤ የግዞት ቤት ዘበኛ ከልካይ የሚቆምበት። የቍጥር ስም፤ የጊዜ ቅጽል፤ ባንድና በሦስት መካከል ያለ ቍጥር ኹለት። ክልእ ክልአ፤ ኹለት ጊዜ። በበ እሕድ ወበበ ክልእ።
ክመ [1]፡-መቼም መች፤–ከመመ።
[2]፡-(ንኡስ አገ) መቼም፤ መቼም መች ፥ ዘወትር ፥ ድንት ዘላለም። እመሂ ትልህቁ እነ ክመ ውእቱ። ወአንተሰ አንተ ክመ። ወክመ ውእቱ እስከ ለዓለም ፡-(ኢሳ፵፮ ፡-፬። ዕብ፩ ፡-፲፪። ፲፫ ፡-፰)። ፪ኛም እንደ ዳእሙ ብቻ ይኾናል። አነ ክመ ወአልቦ እንተ ከማየ። ሕቀ ክመ ዘእምተንተና እገርየ። ሕያዋን ክመ ይባርኩከ ፡-(ሶፎ፪ ፡-፲፭። መዝ ፡-፸፪። ቀሌ)። ፫ኛም ባወራረድ ፍች ከቶ ፈጽሞ ይኾናል፤ ምስጢሩ መቼም መች ካለው ይገባል ፡-(ዕር፳ ፡-ቍ፺፯)።
ክሙ ፡-(ክምው ከ) የቅርብ ወንዶች ጠቃሽ፤ ዝርዝር፤ ከን ተመልከት።
ክሙሳስ ከሞሳስ ፡-ታናሽ ሣቅ፤ ፍግግታ ፥ የሠሐቅ ምልክት፤ ወይም ቅምሻ መፍካትና መንከትከት ሳይኖር ፡-(ዲድ)።
ክማም ፡-(ብ አክማም። ዐረብ) በቁሙ፤ የክንድ ልብስ እንደ እጅ ቤዛ ያለ ባለ መሽቀቅ ፥ ዐጭር ቍምጣ እጅጌ፤ ቀዳሽ ቄስ በቅዳሴ ጊዜ ሲለብሰው እጀ ሰፊውን ሰብስቦ ከምክሞ እጀ ጠባብ ቀሚስ የሚያስመስል። ወእምዝ ይልበስ አክማመ፤ ወይእስሮ በዝናር ፡-(ሥር ፡-ቅዳ)።
ክምር ፡-(ብ ክምራት፤ አክማር) በቁሙ፤ ቍልል። ከመ ክምረ እክል። ከመ ክምረ ሐሠር። በእትወተ አክማሪሁ ፡-(ሶፎ፪ ፡-፱። ሢራ፳፩ ፡-፱። መቃ ፡-ገ፱)። ያገዳ እኽል ሲኾን ክምሩ ፥ ዝራማ እንደ ማለት ዲራማ ይባላል፟፤ ልዑል ማለት ነው።
ክሞስ ኮሞስ ፡-(ዕብ ክሞሽ። ጽር ኻሞስ) ስመ ጣዖት ሞአባዊ፤ ከመ ሰብእ ከመ ብእሲ፤ ሰው የሚመስል ፡-(ዘኍ፳፩ ፡-፳፱። መሳ፲፩ ፡-፳፬። ፫ነገ ፡-፲፩ ፡-፭)።
ክሱብ ፡-(ባን ባት ስብት)
የተገዘረ ፥ ግዙር። ዘኢኮነ ክሱበ ፡-(ኩፋ ፡-፲፭)።
ክሡተ ፡-ገልጦ፤ ተገልጦ ፥ ግልጥ ኹኖ ፥ በግልጥ። ተናገረ ክሡተ። የዐስየከ ክሡተ ፡-(ዮሐ፯ ፡-፲፫። ማቴ፮ ፡-፬)።
ክሡት ፡-(ታን ታት ሥት) በቁሙ፤ የተገለጠ፤ ግልጥ ክፍት። ተወልደ እምኅቡእ ውስተ ክሡት። ወክሡት ገጽየ። ከመ መቃብር ክሡት ጐራዒቶሙ ፡-(ድጓ። ጦቢ፪ ፡-፬። መዝ ፡-፭)።
ክሣቶት ፡-(ዕብራ) የመከዳ ልብሶች እንደ ኪስ ያሉ። አንዱን ኬሤት ይለዋል። እለ ይለፍያ ክሣቶተ ፡-(ሕዝ፲፫ ፡-፲፰)።
ክሣድ ፡-(ዳት፤ ክሣውድ። ዕብ ኬሤድ፤ ካሥዲም፤ ስመ ነገድ። ዐረ ቂስወድ፤ ማዥራት የላይኛው በዦሮ አኳያ ያለው) ዐንገት፤ በራስና በመትከፍ መካከል ያለ ክፍል፤ ሥርና የዥማት ቦታ፤ የቀሚስ ዐንገትጌ፤ ዐነገን እይ። ክሣድእ ጽኑዕ፟። ክሣዳቲሆሙ። ላዕለ ክሣውዲነ ፡-(ዘዳ፴፩ ፡-፳፯። ፴፫ ፡-፳፱። ሰቈ፭ ፡-፬)።
ክሳድ ፡-ዐንገት፤–ከሥዶ ከሠደ።
ክስበት ፡-መግዘር፤ መገዘር ፥ ግዝረት። ወአልቦ ክስበተ መዋዕል ፡-(ኩፋ ፡-፲፭)።
ክሥተት ፡-መግለጥ፤ መገለጥ ፥ አገላለጥ ፥ ግልጥነት። ክሥተተ ኀፍረቶን ፡-(ቀኖ ሎዶቅ)። በቁሙ፤ የያሬድ ድርሰት በታላቅ በዓል ቀን የሚባል።
ክሥዳ ፡-(ዳት) በቁሙ፤ ዥማት ያንገትና የግር የሽንጥ ፡-(ዐማርኛ)።
ክረምት ከረም ፡-(ብ፤ ክራማት) በቁም፤ ዝናም፤ የዝናም ወራት ፥ በጸደይና በመፀው መካከል ያለ ክፍለ ዓመት ፥ ከሠኔ ፳፭ ፡-እስከ መስከረም ፳፭። ያስተዴሉ ክረምተ ለምድር ዘያበቍል ሣዕረ ውስተ አድባር። ቀስተ ደመና ዘክረምት። ዝናመ ክረምት። በክረምት ወበሐጋይ። ክረምት ወመፀው ፡-(ድጓ። ቅዳ ፡-ግሩ። ኢዮ፴፯ ፡-፭። ዘካ፲፬ ፡-፰። ኩፋ ፡-፪)። በክረምት ፈንታ አክራም ይላል፤ ስሕተት ነው፤ ከንትሮስን እይ።
፡-ዓመት ዘመን፤ ዕድሜ። ዕጐልት እንተ ሠለስቱ ክረምታ። ወየአክል ሠላሳ ክረምቱ። በሠላሳ ክረምት። ዘአብዝኀ ክራማተ። ሰብዓ ክራማት ፡-(ኢሳ፲፭ ፡-፭። ሉቃ፪ ፡-፵፪። ቅዳ ፡-ዲዮ። ኢዮ፴፪ ፡-፰። መዝ ፡-፹፱)። በክራማት ፈንታ አክራም ይላል፤ የከረምና የከርም ብዢ ነው ፡-(ስንክ ፡-መስ፩። ጥር፮። አርጋ ፡-፭)።
ክሩይ ፡-(ያን ያት ሪት) የተማሰ፤ የተቈፈረ ቍፍር።
ክርስቱን ፡-የከረሰተነ ፥ ክርስቲያን የኾነ፤ ጥሙቅ። ዘይሜህር አሐደ ገጸ ኢጥሙቅ ወኢቅቡዕ ወኢክርስቱን ውእቱ ፡-(መጽ ፡-ምስ)።
ክርስቲሎቤ ፡-ዝኒ ከማሁ፤ ወምስሌሁ አሐዱ። ማርያም ዕንቍየ ክርስቲሎቤ ፡-(ደራሲ። ራእ፳፩ ፡-፳። ስንክ ፡-ግን፰)።
ክርስቲያናዊ ፡-(ዊት) ክርስትና ያለው፤ የክርስቲያን ወገን። አንሰ አረማዊ እንዘ ክርስቲያናዊ በስም። ብእሲት ክርስቲያናዊት ፡-(ቅኔ። ስንክ ፡-ሠኔ፲፱)።
ክርስቲያን ፡-(ናት) በቁሙ፤ ጥሙቅ፤ ቅቡዕ ቅቡዓዊ፤ መሲሓዊ። ላንድም ለብዙም ይኾናል፤ እንደ ሰበእ ውስጠ ብዙ ነው። ተሰምዩ አርድእት ክርስቲያነ። ወኮኑ አበዊሁ ክርስቲያነ ፡-(ግብ፲፩ ፡-፳፮። ስንክ ፡-ነሐ፭)።
ክርስትና ፡-በቁሙ፤ ክርስቲያንነት። ዘተሐበየ ውሉዶን በክርስትና። ወአጥመቅዎ ጥምቀተ ክርስትና። ክሕደ ክርስትናሁ ፡-(ፍ ፡-ነ ፡-፭። ስንክ ፡-ጥቅ፲፭። ጥር፮)።
ክርስቶሳዊ ፡-(ዊት ውያን ያት) የክርስቶስ፤ ሕግ ሥርዐት፤ ወገን ደቀ መዝሙር፤ የክርስቶስ ገንዘብ ማናቸውም ኹሉ። ስብከት ክርስቶሳዊት። ንጉሣውያን ወአኮ ክርስቶሳውያን ፡-(ፊልክ ፡-፵፩። መጽ ፡-ምስ)።
ክርስቶስ ፡-(ጽር ኽሪስቶስ) የሹመት ስም፤ የተቀባ ቅቡዕ፤ እንደ አሮንና እንደ ዳዊት ተመርጦ ተቀብቶ የተሾመና የነገሠ። መቀባትም ለሦስት ሹመት ነው፤ ካህንና ንጉሥ ነቢይ ለመኾን። እሊህን ሦስቱን የሚሾም ሰው መዠመሪያ ከሕዝብ ይመረጣል፤ ፪ኛ ከካህን ከነቢይ በተቀደሰ ዘይት ይቀባል፤ በተቀባም ጊዜ የሹመቱን ሥራ የሚያስፈጽም ሀብት ሥልጣንና ችሎት ያድርበታል፤ ይህ ለኹሉ ነው ፡-(ዘፀ፳፬ ፡-፯። ዘሌ፬ ፡-፫። ፩ነገ ፡-፲፮ ፡-፲፩–፲፫። ፫ነገ ፡-፩ ፡-፴፱)። ለጌታችን ለመድኀኒታችን ለሥግው ቃል ግን ቀቢውና ሿሚው ፈጣሪ እንጂ ምድራዊ ፍጡር ስላልኾነ ግዙፍ ቅባት የለውምና፤ በዘይቱ ፈንታ መንፈስ ቅዱስ ቅብዕ ይባልለታል። ኢየሱስ ዘእምናዝሬት ዘቀብዖ እግዚአብሔር መንፈሰ ቅዱሰ ወኀይለ ፡-(ግብ፲ ፡-፴፰)። ከሕዝብ እንደ መመረጥ ፥ የኛን ባሕርይ ነሥቶ፤ ናሁ ቍልዔየ ዘኀረይኩ። ወአልዐልኩ ኅሩይየ እምሕዝብየ መባል ነው ፡-(ኢሳ፵፪ ፡-፩። መዝ ፡-፹፰)። ተቀብቶ እንደ መሾም ፥ መንፈስ ቅዱስን ተቀበሎ ካህን ፥ ንጉሥ ፥ ነቢይ ሐዋርያ መኾን፤ ክርስቶስ ፥ ዳግማይ አዳም ፥ ምሉአ ጸጋ ቀዳሜ ጸጋ ፥ በኵረ ልደት ለኵሉ ፍጥረት መባል ነው ፡-(ኢሳ፲፩ ፡-፪)። የሱስ ዐማኑኤል በተዋሕዶ የወጣለት የተጸውዖ ስም እንደ ኾነ ፥ ክርስቶስም የተቀብዖ ስም ነው። በባሕርዩ ቅባትና ሹመት ፪ኛ ልደት የማይሻ ቃል ፥ ዳግመኛ መወለድ ስለሚሹ ስላዳምና ስለ ሔዋን ልጆች፤ ዮም ወለድኩከ ተበሎ በኵረ ልደትና በኵረ ስም ዳግማይ አዳም ይኾን ዘንድ፤ ያው ግን በወልድነቱ ውሉድ ፥ በቅቡዕነቱ ቅቡዓን ክርስቲያን ለማሰኘት ፥ ሰው ኹኖ ቢቀባ ክርስቶስ ተብሏል ፡-(ዳን፬ ፡-፳፭። ማቴ፩ ፡-፲፮)። ኢይጽሕቅ ቅብዐተ በህላዌሁ፤ አላ በሥምረቱ ተሠጊዎ ነሥአ ቅብዐተ። እስመ በዘተሰብአ ተቀብዐ ፡-(ቄር)። ወተሰምየ ክርስቶስሀ በእንተ ዘተቀብዐ ምስሌነ ከመ ሰብእ ከመ ቃለ ዳዊት ዘይቤ በእንተ ክርስቶስ፤ አፍቀርከ ጽድቀ ወዐመፃ ጸላእከ፤ በእንተ ዝ ቀብዐከ እግዚ አምላክከ በዘይተ ፍሥሓ እምኵሎሙ እሊኣከ እለ እሙንቱ ሱቱፋኒከ፤ ወለሊሁ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ ፡-(ሃይ ፡-አበ ፡-ቄር)። ዘይተ ፍሥሓ ያለውን መንፈስ ቅዱስ ብሎ ተረጐመው፤ ሀብትነትና ቅብዕነት የርሱ ነውና። መንፈስ ቅዱስን ዐሎ ብለው ወልድ ቅብዕ የሚሉ ሰዎች ግን ፥ የተሰብአንና የተቀብዐን ምስጢር እንዳውጣኪ ቀላቅለው ደባልቀው ፥ ክርስቶስ ማለት ከ፪ አካል ፩ አካል ፥ ከ፪ ባሕርይ ፩ ባሕርይ የኾነ ፥ በተዋሕዶ የከበረ ዋሕድ ማለት ነው ብለው ፥ ተቀብዐን ተዋሐደ እያሉ አለቋንቋው አለንባቡ ፥ አለስልቱ አላገባቡ ይፈቱታል፤ ቀብዐንና ዋሐደን ተመልከት። ሥግው ቃል በሥግውነቱ ፥ መንፈስ ቅዱስን አልተቀባም ፥ ሀብታተ መንፈስን አልተመላም ፥ ጸጋ አልተቀበለም ፥ በመንፈስ ቅዱስ ቅብዕነት ክህነትና መንግሥት አልተሾመም ፥ የሰውነት ክብር አልከበረም ማለት፤ ሐሰትነቱ ሰማዩም ሰማይ ፥ ምድሩም ምድር አይዶል እንደ ማለት ያለ ነውና፤ እሊህንም ስሞሰ ለክርስቶስ ኢያእመሩ ወዘኢይደሉ ይሜህሩ። እለሰ የአምኑ ርቱዐ ይሜህሩ ከመ በሥጋሁ ተቀብዐ። እስመ ክርስቶስ ብሂል ቅቡዕ ብሂል። ወእፎ ይሰመይ ክርስቶስ ዘኢተቀብዐ ብሎ ቅዱስ ቄርሎስ ነቅፏቸዋል፤ ሐዋርያውም ዘልፏቸዋል ፡-(፩ ፡-ዮሐ ፡-፪ ፡-፳፪)። በብሉይ በሐዲስ በሊቃውንት ዘይት ዘይትን ተቀባ እንዳይባል ኹሉ ፥ ወልድም ርሱው ራሱ ቅብዕ ኹኖ ወልድን ተቀባ አልተባለምና፤ ወልድ ቅብዕ ማለት እንደ ንስጥሮስ ባህል ተዋሕዶን ኅድረት ፥ ወልድ ዋሕድን ኹለት አሰኝቶ ፥ ክርስቶስ መባልን ለሥጋ ብቻ አከናንቦ ሰጥቶ ቃልን ክርስቶስ ከመባል ከመሲሕነት ያወጣዋል። ቅብዕና ቅቡዕ ኅዳሪና ማኅደር ፥ ጥሬና ቅጽል ፥ መንፈስና ቃል ስለ ኾኑ በስምና በግብር የተለዩ ፪ ዐይነት ቃሎች ፥ ፪ ልዩ አካሎች ናቸውና፤ እንኳን በግእዝ በማንም ቋንቋ አንድ ሊባሉ ባንድ ስም ሊጠሩ አይቻልም፤ አፍንጫ እንደ መላስ ወይም ባንዲት ቆብ ውስጥ ፪ ራስ እንደ ማግባት ነው። ወልድ በተዋሕዶ ፩ አካል ፩ ልጅ ፥ ፍጹም አምላክና ፍጹም ሰው ኹኖ በቀባዒነት ከአብ ጋራ ፥ በተቀባዒነት ከኛ ጋራ ፩ነት ስላለው ቀባዒና ቅቡዕ ቢባል እንጂ ፥ እንደ መንፈስ ቅዱስ ቅብዕ አይባልም፤ አብ ቅብዕ እንዳይባል።
ክርስጵራስስ ፡-(ጽር ኽሪሶፕራሶስ) የዕንቍ ስም፤ ቅጠልማ ዕንቍ ፡-(ራእ፳፩ ፡-፳)።
ክርታስ ፡-(ሳት። ጽር ኻርቲስ) በቁሙ፤ ካርት ካርታ ፥ ወረቀት የሚቈረጥና የሚታፈፍ ፥ ቍርጥ ነገር የሚጣፍበት ነዶው ፥ ወይም የተጣፈበት፤ ወረቀን እይ። ንሣእ ክርታሰ ወጸሐፍ ኵሎ። አምጽአ ክርታሰ ወማየ ሕመት። ጦማረ ክርታስ። እሉ ክርታሳት ፡-(ቀሌ። ተረ ፡-ባሮ። ኢሳ፰ ፡-፩። ስንክ ፡-ጥር፲፮)። ተጠውመ ከመ ክርታስ። አብጽሐ ለነ ክርታሰ መጽሐፍክሙ። ኢታርእዮሙ ዘንተ ክርታሰ ዘጸሐፍኩ ለከ። ወጸሐፉ አስማቲሆሙ ውስተ ሠለስቱ ክርታሳት ንኡሳት ፡-(ራእ፮ ፡-፲፬። ተረ ፡-ቄር፲፭። ቀሌ። ስንክ ሚያ፫)።
ክርናዕ ኵርናዕ ፡-(ዓት) ክርን፤ የእጅ ጕልበት ማጠፊያው ሹሉ፤ ወይም መካከሉ ከክርን እስከ መዳፍ ባንድነት። ኵርናዐ እድ። ውስተ ኵርናዓቲሃ ፡-(ሕዝ፲፫ ፡-፲፰። ስንክ ፡-መጋ፳)። በመንጋጋ ፈንታ ጥረስ እንደ ማለት ኵርናዓት ይላል፤ የመላሽ ስሕተት ነው ፡-(ዮኤ፩ ፡-፮)።
ክርዕ ፡-ክርዓ፤ ፡-(ብ ክራዕ፤ ክርዓት። ዕብ ኬሬዕ። ሱር ካርዓ። ዐረ ኩራዕ) ጕልበት ፥ የእግር ማጠፊያ መቃጠፊያ፤ ከጕልበት እስከ ቍርጭምጭሚት ያለው ክፍል።
ክርዝ ተክሪዝ ፡-ስብከት ዐዋጅ፤ ሢመት ቅዳሴ ቡራኬ። አንበረ እዴሁ ሊቀ ጳጳሳት ዲበ ርእሰ ፍሬምናጦስ ወጸለየ ላዕሌሁ ጸሎተ ተክሪዝ ዘሢመተ መጥሮጶሊስ። ኤጲስቆጶስ ብዉሕ ሎቱ ከመ ይስፋሕ እዴሁ ለተክሪዘ ቀሳውስት ወዲያቆናት ፡-(መጽ ፡-ምስ ፡-ገ፵፰። ፫፻፳፮)።
ክርየት ፡-(መከራየት፤ ክራይ) መቈፈር፤ ፡-(ጥቈ) መቈፈር፤አቈፋፈር ቍፈራ ቍፋሮ። ወለእመ ተረክበ ሰራቂ ውስተ ክርየተ ቤት ፡-(ፍ ፡-ነ ፡-፵፯ ፡-፪)።
ክርዱድ ፡-(ዳን ዳት ድድ) የከረደደ የሻከረ፤ ከርዳዳ ሸካራ መጥፎ። ክርዱዳነ ልብ ወክርዱዳነ ኅሊና ወክርዱዳነ ንባብ ወክርዱዳነ ትምህርት እለ ይትካሐዱ ትንሣኤ ሙታን ፡-(መጽ ፡-ምስ)።
ክርዳድ ፡-በቁሙ፤ እንክርዳድ፤ ክፉ ዐረም ከስንዴ ጋራ የሚበቅል፤ ፍሬው ከዳቦ ከጠላ ሲገባ ራስ የሚያዞር የሚያንከረድድ መራራ ሸካራ፤ የክፉ ትምርት ምሳሌ። ፪ኛም ሥሩና ምንጩ ገሪድ ስለ ኾነ ፥ አንዳንድ መጽሐፍ በክርዳድ ፈንታ ግርዳድ ይላል ፡-(ኢዮ፴፩ ፡-፵። ማቴ፲፫ ፡-፳፭–፴)። ክርዳድ ዘያውዕይዎ በእሳት። ዲበ ሥርናይ ኢትኅድጎ ለክርዳድ ይብቍል። በኵረ መላኪ ይምላኅ ክርዳደ እምሰማይ ወረደ። ክርዳድ ወሦክ። ስቴ ክርዳድ ፡-(ቀሌ። ኪዳ። ድጓ። ፊልክ ፡-፪፻፴፮። መጽ ፡-ምስ)።
ክበብ ፡-(ባት) በቁሙ፤ ዘውር ዙሪያ፤ ክብነት። ይቁሙ ካህናት ክበቡ ለምዉት። ክበቡ ከመ ፀሓይ ፡-(ግንዘ። ሔኖ፲፬ ፡-፲፰)።
፡-ኩብ፤ ኳስ። ክበበ አፍትልት ፡-(ታሪ ፡-አኵ)።
፡-ክበብ ያለው ገንዘብ ብር፤ የገንዘብ ቍጥር። የሐስብ ሎቱ ካህን ክበበ ሤጡ ፡-(ዘሌ፳፯ ፡-፳፫)። በክበብ ፈንታ መክብብ ይላል ፡-(፩ዜና ፡-፳ ፡-፮)።
ክበድ ፡-(ዳት)
፤ መክበድ
፣ አከባበድ
ክብደት ፤ ክባድነት ፤ ብዛት። ክበደ ጾርነ አቅልል። ክበዱ
ለጸባሕት ፤
ክበደ ንዋም። ክበደ ቅኔ። ክበዳ ለስብሐቲክሙ። አልቦ ዘይክል ጸዊረ ክበዶሙ ኢአድባር ወአውግር
ወኢቈላት (መዋሥ። ስንክ ፡ የካ፯። ቅዳ ፡ ያዕ። ፪ዜና ፡ ፲ ፡ ፬። ስንክ ፡ ግን፪። ዮዲ፯ ፡ ፬)። ሸክም ፤
ሐሳብ ፥ ሐዘን ፥ ከባድ ነገር። ኢይወዲ
ላዕሌክሙ ክበደ። ለምንት ይከውን ገብርከ ክበደ ላዕእ
እግዚእየ። ግድፍ እምላዕሌከ ክበደ ዕጓለ መሕያው። ከመ
ያቅልል እምኔሁ ክበዳተ (ራእ፪ ፡ ፳፬። ፪ነገ ፡ ፲፱ ፡ ፴፭። ሱቱ ፡ ዕዝ፲፬ ፡ ፲፪። ፊልክ ፡ ፻፷፭። ዕብ፲፪ ፡ ፩)።
፤ ቤት ግንብ ፤ በቤት ያለ ገንዘብ ፤ ብዙ ብዕል ክብር ወርቅ ብር ፤ ሰባራ
ሥንጥር ፣
ደጃፍ የመለሰው ማጀት የጐረሠው
የቤት ዕቃ። እግዚየአምር ክበዲሃ። ወትትካፈልዎ ለክበዲሃ። ማኅፈደ ክበዲከ። አስጠመ ኵሎ
ክበዲሃ (መዝ
፡ ፵፯። ፻፳፩። ሰቈ፪ ፡ ፭)። ርጉዝ ከብት ፤ ላም ባዝራ። የሐር ገመድ የበቅሎ ክበድ እንዲሉ (ዐማርኛ)።
ክቡስ ፡-(ሳን ሳት ብስት) የተከበሰ፤ ክብስ ክብስብስ፤ ጌጥ ወዳድ።
ክቡር ፡-(ራን ራት ብርት) በቁሙ፤ የከበረ፤ የተከበረ፤ የተወደደ ውድ። ብእሲ ክቡር፤ ዕንቍ ክቡር። ክቡረ ስም፤ ክቡረ ሤጥ። ዕደው ክቡራን። አልባስ ክቡራት። ሀገር ክብርት ፡-(ሢራ፵፬ ፡-፩። አርጋ ፡-፪። ሕዝ፳፮ ፡-፲፯)።
ክቡብ ፡-(ባን ባት ብብት) የተከበበ፤ ክብ እንክብል፤ ድንብልብል። እስመ ምድር ክቡብ ከመ ኮራ። ከመ ዐይነ ማኅተም ክቡብ። አእባን ክቡባት ወልሙጻት ፡-(አዋል። ተረ ፡-ቄር፰)። በክቡባት ፈንታ ከበብት ይላል፤ ስሕተት ነው ፡-(ጊ ፡-ወ ፡-ሐ ፡-ገ፲፬። ሄርማ ፡-ገ፲፫። ፹፩)።
ክቡታዊ ፡-የውስጥ የልቡና፤ ረቂቅ መንፈሳዊ። ሥርዐት ክቡታዊ ፡-(ፊልክ ፡-፫)።
ክቡት ፡-(ታን ታት ብት) የተሸሸገ ሽሽግ፤ ክብት ስውር ድብቅ። ጥበብሰ ክቡት ወመዝገብ ዘኢያስተርኢ። ኅቡእ ወክቡት። ክቡተ ተአምር፤ እስመ ውስተ ብርሃን ሀሎከ ፡-(ሢራ፵፩ ፡-፲፬። ፩ቆሮ ፡-፪ ፡-፯። ቅዳ ፡-ሐዋ)።
ክቡደ መዝራዕት ፡-ጡንቻም እጀ ወፍራም፤ ክንደ በርዳዳ።
ክቡዳነ አቅርንት ፡-ቀንዳሞች፤ ቀንደ ትልልቆች ፡-(መዝ ፡-፵፬)።
ክቡዳነ ጾር ፡-ሸክም የከበዳቸው፤ ሐማሎች።
ክቡድ ፡-(ዳን ዳት ብድ) በቁሙ፤ የከበደ ከባድ፤ ጥኑ ብርቱ፤ ክቡር ታላቅ፤ ዐያሌ እጅግ ብዙ። ነገሩ ለአብድ ከመ ጾር ክቡድ። ሕማም ክቡድ። ብፃው ክቡድ። ብእሲ ክቡድ። ተኣምሪሁ ክቡድ ፡-(ሢራ፳፩ ፡-፲፯። ፴፬ ፡-፪። መጽ ፡-ምስ። ፩ነገ ፡-፬ ፡-፲፰። ስንክ ፡-ነሐ፲፬)።
ክብሶ ፡-(ብ ከባስው፤ አው ክብሳት) ክብስ ጠጕር፤ ክብሳት። የራስ የጠጕር ክባስ፤ በስተላይ የሚኾን ጌጥ ሽልማት፤ ቀጸላ ሠርመዲ ዐይነ ርግብ። ውስተ መካነ ሰርጕ ዘክብሶ ሥዕርታ ወደየት ሐመደ። ክብሶሆን ወአልሴሲሆን ዘሜላት ፡-(አስቴ፬ ፡-፲፯። ኢሳ፫ ፡-፳)።
ክብረ ነገሥት ፡-የመጽሐፍ ስም፤ ያኵስሞች መጣፍ፤ ንቡረ እድ ይሥሐቅ በላስቶች ዘመን የደረሰው፤ ወይም ከዐረብ የመለሰው፤ የጽላተ ሙሴን አመጣጥ የአኵስምን ልዕልና፤ የነገሥታቷን ክብር ከሰሎሞን መወለዳቸውን አምልቶ አስፍቶ የሚናገር።
ክብረት ፡-በቁሙ፤ መክበር፤ አከባበር፤ ከበሬታ። ውድነት፤ ክቡርነት።
ክብሪታዊ ፡-የዲን ዐፈር ጭቃ፤ የዲን ውሃ። ይንሣእ ሙዳየ ልሕኵት ወይደይ ውስቴቱ ማየ መሪረ ክብሪታዊተ ወይንሣእ መሬተ ፡-(ፍ ፡-ነ ፡-፳፬ ፡-፮። ዘኍ፭ ፡-፲፯ ፡-፲፰)።
ክብሪት ፡-(ዐረ ኪብሪት። ሱር ካብሪታ። ዕብ ጐፍሪት) በቁሙ፤ ዲን የእሳት ዐፈር እሳታዊ ጭቃ፤ ዐይነቱ ብጫ ክርፋታም ፡-(መቃ ፡-ገ፪)።
ክብራታን ፡-ስመ ሀገር በምድረ እስራኤል ያለች አንዲት ገጠር። ፡-(ኩፋ ፡-፴፪)። አንዳንድ መጣፍ በክብራታን ፈንታ ኬብሮን ይላል፤ ባለብሉዮችም ክብራታንን ኬብሮን ብለው ይፈቱታል። በዕብራይስጥ ግን፤ ሔብሮንና ክብራታን ልዩ ነው።
ክብር ፡-(ራት) በቁሙ ልዕልና ላቂያ ብልጫ፤ ሹመት ሽልማት፤ ታላቅነት፤ ኀይል ብዕል፤ ብዙ ገንዘብ። ወድቀት እምክብራ፤ ትላሑ እምክብራ። በእንተ ክብረ ዘመዱ። ኵሉ ክብሩ ለሰብእ ከመ ፍሬ ሣዕር። መንግሥታተ ዓለም ወክብሮሙ። ዘጌሠ ድኅሬሆን ለክብራት ይጐይያሁ ፡-(ቀሌ። ስንክ ፡-ጳጕ፩። ኢሳ፵ ፡-፮። ማቴ፬ ፡-፰። ማር ፡-ይሥ)።
ክብርና ፡-ክቡርነት። በቁሙ፤ የሴት ልጅ ክብር፤ ማኅተመ ድንግልና።
ክብተት ፡-(ላ ጥ) መሸሸግ፤ ሽሸጋ፤ ሽሽግነት። ክብተት ዘኢየኀልቅ ፡-(ራእ ፡-ሲኖ)።
ክብደ ሑረት ፡-ክብደ ሑረት፤ ዳተኛ ዝግተኛ፤ ቀርሳሳ ፡-(ግብ፳፯ ፡-፯)።
ክቦ [1]፡-ኵበት፤–ከበወ።
[2]፡-ኵበት የደረቀ እበት፤ ፍሕምና ብርሃን የሌለው። ሐመደ ክቦ ፡-(ኵፋ ፡-፳፰)። ከበተንና ለከወን እይ።
ክቱፍ ፡-(ፋን ፋት ትፍት) የታሰረ ፥ እስር። በሐብለ ማእሰር ክቱፍ ፡-(ደራሲ)።
ክታብ ፡-(ባት) መጽሐፍ፤ መልእክት፤ ደብዳቤ ጦማር። ተብህለ በክታበ ዐረቢ። ዘየሐውር ኀበ ንጉሥ ዘእንበለ የአዝዞ ዘይሠይም በቃሉ ወበክታቡ። ጸሐፈ ሎቱ ክታበ በእዴሁ፤ ከመ ይትአዘዙ ሎቱ ኵሎሙ መኳንንት። ክታበ መልእክት ፡-(አዋል። ፍ ፡-ነ ፡-፭ ፡-፱። ስንክ ፡-የካ፱። መስ፯)።
፡-በቁሙ፤ የጠንቋዮች ጥፈት ፥ አስጠንቋዮች የሚያነግቱት፤ ዐሸን ክታብ፤ የደረት መጣፍ። ፡-(ተረት) ማተብና ዐንገት፤ ክታብና ደረት። እለ ይጽሕፉ ክታባተ በምክንያተ ፈውስ ፡-(ፈ ፡-መ ፡-፲፭)።
ክታን ፡-(ዕብ ኪታን። ሱር ኬታና። ዐረ ከታን) ተልባ ፥ የተልባ እግር ፈትል ፥ ልብስ። ለቢሰ ክታን። ልብሰ ክታን። መዋጥሐ ክታን ፡-(ፈላስ ፡-ገ፷፯። አፈ ፡-ተ፳፰። ደራሲ)።
ክትመት ፡-ምልክት፤ መለዮ። ትሕትና ውእቱ ክትመተ ሐራዌ ክርስቶስ ፡-(ፊልክ ፡-፻፶፪)።
ክኑስ ፡-(ሳን ሳት ንስት) የታከበ ፥ የተሰበሰበ፤ ክምቹ።
ክናሴ ፡-አንድነት፤ ሱታፌ ፥ ኍባሬ። አመ ገበርከ በታቦር ምስለ ሐዋርያት ክናሴ። የሀብዎ ንስሓሁ ተስዐተ ሱባዔ ይጹም፤ ወእምድኅሬሁ ይረክብ ክናሴ ምስለ ሕዝብ መሀይምናን ፡-(ስንክ ፡-ነሐ፲፫። ቀሌ)።
ክናት ፡-(ቅናት። ዕብ ክናት) ዐጋዥ ረዳት፤ ባልንጀራ።
ክን ፡-የቅርብ ሴቶች ዝርዝር፤–(ከ ኪ ክሙ) ክን።
ክንሰት ፡-ዝኒ ከማሁ፤ መሰብሰብ፤ መሳተፍ፤ አንድነት። ምስለ እለ ከመ ዝ የአምኑ አኅብር ክንሰተ ፡-(መጽ ፡-ምስ)።
ክንፊፍ ክነፊፍ ፡-ክንፈ ክንፍ፤ ክንነ ክነፍ፤ የጫፍ ጫፍ ፥ የመጨረሻ መጨረሻ ፥ የማእዝን ማእዝን ፡-(ሔኖ፴ ፡-፫)።
ክንፍ ፡-(ብ ክነፍ፤ አክናፍ። ዕብ ካናፍ። ሱር ኬንፋ፤ ጌፋ። ዐረ ከነፍ፤ ጅናሕ) በቁሙ፤ የአዕዋፍ ገላ ፥ መብረሪያቸው፤ የመርከብ ሸራ፤ ዐጽቅ እጅ። መኑ ይሁበኒ ክንፈ ከመ ርግብ። ንስር ዘዐቢይ ክነፊሁ። አሕማር እለ ቦን ክንፍ። ለምጽዋት ባቲ አክናፍ ዘወርቅ ፡-(መዝ ፡-፶፬። ሕዝ፲፯ ፡-፲፯። ኢሳ፲፰ ፡-፩። አፈ ፡-ተ፴፪)። ለባሕር ዓሣም ይነገራል። ፡-(ዘሌ፲፩ ፡-፱–፲፪)።
፡-ጫፍ ዳርቻ ፥ ማእዝን፤ የልብስ የቦታ። ከሠተት ክንፋ። ወተዐቍሮሙ በክነፊከ። ክንፈ ምድር። እምአርባዕቱ ክነፊሃ ለምድር ፡-(ኩፋ ፡-፴፫። ሕዝ፭ ፡-፫። ኢዮ፴፯ ፡-፪። ኢሳ፲፩ ፡-፲፪)።
ክዑብ ፡-(ባን ባት ዕብት) የተካበ፤ ዕጥፍ ድርብ ፥ ንብብር። ልብሰት እንተ ክዑብ ፈትሉ። ክዑበ ከለሜዳ። ነት ክዑብ። ሜላት ክዑብ። በዓሎ ክዑበ ከመ ይግበሩ ፡-(ሢራ፵፭ ፡-፲፩። ዲድ ፡-፫። ዘፀ፳፭ ፡-፬። ፴፮ ፡-፱። ስንክ ፡-ጥር፩)።
ክዒብ ቦት ፡-(ከዐበ ይክዕብ ይክዐብ) መካብ መደርደር፤ ማነባበር አንዱን ባንዱ ላይ ማኖር። ማጠፍ መደረብ ዕጥፍ ድርብ ማድረግ። መጽሐፍ ግን በከዐበ ፈንታ አካዕበተ ፥ አመክዐበ ይላል።
ክዒው ዎት ፡-(ከዐወ ይክዑ ይክዐው። ወክዐ) ማፍሰስ መከንበል መድፋት፤ መገልበጥ መዘርገፍ፤ መርጨት መፈንጠቅ፤ የፈሳሽና የርጥብ ፥ ለደረቅም ይኾናል፤ ነገረን እይ። ደመና ይክዑ ዝናመ ውስተ ምድር። ፈለግ ይክዑ ማየ ውስተ ባሕር። ለክዒወ ደመ ሰብእ። ከዐወ ዘርዐ ውስተ ምድር። አማዑተ ከርሡ ከዐወ ከመ ፀፍዕ ዘላሕም። ከዐዉ ልበክሙ ቅድሜሁ። ምስለ ገዐር ወክዒወ ልብ ፡-(መክ፲፩ ፡-፫። ሔኖ፸፯ ፡-፭ ፡-፮። ኩፋ ፡-፲፩። ፵፩። ስንክ ፡-ነሐ፲፰። መዝ ፡-፷፩። አፈ ፡-ተ፴፩)። እክዑ እምነ መንፈስየ ዲበ ኵሉ ዘሥጋ። ከዐወ ላዕሌሁ ምሕረቶ። እክዑ ቅድሜሁ ስእለትየ ፡-(ዮኤ፫ ፡-፩። ዘፍ፴፱ ፡-፳፩። መዝ ፡-፻፵፩)። ናብልል ናንቀልቅል በማለት ፈንታ ንክዐው ይላል፤ የመላሽና የጣፊ ስሕተት ነው፤ በለለን እይ ፡-(ዘፍ፲፩ ፡-፯። ኩፋ ፡-፲)።
ክዕው ፡-(ዋን ዋት፤ ውት ዑት) የፈሰሰ ፈሳሽ፤ የተዘረገፈ፤ ብዙ ፍጹም። ማይ ክዕው። ሰብእ ክዕው ከመ ማይ። እንዘ ክዕው አማዑቱ። በመዐት ክዕው ፡-(መጽ ፡-ምስ። ደራሲ። መጽ ፡-ምስ። ሕዝ፳ ፡-፴፫ ፡-፴፬)።
ክዕወት ፡-መፍሰስ፤ ማፍሰስ አፈሳሰስ፤ ፈሰሴ ፈሰስ። ክዕወተ ደም። ከሠተት ክዕወተ ደማ ፡-(ሔኖ፺፬ ፡-፱። ዘሌ፳ ፡-፲፰)።
ክዋኔ ፡-(ንያት) [1]፡-መከወን፤ ፡-(ጥ ከ) መከወን፤ አከዋወን ክወና።
[2]፡-ክዋኔ፤ ፡-(ኩነት) መኾን፤ አኳኾን ኹነታ ተፈጥሮ፤ አናዎር ኑሮ። ምስጢሩ እንደ ህላዌ ነው፤ የባሕርይንና የተረክቦን ጾታ ያካልን ኵለንታ ያሳያል። አኀሥሥ እምጥንተ ክዋኔሃ። ገባሬ ክዋኔሁ። ይቤ ፎጢኖስ፤ ለፌ እማርያም ክዋኔሁ ለወልድ። ኅሊና ፍጡራን ይኄሌ አእምሮ ክዋኔሁ፤ ወባሕቱ ይስእን። አልቦ ማኅለቅት ለክዋኔሁ ፡-(ጥበ፮ ፡-፳፬። ፲፫ ፡-፭። መጽ ፡-ምስ። ፊልክ። ቅዳ ፡-ኤጲ)። የህላዌን ፍች እይ፤ ከዚህ ጋራ አንድ ነው።
ክዋን ፡-(ናት። አው ክዋኒት፤ ንያት) የደንጊያ ዐምድ፤ ሐውልት፤ ትክል ደንጊያ ቁሞ ተገትሮ የሚኖር። ዘአዘዝከ ክዋኒተ ወአእመንከ ሐዋርያተ፤ በመስቀልከ ረከብነ ሕይወተ። ወርእየ ክልኤተ ክዋንያተ አሐቲ በየማነ ቤት ወአሐቲ በፀጋመ ቤት፤ ወይቤ አግዚእነ ትሬእዩኑ አርኣያ ..ወተመይጠ ኀበ ክዋኒት ወይቤላ ..በጊዜሃ ቀነጸት ክዋኒት ወነበበት ከመ ሰብእ ፡-(መዋሥ። ስንክ ፡-ነሐ፴)።
ክዋው ፡-(ዋት) ቅለት፤ ውሸት ቅጥፈት። በጠዋይ ቃል ወበክዋው ነገር ፡-(መቃ ፡-ገ፳፫)።
ክዉል ፡-(ላን ላት ውልት) በኋላ ያለ፤ የተከተለ፤ ኋለኛ ደጀን።
ክዉስ ፡-(ሳን ሳት ውስት) የተካወሰ፤ የተናጠ የተናወጠ።
ክዩድ ፡-(ዳን ዳት ይድ) የተረገጠ የተጠቃ ጥቁ። ሕዝብ ቅቡጻን ወክዩዳን ፡-(ኢሳ፲፰ ፡-፪)።
ክዱን ፡-(ናን ናት ድንት) የተከደነ የለበሰ፤ ስውር ሽፍን። ክዱን እብን ዲቤሁ። ክዱን ብከ ዕበይከ። ክዱን ትምህርትነ ፡-(ዮሐ፲፩ ፡-፴፰። ቅዳ ፡-ዮሐ። ፪ቆሮ ፡-፬ ፡-፫)።
ክዳን ፡-(ናት) በቁሙ፤ መክደኛ መግጠሚያ፤ ልብስ ቀሚስ፤ መጐናጸፊያ ለሓፍ ምንጣፍ፤ መጋረጃ ድንኳን፤ ዳስ ጥላ ከለላ፤ ቤት ጐዦ፤ የሚሰውርና የሚሸፍን ኹሉ። ክዳነ ዐዘቅት። ዘቦ ክልኤ ክዳናት። ክዳን ዘሕብረ ዐስቅ። ትከድኖሙ ከዳነከ። ነሣ ክዳነ ወጠምዐ ውስተ ማይ። ክዳንከ ዘታሕተ ገቦከ። ክዳን በዘይትገለበቡ እምጠል ፡-(፪ነገ ፡-፲፯ ፡-፲፱። ሉቃ፫ ፡-፲፩። ዘፍ፴፯ ፡-፫። ሕዝ፭ ፡-፫። ፬ነገ ፡-፰ ፡-፲፭። ምሳ፳፪ ፡-፳፯። ኢሳ፬ ፡-፮)።
ክድነት ፡-መክደን መከደን፤ አከዳደን አለባበስ፤ ክዱንነት። የሌት ልብስ፤ ጭን ኀፍረት። ኢይክሥት ክድነተ አቡሁ ፡-(ኩፋ ፡-፴፫)።
ክፉል ፡-(ላን ላት ፍልት) የተከፈለ ፥ የተካፈለ ፥ የተከፋፈለ ፥ ክፍልፍል። ዘክፉል ጽፈሪሁ። እንዘ አሐዱ ክፍሉ ውስተ ብዙኅ ክፉል። ልሳናት ክፉላት ፡-(ዘዳ፲፬ ፡-፯። ጥበ፯ ፡-፳፪። ግብ፪ ፡-፫)።
ክፉእ ፡-(ኣን ኣት ፍእት) የከፋ ክፉ፤ የጠፋ ጥፉ፤ መጥፎ ፥ ብልሹ። አምሳለ ሕሡመ ወክፉአ ንጻሬ ፡-(አረጋ ፡-መል፲፬)።
ክፋር ፡-(ዕብራ) ገጠር፤ ታናሽ አገር ፥ ጥቂት መንደር የገበሮች ሰፈር።
ክፍለት ፡-መክፈል ፥ መከፈል ፥ አከፋፈል ፥ ክፍያ። ውእቱመ እግዚ ወሰብእ ዘእንበለ ክፍለት። ዘእንበለ ውላጤ ወኢክፍለት ፡-(ቄር ፡-ጰላ። ሃይ ፡-አበ)። ክፍል መክፈልት በማለት ፈንታ ከፍለት ይላል፤ አያሰኝም። በበ ክፍለቶሙ ለካህናት ፡-(፪ዜና ፡-፰ ፡-፲፬)።
ክፍላዊ ፡-ክፍላም ዕድላም፤ ክፍልነት ያለው። ሀኬት ክፍላዊ ፡-(ፊልክ ፡-፵፬)።
ክፍል ፡-(ብ ክፍላት፤ አክፋል) ቀመር፤ የቍጥር መደብ መክፈያ ማካፈያ። ዘወፅአ እምክፍል ፡-(አቡሻ ፡-፲፩)።
ክፍአት ፡-መክፋት፤ አከፋፍ ክፋት፤ ክፉነት መጥፎነት፤ ደግዳግነት፤ የመልክ የግብር። ኢይምህክ ልሑየ በእንተ ርእየቱ ወኢሕሡመ ኢይሜንን በእንተ ክፍአቱ፤ አላ ያስተጋብእ ኵሎ። ክፍኦተ አበሳ። ወክፍልቱ ለአዳም ይሢኒ እምኩሉ ፍጥረት በቅድሜሁ ፡-(ግንዘ። ማር ፡-ይሥ፰። ፴፭)።
ኰሓሊ ፡-(ሊት ልያን ያት፤ ሐልት) የኳስ የሚኵል፤ ኳይ ተኳሽ።
ኮለ ሐቅል ፡-ዕንጐት፤ የሽቱ ቅጠል በርሻ ባዝመራ ውስጥ የሚበቅል፤ አበባው ጥቍር፤ ፍሬው ታናናሽ፤ ዐረቦች ሉፋሕ የሚሉት። ሉፋሕና ትፋሕ አንድ መስሎ ስለ ታያቸው መላሾች ኮል ብለውታል፤ ተርጓሞችም እንኰይ ይሉታል፤ ዕንጐትን እይ ፡-(ዘፍ፴ ፡-፲፬ ፡-፲፭)። ይሰወጥ በአንፍየ ጼናክሙ ኮል። ቅብዐ ጽጌ ለአንፈ ኵሉ ዘይጼኑ ኮለ ፡-(ስንክ ፡-መስ፳፭። መጋ ፡-፲፯)።
ኮለ ወርቅ ፡-የወርቅ ትፋሕ፤ በትፋሕ አምሳል የተሣለ የተቀረጸ ፡-(ምሳ፳፭ ፡-፲፩)።
ኮለለ ፡-(ተቀ ግ) ተንኳለለ፤ ኮለል ኮለል ዱብ ዱብ አለ፤ የፍሬ የእንብ የደም አወራረድ፤ ለውሃም ይኾናል። የሞፈርንና ያባለ ዘርን ጫፍ ቋሩን ክርክሩን ኮለል ማለት ከዚህ የወጣ ነው።
ኮል [1]፡-(ብ አክዋል) የተክል ዕንጨት ስም፤ ትፋሕ ፍሬው ክብ እንክብል ሥጋማ፤ ሲያዩት ሲበሉት ደስ የሚያሰኝ፤ ቶሎ የማይደርስ የማይበስል ወደ ኋላ የሚል። ኮል ዘውስተ ዕፀወ ገዳም። ሰደቁኒ በአክዋል። እምኀበ ኮል አንሣእኩከ። ቅርፍተ ኮል ፡-(ማሕ ፡-፪ ፡-፫ ፡-፭። ፰ ፡-፭። መ ፡-ፈ)። ከወሎ፤ የደጋ ዕንጨት ኰሸሽላ፤ ቅጠሉን አህዮች ፥ ፍሬውን እረኞች ፥ አበባዉን ንቦች የሚወዱት፤ ማራም ማረ መልካም።
[2]፡-ትፋሕ፤–ከወለ።
ኮሞል [1]፡-(ላት) ስመ ዕፅ፤ ፍሬው የሚበላ የኮል ሱታፍ የተክል ዐይነት ዛፍ፤ ባለቅኔዎች ግን ለይተው ሸዬ ወይም እሼ ይሉታል። ፍችው ከመ ኮል አምሳለ ኮል ማለት ነው። ቀነውዎ ውስተ ሥጋሁ ምእተ ወኀምሳ ወሠለስተ ቅንዋተ ዲበ ዕፀ ኮሞል። ወሀለዉ ህየ ዕፀወ ኮሞል፤ ወሰገዱ ሎቱ ለእግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ፤ ወኮኑ ድኑናነ እስከ ዛቲ ዕለት ፡-(ስንክ ፡-መስ፲፩። ጥር፲፩። ግን፳፬)።
[2]፡-ስመ ዕፅ፤–ከወሞል።
ኮሞስ ፡-ስመ ጣዖት፤–ከመወ።
ኰሰረ ፡-(ዕብ ካሼር) አማረ ተከናወነ፤ ንጹሕ ጽሩይ ኾነ።
ኰሰኰስ ፡-(ብ ኰሳኵስ፤ ሳን) ዝንጕርጕር፤ ጠቃጠቆ። ዘኰሰኰስ ሕብሩ፤ ወዘኢኮነ ኰሰኰሰ። ወበግዕተ ላባ ድንግል ዘኢተአምር ተውሳከ ወለደት ኰሳኵሰ ሰብአ ወአምላከ። አምሳለ ወርቅ ይግበሩ ለኪ ኰሳኵሰ ዘብሩር። አፍራስ ኰሳኵሳን ፡-(ዘፍ፴ ፡-፴፪ ፡-፴፫። ቅኔ። ማሕ፩ ፡-፲፩። ዘካ፩ ፡-፰)።
ኰሰየ ፡-(የኰስሐ መንቲያ) ኳሸ፤ ኵሸት ቃል አወጣ፤ ፈጥሮ አስመስሎ ተናገረ፤ የቅኔ የግጥም ፥ የተረት የጨዎች። እገሌ ኳሽ ነው፤ ኵሸት ቅኔ እንዲሉ።
፡-ለየ ነጠለ ፥ ከፋፈለ፤ አጠፋ አበላሸ፤ ነቀፈ ካደ። ንከፍሎ ወንኰስዮ ለዐማኑኤል እምህላዌሁ ዘውእቱ ሕይወት። እለሰ ይብሉ ፥ አኮ ቃል ዘኮነ ሥጋ ወኢተወልደ በሥጋ እምብእሲት ይኰስይዋ ለአሚን። እመሰ ኰሰይነ ልደቶ ዘከማነ። ኰሰይካ ለሃይማኖት ፡-(ቄር ፡-እስት። ጰላ። ተረ)።
፡-ዐበረ ተባበረ፤ ተዛመደ አንድ ወገን ኾነ፤ በስም በግብር በርስት በነገድ። ቅሩቡ ዘይኰስዮ፤ ወእመኒ አልቦ ዘይኰስዮ ፡-(ዘሌ፳፭ ፡-፳፭ ፡-፳፮)። ኰሰየ በቤዘወ ፈንታ ገብቷል ፡-(ዘይኰስዮ) የሚቤዠው ዘመድ ማለት ነው።
ኰሲሕ ሖት ፡-(ኰስሐ ይኰስሕ ይኵሳሕ) መኵሳት፤ ማራት መቅዘን። በረዘንና ዘበለን እይ። ፋሲካ ዘቦቱ በሊዕየ እኰስሕ፤ ወሰትይየ እሠይን፤ ዳእሙ እውዕል ፋሲካ ሰማያዌ ዘአልቦቱ ኵስሕ ወኢሥንት። ተሀውከ ከርሡ ለአርዮስ፤ ወሖረ ኀበ ሙፃአ ኵስሕ ከመ ይኵሳሕ ወወፅአ አማዑቱ ፡-(አዋል። ስንክ ፡-ነሐ፲፰)። ከሳ ኰሰሰ ማለት ዐማርኛው ከዚህ የወጣ ነው። አንዳንድ መጣፍ በኰስሐ ፈንታ አኵስሐ ይላል፤ የጣፊ ስሕተት ነው። አኵስሑ እልኩ አዕዋፍ ውዑየ ውስተ አዕይንትየ። ከመ መዝበር ዘኵሉ ያኰስሕ ውስቴቱ። ነበረ ከመ ያኵስሕ ፡-(ጦቢ፪ ፡-፲። ኤር፲፱ ፡-፲፫። መጽ ፡-ምስ)።
ኰሣኵሥ ፡-ዝንጕርጕር፤–ኰሳኵስ።
ኰስተረ ፡-(ስሯ ግ) ኰሰተረ፤ ጠረገ ጥሩ አደረገ፤ ሰበሰበ ለማፈሥ፤ ቈረጠ ቈጠቈጠ። ኰስተሩ መካነ ጎልጎታ። ቀዲሐ ማይ ወኰስትሮ ኵስሐ አፍራስ። አዘዘ ይኰስትሩ ዐውደ ሀገር። ኵሉ ዕፅ ዘያስተሓምሙ ቦቱ ወይዋሕይዎ እንዘ ይኰሰትሩ ዐውዶ ፡-(ስንክ ፡-መጋ፲። ጥቅ፱። ዮሴፍ። አፈ ፡-ድ፳)።
ኰስታሪ መኰስትር ፡-የሚጠርግ የሚያጠራ፤ ጠራጊ። ኰስታሪተ ቤተ ክርስቲያን ፡-(አዋል)።
ኰስኰሰ ፡-(ዲቃ ወይም ተቀ ግ) ሻከረ፤ ኰሰኰሰ። ዝንጕርጕር ኾነ።
ኰረበ ፡-(ዕብ ካራብ፤ ሐራብ፤ ከረየ ነሠተ) ቈፈረ ዐረሰ፤ ናደ አፈረሰ። ዐበጠ ተነፋ፤ ተከረበ ኰረብታ ኾነ። ኰረብታ ድድ እንዲሉ፤ ድዳም ሲሉ።
ኰሪህ ሆት ፡-(ኰርሀ ይኰርህ ይኵራህ። ዐረ ከሪሀ። ዕብ ሀክሬሕ) ማስገደድ፤ በግድ መያዝ ማሠራት፤ አለውድና አለፈቃድ ማኖር። ትኰርህዎ ለነዳይ ፡-(ሔኖ፺፮ ፡-፰)።
ኮራ ፡-(ራት) [1]፡-ኵሬ፤ ምዕቃል የውሃ መቋሚያ መጠራቀሚያ። የውሃ ዕቃ ታናሹም ታላቁም፤ ጽዋ ጣሳ ምንዛህ ኵስኵስት። ኮራየ ዘብሩር ደይ ውስተ ሐስሉ ለዘይንእስ ወሤጠ እክሉሂ። ወይከውና ጻህራት ዘቤተ እግዚ ከመ ኮራት ፡-(ዘፍ፵፬ ፡-፪ ፡-፱። ኩፋ ፡-፵፪። ዘካ፲፬ ፡-፳)።
፡-ጋን ዝንግሪር፤ ማድጋ ፊቀን፤ እንስራ በርሚል ፣ የመሰለው ኹሉ። ትመልእ ማየ በኮራ ሐዲስ። ምልአ ኮራ ማየ። ይመልኦሙ በኮራቲሆሙ ማየ ፡-(ቄድር ፡-ገ፩። ስንክ ፡-መስ፳፯። ሠኔ፳፬)።
፡-ስመ። ሀገር፤ የደብረ ሊባኖስ ገጠር ታችኛው ገዳም፤ ውሃው የማያልቅ የማይደርቅ ጠበላም ማለት ነው፤ ምስጢሩ ውሃን አይለቅም። ፡-(የታቦት ዘፈን) ትምሩኝ እንደኾን ልም(ን) ጣ ወደ ኮራ፤ ያባ መጋዛብ ልጅ የይቶት እዝጊያራ።
[2]፡-ኮራ፤ ኾራ አንቦ፤ እንብ እንብ የሚል የጨው ውሃ፤ ለከብቶች የሚበጅ፤ የሚያሽርና የሚያወፍር። ወይም ግጦ ቦረቦር፤ ጨው ጨው የሚል ዐፈር። ይኸውም የሚገኝ በወንዝ ዳር ከዚያው ከውሃው አጠገብ ነው።
[3]፡-ኵሬ አንቦ፤–ከዊር ኮረ።
ኰራሲ ፡-(ጽር ኻርሲት። ዕብ ሐርሲት) ሸክላ የሸክላ ዕቃ፤ ወይም ያልተሠራው ዐፈር መሬት ጭቃ፤ የገል ስባሪ ዶቄት። አንቀጸ ኰራሲ ፡-(ኤር፲፱ ፡-፪)።
ኰራኪ ፡-(ዐረ ኩርኪይ። ሱር ኩርክያ) ቍርዬ፤ ታላቅ አሞራ እንደ ራዛ ያለ፤ ሲጮኽ ኵር ኵር የሚል፤ በዝቶ ተንጋግቶ የሚኼድ። ባለቅኔዎች ግን ምሥጥ ጕንዳን ይሉታል። ዘከመ ንህብ ወራዛ ወኰራኪ ፡-(ፍ ፡-ነ ፡-፵፬ ፡-፪)።
ኰራዚ ፡-(ዕብ ኮራዚን) የከተማ ስም፤ በጌንሳሬጥ ባሕር አጠገብ የነበረች ከተማ ፡-(ማቴ፲፩ ፡-፳፩። ሉቃ፲ ፡-፲፫)።
ኮሬ ፡-(ጽር ኾሬ፤ ኾራይ) ሙራደ ማይ፤ የሰን የኵስኵስት ጡት። የላሕመ ብርት አፍ እንደ ቦንቧ አፍ ኹኖ ጡት ያለው፤ የሚከፈትና የሚዘጋ። ባለቅኔዎች ግን የብረት ጋን ይሉታል፤ ፍችው አይዶለም። ወእምላዕሉሁ አናብስት ወአልሕምት ግብረ ኮሬ ሙራዱ ፡-(፫ነገ ፡-፯ ፡-፳፱)። ሙራድና ኮሬ አንድ ወገን ነው፤ ዕብራይስጡ ሞራድ ያለውን ጽርኡ ኾሬ ብሎታል፤ የግእዝ ፣መላሽ ግን ኮሬን በከንቱ አግብቶታል። ወይም መላሽ ግብረ ኮሬሁ ያለውን ተርጓሚ ሙራዱ ብሎ በዳር አመልክቶት፤ የኋላ ጣፊ አግብቶት ይኾናል። በብዙ መጣፍ ውስጥ ስንኳን ትርጓሜው ጥቅሱና ሐተታው ሳይቀር ገብቶ እየተጣፈ ይገኛል፤ ምክንያቱም ጥፈትና ትምርት ተባብረው ተጫፍረው ባንድ ሰው እጅ ስላልተገኙ ነው።
ኮሬ ኤጲስቆጶስ ፡-(ጽር ኾሬፒስኮፖስ) የኤኢስቆጶስ ዐርክ ምክትል፤ እንደራሴ ወኪል፤ ወራሴ መንበር ፡-(ፍ ፡-ነ ፡-፬። ፯ ፡-፫። ፱ ፡-፪)።
ኮር [1]፡-(ብ አክዋር። ዕብ ካር) በቁሙ፤ ኮርቻ ግላስ፤ መከዳ ትራስ፤ ቀንበር። ወሀለወት ሰይፍ ታሕተ ኮር፤ ኮርቻ ፡-(ድር ፡-ሚካ)።
[2]፡-በቁሙ ኮርቻ፤–ከዊር ኮረ።
ኰር ፡-(ዕብ ኮር) የመስፈሪያ ስም፤ ሖሜር፤ ዐሥረ ፈጅ ፲ ገንቦ ዘይት ወይም ፲ ቍና ስንዴ የሚይዝ። ኰርና ሖሜር ፩ ስም ነው ፡-(ሕዝ፵፭ ፡-፲፬)።
ኰርአ ፡-መታ፤ ኰራ፤–ጐርዐ።
ኰርዐ [1]፡-(ቀርዐ) መታ ቈረመ፤ ከረና ኰረኰመ፤ ደሰቀ ጐሰመ፤ የዘንግና የክርን የኵርኵም የቡጢ የጡጫ አመታት። የክርንም አገዳ ቀላል ውስጠ ክፍት ስለ ኾነ በዕብራይስጥ ቃኔ ይባላል፤ ኅለት ማለት ነው። እለ ይኰርዕዎሙ ለዕቤራት ወለዕለ ማውታ። ይኰርዑ አርእስተ ነዳያን። ወይኰርዕዎ ርእሶ በኅለት ፡-(ሚል፫ ፡-፭። ዓሞ፪ ፡-፯። ማቴ፳፯ ፡-፴)።
[2]፡-በቁሙ፤ ኰራ ታበየ፤ ተቈነነ ተጓደደ። ፡-(ተረት) ባሪያ ሲኰራ መድኀኒቱ ዱላ። ለቤትም ጣራ ለባጥ ለመዋቅር ይነገራል። ፡-(ግጥም በቴዎ ጊዜ፤ ኀይለ መለኮት ራስ ዐሊን ከደራው ባላባት ከዋቄ ዳቦ እጅ ስላወጧቸው) ኰርቶ የነበረው የነዋቄ ጣራ ፥ ኀይሉ ቢወጣበት ለመጥ አለ ደራ።
ኰርኰረ ፡-(ዲቃ ግ። ዕብ ካርኬር) ዘለለ ፈንጨ፤ ዞረ ዐወደ፤ በዙሪያ ኼደ፤ ዙሪያውን ዞረ የበዓል ዑደት፤ ላውድማም ይኾናል። በቁሙ ኰረኰረ፤ ለማሣቅ ለማስጮኽ ለማስሮጥ፤ የብብትና የከበሮ ፥ የፈረስ የበቅሎ።
ኰርጐነ ፡-(ረገነ) ከበበ፤ ሰበሰበ ፥ አከማቸ።
ኰብስ ኮብስ ፡-ኰብሽ፤ የደዌ ስም፤ ገላ የሚነፋ የሚያሳብጥ፤ የሚያፈርስ የሚቈምጥ፤ ቍምጥና ቢስ ገላ። አዝልፎ ስካር ያመጽእ ነቀጥቃጠ ወጥፍአተ ልብ፤ ወኰብሰ ወሞተ ግብት ወፈፀንተ ፡-(ፍ ፡-ነ ፡-፶)።
ኮቶሊካ ፡-(ጽር ፡-ካቶሊኮስ) ካቶሊካዊ ፥ የካቶሊክ። ሃይማኖት ኮቶሊካ፤ እንተ ይእቲ ሐዋርያዊት። ወያክብርዎ በስም ዐቢይ ዘኮቶሊካ፤ ዘውእቱ ስመ ሊቃናት ፡-(አትና አዋል። ፍ ፡-ነ ፡-፬)።
ኮቶሊክ ፡-(ጽር ካቶሊክ) የቤተ ክሲያን ስም፤ ኵላዊ፤ ዘኵሉ ፥ እንተ ላዕለ ኵሉ።
ኮነ ፡-ኾነ፤ ነበረ። የነገር ጥንት የንባብ አርእስት እየኾነ እንደ ይቤ አንቀጽ ይስባል። ወኮነ እምድኅረ ሞተ ሙሴ፤ ተናገሮ እግዚ ለኢያሱ። ወኮነ እምድኅረ ሞተ ሳኦል፤ ተመይጠ ዳዊት እምቀትለ ዐማሌቅ። ወኮነ በውእቱ መዋዕል፤ ወፅአ ትእዛዝ እምኀበ ቄሳር ንጉሥ ፡-(ኢያ፩ ፡-፩። ፪ነገ ፡-፩ ፡-፩። ሉቃ፫ ፡-፩)። ፪ኛም በትንቢት አንቀጽ ላይ ሲደረብ፤ ምስጢሩና ፍችው ጽንዕ ይኾናል። ኮነ ያፈቅር፤ ኮነ ይጐይይ፤ ኮነ ይትመዐዕ ቢል፤ ይወድ ነበር ወይም ይወዳል ኾነ ያሰኛል። ዐጸደ ወይን ኮነ ለሰሎሞን ያለውም፤ ኮነ የለ ጽንዕ ይባላል፤ ኮነም ቢቀር ሎቱ ለሰሎሞን ብሎ፤ አለው ነበረው ያሰኛል። ፫ኛም ኢ ስቶድቅበት ዘማችነቱን አሉታ በዝብዞት በኢና በአኮ በነባርነት ይፈታል፤ ምክንያቱም ደራሽና መላሽ አለቦታው ስላገቡት ነው። አንሰ ኢኮንኩ ኪያሁ። ኢኮነ ሠናየ ነሢአ ኅብስተ ውሉድ ወውሂብ ለከለባት። ኢኮለ ለክሙ ታእምሩ መዋዕለ ወአዝማነ። ኦኮንክሙ ነግደ ወፈላሴ። ኢሠናይ፤ ኢለክሙ፤ ኢአንትሙ፤ ወይም አኮ አንትሙ ነገድ ወፈላሲ ማለት ነው፤ አኮና ኢ አንድ ወገን ናቸው። ኮነ ግእዝ መሳቡ ተለዋጭና ዃኝ ሲያገኝ ነው፤ አንዳንድ ጊዜም በግእዝ ፈንታ ለን ይስባል። ወይከውን ፍሬሁ ለሲሳይ፤ ወቈጽሉሂ በፈውስ ፡-(ሕዝ፵፯ ፡-፲፪)። የኮነን አፈታት ፴ ብለው የሚቈጥሩ አሉ፤ ምስክራቸው አያጠግብም፤ ብዙው ልብ ወለድ ነው። ኮነና ሀሎ በዐረብና በዕብራይስጥ አንዳንድ ወገን ናቸው፤ ዐረብ ካነ ብሎ ኾነ አለ ነበረ ይላል፤ ዕብራይስጥም ሀያህ ብሎ ኮነ ሀለወ ይላልና፤ የኮነ አፈታት ስልቱ መብዛቱ ስለዚህ ነው። ዳግመኛም ኮነኒ ኮነነ በቍዐኒ አከለኒ በማለት ፈንታ ኮንየ ይላል የመላሽና የጣፊ ስሕተት ነው። ስእነት ብሂለ ኮንየ፤ እሳት ወማይ ኢይብሉ ኮንየ ፡-(ምሳ፳፬ ፡-፵)። ፡-(ዕር፱ ፡-ቍ፸፯። ዕር፳፯ ፡-ቍ፻፷፰)።
ኰናኒ ፡-(ኒት ንያን ያት) የሚኰንን ኰናኝ፤ ገዥ ፈራጅ፤ ዳኛ ጌታ መምር። ፈታሒ ወኰናኒ። ሕግ ኰናኒ። መኑ ረሰየከ ኰናኔ ሎቱ ፡-(አፈ ፡-ድ፪። ፈ ፡-መ ፡-፬ ፡-፩። ፊልክ ፡-፻፲፰)።
ኰንኖ ኖት ፡-(ኰነነ ይዄንን ይኰንን። ዕብ ኮኔን፤ አዘጋጀ) መኰነን፤ መፍረድ፤ መተቸት፤ መበየን መዳኘት። ይትነሣእ እግዚ ለኰንኖ። ኢትኰንኑ ከመ ኢትትኰነኑ። ዘይኴንን በጽድቅ። ቦኑ እግዚ ይኴንን በዐመፃ ፡-(ኢሳ፫ ፡-፲፫። ማቴ፯ ፡-፩። ፩ጴጥ ፡-፪ ፡-፳፫። ኢዮ፰ ፡-፫)።
ኮንየ ፡-ኮነኒ፤ ኾነኝ በቃኝ፤ በቅቶኛል። ኮንየ እንከሰ ፡-(፬ነገ ፡-፲፱ ፡-፬)።
ኰዓቲ ፡-(ቲት ትያን ያት) የሚኵት የሚኰተኵት፤ ኳች ኰትኳች።
ኰከመ ፡-ካከመ፤ የእግር። ኰመኰመ፤ የምግብ የጨዎት። ዐፈሰ ዛቀ፤ የምርት።
ኰከም ፡-(ማት) የፍም መጫሪያ መተርከሻ፤ ያመድ ማፈሻ። ኢያሚንን እይ፤ ከዚህ ጋራ ፩ ነው። ባለብሉዮች ግን እንቅብ ይሉታል፤ አንኮላ ሽክና የሚሉም አሉ። ጽህርታት ወኰከማት ፡-(ኤር፶፪ ፡-፲፰)።
ኮከበ ምዕራብ ፡-የማታ ኮከብ አስታርቦሽሽ ፡-(ስንክ ፡-የካ፪)።
ኮከበ ገዳም ፡-ቅዱስ እንጦንዮስ ፡-(ስንክ ፡-ጥር፳፪)።
ኮከበ ጽባሕ ፡-ያጥቢያ ኮከብ፤ ማለዳ የሚወጣ ፡-(ኢሳ፲፬ ፡-፲፪)።
ኮከብ ፤ (ብ ከዋክብት። ዕብ ኮካብ። ሱር ካውክባ። ዐረ ከውከብ) ፤ በቁሙ ፤ የብርሃን ቅንጣት የጸዳል ሰሌዳ ፤ ብርሃ የተሣለበት የሰማይ ጌጥ
የጠፈር ፈርጥ
፤ ሌሊት
እንዳሸዋና እንደ ፋና በዝቶ የሚታይ
የሚያበራ ፤
የፀሓይ ሰራዊት
የጨረቃ ጭፍራ ፤ ዘዋሪ ከባቢ። ስምነቱ ከከወወና ከከበበ ከኹለቱ የተዴቀለ ነው ፤ ስለዚሀ በኮከው ፈንታ ኮከብ ይላል። ኣበዝኅ ዘርዐከ ከመ ኮከበ ሰማይ።
ኮከብ እምኮከብ ይኄይስ
ክብሩ። አሰርገወ ሰማየ በከዋክብት። ከዋክብተ ሰማይ። ለወርኅ ወለከዋክብት ዘአኰነኖሙ ሌሊተ (ኵፋ ፡ ፳፬። ፩ቆሮ ፡ ፲፭ ፡ ፵፩። ድጓ። ኤር፲፱ ፡ ፲፫። መዝ ፡ ፻፴፭)።
ኮከብ ዘቦቱ ዘነብ ፡-ዥራታም፤ ባለዥራት፤ የክፉ ምልክት ፡-(አዋል)።
ኮከወ ፡-ዞረ ዋተተ ፣–ከዊው ከወ፤ ከወወ።
ኮከወ ከውከወ ፡-፣ ፡-(ተቀ ግ) ዞረ ዋተተ ተንከወከወ። ከውካዋ እንዲሉ፤ ዘዋሪ ሲሉ።
ኰኵሕ [2]፡-(ሓት። ዕብ ኰሕ፤ ጥንካሬ ብርታት) ጥኑ ደንጊያ፤ ንጥፍ ዐፈር ለበስ፤ ቋጥኝ ገዎቻ፤ ተራራ ኰረብታ፤ ጭንጫ ደረቅ ጥብቅ ጠጠራም መሬት። አንቅዐ ኰኵሐ ዘሐነጸ ቤቶ ዲበ ኰኵሕ። እግዚ ጸወንየ ወኰኵሕየ። ጐዩ ውስተ ኰኵሐ ሬሞን። ቦ ዘወድቀ ውስተ ኰኵሕ ኀበ አልቦ መሬት ብዙኅ ፡-(መዝ ፡-፸፯። ማቴ፯ ፡-፳፬። ፪ነገ ፡-፳፪ ፡-፪። መሳ፳ ፡-፵፯። ማቴ፲፫ ፡-፭ ፡-፳)።
[2]፡-ንጥፍ ደንጊያ፤–ኰኵሕ።
ኰካይ ፡-(ዋከየ ውኩይ) ቡሓ ራሰ ነጭ፤ በግ ቍራ ፡-(ትግሬ)።
ኮክህ [1]፡-በቁሙ፤ ኮክ የተክል ዕንጨት ስም፤ ፍሬው የሚጥም ዐጥንታም። ኮል ወኮክህ። ፍሬሁ ለኮክህ ፡-(ፍ ፡-ነ ፡-፲፯ ፡-፪።መ ፡-ፈ)።
[2]:-ንጥፍ ደንጊያ፤–ኰኵሕ።
[3]፡-ኮክ የኮክ ፍሬ፤–ከወከ።
ኮፒ ፡-(ሮማይ ኮፒያ) ብዛት፤ የጥፈት አበዛዝ፤ ብዥ ቅጅ፤ አንድ የነበረው ብዙ መኾን። የማይጠፋ ቀለምና ርሳስ፤ የሴቴ ሬት ደም የሚመስል።
ኳሄላ ፡-(ላት) የጠፍር ኳስ፤ ዕሩር ጥንግ፤ የተኵስ ዐላማ ጊጤ፤ ከሆድ የሚወጣ ሐሠር ጕድፍ። ጕድ እብድ ልብሱን የጣለ፤ ወይም የእብድ አሻንጕሊት፤ ከዐቢይ ጾም በፊት ከጾመ ነነዌ በኋላ የእብድ ዐሙስ ለት ርሱን በየግንባራቸው ለጥፈው ሲሥቁ ሲያሥቁ የሚውሉበት። ወከመ ኳሄላት ኮነ ውስተ ዓለም። ከመ ኳሄላ ኮንክዎሙ ለብዙኃን ፡-(፩ቆሮ ፡-፬ ፡-፲፫። መዝ ፡-፸)።
፡-መካን የበረሓ ዕንጨት፤ እሾኻም ፍሬ ቢስ። ወይም ብቸኛ በረኸኛ አውሬ፤ ፋደት የዱርድ ድመት። ወይከውን ከመ ኳሄላ በውስተ ገደም ፡-(ኤር፲፯ ፡-፮)።
ኳኳ ፡-(ጽር ኮኮስ) ጥሩ ቀይ ቀለም፤ ወይም በቀይ ቀለም የታለለ ልብስ ፈትል። ባለብሉዮች ግን ጥቍር ሱፋላ ለማለት በርኖስ ይሉታል። እመኒ ኮነ ኀጢአትክሙ ከመ ኳኳ ይጻዐዱ ከመ በረድ፤ ወእመኒ ቄሐ ከመ ለይ ይከውን ከመ ፀምር ፡-(ኢሳ፩ ፡-፲፰)። ቄሐና ኮነ፤ ለይና ኳኳ፤ ይከውንና ይጻዐዱ ከመ ፀምርና ከመ በረድ አንዳንድ ወገን ናቸው።
~ ኸ ~
ኸረጺት ፡-(ዐረ ኁርጽ) ከረጢት፤ ኪስ ቁናማት፤ የገንዘብ መያዣ። አምሳለ ኸረጺት ፡-(ፈ ፡-መ ፡-፴፩ ፡-፭)። ሥሩና ምንጩ ሐረጸ ነው፤ ምስጢሩም ክፍልን ክፍልነትን ያሳያል፤ ሐሪጽን እይ።
ኽጥሜ ፡-ኽጥሜ፤–ሰላጣ ሥንቆ፤–ኅጥሜ።
No comments:
Post a Comment