ሀ ለ ሐ መ ሠ ረ ሰ ሸ ቀ በ ተ ቸ ኀ ነ ኘ አ ከ ኸ ወ ዐ ዘ ዠ የ ደ ጀ ገ ጠ ጨ ጰ ጸ ፀ ፈ ፐ
ለ [1]፡-፲፪ኛ ፊደል በግእዝ አልፍ ቤት በአበገደ፤ ስሙ ለውይ፤ ላዊ። ቍጥሩ ሠላሳ፤ አኃዝ ሲኾን ፡-(ለ–፴) ሠላሳ ይባላል።
[2]፡-(ደቂቅ አገ) በቁም ቀሪ፤ የ፤ ዘርፍ አያያዥ፤ የዘርፍ ደፊ፤ ተጠቃሽ ን፤ ከ ተ፤ ወደ፤ አዳማቂ፤ ተቀባይ፤ አቀብሎ ሸሽ፤ ላይ በ፤ ስለ፤ ቦ ይኾናል። ልየ፤ ሊተ፤ ለከ፤ ለኪ፤ ሎ፤ ሎቱ፤ ላ፤ ላቲ። ለነ፤ ለክሙ፤ ለክን፤ ሎሙ፤ ሎቶሙ፤ ሎን፤ ሎቶን እያለ፤ እንደ በ ይዘረዝራል። ለአበዊነ ለአብርሃም ወለዘርዑ፤ በቁም ቀሪ። ለእግዚአብሔር ምድር በምልኣ፤ የ። ሐማቱ ለስምዖን፤ ዘርፍ ኣያያዥ። ለኖኅ ሐመሩ ፥ ለአሮን በትሩ፤ ደፊ። ኅድጋ ለመዐት ፥ ወግድፉ ለቍጥዓ፤ ተጠቃሽ ን። ተከፍለ ለክልኤ፤ ተሠጠ ለክልኤ፤ ከ ተ። ኢትበል ለየማን፤ ኢለፀጋም፤ ወደ። ለእመ ርኅበ ጸላኢከ፤ ለኀበ ሰማያት፤ አዳማቂ። ስብሐት ለእግዚ። ኵሉ ለአምላክ፤ ማሰሪያ ሰጭ፤ ወይም አቀባይ። ይደሉ፤ ይትከህል አለበት፤ ምስጢሩ ከየና ከበቁም ቀሪነት ይገባል። ለይትጋባእ ማይ፤ ለታውፅእ ባሕር፤ አቀብሎ ሸሽ። የዚህም ምስጢር አዳማቂ ካለው ይገባል። ወአምጽአ ረኀብ ለብሔር፤ በምድር ላይ። ኢትጸሊ ለዝ ሕዝብ፤ ስለ። ለ ላዕልና በእንተ መኾኑ በመላሾች ስሕተት ነው እንጂ ፍችው ኹኖ አይዶለም፤ ጽርኡም ዕብራይስጡም ላዕለ ምድር፤ በእንተ ዝ ሕዝብ ያሉትን ለብሔር ለሕዝብ እያሉ አላገባቡ ጥፈውታል። ነባር አንቀጽ ሲኾን፤ ወሎቱ ብእሲት ወውሉድ እያለ ይዘረዝራል፤ ቦ ቦቱ ማለት ነው። ሊተ ለከ ያለውም በዚህ ኹሉ አፈታት ይፈታል፤ ሊተ ለኔ የኔ እኔን ወደኔ፤ ልኝ አለኝ አለልኝ ያሰኛል። ሊተ ወሀብከኒ፤ ሊተ ውእቱ ስምዑኒ ሊተ፤ አምጽኡ ሊተ፤ ወይ ልየ፤ ሰይ ልየ፤ ወይ ሊተ፤ አሌ ሊተ፤ ሊተ ዐርክ ምእመን እያለ ሌላውን ኹሉ ያሳያል። ዝናም ለመጺእ ቢል ፥ ሊመጣ ያሰኛል፤ የለ ስልትና አፈታት በመጻሕፍት ውስጥ ብዙ ነው። ፡-(ዕር፳፩ ፡-ቍ፻፲፫። ዕር፲፩ ፡-ቍ፺፫)።
ለሓማ ፡-(ዐረብ) በቁሙ የማዕደናት መጣብቅ።
ለሀሰ ፡-ላሰ ላላሰ፤–ለሐሰ።
ለሐሰ ፡-(ዐረ ለሒሰ። ዕብ ወሱር ላሓኽ) ላሰ ቀመሰ፤ በላ ጠጣ ፥ ምላሱን አንቀሳቀሰ፤ ጠረገ አበሰ። ከለባት ይልሕሱ ቍሰሊሁ። ለሐሱ ከለባት ደሞ። እሳት በልዐት መሥዋዕቶ ወለሐሰት መሬቶሂ። ኢትልሐስ መጻብኅተ ፡-(ሉቃ፲፮ ፡-፳፩። ፫ነገ ፡-፳፩ ፡-፲፱። ፲፰ ፡-፴፰። ሢራ ፡-፴፬ ፡-፲፬)።
፡-መጠጠ ፥ መጠመጠ። በከመ ይልሕስ ጽሙእ ወይሰቲ እምነ ኵሉ ማይ ፡-(ሢራ ፡-፳፮ ፡-፲፪)።
፡-ደረቀ ፥ ኰበተ፤ ላሸ ዛገ። ይልሕስ ልሳኖሙ በጽምእ ፡-(ኢሳ፵፩ ፡-፲፯)።
፡-አሰላ ፥ አሾለ፤ አሾተለ፤ ለመላስ ለማልመጥ ወይም በነገር ለመጐነጥ፤ ምስጢሩ የለኈሰ ነው። ከልብ ጥቀ ኢይልሕሶሙ በልሳኑ። አልቦ ዘለሐሶሙ በልሳኑ። ከልብ ኢይልሕስ ልሳኖ በቅድሜከ፤ አሳባቂ ነገረ ሠሪ ፡-(ዘፀ፲፩ ፡-፯። ኢያ፲ ፡-፳፩። ዮዲ፲፩ ፡-፲፬)።
ለኈሰ ፡-(ልሒስ ለሐሰ። ዕብ ላሐሽ) ለኰሰ አቃጠለ፤ ሹክ አለ ፥ በዦሮ ነገረ። ሾከከ፤ ተንሿከከ፤ በዦሮ ለመንገር ፥ ወይም ለመሰማት፤ እንደቅኔ መሪ እንደ ተመሪ። ዘሩ ልሒስ ነው፤ አካኼዱና መንገዱ ሰቈረን ይመስላል።
ለኈሳስ ፡-ሹክታ ፥ ሹክሹክታ፤ ምስጢር ፥ ቀስታ። ይትናገሩ በለኈሳስ። አርአዮሙ በለኈሳስ መጻሕፍቲሁ ፡-(ኢሳ፰ ፡-፮። አስቴ፫ ፡-፲፬)።
፡-ድጋም ኅቡእ ንባብ ፥ ጽራሐ ልብ ፥ ኅሊና ልብ ፥ ጸሎተ ነፍስ። አልቦ ማኅለቅተ ቅኔ በልዑል ዜማ ዘእንበለ በለኈሳስ። ወዓዲ በል በለኈሳስ እግዚኦ መሐረነ ምእተ ጊዜ። ንጸመም ዐውያተ ልሳን ከመ ዘኢይሰምዕ ወነአምር ለኈሳሰ ልብ ፡-(ስንክ ፡-ግን፲፩። ቄድር። ቅዳ ፡-ግሩ)። አልኆሳሰ፤ ለኆሳስ እያለ በሳብዕ ይጥፋል፤ ስሕተት ነው። ግስነቱ እንዳስቈቀወና እንዳስቈረረ ቅጥይ ተቀጥላ ነውና፤ ቈቀወንና ቈረን እይ።
ለሐቀ ፡-(ዐረ ለሒቀ) ለጠቀ አጣበቀ፤ አጣብቆ ያዘ።
ለሓኵ ፡-(ኵት ኵያን ያት) የሚሠራ ሠሪ፤ ፈጣሪ። ይብሎኑ ልሕኵት ለለሓኵሁ። ለሓኵ ወፈጣሪ ፡-(ኢሳ፳፱ ፡-፲፮። አፈ ፡-ድ፪)።
ለሓዲ ፡-(ዲት ድያን ያት) የሚያሟርት ፥ ማርተኛ፤ ጠንቋይ። ለሓዲ በትእምርት ወዘይትኣመር በንቅወተ አርዌ ፡-(ቈስጠ ፡-፲፫)።
ለሐጸ ፡-(ዕብ ላሐጽ፤ ለተመ አጣበቀ) ላጠ መለጠ፤ ቀረፈ ገፈፈ። ሥረዊሁ ይረምፁ በእሳት ወይልሕጹ ፡-(መ ፡-ፈ። ዘፍ፴ ፡-፴፯)።
ለሐፈ ፡-(ዐረ ለሂፈ) ዐዘነ ተከዘ፤ ተጨነቀ ዐሰበ። መጽሐፍ ግን በለሐፈ ፈንታ ተልሕፈ ይላል፤ ስሕተት ነው። ውስተ ዘኢኮነ ትካዝከ ኢትትለሐፍ ፡-(ሢራ፲፩ ፡-፱)።
ለሆሳስ ፡-ሹክሹክታ፤–ለኈሰ።
(ጥ) ለለ [1]፡-(ሌለየ) ደቂቅ አገባበ፤ በበንና ዘዘን የመሰለ። ከተጸውዖ ስም በቀር በብትን ኹሉ፤ ዘርዝሮም ሳይዘረዝርም እየገባ እየ ፥ ደጊመ ቃል ይኾናል፤ በቁም ቀሪነትም አለው። ለለ ዕለቱ፤ ለለ ርእሱ፤ እየለቱ እየራሱ፤ እየለት እየለቱ፤ እየራስ እየራሱ። ለለ አሐዱ፤ እያንዳንዱ ፥ ለያንዳንዱ። አንዱም አንዱም፤ ላንዱም ላንዱም። በበ በማለት ፈንታ። ለለ ይላል፤ የመላሽና የጣፊ ስሕተት ነው። ምዕረ ለለ ዓመት። ይበክዩ ለለ ዓሙ። ወለለ በዓል።
[2]፡-ዐቢይ አገባብ፤ አመንና እንዘን የመሰለ፤ በኀላፊና በትንቢት ይገባል። ለለ ተናገርኩ አዐወዩ በግፍዕ። በተናገርኹ ጊዜ፤ ስናገር ስናገር ፡-(ኤር፳ ፡-፰)። ወለለ ወለዳ ተባዕተ ቅትላሁ፤ ወንድ ወንድ ሲወልዱ፤ በወለዱ ጊዜ ፡-(ፈ ፡-መ ፡-፳፫ ፡-፪)። ለለ ይወፅኡ ውስተ ጸብእ። ወኮኑ ለለ ይሰምዑ ነገሮ ያፈደፍዱ ግዘፈ ፡-(አቡሻ ፡-፶። ዮሴፍ)። ፡-(ዕር፳፩ ፡-ቍ፻፲፫)።
ለለ አሐዱ ለለ አሐዱ አሐዱ ፡-ለያንዳንዱ፤ ላንዱም ላንዱም፤ ለኹሉ ፡-(ዘፍ፲፪ ፡-፬)።
ለሊነ ፡-(ክሙ ክን ሆሙ ሆን) እኛ ቅላችን፤ ራሳችን ባለቤታችን። ለሊነ ሰማዕነ ወጠየቅነ። ዘለሊነ ነአምር አባሁ ወእሞ ፡-(ዮሐ፬ ፡-፵፪። ፮ ፡-፵፪)።
ለል ፡-ርስ ፥ ራስ የራስ ቅል፤ ባለቤት፤ አካል። የተገብሮ ዐጸፋ እየኾነ እንደ ውእቱና እንደ ኪያ እስካሥር መደብ ይረባል።
ለልየ ፡-(ሊከ ኪ ሁ ሃ) እኔ ቅሌ፤ ራሴ ባለቤቴ። ለልየ በእዴየ ፡-(ድጓ)።
ለመጸ ፡-(ለሐጸ፤ መለጠ) ለመጠ፤ ለምጣም ኾነ። ለዘበ ፥ ለሰለሰ። እብን ይለምጽ እማይ ፡-(ኢዮ፲፬ ፡-፲፱። ገድ ፡-አዳ ፡-ገ፲፯)።
፡-ለመጠ ፥ ለማመጠ፤ ዐረቀ፤ ለማስተካከል ፥ ወይም ለማጣ ጐባጣ ለማድረግ።
ለሚድ ዶት ፡-(ለመደ ይለምድ ይልምድ። ዕብ ላማድ። ዐረ ለመደ። ሱር ልማድ፤ ተማረ) መልመድ፤ ማወቅ መውደድ፤ ለማዳ ቤተ ሰብ መኾን፤ ማዘውተር። ዘኢትለምዱ ይበጽሐክሙ። ደም ዘይለምዳ አንስት። እሙንቱ ይለምዱ ቤቶ ፡-(፩ጴጥ ፡-፬ ፡-፲፪። ዲድ ፡-፴፫። ስንክ ፡-መስ፳፰። ታኅ፯። ፊልጵ፬ ፡-፲፪)።
፡-መማር ፥ ልማድ ማድረግ፤ ፊደል መቍጠር ፥ ዕውቀት መጨመር፤ በማየት በመስማት በነቢብ በገቢር፤ ምስጢሩ ከዚያው ከመልመድ አይወጣም። «ማጥራት ማበጠር፤ የምርት የነገር»። ልሳኖሙ ለመደ ተናግሮ ሐሰት። ከመ ኢይልምዱ ፀሪፈ። ዘከመ ይለምዱ ብዙኃን። እለ ቀቲለ ለመዱ። እስመ ኢለመዱ አፍራሲሁ ተጻብኦ ምስለ መስተጽዕናነ ነጌያት። ኢለመደ ከመ ይፃእ እምበኣቱ ፡-(ኤር፱ ፡-፭። ፩ጢሞ ፡-፩ ፡-፳። ዕብ፲ ፡-፳፭። ምሳ፩ ፡-፲፰። ዮሴፍ። ፊልክ ፡-፻፲፭)። በለመደ ፈንታ አልመደ ይላል፤ ስሕተት ነው። እለ ያለምዱ ዝሙተ ፡-(ፈ ፡-መ ፡-፯ ፡-፪። ማቴ፳፯ ፡-፲፭)።
ለምለመ ፡-(ሐመለ፤ አሕመልመለ። ዕብ ላብሌብ) ለመለመ ረጠበ፤ ቅጠል አወጣ። እምከመ ለምለመ አዕጹቂሃ። ከመ ይለምልሙ ዕፀው ፡-(ማር፲፫ ፡-፳፰። ተረ ፡-ባሮ)።
፡-ራሰ ለዘበ ለሰለሰ፤ ልሕሉሕ ኾነ። ከመ እብን ዘኢይለመልም። አእባን እንዘ ይለመልሙ ከመ ሠምዕ። ኢትለመልም አልባቢሆሙ ፡-(ገድ ፡-ተክ። ገድ ፡-ላሊ። ዮሴፍ)።
ለምለም ፡-(ብ ለማልም። ዕብ ሊብሉብ) በቁሙ፤ ሐመልማል፤ ለጋ ቀንበጥ፤ ቅጠል ዐጽቅ፤ ለባልብ ውልብልቢት፤ ጫፍ ሙሽራ። ወመተሮ ኀበ ለምለሙ። ርእሶ አንደየ ለምለመ ዕፅ ተሴሰየ፤ ጠለ ገዳም ሰትየ። ሲሳይከ ልምለመ ዕፅ ፡-(ሕዝ፲፯ ፡-፬። ድጓ። መዋሥ)።
ለምንት ፡-ለምን፤–ሚ ምንት።
ለምአ ፡-ለማ በራ፤–ለምዐ።
ለምዐ ፡-(ለሚዕ። ዐረ ለመዐ) ለማ ፥ ለም ኾነ፤ ያገር። ጠራ በራ ቍልጭ አለ፤ አማረ ተከናወነ፤ የብርሃን የማዕድን የመልክ የግብር። መጽሐፍ ግን በለምዐ ፈንታ ተለምዐ ፥ ተላምዐ ይላል፤ አያሰኝም። በእደ ኬንያሁ ይት(ለ) ላማዕ ግብሩ ፡-(ሢራ፱ ፡-፲፯)።
ለምድ ፡-በቁሙ፤ ደበሎ የደበሎ ዐይነት፤ የወታደሮች ጌጥ ሽልማት። አንቀልባ ነት፤ የልጅ ማዘያ። ፡-(ተረት) የታዘለ በለምድ፤ የተረገዘ በሆድ።
ለምጻዊ ፡-ለምጣም፤ ለምጥ የወጣበት። ፡-(ግጥም) አትቅጣኝ እንደኾን በቍርጥ ፍርድኽ፤ ያለምጣም ምኒልክ ብዬ ልስደብኽ ፡-(የዓለም ጣዕም)።
ለምጽ ፡-(ዕብ ጻራዓት። ዐረ በረጽ) በቁሙ ፥ ለምጥ፤ የቈርበት ደዌ የቍምጥና ወገን የተላጠ የተመለጠ ዕንጨት የሚያስመስል። ሠረጸ ለምጸ ውስተ ፍጽሙ። ወነበረ ውስተ ለምጽ አስከ አመ ሞተ። ናሁ ኀደጎ ሕብረ ለምጹ ለዘለምጽ ፡-(፪ዜና ፡-፳፮ ፡-፲፱ ፡-፳፩። ዘሌ፲፬ ፡-፫)።
ለሰነ ፡-(ዕብ ላሼን) ለፈለፈ ቀባጠረ፤ አፈቸለ ተናገረ፤ ፊት ለፊት። ነገር ሠራ አሳበቀ፤ ባንደበት ፥ ወይም በወረቀት። መጽሐፍ ግን በለሰነ ፈንታ ተለሰነ ይላል፤ ስሕተት ነው። ዘእንበለ ጥበብ ይትሌስኑ ፡-(ቄር ፡-ጰላ)። ለዐለን እይ፤ ይህም እንደዚያ ነው።
ለሰደ ፡-(ዐረ ለሰደ) ጠባ መጠጠ፤ ጨመቀ አፈረጠ፤ የጡት የፍሬ። ረጋ ጸና፤ የወተት የማር የፈሳሽ።
ለሳኒ ፡-መለስን፤ ለፍላፊ ፥ አሳባቂ ፥ ምላሰኛ፤ ለሳኝ።
ለስሐ ፡-(ለትሐ) ለፈጨቀ፤ አፉን ምላሱን አጮኸ፤ እንጯ እንጯ አለ። ኢትልሳሕ እንዘ ትሜጽር ፡-(ሢራ፵፬ ፡-፲፮)። ለስሐና ለትሐ የልሒስ ዘር ናቸው።
፡-ላሸ ፥ ዐለጠ፤ ዐልጫ ኾነ ጣዕም ዐጣ፤ ከዚህ የተነሣ ተናቀ ተጠላ ተነቀፈ፤ የምግብ ያንደበት የነገር። ወእመሰ ጼው ለስሐ በምንት ይቄስምዎ። ውስተ አፉሁ ለአብድ ይለስሕ አምሳል። ከመ ኢትልሳሕ በእበድከ። ለስሐ ኀይልየ ወደከመ በጸሎትከ ፡-(ማቴ፭ ፡-፲፫። ሢራ፳ ፡-፳። ፳፫ ፡-፲፬። ገድ ፡-ተክ)።
ለስኖ ኖት ፡-(ለሰነ ይሌስን ይለስን) መለሰን መምረግ፤ ምርግን ማስተካከል፤ ምላስ የላሰው ማስመሰል፤ የጭቃ። ገብሰሰን እይ ፡-(ዐማርኛ)።
ለስድ ፡-(ዕብ ልሳድ) ጭማቂ ውጤት ፡-(ደም ወተት) ዕትብት አሰጅ ፥ እንግዴ ልጅ። ለስታ ለጋ ትኵጅ ቅቤ፤ ከረጋ ወተት የሚወጣ፤ ዝብድን እይ። ሕልብ ሐሊበ ወይከውነከ ለስደ ፡-(ምሳ፴ ፡-፴፫)።
ለሮስ ፡-(ዕብ ላሮስ) ለማራስ ለማረስረስ፤ ለማበቅ ለማበስበስ፤ ለማርጠብ ለመለወስ፤ ለማፈርፈር ፥ ለመለፈጥ። ዘሩ ራሶስ ራስ ያሩስ ነውና፤ ርሕሰንና አርሐሰን ለፈጸን እይ ፡-(ሕዝ፵፮ ፡-፲፬)። ዳግመኛም፤ ለሮስ በማለት ፈንታ ለለዊስ ይላል፤ ፍችው አንድ ነው።
ለሮን ፡-(ጽር ላሮስ። ሮማይ ላሩስ። ዕብ ሻሓፍ) የወፍ ስም፤ ድምፁና መልኩ ደስ የሚያሰኝ፤ ደረቱ ብጫቴ ፥ ወርቅማ ፡-(ዘሌ፲፩ ፡-፲፮። ዘዳ፲፬ ፡-፲፭) ባለብሉዮች ግን ይብራ ፥ የባሕር አሞራ ይሉታል።
ለቀመ ፡-(ዐረ ለቀጠ። ዕብ ላቃጥ) በቁሙ፤ ሰበሰበ አከማቸ ፡-(ዐማርኛ)።
ለቀሠ ፡-ዐዘነ አለቀሰ፤–ለቀሰ።
ለቀሰ ፡-(ትግ ለቅሰ። ዐረ ለቂሰ) ዐዘነ ተጨነቀ፤ አለቀሰ ፥ እንብ አፈሰሰ። ዕብራይስጡ ግን ላቄሽ ብሎ ለቀመ ቃረመ ሰበሰበ ይላልና፤ በዚህ ዘይቤ ሲፈቱት ልቅሶኛ መጥራትን አልቅሱኝ ማለትን ያሳያል፤ በከየን እይ።
ለቀቀ ፡-(ዐረ ለቀ። ዕብ ላቃህ) መታ ፥ ጸፋ፤ ገረፈ። አዘዘ ይልቅቅዎ ወይኅምይዎ ውስተ ዘነበ ፈረስ ወያዑድዎ ውስተ ሀገር ፡-(ስንክ ፡-ሠኔ፲፬)። ፪ኛም አስረው ይተዉት ዘንድ ያሰኛል።
ለቀወ ፡-አቀጠለ ፥ ቅጥይ አወጣ፤ የሣር የቅጠል የማሽላ።
ለቀወ ለቀየ ፡-(በቂው በቀወ) ለቀቀ ፥ አላቀቀ፤ አዛጋ አፋሸገ፤ ከፈተ ፈታ፤ የአፍ የቍልፍ። መኑ ከልአክሙ አርምሞ፤ መኑ ለቀዎ ለአፉክሙ ከመ ትንብቡ ዘንተ፤ መኑ አገበረክሙ ለተናግሮ ፡-(መጽ ፡-ምስ)። ወና የ ተወራራሾች ስለ ኾኑ በዘረወ ፈንታ ዘረየ እንዲል፤ በለቀወም ፈንታ ፥ ለቀየ ይላል፤ ሥሩና ምንጩ በቀወ ነው። ጐድጐደ፤ ወሶበ አልቦ ዘያወሥእ ለቀየ ወቦአ ውስተ ጽርሕ ፡-(ዮዲ፲፬ ፡-፲፭)።
ለቀየ ፡-ለቀቀ ከፈተ፤–ለቀወ።
ለቀደ ፡-ለቈደ አሰረ፤ የምላስ። ለገደ ዘጋ፤ የጕረሮ።
ለቂቅ ቆት ፡-(ለቀ፤ ለቀቀ ይለቅቅ ይልቅቅ። ለቀወ በቀወ። ዕብ ላቃቅ፤ ላቅሌቅ፤ ላሰ ሞለቀቀ) መልቀቅ፤ መክፈት። መተው መስደድ ፡-(ዐማርኛ)።
ለቂድ ዶት ፡-(ለቀደ ይለቅድ ይልቅድ። ዕብ ላካድ) መያዝ እጅ ማድረግ፤ ፈልጎ ማግኘት፤ ይዞ ማሳየት። ዘይሌቅድ ብዕለ እንበለ ንዋይ፤ ወግርማ እንበለ ሢመት፤ ወኀይለ እንበለ ዕደው ፡-(ፈላስ ፡-ገ፳፮)።
ለቃሒ ፡-(ሒት ሕያን ያት) የሚያለቃ አለቂ፤ አበዳሪ። ወለእመ ኀለፈ ይደልዎ ለለቃሒ ከመ ይምልክ ዘአኀዘ። በቍዔተ ለቃሔ ፡-(ፍ ፡-ነ ፡-፳፯)።
ለቅሀ ፡-አለቃ አበደረ፤–ለቅሖ ለቅሐ።
ለቅሖ ሖት ፡-(ለቅሐ ይሌቅሕ ይለቅሕ። ዕብ ላቃሕ፤ ወሰደ) ማለቃት፤ ማበደር መስጠት፤ ማስተማር፤ ትርፍ ለማግኘት፤ ኋላ ለመቀበል። በደረንና ተበድረን እይ። እመ ለቃሕከ ብሩረ ለነዳይ። ኢትለቅሖ ለዘይብዕለከ። ብዙኃን እለ ኢይሌቅሑ። ወዘኢለቅሐ ወርቆ በርዴ ፡-(ዘፀ፳፪ ፡-፳፬። ሢራ፰ ፡-፳፪። ፳፱ ፡-፯። መዝ ፡-፲፬)።
ለቅለቀ ፡-(ለቂቅ፤ ለቀ) ለቀለቀ ቀባ፤ መረገ ዘጋ ደፈነ፤ የቤት የዐዘቅት ያውድማ የንቅ የሥንጥቅ። ኢገብአ ውስቴቶሙ ማይ ወለቅለቅዎሙ በዐረር ፡-(አዋል ፡-ትርጓሜ። ኤር፪ ፡-፲፫)። ዐጠበ አጠራ፤ የልብስ።
ለቅዳ ፡-በቁሙ፤ ቅምሖ ያንቃር የጕረሮ የምላስ በሽታ፤ ሕበጥ። ቅምሖ የቀምሐ ዘር ነው።
ለቆ ፡-(ዕብ ሌቄሽ) በቁሙ ፥ ደኃራዊ ሣር፤ ዳግማይ ቡቃያ ቅጥይ፤ ከቈረጣና ካጨዳ በኋላ በገፍና በብላጊ ዝናም የሚበቅል ፡-(ዐማርኛ)።
ለቆታ ፡-(ትግሪኛ) አቅማዳ ስልቻ፤ አፋም አፈ ሰፊ ማለት ነው። አቅማዳፍ ፥ ስልቻፍ እንዲሉ።
ለበን ፡-(ዐማርኛ) ለንቦጭ፤ ታችኛ ከንፈር። ለበናም እንዲሉ፤ በዐረብ ግን ርጎ ማለት ነው።
ለበወ ፡-(ዲቃ ግ። ለበበ፤ ወ የበ ለውጥ ነው) ለበመ፤ ልባም ኾነ። ልብ አደረገ ፥ አስተዋለ፤ ዐወቀ ተረዳ፤ ጠነቀቀ። ለበየን እይ፤ የዚህ፤ መንቲያ ነው። ለቡ ዘትሬኢ። ወዘአልቦ ልብ ኢይሌብዎ ለዝንቱ። ለበውኩ ዘትቤ። ንለቡ ገቢረ ዕለተ ፋሲካ ፡-(ዳን፱ ፡-፳፫። መዝ ፡-፺፩። ቄር ፡-ጰላ። ዲድ ፡-፴)።
ለበየ ፡-(የለበወ መንቲያ) ልበ ቢስ ኾነ ዘነጋ፤ ተሳሳተ፤ ተደናገረ፤ ጸየፈ ኰለተፈ፤ የቃል ያንደበት። እመ እሌቢ ውስተ ነገራትየ ስረዩ ሊተ፤ እስመ እለ ይነግሩ እምአፉሆሙ ድንቀተ ወኢቀደሙ ጽሒፈ ዮጊ ይሌብዩ ወኢይክሉ ለብዎ ወነገረ አሰርግዎ ፡-(ተረ ፡-ቄር)።
ለቢስ ሶት ፡-(ለብሰ ይለብስ ይልበስ። ዕብ ላባሽ፤ ላቤሽ። ሱር ልቤሽ። ዐረ ለቢሰ) መልበስ ፥ መክደን፤ በልብስ ውስጥ መኾን ፥ መጐናጠፍ። ፡-(ተረት) ካልበሉ ሬሳ ፥ ካለበሱ እንስሳ። እንዘ ሠቀ ይለብሱ። ወይለብሱ ብሩሀ ወንጹሐ ፡-(ራእ፲፩ ፡-፫። ፲፭ ፡-፮)። በለብሰ ፈንታ ተለብሰ ፥ ተላበሰ ይላል፤ ስሕተት ነው። ተለበሲ አልባሰኪ። አኮ በተለብሶ አልባስ ዘብዙኅ ሤጡ ፡-(ሩት፫ ፡-፫። ፩ጴጥ ፡-፫ ፡-፫)። ወተላበሰ ንጉሠ እስራኤል። ይፈቅዱ ያንሶስዉ ተላቢሶሙ። ይመጽኡ ተላቢሶሙ አልባሰ አባግዕ ፡-(፪ዜና ፡-፲፰ ፡-፳፱። ማር፲፪ ፡-፴፰። ሉቃ፳ ፡-፵፮። ቀሌ)።
ለቢብ ቦት ፡-(ለበ ይለብብ ይልብብ) መለበብ፤ ልባብ ማግባት፤ ሐስለን እይ። መገረም መጨመት፤ ልበ ቅን መኾን፤ እንደ ተገራ ከብት።
ለቢን ፤ ኖት ፡-(ለበነ ይለብን ይልብን። ዕብ ላባን) ማንጣት ፥ ነጭ ማድረግ፤ ማጠብ ማጥራት። መጥበስ መተኰስ፤ ማጠን ማጤስ፤ የብረት የሸክላ የዕጣን። ስኂንን እይ፤ የዚህ ጎር ነው።
ለቢጥ ጦት ፡-(ለበጠ ይለብጥ ይልብጥ። ዐረ ለበደ፤ ላጠ። ዕብ ላጥ) መለበጥ ማስጌጥ፤ ማልበስ መሸፈን፤ መምረግ መለሰን፤ በወርቅ በጨርቅ በጭቃ በንጨት። ገለወን እይ። ብእሲ ዘይክል ለቢጠ ወርቅ ወብሩር። ወለበጠ እንተ ውስጡ በወርቅ ጽሩይ። ወንጌላተ ለቢጦ በወርቅ ወበብሩር ፡-(፪ዜና ፡-፪ ፡-፯። ፫ ፡-፬። ገድ ዘሚ)። መሠንበጥ፤ ማላገጥ ፥ ለበጥ ማውጣት ፡-(ዐማርኛ)።
ለቢጦን ፡-(ቅብጥ ሊቢቱ) ዐጭር ቀሚስ፤ እጅጌው እስከ ክርን የሚደርስ እጀ ቈራጣ እንደ ኪታ ያለ ፥ የመነኵሴ ልብስ። ለቢጦን ዘሡዕ ፡-(ሥር ፡-ጳኵ)።
ለባሲ ፡-(ሲት ስያን ያት) የሚለብስ፤ ለባሽ። ለባሴ አምላክ። ለባሲተ ሞገስ ወግርማ። ለባስያነ መስቀል ፡-(አረጋ ፡-ድ፳። ደራሲ። ቅዳ)።
ለባዊ ፡-(ዊት ውያን ያት) ልባም ፥ ልብ አድራጊ፤ ተመልካች አስተዋይ፤ ብልኅ ዐዋቂ ጠንቃቂ። ኵሉ ለባዊ ይረክባ ለጥበብ። ፍጥረት ለባዊት ወሥጋዊት። ከመ ይኩኑ ለባውያነ ወንቁሃነ። መናፍስት ለባውያት ፡-(ሢራ፲፰ ፡-፳፰። ግንዘ። ዮሴፍ። ጥበ፯ ፡-፳፫)።
ለባዪ ፡-(ዪት ይያን ያት) ልበ ኢ፤ ልበ ቢስ ደፋር፤ አፉ እንዳመጣ የሚናገር።
ለባጢ ፡-(ጢት ጥያን ያት) የሚለብጥ ፥ ለባጭ።
ለቤሳት ፡-(ጽር ሌቢሲ) ጽህርት ፥ የብረት ድስት፤ በገ ፈጅ ወይም ላመ ፈጅ ፡-(፪ዜና ፡-፴፭ ፡-፲፫)።
ለብሐ ፡-(ዐረ ለበከ) ቀላቀለ ፥ ደላለቀ፤ የዕቃ። ለወሰ ፥ አቦካ፤ ሠራ፤ የጭቃ። ለሐኰን እይ።
ለብሓ ፡-ሸክላ ፥ ከተቦካ ጭቃ የሚሠራ። ንዋየ ለብሓ ፡-(መዝ ፡-፪)።
ለብሓዊ ፡-(ዊት ውያን ያት) የሸክላ ወገን፤ የሸክላ ዐይነት ዕቃ። ሸክለኛ ፥ ሸክላ ሠሪ፤ ጠቢብ። ገራህተ ለብሓዊ። እሉ እሙንቱ ለብሓውያን ፡-(ማቴ፳፯ ፡-፯። ፩ዜና ፡-፬ ፡-፳፫። ሮሜ፱ ፡-፳፩)።
ለብሕ ፡-ቅልቅል፤ ድብልቅ፤ ጭቃ።
ለብዎ ፡-ዝኒ ከማሁ። ለብዎ ወአእምሮ ፡-(ምሳ፪ ፡-፮)።
ለተመ ፡-(ዐረ ለተመ፤ ቀጠቀጠ) በቁሙ፤ መታ ገጨ፤ ወገጠ ፈተገ፤ ኅፅቦ ጕርዶ አወጣ፤ ዐሸ አበቀ፤ የቈሎ የሸት፤ ለዶቄትም ይኾናል፤ ለፈጸን እይ። መለተም ከበግና ከፍየል ውጊያ የመጣ ነው።
ለታሒ ፡-መልትሒ ሕ፤ የሚጐርሥ የሚጐነጭ፤ ከታች አላማጭ።
ለታት ፡-(ለታቲ ቲት ትያን ያት) በቁሙ፤ ለታታ ኰልታፋ፤ ክቡደ ልሳን ፥ አፈ ድዳ፤ አጥርቶ የማይናገር። ወለታት ውእቱ ሙሴ ፡-(ተረ ፡-ቄር፪)።
፡-ለክላኪ፤ አለክላኪ፤ በምላሱ ውሃ የሚልስ የሚጠጣ ፡-(ገድ ፡-አዳ)።
ለትሐ ፡-(ለስሐ) ጐረሠ አላመጠ፤ ተጐነጨ ተጕመጠመጠ፤ ጕንጩን ነፋ አሳበጠ። ከተተ ፥ አገባ፤ ልብስን በሣጥን ፥ ወይም ሰውነትን በልብስ በቀሚስ። መክተትና ማግባት ከመጕረሥና ከመጐንጨት ጋራ ይሰማማል፤ ምስጢሩ አንድ ነው። ለትሐና ለስሐም አኀው ናቸው።
ለትቶ ቶት ፡-(ለተተ ይሌትት ይለትት። ላዕልዐ። ዐረ ለትለተ) መለተት፤ መኰልተፍ ፥ መኰላተፍ፤ ለታታ መኾን፤ ያንደበት። ለትቶ የሕፃናት ነው፤ ከልተፈንና ላዕልዐን እይ፤ መጽሐፍ ግን በለተተ ፈንታ ተለተተ ይላል፤ ስሕተት ነው። ወዝንቱ ሕፃን ቦ አመ ይትሌተት በግዕዘ ሕፃናት፤ ወቦ አመ ይነብብ በነገር ጽኑዕ ከመ ወሬዛ ዘዕሥራ ዓመት። እንዘ ይትሌተት ልሳኑ በሥርዐተ ደቂቅ ፡-(ገድ ፡-ተክ። መጽ ፡-ምስ)።
፡-መለክለክ ፥ ማለክለክ፤ ምላስን መጐልጐል፤ ውሃን በምላስ ማንካ መጨለፍ መጠጣት፤ የውሻ የድመት የአራዊት ፡-(ገድ ፡-አዳ)። መድከም ፥ መልፋት ፥ መታከት፤ የኀይል የጕልበት ፡-(ዐማርኛ)።
ለነ ፡-ለኛ የኛ እኛን፤–ለ–ነ ለከ።
ለንጳስ ፡-(ጽር ላምፒስ። ዕብ ላፒድ) የእሳት ላንቃ ፥ ነበልባል ምላሱ ውልብልቢቱ፤ ወይም ችቦ ፋና ቀንዲል። ብርሃን ዘለንጳስ። ሞጣሕተ ሡራኄ ለንጳስ ፡-(ዘፀ፳ ፡-፲፰። ደራሲ)። ባለቅኔዎች ግን ግእዝ መስሏቸው፤ ለንጰሰ አበራ ለበሰ ብለው ይገሱታል፤ ምስክር የለውም።
ለንጳኔ ላምጴኔ ፡-ላምጴኔ፤ ፡-(ጽር ላምፒኒ። ዕብ ማዕጋል) ሠረገላ፤ ወይም ስፈር ፥ የስፈር ቦታ፤ ሰራዊት ንጉሡን ከቦ የሚሰፍርበት። ባለብሉዮች ግን ዐልጋ ድንኳን ይሉታል ፡-(፩ነገ ፡-፳፮ ፡-፭ ፡-፯)።
ለንጽ ለንጼዎን ፡-ለንጼዎን፤ ፡-(ጽር ሌንቲዎን) የሥራ ልብስ፤ መክፌ ፥ ማጠቆ። ከፈየን እይ፤ ባለሐዲሶች ግን ዝናር ይሉታል። መክፌ ለንጽ፤ መዝመዘ በለንጽ። ነሥአ ለንጼዎነ ወኀፀበ እግረ አርዳኢሁ ፡-(ዮሐ፲፫ ፡-፬ ፡-፭። መዋሥ)። መክፌና ለንጽ ፩ ስም ናቸው፤ መክፌ ብቻ ይበቃ ነበረ ፥ ለንጽ እንዲያው በከንቱ ተጨምሯል፤ ኮሬ ሙራዱን እይ፤ ይህም እንደዚያ ነው።
ለዐት አው ላዓት ፡-አው ላዓት፤ በቁሙ ፥ ላት፤ የበግ ዥራት። ቅጠል የበግ ላት የሚባል። ውላጋ እጀታ፤ የሰይፍ የካራ የነፍጥ። ወአብአ ሎቱ አስከ ላዓታ ፡-(መሳ ፡-፳፪)።
ለዐከ ፡-ላከ ሰደደ፤–ልኢክ ለአከ።
ለዓለመ ዓለም ፡-ዝኒ ከማሁ፤ ለዘላለም። ይህ ግን ዕጥፍ ድርብ ቃል ስለ ኾነ፤ ተለይቶ ፍጻሜ ለሌለው፤ ለማይጨረስ ይነገራል። ኢይጠፍእ ለዝሉፉ ወለዓለመ ዓለም። ወደምሰስከ ስሞሙ ለዓለመ ዓለም። መንበርከ እግዚኦ ለዓለመ ዓለም ፡-(ሢራ፳፬ ፡-፱። መዝ ፡-፱ና ፡-፵)።
ለዓለም [1]፡-ድንት፤–ለ ዓለም፤ ዐልሞ ዐለመ።
[2]፡-(ዕብ ልዖላም)
፤ ለወትሮ ፤ ለዘላለም።
ለዝሉፋ ፤ ዘልፈ ፤
ወትረ ፤
በኵሉ ጊዜ ፤ በኵሉ ዘመን። ፍጻሜ
ላለውም ለሌለውም ኹሉ
ይነገራል ፤ እንደ እስከ ነው። ፍጻሜ
ላለው ሲነገር ፤
ምድርሰ ለዓለም
ትቀውም። ኢይትሀወክ ለዓለም ፤ እነብር ቤተከ ለዓለም ይላል
፡-(መክ፩ ፡-፬። መዝ ፡-፳፬) ወፍጻሜ ለሌለው
ሲነገር ፤ ቦኑ
ለዓለ አሐዩ። ቦኑ ለዓለም ይነብር መዐቱ። አኮ ለዓለም ዘእትመዐፅ። ወይነግሥ ለቤተ ያዕቆብ ለዓለም ፡-(ኢዮ፯ ፡-፲፮። ኤር፭ ፡-፭። ኢሳ፳፰ ፡-፳፰። ሉቃ፩ ፡-፴፫)።
፡-አካቶ ፤ ፈጽሞ
፤ በውነት
፤ መቼም
መች። አንሰ ኢየዐልወከ ግሙራ ባለው ፤
ለዓለም ፤
እንዲል ፡-(ማቴ፳፮ ፡-፴፫)። ኢይትሀወክ ለዓለም ያለውም እንደዚህ ሊፈታ ይቻላል።
ለኣኪ ፡-(ኪት ክያን ያት) የሚልክ ላኪ፤ ሰዳጅ።
ለዓሊ ፡-(ሊት ልያን ያት) ላይ ላይ የሚል ፥ ከፍ ከፍ ባይ፤ ወደ ላይ የሚያርግ፤ የሚወጣ ወጣት።
ለከ ፡-ላንተ፤–ለ።
(ጥ) ለከመ ፡-(ይሌክም ይለክም) ለፈለፈ፤ አሳበቀ። ሳበ ጨመረ፤ ከነገር አገባ ፡-(ዐማርኛ)።
ለከወ ፡-(ከበወ። ዐረ ከለ፤ ደከመ) ፈዘዘ፤ ቦዘ፤ ደነገዘ፤ የዐይን የአእምሮ። ወብርንነ አዕይንትየኒ ለከወኒ ፡-(መዝ ፡-፴፯)።
ለኪእ ኦት ፡-(ለክአ ይለክእ ይልካእ። ዐረ ለኪየ፤ ቀነወ) መለካት። መላከክ መቅባት፤ መለጠፍ ማጣበቅ፤ መቀርቀር መቸንከር፤ በሙጫ በምስማር። አምጽአ ቅንዋተ ኀጺን ወለክአ ውስተ ብረኪሁ ፡-(ስንክ ፡-ጥር፭)።
ለኪፍ ፎት ፡-(ለከፈ ይለክፍ ይልክፍ) መልከፍ፤ ፡-(መለኰፍ) በጥቂቱ መንካት፤ መድረስ ፥ መቅመስ፤ ማግኘት። ኢይለክፍዎ በአጽባዕቶሙ። እመ ኢለከፎ በበትሩ። ከመ ኢይልክፉ አረፍተ ቤት። ርእሳ ትለክፍ ሰማየ። ወኢለከፎሙ ሥቃይ ፡-(ማቴ፳፫ ፡-፬። አስቴ፬ ፡-፲፩። ሕዝ፵፩ ፡-፮። ኩፋ ፡-፳፯። ጥበ፫ ፡-፩)።
ለካኢ ፡-(ኢት እያን ያት) የሚለካ፤ የሚላክክ፤ ጣፊ ለጣፊ፤ ሠዓሊ።
ለክአ ፡-ጣፈ ዐተመ፤ ሣለ መሰለ፤ መልክ አወጣ፤ በቀለም በቅርጽ። ለካእክዎ ውስተ መጽሐፍ። ወይልክኦ ውስተ መጽሐፍ። ለክኡ ዝክሮ ፡-(ሢራ፴፱ ፡-፴፪። ኢዮ፲፱ ፡-፳፫። ስንክ)።
ለክዐ ፡-ለካ ጣፈ፤–ለኪእ ለክአ።
ለኰመ ፡-(ዐረ ለከመ) መታ ደሰቀ፤ ጐሰመ ኰረኰመ፤ ገፋ ገጨ። መጽሐፍ ግን በለኰመ ፈንታ አልኰመ ይላል፤ ስሕተት ነው። ወግበር ስግደታተ ምስለ አልኵሞተ ርእስ ወአንገርግሮተ ገጽ ዲበ ምድር ፡-(ፊልክ ፡-፻፲)።
ለወወ ፡-(ለወየ፤ ዐለወ) ጠመመ ጠነነ፤ ልበ ክፋ ኾነ፤ ደፈረ ተኰረ፤ በክፉ አየ። ከለወየና ከዐለወ ከኹለቱ የተዴቀለ ነው።
ለወየ ፡-(ዐረ ለወይ) ጠወየ፤ ጠመጠመ ፥ ጠቀለለ፤ ፈተለ። አከረረ፤ ቀለሰ፤ አጐበጠ፤ ቈለመመ። ጠወየን ተመልከት፤ ሥሩና ምንጩ ርሱ ነው፤ ለ በጠ ፈንታ ገብቷል።
ለዊስ ሶት ፡-(ሎሰ ይለውስ ይሉስ። ዕብ ሉሽ። ሱር ላሽ። ዐረ ላሰ) መለወስ ማቡካት፤ መፈትፈት፤ ማጨማለቅ። ለፈጸን እይ፤ ከዚህ ጋራ አንድ ነው። ነሥኦት ሐሪጸ ወሎሰት። ለዊሶሙ ያምጽእዎ። ሎሰ ጽቡረ ልምሉመ ፡-(፩ነገ ፡-፳፰ ፡-፳፬። ፪ነገ ፡-፲፫ ፡-፰። ዘሌ፮ ፡-፲፬። ጥበ፲፭ ፡-፯)።
ለዋሕቅ ፡-(ዐረብ) ጳግሜን ፡-(አቡሻ ፡-፰)። እንሰይን እይ።
ለዋው ፡-ጠማማ ክፉ፤ ደፋር ተኳር፤ ዕቡየ ዐይን፤ ገጸ ቢስ። አኩይ ወለዋው። ሐራውያ ሐቅል ለዋው። ከመ ለዋው ይመስል ገጹ ፡-(፩ነገ ፡-፳፭ ፡-፫። ፪ነገ ፡-፲፯ ፡-፰። ሄርማ ፡-ገ፳፯)።
ለውሕ ፡-(ሓት። ዕብ ሉዋሕ። ሱር ሉሓ። ዐረ ሉሕ) ሉሕ፤ ሰሌዳ ፥ ዝርግ ሥሥ ጠፍጣፋ፤ ጠርብ ሳንቃ ሰደቃ፤ ብራና ወረቀት፤ የመጽሐፍ ገበታ ፥ ጽሌ ጽላት። ዕፀ ለውሕ። አሐቲ ለውሕ እምዕፀወ ሐመር ፡-(ክብ ፡-ነገ፶፮ ፡-። ስንክ ፡-ጥር፲፬)።
ለውዝ ፡-(ዕብ ሉዝ። ሱር ሉዛ። ዐረ ሎዝ) በቁሙ፤ ስመ ዕፅ። ከርካዕን እይ፤ ከዚህ ጋራ አንድ ነው። ገውዝ ወለውዝ። እመ ተከልከ በለሰ ቦኑ ይበቍል ለከ ለውዝ ፡-(ሆሴ፬ ፡-፲፫። መቃ ፡-ገ፭)።
ለዚዝ ዞት ፡-(ለዘ ይለዝዝ ይልዝዝ) መልዘዝ፤ መራስ ፥ መለስለስ። ሐለዚዝን እይ፤ የዚህ ዘር ነው። ለዛ ላዛ ማለት ከዚህ ወጥቷል፤ ምስጢሩም ጣዕምና ውበት ለስላስነት ነው፤ ለዛ የነገር ፥ ላዛ የጠጕር፤ ላሑጫ እንደ ማለት። ለዛ ቢስ፤ ክቾ ደረቅ ጭንጫ ፥ ዐልጫ።
ለይ ፡-ፈትል ቀይ ልብስ፤–ለወየ።
፡-ፈትል፤ ልብስ፤ ቀይ ቀለም የገባ። አሰረት ለየ ውስተ እዴሁ። እመሂ ለበስኪ ለየ ፡-(ዘፍ፴፰ ፡-፳፰። ኤር፬ ፡-፴)።
፡-ቀይ ቀለም፤ ከጥቍርና ከነጭ ከብጫ ልዩነት ያለው፤ የፈትልና የልብስ መንከሪያ። ሕብረ ለይ። ፈትሉ ዘለይ። ከለሜዳ ዘለይ ፡-(፪ዜና ፡-፪ ፡-፯። ሢራ፵፭ ፡-፲፩። ማቴ፳፯ ፡-፳፱)።
ለገነ ፡-አቦካ፤ ጋገረ አገነፋ።
ለጕም ሞት ፡-(ለጐመ ይለጕም ይልጕም። ዕብ ላጋም) መለጐም፤ ማጕረሥ ፥ በአፍ መወተፍ፤ አፍን መዝጋት ዝም ማሰኘት ፥ መከልከል መግአት። ንኅንቃ ለነፍስነ ወንለጕማ ከመ ፈረስ ኀያል ወድሩክ። ለከናፍር እለ ነበባ ስብሐታተ አርመሞን ሞት ወለጐሞን በልጓም ዘኢይትበተክ። ልጕም ልሳነከ ከመ ኢትተክዝ ድኅረ። ለጐመ ሰማየ ከመ ኢየሀብ ዝናሞ ፡-(አፈ ፡-ተ፴፩። ግንዘ። ፈላስ። አርጋ)። በለጐመ ፈንታ አልጐመ ይላል፤ ስሕተት ነው። ዘኢያለጕሞ ለልሳኑ። በንጽሕ አልጐሙ ሥጋሆሙ ፡-(ያዕ፩ ፡-፳፮። ተረ ፡-ቄር፲፱)። ለገመ ፥ ልግም ፥ ልግመኛ ማለት ከዚህ ወጥቷል። ፈአመን እይ።
ለግርዮን ፡-(ጽር ሊጊሪዮን፤ የዕንቍ ስም፤ ሕብሩ ጥቍር ደባባ፤ ደምማ፤ ወይም ደመርጽማ ፡-(ዘፀ፳፰ ፡-፲፱። ፴፮ ፡-፲፱)። ያክንትን እይ።
ለግን ፡-(ጽር ላጋኖን) ዕንጐቻ፤ እንደ ጣቢታ ያለ ሥሥ ረቂቅ። ባለብሉዮች ግን አንባሻ ይሉታል ፡-(ዘሌ፪ ፡-፬)።
ለጐተ ፡-(ዲቃ ግ፤ ልገት ወሊግ) ስፋ፤ ጥልቅ ኾነ፤ ጐታ ማለት ከዚህ ወጥቷል። ለገተ ፥ ደቀነ አቀረበ፤ ወይም ተለገተ፤ ለመክተት ለመቀበል።
ለጢን ኖት ፡-(ለጠነ ይለጥን ይልጥን) ማመልጠን፤ ማስተዛዘል፤ መቀባበል ፥ መመላለስ፤ መሪና ተመሪ ወይም ግራና ቀኝ በመኾን፤ የዜማ የንባብ። መላልሶ ማመስገን ፥ መለመን፤ መለማመጥ ማቈላመጥ። አንጠየንና አስተብቍዐን በነጠየና በበቍዐ ተራ ተመልከት።
ለጥሐ ፡-(ዕብ ላጣህ፤ ሰደበ ረገመ) ለጥ አለ፤ እጅ ነሣ ፥ ተገዛ ፥ ገበረ፤ ተኛ ተጋደመ ተዘረጋ። ለጥ ይበሉ ማለት ከዚህ ወጥቷል።
ለጺቅ ቆት ፡-(ለጸቀ ይለጽቅ ይልጽቅ። ዐረ ለጺቀ፤ ለዚቀ፤ ለሲቀ) መለጠቅ ፥ መጣበቅ መጠጋት፤ ልክክ ልስቅ ማለት መሰማማት። እንዘ ይለጽቅ። እስከ ለጸቀ ማእስ
ሥጋሁ ዲበ ዐፅሙ። ጠግዐ ወለጸቀ ምስለ መንበሩ ፡-(ዘፀ፳፮ ፡-፳፰። ስንክ ፡-መስ፲፬። ግን፮)።
ለጺጽ ፡-(ለጸ፤ ለጸጸ)
መለጠጥ፤ ፡-(ጥለ) መለጠጥ፤ ለጣጭ ተለጣጭ ልጥጥ መኾን።
ለጽለጸ ፡-(ዐረብ) ተናወጠ ፥ ተውለበለበ፤ ወዲያ ወዲህ ፥ ላይ ታች ፥ ደፋ ቀና አለ፤ ተቅመደመደ፤ የሚዛን የልሳኑና የሰሓኑ፤ ለከይሲም ይኾናል። ባለቅኔዎች ግን መዘነ ብለው ይፈታሉ። ለጠለጠ ፥ ልጥልጥ አደረገ፤ በልክ በሚዛን ፡-(ዐማርኛ)። ዘሩ ለጺጽ ነው።
ለጽሊጽ ፡-የሚዛን ምላስ፤ ውልብልቢት ፥ ላንሴታ፤ ማእከል ኹኖ ግራና ቀኙን የሚያስተካክል። ከመ ለጽሊጸ መዳልው ፍትሐ እግዚ ፡-(ምሳ፲፮ ፡-፲፩። ጥበ፲፩ ፡-፳፫)። አንዳንዱ መጽሐፍ በለጽሊጽ ፈንታ ለጽላጺ እንደ ማለት ልጽላጼ ይላል፤ የጣፊ ስሕተት ነው።
ለጽቅ ፡-ማጣበቂያ መጣብቅ፤ ሙጫ ሙቅ።
ለፈቀ ፡-(ትግ ሐባ ለፍቀ፤ ሰፋ ጠቀመ) ነበዘ ፥ አጥብቆ ያዘ፤ ቀለመ ቢያጥቡ አይጠራ ኾነ፤ የደም የቀለም የርስሐት። በተነስሖቱኒ ኢተሰርየ ሎቱ ኀጢአቱ፤ እስመ ደመ መለኮት ዘለፈቀ ፡-(መጽ ፡-ምስ)።
ለፈየ ፡-(ፈለየ ጠ፤ ሌለየ) ለየ ከፈለ፤ ኹለት አደረገ። ኢትልፍይዎ ለአሐዱ ክርስቶስ፤ ወኢትረስይዎ ለወልድ ለፌ ወለሥጋ ዘነሥኦ ለፌ ፡-(ሃይ ፡-አበ)። ወዲያ ወዲህ አለ፤ ተገላመጠ።
ለፈጸ ፡-(ፈለጸ። ሎሰ) ለፈጠ ለወሰ፤ ዐሸ አበቀ አበሰበሰ፤ የዶቄት የበሶ። ከፈለጸና ከሎሰ ከኹለቱ ሥር የወጣ ነው።
ለፊፍ ፎት ፡-(ለፈ፤ ለፈፈ ይለፍፍ ይልፍፍ። ዕብ ላፌፍ። ሱር ላፍ። ዐረ ለፈ) መለፈፍ፤ መሸፈን፤ መጠቅለል። መልፈፍ ፥ መለፍለፍ፤ መስበክ ዐዋጅ መንገር። ፡-(ተረት) የሹም ሰነፍ ፥ አይለፍ ፥ አይለፈልፍ። ባፍ ይጠፉ በለፈለፉ። መልፋት ፥ መድከም፤ የቈርበት የጕልበት።
ለፋፊ ፡-(ፊት ፍያን ያት፤ ፈፍት) በቁሙ፤ የሚለፍ የሚለፈልፍ ሰባኪ፤ ጠቅላይ። ባለቅኔዎች ግን ለፈፈ ጻፈ፤ ለፋፊ ጣፊ ይላሉ።
ለፌ ፡-(ጽር ዖዴ) ወዲህ ፥ ወደዚህ፤ ወዲያ ወደዚያ፤ የጊዜ የቦታ። ለፌ እማርያም። ለፌ እምጥምቀት፤ የጊዜ። እምለፌሂ ወእምለፌሂ። ነጸረ ለፌ ወለፌ፤ የቦቃ ፡-(አፈ ፡-ተ፰። መጽ ፡-ምስ። ፩ነገ ፡-፲፬ ፡-፲፮። ዘፀ፪ ፡-፲፪)። ዝየንና ከሃን ተመልከት።
ለፍለፈ ፡-በቁሙ፤ ለፈለፈ ቀባጠረ ፥ ነገር አበዛ ፡-(ዐማርኛ)።
ሉል ፡-(ዐረ ሉእሉእ) በቁሙ፤ ዕንቍ ፥ የዕንቍ ስም፤ ባሕርይ፤ ከሰደፍ የሚገኝ፤ ነገሥታት እንደ ሎሚና እንደንቍላል የሚጨብጡት። በሉሉ በዘውዱ እንዲሉ። ብሕረንና ቆቅሐን ዐነቀን እይ፤ ፡-(አርጋ)።
ሉሲፌር ፡-(ሮማይ) የዲያብሎስ ስም፤ ከሽፍትነት በፊት የነበረው። ጸዋሬ በርህ፤ ፍድፉደ በርህ፤ ቤዝ ብሩህ ፥ ኮከበ ጽባሕ ማለት ነው፤ ቤዝን እይ ፡-(ኢሳ፲፬ ፡-፲፪)። በትቢቱና በኵራቱ ብዛት ሳጥናኤል ከኾነ በኋላ ስሙና ብኵርናው ኮከብነቱ ለዳግማይ አዳም ተሰጥታል ፡-(ዘኍ፳፬ ፡-፲፯። ማቴ፪ ፡-፪። ፪ጴጥ ፡-፩ ፡-፲፬)።
ሉባር ፡-የተራራ ስም፤ ታላቅ ረዥም ተራራ፤ ሐመረ ኖኅ የቆመችበት። ወሖረት ታቦት ወአዕረፈት ዲበ ርእሰ ሉባር አሐዱ እምአድባረ አራራት ፡-(ኩፋ ፡-፭። ዘፍ፰ ፡-፬)።
ሉዓላዊ ፡-(ዊት ውያን ያት) ልዕልና ያለው፤ ላይኛ ከፍተኛ፤ የላይ የሰማይ። መሐላ ሉዓላዊ ወማእከላዊ ወዘይቴሐት እምኔሆሙ። ኤስኬዴሬያት ሉዓላውያት። ኀይላት ሉዐላውያን። ረድኤት ሉዓላዊት ፡-(ፈ ፡-መ ፡-፳፪ ፡-፭። ሕዝ፵፪ ፡-፭። አፈ ፡-ድ፫። ተ፲፪)። ሉዓላዊ በማለት ፈንታ ላዕላዊ እንደ ማለት ፥ ልዑላዊ ወመትሕታዊ ይላል፤ ፍችው አንድ ነው ፡-(ፊልክ ፡-፻፸፭)።
ሉዓሌ ፡-ልዕልና፤ ከፍታ ምጥቀት ፥ ርዝመት። ሉዓሌ ዐቢይ። ያእምር ሉዓሌሁ ለሰማይ ፡-(መክ፲ ፡-፮። ቅዳ ፡-ሕር)።
፡-ላይ ጫፍ መጨረሻ፤ ደርብ ሰገነት። ዘወረወ ነፍሶ እመልዕልተ ሉዓሌ ይመውት። ውስተ ሉዓሌ ፡-(ዮሴፍ። አፈ ፡-ድ፩)።
ሉጹይ ልጹይ ፡-(ያን ያት ጺት) የተላጨ ፥ ልጩ። ልጹያን አጽሓሚሆሙ። እስመ ከመ ሉጹት ይእቲ ፡-(ኤር፵፰ ፡-፭። ፩ቆሮ ፡-፲፩ ፡-፭)።
ሉጺት ፡-ቡሓ መላጣ፤–ላጸየ።
ሊሉይ ፡-(ያን ያት ሊት) የተለየ ፥ የተለያየ፤ ልዩ ፥ ልይዩ። ሊሉይ እምነ ብእሲቱ። ተኣኅዎ አሐዱ ነፍስ ውእቱ በሥጋ ፍሉጥ ወሊሉይ። ሊሉየ መልክእ ወአካል ፡-(ስንክ። ፈላስ ፡-ገ፲፫። ደራሲ)።
ሊሊት ፡-(ዕብ) የሌቶፍ፤ ከቀን አዕዋፍ የተለየች ዐይጥማ። ወይም ጉጋ ጕጕት፤ ፊተ ክብ ድመትማ ፣ የቀን ዳፍንታም የሌት ዐይናማ። በሊሊት ፈንታ ሌሎ ይላል፤ ሌሊቶ ሌሊት ቀኑ ማለት ነው ፡-(ጥሬ ፡-ሰዋ)።
ሊላይ ፡-ልየታ፤ ልዩነት፤ መለዮ። ዘእንበለ ፍልጠት ወሊላይ ፡-(መጽ ፡-ምስ)።
ሊቀ ጳጳስ ፡-በቁሙ፤ በትረ ያሬክ፤ የጳጳሳትና የኤጲስቆጶሳት አለቃ፤ ደምሳሽ። እሊህም ሦስቱ ሊቃናት፤ ራስና ንጉሥ ንጉሠ ነገሥት እንደ ማለት ናቸው። ወይርአይ ሊቀ ጳጳሳት በእንተ ኵሉ ግብር ወትእዛዝ ዘይገብርዎ ጳጳሳቲሁ ወኤጲስቆጶሳቲሁ ውስተ በሓውርቲሆሙ ዘተሠይሙ ላዕሌሆን ፡-(ፍ ፡-ነ ፡-፬)።
ሊቃን ሊቃናት ሊቃውንት ፡-(ልሂቃን ናት) አለቆች፤ ሹማምቶች፤ መምራኖች፤ ሽማግሎች። ሊቃነ ሕዝብ። ሰብዓ ሊቃናት። መንበረ ሊቃውንት። ሊቃናትኒ ወመሓዛት ፡-(ዘፀ፲፰ ፡-፲፪። ዘኍ፲፩ ፡-፳፭። መዝ ፡-፻፮። ፻፵፰)።
ሊቃኖስ ፡-ከተስዐቱ ቅዱሳን አንዱ፤ ወይም ሊባኖስ። ባና ቃ ተወራርሰዋል።
፡-ማርጀት መላቅ፤ እርጅና፤ ላቂያ ልቅና፤ ብኵርና። ረከበት ወልደ በልህቀቲሃ። አግብእ ሊተ ልህቀተከ ዘቅድመ ልደት ፡-(ሉቃ፩ ፡-፴፮። ኩፋ ፡-፳፬)።
፡-እርጅና፤ የድሜ ብዛት። ውስተ ልህቃነ ዓመታቲሁ ፡-(ፊልክ)።
፡-ላቂያ ልቅና፤ ብኵርና። ወሀበኩ ልህቃንየ ለያዕቆብ ፡-(ኩፋ ፡-፴፮)።
ሊቃኦንስጢ ፡-(ጽር ሊካዎኒስቲ) ስመ ሀገር፤ በቱርክ አገር ውስጥ ከዚያውም በፍርግያ ክፍል ያለች ታላቅ መዲና ፡-(ግብ፲፬ ፡-፲፩)።
ሊቅ [1]፡-(ቅት ቃን ቃት) በቁሙ፤ አለቃ ታላቅ፤ አባት ጌታ፤ መምህር፤ ሹም፤ አሮጌ ሽማግሌ። ፡-(ተረት) ከሊቅ እስከ ደቂቅ። ልሂቅና ሊቅ ልዩነቱ ሂን በመጕረድ ብቻ ነው እንጂ፤ ምስጢሩና ፍችው አንድ ነው፤ ባለቅኔዎች ግን ሌቀ ይለይቅ ብለው ይገሳሉ። ወዘሰ ብዉሕ ለሊቅ፤ ዘውእቱ ሊቀ ጳጳሳት። ሊቅት። ሊቃነ ኦሪት ፡-(ፍ ፡-ነ ፡-፶፩። ስንክ ፡-ኅዳ፲፯። ሉቃ፭ ፡-፲፯)።
[2]፡-በቁሙ ፥ አሮጌ፤–ልሂቅ ልህቀ።
ሊቅና ፡-(ልህቅና) ሊቅነት፤ አለቅነት፤ ልቅና ሹመት፤ እርጅና። ሢመተ ሊቅና ዘካህናት። ለሊቀ ጳጳሳት ሊቅናሁ ላዕለ መሲሓውያን ፡-(ዮሴፍ። ፍ ፡-ነ ፡-፬)።
ሊባ ፡-(ጽርእ። ዕብ ኔጌብ፤ ዳሮም። ዐረ ጅኑብ) የማእዝን ስም፤ ንኡስ ማእዝን፤ ደቡብ፤ ከዚያውም የደቡብ ምሥራቅ፤ በደቡብና በምሥራቅ መካከል ያለ ፥ የባሕር ትይዩና አንጻር። ሰሜን ወሊባ ወባሕር ወጽባሕ። ውስተ ሊባ ወጰራልያ። ወኮነ ደወሎሙ እምነ ሊባ እስከ አሐዱ ኅብር ፡-(ኩፋ ፡-፲፫። ዘዳ፩ ፡-፯። ፴፫ ፡-፳፫። ኢያ፲፭ ፡-፪)። በሊባ ፈንታ ሊቦስ ይላል፤ ደቡባዊ ማለት ነው።
ሊባኖስ ፡-(ጽር። ዕብ ልባኖን) ስመ አድባር ነዋኃን እለ በሰሜና ለከነዓን። ደጋ ጮቄ ፥ ታላላቅ ተራራ ገመገም፤ ከዐቢይ ባሕር በመለስ ፥ ከሲዶን እስከ ኤርሞን ተያይዞ ፥ በሶርያና በምድረ እስራኤል መካከል ያለ፤ ዛፋም ዕንጨታም ዱራም ደናም፤ የተራሮች ራስ ሰማይ ጠቀስ ፥ ውርጭና በረዶ እንደ ሻሽ ሸፍኖት የሚኖር። ፍችው ቧሒት እንደ ማለት ፥ ነጮ፤ ወይም ነጫም ማለት ነው ፡-(መዝ ፡-፴፭። ማሕ፫ ፡-፱። ኢሳ፵ ፡-፲፮)።
፡-የሰው ስም፤ ሶርያዊ አንጾኪያዊ ቅዱስ፤ ከተስዐቱ ቅዱሳን በፊት የመጣ፤ ደብረ ዐስቦን በስሙ ደብረ ሊባኖስ ያሰኘ። ፪ኛ ስሙ መጣዕ፤ ፫ኛ ስሙ ይስሪን ይባላል ፡-(ስንክ ፡-ጥር፫። ድጓ።ፊልክ ፡-፩)።
ሊቤርጢኖን ፡-(ጽር ሊቤርቲኖን) ግዑዛን፤ ነጾች ነጻዎች፤ ነጻነት ያላቸው። ቃሉ የሮማይስጥ ነው ፥ ሊቤርታስ ከማለት ወጥቷል፤ ይኸውም ፡-(ግዕዛን) ነጻነት ማለት ነው። ከክርስቶስ በፊት ወደ ሮማ ተማርከው ተሽጠው የነበሩ አይሁድ ከሮም ባርነት ነጻ ስለ ወጡ ፥ ከሌሎች ኣይሁድ ተለይተው ሊቤርቲኖሩም ተብለዋል። ምኵራብ እንተ ስማ ሊቤርጢኖን ፡-(ግብ፮ ፡-፱)።
ሊተ ፡-ለኔ የኔ እኔን፤–ለ።
ሊቶስጥሮስ ፡-(ጽር ሊቶስትሮቶስ) የቦታ ስም፤ ጸፍጸፍ ማለት ነው። መካን ዘስሙ ሊቶስጥሮስ ፡-(ዮሐ፲፫ ፡-፲፫)። ፪ኛም፤ ሊቶሶርቶን፤ ሊቶስትሮቶን ይላል፤ ፍችው አንድ ነው ፡-(፪ዜና ፡-፯ ፡-፫)።
ሊጦን ፡-(ጽር ሊታኒያ) መስተብቍዕ፤ ልመና ምልጃ፤ ዝብዘባ ቍልምጫ። ሊጦን ዘሰኑይ፤ ወካዕበ ናስተበቍዕ ፡-(ቅዳ)።
ላሓዊ [1]፡-(ላሐወ) የሚያለቅስ ፥ የሚያዝን፤ አልቃሽ ፥ ዐዛኝ።
[2]፡-(ላሕ) ልቅሶኛ ፥ ሐዘንተኛ፤ የልቅሶ ሰው፤ እንባም።
ላሐየ ፡-ተጫወተ አጫወተ፤–ላህዮ ላሀየ።
ላህ ፡-ልቅሶ፤–ላሕዎ ላሐወ።
ላሕ ፡-(ብ ላሓት) ልቅሶ፤ ሐዘን። ቤተ ላሕ። አልባሰ ላሕ። መዋዕለ ላሕ። ገብሩ ላሐ። ዝንቱ ሠለስቱ
ላሕ ፡-(ሢራ፳፪ ፡-፮። ፪ነገ ፡-፲፬ ፡-፪። ዘፍ፶ ፡-፬ ፡-፲። ኩፋ)።
ላህልህ [1]:-ራሰ ለመሸቀ፤–ላሕልሕ።
[2]:-ላላ ረገበ፤–ላኅልኀ።
ላሕልሐ [1]፡-(ለሕሐ። ሱር ሂትላሕላሕ) ራሰ ረጠበ፤ ልሕሉሕ ኾነ፤ ሎክ ሎክ አለ በሰለ፤ የፍሬ የዕበጥ። ዘይሜህር ወኢይገብር ይመስል ገብላ ዘውስቴቱ ማይ፤ እምኔሁ ይሰትዩ ብዙኃን ወይትኀፀቡ፤ ወቦቱ ይላሐልሕ ግብር፤ ወለሊሁሰ ኢይሰቲኒ ወኢይነጽሕኒ ጽሕኒ እምርስሐታቲሁ፤ ወኢይላሐልሕሂ ፡-(ፊልክ ፡-፻፬)።
[2]:-ራሰ ረጠበ፤–ልሒሕ ለሕሐ።
[3]:-ላላ ረገበ፤–ላኅልኀ።
ላኅልኅ [1]፡-ራሰ ረጠበ፤–ለሒሕ ለሕሐ። [2]፡- (ራኅርኀ) ፤ ላላ
፥ ረገበ ፤
የገመድ የአውታር የኅሊና። ንትዐቀብ ከመ ኢይላኅልኅ መዝርዐ ሐመርነ በአፍቅሮ ውሉድ (አፈ ፡ ተ፴፬)። ላዕልዐንና ራኅርኀን
እይ ፤ የዚህ መንቲያ ነው።
ላህም ፡-በቁሙ ላም፤–ልሕመ።
ላሕም [1]፡-(ብ አልሕምት። ዕብ ልሖም፤ ሥጋ። ዐረ ለሕም፤ ሥጋ) በቁሙ፤ ላም ቁም፤ የቀንድ ከብት ፥ የላም መንጋ ፥ የቤት እንስሳ ታርዶ የሚበላ ፥ ታልቦ የሚጠጣ ፥ ተጠምዶ የሚያርስ። ለዱር እንስሳትም ለጐሽ ላጋዘን ይነገራል፤ ላሕም ያንድነት ስም ነው፤ ተባቱም እንስቱም ፥ ታላቁም ታናሹም ላም ይባላል። ዘይቤው ፥ ሥጋማ ሥጋም፤ ተዋጊ ቀንዳም፤ በላተኛ ሆዳም ማለት ነው፤ የጠጕሩን ልመት የጠባዩንም ልዝብነት ገርነቱን ገራምነቱን ጨምሮ ያሳያል። ላሕም አእመረ ዘአጥረዮ። ላሕም ወለደት በግዐ። አባግዐኒ ወአልሕምተ። አልሕምት ኢይመክና። አልሕምተ ገዳም ፡-(ኢሳ፩ ፡-፫። ዮሴፍ። መዝ ፡-፰። ኢዮ፳፩ ፡-፲። ፍ ፡-ነ ፡-፵፬ ፡-፪)። ቁም ማለት ደግሞ ፥ ቀዋሚ ቅዉም ቁም ነገራም ፥ ደግ ደገኛ ማለት ነው። ፡-(ሙሾ፤ ፪ ሴቶች ስላ፩ ወንድማቸው) ፵ ቁም ከናውራው ሰጥተው ቢድሩት፤ እሸቴ ቀጸላ ይበላል አንዠት። መቼ አየሽውና አንችም እንደ ሌላ፤ የት አንዠት ይበላል እሸቴ ቀጸላ።
[2]፡-የባሕር ጐሽ እንደ ዲኖ ያለ። ወሀሎ አሐዱ ላሕም ዘይወፅእ እምአሐዱ ባሕር ጽዮእ በሀገረ ከሪክ፤ ወይቤሉ እስመ የዐርግ አሐዱ ላሕም በበ ዓመት ወሶበ የሐውር በሐይቀ ባሕር ይትከፈል ወይከውን ፒሳ ወይሠይጥዎ ለሰብአ አፍራጊያ ይቅብዑ ኪያሁ ቦቱ አሕማሮሙ ፡-(ጊ ፡-ወ ፡-ሐ ፡-ገ፳፪)።
ላህቅ ፡-(ቃን) ዝኒ ከማሁ። ወሶበ ሞኦሙ ለጸላእቱ ገብረ ብልጣሶር ምሳሐ ዐቢየ ለላህቃነ መንግሥጉቱ ፡-(ጊ ፡-ወ ፡-ሐ ፡-ገ፻፯)።
ላህብ ፡-(ባት) ነበልባል ፥ ወላፈን፤ ሙቀት፤ ትኵሳት፤ ለብታ፤ ላብ ላበት ወዝ፤ መከራ ጭንቅ። ላህበ ነድ። ላህበ አሳት። ላህበ ፀሓይ። ላህበ መዓልት። ወሶበ ፈትሖ እማእሰሪሁ ወጠፍኦ ላህቡ ቆመ ቅድመ እግዚእነ እንዘ ይገርር ፡-(ጥበ፲፮ ፡-፲፰። ሔኖ። ኢሳ፵፱ ፡-፲። ኤር፵፫ ፡-፴። መቅ ፡-ወን)።
ላሕዎ ዎት ፡-(ላሐወ ይላሑ። ዐረ ናሐ። ዕብ ናሃህ። ሱር ንሃእ) ማልቀስ ማዘን፤ ማሞሽ መጮኽ መንሰቅሰቅ። ጊዜ ለላሕዎ፤ ወጊዜ ለዘፈን። ወላሐዉ ሕዝብ። እለ ይላሕውዋ ለጽዮን። ላሑ ምስለ ዘይላሑ ፡-(መክ፫ ፡-፬። ፩ነገ ፡-፮ ፡-፲፱። ኢሳ፷፩ ፡-፫። ሢራ፯ ፡-፴፬)።
ላሕይ ፡-(ያት) ገጽ ፊት፤ በገጽ ላይ ያለው መልክ ውበት፤ ወዝ ደም ግባት፤ ግርማ ሞገስ። ኢታድሉ ለሰብእ እንበይነ ላሕዩ። ኢያስሕትከ ላሕያ ለብእሲት። ተደሙ እምነ ሥና ወላሕየ ገጻ። ላሕያ ጼወዋ ለነፍሱ ፡-(ሢራ፲፩ ፡-፪። ፳፭ ፡-፳፩። ዮዲ፲ ፡-፳፫። ፲፮ ፡-፲፩)።
ላህዮ ዮት ፡-(ላሀየ ይላሂ ይላሂ። ዐረ ለሃ፤ ለሂየ) መጫወት ፥ ማጫዎት፤ ጨዎታ ማድረግ፤ በእጅ በቃል። ማጸናናት፤ አይዞኽ አይዞኽ ማለት። ኀጥአት ዘይላህያ። ወአልቦ ዘይላህተኒ ፡-(ሰቈ፩ ፡-፲፯ ፡-፳፩)። በላሀየ ፈንታ አልሀየ ተለሀየ ይላል፤ ስሕተት ነው። ዐራትየኑ እንጋ ይናዝዘኒ፤ ወያላህየኒኑ ምስካይየ። እስመ ዮጊ ይትለሀይ ፡-(ኢዮ፯ ፡-፲፫። ፫ነገ ፡-፲፰ ፡-፳፮)።
ላማ ፡-(ዕብ) ለምነት፤ ለምን ፥ ስለ ምን ፡-(ማቴ፳፯ ፡-፵፮። ቅዳ ፡-አት)።
ላሜዳ ፡-በቁሙ፤ ላይዳ ፥ ታላቅ የንጨት መንካ ያውድማ መሣሪያ፤ ነዶው ተበራይቶ ከተመሸነ በኋላ ምርቱን ከግርድና ከብቅ የሚለዩበት። ላዳንም ይህን ይመስላል።
ላሜድ ፡-(ዕብ። ጽር ላምዳ) ስመ ፊደል ለ፤ የአሌፍ ፲፪ኛ ፡-(መዝ ፡-፻፲፰ ፡-፹፬–፺፮። ሰቈ፩ ፡-፲፪። ፪ ፡-፲፪። ፫ ፡-፴፫። ፬ ፡-፲፪)። ፍችው ትምርት ወይም ምሁር ማለት ነው።
ላባን ፡-(ዕብ) የሰው ስም፤ ጸዐዳ ፥ ጽዕድው ፡-(ዘፍ፳፭ ፡-፫)።
ላዕለ ፡-በላይ ወደ ላይ። አንበሮ ላዕለ። ትኔጽሩ ላዕለ ፡-(አስቴ፫ ፡-፩። ኢሳ፰ ፡-፳፩)። ተጽዕነ ላዕለ ኪሩቤል። መጽአ ሞት ላዕለ ኵሉ ሰብእ ፡-(መዝ ፡-፲፯። ሮሜ፭ ፡-፲፪)። ሲዘረዝርም፤ በጥሬነቱ ላዕሉ ላ ልከ ኪ ልየ፤ ሎሙ ን ልክሙ ን ልነ፤ እያለ በዘመድነት ይረባል። ፪ኛም ደቂቅ አገባብ ስለ ኾነ እንደ ዲበ፤ ላዕሌሁ ሃ እያለ በባዕድ ይዘምታል ፡-(ዕር፳፩ ፡-ቍ፻፱)።
ላዕላዕ ፡-(ላኅልኀ) ፤ ለነበደ ፤ ኰለተፈ ፥ ድዳ ኾነ። ፡-(ተረት) ፤ አፈ ድዳ ፥ ቀንደ ጐዳ። መጽሐፍ ግን ተላዕልዐ ይላል ፤
ስሕተት ነው። እንዘ ይትላዐላዕ በልሳን ወይድሕክ በኒቢበ ፊደላት ፡-(አፈ ፡ ተ፳፯። ያዕ ፡ ዘእል)።
፡-(ዓን ዓት) ድዳ ለፍዳዳ ለንባዳ ፥ ኰልታፋ፤ ክቡደ ልሳን። ጸያፍ ወላዕላዐ ልሳን አነ። ለበሃማን ወለጸያፋን ወለላዕላዓን ረሰዮሙ ይትናገሩ ርቱዐ ፡-(ዘፀ፬ ፡-፲። ቀሌ። ኪዳ። ያዕ ፡-ዘእል)።
ላዕሉ ፡-ላይ፤ ላዩ ፥ ላይኛው፤ በላይ ያለው። ዘወረደ እምላዕሉ። በሰማይ በላዕሉ። ኅሡ ዘላዕሉ ፡-(ድጓ። ዮኤ፫ ፡-፫። ቆላ፫ ፡-፩)።
ላዕላይ ዊ ፡-(ዪት ሊት፤ ዊት) የላይ ፥ ላይኛ፤ ታላቅ። ላዕላይ ማኅደር። ላዕላይ ቀመር። ሀገር ታሕታዪት ወላዕላዪት። ላዕላይ ደወለ ግብጽ ፡-(ቀሌ። መር ፡-ዕዉ። ፩ዜና ፡-፯ ፡-፳፬። ጦቢ፰ ፡-፫)።
ላዕል ፡-(ላት) ላይ ላይኛ፤ መጨረሻ ጫፍ፤ ቁመት። ላዕል ወታሕት ፡-(ቅዳ። ኤፌ፫ ፡-፲፰)። ሲናበብና ሲዘረዘር ፥ አገባቦችም ሲጫኑት እንዳወራረዱ ይፈታል፤ ስልቱ ብዙ ነው።
ላዕልዐ ፡-(ላኅልኀ) ለነበደ፤ ኰለተፈ ፥ ድዳ ኾነ። ፡-(ተረት) አፈ ድዳ ፥ ቀንደ ጐዳ። መጽሐፍ ግን ተላዕልዐ ይላል፤ ስሕተት ነው። እንዘ ይትላዐላዕ በልሳን ወይድሕክ በኒቢበ ፊደላት ፡-(አፈ ፡-ተ፳፯። ያዕ ፡-ዘእል)።
ላእክ ፡-(ክት ካን ካት) መልክተኛ ፥ አገልጋይ ሎሌ። አብድሰ ይሬሲ ርእሶ ላእከ። ላእካነ እግዚ ፡-(ምሳ፲ ፡-፬። ሮሜ፲፫ ፡-፬)።
ላእክት ፡-ገረድ፤ ደንገጥር። ወሀበት ላእክታ ለያዕቆብ ፡-(ኩፋ ፡-፳፰)።
ላእፍ ፡-ለስላሳ ምግብ፤ የላመ የጣመ፤ ዋጡኝ ዋጡኝ የሚል። ወሶበ ተፍእማ ለላእፈ ትስብእቱ ረከበ መቃጥነ መለኮት ዘይሰቍር አንቀሮ ፡-(መጽ ፡-ምስ)። ባለመጣፎች ግን ወላፍ ትል ይሉታል።
ላኵዮ ዮት ፡-(ላኰየ ይላኵ) መለጐጥ፤ መጓጐጥ መተንኰስ።
ላኳ ፡-(አው ላኴ) ጠብ ክርክር፤ ንዝንዝ ጭቅጭቅ፤ ስድብ። ማእከለ ላኳ ወላኳ። ለደም ይቀድሞ ላኳ ወጋእዝ። ላኳሆሙ ለአብዳን፤ ያጸምም እዝነ። አብድ እምከመ ሰትየ ያበዝኅ ላኳ ፡-(ዘዳ፲፯ ፡-፰። ሢራ፳፪ ፡-፳፬። ፳፯ ፡-፲፬። ፴፬ ፡-፲)።
ላዊ ፡-የፊደል ስም ለ፤–ለወየ።
ላዊ ላውይ ፡-ስመ ፊደል ለ፤ የአልፍ ፲፪ኛ። ጠማማ ቈልማማ ፥ ጐባጣ ቅልስ ማለት ነው፤ ጠማምነቱም በኹሉ ነው።
ላይዳ ፡-በቁሙ፤ ላሜዳ፤–ለመደ።
ላጽቂት ፡-(ዕብ ልጣኣ) ሸለሊት፤ እንሽላሊት፤ የገበሎ ዐይነት። ወይም ሣሬት ፥ ሸረሪት። ላጽቂት ዘበእዴሁ የሐውር ፡-(ምሳ፴ ፡-፳፰)።
ላጽዮ ዮት ፡-(ላጸየ ይላጺ። ዕብ ወሱር ጋላሕ። ዐረ ማሰ) መላጨት መለጫጨት፤ ጠጕርን ከሥጋ መለየት፤ ከሥሩ መቍረጥ መጋጠጥ፤ ቈርበቱ እስኪታይ እስኪገለጥ። ላጸየ ሥዕርተ ርእሱ። ላጸዮሙ መንፈቀ ጽሕሞሙ። ርእሶ ኢይላጺ ፡-(ኢዮ፩ ፡-፳። ፩ዜና ፡-፲፱ ፡-፬። ዘሌ፳፩ ፡-፲)።
ሌለየ ፡-ሌሊት ተነሣ ፥ ነቃ ተጋ ማለደ፤ ለሥራ ለመንገድ። ለለንና ለልን እይ፤ የዚህ ዘሮች ናቸው።
ሌሊት ፡-(ብ ለያልይ። ዕብ ላይል፤ ላይላ። ሱር ሌልያ። ዐረ ለይል፤ ለይለት) በቁሙ፤ ሌት ሊሉይ እመዓልት፤ ጨለማ ፥ የጨለማ ጊዜ ከሠርክ እስከ ነግህ ፥ ከማታ እስከ ጧት ፥ ከኮከብና ከጨረቃ በቀር ፀሓይ የማይታይበት ፥ የዮም እኩሌታ መንፈቀ ዕለት ፥ ፲፪ ሰዓት ፡-(ዘፍ፩ ፡-፭። መዝ፻፫ ፡-፳፩)። መዓልተ ወሌሊተ። ወአርብዓ ለያልየ ፡-(ኢሳ፳፩ ፡-፲፪። ማቴ፬ ፡-፫)።
ሌልዮ ዮት ፡-(ሌለየ ይሌሊ። ለፈየ፤ ፈለየ) መለየት ፥ መነጠል፤ መነጣጠል። ይሌሊ ሥርወ አመሌሊት። ኢፈለጠ ወኢሌለየ። ሌለዮሙ ለሰራዊት። ይሌሊ አዕርክተ ፡-(ዕብ፬ ፡-፲፪። ሮሜ፫ ፡-፳፫። ፪ዜና ፡-፳፭ ፡-፲። ምሳ፲፮ ፡-፳፰)።
ሌዊ [1]፡-የሰው ስም፤–ለየወ።
[2]፡-(ዕብ) የሰው ስም፤ ፫ኛው የያዕቆብ ልጅ። ተላዊ ፥ መትልው፤ ልጹቅ ፥ መስተላጽቅ ማለት ነው ፡-(ዘፍ፳፱ ፡-፴፬። ኩፋ። ፴፩)።
ሌዋታን ፡-(ዕብ ሊውያታን) የባሕር አውሬ እንስሳ፤ ዘንዶ፤ ታላቅ ዓሣ፤ ማናቸውም። እንስት ዐንበሪ ምድርን እንደ ዝናር እንደ ጋን ሰንበር ፥ ወይም እንደ ቀለበት እንዳንባር ዙራ ተጠምጥማ ዐቅፋ የያዘች የብሄሞት ዘውግ ፥ ጣምራው ኹለተኛው፤ ዘሩ ለወየ ነው፤ ሌዋ ዐቃፊ ተጠምጣሚ፤ ታን ዘንዶ ፥ ወይም ወርድና ቁመት ግዘፈ ምድር። በተገናኝ የምድር መታጠቂያ ቅናት መቀነት ማለት ነው፤ ብሄሞትንና ዐንበሪን እይ። ወዐቀብከ ደእተ አሚረ ክልኤተ እንስሳ፤ ወሰመይካሁ ለአሐዱ ብሄሞት ወለካልኡ ሌዋታን። ወፈለጥኮሙ በበይናቲሆሙ፤ እስመ ኢይክል ዝኩ ሳብዕተ እድ ኀበ ሀሎ ማየ ናጌብ ጸዊሮቶሙ፤ ወወሀብካሁ ለብሄሞት አሐደ እደ የብስ ወለሌዋታን ሳብዕተ እዴሁ ለርጡብ ፡-(ሱቱዕዝ ፡-፮ ፡-፵፱–፶፪)።
ሌዋዊ ፡-(ውያን) የሌዊ ወገን፤ ካህን ፡-(ሉቃ፲ ፡-፴፪። ግብ፬ ፡-፴፮)።
ሌዋውያን ፡-የመጽሐፍ ስም፤ ፫ኛው ብሔረ ኦሪት ፥ የሌዋውያንን ሕግና ሥርዐት የሚናገር። በዕብራይስጥ ግን ዋይቅራእ ይባላል፤ ጸውዐ ማለት ነው፤ ወጸውዖ እግዚ ለሙሴ ያለውን መዠመሪያን ቃል ያሳያል።
ሌዌን ፡-ሌዌን፤ ፡-(ዕብ ዊሎን) ስመ ኃምስ ሰማይ። ኢዮር ወይም ጠፈር፤ ፭ኛነቱ ከላይ ወደታች ነው ፡-(አዋል)። ሰማይንና ምጽናዓትን እይ።
ሌውቄን ፡-(ጽር ሌፍኪ) ዕፀ ዘይት፤ ወይራ ፡-(ኢሳ፵፩ ፡-፲፱። ሌዊቄን ኤሌዊቄን ይላል፤ ኹሉም ስሕተት ነው።
ሌዎጴጤርያ ፡-(ጽር ሌዎፔትሪያ) ልሙጽ ደንጊያ፤ ሰፊ ዝርግ ንጥፍ ፡-(ሕዝ፳፬ ፡-፯ ፡-፰)።
ሌጌዎን ፡-(ጽርእ) ሰራዊት፤ ጭፍራ። የጦር አበጋዝ፤ የጭፍራ አለቃ። ስድስቱ ሺሕ ጭፍራ ከናለቃው አንድ ሌጌዎን ይባላል ፡-(ማቴ፳፮ ፡-፶፫። ማር፭ ፡-፮። ሉቃ፰ ፡-፴)።
ልሑም ፡-(ማን ማት ሕምት) የላመ የለዘበ፤ ልም ልዝብ፤ የከፋ የባሰ።
ልሁብ ፡-(ባን ባት ህብት) የተቃጠለ፤ የጋለ የጋመ፤ የሞቀ ሙቅ። የላበ የወዛ፤ ለብ ያለ። ኮነ ልሁበ ውስተ አፍቅሮተ እግዚ። ዐራተ ኀጺን ልሁብ ፡-(ፊልክ ፡-፹፬። ስንክ ፡-ታኅ፱)።
ልሑኵ ፡-(ኳን ኳት ሕኵት) የተሠራ ፥ የተፈጠረ፤ ሥር ፍጡር።
ልሑይ ፡-(ያን ያት ሒት) በቁሙ፤ ወዛም ፥ ደመ ግቡ፤ ያማረ ያጌጠ፤ ውብ ግሩም፤ መልከ መልካም። ብእሲ ልሑይ። ወኮኑ ልሑያነ በብርሃ ዐቢይ ፡-(ዮሴፍ። አቡሻ)። በልሑይ ፈንታ ለሓዪ ፡-(ዪት ይያን ያት) እንደ ማለት ኹሉ ላሕይ ይላል፤ የጣፊና የመላሽ ስሕተት ነው። ገጽከ ላሕይ። ላሕይ አዕይንቲሁ። ላሕይ ጥቀ ራእያ። ሶስና ላሕይት ጥቀ። ደናግል ላሕያት ፡-(ማሕ፪ ፡-፲፬። ፩ነገ ፡-፲፮ ፡-፲፪። ኩፋ ፡-፳፰። ዳን፩ ፡-፴፩። ዓሞ፰ ፡-፲፫)።
ልሑድ ፡-(ዳን ዳት ሕድ) የለደለደ ወፍራም። ድልድል ቅምጥል፤ ሥራና መከራ የማይችል። ኢትሰመዪ እንከ ልሕደ ወሥብሕተ። አንቲ ልሕድ ፡-(ኢሳ፵፯ ፡-፩ ፡-፰። ሚክ፩ ፡-፲፮)።
ልሑጽ ፡-(ጻን ጻት ሕጽት) የተላጠ፤ የተመለጠ። ስልብ ጐማዳ።
ልሒሕ ሖት ፡-(ለሕሐ ይለሕሕ ይልሐሕ። ዕብ ሌሐ። ሱር ላሕላሕ) መርጠብ ፥ መለዘብ፤ መራስ ፥ መለስለስ፤ የገላ የንጨት የቍርበት።
ልሂቅ ቆት [1]፡-(ልህቀ ይልህቅ ይልሀቅ። ዕብ ላሀቅ፤ ሰበሰበ) ማደግ መጐልመስ፤ አካለ መጠን ማድረስ። ብእሰንና ዐብየን ተመልከት፤ የዚህ ጎሮች ናቸው። ልህቀ ሕፃን ወኀደገ ጥበ። እስከ አመ ይልህቅ ወልድየ ሴሎ። አይድዐቶ አስቴር ለንጉሥ ከመ በቤቱ ልህቀት ፡-(ዘፍ፳፩ ፡-፰። ፴፰ ፡-፲፩። አስቴ፰ ፡-፩)።
፡-መላቅ መብለጥ ታላቅ መኾን፤ በኀይል በመጠን ፥ በብዛት በዘመን። እኁሆሙ ዘይልህቅ። እኅትክን እንተ ትልህቅ። ለሀቁ ውብዝኁ ፡-(ኢዮ፩ ፡-፲፫። ሕዝ፲፮ ፡-፵፮። ኩፋ ፡-፮)።
፡-ማርጀት መሸምገል፤ አሮጌ መኾን። አብርሃኘምስ ወሳራ ልህቁ ጥቀ ወኀለፈ መዋዕሊሆሙ ፡-(ዘፍ፲፰ ፡-፲፩። ፳፬ ፡-፩። ፳፯ ፡-፩)። በልህቀ ፈንታ ተልህቀ ይላል፤ ስሕተት ነው። እለ ይትለሀቁ እምኔክሙ ፡-(፩ጴጥ ፡-፭ ፡-፩። ኪዳ)።
[2]፡-(ቃን ቃት ህቅት)
ኦሮጌ ሽማግሌ፤ ታላቅ። ኢይትረከብ ልሂቅ ውስተ ቤትከ። ልሂቃን ወልሂቃት ፡-(፩ነገ ፡-፪ ፡-፴፪። ዘካ፰ ፡-፬)።
፡-ቄስ ካህን፤ መስፍን፤ መኰንን። ላዕለ ልሂቅ ኢትስማዕ ውዴተ። ልሂቃነ መንግሥቱ። እምውሉደ ልሂቃነ ሀገረ ሮሜ ፡-(፩ጢሞ ፡-፭ ፡-፲፬። ስንክ ፡-መስ፪። ፲፯)።
ልሂብ ቦት ፡-(ልህበ ይልህብ ይልሀብ። ዐረ ለሂበ። ዕብ ላሀብ) መንደድ መቃጠል፤ መንበልበል፤ መሞቅ መተኰስ፤ መላብ መውዛት፤ ለብ ማለት። ወእምዝ ልህበ ልህበተ እምኔሁ ፡-(መቅ ፡-ወን)።
ልሒኵ ኮት ፡-(ለሐኰ ይልሕኵ ይልሐኵ። ዕብ ላሐኽ፤ ላሰ። ያጻር፤ ሠራ) መሥራት ፥ መፍጠር፤ መሣል መቅረጽ፤ የጭቃ የማዕደን። ይልሕኵ እምውስተ ውእቱ ጽቡር አምላከ። በአርኣያሁ ለሐኰነ። እደዊከ ገብራኒ ወለሐኳኒ። ንልሐኵ ውስተ አልባቢነ ተዘክሮ እግዚ ወፈሪሀ ስሙ ፡-(ጥበ፲፭ ፡-፰። መቃ ፡-ገ፳፪። መዝ ፡-፻፲፰ ፡-አፈ ፡-ተ፳፮)።
ልሔም ፡-(ማት። ዕብ ሌሔም) ኅብስት ፥ እንጀራ፤ ከላመ ለለዘበ ዶቄት የሚሠራ፤ ሲበሉት የሚልም የሚጥም። ኤፍራታ እንተ ይእቲ ቤተ ልሔም ፡-(ዘፍ፴፭ ፡-፲፱)። ወአምጽኡ ልሔምሙ።
ልሔምት
፡-(ታት) ሌማት ፥ መሶብ፤ የንጀራ መዝገብ።
ልሕሉሕ ፡-(ሓን ሓት ልሕት) በቁሙ፤ የራሰ ርጥብ፤ ለስላሳ ልዝብ። አብሰሎ ኅቡረ ወገብሮ ልሕሉሐ ወአፍአሞ ለከይሲ ፡-(ዳን፲፫ ፡-፳፮)።
ልኅሉኅ ፡-(ኃን ኃት ልኅት) የላላ የረገበ ልል። ሶበ ይከውን አውታረ መሰንቆ ልኅሉኀ ይጠፍእ ቃናሁ እመ ኢተስሕበ ዘከመ ይደሉ። እሉ አኀው ኮኑ ልኅሉኃነ ፡-(አፈ ፡-ተ፳፱። ፊልክ ፡-፶፱)።
ልኅላኄ ፡-መላላት መርገብ፤ መድከም መዛል፤ መስነፍ መዝለፍለፍ። በእንተ ልኅላኄ ኅሊናሁ ወአኮሰ በእንተ ድካመ ሥጋሁ። እምሀኬት ወልኅላኄ አባል። ልኅላኄ ኀፍረተ ሥጋሁ ለብእሲ ፡-(ፊልክ ፡-፪። ፶፬። ፈ ፡-መ ፡-፬ ፡-፭)።
ልኅልኅና ፡-ልልነት ደካምነት፤ ስንፍና። ወይቈርር እንከ ርስነ ጥብዐቶሙ በእንተ ልኅልኅናሆሙ። ዝኬ ውእቱ ልኅልኅና ወአኮ ተቃትሎት ፡-(ፊልክ ፡-፬። ፸፩)።
ልሕመ [1]፡-(ዕብ ላሐም፤ በላ ፥ ወጋ። ሱር ልሓም፤ ላሰ። ዐረ ለሂመ፤ በላ ፥ አጓመጠ) ላመ ደከመ፤ ለዘበ ለሰለሰ፤ የዶቄት የዐይን የጠጕር የቈርበት። ቀጥቅጥ ወሕርጽ እስከ ይልሕም ፡-(መ ፡-ፈ)።
[2]፡-ላመ ጸና፤ ባሰ። ሰብእሰ አኩይ፤ ወአርዌ ምድር ይልሕም እከየ(ቄር)።
ልህሰ ፡-(ልሒስ ለሐሰ) ኼደ ተጠረገ፤ ጠፋ ታጣ። መሐወኒ እንተ ኵለሄ ወእልህስ። ወይልህስ እመንበሩ። ትፍህቅ ነፍስየ ወትልህስ ፡-(ኢዮ፲፱ ፡-፲። ፳፯ ፡-፳፩። ፴ ፡-፲፭)።
ልሕሰ ፡-ጠፋ ታጣ፤–ልህሰ።
ልሕቀ ፡-ላቀ አደገ፤–ልሂቅ ልህቀ።
ልህቀት ፡-ማደግ ፥ እድገት፤ አስተዳደግ። በእንተ ልደቱ ወልህቀቱ በበ ሕቅ ወሕማማቲሁ ወሞቱ። ልህቀቱ በበ ሕቅ እስከ ወርዘወ። ተወክፈ እሙነ ልህቀት ዘበበ ሕቅ ፡-(አፈ ፡-ድ፭። አርጋ። ሃይ ፡-አበ)።
፡-ማርጀት መላቅ፤ እርጅና፤ ላቂያ ልቅና፤ ብኵርና። ረከበት ወልደ በልህቀቲሃ። አግብእ ሊተ ልህቀተከ ዘቅድመ ልደት ፡-(ሉቃ፩ ፡-፴፮። ኩፋ ፡-፳፬)።
ልህቃን ፡-ዝኒ ከማሁ እድገት ፥ እድጊያ፤ እድግ። አየ ልህቃነ ልህቀ። ዘትስብእት ውእቱ ልህቃን ፡-(ቄር ፡-ጰላ)።
፡-እርጅና፤ የድሜ ብዛት። ውስተ ልህቃነ ዓመታቲሁ ፡-(ፊልክ)።
፡-ላቂያ ልቅና፤ ብኵርና። ወሀበኩ ልህቃንየ ለያዕቆብ ፡-(ኩፋ ፡-፴፮)።
ልህቅና ፡-ልቅና፤ እርግና፤ ብኵርና ታላቅነት። በልህቅናሁ አብደ። ነጺሮ በናእሰ መዋዕሊሁ ወልህቅናሁ ፡-(ፊልክ ፡-፴፩። ፈ ፡-መ ፡-፲ ፡-፫። ኩፋ ፡-፴፮ ፡-፴፯)።
ልህኵት ፡-ሸክላ፤–ልሒኵ ለሐኰ።
ልሕኵት ፡-(ታት) የተሠራች፤ የተፈጠረች። ሸክላ፤ ሥጋ፤ ሰው፤ ያሙስና ያርብ ፍጥረት። ልሕኵት ዘቦቱ አብሰልዎ። ልሕኵት ንጽሕት። ልሕኵተ እግዚአብሔር። ከዐወ ደሞ በሥምረቱ ላዕለ ልሕኵቱ ፡-(ዘሌ፮ ፡-፳፩። ውዳ ፡-ማር፯። መቃ ፡-፳፪። ቅዳ)። ልኵንትንና ልኵትንትን እይ፤ የዚህ ዘር ነው።
ልሕው ፡-(ዋን ዋት ሑት) ያዘነ ያለቀሰ፤ እንብ የፈላበት ፥ ሐዘን የመላበት። ለልሕዋን ይናዝዞሙ ፡-(ኪዳ)።
ልህየ ፡-ወዛ አማረ፤–ልሕይ ልሕየ።
ልሕይ ዮት ፡-(ልሕየ ይልሒ ይልሐይ። ዐረ ላሐ። ሱር ልሓእ) መውዛት መቅለጥለጥ፤ ማማር ማሸብረቅ። እስመ ትልሒ ይእቲ በሥን እምፀሓይ። ሰላም ለገጽኪ ዘጥቀ ይልሒ ፡-(ጥበ፯ ፡-፳፱። ደራሲ)።
ልህደ ፡-ተቀማጠለ፤–ልሕደ።
ልሕደ ፡-(ልሕየ) ለደለደ፤ ወፈረ፤ የተልባ ያብሽ የምራቅ፤ የመሰለው ኹሉ። አማረ ወየዘረ፤ ተደላደለ ተቀማጠለ። አሟረተ ጠነቈለ፤ በሾኽ በንቅፋት በድምፀ አራዊት፤ በማናቸውም።
ልኅደ ፡-ለደለደ፤–ልሕደ።
ልሕጽ
፡-(ጻት) ልጥ
ቅርፍት፤ ጭረት። ፡-(ተረት) የሺ ፍልጥ ማሰሪያው ልጥ። ልሕጸ አዕዋም። ልብሱ ለአባ ሙሴ እምልሕጸ ሆሳዕና ወቈጽሉ ፡-(ስንክ ፡-ሐም፲። መስ ፡-፪)።
ልሙዕ ፡-(ዓን ዓት ምዕት) የለማለም፤ ንጹሕ ብሩህ ፥ ጽሩይ።
ልሙድ ፡-(ዳን ዳት ምድ) የለመደ ፥ ለማዳ፤ ምሁር ሊቅ። እስመ ላህበ ነድ ኮነ ልሙደ ከመ ኢያውዒ እንስሳ። እስመ ኢኮንኩ ልሙደ። ብእሲ ልሙደ ሥላቅ። እመ ኮነ ልሙደ በሰኪር ፡-(ጥበ፲፮ ፡-፲፰። ፩ነገ ፡-፲፯ ፡-፴፱። ሢራ፳፫ ፡-፲፭። ፍ ፡-ነ ፡-፵፯)።
፡-የተለመደ ፣ የታወቀ ዕውቅ። ካልእሪድእዘ ልሙድ:በንበ፣ሴቀካህናት ፡-(ዮሖ፲ቿ2 ፣፲ቹኛ፣፻5)።
ልሙጽ ፡-(ጻን ጻት ምጽት) ለምጻም፤ በራ። የለዘበ ልዝብ ፥ ለስላሳ ልሙጥ፤ ቀጥ ያለ የተካከለ፤ ዐባጣ ጐባጣ ሸካራ የሌለው። ኰኵሕ ልሙጽ። ፍናወ ጽድቅ ልሙጻት። አርዌ ምድር ልምጽት ፡-(ሕዝ፳፮ ፡-፬። ምሳ፪ ፡-፳። ገድ ፡-አዳ)።
ልማድ ፡-(ዳት) [1]፡-በቁሙ፤ ልምድ ዐመል ፥ የተለመደ ግብር። ኢኮነ ሎቱ ልማድ እምቅድመ ዝንቱ። ኢትኅድግ ልማደከ። ወልማዶሙ ለሕዝብ የዐርጉ መልዕልተ ደብር። እኩያነ ልማድ ወግዕዝ ፡-(ፈ ፡-መ ፡-፮ ፡-፪። ዮሴፍ። ቀሌ። ሮሜ፩ ፡-፳፱)።
፡-ትምርት፤ ሕግ ሥርዐት። ወላዲተ አምላክ ኮነት ልማደ። ሀለዉ እለ በልማደ አማልክት። በእንተ ሥነ ልማዳቲሁ። በከመ ልማዶሙ ፡-(ቄር። ፩ቆ ፡-፰ ፡-፯። ፍ ፡-ነ ፳፬ ፡-፩። ስንክ ፡-መስ፰)። አልብነ ልማድ በማለት ፈንታ ኢንለምድ ይላል ፡-(፩ቆሮ ፡-፲፩ ፡-፲፮)።
[2]፡-የግስ ተውሳክ፤ በቀዳማይ አንቀጽ እየገባ አራቱን አዕማድ የሚለይና የሚያስለይ ተጨማሪ ፊደል። እሊሁም ፬ ናቸው አ ፥ አን፤ ተ ፥ አስተ። አገባባቸውን በየቦታቸው እይ።
ልምሉም ፡-(ማን ማት ልምት) የለመለመ፤! የረጠበ ፣ የለሰለሰ፤ ልሕሉሕ ርጥብ፤ ደካማ፤ ለስላሳ ልዝብ። ዕፅ ልምልምት እንተ ኢትውዒ። ደወየ ወፈተወ ኅብስተ ልምሉመ። ናላ ልምሉም ውእቱ በግዕዘ ጠባይዕ። ሎሰ ጽቡረ ልምሉመ። ፈውሳት ልምሉማት። ዐቃቤ አንቀጸ ምኔት ይኩን ልምሉመ ቃል ለርሑቃን ወለቅሩባን ወትሑተ ጥቀ ፡-(ስንክ ፡-ታኅ፳፱። ፊልክ ፡-፻፴። አፈ ፡-ተ፭። ጥበ፲፭ ፡-፯። ፈ ፡-መ ፡-፫ ፡-፫። ፍ ፡-ነ ፡-፲)።
ልምላሜ ፡-(ያት) በቁሙ፤ መለምለም መለስለስ፤ አለሳለስ ልስላሴ፤ ርጥበት ርጥብነት፤ ለምለምነት። ውስተ ገነቱ ይየብስ ልምላሜሁ። ልምላሜ ኅብስት። ልምላሜ መባልዕት ፡-(ኢዮ፲፰ ፡-፲፮። ቅዳ። ፍ ፡-ነ ፡-፳፫)።
ልሱሕ ፡-(ሓን ሓት ስሕት) የላሸ ያለጠ ዐልጫ፤ ሕጹጽ ምኑን። ልሱሕ ነገሮሙ ለአብዳን። ጼው ዘአጥዐሞ ለልሱሕ። ልሱሐ ኀይል ፡-(ሢራ፳ ፡-፳፬። ቅዳ ፡-ዮሐ። ገድ ፡-ኪሮ)።
ልሱን ፡-(ናን ናት ስንት) የተለሰነ ልስን፤ ምርግ።
ልሳነ ሰብእ ፡-የድርሰት ስም፤ መልክአ ልሳን ፥ የልሳንን ጠባይ የሚናገር።
ልሳነ መድሎት ፡-የሚዛን ቀንበር ጋድሙ፤ ወይም ላንሴታው ፡-(ጥበ፲፩ ፡-፳፫)።
ልሳነ ባሕር ፡-የባሕር ጫፍ፤ ሾለቅ አሞጥሙጦ ወደ የብስ ማኽል የሚገባ ፡-(ኩፋ ፡-፮)። ወደ ባሕርም የሚገባ ወንዝ ልሳን ይባላል ፡-(ኢሳ፲፩ ፡-፲፭)።
ልሳነ እሳት ፡-የእሳት ላንቃ ፥ ነበልባል ፡-(ሔኖ፲፬ ፡-፱)።
ልሳነ ዕፍረት ፡-ምዑዘ ቃል፤ ነገሩ እንደ ሽቱ ደስ የሚያሰኝ ፡-(ስንክ ፡-ጥቅ፲፫)።
ልሳነ ወርቅ ፡-ጽሩየ ቃል፤ ነባቤ ቃል ጽሩይ፤ አንደበተ ጥሩ ፡-(ፈ ፡-መ ፡-፪ ፡-፱)።
ልሳናዊ ፡-ነዊኀ ልሳን፤ ምላሰኛ ለፍላፊ አሳባቂ፤ ወይም ቋንቋ ዐዋቂ።
ልሳን ፡-(ናት። ዕብ ላሾን። ሱር ሊሽና። ዐረ ሊሳን) በቁሙ፤ ምላስ አንደበት፤ የአፍ ውስጥ ሕዋስ የመብል የነገር መሣሪያ ፡-(ያዕ፫ ፡-፭ ፡-፮። ሢራ፳፰ ፡-፲፭ ፡-፲፱ ፡-፳፮። መዝ ፡-፭። ፲፩)። በርሱ መሣሪያነት የሚነገር ቃልና ቋንቋም ከርሱ ስም ነሥቶ ልሳን ይባላል። ዘክልኤ ልሳኑ። ልሳን ጥዑም። ጥዑመ ልሳን፤ ቃል ነገር ፡-(ሢራ፮ ፡-፩። ፵ ፡-፳፩። ድጓ)። ሕዝብ ዘኢተአምር ልሳኖሙ። እለ ካልእ ልሳኖሙ። በካልእ ልሳን ይትናገሩ። ሰብዓ ወክልኤቱ ልሳናት፤ ዘሴም ዐሠርቱ ወሰብዐቱ፤ ዘካም ሠላሳ፤ ዘያፌት ዕሥራ ወኀምስቱ ፡-(ኤር፭ ፡-፲፭። ሕዝ፫ ፡-፮። ማር፲፮ ፡-፲፯። ትርጓ ፡-ፊደ)።
ልሳን እንተ ወርቅ ፡-የወርቅ ገንዘብ ፥ በልሳን አምሳል የተሠራ ፡-(ኢያ፯ ፡-፳፩)።
ልስሐት ፡-መላሸት ማለጥ፤ ዐልጫ መኾን ዐልጫነት፤ አለመጣፈጥ። ልስሕተ ጼው ግዱፍ። ልስሐተ ልሳንየ ፡-(ስንክ ፡-ጥቅ፲፪። ደራሲ)።
ልቁሕ ፡-(ሓን ሓት ቅሕት) የተለቃ ፥ የተበደረ ተቀባይ፤ ወይም ተሰጭ።
ልቃሔ ፡-(ሕያት) ማበደር፤ መበደር፤ አበዳደር ብደራ፤ ልቆ የብድር ሥራ። እስመ አፍቅሮቱ በላዕሌከ ልቃሔ። ፍትሐ ልቃሕያት ፡-(ማር ፡-ይሥ፴፫ ፡-፫። ፍ ፡-ነ ፡-፴፬)።
ልቃሕ ፡-(ሓት) ልቆ ብድር ዕዳ። ዘየሐንጽ ቤቶ በንዋየ ልቃሕ። ምጽዋትሰ ልቃሕ አምላካዊት። ወልቃሕሰ ይደሉ ከመ ይኩን በአኅዝ አው በትሕቢት ፡-(ሢራ፳፩ ፡-፰። ፍ ፡-ነ ፡-፲፮። ፳፯)።
ልቅላቄ ፡-መለቅለቅ፤ አለቃለቅ ልቅለቃ፤ ልቅልቃት መጨረሻ ዕጥበት።
ልበ ሰብእ ፡-አስተዋይ ተመልካች፤ የነፍስ ዕውቀት ያለው ፡-(ዳን፯ ፡-፬)።
ልበ ሥጋ ፡-ልሕሉሕ ርኅሩኅ፤ ገር የዋህ ፡-(ሕዝ፲፩ ፡-፲፱)።
ልበ አርዌ ፡-ቍጡ ብስጩ፤ የደመ ነፍስ ዕውቀት ያለው ፡-(ዳን፬ ፡-፲፫)።
ልበ አንስት ፡-ደካማ ሕጹጽ፤ ፈሪ ብቡ ፡-(አዋል)።
ልበ እብን ፡-ጥኑ ጨካኝ ፥ ፈዛዛ፤ ድፍን ደረቅ ፡-(ሕዝ፲፩ ፡-፲፱)።
ልበ ወበልብ ፡-(ዕብ ብሌብ ዋሌብ) በልብ ወልብ፤ ፪ ልብ ፥ ፪ ሐሳብ ፡-(መዝ ፡-፲፩)። ልብ በነገር ኹሉ እየተናበበ እንደ ዘርፉ ስልት ይፈታል፤ ለዳቦም ሳይቀር ውስጥ ላለው ኹሉ ይነገራል። ፡-(ተረት) በገዛ ዳቦዬ ልብ ልቡን ዐጣኹት።
ልበ ፀበርት ፡-(ዕብ ሉላብ) ለጋ ቀንበጥ ሙሽራ፤ ከውስጡ ከልቡ የሚወጣ ፡-(ሕዝ፲፯ ፡-፳፪)።
ልቡስ ፡-(ሳን ሳት ብስት) የለበሰ ፥ የተከደነ፤ ሽፍን። እንዘ ልቡስ አልባሰ መንግሥት። ካህናት ቆሙ ልቡሳኒሆሙ። ይእቲ ሥዕል ትመስል ልብስተ ሥጋ ፡-(አስቴ፰ ፡-፲፭። ዕዝ፫ ፡-፲። ታምር)።
፡-የተለበሰ፤ ልብስ ፥ ውራጅ። ዝንቱ ልብስ ልቡስ ወአኮ ሐዲስ ፡-(ዘረፋ)።
ልቡባዊ ፡-የልብ የውስጥ፤ ውሳጣዊ። ንጸውዖ ለእግዚእነ ለረድኤት በዐውያት ልቡባዊ ፡-(ፊልክ ፡-፻፲)።
ልቡብ ፡-(ባን ባት ብብት) ልበ ቅን፤ ገር ልዝብ፤ ገራም ጭምት። ምስለ ኖኅ ልቡብ ወኵሎሙ የዋሃን። ወአሐዱ እምኔሆሙ ኮነ ልቡበ ፍጹመ ወየዋሀ። ወይኤምሮሙ ፍኖተ ለልቡባን ፡-(ቅዳ ፡-ዮሐ። ፊልክ ፡-፳፯። መዝ ፡-፳፬)።
ልቡና ፡-(ናት) በቁሙ፤ ዕውቀት ሐሳብ፤ ማስተዋል። ልቡና ረሰየተከ መካና። ጸግወነ ጥበበ ወኀይለ ልበ ወልቡና። ወሀቦሙ እግዚ ጥበበ ወአእምሮ ወልቡና በኵሉ መጽሐፍ። ኢይበጽሕዎ ልቡናት ፡-(ድጓ። ቅዳ። ዳን፩ ፡-፲፯። ያዕ ዘእል)። ልብ ልቡና አእምሮ ፥ እሊህ ሦስቱ ባይን ይመሰላሉ፤ ልብ በጥቍሩ፤ ልቡና በብሌኑ፤ እእምሮ በብርሃኑ። ወይም ልብ በነጩ፤ ልቡና በጥቍሩ፤ አእምሮ በብሌኑ ይመሰላል። ኵሊትና ልብም ከናላ ጋራ በሚዛን ይመሰላሉና፤ ናላን ተመልከት።
ልቡይ ፡-(ያን ያት ቢት) ልቡና የሌለው፤ ዝንጉዕ ፥ ስሑት፤ ግብዝ፤ ክፉ ፥ መጥፎ። እነግር ከመ ልቡይ ወህጉል ከፊል ለክልኤ ፥ ወረስዮ በዘዘ ዚኣሁ ሰብአ ወአምላከ ፡-(ቄር ፡-እስት)።
፡-ሐስት ስሕተት ጸያፍ፤ ከስሑታን አፍ የሚወጣ ከንቱ። እቡሰ ወልቡየ ጠበዑ። ልቡይኬ ይእዜ ኀቤነ ወዕቁፍ ከመ ዝ አሚን። ይብሉ ንኤብስ ዐቢየ እመ ንቤ ሐመ ቃል፤ ወኵሎ ክብረ ምስጢር ልቡየ ንሬሲ ፡-(ቄር ፡-ጰላ)።
ልቡጥ ፡-(ጣን ጣት ብጥ) የተለበጠ፤ ልብጥ ፥ ሽፍን። ልቡጥ በወርቅ ወእሱር በወርቅ። ልቡጣን ወቅቡዓን በወርቅ። ደሙ ልቡጥ ውስቴቱ። ልቡጥ በቅድስና። ፡-(ዘፀ፳፰ ፡-፳። ፪ዜና ፡-፬ ፡-፲፰። ዮሴፍ። ስንክ ፡-ኅዳ፳፩)።
ልባብ ፡-(ብ ልባባት) በቁሙ፤ ፉሎ፤ ሕሳልን እይ ፡-(ዐማርኛ)።
ልባዊ ፡-(ዊት) የልብ የውስጥ፤ ጥልቅ ረቂቅ ኅቡእ። ብያኔ ልባዊ። ስፍጠታተ ሰይጣን ልባዊት። ጸሎት ልባዊት ፡-(ፍ ፡-ነ ፡-ፊልክ ፡-፬። ፻፷፩)።
ልባዌ ፡-ልብ ማድረግ፤ ማስተዋል። ዕውቀት የልብ አስተያየት። ቅዱሳን ሲበቁ ከሚያገኟቸው ካሥሩ ማዕርጋተ ንጽሕ አንዱ ልባዌ ይባላል፤ ስማቸውና ተራቸው ቍጥራቸውም ይህ ነው። የንጽሐ ሥጋ መዓርግ፤ ጽማዌ፤ ልባዌ፤ ጣዕመ ዝማሬ። የንጽሐ ነፍስ መዓርግ፤ አንብዕ፤ ኵነኔ፤ ፍቅር፤ ሑለት። የንጽሐ ልብ መዓርግ፤ ንጻሬ መላእክት፤ ተሰጥሞ፤ ከዊነ እሳት። ለነዚሁ ደግሞ ብዙ ዘርፎችና ቅጥዮች አሏቸው ፡-(አረጋ ፡-መል፵፰)። እምአበድ ኀበ ልባዌ። በአጽባዕተ ጥበብ ወልባዌ። ልባዌሁ ፡-(ጥበ ፡-ጠቢ። ደራሲ። ፍ ፡-ነ ፡-፵፬ ፡-፩)።
ልብ ፡-(ብ አልባብ። ዕብ ሌብ፤ ሌባብ። ሱር ሊባእ። ዐረ ሉብ) በቁሙ፤ የታወቀ ሕዋስ ፥ ከንዋያተ ውስጥ አንዱ በሕያው ፍጥረት ውስጥ በየደረቱ የሚገኝ፤ የደም መሰብሰቢያ፤ ደም ከርሱ እየመነጨ ወደ ገላ ኹሉ የሚገናኝበት የሚሠራጭበት፤ ውስጥ ውሳጣዊ ገላ የሐሳብ የፈቃድ የውቀት ምንጭ፤ ወይም ከልብ የሚወጣ ሐሳብ ፈቃድ ዕውቀት። ልብ እንተ ትወልድ ኅሊና እኩየ። ዘክልኤ ልቡ። ወገብኦ ልቡ። ለምንት ትኄልዩ እኩየ በአልባቢክሙ ፡-(ምሳ፮ ፡-፲፰። ያዕ፩ ፡-፰። ሉቃ፰ ፡-፴፭። ማቴ፱ ፡-፬)። ልበ ምድር፤ ልበ ባሕር ቢል ፥ ውስጥ ማለት ነው።
ልብሰት ፡-መልበስ፤ መለበስ፤ አለባበስ ፥ ልብስነት። እምልብሰቱ ለሰበእ ወሑረቱ። ለብሰ ዐማኑኤል ልብሰተ ሥጋ ፡-(ሢራ፲፱ ፡-፴። ቅዳ)። በልብስ ፈንታ ልብሰት ይላል፤ አያሰኝም። ግሩም በልብሰቱ ፡-(ኢሳ፷፫ ፡-፩)።
ልብስ ፡-(ብ አልባስ፤ ሳት) በቁሙ፤ የገላ መክደኛ መሸፈኛ፤በየስሙና በየመልኩ፤ ታላቁም ታናሹም፤ ድንኳንና መጋረጃ ሳይቀር። ልብስ ንዱሕ። አልባሰ ወርቅ ፡-(ራእ፫ ፡-፭። መዝ ፡-፵፬)።
ልብብና ፡-ልበ ቅንነት፤ ገርነት ገራምነት ፡-(ፊልክ ፡-፻፺፬)።
ልብን ኔ [1]፡-ኔ፤ ፡-(ዕብ ሊብኔ። ዐረ ሉብነ) ነጭሎ፤ ነጭ ዛፍ ቅጠሉም ቅርፍቱም ነጭ የኾነ። በትረ ልብን ፡-(ዘፍ፴ ፡-፴፯። ኢዮ፵ ፡-፲፯)።
[2]፡-ልብን፤ ፡-(ዕብ ልቦና፤ ሔልብና። ዐረ ሉባን) ነጭ ዕጣን፤ ልባንጃ ሽቱ፤ ከርቤ፤ ከወተታ ዕንጨት የሚወጣ። ማየ ልብን ፡-(ኩፋ ፡-፲፮። ዘፀ፴ ፡-፴፬። ማሕ፩ ፡-፲፫)። በልብን ፈንታ ሊባኖስ ይላል፤ ስሕተት ነው ፡-(ኤር፲፯ ፡-፳፮)።
ልብው ፡-(ዋን ዋት ቡት) ልበኛ ልባም ፥ ዐዋቂ፤ ልብ ያደረገ ፥ ያስተዋለ። ብእሲ ጠቢብ ወልብው። ንጉሥ ልብው። ዘምሩ ልበወ። ምሁራን ወልብዋን ፡-(ዘፍ፵፩ ፡-፴፫። ጥበ፮ ፡-፳፮። ፩ዜና ፡-፳፭ ፡-፯)።
ልብውና ፡-ልባምነት፤ አስተዋይነት።
ልብጠት ፡-መለበጥ፤ ፡-(ጥለ) መለበጥ፤ አለባበጥ፤ ልበጣ ልባጥ ልብጣት።
ልቱም ፡-የተለተመ፤ ውግጥ ፍትግ ፡-(ዘፀ፳፱ ፡-፵። ዘሌ፪ ፡-፲፬)። ሐሪጽ ልቱም፤ ታጥቦ ተፈትጎ የተፈጨ፤ ስንዳሌ ፡-(፫ነገ ፡-፬ ፡-፳፬)።
ልቱት ፡-(ታን ታት ትት) የለተተ፤ ድኩመ ልሳን ፥ ድዳ ለንባዳ፤ ወይም በጭራሽ መናገር የማይችል በሃም። አስተርአየ መድኅኒነ ከመ ያርትዕ ልሳነ ልቱተ ወያሩጽ ሐንካሰ ፡-(መዋሥ)።
ልታቴ ልተት ፡-ልቱትነት፤ ድካም ልስላሴ።
ልት ፡-ልት፤ በቁሙ፤ የቅጠል ስም ፥ የደጋን መሟዣ ደካማ ለስላሳ የወጥ ቅጠል። ፡-(ግጥም) የዚህ ቤት ሴቶች አትቅበጡ፤ ልቶጡ ናችኹ ልቶጡ ፡-(ልት ወጡ)። ቍስልም ሲለግምና ሲያቀብር ልት ቀጥቅጦ ቢያስሩበት ቶሎ ነፍርቆ ይሽራል።
ልዑል ፡-(ላን ላት ዕልት) በቁሙ፤ ከፍ ያለ የበለጠ፤ በላይ ያለ ታላቅ፤ ረዥም ምጡቅ። ልዑል ውእቱ ላዕለ ኵሉ። አእምር ሚ መጠን ልዑል እምኔከ ደመና። ሰማይ ልዑል። መንበር ልዑል ፡-(መዝ ፡-፺፰። ኢዮ፴፭ ፡-፭። ምሳ፳፭ ፡-፫። ኢሳ፮ ፡-፩)።
ልኡክ ፡-(ካን ካት እክት) የተላከ ፥ መልክተኛ፤ አገልጋይ። ልኡከ እግዚእነ። ግብረ ልኡካን ፡-(፩ጴጥ ፡-፩ ፡-፩። ግብ ፡-፩)።
ልዒት ቶት ፡-(ለዐተ ይልዕት ይልዐት) መላት፤ ላት ማውጣት። መትከል ማግባት፤ ማዋደድ መሰካት፤ ማሰማማት፤ ዕንጨትን ከብረት ፥ ብረትን ከንጨት።
ልዒል ሎት ፡-(ለዐለ ይሌ(ል) ዕል ይልዐል። ዕብ ወዐረ ዐላ) ላይ ላይ ማለት፤ ከፍ ከፍ ፥ አፈፍ አፈፍ ማለት፤ መነሣት ማረግ ፥ ወደ ላይ መውጣት፤ መርዘም መብለጥ፤ መክበር ልዕልና ማግኘት፤ በላይ መኾን፤ ደየበን እይ። አልቦ ባዕድ ዘይሌዕል እምኔሁ። እንዘ ለሊሁ ይልዕል እምሰማይ። አጽባእ ዕጽብት ዘትልዕል እምኀይሉ። በእንተ አውስቦ ራብዕ ዘይልዕል እምኔሃ። ዝንቱሰ ራእይ ይሌዕል ፈድፋደ እምጠባይዕ ፡-(አፈ ፡-ድ፲፩። ተ፲፮። ፊልክ ፡-፻፵። ፍ ፡-ነ ፡-፳፬ ፡-፪። አረጋ መል፵፬። ማር ፡-ይሥ፩ ፡-፲፩)። ዳግመኛም፤ ላዕሎ ፥ ላዐለ ይላዕል ብሎ እንደ ላሐወ በባረከ ቤት ሊገሰስ ይቻላል። አንዳንድ መጽሐፍ ግን በለዐለ ፈንታ ተልዕለ ተለዐለ ይላል፤ ባለቅኔዎችም በዚሁ አካኼድ ይገሱታል፤ ፍጹም ስሕተት ነው። ተለዐለ ማይ ዲበ ኵሉ አድባር ነዋኃት። ተለዐለት ታቦት እምነ ምድር። ከመ ዕፀ ቄድሮስ ተለዐልኩ። ተልዒልየ ተትሕትኩ። ወተለዐለ ላዕለ ኵሎሙ ሰበእ በልቡናሁ ወበጥበቡ ፡-(ኩፋ ፡-፭። ዘፍ፯ ፡-፲፯። ሢራ፳፬ ፡-፲፫። መዝ ፡-፹፯። ስንክ ፡-ጥቅ፮)።
ልኢክ ኮት ፡-(ለአከ ይልእክ ይልአክ)። መላክ መስደድ። ደገመ ልኢከ ኀቤሁ። ለአከ መጻሕፍተ ወተናብልተ ወአምኃ ኀበ ሕዝቅያስ። አመ ለአኩ ኀቤሁ አይሁድ። ለአከ ወነሥኣ ፡-(፫ነገ ፡-፳ ፡-፭። ኢሳ፴፱ ፡-፩። ዮሐ፩ ፡-፲፱። ዘፍ፳ ፡-፪)።
ልኢፍ ፎት ፡-(ለአፈ ይልእፍ ይልአፍ። ዐረ ላፈ ለአፈ) መላፍ መማግ፤ የሙቅ ያጥሚት። መብላት መዋጥ መሰልቀጥ፤ የጥሕሎ የፍትፍት።
ልዕልና ፡-በቁሙ፤ ልዑልነት ታላቅነት፤ ከፍታ ምጥቀት ርዝመት። ልዕልና መዝራዕትከ። የኀስር ልዕልና ዕጓላ መሕያው። የአምር ኀይለ ልዕልና ሰማያት። ገነትሰ በእንተ ልዕልናሁ እምድር ይሰመይ ሰማየ። ልዕልናሁ ለውእቱ ሰማይ ከመ እምድር ለምጽናዕ ፡-(ዘዳ፫ ፡-፳፬። ኢሳ፪ ፡-፲፩። ሢራ፲፯ ፡-፴፪። ፊልክ ፡-፯። ዕር ፡-ኢሳ፯ ፡-፲፰)።
ልኵትንት ልኵንት ፡-(ለሐኰ ልሒኵ) ልሕኵት፤ ልጕን፤ የሸክላ ዕቃ የዘይት ማሰሮ ገንቦ ማድጋ። ልኵንትኪኒ ዘቅብዕ ፡-(፫ነገ ፡-፲፯ ፡-፲፪ ፡-፲፬ ፡-፲፮። ፬ነገ ፡-፬ ፡-፪)። ልኵንትና ልኵትንት በልሕኵት ፈንታ የገባ የጣፊ ስሕተት ስለ ኾነ ፥ አንዳንዱ መጣፍ ልሕኵት ይላል።
ልኵንት ፡-ልሕኵት፤–ልኵትንት።
ልኩእ ፡-(ኣን ኣት ክእት) የተለካ፤ የተላከከ። የተጣበቀ፤ የተቸነከረ። ወልኩእ ዲበ መሳክዊሃ ሰሌዳ መጽሔት። መልክአ ሥጋሁ ልኩእ ላዕለ ዕፀ መስቀል ፡-(አዋል። ስንክ ፡-ጥር፳፯)።
፡-የታተመ፤ የተጻፈ። ጽሑፍ ተዝካር ውስቴቱ ወልኩእ በአምጣነ ኍልቆሙ። ናሁ ልኩእ ውስተ መጽሐፈ ፋርስ ወሜዶን ለተዝካር። ወነገሩ ዘተርፈ ልኩእ በመጽሐፉ ፡-(ሢራ፵፭ ፡-፲፩። አስቴ፲ ፡-፪። ዮሴፍ)።
ልኩፍ ፡-(ፋን ፋት ክፍት) የተለከፈ፤ የተነካ ንክ። ኢልኩፋን ለግሰት አጻብዕ ፡-(መጽ ፡-ምስ)።
ልክአት ፡-መለካት፤ መጣፍ ማተም፤ መታተም ፡-(አርጋ)።
ልክፈት ፡-መንካት፤ መነካት። አነካክ ፥ ንኪት ልክፊያ ቅምሻ።
ልዉስ ፡-የተለወሰ፤ የተቦካ የታሸ። ልዉስ በቅብዕ። ሐሪጽ ልዉስ ፡-(ዘፀ፳፱ ፡-፪። ሆሴ፯ ፡-፬። ኩፋ ፡-፮)።
»ልደት ፡-(ታት) [1]፡-በቁሙ፤ ውልደት፤ መውለድ መወለድ አወላለድ፤ ትውልድ። ዕለተ ልደቱ። በልደቱ እምብእሲት። ከመ ዝ ውእቱ ልደቶሙ ለደቂቀ ኖኅ ፡-(ማቴ፲፬ ፡-፮። ቄር። ዘፍ፲ ፡-፩)።
፡-መውጣት መብቀል፤ መገኘት መፈጠር፤ ፍጥረት። ልደተ ወርኅ። ከመ ልደተ ንጻሬ እምዐይን ወከመ ልደተ አምሳለ መልክእ እመጽሔት። ወልደተ ዓለም ለድኂን። ኦሪት ዘልደት ፡-(መር ፡-ዕዉ። ያዕ ፡-ዘእል። ጥበ፩ ፡-፲፬። ዘፍ ፡-፩)።
፡-ዘር የትውልድ ሥር ሐረግ። መጽሐፈ ልደት። ኍልቈ ልደት ፡-(ማቴ፩ ፡-፩። ፩ዜና ፡-፯ ፡-፱)።
[2]፡-ልጅነት ልጅ መኾን፤ ልጅ መባል፤ መታደስ። ዳግም ልደት ፡-(ቲቶ፫ ፡-፭። ማቴ፲፱ ፡-፳፰)። የደብረ ሊባኖስ ሊቃውንት ልደትን አምልተው አስፍተው ሲተረጕሙና ሲፈቱት እንዲህ ብለው ይዘረዝሩታል። ልደት በ፪ ወገን ነው በባሕርይ በግብር፤ የባሕርይ ልደት የባሕርይ አባትን የባሕርይ እናትን መስሎ ተካክሎ ነው፤ መብለጥና ማነስ የለበትም፤ ከዚህ የተነሣ ጌታችንም በባሕርይ ልደቱ መንቲያና ታናሽ መሳይ ተከታይ ወንድም ስለሌው፤ ላባቱም ለናቱም ወልድ ዋሕድ እንጂ በኵር አይባልም፤ በሰውነቱም ባምላክነቱም ባሕታዌ ልደት ነውና፤ ከዋሕድና በቀር ብኵርና የለውም ብንሰጠውም እንደ ዋሕድናው የባሕርይ ገንዘቡ ስላልኾነ ዕሺ ብሎ አይቀበለንም። የግብር ልደት ግን ለባሕርይ ልደት ምሳሌ ነውና፤ ምሳሌ ከአማናዊ እንዲያንስ እንዳይተካከል የግብር ልደትም ከባሕርይ ልደት አይተካከልም፤ በስም ብቻ ልደት በመባል ይተካከለዋል። አወላለዱም፤ ወዘእንበለ ካሕድ ዘየዐቢ ይባርኮ ለዘይንእስ እንዳለው ኹሉ ፡-(ዕብ፯ ፡-፯) ከሚበልጠውና ከሚቀድመው ተባርኮ ተሹሞ፤ ሀብተ ወልድና ስመ ወልድና ተቀብሎ መውለዱና መወለዱ ሳይኖር በመስጠትና በመቀበል ብቻ አባትና ልጅ መባባል ነው። ናታንና ዳዊት በትንቢት፤ አነ እከውኖ አባሁ ወውእቱ ይከውነኒ ወልድየ። ፡-(ወልድየ አንተ) ወአነ ዮም ወለድኩከ። ውእቱ ይብለኒ አቡየ አንተ ወአነሂ በኵርየ እሬስዮ ያሉት። መልአኩም በብሥራት፤ ዘኒ ይትወለድ እምኔኪ ቅዱስ ውእቱ ወይሰመይ ወልደ እግዚ ልዑል ያለው። ሊቃውንትም ከዚህ አያይዘው፤ ወንሰምዮ ወልደ፤ ናሁ ኮነ ለነ ወልደ በሀብት። ወተሠርዐ ወልደ እግዚ በኀይል ቅብዐ መንፈስ ቅዱስ። እመሰ ኰሰይነ ልደቶ እንተ ከማነ በመኑ ትመሲለነ ንከውን ውሉደ እግዚ በመንፈስ ያሉት በዚህ በግብር ልደት ነው። የግብር ወይም የጸጋ ልደት ከጸጋ ወንድሞች ከተወራራሾች ቢያስተካክል እንጂ ከወላዲና ከሠያሚ አያስተካክልም፤ ይኸውም ዘቀደሶ አብ ወፈነዎ። እስመ አብ የዐብየኒ ባለው ይታወቃል ፡-(ሮሜ፰ ፡-፲፬–፲፯። ዮሐ፲ ፡-፴፮። ፲፬ ፡-፳፰። ፳ ፡-፲፯)። ወረሰየነ ዕሩያነ ምስሌሁ በመንፈስ ቅዱስ። ይቤ እነግሮሙ ስመከ ለአኀውየ፤ ዝኒ ከመ ያግህድ ዕበየ ክብር ዘወሀቦሙ ከመ ይትዓረይዎ። ለሊሁ ርእስ ወንሕነ አባል ወሱቱፋኒሁ በተዋርሶ ፡-(ቄር። አፈ ፡-ድ፬። ፮)። የግብር ልደትም የሚፈጸም ኋላ በትንሣኤ ነው፤ እስከዚያ ዐረቦን ይባላል ፡-(ሮሜ፮ ፡-፫–፱። ፪ቆሮ ፡-፩ ፡-፳፩ ፡-፳፪። ፭ ፡-፭)። ይኸውም ሊታወቅ ሐዋርያው ዮም ወለድኩከን ኹለተኛ ስለ ትንሣኤ ጠቅሶታል። ሊቁም ወውእቱ ቅድመ ዘተወልደ እሙታን ብሎታል ፡-(ግብ፲፫ ፡-፴፫። ሃይ ፡-አበ ፡-ቄር)። ያረቦኑና የትንሣኤው ልደት አንድ ነው እንጂ ኹለት አይባልም፤ ትርጓሜ ወንጌል ግን እየብቻው ቈጥሮ አርባዕቱ ልደታቲሁ ለክርስቶስ ይላል። ይኸውም ቢኾን የትንሣኤን ልደት መባል እንጂ አራተኛነትን አያሳይም፤ ዐረቦን እንደ ፅንስ፤ ትንሣኤ እንደ ልደት ነውና።
»ልድ [1]፡-ውላጅ የቤት ውልድ፤ የባሪያ ልጅ። ልደ ቤቱ ፡-(ዘፍ፲፯ ፡-፳፫። ኤር፪ ፡-፲፬)።
[2]፡-(ዐረብ) ስመ ሀገር፤ ልዳ የቅዱስ ጊዮርጊስ መቃብር። ልድ ልደት ፡-ወሊድ ወለደ።
[2]፡-ልደት ፤–ወሊድ ወለደ።
»ልገት ፡-(ታት) [1]፡-ጐዦ ቅልስ፤ መተሜታ ዋሻ ጐሬ፤ ሾልኮ ተጐንብሶ የሚገቡበት። ልገተ ዐቃቤ ቀምሕ። ወገብረ ሎቱ ልገተ ፡-(ኢላ፩ ፡-፰። ዮና፬ ፡-፭)።
[2]:-ጐዦ መተሜታ፤–ወለገ።
፡-(ሱር ልጊና፤ ላጊና። ጽር ላጊኖስ) ለገን ዋዲያት፤ ማድጋ ምንቸት፤ መንቀል ኵስኵስት። ገንዐ ወልጕነ ፡-(ገድ ፡-ተክ)።
ልግነት ፡-ገንፎ መንካኮ፤ እንቀት አጥሚት።
ልጐት ፡-(ታት። ዐረ ሉጀት) ቀላይ ፥ ጥልቅ ዕመቅ፤ የባሕር የወንዝ ፥ የጕድጓድ የዐዘቅት። ያስጥምዎ ውስተ ልጐተ ባሕር። ልጐታተ አብሕርት። ልጐታተ ምድር ይሜጡ ሎሙ ንዋዮሙ ወልጐተ ምድሮሙ ፡-(ማቴ፲፰ ፡-፮። ኩፋ ፡-፪። ስንክ። ጥቅ፳፫። ኅዳ፲፫)።
ልጓም ፡-(ማት፤ አልጓም። ዐረ ሊጃም። ሱር ሉግማ። ዕብ ልጊማ) ጕርሻ ፥ ባፍ የሚመላ ፥ አንዳፍ ፥ አንድ ቢጆ። በቁሙ፤ ቀለበቃም ብረት፤ በእንስሳት አፍ የሚጐረሥ። ለአፍራስኒ ንወዲ ሎትን ልጓመ ውስተ አፉሆን። ይፈትሕ ልጓማተ ጽኑዓን። በአልጓሚሁ ፡-(ያዕ፫ ፡-፫። ሔኖ፵፮ ፡-፬። ቄር)።
ልጕን ፤ (ሱር ልጊና
፤ ላጊና። ጽር ላጊኖስ) ፤ ለገን ዋዲያት ፤ ማድጋ ምንቸት ፤ መንቀል ኵስኵስት።
ገንዐ ወልጕነ (ገድ ፡ ተክ)።
ልጥር ፡-(ጽር ሊትራ። ሱር ወዕብ ሊጥራ። ዐረ ረጥል) የሚዛን ስም፤ የታወቀ ሚዛን ነጥር፤ ፲፪ ወቄት የሚያነሣ ፥ በዱሮ ሒሳብ። ነሥአት ዕፍረተ ልጥረ። ምእተ ልጥረ። ሠለስቱ ምእት ልጥረ ወርቅ ፡-(ዮሐ፲፪ ፡-፫። ፲፱ ፡-፴፱። አፈ ፡-ተ፳)።
ልጹቅ ፡-(ቃን ቃት ጽቅት) የለጠቀ የቀረበ፤ የተጠጋ የገጠመ፤ የተያያዘ ፅሙር። አዘዘ ጢጦስ ያንኅሉ መካነ ልጹቀ ቍድስ። አግዋር እለ ልጹቃን። እመ ኮነት ነፍስ ልጽቅተ ምስለ እግዚአብሔር ፡-(ዮሴፍ። ፍ ፡-ነ ፡-፴፯። አፈ ፡-ተ፳፯)።
ልጽቀት ፡-መለጠቅ መጣበቅ፤ ልጥቅ ማለት እንደ ድጕስ። ቅርበት አው ልጽቀት ፡-(ቄር ጰላ)።
ልጽቅ ፡-(ብ ልጸቅ) ሳንቃ መዝጊያ፤ ወይም የቤት ታዛይ ጕርጅ ጓዳ። ኆኃት ውሳጥያት እለ ያበውኣ ውስተ ልጽቀ ቤት ፡-(፪ዜና ፡-፬ ፡-፳፪)።
ልፉጽ ፡-የተለፈጠ ልፍጥ፤ የታሸ የታበቀ ልዉስ፤ ፍጹም ሊጥ ቀጭን ብጥብጥ ያይዶለ እንፍርፍር። ልፉጽ በቅብዕ ፡-(ዘፀ፳፱ ፡-፵)።
ልፋፈ ጽድቅ ፡-መንፈሳዊ ክታብ፤ የደረት መጣፍ፤ ማንበቡና መሸከሙ ብቻ የሚያጸድቅ፤ ኋላም ሲሞቱ ዐብሮ የሚቀበር። መንፈሳዊነቱ በአፍኣ ነው እንጂ ፥ በውስጡ ብዙ ጸያፍ ቃል ሐሰትና ስሕተት አለበት። ከሐሰቱም አንዱ፤ እግዜር እንዳሠርቱ ቃላት በጁ ጣፈኝ ይላል። ሌላም ይህን የመሰለ ግብዞችና አታላዮች ፈልስፈው ያወጡት ፥ አርድእት ፥ ባርቶስ ፥ ኅቡእ ስም የሚሉት ልፋፍ አለ።
ልፋፍ ፡-(ዐረ ሊፋፈት) መለፈፊያ፤ መሸፈኛ ሠርመዲ። አምጽአ ልፋፈ ከመ ይክድን አዕይንቲሁ ፡-(ስንክ ፡-መጋ፯)።
፡-የጠንቋይ ክታብ፤ ጠልሰም ዐይነ ጥላ፤ እንደ ፊደል የሚጠቀለል። የጠንቋይም ባይኾን የሚጠቀለል ከኾነ ማናቸውም ጥፈት ልፋፍ ይባላል፤ ልፋፈ ጽድቅ እንዲሉ።
ልፍጸት ፡-ልፉጽነት፤ እንፍርፍርነት ፡-(መ ፡-ፈ)።
ሎሐ ፡-(ዕብ ላዌሕ) ላገ ጠረበ አለዘበ፤ ፋቀ ራመመ፤ የንጨት የቈርበት የደንጊያ የብረት። ባለቅኔዎች ግን ጣፈ ይላሉ።
ሎልዎ ዎት ፡-(ሎለወ፤ ለውለወ ይሎሉ ይሎሉ) መውለብለብ፤ ማውለብለብ፤ ማቃጠል መለብለብ፤ የምላስ የእሳት። ለውለወ ከይሲ ልሳኖ። ወትሎሱ ክቡተ ፍጥረተነ ፡-(መጽ ፡-ምስ። ገድ ፡-ተክ። ያዕ፫ ፡-፮)። በሎለወ ፈንታ አሎለወ አለውለወ ይላል፤ ግስነቱ ዐጕልና ገቢር ነውና፤ አያሰኝም። ለውላዋ ማለት ከዚህ ወጥቷል።
ሎሚ ሎሚን ፡-(ብ ለዋሚን፤ አው ሎሚናት። ዕብ ሊሞን። ሱር ሊሙን። ዐረ ለይሙን) በቁሙ፤ የታወቀ ዕፅ ፥ እሾኻም፤ መዐዛው ጥፍጥ ፥ ፍሬው የሚመጠጥ፤ መጣጣ ሖምጣጣ። ዘሩ ለምለመ ነው፤ ሎሚ ያማርኛ፤
ሎሚን የግእዝ፤ በትግሪኛ ግን ሎሚ፤ ዮም ማለት ነው። ማየ ሎሚ ፤ ወይመትሩ ሎሚነ ፡-(መ ፡-ፈ)።
ሎሰ ፡-ለወሰ አቦካ፤–ለዊስ።
ሎዘ ፡-(ዕብ ላዝ ያሉዝ) ከመንገድ ወጣ፤ ራቀ። ምስጢሩ የለወወ ነው፤ ክፋትና ጥመት ያሳያል።
ሎዛ ፡-ስመ ሀገር፤ ለውዛም የለው ቦታ፤ በኤፍሬም ዕፃ ውስጥ ያለች፤ ይችውም ቤቴል ናት ፡-(ዘፍ፳፰ ፡-፲፱)።
ሎዛን ፡-(ዐረ ላዝን) ዕጣን፤ ሙጫ ከለውዝ ወይም ከሌላ ዕንጨት የሚገኝ። ከርቤ ወሜዓ ወሎዛን ፡-(ስንክ ፡-ሐም፰)።
ሎግዮን ሎግዮ ፡-(ጽር ሎጊዎን። ዕብ ሖሼን) ሴዴርያ ፥ የደረት ልብስ፤ ከአልባሰ ክህነት አንዱ። ልብሰ ሎግዮን። ከመ ልብሰ ክህነት ሎግዮ ፡-(ዘፀ፴፮ ፡-፲፭ ፡-፲፮ ፡-፳፪። ደራሲ)። ባማርኛ መልካም ነገር ሲታይ ወሼን ወሸኔ ፥ ውሽን ማለት ፥ ሖሼን ከማለት የመጣ ነው።
ሎጠ ፡-(ወለጠ። ዕብ ላጥ ያሉጥ) ሸፈነ አለበሰ፤ አጐናጠፈ። ለወጠ ፥ ለዋወጠ፤ የልብስ የመልክ። ወለጠን እይ፤ የዚህ መንቲያ ነው።
ሎጣዊ [1]፡-ሎጥማ፤ የሎጥ ዐይነት። የሎጥ ጎረ ቤት፤ በግብር የሎጥን ጋብቾች የሰዶምን ሰዎች የሚመስል። ሎጣውያን ዘውእቶሙ እለ ይዜምዉ ተባዕተ ፡-(ፈ ፡-መ ፡-፯ ፡-፫ ፡-፭)።
[2]፡-ሎጣዊ፤–ሰዶማዊ፤–ሎጥ ለወጠ።
No comments:
Post a Comment