~የ~

                                 

[1]-፲ኛ ፊደል በግእዝ አልፍ ቤት በአበገደ፤ ስሙ የማን ጥሩ ዐሥር አኃዝ ኾን ዐሠርት ይባላል

[2]-አካል ዝርዝር አነ ለሚል ብቻ ለልየ ኪያየ ዚኣየ፤ነፍስየ

[3]-ሥርወ ትንቢት፤ የካልኣይ አንቀጽ መነሻ ለሦስት ራዊት፤ ለሩቅ ለሩቆች ወንዶችና ቶች ግእዙ ብቻ ስለ ተነገረ ሪብዑና ሳድሱ አይቀሩም። ይህም -(ዖቁ ) የዐውቅ -( ) ይዑቅ ዖቀ -( ) ያዐውቅ ያዑቅ እያለ ሌላውን ኹሉ ያሳያል። የትንቢት አሥራው ብቻ ናቸው

የሂድ ዶት -(የሀደ ይየ ይይሀድ ዕብ ያሄድ) ይሁዲ ማድረግ አሕዛብን ወደ ሕዝብ መሳብ፤ ማስጠጋት ማቅረብ፤ መግዛር በኦሪት ማሳመን፤ ከዚህ የተነሣ እግዜርን ማመስገን ማስመስገን። ገየረንና አፍለሰን እይ፤ የዚህ ጎሮች ናቸው -(ማቴ፳፫ -፲፭)

የመመ -(ትግ -ሐባ) መላ ፈጸመ ቈረጠ ገደበ። ዘሩ ሜመየ ነው

የመን -(ዕብ ቴማን) ሀገር የምድረ እስራኤል ደበብ ምድረ ዐረብ።

የሚን ኖት -(የመነ ይየምን ይይምን። ዕብ ያሜን፤ ዐደመ) መቅናት፤ ቅን ቀኝ መኾን፤ መጽናት መበርደድ፤ መብዛት መፈድፈድ፤ መክበር መወደድ፤ በቀኝ መቀመጥ ወደ ቀኝ መኼድ።

የማናዊ -( ) የቀኝ በቀኝ ያለ ቅን ቀኛም ባለቀኝ ቀኝ አዝማች፤ ቀኝ ጌታ ቀኝ የሚቆም የማናዌ ፍኖተ ዐይኑ የማናይ ነደ የማና() ገቦሁ የማና() ወፀጋማይ እለ ልኤሆን እደዊሆሙ የማናይ() ያን -(ስንክ -ታኅ፭ ኪዳ። ስንክ -ነሐ፲፯ ቀሌ መሳ፳ -፲፮)

የማን -(ዕብ ያሚን። ሱር ያሚና። ዐረ የሚን) ቀኝ፤ የቀኝ እጅ፤ የቀኝ ማእዝን ደቡብ፤ የግራ ይዩ የሰሜን አንጻር ዘትገብር የማንከ ታእምር ፀጋምከ ልቡ ለጠቢብ ውስተ የማኑ ተፈለጥ የማነ አው ፀጋመ መንገለ የማነ ምሥዋዕ -(ማቴ፮ -፫። መክ፲ - ዘፍ፲፫ -፱። ሉቃ - -፲፩) ይል ጽንዕ ብዛት እጅግነት።

የሱስ -መድኅንኢየሱስ

የቢስ ሶት -(የብሰ ይየብስ ይይበስ ዕብ ያቤሽ። ሱር ዬቢሽ ዐረ -የቢሰ) መድረቅ መክረር፤ ርጥበት ልምላሜ ማጣት ፈለግ ይነፅፍ ወይየብስ ወውእቱ የብሰ ከመ እብን ይየብስ ተክሎሙ የብሰ ማእረረ ምድር -(ኢዮ፲፬ -፲፩። ፩ነገ -፳፭ -፴፯። ኢዮ፳፬ -፲፱ ራእ፲፬ -፲፭)

የብስ -በቁሙ ደረቅ ምድር ባሕር የሌለው ውሃ ያልሸፈነው ይቤ ያስተርኢ የብስ ወአስተርአየ የብስ ወሰመዮ እግዚ የብስ ምድረ እለ የኀድሩ የብሰ። በየብስ ወበባሕር -(ዘፍ፩ -፬። ሔኖ፴፯ -፭። ዮሴፍ)

የብቦ ቦት -(የበበ ይዬብብ ይየብብ ዕብ ወሱር ያቤብ ጮኸ አለቀሰ) እልል ማለት፤ በደስታ ቃል መጮኽ ማመስገን የዘፈን የማሕሌት። ባበየን እይ፤ የዚህ ግልባጭ ነው የበበት እሌኒ። መላእክት ዘይዜምር ወቦ ዘይዬብብ -(ድጓ ቀሌ መዝ -፵፮። ፹፰)

የካቲት -(ከቲት ከተ ከተተ) በቁሙ የወር ወር ከመስከረም። የመከር ጫፍ መካተቻ፤ የበልግ መባቻ ማለት ነው፤ ተተን እይ ዐሡሩ ወሰዱሱ ለየካቲት በዘወሀባ ከዳነ ምሕረት -(መቅ -ታም)

የዊም -(ዮመ ይየውም ይዩም) ጊዜን መስፈር መቍጠር፤ መክፈል መተንተን፤ ቅጽበትን በካልኢት ካልኢትን በደቂቅ ደቂቅን በሰዓት ዓትን በዕለት ዕለትን በ፳፬ ዓት መወሰን መቀመር የፈጣሪ የሰዓት ሠሪ

የዋሂ -(ሂት ህያን ያት) የሚያለዝብ የሚያግራራ የሚያሞኝ ሸንጋይ አታላይ።

የዋህ -(ሃን ሃት) በቁሙ የቀና ቅን ልዝብ ገር ገራም ጭምት ደግ ጥሩ እወነተኛ ቅጽልነቱ ዐጕል ሕገ ወጥ ስለ ኾነ ወንድና ያስተባብራል አዳምን እይ። ተመሀሩ እምኔየ እስመ የዋህ አነ። ብእሲ የዋህ። በየዋህ ኵነኔ ይኴንን ቅሩብ ግዚ የዋሃነ ልብ -(ማቴ፲፩ -፳፱ ሢራ፳፭ -፳። ኢሳ፲፩ -፬። መዝ -) ብእሲት የዋህ እመሰ የዋህ ይእዪ ወሠናይ ቃላ -(ሢራ፳፮ -፲፬። ፴፮ -፳፰) ብዙ መጻሕፍት ይህም የጠቀስነው ሢራክ ሳይቀር በየዋህ ፈንታ የዋሂት ይላሉ፤ አያሰኝም። በሲት የዋሂት እምእከይ ርግብ የዋሂት በግዕት የዋሂት -( - - -፰። አፈ -ተ፴፪ ስንክ -ግን፳) ለክፋ ኾን ሞኝ አላዋቂ ያልተማረ ያሰኛል የዋህ የአምን ኵሎ ነገረ -(ምሳ፲፬ -፲፭)

የውሀ -(ዐጕል ዕብ -ያኣህ) አማረ ተዋበ) ዝኒ ማሁ፤ የዋህ ኾነ ለዘበ ቀና፤ በገዛ እጁ

የውሀት የውህና -በቁሙ፤ የዋህ መኾን የዋህነት ገርነት ቅንነት በየውሀት ተናገረኒ ዘየሐውር በየውሀት ይኩነኒ በከመ የውሀትየ ርግብየ ይቤላ በእንተ የውሀታ። ከመ በየውህና ንሕዮ -(ዕር -ኢሳ፯ -፮። ምዳ፲ -፱። መዝ -፯። ቄር -ጰላ)

የውሆ ሆት -(የውሀ፤ ይዬውህ ይየውህ) -(ገቢር) ማለዘብ ማለዛዘብ ማግራራት ማቈላመጥ፤ ቅንነት ማስተማር፤ ገር የዋህ ቅን ማድረግ። ሀሎ ዘይጠብብ ለነፍሱ ይዬውህ በቃሉ አኀ ይየውሃ በቃል ሠናይ። ትጋነይ ወእዬውሃ ትዬውሆሙ ለኃጥኣገ ወትመይጦሙ በብዝኀ ምሕረትከ መዐተ ንጉሥ ከመ መልአከ ሞት ወብእሲ ጠቢብ ይዬውሆ -(ሢራ፴፯ -፳፪። ስቴ -፭። ኢዮ፲፮ -፲፯። ዲድ -፴፮። ምሳ፲፮ -፲፬) ማሞኘት ማታለል፤ መደለል መሸንገል፤ የክፉ ዘይዬውሁ ለከንቱ የዋህናክሙ በቃል -(ቆላ፪ -፰። ፩ተሰ - -) በየውሀ ፈንታ አየውሀ ይላል ስሕተት ነው አየውህዎ -(ስንክ -ሚያ፳፰)

የውጣ -(ጽር ዮታ) ፊደል የ፤ ፲ኛ ዐሥር -(ማቴ፭ -፲፰) ቀዳሜ ስሙ ለኢየሱስ የውጣ በኍልቈ -() ዐሠርቱ ፈጻሚተ ቃላት የውጣ -(ዲድ -፰። ውዳ -ማር፩ ስንክ -ነሐ፲፮) የሱስ በማለት ፈንታ የውጣ ይላል፤ ስሕተት ነው። ርቆሬዎስ ሰማዕተ የውጣ -(ስንክ -መስ፲፰)

የዲዕ ዖት -(የድዐ ይየድዕ ይይዳዕ ዕብ ያዳዕ ሱር ዪዳዕ) ማወቅ መረዳት ልኩን ርግጡን ማግኘት፤ በጠባያዊ ዕውቀት ፈልጎ መርምሮ ተመራምሮ፤ እንደ አብርሃም እንደ ሙሴ ጸሊም። 

-የቅጽል ምእላድ ወይም የስም አርቲክል በሴት አንቀጽ ለሚነገር ቃል። ሐዳስዩ ድንግልዩ ብሊትዩ ዕቤርዩ እያለ ይህን በመሰለ ይገባል ሲፈታም ዐዲሷ ዐዲሲቱ ባልቴቷ ባልቴቲቱ ያሰኛል ይዌድስዋ መላእክት ለማርያም በውስተ ውሳጤ መንጦላዕት ወይብልዋ በሓኪ ማርያም ሐዳስዩ ጣዕዋ -(ሳታት)

- -የሣልስና የኃምስ ሥረዮች የሣልስ የኃምስ የሣልስ የኃምስ ድምፅ ኹሉ ከዪና ወጥቷል፤ ቅጥላቸውም የዪና የዬ ምልክት ነው ፊደል ኹሉ አለየ መሪነት ሣልስና ኃምስ አይኾንም

-የጥሬና የስም ምእላድ ወገናዊ ቅጽል ዊና ይን ተመልከት።

[1]-የጥሬና የስም ምእላድ ፍችው ንያ ሐዋርያ ብልኀተኛ መንገደኛ ትዮጵያ እስክንድርያ የኢትዮጲስ የእስክንድር አገር ወይም ኢትዮጳዪት እስክንድራዪት ያሰኛል፤ ይኸውም በተጸውዖ ስም ገባ ነው

[2]-ያ፤ አብዢ ምእላድ ንና እየተደረበ በሣልስ ቅጽል በሣልስ መስም ይገባል ቀታሊ ያን ያት መምለኪ ክያን ያት ብዙዎቹን ወንዶችና ቶች በሚያስተባብር በመድበል ቅጽል ግን ተውጦ ተጐርዶ ይቀራል ቀተልት፤ መምለክት

ያህ -(ዕብ ሱር ይያ) ዐጭር አምላክ፤ የይሆዋ ክፋይ ዘይቤው እግዚእ፤ ምስጢሩ ምላትና ስፋት ልዕልናና ርቀት ያሳያል ዕብራውያንም ሲፈቱ፤ ዐቢይ ወጽኑዕ ስፉሕ ወምሉእ እግዚእ ዘበአማን ዘያገምር ኵሎ ወኢያገምሮ መካን፤ ይሉታል ሃሌ ሉያ -(ዕብ -ሀልሉ ያህ) የሃሌ ሉያን ፍች እይ

()          ያም -(ዕብ) ባሕር ዐዘቅት ምንጭ ድጓድ ታላቅ የውሃ ቃ። ምዕራብ፤ የፀሓይ መግቢያ መጥለቂያ። ባሕርንና ማርያምን እይ።

ያሬድ -(ዕብራ) የሰው ስም፤ ፮ኛው ትውልድ የሔኖክ አባት ወሪድ ርደት ማለት ነው በርሱ ዘመን የደቂቀ ሴት ከደቂቀ ቃየል መጋባይና መዋለድ፤ ከደብር ቅዱስ ወደ ምድረ ፋውድ መውረድ ተዠምሯል። የወረዱበትም ምክንያት አዋልደ ቃየል እንደ የጁ አርኾ ስለ ኾኑ በመልካቸው ውበት በድምፃቸውና በዘፈናቸው ጣዕም ተመሥጠው ነው ወለደት ሎቱ ዲና ወልደ ወጸወዐ ስሞ ያሬድሀ እስመ በመዋዕሊሁ ወረዱ መላእክተ እግዚ ውስተ ምድር እለ ተሰምዩ ትጉሃነ በእማንቱ መዋዕል ተወልዳ አዋልድ ሠናያት ወልሑያት፤ ወርእዩ ኪያሆን መላእክት ውሉደ ሰማያት ወፈተውዎን ወይቤሉ በበይናቲሆሙ ንዑ ንኅረይ ለነ ንስተ እምውሉደ ሰብእ ወንለድ ለነ ውሉደ -(ኩፋ -፬። ሔኖ -፭። ዘፍ፮ - -) በኢትዮጵያም በሳድሳይ ምእት -(ሴክል) ተነሥቶ ፭ቱን ጸዋትወ ዜማ የደረሰ የድጓና የማሕሌት አባት ሮድዮን እንደሚባለው ወፍ ዜማው ልብ የሚመሥጥ እጅግ ድምፀ መልካም ስለ ኾነ፤ ሰውየው ያሬድ ወፉም ዖፈ ያሬድ ተብሏል፤ ምስክሩን በአሮድዮን ፍች ተመልከት አእመርነሂ ከመ ሀሎ በቀራንዮ ገነ ያሬድ ዘወለዶ ሔኖ ማሕሌት -(ጐዣማዊ ቅኔ)

ያርብሓዊ -ዝኒ ማሁ ዔናቃዊ የዔናቅ ወገን ሐርበኛ ወናሁ ያርብሓዊ -(፩ነገ -፲፯ -፳፫)

ያርብሕ [1]-ዐርበኛ፤ረብሐ።

 [2]-(ሓን) ሐርበኛ ይለኛ የወንዶች ባል፤ ዠግና ስሙዐ ዜና፤ መጠኑ ቁመቱ ኀይሉና ጕልበቱ ከሰው ልክ ያለፈ የተረፈ እንደ ዔናቅ ልጆች ያለ ጢጣኖስንና ናፊልን ተመልከት ኀይለ ያርብሕ ሥጋ ያርብሕ በንእሱ ተለ ያርብሐ። ከመ ያርብሕ ዘይሜርድ ፍኖቶ -(ኢሳ፫ -፪። ሕዝ፴፱ -፲፰ ሢራ፵፯ -፬። መዝ -፲፰) ኀያላን ያርብሓን በማለት ፈንታ እለ ያርብሕ ይላል፤ አያሰኝም -(ዘፍ፮ -፬። ፲፬ -፭። ዘኍ፲፫ -፴፬)

ያቁም [1]-የዐምድ ስም፤ቀዊም ቆመ አቀመ

 [2]-(ጽር ያኹም ዕብ ያኪን) የዐምድ ስም፤ በበለዝ አንጻር በስተቀኝ የቆመ። ቀዋሚ ቅዉም ርቱዕ ድልው ማለት ነው በለዝን እይ -(፫ነገ -፳፩)

ያክንት -(ጽር ኢያኪንቶስ። ዕብ ሌሼም) ክቡር ደንጊያ ንቍ የቀይ ጥቍር ደምማ፤ ቅላቱ የሮማን ፍሬ ደረቅ በርበሬ የሚመስል ደባባ -(ራእ፳፩ - ሔኖ፸፩ - ሕዝ፳፰ -፲፫)

 -ቀይ ቀለም፤ የደም ይነት ዘሢረቱ ሕብረ ያክንት ወእምሕብረ ያክንት ወሜላት -(ዘፀ፳፭ -፭። ፳፮ -)  

ያፌስ -(ዕብ ኤፌስ) ባዶ ደካማ ልምሾ። ባለብሉዮች ግን ፋስ ምሣር ይሉታል ዕብራይስጡ፤ ውብኤፌስ ያድ ይሻቤር ያለውን ወበድክምት እድ፤ ወይም ፅብስት ፅውስት ዘእንበለ ኀይል በማለት ፈንታ ወበያፌስ ይቀጠቅጥ እደ ይላል አንዳንዱም መጣፍ ዘእንበለ እድ ይላል -(ዳን፰ -፳፭)

[1]-ቃለ ብካይ ወሰቈቃው፤ በቁሙ፤ ወዮ ወየው ይብላኝ ብክይዎ ወላሕውዎ እለ ታፈቅርዎ፤ ዐማኑኤል ምላክነ -(ቅዳ -አፈ)

[2]-ቃለ ትፍሥሕት ወአንክሮ ሠይ ኢዮሃ እንሆ መስቀል ጸገየ መንክር እንሆ ድንቅ -(ድጓ) -(ዕር፳ -ቍ፺፬)

ዬም -ማዎት ማየ ሕይወቅ ፍል ውሃ

-የቅጽል ምእላድ፤ እንደ በጥሬና በስም እየገባ ወገን የሚያሳይ ቅድም ቀዳማይዪ፤ -(ዪት ይያን ያት) ፊተኛ የፊት ፈያታይ፤ የወንበዶች ወገን ቀማኛ። ላዕላይ ታሕታይ ላይኛ ታችኛ፤ የላይ የታች፤ በላይ በታች ያለ ብጻይ ብጻዪ የግብጽ ሰው ቀርናይዪ፤ ቀንደኛ ቀንዳም ባለቀንድ የቀንድ ከብት ተዋጊ እያሰኘ እንደ ሙሻዛር እንደ ሣልስ ቅጽል በሚያምርለት ስልት ይፈታል። ምክንያቱም ዊና ሣልሶች ስለ ኾኑ ነው በዪ ፈንታ ግን መጣፉ ተለመደ ነው እንጂ የሚገባው ኹኖ አይዶለም፤ ልስና ድስ ምን ገጥሞት ባማርኛ ግን ድሱን ሲጫኑት ድምጡ እንደ ሣልስ ኾነ ሣልስና ሳድስ ይዋረሳሉ ሰጪ ገዢ፤ ሰጭ ገዥ የመሰለው ኹሉ የዊን ፍች እይ

ይሁዳ -(ዕብራ) የሰው ስም፤ ምስጋና እምነት ወይም አማኒ ምእመን ማለት ነው -(ዘፍ፳፱ -፴፭) ስመ ገድ፤ ስመ ሀገር ይሁዳ የወለደውና የወረሰው የይሁዳ ዘር የይሁዳ ምድር ወኮነ ይሁዳ መቅደሶ ወእስራኤልኒ ምኵናኖ በእንተ ይሁዳ ወኢየሩሳሌም -(መዝ -፻፲፫ ኢሳ፩ -፩። ማቴ፪ -፳፪ -፭። -፳፭)

ይሁድና -ይሁዲነት፤ ይሁዲ መኾን መባል፤ እምነት። ይሁድና ዘአይሁድ። ጾረ ኀጢአት ዘአመ ይሁድና -(ቄር - ተረ -፲፱)

ይሆዋ -(ዕብ ይሆዋሀ) ስመ ኦምላክ፤ ከፍጡራን ስም የተለየ ፈጣሪ በቀር ለማንም ፍጡር የማይሰጥ፤ ፍጡራን የማይጠሩበት። መጽሐፍ ግን በይሆዋ ፈንታ ይሆባ ይላል ይሆባ ጸባኦት አዶናይ -( -ሚካ) ፍችውም እግዚ አምላክ ኵሉ፤ ፈጣሬ ዓለም ንጉሠ ዓለም ያሰኛል እግዚአብሔርን ተመልከት ከዚህ ጋራ አንድ ነው

ይሙነ  -(ንኡ አገ) እጅግ በጅግ ብዙ በብዙ አካቶ ፈጽሞ ጭራሽ እስመ አኅሰርዎሙ ይሙነ በስኩ ይሙነ ይከብደኒ ይሙነ ብዙኀ ይሙነ -(፩ዜና -፲፱ -፭። ፳፩ -፰። ዜና - -) አንዳንድ መጻሕፍት በይሙነ ፈንታ እሙነ ላሉ፤ የጣፊ ስሕተት ነው።  

ይሙን -(ናን ናት ምንት) የማናይ የቀና የጠና፤ ብርቱ በርዳዳ።

ይምን -ዝኒ ከማሁ፤ ቀኝ የቀኝ ክፍል ወገን፤ በስተቀኝ ያለ ማእዝን፤ እጅ ሕዋስ ይምነ ሐመር ዘይምኖሙ እን ይሰርር ይምነ ወፅግመ ይምና ለበድነ ሥጋሁ ነዲፍ ይምን ወበፅግም -(ዮሐ፳፩ - ዘካ፲፪ -፮። ቀሌ ስንክ -ጥቅ፮ ዜና -፲፪ -)

ይበስ -ድርቅ ድርቀት። ይበሰ ኅብስት -(ስንክ -ነሐ፲፱)

ይቡስ -(ሳን ሳት ብስት) የደረቀ የከረረ ደረቅ ከራራ ይብስት ባሕር። ዕፅምት ይቡሳት ይቡሳነ ልብ ይቡስ ኅብስት ይቡስ ክሣድ ይቡስ -(ዘፀ፲፬ -፳፬ ሕዝ፴፯ -፬። ሔኖ፭ -፬። ሢራ፮ -፫። ቄድር ኩፋ -)

ይባቤ -(ብያት) በቁሙ፤ እልልታ ጩኸት፤ ምስጋና መዝሙር በደስታ ቃል የሚነገር ወአልቦ ብዝኅ ለይባቤነ ዐርገ እግዚ በይባቤ ማርያም በይባቤ ትዘብጥ ከበሮ -(መዝ -፵፫ -፮። መዋሥ)

ይቤ -(በዪል ሎት ቤለ ይበይል ይቢል አው ቤለ ይቤ ይበል) የቤለ ልኣይ ትንቢት አንቀጽ። ፍችው፤ ይል ይላል፤ ይል በር የቤለ ትንቢቶች ካልኣዮቹ ይቤና ይበይል ኹለት እንደ ኾኑ አስተውል። መምህራን ግን በቤለ ፈንታ ይቤን ከብህለ ደርበው ቀዳማይ አንቀጽ ያደርጉታል ኛም ዘሩና አርእስቱ በዪል ኾን አርእስት የለውም፤ ነባር አንቀጽ ነው ይሉታል፤ ብሂልን እይ

ይብሰት -መድረቅ አደራረቅ፤ ድርቀት ድርቅና ደረቅነት ሐዘንከኑ በእንተ ይብሰት ሐምሐም ይብሰት ኅብስት -(ስንክ -መስ፳፭ ፊልክ -፸፬)

ይንዋርዮስ -(ሮማይ ንዋሪዉስ) ስመ ወርኅ ጥር የኤውሮፖች መዠመሪያ ወር ዘይንዋርዮስ -(ተረ -ቄር፳፭)

ይእቲ -ያች ርሷ ነች ናትውእቱ

ይእዜ -(ይእቲ ጊዜ) አኹን በዚች ዓት ዛሬ ዘንድሮ አኹን ማለት ቅጽበት ደቂቃ ይቀር የጊዜን መቅረብና ማጠር ያሉበትን ክፍል ያሳያል ይእዜ ትስዕሮ ገብርከ ይእዜኒ ወዘልፈኒ ምንእስየ እስከ ይእዜ እምይእዜ ወእስከ ለዓለም -(ሉቃ፪ -፳፰። ይሁ -፳፭ መዝ -፸። ኤፍ -) አንዳንድ ጊዜም በእንከ ዘይቤ ይፈታል ዮምን ተመልከት የዚህ መንቲያ ነው።

ይዋሄ -ዝኒ ማሁ በፍርሀት ወበይዋሄ ይዋሄ ወህድአት ወስርምሞ -(አፈ - ዮሴ አርጋ -)

ይዱዕ -(ዓን ዓት ድዕት) የታወቀ የተረዳ የተነገረ

ይዶን -(ሮማይ ይዱስ) ክፍል ወርኅ የወር እኩሌታ በዱሮ አከፋፈል የየካቲት ፲፫ኛ ወይም በሠግር ጊዜ ፲፭ኛው ቀን ወበወርኀ ሮሜ ቅድመ ሰማኒቱ ይዶን ፍርፍርዮን -(ተረ -ር፳፭)

-( ዮሙ ዮን) ድርብ ዝርዝር የገቢር ጸፋ ባራት ራዊት በሩቅ በሩቆች የሚነገር ኪያሁ -( ሆሙ ሆን) በማለት ንታ እየገባ ያን ያነን ርሱን ያሰኛል ሀበኒዮ እምውእቱ ማይ ከመ የሀበኒያ ለይእቲ መጽሐፍ። ወሊተ ወሀብከኒዮሙ አልቦ ዘየሀይደኒዮን እስመ ቡየ ዘወሀበኒዮን ውእቱ የዐቢ ምኵሉ -(ዮሐ፬ -፲፭። ራእ፲ -፱። ዮሐ፲፯ - -፳፰ -፳፱)

ዮም -(ዕብ ዮም። ሱር ያውማ ዐረ የውም ዕለት፤ መዓልት) ዛሬ አኹን ዘንድሮ፤ የተወሰነ ክፍል መዓልትና ሌሊት ዕለት ርኅ ዓመት፤ ቀመር ሉበትን ቀን ወራትና መን ከመባቻው እስከ መካተቻው ያሳያል የሰውም ድሜ ተወልዶ እስኪሞት ተሹሞ እስኪሻር የሚኖረው ዮም ይባላል ይእዜንና ዕለትን ተመልከት ዘትማልም ወዮም ዮም ወለድኩከ ወዮም ብሂል አኮ ዘኀለፈ መዋዐለ ዘይነግር አላ ዘሀሎ ዮምኬ ሰብእ ወጌሠመ መሬት ንጉሥ ዮም ወጌሠመ ይመውት -(ዕብ፲፫ -፰። ቄር ድጓ ሢራ፲ -)

ዮማዊ -ሙያተኛ፤ የዕለት ምንደኛ ጧት እስከ ማታ የሚሠራ የዕለት መፍቅድ በየቀኑ የሚወጣ ወጪ ወይም ገቢ ገንዘብ። ዮምዬ እንዲል -(ዐረብ) ዘመናይ ሹም ባለጊዜ፤ ፍለኛ ጐበዝ ወጣት ልጅ እግር።

ዮም [1]:-ዛሬየውም

[2]-(ዕብ ዮም። ሱር ያውማ ዐረ የውም ዕለት፤ መዓልት) ዛሬ አኹን ዘንድሮ፤ የተወሰነ ክፍል መዓልትና ሌሊት ዕለት ርኅ ዓመት፤ ቀመር ሉበትን ቀን ወራትና መን ከመባቻው እስከ መካተቻው ያሳያል የሰውም ድሜ ተወልዶ እስኪሞት ተሹሞ እስኪሻር የሚኖረው ዮም ይባላል ይእዜንና ዕለትን ተመልከት ዘትማልም ወዮም ዮም ወለድኩከ ወዮም ብሂል አኮ ዘኀለፈ መዋዐለ ዘይነግር አላ ዘሀሎ ዮምኬ ሰብእ ወጌሠመ መሬት ንጉሥ ዮም ወጌሠመ ይመውት -(ዕብ፲፫ -፰። ቄር ድጓ ሢራ፲ -)

ዮርዳኖስ -(ጽር ዮርዳን። ዕብ ያርዴን። ሱር ያርድና) ስመ ፈለግ፤ የከነዓን ወንዝ፤ ታላቅ ዠማ፤ ከምድረ እስራኤል ዳርቻ ከነገደ ዳን ክፍል እንደ የወልና እንደ ዳሸን ለው ደብረ ሔርሞን ከሚባለው ደቡብ ወገን ከተራራው እግር ከሔርሞን ሥር ነሥቶ ወደ ደቡብ ወደ ባሕረ ጼው የሚፈስ ዮር ወራጅ ፈሳሽ ዳን ደየነ ዳኘ ፈረደ፤ በተገናኝ ፈለገ ዳን ማለት ነው በዳኖስ ዘይቤ ሲፈቱት ግን ዳናዊ ፈለግ ወይም በጠቅላላው ዮርዳናዊ ያሰኛል -(ኢያ፫ -) ዳን የውነተኛው ዳኛ፤ የውነተኛው መጥምቅ የመሲሕ ምሳሌ ጸዋሬ ስሙ ስለ ኾነ የዮርዳኖስ ነቅ ሥሉስ ቅዱስ ምንጩ አውራጃውና ቀበሌው ገና ነገደ ዳን ሳይወርሱት ሙሴና አብርሃም በፊት አስቀድሞ ባምላካዊ ትንቢት ዳን ተብሏል። ወሐዊርየ ነበርኩ ዲቢ ማያተ ዳን በዳን ንተ ይእቲ እምየማነ ረበ ሔርሞን ተለዎሙ እስከ ዳን። ወአርአዮ ኵሉ ምድረ ገለዓድ እስከ ዳን -(ሔኖ፲፫ ዘፍ፲፬ -፲፬። ዘዳ፴፬ -) ትርጓሜ ወንጌልም ዘአምነ ወዘተጠምቀ ይድኅን ወዘሰ ኢአምነ ይዴየን ያለውን ፈታ ዳንን ደያኒ ደያን መደይን ብሎ ዮርዳኖስን ፈለገ ደይን ይላል ፍርዱን እንደ ውሃው ከሰዶምና ገሞራ ባሕረ ጼው ጋራ ለማያያዝ -(ማር፲፮ -፲፮ ማቴ፲፩ -፳፫ -፳፬) የዮርዳኖስ ራስ ቁና ስሙ በሥላሴ አምሳል ሦስት ነው ያውም አብ ወልድ መንፈስ እንደ ማለት ሐስባኒ ተለልጋዲ ባንያሲ ይባላል ጣዕሙና ሕብሩም እንደ ስሙ ልዩ ልዩ ነው መጠኑም በላይና በታች ትክክል ነው፤ ርሕቀቱም ካንዱ ነቅ እስካንዱ ሩብ ሩብ ሰዓት ያስኬድል፤ ወደ ደግሞ መካከለኛው በቀጥታ ግራና ቀኙ ማሰየፍ፤ ኹሉም በየፊቱ አንዳንድ ሩብ ወይም እኩል ሰዓት ብቻ ብቻውን ይወርድና ሦስቱ ነቅዐ ማይ ካንድ ቦታ ላይ ይገናኛል ተገናኘም በኋላ ወንዝ በመኾን ወደ ታች ሰዓት ወርዶ፤ ማየ ሜሮም ይም ባሕረ ሖሊ ከሚሏት ከታናሽቱ ሐይቅ ይገባና ርሷን እንደ መርከብ ማኽል ማኽል ሠንጥቆ ዐልፎ ከርሷ በታች ደግሞ ሰዓት ጐርፎ ኪኔሬትና ጌንሴሬጥ ባሕረ ገሊላ ወይም ጥብርያዶስ  ከሚባለው ከታላቁ ሐይቅ ይገባል። ጥብርያዶስንም አባይ በጣና ላይ እንደሚያልፈው ማኽል ለማ ሠንጥቆ ዐልፎ፤ ከግራና ቀኝ ብዙ አፍላጋት እየጨመረ፤ ሮቤልን ጋድን መንፈቀ ምናሴን ወደ ግራ፤ የቀሩትን ነገድ ወደ ቀኝ ትቶ ማኽል ለማኽል አቅንቶ የሦስት ቀን ጐዳና ጐትቶ ባሕረ አፍ ይገባና ተውጦና ምጦ ይቀራል፤ የባሕረ ጼው ዙሪያ ተራራና ገደል የቈላ ቈላ መቀራቅርት መትሕተ ታሕቲት ስለ ኾነ ከዚያ ሲወጣ አይታይም። የጥምቀትን ውሃ የንዋየ ቅድሳትን ዕጣቢ የተቀደሰን ፈሳሽ ገር ኹሉ ከመሬት መቅበር የትም አለማፍሰስ የዚህ ምሳሌ ነው ይባላል። ቀድሞ በኢያሱ እስራኤል የተሻገሩበት ኋላም በዮሐንስ ጌታችን የተጠመቀበት ወደቡ ነው፤ ከዚያ በታች እስከ ባሕረ ጼው እኩል ሰዓት ወይም ሩብ ያስኬዳል። «ጌታም በዚህ ወደብ በዮርዳኖስ እግር መጠመቁ ስለ ሦስት ገር ነው ይባላል ፩ኛው፤ ግራዝማች ዲያብሎስ ያዳምን ዘር ኹሉ የላሜ ልጅ ያውራዬ ውላጅ ለማለት አዳም ገብሩ ሔዋን አመቱ ብሎ በደንጊያ የጣፈው ደብዳቤ ከዚያ ነበረና ያነን ለማጥፋት ለመደምሰስ ፪ኛው፤ ጥምቀት የሞቱ አርኣያ የመቃብሩ አምሳል ነውና፤ ከኃጥኣን ጋራ ተቈጥሮ እንዲጠመቅና እንዲሰቀል የተጣፈውን ቃል ንስሓና ጥምቀት የሚሻ ፍጹም ኃጥእ መስሎ በዮሐንስ እጅ ለመፈጸምና ከላይ በዮርዳኖስ ነቅ የተከተትውን የጥምቀት ቀሚስ ሽልማትና ጌጥ ምስጢረ ሥላሴን ለመግለጥ። ኛው የአዳም ጢአት ካናት የፈሰሰ እስከ እግር ድረስ እንደሚሉት እንደ ታላቅ ወንዝ ነውና፤ እስራኤል ዘሥጋ ከፈርዖን ባርነት ወጥተው ዮርዳኖስን በዚህ ወደብ ዐልፈው ተሻግረው ምድረ ከነዓን እንደ ገቡ እስራኤል ዘነፍስም ከሰይጣን ርነት ወጥተው ያዳምን ጢአት በርሱ ጥምቀትና በኵርነት፤ በጽድቁና በትሩፋቱ  በሕማሙና በሞቱ ዐልፈው ተሻግረው ወደ ማያዊት ነዓን እንዲገቡ መጠን መግባታቸውን ለመስበክ » -(ሉቃ፬ -፲፮ ፳፬፳፯ ነገ - -፲፬) ምአፍላግሂ ወአብሕርት እንዘ ይእቲ ነኣስ ይትከሀል በበ ገጹ ኒጊረ ዕበያ ለዮርዳኖስ ምጣነ ዳግማይ አዳም መልክአ ዚኣ ክርስቶስ ወከመ ትኩኖ ብእሲተ አልሀቃ መንፈስ ቅዱስ -(ቅኔ)

ዮቅጣን -የሰው ስም፤ቀጠነ

ዮቶር -(ዕብ ዬቴር ይትሮ) የሰው የሙሴ ማት ተረፍ ትራፊ ቅሬታ ወይም ከቍጥር ያልገባ ጭማሪ ማለት ነው፤ ትርፌ እንደ ማለት -(ዘፀ፫ -፩። -፲፰)

ዮናኒ -ጽርእ . የግሬክ ቋንቋ ከቅብጥ የሚስማማ የቅብጥ ጎረ ቤት ባለ፳፬ ፊደል ቅብጡ ፊደሎች ይጨምራል፤ መለዮው ይህ ነው

ዮናናዊ -ሀዋን ዘር የግሬክ አገር ሰው

ዮናን -(ዕብ ያዋን) ፬ኛው የያፌት ልጅ፤ የግሪኮች አባት የሀገርና የሕዝብ ስም ጽር ግሬክ፤ ፍችው አስሓቲ መስሕት በያዋን ፈንታ ይህያን ይላል፤ ስሕተት ነው -(ዘፍ፲ -)

ዮን ዮና -(ዕብራ) ርግብ ዮን ተባቱ ዮና እንስቲቱ ያባዛ ዮኒም ይላል ፪ኛም ዮና ዮናስ የሰው ይኾናል፤ ስምነቱም እንደ ደስታ ወንድና ሴት ያስተባብራል -(ስንክ -ኅዳ፲፰)

ዮዳሄ -(ጽር ዕብ ይሆያዳዕ) የሰው ም፤ እግዜር ያውቃል -(፬ነገ -፲፩ -) ዳግመኛም በዮዳሄ ፈንታ ኢዮአዳ ይላል፤ ስሕተት ነው -(ዜና -፳፬ -)  

ዮድ [1]-ስመ ፊደልየወድ

 [2]-(ዕብ ዩድ) ስመ ፊደል ፲ኛ ፍችው እጅ -(መዝ፻፲፰ -፸፫፹። ሰቈ፩ -፲። - -፳፬። -) በመዝሙር ዮድ -(መጽ -ምስ)

ዮጊ [1]-እንሆ ወይየወጊ

 [2]-(ንኡስ አገ) እንሆ አኹን ዛሬ -(ይህ ጊዜ) ወይ ምናልባት። ዮጊ በጽሐት እምትሡዒ ለአማልክት ወእምዕጣነ ታዕርጊ ተመትሮተ ክሣድ አብደርኪ ወኀረይኪ ዮጎ። መኑ የአምር ዮጊ በዝንቱ መዋዕል ግሠኪ ገሥጾ ለዐርክከ ዮጊ ኢገብረ። ትፍቅድ ከዊነ መኰንን ዮጊ ትክል ተበቅሎቶ ዘአበሰ፤ ወዮጊ ታደሉ ገጸ ዐቢይ -(ሉቃ፲፩ -፳። ስንክ -ግን፮ አስቴ፬ -፲፬። ሢራ፯ -፮። ፲፱ -፲፫ -፲፬) -(ዕር፳ -ቍ፺፮)


No comments:

Post a Comment

ማውጫ

ሀ   ለ   ሐ   መ   ሠ   ረ   ሰ   ሸ   ቀ   በ   ተ   ቸ   ኀ   ነ   ኘ   አ   ከ   ኸ   ወ   ዐ   ዘ   ዠ   የ   ደ   ጀ   ገ   ጠ   ጨ   ጰ   ጸ   ፀ   ፈ   ፐ