~ፀ~

                                 

-፲፱ኛ ፊደል በግእዝ አልፍ ቤት በአበገደ፤ የጸደይ ተወራጅ፤ ወይም ምክትል፤ ኹለተኛ፤ ዲቃላ፤ ተቀጥላ፤ ስሙ ፀጰ በዐረብ -(ፃፅ) ዳድ ይባላል፤ ፍችውን በቦታው ተመልከት ፲፱ኛነቱ በተራ ቍጥር ነው፤ በፊደልነት ግን ፲፱ኛው የግእዝ ፊደል ቆፍ ነው እንጂ ፀጰ አይዶለም የጸ ኹለተኛ መባሉም በመልክና በድምጥ በኹለት ወገን ነው፤ የኀርም ጎን ፍች መዠመሪያውን ተመልከት የሐ ዲቃላ ስለ ኾነ ክሐ ቢደረብ እንጂ ለብቻው እንዳይቈጠር ደግሞ የጸ ዲቃላ ስለ ኾነ ከጸ ቢደረብ እንጂ ለብቻው አይቈጠርም፤ እንደ ኻያ ኹለቱ ፊደላት አባትነት መደበኝነት የለውም። በፊደል ቍጥር ግን ከታው በኋላ ቀጥሎ ሲጣፍ ፮፻ ይባላል። በዐረብ ፊደል የፀ ድምጥ ከጸ ልዩ ኾን መልካቸው አንድ ነው ነቍጣ በቀር ልዩነት የለውም፤ በግእዝ ግን መልካቸው ልዩ ኹኖ ሳለ ድምጣቸው አንድ ነው፤ የመልክ እንጂ የድምጥ ልዩነት የላቸውም፤ ልዩነታቸውም የጠፋ በኋላ ዘመን ነው። ፍሬምናጦስ በፊት ግን የፀጰ ድምጥ ገባሬ ሰማያት ወምድር በከመ በሰማይ ከማሁ በምድር ወምድርኒ ትገብር ፋሲካ እንደሚባለው እንደ አጠራርና ድምጥ ነበረ እንጂ እንደ ጸደይ አልነበረም፤ ዛሬም በዐረብ እንደ ምድራዊ ይጠራል በዕብራይስጥም ኹለት አለ፤ ኹለተኛው ሳድስ እየኾነ በመጨረሻ ቃል ይገባል ድምፁ ግን አንድ ነው ልዩነት የለውም፤ በፊደልም ቍጥር መጨረሻ ኹኖ ፱፻ ይባላል ከዚህ የቀረውን ሐተታ ተመልሰኽ በፊደል ታሪክ ተመልከት።

ፀሓያዊ -የፀሓይ መት ፀሓያዊ ዓመተ ፀሓይ -(አቡሻ)

ፀሓይ -(ያት ጽሕወ ጸሐየ በራ) በቁሙ፤ ጣይ ታላቅ ብርሃን፤ ቀን የሚያበራ ዘየዐቢ ብርሃን ከመ ይምልክ መዓልተ ፀሓየ ቀትር ፀሓይ ዘያበርህ ወይጠፍእ -(ዘፍ፩ -፲፮ ራ፴፩ -፲፱ ኢዮ፴፩ -፳፮)

ፀመመ -(ጸሚም ጾመ) ዐከመ፤ ገነ አሰረ ፈነ ጠቀለለ ጠመጠመ፤ የቍስል የሰባራ ፀመምዎ ከመ ይትፈወስ። ይፀምምዎ ወኢይቀብዕዎ -(ሕዝ፴ -፳፩ ኢሳ፩ -) ትመልእኑ ታጸግብኑ በማለት ፈንታ () ፀምምኑ ነፍሰ አክይስት ይላል፤ ስሕተት ነው -(ኢዮ፴፰ -፴፱)

 -አዳነ ፈወሰ አሻረ፤ አደረቀ፤ አጠና አበረታ፤ አጨከነ ወይፀምም ሎሙ ቍስሎሙ። ፀመመ ሰሊሆሙ ንበይ ፍሰ ወልድከ ፅምም በከ -(መዝ -፻፲፮ መጽ -ምስ ራ፴ -) በፀመመ ፈንታ አፅመመ ይላል፤ አያሰኝም ጾም ትፌውስ ስለ ፍስ ወታፀምም ፍትወተ ዘሥጋ ፈውሳት እለ ያጥዕያ ወርጢናት እለ ያየብሳ፤ ወቅብዐ ፈዋት እለ ያፀምማ ቍስላተ -(ገድ -ተክ - - -፫። አርጋ -)

ፀመርት -(ራት። ዕብ ሜሬት) ዐጽቃም ቅጠላም ዛፍ፤ ዘንባባ የመሰለው ኹሉ የዛፍ ውልብልቢት ራስ ጫፍ፤ ዐጽቅ ክንፍ ቅጣፊ ዝንጣፊ፤ ሰሌን የዘንባባ ቅጠል፤ ሙሽራው ምስጢሩ ማደግ መቈረጥ ሳይቀር የቅጠሉን ጣምራነትና ዕጥፍ ድርብነት ያሳያል። መጽሐፍ ግን በፀመርት ፈንታ ፀበርት ይላል የተሳሳተ ነው ኀበዘ ብሎ በዝ ፈንታ ኅብስት እንደ ማለት ፀበርተ ተመርት ዘበቀልት። ዳንኤል ዑጹፍ በልብሰ ፀበርት። ወግሉፋን ኪሩቤል ወፀበራት -(ዮሐ፲፪ -፲፫። ስንክ -ታኅ፯ ሕዝ፵፩ -፲፰)

ፀመወ -መተ ዝም አለጸምዎ ጸመወ

ፀሚድ ዶት -(ፀመደ ይፀምድ ይፅምድ። ዕብ ጻማድ ሱር ጽማድ። ዐረ ፀመደ) መግዛት በታች ማድረግ። መጥመድ፤ ማቀናጀት፤ ጥንድ ማድረግ፤ ቀንበር መጫን፤ ከቀንበር ሠረገ ማቈራኘት የበሬ የፈረስ ፀመደከ ሰይጣን ከመ አባዕር ወአንበረ አርዑቶ ውስተ ክሣድከ ፀሚደ አርዑት ያደንኖ ለክሣድ ይፅምዱኒ በአርዑቶሙ ወይቅንዩኒ ለግሙራ ከመ ይፀመዱ ተያፍን ወብዕራ ዘዘ ይፅምድዎሙ ለአፍራስ ሠረገላ -(መጽ -ምስ ራ፴ -፴፭። ስንክ -ግን፲፩ ኅዳ፲፰) ዘመደን ተመልከት፤ የዚህ ጎረ ቤት ነው

 -ማጥመድ፤ በወጥመድ መያዝ ከመ ይፅምዱ ሰብአ በሃይማኖት -(ፊልክ -፵፩) ወሀበ አቅረበ በማለት ፈንታ ፀመደ አስተፀመደ አስተፃመደ ይላል፤ የመላሽ ስሕተት ነው። -(ዘሌ፲፰ -፳፩ -፪ና -)

ፀማመረ -(የፀመረ ድርብ) ጨማመረ ደራረበ ወእፀማምር ሰኑየ ወሰኑየ -(ፊልክ -፻፲፭)

 -ሸላለተ፤ ቈራረጠ፤ ዐጫጨደ ቈጣቈጠ

ፀማሪ -(ሪት ርያን ያት) የሚጨምር ማሪ፤ አጣባቂ፤ አንድ አድራጊ።

ፀማዲ -(ዲት ድያን ያት) የሚጠምድ፤ የሚያጠምድ ጠማጅ፤ አጥማጅ

ፀማድ -(ውስጠ ብዙ) አገልጋይ ሎሌ ሽከር፤ ቤተ ሰብ፤ ልደ ቤት ምፀማዱ። ይሔውጽ ፀማደ። ኖላውያን ወፀማዶሙ -(ግብ፲ -፯። ስንክ -ሚያ፮። ሔኖ -ክ፸)

ፀምር -(ዕብ ሜር ሱር ጻምራ) የበግ ጠጕር ልም ልዝብ ጥሩ ነጭ፤ ቀጫጭን ረዣዥም የሰው የእንስሳ ሥዕርት እያደገ የሚሸለትና የሚቈረጥ ቅጠል ዐጽቅ ልብሰ ፀምር ጠጕር ተፈትሎ የሚሠራ ባለብሉዮች ግን መስክ ብዝት ጠጕር ነጭ ሐር ይሉታል። ምፀምረ አባግዕየ ሥዕርቱ ከመ ፀምር ጸዐዳ። ትለብሱ ፀምረ ወኢይዕርግ ዲቤሆሙ ፀምር ፀምር ግብረ እዱ -(ኢዮ፴፩ -፳። ራእ፩ -፲፬ ሕዝ፴፬ -፫። ፵፬ -፲፯ ስንክ -መጋ፲፰) እሰፍሕ ፀምረ ያለው ግን -(መሳ፮ -፴፯) ነዶውን ጠጕ ነው ብራይስጡ ቅሩፀ ፀምረ ያለውን የግእዝ መላሽ ቅጽሉን ትቶ፤ ልብስ አስመስሎታል አንቀጹም ኣቀውም ኣነብር ነው እንጂ እሰፍሕ አይዶለም።

 -የታጨደ መስክ፤ ዐጽቁ ቅጠሉ የተቈረጠ ጕን ሐረግ፤ ዝናምና ጠል የሚፈልግ ወይወርድ ከመ ጠል ውስተ ፀምር ወከመ ጊሜ ውስተ ፀምር -(መዝ -፸፩። ዘዳ፴፪ -)

()          ፀምሮ ሮት -(ፀመረ ይፄምር ይፀምር ዐረ ሰመረ ዕብ ሳሜር ቀነወ) መጨመር፤ መደረብ፤ ማጣበቅ መለጠቅ፤ ኹለቱን ነገር ማጣመር አንድ ማድረግ፤ አጣምሮ መያዝ መውጋት መስፋት ማሰር መቸንከር ደመረን ተመልከት፤ የዚህ መንቲያ ነው እፄምሮ ለዳዊት ውስተ ረፍት እፅምሮ በምድር ምዕረ ፀመረቶ ምስለ ምድር። ኢትፀምር አሲረ ክልሌቲ ኀጣይእ -(፩ነግው -፲፰ -፲፩ ፳፮ -፰። መሳ፬ -፳፩። ሢራ፯ -)

 -መሸለት መቍረጥ፤ ማጨድ መቈጥቈጥ፤ የጠጕር የሣር የቅጠል፤ ቀረፀን ተመልከት

ፀምዐ -ጠማ ተጠማ፤ጸምአ

ፀሪስ ሶት -(ፀርሰ ይፀርስ ይፅርስ ጠርሰ) መጥረስ መደነዝ፤ መድክም፤ መፍዘዝ መብለዝ፤ የጥርስ የስለት፤ ጠርሰን ተመልከት። አበው በልዑ ቆዐ ወአስናነ ደቂቅ ፀርሱ ሁበክሙ ትፅርሱ ስነኒክሙ -(ኤር፴፩ -፳፱ ሕዝ፲፰ -፪። ዓሞ፬ -)

ፀሪር ሮት -(ፀረረ ይፀርር ይፅርር ዐረ ፀረ ጐዳ ዕብ ጻራር) መፃረር መጠናወት፤ ወደረኛ መኾን፤ መበደል ግፍ መሥራት፤ ክዳት መሸፈት፤ ማመጥ ግብር መንሣት ማቅለጥ መጽሐፍ ግን በፀረረ ፈንታ አፅረረ ይላል፤ የመላሽ ስሕተት ነው አፅረሩ ሰዶም። አፅረሩ ሞአብ ፅረሩ ዶም -(ዘፍ፲፬ -፬። ፪ነገ -፩። -፳ና -፳፪)

 -መፀረር መሰለፍ ለጦር ለውጊያ መዘጋጀት።

ፀሪዕ ዖት -(ፀርዐ ይፀርዕ ይፅራዕ ዐረ ፀረዐ) መታከት መድከም፤ መተኛት መጋደም፤ መስነፍ መቦዘን፤ ማረፍ ሥራ ፈት መኾን ሥራን መተው ማቋረጥ ማቆም፤ ማስታጐል መጽሐፍ ግን በፀርዐ ፈንታ አፅርዐ ይላል፤ አያሰኝም። ዘያፈቅር ውሉዶ ኢያፀርዕ ተግሣጸ ናፅርዕ ቅኔ ግብረ እደዊነ ወኢንትሀከይ። ከመ ኢያፅርዕ ተቀንዮ ቅድመ ሥጋሁ ለአዳም ወእምዝ አፅርዐ ዘንተ ብረ -(ሢራ፴ -፩። ዲድ -፲፫ ቀሌ። ሃይ -አበ)

ፀሪፍ ፎት -(ፀረፈ ይፀርፍ ይፅርፍ። ዕብ ጻራፍ ነጠፈ አኅበረ። ሐራፍ) መፅረፍ መስደብ ማዋረድ ማቃለል፤ ነውረኛ ማድረግ። በእንተ ፀሪፍ ወጽዒል ይፀርፉ ሕዛብ ዕለ ስምየ ዘይፀርፍ ላዕለ ካህናት ፀረፋ በሐሰት -( - - ኢሳ፶፪ -፭። ቀሌ - -፳፬)

ፀራሪ -(ሪት ርያን ያት) የሚፃረር ጠላት፤ ደመኛ። በፀራሪ ፈንታ ፀራዊ ይላል ፍችው ነው

ፀራዒት -ጭቅና፤ጸራዒት።

ፀራዊ -(ዊት ውያን ያት) ፀራሪ የጠላት ወገን፤ ጠላት ደመኛ። ብእሴ ፀራዊ ገብረ ዘንተ ወፀራዊሰ ዲያብሎስ -(ማቴ -፲፫ -፳፰ ፴፱)

ፀራፊ -(ፊት ፍያን ያት ረፍት) ዳቢ፤ ተሳዳቢ፤ አዋራጅ፤ ስድብ ዐዋቂ። ኢያነጽሕ ፀራፌ ኢትኩኑ መዐትማነ ወኢፀራፍያነ ወኢዝኁራነ -(ጥበ፩ -፮። ዲድ -፯። ፩ጢ - -፲፫)

ፀር -በቁሙ፤ ተፃራሪ ጠላት፤ ወደረኛ፤ ጣውንት፤ ዳተኛ ሽፍታ። መጽሐፍ ግን በጣፎችና በመላሾች ስሕተት ላንድም ለብዙም ፀር ይላል ያሰኝም። ብቻ ለወንድና ለሴት ይከታል። ኮኖሙ ፀሮሙ ይከውነከ ፀረከ ሶበ መንደብዎ ፀሩ እንዘ ንሕነ ለእግዚ። መት ለኵሉ እንዘ ፀር ይእቲ፤ መኳንንት ይትጋደሉ ባቲ -(ኢሳ፷፫ - ሢራ፴፯ -፬። ፵፮ -፭። ሮሜ - - ቅኔ)

ፀርቅ -ርቅጸሪቅ ጸረቀ

ፀቈነ -ጨቈነ፤ ካበ፤ጸቍን ጸቈነ።

ፀበረ -ረገጠጸቢር ጸበረ

ፀበርት -ዝንጣፊ፤ፀመርት፤ ፀመረ

ፀበበ -ጠበበጸቢብ ጸበበ

ፀበተ -ዋኘጸቢት ጸበተ

ፀቢስ ሶት -(ፀብሰ ይፀብስ ይፅበስ ፀወሰ) መድከም መዛል መፍራት፤ መላላት፤ ማንከስ፤ ፈሪ ደካማ መኾን። ይፀብሱ ጽኑዓን። ትፅበስ በቅድመ ገጾሙ -(ኢሳ፵ -፴። ዘዳ፴፩ -)

ፀቢጥ ጦት -(ፀበጠ ይፀብጥ ይፅብጥ ዐረ ፀበጥ ዕብ ጻባጥ) መጨበጥ አጥብቆ መያዝ፤ ከእጅ ውስጥ ማግባት ዘይፀብጥ ዐቅራበ ዘይፀብጥ ጽላሎተ። በትረከ ብጥ በእዴከ ቆሙ ኀበ ኆኅት ቍድስ ወፀበጥዋ -(ሢራ፳፮ -፯። ፴፩ - ዘፀ፲፯ -፭። ዮሴፍ) ሠበጠን እይ የዚህ መንቲያ ነው

ፀባጢ -(ጢት ጥያን ያት) የሚጨብጥ ያዥ ባጭ ፀባጤ ኵሉ -(ቅዳ -ሕር) ቈጣቢ ንፉግ፤ እጀ ጥብቅ። ሰጭና ባጭ እንዲሉ ቸርና ቢስ ሲሉ።

ፀብአ -ወጋ አጠፋ፤ቢእ ጸብአ

ፀብጥ -ወጋ አጠፋ፤ቢእ ጸብአ

ፀተመ -ገጨ ሰበረጸቲም ጸተመ።

ፀኒስ ሶት -(ፀንሰ ይፀንስ ይፅነስ ዐረ ፀኒየ፤ ወላድ ኾነ) መፅነስ፤ መቋጠር ማርገዝ፤ በሆድ በማሕፀን መሸከም መያዝ ከዚህ የተነሣ ማበጥ መንዘርጠጥ መንጣርዘዝ እስኪወልዱ ድረስ ቀብዳዳ እንቅብ ሆድ መኾን ጠነሰሰ ጥንስስ ማለት ከዚህ የወጣ ነው ጊዜ ፀኒስ ናሁ ድንግል ትፀንስ ወትወልድ ወልደ ዘእንበለ ትፅንሶ በከርሣ። ፀነስነ ሐመምነሂ ወወለድነ -(መክ፫ -፪። ማቴ፩ -፳፫። ሉቃ፪ -፳፩ ኢሳ፳፮ -፲፰)

 -ማሰብ፤ መመኘት። በከርሦሙ ይፀንሱ ጻዕረ -(ኢዮ፲፭ -፴፭። መዝ -፯። ኢሳ፱ - -፲፫)

ፀናሲ -(ሲት ስያን ያት) የሚፀንስ የሚያስብ፤ ፀናሽ ዐሳቢ -( - -፵፩ -)

ፀንዐ -ጠና በረታኒዕ ጸንዐ

ፀንግዐ -(ፀግዐ) ተጠጋ ስጠጋ ራሱን ተኛ ተጋደመ በፀንግዐ ፈንታ ተፀንግዐ ይላል ኹሉም ስሕተት ነው፤ ፍችውና ዘሩ የፀግዐ ሲኾን በከንቱ ገብቷል፤ ፀግዐን ተመልከት ተፀንግዐ -(አዋል) ባማርኛ አጠነጋ ጥንግ ማለት ከዚህ የወጣ ነው

ፀንፈርት -(ፀፈረ መፅፈርት) የወፍ ወጥመድ ማነቆ ሸምቀቆ ወፈንጠር የማያጨናፍር ደንጊያ ጠጠር ብትን ዐረር ከመ ያመሥጥ ወይጠል እምነ መሥገርት ገሪፍ፤ ወከመ ይድኅን ምፀንፈርት ዖፍ -(ስንክ -ታኅ፲)

»ፀአት -መውጣት አወጣጥ፤ መለየት ተፈሥሑ ብጽ በፀአቶሙ። ሶበ በጽሐ ጊዜ እምዝ ም። ትትፌ ፍስ ርት በፀ ምሥጋ -(መዝ -፻፬ ቀሌ ዮሴፍ)

 -ዘር ትውልድ። እምሀገረ መኑፍ አቱ -(ንክ -ነሐ፲፩)

ፀዓዕ (ዓዓት) መብረቅ ነጐድጓድ የመብረቅ ጓታ ብልጭታ ትፌኑ ፀዓዐ ወየሐውር ቃለ ፀዓዑ ያፈርሃ ምድር መብረቅ ወነጐድጓድ ወፀዓዕ ያል። ልሑ ፀዓዓት (ኢዮ፴፰ ፲፯። ራ፵፫ ፲፯። ቅዳ ያዕ ደራሲ)

ፀዕዐ -(ዕብ ኣህ) ጮኸ ነጐደ፤ ፈረሰ ተናደ፤ ተመመ አስገመገመ፤ በረቀ ፈለቀ ብልጭ ባለቅኔዎች ግን ብልጭታን ብቻ ይፈታሉ

 -ፍታት ልቅሶ፤ ለሙ የሚ ነገር ገብረ ሕዝብ ቀበረ ሌሁ -(፪ዜና -፳፩ -፲፱) ውጤታ፤ ምርት ቄት -(ማርኛ)

ፀክ -ን፤ ሹልዳ፤ጸክ

ፀወን -ጥግ አንባጸወን።

ፀዊስ ሶት -(ፆሰ ፀወሰ ይፀውስ ይፁስ። ፀብሰ) መለምሸት መሸብየት መስለል ልምሾ ሽባ ሰላላ መኾን።

ፀዊግ -(ፆገ ይፀውግ ይፁግ) አው

ፀዋግ -(ግት ጋን ጋት) ክፉ መጥፎ ካኝ ጠማማ ገብር ፀዋግ ርዌ ፀዋግ ፀዋጋን መላእክት። እደው ፀዋጋት -(ምሳ፳፱ -፲፬ ኩፋ -፴፬። ግንዘ። ራ፪ -፲፬)

(ጥወ)        ፀውጎ ጎት -(ፀወገ ይፄውግ ይፀውግ) መክፋት፤ መጨከን፤ እንዳውሬ መኾን ልብን ማጥመም፤ ፊትን ማጥቈር፤ ማጭገግ ጭጐጐት ማስመሰል። ዘይፀውግ እለ ይፄውጉ እምኔሁ -(ዘዳ፳፭ - -፪። ማቴ፲፪ -፵፭) በፆገና በፀወገ ፈንታ ተፀውገ ተፀወገ ይላል፤ ስሕተት ነው እኩያን እለ ይፀወጉ። ዲዮቅልጥያኖስ ቢጾ አራዊት በተፀውጎ -(ኩፋ -፲። ስንክ -መጋ፰)

ፀጊም ሞት -(ፀገመ ይፀግም ይፅግም። ዐረ ፀጊመ) መጥመም፤ መጕበጥ ጠማማ መኾን ወደ ግራ መኼድ መገልበጥ

ፀጊዕ ዖት -(ፀግዐ ይፀግዕ ይፅጋዕ። ዐረ ፀገዐ) ጠጊዕ መጠጋት መደገፍ መንተራስ፤ ጥግ ደገፋ መያዝ ማግኘት ጠግዐን ተመልከት፤ የዚህ መንቲያ ነው። መጽሐፍ ግን በፀግዐ ፈንታ ፀንግዐ ተፀንግዐ ይላል ስሕትት ነው ሰከበ ወተፀንግዐ -(አዋል) ጥሬውንም በምፅጋዕ ፈንታ ምፅንጋዕ ይላል።

ፀጋማዊ -የግራ፤ በግራ ያለ ግራኝ ጠማማ፤ ጐባጣ፤ ሰሜናዊ። ፀጋማዊ ጥቡ ዘቦቱ ፀጋማይ የማናየ ኮነ ዐይኑ ፀጋማይ ዐይን የማኒት ወፀጋሚት -(ኩፋ፴፰ ኪዳ ቀሌ)

ፀጋም -(ማት ዕብ ስሞል) ግራ የቀኝ አንጻር፤ እጅ፤ ጐን፤ ማእዝን፤ ሰሜን፤ ሰሜናዊ ግራኝ ተፈለጥ የማነ ፀጋመ ልቡ ለአብድ ውስተ ፀጋሙ ብእሲ እመ ኮነ ፀጋመ -(ዘፍ፲፫ -፱። መክ፲ - - - -)

ፀጋዒ -(ዒት ዕያን ያት) የሚጠጋ ተጠጊ፤ ተደጋፊ፤ የሙጥኝ ባይ

ፀጰ -(ፀጳ) ስመ ፊደል ፀ፤ ጥንተ ስሙ ነው አጣጣፉም እንደዚህ ነበረ ይባላል ከግእዝ በፊት በነበረው በሳባ ፊደል ድርብ ኹኖ ይባል ነበረ የሚያሰኘውም የከርሡ ሠሪዝ ነው ሠረዙ ሲቀር ሲጨመር ይባል ነበረ ይላሉ የኋላ ዎች ግን የጸደይ ምክትል ሌላ ነበረና ያነን አውጥተው ይህነን ሲያገቡ እንደ ዐይኑ ክፍቱን ዘግተው፤ ኹለተኛ እንደ ማለት ጥንታዊ ስሙን ሳይለቁ ፀጰ ብለውታል ፍችው ፀሓያዊ። ዳግመኛም በፀጰ ፈንታ ፀጳ ይላል ዕፀ ጳጦስ እንደ ማለት ነው ዕፅ ጳጦስ መጥቶ ተገናኝቷል ንባቡ እንጂ ምስጢሩ አንድ ነው፤ ጳጦሳዊ እሳታዊ ማለትን ያሳያል። ጸሐፍት ደግም ፀሓይ ይሉታል ፀጰ መባል በመልክ ቢኾን ይህ የዛሬው ዲቃላ ስለ ኾነ ፈጽሞ ጸን ይመስላልና፤ ለጸደይ ይልቅ ይገባው ነበር

ፀፈረ -ጥፍራም ነ፤ጸፊር ጸፈረ

ፀፈቀ -ፈቀ፤ጸፊቅ ጸፈቀ።

()          ፀፊር ሮት -(ፀፈረ ይፀፍር ይፅፍር ዐረ ፀፈረ) መታታት፤ መሥራት፤ መጐንጐን፤ ማክረር መግመድ፤ መደረብ መሸረብ። ፀፊሮቱ ሥዕርት። ፀፈረት ርእሳ ወተክብሰት ፀፊረ ደጓዕሌ ወፀፈሩ ሐራ ክሊለ ዘሦክ ልሳንከ ፀፈራ ሕብል ጽልሑተ ይፀፍራ ደዊክሙ። እለ ይፀፍርዋ ለምክር -( - -፶፩። ዮዲ -፲፮ -፰። ስንክ -ኅዳ፲፪። ዮሐ፲፪ -፪። መዝ -፵፱ -፶፯። ኢዮ፭ -፲፫)

 -ማበር መጨፈር አንድ ቃል መኾን፤ በዘፈን በምክር -(ዐማርኛ)

 -ማጫፈር፤ በዋዌ ማያያዝ ማቈራኘት ኹለቱን ሦስቱን ብዙውን። ሚካኤል ወገብርኤል። ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ። ጴጥሮስ ወዮሐንስ ወያዕቆብ ወእንድርያስ ወፊልጶስ ወቶማስ -(ግብ፩ -፲፫)

ፀፋሪ -(ሪት ርያን ያት) የሚታታ የሚሠራ ጐንጓኝ፤ ጨፋሪ ዘፋኝ።

ፀፍዐ -በጥፊ መታ፤ጸፊዕ ጸፍዐ

ፀፍፀፈ -ጠፈጠፈ፤ጸፍጽፎ ጸፍጸፈ

ፁማዴ -መጥመድ፤ መጠመድ አጠማመድ ጠመዳ፤ አገልግሎት፤ ባርነት ቤተ ሰብነት። ወዘኒ ፁማዴ -(፩ዕዝ - -፳፮)

ፁገት -መክፋት፤ መጨክን አከፋፍ፤ አጨካከን፤ ክፋት ጭካኔ ጥመት፤ ጠማምነት ፁገተ ንበሳ መንገለ የውሀት አግዐ -(ስንክ -ታኅ፲፪)

ፁግ -(ጋት) ኀጢአት ክፉት፤ ተንኰል፤ ጽነት፤ ጥመት ኵሉ ምግባረ ፁግ ሰብእ ኮኑ እኩያነ በምክረ ፁግ ኢትግበር ፁገ። እለ ይትመየጡ ውስተ ፁግ -(ቀሌ ኩፋ -፲። ፴፯ መዝ -፻፳፬) 

ፂዖት -(ታት ዐረ ፀይዐት) መስክ ፌ፤ ክልክል፤ ሣራም ቅጠላም ሰፊ ቦታ የከብት መሰማሪያ። ከመ ሣዕረ ፂዖት ስሙር አክብ ዖተ ከመ ይብዝኃ መራዕይከ ዖተ መልማል ከመ ባግ ውስተ ዖት ረከቡ ዖታተ ብዙኃተ ወስሙራተ -(ኢዮ፭ -፳፭ ምሳ፳፯ -፳፮ ጥበ፲፱ -፯። ሆሴ፬ -፲፮ ፩ዜና - -)

 -መስክፀየዖት

ፂዋዌ ፄዋዌ -ምርኮ፤ ማረካ፤ ዘረፋ፤ ደት፤ ግዞት። እሜጥዎሙ ለፂዋዌ ወሕቡላንሰ ይከውኑ ለፄዋዌ -(ኩፋ -፩። ምሳ፲፪ -፳፬)

ፂውው -(ውት ዋን ዋት) የተማረከ የተዘረፈ የተጋዘ ተዘከር እግዚኦ ኵሎ ውዋነ ወአገብኦሙ ኀበ ማኅደሪሆሙ። አመት ውውት። ስብክ ሎሙ ግዕዛነ ለፂውዋን -(ግንዘ። ዘፀ፲፪ -፳፱ ሉቃ፬ -፲፱)

ፃሕስ -ሽብሸባ፤ ርግዶ መረግድጅ  ረገዳ፤ ዝላይ ጭፈራ፤ ርግጫ ዳንኪራ። -(ግጥም ዐፄ ውርድ ሲነዛ በነደብቴ) ራቂ ራሱን ታጣቂ፤ አረግራጊ አቴና ወጊ፤ ዘፈን ግብሩ ዳንኪራ መጥኑ፤ የጐመን ትል ዕጥፍ ዘርጋ የሚል። ለቋረኞች ደብተራን መስደብ ልማዳቸው ነው፤ ቀድሞም እቴጌ ምንትዋብ ዲያብሎስ ሴት አያውቅምን ብለው የሞኝ አጠያየቅ ጠየቁና አዎን እቴጌ ሆይ ርሱማ መልአክ እንጂ አይዶለ በዚህስ አይጠረጠርም ቢሏቸው፤ እንኪያማ ደብተራን ማን ወለደው ልበል የማን ልጅ ልበለው አባቱን ንገሩኝ አሉ ይባላል።

ፃሕብ -ዝብዘባ ሸክላ፤ጽሒብ ሐበ

ፃመወ -ጣመነ ደከመ፤ጻምዎ ጻመወ

»ፃት -(ታት) ጣት፤ የእጅና የእግር ቅጥይ። የዛፍ ጫት ሕፃ ርጥብ ቀንበጥ ዐራስ ወጣት ልጅ ጻጹት። እመ ቅላ እናት። እመ እመጫት ዝንጀሮ እንዲሉ -(ተረት) መጫ ሆዷ ቅርጫት

»ፃእፃእ -(ዕብ ኤጻኢም ዐረ ፂእ፤ ልጆች) ጭንጋፍ ውርጃ ሽል አለቀኑ ከ፱ ወር በፊ የወጣ። ዝብጠታተ ፃእፃእ በማሕፀን። ፃእፃእ አድኀፀቶ ማሕፀ ሲት ዘትሰቲ ፈውሰ ታድኅፅ ፃእፃኣ ማሕፀና -(ሔኖ፷፱ -፲፪ ዮ፫ -፲፮ - - -)

 -ጣጣ ዳይ መፍቅድ፤ ዕዳ ግብር፤ ገንዘብ የሚያሻ የሚያስፈልግ ነገር ወጪ ገንዘ ቤተ ራተኞች የሚሰጠ ለደንጊያ ለብ የሚያወጣው ወይም ሕዝብ የሚያዋጣው ግብር የመዋጮ ገንዝብ -(ሉቃ፲፬ -፳፰ ነገ -፲፪ -፲፩ -፲፪) መዝገብ ለፃእፃ ግብር ብዎሙ ምቤተ ጉሥ ለፀእፃኦ እን መጠነ ፃእፃኡ። ዘላዕሌ ፃእፃአ ቤቱ -(ዕዝ፪ -፷፱። - -፰።ነሐ፭ -፲፰ ጦቢ፩ -፳፪)

 -ጭንጋፍወፂ ወፅአ

»ፃእፅአ -(ተቀ -) ጨነገፈ፤ አሶረደ።

ፃፁት -ፃፁት፤ታናሽ ዝንብ፤ጻጹት።

ፃፅ ፃፄ -(ዕብ ሳስ ሱር ሳሳ ዐረ ሱስ) ብል፤ ታናሽ ትል የልብስ የቅጠል ከመ ልብስ ይበልዩ ወይበልዖሙ ወቍንቍኔ ከመ ብላዐ ፃፄ -(ኢሳ፶ -፱። ማቴ፮ -፲፱ - ናሖ፩ -)

 -ነቀዝ፤ ጥንጣን፤ የዕፅ የእክል። አብትር ከመ ዘፃፄ በልዖሙ -(ሄርማ)

ፄአ -ገማ ሸተተጸዪእ ጼአ።

ፄዐ -ገማ ሸተተጸዪእ

ፄወወ -ማረከ፤ፀየወወ።

ፄዋ -ምርኮ ምርኮኛ ግዞተኛ የምርኮ ማኅበር ምርኮነት ምርኮኛነት ይመይጥ ፄዋ ሕዝብየ ሥኡ ብዙኀ ፄዋ እምሕሮሙ ለፄዋሁ ወሀሎኩ ማእከለ ፄዋ -(ኢሳ፵፭ -፲፫ ፪ዜና -፳፰ -፲፯። ኤር፴፯ -፲፰ ሕዝ፩ -)

ፄዋዊ -(ዊት ውያን ያት) የሚይማሀ፤ ማራኪ ዘራፊ፤ ወሳጅ

ፄውዎ ዎት -(ፄወወ ይፄውው ዕብ ሻባህ ሱር ሽባእ። ዐረ ሰባ) መማረክ መዝረፍ መሳብ መጐተት፤ በግድ መውሰድ መንዳት። ፄዊወከ ፄዋ። አኀዙ ይፄውዉ ሀገረ። ወወኒ መንገሌዑ -(መዝ -፷፯። ኩፋ -፲፩። ሮሜ፯ -፳፫ )

ፅሒስ ሶት -(ፀሐሰ ይፅሕስ ይፅሐስ ዕብ ዱጽ ሱር ዳጽ ዐረ ደሐጸ) ማሸብሸብ፤ ማርገድ፤ መንጐራደድ፤ መዝለል መጨፈር መደንከር፤ ዳንኪራ መምታት፤ መርገጥ ማስረገጥ መወሳወስ፤ የእግር የጫማ። ይፅሕሱ በእገሪሆሙ ውስተ እሳት -(ገድ -ተክ) በፀሐሰ ፈንታ ፅሐሰ ይላል ስሕተት ነው ያፅሕሳ በእገሪሆን አፅሕስ በእገሪከ። አፅሐሰት በእገሪሃ ወጠፍሐት በእደዊሃ ጠፊሓ በአእዳው ወአፅሒሳ በአእጋር -(ኢሳ፫ -፲፮ ሕዝ፮ -፲፩ ድጓ። አርጋ)

ፅሙም -የደረቀ የጠበቀ፤ ክራራ ጠንካራ ጽኑዕ ኅቱም ውፅ ሎሙ ማየ ምኰኵሕ ፅሙም -(አፈ -ድ፮) ጽሙምን ተመልከት፤ ጸመና ፀመመ አንድ ናቸው

ፅሙር -(ራን ራት ምርት) የተጨመረ፤ ጭማሪ ጭምር፤ ያበረ የተባበረ የኾነ። መልአክ ዘፅሙር ምስሌሁ -(አዋል) ሙረ ተጨምሮ ኹኖ ባንድነት -(ኤፍ -)

ፅሙድ -(ዳን ዳት ምድ) የተጠመደ የተገዛ፤ ትጉህ፤ መናኝ ባሕታዊ ፅሙዳን ታሕተ ርዑተ ኦሪት። እለ ፅሙዳን ለከርሦሙ ይኩን ቁሀ ወፅሙደ ወልብወ ብፁዕ ጴጥሮስ ፀሙድ ቅዱስ ወፅሙድ መስተጋድል፤ ሰረባሞን -(አርጋ -፭። አፈ -፳፱ ፈላስ። ስንክ -ጥር፳፭ መጋ፭)

ፅማሬ ፅምረት -መጣመር መጨመር፤ አጨማመር ጭመራ፤ አንድነት፤ ተዋሕዶ። ፅምረተ ህላዌ። ፅምረተ ሥላሴ እኁዛን በፅምረት -(ተረ -ቄር አትና)

 -ሩካቤ፤ የሩካቤ ሥራ ለእ ወረደት ላዕሌከ በሌሊት ሕልመ ፅምረት ትዝክራ በመዓልት -(ፊልክ -፻፸፩)

ፅምድ -(ዳት) ጥማድ፤ ጥንድ፤ ኹለት። ፅምደ አልሕምት ምደ ብዕራይ -(ኢዮ፩ -፫። ፫ነገ -፲፱ -፲፱፳፩ ኢሳ፭ -፲። ሉቃ፲፬ -፲፱)

ፅሩር -(ራን ራት ርርት) የተፃረረ የተፀረረ ዝግጁ፤ ሰልፈኛ። በቁሙ ጥሩር የራስ ቍር ድርዕ የሰልፍ ልብስየጦር መሣሪያ ጌራንና ድርዕን ተመልከት እስመ ሩራን ሙንቱ

ፅሩዕ -(ዓን ዓት ርዕት) የቦዘነ ቦዘንተኛ፤ ታካታ ሰነፍ ሥራ ፈት፤ የተጓጐለ ኢታንብሮ ፅሩዐ። ፅሩዓን ጾርሑ። ኮንክሙ ፅሩዓነ ፅሩዕ ምነሶሳው -(ሢራ፴ -፴፮። ዘፀ፭ -፰። ፪ጴጥ - -፰። ጥበ፲፭ -፲፭)

 -ከንቱ ብላሽ፤ ፈራሽ ውሸት ቧልት፤ ዋዛ ፈዛዛ ያለፈ የቀረ የተሻረ ውጥን ዥምር ምግባር ፅሩዕ ዘኢይበቍዕ ይከውን ጻማሆሙ ፅሩዐ ይከውን ፅሩዐ ሰብሳበ ዚኣሃ። ሕንጻ በረ ፅሩ -(አፈ -ተ፪። ዮሴፍ። ማቴ፲፪ -፴፮። - - -፲፪ ዕዝ፬ -፳፬)

ፅሩፍ -(ፋን ፋት ርፍት) የተሰደበ፤ ስዱብ፤ ንቁፍ፤ ነውረኛ መኑ ከመ ፅሩ ወዘእንበለ ትምህርት ሩፍ ዘትሜንን ቢጸከ -(ቄር - ቀሌ) በፀራፊ ፈንታ ፅሩፍ ይላል ስሕተት ነው ኢትኩኑ ፅፍሩነ -(፪ጢሞ - -)

ፅርስ -( ፅረስ) ጥርስ፤ ክራንቻ መንጋጋ ፀና ተወራራሾች ስለ ኾኑ ፅርስ ጥርስ እያለ በኹሉም ይገኛል። ፅርሰ ወሰነ ውስተ ፅረሲሆሙ -(ዘፀ፳፩ -፳፯። ዘኍ፲፩ -፴፫)

ፅርዐት -(ታት) መታከት መቦዘን ሥራ መፍታት፤ መቅረት መታጐል፤ ማስታጐል ፅርዐተ ዕደው የሀቦ ርዐቲሁ ይግበሩ ፈቃደከ ዘእንበለ ፅርዐት። ቅዳስያት ዘእንበለ ርዐታት -(መክ፲ -፲፰ ዘፀ፳፩ -፲፱ ቀሌ ቅዳ።ስንክ -መጋ፳፬)

 -ቦዘን፤ በዓል፤ የዕረፍት ቀን፤ ጊዜ፤ ጉባኤ። በመዋዕለ ርዐቱ። ቀድሱ ፅርዐተ ጣዖት። ጾመክሙ ወፅፀርዐተክሙ -(ጥበ፲፫ -፲፫ ፬ነገ - -፳። ኢሳ፩ -፲፫)

 -ኀጢአት፤ አምልኮ ጣዖት፤ ከንቱ ነገር፤ ከንቱነት ምናምንቴነት። ከመ ያእምሩ ፅርዐተ ሥርዐተ አማልክቲሆሙ ተከሥተ ርዐት ወተኀብአ ጽድቅ ዘይዴግን ፅርዐተ -(ዮሴፍ። ምሳ፲፪ -፲፩)

ፅርዕ -ግሬክ ዮናንጽርእ።

ፅርፈት -(ታት) መስደብ፤ መሰደብ፤ አሰዳደብ፤ ስድብ ውርደት። ኢተኀበለ ይንብብ ቃለ ፅርፈት። ኮነ ቃለ ርፈቱ ሙመ ርፈታት -(ይሁ -፱። - -፳፬ ራእ፲፫ -)

ፅበስ -ድካም፤ ሕማም፤ ስንፍና፤ ፍርሀት። ሴስል ፅበሰ ምላዕሌክሙ -(ዘፀ፳፫ -፳፭ ፊልክ)

ፅቡስ -(ሳን ሳት ብስት) የደከመ ድኩም፤ ልል፤ ፈሪ፤ ሰነፍ ዐንካሳ። ንህብ በኀይላ ብስት። እስመ ኅሊና ፅቡስ ምኑነ ይትበሀል። ትኩን ፅቡሰ በኵሉ ዘገበርከ ደው ፅቡሳን -(ምሳ፮ -፰። ጥበ፪ -፲፩ ሢራ፴፬ -፳፪ ኢሳ፴፭ -፫። ዕብ፲፪ -፲፪)

ፅቡጥ -(ጣን ጣት ብጥ) የተያዘ፤ የተጨበጠ ጭበጥ። ስይፍቲሆሙ ምሉኃን ወፅቡጣን በእደዊሆሙ -(ስንክ -ታኅ፰)

ፅብሰት -መድከም፤ መስነፍ፤ ደካምነት።

ፅብን ፅብጥ -( ፅበን፤ አፅባን) መያዣ መጨበጫ እጀታ ዦሮ፤ ቀለበት፤ የሣጥን የመሣሪያ ፩ኛው ቅጥል ስለ ቀረ የነበረው ተብሏል እንጂ ዘሩ ፀቢጥ ነው። ብን አርባዕ ዘወርቅ፤ በአፅባን ዘዲበ ታቦት -(ዘፀ፳፭ -፲፪ና -፲፭)

ፅብጠት -መጨበጥ -(ጥጨ) መጨበጥ አጨባበጥ በጣ ጭበጣ፤ ጭብጥነት እንተ ትትረከብ ብጠቱ -( - -፴፰)

ፅኑስ -(ሳን ሳት ንስት) የፀነሰ ያረገዘ እርጉዝ ናሁ ንስት አንቲ ወትወልዲ አሌ ሎን ፅኑሳት ፅኑሳተ ገለዓድ -(ዘፍ፲፮ -፲፩ ማቴ፳፬ -፲፱ ዓሞ፩ -)

 -የተፀነሰ፤ የተረገዘ፤ የሆድ ውስጥ ልጅ -(ተረት) የታዘለ በለምድ፤ የተረገዘ በሆድ።

ፅናሴ ተፅናስ -ችጋር፤ጸንሶ ጸነሰ።

ፅንሰት -መፅነስ መፀነስ፤ ፅንስነት፤ እርጉዝነት መዋዕለ ፅንሰታ -(ስንክ -ሠኔ፴ ነሖ፯)

ፅንስ -በቁሙ፤ የማሕፀን ፍሬ የልጅ ቡቃያ ሽል፤ እርግዝና ሐሳብ ምኞት ዘአይኑ ብእሲ ዝንቱ ንስ ፅንስ ንበለ ሩካቤ ምቅድመ ፅንሶን ፅንስ እንዘ ባቲ መዋዕለ ፅንሳ ኪያሁ -(ዘፍ፴፰ -፳፭ ቅዳ - - -፩። ዕር -ኢሳ፲፩ -፭። - -፴፫ -)

ፅንብል -(ጠብለለ) ጫንብላ፤ የራስ የግንባር ጌጥ ሽልማት፤ የሚጠመጠም የሚታሰር ሐዲስ ጥሩ ልብስ፤ መጐናጠፊያ ባለሟል ሲሾም ሲሸለም የሚለብስው። ልብሰ መንግሥት ዘቦ ክሲለ ወርቅ ወፅንብል ሢራየ ሜላት -(አስቴ፰ -፲፭)

ፅንፅንያ -ጥንጣን፤ ዝንብ፤ጸንጸነ

ፅዉስ -(ሳን ሳት ውስት) የለመሸ ልምሹ ሽባ ሰላላ ደካማ ብእሲ ዘፅዉስ እገሪሁ ዘፅውስት እዴሁ ስፍነ ዕደወ ኀያላነ ሰየ ሞት ይትዋነይዎሙ ዕፄያት ፅዉሳት -(ግብ፫ - ማር፫ -፫። ግንዘ)

ፅዉግ ዝኒ ከማሁ ኀበርነ አውግዞ ፅዉጋተ ወጥሉቃተ ትምህርታቶ (ተረ ቄር፲፬)

ፅጉዕ -(ዓን ዓት ግዕት) የተጠጋ የተደገፈ፤ ጥግ የያዘ፤ የተኛ።

ፅግመት -ጥመት፤ ጠማምነት፤ ግራኝነት።

ፅግም -ግራ ጐን እጅ ቦታ ስፍራ የግራ ግራ፤ ቅርብ አጠገብ። ዲፍ በይምን ወበፅግም ማይሰ ሎሙ አረፍተ በይምን ወአረፍተ በፅግም እኅትኪ ዘትነበር በፅግምኪ -(፩ዜና -፲፪ -፪። ዘፀ፲፬ -፳፱ ሕዝ፲፮ -፵፮)

ፅግዕ ፅጋዕ -(ዓት) ጥግ ደገፋ መጨጊያ መከዳ ትራስ ወይገብራ ፅጋዐ ኵሉ ርእስ። ወእሠጥጥ ፅጋዓቲክሙ -(ሕዝ፲፫ -፲፰ -፳፩)

ፅፉር -(ራን ራት ፍርት) የተታታ የተሠራ፤ ጕንጕን ሽርብ። ሥረዊሁ ፅፉር። ትግብር ሥዕርተከ ፍቱሐ ወዝርዙረ ወኢፅፉረ እለ ፉራት በኀጢአት -(ኢዮ፵ -፲፪ - -፲፩። ፪ጢሞ - -)

ፅፍረት -መታታት መሥራት፤ መሠራት አሠራር ሥራ  ሰሌን ወንፊት። በእንተ ፅፍረት ደጓዕሌ ለዘኮነ ይፀፍር ፅፍረተ -(ፊልክ -፻፫ና -፻፹፱)

ፅፍሮ -የጠጕር ሥራ ትት፤ ጕንጕናት፤ ሽርባት ሽሩባ፤ ዐይነ ርግብ፤ የራስ የጠጕር ጌጥ ሽልማት። ሰላም ለሥዕርተ ርእስኪ ዘተንእደ ፅፍሮሁ ወፅፍሮ ርእስኪ። ሐብለት ዘፅፍሮ -(ደራሲ። ማሕ፯ -፮። ዘፀ፴፩ -)

 -ቍጥራት ቅጥል፤ ቅጥልጥል፤ የጠፍር የገመድ የልጥ የሹጥ በኮሶ ቀን

ፅፍዕ ፀፍዕ -ፀፍዕ -(ጸፍዐ ዐረ ፀፍዕ ጻፊዕ) እበት በት፤ ጥፍጥፍ ዐዛባ ፈርስ ፍግ በጠጥ ፋንድያ ወሀብኩከ ፅፍዐ ሕም ህየንተ ፅፍዐ ሰብእ ከመ ፀፍዕ ዱፍ -(ሕዝ፬ -፲፭ ሢራ፳፪ -)

ፆማዕት -ዋሻ በአትጾማዕት

ፆረ -ተሸከመጸዊር ጾረ።

ፆርሮ ሮት -(ፆረረ ይዖርር ጸዐረ) መጨነቅ፤ ማጣር መጮኽ መዛበር መቀባጠር መታወክ መቅበጥበጥ መንቈራጠጥ፤ መናወዝ መቃበዝ የሥቃይ የደዌ የምጥ የሐዘን ፀረረን ተመልከት። መጽሐፍ ግን በፆረረ ፈንታ አንፆረረ ይላል ወኵሎ ሌሊተ ታንፆርር -(ኢዮ፪ -)


No comments:

Post a Comment

ማውጫ

ሀ   ለ   ሐ   መ   ሠ   ረ   ሰ   ሸ   ቀ   በ   ተ   ቸ   ኀ   ነ   ኘ   አ   ከ   ኸ   ወ   ዐ   ዘ   ዠ   የ   ደ   ጀ   ገ   ጠ   ጨ   ጰ   ጸ   ፀ   ፈ   ፐ